zena_methet | Неотсортированное

Telegram-канал zena_methet - ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

-

👋 ሠላም እንዴት ናቹ 👋 ይህ ዜና-መፅሄት/ZENA-METHET የሚለው መረጃ ሠጪ ቻናል ነው። እርሶም ይህን ቻናል በመቀላቀል የመረጃ ባለቤት እንዲሆኑ በትህትና እንገልፃለን። "መረጃ ሙሉ ሰው ያረጋል" 🇪🇹Addis Ababa, Ethiopia🇪🇹

Подписаться на канал

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በሱማሊያ በአንድ ቀን ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በሀገሪቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 32 ደርሷል

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 943 ላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 124 ደርሷል።

የታማሚው ዝርዝር ሁኔታ ፦

- የ45 ዓመት እንግሊዛዊ (በትውልድ ኢትዮጵያዊ) ከእንግሊዝ የተመለሰና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ አገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከህንድ ጋር በመሆን ለኮሮናቫይረስ የሚሆን ክትባት በማዘጋጀት ላይ መሆኗን አሳውቀዋል።

የሰውየው ንግግር ብዙም ያልተጠበቀ አልነበረም።
ህንድና አሜሪካ ለ30 ዓመታት ያክል መድኃኒትና ክትባት በጋራ ሲያመርቱ ከርመዋል። የወባ መድኃኒት፣ ታይፎይድ ክኒን፣ ኢንፍኡዌንዛና የቲቢ በሽታን የሚያክሙ መድኃኒቶችን በጋር አምርተዋል። የወባ ክትባት ለማዘጋጀትም በጋራ እየሠሩ ነው።

ህንድ መድኃኒትና ክትባት በማምረት በዓለማችን ቁንጮ ከሚባሉ አገራት መካከል ናት። የፖሊዮ፣ የማጅራት ገትር፣ የሳንባ ምች፣ የኩፍኝን ጨምሮ የሌሎችም በሽታዎች ክትባቶችን የሚያመርቱ ድርጅቶችም አሏት።

የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለማግኘት ደፋ ቀና ከሚሉ ድርጅቶች መካከል ስድስቱ ህንድ ነው የሚገኙት። ከእነዚህም አንዱ ሴረም የተባለው ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት ክትባት አምርቶ በመሸጥ በዓለም የሚስተካከለው የለም።

ይህ በሥራው ላእ ከ50 ዓመት በላይ የቆየ ድርጅት በዓመት 1.5 ቢሊዮን መድኃኒቶችና ክትባቶች ያመርታል። ፋብሪካው ህንድ ውስጥ ሁለት ትላልቅ ፋብሪካዎች አሉት። ኔዘርላንድስና ቼክ ሪፐብሊክም ውስጥ ማምረቻዎች ገንብቷል። ድርጅቱ 7 ሺህ ያህል ሠራተኞች እንዳሉት ይነገራል።

ኩባንያው 20 የክትባት ዓይነቶችን ለ165 አገራት ያቀርባል። 80 በመቶ ምርቶቹ በጣም ተመጣጣኝ በሚባል ዋጋ የሚቀርቡ ናቸው።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን ወደ ስራቸው ተመልሰዋል!

በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የነበሩት የብሪታኒያው ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን ከቫይረሱ አገግመው በዛሬው እለት ወደ ስራቸው ተመልሰዋል፡፡ ስራ ከመጀመራቸው በኮሮና ምክንያት የሀገሪቱ የእንቅስቃሴ እገዳ ፈተና ሆኖባቸዋል።

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው እገዳው በቅርቡ ካልተነሳ ብሪታንያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የምትገባ ምዕራባዊት ሀገር ልትሆን እንደምትችል የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እየገለጹ ነው፡፡ እስካሁን በብሪታንያ ከ152 ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ከ20 ሺ 700 በላይ የሚሆኑት ሞተዋል፡፡

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

አጫጭር መረጃዎች ፦

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ45,000 በልጧል። በአንድ ቀን ብቻ ከ2,700 በላይ ሰው ሞቷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ824,000 በልጧል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 759 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተድርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 18,100 ደርሷል።

- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 1,194 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 94 ሰዎች ሞተዋል።

- በስፔን የሟቾች ቁጥር መጨመር እያሳየ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 435 ሰዎች ሞተዋል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 21,717 ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪ በአንድ ቀን 4,211 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 204,178 ደርሷል።

- በደቡብ ኮሪያ 11 ተጨማሪ ኬዞች ሪፖርት ተደርገዋል። ከአስራ አንዱ መካከል ስድስቱ (6) ከውጭ የገቡ ናቸው።

- ሲንጋፖር የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመግታት ያወጣቻቸውን ገደቦች እስከ June 1 አራዝማለች።

- በኳታር ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 608 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በቻይና ተጨማሪ 30 ኬዝ ተመዝግቧል። ሀያ ሶስቱ (23) ከውጭ የገቡ ናቸው።

- በማዳጋስካር ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት አዲስ ኬዝ እንዳልተመዘገበ ተሰምቷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 121 ሲሆኑ 52 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

- በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 2,586,639 ደርሷል። 179,942 ሰዎች ሞተዋል። 705,814 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1073 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታው በአፋል ክልል ገዋኔ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 2 - የ54 ዓመት አሜሪካዊ (በትውልድ ኢትዮጵያዊ) ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የለውም።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አምስት (5) ሰዎች (4 ከአዲስ አበባና 1 ከድሬዳዋ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሃያ አንድ (21) ደርሷል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 298 ደረሱ!

በጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 498 የላብራቶሪ ምርመራ 83 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸቅ ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 298 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት አምስት (5) ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ደርሷል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ፦

- ለ65 ዓመታት ያህል በትዳር የቆዩት የ88 ዓመት የእድሜ ባለፀጋዎቹ ባለትዳሮች ሁለቱም ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸው ከወደ ስፔን ተሰምቷል።

- በዩናይት ኪንግደም የሟቾች ቁጥር ወደ 10,000 እየተጠጋ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 917 ሰዎች የሞቱ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 9,875 ደርሷል።

- በስውዲን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10,000 መድረሱን ለማወቅ ተችሏል።

- በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃና ከተማ በነበረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለበርካታ ሳምታት ተዘግቶ የቆየው HONDA ዳግም ተከፍቶ ወደስራ ገብቷል።

- የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የጤና ሁኔታ በእጅጉ እየተሻሻለ መምጣቱን ቃልአቀባያቸው ተናግረዋል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 619 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 4,694 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በስፔን የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። ባለፉት 24 ሰዓት 510 ሰዎች በቫይረሱ ሲሞቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 16,353 ሆኖ ተመዝግባል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.7 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ390,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ105,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት 345 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 69 ደርሷል።

የታማሚዎች ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ33 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከአሜሪካ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።

ታማሚ 2 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊት #ከዱባይ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።

ታማሚ 3 - የ29 ዓመት ኢትዮጵያዊ #ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 4 - የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት እንዳለውና እንደሌለው እየተጣራ ነው።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- በዩናይትድ ኪንግደም በ24 ሰዓት 980 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል። በተጨማሪ 5,195 ሰዎችም በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። በአጠቃላይ 70, 272 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 8,958 ሰዎች ሞተዋል።

- በጣልያን በ24 ሰዓት 570 ሰዎች ሞተዋል። ቁጥሩ ትላንት ከተመዘገበው መቀነስ አሳይቷል። 3,951 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሌላ በኩል ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 30,000 ደርሷል።

- በሩሲያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው። በአንድ ቀን ብቻ 1,786 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በሳዑዲ አረቢያ በ24 ሰዓት ውስጥ 364 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። ቁጥሩ እስካሁን በሀገሪቱ በአንድ ቀን ከተመዘገቡት ከፍተኛው ነው። በተጨማሪ 3 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 47 ደርሷል።

- በስፔን በ24 ሰዓት 605 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞተዋል። በ2 ሳምንት ውስጥም የተመዘገበ ዝቅተኛ የሟቾች ቁጥር እንደሆነ ተገልጿል።

- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር 13,000 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 987 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.6 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ370,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ101,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት በቤልጂየም 283 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 2,523 ደርሷል።

- ዛሬ FNOMCeO ይፋ ባደረገው መረጃ ጣልያን ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ዶክተሮች 100 መድረሳቸውን አሳውቋል።

- በኔዘርላንድ የ107 ዓመት አዛውንት ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸው ተሰምቷል።

- በኢራን የሟቾች ቁጥር 4,110 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት 117 ሰዎች ሞተዋል።

- በስፔን ተጨማሪ 683 ሰዎች በአንድ ቀን መሞታቸውን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 15,238 ደርሷል።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዛሬም በፅኑ ህሙማን ክፍል ይገኛሉ፤ የጤናቸው ሁኔታ ከባለፉት ቀናት በተሻለ መልኩ መሻሻል አሳይቷል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.5 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ342,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ90,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በጎንደር 4 ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደረገ!

በመጋቢት ወር ከውጭ ቆይተው ወደ ጎንደር የገቡ ሰዎች ለይቶ ማቆያ ገብተው ምርመራ ይደረግላቸው ተብሎ የጎንደር ከተማ ኮማንድ ፖስት በውሰነው መሰረት በዛሬው ዕለት ሶስት ሰዎች የበሽታው ምልክት ባይታይባቸውም ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርጓል።

ሶስቱ ሰዎች የጉዞ ታሪካቸው ከውጭ የቆዩ ሲሆን አንደኛዋ ከባህሬን የመጣች ምዕራብ በለሳ፣ ሁለተኛዋ ከጣሊያን የመጣች ጎንደር ዙሪያ ወረደ ፣ ሶስተኛዋ አረብ ሀገር የመጣች ጎንደር ዙሪያ ወረዳ አራተኛው ግን የዩኒቨርስቲው የጥበቃ ሰራተኛ ሲሆን ሄዶ ልጆቹን እጅ ሰላምታ በማድረጉ ወዲያውኑን ለይቶ መቆያ እንዲገባ ተደርጓል።

በተጨማሪ ሌሎች የውጭ ሀገራት 'የጉዞ ታሪክ ያላቸውን' በሁሉም ወረዳዎች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጤና መመሪያ አሳውቋል።

ምንጭ፦ የጎንደር ከተማ አስተዳደር

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

የ24 ሠዓት የጣልያን ሪፖርት ፦

- በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 4,585
- የሞቱ ሰዎች ቁጥር 766
- ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,480

በአጠቃላይ በጣልያን በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች 119,827 ደርሰዋል። 14,681 ሰዎች ሞተዋል፤ 19,758 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 6
• በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 30
• ፅኑ ህሙማን - 2
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 3
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 35

ማስታወሻ፦ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ 2 ታማሚዎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

የተጠቂዎች ቁጥር ከ 1 ሚሊዮን በላይ ሆነ!

በአለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን (1,000,000) በላይ ሆኗል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በኬንያ ተጨማሪ 8 ሰዎች አገገሙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በኬንያ 8 ሰዎች ከኮቪድ-19 ሲያገግሙ 8 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፤ አራቱ (4) ከሞንባሳ የተቀሩት ከናይሮቢ ናቸው። በአሁን ሰዓት በኬንያ በአጠቃላይ 114 ያገገሙ ሲሆን 363 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በኢትዮጵያ 9 ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ አገገሙ!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፣ እስከ አሁን በአገሪቱ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 ደርሷል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው የ943 ላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

የሰሜን ኮርያው መሪ "በሒወት አለ "ስትል ደቡብ ኮርያ ማረጋገጫ ሰጥታለች።

የደቡብ ኮርያ ፕሬዝዳንት የደህንነት አማካሪ የሆኑት ሙንግ ቺንግ- ኢን የሰሜን ኮርያው ፕሬዝዳንት የ36 አመቱ ኪም ጆንግ -ኡን በሀገሩ በምትገኘው በባህር ዳርቻዋ ከተማ ዋንሳን ይገኛል " በሒወት አለ ደህና ነውም " በማለት ሲኤን ኤን ጨምሮ የተለየያ ሚድያዎች ኪም ጆንግ -ኡን በጠና ታሟል ወይም ሞቷል የሚለውን ዜና አስተባብለዋል።
ሙንዲንግ የተባለ በሰሜን ኮርያ የሚታተም የመንግስት ጋዜጣ ትናንት ሚያዝያ 18,2012 ይዞ በወጣው እትም ሞንሶን ከተማ ለቱሪስቶች ተብሎ እየተገነባ ላለው የባቡር መንገድ ፣ ሆቴሎች እና የገበያ ማእከሎች ለሚሰሩ የግንባታ ሰራተኞች ኪም ጆንግ -ኡን" በርቱ ! በግንበሰታው ላይ በንቃት የተሳተፋቹ ጋዜጠኞችን ከልብ ላመሰግን እወዳለው " ማለታቸውን አስነብቧል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

#COVID19

በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ሚሊየን በላይ ሆኗል፤ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 207 ሺህ 254 የደረሰ ሲሆን፤ 882 ሺህ 552 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

#KENYA

በኬንያ ባልፉት 24 ሰዓት 707 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 303 ደርሷል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 8 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት 447 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው በስምንቱ ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።  

ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 82 መድረሱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።    

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው ተጨማሪ 247 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 74 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም። በተጨማሪ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የለውም።

ታማሚ 2 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊትና የአዲስ አበባ ነዋሪ ስትሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት አላት።

ታማሚ 3 - የ72 ዓመት ኢትዮጵያዊና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ በተጨማሪ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የላቸውም።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,577
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 345
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 4
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 54
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 6
• አጠቃላይ ያገገሙ - 10
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 69

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

ዛሬ በወጣ መረጃ
ኮሮና covid-19 102 ቀኑን ይዞል
በ 102 ቀን ውስጥም 102.000
ሰዎች ሂይወታቸው አልፏል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ዘጠኝ (9) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!

ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሁሉም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ አላቸው።

ከግለሰቦቹ መካከል ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የህንድ ዜግነት ያላት ናት።

አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ሁለቱ የቱርክ፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተዋል።

የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም የ40 ዓመቱ ኤርትራዊ ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው።

በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ መውጣቱንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

ባለፉት 24 ሰዓት በዩጋንዳ ሁለት መቶ አስራ አራት (214) የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዙ ተረጋግጧል። በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የታዙ ሰዎችም 53 ደርሷል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

D.rLia Tadesse

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል አሁን በሀገሪቱ በመንግስትም በግልም ሆስፒታሎች ያሉትን ጨምሮ ያሉ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪዎች ቁጥር 435 ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ተጨማሪ የፅኑ ህሙማን መርጃና ልዩ የመተንፈሻ ህክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት በሂደት ላይ መሆኗን ዶ/ር ሊያ ገልፀዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ፦

• በጅቡቲ 162 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 9 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኬንያ 362 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኢትዮጵያ 74 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

የታማሚዎች ሁኔታ ፦

- በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ውስጥ አምስቱ (5) ከአዲስ አበባ ሲሆን አንድ (1) ከድሬዳዋ ነው።

- በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

- በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን የመጀመሪያው የ35 ዓመት ወንድ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጣ ነው። ሁለተኛው የ30 ዓመት ወንድ በተመሳሳይ ከዱባይ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም የመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ሁለቱም አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የገቡ ናቸው።

- ሶስተኛው የ28 ዓመት ወንድ፤ አራተኛውም የ56 ዓመት ወንድ፣ አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው። እነዚህ ሰዎች ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ ነው።

- ስድስተኛዋ ሰው የ33 ዓመት ሴት ስትሆን በድሬዳዋ ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት ነበራት።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…

ዜና-መፅሄት / Zena metsihet

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ።

- 49 የእፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ቫይረሱ ሀገራቸው እንደገባ ሪፖርት አድርገዋል።

- 6,470 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

- 241 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

- 504 ሰዎች አገግመዋል።

@ZENA_METHET

@ZENA_METHET

Читать полностью…
Подписаться на канал