"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
"…ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ። ሉቃ 21፥20 “…የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ…” ዮሐ 16፥12 “…እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።” ማር 13፥23
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…የሟች የሹፌሩንና ሌላዋን ሴት ሠራተኛ የምታወረቋቸው አገናኙኝ። እንዲሁ እዘግብላቸዋለሁ። አሁን አርበኛ ዘመነ ካሤ በስሙ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ባለ ትዳርና የሁለት ልጆች አባት የሆነውን፣ ባለ ማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ በግፍ ገድለውታል። እማሆይ ደብሬ አስረስ የጌቴ እናት ሲሆኑ። ጌቴ ከውድ ባለቤቱ ህፃን ሙሴ ጌቴ ዕድሜ 5፣ ህፃን ኑሃሚን ጌቴ ዕድሜ 3 እና አሁን በቅርብ የሚወለድ ልጅም በባለቤቱ ማኅጸን ተቀምጦ ወደዚህ ዓለም ለመቀላቀል ወራትን እየተጠባበቀ ነበር ተብሏል። ባለቤቱ ነፍሰ ጡር ናት።
• እኔ ጎጃሜ አይደለሁም። የጎጃም ሕዝብ ግን ወገኔ ነው። ብዙ መንፈሳዊ አባቶች በጎጃም አሉኝ። ባህርዳር ሽምብጥ ሚካኤልን እንደ የኔቢጤ ለምኜ ነው ያሠራሁት። ባህርዳር አዲሱ ሚካኤል በአገልግሎት የተባረኩበት ነው። ዲማ ጊዮርጊስ፣ ደብረ ወርቅ ማርያም፣ መርጡለ ማርያም፣ ደብረ ማርያም ወዘረፈ የበረከት ሥፍራዎቼ ናቸው። ደግ ሕዝብ፣ እንግዳ ተቀባይ ሕዝብ እንዲህ እንደ ገና ዳቦ ከላይና ከታች እሳት እየነደደበት ሲጨፈጨፍ ዝም ብዬ አላይም። ጎጃም በጠላት ልጆች እጅ ውስጥ ወድቋል። ጎጃም የገባበትን መከራ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው። ጨካኝ አረመኔዎች ትግሉን ጠልፈውታል። ትሰድበኛለህ፣ ታዋርደኛለህ፣ ፎቶዬን ዘቅዝቀህ ስትረግመኝ ትውል ታድራታለህ እንጂ የጎጃሙን ጎጠኛ አልፋታውም።
"…ተስፋዬ ወልደ ሥላዴ በአባቱ ትግሬና በእናቱ አገው ነው አሉኝ። ጎጃም ዐማራን መጨፍጨፍ አይዘግባትም። በቃሉ አላምረውም እንዲሁ ጎጃሜ ነው አሉ። እሱም የወያኔን ሙታንቲና ካልሲ ሲያጥብ ይውላታል እንጂ የጎጃም ዐማራን ፍዳና መከራ አይዘግብም። የኢትዮ ፎረሙም አበበ ባዩ ጎጃሜ ነው ወያኔ አለቀሰች፣ ትግሬ ራበው፣ ትግሬ ጠማው ነው እንጂ የጎጃም ዐማራን ሞት አይዘግቡም። ሌሎችም የጎጃም ሚዲያዎች እና አክቲቪስቶች ቤተሰባቸው በፋኖ እየታገተ፣ እየተጨፈጨፈም ትንፍሽ አይሉም። የገዛ ወገናቸውን እየጨፈጨፉ የደፈራቸውን፣ የገደላቸውን፣ የወጋቸውን መከላከያ ተብዬ ግን እንዳይደክመው አህያና በቅሎ አቅርበው፣ ነጭ ማኛ እንጀራ በዓይነት ወጥ አቅርበው፣ ጠላ አረቄ፣ ከፍ ሲልም የጎጃም ምስኪን የገበሬ ልጅ ልጃገረድ እያቀረቡ ጠላትን ይንከባከባሉ። ከዚያም አጥበው፣ ልብስ ቀይረው፣ መታወቂያ አውጥተው፣ ዳያስጶራው ዐማራ ደም ተፍቶ የሚልከውን ዶላር ለትራንስፖርት ብለው ሰጥተው ይሸኛሉ።
"…የዐፋጎ መሪዎች ዐማራ አይመስሉኝ። ጊዜ ያውጣው እንጂ አብዛኞቹ ዐማራ አይመስሉኝም። የጨፈጨፋቸውን፣ የዘረፋቸውን የትግሬ ኮሎኔል ተንከባክበው እየለቀቁ። የትግሬ የጦር መኮንኖችን ፈትተው ዐማራን ይወጉ ዘንድ ወደ ትግራይ እየሸኙ፣ በምትኩ ዐማራን የሚጨፈጭፉት ነገርን ሳይ የአፋጎ መሪዎች ዐማራ አይመስሉኝም። ማርያምን ውስጤ እየተጠራጠረ ነው። አርበኛ ዘመነ ካሤን እንኳ ትዘውት ዘጭ አሉ። ታላቁን ዐማራ የሰበከውን ልጅ በብላክ ሜል ቢሉ በሌላ ጉዳይ ታዛዣቸው አድርገው፣ በቁም እስር አግብተው ጎጠኛ አድርገው የተገነባ ስሙን፣ የፖለቲካ ካፒታሉን አወደሙበት። እያከሰሩት ነው። በጎጃም ለሚመጣው ልማት፣ ድልና ነፃነት አርበኛ ዘመነ ካሤ የአምበሳውን ድርሻ እንደሚወስደው ሁሉ በጎጃም ለሚደርሰው ውድመት፣ ጥፋትና ውርደትም ለተጠያቂነት የአምበሳውን ሚና ይወስዳል። ያለበትን አጣብቂኝ ብረዳም ሌላ መንገድ ግን የለም።
"…ሟች ጌቴ ሥመ ጥምቀቱ ገብረ ማርያም ነው። በጸሎታችሁ አስቡት። ያው እንደፈረደብኝ ነገ ወይም ተነገ ወዲያ በቲክቶክና በዘመድ ቴቪ ብቅ ብዬ በሕጻናቱ የወደፊት ሕይወት ጉዳይ እንነጋገራለን። አንዴ ፈርዶብኛል እናም ሕጻናቱን የሚያሳድጉ ቅን ደጋግ ኢትዮጵያውያንን ወደ መለመን እገባለሁ። በጎንደር ሁለት ቤተሰብ፣ በጎጃም ባለፈው አንዲት መምህርና ልጇን የተረከቡኝ ቅን ኢትዮጵያውያን ናቸው። አሁንም እነዚህን ውብ ልጆች ተስፋቸውን የሚያለመልም ተግባር እንፈጽማለን። እናቱ እመሆይንም አዝነው እንዳይሞቱ እናጽናናቸዋለን። ማርያምን ይሄን እኔው ራሴ አደርገዋለሁ። ዘመነ ካሤም እኚህን እማሆይ ሲያይ እናቱን አስታውሶ በኀዘን የሚዋጥም ነው የሚመስለኝ።
• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
አንዴ ጠብቁኝ…!
"…ምሽት ቢሆንም፣ በምሽት ዘግናኝ መርዶ መንገር ባህል፣ ወግ እና ደንብ ባይሆንም ነገር ግን እያሰባችሁ፣ እያንሰላሰላችሁ ታስሩ ዘንድ በጎጃም ሰፍሮ፣ የጎጃም ዐማራንና የጎጃም ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆችን ከምደረ ገጽ እያጸዳ ስለሚገኘው የእነ አስረስ መዓረይ፣ የእነ ማርሸት፣ የእነ አርበኛ ዘመነ ካሤ ጦር ስለረሸናቸው ምስኪኖች ላረዳችሁ ነውና ጥቂት ጠብቁኝ።
• አላችሁ አይደል…?
ፍጥጥ ያለ ውሸት፣ ግልጽ ዘረፋ…!
"…ምን ዓይነት ዘመን ላይ ነው የደረስነው? እንዲየው ምን ጉድ ነው የመጣብን? በፊት በፊት እግር ጀሶ ተጠቅልሎ፣ ጤነኛው ደኅናው ሰው ኩላሊቴን ታመምኩ ብሎ ነበር ዋሽቶ የሚለምነው። ያ ሲነቃ አሁን ደግሞ የድፍረታቸው ጥግ ወደ ቤተ ክርስቲያን ዞሩ። ተመልከቱ ቲክቶከሩ እኮ በአንገቱ ላይ ማዕተብ እንኳን እኮ አላሠረም። በቃ ተቆጣጣሪ የሌለው ቤት ተገኘ ሁሉም ተነሥቶ በስሟ መዝረፍ?
"…የዚህን ቀጣፊ ዋሾ ደፋር ቲክቶከርና የቦሌ መድኃኔዓለም ዲያቆን ተብዬ ዘማሪ ስልክ ቁጥርና ስምም ላኩልኝ። የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ቡፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስም የእዚህችን በአንዲት እህት ተሠርታ በተጠናቀቀች ቤተ ክርስቲያን ስም ለምነው የዘረፉ ደፋሮች የባንክ ቡካቸውን ያሳግዱ። ኧረ ድፍረት በዛ። እኔ ራሴ የማውቀውን ባለችበት በረንዳዋ በመፍረሱ ምክንያት ሙሉ እድሳት እንደ አዲስ ተደርጎላት የተሠራችን ቤተ ክርስቲያን ሥራው የተጀመረ ጊዜ ሄደው የቀረጹት እያሳዩ ሕዝብን መዝረፍ ምን ይሉታል? ምን ጉድ ነው? ደግሞ እኮ ፊቱን እንዴት እንደሚያቅለሰልስ? ባይበላ ቢቀርስ? ኃጢአት እኮ ነው። ኧረ ቲክቶከሮች ተጠንቀቁ። ተረጋጉ። መኪና ልትገዙ፣ ሱቅ ልትከፍቱ ትችላላችሁ። ጫማ ልትቀይሩ፣ ከርሳችሁን ልትሞሉ ትችላላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ፊት መቅረብ እኮ አለ። ድፈረትም ልክ ይኑረው።
• ዝርዝሩን ነገ ከምስጋና በኋላ እለጥፍላችኋለሁ።
• አላችሁ ወይ…?
• ፍልሚያው በድል ተጠናቅቋል። ወደ አየር መመለሻ ምስጢራዊ ቁልፉንም በሰላም ተረክበናል። አላችሁ ወይ…?
• ወይ ንቅን…!
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር…
"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:10 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• ZemedTv 👉 https://zemedtv.com/live.html
• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1zqKVjPqjMYKB
• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6wflhc--zemede-july-20-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a
• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
11977 H 27500
• ላይ ይከታተሉን።
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
• ተናግሮ አናጋሪ አያሳጣኝ…! …አሜን 🙏
"…የጎጃም አክቲቪስቶች በዐማራ ፋኖ በጎጃም ዋና አክቲቪስት ጠበቃ አስረስ መዓረይ ተመርተው እንዳበደ ውሻ እያክለፈለፋቸው ነው። ከበዛ ስግብግብነት፣ ራስ ወዳድነት፣ ሁሉን ለእኔ፣ ከእኛ ውጪ ወደ ውጪ ባይነታቸው ተነሣ በትዕቢት ተነፍተው ከወንድሞቻቸው፣ ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ኅብረት ተለይተው ብቻቸውን ሄጵ ሄጵ ብለው እምቡር እምቡር ብለው ከፈነጩ በኋላ አሁን ላይ በራሱ በጎጃም ሕዝብ ድጋፍና ተጠያቂነት ሲያመጣባቸው የሚይዙትን የሚጨብጡትን አጥተው በማይዘጋው፣ ቴሌ 24/7 በሚለቅላቸው ኢንተርኔት ተጠቅመው በባዶ ሜዳ ሲያቅራሩ ውለው ሲያቅራሩ አድረው ከአንጎበራቸው ሲነቁ በተፈጠረው ነገር አጎንብሰው፣ ድንጋይ ተሸክመው ይቅርታ በመጠየቅ ወደ አፋብኃ እንደመመለስ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል የተለመደውን ቀረርቶአቸውን ማስነካቱን ተያይዘውታል። ይሄ ደግሞ ምንም አይጠቅማቸውም።
"…ሥጋ ቆራጭ ይኸነው የሸበሉ ካነሣው አይቀር እውነቱን መነጋገር ግድ ይለናል። በተለይ በነገው እሑድ ምሽት ላይ በጎጃም የዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪ ማነው? በሚል ርእስ አዲስ አዋራ የሚያስነሣ መራር ሃቅ ይዤ ከቻሳ እላለሁ። በጎጃም የዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪዎች ሦስት ናቸው። እነሱም ፦
፩፥
፪፥
፫፥ በማለት በዝርዝር እመጣበታለሁ። ትፈነዳ እንደሁ አያታለሁ። በጎጃም በስም አንድ አደረጃጀት ሦስት መሪ ነው ያለው። በጎንደር ሁለት አደረጃጀት ሁለት መሪ ነው ያለው። በወሎ ሁለት አደረጃጀት ሁለት መሪ ነው ያለው። በሸዋ ሁለት አደረጃጀት ሁለት መሪ ነው ያለው። በጎጃም ግን አንድ አደረጃጀት የዐማራ ፋኖ በጎጃም ነገር ግን ሦስት መሪ ነው ያለው። በዝርዝር ነገ ምሽት በነጭነጯን ከዘመዴ ጋር አስረዳለሁ።
"…ሕወሓት በቤኒሻንጉል በኩል ወደ ጎጃም ለመግባት ዝግጅቷን ጨርሳለች። ቦታ መረጣም ጨርሳለች። የትግሬ አክቲቪስቶች በሙሉ የዐማራ ፋኖ በጎጃም አክቲቪስት ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በአስረስ መዓረይ ፍቅር ወድቀዋል፣ በተለይ ፓስተሪት ማርያማዊትማ በአርበኛ ዘመነ ካሴ ግርማ ሞገስ፣ በድምፁ ተማርካ ራሷን መቆጣጠር አቅቷት ሆስፒታል ትግባ ዐላውቅኩም እንጂ ክፉኛ ተጎድታለች። ስታሊን ጎጃም ጎጃም ብሎ ሊሞት ነው። ነገ በሰፊው እመጣበታለሁ።
"…ከምር አርበኛ ዘመነ ካሤ ግን ያሳዝነኛል። ማርያምን እውነቴን ነው። ይኸው ሐምሌም ተጋመሰ። ነሐሴም እየመጣ ነው። ዕድሜ ለእነ አስረስ መዓረይ አምና በእስክንድር ሰበብ፣ ዘንድሮ በአፋብኃ ምክንያት ኮተት ደርድረው ዘንድሮም ክረምቱን በወሬ፣ በዲስኩር፣ በሽለላ፣ በቀረርቶ፣ በፉከራ፣ በሰበር የድል ዜና፣ በስቦ ማስከዳት ዲስኩር የዐማራን መከራ ሊያራዝሙበት ነው። ዘመነ ካሤ በዐማራ ሁሉ ልብ የነገሠ ታጋይ ነበር። አንደበተ ርቱዕ። ግን ምን ያደርጋል…? ፀጋውን ጋረዱት፣ ሸፈኑበት፣ ቀበሩት፣ ውጠው አስቀሩት። አሁን በኤአይ እንደ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ አንበሳ ላይ ሥለህ ብትለጥፈው፣ ንስር ትከሻ ላይ አስቀምጠህ በታበረው ምን ይጠቅመዋል? ባላውቀው ይሻለኝ ነበር። አዛኜን ባላውቀወ ይሻለኝ ነበር።
• ከምር ተናግሮ አናጋሪ አያሳጣን። ደኅና እደሩልኝ። የነገ ሰው ይበለን።
"…ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕ 1፥ 7-8 "…እነርሱ በችግር በክፋት በጭንቀት ተዋረዱ እያነሱም ሄዱ” መዝ 107፥39
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…እስከአሁን አልተፈታም…!
"…የአፋጎ ቀጠናዊ ትስስር የአገው ሸንጎው ማሽንክ አቶ የቆየ ሞላ እስከአሁን እዚያው ጎጃም እንደታሰረ ነው። በአጭሩ አልተፈታም።
"…የቆየ ሞላ እስከአሁን ከአራት በላይ ምስኪን የገበሬ ሴት ልጃገረድ ልጆን ደፍሮ ያስረገዘ እንደሆነ ቢነገርም፣ በጥፋቱ በታሠረም ጊዜ የመከላከያ ስላይ ተብላ የታሰረችን እስረኛ ደፍሮ ያስረገዘ ቢሆንም (እሷ እስረኛዋ እንኳ ፈቅዳ ነው ተብሏል) ምንም እርምጃ አልተወሰደበትም ነበር።
"…አሁን ግን ይህ የወንድ ባልታዛር የአፋጎ የብርጌድ አዛዥን ሚስት አስገድዶ በመድፈሩ በእነ አስረስ መዓረይ ውትወታ ሞቱ ቀርቶለት በከዘራ እየተዠለጠ ወህኒ ቤት ከገባ ወራት ተቆጥረዋል። እናም አስረስ መዓረይ በቀደም የለቀወው ፎቶ እኔ መታሰሩን በተናገርኩ ጊዜ እኔን ለማሳጣት ብሎ የለጠፈው ነው። አልተፈታም።
"…ይሄን ባልታዛር ሸንጎ፣ በጎጃም ዐማራ ልጃገረድ ሴቶች ላይ እንዲሸና፣ እንዲጫወትባቸው የፈቀዱለት የአፋጎ አመራሮች ናቸው። ዐማራ ጠል የወያኔ ውላጆች ናቸው። ለዚህ ነው በጎጃም የዐማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች መምህራንን፣ ተማሪዎችን፣ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንትን የሚጨፈጭፉት፣ የሚያርዱት።
"…እኔ ፈጥሬ አላወራም። ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ይሄን ጎጃም የመሸገ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ የሸንጎ ርዝራዥ ቅባቴ የወያኔ የሽንት ጨርቅ ሁላ አምላኬን ይዤ ብቻዬን አሰጣዋለሁ። ቅቡልነታችንን ያሳጣናል ለሕዝብ እንዳይቀርብ የተባለ ነውራቸውን ሁሉ አንድ በአንድ አፈርጠዋለሁ። አስረስ መዓረይ መርጡለ ማርያም ላይ ያረዳቸውን አብሮአደጎቹን ከነስም ዝርዝራቸው እለጥፈዋለሁ። ዘመዴ ናቸው የሚላቸው ብፁዕ አቡነ አብርሃምም ሲያስጥሉህ አያለሁ።
• ለማንኛውም ደፋሪው የአፋጎ ባልተዛር አልተፈታም።
መልካም…
"…አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው። በሆዳችሁ አምቃችሁ በጨጓራ በሽታ ከምትጠቁ በጨዋ ደንብ በመተንፈስ ጤንነትዎን ይንከባከቡ። እነ ስኳር፣ እነ ደም ግፊትም ነገር በሆድ አምቆ ከመያዝ እንደሚመጡ ፓስተሪት ዮኒ ማኛ ዶር ሀቢባ ቤት ተናግሯል ሲባል ሰምቻለሁ። ለማንኛውም ርእሰ አንቀጹን መነሻ ዋቢ በማድረግ እናንተ ደግሞ የራሳችሁን ሓሳብ በራሳችሁ መንገድ ሂዱበት።
"…አደራ አደራ የተወደድክ ወንድማችን ርእሰ አንቀጹን ወደ ሃይማኖት ወስደህ ቤቱን የቁርዓንና የመጽሐፍ ቅዱስ መጨቃጨቂያ እንዳታደርገው። ሌላው ደግሞ በርእሰ አንቀጹ ድንገት 😡 ብው ያላችሁ ሰዎች ተሳስታችሁ በፔጄ ላይ ፀያፍ ስድብ፣ ብልግና ጽፋችሁ የተመልካች ዓይን እንዳታቆሽሹ ተጠንቁልኝ። በጨዋ ደንብ ተቃውሞ ማቅረብ ግን በቤቴ የተፈቀደ ነው። በተለይ ተናግሮ አናጋሪ ጨዋ ኮማች ቢኖር ደስ ይለኛል።
• 1…2…3…ጀምሩ…!
"ርእሰ አንቀጽ"
"…የዛሬውን የምስጋና ቃል የጀመርነው “…ዓይኖችህም ከሚያዩት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ።” …ዘዳ 28፥34 “…በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አይሰማችሁም።” 1ኛ ሳሙ 8፥18 “…ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።” ምሳ 29፥2 “…እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ” መዝ 67፥1 በሚሉ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ልጽፈው ከተዘጋጀሁበት ርእሰ አንቀጽ ጋር በብዙ ስለሚገናኙልኝ ነው አስቀድሜ በምስጋናው ሰዓት ያመጣሁአቸው። 1ሺ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ ባመሰገነበት የምስጋና መልእክት ላይ ወደ 7 ፍሬ ሰዎችም ተበሳጭተው አይቻቸዋለሁ።
"…ወደ ርእሰ አንቀጻችን እንመለስ። “…ዓይኖችህም ከሚያዩት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ።” …ዘዳ 28፥34። ይሄን ጥቅስ ባነበብኩ ቁጥር የእኔን ዘመን፣ በተለይ የዚህን ሰባት ዓመታት ጉዞ፣ በተለይም ደግሞ አሁን በአቢይ አሕመድ አረመኔያዊ የጭካኔ የመጨረሻው የአገዛዝ ዘመኑ ላይ በኢትዮጵያ እየሆነ ያለውን ሳይ፣ ስመለከት ጭው ይልብኛል፣ ጭልም ይልብኛል። ከማየው ከምሰማው የተነሣ ድሮም ድሮ ነኝ አሁንማ የለየለት እንደ እብድ ሊያደርገኝ ይቃጣኛል። ከመላዋ ኢትዮጵያ፣ ከየቤቱ በውስጥ መስመር የሚደርሰኝ ሰቆቃና መከራ አንዳንዱ ጩሄ እንኳ አይወጣልኝም፣ ከምር የልብ ምቴ ሁላ እየተቀየረ ነው። ትንፋሽ እጥር እያለኝም ነው። ማዲያት ፊቴን እስኪወርሰው ድረስ ቁሽቴ አንጀቴ እያረረ ነው። ለብሶ፣ አጊጦ፣ ቅባት ተቅብቶ ከቤቱ ሲወጣ ሰው የሚመስለው ሁሉ፣ ሥራ አለው ተብሎ ሀገር ምድሩ፣ ወዳጅ ዘመድ የሚያውቀው ሁሉ የገባበትን አጣብቂኝ ብታዩ፣ ብትሰሙ ትቀውሳላችሁ።
"…የመንግሥት ሠራተኞች ቁርስና ምሣ መብላት አቁመው ራት ዳቦ መብላት የጀመሩ የትየለሌ እንዳሉ ስትሰሙ ከርማችኋል። በምሳ ሰዓት ወደ ቤተ ክርስቲያን እና ወደ መስጊድ ገብተው ጸሎት ጸልየው ወደ ሥራ ገበታቸው የሚመለሱ ዜጎች እንዳሉም ሰምታችኋል። ማደሪያ አጥተው መሥሪያቤት ውስጥ ቢሮ ውስጥ የሚያድሩ እንዳሉም ሰምታችኋል። የትራንስፖርት ስላጡ ብቻ ጠዋት ሌሊት ተነሥተው፣ ማታ እኩለ ሌሊት በእግራቸው ተጉዘው ቤታቸው የሚገቡ እንዳሉም ሰምታችኋል። ሰፈር ቀይረው ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደው የሚለምኑም እንዳሉ ሰምታችኋል። የመንግሥት ሠራተኞች ሆነው የሆቴል ቤት ትራፊ ፌስታል ይዘው በየሆቴል ቤቱ በራፍ ላይ ቆመው የሚለምኑ እንዳሉ በቀደም ዕለት ነው በፓርላማ የሰማነው። ከዚህ የሚከፋው ደግሞ ምሽት ቡናቤትና መንገድ ላይ ቆመው ሴተኛ አዳሪነት ሠርተው እንቅልፍ ሳይተኙ ቀን ደግሞ ወደ ፋብሪካ ሥራቸው የሚገቡ ሠራተኞች እንዳሉም ከሰማን ቆየን። አሁን ደግሞ ከሁሉ የባሰ የከፋው ደግሞ በወረዳና በክፍለ ከተሞች ላይ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚሠሩ ሴት እህቶቻችንና እናቶቻችን በምሳ ሰዓት በየሆቴሉ " የአጭር ጊዜ የወሲብ አገልግሎት ወደ መሥጠት" መሠማራታቸው ነው የሚሰማው። ሴት ልጆቻቸውን ወጣ ብላችሁ ሠርታችሁ አምጡ ብለው አለባብሰው ወንድ ፍለጋ የሚያሠማራ ቤተሰብ፣ ሚስቱን ለዝሙት አስፓልት ላይ ሸኝቶ ከሩቅ የሚጠባበቃት ባል እንዳለም ስትሰሙ “…ዓይኖችህም ከሚያዩት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ።” …ዘዳ 28፥34። የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ወደ ጆሮአችሁ ያቃጭላል።
"…ማርያምን በቃ ምንም ደስ አይልም። ምንም አልኳችሁ። በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀ አንድ ልጅ ፈግቶ ሥራ ያገኛል። ደሞዙ 9 ሺ ብር ነው። ተቆራርጦ ስንት እንደሚደርሰው ገና አላወቀም። እናም ቤት ለመከራየት ኳተነ፣ እግሩም ቀጠነ፣ ከ12 ሺ ብር በታች ወፍ የለም። 8ሺም አገኘሁ አለ። እናም ሰዎች ጋር ዘመድ ጋር ማለት ነው ተጠጋ። ዘመዶቹም ይህቺን ክረምት እናስተናግድሃለን መስከረም ላይ ግን ውጣልን እንዳሉት ሰማሁ። በጠባብ ክፍል፣ ከሁለት ልጆቻችን ጋር አንተን ደርበን መላወስ አልቻልንም ነው ያሉት። በየቤቱ እሮሮ ነው። ድሮ የተከበረ ሙያ የነበረው ህክምና፣ ዶክተርነት አሁን የለማኝ፣ የየኔቢጤ ማዕረግ ነው ያለው። ወላጆች "ልጄ ቲክቶከር ሆኖ ይጦረኛል ስል ዶክተር ሆኖ ቅስሜን ሰበረው" እያሉ ሙድ የሚይዙበት ሙያ ሆኖ ነው ያረፈው። ነጋዴ በሉት፣ በፊት መካከለኛ ገቢ ነበራቸው የሚባሉት በሙሉ አሁን ሾቀዋል። እነ ሽመልስ አብዲሳ ኢሪሊቫንት እናደርጋታለን ያሏትን አዲስ አበባንም፣ ሀገሪቱንም አፈር ከደቼ ነው ያበሉት።
"…ዛሬ ደግሞ አንድ ዐዋጅ በአቢይ ፓርላማ ጸድቆ ትርምስ ያለ ነገር ከወዲሁ ሲፈጠር እያየን ነው። የሕዝብ ሳይሆን የመንግሥት ተወካዮች ምክር ቤቱ የገቢ ግብር ማሻሻያ ዐዋጁን ከወትሮው በተለየ መልኩ በ5 ተቃውሞ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ነው ያፀደቀው። ዛሬ በጸደቀው ዐዋጅ በቅጥር የሚሠራ ሠራተኛ በእያንዳንዱ ነገር በምግብ ዋጋ፣ በሚገዛው ዕቃ ቫት 15% ይጨምራል። ይሄ በ35% ላይ ሲደመር 50% ይመጣል። 7% የጡረታ አለ እሱ ሲደመር 57% ከደመወዙ ላይ ይሄዳል፣ በቀረችው 43% ልጆች ያስተምራል፣ ምግብ ይበላል፣ ልብስ ይገዛል፣ ቤት ይከራያል ምንድነው የሚያደርገው ? ብለው ብዙዎች ዛሬ ሲጯጯሁ እያየሁ ነበር ያረፈድኩት። ጩኸት ምንም አያመጣም። ኬንያን አይተህ ወደ ኢትዮጵያ ስትመለስ ትደመማለህ። በ43 % ኑሮህን ትገፋላህ ወይስ ወንድ ሁነህ መብትህን ታስከበራለህ ብለው የሚጠይቁም እያየሁ ነው።
• የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ❌
• የመንግሥት ተወካዮች ምክርቤት ✅
"…የሌላ ሀገር የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አይደለም እነሱንም ራሳቸውን በኑሮ ድቅቅ የሚያደርግ ዐዋጅ ሊያፀድቁ ድጋፍም ሊሰጡት ይቅርና ትንሽ ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለው ያሰቡትን የትኛውንም ዐዋጅ እንኳ አያፀድቁም። የፈሪ ሕዝብ ተወካዮች የሆኑት ራሳቸው ፈሪና አብዛኞቹ ርቧቸው ከቸርችና ከየወረዳ ካድሬነት ተመርጠው ፓርላማ ገብተው የቀረበላቸውን በሙሉ ያለማቅማማት እጅ በማውጣት የሚያጸድቁት እንቅልፋሞቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮቹ የሆኑት የምክርቤት አባላት ግን መንግስት አፅድቁ ያላቸውን ሁሉ ሲያጸድቁ ይታያሉ። ዐዋጁ አባላቱ ሁላቸውንም የሚገድል፣ ጾታም የሚያስቀይር ዐዋጅ ቢሆን እንኳ አቢይ አሕመድ አፅድቁ ካላቸው ያለምንም ማቅማማት በጭብጨባ ያፀድቃሉ። አሁን ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈሪነቱን በሳይንሳዊ ግኝት በተጨባጭ ስላረጋገጡ ነጮቹም ባለፈው ጦር አዝምተው መሳፈጣቸው ሳይቆጫቸው አልቀረም። እንዲህ በገዛ ልጆቻቸው አፈር ከደቼ አብልተን ቀጥቅጠን መግዛት ስንችል በከንቱ ነው ደክመን የተዋረድነው ሳይሉም አይቀር። እንዲያ ሰለሆነ ነው እንጂ ይሄን የቀን ጅብ አገዛዝ ግልብጥብጥ አድርጎ ልክ የማስገቢያው ሰዓት አሁን ነበር። ከዚያ ፓርላማው ራበን፣ ጠማን ደሞዝ ይጨመርልን ብሎ ራሱም ያለቅሳል።
"…አቢይ የመጣው በእኛው የጸሎት ውጤት ነው የሚሉት ግን ራበን ሲሉ እየሰማኋቸው አይደለም። ጴንጤ በሙሉ በአብዛኛው አሸሼ ገዳዬ ላይ ነው። የባንክ ቡክ ይዘው እንዲመጡ ፓስተሮቻቸው እያዘዙ ፒፕሉ እንደ በግ እየተነዳ ሚራክል መኒን ሊያገኝ ሊያፍስ አሜን፣ ሃሌሉያ እያለ ሲግተለተል ነው የማየው። የጴንጤ አዳራሾች በወዛም፣ ወዛም፣ በደንደሳም ላታቸው ትልቅ፣ ሻኛቸው ወፍራም በሆኑ ወንዶችና ሴቶች ተጨናንቆ ነው የማየው። ጴንጤ የሚርበው አይመስልም። ሙስሊምም እንደዚያው። ምንም ዓይነት የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ የሉም። ኦሮሞማ ዝም ጭጭ ነው ያለው። ፓርላማው ውስጥ የተሰገሰጉት በአብዛኛው ኦሮሞ፣ እስላምና የደቡብ ጴንጤዎች ሕዝቡ…👇①✍✍✍
“…ዓይኖችህም ከሚያዩት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ።”ዘዳ 28፥34 “…በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አይሰማችሁም።” 1ኛ ሳሙ 8፥18 “…ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።” ምሳ 29፥2 “…እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ” መዝ 67፥1
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ጎዶኞቼ ሆይ… ስለ መዓረይ አንድ ለመኝታ የሚሆን ጦስኝ የመሰለ አጭር ጦማር ብለጥፍላችሁስ…?
Читать полностью…"…ምድር ደም ባመጣው በደል፥ ከተማም በግፍ ተሞልታለችና ሰንሰለት ሥራ። ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁ ቤቶቻቸውንም ይወርሳሉ፤ የኃያላንንም ትዕቢት አጠፋለሁ፥ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ። ጥፋት መጥቶአል፤ ሰላምም ይሻሉ እርሱም አይገኝም። ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል። ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። ሕዝ 7፥ 23-27
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
👆④ ✍✍✍ …አካላት ራሳቸው ከእኔ በባሰ መልኩ የዚያ እኔ ብቻዬን እየተሰደብኩ፣ እየተረገምኩ፣ እየተወገዝኩ፣ እየተዛተብኝ የተጋፈጥኩትን አጀንዳ ተደራጅተው ሺ ሆነው ሲጮሁ ሳይ አምላኬን አመሰግነዋለሁ። እኔ ያኔ እስክንድር ነጋ ሆይ ይሄን ትግል አታውቀውም፣ የትግሉም ባሕሪ አልገባህምና ወይ ገዳም ግባ፣ አልያም በቦሌም በባሌም ብለህ ከትግሉ ወጥተህ ወደ ልጅህና ሚስትህ ዘንድ ንካው ባልኩ ጊዜ፣ አንት ውሻ፣ አንት ሌባ፣ አንት ጋላ፣ አንት ኦሮሞ፣ አንት ቆቱ፣ አንት ወዲ አስገዶም፣ አንት መራታ እንዴት ብትጠግብ ነው? እንዴት ብትዳፈር ነው? አንት መሃይም እያሉ የስድብ መዓት ያወርዱብኝ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ላይ ተደራጅተው " አስክንድርን በሕይት ከሸዋ አውጥተን አሜሪካ የሚገባበትን መንገድ እንፈልግ" በማለት ኮሚቴ አቋቁመው ሲያለቅሱ እያየሁ እየተገረምኩ ነው። እኔማ እኮ አልናገር። ሀብታሙ አያሌው ምክሬን ቢሰማ ኖሮ እንዲህ ዛሬ ብቻውን አይብሰከሰክም ነበር።
"…የሆነው ሆኖ ብንደማመጥ መልካም ነው። እነ አሥረስ መዓረይ ደም እምባ የሚያለቅሱበትም ዘመን ሩቅ አይደለም። በጎጃም ለፈሰሰው ለንፁሐን የተዋሕዶ ልጆች ደምና ለጎጃም ዐማሮች ውድመት ከአራጁ ኦሮሙማ እኩል ተጠያቂ ናቸው። የቴሌግራምና የዩቲዩብ ሰበር ዜና፣ ከብአዴን ጋር በጥቅሴ ሁለት ሦስት ከተማ ገብቶ በመውጣት ሕዝቡን በማስጨፍጨፍ ፕሮፓጋንዳ በመሥራት ወደፊት ለማምጣት አገዛዙ እያደረገ ያለውም አካሄድ ይከሽፋል። ይከሽፋል አልኳችሁ። የዳላስ ቴክሳስ፣ የካናዳና የቨርጂንያ ጉዳይ ሕዝቡና ካሕናቱ ይበቁታል። የዘንድሮው ክረምት ካለፈ በኋላ፣ ብዙ ጥፋት ከጠፋ በኋላ፣ አፋጎዎች መስከረም ላይ ወደ አፋብኃ እንመለስ ብለው መጠየቃቸው አይቀርም ያነዜ አፋብኃ እሺ ብሎ ከተቀበላቸው የዐማራ የመከራ ዘመኑ ሊማሊሞ እንደሚሆን ይህን ዕወቁ፣ ተረዱም። አባ ሰረቀ አቢይን ፍለጋ አዲስ አበባ ቢመጣም አቢይ እርጉም ሂድ ጥፋ ብሎ ወፍ አላገኘውም። አባ ሳዊሮስ ግን ከሕወሓት በቀር መቀሌ ሄዶ ለሌሎቹ ምክርም፣ ማስጠንቀቂያም ሰጥተው እንደሚመለሱ መላካቸው ተሰምቷል። መከራችን ባያልቅም፣ ጦርነት ባይቀርልንም፣ አቋም ሳይቀይሩ ጸንቶ መቆም ግን አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው።
• ቴክሳስ ዳላስ ያላችሁ ካህናትና ምእመናን እንዴት እንዳኮራችሁኝ አትጠይቁኝ።
• ኢትዮ ቤተሰብ ቀሲስ ሳሙኤል፣ መምህር ነዋይ ካሳሁን፣ ቢንያም ሽታዬ እንዴት እንደኮራሁባችሁ አትጠይቁኝ። ሁላችሁንም እምጷ ብያለሁ።
ማስታወሻ…✍
"…ከአንድ ሰዓት በኋላ በጥሞና ታነቡ ዘንድ የቆለፍኩትን አስተያየት መስጫ ሰንዱቅ እከፍትላችኋለሁ። እናም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የእናንተን ሓሳብ ስንኮመኩም እናመሻለን። በንዴት እያነበባችሁ ለስድብ የተዘጋጃችሁ ግን እንደምንም ታግሳችሁ እለፉት። ፀያፍ ተሳዳቢን ከእነው ነው የምቀስፈው።
• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
• የተሰማችሁን አስተያየት መጻፍ ትችላላችሁ።
• አሻራ ሚዲያም እዚያው ጎጃም…
አሳዛኝ መረጃ‼️ በማለት… እዚያው ጎጃም…
"…በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት የመርዓዊ ደብረ ኃይል ቅዱስ ሚካኤል የ፬ቱ ጉባዔያት መምህር የሆኑት መምህር ስሙር ታደሰ በአገዛዙ ኃይሎች ተገደሉ። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትንና የሃይማኖት አባቶቻችንን የሚፀየፈው አገዛዝ አባቶቻችንን እየነጠቀን ነው። በማለት ፋኖ ባየ ደስታን ጠቅሶ መርዶ ለጥፏል።
• ሓሳብ ስጡ፣ ተወያዩ እስኪ…
• የምሽት የውድቅት ሌሊት መርዶ…!
"…አቶ ጌቴ አለባቸው ይባላል። ዕድሜው 36 ነው። ትውልዱ ጎጃም ደቡብ ሜጫ ሲሆን የሚኖረው ደግሞ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ነው። አቶ ጌቴ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሠራተኛ ሲሆን የሚያውቁት ሁሉ ስለ ጌቴ ሲናገሩ በዓለም ላይ ካሉ ደግ፣ የዋህ፣ አዛኝ ክርስቲያን ሰዎች መካከል አንዱ ነው ይላሉ አፋቸውን ሞለተው።
"…ጌቴ ባለ ትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበር። እማሆይ ደብሬ አስረስ የጌቴ አባት ሲሆን ከውድ ባለቤቱ ሙሴ ጌጤ ዕድሜ 5፣ ኑሃሚን ጌጤ ዕድሜ 3 እና አሁን በቅርብ የሚወለድ ልጅም በባለቤቱ ማኅጸን ተቀምጦ ቀኑን እየተጠባበቀ ነበር። ባለቤቱ ነፍሰ ጡር ናት።
"…ሐምሌ 10/2017 ዓም። ጌቴ የሚሠራበት የጢስ እሳት የውኃ ኩባንያ (ኤንጅኦ) የሠራተኛ ደሞዝ ይከፍል ዘንድ ከሹፌሩና እና ከአምስት ሠራተኞች ጋር ወደ አማኑኤል ይሄዱ ዘንድ ታዘው ጉዞ ወደ አማኑኤል ይጀምራሉ። የኩባንያዋን መኪና የሚያሽከረክረው ሹፌር ከማርቆስ ከተማ ትንሽ ወጣ እንዳሉ የዐማራ ምኒሻዎች ያስቆማቸዋል። ሚኒሾቹ መኪናውን አስቁመው ከመኪናው ላይ ጫኑን ይሏቸዋል። በዱላም ያስፈራሩአቸዋል። ለሥራ ነው የምንሄደው እባካችሁ ቢሏቸው ቃታ ስበው ሲያንገራግሩ አማራጭ ቢያጡ ሚኒሻዎቹን ጭነው ጉዞ ይጀምራሉ።
"…ከዚያም ጥቂት እንደተጓዙ ከሩቅ የተኩስ ድምጽ ይሰማሉ። በዚህን ጊዜ ሚኒሻዎቹ እየተኮሱ ሩጠው ያመልጣሉ። እነ ጌቴም ተመስገን ብለው መኪናውን ሳያንቀሳቅሱ ባሉበት ቆመው ፋኖዎቹን ይጠብቃሉ። የሆነውንም፣ የተፈጠረውንም ቢጠይቋቸው ለማስረዳት ነበር ምኞታቸው። ወዲያው የማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ 6ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ኮማንዶ ነን ባዮቹ ይደርሳሉ። እንደደረሱም ሁሉንም ከመኪናዋ አውርደው መደዳውን ያቆሙአቸዋል። ጥያቄ የለ፣ ወሬ የለ። መደዳውን አሰልፈው የጥይት መዓት አርከፈከፉባቸው። ጌቴ፣ ሹፌሩና አንዲት ሴት ወዲያው ይሞታሉ። ሁለቱ የቀሩትም ተረሽነው ወድቀዋል ግን ወዲያው አልሞቱም። ተኩሱን የሰማ ሌላ ኃይል ሲመጣ የጎጃምን ሕዝብ ነፃ ሊያወጡ በረሃ እንደገቡ የሚያወሩት፣ የሚደሰኩሩት የማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ 6ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ኮማንዶዎች እንደተለመደው ሁሴን ቦልትን በሚያስንቅ ፍርጠጣ ፈርጥጠው ወደ ጫካቸው ገቡ።
"…ብዙም ሳይቆዩ ትልቅ ጀብዱ እንደሠራ ሰው በተለመዱት ሚዲያዎቻቸው፣ ንስር ሚዲያ፣ ጊዮን ሚዲያ፣ ኢትዮ ኒውስ፣ ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ፣ መዓዛ መሀመድ ሮሀ ሚዲያ ወዘተ በኩል በጎጃም የተሳካ ደፈጣ መጣላቸውን እና ጠላትን ሙትና ቁስለኛ እንዳደረጉ በሰፊው ዐወጁ። /channel/NISIREamhra/23652 ። በዚህም በአሜሪካ፣ በአውሮጳ፣ በአረብ ሀገር፣ በካናዳ፣ በአውስትራሊያና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ለአፋጎ ዶላርና ዩሮ ለሚልኩት ሪፖርት አቅርበው ጮቤ አስረገጡ። ኮማቾችችም ጨፈሩ፣ ፎከሩ። ደሞቼ፣ ጀግኖቼ፣ በርቱልኝ የበላይ ዘር ብሎ መረቃቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የተረሸኑት ንጹሐን ናቸው።
"…የሚገርመው ነገር ደግሞ እዚያው በጎጃም የ1ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ አመራሮች፣ የአለማየሁ ከቤ ሻለቃ አመራሮቹች አብሮ አደግ አካባሪው ጓደኞቹ ናቸው ናቸው ተብሏል። ሆኖም በጎጃም የጎጃም ሕዝብ እንደ ኩርድ ሕዝብ ከሌላው ዐማራ በተለየ መልኩ ይጸዳ ዘንድ በምስጢር ያይደለ በገሀድ የአማራ ፋኖ በጎጃምን ይመሩ ዘንድ ልዩ ተልእኮ በተሰጣቸው በእነ አስረስ መዓረይ፣ በእነ ማርሸት፣ በእነ ፓስተር ዳዊት መሀሪና በእነ ፓስተር ተሰማ ካሳሁን አማካኝነት የጎጃም ዐማራና አገው እየጸዳ፣ እየተወገደ ይገኛል። የሕዳሴው ግድብ መገንባትን ተከትሎ በመለስ ዜናዊ ጊዜ ተመንጥረው ከፀዱት የጎጃም ዐማሮች በተጨማሪ፣ ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በጎጃም፣ በመተከል ዐማራው ቀበሌ ሙሉ እየጸዳ ይገኛል። ስለ ጋዛ ምን አስወራችሁ ጋዛ እዚያው ኢትዮጵያ ጎጃም እያለላችሁ።
"…ነፃ አውጪዎቹ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ኮማንዶ ተብዬዎቹ ነፃ የሚያወጡት ጌቴንና ሁለቱን የሥራ ባልደረቦችን፣ መሳሪያ ያልያዙ ሲቢሎችን ረሽነው ህጻናት ልጆችን ያለ ጧሪ፣ ያለ ቀባሪ አስቀሩ። ጌቴ የልጆቹ አባት ብቻ አይደለም ይላሉ የሚያውቁት። ጌቴ የጓደኞቹ፣ የዘመዶቹ ሁሉ አባት ነው ይላሉ። ቢያንስ ቢያንስ አሁን ላይ ወደ 6 ልጆችን ከፍሎ ያስተምራል። ሲለፋላቸው ሲደክምላቸው የነበሩ ልጆች ሁሉ አሁን ከሰሩ። ጨለማ ዋጣቸው። የሚገርመው ነገር ጌቴ ደሞዝ ተቀብሎ አንዳንዴ ደሞዙን ለሌሎች አከፋፍሎ ሰጥቶ ባዶውን መጥቶ ያውቃል ነው የሚሉኝ። አማኝ ባለ ማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ። ገንዘብ ያልገዛው ፍፁም ደግ ሰው ነበር ይላሉ።
"…የፋኖ መሪዎች ልጆች አስተማማኝ ቦታ ነው ያሉት። የአስረስ መዓረይ ሚስትና ልጆች በሀገረ አሜሪካ ነው ያሉት። ባለፈው ጊዜ የአስረስ ሚስት ቸገራት ተብሎ ዶክተሩ ዶላር ሰብስቦ ነው የሰጣት ተብሏል። ጎጃምን ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከሸዋ ኅብረት አውጥተው፣ ለይተው አውላላ ሜዳ ላይ አስቀርተውታል። የጎጃም ሕዝብ በጊዜ ነቅቶ እነዚህን ዘር ቆርጣሚ የዐማራ መልክ፣ የዐማራ ወዝ፣ የዐማራ መንፈስ የሌላቸውንና በላዩ ላይ እንደ አልቅት የተጣቡትን ጊንጦች በጊዜ መላ ካላለ እመኑኝ ደም እንባ ያስለቅሱታል። ማርያምን እነ አስረስ፣ እነ ማርሸት ዐማራ አይደሉም። የማርሸትንና የአስረስን ከመሳይ መኮንን ጋር ያደረጉትን ቃለመጠይቅ አዳምጡ። ተመልከቱ። መሳይ መኮንንን የምተቸው፣ የምጸየፈው ሰው ቢሆንም በተለይ ማርሸትን ግን መርዙን ነው ያስተፋው።
"…ትናንትና እና ዛሬ በአርበኛ ዘመነ ካሤ ስም መግለጫ እንደ ጉድ እየጎረፈ ነው። አርበኛ ዘመነ ካሤ ለብአዴን ባለ ሥልጣናት፣ ለሚሊሻ፣ ለአድማ ብተና፣ ለካድሬዎች ሁሉ ጥፉ ወይ ተቀላቀሉን በማለት ጥሪ እያደረጉ ነው። ይሄን ከማድረግ በፊት ግን ቅድሚያ ከዐማራነት ወርደው በጎጥ ተደራጂታችሁ፣ በጎጥ ስም እየተጠራችሁ፣ በግል ጥቅምና ሥልጣን እርስበርስ እየተገዳደላችሁ፣ ለባለ ሥልጣናቱ ጥሪ ማቅረቡ ትንሽ አይጋጭም ወይ? ተብለው ሊጠየቁ ይገባል።
"…ምንም የጋራ ዓለማና የጋራ ግብ የሌለው፣ መነሻውና መድረሻው የማይታወቅ፣ ዕቅድ የሚባል የሌለው፣ የውጭም የውስጥም የዲፕሎማሲ ሥራ የማይሠራ፣ በአረቄ ጠጪ፣ በዘማዊ፣ በቅንዝረኛ፣ በራበውና ለሁዱና ለከርሱ ሲል፣ ሴሰኝነቱን የገበሬ ልጅ በመድፈር ለመርካት ጫከ የሰፈረ፣ የጎጥ አደረጃጀት ይዞ ለብአዴን ባለ ሥልጣናቱ ተቀላቀሉን ወይም ባህርዳርን ለቃችሁ ውጡልን ብሎ ጥሪ ማድረግ አይከብድም?
"…በተለይ የጎጃም ሕዝብ ሊጠይቃቸው ይገባል። በሁለት ዓመት ውስጥ የዐማራን ሕዝብ ነፃ አወጣችሁት ወይስ የበለጠ ሰላምኑን አሳጣችሁት? የባርነት ቀንበር ጫናችሁበት ብሎ ሊሞግታቸው ይገባል። የዐማራ ጠላቱ ጎጠኛው፣ ጥቅመኛው፣ ሆዳሙ እና እንደ እነ አስረስ መዓረይ በጎጥ የተደራጄው፣ ከወንድሙ ጋር የማይስማማው፣ የኬላና የዶላር ጡረተኛው ነው። በጎጥ አደረጃጀት አይደለም የዐማራን ሕዝብ ራስህንም እንኳን ነፃ አታወጣም! ሊባሉ ይገባል።
"…ወስላታውን ሰው በመከራ ጊዜ መተማመን እንደ ተሰበረ ጥርስና እንደ ሰለለ እግር ነው።” ምሳ 25፥19
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ፍልሚያው በድል ተጠናቅቋል። ወደ አየር መመለሻ ምስጢራዊ ቁልፉንም በሰላም ተረክበናል። አሁን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 2:35 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• ZemedTv 👉 https://zemedtv.com/live.html
• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1kvJpymbRBMxE
• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6wftkg--zemede-july-20-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a
• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
11977 H 27500
• ላይ ይከታተሉን።
• ወይ ንቅንቅ…!
"…ስለ እውነት ለመናገር የዛሬው መርሀ ግብራችን ከባድ የጥፋት መንፈስ የሚሰበርበት ድንቅ መርሀ ግብር ነበረ ያዘጋጀሁት። እንደተለመደው የዕለተ ሰንበት የእሁድ ምሽት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሬን ለማስተላለፍ ሁላችንም በስቱዲዮ ተገኝተናል። ሁሉን ጨርሰን በስመ ሥላሴ አማትበን ወደ ቀጥታ ስርጭቱ መርሀ ግብር ልንገባ ቀዩዋን ተጭነን ልናኮበክብ ስንል መጀመሪያ በየኮምፒዩተሮቻችን ላይ፣ በመቀጠል ከሳታላይት ጣቢያው በተሰጠን የቀጥታ ስርጭት የምናደርግበት የምስጢር ቁጥር መስመር ላይ ምን ዓይነት በላ እንደወረደ እንጃ ሁሉ ነገር ቀጥ፣ ዝም፣ ጭጭ አልናገር አልጋገር ብሎ ዱዳ ሆነ።😂
"…አሁን ከጀርመን ከራየን ወንዝ ማዶ፣ ከአማሪካ ከሚሲሲፒ ወንዝ ማዶ፣ ከዓረቢያ ምድር ሆነው መርሀ ግብሩን ያሳልጡ የነበሩ ቴክኒሺያኖች የተፈጠረውን ችግር ለይተው ችግሩንም ዐውቀው ለመፍታት ጥቂት ደቂቃዎች ያስፈልጉናል በማለት ተቀናጅተው በመሥራት ለመፍትሄው እየተረባረቡ ነው። እኔም ጥንቅቅ ብዬ በራሴ በኩል የሚጠበቅብኝን ግዴታም ጨርሼ እነርሱ "አሁን ጀምር" እስኪሉኝ ድረስ እየጠበቅኳቸው ነው። ሀገር ቤት ላላችሁ ሙዚቃ፣ በዩቲዩብና በትዊተር፣ በዌብሳይት እና በሳታላይት የምትጠብቁን ደግሞ ሙዚቃ እያደመጣችሁ ጠብቁን ተብላችኋል።
• በእኔ በኩል ወይ ንቅንቅ 💪
“…የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።” 2ኛ ተሰ 3፥16
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
አልገባኝም… ይሄ እምነት ወይስ…?
"…እግዚአብሔር ይመስገን አባቴንና ወንድሜን ትናንት አጋድመው አረዱብኝ። እግዚአብሔር ይመስገን እህቴን አገቱብኝ። እግዚአብሔር ይመስገን መኪናዬን አቃጠሉብኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ሱቄን ዘረፉት፣ ቤቴን አፈረሱብኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ከሥራ አባረሩኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ጤፍ 20 ሺ፣ ደረቅ እንጀራ 35 ብር፣ አንድ እንቁላል 23 ብር ገባ። እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔር ይመስገን።
"…እግዚአብሔር ይመስገን በ3 ቀን ውስጥ ሱቃችሁን አፍርሳችሁ፣ ቤታችሁን ለቅቃችሁ ውጡ ተብለናል። ወዴት እንደምንገባ እንጃልን። በእውነት ክብሩን ሁሉ እሱ ይውሰድ። እግዚአብሔር ይመስገን ቁርስ፣ ምሣ መብላት ካቆምን ዓመት አለፈን፣ ሕክምና ከተውን እንዲሁ ዓመት አለፈን። ትራንስፖርት ትተን በእግራችን ነው የምንኳትነው። ህክምና መሄድ አልቻልንም ጤናአዳሙም፣ ዳማከሴው ተወደደ። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…እነዚህ ጨካኞች ነገ ደግሞ ምን እንደሚሉን፣ ምን እንደሚያመጡብን አናውቅም። እግዚአብሔር ይመስገን። እግዚአብሔር ይመስገን። እንግዲህ እምነት የሌላቸው ሰዎች እምነት እምነት ያለውን ሕዝብ እንዲህ እያፈረሱት፣ እያፈራረሱትም በነፍስ በሥጋው ባይጫወቱበት ነው የሚገርመኝ።
"…ሁሉም ፈርቷል፣ ተፈራርቷል። በቪድዮው ላይ የምትሰሟት ልጅም የምትለው ይሄንኑ ነው። በደም በላቧ የገነባችው ቤቷ በግሬደር ሲፈራርስ ቆማ እያየች ስትል የምትሰማው እግዚአብሔር ይመስገን ነው።
• በእውነት እሺ ይሄስ የምን ውጤት ነው…? ለመጻፍም፣ ለመናገርም፣ ሓሳብ ለመስጠትም እኮ ነው የቸገረኝ። ይሄም በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው የሚፈጸብን እያልን ነው አይደል? የሆነማ የሆነው ነገር አለ። ምን እያለማመዱን ነው? እሱ ላይ እንወያይ። ይሄማ አይሆንም።
• ግን እስከ መቼ…?
“…ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።” መዝ 32፥9
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ኢንዴዢያ ኖ…
"…የነብሩን ጭራማ ይዤዋለሁ… አረቄ ቤት እየዋሉ… ብአዴን በኔትወርኩ በኩል እያመቻቸ በሚልካቸው የግብፅ ፊት ያላቸው የፈረንጆች መዓት እየተግተለተሉ… ለዐባይ ውኃ ጉዳይ ከእኛ በላይ የሚጠቅማችሁ የለም እየተባለ፣ ደጅ እየተጠና፣ እነ ማርቲን ፕላውትን በማስቸክቸክ… እነ ኢትዮ ወያኔ ፎረሞችን ስለአፋጎ በማስዶስኮር… ስቦ ማስከዳት… ሲመጡብህ መሸሽ… አቢይ አሕመድ ስንመጣበት የሂሊኮፍተሩን ቁልፍ ሳይስነሳ ሩጦ አመለጠን እያሉ በመቀደድ የሚመጣ ድል የለም። ወፍ የለም አልኩህ። ከአንድነት ውጬ አበደን ወፍ የለም።
ዳሞት
ማስተፋቱ ሀሞት
…እሱ የታወቀ ነው። የዳሞት ጀግንነት ጥንትም የተነገረለት፣ የተመሰከረለት ነው። አምጣ የምሥራቅ ጎጃምን ፍልሚያ፣ ደጀን፣ ሉማሜ፣ ደብረ ማርቆስ፣ አምጣ አልኩህ፣ ቢቸና፣ ደብረወርቅ፣ ሞጣ መርጡለ ማርያም። ምሥራቅ ጎጃምን ለብአዴን ሚኒሻ መፈንጫነት አስረክበህ ስታበቃ ደግሞ መጥተህ በአክቲቪስቶችህ በኩል የፎቶ፣ የሰበር ዜና መዓት ስትለቅ ውለህ ብታድር ወፍ የለም አልኩህ። መሬት ያለው እውነታ ሌላ ነው።
"…የወያኔን ነፍስ ያድናል ብለው ካመኑ አይደለም እነ ማርቲን ፕላውት፣ እነ አልጀዚራ፣ እነ ሲኤንኤን፣ እነ ቢቢሲ ሁላ የገጽታ ግንባታ ለመሥራት በጀት ይመድባሉ። መሬት ላይ ያለው እውነት ግን ሌላ ነው።
"…ከጎንደር ዐማራ፣ ከወሎ ዐማራ፣ ከሸዋ ዐማራ ተለይቼ ከወያኔ ህወሓት ጋር ሥልጣን እይዛለሁ፣ ዓባይን ተሻግሬ 4 ኪሎ እገባለሁ ብሎ ማለት ዘበት ነው። እንዳታስበው። እንዳትሞክረው አልኩህ።
• 3 :1 😁
👆②✍✍✍ …ከሚያውቀው ሌላ እነርሱ ለእነርሱ በምስጢር የሚፈስላቸው ነገር እንዳለ አይታወቅም። ነገሩ ሁሉ ግራ የገባ ነው። አብዛኛው ቲክቶከር እንኳ የሚበዙቱ ኦሮሞ፣ ጴንጤና ትግሬ ናቸው። ኦርቶዶክሶቹ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ወጣቱን የሚያደነዝዙትም እነዚሁ ኮተታሞች ናቸው።
"…አሁን ዋይታው በዝቷል። የመከራው ድንኳን በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት ገብቷል። ዘረኞች፣ ጎጠኞች፣ መንግሥታችን ነው የሚሉ ጴንጤዎች፣ ልጃችን ነው የሚሉ ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው እያረሩ የሚስቁት። ዋይ ዋይ ኡኡ የሚሉበት ቀን ግን በጣም ቅርብ ነው። በአቢይ አገዛዝ ምክንያት ሲሰድቡኝ፣ ሲወቅሱኝ፣ ሲረግሙኝ ለነበሩት ሁሉ መልሴ አንድ ነበር። መከራው በቤታችሁ ይግባ፣ ኀዘኑ፣ ችግሩ፣ የአቢይ አርጩሜው በላያችሁ ላይ ይረፍ። የሌላው ሕመም ይመማችሁ። ቁስላቸው ይጠዝጥዛችሁ። ደርሶባችሁ እዩት። ቅመሱት ነበር መልሴ። አቢይን መርጠነዋል። ብልፅግና ሺ ዓመት ይንገሥ፣ አንት ምቀኛ፣ አንት ክፉ፣ አንት እርጉም ተቃጠል፣ እረር፣ ድብን በል ሲሉኝ የነበሩ በሙሉ እያየኋቸው ነው። እያበዱ፣ ብቻቸውን እያወሩ እያየኋቸው ነው። ገና ነው። ገና ገና መቼ ተነካና። የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል። “…በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አይሰማችሁም።” 1ኛ ሳሙ 8፥18። …ዘመዴ… በዚህ ሀገር ምን እየተካሄደ ነው? አትበለኝ።
"…በሁለት ነገር የአቢይ አሕመድ ብልፅግና እንኩትኩቱ ይወድቃል። ይሰባበራል። ተወልዶ፣ አድጎ፣ አርጅቷልና በቅርቡ በራሱ በአፍጢሙ ተደፍቶ ይሞታል። የአቢይ አሕመድ ፈላጭ ቆራጭ ብቸኛው አምባገነን አገዛዝ ይወድቃል ብሎ ለመናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። በዐማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ዋነኛው የአቢይ አሕመድ አገዛዝ መገንደሻው ድጅኖው ነው። ሠራዊቱ በዐማራ ክልል ረግረግ ውስጥ ገብቶ ሰምጦ አልቋል። እንደ አሞሌ ጨው ነው የሟሟው። ይሄ ዋነኛው የመውደቂያው፣ የመንኮቻኮቻው ምክንያት ነው። ጦርነቱ ከሶማሌ ጋር፣ ሱዳንም ድንበሬ ተገፋ፣ መሬቴ ተነካ እያለች ነውና ከሱዳንም ጋር፣ አልፎ ተርፎ ከኤርትራም ጋር ወደ ጦርነት ከተገባ ያበቃለታል። ከሁሉ ከሁሉ ደግሞ ከትግሬዎቹ ጋር ጦርነት ከገጠመ ውድቀቱ ይፋጠናል። ይሄ ማለት ግን የአቢይ ኦሮሙማው አገዛዝ ሲወድቅ በቃ በኢትዮጵያ ሰላም፣ ጥጋብ ይሆናል ማለት አይደለም። እንዲየውም የባሰ፣ የከፋ ትርምስምስ ያለ ነገር ነው የሚፈጠረው። ዘንዶው አቢይ ሲወድቅ ዝም ብሎ አይወድቅም። አውድሞህ፣ ጠባሳ ጥሎብህ ጨፍልቆህ ነው የሚወድቀው። እንጂ ዝምብሎማ አይወድቅም። አቢይ ሲወድቅ፣ መውደቁን ሲያረጋግጥ በቅድሚያ፣ ሱሉልታ፣ ቡራዩ፣ ሰበታ፣ ዱከም፣ እንጦጦና ሸገር ሲቲ አስጠግቶ ያስቀመጣቸውን ፕላን B በደቦ ስማቸው ኦነግ ሸኔ የተባሉትን አራት ኪሎ አዲስ አበባ አስገብቶ ነው የሚሸበለለው። እንዲህ በዋዛማ የሚፋታህ እንዳይመስልህ።
"…ፋኖ እራሱ ገና መች ተስማማና? ሸዋ ያለው ፋኖ ለሁለት የተሰነጠቀ፣ እርስ በእርሱ የሚዋጋ ኃይል ነው። የመከታውና የኢንጂነር ደሳለኝ ጦር አዲስ አበባ ስር ተቀምጦ እርስ በእርሱ እንዲዋጋ እያደረጉት ነው። የሸዋውን ኃይል ጎንደሬዎቹ እስኳድ ጠፍረው እጅ እግሩን ሽባ አድርገው፣ ሚዲያ፣ ገንዘብ፣ የጦር መሪም መድበውለት አፍዘው አደንግዘው አስቀምጠውታል። ወሎ ሁለት ቦታ ተከፍሎ እየተጠዛጠዘ ነው ግዙፉ የምሬ ጦርና የኮሎኔል ሙሀባው ሚልሾች ተፋጥጠው ነው ያሉት። የኮለኔሉን ጦር ያግዘው ዘንድ የአስረስ መዓረይ፣ የማርሸት ዘመድ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤም እዚያው ደቡብ ወሎና ደቡብ ጎንደር እያሉ ነው የተቀመጡት። ጎንደር የሀብቴና የደረጄ ጦር እርስ በእርሱ እየተጠዛጠዘ ነው። ጎጃም ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ጋር አልሠራም ብሎ ከወያኔ ጋር ለመሥራት እየተነጋገረ ነው። አቢይ ቢወድቅም መከራችን ቶሎ አይወድቅም። ትግሬና ሻአቢያ ሲጨመሩበት ደግሞ ኢትዮጵያ ታብዳለች። ይደፈርሳል ግን ደግሞ ይጠራል። ሌላው ቀርቶ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ምሁራን፣ ማኅበራት፣ ሚዲያዎች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ከሚስማሙበት ይልቅ የሚለያዩበት ስንጥቃት ይበዛል።
"…አይናችሁን ጨፍናችሁ ስታስቡት ከባድ ይመስላል። በዚያ ላይ ሁሉም መሳሪያ የታጠቀ ሲሆን ደግሞ ያው ሩዋንዳ በሉት። ሩዋንዳ። በዚህ ስምንት ዓመት የመጣን ክፉ የጭካኔ ልምምድ እና ልማድ መለኮታዊ ርዳታ የእግዚአብሔር እጅ ካልገባበት በቀር በቀላሉ የሚሽር አይመስልም። እገታ ቢዝነስ መሆኑ የታየበት፣ ፍርድ ቤት፣ ዳኛ፣ ፖሊስ፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ወታደር የተናቀበት ዘመን ስላሳለፍን ሁሉን ነገር በፍጥነት ወደቦታው ለመመለስ የሚከብድ ይመስላል። ከውድቀቱ በኋላ ነው እንዲያውም የሚያስፈራው። የአቢይ አገዛዝ በኢኮኖሚው ድቀት እና በጦርነቱ ምክንያት ሽባ መሆኑ፣ እንኩትኩት ማለቱ አይቀሬ ነው። ለዚያ ደግሞ አሁን ጥጋብ ላይ ያሉት ሥልጣን፣ ገንዘብ፣ ሀብትና ሁሉም ነገር በእጃቸው ላይ የሚገኘው ጽንፈኛ ጴንጤዎችና የኦሮሞ የወሀቢይ እስላሞች ሌላው ሕዝብ 7 ዓመት ሙሉ ከአቢይ አገዛዝ እጅ የቀመሰውን መሪር ጽዋ መቅመስ አለባቸው። የአቢይን የቅጣት በትር መቅመስ አለባቸው። አሜን ሃሌሉያ ባሉበት አፋቸው ወየው ወየው ራበን፣ ጠማን፣ ቸገረን፣ ምን ጉድ ነው ማለት አለባቸው። ሌላውን ያስጨነቀው፣ ያሳበደው የአቢይ መንፈስ እነሱንም መጎብኘት አለበት። እኩል ከሌላው ጋር መሆን አለባቸው። የኀዘኑ ድንኳን በየቤቱ መግባት አለበት። ግመል ሰርቀህ አጎንብሰህ እንዲየው አትሄዳት። ልደብቅህ ቢሉት የማይደበቀው ሌሎችን ያገኘ መከራ ሲያገኛቸው ያኔ ነው የለውጡ ቱሩፋት ሁሉንም እኩል የሚያደርገው። መጽሐፍ “…ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።” ምሳ 29፥2። እንዲል አልቅስ። ሶፍት ስጡት አለ ሽሜ አብዲሳ። ኤንዴዢያ ኖ…
"…ሽምግልና፣ ድርድር፣ ምክክር እና ወዘተ አሁን አያድኑም። ዋጋም የላቸው። የአሁኑም ሽምግልና ሆነ የበፊቱ ትግሬን የጎዳ ቢሆንም የኦሮሙማው የሽምግልና ታክቲክ ዞሮ ዞሮ ተጠምጥሞ መጥቶ የሚጠቀሙበት ዐማራን ለማጥቃት ነው። እናም አዋጩ ነገር የዐማራ ፋኖን አንድነት አጥብቆ ወደፊት መጓዝ ብቻ ነው። ጊጃም በአስረስ በኩል ከሦስቱ የዐማራ ኃይሎች በይፋ በመውጣቱ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ ለጎጃም ሕዝብና ሠራዊት የእስከአሁን ሪፖርት አቅርበው ወደፊት መስፈንጠር ነው ያለባቸው። እነ አስረስ የወያኔን ጦርነት ነው መጠበቅ የፈለጉት። ዳግም አራት ኪሎ ከወያኔ ጋር ገብተው መነገድ፣ ኢንቬስተር መሆን ነው የፈለጉት። እናም አፋብኃ መግለጫ ማውጣት አለበት። የጎጃም ፋኖም፣ የጎጃም ሕዝብም የተፈጠረውን ችግር ከነ ችግር ፈጣሪዎቹ ጭምር በይፋ ማወቅ አለበት። ይሄ ግድ ነው። እነ አስረስ መዓረይ በዘመነ ካሤ ስም፣ በየሚዲያውም እየተንጦሎጦሉ ሦስቱን እየከሰሱ ነውና ሦስቱ በፍጥነት ያለውን ሁኔታ ለሕዝብ ማቅረብ ማሳወቅም አለባቸው ብዬ ምክረ ሓሳቤን አቀርባለሁ። ዛሬ ዶክተር አብደላ እንድሪስ የጻፈው መልእክትም የሚያሳየው ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ አንድ ላይ እየሠሩ እንደሆነ እና ጎጃም ግን ከድርጅቱ በውስጠ ታዋቂ እንደወጣ፣ እንደተለየ ነው የሚያሰየው። ባትሰሙት መልካም ነበር። ህመሙን የማይናገር መድኃኒት አያገኝም እና ደፍራችሁ ህመማችሁን ተናገሩና አንድነት የተባለውን ምርጥ መድኃኒት ዋጡና ተፈወሱ።
“…እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ” መዝ 67፥1
• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
መልካም…
"…የገቢ ግብር ዐዋጁ እንደተለመደው በብልፅግና መንግሥት ምክርቤት ጸድቋል። ሕዝቡም ከዳር እስከዳር ጫጫጫጫ እያለ ነው። ይሄን ለማስቀየስ እና ለማረሳሳት እነ ለገሰ ቱሉም ከጠፉበት ብቅ ብለው አዳዲስ አጀንዳዎችን አምርተው እንዲያከፋፍሉ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። የብልፄ አክቲቪስቶችና ቲክቶከሮችም እንዲሁ አጨቃጫቂ አጀንዳ ውለዱ ተብለዋል። ሰሞኑን እንግዲህ የሕዝቤን ራቡን እና ጥሙን የሚያስረሳ አዳዲስ የመጨቃጨቂያ አጀንዳ በገፍ አምርተው በየቲክቶኩ በገፍ መጠበቅ ነው።
"…በእነ አስረስ መዓረይ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎጃም በግልጽ በሓላል ከሦስቱ የዐማራ አደረጃጀት ግዛቶች መውጣቱን ያረጋገጠ መስሏል። ሸዋ፣ ወሎና ጎንደር ተናበው መሥራታቸውን የቀጠሉ ይመስላል። በአፄ ቴዎድሮስ ስም አልጠራም የሚለው ምሥራቅ ጎጃም የመሸገው የወያኔ ርዝራዥ ጎጃምን ከወንድሞቹ በይፋ የለየ መስሏል።
• 3:1
"…ለማንኛውም የዕለቱን ርእሰ አንቀጽ ልለጥፍ ነኝ። የአንድ 100 ያህል ቤተሰቦኝ ድምጽ ይፈለጋል። እስቲ ቀውጡት። 😁
• ቶሎ ጀምሩልን አላለም…? 😂
"…አይ አይተ መዓረይ …ሦስቱን ጥለሽ አንቺ ከወያኔ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘሽ ወደ 4 ኪሎ ልትገቢ? ድፍረትህ…! …ጦርነቱን ቶሎ ጀምሩት፣ አፍጥኑት አላለም? ጉድ እኮ ነው።
"…የአፋጎ ጠበቃው መዓረይ ከሕወሓት ሽማግሌዎች ጋር ባደረገው ሰሞነኘ ውይይት ወያኔዎቹ የሰሜኑን ጦርነት በቶሎ እንዲጀምሩ መማፀኑን ነው ወፎቼ ሹክ የሚሉኝ። "…ወደ 4ኪሎ ለመገስገስ እናንተን ነው እየጠበቅን ያለነው፤ ጦርነቱን መጀመራችሁ በጋራ ለምናደርገው ዘመቻ ወሳኝ ነውና ፍጠኑ።" በማለት የአረጋውያኑን የሕወሓት ስብስብ አሳስቧል አሉ የመዓረይ ልጅ።
"…መዓረይ በሀገር ውስጥ ካሉ ብአዴንና ሕወሓት ጋር እየሠራ የሚገኝ ሲሆን ሁለቱንም ያካተተው የግራንድ አሊያንስ ቡድን (ገዱ፣ ልደቱ፣ ጃዋር፣ ኢ/ር ይልቃል፣ ሕዝቅኤል፣ እነ መዓዛ .. ያሉበት) የሀገር ውስጥ ተቀዳሚ ተወካያቸው ነው። ሥራውን ለማሳካት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በሚገኙ ምሁራን ተወካዮቻቸው በተቋቋመው አሳቢ ቡድን ነው አሉ አቅጣጫ የሚቀመጥለት።
"…እነ መዓረይ ከሕወሓት ጋር በጋራ የሚያደርጉት የ4 ኪሎ ጉዞ ካልተሳካ፣ በነ አሜሪካ ገፋፊነት ከግራንድ አልያንሱ ጋር ተካትቶ 4 ኪሎ ለመግባት Plan B አለው። የአፋጎው እና የዘሜ ጠበቃ ጥብቅናው ለጠላት እንጂ ወገን ለሆነውና ለተጎዳው የዐማራ ሕዝብ አለመሆኑ ገሃድ እየወጣ መጥቷል።
"…ለማንኛውም ነገ ጠዋት ከምስጋና በኋላ ከጮቄ ተራራ ላይ ሆኜ በዘመድ አዝማድ፣ በአክስትና በአጎት ልጆች ስለተተበተበው አፋጎ በርእሰ አንቀጽ መልክ በሰፊው እመለስበታለሁ። ሌላው ደግሞ የማከበረው፣ የምወደው ሻለቃ ዝናቡ የሚጠቀምበት ፌስቡክ ላይ የሚጽፈው እሱ ዝኔ አይደለም። የዝኔን እውነተኛ ፌስቡክ የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ። 360ንም አፋጎ ሊገዛው ነው።
• ሸንጎ፣ ቅባቴና ወያንቲቲ መጣሁልሽ። 😂
"…የእኔን ምልከታ ቆይቼ አስቀምጣለሁ። እነ አቡነ ሳዊሮስ እና እነ ሼህ ኢብራሂም ቱፋ ወዘተረፈ አቢይ አሕመድ ሂዱ ስላላቸው መቀሌ ድረስ ስለሄዱ፣ መቀሌም ሄደው ህወሓትን ሳያገኙ እዚያው አዲስ አበባ ሊያገኙት የሚችሉትን ጄነራል ታደሰ ወረደን አናግራው ስለመጡ ጦርነቱ የሚቀር ይመስላችኋል ወይ…?
"…ከሌሎቹ ሊቃነ ጳጳሳት በተለየ ሁኔታ የትግሬ ኤሊቶች፣ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ጻድቅ፣ ብፁዕ አድርገው ሲያንቆለጳጵሷቸው የከረሙት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስስ መቀሌ ድረስ ሄደው ነጭ እርግብ ይዘው ፎቶ ተነሥተው ስለለቁ የተሰጋው ጦርነት ቀርቶ የተባለው ሰላም የሚገኝ ይመስሏችኋል…?
"…ከትግራይ ድረስ ለፍተው አዲስ አበባ ድረስ አቢይን ለማነጋገር የደኩሙት የሀገር ሽማግሌዎችን አቢይ አህመድ ተቀብዬ አላነጋግርም ብሏል የተባለው ዜና እውነት ከሆነ ይሄ ንቀት ሰላም የሚያመጣ ይመስላችኋል…?
• በአጠቃላይ አጀንዳውን እንዴት አያችሁት…?
መልካም…
"…አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ አስተያየት የሚደመጥበት ክፍለ ጊዜ ነው። እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በጨዋ ደንብ ሓሳብ እየሰጣችሁ አብረን እናመሻለን። በጽሑፍ መልስ የመስጠት፣ የማስረዳት፣ የመግለጽ ልምዳችሁንም አዳብሩ። በጽሑፍ መሰዳደብ ሳይሆን መወያየትንም በዚያው ልመዱ። የእኔ መንደር ደግሞ በዚህ ዕድለኛ ነው።
"…ተንፒሱ… ጤናማ ጨጓራ እንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ ተንፒሱ። በደንብ ተንፒሱ። ጻፉ ✍✍✍ አስተያየት ጻፉ። እኔም ቁጭ ብዬ በተራዬ አስተያየቶቻችሁን እየኮመኮምኩ፣ ባለጌ በጥባጭ ስድአደጉንም እየቀሰፍኩ ላምሽ።
• 1…2…3… ጀምሩ…✍✍✍
👆③✍✍✍ …ቀሲስ አንዷለም ከአንተ ራስ ላይ እንደማይወረድ ልታውቅ ይገባል። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም ይረጋጉ፣ ንዴትዎን ሰከን ብለው ለመወጣት ይመክሩ። ያበሳጮትን አቢይ አሕመድ 4 ኪሎ ይፈልጉት። እናንተ በገንዘባችሁና በሥልጣናችሁ ግፉበት፣ ካህናቱና ሕዝቡም እውነትን ይዘው ይግፉበት። መጨረሻ ላይ አሸናፊው የግድ መለየቱ አይቀርም።
"…የኢትዮጵያው አጋንንት አውጪ ስፔሸሊስቶች አሁን ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካና ካናዳ እየተመሙ ነው። የኢትዮጵያው ብር መውደቅ፣ አኪኖሚውን IMF የተባለ አጋንንት ሽባ ዲዳ ስላደረገው፣ የሰዉ መደህየት እንደ ልብ ቢዝነስ ሊያሠራቸው አልቻለም። ስለዚህ አዋጭ ወደሆነው መከርበት ጀምረዋል። ለዚህ ነው እነ ጆኒ ራጋም ጥሬ ካሽ በሚልየን ዶላር መዥርጥ አድርጎ አውጥቶ በዳላስ ሰፊ ገዳም ገዝቷል። እሱን ተከትሎ የሄደው አጋንንት በቴክሳስ ምድር ረብሾ በጎርፍ እንዲጥቀለቁ ነው ያደረገው። መምህር ግርማና ልጁ ካሊፎሪንያ ቢች ዳር ፎቶ ተነሥተው በለቀቁ ከስንተኛ ጊዜ በኋላ ካሊፎርኒያ ነደደች፣ ወደመች። ግርማ ወንድሙ ወደ ቨርጂኒያ ሄዶ ከቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስ ጋር በአጋንንት ስም ቢዝነስ ሠሩ። ይኸው አልዋለ አላደረ በፈጣኑ የዘመኑ በ5G የጸሎት መልስ ምክንያት ቀሲሱ ሥልጣነ ክህነቱ በሊቀጳጳሱ ተገፍፎ አቶ ደበበ እስጢፋኖስ ተብሎ አረፈው። አሁን ካናዳ የገቡት ባለ ዘይቱ ሄኖኬና ግርማ ወንድሙም እንደ ድሮው አልቀናቸውም። የካናዳ ዶላርም እንደ ሀገሬ ብር ነው ዘጭ ያለው። ሊቀጳጳሱ አብረው ሊሸቅሉ ቢፈልጉም ሕዝቡ ግን ኢግኖር ገጭቶ ባዶ አዳራሽ አስታቅፏቸዋል። 1 ዶላር 190 ብር በገባበት ዘመን እነ ግርማ ወንድሙ፣ ጆኒ ራጋ፣ እና ሔኖኬ ባለ ዘይቱ ሰሜን አሜሪካ እየተመላለሱ እንደ እሳት አደጋ ሠራተኛ ውኃ እየረጩ ከሥርዓተ ቤተ ክርስተያን ውጪ የሚግጡትን ግጦሽ፣ ጋጠወጥ፣ ሕገወጥ ገፈፋና ዘረፋ ላይ ሕዝቡ በመንቃቱ ምክንያት እንደ ቀድሞው ሊሳካላቸው አልቻለም።
"…ነሐሴ ምናም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ ባህታዊ የበረሃው መናኝ፣ ወይም ግርማ ወንድሙ፣ ወይም ፀዴው የመንፈሱ ወራሽ ልጁ፣ አልያም ሔኖኬ ቅባ ቅዱስ የፈውስ አገልግሎት ስለሚሰጡ እናንተ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የአጋንንት ዓይነት ያለባችሁ ሰዎች በሥፍራው ተገኝታችሁ እንድትፈወሱ ስንል እናሳስባለን። በማለት ይሄን ኑሮ ራሱ ስትረስ ያበዛበትን አጋንንት ዲያብሎስ የሆነበትን፣ ከሰይጣን የከፋበትን ምስኪን ሕዝብ ሲግጡት ይታያሉ። የአጋንቱ፣ የዛሩ ብዛት ደግሞ ለጉድ ነው። የፈረቀሳው ንጉሥ፣ ሙጨ ዘሪጋ፣ አዳኝ ወርቁ፣ ሐጎስ፣ ጎለም እሸት፣ ጨንገር፣ ሰይፉ ጨንገር፣ ቆሪጥ፣ ጠቋር፣ አዳል ሞቲ፣ ወሰን አጋጅ፣ ወሰን ገፊ፣ ወሰን ራሔሎ፣ ሻንቂት፣ ሻንቆ፣ ሃደ ሐሮ፣ ሃደ ዓባይ፣ አባ መጋል፣ ሼህ አንበሶ፣ ነቢ ጅላሌ፣ ብር አለንጋ፣ ገውዘ ላዝም፣ ሻንቆ አባዲና፣ አርዱላ፣ 99 መሊካ፣ ሞቲ አረቢያ፣ ግራኝ አባ ጉግሳ፣ አላቲ፣ ሪሣ፣ ኦፋ አቡኮ፣ ኦፋ ጨፌ፣ ኦፋ ለገሰ፣ ኦፋ ደመና፣ ተኮላሽ፣ የታዬ ከራማ፣ የአሩሲዋ እመቤት፣ ቡሎ ገርቢ፣ ሣማ ቀልቢ፣ አርሜት፣ ድማሜት፣ ሙሄት፣ አብድር ቃዲር፣ ዋቅ፣ ቦዥና ጨሌ፣ የወሎ ክብሪት፣ ቤሩድ፣ ሼህ ወልይ፣ የጠረፏ ንግሥት፣ አዬ ሞሚና፣ አቴቴ ዱላ፣ አቴቴ ጊምቢ፣ አውሊያ፣ የታዬ ከራማ፣ አውሊያ ሼክ ሁሴን፣ ጅላሌ አብዱል ቃድር፣ ተኮላሽ እያሱ፣ ወሰን ገፊ፣ አዳኝ ሱማሌ፣ ቆሌ አዳኝ፣
የልክፍት ዛር፣ ቦረንትቻ፣ አሞር፣ ውቃቢ፣ አውልያ፣ መተት፣ ቡዳ፣ ዐውደ ነገሥት አንባቢ፣ ኮከብ ቆጣሪ፣ ስር ማሽ፣ ቅጠል በጣሽ፣ አተላ አንባቢ፣ ስኒ ዘቅዛቂ፣ አሻራ አንባቢ፣ አቴቴ ጊምቢ፣ አቴቴ ዱላ፣ ሼህ አምበሶ፣ ማራም ጁጁ፣ ዛር፣ ዓይነ ጥላ፣ ቡዳ፣ ዛር ጨሌ፣ የአውሊያ ቃልቻ፣ የጨሌ አጋንንት፣ ቃሉ፣ ቃሊቲ ሲንቄ፣ አያንቱ፣ ዋዩ፣ አባ ኬና፣ አባ ገዳ፣ አባ ከኩ… ወዘተ እያሉ አሳሩን ያበሉታል። ጉድ እኮ ነው።
"…እናም በተነሣው አጀንዳ ላይ መከራከር ይቻላል። በተለይ እኔ ዝምታዬን የሰበርኩት አስቀድሞ ከእነ በጋሻው ጋር የእኔ ራሱ ከሳሽ የነበረው መምህር ታሪኩ ዛሬም የሐሰተኛ አጥማቂያንና የዊግ ቀጣጣይ አርቴ ባሕታውያን ጠበቃ ሆኖ ተከስቶ ሳየው ነው። እረፉ እነ ታሬ። ዘርፌን አሜሪካ የወሰዳት የእነ መምህር አንዷለም ቡድን ምን ተጠቀመ? በዘርፌ ቢዝነስ እንሠራለን ያሉ ሁሉ ናቸው እኮ የሌለ የከሠሩት። አሁንም ባሕታውያን፣ አጥማቂዎች አስፈርሞ የሚሠራ ቢዝነስን አጥብቀን እንቃወማለን። ምድረ አጭቤ ሁላ ዝም ብሎ መፈንጨት የለም። እናንተ በጉልበት የሕዝብን ድምጽ አልሰማ ብላችሁ ከሀገር ቤት ጳጳስ አምጥታችሁ በአቋማችሁ ልትገፉ ትችላላችሁ። ነገር ግን ትከሥራላችሁ። በተለይ ጉዳዩን ከደቡብ ጎንደሬነት፣ ከጎጃሜነት፣ ከሸዋዬነት ጋር አጠጋግታችሁ ስትመጡ በኃይለኛው ትጎዳላችሁ። በወያኔ ጊዜ ወያኔ ውጭ ሀገር ያሉ ዜጎችን ትከፋፍል የነበረው በቤተ ክርስቲያን በኩል ነበር። ካድሬ ጳጳሳትን በመላክ ነበር ሕዝበ ክርስቲያኑን ትከፋፍል የነበረው። ለምሳሌ የተቃዋሚው ግንቦት ሰባት ሚዲያ የነበረው ኢሳት ሆላንድ ቢሮ ነበርው። እናም የሆላንድ ኢትዮጵያውያን አንድ ላይ ቆመው ሥርዓቱን በኢሳት በኩል መቃወም ሲጀምሩ አቡነ እንጦንስ የተባሉ ወያኔ ልካ የበሬ ግምባር በምታክል ሀገር ላይ ሁለት የገብርኤል ታቦት በመትከል ሕዝቡን አፋጀችው። ጭቅጭቅ፣ ፀብ ተፈጠረ። ለጊዜው የተጠቀመች መሰለች። ሕዝቡም ተከፋፈለ።
"…አሁንም እንደዚያው ነው እየተደረገ ያለው። ለባህታዊያንና ለአጥማቂዎች ቪዛ እየተሰጠ፣ ምእመኑን ለገፈፋም፣ ለትርምስም ይዳርጉታል። በዚህ ጊዜ ብጥብጥ፣ ልዩነት፣ ጠብ ክርክር ይፈጠራል። በዚህ ተጠቃሚዎቹ ፀረ ኦርቶዶክሶቹ ናቸው። እናም ሁሉም ሊነቃ ይገባዋል። ሰብሰብ፣ ኮስተር በሉ። ተወያዩ፣ ምከሩም። የማንም መንገደኛ እንደ ቦይ ውኃ እንዲነዳችሁ አትፍቀዱለት። መጠየቅ ልመዱ። ቆይታችሁ ተበላሁ፣ ተደፈርኩ፣ ተዘረፍኩ፣ ተጭበረበርኩ ብላችሁ ከማልቀሳችሁ በፊት፣ በግለሰቦች ስህተት ምክንያት ንፅህት፣ ቅድስት፣ ርትእት ሃይማኖታችሁን ከማሰደባችሁ፣ ከመስደባችሁና ከቅዱሳን ኅበረት ከመለየታችሁ በፊት ቆም ብላችሁ አስቡ። በሰለጠነ ዓለም እየኖራችሁ የማንም በሃይማኖት ካባ የተሸፈነ ሰገጤ እንዲጫወትባችሁ አትፍቀዱለት። አመሰግናለሁ።
"…እኔ ግን ዕድለኛ ነኝ። አስቀድሜ ብቻዬን የነበርኩ ቢሆንም አሁን ግን ሚልዮኖች እሳት የላሱ የተዋሕዶ ልጆችን ከጎኔ ቆመው ለማየት በቅቻለሁ። ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ የተባልኩ እኔን ይመስለኛል። የዘራሁት ዘር አሁን ላይ ከእኔ የባሱ፣ ያውም እንደእኔ ጯሂ፣ መራታ ያልሆኑ፣ ስክን ያሉ ተገዳዳሪ፣ የቤተ ክርስቲያን ጠበቆችን በቲክቶክም፣ በዩቲዩብም እያየሁ ነው። እነ ቀሲስ ዲበኩሉ፣ እነ ቀሲስ ቴዎድሮስ ወዘተን እያየሁ ነፍሴ እየረካች ነው። ምእመኑም አንጀት አርስ ሆኗል። አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ ከመሆን ተላቅቋል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…እኔ አክሊለ ገብርኤልም ከፌስቡክ አልፌ፣ ከዩቲዩብ አልፌ፣ ከቲክቶክና ከቴሌግራምም መንደር አልፌ ተሻግሬ ዛሬ ላይ ሠራዊተ ጌዴዎንን ይዤ 24/7 የሚሠራ የሳታላይት ቴሌቭዥን እንዲቋቋም መሠረት ጥዬ ከፍ ብዬ እየበረርኩ ነው። ለዚህም አምላኬ ልኡል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው። ዘወትር ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ የምላት እናቴ እመቤት ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ምስጋናዬ ይድረሳት። እንደ ንስር እንድበር የረዳኝ አምላከ ቅዱሳን ይክበር ይመስገን። ከዚህ በላይ ምን እፈልጋለሁ? ብቻዬን ስጮህበት የከረምኩት ነገር በሙሉ ዛሬ ላይ ይቃወሙኝ የነበሩት…👇③✍✍✍