"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
👆②✍✍✍ …የኦርቶዶክስ ፓስተር ማለት ነው። በዚህ ዘመን አጥማቂና ባሕታዊ ማለት ኤለን ማስክ በሏቸው። ከፖለቲካ ድርጅት ጋር፣ ፍቅረ ነዋይ ካናወዛቸው፣ የገንዘብ ጠኔም ካጠናገራቸው፣ አራጣ ተበድረው ገንዘብ ከፍለው ከጰጰሱ አንዳንድ ጳጳሳትና የደብር አለቆች ጋር፣ የቤት ኪራይ ከከበደው፣ የዕለታዊ ውሰኪና ቢራ መጠጫ ካነሰው የቤተ ክህነት ሠራተኛ ጋር የተሞዳሞደ ባሕታዊ ዕልል የተባለለት ባለፀጋ እሱ ነው። ያውም ታክስ፣ ቫት፣ ግብር የሌለበት፣ ከሸኔም የነዳጅ ጉድጓድም ካለው ባለሀብት የበለጠ ገቢ ያለው፣ የማይነጥፍ ሀብት የተተርፈረፈለት ማለት ነው። ኤድስ፣ ቂጥኝ፣ ጨብጥ፣ ስኳር፣ ኩላሊት፣ ሪህ፣ የልብ ድካም፣ ስንፈተ ወሲብ የገጠመው ሁላ ሲጨንቀው መፍትሄ ባገኝ ብሎ ወደ እነሱ ይመጣል እነሱም በሚገባ አስተናግደው አጥበው፣ አራቁተው፣ ሙልጩን አውጥተው ገድለው ይሸኙታል። ልብ በሉ የአጥማቅያን ተግባር በቤተ ክርስቲያን መዋቅር አይታወቅም። ገቢያቸው ታክስ የለው። ኮሚቴ የለው፣ ገቢ ወጪው አይታወቅ፣ በቤተ ክርስቲያን ስም ይሄን የዋሕ ሕዝብ ውኃ እየረጩ፣ ጡቷ ስር ገብተው ዘይት እየቀቡ በአፅሙ ያስቀሩታል። የገንዘቡ ተካፋይ ግን ብዙ ነው።
"…በዳላስም እያየሁ የከረምኩት ያንኑ ነው። ቤተ ክርስቲያን ከፊቷ አደጋ ተጋርጦባታል። ትግሬዎቹ ተራቸው ደርሶ ተገንጥለው የትግራይ ቤተ ክርስቲያን አቋቁመዋል። ኦሮሞዎቹ ሚኒሶታ ውስጥ እየሞከሩ ነው። የቤተ ክርስቲያን ማስታወቂያ በግብፅ ባንዲራ ከተተካ ቆየ። ዲሲ ውስጥ ቀደም ብለው መስርተውት የነበረው የእነ ጃዋር ቤተ ክርስቲያን ብዙም ስላላዋጣ አሁን ዐውቀውም ይሁን ሳያውቁት እግዚአብሔር ይወቀው በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሀገረ ስብከት በሚኒሶታ የሆነ ደስስ የማይል ምልክት በኦሮሞዎቹ በኩል እየታየ መሆኑም እየተነገረ ነው። እግዚአብሔር ይሁናቸው። ይሄን ያዩት ጎንደሬዎቹ የቀድሞው የስደተኛው ሲኖዶስ አባቶችም ከወዲሁ የሆነ የሚወድቁበትን ስፍራ በማማተር ላይ መሆናቸው ነው የሚሰማው። አቢይ አሕመድን እሽኮኮ ተሸክመው ሲዞሩ ከርመው ድንገት የባነኑትና አሁን ጥለውት፣ ረስተውት ወደ ነበረው ሕዝብ በባህታዊ ጆኒ ራጋ በኩል ለመጠጋት ያሰፈሰፉት አካላት አቢይ አሕመድ ደህና አድርጎ፣ አዋርዶ፣ ጠልዞ አሽቀንጥሮ ሲልካቸው ወደ ቀደመ ሥራቸው ለመመለስ የሚያሟሙቁ እንዳሉም እያየን ያለነው። መቼም ጉዳችን አያልቅ።
"…በካሊፎሪንያ ተገዛ የተባለው ገዳም የገዳሙ የበላይ ጠባቂ ትውልዳቸው ከጎጃም ስለሆነ ለእኛ ለጎንደሮች ደግሞ አንድ ያስፈልገናል ብለው ነው ጆኒ ራጋን ከደቡብ ጎንደር አስፈርመው አምጥተው ይህን ምስኪን ዲያስፖራ ጭንቀት፣ ስትረስ የሚያሰቃየውን ምስኪን ሕዝብ ሰይጣን ነውና እሱን እናስለቅቅልህ በማለት ጥሪቱን ለማራገፍ፣ ለመግፈፍ፣ በዚህም ምርጥ ልምድ ካላቸው መካከል ያንኑ የወንቅሸት፣ የደቡብ ጎንደር ባለ ብዙ ወንጀል ባለቤት ጆኒ ራጋን አስፈርመው ያመጡት። አሁን እነ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በአቢይ አሕመድና በዳንኤል ክብረት የአገልግሎት ጊዜዎ አብቅቷል ተብለው ወደ ጋርቤጅ ሲወረወሩ በፍጥነት የአሜሪካ ባንዲራ ስር ተቀምጠው አራጁን፣ ነፍሰ በላውን፣ እኛ ለዘመናት ስንቃወመው እሳቸው አትንኩብኝ፣ አቢይ አሕመድ ከድንግል ማርያምም በላይ አማላጅ አስታራቂዬ ነው ያሉ እስኪመስሉ ድረስ እንደ አምላክ ጭምር ይቆጥሩት የነበረውን አረመኔ አሁን ደርሰው ጨዋታው አልቆ ፊሽካ ከተነፋ በኋላ ጎልል ብለው ለመጨፈርና እኛ ጨፍረን፣ ጨፍረን የደከመንን ሰዎች በሪፕሌይ እንድንጨፍር ሲራወጡ፣ ሲደክሙ ይታያሉ። ይሄ ልክ አይደለም።
"…ሕዝብ ፈርዷል። የዘመኑ ሰው ነቅቷል። ምእመናን በብዙ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ንቃተ ህሊናቸው ዳብሯል። እንደ ድሮው በቀላሉ የሚሸወድ፣ የሚታለልም ሕዝብ የለም። የዘንድሮ ፍርድ ደግሞ ፈጣን ነው። እግዚአብሔር መልስ ሲሰጥ የፋይፍ ጂ ፍጥነት በሉት መልሱ። መልካም ከሠራህ መልካም መልስ፣ መጥፎ ከሠራህ ደግሞ የመጥፎ መልስ ወዲያው ነው የሚልክልህ። እንደ ድሮው በልጅ ልጅህ ይድረስ ብሎ ነገር ቀርቷል። መልሱ ሁሉ ፈጣን ነው። ለምሳሌ እንመልከት። የሆነ ጊዜ ብራዚላውያን አደባባይ ወጥተው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ቀለዱ፣ አሾፉ፣ ተሳለቁ። ሳይመሽ መልሱን በጎርፍ ተጥለቅልቀው፣ ወድመው አገኙት። የዘንድሮ የእግዚአብሔር መልስ 5G ነው የምላችሁ ለዚህ ነው። እዚያው ሰሜን አሜሪካ በካሊፎርኒያ የሆሊዉድ አክተሮች በኦስካር ሽልማት ላይ ተሰብስበው በእግዚአብሔር ላይ ቀለዱ፣ ተሳሳቁ፣ ተሳለቁም። እግዚአብሔርም አየ፣ ሰማ። ወዲያውኑ ሳይውል ሳያድር ካሊፎኒያን ሰዶምና ገሞራን በሚያስንቅ እሳት አነደዳት። የዚያ ሁሉ ባለሀብት አክተሮች የቢልዮን ዶላር ዘመናዊ ቤቶችና መኪኖች በሰከንድ ውስጥ ወደሙ። 5G የሆነ መልስ ማለትም ይሄም አይደል…? ሰሞኑን ደግሞ እዚያው አሜሪካ ቴክሳስ ውስጥ አንዱ ጥጋበኛ ባለሥልጣን "እግዚአብሔር ራሱ ስደተኛ ሆኖ ቴክሳስ ቢመጣ ጠፍረን አስረን ወደመጣበት እንመልሰዋለን" ብሎ በፈጣሪ ተሳለቀ። እግዚአብሔርም የዘመነ ኖህን ጊዜ ዝናብ አመጣው፣ የሰማይ መስኮቶች በቴክሳስ ላይ ተከፈቱ፣ የዝናብ ጎርፍ ከሰማይ ወደ ምድር ተደፋ፣ ጎረፈ። ቴክሳስ በውኃ ተጥለቀለቀች። 5G ነው ይሄም። ሌላም፣ ሌላም መጥቀስ እንችላለን።
"…አሁንም እነ መምህር አንዷለም ዳግማዊ ለገንዘብ ብላችሁ የምታደርጉትን ቅጥ ያጣ፣ ለከት የለሽ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ብታቆሙ ነው የሚሻላችሁ። አቁሙ። ዶክትሬትህ የሚያስከብርህ ምእመናን እስካሉ ድረስ ብቻ ነው። ምእመናን ከሌሉ ፕሮፌሰር ብትሆንም፣ ጳጳስ ብትሆንም ጥቅም የለውም። ተንደላቀህ የምትኖረው፣ ልጆችህን ዘጭ አድርገህ የምታስተምረው፣ ቤትህን ቀጥ አድርገህ የምትመራው፣ ተከብረህ፣ መምህር፣ ምናምን ተብለህ የምትኖረው ቤተ ክርስቲያን ከነ ምእመኖቿ ሲኖሩ ነው። ቤተ ክርስቲያን ያለ ምእመናን ባዶ አዳራሽ ነው። የካህናት፣ የጳጳሳት ጌጣቸው ምእመናን ናቸው። የሆዳችሁ ጌቶች ምእመናን ናቸው። እና የምእመናንን ድምጽ ብትሰሙ መልካም ነው። ያለበለዚያ የሙዳይ ምጽዋቱ ካዝና ይራቆትና ከምእመናኑ እኩል ኡበር ተራ ተሰላፊ መሆን ይመጣል። መጠንቀቅ መልካም ነው። በፊት በፊት ካሕናት እናንተን በመፍራት ከምእመናን ጋር አይሰለፉም ነበር። አሁን ግን ያ ነገር ተቀይሯል። ሁል ጊዜ እግዚአብሔርንና እውነትን፣ ሃቅን የያዘና ሕዝብ የያዘ ነው አሸናፊው። እናም በዳላስ ካሕናትና ምእመናን እጅና ጓንት ሆነዋል። አታሸንፏቸውም። ይከብዷችኋል። ሕዝብ ጳጳሱንም፣ አንተንም ሊቀይር ይችላል። ከካናዳ ወደ አሜሪካ ዳላስ ያመጣህ ሕዝብ ነው። የቀጠረህም ሕዝብ ነው። መምህሬ ሕዝብን አክብር። ባሕታዊው ብአዴን ነው ነገ ወደ ሀገሩ ገብቶ ዘጭ ብሎ መኖር ይችላል። አየር ላይ የምትቀሩት እናንተው ናችሁ። ደግሞም አሁን ለምታቋቁሙት አዲስ ሲኖዶስስ ቢሆን ባህታዊ ነው ወይስ ሕዝብ ነው የሚያስፈልጋችሁ? ምርጫችሁን አስተካክሉ።
"…ቢንያም ሽታዬን ባለበት የስደት ሀገር ነፍሰ ገዳይ ገዝቶ ማስፈራራት፣ ከዚያም አልፎ በቀሲስ ሳሙኤል ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ ማድረግ ነውርም፣ ወንጀልም፣ ብልግናም፣ ኃጢአትም ነው። ቀሲስ ሳሙኤልም ሆነ ቢንያም ሽታዬም ያደረጉት ነገር ቢኖር የብዙኀኑን ምእመናና ካህናት ድምጽ ማስተጋባት ነው። ከራሳቸው ፈጥረው፣ ዋሽተው፣ ቀጥፈው የሠሩት ነገር የም። እናም ገንዘብ አለን ተብሎ የሥዕለት ገንዘብ አውጥቶ ወንጀል ለመሥራት መጣደፍ ከጳጳሳትና ካሕናት አይጠበቅም። ለቀሲስ ሳሙኤል የላካችሁት ማስፈራሪያ ደርሶታል። ቀሲስ አንድ ነገር ቢሆን፣ ትን ቢለው እንኳ በተለይ…👇②✍✍✍
መልካም…
"…1ሺ አመስጋኙ ሞልቷል። በመቀጠል ደግሞ እንደተለመደው ርእሰ አንቀጻችንን ልለጥፍላችሁ ነኝ።
"…የዛሬው ርእሰ አንቀጻችን የሚያጠነጥነው ሰሞኑን ለወራት ያሕል በአሜሪካ ምድር ሲካሄድ የነበረው ቴክሳስ ግዛት የሃሰተኛ አጥማቂያኑና የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ እንዲሁም የምእመናን ፍልሚያ ከምን እንደደረሰ ትዝብቴን የሚያካትት ርእሰ አንቀጽ ነው። በተለይ ግጥሚያ ፍልሚያውን ከቦታው በቀጥታ ሲያስኮመኩመን የነበረው ተወዳጁ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያም በርእሰ አንቀጹ ላይ ተካትቷል።
"…በቀጣይ ሦስተኛው ሲኖዶስ ለመመሥረት ደፋ ቀና የሚሉ አካላትም ምን እያደረጉ እንደሆነ ርእሰ አንቀጼ በሰሱ ይዳስሳል። ርእሰ አንቀጹ በተጨማሪ ሕዝብን የያዘ፣ እውነትን የያዘ፣ እግዚአብሔርን የሙጥኝ ያለ እንዴት እንደሚያሸንፍም ያመለክታል።
"…ተተኪዎች በማግኘቴ ለወራት ያህል የራቅሁበት የቤተ ክህነት ጉዳይ ፍልሚያው ከምን እንደደረሰም የራሴን ምልከታ አስቀምጥላችኋለሁ። ቅባቴዎች ድጓ ምን ይሠራል የሚሉትን የእነ አባ ማርቆስን ድፍረት ለጊዜው አላካተትኩትም። እሱን ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
"…እናሳ ቤተሰብ ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ፣ አንብባችሁም በጨዋ ደንብ ለመወያየት ዝግጁ ናችሁ…? እስቲ አንድ 100 ያህል ሰው እንደተለመው "አዎ ዘመዴ ዝግጁ ነነ" ይበለኝ።
• ዝግጁ…?
• ታዲያ እኔስ ምን አልኩ…?
"…ጎጃም ብቻውን አያሸንፍም። በተለያዩ 3 ጊዜያት በተደረጉ ምርጫዎች ዘመነ ካሤን ሁሉም በሙሉ ድምፅ ነው የመረጡት። ዘመነ እንዳይመረጥ ያደረጉት እነ አስረስ መዓረይ ናቸው።
መጀመሪያ 4 ወሳኝ ቦታዎች ቀረቡ።
፩፦ለሊቀ መንበርነት
፪ኛ፦ወታደራዊ አዛዥነት
፫ኛ፦የፖለቲካ ዋና ሓላፊነት
፬ኛ፦የውጭ ግኑኝነት
"…ከእነዚ ምርጫዎች አንዱን የወሰደ ሌላውን አይደግምም ተብሎ ተወሰነ። ጎጃሞች መሪነቱ ለእኛ ይሰጠን ዘመነም ይምራን አሉ። ሦስቱም ተስማሙ። በሙሉ ድምጽም ጸደቀ። የቀረውን ቦታ ሦስቱ ተከፋፈሉት። ነገሩ በዚህ አለቀ።
"…የአስረስ ቡድን አበደ። አይሆንም አለ። ከፓስተሮቹ ጋርም መከረ። መከሩና መጡ። መጥተውም ወታደራዊ አዛዥነቱም፣ የፖለቲካ ሓላፊነቱም፣ የውጭ ጉዳዩንም እኛ እንያዘው ብለው ገገሙ። 3ቱም የሚቋቋመው ድርጅት እኮ የዐማራ ፋኖ እንጂ የጎጃም ፋኖ አይደለም ብለው ገገሙ።
"…በማርሸት በኩል የጎጃም አክቲቪስቶች በሀብቴ ወልዴ፣ በወሎው ሔኖክ፣ በሸዋው ዳግማዊ ላይ ዘመቱ፣ ተሳደቡ፣ አቀረሹ። ጎጃምን ይዘን እንቀጥላለንም ብለው ደነፉ። ደነፉ፣ ደነፉና ዘለው፣ ዘለው ሲያዩት የማያዋጣ ሆነው አገኙት። እናም እነ አልሚ ባለጭራዋም ይኸው ይናዘዙ ጀመር።
"…አዳሜና ሔዋኔ ገና ምን አይተሽ። ጎጃምን ያዋረዱት እነ አስረስ መዓረይ በአደባባይ ሦስቱን ይቅርታ ይጠይቃሉ። ከሦስቱ የተለየ ጎጃም ከውኃ የወጣ ዓሣ በሉት። አይደለም አዲስ አበባ ደምበጫም አትገባ። ማርቆስ ሲያምርህ ይቀራል። ባሕርዳር እንደ ሰማይ ይርቅሃል። መፍትሄው ጠቅላይነትን፣ ትእቢትን፣ ያለ እኛ የሚል አጉል ጉራን እርግፍ አድርጎ ትቶ ለክ እንደ አልሚ እንዲህ ንስሐ መግባት ነው።
• ከምር እኔማ ከኢዩ ጩፋ እበልጣለሁ። አቤት በርበሬ እያጠንኩ እኮ ነው ወደ መስመር የማስገባው። 😂 ተሳሳትኩ…?
"…መለኮት ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም ነው። አንድ አምላክ አንዲት መንግሥት አንዲት ሥልጣን አንዲት አገዛዝ ነው። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስባሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይወዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈጽማሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስማማሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከናውናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይልካሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሠለጥናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ምስክር ይሆናሉ።
"…አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሰውን ያስባሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለምዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያነጻሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከብራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨክናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይጋርዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለብሳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ባለሟል ያደርጋሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይቀመጣሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈርዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመረምራሉ።
"…እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን፤ አንድነትን ሳንለይ የተለየ እንዳይሆን። የተቀላቀለ እንዳይሆን እንለይ። ቅዳሴ ማርያም
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም… !
"… የቀረውን የአፋጎ ሰነድ ትወያዩበት ዘንድ እነሆ እንኳችሁ ብያለሁ። ጎጃም ከዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልነት እንዘጭ ብሎ ወርዶ የጎጃም ፋኖ ሆኖ አርፏል። ይሄ ደግሞ ትልቅ ኪሳራ ነው።
"…ይሄ የእነ አስረስ መዓረይ መንገድ ለጎጃም አይጠቅመውም። ለጎጃም የሚጠቅመው ከወንድሞቹ ከጎንደሬዎች፣ ከሸዋዎች፣ ከወሎዬዎቹ ከቤተ ዐማራዎች ጋር አንድ ላይ ሆኖ መታገል እንጂ፣ እኛ ገንዘብ አለን፣ ባለሀብቶች አሉን፣ ሚዲያና መሣሪያ አለን፣ ብቻችንን አሸንፈን 4 ኪሎ እንገባለን የሚሉትን ቅዠት፣ ያውም የቁም ቅዠት በአስቸኳይ ማቆም አለባቸው። ጎጃም ያለ ጎንደር፣ ያለ ሸዋ፣ ያለወሎ ብቻውን ስንዝር አይራመዳትም። ቢመርህም ዋጠው።
"…ቢበዛ ቢበዛ ከጎጃም የምንሰማው አፋጎ "ቡሬ ከተማን ጠዋት ተቆጣጠረ፣ ቡሬ ከተማን ከሰዓት በኋላ ለቅቆ ወጣ" የሚል ሰካራም የጨበራ ተስካር የመሰለ ሰበር ዜና ብቻ ነው። እንዲህ ዓይነት ሰበር ዜና እንደ ፓራሲታሞል ያለ ነው።
"…2 ሚሊሻ በስቦ ማስከዳት መማረክ፣ በጥናት እና በዕቅድ ያልተመራ በግብታዊነት የከተማ ገብቶ መውጣት የጦር ስልት ለጎጃም ሕዝብ ምንም አይጠቅመውም። ትርፉ ፋኖ ከተማ ሲገባ በጦርነት ስለሆነ ብዙ ሰው ይጎዳል፣ ንብረት ይወድማል። ገብተው ቢቆዩ መልካም ነበር። ገብተው አይቆዩም። ፎቶ ይነሣሉ። ወዲያው ኡጋንዳ እና አሜሪካ ለቲክቶከሮች ሰበር ዜና ይልካሉ። ዜናው እየተነበበ እነሱ ከተማዋን ለቅቀው ይፈረጥጣሉ። ሁሴን ቦልቶች። ከዚያ የብርሃኑ ጁላ ጦር ወደ ከተማዋ ይገባል። ከየቤቱ ዐማሮችን እያወጣ ይረሽናል። ይጨፈጭፋል። ወዲያው አፋጎ መግለጫ ያወጣል። "በአፋጎ ከፍተኛ ምት የደረሰበት የብራኑ ጁላ የአቢይ አህመድ ጦር በእገሌ ከተማ ንፁሓንን ጨፈጨፈ።" ይባልልኛል። ወዳጄ የፈለከውን በለኝ የዐማራ መዳኛው አንድነቱ ብቻ ነው።
• ተወያዩበት ✍✍✍
አያችሁልኝ አይደል…?
"…እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ፣ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ ዛሬ ምሽት ላይ ብቅ ብል ይኸው ጨልሞ፣ ደብዝዞ የነበረው የቴሌግራም መንደር በአንደዜ ተነቃቃ። ድብልቅልቁ ወጣ እኮ። አሁን ለብዙዎች የእንጀራ ገመዳቸውን እዘረጋላቸዋለሁ። ቲክቶክ ላይ አጀንዳ ያገኛሉ። ይራወጣሉ። ወዲህ ወዲያም ይላሉ። በሉ ተንቀሳቀሱ።
"…መጣም፣ መጣም የሚገርመኝን አንድ ነገር ደግሞ ልንገራችሁ። አይታችሁ ከሆነ አንዳድ ዐማራ መስለው ዐማራ ዐማራ ሲጫወቱ የምናውቃቸው ሰዎች ቆየት ይሉና ዐማራ መሳይ ዐሞራ የሆኑ ዲቃሎች ሆነው አገኛቸዋለሁ። ድሮ በዐማራ አባታቸው ወይም በዐማራ እናታቸው ዘር ተመክተው እኔ ዐማራ ነኝ ምናምን ይሉ ነበር ሁላ፤ አሁን ዐማራ የወደቀ እና እየተገፋ ያለ ሲመስላቸው ዐማራነታቸውን ክደው አሽቀንጥረው ጥለውም ወደ ተደቀልቡት ዘር ተንደርድረው ሶቶ ገብተው ሲደበቁ፣ ሲወሸቁ ይታያሉ። ይቆዩና ደግሞ ዐማራው የሚያሸንፍ ሲመስላቸው ደግሞ ከፊት ይመጡና እኛ ነን አንደኛ ዐማራ፣ እኛ ትግሉንም፣ ገንዘብ ስብሰባውንም እንምራው ይላሉ። በተለይ የጎንደሩ ፀረ ዐማራ ዲቃላ እስኳድ እና የጎጃሙ ፀረ ዐማራ ሸንጎ ያስቁኛል።
• ነገ ከምስጋና በኋላ እንቀጥላለን። 🙏
"…የአፋጎን አዲስ ድርጅት ምስረታ የሚያሳየውን ሰነድ ለዛሬ በስሱ ላሳያችሁና ትንሽ እንወያይበት ወይስ ለነገ አሳድሬ በጠዋት ከምስጋና በኋላ እንመለስበት…? …ከመሸባችሁ ብዬ እያስመረጥኳችሁ ነው።
"…በነገራችን ላይ እነ እስክንድር ይፈርሳሉ፣ እነ ሀብታሙ ይበተናሉ፣ አሕፋድን የጎንደር እስኳድ ይወርሰዋል፣ ይሄ ግም ስብስብ ብዙም አይቆይ እንደ እምቧይ ካብ ይናዳል፣ ብዬ ትንቢት መሰል ነገር ስናገር እናንተ ገሚሶቻችሁ ስትሰድቡኝ፣ ስትረግሙኝ፣ ስትስቁብኝም ነበር። እናስ እነ በቶሎ ጓ ደና ናቹ እንደምናቹ…?
"…የጎጃሞቹን ደግሞ ለማየት ያብቃችሁ። ብዙም ባልራቀ ጊዜ የጎጃም ዐማራ ሕዝቡ ራሱ እንደ ሞሶሎኒ የገቡበት ገብቶ ባይቀጣቸው ምናለ ዘመዴ በሉኝ። ቱ…! አባቴ ይሙት ማርያምን መዝግቡልኝ።
"…አሁን ልትሰድቡኝ፣ ልትንጫጩብኝ ትችላላችሁ ነገር ግን የተናገርኩት እንደሁ አይቀርም። መሬትም ጠብ አይልም። የአፋጎ መሰሪ ሾተላይ መናፍቅ የሸንጎ መሪዎች፣ ቅባታሞቹ ፀረ ዐማራ ስብስቦች እና መሪዎች ምነው ምድር ተከፍቶ በዋጠን፣ ሰማይ ተደፍቶ በተከደነብን ብለው ቢማጸኑ እንኳ እንደማይድኑ፣ ከሚመጣው ከራሱ ከጎጃም ዐማራ ቁጣና መቅሰፍትም እንደማይድኑ ስነግራችሁ በኩራት ነው። እኔ ዘመዴ ካልኩ አልኩ ነው። አሁን አክቲቪስቱ ሁላ ማበድ፣ ልታቀረሽብኝ ትችል ዘንድ ፈቅጄልሃለሁ። ተንበጫበጭ።
"…ወደ ዋናው ጉዳይ ስገባ ሰነዱን በጨረፍታ ላሳያችሁ ወይስ ይደር…?
ቀጠልኩ…!
"…እኔምለው ይሄ አጭቤ ቶርቶራ ሰካራም የሆነ የሰው ግማሽ ብልፅግና አሳድዶኝ፣ ኦሮሙማ ሊገድለኝ ሲል ጎንደሬው ወዳጄ ታማኝ በየነ ባደረገልኝ እገዛ መሰረት ከፓስተር ፕሮፌሰር ትንግርቱ ጋር ወደ አሜሪካ ተሰደድኩ ብሎ አልነበር እንዴ…?
"…ይሄ በእናቱ ጎንደሬ እንደሆነ የሚናገረውና በዘመነ ወያኔ የብአዴን አባል ሆኖ ለቦሌ ክፍለ ከተማ መምህራንና በፍቼ ሰላሌ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አሰልጣኝ የነበረው፣ የቄሮ ትግል ተቃዋሚ፣ ኋላ ላይ ደግሞ የጃዋርም የቄሮም አፈቀላጤ፣ ቆይቶ የበለጸገ፣ ከዚያም ዐማራን በማሞኘትና ለመግፈፍ በዐማራ ክልል አረጥራጭ፣ አዘጥዛጭ የነበረው ሰውዬ አይደለም እንዴ…?
"…ዳንኤል ክብረት ጃስ ብሎት ቅዱስ ፓትርያርኩን ከዘሪሁን ሙላቱ፣ ከስዩም ተሾመ፣ ከእነ መሳይ መኮንን ጋር ሲያዋርድ፣ ሲሰድብ፣ ሲያቀረሽባቸው የኖረ፣ ለእነ ፓስተር በጋሻው ተደርቦ ሲሰድበኝ የኖረ፣ ገልቱ፣ አቋም የለሽ፣ ጨቅላ፣ የግብዳ ትንሽ የሆነ ሰውዬ ምን ሆኖ ነው እንዲህ ያፈላው…?
"…ይሄ ሰካራም ለቦረና የተሰበሰበ ገንዘብ ዘርፎ መኪና ገዝቶ ሊበላ ሲል ቄሮ ማንቁርቱን አንቆ ያስተፋው፣ ሰክሮ ወድቆ ተደበደብኩ፣ መርዝ አብልተውኝ ተረፍኩ ሲል ቆይቶ፣ ትራንፕ ስደተኞችን ማባረር ሲጀምር አለቃውን ታማኝ በየነን ሳያማክር እንዲህ የጦዘው ምን ቅሞ ነው…?
"…የኢትዮጵያ መንግሥትን ተቃውሜ ጥገኝነት ጠይቄአለሁ ያለው ሶዬ እንዴህ ባንደዜ ከስዩም ተሾመ በላይ አቃጣሪ ካልሆንኩ ያሰኘው ነገር ምንድነው…? …ታዬ ሙት የፈለገ ቢቸግርህ ያንን ፀያፍ ቆሻሻ ሥራ ሠርተህ መቀረጽ አልነበረብህም። 😂 ወይ ብላክሜል… ጉድ እኮ ነው ዘንድሮ። እኔን ጣለባቸው እንጂ እነ ታማኝማ ታዬንና ትንግርቱን ይዘው ከዚያ ቁጥር 2 ግንቦት 7 መሥርተው ይሄን ዳያስፖራ ሊግጡት ነበር።
• ታዬ ግን በጤናው ነው…?
መልካም…
"…እኔማ የተሻለ ከተገኘ ብዬ ፔጅ በከፈቱ ግለሰቦች መንደር እግሬ እስኪቀጥን ድረስ በየቤቱ ዞርኩ፣ ዞርኩ፣ ተንከራተትኩ፣ ቀላወጥኩ ሁላ… ምንም አጣሁ፣ የሚያወያይ፣ የሚያነታርክ፣ የሚያከራክር ሓሳብ አመንጭቶ በቤቱ ግርግር፣ ትርምስ የሚፈጥር ባለፔጅ አጣሁ። ለአእምሮአችንም ሆነ ለጣታችንም ቢሆን ሥራ የሚሰጥ፣ የሚያነቃቃ ሓሳብ የሚያመነጭ የቲክቶክ በሉት የቴሌግራም፣ የፌስቡክ በሉት የዩቲዩብ ቤት አጣሁ። ከዳር ጥጌን ይዤ ሲጨቃጨቁ ልይ ልስማ ብዬ ስንከራተት ውዬ ባድርም እንኳ ወፍ የለም። ሁለት ሚኒሻ በስቦ ማስከዳት ተቀላቀለን ብቻ። 😂 ኧረ ኤዲያ…
"…እናም በየመንደሩ ብዞር፣ ብዞር፣ ብሽከረከር ምንም ጠብ የሚል ነገር ስላጣሁ ያው እንደተለመደው እንደፈረደብኝ እስቲ በእኔ ቤት ደግሞ አንዳንድ ሓሳቦችን እያነሣን አዕምሮአችንና ጣታችንን ሥራ ሰጥተን በማነሣቸው ሓሳቦች ላይ እየተወያየን፣ በጨዋ ደንብ እየተጨቃጨቅን ብናመሽስ ብዬ ስለወሰንኩ ወደ እናንተ መጣሁ። ምን ይመስላችኋል?
"…ልጀምር ነኝ…! አላችሁ አይደል…?
• ውይይቱ በይፋ ተጀምሯል…!
https://www.facebook.com/share/p/14G79Hn6V9C/
• እስቲ ገምቱ ምን የሚሆን ይመስላችኋል…? …እነ አቡነ ሳዊሮስ ቤተ ክርስቲያን ግብር እንድትከፍል ያስደርጓታል ወይስ…
👆③✍✍✍ …አብርሃም እኮ ኦሮሞዎቹ እነ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ያባረሯቸውን፣ ከሥራም ያፈናቀሏቸውን የትግሬ ቄሶች ውዝፍ ደሞዛቸውን ከፍለው ወደ ሥራ እንዲመለሱ ነው ያደረጉት። ቤተ ክህነት ውስጥ የሚሠሩ ትግሬዎች ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ቆመውም፣ ተቀምጠውም ነው የሚያመሰግኗቸው። እነ ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እኮ ዐማራን የጠቀሙት ነገር የለም። ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አኮላሽተው ብልፅግናን የታደጉ አባቶች እኮ ናቸው። ብልጽግናን በሁለንተናዊ መስኩ የደገፉ፣ የተከላከሉ፣ የጠቀሙ አባቶች ናቸው። ጎጃም እንዲህ ስትወድም፣ ጎንደር ስትወድም አቡነ አብርሃምም ሆኑ አቡነ ጴጥሮስ መቼ ትንፍሽ ብለው ያወረቃሉ? ኦሮሞም፣ ትግሬም ዐማራ ስለሆኑ ብቻ ዐመድ አፋሽ ካላደረጓቸው በቀር አቡነ አብርሃምን እና አቡነ ጴጥሮስን ኦሮሞና ትግሬ ያገለገሉ፣ የጠቀሙ እንጂ ጎድተው በኦሮሞና በትግሬ የሚሰድቡበት፣ የሚወቀሱበት፣ የሚታሙበት ምክንያት የለም። በጭራሽ የለም። የበሉበትን ወጪት መስበር ካልሆነ በቀር በፍጹም ትግሬ አቡነ አብርሃምን የሚወቅስበት ምክንያትም የለውም።
"…የትግሬ የጨረቃ ጳጳሳት እነ ተጋዳላይ ሰረቀ ብርሃን እነ አቶ ኢሳያስ፣ እና ሌሎችም የትግሬ ሽማግሌዎች አቢይ አሕመድን ደጅ ለመጥናት ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ መሆኑ ነው የተሰማው። ሲጨንቃቸው በሚጠየፉት አማርኛ የልመና፣ የተማጽኖ ደብዳቤ የግዳቸውን ለመጻፍ በቅተዋል። አማርኛ እኮ ወርቅ ነው። ተለማምጠህ ጠይቀህ፣ ደጅም ጠንተህ ሚስት ታገኝበታለህ፣ ቢርብህ ለምነህበት ከርስህን ትሞላበታለህ። ሰብከህ ታሳምንበታለህ፣ ብትዘፍንበት፣ ብትዘምርበት ደስ ያሰኛል። ዐማራን ብትጠላውም አማርኛን ማጥፋት ግን የማይታሰብ ነው። አሁን ወያኔ ራሱ ትግሬን ሽባ ስላደረገችው መለኮታዊ ጣልቃገብነት ተፈጥሮ ትግሬ ልብ አግኝቶ ከዐማራ ጋር ስምም ካልሆነ በቀር ከእንግዲህ በኋላ ትግሬ ከዚህ የተለየ ቀና የሚያሰኝ ሕይወት አይኖረውም። ቅስሙም፣ ጅስሙም ነው ባሳደጉት ውሻ ተነክሶ የፈሰሰው፣ የደቀቀው። በቀደም የጀርመን ድምጽን የአማርኛ ዜና እያነበብኩ ነበር። በትግራይ ሕዝቡ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል ይላል ዜናው። ዳግም ጦርነት ይፈጠራል ብሎ ጭንቅ ገብቶታል ነው የሚለው። መብራት ሊቋረጥ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ያችው ያለችው የአየር ትራንስፖርት ሊቆም ይችላል ብለው ጭንቅ ላይ ናቸው ነው የሚለው ዜናው። አስቡት ባለፈውን ጭንቅ ጊዜ ያሳለፈ ትግሬ ምን ሊሰማው እንደሚችል። ነዳጅ ቆሟል፣ ሸቀጥም አይገባም ተብሏል። ይሄንንም ዐማራ ነው ያደረገብን ከማለት አይመለሱም። ብቻ አሁን እንዲህ እግር ስሞ፣ ተለማምጦ የበጀት ፍርፋሪ ከኢትዮጵያ እየለመኑ አርፎ መቀመጥ እንጂ ወብርተው፣ ጓ ብለው በድሮ በሬ እንረስ ብለው እምበር ተጋዳላይን እየጨፈሩ፣ እንደ ኮካኮላ ምርት እየተሽከረከሩ እየተደነሱ ለመዋጋት ቢነሡ የመውጊያውን ብረት መቃወም ሆኖ ይብስባቸዋል። ሌላ ብዙ ዊልቸር፣ ሌላ ብዙ ክራንቻም ነው የሚበዛው። የከፋ እልቂት ነው የሚከሰትባቸው። በተለይ ከሻአቢያ ጋር ከገጠሙ ደግሞ ሻአቢያ ከኢራን፣ ከሩሲያና ከቻይና ጋር ናት ብሎ የሚያስበው የእስራኤልና የአሜሪካ መሩ ዓለም ዱቄት ነው የሚያደርጋቸው። እናም ከባድ ነው። ከሆነም ለስሜታቸው ሚዲያ ላይ ጎጃምና ጎንደርን፣ ሸዋና ወሎን እየሰደቡ ቢኖሩ ብዬ እመክራለሁ።
"…ሌላው ራያና ወልቃይት፣ ጠለምትንም በጦር ኃይል እናስመልሳለን ብለው ወደ ጎንደርና ወደ ወሎ ቢዘምቱም በዚያ ጥሩ ዕድል የሚገጥማቸው አይመስለኝም። ከበፊቱ የባሰ ይከፋባቸው ይመስለኛል። የአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋም መቀሌ ድረስ ሄዶ በብርቱ እንደወቀሳቸውና እንደነገራቸው ነው የተሰማው። የራያን ዐላውቅም እንጄ የወልቃይቱን ግን ቢሞክሩት ከበድ ያለ ኪሣራ እንደሚገጥማቸው ነው የሚገመተው። ሻአቢያም ቢሆን ለራሱ ኅልውና ሲል ቢሞት ወያኔን በወልቃይት በኩል ወረራ እንድትፈጽም የሚያደርጋት አይመስለኝም። የጎጃሙም የእነ አስረስ መዓረይ በኩል በምንም በኩል የሚያግዛቸው አይመስለኝም። የሆነው ሆኖ ግን ጦርነቱ አይቀሬ ይመስላል። ሰሜኑን ለኢየሱስ ለማስረከብ ሲባልም ሰሜኑ በኦሮሙማው የጌታ ሰዎች ለመድቀቅ መሞከሩ አይቀሬ ነው።
• አንብባችሁ ስትጨርሱ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው አስተያየታችሁን ጽፋችሁ ጠብቁኝ።
• ሰላም ለሀገራችን…!
• ድል ለዐማራው ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ከህወሓት ወያኔ በፊት ትግራይን ገንጥሎ ሀገር ያደረገው የወንበዴዎቹ የእነ ሰረቀ ቡድን በምናቡ የፈጠራትን፣ በቅዳሴና በጸሎቱ ሁሉ ላይ የሚያወሳትን፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ጽሑፍ ሁሉ አውጥቶ በሀገረ ትግራይ የተካው ወንጀለኛ ቡድን ያችኑ አፋቸው ምላሳቸው ላይ ያለችዋን ሀገረ ትግራይን ወክሎ ከሀገረ ኢትዮጵያው ጊዜያዊ መሪ ከአቢይ አሕመድ ጋር ለመነጋገር ሽምግልናም ጠይቆ እሺታን አግኝቶ፣ "ያሳደግንህ ልጃችን ሆይ ለምን ዳግም እወጋችኋለሁ አልከን" ብለው እግሩም ላይ ተደፍተው ሊለምኑት ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ስላኮበኮቡት አይደለም ዛሬ በርእሰ አንቀጼ የማተኩረው። ወይም ደግሞ በዝርዝር ሲታዩ የዓድዋ ተወላጅ የሆኑ ትግሬዎች ሰሞኑን በየሚዲያው እየተጣዱ ከአቢይ አሕመድ መዓትና ቁጣ ብንድን በማለት በማሰብ በኦሮሞ ፊት ሞገስ ብናገኝ በማለት ነጥብ ለማስቆጠርም በዐማራ ላይ የሚያቀረሹትን ቅርሻታቸውን ልጽፍ አይደለም ብቅ ያልኩት። እሱን ገና በደንብ እየታዘብኩ ነው። ወዳጄ ትግሬ የሚይዘው፣ የሚጨብጠውን ነው ያጣው። ግራም ቀኝም ነው የገባው። ሴራው ሁሉ ነው የጠፋበት። አሁን እንደ አሜባ ራሱን አርባ ቦታ ከፍሎ መልኩንና አቋሙን እየቀያየረ ከመንበጫበጭ በቀር የሚያደርገው መላ ቅጡ ነው የጠፋው። ገሚሱ ትግሬ በጄነራል ታደሰ ወረደ በኩል የአቢይ ገባሪ መስሎ ይተውናል። ገሚሱ ትግሬ ህወሓት ነኝ ብሎ ጫካ ገብቶ ዐማራንና አቢይን ድጋሚ እዋጋለሁ ብሎ ያቅራራል፣ ከሻአቢያም ጋር ገጥሞ ይፎክራል። ገሚሱ ትግሬ ደግሞ አፋር ውስጥ ተቀምጦ ወያኔን ልወጋ ነኝ በማለት ከራሱ ከአቢይ አሕመድ ጥይት ስንቅ እና ትጥቅ ተቀብሎ ትግሬን ገድሎ ለመንገሥ ይሸልላል። ገሚሱ ትግሬ ደግሞ አዲስ አበባ ተቀምጦ ሚዲያ ላይ በወጣ ቁጥር ኦሮሞን ያስደሰተ ይመስል ዐማራ ላይ ሲያስታውክ፣ ሲያቀረሽም ይውላል። እኔ ግን ስለዚህ ጉዳይ ልጽፍ አይደለም የመጣሁት። ብትቀበል ተቀበል፣ ባትቀበል ተወው የራስህ ጉዳይ ነው ትግሬ እንደሁ የሚድነው ትእቢት፣ ጉራ፣ ሽለላ፣ ቀረርቶ፣ በባዶ መኮፈሱን ትቶ በባህል ቢሉ በሃይማኖት አንድ ከሆነው ከጎረቤት ወንድሙ ከዐማራው ጋር ከልብ ይቅርታ ጠይቆ ታርቆ በሰላም መኖር ሲችል ብቻ ነው። ያለበለዚያ አንዴ ለሻአቢያ፣ ሌላ ጊዜ ለኦሮሙማው፣ ከዚያ ለምዕራባውያን፣ የሆነ ጊዜ ደግሞ ለአረብ እየተገረድክ ስትለፈልፍ ብትውል የባሰ ከመደክረት፣ ከመክሰር፣ ከመጫጫት በቀር ምንም አታመጣም። ኢትዮጵያን እየረገሙ በኢትዮጵያ ውስጥ በረከት አግኝቼ እኖራለሁ ማለት ዘበት ነው። ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ ብለህ ፎክረህ ስታበቃ ራስህ ዳውን ሆነህ ቀረህ። እኔ ስናገረው ይመርራል እውነቱ ግን ይሄ ነው። ትናንት መሬት አይንካን ይሉ የነበሩ ትግሬዎች ዛሬ የአሸቦ ዕቃ መስለው የሚታዩት እንዲሁ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም። ቁጣ ነው። ርግማን ነው። ትግሬ በድፍረት ኢትዮጵያንም፣ ዐማራንም፣ ኦርቶዶክስንም ይቅርታ መጠየቅ አለበት። ሌላ ምርጫም፣ አማራጭም የለም። ሰው በባዶ ሆዱ አሁንም ድረስ እንዴት መርዝ ይረጫል?
"…ዛሬ ልጽፍ የፈለግኩት ስለመጪው ጊዜ ነው። በመጪው ወራት ጦርነት ራቡ እንዳለ ሆኖ ለሁላችንም የከፋው ቀን እየመጣ ይመስላል። መጪው ጊዜ እየከበደም ነው። በአሁን ወቅት ጭንቀት የሌለበትን የዓለም ክፍል የሚነግረኝ የለም። ድሮ ድሮ አሜሪካ መግባት ገነት መንግሥተ ሰማያት የመግባት ያህል ይቆጠር የነበረው፣ ዲቪ ከደረሰኝ ተብሎ ለእንጦጦ ኪዳነምህረት፣ ለቅዱስ ዑራኤል ስለት ሁላ ይገባ የነበረበት አሁን እንዲያ ብሎ ነገር የለም። አይደለም በመከራ አሜሪካ የገቡቱ አሜሪካዊ ነን ያሉ ቢሊየነሮቹ እነ ኤሎን ማስክ እንኳ ዲፖርቴሽን የሚያስጨንቃቸው ዘመን ነው እየመጣ ያለው። አውሮጳም፣ እስያም እንደዚያው ነው። በእስራኤል የሚኖሩ ደግሞ ይከፋባቸል፣ የሚበሉት፣ የሚጠጡት፣ ሥራ ሳያጡ ኑሮአቸው ሁሉ የሰቀቀን፣ የአይጥና የድመት የመሰለ ኑሮ ነው የሚኖሩት። የአምቡላንስ ድምጽ፣ የአደጋ ጊዜ ደወል ድምጽ በተሰማ ቁጥር ከአንዱ አረብ ሀገር ሚሳኤል ተተኮሰ ብለው ወደ መደበቂያ ጉድጓድ መሸሽ ነው። ዩክሬንና ሩሲያ ብቻ ሳይሆን መላው አውሮጳም በስጋት ላይ ነው ያለው። በእስያ ሰሜን ኮሪያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን፣ ሕንድና ፓኪስታን ወዘተም በሰቀቀን መኖር ነው። በአፍሪካም እንደዚያው ነው። ዓረቡም ሁሉ ጭንቅ ላይ ነው። እሳትና ጎርፉም ሌላው አስጨናቂ ነገር ነው።
"…ወደ ሀገራችን ስንመጣ ደግሞ ከሁሉ ይከፋል። ይብሳልም። ሀገሪቱ በሕፃናት እጅ፣ ባላዋቂዎች እጅ፣ በማይሞች እጅ ወድቃ እንኩትኩቷም እየወጣ ነው። የአደባባይ ሰው ነው፣ ብዙ ሰው ያውቃል፣ ችግር በደላችንን ብንነግረው ችግራችንን ነግሮ ሊያቃልልን ይችል ይሆናል በማለት ከመላው ኢትዮጵያ ዘግናኝ ዘግናኝ ችግሮች፣ የሚያስለቅሱ፣ እንቅልፍ የሚያሳጡ ሰቀቀናም ታሪኮች በገፍ ይደርሱኛል። ወጥተው እንዳይለምኑ ሼም የያዛቸው፣ የሀገሬ ሰው ትንሽም ቢሆን ሰውን የሚረዳው፣ የሚደግፈው ጎስቆል፣ ቆሸሽ፣ ከሳ ጠቆር ስትል ነውና ሰውነታቸው አልጎሳቆል ብሎ፣ እንደወፈሩ፣ እንዳማረባቸው በብዙ ጭንቅና መከራ ላይ ተከበው መድረሻ ያጡ እልፍ ዜጎች ችግራቸውን በሙሉ እየላኩ አናቴ ላይ ይከምሩታል። በእነሱ ባልፈርድም ሀገሪቱ የገባችበትን ቅርቃር ግን እያየሁ ከሰውነት ተራ እየወጣሁ ነው። ማድያት እየወረረኝ። የአተነፋፈስ ችግር እየገጠመኝም ነው። ቪድዮ መክፈት አቁሜያለሁ። ልቤን ያፍነኛል። ሕፃናት ልጆችን ይዘው፣ ሕመምተኛ ቤተሰቦችን ይዘው በየቤቱ የሚቃትቱ ዜጎችን ሰቆቃ ማየት በእጅጉ ያደክማል። ከምር ያደክማል። በድጋሚ እማጸናችኋለሁ ምንም አልፈጥርላችሁምና እባካችሁ ለአእምሮዬም እየከበደኝ ነውና አትላኩልኝ። በማሪያም፣ በአላህ። ተረዱኝ።
"…አሁን ከሐምሌ በኋላ ደግሞ ይብሳል። የከፋው ነገር የሚመጣው ከአሁን ጀምሮ ነው። የብልጽግና አገዛዝ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ አበዳሪ ድርጅት ጋር በገባው የአራጣ ብድር የተነሣ አይገቡ ኪሳራ ውስጥ ሰተት ብሎ ገብቷል። ተበዳሪው በተበደረው ገንዘብ ፋብሪካ ከፍቶ፣ አትርፎ ባገኘው ትርፍ ብድሩን ከመክፈል ይልቅ በተበደረው ብድር የወንዝ ዳር ልማት፣ መናፈሻ፣ ሪዞርት እየከፈተ ዓለሙን ሲቀጭ፣ ከቱርክ፣ ከኢራን፣ ከኤምሬትስ፣ ከቼክ ሪፐብሊክ፣ ከቤላሩስ ወዘተ ድሮን፣ ቦንብና ጥይት እየገዛ የተበደረውን ብድር እያፈነዳ ስለጨረሰው ገንዘብ የለውም። ተበዳሪው በብድሩ ቤተ መንግሥት እየገነባበት ስለሆነ ዕዳውን መክፈል አልቻለም። በዚህ ምክንያት የተነሣ አራጣ አበዳሪው ድርጅት ሰቅዞ ይዞታል። እናም ኦሮሙማው ኦህዴድ ብልፅግና ብድሩን ለመክፈል ሲል የቤት ዕቃ፣ ቋሚ የአያት አባቶቹን ቅርስ ለገበያ እያቀረበም ነው። አየር መንገድ፣ ቴሌ፣ ባንክ ወዘተ ለሽያጭ ቀርበዋል።
"…አገዛዙ አሁን ምንም ገንዘብ የለውም። እንደ ድሮው በእርዳታ ስም እንኳ የሚመጣ ዶላር፣ ፓውንድ አይደለም ዱቄት እና ዘይትም እንኳ የለም። ወፍ የለም። በፊት በፊት ለራበው ቤተሰብህ ብለው እጃቸውን ይዘረጉ የነበሩ ሀገራትም ራሳቸውም የከፋ ችግር ላይ እየወደቁ ስለሆነ የበጀት ድጋፍ የሚባል እንኳ ቀርቷል። በአጠቃላይ ገንዘብ ጠርሮበታል። ከፍተኛ ግብር በመገበር የሚታወቀው የዐማራ ክልልም አሁን በገባበት ቀውስ ምክንያት ከዐማራ ክልል ግብር መሰብሰብ አልተቻለውም። ከትግራይማ ምንም የለም። ከትግራይ የምትገኝ ወርቅ ቢጤ ብትኖርም እሷኑ ህወሓትና ሻአቢያ ናቸው የሚቀራመቷት። ወደ ፌደራል የሚላከውም ብጥስጣሽ ወርቅ ከዚህ ግባ የሚባል አይደለም። መሶቦ ሲሚንቶን ጨምሮ ፋብሪካዎች በትግራይ እየተዘጉ ነው። ከሁለት…👇①✍✍✍
"…ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤…" ሉቃ 4፥23
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…አይ ፍሎቲካ…!
"…አዛኜን የሴራ ፎሎቲካንማ ጠበቃው መዓረይ ይፎትልካት። የተንኮል ፎለቲካን መዓረይ ይሥራት። አባቴ ይሙት ፎለቲካን አስረስ ይጫወታት። አርበኛ አበበ ይሄን የመዓረይን አሽሙር ሲያይ ሲመለከት ምን ይል ይሆን…? 😂 ባውቀው ደስ ባለኝ ነበር።
"…ከጎንደር ኢያሱ ትልቁን፣ ከወሎ ሔኖክንና አበበን፣ ከሸዋ ዳግማዊ የሚባል አርበኞች ላይ ዘመቻ አስከፍቶ ሲያስቀጠቅጣቸው የከረመው የጠበቃ አስረስ፣ የዐማራ ፋኖ በጎጃምን ከአፋብኃ ገንጥሎ ለይቶ አውላላ ሜዳ ላይ ያቆመው አስረስ፣ በእነ በአበበ እና ሄኖክ ላይ ክፍት አፍ የአገው ሸንጎ የቅባት ሠራዊት ሲያዘምትበት የሚውለው አስረስ ስንትና ስንት ዘመቻ አስከፍቶ ታግሎ ሊጥለው ያልቻለውን የምሬ ወዳጆን ቀኝ እጅ ፋኖ አበበን ዛሬ በፌስቡክ ገፁ ላይ ስሙን እንኳ አበበ ብሎ ሳይጽፍ ፎቶውን ለጥፎ እንኳንም ተወለድክ ይልልኛላ። 😁 ቀጣፊ ሁላ። አታስመስል።
"…አትፎግሩ። ጎጃሞች፣ የጎጃም ዐማሮች በጊዜ ንቁ። ብታምኑም ባታምኑም እነ መዓረይ ጎጃምን ከዐማራ ገንጥለው እልም ያለ በረሀ ላይ አስቀምጠውታል። መራር ሃቅ ቢሆንም ዋጡት። ከእነ አርበኛ ሀብቴ፣ ከባዬ፣ ከምሬ፣ ከሄኖክ፣ ከአበበ፣ ከደሳለኝና ከእነ ዶር አብደላ ጋር አንሠራም ብለው በጎን እነ እስኳድ ጌታ አስራደንና እነ መከታውን ደጅ ሲጠኑ ነው የሚውሉት። እነ ጌታ አስራደም ሆኑ እነ መከታውም ግን ንቀዋቸዋል። መናቅ ብቻ አይደለም በራቸውንም ከርችመው ዘግተውባቸዋል። አዎ በጎጃም የፋኖ ሠራዊትና የእዝ አዛዦች ነገሩ ገብቷቸው በተጠንቀቅ ላይ ናቸው። እየሆነ ያለውን ሁሉ በትኩረት እያዩ ቀን እየጠበቁም ነው። የአስረስ መዓረይና የእነ ማርሸት መርዝ በጎጃም በቅርቡ ይከሽፋል፣ ሾተሉም ሁሉ ከጎጃም ይነቀላል። ጎጃም ከወንድሞቹ ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ጋር አንድ ሆኖ ያሸንፋል። እስከዚያው…
• 3 : 1
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ዛሬ ለወራት ያህል በትኩረት እየተከታተልኩ መጨረሻውንም ለማየት እየጓጓሁ ስለከረምኩበት በዚያውም ስለተደነቅኩበት፣ ደግሞም ለመጀመሪያ ጊዜ እኔ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት ሳልሰጥ፣ እንዲህና እንዲያ ብዬም ሳልቀበጣጥር፣ የጭቃ ዥራፌንም አንስቼ፣ በሁለት ወገን የተሳለ የእሳት ሰይፍ የመሰለ ምላሴንም በጉዳዩ፣ በአጀንዳው ላይ ሳልዘረጋ፣ ከዳር ሆኜ ጥጌን ይዤ እየታዘብኩ ፍልሚያውን ወደ ፍጻሜው እስከሚያመራው ጨዋታውን እያየሁ ፈጣሪዬንም ስላመሰገንኩበት አጀንዳ ጉዳይ ነው በአጭሩ ለዛሬ በርእሰ አንቀጽ መልክ የምጽፍላችሁ።
"…ከምር እያየሁ ነበር በሀገረ አሜሪካን በቴክሳስ ግዛት በዳላስ የተፈጸመን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያፈነገጠ ተሃድሶአዊ፣ ምንፍቅናዊ ተግባር ምእመናንና ካህናት ውድ የተዋሕዶ ልጆች በአንድነት፣ ተቀናጅተው በህብረት የተቃወሙበትን መንገድ እያየሁ ነበር። እሱን እያየሁ ነበር በሀገረ አሜሪካ ሰፊው አዳራሽ ዘጭ ብሎ እስከ ከአፍ እስገደፉ እስከ አፍንጫው ድረስ በምእመናን ተሞልቶ፣ በአዳራሹ ዐውደ ምሕረት፣ በመድረኩ ላይ አበው ካህናትና ወንድሞች ዲያቆናት፣ ሰባኪያነ ወንጌል ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ግጥም ብለው ከነ ክብራቸው፣ ከነ ሞገሳቸው፣ ከነ ሙሉ ሥልጣናቸው የእረኝነትን ተግባር በበጎቻቸው ፊት ሲፈጽሙ እያየሁ በጣም ነበር የተደመምኩት። አምላኬንም ያመሰገንኩት። ጠያቂ ትውልድ በመፈጠሩም ከምር አምላኬን ነው ያመሰገንኩት።
"…ለዚህ ደግሞ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጊዜ ሰጥተው ጉዳዩን ማለትም አጀንዳውን አየር ላይ በማዋል በመረጃና በማስረጃ ጭምር ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይከበር፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አይጣስ በማለት የቤተ ክርስቲያኒቱ ካህናትና ምእመናንን እንባና ሮሮ፣ ፍትሃዊ፣ ቀኖናዊ ጥያቄን በደስታ በመቀበል፣ የተቀበሉትን ደግሞ ለዓለሙ ሁሉ በማስተጋባት፣ አየርም ላይ በማዋል ሰፊ ተጋድሎ ያደረጉ ሚዲያዎች ነበሩ። ከእነዚህ መካከል ወንድሜ እና አባቴ የኢትዮ ቤተሰቡ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው፣ ወንድሜና መምህሬ ቀሲስ ነዋይ ካሳሁን፣ አሁን በቅርቡ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን እቅፍ ተመልሶ ለቤተ ክርስቲያን ድምፅ በመሆን በቲክቶክ በማገልገል ላይ የሚገኘው የቀድሞው ፓስተር የአሁን አቶ ቢንያም ሽታዬ በዋነኝነት ተጠቃሽ ናቸው። የነብርን ጭራ ነክሰው ባለመልቀቅ ድንቅ ውጤት ያመጡ ጀግኖችም ብዬአቸዋለሁ። እውነትን ከነ ቡግሯ ነው የገለጧት።
"…የነገሩ መነሻ መንስኤው ፖለቲካ ነው። ዘረኝነትም ነው። ገንዘብም ነው። የፀቡ መንስኤ ማናለብኝነት፣ ድፍረት፣ ደንታቢስነትና ምንፍቅና የፈጠረው ነው። ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር በሚሉ የተዋሕዶ ልጆችና አባቶች በአንድ ወገን፣ በአንድ በኩል፣ አይ የምን ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይጠበቅ ነው? እናንተ የምትጠየቁትን ገንዘብ አምጡ ስንል ማምጣት፣ ለሆዳችን ምግብ ውኃ፣ የዕለት ጉርስ፣ የዓመት ቀለባችንን መስጠት ብቻ ነው። እናንተ ምንም አታውቁም፣ ምንም አይገባችሁም፣ እኛ ነን እንደፈለግን እናንተን የመወዝወዝ መብትና ሥልጣን ያለን በሚሉ ጳጳሳትና ጥቂት ካሕናት በሌላ ወገን ሆነው የገጠሙት ግጥሚያ ነው። ሂደቱ አጓጊ ነበር። ቀልብ የሚስብም ነበር።
"…ሁለቱም ኃይላት ፍርድ ሰጪው ሕዝቡ ነውና ጉዳያቸውን ወደ ሕዝብ አምጥተው ለፍርድ አቅርበውትም ታይተዋል። ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር፣ ቀኖና አይሻር፣ ሁሉ ነገር በአግባቡና በሥርዓት ይሁን የሚሉት የቴክሳስ ሀገረ ስብከት ካህናት እና የምን ሕግ ነው ገንዘብ እስካገኘን ድረስ ሌላው ምን አገባው? የምን ቀኖና፣ የምን ምንትስዬ ምንግርግርዬ ነው? ባይ ሊቃነ ጳጳሳት እና ካህናት ሁለቱም ወደ ሕዝብ ወርደው አጀንዳቸውን አስገምግመውም ነበር። እናም ሕዝቡ ፍርድ ሰጥቶ ታይቷል። ፍርዱም ግልጽ ነበር። ካሕናቱ በጠሩት ስብሰባ ላይ አዳራሹ ሞልቶ ሕዝብ ቆሞ ሲከታተል፣ አብሮ አደግ ጓደኛማቾቹ ጳጳሳት የጠሩት ስብሰባ ደግሞ ባዶ ወንበር ሆኖ የጠሩት ሕዝብ ቀርቶ፣ ብቻቸውን ሲቆጡ፣ ሲመሰጋገኑ፣ ሲወዳደሱ የዋሉበት የፍርድ ሒደት ነበር የታየው። ሕዝቡ፣ ምእመኑ ግን ቀላል ነቅቷል እንዴ? ከምር የሚደንቅ ነው። በጎች እረኞቻቸውን በሚገባ እየለዩ ነው የመጡት። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…የጸቡ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ የደቡብ ጎንደሩ የወንቅሸቱ ጆኒ ራጋ ሲሆን እኔ ከዚህ ቀደም ጆኒ ራጋን፣ ግርማ ወንድሙንና ሔኖክ ዘይቴን ልክ አይደሉም ብዬ ስናገር ሀገር ምድሩ ነበር ያበደብኝ። ከኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ አባላት ከሳሚ፣ ከሱሬና ከልዑልሰገድ በቀር ከመምህር ነዋይ ካሣሁን በቀር አንዳቸውም ሓሳቤን ገዝተው ከጎኔ የቆሙ አልነበሩም። በኢትዮጵያ ሰማይ ምድሩን ሲያተራምስ የቆየው ጆኒ ራጋ አሁን ደግሞ ውቅያኖስ አቋርጦ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ፎጭ፣ ሆጨጭ አድርጎ አውጥቶ መሬት ገዝቶ ገዳም ልመሠርት ነኝ ብሎ ሲነሣ ነው ነገርየው ያሳሰባቸው ካህናት እና ምእመናን ለምን? እንዴት ብለው ጥያቄ ወደማንሳት የገቡት። ሀገረ ስብከቱና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ ሰጥተው፣ ድጋፍ አድርገው የነበሩ ቢሆንም ካሕናቱና ምእመናኑ ግን ገንዘቡ እንዴትና ከየት መጣ፣ ሰውየውስ ሥልጣነ ክህነት አለው ወይ? በኢትዮጵያ የሠራው ወንጀል አንሦ እንዴት እዚህ አሜሪካ ድረስ መጥቶ በወንጀል ድርጊት ላይ ይሳታፋል? ወዘተረፈ በማለት ነው በሰነድ የተደገፈ ጥያቄ ያቀረቡት። ነገር ግን ማን ሰምቷቸው?
"…ኦሮሞ እና ትግሬ የሆነ ቄስ ሲያፈነግጥ፣ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ፈቀቅ ሲል የዱላ መዓት ይመዘዝና፣ ሰይፍ ተጨምሮበት፣ ከላይ እስከታች በሞንታርቦ ጭምር በተቃውሞ ምድሪቷ ትናወጣለች። በለው ነው። ነገር ግን ነገዱ ከዐማራ የሆነ፣ ከዐማራም ጎንደሬ ነኝ፣ ወሎዬ ጎጃሜ ነኝ የሚል አካል ተነሥቶ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲጥስ ኦሮሞና ትግሬ ላይ ሕዝብ አስተባብረው፣ ቅዳሴ አስተጓጉለው የተቃውሞ ሰልፍ የሚያስተባብሩት አካላት ከፊት ተሰልፈው ደቡብ ጎንደሬው ራጋ በጥባጭ ቢሆንም ለምን ይነካል? በማለት አዋራ ለማስነሣት ይጣጣራሉ። ጎንደር እኮ የቦዘኔ ሀገር አይደለም። ጎንደር የእነ ሊቀ ሊቃውንት አባ ዕዝራ ሀገር መሆኑን ይዘነጉታል። በዱሮ በሬ ዛሬም ለማረስ ይንደፋደፋሉ። ይሄ ልክ አይደለም ብሎ ከፊታቸው የሚቆምን ኃይል ካገኙም ነክሰው፣ ቧጭረውም ለማስወገድ ይላላጣሉ። ሲበዛ ራስወዳድ፣ ብልጣብልጥ፣ አራዳ ከእነሱ በላይ የሌለ፣ ጨፍኑ እናሞኛችሁ ባዮች ናቸው። ሼምለስ፣ ሰው ምን ይለኛል፣ ሀገር ይታዘበኛል አይሉም። በጭፍን ብቻ ወደፊት ነው። ዱሮ በወያኔ እያሳበቡ፣ ሕዝቡን እንደ በግ እንደኑት ሁሉ አሁንም ጨዋታ ሳይቀይሩ በዚያው በድሮ ታክቲክና ቴክኒክ ለማጭበርበር ይሞክራሉ። ይሄ የማይቻል፣ የማይሞከር ነው።
"…አንድ ባሕታዊ ነኝ የሚል አካል በመንግሥትም በጳጳሳት ሲወደድ፣ ሲወደስ የታየው በዚህ ዘመን ነው። ሀገር ሲጨፈጨፍ ጨፍጫፊውን የማያወግዝ ድልብ ሆዳም ባህታዊ ነኝ የሚል ካድሬ የታየውም በዚህ ዘመን ነው። ባህታውያን መታወቂያ መለያቸው በድፍረት በዳዮችን በመገሰጻቸው ነው። መጥምቀ መለኮትን ነቢዩ ኤልያስን ለሞትና ለእስር የዳረጋቸው፣ ለግዞት ያበቃቸው ነገሥታትን በድፍረት መገሰጻቸው ነው። የዘመኑ ባሕታዊ ይለያል። የዘመኑ ባሕታዊ ነኝ የሚል እንደ ሀብታም እስላም ከሁለት ሦስት ሴት ልጅ ሲፈለፍል ነው የሚታየው። ዋሻ ትቶ ቪላውስጥ ነው የሚኖረው። በርገር እንጂ ቆሎ ንክች የማያደርግ ባሕታዊ የታየው በዚሁ በእኛ ዘመን ነው። የ40 ሚልዮን ብር መኪና የሚያሽከረክር ቀፋይ ባሕታዊም የታየው በእኛው ዘመን ነው። የዘመኑ ባሕታዊ እን ጴንጤ ፓስተሮች ያለ…👇①✍✍✍
“…ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!” መክ 10፥16
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
•እኩል ፍረዱ… አታዳሉ…!
"…በዚህ 2 ዓመት ውስጥ ያገኘውን የፋኖ መሪነት ዕድል በመጠቀም ገንዘብ ከማካበት በተጨማሪ 5 የተለያዩ ምስኪን የጎጃም ዐማራ ሴቶችን በማነውር ልጅ በልጅ የሆነው ከኮተቤ አዲስ አበባ በቀጥታ ጎጃም በመግባት የዐማራ ፋኖን በመቀላቀል ጀግና ጀግና የዐማራ ፋኖዎችን በሴራ ሲያቀጥፍ የኖረው፣ የወጣቶችን ሲገድል፣ ባንክ ቤቶችን ሲዘርፍ የከረመውንና ከዘረፈው ብር ጋር በብዙ የጎጃም ዐማሮች ተጋድሎ በቁጥጥር ስር የዋለውን የትግሬ ኮሎኔል ከእስር ያስመለጠው የቆየ በመጨረሻም ሞላ የንፁሐን ደም ፈርዶ አሁን በሌላ አፀያፊ ነውር በዐፋጎ ዘብጥያ ወርዷል።
"…የቆየ ሞላ ከዚህ በፊትም በሌላ ወንጀል ተይዞ በቁጥጥር ስር ውሎ ዘብጥያ ወርዶ የነበረ ቢሆንም እነ አርበኛ ዘመነ ካሤ ጭምር ከእስር እንዲፈታ ሞክረው ነገር ግን ወንጀሉ በዝርዝር ሲነገረው ዘመነም እንዲያማ ከሆነ እንግዲያው እንዳሻችሁ አድርጉ በማለት ጣልቃ ከመግባት መቆጠቡ ይታወሳል። የቆየ በወቅቱ ዘብጥያ በነበረ ሰዓት የአገዛዙ ሰላይ በመሆን ተጠርጥራ እዚያው ዘብጥያ ከነበረች እስረኛ ላይ ደርሶባት አስረግዞ ይኸው የልጅ አባት ሆኗል። ጉድ እኮ ነው።
"…አሁን ግን የቆየ ሞላ የምስኪን የጎጃም ገበሬ ሴት ልጃገረድ ልጆችን ሳይሆን የዐፋጎ የብርጌድ አመራር ሕጋዊ ሚስትን አስገድዶ በመድፈሩ በድርጅቱ እርምጃ ተወስዶበት ዘብጥያ ወርዷል። ይሄ እርምጃ መልካም ነው። ነገር ግን ማርሸትም ሰሞኑን እንደ የቆየ ሞላ አስገድዶ ሴት ቢደፍርም ፖለቲካችን ይበላሻል በማለት በአስረስ ሽፋን ሳይታሰር ቀርቷል። ይሄ በአገው ልጆችና በምሥራቅ ጎጃም ልጆች መካከል ልዩነትን እየፈጠረ ስለሆነ በአስቸኳይ ይስተካከል። ፍርድ ለሁሉም እኩል ነው መሆን ያለበት።
•አሁን እንደምን አደርሽ ሚስቴ ወልዳለች ተረትን ተዉትና የተበላሸ የነወረ ቤታችሁን አጽዱ።
ምልክት ነው…
"…በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትግሬዎች ከተደበቁበት፣ ወጥተው በውጭ ሃገራት መንግሥታት ደጃፍ ሰልፍ ማድረግ መጀመራቸውን ባያችሁ ጊዜ ሁላችሁ ጦቢያውያን ያ ቀፋፊ የተለመደ ደም የሚያፋስስ ጦርነት በኢትዮጵያ ሊጀመር እንደሆነ ዕወቁ። ተረዱም።
"…በጥቂት በጥቂት የሚጀምረው የትግሬዎች የአደባባይ ሰልፍ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ደግሞ ሰማይ ምድሩን በስቶፕ ትግራይ ጄኖሳይድ ያጥለቀልቁታል። እነ ዶር ቴዎድሮስ አድኀኖምም Live እያለቀሱ አቤቶታቸውን ለመላው ዓለም ያቀርባሉ። ዓለሙም ሁሉ ይሰማቸዋል። የተባበሩት መንግሥታትም የማያቋርጥ ስብሰባ በትግራይ ጉዳይ ያለመታከት ይቀመጣል። እነ አልጀዚራ፣ ቢቢሲና ሲኤንኤንም ከትግራይ እኩል ይጮሃሉ።
"…ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት አገኘሁ ተሻገርን ከፌደሬሽን ምክርቤት ለማጽዳት "ሰክሮ ከሂሊኮፍተር ላይ እዘላለሁ ብሎ ወድቆ ተሰብሮ ነው" የሚል ምክንያት ሰጥተው ዱባይ ሃኪምቤት ካሸጉበትም ቆዩ። አቢይ አሕመድም ደመቀ ዘውዱን ሊበላው ይችላል የሚሉ መተርጉማንም አሉ። የሆነው ሆኖ ዐማሮች የሚመጣውን እንደ አመጣጡ ለመመለስ ይቻላችሁ ዘንድ ታጥባችሁና ታጥናችሁ ወደ ሰሜን በመመልከት ተዘጋጅታችሁ ተብቁ።
"…የጎጃሙ የእነ አስረስ ቡድን በአስረስ መዓረይ በኩል አስቀድሞ ነው የተናገረው። ወያኔ ዳግም ጦርነት ብትመጣ አንዲት ፍሬ ጥይት አንተኩስባትም ብሏል። ለወያኔ ወልቃይቶች፣ አሕፋዶች እና መከላከያ አሉላቸው። ለጎንደር ዐማራ ደግሞ አፋብኃ አለለት። ደመቀ ዘውዱና መከላከያ ከተከዜ ዘብ ጋር ሆነው ከወያኔ ጋር ሲተጋተጉ አፋብኃ 😂 በወሎም እንደዚያው። ከዚያ እነ አስረስ መዓረይ በእነሱ ቤት ሊያተርፉ።
"…ለማንኛውም የትግሬ ሴቶችና ወንዶች ከዓመታት በኋላ ሰሞኑን አደባባይ መውጣት ጀምረዋል። ይሄ ጦርነቱ አይቀሬ ያስመስለዋል።
• ይደፈርሳል ግን ደግሞ ይጠራል።
ማስታወሻ…
"…ዓመቱ ደረሰና ውዷ ባለቤቴ የምትዘክራቸው የአብርሃሙ ሥላሴ ዓመታዊ በዓል ዋዜማ ሆነ። ወጉ እንዳይቀርም በስደት ሀገር ያገኘናቸው ወዳጅ ዘመድ ጓደኞች ሁሉ ተጠርተው አብረን እናሳልፋለን። አምና መረጃ ቴቪ እያለሁ እረፍት እንደወሰድኩት ሁሉ ዘንድሮም በዘመድ ቴቪ ፈቃድ ወስጄ ዛሬ ሳምንታዊው የነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር መርሀ ግብሬን አላቀርብም ማለት ነው። በስንት ስለት የሚገኙ እንግዶቼን ጠርቼ ለእንግዶቼ የሌለ ጠብ እርግፍ እያልኩላችው ነው። አቤት በዝክሩ ላይ ጠላና ጠጅ ቢኖር ደግሞ እንዴት ያለ አሸወይና ይሆን ነበር። ለማንኛውም ሳምንት ወይም በመሃል አንዱን ቀን ብቅ እል ይሆናል። የዚያ ሰው ይበለን።
"…እስከዚያው ግን ትናንት በጀመርኩላችሁ ርእሰ ጉዳይ ላይ ስትወያዩ እንድታመሹ የሰነዱን አንድ ሁለት ገፅ እለጥፍላችሁና ስትወያዩ ታመሻላችሁ። በነገራችሁ ታች እኔ ትናንት የሰነዱን የመጨረሻ ገፅ ከለጠፍኩላችሁ በኋላ በጎጃም በአፋጎ ውስጥ የሌለ ትርምስ መፈጠሩን እያየሁ እየሰማሁም ነው። የማከብረው አርበኛ ዝናቡ ልንገረውም በኋትስአፕ የውይይት መድረኩ ላይ ቀርቦ " ይሄን ሰነድ አሳልፎ ለዘመዴ የሰጠውን ሰው በ10 ብር ገመድ ነው የምናንጠለጥለው" ሲል እየሰማሁት እንደመደንገጥ ሲያደርገኝ ነበር። ምንነካህ ዝኔ? ኧረ ኢደብራል። ይሄ ደስስ አይልም።
"…በጎጃም በቀጣይ በሞዓ ተዋሕዶ ስም ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች የሆኑ የአፋጎ ታጋይ ፋኖዎችን ለመጨፍጨፍ እነ አስረስ፣ እነ ፓስተር ዳዊት እና ፓስተር ተሰማ ሁሉን መጨረሻቸውን ደርሼበታለሁ። ደግሞስ መረጃ ለዘመዴ ማነው የሰጠው ይባላል እንዴ? በፍጹም እንዲያ አይባልም። የእኔ ወፎች እኮ በምስጢራዊነታቸውም በሉ በሁለንተናቸው የታወቁ፣ ረቂቃን የሰለጠኑም ፈጣኖች ናቸው። የእኔ ወፎች ሰሞኑን እነ ግርማ ካሣ ሸዋዎችንም፣ ወሎዎችንም ሰብስበው ሲያወያዩ እኔም እነሱም አብረን ነበርን። የትኛውም ምስጥሪዊ የተባለ ጉዳይ ላይ እኔና ወፎቼ አለን።
"…በጎጃም የቆየ ሞላ ሴት ደፍሮ አሁን ስለሺ ዘብጥያ ሲያወርደው እዚያው ነኝ። እነ አስረስ የቆየ ሞላ ባለ ትዳር ሴት ቢደፍርም ይፈታ፣ ደግሞ ለሞላ ሴት። ከተደፈረችዋ ሴት ይልቅ የቆየ ሞላ ለፖለቲካው ይጠቅመናል ብለው እየዘበዘቡ ሲነጫነጩም እዚያው ነኝ። ገና አምላከ ዐማራ ሾተላዩን ሁሉ ይነቃቅለዋል። በነገራችን ላይ ታች ያለው የጎጃም የዐማራ ፋኖ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ከአፋብኃ እንደወጣም አልተነገረውም። ሠራዊቱ አፋብኃ ውስጥ እንዳለ ነው የሚረዳው። ዘመቻው እና ሰነዱ የተዘጋጀው ሠራዊቱ ከአፋብኃ የመለየትን ጥቅም እንዲረዳ ግንዛቤ ለመፍጠር ሲሉ ነው የተዘጋጀው። ግን አሁን የሰነዱን እኔ ማውጣት በጎጃም ቀውጢ ነው የፈጠረው።
"…ማርሸት ፀሐዩ የዐማራ ፋኖ በጎጃም አክቲቪስቶችን ሰብስቦ ከአፋብኃ ወጥተናል፣ ቀጥሎ የሚዲያ ዘመቻ ሊከፈትብን ስለሚችል ሁላችሁም ለጨበጣ ውጊያ ተዘጋጁ ሲላቸው እኔና ወፎቼም አብረን ነበር ተሰብስበን የነበርነው። የማከብረው ወዳጄና ወንድሜ ሞገሴ ሽፈራውም እዚያው ነበር። ባዶ ጭንቅላት የኦንላይን መተተኛው አደራው ዘላለምም እዚያው ነበር። አሻራ ሚዲያዎችም እዚያው ነበሩ። ከሁሉ የገረመኝ ወሎዬው አክባሪዬ አሳዬ ደርቤም ከማርሸት ፀሐዩ መመሪያ ሲቀበል ሳየው በሳቅ ነው የሞትኩት። አሳዬ ችግሩ ይገባኛል። በዚህ ድርጊቱ እሱንና ልጆችን የሚረዱት ሰዎች ሁሉ እየራቁት እንደሆነ ነው የሚነግሩኝ። አሳዬ ከከፍታህ አትውረድ። ከሕዝብ ጎን እንጂ ከኮሚቴ ጎን አትቁም። ወይ ጨበጣ…!
"…ሰነዱን የላካችሁልኝ እዚያው ከአመራሩ ውስጥ ያላችሁ መሆናችሁ ይታወቃል። እናም አሁን በዚህ ሰነድ ምክንያት በጎጃም ዐማሮች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ታጋዮች ላይ ጭፍጨፋ ለመፈጸም አስባችሁ ከሆነ ለእኔ ሰነዱን የላካችሁልኝን በሙሉ በአደባባይ እንደማሰጣችሁ ይታወቅ። ይሄን ሰነድ ስትልኩልኝ ተንኮል አስባችሁ ከሆነ ለተንኮሉ በእኔ ይብሳል። እናም እንደሰለጠነ ሰው ሁኑ። በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በኋትስአፕና በቫይበር፣ በኢሞም፣ በስልክም እየተወያየኋችሁ፣ እየተሰባሰባችሁ ስታበቁ እንዴት ምስጢር ወጣ አይባልም። የአፋጎ ሾተላይ አመራሮች ለመሰልጠን ሞክሩ።
"…ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ የተለየ ጎጃም ሕይወት የለውም። የዐማራ አንገቱ አንድ ነው። የእነ አስረስ መዓረይ መንገድ ለዐማራ መከራውን ነው የሚያረዝመው። እነ ግርማ ካሣ የሚመሩት የሸዋ እና የወሎ ፋኖም እንደ ጎጃም ይሸወዳል ብዬ አልገምትም። እነ አበበ፣ እነ ሄኖክ፣ እነ ደሳለኝ፣ እነ አብደላ ሞኞች አይመስሉኝም። ገንዘቡን ተቀበሉ፣ ምስጢራችሁን ግን ቅበሩ፣ ጠርቁሙትም። በሁለት መቶ ዶላር ልምራችሁ፣ ልዘዛችሁ የሚሉትን አትቀበሉ። ከሁሉም ተስፋዬን የሚያለመልመው በጎጃም የታችኛውና ወሳኙ የፋኖ ክፍል የነቃ፣ የበቃ መሆኑ ነው። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ውጤቱን አብረን እናየዋለን። እነ አስረስም አይናቸው እያየ፣ ጆሮአቸውም እየሰማ የዘሩትን ያጭዳሉ። መዝግቡልኝ።
"…እየተወያያችሁ አምሹ…
"…ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል።” ኢሳ 45፥16
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
እያመመው መጣ …
"…ከማጠቃለያው እንጀምራለን። የዐማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች የባጠው ይፈንዳ፣ የመጣውም ይምጣ ብለው በአቋማቸው ገፍተው ዓላማቸውን ይፋ ወደማድረጉ ተቃርበዋል።
"…አፋጎዎች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የማብራሪያ ሰነድ የሚል ከ3ቱ ተለይተው ብቻቸውን የሚታገሉበተን አዘጋጅተዋል። አሁን ላይ ዘጠኝ ዘጠኝ አመራር መድበው ወደ ሁሉም የጎጃም ፋኖ ክፍለጦሮች አራት አጀንዳ ሰጥተው አሰማርተዋል።
አጀንዳዎቹም፦
1ኛ. ሞዐ ተዋሕዶ እነ የኔታ ገብረ መድኅን ጠላታችን ናቸው። ትግላችንንም ሞዐ ተዋሕዶ ሊጠልፈው ነው። እናም ለፍልሚያ እንዘጋጅ። (በነገራችን ላይ ሞዐ የሚሉት የጦስ ዶሮ ፍለጋ ነው)
2ኛ. እኛ ጎጃሞች የዐማራ ፋኖ መሪ እንዳንሆን ያደረጉን ፀረ ጎጃም የሆኑ ቀጠናዎች ናቸው። እነሱን ለይተን አውጥተን ለጎጃሜ ሁሉ ግንዛቤ ማስጨበጥ አለብን። ሠራዊቱም ዝግጁ ይሁን። በተጠንቀቅም ይቁም።
3ኛ. እኛ ጎጃሞች የምንመራው የራሳችን ድርጅት ያስፈልገናል። እናም ድርጅታችንን ልንመሠርት ነውና ሁሉም ይሄን ዐውቆ ዝግጅት ያድርግ።
4ኛ. በዚህ ዕቅዳችን ላይ ጥያቄ ያለው ኃይል በውስጣችን ካለ አስተንፍሱና ይበተን። የሚሉ ናቸው።
"…ሙሉውን በሰፊው እመለስበታለሁ። በያንዳንዱ ስብሰባም ላይ በአካል ስለምሳተፍ የምሰማውን እና የማየውን ሁሉ ለእናንተ ለወዳጆቼ እነግራችኋለሁ። የእነ አስረስ መዓረይን አካሄድ እንዴት አያችሁት…? …አርበኛ ዘመነ ካሤስ አቋሙ ምን ይሆናል ብላችሁ ትገምታላችሁ…? ይሄ ነገር ያለእሱ ዕውቅና ይካሄዳል ብላችሁ ትገምታላችሁ…? ጻፉ እስኪ።
"…በጨዋ ደንብ አስተያየት መስጠት ይቻላል። ነገር ግን ሸንጎአዊ ጋጠወጥነትህን ይዘህ በቤቴ መጥተህ እየተንተባተብክ አፌን እከፍታለሁ የምትል ሰገጤ 100 ኪሎ ፋራ ካለህ ያው እንደተለመደው እቀስፍሃለሁ። ሰምተሃል።
• 3 : 1
• ይሄንንስ የኦሮሙማ ዜና እንዴት አያችሁት…?
"…በዚህ በብልፅግና አሕዛባዊ አገዛዝ የሰንበት መሻር ዜና ላይ የአንድ የ50 ሰው አስተያየት ከተቀበልኩ በኋላ ግን በቀጥታ የምንሄደው ከሦስቱ የዐማራ ግዛት የተገነጠለው አስረስ መዓረይ የሚዘውረው መሪ አልባው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ብቻውን ዐማራን የሚወክል እና ዐማራን ሁሉ የሚመራ በእርሱ ስር የሚጠረነፍ አዲስ የዐማራ ፋኖ ፓርቲ ሊመሠረት መሆኑን የሚያመላክት አንድ ያዘጋጀው ሰነድ እዚያው ጮቄ ተራራ ላይ ሆኜ ስለደረሰኝ ያንኑ የደረሰኝን ሰነድ ለእናንተም ትመክሩበት ዘንድ በስሱ አካፍላችኋለሁ።
• መጀመሪያ ግን ይሄንን እስከዛሬ በችግኝ ተከላ፣ በማስ ስፖርት፣ በሰላማዊ ሰልፍ ሲሽሩት የቆዩትን ዕለተ ሰንበት አሁን ደግሞ በሥራ ልናሳልፈው ነው የሚለውን እንዴት እንዳያችሁት እንድትነግሩኝ ፈልጌ ነው። የጌታ ልጆች ቀላል አፈሉ…😂
መልካም ከዚህ እንጀምር…
• ነአና ይሄ ሰው እንዴት ሆነ ይሆን…?
፩ኛ፦ ሂሊኮፕተሯ ተከስክሳስ ሌሎች ተርፈው እንዴት እሱን ብቻ ሊጎዳ፣ ሊደቅ፣ እንክትክቱ ሊወጣ ቻለ…?
፪ኛ፦ አገኘሁ ያለበትን ሂሊኮፕተር መትተን ጣልናት ያሉት አፋሕዶች ናቸው። እነ ፋኖ ደረጄ በላይ ማለት ነው። እነ ጌታ አስራደ፣ እነ ፕሮፌሰር ዲያቆን ኢያሱ፣ እነ ፓስተር ምስጋናው፣ እነ አያሌው መንበር… መልካም ተመትቶ ተጣለ በተባለው ሂሊኮፕተር ውስጥ ጎንደሬ ብአዴን መትተው በመጣላቸው ጎንደሮቹ አፋህዶች ምን ይሰማቸው ይሆን…?
፫ኛ፦ ይሄን ሂሊኮፕተር የጎጃም ፋኖ ቢመታው እና ቢወድቅ ከሰኔ 15 ለቀስተኞች ይነዛ የነበረውን ጩኸት አስባችሁታል…? …ስኳድ ግን አገኘሁን ሰብሮ ሰባብሮ አስቀምጦ ዝም፣ ጭጭ፣ ነው ያለው። እጄን በእጄ እያለም ነው አሉ።
"…የሆነው ሆኖ ገሌው ለመጣ ለሄደው መገረድ ልማዱ የነበረው አይተ አገኘሁ ተሻገር ከምን ደርሶ ይሆን…?
~ በቁጥር 50 ሰው አስተያየት ከሰጠ በኋላ አዲስ የመወያያ ርእስ ደግሞ ጽፌ ✍✍✍እለጥፋለሁ…
• በእውነት ነኣ…!
"…እስከአሁንም ሙሉ በሙሉ "…ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ሰቆ 3፣ 22-23
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም…
"…አሁን ደግሞ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ርእሰ አንቀጹን መነሻ በማድርግ የእናንተ ሓሳብ የሚኮመኮምበት ሰዓት ነው። በጨዋ ደንብ፣ ያለ ፀያፍም ስድብ ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ የግል አስተያየታችሁን መስጠት ትችላላችሁ።
"…በተለይ ሀገሪትነ ትግራዮች ስሜታችሁን ተቆጣጥራችሁ በጨዋ ደንብ በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ሞክሩ። በግብር፣ በታክስ፣ በቅጣት ክፍያ ጉዳይም ምከሩ። ቤተ ክርስቲያን ግብር ትገብር፣ ታክስ ትክፈል የሚለውንም ተወያዩበት።
• ጀምሩ…✍✍✍
👆②✍✍✍ …ወገን እንደ ገና ዳቦ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የዐማራ ነጋዴም ከክልሉ ነቅሎ ተሰዷል። በኦሮሚያ ያለው ነጋዴም በማያልቅና በማያቋርጥ ሁሴን ቦልት በሆነ መዋጮ ተማርሯል። አጠቃላይ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ሾቋል። በኢትዮጵያ ምርታቸውን አምርተው ከታሪፍ ነፃ በአሜሪካ ገበያ ይሸቅሉ የነበሩ ኢንቨስተሮችም አሜሪካ የአጎዋውን ከታሪፍ ነፃ ዕድል በትግራዩ ጦርነት ምክንያት ስለከለከለች ከኢትዮጵያ ነቅለው እየወጡ ነው። ቀደም ሲል ወያኔን አስደንብረው ከኦሮሚያ ለማባረር ሲሉ እነ ጃዋር፣ አቢይ፣ ለማና ሽመልስ በኦሮሚያ ያስነሱት አብዮት በአቢዮቱም በቄሮ ያወደሙአቸው ፋብሪካዎችን መልሰው አልገነቡም። በዚያ ላይ ገንዘብ እንኳ ቢገኝ የሚገዛው ድሮን፣ ቦንብና ጥይት ነው።
"…እናም ይሄ በኃይለኛው አራጣ ተበድሮ መያዢያ መጨበጫ ያጣው አገዛዝ አሁን ላይ ገንዘብ ከማጣቱ የተነሣ ገንዘብ ለማግኘት ሲል የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም። ሽንቱን ለሚሸና ከሸኖ 20 ብር፣ ከካካ 40 ብር ቫት መሰብሰብ ጀምሯል። በዚህ ቀቀጠለ በቅርቡ ፀሐይ ለሚሞቅ 600 ብር፣ አየር ለሚተነፍስ 3,000 ብር በወር ሳያስከፍል አይቀርም። ጮክ ብሎ ማውራት፣ መንገድ ላይ መሳቅ፣ ማጨብጨብና ማፏጨትም ቅጣት ይጣልበታል ተብሎ ይጠበቃል። አገዛዙ ባልፈቀደው ቀን ባልና ሚስት ግኑኝነት ማድረግ ሁሉ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል። ወደፊት የማይቀጣ ሰው አይኖርም። ማስነጠስ፣ ማፋሸግ፣ መንጠራራት ሁላ ቅጣት ይጣልበታል። ፎሮፎር የታየበት 1ሺ ብር፣ ቋቁቻ የወጣበት 800 ብር፣ ማድያት 350፣ ቡጉር 2ሺ ብር በደንብ መተላለፍ ሊያስቀጣ ይችላል። ያውም በሰልፍ ነው ከፋዩ ሲጋፋ የሚታየኝ። መዝግቡልኝ።
"…ገንዘብ ስብሰባው በዚህ ብቻ አያቆምም። ከፍ ይላል። ከቤተ ክርስቲያን ከሙዳየ ምጽዋት ከምታገኘው መባ እና የአስራት፣ የስለት ገንዘብ ራሱ አካፍሉኝ ብሎ ኦሮሙማው ከቻሳ ብሎ መጥቷል። ለዚሁ ደግሞ መሰናክል እንዳይፈጠርበት የወደፊቱ ዕጩ ፓትርያርክ ነፍሰ ገዳዩን አቡነ ሳዊሮስን በቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅነት አስቀድሞ አሹሟል። በዘመነ ወያኔ ትግሬ፣ በዘመነ ብልጽግና ዐማራ የሆኑት የራያ አዘቦው ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስም የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ተደርገው ተሹመዋል። አሁን ገዳማት እና አድባራትም ሳይወዱ በግዳቸው ከሚያገኙት ገቢ ለአገዛዙ ለቄሳር ይገብሯቷል። ይሄን የሚቃወም ጳጳስ፣ ቄስና ዲያቆን፣ የሰበካ ጉባኤ አባልና የልማት ኮሚቴ፣ ማኅበራትና የሰንበት ተማሪ ይቀፈደዳታል። ነገርየው ጫን ያለ መሆኑን ለማሳየት ሲባልም አንድ ሁለቱን አጋድሞ በማረድ አስደንብሮ ያስከፍላል። እምቢ ያለ ሁሉ እንደ በግ እየተነዳ ወደ ዘብጥያ ይወርዳታል። ዕዳ ያለባቸውና መክፈል የማይችሉ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ካሉ ደግሞ በግልጽ ጨረታ በሐራጅ ለሽያጭ ይቀርባሉ። ቲክቶከሮችና ፌስቡከሮችም ድንጋይ ተሸከመው እባካችሁ ዕዳችንን ከፍለን ቤተ ክርስቲያናችንን ከሽያጭ እናድናት፣ እንታደጋት ብሎ በቴሌቶን ወደመለመኑ ይገባሉ። ገንዘብ ያለውም ፓስተር ሆጭ አድርጎ ይገዛቸዋል። ሟርት አይደለም መዝግቡልኝ።
"…ታይቶ የማይታወቅ ግብር ጠብቁ። ሠራተኛው ከደሞዙ፣ ሎተሪ አዟሪ፣ ሱቅ በደረቴው፣ ሊስትሮው ሁላ ይገብር ተብሏል አሉ። ፔኒስዮን አልጋ ቤቱ ብቻ ሳይሆን ሴተኛ አዳሪዎችና ወንድኛ አዳሪዎችም ጭምር ይገብራሉ አሉ። ከብት በቁጥር፣ በሬ፣ ላም፣ ፍየል፣ በግና ዶሮ ሳይቀር ተቆጥሮ ግብር ይጣልበት መባሉ ነው የተሰማው። በቃ ምን አለፋችሁ የሚቀጥለው ዓመት አራጣ ተበዳሪው መንግሥት እንደ አበደ ውሻ እየተክለፈለፈ ፒፕሉን መድረሻ ነው የሚያሳጣው ተብሏል። ፌስቡከሮች፣ ቲክቶከሮችና ዩቲዩበሮችም 15% ግብር እንደተጣለባቸው ነው የሚሰማው። እናም ቲክቶከሮቹ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ እስከአሁን ይሠሩ ከነበረው ነውር የበለጠ ነውር ለመሥራት ይገደዳሉ። እስከአሁን ድረስ ግብር፣ ታክስ ሳይቆረጥባቸው ዱቄት በመቀባት፣ ዘይት በመጠጣት፣ ቃሪያ በኮልጌት በመብላት፣ በፒጃማ ሻወር በመውሰድ፣ መቀመጫቸውን ውኃ ውስጥ በመዘፍዘፍ፣ እንደ ፍየል በመዳራት፣ ጡታቸውን በማሳየት፣ በወሬ፣ በንግግር ወሲብ ይፈጽሙና ዶላር ይሰበስቡ የነበሩት ኃይሎች አሁን ደረጃቸውን ከፍ የሚያደርጉ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ብልታቸውን ፎቶ አንሥተው ለደንበኞቻቸው በመላክ አንበሳ ያስወርዱ የነበሩ ቲክቶከሮች አሁን የወሲብ ፊልም መሥራት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
"…በእኔ ዘመን ታክሲ የመጨረሻው 85 ሳንቲም፣ 90 እና 1ብር ከ10 ነበር። አሁን 10 ብር ምንም አይገዛም እያሉኝ ነው። ሁለት ፌርማታ 15 ብር ነው የሚያስከፍለው አሉኝ። አትክልት ተራ ሄጄ 2 ኩርቱ ሙሉ 60 ብር ከፍዬ አስቤዛዬን ጨቅ አድርጌ እገባ እንደነበር ዛሬ ላይ ስናገር የሚሰሙኝ የጃንሆይ ጊዜ ነበርክ እንዴ? ብለው እንደሚደመሙ ሰምቻለሁ። መብራት 26 ብር ቆጠረ ብዬ እንደ እብድ የሚያደርገኝ ሰወዬ በዚያም ምክንያት የሳሎን መብራት ይጥፋ፣ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ መብራት እንዳይበራ፣ እንጀራ አንዳንዴ በአንድ ብር ገዝተን እንበላታለን እንጂ ወይ ደግሞ ፓስታና መኮሮኒ፣ ገንፎም እንበላታለን እንጂ በኤሌክትሪክ ደጋግመን መጋገሩ ኤሌክትሪክ እየቆጠረ ነው ብዬ ሳብድ የነበርኩት ሰውዬ አሁን መብራት በወር 4 ሺ ብር ነው፣ ሁለት ሺ ነው ሲባል ስሰማ ጆሮዬን እንዴት ልመን?
"…ኑሮ መክበዱን ባለንበት ሀገርም እያየን ነው። ሱፐርማርኬቶች በየዕለቱ ነው ነው ዋጋ የሚጨምሩት። ይሄንን ሴቶቹ በተለይ በሚገባ ነው ሲያወሩ የምሰማው። በጀርመን እንጀራ እየጋገርን፣ ሽሮአችንን እያንደኮደክን መኖራችን ጠቀመን፣ የውጭ ተመጋቢ አለመሆናችን ጠቀመን እንጂ ጀርመኖቹም ሲያማርሩ እሰማለሁ። ቢሆንም ግን ሥራ አለ። ሥራ ካለ ደግሞ ጤነኛ ሁን እንጂ አይርብህም፣ አይጠማህም። ሥራ እንኳ ባይኖርህ፣ በተለያየ ምክንያት መሥራት ባትችል ቤት ተሰጥቶህ፣ የጤና ኢንሹራንስ ተከፍሎልህ ለቀለብ የሚሆን ገንዘብ ተቆርጦልህ እስከጊዜው ድረስ ትኖራለህ። የእዚህን ሀገሩን አይደለም ከኢትዮጵያ ከአሜሪካም ጋር ለማነጻጸር አልሞክርም።
"…ጦርነቱ ከተጀመረ ብላችሁ ደግሞ አስቡት። የሰሜኑ ጦርነት ከተጀመረ ብላችሁ አስቡት። ኤርትራን እንውጋ ቢባል እንኳ የውጊያ ሜዳው ትግራይ ላይ ነው። ድቅቅ፣ ውድም ነው የምትለው። ትግሬና ኤርትራ አንድ ላይ ከገጠሙ ደግሞ የባሰ ውድመት ይከተላል። መሸሽ ከመጣ ደግሞ አፋርና ዐማራ ክልሎች ይሾቃሉ። አዲስ አበባ የስንቅ አውጣ ተብሎ ይገፈፋል። ኦሮሚያ ዋና የድግሱ ባለቤት ነውና ሽርጉዱ ይበዛበታል። ደቡብ በብዛት ነቢያቸውን ለማዳን ሲሉ ወደ ግንባር ይተምማሉ፣ ይጨፈጨፋሉ። የገንዘብ ወጪው ከባድ ነው። የነፍስ ኪሳራውም ከባድ ነው። በትግራይ እና በዐማራ በድሮን ብዙ ውድመት ይደርሳል። ታላላቅ ጥንታውያን የዓለም ቅርስ አብያተ ክርስቲያናትም ሊወድሙ ይችላሉ። ከባድ ነው። በተለይ ቤተ ክርስቲያን ግብር ለመንግሥት መገበር ከጀመረች በጣም ነገሮች ይከብዳሉ።
"…በተለይ በመግቢያዬ ላይ እንደጠቆምኩት የትግሬ ሰዎች ወደ ሚዲያ መጥተው ያለቅጥ መለፍለፍ፣ መቀባጠር፣ ማቃጠርም ጀምረዋል። አቡነ ማትያስ ሲሞቱ አቡነ ሳዊሮስን ፓትርያርክ ለማድረግ ከኦሮሞዎቹ በላይ እንደ ትግሬ የጓጓ የለም። በጣም ነው የጓጉት። እየተጣደፉም ያሉት። ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሦስት ዓመት የሥራ ጊዜአቸውን ፈጽመው የሥራ ዘመናቸው በማለቁ ነው የወረዱት። ትግሬዎቹ ይሄን እንደ መባረር፣ እንደመሸነፍ፣ ዐማራን ከሥልጣን እንደማስነሣት ነው እየቆጠሩ የሚገኙት። ዐማሮቹ እነ ብፁዕ አቡነ…👇②✍✍✍
መልካም…
"…ሲያነታርከን፣ ሲያወያየን፣ ሲያጨቃጭቀን፣ አእምሮአችንንም ጂምናስቲክ ሲያሠራን የሚያመሽ የተለመደውን ቃሪያ በሚጥሚጣ፣ ኮሶ መተሬ የሆነ የጭቃ ዥራፍ የመሰለውን ርእሰ አንቀጼን ልለጥፍላችሁ ነው።
"…እስኪ አንድ 100 ያህል ሰው ዘመዴ ዝግጁ ነነ ይበልማ።
• ዝግጁ…?
• የመዓረይ ትእዛዝ ተፈጻሚ ሆኗል…!
"…ሔኖክ የአበበ ወንድም ነው። ሔኖክን ጠልተህ፣ ስታስወቅጠው ከርመህ፣ ለምን የዕዝ አንድነቱን የአፋብኃን ውሳኔ በፌስቡኩ ለጠፈ፣ ቲም ገዱ ነው ብለው የጭቃ ዥራፋቸውን ሲለድፉበት ከርመው፣ ንቅንቅ አልል ሲላቸው መልሰው እንኳን ተወለድክ… በልብ መቃብር እየቆፈሩ በአፍ ወዳጄ ወንድሜ ማለት ነውርም፣ ኃጢአትም ነው። ስቦ ማስከዳት መሆኑ ነው። 😂
"…አበበም መለሰለት "አመሰግናለሁ ወንድም" 😂 አይ ወንድም።
"…ቀልዱን ተዉትና ወደ አንድነቱ ኑ። ብቻችሁን ከዐማራ ተለይታችሁ ምንም አታመጡም። በዚህ ዘመን በብልጠት፣ በቅጥፈት፣ በፕሮፓጋንዳ የሚሸወድ የለም። ለአፋጎ ፋኖ የዋሻችሁትን ውሸት ሠራዊቱ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ ደውሎ እውነቱን አረጋግጦ ሁሉን ተረድቷል። ልትሸውዱት አትችሉም። በጭራሽ።
"…ሰማይ ዝለል፣ ምድር ፍረጥ አበደን ጎጃምን ከሌላው ዐማራ መለየት አትችልም። በጎጃም የተሰገሰግክ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ አገው፣ አንተ ሸንጎ፣ አንተ ቅባቴ የሆንክ ሙሉ ምንም አታመጣም፣ በውጭ የተሰገሰግክ ተረኛ ሆነህ ዐማራን ለመዋጥ የተዘጋጀህ፣ በስመ ምሑር፣ በስመ ባለሀብት የምትውነጠነጥ ምንም አባህ አታመጣም። መፍትሄው በሥነ ሥርዓት አደብ ገዝቶ ወደ አንድነቱ መመለስ ነው። አለቀ።
"…የጦማሬ መልእክት ግልጽ ነው። ጎጃም ከአፋብኃ ወጥቷል። ስብሰባም አይሰበሰብም በጋራ እየሠሩ ያሉት 3ቱ ብቻ ናቸው። ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ። ጎጃም ብቻውን እየዳከረ ነው። ዘመነና ዝናቡም ምንም ማድረግ አይችሉም። ነገርየው ከባድ ነው።
"…ነገ አጠር ብላ ረዘም ያለች፣ ቀጠን ብላ ወፈር ያለች ርእሰ አንቀጽ ትኖረናለች። 1ሺ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ ካመሰገነ በኋላ እንጨቃጨቅበት ዘንድም እለጥፍላችኋለሁ። በጎጃም የአፋጎ ዘብጥያ ስላወረደው አንድ ጋለሞታ ፀረ ዐማራ ሸንጎም በስሱ አወራላችኋለሁ።
"…ንጉሡም ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ለሕዝቡ ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው። እንደ ብላቴኖችም ምክር፡— አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ ብሎ ተናገራቸው። 1ኛ ነገ፥ 13-14
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼