"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
መልካም…
"…የእኔ ሥራ መንቀስ ነው። በንስር ዓይን እየተመለከቱ በሩቅም፣ በጥልቅም ውስጥ ነነ ብለው የሚያስቡትን ነቅሶ ማዋጣት። መግፈፍም ሥራዬ ነው። የሴረኞችን፣ የእወደድ ባይ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችን ለምድ መግፈፍ፣ መሸለትም የሠለጠንኩበት ነው። መንከስም ሥራዬ ነው። ከነከስኩ ደግሞ ሳላደማ መልቀቅ በዘሬም የለ።
"…የሆነ ቀን የሆነ ሰው በስሱ ተው፣ እረፍ ብዬ ስናገር ሀገሩ ሁሉ ይነሣብኛል፣ ይጮህብኛል፣ የምሰደበው ስድብ ራሱ ተቅማጥ የሚያስመጣ ነው። የቤተሰቤ ፎቶ ተዘቅዝቆ ሁላ ነው የምሰደበው። ወዳጆቼም ያኮርፉኛል፣ አይደውሉልኝም። ብደውልላቸውም ስልኬን አያነሡም። ከደወሉልኝም ለምን ኤርምያስ ዋቅጅራን ተናገርከው? ለምን እስክንድር ነጋን ተናገርከው? ለምን ሄኖክ ኃይሌን፣ ለምን ምህረተአብን? ለምን ሀብታሙ አያሌው፣ አቤ እስክስን፣ ለምን ታዬ ቦጋለን የመሰለ ምሑር ኢትዮጵያዊ የዐማራ ወዳጅ ምርጥ የተዋሕዶ ልጅ ትናገራለህ? በጋሻው ደሳለኝ፣ ትዝታው ሳሙኤል፣ ዘርፌና አሰግድ ሳህሉን የመሰሉ ብርቅዬ የኦርቶዶክስ መናገርህ ልክ አይደለም፣ አሁንስ አበዛኸው ይሉኛል። እኔም ጊዜ ይፍታው እላቸዋለሁ። ይመሻል፣ ይነጋል በስንተኛው ቀን እኔ የለከፍኩት ሰው እየለፈለፈ ራሱ ተኩላ ሆኖ ተገልጦ አደባባይ ይወጣል። ከዚያ የእኔ ሥራ ዝም፣ ጭጭ ማለት ሲሆን የሚወበሩት ዘግይተው የባነኑቱ ናቸው።
"…ብዙ ሰው 1G፣ ግፋ ቢል 2G ነው እንዴ እልና እኔ ግን 5G የሆንኩ ሁላ ነው የሚመስለኝ። በዛሬው ርእሰ አንቀጽም የሆኑ የሆኑ ነገሮችን ዳስሼ፣ ነካ ነካም አድርጌ የሆነች ነገር ብልጭ ያደረግሁላችሁ ይመስለኛል። ዘሪሁን ሙላቱም ሆነ ዳንኤል ለአቢይ ለመገረድ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክር ላይ ናቸው እንጂ ሁለቱም አቢይ አሕመድ ክርስቶሳቸው ነው። ታዬ ቦጋለን እንኳ ከቁብም አትቁጠሩት።
• ጻፉ እስቲ…✍✍✍
👆③ ✍✍✍ …ይመለስ የነበረ፣ ዱባይ፣ አውስትራሊያም የሚመላለስባቸው ቤቶቹ የነበሩ፣ ሽቀላው፣ ንግዱ ጦፎለት አኬሩም የቆመለት ነጋዴም ነበር። በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምህረት ላይ ታክስ የማይከፍልበት የሲዲና ቪሲዲ ሸቀጡን እንደ ጉድ የሚያራግፍበት ዘመንም ነበር። ዳንኤል ክብረት በእነ ደጀኔ ኢብሳ መኪና ሊፍት እየጠየቀ፣ የታክሲ ኮንትራት እየከፈለ፣ ታክሲ ቆሞ እየጠበቀ ሲንከራተት በጋሻው ግን በወቅቱ ውድ የተባለ መኪና በካሽ ገዝቶ ይነዳ ነበር። እውነቱ እንደዚያ ነው። በጋሻው በወቅቱ ካልሲ 6 ብር በሚሸጥበት ዘመን ጌቱ ኮመርሻል ገብቶ ካልሲ በ200 መቶ ብር ይገዛ የነበረ ደፋር ነጋዴ ነበር። ዳኒ ተረቱ ላይ የሳተው ይሄን ነው።
"…አሁን ዘሪሁን ሙላትን ከተደበቀበት አንጨርጭሮ አውጥቶ ዳንኤል ክብረትን አያ እንቶኔ፣ አያ እገሌ እያለ እንዲሳደብ ያደረገው ገፊ ምክንያትም እዚህ ውስጥ ነው ያለው። በእርግጠኝነት ዳንኤል ክብረት ጦማረ ቧልቱን ሲጽፍ ያየው አቢይን ማስደሰቱን ብቻ እንጂ ጦማሩን ዘሪሁን ሲያነበው ደሙ እንደሚፈላና ውርጅብኝ እንደሚያስወርድበትም ያወቀ አይመስለኝም። ዘሪሁን የመስቀሉ ስር ቁማርተኞችን ጽፎ ለበጋሻው የሰጠ፣ ቆይቶ ደግሞ በወይዘሮ እጅጋየሁ በየነ አቅራቢነት አቡነ ጳውሎስን አወድሶ በፓትርያርኩ ትእዛዝ በወጣ ወጪ መጽሐፍ ጽፎ፣ መጽሐፉም በግዳጅ በየአቢያተ ክርስቲያኑ እንዲሸጥ የተደረገ እና ከርሱን የሞላ ጉደኛ ሰው ነው። አቡነ ሳሙኤል ላይ የጻፈውም ዘሪሁን ሙላት ነው። ዘሪሁን ሙላት የማይካድ ፈጣን አዕምሮም የታደለ ሰው ነው። ለዕውቀት ብሎ የተሰጠው አብሾው አናቱ ላይ የወጣበት፣ አብሾውን የሰጡት ሰው ከዓባይ ማዶ ከወደ ጎጃም ናቸው ተብሎ ስለሚነገረው ከዓባይ ማዶ በጎጃም ያሉትን በሙሉ በአንድ ቅርጫት ከትቶ እስከ አሁን ድረስ የሚጨፈልቅ ጨካኝ ሰውም ነው። የፌስቡክ ጦማሮቹን ተመልከቱ። ዘሪሁን እስከአሁን ድረስ በእጁ ሰው አይጨብጥም። እጁ ሰላላ ነው። ደም ፊት ለደቂቃ አይቆምም። መንፈሱ ቆሻሻ ኮፍያ የሚሸት፣ የሚገማ በርኔጣ፣ የሚሸት ጫማ ነው የሚያስደርገው። መኝታው በትኋን የተሞላ ነው። የፈለገ ዲዲቲ ቢነፋ ትኋን አያጣውም። ይሄ ከመናፍስቱ ጋር በገባው ኪዳን ምክንያት የመጣበት ርግማን ነው። ዕውቀት እሰጥሃለሁ ውርደትህን ተቀበል ተብሎ ከአጋንንቱ የተሰጠው ነው። ዘሪሁን ሴቶች ለወንድ መደሰቻነት የተፈጠሩ ፍጥረታት ናቸው በሚል ፍልስፍናው ምክንያት ሴቶችን እንደ ዕቃ የሚቆጥር፣ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ አውሎ የሚወረውርም ሰው ነው። እናም ዘሪሁንን ያበሳጨው የበጋሻው መጽሐፍ በወቅቱ የተወደደ፣ በሽያጭም ደረጃ ምድሪቱን ያጥለቀለቀ መሆኑ እየታወቀ ዳንኤል ለምን አጣጥሎ ጻፈው በሚል ምክንያት ነው።
"…ዘሪሁን በጦማሩ መዝጊያ አካባቢ እንዲህ አለ። #የዚያን ጊዜው የፓትርያርኩም ቃል ግን ትንቢት ሆኖ በዚህ ዘመን “አያ እገሌን” "የለውጡ ርእዮት" ሳይሆን፣ "የለውጡ ጎርፍ" ከቤተ መንግሥት ግቢ አስገብቶታል፡፡ ይህ “አያ እገሌ” በጎጋው ሕዝብ ዘንድ እንደ “አማካሪ ሊቅ” ሲታይ በምሁራኑ እና በልሂቃኑ ዘንድ ግን እንደ “ታማኝ ታሣሪ” መሆኑ አሁንም ይነገራል። እርሱ ግን ይህ ማንነቱ አልገባው ብሎት በተለይ “አማካሪነቱ” ትዝ ሲለው “ኢታማጆር ሹም” የሆነ እየመሰለው ወይም “የመረጃ ሹም” የሆነ እየመሰለው “እንትናን” ፍለጡት ! “እንትናን” እሰሩት ! ማለቱ ደግሞ ሰው ማን እንደሚለው አለማወቁን ያሳያል። ይህም አኳሆኑ “ሠራተኛ ሲያቆላምጡት ልጅ የሆነ ይመስለዋል፡፡ ”የሚለውን ብሂል ያስተርትበታል። በሥልጣን ምኞት ስካር ውስጥ ሲሆን ደግሞ ሁሉን አድራጊ ለመሆን ሲቃትት ላስተዋለውም “የፋሲካ ቀን የገባች ሠራተኛ፣ ሁልጊዜ ፋሲካ የሆነ ይመስላታል” የሚለው ፈሊጣዊ ንግግር ያስተርትበታል።
#ከምንግዜውም በላይ ደግሞ በተለይ አሁን ያለበት ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ "አያ እገሌን" ቅርቃር ውስጥ አስገብቶ አስጨንቆታል። የሚያየው ሰው ሁሉ፣ የአንደበቱን “አማራነት” ትቶ “የልቡን ሻዕብያነት” የሚያውቅበት እየመሰለው ይጨነቃል። አልፎ አልፎ ንጉሡን ማጀቡ ሲቀርበት፣ የውጭ ሀገር የአበል ጉዞ ሲስተጓጎልበት እና ጥቅሙ ሲጎድልበት ደግሞ፣ ወደ ተረት ተረቱ ይመለሳል፤ ጳጳሳቱን እንደሚያስፈራራው፣ ሚኒስትሮችን ማስፈራራት ሲያቅተው ደግሞ ከቤተ መንግሥት የተባረረ እየመሰለው ይቆዝማል። ከየጳጳሳቱ ጋር በመሆን ከመንግሥት ካዝና የሚያደርገው የገንዘብ ምዝበራ ትዝ ሲለው ደግሞ “ወይኔ !! አሁንስ ተነቃብኝ ባልፈጠር ይሻለኝ ነበር ፣” እያስባለው የያዘው አባዜ ያስቃዠዋል።
#በአማካሪነት ስም ያለበት “ታማኝ እስረኛነቱ” ድንገት ውል ሲልበት ደግሞ “ሥራዬን እና ሴራየን” ያውቁብኛል የሚላቸውን ግለሰቦችን ያሸሙራል፤ ማንነታቸውን ማጠልሸት እና ባልዋሉበት መንገድ ለማስፈራራትም ይሞክራል። ከዚያም አልፎ፣ “ያደረ ደም” ያለበት ይመስል፣ ሁሉን ይላከፋል፤ የሚቀናበትን ሰው በሐሰት ስሙን ያጠለሻል፣ በሐሰት ወሬ ሰዎችን ከሰዎች ያጣላል፤ ያቀያይማል፤ ይህ አድራጎቱ “የታማኝ እስረኛ መገለጫ” እንጂ “የንጉሥ አማካሪ ጠባይ” አለመሆኑን ለምናውቅ ለእኛ ግን ፣ “ታማኝ እስረኛው” የፈለገውን ቢል፣ ወይ ፍክንች !!!
#ይቆየን !!!
#ከተናግሮ_አናጋሪ_ይሰውረን !!!
#ሻሎም !!!
#ዘሪሁን ሙላቱ
#ሸዋ ፣ አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1/2017 ዓ/ም ከንጋቱ 12: 06 ሰዓት ተጻፈ ።
• https://www.facebook.com/share/19d5vJdQsH/
"…ግድ ነው። ተፈጥሮአዊም ነው። መጽሐፍ እንዲል በሰፈርክበት መስፈሪያ፣ ጣሳ፣ ቁና መልሶ ይሰፈርልሃል። መጨረሻዬን አሳምረው ማለት እኮ እንዲህ ነው። ከብሮ ከመዋረድ፣ አግኝቶ ከማጣት፣ ተሹሞ ከመሻር ፈጣሪ ይጠብቃችሁ። ብልፅግና አረመኔ ነው። ሃይማኖት የለውም። ብልፅግና ለአክቲቪስቶች፣ ለተሳዳቢዎች ልዩ ክብርና ማዕረግ፣ ሥልጣንና ሀብት የሚሰጠው ይሁነኝ ብሎ ነው። የሱማሌ ክልሉን አክቲቪስት ሙስጠፌን አምጥቶ የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ሲያደርገው አስልቶ፣ አውጥቶ አውርዶ ጥቅሙን ዐውቆ ነው። አክቲቪስት ስዩም ተሾመ ከፍርድ ቤት በላይ ሆኖ፣ በፌደራል ፖሊስ የሚጠበቀው በዚህ ዘመን የአክቲቪስት ጥቅሙን አክቲቪስት አቢይ አሕመድ አሳምሮ ስለሚያውቅ ነው። እናም ሳስበው ሳስበው ዘሪሁን ሙላት አንዲት የኦሮሞ ባለ ሥልጣን እህት የሆኑ እማማ አግብቶ አብሮ መኖር ጀምሮ እንደነበር ዐውቃለሁ። እናም የዳንኤል ዘመን በማብቃቱ ምክንያት ሊጀምሩት ይሆን እንዴ? ለዘሪሁን አረንጓዴ መብራት ሳያበሩለት አይቀሩም ባይ ነኝ።
"…ዳንኤል ክብረት ብቻ አይደለም። ከአገኘሁ ተሻገር ሌላም ወዶ ገቡን ብርሃኑ ነጋንም ለመትፋት የፈለጉ ይመስለኛል። ኤፍሬም ማዴቦም ኖሮ ኖሮ ሰሞኑን በብርሃኑ ነጋ ላይ ጓ ማለቱን፣ በዚያ ላይ የኢቢሲው ጋዜጠኛ ምንም ጥያቄዎቹ አግባብነት ያላቸው ቢሆኑም በሚንስትርነት ላይ ያለን ሰው በእንደዚያ በወረደ ቋንቋ፣ ደግሞም እንደ አቻ ባልንጀራም ሳይሆን እንደ አሽከርና ጌታ ሲያሽቆጠቁጠው ባየሁ ጊዜ ይሄም አረንጓዴ መብራት ይሆን ብዬም አሰብኩ። ሆነም አልሆነ ግን የራሳቸው ጉዳይ ነው።
https://www.facebook.com/share/v/168qQaXdw8/ …👇③✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ትናንት ቀኑን ሙሉ ወዳጆቼ የመንፈስ ባሪያው ሰውበሰው ተጫነ ወይም ዘሪሁን ሙላቱ ከዚህ በፊት ሙዐዘ ጥበባት እያለ ያወድሰው የነበረውን የአካል የተግባር ባርያውን ዳንኤል ክብረትን አቶ እገሌ እያለ የሞለጨበትን፣ የቅኔ ተማሪ ጥንቅቅ ምሑርም ነውና ልክ ልኩን በሰምና ወርቅ ያው እንደሁላችንም ሐበሻ ኢትዮጵያዊም ነውና በአግቦ፣ በአሽሙርም ያስነጠሰበትን ጦማር አብዝተው ሲልኩልኝ ነበር የዋሉት። አየኸው ዘመዴ፣ ዘሪሁን ለዳንኤል ክብረት ገባለት እያሉ ነበር የዘሪሁንን ጦማር ሲልኩልኝ የዋሉት። እኔም አዎ ዓይቼዋለሁ። ተመልክቸዋለሁ ነገር ግን ምንም አልገረመኝም። የምጠብቀውም ነገር ነበር እያልኩ ስመልስ ውያለሁ። ሁለት ባሮች፣ ሁለት አሽከሮች የሚያደርጉት የእወደድ ባይነት ግብግብም አድርጌ ነው ስመለከተው ያመሸሁት። የተለየ ነገር ያየሁት ዳንኤል ክብረት በሩን ጠርቅሞ ቢያሸሙርም የተወሰነ ኮመንት ሾልኮ ገብቶ በግድግዳው ላይ መጻፉን እና ዘሪሁንም ቢሆን እኔን ሲሰድብ ያገኝ ከነበረው የኮማቾች ብዛት ከወትሮው የውዳሴ አቢይ ጦማሮቹ በተለየ በዳንኤል የበሸቁ ኃይላት በስፋት በኮመንት ተሳትፈው ቤቱን ማድመቃቸው ነው።
"…ያው እኮ ነገርየው ግልጽ ነው። የሆነ ጊዜ በሕጋዊ ጋብቻም በለው፣ በስርቆሽ፣ በአስገድዶም መድፈር ይሁን በስካር መንፈስ ትፀነሳለህ፣ ከዚያ ትወለዳለህ፣ እንደምንም ብለህ ታድጋለህ፣ ከዚያ ታረጃለህ፣ በመጨረሻም አይቀርልህምና የግድህን ትሞታለህ። ይሄ የሕይወት ዑደት ዕድለኛ ሁነህ ከተገኘህ ብቻ የምታልፍበት የሕይወት መንገድ ነው። ሳታረጅም በመሃል በጉልምስናህ በወጣትነትህም ወራት ልትቀጠፍ ትችላለህ። አንዳንዱ በልጅነቱ፣ በሕጻንነቱ፣ ሲወለድ ራሱ በምጥ ሰዓት ራሱንም እናቱም ሊሞቱ ይችላሉ። ወይም ደግሞ በማኅፀን ሳለም ውኃ ሆኖም ሊቀር ይችላል። ሓኪም በመርፌ፣ በመድኃኒት ሳይወለድ "ያልተፈለገ እርግዝና" ብሎ መርፌ ወግቶ፣ ብረት በሴቷ ማኅፀን ከትቶ፣ ቢወለድ እና ሰው ቢሆን ፓትርያርክ፣ ንጉሥ፣ ሳይንቲስት ሊሆን የሚችል ፍጥረት በጥብጦ ደም በደም አድርጎ ነፍስ አጥፍቶ ሊያስወግደው ይችላል። የሆነው ሆኖ ግን መወለድ፣ ማደግ እና ማርጀት፣ ከዚያም መሞት አይቀሬ ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው። እኛ ብዙ ጊዜ ይሄንን ነው ማመን የሚያቅተን። በፍጹም የምንሞት አይመስለንም። የሆነ ሰው ሞተ ሲባል እና ጫን ያለ ህመምም፣ ጉንፋንም ቢሆን ጠንከር ያለብን ጊዜ ብቻ ነው ሞት ትዝ የሚለን። ሞት እንዳለብን ግን እንመን።
"…ሰው ብቻ አይደለም እጸዋትም፣ እንሰሳትም፣ ሰማይና ምድር፣ ጨረቃና ፀሐይም ቢሆን ያረጃሉ፣ ይሞታሉ። ፓርቲም፣ ድርጅትም፣ ክብር እና ዝና ሥልጣንም ሀብትም እንዲሁ ነው። መኪና በለው፣ አውሮጵላን፣ መርከብ በለው ብሽክሊሊት ጋሪ ራሱ አዲስ እንደሆነ አይቀርም። ሁሉም ነገር ሓሳብም ቢሆን በሆነ አጋጣሚ ይጸነሳል፣ ከዚያ ይወለዳል፣ ሓሳቡ ዕድለኛ ከሆነ ያድጋል፣ በመጨረሻም ይሞታል። መልክም ቢሆን እንዲሁ ነው። የሆነ ሰዓት ላይ አፋጀሽኝ፣ ኡሙንዱኖ እሱ ቦምቦሊኖ የምንመስልበት የአበባ፣ የፍካት ጊዜና ወቅት አለ፣ ከዚያ ዘመን ይመጣና ደግሞ በረዶ እንዳረገፈው ዛፍ ብጥቅጥቅ እንላለን። እንደ ተጨማተረ አሮጌ ጣሳ ተጨማድደን እንገኛለን። ይሄን ማስቀረት አይቻለንም። መልክም ረጋፊ ነው። በሜካፕ በለው፣ በሰርጀሪ ብትታገለው መርገፉ እንደሁ አይቀርም። ባትረግፍ እንኳ እንደ ማይክል ጃክሰን በቁምህ ትፈራርሳታለህ። አንተ እንደ ፓስተር ዮኒ ማኛ፣ እንደ ፓስተር ዮናታን፣ እንደ ቀሲስ ታጋይ ከብብትህና ከብሽሽትህ ፀጉር አስነቅለህ በተፈጥሮ ፈጣሪ ያደለህን ራሰበራነት በቱርክ ሀኪሞች በገንዘብህ ጎፈሬያም ልትመስል ትችላለህ። እሱም ቢሆን ለጊዜው ነው። ይረግፋል። ያውም ሲረግፍ አኮላሽቶህ፣ ጤና አሳጥቶህ ነው የሚረግፈው። ሀብትም እንደ ጥላ፣ እንደ ጉም ያለ ነው። የሆነ ጊዜ በውርስም፣ በሥራም፣ በሎተሪም ይመጣል ከዚያ ይሄዳልም። ከቪ8ትህ ወርደህ የጎዳና ተዳዳሪ ሁላ ልትሆን ትችላለህ። ሁሉም አላፊ ጠፊ ናቸው። የማያልፈው መልካም ስም ብቻ ነው። መጽሐፍስ ከመልካም ሽቱ መልካም ስም አይደል የሚለው? እንደዚያ ነው።
"…ዳንኤል ክብረት ያገኘውን ዕድል ያላገኙ ሰዎች እንደሚቀኑበት ዐውቃለሁ። እኛ ዳንኤል ክብረትን በምንቃወምበት የጠራ ምክንያት ሳይሆን ዳንኤል እንዴት በለጠን፣ በዕውቀት ቢሉ በሌላም የምንበልጠው ሆነን ሳለ እሱ ዳንኤል ክብረት እንዴት ይህን ዕድል አግኝቶ በለጠን፣ ቤተ መንግሥት ገባ ብለው እንቅልፍ የሚያጡ የማኅበር ጓደኞቹ፣ የቅርብና የሩቅ ጓደኞቹም፣ ከጥንት ጀምሮ ያቆሰላቸው የቤተ ክህነት፣ የቤተ መስጊድና የፕሮቴስታንታ ተሃድሶ ሰዎች እንዳሉ ዐውቃለሁ። ልክ እነ በጋሻው ደሳለኝን በወቅቱ እኛ ከሃይማኖት አንፃር አጥብቀን ስንቃወማቸው አንዳንድ ሰባኪዎች የሚቋወሟቸው እንጀራቸውን ስለዘጉባቸው፣ ባለሀብቱን ስለያዙባቸው እንጂ በግብርም፣ በመልክም አንድ ሆነው ሳለ በአፍ ብቻ ይቃወሟቸው እንደነበረው ማለት ነው። ጋለሞታ ሆኖ ትዝታውን የሚቃወመው እንደ ትዝታው ጌታን ተቀብያለሁ ባለማለቱና አሁንም በዐውደ ምሕረቱ ላይ መገኘቱ ብቻ እንደሆነው ማለት ነው። ደበበ እስጢፋኖስ ሁላ…
"…በዳንኤል ክብረት የሚቀኑት ሰዎች ማስተዋል ያቃታቸው ነገር ቢኖር ዳንኤል ያገኘውን ዕድል ተጠቅሞ ቤተ መንግሥት ቢገባም ቤተ ክርስቲያኒቱን አሳልፎ እንደ ይሁዳ ከመሸጥ፣ እንደ ነፍሱም ይወደው በነበረው ሕዝብ እንደ መርገም ጨርቅ ከመጠላት፣ እንደ ቆሻሻ ከመወርወር በቀር ያመጣለት ክብር እንደሌለ ያለማወቃቸው ነው። ይሄን እያወቁም ነው የሚጠሉት፣ የሚቀኑበትም። ዳንኤልን ድሮም አይወዱት ከነበሩትና በማኅበረ ቅዱሳን አባልነቱ ብቻ ሲጠሉት፣ ሲጸየፉት ከኖሩት ሰዎች መሃል ደግሞ ሰውበሰው ተጫነ ዘርሽ ዋነኛው ሰው እንደነበር ዐውቃለሁ። ሰውበሰውና ዳንኤል ክብረትን ያዋደዳቸው፣ ብሎም ያደጋገፋቸው ደግሞ ሁለቱም ትግሬ ጠልነታቸውና ቤተ ክርስቲያኒቱን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለመበቀል ያላቸው ስሜት ተመሳሳይ መሆኑ ብቻ ነው። ዘሪሁንም ሸዋ መፐትረክ አለበት፣ ሥልጣን ከትግሬና ከዐማራ ወጥቶ ወደ ሸዋ መመለስ አለበት። ከኦሮሞ ፓትርያርክ ማግኘት ባንችልም በኦሮሞ ስም የጰጰሱ ዐማሮችን በኦሮሞ ስም አፐትርከን ሥልጣኑን መረከብ አለብን ባይ ነው። ለዚህ ነው የኦሮሚያ ሲኖዶስን ከዳንኤል ክብረት ጋር በጋራ መሥርተው፣ አቋቁመው፣ በኦሮሞ ስም የጳጳሳት ምርጫ ያደረጉት። አቡነ ሳዊሮስ የደራ ዐማራነታቸው እኮ አይፋቅም። ዘመድ ቤተሰቦቻቸው በሙሉ የደራ ሰዎች ናቸው። አባ ተክሌን ዘሪሁን ሲያስመርጥ ምን አስቦ እንደነበር የታወቀ ነው። አለቀ። እናም ዳንኤል በንጉሡ ፊት ሞገስ ማግኘቱ ካልሆነ በቀር በቀረውስ ሁለቱም አይጥና ድመት፣ አይንና ናጫም ናቸው።
"…ዳንኤል ለሀገር፣ ለቤተ ክርስቲያንም ይጠቅም ይሆናል ባልነ ጊዜ ሁላችንም ከኦሮሞ ወሀቢይ እስላሞች ጋር፣ ከፅንፈኛ የደቡብና የኦሮሞ ጴንጤዎች ጋር ጨበጣ ገብተን፣ ዘመቻም ከፍተን፣ ተጯጩኸን ታድገነዋል። "እኔም ዳንኤል ነኝ" የሚል መፈክርም ጽፈን ምድሪቱን በሙሉ አጥለቅልቀንለታል። የሚሆን፣ የሚረባ የሚጠቅም መስሎን። ግን አልሆነም። ከቤተ መንግሥት ደጃፍ ላለመራቅ፣ ከአህዛብ የሥልጣን ፍርፋሪ ለመለቃቀም ሲል ዳንኤል እንደ ጴጥሮስ ከዳን፣ እንደ ይሁዳ ሸጠን። ከእናንተ አሕዛብ ይበልጡብኛል ብሎ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በመርዛማ በፍላጻ ብዕሩ እና ምላስ አንደበቱ ወግቶ ወጋግቶ ደጋግሞ አቆሰለን። የእኛስ ግድየለም የሚያስለቅሰው፣ የሚያሳዝነው ግን እከኩን አራግፋ፣ ከትቢያ አንሥታ …👇① ✍✍✍
"…በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤" ማቴ 24፥ 19-20
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። ማቴ 24፥ 6-8
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
• አላችሁ አይደል…?
👉🏿 በ zemedtv.com
👉🏿 በ 👉 https://x.com/ZemedMedia
👉🏿 https://rumble.com/v6vsv5z--zemede-july-06-2025.html?e9s=src_v1_upp_a
👉🏿 Yahsat 52.5° East 11977 H 27500
• ነጭ ነጯን ጀምረናል…
"…ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ። መዝ 106፥ 1
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ዛሬም…
“…እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።” ኢያ 7፥13
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
“…እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ 8፥44
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
👆⑤ ✍✍✍ …የሚያደርጉ ፋኖዎች ካሉ በጊዜ መንቃት አለባቸው ባይ ነኝ። ይሄንን የመሰለ ታላቅ የበላይ ዘለቀ ልጆች ኃይል በማይመጥኑት ፀረ ዐማራ ብአዴንን በሚያስንቁ ሰዎች መመራት ስለሌለበት ዕዙ ሪፎርም ያስፈልገዋል! ብለው መጠየቅና ማስተካከል አለባቸው። እነ ማርሸት፣ እነ አስረስ፣ እነ ተሰማ የሚመሩት ድርጅት አይደለም ለዐማራ፣ አይደለም ለጎጃም ከጎጃምም ራሱ ለጎንቻም ሆነ ለሜጫም አይጠቅምም።
"…በየትኛውም መድረክ ቅቡልነታቸው የወረደው እነ አስረስ መዓረይ አሁን በሕዝብም፣ በሠራዊቱም ዘንድ ተወዳጅ በሆነው በሻለቃ ዝናቡ በኩል ለመገለጥ ይላላጣሉ። ደጋ ዳሞት ከትናንት እስከዛሬ ድረስ ያልተቋረጠ ተጋድሎ እያደረገ ያለ አካባቢ ነው። ምሥራቅ ጎጃምን ለብአዴን አስረክቦ በምዕራቡ የጎጃም ክፍል የከረመው የእነ አስረስ መዓረይ ቡድን አሁን የእነ ዝናቡን ተጋድሎና ጀግንነት ተጠቅሞ የፕሮፓጋንዳ ሥራውን ይጀምራል። እነ መሳይ መኮንን፣ እነ ደረጄ ሀብተወልድ፣ እነ ፋሲል የእኔዓለም አሁን ሻለቃ ዝናቡን በቃለ መጠይቅ ልቡን ያፈርሱታል። ለብልጽግና ግብአት የሚሆን መረጀ አስፈልፍለው ያስወጡታል። ጎጃም ይዋጋል፣ ይሞታል ይገድላል፣ እዚያው ጭቃውን ሲያቦካ ይኖራል። ዐማራን አሸናፊ የሚያደርገው አንድነት ብቻ ነው። ትግሬ እንኳ 17 ዓመት ታግላ ማሸነፍ ሲያቅታት ኢህአዴግ ብላ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ካሳተፈች በኋላ ነው ጎንደርን ወሎና ወለጋን አልፋ ወደ መሃል ሀገር የገባችሁ። እናርጅ እናውጋ ላይ ብቻ ስትታኮስ ውለህ ብታድር የኦሮሙማው አገዛዝ ምኑ ነው የሚጎዳው? ሁለት ሚሊሻ ማረክን፣ አንድ ልዩ ኃይል ገደልን፣ ሦስት መከላከያ ስበን አስከዳን ብለህ ዜና ሠርተህ ስታበቃ እግረ መንገድህን የአረመኔው ብራኑ ጁላ ጦር በጎጃም እንዲህና እንዲያ ቦታ ላይ ትምህርት ቤት አወደመ፣ ጤና ጣቢያ አቃጠለ፣ ገበሬ ገደለ፣ መንደር አቃጠለ ብለህ ማለቃቀስ ፋርነት ነው። የራስህን አባት ሚሊሻ ገደልህ ፎክረህ፣ 3 መከላከያ ስቤ አስከዳሁ ብለህ ፎክረህ ስታበቃ ወደምኩ፣ ተቃጠልኩ ብሎ ማላዘን አይነፋም። ኦሮሙማው እንደሆነ ትግሉ ዓባይን እስካልተሻገረ ድረስ እዚያው እንደ ጋዛ እያነደደህ፣ እያደቀቀህ፣ ትምህርትና ጤና ጣቢያ እያወደመብህ፣ በበሽታም፣ በጥይትም እየፈጀህ በቢኖር ለእሱ ደስታው ነው። ከፈለገም እናትህንና አባትህን ሰልፍ አስወጥቶ እያስወገዘህ መሳቂያ መሳለቂያ እያደረገህ ይኖራል። የምትጎዳው አንተና ሕዝብህ ናቸው። አሁንም ስርነቀል ግምገማ ተካሂዶ የጎጃም ፋኖ አመራሮች ወደመስመር ካልመጡ በስተቀር የጎጃምም፣ የዐማራም መከራ አያበቃም።
"…እኔ የምጽፈውም፣ የምናገረውም ሲያነቡትም ሆነ ሲሰሙት ይደብራል፣ ይመርራል፣ ይጎመዝዛል። ውዳሴ ከንቱ፣ የውሸት ሰበር ዜና፣ መሬት ላይ የሌለ የድል ዜና ሸላይ በላዩ መጋት የለመደ ጆሮ እንደኔ ዓይነቱን ኮመጠጥ ያለ ራስህን ለካህን አስመርምር፣ ንስሀ ግባ የሚል ጠንከር ያለ ቃል መስማት ያሳምምሃል። ራስህን በራስህ ማርካት የለመድክ አንተ ሳሙናህን ስቀማህና ሚስት አግብተህ በተፈጥሮ መንገድ ተደሰት፣ ዘርተካ ስልህ ልማድህ ትዝ እያለህ ታለቃቅስብኛለህ፣ ትውርድብኛለህ፣ ትሰድበኛለህ። መፍትሄው የእኔ መንገድ ነው። አቢይ አሕመድ ሟች ወታደር አላጣም። የደቡብን ሕዝብ መቀነስ ስለሚፈልግ ከኦሮሚያ እንኳ ሰው ቢያጣ ከደቡብ በገፍ አምጥቶ ይለቅብሃል። ይቀጠቅጥሃል። ያወድምሃል። ከደቡብ እንኳ ሰው ቢያጣ በራሱ በአማራው ሚሊሻ፣ በቅማንትና በአገው ሸንጎ ታጣቂዎች እርስ በእርስ ያፋጅሃል። አንተ ነፃ ባላወጣኸው ከተማና መንደር ውስጥ ያሉትን ሕዝብ በሙሉ የሚያዝባቸው አገዛዙ ነው። ተነሥ፣ ተኛ፣ ታጠቅ፣ ዝመት የሚለው አገዛዙ ነው። ሰልፍ ውጣ፣ ፋኖን አውግዝ ቢለው ከመታዘዝ ውጪ ሌላ ምንም ማድረግ አይችልም። ከሠልፉ ማግስት አገዛዙ ዐውቆ ወደ ኋላ ያፈገፍግና ፋኖ ወደ ከተሞቹ እንዲገባ ያደርጋል። ፋኖም ከተማ እንደገባ ባለፈው ሰልፍ የወጣው ማነው ብሎ የገዛ ሕዝቡን ያስራል፣ በገንዘብ ይቀጣል፣ የሚሊሻና የአድማ ብተና ሰዎችን ደግሞ ይገድላል። ማን ተጎዳ? አቢይ አህመድ? ብራኑ ጁላ? በፍጹም። የምትጎዳው አንተ ነህ። የአንድ ሚሊሻ ሞት ብዙ ቤተሰብ ያለ ወላጅ ነው የሚያስቀረው። አሁን ብዙ ወንዶች በዐማራ ክልል እየሞቱ ነው። መሬት ጦሙን እያደረ ነው። የፋኖ አመራሮች ራሳቸውም፣ ቤተሰቦቻቸውም ኑሮአቸውን ባህርዳር፣ ማርቆስ፣ አዲስ አበባ፣ ዱባይ፣ ኡጋንዳ፣ አውሮጳ፣ አሜሪካና ካናዳ ዘጭ ብለው እየኖሩ ነው። እየተጎዳ ያለው ሕዝቡ ነው። አምርረህ ተሟገት። ፕሮፓጋንዳው ይብቃ። ህመምህን ተናግረህ ፈውስ የሚሰጥህን መድኃኒት በቶሎ ውሰድ። የእነ ፕሮፌሰር ሀብታሙ ምክር ጎጃምን በአናቱ ነው የሚተክለው። ብትፎክር፣ ብትሸልል፣ እሱ መፍትሄ አይሆንም። መፍትሄው ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ወንድሞችህ ጋር አንድ ሆነህ ስትታገል ነው። የሚዘረፈው ሲጠፋ፣ ገበሬው ምርቱ ሲቀዘቅዝ ገንዘቡ እንጀራ አይሆንህም እኮ ጎበዝ። ዘንድሮ ገበሬው ማዳበሪያ አላገኘም። እናም መጪው ጊዜ ይከብድብሃል።
• እስከመስከረም እዚያው ጎጃም ነኝ። ከጎጃም አልወጣም፣ ከጮቄም አልወርድም። የእውነት ይሁን የውሸት ወያኔ ከሻአቢያ ጋር ሆና ለውጊያ እየተዘጋጀች መሆኗ እየተነገረ ነው። በጦርነቱ ተጎጂው አሁንም ዐማራው ነው። በዚህ ጊዜ ዐማራ አንድ ሆኖ ተዘጋጅቶ እንዳይጠብቅ ደግሞ የአፋጎ አመራሮች ከወያኔም በላይ፣ ከኦሮሙማውም በላይ ጠላት ሆነው ተሰልፈዋል። የትግሬ ኮሎኔሎችን፣ አዋጊዎችን ፈትቶ የላከው የአስረስ መዓረይ ቡድን ዐማራ አንድ እንዳይሆን ሽብልቅ ነው የገባበት። ነገርየው ከባድ ነው። ከ5 ሴቶች 4ቱ ጥቁር ከል የኀዘን ልብስ የለበሱበት የጎጃም ዐማራ ትግል በጥቂቶች አፈር ደቼ እየበላ ነው። ዝናቡ መሳይ ጋር ሄዶ በግድ በሚመስል መልኩ የሰጠውን ቃለመጠይቅም አይቼዋለሁ። ዝናቡን በሚገባ ዐውቀዋለሁ። የገባበትና የከረሙበትንም ዐውቃለሁ። ይሕቺን ክረምት በሥልጠና ሰበብ አሳልፈው ዐማራን በበጋው ደቼ ሊያበሉት ነው የሚፈልጉት። ይሄ ደግሞ ለኦሮሙማውም የተመቸ ነው። በእኔ በኩል ለዛሬ ይህን ጽፌአለሁ። እናንተ ደግሞ አንብባችሁ ስትጨርሱ የራሳችሁን ሓሳብ ጻፉ። በጨዋ ደንብም የወያዩ። አመሰግናለሁ።
• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
👆③✍✍✍ …አብዲሳ ሳይቀር የሚመኩበት ሰው ነው። ምንአልባትም ብለው አቢይ ቢወድቅና የጎጃሙ ቡድን እንደተባለው ሁሉን ሥልጣን ጠቅልሎ ቢመጣ ተመስገንን ሥልጣን በመስጠት ይኸው አሁን ደግሞ ዐማራ ነው የነገሠው በማለት ማስተንፈስ ይፈልጋሉ። ይሄ ፕላን B ነው እንጂ ዋነኛው ግን አይደለም። ዋነኛ ዓላማቸው ፋኖን ባለበት ማምከን እና እዚያው ባለበት እየረገጠ አርመጥምጦ ማስቀረት ነው። ይመርራል ግን እውነታው ይሄው ነው።
5ኛ፥ ከጎጃም ፋኖ የዕዝ መሪዎች መካከል ዳብል ኤጀንት ሁነው የሚሠሩቱ ብዙዎች ናቸው። ከብአዴን አመራሮች ጋራ "እኛ ብንጨርስ እናንተን እንጠብቃችኋለን እናንተ ብትጨርሱ እኛን ትጠብቃላችሁ" ተባብለው ተማምለውና ተስማምተው የሚኖሩ አሉ። አርበኛ ዘመነ ካሤና ጠበቃ አስረስ መዓረይ የሚንቀሳቀሱበትን ዘመናዊ መኪና መመልከት ይቻላል። ገና መከላከያ ስምሪት ሲሰጠው በዚህ በኩል ይመጣል ወጣ በል ቦታ ያዝ እየተባባሉ መረጃ ከብአዴኖቹ ጋር ይለዋወጣሉ። ፋኖም ለማጥቃት ወደ ከተማ ሲወጣ ለብአዴን መሪዎች አስቀድሞ እንዲጠነቀቁ መረጃ ይሰጣቸዋል። በሁለቱም መካከል ከፋኖም ሆነ ከብአዴን የሚያስቸግራቸው ካለ በጋራ ያስመቱታል። ያስወግዱታልም። ወደ ፊት በዐማራነቱ ክችች የሚል በዚያ ላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ፋኖ ከሆነና አቅም እንዳለው ከታወቀ በድሮንም፣ በደፈጣም፣ ከጀርባም መትተው በስሙ ብርጌድ ያቋቁሙለታል። እንደዚህ አይነቶቹ ከፋኖ ዘንድ በቶሎ ይወገዳሉ። ከብአዴን በኩል ደግሞ በአፋ ፋኖን እያወገዘ በተግባር የሚረዳቸው አይነካም፣ በአፉም፣ በልቡም ብልፅግና የሆነ አመራር ሊስቱን ብአዴኖቹ ለፋኖዎቹ ይሰጣሉ፣ ከዚያ እያንበረከኩ ቆይተው ይረሽኑአቸዋል። እየሆነ ያለው ይሄ ነው።
"…በ2017 ዓም ሙሉ የፋኖ የማጥቃት ኦፕሬሽኖች በበቂ ሁኔታ ሳይሳኩ የቀሩት እነዚህ አመራሮች ቀድመው መረጃ አውጥተው እየሰጡ በመሆኑ ነው። በዕዝ አመራሮቹ መረጃው እየወጣበት ኦፖሬሽኑ ያልከሸፈበት ብርጌድ እና ክፍለ ጦር የለም። ካሜራ ብቻ። ፕሮፓጋንዳ ብቻ። ሰሞኑን እንዲያውም "አይማን ፍለጋ" የሚል ዶክመንተሪ ይለቀቃል ብለው ሲሉ ሰምቼ ራሳቸው ፋኖዎቹን አይማን ደግሞ ምንድነው ብዬ ጠይቄ ነበር። አርበኛ ዘመነ ካሤና አስረስ መዓረይ በወንዝ ውስጥ እያቋረጡ ቪድዮ ተነሥተው የለቀቁትን አይቼ ነው የጠየቅኳቸው። አይማን ማለት ዘመዴ ወንዝ ነው። ያውም በክረምት ብቻ የሚወርድ እና የሚሞላ ወንዝ ነው። አይማን ወንዝ ከበሙር በእግር ሁለት ሰዓት ይወስዳል። የነሳሚ እና የነሸጋ ጦር መዋያ ቦታ ነው። ከዚህ ወንዝ ተሻግሮ 30 ደቂቃ ከተጓዙ በኋላ አባይ ዳር የምትባል የገጠር ከተማ ትገኛለች። አባይዳር በጣም ሰፊ የእርሻ ቦታ ያለበት ስፍራ ነው። ከዚህ አለፍ ብሎ ደግሞ በጣም ሰፊ የወርቅ ቦታ አለው። የወርቁን ማውጫ ቦታ የሚያስተዳድሩት ደግሞ ወርቀኞቹ የሚያገኙትን ገንዘብ እየቀረጡ የተቀመጡ ፋኖዎች ናቸው። የሰሊጥ ምናምን ሳይጨመር ማለት ነው። እናም "አይማን ፍለጋ" ሲሉ የወንዙን መነሻውን ወይስ መድረሻው ነው? የሚፈልጉት ብለን ዶክመንተሪውን በጉጉት እየጠበቅን ነው የሚሉኝ። ምን አልባት ወደሱዳን ለመሄድ ወንዙን እያቋረጡ ነው ከተባለ እንኳ ከወንዙ ጋር አብሮ በመጓዝ ነው እንዴ የሚሻገሩት። ወንዝን ቆርጠህ ትሻገራለህ እንጂ ወንዙ ወደሚፈስበት እየሄዱ ቪድዮ መቀረጽ አይነፋም። ስንጠረጥር ስንጠረጥር ግን ወርቅ ጭረት ላይ በሰፊው መሰማራታቸው አልቀረም። ሀብታሙ፣ ኢንቨስተሩ የጎጃም ፋኖ በጊዜ ካልታረመ ከአልሸባብም ሆነ ከቦካ ሀራም የከፈ ጨካኝ ሆኖ ጎጃምን ሲኦል እንደሚያደርገው ከወዲሁ መናገር ነቢይ አያስብልም።
6ኛ፦ የአፋጎ መሪዎች ለጎጠኝነቱም፣ ለክልልነቱም ለሀገርነቱም አስቸጋሪው ኢትዮጵያኒስቱና ሃይማኖተኛነቱ ነው ብለው ያምናሉ። ተሞክሮውን የወሰዱት ደግሞ ከህወሓት ነው። ህወሓት ብሔርተኝነቱ የተሳካላት ሕዝቡን ከእምነት እና ከሀገራዊ ስሜት አውጥታ ትግራዋይ ስላደረገችው ነው። እኛም ያሰብነውን ለማሳካት ሃይማኖተኞችን ገለል አድርገን ጎጃሜነትን ብቻ በመስበክ በታጋዩም በማኅበረሰቡም ዘንድ ማስረጽ አለብን ነው የሚሉት። በዚህ ምክንያት 99%ኦርቶዶክስ የሆነ ማኅበረሰብ ከጎንደር፣ ከሸዋ እና ከወሎ መገንጠልን አይወድልንም በማለት በማጥላላት ላይ ተሰማርተዋል። አማኙን ለማሸማቀቅም "የነጠላ ሥር ቁማርቸኞች፣ አክራሪ ኦርቶዶክሶች፣ ሞዐ ተዋሕዶዎች፣ ቲም ክርስቲያኖች፣ ወግ አጥባቂዎች፣ ትግላችንን የጎተተው ፖለቲካ ነው" እያሉ ለማሳቀቅ በስፋት እየሞከሩ ነው። ለዚህ ደግሞ በየጊዜው በአፋጎ የቀረጥ ብር የሚተነፍሱት እነ ሥጋ ቆራጩ ይሄነው የሸበሉ፣ እነ ጥልሚያኮስ አማኑኤል አብነት፣ እነ አስረስ ማረይ እና በመጠጥ፣ በአረቄ ብዛት ጉበቱ ፈርሶ የበለዘው ማርሸት ፀሐዩ ምስክሮች ናቸው።
"…ለምሳሌ በስፋት ዘመቻ የተከፈተባቸው ከጎንደር ዘመነ ካሤንና ሻለቃ ዝናቡን ከድሮን ጥቃት የታደገው ትልቁ ኢያሱን ሲሆን፣ ከወሎ ደግሞ የምሬ ወዳጆን ቀኝ እጆች ሄኖክ አዲሴን እና አበበን ነው። ኤልሻዳይ የጊዮን ልጅ የሚባለው የጎጃም አክቲቪስት እንኳ ነገር ዓለሙ ድንግርግር ሲልበት፣ በሄኖክ አዲሴ ላይ የተከፈተው የጎጃም አክቲቪስቶች ዘመቻ ሲደብረው እንዲህ ብሎ ነው በፌስቡክ ገፁ ላይ ያሰፈረው።
ለመረጃ ያክል
"…ሄኖክ አዲስ የፋኖ መሪዎችን ለመምረጥ በተሳተፈባቸው ሦስት ምርጫዎች ድምጽ የሰጠው ለዘመነ ነው። ዘመነን ነው መሪየ ይሆናል ብሎ በተደጋጋሚ ጊዜ ድምጽ የሰጠው። የመጀመሪያው አፋህድን በፈጠረው ምርጫ ከእስክንድር ይልቅ ዘመነን መርጧል፤ ባለፈው መስከረም ለሚዲያ ይፋ ባልሆነ ምርጫም ለዘመነ ድምፁን ሰጧል። በቅርቡ አፋብኃ ምስረታ ወቅት የመሪዎች ምርጫ ውጤት ተቀባይነት አጦ ሴንትራል ኮማንድ ቢመሰረትም ድምጽ የሰጡው ግን ዘመነ መሪ እንዲሆን ነበር።
"…ሄኖክ ያመነበትን እውነት በጊዜ እና በቦታ ሳይለዋውጥ አንድ ወጥ ሆኖ ቢገኝም ዛሬ ጠላት ተደግጎ በፌስቡክ እና በቲክቶክ እየተዘመተበት ነው። ሄኖክ ከዚህ በላይ ምን ያድርግ? እንደ እየሱስ ክርስቶስ ፍቅሩን ለመግለጽ ተሰቅሎ ማሳየት ነበረበት? በጣም የሚገርመው ነገር ይህ ሁሉ የስድብ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ እየተደረገበት አቁሙ የሚል አንድ አመራር መጥፋቱ ነዉ። ከሰኔ 15 ማግስት ጀምሮ በጎጃም የፓለቲካ፥ የኢኮኖሚ እና የባህል ሊህቃን ላይ የተቀናጀ እና ተከታታይነት ያለው የሚዲያ ዘመቻ ሲከፈት የወሎ ሊህቅ እና አክቲቪስት ነበር ከጎናችን የነበረው። ከዚህ በኋላ የጎጃም ፋኖ አጋርስ ማን ነው? በማለት ነው መልስ የሌለው ጥያቄ የሚጠይቀው። ዘመነ ካሤ በጎንደር፣ በጎጃምና በሸዋ አመራሮች ተመርጦ ሳለ የዘመነ ምርጫ ለአፋጎ እንዳይደርስ ይዘው፣ ደብቀው አቆይተው ዘመነካሤን አፈር ደቼ ያበሉት እነ አስረስ መዓረይ አሁን ደግሞ ዘመነን ብቻ አይደለም እንዳለ ጎጃምን ከዐማራነት አውጥተው ወይ ክልል አልያም ሀገር እናደርጋለን ብለው ነው የሚወበሩት። አዋሳን ደቡቦች ገንብተው ለሲዳማ እንዳስረከቡት ባህርዳንም ዐማሮች ገንብተው ለጎጃም ያስረክቡናል ነው ምኞታቸው። ከጎንደር፣ ከሸዋ፣ ከወሎ የተለየ ጎጃሜነት በራሱ የሞተ ነው። ፕሮፌሰር ሀብታሙ ሰምተሃል። እነ አስረስን ገደል ባትከታቸው ጥሩ ነው። እየመከርኩህ ነው አባቴ። 👇③✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
"…የበቀደም ዕለቱን በጎጃም ያለውን የእነ አስረስ መዓረይን ቡድን አፈንጋጭ እና ትግል ጠላፊ ተግባር በተመለከተ በርእሰ አንቀጽ መልክ ከጻፍኩ በኋላ እንደድሮው በየፌስቡኩ፣ በየዩቲዩቡ፣ በየቲክቶኩ ቅጥረኛው የአፋጎ አክቲቪስት እንደተልባ ይንጫጩብኛል ብዬ ጠብቄ ነበር። ነገር ግን እንደጠበቅኩት አይደለም የሆነው። በረዶ እንደመታው ሰብል ስብርብር ያሉ ጥቂት ድምጾች ሲንፈራገጡ ከማየቴ በቀር አብዛኛው የጎጃም ዐማራ አርምሞን መርጦ ወደ ምርምር፣ ወደማንሰላሰል ነው የገባው። ጥቂት የጎጃም ፕሮፌሰር፣ ዶክተር ነን ባዮችና ከእነ አስረስ መዓረይ ጋር ተጣምረው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ሥልጣኑን ሁሉ ጠቅልሎ ወስዶ ዙፋኑ ላይ ከወጣ በስተ እርጅና ሥልጣንና ሀብት እናገኛለን ብለው ከሚዳክሩት በቀር እውነተኛ የጎጃም ልጆች ነገሩን መመርመር ጀምረዋል። ይሄ መልካምና በጎ ጅምርም ነው።
"…እኔም ጎጃም ገብቼ ጮቄ ተራራ ላይም ወጥቼ አልወርድም ካልኩ መንፈቅ ሊሞላኝ ነው። ጮቄ ተራራ የኢትዮጵያ የውኃ ታንከር ነው። አየሩ ተስማሚ ነፍስን የሚያረካ፣ ሥጋን የሚያለመልም ነው። በአርምሞ ነገሮችን ለማጥናት ለተቀመጠበት ምስጢር ገላጭ ስፍራ ነው። አሁን አሁን ፈረንጆችም ሳይቀሩ እግር ያበዙበት ስፍራ ነው። እዚያ ሆኜ ነው የጎጃምን፣ የወሎና የጎንደርን እንዲሁም የሸዋን እንቅስቃሴ እየጎበኘሁ የምገኘው። እነ ግርማ ካሣ እነ ደሳለኝን በስልክ ሰብስበው ገንዘብ እናፈስላችኋለን እናንተ እኛ የምንላችሁን ሁሉ ስሙን ሲሉም በስብሰባው ላይ ገብቼ እየሰማሁ ነበር። ከእነ መከታው ወደ እነ ደሳለኝ የዞረው የግርማ ካሣ ቡድን አንድ የባህርዳር ተወላጅ የጎጃም ጋዜጠኛም ይረዳቸው ዘንድ ወደ ሸዋ መላኩን እና እነ ደሳለኝም ይቀበሉት ዘንድ እንደተነገራቸው፣ ኢንጂነር ደሳለኝም ጉዳዩን ወደ ዶክተር አብደላ እንደመራውም ሰምቻለሁ። ሸዋን ሊበሉት ነው። የደሳለኝም ሆነ የሸዋ መሪዎች እነ ቡሩኬ፣ እነ ፕሮፌሰር ማርከው፣ እነ ዳግም፣ እነ አብደላና ካሣም የሚፈተኑት አሁን ነው። ግርማ ካሣ ገንዘብ አቅርቦ አፈር ከደቼ ሊያበላህ ነው። አሰግድ መሰበር አለበት ብሎ አሰግድን የሰበረው ግርማ ካሣ እነ ደሳለኝን በፈረንካ ሳያማልል አልቀረም የሚሉ መተርጉማንም አሉ። እኔም ከሸዋ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እየጠበቅኩ ነው።
"…ወደ ጎጃሙ አፋጎ ጉዳይ እንመለስ። በአፋጎ ውስጥ ያለው ድብቅና ግልጽ ችግር የሆነውን አንድ ሁለት ብለን ከስር መሠረቱ ጀምረን ጥቂት በጥቂት ወደመመልከቱ እንግባ። እዚያው ጮቄ ተራራ ላይ ቁጭ ብዬ ከመላው ጎጃም እኔን ለመጠየቅ የመጡ መንፈሳውያን ከሆኑ እውነተኛ የአፋጎ ታጋዮች ጋር ጥልቅ የሆነ ውይይትም አድርጌ ነበር። በውይይታችንም መሠረት ነገርየውን በስሱ ከመነካካት በጥልቀት መመርመሩ ይበጃል፣ ይሻላል በሚልም ለምን ነጭ ነጯን አንነጋገርም። ሕመሙን የማይናገር በሽተኛ መድኃኒት ሊገኝለት አይችልም በማለት ተወያይተን በመጨረሻም የአፋጎ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች የሆኑ ታጋዮች ትክክለኛውን የዐፋጎ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ህመምና በሽታ ከነምልክቱ እንደሚከተለው ነግረውኛል። እናም እናንተም በአፋጎ ህመምና የበሽታ አምጪ ቫይረሶች ላይ ተነጋግራችሁ ለአፋጎ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዐማራ ፈውስ የሚሰጥ መድኃኒት ትሰጡ ዘንድ እንደሚከተለው አድርጌ አቅርቤላችኋለሁ። የምጽፈው ርእሰ አንቀጽ ይመርራል ግን ይፈወሳል። ያደፈርሳል ግን ደግሞ ይጠራል።
1ኛ፥ ጎጃም ውስጥ ያሉ የፋኖ ጎጠኛ አመራሮች በዋነኝነት የሚሉት "በአሁኑ የዐማራ ፋኖ ውስጥ ሥልጣን ያለ ገደብ ያለማንም ከልካይነት ሰፋ አድርጎ የማይሰጠን ከሆነ ከዐማራ ፋኖ ኅበረት፣ አንድነት መውጣት ብቻ ሳይሆን ጎጃምን ራሱ ራሱን የቻለ ክልል አድርገን ከዐማራው ኅብረት እና አንድነት እንገነጠላለን" በማለት ነው የሚደሰኩሩት። የዓባይ ወንዝ በጎጃም መኖሩ ብቻ የውጪውን የዓረብና የእስራኤል ኃይል ትኩረት ስበን ራሱን የቻለ የፖለቲካ የስበት ማእከል እንሆናለን። በተለይ የዕዝ አመራር ነን የሚሉ ሰዎች ከእነ አስረስ መዓረይ ጀምሮ ይህን ሓሳብ ገዝተው አትርፈው ለመሸጥ እየተፍጨረጨሩ ነው። አይደለም ክልል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ በሱዳን መንግሥት ድጋፍ ከሚንቀሳቀሰው ከጉምዝ ነጻ አውጪ ግምባር ጋራ ተስማምተን፥ መተከልን ይዘን ቦርደር ስለምናገኝ ሀገር እስከ መሆን እስከ መገንጠል ድረስ መሄድ እንችላለን እያሉ ነው። እኛ ጎጃሞች ሀገር ለመሆን ምንም የሚያንሰን ነገር የለም ስለ አዲስ አበባም ሆነ ስለ ሌላው ዐማራ ምን አገባን? በማለት በአጃቢዎቻቸው በኩልና በሚድያ ተከፋዮቻቸው በኩል እንደምታዩት ቱሪናፋቸውን እየነዙ ነው። ይሄ የጥፋት ቡድን ፈጽሞ በቀላሉ የሚናቅ አይደለም። ቡድኑ የሚደገፈው በሻአቢያ እና በግብጽ ጭምር ነው። ሻአቢያና ግብጽ ደግሞ ይሄ የጎጃሙ ቡድን አሸባሪ ቡድን ሁኖ እንዲኖር ነው እንጂ የሚፈልጉት ቡድኑ ከሌሎች የዐማራ ፋኖዎች ጋር ኅብረት አንድነት ፈጥሮ አራት ካሎ እንዲገባ አይደለም። ምን አልባት ከተሳካለት ባሕርዳርን ይዞ የጎጃም ክልል መንግሥት ለመሆን ሊጣጣር ይችል ይሆናል። ለዚህም ሲባል ከክልልነት አልፎ የእነ ዶክተር ሙሴን ህልም ለማሳካት ሀገር የመሆን ዕቅድ አለኝ ብሎም ከጎንደር መሬቶች የእኔ ናቸው ብሎ በቤተ ክህነቱም፣ በመንግሥታዊ አስተዳደር መዋቅሩም በኩል ድንበር እየገፋ ትንኮሳና ቁርሾም በመፍጠር በዐማሮች መካከል ራሱ የማያባራ ሁከት ለመፍጠር መንደርደር ጀምሯል።
2ኛ፥ እንደ ፋኖ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ውስጥ ያሉት የዐማራ ፋኖዎች በቁመናቸውም ሆነ በአስተሳስባቸው ልከኛ መሪና በመርህ የሚመራቸው ድርጅት ካገኙ ምንም ችግር የለባቸውም። ሃይማኖተኞች ናቸው። በአንድ ዐማራ ያምናሉ። ከጎንደርና ከወሎ ከሸዋም ዐማራ ተለይተው ብቻቸውን ምንም ማምጣት እንደማይችሉም በሚገባ ይገነዘባሉ። ያውቃሉም። ነገር ግን አሁን ላይ በአረቄ መንፈስ እየተመሩ ከተመስገን ጥሩነህ ጋራም እየተማከሩ በሚዘውሩት የአፋጎ መሪዎች ምክንያት የዐማራ ፋኖ በጎጃም የትም በማይደርስ የመንደር ትግል እንዲታገል ተፈርዶበታል። ጎጃምን ከማውደም፣ ሊቃውንቶቿን ከማስፈጀት፣ ጎጃምን ከማድቀቅ የዘለለ ምንም ዓይነት ትርፍ አያመጡም። እንደ ሆሊውድ በሚዲያ ብዛት የሌለ ድል እዘበዘቡ ጠብ የሚል ነገር ሳይሠሩ ከመኖር፣ እዚያው ባሉበት ከመርገጥ በቀር ምንም አይፈይዱም። አብዛኛወን የአፋጎ የዕዝ መሪዎች ስንመለከት በብዛት ኤርትራ የከረመው የአዴኃን ሰዎች እንደሆኑ እንመለከታለን። ሻአቢያ በጎጃም አስቀድሞ ነው ስፍራ የያዘው። አርበኛ ዘመነ፣ ጥላሁን፣ ዝናቡ ወዘተረፈ በሙሉ ረጅም ዓመታት ግንቦት 7 ሆነው ኤርትራ የከረሙ ናቸው። ስለዚህ የጎጃም ፋኖ ከላይ በሻአቢያ፣ ከጎን በወያኔ፣ በግራና በቀኝ በኢዜማ፣ በአብን፣ በብአዴንና በኦሮሙማው ሳይቀር የተያዘ፣ የተጠረነፈ ነው። አገው ሸንጎና ቅባትን ስትጨምሩበት ደግሞ ይብሳል። ይሄንን ስብስብ ደግሞ መናቅ፣ ቸል ማለት ዋጋ ነው የሚያስከፍለው። የግንቦት ሰባት፣ የኢዜማና የብአዴን ኃይሉ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። የቅባት ሃይማኖትና የአገው ሸንጎ ፍላጎት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። እነግብፅ ሲጨመሩበት አስቡት። 👇①✍✍✍
“…ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ።” ኤር 25፥34
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
• ለዛሬ ይበቃል…!
"…ከስንት ሳምንት እረፍት በኋላ ብቅ ብል ይኸው አነቃቃኋችሁ። አወያየኋችሁ። ሰፈር መንደሩ ብዕር መዝዞ እንዲወያይ አደረግኩት። የተቃውሞ መልስ እንኳ እንዲህ በጨዋ ደንብ ሲቀርብ እንዴት ደስ ይላል። ዘመዴ ማለት ይሄ ነው። እኔማ ሰሞኑን በየቤቱ ዞርኩ፣ በየመንደሩ ተንከራተትኩ ወፍ የለም። ይኸው ዛሬ ብቅ ብል መንደሩ ሁሉ ደመቀ። አእምሮአችንም ምግብ አገኘ። የመኖሬ ጥቅም ለዚህ ነው። እንዲያ ነው በልልኝማ።
"…ነገን ወይም ከነገ ወዲያን ውዬ ደግሞ የቤተ ክህነቱን አካባቢ የጭቃ ዥራፌን ልለጥፈበት ብቅ እላለሁ። አስገድጄ ብደፍርም ኦሮሞ ስለሆንኩ ክህነቴ ታገደብኝ ብሎ እያለቃቀሰ ስላለው ቄስም፣ ስለ ቀጠለው የካህናት እርድ እና የአራጆቹ የወርቅ ሽልማትም እናወጋለን። ያንን አካባቢ የሚያደባይ አንድ ድሮን የመሰለም ርእሰ አንቀጽ ሰሞኑን እለቅባችኋለሁ። እስከዚያው የዛሬውን ርእሰ አንቀጽ ይዛችሁ ስትንጫጩ ክረሙ። ተወያዩ፣ ተከራከሩ። ተሟገቱ። ተጨቃጨቁ። እኔንም በየቤታችሁ ስትዘነጥሉኝ ዋሉ እደሩም።
"…የዘመድ ሚዲያ ቋሚ አባላትም የቋሚ አባልነት ምዝገባችሁን አጠናክራችሁ በሰፊው ቀጥሉ።
• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
👆⑥✍✍✍ …
"…ለዛሬ እዚህ ላይ ላብቃ። በዚህ ላይ ሳምንቱን ሙሉ ተጨቃጨቁበት። ስደቡኝ፣ አዋርዱኝ፣ ኡኡም፣ ቁቁም በሉብኝ። ለደንታችሁ ነው። እኔ ግን ከራሴ አውርጃለሁ። ምስክሬም ማርያም ናት። ሰማይ አድምጪ፣ ምድርም ስሚ፣ ቤተ ክርስቲያን መስክሪ። እናንተም አንባቢዎቼ ምስክሮቼ ናችሁ። የተለመደው የጎጃም ጥላቻ አለበህ፣ ወዘተረፈ አስቀያሽ ትውከት አኞ የሆነ ጋጋታም እንሰማለን። ጎጃምማ የወንዶች ቁና፣ የጀግኖች ምድር፣ የሊቃውንት መፍለቂያ ምድር ነው። እኔ ሠራዊቱን፣ ሕዝቡንና ሙሉ መሪዎቹን ሸክፉ አላነሣሁም። ወመኔውን፣ ሴረኛውን፣ ቀጣፊውን ሁሉ ለይቼ ነው የመታሁት። የቀጠቀጥኩት። እናንተም ምስክሮቼ ናችሁ። ምክሬን ስማ ባትሰማም መከራው ልክ አስገብቶ ይመክርሃል። እኔን ከመሃል አውጡና ደፈር ብላችሁ ለመነጋገር ሞክሩ። እያለቀ ያለው፣ እየወደመ ያለው የእናንተው ቤተሰብ ነው። ድፈሩ፣ ፍጠኑ፣ ልዩነት ካለም ልዩነቱን አጥብባችሁ ወደ አንድነት ኑ። እልኸኞች አትሁኑ፣ እርስ በእርስ መነቋቆሩን ትታችሁ እርስ በእርስ ተመካከሩ። በደጉ ጊዜ ታላላቆቻችሁ ጎንደር ጎጃም ብለው ቢነቋቆሩ የጭንቁ ቀን ሲመጣ እኮ ጎጃምና ጎንደር አንድ ላይ ነው ያበረው፣ ጎንደርን ያወደመው የዓድዋ ትግሬውን ስሁል ሚካኤል ከጎንደር ዐማራ ጫንቃ ላይ ገልብጠው ያራገፉት እኮ ላስታዎችና ጎጃሞች ናቸው። ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ብለው በጎጃም ምድር በትግሬ አግአዚ ስናይፐር አናታቸው የፈረሰው እኮ የጎጃም ልጆች ናቸው። ዘመነ ኳሴ ይፈታ ብለው ባሕርዳር ድረስ መጥተው የጨፈሩት እኮ የጎንደር ከነማ ደጋፊ የአፄ ቴዎድሮስ ልጆች ናቸው። እናም እነ አስረስ ሊመከሩ፣ በጊዜ ሃይ ሊባሉ ይገባል። እንደ አቢይ አሕመድ በፎቶ ቦለጢቃ የሰው አንጀት ውስጥ መጎዝጎዣ ጊዜና ዘመኑም አልፏል። አሁን ዐማራ የሚፈልገው ተግባር እንጂ ፎቶ ሾው አይደለም። ተወደደም ተጠላም በጎጃም ምድር እንዲህም ሆኖ መዋደቁ አይቀርም። ለጎጃም ዐማራ ጀግንነቱ የዘሩ ነው። ኦሮሙማው ሲያወድመው እነ አስረስ ዝም ብለው ቢያዩ ሌላው ዝም ብሎ ያያል ማለትም አይደለም። እዚያው ሞቆ እዚያው መፍላት። 10 መከላከያ ገድለህ 1ሺ ንፁሐንን ማስፈጀት ልክ አይደለም። በፍጹም ልክም አይሆንም። በአንድነት ወደፊት ተስፈንጠሩ። የምናገረው ይመርራል። ግን ዋጠው።
• የአንድ የ10 ሰዎችን አስተያየት ለመቀበል ስል ቆይቼ የአስተያየት ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው መልካም ንባብ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
~ ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
👆④ ✍✍✍ "…ይልቅ ስለ መጻኢው ጊዜ እናስብ። የአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋ ወደ ትግራይ ሄዶ መከረ የተባለው እውነት ከሆነ በቀጣይ ብዙ ደም መፋሰስ ሊከሰት ይችላል እና በሰፊው ይታሰብበት። አሁን ጦርነቱ ከተጀመረ መቆሚያው የሚታወቅ አይመስልም። በትግራይ እና በኤርትራም የሚፈሰው ደም ቀላል ይሆናል ተብሎም አይገመትም። ኤርትራም አርፋ አትቀመጥም። ሻአቢያ ዙሪያችንን እሳት ማንደዱን አያቆምም። በጦርነቱ የውጭ ኃይሎች ከኤርትራና ከኢትዮጵያ ጎን መሰለፋቸውም አይቀርም። እስራኤል ከወዲሁ ለሱዳኑ አልቡሁራን ማስጠንቀቂያ መስጠቷ፣ ኤምሬትስ ከሀሚቲ ጋር መቆሟም ወደ ኢትዮጵያም መሸጋገሩ አይቀርም። ኢራንም፣ ቻይናም፣ ሩሲያም ቀይ ባሕር ላይ ከሱዳንና ከኤርትራ ወገን ማረፊያ ስፍራ መሻታቸውና ማግኘታቸው አይቀርም። የአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋ መቀሌ ሄዶ ተናገረ የተባለው እውነት ከሆነ አማሪካም ከአቢይ ጎን መሰለፏ አይቀሬ ነው። ፕሮክሲ ዋር አለ ሱሬ። አዎ የእጅ አዙር ጦርነት ሁለቱ ኃያላን ኃይሎች በኤርትራና በኢትዮጵያ ምድር ሊያደርጉ ይችላሉ። በዚህ መሀል እነ አፋሕድ ከወዲሁ በጎንደር ስኳድ ስለተጠለፉ፣ ከደመቀ ዘውዱ ጎን ቆመን ብልፅግና ሆነን እንዋጋለን ብለው አውጀዋል። የዐማራ ፋኖ አፋብኃም ከወደ ኤርትራ በኩል ዘጭ የሆነ ትጥቅ ሳያገኝ አይቀርም። እናም ጦርነቱ ከተጀመረ ማን ወደማን እንደሚተኩስም የሚታወቅ አይመስለኝም። ከፊት ብቻ ሳይሆን ከቀኝና ከግራም ወደ ኋላህም ሁላ ልትታኮስ ትችላለህ። እናም ከበድ የሚል ይመስላል።
"…የአማሪካ የስንዴና የዘይት ርዳታ በመቆሙ ከትናንት ጀምሮ በጎንደር ፀለምት፣ በደቡብ ወሎ ለራብተኞች የሚቀርብ እህል በመጥፋቱ መቶ ሺዎች ለአደጋ መጋለጣቸው እየተነገረ ነው። ሐምሌና ነሐሴን በዚሁ ከቀጠልን ይብሳል፣ ይከብዳል። በተለይ ለትግሬ ይከብደዋል። ከወዲሁ ነዳጅ፣ ሸቀጣ ሸቀጥ ወደ ትግራይ እንዳይገባ መከልከሉ ነው የሚነገረው። ኢንተርኔት ዳግም በትግራይ ሊጠፋ ይችላል። በዐማራም እንዲሁ። እንዲያውም በዐማራ ክልል በጎጃምና በጎንደር፣ በወሎም በሸዋም ስፍራ ተለይቶ ኢንተርኔትም፣ ስልክም መቋረጡ እየተሰማ ነው። መድኅኒት፣ መብራት፣ ባንኮች ሊቋረጡ ይችላሉ። ትራንስፖርት በአየርም በምድርም ሊቆም ይችላል። ሰሜኑን በዚህ መልኩ ነው የማንበረክከውና የማስገብረው ባዩ የኦሮሞ ብልጽግናም በአክቲቪስቶቹ በኩል ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ በሚመስሉ ግለሰቦች ጭምር "ኢትዮጵያዊነት" የሚል ዘመቻ አስጀምሯል። ከአቢይ ጎን እንቁም። ከአቢይ ጎን መቆም ከኢትዮጵያ ጎን መቆም ነው የሚሉ ሰባክያን ተነሥተዋል። ልደቱ አያሌው ከተቃዋሚ ወገን፣ አጭቤው ታዬ ቦጋለም ከትራምፕ ዲፖርቴሽን መርሀ ግብር ለመዳን ሲል የእስራኤልን ባንዲራና የአሜሪካን ባንዲራ ከኋላው ሰክቶ ለጊዜው መያዣ መጨበጫው ጠፍቶት ከየትኛው ጎራም እንደቆመ ሳይታወቅ በኃይለኛው የአቢይ አሕመድ ቀንደኛ ደጋፊ ሆኖ ከአማሪካ ከወዲሁ ሰበካ ጀምሯል። መጀመሪያ አማሪካ እነ ታማኝ በየነ ያመጡት ጊዜ ቀልቡን ከገፈፍኩት ወዲህ ሲባክን፣ ሲረግመኝ ከርሞ አሁን ለይቶለት መበልፀጉን እያወጀም ነው። የበፊቱ ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አሰልጣኙ፣ ሲጀምር ብአዴን፣ ቆይቶ ኦህዴድ፣ አንዳንዴ ቄሮ የጃዋር አሽከር፣ የጎንደር ስኳድ፣ የወሎ ህብረት፣ ሲያሻው ግንቦት ሰባት በሞቀበት የሚፈላው ታዬ ቦጋለም ሰሞኑን እያፈላ ነው።
"…ምን አልባት ልደቱ ለብልጽግና አብሶ ለኦሮሙማው የሚናገረዉ ነገር ከሰሞኑ በኢትዮጲያኒስትነቱ ቅኝት ዐማራም በመምሰል ስለ ኤርትራ ነው እየደሰኮረ የሚታየው። ስለ ኢትዮጲያ ለመነጋገር ከሻቢያ ይልቅ ጀዋር ጋር ብነጋገር ይሻለኛል በማለት በፈረንሳይኛ ለኦሮሙማ መገረድ እፈልጋለሁ ያለዉም አይረሳም። ኦሮሙማ ሰሞኑን ሰሜኑን የማድቀቅ ዕቅዱን ለማሳካት ፌክ ካልሆነ እና ከኢሳያስ ጋር ጥቅሴ ሳይሆን የምር ተራዋ ደርሶ ኤርትራን ለመጨፍጨፍ፣ ከኤርትራም ለመግጠም ወስኖ ከሆነ ነገርየውን በቀላሉ ማየት ተገቢ አይደለም። ኢሬቻን ቀይ ባህር ለማክበር ዝግጅት ያለም መምሰሉ እየታየ ነው። አሁን የማሟቂያ ሰዓት ነው። ከጎምቱ የብልጽግና አክቲቪስቶች መካከል እስከአሁን ተከርብቶ ሻአቢያን በግላጭ መስደብ የጀመረውም ስዩም ተሾመ ብቻ ነው። እነ ዶር ዳኛቸው አሰፋ ገና ናቸው። ትግሬን ለማብሸቅ ሲል የኤርትራ ፍቅር ገና አልወጣልኝም ሲል የነበረው ሰው አሁን ምን እንደሚወስን እያሰበበት ነው። እስከዚያው ድረስ አጅሬ ብልፅግና ኢትዮጵያኖችን እያጃጃለ ወዳጁን ኤርትራን እንዲወጉለት እየሰበከ፣ ከኤርትራም ጋር እንካሰለንቲያ እየተሰጣጠ ነው። አሁን ምን አልባት ጭንቅ የሚሆነው እና እነ ልደቱን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከተው ሕወሓት ከሻአቢያ ጋር የሚሰለፍ ከሆነ ነው ብዙ ነገሩ የሚበላሽበት። እንዲያ ከሆነ የሚቸገር ይመስለኛል። ወይም ደግሞ የታባቱንስና የመጣው ይምጣ ብሎ የኦሮሙማውን ሓሳብ በማጠናከር ኢትዮጵያኖች፣ ዐማረውም ጭምር ከኦሮሙማ ጎን ሆነው ኤርትራና ትግሬ ላይ እንዲነሱና እንዲዘምቱ ለማድረግ የሚያስችለውን ንግግር ለማረግ ቃላት እየመረጠ እና እያጠና ያለ ይመስለናል የሚሉ መተርጉማንም አሉ።
"…በዚህ የኑሮ ውድነት፣ በዚህ የጦርነት ጉሰማ ወቅት፣ በዚህ የራብ ዘመን፣ የቤት ኪራይ ሰማይ በገባበት ዘመን፣ መብራት 400% ውኃና ትራንስፖርት ናላ በሚያዞሩበት ዘመን በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ እንዲሉ የአቢይ አገዛዝ የመንግሥት ሠራተኞችን ሊቀንስ፣ ከሥራ ውጪ ሊያደርግ መሆኑም ተነሰምቷል። የጎጃሙ የፋኖ አመራሮችም ከወዴት ወገን እንደሚቆሙ ገና አልወሰኑም። አስረስ መዓረይ ከደቡብ ጎንደሮቹ ከእነ ጌታ አስራደ እና ከሸዋዎቹ ከእነ መከታው ጋር አንድ ላይ እንሥራ የሚል ጥያቄ ማቅረብ መጀመሩ ሲሰማ ግን ግራ የገባቸው ይመስላል። ከሻአቢያ ጥይት ተቀብሎ ሸአቢያን ሊወጉ ነውን የሚሉም መተርጉማን አሉ። ዐማራ አሁን ነው በዚህ የፈተና ወቅት ባህር ከፍሎ አሻጋሪ ሙሴ የሚያስፈልገው። የዘሪሁንን እና የዳንኤል ክብረትን የበለጠ ገረድ፣ የበለጠ አሽከር ለመሆን የሚጋጋጡትን መጋጋጥ እርሱና በመጪው ጊዜ ላይ እንወያይ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
👆②✍✍✍ …ልጆቹን ያሳደገችለትን፣ ሞገስ የሆነችውን፣ ያሳደገችውን እናት ቤተ ክርስቲያኑን ባትሞትም እንኳ ለሞት የሚያበቃ ዱላ እንዳሳረፈባት ባሰብኩ ጊዜ ነው። ትግሬንና ዐማራንማ ጌቶቹን ለማስደሰት ሲል እንደ ጉድ ነው የወረደባቸው። ጁንታ፣ ጃዊሳ እያለ በአረብ ጀበሎ ነው ደበደባቸው። በዚህ የትግሬና የዐማራ ጥላቻ ደግሞ ከሰውበሰው ተጫነ ከዘርሽ ጋር አንድ ናቸው። ሁለቱም ስምም ናቸው።
"…መሸ ነጋ፣ ትናንትም ሆነ። ምቹ ጊዜ ቀንም ይጠብቅለት የነበረው አሁን በአባቴ በኩል ቂጠታ ነኝ ኦሮሞ ነኝ ባዩ ዘሪሁን ሙላቱ እጅ ላይ ዳንኤል ክብረት ወደቀ። እኔ በትናንቱ የዘሪሁን ቅኔያዊ ጦማር ላይ የታዘብኩት የገባኝም ነገር ቢኖር የዳንኤል ክብረት ጀንበር መጥለቋን፣ አበባ መልኩም መርገፉን ነው። ይሄን ያየው ዘሪሁን ሙላት አድብቶ፣ አድብቶ ጀመረው። አያ እገሌም ብሎ ስሙን ሳይጠቅስ ሶቶ ገባለት። ዳኒ አሁን ያረጀ ዝንብ ነው። ማስቲካ፣ ሸንኮራም ነው። ብልፅግና ደግሞ እንደ ኮንዶም ተጠቅሞ መጣል ልማዱም ተፈጥሮውም ነው። ዳኒ አሁን ቢያንስ እንኳ አውሮጳም፣ አሜሪካም ቢሆን መሰደድ እንኳ አይችልም። ወዳጆቼ ዕጣ ፈንታችሁ እንደ ማስቲካ፣ እንደ ሸንኮራም ከመሆን ፈጣሪ ይሰውራችሁ። ዳንኤል ብቻ ሳይሆን አሁን በብልፅግና ቤት ብዙ አሮጌ የጋሪ ፈረሶች ይታዩኛል። ማስቲካው አገኘሁ ተሻገር፣ ላንቲካው ብርሃኑ ነጋ እና ሸንኮራው ዳንኤል ክብረት ሆነው፣ መስለው የሚታዩኝም ታኝኮ ጣእሙ እንዳለቀ ማስቲካ እና ታኝኮ ተጨምቆ ለከፍት መኖ ቢሉ ለእሳት እንደተዘጋጀ ሸንኮራ፣ አገልግሎቱን ጨርሶ ለጅብ እንደተተወ የጋሪ ፈረስ ነው። እንደዚያ ነው የማያቸው።
"…አሁን ላይ የወሊሶ ኦሮሞ ነኝ ባዩ ዘሪሁን ሙላት ወሎ ተወልዶ ባሕርዳር ያደገውን ዳንኤል ክብረትን ኤርትራዊም አድርጎት ቁጭ ብሏል። ዳንኤልን ኤርትራዊ ያስባለው ደንግሞ የዳንኤል ክብረት የአያቱ ስም ነው። ዳንኤል ክብረት ብርሃኔ። ብርሃኔ የትግሬ ስም ነው ባይ ነው ዘሪሁን ሙላቱ ሰውበሰው ተጫነ። በቀደመው ጊዜ፣ የዳንኤል ክብረት መልኩ ሳይረግፍ፣ ወደ ጓሮ ሳይገፋ፣ ከአቢይ አሕመድ ጋር በአንድ አልጋ ካልተኛን፣ አንድ ግልገል ሱሪ ካልታጠቅን፣ በአንድ ፖፖም… ይሉ በነበረ ዘመን ዘርሽ ዳንኤልን ብፁዕ አቡነ ኤልሣዕ ጎንደር ላይ ባወጡለት የማዕረግ በክብር ስሙ ነበር እንዲህ እያለ በፌስ ቡክ ገጹ ፕሮሞሽን ይሠራለት የነበረው። ያኔ ኢሳትም የአቢይ ገረድ በነበረ ዘመን ማለት ነው። "…#ከሙአዘ_ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጋር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቃለ መጠይቅ ዙሪያ የተደረገ ውይይት።" March 2022
https://www.facebook.com/share/p/1AY9PtTkd5/
"…ያኔ ደግሞ ዳንኤል ክብረት ከቤተ መንግሥት፣ ዘሪሁን ሙላት ከቤተ ክህነት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሆነው ጁንታ፣ ትግሬ የተባሉትን ፓትርያርክ አባ ማትያስን አዋርደው፣ ሰድበው፣ አጠገባቸው ያሉትን ትግሬዎችም በሙሉ ጠቁመው፣ ለቃቅመው አስረው፣ አሳስረው፣ ዘሪሁን እንዲያውም በሴት አንቀጽ ጠርቶ ቅዱስነታቸውን "አንቺ" ብሎ በመጥራት በዓላማ ስምም የሆኑበት ዘመንም ነበር። ሰውበሰው ተጫነም ጎፍልቶ ትግሬን በመለስ ዜናዊ አሳብቦ ይሞልጭ የነበረበትም ዘመን ነበር። ትግሬው አቡነ ጳውሎስ አስተምረው፣ ሰው ያደረጉት ሰውበሰው ተጫነም ትግሬዎችን ሲጠላ መቼም ለጉድ ነው። በራበው ጊዜ ከርሱን እየሞላች በተጣላቻቸው ጳጳሳት ላይ መጽሐፍ ታጽፈው የነበረችው የአዝማሪ መሀሙድ አሕመድ ሚስትም ወሮ እጅጋየሁ ከበደም ብትሆን እኮ የዓድዋ ትግሬ ነበረች። ብዙ ትግሬዎች የዘሪሁን የጭንቅ ቀን ደራሾች ነበሩ። አቢይ ሲመጣ ኦሮሞ ነገሠ በሚል ግብታዊነት ነው ብዙዎቹን ወዳጆቹን ያጣው።
"…ታዲያ አሁን ዳንኤል ክብረትን እና ሰውበሰው ተጫነን ያቀያየማቸው ጉዳይ ምንድነው? ወደሚለው ጉዳይ እንግባ። ያጣላቸው ያልነ እንደሆን መልሱን እንደ እኔ ያለው የሁለቱን ተገዳዳሪዎች የትመጣ እና የኋላ ታሪክ፣ መገፋፋትና ስረመሰረት የሚያውቅ ሰው ካልሆነ በቀር ማንም በቀላሉ ሊረዳው አይችልም። ዳንኤል ከእነ አቢይ በፊት ከእነ አቦይ ስብሐት ጋር ይሠራ ነበር። ዘሪሁንም እንደዚያው። የአሁኑን ፀብ ግን የጀመረው ስለእውነት ለመናገር ሳያስበው ራሱ ዳንኤል ክብረት ነው። ዳንኤል ክብረት አቢይን ለማስደሰት ሲል፣ በጌታው ዘንድ ሞገስን ለማግኘት ሲል የጻፈው ጦማር ነው የዘሪሁንን ቁስል ነካክቶበት ያስወረደበት። ዳንኤል በጦማሩ የዛሬው ፓስተር በጋሻው ደሳለኝን ስሙን ሳይጠቅስ በፌስቡክ ገፁ ላይ በዚያው በተለመደው ተረትእንዲህ ብሎ ይነቁረዋል። https://www.facebook.com/share/p/1ZGPViGuWW/
የዐቢይ ምጽዋተኞች
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ(በረከታቸው ይደርብንና) በነበሩ ዘመን አንድ ሰው እሳቸውን ሰድቦ መጽሐፍ ያሳትማል፡፡ (ልብ በሉ ሰዳቢው በጋሻው ደሳለኝ ነው። የመጽሐፉም ርእስ የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች የሚል ነበር፣ የመጽሐፉ ጸሐፊ ግን ማረጋገጫ ባይኖረኝም ራሱ ዘሪሁን ሙላት እንደነበር ነበር የሚወራው) …ቤተ ክህነቱ ይከሰዋል፡፡ እሱም ይታሠራል፡፡ በኋላ አቡነ ጳውሎስ ይሰማሉ፡፡
“ለምን ከሰሳችሁት” አሉ
“እርስዎን ሰድቦ፣ መጽሐፍ አሳትሞ እየሸጠ ነው” ብለው መጽሐፉን አምጥተው አሳዩዋቸው፡፡
“ለመሆኑ ልጁ ሥራ አለው” አሉ
“ኧረ የለውም፤ ይሄንኑ እየሸጠ ነው የሚበላው”
“ሊሸጥ የሚችል ስምስ አለው”
“ኧረ ስሙ መንገድ ላይ ወድቆ ቢገኝ ማንም አያነሣውም”
“በሉ ተውት፤ ከሚርበው ስሜን ሽጦ ይብላ፤ ለእኔም እንደ ምጽዋት ይቆጠርልኛል፤ እሱኮ የሚሠራው ሥራም፣ የሚሸጠው ስምም ስለሌለው ነው” አሉ ይባላል፡፡ አሁን አሁን የዐቢይን ስም ሽጠው የሚበሉ ምጽዋተኞች ብቅ ብቅ ብለዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ሁለት ነገር የላቸውም፡፡ አንድም ሥራ የላቸውም፤ አንድም የሚሸጥ ስም የላቸውም፡፡ ያላቸው አማራጭ የዐቢይን ስም ሸጠው መብላት ነው፡፡ ልጆቻቸውም በዚህ ሽያጭ ነው የሚያድጉት፤ ቢልም የሚከፍሉት ከዚሁ ሽያጭ ነው፡፡ ለዐቢይ በዋናነት የሚጸልዩት እነዚህ ሰዎች ናቸው፡፡ ስሙ እንጀራቸው ነዋ!
እነዚህ የዐቢይ ምጽዋተኞች ናቸው፡፡
ስሙ እንጀራቸው ነው፡፡
ስሙ ልብሳቸው ነው፤
ስሙ የታክሲ ሂሳባቸው ነው፡፡
ያሳደጋቸው የዐቢይ ስም መሆኑን ልጆቻቸውም ያውቃሉ፤ እናም ምኞታቸው አሳዳጊያቸውን ዐቢይን ማየት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ፡-
ለአንዳንዶች በታላላቅ ፕሮጀክቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፤
ለአንዳንዶች የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተመቻችቶላቸዋል፤
ለአንዳንዶች በሪሞት የሚሠሩት ሥራ ተዘጋጅቶላቸዋል፤
ለአንዳንዶች በኮሪደር ልማት የሥራ ዕድል አግኝተዋል፤
ለአንዳንዶች በሌማት ትሩፋት የገቢ ምንጭ ተፈጥሮላቸዋል፤
ለአንዳንዶች በአረንጓዴ ዐሻራ የእንጀራ ገመድ ተዘርግቶላቸዋል፤
ለአንዳንዶች በስንዴና በሩዝ አብዮት ሀብት ተትረፍርፎላቸዋል፤
ለአንዳንዶች ቤት ተሠርቶላቸው ሱቅ ተሰጥቷቸዋል፤
ለነ እንቶኔ ደግሞ ስሙን ሸጠው የመተዳደር የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፤ እናም፤ ምጽዋተኞችን ተዋቸው፤ እዘኑላቸው፤ አትፍረዱባቸው፡፡ ስም በመሸጥ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው “የዐቢይ ምጽዋተኞች” ናቸው፡፡ በማለት የጻፈው ጽሑፍ ነው ዘርሽን ያሳበደው። ዳንኤል የሳተው ነገር ግን በጋሻው ፓትርያሪኩን በሰደበ ጊዜም ሥራ ነበረው። ሥራውም ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝለት ሥራ ነበር። ለአንድ ዘማሪ በስመ አብ ብሎ በድምጽ ገብቶ የዚያን ጊዜ 3ሺ ብር ይቀበል የነበረ፣ ሀገር ምድሩ ሁሉ በጋሻው፣ በጋሻው ብሎ በተጠራባቸው ጉባኤዎች ሁሉ ብር በጆኒያ ተሸክሞ…👇② ✍✍✍
መልካም…
"…የሰውበሰው ተጫነን እና የዳንኤል ክብረትን ለተፈላጊ፣ ተወዳጅ ገረድና አሽከር ለመሆን ሲሉ እርስ በእርስ የተራገጡበትን የፌስቡክ ላይ ጦርነት ምክንያት በማድረግ በዚያውም የከሸውን ሃላል ቃጥራ አጭቤ ታዬን ሸንቆጥ አድርጌ ለማስለፍለፍ የፈለግኩበትን ርእሰ አንቀጽ ልለጥፍላችሁ ነኝ…?
• ምን ትላላችሁ…? 😁
"…የሁለቱንም የእርስ በርስ መነቋቆርም ሆነ የፒፕሉን ሾርት ሚሞሪያምነት የታየበትን ጦማሮች አንብቤአለሁ። ዳንኤል የተረት ጦማሩን ሲጽፍ መልእክቱ ሰውበሰው ተጫነን (ቂጠታን) ያበሳጨዋል ብሎ እንዳልጻፈው እርግጠኛ ነኝ። በዳንኤል የተረት ጦማር ዘሪሁን ለምን ጓ እንዳለ እስከአሁን የሚገባው፣ የሚገለጥለትም አይመስለኝም። ዳንኤል ወሬ አሳመርኩ ብሎ በዘሪሁን ቁስል ላይ እንጨት ነው የሰደደበት። 😂 …ይሄን ደግሞ የማውቀው ብቸኛው ሰው እኔ ዘመዴ ብቻ ነኝ። የዳንኤል የተረት ጦማር ለማን እንደተጻፈ ሳይሆን ዘሪሁን ለምን ጓ እንዳለ የገባው እኔን ብቻ ነው።
"…ዘንድሮ መቼም ጮቄ ተራራ ላይ ሆኜ ተአምር እያየሁ ነው። ዘብጥያ ስላወረዱት ነውረኛ አመራርም እየሰማሁ ደሜ ሲሞቅ ነው የዋለው። የብዙዎች ስጋት ዐፋጎ በእነ አስረስ መዓረይና በእነ ማርሸት ተጠልፎ ዐማራንም፣ ጎጃምንም ያዋርድ ይሆን የሚል ነው። አይመስለኝም። እኔ እያየሁ ባለሁት እንቅስቃሴ ፍፁም ደስተኛ ነኝ። ጎጃም አርበኛ ዘመነ ካሤን ነጻ የሚያወጣ፣ መሰሪዎቹንም ፍዳ የሚያበላ እሳት የላሰ ተናዳፊ ተርብ አራስ ነበርም የሆኑ የበላይ ዘለቀ ልጆች እንዳሉ የገባኝ ነውረኛውን ዘብጥያ ሲያወርዱት ባየሁ ጊዜ ነው። ማንን እንዳትሉኝ በቃ አስረውታል አስረውታል። እና የባለ ትዳር ሚስት ደፍሮ እያዩት ሊምሩት ነው? ዘመነም ለማስፈታት አይሞክራትም። መዓረይም፣ ማርሸትም አቅም ይላቸውም። ብራቮ የበላይ እስትንፋሶች። አንበሶች። 👏👏👏
"…አሳዬ ደርቤ ከወሎ፣ ባዶ ጭንቅላት አደራው ዘላለም፣ የማከብረው ሞገሴ ሽፈራውና ሌሎችን ማርሸት ፀሐዩ ሰብስቦ መመሪያ ሲሰጥ፣ ጨበጣ ግጠሙ ሲላቸውም እኔም ተደብቄ እየሰማሁ ነበር።
"…የትግሬ ፊት ይዘህ ጎጃሜ ነኝ እየልክ ባለ ትዳር የልጆች እናት የቀማኸው የኡጋንዳው ጋዜጠኛም ነብር አየኝ በል።
• ነገ ከምስጋና በኋላ እንገናኝ…
"…ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ኤፌ 5 ፥16
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:00 ሲሆን በዘመድ ቴቪ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• ZemedTv 👉 https://zemedtv.com/live.html
• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/ZemedMedia
• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6vsv5z--zemede-july-06-2025.html?e9s=src_v1_upp_a
• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
11977 H 27500
• ላይ ይከታተሉን።
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
የጨነቀለ’ት…
"…የምን መቀባጠር ነው? …አለቃቸው አቢይ አሕመድ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ቢሆንም… በዐማራ ተሸነፍኩ ማለት፣ ዐማራ ለድርድር ከእኔጋር ተቀመጠ ማለት የሞት ሞት፣ ክብረነክ ነው፣ ትግሬ በሽመል ፀጥ ለጥ አድርጎ የገዛውን እኔ በፈንጂና በድሮን አቃተኝ ብል ዓለሙ ሁሉ፣ ኦሮሞውስ ምን ይለኛል በሚል ምንተ እፍረቱን ያለተወገረ፣ ያልተወቀጠ፣ ያልተቀጠቀጠ ይመስል በልቡ እያለቀሰ፣ በአፉ አልሸነፍ ባይ ሆኖ "ፋኖ መደራደር ከፈለገ እዚያው በክልሉ በቀበሌና በሰፈሩ ይደራደር" ሲል ትሰማዋለህ። ነገርየው ግን እንደ ወሬው አይደለም። ከባድ ነው።
"…በኦሮሙማወረ የተናቀው ዐማራ፣ ብአዴን እስካለ ድረስ እንደ ገረድ፣ እንደ አሽከር፣ እንደ ውሻ እግር ስር እያንከባለልነው፣ እንደ አህያ ረግጠን፣ እየወገርን እንገዛዋለን ብለው አስበው እንደ ቄራ ከፍት አርደን፣ እንደ ዶሮ ጨፍጭፈን፣ እንደ ዕቃ ሽጠን ለውጠን፣ በግሬደር አርሰን ቆፍረን ቀብረነው እንኳ ጠያቂ የለብንም ያሉት ዐማራ አሁን የኤዶም ገነት ደጃፍ ላይ ያለው የእሳት ሰይፍ የያዘ ኪሩቤል ሆኖባቸው ጨንቋቸዋል።
"…የጎጃሙ ስግብግብ ራስወዳድ የዐማራ ፋኖ አመራር ቢስተካከል፣ የጎንደሩ የብአዴን ስኳድ ፋኖ ቢስተካከል፣ የሸዋው የእስክንድር፣ የወሎው የሙሀባው ፋኖ ወደ መስመር ቢገባ አለቀ፣ ደቀቀ ነበር። አሁን ታቦት አሸክመህ፣ መስቀል አስይዘህ፣ ከቤተ ክህነት ጳጳስ፣ ቄስ፣ ከመስጊድ ሼክና ኡስታዝ አግተልትለህ፣ ነጭ ጺም ያለው ሽማግሌ፣ ታዋቂ ሯጭ ሰብስበህ መሳሪያ ጣል፣ በቃ እንታረቅ ብትለው የሚሰማ አንድም ፋኖ የለም። አንድም አልኩህ።
"…አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ሰሜነኞቹ አንድላይ ከገጠሙ ደግሞ ነገርየው ይበልጥ ይከፋል። እናም የምን ሽማግሌ ሰብስቦ ማስጨነቅ ነው? ገጥመሃል ገጥመሃል ነው። ስንቱ ጀግና ከወደቀ በኋላ የምን እየዬ አስታርቁን ነው?
"ርእሰ አንቀጽ"
"…አቢይ ውሸታም ነው። ብልፅግና ጨፍጫፊ ነው። ፓርላማው እንቅልፋም ነው። መከላከያው ጨፍጫፊ ነው። አገዛዙ ፀረ ሕዝብ፣ ፀረ ሰው፣ ፀረ ሃይማኖት፣ ፀረ ባሕል፣ ፀረ ኢትዮጵያ ነው ወዘተረፈ ብሎ እሱ ፓርላማ ቀርቦ በተበጠረቀ ቁጥር፣ ራሱ ጠያቂ ራሱ መላሽ በሆነበት የቴሌቭዥን መስኮት ዲስኩሮቹ በተሰራጩ ቁጥር፣ አሰፍስፎ ጠብቆ እሱን በማሳጣት ለእሱ ግብረ መልስ ለመስጠት በሚል ሰበብ፣ ሱፍና ከረባት ገጭ አድርጎ፣ በቴሌቭዥን፣ በዩቲዩብ፣ በቲክቶክና በፌስቡክ ቀርቦ አቢይ እንዲህ አለ፣ እንዲህ ዋሸ፣ ቀጠፈ ብሎ ሲተነትኑ መዋል ማደር እንዴት ያለ ሰገጤነት፣ ምን የሚሉት ዥልጥ ጅልነትስ ነው? እንዴት ሰው ሰባት ዓመት ሙሉ የአንድ በሃላል ማንነቱ በዓለሙ ሁሉ የታዋቀን፣ ሁሉ ሰው የተረዳውን ሰው የተገለጠ ውሸቱን መልሶ መላልሶ ችክ እስኪል ድረስ ሲተነትን ይኖራል? ጥቅሙ ነው ያልገባኝ።
"…ይሄን ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሥርዓት ገርስሶ፣ ለውጥም አምጥቶ የተሻለ ሥርዓት፣ እውነተኛ ሕዝባዊ መንግሥት መመስረት ነው የሚሻለው ወይስ የአያልቄን የአባ ሳክሶን የሐሰት ዲስኩር በየደቂቃው ልተንትነው ብሎ አየር ይዞ መበጥረቅ ነው የሚሻለው? በቃ ሕዝቡ እኮ ሁሉን ዐወቀ፣ ሁሉንም ተረዳ፣ እንኳን ሰፊው ሕዝብ ይሄን የአገዛዙን ክፋት፣ አረመኔነትና ውድቀት ራሳቸው የአገዛዙ ሚዲያዎች መመልከት በቂ ነው። የአቢይ አሕመድን የማኅበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገፁን የአስተያየት መስጫ ሰንዱቅ ማየቱ ብቻ በቂ እኮ ነው። ሕዝቡ ምንያህል እንደተጠየፈው፣ እንደናቀው ለማወቅ አይደለም በሰውየው፣ በራሱ ደጋፊ የፓርቲ አባላት፣ በሚዲያ ሠራዊቶቹ በካድሬዎቹ ጭምር ምን ያህል እንደተናቀ መመልከት ይቻላል። እናም ቀባሪ ያጣን አንድ ግለሰብና ፓርቲን በየጊዜው እያነሱ እንዲህና እንዲያ አለ ብሎ ማላዘን፣ እንደ ጋማ ከብት መልሶ መላልሶም ማመንዠክ ጥቅሙ አይታየኝም።
"…ይልቅ ይሄን ሥርዓት ለማስወገድ ጫካ ገብቶ ነፍጥ ያነሣውን አካል በደከመው እያበረቱ፣ ጠንክሮ እንዲወጣም እያበረታቱ፣ ተግዳሮቶቹን በድፍረት እየቀረፉ፣ ሾተላይ ሴረኞቹንም ኮምጨጭ እያሉ እየገሰፁ፣ እየነቀሉም ወደፊት እንዲመጣ ማድረግ ነው እንጂ የምን በሞተ እና ቀባሪ ባጣ አስከሬን ፊት ቆሞ ማላዘን ነው? በለስ ቀንቷቸው ቢመጡ፣ ሥልጣን ላይ ቢወጡ ከአቢይ አሕመድ የባሰ ጨፍጫፊ፣ ዘራፊ የመሆን ባሕሪያቸው ከወዲሁ ፈጥጦ የወጣባቸውና የተገለጠባቸውን እንደ ዐማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች ያሉትን ዓይነቶቹን አደብ የሚገዙበትን መስመር ማመቻቸት፣ መፍትሄ መፈለግም እንጂ አቢይ ነዳጅ አወጣለሁ ብሎ ዋሸ፣ ሙፈሪያት ከሚል የጠራችው ቁጥር እና አቢይ አሕመድ የጠራው ቁጥር የተለያየ ነው ወዘተ እያሉ ቁጥር አይፈሬን የሆነን ግለሰብ አስር ጊዜ እኮ አይደለም 7 ዓመት ሙሉ ስሙን እየጠሩ ችክ ምንችክ ብሎ ማላዘን ጥቅሙ ምንድነው? ፐ እገሌ እኮ አቢይን እርቃኑን አስቀረው ብሎ እርቃኑን በቆመ ሰው ላይ ሲንዘባዘቡ መዋልም ልክ አይመስለኝም።
"…አሁን የሕዝብ ጥያቄ እኮ አንተ አክቲቪስቱ፣ አንተ ቦለጢቀኛው፣ አንተ ጋዜጠኛው፣ አንተ ታጋዩ፣ አንተ ተንታኙ ልክ እንደ ሕዝቡ፣ ሕዝቡ የመረረውንና ያንገሸገሸውን ይሄን መርግ ማን ከላያችን ያንሣልን ብሎ የሚያለቅስበትን ጉዳይ መልሰህ፣ መላልሰህ አዲስ ግኝት ያገኘህ ይመስል እንድትዘበዝበው አይደለም። ነዳጅ በሊትር 120 ብር ገባ፣ ምስር በኪሎ 300 ብር ገባ(አሁን ይሄን ከጻፍኩ በኋላ 350 መግባቱን ሰማሁ)፣ አንድ ኪሎ ኮሮሪማ 3ሺ ብር ገባ፣ አንድ ደረቅ እንጀራ 35 ብር ገባ፣ የአንድ ዶላር ምንዛሪ 160 ብር ደረሰ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር በመኪና መሄድ ከባድ ሆነ፣ የቤት ኪራይ ጣራ ነካ፣ ሀኪሞች፣ መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ በወር 71$ ነው፣ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ፍቺ እየበዛ ነው። ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች እየወደሙ ነው፣ ገበሬው ማረስ፣ ማምረት አልቻለም ወዘተረፈ እያሉ ሀገር ምድሩ የሚያውቀውን፣ በድርጊቱ ተማርሮ መፍትሄ ያጣበትን ጉዳይ ልክ እንደ አዲስ ግኝት ፀዳ ኮስተር ብሎ ከሕዝቡ ጋር መልሶ መላልሶ ማልቀስ እንደ አስለቃሽ ደረት አስመቺ ሴት ሕዝብን ያለምንም መፍትሄ ዋይ ዋይ ማስባል ምን ይሉታል?
"…በዕድሩ ድክመት ምክንያት ቀባሪ አጥቶ ከሞተ የቆየውን የሞተ፣ የገማ፣ የከረፋ አረመኔ ሥርዓት አስር ጊዜ እያነሳህ እንደ ቡና ከምትወቅጠው ከዚያ ይልቅ እየመጣ ስላለው ራብ፣ እየመጣ ስላለው ደም አፋሳሽ ጦርነት፣ እየተበራከተ ስላለው ፍልሰት፣ ስደት፣ ዘረፋ፣ እገታ፣ ጭፍጨፋ አድምቶ መወያየት፣ መምከር፣ ስለ የመብራት፣ የውኃ ዋጋ መናር፣ የገበሬው ማዳበሪያ እጦት፣ የምርት መቀነስ ወዘተረፈ የመፍትሄ ሓሳብ ማምጣት አይሻልም። ጨክነህ ስለ ፋኖ ጎታች፣ ሾተላይ፣ ሰልቃጭ፣ ደፍጣጭ ፋኖ መሳይ ፍናፍንቶች ብትወያይ አይሻልም? ሚዲያን ያህል ትልቅ መሣሪያ ይዘህ ስታበቃ ሁልጊዜ አቢይ ውሸታም፣ ዋሾ ነው እያልክ አየር ከምትይዝ ደፍረህ ይሄን አገዛዝ ሊቀይር ይችላል ብለህ ተስፋ የጣልክበትንና የሕፃን ጨዋታ እየመሰለ የመጣውን የዐማራ ፋኖ ትግል መስመር ስለ ማስያዝ ብትመክር አይሻልም? ይሄ ሥርዓት እንደሁ ፋኖም ባይመጣ እንኳ በራሱ ሽግር መውደቁ፣ ተገርስሶ መውደቁ እንደሁ አይቀርም። ከወደቀ በኋላ ታዲያ እነ ዘመነ ካሴና እነ ሀብቴ፣ እነ ምሬ፣ እነ ደሳለኝ፣ በአንድ በኩል እነ እስክንድር፣ እነ መከታው፣ እነ ሙሀቤ፣ እነ ደረጄ በሌላ በኩል ሆነው አራት ኪሎ ሲጨቃጨቁ ሌላ ደም መፋሰስ ከመከሰቱ በፊት ከወዲሁ እንደ ትልቅ ሰው ተሰባስበህ በጊዜ ብትመክር፣ ብትመካከር አይሻልም?
• 3 :1 ።
መልካም…
"…ከወትሮው ዛሬ ይሻላል… ወደ 20 ፍሬ የሚደርሱ ሰዎች 😡 ጓ ብው ብለው አይቻቸዋለሁ። እነዚህ ሰዎች የርእሰ አንቀጹ ተቃዋሚዎች ናቸው ማለትም አይደለም። ባነበቡት ነገር ብስጭት የገባቸውም ሰዎች ይሄን የብስጭት፣ የንዴት 😡 ኢሞጂ ስለሚጠቀሙ ነው።
"…ለማንኛውም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ዛሬ በጻፍኩት ርእሰ አንቀጽ ላይ በጨዋ ደንብ መወያየት እንጀምራለን። እየቆየሁ ስመጣ አገዛዙ እጅ ሰጥተውት የነበሩትን እነ መንግሥቱን እጃቸውን ጠምዝዞ እስከ አፍንጫቸው ድረስ አስታጥቆ ወደ ጫካ መመለሱን ካልሰማችሁ ሰሞኑን እነግራችኋለሁ። ሌላው አንደጊዜ የተከበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ ጀምረውት የነበረውና በጊዜ የተቃጨው ጎንደርና ጎጃምን የሚያቃቅር አጀንዳም በእነ አስረስ በኩል እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ ሰሞኑን ጎንደርና ጎጃም የሚነታረኩበት አጀንዳ ይለቀቃል። መጠበቅ ነው።
• ሓሳባችሁን መስጠት ጀምሩ። እኔም ቁጭ ብዬ ማንበቤን እቀጥላለሁ። ጀምሩ…✍✍✍ ጻፉ።
• ማስጠንቀቂያ…
"…ተቃውሞ እንኳን ቢኖራችሁ በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን ግለጹ። መብታችሁ ነው። በርእሰ አንቀጹ ብትናደዱ እንኳ በመሳደብ ሳይሆን በጨዋ ደንብ በመተንተን ተቃወሙ። ይሄ በጣም ተላላቅ ሰዎች የሚሳተፉበት ገፅ ስለሆነ የመንደር ዱርዬ ጋጠወጥ ስድብ በገጼ አይስተናገድም። ብስጭታችሁን ዋጥ አድርጋችሁ ተሳተፉ። ባለጌ ይቀሰፋል። ሰምታችኋል!
👆④✍✍✍
6ኛ፦ የአፋጎ መሪዎች ሃይማኖተኛ ወታደር እንዳዘዙት አይሆንም በሚል መርህ ታች ያለውን የፋኖ አባል እምነትም ሕይወትም እንዳይኖረው እየሠሩበት ነው። እነአስረስ በደንብ የቀረቡትን የብርጌድ መሪ ሴት እስከ መጋበዝ ድረስ ያደርጉታል። ተዋጊው ወታደር ትምህርት እንዳያገኝ በተለያየ መንገድ አጥረው ይይዙታል። የፖለቲካ መኮንን ተብለው እየዞሩ ያስተምሩ የነበሩትን ሳይቀር አስረስ መዓረይ ወዲያው ነው ያስቆማቸው። "ወታደር አድርግ አታድርግ እንጂ ትምህርት አያስፈልገውም" በማለት ነው ለምን ብለው እንዳይጠይቁ፣ እንዳይማሩ፣ እንዳያውቁ ያደረጓቸው። በተለይም ለሃይማኖቴ፣ ለማዕተቤ ብሎ የወጣውን ስለሚፈሩት በሩቁ ተሸማቆ እንዲኖር ያደርጉታል። ፋኖ ዮሐንስን ጨምሮ የተገደሉት፣ የተወገዱት ምሑራን ፋኖዎች፣ ቀለም ገብ ፋኖዎች በሙሉ ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጆች ናቸው። ከጠጪ፣ ከሠካራም፣ ከቅባቴና ከጴንጤዎቹ አመራሮች እስከአሁን እንኳን ሊሞቱ፣ ሊገደሉ እንቅፋት ጭምር የመታቸው የሉም።
7ኛ፥ ከክፍለ ጦር ጀምሮ እስከ ብርጌድ ሻለቃ ድረስ በየጊዜው ሪፎርም በማድረግ በመገለባበጥ ያማስሉታል፣ የትግሉን ሥነ ባህርይ የለመደው ለምን ብሎ መጠየቅ እንዳይችል አርፎ እንዲቀመጥ ያደርጉታል። በአዲስ የተሾመውም የላይኛውን እያየ እንዳያወርዱት በሥጋት ዝም ጭጭ ብሎ የመሪዎችን ፎቶ እየተቀባበለ "ጀግናው፣ ሙሴያችን፣ ቶማስ ሳንካራችን፣ የትውልዱ መሪ፣ የእኛ ባትሆን ኑሮ፣ አንተኮ ትለያለህ.."እያለ የውዳሴ መአት ሲያወርድ ይኖራል። ልብ ሊባል የሚገባው ከላይኛው መሪዎች ግን ሪፎርምም ግምገማም ተደርጎ አያውቅም። አንድ የብርጌድም ሆነ የክፍለ ጦር መሪ ዕቅድ ሳይኖረው፣ ሥልጠና ሳያገኝ፣ ክትትል ሳይደረግለት ያጥፋ አያጥፋ በምን ይለካል? የሚመጣውም እንዲሁ ነው። በቅንነት ለፊፎርም ሥራ የሚደክሙ ሰዎች ግን ቅን ሓሳባቸውና ቁርጠኛ ድካማቸው የሚዘነጋ አይደለም።
8ኛ፦ ዐማራዊ አንድነቱ ሁለት ሦስት ጊዜ እንዳይሳካ ያደረጉት የአፋጎ መሪዎች ናቸው። ለምን ብሎ የሚጠይቃቸው አባል እንዳይኖር በሚድያ አፎቻቸው በኩል አፉን ለማዘጋት ይሞክራሉ። የውስጥ ሥራችንን እስክንጨርስ ድረስ ጄነራል ተፈራ ማሞ ለ6 ወር ይምራን፣ ከ6 ወር በኋላ አርበኛ ዘመነ ካሤ ይረከበው ብለው ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ በውጭ ያለው ቀጣሪያቸው በፍጹም አይደረግም በማለቱ ስምምነቱን ትተነዋል ብለው ራሳቸው ያመጡትን ራሳቸው ያሮጡት እነ አስረስ መዓረይ እና አርበኛ ዘመነ ካሤ ናቸው። አሁን ደግሞ ከጎንደር፣ ከሸዋ እና ከወሎ ጋራ አንድነቱ ካልተሳካልን ከህወሓት፣ ከጉምዝ ነጻ አውጪ እና ከኦሮሞ ነጻ አውጪው ከኦነግ ሸኔው ከጃልመሮ ጋራ ሁነን አንድ የስምምነት ድርጅት ፈጥረን መጓዝ አለብን ብለው ወዲያ ወዲህ እየተደዋወሉ በመላላጥ ላይ ናቸው። አንዳንዳን የኦነግና የወያኔ ሰዎች በግልጽ ከአፋጎ መሪዎች ጋር መደዋወል መጀመራቸውም ነው የሚሰማው። ከጎንደር፣ ከሸዋና ከወሎ ዐማራ ይልቅ እንዴት እነዚህ ሊቀርቧቸው እንደቻሉ ፈጣሪ ይወቀው።
"…ተመልከቱ ጎንደርን "ሞዐ ተዋሕዶ የሚል ስም ሰጥተው ነው የሚወቅጡት። እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም፣ እነ አያሌው መንበር ሁላ በዚህ ስምም ሆነው ነው ጎንደርን የሚወቅጡት። ወሎን ደግሞ ቲም ገዱና ምዐ ተዋሕዶ የሚል የዳቦ ስም ሰጥተው ነው የሚወርዱበት። ከገዱ አንዳርጋቸውና ከስብሀት ነጋ ጋር፣ ከጃዋር መሀመድም ጋር ቁጭ ብለው የተወያዩት እነርሱ ሆነው ሳሉ ወሎንና ጎንደርን ላም ባልዋለበት ኩበት ካልለቀማችሁ ብለው ፍዳ ያበሏቸዋል። ሸዋን ደግሞ በእስር ቤት እስኳድ (በዶክተር ወንድ ወሰን) ፈርጀው ዋይ ዋይ እያሉ ነው። ደፍራችሁ ተወያዩ።
9ኛ፥ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ወሳኝ እስትራቴጅስት አመራሮች ከሚባሉት መካከል እነ ፓስተር ተሰማ ካሳሁን የአብን አመራር የነበረ እና አባቱ ከአቢይ አሕመድ ጋር በአንድ የጸሎት ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ፣ እሱም የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኝ ወጣቶች ሊቀመንበር እንዲሆን ከታጨ በኋላ ወደ ዐማራ ፋኖ በጎጃም ይቀላቀል ዘንድ በተመስገን ጥሩነህ ተልኮ ጎጃም የከተመውና በብሔራዊ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ይሠራ በነበረው ፓስተር ዳዊት መሀሪ ናቸው። ለእነዚህ ደግሞ ከብልፅግና ወንጌል የተሻለ የጌታ መንግሥት የላቸውም። ባለፈው በበቋራ ቃል ኪዳን ወቅት ተሰማ ያለውን ሰምታችኋል "በዚህ 6ወር ሥራ እንሠራበታለን አንድነቱን እንቢ በሉ"ሲል የነበረው ለዚሁ ዓላማ ነበር። በጎን "እኔ የአብን መስራች ነበርሁ አብንን የሸጡብን ጎንደሬዎች ናቸው ዛሬም ከጎንደር ጋራ አንድ ብንሆን ትግሉን ይሸጡብናል፣ እንሁን ከተባለም እንኳ ወሳኝ ወሳኝ የመሪነት ቦታዎችን መያዝ ያለብን እኛ ጎጃሞች ነን" በማለት ብዙ ሰዎችን ሸውዶና አሳምኖም አንድነቱ እንዲቀር አድርጓል። ጎጃም አሁን በይፋ ከአፋብኃ እንደወጣ ይቆጠራል።
10ኛ፦ በማርሸት እና በአስረስ በኩል የጎጃም ዳብል ኤጀንት ባለሀብቶች አሉ። ብአዴኖች እነ ተመስገን ጥሩነህ በሚረጩት ገንዘብና ከፋፋይ አጠራጣሪ መረጃ ምክንያት አሁን የጎጃም ፋኖ ትልቅ አደጋ ውስጥ ነው ያለው። ይሄ ቲም ማስወገድ ያለበትን ያስወግዳል መጥቀም ያለበትን ይጠቅማል። ዐማራን ነጻ የማውጣት አይደለም ዐማራ የመሆን ዕድል የለውም። ለሚፈልጉት አስወጋጅ ቲምና ብርጌድ ዲሽቃም፣ ስናይፐርም፣ ብሬንም ተተኳሽም ገዝተው ያቀርባሉ። በማርሸት በኩል ብቻ አንደኛው ባለሀብት እስከ አሁን የተለቀቀው ብር 135 ሚልዮን ብር መድረሱን ነው የሰማሁት። ይሄ ካራሱ ከማርሸት የተገኘ መረጃ ነው። ማርሸት እንደሚታወቀው ይቅማል፣ ያጨሳል፣ ይጠጣል፣ ጋንጃ ይስባል ሲመረቅን መረጃዎችን በሀላል ይናገራል። ይሄ ሁሉ ገንዘብ ለፋኖ ትግል የዋለ ሳይሆን ለትግል ማኮላሻ የዋለ ነው። በሌሎች በኩል ምን ያክል ብልጽግና ገንዘብ እንደረጨ ይሄንን ተከትሎ ማሰብ አይከብድም። ነገርየውን አቅልላችሁ እንዳትመለከቱት።
11ኛ፥ እውነት ለመናገር አርበኛ ዘመነ ካሴ የአስረስ መዓረይን ያህል ብስል ፖለቲካ ዐዋቂ አይደለም። እንዴት እንደሚመቱት እና እየመቱት እንደሆላም እንኳ ብዙም ዐያውቅም አይረዳውምም። አርበኛ ዘመነ ካሴ አንደበተ ርቱዕ ነው። በዚህም ተሰጥኦው ምክንያት መናገር እና መቀስቀስ ይችላል እንጂ እስትራቴጅስት ፖለቲከኛ ግን አይደለም። ከአጃቢዎቹ መካከል የተሻለ ደህና አማካሪ እንኳ የለውም። እነ አስረስ መዓረይ የአርበኛ ዘመነ ካሤን ሥነ ልቡናውን በደንብ ስላጠኑት ከላይ ከላዩ በአጃቢዎቹ በኩል ፎቶ እያስነሱ አንተኮ ትለያለህ እያሉ ይፖስቱለታል። እሱም እንደ ሚወዱት አምኖ ይኖራል። የዐማራው ንጉሥ አንተነህ የሚል ቲሸርት ሳይቀር አሠርተው አምጥተው አልብሰው ፎቶ አንስተው ይፖስቱታል። King የሚል ቲሸረት ገዝተው አምጥተው ወንዝ ውስጥ አቁመው ራሳቸው በሌላ ገጽ የውዳሴ ኮሜንት እየጻፉ እሱን ለማስደሰት ጥረት ያደርጉለታል። የዘመነን የዋህነት ተጠቅመው ብዙ ጊዜ ማኖ እያስነኩት ነው። ለትልቅ የተባለውን ዘመነን ወደ ትንሽ እንዲወርድ እያንደረደሩት ነው። ፈጣሪ ይሁነው። እኔ ራሴ እኔና ዘመነ በግል፣ በምስጢር ያወራነውን፣ የነገረኝን እያሰብኩ እሰጋለታለሁ።
12ኛ፥ በመጨረሻም ሁልጊዜ ከገንዘብ ለቀማ ስር፣ ከሴት ቀሚስ ስር፣ ከውስኪ ስር፣ በፍየል ቁርጥ ሥጋ ስር፣ ፎቶ እየለቀቁ ከማያዩት ከኮሜንት ውዳሴ ስር የሚልከሰከስ የዕዝ መሪ ዐማራን አይደለም መንደሯን ነጻ ማውጣት ይቅርና ራሳቸውም ከከባድ ሱስ ነፃ የሚያወጣቸው ያስፈልጋቸዋል። እነዚህ ጉደኞች የጎጃም ዐማራን መርተውና አዋግተው አራት ኪሎ ያደርሱናል ብለው ተስፋ…👇 ④✍✍✍
👆②✍✍✍ …
3ኛ፥ በአፋጎ ከክፍለ ጦር በላይ ያሉ መሪዎች ከዚህ የተሻለ የጥቅም ቦታ ስለማያገኙ ትግሉን ለማራዘም ይገደዳሉ። ትግሉ በአጭር ጊዜ ከተጠናቀቀ ኪሣራ ስለሚገጥማቸው፣ የጀመሩትንም ኢንቨስትመንትና ልክና ገደብ የሌለው ገቢ ስለሚያስቀርባቸው ትግሉ በአጭሩ እንዲቋጭ አይፈልጉም። ሕዝብ አለቀ ለእነሱ ደንታቸው አይደለም። ዛሬ ያለ ከልካይ በሳምንት ውስጥ በሚልዮን ተከፋዮች ናቸው። የገቢ ምንጫቸውም ሰፊ ነው። ራሱ መንግሥት ተብዬው በእጅ አዙር ከፋያቸው ነው። የዐማራን አንድነት በየጊዜው ለሚያኮላሸው ለእነ አስረስ ቡድን አገዛዙ ራሱ በብአዴን በኩል የጠየቁትን ቢሰጥ ምኑ ይጎዳል? አግኝቶ ነው? የባለሀብቶች እና የድርጅት ንብረቶች በጎጃም ምድር በሚያልፉበት ጊዜ ችግር እንዳይገጥማቸው ከተለያዩ ድርጅቶች በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየተከፈላቸው የሚሠሩ ናቸው። ለምሳሌ ከዳሽን ቢራ የማከፈለው አለ። ከሐበሻ ቢራ የሚከፈለው አለ። ከዱቄት ፋብሪካ፣ ከፌቤላ፣ ከብረታ ብረት ምርት፣ ከቀለም ፋብሪካዎች ወዘተ የሚከፈለው አለ። እርሻ ጠብቀው፣ ምርት አሳልፈው የሚከፈላቸው አሉ። እነዚህ ድርጅቶች የጭነት መኪናዎቻቸው በቀረጥም ሆነ በኬላ ከተያዘ አመራሮቹ በአስቸኳይ ተደውሎላቸው ይነገራቸውና ለኬላ ላይ ቀረጥ ሰብሳቢዎች "እሱ የእኛ ነው ልቀቀው" እያሉ በነፃ የሚያስለቅቁለት እነዚህ ዘናጭ የዕዙ የውስጥ አመራሮች ናቸው። ጫማቸው ውድ፣ ልብሳቸው ነጭ ነው የዕዙ አመራሮች። የጀነራል ውባንተ አባተን ሚስት 30 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ምርት በወረሱ ጊዜ የውባንተ ሚስት ለአቤቱታ አስረስ መዓረይ እና ዘመነ ካሤን ጭምር ተማጽና፣ አንቺ የውባንተ ሚስት ስለመሆንሽ የጋብቻ ሠርተፍኪቴ ሁላ አቅርቢ ብለዋት፣ ለአስረስና ለዘመነ ካሤ ጭምር በኋትስአፕ የሠርጋቸውን ሙሉ ዶክመንትም ማስረጃና መረጃ ልካ ጥፊ ከዚህ ብለው ነው ሞጣ ላይ ገሚሱን ጠጥተው፣ ገሚሱን ሽጠውባት የ30 ሚልዮን ብር ንብረት አውድመው ያባረሯት። ሰዎቹ ሲበዛ ጨካኝ ናቸው። መረጃው በሙሉ ስላለኝ ነው እኔ የምናገረው። እኔ በበኩሌ አስረስ መዓረይን ፊቱን ሁላ ትኩር ብዬ ሳየው ከምር ዐማራም አይመስለኝ። የዐማራ መልክም፣ ወዝም የለው። ከምር እውነቴን ነው። የእናንተን ዐላውቅም እኔ ግን እንደዚያ ነው የሚታየኝ።
"…ተመልከቱ ይሄ ብቻ አይደለም ከዚህ በተረፈም በመላው ጎጃም የሚገኘውና በተለያየ መልክ በግብር፣ በቀረጥ የሚሰበሰበውም ገቢም 25% ለዕዙ ነው የሚገባው። በቀን ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ አላቸው። እኔና ዘመነ ካሤን በስልክ አገናኝቶ ካስተዋወቁን ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው አቶ ግርማ አየለም ከዚህ ተነሥቶ ነው እኛ ጎጃሞች ሀብታም ነን፣ አቅምም አለን እናም ከማንም ሳንቀናጅ ብቻችንን ሁሉንም ነገር መፍጠር እንችላለን እስከማለት የደረሰው። አስረስ መዓረይም "ዘመዴ ቤተልሔምንና ግርማ አየለን ከሰው ቆጥረህ ነውን" ቢለኝም የእነ አስረስን ፍላጎትና ዕቅድ የማውቀው በእነዚሁ ገንገበቶች በኩል ነው። ልብ በሉ በቀን 10 ሚልዮን ብር በወር ስንት እንደሚመጣ ምቱት። በዚህ ብር ደግሞ በተወሰነው ብር አክቲቪስት ገዝተው ይቀጥሩበታል። ከጎጃም ወደ ዶላር ተቀይሮ ኡጋንዳና ካናዳ አሜሪካም ጭምር በዶላር ተመንዝሮ ይገባላቸዋል። በተለይ ደግሞ በአፋጎ ስም የሚሰበሰብ ዶላር በውጭ ሀገር ካለም ለአስረስ ሚስትና ልጅ ጨምሮ ለሰብሳቢ አክቲቪስቶቹ እንዲከፋፈሉት ይደረጋል። የቀረውን ብር ግን አመራሮቹ ይከፋፈሉታል። በየወሩም፣ በየሳምንቱም 400ሺህ 500ሺህ ስለ ሚደርሳቸው እነዚህ አመራሮች ትግሉ ቢቋጭ ይሄን ማግኘት ህልም ስለሚሆንባቸው የዐማራ ፋኖ አንድ ሁኖ መንግሥት ከሆነም ይሄ ሁሉ ጥቅም ስለ ሚቀርባቸው ካሉበት ንቅንቅ ማለት አይፈልጉም።
"…በዚህ ብር አንዲት ሴተኛ አዳሪ ሴት በ60 ሺህ ብር ይገዛሉ። ድሮ ሲመኟት የነበሩዋቸውን ሴቶች ያሉበት ጫካና የገጠር ቀበሌ ድረስ በእግር እና በሞተር ሳይክል አስጭነው አምጥተው ይጎለምቱበታል። ድህነት በተንሠራፋበት ማኅበረሰብ ውስጥ ለአንድ አዳር 60 ሺ ብር መክፈልና 60 ሺ ብር ማግኘት ማለት እንደቀላል የሚታይ አይደለም። ሴቶቹ ሴተኛ አዳሪ ብቻ አይደሉም። ኑሮ የከበዳቸው፣ ድህነት ያደቀቃቸው የቤት ልጆች ሁሉ ናቸው በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩት። 2 ሴት ይዞ የሚተኛ ሁሉ እንዳለ ነው የሚነገረው። ውስኪ እንደ ጉድ ነው የሚወርደው። ጾም የለ ፍስግ ፍየል እንደጉድ ነው የሚታረደው። እንዲያውም አንድ ጊዜ ወደ ዳሞት ለግምገማ የተጠሩ የፋኖ አመራሮች የምሳ ሰዓት ደርሶ ምሳ እንብላ ብለው ገምጋሚዎቹ ወደ ገበታው፣ ወደ ማዕዱ ተሰብሳቢ አመራሮቹን ይጋብዛሉ። ተጋባዦቹም ዕለቱ ረቡዕ ሆኖ በዚያ ላይ ጾም መሆኑን ዓይተው እንኳ ስሜታቸውን መደበቅ አልቻሉም። በቀጥታ ሽሮ አንበላም። ለህዝብ ነፃነት ብዬ ወጥቼ ነገ ልሙት ዛሬ ለማላውቀው ሽሮ አልበላም ይላሉ። አመራሩም ግራ ተጋብቶ ኧረ ሽሮ አትበሉም? በሉ እሺ ለእናንተ የፍስክ ምግብ የተዘጋጀው ከዚህ ትምህርት ቤት ጀርባ ነው። መሳሪያችሁን አውርዱና ተከተሉን በማለት፣ መሣሪያ አስወርደው ወደ ጓሮ በመውሰድ አንበርክከው በከዘራ ሳይቀር ቆምጠው፣ ቆምጠው የለቀቋቸው። አክቲቪስቶች ደጋ ዳሞትን ሞልጨው የሚሰድቡትም በብዙ ምክንያት ነው። ደጋ ዳሞት ግን ጀግንነቱ አሁንም አልተቋረጠም።
"…የዐፋጎ አመራር ዘወትር በቃ መቦረቅ ዘና ፈታ ማለት ነው። ባልተገደበው ገንዘብ ፍሰት ምክንያት ዩጋንዳ የነዳጅ ማደያ የሠራ አለ። ባህርዳርና አዲስ አበባ ሪልእስቴት የገዛ አለ። በቤተሰቡ የኢንቨስትመንት ቦታ ተቀብሎ መአድን ቁፈራ የገባ አለ። 4 እና 5 ሲኖትራክ የገዛም አለ። ባህርዳር ላይ ሁለገብ የኤሌክትሮኒክስ ሴንተር የከፈተም አለ። በገጠር የጎጃም የቀበሌ ከተማ ውስጥ ባለ 6 ወለል ፎቅ እየሠራ፣ እየገነባ ያለም አለ። አዲስ አበባ የባህል ልብስ መሸጫ ሱቅ የከፈተ አለ። የሚሆነው አይታወቅምና ዘሬን ሳልተካ እንዳልሞት በማለት ሴቶችን ሲያስወልድ የሚውል አለ። ባህርዳር መሬት ሊገዛ መጥቶ ዋጋው ይሄነው ተብሎ ተነግሮት ችግር የለም ሽጥልኝ ብሎ ሳይከራከር የሚከፍል ከሆነ ወንድሙ የፋኖ አለቃ ነው ማለት ነው። እገታው፣ ዘረፋው ሳይጨመር ማለት ነው። በሶማሌ ክልል በኩል በሶማሊላንድ የገባ 100 ሚልዮን ብር በልቷል የተባለው ማንችሎትን ከሥልጣን ካባረሩት በኋላ አሁን ሲጨንቃቸው ጥያቄ ሲበዛባቸው አጠገባቸው ያስቀመጡትም በምክንያት ነው። ይሄ በውል የሚታወቀው ነው። ያልተወቀውን ደግሞ እግዚአብሔር ይቁጠረው። አስረስ እንኳ አሜሪካ ለሚስቴና ለልጆቸ ቤት የገዛሁት ቪትስ መኪና ነበረችኝ እሷን ሽጨ ነው ሲል ቅሽሽ አላለውም። በዶክተሩ በኩል ተሰብስቦ ለሚስቱ የተሰጠውን ዶላር ግን አይተነፍሳትም። ቪትስ ተሽጦ ሚስቱ በአሜሪካ ቤት ሲኖራት ፈጣሪ ያሳያችሁ።
4ኛ፣ ብዙኀኑ የአፋጎ መሪዎች አማካሪዎቻቸው ሀገር ውስጥ አይደሉም ያሉት። ሀገር ውስጥ ያሉትም ቢሆኑ ብአዴኖች ናቸው። ከውጭ ያሉት ደግሞ እምነት የለሾች፣ ሊበራሎች እና ፓስተሮች ናቸው። እነሱ ደግሞ ከዐማራው ይልቅ አቢይን ስለሚወዱት ትግሉ እንዳያልቅ የማይሆን የህልም እንጀራ ምክር ይመክሯቸዋል። የብአዴን ሰዎች ደግሞ እንዲህ እንዲህ እያደረጉ በፋኖ በኩል የብልጽግናን መንግሥት ከውስጥ ሲያዳከሙ ቆይተው እነሱ ልክ እንደ ኦህዴዶቹ የውስጥ ሰርጄሪ ሠርተው ወደ ፊት መውጣት ይፈልጋሉ። ተመስገን ጥሩነህ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን እያደረገው ያለው ጥረትም የሚዘወረው በዚህ በኩል ነው። ተመስገን ጥሩነህ ድንቁ ከወለጋ የሚመዘዝ ኦሮሞነት ስላለው እነ ሽመልስ…👇②✍✍✍
መልካም…
"…ዛሬ ቤተክርስቲያን ግብር ትከፍል ዘንድ ተወስኖባት፣ ውሳኔውንም ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሰጡ ቀበሌና ወረዳዎች ታዘው፣ እምቢ አልቀበልም የሚል የደብር አለቃ ካለ እየጠፈጠፋችሁ ዘብጥያ አውርዱት ተብለው ቀበሌና ወረዳዎች ጭንቅ ውስጥ ወድቀው እያየሁ ስለሱ ልጽፍ ነበር የፈለግኩት። መርካቶ አውቶቡስ ተራ ያለው አዲሱ ሚካኤል ብቻውን 2 ሚልዮን ብር ግብር እንዲከፍል መወሰኑን ሁላ ነው የሰማሁት። እነ አቡነ ሳዊሮስ ይሄን ለማስፈጸም ነው የተሾሙት። አዳናች አበቤን የሚልዮን ብር ዋጋ ያለው ወርቅ በመሸለምም ነው ሥራቸውን የጀመሩት። ገንዘብ የጠረረበት አገዛዙ ሙዳይ ምጽዋት ሰበራ ሊጀምርልህ ነው።
"…እኔ ግን እዚያው ጮቄ ሆኜ የዐማራ ፋኖ በጎጃምን አሁናዊ አደጋ፣ ለዐማራ እንደ ሕዝብ፣ ለጎጃም እንደጎጃም የደቀኑበትን የከፋ አደጋ ብንወያይበት ብዬ ቀኝ ትከሻዬን ስለሸከከኝ ምርጫዬን አፋጎ አደረግኩ። መቼም እንደድሮው የሚሰድበኝ ባይኖርም ጓ የሚል ጥቅመኛ የአፋጎ ካድሬ አይጠፋም እና፣ በተጨማሪም የአፋጎ የቴሌግራም፣ የፌስቡክ፣ የዩቱዩብ እና የቲክቶክ አክቲቪስቶችም አውርተው የሚበሉበት አጀንዳም ስለጠረረባቸው ለእነሱም በትበት የሚሉበት አጀንዳ ይሆን ዘንድ እንደ ኮሶ የመረረ፣ ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ ደፋር ርእሰ አንቀጽ አዘጋጅቼላችኋለሁ።
• ዝግጁ ናችሁ ጎበዝ…? እስቲ አንድ 100 ያህል የቤቴ ሠራዊት ዝግጁ ነነ ዘመዴ ይበል።
“…በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ምድሪቱ ከፈሰሰባት ደም አትነጻም።” ዘኍ 35፥33
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም…
"…አሁን ደግሞ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በተለመደው መልኩ የእናንተን ሓሳብ የምናደምጥበት ጊዜ ነው። መሳደብ፣ ነውረኛ ቋል፣ ቀፋፊ ቃል በመናገር የአንባቢ ዓይን ላይ ማስታወክ ክልክል ነው። ጦማሬ የሚያበሳጭ እንኳ ቢሆን ብስጭታችሁን፣ ንዴታችሁን ዋጥ አድርጋችሁ በጨዋ ደንብ መቃወም መብታችሁ ነው። አጀንዳ ማስቀየር አይፈቀድም። ለአስተያየት ሰጪዎች የጎንዮሽ መልስ በተለይ ስድድብ አይፈቀድም። ተሳዳቢዎችን በፍጹም አልታገስም። በጨዋ ደንብ መሞገት እየተቻላችሁ ነውረኛ ስድብ ተሳድባችሁ ባትቀሰፉ መልካም ነው።
"…1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍
👆⑤ ✍✍✍ …ተቀምጦ በበጋ ዐማራን በድሮን የሚያስጨፈጭፈው የጎጃሙ የእነ አስረስ ቡድን በጊዜ ወደ መስመር እንዲገባ ካልተደረገ አደጋው ለዐማራ ከባድ ነው። እኔ የምጽፈው ሲያነቡት፣ እኔ የምናገረው ሲሰሙት ይመርራል፣ ያንገሸግሻል፣ ያልተሸቀጠ፣ ያልተቀባባ፣ በይሉኝታ፣ በሼም ያልታጠረ ስለሆነ፣ ኦሪጅናል መድኃኒት ስለሆነ፣ ጨክኖ ለዋጠው፣ በትእግስት ለሰማኝ ግን ፈዋሽ መድኃኒት ነው። ጨክናችሁ ስሙኝ። ስሙኝና ተወያዩ። ከመተኛታችሁ በፊት እኔ የጻፍኩትን እንደ ከብት መልሳችሁ አውጥታችሁ አመንዥኩት። አላምጡት። ታተርፉበታላችሁ።
"…ከእነ ሚሊኬሳ፣ ታዬ ደንደአ፣ ልደቱ አያሌው፣ ገዱ አንዳርጋቸው በፊት እኮ እኔው ዘመዴ አቢይ አህመድ ዐማራን ሊያጠፋ እንደሆነ፣ የሽመልስ አብዲሳን የድምጽ ቅጂ አውጥቼ አሰምቼ አሳይቼአችኋለሁ። ትምህርት ቤትህ ከወደመ፣ የጤና ጣቢያህ ከወደመ፣ ሊቃውንቶችህ ከታረዱ፣ ማዳበሪያ ክልክለህ ገበሬው ካላረሰ፣ ሃኪሞች፣ ዶክተሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች ከተረሸኑ፣ መጪው ጊዜ ራብ ሲመጣ እኮ ኦሮሞ ያመረተውን ስንዴ እየበላ፣ በሀኪሞቹ እየታከመ፣ በትምህርት ቤቶቹ እየተማረ ይሻገራል። አንተ ዐማራው እኮ ነህ የምትደቅቀው። የዐማራ ነጋዴ በፋኖም፣ በመከላከያም ከተዘረፈ፣ ሕዝቡ በሁለቱም ከተጨፈጨፈ ዐማራ ከዚህ በላይ እንዴት ይጥፋ? ለትግሬው ጦርነት እኮ የሟቾች ቁጥር ይገለጽ ነበር፣ የወደመ ንብረት ይገለጽ ነበር። አቢይ አሕመድ አማራን ወርሮ በብአዴን ፊትአውራሪነት መጨፍጨፍ ከጀመረ ጀምሮ የሟቾች ቁጥር ይታወቃል? የወደመው ንብረት ዋጋ ይታወቃል? እንደ ዐማራ ነፍሱ ርካሽ የሆነ ዜጋ በዚህ ዘመን አለ እንዴ? በልጆቹ የተከዳ፣ የተናቀ፣ እንደ ዐማራ የለም።
"…ዋጠው የምነግርህን። ዐማራ እኮ መከላከያን አሸንፎ ነበር። ሬሳ በሬሳ ከምሮት ነበር። ኋላ ላይ ነው ኦሮሙማው ሓሳብ ቀይሮ ለምን ዐማራውን በሆዱ ገዝቼ እርስ በእርሱ አላዋጋውም ብሎ፣ ሆዳም ብአዴን፣ ሆዳም የዐማራ ሚሊሻ፣ ሆዳም የዐማራ ፎሊስ፣ ሆዳም የዐማራ አድማ ብተና፣ ሆዳም ፀረ ዐማራ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ከጎንደር፣ ሆዳም የፖለቲካው አገው ፀረ ዐማራ አገው ሸንጎ ከጎጃም፣ ከወሎ የከሚሴ ኦሮሞ ከኦሮሞም የወሃቢይ እስላም ገዝቶ ከፋኖ ጋር ማፋለም የጀመረው። እነ መከታው ከሸዋ፣ እነ ኮሎኔል ሙሀባው ከወሎ፣ እነ ደረጄና እነ ጌታ አስራደ ከጎንደር፣ እነ ማርሸትና አስረስ ከጎጃም ስለተመቹት የዐማራ መከራው የረዘመው። ለአስረስ ሚስት እኮ በአሜሪካ እኔ ትግል ላይ ስላለሁ ብሎ ዶላር እየተሰበሰበላት ልጆቿን ነው የምታሳድገው። የጎጃም ጎጠኛ አክቲቪስት በሙሉ ገና ለገና የሰፈሬ።ልጅ፣ አብሮአደጌ፣ ጓደኛና ወዳጄ፣ ዘመዴ ሥልጣን ሲይዝ ሀገር ቤት ገብቼ ኢንቨስተር እሆናለሁ ብሎ እኮ ነው የሚላላጠው።የእኔ ዘመዶች ቤት ሥጋ ቆራጭ ሆኖ የሚሠራው ይሄነው የሸበሉ እንኳን ብአዴንነቱ፣ የመሬት ደላላነቱ አልለቀው ብሎ እየዳከረ ነው። የዘመነ ካሤ ወንድም ነኝ ባዩ እኔን ከዘመነ ካሤ ጋር ካገናኘኝ አንዱ የሆነው ግርማ አየለ እንዲህ የሚወበራው ጎጃም የዐማራ ፋኖን ጠቅልሎ እነርሱ በአሸናፊው የፋኖ መንግሥት ውስጥ ጀዋር መሃመድን፣ አሉላ ሰሎሞንን ለመሆን ከመሻት ነው የሚንጠራወዙት። ለዚህ ነው ሌላው አደረጃጀት እኛን በመሪነት ካልተቀበለን የዐማራ ትግል በአፍንጫችን ይውጣ፣ እኛ ከሞትን ሰርዶ አይብቀል የሚል ካርድ መዝዘው እየተጫወቱ ያሉት። ቀሽም በለው።
"…አሁን ሌላውን ወያኔ ለማለት ተጎጃም ፋኖ መሪና አክቲቪዝስቶች ሞራል የላችሁም። ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር በአንድ መድረክ ቁጭ ብሎ የመከረው የጎጃም ፋኖ እንጂ የወሎ፣ ወይ የጎንደርና የሸዋ አይደለም። ሌላውን ፋኖ ወያኔ ለማለት የጎጃም መሪዎችና አክቲቪስቶች ሞራል የላችሁም፣ ከዋናው የዐማራ ችግር ኢንኪዩቤተር ከስብሃት ነጋ ጋር በአንድ መድረክ ቁጭ ብላችሁ የመከራችሁ እናንተ እንጂ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ አይደሉም። ከጃዋር መሀመድ ጋር ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር አይደለም የመከረው፣ የሥልጣን ጥም ብቻ ሳይሆን የዐማራን ትግል የጭቅጭቅ፣ የንትርክ መድረክ ከማድረግ ሌት ተቀን ከሚሠራው፣ በሚዲያ ሞኖፖሊ ብቻ ድምጹ ጎላ ብሎ የሚሰማው፣ መሬት ላይ ጠብ የሚል ሥራ ልጆቹ እንዳይሠሩ እጅ እግራቸውን ጠፍሮ ካሠረው ከጎጃሙ የእነ አስረስ መዓረይ ቡድን ዘንድ ነው የችግሩ ምንንጭና መንስኤው። እደግመዋለሁ በባዶ ሆድ ከመፎከር፣ ከመሸለል፣ ፍርጥ አድርጋችሁ አንደዜ መነጋገር።
"…ይሄ ርእሰ አንቀጽ ከተነበበ በኋላ ምንአልባትም የጎጃሙ ብአዴን ከኦሮሙማው ጋር በመመሳጠር የጎጃሙ ሾተላይ ቡድን ከእጁ እንዳይወጣ ጥቂት የደቡብ ልጆች፣ የኦሮሞና የዐማራ ሚሊሻዎችን እንዲደመስሱ፣ እንዲማርኩ፣ የገጠር ከተሞችንም እንዲቆጣጠሩ ሊያደርጉላቸው ይችሉ ይሆናል። የቆየ የወታደር ሬሳም፣ የቆየ ምርኮም ሊያሳዩን በሚዲያዎቻቸው ሊላላጡ ይሞክሩ ይሆናል። ብአዴን በሪሞት ኮንትሮል የሚመራው ፋኖ ከዚህ በዘለለ ምንም ሊያደርግ አይችልም። አክተሮቹ የማይሞቱበት፣ በዘመናዊ መኪና የሚምነሸነሹበት፣ ያበጠ ጳጳዬ መስለው የሚምነሸነሹት የዐማራ ፋኖ በጎጃም ሾተላይ መሪዎች ዶክመንተሪ ተሠርቶላቸው፣ ወንዝ ሲሻገሩ፣ ተራራ ሲቧጥጡ፣ ሲጋጋጡ ቀርጸው "ይሄ ሁላ ለእናንተ የምንከፍለው መስዋእትነት ነው" ለሊሉ ይችላሉ። እናንተመወ በሏቸው። በቃ አየናችሁ፣ ተመለከትናችሁ። አሁን የምንፈልገው ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ወንድሞቻችሁ ጋር አንድነት ፈጥራችሁ የመከራ ሌሊታችንን እንድታሳጥሩት ነው እንድትሏቸው ነው። ድፈሩ። ያለበለዚያ ኦሮሙማው ይውጣችኋል።
"…ትግሬ የራሱ ሲኖዶስ አቋቁሟል። ኦሮሞም እንደዚያው። የዐማራው ብቻ ነው ሲሾም ዐማራን እያዋረደ፣ ዐማራን እያሳነሰ፣ ዐማራን እያንኳሰሰ ሲያበቃ ይቆይና ሲሻር እንደ አቡነ ጴጥሮስ ኒውዮርክ ተቀምጦ እንደ አዲስ እኛ ስንጮህ ሲያላግጡብን ቆይተው አሁን ደርሰው የሕዝብ አዛኝ፣ ተቆርቋሪ ለመሆን የሚላላጡት። ይሄ ሁሉ መነኩሴ፣ ካህን ሲታረድ ደንታ የማይሰጠው በትግሬና በኦሮሞ የተሞላው ሲኖዶስ ብቻ ሳይሆን ወገናቸው እያለቀ እኔ ከተመቸኝ ሌላው የራሱ ጉዳይ በሚሉ ራስወዳድ አባቶች ምክንያት የተነሣ ነው። አቡነ አብርሃም የአስረስ መዓረይ የአጎት ወይም የአክስት ምናምን ናቸው አሉ። አረጋ ከበደ ለጨፈጨፈው ሕዝብ ባሕርዳር ላይ ካባ እንዲያለብሱት በማድረግ የጅማ ኦሮሞዎቹ ጢባጢቤ ተጫወቱባቸው። ትግሉ አይቆምም። በሰልፍም፣ በሽማግሌም አይቆምም። በጎጃምም፣ በጎንደርም፣ በሸዋና በወሎም ፍልሚያው አይቆምም። እንዲያውም እዚህ ፍልሚያ ውስጥ ወያኔና ሻአቢያም ይሳተፋሉ። ያነዜ ኤምሬት፣ ቱርክ፣ ግብጽና ሳዑዲም ይሳተፋሉ፣ እስራኤል፣ አሜሪካና እንግሊዝም ይሳተፋሉ። ጦርነቱ ገና አልተጀመረም። ነገር ግን ጎጃም በጊዜ ከታ ተካከለ የድል ቀኑ ያጥራል፣ ጎጃም ካልተስተካከለ ግን መዝግቡልኝ የዐማራ መከራው፣ ፍዳው ይረዝማል። የአገው ሸንጎ የጎጃም ፋኖን 90% ተቆጣጥሮታል። ትዕቢቱ ጣሪያ የነካውም ይኸው ቡድን ነው።…👆⑤✍✍✍