zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

311892

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ✍✍✍ …እንዲል፣ የከበረ ስሙ እንዲንቋሸሽ ያደረጉት እነ አስረስ መዓረይ ናቸው። ቀደም ብሎም በጉባኤውም ላይ ዘመነ ካሤ ይገኛል ብሎ በፌስቡክ ገጹ የለጠፈው ራሱ አስረስ መዓረይ ነበር። የትግሬ አክቲቪስቶች እነ ፓስተር ማርያማዊት "ዘመነካሤን እያንቆለጳጰሱ አቤት ግርማው፣ አቤቱ ሞገሱ እያሉ ያሞካሹት፣ የወያኔ ዳይፐሩ በመልኩ ራሱ ቅጭጭ ያለ ጁንታ የሚመስለው አፍቃሬ ወያኔው ጎጃሜው ጋዜጠኛ በቃሉም ዘመነ ካሤ ምን አጠፋ፣ ምን በደለ፣ እንዴት ከስብሃት ነጋ ጋር አንድ ላይ ተገኘ ተብሎ እንዲህ ይኮናል ብሎ ያጓራው በምክንያት ነው። እናም ዘመነ ሲቀጠቀጥ እነ አስረስ ይረካሉ። አለቀ።

"…አሁን ወደ ኋላ ብሎ ነገር የለም። ሦስቱ ወደፊት መቀጠል ብቻ ነው ያለባቸው። ከቋራው ስብሰባ በኋላ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደወል አላነሣ ያሉት ጎጃሞቹ ናቸው። ስብሰባ ቢጠራ አልመጣ ያሉት ጎጃሞቹ ናቸው። ሥራው መቋረጥና መቆም ስለሌለበት ሦስቱ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ የሚገርም፣ የሚያረካ፣ የሚያስደስት ውሳኔ አሳልፈው ግሩም መልእክት አስተላልፈዋል። ውሳኔውን አልቀበልም ያለው የጎጃሙ አማፂ የእነ አስረስ ቡድን ነው። ይሄ የሁሉም የጎጃም ፋኖ ፍላጎትና ውሳኔ በው ብዬ ለመቀበል አልችልም። በአፄ ቴዎድሮስ ስም ዕዝ መስርተን አንዋጋም፣ አንታገልም ያሉት አፍቃሬ ጁንታዎቹ አስረስ መዓረይ እና ማርሸት ፀሐዩ ናቸው። አፄ ቴዎድሮስን አምርሮ የሚጠላው ደግሞ ወያኔ ትግሬ መሆኑ ይታወቃል። እናም እነዚህን ጎጃም ላይ የተተከሉ ሾተላዮች ስንዴውን ከአረሙ ጋር እንዳትነቅሉ እየተጠነቀቃችሁ ከወዲሁ መላ ልታበጁለት ይገባል። ደፍራችሁ መናገር ጀምሩ። መከራከር ጀምሩ። መወያየት ጀምሩ። ጎጃም ከሌላው ዐማራ ተልይቶ ምንም እንደማያመጣ አስረግጣችሁ ነግራችሁ ወደ መስመር እንዲገባ አስደርጉ። ፉከራ፣ ሽለላ ምንም እንደማያዋጣ ጨክናችሁ ንገሯቸው። በግድ ጆሮአቸውን ቆንጥጣችሁ ለዐማራ ቤት አለቃ ብቻ ሳይሆን ዘበኛም፣ ገረድም ሆነህ በተመደብክበት ምድብ ለማገልገል ዝግጁ ሁን በሏቸው። ድፈሩ።

"…አክቲቪስት አሰማርተህ፣ ገንዘብ ስላለህ የራበውን ሁሉ ገዝተህ፣ ጎንደር ወንድምህን፣ ወሎ ወንድምህን፣ ሸዋ ወንድምህን እያሰደብክ፣ እየዘለፍክ አንተ ጎጃምን አታስከብረውም። ደሴት ላይ ለብቻው እንዲቀር እያደረግከው ነው በሉት። አዎ የጎጃሙ ኃይል እንደ አሜሪካዋ ሆሊዉድ፣ እንደ ህንዷ ቦሊዉድ፣ እንደ ናይጄሪያዋ ኖልዊድ የካሜራ መዓት፣ የአክተሮችም መዓት አሏቸው። እንደ አሜሪካኖቹ ነፍ ጋዜጠኞች፣ ሚዲያዎችም አሏቸው። ከጎጃም የወጡ የብአዴን ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች የትየለሌ ናቸው። ቲክቶክ የተሞላው በጎጃሙ ኃይል ነው። ሲፈልግ የዐማራ ፋኖ ሆኖ የሚተውን፣ ሲያሻው የአገው ኃይል ሆኖ የሚተውን፣ ሲያሻው ኃይለየሱስ አዳሙን ሆኖ የሚተውን ጠሽ፣ አውቆ አበድ የኢንተርኔት እብዶች አሏቸው። አፍቃሬ ወያኔ ሆኖ ሲተውን ቆይቶ ወዲያው ደግሞ ጎጃሜ ነኝ የሚል እንደ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ዓይነት በሁለት ቢለዋ የሚበላ ነፍ ጋዜጠኞች ነው ያሉአቸው። የቴሌግራም ሚዲያው በአብዛኛው የግዮን ፕሬስ፣ የግዮን ሚዲያ፣ አሻራ፣ ብላክ ላየኑ ሁሉ በእነ አስረስ መዓረይ የተጠረነፈ ነው። እናም በወንዙ ውስጥ የሚጯጯኸውን ሁሉ እየሰማችሁ ሳትረበሹ ኮስተር ብላችሁ አንድም አራትም ሆነው ማሊያ እየቀያየሩ የሚያጇክቡአችሁን ገስጿቸው። ብአዴኑ አፍቃሬ ወያኔው አንሙት አብርሃ፣ የኢትዮ ፎረሙ አበበ ባዩ በሙሉ አፍቃሬ ብአዴን ወያኔ ናቸው። እናም የዐማራ መከራ በአጭሩ እንዲያበቃ ከፈለግክ ዐማራ የሆንክ የጎጃሙን ሾተላይ መስመር አስይዘህ ሌሎቹንም እየደገፍክ ወደፊት መስፈንጠር ብቻ ነው ያለባችሁ። በቴዎድሮስ የሚያፍር ዐማራ ሰምቼም አይቼም አላውቅም። ጎንደር በበላይ ዘለቀ ዕዝ ሲፋለም እነዚህ ጎጃምን እያሳነሱ ያሉ ሾተላዮች በአፄ ቴዎድሮስ ስም ዕዝ አንመሰርትም ብለው ማፈንገጣቸው ብቻ ማንነታቸውን ይገልጠዋል። ማርሸት ፀሐዩ ዐማራ ጄኖሳይድ አልተፈጸመበትም ያለው በአደባባይ ነው። ወያኔ ብትመጣ ጥይት አንተኩስባትም ያለው አስረስ መዓረይ በአደባባይ ነው። የወያኔን ኮሎኔልና የጦር መኮንኖች ፈትቶ መቀሌ የሰደደው ይሄው አፍቃሬ ወያኔ ቡድን ነው። ወያኔ አሁን በራያና በጠለምት፣ በወልቃይትም ዐማራን ልትወጋ በዝግጅት ላይ ናት። እነዚያ የጎጃም ፋኖ አመራሮች ፈትተው የለቀቋቸው የጦር መኮንኖች ወሎና ጎንደርን ሊወጉ በዝግጅት ላይ ናቸው። ዋጠው።

"…ወንዝ ለወንዝ እየተንከራተትክ በ5ዲ ካሜራ እየተቀረጽክ ለሕዝብ መከራ እየተቀበልኩ ነው ብለህ ፕሮፓጋንዳ ለመሥራት አትላላጥ። እናንት መሪዎች ቦምቦሊኖ ኡሙንዱኖ ኢሹ ጮርናቄ መስላችሁ። ቡርቱካን መስላችሁ፣ በሰም የተወለወለ ጣውላ፣ ቅቤ የጠገበ የቅቤ ቅል መስላችሁ፣ ብራንድ ጫማ፣ ብራንድ ልብስ፣ የአልማዝ ቀለበትና የወርቅ ሰዓት እያጠለቃችሁ፣ በ2025 ሞዴል በ30 እና አርባ ሚልዮን ዘመናዊ መኪና እየተንፈላሰሳችሁ። ሌላው ተዋጊ ቅማል ወርሮት፣ ቅጫም ፈልቶበት፣ ኮሸሮ እየበላ፣ ክረምትና በጋ እየተፈራረቀበት እናንተ ሙድ አትያዙበት። ያልተጠረነፈ፣ ሥርዓት የሌለው፣ በገጠር ከተሞች ከረንቡላና ጆተኒ ሲጫወት የሚውል፣ ቲክቶክ ላይቭ ገብቶ ከሞጣ ቀራኒዮ ጋ አበባ አውርዱልኝ የሚል ጉድ ይዛችሁ አትፎግሩ። አዎ ለመሪዎቹ ተስማምቷችኋል። በብአዴን ጥበቃ እና መልካም ፈቃድ የገበሬ መሶብ እያስደነገጣችሁ፣ የእርሻ በሬ አርዳችሁ እየበላችሁ፣ ግብር፣ ቀረጥ እያላችሁ ዘርፋችሁ እየበላችሁ፣ ለአንዲት ሴተኛ አዳሪ 50 እና 60 ሺ ብር እየከፈላችሁ። ሁለት ሴት አቅፋችሁ እየተኛችሁ። ወይን፣ ቢራ፣ አረቄ በአፍጢማችሁ እስክትደፉ እየጠጣችሁ። ባሕርዳር፣ አዲስ አበባና ደብረ ማርቆስ ቪላ እየገነባችሁ። በዘመድ አዝማድ ስም ባየሀገሩ መሬት እየገዛችሁ። መኪና እየገዛችሁ ሀብታም ሆናችሁ እየኖራችሁ ነው። አሁን ግን በቃችሁ ሊባሉ ይገባል። ምረሩ።

"…ሰበር ዜና በስቦ ማስከዳት ሁለት ሚሊሻ ተማረከ፣ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት ተቀላቀለን እያልክ እየፎገርክ መኖር የተሰለቸ ሆኗል። ዓመት ሙሉ ሪፎርም፣ እገሌ ብርጌድ አመራር ለወጠ ዜና አይሆንም። ድልም አያመጣም። መከላከያ ሲመጣ እየፈረጠጥክ ወገንህን አታስጨርስ። አምልጥ፣ ሲመጣብህ ሽሽ የሚል የጦር መሪ የሰማሁት የኦሮሙማውን ብራኑ ጁላ ሠራዊት ብቻ ነው። ከመቀሌ እስከ ሞላሌ የፈረጠጠ የማውቀው ያንን ብቻ ነው። ዘመነ ካሤ አዝዞን ነው ብሎ በጎጃም የሚፈረጥጥ ሰራዊት መኖሩን የሠማነው በዚህ ዘመን ነው። ጎጃማ በመፈርጠጥ አይታወቅም። ጎጃም የበላይ ዘለቀ እስትንፋስ ጀግና የሞላበት ምድር ነው። ጎጃም የእነ እጅጉ ዘለቀ ምድር ነው። ጎጃም የባድመን ምሽግ የሰበሩ አናብስቶችን የፈጠረ ምድር ነው። ጎጃም በአረቄያሙ ማርሸት የሚለካ ሕዝብ አይደለም። በፍጹም ጎጃም በመልክም ቢሆን አስረስ መዓረይ የሚወክለው ሕዝብ አይደለም። አስረግጬ ነው የምነግርህ ከሌላው ዐማራ አንድነት የሚለይህን ጎጃሜ ነኝ ባይ እንዳትሰማው። ተሟገት፣ ተከራከር፣ ላለመስማማት ተስማምተህም ቢሆን ትግሉ በፍጥነት ከዐማራ ክልል እንዲወጣ አድርግ። ትግሉ ዐማራ ክልል በቆየ ቁጥር የሚደቅቀው ዐማራው ነው። ይሄን አስምሩበት።

"…አቢይ አሕመድ ዐማራን አጠፋዋለሁ ብሎናል የሚለውን የእነ ታዬ ደንደአ እማኝነት፣ የእነ ሚልኬሳ፣ የእነ ገዱ አንዳርጋቸው ምስክርነት እኮ አያስፈልግህም። ዐማራ እየጠፋ ያለው እኮ አሁን በምታየው መልኩ ነው። ዓምና ከእስክንድር ጋር ዘንድሮ ከሦስቱ የዐማራ ግዛት ፋኖዎች ጋር አልስማማም ብሎ ክረምቱን ከአቢይ አሕመድ ጋር ችግኝ እየተከለ፣ ጫካ…👇 ④✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②✍✍✍ …አገኘሁ ተሻገር መኖር የለበትም በሚለው የኦሮሙማው ውሳኔ መሠረት አገኘሁ እንደ ድመት ነፍስ አልሞት ብሎ አስቸገረ እንጂ እንዲወገድ መወሰኑን ማመን የግድ ነው። የወልቃይት ጉዳይ አሁን ሌላ ጣጣ ይዞ እየመጣ ስለሆነ ማለት ነው።

"…በአጠቃላይ የዐማራ ፋኖ ትግል ጠላው ተጠምቋል። አተላው ወደ ታች እየዘቀጠ፣ ገፈቱ ወደላይ እየተንሳፈፈ ነው ያለው። አተላው ፀዳሉ፣ አተላው ቆራጡ፣ አተላው አማኑኤል ከዐማራ ትግል ተደፍተዋል። አሁን የሚቀረው ወይ አተላ፣ ወይ ገፈት  ያልሆኑ ነገር ግን የጠራ ጠላ ያልሆኑቱ አካላት ናቸው። እነሱም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንደ አተላ ይደፋሉ፣ አልያም እንደ ገፈቱ ይተፋሉ። ቱፍ፣ ቱፍ፣ እንትፍ እንትፍ ይደረጋሉ። በሸዋ ያለው አተላና ገፈት፣ በጎጃም ያለው አተላና ገፈት፣ በጎንደር ያለው አተላና ገፈት ይደፋል፣ ይተፋልም። የዐማራ ትግል አሁን የሚያስፈልገው ኮፍጠን፣ ቆፍጠን፣ ኮምጨጭ ብሎ የሚወስን፣ ከዐማራ ሕዝብ በላይ በግለሰብ ስብዕና ላይ የማይንጠለጠል፣ አፍቃሬ ሥልጣን ያናወዘውን ግለሰባዊ አመለካከት፣ ወረዳዊ፣ ዞናዊ፣ ጎጤውን አስተሳሰብ አምክኖ አሽቀንጥሮ ወዲያም ንቆ ትቶ ዐማራን፣ ታላቁን ዐማራነትን ለማንገሥ ነው መፋለም ያለበት። ድሮን በላዩ ላይ፣ መድፍ በጆሮ ግንዱ ላይ፣ ጥይት በአፍንጫው ስር ሲያፏጭ፣ ሞት በአናቱ ላይ ተሸክሞ ዛሬ ይሙት ነገ ይሙት የማያውቅ የዐማራ ፋኖ ታጋይ እሱ እንደማይሞት፣ ድሮን እንደማይነካው፣ ጥይት አጠገቡ እንደማይደርስ፣ የመድፍ ድምጽ የማይሰማ፣ አራት ኪሎን በእርግጠኝነት አልሞ፣ አቅዶ፣ በሌላው ሞት እሱ ተሻግሮ፣ ተረማምዶ ሚንስትር፣ ባለሥልጣን እንደሚሆን ያረጋገጠ ያህል በራሱ ተማምኖ የዐማራ ፋኖ መሪ እኛ ካልሆን፣ አራቱም ወሳኝ የሥልጣን እርከን ለእኛ ካልተሰጠን፣ እኛ ብቻ የዐማራ ፋኖን ትግል ካልመራነው ሞተን እንገኛለን የሚል ጤናቢስ አመለካከት ላለው ቡድንም ሆነ ግለሰብ ቅንጣት ታህል ሊጨነቅ፣ ሼምም ሊይዘው አይገባም። ሞት በላዩ ላይ እያፏጨ ከዛሬ ነገ እኔ ሞቼ ወገኔን፣ ሕዝቤን ነፃ አወጣለሁ የሚል የዐማራ ፋኖ በግለሰቦች የሥልጣን ጥም መናወዝ ምክንያት ብናገር፣ አስተያየት ብሰጥ፣ ልክ አይደለም ብል እነ እገሌ ይቀየሙኛል፣ ሰዳቢ ሠራዊት አስነሥተው ስሜን ያጠለሹታል ብሎ ሊያፍር፣ ሊሽኮረመም አይገባም። ምንም አባቱ አያመጣም። ወጊድ በለው።

"…የጎጃም ዐማራ ሞት ከጎንደር ዐማራ ሞት አይበልጥም አያንስም። የወሎ ዐማራ ሞት ከጎጃም፣ ከሸዋ ከጎንደር አይበልጥም አያንስም። እኔ ከሌላው ዐማራ የተሻልኩ ነኝ የሚል አስተሳሰብ አይሠራም፣ አያዋጣም። እኛ ገንዘብ አለን፣ መሳሪያ፣ የሰው ኃይል አለንና ሁሉን ሥልጣን ጠቅልለን መውሰድ ይገባናል ማለትም ነውር ነው። ሌሎች ትግል ጀምረው በነበረ ሰዓት ይነግድ፣ ይዘፍን፣ ይጠጣ፣ ይዝናና ይጭፍር የነበረ ሁላ አሁን ድንገት መጥቶ የዐማራን አንድነት ሒሳብ እያወራረድን እኔ ልምራው ማለት ተገቢ አይደለም። ወደ ቀልቡ ከተመለሰ ተመለሰ፣ ካልተመለሰ ሌላው ወደፊት መቀጠል ነው ያለበት። አረቄያም ሁላ የሚያወራውን መስማት ትክክልም ልክም አይደለም። ሠራዊቱና መሪዎቹ የተለያዩ ናቸው። ታጋዩ ሁላ እንደ ዐማራ ነው መታገል ያለበት። የጎጃም ፋኖ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋ ገብቶ መታገል ነው የሚፈልገው። የጎንደሩም፣ የወሎና የሸዋውም እንደዚያው ነው የሚፈልገው። በአረቄ ተጽእኖ እየተነሣ፣ በብአዴን መርፌ እየተወጋ የሚለፈልፈው ሁሉ ታችኛውን ታጋይ አይወክልም። በጭራሽ አይወክልም። ተራው የእኛ ነው አይባልም። ተረኛ አገዛዝ ሊያስወግድ የተሰባሰበ ዐማራ ተረኛ ዲክታተር ከወዲሁ የሚያስተዋውቁትን ኢግኖር እየገጨ ወደፊት ሊስፈነጠር ነው የሚገባው። ተናግሬአለሁ።

"…እንድታውቁት ያህል እደግመዋለሁ አርበኛ ዘመነ ካሤን እንደሆነ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎና የሸዋ ፋኖዎች መሪያችን ብለው መርጠውት ነበር። ጎንደርም የሚገባውን፣ ሸዋም ወሎም የሚገባቸውን የሥልጣን እርከን ተቀብለው ጨርሰው ነበር። አርበኛ ዘመነ ካሤ የዐማራ መሪ ሆኖ እንዳይመረጥ ስልኩን ዘግቶ የጠፋው አስረስ መዓረይ ነው። ይሄንን ሁሉም ያውቃል። እነ አስረስ መዓረይ ዘመነን አስገድለው እነሱ መሪ ሆነው ለመምጣት ሲሉ ነው የዘመነ ካሤን ምርጫ ደብቀው የከረሙት። ዘመነም፣ የጎጃም ፋኖዎችም ሲጠይቁ አስረስ መዓረይ ራሱን የዘመነ ምትክ ሆኖ ለመገለጥ እየሠራ ስለነበር  ምላሽ አይሰጥም ነበር። የቆየ ሞላ በራሱ አንደበት "ምርጫው ካለቀ፣ ለምን እንደዘገየ ራሴ እጠይቃለሁ፣ የእኛ ሰዎች እምቢ ካሉ እንኳ ዘመዴ እመነኝ ሠራዊቱን ይዘን ሌላ አመራር መርጠን የዐማራን አንድነት በቅርቡ ዕውን እናደርጋለን ነበር ያለኝ። ይሄንኑ ጉዳይ አስረስ መዓረይም በደወለልኝ ጊዜ እኔ ዘመዴ አባደፋር ኮስተር ብዬ አንስቼለት ነበር። እርግጥ ነው ነገሮች ስላልተመቻቹ ተጓትቷል። መጀመሪያ አካባቢ እነ ባዬ ከእነ ሀብቴ ጋር እየተነጋገሩ ስለነበር ነው የተጋተተው፣ ኋላ ላይ ግን በእኛ ምክንያት ነው የተጓተተው። በእኛም መካከል የተጓተተው እነ ሻለቃ ዝናቡ የወታደራዊ ክፍሉ ካልተሰጠን አንቀበልም ስላሉ ነው። የመሪነቱንም፣ የወታደራዊ ክፍሉንም ደግሞ ለጎጃም አይሰጥም። ስለዚህ እሱን ችግር እስክንፈታው ነው ያለኝ። እኔም ዝናቡ እንዲያ የሚል አይመስለኝም። እስቲ እጠይቀዋለሁ ስል አስረስ በፍጥነት ዝናቡ አይደለም ያስቸገረን፣ ያስቸገሩት ከዝናቡ ሥር ያሉቱ ናቸው ነበር ያለኝ አስረስ መዓረይ። ይሄንንም ቅጂ እስከአሁን ደጋግሜ እየሰማሁት ነው።

"…እነ አስረስ መዓረይ እኔ ጎጃም እስክገባ ድረስ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ነፍስ ነፍስ ያላቸውን፣ ዐዋቂ፣ ምሑራን፣ ታጋይ፣ በተለይ ደግሞ ለዘመነ ካሤ ቀኝ እጅ ናቸው የሚባሉትን፣ በሃይማኖታቸውም ቅባት በዘራቸውም ዐማራ የሆኑትን የጎጃም ልጆች እየለቀሙ አንደዜ በድሮን፣ ሌላ ጊዜ በጥይት ከጀርባ እየተመቱ፣ በጎጃም የጴንጤ አማኞቹና ፓስተሮቹ እነ ዳዊትና ተሰማ ግን ከድሮንም፣ ከጥይቱም ርቀው፣ ግንቦት ሰባቶቹ፣ ብአዴንና ኢዜማዎቹም መምህራንና ኦርቶዶክሳውያኑን እየገደሉና እያስገደሉ ዘና ብለው ነበር የቆዩት። እደግመዋለሁ ዛሬ እነ አስረስ መዓረይ፣ እነ ማርሸት፣ እነ ግርማ አየለ የሚወርዱበትና የጎንደሩ ኢያሱ፣ ሞዓ ተዋሕዶ እያሉ የሚከሱት የባዬ ልጆች ናቸው አርበኛ ዘመነ ካሤና አርበኛ ዝናቡን አንድ ላይ በድሮን ሊጨፈጭፏቸው የጨረሱትን የአገዛዙን ዕቅድ ያከሸፉት። የጎጃምን የፋኖ መሪ የዐማራ ፋኖ ምልክት የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሤን እና የጎጃምን የወታደራዊ መሪ አርበኛ ዝናቡን አንድ ላይ ለመግደል የታቀደውን ዕቅድ ለዝናቡም፣ ለዘመነም ደውለው ያከሸፉት ጎንደሮች ናቸው። ክብር ምስጋና ለቴዎድሮስ ለመይሳው ካሳ ለውባንተ ልጆች። እነ አስረስን የሚያንገበግባቸው ይሄ ነው። ዘመነ ሞቶ አስረስ የጎጃም ዐማራ መሪ ሆኖ ሊመጣ የነበረውን ዕቅድ ያከሸፉት ጎንደሮች ናቸው።

"…ከጫፍ ተደርሶ እኮ ነበር። እነ ጥልምያኮስ አማኑኤል አብነት፣ እነ ሥጋ ቆራጩ ይሄነው የሸበሉ፣ እነ በላይነህ ሰጣርጌ። (በላይ እንኳ አሁን በስተመጨረሻ እየባነነ ይመስላል። ከእኔ የባሰ ነጭ ነጯን መዘርገፍ እየጀመረ ነው። ቆሜ ነው የማጨበጭብለት። የበላይነህ ብዕር ማራኪ ነው። ፍሰቱም ግሩም ነው። አቋም ነው የሚያንሰው እንጂ የመረጃ እጥረት የሌለበት ሰው ነው። አስሬ ለክቶ አንዴ መቁረጥ ቢጀምር ደግሞ የድሮውን ጎንደሬ ሚኪ ዐማራን ይተካል ብዬ የምገምተው ሰው ነው። ለማንኛውም እነርሱ ሁሉ ዘመነ ካሤንና አስረስ መዓረይን ማወዳደር ጀምረው እንደነበር የጻፍኩት ቀደም ብዬ…👇②✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ያን አድርጎ የናፈቃችሁን ርእሰ አንቀጽ እስቲ ለዛሬ ላቅርብላችሁ ብዬ ቀኝ ትከሻዬን ሲሸከሽከኝ ጊዜና ያን እንደ ኮሶ መራር፣ እንደ መተሬ፣ እንደ በረኪና መራር፣ እንደ ዳጣ፣ ቀሪያ በሚጥሚጣ አቃጣይ፣ አንዳጅ የሆነ ርእሰ አንቀጼን ላቀርብላችሁ ወደድኩ። ከርእሰ አንቀጹ በኋላ የተለመደው ጫጫታ ይኖራል ተብሎ ቢጠበቅም ደግሞም መኖርም አለበት ዩቲዩበሮች ምን ሠርተው ይብሉ? የቲክቶክ ኤክስፐርቶች ምን ተንትነው ያምሹ? ለእነሱም ሲባል፣ መንደራቸው ጭር እንዳይል ሲባል ዛሬ ዓለማዊ፣ ነገ መንፈሳዊ፣ ሃይማኖታዊ ርእሰ አንቀጽ ላቀርብላችሁ ወደድኩ። ደግሞም የእናንተም ያ የበሰለ የሚያጓጓ ኮመንታችሁም እንዴት እንደናፈቀኝ አትጠይቁኝ።

• እህሳ…ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የስም ስረዛ…

"…በዛሬው የህንፃ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የቀድሞው ጽርሐ ምኒልክ ህንፃ ከ ጽርሐ ምኒልክ ህንፃነት ወደ ሁለገብ ህንፃ ተሸጋግሯል። ሰዎቹ እንደምንም ብለው የአፄ ምኒልክን ስም ሠርዘውታል። 😂 ታሪክ ስረዛው ተጠናክሮ ቀጥሏል። የምኒልክ ቤተ መንግሥትን ቀደም ብሎ አንድነት ፓርክ ብሎ የሰረዘው ኦሮሙማ ዛሬ ደግሞ ጽርሐ ምኒልክን ወደ ሁለገብ ህንፃነት መቀየራቸወወ ነው የተሰማው።

"…እንደ ቡናቤት በዲም ላይት መብራት ከተንቆጠቆጠው የአዲስ አበባ አደባባይ አደባባዮች መሃል ተለይቶ የምኒልክ አደባባይ ብቻውን በጨለማ እንዲዋጥ እንደተደገም የሚናገሩ መተርጉማንም አሉ። እውን የኮሪደር ልማቷ አዲስ አበባ ለምኒልክ አደባባይ መብራት ማቅረብ አልቻለችምን? እስቲ ፎቶ አንሥታችሁ ላኩልኝማ። እውነት ሐሰት?

"…ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ፣ ሊቃውንቱ ታሰሩ፣ ካህናት መነኮሳቱ ተገደሉ፣ ታረዱ ተብሎ ጫጫታ ሲበዛ በዚያው ፍጥነት አቡነ አብርሃም ባህርዳር ላይ ለአረጋ ከበደ ከባ ይሸልሙታል። በርታ የሀገሬ ልጅ፣ የመንደር የወንዜ ልጅ ብለው ይሸልሙታል። አቡነ ሳዊሮስ ደግሞ ዕድለኛው ሊቀጳጳስ ተብለው አዳነች አበቤን ከምእመናን የተሰበሰበ፣ ከሙዳየ ምጸዋት የተለቃቀመ ፈረንካ ተሰባስቦ ለአዳነች አበቤ የ1 ሚልዮን ብር የወርቅ መስቀል ይሸልሟታል። 😂

• አዳነች አበቤ ጴንጤ ናት።
• በመስቀል አታምንም፣
• ለመስቀልም አትሰግድም
• መስቀል ኃይላችን ነው። መስቀል ቤዛችን ነው። መስቀል መድኃኒታችን ነው፣ መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው ብላም አታምንም። እንደ አይሁድ መስቀልን የካደች፣ እንደኛ በመስቀል አዳኝነት የማታምን ናት።

"…የእምዬ ምኒልክን ስም ግን ከአዲስ አበባ እንደምንም ብለው እየሰረዙት ነው። ትታረዳለህ አራጅህን የግድህን ትሸልማለህ። አለቀ።

• ወይኔ በላቾ አለ ሰውዬው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ዳሩ ግን፦ መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ።” ሉቃ 23፥29

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:00 ሲሆን በዘመድ ቴቪ ላይ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ZemedTv 👉 zemedtv.com

• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1MYGNwVbmgnJw

• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6vherv--zemede-june-29-2025.html?e9s=src_v1_upp_a

• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East 11977 H 27500 ላይ ይከታተሉን።

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia

👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ፈረሰኛው እያፈረሰው ነው።

"…ሰኔ 19/2017 ዓም በብልጽግና ወንጌል እና በኦሮሞ የወሃቢይ እስላሞች የተሞላውና ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኦርቶዶክሱ የኦሮሙማው ጦር በሰሜን ወሎ በራያ ቆቦ የሚገኘውን የኩቢ ቀረንሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ይሁነኝ ብሎ በዚህ መልኩ በመድፍ ካወደመው እና ከቃጠለው በኋላ እግዚአብሔር ከሰማይ የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምሥራቅ ዐማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ከመሬት ያዘነበቡትን እሳት ወደ አካባቢው ደውላችሁ ጠይቁ።

"…ሠራዊቱ በዘመነ ጁንታ የገጠመው የመበተን፣ የመሸሽ፣ የመፈርጠጥ፣ የመደንገጥ ላማዱ ዳግም እንዳገረሸበት ነው የተነገረው። ፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የዓድዋው ጌታ ሊቀሰማእቱ ቅድስ ጊዮርጊስ ፈረሰኛው ሥራውን መሥራት መጀመሩን ነው የዓይን እማኞች የሚናገሩት።

• ኦፍጡነ ረድኤት…

ኦ ፍጡነ ረድኤት ለጽኑዕ ወለድኩም፣
ወለነፍሰ ኵሉ ቃውም፣
ጊዮርጊስ የዋህ እንበለ መስፈርት ወዓቅም፣
ከመ እግዝእትከ ቡርክት ማርያም፣
እስመ ርኅሩኀ ልብ አንተ እምበቀል ወቂም።

ኦ ፍጡነ ረድኤት በብዙኅ ፆታ፣
ከመ እግዝእትከ ርግበ ኤፍራታ፣
በሰማይ በላዕሉ ወበምድር በታህታ፣
አምህለከ ጊዮርጊስ በስመ እምከ ቴዎብስታ፣
ሞገሰ ስም ሀበኒ ከመ ስምከ መንታ።

ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩፀተ ነፋስ ወዓውሎ፣
ለዘይጼውዐከ በተወክሎ፣
ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ፣
ተወከፍ ወትረ ጸሎትየ ወቃለ ጽራኅየ ኵሎ፣
እስመ ልበ አምላከ ርኅሩኀ በኀቤከ ሀሎ።

"…የዘንድሮው ክረምት የፍጻሜ ግጥምያ፣ የዋንጫ ጨዋታ ነው። ዝርዝሩን፣ ምርኮና ተኩለሽን ጨምሮ ሌሎች የወደሙ ካምፖችና ከብልፅግና እጅ የተለቀቁ ከተሞች ጭምር በነገው መርሀ ግብራችን ይዘን እንቀርባለን እና ጠብቁን።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሰላም ለእናንተ ይሁን…

"…ምንም እንኳ ለእኔና የእኔ ቤተሰብ ለሆናችሁ ለእናንተ ለእኔ ወዳጆች አዲስ ጉዳይ ባይሆንም በእኔ በኩል ለዓመታት ስጮህበት የነበረ ጉዳይ ቢሆንም አሁን ግን ከሁሉ ነገር ገለል ብዬ አየር እየሰበሰብኩ ካለሁበት የእረፍት ስፍራ ድረስ ስቅታ እስኪገድለኝ መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ ሰሞኑን ዘማሪት ዮርዳኖስ ደረጄን እና ቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስን እንዲሁም ዘማሪት ፋንቱ ወልዴን በተመለከተ በተደጋጋሚ ስሜ የተነሣበት አጀንዳ ለመመከትና ለአስራ ምናምነኛ ጊዜም ልዘበዝባችሁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንደተለመደው በቲክቶክ መንደር መድረኬ ላይ ነጭ ነጯን ልቀውጠው ለአጭር ሰዓት ልመጣ ነኝ። አላችሁ አይደል…?

zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አጫጭር መረጃዎች

፩ኛ፦ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ለዓመታዊው የብልፅግና ወንጌል ግብር የታረዱት አበው መነኮሳት የአስከሬን ለቀማ ተካሂዶ የኦሮሞ ብልጽግና እንደተለመደው የሬሳ ማስረከብ ሥርዓት ፈጽሟል።

፪ኛ፦ ለ7 ተከታታይ ቀናት በወኅኒ ቤት የከረሙት ሊቁ የኔታ ይባቤ ከወኅኒ ቤት መፈታታቸውና በዚህ ሰዓት ባሕርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ በመንበረ ጵጵስናው እንዳሉ ተነግሯል። ጉዞ ወደ ጉባኤ ቤታቸው።

፫ኛ፦ ከመሥሪያ ቤቱ ወደ መኖሪያ ቤቱ ለማምራት ወደ መኪናው እያመራ ሳለ በብልፅግና ፎሊሶች ተይዞ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ የከረመው መምህር ደረጄ ነጋሽ ፍርድቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት የውጭ ጉዞ እገዳ ጥሎበት በ50 ሺ ብር ዋስትና ይፈታ ብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ቤተሰብ ዛሬ የዋስትናውን ብር ይዞ ለማስፈታት ቢሄድም ከሳሽ ፖሊስ ይግባኝ ስለጠየቅኩበት አይፈታም ብሎ እዚያው ዘብጥያ እንዳስቀረው ተነግሯል።

፬ኛ፦ የአቡነ ቀለሜንጤስ ዘመድ ሁላ እንደሆኑ የሚነገርላቸውና ለገጣፎ ላይ ታፍነው እስከ አሁን የት እንዳሉ የማይታወቁት የአርበሃራ መድኃኔዓለሙ አባት አባ ገብረመድኅንም በእጅ ስልካቸው ወደ ቤተሰብ እየተደወለ እንድንለቃቸው ከተፈለገ አንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ብር በባንክ እንዲያስገቡ አፋኞቹ እየጠየቁ ስለመሆኑ ተሰምቷል።

• ሲኖዶሱ ግን 🙏🙏🙏

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የፍርድ ቤት ውሎ…

"…ከቤሮው ለምሳ እየወጣ በመንግሥት የጸጥታ ሰዎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውሎ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ የከረመው የማኅበረ ወይንዬ ተክለሃይማኖት መንፈሳዊ የጉዞ ማኅበር እና የስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም የፀረ ግብረ ሰዶማውያን ማኅበር መሥራችና ሊቀመንበሩ መምህር ደረጄ ነጋሽ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቡ ተሰምቷል።

"…ሦስት ጠበቆች የቆሙለት መምህር ደረጄ ነጋሽም በፌደራል ፎሊስ መርማሪ አማካኝነት የተከሰሰበትና ለእስር ያበቃውን ወንጀል በችሎቱ ላይ አንብቦ ለፍርድ ቤቱ አሰምቷል። ክሱ የሽብር ክስ ነው።

• መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ
• ሃኪሞቹ ሳይራቡ ተራቡ ብሎ በሚዲያ አውርቷል
• መንግሥት በኅብረተሰቡ ዘንድ አመኔታ እንዲያጣ እያደረገ ነው ወዘተ በሚል ነው የከሰሰው። በዚህም ምክንያት የተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይፈቀደለት ዘንድ ፍርድቤቱን ጠይቆም ነበር ተብሏል።

"…መምህር ደረጄም ይሄ ክስ ፍጹም ሐሰት ነው በማለት የመለሰ ሲሆን ተከላካይ ጠበቆቹም "ይሄ የሽብር ተግባር አያስብልም፣ ደንበኛችን ሓሳባቸውን በሚዲያ በነፃነት ነው የገለፁት በማለት በነፃ ይለቀቅ ዘንድ ወይም በዋስ ይፈታ ዘንድ ያቀረቡ ሲሆን መርማሪውም የዋስትና መብት እንዳይሰጠው ተቃውሟል።

"…በመጨረሻም ግራ ቀኙን ያየው ፍርድ ቤቱ መምህር ደረጄ ነጋሽ በተከሰሱበት ወንጀል በ50 ሺ ብር ዋስትና ከእስር ተፈተው መከራከር እንደሚችሉ ፈቅዶ ነገር ግን የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከሃገር እንዳይወጣ በሚል ወስኖ ፋይሉን ዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት መላኩ ተነግሯል። ነገ ጠዋት የዋስትናው ሂደት ከተሟላ ደረጄ ወደ ቤቱ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል የፍርድ ቤት አከባቢ ወፎቼ።

• በዘማሪት ዮርዳኖስ ጉዳይ ላይ ነገ ከምስጋና በኋላ በርእሰ አንቀጽ መልክ የመጨረሻ ቃሌን እሰጣለሁ።

"…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፡— የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል። 2ኛ ጴጥ 2፥22

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ስለ የኔታ ይባቤ
     አጭር መረጃ

"…በእነ ዳንኤል ክብረት እልህ፣ በእነ ፓስተር ምስጋናው አንዱዓለም ጉትጎታ ዘመነ ካሤን ትነግሣለህ ብለው የቀቡት እርሳቸው ናቸውና እርሳቸውን ይዘን አስረን ስናበቃ የኔታ ለእነ አርበኛ ዘመነ ካሤ ደውለው ትግሉን እንዲያቆሙ እናደርጋለን በሚል የፌደራሉ አገዛዝ የኦሮሙማው ብልጽግና መከላከያ ሠራዊቱን ልኮ ከገዳማቸውና ከጉባኤ ቤታቸው ወስዶ ባህርዳር መኮድ ግቢ እንዳሰራቸው መግለጼ ይታወሳል።

"…የኔታ ይባቤን እነ ዳንኤል ክብረት ወደ አዲስ አበባ መጥተው በዚህ ምርመራ እንዲፈጽማባቸው አዘው ነበር ቢባልም ከመካከለኛው እስከ ከፍተኛው አመራር ድረስ ያሉት የብአዴን አመራሮች ሂደቱን በመቃወማቸው ምክንያት ሊቁ ወደ አዲስ አበባ ሳይላኩ ቀርተዋል። በመሃልም የሀገሬው ሕዝብ በግልጽ ሳይፈራ፣ ሳይሳቀቅ በሰላማዊ ሰልፍ ብልፅግናን "አባታችንን በአስቸኳይ ልቀቁልን በማለት እስከመጠየቅ ደርሷል።

"…በመጨረሻም የአገው ተወላጆች የሆኑ የአገው ሸንጎ አባላት ሊቁን እንዲከሱ ከላይ ከፌደራል ጫና የተደረገ ቢሆንም የአገው ሸንጎ አባላቱም በዚህ ጉዳይ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ነው የተነገረው። በመጨረሻም ከቤተ ክህነቷ በቀር ሕዝቡ ውስጥም ከውጭም የኔታ ይፈቱ የሚለው ጥያቄ እየበረታ በመምጣቱ የክልሉ ብልጽግና ብአዴን ከፌደራል እጅ ተቀብሎ ሊቁን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለምርመራ በሚል በፓሊ እና ጋምቢ መሃል በቀበሌ 12 በሚገኘው 2ኛ ጣቢያ አስገብተዋቸዋል።

• ይልቅ አይበጃችሁም እና ሊቁን ያለምንም ቅድመ ሆኔታ ልቀቋቸው።

• እኔማ ምኑን አረፍኩት…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? መዝ 25፥12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሌላ የአፈና ዜና…

"…የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የሆኑ ጥንታውያን ገዳማትና አድባራትን በማስጎብኘት፣ ሕዝብ አስተባብሮም የፈረሰውን በማሳነጽ የሚታወቀው፣ የማኅበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት መንፈሳዊ ማኅበርና ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልድን ከግበረ ሰዶም እንታደግ የተሰኘው ማኅበር መሥራቹ የአደባባይ ሰው መምህር ደረጄ ነጋሽ (ዘወይንዬ) በዛሬው ዕለት ምሳ ሰዓት አካባቢ ሰዓሊተ ምህረት ኢትዮ ቻይና ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮው ውስጥ በሥራ ላይ እንዳለ ታርጋ ቁጥሩ ኮድ ② አአ 64813 በሆነ መኪና በመጡና የደኅንነት ሰዎች እንደሆኑ የገለጹ አካላት አፍነው ይዘውት እንደሄዱ በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለዘመድ ሚዲያ ገልፀዋል።

"…በጎጃም አራት አይናው ሊቅ የኔታ ይባቤ በታፈኑ፣ በምሥራቅ ሸዋ የዝቋላ መነኮሳት በታረዱና በተጨፈጨፉ ማግሥት በዛሬው ዕለት ደግሞ ደፋሩ፣ ፊትለፊት የግንባር ሥጋ የሆነው፣ ለተጎዱ፣ ለተጠቁ ሁሉ ያለመሳቀቅ በድፍረት ከፊት ረድፍ ተሰላፊው፣ በሀገሩ በኢትዮጵያና በሃይማኖቱ በተዋሕዶ ድርድር የማያውቀው መምህር ደረጄ ነጋሽም ዕጣው ደርሶት መታፈኑ ተገልጿል። ቤተሰቦቹ ፍለጋ ላይ ቢሆኑም እስከአሁን እኔ ጋር ነው የሚል ተቋም እንደሌለም ነው የተገለጸው።

"…በሌላ ዜናም በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም፣ በደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ ራሳቸው ጠላ ጠምቀው፣ ዳቦ ደፍተው፣ እንጀራ ጋግረው፣ ራሳቸው ቆመው ነዳያንን በማብላት የሚታወቁትና በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የታላቁ የአርበሐራ መድኃኔዓለም ገዳም አባት የሆኑት አባ ገብረመድህን አበበም ያለፈው አርብ ለሥራ ጉዳይ አዲስ አበባ መጥተው ለገጣፎ አካባቢ የመንግሥት ኃይሎች ነን በሚሉ አካላት ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ እስከአሁን የት እንዳሉ እንዳልታወቀም ተሰምቷል።

• ማነህ ባለ ሳምንት…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ጀምረናል…

ገባገባ በሉማ…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③✍✍✍ …ነው። "አርበኛ ዘመነ ካሤ አስረስ መዓረይን የሚበልጠው ብረት በመጨበጥ ቀደም በማለቱ ብቻ እንጂ በንባብ፣ በዕውቀት እኩል ናቸው። ጎጃም ደስ ይበልህ ሁለት መሪ አለልህ ብለው ፕሮፓጋንዳ ሁላ መሥራት ጀምረው ነበር። በተለይ ከዘኘነ ካሤ ጋር ቆይቶ ከተለያዩ በ8 ደቂቃ ውስጥ በድሮን የተገደለው ኢንጅነር ከሞተ በኋላ ቀጣዩ ዘመነ ካሤና ልጁ ኪሩቤል ነበሩ። የምሥራቅ ጎጃሙ ተመስገን ጥሩነህ ድንቁም ባህርዳር ሄዶ ዘመነ ካሴ ሞቷል ብሎ ለብአዴን ተሰብሳቢዎች በአፉ የተናገረው ያኔ ነበር። እርግጠኛ ነበሩ ዘመነና ዝናቡ እንደሚገደሉ፣ የጋዜጠኞች ቡድን ተዘጋጅቶ፣ ሂሊኮፕተር ተዘጋጅቶ፣ እነ አንደግምም ወይ ናቲ መኮንን ሁላ የሆነ የሚሰማ ነገር አለ ብለው መለጠፍ ጀምረው፣ እነ ጌትነት አልማው እየጨፈሩ፣ የተመስገን ጥሩነህ አድናቂ እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለምም ዘመነ መሞቱን አላረጋገጥንም እንጂ መቁሰሉን ቆስሏል ብለው በቲክቶክ እስኪበጠረቁ ድረስ ደርሰው ነበር። ነገር ግን ዕድሜ ለሞዐ ተዋሕዶ፣ ዕድሜ ለዶክተር ወንደሰን፣ ዕድሜ ለመምህር ፋንታሁን ዋቄ፣ ዕድሜ ለዘመድኩን በቀለ፣ ዕድሜ ለአርበኛ ውባንተ ልጆች፣ ለአርበኛ ባዬ ልጆች ዛሬ በጎጃም ጎጠኛ ሸንጎ፣ በጎንደር የፖለቲካው ቅማንት ለዉሉደ ብአዴኑ የትግሬ ዲቃላው ስኳድ ቢሰደቡም በአንድም በሌላም አርበኛ ዘመነ ካሤን በእነ አስረስ መዓረይ ከመበላት ታድገውታል። አለቀ።

"…እነ ማርሸት፣ እነ አስረስ መዓረይ ይገደሉ፣ ይታሰሩ፣ ይወገዱ ብለው የፈረዱባቸውን አርበኛ ዘመነ ካሤ ጉዳዩን እንዲሰማ አድርገን ከሞት ያስመለጣቸውና ዛሬ በዐማራ ፋኖ በጎጃም ውስጥ በአመራርነት ያሉ ሺዎች ናቸው። ማርሸት እገሌ የሚባለው ሰው ቤተሰቦቹ ወዳጅ ዘመዶቹ ደውለው ግፍ ነው የተፈጸመበት ብለውኛል ብዬ ስለው "እኔማ ይገደል ብዬ ነበር ትእዛዝ የሰጠሁት፣ ቀሽሞች ትእዛዜን አልሰማ ብለው ነው ያዘገዩት እንጂማ እኔ እጨርሰው ነበር ብሎ በቃሉ፣ በድምፁ የነገረኝን ሰው ከአሜሪካ ድረስ ቤተሰቦቹ በእንባ ስለጨቀጨቁኝ አርበኛ ዘመነ ካሤ ሲደውልልኝ ራሴ ጉዳዩን በአቤቱታ መልክ አቅርቤለት መልካም ወደ እኔ ዘንድ እንዲመጣና ጉዳዩ እንዲታይ አደርጋለሁ። መግደልማ የለም ብሎ ቃል ገብቶልኝ፣ ሞት የተፈረደበትም ሰው አስታውሳለሁ ዘመነ ጋር ሄዶ፣ ግራቀኝ ክርክር ተደርጎ፣ አሸንፎ፣ እነ ማርሸትም እግሩ ላይ ወድቀው ይቅርታ ጠይቀውት አሁን ምን ላይ እንዳለ ባላውቅም ሥልጣን ተሰጥቶት እየሠራ እንደነበር ነው የማስታውሰው። መረጃ ማቅረብ እችላለሁ። አዎ ጎጃም ያለው የጴንጤና የቅባት፣ የአገው ሸንጎና የብአዴን ሴል ተሸናፊ ነው ነፈር ግን ለጊዜው ጎታች በመሆኑ ከባድ ይመስላል።

"…ዛሬ ወደዱም ጠሉም ዘመነ ካሤን የመጠበቅ፣ የመንከባከብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ዘመነ ካሤ አይደለም በድሮን፣ አይደለም በጥይት በትንታ ቢሞት ተጠያቂው አንጃ በደንብ ይታወቃል። ዘመነ ካሴን አሁን ከአስረስ የበለጠ ውስጡ እያረረ፣ እኔን እየረገመ ጤንነቱን የሚከታተልለት ሌላ ሰው የለም። የዘመነ ልጁ ኪሩቤል እንኳን እንደ አስረስ ሊጠብቀው አይችልም። እኔ ጎጃም ገብቼ በድፍረት የምናገረው ነገር ቢኖር ዘመነ ካሤን በእነ አስረስ መዓረይ ከመበላት ማዳኔን ነው። መታደጌ ነው። የሄንን የምናውቅ እናውቃለን። ለመንጋው ግን አይገባውም። ዛሬ ዘመነ ካሤ ካልተመረጠ ሞተን እንገኛለን የሚሉቱ በሙሉ የዘመነ ካሤ ጠላቶች ናቸው። በቀደም ዕለት ማርሸት የጎጃም አክቲቪስቶች የተባሉት በሙሉ ሰብስቦ ከሀብቴ እና ከምሬ ወዳጆ ይልቅ ለጎጃም መከታው ማሞ ይሻላል ብሎ በድፍረት ሲናገር በጆሮዬ እየሰማሁት ነበር። አሁን የጎጃሙ ቡድን ጎጃምን ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከሸዋ ነጥሎ ደሴት ላይ ለማስቀረት እየደከመ ነው። ከእስክንድር ጋር ለመሥራት ፈልጎ የደከመ ቢሆንም እስክንድር ኢግኖር ገጭቶ አሳፍሯቸዋል። የጎጃም ፋኖዎችም ከእስክንድር ጋርማ አንሠራም በማለት ማደማቸው ነው የተሰማው። ዞር ብለው ከመከታው ጋር ለመሥራት የፈለጉ ቢሆንም እነመከታውም አስረስ መዓረይ፣ ማርሸት፣ የቆየ ሞላ ያለበትን ስብስብ አይደለም ማየት መስማት እንደማይፈልጉ መናገራቸው ነው የተሰማው። የጎጃሙን ቡድን የሚደግፉት የጎጃም የዳያስጶራ ምሁራንም አስረስ መዓረይ ወደ ገደል እየከተታቸው እንደሆነ ቢረዱም ገሚሱ ፀረ ጎጃም፣ ፀረ ኦርቶዶክስ ቅባቴና ሸንጎ የሆነ ጎጃሜ መሳይ አረም ስለሆነ አስረስንም እንደ ሊቅ ስለሚያዩት ጥፋት ቢኖርም ከአስረስ ተለይተን ማንን እናመጣለን፣ ትንሽ እናስታምመው በማለት እየተንፏቀቁ ይገኛሉ።

"…አሁን ተተኳሽ፣ መሣሪያ ለፋኖ ከበቂ በላይ አለው። አምና በእስክንድር ሰበብ ክረምቱን በጭቅጭቅ አሳልፎ ዓመቱን ሙሉ ዐማራን ሲያስጨፈጭፍ የከረመው የጎጃሙ የእነ አስረስና ማርሸት ቡድን አሁን ደግሞ ዘንድሮ የተፈጠረውን አንድነት ባለመቀበል የዐማራን አንድነት በማፍረስ ከዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልነት ወርደው ወደ ዐማራ ፋኖ በጎጃም ጎጤ፣ መንደሬነት ወርደው ታይተዋል። ሌሎቹ የዐማራ ፋኖ በጎንደር በላይ ዘለቀ ዕዝ፣ የዐማራ ፋኖ በወሎዎቹ ምኒልክ ዕዝ፣ የሸዋዎቹ አሳምነው ጽጌ ዕዝ ተብለው ሲጠሩ። ዘገባም ሲሠራላቸው ጎጤው፣ መንደሬው፣ አፍቃሬ ወያኔ፣ ሸንጎና የቅባቴው ጥርቅም፣ አዝማሪዋ ጋለሞታ የምትመራው የጎጃሙ የአስረስና የማርሸት ቡድን በአፄ ቴዎድሮስ ስምማ አልጠራም በማለት የዐማራ ፋኖ በጎጃም ወይም አፋጎ ወደሚል ጎጤነት ተምዘቅዝጎ ወርዷል። የቴሌግራም የአፋጎ ዘጋቢዎችም ዐፋብኃን ትተው አፋጎ ነን ብለው ነው የሚዘግቡት። 3:1 ማለት ይሄ ነው።

"…በጎጃም ውድመት እያደረሰ ያለው ራሱ የዐማራ ፋኖ በጎጃም እና ኦሮሙማው ናቸው። በጎጃም ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ ኦሮሙማው ሲያወድም መምህራንና ዶክተሮችን፣ ተማሪዎችን እየገደለ፣ እየረሸነ በአደባባይ የሚፎክረው አርበኛ ዘመነ ካሤ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ነው። ተማሪ በመረሸኑ፣ መምህራን በመግደሉ፣ ዶክተሮችን በመግደሉ ሳይሳቀቅ ዐማራን በማጥፋቱ ልክ እንደ ጁንታው፣ ልክ እንደ ኦሮሙማው በአደባባይ የሚፎክረው የጎጃሙ ጁንታ በምንም መልኩ ከገዳዩ፣ ከጨፍጫፊው ኦሮሙማ ከአቢይ አሕመድ አገዛዝ አይለይም። አርበኛ ዘመነ ካሤ ይሄን ሁሉ እያየ ዝም፣ ጭጭ ጮጋ በማለቱ የዐማራ ፋኖ መሪነቱን ጥያቄ ውስጥ ነው ያስገባው። የጎጃም ፋኖን መርቶ፣ ሥነ ሥርዓት አስይዞ ወደ ከፍታ ማምጣት ያልቻለ ሰው ነው እናም ዐማራን ለመምራት የአቅም፣ የችሎታም ውስንነት ይታይበታል ብለው ለሚከሱት ከሳሾች ማረጋገጫ ነው እየሰጣቸው የሚገኘው። የጎጃም ፋኖ እንደማይታዘዝለት በቀደም ዕለት የኢዜማው መንግሥቱና ሌላ አንድ ልጅ ከዘመነ ጋር የተለዋወጠውን ቃለ መጠይቅ በዘመድ ቴቪ አሰምቼአችኋለሁ። እናም ዘመነ ራሱ ነፃ ሊወጣ የሚገባው ምስኪን ሰው ነው። ዘመነ ካሤ በግሉ እኔ ሳውቀው ሰው አማኝ፣ ሁሉን ለማስደሰት የሚጥር፣ የሚደክም፣ ሃይማኖተኛ፣ የንባብ ሰው፣ አድማጭ፣ ደግሞም ጸሐፊ፣ አንደበተ ርቱዕ ተናጋሪ ሰው ነው። ነገር ግን ዘመነ ካሤ በአራጆቹ ፊት የቆመ ቀን የሚጠበቅለት የአብርሃም በግ ነው። እንደዚያ ነው የማምነው። አንዳንድ ሰዎች ዘመነ ካሤን ሲሰድቡት፣ ሲያዋርዱት የምናደደውም የማውቀውን ስለማውቅ ነው።

"…ዘመነ ካሤን ከኋላው ፖለቲካ የሚሠሩበት ሌሎች ናቸው። ፎቶ እያነሱ እየለጠፉ የሚያሰድቡት እነ አስረስ መዓረይ ናቸው። በቀደም እንኳ ዘመነ ካሤ ከእነ ስብሃት ነጋ፣ ከእነ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር፣ ከእነ አሉላ እና ጀዋር መሀመድ ጋር አንድ መድረክ ላይ ቀርቦ በዚያ መጠን እንዲሰደብ፣ እንዲዋረድ፣ ከፍ ዝቅ…👇③✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…አይገፉበትም፣ ረዘም ሰፋ አድርገው አይተነትኑትም እንጂ፣ ቀጣይነት የለውም እንጂ አንዳንድ የቤተ ክህነቱም ሆነ የቤተ መንግሥቱ የቦለጢቃ ሴራ በደንብ የገባቸው የፌስቡክና የቴሌግራም ጸሐፍትን እያየሁ ነው። ሥራዬ ብለው ቢይዙት፣ ተከታታይነት ያለው ተግባር ቢፈጽሙ፣ አስሬ ለክተው አንዴ ቢቆርጡ ደግሞ ሸጋ ነበር። እሰደባለሁ፣ እነቀፋለሁ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ ጓደኛ፣ ጧሪ ቀባሪ አጣለሁ ብለው ሳይሳቀቁ እውነትን መርሐቸው አድርገው ቢገለጡ ሸጋ ነበር። ጠንካራ፣ ታማኝ፣ አስተማማኝ የሆነ ጠንካራ የመረጃ ምንጭ ቢኖራቸው፣ ሁሉም ሥፍራ የሚገኝ ኔትወርክ ቢዘረጉ ደግሞ የበለጠ አሸወይና ይሆንላቸው ነበር። በመንደር፣ በጎጥ፣ በሰፈር ባይታጠሩም ሸጋ ነበር። የሆነው ሆኖ ገባወጣ እያሉ ብቅብቅ የሚሉ ጦማሪዎችን እያየሁ ነው። ችግሩ እንደ መስቀል ወፍ ናቸው ቶሎ ቶሎ አይመጡም እንጂ ጸሐፍትስ እያየሁ ነው። እንደ ዘመኑ የሴቶች ልብስ አጭር፣ ሚስኮል ነጠላ ዓይነት ድንክ ጦማር ይጦምራሉ እንጂ እያየሁ ነው። በርቱ ተበራቱ ብቅ ብቅበሉም።

"…ደስ የሚለው ነገር አሁን የተፈጠረው ትውልድ አዳዲስ ትግል አስቀያሽ አጀንዳ ከየትም ይምጣ ከየት፣ በማንም ይምጣ በማን እንዲህች አድርጎ የማይቀበል የባነነ፣ የነቃ ትውልድ ነው ነው የተፈጠረው። እነ ጌጡ ተመስገን፣ እነ ጉርሻ ቲዩብ፣ እነ ዮኒ ማኛ፣ ቲክቶከርና ፌስቡከር፣ እነ ጃዋርና አንከር አጀንዳ ፈብርከው ቢያመጡም የማይቀበል፣ እንዲች ብሎ በእጁ ንክች የማያደርግ ትውልድ ነው እያየሁ ያለሁት። በሆነው ባልሆነው በተፈጠረ አጀንዳ ዋናውን ጉዳይ ትተው በተፈበረኩ አጀንዳዎች ሁሉ ነጠላ ዘቅዝቀው በየፌስቡክና በየቲክቶክ ልጥፎች ስር ዋይ ዋይ ሲሉ ይውሉ ያድሩ የነበሩቱ በተለምዶ የማዳም ቅመሞች የሚባሉት የዓረብ ሀገር እህቶቻችን እንኳ በአብዛኛው የባነኑ፣ የነቁ ሆነው ነው ያገኘኋቸው። መሬት ላይ ካለው አንዳንድ ሾተለይ ፋኖ ነኝ ከሚለው ሰነፍ ባንዳ በተሻለ መልኩ የፖለቲካውን የዓየር ጠባይ ተረድተው መተንበይ የሚችሉ ሰዎች ሁላ ነው እያየሁ ያለሁት። ይሄ ይበል የሚያሰኝ ነው። ግፉበት። መርምሩ፣ ተመራመሩ። ፔኒስዮን አልጋ ላይ ተኝቶ በቲክቶክ ትግል የጀመረውን የደቡብ ጎንደሩን ፀዳሉ በቲክቶክ ሲሞግቱ የነበሩት እነዚህ እህቶች ነበሩ። ይሄ ድሮ የማይታሰብ ነው። አሁን ግን አብዛኛው ሰው ነቅቷል። እየበቃም ነው።

"…በእስከአሁኑ ትግል እንኳንም ፋኖ አሸንፎ አራት ኪሎ አልገባ። ሳይጠራ፣ ሳይነጻ፣ እንደቆሸሸ፣ አረሙ፣ እብቁ፣ እሾህ አመኬላው፣ እንክርዳዱ ሁሉ ተግበስብሶ እንኳንም አራት ኪሎ አልገባ። የረጋ ወተት ቅቤ እንደሚወጣው የፋኖም ሁኔታ እንደዚያው ነው እየሆነ ያለው። እንደዚያ ባይሆን ኖሮ የበግ ለምድ የለበሰው ተኩላ ሁላ በፋኖ ስም ተግበስብሶ አይደለም ዐማራን ሀገሪቷንም የሌለ ትርምስ ውስጥ ነበር የሚከታት። አይታችኋል ከዓመት በፊት ፋኖ ተግበስብሶ ወደ ሥልጣን ቢመጣ ሊፈጠር የሚችለውን? አራት ኪሎ ላይ ዘመነ ካሤና እስክንድር ነጋ ሲታኮሱ። ኮሎኔል ፋንታሁን እና ምሬ ወዳጆ ሲጠዛጠዙ፣ ደረጀ በላይና ሀብቴ፣ ጌታ አስራደና ባዬ ሲዋጉ፣ ደም ሲፋሰሱ። እንደው ታዝባችኋል ኢንጅነር ደሳለኝ እና መከታው ማሞ ከሸኖ ጀምሮ እስከ አዲስ አበባ ሲተራመሱ፣ ማስረሻ ሰጤና እነ ማርሸት ሲፋጩ፣ ይሄን የሚያውቅ የዐማራ አምላክ በዐማራ ሕዝብ ላይ መከራው ቢበዛ፣ ቢጠነክርበትም ስንዴው ከገለባ እስኪለይ፣ እስኪ በጠር ድረስ አቆይቶታል።

"…የዐማራ ትግል እየጠራ ነው። የዐማራ ትግል መስመር እየያዘ እየመጣ ነው። በዐማራ ትግል ውስጥ ማን ጎጠኛ፣ መንደርተኛ፣ ተረኛም ለመሆን እንደሚላላጥ በቆይታ እየተገለጠ ነው። የዐማራ ትግል ካንሰር፣ የዐማራ ትግል ደንቃራ ማን እንደሆነ በጊዜ ሒደት እየተለየ ነው የመጣው። አፈ ቅቤ ልበ ጩቤው ሁሉ እየተለየ ነው። ዐማራ መሳይ አሞራው ሁሉ እየተበጠረ ነው። ማን በዐማራ ትግል እንደሚቀልድ፣ ማን በዓማራ ትግል የኢኮኖሚና የሥልጣን ጥሙን ለማርካት እንደሚንከራተት፣ ማን የዐማራ ትግል ላይ ሽብልቅ ለመክተት እንደሚፍጨረጨር በሚገባ እየታየ፣ እየተለየም ነው የመጣው። ከዐማራነት ወርዶ ጎጥ ውስጥ እየተወሸቀ ያለው ማን እንደሆነም ከሊቅ እስከ ደቂቅ እየተረዳው፣ እየገባው ነው እየመጣ ያለው። ማን ከወያኔ ጋር፣ ማን ከብአዴን ጋር፣ ማን ከሻአቢያና ከኦሮሙማው ጋር ጭምር እንደሚሠራ ሁሉም ሰው እየገባው፣ እየተረዳው የመጣበት ወቅት ላይ ነው የምንገኘው። ሕዝቡም ጨክኖ መፍረድ ጀምሯል። በግልጽ መገሰጽም ጀምሯል። ይሄ መልካም ጅምር ነው። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…አሁን ተወደደም፣ ተጠላም ሁለት ምርጫ ብቻ ነው ከዐማራ ፋኖ ፊት የተደቀነው። አንደኛው ምርጫ ልዩነትን አቻችሎ ፣ አቀራርቦ፣ አለዝቦ አንድነት ፈጥሮ ጠላቱን ተፋልሞ ማሸነፍ። በጎንደርና በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ፣ በወሎና ጎንደር፣ በጎጃምና ወሎ፣ በሸዋና በጎጃም ወዘተ መሃል ጠላት የዘራውን የከረመ መርዝ አክሽፎ፣ ሴራውን በጣጥሶ የግዱን አንድ ሆኖ ጠላትን እንደ ዐማራ መጋፈጥ። ይሄ አይስማማኝም ካለ ደግሞ ሁለተኛው ምርጫ እርስ በእርስ ዐማራ ከዐማራ ይጨፋጨፋል፣ በዚያውም ልክ ጠላቱ ገብቶ ይጨፈጭፈዋል። ሰኔ 15 እያለ ለሞተ ብአዴን ጎራ ለይቶ መጠዛጠዝ አልያም የሰኔ 15 አጀንዳን ለብአዴን ትቶ አዲስ ትውልድ ፈጥሮ በአዲስ አጀንዳ አዲስ አስተሳሰብ ይዞ በአንድነት መታገል። ምርጫው የዐማራ ነው። በተለይ የጎጎዎች። የሁለቱ ጎጎዎች። ጎጃምና ጎንደሮች። አለቀ።

"…ባለፈው ጎርጎራ ላይ ሂልኮፕተር ተከሰከሰ በተባለ ጊዜ እኮ ነው የሁለቱ ጎጎዎች አክቲቪስቶች በሳቅ ያነፈሩኝ። እንዋጋዋለን የሚሉት የዐማራ ብአዴን ብልፅግና ባለሥልጣናት ከጎንደር ወደ ጎርጎራ በመሄድ ላይ ሳሉ ሂሊኮፍተሩ በብልሽት ቢሉ በአርፒጂ በዐማራ ፋኖ ተመትቶ ወደቀ ሲባል በአዝማሪዋ፣ በኦሮሸኔዋ ጋለሞታ በቅዳሜ ገበያ የሚመራው የጎጃም አክቲቪስት ቡድን አጓራ፣ ደነገጠ፣ ያዙኝ ልቀቁኝ አለ። ጎንደሬዎቹ ሆን ብለው ጎጃሜዎቹን ባለሥልጣናት በሂሊኮፕተር አንድ ላይ ጭነው ጨረሷቸው። ወይኔ ወይኔ፣ ወይኔ ብለው ፀጉራቸውን እየነጩ፣ ደረታቸውን እየደቁ እዬዬአቸውን አስነኩት። በተለይ አዝማሪዋ አያሌው መንበር እንኳን ደስ አለህ፣ ይኸው ጎጃሞች ተለይተው አለቁልህ ብላ አለቀሰች። ብአዴን የሆነ፣ ሕዝቡን እያስጨረሰ ያለ አካል በእግዜሩ መብረቅ፣ በፋኖ ጥይት፣ በራሱ በአቢይ አሕመድ ተንኮል ጅም ብለው ቢያልቁ የዐማራ ፋኖ ትግል እዳው ቀለለት ተብሎ ጮቤ ይረገጣል፣ ስለት ይገባል እንጂ እንዴት ድንኳን ደኩኖ፣ ነጠላ ዘቅዝቆ ለቅሶ ድረሱኝ ይባላል። ጉዱ እኮ ነው። እናም ነፍ የትየለሌ አፍቃሬ ብአዴን የሆነ መንጋ አሁንም የሆነውን የዐማራ ፋኖ ወሳኝ ክፍል ሁላ እንደተቆጣጠረ ይሰማኛል። ብአዴን በፋኖ ውስጥ አልሞተም የሚያስብል ነው።

"…የጎንደሮቹም አክቲቪስቶች እንደዚያው ነው የተንጫጩት። ጫጫታው ግን በስሱ ነው። ኋላ ላይ የተጎዳው በወልቃይት ጉዳይ በቀጣይ ለሚሠራው ፖለቲካ እንቅፋት ይሆን ይሆናል ተብሎ የሚገመተው ኡዞ አገኘሁ ተሻገር መሆኑ ሲሰማ የጎጃሙ ሸንጎ ሰጥ አለ። አረጋ ከበደ፣ ተመስገን ጥሩነህ ምንም እንዳልሆኑ ሲያውቅ እፎይ ተመስገን አምላኬ ብሎ ጭጭ አለ። አገኘሁ ተሻገር ከሆነስ ይበለው አሉ እነ አዝማሪዋ ቅዳሜ ገበያ። አገኘሁ ተሻገር መወገድ ስላለበት ነው የተወገደው። መጪው የወልቃይት ጉዳይ መታየት ያለበት በፌዴሬሽን ምክርቤት ነውና እዚያላይ ደግሞ አቃጣሪ፣ ታማኝ ባሪያ፣ የመጣ የሄደው ሁሉ የሚጭነው የህዳር አህያ ቢሆንም…👇① ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም።” ዘጸ 18፥18

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጸሎተ አቡነ ሩፋኤል በእንተ ሃጫሉ…

ሃጫሉ…! ምንም ማድረግ አልቻልኩም። ነፍስህን አብርሃምና ይስሃቅ አጠገብ ያስገባልኝ። ሃጫሉ! እኔም ከአንተ በኋላ እመጣለሁ። ሃጫሉ! ሃጫሉ ልጄ ለኦሮሞ ሕዝብ እኮ አንተ፣ ለእምነትህም እኮ አንተ ኪዳነምሕረትን ትወዳት ነበር። ሃጫሉ ደምህን እግዚአብሔር ይበቀልልህ። እግዚአብሔር ቃየልን ጠርቶ የወንድሙን የአቤልን ደም እንደጠየቀ ደምህን እግዚአብሔር ይበቀልልህ።

ሃጫሉ፣ ሀጩ ኮ፣ በቋንቋችን ለሕዝብህ የታገልክ ነፍስህ በሰላም ትረፍ፣ እውነት ነው የተቀበረው። ልጆችህንም ያሳድግልህ፣ ሃጫሉ ምንም ላደርግልህ አልችልም፣ ነፍስህን ፈጣሪ ይቀበል፣ እንዳንተ መሆን አንችልም፣ ፈጣሪ እንዳንተ እንዲያደርገን እንማጸነዋለን። ነፍስህን በአብርሃም፣ በይስሐቅ አጠገብ ያኑርልን። በማለት የመቃብሩን ብረት በመሳም፣ ለሃውልቱም በመስገድ ፈጽመዋል።

"…ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በአባታቸው ጎንደሬ በእናታቸው ትግሬ እንደሆኑ ነው የሚታወቀው። ምን ዓይነት ጉድ ነው ዘንድሮ የመጣብን። የዝቋላ ገዳም መነኮሳት ሲታረዱ ጭጭ የሚሉት ሁላ አንድ እነ አቢይ አሕመድና ሽመልስ አብዲሳ ከእነ ጃዋር መሀመድ ጋር ተጠቃቅሰው ነፃ እርምጃ ወስደው ያስወገዱትን አዝማሪ በዚህ መጠን ቅረጸኝና ቪድዮውን በትነው በማለት የዘቀጠ ፖለቲካ መሥራት አንድ ጳጳስ ነኝ ከሚል ሰው ዘንድ መታየቱ አስደማሚ ነው።

"…ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ሲሞቱ ቀጥሎ የሚሾመው የኦሮሞ ጳጳስ ነው ሲባል በቃ አዳሜና ሄዋኔ በኦሮሞ ቄሮ ዘንድ ለመወደድ ሲል እንዲህ በአደባባይ ይላላጣል አይደል?  

• ቱ…! ሰውረነ 🙏 ሃጫሉኮ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ አላሉም። 😂😂 …ሃጫሉን የበላ ጅብ ፊት ሃጩሉ ጥራኝ ማለት የጤና ነውን?

• © ቪድዮ ምንጭ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• አላችሁ አይደል…?

👉🏿 በ zemedtv.com
👉🏿 በ https://zemedtv.com/live.html
👉🏿 https://rumble.com/v6vherv--zemede-june-29-2025.html?e9s=src_v1_upp_a
👉🏿 Yahsat 52.5° East 11977 H 27500

• ነጭ ነጯን ጀምረናል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ…ቆላ 3፥9 …" ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል አምላኬ። ኢሳ 57፥21 "…ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም። ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፤ በኃይሉም ብዛት አያመልጥም። መዝ 33፥ 16-17

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፤ በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት…" መዝ 92፥ 1-2

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።” ማር 13፥23። “…ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።” ማር 13፥37። “…የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥።” ዮሐ 16፥12። “…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።” "…በልቡም የተሰወረ ይገለጣል… 1ኛ ቆሮ 14፥28

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በበሬና በአህያ በአንድነት አትረስ። ዘዳ 22፥10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እየጠራ መጣ ኩል እየመሰለ…

"…የሚሰማኝ አድማጭ ባይኖረኝም እየሆነ ስላለው ነገር ራሴው እኔው ዘመዴ እንዲህና እንዲህ ይሆናል ብዬ አስቀድሜ የነገርኳችሁ ነገር እኮ ነው እየሆነ ያለው። መቼም ሐበሻ የሞተና ከዓይን የራቀ ሰው አመስጋኝ ሆኖ ነው እንጂ…ሃኣ…?

"…ምንም አትላኩልኝ። አዲስነቱ እያያችሁ ለማታዩ፣ እየሰማችሁ ለማትሰሙ ለእናንተ ነው እንጂ ለእኔማ ምንም አዲስ ነገር የለውም። ከዚህም የባሰ የከፋው ቀን ደግሞ ከፊት የሚመጣው ቀን ነው። እኔማ በዚህ ጉዳይ እኮ ከስንቱ የተጣላሁበት፣ ከምወደው ከመረጃ ቲቪና ከኤልያስ ክፍሌ፣ ከማከብራቸው እንደ ቤተሰብም ከማያቸው ከእነ ጋሽ ሰሌና ከመሲም የተለያየሁበት ጉዳይ እኮ ነው። ተፋቱኝ። ምንም አታምጡብኝ። አትላኩልኝ።

"…በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ እኔ ከኢዩ ጩፋ፣ ከእስራኤል ዳንሳና ከፓስተር ዮናታን በተሻለ መልኩ ትንቢት መናገር የምችል ይመስለኛል። ከምር እኔ እኮ የሚሰድበኝ፣ የሚረግመኝ፣ የሚያዋርደኝ እንጂ የሚሰማኝ፣ ከልቡ የሚያደምጠኝ የለም እንጂ ከዘመኑ የጴንጤ ማፍያ ነቢያት በብዙ ሳልሻል አልቀርም ብላችሁ ነው? 😂 ቀልድ ነው ደግሞ የምር አርጋችሁ እንዳትይዙት።

"…በአሁን ሰዓት አስረግጬ የምነግርህ ነገር ቢኖር እንደ እኔ የኢትዮጵያም፣ የዐማራም፣ የትግሬና የኦሮሞም ቦለጢቃ የገባው ሰው ያለ አይመስለኝም። ከምር እውነቴን ነው። ይሄ ጅማሮ ነው። ከባዱ ቀጥሎ የሚመጣው ነው። ዐማራ ግን ይሄንንም ተሻግሮ ያሸንፋል።

"…ይልቅ ልንገራችሁማ የኔታ ይባቤ ከፎሊስ ጣቢያ ወደ መንበረ ጵጵስና ተወስደው በዚያ ነው ያደሩት። እስከ አሁን ግን አልተፈቱም። መምህር ደረጄ ፍርድ ቤት ቀርቦ ወንጀሉ ተነብቦለታል። ሃኪሞች ሳይራቡ ተርበዋል ብለሃል ነው አንደኛው ክሱ። ዐቃቤ ሕግ የምርመራ ቀን ጠይቋል። ዐርብ ርዕሰ አንቀጽ ይኖረናል።

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

😂😂😂

• ደኅና እደሩልኝ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰማእትነት ዜና…

"…በሶሪያ ደማስቆ በቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥርዓተ ቅዳሴ ላይ በነበሩ የሶርያ የግሪክ ኦርቶዶክስ አማኞች ላይ የሶሪያ ጽንፈኛ የእስልምና አሸባሪዎች በፈጸሙት የአጥፍቶ መጥፋት የቦንብ ጥቃት ወደ 25 ያህል ምእመናን፣ ካህናት እና ዲያቆናት ሕፃናት ጭምር ሲሞቱ ወደ 80 ያህሉ ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ገብተው ህክምና በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

"…ወዲያው ነው የአንጾኪያው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኤፍሬም ፪ኛ እና በዱሊያ የማር ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ፲ኛ በደማስቆ ዱሊያ አካባቢ ወደሚገኘውና ጥቃቱ ወደደረሰበት የቅዱስ ኤልያስ ቤተክርስትያን በመሄድ ለሞቱት ጸሎተ ፍትሃት፣ ለቆሰሉትና በህክምና ላይ የሚገኙትን ደግሞ በሆስፒታል በመሄድ ሲያጽናኑ፣ ሲያበረቱና ሲጸልዩላቸው እንዳረፈዱ የተነገረው።

"…በኢትዮጵያ ይሄ ይናፍቅህሃል። በዝቋላ ለታረዱ አባቶች የቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቭዥን ሳይቀር የሀዘን መግለጫ እንኳ የሰጠው አሁን ከደቂቃዎች በፊት ነው። በሸገር ዙሪያ አቡነ ሳውሮስ ሀገረ ስብከት እየታረዱ ስላሉት ካህናት የተነፈሰ የለም። የኔታ ይባቤ ታፍነው አቡነ አብርሃም፣ አባ ገብረ መድህን ታፍነው አቡነ ቀለሜንጦስ ትንፍሽ አላሉም። የቲክቶክ ሐዋርያቱ እነ አኬም እንኳ የዝቋላው እርድና ጨፍጫፊ ሳይታያቸው የሶሪያውን አራጅ እስላም ጠቅሰው ሲወበሩ እያየሁ ያሁኔያ… ለማንኛውም የሰማዕታቱ በረከታቸው ይደረንብን…!

"…የዘማሪት ዮርዳኖስ ደረጀን ጉዳይ በተመለከተ ሓሳቤን በነገው ዕለት አቀርባለሁ። የኔታ ይባቤ እስከአሁን እዚያው መኮድ ናቸው፣ አባም እስከአሁን የትእንዳሉ አልታወቀም። ደረጄ ዘወይንዬም ፍርድቤት አልቀረበም እንጂ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ እንደሚገኝ ታውቋል።

• ምኑን አረፍኩት ግን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የግድያ እና የአፈና ዜና…!

"…በፎቶው ላይ የሚታዩት ቄስ ዮሐንስ ግርማ የተባሉና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሀገረ ስብከት በሸገር ሀገረ ስብከት የዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ካህን ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለአገልግሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ላይ ሳሉ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ደጃፍ ላይ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ በተባሉ ኃይሎች በጩቤ ተወጋግተው መገደላቸውን ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ዘግቧል።

"…በዚያው በሸገር ሲቲ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት የቦሌ አራብሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የስብከተ ወንጌል ሓላፊ እና የአንድ ልጅ አባት የሆኑት መምህር ብርሃነ መስቀል የካቲት 16/2017 ዓም ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ ምንም ዓይነት መለዮ ባልለበሱና የፖሊስ ፓትሮል በያዙ በቁጥር ስምንት በሚሆኑ አፋኞች ታፍነው የደረሱበት ከጠፋ እነሆ አምስት ወር እንደሆናቸው ተነግሯል።

"…በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለት ከሥራ ቦታው የታፈነው መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) ከዜናው መበተን በኋላ በስተመጨረሻ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ በሚገኘው የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሚገኝ የመረጃ ምንቼ አድርሰውኛል። የእስሩም ምክንያት መምህሩ በጤና ባለሙያዎቹ የደሞዝ ጥያቄ ዙሪያ በሠራው ቪድዮ ምክንያት በጠቅላይ ሚንስትሩ በአቢይ አሕመድ ቀጥተኛ ትእዛዝ ምክንያት ለምርመራ መወሰዱ ነው የፖሊስ ምንጮቼ የገለጹልኝ።

"… የሰኔ የደም ግብርም ያለእንከን እየተፈጸመ ነው። ከኦሮሚያና ከሸገር ሲቲም ካህናት መነኮሳትም እየጸዱ ነው። አቡነ ሳዊሮስ እና አቡነ ዲዮስቆሮስም ሥራቸውን አገዛዙን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እየፈጸሙ ይመስላል። የኔታ ይባቤም እስከአሁን ድረስ አልተፈቱም። እዚያው ባሕርዳር መኮድ ጨለማ ቤት እንደታሰሩ ነው።

• ማነህ ባለ ሳምንት…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው! ኢሳ 29፥15 

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:05 ሲሆን በዘመድ ቴቪ ላይ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ZemedTv 👉 zemedtv.com

• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1dRKZYLQZygxB

• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6v5usp--zemede-june-22-2025.html?e9s=src_v1_upp_a

• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
                                       11977 H 27500
• ላይ ይከታተሉን።

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia

👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!

Читать полностью…
Подписаться на канал