zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

311892

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እሺ…

"…የዛሬውን ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር እንዴት አገኛችሁት…?

• ዘመድ ቴቪአችንስ እንዴት ነው…?

"…የተሰማችሁን ተንፒሱ እስቲ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር…

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:00 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• በዛሬው ዕለት በዕለተ ሰንበት በቅፅረ ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴ ላይ ሳሉ አባቱ የተረሸኑበት የቤተ ዐማራው ፋኖ የአርበኛ አበበ ፈንታው መልእክትም ይደመጣል። ሌሎች መርሀ ግብሮቻችንም እንደተጠበቁ ነው።

• ZemedTv 👉 https://zemedtv.com/live.html

• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1nAKEgplvjVJL

• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6wr3m0--zemede-july-27-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a

• በሳታላይት ቴሌቭዥን

👉 Yahsat 52.5° East
       11977 H 27500 • ላይ ይከታተሉን።

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia

👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው። መዝ 132 ፥ 8-9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እኔም ዐላወቅኩም…

"…የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችንን ሞቅ ደመቅ እያደረግን ሳለ ድንገት አንድ ወዳጄ ረዘም ያሉ ተከታታይ ቪዲዮዎችን ከኢትዮጵያ ይልክልኛል። እኔም የተላኩትን አንድ ሁለት ቪድዮዎች እንዳየሁ ቀሪዎቹም ቪድዮዎች ተመሳሳይ ያው የተለመዱ እና ተመሳሳይ ይሆናሉ ብዬ ንቄአቸው ወደ መርሀ ግብሬ ልመለስ ስል ወዳጄ ደወለልልኝ። ስልኩንም አነሣሁ። አነሣሁና አወራን።

• ዘመዴ ድራማውን፣ ቲአትሩን፣ ድራሚስቶቹንና አርቲስቶቹን እርሳቸው። እንዲየው አዳራሹን፣ መንደሩን የሞሉትን ሰዎች አይተሃቸዋል? ተመልክተሃቸዋል? እሺ ወጣቶቹና ህፃናት ይሸወዱ፣ ይታለሉ ይባል። እነዚህ ትላልቅ ሰዎች እንዲህ የሚሆኑት ምን ሆነው ነው? ምን ነክቷቸው ን? የተማሩ፣ የተስተማሩ ሰዎችንም እኮ አያለሁ። ምን መዓት ነው የመጣብን? ዝም ብለህ አሜን የሚሉትን ብቻ ተመልከትልኝ ይለኛል።

"…እንደቀልድ አንድ ሁለት ብዬ ቁጭ ብዬ በሙሉ ማየት ጀመርኩኝ። ወዳጄንም ባላየሁበት አንግል ዓይቶ እንዳይ ስላደረገኝ አመሰገንኩት። ከምር በተለይ የደቡብ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ አሳዘነኝ። አንጀቴን ነው የበላኝ። መጫወቻ አይደል እንዴ የሆኑት? እንደዛር ሲርገፈገፉ፣ እንደ አጋንንት ሲንፈራፈሩ፣ በእውነት በክፉ መንፈስ ተይዘው በጌታ ስም ሲወራጩ እያየሁ አዘንኩ። ራሴንም ጠየቅኩ።

• ቆይ ይሄ ነገር የማን ጥፋት ነው? 

• በዚህ እንዲህ መጫወቻ እንዲሆን ለተፈረደበት ሕዝብ ተጠያቂውስ ማነው?

• በጥንት ጴንጤዎች የአምልኮ ሥርዓት ውስጥ ያልታየ ይሄን እንግዳ የአምልኮ ሥርዓት አምጥቶ የዘራው ማነው?

"…ለቅዱሳን አንስግድም ሲሉ የሚሰሙት ሁሉ በመድረክ ላይ ለራሱ የሚያሰግዳቸው ሲመጣ እንዴት እሺ፣ በጄ ብለው ተቀበሉት።

"…ከምር አያገባኝም አይባልም። እግዚአብሔር ይሁናቸው ከማለት በቀር ሌላ ምን ይባላል? አያስቅም። ይሄ ያስለቅሳል እንጂ ከምር አያስቅም። ፈዝዤ ነው የዋልኩት። ያመሸሁት። እንዲህ ትኩረት ሰጥቼ ያላየሁትን ነውር ሁላ ነው ሳይ ያመሸሁት።

• ፈጣሪ ይድረስላቸው። 🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…፫

• ክልል መሆን ያማራችሁ ፓስተሩን ስሙት…😂

"…ከዞንነት ወጥታ ዱራሜ ክልል ትሆን ዘንድ ፓስተር ሶፍት ብሉ፣ በቴሌቭዥን የሚያዩትን በሙሉ የሚያስረግዘው መስፍኔ ዐውጇል። መቼም ዘንድሮ ይሄን ምስኪን የደቡብ ሕዝብ፣ ይሄን መልካም እረኛ በማጣቱ ምክንያት ለተኩላና ለቀበሮ መጫወቻ ይሆን ዘንድ ተላልፎ የተሰጠን የዋሕ የደቡብ ሕዝብ ማፍያዎቹ እነ መስፍኔ በጠራራ ፀሐይ እንዲህ ጢባጢቤ ይጫወቱበታል።

• ክልል መሆን የምትፈልጉ አሜን ነው? 😁

• እስቲ ምናችሁ ክልል እንዲሆን ትፈልጋላችሁ?

• የሱሳቸው ምንም አይሳነውም እና እስቲ እናንተም ቀበሌአችሁ? …ወረዳችሁ? ዞናችሁ? …የቱ ክልል ይሁንላችሁ…? ምረጡ…?

• በተለይ የእናንተ ሰፈር ክልል ይሆን ዘንድ ከበቂ በላይ ምክንያት አለን የምትሉ ምክንያታችሁን ጭምር ብትገልፁል ቅዳሜ ከሰዓታችን የበለጠ ከፓስተር መስፍኔ ጨዋታ ጋር ይደምቅልን ነበር።

• ቂርቆሶች፣ ፒያሳዎች፣ ፈረንሳይ፣ ልደታ፣ ቄራ፣ 22ቶች፣ ደጃች ውቤ ወዘተ ክልል ስለመሆን ምን ታስባላችሁ? በተለይ መርከብ የሚያንሳፍፍ ጎርፍ ያላችሁ ቅድሚያ ብትሞክሩ መልካም ነው።

• በዘመነ ጴንጤ ገና 10 ትናንሽ ነው የምንሆነው።

• አጠገባችሁ ያለውን ነካ አድርጉትና ዱራሜ ክልል ትሁን በሉት። 😂 አሜን ነው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል… ፩

• ሰድበሽኛል… ኛል… ኛል… ኛል…

• ሂድ እንግዲ…😁

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወበዛቲ ዕለት እንዲል መጽሐፈ ስንክሳር በዛሬው ዕለት የ3 ዓመቱ ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስ እና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በሃይማኖታቸው ምክንያት ሰማእትነትን ይቀበሉ ዘንድ ተፈርዶባቸው ድምፁ በሩቅ እስኪሰማ ድረስ እንደነጎድጓድ በሚፍለቀለቅ ንፍር ውኃን በያዘ የነሀስ ጋን ውስጥ ተጨምረው ሳለ በዚያ በጋኑ ውስጥ የሚፍለቀለቀውን ውኃ የውኃውንም ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዝቃዛ አድርጎ ከእግዚአብሔር የታዘዘው የመላእክት አለቃ አብሳሪ ትስብእት ወመጋቢ ሀዲስ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዝቅዞ እናትና ልጅን ያዳነበት ዕለት ነው።

“…በራሳችን ላይ ሰውን አስረገጥኸን፤ በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን፥ ወደ ዕረፍትም አወጣኸን።” መዝ 66፥12

~"…ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ስለ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ የጸለየው ጸሎት"

"…ጌታ ሆይ እርሻውን አቃጥለህ ሰብሉን ብትባርክ ምን ይጠቅማል? ዛፉንስ ቆርጠህ ቅርንጫፉን ብትባርክ ምን ይረባል? እናቴ እርሻ ናት እኔ ሰብል ነኝ። እናቴ ዛፍ ናት እኔ ቅርንጫፍ ነኝ። እባክህን እናቴ ብትክድ እኔ ባምን ምን ይጠቅማል። ጌታ ሆይ የእናቴን ልብ በሃይማኖት አጽናልኝ"

"…የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል" መዝ 19፥7

"…ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ይላክልን። እኛንም በቅዱስ ቂርቆስና በእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አላችሁ አይደል…?

• ጀምረናልና ገባ ገባ በሉ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አሁን ደግሞ ምሽት 1:30 ላይ ዛሬ በሰበር ገብቼ በዘመድ ቴቪ የቀጥታ ስርጭት የማቀርብላችሁ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር እስኪጀምር ድረስ መቶ አለቃ ላቃቸው አንለይ ለምን በምን ምክንያት እጁን ከአገዛዙ ሰጠ በሚለው ሓሳብ ላይ የተለየ ሓሳብ ያለው ካለ በመስማት በመፍትሄውም ላይ በመወያየት እንቆያለን።

• ሓሳብ ተንፒሱ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ምሽት 1:30 ላይ በቲክቶክ አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን እናሠራለን በማለት ዘረፋ ላይ የተሰማሩና መልካም ለሚሠሩትም ወጣቶች እንቅፋት ስለሆኑ ጩሉሌ፣ ጭልፊት ቲክቶከሮችና ሌሎችም አጭበርባሪዎች በዘመድ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የተሰኘው መርሀ ግብር ይኖረኛል።

"…እስከዚያው ድረስ ግን ትላንት ስለጠየቅኩት ስለ መቶ አለቃ ላቃቸው አንለይ ትግሉን አቋርጦ ለአገዛዙ ለምን እጅ ሰጠ ብዬም ጽፌ ነበር። እናም ለጥያቄዬ በድፍረት መልስ የሚሰጠኝ ቢጠፋም ከእነሱ የፌስቡክ ገጽ ላይ ግን በቀጥታም ባይሆን በገድምዳሜ መልስ ሰጥተውኛል። መልሳቸው ግን እኔ ካለኝ መረጃ ጋር በፍጹም አይገናኝም። የቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ እስኪጀመር ድረስ የእኔንም ሆነ የእነሱን መረጃ ባቀርብላችሁ ምን ይላችኋል?

• ወገን ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልስ አዘጋጅታችሁልኝ እደሩ…!

"…በሙስናም፣ በባንዳነትም የማይታማው፣ ቆራጡ ጀግና የበላይ ዘለቀ ልጅ የዐማራ ፋኖ በጎጃም የደጋ ዳሞት ቀጠና ዘመቻ መምሪያ የሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ቀኝ እጅ የነበረው መቶ አለቃ ላቃቸው አንለይ በዐማራ ክልል ብአዴንን አላምንም ብሎ ዓባይን ተሻግሮ አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ እያዘነ፣ እያለቀሰ ለምን ለአገዛዙ እጁን ሰጠ?

"…የአፋጎ የፌስቡክ፣ የቲክቶክ፣ የቴሌግራምና የዩቲዩብ አክቲቪስቶች ከጎንደር ጸዳሉ፣ ከሸዋ ከወሎ እገሌ እጁን ሰጠ። ጎጃም ግን እያሉ የሌለ የተለየ ምሥል ለራስ ከመስጠት በቀር እንዲህ ዓይነቱን ጉዳይ አይደፍሩትም። በሉ ተንፍሱ። አፋጎ ከወሬና ከፎቶ የዘለለ ሪፎርም ካላደረገ መጪ ጊዜው ከባድ ነው የሚሆንበት። ህመሙን፣ በሽታውን ዘርዝሮ፣ በድፍረት ለሀኪም ያልተናገረ መድኃኒት አያገኝም። አይፈወስም። አይድንምም። ፎቶም፣ ዶክመንተሪም፣ ፉከራና ሽለላ፣ ሰበካና ቀርቶ የማይደብቋቸው እውነቶች መገለጣቸው እንደሁ አይቀርም።

"…ነገ በጠዋት 1ሺ ሰው አመስግኖ ከጨረሰ በኋላ ይሄንና ይሄን የመሳሰለውን አንሥተን እንወያያለን።ደኅና እደሩልኝ የነገ ሰው ይበለን።

• ዘመዴ ነኝ ከዚያው ከጮቄ ተራራ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሃልማዜ ሙን ኦና ኖ…?

"…ሃዸ ስንቄ አዝማሪት አዴ አልማዝ (ቤተልሔም) ዳኛቸው ዘውዴ መገርሳ ምን እያለች ነው? ቆይ ምን አድርጌአት ነው እንዲህ ምርር ያለችብኝ? በጣም ነው እንዴ ጢባጢቤ የተጫወትኩባት? አልገባኝም እኔ እኮ እረሳለሁ። ሲያመኝ ደግሞ ጤና የለኝም አይደል…?

"…የእነ አልሚ ባለጭራም ትእቢት ተንፍሶ፣ በዐማራም፣ በሌላውም ላይ ይዘረጋ የነበረው ልቅ የጋለሞታ ዘንዶ ምላስም ተሰብስቦ፣ ተኮማትሮ፣ ግቡ ግቡ፣ ወገን እገሌ ላይ ልርድበት ነው። እገሌ ላይ ልሄድበት ነው ተብሎ ሺ ዎች የጋለሞታ ስድብ ለመስማት በቤቷ ይኮለኮሉ እንደልነበር አሁን አሁን ምነው ድምጿም አልሰማ አለ? ሳላም ኖ…?

"… የሚገርመው ለምንድነው ጉሮሮዬን፣ ላንቃዬን እመብርሃንም፣ ኢየሱስ ክርስቶስም ዘግተው የሚያሳዩሽ? በምኔ ልበላ ነው? በምኔስ ልጠጣ ነው አልሚ…? ባይሆን አንደበታችን ይከፈትና ሁላችንም ሓሳባችንን ሽጠን እንኑርበት እንጂ? ተይ እንጂ አልሚዬ።

"…ደግሞ የሰው ሥጋ ከመቼ ወዲያ ነው ምግብ የሚሆነው? ይድፋህ፣ አፈር ያስበላህ፣ ድፍት ያድርግህ፣ ሙተህ በቀረህ ወዘተረፈ ይባላል። መቼም የተናደደ ሰው ከዚህም በላይ ሊል ይችላል። ሆኖም ግን ሙተህ ሥጋህን ጠብሼ በበላሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰምቼም ዓይቼም አላውቅ። የሰው ሥጋ እንዴት ይበላል? ልምድ አለሽ ማለት ነው አልሚዬ። ይሄ ከባድ ነው። 😁

"…ለማንኛውም ከጎጃም አልወጣም። ከጮቄም አልወርድም። ከምር በጣም ነው እንዴ ህበለ ሠረሰሯን የነካሁት? ጠብሼ ነው የምበላው አሜን በሉ አላለችም? ሆ ሆ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አሁን ደግሞ የእናንተ ሓሳብ የሚደመጥበት ሰዓት ነው። እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በጨዋ ደንብ ስንወያይ እናመሻለን።

"…በነገራችን ላይ አገዛዙ በራሱ ችግር መውደቁ አይቀርም። ይሄን የተረዱት ኦሮሞዎቹ ከአቢይ መውደቅ በኋላ እንዴት አድርገን ሥልጣኑን እንረከብ በማለት እንቅልፍ አጥተው በመምከር ላይ ናቸው።

"…የብአዴን ሴሉ የጎጃሙ የእነ አሥረስ መዓረይ ቡድን ጠፍርንግ የያዘው የጎጃም ዐማራ ፋኖም በመባነኑ እና በመንቃቱ ምክንያት እጅግ የተለየ ደስታም እየተሰማኝ መጥቷል። በተለይ ደግሞ በውዛሬ የሦስተኛ ክፍለ ጦር ጀግንነትም ስደመም ነው የዋልኩት።

"…በአፋጎ የጽ/ፈት ቤት ሓላፊ (በይትባረክ) የሚመራ 7 አባል ያለው የዕዙ  የፕሮፖጋንዳ ቡድን ወደ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር በመምጣት "ከአፋብሀ የወረድንበት ምክኒያት" የሚል አጀንዳ ይዘውለማወያየት ሂደው የነበረ ቢሆንም የዋዛ ያልሆነው ክፍለ ጦር ለእነ ይትባረክ ከባድ ማስጠንቀቂያ እና አራት አስቸኳይ ጥያቄያዊ  ትእዛዝን በአስቸኳይ እንዲፈጽሙ በማዘዝ አባረዋቸዋል። ጥያቄዎቹን ነገ እመለስባቸዋለሁ።

"…በመጨረሻም ይሄን ለማድረግ ካልቻላችሁ ሁለተኛ ወደ እንዳትመጡ ብሎ ከእነ ያዙት አጀንዳ ያአባሯቸው ሠራዊቱ ከትግሬው ከኮረኔሉ ማምለጥ ጋር እጅህ አለበት በሚል ሊታሰር የነበረዉ ይትባረክም በሽምግልና ዛሬ ከመታሰር ተርፏል።

"…ከዘጎት የአክስታቸው ከዘመዶቻቸው ከእነ ተመስገን ጥሩነህ ጋር በመሞዳመድ የዐማራን አንድነት እነ አስረስ መዓረይ አሁን የንፁሐን ዐማሮች ደም ሊፋረዳቸው ከደጃፋቸው ቆሟል። የሆነው ሆኖ የአብይ አሕመድ አገዛዝ ይወድቃል። ሌሎቹ ሥራ ላይ ናቸው። ዛሬ በጎንደር በጌምድር ክፍለ ጦር ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ እየተካሔደ ባለው ውጊያ ሦስት ምሽጎችን በመስበር ጣቁሳ-ደልጊን መቆጣጠሩ ተነግሯል። ጯሂት፣ ደልጊ፣ ቆላድባ፣ አይባ፣ በለሳ፣ እብናት ታች ጋይንትም ነፃ መውጣታቸው ተነግሯል።  በርካታ ሠራዊትም በፈቃዱ እጅ መስጠት ጀምሯል።

"…ዐማራ ማሸነፉ ግድ ነው። ግዴታ ነው። ሌላ አማራጭም የለውም። ጎጃሞች አርበኛ ዘመነ ካሤንም ከእነዚህ ኮተታሞች ነፃ አውጥተው ወንድሞቻቸውን መቀላቀል አለባቸው። ዘመነ ካሤ የዐማራ ፋኖ ምልክት ነው። ከአጣብቂኙ ነፃ የሚያወጡት ወገኖቹ ዐማሮች በሙሉ ናቸው።

"…አንድ ሁለት ሦስት… ጻፉ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③✍✍✍ …ጠላት ሆነው እየተፋጁ፣ የገዛ ወገኑን መድፈር፣ መዝረፍ፣ ማገት፣ ማረድ፣ የወገኑን እምባ ያብሳል ተብሎ ሲጠበቅ ጭራሽ እናት አባትን ያለጧሪ፣ ያለቀባሪ፣ ልጆችን ያለ አባትና ያለ እናት የሚያስቀር ሆኖ ተገኝቷል። ይሄን ያ በደግነቱ፣ በርህራዊ፣ በጀግንነቱ፣ በሀገር ወዳድነቱ፣ በሃይማኖቱ፣ በአማኝነቱ የሚታወቀውን የፋኖነት መታወቂያ ሥነ ምግባር በጥቂቶች እየተጣሰ መጥቶ ዛሬ ሕዝቡ ፋኖን ከአቢይ አሕመድ፣ ከብራኑ ጁላ ሠራዊት እኩል አድርጎታል። አንድ ሳይሆኑ ማሸነፍ የለም። ማርሸትና አስረስ በላይ ማናዬ፣ መዓዛ መሀመድ፣ መሳይ መኮንን ጋር ቢራወጡም ወፍ የለም።

"…እኔ እስከማውቀው ድረስ በነፃ የተሰጠ፣ በርዳታ የተገኘን ጥይት ልክ እንደ ጎንደርና ወሎ በነፃ ለታጋይ ፋኖዎቹ እንደማከፋፈል ለጦር አዛዦቹ ከፍላችሁ ነው መውሰድ፣ ለአንድ ጥይት መቶ ብር ክፈሉ ብሎ በጎጃም እነ አስረስ መመሪያ አስተላልፈዋል መባልም አስገርሞኛል። አስረስ መዓረይ የሥጋ ዘመዶቹ የሆኑ አጃቢዎቹን በሙሉ ወደ ክፍለጦር አመራርነት በማሳደግ፣ የክፍለጦር አመራሮችንም የሥጋ ዘመዶቹን አጃቢ በማድረግ ጠርንፎ ይዟቸዋል። አብዛኛው ጀግና ጀግና የጎጃም ፋኖ ትግሉን ጥሎ ወደ አዲስ አበባና ወደ ኡጋንዳ እየፈለሰ ነው። አንድም የጎጃም ልጅ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ ገብቶ ሲታገል ቢታይ፣ ቢሰማ ቤተሰቦቹን እንደሚረሽኑና ያለ ዘር እናስቀርሃለን ብለውም ያልተጻፈ ዐዋጅ ስላወጁ የጎጃም ልጆች ቤተሰቦቻቸውን ለመታደግ ሲሉ ስደትን፣ ፍልሰትን ምርጫቸው አድርገዋል። በሸዋም መከታው ስር ሆነው በእነ ደሳለኝ ላይ ተኩሱ የተባሉ ፋኖዎች ወደ እነ ደሳለኝ አንተኩስም፣ ከወንድሞቻችን ጋር አንመታታም። አንጎዳዳም በማለት ወደ እነ ደሳለኝ የገቡትን ቤተሰቦቻቸውን አግተው ስለሚረሽኑ፣ ታጋዩ መሳሪያውን እየሸጠ ወደ አረብ ሀገር እየተመመ ነው። ከባድ ነው። ሆኖም ግን ሞትና ጦርነቱ ባይቆምም የዐማራ ክልሉ ነፍጠኛ በተወሰነ መልኩ የኃይል ሚዛን አስጠብቋል።

"…ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ከባዱ ነገር የውጪ ኃይሎች ኃያላኑ ሀገራት በኢትዮጵያና በቀጠናው ላይ የሚያሳዩት ተግባር ከበድ ያለ ነገር እንደሚከሰት አመላካች ነገሮችም እየታዩ ነው። ኃያላኑ ሀገራት ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ጂኦፖለቲካል ውሳኔዎችን ሰሞኑን እንዳሳለፉ በስፋት እየተዘገበ ነው። አሜሪካ፣ እስራኤል ተደጋግሞም በዚህ ጉዳይ ስማቸው እየተጠራ፣ እየተጠቀሰም ነው። ጉዳዩን ተከታትለው የሚዘግቡ የቦለጢቃ ጠንቋዮች አማሪካና እስራኤል ዓቢይን ይዘው ኢሳይያስንና አገዛዙን ለማስወገድ የመጨረሻ ያሉትን የጋራ ዕቅድ ወጥነዋል ነው የሚሉት። በዚህ ጉዳይ ኤምሬትስ ከአቢይ ጋር ሳዑዲም ከኢሳይያስ ጋር ተሰልፈዋል ነው የሚባለውም። ከተሳካ ልክ በኢራን እንደፈጸሙት ባለ ቅንጅት፣ የቴክኒኩን ሥራ ኦፕሬሽኑን ጭምር ኃያላኑ መርተው የኤርትራ ወሳኝ፣ ወሳኝ መሪዎችንና ባለሥልጣናትን ዒላማ በማድረግ በመምታትም፤ የአውሮፕላን ማረፊያውን፣ አየር ኃይሉንና የኤርትራ ድሮኖች ያሉበትን ቦታ ለመምታት መታቀዱን ነው የሚያንሾካሽኩት።

"…የአየሩ በዚህ ከተሸፈነ የእግረኛው ጦር በማስገባት ኤርትራን መቆጣጠር የዓቢይ ድርሻ ነው የሚሆነው ይላሉ የቦለጢቃ ተንባይ ጠንቋዮቹ። ከወዲሁም ከኤርትራ ኢሳይያስ ተወግዶ የሚቀመጥ አሻንጉሊት የሆነ መሪም ተዘጋጅቷል ነው የሚሉት። ኢሳይያስና አብሮአደጎቹ የአገልግሎት ዘመናቸው መፈጸሙን እና ማለቁን ነው የሚናገሩት። ለኢትዮጵያ ውለታ የኤርትራ ነው ከተባለው ግዛት የተወሰነውን ስፍራ ለመስጠት ቃል ቢገባም ቀጠናዊ ትርምስ እንዲፈጠር በማድረግ ስፍራው በውጪ ኃይል እንዲተዳደርም መፈለጉም ነው የሚነገረው።

"…ፋኖዎችን በተመለከተ በአየር ኃይልና በድሮን ለመምታት በተደጋጋሚ ተሞክሮ ባይሳካም፣ አሁን ግን እንደ አማራጭ ከሰሜን በሰሜን በኩል የወያኔ ክፋይ የሆነውን TPF በጌታቸው ረዳ እየተመራ ከመከላከያው ጋር በመሆን የዐማራ ፋኖን ለመውጋትና ሽማግሌዎቹን የወያኔ መሪወዎች በክፋዩ የእነ ጌቾ ቡድን ለመተካት እየተሠራ እንደሚገኝም ተሰምቷል። ሽማግሌዎቹ ወያኔዎች ሳት ብሏቸው ሞት የተደገሰለትን ኢሳይያስን ከወዲሁ እንዳያግዙ የአማሪካው አምባሳደር ማሲንጋን መቀሌ ድረስ በመላክ እንዳስጠነቀቋቸውም ተሰምቷል። ጁጁ ሽማግሌዎቹ የወያኔ ሰዎች ከተስማሙ ለውሳኔው ተገዢ ሆነው እሺ ካሉ በፈቀዱት ሀገር ወደ አሜሪካና ወደ አውሮፓ ሄደው እንዲኖሩ ተመቻችቷል። ካልተስማሙ እርምጃ ይወሰድባቸዋል። ይጠረጋሉም ተብሏል። አቢይ አሕመድም ድሮን አለኝ፣ የገባችሁበት ገብቼ እደመስሳችኋለሁ የሚለው ይሄንኑ ታሳቢ አድርጎ ነው የሚሉ መተርጉማንም አሉ። የሆነው ሆኖ ግን አይደለም ነገሩ ሌላ ነው ወያኔዎቹ አቢይን የተጣሉ፣ የተከፋፈሉ፣ የተለያዩ መስለው ሸውደውታል። በራሱ መሳሪያ፣ ታጥቀው፣ ሐራ መሬት በሚሉት ስፍራ ሰፍረው፣ ተዘጋጅተው እነሆ አሁን ይኸው በራያ በኩል ሰተት ብለው መግባት ጀምረዋል። ወያኔ አቢይን ጉድ ሠርታዋለች። ሽማግሌ፣ ጳጳስ ገለመሌ እየላከች አደንዝዛዋለች። እናም የትግራዩ እንኳ አይሳካም የሚሉም አሉ። ብርሃኑ ጁላም አትበጥብጡን መገነጠል ከፈለጋችሁ ጡሩግ በሉ እንጂ አትበጥብጡን። የቀበራችሁትን ታንክ መልሱ፣ መድፍም አስረክቡን እያለ ሲያለቃቅስ የሚታየው ለዚያ ነው የሚሉ አሉ። ትግሬ እንዲህ አንድ ሆኖ ሳለ ጎጃም ያለው የአስረስ መዓረይ ቡድን ግን ጎንደርን፣ ወሎንና ሸዋን አልይ ይላል። ጎጤ።

"…በመጨረሻም በኃያላኑና በአድራሽ ፈረሶቻቸው ተላላኪነት እንደ እነሱ ቀመር ፋኖን አስወግደው ሲያበቁ የዐማራውን ክልል ለአራት ለመከፋፈል መጨረሳቸው ነው የተሰማው። ዐማራው ለአራት ሲከፋፈልም ሰሜን ጎንደር ከደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ ከደቡብ ወሎ፣ ምሥራቅ ጎጃም ከምዕራብና ከሰሜን ጎጃም የሚጣሉበት የድንበር፣ የመሬት፣ የካርታ ፈንጂ አብሮ እንደሚቀበር ነው የሚጠበቀው። ጎጃም ብቻ ከአገው ጋር የሚዋጋበት ካርታ ተዘጋጅቷል። ጎጃምና ጎንደር እንዲሁ ጳጳሳቱ የተሳተፉበት ሁለቱን ሕዝቦች የሚያፋጅ ካርታ መዘጋጀቱ ነው የሚነገረው። የጎንደሩን ፓርት የአማቺዝም ቦለጢቀኞች በኦሮሙማው ሲታገዙ የጎጃሙን ፓርት ደግሞ ብአዴን ራሱና ባለሀብቶች ከውጭ ኃይሎች ጋር እንደሚደግፉት ነው የሚነገረው። ዛሬ ላይ እኔ ስጽፈው ብትደነግጡም፣ ግር ቢላችሁም ሩቅ ባልሆነ ጊዜ የሚፈጸም ስለሆነ መዝግባችሁ አስቀምጡልኝ።

"…በሌላ በኩል፣ የእስራኤሉ መሪ ቤንጃሚን ኔታንያሁና የአማሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጋዛ የሚነሱትን የጋዛ ነዋሪዎች በግብፅ ለማስፈር የወሰኑ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜያዊ እክል እንደገጠማቸው ነው የሚነገረው። ግብፅም ትእዛዝ ደርሷታል ነገር ግን አልቀበልም ማለቷም ተሰምቷል። ግብፅ የጋዛን ተፈናቃዮች ብትቀበል ለግብፅ ወሮታ በግድቡ አጠቃቀም ላይ ኃያላኑ ምቹ ለም መሬት የሆነውን አቢይ አሕመድን አስገዳጅ ውል በማስፈረም፣ ፈርቶ ጫናም በዝቶበት እምቢ አልፈርምም ካለ ደግሞ ግድቡ አገልግሎት እንዳይሰጥ ግብፅ እንድታጨናግፈው በቴክኒክም በመሣሪያም በዲፕሎማሲም ለማገዝ እንዳቀዱ ነው የሚነገረው። የአማሪካው ፕሬዘዳንትም ለሦስተኛ ጊዜ የኢትዮጵያው ግዙፉ ግድብ በአሜሪካ ገንዘብ ነው የተገነባው በማለት ደጋግመው ቢናገሩም ከኢትዮጵያ በኩል ግን አገዛዙ እስከአሁን ምንም ትንፍሽ አላለም። እነርሱ እንዲህ እንዳቀዱ ነው የሚታማው የእግዚአብሔርን ዕቅድ ደግሞ ቆይቶ እናየዋለን።👇 ③✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ከፊታችን በሚመጡት ጥቂት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 7 ዓመታት አጨብጭበን የዘራናቸው የመከራ ዘሮች ኮትኩተን፣ ውኃ እያጠጣን ስላሳደግናቸው አሁን እነዚያ የመከራ ዘመን ዘሮቻችን አብበው፣ ፍሬም አፍርተው ምርቱ ስለደረሰ በሰፊው አጨዳ የምንጀምርበት ዓመት ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል። ይቅሩ ቢባሉም እንኳ የግድ የማይቀሩ ሀገራዊም፣ ቀጠናዊም የትርምስ ሁነቶችም እንዲሁ ከፊታችን ይከሰታሉ ተብሎም ይጠበቃል። ሆኖም ግን አሁን ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ መሄድ አይቻልም። ምነው እንዲህ ባላደረግነ? ምነው ያኔ ነውጡን ለውጥ ብለን ባላበድነ? ምነው ረጋ፣ ሰከን፣ ቆም ብለን ተረጋግተን ነገሮችን ብናይ ኖሮ? ብለው ቢፀፀቱ፣ ደረት ቢደቁ፣ ፀጉር ቢነጩ፣ እንባ በጉንጭ ላይ እንደ ጎርፍ ቢያወርዱ፣ ኡፍፍፍ እያሉ በቁጭት ቁና ቁና ቢተነፍሱ ምንም የሚለወጥ፣ የሚፈጠር ነገር አናመጣም። መጀመሪያ የዘራነውን ማጨድ ይቀድማል። ያንጊዜ ጩኸት ይሆናል የማይጠቅም ጩኸት ነው። ያን ጊዜ ለቅሶ ይሆናል የማይጠቅም ለቅሶ ነው እንዲል መጽሐፍ።

"…ይሄን ርእሰ አንቀጽ የምታነብቡ ሁላችሁ የምጽፈው፣ የምለው ነገር በሙሉ አሳምሮ በደንብ ይገባችኋል። ግለሰባዊም ሆነ ተቋማዊ የጥፋት አጀንዳችሁ ፊት ቆሜ ስለተጋፈጥኳችሁና መሰናክል እንቅፋት፣ ደንቃራም ሆኜ ከፊታችሁ በመጋረጥ ወግሜ መላወሻም፣ መተንፈሻም አሳጥቼ ምሳችሁን የሰጠኋችሁና ወደ ጉሮሮአችሁ በመስደድ ልትውጡት የነበረውን የጥፋት ጮማችሁን ማንቁርታችሁ ላይ ተቀርቅሬ አላስውጥ ያልኳችሁ፣ የጥፋት ሕልማችሁን እንዳትኖሩት እያባነንኩ እንቅልፍ ያሳጣኋችሁ ወገኖችም ቢሆን እየጠላችሁኝ፣ እየሰደባችሁኝም፣ እየረገማችሁኝም ቢሆን የምጽፈውን በፍቅር፣ በጉጉት ታነባላችሁ። ማይም፣ ዴደብ እያላችሁ እየሰደባችሁኝም ፍሮፌሰሮቹም፣ ዶፍተሮቹም፣ ኢንጂነሮቹም፣ ጋዜጠኛና አክ እንትፊስቶቹም የግዳችሁን ታነቡኛላችሁ። የጎንደር ስኳድ የለ፣ የትግሬ ጁንታ፣ የጎጃም ሸንጎ፣ የወሎ ኅብረት፣ የኦሮሞ ነፃ አውጪ የሌ፣ ቦለጢቀኛ ነሽ ካድሬ ታነቡኛላችሁ። እየጠላችሁኝ፣ እየቀፈፍኳችሁ፣ እየሰቀጠጣችሁም ቢሆን በጉጉት ጠብቃችሁ በፍቅር ታነቡኛላችሁ። የምለውም በደንብ  ይገባችኋል አይደል? ዋሸሁ እንዴ…?

"…እኔ ነጋዴ ነኝ። ኢንቨስተር ነኝ። በኢትዮጵያ የሚፈጠረው ነገር አይመለከተኝም ብሎ እስከዛሬ ድረስ ከዳር ቆሞ በትዝብት የሀገርን መከራ ያይ ይመለከት የነበረው፣ በገንዘቡ፣ በሳንቲሙ ተመክቶ ሲያቅራራ፣ ሲኩራራ፣ የጣመ የላመ እየበላ፣ እየጠጣ፣ ገንዘቡን ለሴት፣ ለቪትስ እየረጨ፣ በደሀው ሕዝብ ላይ ለኬጂ ተማሪው ምርቃት ሚልዮን ብር አውጥቶ እየደገሰ ሲያላግጥ የነበረው ነጋዴ ነኝ ባይ በሙሉ አሁን ተራው ደርሶ ደም እንባ የማልቀሻው ሰዓት ደረሰ። መጣ። በዐማራና በኦርቶዶክስ ላይ የደረሰው በደል፣ ግፍና ስቃይ ከቤቱ፣ ከደጃፉ የማይመጣ መስሎት ሀገር ሲያለቅስ ዘጭ ብሎ ተዘልሎ ተቀምጦ የነበረ በሙሉ አሁን ያ ሩቅ የነበረው መከራ ሰተት ብሎ ከክልሉ ገባ። ኢትዮጵያ ሲታመስ እኛ ትግሬዎች ሰላም ነን እያለ ሲያላግጥ የነበረ ትግሬ በሙሉ ደቂቃ ሳይፈጅ ማቅ እንደለበሰው ያለ ማለት ነው። መከራው ከክልልህም አልፎ ከተማህ ደረሰ። በወረዳህ በቀበሌህ፣ በሰፈር መንደርህ አልፎም ከቤትህ፣ ከጓዳህ ገባ። እንደ ዐማራና እንደ ኦርቶዶክሱ በሰይፍ፣ በገጀራ፣ በሜንጫ፣ በጥይት፣ በድሮን መጨፍጨፉ ለነገ በይደር የተያዘልህ፣ የታቀደልህ ቢሆንም አሁን በሀሳብ፣ በጭንቀት፣ በትካዜ በቁምህ ሟምተህ እንድታልቅ እየተደረግክ ነው። እንኳን ደስ ያላችሁ ነጋዴዎች። አይደለም እንዴ? ዋሸሁ እንዴ…?

"…ይሄን ጦማር ይሄን ርእሰ አንቀጽ የምታነብ አንተ፣ አንቺ፣ እርስዎ እውነቱን እንነጋገርና አሁን አላችሁ ይባላል? ጭንቀት ቤትዋን በራሳችሁ፣ በላያችሁ አልሠራችምን? የሰቀቀን ኑሮ አይደለምን የምትኖሩት? ጓዳችሁ፣ መሶባችሁ የሚያስጨንቃችሁ እናቶች ጭንቀታችሁ ይገባኛል። በተለይ ልጆች ያላችሁ የገባችሁበት ጨንቅ በቃላት የሚገለጽም አይደለም። ኪሳችሁ፣ ቦርሳችሁ፣ ባንካችሁ ውስጥ ያለው ሳንቲም ከላዩ ላይ ለቤት ኪራይ፣ ለትምህርት ቤት፣ ለህክምና፣ ለምግብ በወጣ ቁጥር ሙዳ ሙዳ ሥጋ ከላያችሁ ላይ እየተነሣ ለተጓዳኝ በሽታዎች ለእነ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ልብ ድካም የምትዳረጉትንማ ቤት ይቁጠራችሁ። እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ፣ የሕዝብ መከራ ስቃይ አይመለከተኝም፣ አቢይ ሺ ዓመት ይንገሥ ብላችሁ ከዳር ቆማችሁ በታዛቢነት ስትመለከቱ የነበራችሁ በሙሉ አሁን ተራው የእናንተም ሆኖ መከራው በአበባ ታጅቦ መለከት እየነፋ ቤታችሁ በመግባቱ ከእኛ እንደ አንዱ ሆናችሁ ተገኝታችኋል። በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ። ሸሽተህ ኬኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ዱባይና አሜሪካም ብትሄድ እንደ ኢትዮጵያ እንደው አይሆን።

"…ዘንድሮ ጉድ ነው የሚታየው። በተለይ አዲስ አበባን ማየት ነው። የከተማ ራብ ገብቷል። ሰው የሚበላው እየተቸገረ ነው። ከምር ሰቆቃውን ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው። 17 ሺ ያህል ነጋዴዎች ምንም መሥራት፣ መነገድ አልቻልንም ብለው የንግድ ፈቃዳቸውን ለመመለስ የንግድ ፈቃዱን ወደ ሰጣቸው አካል ቢሄዱም "ንግድ ፈቃድ መመለስ አይቻልም" ተብለው ጨርቃቸውን ጥለው ማበድ ነው የቀራቸው። ሥራ ያልሠሩበትን 0 0 የሽያጭ ሪፖርት ቢያቀርቡም ባትሠሩም ቫት፣ ግብር፣ ታክስ መክፈል ግዴታችሁ ነው። ንግድ ፈቃድ አትመልሷትም። ዓምና አንድ ሚልዮን ብር ግብር ከፍላችሁ ዘንድሮ ምንም አልሠራንም እንዴት ይባላል። ክፈሏት፣ ክፈሏት ተብለው ዱብዳ እንደወረደባቸው እየሰማሁ ነው። አቅም ያላቸው ነጋዴዎች ከሀገር እየወጡ መሆኑንም ሰምቻለሁ። ወደ ዱባይ፣ ወደተለያዩ አፍሪካ ሀገራት እና አውሮጳም እየሸሹ መሆናቸውን ሰምቻለሁ። የአቢይ ሽመልስ ቡድን እንደዛተው፣ እንደፎከረው ለማንም የማትመች አዲስ አበባን ፈጥረው በምትኩ ከምዕራቡ ዓለምና ከዓረቦቹ ጋር ለዚህ ሀገር የማውደም፣ ኢትዮጵያን የማድቀቅ ተግባራቸው በሳንቲም የታተመን ዶላር በቦርሳ ቋጥረው አምጥተው ለዲም ላይቱና ለቤተ መንግሥቱ፣ ለመናፈሻው ማሠሪያም ሰጥተው ሕዝብ ማደንዘዣ ሽሮ ፈሰስ ልማት ተብዬንም ገንብተው በቶፕ ቪው የቴዲ ተሾመ ቪድዮ አደንዝዘው እሬቻውን እያበሉት ነው።

"…ታዘብቻሁ ከሆነ ዓረቦቹም፣ ነጮቹም በስፋት በብዛት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው። ሶሪያ ስደተኞች ናቸው የተባሉ አዋሳ፣ ድሬ፣ ሀረር፣ ባህርዳርና ጎንደር ድረስ ሁላ ሄደው እየለመኑ ነው ነው ተብሏል። በአዲስ አበባ አዲስ የባህል አቢዮትም ተፈጥሯል ተብሏል። ከባድ የባህል አቢዮት እየመጣ ነው የሚሉት። የዓረቦቹን በገፍ መግባት ተከትሎ ሀገር ምድሩ በሙሉ ሻወርማ በሻወርማ፣ ዶሮ በዶሮ መሆኑ እየተነገረ ነው። እነ ቋንጣ ፍርፍር፣ እነ ቦዘና ሽሮ ቻዎ። ባይባይ። አስቀድመው የገቡ ሶሪያውያን በቤተ መንግሥት ከሚደረግላቸው የእራት ግብዣ ባሻገር ከኢትዮጵያውያን ዜግነት በላይ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ዘጭ ብለው እየኖሩ ነው ተብሏል። የሳዑዲና የኤምሬትስ ዜጎች ሆነው በኑሮ ደከም ያሉቱ፣ ያልተማሩትና ህመምተኞች መሃይሞቹም ተለቅመው ወደ ኢትዮጵያ የማዘዋወር ሥራ በሰፊው እየተካሄደ ነውም ተብሏል። አቢይ የተባበሩት ኤምሬትስ የንጉሣውያን ቤተሰቦች በጉዲፈቻ ስም የጡት ልጅ ሆኖ በመግባቱ የተባበሩት ኤምሬትስ ሁለተኛ ለም ሀገር በምሥራቅ አፍሪካ እየገዛች ነው። ኢትዮጵያ ለዓረቦች የተሸጠች ያህል መቁጠር ቀሽም አያስብልም። በቲክቶክ፣ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ ዓረቦቹ ማሻ አላህ እያሉ የሚሠሩትን ቪድዮም ማየቱ ብቻም በቂ ነው። የገዛ ዜጎቹን የሚጨፈጭፈው እና ከቦታ ቦታ…👇①✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ጀምረናል…

ገባ ገባ በሉማ…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የርሸና ዜና…

"…የምሬ ወዳጆን ቀኝ እጅ የአፋብኃ ሚኒልክ ዕዝ ቃል አቀባይ የሆነውን የአበበ ፈንታውን አባት፣ አባ ፈንታው ደርበውን ዛሬ ሐምሌ 20/2017 ዓም በሰሜን ወሎ በቆቦ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥርዓተ ቅዳሴ ጸሎት ላይ እያሉ ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ ጠቅጥቀው በገቡና የሌላ እምነት ተከታይ በሆኑ በአገዛዙ የወርቄ ሚሊሻዎች አባ ፈንታውን በቅዳሴው ላይ በነበሩ ምእመናንና በካህናቱ፣ በአዛውንትና በሕፃናቱ፣ በወጣቶችም ፊት ረሽነዋቸው ወጥተዋል። ነገርየው የሃይማኖት ጦርነት ለማስነሣትም የፈለጉ ይመስላል።

"…ዝርዝር ሁኔታውን በምሽት የዘመድ ቲቪ "በነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" ሳምንታዊ የቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት መርሐ ግብራችን ላይ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።

"…ለሟች ለአርበኛ አበበ ፈንታው አባት እረፍተ ነፍስ ይስጥልን ለአርበኛውና ለመላ ቤተሰቡ ፈጣሪ መጽናናትን ይስጣቸው።

• ዝርዝሩን ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ ይጠብቁን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው። መዝ 132 ፥ 8-9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…፬

"…ለዚህ ዥዋዥዌ፣ ቢራቢሮ፣ ፌንጣ፣ አይጨበጤ፣ ዓሣ፣ የተልባ ስፍር ለሆነ ሶዬ…  እስቲ ተጠልዞ ደግሞ ዳግም ዓይኑን በጨው ታጥቦ እስኪመለስና ሾርት ሚሞሪያሙን ፒፕል አንጀት ጉበት እየበላ እስኪዘርፈው ድረስ ለዛሬ ወደ ሃዲግ ኦዴድ ብልግና መሄዱ ነውና እንዲያው የመሰናበቻ አንዲት ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነች ግጥም ግጠሙለት… ባናታቹ፣ ባባታቹ…

• ጢሙ ግን ሙንኡኖ ኖ የመማርን እጅ የመሰለው?

• ግጠሙለት…

ተቀበል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…፪

• ሲጀምር ውሸት ነው…😂

"…ጮቄ ላይ ያለሁት እኔ ዘመዴ ነኝ። ፓስተር ዳዊት መሐሪ አትዋሽ።

"…የሚገርመው ግን… አስረስ መዓረይ ነው። መዓረይ ምን አለ? ጄነራል መሀመድ ተሰማ ከእስልምና ወደ ጴንጤነት ተቀየረ ብሎ ሲበጠረቅ ይታያል። ፓስተር ዳዊት መሐሪን አጠገቡ አስቀምጦ እኮ ነው በመሀመድ ተሰማ የሚደመመው። ሃስመሳይ…

"…ፓስተር ዳዊት መሀሪ አባቱ ከአቢይ አሕመድ ጋር እሁድ እሁድ አብሮ የሚያመል ጴንጤ ነው። ፓስተር ዳዊት መሀሪም በአባቱ አቅራቢነት ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች የወጣት ካውንስል ፕሬዘዳንትነት ከታጨ በኋላ እስከአሁን ነገሩ ግልፅ ባለሆነ መንገድ የጴንጤ ወጣቶች ፕሬዘዳንትነት ዕጩ የሥልጣን ሓሳቡ ተቀይሮ ወደ ጎጃም በመሄድ እነ አርበኛ ዘመነ ካሤንን እና አስረስ መዓረይን እንዲቀላቀል ተደረገ። ከዚያ ያው እንግዲህ በአዲሱ አስተሳሰብ መሠረት ስንቱ የጎጃም ዐማራ ነፍስ ነፍስ ያለው ባለ ማዕተብ ፋኖ እንዲወገድ እንዲጸዳ ተደረገ። ጴንጤው ፓስተር ዳዊት አይተኩስም፣ አይዋጋም፣ አይገድልም። ግን የሞቱ ጀግና የተዋሕዶ ልጆችን አስከሬን ሲቆጥር ይኖራል።

"…ትግሉን የተሸከመው ድርጅታችን አዲሱ አስተሳሰብ ላይ የተጣበቀውን ሰንኮፍ አስወግዶ፣ በአዲሱ ትውልድ ውስጥ ሰርጎ የተገኘውን ቆሻሻ አራግፎ እና አዲሱን አማራዊ ዕጣ ፈንታ እና ተስፋ ሊያደበዘዝ እና ሊጋርድ የሞከረውን የውጭ እና የውስጥ ጥገኛ አቆርቋዥ በማስወገድ አጥርቶ ለማየት ቆርጦ ተነስቷል።" ፓስተር ዳዊት ነው እንዲህ የሚለው።

"…የማይተኩሱ ነገር ግን ጎጃም ገብተው ሥልጣን ይዘው የጎጃም ዐማራን ፍዳውን የሚያበሉት ፓስተሮች አሉ። እስር ቤት ሆነው ጎጃምን፣ ጎንደርን እና ሸዋን ሸብበው ያሠሩ ፓስተሮች አሉ። ስደት ወጥተናል ብለው አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛና ቦለጢቃ ተንታኝ የሆኑ ፓስተሪትና ፓስተሮች አሉ። የሚያልቁት፣ የሚጸዱት ግን ባለማዕተብ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው። በተለይ የጎጃም ፋኖ ትግል ከምር በጣም ነው የሚያሳዝነኝ። ሌላ ቦታ የሚያስተምሩ የነበሩ የጎጃም ተወላጅ መምህራን በክረምት ወደ ጎጃም ሄደው በእረፍት ቤተሰቦቻቸውን መጠየቅ አልቻሉም። ደቡብ ጎንደርና ጎጃም ውስጥ መታወቂያህ መምህር የሚል ከሆነ ፋኖ ነኝ ባዩ ነው አጋድሞ የሚያርድህ።

"…በጎጃም ትግሉ እንዲያልቅ አይፈልጉም አመራሮቹ። ባለ መኪና፣ ባለ ቪላ ናቸው ባሕርዳርና አዲስ አበባ ኡጋንዳ። ጦርነቱ በጊዜ ካለቀ ባዶ እጃችንን ነው የምንቀረው በማለት ሽቀላ ላይ ናቸው። እጅ እንኳ ብንሰጥ፣ ድርድር ቢኖር እንኳ መጦሪያችንን ይዘን መሆን አለበት ነው የሚሉት አሉ። የደሀ ልጆችን ማግደህ፣ አስጨፍጭፈህ ስታበቃ አንተ ዘና ብለህ ዓለምህን ልትቀጭ?

• ለማንኛውም ጮቄ ያለሁት እኔ ዘመዴ ነኝ። ሥነ ሥርዓት ግብረ አይተ ፓስተር ወዲ መሐሪ። 😁

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…

"…ውድ የእኔ የዘመዴ ነጭ ነጯን በቴሌግራም ተከታታዮች በሙሉ ለጥቂት ወራት አቋርጠነው የነበረውን የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል የግጥም መርሀ ግብራችንን ለዛሬ ብናስኬደው ምን ይለናል?

• ግጥም እንደ ጉድ ቢገጠምስ?

• ነቆራ በየዓይነቱ ቢዥጎደጎድስ?

• መራር ሃቆችን እንደ ጉድ ብንጋትስ?

• ቅኔም እንደ ጅረት ቢፈስስ?

• ለምን? እንዴት? ወዴት? መቼ? እያሉ መጠየቅ መቸም የዚህ ቤት ልማድ እንደሆነ በሁሉ ዘንድ የታወቀ የተረዳ ነው።

• እናም በሚያስቀው እየሳቅን፣ በሚያስለቅሰውም እያለቀስን፣ በሚያበሳጨው እየበሰጨን፣ አንጀታችንን እያኮማተርን፣ ጨጓራችንን እየላጥን፣ ደማችንን እያፈላን፣ እየተንገበገብን፣ እየቆሰልን፣ ግድግዳ በቡጢም እየነረትን፣ በተስፋም እየተሞላን፣ አንዴ የበጋ ፀሐይ፣ ደግሞ ደመና ፊት እየመሰልን እስከምሽት አብረን አብረን ብንዘልቅስ…? እንዘልቃለን።

• ማስጠንቀቂያ፦

"…በዚህ ቤት ውስጥ ገብቶ ክፍት አፍ ጋለሞታ፣ ስድአደግ ባለጌ፣ ከርእሱ ጋር የማይገናኝ አጀንዳ አስቀያሽ ጎጋ መንጋ ሁሉ ያለምህረት ብሎክ፣ ባን በተባለ ሰይፍ ይቀሰፋል።

• እናንተም ጋር ያለ አስቂኝ ቪድዮ፣ ፎቶ ካለ ላኩ።✍✍

• የምትገጥሙበትን፣ የምትቀኙበትን ርእስ ልለጥፍላችሁ እና ይጀመር አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ። መዝ 106፥1

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:30 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ZemedTv 👉 https://zemedtv.com/live.html

• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1mrGmPyYlLgKy


• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6wmkl6--zemede-july-24-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a

• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
                      11977 H 27500
• ላይ ይከታተሉን።

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia

👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

• መቶ አለቃው ለምን ለመንግሥት እጁን ሰጠ…?

"…በጎንደር እነ ፀዳሉ እነ ቆራጡ፣ በወሎም፣ በሸዋም ባንዳ ፋኖዎች ለአገዛዙ እጅ ሲሰጡ የአፋጎ አክቲቪስት ነን ባዮች ግን ይሄንን ሁኔታ ከጎጃም እጅ የሚሰጥ እንደሌለና ሌላውን ግን እንደከሃዲ፣ እንደማይችል አድርገው ሲኩራሩበት፣ በየቲክቶኩም እኛ እኮ እያሉ ሌሎችን እንደ ማብሸቂያ ሲጠቀሙበት እና ቦለጢቃም ሲሠሩበት ይታያል። በፍጹም ይሄ ልክ አይደለም።

"…በትናንት ምሽቱ ልጥፌ ላይ የአፋጎን አክቲቪስቶች መልስ አዘጋጅታችሁልኝ እደሩ…! በማለት በሙስናም፣ በባንዳነትም የማይታማው፣ ቆራጡ ጀግና የበላይ ዘለቀ ልጅ የዐማራ ፋኖ በጎጃም የደጋ ዳሞት ቀጠና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ቀኝ እጅ የነበረው መቶ አለቃ ላቃቸው አንለይ በዐማራ ክልል ብአዴንን አላምን ብሎ ዓባይን ተሻግሮ አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ እያዘነ፣ እያለቀሰ ለምን ለአገዛዙ እጁን ሰጠ?

"…የአፋጎ የፌስቡክ፣ የቲክቶክ፣ የቴሌግራምና የዩቲዩብ አክቲቪስቶች ከጎንደር ጸዳሉ፣ ከሸዋ ከወሎ እገሌ እጁን ሰጠ። ጎጃም ግን እያሉ የሌለ የተለየ ምሥል ለራስ ከመስጠት በቀር እንዲህ ዓይነቱን ጉዳይ አይደፍሩትም። በሉ ተንፍሱ። አፋጎ ከወሬና ከፎቶ የዘለለ ሪፎርም ካላደረገ መጪ ጊዜው ከባድ ነው የሚሆንበት። ህመሙን፣ በሽታውን ዘርዝሮ፣ በድፍረት ለሀኪም ያልተናገረ መድኃኒት አያገኝም። አይፈወስም። አይድንምም። ፎቶም፣ ዶክመንተሪም፣ ፉከራና ሽለላ፣ ሰበካና ቀርቶ የማይደብቋቸው እውነቶች መገለጣቸው እንደሁ አይቀርም።

"…ነገ በጠዋት 1ሺ ሰው አመስግኖ ከጨረሰ በኋላ ይሄንና ይሄን የመሳሰለውን አንሥተን እንወያያለን።ደኅና እደሩልኝ የነገ ሰው ይበለን። ዘመዴ ነኝ ከዚያው ከጮቄ ተራራ… በማለት ነበር የተለያየነው። መሸ ነጋ አርፍጄም ተነሣሁ አመስጋኙም 1ሺ ሞላ። እናም እነሱ የጻፉትን በኮፒ፣ የእኔን ደግሞ በአጭሩ ላስቀምጥ መጣሁ።

"…በዚህ በአጭሩ ጊዜ የዐማራ ፋኖ ትግል በተለይ በጎጃም ፋኖ ትግል ውስጥ እንደ መቶ አለቃ ላቃቸው የደጋ ዳሞት ቀጠና ዘመቻ መምሪያ ያለ ደጋ ዳሞትን፣ ቋሪት፣ ከሰከላ እስከ ቡሬ ጠላትን እንደ ቅጠል ሲያረግፍ የነበረ የጦር መሪና አዋጊ አልታየም ነው የሚባለው። ታዲያ መቶ አለቃ በሙስና፣ በባንዳነት፣ በአቅም ማነስ፣ በግልሙትና የማይጠረጠረው ጀግና ምን ቢሆን ነው ጎጃም ውስጥ ማንንም አምኜ እጄን ለመከላከያም፣ ለብአዴንም አልሰጥም በማለት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ እጁን ለአገዛዙ የሰጠው? መቶ አለቃ ላቃቸው ምክንያቱ ምንድነው? ጠይቄ ነበር። ከብዙዎቹ ተቀራራቢና ተመሳሳይ የሆነውን የበለጠውን አቅርቤላችኋለሁ። ተቃዋሚ ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ።

• መቶ አለቃ ላቃቸው እጅ የሰጠበት ምክንያት፦

"…ከወራት በፊት ኬላ ላይ በነበረው የደጋ ዳሞት እና የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ መካከል ግጭት ይፈጠራል። እናም ከዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ አባላቶች እና ከዋሸራ ሕዝብ፣ በደጋ ዳሞት ብርጌድ ጦር አማካኝነት መመታታቸውም ይመታታሉ። ጥቂት ፋኖዎችም ይሰዋሉ። ከዚያም ሽማግሌ ጣልቃ ይገባና ግጭቱ በርዶ ጉዳዩም በሀገር ሽማግሌ ይይዛል። ያነዜ ትእዛዙን የሰጠው ማለትም የደጋ ዳሞት ጦር እርምጃ እንዲወስድ ያዘዘው ሻለቃ ዝናቡ ነበር። ሻለቃ ዝናቡ ዝናቡ ለላቃቸዉ ትእዛዝ ሰጠ፣ ላቃቸውም የሺአለቆችን አዘዘ፣ ነገር ግን ጉዳዩ ሲጦዝ እና የዋሸራ (ዮሐንስ አለማየሁ ) ጦር ሲያምፅ፣ ሕዝቡም ሆ ብሎ ሲነሣ፣ ሻለቃ ዝናቡ እኔ ትእዛዝ አልሰጠሁም ብሎ ይክዳል። በመሃል ላቃቸውን የጦስ ዶሮ ለማድረግ የእስር ትእዛዝ ሲያወጣበት ሌሎቹ ጓዶቼ እንደተበሉ እኔንም ሊበሉኝ ነው በማለት አመለጠ። አመለጠናም ዓባይን ተሻግሮ፣ አዲስ አበባ ድረስ ሂዶ እጁን ለአገዛዙ ያደረግከውን አድርገኝ በማለት እጁን ሰጠ። ይሄ ነው እውነታው። እውነቱን ደግሞ ሕዝብም ጦሩም ያውቀዋል ነው ነው የሚሉኝ።

"…የላቃቸውን በዚህ እናበቃና የሌሎች ጀግና የጎጃም ልጆች እንዴት በሴራ፣ በዘዴ እንደሚመቱ፣ እንደሚወገዱ በተከታታይ እናያለን። እንመለከታለን። አሁን ደስ የሚለው ጦሩ አምርሯል። አርበኛ ዘመነ ካሤ ወይ አስተካክሎ ይምራን፣ አልያም ቁርጡን ይንገረንና እሱም በእነ አስረስና በእነ ማርሸት ሥር ነኝ። ምንም ልረዳችሁ አልችልም ብሎ ይንገረንና በይፋ መወሰን ያለብንን እንወስን በማለት ላይ ናቸው። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…በነገራችን ላይ የአስረስ መዓረይ ቡድን እጁ ረጅም ነው። የለንደን ፋኖን ባህር ተሻግሮ አንቆ የያዘውም ይኸው የእነ አስረስ መዓረይ ቡድን ነበር። ስለሺ ከበደ የዐፋጎ አመራር ነው። ወንድሙ ግርማ ከበደ ደግሞ በእንግሊዝ የዐማራ ፋኖ አስተባባሪ ነው። የለንደን ፋኖ ሰልፍ ወጥቶ ደብዳቤ ለእንግሊዝ መንግሥት የሚያስገባው በግርማ በኩል ነው። እናም የለንደን ፋኖ ይጠይቃል። ግርማ እንግሊዝ ምን አለች? ግርማም ምንም አላለች። እስከአሁን ኢሜል እየጠበቅኩ ነው ይላላቸዋል አሉ። በቀደም ግን ግርማን ጥለው የለንደን ፋኖዎች በራሳቸው በቀጥታ ሰልፍ አድርገው፣ በራሳቸው ኢሜል መልሱን ስጡን ብለው ጠየቁ። የእንግሊዝ መንግሥትም በፍጥነት መልሱን መለሰላቸው። እናም ተገረሙ። ተደነቁ። የእንግሊዝ መንግሥት የፋኖ መሪ ብሎ ለካስ የሚያውቀው አርበኛ ዘመነ ካሤን እንኳ አይደለም አሉ። ማን ቢሆን ጥሩ ነው? አስረስ መዓረይ…! ጉድ እኮ ነው።

"…የለንደን ፋኖ እሁድ በነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር ቀርበው ይመረመራሉ። ቃላቸውንም በይፋ ለሕዝብ ይሰጣሉ። የአውሮጳው ሴራ ፈርሷል። የኢትዮጵያውም ይፈርሳል። አርበኛ ዘመነ ካሤ ግን መፍጠን አለበት። ካልፈጠነ ታሪኩ ይበላሻል። የምታገኙት ንገሩት። በግዞት ካለም ይተንፍሰው። ይተንፍሰውና ሠራዊቱም፣ ሕዝቡም ነፃ ያውጣው። አሊያ ግን ሲቆይ በሴራው ውስጥ ዘመነም አለበት ብሎ ሠራዊቱም፣ ሕዝቡም ራሱንም መክሰስ ይጀምራል። የጎጃም እናቶችም ምርቃታቸውን ትተው ዘመነ ካሤ ልጆቻችንን አስጨረሰብን ወደሚል እርግማን ይዞሩበታል። ዘሜ ፍጠን።

• ሙስና ተፀያፊው፣ ጀግና አዋጊው መቶ አለቃ ላቃቸው ምርር ብሎት ለአገዛዙ አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ እጅ የሰጠበት ምክንያቱ ይሄ ነው።

አንድ ሁለት ሦስት አራት
እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ
አምስት ስድስት ሰባት
እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ
ለብልቦ፣ ለብልቦ፣ አቃጥሎ ፈጃችሁ።

"…ዛሬም በአዊ በኩል የተወሰነ ኃይል እጁን ሰጠ እየተባለ ብልፅግና ፕሮፓጋንዳ እየሠራ ነው። ጎጃም ካልፈጠነ። ልዩነትን አቻችሎ፣ ወሬኛን፣ ጎጠኛን፣ ብአዴንና አፍቃሬ ወያኔን አርቆ በጀግና ልጆቹ እየተመራ ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ወንድሞቹ ጋር በመምከር ወደ አንድነቱ ካልመጣ እነ አስረስ ያፈርሱታል። የፎቶ ቦለጢቃ መሬት ላይ አይዋጋም። የፎቶ ብሮባጋንዳ ውጭ ያሉትን የወሬ ሱስ ይቆርጥ ይሆናል እንጂ መሬት ላይ ምንም አይፈይድም።

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ሉቃ 12፥ 1-2 “…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።” ሉቃ 8፥17

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አዲስ አበባ ዛሬ…!

"…የእነ ቶሎቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ…

"…ይሄ ዛሬ በአዲስ አበባ የተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ ነው ተብሏል። እንግዲህ ዋናው ክረምት ሳይገባ ከወዲሁ በሐምሌ አጋማሽ እንዲህ ከሆነ ዋናው ክረምት ነሐሴ ሲመጣና እስከ መስከረም ጥቅምትም ድረስ የሚቆየው የዝናብ ወቅት ሲመጣ እንዴት ሊኮን ነው? እኔ በዘመዴ በዕድሜዬ፣ በዘመኔ በአዲስ አበባ እንዲህ ዓይነት የባንግላዲሽን የጎርፍ መጥለቅለቅ የመሰለ የአዲስ አበባን መጥለቅለቅ አላየሁም።

"…ቤት አፍረሶ፣ መንደር አውድሞ፣ ከተማን ከሰው ንኪኪ ሙልጭ አድርገህ ስታበቃ የውኃ መፍሰሻ ቦይ እንኳ በአግባቡ ሳይትሠራ ሳር እና አበባ ዛፍም ብቻ በመትከል፣ የብሽኪሊሌት መንገድ በቀይ ቀለም በመቀባት በማሳማር፣ ዙሪያ ገባውን ዛፍ ግድግዳውን፣ ሕንፃና ቤቱን በሙሉ ቀለም በቀለም ቀብተህ በማሳመር፣ በዲምላይት በቡና ቤት መብራት ሀገር ምድሩን፣ በማስጌጥ ምሽት ብቻ በቶፕ ቪው ቀረጻ ያበደ ቪድዮ በመልቀው ሰው አልባ ልማት አመጣን ብሎ ብቻ መደስኮር ትክክል አይደለም።

"…እንዲህ ስንት ቢልዮን ብር የወጣበት፣ ዶላር የፈሰሰበት፣ የእነ ቶሎቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ ልማት ያለ ዕቅድ፣ ያለ ፕላን፣ በአዳነች አበቤና በዣንጥራር ዓባይ፣ በአቢይ አሕመድ ምህንድስና ዕውቀት ተገንብቶ በደቂቃዎች ውስጥ እንዲህ ውኃ ሲበላው ማየት መጣም፣ መጣም ያሳዝናል…! ደግነቱ ንብረት ይተካል እንኳንም የሰው ሕይወት አልጠፋ። 🙏

• ሰንበት ተሽሮ፣ በዚያ ላይ ጳጉሜን ከካላንደር ስትወጣ ደግሞ ማየት ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል። ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም። እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።”  ዮሐ 16፥ 20-23


"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ✍✍✍ "…ከዚህ ቀደም በሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በውጭ ያለው ዲያስጶራ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ሆ ብሎ በመውጣት ነበር ለሀገሩ የሚሞግተው። ኦሮሙማው አቢይ አሕመድ፣ ያንን ኃይል ስብሃት ነጋን ፈትቶ ጃስ ብሎ በመልቀቅ ቀንዱን ሰብሮ፣ አከርካሪውን አንክቶ፣ ወገቡን ቆርጦ፣ ቅስሙን፣ ሐሞቱንና ጅስሙን ሳይቀር አፍስሶ ሽባ አድርጎ አስቀምጦታል። እነ ታማኝ በየነ፣ እነ ነአምን ዘለቀ፣ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ አሁን የሉም። አሜሪካ እጅሽን ከኢትዮጵያ ላይ አንሺ ሲሉ የነበሩ ሁሉ አሁን የሉም። ከኦህዴድ ብልጽግና ኦሮሞ በቀር ትግሬና የኦነግ ኦሮሞ በፊትም በዚህ ጉዳይ አልነበሩምና አይጠቀሱም። የዐማራው ኤሊት ነበር አንደኛ አሁን እሱም ገሚሱ ብላክ ሜል ተደርጎ፣ ገሚሱ እንደ ማስቲካ፣ እንደ ሸንኮራ ተመጥጦ ታኝኮ ተተፍቶ ወደ ጋርቤጅ ተጥሎ ድራሹ ጠፍቷል።

"…በአሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪዎቹ፣ ነጩን ቤተ መንግሥት በሰላማዊ ሰልፍ አጥለቅላቂዎቹ፣ በየሴናተሮቹ ቢሮ፣ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ቢሮ ተግተልትለው በመግባት ዋይ ዋይ በማለት ለአቢይ ጥብቅና ይቆሙ የነበሩት የውጪው ሲኖዶስ አባላት የነበሩት ጳጳሳትም ዘንድሮ ገሚሶቹን አቢይ አህመድ ስሜታቸውንና መንፈሳቸውን በቆመጥ አንክቶ አንክቶ ሽባ አድርጎ ስላስቀመጣቸው የሉም። በዚያ ላይ አብዛኞቹ አሜሪካዊ ዜግነት ስላላቸው ከአሜሪካ ጥቅም በተቃራኒ መቆም ደግሞ በዘመነ ትራምፕ እንኳን ለአቡነ ጴጥሮስ፣ ለእነ ዲያቆን፣ ቄስ እከሌ ይቅርና የትራምፕ አስተዳደርን በመቶ ሚልዮን  የሚቆጠር ዶላር ከኪሱ ሆጭ አድርጎ ያስመረጠውን ቱጃሩን ኤለን ማስክን አላርፍ ካልክ እና በአስተዳደሬ ጣልቃ የምትገባ ከሆነ ወደ ደቡብ አፍሪካ ነው ዲፖርት የማደርግህ ብለው በድፍረት፣ በአደባባይ ሲናገሩ ስለተደመጡ የሚደፍሩም አይመስልም። በፊት በአቢይ አሽከርነታቸው፣ በአማቺዝም ቦለጢቃ፣ የባልደራስን ጠጅ፣ የጊርጊሮን ቁርጥ፣ ሶደሬና ላንጋኖ ከሸመረን ጋር ለመዳራት ሲሉ ደጋፊ የነበሩቱ ሁላ አሁን ወፍ። ወፍ የለም አልኳችሁ።

"…የሕዝብ ድጋፍ በነበረ ጊዜ ትራንፕን በኖቤል ሽልማቱ የተቸው አቢይ አሕመድ፣ በጁንታው ጦርነት ወቅት ሲደነፋ የነበረው አቢይ አሕመድ፣ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳይ ትራንፕ ለአቢይ ደውሎ አቢይን ሲያስፈራራው አቢይም "ከማን ሀገር መሪ ጋር እየተነጋገርክ እንደሆነ አታውቅም እንዴ? እንከባበር፣ ትእግስታችንን አታስጨርሱን" በማለት ትራንፕ ላይ ስልኩን ከጆሮው ላይ ጠርቅሞ ነው ያሳፈረው። ብሎ ሌንጮ የነገረንን አስታውሰን አሁን ትራምፕ ሦስት ጊዜ አደባባይ ወጥተው "ግድቡ የተሠራው በአሜሪካ ገንዘብ ነው" ብለው በድፍረት ሲናገሩ ኦሮሞዎቹ ባለ ሥልጣናት ባጫን ያየ ከአሜሪካ አይሳፈጥምና ቢያንስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መሥሪያ ቤት የፈረደበት አንዱ ዐማራ ወጥቶ የሆነ ነገር እንዲናገር እንኳ ለምን እንዳልተደረገ እስከአሁን አልታወቀም። የሩሲያ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ ሲመጡ የሚቀበሏቸው ዐማሮቹ ደመቀ መኮንን እና አገኘሁ ተሻገር ነበሩ። አይ ኦሮሙማ ማጣቆር ሲችልበት እኮ ለጉድ ነው። አሜሪካኑ ሲመጡ ደግሞ አቢይ አሕመድ።

"…ለማንኛውም የዛሬውን ርእሰ አንቀጽ ስንቋጨው። የዘራነውን በግድ እናጭዳታለን። ቀለም የተቀቡ የሞመስሉትንና የክረምቱ ዝናብ ጠርጎ የወሰዳቸውን አስፓልቶች ለብ ለብ አድርገን፣ በተሠሩት መናፈሻዎች አየር እየተመገብን መቆየት ግድ ነው። ነጋዴው በተራው የሚያለቅስበት ዘመን ነው። ንግድ ፈቃድ ለመመለስ እንኳ የማይቻልበት ዘመን ነው የመጣው። ያልሠራህበትን የግድህን ትከፍላታለህ። የኦሮሞ ኤሊቶች የሰሙትን እንጃ አቢይ ከወደቀ በኋላ ምን እናድርግ ብለው ምክክር ይዘዋል። የአቢይ አሕመድ አገዛዝ በራሱ መገርሰሱ አይቀርም። ትግሬ አንድ ሆኖ፣ ኦሮሞ አንድ ሆኖ፣ ጎጃም ያለው የእነ አስረስ መዓረይ ቡድን ብቻ በጎጡ ተወሽቆ ዐማራን አንድ እንዳይሆን አድርጎም የመከራ ዘመኑን አባሰበት፣ አስረዘመበትም እንጂ የአቢይ አሕመድ አገዛዝ መውደቁ እንደሁ አይቀርም። ክረምቱም በዐማራ ፋኖ በጎጃም ጎጠኞች ምክንያት ተጋምሷል። ክረምቱም በከንቱ በዋልፈሰስ እንዲያልፍ ያደረጉት እነ አስረስ መዓረይም አሁን አሁን ደግሞ ወደ ሚዲያ ቀርበው አንድነት፣ አንድነት፣ የዐማራ አንድነት እያሉም በኃይለኛው እየለፈፉም ነው። የሆነው ሆኖ የአቢይ አሕመድ አገዛዝ መውደቁ አይቀርም።

"…ታላቁ ጎጃም፣ መለኛው ጎጃም፣ መሠሪውን፣ የትግሬ ጁንታ ቫይረስ ተሸካሚዎቹን፣ ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ሃይማኖት፣ ፀረ ዐማራ የሆኑትን መሰሪ ቅጥረኞች ነፍሰ ገዳይ ዐማራንም ጎጃምንም አዋራጆቹን አቶ ጠበቃ፣ ሞላጫ አፈ ጮሌ አስረስ መዓረይን እና ሰካራም፣ የዐማራን ሕዝብ፣ ታሉቁን ጎጃምን የማይመጥነውን፣ ዋሾ፣ ቀጣፊውን ማርሸት ፀሐዩን ገምግሞ ካልተስተካከለ በቀር አደጋው የከፋ ነው የሚሆነው። በሞዓ ተዋሕዶ ስም መሸቀጥ አይቻልም። አርበኛ ዘመነ ካሤም በቶሎ ካልቀደማቸው ምንአለ ዘመድኩን በሉኝ ይበሉታል። የዐማራ ፋኖ በጎጃም በተለይ እኔ ባወጣሁት መረጃ፣ ሰነድ ዙሪያ ለማወያየት ወደ ሠራዊቱ የተላኩትን አመራሮች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሆኔታ ወደ ዐማራ አንድነት ካልተመለስን የራሳችንን አማራጭ እንጠቀማለን በማለት የአፋጎ ሠራዊት ያሳየው አቋም በደስታ እንድዋጥ አድርጎኛል።

"…አረቄያሙ፣ ጎጃምን አንገት ያስደፋው አዋራጁ ማርሸት ፀሐዩም ወግ ደርሶት እንዲያወያይ የተላከው ወደ 5ኛ ክፍለ ጦርን ነበር። ውይይቱ እንደተጀመረ ማርሸት ፀሐዩ አፋብኃ የፈረሰው በሞዐ ተዋሕዶ ነው ብሎ ገና መናገር ሲጀምር ሠራዊቱም፣ አመራሩም ዝምበል፣ ቁጭ በል፣ የምን ሞዐ ተዋሕዶ ነው? ፀረ አንድነቶቹም፣ አንድነቱን ያፈረሳችሁትም አንተና አስረስ ናችሁ። እናንተ እያላችሁ አንድነቱም አይመጣም። ስለዚህ አንተ አትሰበስበንም፣ አታወያየንም በማለት ስብሰባውን በትነው እነ ማርሸትን ውኃ ገብታ የወጣች አይጥ አስመለዋቸው ሸኝተዋቸዋል መባልን ሰምቼ ውስጤ ሐሴትን ተሞልቶ መዋል ማደሩን ስነግራችሁ በደስታም በኩራትም ነው። ለዚህ ነው አስረስንና ማርሸትን ለማዳን እነ መዓዚ መሀመድ፣ እነ መሳይ መኮንን፣ እነ በላይ ማናዬና ኢትዮ ፎረም፣ ማሪትን ፕላውት ጭምር ሲንበጫበጩ የሚታዩት። ጎጃም አምርሯል። ስለጎንደር፣ ስለሸዋ፣ ስለወሎም ወንድሞቻችን አትነግሩንም ብለው አሳፍረው መልሰዋቸዋል መባልን ነው የሰማሁት።

"…የጎጃም ዐማሮችም ሆኑ የዐማራ ፋኖ በጎጃሞች  ድርጅታቸውንም የድርጅታቸውን መሪ ዓርማ ምልክት የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሤን ዐውቆ ፈቅዶ ካልሆነ በቀር በእነዚህ ትብታቦች ከታሰረበት የይሉኝታ እስር ቤት ነፃ እንዲያወጡት ድምጼን ከፍ አድርጌም እጠይቃለሁ።

• አፋጎ እ…ም…ጷ…!

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ✍✍✍ …መንቀሳቀስን ዝግ ያደረገው የአቢይ አሕመድ አገዛዝ አረቦቹን "ይህ የእናንተ ሀገር ነው እንደፈለጋችሁ ተዝናንታችሁ ኑሩ" የሚልበትን ቪድዮ በቀደም አረቦቹ ለጥፈውት እያየሁ ነበር። እናም ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ረመጥ፣ እሳት እየሆነች እንደመጣች እያየን ነው።

"…ቻይኖች እንኳ የሚያበላው ጴንጤነት ነው። መንግሥቱ አገዛዙም ኦሮሞ ጴንጤ ነው በማለት ፓስተር ሁላ እስከመሆን መድረሳቸው ነው የሚነገረው። የደቡብ ሕዝብማ መጫወቻ ነው የሆነው አሉ። ሕዝቤ ሲርበው የግዱን ኢየሱሴ እያለ ለራቡ ማስታገሻ እንደ ፌንጣ እየዘለለ ባዶ አንጀቱን እየበጠበጠው ነው የሚሉም አሉ። የፊልም ሥራ የቀዘቀዘባቸው አርቲስቶች፣ ቲክቶከሮች ሳይቀሩ በብዛት ወደ አዳራሽ እየተመሙ ነው አሉኝ። ቻይኖቹ እንኳን ሙድ ሲይዙ ነው የገረመኝ። ሙስና ጥርስና ጥፍር አብቅሎ አፍጥጦ ነው የሚታየው ተብሏል። የሚገርመው ደግሞ አብዛኛው ባለ ሥልጣን ጴንጤ በሆነበት፣ የጌታ ልጅ፣ የኢየሱስ ልጆች ነን በሚሉበት ዘመን ኢትዮጵያ ረድኤት በረከት አጥታ፣ ቀልቧም፣ ቆሌዋም ተገፍፎ ዐመዳም፣ ግራጫ መሆኗን እያነሱ ይገረማሉ። አንድ ፓስተርም በዚህ ጉዳይ በእኛ በጴንጤዎች ዘመን እንዲህ መዋረዳችን አንገቴን አስደፍቶኛል ሲልም ሰምቼዋለሁ። ቻይና እንኳ ጴንጤ ሆኖ ሙድ ሲይዝብን። የፈጣሪ ያለህ።

"…ኦሮሚያ ደግሞ ይብሳል። የኦሮሚያው ግን እንዴት ይነገር? ማን ደፍሮ ያውራው እንጂ፣ ማውራቱም እንደ ውርደት፣ እንደ ሽንፈት ስለሚቆጠር ፈርተው፣ አፍረው ተፋፍረው ነው እንጂ የኦሮሚያው ደግሞ ከሁሉም ይከፋል ነው የሚባለው። የኦሮሞ ወጣት የተባለ በሙሉ ስደት ላይ ነው። በየመንና በሳዑዲ በረሃዎች የላስቲክ ቤት ሠርቶ እየሠፈረ ነው። ከባህር መስጠም፣ ከየመን ጦርነት ያመለጠው፣ በራብ፣ በመደፈር፣ በመገረፍ፣ ፍዳውን አይቶ እዚያ በረሃ የደረሰው በሙሉ በከባድ መሣሪያ አረቡ አፈር ከደቼ እያበላው ነው። መሬቱን ለአረብ ለቅቆ አረብ ሀገር ሄዶ ይታረዳል። እኔ ቪዲዮዎቻቸውን ስለማይ አብረው የትግሬና የዐማራ ስደተኞች ቢኖሩም የኦሮሞው ግን ነቅሎ እየተሰደደ ነው። ኦሮሞ እንዳይናገርም፣ ዝም እንዳይልም ተሸብቦ ነው የተያዘው። ሥርዓቱን መቃወም ኦሮሞን መቃወም ስለሚመስለው ያፍራል፣ ዝም እንዳይል ራቡ፣ ጥሙ፣ ግብሩ፣ ሚሊሻው በዱላው ስለሚነርተው መድረሻ አጥቷል። አሁን በኦሮሚያ ከወታደር፣ ከፖሊስ ይልቅ ሚሊሻ ነው ሥልጣን የተሰጠው። ኦህዴድ ሥልጣኑን ለሚሊሻ ሰጥታ እኔን አትንኩ እንጂ ዘርፋችሁ፣ ቀምታችሁ ኑሩ ብላቸው በኦሮሚያ ሚኒሻ ነው የነገሠው። ከዋሸሁ እቀጣለሁ።

"…በኦሮሚያ አሁን ዶሮ ፊትለፊት አንጠልጥሎ ገበያ መውጣት እና ልሽጥ ማለት የማይታሰብ ነው። አንድ ዶሮ ለመሸጥ ቀረጡ ብዙ ነው። በሬም፣ በግም፣ ፍየልም እሳት ነው ቀረጡ። የጓሮ ጎመን፣ ሽንኩርት ሁላ አንዳንድ አካባቢ እግሩ ተቆጥሮ በግምት ነው የምትከፍለው ተብሏል። ዶሮ በጋቢ ጠቅልለህ፣ በነጠላ ሸፍነህ ቋቅ ብሎ ሚሊሻ እንዳይጠራብህ አስተኝተህ ነው የምትወጣው ተብሏል። የኦሮሚያው ይከፋል። ነገር ግን ማን ይናገረው? እነ መንሱር ጀማል በቲክቶክ ሸፍነውት፣ ጋርደውት፣ ሽቶ እየነፉ ተመልካቹን አደንዝዘውት እንዴት ይታይ? ቢታይስ ላም እሳት ወለደች ነው የሆነባቸው ኦሮሞዎቹ። ከመጪው ነሐሴ በኋላ አገዛዙ ገንዘብ ስለሚፈልግ ደግሞ የበለጠውን ትርምስ ማየት መጠበቅ ነው። የዘራነውን በሚገባ እናጭዳለን። አይቀርማ ግድ ነው። የኀዘን፣ የመከራው ድንኳን ሁሉንም ቤት መዳሰስ፣ መጎብኘት አለበት። የግድ ነው።

"…በአንጻራዊነት አሁን ዐማራው ይሻላል። ከጎጃም፣ ከደቡብ ጎንደርና የእነ መከታው ፋኖዎች ካሉባቸው ቀጠናዎች በቀር የዐማራ ክልል ይሻላል። ነፍጥ ባነሡ ልጆቹ ምክንያት በተወሰነ መልኩ ከዘረፋ ድኗል። ይሄን ስል ጎጃም ያለው የእነ አስረስ ፋኖ ለአቢይ አሕመድ የሚመች ሕዝብን የማማረር፣ የማስለቀስ፣ ረግጦ፣ አስመርሮ፣ ደፍጥጦ የመግዛት ፖሊሲው በጎጃም እየተተገበረ ስለሆነ ከሌላው የዐማራ ግዘት በተለየ መልኩ ፍዳውን እያየ መሆኑን ሳንዘነጋው ማለት ነው። አሁን በድራማ፣ በፎቶ ቢለጢቃ፣ በዲስኩር ሕዝብን አሞኝቶ፣ አታልሎ መግዛት ፋሽኑ አልፎበታል። በዚያ መንገድ ሁሉንም ታክቲኮችና ቴክኒኮች አቢይ አሕመድ በልቶበት ጨርሷል። እስክንድር ነጋም ሞክሮ ትንሽ ሸቅሎበት በኋላ ተባንኖበት ላሽ ብሏል። በዚያ መንገድ ሕዝብን ማደንዘዝ የማይታሰብ ነው። የፎቶ ድራማውም፣ የፎቶ ፖሊቲካ ጨዋታውም እንዲሁ ተበልቶበት አልቋል። ሁለት ሦስት ሚሊሻ ማረክን ከበሮ ምቱልነ፣ ወረብ ወርቡልነ፣ ድቤ ደልቁልነ፣ ጡሩንባ፣ መለከት ንፉልነ የሚባልበት ዘመንም አልፏል። አሁን ሕዝብ የሚፈልገው ለውጥ፣ መዋቅራዊ፣ ሀገራዊ፣ ሥርዓታዊ ለውጥ እንጂ ከከተማ ወጥቶ ገጠር በመሸሸግ ለውጥ ብሎ ነገር የለም። አስር ጊዜ መሳይ መኮንን ጋር፣ መዓዛ መሀመድ ጋር፣ በላይ ማናዬ ጋር ወጥተው በመበጥረቅ የሚመጣ ለውጥ የለም። አንድነትን አፍርሶ በጎጥ ተደራጅቶ የሚመጣ ለውጥ የለም። የምጽፈው ይመርራል ነገር ግን ዋጠው።

"…ሰሞኑን እየሰማሁ ነው። በሞጣ መስመር መኪና እንዳያልፍ በመከላከያ በመታገዱ የመኪና መዓት አትክልትና ፍራፍሬ እንደጫነ ሞጣ ከተማ ተገሽሮ ቆሟል አሉ። አምስት ወይም ስድስተኛ ቀናቸው ነው ተብሏል። ወደ ባህርዳር፣ ወደ ጎንደር ይሄድ የነበረ አትክልትና ፍራፍሬ በስብሶ ገምቷል ነው የሚሉኝ። መከላከያው ከሞጣ አላልፍም፣ እናንተ ናችሁ ፋኖውን እየቀለባችሁ በረሀ እንዲቀመጥና በደፈጣ እንድንመታ የምታደርጉን፣ ስለዚህ መኪና ባለፈ ቁጥር ቀረጥ ከእናንተ እየሰበሰበ መልሶ የሚወጋን እሱ ስለሆነ አታልፏትም ብሏቸው ነው አሉ መኪኖች የቆሙት። ማንትስዬ የሚባለው የአስረስ መዓረይ ብርጌድ ግን የለም። ይሄም ብቻ አይደለም በዚያው በጎጃም በምሥራቁ ክፍል ሌላ አንድ በጣም አሳሳቢ እና አንገብጋቢ ችግር መፈጠሩንም ነው የምሰማው። በዐማራ ክልል እስከዛሬ ሁልጊዜ የሚቀርብ የማዳበሪያ ብድር ዘንድሮ ለአርሶአደሮች አልቀረበም። እንደምክንያት የሚያቅርቡት ገበሬው ብድር ወስዶ ነገር ግን ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቀበሌዎች የሚኖርሩ አርሶአደሮች ብደር ስላልመለሱ ነው የሚሉት። በዚህ ምክንያት ብድር የመለሰው ደሀው አርሶአደር እንኳ መሬቱን አርሶ ዘር ሳይዘራ መክረሙ ነው።

"…አሁን ገበሬዎቹ በጣም ከባድ ችግር ውሰጥ ናቸው። ፋኖም ከመንግሥት ማዳበሪያ ከፍሎ የሚገዛ እቀጣለሁ ስላለ ዘንድሮ ጉድ መዓት ነው የሚጠበቀን ይላሉ። አንድ ወራዳ ብቻ እንደምሳሌ ብንመለከት በምሥራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወራዳ ከክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ ምርት የሚገኝበት ነበር። አሁን ግን ዘንድሮ የማዳበሪያ ብድር የለም። ብር ኖሮህ ለመግዛት ብትፈልግ እንኳን አንድ ሰው መጀመሪያ 30 ኪሎ ግራም ጤፍ ለሚኒሻ ማዋጣት አለበት። ካላዋጣ በብሩም መግዛት አይችልም። እንዲያም ሆኖ ጨክኜ ልግዛ ብትል እንኳን አንድ ለመግዛት በትንሹ ከ5 ቀን በላይ ተሰልፈህ፣ ከዚያ ሰልፉ ሲደርስህም አንድ ኩንታል ከ6,600 ብር በላይ አውጥተህ ነው የምታገኘው።እንግዲህ ፋኖውም፣ ሚኒሻና አድማ በታኙም፣ በሚቀጥለው ዓመት ምን እንደሚበላ አብረን የምናየው ይሆናል ነው የሚሉት። በተለይ ደግሞ ፋኖ ነኝ ብሎ ሕዝብን ነፃ ለማውጣት የወጣ አካል ከገዛ መንደሩና ከገዛ ቀየው ፈቀቅ ሳይል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀጥ ብሎ የሚቀልበውን፣ አልባሽ አጉራሹን አርዶ የሚጥል፣ ገና ከወዲሁ ምኑም ሳይያዝ በገንዘብ እና በሥልጣን እየተባሉ። እንደ ዐማራ የሚጨፈጭፋቸውን የጋራ ጠላታቸውን ትተው እርስ በእርስ…👇②✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እዚያው ጮቄ ተራራዬ ላይ ሆኜ ስብሰባ ላይ ነው የቆየሁት። ያን እኔ ከአፋጎ ሰንዱቅ መዥረጥ አድርጌ ያወጣሁትን ሰነድ ይዘው እነ ማርሸት አምስተኛ ክፍለጦሮችን ሊያወያዩ ሄደው ውኃ ገብታ የወጣች አይጥ አስመስለው ጀግኖቹ የበላይ ዘለቀ ልጆች ስብሰባውን በትነው መብረቅ እንደመታው ዛፍ ክው አድርገው አድርቀው ሲሰዷቸው እያየሁ ሰሞኑን ስገረም ነበር የከረምኩት። 😁

"…ጎጃም ለጃል ቆቱ ዝግ ነው ይባልልኛላ። አቤት አቤት መቼም ወግ ወጉ አይቀርም። እዚያው ጎጃም ጮቄ ተራራ ላይ ሆኜ ለጃል ቆቱ በሩ ዝግ ነው ይልልኛል ይሄ 100 ኪሎ ሰገጤ ሥጋ ቆራጭ አክቲቪስት ነኝ ባይ ሁላ። ጎጃም ተስፋ አለ። መዥገሮቹን ከላዩ ላይ አራግፎ ወደፊት ይስፈነጣል። በበላይ ዘለቀ ልጆች የሚያፍር ዐማራም የለም።

"…ለማንኛውም ስንጨቃጨቅ፣ ስንወያይ፣ ስንነጋገር የምናመሽበትን የጭቃ ዥራፍ የመሰለች ጦማር አዘጋጅቼላችኋለሁ። እናሳ አንብባችሁ አስተያየታችሁን በነፃነት ከጨዋ ደምብ ጋር ለማንሸራሸር ዝግጁ ናችሁ ቤተሰብ?

• አንድ 100 ያህል ሰው እስቲ ዝግጁ ነነ ዘመዴ ይበል። 😂

Читать полностью…
Подписаться на канал