zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጥያቄ ነው…?

"…በየት ሀገር ነው ወንዝን በጭራሮ የምትሻገረው? …እኔ በበኩሌ በከዘራ እንጂ በጭራሮ የሚሻገሩትን ወንዝ አላውቅም። በልጅነቴ ከአባቴ ጋር በሐረርጌ የጋሌቲን፣ በሸዋ የጊቤን ወንዝ ተሻግሬአለሁ። ወንዝን ለመሻገር ከዘራ፣ ወፍራም ዱላ፣ ክትክታ ይዘህ እንጂ በቀጭን ጭራሮ፣ ያውም በተጣመመ ጭራሮ በፍጹም አይሆንም። አይሞከርምም።

"…ዶላር ከመቀፈል ዳያስጶራን አንጀት ለመብላት ሲባል ፊልሙን ያለ ዳይሬክተር መተወን እንዲህ ለትችት ያጋልጣል። ደግሞስ የጦር መሪ ከዘራ እንጂ ጭራሮ ነው እንዴ የሚይዘው?

"…ደግሞስ ጭራሮ በጭራሮ የዐማራን ትግል እንዴት ያሻግራል? ይመራል? እኔ እንጃ አይመስለኝም። ወንዝ በድልድይ እንጂ በምርኩዝ ተሻግራችሁ የማታውቁ የከተማ ልጆች ዝም በሉ። መልስ እንሰጣለን ብላችሁ አታዝጉኝ። ወንዝ የምታውቁ የገጠር ልጆች ግን መልሱልኝ። ወንዝን በጭራሮ መሻገር ይቻላል ወይ?

"…እኔ ልክሳ፣ እኔ ልጥቆር? አንጀት ልትበዪ፣ አዪዪዪ… መልሱልኛ በጭራሮ ወንዝ መሻገር ይቻላል ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…19 ሺ ሰው አንብቦት 25 ሰው 😡 ብው ብሎ የተናደደበትን ርእሰ አንቀጽ አሁን ደግሞ ተራው እናንተ የራሳችሁን ሓሳብ በጨዋ ደንብ የምትሰጡበት ክፍለ ጊዜ ነው።

"…እኔ ዘመዴ ደግሞ በተራዬ አረፍ ብዬ የእናንተን አስተያየት እያነበብኩ ምሽቴን አሳልፋለሁ። ጀምሩ።

"…1…2…3…ተንፒሱ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሲያሳምጹ እነ ቤተልሄም ዳኛቸው ቀልቡንና ቆሌውን ገፈው ከጎጃም ምድር ብቻ ሳይሆን ከዐማራ ትግል አውጥተው አሁን ይኸው የቲክቶክ ኮይን ለቃሚ ሱሰኛ አድርገው አስቀሩት። ጎጃም ከምር አሸነፈ። ጎንደር ከጎጃም ጎን ቆመ። ወሎና ሸዋም ከጎኑ ቆሙለት። ስኳድ ግን አበደ። ግንቦት ሰባት፣ ግምባሩና ሠራዊቱም አበዱ። ብልጽግናም ነርቩ ተነካ።

"…የእስክንድርን የሞተ፣ የተቀበረ ዝና ለመመለስ አዲስ አጀንዳ ተቀረጸ። የጎንደር ፋኖ ጎንደር እንዲገባ፣ መከላከያው እንዲፈረጥጥ ተደረገ። እነ ሀብታሙ አያሌው እንቅልፍ አጥተው በሰበር ዜና ምድሪቷን ለማናወጥ ሞከሩ። እነ ምስጋናው አንዷለም ይኸው ጎንደር ነፃ እየወጣ ነው ለእስክንድር ነጋ ያልተገረዳችሁ በቶሎ ኑ ሲሉ በፓስተራዊ አባትነት ቡራኬ ሰጡ። ስኳድ በቲክቶክ ተንተከተከ። ብልፅግና ለጎንደሩ ድል ኢንተርኔት ፈቀደ፣ ከፈተ፣ የጎንደር ፋኖ ነን ያሉ ቲክቶክ ላይቭ ገብተው ጎንደር ነፃ ወጣች ብለው ፎከሩ። እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ያለ ዕቅድ ለፖለቲካዊ ቁማር ሲባል ለሰበር ዜና ተፈልጎ ጎንደር ገብቶ ሊሰባበር የነበረው የጎንደር የዐማራ ፋኖ ከባድ ዶፍ ዝናብ መጥቶ ሽፋን ሰጥቶት ከጎንደር ከተማ ወጥቶ ሳይደመሰስ ከሞት አመለጠ። የጎንደር ዐማሮች ጸሎት የጎንደር ፋኖን የተጠመደለትን ወጥመድ ሰብሮ አስመለጠው። እኔም አንድ ሳትሆኑ ድል የለም። እንዲያውም በዚሁ ልዩነት ከቀጠላችሁ ጎንደርን ትደመሰሳለች፣ ጎንደር ትወድማለች፣ ጎንደር አንገቷን ትደፋለች። መጀመሪያ አንድ ሁኑ በማለቴ በእነ እስክስ አበበ በለው ዘመቻ ተከፈተብኝ። ነገር ግን ወፍ የለም።

"…በመጨረሻም ሁሉ ነገር የጨለመበት እስክንድር ነጋን በማዳን በዐማራ ፋኖ ስም ድርድር እንዲያካሂድ እስክንድርን ጫካ የላኩት ኃይሎች አሁን ስሟን ያላረጋገጡኳት አንዲት ሴት ጫካ ተላከች። የጌታቸው አሰፋ ቀኝ እጅ እና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ወሳኝ ሰው ከእስክንድር ነጋ ጋር አብሮ ጫካ የገባው፣ በእናቱ ጎጃሜ በአባቱ ወሎዬ የሆነው ተስፋዬ ወይም ተስፋሁንም ኮሎኔል ፋንታሁንን ጠርንፎ እንዲይዝ ከእስክንድር ተለይቶ ወሎ ተሻግሮ ኮሎኔሉን ጠርንፎ አብሮት ሆነ። ሥራዎች ተሠሩ። ሁሉም ነገር ዝግጁ ሆነ። የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋና የጎንደር ፋኖን ለመምታት፣ ከጎንደር የባዬንና የሳሚን፣ ከጎጃም ሙሉ ጎጃም፣ ከወሎ ምሬ ወዳጆን፣ ከሸዋ የኢንጂነር ደሳለኝን አደረጃጀት ለመምታት ነው የተፈለገው። ስለዚህ የጎንደሩ በተለይ የጌታ አስረደ ቡድን ሦስት ቦታ ተበጣጥሷል። የሸዋው ከእነ መከታው እየፈለሰ ነው። ስለዚህ መሬት ላይ የሚያዘው ኃይል እንደሌለ ስለተረዳ በድርድር ሰበብ ትግሉን ለመጥለፍ ነው እንዘጭ እንዘጩ።

"…ከሸዋ ማይሙ መከታውን አግልለው አበበ ጢሞና የኢዜማ አባሉ መምህር ምንተስኖት ወይም ቹቹን፣ ከጎንደር ሀብቴ ወልዴን በዋናነት ይዘው አንተነህ ድረስ፣ እነ ኢያሱን (ሲሳይነ) ከወሎ ኮሎኔል ፈንታሁንን ይዘው ለመደራደር ነው ከተባለ በኋላ ድርድሩ ቀርቶ ወደ ቴሌ ኮንፍረንስ ተቀይረ። የመረጃ ምንጮቼ እንደሚሉት ከሆነ እስክንድር የሸዋው ነገር ስላላማረው ወደ ጎንደር መንቀሳቀስ ሳይፈልግ እንዳልቀረ። ኮሎኔል ፋንታሁንም ከሰራዊቱ ገለል ብሎ እንደቆየ፣ ይሄም በማይክ ሐመር ሰብሳቢነት፣ ባላረጋግጥም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና አቶ ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባሉበት፣ እስክንድር ነጋ የዐማራ ፋኖን ወክሎ ድርድር ሳይሆን እንደተወያዩ ተሰምቷል። ስሙ የተጠቀሰው ፋኖ ጸዳሉ ብቻ እኔ የለሁበትም ያለ ሲሆን ሌላም አንድ ስሙን በዚህ መጥቀስ የማልፈልገው የፋኖ አለቃም ተሳትፎ ነበረው ሲባል ተሰምቷል። "…አንዳርጋቸው ጽጌ ማንን ወክሎ እንደተገኘ አልታወቀም ተብሏል። አቶ አንዳርጋቸው ይሄንን እንደተለመደው ያጠራልኛል ብዬ እጠብቃለሁ። አንተነህ ድረስ፣ ታዬ አፅቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክሎም ሸዋና የወልቃይት ዐማራ ነኝ ስለሚል ስኳድነት ሊኖረውም ይችላል ነው የሚሉት። አበበ ጢም ከሸዋ ወኪል ሆነው ማለት ነው። ሰሞኑን ይሄን በተመለከተ ዘርዘር ያለ ነገር እንጠብቃለን።

"…ይህን ተከትሎ ለእነ እስክንድር ነጋ መደላድሎችን ለመፍጠር ሲባል የጎንደር ስኳድ ሆነው በፌደራል መንግሥት አስተዳደር ውስጥ ወሳኝ የሆነ ሥልጣን ያላቸው የብአዴንና አብን የጎንደር ስኳድ አመራሮች እና ከጎንደር የመጡ የጸጥታና የብልፅግና አመራሮ፣ ትውልደ የጎንደር የሆኑ በለሀብቶችና አመራሮች ጋር በመሆን የዐማራን ክልል እኛ እንምራው። ለዚህ ደግሞ እንቅፋት የሚሆኑብንን ከጎጃም፣ ከሸዋና ከወሎ፣ ከጎንደርም በሥልጣን ላይ ያሉ ይወገዱልን፣ ይታሠሩልን ማለታቸው ተሰምቷል። በዚሁ መሠረት በስኳድ ጥያቄ መሠረት በዐማራ ክልል ብልፅግና የጅምላ እስሩን በገፍ በመፈጸም ላይ ይገኛል። በወሎ ዩኒቨርስቲ የግዕዝ መምህራን አልቀሩም ሲታሰሩ። አሁን በአሁን ሰዓት የጅምላ እስሩ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ይፈጸማል። በጥቅሴ የሚታሰሩ እንዳሉ ሁሉ እግረመንገዳቸውን የሚወገዱ ይኖራሉ ማለት ነው። ትግሬ ከትግራይ አምጥቶ ዐማራን ለ27 ዓመት ገረድ አድርጎ እንደገዛው ኦሮሞም አማርኛ ተናጋሪ የትግሬ ዲቃላ ቅማንት የሆኑና ኦሮሞዎች አገው ሸንጎዎችን በስፋት ሥልጣን ላይ አውጥቶ ዐማራን ለእነ እስክንድር ነጋ ለማስረከብ የመጨረሻዬ የሚለውን ዘመቻ ነው የጀመረው።

"…አሁን ቤት ለቤት የሚጠቁሙት ራሱ የጎንደር ስኳዶች መሆናቸው ተነግሯል። አቶ ጋሻው ፀጋዬ በባህርዳር አባይ ማዶ ቴዎድሮስ ክፍለከተማ ሰላም እና ፀጥታ ሠራተኛ ነው። የአድማ ብተና ኃይል ይዞ የነቁ  በባህርዳር ከተማ የሚኖሩ የዐማራ ምሁራንንና ወጣቶችን ቤት ለቤት ይዞ እየዞረ የሚያስለቅም ባንዳ ነው ይባላል። ይኽ ትውልዱ ጎንደር ስማዳ የሆነ ዘራፊ ባንዳ በዐማራ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ደህንነት  ሠራተኞች ሰው በማገት፣ ገንዘብ በመቀበል፣ የጦር መሳሪያ በመሸጥ እና በተለያየ መልኩ ከሕዝብ በተዘረፈን 130 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ ለማድረግ የግል ድርጅት  ማለትም One Home Company ዋና መሥራች አባልና ባለ ትልቅ ድርሻ አክሲዮን ባለቤት አድርገው አምጥተውታል። አፋኝ ኃይሉ ሕዝብ እያገተና እየዘረፈ ያቋቋመውን ግዙፍ የንግድ ድርጅት የመመስረቻ እና ቃለ ጉባዔ በውስጥ አርበኞች አማካኝነት ደርሶኝ እኔም እንደ ሌሎቹ በእጄ ይዤዋለሁ።👇 ④ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በሱዳን በኩል ዐማራን ለመውረር ተሞከረ። አቢይ አሕመድም ለሱዳኖች በብዙ አቃጠረ፣ ደሰኮረ፣ ዳከረ። ሱዳንም የነቢያቸው የመሀመድን "ሀበሻን አትንኩ" የሚለውን ቃል ተላልፈው፣ የእብድ፣ የሕፃኑን የአቡሽን ምክር ሰምተው ዐማራን ለመውረር ሞከሩ። ወበሩ። ሳይውል ሳያድር ግን ዐማራ ሳይነካቸው ሱዳኖች ለሁለት ተሰበሩ። ሀሚቲና አልቡሁራን ተወጋገሩ። የኢትዮጵያ አምላክ ሱዳንን አፈር ደቼ አበላ። የመከራ ዶፍ አዘነበባቸው። ጌታቸው ረዳ ከመቀሌ፣ አቢይ አሕመድ ከሸጎሌ ሱዳኖች ሆይ ኧረ እረፉ ቢል ማን ሰምቶ። የዐማራ አምላክ በዐማራ ላይ የተቃጣውን ሴራ ሁሉ ሰባበረ። እንኩትኩቱን ነበር ያወጣው። አሁንም እንደምታዩት ነው። እንዲያውም አንደኛው የሱዳን ኃይል ተተኳሽ ለፋኖ እያቀረበ ነው ይባላል። እውነት ያድርገው።

"…ኦሮሙማው ብልፅግና ጅሉ የበሻሻ አራዳ የዐማራን ገበሬ ማዳበሪያ ከለከለ። በጨዋ ደንብ ሰልፍ ወጥተው ቢጠይቁም ብአዴን ገበሬዎቹን "የጅራፍ ፖለቲካ" ብሎም አሾፈባቸው። በፎሊስ ዱላም ዠልጦ አባረራቸው። ይሄም ለዐማራ ፋኖ ሌላ ፍርቱና፣ አሸወይና ዕድል ይዞ ከች አለ። ቀድሞ በረሃ ፋኖ ወረደ። ቀጥሎ ልዩ ኃይሉ ወረደ፣ አሁን ደግሞ የልዩ ኃይሉና የፋኖው አባቶች የዐማራ ፋኖን ትግል ገበሬውም ተቀላቀለው። መንገድ መሪ ሆነ። ፋኖ ትጥቅ ከብርሃኑ ጁላ ሽንኩርቴ ወታደር፣ ስንቅ ከገበሬው አባቱ ማግኘት ጀመረ። አለቀ። ለዐማራ እግዚአብሔር በራሱ ጥበብ ቆመለት። አደራጀው። አስታጠቀው። አሸናፊም አደረገው። ከባዶ እጅ ወደ ክፍለጡር አሳደገው።

"…ብራኑ ነጋ ከማይሙ አቢይ አሕመድ ጋር ሆኖ በዳንኤል ክብረት ተመክሮም የዐማራን ተማሪዎች ፈጥፍጦ ጣላቸው። ዩኒቨርሲቲም ያሉትን አባረራቸው። ወደ አዲስ አበባ ለመግባት 1ሚልዮን ብር ካልከፈልክም አትገባም ተባለ። ሰላሌ ሜዳ ላይ ኦሮሙማው ዐማራን አማረረ። ከአዲስ አበባ ዙሪያ ዐማራውን ቤቱን አፍርሶ አፈናቅሎ አባረረ። ከኦሮሚያም ብዙ ሚልዮን ዐማራ ተገደለ፣ ታረደ፣ ተጨፈጨፈ፣ ተፈናቀለ፣ ከሞት የተረፈውም የዐማራ ፋኖን ተቀላቀለ። ለበቀል ማለት ነው። የገደለውን ሊገድል። ዘሩን የጨፈጨፈውን ኦነግንና ቆሞ ያስጨፈጨፈውን መከላከያ ተብዬውን ሊበቀል ማለት ነው። በቃ አሁን የልቡ እየደረሰ ነው። እስከ አፍንጫው ታጥቋል። ጥሎ ይወድቃል። በብላሽ መታረድ ብሎ ነገር የለም። ቀረ።

"…ንቀውት ነበር መጀመሪያ ላይ። በስድብ የሚሸማቀቅ መስሏቸው በስድብ አምራቹ ዳንኤል ክብረት ጃዊሳ፣ ሳቢሳ፣ ግሪሳ፣ ወዬሳ፣ መገርሳ፣ ፈይሳ፣ ቶሎሳ፣ አብዲሳ፣ ዱሬሳ፣ ጃርት፣ ዐሞሌ ጨው፣ ዱባ፣ ጽንፈኛ፣ ሌባ፣ ቀማኛ፣ ዱርዬ፣ ዘራፊ፣ ማጅራት መቺም ብለው ሰድበውት ነበር። እነ ስታሊን ገብረ ስላሴም እንደ ፈጣን ፓስታ በ3 ደቂቃ እንደሚፈርስ ኢንዶሚን ብለው ተሳለቁበት። ቀበቶውን እናሰፈታዋለን፣ ሱሪውን እናስወልቀዋለን፣ እንጠርገዋለን ብለውም ፎከሩ። የዐማራ ብአዴን፣ የኦሮሞ ነፃ አውጪ፣ እና የትግሬ ነፃ ዐውጪ አክቲቪስቶች፣ ሚዲያና ጋዜጠኞች ልባቸው እያወቀ በአፋቸው አጣጣሉት። የዐማራ ፋኖ ግን ፈጣሪ ለዐማራ ያስነሳው ነበር እና ከዕለት ወደ ዕለት እየጠነከረ መጣ። የማይነቃነቅ ዐለትም ሆነ። ትግሬዎቹ እነ ስታሊን ተሸበለሉ። ካፈርኩ አይመልሰኝ ባዩ ከፀረ ዐማራው ከዳንኤል ክብረት በቀር በሙሉ ከአቢይ አህመድ ጀምሮ የዐማራ ፋኖን በክብር መጥራት ጀመሩ። የታጠቁ ኃይሎች፣ ጫካ የገቡ ወንድሞቻችንም ተባሉ። በዐማራ ፋኖ ማላገጥም ቀረ።

"…ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የዐማራ ፋኖ ጫካ መግባቱ ሲረጋገጥ፣ መረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የታጠቀው ወኔ ሳይቀር አሸናፊ እንደሚያደርገው ሲታወቅ የተለያዩ ኃይሎች የዐማራን ትግል ለመጥለፍና በባለቤትነት ለመያዝ መራወጥ ጀመሩ። ተንፈራገጡ። ግንቦት ሰባት፣ ባልደራስ፣ ብአዴን፣ ሕወሓት፣ ሻአቢያ፣ አሜሪካ፣ ወዘተ ተራወጡ። ተሯሯጡ። ሁሉ ነገር እንደሚመጣ የሚያውቀው የዐማራ ፋኖም በተጠንቀቅ ሁሉንም እንደየአመጣጡ ለመመለስ ዝግጁ ሆኖ ይጠባበቅ ጀመር። የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችን በሙሉ ከጉያ አስገብቶ ያሻቸው፣ ይፈትጋቸው ጀመር። አቅርቦ ነው የፈተጋቸው። ሜካፓቸውን አስለቅቆ አመድ ዱቄት ፊታቸውን ነው የገለጠባቸው። በሚዲያ ጫጫታ የተገነባ እና እንደ ሰናኦር ግንብ፣ እንደ ግብጽ ፒራሚድ የተገነባ የመሰለ የእንቧይ ካብ ስማቸውንም ነው ፍርስርሱን ያወጣው። ታላቁ የተባለውን ታናሹ፣ ኩርማኑ፣ ኩሩሩ አደረገው። የነጋበትን ሁሉ አጨለመበት። አፈር ከደቼ አበላው። የዐማራ ፋኖ ትግል።

"…ብአዴን በአረጁ፣ ባፈጁ፣ ፀረ ዐማራ የወያኔ አቃጣሪ የቀን ጅብ የነበሩ ካድሬዎች የነበሩና ባለሥልጣን የነበሩት በሙሉ ገሚሱ ወደ ውጭ ሀገር፣ ገሚሱ ወደ ጫካ ገብቶ ፋኖና የፋኖ ደጋፊ መሰሎ ተከሰተ። ብልፅግናም እንዲሁ የራሱን ሰው አዘጋጅቶ ወደ ፋኖ ትግል ላከ። እነ እስክንድር ነጋም የድርሻችንን እንያዝ ብለው መጀመሪያ አማሪካ ሄደው ዳያስጶራውን አፍዝዘው፣ አደንግዘው፣ ዶላሩን ገፍፈው ራቁቱን አስቀርተው ማይም ማይሙንና ፀረ ዐማራውን አማራ መሳይ ጎፍላ ጎፍላውን መርጠው የበግ ለምድ ለብሰው ወደ ትግሉ ተቀላቀሉ። ከብአዴን ጋር ባደረጉት ስምምነት መሠረትም እስክንድ በዐማራ ክልል እንዲንቀሳቀስ ተፈቀደለት። የአቶ ተመስገን ጡሩነህ የደህንነት መሥሪያ ቤትም ምቹ ሁኔታን ፈጠረለት። እስክንድርን ይዞ እስከ ደጀን ድረስ አምጥቶ፣ በሞጣ በኩል ባሕርዳር ድረስ ልኮ አሸባሪ የተባለውን እስክንድርን በመታወቂያ ዋስ ፈትቶ "መልሰህ በጦር ውጋኝ" ብሎ ለቀቀው። አቤት ቀልድ ብልፅግና እኮ አይቀልድ። ወያላውን ስንታየሁ ቸኮልን ባህርዳር ላይ ይዞ በአውሮጵላን አስሮ አምጥቶ ሊያጀግነው የደከመለት ብልፅግና እስክንድርን አስሮ ፈትቶ ለዐማራ ትግል ጫካ እንዲገባ ለቀቀው። አትስቁም ግን?

"…የዐማራ ፋኖ ጥርስ ሲያወጣ፣ መናከስ ሲጀምር ጥድፊያው በዛ። ጎንደር ዩኒቨርሲቲም በራሱ በጀት ፋኖ ወደ ማቋቋም ገባ። የጎንደር ድቅል የዐማራና ቅማንት የትግሬ ልጆችም የራሳቸውን ፋኖ አቋቋሙ። ወልቃይት ያለው የትግሬ ተጠሪ ደመቀ ዘውዱ ማረፊያ፣ የጎንደር ዩኒቨርስቲ መኪና፣ የጎንደር ብአዴንም ጥበቃ መደበ። ሻአቢያም ለዚህ ቡድን በአንዳርጋቸው ጽጌ በኩል ድጋፏን መስጠት ጀመረች። የእናት ፓርቲ መሥራቹ ጌታ አሥራደ እና ኢያሱም የእነ ውባንተን ቡድን እንዲቀላቀሉ ተደረገ። ጌታ አስራደ በሁሉም የጎንደር ፋኖዎች ቅቡልነት እንዲኖረው ለማድረግ ሲባል ሻአቢያ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አማካኝነት 52 ሺ ተተኳሽ ጥይት ለጌታ አስራደ አስረከበች። መነኩሴው ከሻአቢያ ተቀብለው ወልቃይት ድረስ አመጡት የጎንደር ዩኒቨርስቲ ዶፍቶር አሥራት አፀደወይን መኪና መድቦ በጌታ በኩል ከፋኖ ደረጀ በቀር ለጋሽ መሳፍንት ጭምር አስረከበ። ይሄንን ጌታ አስራደ ራሱ በቃል፣ ጋሽ መሳፍንትም መቀበላቸውን በቃል በመረጃ ከኔ ዘንድ ይገኛል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌም ይህንን ማደረጉን ለእኔው በጽሑፍ አረጋግጦልኛል።…👇② ከታች ይቀጥላል✍✍✍

👆③ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍

"…ይሄ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የፋኖ ቡድን መነሻውን ወልቃይት ካደረገው መከላከያ ጋር እየተናበበ፣ በውስጥ ሰርጎ ከገባ በኋላ ከእስክንድር ነጋ ጋር ኅብረት ፈጥሮ መንቀሳቀስ ጀመረ። ጎንደር በሙሉ ለእስክንድር ይደር፣ ይገዛም ተብሎ ታወጀ፣ እነ ጋሽ መሳፍንትም ለእስክንድር ከተዋጣው ዶላር ቢደርሰን ብለው ለእስክንድር ነጋ ተገረዱ። ሀብቴም ለእስክንድር አደረ። አስቸጋሪው ውባንተ ነበረ ውባንተን መጀመሪያ መግለጫ አወጡበት፣ በሚዲያ ሞት ዐወጁበት፣ የሞት ዐዋጁንም የሀብቴ የቅርብ ጓደኛው ሙላት አድኖ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ከምስጋና በኋላ ትናንት መቅረብ የነበረበት እና ሳይቀርብ የቀረው ርእሰ አንቀጻችን አሁን ቢቀርብ ምን ይለናል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አላችሁ አይደል…?

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይቅርታ…!

"…አዲሱ የታናሹ እስክንድር ነጋ የዶላር መቀፈያ ድርጅትን እንደሆነ በሚታመነው ዶክተር አምሳሉ በሚመራው እና እስክንድር ገንዘብ በእሱ በኩል ስጡን ብለው በሚያውጀት የገንዘብ መቀፈያ ድርጅት ውስጥ ገብቼ መረጃ እየቦጦቦጥኩ ስለለነበር ነው የዘገየሁት።

• እህም…„ሊበላ…? 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ታላላቆቹንና ሹማምቱንም የቀሩትንም ሕዝብ፦ አትፍሩአቸው ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስቡ፥ ስለ ወንድሞቻችሁም ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻችሁም ስለ ሚስቶቻችሁም ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ…።” ነሀ 4፥14 …“…እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥” መዝ 62፥11

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አጭቤዋ ርስተይ ተስፋይ ምንአለች? ኣ…? ምንአለች…? ምንአለች…?

• መልሱን በአስተያየት መስጫው ሰንደቅ ውስጥ ይጻፉ። 😂😂 ፍጠኑ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በፈለጋችሁት እናስይዝ። ኮሎኔል ርስተይ ተስፋይ ትግሬ ናት…? ወልቃይቴ ነኝ እንጂ ዐማራ ነኝ የማትለው ለምን ይመስልሃል? ቀጥሎ ቪድዮዋን ኣሳያለሁ። አስይዙ ትግሬ ናት።

"…ይሕቺን ዐማራ ገዳይ የትግሬዋ ነፃ አውጪ ኮሎኔል የምትሰድበኝ በጤናዋ ይመስልሃል? አዎ በጤናዋ አይደለም። ጅራት ጭራዋን ይዤዋለሁ። በጎንደር ዐማራ ስም አላስነግድም። መስቀል እንዳየ አጋንንት፣ ጠበል እንደነካው ሰይጣን ነው የማስጓራት።

"…እናንተ እኮ አታፍሩም። አሁንም ዘመዴ ጎንደርን እየሰደበ ነው ትሉኝ ይሆናል? 😂

• እናስይዝ ትግሬ ናት። ቪድዮ ነው የማመጣው። አያሌው መንበር፣ መሳፍንት፣ ፎሮፈር ሲሳይ አልታሰብ፣ ሰሎሞን ቦጋለ ማንም አያድናትም። እናስይዝ አልኳችሁ ርስተይ ትግሬ ናት። 😂😂😂

"…ቀጥሎ ቪድዮ ነው የማቀርበው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጀመርኩ…✍✍✍

"…ይሄ በፎቶው ላይ የምታዩት ዳዊት ይባላል። የ ቮይስ ኦፍ ዐማራ የቲክታክ ባለቤት ነኝ፣ ደግሞም የጎንደር ዐማራ ነኝ የሚለው። እስክንድር ነጋ ለምን ተነካብኝ ብሎ ካልታነቅኩ ሞቼ እገኛለሁ ባይም ነው። እዚሁ ጀርመን ነው የሚኖረው። እንዲህ በወታደር ልብስ ድምቅ ብሎ ቲክታክ ላይ ተጥዶ የጎንደር የዐማራ ሴቶችን ከፋሲል ከነማ ኳስ አስጨፋሪው በአባቱ እስላም በእናቱ አባት ስም ቦጋለ ሰሎሞን ቦጋለ ተብሎ ከሚጠራው ነውረኛ የማንነት ቀውስ ካለበት ፀረ ዐማራ፣ ዐማራ አሰዳቢ ጋር ሆነው በቲክታክ ግደለው፣ ገድለህ አሳየኝ፣ እንድንገድለው ላኩልና እያለ የሚደነፋው ሰው ዕድሜ ለወፎቼ ምን ሆኖ ቢገኝ ጥሩ ነው?

• ገምቱ እስኪ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አዲስ እርድ ነው…

"…ዘሬ ደግሞ እዚሁ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ በሚያስተዳድሩት በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት በሙዳ ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ ቅዳሜ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓም እንደተለመደው እረኛም፣ ጠባቂም የሌላቸው፣ በኦሮሚያ ውስጥ እንደ ዜጋ የማይቆጠሩትና ከኦሮሚያ ምድር ይጸዱ፣ ይጠረጉ ዘንድ የተፈረደባቸው 8 ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ አማኞች በዚያው በተለመደው "ያልታወቁ ኃይሎች" ተብለው በሚጠሩት ኦርቶዶክስ ከኦሮሚያ አስወጋጅ የማይጠየቁ ኃይሎች በተለመደው በግፍና በጭካኔ ሁኔታ ታርደው ደማቸው እንዲፈስ መደረጉ ተዘግቧል።

"…በዚህ በሙዳ ሰንቀሌ ቀበሌ በሙዳ ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች እነዚያ "የማይታወቁ የታጠቁ ኃይሎች" ቅዳሜ መስከረም18 ቀን 2017 ዓም ሌሊት ቀደም ተብሎ በተሰጣቸው ሊስት መሠረት ከየመኖሪያ ቤታቸው እየዞሩ በመልቀም ይዘዋቸው የሄዱ ሲሆን፣ በመጨረሻም የኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ጀቢሳ በሚባል አነስተኛ ወንዝ ሥር በግፍ አርደው የሰማዕትነት ጽዋ እንዲቀበሉ አድርገዋቸዋል፡፡ በቦታው የደረሰው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት አስክሬናቸውን በክብር በማንሳት በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን  አሳርፏቸዋል።

"…ኦርቶዶክሳውያኑ ከታረዱ በኋላ መከላከያ ተብዬው የኦሮሙማ ዘበኛ የሟች ኦርቶዶክሳውያኑን አስከሬን ለቅሞ አንሥቶ እንዲቀበሩ ተባብሯል። ላለፉት 30 ዓመታት የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስም በክስተቱ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው ሕይወታቸውን ላጡ ክርስቲያኖች ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያሳርፍ መመኘታቸውን ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።

"…በቀደም 5 በማግስቱ 8 እስከአሁን 13 ኦርቶዶክሳውያን ታርደዋል የኢሬቻ በአል እስኪያልፍ በኦሮሚያ ስንቶች ይታረዱ ይሆን?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ምላሱን ከሚያጣፍጥ ይልቅ ሰውን የሚገሥጽ በኋላ ሞገስ ያገኛል።” ምሳ 28፥23

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 2:25 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/rlg7EHDfz7c

• Mereja TV: https://mereja.tv

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እኔና ሰሎሞንን ፍረዱን…!

እኔ ዘመዴ… "…ዐማራ ቅማንት ነው። ቅማንትም ዐማራ ነው። ስህተት አለው?" ብዬ ሰሎሞንን ጠየቅኩት።

እሱ ሶሎሞን ደግሞ እንዲህ ብሎ ነው የመለሰልኝ። "…ቅማንትም አገውም የቆቱ ኦሮሞም አማራ አይደለም 44ነጥብ!!! ብሎ ነው የመለሰልኝ።

"…ታዲያ ይሄ ሰው ምንድነው? አያሌው መንበር፣ ምስጋናው አንዷለም፣ ሙላት አድኖ፣ ሲሳይ አልታሰብ፣ ሳሚ ቅማንቴው እንዴት የጎንደር ዐማራን ሊወክሉ ይችላሉ?

"…ጎንደሬ ከመሬት ተነሥቶ ጎጃሜን አይጠላም። ጎጃሜም ከመሬት ተነሥቶ ጎንደሬን አይጠላም። ጎንደሬ ነኝ ብሎ በጎጃም ላይ ስር የሰደደ ጥላቻ የሚያራምድ ከሆነ፣ እሱ የተከዜ ማዶ ዲቃላ ነው። ጎጃሜ ነኝ ብሎ ጎንደሬ ነኝ ካለም በአገው ሸንጎ ስር የተሸጎጠ ኩሻንኩሽ ዲቃላ ነው። አለቀ።

"…እስቲ ፍረዱ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ማሉልኝ እስኬው…!😂

"…እስኬው የጨሰ የድሮ አራዳ ነው። ጎንደር ሄዶ ባለ ማዕተቡን አዛውንቱን ጋሽ መሳፍንትን መስቀል አስጨብጦ ላልከዳህ ላትከዳኝ፣ አስብሎ አስምሎት በእጁ አስገብቶት የዓለም ብርሃን አማኝ አስደርጎ አስቀራቸው።

"…እስክንድር ወደ ሸዋም ሄዶ መከታውንና ከባልደራስ ምሥረታ ጀምሮ አብሮት የነበረውን አቤ ጢሞን እንዲሁ ነው ያደረጋቸው። መስቀል አስጨብጦ፣ የቤተ ክርስቲያን በር አዘግቶ፣ ብከዳህ የጻድቃኔዋ ማርያም ትክዳኝ አስብሎ አስምሎ፣ ገዝቶ የግሉ ባርያ አድርጎ አሳስሮ ገረዱ አደርጎ አስቀመጣቸው።

"…እስክንድር ተኩሶ አያውቅም ተኳሾችን ይገዛል እንጂ። አደራጅቶ አያውቅም የተደራጀ ተቀላቅሎ ያፈርሳል እንጂ። እስክንድር የመራው ውጊያ ኖሮ አያውቅም። መዋጋትም ውጊያ ባለበት አልፎም አያውቅም። በሸዋ ተራሮች በጠንቋይ ምሪት በሬ እየገበረ በልዩ ጥበቃ ይኖራል እንጂ ራሱ የተቆጣጠረው ከተማም መንደርም የለም። ኦፕሬሽን ምን እንደሆነ አያውቅም። የማረከው ወታደርም፣ መሣሪያም የለም። ለእነ መከታው፣ ለእነ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ በሚከፍለው ዶላር የሰበሰባቸው ጥቂት ፋኖዎች እንጂ የራሱ ፋኖዎች እንኳ የሉትም።

"…እስክንድር ከጎንደር እና ከሸዋ በመሃላ፣ ከጎጃም ማስረሻንና ከወሎ ሙሃባውን በፈረንካ አንቆ ይዞ ቢቆይም ይሄንኑ ጨዋታውን በእነ ዘመነ ካሤ፣ በጎጃም፣ በእነ ባዬና ሳሚ በጎንደር፣ በእነ ምሬና አቤ በወሎ፣ በእነ አሰግድና ደሳለኝ በሸዋ በመሃላ ስም መሸወድ አልቻለም። ፊደል የቆጠረን ሰው በመሃላ መሸወድ አይቻልም። ይኸው እየዬ ብሎ እስከአሁን ከሃብታሙ ጋር ቆሞ ሲያለቅስ ይውላል። የሌለ ምርጫ አለ ብሎ የምን እሪሪሪ ቋቀምበጭ ነው። ጥፋ ተብለሃል ጥፋ። ድራሽ አባክ ይጥፋና ይል ነበር አጎቴ ሌኒን።

• ምንድነው ምንድነው ቀለበት ምንድነው መሃላ? የሚለውን ዘፈን ለእስኬው ጋብዙልኝ። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆⑤ ከላይኛው የቀጠለ …✍✍✍

"…ሕዝቡ እንዲያውቀው ይደረግ የሚሉት የመረጃ ምንጮቼ እንደ ቁራጭ መሬት የሚያዩአት የኦሮሞ ብልፅግና ሰዎች ቢኖሩም ወልቃይትን በብላሽ አሳልፎ ለወያኔ መስጠት አደጋው ቀላል ስላልሆነ ወልቃይትን ለዐማራ መሳይ የትግሬ ድቅሎች ሰጥቶ ማቆየት፣ አልያም ራስ ገዝ ሆኗ በፌደራል መንግሥቱ ሥር ልክ እንደ ድሬደዋ ሆና እንድትቆይ ይፈልጋሉ። በወልቃይት ምክንያት ከነጮቹ ማግኘት ያለብንን ፈረንካ በማጣት እየሟሟን ነው የሚሉት። በዚህ በወልቃይት አካባቢ ያለውን ውጥረት የጎንደር ዐማሮችን የሚያስቆጣ ሊሆን ከቻለም በወልቃይት ምትክ ፌደራል መንግሥቱ የጎንደር ስኳዶችን በሚጠቅም መልኩ ሰሜን ጎጃም የሚባለውን ጠንካራ የፋኖ አደረጃጀት ያለበትን ቀጠና አፍርሶ፣ የእነ እስክንድር ፋኖ በድርድር ከስገባ በኋላ ቀሪዎቹን በአሸባሪነት፣ በፅንፈኝነት ከስሶ ሙሉ ጦርነት በማድረግ ደፍጥጦ ያሻውን ለመፈጸም ነው በጥድፊያ ነገሮችን እያካሄደ ያለው ተብሏል። የጎጃም ባለሀብቶችን በማዳከም፣ ባሕርዳርን የፌደራል መንግሥቱ ስር ያለች ከተማ በማድረግ ነገር ግን በከተማዋ ላይ የጸጥታውንም ሆነ የኢኮነሚውን መስክ የጎንደር ስኳድ እንዲቆጣጠረው በማድረግ ሆኔታዎችን መቆጣጠር ይፈልጋሉ ነው የሚሉት የመረጃ ምንጮቼ።

"…እስከአሁን የትየለሌ የብአዴን ባለሥልጣናት ተለቅመው የታሠሩ ሲሆን፣ እነዚህኑ እስረኞች ወደ ብርሸለቆ ለመውሰድ ከ200 በላይ መኪኖች ወደ ክልሉ መግባቱ ተነግሯል። የዐማራ ፋኖ ተኩስ የሚከፍት ከሆነ እነዚህን እስረኞች እገረመንገዱን ብልጽግና በራሱ ገዳይ ስኳድ ሊጨፈጭፋቸውና ፋኖን ዓለም አቀፍ አሸባሪ ለማስባል ሊሠራ እንደሚችል ነው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት የሚናገሩት። እስከ አሁን ባለው የጅምላ እስር እነ ድረስ ሳህሉን ጨምሮ በአገዛዙ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች መካከል… የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የመረጃ ሓላፊ ረ/ኮ/ር ግርማ ፈንታሁን፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/የመረጃ ሓላፊ ኮማንደር መኮንን አለነ፣ የዐማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕግ ክ/ሓላፊ ረ/ኮሚሽነር ሙሉጌታ አያልነህ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የክትትል ሓላፊ ኮማንደር አብዮት ይሁኔ፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሓላፊ ኮማንደር ዋለልኝ፣ የባህርዳር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክ/ ሓላፊ ኮማንደር ንብረቱ ሞላ፣ በባሕር ዳር ፖሊስ መምሪያ የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኮማንደር ዘሪሁን አስራደ፣ የክልሉ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ የመረጃ ሠራተኛ አቶ ጥላሁን ታደሰ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።

"…ይህን ሁሉ ካደረገ በኋላ በቀጣይ ብልጽግና ሊፈጽማቸው ያሰባቸውን በሙሉ ለመፈጸም

1ኛ፦ ከመረጃ መቁረጥ (በመዋቅር ውስጥ እና በከተማ የነበሩትን በማሰር ኦፕሬሾኑን መረጃ እንዳይኖር ማድረግ) ለዚህ ደግሞ ፍቱን መድኅኒቱ በተቻለ መጠን በቅብብሎሽ እና በተለመደው መንገድ አጋር በመጠቀም መረጃ መሰብሰብ ነው።

2ኛ፦ የእርስበርስ ኮሚኒኬሽን እንዳይኖር የስልክ ግንኙነቶችን የምር ያቋርጣል። በዚህም ፋኖ መረጃ አጥቶ መንግሥት የተወሰደበትን የመረጃ የበላይነት ለማስመለስ ይዳክራል። ይሄም በተለመደው ባህላዊ መንገድ በመጠቀም ግኑኝነቱ ይቀጥላል።

3ኛ፦ የሎጀስቲክ መስመሮችን እና ምንጮችን መቁረጥ ነው። ይሄን በቀጣይ የተጠኑ የወገን የሎጀስቲክ መተላለፊያ መስመሮችን በመቁረጥ በመስፈራት እና  የማስራብ stratgey ይጠቀማል። ለዚህም ቀደም ብሎ በተዘጋጀው መንገድ ማለፍ።

4ኛ፦በሚሰማራባቸው አካባቢዎች የፓለቲካ ሥራ በማከናወን የፓለቲካ መነጠል ሥራ ለመሥራት ይሞክራል። የፓለቲካ መዋቅሩን መልሰው የሚያደራጁ ከተለያዩ ክልሎች የተመረጡ አማርኛ ተናጋሪ ካድሬዎች በገፍ ወደ ክልሎ ይመጣሉ። በዚህም መሠረት የበቀል ስሜታቸውን የሚወጡ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ፋኖ (አክራሪ የወሃቢያ እስላሞችን፣ የብልፅግና ወንጌል ጴንጤዎችን፣ እና ከቅማንት እና ከዐማራ የተወለዱ ፀረ ዐማራ ዲቃላዎችን፣ የአገው ሸንጎ እና ሆዳም አማራዎችን በብዛት ይሾማሉ።

5ኛ፦ ፋኖዎቹን የመበተን ሥራ መሥራት፣ በውጊያ ጫና ውስጥ በማስገባት የፋኖ አመራርችን በመምታት  እንቅስቃሴዎችን ማክሰም። ለዚህ ተልእኮ ሲባል የጎረቤት ክልሎችም በገፍ እንዲሳተፋ ያደርጋል።

"…በዚህ መልኩ መጀመሪያ የጎጃሙን ኃይል ከተመታ በኋላ፣ የጎንደሩን የእነ ባዬን፣ የወሎውን የእነምሬን፣ የሸዋውን የእነደሳለኝ ፋኖ በቀሪዎቹ የእስክንድር ፋኖዎች፣ የጎንደሩን በቅማንት፣ በደመቀ ዘውዱ የተከዜ ዘብ፣ በመከላከያና በጁንታ፣ የእነ ምሬን በጁንታ፣ በኦነግ እና በእነ እስክንድር ገሌ በኮሎኔሉ ታጣቂዎች መምታት ነው የሚሉት። ለዚህ ደግሞ የአራቱም ግዛት ፋኖዎች የተዘጋጁ ሲሆን አመራሮቹ ቢከዱም ታጣቂው ፋኖ ግን ለእነ ሀብቴ፣ መከታው እና ኮሎኔል ይታዘዛል፣ ወንድሞቹም ላይ ይተኩሳል ብዬ አላምንም። አልቀበልምም። ለምሳሌ በሸዋ የመንዝ፣ የተጉለት፣ የሞጃና ወደራ፣ በደጋ ጅሩ ያሉት በመከታው ስር ያሉት ፋኖዎች ከእነ ደሳለኝ ጋር ተዋጉ ቢሏቸውም እምቢ ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም። የጋራ አራጅ የኦነግና የኦሮሙማ መከላከያን አስቀምጠን ከእናት አባት ከወንድሞቻችን ጋር የምንዋጋው ለምንድነው በማለት እምቢኝ ብለዋል። በዚህ ምክንያት ሙሉ መንዝን ሰብስበው ወደ ቆላው በማውረድ አስቀምጠዋቸዋል ተብሏል። አሁን መከላከያው ከረዳቸው ሸዋሮቢት፣ ራሳና ደብረ ሲና አካባቢ ያሉትን ብቻ ይዘው ከሸዋ ፋኖ ጋር ሊዋጉ እንደሚፈልጉ ከዚያው ከውስጣቸው ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል። ዳጋው ተዋጋ ቢባልም መሣሪያውን ይዞ አልዋጋም ብሎ መጥፋቱ አክስሮአቸዋል። የቆላውን የይፋት ሕዝብ ደገኛ ነው ብለው እነሱ ከሚያስቡት ወንድም ዐማራ ጋር ከመዋጋት እንደወሰኑ ነው የተሰማው።

"…አንባቢ ሆይ አንተስ አንተ የዐማራ ፋኖን በገንዘብ፣ በሓሳብ፣ በጸሎት የምትደግፍ ምን ትመክራለህ? ያ ተው ሲባል እምቢ ያለው፣ ማይም፣ ፀረ ዐማራ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረው የዐማራ አድማ ብተና ተብዬ ፀረ ዐማራ የአገው ሸንጎና ቅማንት የትግሬ ድቅል በዐማራ ምድር ዋጋውን እያገኘ ነው። አቢይ ይሸነፋል። እሱ ግን ሕይወቱን ለብልጽግና ገብሮ፣ ከወገኑም ደም ተቃብቶ አየር ላይ ይቀራል። እንደ አቢይ አሕመድ አገዛዝ ለዐማራ የጠቀመ አገዛዝ መቼም ጊዜ ቢሆን በኢትዮጵያ ተከስቶ አያውቅም። አቢይ ለዐማራ የዋለውን ውለታ ማንም አልዋለለት። የዐማራን የቤት ሥራ ቀድሞ የሚያቀልለት እኮ ራሱ አቢይ አሕመድ ነው። ያኔ ልዩ ኃይሉን ቀድሞ እንደበተነው፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስት ፀረ ዐማራውን ሁሉ ጭምብል ያወለቀለት ጭምብል ያወለቀ ከይሲ ሰው ነው። ርእሰ አንቀጹን እያነበባችሁ ቆዩኝና በመጨረሻ አስተያየት መስጫ ሰንዱቁን ስከፍትላችሁ ሓሳብ አስተያየታችሁን ትሰጣላችሁ። 

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
መስከረም 21/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በኢትዮ 251 ሚዲያ ላይ ዐወጀ፣ የእስክንድር የሚዲያ ሠራዊት በሀብታሙ አያሌው እየተመራ ውባንተ ላይ ዘመቻ ከፈተ። ውባንተም የሚደርስለት፣ የሚረዳው አጥቶ ከጦርነት መልስ በሰላም በቆመበት በስናይፐር ተመቶ ወደቀ። ሞተ።

"…የጎንደር ስኳድም ጮቤ ረገጠ። የእስክንድር ግሩፕም ፈነጠዘ። የውባንም ልጆች ባዬን መርጠው ቀጠሉ። እነ እስክንድር ነጋ ግን አበዱ። ጎንደር ለእስክንድር እንጂ ለማንም አይገባም ብለው ተቆጡ። የጎንደር ዩኒቨርስቲ የዶር አሥራት ዐፀደወይን ፋኖዎችም ከእነ ባዬ ቡድን በይፋ ተለዩ። ሰሎሞን አጣናው የተባለም የቆየ ፋኖ መሪ አድርገው መረጡ። የቅማንትና የዐማራ ድቅል ማንነት ያላቸው በሙሉ ከእነ ሰሎሞን አጣናው እና ከእነ ሀብቴ ጋር ቆመው መሪያችን እስክንድር ነው አሉ። እነ ምስጋናው አንዷለም፣ እነ ርስተይ ተስፋይ፣ እነ አያሌው መንበር፣ እነ ሲሳይ አልታሰብ፣ እነ ሙላት አድኖ፣ እነ ሰሎሞን ቦጋለ ወዘተ በሙሉ ከእስክንድር ጋር ተሰለፉ። እነ ፕሮፌሰር ግርማ ብራኑም በቦርከና ላይ በጻፉት ጽሐፍ መነሻዬ ዐማራ መድረሻዬ ዐማራ የሚሉትን በሙሉ አሳድዶ መደምሰስ ነው ብለውም ዐወጁ። በዚህ መሠረት በውባንተ የተጀመረው ማሳደድ ሸዋ ዘልቆ በአቶ አሰግድ መኮንን ላይ ተተገበረ፣ ቀጥሎም ወደ ጎጃም ሄዶ ዘመነን ለመብላት ይኸው የጎንደር ስኳድ በብዙ ዳከረ። ወሎም ተሻግሮ በምሬ ወዳጆ ላይ ፎከረ። ነገር ግን ጎጃምና ወሎ የስኳድን ሴራ አክሽፎ፣ የስኳድን ተላላኪዎች ደምስሶ አሳፈረ። አሸነፈም። አሁን ስኳድም ሆነ እስክንድር በጎጃም ሙሉ በሙሉ በወሎ ከጥቂት የኮሎኔል ሙሃቤ ጀሌዎች በቀር ከስኳድ ነፃ ሆኗል። የሸዋውም ፍርክርኩ ወጥቷል።

"…ስኳድ እኔ ከጀርባ የሌለሁ መስሎት የዐማራ ፋኖዎች ወደ አንድነት ለመምጣት ያደረጉትን ውይይት ጠልፎ እስክንድርን መሪ አድርጌ መርጫለሁ ብሎ ዐወጀ። የጎንደር ስኳድ ከበሮም፣ ነጋሪትም ጎሸመ። እነ ሀብታሙ አያሌው ምእመናን እልል በሉ ታላቁ እስክንድር የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መሪ ሆኖ ተመረጠ። እነ ዘመነ፣ ምሬ፣ ባዬ፣ አሰግድ እና ኢንጂነር ደሳለኝ አአኩርፈው ወጥተዋል ብለው መሰከሩ። እነ እስክንድር ነጋም እነ ሀብታሙ እንቅልፍ ላይ ስለነበሩ ሰበር ዜናውን ለስታሊን ልከው ስታሊንም ዐማሮች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የእስክንድር ነጋን መመረጥ ጮቤ እየረገጠ በሚዲያው ዓይኑ እንዳፈጠጠ ዐወጀ። ሕዝቡ ሁሉ ግራ ተጋባ። የሚዲያው ጩኸት አደንቋሪ ስለነበር ሁሉም ሰከረ። ተጨብረበረ። የማታ ማታ እኔ ዘመዴ በዕለተ ረቡዕ በሰበር ገብቼ የምርጫውን ሂደት የድምጽ ቅጂ በመረጃ ቴሌቭዥን ይፋ አወጣሁት። የስኳድም፣ የብአዴንም፣ የትግሬዎቹም፣ የኦሮሙማዎቹም የጋለ የአሸናፊነት ስሜት ላይ በረዶ ቸለስኩበት። እስክንድር ነጋ የተባለ ሾተላይ ሞት እንቢ ጠንቋያም የዐማራ ድል አጨናጋፊም ቅስሙንም፣ ጅስሙንም ሰበርኩት። ዋሸሁ እንዴ?

"…የትግሬ ዲቃላዎች መሩ የጎንደር እስኳድ ከዚያ ወዲያ አበደብኝ። አጓራብኝ። እኔም ብቻዬን ገጠምኳቸው። ገመናቸውንም ገላልጬ ርቃናቸውን አስቀረሁት። ልሣናቸው አበበ በለውንም ከነ አዲስ ድምጹ ጉረሮውን አንቄ እኚኚ እንዲል አደረግኩት። ኢትዮ 360 እና አበበ በለውን ከአድሚኖቸቸው ውጪ የሚያያቸው፣ ገንዘብ የሚሰጣቸውም ጠፋ። የዐማራ ሕዝብ ዳር እስከዳር ነቃ። ተነቃነቀም። ስኳድ ጨነቀው። የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ የዛቻ፣ የማስፈራሪያ ማዕበል አጎረፈብኝ። እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር ወይ ፍንክች። ዶላር ለአንዳቸውም የእስክንድር ገረዶች፣ አሽከሮች እንዳይደርስ ተደረገ። ከምኒልክ የሳተላይት ቴሌቭዥን በስኳድ በኩል ጎንደሬውን ገንዘብ ሊዘርፉት ሲሉ እኔ ዘመዴ ገጀራ ሆኜ ከፊታቸው ቆምኩ። የእስክንድር ነጋ ዋሌት የሆነው ዶር አምሳሉና በረደድ በምስጋናው አንዷለም በኩል ሊያቋቁሙት የነበረው የዶላር መሰብሰቢያ ማሽን ሞተሩን ሰበርኩት። በፋኖዎች ማኅተም በእኔና በመረጃ ቲቪ ላይ መግለጫ ቢያወጡ እኔ ዘመዴ ወይ ፍንክች። መግለጫው ፌክ ነው ብዬ ገገምኩ። ፋራው ስኳድ ቀማቴው ብርቧክሳም የጠንቋይ ልጅ ምስጌ መግለጫውን ደንግጦ አነሣው። ይቅርታም ጠየቀ። ኢትዮ 360 ግን ካፈርኩ አይመልሰኝ ብሎ ወገመ። እንግዲህ በዚህ የተነሣ የስኳድ ምኞት ውኃ ሆኖ ቀረ።

"…ስኳድ አሁን በብዛት ወደ ኡጋንዳ እየተሰደደ ነው። እነ ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ሁላ ወደ ኡጋንዳ ተሰድደዋል። መጀመሪያ ኤርትራ ይሄዳሉ። እዚያ ከሻአቢያ ሥልጠናና ስምሪት ይሰጣቸዋል። ከዚያ ወደ ኡጋንዳ ይሰደዳሉ። በካምፓላ የሚኖሩት ከኤርትራና ከትግራይ ትግሬዎች ጋር አንድ ሰፈር ተጋርተው ነው። ካምፓላ ኮሎሎ የሚባል የመኖሪያ ሰፈር አለ። ይሄ ሰፈር ማለት እንደ አዲስ አበባው የሀብታሞች መኖሪያ ሰፈር እንደ ቦሌ ዓይነት ማለት ነው። የስኳዶች የካምፓላ ቢዝነስ ቀላል አይምሰላችሁ። ኢንዱስትሪዎች፣ በግብርና መስክ ተሰማርተው ወዘተ እጅግ ግዙፍ የሆኑ የሀገሪቱ ቢዝነሶች በአብዛኛው በእነሱ እጅ ይገኛሉ። አዳሜና ሔዋኔ ጨዋታውን ተመልከትልኝ ብቻ። ግን ግን ለምንድነው የጎንደር ስኳድ ብቻ የሚሰደደው? ከተሰደደ በኋላስ በትንሹ ስቱዲዮ ከፍቶ በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ላይ የሚያሰፈስፈው ለምንድነው? ለምንድነው የጎንደር ስኳድ ወሳኝ ሰዎች ከተሰደዱ በኋላ ከትግሬና ከኤርትራ ትግሬ ጋር ግንባር ገጥመው በዘመነ ካሤ ሰበብ የጎጃም ዐማራ ላይ የሚዘምቱት? መልሱን ተመራምራችሁ ድረሱበት።

እንቀጥል…

"…ከላይ ያን ሁላ የዘበዘብኩ ዛሬ የምጽፍላችሁ እንዲገባችሁ ብዬ ነው። በዐማራ ፋኖ ውስጥ አስርገው ያስገቡት ትግል ጠላፊ ሾተላዩ እስክንድር ከፍተኛ ኪሳራ ደረሰበት። በኢኮነሚ ፋኖ የሚገዛበት ዶላር ነጠፈበት። በፖለቲካው አር የነካው እንጨት ተደረገ። በሚዲያው በኩል ቀለብ የሚሰፍርላቸው የአፍራሳና የሂርጶ 360 እንደ ቁራ አንቋርሮ ቀረ። ቆይ ብሎ ለወጥ ላድርገው ብሎ ቅንቅናሞቹን ፀረ ዐማራ ፓስተሮች እነ ምስጋና አንዷለምን ከፊት አሰልፎ እነ በረደድንና እነ ደረጀን፣ ከጀርባ ሸሽጎ፣ ዶር አምሳሉን በስሙ ጣና ቴሌቭዥን በማለት ሊግጠው ቢመጣም ገጀራ ሆኜ አነጠፍኩበት። መሬት ላይ የመከታው ማሞ ታጣቂዎች ወደ ከሰም እና ቡልጋ ተሸበለሉበት። ጨነቀው፣ ጠበበው። በጎንደር ሀብቴ ብቻውን ፈጠጠ፣ የእነ ጌታ አስራደ ቡድን ለሦስት ተከፈለ። ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባው ጦሩ ከድቶት ገሚሱ ወደ እነ ምሬ፣ ገሚሱ ወደ እነ ደሳለኝ ገባ። ጨነቃቸው። ጎጃም ላይ ኮሎኔል ጌታሁንን ቢቆሰቁሱት ቡዳ ነው ብለው የሰደቡት ጎጃሜ ፀረ ዐማራውን ኃይል በላው። ለልጁም ሳይራራ የእስክንድር አሽከር ነህ ያለውን ማስረሻ ሰጤን ቆረጠመው። ማስረሻም ፈርጥጦ አሁን ደቡብ ወሎ መካነ ሰላም ይንከራተታል። የጎጃም መጠንከር፣ የሸዋ መጠንከር፣ የወሎና የጎንደር ግግም ማለት ሁሉንም ፀረ ዐማራ ኃይሎች አበሳጨ። 👇③ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

👆④ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍

"…የጎንደር ስኳድ ድቅል ፀረ ጎንደሬ የሆነው ኃይል በሰፊው ጎጃም ላይ ዘመቻ ከፈተ። የትግሬና የኦሮሞ አክቲቪስቶችም ለዚህ ድቅል ጎንደር አሰዳቢ የጎንደር ዐማራ ጠላት ስኳድ ድጋፋቸውን ሰጡ። ጎጃም ላይ ዘመቻ ተከፈተ። የሚዲያም፣ የምድርም ዘመቻ ነው የተከፈተው። አባቷ ትግሬ፣ ሚስትየው ጎንደሬ የሆነችው ሕፃን ልጃቸውን ሞት ተከትሎ አየር ምድሩ ጎጃም ላይ አፉን ከፈተ። ፍርድ ላገኘ ጉዳይ የሌለ ተጯጯሁ። በዚያው ሰሞን በጎንደር፣ በኦሮሚያና በአዲስ አበባም ዘግናኝ ወንጀሎች ቢሠሩም ዘመቻው ጎጃም ላይ ነበር እና ጆሮ ዳባ ልበስ አሉት። እነ በቀለ ወያ ከመሸጉበት ጎጃም ባህርዳር ላይ ሆነው ጎጃም ላይ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ”

"…ጁንታ ያሏት የወያኔ ወረራ ለዐማራ ሰሞነ ህማማት ሆኖበት ቢሰነብትም ስቅለትን አልፎ ትንሣኤ እንደሆነለት ሁሉ አሁንም ለዐማራ ድርድር በሚል ሰበብ የተጀመረው ቀሽም ዐማራ ጠል የቦለጢቃ ሴራ ሌላ ፍርቱና የሆነ ዕድል እያመጣለት ነው። የወያኔ ወረራ ዐማራን መሳሪያ አስታጥቆታል። ወያኔ ከዐማራ ላይ ገፍፋ የወሰደችውንና በትር ያስያዘችውን እጁን ዳግም በነፍጥ እንዲንበሸበሽ ነው ያደረገው። ያውም ምስኪን ነፍ የትግሬ ወጣቶች በዐማራ ምድር ተሸክሽከው፣ እምሽቅ ብለው አልቀው ነው ዐማራ የታጠቀው። ቀሪ የትግሬ ወጣቶች በትግራይ ተቆማምጠው ቆስለው ተቀምጠዋል። ወረራው ለዐማራ በህማም ውስጥ የተገኘ ፈውስ ነበር።

"…እደግመዋለሁ አሁንም ለዐማራ ፋኖም ሆነ ለዐማራ ሕዝብ የመጨረሻ አሸወይና የሆነ ዕድል በጅሉ ሞሮ በእስክንድር ነጋበት በኩል እየመጣለት ነው። ሁልጊዜም እንደምለው ዐማራ ላይ የሚጎነጎኑ ሴራዎች በሙሉ እየተበጣጠሱ፣ ምክሮች እየፈረሱ፣ ሟርቶችም እየከሸፉ፣ እርግማንም ወደ ምርቃት እየተቀየረ ዐማራ ከዚህ ደርሷል። ከላይ ከመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት የጁንታው ጦርነት መምጣት ምርጥ ጮማ የሆነ ዕድል ነበር ይዞ ነበር ለዐማራ ፋኖ እንደ ፋኖ ለዐማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ይዞ የመጣው። ጦርነቱ ጭና ተክለ ሃይማኖት ላይ፣ ማይካድራ ላይ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ሸዋ ላይ ዘግናኝ ጉዳት ቢያደርስም ከልጾሙ ፋሲካ፣ ካላዘኑ ደስታ፣ ካልወደቁ መነሣት የለምእና በጉዳቱ ውስጥ ግን ለ27 ዓመታት አረመኔዋ በሴራ በግፍ ነፍጡን ነጥቃ አንገቱን አስቀርቅራ፣ ነፍጡን የዘቀዘቀ ሽማግሌ ሃውልት ሠርታ በትር እንኳ በእጁ እንዳይዝ አድርጋው የነበረውን ዐማራ፣ መሣሪያውን ገፍፋ ወደ ትግራይ አሽሽታ የነበረውን ነፍጡን የትግሬ ልጆች 4ኪሎን እያሰቡ እየተዋጉ ተሸክመውት መጥተው ልጆቿ ተገድለው፣ መሣሪያውን መልሶ ዐማራ በገፍ ታጠቀው። ጦርነቱ ለዐማራ ከጦም በኋላ ፋሲካ ነበር የሆነለት።

"…ልዩ ኃይል ይፍረስ ተብሎ የተሠራውም የቦለጢቃ ፋውል ለዐማራ ጮማ የሆነ ዕድል ነበር ያመጣለት። የዐማራ ልዩ ኃይልን አፍርሶ፣ በራሱ በዐማራው ልዩ ኃይል አልማዝን በአልማዝ መቁረጥ በሚለው ብሒል መሠረት በፈረሰውና መከላከያን ይቀላቀል በተባለው የዐማራ ልዩ አማካኝነት የዐማራ ፋኖን መደምሰስ የሚለው የቦለጢቃ ሴራ ከሽፎ ልዩ ኃይሉ ይፍረስ የሚለውን ምስጢራዊ ደብዳቤ እኔው ዘመዴ በትኜው የዐማራ ልዩ ኃይል ሳይፈርስ፣ መከላከያም ሳይገባ "ከነመሣሪያው፣ ከነትጥቁ፣ ከነስንቁ፣ ከነ ጀግንነቱ" የዐማራ ፋኖን በመቀላቀል ለዐማራ ሌላ ትንሣኤን አበሰረ። ኦሮሙማ ወትግሩማም በሃላል ከሠረ።

"…ቀጥሎ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሌላው ለዐማራ አሸወይና የሆነ እምጷ የሆነ ዕድል ይዞለት የመጣ ክስተት ነበር። ዐማራ ከስምምነቱ፣ ከፕሪቶሪያው ንግግር ገለል ተደርጎ፣ በወያኔ ተኮትኩቶ ባደገውና በፀረ ዐማራው ስልጤ ሬድዋን ሁሴን ተወክሎ የኦሮሞ ብልፅግናና ህወሓት በጓዳ ውል ስምምነት ተፈራርመው ዳግም የዐማራን መከራ ለማረዘም ተማምለው፣ በጦርነቱ ላይ ስለሞቱት የትግሬ ወጣቶች ህወሓት ላታነሣም ተስማምተው፣ ነገር ግን በጥበብ አንድ ላይ ሆነው የጋራ ጠላታቸው የሆነውን የዐማራ ነገድ ለመቀጥቀጥ ተዋውለው መምጣታቸው ለዐማራው ለጊዜው ቢያስከፋም ፍጻሜው ግን በዘመናት ውስጥ ድጋሚ የማይገኝ ዕድል ነው ለዐማራው ይዞለት የመጣው።

"…በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ህወሓትና የኦሮሞ ብልጽግና አስቀድሞ እንዲፈጸም የፈለጉት የኦሮሞ ልዩ ኃይል ሳይነካ የሌሎች ልዩ ኃይሎች እንዲፈርሱ ነበር። መጀመሪያ ለማጃኮሚያ በአራዳ ሙድ ቀድሞውኑ በድሮንና በዐማራ ታጋዮች ተቀንድቦ ያለቀውንና የፈረሰውን የትግራይ ልዩ ኃይል ተብዬ ማፍረሳቸውን ማወጅ፣ አስከትሎም ወያኔ ይኸው በእጇ የሚገኘውን የጦር መሣሪያ አስረከበች ተብሎ ሕዝበ አዳምን ለመሸወድ ነበር የተሞከረው። አምባሳደር ተሾመ ቶጋም ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል በቀር ሁሉም ክልሎች ልዩ ኃይላቸውን ያፈርሳሉ። ትግሬም ይኸው የጦር መሳሪያዋን አስረክባለች በማለት የተሰባበሩ፣ የዛጉ፣ የጨረጨሱ የጦር መሣሪያዎችን በይፋ በቴሌቭዥን አሳዩ። አስከትለውም ወዲያው ከባድ የህልውና አደጋና ስጋት ያለበትን ዐማራን ፋኖን ትጥቅ ይፈታል፣ ልዩ ኃይልህም ወደ መከላከያ ይገባል ብለው ዐዋጅ መሰል ትእዛዝ አስተላለፉበት። ይሄን ጊዜ ነው ለዐማራ ሕዝብ ሌላ ከፍ ያለ ፍርቱና የሆነ ዕድል ከቻሳ ብሎ የመጣለት።

"…ብራኑ ጁላ ተርዚናውን ተፍቶ ሉሉ ሳያደርግ የጫት ቅጠል ጥርሱ ውስጥ እንደ ጎመን ተመርጎ እየታየ፣ ሲጋራ ኩበት ያስመሰለው የደረቀ ከንፈሩን በምላሱ ምራቅ ለማርጠብ እየጣረ፣ በተቆራረጠ፣ በወኔቢስ ድምጽ "መሳሪያ አልፈታም፣ ስምምነቱንም አልቀበልም የሚለውን እንደመስሳለን ብሎ ሲደነፋ ዐማራው አየ፣ ተመለከተም። ትግሬው አበባው ታደሰም "እምቢ ካሉ ይጠረጋሉ" በማለት ጓ ሲል ዐማራው አየ። ተሸናፊው የትግሬም ነፃ አውጪ ባለሥልጣናትም ከመቀሌ ወበሩ። በወቅቱ የመከላከያ ሚንስትር የነበረው ትግሬው አብርሃም በላይም ፅቅርፕፅጻቓቔ ብሎ ደነፋ። የመከላከያ ጀነራል፣ ኮሎኔል የተባሉ ትውልደ ቅማንት ወትግሬ፣ አገው ወሶደሬ የሆኑና በዐማራ ኮታ የከበሩ ሁሉ ደነፉ። የኦሮሞዎቹም አሽላሉ። ዐማራው ግን ሥራ ላይ ነበር።

"…ቀድሞ ጫካ የገባው የዐማራ ፋኖ ወጣቶች ነበሩ። ብልፅግና ወጣቶቹን በጦርነቱ ላይ በደንብ አይቷቸዋል። በውጊያው ላይ ከመከላከያው ወታደሮች ይልቅ የፋኖዎቹን ጀብድ አሳምሮ አይቷል። እናም ፋኖን አልማዝን በአልማዝ መቁረጥ በሚለው ብሂል መሠረት አልማዝ የዐማራ ፋኖዎችን አልማዝ በሆኑት የዐማራ ልዩ ኃይል አማካኝነት ለመቁረጥ ፈልጎ ወሰነ። እናም ውሳኔውን ይፋ ሳያደርግ ተቀደመ። የዐማራ ልዩ ኃይል በአስቸኳይ ፈርሶ መከላከያን ይቀላቀል የሚል ደብዳቤ በምስጢር ጽፎ ለውስን የዐማራ ኃላፊዎች በተነ። ደብዳቤዋም ለእኔ ደረሰችኝ። እኔ ዘመዴም ደብዳቤዋን በቴሌግራሜና በመረጃ ቴቪ በነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ በተንኳት። ይሕቺ ለዐማራ ሕዝብ ፍርቱና የሆነ ዕድል ይዛ የመጣች ደብዳቤ ለሁሉ በይፋ እንደታየች የዐማራ ልዩ ኃይል ከነ የጦር መሣሪያው፣ ከነ ልምዱ፣ ከነ ጀግንነቱ የዐማራ ፋኖን ተቀላቀለ። የዐማራ ፋኖም ሆነ። የዐማራ ፋኖ በአንድ ጀንበር ግዙፍ ጦር ሆኖ አደረ።

"…ዐማራ ቆቅ ነው። ዐማራ በተፈጥሮም ብልህ ነው። ዐማራ የትግሬው ጦርነት ሲያልቅ ቀጥሎ ኦሮሙማው እሱ ላይ ፊቱን እንደሚያዞርበት ያውቃል። ተረድቷልም። ስለዚህ ራሱን በተለያዩ መንገዶች ሲያዘጋጅ ነበር የከረመው። ለምሳሌ በጁንታው ጦርነት ላይ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖና የቤተ ዐምሓራ ፋኖዎች የማረኩዋቸውን ከባድና ቀላል መሳሪያዎች በወቅቱ በዚያው ግንባር ጦርነቱን ይመሩ የነበሩ የራሱ የአገዛዙ ጀነራሎችና ኮሎኔሎች መሳሪያውን በምስጢር በጥንቃቄ ቅበሩ፣ ሸሽጉ በማለት ነግረዋቸው ቁጥሩ የማይገለጽ ተተኳሽ እና የጦር መሳሪያ በወሎ ክፍለ ሀገር መቀበሩን እኔ ራሴ በቅርብ ዐውቃለሁ። ነገ ወደ እናንተ ነው ጦርነቱ የሚዞረው እናም ከወዲሁ በጦር መሣሪያ ራሳችሁን አደራጁ በማለት ነበር የጦር መሣሪያው ይደበቅ የነበረው። እንደተባለው አልቀረም ጦርነቱ መጣ። መሳሪያውም ወጣ።👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

👆②ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤” ዮሐ 10፥1

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ዛሬ ምሽት ልክ 2:00 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና
ጠብቁን።

"…አንድ ሰው ብቻ መሆኔ እንደዛሬ ቆጭቶኝ አያውቅም። ስንት ቦታ ልሁነው? የመድኃኔዓለም ያለህ። ርእሰ አንቀጹ ተዘጋጅቷል። ግን እንዴት ልለጥፈው? በቃ ነገ ጠዋት በጠዋት እለጥፈዋለሁ።

• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/YJVcyQziZV0

• Mereja TV: https://mereja.tv

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ከምስጋና በኋላ የሚጠበቀው ከዕለተ ማክሰኞ እስከ ዕለተ አርብ ጠዋት ጠዋት የሚቀርብላችሁ ተወዳጁ ርእሰ አንቀጻችን ነው።

"…የዛሬው ርእሰ አንቀጻችንም አደገኛ የሚመስል ቀሽም የድርድር ቦለጢቃ ሴራ ነው የሚያከሽፈው። የከሰረው እስክንድር ነጋና ቡድኑ የመጨረሻ ዕድላቸውን ለመሞከር የሚላላጡትን መላላጥ ነው በሃላል የማሰጣው። እስክንድር ከሽፏል። ከጨዋታ ውጪም ወጥቷል። እስክንድር የማይጠቅም ዕቃ ሆኗል። ለደጅ መውጫ ጣሳናት እንኳ አይፈለግም።

"…የጎንደር ስኳድንም መትቼዋለሁ። ልሳናቸው አበበ በለውን ልሣኑን ዘግቼ፣ ፈረንካ አሳጥቼ፣ ኮቱ በላዩ ሰፍቶበት፣ ብቻውን እንዲያወራ አድርጌዋለሁ። ወልቃይትን በዐማራ ስም የያዙ ድቅል የትግሬ ልጆችን፣ የጎንደር ዐማራን በዐማራ ስም ተብትበው የያዙ ስሁላውያንን አፈር ከደቼ አብልቼቸዋለሁ። ጎንደር እከኩ እየተራገፈ ነው። ደቡብ ጎንደር ያለው ዐማራ ያልሆነው ታጣቂ ሲቀር አሁን ጎንደር ከትብታቡ እየተፈታ ነው።

"…በዛሬው ርእሰ አንቀጻችን ወልቃይትን ለትግሬ በመስጠት በምትኩ ለስኳዱ ሰሜን ጎጃምን ከባሕርዳር ከኢኮነሚው ጭምር ለመስጠት የጨረሱትን ሴራ እናያለን። እነ ማይክ ሀመር ከእስክንድር ነጋ ጋር ያደረጉት የመጀመሪያው የስልክ ኮንፍረንስ ምን ይመስላል? የዐማራ ክልል የብአዴን ዐባላት ያውም የጎጃምና የወሎ ብአዴኖች፣ የዩኒቨርሲ መምህራኖች፣ እና የጎጃም ዐማሮች እስር ለምን ይሆን? የሚለውን አበጥረን እናያለን። ወልቃይትን ለትግሬ ለመስጠት ሲባል ያለ ጎንደርና ጎጃም ሕዝብ ፈቃድ ጎጃምን ለስኳድ መስጠትስ እንዴት ይታያል? ጣና ቴሌቭዥን 😂😂😂።

"…ለማንኛውም ዛሬ ማታም በሰበር የእነ እስክንድር ነጋበትን ሴራ ለማክሸፍ በዚያውም ስለ ኢሬቻ ለመነጋገር በመረጃ ቴሌቭዥን እከሰታለሁ። እስከዚያው ርእሰ አንቀጼን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በመጨረሻም… 😂

"…የእኔ ወፎች እኮ ገራሚ ናቸው። ዝርዝሩን ጠዋት ከምስጋና በኋላ በርእሰ አንቀጻችን ላይ እንከካዋለን። የብልጽግና የፌክም፣ የምርም የዐማራ ብልጽግናዎችን በጅምላ ማሰር ምን ለማሳካት ነው? የሚለውንም እናያለን።

"…ለቀረጻ ስትሉ ከፋኖ ተሰውራችሁ ስትንከራተቱ መዋል ማደራችሁ ነው የገረመኝ፣ ያሳቀኝም።

• አይ ድርድር እቴ…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• አትጫጩ ~ አትንጫጩ
• የህውሃት ~ የህወሓት
• አዳሪ ~ አደር
• የ ይትብ ~ የዩቲዩብ
• ጥሮቶኛ ~ ጡረተኛ
• መሰላቹሁ ~ መሰላችሁ

"…እንደፈረደብኝ እኔ ዘመዴ የሐረርጌው ቆቱ አማርኛም ላስተምር እንጂ። እኔ ደፍተራው፣ እኔ ጦንቃሊው ዘመዴ አልተቻልኩም አይደል? የጎንደር ዐማራ ነኝ የሚል ትግሬ አማርኛ ሳስተምር ግን እንዴት ነኝ? 😂


"…እናስይዝ ይህቺ የወያኔ ታጋይ ትግሬ ናት። ትግራይን ነፃ ለማውጣት ስትታገል ኖሯ አሁን እነ አያሌው መንበርን፣ እነ ምስጋናው አንዷለምን፣ እነ ሰሎሞን ቦጋለን ይዛ የጎንደር ዐማራን ለማደንዘዝ የተላከች፣ ተልካም ስምሪት ወስዳ በስተ እርጅና በወጣትነቷ በዐማራ ላይ የሠራችው ግፍ፣ ያፈሰሰችው ደም የሚያክለፈልፋት ነፍሰ ገዳይ ፀረ ዐማራ ፋኖ ወያኔ ናት።

• እናስይዝ…! አትፍሩ እንጂ። አንተ ዘመዴ ግን ከእኛ ከጎንደሮች ራስ ላይ ውረድ የሚሉኝ እነ አበበ በለው ሁላ የት ጠፉ ግን?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቁርበቱን ስሙት…

"…በትግራይ እኔን ዘመዴን ከወያኔ ደጋፊ ትግሬ በቀር የትግራይ ትግሬዎች አይጠሉኝም። አይጣሉኝም። በጎንደር የጎንደር ዐማራና የጎንደር ቅማንት አይጠላኝም። አይጠላኝምም። በጎንደር የሚጠላኝና የሚጣላኝ ቅቅማንት ሆኖ ከትግሬ የተዳቀለ፣ ከዐማራም የታደቀለ ትግሬ፣ ግማሽ ግማሽ ማንነት ያለው፣ በሙሉ አፉ ዐማራ ነኝ ማለት የማይደፍር፣ ዐማራ ነኝ ከሚል ይልቅ በጌምድሬ ነኝ፣ ጎንደሬ ነኝ ብሎ በጎንደሬነት ካባ ስር የሚደበቅ የድቅል ማንነት ባለቤት የሆነ ብቻ ነው አምርሮ የሚጠላኝ።

"…ይሄ የቅሪላ አስጨፋሪ ሶሎሞን ቦጋለ ነው እንግዲህ በትግሬ ዘመዶቹ አማካኝነት በጎንደር እና በጎንደሬነት ስም "ዘመዴን ግደሉልኝ" ሲለው እንገድለዋለን ግን ገንዘብ ላኩልኝ ሲለው ያመሸው። ይሄ ቁርበት የማንነት ቀውስ ያለበተት ዳዊት የተባለ አጭቤም ዐማዳም ነው ዳርምሽታት ባንሆፍ ሆኖ ሲበጠረቅ ያመሸው። መደቡ ከዚሁ ወገን ነው። ስሙትማ። ይሄን ቀርበት…

"…እያንዳንዱን በጎንደር ዐማራ ላይ የተጣበቀ ዐማራ መሳይ የጎንደር ዐማራ ጠላት እኔ ዘመዴ በወረንጦ፣ በመርፌም እየለቀምኩ አውጥቼ አሰጣቸዋለሁ። ጎንደሮች እኔ እንደ ሻማ እቀልጥላችኋለሁ እናንተ ደግሞ ከስር ከስር ኅብረት አንድነታችሁን ፈጥራችሁ ተወያዩ። በዲቃላ ማንነቶች አትጠርነፉ። ተናግሬአለሁ።

• ቆይቼ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬ ዕለተ ሰኞ የዶርዜ ማርያም የዕረፍት ቀኔ ቢሆንም አሁን ደግሞ እስቲ ይሄን በታላቁ የጎንደር ሕዝብ ላይ የተጫነን መርግ የሆነ የድቅል ማንነት ባለቤት ሆኖ በዐማራነቱ የሚያፍር ፀረ ቅማንት፣ ፀረ አገው፣ ፀረ ጎንደርና ፀረ ጎጃም አጠቃላይ ዐማራ አሰዳቢ ከርሳም የሆነ በበታቸኝነት ስሜትም ሲሰቃይ ውሎ የሚያድር ሾተላይ ትግል አጨናጋፊ ነውረኛ፣ የዐማራ ሥነ ልቦናም፣ ስብዕናም፣ ሃይማኖትም የሌለው ዘ ስኳድ የተሰኘ ገፋፊ፣ ቀፋፊ፣ አእምሮ ቢስ በጡንጫው የሚያስብ አስጨፋሪ ቡድን ሱሪውን ዝቅ አድርጌ በታወቀው በጭቃ ዥራፍ ሳማ ብዕሬ እልለበልበው ዘንድ አማረኝ። አዛኜን ልለበልበውና ቆይቶ በቲክቶክ ሲያጓራ እንዲያመሽ ላደረግው ነኝ። እሺ ጎዶኞቼ ምን ትመክሩኛላችሁ…?

• የአንድ የ100 ሰው ምክረ ሓሳብ ካየሁ በኋላ እገባላቸዋለሁ።

• ተንፒሱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ኢሬቻ እስኪያልፍ ቁጠሩ ብቻ…!

"…በቀደም ዕለት ከ3 ቀን በፊት ማለት ነው በተሠራ ዜና በኦሮሚያ ክልል በሞጆ አካባቢ አንድ የቅዱስ ሚካኤል ደብር አገልጋይ የሆኑ ካህን ከባሌቤታቸውና ዲያቆን ከሆነው ልጃቸው ጨምሮ ሦስት ልጆቻቸው ጋር በአጠቃላይ 5ቱም የቤተሰብ አካላት "ማንነታቸው የማይታወቁ አካላት" በሚል የዳቦ ስማቸው በሚታወቁ አራጅ አካላት ታርደው ለዋቃ ጉራቻ መስዋዕት ሆነው ቀርበው ነበር።

"…የእኚህ ትውልዳቸው ከወደ ላስታ የወሎ ሰው የሆኑ ሰማእት በአንድ ጊዜ፣ በተመሳሳይ ሰዓት የዘር ሐረጋቸው ዘራቸው በኦሮሚያ ውስጥ ተቋረጠ፣ አበቃ፣ ከተተ፣ ዘጋ ማለት ነው። ዘራቸው ጸዳ። ዘራቸው እንዲጠፋ ተደረገ ማለት ነው። ዘር እንዳይተኩ ሁነው ተጨፈጨፉ። ጄኖሳይድ ተፈጸመባቸው ማለት ነው።

"…ዛሬ ደግሞ ከዚያ ድንጋጤ ሳይወጣ እዚያው ኦሮሚያ ክልል ስንት ሰዎች ከየቤታቸው ተለቅመው ወንዝ ዳር ወስደው ያረዱ፣ የጨፈጨፉ ይመስላችኋል? ገምቱ እስቲ? እንዲያው ይሄ የእሬቻ በአል እስኪያልፍ ድረስ የስንት ኦርቶዶክሳውያን ደም ይፈስስ ስንትና ስንት ምስኪኖች ይታረዱ፣ ይጨፈጨፉ ይመስላችኋል? እስቲ ገምቱ?

"…የዛሬው ደግሞ በጣም ይዘገንናል። የኦሮሚያ ምድር እንዲህ ዓይነት የሰው መታረጃ ቄራ ሆናለች።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አላችሁ አይደል…?

~ የሳይበሩ ዓለም ፊልድ ማረሻ ዘመዴ ገብተዋል።

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለዛሬ የመጨረሻዬ ነው።

"…በጁንታው ጦርነት ጊዜ ከሀገረ እስራኤል ድረስ ተነሥተው ጎንደር መጥተው ለዐማራነታቸው ሊዋጉ ከሄዱ በኋላ በግንባራቸው ሳይሆን ከኋላ በጀርባቸው በጥይት መትተው የጨረሷቸው ምስኪን የጎንደር ዐማራዎችን ማን እንደሆነ የፈጃቸው ጊዜ ያወጣዋል።

"…በጁንታው ጊዜ ዘመትን ያሉት እነ ሰሎሞን ቦጋለ፣ እነ ሙላት አድኖ፣ እነ ጌትነት አልማው፣ እነ ጋሻው መርሻ፣ እነ ቶማስ ጃጀው፣ እነ ጣሂር፣ እነ የሱፍ፣ እነ መኮንን ከበደ ሞረዳ፣ ቀሪዎቹን እናንተ ሙሉበት። አንዳቸውም አልሞቱም። የጥይት ጭረትም አልነካቸውም። አልቆሰሉም ጭራሽ። ጀግኖች ዐማሮች ግን ግንባራቸውን ከፊት ለፊት በትግሬ፣ ከጀርባቸው ደግሞ በወዳጅ ጠላት ዲቃሎች ተመትተው አልፈወዋል። ገድሏቸዋል አይገለፀውም።

"…ፋኖ አርበኛ አጋዬን ከዐማራ ፋኖ ትግል ያሰወጡት እነማን ይመስሉሃል። አንተ ቅማንቴ ነህ። ከመከላከያ ጋር መዋጋት የለብህም ብለው በደመቀ መኮንን አሸልመው ሽባ ያደረጉት እነማን ይመስሉሃል? እነ ሰሎሞን ቦጋለ፣ እነ ርስተይ ተስፋይ፣ እነ ኮሎኔል ደመቀ፣ እነ አያሌው መንበር፣ እነ ሲሳይ አልታሰብ፣ እነ ሙሉዓለም ገብረ መድኅን፣ እነ ዶፍተር ምስጌ እኮ ናቸው ያስወጡት።

"…አዎ ደመቀ ዘውዱ ስሁል ሚካኤል ነው። ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ጎንደሬ ነው። እበድ ምንም አባክ አታመጣም። ፀረ ፋኖ፣ ብልፅግና ነው። የዐማራን ጄኖሳይድ የካደ፣ ከወልቃይት ዐማራን አፅድቶ የጨረሰ ፋሽስት ነው። በቃ ትግሬ ትግሬ ነው። ትግሬ እንዴት የዐማራ፣ ያውም የወልቃይት መሪ አስተዳዳሪ ይሆናል?

"…በኋላ በሰዓታችን መረጃ ቲቪ ላይ ያገናኘን። እኔ ግን ነክሻለሁ ሳላደማ አልፋታም። 💪🏿💪💪🏿

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

😂😂😂

"…እሺ ጎዶኞቼ እንደምን አላችሁ? ፈራችሁ እንዴ? ወይስ ደነገጣችሁ? ወይስ በነገሮች ሁሉ ተደመማችሁ? እህሳ ልቀጥል?

"…ገና እስክንድር በሀብታሙ አፍራሳ በኩል መግለጫ አውጥቶብኝ ከብልፅግና ሊታረቅ ነው እናንተ ምን ሁናችሁ ነው የፈዘዛችሁት?

"…እኔ እኮ ዘመዴ ነኝ። የአሸናፊው የእግዚአብሔር አማኝ። የዳዊት ወንጭፉ፣ ጠጠሩ እኮ ነኝ። ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ የምላትን ወላዲተ አምላክን ይዤ የማላሸንፈው ጠላት የለም።

"…ይሄ ሁላ መንጋ ሲዘምትብኝ አይታችሁ አትደንግጡ። ተራ በተራ ነው አደብ የማስገዛቸው። በተለይ የጎንደር ዐማራ ሾተላይ ከተነቀለ በቃ የዐማራም፣ የኢትዮጵያም መከራ ያበቃል። እሱን ደግሞ እኔ ዘመዴ አክሊለ ገብርኤል ድንግልን ይዤ አደርገዋለሁ። ማርያምን አደርገዋለሁ።

"…አንድ የሚያግዘኝ፣ የሚረዳኝ፣ የሚከራከር የሚሟገትልኝ ሰው አልፈልግም። ብቻዬን ለሚልዮን ፀረ ዐማራ በቂ ነኝ። ያውም በቴሌግራም ጦማር። ድራሽ አባቱን ነው የማጠፈው። በመረጃና በማስረጃ ነው እርቃኑን የማስቀረው። ሰምተኸኛል አባው።

• ልቀጥል ወይ…? 😁

Читать полностью…
Подписаться на канал