zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይርግቧ መልእክት ከምን ደረሰ…? አዲስ አበባ እንዴት አደረች…? የትኛውን ሰፈር ሲበረብሩ አደሩ…? …ፍተሻው ተካሄደ ወይስ ዘለሉት…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት።” መዝ 150፥1

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• አስቸኳይ ነው ብላለች…!  አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• እኔ አንገቴን ልድፋ ላቀርቅልሽ… ኢን THኢ ኔm Oፍ … አለ ኢዩ ጩፋ…! አይዞሽ ገለቴ…! አሜን ነው አሜን… ሃሌሉዣ…

• ለእንግልጣር አፉ ይቅርታ ይሄን ሓላፊነት ሱሬ አይወስድም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጹን እንዳነበባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። የታሰረችውም የወሎ ዩኒቨርሲቲ የ12 ዓመት የማስተማር ልምድ ያላት መምህርትም በተፈጠረው የማኅበራዊ ሚድያ ጩኸት መፈታቷ ተሰምቷል። በሌላ በኩል ኑሮው በብልፅግና ካድሬነቱ ገነት የሆነለት ለዘንዶው እየሰገደ ዓለሙን ይቀጫል።

"…በርዕሰ አንቀጹ ላይ… እናንተስ ምን ትላላችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የብልጽግናዋ ኢትዮጵያ ውሸታም ናት። እንደ ብልጽግና ሴትና ወንድ ሚኒስትሮች በሜካፕ ያበደች ናት። እውነተኛ መልኳ በፌር የተሸፈነ ነው። ደመና ናት የብልጽግናዋ ኢትዮጵያ። የማትጨበጥ ጉም። ሲያዩዋት ክምር ቁልል የጥጥ ተራራ የመሰለች ደመና። እያያችኋት የምትተን ጤዛ ናት የብልጽግናዋ ኢትዮጵያ። ስብሰባ የምትወድ። ሰብሳቢዎቿ ሞዴላ ሞዴል የመሰሉ። የሴቶቹ የፀጉራቸው ርዝመት። የነልካቸው ቱምቡክ ቱምቡክ ኡሙንዱኖ እሹ የመሰለ ፊት መሆን። የወንዶቹ የጺም አቆራረጥ፣ የመልካቸው ማብረቅረቅ፣ የፊጣቸው ማብለጭለጭ፣ ጥራቱ። በቴሌቭዥን መስኮት ሁሉም ተሰብሳቢ እንደ ፋሽን ሾው አቅራቢ አንድ አይነት ልብስ እንደ መንታ ልጆች ለብሰው ሲታዩ በዜና ለሚከታተል የሩቅ ሰው እንዴት እንደሚያጓጉ ልነግራችሁ አልችልም። አውሮጳና አረቡ ዓለም ሳይቀናብን ይቀራል?

"…እውነታው ግን በገሀዱ ዓለም ሃቁ ሌላ ነው። ድሮ ድሮ ለልመና አደባባይ የሚወጣው በቃ ዘመድ ወገን የሌለው። ራዳት አጋዥ የሌለው። መሀን የሆነ፣ ማጠፊያ ያጠረው። ጉልበት የከዳው። ጽኑ ህመምተኛ፣ ተፍተፍ ብሎ መሥራት ያቃተው ሰው ነበር። አሁን በዘመነ ብልጽግና ግን እንደ ድሮው አይደለም። ሁሉም ሰው አደባባይ መውጣት ፈርቶ፣ አፍሮ ነው እንጂ በፍፁም ተጎድቷል። ይሉኝታ ጠርንፎት ነው እንጂ ደህይቷል። ዲግሪ፣ ዲፕሎማውን ይዞ፣ ተመርቆ በቤቱ ሥራ አጥቶ የተቀመጠውን ቤቱ ይቁጠረው። በየቤቱ ያለው ጭንቀት ይሄ ነው ተብሎ አይነገርም። መግለጽም አይቻልም።

"…አደባባይ መውጣት ፈርተው ቢያንስ ገመናችንን ይደብቅልናል ብለው በቀን ከ20 የማያንሱ ሰዎች ወደ እኔ የቤታቸውን ገመና፣ ችግር፣ ሰቆቃ፣ ሰቀቀን በውስጥ መስመር ይልኩልኛል። እኔ ምንም ማድረግ ባልችልም፣ ምላሽ ባልሰጣቸውም የሀገሪቱ ሁኔታ ግን በእጅጉ ያሳስበኛል። የቤተ ሰብ ችግር፣ ጭንቀት መመልከት አቅቷቸው ስደትን እንደ አማራጭ ቆጥረው ከአስቸጋሪ ስደት በኋላ ሊቢያ ደርሰው በሊቢያ ደላሎች እጅ ወድቀው ታግተው ተይዘው እንደገና ብር ከሚጠይቁና ከሚለምኑ ዜጎች ውጪ በየቤታቸው በቀላሉ መዳን እየቻለ በአቅም ማነስ ምክንያት ህመምተኛ ይዘው፣ አልጋ ላይ የዋለ በሽተኛ እየተንከባከቡ፣ የመድኃኒት መግዣ፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ አልፎም ተርፎም የምግብ አጥተው የሚያለቅሱትን የትየለሌ ዜጎች ማየት መስማቱ ራሱ ያሳብዳል።

"…ብዙ ሰው ልብስ ለብሶ ከቤቱ ሲወጣ የደላው ይመስላል። የሞላለት፣ ጠግቦ በልቶ የማይርበው፣ ደስተኛ፣ ጎዶሎ የሌበት፣ ሳቅ ጨዋታ በሽ የሆነለት ይመስላል። ብዙ ሰው እንደዚያ ነው። ነገር ግን እንደርሱ አይደለም። ሰዉ በየቤቱ ሊያብድ እየደረሰ ነው። ቁርስ ሳይበሉ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ተማሪዎች አዲስ አበባ አካባቢ በሁሉም ትምህርት ቤት ይሁን አይሁን አላውቅም እንጂ እንደ ነገሩ ቁርስ እንደሚዘጋጅላቸው ሰምቻለሁ። ወላጆች ግን ቁርስ ሳይበሉ፣ ምሳ ሳይበሉ፣ ወይ ደረቅ ዳቦ በልተው ውለው ማታ በእግራቸው ወደቤታቸው የሚገቡ እንዳሉ ሰምቻለሁ። የቤት እቃ ሽጠው ጨርሰው፣ አራጣም ተበድረው መክፈል አቅቷቸው እያበዱ ያሉ ቤተሰቦችንም ሰምቻለሁ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ እንዲሉ በኦሮሚያ የነበረው ሰው አግቶ ብር መቀበል አዲስ አበባ ገብቶ እገታ ተጀምሮ ሰዉ መግቢያ እንዳጣም ሰምቻለሁ። ከምሬ ነው።

"…የታፈነ ጩኸት ነው በየቤቱ የሚሰማው። በዚያው አንጻር ደግሞ የብልጽግናዋ ኢትዮጵያ ለጥቂቶች ገነት ሆናላቸዋለች። በድነገቴ የሀብት ማማ ላይ የተቀመጡ ሚጢጢ ቢልየነሮችም እንደ እንጉዳይ መብቀላቸው፣ እንደ ችግኝም መፍላታቸው ነው የሚነገረው። የሰው ልጅ አግተው ከዚያ በሚገኝ ገቢ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ የሚሠሩ እንዳሉ ብትሰሙ ትገረማላችሁ። አፋኝ ቡድን አሰልጥነው አሰማርተው ከፖሊስ ጋር በቅንጅት የሚሠሩ፣ አንድ ሰው አግተው ለማስለቀቂያ እስከ 1ሚልዮን ብር የሚጠይቁ እንዳሉም ነው የሚሰማው። ይሄ ኦሮሚያ አይደለም አዲስ አበባ እንጂ። በቅርቡ ይሄ የኦሮሚያ የእገታ ቢዝነስ ወደ ትግራይ ዓድዋ ሄዶ አንዲት ትንሽዬ ልጅ ሚልዮን ሲጠየቅባትም ተመልክቻለሁ። ዜናውንም አስቀርቼዋለሁ። እገታ የንግድ ፈቃድ ያልወጣለት አንድ የሥራ ዘርፍ መሆኑ ነው እየተነገረ ያለው።

"…ምን እገታ ብቻ አፍቃሬ ብልጽግናዎች ለአንዲት ሴተኛ አዳሪ በጨረታ ሁለት ሚልዮን ብር የሚከፍሉ የኦሮሞ ባለ ጊዜዎች እንዳሉም ጭምር OMN ራሱ ሲዘግብም ሰምቼዋለሁ። ፓስተሮችና ኡስታዞችም የሌለ የሀብት ማማ ላይ መፈናጠጣቸውም እየተነገረ ነው። እንደ ጴንጤ ነብያት እና እንደ ወሃቢ ኡስታዞች በፈረንካ ላይ የተንበሸበሸ የለም ነው ነው የሚሉት ምስኪኖቹ። ባንክ ዘርፎ ሚራክል መኒ ነው ተጠቀሙ የሚል እንደመስማት የሚሸክክ ምን አለ? ሀገር ለእነርሱ ብቻ ሆኗል የሚሉም አሉ። ለአንድ አዳር ለግብረ ሥጋ ግኑኝነት 2 ሚልዮን ብር መክፈል ማለትን እንግዲህ አስቡት እስኪ። ገንዘቡ እንዴት ቢገኝ ነው ለአንዲት ሴተኛ አዳሪ ሁለት ሚልዮን ለአንድ አዳር የሚከፍለው? ቢያገባት ራሱ ይሄን ያህል ወጪ ያወጣባታል እንዴ?

"…ብልጭልጩ የብልጽግና ቀለም እውነታውን ሸሽጎታል። በገሀዱ ዓለም ያለው ነበራዊ ሁኔታን ሰውሮታል። በየመንገዱ ህፃናት ያዘሉ ራሳቸው የሆኑ ህፃን ለማኞች በዝተዋል። በቅርብ አጥተው ነጥተው ለልመና እንደወጡ የሚያሳብቅ ያልተጎሳቆለ ፊት ይዘው አውራ ጎዳና የወጡም እናት አባቶች የትየለሌ ናቸው። ዝንጥ ብለው አምሮባቸው በፌስቡክ በማርያም፣ በአላህ ደከመኝ ሥራ ፈልጉልኝ የሚሉም በሽ ናቸው። ገበሬው ከተማ ለልመና መጥቷል። በጦርነት ከደቀቀ አካባቢ የመጡ ምስኪኖችም የቲክቶከር መለመኛ ሆነዋል። የቲክቶክ ልመናው ለጥቂት ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራም ሆኖላቸዋል። አንድ በፌስቡክ ድሆችን በመርዳት የማውቀው በመልካም ሥራው የምቀናበት ልጅ እንኳ ሰሞኑን ከአንድ ሰው ጋር ተመካክሮ የፈጠራ ድራማ ሠርተው የዳያስጶራውን ኪስ ሙልጭ አድርጎ ማጠቡንም ሰምቼ፣ ድራማ የሠራውንም ሰው አይቼው ተደምሜያለሁ።

"…እንዲህም ሆኖ፣ ሥራም ሳይኖር፣ ገቢም ሳይኖር፣ ጥቀቶች ሥራም ሳይኖራቸው በቀን 20 ሺ ብር እያጠፉ በሚውሉባት ሀገር፣ ደካሞች በአቅማቸው ከሆቴል ቤት ተርፎ የተጣለ ትርፍራፊ ጉርሻ እየገዙ በሚበሉበት ሀገር ያው የምስኪኖች ፍርፋሪ መልቀሚያ ሰፈር መንደር እየፈረሰ ነው። በምስኪን፣ በደሳሳ ሰፈሮች ውስጥ እንዴት የሺዎች ሆድ እረፍት አግኝቶ እንደሚያድር በድሆች ሰፈር ያደገ ያውቀዋል። ስንቱን መካከለኛ ገቢ ያለው ኗሪ ቀጥ አድርጎ የያዘ የምስኪኖች ሰፈር እንዳለ ቢታወቅ መልካም ነበር። የመንግሥት ሹፌሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የባንክ ሥራ አስኪያጆች፣ አርቲስቶች፣ ሹፌሮች ከነ ረዳቶቻቸው፣ የቀን ሠራተኞችን ሆድ ሸክፈው የያዙ ስንትና ስንት ደሳሳ የድሀ መንደሮች፣ ኮንቴነሮች ነበሩ መሰሏችሁ። የሚጨንቀኝ አሁን የመዘጋጃ ቤት ሠራተኞች ፒያሳ ሙሉ ለሙሉ ሲፈርስ የት ይገባሉ? የሚለው ነው። ከምር ይጨንቃል።

"…አስታውሳለሁ አንድ ጊዜ መርካቶ የሥራ ቦታው የሆነ ተክሌ ሴራ የሚባል ወዳጃችንን እኔና ጓደኛዬ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ ፒያሳ እናገኘዋለን። ወዴት እየሄዳችሁ ነው ይለናል። ምሳ ሰዓት አይደል? ምሳ ልንበላ እንለዋለን። እኔም ምሳ ልበላ ነው የት ነው የምትበሉት ይለናል። ሲኒማ አምፔር ጋር ሆነን በአመልካች ጣታችን እያሳየነው አርሾ መዞሪያው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚባል ምግቤት እንለዋለን። እርሱም አለን ለምን እዚያ ትበላላችሁ? ኑ ዛሬ እኔ ልጋብዛችሁ ብሎ እሱም እዚያው ሲኒማ አምፔር ጋር ቆሞ ፊት ለፊት እያሳየን…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አትርቅም።” ምሳ 17፥13

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• መንዙማስ ነበረው…? ወረብ ደግሞ ክልክል ነው። ከካፊር ጋር ምን ዓይነት ጸሎት ነው እነ ሙጂብ አህመዲን የጸለዩት።

"…የቸገረ ነገር ነው የገጠመን እኮ ጎበዝ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዘመቻ ሚጀር ጀነራል ውባንተ አባተ
          መታሰቢያ ድል በሸዋ
                🔥🔥🔥

"…ረጅም ሰዓት የፈጀ የስልክ ስብሰባ ላይ ተሳትፌ ወደ መንደራችን ስመለስ በመልእክት መቀበያ ሰንዱቄ ውስጥ የሸዋ ፋኖን ድል እና "ዘመዴ ዛሬ ሞጣ ወጥሮ ይዞሃል፣ የሰማዕቱ ስመኘውን የተሰበሰበ ዶላር በልተሃል እያለ እየረገጠህ ነው የሚሉ መልእክቶችም ይገኝበታል። ወፎቼን የሞጥሻን ቅዱት ብዬ አስቀድቼው እያደመጥኩት ነው" አዎ ብሩ ተሰብስቧል እውነት ነው። እና የተሰበሰበው ብር ግን የት ደረሰ? ለስንት ሰውስ ነበር የተሰበሰበው? ብሩስ አሁንስ በማን እጅ ነው ያለው? ለምን ለተጎጂዎቹ በጊዜ አልደረሰም? ባይቸኮልበት ጥሩ ነበር። ነገር ግን የግድ ከተባለ ግን ብሩ እጁ ላይ ያለውን ሰው በማክሰኞው በተለመደው የቲክቶክ መርሀ ግብራችን ላይ ይዤው ከች እልና የእነ ሞጣን የብአዴን ቦለጢቃ አፈርደቼ አበላዋለሁ። እስከዚያው ሲበጠረቁ ቅዱልኝ። አበደን በገንዘብ ጉዳይ ዘመዴን ማግኘት አይቻልም። አበደን አልኩህ። ስለእሱ አታስቡ።

ይልቅ ወደ ድል ዜናው እንሸጋገር።

"…ትናንት ሌሊት ከአዲስ አበባ በ130 ኪሜ ርቀት ላይ በዐማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በተሠራ ድንቅ ኦፕሬሽን አንድ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆነ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሥልጣኑን ተጠቅሞ የአማርኛ ትምህርት በተቋሙ እንዳይሰጥ ያገደ፣ የታሪክ ዲፓርትመንትን ያገደ፣ የተቋሙን በጀት ለ"መከላከያ" ያዋለ፣ ተቋሙን እንደ ማሰልጠኛ እና ካምፕ እንዲያገለግል የፈቀደ፣ የግቢውን ታሪካዊ ነገሮች በሙሉ ያፈረሰና እያፈረሰ ያለ ከየትኛውም የብልፅግና ከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ አመራሮች ያልተናነሰ ነውረኛ ተግባር በዐማራነት ላይ የፈፀመ ባንዳ ዶር ንጉሥ ታደሰን የዐማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በቁጥጥሩ ስር አውሎታል። ደብረ ብርሃን እኮ ሸገር አፍንጫ ሥር ነው።

•እህ💪

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የምንጠብቀው አንድ ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። ከምስጋናው በመቀጠል እንደተለመደው የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ጥያቄ ነው የሚሆነው። ሃኣ… ጎዶኞቼ ሆይ በጥያቄ መልክ የተዘጋጀውን የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ አንብባችሁ መለስ ለመመለስ ዝግጁ ናችሁ…?

• አንድ 100 ያህል ጓደኞቼ ተንፒሱ እስቲ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የማትሻር፣ የማትቀየረዋ የኦሮሙማዋ ሊቅ ባልተሠራ ቅንጭላት የተሠራ ከተማ አፍራሿ አዴ አዳነች አቤቤ የተከበረችዋ ከንቲባዋ እና ምስኪኗ የዐማራዋ ገበሬን ባነጻጸርን ግዜ… ለአራዳው፣ ለብልጡ አዲስ አበቤ አለቀስነ። ዐማራን ለምን እንደሚጠሉት፣ ለምንስ እንደሚያርዱት፣ ለምን እንደሚያሳድዱት ልነግርህ ፈልጌ ነበር። አዛኜን ትፈነዳታለህ እንጂ አልነግርህ።😂

"…ስማ ነገርኩህ ዐማራ አይደለም ቆሞ ሞቶ ይበልጥሃል ስልህ…!… ምኒልክ ዛሬም ንጉሥ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ይጀምራል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉በዩቱብ /YouTube
https://www.youtube.com/live/D1Jdb6d1Yf8?si=aQF6sHWU1vo7sDp5

👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v4m2h36--ethiobeteseb.html

👉በፌስቡክ Facebook
facebook.com/ethiobeteseb

👉 በቲውተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb

👉 ቴሌግራም / Telegram
/channel/ethiobeteseb

ደግሞ መጣን እስቲ ገባ ገባ በሉ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ጋር ይዞ እየተጋፈጠ ነው። ጨዋታው ይህ በቁጥር ብዙ ሰፊ የሆነ ነገር ግን ብዙው 95%ቱ በአብዛኛው የትናንቱን ግፍ በቶሎ የሚረሳና በዚሁ ምክንያት ጀዝባ፣ ሾርት ሚሞሪያም ተብሎ የሚሰደበውን ሕዝብ በማንቃት ከዘራፊ፣ ሜካፓም የሮብዓም ጓደኞች ጋር ማጋፈጥ ነው። በሙያ በመርህና በተግባር ነገሮችን የሚለካው ሕዝብ እውነቱን አውቆ ወይ በተግባር ከዐማራ ፋኖ ጋር ይሰለፋል አልያም ወይ በሆዱ ከአራጅ የሮብዓም ሰራዊት ጋር ይሠለፋል። አሉባልተኛውንና ባለሾርት ሚሞሪውን ከዥዋዥዌ እንዲወጣ መሥራት ብቻ ነው አሁን የሚያስፈልገው። (የ1000 እናቶች ቤት በዶዘር ሲፈርስ ዘራፍ ብሎ ሲያበቃ የአንዲት እናት ቤት በአዳነችና አብይ ዶማ ፈርሶ ሲታደስ ልቡ ፍስስ የሚለውን አሉባልተኛና ባህላዊ፣ በሴፍቲኔት ዘይት ጉልበቱ ሽባ የሆነን ሕዝብ ይበላሃል፣ ይበለሃል ጅቦ እያሉ ማሳየት ነው።

"…የአብይን የአሉባልተኝነት መንገድ ለማክሰም ተራ ሰው መሆን ይጠይቃል። የወረዱና የረከሱ ሃሳቦችን ማንሳትና መተንተን ይጠይቃል። ሃሜተኛና አሉባልተኛና ባህላዊ ሆኖ መምጣትን ይጠይቃል። እንደሱ ጨካኝ፣ ክፍት አፍ ባለጌ መሆንን ይጠይቃል። አሳዳጊ የበደለው ቦርኮ መሆንን ይጠይቃል። ይሄን ተርካሻ ሰው ለማስወገድ ትህትና፣ ትሁት መሆን አሸናፊ አያደርግም። ለጨካኝ ብልፅግና ጨካኝ መሆን ብቻ ነው መፍትሔው። እሾህን በእሾህ። ይህን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ በአንድ ቀላል መንገድ ብቻ ነው። በእለት ተእለት እጀንዳ አደንዝዞ ሕዝቡን በቃል ሲያደነዝዘው፤ የራሱን ተቃራኒ ሓሳብና መሬት ላይ የሠራውን ሥራ በቪዲዮ ማስታወስ ሲቻል። እንጂ ባልተጨበጠ፣ መሬት ላይ በሌለ ሰበካ ርብዓም አቢይ አይሸነፍም።

"…ይሰመርበት በቀን ሦስት ሺህ የዐማራ ነፍስ በኦሮሚያ ወለጋ ጨፍጭፎ ሲያጸዳ፣ በሻሸመኔ፣ በቤኒሻንጉል በመላው ኢትዮጵያ በገዳማት፣ በመነኮሳት፣ በሾፌሮች፣ በታዋቂ ሰዎች እልቂት ቢያንስ መግለጫ ቢሰጥ፣ የኀዘን ቀንም ቢያውጅልን ብሎ ለሚጠብቀው ባለ ሾርት ሚሞሪያም ሕዝብ ምናባታችሁ ታመጣላችሁ? የምን የኅዘን ቀን ነው። ሞት ብርቅ ነው እንዴ? ገና ትሞታለህ። ገና ቤተ ክርስቲያንም መስጊድም ይፈርሳል እያለ ሲያላግጥብህ ባላየ ባልሰማም እያለፈ ስድስት ዓመት ሙሉ በቁስልህ ላይ እንጨት ሲሰድ የነበረው ሰውዬ ነው ሰሞኑን ባልተለመደ መልኩ በራሱ የፌስቡክ ገጽ፣ በፋና እና በኢቲቪ በተከታታይ የስብሰባና የውይይት ናዳ እየለቀቀብህ የሚገኘው። ይህ የሳክስ ናዳ የተጀመረው አዲስ አበባ እንድትፈርስ ትእዛዝ በሰጠበት ሳምንት መሆኑንም አትዘንጉ እንጂ እናንት ሾርት ሚሞሪያም አዲስ አበቤዎች።

"…ዳንኤል ክብረት ያመጣለት አስማተኛ ጠንቋይ ከባድ ነው። ፓትርያርክ አሰድቦ፣ ጳጳሳትን መዥልጦ፣ መነኮሳትን አሳርዶ፣ ካህናትን ከነቤተሰባቸው አስጨፍጭፎ፣ 6 ዓመት ሙሉ የሠራው የዘር ማጥፋት ወንጀል በአንዲት አጭርና አስማጭ ንግግሩ እንዲረሳለት፣ እንዲድበሰበስለት ያስደርገዋል። ምን ዓይነት አዚም ነው? አትበለኝ። ዳንኤል ክብረት ከምን ዓይነት አስማተኛና ሟርተኛ ጠንቋይ ጋር ነው አገናኝቶ እንዲህ አንድ ተራ የበሻሻ አራዳ መፈንጫ ያደረገኝ አትበለኝ። አዲስ አበቤ ዕድለኛ ነው። ወዲያው ወዲያው እየተጽናና ነው። ፒያሳን አፍርሶ ወዲያው ሳያጽናናው ወደ ሜክሲኮ አይሻገርም። በፍጹም። ነጥሎ ነው ነጣጥሎ የሚበላው። ሰሞኑን እናቶች በቲክቶክ፣ በዩቱዩብ ሲያለቅሱ ዓይቶ አዳናች አቤቤን ጠርቶ እናቶችን አታስለቅሱ አለ። ዛሬ ደግሞ እናቶች፣ ሴቶች የተባሉ ጠርቶ ማነጋገሩ ሳይሆን ሴቶችን እንዳነጋገረ ለሾርት ሚሞሪያሙ ለአማርኛ ተናጋሪው በአማርኛ ቋንቋ እና ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ደግሞ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተረከው። ይሄን ርዕሰ አንቀጽ አንብቦ በኦሮሚኛ ካልጻፈው በቀር ለወትሮው እንደሚያደርገው በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዝኛ ሳይሆን ኦሮሞ ኮዱ ስለሚገባው ሳይገባው ቀርቶም ጓ እንዳይልበት ዘልሎታል። ይኸው ነው የዛሬ ርዕሰ አንቀጼ። ሓሳብ አስተያየታችሁን አደራጅታችሁ አዘጋጅታችሁ ቆዩኝ። እስከዚያው ሻሎም ሰላም…!

• ድል ለአዲስ አበባ ሕዝብ…!
• ድል መድረሻ ላጣው ለአዲስ አበባ ሕዝብ…!

"…ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"
1ኛ ነገ 12፣ 3-19።
2 ዜና 10፥1-19

"…በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን የእስራኤሉን ሮብዓም እና የኢትዮጵያውን አቢይ አህመድ በንፅፅር እንመለከታቸዋለን። ሁለቱም ለሕዝብ እና ለሽማግሌ ያላቸውን ንቀትም እንመለከታለን። የሁለቱም መጨረሻ እንዴት እንደሚመሳሰልም እንተነብያለን።

"…በአፍላ ጉርምስና በዘመነ ፍንዳታ ወደ መንበረ ሥልጣኑ ለመጣው ሮብዓም ኢዮርብዓምና የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ መጥተው፦ "አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፤ አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ፥ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቃልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን ብለው ተናገሩት።" ሽማግሌዎች አረጋውያን ናቸው እንዲህ የሚሉት። ልክ አቢይ አሕመድን አረጋውያን ዕድሜ ጠገቦቹ፣ ክፉ ደግ ያዩት፣ ያለፈውን ሥርዓት ይቀይርልን ይሆናል፣ አጋዳዩን የመርዝ ብልቃጥ ሕገ መንግሥት ተብዬ ሕገ አራዊት ይሽርልናል ብለው ተስፋ እንዳደረጉት ማለት ነው። ገሚሱ ክብሩን ሁላ ጥሎ ከእግሩ ስር ተደፍቶም አልነበር? እንደዚያ ነው ሙሴአችን አሻግረን… እንዳሉት እርሱም አሻግራችኋለሁ እንዳላቸው ማለት ነው።

"…እርሱም፦ ሂዱ፥ በሦስተኛውም ቀን ወደ እኔ ተመለሱ አላቸው። ሕዝቡም ሄዱ። ንጉሡም ሮብዓም፦ ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ። እነርሱም፦ ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸውም፥ መልሰህም በገርነት ብትናገራቸው፥ በዘመኑ ሁሉ ባሪያዎች ይሆኑልሃል ብለው ተናገሩት። ይሄ የሽማግሌዎች ምክር ነው። እታዘዛችኋለሁ፣ አገልግላችኋለሁ፣ እንደ ንጉሥ ሳይሆን እንደ ባርያ እሆንላችኋለሁ በላቸው አሉት አረጋውያኑ። እንዲያ ካልክ ሕዝቡ ባርያህ ይሆናል። አንተም ረዥም ዘመን ትገዛለህ። ዘመንህም ዘመነ ሰላም፣ ዘመነ ፍስሀ ይሆናል።

"…እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ። እርሱም፦ አባትህ የጫኑብንን ቀንበር አቃልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? አላቸው።" …ነገር የሚበላሸው እዚህ ጋር ነው። ሽማግሌዎቹ የመከሩትን ትቶ ጎረምሶች፣ ወጠጤዎች፣ የጂም ቤት ጓደኞቹን፣ የጅማ የእረኝነት ዘመን፣ የኢትዮ ኤርትራ የውትድርና ዘመን፣ ሚንስትር እያለ፣ ፍንዳታዎቹን፣ የቸርች ጓደኞቹን ወደ ማማከር ፊቱን አዞረ። ምን ትመክሩኛላችሁ አላላቸውም…? ጉድ እኮ ነው።

"…ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች፦ አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፥ አንተ ግን አቃልልልን ለሚሉህ ሕዝብ፦ ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች። አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችኋል፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችኋል፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ በላቸው ብለው ተናገሩት። "…የፍንዳታ ምክር ድሮም ከዚህ አያልፍም። ጉልበት፣ አረመኔነት፣ ጨካኝነት ተፈሪ፣ የምትከበር፣ የምትፈቀር ያደርግሃል ብለው ነው የሚያስቡት። ሴት ልጅ እንድታፈቅረው ብሎ አሲድ የሚደፋባት፣ ፊቷን በምላጭ የሚተለትላት፣ በቦክስ አይኗን፣ በቴስታ ጥርሷን የሚያረግፍላት፣ በርግጫ ኩላሊቷን የሚያፈርሰው ጎረምሳ ለመፈቀር፣ ለመከበር፣ ለመወደድ ብሎ እንደሚያደርገው ማለት ነው። ፍቅር በዱላ፣ በሜንጫና በግሬደር ቤት በማፍረስ ይገኛል እንዴ? እናም የሮብዓም አማካሪ ወጠጤዎችም ለሮብአም ሁን ብለው ያሉት የመከሩትም "ጨካኝ ሁን" ነው።

"…ህወሓት መሩ ኢህአዴግ ትንሽ ሰው ገድሎባችሁ እንደሆነ እኔ በጅምላ እፈጃችኋለሁ። ለአስከሬናችሁ ጥላ ይሆን ዘንድ በመቃብራችሁ ላይ ችግኝ እተክልላችኋለሁ። ህወሓት መሩ ኢህአዴግ በዱላ ቀጥቅጧችሁ ከሆነ እኔ በሜንጫ እጨፈጭፋችኋለሁ። በየከተሞቻችሁ በድሮን፣ በጀት አወድማችኋለሁ። አባቴ ወያኔ ጥቂት ቤቶች አፍርሶ ከሆነ እኔ ሙሉ ሀገር፣ ሙሉ ፒያሳና መርካቶን አፈርስላችኋላሁ። አናታችሁንም እናታችሁንም በጥይት አፈርሳለሁ። መድረሻ አባታችሁን ነው የማሳጣችሁ። በራብ በጠኔ እፈጃችኋለሁ። በግብር በታክስ አስጨንቃችኋለሁ። የሌለ ከዚህ በፊት ያላያችሁትን የተለየ ጭካኔ አሳያችኋለሁ። ከደርግም፣ ከወያኔም የእኔ ደግሞ ይብሳል በላቸው እንዳሉት ቁጠሩ።

"…ንጉሡም፦ በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ ብሎ እንደ ተናገረ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ። ንጉሡም ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ለሕዝቡ ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው። እንደ ብላቴኖችም ምክር፦ አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ ብሎ ተናገራቸው። ይኸው ነው። ሕዝብ ምን ያመጣል? ሽማግሌ ምንአባቱ። ዘመኑ የእኛ ነው። እኛ ደግሞ ወጣቶች ነን። ሁሉ ነገር የሚፈታው በጥበብ ሳይሆን በጉልበት ነው። እንዲህ ነው የጎረምሳ ምክር።

"…ለዚህ ነው በአቢይ አሕመድ መንግሥት ውስጥ አንድ ምራቅ የዋጠ ትልቅ ሰው የምታጡት። የአቢይ ሚንስትሮችን ሁሉንም ሴቶቹ ያያችሁ እንደሆነ ከአዕምሮአቸው ይልቅ መቀመጫቸው የሚያድግ፣ ከሜካፕ ውጪ ሰው የማይመስሉ፣ ዊጋም፣ ሜካፓም፣ ደንደሳም፣ የሐረር ሰንጋ የመሰሉ ድልቦች፣ በአብዛኛው ወሴዎች፣ የማይናገሩ፣ የሳሎን ውሾች። ወንዶቹ በሙሉ ሜካፓም ጎረምሶች፣ ቤተሰብ የሌላቸው መንገደኞች፣ መደዴዎች ናቸው። ሲበዛ ቀጣፊ ሐሰተኞች፣ ደም አፍሳሽ፣ ርኅራሄ ያልፈጠረባቸው አረመኔዎች።

"…በመጨረሻም እግዚአብሔርም በሴሎናዊው በአኪያ አድርጎ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ነገር እንዲያጸና ከእግዚአብሔር ዘንድ ተመድቦ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም። እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ፦ በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን ቤትህን ተመልከት ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደ ድንኳኖቻቸው ሄዱ። በሮብዓም ጥጋብ የእስራኤል መንግሥት ለሁለት ተከፈለ ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ። ዛሬም እንዲሁ ነው። በኦሮሞው ደርግ በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ጥጋብ እና ጉልበት በመለስ ዜናዊዋ ህወሓት ሴራ ኤርትራ፣ በመንግሥቱና በመለስ ዜናዊ ልጅ በኮሎኔል አቢይ አህመድ ድድብና እና ጥጋብ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ስንት ቦታ እንደምትከፈል እንጃልን።

"…በመጨረሻም… ይላል መጽሐፍ ቅዱስ ንጉሡም ሮብዓም አስገባሪውን አዶኒራምን ሰደደ፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ደበደቡት፥ ሞተም። ንጉሡም ሮብዓም ፈጥኖ ወደ ሰረገላው ወጣ ወደ ኢየሩሳሌምም ሸሸ። እስራኤልም እስከ ዛሬ ድረስ ከዳዊት ቤት ሸፈተ። 1ኛ ነገ 12፣ 3-19።

"…ቀጥሎ አሁን የኢትዮጵያም ሕዝብ በአረመኔው አቢይ አሕመድ ላይ የሚወስደው እርምጃ ነው የሚጠበቀው። ልክ እንደ እስራኤል የሮብዓምን ካድሬዎች፣ ሚኒስትሮች በድንጋይም፣ ባገኙት ነገር ሁሉ ቀጥቀጠው በመደብደብ እንደገደሉ፣ እንዲሁ በብልጽግናው ሮብዓም በአረመኔው እቡይ አህመድ ጀሌ ካቢኔዎችም ላይ ይፈጸማል። በዐማራ ክልል የሮብዓም እቡይ አህመድ መልእክተኛ ብአዴን በድንጋይም በጥይትም መገደሉ የዚሁ ታሪክ ምሳሌ ነው። በኢትዮጵያችንም ርኩሰትን፣ አምልኮ ጣኦትን፣ ጭካኔን፣ ግድያን፣ እገታን ያስፋፋው፣ ጨካኙና የልበ ደንዳናው የአረመኔው የሮብዓም መጨረሻውንም መጠበቅ ነው። ኢትዮጵያስ በአረመኔው በእኛው ሮብዓም ዘመነ መንገሥት ከስንት ትከፈል ይሆን?

"…ሮብዓም እቡይ አሕመድ አዲስ አበባ ላይ ልክ እንደ ኦሮሚያ እና…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…አቤቱ፥ ግፍንና ጠብን በከተማ ውስጥ አይቼአለሁና አስጥማቸው አንደበታቸውንም ቍረጥ።” መዝ 55፥9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

• የፊት ዳር ኮሪደር ፕሮጀክት…

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አስቸኳይ ነው
ለአዲስ አበባ ዐማሮች…!

"…ዘሬ ምሽት ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ፋኖዎች ይገኙበታል ተብሎ በሚታሰብና፣ የጦር መሳሪያ ይኖራቸዋል ተብለው የሚታሰቡ የዐማራ ተወላጆች ቤት ላይ ኦፕሬሽን ይሠራል። እናም ከመሸ ስለሆነ ትእዛዝ የወረደልን መረጀውን በቶሎ አድርስ ብለውኛል።

• ዛሬ ሌሊት የአዲስ አበባ ዐማሮች ቤት በኦሮሙማው አራዊት ይበረበራል። ወርቅ፣ የከበረ ማዕድን፣ የውጭ ሀገር ገንዘብም ይዘረፋል። ውድ ውድ ሞባይልም ይነጠቃል።

• ዐማሮች ሰምታችኋል…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጥያቄ ነው…?

"…እንዳትቀየሙኝ ጥያቄ ልጠይቅ ነኝ። በዚህ ዘመን፣ በአሁን ጊዜ፣ በዚህ ወቅት፣ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘና ፈታ ፏ ሽር ብትን ብሎ ተንደላቅቆ የሚኖረው ማነው?

"…ከፍሮፌሰር፣ ከዶፍተር፣ ከኢንዢኔር፣ ከወጥቶ አደር፣ ከኮለሮኔል፣ ከፖርሶኔል፣ ከማናዠር እና ከቲክታቶከር ማነው ያለሰቀቀን የሚኖረው…? ሃኣ…?

• ከቲክታቶከር አቢይ እና ከፌስቡከር አዳነች ጋር አላልኩም። እነርሱ ኦርጋና ኦርገ ኦርገናይ አርጋገጋገና ኤጭ ኦርጋናይ ቢቀርብኝስ He are…😂😂😂

"…መልሱልኝ ከፍሮፌሰርና ከቲክታቶከር ማነው ዘና ፈታ ብሎ ዱባይ እየተመላለሰ የሚኖረው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ክብረ ቢሱ EBC

"…ጋዜጠኛ ታ ፋዬ ወልደ ሥላሴ EBC የብልፅግና መንግሥቱን ገመና ለመሸፈን ከመጣደፉ በፊት ዜናውን ሙያው በሚፈቅደው ሥነ ምግባር ሠርቶ በፌስቡክ ገፁ ለጥፎት ነበር።

• ሥራ ለምን ለቀቅሽ?
~ አሞኝ ነው ታምሜ ነበር ያለችው። በቃ ሴትየዋ መንግሥትን አልከሰሰችም። ዩኒቨርስቲውን አልከሰሰችም። አልወቀሰችም። አሞኝ ተቸገርኩ፣ ራበኝ፣ እርዱኝ ነው ያለችው። ይሄ ምን ያሰድባል? ምንስ ያስወቅሳል?

"…ዜናው ከተሠራ ከ5 ሰዓት በኋላ የመጣው EBC ወሎ ዩኒቨስቲ ደውሎ የሠራውን ዘገባ ተመልከቱትማ። ወደ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደውዬ እውነታውን አጣርቻለው በማለት እጅግ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ ዘገባ ነው የሠራው።

"…ይህች እህት "ወሎ ዩኒቨርስቲ 12 አመት ልምድ አለኝ" አለች እንጂ ዩኒቨርስቲው አባረረኝ ወይም ከሥራ ገበታ አፈናቀለኝ አላለችም። በተቋሙ ላይ ምንም ክስ ይሁን አሉባልታ አላነሳችም። የዩኒቨርስቲው ተወካይ ነኝ ያለውም ሰው እንደምትሰሙት የዚህችን ሴት ችግር ያስረዳበት ቋንቋ ከትልቅ ተቋም የማይጠበቅ ከመሆኑም በላይ በምስጥር ሊጠበቅ የሚገባ የግል ጉዳይ ሁሉ "የአዕምሮ ታማሚ ነች" ከዚያም "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" የሚሉ ቃላት በመጠቀም የግለሰቧን የግል ምስጢሮች በአደባባይ አዝረክርኳል - ዝርክርክ ተቋም - ዝርክርክ ሚዲያ።ነውረኛ እና በጣም አሳፋሪ ሚዲያ - EBC

"…እጠይቃለሁ በአሁን ሰዓት ከሌባ፣ ከዘራፊ በቀር ጋዜጠኛ፣ ፕሮፌሰሮች፣ የህክማና ባለሙያ ዶክተሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ኑሮ ነው እየኖሩ ያሉት? የቤት ኪራዩ ከደሞዙ ያልበለጠበት አለ? ባልና ሚስቶች በኑሮ ውድነቱ ምክንያት እየተፋቱ አይደለምን? የሚገርመው በቅርቡ የዩኒቨርስቲው አስተማሪም ሆነ የ EBC ጋዜጠኛው ለህክምና ብለው የልመና አቁፋዳቸውን ይዘረጋሉ።

• ቲሽ ጨቅላ ሁላ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ተከተሉን አለን። ተከተልነው።

"…ከንብ ባንክ ጎን ይመስለኛል ወደ መንደር ውስጥ በሚያስገባ ደረጃ ይዞን ወረደ፣ ጉራንጉሩን በእግር ፈጨነው። የተሰጣ ልብስ፣ የተሰጣ ሽሮ እያለፍን፣ አነስተኛ የቀበሌ ቤቶችን እየታከክን፣ ስንትና ስንት ጎሬ እያለፍን ተከተልነው። ተክሌ ሴራ ሃይማኖተኛ፣ በጣም መልካም ሰው፣ የምናከብረው የምንወደውና የማናምነው ሰው ባይሆን ኖሮ በዚያ ጉራንጉር እየተሽሎኮለክን ሲወስደን አንከተለውም ነበር። ማጅራት ሊያስመታን ነበር የሚመስለው። አይዟችሁ ደርሰናል እያለ ከፊት ከፊት እየመራ ወሰደን። እኔና እንግዳ መጨረሻ ጉዱን እንይ ብለን ተከተልነው። ከስንት ልፋት በኋላ ደረስን።

"…የቀበሌ መኖሪያ ቤት ነው። ሰፊ ሳሎን እና በረንዳ ቢጤ አለው። እኛ ስንደርስ ሱፍ ልብስ ግጥም አድርገው የለበሱ ደህና ደህና የሚባሉ ሰዎች ተቀምጠው እየበሉ ነው። ድግስ ቤት እንጂ ምግብ ቤት አይመስልም። የሆነ ማኅበር ወይ ዝክር ነው የሚመስለው። አብዛኛው ሰው ፓስታ በእንጀራ፣ መኮረኒም በእንጀራ፣ ጥቂት ሰው ደግሞ በየዓይነቱ ምግብ አዟል። ተክሌ ይሄ ነው ምግብ ቤቱ አለን። ፓስታቸው ጣፋጭ ነው እዘዙና ቅመሱ አለን። አዘዝን፣ ቀመስን አይደለም በላነው። ደገምነው። ሒሳቡን እንክፈል ብንለውም ጋባዥ እኔ ነኝ ብሎን ጋብዞን ተለያየን። ከዚያ በኋላ እኔ ራሴ ስንት ሰው እዚያ ቤት እንደጋበዝኩ አትጠይቁኝ።

"…በዚያ ምግብ ቤት ያየናቸው ሰዎች በሙሉ የባንክ ማናጀሮች፣ የወርቅ ቤት፣ የቡቲክ ባለቤቶች፣ የታክሲ ሹፌሮች፣ አርቲስቶች፣ የመዘጋጃ ቤት ሠራተኞች፣ ከመገናኛ፣ ከመርካቶ፣ ከአራት ኪሎ ድረስ የሚመጡ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሁላ መሆናቸውን የነገረን ተክሌ ሴራ ነው። እርሱም ከመርካቶ ቦንብ ተራ ሱቁ ፒያሳ ድረስ አምጥቶ በዚህ ጉራንጉር ውስጥ የሚያስመግበው የምግቡ ጥራት እና ኪስ የማይጎዳው ተመጣጣኝ ዋጋው ነው። ምግብ ቤቱ ከሰፈሩ ውጪ ማስታወቂያ የለውም። አንዱ ላንዱ ነግሮ ነው በአፍ ማስታወቂያ ጉራንጉር አልፎ ሰው የሚመገበው። እንዲህ ዓይነት ቤቶች በየቦታው ነበሩ። ብሔራዊ ቲያትር ቤት አካባቢም አስታውሳለሁ። እኔ ሰፈር ደጃች ውቤም ሸራተን የሚባል ምግብ ቤት እነደነበረም አስታውሳለሁ። ታዋቂ ዘፋኞች ሁላ ነበር የሚጠቀሙበት ቤት። ልዩ፣ ልዩ፣ ልዩ ቀን የሚለው አዝማሪ ሄኖክ የሚባል ቀጫጫ ዘፋኝ እዚያ ቤት ነበር የማውቀው።

"…እንደነዚህ ዓይነት ገበና ከታች ቤቶች ሲፈርሱ፣ ሲወገዱ ተጎጂው ደሀው፣ ዝቅተኛው ማኅበረሰብ ነው። ፒያሳ ከነቆሻሻዋ ትኑር የሚል እምነት የለኝም። የሆነው ሆኖ በዚህ ክፉ የሙሰኞች ዘመን ፋብሪካ መገንባት እና የሥራ ዕድል መፍጠር ቀርቶ መናፈሻና ህንጻ እያቆሙ፣ እየገሸሩ ለላንቲካ አስፓልት ግድግዳ ቀለም እየቀቡ ሀብታም ሀብታም በሚጫወቱበት፣ ሙላው ማኅበረሰብ ከድህነት ወለል በታች በሚኖርበት ዘመን የባሰ ቀውስ፣ ምስቅልቅል ይፈጥራል።

"…ብልጽግና ቆሻሻ፣ ለማኝ፣ ደሀ ማየት እንደማይፈልግ የታወቀ ነው። ደሀን የሥራ ዕድል ፈጥሮ መቀነስ አይፈልግም። ደሀን ማጥፋት የሚፈልገው በጦርነት፣ በራብና በችጋር ነው። ኢንቨስት የሚያደርገውም ቦንብ፣ ጥይት በመግዛት ነው። የብልጽግና ተድህነት መቀነሻው ህዝቡን በመጨረስ ነው። የዐማራው ሳይቆጠር በትግራይ ብቻ ስንት ዜጎች ተቀነሱ፣ በዐማራ፣ በአፋር፣ በሱማሌ፣ በደቡብ፣ በጋንቤላ፣ በቤኒሻንጉል ስንትና ስንት ዜጎች ተቀነሱ? በኦሮሚያማ አይነገርም።

"…ዛሬ አንዲት ባለ ዲግሪ አልቻለችም ቸግሯት ለልመና አደባባይ ወጣች። አንዱ ፎቶ አንሥቷት በፌስቡክ ለጠፋት። ቫይራል ሆነ ፎቶው። ወዲያው ፌስቡክ ላይ ተጥዶ የሚውለው የጠቅላይ ሚንስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪው ዳንኤል ክብረት ክብረት አየው። አይቶም ዝም አላለም ለፖሊስ መመሪያ ሰጥቶ በአስቸኳይ ገፅታችንን የምታበላሽ ናትና እሰሯት ብሎ በማዘዝ ሴትየዋ ተሰረች ነው የሚሉት። አይቻልም ዘንጦ መለመን አሏት በቃ።

• ከካድሬ በቀር አሁን በኢትዮጵያ ያልቸገረው ማነው? በየቤቱ ያለውን ሰቆቃ ከፈጣሪ በቀር የሚያውቅ ሌላ አለን? ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? በራብ መሞት ወይስ በሰይፍ መሞት? የትኛው ይቀላል?

"…ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እንደ ሁል ጊዜው አንድ ሺ አመስጋኝ ዘሬም ደስ እያለው እግዚአብሔር ይመስገን እያለ አመስግኗል። ከምስጋናው በኋላ የተለመደው ጥያቄ ይከተላል። ጥያቄው አይቀርም። ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብና እናንተም ሓሳባችሁን ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ ወይ…? የሚለው ጥያቄ ነው።

"…አዎ ለዛሬ ያዘጋጀሁት ርዕሰ አንቀጽ በራያና በወልቃይት ጉዳይ፣ በብአዴንና በህወሓት በኩል ያለውን ድራማ ለማሳየት ነበር። ኋላ ግን ይህቺ ምስኪን ምሁር ሴት ቸግሯት ለልመና ብትወጣ በልፃጊው ሜካፓም የኦሮሙማ አገዛዝ መለመን አትችዪም። በራብ ተቆራምዶ መሞት እንጂ የምን ልመና ነው በማለት ወደ ዘብጥያ እንዳወረዳት ስሰማ ስለ አዲስ አበባ ድህነት፣ ስለ ዜጎች በየቤቱ መጎሳቀል ጻፍ ጻፍ አለኝና ቀኝ ትከሻዬን ሲሸክከኝ ጊዜ ጻፍኩት።

• እህሳ አዲስ አበቤ ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የግድያ ዜና

"…የካቲት 17/2016 ዓም እሁድ ንጋት ላይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ኢሉ ወረዳ በአስጎሪ ርጳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ካህናቱ ጸሎተ ኪዳን አድርሰው ቅዳሴ ሊገቡ ሲሉ የታጠቁ የኦነግ ሸኔ ኃይሎች ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት 5 ቀዳሽ ካህናትና 8 አስቀዳሽ ምእመናንን አግተው ወሰዱ። ቆይተው ስምንቱ ምእመናንና የደብሩ አስተዳዳሪ አጋቾቹ የጠየቁት ገንዘብ ተከፍሏቸው ይለቋቸዋል። ለተቀሩት አገልጋይ ካህናትን የማስለቀቂያ ገንዘብ ቢከፈልም ሳይለቋቸው ቅዳሜ መጋቢት 14/2016 ዓም በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋቸዋል።

• የተገደሉት አገልጋዮች ስም…

1.ቀሲስ ቸርነት ብዙወርቅ ቄሰ ገበዝ
2.ቀሲስ ሳሙኤል ወደጆ ቀዳሽ ካህን
3.መሪጌታ ያሬድ የደብሩ መሪጌታ እንዲሁም
4.ዲ/ን ቤዛ ባዬ የደብሩ ጠቅላላ አገልግሎት ናቸው።

"…በተለይም የደብሩን መሪጌታ መጀመሪያ እጃቸውን ቆርጠው ለውሻ በመስጠት ከዚያ በኋም እያንዳንዱን አካላቸውን በገጀራ በመቆራረጥ እንደገደሏቸው የዐይን እማኞች መግለጻቸውን፣ ሌሎቹንም አገልጋዮች በተመሳሳይ ሁኔታ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንደተገደሉ፣ ከዚህ በተጨማሪም በቾ ወረዳ ሶየማ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ቀሲስ መልአኩ የተባሉ አንድ ካህን መጋቢት 17/2016 ዓም ሌሊት ታግተው ተወስደዋል። ቶሌ ወረዳ ላይ እንዲሁ አንድ ዲያቆን በመውሰድ ለመልቀቅ 1 ሚልዮን ብር እንደጠየቁ ለማወቅ ተችሏል በማለት ስምዐ ተዋሕዶ ዘግቧል።

"…ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የአማሪካ ዜግነቴን እንደያዝኩ በኢትዮጵያ ሥልጣኔን ይዤ ሸገር ገብቼ ልቀጥል በማለት ሙግት ላይ ናቸው። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ከመጅሊሱ ጋር የኢድ ሶላት ሰግደው ዱዓ በማድረግ ጸሎት ላይ ናቸው። አቡነ ሳዊሮስ ጭፍጨፋው የተፈጸመው በእርሳቸው ሀገረ ስብከት ቢሆንም ኬሬዳሽ…

• በቅርቡ አዲስ አበባ ይቀጥላል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• እንዴት ያለ ጸሎት ነው ግን…!

• ኢስመዳብ አሊወልድ አሩዋል ቅዱስ አልዋህድ ይፈክር ዱንያ…አለች ይቴ ጭሷ…😂

• አይ ወሮሞ… አቡነ ሄኖክም አፈጠሩ ነው የምትሉኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…እንደ ሀገር የዐማራ ፋኖ የሰበረውን የኦሮሙማ ጨፍላቂ ሰልቃጭ አውዳሚ መንፈስ እና አዚም እንደ አዲስ አበባ ይሄን የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ አዚም መስበር ያልተቻለው ለምንድነው…? አዲስ አበባ ይሄ ጭቃ የሆነ ፍልስፍና መጠየፍ ያልፈለገው ለምንድነው…?

• ድል ለአዲስ አበባ ሕዝብ…!
• ድል ለተጨቆነው አዲስ አበቤ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባላል፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ።” አሞ 5፥16። “…የመቅደሱ ዝማሬ በዚያ ቀን ዋይታ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የሰዎችም ሬሳ ይበዛል፥ በስፍራውም ሁሉ በዝምታ ይጣላል።” አሞ 8፥3

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አዲስ አበባ ስማ…!

"…ማርያምን ስልህ አዛኜን በተአምር የምድረ ኦሮሙማ የሸአቢያና የወያኔ የምርኮኛ ስብስብ የሚመራው መንጋ ጦር የታላቁን ዐማራ ፋኖ አያሸንፈውም። አራት ሞቶ ሚልዮን ነጥብ። አከተመ።

• ኔቨር አለ ሱሬ… ኔቨር😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እናንት ኦሮሞ ጠል ተብላችሁ በዚህ እብድ ንክ ሰው ፍዳችሁን ትበሉ ዘንድ የተፈረደባችሁ አዲስ አበቤዎች ሆይ ርዕሰ አንቀጹን ካነበባችሁ በተራችሁ እስቲ እናንተ ደግሞ ተንፒሱ።

"…ከባህርዳር በቀር በመላ ሀገሪቱ መብራትም ጠፍቷል። ንግድ ባንክን ያጨለሙት ሃከሮች ዛሬ መብራት ኃይልንም ሳይደግሙት አይቀሩም የሚሉ መተርጉማንም አሉ። ትግሬዎቹ የዐማራ ሃከሮች ሳይሆኑ በተቋሙ ውስጥ ያሉ ዐማሮች ናቸው በማለት ሲያለቃቅሱም እያየሁ ነው። ዲጅታል ፋኖም የተቻለ አይመስልም።

"…ኦነግ ሸኔም አሊ ዶሮ አከባቢ በብዛት ታይቷል። አዲስ አበባ ዙሪያም እንዲሰፍር ተደርጓል እየተባለም ነው። ዘንድሮም ባላፈው በ16 የኪዳነምህረት እለት ወያኔ መከላከያን በራያ በኩል ከጀርባው መትታ ረፍርፋዋለች የሚሉም አሉ። ፋኖ ቀድሞ አዲስ አበባ ከሚገባ ኦነግ ሸኔ ቀድሞ ይግባ የሚሉ እንዳሉም ተሰምቷል። ለማንኛውም ከአንድ ሰዓት በኋላ በኢትዮ ቤተሰብ ሚድያ እስክንመጣ ደረስ ሓሳባችሁን አውጡ።

• ተንፒሱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ ሸገር ሲቲ እንዳሉት ክፍለ ከተማ እስከ አሁን አልጨከነበትም። የደቡብ ዕዝ በ20 ኪ.ሜ ርቀት በሚገኝባት በሻሸመኔ የዐማራና የጉራጌ ባለሀብቶችን በእሳት እያቃጠለ፣ በሳንጃ፣ በሜንጫና በዱላ እየጨፈጨፈ፣ በባዶ እግሩ ባዶ እጁን አሯሩጦ እንዳስወጣው እስከአሁን አላስወጣውም። "ኧረ ሕዝቡ እየተጨፈጨፈ ነው አንድ ነገር አድርጉ ብሎ ለሽመልስ አብዲሳ የደወለው ከንቲባ "አያገባህም አርፈህ ገብተህ ተኛ" የሚያስብል ጭፍጨፋም አልተደረገበትም እስከአሁን። አዲስ አበቤ በሮብዓም እቡይ አህመድ "የአዲስ አበባ የሃይስኩል ተማሪዎች በግድ ኦሮሚኛ አንዘምርም በማለታቸው፣ በጊንጡ ፖሊስ ለመግረፍ ሞክሮ ስላልተሳካለት እብድ ሆኖ "አዲስ አበባ ውስጥ ከፍተኛ ኦሮሞ ጠል የሆነ ሕዝብ አለ" ብሎ እንደ ደነፋው አሁን መደንፋት አላስፈለገውም። እየሳቀ አፈረሳቸው።

"…የነገን እንጃለቱ እንጂ ለአሁኑ አዲስ አበባ ዐማሮችን በወለጋ በውድቅት ሌሊት በቤታቸው ውስጥ አቃጥሎ፣ ህጻን አርዶ፣ እናትና ሴቶችን ደፍሮ፣ ከብቶቹን አርዶ፣  ከሞት ተርፈው ጎጃም ለመግባት በመኪና ታጭቀው ሲሄዱ የነበሩትን ከመኪና አስወርዶ እንደጨፈጨፋቸው እቡይ አህመድ፤ በአዲስ አበቤው ላይ እስከአሁን በዚህ መልኩ አልጨከነበትም። እስከነ ቤቱ ሚስቱን፣ እናቱንና ልጆቹን በእሳት አላጋዩትበትም። እንዲያውም ፍቅርና እንክብካቤ ሁሉ ለግሶታል። ቢያንስ እንደወለጋ፣ ሻሸመኔ ቤኒሻንጉልና አጣዬ ኗሪዎች የውኃ መጠጫ ኮዳና ጫካ ማደሪያ ምንጣፍ ሳይዝ ደንግጦ እንዲወጣ አላደረገውም። ሙሉ የቤት እቃውን ይዞ እንዲወጣ ፈቅደውለታል። ነጋዴውም ለትርፍ የያዘውን እቃ በእጥፍ ቀንሶ ለመንገደኛ በሁለት ቀናት ውስጥ በርካሽ እንዲሸጥ ጊዜ ሰጥተውታል። ጣሪያውን ራሱ እንዲነቅል፣ በርና መስኮቱን ወስዶ እንዲሄድ፣ ህንፃውን በግሬደር ራሱ እንዲያፈርስ ዕድል ሰጥቶታል። ከዚህ ለሮብዓም እቡይ አሕመድ እንዲያውም ስደተኛው አዲስ አበቤ በሰላማዊ ሰልፍ ማመስገን ነው ያለበት። ዳግማዊት ጣይቱ አዳነች አበቤን ወፍራም እግሯ ስር አጎንብሶ በመስገድ ማመስገን ነው ያለበት።

"…የሮብዓም እቡይ አሕመድ አማካሪው ዳንኤል ክብረት ነው። ዳንኤል የሕዝቡን ስነ ልቦና ቀርጥፎ የበላ ነው። ለባለ ሾርት ሚሞሪው ሕዝባችን ምን ቢነገረው ጮቤ እንደሚረግጥ፣ ምን ቢነገረው እንደሚያዝን፣ እንደሚያለቅስ አሳምሮ የሚያውቅ ሰባኪ ነው። ሕዝቡ ሲዝቱበትና ሲያስፈራሩት የባሰ እንደ ሚገነፍል፣ ደንፉም እንደሚይዘው፣ በመቅለስለስና በትህትና ሲያጭበረብሩት ግን ልቡን ከፍቶ ግባልኝ በሞቴ፣ በሳንቃው ደረቴ እንደሚል ያስቀጸለው እርሱ ነው። ታስታውሱ እንደሆን አቢይ አዲስ አበባን በሚታይ በኃይል፣ በቁጣ፣ በዱላ፣ በጥይት ተኩሶ በመግደል ለማንበርከክ ሞክሮ ነበር። "አዲስ አበባ ውስጥ ከፍተኛ ኦሮሞ ጠል የሆነ ሕዝብ አለ"  ብሎ አብይ ይህን ንግግር ያደረገውም የአዲስ አበባ ታዳጊ ተማሪዎች በሃይል ቋንቋ አይጫንብንም ብለው ኦህዴድን በአንድነታቸው፣ በኅብረታቸው ካብረከረኩት በኋላ ነበር። እቡይ አሕመድን ያበሳጨው መግቢያ ቀዳዳም ያሳጣው የእነዚህ የአዲስ አበባ ታዳጊ ተማሪዎች ፅናት ነበር። አቢይ አሕመድ ተኩሶ አንድ ተማሪ ቢገድልም፣ መምህራንን ሰብስቦ ሲያስርም፣ ተማሪዎቹ ባሰባቸው። በተማሪዎቹ ጀግንነት ዕቅዱ የተኮላሸበት አብይ አህመድ ሽንፈቱንና ብስጭቱን መደበቅ አልቻለም። መላው አዲስ አበቤን "ኦሮሞ ጠል ነው" ብሎ የዛተበት ለዚያ ነበር።

"…አዲስ አበባ እንደ ወለጋ ጫካ ለእርድ ያለተመቸው አቢይ አሕመድ፣ እንደ ሻሸመኔ እሳት ለመልቀቅ፣ በጅምላ ለመጨፍጨፍ፣ እንደ ሀረርጌ የመስፍንን አስከሬን በገመድ አስሮ "አላህ ወአክበር" እያለ ጎትቶ ለመሳለቅ አይመችም። አዲስ አበባ ዘማዊው የኦሮሞ ቄሮ ቤተሰብ ፊት፣ ባል ፊት ሚስትን መድፈር፣ እርጉዝ ሴት አርዶ ጽንሷን ለመብላት አይመችም። አዲስ አበባ የዲፕሎማት መቀመጫ፣ አነፃራዊ የሕዝብ ንቃተ ህሊና ያለበት ከተማ ስለሆነ እንደ ጅማ ጫካ፣ እንደ ቤኒሻንጉል መተከል በጅምላ ቀበሌ ሙሉ ዐማራ ጨፍጭፎ በግሬደር ለመቅበር አይመችም። ለዚህ ነው እቡይ አሕመድ እንደ አባቶቹ በመንግሥቱ ኃይለማርያም ቀይ ሽብር፣ በመለስ ዜናዊ የአግአዚ ጭካኔ መንገድ ሞክሮ የከሸፈበት። ሮብዓም እቡይ አሕመድ በአዲስ አበባ ላይ ዛቻና ቁጣ እንደማያስፈልግም ተመከረ። ዛቻ ማስፈራሪያና ጉልበት አዲስ አበቤ ላይ እንደማያዋጣም ተመከረ። ይሄን የመካሪዎች ምክር የተረዳው አብይ አህመድም ጊዜውን ጠብቆ በኮብራ ምላሱ እያነሆለለ ለበቀል ተነሣ። አይደለም የጨኦሮሞን መዝሙር አለመዘመር ገና ከቀዬህ በዶዘር እዝቅሃለሁ ብሎ ጊዜውን ጠብቆ ከች አለ። እቡይ አሕመድ ይህን የሚያደርገው ግን በትህትና ነው። በጅንጀና። በኃይል ከሞከረ የሚገጥመውን የሚያውቀው አብይ አህመድ ከተማህን እናልማልህ፣ አምስት ወር ስድስት ወር ስጠኝ ብሎ መጥቶልሃል። ቀስ አድርጌ ሳትሰባሰብና ሳታጉረመርምብኝ በፍጥነት ልበታትንህ ነኝ ብሎ ነው የመጣበት።

"…ሽመልስ አብዲሳም አዲስ በመሰረተው የሸገር ከተማ ዙሪያ ሚሊሻዎችን ካምፕ አስገብቶ እንዲያሰለጥን ተነግሮታል። ቤትህ ይፈርሳል። ለዘመዶቻቸውም ይሰጣል። እሺም ብትል ትፈናቀላታለህ። እምቢም ካልክ አራጅ ሚሊሻ እንደወለጋ ፈትቶ ጃስ ብሎ ይለቅብሃል። ከዕድርህ፣ ከዕቁብህ፣ ከማኅበራዊ ሕይወት ትስስርህ ያፋቱሃል። አንዱን ጣፎ፣ ሌላውን አንፎ ይበቱኑታል። መላወስ፣ መቃወም እንኳ እንዳትችል አድርገው ድራሽ አባትህን ያጠፉታል። እናም ሳይመሽብህ ትስስርህ ሳይበጣጠስብህ ተሰባሰብ። ምከር ዘከር። ኦሮሞን ሊያስፍር ነው ይላሉ እያልክ ነጠላ ዘቅዝቀህ፣ ፍራሽ አንጥፈህ፣ እየተቅለሰለስክ አታልቅስ። አጭቤው የሚያደነዝዘህ፣ እያሰባ ለእርድ የሚያዘጋጅህ "ከፍተኛ ኦሮሞ ጠል ኃይል አለ" በሚለው እውነተኛ የቁጣ ንግግሩ ውስጥ ነውና የተገለጠው እርሱን ንግግር ይዘህ ኦሮሞ ጠል የባልክ እየተፈናቀልክ ሽመልስ ያላቸው ተፈናቃይ የፖለቲካ ኦሮሞዎች ሊሰፍሩበት መሆኑን ዐውቀህ እንደዜጋ ይሄን የአፓርታይድ ሥርዓት ለመቃወም ተነሥ። ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች ነጥሎ ኦሮምኛን ብቻ በአዲስ አበቤ ላይ ለመጫን በግልጽ ዛቻ የተናገረው ሰውዬ ነው ዛሬ "ኦሮሞን ሊያሰፍር ነው ይላሉ" እያለ የሚያታልለው። እናም ነቃ በል አዲስ አበቤ።

መፍትሔው…

"…አሁን ዐማራንም ሌሎች መታገል የሚፈልጉ ኃይሎችን የሚያታግል ከባቢ ተፈጥሯል። እንደ ቅንጅት በዲስኩር፣ በሰላማዊ መንገድ ያልሆነ፣ ገዢው ፓርቲ በሚወደው፣ በለመደው መንገድ ምሱን እየሰጠ የሚያነጋግረው ኃይል ተፈጥሯል። በጫካ፣ በበረሃ ያልተወሰነ፣ ቀበሌ፣ ወረዳና ዞን ማስተዳደር የጀመረ ኃይል ተፈጥሯል። ታግሎ የሚያታግል ኃይል ተፈጥሯል። በ80 እና በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አገዛዙን አሽቀንጥሮ የወረወረ ኃይል ተፈጥሯል። የኦሮሙማውን ምንነትና አካሄድ ተረድቶ ላልተረዱት የሚያስረዳ ኃይልም ተፈጥሯል። በአሁኑ ሰዓት በኦሮሙማ ላይ የሰላ ሙያዊ ትችት ለማቅረብ መድከም አያስፈልግም። ትችቱም ከበቂ በላይ ነው። አሁን የሚያስፈልገው የተግባር ኃይል ብቻ ነው። ቀልድ፣ ቧልት፣ ወሬ፣ ዲስኩር ጊዜው እያለፈበት ነው።።ፉከራና ሽለላም እንደዚያው። ተግባር። ጊዜው የተግባር ነው። በኢትዮጵያ አሁን ሁለት ኃይል ተፈጥሯል። ኢትዮጵያን አፍራሽ ኃይል እና ኢትዮጵያን ታዳጊ ኃይል። አፍራሹ ኃይል የኢትዮጵያን ባንክና ታንክ የያዘ ሲሆን የገንዘብ አቅሙም ከባድ ሰፊም ነው። ኢትዮጵያን ታዳጊው ኃይል ደግሞ ከላይ ከሰማያት ፈጣሪውን፣ በምድር ነፍጡን ከመላ ሕዝቡ …ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ በመስገብገብ፣ በመሻማት፣ በመጣደፍ፣ በመሯሯጥ፣ በችኮላ፣ ደግሞም በደስታ፣ በፍጹም ፍቅር ያመሰግን ዘንድ የምጠብቀው 1ሺ ሰው ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከምስጋና ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ደግሞ ወደ ተወዳጇ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። ርዕሰ አንቀጻችን ከመለጠፏ በፊት ደግሞ የመንደሬ ነዋሪዎች ድምጻችሁን መስማት የግድ ነው። መንደራችን አለን፣ ዝግጁ ነን በሚሉ ድምጾች ሲቀወጡ ጠላት ያፍራል። ይደነግጣል። ይሄ ሁሉ ባለ አእምሮ ሕዝብ ብሎም ይጨነቃል። ይሁነኝ ብዬ ነው ከምስጋና በኋላ ዝግጁ ናችሁ ብዬ የምጠይቃችሁ።

"…ዛሬ የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን መነሻውን መጽሐፍ ቅዱስ አድርገን ነው በንፅፅር የምጽፍላችሁ። ከዚህ ቀደም በጻፍኩት ርዕሰ አንቀጽ ላይ ነው ዛሬ የምጨምርላችሁ። አዲስ አበቤ እየተደረገለት ያለውን ቀዝቃዛ ወላፈን ሞትና ምት የሚያሳይ ነው። በሰመመን እንቅልፍ እንዴት እንደሚያሸልቡት፣ እንዴት እንደጨው እንደሚያሟሙት የሚያሳይ ነው።

"… እህሳ… እናንት ከፍተኛ ኦሮሞ ጠል የተባላችሁ አዲስ አበቤዎች ሆይ የወሎዬውንና በሞጋሳ ለኦሮሞ ፈርሞ በኦሮሞ ስም የሚያሟሟችሁን ባለ ኮብራ ምላሱን የተናዳፊውን የእቡይ አሕመድን የጊንጥ ጅራፍ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?

• እደግመዋለሁ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ፓስተር ቪያግራ…!

"…የኦሮሙማው አገዛዝ ፈትቶ የለቀቃቸው የኦሮሞ ጴንጤ ፓስተሮች እና የኦሮሞ የወሃቢይ እስላም ኡስታዞች ገና ብዙ ነገር ያሳዩናል። ያሰሙናልም። ይሄ አንደኛው ክርስትና የማራከስ የዋቀፌታ ሴራ መሆኑ ነው።

• ፓስተር ቪያግራ… ስንት ደቂቃ ላድርግልህ…?

~ ባል… 20 ደቂቃ

• ፓስተር ቪያግራ… ስንት ደቂቃ ላድርግልሽ

• ሚስት… 30 ደቂቃ

• ፓስተር ቪያግራ… ጨምሬላችኋለሁ። በሚስትየዋ ጥያቄ መሠረት 30 ደቂቃ ተደርጎላቸዋል። በኋላ በዛብን፣ ቀንስልን እንዳትሉም ብሏቸዋል።

~ ይሄን ቪድዮ ልጆች፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጓደኛ ቤተሰብ ሲያየው ምን ይሰማቸው ይሆን…? የመድኃኔዓለም ያለህ። ኧረ ተዉኝ ልተኛበት…?

• ኢስመላብ አለወልድ አልወቅዱስ አላህ ዋህድ አሜን አለ ይቴ ጭሱ…

Читать полностью…
Подписаться на канал