"…መማር አለባቸው የስደተኛ ብር መልሺ…!
"…መማር አለባቸው። በእውነት ደግመሽ ደጋግመሽ መማር አለብሽ። ስምን መልአክ ያወጣዋል የሚባለው እውነት ነው። ሰገጤ ፒፕል ተገኘ ተብሎ እንዲሁ በብላሽ መጋለብ፣ መጋጥ ነውር ነው። ደግሞም በየትኛውም መመዘኛ የስደተኛ፣ የተፈናቃይ፣ የምስኪኖችን ብር ሰብስቦ ሳይሰጡ መብላት ነውርም፣ ወንጀልም፣ ኃጢአትም ነው።
"…ሳይሠሩ ለስደተኞች በተለመነ ብር ወርቅ በወርቅ መሆን መጨረሻው ሞት ነው። ነቀርሳ ነው የሚሆንብሽ። አሁንም በጎንደር ስም ለምነሽ ከመብላትሽ በፊት የስደተኛ ጎንደሬዎችን ብር መልሺ። መልሺ እግዚአብሔር ሳይፈርድብሽ፣ ከባድ ክንዱን በአንቺና በአንቺ በሆኑት ላይ ሁሉ ሳያነሳባችሁ የስደተኞችን ብር መልሺ።
"…ጎንደሬ ነኝ ብለሽ እየፎከርሽ፣ እየጨፈርሽም እንዴት የምስኪን ስደተኛ ጎንደሬዎችን ገንዘብ፣ ትነጥቂያለሽ? ትቀሚያለሽም? እንዴት ከምስኪኖች አፍ ትነጥቂያለሽ? ትዘርፊያለሽም? ስሚ የያያ ያሬድ ዘልደታ እና የስኳድ የምስጋናው አንዱዓለም ማንቆለጳጰስ ከሚመጣብሽ ከፈጣሪ ቁጣ አያድንሽም። አይታደግሽምም።
"…እኔ ዘመዴ ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ሳላደማሽ አልፋታሽም። ሌባው ስልጤ ካሊድም አያድንሽም። ተናግሬአለሁ።
• ምእመናን ሌቦን መልሺ በሏት።
የጠበቃው ነገር…
"…ስኳዶች በይህ ጠበቃ ላይ ለምንድነው እንዲህ የጮሆት ብይ እጠይቃለሁ። እጠይቃለሁ። እደክማለሁ። ኋላ ላይ መልሱን አገኘሁት። ለካስ ነገሩ ወዲህ ነው።
• ለካንስ ጠበቃው…
~ በሰኔ 15 ጉዳይ ተጠርጥረው ለታሰሩ እስረኞች ብዙዎቹን ተከራክሮ ያስፈታቸው እርሱ ነው።
~ ይኸው ጠበቃ አርበኛ ዘመነ ካሤም ተጠርጥሮ በታሰረ ጊዜ በፍርድ ቤት ተከራክሮ ነፃ አስብሎ ከእስር ቤት ያስፈታ ባለሙያ ነው።
"…የጎንደርን እስኳድ እንዲህ አንጨርጭሮ አንጨርጭሮ በምስኪኗ ሟች ሕጻን እናት በኩል አሸማቆ፣ አሰድቦ፣ ጠበቃው ይገደል፣ ፈቃዱም ይነጠቅ ያስባለው፣ በጉርሻ የፌስቡክ ፔጅ እና በእነ ያሬድ ያያም በኩል ዘመቻ ከፍቶ ያስወገዘው በሙያው ለተከሳሾች በመቆሙ ነው።
• ከሁሉ ከሁሉ ደግሞ የሚደንቀው ጠበቃውም የጎንደር ተወላጅ መሆኑ ነው። እንዲያውም እነ አያሌው መንበር ቤተሰቡ ጋር ሁላ ደውለው እንዴት ለጠላት ጥብቅና ይቆማል እስከማለትም ደርሰው እንደነበር ሰምቻለሁ።
• ልጠይቅ…?
"…አንድ ጠበቃ ጥብቅና መቆም አትችልም የሚባልበት የሕግ አግባብ አለ ውይ? ጥብቅና ራሱን የቻለ ሙያ አይደለም ወይ?
• የባለሙያ ሙያው ይከበር። ሌባ ሁላ።
"…እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? መዝ 25፥12
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
እልልልልልል ኣሸንዳ በመቀሌ…
"…ዘመዴ ተውጠን ነው እንጂ እኛም እንዲሁ በደመቀ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በዝማሬ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን የዕርገቷን በዓል አክብረናል ብለው ይሄን ግሩም ዝማሬ ልከውልኛል።
• እልልልልልልልልልልልል
በሰላም እረፍ…!
"…እኔ በበኩሌ ሞተ አልልም አረፈ እንጂ። ሞት ላይቅር እንዲህ የልብን ተናግሮ፣ እውነትን መስክሮ፣ ሃቅን ሰብኮ መሞት መታደል ነው። ያውም እንደ እኔ ፈርጥጦ፣ ርቆ፣ ሸሽቶ ሳይሆን እሳት መሃል ቆሞ ዝቅ ብሎ ባቱን፣ ከፍ ብሎ አንገቱን እንደሚያስቆርጠው እያወቀ፣ ቅረፅ እያለ ለትውልድ የሚቀር ታሪክ እያስቀረፀ እንደ ሐዋርያትና ሰማእታት እውነትን መስክሮ መሞት መታደልን ይጠይቃል። መመረጥ አለብህ። ይሄ ወንድም ሞተ አይባልም አረፈ እንጂ።
"…ዐማራ ነኝ ምርጥ ወሎዬ እያለ ሳይፈራ ሳያፍር፣ ሳይሸማቀቅ ተናግሮ፣ ለምን ዜጎች በነገዳቸው፣ መርጠው ባልተወለዱበት ብሔራቸው ይገደላሉ። የሃገሪቱን መሪ ጭካኔ፣ ሰው እየሞተ ፂሙን ኦ ተቆርጦ፣ የሚያምር ሱፉን ለብሶ፣ ሰው ሲጨፈጨፍ ቅጠል እንደተበጠሰ እንኳን የማይሰማው ለምንድነው ብሎ ነው በግልጽ የጠየቀው። እና አሁን ይሄ ሰው ቢሞት እንዴት ሞተ ይባላል? ቀኑ ደርሶ ቢያርፍ እንኳ ሞተ አይባልም።
"…በዚህ ልጅ ሰይፉ ፈንታሁንን ጨምሮ፣ ኢቢኤስ ቲቪ፣ ብዙ ዩቲዩበሮች ቃለመጠይቅ እያደረጉ ሲሸቅሉበት ኖረዋል። ብዙ የፊልም ካምፓኒዎች ፊልም አሠርተውታል። ልጁ ታሞ ሆስፒታል ሲሄድ ግን ብቻውን ነበር አሉ። ሆስፒታል ገብቶም ብቻውን ሞተ አሉ። ዛሬ ግን ከሞተ በኋላ የአዞ እንባ እያነባ ይሄ የማኅበራዊ ሚዲያ ዓለም በልቅሶ ኢሞጂ 😭 ተጥለቀለቀ። አሁንማ ሰዎች እንባ አውጥተው ማልቀስ ሲያቅታቸው አልቃሽ ኢሞጂ ቀጥረው ሲያለቅሱ ይውላሉ።
"…የዚህ ደፋር ልጅ አስከሬን አሁን ክብር ያገኛል። በብቸኝነቱ ጊዜ አብረውት ያልቆሙ ሁሉ፣ ታሞ ያልጠየቁት በሙሉ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ለመሆን፣ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት፣ ስለ ልጁ ለመመስከር፣ ጥቁር መነጽራቸውን ሰክተው ይገለጣሉ። ሞት ላይቀር ከሞቱስ አንደዚህ ልጅ ሃቅ ተናግሮ መሞት ነው።
• በሰላም እረፍ…!
“…ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ።” ፊል 3፥2 “…ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።” ራእ 22፥15
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ጣሳቴ…!
"…ዘኬው ላይ ሆኜ መጻፍ ባልችልም በመሃል ግን አዲሱን ጎጃምና ጎንደርን ያጣልናል ብሎ አጅሬ ስኳድ ሊመሰርተው ባሰበው ጣና የሳታላይት ተሌቭዥን (ጣሳቴ) ምስረታ ስብሰባ ላይ በድብቅ መገኘቴ አልቀረም። ገና ሳይጀምር ባቢሎን ሆኑ፣ ዘመድኩን፣ ዘመድኩን ብለውም ሊሞቱ ነው።
"…አቶ ስኳድ ዶር ምስጋናው ለእነ አርበኛ ባዬ በDMV ላይ የሰበሰበውን 63ሺ ዶላር እስከ አሁን አልሰጣቸውም። በጎንደር ፋኖ ስም በስኳድ የተሰበሰበን የት እንዳደረሱት ወጥሬ እጠይቃቸዋለሁ። እሞግታቸዋለሁም። ቀደም ሲል ጎጃሜ ይበዛበታል በማለት እነመሳፍንት ባዘዘው ለዐብን የተሰበሰበውን ገንዘብ ቀርጥፈው በሉት፣ እኔ ራሴ ለምኜ ያቋቋምኩላቸውን አሥራት ቴቪን እነአያሌው መንበር፣ እነ ዓምደማርያም ዕዝራ ፍርስርሱን እወጡት፣ አሁን ደግሞ ጎንደርን ከሌላው ዐማራ ወንድሞቹ ለመነጠል ሲባል እነ ምስጋናው ተፍተፍ በማለት ላይ ይገኛሉ።
"…ዶር ምስጋናው ስኳድ ለእነ ባዬ የሰበሰበውን ገንዘብ የማይሰጣቸው ለምንድነው ብዬም ጠይቄ ነበር። ያገኘሁት መልስ የሚደንቅ ነው። ዶፍተሩ የሚለው እነ አርበኛ ባዬ በእስክንድር ነጋ ስር ካልሆኑ፣ ዘመነ ካሤን ካላወገዙ ገንዘቡን አይሰጥም። በዚያ ላይ ዶፍቶሩ ጴንጤ የጌታ ልጅ ስለሆነ እነ ባዬ ባለማዕተብ ጎንደሬዎች ስለሆኑ፣ ትልቅ መስቀል ደረታቸው ላይ አንጠልጥለው ስለሚዋጉም በዚያ ደስተኛ አይደለም ነው የሚሉት።
"…መዝግቡልኝ ምሬ ወዳጆን አንቆ ለመያዝ ሞክሮ የነበረው አቶ ጌታቸው በለጠ ከዝናሽ ታያቸው ጋር አንድ ቸርች ያመልክ የነበረ ሰው ነው። ወሎን በጌታቸው በየነ በኩል ሊይዝ ነበር አሉ። ቀጥሎ ተመልከቱ እነ መከታው ተደራዳሪያቸው ፓስተር ዮናስ ነው። እርቁን ሁሉ አፈር ደቼ ያበላው ማለት ነው። ጎንደር ደግሞ ሌላ ጉድ እየመጣባት ይመስላል።
•ስለ ጎንደር ያገባኛል። እነስኳድ ፈንዱ፣ ጧ በሉ።
ዳዊት ዲሪባ
"…በ1993 ወይም 94 አካባቢ በዘመነ ወያኔ ኢህአዴግ ሀገር ጉድ ያስባለ፣ በፖሊስ ፕሮግራም ላይ ስሙ ደንበኛ የነበረ ስመጥር ዘራፊ ነበር። በተለይ መርካቶ ተክለሃይማኖት አካባቢ በሚገኘው የሜታ አቦ ቢራ የገንዘብ ዝርፊያ እና በባንክ ዝርፊያ ከፖሊስ ጋር ሲታኮስ የኖረ ወንበዴ ነበር። ዳዊት ዲሪባ የሞት ፍርደኛ ነበር። 20 ዐሰመት ታስሮ ነው አዲሱ የለውጥ ነውጥ መንግሥት ሲመጣ ከጓደኛው ይባስ አሰፋ ደበሌ ጋር የተፈታው።
"…ይባስ (ፈንታሁን) አሰፋ ደበሌ የመኖሪያ አድራሻው ተክለሃይማኖት ከረዩ ሰፈር በሚባለው መንደርም ነዋሪ ሲሆን በ1997 ዓም በቃሊቲ ወኅኒ ቤት የተነሣውን ረብሻ በማሥነሣት ብዙዎች እንዲገደሉ ያስደረገ የነበረ፣ በቃሊቲ ታስረው ለነበሩ የኦነግ አባላት ይላላክላቸው የነበረ፣ እናም ከለውጡ በኋላ ተፈትተው የእስር ቤቱን መላላክ እንደ ውለታም ቆጥረውለት በኦሮሞነቱ ሽጉጥ ታጥቆ እንዳሻው እንዲሆን የተፈቀደለት፣ የለውጡ የእነ አዳነች አቤቤ መንግሥትም ኢመደበኛ የስውር ክትትል ሥራ እየሠራ እንደ ደህንነት አክት እያደረገ ሰፈር ውስጥ ሁላ ወጣቶችን በሽጉጡ እያስፈራራ እየወቀጠ የሚኖር ቀን የወጣለት፣ በእስር ቤት እስክንድርንና አንዷለም አራጌን ይሰድብ፣ ይተናኮል እንደነበር ይነገርለታል።
"…የእኔ ጥያቄ ትግሬው ጴንጤ ጆን ዳንኤል ልጅ ነው። ቢተዋወቁም ዳዊት ከተፈታ በኋላ ነው የሚሆነው። ነገር ግን ዱባይ ይኖር የነበረው ዳዊት ድሪባ ምንም ዓይነት የዘር የቤተስብም የስፈርም ትውውቅ ዝምድናም ከሌለው ከጆን ቤተስብ ጋርስ በምን ምክንያት ተዋወቁ ተቀራረቡ? ከዚህ ተነሥተን ጆን ዳንኤል ማነው ? ከነማን ጋርስ ግንኙነት አለው? መቀሌስ የሚሄደው ለምን ተልእኮ ነው? በዚያ በሚፈጸሙ ወንጀል ጀርባ የእነ ዳዊት ተሳትፎ ይኖርበት ይሆን ወይ?
• ዳሩ ምንአገባኝ… ፍሪ ጆን ዳንኤል…!
መልካም…
"…የፍለሰታ ማግሥት ድግስ ተጠርቼ ዘኬ ልለቅም እየሄድኩ ነው። ለማንኛውም በመሃል በመሃል ብቅ ማለቴም አይቀርም። ለማንኛውም በኋላ ብቅ እስክል ድረስ ግን ጥያቄ ልጠይቅ ነኝ።
"…ጥጋበኛው ቲክቶከር አይተ ዮሐንስ ዳንኤል በርሔ በቀደም ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቀውጢ ሲያደርግ በነበረ ጊዜ በራሱ በጆን ዳንኤል የካሜራ አይን ውስጥ የቀረ የአንድ ሰው ምስል አየሁ። ይሄም ሰው በቀይ ያከበብኩበት ሰው ነው። የማይታመን ነው። ይሄ ሰው ማነው? ለምንስ ነው መቀሌ የሚሄደው? ለምንስ ነው አየር መንገዱ ውስጥ እንዲህ ቀውጢ የፈጠረው? መቼም ስለ እስክንድር ነጋ እና አንዱአለም አራጌ ስጽፍ ይህንን ሰው ደጋግሜ ጠቅሼው ነበር። ይሄ ሰው ማነው? መቀሌ ምን ይሠራል? ትግሬ ለዚህ መልስ ካለው በብዙ ጥያቄ መጠየቅ ይጀምራል።
• ይሄ ሰው ማነው? ገምቱ እስኪ። የምታውቁት ደግሞ ዘርዘር አድርጋችሁ ጻፉ። እኔ ወደ ዘኬዬ ልሂድ።
አትላኩልኝ…!
"…በአንድ ሰዓት፣ በተመሳሳይ ደቂቃ በፖለቲካዊ ትእዛዝ እንዲበተን ያደረጋችሁትን የሟች ሕፃን ፌቨንን መደፈር የሚያሳይ ነው ብላችሁ የበተናችሁትን ፎቶ ልካችሁልኝ አየሁት። እንደውም የእኔ ጥርጣሬ ሕፃን ፌቨን ከሞተች በኋላ የሆነ ሰይጣናዊ ግሩፕ ለፖለቲካ ፍጆታ ብሎ የሆነ ፀያፍ ድርጊት ሠርቶ ወንጀል ሠርቷል ብዬ እንድጠራጠር እያደረገኝ ነው። ጨካኞች ናችሁና ይሄን ወንጀል መፈጸም ያቅታችኋል ብዬም አልጠራጠርም። ሁለት ዓይነት የተሳከረ ህክምና ወረቀት ይዘህ ያላሳመንከኝ በፎቶማ እንዴት አምንሃለሁ። የትአል አሸዋው፣ የታል በምላጭ ተተልትላለች የተባለው? የትአል? አሳዩና። ይሄን ደግሞ በደንብ እሄድበታለሁ። ለማንኛውም ፎቶ አትላኩልኝ።
"…ፎቶውን አይቼዋለሁ። እናንት አስመሳይ ሁላ። አሁን ማን ይሙት እናንተ ናችሁ የህፃኗ መሞት ያሳዘናችሁ? የሆነው ሆኖ ግን እኔ ናላዬ የሚዞርበት፣ ዘላለሜን እንደ እብድ ብቻዬን ስጮህ ከዳር ቆማችሁ የተሳለቃችሁበትና በግፍ፣ በጭካኔ፣ በኦሮሞ ነፃ አውጪ ኦነግ ሸኔ ብልፅግና የታረዱ፣ የተጨፈጨፉ የዐማራ ሕፃናት እና እናቶች የትየለሌ ፎቶ ስፍር ቁጥር የሌለው ፎቶና ቪድዮ ስላለኝ የፌቨንን ፎቶ አትላኩልኝ። አትላኩልኝ ምድረ አስመሳይ ሁላ። አትላክልኝ አልኩህ። አንት መርጦ አልቃሽ ሁላ አትላክልኝ አልኩህ።
"…እኔ ከበቂ በላይ ዘግናኝ ፎቶ አለኝ። እግዚአብሔር ይፍረድ ብዬ ዘወትር የማነባበት ፎቶ አለኝ። እናም ዛሬ ጎጃምንና ጎንደርን ለማናከስ ስትል በግፍ የሞተችን የአንዲት ምስኪን ህፃነወ ፎቶ ይዘህ ጻድቅ፣ አዛኝ መስለህ አትተውንብኝ። ምደረ መርጦ አልቃሽ። አዛኝ ቅቤ አንጓች። የአዞ እንባ አንቢ ሁላ። ቢያንስ ፌቨን እኮ 25 ዓመት ተፈረደላት። ፍትሕ አገኘች አይደለም እንዴ? እነዚህስ ህፃናትና ሴቶች? እ… ንገረኛ…!
• አጀንዳዬን አልቀይርም።ጧ በል ፈንዳ…!
"…እናንተው ዛሬ በቲክቶክ መንደራችን…
• የሴረኞችን ቀልብ እና ቆሌ ልገፍ… ሴራቸውንም ላከሽፍ፣ ወሽመጣቸውንም ልቆማምጥ… የተንኮል ድራቸውንም ልበጣጥስ እና ስለ ሌሎችም አጫጭር ጉዳዮች አንሥተን ውኃ የሚያነሣ ቁምነገር ያለው ነጭ ነጯን የሆነች ሃቅ ለማውጋት በቲክቶክ መንደራችን ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ሲል ልመጣ ነኝ።
• ዛዲያ እናንተ ደግሞ ታብታብ፣ ኮፒሊንክና ሼር ለማድረግ ጣታችሁን ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ። 😂😂😂
ሥራ ለሠሪው እሾህ…
"…እንደ ሀገር አንደ አንድ የሚያደርገን የቀረን ሀብት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነበር። ሰንደቅ ዓላማውም እስከአሁን ያልተፋቀው ከዚህ ግዙፍ ድርጅት ላይ ነው። በተለይ በውጭ ሀገር ሰማይ ላይ፣ በአየር ማረፊያ ጣቢያዎች መሃል ጉብ ብሎ ሲያዩት እንባ በዓይን ይሞላል። እኔ ደግሞ ከምር ባለ ውለታዬ ነው አየር መንገዱ። ክፉውን የማልመኝለት። ቋንቋዬነሽ በታመመ ጊዜ ባንኮክ ደርሶ መልስ ትኬት የሰጠን ነው አየር መንገዱ። ሳየው የእኔ ነው የሚመስለኝ።
"…ትናንት አንድ ዮሐንስ ዳንኤል በርሔ የተባለ የትግሬ ተወላጅ ቲክቶከር በዚህ አየር የተከበረ አየር መንገድ ላይ ያልተገባ ድፍረት በማሳየት ለዓለሙ ሁሉ መሳቂያ፣ መሣለቂያ ነው ያደረገው። 27 ሺ ሰዎች ላይቭ እያዩኝ ነው ብሎ በቲክቶክ ብር ልቡ ያበጠበት ዘረኛ ወጠጤ አየር መንገዱን ሲረብሽ ነበር ያመሸው።
• አየሩ ጥሩ አይደለም ይለዋል ባለሙያ
~ አይሁን ይላል ጆን ዳንኤል
• ይከሰከሳላ ይላል ሠራተኛው
~ ይከስከሳ ይላል ጥጋበኛው
"…ዱቄት የተለቀለቁ ሰው መሳይ በሸንጎዎችም ያጅቡታል። ቲክታከሮችም ታብታብ እያደረጉ በርታ እንዳትወርድ ይሉታል። በመጨረሻም ወደዘብጥያ ወረደ። አሁን ይተነፍሳል።
"…ሁለት ተቋማት ይከሱታል። አየር መንገድ እና ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት። አብረውት 8 በጥባጭ ቲክታከሮችም ሸቤ ገብተዋል። የሚከፈትባቸው ክስ እስከ 15 ዓመት ድረስ የሚያሳስር ነው። ሞጣን ሳያሳስር ጆን ዳንኤል ታሠረ። ቲክታከሮችህ ያስፈቱህ።
"…ነገር ስቦኝ እኮ ነው። ቆይ ያንኛውን ቪድዮ ልለጥፍላችሁ። ይሄን ወጠጤ ሥራው ያውጣው። በአየር መንገድ ቀልድ የለም።
እና ለምን…?
ሀ፦ ተከሳሽ በአባቱ ጎንደር ከሆነ
ሁ፦ የተከሳሽ ሚስት ጎንደሬ ከሆነች
ሂ፦ የሟች እናት ጎንደሬ ከሆነች
ሃ፦ የሟች አባት ትግሬ ከሆነ
"…አሁን ላይ የምንዳኘው፣ የምንመዘነው፣ በዘራችን፣ በጎጣችን ነው ካልን በኋላ ይሄ እየታወቀ የጎጃም ሕዝብ ላይ የተዘመተው ለምንድነው? የትግሬ እና የኦሮሞ ነፃ አውጪ አክቲቪስቶች የጉራጌ አክቲቪስቶችን ከፊት አሰልፈው በሞጣ ሰበብ ጎጃም ላይ የተዘመተው ለምንድነው? መልሱልኝ።
"…እነ አያሌው መንበር ደቡብ ጎንደሬ ሆነው ያደጉት ባሕርዳር ነው። ምን አስበው ነው ጎጃም ላይ የቲክቶክ ሠራዊት እንዲህ ያዘመቱት?
"…ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል። በተቀነበበ፣ በጥንቃቄ በተዘጋጀ፣ የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ በሚመራው በዚህ የከረፋ የሴራ ፖለቲካ ውስጥ የተሳተፉትን በሙሉ አልፋታቸውም። እመብርሃን ምስክሬ ናት አልፋታቸውም።
"…መማር አለባቸው፣ ያሬድ ያያ፣ በላይ በቀለ ወያ፣ ወዘተረፈ የምርመራ ፋይል ነው የምከፍትባችሁ። ቱ…እኔ ዘመዴ መራታው የሀረርጌ ቆቱው የምሥራቁ ሰው፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር አይደለሁም። ጠብቀኝ አንት ደፋሪ ሁላ። ጠብቁኝ አልኳችሁ እናንት ዘራፊ፣ የሴት ገንዘብ አጣቢ ጩሉሌ ቀማኛ ሁላ።
"…እግዚአብሔር ታላቅ ነው። ክሊኒኩም አሁን የማላወጣው መረጃ አድርሶኛል። በውሸት የሟች ሕፃንን እውነትና ሃቅ እንዳይወጣ ያደረጋችሁ በሙሉ በቤታችሁ የማይነቀል የኀዘን ድኳን ይተከል። እረፍትም፣ እንቅልፍም ያሳጣችሁ። ጎንደርና ጎጃምን እንደ ሕዝብ ያዋረዳችሁ ተዋረዱ፣ ለማለያየት የሞከራችሁ ነፍስና ሥጋችሁ ይለያይ። ለሲኦል ሁኑ።
"…ያን ሁሉ ጣሪያ የነካ፣ በጎጃምና በጎንደር መካከል የተሰካ ሽብልቅ የነቀልክ አምላክ፣ የፌስቡክ፣ የቲክቶኩን እና የዩቲዩቡን ጩኸት ሞገዱን ፀጥ ያሰኘህልን ጌታ ክበርልን።
• ጥያቄዬን አልጨረስኩም። እቀጥላለሁ።
ነብር አየኝ በል።
"…ልጅ ካሊድ ናስር ነበር አየኝ በል አንት ቆሻሻ… ከመማር አለባቸው ጋር የጎንደር ተፈናቃዮች ላይ እንዳላገጥክ አትቀርም። በዳንኤል ክብረት ሽልማት ተደብቀህ አትቀርም። የምለውም ይገባሃል ኣ? …ቱ…! ነበር አየኝ በል አልኩህ።
• አልፋታህም…! ጨበርበርቱ ሁላ…!
"…አይ ትግሬ አለ አቢይ አህመድ አሊ… 😂 ይቅርታ ማነው? አይ ኦሮሞ ነው ያለው። ይቅርታ አስተካክላችሁ አንብቡት።
"…ከነገረኛ ካሜራማን ፈጣሪ ይሰውራችሁ። መልካም የኣጀንዳ በአል… ኦኦ ምን ሆኜ ነው መልካም የኣሸንዳ በአል።
• በስቶኮሆልም ሲንድረም ደግሞ ምንድነው? አለዛሬ ሰምቼም አላውቅ።
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ምሽት 2:00 ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b
• ትዊተር 👉https://twitter.com/MerejaTV
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/bbq3nw3EGag
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሻሎም… ሰላም…!
"…የኣሸንዳ በአል ነው አሉኝ።
"…የጾመ ማርያምን ፍጻሜ ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ በተለይም የላስታ ዐማራና የአገው እና የትግሬ ልጃገረዶች የሚያከብሩት በዓል ነበር። ሶለል፣ አሸንድዬ፣ ኣሸንዳ ይሉታል በየቋንቋቸው። ይሄ በዓል ፍጹም መንፈሳዊ በዓል ነበር። የሚታወቀውም በዚያ መልኩ ነበር። ዕድሜ ለወያኔ መጥታ ይኸው ያን የመሰለ አፈር ከድሜ አስጋጠችው።
"…አሁን ለመጪው ትውልድ ኣሸንዳ በዚህ መልኩ ዘመናዊ ሆኖ፣ በሜካፕ ተሸፍኖ በዚህ መልኩ እንዲተላለፍ እየተደረገ ነው። መልካም የአጀንዳ በአል።
መልካም…
"…ዘወትር እግዚአብሔርን ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ቁጥሩ ሞልቶ 5መቶ አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…እሁድ እሁድ ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ዕለቱ ማስታወቂያ ነው። የዛሬው ማስታወቂያ የሚያስተዋውቀው የመረጃ ቲቪን በሰዓቱ እንድትከፍቱ፣ እና ጫ ብላችሁ እንድትጠብቁ ነው።
"…የዐማራ ትግል ወደ መቋጫው እየቀረበ ነው። ነጠላ ኩታ ሸማ ጋቢው ታሽቶ፣ ተረግጦ በሳሙና ታጥቧል። ተጠምዝዞም እድፍ ጉዱፉም ወጥቷል። አሁን ያለችዋ ውኃ ከነጠላው ጫፍ ላይ ነው። እና እሷን ደግሞ ጨመቅ አድርገን እድፍ ጉድፉን መገላገል ነው። አለቀ።
"…ዛሬ ጎልያድን ለመገንደስ፣ ሠራዊቱንም ለመበተን እኔ ዘመዴ የዳዊት ጠጠርን ሆኜ ልከሰት ነኝ። መራር እውነት ልግትህ፣ አፍህን ፈልቅቄ ላጠጣህ ልመጣ ነኝ። ወደህ ሳይሆን በግድህ ጨጓራህ እየነደደ፣ ሀሞት እየተፋህ፣ እያፋሸክ፣ እያንጠራራህ ትሰማኛለህ። እውነት መራር ናት ነገር ግን ፍሬዋ ጣፋጭ ነው።
• ዛሬ በዕለተ እሁድ ምሽት 2:00 ሰዓት በመረጃ ቲቪ እኔ አፍራሹ ዘመዴ የጠላትን ሴራ ለማፍረስ እመጣለሁ እና ጠብቁኝ። ሰምታችኋል አይደል?
ይሄንንም አትላኩልኝ…!
"…ዘመዴ የዋን ዐማራዎቹ ዘርዓያዕቆብ (ናቲ)፣ ሮቤልና አኪላ (ኤልያስ) የመረጃ ቲቪን ባለቤቶች እና አንተን እየረገጧችሁ ነው ብላችሁ ብዙዎቻችሁ ይሄን ምስል ልካችሁልኛል። አትላኩልኝ። እኔው ራሴ ነኝ ይረግጡኝ ዘንድ የፈቅላቸው። 😂
"…የመረጃ ቲቪ ባለቤቶችን በመዘቅዘቅ የሚቆም ትግል የለም። እነሱም በስድብ የሚሸበሩ አይደሉም። መረጃ ቲቪ ደግሞ የራሴ በሉት። የእኔ የዘመዴ። እናም እነሱን ስንሰድብ፣ ስናዋርድ እኔ የመረጃ ቲቪ ቅጥረኛ መስያቸው ባለቤቶቹ በቃ በአንተ ምክንያትማ ሽመልስ የባልደራሱ፣ የጎንደሩ ስኳድ፣ እነ አኪላ ከሰደቡን ዘመዴ ውረድ የሚሉኝ መስሏቸው ነው። እሱ አይታሰብም። አይሞከርም።
"…ደግሜ ልናገር እናንተም ፃፉ። ስመ ጥምቀቴ አክሊለ ገብርኤል፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው፣ የሐረርጌው ቆቱ መራታው ባለ ማዕተቡ ዘመዴ የዐማራን መርገምት ላፀዳ፣ ሾተላዩን ልነቅል፣ ጎልያዱን ልገነድስ የዳዊት ጠጠር ሆኜ ነው የመጣሁት። ብዙዎች ቀልድ ይመስላቸዋል። የምሬን ነው።
"… አሁን የዐማራ ትግል ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ ነው። እኔ ለክፌው ያልቀለለ፣ ነቅንቄው ያልተነቀለ፣ ሳልሟገተው ያልሟሟ፣ ያልሟሸሸ፣ ከብሮ የነበረ ያልተዋረደ፣ ውቃቢ ያልራቀው፣ ድምፁ ያልሰለለ፣ ውቃቢ ያልራቀው፣ የበግ ለምዱን ገፍፌ ተኩላነቱ ያልተገለጠ ማን አለ?
"…እነአኪላ አውርተውኝ፣ ተሟግተውኝ፣ ሓሳቤን እንደማልቀይር አስረግጬ ነግሬአቸው፣ ሳትፈሩ እርገጡኝ ብያቸው፣ ፈቅጄላቸው ነው መርቄ ይቅናችሁ ብዬ የሸኘኋቸው። ወዳጄ የነጠላው ጫፍ እየተጨመቀ ነው። ማበጠሪያው ቀርቧል። ወንፊቱ ሰፌዱ ላይ ትወጣለህ ትበጠራለህ።
"…ጥፋ ሲልህ ወስዶ ከእኔ ጋር ያላትምሃል። እኔው አይደል እርገጡኝ ብዬ የፈቀድኩላችሁ? ይልቅ የመረጃ ቲቪን በማሸማቀቅ አትድከሙ። ሌላ ሞክሩ።
• ይኸው ነው።
ምስጋና ለጋሽ አስታጥቄ።
"…ዘመዴ ጋሽ አስታጥቄ የላከልን ስንቅና ትጥቅ በሰላም ከሰፈራችን ደርሷል። እናም በደንብ አድርገህ አመስግንልን ብለውኛል። ፋኖዎቹ።
• ብሬ ጁላ ሆይ ሰሞኑን ደግሞ ጨምርላቸው።
ይሄን ማመን ነው የሚያቅተው።
"…ተወው ተወው ይውሰደኝ ዴቭ። ይውሰደኝ አለ ዮሐንስ ዳንኤል በርሄ። ዴቭም አይወስዱትም፣ አይወስዱትም ይላል በድፍረት። ባለጊዜ ጀቲ ኑዋምቲ ጀርቲም ብሏል የኦሮሞው አዝማሪ። ጋይስ እኔ ተደምሜያለሁ። እኔ ዮሐንስ በርሄንና ዴቫን ምን አገናኛቸው? ይሄ የቲክቶክ ብር ብቻ አይደለም ልጆቹን እንዲህ ያወበራቸው። ወቸ ጉድ…
• ኢትዮጵያዬ ፈጣሪ ይሁንሽ። ታከለ ኡማሆይ የኢትዮጵያ አምላክ የእጅህን ይስጥህ።
• በመቀሌ ሴት ተደፈረ፣ ሰው ተዘረፈ ይባልልኛላ… ጉድ እኮ ነው።
“…አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።”
ዘፍ 4፥11
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ናቲ አንደግምም ወይ ምን እያለኝ ነው…? ደፋሪ በመንግሥት እና በሕዝብ ገንዘብ ምስኪን ሴት ደፋሪ፣ የወንድኛ አዳሪ፣ ናቲ አንደግምም ወይ? …መጫወቻ ሜዳው ሪንጉ ውስጥ ገብተናል። ወይ እናንተ ወይ እኔ በዝረራ እንሸናነፋለን።
"…ናቲ በአባቱ ጎንደሬ በእናቱ ጉራጌ፣ በሃይማኖቱ ጴንጤ ነው። እና ስኳድ ሆኖ ጴንጤ ሆኖ ባይጋተተኝ ነበር የሚደንቀው። ዶር ምስጋናውም ጰንጥጧል አሉ። ወዳጄ ውጊያው የመንፈስ ነው። ድብን አድርጌ አሸንፋችኋለሁ።
"…ደፋሪ፣ ሴት አሳዳጅ፣ ወንድኛ አዳሪ አንደግምምወይ ዘማዊ ጋለሞታ ለሴቶች መደፈር፣ ጥብቅና ሊቆም አይችልም። ሃገር ሙሉ ሕፃናት ሲደፈሩ ዓይቶ እንዳላየ ዝም ያለ መርጦ አልቃሽ አሁን ጎጃምን ለመስደብ፣ ዘመነ ካሤን ለመግደል ምድረ ግንቦቴና ስኳድ ቢንደፋደፍ ንቅንቅ የለም። አፍራሹ ዘመዴ አፍርስሃለሁ። እኔ የዳዊት ጠጠር ነኝ። አንጫጫችኋለሁ ስል በሙሉ ልቤ በኩራት ነው።
• ይኸው ነው።
ዱለታ በቲክቶክ መንደር።
"…የዱለታ መድረኩ የቤቱ ባለቤት Kidus ዘተዋሕዶ ይባላል። ዘሩን አላውቀውም። ብር ሰብሳቢዋ ቃልኪዳን ትባላለች። የምትሰበስበው ብር ለሰላማዊ ሰልፍ ማዘጋጃ ነው።
"…ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ለፈቃድ 75 ሺ ብር ነው ተብለናል ነው የምትለው። … እንግዲህ ለሟች ለሕፃን ፌቨን ድምጽ ለመሆን ስለፈለግን ብር አግዙን።
• ኢሊሌ 9 ሰዓት ፕሮግራም ነገ አለን። (ዛሬ ማለት ነው) 75 ሺ ብሩ የሚከፈለው ለወዳጅነት ፓርክ ነው ትላለች።
• ማክሰኞ በግዮን ሆቴል ደግሞ የሻማ ማብራት ይካሄዳል ይላል አንዱ። በሻማ ማብራት ፕሮግራሙ ላይ ታላላቅ የመንግሥት ባለ ሥልጣናትም ይገኛሉም ይላል። አዘጋጁ ደግሞ የሟቿን ሕፃን እናት በቤቱ ያስቀመጣት ዮናስ ቬጋስ ነው ይላል። ዮናስ ቬጋስ በጆን ዳንኤል መታሠረም ምክንያትም ጠርተውት ሄዶ ነው። ጠሪው ራሱ ዮኒ ቬጋስ ነው ነው የሚለው።
"…በሁለተኛው ቪድዮ ላይ ቃል ትላለች። እንደ ሌባ 35 ሲም ካርድ ስላለኝ እኔን በተአምር አይዙኝም ትላለች። ሜካፓም ሴቶች ዘረፋውን ያጧጡፉት ይዘዋል። ማማር 1 ሚልዮን ብር በላችን ብለው የሚያለቅሱ ስደተኞችን አስታውሱ።
"…ሌባ ሁላ…!
"…ለምን እንተቋረጠ እነግራችኋለሁ። አሳያችሁማአለሁ።
"…በሕፃን ሄቨን ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት በኢሊሊ ሆቴል የጠራው መግለጫና የሻማ ማብራት ፕሮግራም እንዲቋረጥ ተደርጓል። ለግዜው ምክንያቱ በይፋ አልተገለጸም።" በማለት በፌስቡክ ገጿ ላይ መረጃ ያሰፈሩት ጋዜጠኛ Konjit Teshome እና የጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት አዲሱ መሠረት ሚድያ ናቸው። ፌስቡክ ገጻቸውን ተመልከቱ።
"…ለምን ኢሊሊ ሆቴል እንደተመረጠ፣ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ባህርዳር ድረስ ምን ታስቦ እንደነበር ቪድዮ እለጥፍላችኋለሁ። ዕድሜ ለወፎቼ።
"…ፀረ ዐማራዎቹ እነ ኤልያስ መሠረት፣ መርጦ አልቃሾቹ ለጎንደር እና ለጎጃም ሕዝብ አዘጋጅተውት የነበረውን የጥፋት ድግስ አምክኜዋለሁ። እኔ ዮኒ ቬጋስ፣ እነ መማር አለባቸው፣ እነ ጆን ዳንኤል፣ አጠቃላይ ቀፋይ ቲክታከሮች እነ ያሬድ ያያ ዘልደታ፣ ለጎጃም ሕዝብ አዘጋጅተው የነበረውን የሞት ድግስ አክሽፈነዋል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ኢሊሊ ሆቴል የኦሮሞ ሆቴል ነው። እስኳድ ኦሮሞን ከዐማራ የበለጠ ለማጋጋል ነበር የመረጠው። ኦሮሞዎቹ አጀንዳውን ፈልገውት የነበረ ቢሆንም እኔ ጣልቃ ገብቼ አፍርሼዋለሁ።
• ገና ሕፃኗን ማን ገደላት ብለን ሁላ እንጠይቃለን። ነክሻለሁ፣ ነክሻለሁ። ሳላደማማ አልፋታህም። እንዴት ብር ሊሰበሰብ እንደነበረም ቪድዮውን እለጥፍላችኋለሁ። የህፃኗን ነፍስ ይማር። ሴራውን ግን እናጋልጣለን። ክሊኒኩም የለሁበትም እያለ ነው።
• ቆይቼ እመለሳለሁ።
በድጋሚ እጠይቃለሁ።
"…የሟች ወላጅ አባት አቶ አወት ግርማይ ትግሬ ነው። ትግሬዎች የተንጫጩት ለዚህ ነው። የአወላጅ አባት ዘር የታወቀ ነው። ትግሬ ነው ትግሬ ነው። እነ ፓስተር ኤድመንድን ሰብአዊነት ሰብአዊነት ያጫወታቸው፣ የሞጣ ነውር እና ብልግና እንዳለ ሆኖ ሞጣን ካልከሰስኩ ሞቼ እገኛለሁ ያለው ለዐማራ አዝኖ አይደለም። አሁን እኔ የምጠይቀው ሌላ ነው።
ሀ፦ የሟች ህፃን ወላጅ እናት አበቅየለሽ፣
ለ፦ የተከሳሹ አቶ ጌትነት እና
ሐ፦ የተከሳሹ የአቶ ጌትነት ሚስት
• የሦስቱ ሰዎች የትውልድ ሀገር የት ነው። በድጋሚ እጠይቃለሁ። ሦስቱም ጎጃሜዎች ናቸው ወይስ ጎንደሬዎች አስረዱኝ።
•…ባሕርዳር ሰው የለም እንዴ? እነዚህን ሰዎች የሚያውቅ ጎረቤት የለም እንዴ? ፍጠኑ ንገሩኝ። እኔ የያዝኩት የነብር ጭራ ነው። ነክሼ ሳላደማው አልመለስም። ጎጃም ባሕርዳሮች ጻፉልኝ፣ አናግሩኝ። መልሱልኝ።
• ፍጠኑ። ሌላ አትዘብዝቡብኝ። ወደ ቀጣይ ጮማ መረጃ እንድናልፍ ቶሎ መልሱልኝ። የአሜን ሆስፒታል የሥራ ኃላፊዎች ሌላ ጉድ ይዘው እየመጡ ነው። ጉድ በል ጎንደር። ፍጠኑ አልኳችሁ ፍጠኑ።