zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሐምሌ ፲፭ ዕረፍቱ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ (ከ306-373 ዓም) … ታሪኩ ከላይ ይነበብ።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…26 ሺ ሰው አንብቦት 16 ሰው 😡 ብው ብሎ የበሰጨበትን ርዕሰ አንቀጽ አንብበናል። አሁን ደግሞ ተራው እናንተ በጨዋ ደንብ በጉዳዩ ላይ በተነሣው ሓሳብ ላይ አነሰ የምትሉትን ጨምራችሁ በዛ የምትሉት ካለ ደግሞ ቀንሳችሁ የራሳችሁን ሓሳብ የምትሰጡበት ጊዜ ነው። እስከ መኝታ ሰዓታችን ድረስ የእናንተን ሓሳብና ምልከታ ነው የምንኮመኩመው።

"…ጨዋነት የጎደለው የመደዴ፣ የስድአደግ፣ የባለጌ፣ አሳዳጊ የበደለው፣ የወኔ ፀያፍ የስድብ ቃላትን ፔጄ እንደማያስተናግድ ለፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ ለፀረ ዐማራ የብአዴን ስኳዶች እንዲደርስልኝ እፈልጋለሁ። እቀስፋችኋለሁ።

"…ኦነግ ዐማራን ሲገድል ኡኡ፣ የዐማራ ፋኖ ነኝ ባይ ዐማራን ሲገድል ለምን ይጮሃል? በውስጥ ፍቱት፣ በስር ተነጋገር የምትል አስመሳይ ሰረሰርህ ይውለቅና እዚህ ቤት ዝር እንዳትል።

• ገበሬ አባት ያላችሁ፣ እነ መከታው ማሞ፣ እነ አበበ ጢሞ፣ እነ ሀብቴ ወልዴ፣ እነ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ፣ እነ ኮሎኔል ታደሰ፣ እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ እስኪያወግዙት እኔ ችክ ብዬ እቀጥላለሁ።

"…ጎጃም ላይ ብአዴን ተንበረከከ ብሎ ዋይ ዋይ ሲል የነበረው ሀብታሙ አያሌው፣ ወለጋ ላይ ዐማራ ታረደ፣ ጋዜጠኛ ወግደረስ ታፈነ ብላ መሃረቤን አቀብሉኝ ስትል የነበረችው ጄሪም አላየችውም አሉ። የኡጋንዳው እስኳድም፣ የአሜሪካው ስኳድም ይሄን የእነ መከታው ጦር መሪ የሠራውን አላዩትም አሉ። እነ ፋኖ ባርች አባቷ ሲገደሉ አላየችም አሉ።

"…እኔ እንቅልፍ ያጣሁበትን ይሄን ዘግናኝ የግፍ ቪድዮ የማያወግዝ ዐማራ ነኝ፣ ለዐማራ ነው የምታገለው ባይ ሁላ አምላክ አይለመነኝ አልምረውም። ችክ ምንችክ ነው የምልበት። ጠብቅ።

• በሉ የእናንተን ሓሳብ መስጠት ጀምሩ…✍✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይቀጥላል…✍✍✍

👆ከላይ② የቀጠለ…✍✍✍  "…ይሄን የተቀደሰ ተግባሬን ትናንት በትግራይ ልጆች ላይ ብልጽግና፣ ሻአቢያ ሲፈጽሙት በቴሌቭዥን አሳይቼ ሞግቻለሁ። ያኔ ትግሬ ስለሆነ ነው። እናቱ ሽሬ፣ አባቱ ጉራጌ ስለሆነ ነው። በረከት ስምኦን ከፍሎት ነው ብሎ ከብልፅግናው ካድሬ እኩል በወቅቱ ወዶ ገቡ ኖሞር ቡድን ሆኖ ያልዘበዘበኝ ስኳድ አልነበረም። እኔ ግን ጁንታን እየተቃወምኩ በንፁሐን የትግራይ ተወላጆች ላይ ይፈጸም የነበረውን ግፍ ለዓለም አሳይ ነበር። ምስጋና ለኤልያስ ክፍሌ ይድረስውና ዛሬ ስኳዱ አፉን የሚከፍትበት ኤሊ የፈረንሳዩን የመረጃ ቲቪ የሳታላይት ካምፓኒ በብዙ "ጭቅጭቅና ውትወታ" አሳምኖ፣ ሬሳ አስከሬን በቴሌቭዥን ማሳየት አይቻልም የሚለውን ሕግ ይሄን ጭካኔ ካላሳየን ታዲያ ዓለም እንዴት ያወረቀዋል? በማለት በመሞገት ነበር የትግራይ ተወላጆችን ግፍ ስናስተላልፍ የነበረው። ትግሬ እንዲደግፈኝ ብዬ አይደለም። ትግሬ ወያኔን አምላኪ ይበዛዋል፣ ሊደግፈኝ አይችልም፣ እኔ ግን ድጋፍ ፈላጊ ሳልሆን ፍትሕ፣ ርትዕ እንዲመጣ ፈላጊ ስለሆንኩኝ በሕዝብ፣ በንፁሐን ላይ የሚፈጸምን ግፍ፣ ወንጀልን፣ አረመኔነትን አጥብቄ ስቃወም ነበር። መንጋው የአቢይ ካዳሚ የመበረው ኖሞራም ሁላ ሲንጫጫብኝ አልሰማውም ነበር። ዛሬም እንደዚያው ነው። ወንጀል ሲፈጽም የሚደበቅለት፣ ወንጀል ሲፈጽም የሚያምርበት ነገድና ግለሰብ አላውቅም። ወንጀል ወንጀል ነው። ከቻልክ አብረኸኝ ተቃወም። ካልቻልክ ፈንዳ ጧ በል መብትህ ነው። ይሄን አልክ ብለህ ምንአባህ ልታመጣ ነው?

"…ትናንት እነ መከታው አንድ ቪድዮ አሰራጭተው ደርሶኝ አይቼው ነበር። በዘመቻ ምናምን ከመከላከያ ጋር ተዋግተን ቆስለው የተማረኩ ወታደሮች ናቸው ብለው ነው ቪድዮውን የሚያሳየት። ቪድዮ ቀራጩ ለመከላከያው ጥያቄ ያቀርባል። ስምህ ይለዋል። ይነግረዋል። የጦር ምድብህ ይለዋል፣ ማእረግህ ይለውና በመጨረሻ ብሔርህ ይለዋል መከላከያውን፣ መከላከያውም ይመልሳል። ብሔሬ ዐማራ ይለዋል። ዐማራ የት ሲለው ዐማራ ጎንደር ነኝ። ደቡብ ጎንደር ይለዋል። ስሰማው ለእኔ ግልፅ ነበር። ተመልከቱ የመከታውን ጦር ከሚመሩት፣ የአሰግድንም ጦር ይመሩ ከነበሩት ፋኖዎች አብዛኞቹ የጎንደር ሰዎች ናቸው። አርበኛ አሰግድን በማሳደድ፣ መከታውን በማገዝ፣ እስክንድርን በሸ በማጽናት ፋኖ ድርሳን ብርሃኔ አንደኛ ነበር። ፋኖ ድርሳን የታረቁትን መከታውንና አሰግድን ካለያዩ ሰዎች መካከል አንዱና ለእኔ ዋነኛው ክፉ መሰሪ የሆነ ሰው ነው። ከወሎ ተነሥቶ የሸዋን ፋኖ እየፈጀ ካለው ከስኳድ በላይ የሸዋን ፋኖ እየፈጀ ያለ ሰው ነው። የድርሳንን መርዝ እኔ ዘመዴ ነኝ የማስተፋው። ጠብቁኝ። ድርሳን አሁንም ከእስክንድር ተለይቻለሁ በማለት ምን ይዞ ሊመጣ እንዳሰበ የማውቀው እኔው ዘመዴ ነኝ። ፕላን ቢ ህን እዚያው ቀቅለህ ትበላታለህ። እጠይቃለሁ። በሸዋ የሸዋ ፋኖን የሚመራ የሸዋ ሰው ጠፍቶ ነው በጎንደር እና በእነ ድርሳን የሚመሩት? የመከታው የጦር አዛዦች እንዴት ጎንደሬ ብአዴን የጎንደር ተወላጆች ሆኑ? በዚህስ ልማድ በጎንደር፣ በጎጃም የሸዋ ፋኖ መሪ ሆኖ የሚመራ የምታውቁት ካለ ንገሩኝ። የጎንደር ስኳድ ሸዋ ላይ ምን እየሠራ ነው? ኡጋንዳ ምን እየሠራ ነው? አቶ አሰግድ ሲያዝ፣ ውባንተ ሲገደል፣ ዘመነንና ምሬ ላይ ዘመቻ የሚከፍቱት ለምን ጎንደሬ ነን የሚሉ እነ ቅማንቴው የእንግሊዝ ሳሚ ስኳዶች ሆኑ? ሸዋዎች ደፍራችሁ ጠይቁ። አለበለዚያ በስኳድ ትበላላችሁ።

"…እነ ሀብታሙ በሻህ በአደባባይ ጋላ ነኝ እያሉ ለምንድነው የእነ መከታውንና የእስክንድርን ቡድን በይፋ የሚደግፉት? አቶ አሰግድን፣ እነ ደሳለኝን ለምንድነው በአደባባይ ይረሸኑ፣ ይወገዱ ብለው በድፍረት የሚናገሩት? ከመከታው ቡድን ውጪ ያሉትን የፋኖ አደረጃጀቶች ጨፍጭፉ ብለው በአደባባይ በቪድዮ የሚያውጁት ምን ስለሆኑ ነው? እደግመዋለሁ ጠርጥሩ። ለዘሁኑ በጊዜ በእንጭጩ የእኚህ ሽማግሌን ግፍ አይቶ እግዚአብሔር እንዲጋለጡ አደረገ እንጂ በሸዋ የሚገኙ የሸዋ ዐማሮች በጎንደር እስኳድ እና በቱለማ ኦሮሞ በስፋት እየተፈጁ ነው። አርበኛ አቶ አሰግድ ለጎንደሩ አርበኛ አቶ መሳፍንት ያለውንም ማስታወስ ያስፈልጋል። "ምንድነው አቶ መሳፍንት ለምንድነው ሸዋን መጨቆን የፈለጋችሁት? ሸዋ ላይ ያሰባችሁት ተንኮል አለ ማለት ነው?" እያለ በግልፅ ይናገር የነበረውንም ማስታወስ አስፈላጊ ነው። አዳሜና ሔዋኔ ፈንዳት እንጂ እኔ እንደሁ ይሄን ነቀርሳ የስኳድ ቡድን መንቅዬ እስክጥለው ድረስ በድፍረት ብቻዬን መሟገቴን አልተውም። ጎንደሬው የብአዴን እስኳድ እስክንድርን ሸዋ ላይ ጭኖ የሸዋን ሕዝብ እንዲያስፈጅ አልፈቅድም። እፉ ነው። ካካ ነው። ወጥሬ እዋጋችኋለሁ። በበቃኝ እስክዘርራችሁ ድረስ አልፋታችሁም። ደግሞስ ምንም አባክ አታመጣም።

"…ዶ/ር ለመባል 12 ዓመት የፈጀበት ቅማንቴው የጎንደር ስኳድ መሪ ምስጋናው አንዷለም እንኳ የቲክቶክ ቤት አስከፍቼው የጎንደር ዐማሮችን ሰብስቦ ሲንበጫበጩብኝ ነበር ያመሹት። ደግሞ እኮ ቀድተው የሚልኩልኝ የጎንደር ዐማራ ወዳጆቼ ናቸው። ሲጠቃለል እነ ምስጋናው፣ እነ መሳፍንት ባዘዘው እና ሌሎች አነስተኛና ጥቃቅን ምድረ ኮተት ሌባ ሁላ ሌባ ነጥዬ የምመታውን እኔ ዘመዴን ከጎንደር ሕዝብ ጋር እንደተጣላሁ አስመስለው ሲያወሩ ስሰማቸው በሳቅ ነበር ፍርፍር የሚያምረኝ። "ዘመድኩን ሳይሆን አለ አንዱ ጀዝባ ስኳድ ከዘመድኩን ጀርባ ያለውን ኤልያስ ክፍሌ እና መረጃ ቲቪን ነው መቃወም" እያለምሲዘበዝብ ነበር። ምድረ ደናቁርት መረጃ ቲቪ በባለሙያ የተመሠረተ፣ በእውቀት የተገነባ ነው። መረጃ ቲቪ ደግሞ የእኔ ነው። የዐማራ ድምጽ ነው። የጭቁኖች ድምጽ ነው። አለቀ። መረጃ ቲቪን መረጃ ቲቪ እንዲሆን ደሜን የሰጠሁ ሰው ነኝ። እኔ ኤልያስ ክፍሌም ቢሆን እኔ የማውቀው ድሮ በሥራው ሲሆን በደንብ ያወቅኩት ግን ወደ መረጃ ቲቪ ከመጣሁ በኋላ ነው። ኤልያስን በማግኘቴ የማልደብቃችሁ እድለኝነት ይሰማኛል። ኤልያስ ክፍሌ ምርጥ ሰው ነው። በዘሩ ልቅም ያለ ዐማራ ነው። ኤልያስ ምሑር ነው። ዲሞክራትም ነው። ኤልያስ እነ አበበ በለውን እንጀራ የጋገረላቸው፣ እነ ሀብታሙ አያሌውን ሰው ያደረጋቸው፣ እስክንድር ነጋን በጎዶሎው ሁሉ ሲሞላለት የኖረ ሰው ነው። አሁን እስክንድር ነጋ የያዘውን የሳታላይት ስልክ ገዝቶ የላከለት ኤልያስ ክፍሌ ነው። ግንባሩ በፋኖ ስም ሰብስቦ የበላውን ዶላር ሥራ ፈትቶ ፕሮጀክት ቀርጾ ያሰባሰበላቸው ኤልያስ ክፍሌ ነው። ኤልያስ ክፍሌ ዌብሳይት፣ ዶነር ቦክስ መክፈት ለማይችሉ ደናቁርት በነፃ ከፍቶ ያስረከበ ወንድም ነው። እዩኝ እዩኝ የማይል፣ ተደብቆ ለሀገር የሚጠቅም ሥራ የሚሠራ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው።

"…እኔ ኤልያስን በአካል ያየሁት ሁለቴ ነው። እስከዛሬ የማወራው በስልክ ነው። ኤልያስ ክፍሌ አንድም ቀነረ በሥራዬ ላይ ጣልቃ ገብቶ አያውቅም። እኔና ኤልያስ የምንገናኘው እኔ እሁድ የመረጃ ቲቪ የቀጥታ ስርጭቴን ላቀርብ አንድ ሰዓት ሲቀረኝ እሱ የዕለቱን የፎቶና የቪድዮ መረጃዎቼን ሊያዘጋጅልኝ ስፈልገው ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ ኤልያስም እንደማንኛውም ሰው እኔ የምለውን ከመስማትና ከማየት በቀር አስተያየት እንኳ ሰጥቶኝ አያውቅም። የማስታውሰው አንድ ቀን ብቻ ነው። መርሀ ግብሬን ከጨረስኩ በኋላ እንዲህ አለኝ።

ኤልያስ ክፍሌ፦ ዘመዴ ስለ አንድ ጉዳይ ላወራህ ነበር። ብዙ ሰው አስተያየት እየሰጠ ስለሆነ አለኝ። (እኔም ስለምን እንደሆነ ስለጠረጠርኩ ጠየቅኩት በቀጥታ እንዲህ አልኩት።

እኔ ዘመዴ፦ 👇② ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አመሰግናለሁ…🙏🙏🙏

"…እስክንድር ነጋ የሚመራው፣ እነሀብቴ፣ እነ ኮሎኔል ታደሰ፣ እነ ኮሎኔል ፈንታሁን መሁባው፣ እነ ማስረሻ ሰጤ በሚመሩት በአዲሱ የዐማራ ድርጅት ውስጥ ያለውና በእነ ሻለቃ መከታው ማሞ እና በእነ አቤ ጢሞ የሚመራው የሸዋ ፋኖ ጠቅላይ ዕዝ የመኮይ ፋኖ መሪ ደጀኔ ከተማ የተባለ ጨካኝ አረመኔ በግፍ የገደላቸውን እኚህን ምስኪን አዛውንት ጥርት ያለ ቪድዮ ላኩልኝ ብዬ ነበር። እናም ጥርት ያለውን ቪድዮ ስለላካችሁልኝ እጅግ አድርጌ አመሰግናችኋለሁ።

• ርዕሰ አንቀጼን አዘጋጅቼ ጨርሻለሁ። እስከዚያው እኚህን አባት ስሟቸው። አባት ያላችሁ፣ አባታችሁን የምትወዱ አልቅሱላቸው። እሪሪ በሉላቸው። ይሄ ከአሁኑ በዐማራ ላይ እጁን በዚህ መልኩ የጫነ አረመኔ ቡዱን አሁን ዝም ከተባለ ነገ ሥልጣን ቢያገኝ ማን ሊተርፈው ነው? እነሱ ዝም ቢሉ እኔ ዝም አልልም።

"…ዶላሩ፣ ፓውንዱ፣ ዩሮውን ሕዝቡ እያዋጣ የሚልክልህ ንፁሐንን ልትጨፈጭፍ ነው እንዴ? ህጻን ሄቨን በግፍ ተደፍራ ተገድላለች፣ ፍርድ ቤት ፍትሕ ነው የሚለውን ወስኗል። ሕዝብ ግን ስላልረካ ፍትሕ እያለ እየጮኸ ነው። እናስ እኔ ይሄን ግፍ ብቃወም ምን ይፈረድብኛል።

• ይሄን ሸዋ ገብቶ የሸዋ ዐማራን እያሳደደ እየፈጀ ያለ የዐማራ ሸኔና እስኳድ ድራሹን ሳላጠፋማ አልመለሳትም። እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው። ማርያምን እነ ዶክተር ምስጋናው አታሸንፉኝም። እነ ሙላት አድኖ አታሸንፉኝም። እኔ ዘመዴ መርጬ አላለቅስም።

• ወገን ይሄን ሰቅጣጭ ቪድዮ እያያችሁ፣ እያለቀሳችሁ ጠብቁኝ። መጣሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘወትር እግዚአብሔርን ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። ቀጥሎ የምናመራው በአዲሱ መርሀ ግብራችን መሠረት ከማክሰኞ እስከ አርብ ድረስ ወደማቀርበው ተወዳጁና ተናፋቂው ርዕሰ አንቀጻችን ይሆናል።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን እንቅልፍ ባሳጣኝ በእኚህ አረጋዊ አባት የግፍ ግድያ ዙሪያ ነው። በሚገርም ሁኔታ ከሌላ የቲክቶክ ፔጅ ላይ ሰውየው የተከሰሱበትና ለተከሰሱበት ክስ ለገዳዩ የመከታው ፋኖ የሰጡት አንጀት የሚበላ ሙሉ ቃል ያለበት ቪዲዮም ሲንሸራሸር አግኝቼው ለርዕሰ አንቀጽነት መርጬዋለሁ።

"…አንዳንድ ግንቦቴዎች፣ የግንባሩና የስኳዱ፣ የአዲሱ የእስክንድር ነጋ ደጋፊዎች ነን የሚሉ አካላት "ለምን ቪድዮው ታየ? ፋኖን ለመከፋፈል ነው። የፋኖን ስም ለማጠልሸት ነው ብላብላ ብለው ለሃጫቸውን ሲያዝረበርቡም እያየሁ ነው። ኦነግ ሸኔ ዐማራን ጨፈጨፈ ብዬ ስጮህ ግፍ ነው፣ አረመኔነት ነው እያለ ሲደሰኩር የነበረው ሁላ እኮ ነው አሁን ይሄኛውን ዐማራው ዐማራውን በጭካኔ የሚገድለውን "ለምን ታየ? ፋኖ ለምን ተወቀሰ? እያለ የሚንዘባዘበው። እኔ ደግሞ እነ እስክንድር፣ እነ መከታው፣ እነ አቤ ጢሞ ለዚህ ምስኪን ሽማግሌ የግፍ አገዳደል መግለጫ እስካልሰጡ፣ ገዳዩን የፍትሕ እርምጃ እስካልወሰዱበት ድረስ የነከስኩትን ሳላደማ መች እተውህና ነው። ገና ጭካኔውን በቴሌቭዥን ሁላ ነው የማሳየው። ሌባ ሁላ።

"…ይሄ ወንጀል ሊያስለቅስህ ሲገባህ መጥተህ በፔጄ ላይ ድርጊቱን ደግፈህ እኔን ለመስደብ የምትላላጥ አረመኔ ፀረ ዐማራ ገተት ስኳድ ሁላ እቀስፍሃለሁ። መልስ እንኳ አልሰጥህም። ንጹህ ዐማራ በሸኔ፣ ንፁህ ዐማራ በወያኔና በብልፅግና ሲገደል ዋይዋይ፣ ንፁሕ በራሱ ዐማራ በፋኖ በግፍ ሲገደል ለምን ምስጢር ይወጣል ስትል ልሰማህ ነው? ገተት ሁላ…

"…በርዕሰ አንቀጹ ለመወያየት ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለማስታወስ ያህል ነው…

"…ጎጃም ውስጥ የብአዴን አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ለመቀጣጫ በሚል ሕዝቡ እንዲንበረከኩ ያደርጋል። እንደሌላው ከመግደል፣ ከመደብደብ፣ ከማረድ ጋር የማይነጻፀር ቢሆንም ይሄም ቢሆን እጅግ ነው፣ በካሜራ ቀርጾ መበተኑም ጽዩፍ ነበር። የሚወገዝም ነው።

"…ግርማ የሺጥላ አሬሮ አያቱ ኦሮሞ ነው በለው፣ ድፋው ሲል የከረመ መንጋ ግን በጎጃም ውስጥ ቅቡልነት ማጣቱን ተከትሎ "የብአዴኖችን መንበርከክ" ምክንያት በማድረግ በሁለት ወገን የተሣሉትን ሰይፎቹን ሰይፍ ማሲንጋን እና ሰይፍ እስክንድርን ይዞ ይከትፈው ገባ። ከዚያ በሀብታሙ አያሌው ባራኪነት ድርጊቱ በፅኑ ተወገዘ።

"…አምባሳደር ማሲንጋ መግለጫ አወጣ። ስኳድ በቲክቶክ ተንጫጫ፣ ብአዴንም፣ ብልጽግናም፣ የኦነግና የሂው ሠራዊትም ኡኡ አሉ። እስክንድር ነጋም "ዓለምአቀፍ አጣሪ ቡድን ገብቶ ያጣራ አለ" ዘይገረም ነበር።

"…ቆይቶ ራሱ ሀብታሙና እስክንድር ባቋቋሙት፣ እስኬው ብሬዘዳንት በሆነበት፣ በአዲሱ ድርጅት፣ በዐፋሕድ ዘመቻ መምሪያ በሻለቃ መከታው ማሞ ጦር ስር እኚህ ሽማግሌ "አልፈራም ግደለኝ" እያሉ በምታዩት መልኩ በእስኬው ፋኖዎች በግፍ ተገደሉ። አባት ያለው ሁሉ አለቀሰ። አዘነ። ድርጊቱንም አወገዘ።

"…እስከ አሁን ግን አምባሳደር ማሲንጋም፣ ብሬዘዳንት አስክንድርም ግፉን አላወገዙም። ሀብታሙ አያሌው፣ አበበ በለውም ትንፍሽ አላሉም። ለሸዋ ሰሞነኛ መንሰፍሰፍ እያሳየ ያለውና በዘመነ ካሤ ሰበብ የጎጃም ሕዝብ ላይ እየዘመተ ያለውም የጎንደሩም ስኳድ እስከአሁን በእኚህ የሸዋ አዛውንት ግድያ ትንፍሽ አላለም። ክርስቲያኖቹና በጻድቃኔዋ ማርያም ሲምሉ ፍዝዝ የሚያደርጉት መከታው ማሞና አቤ ጢሞም ጭጭ ብለዋል። የተገደለው የሸዋ ሰው ስለሆነ ዝም ጭጭ ማለት ይደብራል። ሸኔስ ከዚህ በላይ ምን አደረገ?

"…ሸዋ ግን ፈጣሪ ይሁንህ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘወትር በቤቴ እግዚአብሔርን ያመሰግን ዘንድ የምጠብቀው 1ሺ ሰው ሞልቷል። ባለፈው ሳምንት በወሰንኩት ውሳኔ መሠረት ከሳምንት እስከሳምንት ከምስጋና ቀጥሎ ሳይቋረጥ ይቀርብ የነበረው ርዕሰ አንቀጻችንም ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ እንደማይቀርብ መወሰኔ ይታወቃል። ሰኞን ማረፍ ስላለብኝ ማለት ነው።

"…ሆኖም ግን በእረፍቴ መሃል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አጫጭር የሆኑ መረጃዎችን ወደ እናንተ ማድረሴ አይቀርም። በዚሁ መሠረት ዛሬም ወደ ከሰዓት በኋላ ላይ አንድ አጣርቼ የደረስኩበትን መረጃ ወደ እናንተ ለማድረስ እሞክራለሁ።

"…ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ዘግናኝ፣ ሰቅጣጭ ቪድዮ የደረሰኝ በቀደም ዕለት ነው። ቪድዮውን ያደረሰኝ ወንድም ቪዲዮው በሸዋ ፋኖዎች የተፈጸመ መሆኑን እንጂ ቦታውንና ሟቹን እንደማያውቅ፣ ገዳዮቹም የእነ መከታው ፋኖዎች ይሁኑ የእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ፋኖዎች እንደማያውቅ ነው የነገረኝ። እኔም ቪድዮውን ይዤ ቀደም ሲል በነበረኝ መልካም ግኑኝነት ወደ ሁለቱም የፋኖ አደረጃጀቶች ቪድዮውን በመላክ መቼና በማን እንደተፈጸመ፣ ገዳይ ማን እንደሆነ፣ የየትኛው ፋኖ አደረጃጀት መሪ እንደሆነም ለማጣራት ሞክሬአለሁ።

"…አንደኛው የፋኖ አደረጃጀት በፍጹም እንዲህ ዓይነቱ ነውር የእኛ አይደለም። ቦታውም እገሌ የሚባል ቦታ ነው። ስሙ የተጠራው ሰውም በእነ እገሌ የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ የዚህ አካባቢ ያለው የፋኖ መሪ ነው በማለት ቃላቸውን ሰጥተውኛል።

"…ሁለተኛው የፋኖ አደረጃጀቶችንም እንዲሁ ጠይቄ ነበር። ገዳዩ የራሳቸው የጦር መሪ እንደሆነ፣ አሁንም ጦሩን በመምራት ላይ እንዳለ፣ ሟችንም በምን ምክንያት በዚያ መልኩ የትና እንዴት በግፍ እንደገደላቸው ሙሉ ቃላቸውን ሰጥተውኛል።

"…እና አንድ የምተቀረኝን የማጣራት ሥራ ፈጽሜ ወደ ምሽት አከባቢ ከነቪድዮው ጭምር ሙሉ መረጃውን እለጥፍላችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ምሽት ከ2:00 ሰዓት ላይ ጀምሮ እንተለመደው በመረጃ የሳታላይት ቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የተሰኘው ለጠላት ሬት ለወዳጅ ወተት ሆኖ የሚዘጋጀው መርሀ ግብር ጓ የሚያደርግ መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።

• እህሳ… ዝግጁ ናችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በወንድ መደፈር ብርቅ ነው እንዴ? በወንድ መደፈር ተገኝቶ ነው እንዴ? ህመምስ አለው እንዴ? የሚል አመለካከት እና እምነት ያለው አረመኔ የሆነ መሪ ተብዬ ጨቅላን "ሺ ዓመት ንገሥ" እያልክ እያወደስክ ትውል ታድርና መልሰህ ደግሞ በወንድ ተደፈርን፣ ተገደልን ብለህ የምን እዬዬ ነው? ማን እንዲሰማህ ነው የምትጮኸው? ለማነው አቤቶታህን የምታሰማው?

"…ይልቅ ይሄን ነውር ጌጡ የሆነ የነውር ጥግ፣ የአረመኔነት ሁሉ መገለጫ የሆነ አስቀያሚ ነፍሰ ገዳይ ሥርዓት ለመቀየር፣ በአፍጢሙም ለመድፋት፣ ለመገልበጥም ወጥረህ ታገል።

• ይኸው ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②…ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ካለው ዐማራ ሕዝብ ጎን ቆሜ ድምጼን ካለው ዐማራ ሕዝብ ጎን ቆሜ ድምጼን

እያሰማሁ ነኝ። ዐማራው እንደ ሕዝብ ትግል ላይ ነው ያለው። እኔ እየጻፍኩ፣ እየጮህኩ ያለሁት እናንተ መርጦ አልቃሾች በምትፈሩት ርዕስ፣ መንካት በማትፈልጉት ጉዳይ ላይ ነው። በጎንደር የጎንደር ጀግኖች እየፈጸሙ ያሉትን ተጋድሎ፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ ያለውን ትንቅንቅ። ጥሎ መውደቅ፣ የጎንደሩን አረም የብልፅግና ስኳድ ሴራ፣ የግምባሩን ሾተላይነት እየጻፍኩ በብዕሬ እየታገልኩ ነው። እናም ወጉ ደርሷችሁ፣ ስለ ፍትሕ መከበር ድምፅ ለማሰማት ወኔ አግኝታችሁ የእናንተን ለሕፃን ሔቨን መጮህ አልቃወምም። ግን ራሳችሁን ቻሉ ለማለት ነው።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ዐማራ ሕዝብ…!
• ሞት ለአረመኔው የብልፅግና ሥርዓት…!
• ፍትሕ በግፍ ተደፍረው ለሚገደሉ ለኢትዮጵያ ሕጻናትና ሴቶች።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዕለቱ አመስጋኞች ቁጥር እንደተለመደው 1ሺህ ሞልቶም አልፏል። ያው ሁለዜ ለዓመታት ያህል ከምስጋና በኋላ ዘወትር ሳምንቱን ሙሉ አቀርብ የነበረውን ተወዳጁን "ርዕሰ አንቀጽ" የሚለው ጦማሬን ከትናንት ቅዳሜ ጀምሮ በሳምንት ሦስት ቀን ማለትም ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ ብቻ እንደማቀርብም የዛሬ ሳምንት ሰኞ መግለፄ ይታወቃል። እናም ዛሬም እንደ ትናንቱ ቅዳሜ እንደ ነገው ሰኞ ርዕሰ አንቀጽ አይኖረንም ማለት ነው። ሆኖም ግን ለዛሬ ርዕሰ አንቀጻችንን የሚመስል ጦማር ወደ እናንተ ላቀርብላችሁ ወደድኩ።

"…ስለዚህች ሕፃን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት በተለይ የብልፅግና አባላት፣ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪ አባላት ጭምር "ምነው ዘመዴ ዝም አልክ? በማለት ስለጨቀጨቁኝ ከነበርኩበት አጀንዳ ወረድ ብዬ የማውቀውንና የደረስኩበትን ላካፍላችሁ ወደድኩ።

"…ለማታው የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ ዝግጅት ላይ ስለሆንኩ እረፍት ቢያስፈልገኝም። ጭቅጨቃው ስለበዛብኝ የሆነ ነገር ልተነፍስ ነው። እናስ ጎዶኞቼ አላችሁ አይደል?

• እስቲ አንድ 100 ያህል ሰው ጮክ ብሎ "አለነ ዘመዴ" ይበል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ንሳ ተቀበልማ አንተው…

ጎንደር እንዴት አለህ?
የውባንተ ወንድም የነሳሚ ሀገር
የእነ ደሬ ሀገር
ጎጃም እንዴት አለህ?
የሳሙኤል ወንድም የዘመነ ሀገር
ወሎ ገራገሩ የአሳምነው ወንድም የነምሬ ሀገር
ሸዋስ እንዴት አለህ?
የሀገር ማገሩ
የምጡቁ አእምሮ የእወቀት መንደሩ
የእነ አሥራት ወልደየስ የእነ አስግድ ሰፈር
እንዲህ የተማረ
ለዐማራ ሕዝብ ሲል የተመራመረ

• ያዝ እንግዲህ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…

እስኪ ዘራፍ ብዬ ልጀምር ግጥም
ወኔን በሚያሞቀው እጅግ በሚጥም
ሸዋ ተነስቼ ልገስግስ ጎጃም
ወሎም ተነስቼ ጎንደር ላይ ልክተም
ከሠርጉ ጠርቶኛል ፋኖ ክንዳለም

አውድማ ተጥሎ ምርቱ እየታፈሰ 
በ 4ኪሎ ሰፈር ሙሾ ተደረሰ።

ሙሾው እንዲህ ይላል…

በሸዋው ምኒልክ ካሣ የጎንደሩን
የጎጃሙን በላይ የወሎ ራስ ሚካኤልን
ከሴት የጣይቱን ስሟን እየጠራ
በነበልባል ክንዱ መጣብን ዐማራ!!

እያለ ያለቅሳል በፍርሃት ርዶ
ፋኖ የ'ርሳስ ዝናብ ሲያወርድበት ማልዶ።

"…እንዲያ ነው…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በተቀበል መሃል…!

"…ይድረስ በአራቱም የዐማራ ጠቅልይ ግዛት ውስጥ ለምትገኙ የፋኖ አባላት…ይሄን ቪድዮ በውጊያ ላይ በትግል ሜዳ ለሚገኙ ፋኖዎች አድርሱልኝ። ይድረስ የዐማራ ፋኖን ሳትቀላቀል አንተ የተለየህ ሁነህ ይምርህ ይመስል በየከተማው በየመንደሩ ለምታውደለድል ለዐማራ ወጣት። ልብ ብለህ ስማኝ ቪድዮውንም ሰብሰብ ብለህ እየው፣ ተመልከተውም።

"…በፀረ ዐማሮቹ፣ በፖለቲካው ቅማንት፣ በአገው ሸንጎና በወሎ ኅበረት፣ በአንዳንድ ማይም ዐማሮች የተሞላው የዐማራ ልዩ ኃይል ተብዬውና የሀገር መከላከያ ተብዬው የኦሮሙማ አራዊት ሠራዊት ወደ ዐማራ ክልል ከፋኖ ጋር ለመግጠም ሲገቡ፣ ፋኖን ቢያጡት በዚያ ያገኙትን የዐማራ ወጣት እንዲህ አድርገው ነው የሚበቀሉት።

"…ዐማራ ጠሉ የብልግና መንግሥት ሥርዓት በዐማራ ላይ ይፈጽም ዘንድ የሚታዘዘው በምታዩት መልክ የሚታየውን አስፀያፊ ድርጊት በመፈጸም ነው። የብልጽግና አራዊት እንዲህ አይነቱን ፀያፍ ድርጊት በትግሬ ሕዝብ ላይ ፈጽሞታል። በኦሮሞ፣ በሱማሌ፣ በደቡብ ሕዝብ ላይም ፈጽሞታል። የዐማራው ግን ይከፋል።

"…እናስ ወዳጄ ልቤ… ይሄን በዳንኤል ክብረት ፅንፍ የረገጠ፣ ጥግ በሌለው የዐማራ ጥላቻ የሰከረን የዐቢይ አሕመድ እና የብራኑ ጁላን ጦር ማርኮ መቀለብስስ ተገቢ ነው ወይ?

"…እባክዎ ለሽ ብሎ ለተኛው፣ ለዳተኛው፣ ለሰነፉ፣ ለአቃጣሪው፣ ለአስጠጪው፣ ለሾተላዩ፣ ለስኳዱ፣ ለሆዳሙ ዐማራ አሳዩልኝ። ወንድምሽ፣ ወንድምዎ፣ ልጅህ፣ ልጅሽ እንዲህ ሲደረግ ቢያዩ ቢመለከቱ ምን ይሰማዎታል? የዘራውን አዝመራ ሊያይ፣ ሊያርም፣ ሊኮተኩት የመጣን ገበሬ እንዲህ ማሰቀያት ያውም ከወታደር አይጠበቅም ነበር።

• ተበቀል ዐማራ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ

"…ሀገሩ ሶርያ የያዕቆብ ዘንጽቢን ደቀመዝሙርም ነው፡፡ ያዕቆብ ዘንጽቢን ለአውግዞተ አርዮስ ወደ ኒቅያ ሲሄድ አስከትሎት ሄዶ ነበር፡፡አርዮስን አውግዘው ሃይማኖት መልሰው ካደሩበት ሌሊት ዓምደ ብርሃን ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ብርሃኑ በዓለሙ ሞልቶ ራዕይ አየ፡፡
ባለቤቱን ግለጽልኝ ብሎ ቢያመለክት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ነው የሰውን ልቦና በትምህርቱ ብሩህ ያደርጋልና እንዲህ ባለ አርአያ አየኸው ለመርዳት ቂሣርያ ሄደ፡፡ በወቅቱ በወርቅ ወንበር ተቀምጦ በወርቅ አትሮንስ የወርቅ ወንጌል አዘርግቶ ኩፋር ጠምጥሞ ካባ ላንቃ ለብሶ እጀታው የወርቅ የሆነ የወርቅ መነሳንስ ይዞ ሲያስተምር አገኘው፡፡ ወተሐዘቦ ልቡ ለኤፍሬም ከመሥጋዊ ውእቱ ይላል፦እርሱ መሆኑን ተጠራጠረ አራት ነገር አይቶ ይረዳል፡፡

"…መጀመሪያ ከአፉ ነጸብራቅ እሳት እየወጣ ያያል። እሳቱ ሕዝቡን ሲዋሓዳቸው ያያል ትምህርቱ ነው፣ ሶስተኛ ነጭ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ ስታርፍበት ያያል። አራተኛ ስሙን ያውቃል ሀገሩን ሳይጠይቅ ኤፍሬም ሶርያዊ ኤፍሬም ለብሐዊ ብላችሁ ጥሩልኝ ከማዕዘነ ቤተክርስቲያን ባንዱ ቆሞ ይጸልይላቹሀል ብሎ አስጠራው። እያደነቀ ቀርቦ የባስልዮስ ቋንቋ ለኤፍሬም የኤፍሬም ቋንቋ ለባስልዮስ ተገልጾላቸው ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አሰናብቱኝ ልሂድ አለው። ልትኖር እንጂ ልትሄድ አምጥቶሀልን ብሎ ሕዝባዊ ነው ቢሉ ዲቁና ዲያቆን ነው ቅስና ሹሞ ከሀገር ስብከቱ ሀገር ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው፡፡

"…ባስልዮስ ይህን መልበሱ ስለ ክብረ ወንጌል ነው፡፡ ዛሬ ካህናት አክሊል ደፍተው ካባ ላንቃ ለብሰው ሥጋውን ደሙን እንዲያከብሩ እንዲለወጡ እሱ ግን በውስጡ የሚለብሰው ማቅ ነበር። ለብሐዊ የተባለው ሞ ብረሌ መርጠብ ብርጭቆ ኩዝ ካባ እየሠራ ሽጦ የዓመት ልብሱን የዕለት ጉርሱን እያስቀረ ሌላውን በእመቤታችን ስም ይመጸውት ስለነበረ ነው። እመቤታችንን ከመውደዱ የተነሳ የእመቤታችን ምስጋናዋ እንደሰማይ ኮከብ እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤው ጠግቤው እንደ ውኃ ጠጥቼው ረክቼው እያለ ሲመኝ ይኖር ነበር። የሹትን መግለጽ ለመንፈስ ቅዱስ ልማዱ ነውና ገልጾለት እልፍ ከአራት ሺህ ደርሶት ደርሷል። አኃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋኪ እስኪል ድረስ ጸሎቱም ከወንጌለ ሉቃስ ወበሳድስ ወርኀን፣ ጸሎተ እግዝእትነን አውጥቶ 64 ጊዜ ይደግም ነበር።

"…ከጊዜያት በአንዱ ዕለተ ሰኑይ ጊዜው ነግህ ነው። የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል የብርሃን ድባብ ይዘረጋል። ከዚያ ላይ ሁና "ሰላም ለከ ኦ ፍቅርየ ወፍቁረ ወልድየ ኤፍሬም" ትለዋለች ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል፡፡ ወድስኒ ትለዋለች እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ ሰማያውያን ወምድራውያን ሰማያውያን መላዕክት ምድራውያን ጻድቃን ሰማዕታት አንቺን ማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል አላት። "በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ" መንፈስ ቅዱስ እንዳቀበለህ ተናገር አለችው፡፡ ባርክኒ ይላታል በረከት ወልድየ ወአበሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኀድር በላዕሌከ ትለዋለች። ተባርኮ እንዳጸናው ቀለም ሰተት አድርጎ አመስግኗል። ስታስደርሰውም በሰባት ከፍላ አስደርሳዋለች። ምስጋናውም የሰባቱ ዕለታት ውዳሴ ማርያም ነው። ዜማውን ቅዱስ ያሬድ ደርሶታል። በያዘችውም መስቀለ ብርሃን ባርካው ተስፋውን ነግራው አርጋለች። እሱም የበለጠ ሲያገለግላት ኑሮ በዚህ ዕለት በሐምሌ 15 አርፏል። ለቅዱስ ኤፍሬም የተለመነች ድንግል ማርያም ለኛ ለኃጢአተኛ ልጆቿ ትለመነን። የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በረከቱ ይደርብን። አሜን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ስለምንድነው? ስለ ኤርሞያስ ለገሰ ዋቅጅራ ነው? አልኩት።

ኤልያስ ክፍሌ፦ ሳቅ አለ እና "አዎ" አለኝ።

እኔ ዘመዴ፦ አይመለከትህም፣ አያገባህም። እኔ በቀጥታ ለኤርሚያስ ለገሰ ነው መልእክቱን ያስተላለፍኩት። እኔና እሱ ተግባብተናል። ሌላው ብዙ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶችም ኤርሚያስን ከነሜካፑ ስለሆነ የሚያውቁት ብዙዎች ደውለው ሁሉ አስፈራርተውኛል። ኋላ የኤርሚያስን ወንጀል ዘርዝረው ሊነግሩኝ ኢትዮ 360 ዎች ራሱ "ኧረ ዘመዴ ምንሼ ነው?" ብለው አዝገውኛል። እናም ኤልያስን አይመለከትህም አልኩት።

ኤልያስ ክፍሌ፦ ለመወያየትም ጭምር አለኝ።

እኔ ዘመዴ፦ አዎ አልኩት አስረግጬ። ኤልያስም ጨዋ፣ የተማረ፣ ጋጠወጥ ዱርዬ ያልሆነ፣ አሳዳጊ የበደለው አግድም አደግ ስላለሆነ፣ የበሰለ፣ ባለ ምጡቅ አእምሮ ባለቤት ስለሆነ ስንዝር አልተራመደም። ተሰነባበትን። በሳምንቱ ሥራችንን በተለመደው መንገድ ቀጠልን። ቆይቶ ግን ኤርሚያስ ሜካፑ ሲለቅ ኤልያስ ይቅርታ ጠየቀኝ። ሌሎችም ይቅርታ ጠይቀውኛል። አለቀ።

"…ምደረ ገተት ሰገጤ ሁላ እኔ ዘመዴ እንደ ዶ/ር ምስጋናው 12 ዓመት እንደ ኳትኜ ዶፍተር ስላልተባልኩ ሊንቀኝ ይፈልጋል። እኔ ዘመዴ መሃይም ነኝ ብዬ በአደባባይ ስላወጅኩ በቃ ደነዝ እርጥብ መሃይምም እመስለዋለሁ። እኔ ዘመዴ እብድ እብድ ስለምጫወት ምድረ መቶ ኪሎ እርጥብ እንደወረደ ፋራ ሁላ የምርም እብድ እመስለዋለሁ። ጅል፣ ጅልጥ ሁላ። እኔ ዘመዴ እንደ ስኳድ አይነቱን፣ እንደ ፀረ ዐማራ ኮተት የብልፅግና አክቲቪስትና ካድሬ አይነቱን፣ አሁን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አለን የሚሉትን ከጥቂቶች በቀር አብዛኛዎቹን ጠፍጥፌ ልሠራቸው እችላለሁ። ስደት ነው እኮ ሁላችንንም በአንድ አግዳሚ ወንበር ላይ እኩል ያስቀመጠን። እኔ 20 ሠራተኛ ቀጥሬም፣ በኮሚሽንም ሳሠራ እነ ምስጋናው አንዷለም፣ እነ እስኳድ የት እንዳሉ አይታወቅም ነበር። እናም አዳሜ ስታላዝን ብትውል ለደንታህ ነው። አይመለከተኝም። ኬሬዳሽ

"…እኔ ዘመዴ ኦነግ ሸኔ ዐማራን ሲገድል ስቃወም ጀግናችን፣ አንበሳ የሚለኝ ኮተት፣ ወያኔም ዐማራን ሲገድል ስቃወም መልአክ የሚያስመስለኝ ሰይጣናም አጋንንታም ሁላ የዐማራ ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ዐማራውን በግፍ ሲገድል ስቃወም ግን አውሬ፣ ጨካኝ፣ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ፋኖ የምሆነበት ምንም ምክንያት የለም። ይሄን ለማሰብ ቀላል ደደብ መሆን ብቻ በቂ ነው። ፀረ ዐማራ የፖለቲካ ቅማንቴ መሆን ብቻ በቂ ነው። ፀረ ዐማራ አገው ሸንጎ መሆን ብቻ በቂ ነው። እና ወንጀል ሠርተህ ልፋታህ ነው? አልፋታህም። አልለቅህም። ኦነግን የሚያስንቅ ሥራ ወንጀል እየፈጸምክ ልምርህ ነው ወይ? ንገረኛ? የማንን ወንጀል እንደ ደበቅኩ ነው የምደብቅልህ? የማንን እንደ ሸሸግኩ ነው የምሸሽግልህ? አንተን ያስጨነቀህ የፋኖ ስም መጥፋቱ ነው። እኔ ደግሞ የሚያስጨንቀኝ እንቅልፍ የሚነሣኝ በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመው ግፍ ነው። ዐማራን ዐማራ ሲገድለው እንዴት በቃ አጀንዳ አይሁን ይባላል? ዛሬ ይሄን ግፍ የሚቃወመኝ እስኳድ እኚህን ሽማግሌ አረጋዊ በዚህ መልክ የገደላቸው ኦነግ ወይም ወያኔ ቢሆን ኖሮ እነ ሀብታሙ አያሌው ዋይዋይ፣ እነ አበበ በለው ጎፈንድሚ፣ ስኳድ መግለጫ በመግለጫ፣ የአሜሪካ የዐማራ ማኅበራት ሲምፖዚየም ከፍተው ተቀምጠው ነበር። ሌባ፣ ወመኔ ሁላ። ዐማራው አባትህ እንዲህ ሲገደል ያላወገዝክ ምንአባህ ትፈይዳለህ ብዬ ነው አንተን ተስፋ የማደርገው? አስመሳይ ሁላ።

"…ሌላው ደግሞ የሞተው አንድ ሰው ነው፣ ከዚህ በላይ ባይጮህ፣ ለፋኖ አንድነት ጥሩ አይደለም። ፋኖ ድጋፍ ያጣል የሚሉም አሉ። እናስ አንድ ሰውስ ቢሆን ፍትሕ ማግኘት የለበትም? የእኚ ሰውዬ እንኳን እሺ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦአቸው ራሳቸው ወንጀለኞቹ  በቪድዮ ቀርጸው ለኦሮሞ ሚዲያዎች በትነው ተጋለጡ። እሺ በቪድዮ ያልተቀረጹ በሲስተም በዘዴ በሸዋ ምድር እየተፈጀ ያለው ዐማራ ምንያህል ይሆን? በዚህ ዓይነት ጥጋበኛ የዐማራ ሸኔ ስንትና ስንት ንፁሐን የዐማራ ገበሬዎች ተገድለው፣ ተጨፍጭፈው ይሆን? ስንቶች ናቸው ሀብት ንብረታቸውን እየተነጠቁ ያሉት? ስንቶች ናቸው ታግተው ብር ክፈሉ እየተባሉ ያሉት። እናም በጊዜ መንቃት አለብህ ወገኔ።

"…ደግሜ እላለሁ የደቡብ ጎንደር እስኳድ ከሸዋ ይውጣ። እያየሁ ነው። የሙላት አድኖን፣ የሲሳይ አልታሰብን ገፅ እያየሁ ነው። እነ አምባቸውን ገድሏል ብለው አሳደው የገደሉትን ጄነራል አሳምነው ጽጌን ሳያፍሩ ፎቶውን ለጥፈው ሊሸቅሉ ይፈልጋሉ። ዘመነ ካሤ በሰኔ 15ቱ ግድያ ተጠርጣሪ ነው ብለው ሲያበቁ በሰኔ 15ቱ ተጠርጥሮ የታሠረውን ማስረሻ ሰጤን መሪያችን ነው ይላሉ። በኋላ ቀርጥፈው ሊበሉት የአሳምነው ጽጌ ጓደኛን ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃባውን መሪዬ ይላሉ። ጨበርበርቱ ወዪ… ሃይ…

"…እደግመዋለሁ። ሸዋ እያለቀ ነው። ከወያኔ ጭፍጨፋ የተረፈው ሸዋ፣ በኦነግ እየተጨፈጨፈ ያለው ሸዋ፣ አሁንም በብልፅግና እየተጨፈጨፈ ያለው ሸዋ፣ በዘዴ በደቡብ ጎንደር የብአዴን ስኳድ እየተጨፈጨፈ ነው። የሸዋን ፋኖ የሸዋ ልጆች ይምሩት። ኡጋንዳ የመሸገው የስኳድ ሴል እጁን ከሸዋ ሕዝብ ላይ ያንሳ። ሸዋ ቀድሞን አዲስ አበባ ከገባ እኛ ዳር ሀገር ነንእና ሥልጣን እናጣለን በሚል የጅል ቦለጢቃ ተቀፍድዶ፣ ሸዋ ላይ በጥብጠን ፋኖን ካልመራን ወልቃይትን ከጎንደር ጋር ገንጥለን ሀገር እንሆናለን የሚለው ሕልመኛ የጎንደር እስኳድ እጁን ከሸዋ ላይ ያንሣ። የሰሊጥ ቦለጢቀኛ ሁላ ይረፍ። ገለል ይበል። አደብ ይግዛ። እደግመዋለሁ ስትንጫጫ ዋልና እደር ሸዋን እጅና እግሩን ያሰረው የደቡብ ጎንደር የብአዴን የስኳድ ቡድን እጁን ያንሣ።

• አስቸኳይ ትእዛዝ ለሸዋ ጠቅላይ ግዛት ፋኖ

"…በስኳድ የተጠረነፈው የዐማራ ፋኖ የመከታው ቡድን በአስቸኳይ ይሄን የተፈጸመ ግፍ በአደባባይ ያውግዝ። ወንጀለኛውንም፣ ቪድዮ ቀራጩንም ሕጋዊና ፍትሐዊ እርምጃ ይውሰድባቸው። በቶሎ ይሄን ፈጽማችሁ አሳዩን። እኔ ግን ከነከስኩ ነከስኩ ነው ቀጥሎም የሚዘገንኑ ቪድዮዎችን፣ ድራሽ አባታችሁን የሚያጠፉ መረጃዎችን በቴሌቭዥን ጭምር ለቅቄ አሳር መከራችሁን አበላዋለሁ። ትፈነዳታለህ በመረጃ ነው እኔ ምድር ተከፍታ እንድትውጥህ የማደርግህ። ፍጠኑ።

"…ፍትሕ ለአረጋዊው አቶ ከተማ ሞላ።

"…ይሄን በማለቴ ቅር የሚልህ ካለህ በአናትህ ተተከል። እኔ የአቢይ አሕመድን ሥርዓት የምሞግተው ርስቴንና ሚስቴን ቀምቶ አይደለም አረመኔ ገዳይ ማንም ይሁን ማን እቃወመዋለሁ። በብዕሬም እፋለመዋለሁ። እናንተስ? አጠፋሁ እንዴ ጎበዝ? እናንተም ሃሳብ ስጡበትማ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው፣ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በቅድሚያ ሟች ሽማግሌ አረጋዊው አቶ ከተማ ሞላ በግፍ ቪድዮ እየቀረጸ ለሚገድላቸው ለመከታው ፋኖ ለአቶ ደጀኔ ከተማ በቅንነት የሚናዘዙትንና በመጨረሻም "…እኔ እውነቱን ነግሬአችኋለሁ ብትገድሉኝም ፈቃደኛ ነኝ" የሚሉትን የእሸቴ ሞገስ ሀገር ሰው ንግግራቸውን እናንብብ። (ገዳይ ደጀኔ ከተማ ልጃቸው አይደለም። ስመ ሞክሼ የመከታው ማሞ የመኮይ የፋኖ አዛዥ ነው።"

"…እኔ መቼም ተጽኖ አለብኝ። ጆሮዬንም በላኝ። እጄን ሁላ ሰበረኝ። ያን ሁሉ ችዬ ተቀምጫለሁ። አሁን ቦታ ስጠኝ አለኝ ቦታ ሰጠሁት። እንግዲህ ምን እሆናለሁ ብዬ። አሁን ተዚያ ሲመልስ ሄደ። ወዲያ ወደ ሆነችበት ወደ ዳሯ ሠራና እንደገና ደግሞ ተመልሶ ሲመጣ ደግሞ ያንን ተውና መሃል ስጠኝ አለ። ታዲያ ይሄን በሽተኛ ልጄን ወየት ላድርገው አልኩት። ያን ትሰጠዋለህ፣ ያን የተሠራውን አለኝ። ደግ ብዬ ሰጠሁት። ደግሞ እንደገና እዚያው አጠገቤ ሠራ። ሠራ ስንቀመጥ መጠጥ ነው ሌላ ሥራ የለውም መጠጥ ነው መስከር ነው። ማንም ያውቃል። በቃ ማጮህ አመጣ። እንዴ? ጥይት ለምን ታጮሃለህ? እኔ ሽማግሌ ነኝ፣ ክብር ያለው ሰው ነኝ፣ ለምን ጥይት ታጮሃለህ? ስለው አያገባህም አለ።በቃ የጨረሰ ጊዜ ተነሁሉ ገንዘቡን፣ አይ ከእንግዲህ  ወዲህ አትምጣብን ተወው ቤቴም አትግባ፣ ስሜን እያሰደብከው ከሆነ፣ ሠርተህ ካልበላህ፣ መሬት እያለህ ሰጥቼህ ሠርተህ የማትበላ ከሆነ ተወው ግቢዬን እሸግጋለሁ አልኩት፣ ግቢዬን… ኋላ ሰደቡኝ በረንዳዬ ቁጭ ብለው። ኧረ ተዉ፣ ኧረ ተዉኝ እባካችሁ እኔ ደካማ ነኝ ስል እንዲያው ገባ አለና ብቅ አረገ በሁለት ጥይት ሳተኝ።  አይ ይሄ ሰው እንግዲህ አልማረኝም አልኩኝ በቃ እንደው መታሁት። ሌላ የለኝም።

"…ከዚያ የመከታው እና የአበበ የሸዋ ጠቅላይ ዕዝ የመኮይ ፋኖ አዛዡ ገዳይ ደጀኔ ከተማ ይጠይቃል። እውነቱን ንገረን ይሉአቸዋል። እውነቱን ፋኖዎቹም አይተውታል ይላሉ አቶ ከተማ። ደግመው ከምንገድልህ ንገረን ይሉታል ፋኖዎቹ። "…እኔ እውነቱን ነግሬአችኋለሁ ብትገድሉኝም ፈቃደኛ ነኝ ይላሉ ሟች።" የሟችን ለመሞት ፍርሃት ያለማሳየት ያየው የተመለከተው የፋኖ አለቃ ደጀኔ ከተማም ክላሹን ወደ አዛውንቱ ሽማግሌ ጭንቅላት አስጠግቶ ምላጩን ስቦ ይተኩስባቸዋል። አንጀቴን የበላኝ ትእይንት ያየሁት ከዚያ በኋላ ነው። በኑሮ ድቅቅ ያሉት የሸዋ ዐማራ ሽማግሌ ቋጥኝ ድንጋዩ ስር ኩርምት ብለው ተደፉ። ደማቸውም እንደ ጅረት ፈሰሰ። ገዳይ የፋኖ አለቃ ደጀኔም ከገደላቸው በኋላ በኩራት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራውን አገልድሞ ለብሶ "አስከሬኑን ፀሐይ እንዳይመታው የገዛ የሟቹን አረጋዊ የአቶ ከተማን ነጠላ አለበሳቸው። አቢይ አሕመድ ለሚሞት ዐማራ፣ ለሚገደል፣ ለሚጨፈጨፍ ዐማራ ጥላ እንዲሆነው ችግኝ እተክላለሁ እንዲል ይሄ የዐማራ ፋኖ ሸኔ ደግሞ ለአስከሬኑ ነጠላ ወደ ማልበስ ገባ። የኦነግ ወራሪን ከፋኖ ፊት ቆመው የመከቱት አቶ ከተማም በዐማራ ሸኔ ፋኖ ተደፉ። ይሄ ብቻ ሳይሆን ወራሪው ኦነግ ሸኔ ደስ እንዲለው የግድያው ቪድዮ በእነ ጉማ ሰቀታ በኩል እንዲለቀቅ ተደረገ። አሰግድን ቤቱ ገብተው ያዋረዱት የመከታው ፋኖዎች ቪድዮ ቀርጸው በመጀመሪያ ለኦሮሞ አክቲቪስቶች እንደላኩት አሁንም እንደዚያው አደረጉ? … መጠርጠር ነው።

"…እደግመዋለሁ። ይህ ሁሉ ሲሆን ገዳይ የመኮይ ፋኖ አለቃው ደጀኔ ቪድዮ እያስቀረጸ ነበር። ቪድዮው ከተቀረጸ በኋላ ደግሞ ይሄ ቪዲዮ በኦነግና በህወሓት ሚዲያዎች ሲንሸራሸር ነበር። እኔም ያገኘሁት እንደ እናንተው ከእዚያው መንደር ሲሽከረከር ነው። በነገራችን ላይ ይሄ በቪዲዮ እየቀረጸ የሚገድለው ገዳይ ፋኖ ደጀኔ ሰምታችሁት ከሆነ "ልጅህን የገደልከው በፖለቲካ ስለማትስማሙ ነው" ሲል የሰማሁ መሰለኝ። ይሄ ማለት እንግዲህ ሟች ምንአልባትም የእነ እስክንድርን የእነ መከታውን የፖለቲካ መስመር ትክክል አይደለም። የእነ አቶ አሰግድ መኮንን መስመር ነው ትክክል የሚሉ ይሆናል። እናም የተገደሉት በፖለቲካ አመለካከታቸውም ሊሆን ይችላል ብዬ እጠረጥራለሁ።

"…ገዳዩ ፋኖ ደጀኔ ከተማ ሁለት ልጆች አሉት አሉ። ሚስቱም ፋኖ ናት አሉ። እዚያ የሸዋ ፋኖ ጠቅላይ ዕዝ ጋር ገብታ እንጀራ እየጋገረች ለፋኖ እየሸጠች ደንበኛ ነጋዴ ሆና ነው የምትኖረው ተብሏል። አሁን በሽተኛ ነው የተባለው የሟች የሽማግሌውን ልጅ የሚንከባከብ የለም። እነ ደጀኔ በተዘዋዋሪ መንገድ የሰውየውን ርስት ነቅለው ወይ ይሸጡታል። መሳሪያውን ገፈው ወስደውታል። ሟች መስኖን ለመውረር የመጣውን ወራሪ የኦሮሙማ ጦር ሁለቴ ተዋግተው የመከቱ ናቸው ይላሉ ስለ ሰውየው መረጃውን የሰጡኝ ፋኖዎች። ሁለቴም መቁሰላቸውን ነግረውኛል። ጀግና፣ ደፋር፣ ቆራጥ ተዋጊ ገበሬ ናቸውም ተብሏል። እናም ከላይ እንደነገርኳችሁ የእኚህ ሰው በግፍ መገደልን በቅድሚያ ለሕዝብ የበተኑትን የኦሮሞ ሚዲያዎች መሆናቸውን ሳይ የእነ መከታው የሸዋ ፋኖ በቱለማ ኦሮሞ ተውጦ፣ በፋኖ ስም የሸዋን ዐማራ እያጸዳው ነው ብዬ ለመጠየቅ እገደዳለሁ።

"…የሚገርመው በጎጃም ክፍለ ሀገር የብአዴን አባላትን አንበርክከው የሚቀጡ ፋኖዎችን በተመለከተ ድርጊቱ የሚወገዝ ቢሆንም ሀብታሙ አያሌው ተሾመ አፍራሳ፣ ትግቅማው እስክስ አበበ በለው፣ ደቡብ ጎንደሬ እና ጎጃሜው እስክንድር ነጋና የታንዛንያ ኦሮሞ ነው ተብሎ የሚታማው የአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋ ተሯሩጠው ነው መግለጫ ያወጡት። እስክንድር ነጋ እንደውም ወደ አባቱ ሀገር ጎጃም አጣሪ የውጭ ኃይል እንዲገባ ሲል ሁላ ነው የጠየቀው። የአምባሳደሩን መግለጫ ተከትሎ የስኳዱ ቡድን 24/7 ጎጃም፣ ጎጃም፣ ዘመነ፣ ዘመነ እያለ ሲዘበዝብ ነበር የከረመው። ነገር ግን ይሄን ሰቅጣጭ ግፍ ካዩ በኋላ ግን አንዳቸውም ምንም አልተነፈሱም። ዝም ጭጭ ነው ያሉት።

"…አንዳንዱ ዴየዴየብ እማ ዘመድኩን ይህን የቆየ ቪድዮ ያወጣው ጋላ ስለሆነ ነው። ኦሮሞ ስለሆነ ነው፣ ብልፅግና ከፍሎት ነው እያለ ሲበዘብዝ አየዋለሁ። ቪድዮው የቆየ አይደለም ለምን የጥንት የጋርዮሽ ዘመን አይሆንም። እንኳን የአሁን ሆኖ ይቅርና። ታዲያ ይሄንን ሰቅጣጭ፣ ዘግናኝ ግፍ ኦሮሞ ሆኜ፣ ጋላም ሆኜ ከተቃወምኩ በቃ እንደ እኔ ትክክለኛ ጋላ እና ኦሮሞ የለም ማለት ማለት እኮ ነው። ዛሬ የእሱን ጭካኔ ተቃውሜ ስሟገት ዘመዴ ጋላ፣ ኦሮሞ የሚለኝ የወልቃይት ርስቱ፣ የደቡብ ጎንደር ሴሉ፣ ኡጋንዳን ማረፊያው፣ አሜሪካንና ቲክቶክን መቀመጫው ያደረገው የሚንጨረጨረው ስኳድ ስስ ብልቱን አግኝቼበታለሁ ማለት ነው። ትናንት በኦሮሚያ ምድር ውስጥ በግፍ ሲረሸኑ፣ ሲታረዱ የነበሩትን ዐማሮች ዓለሙ ሁሉ ግፋቸውን እንዲያይ ስጮህ ምነው ያኔ ጋላው፣ ኦሮሞው ዘመዴ ብለህ ለመሳደብ አልሞከርክም? እኔ ዘመዴ ግን ጋላም ኦሮሞም አይደለሁም። እኔ ትግሬም፣ ጉራጌም፣ ዐማራም፣ ሱማሌ፣ አፋርም አይደለሁም። ሲጀመር እኔ በአርዓያ ሥላሴ የተፈጠርኩ ሰው ነኝ። በቃ ሰው የሐረርጌ ቆቱ የሆንኩ ምርጥዬ መራታ ሰው ነኝ። ሰው ስለሆንኩ ነው ለሰው ልጆች ሁሉ ግፍ ሲሠራባቸው ዘር ሳልመርጥ የምጮኸው። ኦሮሞ ግፍ ሲሠራ፣ ትግሬ ግፍ ሲሠራ ማንንም ሳላስፈቅድ ሰው ስለሆንኩ ያውም ባለ ማዕተብ ሰው ስለሆንኩ ለፍትሕ ጮሄአለሁ። ዛሬም ዐማራ ነኝ ብሎ ዐማራን ነፃ ያወጣል ተብሎ የሚጠበቅ በፋኖ ስም የተደራጀ ግፈኛ ይሄን የመሰለ አረመኔያዊ ግፍ ሲፈጽም እቃወመዋለሁ። አለቀ። አንተ አበድክ አላበድክ ለደንታህ ነው። እኔ ግን ማንም ይሁን ማን፣ የትም ይሁን የት ግፍንና ግፈኞችን አጥብቄ እቃወማለሁ። ቢመር፣ ቢጎመዝዝህ ለደንታህ ነው። ዋጠው።👇① ከታች

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በርዕሰ አንቀጹ ላይ ከመወያየታችን በፊት የሟችን ያልተቆራረጠ ቪድዮ ሰዎች ልከውልኝ አይቼዋለሁ። ቪድዮው ሌላ ልጥፍ በላዩ ላይ ስላለ ልጥፉን ማንሳት አልቻልኩም። የጠራ ልጥፍ የሌለበት ንፁሕ ቪድዮ ያላችሁ ግን ላኩልኝ። ይሄን የማደርገው እናንተም ቪድዮውን ጨክናችሁ አይታችሁ በንፁሕ ልብ ትፈርዱ ዘንድ በማሰብ ነው።

ሟች ፦ አቶ ከተማ ሞላ
ገዳይ፦ አቶ ደጀኔ ከተማ
የግድያው ቦታ፦ አሰለለኝ ገበያ

"…እዚህ ጋር አንድ ነገር ለማጥራት ገዳይ ደጀኔ ከተማ ማለት የሟች ልጅ አይደለም። ስመ ሞክሼ ነው። ገዳዩ የአበበ ጢሞ አብሮ አደግ የአንድ ሀገር ልጅ ነው። ገዳይ እስክንድር ነጋ ሊቀመንበር በሆነበት፣ የጎንደሩ እነ ሀብቴና መሳፍንት፣ የጎጃሙ መቶ አለቃ ማስረሻ፣ የወሎው ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው፣ የጎንደሩ ጌታ አስራደ፣ እነ ኮሎኔል ታደሰ፣ እነ ዶ/ር ምስጋናው አንዷለም፣ እነ ሙላት አድኖ ወዘተ የሚደግፉት፣ ሻለቃ መከታው የሚመራው የመኮይ ፋኖ መሪ ነው እንጂ ገዳይ የሟች ልጅ አይደለም።

"…ገዳዩ ሟችን ከመግደሉ በፊት ቪድዮ እየቀረጸ አናዟቸዋል። ሟችም ልጇቸውን እንዴት እንደገደሉት በትህትና አስረድተዋል። ይሄን ሀገርም ያውቃል። ልጃቸው ተኩሶ ሳታቸው፣ እሳቸው ተኩሰው ገደሉት። የሆነውን ተናግረዋል። ከዚህ የዘለለ ግን ይሄ ገዳይ ከጭካኔው የተነሣ የፖለቲካ ልዩነትም ሊኖራቸው ይችላል ብዬም እጠረጥራለሁ።

"…ዛሬ በዚህ ዘግናኝ ግፍላይ ስንወያይ እንውላለን። በወለጋ፣ በአሩሲ፣ በባሌ፣ በሐረርጌ፣ በጅማ፣ በሸዋ በኦነግ ሸኔ በግፍ የተገደሉ ዐማሮችን በቴሌቭዥን፣ በቴሌግራም ስለጥፍና ሳስወግዝ ኖሬ ዛሬ ይሄንን የዐማራ ፋኖ ነኝ የሚል ነውረኛ ቡድን በአደባባይ ቪድዮ ቀርጾ የራሱን ወገን እንዲህ በግፍ ሲገድል እያየሁ ዝም እንድል ኦነግ እያልክ የምትሰድበኝን ነፈዝ ሁላ አልሰማህም።

• በቅንነት ዓይታችሁ ፍረዱ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሐተታ፦ 13 አድርጎ መቍረሱ ስለምን ነው፤ ጥዒሞ አጥዐሞሙ እንዲል። አንዱን እሱ የሚቀበለው ነውና፤ ስለምን ቢሉ ለእሱ የሚረባው የሚጠቅመው ሆኖ አይደለም፤ ዝ ውእቱ ሥጋየ፤ ዝ ውእቱ ደምየ ባላቸው ጊዜ ተለውጦ ትኩስ ሥጋ፤ ትኩስ ደም ሆኗልና፤ እንዳይገርማቸው ለማስደፈር፡፡ አንድም እንደ ባለመድኀኒት ቀምሶ ይሰጣል፡፡ ለእሱ አይረባውም ያን የሚጠጣውን ሰው ለማስደፈር ነው፡፡ አንድም ለአብነት ነው፡፡ ጌታ ሳይቀበል አቀብሏቸው ቢሆን የዛሬ ቄስ ሳልቀበል አቀብዬ ልሂድ ባለ ነበርና፤ አንድም 13ቱ ህማማተ መስቀል አክሊለ ሦክ፤ ተኮርዖተ ርእስ፤ ተጸፍዖ መልታሕት፣ ወሪቀ ምራቅ፤ ተቀሥፎ ዘባን፤ ተአስሮ ድኅሪት፤ ኵትፈተ እድ፤ ጸዊረ መስቀል፤ ዐራቱ ቅንዋት፤ ርግዘተ ገቦ፤ ርግዘተ ገቦስ ከሞተ በኋላ ነው ብሎ ሰትየ ሐሞት፤ አንድም አክሊለ ሦክና ተኮርዖተ ርእስ አንድ ወገን ተጸርዖ መልታሕትና ወሪቀ ምራቅ አንድ ወገን፤ ተቀሥቶ ዘባን 3 ተአስሮ ድኅሪትና ኵትፈተ እድ አንድ ወገን ዐራት፤ ዐራቱ ቅንዋት 8መስቀል 9፤ጸዊረ መስቀል 10፤ርግዘተ ገቦ 11፤ሰትየ ሐሞት 12ተቀብረ በእነቲኣነ፤ ሞተ በእንቲኣነ እንዲል፡፡ ሁሉም ስለ እኛ ነውና፤ ወሪደ መቃብር ዐሥራ ሦስት ዐራቱ ቅንዋ ሁለቱ ከግራ ከቀኝ እጁ፤ ሁለቱን እግሩን ባንድ ቀኖት ደርበው ቸንክረውታል፤ አንድ ከደረቱ፤ ይህስ ኢትስብሩ ዐፅሞ ለበግዕ ያለው ይፈርሳል ብለው እግሩን እየራሱ ቸንክረውታል ቢሉ የተመቸ አንድ ነው ቢሉ ስቍረቱን ቆጥሮ ነው፡፡ እንዘቅዱ ውእቱ አለ፤ ከሰው አብርሃም ከእህል ስንዴን፤ ከአታክልት ወይንን፤ መረጥሁ ብሎ በዕዝራ እንደ ተናገረ፤ ወእምኵሉ ዖማ ለምድር ኀረይኩ አሐተ ዐጸደ ወይን እንዳለ፡፡

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እነሆ መረጃው…

"…ሟች አቶ ከተማ ሞላ መስኖ በሚባል ስፍራ በግብርና ሥራ የሚኖሩ ነበሩ አሉ። ሟች ግርማ ከተማ ለሚባል ህመምተኛ ልጃቸው በሰጡት ቤት መሥሪያ ቦታ ምክንያት አረጋ ከተማ ከሚባለው ልጃቸው ተቃውሞ ይቀርብባቸው እንደነበር፣ ለልጃቸው ለአረጋም የድርሻውን ቢሰጡትም ሁሉን መጠቅለል በመፈለግ ቅሬታው ወደ ፀብ ተቀይሮ ልጅ አረጋ የአባትን ጆሮ እስከመበጠስ የሚያደርስ ጥቃት እንዳደረሰባቸና በሌላ ጊዜም ይኸው ልጃቸው የግድያ ሙከራ ሲያደርግባቸው ራስን በመከላከል እንደገደሉት ተሰምቷል።

"…ሟች አቶ ከተማ ለ2 ጊዜ ያህል በኦሮሞ ወረራ ወቅት ወደ መስኖ የመጣውን ወራሪ መክተው የመለሱ፣ በውጊያም ላይ በመቁሰላቸው ምክንያት ያለ ምርኩዝም መሄድ እንደማይችሉ ነው የተሰማው። ሰውየው ሀገር ያወቀው ከፋኖ ፊት ጦርነት የሚገባም ጀግና ነበር ተብሏል።

"…ገዳዩ ፋኖ ደጀኔ ከተማ የሚባል የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአንፆኪያ ገምዛን ፋኖ መሪ ሲሆን የትውልድ ሀገሩም እዚያው ከአበበ ጢሞ ሀገር ሲሆን ሟችን ከሚኖርበት መስኖ አፍነው ካመጡት በኋላ አሰለለኝ በተባለ የገበያ ቦታ በምታዩት መልኩ ያለፍርድ በግፍ ረሽኗቸዋል። ገዳዩ አሁንም በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ስር በመከታው ጦር ውስጥ በሓላፊነት የቀጠለ ሲሆን እንዲህ ያለ ግድያ በዚህ ከቀጠለ በሸዋ ለዘር የሚተርፍ ወንድ የሚኖር አይመስልም እየተባለ ነው።

"…ሸዋ እጅግ በረቀቀ መንገድ እጅተወርች ተጠርንፏል። ገበሬዎች በጭካኔ እየተገደሉ፣ በኢኮኖሚም እያደቀቁ ነው። መከላከያና ፖሊስ ማርኮ እየቀለበ የሚፈታው የመከታው ጦር ሰሞኑን በፋኖ ትግል ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በመከላከያ ተጨፍጭፎ ለመቀጣጫ በሚል የሸዋ ወጣቶች አስከሬን በከተማ አስፋልት ላይ በአስነዋሪ መልኩ ተሰጥቶ ውሏል።

• ሸዋ በጊዜ ምከር። ስኳድ ይውጣ፣ የሸዋ ፋኖ በሸዋ ልጆች ይመራ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ድንግል ሆይ እሳተ መለኮት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ፊቱ እሳት፣ ልብሱ እሳት፣ ቀሚሱ እሳት ነው እንደምን አላቃጠለሽም? ሰባት የእሳት መጋረጃ በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘጋጀ ወዴትስ ተጋረደ? ከጎንሽ በቀኝሽ ነውን ወይስ ከጎንሽ በግራ ነውን? ትንሽ አካል ስትሆኝ የሚያንጸባርቅ ነደ እሳት የሚከበው ኪሩቤል የተሸከሙት ዙፋን በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘጋጀ? ወዴትስ ተተከለ? ታናሽ ሙሽራ ስትሆኝ ከአገልጋይነት ጋር እናትነት እንደምን ያለ ነው?ከስፋት ጋር የሆድ ጥበት እንደ ንብ ያለ ሩካቤ ከቃል ድምጽ የተገኘ ጽንስ፤ ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሐሊብ፤

"…ይህንን ባሰብኩ ጊዜ ልቤ የልጅሽን የባህሪውን ጥልቀት ሊዋኝ ይወዳል። የወዳጅሽ የመሰወሪያው ማዕበል ያማተዋል፤ ዳግመኛ ባሰብኩ ጊዜ ህሊናዬ ተሠውሮ ወደ ላይ ወጥቶ የህያው መሠወሪያው የሆነውን ሊገልጥ ይወዳል፤ ከነደ እሳትነቱ የተነሳ ይፈራል ከአየራት ከሩባቸው ሩብ አንደርስም። ይህን ባሰብኩ ጊዜ ህሊናዬ በንፋስ ትከሻ ተጭኖ በምሥራቅና በምዕራብ፤ በሰሜንና በደቡብ፤ በዳርቻውም ሁሉ ሊበር ይወዳል፤ የፍጡራንን አኗኗር ያይ ዘንድ የአብሕርትንም ጥልቀታቸውን ይለካ ዘንድ በሁሉ ይዞራል አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል።

"…አሁንም ገናንነቱን አንመርምር፤ ጥልቀቱንም አንጠናቀቅ የገናንነቱን መጠን ለማመስገን የነብያትንና የሐዋርያትን አንደበት፤ የማይቻለው ነው የማይደፈር ግሩም ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን ትሁት ነው፤ የማይገኝ ልዑል ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን አርአያ ገብርን ነሳ፤ የማይዳሰስ እሳት ነው፤ እኛ ግን አየነው ዳሰስነው ከእርሱም ጋር በላን ጠጣን፤ አሁንም እንዲህ እያልን እናመስግነው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በመዝግየታችን ይቅርታ

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር አሁን 2:30 ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

• ትዊተር 👉https://twitter.com/MerejaTV

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/bbq3nw3EGag

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወይ ፍንክች አበደን…

"…እኔ ዘመዴ እንደሁ አጀንዳዬን አልቀይርም። እናንተስ…?

• መርጦ አልቃሽ ሰምተሃል…!

• እደግመዋለሁ… አጀንዳዬን አልቀይርም…!

"…በተለይ ሰሞኑን ማኅበራዊ ሚድያውን ለመቆጣጠር የብልፄ የሚዲያ ሠራዊት መመሪያ ወርዶለት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ሥራ ገብቷል። ከእኛ የሚጠበቀው ዕቅዳቸውን በአጭሩ በእንጭጩ መቅጨት ነው።

"…አጀንዳዬን አልቀይርም አልኩህ። ዓይኔን ከእስኳድ እና፣ ከፀረ ዐማራ ፋኖዎች ላይ አላነሣም። አጀንዳዬን አልቀይርም።

• እምቢኝ፣ እምቢዮ፣ አጀንዳዬን አልቀይርም አልኩህ እንግዲህ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አገዛዙ አጀንዳ ለማስቀየስ አይደለም ዓመት ያለፈው አሰቃቂ ወንጀል ገና ወደፊት ራሱ በራሱ ደራሲነት እና ተዋናይነት አረመኔ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመ አጀንዳ በመሆን መንጋውን እያላቀሰ ይቀጥላል ባይ ነኝ። የዛሬ 150 ዓመት ሚኒሊክ ጡትህን ቆርጧል ብሎ ሃውልት የሠራ አገዛዝ ከዚህም ሌላ ነገር ባይፈጽም ነው የሚገርመው።

"…በዚህ ላይ አስተያየታችሁን ስጡና ወደ ሌላ መርሀ ግብራችን እንለፍ። በጨዋ ደንብ ተንፒሱ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አዎ ስለ ሕፃን ሔቨን ሰምቻለሁ።

"…ከትናንት ጀምሮ ከምር ደንግጠው ስለ ወንጀሉም አረመኔነት ዓለም እንዲያውቀው በቀና ልብ የወንጀል ድርጊቱን የሚቃወሙ፣ ወንጀለኛው እንዲቀጣ፣ ቤተሰብ ፍትሕ እንዲያገኝ የሚጮሁ አሉ። ነገር ግን በእነዚህ ኑፁሐን ፍትሕ ፈላጊዎች ጀርባ ተከልሎ በተለይ የራሱ የብልጽግና አክቲቪስትና የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ከላይ በወረደለት መመሪያ በሚመስል መልኩ ማኅበራዊ ሚዲያውን ከላይ እስከታች ተቆጣጥሮ ቲክቶኩን በሉት ዩቲዩቡን እና ፌስቡክ ቴሌግራሙን ሁሉ እንደ ሱናሚ ማዕበል አጥለቅልቀው የአዞ እንባቸውን ሲያነቡም ታይተዋል። እኔን የሚገርመኝ እነዚህ ከንቱዎች ሌላውን ማጀዘባቸው ሳያንስ አዛኝ አንጓች መስለው እኔንም ለማጀዘብ ሲላላጡ መታየታቸው ነው። ለወትሮው በፔጄ ላይ "እግዚአብሔር ይመስገን" ለማለት አገዛዙን የሚፈሩና ወኔያቸው የተሰለበባቸው መበለቶች ሳይቀር በድፍረት ወደ ፔጄ መጥተው "ዘመዴ ምነው ዝም አልክ? ዘመዴ ሴት ልጅ የለህምን ምነው ጨከንክ? ዘመዴ አንተን ብዙ ሰው ያነብሃልና እባክህ የሆነ ነገር በል እንጂ? ሕፃኗ ፍትሕ እንድታገኝ ድምፅ ሁናት? ሲሉኝ ውለው አድረዋል። ብልፅግና ያሸንፋል! አቢይ ይግዛን ሲሉኝ የከረሙ ሁላ "ዘመዴ ምነው ዝም አልክ? ሲሉኝ ነው የዋሉ ያደሩት።

"…የዛሬ ዓመት ሐምሌ 25/2015 ዓም የተፈጸመን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ዓመት ጠብቆ ልክ በዓመቱ ሐምሌ 12/2016 ዓም ወደ አደባባይ አምጥተው አጀንዳም አድርገው ለምን በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ እንዲጮህ ተፈለገ? ዓመት ሙሉ ለምን ተደብቆ፣ ተከድኖ፣ ተሰውሮ ቆየ? ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው የአገዛዙ ደጋፊ የሆኑ ሚዲያዎች እና የአገዛዙ ተቃዋሚ ነን የሚሉት ሳይቀር የኦሮሞ ነፃ አውጪ እና የትግሬ ነፃ አውጪ አክቲቪስቶች ጭምር አንድ ላይ ቆመው ዋይ ዋይ የሚሉት? ብልፅግና፣ ህወሓት እና ኦነግ አንድ ላይ ሆነው እኮ ነው በግፍ የተገደለችን ሕጻን ሲያዝኑላት የሚታዩት። ታየኝ እኮ። ኧረ አልሰማህም።

"…ወላሂ ከዛሬ ጀምሮ ዐማራ አልሆንም እያለች የታረደችዋን የዐማራ ሕፃን ባላየ በዝምታ አልፈህ ስታበቃ፣ የዘጠኝ ወር እርጉዝ ድርስ ነፍሰ ጡር ማኅፀኗ በሳንጃ ተዘክዝኮ በኦሮሚያ ስትገደል እያየህ ዝም ብለህ ስታበቃ፣ የዐማራ ልጅ በኦሮሚያ ምድር አይወለዳትም ብለው በሻሸመኔ ያችን የዐማራ ሴት በአሰቃቂ ሁኔታ ስትገደል በዓይንህ እያየህ፣ በጆሮህ እየሰማህ ስታበቃ፣ በመተከል፣ በወለጋ የዐማራ ሕፃናት በጅምላ ተጨፍጭፈው አስከሬናቸው ተከምሮ እያየህ እኔ ስጮህ እየታዘብክ፣ ስትሰድበኝ ጭምር ከርመህ፣ በፍርሃት ቆፈን ተይዘህ ዝም ጭጭ ብሎ ኖረህ ኖረህ፣ ዛሬ መንጋ ሙሉ አድርባይ ሁላ ዛሬ ድንገት ተነሥተህ "ፍትሕ ለሕፃን ሔቨን" እያልክ የአዞ እንባህን ስታፈስ ብትውል እንዳንተ ባልቃወምህም ግን አብሬህ አልጮህም፣ ደግሞም አልሰማህም። እኔ ምኔ ሞኝ ነው መንግሥትም፣ ፍትሕም በሌለበት ሀገር መንግሥትም ፍትሕም እንዲመጣ እየተዋደቀ ካለው አካል ጋር ቆሜ ለፍትሕ እታገላለሁ እንጂ ምን ይሁነኝ ብዬ ነው የአረመኔነት መፈልፈያ ማሽን የሆነውን ብልፅግና ስለ ፍትሕ የምጨቀጭቀው? ለሕፃኗ ቤተሰቦች ፍትሕ ያስፈልጋቸዋል? አዎ ያስፈልጋቸዋል። ነገር ግን ከአቢይ አሕመድ አገዛዝ ችግኝ እንጂ ፍትሕ ኢንጂሩ። እናም አንተን አስመሳዩን ሰሞነኛ ጯሂ አበደን አልሰማህም። አልሰማሕም አልኩህ።

"…ጭራሽ አንዱ ፔጅማ የብዙ ሰዎችን የቴሌግራም እና የፌስቡክ ፔጆችን፣ ታዋቂ አክቲቪስቶችን በስም ዝርዝር እየጠራ፣ እየዘረዘረም እነ እገሌ እኮ ጽፈዋል፣ እነ እገሌ ቪድዮ ሠርተው ለቀዋል፣ እነ እገሊት ድምጽ እያሰሙ ነው። ሌሎችም ብዙ ተከታይ ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ድምጻችሁን ታሰሙ ዘንድ እየጠበቅን ነው እያለ በጉዳዩ ላይ ያልጻፉትን የፍትሕ ጠላት፣ የወንጀለኛው ተባባሪ አድርጎ ለማቀሳሰር ሲላላጥ ሁላ አይቼው ሞኝህን ብላ ብዬው ነው ያለፍኩት።

"…በግፍ፣ በጭካኔ የተገደለችዋ ሕፃን ከምር እውነት ነው ታሳዝናለች። ፍትሕም ማግኘት አለባት። ነገር ግን ከዚህ አረመኔ አገዛዝ ፍትሕ አይጠበቅም። የዚህችን ሕፃን አረመኔያዊ አሰቃቂ ግድያና ሞት ባለፉት 6 ዓመታት ውስጥ አቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ በሌሎች የኢትዮጵያ ሕፃናት ላይ እየተፈጸመ ካለው አሰቃቂ፣ አረመኔያዊ ወንጀሎች የተለየ አያደርገውም። እንደ ሕዝብ ነው አቢይ አሕመድ እየጨፈጨፈን ያለው። ሚልዮን ትግሬ በአቢይ አልቋል። ዐማራም እንደዚያው። ኦሮሞም አገዛዙን መንቀፍ ይሆንብኛል ብሎ አፍሮ ነው እንጂ በሸኔ ሰበብ እያለቀ ነው። አረመኔነት የሥርዓቱ መገለጫ ነው። ሕጉ አረመኔነትን የሚያበረታታ ነው። ሕፃናትን ያረደች ወንጀለኛ ኦሮሞ ስለሆነች ብቻ  መርማሪ ፖሊሱ "አይዞሽ አታልቅሺ፣ ተረጋጊ" እያለ ሚሪንዳ እየሰጠ ቪድዮ ቀርጾ እንዲበተን የሚያደርግ ነው። በሕፃናት ላይ ግበረ ሰዶም የሚፈጽሙ የሚሸለሙበት ሥርዓት ነው። ሥልጣኑ በሙሉ በዓረመኔዎች፣ ልቡሣነ ሥጋ በሆኑ ጋኔሎች የተሞላ፣ የተያዘ ነው። እናም ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው እኔ ከያዝኩት የዐማራ ፋኖ ተጋድሎ ንቅንቅ ብዬ ያውም በብልፅግና ካድሬዎች መሪነት የሚንጫጫን አጀንዳ ይዤ አብሬ የምንጫጫው። ክላልኝ የእንጭቅ ልጅ…

"…እኔ ዘመዴ የሕፃኗ አጀንዳ መራገቡን አልቃወምም። የምቃወመው አጀንዳ ፈጣሪዎቹ ራሳቸው መልሰው እኔን የአጀንዳው አራጋቢ ለምን አልሆንክም ብለው ሲጋተቱኝ ሳይ ብቻ ነው። ትግሬዎቹ የጮሁት ለሞተችዋ ሕጻን አዝነው ነው ብዬ አላስብም። ኦሮሞዎቹም እንደዚያው። ሁለቱን ያስጮሃቸው ድርጊቱ የተፈጸመው ዐማራ ክልል ያውም ባህርዳር ላይ መሆኑ ብቻ ነው። ይሄ ነው እነሱን የሚያስጮሃቸው። ትግሬዎቹ ድርጊቱ ባህርዳር ከመፈጸሙም ሌላ የልጅቷ አባት ትውልዱ ወይም ዘሩ ትግሬ ስለሆነም ጭምር ነው። ለሥጋቸው ማድላታቸው መሆኑ ነው። ኦሮሞዎቹ አክቲቪስቶችም ወንጀሉ የተፈጸመበትን ቦታ ለማጉላትና ትግሬዎቹን አክቲቪስቶች ለማጽናናት ብለው ነው። ሌላ ምንም ኀዘኔታ ኖሯቸው አይደለም። አጭቤ ሁላ።

"…ልብ በሉ የኢዜማ አመራር የነበረው የፖለቲከኛው ዳንኤል ሽበሺ ሕፃን ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ የተደፈረችው እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ነው። ወንጀሉ ተፈጽሞባት ፖሊስ ጣቢያ ስትሄድ ግን ፖሊስ የአባቷን ስም አይቶ አንቺማ የአገዛዙ ተቃዋሚ የዳንኤል ሽበሺ ልጅ ነሽ፣ ጥፊ ከዚህ ያላት እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ነው። ይሄንን ዜና እነ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት አይዘግቡትም። የኦሮሞ እና የትግሬ አክቲቪስቶች አይጮሁለትም። መንጋው ገተቴ የማኅበራዊ ሚዲያ አዛኝ አንጓችም ትንፍሽ አይላትም። እነ ያሬድ ያያ ዘልደታም በቪዲዮ ወጥተው "ደፋሪዎቹን ገድላችሁ አሳዩን ብለው አይጮሁም" ፍትሕ ለሕጻን ሔቨን ግን ደግሞ ፍትሕ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊባል ይገባል።

"…እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው መሰላችሁ? ወንጀለኛው በብአዴን እጅ ነው። የተያዘውን ወንጀለኛ አሁኑኑ ስቀሉት። ግደሉትም። ሥልጣኑ ሁሉ በእናንተ እጅ ነው ያለው። ሌባ ተይዞ እኮ ዱላ አይጠየቅም። ከምታጯጩሁ። አጀንዳ ለማስቀየስ የቆየ የተረሳ ወንጀል አጀንዳ አድርጋችሁ ፒፕሉን ከምታንጫጩ፣ ወንጀለኛውንም፣ ወንጀለኛውን ለማስፈታት የሚዳክሩ ፖሊሶችን፣ ዳኞችን ሁሉ ሰብስባችሁ ስቀሉ። ስቀሉናም አሳዩን። እኔ እያልኩ ያለሁት ግን እናንት መርጦ አልቃሾች ራሳችሁን ችላችሁ ጩሁ ነው። ለምን ከእኛ እኩል አትጮህም ብላችሁም አታዝጉኝ ነው። አሁን እኔ ዘመዴ ሥራ ላይ ነኝ። ይህን ሰው መሳይ በሸንጎ አረመኔ ወንጀልን የሚያበረታታ አገዛዝ ለመጣል እየተዋደቀ…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ፀምር ዘጌዴዎን
የጌዴዎን ብዝት አንች ነሽ።
      "መሳ 6፥ 36-40"

"…ጌዴዎንን መልአኩ ጌታ ባንተ አድሬ እስራኤልን ከምድያም ሰዎች አድናቸዋለሁ ብሎሃል ሂድ አለው፡፡ እንኪያስቆየኝ መሥዋዕት ልሠዋ ብሎት ሄደ። መሥዋዐት ሰውቶ ሥጋውን በቅርጫት ደሙን በብርት አድርጎ አቀረበ። ደንጊያውን ጸፈጸፈ አንጨቱንም ረበረበ። ሥጋውን እዚያ ላይ አደረገው። መልአኩ በዘንግ ቢነካው ተቃጥሏል፡፡ እሳት የመቅሰፍተ እግዚአብሔር፣ ሥጋው የአሕዛብ ሕለት የኩናተ ጌዴዎን ምሳሌ ነው፡፡ ሁለተኛ ጸምር ልዘርጋ ጠል ከብዝት ላይ ይውረድ ዳርና ዳሩ ይቡስ ይሁን ሲለው ይሁንልህ አለው፡፡ ሦስተኛ ፀምር ልዘርጋ ጸምር ይቡስ ይሁን ጠል በዳርና በዳር ይውረድ አለው ይሁንልህ አለው፡፡ ሁሉም ሆኖለታል፡፡ ለጊዜው ፀምር የእስራኤል ጠል የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ፣ ጠል ከፀምር መውረዱ እስራኤልን የመርዳቱ፣ በዳርና በዳር አለመውረዱ አሕዛብን ያለመርዳቱ ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ፀምር አይለወጥም የእስራኤል ጠል የመቅሰፍተ እግዚአብሔር፣ ጠል ከፀምር አለመውረዱ እስኤልን ያለማጥፋቱ፣ በዳርና ባዳር መውረዱ አሕዛብን የማጥፋቱ ምሳሌ ነው። ፍጻሜው ግን ፀምር መውረዱ ጌታ በእመቤታችን የማደሩ ምሳሌ ነው፡፡ በዳርና በዳር አለመውረዱ ጌታ በሌሎች ሴቶች ያለማደሩ ፀምር ይቡስ መሆኑም እመቤታችን እንበለ ዘርዕ የመውለዷ ምሳሌ ነው። በዳርና በዳር መውረዱ ሌሎች ሴቶች በዘር በሩካቤ የመወለዳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ጌዴዎን ማለት ጽንዕ ጽንዕ እግዚአብሔር ኀያል ማለት ነው። ትውልዱ ምድረ ርስት ከገቡት ከመንፈቀ ነገደ ምናሴ ነው፡፡

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እንደማመጥ…!

"…ወያኔ ያ ሁሉ ጣት ተዋጊዎቿ እንደ ሕዝብ ያለቁት እንደ መንጋ አንድ ላይ እጅብ ብለው ሲግተለተሉ ነው። እናም ፋኖዬ ድሮን የሚባል ነገር አለ እሺ።

• የመጨረሻው ባይሆንም ድሉ ግን ደስ ይላል። ቢሆንም፣ ቢሆንም ግን እየተደማመጥን። ስሜት በልኩ ይገለፅ፣ ደግሞም ተበተን፣ ሰብጠርጠር በል። አትዘናጋ ለማለት ነው።

• ስላዳመጣችሁኝ አስመሰግናላሽ 🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዐማራ ፋኖ ሆይ…!

"…የብህትውና ቦለጢቃ፣ ጻድቅ ጻድቅ መጫወቱም ይብቃህ። አንተ ገዳይህን፣ አራጅህን፣ አነዋሪ ደፋሪህን፣ የፈለገውን አሟልተህለት፣ ወርቅ አንጥፈህ፣ ወርቅ አልብስህ ብትልከው፣ ብትሸኘው እሱ መልሶ አንተን ማረዱን፣ መግደሉን አይተውም።

"…ኦሮሙማው፣ የህወሓት መርዝ ትውልዱ አእምሮ ላይ የሞላው፣ የተጠቀጠቀው፣ ዐማራ ኦርቶዶክሱም፣ እስላሙም ጠላት ተደርጎ ነው። ህወሓት እና ኦህዴድ ኦነግ ሃውልት ቀርጸው ልጆቻቸውን በትምህርት ሥርዓት ውስጥ ቀርጸው እያስተማሩ በሐሰት ትርክት፣ በኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረ አብባ ድርሰት ያሳደጉት ዐማራ የተባለን ፍጡር ስለመበቀል፣ ከምድረ ገፅ ስለማጥፋት ነው።

"…ጥይት መግዣ አጥቶ የሚሞተው ፋኖ አያሳዝንህም ይሄን ደም መጣጭ አረመኔ ስምንት ሺ ብር ሰጥተህ ድጋሚ እንዲገድልህ ከምትልከው? አዝመራውን ሊያይ የመጣ ገበሬ አባትህን እና ወንድምህን እንዲህ ረግጦ ሲጨፈጭፍ የከረመን አረመኔ ተንከባክበህ መልሶ እንዲወጋህ ማድረጉስ ተገቢ ነው ወይ?

"…አሜሪካ እንድትራራልህ፣ አውሮጳ አይ ዐማራ እንዴት ያለ ደግ ፍጥረት ነው እንዲልህ ፈልገህ ነው? ሞኝ አትሁን። ገዳይ የብአዴን አባላትን አንበርክከህ ስለቀጣህ አሜሪካ በአምባሳደሯ በኩል፣ ሀብታሙ አያሌው እና እስክንድር ነጋ አምባሳደሩን ደግፈው እንደውም ሰላም አስከባሪ፣ አጣሪም ቡድን ጎጃም ይግባ እኮ ነው ብለው በድፍረት የፈረዱብህ። አትሞኝ። አታብዛውም።

"…ምርኮኛ ሁሉ ይገደል፣ ይታረድ አይባልም። ምርኮኛን ግን እንደ ሻአቢያ መንገድ፣ እርሻ ታሰራዋለህ። እንደ ወያኔ ዋሻ ታስቆፍረዋለህ፣ እርከን ታስደረድረዋለህ። ይሄን የመሰለ ወጠምሻ አራጅ ጎረምሳ ማርከህ፣ ቀልበህ፣ ከዚያም በላይ የአንተን እናት ገድሎ የእሱ እናት ስለናፈቀችው ገንዘብ ሰጥቶ መልቀቅ መሰልጠን፣ ደግነት አይደለም። ይሄ እልም ያለ ፋርነት ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችን እንደቀጠለ ነው። አዎ በተቀበላችን መሃል ደግሞ የኢትዮጵያ ሕጻናት፣ ነፍሰጡሮችና የደም ግፊት፣ የልብ ድካም ያለባቸው ዐማሮች እንዳያዩት የሚመከር አንድ ዘግናኝ በዐማራ ወጣቶች ላይ የፀጥታ ኃይሉ የሚፈጽመውን ዘግናኝ ቪድዮ ላሳያችሁ ነኝ እና ዐማሮች የሆናችሁ በሙሉ ለማየት ተዘጋጁ።

"…አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…
Подписаться на канал