ተቀበል አንተው…
ቀሳውስቱ ጎንደር ጳጳሱ ጎጃም ነው
ዲያቆናቱ ወሎ ተማሪው ሽዋ ነው
የዚህ ሁሉ መምህር ዐማራ ፋኖ ነው
ጨቅላውን አውርዶ ቀሚስ ሊያለብሰው ነው
ተጉዞ ተጉዞ ማረፊያው ሸገር ነው
ይዘገያል እንጂ ድሉ የፋኖ ነው።
በሮቹ ቆፍጣና ስማቸው ፋኖ ነው
አራሹም ዐማራ ሞፈሩ ጎንደር ነው
ማረሻው ወልቃይት ወገሉ ጎጃም ነው
ድግሩ ወሎ ሁኖ መርገጨው ሽዋ ነው
ቀንበሩ ዳሞት ማነቂያው ደንብያ ነው
የዘሩ መጫኛ አህያው ጁላ ነው።
ዘሪታው ዘመነ አራሹ ምሬ ነው
አራሚው ባየ አጫጁ ሳሚ ነው
ደሳለኝ ከማሪ ማንችሎት ወቂ ነው
ሰለሞን አይዞህ ባይ ዝናቡ ከፊት ነው
ጋይንት እያጨደ መሬ እየወቃው ነው
የምርቱ መክተቻ አዲስ አበባ ነው
አትጠራጠሩ ድሉ የፋኖ ነው💪
• ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት።
"…እርሱን ከወለድሽ በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ኑረሻልና የክርስቶስ እናቱ ተባልሽ፡፡ ድንቅ በሚያሰኝ ተዋሕዶ አማኑኤልን ወልደሸዋልና ባለመለወጥ አጸናሽ፡፡ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን መምህር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለማንም ሴት ያልተሰጠ ለድንግል ማርያም ብቻ የተሰጠ ድንግልና ከእናትነት ጋር አስተባብራ ስለ መገኘቷ ሲገልጥ “ ከድንግል ተወለደ፤ በወለደችውም ጊዜ ድንግልናዋን ያለመለወጥ አጸና፡፡ ድንቅ የሚኾን ፅንሷ ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ” በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን ስትወልድው ማኅተመ ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ ጌታም ሰው ሲኾን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ፣ እርሷ ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም) ስትባል እንደምትኖር አካላዊ ቃል ክርስቶስም አምላክ ወሰብእ (ሰው የኾነ አምላክ) ሲባል የሚኖር የመኾኑን የተዋሕዶ ልዩ ምሥጢርን ያወቅንባት የተረዳንባት እርሷ ብቻ መኾኗን አስተምሯል "ሃይማኖተ አበው.66፥32"፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
👆④ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ነገር ግን እኔ እነ ድርሳን መጡ፣ እነ ኑረዲን ወጡ ሲባል ሰፍ ብዬ አልቀበልም። እነ ድርሳን ወሎን አንድ ለማድረግ ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር ተቀላቅለው አንድ ጠንካራ የወሎ ፋኖ ለመፍጠር ከሆነ እቀበላለሁ። አልያ እስክንድርና እስኳዱ ሲመቱ ከእነሱ ጋር ሆነን ከምንወድቅ ተገንጥለን ፕላን ቢ እንጠቀም ብለው ከመጡም አልፋታቸውም። እኔ አስቀድሜ ድርሳንን ሸንቆጥ ለማድረግ ስፈልግ እነ አቤ ናቸው እነ ምሬ ዘመዴ ድርሳን እኮ የዋህ ናት፣ በእውነት አሳስተዋት እንጂ ጀግና ወሎዬ ቤተ ዐምሓራ ናት። በትእግስት መጠበቅ ነው የሚሻለው እያሉኝ ነው ሸንቆጥ ሳላደርጋት የተውኳት። አሁንም ድርሳን ሌላ መሠሪ ተንኮል ይዛ ከሆነ የመጣችው አምላከ ዐምሓራ ያጋልጣታል። የንፁሐን ደም ይፋረዳታል። የሚወዷትን ወንድሞቿን ዳግም ትከዳለች ብዬ አላስብም የሆነው ሆኖ ብትከዳ ግን ያው አይማረኝ አልምራትም። ታላቁ አሳምነው ጽጌ እንዳለው አንድ ሁኑ። መድኃኒቱ አንድ መሆን ብቻ ነው። አለቀ።
"…አሁን ኡጋንዳም፣ አሜሪካም ያለውን የስኳድ ስልክና ፎቶ እለቃለሁ ብዬ ስላልኩ ነው መሰል ስኳዶች አስቀድመው ራሳቸውን መግለጥ ጀምረዋል። በኤርትራ በኩል አቋርጦ ኡጋንዳ የከተመው የስኳድ ማስተር ማይድ ተብሎ የሚነገርለት በትውልድ ዘር ትግሬ ነው ተብሎ የሚታማው፣ ከወልቃይት በቀር ስለ ሌላው የዐማራ ፋኖ ግድ የማይሰጠው፣ በፌስቡክ ገጹም ከወልቃይት በቀር ሌለላው ብዕሩ የማይታዘዝለት ስኳድ ሙሉአለም ገብረ መድኅንም በአካል ተገልጦ ለስንት ግዜ ዘግቶት የነበረውንም የፌስ ቡክ አካውንቱን ከፍቶ ሽምቅ ውጊያውን መቀላቀል እንደሚፈልግ በግልጽ ዐውጇል። ተብታባው ጆሮ ቆሮቆራሙ ሲሳይ አልታሰብም ልክ ተአምረኛ የፖለቲካ ልሂቅ የመጣ ይመስል የተደበቁት ወድሞቻችን ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል ብሎ ሲፈነድቅ አይቼው በሳቅ ነው ፍርፍር ያማረኝ። ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ኡጋንዳ ያሉትን በሚዲያ ስም የተሰገሰጉትን ወንበዴ ስኳዶች ነው ማዘዝ፣ መምራት የሚችለው። ሙሉዓለም ገብረ መድኅን የወልቃይት አስመላሽ ኮሚቴን ማኅተም በኪሱ ይዞ እየዞረ፣ መግለጫ ለደመቀ ዘውዱ እየጻፈ ከመንበጫበጭ በቀር አሁን ምንም ማምጣት አይችልም። እርግጥ ነው እነ ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ከሙላት አድኖ ጋር ሆነው አርበኛ ውባንተን አስበልተውታል። አሰግድ መኮንንን አስበልተውታል። ጎጃምና ወሎን ግን አልቻሉም። የጎንደር ዐማራ ራሱ ነቅቷል። ወልቃይት ገብቶ እንዳያርስ የተከለከለ የጎንደር ዐማራ እንዴት እነዚህን ጥቂት ወንበዴዎች አምኖ ይከተላል? የማይሆነውን። ጎንደር እኮ ታላቅ ሕዝብ ነው። ሙሌ ግን እንኳን ደኅና መጣህ። እኔም ዝግጁ ነኝ።
"…እኔ አሁን እዚህ ቦታ ፋኖ ድል አደረገ፣ አሸነፈ፣ ማረከ፣ አልልም። አልጽፍምም። በአሩሲ ዐማራ ታረደ፣ ተገደለም ብዬ ትንፍሽ አልልም። አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት እየተመዘበረ ነው። የደብር እልቅና ለመሆን ጉቦው 1ሚልዮን ብር ገባ ምናምን ብዬም ለቄሶቻችን ጥብቅና አልቆምም። እኔ አሁን ደረጃዬን ከፍ አድርጌአለሁ። እኔ ሰንኮፍ ነቀላ ላይ ነኝ። እኔ አይነኬ፣ አይደፈሬ ምሽግ እየደረማመስኩ ለዐማራ ፋኖ ትግል ምቹ የመጫወቻ ሜዳ በመፍጠር ላይ ነኝ። ባህርዳር እንዲህ ሆነ፣ ጎንደር በዚህ ወጣ፣ በዚህ ገባም አልልም፣ የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የሸዋ፣ የላስታዎችን፣ የጎንደርን፣ የጎጃምን ድላቸውን ሌሎች የዐማራ ሚዲያዎች ይመስክሩ። እኔግን ዋናውን መርግ፣ የዐማራን እርግማን በማፍረሱ ሥራዬ ላይ እቀጥላለሁ። እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው፣ የሐረርጌው ቆቱ መራታ፣ ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ የዐማራን የመርገም ጨርቅ በጦማሬ በሥላሴ ስም ቀዳድጄ አወድመዋለሁ። ማርያምን የጣንቋይ ልጆች አያሸንፉኝም።
"…ከምር እግዚአብሔር ድንቅ አምላክ ነው። በአንድ በእኔ በዘመዴ በኃጢአተኛው፣ በወራዳው፣ በጎስቋላው፣ በወንበዴው፣ ከሁሉ በማንስ በእኔ በጭንጋፉ ላይ አድሮ ያለምንም በጀት እና ጀት የዐማራን ሰንኮፍ እየነቃቀለ ነው። በሜዳ፣ በበረሃ ያሉ ፋኖዎች፣ ጠላትም ወዳጅም እንዲያነበኝ፣ እንዲሰማኝ እያደረገ ነው። ለሰማይ ለምድር እንደከበደ ሰው የሚቆጠረው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ራሱ በትህትና ራሱን ዝቅ አድርጎ "እንዳንተ ያለ አንድ ሰው መኖሩ ጥሩ ነው። መረጃ ይኑርህ እንጂ ጥፋት ከተገኘብኝ እኔንም ቢሆን አትማረኝ፣ በእኔ ጉዳይ መረጃ ሲደርስህ አስቀድመህ ከመጻፍህ በፊት ብትጠይቀኝ ለመመለስ ዝግጁ ነኝም" ብሎ እንዲጽፍልኝ ያስደረገው የድንግል ልጅ ራሱ መድኃኔዓለም ነው። እኔም መልሼ አልኩት… "እንኳን አንተን ጎምቱ ቦለጢቀኛ የአደባባዩን ሰው ይቅርና አልኩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን "እንኳን አንተን የአደባባዩን ሰው እኔ ለራሴም ቢሆን ጥፋት ሲገኝብኝ ራሴን ከማጥረግረግ አልመለስ" ይኸው ነው። ለወዳጅ ማር፣ ወተት፣ ለጠላት ሬት ስላደረገኝ አምላኬን አመሰግነዋለሁ።
• ማርያምን ዐማራ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው፣ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍✍ "…ጌታ አስራደ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር ወልቃይት ነው የከረመው። ውብአንተ ለእነ ጌታ አስራደ ነበር ይከራከር የነበረው። የውባንተ ሞት የሚቆጨው አሁን እዚህ ጋር ነው። ተመልከቱ እነ ጌታ አስራደ፣ እነ ዶር ምስጋናው አንዷለም፣ እነ አያሌው መንበር፣ እነ ሲሳይ አልታሰብ፣ እነ ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ጦርነቱ አልቆ በስናይፐር ተነጥሎ እንዲመታ የተደረገው ውብአንተ ከተገደለ በኋላ በቀጥታ ያደረጉት ምንድነው ያልን እንደሆነ በቀጥታ ወደ እስክንደር ዕዝ ነው የገቡት። እስክንድርን ነው መሪያችን ብለው የመረጡት። ልብ በሉ። ፍረዱም። ስለዚህ አርበኛ ውባንተ የሞተው የተገደለውም በጠላት ነው ማለት ይቻላል ወይ? እስኪ ንገሩኝ? የውባንተ አርባው እንኳ ሳይወጣ እኮ ነው እነ ኮሎኔል ታደሰ እስክንድር ነጋ መሪያችን ነው ብለው ያወጁት። ይሄ ብቻ አይደለም ቀጥሎም እኮ አርበኛ ባዬ ቆስሎ በመከራ ነው የዳነው። ቀጥሎም አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ይገደል የሚለው ይሄው ስኳድ እኮ ነው። አያችሁ የስኳድን ሰርጎ ገብንት።
"…ስኳድ ጎንደሬዎችን እንዲህ ቀርጥፎ ከበላ በኋላ በቀጥታ ያመራው ወደ ሸዋ ነው። ሸዋ ላይ አስቀድሞ የጎንደር ተወላጅ ነን ያሉ ልጆችን ልኮ በአሰግድ መኮንን በኩልም፣ በአርበኛ መከታው ማሞም በኩል የሸዋ ፋኖ አመራርነት ቦታን አስይዞ ሸዋን በእጁ የማስገባት ያህል ነበር የሠራው። አሁንም ልብ ብላችሁ ተከተሉኝ ሸዋ ላይ እነ መከታው ማሞ የሚመሩት የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ የሻለቃ እና የብርጌድ መሪዎቹ በአብዛኛው የጎንደር ተወላጅ የሆኑ ናቸው። በስም ዝርዝር ላስቀምጥላችሁ እችላለሁ። እነዚህ የጦር መሪዎች ደግሞ ተጠሪነታቸው ለእስክንድር ነጋና ከወልቃይት በኡጋንዳ እስከ አሜሪካ ለተዘረጋው ለአደገኛው የብአዴን ስኳድ ቡድን ነው። ተመልከቱ ብቻ እጃቸው ርዝመቱን።
"…ይሄ ወልቃይቴ ስመ ጎንደሬ ስኳድ በፊት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ባለማገዝ ቀርጥፎ የበላ ብአዴናዊ አፍቃሬ ወያኔ ቡድን አሁን ደግሞ በወልቃይት የሰሊጥ ብር፣ በደቡብ ጎንደር ወያኔያዊ የብአዴን ስኳድ ቡድን ረጅም እጁን በደቡብ ጎንደሬው እስክንድር ነጋ አማካኝነት ውድና እንቁ የሸዋ ልጆችን መሪ እንዳይሆኑ ተመርጠው በሴራ እየተመቱ ነው። በሸዋ የሌለ ጭካኔ ነው ስኳድ የሸዋ ፋኖዎች ላይ እየፈጸመ ያለው። የፋኖ አለቆችን በጩቤ፣ በሳንጃ ዓይናቸውን ሁሉ ጎልጉሎ፣ አንጀታቸውን ዘርግፎም ነው እየገደለ ያለው። ጭካኔው የዐማራ አይመስልም። ማርያምን እውነቴን ነው።
"…ይሄ የስኳድ እጅ አይደለም እነ መከታው ጋር ራሱ አርበኛ አሰግድ ከሚመራው ፋኖ ውስጥ የሦስት ብርጌድ መሪዎች ትውልደ ገንደሬዎች እንደነበሩና መጨረሻ ላይ ግጭቱ አድጎ ጦርነት ሲገጥሙ እነመከታው ውስጥ ያሉት እስኳዶችና አሰግድ ጦር ውስጥ የነበሩት እስኳዶች እንዴት እንደተናበቡ ብትመለከቱ ትደመማላችሁ። ለምሳሌ ሰኔ 23/2016 ዓም ማጄቴ በነበረው ግጭት ሰኔ 24 ለጋሽ አሰግድ ደውሎ አሰግድ የነገረውን አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን ልንገራችሁ። "የጦር መሪዎችን ስም ዝርዝር እየጠራሁ አለ ጋሼ እነማን አብረውህ አሉ? ስለው አሁን የሸዋ ተወላጆች ብቻ ናቸው አብረውኝ ያሉት አለኝ። ከምርህ ነው? ጋሼ ስለው…ተወውማ "ዐማራ አንገቱ አንድ ነው" ብዬ ተሸወድኩ አለኝ። እኔም ይህን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ ነው የሚለኝ ይሄ ወዳጄ። ከዚህ ተነሥታችሁ ሌሎች የሸዋ ፋኖዎችም በአመራርነት ቦታ ያሉትን ሰዎች ከወዲሁ ልትፈትሹ ይገባል። በተለይ ሸዋ አስቡበት። ስኳድ ሸዋ ላይ የሠራውን ሌላ ቦታ የትም አልሠራም። ሸዋን ሽባ አድርጎ ነው ነው ያስቀመጠው። ለዚህ ነው ሸዋ ደብረ ብርሃን ሊገባ መንገድ ሲጀምር መከላከያ ሲፈረጥጥ ከኋላ በጎንደር ስኳድ የሚመራው የእነ መከታው ጦር የሸዋ ልጆች ላይ ተኩስ የሚከፍተው። ደቡብ ጎንደር ያለው የወያኔ መርዝ ስኳድ አደገኛ ነው ነው የምልህ። ጎንደርን ሦስ ቦታ የከፈለ ስኳድ ሸዋን ሁለት ቦታ፣ ወሎን ሁለት ቦታ ቢከፍል አትገረም ልልህ ነኝ።
"…መረጃው ውሸት ነው የሚል ካለ ወጥቶ ይሟገተኝ። እኔ ገና የቁስሉን ዳርዳር እያከኩት እንጂ አላፈረጥኩትም። ደግሞም አሁን አላፈርጠውም። ገና መዝምዤ፣ መዝምዤ ነው የማፈነዳው። አሁን ሸዋ ላይ ካሉት የፋኖ የታችኛው እርከን መሪዎች 80% በጎንደር ልጆች ነው የተያዘው። ይሄን ሴራ ሸዋ ካፈረሰው አለቀ ሁሉ ነገር አሸወይና ነው የሚሆነው። ሴራው እየተገለጠላችሁ ነው አይደል? እነ ስኳድ እያሉ ያሉት ምን መሰላችሁ በሸዋ ያሉትን የነቁ ዐማሮች በእነ አቤ ጢሞ፣ በእነመከታው እጅ ተቀርጥፈው ይበሉ። ጅሉ መከታው፣ ሞኙ አቤ ጢሞ ሸዋ ላይ ያሉትን የነቁ ዐማሮች በእኛ ሳይሳበብ፣ ሳይነቃም በልተው ከጨረሱልን መጨረሻ ላይ አያስፈልጉንም እና እኛ ራሳቸውን በልተን ነው የምንጨርሳቸው ነው ብለው የወሰኑት። ናሁሰናይ የተገደለው እኮ ናሁሰናይ በእነ ባዬ፣ በእነ ውባንተ ጦር ውስጥ ስላለ ነው። ናሁሰናይ ሲሰዋ እኮ ቀድሞ መግለጫ የሰጠው የእነ መከታው ቡድን ነው። የእነ መከታው ቡድን ደግሞ አሁን በእስክንድር ነጋ እጅ ወድቋል። በተዘዋዋሪ ስኳዱ ነው የመከታውን ጦር የሚመራው። ተመልከቱ የሰሞኑን የሸዋ ተጋድሎ ስትሰሙ ስኳድ ድባቅ ስለተመታ በሸዋ የኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ ጦር ብዙ አካባቢዎችን ነፃ እያወጣ ነው። ምክንያቱም የስኳድ እጅ እየተቆረጠ ስለሆነ ነው። በደንብ ደግሞ ሳንቲምና ሚዲያ ሲያጣ ሸዋ ብቻውን ያሸንፋል።
"…አሁን ደስ የሚለው ነገር በስሙ የሚነገድበት የጎንደር ዐማራ ከምንጊዜውም በላይ ነቅቷል። ሁል ጊዜ አበበ በለው በጎንደር የሆነ ነገር ሲሠራ ሩጦ የሚጠራው የምወደው፣ የማከብረውን አርበኛ ደረጀ በላይ መሆኑ ይገርመኝ ነበር። እርቅ ሲፈጸም የሚያጣጥለው አበበ በለው ነበር። ኋላ ስጠይቅ አበበ በለው እናቱ ትግሬ፣ እሱ ደግሞ ቅማንቴ ነው ነው አሉኝ። ነው እንዴ ብዬ መገረም፣ መደነቄን ትቼ ልግጠመው እንጂ ብዬ ቆርጬ ተነሣሁ። አበበ በለው ከሸዋ ሁል ጊዜ የሚያቀርበው የመከታውን ጦር ሰዎች ነው። ቀላል ይናበቡታል እንዴ? አበበ በለው ከሀብታሙ አያሌው ጋር ሆኖ መረጃ ቲቪን በጥበብ ለማፍረስ ሲንቀሳቀስ መረጃ ቲቪ በጊዜ ነቅቶ መንግሎ ነው የጣለው። አበበ በለው አሁን ገንዘብም፣ ተመልካችም ሲያጣ ሁል ጊዜ ወጥቶ የሚለፈልፈው "መረጃ ቲቪ በአስቸኳይ ዘመድኩን በቀለን ከቴሌቭዥን ላይ ያውርድ" እያለ ነው። እኔን ማውረድ ብቻ ሳይሆን ዘመድኩን መረጃ ቲቪ ላይ ከቆየ "ኡጋንዳ ሆነው ሙሉዓለም ገብረ መድህን እየጻፈ የሚሰጣቸውን መግለጫ የሚያነቡት የስኳድ አባላትም ይጎዳሉ ነው የሚለው። ተመልከቱ እስኳድ ሰንኮፉ ሲነቃነቅ።
"…አሁን ጎንደርና ሸዋ እንዳይጋጭ በጥንቃቄ መጓዝ አስፈላጊ ነው። ሾተላዮቹ ቢጨመቁ 30 አይሞሉም። እነዚህን አረሞች በጥበብ ከስንዴ ምርቱ ጎንደርና ሸዋ መሃል ነቅሎ ሁለቱን ሕዝቦች አንድ ናቸው በአንድነታቸው እንዲቀጥሉ ማድረግ ይገባል። በዚህ በኩል የሁለቱም ምሑራን ጨክናችሁ ምከሩ። ሸዋን በሸዋ ምድር በሸዋ ልጆች በዘዴ እያስወገዱ ያሉት የጎንደር ስኳዶች ሸዋን ለቅቀው በጊዜ ቢወጡ መልካም ነው። ይሄ ሰሊጣም ወልቃይትን ጋጭ የብአዴን ህወሓት ብልፅግና ስኳድ ዘመነ ካሤን በመጥላት ስም ጎጃም ላይ እንደ አበደ ውሻ ለሃጩን የሚያዝረከርከውም እኮ ወደ ጎጃም እንደ ሸዋ ሰተት ብሎ መግቢያ መስመርና ቀዳዳም ስላጣ እኮ ነው። በኮሎኔል ደመቀ…👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም… ርዕሰ አንቀጹን ለመጻፍ የዘገየሁት ጎጃም ሄጄ የተዘጋውን መንገድና ተጋድሎ፣ ጎንደርም ዘልቄ ትንቅንቁን፣ ሸዋም ሔጄ ነፃ የወጡ መሬቶችን ስቆጥር፣ ወሎ ሄጄ የእነ እስክንድር ነጋንና እስኳድ ዶር ምስጋናውን የህልም ዣት የሆነው አዲሱ ፌስታሌ ድርጅታቸው ተቀድዶ ሹመት የተሰጣቸው በሙሉ "ወራጅ አለ" በማለት ተንጠባጥበው ሲፈርሱ እያየሁ ስለነበር ነው።
• ፋኖ ድርሳን ብርሃኔ
• ፈኖ ሲሳይ ሳተናው
• ፋኖ እስራኤል እሸቴ ከእስክንድ ከኩርቱው ተንጠባጥበው መውጣታቸው ታይቷል።
"…በዚያው በወሎ በወዳጄ በእነኑረዲን አማካኝነት በእስክንድር ነጋ ስም ተቋቁሞ የነበረው እስክንድር ነጋ ክፍለጦር መፍረሱንና አዲስ ክፍለጦር ማቋቋማቸው ተሰምቷል።
"…አሁን ከእስክንድር ጋር የቀሩት በአሜሪካ መንግሥት የተያዘው ዶላር ሲለቀቅ የድርሻችንን እናገኛለን ብለው ዶላር ተስፋ አድርገው ጎንደር አንድ ሆኖ እንዳይታገል በእስክንድር መሃላ ተጠፍረው ለጎንደር ዐማራ ትግል እንቅፋት የሆኑት አርበኛ መሳፍንት ተስፉ በበላይ ጠባቂነት የሚመሩት የሀብቴ ጦር፣ እንዲሁም የወልቃይት የሰሊጥ ብር እና እነ ስኳድ የሚመሩት የጌታ አስራደ የደቡብ ጎንደሩ የፋፍዴን ጦር፣ ከወሎ ሸሽቶ ጋይንት የገባው ኮሎኔል ሙሀባው፣ ሠራዊቱ እየከዳው፣ የሸዋ ሕዝብ አንቅሮ እየተፋው የመጣው የመከታው ሚሊሻ ብቻ ናቸው። እነሱም የሕዝብ ጫና ሲበረታ ወደ ቀልባቸው ይመለሳሉ።
"…በነገራችን ላይ እነ ድርሳን፣ እነ ፋኖ እስራኤል፣ እነ ሲሳይ ሳተናው ከእስክንድር ስር ወጥተው ሌላ ዕዝ ከመሰረቱ መጠርጠር ነው። አስቀድሜ የሰማሁት ነገር ስላለ መጠርጠር ደግ ነው። ብዙ ጊዜ ፋኖ ድርሳን ላይ ተግሳጽ ልጽፍ መረጃ ሳሰባስብ እነ ምሬ፣ እነ አቤ ግዴለም ዘመዴ "ድርሳንን እንታገሳት" ስለሚሉኝ ተንፍሼባት አላውቅም።
• ርዕሰ አንቀጽ ልለጥፍ ነኝ። አላችሁ አይደል?
• ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ አርብ።
"…ቅድመ ዓለም የነበረ እርሱ ሰው ኹኗልና (ካንቺ ተወልዷልና) የእኛን ሥጋ ነሥቶ የርሱን ሕይወት ሰጥቶ ከርሱ ጋራ አስተካከለን። በቸርነቱ ብዛት እንድንመስለው አደረገን "ፊል.3፥10-11። ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ክብር የክብር ክብር ካላቸው ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ "ሉቃ 1፥28።" ንጉሥ በከተማው እንዲኖር ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን ማኅፀንሽን ዓለም አንድርጎ ኖሮብሻልና አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በኪሩቤል በሱራፌል አድሮ የሚኖረው እርሱን በማኽል እጅሽ ይዘሽዋልና ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በቸርነቱ ብዛት ፍጥረቱን ኹሉ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ አንድም ለሰው (ለመንፈሳውያን) ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ ይኸውም ፈጣሪያችን መድኃኒታችን ነው፡፡ እንሰግድለት እናመስግነውም ዘንድ በሐዲስ ተፈጥሮ በጥንተ ተፈጥሮ ፈጥሮናልና ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል ዮሐ.6፥37፡፡ ሰጊድ (አምልኮ) ከሚገባው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም…
"…ርዕሰ አንቀጻችንን 20 ሺ ሰው አንብቦት 25 ሰው ብው 😡 ብሎ መበሳጨቱን እያየሁ ነው። ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው በርዕሰ አንቀጹ ላይ በጨዋ ደንብ ሓሳብ ወደ መስጠቱ ነው።
"…የእኔ ቤት ያው የታወቀ ነው። አግድም አደግ፣ አምቡሌያም፣ ስድአደግ ባለጌ እንደ ሌሎች ፔጆች ዘው ብሎ ገብቶ አፉን መክፈት አይችልም። የእኔ ቤት የአስተያየት መስጫ ሰንዱቅ ለሁሉም ክፍት ነው። ክልከላ የለበትም። ሙግትም፣ ተቃውሞም ይስተናገዳል። ታዲያ ሁሉ ነገር በጨዋ ደንብ ነው። አልያ ያስቀስፋል።
"…እኔንም ይሁን ሌላ ሰው ነውር በምንለው በባህላችን ፀያፍ በሆነ ስድብ መሳደብ አይቻልም። እሱም ያስቀስፋል። ለእኔም ሆነ ለሌላ ሰው አግዛችሁ፣ እናንተም መልሳችሁ ሌላ ሰው በገፄ ላይ ብትሳደቡ ያ የመጀመሪያው ተሳዳቢ የገጠመው ዕጣ ፈንታ ነው የሚገጥማችሁ፣ የሚደርስባችሁም። ማንም ይሁን ማን ፀያፍ ቃል ከአፉ በፔጄ ላይ የሚያወጣ ይቀሰፋል። ለእኔ አግዞ ስለተሳደበልኝ አልሸልመውም።
"…ባለጌ ስታዩ ጠቁሙኝ። ዘመዴ 👈…👉🏿 Block ብላችሁ መጠቆም ብቻ ነው። በፆም ምን አፍ አካፈታችሁ። ከዚያ እኔ ወገብ ዛላ መቁረጫ የብሎክ ሰይፌን ይዤ እመጣና እቀስፈዋለሁ። ይኸው ነው።
"…በሉ ስለ እስኳድ ደፈር ብለን መነጋገር እንጀምር። ጎንደርን እንደ ሕዝብ በእስኳድ ስም የሚናገር ካለ እቀስፈዋለሁ። ስኳድን ብቻ ለይተህ ተች። አጋልጥ። ሞግት።
"1…2…3… ጀምሩ…✍✍✍
👆③ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …አሸተ ደምለው ሕዝብ ሰብስበው ወልቃይት ከተያዘ በቃ አለቀልህ። ዐማራ የሚባል ይጠፋል፣ ጎንደር ያበቃለታል። የአባ አመሀ ኢየሱስ ትንቢት ይፈጸማል ብለው ቀስቅሰው ለሞት የሚማግዱት። በወልቃይት ጉዳይ ጎንደሬ ዐማራ የሚፈለገው እንዲሞት ብቻ ነው። አዎ ሞት ብቻ ነው ለጎንደር ዐማራ የሚፈቀድለት።
"…እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለወልቃይት የስኳር ፋብሪካ መሥሪያ ነው ተብሎ የመጣን ብረታ ብረት፣ ጄኔሬተር ሁላ አውጥተው ነው የሸጡት። ኮሎኔል ደመቀ ጎንደር ከተማ እኔ ነኝ ያለ የራሱን ህንፃ እየሠራ ነው ያለው። ዐመዳም የትግሬ ወታደር እያለ ያላመጣውን ሀብት ከየት አምጥቶ ነው አሁን ህንፃ ፎቅ በዐማራ ምድር፣ ፋኖን እየሰደበ፣ እያሳደደ የሚገነባው? አዎ ከየት አምጥቶ ያልከኝ እንደሆነ ወልቃይት የተባለ ዐማራ ሞቶ ያስከበረው የዐማራን ርስት የግሉ የነዳጅ ጉድጓድን የሚያስንቅ ሀብት ስላደረገው ነው። በወልቃይት ጉዳይ ደቡብ ጎንደሮች ተለይተን ነው የተገደልነው የሚሉ አልቃሾች በሟች ብአዴኖች ሰበብ በጎጥ ተደራጅተው በማኅበር ነው የሚግጡት ወልቃይትን። የመሳሪያ፣ የሰሊጥ ንግድ ነፍ ነው። ገቢ ዘጭ ነው። ወልቃይቴ እንጂ ጎንደሬ መባልንም አይፈልጉም። እንደ ድሬደዋ ራስገዝ እንድትሆን ነው የሚፈልጉት። የጎንደር ዐማራን አጥፍተው በፖለቲካው ቅማንት ነው መተካት የሚፈልጉት። አዎ ደመቀ ዘውዱ ሽፍታ ከሀዲ ፀረ ፋኖ ፀረ ዐማራ ነው። ደመቀ ዘውዱና ካቢኔው ከገዳዩ መከላከያ እኩል መወቀጥ ያለበት አደገኛ ፀረ ዐማራ የተቀበረ ፈንጂ ነው። አባቱ ትግሬ ነኝ እያሉ እሱ ዐማራ ነኝ የሚለው ለምን ይመስልሃል? ተንጫጫ፣ እበድ፣ ስኳድ ፀረ ዐማራ ሁላ።
"…ራያ ሲወረር ኮሎኔል ደመቀ ምን አለ? ስኳዱስ ምን አለ? ምንም። ስለ ሸዋ ደራ ኮሎኔል ደመቀ ምን አለ? ስኳዱስ ምን አለ? ምንም ምንም አላሉም። በመተከል ለሚጨፈጨፈው ዐማራ ስኳዱ ምን አለ? ኮሎኔሉስ ምን አለ? ምንም ምንም አላለም። አሁን በዐማራ ምድር ይሄ ሁሉ ዐማራ ሲረግፍ ስኳዱና ግማሽ ትግሬው የብልጽግና የወልቃይት ተወካይ ደመቀ ዘውዱ ምን አለ? ፋኖ መከላከያ ላይ መተኮስ የለበትም ነው ያለው። ደመቀ ዘውዱ ከራያ፣ ከመተከል፣ ከደራ አስመላሽ ኮሚቴ ጋር ተባብራችሁ ሥሩ ሲባል ምንድነው ያለው? አይ እኛ ከኦህዴድ መጣላት አንፈልግም። ሁሉም በራሱ ይንቀሳቀስ። ወልቃይት ሲነካ ብቻ ግን ሁሉም ለእኛ ይሙት ነው ያለው። ደመቀ ዘውዱ ስለ ጄነራል አሳምነው ጽጌ ምንድነው ያለው ትክክል አላደረገም፣ አጥብቄ ነው የምቃወመው ነው ያለው። እናም ይሄ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ፋኖ ስብስብ አደብ መግዛት አለበት። ወልቃይት ሲነካ ግርር ብሎ መጥቶ፣ ሚዲያውን ሙልት አድርጎ ዋይዋይ የሚለው አጭቤ ቡድን ልሣኑ መዘጋት አለበት። ወልቃይት የሚወረር ሲመስለው ዐማራ አለቀለት፣ ዐማራ ሊጠፋ ነው፣ ዐማራ ጉዱ ፈላ፣ የደብረ ማርቆስ፣ የጎጃም ዐማራ ተነሥ፣ ናና ሙትልኝ፣ ተቀበርልኝ፣ ተሰዋልኝ። ወሎዬዎች ኑና ሙቱ፣ ዐማራ ተጠቃ፣ ሸዋ ዝም አትበል፣ ወልቃይትን ትግሬ ከወሰደው የዐማራ አንገት ተቆረጠ፣ ዋይዋይ፣ ቀይመስመራችን ተደፈረ የሚልን ራስወዳድ ፀረ ዐማራ ቡድን በጊዜ ሃይ መባል አለበት። ጋሽ መሳፍንት በሰፈሩ ከመከላከያ ጋር ሲጣላ እስኳድ ወጥቶ ጎጃሞች መንገድ ዝጉልኝ እንጂ ይላል። ሰው ላኩልኝ፣ አግዙኝም ይላል። ጎጃም መከራው ውስጥ ሲገባ ግን ስኳድ ድምጹም አይሰማም። ጎጃም ጎንደር ተሻግሮ ሲያግዝ ስኳድ ጎጃምና ጎንደር እንዳይገናኝ ድልድዩን ይሠብራል።
"…እደግመዋለሁ የትኛውም የጥፋትም ይሁን የልማት ማኅበር አንተ መስርተው እንጂ ገንዘብና ሰባኪ ካለህ ተከታይ አታጣም። በተለይ ገንዘብና መሳሪያ ካለህ ተከታይህ ነፍ ነው የትየለሌም ነው የሚሆነው። ባህርዳር ላይ የእኛ ወዳጅ፣ የአገልጋዮች እንግዳ ተቀባይ፣ እነ አበበ እና ሌሎች ጎጃሜዎች "ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" ብለው መፈክር ይዘው ወጥተው በአግአዚ ጥይት ሞተው ስኳድ የጎጃሜውን አበበን ባነር እየለጠፈ ጎጃምን እንደ ሕዝብ ሲሳደብ ይውላል። ሌላው ቢቀር እቤተሰባቸውን እንኳ የጠቀመው ነገር የለም። በወልቃይት የተጠቀሙት ጎንደሬዎች እንኳ አይደሉም። በወልቃይት ጉዳይ በቃሊቲ በስብሶ ከተፈታ በኋላ እንደገና ተገድሎ ሚስቱ ይኸው ራበኝ ብላ ለእኔ ነው ቪድዮ ሠርታ የምትልከው። ስኳድ ጨካኝ ነው። የስኳዱ መሪዎች ግማሽ ቅማንት እና ግማሽ ትግሬ መሆናቸው ደግሞ ችግሩን ያብሰዋል። ያጎላዋልም። አሁን እስኳድ የሰሊጥ ብር ይዞ እስክንድርንና መከታውን ቼ ፈረሴ ብሎ እየጋለበም ነው። የመከታው ልጆች ሰሞኑን እነ አዶናይ "እናትዋ ጎንደር፣ እህልዋ ጎንደር" ብለው ፌስቡክ ላይ መለጠፍ የጀመሩት እጀ ረጅሙ የስኳድ የሰሊጥ ብር ሸዋ ገብቶ በእስክንድር በኩል ሸዋ ቀድሞ 4ኪሎ እንዳይገባ አንቆ ስለያዘላቸው ነው። አብዛኛው የመከታው ጦር አዛዦች ትውልደ ጎንደሬዎች መሆናቸውን ስታይ ትጠረጥራለህ። አንድ ላይ መታገሉ ችግር ባይኖረውም ሸዋ ተቀምጦ አሰግድ ይገደል የሚል ጎንደሬ የጦር መሪ ስታይ መጠርጠር ግድ ነው።
"…ተመልከት ጎንደር በውኃ ጥም እየተቃጠለ እስኳድ ሥልጣኑን በእጁ ይዞ እየታየ፣ ሀብቱ በእጁ መሆኑ እየታየም ለጎንደር ሕዝብ ደንታ አይሰጠውም። በዓመት አንድ ጊዜ ጎንደር ለጥምቀት እያለ ሄዶ አረቄውን፣ አምቡላውን፣ ዳሽን ቢራውን እየተጋተ፣ ጮማ ቆርጦ፣ በቢራ እና በውስኪ ታጥቦ፣ ደሀ የጎንደር ዐማራ ምስኪን ሴቶችን አማግጦ፣ አነውሮ፣ በየ አዝማሪው ቤት የሰሊጥ ብር፣ የግፍ ብር ለአዝማሪና ለሸርሙ* በትኖ፣ የካህናቱን፣ የቅዱሳኑን ሀገር በዝሙት፣ በግልሙትና አርክሶ፣ አውራ ጎዳና ላይ እናትዋ ጎንደር፣ እህልዋ ጎንደር እያለ ጨፍሮ፣ ተዝረክርኮ ነው የሚመለሰው። አዎ ጎጃምን ከጎንደር ለማጣላት፣ ሕዝብን ከሕዝብ ለማፋጀት፣ ፕላን አውጥቶ ነው የሚለያየው። ስኳድ ቁጥሩ ትንሽ ነገር ግን እጁ ረጅም የሆነ ድንጉጥ፣ አቅመቢስ ስብስብ ነው። አንዳርጋቸው ጽጌ ጆሮውን ቆንጥጦ የሚያዘው፣ ሻአቢያ ቁጭ ብድግ የሚያደርገው፣ አቢይ አሕመድ በየአይነት አቅርቦ በሆዱ የሚያንበረክከው ሆዳም ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያ ስብስብ ነው። ለጎንደርም፣ ለጎንደሬም ጠብ ያለ ነገር የማያመጣ ስብስብ ነው። ከደቡብ ጎንደር ለሄደው ለጋሻው መርሻ የመሬት ባለቤት፣ ባላባት ያደረገው ስኳድ ለወልቃይት ደማቸውን ካፈሰሱ፣ አንድያ ነፍሳቸውን ለሰጡ የጎንደር ዐማራ ፋኖዎች ግን ወፍ የለም። አሁን እስኳድ ሲቀጠቀጥ ጎንደር ተነካ ማለት አይሠራም። እኔ ለጎንደር ዐማራ መስሎኝ ጥብቅና ቆሜ ሽንጤን ይዤ የምሟገተው? ሃኣ?
"…ውባንተን የገደለው ይሄ ስኳድ የተባለ ሾተላይ ቡድን ነው። ለአቶ መሳፍንት ብር ሰጥቶ ውባንተ ፋፍዴን ነው ብሎ፣ ውባንተ ብአዴን ነው ብሎ፣ ሻለቃ ዳዊት፣ ሀብታሙ አያሌው እስክንድር ስር እንደነ ሀብቴ ካልገባህ ብለው፣ ሰድበው፣ አዋርደው፣ ጦርነት ካለቀ በኋላ በስናይፐር ያስደፋው ይሄ ስኳድ የተባለ ቡድን ነው። ልብ በሉ ውብአንተን እስኳድ ያስባለው እነ ጌታ አስራደ፣ እነ ኮሎኔል ታደሰ፣ እነ ኢያሱ ፋፍዴን ናቸው፣ ለምን እነሱን አንተ ጋር አስጠጋህ ተብሎ ነው። ዛሬስ ውብአንተን ካስገደሉት በኋላ እነ…③ 👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…እኔ ዘመዴ ዛሬ ድንገት ብድግ ብዬ ተነሥቼ አዲስ ሃይማኖት መሥርቻለሁ እና ተከተሉኝ ብዬ ባውጅ በአንደዜ ሚልዮን ተከታይ አላፍራ አላግኝ እንጂ ቀስ በቀስ እየዋለ እያደረ የሚበዛ አሜን ብሎም የሚከተለኝ ሰው ግን አላጣም። ሃይማኖት ብቻ አይደለም፣ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የውይይት፣ የምክክር ማኅበር፣ የሌብነት፣ የዝርፊያ፣ የቅሚያ ማኅበር፣ የቢዝነስ ድርጅት ብመሠርት ተከታይ ማኅበርተኛም አላጣም። ጠንቋይ፣ አስማተኛ ነኝ ብዬ ስር እየማስኩ፣ ቅጠል እየበጠስኩ እፈውሳለሁ ብዬ ባውጅም እንዲሁ ተከታይ፣ አድናቂ እና አምላኪም አላጣም። እንዲያውም ስለ እኔ ሌት ተቀን የሚሰብኩ ደቀ መዛሙርትም ሁላ ላፈራ እችላለሁ። ተከታይ የማገኘው እኔ ጎበዝ፣ ቆንጆ፣ ውብ፣ አንደበተ ርቱዕ ስለሆንኩ፣ ባለፀጋ፣ ሀብታም ዲታም ስለሆንኩ አይደለም። ሰዎች ስንባል ነፃ ፈቃድ ከፈጣሪ የተሰጠን ስለሆነ በዚያ ነፃ ፈቃዳችን ነጻነታችን ተጠቅመን የፈለግነውን፣ የፈቀድነውን የማመን፣ የመከተል ተፈጥሮአዊ መብት ስላለን ነው። እንደየሀገራቱ መንግሥታት ሕግ በሕግ የተከለከለ ነገር ካልሆነ በቀር የሆነ ነገር መስርቶ ተከታይ ማፍራት እጅግ ሲበዛ ቀላል ነው። እግዚአብሔር እንደሁ ፍጹም ዲሞክራት አምላክ ስለሆነ እኛን አስገድዶ የሚያሳምን የሚያስመልክ አምላክ ስላልሆነ እሳትና ውኃ ያቀርብልናል የእኛ ሥራ እጃችንን ወደ ወደድነው መዘርጋት እና መንከር ብቻ ነው። አለቀ።
"…በዓለም ላይ ሀሺሽ፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ የጦር መሣሪያ የሚያዘዋውሩ፣ የሚሸጡ፣ የሚለውጡም ማኅበራትና ቡድኖች አሉ። ህጻናትን ለወሲብ ንግድ የሚያሰማሩ፣ የሚያዘዋውሩ የሚሸጡ፣ ሴቶችን ለወሲብ ንግድ የሚሸጡ፣ የሚገዙ፣ የሚያዘዋውሩም አሉ። በሲና በረሃ የሰደተኞችን ልብና ኩላሊት ያለማደንዘዣ ቀደው የሚሸጡ የተማሩ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የህክምና ዶክተሮችም አሉ። ጄነራሎች፣ ኮሎኔሎች፣ ወታደራዊ አዛዦች ሆነው በኮንትሮባንድ የከበሩ፣ የሚከብሩም ግለሰቦች አሉ። እነዚህ ሁሉ ቡድኖች ናቸው። ተከታይ፣ ሰባኪ፣ ሠራተኛም አላቸው። የሀገር፣ የታሪክ መውደም ደንታቸው ያልሆነ፣ አንድ ሚልዮን ትግሬ ቢሞት ጉዳያቸው ያይደለ፣ ዐማራ ከምድረገጽ ቢጠፋም የማይሞቃቸው የማይይበርዳቸው ነፍ ናቸው። ይሄ ሁሉ ሲሆን ከሀገር ውስጥ እስከ አውሮጳና አማሪካ እስከ ቻይናም ድረስ የተዘረጋ አደገኛ በሆነ መረብ ውስጥ ተሳትፈው የሚሠሩቱ የሰዎች ልጅ የተባሉ የመንጋ ስብስብ ናቸው።
"…በየመንደሩ ያለ ጠንቋይም እኮ ካዳሚ አለው። ገባሪም አለው። ሰባኪም፣ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛለት፣ የአፍ ማስታወቂያ የሚነግርለት አለው። አቤት እሳቸው እኮ ዐዋቂ ቢሉሽ ዐዋቂ አይምሰሉሽ፣ ለከሰረው ሱቅህ ዐዋቂ እገሌ ጋር ብትሄድ ብለው የሚሰብኩ ደላሎችም አሉ። ጠንቋዩ ሳትጠራጠር አድርግ የሚለውን ዘግናኝ አፀያፊ የወንጀል ድርጊት የሚፈጽሙ፣ የአብራካቸውን ክፋይ ለአጋንንት እስከመሰዋት ድረስ የሚደርሱ አንቱ የተባሉ ሰዎች እኮ ያለምንም አስገዳጅ ሁኔታ ነው የዚህ ማኅበር አባል የሚሆኑት። ጠንቋይ ያዘዛቸውን ፈጽመው ለመክበር ሲሯሯጡ የምታዩአቸው እኮ በነፃ ፈቃዳቸው ተጠቅመው ነው። ፎጋሪ ጠንቋዮች እንዳሉ ሁሉ አጋንንቱ ሰፍሮባቸው የሚጠቀምባቸው ጠንቋዮችም አሉ። የእኔ መነሻ ነጥብ ጠንቋይም ይሁን መተተኛ የፈለገው ይሁን የቁጥር መብዛትና ማነስ እንደሁ እንጂ ተከታይ ሰው ግን አያጣም።
"…የፖለቲካ ፓርቲም እንደዚሁ ነው። የሆነ ሰውዬ የሆነ ቦታ፣ የሆነ ቀን ተኝቶ በልቡ ያሰበውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት ያስባል። ያን ያሰበውን ጉዳይ ደግሞ የእኔ ለሚላቸው ሰዎች ጥቅሙን ዘርዝሮ በማስረዳት የፖለቲካ ፓርቲ አብረውት እንዲመሠርቱ ይወሰውሳቸዋል። ነገርየውን የሰሙ ወዲያው እሺ ብለው የሚስማሙ የኖራሉ፣ ቆይ ነገርየውን ልመርምር ብለው የደመራውን አወዳደቅ የሚጠብቁ ይኖራሉ። የታቀደው ነገር ከተሳካ እምቢ በማለታቸው የሚቆጩ፣ ካልተሳካ ደግሞ እግዚአብሔር ነው ያወጣኝ ብለው ስለት የሚያስገቡም ይኖራሉ። እናም የሆነ ሰው ሓሳብ የሆነ ሰው ያመነጫል። ከዚያ 6 ትግሬ አንድ ጎንደሬ ዐማራ ሆነህ ደደቢት በረሀ ወርደህ ህወሓትን ትመሠርታለህ። ከዚያ 17 ዓመት በረሃ ቆይተህ፣ ሚልዮኖች ገድለህ፣ ሚልዮኖች ተገድለውብህ አንተ 6 ሚልዮን ሆነህ ትወጣለህ፣ ከዚያ 27 ዓመት ሙሉ ሀገር ትገዛለህ፣ ትበዘብዛለህ። ከዚያ ሲበቃህ ተዋርደህ ትባረራለህ። ሰማኸኝ አይደል? ሁሉ ነገር የሚጀመረው በሆነ ሰው ሓሳብ አመንጪነት ነው።
"…ጭካኔው የሚወደድለት፣ በጭካኔው የሚፈቀር ሰው አለ። ጀግንነት የሚል ቅጽል ስም ይሰጠውና ወዳጅ፣ ተከታይ በጭካኔው የሚያፈራም ሰው አለ። እንደ አቢይ አሕመድ ሚልዮን ትግሬ አርዶ በልቶ በሚልዮን ትግሬ የሚፈቀር፣ የሚወደድ፣ የሚከበርም ሰው አለ። ቦዘኔ ዱርዬን ውድድ፣ ፍቅር የሚያደርጉ ፀባየ ሸጋ፣ የተከበሩ ቤተሰቦች ፍሬ፣ መልከ መልካም ቆንጆ ሴቶች አጋጥመውኛል። ይሄ ነፃ ፈቃድ ነው። ቦዘኔው፣ ወያላው፣ ደሀው፣ ዱርዬው አስደግሞባት ነው፣ መተት ውሎባት ነው የሚሉ የምቀኛ ሰፈር መልከጥፉ ፉንጋ ሴቶች እና ወንዶች ቢኖሩም ነገርየው ግን ሰዎች በነፃ ፈቃዳቸው ተጠቅመው የሚተገብሩት ነገር ነው። ዱርዬ፣ ተደባዳቢ፣ ሰካራም፣ አጫሽ ቃሚ የሚያፈቅሩ፣ አፍቅረውም ብቻ አይቀሩም ሀገር ጉድ እያላቸው አግበተዋቸው ልጅ ወልደው አብረው የሚኖሩ አሉ። ዘወትር በባሏ በቦክስ እየተጠለዘች፣ አይኗ እየበለዘ፣ ገላጋይ ሽማግሌ ሲመጣ ምን አገባችሁ በባሌና በእኔ መካከል ብለው ኩም የሚያደርጓችሁ ነፍ ናቸው። የትየለሌ። ወዳጄ አንተ ነህ በጤናማ አእምሮ እያሰብክ ይህ እንዴት ይሄ ይሆናል? እያልክ በቅናት፣ በምቀኝነት፣ በየዋህነትም ስትብሰለሰል የምትኖረው እንጂ ነገርየው የነፃ ፈቃድና የምርጫም ጉዳይ ነው።
"…ጥሬ ሥጋ በዳጣ በላተኞች፣ የጠጪዎች ማኅበርም እንዳለ አውቃለሁ። የቃሚ በደቦ ሺሻ የሚያጨሱ ማኅበራትም እንዳሉ ሰምቻለሁ። የትኛውም ነገር በአንድ ሰው ተጠንስሶ በጥቂት በትንሽ ሰው ይጀመርና ቀበሌ ሙሉ ሊዳርስ፣ ሀገር ሙሉ ሊያካልልም ይችላል። የሰው ልጅ ሞራል ካልከለከለው በቀር ምንም ነገር ለማድረግ ነፃ ፈቃድ አለው የምንለው ለዚህ ነው። አዚህ አውሮጳ ውስጥ አለ ተብሎ የሰማሁት ደግሞ በግሩፕ በማኅበር ተሰባስበው ልቅ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት የሚፈጽሙ እንዳሉ ነው። አሁን ይሄን ጽሑፍ የሚያነብቡ አስቀዳሽ፣ ጿሚ ጸሎተኛ ምእመናን አስር ጊዜ አማትበው ሊሆን ይችላል። በማማተብ እውነታውን ግን አይቀይሩትም። ጥቂቶች የጀመሩት ቀስ በቀስ ሚልዮኖች የተቀላቀሉት ብዙ ድርጅቶችን ማንሳት ይቻላል። እርስዎ አንድ ሰው ጀምሮት አሁን ብዙ የሆናችሁበትን የሚያስታውሱት ማኅበር ወይ የሆነ ነገር እስቲ ይንገሩን። ጀማሪው ይሄኔ ሞቶ ሁላ ሊሆን ይችላል።
"…እህተ ማርያም ስንዱ የደብረ ዘይት እለት በእኩለ ጾም ፋሲካ ነው ብላ ሰንጋ አርዳ የምታባላው እኮ የሰዎችን ስብስብ ነው። እንቁጣጣሽ የሰኔ ሚካኤል ቀን ነው። መስቀል ህዳር ጽዮን ላይ ነው የሚከበረው ብላ ተነሣች ይኸው ከመቶ በላይ ሰው አምኖ ይከተላታል። ባለሀብቶችም፣ የእንግሊዝ የስለላ ድርጅትም ፈንድ ይሰጣታል አሉ። ደመቀ መኮንን ወልቃይት ላይ አስሯት እንድትፈታ ያደረጋት ብልፅግና ከእንግሊዝ በደረሰበት ጫና ነው ሲባል ሰምቻለሁ። ኦሮሚያ ውስጥ እኔ ማርያም ነኝ ብላ የተነሣች ሴት በፖሊስ ፕሮግራም ላይ ቀርባ ተከታዮቿ በመያዟ ሲያለቅሱም አይቻለሁ። ጎንደር ውስጥ እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ 12 ሐዋርያት ሁሉ መርጦ፣ በመጨረሻ ንጉሡ ሰምተው… 👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
• ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሐሙስ
"…ይህ ዕለት ለምስጋና አራተኛ ለፍጥረት አምስተኛ ቀን ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናውን ጀምሯል፡፡ ከወትሮ ይልቅም ነቢያትንና ሐዋርያትን አስከትላ መጥታለች፡፡
"…ነደ እሳት ሰፍሮባት፣ በነደ እሳት ተከባ፣ ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ ድንግል ማርያምን ትመስላለች። “ዘጸ 3፥ 1-3” አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኹኗልና፤ ባሕርየ (እሳተ) መለኮቱም አልለወጣትምና (አላቃጠላትምና) ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡
"…ዳግመኛም እርሱን ከወለደችው በኋላ ማኀተመ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ እርሱም ምንም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ፍጹም ሰው ቢኾንም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና እሳቱን ይመስላል፡፡ ሰውም ቢኾን ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሰው ኾኖ ያዳነን የባሕርይ አምላክ ነው።
"…ሰው ኾኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋዉን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …አቅም የላቸውም። እንዲያውም ሰሞኑን ምን እንደገመገሙ የሰማሁትን እንደወረደ ልንገርህ።
"…የእስክንድር ነጋ የውጭ ሀገር ወኪሎች ማለትም ዶፍቶር አምሳሉ፥ የዲሲ ግበረ ኃይሎቹ አቶ ሙሉጌታ፣ አቶ ኤርሚያስ እና ወሮ ሕይወት፤ ለእነ ሀብታሙ አያሌው የሳተላይት እና የወር ደሞዝ ክፍያ ውጭ ስለበዛባቸው በእስክንድር ነጋ ትእዛዝ ሌላ አዲስ ሚዲያ ለመክፈት እንቅስቃሴ ላይ ናቸው። ኡጋንዳ ላይ መሆኑ ነው። እስክንድር አሜሪካን ሀገር በባልደራስ ስም የሰበሰበው ወደ አራት መቶ ሺ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ስላለ ይህንን ገንዘብ ተጠቅመው ነው ሚዲያ ለመክፈት እንቅስቃሴ የጀመሩት። ለ360 ዎች በወር 50 ሺ ዶላር በላይ ስለሚያወጡ ይህንን ወጭ በቀጣይነት ለመሸፈንም ስላልተቻለ ሌላ ሚዲያ በቶሎ እንዲከፈት ከእስክንድር ነጋ ትእዛዝ ተቀብለው እየሠሩ ነው። በተለይ እነ ሀበታሙ አያሌው ከዳያስጶራው በኢሳት መንገድ ዶላር ለመስብሰብ ያደረጉት ጥረት በዘመድኩን ገጀራነት ምክንያት ባለመሳካቱ ወጭው ቀነስ ያለና በመለስተኛ ወጭ ሌላ ሚዲያ መክፈቱ በእነ አስክንድር በኩል አማራጭ ተደርጎ ተወስዷል። በእዚህ ውሳኔ እነ ሀብታሙ አያሌው ከእስክንድር ነጋ ድርጅት ጋር ሊኖራቸው የሚችለውንም ግኑኝነት ገምግመዋል። በግምገማቸውም መሰረት እነ ሀበታሙ አያሌው ከሌላው የፋኖ አደረጃጀት ጋር የመገናኘት እና አብሮ የመሥራት ዕድል እንደሌላቸውና የቀረችዋ ገንዘብ እስክታልቅ የእስክንድር ነጋን ኃይል ከመደገፍ ውጭ ምንም ምርጫ ስለሌላቸው የትም አይሄዱም የሚል ግምገማ ላይ ስለደረሱ እነ ሀብታሙ አያሌው ከመገረድ ውጪ ሌላ አማራጭ የላቸውም ተብሏል። እስክንድር ነጋ በ360 ላይ ሁሌ ወጥቶ መናገር ስለማይችል አጠገቡ ባለው በጋዜጠኛ ጌጥዬ በኩል መዘብዘቡም ይቀጥላል ተብሏል። እስክንድር ጌጥዬን ፎቶውን ለጥፈው እንደ ፍሮፌሰር ዶክተር ሲተነትን እነ ኢየሩስና ብሩክ ሻይ ጠጥተው መመለሳቸውንም አልወደደውም ተብሏል። ጌጥዬ ተናግሮ እስኪጨርስ እየሩስም ሆነ ሀብታሙ ከስቱዲዮ እንዳይወጡም መመሪያ መሰጡቱ ነው የተሰማው። የሚያሳዝነው አበበ በለው እበላ ብሎ መበላቱ ነውም ተብሎ መገምገሙ ተሰምቷል።
"…በመጨረሻም የምለው የድሮው ዐማራ አሁን የለም። ነገ የሚመጣው ዐማራ ደግሞ ከዛሬውም የባሰ ቆቅ፣ ንቁ፣ ጀግና፣ አሸናፊ፣ አጀንዳ ፈብራኪ እንደሚሆን አምናለሁ። አሁን ያልነቃው የተኛው፣ ዳተኛው ዐማራም የነቃ ጊዜ፣ የተነሣ ወቅት ሁሉ ነገር አሸወይና ይሆናል።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው፣ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ድሮ ቢሆን ድሮ ከዘመነ ፋኖ በፊት ዐማራ ሆዬ ይሄን ጊዜ በማያገባው ገብቶ በኃይለኛው የተወረወረለትን አጀንዳ ያቦካ፣ ያማስል ሁላ ነበር። ማኅበራዊ ሚዲያውን በንትርክ፣ በውዝግብም ያጫጭሰው ነበር። ዐማራው ጠላት በቀደደለት ቦይም ፍስስ ብሎ እስከ አፍንጫው ድረስ በመዘፈቅ 24/7 ይምቦራጨቅም ነበር። ድሮ ቢሆን ስል ድሮ ድሮ ማለቴ አይደለም የዐማራው ድሮ አሁን ቅርብ ከዓመት በፊት ማለቴ ነው። ከዘመነ ፋኖ ትግል በፊት ማለቴ ነው።
"…ድሮ ቢሆን ይሄኔ ዐማራው በፓሪስ ኦሎምፒክ እገሌ ወርቅ አላመጣም፣ እገሌ ተበደለ፣ እገሌ ሆቴል፣ ካምፕ አላስገባ አሉት ብሎ ነጠላ ዘቅዝቆ፣ ምንጣፍ አንጥፎ፣ ድንኳን ተክሎ፣ ንፍሮ ቀቅሎ እየዬውን ያስነካው ነበረ። ዘንድሮ ግን ወፍ የለም። የዐማራ ልጆች ሌላ ኦሎምፒክ ላይ ናቸው። ሌላ ውድድር ላይ። የነፃነት ውድድር ላይ ናቸው። እና ከፓሪስ ኦሎምፒካ ጋር ተጣብቆ እኚኝ ሲል ያየሁት አንድም ዐማራ የለም። ዐማራ ስል ነፍስ ያለው ዐማራ ማለቴ ነው። አእምሮ ያለው፣ ስኳድ ያልሆነ፣ እንደ ሰው የሚያስብ፣ ሰው የሆነውን ዐማራ ማለቴ ነው። ስለ ሆዳም ዐማራው መቼም ጊዜ አናጠፋም ብዬ ነው።
"…ድሮ ድሮ ከዓመት በፊት ቢሆን ትናንት በቤተ መንግሥት በተደረገው የአትሌቶች አቀባበል ላይ አንዱ ባለ ጊዜ ሁለት ሚልዮን ብር ሽልማት ተቀበል ማለት ለእኔ እንደ ስድብ ነው የምቆጥረውና አልቀበልም ብሎ ፕሬዘደንቷ ፊት ወርውሮ ሲሄድ ከሁሉ ቀድሞ እሪሪ ብሎ የሚጮኸው፣ ከኦሮሞም ከትግሬም ወንድሞቹ ጋር የሚቃቃረው ዐማራው ነበር። ዘንድሮ ግን ዐማራው ሌላ የራሱ የግል ሥራ ላይ ስለሆ፣ ሌላ ዓለምም ላይ ስላለ አጀንዳውን አባከና ሲለው አላየሁም። ዐማራው ዓይኑም፣ ጆሮውም 70 ሚልዮን ዐማሮችን ነፃ ለማውጣት በዱር በሸንተረሩ እየተዋደቁ ባሉት ልጆቹ ላይ ስለሆነ የሁለት ሚልዮን ብር አልቀበልም አጀንዳ ጉዳዩ አልነበረም። አንድ ንፁህ ዜጋ አፍኖ 10 ሚልየን ብር በባንክ መቀበል በተለመደበት ሀገር ሁለት ሚልዮን ብር በሽልማት መልክ አልቀበልም ቢልስ ሶዬው እንዴት ይፈረድበታል? ወጣ ብሎ አንዱን ማፈን እኮ በቂው ነው። ደግሞስ በሁሉ እንደሚታውቀው አሁን ላይ ለባለ ጊዜ ኦሮሞ 2 ሚሊዮን ብር ማለት ምን ማለት ነው። ለአንድ አዳር ለሸርሙጣ ሴት በጨረታ ለሚከፈሉት ባለጊዜዎች ኦሎምፒክ ደርሶ ለመጣ ሶዬ 2 ሚልዮን ብር እንካ ማለት መጣም፣ መጣም ስድብ ነው። ደግሞ ፕሬዘዳንቷ ዐማራ መሆኗ አይረሳ እንጂ። ደደፎ አቢይ ወይ ሽመልስ ፊት እንዲህ ደፍሮ ይናገር ነበረ? እእ አይመስለኝ። ለማንኛውም አጀንዳው ፉርሽ ሆኗል። ዐማራው ሥራ ላይ ነው።
"…ድሮ ድሮ ዐማራው ድስት ጥዳ ሩዝ እያማሰለች በቲክቶክ የምታወራን ሴት ወሬዋን ከቁምነገር ቆጥሮ ሲነታረክ ይውል ነበር። ሩዝ ቀቃይዋን፣ ቡና አፍዪዋን፣ ድራፍት እየጨለጠ፣ በጋንጃ ጡዞ የሚዘባርቀውን ገተት ጎረምሳ፣ ምድረ ቲክቶከራሙን ሁሉ ሰምቶ ሀገር ይያዝልኝ ይልም ነበር። በፌስቡክ ላይ አንድ ገጠሬ ተመርጦ አጀንዳም ሰጥቶት ሰላማዊ ሰልፍ ሁላ ለመውጣት ይዳዳው ነበር። አሁን ግን ዐማራው ባንኗል። አጀንዳ ከመቀበል ወደ አጀንዳ መስጠት ተሸጋግሯል። አይደለም ሩዝ ቀቃይ፣ ውታፍ ነቃይ፣ አይደለም ባለ ጋንጃ፣ አንጃ ግራንጃ፣ አይደለም ባለድራፍት አምቡሊያም ይቅርና የተደራጀ ሚዲያ አያታልለውም። የዘንድሮው ዐማራ ከጋዜጠኛ ሀብታሙ አያሌውን፣ ከአርቲስት ታማኝ በየነን፣ ከእስክስታ አበበ በለውን፣ እንቅልፎ ጄሪን፣ ልጋጎ ኤርሚን አልሰማ ብሎ ባዶአቸውን አስቀርቷቸዋል። ግዙፉን 360 ሚዲያ በቂጡ ዘጭ ያደረገ ነው የዘንድሮ ዐማራ። አንድሺ ሰብስክራይበርም፣ አንድ ዶላርም የከለከለ፣ የነፈገ ነው የዘንድሮ ዐማራ። መቼም የዘንድሮው ዐማራ ልዩ ነው።
"…ድሮ ድሮ የጎንደር እስኳድ አጀንዳ ቀርጾ፣ አጀንዳ በትኖ ዐማራው በእሱ ይራኮት ነበር። ምስጋናው አንዷለም፣ አያሌው መንበር፣ የአብን የጎንደር ስኳዶች አንዲት ነገር ተነፈሱ ማለት ዐማራው በአጀንዳ ይጦዝ ነበር። ሥራ ፈትቶ፣ ማዶና ማዶ ሆኖ ይጣለዝ፣ ይሻኮት፣ ይራኮት ነበር። ዘንድሮ ግን ወፍ የለም። የስኳድም ዘመን አብቅቷል። እንኳን አጀንዳ ሊሆኑ መደበቂያ ጉድጓድ አጥተው ተቅበዝባዥ ሆነዋል። እንኳን ጎጃምና ጎንደርን፣ ወሎና ሸዋን እንደ ሕዝብ ሊያጣሉ ይቅርና ራሳቸውም መስማማት አቅቷቸው አንዱ ኡጋንዳ፣ አንዱ ኤርትራ መደበቂያ ፍለጋ መርመጥመጥም መራወጥም ይዘዋል። ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ወጥቶ ከተማ መታየት ያቃተው፣ የፈራ፣ የተንቦቀቦቀ ስኳድ በግቢው ውስጥ ኮንቴነር ውስጥ ሽሮ እየበላ ሕይወቱን እንደሚገፋም ሰምቻለሁ።
"…ድሮ ድሮ የዐማራ ባንዳዎች በዐማራ ተላላቅ ከተሞች እየተዘዋወሩ ነበር መርዛቸውን የሚተፉት። ማን ይነካናል? ማን ይደርስብናል? ዐማራ ፈሪ ነው፣ ዐማራ ሽንታም ነው፣ ዐማራ ቦቅቧቃ ነው ብለው በግልጽም ይፎክሩ ነበር። በእርግጥም እነዚህ ገተቶች ደጋፊም፣ አቃፊም ነበራቸው ድሮ። ከዐማራው ትእግስት የተነሣ የሚሉትም ለእውነት የቀረበ ይመስልም ነበር። ለዚህ ነው እነ ቶማስ ጃጀው፣ እነ ጌትነት አልማው ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ ወልድያ፣ ደብረታቦር ሄደው በሸነና ብለው ይመለሱ የነበሩት። ዘንድሮስ? ዘንድሮማ ወፍ የለም። ቶማስ ጃጀውን ከፌስቡክ ላይ በቀር እዚህ ቦታ አየሁት የሚል ሰው የለም። ጌትነት አልማው ባህርዳር እንደናፈቀችው፣ ደብረ ማርቆስ አይኑ ላይ እንደዞረች ይኸው እንዳለ አለ። የዐማራ ምድር አይደለም ለአክቲቪስቱ ለብአዴን ራሱ ስጋት ሆኖበት መሄጃ ያጣው በመከላከያ ተጠብቆ፣ መሄጃ ያገኘ ደግሞ ወደ አዲስ አበባና ወደ ኡጋንዳ ፈርጥጦ ነው ያለው። ያ ሽንታም የተባለ ዐማራ እኮ ነው ዘንድሮ ሽንት በሽንት አድርጎ አዳሜና ሄዋኔን ወደ አዲስ አበባ እንዲሰደዱ ያደረገው።
"…ድሮ ድሮ ስኳድን መቃወም ያስወግዝ ነበር። መደበቂያ፣ መሸሸጊያ እስኪታጣ ዋይ ዋይ ባዩን ያበዛ ነበር። ስኳድን መንካት ጎንደርን እንደመንካት ተቆጥሮ ያስወግዝ ነበር። ጩኸቱን የሚፈሩ፣ የሚሰጉም ጣልቃ ገብተው ይሄ ነገር ይቅር ይሉ ነበር። ሕዝብ ከሕዝብ እንዳይጣላ፣ እንዳይለያይ ብለው የሚንጰረጰሩ፣ ጉዳዩ እንዳይነሣ የሚሉ ሁላ ነበሩ። ዛንድሮስ? ዘንድሮማ ዘመነ መሪዬ ነው የሚል ጎንደሬ ታያለህ። ባዬ መሪዬ ነው የሚል ጎጃሜ ታያለህ፣ አሰግድ መሪዬ ነው፣ ደሳለኝ መሪዬ ነው የሚል ወሎዬ ታያለህ። ምሬ ወዳጆ መሪዬ ነው የሚል ሸዋዬ ታያለህ። ለይቶ ወንጀለኛውን ብቻ የሚመታ ሌላ ግሩም ዐማራዊ ስኳድ ነው የተፈጠረው። ይሄንን ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ እኔ ላይ የሚጽፉ ሰሊጣም የጎንደር ስኳዶች ኮመንት መስጫ ሳጥን ስር ገብታችሁ አስተያየቶቹን አንብቡ። ወንጀላቸውን በጎንደር ሕዝብ ስም በመደበቅ እንደ ድሮው ማምለጥ አይቻልም።
"…የዘንድሮው ዐማራ በመቀሌ እየተካሄደ ስላለው የህወሓት ክፍፍል በቀልድም መልክ፣ የምርም አድርጎ አጀንዳ አድርጎ ሲያወራበት አላየሁም። ከነመፈጠሩም በመቀሌ ስላለው ሁከት እየሰማም፣ እያየም ያለ አይመስልም። ድሮ ቢሆንስ? ዐማራው ነበር ሲቀደድ የሚውለው። ዐማራው ነበር ሲያራግብ የሚውለው። ዐማራው ነበር ደብረ ጽዮን እንዲህ ሆኖ፣ ጌታቾ ረፋ በዚያ ወጥቶ፣ ሞንጀሪኖ በዚህ ገብታ ብሎ አሽኮለሌ ሲል የሚውለው። የራሱን ስንት አጀንዳ ትቶ የሰው ቤት ሲያማስል የሚውለው። ዘንድሮስ? የዘንድሮው ዐማራ እቴ ሌላ ሥራ ላይ ነው። የጎጃም ፋኖን ድል፣ የጎንደርን ተጋድሎ፣ የወሎን፣ የሸዋን ፍልሚያ ነው የሚዘግበው። ደንበጫ የገባ የጠላት ጦር ተደመሰሰ፣ በበለሳ በኩል…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
• ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ረቡዕ።
"…የማኅፀንሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለበት በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል ነው፡፡ ለሰው ከማያዝን ከማይራራ፤ አንድም ለእርሱ ከሥላሴ ዘንድ ምሕረት ከሌለው፤ አንድም ኃጢአቱን ሸሽጎ ከማይሠራ ከዲያብሎስ እጅ ያዳነን ጌታችንን የወለድሽው ሆይ! በደንግሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት ነሽ፡፡ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ ኢሳ 1፥9 በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለድሽ የምታሰጭ ነሽ፡፡
"…ጌትነቱ እንደ ነገሥታት በጉልበት፣ እንደ ካህናት በሀብት፣ እንደ ጣዖታትም በሐሰት ባይደለ በክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና በዚህ ዓለም ከሚኖሩ ሰዎች ኹሉ ይልቅ ክብር ላንቺ ይገባል፡፡ አካላዊ ቃል መጥቶ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ ሰው ሰውኛውንም ኖረ፡፡ መሐሪ፣ ይቅር ባይ፣ ሰው የሚወደው ሰው ወዳጅ ነውና በልዩ አመጣጡ መጥቶ አዳነን፡፡ “አኮ በተንባል ወአኮ በመልአክ አላ ለሊሁ እግዚእ መጻእ ወያድኅነነ - በአማላጅ አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፡፡ እርሱ ራሱ፣ በራሱ ደም፣ በራሱ ሊቀ ካህንነት መጥቶ ያድናቸዋል እንጂ ”/ኢሳ 63፥9 እንዲል እንደ ቀደመው በረድኤት ሳይኾን በኩነት (ሰው ኹኖ) መጥቶ አዳነን፡፡ አንድም አምስት ሺሕ ካምሰት መቶ ዘመን ሲፈጸም አንድ ሰዓት ስንኳ ሳያሳልፍ በጽኑ ቀጠሮው መጥቶ አዳነን፡፡ በጽኑ ቀጠሮ መጥቶ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…እኔ ለዐማራው ፋኖ የዳዊት ጠጠር ነኝ። ጎልያድ የሆነን የዐማራ ፈተናውን ገንድሼ የማጋድምለት የዳዊት ጠጠር ነኝ። አሁን ያቺን የድምጽ ቅጂ ባላወጣ ኖሮ ዛሬ እነ ሀብታሙ አያሌው፣ እነ እስክንድር፣ እነ ዶር ምስጋናው አንዷለም እንዴት አድርገው በፏለሉ ነበር። ከእኔ ጋር ያለው የሰማይ አምላክ ብቻ ነው። ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ የምላት የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማረረያም ናት። በገዳማውያን አባቶች፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቁንም በዐማራ እናቶችና አባቶች ጸሎት ነው ያለሁት። እኔ ዐማራ አምስት ሳንቲም አይከፍለኝም። መረጃ ቲቪ በነፃ ነው የማገለግለው። እኔ ጎፈንድሚ አልጠየቅኩም። እኔ ዐማራው የመከራው ቀንበር ሲወድቅለት እና ሥልጣን በእጁ አስገብቶ ከመሞት፣ ከመሰደድ፣ ከመፈናቀል፣ ከመታረድ፣ ከመዋረድ ሲድን፣ ከተቻለው ሀገሬ እንድገባ ያደርገኛል ብዬ ተስፋ ከማድረግ፣ ሀገሬ ባልገባም ባለሁበት ሆኜ የዐማራን ሰቆቃ ከመስማት አርፌ እስክሞት በሰላም እኖራለሁ ከማለት በቀር ትርፍ ነገር የለኝም። ዐማራ መርገምቱ ወድቆለት ብሞትም አይቆጨኝ። እኔ ከዐማራው ሥልጣን፣ ገንዘብ፣ ክብርም አልፈልግም። ዐማራው ያሸነፈ ቀን እኔ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኔ እመለሳለሁ። በዚያ የአባቶቼን ሰፊ ቀዳዳ ለመሸፈን፣ ዐማራም ድል ያደርጋል።
"…ይልቅ መንገድ ዝጋ፣ ከጎጃም ፋኖ እኩል ተናበህ እንደ ሕዝብ፣ እንደ ጎጃም ሕዝብ ይሄን ሥርዓት መክተው፣ አንክተው። ዳር ቆመህ አትመልከት። ሰኔ 15 ላይ ተቸንክረህ አትቁም። ቆሞቀርም አትሁን። ዛሬ አዲስ ቀን ነው። አዲስ አስተሳሰብ ነው። አንድ ዘመነ ካሤን በመጥላት ብቻ የዐማራን መከራ አታራዝመው። ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋ ወሎ አንድ ላይ ተነሥ። ተነሥ ጠላትህን ደምስስ። ስለ ህወሓት ጉባኤ ማድረግ አለማድረግ አንተን ምን አገባህ? እሱን ለገሰ ቱሉና ደብረ ጽዮን ይፈሳፈስ። ስለ ኦሎምፒክ ሜዳልያ አይመለከትህም። አያገባህም። ስለ ችግኝ፣ ስለ ኪሪደር ልማት ምን አገባህ? ነገርኩህ እንደ ጎጃም እንደ ሕዝብ ተነሥ። ሸዋ ልብ ግዛ። ነግሬሃለሁ ልብ ግዛ። ስኳድ እጅህን ከጎንደር ዐማራም ከዐማራ ፋኖም ላይ በቶሎ አንሣ። አከተመ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …እስክንድር ለእነ ሀብታሙ አያሌው ሲከፍት ዋነኛው ሰው ዶር አምሳሉ ነበር። የዶር አምሳሉ ወንድም የደቡብ ጎንደር የብልፅግና ሓላፊና አስተዳዳሪም ጭምር ነው። የእስክንድርም የዶክተር አምሳሉም ሚስቶች ትግሬዎች ናቸው። እስክንድር በአባቱ በኩል ጎጃሜነቱን ተጠቅሞ ጎጃም ገብቶ ሊበጠብጥ ቢሞክርም ጎጃሜዎቹ ነቅተው ሂድ ከዚህ ጥፋ ብለው አብርረው ወደ ሸዋ ሸሽቷል። ሸዋ ሆኖ ነው በስኳድ እየተደገፈ ሸዋን እግሩን በሰንሰለት ተብትቦ የያዘው። እነ ምስጋናው አንዷለም እስክንድር የአዲሱ ድርጅት መሪ ሆኗል ብለው አዋራ ያጨሱት እስክንድር በጎንደሬነት ቦታ ይዞልናል በሚል እሳቤ ነው። የእናት ፓርቲ መስራቹ ፕሮፌሰር ጌታ አስራደን በፋፍዴንነት ደቡብ ጎንደር አምጥተው እስክንድርን አልቀበልም፣ በሻለቃ ዳዊት፣ በሀብታሙ አያሌውም አልመራም ሲል ሽማግሌው ጋሽ መሳፍንት ውባንተን ረግመው፣ እነ ሀብቴን አዝዘው፣ በውባንተ ላይ የሞት ዐውጀው፣ የሞት ዐዋጁንም ኡጋንዳ ባለው በወንድማችን በሙላት አድኖ በኩል በ251 ሚዲያ ላይ መግለጫው እንዲነበብ አድርገው፣ በመረጃ ቴሌቭዥንም ላይ አቅርበው፣ መግለጫውን ማንበብ ብቻ ሳይሆን መግለጫውን በመተንተን ጭምር ውባንተ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በሃላል ዐውጀው፣ ጦርነት ካለቀ በኋላ በሰላም በቆሙበት ውባንተ ለብቻው በስናይፐር ተነጥሎ እንዲሞት የተደረገ ገና መመርመር አለበት። ይሄ ሁሉ ይሄ ስግብግቡ፣ ሴረኛው የጎንደር እስኳድ የሚሠራው ክፉ ሴራ ነው።
"…ዛሬስ ዛሬም እነዚያ የተለያዩ ይመስሉ የነበሩት የእነ ጋሽ መሳፍንት እና የእነ ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ ቡድኖች አስጠግቷቸው ከነበሩት ከእነ አርበኛ ባዬ ቡድን ወጥተው ሄሮድስና ጲላጦስ ሆነው በክርስቶስ ሞት ተስማምተው ዛሬ እስክንድር መሪያችን ነው ብለው ጓ ብለው በሃላል እየተንበጫበጩ ነው። ከውባንተ ቀጥሎ አሰግድን ነበር መብላት የፈለጉት አሰግድ አልታኮስም፣ ከልጆቼ ጋር አልገዳደልም ብሎ ተላልፎ ራሱን ሰጠ። ለዚህ ነው እነ ሀብታሙ ለምን ራሱን በሽጉጥ አያጠፋም ነበር ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ የነበሩት። ይሄ በጎንደር ስም ሥልጣን ያናወዘው ስኳድ የተባለ ልቡሰ ሥጋ ሰይጣን ቡድን በቀጥታ ጎጃም በመግባት ነበር ጎጃምን አበጣብጦ ዘመነ ካሤን በማስገደል ጎጃምን ለእስክንድር ነጋ ለማስገበር ተፍተፍ ብሎ የከረመው። ኮሎኔል ጌታሁንን አባብለው፣ ደልለው፣ አታለው ካስካዱት በኋላ ኮሎኔሉ ከጎጃም ወንድሞቹ እንዳይነጋገር እንዲጠፋ አድርገው፣ በመጨረሻም ጌታሁን ጎንደር ተሻግሮ ፋኖ አርበኛ ደረጄ በላይ ጋር መግባቱ በይፋ ከተነገረ በኋላ በስንተኛው ቀን ከደረጀ እጅ ወጥቶ ለመከላከያ እጁን እንዴት እንደሰጠ ሳይታወቅ ኮረኔሉ በተዋረደ መልኩ ፀጉሩንና ፂሙን ብቻ ሳይሆን ቅንድቡን ጭምር ላጭተው በኦሮሞና በትግሬ ሚዲያዎች ቀድመው በትነው መሳቂያ መሳለቂያ አደረጉት። ስኳዶቹ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት ነበር በዚያውም አርበኛ ሳሚ ትግሬ ነው። ክፍለ ጦሩን ዓድዋ ክፍለ ጦር ያለው ትግሬ ቢሆን ነው በማለት ወዲያውም "ኮኮኔሉን ወደ ጎንደር አላሳልፍ አለ" በማለት ዘመቻ ከፍተውበት ሳሚም ለኮረኔሉ ደውሎ እኔ መቼ ነው አላሳልፍ ያልኩህ ብሎ ጠይቆ፣ ኮሎኔሉም "ሳሚዬ ዝም በል አትስማቸው፣ ወሬ ነው የሚያወሩት፣ እኔ ምንም አላልኩም በማለት አከሸባቸው። እስኳድ አደገኛ ነው ስል በምክንያት ነው።
"…ጎጃም መለኛው የስኳድ አካሄድ ስለገባው፣ ስለደረሰበትም አርበኛ ዘመነ ካሤን እቅፍ፣ ድግፍ አድርጎ ደበቀው፣ በዘመነ ካሤ ላይ ቅሬታ የነበራቸው የጎጃም ልጆች ጭምር ናቸው የባነኑት። ጎጃም እንደ ሕዝብ ዘመነን ሸሸገው፣ እንደ ውባንተ እንዳይገደል፣ እንደ ጋሽ አሰግድ ተላልፎ እንዳይሰጥ እንደ ንብ ከበበው። ጎጃም ዘመነን መክበብ፣ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን በጎጃም ውስጥ የእስክንድር ነጋን ኤጀንቶች በሙሉ ለቃቅሞ ምክር ሰጥቶ አጠፋ። በሙሉ መክሮ አንድ ሆነ። የጎጃም ፋኖ ወጥ ፋኖ ሆነ። አሁን የቀረው ጥቂት ሚሊሻ የያዘ እና በማስረሻ ሰጤ የሚመራ በረሃ ያለ የእስክንድር ወኪል የጎጃም ጦር ብቻ ነው። እነሱ እኔንም አነጋግረውኛል። ከእስክንድር እና ከዘመነ ካሤ የሚበጃችሁን የምታውቁት እናንተው ናችሁ። እናንተ ትላልቅ ሰዎች ናችሁ ወስኑ ብያቸዋለሁ። እነሱ ወደ ወንድሞቻቸው ከገቡ ስኳድም፣ እስክንድርም በጎጃም ውስጥ ማዳበሪያ የሆነ የመራቢያ መሬትም አፈርም አያገኝም ማለት ነው።
"…ስኳድና እስክንድር የጎጃሙ ነገር የማይሆን መሆኑን ሲያዩ ፊታቸውን ወደ ወሎ ነው ያዞሩት። የዋርካው ምሬ ወዳጆን ነው አሁን እያጣጣሉ የግደለው፣ ውቀጠው ዘመቻ የከፈቱበት። ነገር ግን የሚሰማው አጥቶ ተንገብግቦ እንደገደሉት እንደ ጎንደሬው ጀግና እንደ ውባንተ ቀላል አልሆነላቸውም የወሎው ምሬ። ረዳት አጥቶ እንደ ተንከራተተ እንደ ተያዘው እንደ ጋሽ አሰግድም አልተቀመሰላቸውም ምሬ ወዳጆ። ይልቅ ጎጃም እንደ ሕዝብ ከዘመነ ካሴ ጎን እንደቆመው ወሎም ከምሬ ወዳጆ ጎን ነው የቆመው። እስክንድር በገንዘቡ የገዛው ኮሎኔል ፈንታሁንንም የምሬ ጦር ከድርጅቱ በይፋ ነው ያባረረው። በኮረኔሉ መባረር ኮረኔሉ ሳይሆን የተበሳጨው የጎንደሩ እስኳድ መሆኑ ሲታይ ያስቃል። የሸዋው ጉዳይ የማይሆን ከሆነ፣ ኮረኔሉ ስር ያሉት ወደ እነ ምሬ የሚሄዱ ከሆነ በማለት እስክንድር ነጋና ኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባው ወደ ደቡብ ጎንደር በመሄድ ውባንተ በተገደለበት መሬት ላይ ቤዝ ለመፍጠር እየመከሩ እንደሆነም ተሰምቷል። ኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባን የጎንደሩ ስኳድ ያቀፈበት ዋናው ምክንያት ኮረኔሉ በወቅቱ በአሳምነው ሞት ጊዜ በነበረው ወታደርን የማዘዝ ሥልጣን ተጠቅሞ አሳምነው እንዳያመልጥ እና እንዳይ ሸሽ አድርጓል ብለው እንደሆነ እኔ ራሴ አያሌው መንበር ሲናገር ሰምቼዋለሁ የሚሉ አሉ። ለዚያ ነው ኮረኔሉ ላይ ሙጭጭ ያሉት።
"…ሲጠቃለል አሁን የሚታየው ነገር ለተመልካች ከባድ ይመስላል። ነገር ግን ሲበዛ እጅግ ቀላል የሆነ ነገር ነው ከፊታችን ያለው ወቅት። በሽታው ሁሉ በጊዜ ታውቋል። በሽታውን በጊዜ ያወቀ ደግሞ መድኃኒት አግኝቶ የመዳን የመፈወስ ዕድሉ አስተማማኝ ነው የሚሆነው። የዐማራ ፋኖ አገዛዙን መዋጋትና መደምሰስ እጅግ ቀላል እንደሆነ በሚገባ ዐውቆ ተረድቷል። እጅግ ከባዱ የውስጥ ጠላት፣ ተመሳስሎ የበቀለው አረም ነበር። እሱ ነበር አደገኛው ነገር። ጠላትማ ጠላት ነው አደገኛው የወዳጅ ጠላት ነው። መርዝ ላለመብላት፣ ላለመጠጣት የሚጠነቀቅ ሰው ጠላቴ ነው የሚለውን ይጠነቀቃል። ወዳጄ የሚለውን እንዴት ብሎ ይጠንቀቀው? ሶምሶን ጠላት ፍልስጤማውያን አላሸነፉትም ነበር። ሶምሶምን ፀጉርን ላጭታ፣ ኃይሉን፣ ፀጋውን ገፍፋ ከጠላት እጅ እንዲወድቅ ያደረገችው ወዳጁ፣ ምስጢረኛው ገርል ፍሬንዱ ደሊላ ነበረች። አዎ ከታወቀ ጠላት የማይታወቅ ወዳጅ ነው አጥፊህ ነው። አሁን በዐማራ ትግል ይሄ አጥፊ ቡድን ታውቋል። በጋራ ከታገልነው፣ የገንዘብ ምንጩም ከደረቀ። የዐማራ መከራው፣ የመከራውም ቀንበር በቀላሉ ይሰበራል።
"…መሰሪው የጎንደር እስኳድ ድልድይ የነበረው አበበ በለው 1ሺ ሰብስክራይበር አጥቶ ሚዲያ ላይ ወጥቶ የስኳድን ሴራ ማስታወክ፣ መለፋደዱንም አቁሟል። እነ ሀብታሙ አያሌው ካናዳ ቢሉ፣ ላስቬጋስ ነዳጅ ማቀጣጠያው ዶላር ከስሩ ስለተቆረጠ አፈር ከደቼ በልተዋል። ለእስክንድር የተዋጣው ገንዘብ አሁን እያለቀ ነው። የእስክንድር ሚስትም በፋኖ ስም የተሰበሰበው ዶላር ከዚህ በላይ ለምኒልክ ቲቪም፣ ለእስክንድርም እንዲላክ የምትፈልግ አይመስለኝም።👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም…
"…ያለፈው ሰኞ ዕለት ባወጣሁት ሳምንታዊ የቴሌግራም መርሀ ግብራችን መሠረት ከዛሬዋ ዕለተ ቅዳሚት ሰንበት፣ እሁድ እና ሰኞ ከማክሰኞ እስከ አርብ ድረስ የሚኖረን "ርዕሰ አንቀጽ" አይኖረንም ማለት ነው። ከምር እኔማ በማየው፣ በምሰማው የዐማራ ሁኔታ ከወዲሁ ኩራትም፣ እረፍትም እየተሰማኝ ነው። እንዲያውም ባይገርማችሁ ከቤተሰቦቼ ጋር ሁሉ ወጣ ብዬ ከራየን ወንዝ ማዶ በሚገኝ የጸሎት ቤት በመገኘት በስንት ዓመቴ የውዳሴ ማርያምና የቅዳሴ ማርያም ትርጉም ከካህናት አባቶቼ አንደበት ስኮመኩም አርፍጄ መምጣት ሁላ ጀምሬአለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ስለ እውነት ዛሬ እጅግ በጣም ነው ደስስ ያለኝ። በዓይነ ሕሊናዬ ሁላ በልጅነት ክብር ባገኘሁበት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም፣ ብዙ ፀጋ ባገኘሁባቸው የፍልሰታን ጾም ያሳለፍኩባቸው የአራዳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም፣ መንዝ እመጓ ኡራኤል እና እመቤታችን በዓይኔ ላይ ሲዞሩ ነው የዋሉት። ምንአልባትም ማን ያውቃል ብልፄ ወድቆ፣ ሾተላዩ ስኳድ ከዐማራ ትግል ተነቅሎ ወድቆ፣ በሚቀጥለው ዓመት…?
"…ለማንኛውም በመርሀ ግብራችን መሠረት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለጥቂት ወራት ተቋርጦ የነበረው የተቀበል የግጥም መርሀ ግብራችን በይፋ ይጀምራል። እናም እንደተለመደው እናንተም ከወዲሁ ግጥማችሁን አዘጋጁና ለባለ ማሰንቆው ለመስጠት ተዘጋጁ። ዛሬ ትንቢት፣ ትንቢት የመሰለ ግጥም ነው ከእናንተ የምጠብቀው።
"…ተዘጋጁ እሺ። ጻፉ። ሞክሩ። ግጥሙ ግሩም የሆነውን እኔ ራሴ አውጥቼ እለጥፈዋለሁ። ዘመኑን የዋጀ ቅኔያዊ ግጥም በብዛት ይጠበቃል።
• ሰምታችኋል አይደል…?
መልካም…
"…21 ሺ ሰው አንብቦት 14 ሰው 😡 ብው ብሎ መናደዱን፣ መበሳጨቱን የገለጸበት የዛሬውም ርዕሰ አንቀጻችን ይህን ይመስል ነበር። ቀጣዩ ደግሞ እኔና ብዙ የዚህ መንደር ኗሪዎች በጉጉት የምንጠብቀው የአድማጭ ተመልካቾቻችን አስደማሚ ብስል ያለ አስተያየት የሚኮመኮምበት ሰዓት ነው።
"…የሚገርመው ነገር አንድም ከመሬት የሚጣል አስተያየት የሚሰጥ ሰው የለም። ሁሉ ገራሚ ሆኗል። ከጦማሩ አስተያየቱ ይልሃል ይሄ ነው።
"…ብዙዎች እኔ ፔጅ ላይ ሲመጡ እረፍት ይሰማቸዋል። ባለጌ ስድአደግ ቦታ የለውም። አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ለቅላሚ ቦታ የለውም። አጀንዳ አስቀያሾች ቦታ የላቸውም። በጨዋ ደንብ ተቃውሞአቸውን የሚገልጹ የሚበረታቱበት ቤት ነው። እንደነ ዳንኤል ክብረት፣ ምስጋናው አንዷለም፣ አያሌው መንበር፣ ሙላት አድኖ የኮመንት መስጫ ሳጥን ተዘግቶ ራስ ብቻ ለፍልፎ ሌላው እንዳይተነፍስ አይደረግም። ሁሉም ከአጀንዳው ሳይወጣ በጨዋ ደንብ ሓሳቡን ተንፍሶ ከጨጓራ ህመም ይገላገላል። እናም ቀጥሎ ዛሬ በተጻፈው ርዕሰ አንቀጽ ላይ ያላችሁን አስተያየት በጨዋ ደንብ ግለጹ። ተንፒሱ።
• 1…2…3…ጀምሩ ✍✍✍
👆③ ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …የሰሊጥ ብር፣ በኡጋንዳው ስኳድ አማካኝነት እስክንድርን ተጠቅመው በኃይለኛው ሞከሩ አልተቻለም። ጎጄ መለኛው አስቀድሞ ስለነቃ የእስክንድር ነጋን ሴል ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ጠራርጎ ነው ሰብስቦ የመከረው። ከጎጃም የስኳድ ሴል መጽዳቱን ያየው ወሎም አስቀድሞ ነው በሩን የዘጋው። እናም አሁንም አልረፈደም። ረጅሙ የስኳድ እጅ ከዐማራ ፋኖ ትግል መቆረጥ አለበት። ስኳድ ከጀርባው ብዙ ኮተት፣ ከግንቦት ሰባት እስከ መዓት ድረስ የተሸከመ ባንዳ ስለሆነ መላ ሊፈለግለት ይገባል።
"…እመኑኝ መጨረሻ ላይ ይሄ ቀርጣፊ ፀረ ዐማራ የወያኔ ዲቃላ ቡድን ራሱ ጅሉን እስክንድርን ነጋ እና መሃይሙን መከታው ሞሞን ቀርጥፎ ነው የሚበላው። ባለፈው ሳምንት ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው ማንገራገር ሲጀምር በመከላከያ እንዲከበብ እና እንዲደመሰስ ተወስኖ ነበር የነበረው። ኮሎኔሉ መውጪያ ሲያጣ በር የተከፈተለት ወደ ደቡብ ጎንደር ወደ ጋይንት መሄጃ ቀጭን መንገድ ብቻ ነበር። የኮሎኔሉን ጋይንት መግባት ተከትሎ እስክንድርም ወደ ደቡብ ጎንደር ይሻገራል መባልን ሰምቼም ነግሬአችሁ ነበር። ታዲያ አጅሬ እስክንድር ምን እንደሰማ አይታወቅም በፍጹም ወደ ደቡብ ጎንደር አልሄድም ማለቱ ነው የተሰማው። ስኳድ አደገኛ ነው ብዬ ተናግሬአለሁ። ኡጋንዳ የመሸገው ጎንደር አሰዳቢ ስኳድ የተባለው ቡድን አደገኛ ነው አልኳችሁ። ግን አሁን የዐማራ መከራ የነጠላው ጫፍ ላይ ስለሆነ ይጨመቃል። ይራገፋል። ይደርቃል።
"…ሰሞኑን አያ መከታውን ሽማግሌዎች ቀርበው እንዲህ ይሉታል። "አንተ ግን ለምን ከእስክንድር አትለይም? ምንድነው እንዲህ ከእሱ ጋር ያጣበቀህ? ለምን የሸዋን ትግል በእስክንድር ምክንያት ታዳክማለህ? በአስቸኳይ ከእሱ መለየት አለብህ" ይሉታል። እናም ሞኙ ሰው አማኙ፣ መሃይሙ መከታው (ማይም አላልኩም መሃይም እንጂ፣ ሰደበው እንዳትሉኝ ነው) መሃይሙ ምን ብሎ ለጠየቁት ጥያቄ ቢመልስ ጥሩ ነው። "እኔ እኮ የጨነቀኝ ራሱ እስክንድር ቤተ ክርስቲያን ወስዶ ላንከዳዳ ብሎ እስምሎኛል። እናም እኔ እንዴት ላድርግ? አሁን ያለው ሴራ ቆይቶም ቢሆን ገብቶኝ ነበር። ግና መሃላውን፣ ቃልኪዳኑን እንዴት ላፍርስ? ብሎ ቃሉን መስጠቱን ነው የሰማሁት። አይ ዐማራ በእውነት አንዳንዴ እኮ ሃይማኖቱ ገራሚ ነው። አሁን ስኳዶች መከታውን ከሸዋ ልጆች አራርቀው ራሳቸው ዙሪያውን ከበውታል። የሆነ ቀን ያው እንደለመዱት ራሳቸው ይበሉታል። የሚሻለው በጊዜ ዘመድ፣ ከወገኖቹ መቀላቀል ነው።
"…አሁን በሸዋ ያለው መከታው ማሞ የሚቆጣጠረው የጎንደር ስኳድ ምን እያደረገ ነው? አዎ ሸዋን እያስጨነቀ ነው። የሸዋ ሕዝብ በፋኖ እንዲማረር እያደረገ ነው። በማታለል የሸዋ ዳያስጶራን ገንዘብ እየተቀበለ ትግሉን ቆርጥሞ ሲበላ የከረመው የመከታው ጦር ርዳታው ስለተቋረጠበት አሁን በሚዲያ ወጥታ ስትለፈልፍ የምትውለው ፋኒት ባርች ሳትቀር የሞዴስ መግዣ፣ የካርድ መግዣ ሁሉ አጥተው ተጨንቀዋል። ይሄ መፈጠሩን የየው የስኳድ ቡድን የዐማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ በሙሉ ከነጋዴው ማኅበረሰብ ከ50 ሽህ እስከ 500 ሽህ ብር እያስገደዱ እንዲቀበሉ አዝዞ እነ ጅሉ አበበ ጢሞ፣ እነ ሞኙ መከታው ማሞ የራሳቸው ወገን እየጋጡት፣ እያስጨነቁት ይገኛሉ። የሸዋ ዐማራ እንዲጎሰቁል ከገጠር አርሶ አደር ማኅበረሰብ ጭምር በአባወራ ብዙ ሽህ ብር እያስከፈሉ ይገኛሉ። ካላመናችሁኝ ደውላችሁ አረጋግጡ። እነ ምስጋናው አንዷለም ካሸነፉንማ ሞተናል ማለት ነው። የእንጭቅ ልጅ ሁላ።
"…እስክንድር በምርጫ ቦርድ ኦዲት የተረጋገጠ 20 ሚልዮን ብር የባልደራስ ገንዘብ አስዘርፎ ነው ፈርጥጦ ጫካ የገባው። ቀለብ ስዩም፣ አስቴር አሁን ኡጋንዳ የሄደችው ልጅ ለእኔ ሲበዛ ወዳጄ ናት። አሁን አሁን ቁጭ ብዬ ግን ነጥቦችን ማገጣጠም ስጀምር ደነገጥኩ። ቀለብ የአርማጨሆ ልጅ ናት። ያዙልኝ። እስክንድር ደግሞ በባልደራስ የሰበሰባቸው በሙሉ አብዛኛዎቹ ጎንደሬና ትግሬዎችም ጭምር ናቸው። በአሜሪካ ገንዘብ ያዡ ዶር አምሳሉ ደቡብ ጎንደሬ ነው። ኦሮሞዎቹ እነ ኤርሚያስ ዋቅጅራን ሳትዘሉ ማለት ነው። የመሳይ መኮንን ተንታኝ ገለታው ዘለቀ ግን ዘሩን ዐላውቀውም። ባልደራስን በገንዘብ የደገፈው፣ በዶላር ያንበሻበሸው ደግሞ ሞኙ ዐማራ ነው። የፈረንጅ ላሙ ዐማራ። ቀለብ አስቴር ስዩም የፖለቲካ ፓርቲዋ ግንቦት ሰባት ነበር። የታሰረች፣ የተፈታችውም በግንቦት ሰባትነት ነበር። ወዲያው ከእስር እንደተፈታች በቀጥታ የገባችው ወደ ባልደራስ ነበር። ጎንደሬዋ የአርማጨሆ ልጅት የደቡብ ጎንደሬው እስክንድር ነጋ የቀኝ እጅ ነው የሆነችው። ጎንደር ድረስ ከእስክንድር ጋር ሄዳ ከአርበኛ መሳፍንት ጋር ቃል ሲገባቡ በዚያው ነበረች። እናም የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎ ተወላጅ፣ የጉራጌም ተወላጅ የባልደራስ አባላት ተለቅመው ተመንጥረው ሲባረሩ እስከመጨረሻው ድረስ በባልደራስ ቆይታ አሁን ኡጋንዳ ገብታ ትልቅ የጎንደር ስኳድ ሚዲያ ልትከፍት ነው መባልን ስሰማ የማልደብቃችሁን ነው የደነገጥኩት። የእስክንድር የአክስቱ ልጅ የጃጀው ቀማቴ ጫታሙ ተብታባው ጋዜጠኛ ወንደሰን ተክሉም ከኬንያ ወደ ኡጋንዳ የተወሰደው እንግዲህ ለዚህ ነበር ማለት ነው። ነገር ግን አይሳካም አፈርሰዋለሁ።
"…ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ እንዝጋው። አሁን የእስክንድር የዶላር ፌስታል እየተቀደደ ነው። በአሜሪካ የታገደው ዶላር ሲለቀቅ ድርሻዬን አገኛለሁ ብሎ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ የሆነበት የጋሽ መሳፍንት ተስፉው አርበኛ ሀብቴ ከሚመራው ብርጌድ እና የደቡብ ጎንደር የወልቃይት መሩ በጎንደር ስም ከሚያጭበረብረው የእነ ጌታ አስራደ እና የኮሎኔል ታደሰ የእስክንድር ገባሪ ስኳድ በቀር የወሎ ፋኖዎች አንድ አንድ እያሉ እየወጡ ነው። ጎንደር ላይ ያሉትም ሊንጠባጠቡ እንደሆነ ነው የምሰማው። ሲወስኑ እነግራችኋለሁ። ከወሎ ትናንት ፋኖ ድርሳን ብርሐኔ ዛሬ ደግሞ ፋኖ ሲሳይ እና ፋኖ እስራኤል ከስኳድ ቡድን መለየታቸውን በይፋ አውጀዋል። መላው ወሎዬ ቤተ ዐምሓራ ነው ጮቤ እየረገጠ ያለው። ገንዘብ ያደነቆራቸው እነ ሀብቴና መከታው ካልሆኑ በቀር ሌሎችም የሀብታሙ አያሌውንና የእስክንድርን የዶላር ዕዝ በቅርቡ ፍርስርሱን አወጣዋለሁ። ለሕዝብ የሚታገል ሕዝብን ሲሰማ ለዶላር የሚታገል ቀጣሪውን ነው የሚሰማው። እርግጠኛ ነኝ የእስክንድር ሴራ፣ የስኳድ ሴራ ከከሸፈ፣ ሁሉም እንደ ጎጃም አንድ ወጥ ከሆነ፣ አራቱም ክፍላተ ሀገራት አንድ ሆነው፣ በአንድ ቀን ዘመቻ ድባቅ መምታት አያቅታቸውም። እስከዚያው ግን ስኳድን እኔ ብቻዬን የገባበት ገብቼ እወቅጠዋለሁ። እረፍት ነው የማሳጣው። የዳዊት ጠጠር ሆኜ እንደ ጎልያድ እገነድሰዋለሁ።
"…የእስክንድር ነጋን ክፍለጦር በእስክንድር ነጋ ስም የመሠረተው ፋኖ እንድሪስ ከማንም በፊት የሚያውቀው እኔን ነበር። ከግንባር የሚልክልኝን መረጃም በመረጃ ቲቪ የምለቅለት እኔው ነበርኩ። ኋላ ላይ እነ ሀብታሙ አያሌው አግኝተውት ሲያሸፍቱትም አንዲት ክፉ ቃል ተናግሬው አላውቅም። ደውሎ እንኳ ሲያናግረኝ ሳላውቀው እንደ ወንድም ነበር ትክክል አይደለህም እለው የነበረው። እነ ሀብታሙ ብዙ አስለፈለፉት። አሁን ግን ዛሬ ስሰማ እነ ፋኖ እንድሪስም ከእስክንድር እና ከስኳዱ መውጣታቸውንም ሰማሁ። በእስክንድር ነጋ ስም የመሰረቱትን ክፍለጦር ስሙን መቀየራቸውን ሰማሁ። ይሄ በእውነት ለእኔ ትልቅ ድል ነው። ኑረዲን ወንድሜ እንኳን በሰላም መጣህ ለማለትም እፈልጋለሁ። 👇③ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ሰሞኑን የዐማራ ፋኖ በጎጃም አንድ የዐዋጅ ታናሽ ወንድም የመሰለ ቀጭን መመሪያ ለጎጃም ዐማራ ሕዝብ አስተላልፎ ነበር። በሦስት ጀነራሎች የሚመራ ቁጥሩ እጅግ ከፍ በርከት ያለ የኦሮሙማው ገዳይ ጦር ከወትሮው በተለየ መልኩ ወደ ጎጃም ስምሪት ተቀብሎ በዘመቻ መልክ እየመጣ ነው። አገዛዙ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የጎጃሙን የፋኖ አደረጃጀት አፈር ደቼ ካበላሁት የሌላው ቀላል ነው ከሚል ግምገማ ተነሥቶ ነው። እናም ይሄንን መንጋ ገዳይ አራዊት ሠራዊት የገባው ሳይወጣ አፈር ከደቼ ለማብላት ያመቸኝ፣ መክቼም ለማነከት ይቀለኝ ዘንድ ማንኛውም ተሽከርካሪ በጎጃም ምድር እንዳይንቀሳቀስ ዐውጆ ነበር። እናም ዐዋጁ በታወጀ በሰዓታት ውስጥ በመላዋ ጎጃም ትእዛዙ ተግባራዊ ሆኖ ትራንስፖርት የተባለ በሙሉ ቀጥ ብሎም ቆመ። ተመልከቱ ይህ የሆነው በጎጃም አንድ የፋኖ አደረጃጀት በመኖሩ ምክንያት ነው። በአንድ አመራር ውስጥ መሆን ያለውን ጥቅም አያችሁልኝ አይደል? ጎንደር፣ ሸዋ ይሰማል?
"…የዐማራ ፋኖ በጎጃም ይሄን ቀጭን ወፍራም ዐዋጅ ሲያውጅ በመጀመሪያ ቀድሞ የተቃወመው ኡጋንዳ የመሸገው የትግሬዋ የህወሓት ቻናል የሆነ የትግሬ ሚዲያ ነው። "የጎጃም ፋኖ እንዴት በሕዝቡ ላይ መንገድ ይዘጋል? እንዴት ትራንስፖርት ይቋረጥ ይላል? ብሎ የጮኸው የትግሬ ሚዲያ ነው። እኛ ትግሬዎች መንገድ ተዘግቶብን የደረሰብንን እናውቃለን። እናም ልክ አይደለም ብሎ ነው ጓ ያለው።" ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሽዋን ምች አጠናገራት ማለት ይኽም አይደል? በመቀሌ ሁለት ቦታ እንደ አሜባ ተቆራርጠው የራያና የዓድዋ ህወሓቶች ሲፈሳፈሱ ዓይቶ እንዳላየ ዝም የሚለው ትግሬ አክቲቪዝም፣ በወለጋ፣ በጎጂ፣ በምዕራብ ሸዋ እርስ በእርሱ የሚጣለዘው የኦሮሞ አክቲቪስትም የጎጃም ፋኖ ዐዋጅ አሳስቦት ጨንቆትም ዐማራን ሲመክር ፈጣሪ ያሳያችሁ። እነሱን ተከትሎ ነው የብልፄም፣ የኦነግም አክቲቪስቶች ዋይ ዋይ ማለት የጀመሩት። በተለይ ራዕየ እስክንድሮች ተንጫጩ አይገልጸውም።
"…ጎጃም መዋቅራዊ ሥሪቱ በመጠንከሩ ከላይ ወደታች የሚወርዱ መመሪያዎች ወዲያው ነው ተፈጻሚ የሚሆኑት። በጎጃም ፋኖ ወደ አንድ መምጣቱ በፋኖ ስም የሚሠሩ ወንጀሎችን ይቀንሣል። ያጠፋልም። ተጠያቂነትንም ከፍ ያደርጋል። የዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪ አርበኛ ዘመነ ካሤ ለክፍለጦር መሪዎቹ ያስተላለፈውን መልእክት ስሰማ የተረዳሁትም ይሄንኑ ነው። በቃ ጎጃም አስደማሚ ሆኗል። ጎጃም እንደ ሕዝብ ነው የተነሣው። ይሄ ነው የሚፈለገውም። ጎንደር እንደ ጎጃም ለምን አልሆነም? ሸዋ እንደ ጎጃም ለምን አልሆነም? ወሎም እንደ ጎጃም ለምን አልሆነም? የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም። ችግር ስላለባቸው፣ ፈተና ስለገበባቸው፣ ደንቃራ በውስጣቸው፣ ሾተላይ በመሃላቸው ስላለ ብቻ ነው እንደ ጎጃም ያልሆኑት። መልሱ ይሄው ነው። ጎጃም ይሄን አጽድቶ ነው ወደ ሥራ የገባው። ጎጃም እስክንድር ነጋን ከመሃሉ አባርሮ ወደ ሸዋ ሰድዶ፣ እስክንድር ሸዋ ተቀምጦ ገንዘብ እየከፈለ ጎጃምን ይበጠብጡ ዘንድ ያሰማራቸውን በሙሉ ከጎጃም ምድር ለቃቅሞ ይዞ መክሮ "በአንድ ቤት አንድ አባወራ" ብሎ አንድ ሁኖ ነው ውጤታማ የሆነው።
"…ጎንደር እንዲህ እንደ ጎጃም እንዳይሆን ጎንደሬው ራሱ ምልክት የሚያደርገው ፀረ ዐማራው ስኳድ በየት በኩል ያላውሰው? በለሳ፣ ጋይንት መከላከያ ጋር ደም የሚፋሰሰው የጎንደር ዘአማራ ፋኖ፤ ወልቃይት ላይ ከመከላከያው ጋር ቢራ እየጠጣ፣ መሬት የሚቸበችብ፣ የዐማራን ሴቶች የሚያነውር፣ የሚያማግጥ ወንበዴ ከሃዲ ስኳድ በየት በኩል ያንቀሳቅሰው? የወልቃይቱ ዐማራ ነኝ ባይ የሰለጢ ነጋዴ ፀረ ዐማራ ስኳድ የጎንደር ዐማራን እየገደለ፣ እየጨፈጨፈ ያለውን መከላከያ ፋኖ ከነካው ቀይ መስመራችን ተነክቷል። ፋኖ መከላከያን መውጋቱ ትክክል አይደለም ብሎ ስንቅና ተተኳሽ ጭምር ሰጥቶ የሚያሰማራው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እያለ በየት በኩል የጎንደር ዐማራ አንድ ይሁን? የማይካድራውም፣ የመራዊም ጭፍጨፋ የማይሰቀጥጠው የጎንደር ነቀርሳው ስኳድ እያለ በየት? ጎጃምን አልፎ ጎንደር የማይገባው መከላከያ በትግራይ በኩል ወልቃይት ገብቶ ነው እኮ ራሳቸው ጎንደሬዎችን የሚጨፈጭፈው። በጣም አስቂኝ ነገር እኮ ነው ጎበዝ።
"…ጎንደር እንደ ጎጃም አንድ እንዳይሆን በአሜሪካ የተያዘው፣ የታገደው የእስክንድር ዶላር ተለቅቆ የድርሻችንን እስኪሰጠን ለእስክንድር ነጋ እንገረዳለን ባሉ ጎንደር አሰዳቢ እዞች ምክንያት፣ በተለይ በታላቁ አርበኛ ክቡር አቶ መሳፍንት በአፄ ቴዎድሮስ አጽም የገዘቱት አርበኛ ሀብቴ የሚመራው ጦር ለእስክንድር ነጋ አልታዘዝም፣ እነ ሀብታሙ አያሌው እና ሻለቃ ዳዊት አያዙኝም ባዩን ሻለቃ አርበኛ ባዬ የሚመራውን ጦር በመደምሰስ ለእስክንድር ነጋ ለማስገበር ስለሆነ የሚሠሩት አልተሳካላቸውም። ጎንደር አንድ ባለመሆኑ ምክንያት መከላከያው ከወልቃይት እየተነሣ ጎንደሬ ዐማሮችን በዘዴ ይጨፈጭፋል። ያርዳል። በቃ ሊባል ይገባል። የጎንደር ዐማራ ሲሞት ሲጨፈጨፍ ጭጭ እያሉ ወልቃይት ቀይ መስመራችን ነው ማለት ትርጉሙ አይገባኝም። እንዱገባኝም አልፈልግም።
"…አሁን ጎንደር ሦስት የፋኖ አደረጃጀቶች ተፈጥረዋል። አንደኛው የእስክንድር ነጋ የተያዘው፣ የታገደው ዶላር ሲለቀቅልን የተወሰነ ዲላር እናገኛለን ብሎ ለእስክንድር ነጋ የተከበረ ጎንደሬ ማንነቱን ለገንዘብ ብሎ የሸጠ፣ የሸቀጠውና እስክንድር ነጋ መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ እንዳልከዳው በመሃላ አስሮ ይዞኛል በሚሉት በአርበኛ መሳፍንት ተስፉ የበላይ ጠባቂነት፣ በአርበኛ ሀብቴ የሚመራው ዕዝ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በጎንደር ዐማሮች የሚመራው፣ አርበኛ ውባንተን የመሰለ ጎንደሬ ጀግና ለእስክንድር ነጋ አልገብርም በማለቱ በአርበኛ መሳፍንት ርግማን፣ ኡጋንዳ ባለው ስኳድ በሙላት አድኖ አርቃቂነት በኢትዮ 251 ሚዲያ፣ በመረጃ ቲቪ በታወጀ የሞት ዐዋጅ ምክንያት በግፍ የተገደለውና ከእርሱ ሞት በኋላ በአርበኛ ባዬ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎንደር ነው። ሦስተኛው ደግሞ አሁን ከዐማራ ፋኖ በጎንደር በስኳዱ ምክንያት የተገነጠለው እና ወደፊት ክልል ሀገር ወይም ራሷን የቻለች ክልል ትሆናለች ብለው የሚቃዡት ስኳዶች ጎንደርን በፕሬዘዳንትነት ትመራለህ ተብሎ ቃል እንደተገባለት በሚነገረው የእናት ፓርቲ መሥራች፣ ኋላም ፋፍሕዴን አሁን ተገንጣይ የሆነው እና ለእስክንድር የገበረው ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ የሚመራው ፋኖ ነው። ታላቋ ጎንደር ሦስት ፋኖ አደረጃጀት ነው ያላት። አያሳዝኑም ወይ?
"…ልብ ብላችሁ ተከተሉኝ። አሁን የምነግራችሁንም ደጋግማችሁ መርምሩት። እነ ኮሎኔል ታደሰ፣ ጌታ አስራደ፣ እነ ፋኖ ተስፋሁን እና ኢያሱ የነበሩት ከአርበኛ ውባንተ ጋር ነበር። እነዚህ ሰዎች የሚደገፉት ደግሞ በእነ ዶር ምስጋናው አንዷለም ነበር። ልብ ብላችሁ ተከተሉኝ። እነ ሀብቴና ጋሽ መሳፍንት ደግሞ ውባንተን ከሰውት በሚዲያ የሞት ዐዋጅ ያወጁበት ምክንያቱ እንዴት እነዚህን ሰዎች አንተ ጋር ታስጠጋለህ ተብሎ ነበር። ውባንተ ይመልስላቸው የነበረውም "እነዚህ ልጆች ጎንደሬ ናቸው። የጎንደር ዐማራ፣ ብአዴንም፣ ፋፍዴንም ቢሆኑ ያለፈ ታሪክ ነው። አሁን ያሉት በዐማራ ፋኖ በጎንደር ድርጅት ውስጥ ነው። እንኳን ጎንደሬ፣ የጎንደር ዐማራ ሆነው ይቅርና ኦሮሞም፣ ወላይታም አብሬአችሁ ልታገል ብሎ ቢመጣ መቀበል ነው ያለብን። እናም ልጆቹን አታሳዱአቸው" ነበር የሚለው። አሁንም ተከተሉኝ። 👇① ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍
መልካም…
"…ዘወትር ያመሰግን ዘንድ የምንጠብቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…እንደተለመደው ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን አጠር ያለች ነው የምትሆነው። አጠር ብላ ወፈር፣ ደልደል ያለች ለብላቢ ሚጥሚጣ በቃሪያ ናት። እሷን ገምጦ ለመቃጠል አብረን እንሂድ አይደል?
"…እህሳ…ዝግጁ…?
"…ሕወሓት ተሰነጠቀች፣ ደብረ ጺዮንና ጌታቾ ረዳ ተጣሉ፣ ተቃቃሩ፣ ለገሰ ቱሉ ደነፋ፣ ምርጫ ቦርድ ተቆጣ ለደንታቸው ነው። አያደርጉትም እንጂ ለምን እርስ በርሳቸው በዳጣ በሚጥሚጣ እያጠቀሱ አይበላሉም። አይናጩም። ዐማራ አይመለከትህም።
"…የፋኖ ትግል ከጎመራ፣ ከአሸተ ወዲህ ነው ተጣሉ ተጣሉ ሲባል የሚሰማው። ጠቡ ቧልት ነው። ከአቢይ ጋር በነበረው የትግሬ መቀነሻ፣ አፋር እና የዐማራን ማውደሚያ፣ ነባሩን የመከላከያ ጦር ቆርጥሞ የመብያ የፌክ ጦርነት ባደረጉ ጊዜ አንተ እንዲህ አደረክ፣ በፕሪቶሪያ እንዲያ ብለህ ተስማማህ ወዘተ ነው ንትርካቸው። ፌክ ነው ጸብ የላቸውም። ወዳጄ የትግሬ ነፃ አውጪን ማመን ቀብሮ ነው። አሁን እየተጣሉ ነው ሲባል ድንገት አዙረው ዐማራ ላይ ጉብ ሊሉም ስለሚችሉ ዐማራ መጠንቀቅ ነው ያለበት።
"…አሁን ትግሬ ከሆነ አካል ጋር ካልተጣበቀ ማንንም መውጋት አይችልም። ከአቢይ ጋር ተሞዳምደው አዘናግተው የሆነ ነገር አይሞክሩም ማለትም አይቻልም። አሁን እነ ህወሓትን ምን ያጣላቸዋል? ራያ እንደሆነ ተሰጥቶአቸዋል። ጠገዴ ተመልሰዋል። ወልቃይት ነው የሚቀረው እሱንም መላ እየፈለጉለት ነው። እና ምኑ ነው የሚያጣላቸው? ጌታቸውና ደፂ ሁለቱም ለአቢይ ወዳጆች ናቸው። አቢይ ጨክኖ ጓ ቢል እንኳ ማይክ ሐመር በርሮ መጥቶ ፓርላማውን ሰብስቦ፣ አቢይን ጆሮውን ጠምዝዞ ሂዊ የፈለገችውን ሕግ ያጸድቅላታል። እና ምን አጣላቸው? መልሱ ምንም ነው።
"…ፋኖ ይህችን ክረምት በአንድነት እንዳይገጥም የጎንደሩ የወልቃይት ስኳድ በእስክንድር በኩል ደንቃራ ሆኗል። ትግሬ ሲያይል ትግሬ ዐማራ ሲያይል ዐማራ ነኝ የሚለው ዐማራ ጠሉ የወልቃይት ስኳድ እንደሁ ወያኔ ዕለቱን ብትመጣ ደስተኛ ነው። ጀትና ድሮኑም በዚህ ጭጋግ ስለማይሠራለት ድራማ እየሠሩ ነው ባይ ነኝ።
• እናም ዐማራ አይመለከትህም ለማለት ነው።
👆④ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ዶር ምስጋናው አንዷለም ከነ ሀብቴ ጋር፣ ከጋሽ መሳፍንት ቡድን ጋር አብረው እስክንድርን መሪ አድርገው በይፋ ወጥተዋል። የጠንቋይ ልጅ ሁላ። አርበኛ አሰግድ መኮንን አዋክቦ ለአገዛዙ አሳልፎ የሰጠው ይሄ ስኳድ የተባለ የጎንደር ሾተላይ ቡድን ነው። አሰግድን በአቶ መሳፍንት በኩል አሰድቦ፣ አዋርዶ፣ አሳድዶ ያስያዘው ይሄ ነውረኛ ቡድን ነው። ምሬ ወዳጆን እንዴት በድርጅቱ ዓርማ መሃል የጄነራል አሳምነው ጽጌን ፎቶ ይጠቀማል ብሎ ምሬ ወዳጆ አሁኑኑ ካልተገደለ እያለ የሚፎክረውም ይሄ ስኳድ የተባለ የሰኔ 15ቱ ተቸንካሪ ቡድን ነው። ዘመነ ካሤ ጎጃሜ ነው። ጎጃም እኛ እያለን እንዴት የዐማራ ፋኖን ይመራል? አይደለም ዘመነ፣ ከነ ዘመነ ጋር የሚተባበር፣ ከጎጃም ሕዝብ ጋር የሚሠራ የጎንደር ፋኖ ካለ መጥፋት አለበት፣ መገደል አለበት ብለው ዋይ ዋይ የሚሉት ስኳዶች ናቸው። አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ክፍለ ጦሩን የዓድዋ ክፍለጦር ብሎ የሰየመው ትግሬ ስለሆነ ነው ብለው ካልተገደለ የሚለው ይሄ እስኳድ የተባለ ቡድን ነው። የውባንተ ምትክ አርበኛ ባዬን፣ አርበኛ ሳሚን በኮሎኔል ደመቀ የተከዜ ዘብ ጦር፣ በአቶ መሳፍንት እና በሀብቴ ጦር፣ በወደፊቱ የጎንደር ክልል ፕሬዘዳንት ተብሎ በእጩነት የተያዘው፣ የእናት ፓርቲ መሥራቹ፣ በፋፍዴኑ ሊቀመንበር በደቡብ ጎንደሩ ጌታ አስራደ የእስክንደር ነጋ ጦር ከበባ አስድርገው ዐማራ የሆነውን የጎንደር ዐማራ ፋኖ ለመደምሰስ እየተፍጨረጨረ ያለውም ይሄው ስኳድ የተባለ ክፉ የዐማራ ነቀርሳ ነው። ጎንደር፣ የጎንደር ዐማራ ግን ለእዚህ ከሀዲ ቡድን እጁን ይሰጣል ብዬም ለሰከንድም አላምንም። ጎንደሬ ብልህ ነው። ጎንደሬ የፖለቲካ ነቢይ ነው። ውባንተን ሳያውቅ ሳይደርሰልት የበሉትን አውሬዎች አሁን ደግሞ እነ ሳሚን እነ ባዬን ያስበላቸዋል ብዬም አላምንም። ለእነ ዘመነ ካሤ ጎጃም ሕዝቡ፣ ለእነ ምሬ ወዳጆም ወሎ ሕዝቡ ተገን፣ ከለላ እንደሆናቸው ጎንደርም ለእነ ባዬ ተገን በመሆን ከስኳድ ሰይፍ ይታደጋቸዋል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ።
"…ኡጋንዳ የሰፈረውና በስኳድ ማስተር ማይንድ በእነ ሙሉዓለም ገብረ መድህን የሚመራው የሚዲያ ሠራዊትም ይበተናል። በእነ መላኩ ፈንታ በእነ መልካሙ ሹምዬ የሚመራውም፣ በደመቀ ዘውዱ የሰሊጥ ብር የሚታገዘውም የስኳድ ቡድን ምንጩ ይደርቃል። እኔ ደግሞ እንዴት ጎጃሜ ነው ብለው የፈረጁትን ማማር ጌትነትን እንዳረዱት አሳያችኋለሁ። ያበጠው ይፈነዳታል እንጂ እኔ ዘመዴ እነዚህን ሾተላይ የዐማራ ትግል ደንቃሮች ሳላሸንፋቸው እረፍት አላደርግም። እነ ሙላት አድኖ፣ እነ ሙሉዓለም ገብረ መድህን፣ የደቡብ ሱዳን ኤርትራ የመሣሪያ ንግዳችሁን ውኃ ነው የማበላው። ምድረ የጠንቋይ ልጅ ሁላ የዐማራን ትግል፣ የአማኙን የጎንደርን ስም ስታረክስ ዝም ብዬም አላይህም። ከወልቃይትም ከዐማራም ትግል ላይ ትመነቀላላችሁ። ወልቃይትም ከፖለቲካው ቅማንትና ከትግሬ ልጆች እጅ ወጥታ በጎንደር ዐማሮች እጅ ትተዳደራለች። የምጽፈው ይመራል ነገር ግን ጨክነህ ጠጣው ያሽርሃል። ይሄ ወቅት ስህተት የማይፈቀድበት ወሳኙ የዐማራ የትግል ወቅት ነው። የሞት ሽረት የሚደረግበት የዐማራ የትግል ወቅት ነው። ደፈር ብለን አይነኬ የሚመስሉ የዐማራን ሰንኮፎች ለመንቀል እንዘጋጅ። ትግሉ ዐማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ኡጋንዳም ጭምር ነው። በዚያም ያላችሁ ተዘጋጁ። ልብ በሉ እነዚህ የስኳድ ስብስቦች የሚመሩት ደግሞ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል አይደለም። ሰዎች ናቸው ለማለት ነው።
"…ትዝብቴን ተናግሬ የዛሬውን በዚህ ላብቃ።
"…ታስታውሱ እንደሆን የሆነ ወቅት የሕዝቡን ሙቀት ለመለካት ብዬ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በስሱ ተንኮስ አደረግሁት። 50% ከመቶው ሕዝብ ጮኸብኝ። ነገር ግን ሲተኛ ሲነሣ እንዲያንሰላስል፣ እንዲያስብ እርሾ ነበር አእምሮው ውስጥ ያስቀመጥኩት። አልደገምኩም። ቆይቼ የዛሬ ዓመት አካባቢም ኮሎኔሉን ሸንቆጥ አደረግኩት። ስኳዱ ብቻና ጥቂት ሰው ነበር የተንጫጫብኝ። ሌላው በሆዱ እያማ፣ ዘመዴ ልክ ነው እያለ ቆየ። እኔ ደመቀን ስጎነትል ስኳዱን አልነካውም ነበር። ስኳዱ ግን አካሄዴን ስለሚያውቅ በጊዜ በስድብ ሊያስቆመኝ ነበር ይውተረተር የነበረው። ከትናንት ወዲያ ግን ኮሎኔሉንም፣ ስኳዱንም አውቶሚክ ቦንብ በሆነው ጦማሬ በስሱ ስሸነቁጥ ሕዝቡ ከእኔ በላይ ነው መረጃ መዘርገፍ የጀመረው። እኔ ጠላትን እንዲህ ነው አመንምኜ የማሾቀው። በአንደዜ አልላተምም፣ ጦርነት ተጀምሯል ብዬ ካርታ ሙሉ ጥይቴን አልጨርስም። እየቆጠብኩ ነው የምተኩሰው።
"…አሁን ስኳድ ሲሰድበኝ ምላሽ የሚሰጠው ጎንደሬ ነው። ጎንደሬ የእኔ ወዳጅ። እኔ ለጎንደር የሠራሁትን ያህል ስኳድ አልሠራም። ዋልድባ ዳልሽሃ ኪዳነ ምህረት ገዳምን ያለማኋት እኔ የሀረርጌው ቆቱ ዘመዴ ነኝ። ለወላድባ አብረንታት 23 ሚልየን ብር ለምኜ ገቢ ያደረግኩት እኔ ዘመዴ ነኝ። ለጎንደር መድኃኔዓለም፣ ለጎንደሮች ዳቦ ቤት አልቅሼ ለምኜ የከፈትኩት እኔ ዘመዴ ነኝ። ከፈለግክ የኔታ እዝራን ጠይቅ። ደቡብ ጎንደር ዙርአምባ አቡነ አረጋዊን ያለማሁት እኔ ዘመዴ ነኝ። ፎገራ ደብረ ጓንጉት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ያሳነፅኩ እኔ ዘመዴ ነኝ። ጣና ቂርቆስ፣ ማንዳባ፣ ጎርጎራ ማርያም ብትሄድ አሻራዬ ጉብ ብሎ ነው የምታየው። የጎንደርንና የትግራይን ያህል በወሎና በጎጃም፣ በሸዋ አሻራዬ ያረፈበት ሌላ ስፍራ የለም። የማንም የጠንቋይ ልጅ ጀዝባ ስኳዳም ሁላ በጎንደር ጉዳይ ከፊቴ ሊቆም አይችልም። አጥብቀህ ስትይዘው ትግሬ ሲያይ ዐማራ ለማኝ ነው እያለ፣ ዐማራ ሲያይ ትግሬ ቆማል እያለ አንዴ ትግሬ አንዴ ዐማራ ሆኖ ጎንደርን ከመላው ዐማራ ለማቆራረጥ ሲዳክር ከሚውለው ሰገጤ ወልቃይትን ጥገት ላሙ ካደረገ ነውረኛ እስኳድ ጋርማ እንዳታመሳስለኝ። በጭራሽ እንዳታስበው። ስኳዳም፣ የጎንደርን አጥንቷን አስቀርቶ ሲግጥ የከረመ የቀን ጅብ ሁላ እኔ ዘመዴ ለምኜ የገነባኋትን ጎንደርን ሲያዋርዳትማ ቆሜ አላይም። ደግሞ እኔ እኮ የሀረርጌ ቆቱ ሆኜ በጎንደር ጉዳይ ብጎርር፣ ብበጠረቅ ያምርብኛል። ይኸው ሚልዮኖች ፊት ቆሜ በኩራት ደረቴን ነፍቼ ነው የምመሰክረው። ወንድ የሆንክ ሆዳም ስኳድ ናና ተቃወመኝ እስኪ። ሰገጤ ሁላ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆② ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …በል እንግዲህ በሦተኛው ቀን ስትነሳ እንይህ ብለው በሰይፍ ቀልተው እሱም ሳይነሣ፣ ደሙ በከንቱ ፈስሶ የቀረውን ሰውዬ ታሪክ ይነግረናል። መምህር ግርማና፣ ቅባቅዱስ በአፍንጫ ሄኖኬ እኮ ተከታዮቻቸው ነፍ ናቸው። ሄኖክ አሁን የት ነው ያለው? ስንዱ ከእንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳ ሥራዋን እየሠራች ሄኖክ እንግሊዝ ምን እየሠራ ነው? አሁን ገልቱ ሞኝ ደናቁርት ተከታዮቹ ፀበል እያጠመቀ፣ በፈረንጅ ሀገር ትብታብ፣ ዛር፣ ቡዳ አይነ ጥላ እያወጣ ይመስላቸዋል። ጅል ሁላ። እናም ከአንተ የሚጠበቀው ወለላይቱ ማርያም እያልክ ይሄን ወለላ መንጋ ዩሮ፣ ዶላርና ፓውድ ማጠብ ነው።
"…እስክንድር ነጋ በየወሩ አንድ ፓርቲ የሚመሠርተው በነፃ ፈቃዱ ተጠቅሞ ነው። ለሚመሰርተው ፓርቲም ተከታይ ሰው እስካላጣ ድረስ ደንታው አይደለም። ነፃ ፈቃድ የሚባል ነገር ስላለ ደግሞ ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው ለእስክንድር የሚገረዱ ሰዎች አይጠፉም። የምትመሠርተው ፓርቲም ይሁን ሃይማኖት ገንዘብና ሰባኪ ካለው ገንዘቡ እስኪያልቅና ሰባኪም እስክታጣ ድረስ በጥሩ ሁኔታ ይዘልቃል። መንደር ውስጥ ያለ ጠንቋይ ተከታይ ካፈራ፣ በሁላችን ግንበኝነት የተገነባ መልካም ስም ያለው ስመ ጥሩው እስክንድር ነጋማ እንዴት አይከብር አይከበር? የቀደመ የእስርቤት ስሙን በመጠቀም፣ በመታሰር ብቻ የጀገነን፣ የገነነ ሰው በዚያ ላይ በባልደራስና በግንባሩ ስም የሰበሰበውን ሚልዮን ዶላር ይዞ ማኅበርተኛ፣ ተከታይ፣ ሰባኪ ጭምር ቢያጣ ነበር የሚገርመው። እንደ መምህር ሀብታሙ አያሌው፣ እንደ ጭንብሴ ጄሪ፣ እንደ ብሩክ ይባስ (አቤት የብሩኬን ስም ስጠራ አፌን እንዴት እንደሚመረኝ። ምን ላድርግ ቡሩኬ ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ሆንክብኝ) እንደ አርቲስት ሽመልስ አበራና፣ እንደ እስክስ አበበ በለው ያሉ ዳንኪረኛ ይዞማ እንዴት አይከብር። የሳታላይት ቴሌቭዥን ዲስኩር ጨምሩበት። እናም እስክንድር ገንዘብም ሰባኪም ስላለው ለጊዜው እንዘጭ፣ እንዘጭ ማለት ይችላል። ችግሩ ገንዘቡ ያለቀ ቀን ነው ጉድ የሚፈላው።
"…ወተቴ ማሬ የፈረንጅ ላሟ ወልቃይትን የሚመራው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከእስክንድር እና ከእስኳዱ ጋር ነው የሚሠራው። የአሜሪካው ዶላር ለእስክንድር ሲቋረጥበት መረጃዎች የሚጠቁሙት የወልቃይት መሬት የሰሊጥ ሽያጭ ለእስክንድር ቡድን እንዲደርሰው መወሰኑ ነው የሚሰማው። የጌታ አስራደ ወልቃይት መክረምም አንደኛው ተልእኮ ለዚሁ ነው ተብሏል። ሁለት ባንኮችም በዚህ የእስክንድር በጥባጭ ፀረ የዐማራ ፋኖዎች ውስጥ ለእስክንድር አካላት ስንቅ እንዲያቀርቡ መደረጉም ነው የሚነገረው። እነ አቶ መላኩ አለበልም በዚህ ፈንድ ማሰባሰብ ውስጥ ንቁ ተሳታፊም ናቸው የሚሉ አሉ። እስኳዱ ቀደም ሲል ሀብታሙ አያሌውን አሁን በመጽሐፍ ጭምር መሠረተ ኦሮሞ መሆኑን የኦቦ አፍራሳ የልጅ ልጅ መሆኑን እስኪያውጅ ድረስ በወሎዬነት በአሳምነው ጽጌ የትውልድ ሀገርነት ፈርጀው ጎጃሜነትም አለው በማለት ከዘመነ ካሤም ጋር እንደማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ሲማማል ስለሚያዩት "ቀበቶ ሻጭ" የሚል ስም አውጥተው ይሞልጩት የነበረውን ሰው አሁን በእናቱ የደቡብ ጎንደር የሊሞ ከምከም ተወላጅ ነው ብለው ወደ ግሩፓቸው ያቀረቡት፣ የሳቡት የእስክንድር ነጋ ደንገጡር አገልጋይ ሆኖ ስላገኙት ስኳድ ሀብታሙን ለዐማራ ፋኖ ማፍረሻ መዶሻነት ይጠቀሙበት ይዘዋል። 360 ከዩቲዩብ ሲባረር ገንዘብ ያለው እስክንድር ነበር የገዛቸው።
"…ስኳድ ተብዬው ፀረ ጎጃም፣ ፀረ ወሎ ቡድን ሟቾች ጎጃሜዎች ስለሆኑ የመርዓዊን ጭፍጨፋ የፈጸመውን መከላከያ ተብዬ የኦሮሙማ ጦር አያወግዝም። እንዲያውም ኮሎኔል ደመቀ ምን አለ? በወሎ፣ በሸዋ ጭፍጨፋ ሲፈጽም፣ ዐማራን ሲያርድ የሚውልን የአገዛዙን አራዊት መንካት ቀይ መስመሬን ማለፍ ነው ብሎ ነው በሙሉዓለም ገብረ መድኅን አጽፎ፣ በበለጠ ካሣ በኩል ያስነበበው። ይሄ የሰሊጥ ብር ናላውን ያደነዘዘው ሆዳም ቡድን ጎንደር ያሉ ዐማሮች መከላከያን ሲዋጉ መከላከያን መንካት የወያኔ ተላላኪነት ነው፣ ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ እንደመስጠት ነው። መከላከያን መንካት ከእኔ ጋር ያጣላችኋል ብሎ እንደ ብርሃኑ ጁላ በትግርኛ አክሰንት በአማርኛ በድፍረት እስከመናገር፣ መግለጫ እስከማውጣት የደረሰ ድፍረት ሁላ ነው ያየነው። ይሄን ቆሻሻ፣ ግማታም፣ ክርፍ ጥንባታም የበሰበሰ ፀረ ጎንደር፣ ፀረ ዐማራ የበለፀገ አካል በጊዜ መቁረጡ ላይ ካልፈጠንክ ዐማራ ሆይ የስኳድ ጥንባቱ የዐማራን ትግል ማሽተቱ፣ ለሳይነስና ለጉንፋን ማጋለጡም አይቀርም። ስኳድ ጨካኝ ነው። ስኳድ የሰፊ ድንግል መሬት ሀብት ለብቻው ተቀራምቶ የያዘ ቡድን ነው። ስኳድ የመሳሪያ ነጋዴ ነው። ስኳድ ከሻአቢያ ጋር ወዳጅ ነው። ስኳድ ኔትወርኩ ሰፊና እጁ ረጅም ነው። ስኳድ ከኤርትራ ተነሥቶ ደቡብ ሱዳን የሚዘልቅ የመሳሪያ ንግድም ላይ ተሳታፊ ነው። ስኳድ በኡጋንዳ ቢዝነስ ከፍቶ፣ ሚዲያና ጋዜጠኛ ሰብስቦ፣ በሙሉዓለም ገብረ መድኅን አቅጣጫ ሰጪነት፣ ጽሑፍ አርቃቂነት ጎንደርን ከሌላው ዐማራ ጋር በማላተም ጎንደርን ለብቻው ክልል እናደርጋለን በማለት ዐማራ ከጎንደር መውጣት አለበት ብሎ የሚደክም ፀረ ዐማራ የትግሬዋ ህወሓት እና የፖለቲካው ቅማንት የበድኑ ብአዴን ኮንዶም የሆነ ቡድን ነው።
"…እነ ሙክታሮቪች እንኳ የሱማሌውን መንገድ እንዲይዙ፣ እነ ጠበቃ አንዷለም በቆቶ ኦሮሞውን እንዲይዙ ከእስኳዱ ጋር ተመልምለው የሚሠሩ ነበሩ። ስኳድ የአሥራት ቲቪን ለትግሬው ዓምደማርያም እዝራ ሰጥተው ያስፈረሱ፣ እነ አያሌው መንበር ጎጃምን እንደሕዝብ ለማናከስ ገብተው ያፈረሱ ጨካኝ የዐማራ ሾተላዮች ናቸው። ከአንድ ጎንደሬ የጎንደር ፋኖ ይልቅ የኦሮሞውን የአንዳርጋቸው ጽጌን እህት ወልቃይት ድረስ ጋብዘው መሬት ተሰጥቷት፣ ከእነ ጋሻው መርሻ ጋር በሰሊጥ እርሻ ላይ እንድትሳተፍ ሀብት እንድታፈራ ሲያደርጉ የከረሙ ናቸው። ዶር ወንደሰን ከእስክንድር ጋር መግጠሙ ታይቶ እንዲታሰር ከተደረገ በኋላ ነው የአንዳርጋቸው ጽጌ እህት ከወልቃይት የወጣችው። ተተኳሽ ጥይት ሁለት ስማቸውን ለጊዜው የማልጠቅሳቸው ሰዎችና ለባዬ ይደርሳል ብሎ ለጌታ አስራደ ከሻአቢያ 52 ሺ ፍሬ ጥይት አምጥቶ ሰጥቶ ውባንተ ጋር ሆኖ ለሀብቴ የሚያከፋፍል ሸፍጠኛ ቡድን ነው ስኳድ። እንዲህ እንደ ቀላል እንዳትመለከቱት። የጎንደር ኤሊቶች በጊዜ ካልመከራችሁ ፍዳ መከራችሁን ነው ይሄ ቡድን ይዞባችሁ የሚመጣው። አሁን ሰሞኑን ነካ ነካ ስላደረግኩት ግርር ብሎ ቢመጣም እንደ በፊቱ በጎንደር ስም መነገድ አልቻለም። የኮመንት ሳጥኑን ሁሉ ዘግቶ ነው እዬዬውን የሚያቀልጠው?
"…የኦሮሙማው የጀነራሎች የትግሬ ጀነራሎችን አባርረው ከፀረ ፋኖው ኮሎኔል ደመቀ ጋር ሆነው የወልቃይትን መሬት እንዴት እንደሚቸበችቡት ብታዩ ትደነቃላችሁ። አንድም ጎንደሬ ግን በወልቃይት ተጠቃሚ አይደለም። ጭራሽም አያቀርቡትም። የጎንደር ዐማራ ከወልቃይት መሬት ሃባ ቅንጣት ታህል አይጠቀምም። ወልቃይትን የሚግጧት ሻአቢያ፣ በግማሽ ጎናቸው ቅማንትና ትግሬ የሆኑ ሰዎች ናቸው የሚዘውሩት። ሙሉ ዐማራ የሆነ ጎንደሬ ግን በወልቃይት አካባቢ ድርሽ እንዲል አይፈቀደልተም። ወልቃይት ለጎንደር ዐማራ ላምአለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ናት። ወልቃይት ከወያኔ ጋር ችግር ገጠመው ሲባል ነው የዋሁ ጎንደሬ የአፄ ቴዎድሮስ፣ የመልኬ ጎቤ ስም እየተጠራበት፣ በጎንደር አዳራሽ የስኳዱ መሪ ኮሎኔል ደመቀ እና…👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…መልካም…
"…ያመሰግን ዘንድ ይጠበቅ የነበረው 1ሺ አመስጋኝ ቁጥሩ አልፎ 1ሺ 6 መቶን አልፏል። እግዚአብሔር የምሰግን።
"…በነገራችን ላይ የእኔ የልብ ጓደኞች፣ ወዳጆች ቁጥራቸው ይሄው ነው። 300 ምናምን ሺው ታዛቢ ነው። በተለይ 1ሺዎቹን በስም ሁላ እየለየሁአቸው መምጣት ጀምሬአለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን ብለው ካልጻፉ እንኳ ከምር ምን ሆነው ይሆን ብዬ ማሰብ፣ ቅር ይለኝ ሁላ ጀምሯል። ከሥራ ቦታቸው ሁኔታ፣ ካሉበት ሓላፊነት አንጻር በእኔ ጦማር ላይ ሲጽፉ ባይታዩም በጀርባ ሆነው ስለ እኔ የሚጸልዩም ከሺ በላይ የሚሆኑ ወዳጆች እንዳሉኝም ይሰማኛል። ለማንኛውም እኔ እንቅልፍ አጥቼ የምተጋው ለእነዚህ ትጉህ አመስጋኝ ወዳጆቼ ጭምር ነው።
"…ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንሄደው እንደተለመደው ወደ ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። መቼም ርዕሰ አንቀጼ እንደ ጠበል የምታስለፈልፈው ብዛቱ ለጉድ ነው። እናም ዛሬም ስስ አውቶሚክ ቦንብ በጀመርኩት ስኳድ ላይ በተን ላደርግ ነኝ። የነብሩን ጭራ ይዤው የለ? አዎ አልፋታውም። እመ አምላክ ምስክሬ ናት የስኳድን ኔትወርክ ሳልበጣጥሰው ራሱ ተበጣጥሶ ወድቆ እንዳይቆጨኝ ጸልዩልኝ። ማርያምን አልፋታውም። የነብሩን ጭራ ይዤዋለሁ። ገደል ሃንቁፍቱ ሳልከተው አልመለስም። አይደለም ወልቃይት፣ ሸዋ ኡጋንዳም ድረስ ዘልቄ ከስኳድ ጋር ጦርነት ነው የምገጥመው። ሙላት አድኖ ጋብዘኸኛል እንግዲህ እንሞካከራለን። ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ያዋጣህ እንደሆነ እናያለን። ውባንተን አስገድለህ እንዲሁ በዋዛ የምንፋታስ ይመስልሃልን?
"…እናስ ጎደኞቼ ስኳድ ላይ ልተኩስ ነኝ። እናንተስ ተኩሱን ለመስማት፣ ሰምታችሁም የሰማችሁትን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁን?
• እደግመዋለሁ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?
መልካም…
"…ይሄን እስከአሁን ድረስ 25 ሺ ሰዎች አንብበውት 14 ሰዎች ብው ብለው የተናደዱ፣ የበገኑበትን ርዕሰ አንቀጽ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ የአድማጭ ተመልካቾቻችን ተራ ነውና የራሳችሁን ሓሳብ ስትፈልጉ ጨምሩበት፣ ስትፈልጉም ቀንሱና ሓሳባችሁን በጨዋ ደንብ አካፍሉን።
"…እስከ ምሽት እስከ መኝታ ሰዓታችን ድረስ በእናንተ አስተያየት ስንደመመም እናመሻለን። ለአቅመ አስተያየት መስጠት ያልደረሳችሁ የሓሳብ መሀኖች ጥጋችሁን ያዙ። ሰምታችኋል።
• 1…2…3…! ጀምሩ…!
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …የመጣው መከላከያ ሙትና ቁስለኛ ሆነ። በቆቦ የሰራዊቱ አዛዦች ተደመሰሱ፣ በምንጃር፣ በከሰም የጠላጥ ኃይል ተቀረጠፈ ነው የዐማራው ወሬ። ደስስ ሲል።
"…ድሮ ድሮ ዐማራው የጠላትን የምስጢር ወሬ ለመስማት ይቸገር ነበር። የትግሬ ነፃ አውጪ በትግርኛ፣ የኦሮሞው በኦሮሚኛ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ ላይ ስለሚመክር ዐማራው ይቸገር ነበር። ዘንድሮስ? ዘንድሮማ ትግሬው ሁላ ሙሉ ፕሮግራሙ በአማርኛ ነው። ኦሮሞው ራሱ ያለ አማርኛ አይተነፍሳትም። ስታሊን ለዪቲዩቡ በአማርኛ ልመና ጀምሮ አይቼው ተገርሜአለሁ። ሱፐር ቻትና፣ ሱፐር ስቲክ፣ በዜል አካውንታችን እርዱን፣ በማርያም ጽዮን እናት አባቶቼ አትለፉን ሲል ነው የምሰማው። በአማርኛ እኮ ነው። ኦሮሞዎቹም የቴሌግራም በሉት፣ የቲክቶክ፣ የዩቲዩብ ልመናቸው በአማርኛ ነው። በቁቤኛ ሼሪ ጎዻ የሚል ኦሮሞ ነፃ አውጪ አላየሁም። ሁሉም በአማርኛ ነው የሚለምኑት። ሙሉ ፕሮግራማቸውን አስገዳጅ ሆኔታ ሳይፈጠርባቸው በአማርኛ አድርገውታል። መቼም ፋኖ ነው የጫነብን አይሉም። ሲሳደቡም፣ ሲለምኑም በአማርኛ ሆኗል። ማስታወቂያ ሲሠሩም በአማርኛ ሆኗል። የዘንድሮው የተለየ ነው። እናንተስ አልታዘባችሁምን?
"…ግንቦት ሰባት፣ ባልደራስ፣ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስቱ፣ እነ ነአምን ዘለቀ፣ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ እነ ታማኝ በየነ ፣ እነ ደረጄ ሀብተ ወልድ፣ እነ ሲሳይ አጌና ነበሩ ድሮ ድሮ አጀንዳ ሰጪዎች፣ ቀጥሎ እነ ኤርሚያስ ዋቅጅራ፣ ከዚያ እነ ሀብታሙ አፍራሳ ነበሩ አጀንዳ ሰጪዎች፣ ከዚያ የጎንደር ስኳድ ነበር አጀንዳ ሰጪው፣ ብልፅግና፣ የህወሓትና የኦነግ ሴልም አጀንዳ ሰጪ ነበር ለዐማራ። ይሄ ታዲያ ድሮ ድሮ ነበር ከዐመት በፊት። ዐማራውን በፈለጉት ሰዓት፣ እንደፈለጉ አድርገው ይጋልቡት ነበር። እንደ ፈረንጅ ላም ደሙንም፣ ላቡንም፣ ገንዘቡንም ያልቡት ነበር። ዘንድሮስ? ዘንድሮማ ወፍ የለም። አበበ በለው ትናንት ሲያለቅስ አይቼው አሳዘነኝ። ሀብታሙ አያሌው እና ሽመልስ አበራ ጆሮ ካናዳ ድረስ ሄደው ባዶ እጃቸውን ሲመለሱ አይቼ አሳዘኑኝ። ከምር አንጀቴን ነው የበሉት። ለምን ይሄ ሆነ ያልን እንደሆነ የነቃ፣ የበቃ የዐማራ ትውልድ ዘንድሮ እየተፈጠረ ስለሆነ ነው።
"…ድሮ ድሮ እስክንድር አይነኬ ነበር። ጋሽ መሳፍንት አይነኬ ነበሩ። ዘንድሮ ግን የማይነካ የለም። ዐማራ የእውነት፣ የሀቅ ሚዛን ይዞ ቀርቦ ሁሉን እየመዘነ የቀለለውን ወዲያ ወደ ጓዳ እየሸከፈ፣ የከበደውን ወደፊት እያመጣ ወደፊት እየቀጠለ ነው። ድሮ ድሮ የዶላሩ ቆጣሪ መዝጊያና መክፈቻ በተለመዱ አጭቤ ዳያስጶራ ግለሰቦች እጅ ላይ ነበረ። ዘንድሮ ግን የዶላሩ በተን ሕዝብ እጅ ላይ ሆኖ ተገኘ። ድሮ ድሮ አንድ ሰው ኢሀአፓ፣ ቀጥሎ ኢዲዩ፣ ከዚያ ቅንጅት፣ ከዚያ ግንቦት ሰባት፣ ከዚያ ባልደራስ፣ ከዚያ ግንባሩ፣ ከዚያ ሠራዊቱ፣ ከዚያ እስኳድ፣ ከዚያ እዙ ሆኖ በሊቀመንበርነት፣ በገንዘብ ያዥነት እንዳሻው ሆኖ ይቀልድ ነበረ። የዛሬ ሳምንት እንደ ደረጄ ሀብተወልድ ለአቢይ ተገርዶ፣ ፋኖን ሰድቦ፣ ዛሬ አይኑን በጨው ታጥቦ የፋኖ ገንዘብ አሰባሳቢ ሁላ ለመሆን የተለየ ደደብ መሆንን ይጠይቅ ነበረ። ዘንድሮስ ዘንድሮማ አይቻልም። ተመንጥረህ፣ ተራግፈህ ነው አይደለም የዐማራ ፋኖ መሪ የዐማራ ፋኖ ደጋፊም ለመሆን የምትችለው። የዘንድሮው ዐማራ ይለያል።
• ዐማራ ወደፊት ምን ይጠብቅ?
"…አሁን አሁን ዐማራ ማሸነፉ እንደማይቀር ሁላቸውም በሚገባ እየተረዱ መጥተዋል። እስከ አሁን ከዳር ቆመው ደመራው የሚወድቅበትን አቅጣጫ በመገመት ደመራው በወደቀበት አቅጣጫ ለመሰለፍ አሰፍስፈው የነበሩት አካላትም እንደ ግሪሳ ወፍ ግርር ብለው መምጣታቸው አይቀሬ ነው። እነሱን እነዚህን ኦፖርቺንስቶች ወንጭፍ አዘጋጅተህ መጠበቅ ነው። የድል አጥቢያ አርበኛውን ከዚህ በኋላ ነው መጠበቅ። እስክንድር ለምን ይነካል እያለ በልቡም በአፉም ሲደሰኩር የከረመው ሁላ አሁን እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ በእስክንድር ላይ ሲዘምት ታየዋለህ። የድል አጥቢያ አርበኛ ልማዱ ነው። አስከዛሬ ዐማራው ተከራክሮ፣ ተሟግቶ ያሸነፈባቸውን ምሰሶዎች ተጠግቶ ለመነቅነቅ መምጣቱ አይቀሬ ነው። እስከ ዛሬ ዐማራ ነኝ ማለት ውርደት ነው ሲል የከረመው ወራዳ ሁላ የትምህርት ዝግጅቱን፣ ሱፍና ከረባቱን፣ ጃንሜዳ፣ አይጠረቄ ሆዱን አስፍቶ ከች ማለቱ አይቀሬ ነው። እና ይሄን የድል አጥቢያ አርበኛ ማረፊያ ቦታ አዘጋጅቶ ከከተም በሪው ውጪ ማነጋገር ነው ያለበት ዐማራው።
"…የድል አጥቢያ አርበኛ አደገኛ ነው። ወያኔን ከአምቦና ከደብረ ብርሃን፣ ከአስኮና ከኮተቤ፣ ከሱሉልታ የተቀላቀሏት ናቸው ጉድ የሠሯት። ብልፅግናን ክፍለ ሀገር የጴንጤና የወሀቢይ እስላም የአራዳ ልጆች ናቸው ጉድ የሠሯት። እናም ዐማራው ዘር ማንዘሩን እየቆጠረ፣ የፊውታውራሪ፣ የካህን ዘር ነኝ እያለ ተሰልፎ የሚመጣውን ባጣ ቆየኝ አይደለሁም ብሎ አደብ ያስገዛው። አናቱ ላይ ፊጥ አያድርገው። ዐማራው ዋጋ የከፈሉለትን ወደፊት ያምጣ። እኛን አራት ኪሎ አድርሰህ ነው አንተ ወደ ግብርናህ መመለስ ያለብህ ያሉትን ክፍት አፍ ቀዳዶችን አይስማ። አይመላለሳቸውም። የፋኖ ትግል በዚህ ቁርጠኝነት ነው መሄድ መሻገር ያለበት።
"…ሁሉ ከጠራ በኋላ ዶላሩም፣ ፓውንዱም ያስፈልጋል። ነገር ግን ለህልውና ትግል ዶላር የግድ አስፈላጊ አይደለም። ፋኖ ቢያጣ ቢያጣ እዚያው ክልሉ ውስጥ ያሉትን የመንግሥት የልማት፣ የገንዘብ ተቋማትን መጠቀም ይችላል። እንደ ኦነግ ዘርፎ ሳይሆን በሕግ በሥነ ሥርዓት መጠቀም ይችላል። ፋኖ መነገድ አለበት። ወያኔ፣ ሻአቢያ፣ ኦነግ ለሠራዊታቸው በተለያየ መልኩ የንግድ ተቋማትን ከፍተው ይንቀሳቀሳሉ። ፋኖም ወደዚያ ነገር መሸጋገር አለበት። አዎ የብህትውና ቦለጢቃ አስፈላጊ አይደለም። ስኳዶች የወልቃይትን መሬት ከጎንደር ቀምተው አይደል እንዴ ጥሬ አራቸውን ዐማራና ጎንደር ላይ የሚዘፈልሉት? አዎ ፋኖ ለወደፊቱ ከኬላ ላይ ክፍያ ባሻገር ቢዝነስ ከወዲሁ ማሰብ አለበት። አፍጋኒስታን ሀሺሽ ይነግድ የለም እንዴ? ከምሬ ነው። አስቡበት። መቼም ዛሬ ፀረ ዐማራው ቡድን የሌለ ነው የሚያብድብኝ። ለደንታው ነው። ኬሬዳሽ።
"…ዐማራው ግንባሩን ማስፋት አለበት። ጎረቤት ክልልም፣ ጎረቤት ሀገርም። የጎንደር አሰዳቢው እስኳድ አባል ሆኖ ባህርዳር ላይ የጎጃም ዐማሮችን ሲዘርፍ፣ ሲቀማ፣ ሲያግት ከርሞ አሁን ኡጋንዳና ኬንያ ሄዶ ባለ ቢዝነስ የሆነውን ወራዳ ስኳድ ለመጋፈጥ መዘጋጀት አለብህ። ከጎጃም ጎንደርን ሲያቃቅር ከርሞ አሁን ኡጋንዳ የገባም ካለ ለመጋፈጥ መዘጋጀት አለብህ። ዐማራ ማለት ክንዱ ምን ያህል እንደሚረዝም ድንበር ተሻግረህ ማሳየት አለብህ። ወደፊት ፎቶና ስልካቸው በሚለጠፍ፣ ወንጀላቸው በቪድዮ ተደግፎ የሚቀርብን ፀረ ዐማራ ዐማራ አሰዳቢ፣ በጋዜጠኝነት ስም ይሁን በነጋዴነት ካለበት ሆነህ በሕግ ልክ ልታስገባው ተዘጋጅ። ኮረንቦላ እየተጫወትክ፣ ድራፍት እየጨለጥክ፣ ዳሌና ጭን እያሳደድክ ብቻ መቅኔህን አትጨርስ። አዎ አሸማቀው። መግቢያ መውጫ አሳጣው። ልክ እንደ እስራኤል ለወገንህ በየትም ስፍራ አለሁ በለው። ይሄ ምክሬ ነው።
"…በመጨረሻም አትፍራ። አሁን የመከራው ቀንበር ባያልቅም ነገር ግን እየቀለለ ነው የሚመጣው። ዋነኛው አስፈሪ ጊዜ አልፏል። እኔ ዘመዴም ዋነኛውን የዐማራ አስፈሪ የፈተና ጊዜ ተጋፍጬ፣ አጋልጬ አሻግሬሃለሁ። ከዚህ በኋላ ያለውንም በጥበብ፣ በእምነት፣ በድል ትሻገረዋለህ። እስክንድርን፣ ሀብታሙን፣ ግንቦቴን፣ አበበ በለውን አትፈራም። አይረብሹህም ሳይሆን…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም…
"…አንድ ሺ አምሰጋኙ ሞልቷል። ቀጥሎ የሚከተለው ደግሞ ርዕሰ አንቀጻችን ይሆናል ማለት ነው።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን በድሮ ድሮ ዐማራ እና በዘንድሮ ዐማራ መካከል ያለውን አንድነትና ልዩነት በአጉሊ መነጥሬ ልቅም አድርጌ ቃኘት አደርጌአለሁ። እናንተም ደግሞ አይታችሁ የጎደለ ካለ ሞልታችሁ፣ የበዛም ከልክ ያለፈም ካለ ቀንሳችሁ አስተያየታችሁን ትሰጡበት ዘንድ አዘጋጅቼላችኋለሁ።
"…በወንድ አቅሜ፣ በጎልማሳነቴ ዘመን፣ ተፍ ተፍ ብዬ ያዘጋጀሁትን የዛሬውንም ርዕሰ አንቀጼን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ ወይ?
"…አጠገባችሁ ያለውን ሰው ነካ አድርጉትና ዝግጁ በሉልኝማ። አደራ ታክሲ ውስጥ ሆነህ አጠገብህ ያለውን ነካ አድርገህ ራስህን ዘብጥያ እንዳታገኘው ተጠንቀቅ። 😂
• ዝግጁ…?
መልካም…
"…30 ሺ ሰው አንብቦት 30 ሰው 😡 ብው ብሎ መናደዱን የገለጸበትን የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ ስታነቡ አድራችሁ ለነገ እንወያይበታለን ብዬ ቅድም ነግሬአችሁ እንደነበር ይታወቃል። ነገርን ብዙዎቻችሁ ዘመዴ ነገም ስንወያይበት እንዋል ችግር የለም። ነገር ግን ምሽቱን ተቃጥለን ከምናድር እንተንፍስ የኮመንት ሰንዱቁን ክፈትልን ብላችሁ ተማጽናችሁኛል። እናም ጭቅጨቃችሁ ስለበዛብኝ ሰንዱቁን ከፍቼላችኋለሁ። በጨዋ ደንብ መተንፈስም ትችላላችሁ።
"…እኔ ትንቅንቁን ጀምሬዋለሁ። አጋዥ፣ ረዳት፣ ተከራካሪ፣ ተሟጋች አልፈልግም። ብቻዬን እበቃቸዋለሁ። ይሄ የመጨረሻው የዐማራ የሞት ሽረት የትግል ወቅት ነው። የደቡብ ጎንደርን የስኳድን አረመኔያዊ ጭካኔና ሸዋ ላይ እየተሠራ፣ ጎጃም ላይ እየተነዛ፣ ወሎ ላይ እየተዘመተ፣ ራሱ ጎንደር ላይ እየተሴረ ያለውን ሴራም በሃላል ፊት ለፊት በመዘርገፍ እንፋለማቸዋለን። ባህርዳር ሰው አፍኖ ሲገድል የከረመው የስኳድ ቡድን ተጠራርቶ ኡጋንዳ እንዴት እንደከተመም እናያለን። የእስክንድር ነጋ የባልደራስ ወዳጆቹ እነ ጋዜጠኛ ይድነቃቸው እንኳ ሚዲያ ሊከፈትላቸው ኡጋንዳ መሄዳቸውንም እናያለን። ወንድ እናታችሁ ወልዳችኋለች። የወልቃይት ኮሚቴን መግለጫ አርቅቆ ጽፎ የሚለጥፈው ሙሉዓለም ገብረ መድህንንም ፊት ለፊት እፋለምህሃለሁ።
"…ጠብቀኝ መንጋው። ስማችሁን፣ ፎቶአችሁን፣ ስላካችሁን እለጥፈዋለሁ። መውጫ መግቢያ ነው የማሳጣችሁ። ሸዋን አንቃችሁ የያዛችሁ እኔን አያድርገኝ። ቀልድ አይደለም። ጠብቀኝ አልኩህ። ከሸኔ የበለጠ የሠራችሁትን የቪድዮ መረጃ እበትነዋለሁ። ምድር እንድትጠባችሁ ነው የማደርገው። መልካሙ ሹምዬ ስምህን ስጠራው እንዴት ሽንትህ እንደሚያመልጥህ መቼም ይገባሃል አይደል? አንተ ሳዲስት አረመኔ። ጠብቀኝ።
• እናንተም ተንፍሱ። ተሳዳቢ ግን ይቀሰፋል። ሰምታችኋል።
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …የእስክንድር ነጋ የግል የገንዘብ ግምጃ ቤቶቹ የዲሲ ግብረኃይሎቹ እነ ሕይወት፣ እነ ሙልጌታና እነ ኤርሚያስም አዲስ ገንዘብ ካልተሰበሰበ በቀር ያለውን አውጥተው ባዶ እጃቸውን መቅረት አይፈልጉም። ሽመልስ አበራ ጆሮ ነው አሁን እልል የሚለው እሱም 4ሺ ዶላር ደሞዙን ሀብታሙ እንዳይከለክለው ብሎ እንጂ ወድዶ አይመስለኝም። በላስ ቬጋስ ገቢ ለመሰብሰብ ያዘጋጀችው ልጅ የግንቦት 7 አባል ነበረች። ዐማራ የሆነ ሰው ግን የሚገባ አይመስለኝም። ኢትዮ 360 በወር ከኪራይ ውጪ ደሞዛቸው ከ35 ሺ ዶላር በላይ ነው። እናም ይሄ ዶላር አሁን ባለው በሀብታሙ አያሌው ጥጋብና ድፍረት ምክንያት ከትግሬ፣ ከብልፅግናና ከኦሮሙማው ካልሆነ በቀር ከዐማሮች ማግኘት አይቻልም። አበበ በለውም ከእነ ሀብታሙ አያሌው ጋር አብሮ አሁን ዜሮ ገብቷል። እናም የስኳድ ልሣኑ ተዘግቷል ማለት ነው። አበቃ።
"…አሁን ስኳድ ኡጋንዳ ነው ያለው። እዚያ ሚዲያ ሊከፍት ደፋ ቀና እያለም ነው። የባልደራሷ የጎንደር አርማጨሆዋ ወዳጄ ቀለብ (አስቴር) ስዩምም ኡጋንዳ የሄደችው ይሄንኑ ሚዲያ ለመክፈት ነው መባልን ሰምቼ ባለፈው ነገርየውን ብልጭ ባደረግኩ ጊዜ ወዳጄ የሆነችው አስቴር ወይም ቀለብ ስዩም "ሚዲያ የመክፈት ሓሳብ እንዳላት፣ ነገር ግን በባልደራስ ገንዘብ አይደለም። ከእነ ዶክተር አምሳሉም ጋር ግኑኝነት የለኝም" በማለት እንደ ወዳጅነታችን ደውላ አረጋግጣልኛለች። የእስክንድር የአክስት ልጅ የሆነው ቀማቴው ወንደሰንም ከኬኒያ ኡጋንዳ የተወሰደው ለዚሁ የሚዲያ ተግባር ነበር። እናም ኡጋንዳ ተቀምጦ መረጃ ቲቪ በነፃ የሚሰጠውን የአየር ሰዓት ተጠቅሞ፣ ልክ እንደ 360 እና እንደ አበበ በለው መረጃ ቲቪን አፍርሶ የጎንደር እስኳድ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለመክፈት የሰፈሰፈውን ቡድንም ወገብ ዛላውን ቆምጬ ነው የምለቀው። ሲፈልግ መረጃ ቲቪ ያባረኝ እንጂ በሕይወት እያለሁ በመረጃ ቲቪም ስም ወንጀል ሲሠራ ማየት አልፈልግም።
"…አሁን የጎንደር ስኳድ ዋና መመሸጊያው ኮሎኔል ደመቀ ዛውዱ ነው። ይሄ በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ዙሪያ እንደ አንበጣ መንጋ የተከመረን ሆዳም ቡድን ብትንትኑን ማውጣት አለብን። ካልቀደምነው ይሄ ቡድን መጀመሪያ እዚያው ጎንደር ላይ በሀብቴና በባዬ መካከል ጦርነት ነው የሚከፍተው። መዝግቡልኝ። አሁን እንኳ በፎገራ ከሁለት ተከፍለው የሀብቴና የባዬ ነን የሚሉ ፋኖዎች ሰሞኑን ተገዳድለዋል። እስክንድር አይመራንም የሚለውን ሁሉ በለው ብለዋል እነ ዶር ምስጋናው አንዷለም። ሁልጊዜ ወያኔ እዚህ ወጥታ፣ እዚያ ገባች፣ መከላከያው መነካት የለበትም፣ ፋኖ ሌባ ዘራፊ ነው (አያሌው መንበር) እያለ የዐማራን ትግል እንዳይወለድ ፅንሱን የሚጎትት ሾተላይ የጠንቋይ ልጅ ስብስቦችን ማጋለጥ አለብን። በኤርትራ አድርገው ኡጋንዳ ገብተው በኡጋንዳ በፕሮፓጋንዳ ሚዲያውን ተቆጣጥረው የጎንደር እስኳድ ኢምፓየር ለማምጣት የሚላላጡትን ተረፈ አብን የሰሊጥ ነጋዴ ማፍያዎችን መጋፈጥ አለብን። ይሄን ማድረግ ለዐማራ ፋኖ ትግል የመጨረሻው ወደ አራት ኪሎ መገስገሻ መንገዱን የሚያሳምርለት ፍርቱና የሆነ ዕድል ነው።
"…በሸዋ አሁን በመከታው ስር ያሉት የጦር አመራሮች በእስክንድር አካሄድ ላይ ስለነቁ መታዘዝ እያቆሙ ነው። እኛ የዐማራ ሕዝብ ታዛዦች እንጂ የመከታው ማሞ ታዛዥ አይደለንም የሚሉ ጀግና የዐማራ ልጆች ተፈጥረዋል። እነ መከታው ማሞን በፋይናንስ ይረዳ የነበረው በሀገረ አሜሪካ የሚገኘው ጠንካራው የሸዋ ተወላጆች ቡድን አምስት ሳንቲም፣ ጢና ዱዲ መርዳት አቁሟል። ለመከታው ሴት ፋኖዎች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ጨርቅ፣ መድኃኒት ጭምር ይልክ የነበረው ጠንካራው የሸዋ ቡድን እስክንድር ነጋና የጎንደር እስኳድ ከእኛ የሚያዋጣችሁን እናያለን በማለት እግራችሁን ብሉ ብሎ እርዳታውን አቁሟል። አሁን አምስት ሳንቲም አያገኙም። ብልፅግና ከፀደይ ባንክ ገንዘብ ወጥቶ ይሰጣቸው እንዳለም ጭምጭምታ ሰምቻለሁ። እሱም ቢሆን አያዛልቅም። አሁን የመከታው ጦር ለስልክ መደወያ ካርድ ሁላ እያጣ መሆኑ ተሰምቷል። እናም ዋናው ስኳዱንም፣ እነ ሀብታሙና አበበ በለውንም የሚያንጠባርራቸው ከምስኪኑ ዐማራ እየታለበ ይሰጣቸው የነበረው ዶላሩ ነበር። ተመልከቱ የሀብታሙ አያሌው ወርሃዊ ደሞዝ እኮ 7,000 ዶላር ነበር። ይሄ ማለት ከአበል ውጪ ማለት ነው። አሁን እሱ ከየት ይመጣል? አለቀ። ወፍ የለም።
"…በዚህ ሰዓት ጎጃም መንገድ ዘግቶ ከአገዛዙ ጋር ፍልሚያ ላይ ነው። ጎንደርም በነፍስ እየተዋደቀ ነው። ሸዋም የእስክንድር እና የመከታው ጦር ከመከላከያ እየተደረበ አላላውስ አለ እንጂ እየተዋደቀ ነው። ወሎ ጠንክሯል። ስኳድና የሰኔ 15 ተቸንካሪዎች ገለል ካሉ ደግሞ ዐማራ በቅርቡ ያሸንፋል። ስኳድ ገለል አለ አላለም ግን አብሮ ከብልጽግና ጋር ይወገዳል እንጂ ዐማራ እንደሁ ማሸነፉ አይቀርም። ካካ ነው። በ70 ሚልዮን የዐማራ ደም መቀለድ አይፈቀድም። ስኳድ ይሸነፋል። ኡጋንዳ ተቀምጦ የወልቃይትን ማኅተም ይዞ መግለጫ እየጻፉ መዘብዘብም የለም። አከተመ።
"…ይሄ ለእኔ ለዘመዴ የመጀመሪያ የውጊያ አብሪ ጥይቴ የተኮስኩበት ርዕሰ አንቀጼ ነው። ጦርነቱን እንደምጀምር አሳወቅኩ እንጂ አልጀመርኩም። ጦርነቱን እንደምጀምር ግን በይፋ ይኸው ነግሬአችኋለሁ። የፈለግከውን በለኝ። ጋላ ስትፈልግ ኦሮሞ፣ ስትፈልግ ትግሬ፣ ጉራጌ፣ ጎጃሜ፣ ሸዋዬ፣ ወሎዬ የፈለግከውን በለኝ በዐማራ ትግል አልደራደርም። የዐማራ ፋኖ ትግል በግሌ በቤተሰቤ ፊት የተሰደብኩበት፣ የምወዳትን ሀገሬን ያጣሁበት፣ አሸባሪ ተብዬ የተከሰስኩበት፣ እንደ ውሻ፣ እንደ እብድ የተቆጠርኩበት፣ የማንም ልጋጋም፣ ልፋጫም የሰው ልክ አያወረቄ ክፍት ጥንብ አፉን እየከፈተብኝ፣ እያዋረደኝ፣ እየሰደበኝ፣ እያስፈራራኝ ተጋፍጬ፣ ከዐማራ በላይ ዐማራ ሆኜ፣ በቄስ በጳጳስ ተጠምጄ፣ ተገስጬበት፣ ወዳጅ ዘመድ ያጣሁበትና ገነት መንግሥተ ሰማያት የምገባ እንኳ ብሆን በዐማራው እና ለዐማራው ባደረግኩት ጩኸት ምክንያት ነው ብዬ የማምንበት ስለሆነ እንዲሁ በቀላሉ አሳልፌ የምሰጠው አይደለም።
"…ዛሬማ ዐማራ ማሸነፉ ሲረጋገጥ ሁሉም ከተደበቀበት ጎሬ ወጥቶ ተንታኝ፣ ተከራካሪ፣ ተሟጋች ሆኗል። ዛሬማ ዐማራ ነኝ ብሎ ደረቱን ነፍቶ በሀላል የሚናገረው የትየለሌ ነው። ዛሬማ ከፊት መስመር በመሰለፍ የድል አጥቢያ አርበኛ በመሆን መግለጫ ጭምር የሚያወጣው ምሁር ተብዬ የተማረ መሃይም ነፍ ነው። የትየለሌ መንጋ አሁንማ የዐማራ ፋኖ ፊትአውራሪ ነው። አንዳቸውም ግን ከፊቴ አይቆሙም። በዐማራ ፋኖ ትግል ላይ እንደኔ በመታመን፣ በጽናት፣ ቀንና ሌሊት በመጮህ ትግሉ እዚህ እንዲደርስ ያደረገ የለም ብዬ ስናገር በሙሉ አፌና በኩራት ጭምር ነው። ይሄን ስናገር ደረቴን ነፍቼ ነው። በኩራት ነው። ብጥርር፣ ጥብርር ብዬም ጭምር ነው። ውዳሴ ከንቱም አይደለም። ቢሆንም ግድ የለኝም። እና ይሄን መንግሥተ ሰማያት መግቢያ የጽድቅ መንገዴ ነው ብዬ ያስጀመርኩትን የዐማራ ፋኖ ትግል እስከመጨረሻው ድረስ መቃብር እስክወርድ ብቻዬን ባታልዮን ጦር አክዬ ከፊት እታገልለታለሁ። ነቀርሳውንም አጸዳለታለሁ እንጂ እዚህ ደርሼ ለሸታታ ግም የብአዴን የግም ድግሶች አሳልፌ አልሰጥም።👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …በወልቃይት በኩል በሱዳን በኩል አስወጥተን እንሸኝሃለን ብላችሁ ካለበት ስፍራ ደቡብ ጎንደር ድረስ አታላችሁ ወስዳችሁ አረመኔያዊ ተግባር ፈጽማችሁ ከገደላችሁት በኋላ ለጓደኛችሁ ለክርስቲያን ታደለ ደውላችሁ ተበቅለነዋል፣ ጎንደሬ እንዲህ ነው እያላችሁ የጨፈራችሁ ስኳዶች እረፉ። አይደለም ዘመነ ይሄም ያሰጋናል ብላችሁ አቢይ አሕመድን ለምናችሁ፣ ተማጽናችሁ ክርስቲያን ታደለን የመሰ ወንድማችሁን በጎጃሜነቱ፣ የማማር ጌትነት የሀገር ልጅ ስለሆነ ብቻ በወህኒ ቤት እንዲማቅቅ እያደረጋችሁ ያላችሁ ጎንደር አሰዳቢ ስኳዶች አደብ ግዙ። እኔ እጄ ላይ ያለውን ቪድዮ ከቁጥጥሬ ውጪ ሆኜ ከለቀቅኩት የሚተርፍ፣ ለንስሀም የሚበቃ የለምና እረፉ። ስኳዶች እረፉ። እነ ምስጋናው አንዷለም፣ እነ አያሌው መንበር እረፉ። አደብ ግዙ። ተናግሬ ያስቀረሁት የለም እና እረፉ። ኡጋንዳዎች እረፉ።
"…ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከወያኔ ጋር ፊት ለፊት ሲሟገቱ ጎጃም እና ሸዋ ወሎም ድጋፍ ሲሰጣቸው ጥቂት የጎንደር ብአዴኖች ነበሩ "ሸዋ ወደ ሥልጣን እንዲመጣ አንፈልግም" በማለት ፕሮፌሰር አሥራት በወያኔ እንዲገደሉ ምክንያት የሆኑት። አሁንም ቢሆን ሸዋን በማዳከም፣ ሸዋ ወደፊት እንዳይመጣ በማድረጉ በኩል በአንድ ወገን በእናቴ ወገን ጎንደሬ ነኝ የሚለውን እስክንድር ነጋን ሸዋ በመላክ፣ ሸዋንም በማደንዘዝ፣ ሸዋን በማበጣበጥ፣ ሸዋ ቀና ብሎ እንዳይሄድ፣ ደብረ ብርሃን እንኳ እንዳይገባ ጠፍራችሁ የያዛችሁ እናንት በእናት ዓለም ጎንደር ስም የምትነግዱ ጎንደር አሰዳቢ ነቀርሳዎች እረፉ። በመከታው ጦር ውስጥ የጎንደር ተወላጆች የበዙት ለምን እንደሆነ የማላውቅ ይመስላችኋል? ክፍለጦር፣ ብርጌድ የሚመሩ የጎንደር ልጆች ሸዋ መከታው ጋር ገብተው በአንድ ወገን ጎንደሬ ነኝ የሚለውን እስክንድርን እየጠበቁ፣ እየደገፉ እንዲቀመጡ ያደረጋችሁበት መንገድ የጠፋኝ ይምስላችኋልን? የሴራው ትብትብ የመፈቻው ቀን ስለደረሰ ከቀኑ በፊት ጦርነት አልገጥምም ብዬ ነው እንጂ አስቀድሜ እናንተን ማጋለጥ ጠፍቶኝስ ይመስላችኋልን? እረፉ።
"…የሸዋ ዐማራውን አቶ አሰግድ መኮንን በጎንደሬው አርበኛ መሳፍንት አንገብግባችሁ፣ አሰድባችሁ፣ አቃጥላችሁ አሳልፋችሁ እንደሰጣችሁት የማላውቅ ይመስላችኋልን? ኡጋንዳ ያለው የጎንደር ስኳድ ቡድን በመረጃ ቴሌቭዥን ላይ በሚያቀርበው ዜና በሸዋ የጋሽ አሰግድን ፋኖ፣ የእነ ኢንጂነር ደሳለኝን ተጋድሎ በዜና መልክ ይሠራልን? መግለጫቸውንስ ያነባልን? ጭራሽ በለጠ በቀደም "መንግሥት መሳሪያ የሚያቀብላቸው አሉ" ብሎ የእነ ኢንጅነር ደሳለኝን ፋኖ እንደመክሰስ ሲቃጣው አልነበረምን? ሸዋና ጎጃም፣ ሸዋና ወሎ እንዳይስማማ የጎንደር እስኳድ በወልቃይት የሰሊጥ ብር በሸዋ መከታው ማሞን በደቡብ ጎንደር ተወላጅ ነኝ በሚለው በእስክንድር ነጋ አማካኝነት ጠምዝዞ ይዞ የሚፈጸመውን ገመድ ጉተታ የማላውቅ ይመስላችኋልን? የእነ አሰግድ ጦር መከላከያን ሲመታ፣ ወደ ጫጫ ሲሄድ የመከታው ጦር እየተከተለ ከኋላቸው ጥይት ያርከፈክፍባቸዋል የሚባለውን ስሞታ ሳንሰማ ቀርተን ይመስላችኋልን? ለዚህ የቪድዮ መረጃ ሁላ አለኝ። ፋኖዎቹ ብሶታቸውን ሁሉ ሲናገሩ መረጃው አለኝ። እናም ስኳድ ሲባል እንደቀላል የምታዩ ሰዎች እንዳትሳሳቱ። ስኳድ በወልቃይት ገንዘብ መላውን የዐማራ ፋኖ ትግል ከአገዛዙ በላይ እያቀጨጨ ያለ አደገኛ ቡድን ነው።
"…ከልምድ እንደሚታወቀው እኔ ዘመዴ ጀምሬ ያላሳካሁት አንዳች ጉዳይ የለም። ከዘመነ ተሃድሶ ጀምሮ እስከዛሬ እስከአሁኑ እስከ ዐማራ ፋኖ ትግል ድረስ ክብሩን እሱ ይውሰድና ፈጣሪ አምላኬ እየረዳኝ ሁሉንም በዝረራ እያሸነፍኩ እዚህ መድረሴን ሁላችሁም ምስክር ናችሁ። አሁንም እንደዚያው ነው። ለሰሚና ለተመልካች ከባድ የሚመስለውን ይሄን የዐማራ ፋኖ ሾተላይ አካል ብቻዬን ልዋጋው፣ ልገታገተውም ፈጣሪዬን ይዤ በዕለተ ሥላሴ ቆርጬ ተነሥቻለሁ። ይሄን የዐማራ ፋኖ ትግል ማነቆ ማንቁርቱን ይዤ አፈር ከደቼም አበላዋለሁ። ማርያምን፣ አዛኜን እንኩትኩቱን ነው የማወጣው።
"…ተመልከቱ ብዙ ሰው ያልበላውን ነው የሚያከው። የጎንደር ስኳድ የፖለቲካ ቀመር ቀምሮ ነው የሚንቀሳቀሰው። እሱ ዋና ግቡ ሥልጣን ነው። በዚህ በተጀመረው የዐማራ ፋኖ ትግል የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ ጠንክሮ መውጣት ያሳስበዋል። ለወያኔም፣ ለአቢይም ተገርዶ የሚኖረው ብአዴናዊ እስኳድ አሁን በሚመጣው የዐማራ ፋኖ መንግሥት ሥልጣን አጣለሁ ብሎ ይሰጋል። እዚያው ጎንደር ያሉ የዐማራ ፋኖዎችን በአምሳሉ ቀርጾ መንቀሳቀስ ነው የሚፈልገው። ለዚህ ነው እንደ ትግሬዋ ወያኔ እና እንደ ኦነግ ኦሮሞው አጥንት እየቆጠረ ሥልጣን መቆናጠጥ የሚፈልገው። በጣም በተጠና መልኩ ነው የሚንቀሳቀሱት። በቀደም ዕለት እነ ዶክተር ምስጋናው አንዷለም በምስጢር ባዘጋጁት የዙም ውይይት ላይ እኔም በድብቅ ተገኝቼ ውይይቱን ስቀዳው ነበር። ጋባዥ ወዳጆቼን ከምር ከልብ አመሰግናቸዋለሁ። እኔ አኩርፈውኝ የቀሩ መስሎኝ ነበር ነገር ግን ስማ ብለው በሌላ ሀገር ስልክ እንድገባ አድርገው ስሰማ የነበረውም አሁን ለጀመርኩት ትግል ግብአት እንዲሆነኝ ፈጣሪ እንዳዘጋጀልኝ ነው የቆጠርኩት። በውይይቱ ላይ ተዉ ይሄ ነገር ጥሩ አይደለም ያሉትን ጎንደሬዎች ሚዩት እያደረጉ፣ የጥፋት መንገዳቸውን የሚያበረታቱላቸውን ደግሞ በአንፃሩ ጀግና ጎበዝ እያደረጉ የሄዱበትን የጥፋት ዕቅድ አሁንም መላልሼ መላልሼ እየሰማሁ እስቃለሁ። በተለይ " ጎንደር መራጭ ብቻ መሆን የለበትም፣ ጎንደር እንደ ጎጃም ተመራጭ ሆኖ መምጣት ነው ያለበት። ከዚህ በኋላ ምርጫ የሚኖር ከሆነ ራሳችሁ ተመራጭ ሁኑ እንጂ መራጭ አትሁኑ። ይሄን መስማት አንፈልግም" ብለው ለፕሮፌሰር ኢያሱ እና ለሰሎሞን አጠናው መመሪያና ትእዛዝ ሲሰጡ እየሰማሁ ነው ቀድቼ እያዳመጥኩ ስስቅ የምውለው። እናም ውድድር መብት ቢሆንም ባልበላውም ጭሬ ልበትነው ማለት ግን ነውር ነው።
"…እስክንድር ነጋ ፈንታ ጎጃሜ መሆኑን ዘመዱ ነኝ ያሉ ሰው ነግረውኛል። የእስክንድር ነጋ የአባቱ የነጋ ፈንታ እናት ህብሬ ምህረቴ ነው የምትባለው። የእስክንድር የሴት አያት ማለት ነው። እስክንድር እንኳን አያቱን ወላጅ አባቱን አያውቀውም። የእስክንድር እናት ወሮ በላይነሽ ዐወቀ እስክንድር ሦስት ዓመት ሲሆነው ስለተፋቱ አባቱንም በደንብ አያውቀውም። ዘመዴ ባለፈው እንዲህ የሚሉ አሉ ብለህ የእናቱ ሀገር ወለጋ ከተወለዱ ጉራጌ ቤተሰቦች የተገኘ ነው ብለው ሲያወሩ ሰምቻለሁ ያልከው የተሳሳተ መረጃ ነው። እናቱ በላይነሽ ዐዋቀ ደቡብ ጎንደር ሊቦ ከምከም ናት። ስለዚህ እስክንድር በአባቱ ጎጃም በእናቱ ደቡብ ጎንደሬ ነው። በእናቱ ወገን በኩል የተንቤን ትግሬነት ሊኖር ይችል ይሆናል ያሉኝ ሰዎችም ተገኝተዋል። ሀብታሙ አያሌው በቀደም ደማዊ ማንነትህ ጥያቄ ተነሥቶበታል እና መልስ ስጥ ሲለው "ዐማራነት በደም ብቻ አይደለም ታዲዮስ ታንቱ እኮ ወላይታ ቢሆንም በአስተሳሰቡ ዐማራ ነው" ብሎ የሸሸውም በምክንያት ነው ነው የሚሉት እኒሁ ታዛቢዎች።
"…ልብ በሉ እስክንድርን ድጋፍ የሰጠው ኃይል አብዛኛው በትውልድ ጎንደሬ የሆነው ነው። ከአቶ መሳፍንት ጋር እስክንድር የተማማለው በጎንደሬነት ነው። ባለፈው እስክንድር ጎንደር የሄደ ጊዜ ያረፈው የዶክተር አምሳሉ እናት ቤት ነው። ዶር አምሳሉ ከግንቦት ሰባት፣ እስከ ባልደራስ፣ ከባልደራስ እስከ ግንባሩ፣ ከግንባሩ እስከ ሠራዊቱ ድረስ የእስክንድር ነጋ የአሜሪካ ዶላር ሰብሳቢ ተወካዩ ነው። ሚኒሊክ ቴሌቭዥንን 👆 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍