zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ርዕሰ አንቀጹን ሴራ አፍራሽ አድርጌ እያመሰጠርኩት ስለሆነ በናታቹ፣ ባባታቹ ጥቂት ታገሱኝ እሺ…?

• ለደግነቱ ዐማራው ቀድሞ ባንኗል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ምድር ደም ባመጣው በደል፥ ከተማም በግፍ ተሞልታለችና ሰንሰለት ሥራ። ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁ ቤቶቻቸውንም ይወርሳሉ፤ የኃያላንንም ትዕቢት አጠፋለሁ፥ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ። ጥፋት መጥቶአል፤ ሰላምም ይሻሉ እርሱም አይገኝም። ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል። ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። ሕዝ 7፥ 23-27

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ዘወትር እሑድ በመረጃ ተለቭዥን በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው ሳምንታዊው መደበኛ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብራችን ከሁለት ወራት ቆይታ በኋላ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ይጀምራል።

• በዩቲዩብ 👉 https://www.youtube.com/channel/UCG2sR22rR_Zoe323jz0xtvQ?sub_confirmation=1

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው። ሜዳውም ፈረሱም ያው… ብልፅግና በጅምላ እየገደለ፣ ሕዝቡም እየተገደለ እስከመቼ ነው የሚቆየው?

"…የሰው ሞትና፣ ጭፈጨፋስ እንዲህ ይለመዳል?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የ7ተኛ ጨ ው 7ተኛ ንጉሥ አረመኔው አቢይ አህመድ የዘንድሮውን 666 6ተኛ ዓመት በአለ ሲመት በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ኦሮሙማዉ ዝግጅት ያደረገው ከመጋቢት 7/2016 ዓም ጀምሮ እስከ በአለ ሲመቱ ድረስ ሪፐብሊካን ጋርድ የተባሉት ልዩ ኮማንዶዎች የተሳተፉበት ልየ የተባለ ኦፕሬሽን በማካሄድ የዐማራ ፋኖን በመደምሰስ ማክበር ነበር የታቀደው። መረጃው ለፋኖ በመድረሱ ፋኖ ከመጋቢት 7 አስቀድሞ መጋቢት 5 ጀምሮ ኮማንዶውን እንደ ከፍት ነዳው። ዘመቻ ውባንት ተቀጣጠለ።

"…የመጀመሪያው ዕቅድ ሲከሽፍ መከላከያው ከመጋቢት ከ20 እስከ 23 ያጥቃ፣ አየር ኃይሉ በድሮን ታግዞ ፋኖ ይደብደብ ብለው ወስነው ወደ ተግባር ገቡ። በነገራችን ላይ ድሮን አለ ጥይቱ ቦንቡ ብዙ ሺ ዶላር ስለሆነ እጥረት አለ። ፋኖም ከድሮን ጥቃት ራሱን ሰውሮ መከላከያውን አፈር ደቼ አበላው። በአለ ሲመቱም ደረሰ። የተጠበቀውም ድል ጠፋ። ልዩ ኮማንዶውም የተለያዩ ምስኪን ሰዎችን በፎቶ አስደግፎ ፋኖ ናቸው፣ ተማርከው ነው ብሎ ቢያቀርብ ማን ይመነው? እኛም ከዋዜማው ጀምሮ በአለ ሲመቱ መክሸፉን ዐወጅን። አቢይም፣ አዳነችም ተደበቁ። እንኳን አደረሳችሁ ሳይል፣ ድግስ ደግሶም ሆዳም አርቲስቶችን ሳያበላም ቀረ።

"…በአለ ሲመቱ ካለፈ በኋላ አቢቹ ነገሩን ሲገመግም ተዋርዷል። ስለዚህ በአለ ሲመቴ ይደገም አለ። በሁሉም ክልሎች ይደገም። በተለይ አዲስ አበባ ላይ ይደገም አለ። የፈለገ ሕዝቡ ቢጠላኝ አደህይተን በሆድ የያዝናቸው ሴፍቲኔታሞች አሉ አይደል እንዴ? እነርሱ ይውጡ አለ። ተገደው ይውጡ ተብሎም ተወሰነ። በውሳኔውም መሠረት ከ119 ወረዳ፣ ከ11 ክፍለከተማ የተውጣጡ 30×119= 3570 ደንቦች፣ 37×119= 4403 የወረዳ አመራሮች፣ 100×119=11900 ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች፣ 25×119=2975 የወረዳ ቢሮ ባለሙያዎች፣ 50× 119= 5950 የኦሮሞ ብልፅግና አባላት፣ 35×11=385 የክፍለ ከተማ አመራሮች፣
40×11=440 የክፍለከተማ በለሙያዎች፣ 1500 የፖሊስ አባላት፣ 3ሺ መሄጃ የሌላቸው ከቀበሌ በማቃጠር ያማይጠፉ ቀውላሎች። በጠቅላላ 34,303 ሰው መሳይ በሸንጎ ቡልጉዎች በሰልፉ ላይ በግዳጅ እንዲገኙ ተደርገዋል።

"…በአሉ ላይ ላለመገኘት አብይ አህመድ አዳነችን ይዞ የዘር ጭፍጨፋ እንዴት እንደሚካሄድ ለማሳየት ለማስቀጸል ወደ ሩዋንዳ ይዟት በረረ። ሽመልስ አብዲሳ በፍቼ ጨመብላላ ላይ ለመገኘት ወደ ፊት ኦሮማይዝ ወደምትደረገው ሲዳሞ በረረ። አዲስ አበባ ማንቀረ? የአዳናች የፈረስ ስም ዣንጥራር አባይ ብቻውን ቀረ። በዓሉ ላይ ግዳጅ ብቻ መስሎ ሕዝቡ በጨፈገገ ፊት እንዳያከብር ምን ይደረግ ተባለ? በዚህም ተወሰነ። ቢያንስ ኦሮሞ እየጨፈረ እንዲያከብር ምን እናድርግለት ብለውም ተጨነቁ። ተጨንቀውም አልቀሩ ኦሮሞን ሊያስደስተው የሚችለው፣ በአሉን በደስታ እየጨፈረ እንዲያከብር የሚያደርገው የፋኖ መደምሰስ ነበር። እርሱ አልተሳካም። ስለዚህ ለጫካው ሸኔ ሚሽን ይሰጠው ተባለ። ትእዛዝም ተሰጠው።

"…ኦሮሞ በቅዳሜው ሰልፍ ላይ እየጨፈረ እንዲወጣ በዐማራ ክልል የሚደመሰስ ፋኖ ከጠፋ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዐማሮች ይታረዱለት ተባሎም ተወሰነ። ለዚሁም የብራኑ ጁላ መከላከያ ሠራዊት ተብዬው የሚገደሉ ዐማሮችን ቦታ ለይቶ፣ ለገዳዩ ኮሬ ነጌኛ ኦነግ ሸኔም አመቻችቶ እንዲወጣም ተደረገ። ዕጣውም በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ልዩ ስሙ ቆታ በተባለ አካባቢ በሚኖሩ ዐማሮች ላይ ወደቀ። በዚሁ ምክንያት ኦነግ ሸኔ በተሰጠው መመሪያና ትእዛዝ መሠረት የአዲስ አበባ ዲሞግራፊያ ኦሮሞ በደስታ እየጨፈረ በአለ ሲመቱ ላይ ይገኝ ዘንድ በአመያ 43 ዐማሮች ታረዱለት። የሚገርመው ከጥቃቱ ተርፈው የሚሰደዱትን የትም አትሄዱም በማለት መከላከያው እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አግደው ያዙት። እንደምንም ብለው ራሳቸውን የተከላከሉ፣ ኦነግን መክተው የያዙም ዐማሮች በመከላከያው ተወቀሱ፣ ታሰሩ።

"…በአመያ 43 ዐማሮች ተጨፍጭፈው የኦርቶዶክስ ዐማሮቹ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ዳርጌ በሚገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የሙስሊም ዐማሮቹም በዚያው በመስጊድ መፈጸሙን የአዲስ አበባ ዲሞግራፊያ ኦሮሞዎች በሁለተኛዉ በአለ ሲመት ብዙም ባይሆን በዐማራዎቹ ጭፍጨፋ በጥቂቱም ቢሆን ደስ ብሏቸው በአለ ሲመቱን በደስታና በጭፈራ በተሻለ ከመጋቢት 24ተ በተለየ መልኩ አከበሩ። እነርሱ ዐማራ በመጨፍጨፉ እዚህ ሲጨፍሩ እዚያ እነርሱ ክልል በሰሜን እና በምዕራብ ሸዋ ዞኖች እና ወረዳዎች ውስጥ የፈጣሪው የክፉኝ ወረርሽኝ ተከስቶ በሰሜን ሸዋ ዞን ማለትም በኩዩ፣ በወረ ጃርሶ፣ ሂዻቡ አቦቴ እና ደገም ወረዳዎች እንዲሁም በምዕራብ ሸዋ ዞን ደግሞ እንደ ግንደበረት፣ አድአ በርጋ እና ሜታ ወልቂጤ ወረዳዎች የህፃናትንና የወጣቶችን ሕይወት እየረገፈ መሆኑን ራሳቸው መናገር ጀምረዋል።

"…በኢትዮጵያ የዜጎች መጨፍጨፍ እና መታረድ ተለምዶ የሚደነግጥ ሰው ከቀረ ቆይቷል። በተለይ ተጨፍጫፊው ዐማራ ከሆነ፣ የኦሮሞም ኦርቶዶክስ ከሆነ ብዙም አያስደንቅም። የኢትዮጵያውያን ጆሮ ሞት እንዲለምድ አድርጓል አቢይ አሕመድና ብልፅግናው። አንድ ወረዳ ቤት ሲፈርስ ገሚሱ እቃ ለማውጣት፣ ገሚሱ እቃ ለመስረቅ ከመራኮት በቀር ቤቴ ፈርሶ የት እገባለሁ ብሎ የሚያስብ ሰው ጠፍቷል። መከራን ከመልመዱ የተነሣ የመከራ ዜና የሚያይበት ዓይኑ፣ የሚሰማበት ጆሮውም ደንድኗል። ድሮ አንድ ሰው ሞተ ሲባል ደንግጦ 2 ሊትር እምባ የሚያፈሰው ኢትዮጵያዊ አሁን ደንገጥም አይል? ሰዎች ታገቱ ሲባል ስንት ሰዎች አይልም? ለምን የት አይልም። የሚጠይቀው ስንት ብር ክፈሉ ተባሉ ነው? ሰዎች ተገደሉ ሲባልም የት አይልም ስንት ሰዎች ነው የሚለው? 50፣ 100፣ 300 ስትለውም አይደነግጥም። ደግሞስ 1ሚልዮን ሰው በተጨፈጨፈበት ሀገር 300 እና 3ሺ ሰው ምንማለት ነው? አይደነግጥም ሰዉ። እነ አቢይ አሕመድም፣ እነ ሽመልስ አብዲሳም የሰዉን ሞት መለማመድ አይተው ተጠያቂነት ስለሌለ፣ የሚጠይቃቸውም ስለሌለ ዘና፣ ፈታ እያሉ ይጨፈጭፉታል፣ ያስጨፈጭፉታልም።

"…ለምሳሌ መጋቢት 25/2016 ዓም ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ጆር ወረዳ ውስጥ ብቻ ከ50 በላይ ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለው ተገኝተዋል። ገዳዮቹ እንደ ኦሮሚያ ህፃናትን ሳይገድሉም አግተው ወስደዋል። ቁጥሩ ብዙ የሆነ ቤቶችንም አቃጥለዋል። በተለየ ሁናቴም ግድያውን የፈፀሙት ታጣቂዎች ናቸው አስቀምጠው የሄዱት የተባለ ጽሑፍም በወረቀት ተጽፎ ተገኝቷል። "እኛ ኑዌሮች ነን" የሚል። አሁን በወረዳው ሙሉ በሙሉ የኔትወርክ አገልግሎት ተቋርጧል፣ አስከሬን በየጫካው ስለሞላ እየተለቀመ በመቀበር ላይ ነውም ተብሏል። አቢይ መልአከ ሞት ነው። ሞቱም ይቀጥላል ነው የሚለው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሺ ሰው ሞቶ መሞቱ አይሰማም። ይታፈናል። ዐማራ ክልል 1 እስላም የሞተ ጊዜ ነው ምድር ቀውጢ የሚሆነው። አኬር መገልበጡ እንደሁ አይቀር።

"… ጀዋር ወደ ኢትዮጲያ ሲገባም የተሰቀለለት ሰው ነው። ኦነግ ኢትዮጵያ ሲገባም የታረደለት በሬና በቡራዩ ሰው ነበር። የፓርላማ ስብሰባ በመጣ ቁጥር አቢይ አሕመድ ጥያቄ እንዳይበዛባት አጀንዳ ለማስቀየሪያ እያለ የሚያሳርደው ዐማራውን ነው። ዐማራው ሲታረድ የኦሮሞ መጅሊስ ራሱ ጮቤ ነው የሚረግጠው። መቶ ሁለት መቶ የዐማራ እስላሞች በኦሮሚያ ሲታረድ ባላየ ባልሰማ ጮጋ የሚለው የኦሮሞ እስላም በዐማራ ክልል በእለታዊ ግጭት 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

"…ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

"…ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል። እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥" ማቴ 24 ፥ 3-15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በነገራችን ታች…

"…ይህቺ ፊቷን ዚግዛግ፣ ዓይኗን እዚያና እዚህ፣ ከንፈሯን ማዶ ለማዶ ግራቀኝ እግር አስመስላ ልትደባደብ የተጋበዘችው የመምር ግርማ ጋንጩር ፊት የመሰለች እህታችን ወይም እናታችን ግን ማንናት? ምንድንስ ናት…?

• ገርማኝ እኮ ነው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጃንደረባውን ትውልድ ልጠይቀው ነኝ…!

"…የጃንደረባው የስልቡ ትውልድ መሪው ጠዋት ያለሜካፕ ሲወጣ ይህን የሚመስለው አጅሬ ፀረ ሰንደቅ አላማው ሄኖክ ኃይሌ ምን አስቦ ነው "ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ነን" የሚል ማስታወቂያ ማስነገር የጀመረው?

"…ጣልያን ሮም ደርሶ ተጠምቆ ከተመለሰ በኋላ የወሴ መዓት ሰብስቦ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ሊውጥ የተነሣው ዘንዶ ከዐውደ ምህረት እና ከነጠላ ላይ ሰንደቅ ዓላማችን እንዲነሣ፣ እንዲፋቅ ካደረገ በኋላ ጠፍቶ፣ ጠፍቶ ተደብቆ ሲያበቃ አሁን ቀሲስ ዶር አንዷለም ዳግማዊ ዳላስ ቴክሳስ ሚካኤል ቪዛ አስጨርሶለታል ከተባለ በኋላ "ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ነን" ማስባል የፈለገው ለምንድ ነው?

• ጥያቄው ኢትዮጵያን ለምን አወጣት?

"…በቀላሉ እናንተ ባለ ማዕተቦችን ብጠይቃችሁ ምን ብላችሁ ነው የምትመልሱልኝ።

ሀ፦ "ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ነን"
ሁ፦ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ…

• ሄኒሻ… እረፍ…! ተደበቅ ብዬሃለሁ…!

"…ማሳሰቢያ የትግሬ ተወላጅ የሆንክ ደፋር ለሄኖክ ኃይሌ ጥብቅና ለመቆም አስበህ ወደ ፔጄ ብትመጣ ቆምቼጬ እንደምለቅህ ከወዲሁ እወቅ። ቀልድ የለም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ኦሬክስ…!

"…የለውጡ ፍሬ ተጠቃሚ ኦሬክሶች እነሆ ስድስተኛ ዓመት የነውጥ በዓላቸውን በዚህ መልኩ እያከበሩ ነው። ባለ ጊዜ ጀቲ ነዋምቲ ጀርቲ አለ አዝማሪው።

"…የሚገርመው የአዳነች አበቤ የፈረስ ስም ነው የሚባለው ዣንጥራር ዓባይ እንዴት በአማርኛ የሚያወራውን ቢሰሙት ነው ደፍሮ በበአሉ ላይ የተገኘው? ብአዴን ግን በኦህዴድ በዓል ላይ የምን ማቃጠር ነው?

• ይሄ ጭፈራ እና ንቀት ለትግሬዎቹም አልበጀ የሚሉ አንዳንድ መተርጉማንም አሉ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…

"…ኤሌ ኤሌ ያባ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እናንተ፦ እኛ ኃያላን በሰልፍም ጽኑዓን ነን እንዴት ትላላችሁ?” ኤር 48፥14

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እንኳን እሱን ራሳቸውንም ማዳን አይቻላቸውም። መትረፊያም የላቸው። አለቀ።

"…የነገው የግዳጅ ሰልፍ የሽኝት ነው።

አትሸኙትም ወይ
አትሸኙትም ወይ
መደየሙ አይደለም ወይ… 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በነገው የዐቢይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዲህ ዓይነት ቃለመጠየቅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ራሳቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ነወሪዎች ገልጸዋል። የማሽቃበጣችን ጥግ እዚህ ድረስ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በዲሲም ተጀምሯል…🔥🔥🔥

"…ጠዋት በርዕሰ አንቀጼ ላይ የወቀሳ የጭቃ ዥራፌን ያሳረፍኩበት የዲሲ ግብረ ኃይልም ልክ እንደ ለንደኑ ፋኖ በአሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመገኘት በግፍ ለሚጨፈጨፉት ወገኖቹ ድምፅ በመሆን አጋርነቱን አሳይቷል።

"…በአሜሪካን ተቃውሞ ያልገጠማቸውን መነኩሴ በለንደን የዐማራ ፋኖዎች በጨዋ ደንብ በመቃወም አጠቃላይ የሥርዓቱን ምሰሶዎች መነቅነቅ ጀምረዋል።

"…በተለይ በአሜሪካ ሥርዓቱና የሥርዓቱ አገልጋዮች ላይ እንዲህ ያለ ተቃውሞ ከበዛ፣ ለእረፍት፣ ለአስቤዛና ልብስ ሸመታ ጭምር፣ ለመዝናናት፣ ለማመንዘርም ወደ አሜሪካ በሚመላለሱ ብልጽግናዎች ላይ ፀሐይ ትጨልማለች።

"…ዳንኤል ክብረት ለኦሮሙማው ብልጽግና ከዋለው ውለታ ዋነኛው በአሜሪካ የነበረውን ተቃውሞ ፀጥ ማሰኘቱ ነበር። ባለ ሥልጣናት ከቦሌ አየር መንገድ ሲነሡ ጀምሮ አሜሪካ ሲደርሱ የሞቀ የተቃውሞ አቀባበል የሚደረግላቸው ከሆነ የሚከተለውን መጠበቅ ብቻ ነው።

"…አሁን አሜሪካ የመሸገው ዋነኛው ኃይል ያለው ሌላ ቦታ አይደለም። ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻ ነው። በአሜሪካ የምትገኘዋ ቤተ ክርስቲያናችን መሪዎች አብዛኛዎቹ ከዐቢይ አሕመድ እኩል እንደ አራጅ የሚቆጠሩም ናቸው። ትንፍሽ እንኳ አይሉም። ዶላር መሰብሰብ ብቻ።

• ብራቮ የዲሲ ግብረ ኃይሎች…!✊✊✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…በርዕሰ አንቀጹ ላይ ቀረ የምትሉት ካለ ትጨምሩና የተሟላ ታደርጉት ዘንድ የአስተያየት መስጫውን ሰንዱቅ እከፍትላችኋለሁ።

• እህሳ… የለንደን የዐማራ ፋኖን እንዴት አያችሁት…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የሚፈለገው 1 ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። ከምስጋና በኋላ እንደተለመደው ቀጥሎ የሚቀርበው ርዕሰ አንቀጻችን ነው።

"…በዛሬው ርዕሰ አንቀጼ ላይ ደግሜ ይሄ ጦሰኛ "ይዞ ሟች" ሰውዬ ከሩዋንዳ መልስ እንደ አዲስ አበባ በአዳነች አቤቤ በኩል፣ እንደ በኢትዮጵያ አጠቃላይ በኩል በራሱ በእቡይ አመድ በኩል እንደ ሀገር ስለተደገሰልን አጠቃላይ የጅምላ እልቂት ድግስ ቀኝ ትከሻዬን የሸከከኝን ነገር መጻፍ አማረኝ። አማረኝናም እናንተን ማስፈቀድ ፈለግኩ።

"…ቀጥሎ እንደ ሀገር በተለይ በዐማራ ክልል ራሱ አገዛዙ የእምነት ካርድ ስቦ ተነሥቷል። ጉዳዩ አደገኛ ነው። መቆሚያ ድንበርም የለውም። ከተሸነፍክ መልቀቅ እንጂ ማጫረስ ለማንም አይበጅም። ማቆሚያም የለውም።

• ልጽፍ ነኝ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አላችሁ አይደል…?

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉማ

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ቆይ ግን እኔምለው… ሁሉን ሰው ወታደር አድርገውት ማን አርሶ እንደያበላቸው ነው የሚፈልጉት…? ቦንቦ በቆሎ፣ ጥይቱ ባቄላ መስሏቸው ይሆን እንዴ…?

• አሁን ይሄ ገበሬ ከማን ጋር እንዲዋጋ ነው እንዲህ በሥራ የደረቀ ወገቡን በስፖርት የሚያንቋቁበት…? እህዕ ምን ጉድ ናቸው?

"…በዛሬው የ2:00 ሰዓቱ የመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ ላይ የቀጥታ የስልክ ውይይት ነው የሚኖረን ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍

"…ወይም በሴራ ሁለት እስላሞች ሲሞቱ ነጠላ ዘቅዝቆ፣ ዐዋጅ አውጆ፣ ሀገር ምድሩን አደበላልቆ፣ የሟች አስከሬን አሸክሞ፣ ከተማ ለከተማ ሲያዞር ውሎ ፖለቲካ ሠርቶ፣ ፋኖ ነው የገደለው አስብሎ ይቀብራል። በኦሮሚያ የሚጨፈጨፉትን ዐማሮች ግን ራሱ መከላከያውና ፖሊስ በግሬደር፣ በአንድ ጉድጓድ ይቀብራል። ልቅሶ መቀመጥም ይከለክላል።

"…በዚህ ያልረካው አቢይ አሕመድ በአለ ሲመቴ በዋና ዋና ከተሞች ይከበርልኝ ብሎም አዟል። ደሴና ኮምቦልቻ ዝግጅት ላይ ናቸው። በተለይ በኮምቦልቻ ከትናንት ጀምሮ አብይን ደግፋችሁ ውጡ እያሉ ቤት ለቤት እየዞሩ እያስፈረሙ ነው። ቁጠባ ሚባለው ሰፈር ላይ አልፈርምም ያሉ ዜጎች ወደ ዘብጥያ መውረዳቸውም ተሰምቷል። ኮምቦልቻ ነገ ሰኞ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ በሰልፉ ላይ ለማይገኙ የቀበሌ ጥቅማ ጥቅም አታገኙም እያሉም እንዳለ ተሰምቷል። አርባ ምንጭ 7 ሰዎች ሰልፍ ወጥተው አክብረውለታል። በጉምዝ 23 ሰዎች ወጥተው አክብረውለታል። አሳይታም እንደዚያው የአፋር ፖሊስ መንገደኛ ሰብስቦ ፎቶ ተነሡ ብሎ በማስገደድ እያከበሩለት ነው። ትግራይ በሌብነት ታሥሮ የተፈታውን ክንፈ ዳኘውን ፈንዲሻ እየበተነች ሌላ ሰልፍ ላይ ናት። የጦርነት ዝግጅት ሰልፏም እንደተጠበቀ ነው።

"…እየታዘባችሁ…! እየተሰለፋችሁም…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…1ሺ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ እስኪጽፍ ድረስ ወደ ሌላ ጦማር መጦመር እንደማልገባ ይታወቃል። አመስጋኙ ከፈጠነ እፈጥናለሁ፣ ከዘገየም እዘገያለሁ። 1ሺ አመስጋኝ እስኪገኝ የምጠብቀው መጠበቅ ዛሬም እንደ ወትሮው 1ሺ ሰው እግዚአብሔርን በማመስገኑ እኔም ወደ ቀጣዩ መርሀ ግብራችን አመራለሁ።

"…በዚህ እንደ ቴሌቭዥን ምርጥ መርሀ ግብር ተወዳጅ፣ አዝናኝ፣ ቁምነገር፣ መረጃ በምናገኝበት የቴሌግራም መንደራችን ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ስለ አረመኔው ጨፍጫፊ በዓለ ሲመት የተመለከተ ነው።

• እህሳ…ርዕሰ አንቀጹን አንብቦ የራሳችሁንም ሓሳብ ለማካፈል ዝግጁ ናችሁ? እስቲ አንድ መቶ ያህል ጓደኞቼ ዝግጁነታችሁን ግለጡ።

• ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ቆይ ግን የዛሬው ሰልፍ "የቀበሌ እናቶች ቀን" ነበር እንዴ…?

• ወንዱ ሁላ የት ሄዶ ነው…?

• ሴት ሲበዛ ካቤጅ… ይል ነበር አጎቴ ሌኒን…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከሞት ባሻገር…

"…እውነት ነው በአክሱም ጽዮን፣ በማርያም ደንገላት፣ በማኅበረ ዶጔ አብያተ ክርስቲያናት በራፍ በግፍ ለተጨፈጨፉ ምእመናን ወዘተ ሰማእትነት የተቀበሉ ክርስቲያኖች በሙሉ በረከታቸው ይደርብን። መታሰቢያም ይገባቸዋል።

"…ደጋግሞ ለትግሬ ሞት የጻፈው ጃንደረባው ጸሐፊ ምነው በጎጃም መርዓዊ፣ በወሎ፣ በደሴ፣ በሸዋ፣ በጎንደር፣ በዝቋላ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በጋምቤላ፣ በጉምዝ በግፍ ለተገደሉትስ?

"…ፌስቡክ ገፁ ለትግሬ ጦርነት ስብከት ሲጠቀምበት የነበረው ሰው አሁን ለዐማራው ሲሆን ምን ዋጠው?

• እኔ እኮ አንዳንዴ የማበዛው ነገር ግርርም ይለኛል። አሁን በዚህ ደግሞ ምን አገባኝ እና ነው የምበጠረቀው?

• በሉ ወደ ዛሬው ሰልፋችን እን Go…🚶‍♂‍➡️🚶‍➡️🚶‍♂‍➡️

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ደግሞ እንደፈረደብኝ ጥያቄ መጠየቅ አማረኝ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ያልገባኝ ነገር…

"…ኦሮሙማዎቹ አዳነች አበቤና አቢይ አሕመድ ሲወደሱ ለዋሉበት እና እነሱም አወዳሽ፣ አሸርጋጅ ሰልፈኞቻቸው የሴፍቲኔት ተጠቃሚ እናቶች፣ የጽዳት ሠራተኞች፣ የፓርኪንግ ሠራተኞች፣ የቀበሌ፣ የወረዳና የጤና ጣቢያ ሠራተኞች፣ ያውም በግድ የወጡ መሆናቸውን ዐውቀው፣ ደግሞም ነቀዋቸው ቀርተው ሳለ ይሄ በዐማራ ኮታ ስም የተመረጠ፣ ሁሌ ምክትል ዣንጥራር ዓባይ ምን ልሁን ብሎ ነው በቦታው ተገኝቶ የሚደሰኩረው።

"…ለውጡ የዓቢይ እና የአዳነች ከሆነ፣ ለውጡን ለማምጣት ከአቢይና ከአዳነች በቀር ተሳትፎ ያደረገ ሌላ ሰው ከሌለ፣ የለውጡ አመራሮች ሊያመሰግናቸው አደባባይ ከወጣው ሕዝብ ፊት መቆም ካፈሩ፣ አሽከር ዣንጥራር ዓባይ ምንአባቱ አግብቶት ነው…? ብዬ አፌን ሞልቼ ልናገር አልኩና እንደምንም ብዬ ታግዬ ከአፌ ላይ የመለስኩት። ቱ…! አሳስቶኝ ነበር።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…✍✍✍

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሰልፉ የግዳጅ ነው…!

"…በነገው ዕለት መስቀል አደባባይ አቢይ አሕመድን ለመደገፍ ተብሎ የተጠራው ሰልፍ የግዳጅ ሰልፍ መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

"…የሰልፉ አዘጋጆች የፈሩት ሰልፉ ላይ በድንገት ሆድ የባሰው ሕዝብ ነፍሱን ይማረውና እንደ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ድንገት በሰልፉ መሃል…

• Abiy አhimeድ is Killer
• Abiይ Aህmed Is Genocider
• አቢy አhiመድ is Terrorist

"…የሚል መፈክር ይዘው እንዳይወጡ የፈሩ ይመስላል።

• አዲስ አበባ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ፍትሕ ከጠፋ
• ርትዕም ከጠፋ
• ሕግ ከሌለ
• ዘራፊ፣ ሌባ፣ ቀማኛም ከበዛ
• የዘር ጭፍጨፋው ላይ የቤት ማፍረስ፣ ማፈናቀል፣ ዜጎችን ያለ ሕጋዊ መሠረት ወደ ወኅኒ ወደ ዘብጥያ ማጋዝ ከበዛ፣ ሥራ አጥነት ከተስፋፋ፣ ከቦታ ቦታ በነፃነት መንቀሳቀስ ከተገደበ፣ መማር ማስተማር፣ ነግዶ መሥራት ከተከለከለ፣ ሁሉ ቀማኛ፣ ሁሉ አለቃ ከሆነ፣ አገዛዙ አፓርታይድን የሚያስንቅ አረመኔ ነፍሰ ገዳይ ከሆነ፣ የሆነ ቀን ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ ሕዝብ ያለምንም ቀስቃሽ እነደ ሱናሚ ሞልቶ ፈስሶ አደባባይም ወጥቶ አገዛዙን እንደ ሲሪላንካው መንግስት እንክት አድርጎ ያለማባያ አጣጥሞ ቆረጣጥሞ ይበላዋል።

• የራበው ሕዝብ የጠገበን መንግሥት ቀርጥፎ መብላት ሕጋዊም፣ መጽሐፋዊም ነው። አለቀ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዘር ጭፍጨፋ መረጃ

"…መጋቢት 26/2016 ዓም ከለሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ልዩ ስሙ ቆታ በተባለ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 43 ንፁሃን ዐማራዎችን የአረመኔው አቢይ አሕመድ እና ሽመልስ አብዲሳ የዘር ማጽጃ ማሽን ጨፍጭፎ አድሯል።

"…የተጨፈጨፉት ዐማሮችም የቀብር ሥርዓታቸው በምትመለከቱት መልኩ ትላንትና ዳርጌ በሚገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ተፈጽሟል።

"…ኦነግ ሽሜዎቹ የአስከሬኖቹ መነሣት እና መቀበር ቆጭቷቸው የቀረውን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ተመልሰው ቢመጡም የኦሮሚያ ፖሊስ ሸሽቶ ሕዝቡን ለማስጨፍጨፍ ቢያሴርም ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ ያሉት የአካባቢው ማኅበረሰብ ተደራጅቶ በመጠበቅ ከሸኔ ጋር ሲታኮስ አድሯል።

"…በኅበረተሰቡ ተደራጅቶ ሸኔን መክቶ መመለስ የተበሳጨው የኦሮሙማው መንግሥት የሽመልስ አቢይ አህመዱ የብልፅግና መንግሥት ራሳቸውን በተከላከሉት ዐማሮች ላይ ከመሳሪያ ገፈፋ እስከ እስራትና ግድያ የሚደርስ ቅጣት ሊፈጽምባቸው እየዛተ መሆኑም ተሰምቷል።

"…ይሄን የመሳሰለ ዘግናኝ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በለንደንና በዲሲ የሚገኙ ዐማሮችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሲቃወሙት በሸገር ሲቲና ነገ ደግሞ በመስቀል አደባባይ የአዲስ አበባ ነዋሪ የብልጽግና ደጋፊዎች ለጨፍጫፊው አቢይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ለመስጠት መወሰናቸውም ተነግሯል።

• ነፍስ ይማር…! ዐማራ ማልቀስ የለም። 😭😭😭 የእንባ ኢሞጂ አትለጥፉ። ነዝግቡት፣ ለመከላከል በያላችሁበት ወጥራችሁ ተደራጁ። የገዳይ ገረድ፣ አቃጣሪም አትሁኑ። ፋኖን እርዱ አግዙ። መፍትሄው መመከት፣ መደራጀት፣ ማነከት ብቻ ነው። ለቅሶ መፍትሄ አይሆንም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሌላ ሰበር ዜና አለኝ። ከዲሲ ግብረ ኃይል…! ያዝ እንግዲህ… ተቀጣጠለ በለው…🔥🔥🔥

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍

"…እነሆ በፊት ኦሮሞ ጳጳስ፣ ቄስ ዲያቆን የሌለ ይመስል ኦሮሞ ኦሮሚኛ የሚናገር ጳጳስ፣ ቄስ ዲያቆን ያስፈልገዋል ብለው ከቀወጡ በኋላ በኦሮሞ ኮታ የተሾሙት በሙሉ ኦሮሚያ እንደመሄድና ሕዝቡን እንደማገልገል አዲስ አበባና አውሮጳ፣ አሜሪካ ካልተመደብኩ ብለው ጎፈሉ፣ አመፀውም ተቀምጠዋል። ከእነዚያም መካከል ይሄ ሳህለ ማርያም ቶላም አንደኛው ነው። የአቡነ አረጋዊን ሞት ተከትሎ ነው ሳህለማርያም ቶላ እንግሊዝ የተመደበው። የሚገርመው በእንግሊዝ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ካልተቋቋመ ብለው የቀወጡት ኦነጎች ይሄን በኦሮሞ ስም የተሾመና የተላከ ጳጳስ አልተቀበሉትም። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ኦነጎች ጴንጤና እስላም ስለሆኑ ኦርቶዶክስን ለመበጥበጥ እንጂ ለመቀበል፣ ለመደገፍ አይፈልጉም። እናም ይሄ ንፁሕ ኦሮሞ የተባለን መነኩሴ የዐማራ ካህናት እንዲቀበሉት፣ የኦሮሞ ዲያቆናት እንዲያጅቡት ተደረገ።

"…የለንደን የዐማራ ፋኖዎችም ጳጳስ ተብሎ የሄደውን ንፁሕ ኦሮሞ ጥያቄ ለመጠየቅ ሄዱ። ነገር ግን ሴትየዋ የምትሆነውን ተመልከቱ፣ ቄሶቹና መነኮሳቱ፣ ዲያቆናቱ ምድር ጠበበቻቸው። ሴቷ ግን ባሏ የተጠየቀ ይመስል ጎፈላች። በዲሞክራሲ ሀገር ኖራ ዲሞክራሲ የማይገባት ሃዸ ሲንቄም ሆነች። በኢትዮጵያ እንደለመደችው በለንደንም ተቃዋሚን ቢቻላት አርዳ፣ ወይ አንቃ ለመድፋት ተጣደፈች፣ ተፍጨረጨረች። የለንድን የዐማራ ፋኖዎችም ተልእኮዋ ስለገባቸው የበሰሉ ናቸውና እስከመጨረሻው በዲሞክራሲያዊ መንገድ፣ የሀገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት በጨዋ ደንብ ጥያቄአቸውን አቀረቡ።

"…እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው የብልጽግና ሥርዓትን የሚደግፍ ቄስ በለው ጳጳስ ከእንግዲህ በምእመናን ዘንድ ምንም ቦታ የለውም። በአሜሪካ ያለው የዐማራ ፋኖ ፈሪ፣ ሽንታም፣ ቅዘናም፣ መስሎ አዳሪ ቢሆን እንኳ በለንደን ያለው በሀገረ እንግሊዝ እግዚአብሔር ያስነሣው ፋኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሬት ላይ ካለው ፋኖ እኩል ታላቅ ጀብዱ ይፈጽማል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ቄሶቹም የደም ነጋዴዎች መሆናቸው ታየ። በምእመናን ገንዘብ በሀገር ቤት ፎቅ የሠሩት እነ ቄስ ግርማም ቀድሞ ከወያኔ ጋር፣ አሁን ደግሞ ከብልጽግና ጋር ሆነው ተሰልፈው የምእመናንን አእምሮ አደሙ። ቆይ የት ሊያስቀድሱ ነው? ተቃውሞው መብት ነው። እንዴት ሊያደርጉት ነው ይሄን በጥባጭ ወደ እንግሊዝ የላኩት።

"…የለንደን ፋኖዎች ግን የፍርሃትን የእንቁላል ቅርፊት ሰብራችሁ ስለወጣችሁ ክበሩልኝ። ብዙ ተባዙልኝ፣ ኢትዮጵያ ውለታችሁን አትረሳም። የደም ነጋዴዎችን እረፍት ማሳጣት ጽድቅ ነው። መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ ነው። ይሄ ከምንም ጋር አይያያዝም። አቡነ ኤርሚያስ እንዳሉትም አይደለም። ከሥርዓቱ ጋር ተባብሮ ዜጎችን የሚያሳርድ፣ መነኮሳትን የሚያስጨፈጭፍ ማንኛውም አካል ከተጠያቂነት አያመልጥም። በርቱ…!

"…ከ30 ደቂቃ በኋላ እመለሳለሁ። እስከዚያው ኮመንታችሁን ጽፋችሁ ጠብቁኝ። በወለጋ ስለተጨፈጨፉት ዐማሮች እና ነገ በመስቀል አደባባይ ስለተጠራው የብልጽግና ሰልፍ አንወያያለን።

• ለማንኛውም ግን በቅድሚያ እስቲ ለለንደን የዐማራ ፋኖዎች ሞራል ስጡልኝ። 👏👏👏👏🙏🙏🙏✊💪🏿💪✊👌


• ድል ለ ለንደን የዐማራ ፋኖ…✊✊✊
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…💪✊👌

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…
Подписаться на канал