zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የለንደን፣ በአጠቃላይ የሀገረ እንግሊዝ ፋኖዎች አልተቻሉም። በፊት በፊት የዲሲ ግብረ ኃይል የሚባል በሀገረ አሜሪካ የሚኖር በብዛት የግንቦት ሰባት አባላት ያሉበት አስጨናቂ ቡድን የቀደመውን የወያኔ መር አገዛዝ በየደረሰበት መግቢያ መውጪያ በማሳጣት ሀገር ቤት በንፁሐን ደም ታጥበው ውጭ ሀገር ዘና ፈታ ለማለት፣ ከዘረፉት ብር አስቤዛና የመዋቢያ ቁሳቁስ ለመሸመት፣ አልፎ ተርፎም ለዝሙት፣ ለግልሙትና የሚንሸራሸሩትን በሰለጠነ ሀገር በሰለጠነ መንገድ ይቃወሙ ነበር። በዚያ መንገድ ይደረግ የነበረው ተቃውሞ ስለ እውነት ከሆነ የተጎጂውን ሕዝብ ስሜት የገነባ፣ የወንጀለኞቹን ሹመኞች ቅስምም፣ ጅስምም የሰበረ ነበር።

"…በዚያ የዲሲ ግብረ ኃይሎች ተቃውሞ የተነሣ ስለ እውነት ከሆነ የዘመነ ህወሓት መሩ የኢህአዴግ ሹመኞች ወደ አሜሪካ ከመሄድ ተቆጥበው ራሳቸውን የቁም እስረኛ እስከማድረግ፣ ሞሪሽየስ፣ ሞምባሳ፣ ባንኮክና ዱባይ እንጂ ወደ አሜሪካ ዝር ከማለት ተቆጥበውም ነበር። ኋላ ላይ ነውጣሙ ለውጥ የሚባለው መጣ። ህወሓት መሩ ኢህአዴግ መልኩን ቀይሮ፣ መስክ ለብሶ መጀመሪያ ኦሮማራ መር ኢህአዴግ ቀጥሎ ኦሮሞ መር ኢህአዴግ ሆኖ ተከሰተ። ኦሮማራ መሩ ኢህአዴግ ገና ሥልጣን ላይ እንደወጣ ያደረገው ነገር ቢኖር በቀጥታ የዲሲ ግብረ ኃይልን እና ስደተኛው ሲኖዶስን መስበር ነበር። ሰበራቸውም።

"…የአሜሪካ ዳያስጰራን ስስ ልቡን በመመላለስ አሳምሮ የሚያውቀው ዳንኤል ክብረት ድልድዩን እንሻገር፣ ግንቡን እናፍርስ በማለት የህወሓት መሩን ኢህአዴግ ሲቃወም የነበረውን ዳያስጶራ በተነው። አደቀቀው። እነ ታማኝ በየነ የመሳሰሉትን ጎምቱ ተቃዋሚዎች ጠቅላዩ እግር ስር ደፋቸው። ብዙዎቹን የተማሩ፣ የተመራመሩ የተባሉትን ዜጎች አነሆለሏቸው፣ ያልሸወዱት ሰውም አልነበረም። ቄስ፣ ጳጳስ፣ ዲያቆን አልቀረ፣ ፕሮፌሰር፣ ዶክተር፣ ወዛደር አልቀረ፣ የቤት እመቤት፣ የቤት ሠራተኛ፣ የመኪና ፓርኪን ዘበኛ አልቀረ፣ ሁሉንም አፈዘዙት፣ አደነዘዙት። ዳያስጶራው ግራ ቀኝ ሳያይ፣ ይዋል ይደርም ሳይል የአውሬው አቢይን ቲሸርት ለብሶ በፍቅሩ ወደቀ። ከፍቅሩ ፅናት የተነሣ ምግብ ሁላ አልበላ፣ ውኃም አልጠጣ ያላቸውም የትየለሌ ነበሩ። አቢይ ተኛ ወይ፣ የት ጠፋ ብለው ከሚስቱ ከዝናሽም በላይ ለእሱ አሳቢ ሆነው ታዩ። እንዲያውም በቀን 1 ዶላር፣ በወር 300 ዶላር እያዋጡ ለሻይ ይልኩለት ሁላ ጀመር።

"…ዳንኤል ክብረት ለአቢይ ከዋለለት ትልቅ ውለታ መካከል አንደኛው ዳያስጶራውን አፍዞ፣ አደንግዞ ለኦሮሙማው ማስገበሩ፣ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናንን እጅና እግራቸውን አስሮ ገሌ ማድረጉ ነው። የዲሲ ግብረ ኃይልም ለሦስት ተሰነጠቀ። አንደኛው ግሩፕ ኮንዶሚንየምና ጨላ መሬትም ተሰጥቷቸው በለፀጉ፣ ሁለተኛው አኩርፎ በቤቱ ተቀመጠ፣ ሦስተኛው የዲሲ ግብረ ኃይል ከግንቦት ሰባት ወደ ባልደራስ፣ ከባልደራስ ወደ ግንባሩ፣ ከግንባሩ ወደ ሠራዊቱ ዞሩ። ገንዘብ ላይ በመመደባቸው ትግሉንም ረሱ፣ አቋረጡ። በዚህ ምክንያት ዳግማዊ ኢህአዴግ ብልጽግናዎች በአሜሪካ ተንዘራፈጡ። ተቆጪ፣ ገልማጭ ዳያስጶራም አጡ። በአጠቃላይ የዳያስጶራ ቦለጢቃም ተቀዘቃዘ። ቤተ ክርስቲያንም አስታርቆናል በሚል ሰበብ ሼም ይዟት ዱዳ እንድትሆን ተደረገ። በዘመነ ወያኔ ሁለት ሰው ሞተ ተብሎ ቅዳሴ አቋርጠው ኋይት ሀውስ ድረስ ሄደው ሰልፍ ይወጡ የነበረቱ ጳጳሳት ካህናት ምእመናን በዘመነ ዐቢይ በዶዘር ሕዝብ እየተቀበረዝም ጭጭ ሆነ። እነርሱ ለካ ትግላቸው በሕዝብ ትከሻ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ተንፈላስሶ መኖር እንጂ ቀድሞውኑ ወያኔ አልነበረችም ችግራቸው። ወያኔ ሥልጣን ብትሰጣቸው ካህናት ጳጳሳቱ፣ ኮንደሚንየም፣ መሬት ብትሰጣቸው የዲሲ ግብረ ኃይልም፣ ምእመናን ቦለጢቀኞቹም አይቃወሟትም ነበር ማለት ነው። ወያኔም ያለችው ያንን ነበር። ዐውቄ ቢሆን ኖሮ ኮንዶሚንየም እየወረወርኩላቸው አፋቸውን አዘጋ አልነበር እንዴ ነበር ያለችው። በፍርፋሪ ፀጥ የሚለው ደግሞ ቡቺ ብቻ ነው። ውሻ…

"…መቼም ሳይደግስ አይጣላም እንደሚባለው የአሜሪካው ግብረ ኃይል የኢትዮጵያኒስት ካምፕ አቀንቃኝ፣ የግንቦት ሰባት እርሾ፣ የባልደራስና የግንባሩ ሆኖ ዐማራ፣ ዐማራ ማለት የሚሸክከው ስለሆነ ከባህሪው የተነሣ ደክሞት ቢያርፍም እግዚአብሔር በሌላ በኩል ደግሞ በሀገረ እንግሊዝ ተርብ፣ ተርብ አራስ ነበር የሆኑ አንበሳ ዐማሮችን አስነሣ። አስነሣ፣ አስነሣ በቃ። የብልግናውን መንግሥት ቁም ስቅል የሚያሳዩ፣ የሚነሡ አናብስትን አሥነሣ። ሥርዓት፣ ሕግ፣ ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ አርበኞች፣ በዲሞክራሲ በበለፀገ ሀገር ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ልጆችን እግዚአብሔር አስነሣ። እናም ከተቋቋሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚከተሉትን ተግባራት ፈጽመው ዐማራን ቀና ብሎ እንዲሄድ፣ እንዲከበርም አደረጉ።

• በኢትዮጵያ ኤምባሲ ሀገር ሰላም ነው ተብሎ የተዘጋጀ ዝግጅት እንዳይካሄድ አደረጉ።

• በለንደን ፕላዛ ሆቴል መግቢያው 1ሺ ፓውንድ የሆነ የቢዝነስ ፎረም እንዳይካሄድ አስተጓጎሉ።

• ወርልድ ትሬድ ኤክስፖው ላይ በመገኘት ኢትዮጵያ በጨፍጫፊ አረመኔ ሥርዓት እጅ መውደቋን በማሳያት ዓለምን አስደመሙ

• የኢትዮጵያ ኤምባሲ በለንደን ኢትዮጵያ ሰላም ናት በማለት ያዘጋጀውን የአስረሽ ምቺው የግብዣ ድግስ ዝግጅት ላይ በመገኘት በተቃውሞ እንዲቋረጥ አደረጉ።

• የኢትዮጵያ ኢምቤሲን ተቆጣጥረው የለንደን የዐማራ ፋኖን ዓርማ በመለጠፍ ባደረጉት ተቃውሞ ምክንያት እስከ አሁን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተዘግቷል፣ ሠራተኞቹም ሀገር ቤት ተጠርተው ወደ ሥራ አትመለሱም ተብለው በአዲስ አበባ ታግተዋል። በዚህ ምክንያት የዐማራ ተወላጅ የሆኑና በመላ አውሮጳ በኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሠሩ ሠራተኞች ወደ ሀገር ቤት ተጠርተው ሄደው በዚያው እንዲቀሩ አድርገዋቸዋል። አሁን በዐማሮቹ ፈንታ ኤምባሲዎቹን በጥቂት ትግሬና በበብዙ ኦሮሞ፣ በጣልጣል ደቡብ ለመሙላት ታስቧል። ለዚህም ደግሞ የለነደን ፋኖ አድማሱን በማስፋት በአውሮጳ ሙሉ የአውሮጳ ፋኖ በመመሥረት ሥርዓቱን ሽባ በማድረግ ርቃኑን ለማስቀረት በዝግጅት እንደሆነ ለእኔ ለዘመዴ አሳውቀዋል።

"…ወደ ዛሬው ተቃውሞ ስንመለስ በሀገር ቤት ከፋኖ ደረጀ ከጎንደሩ ፋኖ በመቀጠል ካድሬ የሥርዓቱ አገልጋይ አባት ተብዬዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ የለንደን ፋኖዎች በአካል ተገኝተው ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ይህ ጳጳስ በዘር ኮታ "ንፁሕ ኦሮሞ" ያውም ሳህለማርያም ቶላ ተብለው መመረጣቸው በቴሌቭዥን የታወጀ፣ በአሜሪካ በሰካራምነታቸው ምእመናን ያፍሩባቸው እነደነበሩ የሚነገር፣ በአቡነ ፋኑኤል ጠቋሚነት በዲሲ ኦሮሞና የዐማራ ቄሶች ድጋፍ እንክብካቤ የሚደረግለት። ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለምን አቢይ አሕመድን አወገዘ ብለው እኔም አውግዤዋለሁ ያለ ደፋር፣ በኦሮሚያ በተለይም በሻሸመኔ ሕዝብን ያስጨረሰውን ጠበቃ ኃይለ ሚካኤልን በዐውደ ምህረት ሥልጣንና ማዕረግ ያሰጡ፣ ደፋር። የሚጠሉት ዐማራ በብዛት ወዳለበት ለንደን ተሹመው እንዲሄዱ መደረጉን አስቀድሜ መጻፌ ይታወቃል። መናገሬም ጭምር። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ለዓመፀኛይቱና ለረከሰች ለአስጨናቂይቱም ከተማ ወዮላት! ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፤ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም። በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው። ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፤ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል። ሶፎ 3፥ 1-4

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተመልከት የዐማራን ከፍታ…!

"…ዐማራ ስትሆን ብቻ ነው ሕግ፣ ሥርዓት፣ ፍትሕ፣ ርትዕ ምን እንደሆኑ የሚገባህ። ጠላትህን እንደራስህ ውደድ የሚለውን አምላካዊ ቃል በካል ለማየት ከፈለግክ ዐማራ ዘንድ ሂድ። እንደ ኦሮሙማ ሬሳ ላይ ቆሞ ፎቶ እየተነሣ አይላገድብህም ዐማራ።

"…የአሳምነው ጽጌ ልጆች ናቸው ከምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ የደቀቀ፣ ሞራሉ የሞተ፣ የመዋጋት ወኔም፣ ፍላጎትም የሌለውን የአንድ ግለሰብ ህልም ለማሳካት ሲል የሚፈጋውን ሠራዊት ከማረኩ በኋላ ኢትዮጵያን እያሰቡ መክረው፣ ዘክረው፣ አብልተው፣ አጠጥተው፣ ሰውነቱን አጥበው፣ በምህረት የሚለቁት።

"…የትግሬ ነፃ አውጪዋ ህወሓት እና የኦሮሞ ነፃ አውጪው ኦህዴድኦነግ ጭካኔ ዐማራን ሥርዓት እንዲጥስ፣ ከመርህ እንዲያፈነግጥ፣ ከዓለም አቀፍ የምርኮኞች አያያዝ ሕግ እንዲቃረን አላደረገውም።

"…የብራኑ ጁላ ሠራዊት እኮ ፋኖ ሞላ ደስዬን ከወልድያ ሆስፒታል አውጥቶ በመኪና ጭንቅላቱን ጨፍልቆ የገደለ ሰራዊት ነው። የሄ ሠራዊት እኮ በመርዓዊ ብቻ ዐማራ የተባለ የጨፈጨፈ አረመኔ አራዊት ነው። ግን ምን ያደርጋል ሕግ ዐዋቂው፣ ባለ አእምሮው እጅ ወደቁ። ዐማራም እያመመውም ቢሆን የትላንቱን ደግነቱን ዛሬም መድገም ብቻ ነው።

"…ጨፍጫፊውን ጣልያን በውጊያ መሃል መልሶ ጨፈጨፈው። ጣሊያን ተሸንፎ ሲማረክ ግን ከሞት የተረፉትን በዓለም አቀፍ የጦርነት ሕግ መሠረት፣ ይዞ በሰላም ወደ ጣሊያን መለሰ። በጣሊያንም ቪቫ ምኒልክ ተብሎ ተዘመረ። ምኒልክም ከበረ።

• ማርያምን ዐማራ ያሸንፋል…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉ…!

"…አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ወደ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የእለተ ሐሙስ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን እየሄድኩ ነው። መንገድ ላይ እያነበብኩ እንድሄድ በርዕሰ አንቀጹ ሓሳብ ላይ ያላችሁን የራሳችሁን ሓሳብ መስጠት ትችላላችሁ።

• ጀምሩ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ኦሮሞዎቹ በጉምዝ፣ በአገውና በቅማንት በኩል ዐማራውን መበጥበጥ ፈልገው ነበር። በወሎ በኩል በኦሮሞ እስላም በሃይማኖት ነበር የፈለጉት። አጅሬ ብአዴን ቀድሞ ገብቶ ጉምዞችን ከፋኖ አስታረቀ። (ሲታረቁ ቪድዮ ሁላ አለኝ) እውነተኛ የሕዝብ ልጆች የሚሠሩት እንዳለ ሆኖ ብአዴን ቀጥሎ አገው ሸንጎዎችን ለሁለት ከፈላቸው። አንዱን አገው ሸንጎ በተለይ አመራሩን የኦህዴድ ደጋፊ ሸንጎ ወደ ናዝሬትና ወደ አዲስ አበባ ሲያፈናቀል ዐማራ አገዎቹ በቦታቸው ላይ አሉ። እናም በቀደም የአገው ተቃዋሚ መስሎ ዐማራን ሲከስ ያመሸው ወደል ሶዬ ሽመልስ አብዲሳ የሚጋልበው አድራሽ ፈረስ አገው ሸንጎ ነው። ከአገው ሸንጎ ሌላ በጥባጩን የፖለቲካውን ቅማንት ደግሞ የሚዘውሩት እነ ደብረ ጽዮን ስለሆኑ አሁን ለጊዜው የፖለቲካው ቅማንት እረፍ አትበጥብጥ ስላሉት እስከአሁን በጎንደር በኩል ቅማንት ተብዬው ጮጋ ብሏል። ታዘቡኝማ… በወሎ በኩል ያለው የኦሮሞ ወሀቢይ እስላም አልለየለትም። ግን ለዐማራ ፋኖ አስጊ አይደለም። ከጀመረም ግን ይጨፈለቃል።

"…ትናንት አሳይታ ላይ ያየሁትና ቪድዮው የተላከልኝ አንድ ጀነራል የሚያወራው ስለ ጨው ንግድ ነው። በድብቅ የተቀዳ ስለሆነ አደጋውን ፈርቼ ነው እንጂ እለቅላችሁ ነበር። ጀነራሎቹ ዘረፋ ላይ ናቸው። የጨው ንግድ ላይ የተሰማሩ ጀነራሎች አሉ። ዱባይ ቪላ የተገዛላቸው አሉ። ኮንትሮባንድ እና የሐሺሽ ንግድ ላይ የተሰማሩ አሉ። የዐማራ ክልሉን መከላከያ እያሾቁ በፋኖ እያስመቱ አገዛዙን አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱም አሉ፣ ኦህዴድና ኦነግ መከላከያን በኦሮሚያ በሸኔ አስመትተው ሸኔን መሳሪያ እንደሚያስታጥቁት ሁሉ በዐማራ ክልልም ያንኑ የኦህዴድኦነግን መንገድ ተከትለው መከላከያውን በማስመታት ፋኖን የሚያስታጥቁ ጀነራል፣ ኮሎኔሎችም አሉ ነው የሚሉት የነገሩ ታዛቢዎች። በመሃል የሚያልቀው ማነው? ምስኪኑ የደሀ ልጅ መከላከያው።

"…ሌላው አዲስ አበባ ዙሪያ የሰፈረው የእነ ሽመልስ አብዲሳ ሸኔ ወደ ኋላ ካልተመለሰ አዲስ አበባን ቆይቶ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚፈራ ቀውጢ ብልጽግናን እንዳመሳትም ይነገራል። ቤት ለቤት እየተካሄደ ያለው ፍተሻም በዐማራና በጉራጌ ላይ ብቻ የጠነከረው ለምን ይመስልሃል ብለው መልስ የማይመልሱበትን ጥያቄ የሚጠይቁመወ አሉ። የእነ ደብረ ጽዮንን ህወሓት ይደግፋሉ ተብለው የሚጠረጠሩ አንዳንድ ትግሬ ቤቶችም የፍተሻው ሰለባ ናቸው ተብሏል። ምንም እንኳ ደመቀ መኮንን ገሸሽ ቢደረግም አቶ ሰማ ጥሩነህ በህወሓት በኩል ቁሞ ብዙ ነገር ያሳልጣልም ነው የሚሉት፣ የጀነራል አበባው ታደሰ ሁል ጊዜ " እንዴት በማረኩት የደርግ ወታደር እታዘዛለሁ" ብሎ መብሰልሰሉን ተከትሎ ከየትኛው ወገን እንደሆነ ባይታወቅም አለኝ የሚለው ታማኝ የግል ጠባቂው መገደሉ በዝምታ ባሕር እንዲሰምጥ አድርጎታል ነው የሚሉት። የኦሮሞ፣ የትግሬና የዐማራ የኢትዮጵያ ቦለጢቃ እንደ እሳተ ገሞራ እየጋመ ነው። ነይ በክረምቱ አለ አዝማሪው።

"…ሌላው በግንቦት ሰባት በኢዜማ አቅራቢነት ከንቲባ አዳነች አበቤ ራሷ በቅርብ የምትከታተለው ፀረ ብልፅግና አደረጃጀት ያለው የሚመስል በአብዛኛው አዲስ አበባ ተወልደው ባደጉ የኦሮሞ ልጆች የሚመራ አደረጃጀት መፈጠሩም ነው የሚነገረው። ይሄ ቡድን ፋኖ አዲስ አበባ ውስጥ አደረጃጀት ፈጥሯል መባልን ሰምቶ ያንን አደረጃጀት ፈልጎ ሴሉንም አግኝቶ ለመምታት ሲባል የተፈጠረ ነው የሚሉም አሉ። መስቀል አደባባይ የባቡር ኃዲዱ ላይ ወጥቶ ባነር መስቀል የሚችለው፣ ባነሮቹም እስከ ማታ ድረስ ሲታዩ እንዲውሉ የተደረገበት ምክንያት ብዙ ነገሩን አስፎግሯል ነው የሚሉት አቃቂር አውጪዎቹ።

"…በወልቃይት የሰኔ 15 ቱ ዓይነት ድራማ ይፈጸማል የሚሉም አሉ። የሀዋሳው ትግሬ ልጅ አሁን የኦህዴድ አሽከር የእነ ጌታቸው ረዳ ቡድን ደጋፊ የሆነው አክቲቪስት ከወዲሁ ሊበሏት ያሰቡትን አሞራ ጅግራ ናት ማለት መጀመራቸውን ያዙልኝ። ቃል በቃል ከመቸኮሉ የተነሳ ኮሎኔሉን ጀነራል ብሎ ነው የጻፈው። " ጀነራል ደመቀ ዘውዱበአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት መገደሉ መረጃዎችን እየሰማን ነው።" በማለት ከለጠፈው በኋላ በፍጥነት እንዲያነሣው ተደርጓል። እሱ ልጥፉን ቢያነሣውም የእኔ ወፎች ቀልበው አስቀርተውታል። ጸሐፊው አዋሳ የሚኖር ትግሬ ሲሆን ኦነግን እና ህወሓትን በፍቅር ይደግፍ የነበረ። አዋሳ ተቀምጦ አቢይ አሕመድን ራሱ ደም መጣጭ ብሎ ይስለው የነበረ ፍንዳታ ትግሬ ነው። አሁን ወደ እነ ጌታቸው ረዳ ግሩፕ ሳይቀላቀል አልቀረም። ምሳውንም የሚችሉት የኦሮሞ ብልጽግና ሰዎች ይመስላሉ።

"…ዋናው ነገር ወልቃይት እንዲደበላለቅ የእነ ደመቀ መኮንን ቡድን የሚፈልግ ይመስላል። ብልፅግና ወልቃይትን ማጣት እና ለህወሓት አሳልፎ መስጠት ባይዋጥለትም ዐማራን ለማብሸቅ ሲል ግድ ሊያደርገው ይችላል የሚሉም አሉ። ያም ሆነ ይህ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አደጋ ላይ ነው። መዝግቡልኝ። ቀኝ ትከሻዬን ከሸከከኝ ሸከከኝ ነው። ኮሎኔሉ በዐማራ ፋኖ ላይ በሚያራምደው አሉታዊ አመለካከቱ ቢሞት ቢኖር ዐማራው ደንታው ባይሆንም የኮሎኔሉ መገደል ግን አካባቢው ላይ ትንሽ የስኒም ባይሆን የመለኪያ ላይ ማዕበል ማስነሣቱ አይቀርም። የሆነው ሆኖ የዐማራው ትግል ከግለሰብ አምልኮ እየወጣ እየመጣ ስለሆነ ብዙም አያሰጋም። ግን እንደሚገድሉት ጽፈዋል። መዝግቡት።

"…ግንቦት 7፣ ህወሓት፣ ብአዴን፣ የኦሮሞ ብልጽግና፣ የዳያስጶራው ኃይል በዐማራ ክልል የራሳቸው የፋኖ አደረጃጀት ፈጥረው ተፋጠዋል። የሕዝብ ልጅ የሆነው እውነተኛው ፋኖም አድፍጦ ተቀምጧል። የሆነ ቀን ከመኝታችሁ ስትነሡ እነዚህ ኃይሎች ተባልተው አድረው የሕዝብ ልጅ ፋኖ ከላይ ጉብ እንደሚል ግን በሙሉ አፌ መናገር እችላለሁ። የብአዴን ፋኖ ተስፋ የሚያደርገው ህወሓትን ነው። ህወሓት ደግሞ በመሃል ያለው የሕዝብ ፋኖ ደንቃራ ሆኖባታል። ግንቦት ሰባት እነ ነአምን ዘለቀ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ጎንደር ያለውን ለብአዴንም የሚሠራውን ፋኖ ይዘው፣ ከጎንደር 7፣ ከጎጃም 2፣ ከወሎ 2፣ ከሸዋ 2 የፋኖ አመራሮችንም መርጠው፣ እነዚያም ሰዎች ስብሰባ ጠርተው፣ ስብሰባውን በመሃላ ሊያስጀምሩ ሲሉ የሸዋ ፋኖዎች መሃላውን ምን አመጣው? እነ እገሌስ፣ እነ እገሌስ የት አሉ? እኛ በእነ መምህር ዘመዴ በኩል የጀመርነው ውይይት ተስማምቶናል። እሱን ሳንቋጭ ወደ ሌላ አንሄድም በማለት አቋርጠው ወጥተዋል። ጎጃምና ወሎዬዎቹም ሸዋን ተከትለው ግንቦቴዎቹን ወጊዱ ብለዋል። ግንቦቴ አብዶብኛል አይገልጸውም።

"…አሜሪካ ጎንደሬዎቹን የግንቦቴ ፋኖዎች አነጋግራለች። ከህወሓት ጋር ታረቁና፣ ከብአዴን ፋኖዎች ጋርም አብሩና አንድ ሁናችሁ መጥታችሁ እኛ ከምንነግራችሁ አደረጃጀት ስር ሁኑና፣ (አደረጃጀቱን ዐውቀዋለሁ ነገር ግን ዛሬ አልነግራችሁም) ከዚያ አንድ ሁናችሁ ስትመጡ እኔ አብይ አህመድን በአንድ ሳምንት በአናቱ ተክዬ ሥልጣኑን አስረክባችኋለሁ እንዳለቻቸው ነው የሚሰማው። ከጎጃም ጥቂት፣ ከወሎም ጥቂት ሰምተዋል፣ አግኝተዋቸዋልም። የሸዋን አልሰማሁም። አልነገሩኝምም። ድካሙ ብቻ ብዙ ነው። ብአዴን ሆኖ በፋኖ ተገደለ የሚባል ከሰማችሁ ከብልፅግና ጋር የገገመ ብአዴን በመሆኑ የተወገደ እንደሆነ ዕወቁም ተብሏል። ብአዴን ሆነው ከፋኖ ጋር የሚሠሩ አይነኩም። ሻለቃ ውባንተ ተዋግቶ በተገደለ ጊዜ መከላከያውን መርቶ ያመጣው ብአዴን ከነካቢኔው ሲገደል፣ ዋና አስተዳዳሪው ግን ተቆራርጦ ነው እንዲገደል የተደረገው። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም…

"…ከምስጋናው በመቀጠል የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። እን Go…🚶‍♂‍➡️🚶‍♂‍➡️

"…የዛሬውን ርዕሰ አንቀጼ የሰካራም እርሻ፣ የዝንጀሮ ደብተር፣ የወንደላጤ ቤት፣ ሴት ልጅ ቤት የዋለች እለት የምትመስለውን ዝብርቅርቅ ያለ ቅቤ ተቀብታ፣ ፌስታል በሻሽ፣ ሁለት እግር ካልሲ፣ ታይት በቁምጣ በተቀደደ ጅንስ ፊት እንዲመስል አድርጌ ያዘጋጀሁት። የሚቀየመኝም ይበዛ ይሆናል ግን ደግሞ ኬሬዳሽ። እንደ ፐዝል ጨዋታ ደበላልቄ ልጽፈው ነኝ። ጤፍና አሸዋ ተቀላቅሎ ዓይነት በሉት።

• እ… አላችሁ አይፈል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ምክር ለዘመድኩን ነቀለ…!

• ለዘመዴ አድርሱለት

"…ሲያቀብጠኝ አንዳንዴ ሲያመኝ ጤናም የለኝ አይደል…? ብድግ ብዬ የጃነደረባውን ትውልድ የስልቡ ትውልድን መሪና ሰብሳቢ፣ በሮማ ካቶሊክ ተልዕኮ በብልፅግና ወንጌል ድጋፍ የሚንቀሳቀሰውን ሄኖክ ኃይሌ የተባለ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ መተንኮስ። እኔ በስሱ ነው የነካሁት። እኔ ስነካው እንደ በጋሻው እንደ ትዝታው ጓ ብሎ በደንፉ ምላሽ ይሰጠኛል ብዬ ብጠብቅ፣ ባስጠብቅ ልጁ አራዳ ማፍያ ሸቃይ ነው ጠላታችሁ ዝም፣ ጭጭ ይበል ጭጭ ይላል። ጭጭ ማለት ብቻ ሳይሆን ይደበቃል። እኔም ብቅ ሲል ልኮረኩመው ፈልጌ ተውኩት።

"…ኋላላችሁ ይሄ ነዋሪነቱ ናዝሬት የሆነ፣ አዲስ አበባ ከገባ አምስት ዓመት የሆነው፣ ዱባይ ያሉ እህቶቹ በሚልኩለት ብር አዲስ አበባ ውስጥ የአርሴናል ደጋፊ ሆኖ የቀረው የወጣት ጡረተኛ ለምን ሄኒን ተናገርክ ብሎ የምክር መዓት ሲያወርድብኝ ከረመ። ከረመ አልኳችሁ ይሄ የአዳማናዝሬት መንገድ ፊት የመሰለ ልጅ። 😂😂

"…ዘመድኩን ነቀለ እያለ አስገባልኝ አልኳችሁ። የአውሮጳ የቅሪላ መንፈስ የሰፈረበት፣ ግርማና ሄኖክ በመቁጠሪያና በቅብአ ሜሮን የማያላቅቁ ቬንገር የተባለ አጋንንት እና ባካሪ ሳኛ የተባለ ዛር ያረፈበት ልጅ ወረደብኝ አልኳችሁ።

"…የሄኖክ ኃይሌ ምልምሎች አብዛኛዎቹ ወሴ ናቸው። በመረጃም ማውራት እንችላለን። ጨፋሪ፣ ደናሽ፣ ጀንደራም ሁላ ናቸው። ሰንደቅ ዓላማ ጠል፣ መርጦ አልቃሾች ሁላ ናቸው። ለትግሬ ሲጮሁ አይታችሁ ለዐማራና ለኦሮሞ የማታገኟቸው አጭቤዎች ሁላ ናቸው። ጨበርበርቱ ወዪ…

"…ይሄ የአእላፋት ዝማሬ አድናቂ፣ የናዝሬቱ ሰገጤ፣ የባካሪ ሳኛ መንፈስ የሰፈረበት፣ የሴት እህቶቹ ጡረተኛ "ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነው? ብሎ ይዘምራል ብዬ ስጠብቀው አባው "አርሴ ካንተ ሌላ ብሞት አልመኝም ብሎት አረፈው።

• ኤትአባሽ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከዚህ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ በኋላ እመለሳለሁ። የአባት ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ ስለማውቅ ነው የተባበርኩት እንጂ እኔ በፔጄ ላይ የአፋልጉኝ፣ የእርዳታ ወዘተረፈ አልለጥፍም። ይሄ ልጅ ግን አንጀቴን ነው የበላው። ምፅ…

"…አባትና ልጅን በማገናኘት ትብብር ታደርጉ ዘንድ ድርጅቱ በትህትና አዳሜና ሄዋኔን ያዛችኋል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከጅማ የተላከ ነው።

"…ትናንት ልማታዊውን የኦሮሞ መንግሥት ያልደገፈ ቤቱ ይፈርሳል፣ እርሻው ይወረሳል ተብሎ በከባድ ማስጠንቀቂያ መኪና ተልኮላቸው ወደ ጅማ ጉዞ የጀመሩ ሰልፈኞች ፈጣሪ ዝናብ ጥሎ ኮንኮላታዎቹ በጭቃ ስለተያዙ የድጋፍ ሰልፉ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸውን ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።

"…በሰልፈኞቹ በድጋፍ ሰልፉ ላይ አለመገኘት የተበሳጨው መንግሥት አንድ አጣሪ ቡድን ከጅማ የላከ ሲሆን አጣሪ ቡድኑም ራሱ በተመሳሳይ በጭቃ በመያዙ ምክንያት የተላከበትን የማጣራት ሥራ ሳይፈጽም ቀርቷል።

"…ልማታዊ የብለፀገው አገዛዛችን አሁንም ሌላ አጣሪ ኮሚቴ መርጦ ወደ ሥፍራው ለመላክ ሳይዘጋጅ አይቀርም ብሏል የዜና ወኪሉ ከጅማ…

• ዝናብ ለዘላለም ይኑር…✊✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ምን ብሏቸው ነው 7 ጨዌክስ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሰበር መረጃ ነው…!

"…ሰሞኑን በአምባሰል ተራሮች ላይ ከፋኖ ጋር በውጊያ ላይ የከረመው የብራኑ ጁላ ሠራዊት በግሸን ደብረ ከርቤ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ለማካሄድ መወሰኑ ተሰምቷል።

"…ለዚሁም ከቆጋት ተስቦ ግሸን ድረስ የተዘረጋውን የውኃ ቧንቧ ቆርጦታል። ውኃው ከተቋረጠ ግሸን ላይ ያሉት ነዋሪዎች በሙሉ በውኃ ጥም ይሞታሉ።

"…ሌላው እታች አውቶቡስ ማቆሚያው ጋር ያለውን ወፍጮ ቤት ነቅሎ በአይፋ መኪና ጭኖ መውጣቱም ተነግሯል።

"…ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ በአክሱም፣ በትግራይ የተደረገው ጦርነት እንዳለ ሆኖ፣ አሁን ደግሞ የክርስቶስን መስቀል ፍለጋው በአረመኔው የኦሮሙማ ኢሉሚናቲ አገዛዝ ቀጥሏል።

"…ቀጥሎ የሚከሰት ነገር ካለም መረጃው ሲደርሰኝ እነግራችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አይ ዘመዴ…😂

"…እኔ እኮ አልጥመድ… ከጠመድኩኝ መረቤን ሳልሞላ አልመለሳትም። ይኸው ብዬ ብዬ ሞጣን እንኳ በቲክቶክ ፔጁ ላይ መዝሙር አስጀመርኩት እኮ… ገና ምን አይቶ…? አሰግደዋለሁ…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጋቸነ ሲርና…😂😂

"…ከፋኖ ጋር ለሚደረገው ፍልሚያ ጋቸና ሲርና በወታደራዊ ሥልጠና ላይ ነው። ፐ… ፋኖ ጉዱ ፈላ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወደው አይስቁ አሉ…😂😂

"…እሺ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች…ሰልፉ እንዴት ነበር…? …የፈረስ አገልግሎቱስ እንዴት ነው? ራይድስ በጥራት አገልግሎት እየሰጠ ነው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ይቅርታ…!

"…መልካም ከምስጋና በኋላ የሚቀርበው ርዕሰ አንቀጻችን ነበር። ዛሬ ርዕሰ አንቀጻችን የዘገየው በምክንያት ነው። ምክንያቱምንም እነሆ እንደሚከተለው በአጭሩ እገልጻለሁ። ዛሬ የጎንደር ፋኖዎች ልክ እንደ ሸዋ ፋኖዎች ዘመዴ አነጋግረን ብለው ደውለው በቀጠሩኝ መሠረት ከዚህ በፊት አንደኛውን ግሩፕ አግኝቼ ይህ የዛሬው ሌላኛው ግሩፕ ይቀረኝ ስለነበር ዛሬ በዕለተ መድኃኔዓለም የቀረው ግሩፕ ደውሎልኝ በቴሌ ኮንፍረንስ ከ2:00 ሰዓት በላይ ጊዜ ወስደን ስንወያይ ቆይተን፣ ከቀሪው ግሩፕም ቀድመው ካነጋገሩኝ ጋር በጋራ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘን ተለያየን። እናም እዚያ ቆይቼ ነው የዘገየሁት።

"…ዛሬ የቆየሁት ከጎንደር የበላይ ጠባቂ ሽማግሌዎች ከእነ አርበኛ ጋሽ መሳፍንት፣ ጋሽ ሰፈር መለሰ፣ ጋሽ እሸቴ ባይሁ፣ ከእነ ሻምበል ገብሩ፣ ከእነ ሻምበል መሠረት ዓለሙ ጋር ነበር። የደስታዬን መጠን አትጠይቁኝ። ችግሩም በጣም ሲበዛ ቀላል ነው። ወይፈኑን ከበሬ ጋር ማጥመድ ብቻ ነው። አለቀ።

"…ወደ ርዕሰ አንቀጻችን እንመለስ። የለንደን ፋኖ ተጋድሎን ርዕሰ አንቀጽ አድርገነዋል። እስከዚያው ይሄን እያያችሁ ጠብቁኝማ። የዐሜሪካው የዲሲ ግብረኃይል ከሞተ በኋላ በለንደን የተወለደው የዐማራ ፋኖ አልተቻለም። እስቲ በርዕሰ አንቀጼ ልዳስሳቸው። እስከዚያው ይሄን ቪድዮ እያያችሁ ጠብቁኝ። የኦሮሚያ ሕዝብ በቋንቋው የሚያስተምረው ጳጳስ አጥቷል ተብሎ ሰካራም ነውረኛ ከተሾመ በኋላ ወደ እንግሊዝ፣ አውሮጳና አሜሪካ ጳጳስ መላክ ምን ማለት ነው? የዐማሮቹ ቄሶች ማሽቃበጥ ነው የገረመኝ።

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ገድለውቷል። ዘርፈውታልም።

"…ጎጃሞች አንዲህ ነበር መከራ የበዛባቸው። አዲስ አበባ ለመግባት ሚልዮን ብር ክፈሉ ተባሉ። ሾፌሮች ኦሮሚያ ላይ ይገደላሉ። መኪናው ይቃጠላል። ፍትሕ አጡ ጎጃሞች። ወሎዬዎችም ከወለጋ ታርደው ተሰደዱ። ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን እንዳታልፍ ተባለ። ጎንደሮችም እንደዚሁ። መጨረሻ ላይ ሲመራቸው ዛሬ አገዛዙን በእንብርክክ እያስኬዱት ነው።

"…ይሄ ወጣት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሶፎንያስ ዓሥራት ይባላል። የ24 አመት ወጣት ሲሆን ማክሰኞ ለሊት 8 ላፍቶ አካባቢ ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት ሆነው ኖሆም ሆቴል አካባቢ የሰፈሩ ስም ላፍቶ ቦሌ ሚካኤል ውሰደን ብለውት ኮንትራት ይዘውት ይሄዳሉ።

"…ናሆም እንደሄደ አልተመለሰም። በማግስቱ እናቱ ስልኩ ላይ ስትደውል አይሠራም። ጓደኛው ጋር ስትደውል ቦሌ ሚካኤል ብሎ እንደወጣና እንዳላገኘው ይነግራታል። የፈለገ ነገር ቢፈጠር ከእናቱ ጋር ይደዋወል የነበር ልጇ ደብዛ መጥፋቱ ያስጨነቃት እናትም ቦሌ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ትጠይቃለች። የተመዘገበ ነገር  ካለ እናሳውቅሻለን ይሏትና ተመልሳ ላፍቶ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ጠየቀች። እነሱም ተመሳሳይ ነገር ነገሯት እና የአቃቂ ቃሊቲን ስልክ ይሰጧታል። እዚያ ስትደውል ስልኩን ለሌላ ሰው ስጪ ብለው ያለውን ነገር ማለትም ወጣቱ መገደሉንና አስክሬኑ ማሰልጠኛ አካባቢ እንደተገኘ እንዲሁም ለምርመራ ጳውሎስ እንደተወሰደ ይነግሯታል።

"…ዛሬ 5 ሰዓት አካባቢ አስክሬን ተቀብለው ወደ መኖርያ ቤቱ ወደ ላፍቶ ኮንደሚኒየም ወሰዱት። ገዳዮቹ እስከአሁን አልተገኙም። ኮድ 2 A 93488 ቪትዝ መኪናውንም ይዘው መሠወራቸውን የሟች ሶፎንያስ የቅርብ ወዳጆች መረጃውን ለየኔታ ቲዩብ አድርሰው ተዘግቧል። ነፍስ ይማር…!

• አዲስ አበቤ በብላሽ መሞት አይባቃም ግን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሰዓት አለን ወይ…? ካልደከማችሁ እንቀጥል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ይጀምራል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉በዩቱብ /YouTube
https://www.youtube.com/live/a591fucC63k?si=CSiiT3yhDNfXsXU9

👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v4nfwou-...-ethiobeteseb.html

👉በፌስቡክ Facebook
facebook.com/ethiobeteseb

👉    በቲውተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb

👉 ቴሌግራም / Telegram

/channel/ethiobeteseb
ደግሞ መጣን እስቲ ገባ ገባ በሉ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ "…የጎጃም ገበሬን ወደ ፋኖ ለመቀላቀል፣ የዐማራ ልዩ ኃይልን ወደ ፋኖ ለመቀላቀል ብአዴን በከባዱ ጨዋታውን መጫወቱ ነው የሚነገረው። የሚሰማውም። ፋኖን ለማጠናከር ብአዴን አሻራው ከባድ ነው የሚሉም አሉ። ገበሬውን ማዳበሪያ የከለከለው ብአዴን ነው። ገበሬው ሰልፍ እንዲወጣ ያደረገው ብአዴን ነው። ሰልፍ የወጣውን ገበሬ "የጅራፍ ፖለቲካ" ብሎ የተሳለቀበት፣ ሰድቦ፣ ደብድቦ፣ አዋርዶ ያባረረውም ብአዴን ነው። የዐማራ ልዩ ኃይልን ከነ መሳሪያው፣ ከነ አደረጃጀቱ የበተነው ብአዴን ነው። ዋነኛውን የመከላከያ ኃይል ዐማራ ላይ በተለይ ጎጃም ላይ የሰበረው ብአዴን እንደሆነ ዳንኤል ክብረት ራሱ ገልጾታል። ሲቆይ ፋኖው ከብአዴን እጅ ወጥቶ ከብልቃጡ ውስጥ የወጣ ጂኒ ሆኖባቸው እንጂ አጀማመሩስ ብአዴን ሳልቀደም ልቅደም ነበር ነገሩ። ቀጥሎ ምን ይፈጠራል…? አብረን የምናየው ይሆናል።

• ኦሮሞዎቹስ ምን እያሰቡ ነው…?

"…ኦሮሞዎቹማ ያስቃሉ… የነገ ሰው ይበለን… ወይም በኋላ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ሳምንታዊ መርሀ ግብሬ ላይ እነግራችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በትግራይ ሦስት ግሩፕ ተፈጥሯል። የደብረ ጽዮን ህወሓት፣ የእነ ጌታቸው ረዳ ለብልፅግና የቀረበው ህወሓት፣ እና የህወሓትም፣ የእነ ጌቾም ደጋፊ መሃል ሰፋሪ የተቃዋሚ ፓርቲ ደቂ ህወሓት። የደፂዋ ህወሓት ከወራጁ አሮጌው ብአዴን ከደመቀ መኮንን ግሩፕ ጋር ግንባር ፈጥራለች። አሮጌው ብአዴን የሚመራው ኃይለኛ የፋኖ ግሩፕም ዐማራ ክልል ላይ ሆኖ ከእነ ደብረ ጽዮን ህወሓት ጋር ግኑኝነት ፈጥሮ የአብይን ብልጽግና ለመታገል ያስባል። በአንጻሩ ደግሞ የጌታቸው ረዳ ግሩፕ ከእነ አቢይ ግሩፕ ጋር ነው ያለው። ለእነ ደብረ ጽዮንም ፈተና እየሆነ ያለው ይሄ ግሩፕ ነው። የእነ ደመቀ መኮንን ግሩፕ ደግሞ ከእነ ደብረ ጽዮን ጋር ነው። የትግሬ ሕዝብም ሁለት ልብ ይዞ ነው ተወጥሮ ያለው። አብዛኛው ትግሬ ከእነ ጌታቸው ረዳ ግሩፕ ጋር ነው መንቀሳቀስ የሚፈልገው የሚሉ አሉ። ምክንያቱ ደግሞ ኩርፊያ ነው። "ህወሓት ልጆቻችንን አሳጥታናለች" የሚለው አኩራፊ በሙሉ ከእነ ደብረ ጽዮን ተለይቶ ከእነ ጌቾ ጋር ተሰልፏል ነው የሚሉት።

"…የእነ ደብረ ጽዮን ቡድን ወልቃይት እና ራያን መተው ሳይሆን ለጊዜው በዐማራ ዘንድ ይቆዩ ባይ ነው ይሉና አሁን ላይ ስለሱ ብዙም ባናነሳ መልካም ነው ይላሉ ነው የሚሉት። እነ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ትግሬንና የትግሬን ድጋፍ፣ የውጭውንም ድጋፍ የምናገኘው ወልቃይትና ራያን ስናጮኸው ነው። አቢይም መከላከያውን ተጠቅሞ ራያና ወልቃይትን ለትግሬ ካስመለሰ ክሬዲቱ ለእነ ጌቾ ቡድንና ለብልፅግና ይሆንና እነ ጌቾ ትግራይን ብልፅግና አድርገው ወደ ማእከል ለመመለስ ያግዛቸዋል ነው የሚሉት።

"…የእነ ደመቀ መኮንን ቡድን ደግሞ ወልቃይት ላይ እነ ደብረ ጽዮን ጦርነት እንዲከፍቱ ይፈልጋሉ። እነ ደብረ ጽዮን ደግሞ ለእነ ደመቀ መኮንን ግሩፕ ለብአዴኑ የሚሉት አሁን ጦርነት ወልቃይት ላይ መክፈት ለትግሬ ከባድ አደጋ አለው ነው የሚሉት። በወልቃይት በኩል ኤርትራም ጥቅሟ ስለሚነካ ነገሩ ይጦዝና ከቁጥጥራችን ውጪ ወጥቶ የባሰ እልቂት ይከተለናል በማለት ጦርነቱ እርሱ ይቆይ ነው የሚሉት። የእነ ደመቀ መኮንን ግሩፕ ደግሞ የሚለው ወልቃይት ላይ ጦርነት መከፈት አለበት። ምክንያቱም ከተጎዳን ሁላችንም ማለትም ትግሬም፣ ዐማራም፣ ብልጽግናም መጎዳት አለበት ነው የሚሉት። ዝርዝሩ ሰፊ ነው እዚህ የማይገለፅ ጭምር። ህወሓት ደግሞ ፕሮጀክቱ አጓጊ ቢሆንም ለጊዜው በዚህ አልተስማማችም ነው የሚሉት። ቆቅ አይደለች…

"…የህወሓት ግሩፕ የትግሬ አክቲቪስቶችም በዐማራ ፋኖ ላይ ያላቸውን እይታና የእስከአሁኑን አካሄድ እንዲያስተካክሉ የእነ ደብረ ጽዮን ቡድን ትእዛዝ አውርዷል። በወረደው ትእዛዝ መሰረትም እነ አሉላ ሰሎሞንና እነ ስታሊን ከጌታቸው ሽፈራው፣ ከሙሉቀን ተስፋው፣ ከእነ አኪላና ከእነ አበበ በለው፣ ከእነ ሄኖክ የሺጥላም በላይ ሆነው የመጨ የዐማራ አክቲቪስትን አስንቀው የፋኖ ደጋፊ መስለው ተከስተዋል። እኔም የፋኖ ደጋፊ ነኝ አለ ስታሊን። ወይ ድጋፍ እቴ።

"…አቢይ አሕመድም የወዛ አይደለም የደመቀ መኮንን ግሩፕ ላይ በጊዜ የነቃ ለመምሰልና ቁማሩን ላለመበላት እየተውተረተረ ነው ይላሉ። የእነ ደብረ ጽዮንን እና የደመቀ መኮንንን ድብቅ የግኑኝነት መስመር ቀድሞ ስለደረሰበት ደመቀን ከምክትልነት ሥልጣኑ ገሸሽ በማድረግ ለጊዜው ግንኙነታቸውን በሳሳ መልኩ ያቋረጠ መስሎታልም ይባላል። የእነ ደመቀ ቡድን ግን አስቀድሞ የሠራው ሥራ የዋዛ አይደለም። እነ ገዱ አንዳርጋቸውም እንደዚያው ተፍተፍ ለማለት ሞክረዋል ነው የሚሉት። አቢይ ደመቀን ካራቀው በኋላ ግን በጎጃም በደረሰበት ድቀት ምክንያት፣ ብዙ ባለሀብቶችም በኤርትራና በቦሌ ከሀገር ሲወጡ እያየ እንዳላየ ማለፉን ምክንያት በማድረግ አቶ ተመስገን ጥሩነህንም ከደኅንነቱ አካባቢ አነሥቶ በስልጤው ወሃቢስት በሬድዋን ሁሴን ተክቶ ተመስገንን በቅርብ ለመቆጣጠር ያመቸው ዘንድ ወደ ቢሮው ምክትል ጠቅላይ አድርጎ አምጥቶታል። ተመስገን አሁን ሽባ ነው። የተመስገንን ሥራ የሚሠሩት አቶ ምስጋኑ እና ወሮ ብርቱካን ናቸው የሚሉም አሉ። የብአዴን ፋኖ ኔትወርክ ግን ሥራውን በሚገባ ቀጥሏልም ይላሉ ወፎቼ።

"…ይሄን ነገር አገዛዙ እንደነቃበት ለማመልከት አቢይ አሕመድ ሰሞኑን በአንድ በወር 200 ሺ ብር ድርጎ በሚጥልለት የቀድሞ መምህር የአሁን አክቲቪስት ሹሉቃ ስዩም ተሾመ በኩል በቪድዮ አስነግሯል። ስዩም ሲናገር ምን ይላል። የዐማራና የትግራይ ጦርነት እንዳይበርድ፣ የፋኖና የመከላከያ ጦርነት እንዳይቋጭ ዋነኛው በጥባጮች አቶ ደመቀ መኮንን እና አይተ ደብረ ጽዮን ገረ ሚቻኤል ናቸው። አቢይ አሕመድ ደመቀ መኮንን ልክ እንደነ ዮሐንስ ቧ ያለው አዋሽ አርባ ወስደህ አስረህ ካልቀረቀርክበት በቀር በቅርቡ ይበሉሃል ብሎ ነው ሲደነፋ የሚታየው። ስዩም በል የተባለውን የሚል በቀቀን ቢሆንም ከሁሉ በላይ ደግሞ የገዛሁለት ሓሳብ " ክረምት ሳይገባ በዚህ ሁለት ወር ውስጥ አቢይ ኦፕሬሽኑን መርቶ ካልጨረሰው እንደአበቃለት ይቁጠር፣ ይበላል። ፋኖም ሆነ ህወሓት ክረምት ላይ የሚያደርጉት ጦርነትን አሁን ያለው መከላከያ ሠራዊት አያስቆማቸውም የሚለው ስጋት አስቆኛል። ስዩሜ ግን ከሲሳይ አጌና ይሻላል መሰለኝ። ጥርጣሬው የውስጥ ዐዋቂ ያስመስለዋል። የሆነው ሆኖ ነገርየውን ሳየው ሁለቱም ግሩፖች በነገሩ እንደተግባቡ ነው እኔ እየገባኝ ያለው። ከምር ጠርጥረዋል።

"…የሚገርመው የዐማራ ፋኖን እየመሩ በረሃ ወርደው ሳለ እስከ አሁን ድረስ ደሞዝ ከመንግሥት የሚከፈላቸው የዐማራ ፋኖ መሪዎች እንዳሉ የሚሰማ ነገር አለ። የአንዳንዶቹ እንደውም ሰነዳቸው ጭምር እንዳለ ይወራል። ነገር ግን ፋኖዎቹ የሚሉት ከእኛ ትግል ጋር ሆነው እስከሞቱ፣ እስከተጋደሉ ድረስ፣ አይደለም ብአዴን ለምን ሸይጣን አይሆንም ምን አገባን ነው የሚሉት። ሁሉንም ገፍተን አይቻልም። ሁሉም ብአዴን ፀረ ዐማራ ሓሳብ ይኖራል ማለትም አይደለም። ስለዚህ በአይነ ቁራኛ እየተከታተልናቸው ትግሉ ይቀጥላል። በድልም ይጠናቀቃል። ደግሞም እነርሱ እርስ በእርስ ለእራት ለመበላላት ሲተሳሰብ እኛ ለቁርስ እንደምናጣጥማቸው ሊታወቅ ይገባል። ሲመስለኝ ብአዴን ከብልጽግና ጋር በጥይት እየተነጋገረ ይመስለኛል። ብልፅግና የፈራው ህወሓት እና የብአዴን ፋኖዎች ግንባር ፈጥረው ዳግም ወደ አራት ኪሎ ጉዞ የሚያደርጉ መስሎት ነው የሚባንነው። መሃል ላይ ተጎማሽሮ የተቀመጠውን አንበሳ የሕዝብ ልጅ ንፁሑን ፋኖ አላሰቡትም። (ብአዴኖች ቆቱው ዘመዴ ከዐማራ ትግል ውጣ) የሚሉኝ ለምን እንደሆነ የገባኝ እኔንና ወፎቼን ብቻ ነው።

"…ጎንደር ላይ ፍላጎቱ ብዙ ነው። ግንቦት ሰባት እና የብአዴን ፋኖዎች እንደ ጉድ ተፋጥጠዋል። ፎቆ ቤት፣ ቪላ ቤት የጀመረ የፋኖ መሪ ቤቱን የማስጨረሻ የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል ብሎ ሲያወራ እንደመስማት የሚያስደነግጥ ሌላ የሚያስደነግጥ ምን አለ? እንዲህ ሲያወሩ ስቅጥጥ የማይላቸውም ሰዎችም እንዳሉ ይሰማል። "አንድ ትንሽ ቤት ከተማ ጀምሬ እኮ ሳንቲም አጠረኝ" የሚል የፋኖ መሪ ምን ተማምኖ እንደሆነ መገመት ነው። ግንቦት ሰባት እነዚህን በገንዘብ ለመግዛት አልተቸገረም። ሰዎቹ ገንዘብን ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱ ስለሆነ ግንባሩም፣ ሠራዊቱም፣ ግንቦቴውም፣ ብአዴንም ሲከፍላቸው ቀሚስ ገልበው ይተኙላቸዋል። የሚገርሙ የፖለቲካ አመንዝራዎችንም አይቻለሁ። ብቻ ብአዴንም የራሱ ፋኖ እንዳለው ሊታወቅ ይገባል ነው እያልኩ ያለሁት።…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም።” ምሳ 27፥22 “…ጉዳትን ይፀንሳሉ፥ በደልንም ይወልዳሉ፥ ሆዳቸውም ተንኰልን ያዘጋጃል።” ኢዮ 15፥35

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ኮመንት እያነበቡ በቲክቶክ Live ልቅሶ ግን አይከብድም…? …አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ። አሁን እኔ ልሳቅ ወይስ ላልቅስ…?

• ለዚህም Live ታብታብ ኮፒሊንክ ሼር… ጊፍት ላኩ ይባል ይሆን እንዴ? ሪፖርት እያደረጉብን ነው ምናምንስ… ቢጨንቀኝ እኮ ነው አትፍረዱብኝ። አንበሳ ነው የሚወርደው አበባ የሚሰጠው?

• ምን አገባኝ ግን ምን ጥልቅ አደረገኝ? አንዳንዴ እኮ ሲያመኝ ጤና የለኝም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሚንስትር ኦቦ ዓለሙ ስሜ በነዳጅ የሚሠሩ መኪኖች ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት አቁመናል ባሉ ማግሥት ቄሮ በፀሐይና በሳር ኃይል በጭድ ጭምር የሚሠሩ ዘመናዊ 00 ባለጊዜ አህዮችን በመጠቀም የትራንስፖር አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የደረሰኝ ዘገባ ያመለክታል።

• ዘገባው የሪፖርተሮቼ ጉማ ሰቀታ እና ዳንኤል ዻባ ነው።

• ቦሌ ቦሌ…😂 ጉድሽ ፈላ በፋንድያ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዜና ንግድ ባንክ…

"…ባለፈው ወር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ አግባብ ብር የወሰዱ ናቸው የተባሉ ከ95 ሺህ እስከ 80 ሺህ ያህል ሰዎች ብሬን ካልመለሱ ፎቶግራፋቸውን አሰራጫለሁ ማለቱ ይታወሳል። ይኽው እንደ ፎከረው ንግድ ባንክ ፎቶአቸውን መለጠፍ መጀመሩ ተሰምቷል።

"…ባንኩ አለግባብ የወሰዱትን ገንዘብ የማይመልሱ ግለሰቦችን ምስል ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁንም አስታውሷል።

"…እናም በዚህም ለ2 ዙር የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶ ማሰራጨቱን አመልክቶ አሁን ደግሞ ዛሬ በ3ኛ ዙር ያልመለሱት የገንዘብ መጠን ከ95 ሺህ እስከ 80 ሺህ ብር ድረስ የሆነ ግለሰቦችን መረጃ ለማውጣት መገደዱን ገልጿል።

• ኧረ መልሱለት… 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እስከ አሁን 3 ሞተዋል…!

"…የዐቢይ አሕመድን የገጽታ ግንባታ ለማካሄድ እና በዚያውም በኦሮሞ ሕዝብ እንዴት እንደሚወደድ፣ እንደሚፈቀድ ለማሳየት የኦሮሙማው የብልጽግና ካድሬዎች ሕዝቡን ሰልፍ ለማስወጣት ዘዴ የዘይዳሉ። ለራበው ሕዝብ እርዳታ አለ እንዳትቀር አሉት። ለሆዳሙ ደግሞ የጫት የበርጫ መግዣ አበል ተለቋል እንዳትቀር አሉት። ሁለቱም ግልብጥ ብለው ወጡ።

"…ይህ የሚሆነው በምዕራብ ሀረርጌ በትላንትናው እለት መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓም ነው። ሕዝቡ በቦታው ሲደርስ ካድሬና የቀበሌ አዘጥዛጭ "አቢቹ አማላጅ ነው" የሚል ባነር እና የOBN ጋዜጠኞች እና የካሜራ ባለሙያዎች ሊፖተልኩ ሰፍ ብለው ቆመዋል።

"…ስፍራው በአራዳ ጥቂት ጨፍጫፊውን ሥርዓት በሚደግፉ፣ አበል ፈልገው በወጡ እና ለራባቸው የርዳታ ስንዴ ለመቀበል በወጡ ምስኪኖች ተጥለቀለቀ። ሕዝቡ ጥያቄ መጠየቅ ጀመረ። የት አለ አበሉ? የት አላ ስንዴው? በሚል ጭቅጭቅ ተጀመረ። ጭቅጭቁ ወደ ግርግር ተቀየረ። መግባባት ከየት ይምጣ።

"…ቆይቶ ብልጽግና ግርግሩንና ጥያቄውን ለማብረድ ሚሊሻውን አዘዘች። ቀጥቅጠው ማልአባሺ ብለው አዘዙት። ሚሊሻም ያን የተራበ ሕዝብ እንደምታዩት ባልበላ አንጀቱ አናት አናቱን ይነርተው ጀመር። አበልም ዘይት ስንዴም ሳይቀበል ኦሮሞ ተወግሮ ደሙን ለመሬት አፍስሶ ወደ ቤቱ ተመለሰ። እስከአሁን ሦስት ሰዎች መሞታቸው እየተነገረ ነው።

"…ኦነግም፣ ኦነግ ሸኔም፣ ፋኖና ጁንታ፣ አልሸባብም በዚህ ግድያ የሎበትም። ገዳዩ አቢይ አሕመድ ነው። ኮሬ ነጌኛ፣ ጋቸነ ሲርና። የሞቱትን ነፍስ ይማር።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እየተደነሣቹ…

"…ፋኖማ ዘንድሮ ጉዱ ነው የፈላው…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እግዚአብሔር ይመስገን…!

"…ፕሮቴስታንት ካልሆንሽ ጌታን ካልተቀበልሽ ፍዳሽን ነው የምትበዪው ብለው። ዐማራ ሆና ሳለ ትግሬ ናት ብለው አስረው ፍዳዋን ያበሏት እህታችን ዛሬ ሥራ ማግኘቷ ተሰምቷል።

"…የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንና እና የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተባብረው ሞራሏን ለማድቀቅ የደከሙባት ትዝታ ገረመው በኢትዬጵያን ቢዝነስ ሪቪዊ (Ethiopian Business Review) የመረጃ ጥንቅር እና ምርምር ኦፊሰር (Data Researcher) ሆና ከሚያዝያ 1/2016 ዓም ጀምሮ ሥራ ለመጀመር ከድርጅቱ ጋር ተፈራርማ ዛሬ የቅጥር ደብዳቤዋን ተቀብላለች።

“…በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።” ምሳ 27፥18 …ስንቱ ለሆዱ ብሎ ሃይማኖቱን ቀየረ። ማዕተቡንም በጠሰ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ባለ ጊዜ… ጋቸነ ሲርና… ኮሬ ነጌኛ…

"…አፋኝ፣ አፍራሽ፣ ወራሽ … አያችሁልኝ ደረቱን…?

"…ብልፅግና ማለት ደርግ ማለት ነው። መሪዎቹም ኮሮኔሎች። ኮሮኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም እና ኮሮኔል አቢይ አሕመድ… ሁለቱም በኢትዮጵያ ስም ጨፍጫፊዎች።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አይ አማሪካ…አንቺ እኮ…😂 ታስቁኛለሽ

Читать полностью…
Подписаться на канал