zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የታሉ እነ ፍትህ ለፌቨን…!

"…ይቺ ኦርቶዶክሳዊት ሰንበት ተማሪ ልጅ ሰሞኑን ከ4 ቀናት በፊት ነው ጀቤቷ ወጥታ ታፍና ተወስዳ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ የተገኘችው።

"…ይህችን ኦርቶዶክሳዊት ታዳጊ ልጅ የገደሏት ሰዎች ደፍረው ጭምር፣ ዓይኗንም በሹካ ወጋግተው አፍስሰው እንደሆነም ተነግሯል። ግን ዐማራ ክልል ስላለሆነ ወንጀሉ የተፈጸመው አንድም ጃል አክቲቪስት ትንፍሽ አላለም።

"…አኬሩ የሆነ ቀን፣ የሆነ ጊዜ መገልበጡ አይቀርም። ግን መርጦ ማልቀስ ቢቀር ለማለት ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ዱላው ጎማ ነው አይደል?

"…ይሄ ቀፋፊ ነገር ዐማራ ክልል ቢሆን፣ ያውም ከዐማራም ክልል ጎጃም፣ ፖሊሱም ከነገደ ዐማራ ቢሆን ኖሮ ዛሬ በማኅበራዊ ሚድያውም ሆነ በእነ ኢቲቪ ፋና ቴቪ ምን ይፈጠር ነበር ብላችሁ ትገምታላችሁ?

• OMN,KMN, ወዘተ ምን ይሉ ነበር?
• እነ ጃል ወያስ፣ ጃል ያያ፣ ጃል ሀፍታሙ፣ እነ ጃል ማኚቲስ፣ ጃልቲቲ ሮማንቲቲስ ምን ብለው ቲክቶኩን ይቀውጡት ነበር?

• አህመዲን ጀበል፣ ሙጂቦ፣ የሴቶች ጉዳይ፣ የእስልምና መጅሊስ፣ በቅርቡ ገሌ የገቡ የኦሮሞ አክቲቪስቶች፣ የስልጤ ሙስሊሞች፣ ፕሮዎች ምን ይሉ ነበር?

• ኤርሚያስ ዋቅጅራና ገመድ አፍ ተብታባው የግብዳ ጩጬ አራስ መሳዩ አኞ ሞገስ ዘውዱስ ምን ብለው ይተነትኑት ነበር?

"…ዮናስ ቬጋስ የሻማ ማብራት፣ አዳነች አቤቤ ኮንዶሚንየም ትሰጥ ነበርን? ለልጅቷ አዝናለሁ ድርጊቱ ግን እንኳንም ጎጃም አልተፈጸመ።

"…ግንባሩና ባልደራስ ሁሉ ዘመነ ካሤ እኚኚ ይሉ ነበር። ብቻ መቺውም፣ ተመቺዋም እንኳንም ኦሮሞ ሆኑ። ቦታውም እንኳንም ኦሮሚያ ሆነ። እንቁጣጣሽ ይረበሽ ነበር።

"…ሁሉንም ዐማራ ላይ ጓ የሚሉ አክ እንትፍ ስቶችን ተዟዙሬ ሳይ ፀጥታ ሲያበዙ፣ ዝም ጭጭም ሲሉ ባይ እንዲያውም ልጅቱና ፖሊሱ ተጠቃቅሰው አጀንዳ ለመስጠት ድራማ የሚደርሙ ሁላ ነው የመሰለኝ። እደግመዋለሁ ይሄ ወንጀል እንኳንም ጎጃም ያልተፈጸመ፣ አያሌው መንበር ራሱ አረፋ እየደፈቀ ከች ይል ነበር።

• የምትደበደበው ልጅ ወንድ ቢሆንስ፣ መመታቷን እንጂ በምን እየተመታች እንዳለ የማያገናዝብ ሰው ፍልጥ መስሎት ይደነግጥ ይሆናል፣ እናም ተመቺዋ ወይም ተመቺው ከውስጥ የጎማ አለንጋው መከላከያ አድርጎ ቢሆንስ፣ የሚሉ ጨካኞችም ገጥመውኛል። ዱላው ግን ከምር ጎማ ነው?

• ፍትሕ ለእሕታችን፣ ለእናታችን። ምን አገባህ በለኝ አሉህ ደግሞ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዛሬውን መብረቅ ነጎድጓድ የመሰለ፣ ሱሰኞች ላይ የሰነዘርኩትን የጭቃ ዥራፍ ርእሰ አንቀጽ አንብበው ሲጨርሱ ብዙ ሱሰኞች ብው ብለው ይበሳጩብኛል፣ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠሩብኛል፣ ሺሻ ቤት ያላቸው ቲክታከሮችም ፎቶዬን ዘቅዝቀው ቡቺ ቡቺ ብለው ይዝረከረኩብኛል ብዬ ጠብቄ ነበር። ስኳድም አኩርፎ ይሄ ተሳዳቢ ምናምን ይለኛል ብዬ ጠብቄ ነበር። ነገር ግን ወፍ የለም።  ሙንኦኖነው? በሰላም ነው?

"…ለማንኛውም የአንድ 50 ያህል ሰዎችን አስተያየት እቀበልና ወደ ሌሎች ዜናዎቻችን እንሄዳለን። የቀበሮ ሜዳ ልጆቻችንን የጀመርነውንም ጉዳይ ወደ ማታ ላይ እንረባረብበታለን።

"…አትፍሩ፣ አትሽኮርመሙ፣ እናንተስ ስስ እንዴት እያደረጋችሁ ነው? …ሱስ አፈር ከደቼ ያበላቸው፣ ከሰውነት ተራም ያወጣቸው ሰዎችስ የሉምን? በመጪው አዲስ ዓመት አንተ ሱሰኛው ምን ወሰንክ? እስቲ ተንፍስ…!

• 1…2…3…ጀምሩ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

ETHIOPIA| ~ ለሚሂኢኢኢ ፍየሊት ጫታም ትውልድ የጦመርኩት ነው።
       
"…ዛሬ ጷጉሜን ፭ ከሱስ ለመላቀቅ የውሳኔ ሓሳብ የምናጸድቅበት ቀን ነው። በዚያውም ከዚሁ የውሳኔ ሓሳብ የማጽደቅ ጎን ለጎን ደግሞ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን ካለን አካፍለን አረጋውያንን የምንረዳበት፣ የምንጎበኝበትም ቀን ነው። እናም ለዛሬ ከሱሶች ሁሉ ቀፋፊ ስለሆነው የጫት ሱስ ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁን ደግሜ እለጥፍላችኋለሁ። ሲጋራም፣ ሃሺሽ ሺሻ፣ ካቲካላ ዝሙትም ያው ነው።

"…ጦማሩን እያነበባችሁ በሳቅ ፍርፍር እንዳትበሉ ተጠንቀቁ። እያጓራችሁም ሰው አትረብሹ። ለጫታሞች ግን SHARE በማድረግ ተባበሩዋቸው። ከምሳ በፊት ካነበባችሁት የምግብ ፍላጎታችሁን ሊዘጋ ስለሚችል ባታነቡት፣ ከምሳ በኋላም ከ30 ደቂቃ በኋላ ብታነቡት ይመከራል። ዘጋኝ፣ ዘጋኝ፣ ዘጋኝ እንዳትሉ ብዬ ነው።

"…ዛሬ አመስጋኙ ሁሉ ዘግይቷል። ምክንያቱም ደግሞ ሲመስለኝ በፎቶው ላይ የሚታየው የጫት፣ የሺሻና የሰካራሞች ፎቶ ስለሚያስደነግጥ ይመስለኛል። ይቀፍፋል ግን የግድ ማየት፣ ማንበብ ይጠቅማል። በዛሬው ርእሰ አንቀጽ ለጫትና ለጫታም አግዛችሁ የሚሰድበኝ አይጠፋም። ስትፈልግ ለምን ጧ አትላትም ኬሬዳሽ…እኔ ደስ እያለኝ እንዲህ እጦምረዋለሁ።

"…ጫት ማለት የኢትዮጵያን ወንዶች በሙሉ ወንድነታቸውን ሰልቦ ቀምቶ ሰንርቆ ስንትና ስንት ጀግና ጀግና ወንዶችን እንደ ለማዳ ድመት ፍራሽ ለፍራሽ ሲያንደባል፣ ሲያንከባል የሚኖርረ ወኔ ሰላቢ፣ አነፋራቂ አደንዛዥ ዕፅ ነው። ጫት በክርስትናም ክልክል ነው። በእስልምናም ሃራም ነው።

"…ጫት ማለት የስንቱን ጀግና ወንድ መቀመጫውን ሳይቀር ክው ብሎ ደርቆ የተላገ፣ የተፋቀ የጣውላ እንጨት አስመስሎ በማሽላ እርሻ ውስጥ እንደተሰቀለ የግሪሳ ወፍ ማስፈራሪያ አሻንጉሊት በባዶ ሜዳ በነፋስ ጭምር እየታገዘ ሲወዛወዝ እንዲኖር አድርጎ እያዋረደ ያለ አደገኛ አደንዛዥና አጀዛቢ መርገምትም የሆነ ዕፅ ነው።

"…ጫት ጥንቱን የተፈጠረው ለፍየል ምግብነት ነበር። የፍየልን ፈንታ የተፈጥሮ ምግቧን ነው የኢትዮጵያ ሰው በግፍ በአደባባይ መንግሥት ባለበት ሀገር ቀምቶ የወረሰው። ወርሶ መች በዚያው ቀረ? ለቅርብ ጎረቤት ሀገራት ለየመን፣ ለጅቡቲና ለሱማሌ በእርጥቡ፣ ለአማሪካና ለአውሮጳ ለአውስትራሊያና ለአረቦች ደግሞ ጫቱን አድርቆ፣ ወቅጦ፣ ፈጭቶ በዱቄት መልክ አሽጎ እየላከ በመአብቸብ ስንቱን ስደተኛ ያጀዘበ ዕፅ ነው። ክቡር የሆነው የሰው ልጅ የፍየልን ምግብ በግፍ ቀምቶ በመብላቱ ተዋረደ፣ ክብሩንም አጣ፣ ዓይኑ ፈጠጠ፣ ጥርሱም ገጠጠ፣ ሻገተ፣ ገማ፣ ከረፋ፣ ሸተተም፣ ረገፈ። እንቅልፍ ያጣ ፈጣጣ ጀዝባ ፍጡርም ሆኖ ቀረ። ጀዝባ።

"…ጫታሞች ሲበዛ አልቃሾች ናቸው። ደግሞም በባዶ ቤት የሌለ ህልመኛም ጭምር ናቸው። ጫታሞችን በምርቃናና ሺሻ ቤት ተቀምጠው በአንድ ጊዜ ቢልጌትስንና አላሙዲንን ሆነው ራሳቸውን በራሳቸው እያረኩ እንዲያስደስቱም የሚገፋፋቸውም ይኸው ወስዋሽ ሰይጣናም የሆነ ዕፅ ነው። በጫት ምርቃና የተደረሰ የፊልም ድረስት፣ የዘፈን ግጥምና ዜማ እንዲሁ በማሽተት ይታወቃል። ዜማው ዝሙት ነው፣ በትዳር ላይ ማማገጥ የበዛበት ፊልም ካያችሁ የጫት ምርቃናና የሺሻ አጫጫሿን ቀዮ ገላ እያየ በምርቃና ለሃጩን ያዝረከረከ ህልመኛ ደረሲ የደረሳቸው የድርሰት ውጤት መሆናቸውን ማወቅ ይገባል። ጫታም ደራሲ ካለ ዝሙት፣ ካለማማገጥ ሌላ አይታየውም። ይሄ ዝሙታም።

"…ጫት የሱሳ ሱሶች ሁሉ ሰብሳቢ ማግኔትም ነው። ጫት ሲጋራንና ሐሺሽን ያስከትላል። ከዚያም ለጨብሲ ብሎ ካቲካላ አምቡላን አረቄንም የሚስብ ማግኔት ነው አጅሬ ጫት። ጫት ቀላል አይምሰልህ። አዳሜ እና ሔዋኔ ሁሉ ይሄን ሁሉ የሱስ መዓት በላዩ ላይ እንዲከምር እና እንዲግፍ፣ የሱስ ጎተራም እንዲሆን ያደርገውና ከዚያ ሱሰኛው ሁሉ በየጎዳናው ሲያስመልስ፣ ከስልክ እንጨትና ከፖሊስ ከመንገደኛ ጋር ሲጋጭ፣ በሌባ ሲበረበር፣ ከቱቦ ሲደፋ፣ ክብሩን አጥቶ እንዲኖር ሲሚያደርግ፣ ከጋለሞታም ጭን ስር ሳይወድ በግዱ እንዲወሽቅ፣ በዝሙት ጦር እንዲወጋ የሚያደርግ አደገኛ ዕጽ ነው። በተለይ ለክርስቲያን ጫት አዋራጅ ነው። ግማቱም አይጣል። ክርፋቱ።

"…የጫት ሱሰኛ የሆነ ወንድና የሆነች ሴት ታመው ለሀኪም ምርመራ ሰገራ አምጡ ቢባሉ እንኳ የገዛ ሰገራ አይኖራቸውም። ሰገራ የላትም። ቢኖረውም በመከራ፣ በስቃይ፣ በስንት ምጥ ነው የሚመጣው ይላሉ የጫት ሱሰኞቹ። የጫት ሱሰኛ የሆነ ግለሰብ ከአንተ ቀድሞ መጸዳጃ ቤት ከገባ አንተ ያለህ ምርጫ እርምህን አውጥተህ ኮንትራት ታክሲም ጠርተህ፣ ራቅ ያለ ጫካ ወይም ከመኖሪያ ቤትህ ብትሄድ ይቀልሃልም ይላሉ። ጫታም መጸዳጃ ቤት ገብቶ 4 ሰዓት ሙሉ እንደ ወላድ ሴት የሌለውን ካካ እንዲኖረው በመመኘት እንደ ወላድ ሴት ሲያምጥ ለመኖር በራሱ ላይ የፈረደ፣ ራሱንም ለመከራና ለምጥ ፍርድ አሳልፎ የሰጠም ጉደኛ ነው። ጫታም ሰው "የወንድ ምጣም" ነው ይላሉ። ጫታሞቹ።

"…ጫታምን ሰው አፉ እንዲከረፋ፣ እንዲሸት፣ እንዲገማ፣ እንዲጠነባ ያደርገዋል። የጫታም ሰውን አፍ እንደፈነዳ ሽንት ቤት ቁጠሩት። ቁናሱ አይጣል ነው። ጫታም በጫት ጥርሱ እንዲቦሮቦር እና ለጥርስ ህመም እንዲጋለጥ ያደርገዋል። ጫታም ሰው ከሰው መሃል ጮክ ብሎ ማውራት እንኳ አይችልም። ገርልፍሬዱንም ሆነ ያገባትን ሚስቱን ከንፈሯን መሳምም አይችልም። የራሱን ልጆችም ሆነ የሌላ ሰው ልጅ ዓይቶ መሳም፣ ማድነቅም አይችልም። በአፉ መጥፎ ጠረን ምክንያት ሲሳቀቅ ይኖራል። ጫት የ40 ዓመቱን ጎልማሳ ጎሮምሳ ከ30 ኪሎ የቀለለ ገለባ ያደርገዋል።

"…ጫታም ሰው መውለድም ማስወለድም አይችልም። ነገርየው አይታዘዝለትም ይላሉ በዘርፉ ብዙ ያጠኑ የመራቢያ አካላትን እንቅስቃሴ የሚያጠኑ ባለሙያዎች። የጫታም ሚስት ጫታም ባሏ አጠገብ ተኝታ ስትቃጠል ነው የምታድረው። ስትነድ ነው የምታድረው ይባላል። ሞቷላ። እንደ አጋጣሚ፣ እንደ ዕድል ሆኖ በድንገት ቢያስወልድ እንኳ ልጆቹ የራብ ማስታወቂያ፣ ሚስቱ ጎስቋላ ነው የምትሆነው ይላሉ። ምክንያቱም ሱሰኛ ነዋ። የጫታም ሰው ትዳር አይጸናም። ጫታም ሥራ ጠል ደካማም ነው። ሐሞቱም የፈሰሰ፣ ወንድነቱ የተሰለበ ነው። ስለሀገር ፍቅርም፣ ስለ ሚስት ፍቅርም ደንታ የማይሰጠው ወኔው የተሰለበ ነው። ጫት መግዣው ውድ ስለሆነም ጫታም ሰው በተፈጥሮው ሌባ ነው የሚሆነው። ባለ ሥልጣን ጫታም ሀገር ይሰርቃል። ወጣት የቤት ዕቃ ሰርቆ ይሸጣል፣ የሚሰረቅ ሲያጣ ማጅራት ይመታል። አዎ ለሱሱ ሲል ይሰርቃል፣ ይዘርፋል፣ ይገድላል። ጽንፈኛው ቄሮ ሰምተሃል !!

"…የተማረ ጫታም ደግሞ አይጣል ነው። በቢሮው አይገኝ። የሰዓት ሌባ ነው። ፀሐይ ከበረታ ስብሰባ ላይ ናቸው ብሎ የሀገር ሰዓት፣ የሀገር እድገት የሚሰርቅ ሌባ ነው። ሱፍና ከረባት አጥልቆ፣ V8 ቱን እያሽከረከረ በየስርቻው በየጉራንጉሩ የአይሬ ሰዓት እያለ እየተወሸቀ፣ ሲርመጠመጥ፣ ቀትረ ቀላል ባለ ሥልጣን፣ የቢሮ ሓላፊም ይሆናል። ጫታም ዳኛ ፍርዱ ጠማማ ነው። ጫታም ትራፊክ መራታ ዘራፊም ነው። ጫታም በቃ ጫታም ነው። አለቀ። 👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ሮሜ 13፥1114

“…የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።” 1ኛ ጴጥ 4፥3

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች
አጭር የምሥራች ሪፖርት

1ኛ፦ 5 ~ ኩንታል ጤፍ ተችሏል።
2ኛ፦ 5 ~ ሰንጋ ተችሏል።
3ኛ፦ 5 ~ ፍየል ተችሏል።
6ኛ፦ ውኃ፣ ለስላሳ በሙሉ ተችሏል
7ኛ፦ ቅቤ፣ ሽንኩርት፣ በርበሬ፣ ጨው፣ ቅመማ ቅመሙ፣ ማገዶው ሁሉ ተችሏል። ተዘጋጅቷልም።
8ኛ፦ ድንኳን ኪራይ፣ የወንበር፣ የወጥ መሥሪያ ድስቶችና ሰሀኖች ተችለዋል። አዝማሪ ሁላ አይቀርም የበዓሉ ዕለት። ደስ ብሏቸው እንደ ሀገራቸው በዓል ያሳልፋሉ። ይሄ ለበዓሉ ነው። ለእንቁጣጣሽ፣ ለአዲስ ዓመት። ድፎ ዳቦ ቄጤማ ሁሉ አልቀረም ሲዘጋጅ።

9ኛ፦ 1200 ብርድልብስ ተችሏል።
10ኛ፦ 2400 አንሶላ ተችሏል።
11ኛ፦ 1200 ፍራሽ ተችሏል

"…ይሄ ለመኝታቸው ነው። አፈር ላይ ከሚተኙ፣ በትል ከሚበሉ ብዬ እናንተን ለምኜ ነው ያሟላላችሁልኝ። በጣም ነው ደስ ያለኝ። ቀጥሎ ለተማሪዎቹ ያሰብኩት ነው።

11ኛ፦ ትምህርት ቤት። ሊሊ ጀምራው የቆመውን ግማሽ ሚልዮን ብር አውጥቶ ለበዓሉ ሰንጋ የገዛላቸው አቶ ወርቁ አይተነው እኔ አስፈጽመዋለሁ በማለት ዘግቶታል።
12ኛ፦ 3,300 የተማሪ ቦርሳ ተችሏል
13ኛ፦ለ3,300 ተማሪዎች ደብተር
14ኛ፦ለ3,300ተማሪዎች እርሳስ
15ኛ፦ለ3,300 ተማሪዎች እስክሪብቶ ጎንደሬው የአፄዎቹ ልጅ አውሮጳ ስዊድን የሚኖረው ወዳጄ አቶ ቴዎድሮስ መለስ በሙሉ ዘግቶታል።

"…አሁን የሚቀረው ለ3,300 ተማሪዎቹ የሚሆን የደንብ ልብስ ነው። መለመን ጀምሬአለሁ። የአንዱ ዩኒፎርም ዋጋ 700 ብር ነው። 100$ 17 ይችላል። ተረባርበን እንፈጽማት። ደግሞም እንችላለን።

👉🏿 +4915215070996 የእጅ ስልኬን ሴቭ አድርጉና በኋትስአፕ ወይም በቴሌግራም ቃል የገባችሁትን ጻፉልኝ። እኔም የባንክ ቁጥራቸውን እሰጣችኋለሁ።

"…ዘመቻ 3,300 የደንብ ልብስ ማሰባሰብ በይፋ ጀምሬአለሁ። ተቀላቀሉኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ታርሟል…!

"…በትናንትናው ዕለት የቴሌግራም ጥቆማዬም ሆነ በምሽቱ የመረጃ ተለቭዥን የነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ ቢስተካከል ብዬ በቅን ልቦና ተነሣስቼ ወደ ላይ ተንጠራርቼ ለብልፅግናው ሊቀመንበር ያቀረብኩት የማስተካከያ ሓሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ተረስቶ የነበረው የአፋን ኦሮሚፋው የላቲን ቁቤው መልእክት ተጨምሮ ታትሟል። ፈረንጆቹ ቅር እንዳይላቸው ነው የእንግልጣር አፉ የተረሳው? 😂

"…ቆይቶም ቢሆን በላቲን በቁቤ አፍ ኢትዮጵያ ተጽፋለች። ከትናንቱ የይታረም መልእክቴ የሚቀረው፣ ያልታረመው አረፍተ ነገሩን "በ አራት ነጥብ መዝጋትና። ያው እንደ ሌላ ግዜው በእንግልጣር አፍ መጻፉ ብቻ ነው።

"…የሀገሪቱ ርእሰ ብሔር የፌስቡክ ገጽ ላይ የሀገሪቱን ብሔራዊ ቋንቋ ሆሄያቱንም ሆነ ሥርዓተ ነጥቡን 👉🏿 ። ፣ ፤ ፡ ወዘተ በተገቢው መንገድ ያለመጠቀም ያስገምታል። ይስተካከል።

"…በላቲኑ መልእክት ላይ አረፍተ ነገሩ የተዘጋው 👉🏿 . ነው። ለላቲኑ ሥርዓተ ነጥብን ጠብቆ ለአማርኛ 👉🏿 ። መንፈግ ልክ አይደለም። ይሄ እኔ አሁን የምተቸው ነገር ለእነ ስዩም ተሾመ፣ ለእነ ዮኒ ማኛና ለእነ ጉማ ሰቀታ ሊገባቸው አይችልም። በፍጹም አይገገባቸውም። የምጽፈው መልእክቴንም የማስተላልፈው ለሚመለከታቸው ነው። አንድ የሀገሩን ቋንቋ ሥርዓተ ፊደል የማያውቅ ጠቅላይ ሚንስትር አለ ቢባል የሚያሳፍረው እኔንም ጭምር ነው። እነ ሪፖርተር፣ የቀድሞዎቹ አዲስ ነገር ጋዜጦች፣ አዲስ ዘነመንም አርታኢዎች አሏቸው። ቶፕ ቪው ቀረጻ የሚሠሩ የካሜራ ባለሙያ እንደሚቀጥሩት ሁሉ ፊደሉን የሚያርሙ ባለሙያዎች መቅጠር አይጎዳም።

"…ፀሎት አይባልም ጸሎት እንጂ፣ ጸሐይ አይባልም ፀሐይ እንጂ መንግስት አይባልም መንግሥት እንጂ፣ በጭካኔው እኔ ስለ ናቅሁት አቢይ ብዬ እጽፈዋለሁ እንጂ አቢይ አይባልም ዐቢይ እንጂ።

• ቆይቼ እመጣለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

ETHIOPIA |~ ጳጉሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማ እና
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን።

"…ኢትዮጵያና ቤተ ክርስቲያን ሁለቱም አንድ ናቸው። ድርና ማግ። የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎችም ናቸው። ይሄን ማለት ሌላውን ማበሳጨት አይደለም። ሌላውም ታሪክ ጠቅሶ በራሱ መንገድ የራሱን ነገር የመግለጽ መብቱ የተጠበቀ ነው። አትበሳጭ። አትናደድ። አንተም አለኝ የምትለውን መረጃና ማስረጃ እየጠቀስክ ጻፍ፣ መስክር፣ ተናገር። መብትህ ነው።

"…በዘመነ ፌስቡክ የጀመርኩት የወርሀ ጳጉሜን ዕለታቱን ሰይሞ ሲያስቡ መዋል ይኸው ከመንደረ ፌስቡክ ተባርሬ ወደ መንደረ ቴሌግራም ስመጣም ሳይቋረጥ መከበር ቀጥሏል። እንደ መርሀ ግብራችን መሠረት ዛሬ ጳጉሜን ፬ አስበን የምንውለው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ዓላማችንን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነው። እናም ዛሬ ቴሌግራማችን በሁለቱ ምሥሎች ተጥለቅልቆ ይውላል ማለት ነው። ከዋሻ እስከ ካቴድራል፣ ከገጠር እስከ ከተማ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ፎቶዎች ይለጠፋል፣ የአጥቢያችሁ፣ የደብራችሁም ፎቶ ይለጠፋል። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀሚስ፣ ሻሽ፣ ነጠላ፣ ጃኖ፣ ጥንግ ድርብ፣ ኩታ እና ኮፍያ ጭምር ይወጣል፣ ይገለጣል፣ ይለጠፋልም።

"…በኢትዮጵያ ምድር ሁለቱም ሲዋረዱ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይዋረዳሉ። ሁለቱም ሲሰደቡ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይሰደባሉ። ሁለቱም ሲናቁ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይናቃሉ። ሁለቱም ሲቃጠሉ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይቃጠላሉ። በሥጋ ይቃጠላሉ፣ አንጀታቸውም እርር ድብንም ይላል። መንፈሳቸውም ይታወካል።

"…በኢትዮጵያ ምድር ሁለቱም ከተደበቁበት፣ ከወደቁበትና ከተጣሉበት ሲነሱ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይነሳሉ ከፍከፍም ይላሉ። ሁለቱም ሲከበሩ ኢትዮጵያውያን አብረው ይከበራሉ። በየሄዱበትም መንገድ ይከፈትላቸዋል፣ ወንበርም ይለቀቅላቸዋል። ሁለቱም ሲወደዱ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይወደዳሉ። ሁለቱም ሲወደሱ፣ ሲዘመርላቸውም ኢትዮጵያውያንም ሁሉ አንጀታቸው ቅቤ ይጠጣል። ህሊናቸው ያርፋል፣ መንፈሳቸው ይረካል። ልቦናቸውም ሀሴት ያደርጋል። የደስታ ዕንባም ያነባል።

"…የሰንደቅ ዓላማ ክብር፣ ፍቅር የሚገባህ በባዕድ ሀገር ተቀምጠህ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በሰማይ ላይ ሲበር ድንገት ስታየው ነው። በየአውሮፕላን ጣቢያው በትኬት መሸጫ ቢሮዎች ተርታ ስታየው ነው፣ በኦሎምፒክ እና በአለም ሻምፒዮና የስፖርት ውድድር ላይ አትሌቶቻችን አሸንፈው በቴሌቭዥን መስኮት ለብሰውት ሲሮጡ ስታየው ነው፣ በባዕድ ሀገር እናቶች፣ እህቶች፣ አባቶችና ወንድሞች፣ ኢትዮጵያውያንም፣ የውጭ ሀገር ዜጎች ድንገት ለብሰውት ስታየው አቤት የምታደርገውን ነው እኮ የሚያሳጣህ። ያቁነጠንጥሃል።

"…በውጭ ሀገር ብቸኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። ካለችበት የስደት ሀገር በቀኝ በኩል ከመቅደሱ ከታቦቱ ፊት፣ በውጭ በሕንፃው ላይ፣ በሰንደቅ ዓላማ መስቀያው ላይ በክብር ታየዋለህ። ኤምባሲዎችም ስሜት አይሰጥም እንጂ አምባሻው ያለበትን ይሰቅሉታል። የሐበሻ ሆቴሎች፣ የሐበሻ ሱቆች፣ ሰንደቅ ዓላማችን በግልፅ የሚታዩባቸው ስፍራዎች ናቸው። አውርድ፣ አንሳ፣ አውልቅ፣ ላቃጥለው የሚል ቄሮ ስለሌለበት እሱን ስታይም እንዲሁ ልቦናህ በሐሴት ይሞላል። በሀገር ቤት ሳለ ቅደሴ የማያስቀድስ ሁሉ በውጭ ሀገር አስቀዳሽ ነው። በሀገር ቤት አልጋው ላይ ተኝቶ እንደሬሳ እንደ አስከሬን ተኝቶ ከቤተ ክርስቲያን በድምጽ ማጉያ በሚሰማ ጸሎት ላዩ ላይ የሚቀደስበት ሰውዬ በውጭ ሀገር ቤተ ክርስቲያን ፍለጋ 4 ሰዓት መኪና ነድቶ፣ ባቡርና አውቶቡስ ተሳፍሮ፣ ተንከራቶ ሄዶ ነው የሚያስቀድሰው።

"…በሀገር ቤት የምንንቀው እንጀራ እንኳን እንደ ሃሺሽ ሱሰኛው መሆናችን የሚታወቀው ኢትዮጵያን ለቅቀን የወጣን ጊዜ ነው። ለዚህ ነው ጤፍ ባይገኝ እንኳ ስንዴ እና ሩዝ አቡክተው በሥጋ መጥበሻ ጋግረው እንጀራ የሚመስል ቂጣ ለመብላት መከራ የሚበሉት። ወዳጄ እነ ሩዝ በውጭ ሀገር የጎጃምና የአድአ ነጭ የማኛ ጤፍን አስንቀው ነው የሚያስደምሙህ። የፈለገ ቢሆን ግን ጤፍን አይተኩም። የኢትዮጵያውያን ጤና መሆን ያሳሰበው አቢይ አህመድ ቢልጌትስን ጋብዞ ጤፍን በስንዴ ካልተካሁ ብሎ ሲፎገላም ታይቷል። ስንዴ።

"…ሁለቱም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ሰንደቅ ዓላማችን ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደርጋሉ። ያስማማሉ። ያኮራሉ። ያዋድዳሉ። ያፋቅራሉ። በአንድነት በአንድ ዓላማ ጥላም ሥር ይሰበስባሉ። በትግራይ ይሄን መንፈስ ወያኔ ሰብራዋለች። ኢትዮጵያ የሚለው ስም በትግራይ በባንክ እና በአየር መንገዱ ሮጲላ፣ ጠያራ ላይ ብቻ ነው የቀሩት። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ አየር መንገድ። በቀር እነ አባ ሰራቂ መናፍቅ ከትግራይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለውን ስም ፍቀው በትግራይ ተክተዋል። ኦሮሞም እንደ ትግሬ ኢትዮጵያ ከሚለው ስም እና ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለመነጠል እየተፍጨረጨረ ነው። እናም ዛሬ ሁለቱንም ስናከብር እንውላላለን። ሰንደቅ ዓላማችንንም፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንንም ከፍ ከፍ አድርገን ስናከብር እንውላለን። እኛይ ይሄን በማድረጋችን አንተ ልትበሳጭ፣ አረፋ ልትደፍቅ አይገባም። ለምን ይነስርሃል?

"…ዛሬ በመሃል በመሃል ቀበሮ ሜዳዎችን የጎደላቸውን ዩኒፎርም እያሟላን እንውላለን። የአንዱ ተማሪ ዩኒፎርም ዋጋ 700 ብር ነው። ይህን ርዕሰ አንቀጽ እያነበቡ ስንት ተማሪ ፏ ሊያደርጉ እንደሚችሉ እያሰቡ ይቆዩን። የቦርሳው አልቋል። ደብተርና እርሳስ፣ እስኪሪፕቶውን አቶ ቴዎድሮስ የተባለ ነፍጠኛ ጎንደሬ ወዳጄ ዘግቶታል። የቀረውን እያሟላን እንውላለን። 👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና በኋትስአፕ አልያም በቴሌግራም ላይ ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን የደንብ ልብስ ብዛት የአንዱን ዋጋ በ700 ብር አባዝታችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ። እኔም ወዲያው በፍጥነት ቃላችሁን እመዘግብና የተፈናቃይ ስደተኞቹን ሕጋዊ የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁና በዚያ ትልኩላቸዋላችሁ። በRIA የምትልኩ በጎ አድራጊዎች እርያ ለዐማራ ሲሆን እምቢ ስለሚሏችሁ፣ ሀገር ቤት ላለ ቤተሰብ ልካችሁ ቤተሰብ ሊያስገባላችሁ ይችላል። አመሰግናለሁ። መልካም የሰንደቅ ዓላማ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን ይሁንላችሁ። ዘመቻ የተማሪ ደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) 3,300 ይፋፋም።

"…ነገ ጳጉሜን 5 ደግሞ በመላው ዓለም የምንገኝ ኦርቶዶክሳውያን የሆን በሱስ የተጠቃን ሱሰኞች ከሱስ ለመላቀቅ የምንወስንበት ዕለት ነው። ሲጋራ ይረገጣል። ጫት ይረገጣል። እነ ሺሻ ይጣላሉ። ድሆች ይረዳሉ ይጠየቃሉ። ኢትዮጵያና ሰንደቅ ዓላማዋም፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ሁለቱም ይነሣሉ። ከፍ ከፍም ይላሉ። ሩቅ ባልሆነ ጊዜ በቅርቡ ይነሣሉ። ይነሣሉ አልኩህ ይነሣሉ ነው። ክብራችን፣ ማንነት ጌጣችን፣ ሞገሶቻችን ናቸውና ሁለቱም ዛሬም ነገም ወደፊትም ይከብራሉ። ከፍ ከፍም ይላሉ። ይህ ለምን ሆነ? የሚል፣ የሚናደድ ካለ እርሱ ኢትዮጵያዊ አይደለም። እርሱ ባንዳ የባንዳ የልጅ ልጅ ነው። አከተመ።

•••

ሻሎም…!   ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጳጉሜን 4/2016 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጳጉሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማችንን የክብር ቀን አስበን የምንውልበት ቀን ነው። ነገ የቴሌግራም መንደራችን በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማችን ተጥለቅልቆ ይውላል።

• ማርያምን ኢትዮጵያማ ታሸንፋለች…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 2:10 ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ዛሬ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ በሚገኙ ስደተኞች ካምፕ ነው የምናመሻው። በዚያም እያለቅስንም፣ እየሳቅንም አብረን እያወጋን እናመሻለን። 

• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

• ትዊተር 👉https://twitter.com/MerejaTV

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/sqGQeWriBOA

• Mereja TV: https://mereja.tv

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

ETHIOPIA |~ ጳጒሜን 3 የክብረ ክህነት ቀን

"…በዛሬው ርእሰ አንጻችን ደግሞ ካህናት አባቶቻችንን እና ክህነት እያነሳን፣ እያወደስን፣ እያመሰገንም እንውላለን። ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ካህናቱን ባወደሰበት፣ በመረቀበት ቃል ነው አበው ካህናትን እና ቅድስት ክህነታቸውን እያከበርን በነቢዩም ቃል እኛም እየመረቅናቸው የምንውለው። "…አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው። መዝ 132፥ 8-9 እንዲል እኛም እንላለን አሜን ጽድቅን ይልበሱ። ረጅም የአገልግሎት ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን እያልኩ ስለ ካህኔ መጻፍ እጀምራለሁ።

"…የእኔ ካህን ይህ ነው። ከላይ በምሥሉ ላይ ያያችሁት። አራሽ፣ ቀዳሽ፣ ተኳሽ። ለፍጥረት ዓለሙ ሰዎች ሰዎች በሥጋ እንዳይራቡ አርሶ የሚያበላ ጠንካራ ትርፍ አምራች ገበሬ ነው። ለነፍሳችን ምግብ፣ ለሰማያዊው ቤታችን የሚሆነን ምግበ ነፍስ ቃለ እግዚአብሔርን በልባችን የሚዘራም የነፍሳችን ስንቅ አምራች ነው። ሀገር፣ ድንበር እንዳይደፈር፣ ሃይማኖት እንዳይረክስ ደግሞ በጦርነቱ ጊዜ ተኳሽ፣ ቀንዳሽ ብሎም ሕይወቱን ለሀገሩ አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ የሚያልፍ ነው። የእኔ ካህን እንዲህ ነው። ሌጦ ቆዳ ፍቆ፣ ብራናውን ዳምጦ፣ ቀለም በጥብጦ፣ ብዕሩን ስሎ አእምሮውን ተጠቅሞ በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጽፎ፣ ደጉሶ፣ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ፣ አሳንጾ። የቀን የዘመን መቁጠሪያ ካላንደሩን አዘጋጅቶ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያኔን ከምስረታዋ ጀምሮ ያለ ዕረፍት፣ ያለድካም በታላቅ ትጋት አገልግሎ እስከዛሬዋ ዕለት ድረስም ከወራሪ ጠላት፣ ከመናፍቃን ሠራዊትም ጠብቆ፣ ያቆየለኝ ካህኔ ነው።

"…ከህኔ የጥንቱ የጥዋቱ። ሲያወራ አነጋገሩ ጎልዳፋ፣ ሲታይ ልብሱ አዳፋ፣ ከወደ ዕድሜው ግን የገፋ፣ ዘለግ ያለ ረጅም ዓመታትን በጤና የሚኖር፣ ዕድሜ ጠግቦ የሚያርፈው እሱ ነው ካህኔ። ልብሱ፣ ጠረኑ፣ ዕጣን፣ ዕጣን የሚሸት፣ መዓዛው ከሩቅ የሚያውድ፣ ቃል ከአንደበቱ ሲያወጣ የሚፈውስ፣ ምክሩ የሚያሳርፍ፣ ቁጣው የሚመልስ፣ ተግሳፁ የሚያንፅ፣ በእኔና በእናንተ በማናችንም ላይ ቢዝነስ የማይሠራ፣ ረግጦ ያልገዛን፣ ያላዋረደን። አውቅልሃለሁ ብሎም ያላታለለን፣ ወደ ሕይወት መንገድ፣ ወደ ጽድቅ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ብቻ የመራኝ እሱ ነው የነፍሴ ንጉሥ ካህኔ የነፍሴ አገልጋይ።

"…ከህጻንነቱ ወራት ጀምሮ እውቀትን ሽቶ፣ ፈልጎ፣ ከእናት አባቱ ከቤተሰብ ጉያ ወጥቶ፣ ከዘመድ አዝማድ፣ ከቀዬው፣ ከሰፈሩ፣ ከደብር ከአድባሩ፣ ከመንደሩም ርቆ፣ ከተራበ ውሻ ጋር ታግሎ፣ በረሃ ለበረሃ ተንከራትቶ፣ ጥፍሮቹ በእንቅፋት፣ ሰውነቱ በእሾህ፣ በጋሬጣ ተቀዳዶ፣ ተበሳስቶ፣ ከትግራይ ጎጃም፣ ከጎጃም ጎንደር፣ ከጎንደር ወሎ፣ ከወሎ ሸዋ ቆላና ደጋ ወይና ደጋ በረሃም ወርዶ። ወለጋ፣ አሩሲ ጅማ፣ ጋምቤላ አፋር፣ ኦጋዴን ጎዴ ድረስ በባዶ እግሩ፣ በባዶ ሆዱም ተንከራቶ፣ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ የዕውቀት፣ የእውነት፣ የጽድቅ ሻማዋ እንደበራ እንዲቀጥል ያቆየልኝ እሱ ነው ካህኔ። አመሰግነዋለሁ።

"…በየሊቃውንቱ ደደጃፍ ተንከራቶ፣ ዕወቀት ምድራዊ፣ ዕውቀት ሰማያዊውን ሸምቶ፣ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ቀኖናና ዶግማዋ ሳይሸራረፍ ለትውልድ እንዲተላለፉ ያደረገልኝ ታማኝ አገልጋይ ካህኔ ነው። ከዋዜማ ቁመት የጀመረ፣ ሰዓታት ማኅሌቱን የሚያሳምር፣ በጸሎተ ኪዳኑ የሚፈውስ፣ ቀድሶ የሚያቆርበኝ፣ ወንጌል የሚያስተምረኝ፣ የሚባርከኝ፣ የሚቀድሰኝ፣ እያወቅኩ በድፍረት፣ ሳላውቅ በስህተት የሠራሁትን ኃጢአት እግዚአብሔር ይፍታህ ብሎ ከኃጢአት ማሰሪያ በተሰጠው ሥልጣን የሚፈታኝ፣ እሱ ነው ካህኔ፣ የልተነካካ ድንግል፣ ያላፈረሰ፣ ያልረከሰ፣ ያልተልከሰከሰ፣ በየመጠጥ ቤቱ፣ ቡና ቤቱ ራሱን ያልሰየመ፣ ታማኝ የሚስቱ ባል ቅዱሱ አገልጋይ እሱ ነው ካህኔ። ጸልይልኝ አባ።

"…ቢታመም፣ ቢርበው፣ ቢጠማው፣ ቢታረዝ፣ ቢያጣ ቢነጣ፣ ቢገረጣ ቅር የማይለው። ደሞዝ ባይከፈለው የማይከፋው። ለምኖ አዳሪው። በ40 ቀኔ ያጠመቀኝ፣ የሥላሴ ልጅነትን የሰጠኝ፣ ሥጋ ወልደ አምላክን ያቆረበኝ፣ ደግሞም በእጆቹ የባረከኝ፣ የቀደሰኝ፣ ለእኔ አማላጄ ከፈጣሪዬም መገናኛ ድልድዬ እሱ ነው ሳወድሰው የምውለው የምታዩት ካህኔ ነው። ለተዋሕዶ ሃይማኖቴ መቀጠል፣ ከዚህም ለመድረሷ በብርቱ የታገለ፣ በነፍሱ ተወራርዶ ፀበ አጋንንትን ታግሶ፣ ግርማ ሌሊቱ ሳያስፈራው ራብና ጥምም ሳይበግረው፣ ዝቅ ብሎ ባት፣ ከፍ ብሎ አንገት የሚቆርጡ የአላውያን፣ የአህዛብ ሰይፍ ሳያስቆመው፣ ሳይሰቅቀው፣ ዘመን የዘመን እኩሌታውን በሙሉ በትምህርት አሳልፎ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኔን ያቆየልኝ ታማኝና ለዘመናት ከፍዬ የማልጨርሰው ውለታ ያለብኝ ለእኔ ፕሮፌሰሬ፣ ደብተራዬ ዶክተሬ፣ ሳይንቲስቴ አባቴ፣ ካህኔ ይህ ነው።

"…የእኔ ካህን ነጋዴ አይደለም። ቃሉን አይሸቅጠም። እግር አያረዝምም። የባንክ ዕዳ አይሰርዝም። የፈውስ አገልግሎት ብሎ ድራማ አይሠራም። ስልክ ቁጥር እና የፌስቡክ ፕሮፋይል በቃሉ አጥንቶ በመናገር ተአምር ሠራሁ አይልም። ውኃ ወደ ወተት፣ ውኃ ወደ ደም ለወጥኩ ብሎ አያጭበረብረኝም። ካህኔ የነፍሴ አገልጋይ አባቴ በምድር ያለ ሰማያውያን መላእክትን የሚመሰስ ፀጋን የተሞላ አስደናቂ ፍጥረት ነው። ስታቅፉት፣ ትከሻውን ስትሰሙት ጠረኑ ዕጣን፣ መዓዛው የሚያውድ ነው ነው የእኔ አባት የእኔ ካህን።

"…ፀበል ሲያዩት ውኃ እንዲመስል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶቼም ሲያዩዋቸው ሰው ይመስላሉ። ፀበል ውኃ ቢመስልም የእግዚአብሔር መንፈስ የተመላ ነውና ሲፈውሰን ይኖራል። ካህኔም እንደዚያው ነው። ምድራዊ መልአክ እኮ ነው የእኔ ካህን። የሥላሴን ልጅነት እንዳገኝ ያጠምቀኛል፣ ስታመም ያጠምቀኛል፣ ያስተምረኛል፣ በኀዜኔ ያጽናናኛል፣ ስጣላ፣ ስቀያየም ያስታርቀኛል። ሲጨንቀኝ ያረጋጋኛል፣ ተስፋ እኮ ነው ካህን። በደስታዬ እለት በሠርጌ ዕለት ይባርከኛል፣ ስታመም ጸልዮ፣ ስሞት እያለቀሰ ፈትቶ ይቀብረኛል። ይሄነው የእኔ ካህን።

"…ካህኔ እንደኛ ሰው ቢመስልም በምድር ላይ ያለ ሰማያዊ መልአክ ነው። ከፍጥረት ዓለሙ ሁሉ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ የተሰጠው ብቸኛው ፍጥረት ካህኔ ብቻ ነው። ማንንም የማሰርና የመፍታት ሙሉ ሰማያዊ ሥልጣን የተሰጠው ለእኔ ለካህኔ ለተዋሕዶ ወታደር ለእርሱ ብቻ ነው። በየዕለቱ የማይደክም፣ ለዘመናት በቤተ መቅደሱ ተገኝቶ ያለ እረፍት ዕለት ዕለት ሲዘምር፣ ሲያዜም፣ ጸናጽሉን እየጸነጸለ፣ በመቋሚያው እያሸበሸበ፣ ከበሮ እየመታ፣ እየቀደሰ፣ እያወደሰ፣ ወንጌል ፈትፍቶ ሲያጎርሰኝ የኖረው ከህኔ ነው። እናም ዛሬ አንተ፣ አንቺ፣ እናንተ ሁላችሁ ካህኔን አክብሩልኝ። የራቃችሁ በስልክ ደውላችሁ ተባረኩ። በቅርብ ያላችሁ በአካል ቀርባችሁ ተባረኩ። ለበዓሉ፣ ለመጪው አዲስ ዓመት፣ ለዘመን መለወጫው ለቅዱስ ዮሐንስ እንኳን አደረሰህ በሉት። ይሄን በፎቶ ከተቻለ በቪድዮም ማየት እፈልጋለሁ። አድርጉት።👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ጨምቄ ያገኘሁት ነፍስ ያለው ሰው ቁጥሩን መጨረሻ ላይ እነግራችኋለሁ። የሚበዙቱ ግን መስጠት እየፈለጉ እጅ ያጠራቸው እንዳሉ መዘንጋት የለበትም።

"…በመጨረሻም ዛሬ እስከ ምሽት 2:00 ሰዓት ድረስ ባለን ሰዓት ስናወጋ የምናመሸው ስለ ክብረ ካህነት፣ ስለ ቅዱስ ሩፋኤል በዓል ነው። በዚህ መሐል እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ ጓደኞቼ ቀሪዋን 964 ቦርሳ መግዣ ትሰጡኝ ዘንድም ድንጋይ ተሸክሜ እለምናችኋለሁ። 100 $ 12 ቦርሳ ነው የሚገዛው፣ 200$ 24፣ 300$ 36 ቦርሳ ይገዛል። ገንዘቡ ሓላፊ ጠፊ ነው። ያላችሁ ሰዎች በተለይ 500 ም 1ሺም አርጋችሁ ብትሰጡልኝ በቀላሉ ተዘጋ ማለት ነው። ይሄን ከማሟላት ደግሞ 80 ሰዎች 100$ ቢያወጡ፣ 40 ደጋጎች 200$ ዶላር ቢያወጡ፣ 26 ሰዎች 300$ ዶላር ቢሰጡ 964 ቱም ቦርሳ ተዘጋ ማለት ነው። ዶላር ዶላር የምለው የእኔ ዕዳ ተሸካሚ የሚበዛው ከወደ አሜሪካ ስለሆነ ብቻ ነው። ካናዳ ሳስቷል። አውስትራሊያማ ጭራሽ የለም። ከአውሮጳ በአሁኑ እንግሊዞች እጃቸው ሲፈታ አይቻለሁ። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ሆላንድ፣ ስዊድን ወዘተ ከጥቂቶች በቀር የዳር ተመልካች ይበዛዋል። ፍታ እጅህን፣ ተረባረብ፣ እርዳ። ቦርሳውን እስከማታ ጨርሼ ማታ ዩኒፎርሙን እጀምራለሁ። የነከስኩትን ሳላደማ የምለቀው ሞቼ ነው ቆሜ። እህዕ…

"…1 ቦርሳ 1ሺ የኢትዮጵያ ብር ነው። 100 ዶላር 12 ቦርሳ ይገዛል፣ 100 ፓውንድ 14 ቦርሳ ይገዛል፣ 100 ዩሮ ስንት እንደሚገዛ እናንተው ድረሱበት። ማነው አግተው ላጡ የጎንደር ሕፃናት አንድ ቦርሳ በመግዛት ተስፋቸውን የሚያለመልም? አግኝታችሁ ከማጣት ፈጣሪ ይሰውራችሁ። እደግመዋለሁ፦

• ብዛት 964 ፍራሽ
• የአንዱ ዋጋ 1ሺ ብር

👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና ወይ በኋትስአፕ፣ አልያም በቴሌግራም ላይ ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን የፍራሽ ብዛት የአንዱን ዋጋ በ1ሺ ብር አባዝታችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ። እኔም ወዲያው በፍጥነት ቃላችሁን እመዘግብና የስደተኞቹን ሕጋዊ የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁና ትልኩላቸዋላችሁ። በRIA የምትልኩ ለዐማራ ሲሆን እምቢ ስለሚሏችሁ፣ ሀገር ቤት ላለ ቤተሰብ ልካችሁ ቤተሰብ ሊያስገባላችሁ ይችላል።

• አመሰግናለሁ። መልካም የክብረ ክህነት ቀን ይሁንላችሁ።

• ዘመቻ ቦርሳ 964 ይፋፋም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘወትር እግዚአብሔርን ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው አመስጋኝ ቁጥር ሞልቷል። ቀጥሎ እንደተለመደው እንሄድ የነበረው ወደ ርእሰ አንቀጻችን ነው። ዛሬ ግን ርእሰ አንቀጻችን ከአጭር የምሥራች በኋላ ቢቀርብ ብዬ ተመኘሁ። ተመኘሁናም የምሥራቹን ልነግራችሁ ወሰንኩ።

"…ድንኳን ውስጥ እንደ ሳጥን፣ ትምህርት ቤት ደግሞ እንደ ቦርሳ ያገለግላቸው ዘንድ ለ3300 ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ጥርሴን ነክሼ ማሰባሰብ የጀመርኩት ቦርሳ አሁን ስንት እንደቀረኝ ልነግራችሁ ነኝ። ትናንት ትንፍሽ ሳልል ውዬ ዛሬ እስቲ ልንገራችሁ ብዬ ነው። በዙያውም ተረባርበን ቀሪውን እናሟላለንም ብዬ ተስፋ ስለማደርግም ጭምር እሱንበላስቀድም ብዬ ነው።

• እስቲ ገምቱ ስንት ቦርሳ የቀረኝ የመስላችኋል? አንድ 100 ሰው እንደገመተ የምሥራቹን እለጥፍላችኋለሁ።

• 1…2…3…ገምቱ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ዓይኔ መቼም አያርፍ እኔ ደግሞ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ የሞተችው የሕፃን ፌቨን እናት መስላኝ እንደፈረደብኝ ከምኔው ጥቁር ልብስ አወለቀች፣ ባለፈው ቤት ተሠርቶ ተሰጥቷት ነበር። አሁን ደግሞ ሁለተኛ ቤት ልትቀበል ነው ወይ? ፍትሕ ፍትሕ ብላ የጮኸችው ቤት እስኪሰጣት ደረስ ነው ወይ ብዬ ከምር ልጠይቅ ነበር። እሷ መስላኝ ማለት ነው።

"…በነገራችን ላይ ዛሬ ስለቀበሮ ሜዳ ሕፃናት የቦርሳ ጉዳይ አልተነፈስኩም። ምክንያቱም ደስስ ስላለኝ። ነገ ምሽት ከነጭ ነጯን ከመረጃ ቴቪ መርሀ ግብሬ በፊት ዩኒፎርማቸውን እጀምርና ከዚያ እስራስ፣ ደብተር እና እስኪሪብቶውን መለመን እጀምራለሁ። የነገ ሰው ይበለን።

"…ነገ ጳጉሜን ፫ የክብረ ክህነት ቀን ነው። ካህኔ ነገ ሲከብር ይውላል። በዚያውም ቅዱስ ሩፋኤል ነው። በዚያ ላይ የካህኑ መልከ ጸዴቅም በዓል ስናከብር እንውላለን።

"…ለንስሀ አባቶቻችሁ እየደወላችሁ ፍቅራቸውን ግለጹላቸው።

• ሻሎም…! ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከሱማሌና ግብፅ የወረራ ዜና በፊት ነው…!😂

ኦነግ በአማርኛ መፈክር ሲያሰማ…
እስቲ አንደዜ አብራቹ በሉ…! 😂😂😂

• ካሲልጣን ኢናባራሌን…!✊✊✊
• አቢዪ ሌባ ኖ…!✊
• ነፍጠኛ ሌባ ኖ…! ✊
• የፈረስ ሌባ ኖ…! ✊
• ያታሪክ ሌባ ኖ…! ✊
• የሃገር ሌባ ኖ…! ✊
• የማሬት ሌባ ኖ…! ✊
• ናፍጣኛ ላማኝ ኖ…! ✊
• ለሊመና ማጣቹ፣ ዛሬ ሃገራቺን ቲፋለማላቹ…!✊
• ወዳቹም፣ ጠላቹም፣ ከኦሮሚያ ቲዋጣላቹ…!✊
• ወደ ጎንዶር ትገባላቹ…! ✊
• ወዳ ቆማጤ ቲመለሳላቹ…! ✊
• ከአሂያቹ እናባሪራቻለን…!
• አንዲም ንቢረት ይዛቹ መውጣት አይችሉም…!
• ከሃገራቺን አንድ ሳንቲም፣ ያላቆማጤ፣ ያለ አሂያ ምንም ዪዛቹ አቶጡም…!✊
• ለራሳቹ ቲዋጣላቹ…!✊
• በሰላም ሃጋራቺን ሊቀቁ…! ✊
• ኢኛ ኦሮሞ ወዳጂ ናን ቢሌን ኢናንቴን አስገባናቹ፣ ኢናንቴን ኢያበላን፣ ኢያጠጣን፣ ኦሮሞ ሲፈናቄል፣ ቲደሰታላቹ፣ ኦሮሞ ሲሞት ቲጨፋራላቹ፣ ኢንደዚ አብሯቺን መኖር አንቺሊም…!✊
• ኢናንቴ ለራሳቹ የሚትሞቱበት ጉድጓድ ኢየቆፈራቹ ኖ…! ✊
• ሁላቹም ወደ አሰር ሺ/አስር ሚሌየን ኦሮሚያ ዊስጢ ናቹ። ኦሮሞን ማጥቃት አትቺሉም።


• ብልጽግና ወዳ ጎንዶር…!✊
• ብልጽግና ወዳ ጎንዶር…!✊
• አዳ ቢሊሲማ ኦሮሞ አቃፊ ኖ…!😂😂

• ኡፍ ማርያምን ደከመኝ…! እናንተ ቀጥሉ…! አግዟቸው። አይ ኦሮሞ አለ አራጁ አቢይ…!

"…በነገራችን ላይ ይሄን ነገር ደጋግማችሁ ስሙት። ሆድ ያባውን ሰልፍ ያወጣዋል የሚባል አባባል አለ። ይሄ እንደዋዛ ስቃችሁ ብቻ የምታልፉት ነገር አይደለም። ደጋግማችሁ ስሙት።

"…አይ አማርኛ ነፍስ ነገር እኮ ነሽ…! እምጷ አማርኛዬ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ፎሊሱ ግን…

• በጎማው ለምንድነው መሬቱን የሚደበድበው?

• ቪድዮ ቀራጩ ፊት ያለው ሰውዬስ ለምንድነው እንደ ፊልም ዳይሬክተር ለደብዳቢው ፎሊስ አቁም የሚል የእጅ ምልክት ሲሰጠው ፎሊሱ ከት እንደተባለ አክተር መሬት መደብደቡን ያቆመው?

• ብቻ እንደ ዕድል ሆኖ የእኔ ዓይን ችግር አለበት እንጂ ቪድዮው እንኳ በጣም ያሳዝናል። ሲያዩት ያማል፣ ያስደነግጣልም። "ዱቴ" አለ እኮ ሞተች ማለት ነው።

• መንሱሬ ባለ ሽቶው ሰምቶ ይሆን?

• ፍትሕ ለልጅቷ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እኔምለው ያ የሱማሌና የግብጽ ወረራ ጉዳይ ከምን ደረሰ…? …አይበለውና እነሱም አያደርጉትም እንጂ ሱማሌና ግብፅስ ቢሆኑ ተሳክቶላቸው ቢመጡ እንዲህ የሚደፍሩ ይመስላችኋልን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ብልጦ ህወሓት ጫት አደንዛዥ ዕፅ እንደሆነ ስለምታውቅ በዘመኗ በአቶ ገብሩ አሥራት የትግራይ አስተዳደር ዘመን ጫት መቀሌ እንዳይገባ በሕግ አግዳ የትግሬን ወጣት ከሱስ ለመታደግ ሞክራ ነበር። የሂዊ ክፋቷ ግን በሌላው ክልል የሚገኝ ወጣት ጫታም እንዲሆን ነበር ያደረገችው። በትግራይ ስለ ልቅ ወሲብ የሚያወሩ መጽሔቶች፣ የፖለቲካም ጋዜጦች እንዳይገቡ አድርጋው ሌላው የኢትዮጵያ ወጣት ጋለሞታ፣ ወንድኛ አዳሪ እንዲሆን ነበር የፈረደችበት። የጎጃም ባህርዳርና ጎንደር እንፍራንዝ ሁላ ጫት ቃሚና አምራችና ሻጭ ሁላ አድርጋ አጀዘበችው። የዐማራ ጫታም ደግሞ ብታዩት ሲያስጠላ። ልምድ ስለሌለው ሲቅም ከነ እንጨቱ ነው አሉ። አንደ ዳቦም በሻይ እያማገ ሲበላው ልታገኘው ትችላለህ ብሎኛል አንዱ የድሮ ቃሚ። ከምር ጫትና ዐማራን አስቡትማ። ምን የመሰለ የዶሮ አይን የመሰለ ጠላና የመኳንንት ጠጅ እያለለት ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ዐማራ፣ ትግሬ ጫት ሲበላ፣ ሲያመነዥግ። ቱ…! ማርያምን አያምርበትም። ክፋቷ ደግሞ ህወሓት በትግራይ ጫት ከልክላ አልኮሉን ፈቅዳ የትግሬ ወጣት በዳሽን ቢራና በጊዮርጊስ ቢራ የመቀሌን ወጣት የጠላ ጋን አስመስላው አረፈችው። የትግራይ ወጣት ከጫት ቢርቅም ከአንቡላው ግን አልራቀም። ያለነው አንድ ኮንዶሚንየም ላይ ስለሆነ ጉዳቱ የጋራም አይደል? አዎ እንደዚያ ነው። በትግራይ ውኃ ጠፍቶ በበቢራ እጃቸውን ሲታጠቡ በዓይኔ በብረቱ አይቼ አውቃለሁ። ጫትም ቢራም ጋለሞታ ነው የሚያደርጉት።

"…ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ከዐማራ ክልል ጫት ሲወገድ፣ ሲቃጠል አይተን ነበር። ከጫት የራቀ ትውልድ ሲፈጠር ጠያቂ ተመራማሪ፣ አእምሮው ብሩህ ይሆናል። ለቤተሰቡም፣ ለሀገር ለመንደሩም ሳይቀር ይራራል። ነፃነትን ይመኛል። ነፃ ለመውጣት ይጥራል፣ ይታገላል። ጫት የተወ ትውልድ ንፁህ አዕምሮ፣ ንፁህ ልብስም ይኖረዋል። ንፁሕ ጠረንም ይኖራል። አፉ አይሸት፣ ልብሱ አይሸት። ሚስቱን ቢስም፣ ልጆችን ቢያቅፍ አይሸክክ፣ አይደብር። እናም ወጣቱ ከጫት ከራቀ በሀገር ግንባታውም ተሳታፊ ይሆናል። በመይምና ሀ ገደሉ ካድሬም አይመራም። የሆነ ሰሞን ወደ ትግራይም ጫት ወደ መቀሌ እንዳይገባ ሲያደርጉ አይቻለሁ። በጣም ደስስ ይላል። ይደገፋልም።

"…የሆነ ወቅት በኮሮናው ሰሞን በኦሮሚያም ፖሊሶች በኮሮናው ምክንያት በግለሰብ ቤት የተጠራቀመ ነው የተባለ ጫት አስወጥተው ሲያስወግዱም አይቻለሁ። ይሄም ይበረታታል። የሆነ ሰሞን ጃዋር መሐመድም በኮሮናው ምክንያት መቃም ካቆመ ወዲህ ሞትን ፈርቶ ከምህረተ አብ የበለጠ ሰባኪ ሆኖ ታይቷል። ጫት በሳኒታይዘር አይጸዳ? ምን ያድርጉት? በሰሜን ሸዋ የሚገኙ አንዳንድ ነፍጠኞችም የሸዋን ወንድ ሁሉ የማጀት ድመት አድርጎ አኮላሽቶ ያስቀረባቸውን አጅሬ ጫት አደንዛዡን ዕፅ የፍየሎችን ምግብ ነው በማለት በገፍ ሲያስወግዱና ሲያቃጥልም አይቻለሁ።

"…የዐማራ ወጣት እንኳ የባነነው የውሻና ፈረስ ቁማር ያቆመ ጊዜ ነው። የጫት እርሻ መንጥሮ፣ የጫት ነጋዴዎችን የዠለጠ ጊዜ ነው። ቀደም ብለው ነቅተው የዐማራ ፋኖን ያደራጁ ፋኖዎች ብዙ ወጣት የተቀላቀላቸው ቁማር ቤትን በዐዋጅ ካስዘጉ በኋላ ነው። በጎጃም፣ በሸዋ፣ በጎንደር በወሎ ይሄን ዐዋጅ ተከትሎ ወጣቱ ከቁማር ቤት ወደ ነፃነት ሜዳው ተምሟል። አዎ ሱስ ገዳይ ነው። ሱስ ቁልቁል ይቀብርሃል። ሱሳም ባል ሚስቱ ለሠርጓ ቀን ተሠርታ ያሰረችውን ሻሿን ከጠጉሯ ላይ አትፈታም። ገንዘብ የለማ። ሚስቱ የቆሸሸ ቀሚስ፣ የተቦጨቀ ጫማ አድርጋ ነው ከጓደኞቿ በታች የምትቀረው። ሱሳም ባል አያኮራም፣ አያስፈራም፣ የተናቀ ቀትረ ቀላል ውቃቤቢስ ነው። ሱሳም ባል አንገት ያስደፋል። ሱሳም ሴትም እንደዚያው ናት። ሱሳም ሴት ማይም ናት። ሱሳም ሴት የወንድ ሁሉ መጫወቻ ናት። ሱሳም ሴት ክብሯን በአደባባይ ታዋርዳለች።

"…ሱሳሞች ወላጆቻቸው አይኮሩባቸውም። ማኅበረሰቡ እምነት አይጥልባቸውም። ሱሳሞች ይናቃሉ፣ መሳቂያ መሳለቂያ ይሆናሉ። ሱሳሞች አያስቀድሱም፣ አይጾሙም፣ አይጸልዩም። ሱሳሞች አኗኗራቸው እንደ አሳማ ነው። ቀና ብለው አይሄዱም። ሱሳም ወጣት በሰፈር ውስጥ ከታየ ዶፍ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ የመጣ ይመስል መንደርተኛው ሁሉ የተሰጣ ልብስ ይሰበስባል። ዶሮ ካለ ይጠብቃል። ሱሳም አዋራጅ ነው። አስበኸዋል ቆንጅዬ ሴት ሆኗ፣ ሥራ ኖሯት ሺ ሻ ቤት ሱሰኛ ሆኗ የማንም ወንድኛ አዳሪ ስሜት ማራገፊያ ስትሆን? ከምር ሱሳምነት ይውደም።

"…ሱሰኛ አባት ልጆቹ ይጫጫሉ፣ ይራባሉ፣ ይጠማሉ፣ ዐመዳም ቀጫጫ፣ ሲምቢሮ ይሆናሉ። ቅጫማም፣ ፎሮፎራም ሁላ ይሆናሉ። የሱሳሞች ልጆች በትምህርት ውጤታቸውም ዝቅተኛ ውጤት ያመጣሉ። በመጨረሻም የሱሳም ልጆች ወንዱ ዘራፊ፣ ሴቷ ሴተኛ አዳሪ ይሆናል። ሱሳም አባት የውጭ አልጋ የቤት ቀጋ ነው። ኤትአባክንስና አንተ የሞትክ ሙትቻ። የቤትህን መብራት አጥፍተህ፣ የቤተሰብህን ሕይወት አጨልመህ ለውጭ ሰው የምታበራ አንተ ከንቱ የሆንክ ፍጥረት በቶሎ ተመለስ። አንተ ከውጭ ቁርጥህን እየቆረጥክ፣ የጣመ የላመ እየበላህ አንተን ብላ ሚስትህ የሆነች ስትራብ፣ ልጆችህ ሲራቡ ምንአባህ ነው የሚሰማህ አንተ ደነዝ? ሚስትህን ገረድ፣ ባልሽን አሽከር ያደረግሽ ነውራኛ በቶሎ ተመለሽ። ሱስህንም ተው። ሚስትህን ፀጉሯን አስተኩስ፣ አልብሳት፣ አሰማምራት፣ ከጓደኞቿ፣ ከእድርተኞቿ፣ ከማኅበርተኞቿ እኩል አድርጋት። ሰምተኸኛል? ልጆችህን ጎብኝ፣ አብላቸው፣ አጠጣቸው። አባት ሆኗቸው። አልብሳቸው፣ ትምህርታቸውን ተከታተል። በሚቀጥለው ዓመት ራስህን ለመለወጥ አሁን ይሄን ጦማር እያነበብክ ወስን። ማርያምን ወስን። ተለወጥ አባቴ፣ ወንድሜ። ተለወጭ እህትዓለሜ። ለውጥ አሁኑኑ። የትኛውንም ሱስ ተው። ያለፈውን የሱስ ዘመን እርገም። ለርእሰ አንቀጼ ጫትን ጠቀስኩ እንጂ ሱስ የሆኑ ሁሉ በዚህ መልኩ ይነበቡልኝ። እኔ ደግሞ ጥሎብኝ አለሳልሶ መምከር፣ ማስተማር ብሎ ነገር አይመጣልኝም። የሐረርጌ ልጅነቴ ለዚህ የዳረገኝ ይመስለኛል። ሱሳም ስትፈልግ ሰልፍ ጥራብኝ እንጂ እኔ የምነክርህ በዚህ መንገድ ነው። አለቀ። ስትፈልግ ስማኝ፣ ሳትፈልግ ተግማማ። ለደንታህ ነው።

"…ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ሮሜ 13፥1114

“…የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።” 1ኛ ጴጥ 4፥3

•••

ሻሎም…!   ሰላም…! 

ድርጅቱ ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
"አሸበርቲው አስነቀልቲው"
ነሐሴ ጳጉሜን 5/2016 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬ ጳጉሜን ፭ ከሱስ ሁሉ የምንላቀቅበትን ዕለት ስናስብ፣ ስንዘክር፣ ቃል ስንገባ፣ ስንወስን የምንውልበት ዕለት ነው።

"…ለዚህ ርዕስ የሚሆን ሱሰኞች ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩብኝን ጠጠር ያለ ርእሰ አንቀጽ ጽፌ አዘጋጅቼ ላቀርብላችሁ ነኝ። እናንተስ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?

"…አንድ ጓደኛዬ እንዲህ አለኝ። "ዘመዴ የቀበሮ ሜዳን የተማሪዎች ዩኒፎርም አሰባስበህ እስክትጨርስ ድረስ እንዲህ ዓይነት ነገር ባትጽፍስ ይለኛል። እኔም ለደንታው ነው ብዬ ምክሩን ጥሼ ጽፌዋለሁ። ለተፈናቃዮቹ የቀረኝ ዩኒፎርም ብዛት ትንሽ ነው። በዚህ ምክንያት ተናድዶ አልረዳም የሚል ለደንታው ነው። ሲፈልግም በአናቱ መተከል ይችላል። እኔ ግን ጽፌዋለሁ። እናንተስ ለማንበብ፣ አንባችሁም የመሰላችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ ወይ?

•,እደግመዋለሁ ዝግጁ ናችሁ ወይ…? 😂😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ልናገባድደው ነው…!

"…በጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቅለው ለሚገኙ ህፃናት ተማሪዎች የደብተር መያዣ ቦርሳውን ጨቅጭቄአችሁ አስገዝቼአችሁ። አቶ ቴዎድሮስ መለስ ከስዊድን የተማሪዎቹን ሙሉ ደብተር፣ እስራስና እስኪሪብቶ ዘግቶላቸው በደስታ በቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሬ ላይ አስለቀሰኝ፣ የቀረኝ የተማሪ ደንብ ልብስ ነበር። እሱንም አሁን ነግሬአችሁ ጀምሬው ነበር።

"…የመረጃ ቲቪዎቹ የቀድሞ መሥራቾች ወሮ መሲና ሶል በ2ሸ$~ የሦስት መቶ 342 ተማሪዎች ዩኒፎርም በመግዛት የጀመሩትን፣ የአማሪካ አስተናጋጄ ወሮ ሕይወትና ልጇ ዘላለም ብሩክ ከነቤተሰባቸው የ150 ተማሪ፣ ቴዲ ከስዊድን~ የ142 አቢሲንያ~ የ130፣ ንጉሤ~ የ91፣ እህትዓለሜ~የ100 ተማሪ፣ ዜና ሥላሴ~የ24 ቲጂ~የ24፣ ጥበቡ~የ20፣ ቲጂ~የ17 አጥላባቸው~17፣ መብራቴ~15፣ ቶማስ~14፣ ወልደ አማኑኤል~13 ኧረ ደከመኝ። እፎይ ቆይ ትንሽ ልረፍ። አይኔ ቦዘዘ፣ እንባ አቀረረ እኮ።

"…ለማንኛውም በዚህች አጭር የልመና መልእክት ብቻ ለ1,321 ተማሪዎች የሚሆን ዩኒፎርም መግዢያ አግኝቻለሁ። ከጠቅላላው 3,300 – 1321= የ1979 ተፈናቃይ ምስኪን ሕፃናት የተማሪ ደንብ ልብስ መግዢያ ይቀረኛል። ምን አላት። በተለይ እንደ ወሮ መሲ 2 ሺ ዶላር የሚሰጥ ከተገኘ፣ 1ሺ$፣ 500ም$፣ 2መቶና 1መቶ ዶላር የሚሰጥ ከተገኘ እስከ ነገ ድረስ የምንዘጋው ይመስለኛል። "…100 $ የ17 ተማሪዎች ዩኒፎርም ይገዛል።

• ዘመቻ 1,979 ይፋፋም…!!!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አራት ነጥቧ እዚህ ጋር ተስተካክላለች።

"…ትችቴ ቀላል ይመስላል። ነገር ግን ለሚገባው ከባድ ነው። እዚህ ፌስቡክ ላይ ጋዜጠኛ፣ አክቲቪስት፣ ባለ ሥልጣን ሆነው በአማርኛ መልእክት ሲያስተላልፉ ሳይ አይኔን እንቅፋት ነው የሚመታኝ። አንድ አማርኛ አስተካክሎ የማይጽፍ ጋዜጠኛ ጋዜጠኛ ነኝ ሲል ያስቀኛል። ወያኔ የትግሬ ነፃ አውጪው ኦሮሞ ላይ በነፍስ በሥጋው ጢባጢቤ ከተጫወተበት ነገር አንዱ ላቲን ቁቤ የተባለ ፊደል አምጥቶ አናቱ ላይ እንደ ቂቢ የመረገበት ነው። ዐማራና አማርኛን ጎዳሁ ብሎ ኦሮሞን ኪሣራ ላይ ነው የጣለው። ለምሳሌ፦

"…ለምሳሌ ይሄን የአቢይን ልጥፍ ብቻ ተመልከቱ። አማርኛው ዘርዘር ተደርጎ ተጽፎም 5 መስመር ሲፈጅ ቁቢቲ ግን ደብል ደብል ሆና እንደ ሞላ የታክሲ ተሳፋሪ ተደራርባ ታጭቃ ተጽፋ 9 መስመር መኘነው የፈጀችው።

"…ወያኔ ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ለመነጠል ብላ በሠራችው ሴራ ዛሬ ኦሮሞ ሁለት መስመር ደብዳቤ ለመጻፍ አራት ሉክ፣ በአማርኛ 100 ገጽ የሚፈጅ መጽሐፍ 700 ገጽ እየፈጀ በሰው በጉልበት፣ በቀለም፣ በወረቀት ላይ ኦሮሞ ቢልዮን ብር እንዲከሰክስ አድርጎታል። ወያኔ ግን ያው በግዕዝ ፊደል እንደ አማርኛው ነው የምትጠቀመው። ኪሣራ…

"…ኧረ እኔ አሁን እዚህ ላይ ምንአገባኝ። ይልቅ የቀበሮ ሜዳ አጭር ሪፖርት ላቅርብና ምሽታችንን የተማሪዎቹን የደንብ ልብሶች በሟሟላት ደስ እያለን እናሳልፍ።

• ይሄን እርሱት ተዉት ይልቅ ጠብቁኝ የምሥራች አለኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀናችንን ስናስብ የምንውልበት መርሀ ግብራችን በይፋ ተጀምሯል።

"…የፎቶ መላኪያ ሰንዱቁም ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ክፍት ነው። ተምነሽነሹበት። መንደሩን በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማም አጥለቅልቁት።

• ክብር እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ላልካዱት፣ ላላዋረዱት ለዐማሮች።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝ 68፥31 …“…በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።” መዝ 72፥9 …“አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።” መዝ 74፥14

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ዳይ ወደ ቀደመው ኦርቶዶክሳዊ ማንነታችን እንመለስ። ወደ ኢትዮጵያዊው ማንነታችን እንመለስ። ይሄ ዘመን የጣለውን ካዛንችስና ፒያሳ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጦ ለእኔም አምጪ ለአንቺም ጠጪ የሚለውን ዘመን የወለደው ነቀርሳ የሆነ “ካህን መሳይ” ክብረ ክህነት አዋራጅ እርሱን እርሱት። እርሱን ተዉት። እርሱን አትስሙት። የእኔ ካህን ይሄኛው ነው። ቀን እያረሰ ሰዓት ሲደርስ ከነ አፈሩ ቅዳሴ የሚገባው። እሱ ነው የእኔ ካህን። መተተኛ፣ አጋንንት ሳቢው እሱ የእኔም የእናንተም፣ የማንም ካህን አይደለም። ቤተ ክርስቲያኔም አታውቀውም። እሱ አጭበርባሪ ነው። ሌባ ነው። ነጣቂ ተኩላ ነው። ልብሱ ነጭ፣ አነጋገሩ ምላጭ፣ ከወደ ዕድሜው የሚቀጭ ነው። የእነ ፓስተር ዮናታን፣ የኢዩ ጩፋ፣ የእነ እስራኤል ዳንሳም ጓደኛ ነው። በፍጹም እኔን አይወክለኝም። ባለ ሽቶው፣ ባለ ድራፍት ባለ ውስኪው፣ ኮማሪት ቤት፣ ባለጌ ወንበር ይዞ እንደ ጋን ፣እንደበርሜል አምቡላውን ሲጋት፣ የጋለሞታ ጭን ሲያሻሽ የሚውለው እሱ ካህኔ አይደለም። ጠንቋይ ነው እሱ።

"…ወዳጄ የካህን ያለህ የሚባልበት ዘመን ይመጣል ከተባለው ከዚያ ዘመን አያድርሰን። ዛሬ የናቅከውን፣ ያቀለልከውን፣ የሰደብከውን፣ ያላከበርከውን እውነተኛ ካህን ነገ ድንጋይ ተሸክመህ፣ በእንብርክክ፣ በእንፉቅቅህ ብትሄድ አታገኘውም። መቃብሩ ላይ ሄደህ ይፍቱኝ አባቴ የምትልበት ዘመን ይመጣል። እስከዚያው ሰላም ለሃገራችን፣ ሰላም ለተዋሕዶአችን፣ ሰላም ለሁላችን። ክብር ለካህኔ ለነፍሴ አገልጋይ ሃይማኖቴን ላጸናልኝ አባቴ። ክብር ለአንተ። ክብር ለእናንተ። ቆይቼ እመለሳለሁ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ጸልይልኝ አባ አክሊለ ገብርኤል ብለህ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከጥንት እስከዛሬ ከክብር፣ ልቆ ከመገኘት እና ከነጻነት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው

የእኔ አስተያየት…

፩ኛ፦ ነው ብሎ ። አራት ነጥብ ቢኖረው።

፪ኛ፦ እንደ ሌላው ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ስታወራ በቁቤ በአፋን ላቲንና በእንግልጣር ቢጻፍ መልካም ነበር። ግን አልሆነም። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሲባል ኦሮሚያ፣ ኦሮሚያ ሲል ለከረመ አካል ከባድ ነው።

"…ጦርነት ሲመጣ በአማርኛ ብቻ መፎከር፣ መቀስቀስ፣ መዘመር አይነፋም። በኦሮሚኛም፣ በትግርኛም ቢፎከር ሸጋ ነው ለማለት ነው። የእንግሊዝኛው ቢቀር ቶሎ በቁቤም ጻፉት ለማለት ነው። ከመስከረም አንድ ውጪ ስለ ቦለጢቃ አላወራም እልና እጄን የሚበላኝ ነገርስ…?

"…በነገራችን ላይ ቦርሳውን 792 ቀርቶኛል። ሊያልቅ ነው ፍጠኑ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የምሥራች ሪፖርት…!

"…የበዓል 5 ሰንጋ፣ 5 ፍየል ከነ ውኃ ለስላሳው በአቶ ወርቁ አይተነው ተችሎ፣ በወልደ ገብርኤል እና ትርሲተ ሚካኤል 5 ኩንታል ጤፍ፣ ቅቤው እና ማገዶው በጆኒ፣ ሽንኩርቱ፣ ማገዶው ሁሉ ተችሎ፣ ሽንኩርት፣ ጨው በርበሬው ሳይቀር ተችሎ፣ ድንኳን፣ ወንበሩ ሁሉ ተዘጋጅቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። የበዓል ዝግጅቱ በቀበሮ ሜዳ ጎንደር ጡፏል በጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ካምፕ በተስፋና በሌላ የምሥራች ዜናዎችም ተሞልተዋል። የሚደንቀው የዐማራ የሞራል ከፍታው ነው። ተፈናቃዮቹ ለእነሱ ለምኜ ከገዛሁላቸው ሰንጋዎች መሐል አንድ በሬና አንድ ኩንታል ጤፉን በራሳቸው ፈቃድ ከተፈናቃይ ስደተኞቹ ካምፕ ውጪ ለሚገኙና በጎንደር ከተማ በቀበሌ ዘጠኝ ሸዋ ዳቦ አካባቢ ለሚገኙ የአእምሮ ውስነንት ያለባቸው "ካለን እናክፍል" ለሚባል ድርጅት ተረጂዎች ያላቸውን አካፍለዋል። የዐማራ ስብእነናው፣ የሞራል ከፍታው ይገርመኛል። ማካፈል ከአማኝነት ባሕሪ የሚመጣ ነው። በትምህርት ብቻም የሚገኝ ፀጋ አይደለም። ለመስጠት፣ ለማካፈል ከመስጠት፣ ከማካፈል ቅመም መሠራት አለብህ።

"…በቁማቸው ትል የፈላባቸውን ሕፃናት ትሉን ለማስወገድ መሬቱን ሊሾ፣ የፕላስቲክ ምንጣፍና ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ፍራሽና ብርድ ልብስ ያስፈልግ ነበር። መጀመሪያ ሁለትም ሦስትም ሆነው ቢለብሱት ተብሎ 1,200 ብርድ ልብስ ያስፈልግ ነበር እሱ ወዲያወረ ተችሏል። ከዚያም 2,400 አንሶላ ያስፈልግ ነበር እሱም በፍጥነት ተችሏል። 1,200 ፍራሽም ያስፈልግ ነበር እሱም ተችሏል። ፋብሪካ አነጋግሬአለሁ በጅምላ አከፋፋዮች ሒሳብ እንሸጥልሃለን ብለውኛል እግዚአብሔር ይመስገን። የሚቀረው ፍራሹን ለማንጠፍ ሲሚንቶ አሸዋና ጠጠር ያስፈልጋል። ምክንያቱም ፍራሹ አፈር ላይ ከተነጠፈ ተመልሶ ወዲያው ስለሚበላሽ ማለት ነው። እሱን መጨረሻ ላይ ጥቂት ሰዎች ገዝተው የሚፈጽሙት ተግባር ነው የሚሆነው። ደግሞም ቀላል ነው።

"…ከዚህ ሁሉ በመጨረሻ የሚያስፈልገው ሕፃናቱ ማይም ሆነው እንዳይቀሩ ትምህርት ቤት ማሠራት ነበር። እርሱን ደግሞ በሀገረ ስዊድን የምትኖር ወሮ ሊሊ የምትባል የእነ እቴጌ ምንትዋብ ጎንደሪት ልጅ ጀምራው በአቅም ማጠር ምክንያት ተቋርጦ ነበር። የተቋረጠውን የጎጃም ባለሀብቱ የበላይ ዘለቀ ልጅ አቶ ወርቁ አይተነው "ዘመዴ ትምህርት ቤቱን እኔ ሠርቼ አጠናቅቄ አስረክብህሃለሁ" ብሎ ነው በደስታ ያሰከረኝ። ለአቶ ወርቁ ጨምሮ ጨማምሮ እግዚአብሔር ይስጠው። የጎንደር ባለሀብቶች ዝምታ ግን አስገርሞኛል። የመድኃኔዓለም ያለህ። የትምህርት ቤቱ ነገር ከተያዘ ቀሪ የሚያስፈልገው ለተፈናቃይ ተማሪዎቹ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች ማሟላት ነው። እሱንም የእናንተን ኪስ ተማምኜ በድፍረት ጀምሬዋለሁ። ከእግዚአብሔር ጋር አጠናቅቀዋለሁ።

"…እኔ ቅድሚያ የሰጠሁት ለቦርሳ ነው። ብዙዎች "ዘመዴ ለምን ግን ቦርሳው ቀደመ? ደብተርና እስኪሪብቶ ብታስቀድም አይሻልም ነበር" ብለውኝም ነበር። እኔም የመለስኩላቸው ደብተርና እስኪሪብቶውን አስቀድሜ ብገዛላቸው ሕፃናቱ ደብተርና እስክሪብቶውን የት ያስቀምጡታል? ላስቲክ ድንኳን ውስጥ አንድ ፍራሽ ላይ አራትና አምስት ሆነው እየተኙ ደብተሩን የት ያደርጉታል? በየቤታችሁ የሚያደክማችሁ የተዘርከረከውን የልጆች ደብተርና እስራስ መሰብሰብ አይደለም እንዴ? ቤት ላለው ነው መጀመሪያ ደብተር የሚገዛው። ለተፈናቃይ ሕፃናት መጀመሪያ መግዛት ቦርሳውን ነው። ምክንያቱም ቦርሳው ከተገዛ አገልግሎቱ ብዙ ነው። ቦርሳው በትምህርት ቤት የትምህርት መርጃ መሣሪያ መያዣ ቦርሳ ሆኖ ሲያገለግል በመኖሪያ ድንኳናቸው ደግሞ ደብተር፣ እርሳስ፣ እስኪሪብቶ ሁሉ ሸክፎ እንደ ሳጥን ሆኖ ይይዝላቸዋል። ለዚያ ነው ቦርሳ ይቅደም ያልኩት።

"…የሚያስፈልገው ቦርሳ አጠቃላይ 3,300 ነበር። እሱን ከትናንት ወዲያ ጀምሬው ትናንትን ትንፍሽ ሳልል ውዬ ዛሬ የደረሰበትን ልነግራችሁ ነኝ። እስከ አሁን ለ2,336 ሕፃናት ቦርሳ የሚገዙልኝ ደጋግ ቅን ልብ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን አግኝቻለሁ። በሚገርም ሆኔታ በዚህ የጎንደር ተፈናቃዮች ጉዳይ የእስላሞች ተሳትፎ ምንም ሆኖ ነው ያገኘሁት። እኔ ግን ክርስቲያን ብሆንም በመጠለያው ውስጥ ላሉት እስላሞች አንዲት ነገር አላጓድልም። ከሙክቱም ከሁሉም አንዲት ነገር አላቋርጥም። ገርሞኛል ግን ማርያምን። ሳልናገረው ባልፈው ይቆጨኝ ነበር። ደግሞም በደንብ እናገረዋለሁ። ፕሮቴስታንቶች የማውቃቸው ጥቂቶች ተካፍለዋል። ሌላው ግን ዝም ነው ያለው። ከእስላሞቹና ከፀረ ዐማሮቹ እኩል የጎንደር ባለሀብቶች ለገዛ ወገናቸው አንዲት ፍራሽ ለመግዛት አቅም፣ ወኔ ማጣታቸውም አሳፍሮኛል። ይሄ መረገም ነው። ማርያምን መረገም ነው። አንዳንዶችማ እንኳን ሊሰጡ ሌሎች ለሰጡት ፎቶዬን ዘቅዝቀው ሁላ ሲሰድቡኝ ነው የሚውሉት። አንድ ሚልዮን ብር ከእነዚህ ትል ከላያቸው ላይ ከሚፈልቀው ተፈናቃይ ቀርጥፋ የበላቸው የቲክቶከሯ መማር አለባቸው ጠበቃ ሁላ ሆነው ነው ያገኘኋቸው። የቲክቶክን የዘረፋ ስልት ብትንትን አድርጌ ሰሞኑን በዚያው በቲክቶክ እመጣበታለሁ። እነ መማር አለባቸው እንዴት ከስኳድ ጋር ሆነው ይሄን የዋሕ ሕዝብ እንደሚግጡት አሳያችኋለሁ። ጠብቁኝ።

"…አሁን ከ3,300 የሚፈለግ ቦርሳ ውስጥ የ2,336 ቦርሳ ገዢ አግኝቼ አሁን የሚቀረኝ የ964 ሕፃናት ቦርሳ ብቻ ነው። እንደነገርኳችሁ ቦርሳው ለጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃይ ተማሪዎች ቤት ቤት በድንኳናቸው ውስጥ እንደ ሳጥን ትምህርት ቤት እንደ ቦርሳ የሚያገለግላቸው ቦርሳ ነው። ይሄንንም ከእናንተ ጋር እንደማሳካው ቅንጣት ታህል አልጠራጠርም። ቦርሳውን እንደጨረስኩ በቀጥታ የምዞረው ወደ ተማሪዎቹ ዩኒፎርም ማሟላት ነው። ቦርሳና ዩኒፎርም ከገዛንላቸው ደብተርና እርሳሱን ደግሞ አዳሜና ሔዋኔ ወደህ ሳይሆን በግድህ ታሟላታለህ። በግድህ አልኩህ። እና ላታሟላ ነው? ተኗኗርናታ…!

"…እኔ ዘመዴ በሕይወቴ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር እንዳለ ያረጋገጥኩበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው። አሁን በዚህ በቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ጉዳይ። ይሄን ጉዳይ በዩቲዩብ፣ በቲክቶክ፣ በፌስቡክ ሳልጮኸው፣ ኮሚቴ ሳላቋቁም። ታዋቂም፣ ዐዋቂም ነን የሚሉ ሰዎች ሳልለማመጥ፣ ሳልለምን፣ ሳላካትት። ስብሰባ፣ ውይይት ሳላደርግ፣ ደጅም ሳልጠና፣ አትሌት፣ አርቲስት፣ ሞዴል፣ ሯጭ፣ ነጋዴ ወዘተ ብዬ ሳልለማመጥ። እግዚአብሔርን ይዤ፣ ዘወትር ከአንደበቴ የማልለያትን ድንግል ወላዲተ አምላክ እመ ምሕረት እመቤቴ ማርያምን ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ ብዬ፣ ተማጽኜ፣ የቅዱሳኑና የእናንተን ጸሎት አጋዥ፣ ረዳት አድርጌ በቴሌግራም ጽሑፍ ብቻ በጥቂት ሰዎች ተሳትፎ የሺ ሰዎችን ችግር ሲቀረፍ ያየሁበት ጊዜ በመሆኑ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር እንዳለ አረጋግጫለሁ። ይሄን ድል፣ ስኬት እንደማየት ምን የሚያስደስት ነገር አለ? ምንም።

"…በቴሌግራም ገፄ ላይ 360 ሺ ሰዎች አሉ። ይገኛሉም። ነገር ግን ሁሌ እንደምለው ይሄ ሁሉ ሰው ማለት ወዳጄ ነው፣ በምናገረው፣ በማወራው ሁሉ የሚስማማ ነው ማለት አይደለም። መጽሐፍ እንዲል የተጠሩ ብዙዎች የሚገቡት ግን ጥቂቶች ናቸው። ሁል ጊዜ መጸለይ ከተመረጡ ምርጥ ጥቂቶች ውስጥ እንደሚደበን ነው። የተጠራ ብዙው ሳይሆን የተመረጠ ጥቂቱ ነው ተአምር የሚሠራው። ዓለም በወንጌል የተከደነው በ12 ሐዋርያት ነው። ከሙሉ እስራኤል ሕዝብ የተመረጡት 12 ሐዋርያት፣ 36 ቅዱሳት አንስት፣ 72 አርድዕት፣ በአጠቃላይ 120 ቤተሰብ ነው። ከሚልዮን እስራኤላዊ ተጨምቆ የተገኘው 120 ሰው ብቻ ነው። በእኔም ፔጅ ላይ…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው። መዝ 132 ፥ 8-9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዘመነ መንደር
ለበለፀገ ሀገር

ተመስገን ከጎጃም
ዝናሽም ከጎንደር
ወለዬው አቢቹ ከአባጅፋር ሰፈር
ከጎንደር ስኳዱ አገኘሁ ተሻገር

በአንደነት መከሩ
እየመሰከሩ ለዓለም ነገሩ
ለዘመነ ሀገር
የበለፀገ መንደር

• ጥቅሱን የጻፈው ግን መሰሪ ተንኮለኛ ነገር ነው። 😂😂😂 ወሎዬው ዳንኤል ከሆነ የጻፈው ቅኔው ይገባኛል። ወይ ቅኔ። ጉድ እኮ ነው። ሁሉም ደግሞ ሳቅ ብለው ነው የተነሱት።

የአሩሲዋን እመቤት
አዳነች አበቤንም ከፎቶው አላስገቧት

• እየገጠማችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"… ጳጉሜን ፪ ፦ የፊደል ገበታ ቀን…። "

• ኢትዮጵያዬ … እ…ም… ጷ  !!

Читать полностью…
Подписаться на канал