መልካም…
"…ርዕሰ አንቀጹ በጥሞና እንደተነበበ ተስፋ አደርጋለሁ። ለፈተና ያህል በርዕሰ አንቀጹ ላይ ብቻ አስተያየታችሁን ወደ መቀበል አመራለሁ። ስሜታችሁን ተቆጣጥራችሁ ሓሳባችሁን በጨዋ ደንብ ወደመስጠቱ ሂዱ።
"…በኢሞጂ እንደምታዩት የምጽፈውን ጽሑፍ፣ የማቀርበውን መረጃ ሁሉም ሰው ይወደዋል ማለት አይደለም። ይሄን መልእክት እየጻፍኩ ወደ 11 የሚደርሱ አንባቢዎቼ ከንዴታቸው የተነሣ ቁጣቸውን እንዲህ ግለው ሲሰጡ ታይተዋል። 😡😡😡። ይሄ መብታቸው ነው። የሚያስቀስፋቸው እንዲህ ብው ብለው መጥተው በአፋቸው እዚህ ፔጅ ላይ እጸዳዳለሁ ሲሉ ብቻ ነው።
"…በተረፈ ሌሎች ፔጅ ያላችሁ ሰዎችም ሕዝብን በጽሑፍ ብቻ ሥነ ሥርዓት ማስያዝን ከእኔ ተማሩ። እኔ ዘመዴ አባ ደፋር በብዕሬ ብቻ ነው መረን የለቀቀ፣ ክፍት አፍ፣ አሳዳጊ የበደለውን ነውረኛ ጋጠወጥ ሁላ ሰጥ ለጥ ነው የማደርገው። ይሄን አንብቦ በደንፉ ጓ ብሎ የሚመጣውንም እቀስፈዋለሁ።
"…ተቃውሞን በጨዋ ደንብ ተረጋግተን መግለፅ እንልመድ። ፀያፍ የዱርዬ፣ የአግድም አደግ የቦዘኔ ስድብ ግን ክልክል ነው። ሰምተሃል። ፔጁ ደግሞ የእኔ የዘመዴ ነው። ሕግ አክብር። ሥርዓትህንም ያዝ። በተለይ የ ልማደኛው የ GGጂጂግግ ግሪሳዎች እዚያው በለመዳችሁበት አፋችሁን ክፈቱ።
• ቀጥል ሓሳብህን በጨዋ ደንብ ተንፒስ…
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ትናንት አንድ ማስጠንቀቂያ ጽፌ ነበር። ይኸውም በምስጋና ሰዓት እግዚአብሔር ይመስገን የሚል ቃል ብቻ ሰሌዳውን በሚያጥለቀልቅ ወቅት ማንም ይሁን ማን በምስጋናው ጣልቃ ገብቶ አስተያየት እሰጣለሁ ቢል አስተያየቱ ምንም ይሁን ምን፣ ምርቃትም ይሁን ርግማን ብሎክ ይደረጋል ብዬ ጽፌ ነበር። እናም ዛሬ ጨሁን እየቀዘቀዙ የመጡት ኮሚንስቶቹ ፀረ ዐማራ የበግ ለምድ ለባሾቹ እነ GGጂጂግግዎች ቃሌን ሰምተው፣ ትእዛዜንም አክብረው ትንፍሽ ሳይሉ ታይተዋል። አንድ 7 ትናንት የሚሆኑ ትናንት ሰክረው ወይም ትእዛዜን ሳይሰሙ የቀሩ ደናቁርት GGጂጂግግዎች ግን ያለ ርህራሄ ተቀስፈዋል። በቀጣይም እንዲሁ እንቀጥላለን። ይሄን ክፍት አፍ ተሳዳቢ ለከት የለሽ በየፔጁ ስድብ ተሸክሞ ሲያራግፍ የሚውል የስድብ ኩሊ ልክ አስገባዋለሁ። በፀያፍ ስድብ ቤት መረበሽ የለበትም።
"…እኔ አንድም ሰው ቤት ሄጄ አስተያየት አልሰጥም። በሰው ቤት ምንአግብቶኝ ሄጄ እንበጫበጫለሁ። በራሴ ቤት ግን እንደ ዳንኤል ክብረት፣ እንደ መሳይ መኮንን በሬን ዘግቼ ብቻዬን አውርቼ ጨጋራህን አልልጥም። በሬን ከፍቼ ሥነ ሥርዓት አስተምርሃለሁ። አደብ አስገዛሃለሁ። አስተያየት በጽሑፍ መስጠት አስተምርሃለሁ። የፊደል አጣጣል ሁላ በነፃ አስቀጽልሃለሁ። ስሜትን መቆጣጠር፣ አሳዳጊ የበደለውን መግራትም እችልበታለሁ። በሱፍ በከረባት የታነቀ፣ በቆብ ስር የተደበቀን ድብቅ ማንነት አደባባይ በማስጣትም እታወቃለሁ። እናም ሥነ ሥርዓት ወሳኝ ነው።
"…በማኅበራዊ ሚድያ አንድ የተለመደ ልማድ አለ። ልማዱ ፀያፍ ልማድ ነው። በተለይ እነ እነ GGጂጂግግ ቤት የተለመደች ናት። በሃይማኖት በለው በቦለጢቃ ቀድመው ተቧድነው የተደራጁ ናቸው። እናም አንድ የተለየ ሓሳብ ስታነሣ እንደ ግሪሳ ወፍ ተሰብስበው መጥተው በመንጫጫት ፀጥ ሊያሰኙህ ይፈልጋሉ። ይሄን ጫጫታ ከቁብ ሳይቆጥር የተሻገረ አንድ ሰው ብቻ ዐውቃለሁ። እሱም አቶ ልደቱ አያሌው። ልደቱ ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ቢል ወፍ የለም። ስትንጫጫ ውለህ ታድራለህ እንጂ ልደቱ ከአቋሙ ዝንፍ አይልም። ደክሞህ ትሄዳለህ። በተለይ ለእ ነ GGጂጂግግ ዎች ጦስኝ ቀበርቾአቸው ነው። መድኃኒታቸው ነው። የአቋም ሰው። ሙግት የማይፈራ። ልደቱ አያሌው።
"…በማኅበራዊ ሚድያው ከሃይማኖት የመምህር ግርማ ሠራዊተ አጋንንት ዋነኛ ተግባሩ ግርማ ወንድሙ ሲተች ፈትቶ ይለቃቸውና በፔጄ ላይ መንጫጫት ይጀምራሉ። ምስኪኖቹን የሰው የተመልካች ዓይን የማያቆሽሹትን በይቅርታ አልፋቸዋለሁ። ባለጌውን የግርማ ወንድሙን ተፈትቶ የተለቀቀ አጋንንት ግን እቀስፈዋለሁ። ከፔጄ ተባርሮ ብንን ሲል፣ ወደ ቀልቡም ሲመለስ በጓሮ በር፣ በዘመድ አዝማድ የአማላጅ መዓት ልኮ መልሰኝ ዘመዴ፣ አጥፍቻለሁ ይቅርታ ቢል አልመልሰውም። ቀሰፍኩ፣ ቀሰፍኩ ነው። አከተመ። መጀመሪያ ነው መጠንቀቅ፣ አፍን መሰብሰብ እንጂ ለግርማ ወንድሙ አጭበርብሮት ጠበቃ ሆነህ መጥተህ ክፍት አፍህን ከከፈትክ በኋላ የምን መርመጥመጥ ነው? እቀስፍሃለሁ።
"…የጊዜ ጉዳይ እንጂ እኔ የማልነካው ሰው የለም። እኔ ራሴንም አልምርም። እኔ ቋሚ ወዳጅም፣ ቋሚም ጠላት የለኝም። መልካም የሠራ ሁሉ ሃይማኖቱን፣ ዘሩን፣ ቀለሙን ሳላይ እደግፈዋለሁ። የተጠቃ ለመሰለኝ ሁሉ ድምጼን ያለ ስስት አውጥቼ እጮሃለሁ። አጠፋ ያልኩትን ደግሞ በውስጥ ለውስጥ መክሬ ዘክሬ አልሰማ ሲል በአደባባይ አሰጣዋለሁ። ያኔ ነው ከየጎሬው ላያዛልቁት፣ ላያዋጡት ወጥተው የሚለፈልፉት። እኔ ደጋፊው መስለው የሚጮሁትን በሁለት መልኩ ነው የማያቸው። አንዳኛው ከምር ደግፎ የሚመጣ ተሳዳቢ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ደጋፊ መስሎ እኔን ያበሳጨም መስሎት ለታክቲክ ሴራ ሊሠራ ብልጥ ሆኖ አፋጀሽኝ፣ አፋጀሽኝ ለመጫወት የሚመጣ ሰገጤ፣ የፋራ አራዳ ነው። እኔ ምኔ ሞኝ ነው? ሁለቱንም ቀስፌ ወደ መዝገብ ቤት ፋይሉን ዘግቼ እልካቸዋለሁ። አለቀ። አተራምሳለሁ ብሎ የሚመጣውን አተራምሼ አሳርፈዋለሁ።
"…ሁል ጊዜ የማይነካውን መንካት ስጀምር ግሪሳው መንደሩን ያጥለቀልቃል። ቄስ የለ ሼክ፣ ዳያስጶራ የለ ላሜቦራ፣ ወሃቢይ፣ ወያኔ፣ ኦነግ፣ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ብልጽግና የለ ብልግና፣ ተሃድሶ በለው የግርማ ቡችሎች፣ ጽንፈኛ ጴንጤዎች በሙሉ ግርር ብሎ ይመጣል። አንዳንዶች አሉ አድፍጠው የሚጠብቁ። ዘመዴ አሁን ተሳስቷል፣ የማይነካም ነክቷል ብለው ከምር ተናደው ሊሰድቡኝ ከመጡ ሰዎች ጋር ተደርበው መጥተው ነገር ለማባባስ የሚደክሙ። ወዳጄ እኔ ምኔ ሞኝ ነው ጊዜም አልሰጠው ስቀስፈው። በማኅበራዊ ሚዲያው 7 ዲግሪ ነው ያለኝ።።የማኅበራዊ ሚዲያውን ኗሪ ሥነ ልቦና በልቼ የጨረስኩ ነኝ። ጠንቅቄ ዐውቀዋለሁ። እናም በሌላ ሸውደኝ እንጂ እኔን መሸወድ ኖ ኤለም። አታስበው።
"…እነ በጋሻው ደሳለኝን የመሰሉ ናቡከደነጾሮች፣ እነ ትዝታው ሳሙኤል፣ ዘርፌ ከበደን የመሰሉ አርጤምስሶች። ተሃድሶን በሙሉ ስገጥም እግዚአብሔርን ይዤ ብቻዬን ነበር። እነርሱን ለማዳን አቦይ ስብሃት ነጋን ጨምሮ፣ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ጭምር፣ እነ ጌታቸው ዶኒ፣ ዘሪሁን ሙላት ለፍርድ ቤት ደብዳቤ ሁላ ጽፈው፣ ሙሉ የተባለ ትግሬ ዳኛ እንዲፈርድብኝ አድርገው ዘብጥያ ወርጄም አላስቆሙኝ። ይኸው እኔ በተዋሕዶዬ እንደጸናሁ አለሁ። ስብሃት ነጋ ተሰደደ፣ በጋሻው ደሳለኝ፣ ትዝታው ሳሙኤል፣ እነ ዘርፌም ጰነጠጡ። እኔ አሸነፍኩ። እነሱ ግን ከነደጋፊ ግሪሳቸው ተሸነፉ። አለቀ።
"…ከዚያ ወዲህም ማነው ከእኔ ጋር ተሳፍጦ የቆመ፣ የተረፈ? የማደንቀው ኤርሚያስ ለገሰን ነው። አፍ አልተካፈተኝም። ዋ ስለው ሹልክ ብሎ ነው የወጣው። ኢትዮ 360 ዎች ወዳጆቼ ምነው ዘመዴ ችግር አለ እንዴ ብለው ሲጠይቁኝ እንኳ ኤርሚያስ ለገሰ ማን እንደሆነ አያውቁም ነበር። ኤርሚያስን ተናገርከው ብለው እነ GGጂጂግግ ልክ እንደዛሬው ምድረ ፌክ ኢትዮጵያኒስት መንጋ ሁላ ፕሮፌሰር ነኝ፣ ዶክተር ነኝ እያለ አፉን ሲከፍትብኝ ነበር። ኤርሚ ነፍሴ ኩም አድርጎ ምላሳቸውን አስዋጣቸው እንጂ። ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስን፣ ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌን እረፉ እንጂ ስል ማነው ያልጮኸብኝ፣ ምህረተአብን እረፍ ተው ስለው ማነው አፉን ያልከፈተብኝ? ማን ምንአባቱ አመጣ? ማንም። እኔ ብቻዬንም ብሆን አሸንፌአለሁ። የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን ያዝረጠረጥኩ እኔ ዘመዴ ነኝ። ድምጥማጡን ያጠፋሁት፣ ሽባ ያደረግኩት እኔ ዘመዴ ነኝ። መንጋ መች እሰማና አባቴ። ከነከስኩ ነከስኩ ነው ሳላደማ መች እመለሳለሁ።
"…ሰሞኑን በሀብታሙ አያሌው፣ በእስክንድር ነጋ እና በ360 ሚድያ ላይ ጥያቄ በስሱ አንስቻለሁ። ከዴቭ ዳዊት በቀር ምክንያታዊ ሆኖ ለመሟገት የመጣ አንድም ሰው የለም። እኔ በግሌ የዴቭ ዳዊት የግል አድናቂው ነኝ። የጎነች ስስ ጎጠኝነት ብትኖርበትም ጥንቅቅ ያለ ደፋር የዐማራ ምሑር ነው። መቶ በመቶ በሚያነሣው ሀሳብ ባልስማም ከ95% በላይ ግን የውስጤን፣ የአንጀቴን የሚገልጽልኝ ሰው ነው። እኔን ሲተቸኝ እንኳ በምሑር ብዕር ነው። ለእኔ አግዘው ሲሰድቡት ሳይም ይበሰጨኛል። እንደ ዴቭ ዳዊት ባለው ሰው ዐማራው እስከአሁን አልተጠቀመበትም። ወደፊት ይጠቀምበታል ብዬም አምናለሁ። ከዚያ ውጪ ግን ወደ ውጪ። ሰውየውን በስልክ አግኝቼው ባወራው ሁሉ በጣም ነው ደስስ የሚለኝ። እኔ የዐማራ ትግል መሪ አይደለሁም። የዐማራ ትግል ደጋፊ ነኝ። ቆቱነቴን አልደበቅኩም። ዐማራን መደገፍ ደግሞ ተፈጥሮአዊ መብቴ ነው። በዐማራ ትግል 05 ሳንቲም የሚከፍለኝ፣ የምቀበለውም ድርጅትም ሰውም የለም። ቋሚ ወዳጅ፣ ዘላቂም ጠላት የለኝም።…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም…
"…እንደተለመደው ዛሬም እንደ ሁልጊዜው እግዚአብሔር ይመስገን ይል ዘንድ የሚጠበቀው የአመስጋኝ ቁጥር ሞልቷል። በመቀጠል ወደ ተለመደው መርሀ ግብራችን እንገባለን። ርዕሰ አንቀጽ።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ስለ ራሴው ስለ ዘመዴ የቲጂ መንደር ፔጅ ተሳታፊዎች ደንብና ሥነ ሥርዓት ይሆናል የምንነጋገረው። በፔጄ ላይ ሓሳብ ሊሰጥ የሚመጣ ማንኛውም ሰው ሊያከብረውና ሊጠብቀው ስለሚገባ ሥነ ሥርዓት የሚወጣ መመሪያ ይሆናል የምንነጋገረው።
"…በፔጄ ውስጥ ረጅም ዓመታትን ለመቆየት እና ለመዝለቅ የሚሹ የመንደሬ ነዋሪዎች አብዛኛዎቹ የሚያውቁት ቢሆንም ድንገት ቀፎውን የምነካበት መንጋ ግርር ብሎ ሲመጣ ሊያከብረው፣ ሊጠብቀው እና ሊያልፈው ስለማይገባ ቀይ መስመር ያውቅ ዘንድ በርዕሰ አንቀጹ መልክ ለብቻው መጻፍ በማስፈለጉ ዛሬ ርዕሰ አንቀጻችን በዚህ ዙሪያ እንደ መተሬ፣ ኮሶ ያለ መመረር የሚል፣ ሰናፍጭ የበዛበት ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ ሊያቀርብላችሁ ወድዷል ዘመዳችሁ ዘመዴ።
"…ፍሮፌሰር ሁን አንጅነር፣ ዶፍቶር ሁን ፍሮፌሰር፣ ሼክ ሁን ቄስ፣ ወታደር ሁን ወዛደር፣ ሰገጤ ሁን አራዳ፣ ታጋይ ሁን አታጋይ፣ ትግሬ፣ ዐማራ ሁን ወረሞ፣ ወንድ ሁን ሴት ለደንታህ ነው። የቤቴን ሥርዓት መመሪያ ታከበራለህ፣ ታከብራለህ። ልክም ትገባለህ። በንዴት ፎግልቼ ጓ እላለሁ ብትል ሰከንድም አላቆይህ በወሬ ጠኔ በአፍጢምህ ትደፋ ዘንድ ብሎክ ባን በተባለ ሰይፌ ወገብ ዛላህን ቆምጬ የደም ግፊትህን እጨምርልሃለሁ።
• እህሳ ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…? እንደ ወታደር ያለ ጥያቄ ነው። ሌላ ዝባዝንኬ መልስ ያስቀስፋል። ሰምተሃል?
"…ለዛሬ ይበቃናል። በሉ ደኅና እደሩልኝ ዐማሮች…! 😂 …ነገ ደግሞ እንዲሁ ተሰባስበን እናወጋለን። ዐማሮች ሰምታችሁኛል አይደል? ደኅና እደሩ አልኳችሁ እኮ። ሃይ አቦ ምንድነው ሳ…!
• ይቅርታ ሌባ ሁላ የሚለውን ነጠላ ዜማዬን ጭየሰማችሁ። ዐማራ ብሔርተኛ ይሆናል። ያውም ጽንፈኛ የፀነፈ ብሔርተኛ። ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ እነ GGጂጂግግ ግን በአናታችሁ ተተከሉ። አልሰማችሁም። አልፋታችሁም።
• ሌባ ሁላ…!
መጣሁ ደግሞ…
ምን ላይ ነበር ያቆምኩት…? አዎ ጋሽ ቮድካ ክንፉ ወዳጄ ጋር ነኝ።
"…ዶር አምሳሉና አቶ ክንፉ ሁለቱም ቦስተንና ኒውዮርክ ያለውን ዐማራ አንዴ በግንቦት 7፣ ከዚያ በባልደራስ፣ ከዚያ በግንባሩ ገንዘቡን እጥብ ያደርጉ ዘንድ በእስክንድር ነጋ የተመረጡ ናቸው።
"…ልክ ኤልያስ ክፍሌን ለምነው በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ካሰባሰበላቸው በኋላ በቀጥታ መረጃ ቲቪን አፍርሰው ኢሳትን የመሰለ የቴሌቭዥን ጣቢያ ወደመክፈት ነበር የተንቀሳቀሱት። የዚህ ፊት አውራሪዎች ደግሞ እስክንድር ነጋ፣ ሀብታሙ አያሌው እና ጄሪ ነበሩ።
"…ዘመቻው በዶር አምሳሉ ተጀመረ። ጎጃሞችን ስልክ እየደወለች እንድትከፋፍላቸው ደግሞ ሀብታሙ ወሮ ሕይወትን አሰልጥኖ መቅረጸ ድምጽ ሰጥቶ ላከ። አሁን ከሸፈባት እንጂ እነ ማርሸትን ለማጣላት መስከረም ላይ ነበር እነ ሀብታሙ ተንኮላቸውን የጀመሩት። ነገሩ ግን ከሸፈ። ጎጄ መለኛው።
"…ከዚያ ከሕዝብ የተሰበሰበ ዶላር ይዘው ሲያበቁ፣ ሁሉንም ኮሚቴ አባረው ግንቦቴዎችና ባልደራሶች ብቻ ቀሩ። ከዚያም በዚያ ብር የእስክንድር ነጋን የቀድሞ "ምኒልክ ጋዜጣን" ሚኒሊክ ሳታላይት ቴሌቭዥን አድርገው ከች አሉ።
"…በእውነት መረጃ ቲቪ ላይ የሸረቡት ተንኮልና ሴራ ይሄ ነው ተብሎ አይገለጽም። ኤልያስ ክፍሌ የለፋላቸው ልፋትም ይሄ ነው ተብሎ አይነገርም። ግን በሰላም መውጣት እየተቻለ እነ እስክንድር ነጋና ሀብታሙ አያሌው መረጃ ቲቪን አድቅቀው፣ አፍርሰው ሊወጡ ሞከሩ።
"…ታዲያ እኔ ምኔ ሞኝ ነው…? ይሄን ክብር የማይወድለት ከፋፋይ ወንበዴ አስመሳይ አጭቤ ሁላ ጉሮሮው ላይ ቆምኩበታ። አልፋታህም።
"…ፋኖ በገንዘብ አይገዛም። በጋዜጠኛ ነኝ ባይም አይመራም። ፋኖ በራሱ ነው መመራት ያለበት። ጥግህን ያዝ። ሠርተህ ብላ አዳሜ።
• እየኮመታችሁ…!
"…እሺ…እንዴት ነኝ…? እናንተንስ እንዴት ይዟችኋል ጭዌውን ልቀጥል አይደል…? 😂😂 አንድ 100 ያህል ሰው ቀጥል ካለኝ በኋላ እቀጥላለሁ።
• እነ GGጂጂግግ ዎች ቀዝቃዛ ውኃ እየተጎነጫችሁ…
"…በፊት ግንቦቴው አሁን ደግሞ የእስክንድር ነጋው ሕዝባዊ ሠራዊት ቀንደኛው አቶ ክንፉ እንዲህ ይላል።
መረጃ
ሚያዝያ 16 ,2016 1888 ሬዲዮ
"…የአማራ ፋኖ በጎንደር" እና "የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ" የአንድነት ስምምነት ተሳክቷል።
ከቦታው የተገኙ ምንጮች እንዳረጋገጡት ስምምነቱ እንዲፈፀም በርካታ በውጭና በውስጥ የሚገኙ አርበኞች ጥረት ሲያደርጉ ቆይተው ነበር። ሰፊ ምክክርም ተካሂዷል እናም ይህ ሀሳብ ውጤት አግኝቶ ዛሬ ከስምምነት ላይ ተደርሷል። የተዋሃዱት ታጣቃዎች በአንድነት በመሆን የደስታ ተኩስ በማሰማት ላይ ናቸው በማለት ዜና ይሠራል።
"…ሁለቱን አካላት ያስታረቅኩት ግን እኔ ዘመዴ ነኝ። በሀብታሙ አያሌው ሲሰደብ፣ ሲደበደብ፣ ሲረገም የከረመውን የሚጀር ጀነራል ውብአንተን ቡድን ብሶት ስሰማ ከርሜ ጎንደሮችን ፈጣሪ ረድቶኝ ጎንደሮችን ያስታረቅኩ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር እኔ ዘመዴ ነኝ። ከእኔ ውጪ ያነጋገራቸው፣ የተቆጣቸው፣ የተማጸናቸው አንድም ሰው የለም። በጸሎት የሚከፍቱ እና በጸሎት የሚዘጉ ሁለት አባቶች ነበሩ። የቴክኒክ ሥራ የሚሠሩ አቶ አዱኛውና አቶ ዘመን ከአሜሪካ ነበሩ። ፋኖ ጂኒ ከጎንደር ይላላከኝ፣ ይራዳኝ ነበር። በተረፈ ከእኔ በቀር የተናገረም፣ ያሸማገለም አንድም ሰው የለም።
"…በጎንደሮች አንድ መሆን የተበሳጨው ማነው? ሀብታሙ አያሌው እና ሠራዊቱ፣ ክሬዲት ፈላጊ አይደለሁም ነገር ግን የእኔ የማስታረቅ ስም እንዳይነሣ በግንቦቴዎቹ ኢትዮ 360 ዎች በአቋም ደረጃ ነው የተወሰነው። የሆነው ሆኖ በእመቤታችን እለት የተጀመረ ሽምግልና በኪዳነ ምህረት እለት በድል ተጠናቅቋል። እኔ በደስታ አልቅሻለሁ። እነሱም ጥይት ተኩሱልኝ ብዬ ጋሽ መሳፍንት አዘው ተተኩሶልኛል። ይኸው ነው።
• ተናግሮ አናጋሪማ አግኝቼ ነው? ከነከስኩ ሳላደማ መች እፋታሃለሁ። መጣሁ…
መልካም…
"…አሁን ደግሞ ወደ ነቆራው እናመራለን። ትንሽ የብዕሬን ወላፈን ብልጭ ላድርጋቸውና እንደ የራሺያው ተማሪ፣ የግንቦቴ ሽንት፣ የሀብታሙ አያሌውና የእስክንድር ነጋ ጠበቃ ነኝ ባዩን ጋሽ ክንፉ ወዳጄ አይነቶቹን የበግ ለምድ ለባሾች ላንጫጫቸው።
"…እነ GGጂጂግግ ዎች በጨዋ ደንብ ለመንጫጫት ተዘጋጁ። በእስክንድር ነጋ በኩል የዐማራን ትግል ለመጥለፍ ያሰፈሰፈውንና መረጃ ቲቪን በሀብታሙ አያሌውና በጄሪ በኩል ሊያፈርስ አሰፍስፎ የነበረውንና በመረጃ ቲቪ የቦርድ አባላት ቅልጥፍና አከርካሪውን ተመትቶ አሁን ሚኒሊክ ቲቪ ብሎ የመጣውን ቡድን አፈር ከደቼ ላብላው።
"…ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ሳላደማህ መች እፋታህና። እኔን በዐማራ ጉዳይ የሚሰድበኝ ካለ የኋላ ታሪኩን መብረብር ብቻ ነው። በትግሉ የማደንቀው እስክንድር ነጋ በእነዚህ ሰዎች የተከበበ ከሆነ የማምሻ እድሜው በቆሸሸ፣ በነተበ፣ በሚከረፋ ታሪክ ይደመደማል። እኔ ግን ለሀብታሙ አያሌው፣ ለእስክንድር ነጋ፣ ለኢትዮ 360 አግዘው ዐማራ ዐማራ ለመጫወት የሚመጡትን ግም ቦቲዎች በሙሉ ለምዳቸውን ገፍፌ ተራ በተራ ሱሪያቸውን ዝቅ አድርጌ በብእሬ ሳማ እለበልባቸዋለሁ።
"…አንድ ለእናቱ፣ ሺ ለጠላቱ እኔ ዘመዴ እበቃቸዋለሁ። ለእኔ ተደርቦ የሚመላለስልኝ አንድም ሰው አልፈልግም። መሞገት አቅቶት ክፍት አፉን የሚከፍት ግም ቦቲ ካለም እቀስፈዋለሁ። በጨዋ ደንብ ግን " አሁንስ አበዛኸው፣ መስመር ሳትክ፣ ከሀብታሙ ራስ ላይ ውረድ፣ እሰኬውን አትንካ፣ 360 መዳኛችን ነው፣ ሠራዊቱ ያማልደናል" ማለት ግን ይቻላል። የተፈቀደም ነው።
"…አቶ ክንፉ የጦስ ዶሮዬ ነው። ተናግሮ አናጋሪዬ፣ በእሱ አስታክኬ ጦርነቴን ልጀምር ነኝ…?
ርዕሰ አንቀጽ”
"…የፕሪቶሪያው ውል የተግባር መርሀ ግብር ላይ የራያንና የጠለምትን ጉዳይ እስከ ግንቦት 30/2016 ዓም የወልቃይት ጠገዴን ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓም ለመጨረስ ስምምነት ፈጽመን ወደ ሥራ ገብተናል። ብሎ ጄነራል ታደሰ ወረደ ትናንት መግለጫ ሰጥቷል። ይሄን መግለጫ ደግሞ ሁሉም ሰው ሰምቷል። ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱም የሰሙ ይመስለኛል። ጥያቄዬን አሁን ላስከትል።
"…የፕሪቶሪያው ስምምነት የፈረሙት ወያኔና ብልፅግና ናቸው። ኮሎኔል ደመቀ ደግሞ የብልፅግና አባል ናቸው። ብልፅግና ከወያኔ ጋር ሲስማማ ኮሎኔል ደመቀስ አብረው ይስማማሉ? ወይስ እንደ ራያ አላማጣ በመከላከያ ተገርፈው ለወያኔ ወልቃይትን ለቅቀው ውልቅ ብለው ወደ ጎንደር ይሰደዳሉ? ወይስ እንደ ሀምሌ አምስቱ አንድ ጥይት እስኪቀራቸው ድረስ ተታኩሰው ከወያኔም ከከሀዲው የአቢይ ጦር ጋርም ይተጋተጋሉ?
"…ኮሎኔሉ የዐማራ ፋኖ መከላከያ ላይ መተኮሱን አምርረው በመቃወማቸው ይታወቃሉ። አሁንስ ያአቋማቸው አብሯቸው አለ ወይ? ከሀዲው መከላከያ ከሳምሪና መከላከያውን ባረዱበት በጥቅምት 24 የሰየሙት ከአርሚ 24 ጁንታ ኃይል ጋር ወደ ወልቃይት ገስግሶ ሲመጣ ምን ይወስኑ ይሆን? የተከዜ ዘብ ብቻውንስ ሦስቱንም ለመመከት በቂ ነው ወይ? ኮሎኔሉ ዝምታቸው ይሰበር ዘንድ በጨዋ ደንብ እንዲህ ብንጠይቃቸውስ?
"…የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ኮሎኔሉ ቢከዱና የብልፅግናንና የወያኔን የጓዳ ስምምነት ላስፈጽም ቢሉ የወልቃይትስ ሕዝብ ዳግም ዘሩን በበቀለኛዋ ወያኔ እንደ ማይካድራ ለማስጨፍጨፍ ፈቃደኛ ነው ወይ? ወዲ ወረደ እንዳለው ሰኔ 30/ 2016 ዓም ወልቃይትን ለወያኔ ያስረክባሉ ወይ?
"…የተባበሩት አረብ ኤምሬትስስ የወልቃይት ለም መሬት እንደጎመጀችበት ቀብድ ከፍላ ስትጠብቅ ወያኔ ወስዳው ለሃጯን እንዳዝረበረበች ትቀራለች ወይ…?
መልካም…
"…እግዚአብሔር ይመስገን የምትል ባለ 12 ፊደል ቃል ጻፍና እግዚአብሔን አመስግን ብዬ ሳዝህ አንተ አላስችል ብሎህ በምስጋና መሃል ጣልቃ ገብተህ "ከሀብታሙ ራስ ላይ ውረድ፣ እስክንድርን አትንካብን፣ ቀንተህ ነው፣ ከዐማራ ትግል ውጣ፣ ኢትዮ 360 ምን አደረገ? አሁንስ አበዛኸው ወዘተረፈ የሚሉ ለከት የለሾች፣ ማርኪስስቶች፣ የ60 ዎቹ አብዮተኞች ትራፊ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች እና ልጆቻቸውን ሥነ ሥርዓት ሳስይዝ እና ሳጸዳ ነው የምውለው። ምክንያቱም ጭምብላም ስለሆኑ መቼና መቼ አስተያየት እንደሚሰጥ አያውቁም። እነዚህ ቅዳሴ መሃል ቲክቶክ ሊጠቀሙ ይችላሉ።
"…ለማንኛውም "እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ" ማለት ሌላ ዝባዝንኬ፣ ኮተት፣ ሐተታ ሳትጨምር እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ብለህ ጻፍ ማለት ነው። ሀብታሙንም፣ ኢትዮ 360ንም፣ እስኬውንም ለማዳን የራሱ የሆነ ሰዓት አለህ። በቦታው በጨዋ ደንብ በአፍህ ሳትጸዳዳ መሞገት ትችላለህ። ለዚህም ራስህ ምስክር ነህ። የእኔ ቤት እንደ መሳይ መኮንን፣ እንደ ዳንኤል ክብረት ዝግ አይደለም።
"…መልካም…ቀጥሎ የምንገባው ወደ ተወዳጁ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን "በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ" ላይ አጠር ያለ ጥያቄአዊ የመወያያ አጀንዳ የምታነሣ ናት። የምታመካክር፣ የምታወያይም ርዕሰ አንቀጽ ናት። ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። መወያየት መልካም ነው።
• እህሳ ዝግጁ ናችሁ…?
በነገራችን ላይ…
"…እኚህን አባት አግኝቼአቸዋለሁ። የጎጃም የደጀን አካባቢ ነዋሪ ናቸው። ኑሮ ቢከፋባቸው ወደ ሸዋ መጥተው ሰበታ አካባቢ ለአንድ ኦሮሞ ገበሬ ሆነው 4 ዓመት ካገለገሉ በኋላ የሠሩበትን ገንዘብ ከልክሎ ሲያባርራቸው ነው እነዚያ ቄሮዎች አግኝተው በዐማራነታቸው አዋርደው የደበደቧቸው።
"…ከድብደባው በኋላም ኦሮሚያ እዚያው ሸገር ሲቲ አስረዋቸው ነበር። ለፖሊስም ይሄንኑ የደረሰባቸውን በደል ቢያስረዱም "ገንዘቡን አሠርቶ የከለከላቸው ኦሮሞ ስለሆነ ዘመኑ የኦሮሞ ስለሆነ ምንም ፍትሕ ሳይሰጧቸው ወንጀል እንደሌለባቸው አጣርቶ ከእስር ቤት ፈትቷቸዋል።
"…ከተፈቱ በኋላም ሀገሩን ስለማያውቁት ማደሪያ አጥተው ጎዳና ላይ ለማደር ተገደው የነበረ ሲሆን ከጥቂት ቀን የጎዳና ላይ መንገላታት በኋላ አንድ ለነፍሱ ያደረ ኢትዮጵያዊ መምህር እጅ ላይ ወድቀው ወደ ቤቱ ወስዷቸዋል። እሱንም አፈላልጌ ደውዬ አመስግኜዋለሁ።
"…ሰውነታቸውን አጥቦ፣ ልብሳቸውን ቀይሮ፣ መኝታ አዘጋጅቶላቸው ከእርሱ ቤት አሳርፏቸዋል። "…ስለምጾም ነው እንጂ ምግብማ እንደ ልቤ ልኛል" ነበር ያሉኝ። በመከራ ውስጥም ሆኖ ፈጣሪን የሙጥኝ ማለት ይኸው ፍጻሜው ያማረ ነው የሚሆነው። መከራ ለጥቂት ጊዜ ነው የሚከብደው። ያልፋል።
"…አሁን ዛሬ ባንክ ዝግ ስለሆነ የባንክ ደብተር ማውጣት አልተቻለም። ነገ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ደብተር ይወጣላቸዋል። ከዚያ የሚሆነው ይሆናል። እግዚአብሔር ይመስገን።
• አይ ኦሮሞ አለ አቢይ አሕመድ…!
ይሄኛውን አጀንዳዬን አልረሳሁትም…!
"…እኔ ዘመዴ ማለት አንደዜ ከነከስኩ ነከስኩ ነው። የነከስኩትን ሳላደማው አልመለስም። አልፋታውም። ዐማራን እንደ ትናንቱ በሚወደው በአርንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማው ተጀቡኖ፣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እየዘመሩለት በስሙ አደንዝዞ መቀፈል የማይታሰብ ነው።
"…እኔ ዐማራው ነፃ እስኪወጣ የሚመጣበትን መከራ ሁሉ አብሬው ልጋፈጥ፣ ሰንኮፎቹን በሙሉ በድፍረት እንደ እብድ ውሻ ሆኜ ጭምር ልነክስለት፣ ልነቅስለትም ቃል ገብቻለሁ። አይደለም የዐማራ ጠላት ራሱ ዐማራ ነኝ የሚለውና እንደ ድሮ ካውያ ቀስ ብሎ የሚሰማው ሰገጤ ዐማራ ነኝ ባይ ጎጋ ሁላ ቢጮህብኝ አልሰማውም። ለዐማራ የቀጠረኝ የለም። የሚከፍለኝ የለም። ህሊናዬ ነው ለዐማራ ግፍ ጥብቅና የሚያስቆመኝ። እንጂ ዐማራው ሰማኝ አልሰማኝ፣ አደመጠኝ አላደመጠኝ ለደንታው ነው።
"…የዐማራው ትንሣኤ ደርሷል። ከትንሣኤው በፊት ግን ዐማራ መሳይ ማስኮች መውለቅ፣ መገለጥ አለባቸው። በዐማራ ማኅበራት ስም ዐማራን ገንዘቡን ዘርፈው ትግሉ ፍጻሜ እንዳይኖረው የሚንተፋተፉትን ሁሉ እኩል እገጥማቸዋለሁ። እነ GGጂጂግግ (ግንባሩና ግንቦቴዎችን) እኩል እገጥማቸዋለሁ። ረዳት አልፈልግም፣ አጋዥም አልፈልግም። አምላኬን ይዤ፣ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ የምላትን የአምላክ እናት ድንግል እናቴን ይዤ ባዶ ኪሴን፣ ባዶ እጄን ከዐማራ በተዘረፈ ብር ብር ቢልዮን ብር ከሚያንቀሳቅሱ ፀረ ዐማሮች ጋር እጋፈጣለሁ። አሸንፋቸዋለሁም።
"…ኢትዮ 360 ሀብታሙ አያሌው፣ እየሩሳሌም ጄሪና ዶ/ር አምሳሉ የተባለ ጁንታ ሚስት አቅፎ የሚተኛ ፀረ ዐማራ ግለሰቦችን እዋጋቸዋለሁ። ዘመኑ ዘመነ መገለጥ ነው። እስክንድር ነጋ ሥር ተኮልኩሎ ዐማራን ማጭበርበር አይቻልም። አይፈቀድምም። ፋኖን ገንዘብ ከፍሎ የምስጋና ማስታወቂያ ማሠራት አያድንም።
• እሺ ጋላው በል ንካው…!
የትግሬ አዲስ አጀንዳ…
"…የፕሪቶሪያው ውል የተግባር መርሀ ግብር ላይ የራያንና የጠለምትን ጉዳይ እስከ ግንቦት 30/2016 ዓም የወልቃይት ጠገዴን ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓም ለመጨረስ ስምምነት ፈጽመን ወደ ሥራ ገብተናል። (ታደሰ ወረደ)
"…ይህ ዛሬ በድምፂ ወያነ የተለቀቀው ዜና የሳይበሩን ዓለም እንዲሞላው ተደርጓል። የትግሬና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከብልፅግና የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ጋር በመሆን ስለ ሌላ ዙር ጦርነት ዝግጅት፣ ስለ ሌላ ዙር የይግሬና የዐማራ መከራ፣ ስለ ሌላ ዙር የጅምላ ብሔራዊ መርዶ ዝግጅት ጽፈዋል።
"…አገዛዙ ይሄ ክረምት እስኪያልፍለት ድረስ የዐማራው ትኩረት ትግራይ ብቻ እንድትሆን አቅዶ እየሠራ ነው ባይ ነኝ። ጦርነቱን በማጓተት ስትራቴጂ አድርጎ እየሠራ ነው። የትኩረት አቅጣጫን በማስቀየር በተለይ ይህችን ክረምት እንደምነም የፋኖን ትኩረት ወደ ራያና ወልቃይት በማዞር ለሚመጣው በጋ በድሮን እና በከባድ መሣሪያው ለመጠቀም ያስባል። ለማንኛውም ፋኖ ለሁለቱም ከወዲሁ መዘጋጀት ይኖርበታል ባይ ነኝ። በተለይ ትኩረቱን መንግሥት ላይ አድርጎ ለ4ኪሎ መዋጋት አለበት። ወያኔ እንደሆነች ዛሬ ብትገባ ነገ በዐማራው መነጠቋ አይቀርም። ኦሮሙማው አያዛልቃትም የሚሉ መተርጉማንም አሉ።
"…የብአዴንን ዝተት መግለጫ፣ የተመስገን ጥሩነህ ዛቻ፣ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሓላፊ ሚንስትር ለገሰ ቱሉን ቱሪናፋ ቀደዳ፣ ከመቀሌ ከመሴ፣ ከመቀሌ ደብረታቦር በሲሚንቶ ጫኝ መኪና ውስጥ መትረየስ፣ ቦንብ ለፋኖና ለሸኔ ሊላክ ሲል ተያዘ ወዘተ የሚለው የማደናገሪያ ዜና አይሠራም። ትግሬ ከኦሮሞ ጋር ሆኖ እየፎከረ ነው። በራያ ዘረፋው እንደተጧጧፈ እየተሰማ ነው። የጁላ ጦር የገበሬ ቤት በእሳት እየለኮሰ እያነደደ ነው ተብሏል። መፍትሄ ጨካኝ መሆን ብቻ ነው።
• በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ…
"…ለሽንት እና ካካ ቤቱ…
"…የአባ መዓዛ ተማሪው፣ የቀድሞው ዝነኛ ሰባኬ ወንጌል፣ አሁን መኖሪያውን በሀገረ አማሪካ ያደረገው፣ የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ የምእመናን አባት፣ የበጎች እረኛው የተከበረው ቀሲስ ደረጀ ስዩምም ለካካ ቤት ማሠሪያው 5 ሺ ብር መርዳቱን ራሱ በፌስቡክ ገጹ ለጥፎ አንደዜ ምእመናን ሴቶች በእልልታ ወንዶች በጭብጨባ አመስግኑልኝ ሲል ታይቷል። 5ሺ ብር ግን በዶላር ሲመታ፣ ሲታሰብ ስንት ዶላር ነው ማለት ነው? ውይ ለ41 ዶላር ብሎ ነው እንዲህ ላንቃችንን ያሰነጠቀው? ኤጭ…
"…ደሬ ድሮ ጎበዝ መምህር ነበር እኔ ሳውቀው። በነገራችን ላይ ሳስበው ሳስበው ደሬም ኦሮሞ ነው ማለት ነው…? ኤፍሬም እሸቴ፣ ብራኑ ጎበና፣ ደረጀ ስዩም… ኦሮሞ ከሆነ ደግሞ የዐማራና የትግሬ ችጋርና ችግር ባይመለከተው፣ ባይራራላቸው እንኳ እነ አቢይ IMFን ለመሸወድ ሲሉ ላመጡት የማጭበርበሪያ ዘዴ እወደድ በንጉሡም ፊት ሞገስ አገኝ እንደሁ ብሎ ለካካ ቤት ማሠሪያ 5ሺ ባላወጣ ነበር። ደግሞስ ለዚህ ብር ከሚያዋጣ ለተራበው ለሐረርጌ ኦሮሞ ለወገኑ አንዲት ዳቦ መግዣ ቢያስተባብር ምንአለበት? ኤጭ አላበዛሁትም እንዴ አሁንስ? ምንአገባኝ ግን? እኔን ብሎ መካሪ…
"…በወይራ ጢስ የምትጠነቁለው የሻሺቱ እንግዳን የልጅ ልጅ የአቢይ አሕመድን እናት ባለ ራዕይ ብሎ ማንቆለጳጰሱ ግን አልዋጥልህ ነው ያለኝ። እኔ ግን ምን ሆኜ ነው? እስከ ዛሬ ያልለኮፍኩት ደሬ ብቻ ነበር። ይኸው ይሄ ዓይኔ ወስዶ ከወዳጄ ከደሬም ጋር አላተመኝ። እንዲያው ምን ይሻለኛል? አሁን ይህን በማለቴ ደሬም ይቀየመኝ ይሆን…? የራስዎት ጉዳይ…😂 ኬሬዳሽ።
"…ወይ የካካ ቤት ከስንቱ ሊያጣላኝ ነው ደግሞ…
"…መጪው በዓል ማለት ፋሲካ የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው አይደል እንዴ? …ረመዳን አልፏል አይደል?
• ሳንሰማ ካላንደሩ ከተቀየረ ብዬ ነው።
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ "…እነ ሀብታሙ ዝም ብለው አልተነኩም። ከብዙ ውጣውረድ፣ ምክክር በኋላ ነው በእኔ በዘመዴ አባ ደፋር በኩል የተነኩት። ከእስክንድር ነጋ ጀርባ የተከማቸው ኤክስፓየር ዴቱ ያለፈው የGGጂጂግግ መንጋ ነው አሁን ግርር ብሎ ወደ መንጫጫቱ የገባው። ለእነሱ ደግሞ እኔ ዘመዴ የብዙ ዓመት ልምድ ስላለኝ እንዴት አባታቸው አድርጌ ጆሮአቸውን እየጠመዘዝኩ ልክ እንደማገባቸው ዐውቅበታለሁ። ሀብታሙም፣ እስክንድርም፣ ኢትዮ 360ም ሥነ ሥርዓት ይይዛሉ። እስክንድርም ሸዋም ሆነ ወሎ፣ ጎጃምም ተቀምጦ ከእንግዲህ ወዲህ መሬት ላይ በሌለ ፋኖ እና ሠራዊት አይነግድም። አይነግድም ብቻ ሳይሆን መግለጫም አያወጣም። በእነ መከታው ፋኖዎች እየተጠበቀ እነ መከታው ጋር ሆኖ፣ በእነ ዘመነ ፋኖዎች እየተጠበቀ እነ ዘመነ ጋር ሆኖ፣ ወሎም ሆኖ ሠራዊቱ ግምባሩ እያለ የፋኖ ገቢ ብቻውን አይሻማም፣ መግለጫም አያወጣም። ፔሬድ።
"…የዐማራ ፋኖ ባለቤት አለው። የዐማራ ፋኖ ውክልና የሰጠው አካል ብቻ ገንዘብ ይሰበስባል። ከዚያ ውጪ ኡበርህን ሥራ ምድረ ሰገጥ። ከአቢይ አሕመድ ጋር አንሶላ ስትጋፈፍ የከረምክ ፀረ ዐማራ ጋለሞታ ሆላ ሁላ አሁን መጥተህ ዐማራ ዐማራ ልጫወት አትበል አንት ቀፋይ ሁላ። ምድረ ግም ቦቴ ሁላ ሀብታሙ አያሌውን መናጆ፣ እስክንድር ነጋን የመብረቅ መከላከያ አድርገህ ብትቀርብም አልፋታህም። ሠርተህ ብላ አልኩህ። ኢትዮ 360፣ መረጃ ቲቪ፣ ኢትዮ 251 በለው አበበ በለው የሚዲያ ሥራ፣ የአስተራቂነት ሥራ እንጂ መሥራት ያለባችሁ የራሳችሁን ፋኖ እያደራጃችሁ፣ ማኒፌስቶ እያዘጋጀችሁ። የዐማራን መከራ በማራዘም ኑሮአችሁን በዶላር ቅፈላ የምትመሩ በመረጃና በማስረጃ ልክ ትገባላችሁ። ምድረ ቀፋይ፣ ከፋፋይ ሰው መሳይ በሸንጎ አጋንንታም ሁላ በመረጃና በማስረጃ በአደባባይ ትጋለጣላችሁ። እኔ አሁን እያደረግኩ ያለሁት ዋናውን ምግብ ከማቅረቤ በፊት አፒታይዘሩን ነው እያስኮመኮምኳችሁ ያለሁት።
"…የኦነግ ፔጆች ጮቤ እየረገጡ ነው። እነ GGጂጂግግ ሲንበጫበጩብኝ አይተው "ዐማሮቹ እየወረዱበት ነው" ብለው የሌለ ለጥፈውኝ እየተንበጫበጩ ነው። ምድረ GGጂጂግግ ስለተንጫጫ እኔ የሆነ የበሬው ቆ*ጥ የሚወድቅላቸው መስሎአቸው ለሀጫቸውን እያዝረበረቡ ነው። እኔ ዘመዴ መስሚያዬ ጥጥ ነው። ከልምዴ አንጻር እያሸነፍኳቸው ነው። 💪✊ በመጨረሻም የርዕሰ አንቀጼ መዝጊያ የሚሆነው "ቤቴ ሕግ አለው። ሥነ ሥርዓትም አለው። የቤቴን ሕግ አክብረህ፣ በሥነ ሥርዓት መመሪያዎችን አክብረህ ኑር ነው" አንዳንዶች በቤቴ መጥተው "አንተን የማላይበት ወዴት ልሂድ? ብሎክ ላደርግህ ነው? ወዘተረፈ የሚሉና ለቀልድ ብለው የሚጽፉትንም ጊዜ አልሰጥም። በፔጄ ውስጥ ቆይተው በልብ ድካም፣ በደም ግፊት፣ በደም ማነስ፣ በስኳር ክልትው ከሚሉ ወዲያው ነው የምቀስፋቸው። ሽማግሌ ልከው ኧረ ለቀልድነው ቢሉም አልምራቸውም። አልመልሳቸውም። እናም አስተያየት ያለወሰጠ ወላጅ ያመጣል እስካላልኩ ድረስ መሳቂያ መሳለቂያም ከመሆን በፊት ጮጋ በሉ። እኔን ብቻ ሳይሆን የቤቴን ደንበኞች፣ በውስጥም፣ በውጪም የሚሳደብ፣ የሚያስፈራራ ካለም እቀስፋለሁ።
• ድል ለዘመዴ ለአባ ደፋር…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…የሁሉም ሰው ቤት የራሱ መመሪያ አለው። በሰዓት አጠቃቀም፣ በድምፅ ብክለት፣ በአለባበስ፣ በንግግር፣ ወዘተ በብዙ ነገር የራሱ መመሪያ አለው። የሁሉም ሰው ቤት የራሱ የሆነ ሥነ ሥርዓትም አለው። በዚህ መሠረት የእኔም ቤት እንደዚያው ነው። ሥነ ሥርዓት።
"…አንዳንድ ቤቶች የምግብ ሰዓት አላቸው። የምግብ ሰዓት ካለፈ ትሪ ይሰቀላል። ጭካኔ፣ ስግብግብነትም አይደለም። የቤቱ ሕግ ነው። በተቃራኒው ደግሞ በፈለገ ሰዓት መጥቶ መሶብ ደፍቶ፣ ድስት ገልብጦ አደፋፍቶ እንዳሻው የሆነም ቤት አለ። የሥነ ሥርዓት ጉዳይ ነው። መሶብ መክፈት ነውር የሆነበት፣ ወላጅ መጥቶ ምግብ እስኪሰጠው በራብ ራሱን እየቀጣ የሚቆይም አለ። ይሄም ራሱን የቻለ ራስን የመግዛት ዲሲፕሊን ነው። ዐዋቂ ሲናገር ዝም ብሎ የሚደመጥበት ቤት አለ። እንግዳ ሲመጣ ወደ ጓዳ የሚገባበት ቤትም አለ። ከእንግዳ ጋር አፍ ተካፍቶ የቤተሰብ አንገትም፣ ቅስምም፣ ጅስምም የሚያሰብርም አለ። ሥነ ሥርዓት ወሳኝ ነው።
"…እኔ ከዘመነ ፌስ ቡክ ጊዜ ጀምሮ የሚገረመኝን ነገር ልንገራችሁ። መንደር እገነባለሁ። በገነባሁት መንደር ውስጥ የሓሳብ መሸጫ ኪዮስክ እከፍታለሁ። አዳራሽ ነገር በሉት ኪዮስኩን። የመንደሬ በር ስተኛ እና ርዕሰ አንቀጽ ስጽፍ ብቻ ነው የሚዘጋው። ስተኛ ሌባ እንዳይገባ እና እንዳይበጠብጠን። ርዕሰ አንቀጹም ሰው ተረጋግቶ አንብቦ በርዕሰ አንቀጹ መሠረት እንዲወያይ የጥሞና፣ የማሰቢያ ጊዜ ለመስጠት ብዬ ነው። በዚህ መሠረት አንባቢ ደንበኞቼ አንብበው ሲጨርሱ ባነሣሁት የመወያያ ርዕስ ላይ የራሳቸውን አስተያየት ሥነ ሥርዓታቸውን ጠብቀው በጨዋ ደንብ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። አንባቢም የተሰጠውን አስተያየት አንብቦ ይረካል። ይሄ እንዲለመድ አድርጌአለሁ። በዚህም እኮራለሁ።
"…ይሄ የእኔ ግዛት ነው። ይሄ የእኔ መንደር ነው። በግዛቴ በመንደሬ አለቃው እኔ ነኝ። በግዛቴ በመንደሬ ራሱን የቻለ አንድ ግዙፍ ማኅበረሰብ በጓደኝነት፣ በቤተሰብነት አግኝቼበታለሁ። እኔ በመንደሬ ልማዴን፣ ፍላጎቴን በግልፅ አሳውቄአለሁ። ከጠዋት እስከማታ ምሽት ድረስ በመንደሬ ውስጥ የሚከናወኑት ኩነቶች የሚታወቁ ናቸው። ጠዋት በምስጋና ይጀመራል። ከምስጋና በመቀጠል ርዕሰ አንቀጽ ከመጻፉ በፊት ዝግጁ ናችሁ? ተብሎ የመንደሩ ኗሪ ይጠየቃል። ከጥያቄው በኋላ ርዕሰ አንቀጽ ይከተላል። ርዕሰ አንቀቅ ከተለጠፈ በኋላ በር ይዘጋል። የመንደሩ ኗሪ አንብቦ ጨርሷል ተብሎ ሲገመት የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁ ክፍት ይሆናል። አስተያየትም መስጠት ይጀመራል።
"…እዚህ ላይ ነው ሽግር የሚመጣው። ያልተጻፈ የሚያነብቡ ሰዎች ተለቃቅመው ይመጡና የውይይት አቅጣጫውን ለመበጥበጥ ይገባሉ። አንድም ወይ ጽሑፉን አላነበቡትም። ቢያነቡትም አልገባቸውም። ስለዚህ መበጥበጥ ይጀምራሉ። ርዕሰ አንቀጼ ደግሞ የሚያበሳጫቸው የትየለሌ ናቸው። እናም በዕለቱ የሽንቆጣ ብዕሬ ያረፈበት አካል ወባ እንደያዘው ሰው መንዘርዘር ይጀምራል። እኔም ሁሉም ሰው እያየ ምሱን እሰጠዋለሁ። ቤቴ ለተቃወሚዎች ሓሳብ ክፍት ነው። ራሴን በተመለከተ ለሚነሡ ጥያቄዎችም ምላሽ ለመስጠት አልቦዝንም። በሚያስቀው እየፈገግን፣ በሚያላግጠው እያላገጥኩ እንወያያለን። መቀሰፉ የሚመጣው "እናትን በተመለከተ፣ ፀያፍ ስድብ፣ ሃይማኖቴን በተመለከተ ነውረኛ ስድብ፣ አስተያየት የሰጡ እንግዶችን በግል በአደባባይ የነውር ቃላት ሰድቦ ማሸማቀቅ የሚሞክረውን ወገብ ዛላውን ከንጥሼ በወሬ ጠኔ እንዲማቅቅ እስወግደዋለሁ።
"…ቤቱ ከእነ ሞጣ ቤት የተለየ ነው። ብሪጅስቶን የለችበትም። ዮኒ ማኛ ቤትም አይደለም። ትንሽ ደረጃው ከፍ ያለ ቤት ነው። እናም እዚህ ቤት ጫት እየቃሙ ባያነቡ ይመረጣል። ካነበቡም ደግሞ በምርቃና አስተያየት መስጠት ያስቀስፋል። ሀሺሽ እየሳቡ፣ አምቡላ አረቄ እየጋፉ በሰከረ፣ በደነዘዘ አእምሮ በደባል ወኔ፣ በአርቴፊሻል የድራግ እና የመጠጥ ድፍረት ወደ ፔጄ መግባት ለፀፀት ይዳርጋል። ምክንያቱም 400 ሺ ሰው ዘጭ ብሎ በተቀመጠበት ቤት ጂጂ ኪያን ሆኜ እገለጻለሁ ማለት ካካ ነው። እፉ ነው። አንዳንድ ሰው አንተ ማን ስለሆንክ ነው እንደፈለግን የማንሆነው ብሎ ጓ የሚል አለ። ወዲያው ነው ማንነቴን ቀስፌ በማሰያት ትንፋሽ አሳጥሬ የማሳየው። የእኔ ትምህርት የተግባር ነው።
"…ጠርቼው፣ በቀበሌ፣ በወታደር፣ በደንብ ማስከበር አስገድጄ ወደ ቤቴ ያመጣሁት አንድም ሰውየለም። ሁሉም ሰው የሚመጣው ፍላጎቱን ለማሟላት ነው። ጠዋት ጠዋት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አንብቦ እግዚአብሔር ይመስገን የሚል ሱስ ይዞት በነጋለት ቁጥር ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ በቀጥታ ወደ ፔጄ ገብቶ የሚሻውን ምስጋናና የምስጋና ቃል አስፍሮ ውልቅ የሚል አለ። ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ የሚመጣ አለ። አዳዲስ መረጃ ለማየት የሚመጣ አለ። ሁሉም የሚመጣው የራሱን የሚፈልገውን ነገር ለማየት ነው። የአገዛዙ ሰዎችም፣ የአገዛዙ ተቃዋሚዎችም ወደ መንደሬ ይመጣሉ። የሚፈልጉትን መጥጠው ይሄዳሉ። ኮመንት በማንበብ ፈታ፣ ዘና ለማለት የሚመጡም አሉ? እርስዎ ከየትኛው ወገን ነዎት?
"…የእኔ ፀቤ በሚመጣው ሰው ማንነት ላይ አይደለም። የእኔ ፀብ የሚመጣው ሰዎች ከመጣ በኋላ ስምህ ማነው ሲባል አጎቴ እገሌ ነው? እድሜህ ስንትነው? ለሚል ጥያቄ የተወለድኩት ሙከጡሪ ነው ከሚል አራምባና ቆቦ ሰው ጋር ነው። በፍጹም የቤቴን ሥርዓት ከማያከብር ደነዝ ጋር አፍ አልካፈትም። የእኔ ቤት ነፃ ቤት ነው። የውይይት፣ የምክክር ቤት ነው። በጨዋ ደንብ መቃወም ሁላ ይቻላል። ለዚሁም የኮመንት ሳጥኑን ዞር ዞር ብሎ መጎብኘት ነው። ከዚህ ከዘለለ መሬት ሳይደርስ በአየር ላይ እቀጨዋለሁ። ለኘንደሬ ኗሪዎች አይን ስል ቆሻሻውን ሓሳብ በሙሉ አፀዳዋለሁ። እኔ ባላየው እንኳ " ዘመዴ BLOCK " በማለት ራሱ የመንደሩ ኗሪ ጥቆማ ሰጥቶ ይጠብቀኛል። እኔ እንደመጣሁ በቀይ ካርድ አሰናብተዋለሁ።
"…የእኔ ፔጅ እንደ ገነት ያለ ፔጅ ነው። አንዴ ከገቡበት የማይወጡበት። ከወጡ ደግሞ በራሴ ስህተት የተቀሰፉ ካልሆነ በቀር ተመልሰው የማይገቡበት ፔጅ ነው። ለእኔ ይሄ ፔጅ መዝናኛዬ ነው። መሥሪያ ቤቴ ነው። መቅደሴም ነው። መዋያዬም ነው። እና ቤቴን አክብሬ መስከበር ውዴታ ሳይሆን ግዴታዬ ነው። የግዱን ስንቱ እየተቁነጠነጠ፣ ስድብ እያማረው፣ አፉንም እጁንም እየበላው፣ እያሳከከው ብሎክን ስለሚፈራት ጭሶ፣ ጭሶ የሚቀመጥ አለ መሰላችሁ? እኔ ፔጅ ላይ ከተሳደበ ስለምቀስፈው በየ ፔጁ እየዞረ ስድብ ተሸክሞ በመለጠፍ ራሱን በራሱ የሚያረካ ሰው አለ መሰላችሁ። ለምሳሌ ለስድብ ብቻ ለሌሎች ተቀጥሮ የሚሠራም ምስኪን ሰው አለ። በፊት ኬንያ የሚኖር፣ አሁን ወደ አሜሪካ እንወስድሃለን ብለው ኡጋንዳ የወሰዱት ወንደሰን የሚባል ያለ አልኮል፣ ያለ ጫት የማይንቀሳቀስ ሰው አለ። ጋሻ የሚባል ሚድያ ከፍቶ በአፉ ሲጸዳዳብኝ ነው የሚውለው። ዶር አምሳሉ ነው የሚጋልበው። በፔጄ ላይ እስካልሆነ ድረስ ግን ለደንታው ነው። ሽመልስ፣ ሀብታሙ በሻህ፣ ሚኪ ሚዲያ ወዘተ ለደንታቸው ነው በፔጃቸው። በመንደሬ ውስጥ ግን ክልክል ኖ… 👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ ዓመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም… የስቅለት ዐርብ ይባላል።
• ምሽት ፫ ሰዓት ተላልፎ ተሰጠ ማቴ 26፥47፣ ዮሐ 18፥3
• ሌሊት ፮ ሰዓት ሲሆን አሰሩት ዮሐ18፥12
• ጠዋት ነግህ በጲላጦስ ፊት አቆሙት ማቴ 22፥1
• ዐርብ ጠዋት ፫ ሰዓት ጲላጦስ ፊት አቅርበው ገረፉት። ማቴ 27፥ 27-31፣ ማር 15፥16-20 ዮሐ፥19፥1
• ቀትር ፮ ሰዓት፥ እጅ እና እግሩን ቸንክረው ሰቀሉት ዮሐ 19፥ 14-18 ኢሳ 53፥ 1-12
• ፱ ሰዓት፦ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በገዛ ሥልጣኑን የለየበት ማቴ 27፥50፣ ማር 15፥37፣ ዮሐ 19፥30
• ፲፩ ሰዓት፦ ከመስቀል ወደ መቃብር የወረደበት ማቴ 27፥60
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ይሄም ልክ አይደለም…!
"…በዐማራ ስም በየ አህጉራቱ እየዞሩ የደሀውን፣ የምስኪኑን ዐማራ ገንዘብ መቀፈል ልክ አይደለም። መሬት ላይ ያለው ዐማራ፣ የዐማራ ፋኖ ዱዲ፣ ጢና፣ አምስት ሳንቲም ሳይደርሰው አጭቤ ሁላ በዐማራ ስም ከዳያስጶራው ገንዘብ መሰብሰብ የለበትም።
"…ጎጃሞች ወክልና የሰጡት አካል ብር እየሰበሰበ ነው። ሸዋዎች ወደ አንድ እስኪመጡ ድረስ ሁለቱም የወከሏቸው ሰዎች ሰብስበዋል። ጎንደሮችም ወደ አንድ ሲመጡ ይወክላሉ። ወሎዎች አንድ ሳይሆኑ በፊት ሁለት አካላት ወክለው ነበር። ባለፈው ሳምንት እነ ምሬ የወከሉት ቡድን ጥቂት ሰብስቧል። በሸዋ በሁለቱም፣ በወሎ በምሬ ተጠርቼ ተጋብዤ አገልግያለሁ። ኮሎኔል ሙሀባው የፊታችን ቅዳሜ ደግሞ ቀድሞ በተያዘ መርሀ ግብር አለ እሱ ተገኝልን ብለዋል እገኝላቸዋለሁ። እናንተም ተገኙላቸው።
"…ከዚያ ውጪ የግንባሩ ቻብተር የሚባለው ሁሉ መፍረስ አለበት። በዐማራ ጉዳይ ዐማሮቹ ውክልና ያልሰጡት አካል ገንዘብ በፋኖ ስም መሰብሰብ የለበትም። በዐማራ ስም ቴስላ ማሽከርከር፣ የሚልየን ዶላር የተከፈለ ቪላ መሸመት ሊያበቃ ይገባል።
"…ሀብታሙ 7500 ዶላር ደሞዝተኛ ነው። ዶክተሮችም አይከፈላቸው። ሽመልስም ከ3 ሺ ዶላር በላይ 360 ይከፍለዋል። ፔሮላቸው በእጄ ነው ያለው። ለዐማራ ነው የምታገለው ብሎ በዐማራ ስም ከፕሮፌሰር በላይ ደሞዝተኛ ከሂንክ ያንን ይዘህ እንደማመስገን የምን መንበጫበጭ ነው?
• ይህን በማለቴ የሚከፋ ካለ በአናቱ ይተከል። 😂
መልካም…
"…ከእኔና ከሀብትሽ አንዳንድ የኦሮሚኛ ሙዚቃ በኋላ ቅጥቀጣውን እንቀጥላለን።
• አሁን ያበጠው ጫጫታም ሁሉ እየተነፈሰ ነው። ማንም የዐማራን ትግል አይጠልፈውም። መሬት ላይ ባሉት ዐማሮች ፈቃድ ውጪ የማንም ፀረ ዐማራ ግንቦቴያም ሁላ የዐማራን ትግል መጥለፍ አይችልም።
• እኔም አልበላ ሌባም ሰውም አላስበላ…😂😂
• ከኦሮሚኛው ሙዚቃ በኋላ እንመለሳለን። ከዚያ እነ GGጂጂግግ ስታሸንፉኝ አብረን እናየለን።
• ሌባ ሁላ… በዘመዴ… ያዲኒ ኮ በፋኖ ሀብትሽ አያሌው። እየተሞዘቃችሁ…
• ከአንድ 100 ያህል አድናቂዎቻችን አስተያየት በኋላ እመለሳለሁ።
ግንቦቴው ይቀጥላል…!
1ኛ፦ በፋኖ እስክንድር
2ኛ፦ በፋኖ ሻለቃ ዳዊት
3ኛ፦ በፋኖ ሀብታሙ አያሌው
4ኛ፦ በፋኖ ኢትዮ 360… አንደራደርም ይልልሃል የቮድካ አርበኛው አቶ ክንፉ ወዳጄ ? ፉንፉናም ሁላ። እኔን ፋኖ ያድርገኝ። ወግ ወጉማ ተይዟል እኮ።
"…አሁን ሻለቃ ዳዊት አላስበላም ስላሉ ተገፍትረው ተባርረዋል። አበበ በለው አቧሯቸዋል። የቀሩት ፋኖዎች ግን እንዳሉ አሉ።
"…በዐማራ ፋኖ ስም መለመን ካካ ነው። አይቻልም። መሬት ላይ በሌላ ሠራዊት ስም የዐማራን ኪስ ማራቆት ነውር ነው። በጣም ነውር ነው።
"…ግንቦት ሰባት በሀብታሙ አያሌው በኩል 360 ሚድያን ልክ እንደ ኢሳት አድርጎ ለጠቀምበት ነው የሚፈልገው። ይሄን ደግሞ እኔ አስቀድሜ ባንኛለሁ። ዐማራ ድጋሚ በግንቦቴዎች አይጠለፍም።
"…ለዐማራ ፋኖ የሚሰበሰብ ገንዘብ በሙሉ በዐማራ ፋኖ መሪዎች የተረጋገጠ፣ የታዘዘ መሆን አለበት። ተቆጣጣሪ፣ ታዛቢ እንደሌለው ሰው የዐማራን ኪስ በዐማራ ፋኖ ስም ማራቆት ትክክል አይደለም። በፋኖዎች ፎቶ እየለመኑ ገንዘቡን ለፋኖዎች ካልሰጡ፣ በገንዘቡ ፋኖዎችን ከከፋፈሉበት ለምን ዝም እላለሁ። ብቻዬን አስቆማችኋለሁ አልኳችሁ።
"…እነ GGጂጂግግ ዎች ተንጫጩ። በደንብ ተንጫጩ። እስኪወጣላችሁ ተንጫጩ። እኔ ተናግሮ አናጋሪ የሰጠኝን አምላኬን እያመሰገንኩ መደብደብ ነው ምድረ አጭቤ፣ አሽቄውን ሁላ።
• በነገራችን ላይ ገና ወደ ዋነኛው አስኳል ጉዳይ አልገባሁም። ይሄ ለአቅርቦተ ሰይጣን የሚተኮስ የብዕር መድፍ ነው።
"…በመጀመሪያ አቶ ክንፉ የእነ እስክንድር ነጋው ሕዝባዊ ሠራዊት ደጋፊ ነው። አቶ ክንፉ በሀገረ አማሪካ በ Buffalo, NY ከተማ የሚኖር ቤተሰቡን እንኳ በሥርዓቱ መምራት የማይችል ቅቅል እየበላ ቮድካ ሲገሽር የሚውል አረቄያም ነው።
"…የራሺያ ተማሪ የሆነው አቶ ክንፉ መጀመሪያ ግንቦት ሰባት ሆኖ ዐማራን ሲያደማ የኖረ። በመቀጠል ባልደራስ፣ ከዚያ በቅርብ ደግሞ የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር ሆኖ ከቆየ በኋላ ግንባሩ ሲፈርስ ወዲያው በአርቲስት ጋዜጠኛ አበበ በለው እና ሀብታሙ አያሌው አማካኝነት በእነ ግንቦቴው ዶር አምሳሉ ሰብሳቢነት ዐማራውን ብር ለመጋጥ እነ እስክንድር ነጋ ዙሪያ የተሰበሰቡ አረቄያአሞች ናቸው።
"…በቅርቡ ሸዋና ጎጃም ውስጥ በፋኖዎች መካከል ለሚደረገው ጦርነት ከእነ ሀብታሙ አያሌው ቀጥሎ ሓላፊነቱን የሚወስዱት እነ አቶ ክንፉና እነ ዶር አምሳሉ ናቸው። እመኑኝ በቅርቡ በጎጃም እና በሸዋ ውስጥ ሕዛቢዊ ሠራዊት ተብዬዎቹ በሕዝብ ገንዘብ እነ ሀብታሙ የገዟቸው እና እውነተኞቹ ፋኖዎች እርስ በእርስ ይመታታሉ።
"…መዝግቡልኝ ተናግሬአለሁ። ትንሽ ቆይቼ ግምቦቴውን መተግተጌን እቀጥላለሁ። ጠብቁኝ።
የሚገደሉም ይኖራሉ እየተባለ ነው።
"…ቅድም ከነገርኳችሁ እና በብልፅግናው የኦሮሙማ አገዛዝ ወደ ዘብጥያ ከተጋዙት ከማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና ዋና ከጸሐፊው መምህር ዋሲሁን በላይ በተጨማሪ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ የሆኖኑቱና በቅርቡ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን እንዲያገለግሉ የተመደቡት ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድም በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ ለጥያቄ ይፈለጋሉ በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለመገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ተሰምቷል።
"…እስራቱን በተመለከተ ምክንያቱ ምን ይሆን? በማለት የጠየቅኋቸው የመረጃ ምንጮቼ "… እስራቱ ከግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጋር ይገናኛል። በቀጣይ የፖትርያርኩ እንደራሴና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የመሰየም ሂደት ይኖራል። አገዛዙ ይኸንን ልክ እንደ ፕሮቴስታንቱ ካውንስል እና እንደ እስልምናው መጅሊስ ያለ ማንም ተቀናቃኝ የሚፈልገውን ለማድረግ ፈልጓል። ለዚህም ሲባል በቀጣይ በታዋቂ መምህራንን ላይ ሳይቀር የእስር ማዘዣ በማውጣት በገፍ የማሰር እቅድ ይዞ እየሠራበት ይገኛል። ምንአልባትም የሚገደሉም ይኖራሉ ብለው የሚሰጉም አሉ።
"…ቤተ ክህነት የመሸገው አድር ባይ ጳጳስና መነኩሴ፣ አስተዳዳሪ ሁሉ "ያስቸገረን ይኸ ማኅበር ነው።" ብለው አቤቱታ ለአገዛዙ በማቅረባቸው አገዛዙም የማኅበሩን ተጽዕኖ ለመቀነሰ ዘመቻውን ከእናቱ ጀምሮታል። በተያያዘ ዜናም የዱባዩ ንጉሥና የሮም ቤተ ክርስቲያን በጥብቅ ይፈልጉታል ተብሎ የሚነገርለትንና የንጉሥ ሰሎምን ቀለበት ይገኝበታል ተብሎ የሚታመነውን የተድባበ ማርያም ገዳምን "ክረምቱ ሳይገባ በፊት ለመዝረፍ ከዛሬ ጀምሮ የወሎ ኦሮሞ ነን ባይ ጽንፈኞች አስከትሎ በከባድ መሣሪያ በመታገዝ ወደ ገዳሙ መቃረቡም ተሰምቷል።
ከርዕሰ አንቀጹ በፊት ሰበር ዜና…!
"…ከፖሊስ አካባቢ ካሉት ወፎቼ በደረሰኝ መረጃ መሠረት (ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማፈራረስ እንቅፋት የሆነውን ማኅበር ማፍረስ) በሚለው የመናፍቃኑና የተሃድሶዎቹ ፉከራ መሠረት በዛሬው ዕለት የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መታሠራቸው ተሰምቷል።
"…ወዳጄ ጸባየኛ ሆንክ አልሆንክ፣ ተገረድክ አልተገረድክ፣ ከብልፄ ሰይፍ የሚያመልጥ ከመታሰር፣ ከመዋረድ የሚቀር አንድም ሰው የለም። አይኖርምም። ባለ ጊዜው ተረኛውና ጽንፈኛው የጴንጤና የአክራሪው የኦሮሞ ወሀቢያ እስላም አገዛዝ የሚምረው አንዳችም ሰው የለም። ወዳጄ ዳንኤል ክብረት እያንዳንዱ የማኅበሩን ሰዎች እና ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚበቀልበት ምቹ ጊዜው አሁን ነው።
በሉ እናንተ ሂዱ የእኛም ወደዚያው ነው
ድሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው
"…ነገርየው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በዓል በመጣ ቁጥር አማኙ በዓሉን በደስታ፣ በፍቅር፣ በሐሴት እንዳያከብር ለማድረግ አጋንንታሙ አገዛዝ ሲጠቀምበት የኖረው አጀንዳ ማስቀየሻ ዘዴው ነው።
"…በርዕሰ አንቀጹ መጣሁ ጠብቁኝ።
"…እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ ዓመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም…
፩፥ የምሥጢር ቀን
"…ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ማቴ 26፥ 26-28
፪፥ ሕጽበተ እግር/
"…ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ዮሐ 13፥ 4-5
፫፥ ምሴተ ሐሙስ/ሐሙስ ምሽት/ጸሎተ ሐሙስ
"…በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ መጣ ደቀ መዛሙርቱንም፦ ወዲያ ሄጄ ስጸልይ ሳለ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። …ወደ ደቀ መዛሙርቱም መጣ፤ ተኝተውም አገኛቸውና ጴጥሮስን፦ እንዲሁም ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳ ልትተጉ አልቻላችሁምን? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው። ማቴ 26፥ 36-41
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
እንመጣለን ነው የሚለው ትግሬው።
"…መከላከያ ሠራዊቱን አቁሞ ነው የሚያጠጣው። ዱርዬ የሚለው ዐማራን ነው የዐማራን ፋኖ። ህጻናት፣ ሴቶች፣ ባንዲራ ይዘን አይደለም የምንመጣው። ይዘን የምንመጣው ምን እንደሆነ በሁሉ ዘንድ ይታወቃል ነው የሚለው። አይደለም ዱርዬው የዐማራ ፋኖ መከላከያ ራሱ ያውቀናል ነው የሚለው።
"…አንዳንድ ምስኪን ዐማሮች በትግሬ ነፃ አውጪ በህወሓት ካድሬዎች ምላስ ሲደነዝዙ አያለሁ። ህወሓት በሕይወት እያለች አበደን ቃለ ለሰማይ ቃል ለምድር ዐማራና ትግሬ አይታረቁም። አይቀራረቡም።
"…ትግሬ ደም የፈሰሰበት ቦታ በበጋ አይዋጋም። ሰይጣኑ ክረምት ጠብቆ ወይ ዝናብ ጠብቆ ነው ለደም ግብር የሚገፋው፣ የሚነዳው። አሁን ክረምቱ መጥቷል። ትግሬም ቀሪ ሕዝቡን፣ ወጣቱን መገበር አለበት። ለዚያ ነው እንዲህ የሚሠራ የሚያደርገውን የሚያሳጣው።
"…በሱዳን ያለው የማይካድራው ጨፍጫፊ አራጅ ሳምሪ ቡድን ወደ ሁመራ፣ ወደ ወልቃይት ይንቀሳቀሳል። በሽሬ በኩልም የሚመጣ አለ። ወልቃይት የሚገባም አለ። መሳሪያ እስከ አፍንጫው ታጥቋል። ስዩም ተሾመ በግልፅ ተናግሯል። ቀለብም እንደጉድ በርዳታ መልክ ገብቷል። በጀትም በቢልዮን የሚቆጠር ብር ለህወሓት ከኦሮሙማው ተለግሷል። የሚቀረው በሰሜን ጎንደር፣ በወልቃይትና በሰሜን ወሎ ከዐማራ ጋር መፈሳፈስ ነው።
"…አሁንም ሌላ ዙር ሺ ቆማጣ፣ ሚልዮን አስከሬን፣ ውድመት፣ እሪታ፣ ኡኡታ፣ ቁቁታ ተዘጋጅቷል። አቢይ አሕመድ አያስጥልህም። የማትኖርበት ቤት አታምሽ። የትግሬንም የዐማራንም የመከራ ዘመን በኦሮሙማው ሴራ አታርዝም።
"…ዐማራ ዱርዬ የተባልከው ፋኖ አትራራ፣ እንደ እስራኤል ፍፁም አረመኔ ጨካኝ ቆራጥ መሆን ነው የሚጠበቅብህ። ዐማራና ትግሬ አንድ ሕዝብ ነው የሚለውን የሂዊ ሰበካ ለጊዜው ኢግኖር ግጨው።
• ሲያበሽቁ እኮ በማርያም…
"…በሉ ጉማ ሰቀታን ጥሩልኝ። እኔምለው ይሄ ግማሽ ጉራጌ፣ በእግሩ በሜክሲኮ በኩል አማሪካ የገባው የመርካቶ ልጅ፣ አሁን የኦሮሞ ነፃ አውጪ የሆነው ዳንኤል ዳባ በለፀገ እንዴ? ጉማዬ ጉማ የድሬው ልጅ አፍቃሬ ወያነው፣ ፀረ ዐማራው ጉማ ና ይህን መልስልኝ። ዳኒ በልጽጓል ወይ…?
• ዶካር ደግሞ ምንድነው? 😂
"…ሐረርጌ ተርቦ ስለ ካካቤት መጨነቅ ምን የሚሉት ነው? እነ ጃዋርስ የት ጠፉ…? ኧረ ተንቀሳቀሱ። የካካ ቤቱ እህል ሲገኝ ይደርሳል።
"…ቄሮ ሁላ ተበላሽቶ የለም እንዴ? ከናሁሰናይ አዲስ አበባ መከሰት በኋላ ኦሮሙማ ምን ነክቶት ነው ሽንት ቤት ካላሠራችሁልኝ ብሎ ሙጭጭ ያለው? መንገድ ዳር ያለ የህንጻ ባለቤት ሁሉ ሽንት ቤት ካላሠራ ፎቁን ነው የማፈርሰው የሚል መመሪያም አርቅቀው ጨርሰዋል አሉ። ኧረ መጀመሪያ ለተራቡት ድረሱ።
ጥያቄ ነው።
"…ትግሬ ቢርበውም ራያና ወልቃይትን ከሰጣችሁኝ ራቡን እንደምንም እችለዋለሁ ብሏል አሉ። ዐማራ ቢርበውም አቻዮ ብረት ስለሆነ ራቡን እየተጋፈጠ እየተዋጋም ይገኛል። ሐረርጌ ግን ራቡ ስለጠናበት ፈንቅሎ ወጥቶ ወደ ሀረር ከተማና እና አዲስ አበባ ድረስ መጥቶ ሜዳ ላይ ፈስሷል። ይሄ ሁሉ ሆኖ ሳለ ግን ግራ የሚያጋባ ነገር እየታዘብኩ ነው።
"…ለራባቸው ዜጎች ምግብ ለምኖ መስጠት፣ ራባቸውን ማስታገስ፣ እርዳታ ማሰባሰብ ነው ወይስ መናፈሻና ሽንት ቤት ልሠራልህ ነውና አዳሜና ሔዋኔ ለሽንት ቤት ማሠሪያ የሚሆን ገንዘብ በዶላር እና በብር አዋጡልኝ ማለት? አልገብቶኝም።
"…እሺ እናንተ አቶ አቢይም፣ ወሮ አዳነችም ሆናችሁ ኦቦ ሽመልስ እውነት ነው ያለ ሃሳብ፣ ያለ ችግር ትበላላችሁ። እድሜ ለኦሮሞ ሕዝብ የእናንተን ብቻ ሳይሆን የዘር ማንዘራችሁን ችግር አቃላችኋል። ያለ ሰቀቀን ስለምትበሉም ሽንት ቤት የግድ ያስፈልጋችኋል። የተራበው ሕዝብ ግን ያልበላውን ካካ ለማድረግስ ከየት ያመጣዋል? ሰው ሲበላ እኮ ነው ካካ የሚያደርገው? ፈጣሪ ግን ምን ብንበድለው ነው እነዚህ ጉዶች የጣለን። የፈጣሪ ያለህ…!
"…ደግሞ እኮ በዶላር ሁላ ነው የሚለምኑት። ካካው ከየት ይመጣል ነው የምልህ?
መልካም… አሁን ደግሞ በርዕሰ አንቀጹ መሠረት በተለይ የኦሮሞ ነጻ አውጪ አፈቀላጤዎች በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን ስጡ።
• ማሳሰቢያ፦ ሓሳብ እንጂ ዱላ ይዘህ መጥተህ ሜንጫህን እያወዛወዝክ ማለባሺ ምናምን ብትል አልሰማህም። ውይይት ልመድ። የእኔ ሥራ የሚያበሳጭም ይሁን የሚያስደስት፣ የሚያስለቅስም የሁን የሚያስቅ ሓሳብ አቀርባለሁ በዙያ ላይ ተረጋግተህ አንተ ትመልሳለህ ማለት ነው።
"…እነ GGጂጂገግ እናንተ ደግሞ አረፍ በሉና ወደ በኋላ አጀንዳ ሰጥቼ ትንሽ አንዘረዝራችኋለሁ። ለአሁኑ አረፍ በሉ። ትእዛዜን ጥሰህ ዱላና ሜንጫ ይዘህ የምትመጣ ወነግም ሆነ "ከእስክንድርና ከሀብታሙ ራስ ውረድ የምትል GGጂጂገግ እቀነድብህሃለሁ። እቀስፍሃለሁ። ሰምተሃል።
• ዳይ ወደ ውይይቱ። የፋኖን ሴራ አከሸፍኩ የሚለው የኦሮሞ መንግሥት የአቶ በቴን የግፍ ገዳዮች ከምን አደረሳቸው? ወይስ ገዳዩ ራሱ ነው?