"ርዕሰ አንቀጽ"
"…የከሸፈው ሴራ የተሰኘውና በሁሉም መንግሥታዊና ክልላዊ መንግሥታት መገናኛ ብዙሃን የቀረበው ዘጋቢ ፊልም የከሸፈው ወዲያው ነበር። ፒፕሉ ኢግኖር ገጭቶት ነው ኩም ያደረገው። የኦሮሙማው ሓሳብና ምኞት የነበረው ሀገሪቷ ጠንካራ የሆነ የስለላና የደኅንነት ተቋማት እንዳሏት በማሳየት እና ሕዝቡንም "ምንም ብትሠሩ አይደለም በልባችሁ ብታስቡ እንኳን "በየሱስ ስም፣ በጌታቸው ስም" ብዬ እይዛችኋለሁ አታመልጡኝምም፣ አሳድጄ እይዛችኋለሁ፣ በቁጥጥር ስርም አውላችኋለሁ የሚል መልእክት ነበር ማስተላለፍ የፈለገው። ነገር ግን ያሰበው ሳይሆን በሌላ በኩል ዘጋቢ ፊልሙ ሌላ ጣጣ ነው ያመጣበት።
"…አጥፍቼዋለሁ ያለው ፋኖ፣ ደምስሼዋለሁ ያለው ፋኖ፣ አቅሙ ደካማ ነው። በእጁም ያለው ቆመህ ጠብቀኝ የድሮ መሳሪያ ብቻ ነው ብሎ የሚያናንቀውና መግለጫም፣ ዜናም ሲሠራበት የከረመው የዐማራ ፋኖ መሀል አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ ገብቶም ተቀጣጣይ ፈንጂ፣ ቦንቦች፣ ክላሽን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ይዞ በ3 ፋኖ ግማሽ ቀን መንገድ አዘግቶ ሲታኮስ መዋሉና መገኘቱን በሃላል ማወጁ መጥፎ መልእክት ነበር ያስተላለፈበት። የመንግሥትን መግለጫ እያመኑ አገዛዙን እንደ ቁምነገረኛ መንግሥት የሚቆጥሩት የዓለም መንግሥታት በሙሉ አገዛዙ እየዋሻቸው እንደሆነና የፋኖ ኃይላት ከሚጠበቀውም ከሚገመተውም በላይ የተደራጁ መሆናቸውን እንዲያምኑ ነው ያስገደዳቸው። ተገደዱ። ኪሣራ…
"…አራዶቹ ምዕራባውያንም ሁል ጊዜ እንደሚያደርጉት ጊዜ ሳያጠፉ ነው በዐማራ ጉዳይ ለቃለ መጠይቅ ሰው በፈለጉ ጊዜ በቅርብ ወደሚያገኟቸው ትሪፕል AAA የእነ ቴዎድሮስ ትርፌ ዘንድ የደወሉት። እባካችሁ የፋኖ መሪዎችንም እንዴት እናግኛቸው? በማለት ጥያቄ ያቀረቡላቸው። እነ ቴዎድሮስ ትርፌም ወደ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ በመደወል የፋኖ መሪዎችን አነጋገሯቸው። ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀው የጋዜጠኞቹ ቃለመጠይቅ ውስጥ ዋነኛው ነጮቹ የፈለጉት ሁለት ጥያቄ ብቻ ነው። አንደኛው አዲስ አበባ የተደረገው ሙከራ ላይ እጃችሁ አለበት ወይ የሚል አንደኛው ሲሆን ለዚህም ፋኖዎቹ አዎ እኛ ነን፣ ገና ከዚህ የባሰ ተግባር እንፈጽማለን። ይኼኛው ቅምሻ ነው በማለት የመለሱላቸው ሲሆን ድርድርን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄም "አረመኔ ጨፍጫፊ አቢይ አሕመድን ለፍርድ ሳናቀርብ፣ 4 ኪሎም ሳንገባ ድርድር የለም።" በማለት ነበር እቅጩን የነገሯቸው። ምዕራባውያኑም ይህቺን ነበር የፈለጉት ቁርጣቸውን ዐውቀው ጮጋ ብለው ወደ ራሳቸው ውሳኔ ነው የሄዱት።
"…የአሜሪካን እንጃላቷ እንጂ እነ እንግሊዝ፣ ካናዳ ወዘተ ወዲያውኑ ነው ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያዘገዩ መግለጫ ያወጡት። ይሄ ማለት በራሳቸውም የደረሱበት ጉዳይ አለ ማለት ነው። አዲስ አበባ የገባ ኃይል አለ ብለው ያምናሉ። ዛሬ እንኳ አዲስ አበባ ውስጥ የተገደለው የፀጥታ ሓላፊ አገዛዙን አስደንግጦታል። መረጃውንም እስከአሁን ድረስ አገዛዙ ይፋ አላወጣውም። ሰሞኑንም የሆነ ነገር ይከሰታል ብለው እየተሸበሩ ነው። እናም የከሸፈው ሴራ በተለቭዥን ዘጋቢ ፊልም ብቻ ነው እንጂ መሬት ላይ የሚገርም ሆኗል።
"…ወደ ጥያቄው እንገባለን…?
"…የዐማራ ፋኖን ሴራ ለማክሸፍ ኦሮሙማው ተአምር መሥራቱን ሲበጠረቅ ቆሞ ሲያጨበጭብ የነበረው ኦሮሞው መሆኑን ስታይ ግን በሳቅ ነው የምትፈርሰው። እነ ጉማ ሰቀታ፣ እነ ዳኒ ዳባ፣ ወዘተረፈ የፋኖ ሴራ ከሸፈ እያሉ ከብልፅግና በላይ ላንቃቸው እስኪሰነጠቅ ድረስ ሲጮሁ እያየሁ እነዚህ ሰዎች ምን ዓይነት ክትባት ነው የዘለላቸው ይሆን በማለት ወደ መጠየቅ ነው የሄድኩት።
"…ይሄ ያደነቃችሁት እና የዐማራን ፋኖ ሴራ አከሸፈ ብላችሁ ያንጨበጨባችሁለት የኦሮሙማ ብልጽግና የስለላ ተቋም፣ የደኅንነት መሥሪያ ቤት፣ የፖሊስም ኃይል "6 ፖሊሶች ሆነው ከሌሊቱ 6 ሰዓት፣ ከሆቴሉ አውጥተው፣ በገዛ ቀበቶው የፊጥኝ አስረው በ6 ጥይት በሳስተው፣ በገዛ ሀገሩ በመቂ ከተማ ቆሻሻ መጣያ ስፍራ ወስደው የጣሉት አቶ በኬ ኡርጌሳን የገደሉት እስከአሁን እንዴት አልተያዙም። ወደ ኋላ ሄጄ ሃጫሉ ሁንዴሳን መኪናው ውስጥ አፍኖ ገድሎ ጎኑን በጥይት ያፈረሰው አካል ምነው እስከዛሬ የያዘው ሰው የለም? አይ ኦሮሞ አለ አቢይ አሕመድ። ኦሮሞ አንተ ዐማራ ላይ እንዳፈጠጥክ ኦህዴዶች የአንተን ልጆች ቀንድሸው፣ ቀንድሸው ሊጨርሱልህ ነው።
• ሌሊት 6 ሰዓት፣ 6 ፖሊሶች፣ በ6 ጥይት (666) በኦሮሚያ መሬት ላይ ኦሮሞውን ሰው በግፍ የገደሉት ወንጀለኞች ጉዳይ ከምን ደረሰ? ያ በሓሳብህ ጭምር ስለምታስበው ቀድሞ ነቅቶ የሚያከሽፈው፣ ወንጀለኞችን የገቡበት ገብቶ መንጥቆ የሚያወጣው ፀረ ሽብር ኃይሉ ምነው የቡቴ ሲሆን ወገቤን አለ? ለማለት ነው?
• አስመሰግናለሁ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
መልካም… ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። ከምስጋናው ቀጥሎ በቀጥታ የምንገባው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን በጥያቄ መልክ ነው የተዘጋጀ ነው።
• ማሳሰቢያ ለ GGጂጂግግ አባላት እና አድናቂዎች በሙሉ።
"…ሰሞኑን በፔጄ ላይ በፉጨት ተጠራርታችሁ መምጣታችሁ ይታወቃል። መምጣታችሁ ጥሩ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ታከብሩት ዘንድ የቤቱን ሕግ በድጋሚ ልነግራችሁ እወዳለሁ።
"…አብዛኛው የGGጂጂግግ አባላት ከርዕስ ውጪ ያልተጻፈ በማንበብ፣ ያልተባለ በመዘባረቅ ትታወቃላችሁ። በጩኸት፣ በሚገማ፣ በሚከረፋ፣ በሚሸት ስድብ ተናጋሪን በማጥረግረግ ሰውን በማሸማቀቅ ፀጥ በማሰኘት እንደምትታወቁ ይታወቃል። ይሄን አብሮአችሁ ተወልዶ፣ አብሯችሁ አድጎ አብሯችሁ ያረጀን ድንቁርና በፔጄ ላይ እንድታራግፉ አልፈቅድም። አንድ በሉ።
"…ሌላው በምስጋና ሰዓት እግዚአብሔር ይመስገን የሚል ጽሑፍ ብቻ ነው የሚጻፈው። በዚያ ወቅት እናንት ኮሚንስቶች አደብ ገዝታችሁ ተቀመጡ እንጂ በምስጋናው መሃል ክፍት አፋችሁን እከፍታለሁ ማለት አይፈቀድም። ቤቱ ሥነ ሥርዓት ያለበት ቤት ነው። መንበጫበጫቻችሁን እዚያው የለመዳችሁበት እሺ?
"…በተረፈ ለአቅመ አስተያየት መስጠት ያልደረሳችሁ ደናቁርት፣ ከተጻፈው ሓሳብ ውጪ የምትቀባጥሩም ብትኖሩ። "ቀንተህ ነው፣ ከራሱ ላይ ውረድ፣ እሱን አትንካብን፣ ይቦንስህሃል፣ አትደርስበትም፣ ከትግሉ ውጣ" ወዘተ የሚሉ ኮዋሻኮር የሆኑ ኮመንቶች ብትሰጡም በአፋችሁ እስካልተጸዳዳችሁ ድረስ መብታችሁ ነው። ለተቃውሞ ሓሳብም ቦታው ክፍት ነው። እኔን ብቻ ሳይሆን ሌላ አስተያየት ሰጪ መሳደብ ግን ያስቀስፋል።
"…ብትበሽቁም፣ ብትናደዱም፣ ጨጓራችሁ ቢያርም፣ ቆሽታችሁ ቢነድም እንደምንም ዋጥ አድርጋችሁ በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን ተንፍሱ። ለኒው ካመርስ ነው።
• ዝግጁ…?
ነገርየው እየበሰለ ነው።
"…በየትኛውም ስፍራ እንደ እኔ ዓይነት አንድ መራታ ዐውቆ አበድ የግድ ያስፈልጋል። የግድ ነው። ሁሉም ለክብሩ፣ ለስሙ ሲል የሚጠነቀቅበትን ጉዳይ ነካክቶ አፈር ከደቼ የሚያበላ እንደ እኔ ዓይነት መራታ ያስፈልጋል።
"…አስኳሉን ለማፍሰስ አሁን ቅርፊቱን እያሻሸሁ ነው። ኩርኩሜን ለማሳረፍ አሁን የእነ ሀብትሽን፣ የእነ 360ን ፀጉር እያሻሸሁ ነው። በጥፊ ከማጮሌና አይነስቡን ከማጥፋቴ በፊት ጉንጮቹን እየዳሰስኩ ነው። ዐማራ በሀብታሙ አያሌውም ሆነ በአበበ በለው መበጥበጥ የለበትም።
"…አይደለም ለፀረ ዐማራው የትግሬው ፓስተር ለምን ኦነግ ጋር የፈለጋችሁበት ሄዳችሁ አታለቅሱም። ይኸው የእስክንድር ነጋና የሀብታሙ አያሌው ቡችላ ለወያኔው ፓስተር ሄዶ ሲከሰኝ ተመልከቱት። ምን እንዳያደርገኝ ነው አንት መሳቂያ። እኔ እኮ የምትቆጣኝ ጁንታ ሚስት አይደለም ያገባሁት። ገና ደም ነው የማስተፋህ አዳሜ። ሳይገባው ለሚንጫጫው መንጋ እኔ ምንም ቦታ የለኝም።
"…ለጊዜው ጋዜጠኛ ብሩክ ይባስን ብቻ ነው የማልነካው። ሌሎቹን ግን አልለቃቸውም። የእስክንድር ጉዳይ በጣም ቀላል ነው። እሱ በረሃ ስላለ ከወንድሞቹ ጋር ፋኖዎች ጋር ተመካክሮ ይሠራል። በእሱ ስም ዶላር ሰብሳቢው፣ ከፋፋዩ የጂጂግግGG መንጋ ነው ደቼ የማበላው። እንደ ሀብታሙ አያሌው ዓይነቱ ተመክሮ፣ ተዘክሮ አልሰማ ያለውን ነው በጋዜጠኝነት ስም ፋኖ ገዝቶ መከፋፈሉን የማስቆመው። የዳያስጶራ ዶላርም በእነ አበበ በለው እና ሀብታሙ አያሌው በኩል፣ በየGGጂጂግግ ዎች በፌክ ኢትዮጵያኒስት በኩል አይደለም መሄድ፣ መሰብሰብ ያለበት። ራሱ ምድር ላይ ያለው ፋኖ በመረጠው፣ በወደደው በኩል ነው ማለፍ የለበት። ቀልድ የለም። ደፈር ካላልኩ አይስተካከልም። በግል ሚስቴን አልቀማኝ፣ ርስቴን አልነጠቀኝ። ሂእ
• መንጋ እያረፍክ ተንጫጫ…!
"…ከዚህ ከመሸጋገሪያ… 😂 በኋላ ወደ ሕዝባዊ ዲሞክራሲ ምርጫ እንሸጋገራለን።
"…የአቀናባሪው ልጅ አድናቂው ነኝ። የምታውቁት ከፍ ያለ ምስጋናዬንም አቅርቡልኝ። ስንትና ስንት የመዝሙር ግጥምና ዜማ ስደርስ፣ ዘማርያንን መዝሙር ሳስጠና እድሜ ዘመኔን የኖርኩ ያሳለፍኩ ሶዬ በ50 ዓመቴ ሲያቀብጠኝ ይህን "ሌባ ሁላ" የሚል የኦሮሚኛ ዘፈን ሌቦችን አበሽቅ ብዬ በቲክቶክ መርሀ ግብሬ ላይ በማንጎራጎር ስም ስቀልድ፣ ሳሾፍ ይኸው ተያዝኳት አይደል? ወደው አይስቁ አሉ።😂
• ድምጤ ግን እንዴት ነው? እስቲ ደግሞ የሆነ ቀን አንድ የህንድ ሀገር እንጉርጉሮ አንጎራጉርና ለዚህ አቀናባሪ ትሰጡልኛላችሁ። ከዚያ የሚሆነውን እናያለን። ወይ ቲክቶክ እንዲህ ጉድ ይሥራኝ። ሌባ ሁላ…!
"…በነገራችን ላይ ዛሬ ቲክቶክ፣ ሐሙስ ኢትዮ ቤተሰብ አይኖረንም። እሑድ የትንሳኤ ዕለት ግን ሞቅ፣ ሸብረቅ አድርገን ነው የምናሳልፈው።
• GGጂጂግግ ሌባ ሁላ አለ አዝማሪው ዘመዴ… 😂😂
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ተዘጋጅተው፣ ይሄን ሁሉ መንገድ ርቀት ሄደው ተያዙ የተባሉት "አሸበርቲዎች" ምን ያህል የደኅንነት፣ የስለላ፣ የወታደራዊ ሙያ እውቀት እንዳላቸው አመላካችም ነው እኮ የሚሆነው። ስለዚህ ይሄኛው ቢከሽፍ ሌላ ኃይል አለ ብሎ አመላካች አለ ብለው እንዲያስቡም ነው የሚያደርገው። ትሪፕል AAA ዎች ሊቀሽቡባት እና ራሳቸውን ሊያሻሽጡባት በፈለጉትና AFP የአዲስ አበባውን ኦፕሬሽን ለማጣራት የደወለላቸው የፋኖ አመራሮች ያረጋገጡለትም ይሄንኑ ነው። ነገር ግን የኢንሳው አቢይ አህመድ በዘመነ ወያኔ አብዛኛው ጅሀዳዊ ሀረካት በእስላሞች ላይ የተሠራ ስለሆነ አሁን ከስልጤው ሬድዋን ሁሴን ጋር በመሆን ኦርቶዶክስን አሸባሪ ለማስባል እየተላላጡ ይመስለኛል።
"…ከእነ አርበኛ ነናሁ ሰናይ ተጋድሎ በኋላ በሥጋት ላይ ያሉት ባለስልጣናት በሙሉ አዲስ መዋቅር ዘርግተውም በየቦታው በየጉራንጉሩ ሁሉ ምስኪን ሁላ መስለው የሰላይ መአት ማሰማራታቸው ተነግሯል። በአገዛዙ ፕላን ቢ መሠረት መጪውን የትንሣኤን በዓል ወዳጅ ዘመድ ለበዓሉ እንዳይገናኝና ምርት ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወር መንገድ ለመዝጋት ትእዛዝ ብቻ እየጠበቁ ነው የሚል መረጃም እየወጣ ነው። አሁን ከአሁኑ የወሀቢያው ቡድን ደጋፊ ነጋዴዎች በአንድ ቀን ልዩነት ዘይት የጠፋ በማስመሰል የሌለ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸው ነው የሚሰማው። ጎርፉ አለ፣ በዚያ ላይ በኑሮ ማቀውስ። በዚህ ላይ ምንአልባትም በፋኖ አሳብበው በተከታታይ "ጅሀዳዊ ሀረካት ፍንዳታዎችን በመፈጸም እነ አቢይ አህመድ የኢንሳ ሥራቸውን ሊደግሙም ይችላሉ። መጠንቀቅ ነው።
"…በመጨረሻም ጋዜጠኛ ዳዊት በዶክመንተሪው ላይ ሊያሳየን የፈለገው የዚህ ትግል ዋነኛ አንቀሳቃሽ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን" እንደሆነች ነው። አቢይ አሕመድ ባለፈው "ዲስኩሩ ወታደራዊ ሥልጠና የሚሠጠው እኮ በገዳማት ውስጥ ነው" በማለት የተናገረውን ማስታወስ ይመከራል። በዚህም ዶክመንተሪ ላይ ቶርች የተደረጉት ልጆች ደጋግመው "አባ እገሌ ነው የመለመለን፣ የመራን፣ የመረቀን፣ የጸለየልን፣ የጥይት መከላከያም የሰጠን" ወዘተ ብለው እንዲናገሩ የተደረገው በቀጣይም የቤተ ክርስቲያኒቱ ፈተና በከባዱ እንደሚመጣ ለመጠቆም ይመስላል። ተዘጋጅቶ መጠበቅ ነው እንግዲህ።
"…ይህ የእኔ ምልከታና እይታ ነው። የ GGጂጂ ዎችም ጉዳይ በደንብ ይታሰብበት። GGጂጂ ዎችን በአይነ ቁራኛ ማየቱም ይቀጥል እያልኩ የእኔን ምልከታ እዚህ ላይ እቋጫለሁ። እናንተስ እንዴት ዓያችሁት…? እስቲ እኔ ያላየሁትን አሳያታችሁ አስደምሙኝ። እጠብቃችኋለሁ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
መልካም… ዛሬም እግዚአብሔርን ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው አንድ ሺ ሰው ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። 1300 ሰው እግዚአብሔር ይመስገን እያለ በየቀኑ ስሙን እንዲያመሰግን ማስደረግም ቀላል እኮ አይደለም። እግዚአብሔር ይመሰግን።
"…በመቀጠል የምናልፈው ወደ ተለመደው ርዕሰ አንቀጻችን ነው። በነገራችን ታች የእኔ የዘመዴ ቴሌግራም ገጽ እንደ አንድ ተወዳጅ ዕለታዊ ጋዜጣ ዓይነት በሏት። ሁልጊዜ ርዕሰ አንቀጽ ያላት ጋዜጣ፣ የቲጂ ገጼ እኮ ሺ ሠራተኞች ያሉት ትልቅ የቴሌቭዥን ካምፓኒም ይመስላል። እነ ፋና፣ ኢቢሲ እና ዋልታም ቢጨፈለቁ የማይሰተካከሉኝ ምናምን ብዬ ራሴን በራሴ ባንቆለጳጵስ ምን ይለኛል? ምንም። 😂
"…ለማንኛውም በፔጄ ላይ የመረጃዬ፣ የቧልቴ፣ የቀልዴ፣ የርዕሰ አንቀጼ፣ የምስጋናው ሁሉ ሱሰኛ ከሆናችሁ በኋላ የፔጄን ሕግ ባለማጀክበር፣ ስሜታችሁን መቆጣጠር አቅቷችሁ በአፋችሁ ስትጸዳዱ አግኝቼ ወገብ ዛላችሁን ቀስፌ ከፔጄ ካባረርኳችሁ በኋላ ቄስና ሼክ ይዛችሁ ብትመጡም እንደማልመልሳችሁ እያወቃችሁ በጓሮ በር እየመጣችሁ የምታዝጉኝ ተቀሳፊዎች ሥነ ሥርዓት ብታደርጉ ይሻላል። (በስህተት የተቀሰፈ ብቻ ነው የምመልሰው) አይደለም እኔን ሌላ አስተያየት ሰጪ ሓሳቡን መሞገት እንጂ ስድብ ብትሰድበው እቀስፍሃለሁ። ሰምተሃል።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጼ የትናንቱን "ጅሃዳዊ ሀረካት" በተመለከተ የእኔን እይታ ልጽፍላችሁ ወደድኩ። ለእነ ( GG ግግ) የተሠራውንም ማስታወቂያ ቀኝ ትከሻዬና ዶክመንተሪው ሲሠራ የነበሩት የነገሩኝንም የወፎቼ ምልከታ ተጨምሮበታል።
"…እህሳ ጎበዝ የእነ "GGግግ" ን በተመለከተ ያዘጋጀሁትን ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ፣ አንብባችሁም አስተያየታችሁን ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…? 😂 እስቲ አጠገባችሁ ያለውን ሰው ነካ አድርጉትና ዝግጁ… በሉት?
• ዝግጁ…?
ይህቺን ነገር ሙድ ባንይዝባት…!
"…ይህቺን ነገር ሁሉም ሰው እንደ ወዛ በፈዛዛው እንደ ተራ ነገር እያያት ነው። ብዙዎቻችንም ሙድ ይዘን እየቀለድን የሳቅ ምንጫችን ሁላ እየሆኑ ነው። ብዙ ሰው እንደዚያ እያሰበም ነው። ነገር ግን ይሄ ነገር እንደቀልድ መታየት ያለበት አይመስለኝም።
"…አዳሜና ሔዋኔ በዚህ የኦህዴድኦነግ ብልጽግና ግብጻዊ የኦሮሞ ሠራዊት ሥልጠና ላይ ሙድ መያዙን ገታ ቢያደርግ እላለሁ። የሠራዊቱን በአሮጊቶች፣ በሽማግሌዎች፣ በሴቶች፣ በቀሬና ቄሮዎች፣ በአካለ ስንኩላን፣ በዓይነ ስውራንና በነፍሰጡሮች ጭምር መሞላት እያየን በሰልጣኞቹ እየተሳለቅን እንገኛለን። እደግመዋለሁ ይሄን እሳቤ በድጋሚ መርምሩ። ለምን ብላችሁም ጠይቁ።
"…ሰልጣኞቹን በተመለከተም አሰልጣኙ ክፍል እያለ ያለው "የማሠለጥነው ለአካባቢ ሰላም ጥበቃ ነው፣ ኦነግ ሸኔንና የዐማራ ፋኖን ለመመከትን የሚል ነው። ነገር ግን ይሄ በፍጹም ሊሆን አይችልም ባይ ነኝ። ምክንያቱም እነዚህ አሮጊቶች ጫካ የገቡ ልጆቻቸውን ለመግደል የሚጨክኑበት አንጀት ይኖራቸዋል ብዬም አላስብም።
"…ይልቅ እኔ እየሸከከኝ ያለው እነዚህ ሰዎች በዚህ መልኩ፣ ገጠር ከከተማ የሚሰለጥኑት ኢንተርሃምዌይ የዘር ጭፍጨፋ ለመፈጸም እንዳይሆን ብዬም እሰጋለሁ። ገጀራ፣ ቆንጨራ፣ ጩቤና ቢለዋ ይዞ መሰልጠን ለሸኔም፣ ለፋኖም አይሆንም። በፍጹም አይሆንም። የሚሆነው በጎረቤታቸው ለሚገኝ ጠላት ላሉትና በግፍ እንዲጨፈጨፍ ለተፈረደበት ምስኪን ወገን እንዳይሆን እሰጋለሁ። ዝግጅቱ አስፈሪ ነው።
"…የአገዛዙ ቁንጮዎች በተለያየ ጊዜ ሩዋንዳ የሚመላለሱት ወደው አይመስለኝም። ለማንኛውም ቀልዱን ትቶ መጠንቀቁ አይከፋም ባይ ነኝ።
• ተናግሬአለሁ።
👆ከላይኛው የቀጠለ✍✍✍ "…በተረፈ እደግመዋለሁ። አንተ በዐማራ ጉዳይ ምን አገባህ የምትለኝን መደዴ ወንበዴ አልሰማህም። ስለሚያገባኝማ ነው 24/7 365 ቀን ዋይ ዋይ የምለው። ዐማራ ከስድብ በቀር ደሞዝ አይከፍለኝም እኮ። ከዐማራ የማተርፈው ውርደት፣ ስድብ እኮ ነው። እኔ የዝሆን ጆሮ፣ የአዞ፣ የጉማሬ ቆዳ ስለተሰጠኝ እንጂ ዐማራ ነን የሚሉ ዘረጦ ዝርንክት በዋል ፈሰሶች እኮ እንደሚያወርዱብኝ የስድብ ናዳ ቆሜም አክሄድ ነበር። አንዳንዱ ስድባቸው ተቅማጥ በተቅማጥ የሚያደርግ እኮ ነው። አዎ እነግርሃለሁ እኔ ከዐማራው ሕዝብ የተረፈኝ ስድብ፣ መዋረድ ነው።
"…የዘር ቦለጢቃ ውስጥ አልቡካካም ብሎ ከብአዴን አባልነት ሲወጣ፣ እኔ አዲስ አበቤ ነኝ ብሎ ከኤርሚያስ ለገሰ ጋር ዐማራነትን ሲያንቋሽሽ ( ቪድዮውን በእጄ ይዤ) እኔ ግን ዐማራው ዐማራ ነኝ ብሎ በጊዜ ይደራጅ ብዬ ብቻዬን በምድረ በዳ ስለፈልፍ የነበርኩ ነኝ። ካህናት አባቶቼ፣ መምህራን ወንድሞቼ አካሄድህ ልክ አይደለም እንዴት ዐማራን በዚህ መጠን ዘረኛ ታደርገዋለህ ብለው ሲያወግዙኝ "ግድየለም ዐማራው መዳኛው ዐማራነቱ ብቻ ነው" ብዬ ድርቅ ክችች በማለት ያቀረሁት። ዛሬ ደስተኛ ነኝ። ዐማራው በዚህ መጠን ተነሥቶ ማርሽ ቀያሪ ሆኖ ሳየው ደስተኛ ነኝ። እናም ትናንት የዐማራን መደራጀት እንደ ውርደት ሲቆጥሩ የነበሩት ኃይሎች ዛሬ መጥተው በዐማራ ትግል ውስጥ በሴራ ልፈትፍት ቢሉ እኔ አልፋታቸውም። እኔ እንደነሱ የጎፈንድሚ ብር የለኝም። እኔ ያዘጋጀሁት ታጣቂና ሠራዊትም የለኝም። እኔ ያለኝ ትልቁ ሚሳኤል "ብዕሬና ምላሴ፣ አንደበቴ" ብቻ ነው። እሞግታለሁ። ሞግቱኝ።
"…ሌላው ቀንቶ ነው የሚልም ሰው አያለሁ። በማነው የሚቀናው? ቢቀና ቢቀና በእኔ ይቀናል እንጂ እኔ በማን እቀናለሁ? በምንስ እቀናለሁ። ሰው ቤት ሄጄ በምግብ አልቀላውጥ፣ ደውዬ ገንዘብ ስጡኝ አልል፣ ጎፈንድሚ ገቢዬ አይደለም። የገንዘብና የሴት ጾር ባይጠፋልኝም ኃጢአተኛና የኃጢአተኞች አለቃ ብሆንም አሳልፎ ያልሰጠኝ፣ ከባቴ አበሳ መድኃኔዓከም ከእነ እናቱ ክብር ይግባውና በሞገስ ከፍ ብዬ ያለው እኔ ወራዳው፣ አህያው ዘመዴ፣ ውሻነቴን በአደባባይ የምገልጽ፣ አቦ አቦ በሉኝ፣ አሞካሹኝ የማልል ዘመዴ በማን አባቱ ነው የምቀናው? ቅናታም ሁላ አለ ሌኒን… በተረፈ ወደ መቃብር እስክገባ ድረስ በዐማራ ትግል ለመሞገት፣ ለመደገፍ የማንንም ፈቃድ አልሻም። ተሳስቼ ስገኝ ራሴንም አልምርም።
"…ዐማራ ነን ባይ አንዳንድ አስመሳይ የቅናታም ሰፈር ልጆች በእኔ በዘመዳችሁ አትቅኑ። ሥራ ሥሩ። እኔ የሠራሁትን ባታደንቁ እንኳ አፋችሁን በስድብ አታበላሹ። ተንቀሳቀሱ። በአፍህ ዐማራ ነኝ አትበል በተግባር አሳይ። ወሬያም ሁላ እንደ ቡና ላይ ዲስኩር እንደ መንደሬ ሴት በፌስቡክና በቲክቶክ አትበጥረቅ። ላታስቆመኝ አትንበጫበጭ። አንተ ስለሰደብከኝ ከሚዛኔ ዝንፍ አልልም። የሚበሳጭ ልቦናም የለኝም። ጨጓራህን እልጣለሁ፣ አንጀትህንም አሳርራለሁ እንጂ እኔ ኬሬዳሽ ነኝ። እኔን ከዐማራ ትግል ማውጣት አይቻልም። ወንድ አባቱ ነዋ። ይሞክረኝ። ገና በውጭ ሀገር ያለውን ሌቦቹን፣ ማፍያዎቹን ፈርቶ የተደበቀውን ዐማራ አስታርቄ፣ አሰባስቤ ተአምር ነው የምሠራው። ገና ምን አየኽና አባቴ። ደግሞ አደርገዋለሁ። ይሄንንም መዝግበው።
"…አረፍ እንድትሉ ግን የሚከተለውን ቃል እገባላችኋለሁ። የዐማራ ፋኖ በድል አሸንፎ ነፃ ሀገር ሲያስረክበኝ በቀጣይ እድሜ ካለኝ ሳላየው የሚቆጨኝን ማኅበረ ሥላሴን፣ ጉንዳ ጉንዶ ማርያምን፣ ዋልድባ አብረንታንትን፣ ብርብር ማርያምን ባይ ደስ ይለኛል። ቢቀርም ደግሞ ችግር የለም። ዐማራ የራሱን ሀገር ቢመሠርት እንኳ ወይ ዙር አምባ፣ ወይ ጣና ደሴት ውስጥ መቃብር ቤት እንዲሰጠኝ እማጸነዋለሁ። ከዚያ በዘለለ እኔ የዐማራ ፋኖ መሪ አይደለሁም። አትስጉ። ሥልጣንም፣ ሀብትም፣ ዝናም አልፈልግም። በሀገሬ ተወዳድሬ ሥልጣን መያዝ እኮ ኃጢአት ሆኖ አይደለም። ግን አልፈልግም። ዐማራ ፋኖ አሸንፎ ሥልጣኑን ቢይዝ እኔ በማግሥቱ ወደ ዐውደ ምሕረቴ ነው የምመለሰው። በዚህ ስጋት አይግባችሁ። ከኦሮሞ ነፃ አውጪና ከትግሬ ነፃ አውጪ ካንሰሮች የሚገላግለን ዐማራው ብቻ ነው የማምን ስለሆነ ዐማራን በመደገፉ ትግሌ እቀጥላለሁ። ቃሌ ቃል ነው። አከተመ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
“…እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፦ ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ?” ዘፍ 4፥6
"…እስከአሁን ድረስ በፋኖ እስክንድር ነጋ ጥላ ሥር የተጠለሉት፣ የተከለሉት የዐማራ ታጋይ ነን ባይ ኢትዮጵያኒስቶች በሙሉ "በጎንደር ዐማራ ፋኖ እርቅም" ሆነ "በዐማራ ፋኖ የወሎ ዕዝ" እርቅና አንድነት ላይ ትንፍሽ አላሉም። ዓለሙ ሁሉ በሆነው ነገር ጮቤ ሲረግጥ በፌክ ኢትዮጵያኒስቶች መንደር መርዶ ነው የሆነባቸው። ነጠላ ዘቅዝቀው ኀዘን ነው የተቀመጡት። በሙሉ ድምጻቸው ሰለለ። ውኃ ውስጥ ገብታ የወጣች አይጥ ነው መስለው የተገኙት።
"…ስማኝማ የዐማራ ትግል መለኮታዊ ጥበቃ ስላለው በቀላሉ አይፈርስም። የበግ ለምድ ለብሶ ዐማራ ዐማራ እየተጫወቱ የዐማራን ትግል በወሬ መበታተን አይቻልም። አይፈቀድምም። ግንቦቴ ያው ግንቦቴ ነው። የመርዝ ብልቃጥ። ኢህአዴግ የነበረ ሁሉ የቫይረሱ ተጠቂ ነው። አንዴ ብአዴን የሆነ ሰው ዐማራ ለመሆን የፈጣሪ እርዳታ ያስፈልገዋል እንጂ ዐማራ መሆን አይችልም። ይከብደዋል። ፀረ ዐማራ ቫይረስ አንዴ ከለከፈህ የፈለገ በግ መስለህ ለመታየት ብትሽለጠለጥ ተኩላነትህ መገለጡ አይቀርም። ይሄን አስረግጬ ነው የምነግርህ።
"…እስቲ ተመልከቱ በጎንደሩም፣ በወሎውም ሰበር ዜና የለ። ምናሉሽ፣ ምናሉ የለ። እንግዳ መጋበዝ፣ ፋኖ ጋር ደውሎ ማነጋገር የለ። ልዩ ፕሮግራም የለ። የደስታ፣ የፈንጠዝያ መርሀ ግብር የለ። ኀዘን ቤት። ጭለማ እኮ ነው ዋጣቸው። ፕሮግራም ሁላ እንዴት ያቅርቡ? የፈለገ ቢሆን እንደምንም ብለው ትናንት በሰበር ዜና ይገባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ጭራሽ ዘግተውት ነኩት። ጎፈንድሚም ቀረ። በዐማራ ችግር እከክ ማራገፍም ቀረ። ልዩነትን በማጦዝ ትግሉን በማራዘም ከርስን መሙላትም ቀረ። በእኛ በኩል ካልሆነ ገንዘብ ለዐማራ አይሰበሰብም ብለው በዐማራ ገንዘብ ቴስላ፣ ቪ8 ማሽከርከሩ፣ ሚልየን ዶላር የተከፈለ ቪላ ውስጥ መኖሩም ቀረ። እናም ዝም ጭጭ። አይገርምላችሁም…?
"…ፌስቡካቸው፣ ዩቲዩባቸውን ከፍታችሁ እዩ። ወፍ የለም። ሰው ለማስመሰል እንኳ እንዴት አይጥርም። ሀብታሙ አያሌው የዋሁንና ፎልፏላውን ሁሉን አማኙን ዘመነ ካሴን በአደባባይ "ከእስክንድር ጋር ምንም ዓይነት ጸብ የለንም።" እንዲል ካስደረገው በኋላ መላውን ዐማራ ደስ ይበልህ በእስኬውና በዘሜ መካከል ጸብ የለም እያለ ሲያጮህ የነበረው ሀብታሙ አያሌው ዛሬ ከግለሰብ ያለፈ ዐማራዊ አንድነት ሲመጣ ምነው ዝም አለ? ከሁሉ ቀድሞ እንዲህ ዓይነት ብሥራት የሚያበሥረን እሱ ነው ብለን ስንጠብቅ የት ገባ ምን ዋጠው? ቆፍጣናው ዘመነ በጊዜው ለዐማራ አንድነት የሚሠሩ መስሎት በምድር ላይ እንደ እስኬው የማምነው ሰው የለም ብሎ እንደነበርም ይታወስ።
"…አንጋፋው ታጋይ አርበኛ አሰግድ መኮንን "ኢትዮ 360 ትግል እያበላሸ ነው።" ብሎ በአደባባይ ሲናገር፤ ሕዝቡ በሀብታሙ አያሌው ላይ ካለው ጽኑ እምነት የተነሳ ሀብታሙ አሰግድን የምክር፣ የተግሳጽ ሳይሆን በፀብ ዱላ ሲያብጠለጥለው፣ ሀብታሙን ያመነው ሕዘበ አዳም አሰግድ ምን ሆኖ ነው? በብአዴን ተገዝቶ ዐማራን ካደ ማለት ነው?" ያለለ ነበርን? መከታውና ደሳለኝ ጊዜአዊ ፀብ ተጣልተው ሳለ እነ ሀብታሙ በሻህ "ሂድና ሬሳህን ቁጠር" እያሉ በወንድማማቾች እልቂት ሲሳለቅ እኔ ብቻ ስቃወም አዳሜ ዳር ሆኖ ይመለከት፣ ይታዘብ አልነበረምን?
"…ሜጀር ጀነራል ውባንተ ባለብረቱ " እኔ ውቤ በገንዘብ አልገዛም። ማንም በገንዘብ አያንበረክከኝም። ባለገንዘብ ገንዘብህን ይዘህ ገደል ግባ" ብሎ ተናግሮ ቀደም ብሎ በጥድፊያ ከተመሰረተው የጎንደር ዕዝ ሲወጣ "ውባንተም ካደን?አይ ዐማራ" ብሎ ከመጮህ በቀር ነገሩን ለመመርመር የፈቀደ ነበርን? ውባንተ ከመሞቱ በፊት ሀብታሙ ውባንተ በእስክንድር ግንባር በሻለቃ ዳዊት ጉያ ስር አልገባም በማለቱ የወረደበትን ውርጅብኝ አታስታውሱምን?
"…የዘነ ቀኝ እጅ ጠበቃ አስረስ (ባገኘው እኔም ጥያቄ አለኝ) "እስክንድርን እናከብረዋለን። ነገር ግን ግንባር የሚባለው ነገር ሲመሰረት የምናውቀው ጉዳይ የለም።" ብሎ ሲናገር "እንዴት አስረስ እስክንድርን ይናገረዋል?በቃ አስረስ ብአዴን ነው። ዘሜን እንዳያስበላው። ዘሜ ነቃ ይበል።" ብለሎ ያልጮኸ ነበርን? አንዴ እነ ዘመነን አቅርቦ እነ ዝናቡን አርቆ፣ ሌላ ጊዜ እነ ዘመነን አርቆ እነ ዝናቡን አቅርቦ ሲያጮህ የከረመ ኃይል ሁለቱም ሲታረቁ በንዴት ለምን ሆስፒታል ይገባል? የጤና እኮ አይደለም። መሪዎችን መተቸት፣ መሞገት ተፈጥሮአዊ ነው። ሌላው ነገር ግን ከዚያ ሲያልፍ ኢዳቢራል… እንዲያውም በግልፅ ይቅርታ ጠይቀው በይፋ እስካልተመለሱ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ እነዚህ ከላይ ከለጠፍኳቸው አካላት ጋር ተገናኝቶ ስለ ዐማራ ትግል የሚያወራ ፋኖ ካለ እርሱ ዋነኛው ቀንደኛ የአፍራሾች አድራሽ ፈረስ መሆኑም ይታወቅ።
"…የምትሰድቡኝ መብታችሁ ነው። ድሮስ ግንቦቴ፣ ብአዴንና ፀረ ዐማራ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች እንድትመርቁኝ መች እጠብቃለሁ እንዴ? ድሮስ ጽንፈኛ የወሐቢይ እስላሞች፣ አክራሪ ጴንጤዎች እና የፖለቲካው የአገው ሸንጎ፣ የፖለቲካው ቅማንት ኦርቶዶክሶች እንድታሞግሱኝ እጠብቃለሁ እንዴ? በፍጹም የማይደረገውን? እኔ በድፍረት አጀንዳዎችን አነሣለሁ። አካሄዶችን እተቻለሁ። እኔ ዘመዴ ቋሚ ጠላት፣ ቋሚ ወዳጅም የለኝም። ማንም ይሁን ማን ሲያጠፋ እወቅሳለሁ፣ ሲሠራ አሞግሳለሁ እመርቃለሁ። እስክንድር "መምህሬ ነው" ስላለኝ ጥፋት ሲያጠፋ አላልፈውም። ዘመነም፣ አሰግድም፣ ምሬም ሆነ ሌላው "ወንድምዓለም" ስላሉኝ የሳቱ በመሰለኝ ጊዜ የጭቃ ዥራፌን ከማንሣት ወደ ኋላ አልልም። ሁላቸውንም ተችቼ ዐውቃለሁ። እነሱም በመተቸታቸው አኩርፈውኝ፣ እኔም በመተቸቴ ተጽጽቼ አላወረቅም። አገኘነው ዘመዴን ያሉ ሰዎች ለዘመነም፣ ለአሰግድም፣ ለምሬም ነግረዋቸዋል። ፈገግ ብለው ስቀው መልሰው ከእኔ ጋር ነው ያወሩት፣ የሚያወሩት። የሆነው እንዲህ ነው በቃ። በዚያ መንደር ያላችሁ ፌካፌካሞች እንደማትወዱኝ የታወቀ ነው። እኔ ግን ኬሬዳሽ።
"…የተለመደ አዝግ አስተያየትም ደግሞ አለ። "በውስጥ ብትጨርሱ ምን አለ?" የሚል። በአደባባይ ሊጨረወስህ የተዘጋጀን የምን በውስጥ መጨረስ ነው? የምን ድርድር ነው። የአደባባይ ሰው በአደባባይ ነው የሚዠለጠው፣ የሚተቸው፣ የሚመረቀውም። በሕዝብ ትግል ድርድር ብሎ ነገር የለም። አሜሪካ የሄድኩ ጊዜ ሀብታሙን በምስክሮች ፊት ሁለት ሌሊት በጉዳዩ ዙሪያ አውርቼዋለሁ። አንተ ጋዜጠኛ ሁን፣ በጋዜጠኝነትህ የጋዜጠኝነት፣ በመምህርነትህ የመምህርነት ሚናህን ብቻ ተወጣ ብዬ ወትውቼዋለሁ። ብዙ ስሞታ፣ የበዛ አቤቱታም እየጎረፈብህ ነው ብዬም መክሬዋለሁ። የፋኖ መሪ የመምረጥ፣ ለዐማራ ፋኖ ማኒፌስቶ የማዘጋጀት አቅሙም፣ እውቀቱም፣ ብቃቱም እንደሌው እያወቀ ሰው በዚያ መጠን እጁን በፋኖ አሠራር ውስጥ ከትቶ መፈትፈት እንደሌለበትም አበክሬ ነግሬዋለሁ። ለሀብታሙ ከእኔ በላይ ወዳጅ የለውም። በስልክ የምናወራውንም በጥንቃቄ ነበር የማወራው። ሀብትሽ ሰው ቀርጾ ቆይቶ ሲጣላ የማሸማቀቅ ባህሪ ስላለው እኔስ ምኔ ሞኝ ነው። ሃኣ…? 👇 …ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ አመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም…
"…በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች። ማቴ 21፥ 18-19
"…የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው። ዮሐ 2፥ 13-16
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ዘወትር እሑድ በመረጃ ተለቭዥን በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው ሳምንታዊው መደበኛ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብራችን ከሁለት ወራት ቆይታ በኋላ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2:15 ላይ ይጀምራል።
• ዩቲዩብ 👉 https://www.youtube.com/watch?v=IoQqARsRDKo
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
"…ሻሎም ! ሰላም !
የምሥራች ሰበር ዜና
ከወሎ ቤተ ዐምሓራ…!
"…ረዘም ላሉ ወራት፣ ጊዜ ወስደው ሲነጋገሩ፣ ሲመካከሩ የቆዩት የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ እና የወሎ ዐማራ ዕዝ በዛሬው እለት ልዩነታቸውን ሁሉ አጥፍተው ወደ አንድ ዕዝ መግባታቸውን አብሥረዋል።
"…እስከዛሬም ሲያጨቃጭቅ የነበረው የዕዙ መሪና የዕዙ ስምም መቋጫ፣ መደምደሚያ ማግኘቱ ነው የተነገረኝ።
"…የምሥራቅ ዐማራ የሚለው የእነ ምሬ ስም በየዐማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ የተተካ ሲሆን፣ የዕዙ መሪ ማን ይሁን የሚለውም ምላሽ አግኝቶ የአዲሱ የዐማራ ፋኖ የወሎ ዕዝ ዋና አዛዥ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ሲሆን የዕዙ ምክትል ዋና አዛዥ ኮረኔል ፋንታሁን ሙሐቤ ሆነው ዐማራ ፋኖ በወሎ ዕዝን በጋራ እንዲመሩ መመደባቸውን ከሥፍራው የደረሰኝ መረጃ አመላክቷል።
• ጎጃም ፩ ሆኗል
• ወሎም ይኸው ዛሬ ፩ ሆነ
• ጎንደር ጣጣውን ጨርሶ ብሥራት እየጠበቅን ነው።
"…የሚቀረው ሸዋ ብቻ ነው። ሸዋም እርቅ ጨርሶ የጎደለው አፈጻፀሙ ነው። እሱም ቢሆን የግዱን ይሳካል። 💪🏿💪💪🏿
"…እንኳን ደስስ ያላችሁ…!
የእኔ ሱቅ…!
"…እኔ ኢንቬስተር ነኝ። ሰዎች ሓሳባቸውን የሚሸጡበትን ግብዳ ሱቅ፣ ምን የመሰለ መደርደሪያ ሁሉ በስማቸው አሠርቼ፣ ክፍት ቦታም አዘጋጅቼ፣ በሩን ብርግድ አድርጌ ከፍቼ በነፃ ይጠቀሙበት ዘንድ ያበረከትኩ ዲታ ነኝ። የሰው ዲታ። አይገርምም ለ400 ሺ ሰው የሓሳብ መሸጫ ሱቅ ከፍቶ ማበርከት?
"…የእኔ የሓሳብ መሸጫ ሰንዱቅ እንደ ዳንኤል ክብረት ሱቅ የተከረቸመ፣ የተዘጋ አይደለም። የጌትነት ዓልማው፣ የመሳይ መኮንን እንኳ ሓሳብ እየሸጡ በራቸው በ12 ቁጥር ሚስማር የተጠረቀመ ነው። ሱቅ ከፍተው ነገር ግን የደንበኛ አስተያየት አይቀበሉም። እንደ ነገረኛ የመንደር ሴት፣ ወይም እንደ አቅመቢስ ታማኝ የመንደር ውሻ በተዘጋ የሰፈራቸው ጊቢ ውስጥ ቆመው "ነጠላዬን አቀብዪኝ" ብለው ሲጮሁ፣ ሲሳድቡ ውለው የሰው ምላሽ አይቀበሉም። እኔ ሓሳብ ለገበያ አቅርበው ሓሳብ እንደማይቀበሉቱ፣ እንደማያስወሩቱም አይደለሁም።
"…ሓሳባቸውን የሚገልጹትን እጅግ አድርጌ አከብራለሁ። ሓሳባቸው በተቃራኒ ወገን ሆኖ በጨዋ ደንብ ተግሳጽ፣ ቁንጥጫ፣ እንደ ምንአባክ፣ ምቀኛ የመሳሰለ ሀገር በቀል ምርቃት መሳይ ስድብም አከብራለሁ። የሚያስቁኝ ተደብቀው የሰው የስድብ ሓሳብ ሲለይኩ የሚውሉት ሶዬዎች ናቸው። እንዴኤኤ አትደበቁ፣ እናንተም ሓሳብ ስጡ። በአፋችሁ አትጸዳዱ እንጂ በተቃውሞም አስተያየት ለመስጠት አትቦዝኑ። ክልክልም የለው።
"…የአያልነህ ላቀው "ምቀኛ ነገር ነህ" 12 ላይክ ካሰጠው፣ የሞጣ እና የብሪጅ ስቶን የሚኪ "ድራግ" ስድብማ ስንቶች ያስለይካቸው ይሆን…?
• እየተመቀኛችሁ…!
ያስገኘች እናቱን ሲሰድብ፣ ሲያንቋሽሽ ስታይ ትሸማቀቃለህ።
"…ከአህያማ አንነስ። አህያ የሚል ቃል ለስድብ የሚጠቀሙ ይፈሩ። ይደበቁም። አህያ ያገኘችውን ክብር ያላገኘ የሜዳ አህያ ብቻ ነው። በሌባው በዲያብሎስ ታስረን በጫት፣ በሺሻ፣ በዝሙት፣ በዘረኝነት፣ በሴሰኝነት፣ በአምቡላ፣ በሐሺሽ፣ በሌብነት፣ በአጋንንት መንደር የተደበቅን እኛ መፈታት ይሁንልን። አሜን።
"…እኔ አህያው ዘመዴ ሰናይ ቀን ተመኘሁላችሁ።
"…የዛሬው "ርዕሰ አንቀጼ" ይህን ምስኪን ደመ ከልብ የተደረገ ሰው ጉዳይ ስለሚመለከት ለመልሱ የኦሮሞ ነፃአውጪ አክቲቪስቶች ተዘጋጁ።
• አንድ ሦስት ደቂቃ ጠብቁኝ መጣሁ…
"…እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ አመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም…
፩፥ ምክረ አይሁድ
"…በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥ ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፤ ማቴ 26፥ 3-4
፪፥ የመልካም መዓዛ ቀን
"…ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። ማቴ 26፥ 6-7
፫፥ የእንባ ቀን
"…በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።” ሉቃ 7፥38
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ምኒልክ ቴሌቭዥን…
"…መገናኛ ብዙኀን መብዛት አለበት። በብዛትም በጥራትም መጨመር አለበት። በዚህ ዘመን ሚድያ ሁሉን ነገር ቀያሪ ነው። መንግሥታት የሚፈሩት እጅግ አደገኛ መሣሪያ ቢኖር እሱም ሚድያ ነው። ይሄ እውነት ነው።
"…ምክር ልሰጥ ነኝ። ሀብታሙ አያሌው ልክ እንደ ምናላቸው ስማቸው በስምምነት፣ አመስግኖ እንደመውጣት፣ እንደ ማደግ የነበረበትን ሚድያ አፈራርሶ አፈር ከደቼ አብልቶ ነበር መሄድ የፈለገው። ይሄ ነውር ነው። ትልቅ ነውር።
"…መረጃ ቲቪ የወያኔ ልሳን የሆነውን ኢትዮ ፎረምን አየር ሰዓት በሰጠው ጊዜ ምድር ሲቀወጥ ወዲያው ነው ያወረደው። ግንቦቴው መሳይ መኮንንን፣ አበበ ገላውም ሲመጡ ወዲያው ነው ያወረዳቸው። ኢትዮ 360 ግን በሀብታሙ በኩል መረጃ ቲቪን እንደ ተቋም፣ በኢየሩስ በኩል ግርማ ካሣን መሞለጭ፣ ማዋረድ፣ ከሕዝብ ጋር ማቀሳሰር ነበር የያዙት። ይሄ ነውር ነበር። በነፃ ያለምንም ጣልቃገብነት የተሰጠህን ገበታ መድፋት ተገቢ አይደለም። አሁን በሀብታሙ አያሌው ምክንያት መረጃ ቲቪን የሚወቅስ አንድም ፋኖ የለም። ይሄ ግልግል ነው።
"…አሁን እነ ሀብታሙን ለመምከር የመጣሁት ስለ ገንዘቡ ሌላ ጊዜ እናወራለን። ነገር ግን ምኒልክ ቴለቭዥን ብላችሁ የከፈታችሁት በአሜሪካ የተመዘገበ የሳታላይት ቴሌቭዥን ነው። ሀብታሙ የሳታላይት ቴሌቭዥኑን ባለቤት እያወቅከው፣ ጣጣ እንደሚያመጣብህም እያወቅክ በሰው ድርጅት ስም መክፈት አልነበረብህም። ሰዎቹ ጉዳዩን ለጠበቃ ሰጥተው ወደ ፍርድ ቤት ሊሄዱ ስለሆነ አስተካክል። ወንድማዊ ምክሬ ነው።
"…GG ጂጂግግ ዎችን ነክሻለሁ። የገንዘብ ምንጮቹን በሙሉ ቆልፌአለሁ። በዐማራ ስም ዐማራን እየጋጡ ዐማራን ማዋረድ አልፈቅድም። ተናግሬአለሁ፣ ተናግሬአለሁ። ምንአገባህ አንተ ቆቱ ነው ያልከኝ?
• ገደል እንጦሮጦስ ግባ ልል ብዬ ተውኩት።😂
"…እኮ እናንተ አሸባሪ…?
• አይ GGጂጂግግ…!
• ከዚህ ቀልድ ቀጥሎ አንድ ሰሞኑን በስሜ የተለቀቀ ሀገርኛ ሙዚቃ ወጥቷል እሱን እለቅላችሁና አስተያየታችሁን ትለግሳላችሁ።
• አንት ማንትስዬ ምንጥሶ ደግሞ ቀንተህ ነው በለኝ አሉህ …😂
መልካም… እኔ በርዕሰ አንቀጼ የትናንትናውን ጅሃዳዊ ሀረካት በእኔ እይታ ትን እስኪላችሁ ተንትኜ ሓሳቤን አስቀምጫለሁ። ቀጥሎ ደግሞ ተራው የእናንተ ነው። የእናንተን እይታ የምንሰማበት ሰዓት ነው።
"…እነ GGጂጂግግ ም ተረጋግታችሁ እንደሰለጠነ ሰው። ያውም አማሪካና አውሮጳ እንዳለ ሰው በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን ስጡ። የእኔ ቤት ለሁሉም ክፍት ነው። ሰው መተንፈስ አለበት ብዬም አምናለሁ። ይሄ ግን በአፉ የሚጸዳዳን ሰው አያካትትም። ደናቁርት መሃይምናንም ያስገደዳችሁ፣ አስተያየት ካልሰጣችሁ ወላጅ ታመጣላችሁ የሚላችሁ ስለሌለ፣ አስተያየት መስጠትም የግድ ስላልሆነ ከምትዋረዱ፣ መሳቂያ መሳለቂያ ከምትሆኑ ጮጋ በሉ።
"…ሌላው በአደባባይ የፈራኸውን ስድብ እና ሙግት ይዘህ እንደ ስድ አሳዳጊ እንደበደለው፣ እንደ ጋለሞታ በጓሮ በር፣ በውስጥ መስመር መጥህ እለፋደዳለሁ ብትልም አልመልስልህም። እቀስፍሃለሁ እንጂ። ሰምተሃል።
"…የሆነ ጊዜ ለዋልድባ 100 ዶላር፣ ለልደት ለጃንሜዳው የነዳያን ግብዣ ሁለት ኪሎ ቅቤ ለግሻለሁ፣ ለዘመዴ 10 ዶላር በፔይፓል አግዛለሁ ምናምን ብለህ፣ የምኖረው አውሮጳ፣ አማሪካና ካናዳ ነው፣ በሙያዬ ዶፍተር፣ ፍሮፌሰር፣ ሂንጂነር 😂 (ኢ ነው በለኝ አሉህ ደግሞ) ነኝ ብለህ ብትመጣም አልምርህም። ብትናደድም ተረጋግተህ አውራ።
"…አቤት ስንቱን ሰው ትእግስተኛ አደረግኩት። እኔን ነበር ዶፍተር ማለት። አባቴ ይሙት የመንጋው አለቃ እኮ ነኝ እኔ ዘመዴ። 😁
"…በነገራችን ታች የአምባገነን ልጅ በዶክመንተሪ ብዛት አይድንም። አበደን።
"…በሉ ተንፍሱ እናንተም በተራችሁ…!
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ታስታውሳላችሁ አይደል የኢቴቪውን የጋዜጠኛ አብዲ ከማልን እነ አኬልዳማን፣ እነ ጃሀዳዊ ሀረካት፣ እነ አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ ወዘተ የመሳሰሉ አስደማሚ የወያኔ የሆልዩድን ፊልሞች የሚያስንቁ ዘጋቢ ፊልሞችን? እነዚያን ከፔንታጎን፣ ከሞሳድ፣ ከኤፍቢአይ ወዘተ በበለጠ የስለላ መረብ አማካኝነት በተደረገ ጥረት ጥፋት ሊያደርሱ ሲሉ የከሸፉ የዶክመንተሪ ፊልሞችን? እርግጠኛ ነኝ አብዲ ከማልና ዘጋቢ ፊልሞቹን የሚረሳ በተለይ ግንቦቴና ወሀቢይ ይኖራል ብዬ አልገምትም። ታዲያንላችሁ እነዚያን የዘመነ ወያኔ የዘጋቢ ፊልም ትሩፋት የነበሩ አስደማሚ ዘጋቢ ፊልሞችን ባየንበት ዓይን የትናንቱን የኦሮሙማ እዚህ ግባ የማይባል ቀሽም ከቁብ የማይቆጠር ተራ የጀማሪ ደራሲ ድርሰትና ፊልም ዓይተን ባንበሳጭ ነው የሚገርመን። በዘመነ ወያኔ የኢንሳ አለቃ የነበረው አቢይ አሕመድ ከአብዲ ከማል ጋር ያዘጋጀው የነበረው ዘጋቢ ፊልም አሁን አቢይ ጠቅላይ ከሆነ በኋላ አብዲ ባለመኖሩ ነው ወይ እንዲህ የቀሸመው? እንድል ነው ያደረገኝ እኔን።
"…ዘጋቢ ፊልምንስ ከምር ወያኔ ትሥራው። ትረካውንም ጋዜጠኛ አብዲ ከማል አዘጋጅቶ ይተርከው። አይደለም እንዴ? እኔየምለው ጋዜጠኛ አብዲ ከማል የነውጡ ሰሞን ከአቢይ አሕመድ ስር አይጠፋም ነበር። አቢይ ቤተ መንግሥት የገባ እለትም አብሮ ገብቶ የዘገበው፣ ሳኡዲ አረቢያ ድረስ አብሮት የሄደውም እርሱ ነበር። ምክንያቱም ዶክመንተሪውን ያዘጋጁ የነበሩት አቢይ አሕመድና አብዲ ከማል ስለነበሩ ነው። እነ አህመዲን ጀበል እና ግንቦቴዎች ይሄ ጋዜጠኛ ከሥራ ካልተባረረ ብለው ጓ ሲሉበት እንደነበርም አስታውሳለሁ። አሁን ከወዴት ይሆን ያለው ጋሽ ሀረካት አብዲ ከማል…? ነፍስ ይማር። ሞቶ ብቻ እየወቀሱኩት እንዳይሆንብኝ እና ሙት ወቃሽ እንዳልሆን።
"…የትናንቱ "የከሸፈው ሴራ" ዘጋቢ ፊልምን በደንብ ነው ያየሁት። እኔ በራዲዮ ፋና ተለቭዥን የቀረበውን ነበር ያየሁት፣ የተመለከትኩትም እሱን ነው። በሌሎችም ተላልፍ ሊሆን ይችላል። እኔም ራሱ በትናንቱ ላይ በቲክቶክ ገጼ ላይ ታጋይ እስክንድር ነጋን "አንተ ውጭ ሆነህ በማስተባበር ትግሉን ብታግዝ ነው የሚሻለው፣ ለትጥቅ ትግል የሚሆን ዕውቀትም፣ አቅምም የለህም፣ ከጥቅምህ ጉዳትህ ያመዝናል፣ እናም በባሌም ይሁን በቦሌም ቢሆን ከሀገር ወጥተህ ትግሉን በሌላ መልኩ ብታግዝ ይሻላል ብዬ በቲክቶክ የሰጠሁትን አስተያየት ቆርጠው አምጥተው ለእስክንድር ነጋ "አቅም ለመጨመር፣ ጉልበት ለመስጠት ሲላላጡበት አይቼአለሁ። ሴራዋ ስስ ናት። አቅመቢስ ሴራ…
"…የትናንቱ የከሸፈ ሴራ ዘጋቢ ፊልም አቀናባሪ እና አንባቢ ከወደ ደሴ እንደመጣ የሚነገርለት የለውጡ ፍሬ ከሆኑት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው የወሎ ዐማራው ጋዜጠኛ ዳዊት መስፍን ነበር። ወሎ ሲሉ ስለሰማሁ ነው። ከተሳሳትኩ እታረማለሁ። ጓደኞቹ ሲነግሩኝ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሥራ ባልደረባ እና በመሃል አዲስ አበባ አምባሳደር ፍል ውኃ አካባቢ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ባለ1 መኝታ መኖሪያ እና የመንቀሳቀሻ አንድ ኮሮላ መኪና የእጅ መንሻ የተሰጠው ባንዳ ነው ነበር ያሉኝ። ዳዊት በትናንቱ ዶክመንተሪ ፊልሙ ላይ የኦሮሙማው መንግሥት በቀጣይ ምን እንዳሰበ ጭምር ነው ለማሳየት የሞከረው። በተለይ ኦርቶዶክስን እስላማዊውና የጴንጤው መንግሥታችን የከፋ መከራ እንደደገሰልን አመላካችም ነው።
"…በትናንቱ "የከሸፈፈው ሴራ" ዘጋቢ ፊልም ድርሰታቸው እኔና ጓደኞቼ የታዘብነውን ሦስት አንኳር፣ አንኳር ነጥቦችን እናንሣ። እንመልከትም።
፩ኛ፦ የዲያስፖራ አሸባሪ ተብለው የተወነጀሉት በሙሉ የትምህርት ሚኒስትሩ የብርሃኑ ነጋው ግምቦቴ ልጆች ናቸው። የአንዳርጋቸው ፅጌ ፍሬዎች ናቸው። እነ መሳይ መኮንን እና ደረጀ ሀብተ ወልድ ከጂ 7 ሲሆኑ ይሄን ትግል ከግንቦቴዎች ጋር እየመሩ ያሉት ሌሎች በኦሮሙማው አገዛዝ የተከሰሱት "የገዳ ሥርዓት አድናቂው፣ ቀድሞ የዐማራ ሕዝብ ሳይሆን የዐማራ ብሔርተኝነት ተፀያፊው፣ አሁን የግምባሩ ፕሮፓጋንዳ ክፍል ዋና ሓላፊው ሀብታሙ አያሌው እና የግንባሩ መሥራችና ግንናባሩ ሲፈርስ እንደፈረሰ ሳይነገራቸው ሕዝባዊ ሠራዊቱ በሀብታሙ አያሌው እና በአበበ በለው መልሶ ሲቋቋም ከቦታው እንዳይገኙ የተከለከሉት ሻለቃ ዳዊት ናቸው። የሚገርመው በዚህ ዶክመንተሪ ላይ ወንድሜ ጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ እንኳ አልተካተተም። ኢየሩሳሌምም እንዲህ እየደከመች ስሟ አልተነሣም። ለምን ያልን እንደሆነ ዘጋቢ ፊልሙ ሊያሳየን የፈለገው ፋኖዎችም፣ ዳያስጶራውም መንግሥት የጠመደው እነዚህን ነውና ከእነዚህ ጋር መሥራት አለብን ብለው አሠላለፋቸውን ከእነ መሳይ፣ ደሬ፣ ሀብትሽ እና በአጠቃላይ ከ (GGጂጂግግ) ዎች ጋር እንዲያደርጉ የፈለጉ ይመስለኛል። ሌባ ሁላ…
"…እኔ እስክንድርን ስወቅሰው የቀረበውም ለእስክንድር ጉልበት፣ አቅም ለመስጠት አስበው ይመስለኛል። እስክንድርን ዘመነ ካሴ ስሙን ሳይጠቅስ ሲወቅሰው ሀብታሙ አያሌው "አረቄያም፣ ሰውነቱ በአረቄ የተሞላ፣ በመርፌ ቢነኩት አረቄው የሚፈስ" እያለ ሲሰድበው የሚታየውም ሲመስለኝ፣ (መሰለኝ ነው) አርበኛ ዘመነ ካሴን በሕዝብ ዘንድ አስጠልቶ የእስክንድርን ስብእና ለመገንባት የታቀደ ይመስለኛል። ዶክመንተሪው ላይ ለአገኘሁ የተነገረ ይመስለኛል የሀብታሙን "እንደዚያ የወረደ ስድብ" በዚያ መልክ ማቅረብ ዶክመንተሪው ይመታ ዘንድ ለታሰበው ግብ ጠቀሜታው አልታየኝም። በአጠቃላይ ግን ትግሉን ለመጥለፍ በሚፀየፉት የዐማራ ፋኖ ትግል ውስጥ እጃቸውን ለመንከር የሚሯሯጡትን ጂጂዎች ጂጂ GG ግንቦቴና ግንባሩ ለማለት ነው ለማጠናከር ነው ዶክመንተሪው የደከመው።
፪ኛ፦በፋናው የዳዊት ዶክመንተሪ ላይ የታዘብኩት በፊልሙ ላይ "ሊያሸብሩ ሲሉ ያዝናቸው" ብለው ያቀረቧቸው ተዋናዮች በሙሉ "ከጎንደር ነው የመጣነው ከጎንደርነው እንዲህ ያደረግነው… ጎንደር፣ ጎንደር የሚል ገፀባህሪ ተሰጥቷቸው በዘጋቢ ፊልሙ ነጠላ ዜማ ላይ እንዲተውኑ ተደርገው አይቻለሁ። በተለይ ነጭ ቲሸርት አድርጎ ስለ ናሁሰናይ እና ስለ አርቲስት አዲስ ዓለም ጌታነህ የሚናገረው ልጅ (ሰሜን ሸዋ የመራቤቴ ልጅ ይመስለኛል የሆነ ቡናቤት የነበረውና የጎደፈ ታሪኩን ሲያወሩ የሰማሁም ይመስለኛል፣ እናም እርሱን ልጅ የሚያስለፈልፉበት መንገድ አስቂኝ ነው። ልጁ ሚስት እንዳለችው እየታወቀ እንዲያ መቀባጠር የጤና አይመስልም። ሲመስለኝ ወሎዬው ዳዊት፣ በወሎዬው ዳንኤል ክብረት እና በወሎዬው አቢይ አሕመድ ምክር ጀግናውን ጎንደሬ ከወንድሞቹ ከጎጃም፣ ከራሱ ከወሎ ከቤተ አምሓራው እና ከሸዋ በመነጠል እንዴት እኛ ብቻ አሸባሪ እንባላለን ዓይነት ስሜት እንዲፈጠርና ለተልእኮስ ቢሆን እንዴት ጎንደርን ብቻ እየላኩ ያስገድላሉ ዓይነት ስሜት እንዲፈጠር የፈለጉ ይመስለኛል። ሸዋን በስሱ ጠቅሰውም ታይተዋል።
፫ኛ፦ ሦስተኛው ትዝብቴ በተለየ ሁኔታ ፅንፈኛ ባሏቸው የፋኖ መሪዎች ዝርዝር ውስጥ አርበኛ ፋኖ የዋርካው ምሬ ወዳጆን ስም አላካተቱትም። አላካተቱትም ብቻ ሳይሆን ስሙንም ለመጥራት እንኳን አልፈቀዱም። አልደፈሩምም። ሲመስለኝ ምሬን ያልወነጅሉበት ዋነኛ ምክንያት ከፋኖ ትግል ገንጥለን ከፋፍለንም ትግሉን እናዳክመዋለን ብለው ስለሚያሰቡ ነው። ወይ መዳከም እቴ… እንዲያውም እኮ ይሄ የፈጠራ ድርሰት ተሳክቶ ቢሆን የፋኖ ትግል የት እንደደረሰ ማሳያ እኮ ነው የሠሩት። ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ሆነ ተቋማት የሚታዘቡት አገዛዙ አጠፋሁት የሚለው የዐማራ ፋኖ በዚህ ዶክመንተሪ ነፍስ ዘርቶ አጥፍቶ ለመጥፋት በዚህ መጠን…👇ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍
"…እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ አመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም… ማግሰኞ… የጥያቄ ቀን፣ የትምህርት ቀንም ይባላል።
ጥያቄ…?
"…ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና፦ በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።” ማቴ 21፥23
መልስ…
"…የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይን ወይስ ከሰው? አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፦ ከሰማይ ብንል፦ እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤ ከሰው ግን ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ያዩታልና ሕዝቡን እንፈራለን አሉ። ለኢየሱስም መልሰው፦ አናውቅም አሉት። እርሱም ደግሞ፦ እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው። ማቴ 21፥ 24-27
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም… መጪው ዓመት በዓልም አይደል…? የቤት ጽዳቱም የዚያኑ ያህል ከወትሮው ይለያል። ጣራ መሠረቱ ሁላ አይቀርም ሲጸዳ። እኔም ወጉ ይድረሰኝ ብዬ የቤት ጽዳት ላይ ስሳተፍ ቆይቼ አሁን ገና መምጣቴ ነው። እስከአሁን ሁላችሁም ርዕሰ አንቀጹን ያነበባችሁ ይመስለኛል። የምትሰጡትንም አስተያየት ያዘጋጃችሁ ይመስለኛል። እናም አሁን ወደ ውይይቱ መግባት እንችላለን።
"…ፀረ ዐማራ ግንቦቴዎችም፣ ኢዜማዎችም፣ አሽቄ ግንባሬዎችም፣ ሠራዊቶችም፣ አክራሪ ፀረ ዐማራ ወሀቢስቶችም፣ የፖለቲካ አገው ሸንጎዎችም፣ የፖለቲካ ቅማንቴዎችም፣ በአጠቃላይ እኔን ስታዩ፣ ስትሰሙ ቋቅ የሚላችሁ፣ የሚነስራችሁ ሁሉ በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን እኔን በመቃወም ሁላ ማንሸራሸር ሁላ ትችላላችሁ። የሚቀሰፈው ተሳዳቢ ብቻ ነው።
"…ቀንተህ ነው፣ ምንአገባህ አንተ፣ እኔን ብቻ ስሙኝ ትላለህ፣ አንተ ማን ስለሆንክ ነው፣ ውጣ ከዐማራ ትግል ወዘተረፈ የሚሉ ገተት ጥያቄዎች ከላይ በርዕሰ አንቀጹ መልስ የተሰጠባቸው ስለሆነ ባይደጋገም ይመረጣል። በውስጥ ጨርሱ፣ በውስጥ ተበጋገሩም አይሠራም። ውጪ እያለ የምን ውስጥ ነው? እገሌን መናገር፣ ሀብታሙን መተቸት ኃጢአት ነው የሚል ካለ እርሱ ገና ጥሬ ነው። አልበሸለም።
"…ይሁዳ ሐዋርያ ነበር። ሐሙስ እለት ሲክደው፣ ሱሸጠው ታየለህ። እናም ፍጻሜህን እንዲያሳምርልህ መጸለይ እንጂ በድሮ በሬ ለማረስ መሞከር ዥልጥነት ነው። እኔ ቋሚ ወዳጅ የለኝም፣ ቋሚ ጠላትም የለኝም። የሚገዛኝ፣ የሚልከኝ ፓርቲና ግለሰብም የለም። የምታመነው ለህሊናዬ፣ የምታዘዘው ለፈጣሪዬ ብቻ ነው። ተልባ ቢንጫጫ ለደንታው ነው። ወይዘሮ እገሊትም፣ አቶ እገሌም፣ ዶር፣ ፕሮፌሰር ወዘተረፈ የሚያዘኝ የለም። የምገዛለት ሀብታም የለም። ከዓላማዬ ወይ ፍንክች። በብዕሬ ብቻ አደባየዋለሁ።
"…ከምር እኔም ሳይታወቀኝ ፋኖ እኮ ነኝ። ተንፒሱ እስቲ…!
👆…ከላይ የቀጠለ…✍✍✍ "…እስክንድር ነጋን የዐማራ ፋኖ መሪ አድርጎ ለመምረጥ የዐማራ ፋኖ እንጂ መክሮ፣ ዘክሮ፣ ተወያይቶ መወሰን ያለበት እነ ሀብታሙ፣ እነ አበበ በለው መሆን የለባቸውም። እስክንድርን ያልመረጠ፣ ያልተቀበለ፣ በእርሱ ስር ያልገባ ሁሉ እንደ ማርያም ጠላት መቆጠርና መወገርም አልነበረበትም። በጎንደር ውባንተ በእስክንድር ዕዝ ስር አልገባም ስላለ ሀብታሙ አያሌው ሚድያውን ተጠቅሞ እንዴት እንደጨፈጨፈው የሚታወስ ነው። ምሬ ወዳጆ፣ አቶ አሰግድም እንዴት እንደተወገሩ የሚታወስ ነው። ዘመነ በወዳጅነቱ ጊዜ አንግሦ፣ ዘመነ ከእስክንድር ኅብረት ሲያፈገፍግ የደረሰበትን ታስታውሳላችሁ። ይሄ ልክ አይደለም።
"…እነ ሀብታሙ አያሌው ኢትዮ 360 ዎች በእስክንድር በኩል ምን እንደፈለጉ የሚያውቁት እነርሱ ብቻ ናቸው። የግንቦት ሰባት፣ የኢዜማ እና ፀረ ዐማራ ኃይሎች በሙሉ በእስክንድር ነጋ ጀርባ ለምን እንደተኮለኮሉ የሚያውቁት ራሳቸው ኮልኮሌዎቹ እና ራሱ አቶ እስክንድር ነጋ ብቻ ናቸው። ግንባሩ ብለው ሚልዮን ዶላሮችን ጦር ለሌለው፣ ሠራዊትም ሌለው እስክንድር ብቻ ይሰጥ ብለው ማዋከባቸውም ልክ አልነበረም። ግንቦቴዎች በሙሉ ገንዘቡ ያለበት ስፍራ ሰፍረው እንደ ጆፌ አሞራ መከማቸታቸውም ልክ አልነበረም። በአጠቃላይ በእኔ ግምገማ ግንቦቴዎች ከዐማራ ትግል አካባቢ ህፃናት በማይደርሱበት ሥፍራ ይቀመጥ እንደሚል መርዝ ርቀው መቀመጥ ሲገባቸው ገብተው ፈትፋች ከምን ይሆናሉ? ሓሳብ ነው እያነሣሁ ያለሁት። ዐማራ ስለሚግደረደር እኔ ቆቱው ላንሳ ብዬ ነው ሓሳቡን።
"…ጉዳዩን በውስጥ ለመፍታት ያልተሞከረ ሙከራ አልነበረም። ያልተጣረ ጥረት አልነበረም። ጭራሽ ሻለቃ ዳዊት ለግንባሩ የተሰበሰበው ገንዘብ በኢትዮ 360 የባንክ አካውንት ላይ የተሰበሰበ ስለሆነ ለግንባሩ ገንዘቡ ሲላክ የኢትዮ 360 ዎች ገንዘብ በባንኩ ውስጥ ቀሪ ሆኖ ነው መላክ ያለበት ብሎ በድፍረት እስከመናገርም የደረሰው ለዚያ ነው። ግምባሩ በይፋ ሲፈርስ አቶ አበበ በለው እና ሀብታሙ አያሌው አጋፋሪ የሆኑበት የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚል አቋቁመው አሁንም ይሄን ሕዝብ ገንዘቡን ለማለብ አዲስ የልመና ኮሮጆ ከፍተው ብቅ አሉ። ሻለቃ ዳዊት እንደተናገሩትም "…በሠራዊቱ ምሥረታ ጉባኤ ላይ አበበ በለው በስፍራው እንዳልገኝ አድረገኝ" በማለት ለመሳይ መኮንን ሲናገሩ በጋራ የሰማነው ነው።
"…እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የዛሬው የሰሙነ ሕማማት የመጀመሪያው ቀን ሰኞ "አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ይባላል። ጌታ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ካህናት መስለው፣ ዲያቆናት መስለው፣ የመቅደሱ አገልጋይ መስለው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ነጋዴዎች ገበታቸውን ገልብጦ፣ በጅራፍ እየገረፈ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን በሙሉ “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ 21፥13 በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ ያሰወጣበት እለት የሚታወስበት እለት ነው። የዐማራም ጉዳይ እንዲሁ ነው። በዐማራ ስም አስመሳይ ቀፋይ፣ ነጋዴው ሁሉ በጅራፍ እየተገረፈ የሚጸዳበት ጊዜ ነው ብዬ ነው የማምነው።
"…የዛሬዋ ሰኞ በሌላም ታሪክ ትታወሳለች፣ ትዘከራለች። "መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞም በመባል ትታወቃለች። በዚህ እለት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር አላገኘባትም “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር 11፥14 በማለት በለሲቱን የረገመባት እለት ስለሆነ በዚያ ታስቦ ይውላል። በትርጓሜ መጻሕፍት ሊቃውንቱ "በለሲቱን የእስራኤል ምሳሌ" አድርገውም ይተረጉማሉ። ይሄንንም በዐማራ ትግል በለስ የሆኑ፣ ልምላሜያቸው፣ ምላሳቸው፣ ብዕራቸው ከሩቅ አረንጓዴ መስሎ የሚታይ፣ ርቦህ ፍሬ ዘለው ብለህ ስትጠጋው ጎፈንዲያም ለሆነው የዐማራ ትግል ጠላፊ አፈ ጻድቅ ሁላ ቢተረጎም ያስኬዳል።
"…እንግዲህ ይሄ እንደ መግቢያ ነው። እንደ አፒታይዘር፣ ጨዋታ እንደማስጀመሪያ ፊሽካ ያለ ነው። ወደ ዋናው ፍሬ ቅዳሴ አልገባንም። ማኅሌቱም አልደመቀም። ይሄ የዋዜማ ቁመት ነው። የማንንም የግል ኃጢአት፣ የግል ስብእናም አልነካም። ነገር ግን በሌላው ጉዳይ ደፍሬ ሓሳቤን አውጥቼ እተቻለሁ። IRS ችግር ካልፈጠረባቸው በቀር አዳሜና ሄዋኔን በዐማራ ስም የሰበሰቡትን ማስተፋትም ቀላል ነው። ሙግታችን ትግሉ ቅዱስ ነውና አናቆሽሸው የሚል ብቻ ነው። ከተቻለ እኔና ሀብታሙ፣ እኔና እስክንድር፣ እኔና ሻለቃ፣ እኔና ዶር አምሳሉ የምንገናኝበትን መድረክም አመቻቹልን። ከተቻለ በአዲሱ ምኒልክ ቴሌቭዥንም ላይ ቢሆን ይመረጣል። ቡሩኬ አወያይ ሆኖ ቢቀርብ ተቃውሞ የለኝም። እውነት መጋፈጥ ደስ ነው የሚለኝ። በስሱ የነካሁትን በወፍራሙ ነክቼ አፈራርጠዋለሁ።
"…የሁሉም የዐማራ ግዛት ፋኖዎች (በተለይ ውባንተና ማርሸት) ቤታቸውን ኢትዮ 360ን እርግፍ አድርገው ትተው የጠላት ሚዲያ እንደሆነ እያወቁ ወደ ግንቦት ሰባት ሚዲያ ሲመላለሱ 360 ውስጥ ምን ዓይተው ነው? ምን ብለዋቸው ነው ብላችሁ መጠየቅና መጠርጠር አልነበረባችሁም ወይ? ለካ አማራጭ አጥተው ተገደው ነው ያለ አለ? የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር ሲመሰረትና ግንባሩ ፈርሶ ሕዝባዊ ሠራዊት ሲባልና በሰበር ዜና ሲወክበን የነበረው ኢትዮ 360ና ሀብታሙ አያሌው ዛሬ የት ገቡ? እንዴት ለዐማራ እየሠራሁ ነው ብሎ የትናንቱን የወሎ ገራገሩን የምሥራች አልሰማም? ብሎ መጠየቅ ነውር ነው እንዴ? የእስክንድርን ነጋን የፊት ገጽ በጭንብል አስቀርጾ በአደባባይ መታዬትና የህጻን ጨዋታ መጫዎትን ምን አመጣው? ቆይ እስክንድር ምንድን ነው? የምን መሪ ነው? ማነውስ የመረጠው? የትኛው ፋኖ ወከለው? ብሎ መጠየቅ እንዴት ያስደነግጣል? ጥያቄው መቼም ይነሣ፣ ማንም ያንሣው ለምን ያስደነግጣል? ጥቂት ምስኪን ፋኖዎችን አቁሞ የእስክንድርን ጉልበት እንዲስሙ እያስደረጉ ቪዲዮ መቅረጽና በኢትዮ 360 ማስተላለፍ ምንድን ነው ማስተላለፍ የተፈለገው? አልገብቶንም። ምን ታስቦ ነበር? ዘመነ ካሴ በትህትና እውነቱን ተናገረ። ውባንተ ችሎ ችሎ አንጀቱ ሲያር ጫፍ ጫፉን ነገረን። ለትግላችን ብዬ እንጅ ያለዚያ ሁሉንም ነገር ለሕዝብ እናገራለሁ ብሎን ነበር። በጊዜ የሚረዳው ባይኖርም ጋሽ አሰግድም በጊዜ እንቅጯን ተናገረ። የሚያሳዝነው ነገር እነ ሃብታሙ በሥራቸው አድርገው በገንዘብ እያስፈራሩ ለመምራት ዓይናቸውን የጣሉባቸው ፋኖዎች በሙሉ የዋህ ነገር ግን አልሞ ቀንዳሽ የዐማራ ፋኖዎችን ነው። እነዚህ ፋኖዎች ዐማራ ሊጠፋ እንደሆነ ገብቷቸው ልጆቻቸውን ሳይቀር ይዘው ጫካ የከተቱ የቁርጥ ቀን ፋኖዎች ናቸው። እነዚህ ፋኖዎች ስለ ፖለቲካ ርእዮተ አለም የሚያውቁት ነገር የለም። ዘራቸውን ከወራሪ መታደግና እኛ ደማችንን ሰጥተን የዐማራን ዘር ማትረፍ እንችላለን ብለው የቆረጡ ፋኖዎች ናቸው። የማራን ዕጣ ፋንታ በሚገባ የተረዱና የማሸነፊያ መንገዱንም መሬት ላይ ቀርጸው ሕዝብን አንቅተው አንቀሳቅሰው ፖለቲካዊና ወታደራዊ ትግል መምራት የሚችሉትን ግን ማታለል አልቻሉም። ሲነቃባቸው ስማቸውን ማጥፋት ጀመሩ። ውባንተ አባተ አሰግድ ወዘተ ምርጥ ምሳሌዎች ናቸው። 👇 ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍
መልካም…
"…እንደተለመደው ዛሬም 1ሺ ሰዎች በአደባባይ በዓለሙ ሁሉ ፊት፣ ሳይፈሩ፣ ሳይኮሩ፣ ሳያፍሩ፣ ሳይሸማቀቁ በደስታ፣ በሐሴት እግዚአብሔርን አመስግነዋል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ከምስጋና በኋላ ያው እንደተለመደው በቀጥታ የምንሄደው ወደ ተናፋቂዋ ነጭ ነጯን ወደምናነብበት ተወዳጇ፣ እንደ ኮሶ፣ እንደመተሬ፣ እንደ እንቆቆ እየመረረች ገብታ ወደ ምታሽረው፣ ቃሪያ በሚጥሚጣ ወደ ሆነችው ርዕሰ አንቀጻችን ነው?
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን “…እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፦ ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ?” ዘፍ 4፥6 በሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለቃል መነሻነት ይሆናል።
"…በጎንደሮች፣ በጎጃሞች፣ በወሎዬዎቹ ቤተ ዐምሓራ ዎቹ አንድ መሆን እስከአሁን በፌስቡካቸውም፣ በሚታወቁበት ሰበር ዜናቸውም እንዳልዘገቡት ሳይ፣ ጭራሽ እለታዊ የቴሌቭዥንም ሆነ የዩቲዩብ መርሀ ግብራቸውን አቋርጠው ፍራሽ አንጥፈው፣ ነጠላ ዘቅዝቀው ኀዘን መቀመጣቸውን ሳይ ጊዜ ቀኝ ትከሻዬን ቢሸክከኝ ጊዜና ያዘጋጀኋት ርዕሰ አንቀጽ ናት። ካላመናችሁኝ በየደጃፋቸው ተንከራተቱ። እስከአሁን ወፍ የለም።
"…ዛሬ ጌታ ቤተ መቅደሱን ከሻጭ፣ ከለዋጭ ነጋዴዎች የለየበት፣ በጅራፍ ገርፎ ያባረረበት ዕለት ነው። ከዐማራ እንዲሁ በስሙ ነጋዴው የተገረፈበት እለት ነው። ዛሬ ጌታ በለሷን አይቶ ፍሬ ባለማፍራቷ የረገመበት እለት ነው። የዐማራም ጉዳይ እንደዚሁ። ፍሬ ያላፈሩ ዛፍ መሳይ ቅጠሎች የሚረገሙበት እለት ነው። ዐማራም ኢትዮጵያም ይነሣሉ። ትንሣኤ ከፊት ነው። እነ ይሁዳ ከነሰበሰቡት ፈረንካ ይሰቀላሉ። አልቅሰው የሚመለሱ ጴጥሮሶችም ይጠበቃሉ።
"…ሃኣ…? ልጽፈው ነኝ…
"…ሁለቱም የጦር መሪዎች አነጋግረውኛል። የምሥራች ዜናውንም ለዓለም ሁሉ ንገርና አድርስም ብለውኛል። ለዐማሮችም መልእክት አላቸው።
"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ በጉጉት በምትጠብቁትና ዘወትር ሳምንት እሁድ እሁድ በመረጃ ተለቭዥን በሚቀርበው "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" በተሰኘው መርሀ ግብሬ ላይ ድምጻቸውንም፣ መልእክታቸውን አሰማችኋለሁ። የምሥራቹንም አበሥራችኋለሁ።
"…ሳስበው፣ ሳስበው የኢትዮጵያንም ትንሣኤ በዚህ መልኩ የማበሥራችሁ ነው የሚመስለኝ። በድጋሚ እንኳን ደስስ አላችሁ…!
• ሸዋ ሰምተሃል…!
"…በኦሮሚያ እየሰለጠኑ ከሚገኙት ልዩ ኮማንዶዎች ብዛትና ጥራት የተነሣ መጪው ክረምት ለዐማራ ፋኖ እጅግ ሳይከብደው አይቀርም የሚሉ መተርጉማን አሉ።
• ፋኖ ሆይ ምን ተሻለህ…? ወይ በጊዜ እጅ ትሰጥ ይሆን…? 🙏🙏🙏
መልካም… እሺ የዛሬውን የእኔ የአህያው የዘመዴን ርዕሰ አንቀጽ እንዴት አገኛችሁት…?
"…ከቆይታ በኋላ የዛሬው የመረጃ ተለቭዥን መርሀ ግብራችን እስኪ ጀምር ድረስ የልብ የልባችንን እያወጋን እንቆያለን።
"…ርዕሰ አንቀጽ"
• አህያ…!
"… ዛሬ የሆሣዕና በዓል ነው። ታስረው የነበሩና በጌታ መፈታት ስለሆነላቸው አህዮች በዓለሙ ሁሉ የሚሰበክበትም ዕለት ነው። በሰልፍና በጦርነት በክብርም ዘወትር በአደባባይ የሚታዩት ፈረሶች ያልተመረጡበት። ኢየሩሳሌም ለመግባት መንገድ የጀመረው ጌታ ለጉዞው አህዮችን የመረጠበት ዕለትም ነው ዛሬ።
"… ሳያቀምሷት ለአህያ ማር አይጥማትም እያሉ ሰዎች የሚያሟት አህያ መሃሪውን ጌታ የተሸከመችበት፣ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከእመቤታችን ቀጥሎ ጌታን በጀርባዋ ለመሸከም ልዩ ዕድል እና ፀጋን ያገኘችበት፣ ሐዋርያት ልብሳቸውን እያነጠፉ ሕዝቡም ሁሉ ዘንባባ እየነሰነሱ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ እየዘመሩ በደስታ በዝማሬም ታጅባ የከበረችበት ዕለት ነው አህያ…
"… አህዮቹ በሌባ ተሰርቀው በመንደር በድብቅ የታሰሩ ነበሩና ይህን የሚያውቅ ጌታ ከእሱ በተላኩ ሐዋርያት ከእስራታቸው ተፈተው ጌታን ለመሸከም የተመረጡበትም ዕለት ነው የዛሬው እለት። በድሆች መንደር በቤተ ፋጌ የሆነውም ይሄው ነው። በልደቱ እለት በዚያ በብርድ ወራት በቤተልሄም ከተማ በከብቶች በረት እርሱ አምላካቸው መሆኑን አውቀው በእስትንፋሳቸው ያሞቁትን አህዮች ውለታ ከፋዩ ጌታ ቀን ጠብቆ ዘመን ቆጥሮ፣ ሲመሽ ወደ ማታ ዛሬ ብድራታቸውን ከፈለ። በበረት ውስጥ የገበሩለትን እስትንፋስ በአደባባይ አክብሮ አስከብሮ መለሰላቸው። ለአህዮች።
"… ጌታ ሲወለድ ከሰዎቹ ቀድመው አህዮቹ ናቸው ያወቁት። ከሰብዓሰገል ወርቅ ዕጣን ከርቤ በፊት እስትንፋሳቸውንም የገበሩለትም አህዮቹ ናቸው። በስደት ዘመኑም አህያ አልተለየችውም። ከእስራኤል እስከ ኢትዮጵያና ግብጽ ድረስ አብራው ደክማለች አህያ። የሚገርመው በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ አህዮች ከጀርባቸው ላይ የመስቀል ምልክት መኖሩ ነው። መስቀል ደግሞ መከራ ነው። እንደ አህያ በዚህ ምድር መከራንና ፍዳን የሚቀበል ማን አለ? አህያ ከጀርባዋ የተሣለላት መስቀል የማያስችለው የለምና መከራን እንድትታገስ አድርጓት ቢሆንስ? ባለቤቷ እስላም ይሁን ክርስቲያን፣ ሂንዱ ይሁን ቡድሀ፣ አይሁድ ይሁን ኢ አማኒ ብቻ አህያው ከጀርባዋ መስቀል አላት። መስቀል።
"… ቤተ ፋጌ አህዮቹ ተሰርቀው እና ታስረው የተገኙበት የድሆች መኖሪያ መንደር ናት። በድሆቹ መንደር በሌቦች ታስረው የነበሩ አህዮች የነበሩበትን የድሆች መንደር ነው ጌታ የወደደው። ሐዋርያቱን ሂዱና በሌባ ተሰርቀው ታስረው የሚገኙትን አህዮች ፈታችሁ አምጡልኝ ብሎ አዝዞ አህዮቹን ከእስራታቸው አስፈትቶ አምጥቶ ሳያስቡት ክቡር የሆነው ጌታ አክብሮ አስከበራቸው።
"… ቤተ ፋጌ ለእየሩሳሌም በጣም ቅርብ ናት፡፡ የተመሳቀለ መንገድ ላይ የምትገኝም መንደርም ናት። እዚህ መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆሞ ነው መስቀል ላይ ወደሚውልባት ኢየሩሳሌም ይወስዱት ዘንድ አህዮቹን የመረጠው። ብዙ ያልታሰሩ በሜዳው የሞሉ አህዮች ቢኖሩም ጌታ የመረጠው ግን በሌባ ተሰርቀው በድብቅ ተሸሽገው የነበሩትን አህዮችን ነበር።
"… ጌታ ሐዋርያቱን ሲልካቸው እንዲህም ብሏቸው ነበር። የታሰረ አህያ ፈትታችሁ ይዛችሁ ስትመጡ "ምን ታደርጋላችሁ? የሚላችሁ ሰው ቢኖር "ጌታቸው ይሻቸዋል" በሉአቸው ነበር ያላቸው። ደግሞ ሌባ የሰረቀው አህያ ሁለት ብርቱ መጥቶ ሲፈታቸው እንደ ባለቤት አይንጫጫም። ሌባ ነውና ጣጣ ቢያመጣበትስ? ዝም፣ ጭጭ ከማለት ውጪ ምን አፍ ይኖረዋል? ምንም።
"…ሐዋርያቱም እንደታዘዙት አደረጉለት። አህያዋንና የአህያዋን ውርንጫም አመጡለት። ከአህያዋ ጀርባም ሐዋርያቱ ልብሳቸውን አነጠፉለት። አህያ ዓለሟን አየች። የዘመናት መጨቆን፣ የዘመናት መወገር ለአንድ ቀንም ቢሆን ቀረላት። የሐዋርያትን ልብስ ለበሰች። ታድላ። በሐዋርያት ልብስ ላይ ጌታ ተቀመጠ። ታድላ። ሕዝብና ሐዋርያቱ ዘንባባና ልብሳቸውን አነጠፉ። ለጌታ ቢሆንም አህያዋም ጌታን ተሸክማለችና በሐዋርያቱ ልብስ ላይ እየተረማደች እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ተጓዘች። የዚያን ቀን የመታት፣ የሰደባት አልነበረም። ታድላ።
"…በዚህ ዕለት ፈረስም፣ ኮርቻም አልተመረጡም። ፈረስም ጦረኛ ነው። ኮርቻም ይቆረቁራል። ሁለቱም አልተመረጡም። ለስላሳ ሕግ ሊሠራልን እንደወደደ በኮርቻ ፈንታ ሐዋርያት ልብሳቸውን አነጠፉለት። አንተ ለስላሳ የፍቅር አባት ነህ ሲሉ ነው እንዲህ ማድረጋቸው፡፡ ለስላሳ ሕግ የተባለው ደግሞ ሕገ ወንጌል ነው። ወንጌል ፍቅር ናት። የሚረግማችሁን መርቁ ትላለችና፡፡ ልብስ የሰውነት ነውር እንዲሸፍን አንተም ነውር ኃጢአታችንን፣ በደል አበሳችንን የምትሸፍንልን አምላክ ነህ ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት። እወነትም ነውራችንን የሚሸፍንልን እሱ ነው፡፡
"…እንደ ሊቃውንቱ አስተምህሮ ጌታችን በሁለቱ አህዮች በአንድጊዜ በጥበብ ነው የተቀመጠው። በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የሚቻል ጥበበኛ፣ ሁሉን የሚችል አባት በመሆኑ እንዲያ አደረገ። አንድም ወንጌልን ኦሪት እና ሀዲስን ሁለቱ ኪዳናት አስታርቆ እና አስማምቶ አንዱ አንዱን እየመገበ እንዲሄድ አድርጓልና በሁለቱም ተቀመጠ።
"…አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።” ዘካ 9፥9 የሚለውም የነቢዩ ትንቢት ፍጻሜውን ማግኘት ስለነበረበት በአህያ ላይ መቀመጡ ግድ ነበር።
"… በበረት እንደተወለደ በአህያም ላይ ተቀምጦ ትህትናን አስተማረን። ፈረስ የጦር ምልክት ነው። መጪው የሰላም ዘመን ነው ሲል በአህያ ተቀመጠ። ፈረስ ሯጭ ነው። ሽምጥ ይጋለበብበታል። የበረታ ብቻ ነው ፈረሰኛ ላይ የሚደርሰው። እሱ ግን ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና እና በየዋህነት ለሚኖሩ መእመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል ረጋ ብላ በምትጓዘው አህያ ላይ ተቀመጦ መሄድን መረጠ። ምክንያቱም አህዮች ትሁታን ናቸው። ረጋ ብለው ነው የሚሄዱት። አይሮጡም። በቀላሉም ይወጣባቸዋል። በቀላሉም ይያዛሉ። እንደፈለግንም እናዝዛቸዋለን። እኛስ? በቀላሉ ለጌታ እንታዘዛለን?
"…ትልቋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ናት። ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት። ሕገ ኦሪትም የተለመደች ሕግ ናትና፡፡ በትልቋ አህያ ተቀመጠ። ትልቋ አህያ የእስራኤል ምሳሌም ናት። ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ሕግ ለመፈጸም በሕግ ለመራመድ የለመዱ ናቸውና፡፡ ትልቋ አህያ የአዳም ምሳሌ ናት። አባታችን አዳም ሸክም የበዛበት ነበር ሸክሙን ሊያራግፍለት። ከዲያብሎስ ከሠራቂ ሌባው ነፃ ሊያወጣው እንደመጣ ሊያጠይቅ በትልቋ አህያ ተቀመጠ።
"…ውርጭላዋ በሕገ ወንጌል ትመሰላለች። ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት እና የሠራት አዲሲቱ ሕግ ናትና፡፡ ውርንጫይቱ በአህዛብም ትመሰላለች። ምክንያቱም ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች እንዳይደለች ሁሉ እንዲሁም አህዛብም ሕግን የመቀበል የለመዱ አይደሉም፡፡ ለሕጉም አዲስ ናቸውና፡፡ ውርንጭላይቱ የእመቤታችንም ምሳሌ ናት። የዓለምን ሸክም ለማቅለል የተመረጠች እናት ናትና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ናት። የዓለሙን ፈጣሪ እግዚአብሔር ወልድን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከንም ነውር ነቀፋም የሌለባት እናት ናትና፡፡ ህዝቡም ልብሳቸው እያወለቁ በጎዳና አነጡፉለት ለምን? እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያም ክብር ይገባታል ብለው አነጠፉለት። እስራኤላውያን ጌታ የተቀመጠባትን አህያ አከበሩ፡፡ ጌታ የተቀመጠባትን አህያ ያከበረ ሰው ጌታን