መልካም… ጠዋት ጠዋት እግዚአብሔር ይመስገን እያለ በማመስገን ቀኑን አሳምሮ የሚውለው የእኔ የቴሌግራም ቤተሰብ የሚፈለገውን ቁጥር አሟልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። እንግዲህ በመርሀ ግብራችን መሰረት ከምስጋናው በመቀጠል የምናልፈው እንደተለመደው ወደ ተወዳጇና ተናፋቂዋ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።
"…በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ስለ አህያ መጻፍ አማረኝ። አንዳንድ በንግግሬ፣ በጽሑፌ እና በአመለካከቴ የሚከፉብኝ የነፃ አውጪ ድርጅት አባላት ብዙ ጊዜ ጮክ ብለው የሚሰድቡኝ "አንት አህያ፣ ሀድጊ፣ ሃሬ" እያሉ ነውና ስለ አህያ ልጻፍላቸው ወደድኩ።
"…አህያው ዘመዴ የሚጽፈውን ለማንበብ እናንት ሰው የሰው ዘሮች ዝግጁ ናችሁ? እስቲ አንድ መቶ ያህል ሰው ዝግጁ ነኝ ይበለኝማ።
• ዝግጁ…?
ጸሎት…
"…እሺ… እንዴት አመሻችሁ…? በወር ሁለት ቀን ከራየን ወንዝ ማዶ የምንኖር ስደተኞች ሰብሰብ ብለን የምንጸልይበት እለት ነው። እዚያ አምሽቼ አሁን ገና በኦቶቢሲ ማሞ ካቻ ተሳፍሬ ወደ ዋሻዬ እየተመለስኩ ነው።
• ሰፈር መንደሩ እንዴት አመሸ? አማን ነው ቀዬው? ደግሞ ያንተ ነፍስ ይማራል እንዴ? በለኝ አሉህ… ሃኣ…! 😂
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ጥያቄአዊ ርዕሰ አንቀጽ ነው። ጠያቂ እኔ ዘመዴ ነኝ። ተጠያቂ ደግሞ እናንተ ዘመዶቼ። 😂
"…በመጀመሪያ ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ቢል የተጀመረው የዐማራ ፋኖ ትግል ከድል ደጃፍ ሳይደርስ አይቆምም። አይገታምም። መውደቅ መነሣት፣ መጓተት፣ መነታረክ ሊኖረው ይችላል። እሱ ደግሞ ተፈጥሮአዊ ነው። እንኳን በብዙ በደልና ግፍ ተገፍቶ የህልውና ትግል ውስጥ ተገድዶ የገባው ዐማራ ይቅርና ሀገር ለመገንጠል፣ ሕዝብ ለማፋጀት 7 ሆነው ጫካ የገቡት ወያኔዎችና የኤርትራ ሰዎች 17 እና 30 ዓመታትን ፈጅተው የልባቸውንም መሻት ፈጽመው የለም እንዴ? እናም ይሄም ንፁህና በሃቅ የተሞላው የዐማራ ፋኖም ትግል የፈጀውን ፈጅቶ፣ የወሰደውን ጊዜ ወስዶ ማሸነፉ እንደሁ አይቀርም። ይሄን እርግጠኛ ሆኜ ነው የምናገረው።
"…የዛሬው ጥያቄ ለእናንተ ነው። የዐማራ ፋኖ ችግር ውሳጣዊ ሳይሆን ውጫዊ ነው። ይሄን ውጫዊ የሴራ ፖለቲካ ትግል በውስጥ ለመፍታት ለዓመታት ተሞክሯል። ነገር ግን አሁን ከአቅም በላይ ሆኗል። ይሄ ጉዳይ ወደ ሕዝብ መጥቶ ሕዝብ ካልተወያየበት ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ እልቂት በጀግኖች መካከል ይፈጠራል። እናስ ምን ታስባላችሁ? ይነገር አይነገር?
"…ደፋር ሆነን ያበጠው ፈንድቶ ሰላም ማግኘት ይሻላል ወይስ እየተቋሰሉ የፋኖን እልቂት መጠበቅ? ከዚያ ኋላ ኘላይ ቀደም ብላችሁ ብትነግሩን ምን አለበት ብሎ ጓ ማለት ይሻላል ወይስ አሁን በጊዜ ሰምቶ በጊዜ መፍትሄ መፈለግ? ምርጫው የእናንተ ነው።
"…በጥባጩን መክሮም፣ ዘክሮም፣ ገስጾም ልክ ማስገባት፣ መስመር ማስያዝ ነው የሚያስፈልገው ወይስ ከነ ፈንገሱ ሊጡን እንዲያቦካ መፍቀድ? የቱ ይሻላችኋል? ከሕዝብ በተዋጣ ዶላር የግል ፋኖ መግዛትስ ለዐማራ ትግል ምን ይረባዋል?
•ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
“…ክፉ ለማድረግ የሚያስብ ተንኰለኛ ይባላል።” ምሳ 24፥8 "…ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፤ ዘለፋን የሚጠላ ግን ደንቆሮ ነው። ደኅና ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል፤ ተንኰለኛውን ሰው ግን ይቀሥፈዋል። ምሳ 12፥ 1-2
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ገና በሽታውማ አትስከሩ…!
"…ሲጀመር ገና ምኑንም አልተናገርኩም። አላወራሁም። አላሳየሁም። ነገር ግን ወዴት እንደምሄድ የገባው ፀረ ዐማራ፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስት ምድረ ግንቦቴ ሁላ መስቀል እንዳየ ፀበም እንደነካው አጋንንት እምቧእሪቁቀምበጭ ማለት ጀምሯል። ምኑ ተያዘና ነው የምትለፈልፈው።
"…በእርቁ ሰዓት ዋነኛው የፋኖዎች ችግር የነበረው ሁሉ በድምጽ የተቀዳ፣ ሽማግሌዎቹ ሁሉ ያዘኑበት፣ በመሬት ላይ ያለው ፋኖ የሚያደርገው የሚሠራው የጠፋበት፣ በእስክንድር በኩል ተጠግተው የመጡት ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ገና ለገና ብልፅግና መውደቁ አይቀርምና እኛ ከአሁኑ የራሳችንን ፋኖ ገዝተን አዘጋጅተን ቦታ ሥልጣን መያዝ አለብን በማለት በማወክ ፋኖን በጋዜጠኝነት ስም አሸማቀው መድረሻ ለማሳጣት የተኬደበትን ርቀት ይፋ አወጣዋለሁ።
"…ለሽምግልና የተጠራን ሽማግሌዎች በምንችለው ሁሉ ፋኖዎችን ተማጽነን በስግብግቦች ሴራ ምክንያት ደም እንዳይፋሰሱ አድርገናል።
"…እኔ እዳ የለብኝም። በኋላ ከተጠያቂነት ለመዳን አሁኑኑ የችግሩን ሰንኮፍ ውልቅ አድርጎ ማውጣት ያስፈልጋል። ሽመልስ ለገሰን እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁ። ተናግሮ እንድናገር ስላደረገኝ አመሰግነዋለሁ።
"…በተረፈ ቀንተህ ነው፣ ምናምን ለእኔ አይሠራም። በምኑ ነው የምቀናው? የዐማራ ፋኖን መከራና ሙጀሌ ግን በመረጃ እና በማስረጃ ሰንኮፉን ነቅለን እናወጣዋለሁ።
"…ሺ ሆነህ ና፣ ተደራጅተህ ና፣ ተሰባስበህ ና እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር ዱቄት ነው የማደርግህ። ምድረ መኒ ላውንደሪ፣ ገንዘብ አጠባ ላይ የተሰማራህ የደም ነጋዴ የዶላር ቀበኛ ሁላ አሁን ነው የሚለይልን።
"…እኔ አንድም አጋዥ ሰው አልፈልግም። ግንቦቴዎች ልትሞግቱኝ ትችላላችሁ የሰው አይን የሚያቆሽሽ የተለመደ ነውረኛ ስድባችሁ ግን ያስቀስፋችኋል።
• ሰምተሃል…!
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…የጎንደር ፋኖዎችን ዕርቅና ወደ አንድ መምጣት፣ የሸዋዎቹ ፋኖዎች የእርቅ ሥርዓቱን ፈጽመው ነገር ግን ንብረትን በተመለከተ መቋጨት ያልቻሉበትን ጉዳይ በዚያም ምክንያት የሽምግልናው ጉዳይ ፍጻሜ ያለማግኘቱ አሁን የፈጠረውን ውጥረት፣ አጠቃላይ የሽምግልናውን ሂደት እና ውጣውረዱንም ሁሉ በተመለከተ እዚህና እዚያ የሚወራውን ሁሉ ለማጥራት የፊታችን እሁድ "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" በተሰኘው በመረጃ ቴሌቭዥን የቀጥታ ሥርጭት በሚተላለፈው መርሀ ግብሬ ላይ እነግራችኋለሁ። ከጎንደሮች መስማማት በኋላ ቅር ያላቸው ጎንደሬዎች፣ የግንባሩም፣ የሠራዊቱም፣ የግንቦቴም ሰዎች እያየሁ ነው። አገዛዙም ከጎንደሮች አንድ መሆን በኋላ ያለ የሌለ ኃይሉን በማሰባሰብ ወደ ጎንደር በመላክ እየተፍጨረጨረ ይገኛል። ሁሉንም የፊታችን እሁድ በሰፊው እመጣበታለሁ።
"…ለዛሬ ግን አረመኔው የአቢይ አገዛዝ ቀጥሎ ስለሚያስበው ሴራና ቁጭ ብሎ ስለሚሸርበው፣ ስለሚጎነጉነው ትብታብ ቀኝ ትከሻዬን ስለሚሸክከኝ ቀጣይ እቅድ ለማውራት ልሞክር ነኝና በጥሞና አንብቡኝ። ተከታተሉኝ። የኦሮሙማው ብልፅግና ሁልጊዜ የሚያቅደው እለታዊ ዕቅድ ነው። ለሳምንት እንኳን የሚቆይ በመርህ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ዕቅድ ማቀድ እንኳን አይችልም። ብቻ ዛሬን ሥልጣን ላይ አውሎ የሚያሳድረው ካገኘ፣ ለነገ ሌላ እቅድ አውጥቶ እግሩ ወደ መራው ሄዶ ወይ ሠርቶ፣ አልያም ሰርቆ፣ ወይ ደግሞ ለምኖ እንደሚበላ ምስኪን ሰው ነው የብልጽግናው ኑሮ። አምላኬ ሆይ የእለት አጀንዳዬን ስጠኝ። በዚህ ስሸነፍ የቱኛውን ካርድ ልምዘዝ እና ምን አልባት የማሸንፍበት አማራጭ ካለኝ ልሞክር ሲል ነው ሲቃዥ የሚያድረው።
"…በምሳሌ እንመልከተው። ለምሳሌ የአዲስ አበባው የእነ ፋኖ ናሁሰናይ ኦፕሬሽን ሲያስደነግጠው ብልፅግና ወዲያው የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቶ ህወሓት ላይ ሄዶ ነው የተለጠፈው። የህወሓት እና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ሳይቀር የኦፕሬሽኑን ጀብድ አሟሙቀው ማውራት የምር አስደነገጠው። ህወሓት እንኳ ያልሞከረችውን ፋኖ እንዴት ሞከረው ብለው ማርገብገባቸው አቃጠለው። አስደነገጠውም። ለዚህ ነው ህወሓት በዐማራ ላይ ያላትን ነገር ስለሚያውቅ እያለከለከ ሂዶ የጠራት። ዐማራንም ያስወረራት። ደግሞ ጨነቀው። ህወሓት ከአላማጣ ራያ እንዳታልፍ፣ ከዐማራ ፋኖም ጋር ተጣምራ ወደፊት እንዳትገፋ ከመከላከያ እርዳታ ውጪ ወደፊት መግፋት እንደማትችል አሳይቶ ወደፊት እንዳትመጣ እዚያው አንቆ ያዛት። በዚህች እቅድ አሁን ተንፍሷል። ግን ደግሞ እንቅልፍ የለውም።
"…የአቢይ ብልፅግና በዚህም አያቆምም። ሌላ አጀንዳ ይከፍታል። ከሱማሌ ጋር ንትርክ ውስጥ ይገባል። አምባሳደር ያባርራል፣ አምባሳደሩም ይባረራል። እሱ ሱማሌን ለሁለት ቆርጦ ካርታ ሠርቷል። ሱማሌዎቹም አሁን በሚዘገንን መልኩ ከኢትዮጵያ ቆርሰው አዲስ ካርታ ሠርተው ለቅቀዋል። ይሄን አስመልክቶም የኦሮሞ ሰዎች በተደፈርን ስሜት መንጫጫት ጀምረዋል። ቀጥሎ ሱማሌ የኢትዮጲያ ኤንባሲ ህንጻ ላይ የቦንብ ጥቃት ፈጸመች፣ አልሸባብ እና ሱማሌ አንድ ላይ ተጣምረዉ ኢትዮጵያን ለመውጋት ተስማሙ፣ ሱማሌ የኢትዮጵያን መሬት ይሄንን ያህል ኪሜ ገብታ ያዘች በማለት ማስጮህ ይጀምራል። ምን አልባት ከዚህ ከፍ ያለ የራሱን ሸኔ ፊታቸውን ሸፋፍኖ አልሸባብንም አስመስሎ በባሌ አካባቢ ክርስቲያኖችን ይገድል እና የእምነት ጦርነት የማስነሳት ሴራም ሊሠራ ሁሉ ይችላል።
"…አልሸባብ በኢትዮጵያ ገብቶ በባሌ ውስጥ እንዳለ ያስወሩት የኦሮሞ አክቲቪስቶች ናቸው። አልሸባብን እንደ ሃይማኖት ስላዩት የኦሮሞ እስላሞችም የባሌውን አልሸባብ በገፍ በመቀላቀላቸው ክርስቲያኖቹ እነ ጉማ ሳቀታ ጭምር አደገኛ አዝማሚያ በማለት ሲቃወሙት ታስታውሳላችሁ። እናም ያ አልሸባብ የተባለው ራሱ ኦነግ ሽሜ ሊሆን ሁላ ይችላል። ስለዚህ የእለት አጀንዳ ፈጥሮ ትኩረት ለማስቀየስም መንደፋደፉ ስለማይቀር ሁሉም ሰው ሊነቃበት ይገባል። የአቢይ ብልፅግና እስኪወገድ ድረስ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ያሉበት አዳዲስ አጀንዳዎች እየፈበረከ ሊያከፋፍል ስለሚችል ሊያስደነግጥ አይገባም።
"…ሌላው ዐማራው በጀመረው በራስ አቅም በመተማመን መንገድ መዝለቅ ነው ያለበት። ዐማራው የትግሬን አክቲቪስቶች ሙገሳና መደነቅ እየሰማ መደንዘዝ የለበትም። የትግሬና የኦሮሞ አክትቪስቶች ውሎአቸውን ማየቱ ብቻ በቂ ነው። በዩቱዩባቸው ሲወያዩ፣ ሲደሰኩሩ የሚውሉት በሙሉ የዐማራ ጠላቶች፣ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን ባዮች መሆናቸውን ስታይ መጠርጠር አለብህ። ሁለቱ ለጋራ ዓላማ ይደማመጣሉ፣ ዋና ታርጌት ጠላታቸው ይታወቃል። ዐማራው ነው። ድንገት እግር ጥሎ ላያቸው መንግሥትን ይወቅሳሉ። ነገር ግን ደግሞ ሸኔን ይደግፋሉ። ትግሬዎቹ ዐማራን የማሸነፊያ ዋነኛ መንገድ አድርገው የሚጠቀሙት በለመዱት ማታለል፣ ተለሳልሶ በመጠጋት የለዘቡ ቃላቶችን በመጠቀም፣ በማዘናጋት ውዳሴ በስሱ በማቅረብ ማጃጃልን ነው። በአዝማሪ ግጥም ሲኮፈስ የሚውል ዐማራን በማማለል ማደንዘዝ ይፈልጋሉ። እውነታው ግን ሌላ ነው። መርዞች ናቸው።
"…የዐማራን ፋኖ ሲያወድስ የምታየው ስታሊን የዐማራ ፋኖን በጠላትነት ፈርጆ ከአገዛዙ እኩል ሊዋጋው የሚፍጨረጨረውን ኦነግ ሽሜን ሲደግፉት፣ ሲያወድሱት፣ ሲሟገቱለት ታያለህ። ይሄ የትግሬ አክቲቪስት ፍጥጥ ያለ ስግጥና የሚታይበት እባብነታቸው ነው። በእነርሱ ብቻ እባብነቱ ቢቀር መልካም ነበር። የትግሬዎቹ አክቲቪስቶች ይሄንኑ እባብነት፣ መርዝ በጉንጭ ደብቆ መንቀሳቀስን እንደ ምርጥ የትግል ስልት ቆጥረው የኦሮሞቹንም አክቲቪስቶች በማሰለሰጠን በተመረጡ ቃላት ለነሱ በሚመች መንገድ ፋኖን እንዲያደንቁ ሲያስደርጉ ታያላችሁ። ይታያችሁ ኦነግ ሽሜ ፋኖን ሲያደንቅ።
"…የጠላት ምክር አይጠቅምም። አጥፊህም ነው። ይህን በተመለከተም መጽሐ ሲራክ እንዲህ ይለናል። "…መካር ሁሉ ይመክራል፤ ነገር ግን ራሱን ይጠቅም ዘንድ የሚመክር አለ። ከሚመክርህ ሰው ልቦናህን ጠብቅ። ስለ ራሱ ይመክርሃልና፤ ይወድድህም ዘንድ አስቀድመህ ፍላጎቱን ዕወቅበት። ገንዘብህን የሚያጠፋብህን ነገር ያመጣብሃል፥ በጎ ነገር አደረግህ ይልሃል፤ በተቸገርህም ጊዜ አይቶ ይስቅብሃል። ከሚጠባበቅህ ሰው ጋር አትማከር፤ ለሚመቀኝህም ሰው ነገርህን ሰውር።" ይልሃል። ለእኔ የወያኔና የኦነግ ምክር ለዐማራ ፋኖ አጥፊው ነው ባይ ነኝ። የኦነግና የወያኔ ብቻ ሳይሆን ራሱ በዐማራው ትግል ውስጥ የተሰገሰጉቱ ክፉ መካሪዎች ሁሉ አይጠቅሙትም እና ከውስጥም ከውጭም ጠላት በማራቅ ይጠበቅ።
"…ዐማራ "ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ድሪ ይሆንልሃልና።" ምሳ 1፥8። የተባለው የባዕድ፣ የጠላት ሳይሆን የወዳጅ፣ የእናትና የአባቱን ምክር እንዲሰማ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ምክር ከእግዚአብሔር ነው። "የጥበብ፥ የማስተዋል፥ የምክር፥ የኃይል፥ የዕውቀትና የእውነት መንፈስ ከእግዚአብሔር ነውና። ኢሳ 11፥2። የሚገርመው ነገር እግዚአብሔር የሽማግሌዎችን ምክር ያውቃል። ኢዮ ፲2፥20። ብዙ ጊዜ በሐሰት፣ በተንኮል የተሸረበ፣ የተመከረ ምክር ፈራሽ ነው። "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም፤» እንዲል፦ የማይጸናውንም ምክር እርሱ ያውቃል። ኢሳ 7፥7 …👇 ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍
“…በከረጢትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት ሚዛን አይኑርልህ። በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት መስፈሪያ አይኑርልህ። ይህን የሚያደርግ ሁሉ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ። ዘዳ 25፥ 13-16
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…አይኔን ተጠራጥሬ ፎቶውን አቅርቤ አፍጥጬ አየሁት… ምንም የተጻፈ ነገር አይታየኝም። እናንተስ የሚታያቸሁ ነገር አለ ወይስ ስታይል ነው…? 😂
Читать полностью…"…ሳምንታዊው የእለተ ሐሙስ የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ መርሀ ግብራችን እስኪጀምር ድረስ አሁን ደግሞ ተራው በርዕሰ አንቀጹ ላይ ብቻ የራሳችሁን ሓሳብ የምታክፍሉበት ሰዓት ነው።
• ተንፒሱ…!
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ "…ብዙ ድምጾች ዐማራ አንድ ይሁን፣ አንድነት ያምጣ፣ ወደ አንድ ይምጡ ሲሉ ይሰማሉ። ዐማራ አሁንም አንድ ነው። አንድ የሆነው ደግሞ የግዱን ነው። ወዶ ሳይሆን በግዱ፣ ተገድዶ ነው። ተቀፍድዶ፣ ተዠልጦ ነው። አሁን ዐማራን አንድ ለማድረግ መጣር ብዙም አያስፈልግም። ስብሰባ፣ ወርክሾፕ፣ ሲምፖዚየም አያስፈልግም። መከራው ራሱ ወዶ ሳይሆን በግዱ አንድ ያደርገዋል። ከጥቂቶች ያውም በጣት ከሚቆጠሩ በቀር በእምነት እስላም የሆነው ዐማራ እና ጴንጤው ዐማራ እኮ በኦርቶዶክስ ዐማራው ጥላቻ ታውረው ከጠላት ጋር አብረው ተሰልፈው የቆዩ ናቸው። እስላሙ ዐማራማ የኦሮሞው እስላም ማይክራፎን ሆኖ ሲያገለግል እኮ ነበር። ከኦሮሙማ ይልቅ የዐማራ ፋኖን ይታገል የነበረው እኮ የዐማራ እስላም እኮ ነበር። በተለይ የወሎ እስላም እልል የተባለለት የኦሮሙማው አቃጣሪ ሆኖ የኦሮሞው ወሃቢይ እንደ ኮንዶም ይጠቀምበት የነበረ ነበር። ለምን ይዋሻል? የወሎ እስላምን ከኦሮሙማው የወሃቢይ እስላም ሴራ ለማላቀቅ የደከመ ዐማራ አላስታውስም። የወሎ ዐማራን ወደ ዐማራ ትግል የመለሰው፣ ያመጣው እኮ የራሱ የኦሮሙማው ሰይፍ የዐማራን እስላም በመጨፍጨፉ እኮ ነው። በወለጋ ኦነግ፣ በወሎ ወያኔ ገልባ ገልባ ስትለበልበው፣ ስትገርፈው ነው እኮ እየተቅለሰለሰ፣ እየተሽኮረመመ ወደ ዐማራ ትግል የገባው። ዋናው ነገር እስላም መሆኑ ሳይሆን በጠላት የሚያጠፋው ዐማራ መሆኑ ስለገባው እኮ ነው ዛሬ በሳይበሩም በከተም በሪውም የወሎ እስላም ዐማራ ግርር ብሎ ወደ ዐማራ ፋኖ ትግል ገብቶ አየተዋደቀ የሚገኘው። ዛሬ ላይ የዐማራ እስላም ቁጥር አንድ ታጋይ እንዲሆን የተደረገው እኮ በመከራ በራሱ ነው። እናም ዐማራን አንድ ለማድረግ አሁን መድከም አስፈላጊ አይደለም። መከራው ራሱ የግዱን አንድ ያደርገዋል። ወዶ ሳይሆን በግዱ አንድ ይሆናታል አልኳችሁ። አለቀ።
"…ዐማራ በመገገም፣ ክችች በማለት ነው ህልውናውን የሚያረጋግጠው የሥልጣን ባለቤትም የሚሆነው። ዐማራ እንደዚያ ሲሆን ብቻና ብቻ መሆኑን ዐውቆ ወጥሮ ሲታገል ብቻ ነው የሚያሸንፈው። አሁን መግደርደር፣ መልመጥመጥ፣ መወላወል፣ መቀላመድም ለዐማራ አያስፈልገውም። ዝም አለ አላለ፣ አርፎ ተቀመጠ አልተቀመጠ፣ ፀባይ አሳመረ አላሳመረ፣ አቃጠረ አላቃጠረ፣ ባርያ፣ አሽከር፣ ገረድ ሆነ አልሆነ፣ እግርም ሳመ አልሳመ፣ ተለማመጠ አልተለማመጠ ዐማራ እንደሁ በትግሬ ነፃ አውጪም ሆነ በኦሮሞ ነፃ አውጪ መታረድ፣ መታደን፣ መሞቱ፣ መዋረዱ፣ መሳደዱ፣ መፈናቀሉ አይቀርለት። እናም መፍትሄው የሞተው ይሙት፣ ያለቀው ይለቅ ዐማራ ግን በዓላማው ድርቅ፣ ክችች፣ ቀጥ ብሎ ባላየ ባልሰማ ወደ 4ኪሎ ብቻ። ዐማራ ሥልጣን ሲይዝ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚለውን የስልጤ በጭባጫ፣ የትግሬ መጋጫ፣ የኦሮሞ አልጫ፣ የጴንጤ ፍጥጫን፣ የወሃቢን ግልምጫ እርሳው። እነሱ ያላፈረሷትን ኢትዮጵያ ሰንደቋን በእጁም፣ በግንባሩም አስሮ የሚመጣው ዐማራ እንዴት ሆኖ ነው የሚያፈርሳት? ሌባ ሁላ አልኩህ። ምድረ አጭቤ በጭባጫ ሁላ…
"…ገገማ ዐማራ ያሸንፋል። ድርቅ ያለ፣ የማይወላውል፣ የማይሽለጠለጥ፣ የማይቀባጥር ዐማራ ያሸንፋል። የማይሳሳ፣ የማይራራ፣ ፍፁም ጨካኝ የሆነ፣ የቆረጠ፣ ሞትን የተጸየፈ ዐማራ ያሸንፋል። የገረድ ሜንታሊቲ፣ የባንዳ፣ የባሪያ፣ የአሽከር፣ የተላላኪነት ሜንታሊቲ የሌለው ዐማራ ያሸንፋል። አቃጣሪ፣ ተንበርካኪ፣ ጥገኛ፣ ወሬኛ፣ መተተኛ፣ መጋኛ፣ የዐማራ ስም እንጂ ግብሩ የሌለው አውርቶአደር ዐማራ መሳይ ዐሞራ ያልሆነ ዐማራ ያሸንፋል። ዋሾ፣ ቀጣፊ፣ ሌባ፣ ዘራፊ፣ አስመሳይ ዐማራ አያሸንፍም። አፉና ልቡ የተለያየ ዐማራ አያሸንፍም። ከላይ ፈጣሪን የያዘ፣ ከታች በነፍጡ የታመነ በክንዱ የተማመነ ዐማራ ያሸንፋል። ዶላር፣ ፓውንድ፣ ዩሮ የማይቀፍል፣ ጎፈንዲያም ያልሆ ዐማራ ያሸንፋል። ስንቅ እና ወኔ ከእኔ ትጥቅ መሳሪያ ከኦነግና ከወያኔ ብሎ የተነሣ ዐማራ ድብን አድርጎ ያሸንፋል። ትግሉን እንጀራው፣ መተዳደሪያው ያላደረገ ዐማራ ያሸንፋል። በፕሮግራም የሚመራ ዐማራ ያሸንፋል። ቆፍጠን፣ ኮስተር ያለ ዐማራ ያሸንፋል። አጀንዳ ተቀባይ ሳይሆን አጀንዳ ሰጪ ዐማራ ያሸንፋል።
"…አሁን ዐማራ በሌሎች የሚታይበት ዓይን ልዩነቱ እየሠፋ ነው። በሀገር ውስጥ ያሉ ቤርቤረሰቦች፣ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ለዐማራ ያለው ምልከታ እየሰፉ ነው። የዐማራ ወንድነት፣ ጀግንነት ከዘር የሚገኝ መሆኑም እየታየ ነው። እንደ ትግሬ ባንክና ታንክ ቢታጠቅ ሊደርስበት የሚችለውም ስፍራ ተገምግሟል። እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪም በመንግሥት በጀት ቢንቀሳቀስ ምን ሊያስከትል እንደሚችልም ተመስክሯል። በክላሽ ብቻ በኢትዮጵያ ስም የተሰማራውን የኦሮሚያን መከላከያ ድራሽ አባቱን ማጥፋቱም እየታየ እየተደነቀም ነው። ዐማራነት ዐማራን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም የሚያስከብር መሆኑም እየታየ ነው። ፋኖነት መኩሪያ፣ መድመቂያም መሆኑ እየተመሰከረ ነው። ኦሮሞ ትግሬው ዐማራ ይግዛን እያለ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። የዐማራ ፋኖን ማሞገስ፣ በተግባሩ መደነቅ እንጂ አሁን አሁን መስደብ ቀርቷል። ሴረኛና ድብቅ አጀንዳ ቢኖራቸውም እነ ስታሊን፣ እነ አሉላና እነ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ወዘተ እንኳን ለዐማራ ፋኖ ያላቸውን አክብሮት መደበቅ አልተቻላቸውም።
"…ዐማራ የግዱን አንድ ይሆናል። የነብር ጅራት ስለያዘ የትም አባቱ አይሄድም። አማራጩ የነብሩን ጅራት አልመልቀቅ ነው። ከለቀቀ ይበላል። ከለቀቀ እንዳይኖር ተደርጎ ይጠፋል። ዐማራ በህይወት ለመኖር ነብሩን ጅራቱን እንደያዘ ነክሶ መግደል። አለቀ። በሀገር ቤት ያለውን ዐማራ፣ በውጭ ሀገር ያለውን ዐማራ አንድ ለማድረግ መድከም አያስፈልግም። መከራው ሲዠልጠው፣ ሲጨረግደው፣ ሲያስረበው፣ ሲቀጠቅጠው፣ ልቡ እስኪጠፋ ድረስ ሲገርፈው፣ ያኔ ልክ ይገባት የለ? እናም ብዙ አትስጉ አትድከሙም። የዐማራ ሌባ በራሱ ጊዜ ይጠራል፣ ይወገዳል። የዐማራ ባንዳ በራሱ ጊዜ ይሟሽሻል፣ ይከስማል። ሆዳም ዐማራው ይጠፋል፣ በራሱ ጊዜ ይተንናል። ፈዛዛው፣ ዳተኛው፣ መሃል ሰፋሪው፣ አስመሳዩ፣ ሰነፉ፣ አቃጣሪው፣ መስሎ አዳሪው ዐማራ በራሱ ጊዜ ተጠርቦ ይስተካከላል። ኦሮሙማው ጠርቦ፣ ጠርቦ ዐማራ ያደርገዋል። ቤቱንም፣ ትዳሩንም፣ አናቱንም ሲያፈርሱለት ያኔ ይባንንና ዐማራ ይሆናል።
"…ለዐማራ ሚሊሻ፣ ለዐማራ አድማ ብተናም ብዙ አትጨነቁ። የራበው ነው ወይም መሃይም ነው፣ ወይም አቃጣሪ ባንዳ ነው። ሊወጋህ ሲመጣ ጥረገው፣ ዘርረው፣ አናት አናቱን በለው። ያኔ ከኋላ የቀረው ባንዳ የግዱን ዐማራ ይሆናል። አገዛዙ ያስታጠቀውን መሣሪያ እንደ ተሸከመ ፋኖን ይቀላቀላል። አታባብለው፣ አትለማመጠው፣ ባገኘህበት ሊወጋህ ሲመጣ አናት አባቱን አፍርሰው። መከላከያ ሆኖ ሊወጋህ የመጣውንም አትማረው፣ አረመኔ ሁንበት፣ ስትዋጋ እንደ ጭራቅ፣ እንደ ቫንፓየር፣ እንደ ቡልጉ ሁንበት፣ እጅ ከሰጠ መልአክ፣ ከተዋጋህ አረመኔ ዲያብሎስ ሁንበት። አትማረው፣ እትልቀቀው፣ አትሳሳለት። ሊያጠፋህ የመጣውን አጥፋው፣ አጥፍተኸው ከፈለክ ጥፋ፣ ጥለኸው ውደቅ። አታልቅስ፣ ሙሾ አትውረድ፣ ከፈጣሪ በቀር የሚደርስልህ ስለሌለ ድረሱልኝ ብለህ አትጩህ። አጀንዳ ሁናቸው። አጀንዳ ስጣቸው። ስለዐማራ እንዲያወሩ፣ ስለፋኖ እንዲከራከሩ አድርጋቸው።
"…ድርቅ በል አልኩህ። ይሄ ውሸታም፣ አስመሳይ፣ አቃጣሪ፣ መስሎ አዳሪ ሕዝብ ማርያምን እልሃለሁ አሁን አሁን… 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም…
"…የእኔ ወዳጆች፣ ቤተሰቦች ዘወትር ጠዋት ጠዋት እግዚአብሔር ይመስገን ብለው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ የምጠብቃቸው 1ሺ ምርጦቼ እግዚአብሔርን እንተለመደው ተሽቀዳድመው አመስግነውልኛል። እግዚአብሔር ይመስገንልኝ።
"…እንግዲህ ከምስጋና ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ተናፋቂው ቃሪያ በሚጥሚጣ ወደ ሆነው ወደ ፈዋሹ፣ አነጋጋሪው፣ አመራማሪው፣ አስተንፋሹ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ማየት መዳሰስ የፈለኩት ዐማራውን መምከር ነው። ቀኝ ትከሻዬን ሸከከኝ እና ዘመዴ ዐማራውን ምከረው፣ ምከረው አሰኘኝ።
"…የእኔ ምክር ደግሞ የታወቀ ነው። ነጭ ነጯን ነው። መሸፋፈን፣ መቀባባት፣ ቅኔ ገለመሌ የለው። ምን ተሻለኝ…? ኣ…ዐማራን ልምከር…? ወይስ ይቅር…?
እንደ ፎከሩት እየተበቀሏት ነው።
"…የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን በተለምዶ የመሐሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ የሚታወቀውን ህንፃ በወታደር "መንገድ ዘግተው" አቧራ የዓድዋ ሚዝየሙን እንዳያቆሽሸው የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪና አምጥተው ቅርሱን እያፈረሱት እንደሆነ ተነግሯል። ኤትአባታችን።
"…በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ከተማ ከተማም የሚገኘው ጥንታዊው እንቁላል ቤት ወይም የቀድሞ እስታስቲክስ ቢሮ የነበረበት እስከ 2016 ዓም ድረስ የግብር አበል ለቤተ ክርስቲያኒቱ ግብር እየከፈለበት የነበረውንና በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት እግድ ያለበትን የቤተ ክርስቲያኒቱን የግል ቅርስ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቤት እንዲሁ "የምን አባቱ ፍርድ ቤት ነው" በማለት ግሬደር አምጥተው በጉልበት ማፍረሳቸው ተነግሯል።
ቤተ ክህነቱ፦ በፍርድ ቤት የተያዘ ሕጋዊ ንብረታችንን አኮ ነው።
ኦሮሙማው ወሐረሪማ፦ የምን አባታችሁ ፍርድ ቤት ነው ምድረ ነፍጠኛ ሁላ።
ቤተ ክህነቱ፦ ለምንድነው የምታፈርሱት…?
ኦሮሙማ ወሐረሪማ፦ ለብልፅግና ጽሕፈት ቤት ህንጻ ልንሠራበት።
"…የኦሮሞ እስላሞቹና ጴንጤዎቹ ወንዶች ናቸው። ታግለው ሥልጣን ይዘው ይሄን ቡካቲያም ኦርቶዶክሳዊ ወገኔን ሽንቱን ያስጨርሱታል። የምንአባክ ሕግ አለ ሐረሪማም… ? አይ አደሬ… አሸናፊ ሁሌም ጌታ ኖ፣ አለቃ ኖ…
• እኛ ግን አናሳዝንም ወይ…?
ሲንቄ ባንክ በጅማ ዞን…!😂😂
"…የኢትዮጵያ ባንኮች የገንዘብ እጥረት እንደገጠማቸው፣ ብድር መስጠት እስከማቆም የደረሱም እንዳሉ ይነገራል። ከዚህም በላይ ዋናው አሳሳቢው ነገር በገላን ከተማ የኦሮሚያ መንግሥት በማተሚያ ማሽን ብር ማተም መጀመሩ ነው። የመሃይም ስብስቡ ብልጽግና ጦርነት አቁሞ ኢኮኖሚው ላይ እንደመሥራት ቦንብና ጥይት በዶላር እየገዛ እንደ ሎተሪ የወረቀት ገንዘብ ያትማል።
"…ይሄ በምሥሉ ላይ የምታዩት የገንዘብ ክምር ሃርጌሳ ሳይሆን በኢትዮጵያዋ በአቢይ አሕመድ የትውልድ አከባቢ በጅማ ዞን ነው። በምሥሉ ላይ በቀይ ያከበብኩት ሰውዬ የጅማ ዞን አስተዳዳሪው አቶ ቲጃኒ ይባላል። ከአብይ ጋር የሥጋ ዝምድና ቢጤም ስላለው ከመከላከያ አምጥቶ የሾመው ራሱ አቢይ አህመድ ነው የሚሉም አሉ። ልክ እንደ አዲስ አበባ በጅማም ቀደምት ሰፈሮችንና መንደሮችን በተለይም የዐማራ ይዞታዎችን ልክ እንደ አዳነች አበቤ በጭካኔ ያለ ርህራሄ ይደመስስ ዘንድ ለጥፋት ያመጣው ሰው ነውም ይላሉ።
"…የምታዩት ብርም የአካባቢው ገበሬዎች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘባቸውን አውጥተው በምታዩት መልኩ በመሃላ😂 ወደ ስንቄ ባንክ ያስገቡ ዘንድ በግዳጅ ያመጡት ነውም ተብሏል። በኦሮሚያ ኢትዮጵያ የሚል ስም አዳክመው የራሳቸውን የቤት ሥራ በሚገባ እየሠሩ እንዳለም ማሳያ ነው። እንደ አየር መንገድ ወዘተ የመሳሰሉት በሙሉ የሠራተኛ ደሞዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አውጥተው ወደ ኦሮሞ ባንኮች እንዲያስገቡ መደረጉም ይታወቃል።
"…በቅርቡ 1የአሜሪካ ዶላር ከ90-120 ብር ይዘረዘራል። ባለ 1ሺ ኖት ይታተማል። 1ዳቦ ለመግዛት አንድ ፌስታል ሙሉ ብር ተሸክመን እንዞራለን። በዚንባቡዌ ላይ ያሾፍን፣ ያላገጥን ሁሉ የዚንባቡዌ አምላክ ይቅር ካላለን በቀር እንጃልን የሚሉ መተርጉማንም አሉ።
• አዲስ አበባስ ብር እንዴት ነው? 😁
“…እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ። ማንም አንዳች ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል። ማቴ 21፥ 2-3
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ጥሎብኝ ከድሮ ጀምሮ አንድ አጀንዳ ስጀምር ከቤተሰቦቼ አንስቶ ጫጫታ ይበዛብኛል። አላፊ አግዳሚው ሁሉ ይጮህብኛል። የእኔ ትልቁ ፀጋ ግን ጫጫታ አልሰማም። እኔ ጊዜ የሚወስድብኝ በአጀንዳው ማመኑ ላይ ነው። እስካምን ድረስ እቃትታለሁ፣ አምጣለሁ። እጨነቃለሁ። ከአመንኩበት በኋላ ግን ለምን መብረቅ አይጮህም ደንታዬም አይደለም። ማንንም አልሰማም። ኬሬዳሽ…
"…ይሄ ከዘመነ ባህታዊ ገብረ መስቀል፣ ከዘመነ ተሃድሶ፣ ከእነ በጋሻው፣ ዘርፌ፣ ትዝታው ዘመን ጀምሮ ያየሁት ነው። በብፁዕ አቡነ ኤርምያስም፣ በቦለጢቀኛው ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራም፣ በሄኖክ ኃይሌም በወዘተረፈም የተረጋገጠ ነው።
"…አሁንም ከዚያ የተለየ ነገር አይደለም። ትናንት የያዝኩትን አጀንዳ በስሱ ብልጭ ሳደርግ ጫጫታው አየሩን ሞላው። ወዳጄ የሆኑ ሰዎች ቤቴ ላይ መጥተው አስተያየት መስጠት ሼም ይዟቸው የለንደን ፋኖ ግሩፕ ጋር ሄደው ሲተነፍሱ አየኋቸው። ደግነቱ እዚያም ውስጥ እኔም አለሁ።
"…አሁን ህመምተኛውን ትርፍ አንጀቱን ቆርጬ እንደምጥልለት ነግሬዋለሁ። ለቀዶ ጥገናም እንዲዘጋጅ አሳምኜዋለሁ። የትናንቱ የወዳጅ ዘመድ ጩኸት ዛሬ ላይ ቀንሷል። ኦፕራሲዮኑ የግድ ነው። ትርፍ አንጀት መጥፎ ነው። ካልተቆረጠ ሊገድልህ ሁላ ይችላል።
"…ሪፖርቱን በነገው የመረጃ ቴሌቭዥን ዝግጅቴ ላይ ነው የምዘረግፈው። ሪፖርቱ የሚጠቅመው መሬት ላይ ላሉት ፋኖዎች ነው። የሚጎዳው ደግሞ በፋኖ ትግል ኢንቨስተር ለመሆን ለሚላላጡ ዘመናዊ የጎፈንድሚ ለማኞች ነው። ፋኖዎች ከታረቁ የእንጀራ ገመዱ የሚበጠስ የሚመስለውን ሌባን ሁላ ነው የማስተነፍሰው። ቀልድ የለም።
"…አየሩ አሁን ተረጋግቷል። መንጋውም ሰከን ብሏል። ይሄ ችግር በድፍረት ከተፈታ ያለምንም ጥርጥር ፋኖ ባህርዳርም፣ ደሴም ጎንደርና አዲስ አበባም ሰተት ብሎ ይገባል። መጀመሪያ ትርፍ አንጀቶቹን እንቁረጥ።
መልካም… እንደተለመደው ጠዋታችንን እግዚአብሔር ይመስገን በሚል ነጎድጓዳማ፣ ብርሃናማ ድምጽ በሚያጥለቀለቁ 1ሺ ሰዎች ተሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ከምስጋና ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው እንደተለመደው ያው ወደ ቃሪያ በሚጥሚጣ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችንም ትናንት በጀመርነው "በፋኖዎች መሃል እጃቸውን ስለሚያስገቡ ሰዎች እና የእነዚያን ሰዎችም ሆነ ድርጅቶች እጅ እንዴት መቁረጥ" እንዳለብን ያነሣነውን ሓሳብ አንሥተን ስንወያይ እንውላለን።
"…የእኔ ቤት ክፍት ነው። የሓሳብ መስጫ ሳጥን ሰንዱቁ አይዘጋም። እንደ ሌላው ሓሳብ ለጥፌ በር ዘግቼ አንጀት ጉበትህ እንዲቃጠል አላደርግም። በጨዋ ደንብ የተቃውሞ ሓሳብ መስጠትን አበረታታለሁ። እንድትተነፍስ አደርግሃለሁ። ከዚህ በላይ ዲሞክራትነት የለም። አስተያየት መስጫ ሳጥኑን የሚቆልፍ ደንቆሮ መሃይም ነው። አምባገነን። እኔ ግን ለመወቀስ፣ ለመሟገት ሁሌ ዝግጁ ነኝ። ጥይት እንጂ ሓሳብ አልፈራም። 😂
"…በፋኖዎች መሃል ስለነበረኝ የሽምግልና ቆይታ ግማሽ ሪፖርቴን ነገ ማታ በመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ ላይ እዘረግፈዋለሁ። ማንም አያስቆመኝም። እኔ የምሰማው፣ የምከተለው፣ የማደምጠው፣ የምታዘዘውም በምድር ላይ ላሉት ፋኖዎች እና የፋኖ አለቆች፣ አዛዦች ብቻ ነው። አለቀ።
"…ገና ምኑንም ሳልጀምረው ደግሞ መንበጫበጭ ጥሩ አይደለም። ግንቦቴዎች፣ በፋኖ ስም የተሰበሰበ ብር ቀፋዮች፣ ሌቦች፣ ፋኖ በተለመነ ዶላር ገዢዎች፣ መተዳደሪያችሁን የዐማራ ችግር ያደረጋችሁ ኮተታሞች፣ ጎጠኞች፣ መንደርተኞች፣ ፋኖ በመታረቁ ኤሌክትሪክ ካልጨበጥን፣ በረኪና ካልጠጣን ባዮች እናንተን በስም ዝርዝር ጠቅሼ አልፋታችሁም። እኔ ሓሳብ አነሣለሁ አንተ ደግሞ ሓሳቤን በጨዋ ደንብ ሞግት። ሓሳቤን በጨዋ ደንብ መሞገት ካልቻልክ ጮጋ በል።
• ኣ… ዝግጁ ናችሁ…?
ማስታወቂያ…!
"…ይህ አዲሱ የኢትዮ 360 የሳታላይት ቴሌቭዥን ጣቢያን የምታገኙበት ማስታወቂያ ነው። ተከታተሉት።
"…ምንሊክ የሚለውን ብቻ ምኒልክ በሚለው አስተካክሉት እንጂ ሌላው ልክ ነው። የሐረርጌ ቆቱ ነገር ለዐማሮች አማርኛ ላስተምር ብዬ እኮ መከራዬን በላሁ። ዐማራ ተሁኖ፣ ለዐማራ እየታገሉ ቢረሳ ቢረሳ የታላቁን ንጉሠ ነገሥት የእምዬ ምኒልክን ስም አስተካክሎ ያለ መጻፍ ልክ አይሆንም።
"…ይሄን ማስታወቂያ ደጋግሜ በፔጄ አስተዋውቀዋለሁ። ይሄ አይደለም ቁም ነገሩ። ቁምነገሩ ምድር ላይ ያሉትን ፋኖዎች ከፋፍሎ ማጋደሉን ማስቆሙ ላይ ነው። እገሌ ስር ካልገባችሁ በቴሌቭዥን ድራሽ አባታችሁን ነው የማጠፋው ማለትን ነው ማስቆም።
"…የሸዋም፣ የጎንደር የጎጃሞችም፣ የወሎም ፋኖዎች የሁሉም ችግር እርሱ ነው። በጥቂት የሥልጣን ጥመኞች ክፉ ሴራ ምክንያት በቅርቡ የሺዎች ፋኖዎች ደም በከንቱ ሲፈስ፣ እርስ በእርስ ሲጨራረሱ ታያላችሁ። አቅም ያላችሁ ሸዋዎች መሃል በቶሎ ግቡ። ጎንደር ትናንት ታርቀው በመታረቃቸው የተናደዱ ዛሬ ሲያታኩሱአቸው ነው የዋሉት።
"…ግንቦት 7፣ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ፣ በግል ወንድሜ ጋዜጠኛ ሀብታሙ አያሌው ከፋኖዎች መሃል ውጣ በሉት። እኔ የምመክረው ይመራችኋል ነገር ግን ደም እንባ ነው የምታለቅሱት። ተናግሬአለሁ። ያገባኛል የምትሉ በቶሎ ጣልቃ ግቡ።
"…ባይገርምላችሁ እህተ ማርያም(ስንዱም) ሆነች የዓለም ብርሃኖች የራሳቸው ጦር አላቸው ብላችሁስ። ስንዱ እንግሊዛዊ ናት አንዱን ትነግሳለህ ብላ ቀብታ አስቀምጣዋለች። 😂። ደብረ ኤልያስ መሽገው የነበሩት ደግሞ አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ እገሌ ነው መንገሥ ያለበት ብለዋል ብለው ፋኖ ሁሉ ለዚያ ሰው ይንበርከክ ይታዘዝ ብለው ጉድ አፍልተዋል። ይሄ ሁላ ቅዠት ግን ያልፋል። ዐማራም አሳምሮ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።
• እየኮመታችሁ…!
🔥 መረጫጨት ልጀምር ነው…
• ላምጪው ይከፈል ዘንድ ሕግ ያስገድዳል።
"…አሁን በሸዋም፣ በጎጃምም፣ በጎንደርም፣ በወሎም ላሉት ፋኖዎች ለመከፋፈላቸው ትልቁን ምክያትና ዋነኛውን ነቀርሳ ወደ መዋጋቱ ለመግባት እገደዳለሁ። አቶ ሽመልስ ለገሰ አድራሽ ፈረስ ነው። ከዚያ የዘለለ ሙያም፣ ብቃትም፣ አቅምም የለውም። እኔ ከሽመልስ ጋር አይደለም አፌን የምካፈተው። እኔ ከዋነኞቹ የሽመልስ ጋላቢዎች ጋር ነው የምጠዛጠዘው።
"…ኤልያስ ክፍሌ በሀብታሙ አያሌው፣ በኢየሩሳሌምና በሽመልስ ተፈራ፣ በኢትዮ 360፣ በግምባሩና በሕዝባዊ ሠራዊቱ አይደለም ሊሰደብ ሊዋረድ ቀርቶ በክፉ አይን የሚታይ ሰው አልነበረም። ኤልያስ ክፍሌን የማውቀው ከፌስቡክ እና ከዩቲዩብ ተባርሬ ቴሌግራም ላይ ብቻ በነበርኩበት ጊዜ ለምን ቴሌቭዥን ላይ አላወጣህም ብሎ የአየር ሰዓት የሰጠኝ ጊዜ ነው። በአካልም ሁለት ቀን ነው መልኩን እንኳ ያየሁት። ከልጅነቴ ጀምሮ ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የነበረውን ተጽእኖ ሳነብ ነው የኖርኩት። ስለብዙ ነገር ኤልያስን በማግኘቴም ፈጣሪዬን አመስግናለሁም። በዚህ አጋጣሚ በሁሉ ሰው ፊት እጅግ አክባሪው እንደሆንኩም መግለጽ እፈልጋለሁ።
"…መረጃ ቲቪን በነፃ እየተጠቀሙበት ቆይተው መረጃ ቲቪን ለማፍረስ እነ ሀብታሙ አያሌው የሄዱበትን ርቀት የሚያውቅ ያውቀዋል። በፋኖ እና በዐማራ ስም በሚሰበሰብ ዶላር ኑሮውን የመሠረተ አቀንጭራ ሁላ የተለየ አደረጃጀት መጥቶበት በአጭር ቀን ልዩነቱ ሲታይ ደንግጦ መንበጫበጭ አያዋጣም። አያዛልቅም።
"…ሰው እንዴት ጎንደሮች ታረቁ ብሎ ይበሳጫል? እንዴት ደም ያስመልሰዋል? ሰው ሸዋዎች ወደ አንድ እንዳይመጡ በዚህ ልክ እንዴት ይደክማል? ሰው ጎጃምን፣ ጎንደርን የዐማራ ጋዜጠኛ፣ አክቲቪስት መስሎ እንዴት ይከፋፍላል? ወንድሞች ቢገዳደሉስ ምንድነው ጥቅሙ?
• ማርያምን አልፋታችሁም…!
👆ከላይኛው የቀጠለ "…በቀደም እለት በጎንደሮች የሽምግልና መድረክ ላይ የታላቁ ደብር የቅዱስ ላሊበላ አስተዳዳሪ የነበሩት እና አሁን በአሜሪካ የሚገኙት አባ ጽጌ ሥላሴ ምክርን በተመለከተ ያስተላለፉትን ግሩም ቃል እዚህ ጋር ልጥቀስ። አባ ምክር ሲባል ከራስ ጥቅም አንፃር ብቻ የሚመክርም ስላለ እሱን ተመካሪው ማመዛዘን እንዳለበት መክረው ይኽንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ኩሲን እና አኪጦፌልን ጠቅሰው እንደነዚህ ዓይነት ብዙ ሰዎች አሉና ተጠንቀቁ በማለት ያስተላለፉት መልእክት ሊያዝ ይገባል። "…አኪጦፌል የንጉሥ ዳዊት አማካሪ ነበር። ነገር ግን ልጁ አቤሴሎም አባቱን ንጉሥ ዳዊትን ባሳደደው ጊዜ፦ ከአቤሴሎም ጋር ሆኖ ክፉ ምክር ይመክረው ነበር። 2ኛ ሳሙ 15፥12፤ 17፥1-23 ያንብቡ። በሌላ በኩል ደግሞ የተሻለ መካሪም ሲመሰከርለት እናያለን። “…አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ። የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጦፌል ምክር ይሻላል አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።” 2ኛ ሳሙ 17፥14። አይደለም የወያኔና የኦነግ አክቲቪስቶች ምክር እናትም፣ ሚስትም ክፉ መካሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። "…የሃያ ሁለት ዓመት ልጅ አካዝያስም በነገሠ ጊዜ፦ ጎቶልያ የተባለች እናቱ ብዙ ጊዜ ክፉ እንዲያደርግ ትመክረው ነበር። 2ኛ ዜና 22፥1። ንጉሥ አክዓብ ናቡቴን አስገድሎ ርስቱን የነጠቀው በሚስቱ ምክር ነው። 1ኛ ነገ 2፥1-16። ስለዚህ ፋኖ ከክፉ መካሪዎች ሁሉ ራሱን ሊጠብቅ ይገባል።
"…የአቢይ አማካሪዎች ከኦርቶዶክስ ዳንኤል ክብረት፣ ከጴንጤ እነ ምህረት ደበበ፣ ከእስላሞችም ነፍ ኡስታዞች ናቸው። የሕዝቡን ሥነ ልቦና የሚያውቁ፣ ጠንቅቀው የተረዱ ናቸው። የሃይማኖት ሰባኪ አማካሪ ሲሆን ስለ ፖሊሲ፣ ስለ ቴክኖሎጂ አይደለም የሚያማክረው። የጎንደር፣ የሸዋ፣ የወሎ፣ የትግራይ፣ የጎጃም፣ የወለጋ፣ የአፋር፣ የአሩሲ፣ የባሌ፣ የሱማሌ፣ የጋምቤላ፣ የጉራጌ፣ የወላይታ፣ የሲዳማ፣ የከንባታ፣ የሐረሪ ወዘተ ሰው ምን ቢያደርገው፣ ምን ቢሰብከው ልቡ ወከክ እንደሚል ነው። ለዚህ ነው አቢይ አሕመድ በየክልሉ በሄደ ቁጥር የክልሉ ነዋሪ ብቻ መስማት የሚፈልገውን እየነገረ ሲያስጨበጭብ፣ ጮቤ ሲያስረግጥ የሚታየው። ዐማራን እንዲህ፣ ትግሬን እንዲያ፣ ኦሮሞን እንዲህ ካልከው፣ ከሸነገልከው በቃ ይገዛልሃል ብለው ነው የሚሰብኩት። አቢይም የእነሱን ምክር ይዞ ነው ትግሬን ሞተር፣ ዐማራን ጎማ፣ ኦሮሞን መሪ፣ ሱማሌን ማርሽ፣ ደቡብን ስኮፒዮ ወዘተ እያለ ጮቤ የሚያስረግጠው። ሕዝብ ደግሞ የተነገረውን አይረሳም። አቢይ "ነዳጅ ተገኝቷል። ከነገ ጀምሮ ለውጭ ገበያ ይቀርባል" ብሎ ዐውጆ እስከአሁን ወፍ የለም። ለጉራጌ ሆስፒታል እሠራለሁ ብሎ ይኸው 6 ዓመት ሆነው የውኃ ሽታ ነው የሆነው። ለዐማራማ የገባው ቃል አይቆጠርም። ልክ እንደ ብአዴን መሰረት ድንጋይ የትየለሌ ነው።
"…ቀድሞ መንቃት። ሱማሌና አፋር ጦር ከመማዘዛቸው በፊት ቆም ብለው ማሰብ፣ መመካከር። ደቡብ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ ላይ የአቢይን አገዛዝ አጀንዳ ይዞ ከመዳከር፣ ከመፈሳፈስ፣ ደምም ከመፋሰስ አስቀድሞ ቆም ብሎ መመካከር። የኦነግና የወያኔን ምክር አለመስማት፣ አለመቀበል። መጀመሪያ ትግሬ ደቅቋል፣ ቀጥሎ ዐማራ እየተናነቀ ነው። ከዐማራ ቀጥሎ አዲስ አበባ እየፈረሰ እየጸዳም ነው። አፋርና ሱማሌ እያረፉ እየተጠዛጠዙ ነው። ሐረሪ በኦሮሞ ተውጧል። ድሬደዋ ከሱማሌ እየጸዳ ነው። ጉራጌ ብዙ ወረዳዎቹ በኦነግ ሽሜ ተይዘዋል። ሲዳማ በኦነግ ሸኔ እየተቀጠቀጠ ነው። ጋምቤላም በሸኔ እንዲያዝ ተደርጓል። ቤኒሻንጉል ውጥረት ላይ ነው። ዐማራ ከትግሬ በፈለጋቸው ጊዜ እንዲጋደሉ ድግስ ተደግሷል። ከኤርትራም፣ ከሱማሌም አይቀርልንም ብልፅግና ሲያናክሰን። ሁለቱም ሱዳኖች አይሞክሩንም አይባልም። አሁንም ቢሆን መሬታችንን ኦሮሙማው አስወስዷል።
"…ብስል፣ ሙክክ በሉ። ጥሬ አትሁኑ። ንቁ ሁኑ። ቆፍጣና፣ ተጠራጣሪም ሁኑ። ዥሎች አትሁኑ። ዥልጥ፣ ፋራ፣ ሰገጤ አትሁኑ። የክፍለ ሀገር ልጆች ከበሻሻና ከማሻ፣ ከደንበጫ፣ ጃናሞራ እና ከመተሃራ፣ ከመቄት እና ከዋጀራት፣ ከሞላሌና ከባሌ፣ ከሰላሌ፣ ከደምቢዶሎና ከከክልአተ አውላሎ ከጊንጪና ከወንጪ መጥተው 4 ኪሎም ገብተው አንተ አራዳ ነኝ፣ ብልጥ ነኝ ባዩን አናትህ ላይ ጥሬ ካካቸውን እንዲዘፈልሉ አትፍቀድ። አናትህንና ቅርሶችህን፣ ትዝታህን ሲያፈርሱት እያየህ አትብሰልሰል። ሴራቸውን ቀድመህ አንተም አፍርስ። የሸኔን እገታ ፈርተህ ላይቀር መሞት ታሪክህን አታልከስክስ። ሰምተሃል የአቢይ ብልፅግናን ሴራ ከወዲሁ አፍርስ። ያኔ እኮ ዘመዴ ተናግረህ ነበር እያልክ በኋላ ላይ መሃረብ ይዘህ አታልቅስ። አታስለቅስ።
• ፋኖ ይልቅ ክረምት ሳይገባ አዲስ አበባን ጎብኛት።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
መልካም… እንደተለመደው ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወደተለመደው ተናፋቂ ቃርያ በሚጥሚጣ ወደ ሆነችዋ ርዕሰ አንቀጻችን ይሆናል።
"…ትግራይ ውዝፍ ደሞዝ የለም። በደቡብ ለመምህራን የሚከፈል ደሞዝ ጠፍቶ መምህራን የቀን ሥራ ፍለጋ እየሮጡ የማስተማሩን ሥራ አቁመዋል። አንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ደሞዝ አዘግይተው መክፈል ጀምረዋል። ዐማራ ክልል ለሠራተኛ ደሞዝ ለመክፈል "ነጠላ ዘርግቶ መለመን" ነው የቀረው። ባንኮች ለደንበኞች የሚከፍሉት ካሽ አጥሯቸው ተቸግረዋል። ብድር ማበደርም አቁመዋል። ሌሎች ክልሎች ደቅቀው ኦሮሚያን በሀብት ማንበሻበሹን ተያይዘዋል። ብሩ እነ በተለይ ጅማዎቹ እነ መንሱር ጀማል እጅ ሰተት ብሎ ገብቷል።
"…በኦሮሚያ ግን የኦቦ ሽመልስ ስንቄ ባንክ የካሽ እጥረት የለበትም። እንደ ጉድ ይታተማል። እንደ ጉድ ይበተናል። ህፃናት እጅ የወደቀች ሀገር እየማቀቀች ነው። ዶላር 120 ሲገባ ደግሞ አበቃ፣ አለቀልን።
"…ለማንኛውም የዛሬ ርዕሰ አንቀጼ ይሄ አይደለም። በሚታተመውና እንደ ጉድ ለኦሮሞ ስለተበተነው ገንዘብ አይደለም የማወራው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጼም የእቡይ አሕመድን ቀጣይ ሴራ ማፍረሱ ላይ ነው የሚያውጠነጥነው። የዘገየሁትም ለዚያ ነው።
• አላችሁ አይደል ጉበዝ…?
"…እሊህ አጋንንታሞችም ዐማራ ክልል ዘምተው ይሆን…? እንዲህ ዓይነቱ አጋንንት ግን በጩፋ ካራቴ ብቻ የሚወጣ አይመስለኝም። ደግሞ አይመስለኝም ነው ያልኩት።
• አጋንንታም…!
• አላችሁ አይደል…? በዘህ ደግሞ እንቀጥል…?
"…ፐ ውበት ብሎ ዝም እኮ ነው። አዲስ አበባችን እንደስሟ አዲስ አበቤ ሆና የለም እንዴ? ሃኣ…?
መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!
"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ይጀምራል።
የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ
👉በዩቱብ /YouTube
♦https://www.youtube.com/live/BMflQCZjTfo?feature=shared
👉በረንብል /Rumble
♦ https://rumble.com/v4riszr--...-ethiobeteseb.html
👉በፌስቡክ Facebook
♦facebook.com/ethiobeteseb
👉 በቲውተር / Twitter
♦https://twitter.com/EBeteseb
👉 ቴሌግራም / Telegram
♦/channel/ethiobeteseb
"…ሻሎም ! ሰላም !
👆…ከላይ ይቀጥላል…✍✍✍ …በአንተ በዐማራው ፋኖ ነው ተስፋ ያደረገው። አፉን አውጥቶ አይናገር፣ አያውራ እንጂ በልቡ ከዐማራ ፋኖ ጋር ነው። መቼ በመጣና ከዚህ ከአረመኔ በገላገለኝ ነው የሚልህ ፒፕሉ። የኦነግና የወያኔ አክቲቪስቶች እንኳ አሁን አሁን ከየቲክቶኩ መንደር እየለቃቀሙ ዐማራ አጀንዳቸው ከሆነ ሰነባበተ። ድርቅ በል አልኩህ። እዚያው መከላከያውን አድቅቀህ፣ ውጠህ አስቀርተህ፣ ፔርሙዳ ሆነህ ውጠህ ከች በል። የገባው እንዳይወጣ አድርገው። ባህርዳር ለብአዴን ሲኦል ትሁነበት፣ ደሴን ክበባት፣ ጎንደርን ክበብ፣ የመጣውን የኦሮሙማ ሠራዊት በደፈጣ ጨፈቃ እያደረግክ ተተኳሽ፣ ጥይት ተቀበለው። በቃ ግግም በል። ደም በደም ብቻ ነው የሚመለሰው። መጀመሪያ ዐማራን በዐማራ ክልል ነጻ አውጣ። ከዚያ ሌሌላው ዐማራ ትደርስለታለህ።
"…ግግም በል አልኩህ አባቴን…!አሁን ቁጭ ብሎ እያየህ ያለው ቆሞ አጨብጭቦ ይቀበልሃል። ደግሞ ለማጨብጨብ። ኢትዮጵያ በኤድስ ከዓለም ሁለተኛ፣ ከአፍሪካ አንደኛ ሆነች እኮ ሲባል ትናጋው እስኪናጋ፣ እንጥሉ እስኪወርድ፣ ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ፣ ምላሱ ስትራፖ እስኪይዘው፣ ምራቁ እስኪደርቅ፣ እጁ እስኪላጥ እልልል እያለ የሚያጨበጭብ እኮ ነው። አቢይ አህመድ ስላስነጠሰ፣ ምድረ ጀዝባ፣ ሾርት ሚሞሪያም እያለ ሲሰድበው ቆሞ የሚያጨበጭብ ሕዝብ እኮ ነው። አሸንፍ እንጂ አጨብጫቢ አይጠፋም። ዓለም አልቃሻ አትወድም። ወሬኛ አትወድም። ዓለም ጀግና ቆራጥ ነው የምትወደው፣ የምታከብረው። ጀግና ሁን፣ ጀግና አፍራ።
"…አሁን ጠላትን ወደ ማተራመስ ተሸጋገር። ወደ አዲስ አበባ፣ ናዝሬት ወዘተ ዝለቅ። ግባ ወደ ሸገር፣ ወደ ሸዋ። እነ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ ያዩትን ስላዩ ነው ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄዱ እየከለከሉ ያሉት። በፕላኑ መሰረት የእነ ናሁሰናይ ጉዳይ ስለታየ አሁን ቀስቀስ በሉ። በ3 ፋኖ ግማሽ ቀን ከተዋጋህ በ300 ፋኖማ ምን ይነገራል? ሞት የተጠየፈ የዐማራ ፋኖ አሁን ይንቀሳቀስ። በመከላከያውስጥ የመሸገውም ሥራውን ይጀምር። ለዐማራ ሲኦል የሆነችው ኢትዮጵያን ወደ ገነትነት ለመቀየር ተራመድ፣ ተንቀሳቀስ። ምድረ ቅዘናም፣ አራጅ የአራጅ ልጅ፣ ዘራፊ፣ ሌባ፣ ቀማኛ ወንበዴን ልክ ለማግባት ተንቀሳቀስ። ትችላለህ በካላንደሩ መሠረት ተንቀሳቀስ። አሸብረው ይሄን አጋሰስ ሜካፓም አገዛዝ። ጥለኸው ውደቅ። ማንንም አትስማ። ግግም፣ ድርቅ በል። ራስህን ብቻ አድምጥ። ከውስጥህ ሌባ፣ ባንዳውን መንጥር፣ ጥረብ፣ አስተካክል።
"…ይኸው ነው ምክሬ… ካነሰ እያየሁ እጨምራለሁ። ይህን በማለቴ ቅር የሚልህ አይደለም ሌላ ዐማራ ነኝ የምትል ገተት ካለህ በአናትህ ተተከል። አመሰግናለሁ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…አሁን ዐማራ የሚያዋጣው መገገም፣ ድርቅ፣ ክችች ማለት መሆኑን እያስመሰከረ ነው። መተጣጠፍ፣ መዋሸት፣ መቀላመድም አያስፈልገውም። እንደ ትግሬ ነፃ አውጪም፣ እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪም የገበቴ ውኃ መሆን አያስፈልገውም። ለዐማራ የሚያዋጣው ድርቅና ብቻ ነው። አልሰማህም፣ አላዳምጥህም፣ የምልህን ስማኝ አልያም በአናትህ ተተከል ማለት ብቻ ነው የሚያዋጣው። አሸናፊ የሚያደርገውም እሱ መንገድ ብቻ ነው። በዙያ መንገድ ከሄደ ዐማራ አድማጭም ተከታይም ያገኛል፣ የሚሰማውም ያገኛል። ፍላጎት ዓላማውንም ድብን አድርጎ ያሳካል።
"…እስከዛሬ ድረስ በደረሰበት መከራ ያላዘኑለት፣ ያላለቀሱለት፣ ያላስተዛዘኑት ወላ የሃይማኖት አባቶች በላቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መጡ፣ ቀሩ ምን አባታቸው ሊረቡት? ምንስ ሊፈይዱለት? ዘሩ መጨፍጨፉን፣ መሰደዱን፣ መፈናቀሉን፣ መንከራተቱን፣ መገፋቱን፣ መሰደቡን፣ መታረዱን እስከዛሬ ሳይሰሙ ቀርተው ነው? አይደለም። ሁላቸውም ሰምተዋል። ሁላቸውም የጥፋቱ ተባባሪ፣ አልያም ደጋፊ በመሆናቸው ነው ዝም ያሉት። አፈር አባታቸው ያስበላቸውና አሁን በመጨረሻ ወንድ ልጅ ከቆረጠ በኋላ መጡ፣ ቀሩ፣ አዘኑለት፣ አላዘኑለት ምንአባታቸው ይጨምሩለታል? ምንስ ይቀንሱለታልኝ? ዐማራ ወደፊት ብቻ።
"…ከኤርትራ ነፃ አውጪ እንጀምር። ሻአቢያ ዐማራ ላይ የሠራው ግፍ፣ የሠራው ፕሮፓጋንዳ በትሪልዮን ብር በጀት ነበር ሲያቀላጥፈው የኖረው። በፕሮፓጋንዳው ዐማራ ምንም አልሆነም ማለት ባይቻልም ሻአቢያ ደክርቶ ዐማራ ደርጅቶ ይኸው እንዳለ አለ። የትግሬ ነፃ አውጪ በዐማራ ላይ ያልፈጸመውን፣ ያላስፈጸመውን ወንጀል ንገሩኝ። ተነግሮም፣ ተወርቶም አያልቅም። ወያኔ እኮ ብሔር ብሔረሰቦች አፋቸውን "ነፍጠኛ" በሚል ቃል እንዲፈቱ በማድረግ ነበር ዘመኗን የፈጀችው። የተቆረጠ ጡትና ብልት ሃውልት ስታሠራ፣ ስትገነባ ኖሯ ነው በመጨረሻ ዱቄት አባቷ የጠፋው። ኦነግ፣ ብልጽግና ሁላቸውም ለዐማራ ያልደገሱት፣ ያላደረጉበት ግፍ ምን አለ? ነገር ግን ዐማራው በሻአቢያም፣ በወያኔም፣ በኦነግም፣ በብልፅግናም እቶን እሳት ውስጥ አልፎ ዛሬ ላይ ወርቅ ሆኖ እየወጣ ነው። እየተገለጠ ነው።
"…ወርቁን ዐማራ አሁን ፈላጊው ይበዛል። ዐፈሩን ዐማራ የተጸየፉት በሙሉ እሳት ገብቶ ቀልጦ ወርቅ ሆኖ የወጣውን ዐማራ ከጭንቅላት፣ ከጣት ከአንገቱ ለማጥለቅ፣ ለመወዳጀት የማይፈልግ ማን ይኖራል? ወዳጄ ጥሬ በቆሎ ዋጋው ትንሽ ነው። እሳት የገባው በቆሎ፣ የተለበለበ፣ የተጠበሰ፣ የተቀቀል በቆሎ ዋጋው ውድ ነው። ዐማራም እንደዚያው ነው። አሁን በመከራ ብዛት ተጠብሶ፣ ተቀቅሎ ወጥቶለታል። አሁን ሲያዩት ሁሉም ለሃጫቸውን የሚያዝረከርኩበት አጓጊ እሸት ጥብስ ሆኗል። ለመወደድ ትንሽ የመከራ እሳት ለብለብ ሲያደርግህ ዐማራን ነው የምትመስለው። ወያኔና ብልጽግና ኦነግና ኦህዴድ ተባብረው እሳት ባየነዱበት ኖሮ ዐማራው መች ይንቀሳቀስ ነበር? መች ነቅነቅ ይል ነበር። ድስት ላይ ተጥዳ ከስር እሳት ለቀውባት ለብ እያለ የሚሄደው ውኃ ሲቆይ እንደማይመሸልቃት እንቁራሪት ዘጭ ብሎ ይዋኝ የነበረ እኮ ነው ዐማራ። በግሬደር እየቀበሩት እያየ፣ ቀበሌ ሙሉ እየጨፈጨፉት እያየ፣ ሙት ለሬሳህ ችግኝ እንተክልልሃለን ሲሉት እየሰማ ጮጋ ብሎ የተቀመጠ ነበር እኮ ዐማራ። መከራ ጠርቦ፣ ጠርቦ ዛሬ ጀግና ፈጠለት እንጂ ራሱ መገደሉ የተስማማው መስሎ እኮ ነበር ዐማራ። ያውም በትግሬና በኦሮሞ እንደፈሪ እስኪቆጠር ድረስ።
"…አሜሪካ በላት፣ አውሮጳ፣ ዓረብ በለው ቻይና፣ አፍሪቃ በለው ካናዳ በዐማራ ላይ ለሚደርሰው ጭፍጨፋ፣ የዘር ማጥፋት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊዎች ይመስላሉ። የዐማራ ቁመናው፣ ለባርነት ተንበርካኪ አለመሆኑ፣ የብሩህ አእምሮ ባለቤት መሆኑ፣ ጀግና ተዋጊ፣ ሃይማኖተኛ መሆኑ፣ የቆንጆዎች መፍለቂያ፣ የውኃ ሀብት ባለቤት መሆኑ፣ ታጋሽ፣ አርበኛ፣ ሀገር ወዳድ መሆኑ፣ ለኩርማን እንጀራ ለሆዱ ብኩርናውን የማይሸጥ ሀገር ወዳድ መሆኑ፣ ቀለም ገብ፣ ፊደል ነክ መሆኑ ወዘተረፈ ይበሰጫቸዋል። እንደወያኔ ሲልኩት ወዴት፣ ሲጠሩት አቤት ለማለት ሀሞቱ የማይፈቅድለት፣ ህሊናው የማይታዘዝለት መሆኑ ይበሰጫቸዋል። እናም በባሌም ሆነ በቦሌ ሊያጠፉት ይፈልጋሉ። እነሱ ሳያጠፉት የሚያጠፋላቸው ቅጥረኛ ሲያገኙ ደግሞ አሸወይና ነው ለእነርሱ። ያ ሁሉ ዐማራ ያኔ ሲጨፈጨፍ እነርሱ ቀጥልበት እያሉ ባላየ ባልሰማ ላሽ ነበር ይሉ የነበረው። ዐማራ ግን እንደ ስንዴ ዘር ሞቶ ተነሣ። ወይ ፍንክች።
"…አቢይ አሕመድ እንኳ ንቆት በወር ውስጥ ሱሪ ሊያስፈታው የሞከረው ዐማራ አሁን የአቢይን የራሱን ሱሪ ወደ ማስፈታቱ እየመጣ ነው። በሰማይም በምድርም አቢይ ዐማራው ላይ ያልሞከረው ነገር የለም። ዐማራን ለማንበርከክ ያለቆፈረው ጉድጓድ የለም። ዐማራው ግን ድርቅ፣ ክችች ማለቱ አቢይን ምላሱን እንዲውጥ ነው ያስደረገው። በጭባጫ ሁላ አሁን ስለ ዐማራ ፋኖ የሚያወራው በስጋት ነው። ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ይልልሃል። ዐማራው ካሸነፈ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚል ጩኸትም ተበራክቷል። እናም አቢይ አሕመድ የመጨረሻ ጥይቱን የምክክር ኮሚሽን ተብዬውን የትግሬና የኦሮሞ ባንዳ ስብስብ፣ የጴንጤና የወሃቢያ እስላም ጥርቅም ከመሳቢያ ከሰንዱቁ ውስጥ አውጥቶ ሊጠቀምበት እየተሰናዳ ነው። ዐማራው ግን በአቋሙ መጽናት አለበት ባይ ነኝ። ግግም፣ ድርቅ፣ ክችች ማለት አለበት ባይ ነኝ።
"…ወያኔ መርዙ ሲገዛት ያልፈረሰች ኢትዮጵያ፣ ጨበራ ጩርጩራው አቢይ አህመድ ሲገዛት ያልፈረሰች ኢትዮጵያ፣ ዐማራው ሲገዛት፣ ሲያስተዳድራት እንደ አሸዋ ክምር የምትፈርሰው ምን ሆና ነው? አጭቤ ሁላ። ዐማራ በገዛበት ዘመን የነበረችዋ ኢትዮጵያ እና አሁን የሰው ሥጋ የምትበላዋ ኢትዮጵያ ልዩነታቸው እኮ የሰማይና የምድር ያህል ለየቅል ነው። ዐማራ ሲገዛ የነበረችዋ ኢትዮጵያ የነበራት ሰላምና አሁን ከአዲስ አበባ ከወረዳ ወረዳ እንኳ መሄድ ያቃታት ኢትዮጵያ ምንና ምን ናቸው? እንዲህ በመጨናበር ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረግን ቱሪናፋም፣ ቱልቱላ ቀደዳ ዐማራው መስማት የለበትም። ዐማራ የኢትዮጵያ ባል ነው። ውሽማም ባል ሆኖ አየነው እኮ ምድረ ሌባ፣ ዘራፊ፣ ዋሾ ቀጣፊ ሁላ። ኢትዮጵያ ወደ ሕጋዊ ባሏ መመለስ አለባት። ባለቤት ቤቱን አያፈርስም፣ ባለቤት ልጆቹን አርዶ አይበላም። ውሽማ ነው አራጅ፣ ነፍሰ በላ ወንጀለኛ። ውሽሞች ልክና ቦታቸውን መያዝ አለባቸው። ሌባ ሁላ።
"…አልበላሽምን ምን አመጣው እንዳለች ጦጢት አሁን ኢትዮጵያ አትፈርስምን ምን አመጣው? ሌቦ ወያኔም፣ መሃይሙ አብይም በንግግራቸው፣ በዲስኩራቸው፣ በሪፖርታቸው፣ በጽሑፋቸው፣ በደረሱበት ሁላ "ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ" ወዘተረፈ ሲሉ ይደመጣሉ። ወትሮውንስ በሚጢጢ፣ ኩርማን፣ የሰጎን ጭንቅላታቸው ውስጥ ማፍረስ እንጂ መገንባት፣ መለያየት እንጂ አንድነት ስለሌለ እንጂ ከመሬት ተነሥቶ እንዴት አንድ ጤናማ አእምሮ ያለው አካል ስለ ማፍረስ፣ መፍረስ ያወራል? እንዲህ ብሎ ለሚልዮኖች በየጉዜው ማውራትን ምን አመጣው? አፍራሽ ነው ስለሚያፈርሰው አበክሮ የሚያወራው። አንጀት ጉበትህ፣ አናትህ ይፍረስና ምድረ ፈርሳም ሁላ አንተው እንደመለስ ዜናዊ በቁምህ በስብሰህ ትፈርሳለህ እንጂ ኢትዮጵያማ አትፈርስም። አፍራሹን ማፍረስ ግን ያስፈልጋል። ሥርዓቱንም እርሱንም ማፍረስ ግን ያስፈልጋል። ይሄን ለማድረግ ደግሞ አሁን ላይ ከዐማራው በቀር ሌላ አይታየኝም። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…እርስ በርሳቸው የተቀራረቡ ናቸውና ነፋስ በመካከላቸው መግባት አይችልም። እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፤ እስከማይለያዩም ድረስ ተያይዘዋል። ኢዮ 41፥ 8-9
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
የባህር ኃይል ማሪን ኮማንዶ ነገር…!
"…መለስ ዜናዊ የሸጠውን የኢትዮጵያ የባህር በር ዐማራ ክልል ገብቼ የዐማራን ፋኖ በመደምሰስ ዐማራን የኦሮሞና የትግሬ ዘላለማዊ ባርያ፣ ገረድ፣ አሽከር አድርጌ አሳያችኋለሁ ብሎ የማይነካ የነካው ሀ ገደሉ አቢይ አህመድ ከገባበት ቅርቃር ለመውጣት ሲል እንደ አጀንዳ ማስቀየሻነት "የባህር በር የምትል ካርታ መዘዘ" መጀመሪያ ምጽዋ ላይ፣ ቀጥሎ አሰብ ላይ ደነፋ። ዐማራውም ትግሬውም ጮጋ አሉት። ሶማሊላንድ ሄደ፣ ወፍ የለም። አሁን የት እንደደረሰ አላውቅም። ኡጁንቡራ ደርሶ ይሆን?
"…አጭቤክሱ አቢይ አሕመድ ለባህሩ ባሕር ኃይል አቋቁሞ ሥልጠና ያሰጥ ነበር። አስመርቋልም። ኋላ ላይ የባህር በሩ ሲጠፋ፣ የባህር ኃይል ምሩቃኖቹን ወደ ዐማራ ክልል ልኮ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት በሰሜን ሸዋ ውስጥ ባሉ ወረዳዎችና አካባቢዎች ዘመቻ እያካሄደ እንደሚገኝ የባህር ኃይሉ ዋና አዛዥ ተወካይ በሬር አዲሚራል ናስር አባድጋ በኩል ገለጸ።
"…እናንላችሁ… ይሄ እሳት የላሰ የአቢይ አሕመድ ውኃ በሌለበት የባሕር ኃይል ነኝ የሚለው ቡድን በደረቅ መሬት ላይ ከሰሜን ሸዋ አናብስቱ ከእምዬ ምኒልክ የመንፈስ ልጆች ጋር ከአርበኛ አሰግድ እና ከሻለቃ መከታው ጋር ገጥመው አይሆኑ ሆነው ተበለሻሽተዋል። ድንቄም ባህር ኃይል። 😂 ኡኡቴ… አልቀረብሽም አለ ገለቴ። አቢይ አሕመድ እና ኮተት አገዛዙ አልቆለታል። ዐማራ አሸንፏል። ምስኪን ወታደሮቹን ግን ነፍስ ይማር።
• ነፍስ ይማር…!
የምሥራች ለዐማራውያን…!
"…በራሳቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነቢያት በሆኑት ጎንደሬዎች፣ በአፄ ቴዎድሮስ ልጆች፣ በጀግኖቹና በአርበኞቹ ጋባዥነት ለአንድ ዓላማ ቆመው ሳለ በሓሳብ ልዩነት ከሁለት ጎራ ተከፍለው ቁርሾ ገብቷቸው የነበሩት ጀግኖች ባቀረቡልኝ "የአሸማግለን" ጥሪ መሠረት እኔ ዘመዴ አባ ደፋር አንድ ለእናቱ፣ ሺ ለጠላቱ፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው፣ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ፣ የሐረርጌውን መራታ ጥሪያቸውን ተቀብዬ እንደ መጽሐፍም ቃል “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።” ማቴ 5፥9 ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት የማሸማገል ሥራውን ጀመርኩ።
"…ጎንደሬዎቹን ጆኒ፣ ዘመንና አዱኛን ከጀርባ አሰልፌ፣ የሸዋውን ካህን ከኦሀዮ በጸሎት አስጀምሬ፣ በመጨረሻም ከወሎ የደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ አስተዳዳሪ የነበሩትን አባ ጽጌሥላሴን ጨምሬ፣ ገዳማውያን በጸሎት እንዲያግዙን ፈቃደ እግዚአብሔርንም ጠይቀን ስናበቃ ወደ ውይይቱ ገባን። ውይይቱ ሲጀመር ከባድ ነበር። ውሎ ሲያድር እየቀለለ መጥቶ ዛሬ ሚያዚያ 16/2016 ዓም እግዚአብሔር ከብሮ ሰይጣን ዲያብሎስም አፍሮ፣ በእለተ ኪዳነምህረት በደስታ፣ በእንባ፣ በፍቅር የሽምግልናውን ሂደት በይቅርታ ተፈጸመ።
"…አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የጎንደር ዕዝ የበላይ ጠባቂ፣ አርበኛ ባዬ ቀናው የዐማራ ፋኖ በጎንደር ሰብሳቢ፣ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ መሪ፣ ኮ/ል ታደሰ የዐማራ ፋኖ በጎንደር የጦር አዛዥ በተለይ አርበኛ ፋኖ ደረጀ ሁላችንንም አስለቅሶን ሁላቸውም ታርቀው፣ ይቅር ተባብለው፣ የደስታ ጥይት ተተኩሶ፣ የተራራቁት ተቀራርበው በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ የተዋሐደ አመራር መርጠው በአንድ የጎንደር ፋኖ ሊገለጡ ወስነው ይሄንኑ ለመላው ዐማራ ንገር ብለው አዘውኝ ነገሩ ተቋጭቷል።
• እግዚአብሔር ይመስገን 🙏