zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እናንተው ዛሬ እኮ ልደቴ ነው። እንደ ቀልድ በዋዛ ፈዛዛ ምንም ዓይነት ቁምነገር ሳልሠራበት ዘመኔ እንደ ሸማኔ መወርወሪያ ሩጦ ተወርውሮ ዛሬ ሚያዚያ 12/2016 ዓም በእለተ ቅዱስ ሚካኤል ድፍን 50 ዓመት ሞላኝ። ለማንኛውም ስላሳለፍኳቸው 49 የውጣ ውረድ፣ የኀዘንና የደስታ፣ የስደት ዓመታት ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን። “…የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንገሠጻለንና።” መዝ 90፥10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ከጠዋቱ የቀጠለ…

"…ውይይቱ በተቋረጠ ቀን የቀረ የጎንደር ፋኖ አልነበረም። እኔም የሆዴን በሆዴ፣ የልቤን በልቤ ይዤ ለጀማው ሰላምታ አቀረብኩ። ሁላቸውም ሰላምታዬን ተቀበሉኝ። እንደልማዳችን ማን መጣ? ማንስ ቀረ ብዬም ጠየቅኩ። አንደኛው ወገን ብቻ መምጣቱን፣ ሌላኛው ወገን ግን ዛሬም አለመቅረቡ ተነገረን። የቀሩበትም ምክንያት ተነገረ። የቀረበውም ምክንያት አሳማኝ ስለመሰለኝ ምክንያታቸውን ተቀብለን በይደር አቆየነው።

"…መሽቶ ነጋ። በሁለተኛው ቀን የተባለው የቀጠሮ ሰዓት ደረሰ። ሁላችንም በሰዓታችን ተገኘን። እንቅልፍ እንዳይጥለው ቀዝቃዛ ውኃ እግሩን ዘፍዝፎ የሚቀመጥም ነበር። የሆነው ሆኖ ዛሬም ግን አንደኛው ወገን አልመጣም። አለመምጣቱን ሳውቅ ዛሬም ለጸሎት እንነሣ ብዬ ቀቀሪውን አዘዝኩ። ጸሎት አድርገን ከፈጸምን በኋላ ግን የመረረ ንግግር አደረግኩ። ሽምግልናው የደረሰበትን አጠቃላይ ሂደትም ለሕዝብ ይፋ አድርጌ እቋጨዋለሁ ብዬም ሽምግልናውን አክብረው ለቀሩቱ ገለጥኩ። እናንተ ግን እግዚአብሔር ያክብራችሁ በርቱ በማለትም ተሰናበትኳቸው። ለምንአልባቱ ተፀፅተው ከተመለሱ፣ ለጎንደር አንድነት፣ ለዐማራ አንድነት አስበው ከተመለሱ አለሁ በእገሌ በኩል ልትጠሩኝ ትችላላችሁ ብዬ ነበር የተሰናበትኩት።

"…መሸ፣ ነጋ በሌላኛው ቀን ዛሬ ሆነ። የሽምግልናውን ውጤት ለሕዝብ ይፋ የማደርገው ነገ ቢሆንም ዛሬ ለነገው ዐዋጄ የመግቢያ ምልክት የሚሆን መብረቃዊ ብልጭታ ያለው ምልክት የመስጫ ዕለቴ ነበር።

"…የጎንደሩን ብቻ ሳይሆን የሸዋዎቹም የእርቁ ነጠላ ተሸምኖ አልቆ ቁጭቱ፣ መቋጭያው ላይ አንደኛው ወገን አስከ ዛሬዋ ድረስ አልተሳካለትም ነበር። እርቁ አልቆ፣ ይቅር መባባሉ አልቆ መቋጫው ላይ ሰይጣን ገብቶ ግግም ብሎም ነበር። በመሃል ሰይጣን የሸዋውን የተሰበሰበ ምርጥ ስንዴ ለመበተን ያልደከመው ድካም፣ ያል ጫራው ጭረት፣ ያልቆፈረው ጉድጓድ አልነበረም። እሳቱን እንደማጥፋት ቤንዚን ይዘው ለማቀጣጠል የሚሮጠውን መንጋ እያየሁ እታዘብ ነበር። ዐውቆ በድፍረት፣ ሳያውቅ በስህተት የተፈጠረን በደል ኃጢአት ይቅር እንደማለት ድንጋይ ይዞ ወጋሪው ለጉድ ነበር። እኔ ግን በደለ፣ ኃጢአት ሠራ የተባለውን ሁላ እያቀረብኩ ሁለተኛ እንዳትበድል የሚለውን የአምላኬን ወርቃማ ቃል እየጠቀስኩ በሰላም ኑሩ እያልኩ በመሸኘት በማጽናናትም በሁለቱም በኩል የሚረጨው ቤንዚል አካባቢ እሳትና ክብሪት እንዳያልፍ እየተሟገትኩ አይደረስ የለም ዛሬን ደረስኩ።

"…ጎንደሮችም ደወሉ። በቃ ልክ አላደረግንም። የጎንደር ታጋዮችንም ደም፣ የአጼ ቴዎድሮስንም አፅም አስወቅሰናል፣ በንፁሐን ዐማሮች በሚፈሰው ደማቸውም ጭምር ተወቅሰናል እናም ከወንድሞቻችን ተመልሰን በይቅርታ ለመቋጨት ተመልሰናል። አንተንም ዘመዴንም፣ ታዛቢ ሽማግሌዎችንም ቅር አሰኝተናል፣ እናም እንመለስና እንቋጨው በማለት ለእርቅ እጃቸውን ወደላይ ከፍ አድርገው ተማርከው ተመልሰዋል። እኔም የጠፋው ልጅ በተገኘ ጊዜ አባት የተደሰተውን ደስታ በሚያስንቅ መልኩ ተደስቼ እጄን ለሽምግልናው ዘርግቼ የቀጠሮውን ቀን በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ።

"…ሸዋዎቹም ደወሉ። አነጋገሩኝም። በኔትወርክ፣ በእኔ ያለመመቸት፣ በስንፍና፣ በቸልተኝነት የዘገየውንና የታዘዙትን በዛሬው ዕለት ፈጸሙ። አቅርቡ የተባሉትንም በሙሉ አቀረቡ። ተነጋገርን፣ ተወያየን፣ በደስታም ተቀጣጠርን። ውጤቱን በጋራ እናየዋለን። ሁሉም ውይይቶቻችን የተቀረጹ ናቸው። ታሪካዊ ቀረጻ። ለትውልድ የሚተላለፍ ቀረጻ ነው። እናም አሁን ልቤ አርፏል።

"…የእኔ ሽምግልና በሁሉም ጥሪና ምርጫ ነው። ሲያጠፉ በእኔ መገሰጽን መርጠው፣ ፈቅደው ነው የመረጡኝ፣ የጠሩኝም። ብዙ ሰዎች እሱ ምን አገባውም ሲሉ አደምጣለሁ። በተለይ ርእዮተ እስክንድር የሚለው የኋትስ ግሩፕ ላይ እሱ ምን አገባው? አለምአቀፍ የግጭት አፈታት አልተማረ፣ ማንበብና መጻፍ አይችል፣ እንግሊዝኛ አይናገር አይሰማ አይጽፍ፣ አያነብ፣ ምን አገባውና ነው እሱ ብለው ሲንጨረጨሩብኝ እንደሚውሉም አያለሁ፣ እመለከታለሁም። እግዚአብሔር ያሳያችሁ ጋሽ መሳፍንትን፣ ጋሽ ባዬን፣ ጋሽ መከታውንና ጋሽ አሰግድን ለማስታረቅ እንግሊዝኛ ማወቅ መስፈርት ሲሆን። ኮተታም ሁላ። ለማንኛውም በአማርኛ ቋንቋ እየተወያዩ ከዚህ ደርሰዋል።

"…ቲክቶክ ላይ አብዮት የሚያቀጣጥሉ፣ የሚያጫጭሱ፣ ፌስቡክ ላይ አቧራ የሚያጨሱ የትየለሌ ናቸው። ዐማራ የሚያሸንፍ መሆኑ ቁርጥ እየሆነ ሲመጣ በዐማራ በኩል ታዝለው 4ኪሎ የሚናፍቁም የትየለሌ ናቸው። የከሰረ ጡረተኛ ዳያስጶራ ሁሉ ቀሪ ዘመኑን በፋኖ ታዝሎ አንቱ፣ የተከበሩ ምኒስትር መባልን ፈልጎም ቋምጧል። ከአሁን ስንት ሕንፃ እንደሚሠራ ወስኖ ፕላንና ዲዛይን አሠርቶ የተቀመጠ የኡበር ሹፌር ሁላ አለ። እነ ወይዘሮ እገሊትም በቀረቡት ፋኖ ልክ ሙቀት እየተሰማቸው አዛዥ ናዛዥ የሆኑ ሁላ ቁጥር ስፍር የላቸውም።

"…ከጋዜጠኝነት ባሻገር የትግል ማኒፌስቶ አዘጋጅተው ፋኖን ለመጠምዘዝ የሚሞክሩ ምስኪኖች ሁላም አይቻለሁ። የፋኖ ትግል ከባድ ነው። አትችሉትም። የፋኖ ትግል የእግዚአብሔር ቁጣ ነው። ስዩም ተሾመ ተበሳጭቶ አረፋ ሲደፍቅ ሳየው አቢይ አሕመድ እንደተዠለጠ እና እየተነፋረቀ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። አሁን በዚሁ ከገገሙ። እኔንም ቢሆን በመሃላቸው አድርገው መነጋገር አቁመው በራሳቸው መንገድ፣ ባህል፣ ሃይማኖት መወያየት ከጀመሩ በዐማራ በኩል ነፋስ አይገባም።

"…በትግሉ የቆዩት አረጋውያኑ ለወጣቶቹም ዕድል እየሰጡ፣ እነሱ እንደበሬ፣ ወጣቶቹን እንደወይፈን አንድ ላይ አጣምሮ ማረስ ከጀመሩ ትግሉ ከዳር ይደርሳል። ከህወሓት ጋር ሳይሆን ከትግሬ ከሕዝቡ ጋርም ውይይት ቢጀመር ኦሮሙማው አይቀልድባቸውም ነበር። ብአዴኖችንም ቢሆን ሁሉንም ከመግፋት የሚመከረውን በቄስ በሼህ እየመከሩ የትግላቸው አጋር ቢያደርጉም መልካም ነው። አልመለስ ያለውን ደግሞ ያው መኮርኮም ተፈጥሮአዊ ነው። ከኦሮሞም ሆነ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ቢገፉአቸውም ዐማሮቹ ግን በቀደመ ፍቅራቸውና አቃፊነታቸው መቀጠል። መከላከያ ሠራዊቱ ሲማረክ በፍቅር መያዙን አጠንክረው መያዙ ያተርፉበታል።

"…በተረፈ በዐማራ ትግል ላይ መሽንክ ለመሆን የምትሞክር ዐማራ ነኝ ባይም ብትሆን እኔ የሀረርጌው ቆቱ መራታው ዘመዴ፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ አልፋታህም። የፈለግከውን በለኝ አልፋታህም። ጩህ እሪ በል። ቀውጠው ምንም አባክ አታመጣም። አልቅስ። መጪው ጊዜ የዐማራ ነው። ዐማራ የሚመራት ኢትዮጵያ እውን ትሆናለች። ፍቅር፣ ፍትሕ በምድሪቱ ይነግሳል። ክልል ይፈርሳል። ድንበር ከጎረቤት ሀገር ጋር ብቻ ነው የሚሰመረው። ደም አፍሳሾች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ዘራፊ ወንበዴዎች በሙሉ በፍትሕ ይዳኛሉ። የጃቸውንም ያገኛሉ። ኢትዮጵያዊ የሆነ በሙሉ ልቡ ከፈቀደበት ሥፍራ ሁሉ ለጤናው ተስማሚ ከሆነ ስፍራ ሂዶ የሚኖርበት፣ ሀብት አፍርቶ የሚኖርበት የተረጋጋ ሀገር ይፈጠራል። ለዚህም ተስፋ ሳልቆርጥ እደክማለሁ።

"…አንተ ቁጭ ብለህ አውራ፣ ፎግር፣ ፎትት፣ ተርብ፣ ደስኩር፣ እኔ ዘመዴ ግን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር በሟሟቅ ላይ እገኛለሁ። አለቀ።

• ድል ለዐማራው ፋኖ…!
• ለተገፋው ለዐማራው ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…እኔ ወደ እርቅ ውይይቱ ውስጥ ከመግባቴ በፊት ግን አምላኬ ባመለከተኝ ቀኝ ትከሻዬንም በሸከከኝ መልኩ የሁለቱንም አካላት የግለሰባዊም ሆነ የቡንድን ፍላጎት፣ ጠባይ፣ ርዕይ፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ አቋም ወዘተ ጥናት ለማድረግ ፈቃድ ጠይቄ፣ በዚያ ላይ ገዳማውያን በጸሎት እንዲያግዙኝ ሱባኤ አስይዤ፣ የጥሞና ጊዜም ወሰጄ፣ እነሱ እየቸኮሉ፣ አፍጥንልን እያሉ፣ እኔ ግን እንደ ሰጋር ፈረስ በልጓም ይዤ፣ ይዋል ይደርም ብዬ። ትእግስትን አስተምሬ፣ የምፈልገውን የተሟላ መረጃና ማስረጃ ከሰበሰብኩ በኋላ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ መጋቢት 27/2016 ዓም እነ ጋሽ መሳፍንት የሚመሩት ግሩፕ ደውሎልኝ የሽምግልናው ሂደት ተጀመረ። የአባቶች ጸሎት ሳይለየኝ ሁሉንም ገራም አደረገልኝ። ቀጥሎ የእነ ሟቹ ሜጀር ጀነራል ውብአንተ ቡድን የነበረውና አሁን አርበኛ ባዬ የሚመራውን ቡድን አነጋገርኩ። በመቀጠል ሁለቱንም ቡድኖች አገናኝቼ አነጋገርኩ። ተወያዩ፣ ተራረሙ፣ ወደ አንድነት የማየመጧቸውን ነገሮች ሁለቱም ሊተዉ ቃል ተገባቡ። አንደኛው ቡድን ምሎ፣ ያውም በአፄ ቴዎድሮስ አፅም፣ በታጋዮች በተሰዉት ደም፣ በጎንደር፣ አልፎም በዐማራ ሕዝብ ስም ምለው ከጨረሱ በኋላ ሌላኛው ቡድን ያፈርስ፣ ይተወው ዘንድ እንደ አንደኛው ቡድን ይምል ዘንድ ሲጠየቅ ስልኩ ተቋረጠ። ቡድኑ በሙሉ ድራሽ አባቱ ጠፋ። ለወትሮው በሰከንድ ይገኙ የነበሩት ሁሉ ጠፉ።

"…እኛም ተስፋ ሳንቆርጥ ውይይቱን አሳደርነው። ያኛውን ቡድን አመስግኜ፣ እነዚህንም ኔትወርክ ይሆናል ብዬ አሳምኜ፣ ክፉ ደግ ቃላት እንዳይናገሩም አሳስቤ። እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔርም ያክብራቸው እኒህኛዎቹ ክፉ ደግም ሳይናገሩ በይደር አሳደርነው። ያኛው ቡድን በተደጋጋሚ ይሠራ የነበረውን ዐውቃለሁ። ኔትወርኩ የተቋረጠበት እያስመሰለ የት ሄዶ ከማን ጋር እንደሚማከርም ዐውቃለሁ። የሚገርመው ነገር ግን እዚያኛው ቡድንም ውስጥ ሲገቡ ከዚያኛው ቡድን ውስጥ ያሉት ወፎቼ እኔን በጎን አስገብተው የሚሆነውን ሴራ ነሁሉ ማዳመጤ አልቀረም። እኔ ግን ይሄ ሁሉ ሴራ እያለ እያወቅሁ ውይይቱ ፍሬያማ እንደሆነ እና 99. 99999% ማለቁን ለሕዝቡ ሁሉ በቴሌግራም ገጼ አወጅኩ።

"…መሸ ነጋ፣ በነጋታው የስብሰባው ሰዓት ደረሰ። እንቅልፍ አጥተን፣ ከሰውነት ተራ ወጥተን፣ በስንት ድካም የጀመርነው ጉዳይ ከጫፍ ሳይደርስ በዚያኛው ወገን መጥፋት የተቋረጠውን ውይይት ለማስቀጠልና ቃላቸውን ለመቀበል ሁሉም ጓጓ። ዘወትር በሸዋውም፣ አሁንም በጸሎት ከፍተው በጸሎት የሚቋጩልን ካህንም ተገኝተዋል፣ የሁሉም ወገን ታዛቢዎች ገሚሱ ከእንቅልፉ ተቀስቅሶ፣ ገሚሱ ሥራ አስፈቅዶ፣ ገንዘቡን ከስክሶ፣ ተገኝቷል። ማሰንቆ አልቀረም ባለፈው ቀን ሲገኝ። የቀረ የጎንደር ፋኖ አልነበረም ውይይቱ የተቋረጠ ቀን። እናም እኔ የሆዴን በሆዴ፣ የልቤን በልቤ ይዤ ሰላምታ አቀረብኩ ለሁሉም…

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ቆይቶ ይቀጥላል… በትእግስት ጠብቁኝ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ማስታወሻ…

"…ይቅርታ ይሄ ከርዕሰ አንቀጼ ጋር የሚያያዝ ስለሆነ እያደመጣችሁት ጠብቁኝ። ልጁ ሞኝ መስሏችሁ ንቃችሁት የምትስቁ፣ የምታጣጥሉት ሰዎች እረፉ። ልጁን የሚጋልበው እና እንዲህ እንዲናገር የቀጠረውን ነው ያደቀቅነው። ያኮሰመንነው። ሞጣ ለምንድነው እንዲህ በል ተብሎ የሚለው። መልሱን የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ላይ ታገኙታላችሁ።

"…የማይሞቀኝ እኔ ዘመዴን፣ በመስደብ፣ በማዋረድ፣ በማበሻቀጥ ፀጥ የሚያሰኙኝ መስሏቸው የዳከሩት በሙሉ አፈር ከደቼ አስግጠናቸዋል። ሞኝ መሳይ የገደል ማሚቶ በበቀቀናቸው ነገ አረሳስተው ቢመጡም ሞጣንና ላኪዎቹንም ከቲክቶክ መንደር ጫማ ሰቅለው ለጊዜው እንዲያርፉ አድርገናቸዋል።

• 99. 99999% ያለቀው የዐማራ ፋኖ አንድነት ከምን እንደደረሰ ልለጥፍላችሁ ነኝ። ዋግም፣ ጠንቋዩ፣ አስማተኛው፣ ባለ ቆሌው ሁሉ ቆሌውን ገፈናዋል። ዐማራ አይሸነፍም። ኢትዮጵያን የሚያሳርፋት ዐማራ ብቻ ነው። አራት ነጥም።

"…ተመልሼ እመጣለሁ። እያደመጣችሁኝ ጠብቁኝ። በዚህ ጦማር ላይ ነገርየውን ከመመርመር በቀር ሞጣን አናንቆ የሚሳደብ ሰው ካየሁ እቀስፈዋለሁ። ሰምተሃል።

• እመለሳለሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤” 2ኛ ጢሞ 2፥20

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሓሳብ ስጡበት እስቲ…!

"…ሰውየው የጎጃም ዐማራ ናቸው። ቀን ጥሏቸው ቢርባቸው እንጀራ ፍለጋ እግራቸው ወዳመራቸው ሄዱ። ኦሮሚያ ደረሱ። እናም ኦሮሞዎቹ በዚህ መልክ እያስተናገዷቸው ነው።

"…ሰውየው የተራቡ፣ የደኸዩ፣ የተቸገሩ፣ ያጡ፣ የነጡ መሆናቸውን ለኦሮሞዎቹ በተማጽኖ እየነገሯቸው ነው። በማርያም በእግዚአብሔር እያሉም እየተማጸኑአቸው ነው። ኦሮሞዎቹ ግን  ለምን ክልላችን ኦሮሚያ መጣህ እያሉ በጥፊ፣ በዱላ፣ በእርግጫ፣ በጡጫ እየወገሯቸው ነው። ኦሮሞ እኮ አቃፊ ነው ይልሃል ቆይቶ…

"…የተሰበከው ጥላቻ ፍሬ አፍርቷል። አሁን ከፖለቲከኞቹ መንደር አይደለም ጥላቻው። በዘፈን፣ በቀረርቶ፣ በሽለላ የዐማራን ጥላቻ እየጋቱ ያሳደጉት ትውልድ አሁን የጥላቻ ስብከቱን ትርክት ፍሬ ማፈስ ጀምሯል። እንደ ሕዝብ በጥላቻ ማበዱን ከዚህ በላይ ማሳያ የለም። የዐማራ ጥላቻው የጾታ እና የእድሜ ገደብ የለውም። ሽማግሌው በከዘራ፣ ታዳጊዎቹ በጥፊ ነው ዐማራ ነው የተባለ የሚደበድቡት። ኅዘኔታ፣ ርህራሄ የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም። ደግነቱ ኦሮሞ ጣጣ የለውም። ይሄንን ግማታም፣ የከረፋ ዘግናኝ ወንጀሉን በገዛ ስልኩ ቀርጾ በቲክቶክ ይበትነዋል። ከኦሮሚያ ወደ የመን ለመሰደድ ሱማሌላንድ ላይ የተያዙ ኦሮሞዎች ዛሬ የዜና መነጋገሪያ ነበር። ስደት ክፉ ነው። ስደተኛ፣ ራብ ያጠቃው ሰው መደብደብ፣ ማዋረድ ወንጀልም፣ ግፍም፣ ኃጢአትም ነው። ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ።

"…ዐማራ የምትታገለው ከዚህ ብሔራዊ ውርደት ለመገላገል፣ ለመውጣት መሆኑን እመን። የማንም ጨቅላ የሚያነውርህ፣ የሚያሸማቅቅህ እንዳትሆን፣ ለልጆቻችሁም ጭምር ይሄንን ውርደት እያሳያችሁ ልጆቻችሁ አምርረው ለነፃነታቸው እንዲታገሉ አድርጉ። ኦሮሞዎቹ ግን ክፉ ዘር ነው የተዘራባቸው።

• ከምር አሁን ይህስ ምን ይባላል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጻችን አጠር ያለች ስለሆነች ወደ ውይይቱ መግባት እንችላለን። ቅዳሴ የማይቀድስ ሶዬ እንዲ ሚልዮን በሚልዮን ዶላር ተጥለቅልቆ ስታዩ አይገርምላችሁም?

"…በኦሮሞ ስም የሚዘርፉት ባለ ጊዜዎች ከዚህ በፊት በትግሬ ስም ሲዘርፉ እንደከረሙት ዘራፊዎች ጊዜ፣ ዘመን ፊቱን አዙሮ እንደፈረደባቸው ሰዎች አበላሉን፣ አሰራረቁን፣ አዘራረፉን ያወቁበት አይመስለንም። የኦሬክስ ወኪል ነን የሚሉት ሌቦች እንደ ትጌክሶቹ ወኪል ነን እንደሚሉት አዘራረፉ ወዝ የለውም። መጣም፣ መጣም ፍጥጥ ግግም ግጥጥ ያለ አዘራረፍ ነው የሚሉ መተርጉማንም አሉ።

"…አሁን ጥያቄው ቀውሲ በላይ ኦሮሞነቱ የቡዳ መድኃኒት ሆኖት ከዘብጥያ ይለቁታል ወይስ… እንትን ያደርጉትና … ምን ማለት ፈልጌ ነበረ ጠፋብኝ። 😁 …ብቻ እናንተ ግምታችሁን አስፍሩ፣ ሓሳብ አስተያየታችሁንም በጨዋ ደንብ ግለጹና ወደ ቀጣዩ መርሀ ግብራችን እናመራለን።

• ተንፒሱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እንደተለመደው ከምሥጋና ቀጥሎ ርዕሰ አንቀጽ ልጽፍ ነኝ። አንብባችሁስ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ? …የምጠይቃችሁ ይሁነኝ ብዬ ነው። መንደሩን ድብልቅልቅ ስታደርጉት የጠላት መንጋ ሰራዊት እንዴት እንደሚሸበር ስለማታውቁ ነው።

• ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…መቼም ያን ሊማሊሞ፣ አርበረከቴ ግራካሱ የመሰለ እኝኝብላ የሆነ የዛሬውን ርዕሰ አንቀጼን እንዳነበባችሁ በላይክ አድራጊው ብዛት ገምቻለሁ። አይናችሁን እስትራፖ ሳላስየዘው አልቀርም። የሆነው ሆኖ የጻፍኩት ጊዜ አግኝተው የማንበብ ፍላጎት ላላቸው የቲጂ መንደር ጓደኞቼ ነው። ያው በል በል ሲለኝ፣ ግራ ትከሻዬንም ቀኝ ትከሻዬንም ሲሸክከኝ እና ሲያመኝ ጤና የለኝም አይደል? ለዚያ ነው ያስረዘምኩባችሁ። እስከ ነገ ድረስ ሌላ ነገር አልጽፍባችሁም። 🙏🙏🙏 በመሃል ካልሸከከኝ በቀር ቃሌን እጠብቃለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ብጽፍስ ደግሞ ምን አለበት? ምን ክፋት አለው? አይደል…? 😂

"…ለማንኛውም በሥራ ምክንያት ትናንት ያልገባንበት የቲክቶክ መንደራችንን ለመጎብኘት ገባ ብዬ ወጣ ለማለት ወደዚያው እየሄድኩ ነው። እስከዚያው በርዕሰ አንቀጹ ላይ ያላችሁን የራሳችሁን አስተያየት ለማንበብ ዝግጁ መሆኔን ስገልፅ ከፍ ባለ አክብሮት እና ትህትና ነው። (ወይ ትህትና እቴ) 😁

• እየጻፋችሁ…እየሄዳችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …እየረበሸች ነው። የዐማራ ክልል ሰላም እንዳይሆን እየረበሸች ነው ብሎም መግለጫ እስከመስጠት ደርሶ ነበር። ሲገመገም ሕወሓት የምትፈልገውን ሰጥተን ከዐማራ ጋር መቆሟን እንድታቆም ማድረግ አለብን፣ ሁሉንም ከምናጣ አንዱን እንጣ ነው ነገሩ። ትናንት እንዳልኩትም መከላከያ ተብዬው ራያ አላማጣን አስተዳዳሪ ገድሎ ህወሓት እንድትገባ ካደረገ በኋላ ለገሰ ቱሉ ወደ ሚዲያ ወጥቶ ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሳለች ብሎ ዋይ ዋይ እያለ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆኖ ይተውናል ባልኩት መሠረት ይኸው ዛሬ ወደ ሚዲያ ወጥቶ "ህወሓት የፕሪቶሪያን ስምምነት ጥሷል" እያለ ይፎግራል። ማፈሪያ።

"…ብልፅግና ስር እደሌለው ዛፍ ነው። ተቦርቦሮም ያለቀ ነው። ማድያት ፊቱን ወርሮት በሜካፕ ሸፍኖ የሚዘንጥ ነው ብልጽግና። ውኃ ሲነካው የሚለቅ ቡራቡሬ ነው ብልጽግና። ምስጥ በልቶት ሊወድቅ የደረሰ፣ ነገር ግን በቀለም ያማረ፣ በመብራት ያሸበረቀን ቤት ነው የሚመስለው። ብልጽግና እስስት ነው። መናፍቅ ከሃዲ ነው። ብልጽግና አራጅ ነው። የአውሬ ገባሪ ነው። ብልፅግና ውሸት ሀሰትም አይደለም። ራሱ የሀሰት ፈጣሪዋ ነው። በብልፅግና ሴራ መታለል፣ መሸወድ አይገባም። እያንዳንዱ የብልጽግና ሴራ ለዐማራ ፋኖ እንደ መልካም እድል መጠቀም ያስፈልጋል። ሁሉም ዐማራ ዓይኑን ከ4ኪሎ ላይ ማንሣት አይገባውም። ለወያኔ የራያን ፋኖ ብቻ ይዞ መግጠም ይቻላል። የብልፅግና ሴራ በፈጠጠ ቁጥር ዐማራው ይነቃል። በሰው ኃይል ሁላ ይደራጃል። ብአዴን ይፈርሳል።

"…በመጨረሻም ይህቺን ከትግሬ ቦለጢቀኞች ቤት የተገኘች የፖለቲካ ትንተና እና ግምት፣ ትንቢትም በሉት ደጋግማችሁ ታነቡት ዘንድ በመጋበዝ ርዕሰ አንቀጼን ልቋጭ።

"…የወዲ ወረደ የትላንቱ መግለጫ፣ የጌታቸው አጭር የፌስቡክ ጽሑፍ እና የዛሬው የዐማራ ክልል መግለጫ

"…የትግራይ ክልል መንግሥት ከብአዴን ጋር የተፈራረመው ምንም ዓይነት ውል የሌለ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት በዐማራ ክልል መንግሥት መግለጫ ላይ ምላሽ ይሰጣል ብዬ ባላምንም. . .ይህንን በሚመለከት ግን በቅርቡ የፌደራል መንግሥቱ የሚሰጠው መግለጫ ምላሽ ሁሉን ነገር ግልፅ ያረገዋል የሚል እምነት አለኝ…!

"…የሆነው ሆኖ የብአዴን እና የወጣት ሊጉ አብን ከቀናት በፊት የሰጠው መግለጫ መመሳሰል የሚነግረን ነገር ቢኖር

1. የክልሉ መንግሥት በዚህ አጋጣሚ ድጋፍ ለማግኘት እና ወልቃይት እና ራያ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበሩበት ሲመለሱ እኔ የለሁበትም ወረራ ሰጠ! ወረራ ነሳ በማለት ከደሙ ንፁህ ነኝ ለማለት!

2 በብአዴን እና በፌደራል መንግሥቱ መሃል ምናልባትም የፕሪቶሪያ ስምምነቱ አፈፃፀም ላይ አለመግባባት መኖሩን

3.ወይም በክተት ሰበብ ተበትኖ በየቀበሌው በደፈጣ ያስቸገረውን የፋኖ አደረጃጀትን ወልቃይት እና ራያ ላይ ለመሰብሰብ እና በመደበኛ ውጊያ ለመደምሰስ

4. የትግራይ ክልል መንግሥት ልክ የዛሬ ዓመት ጌታቸው ረዳ አሜሪካ ከትግራይ የዲያስፖራው ማኅበረሰብ ጋር በነበረው ውይይት እንዳለው. . ''.የፌደራል መንግሥቱ በወረራ የተያዘብንን ግዛት በጉልበት እንድናስመልስ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብልንም. . ይህ ሃላፊነት የፌደራል መንግሥቱ በመሆኑ እና ከአቅሙ በላይ ይሆናል የሚል እምነት ስለሌለን አልተቀበልነውም! ነገር ግን ከአቅሙ በላይ ሆኗል ብለን ካመንን እና ጥያቄ ከቀረበልን ሕገ መንግሥታዊ ግዛታችንን ለማስመለስ አስፈላጊውን ትብብር ማድረጋችን አይቀርም'' እንዳለው በፌደራል መንግሥት ይሁንታ በወረራ የተያዙ ግዛቶችን በጉልበት የማስመለስ ሂደት ላይ መኮኑን መደምደም ይቻላል!

5. የመጨረሻው እና የመሆን ውስን አጋጣሚ ያለው ግምቴ ደግሞ የፌደራል መንግሥቱ በብአዴን በኩል ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማስተላለፍ እና ሁኔታውን ማወዛገብም ሊሆን ይችላል! የቼሪ እና አስረስ ጨዋታ ማለቴ ነው! የሆነው ሆኖ. . .ምክንያቱ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱ ይሁን ወይም ሌላ ፍፃሜው ግን አጓጊ ነው! ይልና ይሄንኑ የታደሰ ወረደን መግለጫ መነሻ በማድረግ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት መድረሳቸውን በማተት ሌላ ትንተና ይሰጣል። አደገኛውንና በከባዱ የተመከረበትን ምክርም የሚያሳይ ምልክትም ይሰጣል።

"…ታዲያ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል ፖሊስ፣ የዐማራ ፋኖን ከመሬቱ በማንፃት የራሱንን አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲገነባ ከፈቀደ ይህም በምዕራብ ትግራይ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህ ሆነ ማለት ደሞ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተተግብሯል ማለት ነው!! በዚህም የፋኖ ኃይል ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር አጋርነት ሲሆን ለፌደራሉ መንግስሥት ደግሞ የዓለም መንግሥታት የሚለቁትን የዶላር ገንዘብ ይለቀቅለታል ማለት ነው።

"…ነገር ግን የሻብዕያ ልጅ የሆነው ፋኖን ይላል "ነገር ግን የሻብዕያ ልጅ የሆነው ፋኖን የፌደራሉ እና የትግራይ ኃይል በጋራ ጥምረት የሚመቱት ከሆነ እና የምዕራብ ትግራይ ጉዳይም እንደ ደቡብ ትግራይ በትግራይ ሠራዊት የሚፈታ ከሆነ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ቀጠናዊ ቆርሾ ከፍ ይላል ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ የዓለም መንግሥታት በአፍሪካ ቀንድ በዚህ ሰዓት ውጥረት ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለማይሆኑ አንዱ ኃይል በዓለም መንግሥታት ይመታል ማለት ነው።

"…የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም መንግስታትን ፍላጎት በፕሪቶሪያው ስምምነት የሚያስፈፅም ከሆነ የኤርትራ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን ከዓለም መንግሥታት ጋር ስለሚሆን ጨዋታው በትግራይ መንግሥት እና በፌደራል መንግሥቱ ስምምነት ወቅት ተጠናቅቋል በማለት በጓዳ ተመክሮ የወሰኑበትን ጉዳይ ይዘረግፈዋል። ዐማራ ከትግሬ ጋር ፍቅር ይኖረኛል ብለህ መጃጃሉን ትተህ በእነሱው የጭካኔ መስመር ሄደህ መብትህን እንድታስከብር እመክርህሃለሁ። ሲያዩት የሚከብድ የሚመስል ቢሆንም ዓረቡም ሆነ እነ አሜሪካ ተደርበው ቢገቡ ሱማሌና አፍጋኒስታን ድል የነሱትን ኃይል የዐማራ ፋኖ ያቅተዋል ተብሎ አይታሰብም። ስለዚህ ከዚህ የትግሬዎቹ ትንተና ተነሥተን ትግሬም አቢይም የሚፈልጉትን ፍላጎት ለሟሟላት ዐማራውን ተጠቃቅሰው ጭዳ ለያያደርጉት መጨረሳቸውን ዐወቆ በዚያው ልክ መዘጋጀት ያስፈልጋል።

• ድል ከዐማራው ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራው ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ኃይል ስለመኖሩም ግን አላውቅም። የሰማሁት ነገርም የለም። (ጥርት ብሎ እንዲገለጽልኝ ግን ጸልዩልኝ ወይም የገባችሁ አስረዱኝ) በግሌ ግን እኔ በበኩሌ ከነ ጥርጣሬዬም ቢሆን የማርሸት የግሉ አድናቂ ነኝ። ንግግሩ፣ የቃላት አሰዳደሩ፣ ፍጥነቱ ሁሉ አፍ የማያስከድን ነው። አንደበተ ርቱዕም ነው። (በዐማራ ላይ ጄኖሳይድ አልተፈጸመም) የሚለው ሙግቱን ደጋግሜ ስሰማው ነገርየው ሊገባኝ ባይችልም ብቻ የጠራ ነገር የለኝም። ኦሮሙማው በጎጃም ይቀበራል። ጎጃም ፔርሙዳ ነው።

ሆ፦ ሸዋ

"…የሸዋም ለየት የሚል ባህሪ ነው ያለው። ከሌላው የዐማራ ክልል እንደሸዋ ቅጥቀጣ የደረሰበት ስለመኖሩ አላውቅም። ወያኔ የአጼ ዮሐንስን ለመበቀል፣ በጠላትነት የፈረጀችውን የሸዋ ሕዝብ ሽፍታ በማጥፋት ሰበብ ጄኖሳይድ የፈጸመችበት ገና ድሮ ጠዋት አዲስ አበባ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት የገባች ጊዜ ነው። ቀድመው የነቁትን የሸዋ ዐማራው ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን ቀርጥፋ የበላችውም በጠዋቱ ነው። እነ አጣዬን ከ10 ጊዜ በላይ ያቃጠለው ኦሮሙማም እንደ ሸዋ የፈጀው የለም። እነ ጃራ የሸዋ ዐማራን በግድ በኃይል ያሰለሙትም እዚያው ነው። ወያኔ እንኳ ከመቀሌ ተነሥታ የጁላ ጦር እየሸሸላት ያወደማት ሸዋን ነው። እናም ሸዋ በተለየ መልኩ ጫና ይበዛባታል።

"…ሸዋ ለ4 ኪሎ ቅርብ በመሆኑም የአገዛዙ ሙሉ ትኩረት እዚሁ ይሆናል። ሸዋ በሰሜኑ በኩል ከኦነግ፣ ከኦሮሞ መከላከያና በኦነግ መንፈስ ከሚመራው የወሃቢያ እስላሞች ጋር ይገጥማል። ሸዋ በምሥራቁ ክፍል የኦነግ፣ የኦሮሞ መከላከያና የኦሮሞ ሚሊሻ ከኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ኦነግ ሸኔ ጋር ይገጥመዋል። መንዝ፣ መሃል ሜዳ፣ መራቤቴ፣ ደራም ያለው ዐማራ ከኦሮሞ ልዩ ኃይል፣ ከኦነግ ሸኔና ከመከላከያው ጋር ነው የሚገጥመው። ያ ውኃ አይገባው ድንጋይ የዐማራ አድማ ብተናና የአማራ ሚሊሻም በብአዴን እየተነዳ የሸዋዎች ተጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል። ከላይ እንዳልኩት ሸዋ ለማዕከላዊ መንግሥቱ፣ ለሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ለ4ኪሎም ቅርብ ስለሆነ ዱላውም የዚያኑ ያህል ይበዛበታል። ነገር ግን ሁሉንም የሚመጣበትን ከመመከት በቀር ሌላ አማራጭ የለውም።

"…ይሄ በዐማራ ክልል የሚገኙ ዐማሮች የሚጠብቃቸው ግጥሚያ ሲሆን ከክልሉ ውጪና በውጭ ሀገር የሚገኙ ዐማሮች የሚገጥማቸውን ዐውደ ውጊያ ደግሞ በስሱ አብረን ለማየት እንሞክር።

• ከክልሉ ውጪ ያሉ ዐማሮች

ሀ፦ አዲስ አበባ

"…በአዲስ አበባ የሚገኘው ዐማራ በተለይ እዚያው አዲስ አበባ ከተማ ተወልዶ ያደገው ዐማራ የዘር ፖለቲካ ጨዋታው ምንም ሊገባው አልቻለም። እንዲገባው ስለማይፈልግም ሊገባው አይችልም። አዲስ አበባ ያለው ዐማራ ማንም ይግዛ ማን ሠርቶ፣ ተምሮ፣ በሰላም ውሎ መግባቱን ብቻ እንጂ ወደ ፖለቲካው አካባቢ ድርሽ ማለት የማይፈልግ ነው። ፖለቲካና ኮረንቲን በሩቁ ባይ ነው። ሀገሩን መውደዱን የሚገልጸው የኢትዮጵያ አትሌቶች፣ የብሔራዊ ቡድኑ ውድድር ሲኖርበት መደገፍ፣ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ የሚል ዘፈን ሲያወጣ በስሜት አብሮ ማንጎራጎር፣ ካምቦሎጆ ገብቶ ኢትዮጵያ የእኛ መመኪያ፣ ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን አም፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም ብሎ ዘጠና ደቂቃ በድራፍት ኃይ በአቼኖና በአዳነ እየተመራ መጨፈር ይመስለዋል። እናም ጣጣ የለውም።

"…ቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት መሰቃየቱን በገንዘብ ኃይል ለመፍታት መሞከሩንም እንደ ብልጠት፣ እንደ አራድነት የሚያይ ነው የአዲስ አበባ ዐማራ። ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ክፍለከተማ፣ ክልል፣ ፓርላማ ገብቶ መሥራት ይሸክከዋል። ቀበሌውንም ፓርላማውንም ለክፍለ ሀገር ልጆች ለቆላቸው እሱ ፍዳውን ይበላል። ፖለቲካ እንደሆነ አይገባውም። እናቱን የሴፍቲ ኔት ተጠቃሚ አድርጎ ከዚያ በሚመጣ የምጽዋት ዘይት እየበላ ልክ ደህና ቤተሰብ እንዳለው ሰው በአደባባይ ሲጎርር ጉራውን ሲቸረችር ይውላል። እሱ አራዳ ነው። እየመጡ ነው ብሎ በመጨፈር ለፋኖ ደሙን የሰጠ ይመስለዋል። ሀገሪቷ ግልብጥብጥ ብትል አርሰናል አይሸነፍበት፣ ማንችስተር ነጥብ አይጣልበት እንጂ ደንታው አይደለም። ፖለቲካው ቡናና ጊዮርጊስን አዲስ አበባ ላይ እንዳይጋጠሙ አድርጎ ዱባይ ወስዶ ሲያጣልዝ እሱ አይገባውም። የሰው መሰባሰብ ችግር ይፈጥርብኛል ብሎ ጨዋታ ከአዲስ አበባ ማራቁን አይባንንም።

…ድሉ የዐማራው ነው። የተደራጀ ዐማራ ያሸንፋል። ድሬደዋ፣ ሀረር ሕብረታቸው ደስ ይላል። ደቡብም እንደዚያው። የሚያሰጋው ጋምቤላ ኢሉአባቦራ ነው። ባሌና አሩሲ ከተደራጀ አይደፈርም።

ሂ፦ ዳያስጶራው ዐማራ

"…ኬንያም፣ ጅቡቲም ያለው ስደተኛ ያው ዳያስጶራ ነው የሚባለው። ቅርብ አፍሪካ ያሉት ቢፈሩ አይፈረድባቸውም። ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ናይሮቢ ሆኜ ብቃወም የሚጠብቀኝን አስባችሁታል? እናም በእነሱ መፍረድ አይቻልም። ባህር ተሻግሮ አውሮጳና አሜሪካ የገባው ግን ያስቀኛል። በአየርም፣ በባህርም የመጣው ስደተኛ ዐማራ ፍርሃቱ ዘርፈ ብዙ ነው። አንዳንዳንዱ ዐማራ የተሰደደው ርቦት ነው። እናም ሠርቶ ሲያገኝ ማምሻ ዕድሜውን ሀገሩ ገብቶ በሸነና ብሎ መሞት ስለሚፈልግ ስለ ቦለጢቃው አያገባውም። በቃ ሆዱን እንዳሳደደ ይኖራል። ውስኪ በ30 ዩሮ፣ ቢራ በሳንቲም መጠጣት የልጅነት ሕልሙን እንደማሳካት ስለሚቆጥረው ለቦለጢቃው ደንታ የለውም። እንዲህ ዓይነቱ ሰው እንኳን በሀገሩ ጉዳይ ከቤተሰቡ ጭምር አድራሻውን ሰውሮ ነው እንደ ጅብ ተደብቆ እየበላ የሚሞተው። ሲበዛ ሆዳም፣ ራብ ያጠቃው ነው።

"…ይሄ ሆዳም ዐማራ ሴትም ከሆነች ቲክቶክም፣ ዩቱዩብም ላይ በአውሮጳና በአሜሪካ ርካሽ የሆነውን ምግብ እየሠሩ እየበሉ በራብ ለሚሰቃየው ወገናቸው የምግብ ጥያቄአቸው እንደተመለሰ በማሳየት ሲያስጎመጁ ይውላሉ። ቁርስም፣ ምሳም፣ ራትም ሲበሉ፣ ቡናም ጭማቂም ሲጠጡ Live ቀርበው ይለፋደዳሉ። ራብና ጠኔ ከሀገር ያስወጣቸው ስለሆኑ በቀል ላይ ናቸው። ውራጅ ጨርቅ፣ ሜካፕ ተቀብተው ሀብታም ሀብታም ይጫወታሉ። ሀገር ቤት ለእረፍት ሄደው ወር የማያቆይ ሳንቲም ያላቸው ሁሉ፣ እቁብ ጥለው የአውሮጵላን ትኬት ቆርጠው ዛር ወጥቶ ተንቀጥቅጦ የሚሄደው ሁላ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ሲያክት አይጣል ነው። አመንዝራ፣ ሆዳም፣ መሃይም ስደተኛ ዐማራው ለቦለጢቃው ደንታ የለውም።

"…የተማረ፣ ደኅና ቦታ ደርሷል የሚባለው ዐማራ ድሮ በኢህአፓ ጊዜ፣ ከዚያም በዲቪ የሄደው፣ ቀደም ብሎ የወጣው፣ ወጥቶም ራሱን በትምህርት አሻሽሎ የእውቀት ወረቀትም፣ ገንዘብም ያለው ነው። እሱ ደግሞ ድሮ ላይ ተቸንክሮ የቀረ ነው። ዐማራ ሆኖ ከኢትዮጵያዊነቴ አልወርድም በማለት 1960 ላይ ተቸንክሮ የቀረ ነው። አሁንም አብዮተኛ ነው። ኢህአፓው ኢህአፓ፣ ደርጉም ያው ደርግ ነው። እናም የቦለጢቃ ጨዋታው አልገባውም። የገባቸው ደግሞ ገሚሶቹ ጩሉሌ ናቸው። አራዶች። በትምህርት ያጡትን ሀብት በትግሉ ስም ቀፍለው ፏ ብለው የሚልዮን ዶላር ቤት እና ቴስላ መኪና እየነዱ ይኖራሉ። ቦለጢቃውን በሩቁ የሚሉት ዳያስጶራዎች ለእነዚህ አጭቤዎች ገንዘቡን ወርውረው እነርሱ ድራሻቸውን ያጠፋሉ። እናም አጭቤው እየከበረ፣ ትግሉ እየከሰረ ይሄዳል።

"…እንጂ ዳያስጶራው ዐማራ መገፋፋቱን፣ ተቸንካሪነቱን፣ ጎጠኝነቱን፣ መንደርተኝነቱን ትቶ እንደ ዐማራ ተደራጅቶ ቢነሣ ተአምር ነው የሚሠራ የነበረው። አገዛዞች ደግሞ ሆዳም አማራውን በሽታ ነው የሚያውቁት። ሆዳምና መሃይም ዐማራ ለአምባገነኖች ምቹ አፈር ነው። መሃይም እና ሆዳም ዐማራን ኤምባሲ መጋበዝ ብቻ በቂ ነው። አምባሳደሩ ከደወለለት ክርስቶስን ያገኘ ነው የሚመስለው…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የበሻሻው አራዳ ልቡሰ ሥጋው ከሃዲ ውሸታም ደም አፍሳሹ እቡዩ አህመድ በሊቀ ሰይጣናቱ በክፉ ጨካኙ በዳንኤል ክብረት መሰሪ የይሁዳ ምክር ኖረውም የማይጠቅሙትን የዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩን አረጋ ከበደን ጨምሮ ለሱሙ ወሳኝ የሚባሉትን ዋና ዋኖቹን የዐማራ ክልል ባለ ሥልጣናት በፕሪቶሪያው የኦህዴድና የህወሓት ስምምነት መሠረት በፌደራል መንግሥቱ ይሁንታ በመከላከያው ድጋፍ "ህወሓት ራያ አላማጣ ወረዳዎችን በሚያስረክቧት ወቅት" እኛ በሀገር ውስጥ በልነበርንበት ጊዜ ነው" የሚል ምክንያት እንዲኖራቸው ለማድረግ በመምከር "በዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ የዐማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ አመራሮችና የሚዲያ ሓላፊዎችን ያካተተ ልዑክ ከአፕሪል 12/2024 ወይም ከሚያዝያ 4/2016 ዓም ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት ለሥራ ጉዳይ በሚል ምክንያት ወደ ሰሜን አሜሪካ እንዲሄዱ ተደርገዋል። የዐማራው ወኪሎች በቆይታቸው ወቅት ወጪያቸውን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት እንደቻላቸው የተነገረ ሲሆን ለቀን አበል የሚሆን የኪስ ገንዘብም ከዚያው ከፈረደበት የዐማራ ሕዝብ ኪስ ካቋቋመው ከአሚኮ በጀት ላይ ለእያንዳንዳቸው በዶላር እንዲከፈላቸው ነው የተደረገው ተብሏል። አሁን ሀገረ አሜሪካ እንዲሄዱ የተገደዱት የክልሉ ባለ ሥልጣናት ሄደው በላስ ቬጋስ ከተማ የሚገኙ ሲሆን በዚያም በቬጋስ በሸነና እያሉ እንደሆነ ነው የተሰማው። ላስቬጋስ ካዚኖ ቤት ተገብቶ 8 ሺ ዶላር ምን ልትጠቅማቸው ነው?

"…ቀደም ሲል አቢይ አሕመድ እነ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ያሉበት ኮሚቴ በማቋቋም፣ አረጋ ከበደና ቡድኑ በአገው ሸንጎው በአቶ ሰማ ጥሩነህ ተጠርንፎ ህወሓት መጀመሪያ ራያን፣ ቀጥሎ ደግሞ ወልቃይትን እንድትረከብ ከህወሓት ጋር እንዲስማሙ አደረገ። ከሕዝቡ ለሚነሣብን ተቃውሞስ ምን እንመልሳለን ለሚለው ስጋታቸውም የተሰጣቸው መልስ "የዐማራ ሕዝብ ምንም አያመጣም። ትንሽ የአፍ ድለላ ማድረግ ብቻ ፀጥ ለማሰኘት በቂ ነው። ዐማራ ስለ ፍቅር፣ ስለ አንድነት ከተሰበከ ይሸነፋል። ይተወዋል። ስለ ዐማራ ሕዝብ እኛ አለን ስለ ሕዝቡ አታስቡ። ለእሱ እሱን ዝም ለማሰኘት እኛ በሚገባ ተዘጋጅተናል። አስቸጋሪ የሚሆኑ የዐማራ ብልጽግና ሰዎች ካሉም እርምጃ ይወሰድባቸዋል። የዐማራ ብልጽግና ሰዎች አኩርፈው የሚሄዱበት መጠጊያ እንዳይኖራቸውም ተደርጓል። እሺ ብለው ለእኛ ከታዘዙ መልካም እምቢ ካሉም ግን ወይ በእኛ አልያም በፋኖው ይበላሉ። እናም ስለ ሕዝቡ አታስቡ በማለት ነው ወደ አማሪካ የሸኟቸው። ንግድ ባንክም በታዘዘው መሠረት፦

1ኛ፦ ለአረጋ ከበደ የዐማራ ክልል መስተዳድር 8350$ 2ኛ፦ ለይርጋ ሲሳይ የአሚኮ ቦርድ ሰብሳቢ 8350$
3ኛ፦ ለአህመዲን መሐመድ የአሚኮ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ 8350$
4ኛ፦ለመንገሻ ፋንታሁን የአሚኮ ቦርዳባል 7450$
5ኛ፦ሙሉጌታ ሰጥዬ የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ 8350
5ኛ፦ለግዛቸው ሙሉነህ የአሚኮ አማካሪ 7450$
6ኛ፦ለተሾመ ውዱ የአሚኮ ምክትል ስራ አስፈጻሚ 6850$
7ኛ፦አንዳርጌ መዓዛ የርዕሰ መስተዳድር ፕሮቶኮል ሹም 6850$ ያህል ገንዘብ ነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህርዳር ቅርንጫፍ ከሚገኘው የኮርፖሬሽናችን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ተቀናሽ ሆኖ ሰጥቷቸው "ጎሽ የእኛ አንበሶች፣ መልካም የበሸነና ጊዜ ይሁንላችሁ። አቶ ገዱን ካገኛችሁት በዚያው ሰላም በሉልን በማለት ነው የሸኟቸው።

"…በትናንቱ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ መግለጫ በተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተጠቀሰው "የዐማራ ሕዝብ በብአዴን መሪነት የሚመጣ ውርደት እንጅ ነጻነት የሌለ መሆኑን ካወቀ ውሎ አድሯል፡፡ ይሁን እንጅ በዋና ዋና ከተሞች የሚታየው መዘናጋት ዋጋ የሚያስከፍለን በመሆኑ ዘላቂ ነጻነቱን ለማረጋገጥ ፍጹም መራራ ትግል በማድረግ ትግሉን ማቀጣጠል አለበት፡፡ የዐማራ ሕዝብ በመስዋዕትነቱ ወደእናት ግዛቶቹ የመለሳቸውን እነ ራያ ወልቃይትን አሳልፎ እየሰጠ ያለውን ብአዴን፣ ገጠር ከተማ ሳይል የፈራረሰ መዋቅሩን ጨርሶ ግብዓተ መሬት ለማስገባት ሁሉም በያለበት እንዲፈንን (ፋኖ እንዲሆን) የትግል ጥሪያችንን እናቀርባለን በማለት የጠቀሱትንም የምንመለከተው የብአዴንን አይረቤነት ሁሉም የሚረዳው መሆኑን ነው።

"…የሚገርመው ደግሞ እነ አረጋ ከበደን በላስቬገስ ተቀብሎ እንዲያስተናግዳቸው በአቢይ አሕመድ የታዘዘው ግለሰብ ኤርትራዊ ባለሃብት መሆኑ ነው። ሻአቢያ፣ ወያኔ እና ብልፅግና አሁንም ቁማር ላይ ናቸው ማለት ነው። ከድሮ ጀምሮ ከጥንትም ሁሌ እንደምለው "የመለስ ዜናዊን ቡድን የበሉት ሻአቢያ፣ አቢይ አሕመድና የዓድዋው ወያኔ በመጨረሻ ግንባር እየፈጠሩ መገለጣቸው እውን መሆኑን ነው። የዋህነት ብቻ ሳይሆን በብዙ ደንታ ቢስ፣ ዳተኛ፣ ቸልተኛ፣ ሰነፍ ጅልነት እና ፈሪ ቦቁባቃ የተሞላው የዐማራ ቦለጢቀኛም የሚሆነውን እያየ አፉን ለጉሞ ተቀምጧል። አሁን ላይ ምድር ላይ ያለው ዐማራ ጥሩ ነው። አየር ላይ ያለው ዐማራም አሁን ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም አሁንም ግን ይቀረዋል። ዐማራም እንደ ትግሬ እና ኦሮሞ ቦለጢቀኞች ጨካኝ፣ ከሃዲ፣ አረመኔ ካልሆነ በቀር ሕዝቡን በቀላሉ መታደግ የሚችል አይመስለኝም።

"…የራያው ወረራ በዚያ የሚቆም አይደለም። አይቆምም። ጠለምት፣ ከዚያ ወልቃይት ልክ በራያው መንገድ ነው ከዐማራው ፈልቅቀው ለመውሰድ የተዘጋጁት። ብልጽግናን አምነው በራያ፣ በወልቃይት እና በጠለምት ከሕዝባቸው ወኪል ከዐማራ ፋኖ ጋር የተቀያየሙ በሙሉ የሚጠብቃቸው ሞት ብቻ ነው። ካልሸሹ ወያኔ፣ ከሸሹ ብልፅግና ይገድላቸዋል። የሚሞተው የብልፅግና ባለ ሥልጣን ዐማራ ስለሆነ ችግር የለም። ዐማራ ብልጽግና ሆነ፣ ብአዴን ሆነ፣ አብን ሆነ፣ ተራ ሕዝብ ሆነ ሞቱ ጣጣ አያመጣም። ለዚህ ነው ብልፅግናን አምኖ የራያ አስተዳዳሪ ሆኖ የሄደው የደብረታቦር ዩኒቨርስቲው አቶ ደርበው፣ የቅርብ ጊዜ ሙሽራው የጫጉላ ጊዜውን ያልጨረሰውን ሰው የህወሓትን ወደ ራያ መግባት ተከትሎ የደፉት፣ የገደሉት። በዚህ ሰው ሞት ሚስቱና ቤተሰቦቹ ያዝናሉ። ህወሓት እና ብልፅግና ይደሰታሉ። በሰውየው ሲሳደድ የኖረው፣ የከረመው ፋኖም ሥራው ያውጣው ባይ ነው። ደመ ከልብ በሉት። ይኸው ነው ወልቃይት ላይም የሚከሰተው። መዝግቡልኝ። 

"…ከዚህ ተነሥቼ ለዐማራ የእኔ የዘመዴ ምክር የሚከተለው ነው። ዐማራ በቀጣይ ከፊቱ ብዙ የጦር ግንባሮች ከብዙ ኃይሎችም ጋር ከባድ ጦርነት ይገጥመዋል ብዬ እጠብቃለሁ። ለሁሉም የጦር ግንባሮች ግን እኩል መዘጋጀት ይኖርበታል። ዐማራ ሰፊም ጀግናም ሕዝብ ስለሆነ ከተናበበ አሸናፊነት የእጁ ነው የሚሆነው። ዐማራ ከበፊቱ በተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የታወቀ ነው። እንደ በፊቱ በጥቂት ሰዎች የሚታገል አይደለም። በሀገረ መንግሥቱ ተስፋ የቆረጠ እና ወደ አባት ሀገር ዐማራ ፊቱን ያዞረ ዕልፍ ዐማራ የዐማራ ትውልድ ስለተፈጠረ አያሳስብም። ፈተናው እንዳለ የተረዱ ምሑራን፣ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ገበሬዎች፣ የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የዐማራ ልዩ ኃይል እና ሚኒሻዎች የዐማራ ፋኖን ተቀላቅለው ዐማራ ትግሉን በብረት ጀምሯል። እናም ገና ለጋው የዐማራ ትግል ገና ከአሁኑ ሀገሪቷን ሽባ አድርጓት ተገኝቷል። መሀል ሰፋሪው፣ ሰነፉ፣ ደንታ ቢሱና ባንዳው ዐማራም ሲመርረው ትግሉን መቀላቀሉ አይቀርም። እናም ዐማራ ውሎ ሲያድር ወጥሮ በመመከት ሃቅ ስላለው ሁሉንም ጠላቶቹን ያሸንፋል። እኔ በዐማራ መቼም ተስፋ አልቆርጥም። የጦር ግንባሮቹንም እጠቅሳለሁ።

ሀ፦ ሰሜን ወሎ ራያ … 👇 ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም። ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን? ወንድሞቼ ሆይ፥ በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውኃም ጣፋጭ ውኃ አይወጣም።” ያዕ 3፥10-12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይሄም ኦሮሚያ ነው…

"…በኦሮሚያ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ቄሮ ያወጀውን ዐዋጅ ተላልፈው የተገኙ ናቸው የተባሉ ባጃጆች እና መኪኖች ዐዋጁን ባወጀው ቄሮ አቶ በቴ በተገደሉበት መቂ ከተማ በዚህ መልኩ ሲቃጠሉ፣ ሲነዱ አምሽተዋል።

"…ኦሮሚያ ግን እየለማች ነው። ሥልጣኔአቸውም በጣም፣ በጣም ይገርማል። የአቶ በቴ አሟሟት ግን ከምር ይዘገንናል። በስመ አብ ኦሮሚያ ያለው ጭካኔ ግን ያስደነግጣል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ቦታው ስዊዘርላንድ ጄኔቭ ነው።

"…የስብሰባው ምክንያት በኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ለተጠቁ አካባቢዎች እስከ አንድ ቢልየን ዶላር የሚደርስ ዶላር እርዳታ ከዓለም መንግሥታት ለመለመን የተዘጋጀ ነበር።

"…ይሄንኑ ጉዳይ ለዓለም መንግሥታት አስረድቶ ለመለመን አቁፋዳቸውን ተሸክመው ጄኔቫ ድረስ የሔዱት ደግሞ የሰሜን ሸዋው እና የወልቃይት ዐማራ ተወላጁ የበላኤሰቡ የአብይ አሕመድ አገልጋይ ሆነው በወገናቸው እልቂት በንፁሐን ደም የቆሸሹት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሆኑት የአቶ ታዬ አጽቀ ሥላሴ ነበሩ። ወይዘሮ ሶፊ ገብረየስ የሚባሉ ሌላ ለማኝ የኔ ቢጤም አብራዋቸው ነበሩ።

"…ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይም ሚንስትር ቢሮም Rt Hon Andrew Mitchell, Deputy Foreign Secretary and Minister for Development and Africa, Government of the United Kingdom of Great Britain and Northern Ireland ተገኝተው ነበር። ከዓለም የምግብ ድርጅትም Mr. Carl Skau, Deputy Executive Director and Chief Operating Officer, ተገኝተው ነበር።

"…በዚህ መሃል ነው የለንደን ፋኖዎችም በክብር እንግድነት በዚያ ሁሉ የዓለም መንግሥታት ተወካዮች መካከል የተገኙት። አቶ ታዬ አጽቀ ሥላሴ የልመና አቁፋዳቸውን ይዘው ተነሥተው ምንተ ስሟ ለማርያም ብለው መለመን ሲጀምሩ የለንደን ፋኖዎች በየተራ ተነሥተው በተለያየ ሰዓት የቀወጡት። የኢትዮጵያ ድርቋ አቢይ አሕመድ ነው። ታዬ አቢይ አንተንም እንደነ ዶር አምባቸው ይበላሃል ብለው ትንቢት ተናግረው አንገቱን አስደፉት።

"…ብራቮ የለንደን ፋኖዎች። በኦሮሙማው የድሮን መግዣና የቤተ መንግሥት ማስገንቢያ ቅፈላ ጉሮሮው ላይ ነው የቆሙት። ብራቮ የለንደን ፋኖ።💪🏿💪✊👏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ በተመለከተ የሁለቱም የአስተያየት መስጫ ሰንዱቆች ተከፍተዋል። ወደ መኝታ የመሄጃ ሰዓታችሁ እስኪደርስም ድረስ በጨዋ ደንብ መተንፈስ ትችላላችሁ። ሃላስ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እናንተው… ርዕሰ አንቀጹን ልቀጥልና ልቋጨው አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ዐማራ ማሸነፉን 100% አረጋግጧል። መጪው ጊዜም ዐማራ የሚመራት ኢትዮጵያ መወለዷ እውን ሆኗል። ይሄን ተቃራኒ ወገኖችም፣ የሩቅም የቅርብም ታዛቢዎች በሚገባ ተረድተዋል። ህወሓትም ብልፅግናም አምነዋል። ነገር ግን ዐማሮቹ እየተጨቃጨቁ ያሉት እዚህ ላይ ለመግለጽ በምቸገርበት አስቂኝ ቀላል ጉዳይ ላይ ነው። ትግሉ ነገር ዓለሙን ጣጣውን ጨርሷል። አሁን በማይረባ አጀንዳ ላይ ተቸንክረው እንዲቀሩ አኞ ሥጋ ወርውረውላቸው ከእርሱ ጋር ሲታገሉ እንዲውሉ አድርገዋቸው ነው እንጂ ዐማራው ተራራው 99. 99999% የቤት ሥራ ጣጣውን ጨርሷል። የቀረችዋ ነጥብም ቀላል አይደለችም። የምትናቅም አይደለችም። ከራስ ደጀን ተራራ፣ ከዝቋላና ከኪሊማንጃሮ ተራራ፣ ከሂማሊያ ተራሮች የገዘፈ፣ የረዘመ መስሎ የሚታይ የሚመስል ሽርፍራፊ ነጥብ ነው የቀረው። ነገር ግን ጫን አድርጎ የሚይዝ ገለልተኛ ሽማግሌ ፈጥርቆ ቢይዘው የሚበን፣ የሚተን ተራራ ነው ነጥቡ። የጥጥ ከረሜላ በሉት፣ ሲያዩት ግዙፍ ሲቀርቡት ጥጥ። ደፋር ከተገኘ ይፈታል። ደግሞም ይፈታል። እየፈታነውም ነው።

"…ወያኔ የዐማራውን አቅም አይታዋለች። ገምግማዋለችም። ወያኔ ከነገሩ፣ ከአጀንዳው ወጥታ ትግሬዎች ከዐማራ ጋር ከተጠቃቀሱ፣ በመሬት ጉዳይ ማለቃቀስ አቁመው ከተጣመሩ የብልፅግና ጉዳይ አፈር ከደቼ ነበር የሚበላው። ዐማራው ያለ ትግሬ እገዛና ያለማንም እርዳታ ሥርዓተ መንግሥቱን ከወንበዴ አራጁ ለመቀበል ከጫፍ ደርሷል። ለትግሬ መዳኛ መድኅኑ ወንድሙ ዐማራው ብቻ ነበር። ከፈለገ ከነቃ ብቻ። አዲስ አበባ የተጎለተው ብልጽግና የቀብር ስፍራውን ማሳመር ብቻ ነው የተያያዘው። ገላን ከተማ ላይ የብር ማተሚያ ፋብሪካ ከፍቶ እንደ ጉድ የሚያትመው ብር የሚያድነው መስሎታል። ፋብሪካውን እለጥፍላችኋለሁ። አለሁ አለሁ ለማለት ሜካፕ ተቀብቶ ስብሰባ የሚያበዛው ብልፅግና ከወዲሁ እንደሚሞት ወላጆቹ የሆኑት እነ አሜሪካም፣ አውሮጳም ዓረቦቹም ዐውቀዋል። ተረድተዋልም። በቀደም ጄኔቫ የተሰበሰቡትም የተዝካር፣ የ40 እና የ80 ማውጫ፣ የሃውልት እና የቀብር ሥርዓት ማስፈጸሚያ ብር ለማዋጣት ፈልገው ነው። የማደጎ ልጃቸው ምን አልባት ታክሞ ከዳነም ብለው ነው የወላጅ ነገር ሆኖባቸው ገንዘብ ለማዋጣት የደከሙት። ለሞተ፣ ለበከተ፣ ለገማ፣ ለሸተተ፣ ሰው መሳይ በሸንጎ ነው ገንዘብ ለማዋጣት መዘፍዘፋቸው ያተረፈላቸው ውርደት ነው። የሚገርመው ነገር በጄኔቫው ስብሰባ የስደት ሀገሬ ጀርመንን ጨምሮ በአካል እየረዱት፣ እያገዙት ያሉት እነ ጣልያን፣ ፈረንሳይ እና የዓረብ ሃገራት አልረዱትም። RIP ብልጽግና።

"…እነ ግንቦት 7ን ፋኖን እስከ ማጣጣል፣ አናቱ ለሁለት ይከፈልና የአንዳርጋቸውም ጽጌ ፋኖ ተከፋፍሏል ብሎ እስከመበጥረቅ ያደረሰው የዐማራ ፋኖ የሌሎችን ጣልቃ ገብነት የመከላከል አቅሙን ከ0% ወደ 99. 99999% መድረሱን ስላዩ ነው። የፈረሰውና እስክንድር የሚመራው ሕዝባዊ ግምባር ወደ ሕዝባዊ ሠራዊት ከተቀየረ በኋላም ከእስክንድር ኋላ ያሉ ሰዎች በእስክንድር በኩል እጃቸውን አስረዝመው በዐማራ ፋኖ ውስጥ ለመዳከር መራወጣቸው አልቀረም። እሱም ቢሆን ይሄ መራወጥ አሁን የዐማራው ፋኖ መንቃት ከ0% ወደ 99. 99999% ማደጉ ፉርሽ እያደረገው መጥቷል። ግንባር በለው ሠራዊት በለው፣ ወያኔ በለው አደጋ የመሆን መጠናቸው ቀንሷል። ማዶና ማዶ ሆነው በስደት በጋዜጠኝነት ስም የጋዜጠኝነት ካባ ለብሰው ለዐማራ ፋኖ የመታገያ ማኒፌስቶ የሚያዘጋጁ ፌስታል ፊቶችም በጊዜ ተገፍተው ጥጋቸውን እየያዙ ነው። እነሱ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር ቢኖር ድሮ በደኅና ጊዜ በድብቅ የቀረጹትን የስልክ ውይይት ለማፍረሻነት መጠቀም ብቻ ነው። ልክ የጎጃሙን ማርሸት የእስክንድር ነጋዋ ገንዘብ ያዥ ወሮ ሕይወት በጄኖሳይድ ጉዳይ ቀርጻው አሁን እንደበተኑት ማለት ነው። ወዳጄ በግለሰቦች የግል የስልክ ሀሜት ምክንያት የሚቆም የዐማራ ትግል ግን የለም። አበደን የለም።

"…ሌላው ሞጣ ቀራንዮ እንዳለው የብአዴንም አልሞት ባይ ተጋዳይነት እንቅፋት መፍጠሩ አልቀረም። አሁን ባለው መረጃ አንደኛው ብአዴን በራያ በኩል ከትግሬዎቹ ጋር ተጠቃቅሶ አስቸጋሪ ናቸው የተባሉትን የብልጽግና ሰዎች ማጽዳታቸው፣ የፋኖም ኃይል በዐማራ አድማ ብተናና በዐማራ ሚልሻ እንዲጠናከር ማድረግ ሲታይ የሆነ ነገር መሽተቱ አይቀርም። ብአዴን ሙሉ በሙሉ አደረጃጀቱን ይዞ እኔ ካልመራሁት የሚለውን ዲስኩሩን ይዞ የነበረው ነገር ነው ሞጣ ፋኖ አዲስ አበባ አይገባትም ሲያስብለው የኖረው። በተለይ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቡድን በኩል ከኤርትራ ጋር ባለው ግኑኝነት በሚያቀርበው ሎጀስቲክ የዐማራ ፋኖን ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው መፍጨርጨርም 99. 99999% እየሞተ ስለሆነ አሁን ፋኖን ለመከፋፈል አቅም የለውም። RIP ገዱ።

"…ብዙዎቻችሁ የምትንቁት በሳቅ በፈገግታም ነውር ቃሉን እየጠጣችሁ የምታልፉት ሞጣ ቀራንዮ ወይም ወንድሙ የጎጃም ብአዴን የብልጽግና ሰው የሆነው ሂውስተን ቴክሳስ የሚኖረው አቶ ማማሩ መንግስቴ አንለይም የዋዛ ሰው አይምሰላችሁ። ሞጣ ቀራንዮ "ፋኖ አዲስ አበባ አይገባም። ፋኖ አዲስ አበባ እንዳይገባ ያደረግነው እኛ ነን። የሚኒልክ ቤተ መንግሥት እንገባለን ብላችሁ አልነበር? ታዲያ ከምን አትገቡም? ፋኖ አዲስ አበባ እንዲገባም፣ እንዳይገባም የምናደርገው እኛ ነን ብሎ የሚበጠረቀው እንዲሁ ዝም ብሎ ፋራ ስለሆነ የሚመስለው የትየለሌ ሰው ነው ያለው። ሞጣ እውነቱን ነው። ሞጣን የያዙት የወሎ ብአዴኖች እነ ደመቀ መኮንን እና እነ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው። ለዚህ ነው ሞጣ ገዱንና ደመቀን የሚያሞካሸው። ሞጣ በከፈሉት ገንዘብ ልክ ነው የነገሩትን ይዞ የሚበጠረቀው። ብአዴንም በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ፋኖን ይዘናታል ብለው ነበር የሚያምኑት። ደግሞም እውነት ነበር። አሁንም የብአዴን እጁ በፋኖ ውስጥ ጠፍቷል ማለት አይደለም። የብአዴን እጁ ረጅም ነው። ይሄንንም በራያ እና በወልቃይት በኩል ስላለው ሁኔታ መረጃው የለኝም እንጂ አምላከ ዐማራ ወኢትዮጵያ ልዑል እግዚአብሔር ረድቶኝ በሸዋና በጎንደር 99. 99999% የብአዴንን ሴል አፍርሰን ጨርሰነዋል። አንገቱ ላይ የቆምንበት አለ። የሚያጣጥር አለ። ለፋኖ የገበረ እጁን የሰጠም አለ። ብአዴን በሸዋ እና በጎንደር ያለውን እጁን ቆርጠነዋል። ጎምደነዋል። እስትንፋሱ ደግሞ በቅርቡ ያቆማል።

"…የጎንደር ፋኖዎች በሰው ኃይል፣ በፖለቲካ ንቃተ ህሊና፣ በሎጀስቲክ፣ በኔትወርክ፣ በጀግንነት፣ በመግባባት፣ በመደማመጥ ቀድሞ በመንቃት ከሌሎቹ የተሻለ ልምድ ያላቸው ናቸው። ከኋላ የመጣው ጎጃም እና ወሎም ጀግንነቱ ተነግሮ፣ ተዘርዝሮም አያልቅም። ሸዋ ወያኔ በልታ ጨርሳው። ብአዴን ሽባ አድርጎት ቢኖርም በዚህ 4 ዓመት እንደ እንቦሳ ጥጃ ነው እንደ አዲስ ተወልዶ የወይፈን ጉልበት ይዞ ጋራ ሸንተረሩን የሞላው። ጎንደሮች ምን ቀድመው ቢደረጁ ለሁለት መከፈላቸው አልቀረም። አንደኛው ቡድን ፋፍዴን፣ ብአዴን ወዘተረፈ፣ ሌላኛውን ቡድን ግምባሩ፣ ሠራዊቱ የሚባሉት ቀርበው አንቀው ይዘዋቸው ነበር። ሌሎቹን ቀፍዳጆች እዚህ ላይ አላነሣም። የሆነው ሆኖ በሸዋ በእነ ጋሽ አሰግድ እና ሻለቃ መከታው መካከል የነበረውን ጠብ ለዝቦ፣ አርቀነውም ወደ አንድነት ለማምጣት የነበረኝን የሽምግልና ውጤት የሰሙት ጎንደሮች ሁለቱም ቡድኖች አሜሪካና ጎንደር ባሉ ወኪሎቻቸው በኩል ቀረቡኝ። መረጡኝም። እኔም ሁለቱንም አገኘኋቸው። ሁለቱም ያለልዩነት ይሁንታቸውን ሰጡኝ። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የአመስጋኙ ቁጥር የሚፈለገውን 1ሺ የአመስጋኞች ቁጥር ስለሞላ አሁን የምስጋናው ክፍለ ጊዜ ተጠናቅቋል። ከምስጋናው ቀጥሎ የምንሄደው ያው እንደተለመደው በሁሉ ዘንድ ወደሚናፈቀው የ"ርዕሰ አንቀጽ" መርሀ ግብራችን ነው የምናመራው።

"…በዛሬው የርዕሰ አንቀጽ መርሀ ግብራችን እኔ እንድመራው በፍጥነትም እንድጨርሰው በሁሉም ወገን ሓላፊነት ተጭኖብኝ ተገድጄ የገባሁበትና 99. 99999% "የጎንደሩና የሸዋ ፋኖ አንድነት የሽምግልና ጉዳይ" ከምን እንደደረሰ ላሳውቃችሁ ወደድሁ። ፈለግሁም። ደግሞም አማረኝም። የሁላችሁም ጭንቀት ስለሚገባኝ፣ ስለምረዳውም ጥቂት ባካፍላችሁ እና ባስተነፍሳችሁስ ብዬም ወሰንኩ?

"…የቀረችኝን ፐርሰንት በማወቅም ባለማወቅም፣ በስንፍናም፣ በሴራም ይሁን በሥራ፣ በዳተኝነትም የሁን በዳታ ማስቸገር የዘገዩብኝን እናንተው ደውላችሁ ጫና በመፍጠር ታግዙኝ እንደሁ ብዬ ነው ወደ እናንተ መምጣቴ። በጣም፣ ቀላል፣ የማይረባ ነገር ነው የቀረው። የከበደው ነገር አልቋል። ተጠናቅቋል። በይቅርታም ታልፏል። ተማምለዋል። ይቅርም ተባብለዋል።

• እህሳ ለመስማት ብቻ ሳይሆን እኔን ለማገዝ ዝግጁ ናችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ተወዳጆች ሆይ…!

"…እነሆ ትእግስትን በአካል ተዋወቋት… ትእግስት፣ መልኳ፣ ቁመናዋ፣ አቋሟ ምን ይመስላል ቢሉ ይኸው ይሄንን የምታዩትን ባለማዕተብ ልጅ ነው የምትመስለው። ቁርጥ እሱን።

"…አከበርኩት ልጁን፣ ባለ ማዕተቡን። እጁን ቢሰነዝር፣ ሰውየው ሽማግሌው ቢጎዳም፣ ባይጎዳም ፖሊስ ቢመጣ፣ የአንገቱ ማዕተብ ብቻ ልጁን ያስቀጠቅጠው ከዚያም አልፎ ያስገድለው ነበር። በዚያ ላይ ሼኪው…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መረጃ ናሁሰናይ…!

"…የአርበኛ ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይን በተመለከተ የኦሮሙማው የብልጽግናው አገዛዝ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሠርቶ በዩቲዩብ የጫናውን ዜና አንሥቶታል።

"…በሌላ ዜና የኦሮሞው ብልጽግና ገድየዋለሁ ብሎ በይፋ ያወጀውን የሟቹን አስከሬና እስከዛሬ ድረስ ለቤተሰቡም አልሰጥም ማለቱም ተነግሯል። አስከሬን አንሰጥም ጥፉ ከዚህ ብሎ ቤተሰብ እንደሚያባርር ነው የሚነገረው።

"…ማረጋገጫ ባይኖረኝም፣ የደረሰኝ መረጃም ባይኖርም ናሁሰናይን በተመለከተ አንዳንድ ሰዎች እንዳልሞተና በቅዱስ ጳውሎስ የጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ በጥብቅ የመንግሥት ፖሊሶች ክትትል ህክምና እየተሰጠው ነው የሚሉ አሉ። አሉ ነው እንጂ ያረጋገጠልኝ ሰው ግን የለም።

"…የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የሠራውን ዜና ከዩቱዩብ ማውረዱ ከዚህ በሕይወት ከመኖር ዜና ጋር ይያያዝ አይያያዝ ግን የማውቀው ነገር የለም። አስከሬኑን ለቤተሰብ አንሰጥም ያሉበትም ምክንያት ከዚሁ ልጁ በሕይወት ከመኖሩ ጋር የተያያዘ ይሆን? እንጠይቃለን።

"…ምንአልባት መረጃ እናገኝበት እንደሁ ብለው በሕይወት አትርፈው ከዳኑት በኋላ ቁስሉን እየነካኩ በመመርመር ኋላላይ ሊገድሉት አቅደው አስቀድመው ሞቱን ያወጁት ለዚያ ነው የሚሉም አሉ።

• ለማንኛውም EBC ያወረደውን ቪድዮ ለታሪክ አስቀምጡት። ያዙት።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ”

ቀወሲ በላይ Vs ቅድስት ሥላሴ

"…ኦሮሞነቱ ጊዜ የሰጠው፣ የጃዋር፣ የአቢይ አሕመድ፣ የአዳነች አበቤ፣ የሽመልስ አብዲሳ የጡት አባት፣ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት መሥራች፣ የፈይሳ አዱኛ ታቦት ቀራጭ፣ የኮሬ ነጌኛው አባል፣ የኦህዴድ የፓርላማ ተመራጭ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድቤት ዳኛ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀውሲ በላይ መኮንን 6 ሚልዮን 50 ሺ ዶላር በውጭ ሀገር ወደሚገኘው ባንክ ዶላር ሲያዘዋውር ቁጥጥር ስር መዋሉን ቀደም ሲል ዘግቤ ነበር። ዘገባዬን ፋና ዛሬ አረጋግጦልኛል። ክብር ለወፎቼ። 🙏

"…በሌላ ዜና ጥንታዊው እና 4ኪሎ የሚገኘው የአጋእዝተዓለም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለእድሳት ከሚፈልገው 172 ሚልዮን ብር,90 ሚልዮን ብር ብቻ አግኝቶ ቀሪ 82 ሚልዮን የኢትዮጵያ ብር የሚሰጥ ሰው ስለጠፋ የእድሳት ጊዜው መራዘሙን በይፋ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

"…ለበላይ መኮንን ኦሮሞነቱ ያድነዋል። አቢይ አህመድ ይደርስለታል ተብሎ ይጠረጠራል። በላይ ሲያዝ "ቆይ አንድጊዜ አቢይ ጋር ልደውል" ያለውም እኮ የሚያውቀው፣ የሚተማመንበት ነገርም ስላለው ነው። ዳኞቹም፣ ፎሊሶቹም፣ ዐቃቤ ሕጎቹም በአንዲት ስልክ ከጥፍራቸው ውስጥ ማስደበቅ ይችላል። የውጭ ምንዛሬ ሃራራ ያለበት አገዛዙ ለመውረስ ካልፈለገ በቀር፣ ገንዘቡም የየማይፈለጉ ባለሥልጣናት ወይም ድርጅቶች ካልሆነ በቀር፣ አልያም ኦሬክሶችን አስከፍቷቸው ሊበቀሉት ካልፈለጉ በቀር ሰሞኑን ሊፈቱት ይችላሉ።

"…ለቅድስት ሥላሴ ግን ከእኛው ውጪ ማን ይድረስ?…“…በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?” ሐጌ 1፥4

• ይሄ ይሄ እየታየ ሰዉ ግን ሙዳየ ምጸዋት አልሰጥም ቢል ይፈረድበታልን?

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ጠላትነቱን በተንኰል የሚሸሽግ፥ ክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል።” ምሳ 26፥26 … “…ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።” ያዕ 3፥16

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …ማወዛገብም ሊሆን ይችላል! የቼሪ እና አስረስ ጨዋታ ማለቴ ነው! የሆነው ሆኖ. . .ምክንያቱ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱ ይሁን ወይም ሌላ ፍፃሜው ግን አጓጊ ነው! ይልና ይሄንኑ የታደሰ ወረደን መግለጫ መነሻ በማድረግ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት መድረሳቸውን በማተት ሌላ ትንተና ይሰጣል። አደገኛውንና በከባዱ የተመከረበትን ምክርም የሚያሳይ ምልክትም ይሰጣል።

"…ታዲያ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል ፖሊስ፣ የዐማራ ፋኖን ከመሬቱ በማንፃት የራሱንን አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲገነባ ከፈቀደ ይህም በምዕራብ ትግራይ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህ ሆነ ማለት ደሞ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተተግብሯል ማለት ነው!! በዚህም የፋኖ ኃይል ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር አጋርነት ሲሆን ለፌደራሉ መንግስሥት ደግሞ የዓለም መንግሥታት የሚለቁትን የዶላር ገንዘብ ይለቀቅለታል ማለት ነው።

"…ነገር ግን የሻብዕያ ልጅ የሆነው ፋኖን ይላል "ነገር ግን የሻብዕያ ልጅ የሆነው ፋኖን የፌደራሉ እና የትግራይ ኃይል በጋራ ጥምረት የሚመቱት ከሆነ እና የምዕራብ ትግራይ ጉዳይም እንደ ደቡብ ትግራይ በትግራይ ሠራዊት የሚፈታ ከሆነ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ቀጠናዊ ቆርሾ ከፍ ይላል ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ የዓለም መንግሥታት በአፍሪካ ቀንድ በዚህ ሰዓት ውጥረት ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለማይሆኑ አንዱ ኃይል በዓለም መንግሥታት ይመታል ማለት ነው።

"…የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም መንግስታትን ፍላጎት በፕሪቶሪያው ስምምነት የሚያስፈፅም ከሆነ የኤርትራ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን ከዓለም መንግሥታት ጋር ስለሚሆን ጨዋታው በትግራይ መንግሥት እና በፌደራል መንግሥቱ ስምምነት ወቅት ተጠናቅቋል በማለት በጓዳ ተመክሮ የወሰኑበትን ጉዳይ ይዘረግፈዋል። ዐማራ ከትግሬ ጋር ፍቅር ይኖረኛል ብለህ መጃጃሉን ትተህ በእነሱው የጭካኔ መስመር ሄደህ መብትህን እንድታስከብር እመክርህሃለሁ። ሲያዩት የሚከብድ የሚመስል ቢሆንም ዓረቡም ሆነ እነ አሜሪካ ተደርበው ቢገቡ ሱማሌና አፍጋኒስታን ድል የነሱትን ኃይል የዐማራ ፋኖ ያቅተዋል ተብሎ አይታሰብም። ስለዚህ ከዚህ የትግሬዎቹ ትንተና ተነሥተን ትግሬም አቢይም የሚፈልጉትን ፍላጎት ለሟሟላት ዐማራውን ተጠቃቅሰው ጭዳ ለያያደርጉት መጨረሳቸውን ዐወቆ በዚያው ልክ መዘጋጀት ያስፈልጋል።

• ድል ከዐማራው ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራው ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ በራሴ ጥፋት ጥፋቴ ቤተሰቤን አስፈጅቼ ነበር። በጣም ይቅርታ አድርጉልኝ እስኪል ድረስ ያደረሰው የቦንቡ ውርጅብኝ ነው። የዐማራ ብልጽግና፣ የብአዴን ሰዎችን በዚህ መልክ እረፍት ካሳጡ ነገሩ ሁሉ ይቀላል። አሸወይና ነው የሚሆነው። ኦነግ ሸኔ ኦሮሚያን የሚፏልልባት ኦህዴድን ቀንድሾ ቀንድሾ ስለጣለ ነው።

"…በራያ ላይ የነበረው የብልፅግና አመራር ገሚሱ ወደኋላ ወደ ወልድያ ይሰደዳል። ገሚሱ ደግሞ በወያኔም፣ በመከላከያም፣ በፋኖም ይገደላል። የዐማራ ብልጽግናን አምኖ አብሮ ማዘጥዘጥ መጨረሻው ሞት ነው። ዕድል የቀናው ነው ስደት እንኳ የመውጣት ዕድል የሚያገኘው እንጂ በቀረ አቢይ አሕመድን አምኖ ኦሮሙማውን እና ወያኔን የሚያገለግሉ፣ ሕዝባቸውንም ዘላለም ባሪያ አድርገው እንዲገዛ ያስደረጉ የሚያስደርጉ ብአዴኖች በሙሉ የሰቡቱ ፍሪዳዎች ናቸውና ይበላሉ። ብልፅግና አሁን በራያ ተጀመረውን የራሱን ገረዶች አርዶ መብላት ካልነቁና በጊዜ ካልባነኑ፣ ወደ ሕዝብ ማዕቀፍ ካልገቡ ይኸው መበላት በወልቃይትም ይቀጥላል። ብልፅግናን ደግፎ እንጀፍ እንጀፍ ሲል የከረመው ሁላ አይኑ እያየ፣ ጆሮው እየሰማ ይበላል። ስም አጠራሩም ይጠፋል። ቢሰደድ እንኳ በተሰደደበት ሀገር ቀና ብሎ ለመሄድ እጁና ግንባሩ በሰው ደም የጨቀየ ስለሆነ ይሸታል፣ ይጠነባል፣ ይከረፋል። ከሰው መቅረብ አይችልም። እንደ ጎበጠ፣ በብቸኝነትም እንደማቀቀ፣ ከሰው ሳይቀላቀል እንደ መርገም ጨርቅ እንደተቆጠረ ይኖራል። በዚያው ይሞታል።

"…አሁን ሸዋ የሸዋ ፋኖ ወደ አንድ እየመጣ ነው። ጨርሷል። የጎንደር ፋኖንም ከብዙ ድካም በኋላ ወደ አንድ ለማምጣት እንቅልፍ አጥተን በስተመጨረሻ በትናንትናው እለት ለማቀራረብ ተሳክቶልናል። ዐዋጅ ማወጅ ነው የሚቀራቸው። ከምር ሆኗል። ወደ አንድነቱ ያልመጡ በጎጃም ያሉ ጦሮችም አሁን ልዩነታቸውን አጥበው፣ አስወግደውም የግድ ወደ አንድ ቢጠቃለሉ ሸጋ ነው የሚሆነው። በጎጃም ከአንድነቱ ያልገቡ ስላሉ፣ ስለየሚቀሩም ይሄን የምለው። በጎጃም አንድነት ላይ የደከማችሁ ሰዎች አሁንም ግዙፍ ጦር ያላቸውን የፋኖ አደረጃጀቶችን ጊዜ ወስዳችሁ ወደ አንድ ብታመጧቸው መልካም ነው። ጎጃም በተለይ ዳሞት ስለ ተጋድሎው አይነገርም። አይወራምም። ጎጃም ጥሩ ላይ ነው ያለው። ከአደባባይ ፉከራ ባሻገር በዓይን የሚታይ ተጋድሎ በማድረግ ግንባር ቀደም ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋም እንደዚያው። አሁን ግን የጦር ግንባሩ በዛ ያለ ስለሆነ ከምን ጊዜውም በላይ አንድነት ወሳኝ ነው። በውጭ ያለውም ዐማራ አንድ ላይ ከመቆም በቀር ሌላ አማራጭ የለውም። በመሬት ላይ ያለው ዐማራም አላማጣ ሲያዝ ወደ ቆቦ፣ ቆቦ ሲያዝ ወደ ደሴ መሸሹን ትተህ ወስነህ እንደ ትግሬ እንደ ሕዝብ ተነሥ። ከአቢይ ጋር ተስማምቶ ሊወጋህ የመጣን ከሃዲ የትግሬ ሠራዊት ከወያኔ ትግሬ ጋር አንድ ላይ ሆነን ሠርተን አቢይን እናወርደዋለን ብለህ አትጃጃል። ህወሓት ሳትኖር የትግሬ ሕዝብ የሚመራው ፖለቲካም ቢሆን እንኳ እሺ ይሁን ይታሰብበት፣ ይመከርበትም ይባል ነበር። አሁን ግን በጭራሽ አይታሰብም። አትጃጃል።

"…አቢይ ዐማራ እና ትግሬን እያጫረሰ በዚህ መሀል ግዙፍ ጦር ያዘጋጃል። ትግሬና ዐማራን በልቶ በሻሻ ካረገ በኋላ ከዚያ የቀሩትን እነ አፋርን፣ ሱማሌን፣ ደቡብን ወዘተ በአስተማማኝ መልኩ በሻሻ ያደርጋል። ከዚያ የነጻነት ሃውልቱን አምቦ ላይ ያቆማል። ይሄ ነው ቃሉ። ስለዚህ አሁን እነ አቢይ ጉዞ ወደ ደቡብ አድርገው ሟች ወታደር ይመለምላሉ። ለኦሮሞ አሁን ታማኝ ኃይሉ የደቡብ ጴንጤው ነው። በአዲስ አበባ በቀን ሥራ ላይ፣  በህዳሴ ግድብ የጉልበት ሥራ ላይ ጭምር እንዲሠሩ የሥራ ዕድል ሳይቀር የተመቻቸላቸው የደቡብ ጴንጤዎች ናቸው። የደቡብ ጴንጤው በየቸርቹ ነው በፓስተሮቹ የብልጽግና ወንጌል ቦለጢቃ የሚጠመቁት።

"…ሰሞኑን በየከተማው በሰሜኑ ጦርነት አሳብበው ዐማራንም ትግሬንም ያፍሳሉ። ከምላሴ ጠጉር ይነቀል። ዐማራ ከፌደራል መሥሪያ ቤቶች በሙሉ ተለቅሞ ይወጣል። የኦሮሙማው ኃይል የአዲስ አበባን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚቻለኝ በአዲስ አበባ የተከማቸውን የዐማራ ሕዝብ ቁጥር ማጥፋት መቀነስ ስችል ነው በማለት በጀመረው መንገድ የዐማራን ርስቱን፣ ታሪካዊ አሻራውን በሙሉ ይንዳል። ያፈርሳል። ያፈናቅለዋልም። ከሥራ ገበታውም ጠልዞ ያባርረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ የፌደራል መሥሪያ ቤቶች በሙሉ በፌደራል ፖሊስ የታዘዘ ነው በሚል ሁሉም የፌደራል መሥሪያ ቤቶች "ብሔራቸውን" እንዲሞሉ የተላከላቸውን ፎርም ደርሶኝ አይቼዋለሁ። እናም ዘጸአት የሆነ መፈናቀል በኦሮሙማው በኩል ዝግጁ ሆኖ ይጠባበቃል።

"…ሁሉም ክልል ሊበላ የተዘጋጀ እንደሆነ በማወቅ መከላከያው ውስጥ የሚገኙ ወታደሮች ጭምር አሁንም አልረፈደም ወደ ፋኖ ትግል በመቀላቀል ሀገሩንም ማዳን ራሳቸውንም ማትረፍ ይችላሉ። ያ ሲሆን ህወሓት በዚያው ትቆማለች። አቢይም ዐማራን ቀርጥፎ በልቶ ትግሬ ላይ መልሶ የማጣሪያ እኘካ በመፈጸም ወደ ሌላ ክልል በሻሻ ወደ ማድረጉ አይሄድም። ስልጤም ህወሓት ወደ ውጊያው ከገባች የወሎና የጎጃም፣ የጎንደር ዐማሮችን በሃይማኖት ስም መርዝ እየጋተ በገንዘብ እየረዳ ዐማራ ላይ ማዝመቱን ያቆማል። ብዙም ኃይል አይኖረውም። አቢይ አሕመድ ፋኖ ሊውጠው ሲደርስ የፋኖን ቀጣይ ዕቅድ በነመሳይ መኮንን በኩል እያስጠና፣ የፋኖ ቀጣይ ዕቅድም ምስጢር ስለማያውቅ ሃላል ስለሆነ ህወሓትን አላማጣን ከማሲያዙ በፊት የኦነጉን በቴን ገድሎ ኦሮሞ በራሱ አጀንዳ ተወጥሮ፣ ራሱን በቀበቶ አስሮ ፌስቡክ ላይ እየተንደባለለ እንዲያለቅስ አድርጎ ቁማሩን በሚገባ በጥንቃቄ ያስኬደዋል።

"…ዐማራ ከትግሬ፣ ትግሬ ከዐማራ፣ ኦሮሞ ከዐማራ እንዲናቆሩ ሒሳቡን ሠርቶታል። ኦሮሞ ወሎን የራሱ ለማድረግ ወሎ ከትግሬ ጋር መዋጋት አለበት። ትግሬ ለጊዜው በራያ ላይ ለሀጩን ቢጥልም በዐማራ ጥላቻ የታወረው ትግሬ የኦሮሚያ ካርታ ራያንም አጠቃልሎ እንደተዘጋጀ ማወቅም፣ ማየትም አይፈልግም። ኦሮሞ አቢይን እንዲያግዝ አውራ ጎዳናን ወደ ኦሮሚያ ክልል አጠቃልሎ አስገብቶለታል። ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ሲናና ሸዋሮቢት ሲቀር ሌላው ለኦሮሚያ ለማካለል የሰሜን ሸዋን ሕዝብ የማያባራ ጦርነት ውስጥ አስገብቶታል። ቤቱ፣ ንብረቱ፣ እርሻው ወድሞ፣ ከብቱን እየነዳ በግፍ ወስዶበታል። ዘመቻ ወሎን የኦሮሞ ቲክቶከሮች ሳይቀሩ ዋይዋይ የሚሉበት ነው። ኦሮሞ አዲስ በመጣለት የመሬት ደስታ ምክንያት አቢይን በፋይናንስም ህውሓትን በፕሮፓጋንዳ በማሞካሸትም እየደከመ ነው። የኦሮሞ አክቲቪስት አሁን ተጋሩ ጀግና! ደቡብ እና እኛ አንድ ነን! አገው እና ቅማንት ኩሽ ናቸው! የሚሉት ለመብላት ሲያዘናጓቸው ነው። የፖለቲካው ቅማንትም፣ የፖለቲካው አገው ሸንጎም ሁለቱም ጥገኞች በራሳቸው ምንም ማረግ የማይችሉ መሆናቸውን ስለሚያውቁ እንደ እስስት እየተቀያየሩ ያጃጅሏቸዋል። ቆይቶ አይሸነፍም እንጂ ዐማራ ቢሸነፍ በግሬደር ሰብስቦ በአንድ ጉድጓድ ነው የሚቀብሯቸው።

"…ስለዚህ ኦሮሙማው ሓሳብ ነው የፈጠረው። ይሄን ሓሳቡን ደግሞ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ደቡቡም፣ አፋሩም ልቡ ወደ ፋኖ ከሆነ አቢይ ኦሮሞን ብቻ ይዞ ምንም ማድረግ አይችልም። ትግሬም የጎጃም ፋኖ የወታደራዊ አዛዦቹን ከፈታላቸው በኋላ ፋኖ ፋኖ ማለት መጀመሯ አደጋ ስለፈጠረበት ነው አሁን በቶሎ ራያን ያዙ፣ ግን ከዐማራ ፋኖ ጋር አታብሩ ብሎ ያዘዘው። የአባዲ ዘሙ ልጅ በፌስቡክ ገጹ ህወሓት ለዐማራ ፋኖ መሳሪያ እያቀረበች ነው ብሎ ከለጠፈ በኋላ ለገሰ ቱሉ ወጥቶ ህወሓት…👇 ከታች ይቀጥላል ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…በሰሜን ወሎ ራያ ዐማራው ከፊት ከትግሬ ኃይሎች እና ከኦሮሞው መከላከያ ጋር፣ ከኋላው ከደነዙ የብአዴን አድማ ብተናና ምስኪኑ ሚሊሻ ከፍ ያለ ጦርነት ይጠብቀዋል። የኦሮሞ ብልፅግናም ሆነ ብአዴን እስከ አሁን በፋኖ ላይ ያላገኙትን ድል በዚህ ግንባር ሊያገኙ ያሰፈስፋሉ። ተጠቃቅሰው ራያና ወልቃይትን እንዳላስወረሩ ይሄ ሕዝብ ዥል፣ ዥልጥ ስለሚመስላቸው አቢይ አህመድ በለገሰ ቱሉና ብአዴን በክልል መንግሥቱ ስም ዐማራ በሕወሓት ተደፈረ ብለው መግለጫ ያወጣሉ። ሕዝቡም፣ ፋኖውም የሕወሓትን ወረራ ለመመከት ከክልሉ የፀጥታ ኃይልና ከከሃዲው መከላከያ ጋር ይሰለፍ ብለው ያውጃሉ። እንደ አገኘሁ ተሻገርም መሳሪያ ያለህ በመሳሪያ፣ መሳሪያ የሌለህ በገጀራ ህወሓትን መክት፣ የማረከው መሣሪያም የራስህ ይሆናል ውሰደው ሁላ ይሉታል። እናም እሺ ብሎ እነርሱን አምኖ ወደ ውጊያ የሚገባ ፋኖ ሲያገኙ በጥይትም፣ በፈንጂም፣ በድሮንም ከፊትም ከኋላም በመደምሰስ በውጊያ ያልቻሉትን በዘዴ ከመሃል አስገብተው ሳንድዊች ሊያደርጉት ቋምጠዋል። የወልድያው ስብሰባም በዚሁ አግባብ መፈጸሙም መረጃ ወጥቷል። የኦሮሙማው አየር ኃይልም አሁን ከትግሬ ጦርና ከመከላከያው ጋር ለመግጠም እጅብ ብሎ ይመጣል ብሎ ጓጉቶ የሚጠብቀውን የዐማራ ፋኖ በድሮን ሊያጠቃው ዝግጅቱን ጨርሷል። የጦር ጀቶችም የድሮን በራሪዎችም ወደ አፋር ሰመራ ገብተው በተጠንቀቅ ቆመዋል። የዐማራ ፋኖ ግን የሴራ ቦለጢቃውን ነቅቶበት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ አኩርፎ በገፍ ሊቀላቀለው የሚመጣውን ሚሊሻም ሆነ አድማ ብተና ተቀብሎ ኃይሉን በማጠናከር ሕዝቡን ከያዘ ለትግሬም ጦር ሆነ ለኦሮሙማው መከላከያ ዋጋቸውን ለመስጠት እምብዛም አይቸገርም። ከመ ጤፍ…

ሁ፦ ሰሜን ወሎ ዋግ ኽምራ ሰቆጣ

"…የዐማራ ፋኖ በዚህ ግንባርም ከሦስት ኃይሎች ጋር ይጋፈጣል። ከትግሬ ኃይል፣ ትግሬና ኦሮሞ ካዘጋጁት የአገው ሸንጎ ኃይልና ከኦሮሙማው መከላከያ ጋር ውጊያ ይጠብቀዋል። የአገው ሸንጎ የሚባለው ራሱ የትግሬ ጦር ሌላኛው ክንፍ ስለሆነ ያው ስም የቀየረ ትግሬ ነውና አያሳስብም። እናም ይሄን ኃይል ለመመከት ከወዲሁ ከላስታ ጀምሮ ያለው የዐማራ ሕዝብ ለአርማጌዶኑ ጦርነት መዘጋጀት አለበት። የቤት ሥራው ከወዲሁ ተሠርቶ ማለቅ አለበት። የትግሬ ጦር ሲሸነፍ የአገው ሸንጎም አብሮ ነው የሚሸነፈው። የሚበተነውም።

ሂ፦ ደቡብ ወሎ

"…በዚህ ግንባር የዐማራ ፋኖ የሚጠብቀው የኦሮሙማው የመከላከያ ሠራዊት፣ የብአዴን አድማ ብተና ብቻ አይደሉም የሚጠብቁት። በደቡብ ወሎ የሃይማኖት ውጊያም ሊኖር ይችላል። በእነ ሙጂብ አሚኖ በጀት ወሎን ክልል እናደርጋለን ብለው በየመስጊዱ ጭምር ከሚፎክሩት፣ የዐማራ ፋኖን የክርስቲያኖች ስብስብ ነው ከሚለው የወሎ ኅብረት ፅንፈኛ የወሃቢይ እስላሞች ጋር ጦርነት ይጠብቀዋል ብዬ እሰጋለሁ። በጁንታው ጦርነት ወቅት ከዐማራ ፋኖ ጋር ገጥሞ ይዋጋ የነበረው የሐሰን ከሪሙ ቡድንም በዚሁ ቡድን መጠለፉም አይረሳ። ኮምቦልቻ አካባቢ ከከሚሴ የሚነሣ የኦነግ ጦርም ከኦሮሙማው መከላከያና ከወሎ ፅንፈኛ ዐማራ ጠል የወሓቢያ እስላሞች ጋር ፍልሚ ይጠብቀዋል። ምንአልባት ህወሓት እስከደሴ ድረስ መጥታ ከዚያ የወሎ ክልልነት ተመቻችቶ ኦሮሙማው በሠራው ካርታ መሠረት ወሎን ልክ እንደ አውራ ጎዳና ለመጠቅለል ይሞክራል። ነገር ግን በዐማራ ክልል ከዐማራ ፋኖ በቀር አሸናፊ አካልም ሓሳብ የለም። አይኖርምም።

ሃ፦ ሰሜን ጎንደር

"…በጠገዴ፣ በማይ ፀብሪ እና በአዲአርቃይ የኦሮሞው መከላከያ ሠራዊት እና የትግሬው ኃይል ጋር ይገጥማል። በወልቃይት ደግሞ አርማጌዶን በሉት ከበድ ይላል ተብሎ ይጠበቃል። የወልቃይቱ ኮሎኔል ከብልፅግና ጋር ከሆነ ወልቃይትን አስረክቦ ወደ ካደው ሕዝብ ወደ ጎንደር መጥቶ የገነባውን ህንፃ እያከራየ ዘጭ ብሎ ይኖራል። ምክንያቱም ኮሎኔሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ መተኮስ ወንጀል ነው ብሎ በአደባባይ ፋኖን ያወገዘ ሰው ስለሆነ አሁን መከላከያ ውጣ ሲለው እምቢ ይላል ተብሎ ይጠበቃልን? የኦሮሞው መከላከያ፣ የትግሬው ኃይልና ሱዳን የተሰደደው ገዳዩ የትግሬ የሳምሪ ቡድንም አሁን አንድ ላይ ሊሠለፉበትም ይችላል። የኦሮሞ ብልፅግና፣ የአማች ፖለቲካ ተጋቢዎችም የዋዛ አይሆኑበትም። በውስጥ ያለው የትግሬ ወለዱ የፖለቲካው ቅማንትም ሌላው ፈተና ሊሆንበት ይችላል። የሆነው ሆኖ በዚያ አካባቢ መለኮታዊ ጣልቃገብነት ከሌለ በቀር ትርምስምሱ ይወጣል። ደፍርሶም ግን ይጠራል። ሌላ አማራጭ ስለሌለው ዐማራም የግዱን ያሸንፋል። እንደ ራያ፣ እንደ አላማጣው ብዙ የብልፅግና ባለሥልጣናት ከወልቃይት እስከጎንደር ተቀርጥፈው የሚበሉበት ጊዜም የቀረበ ይመስላል።

ሄ፦ ደቡብ ጎንደር

"…ትልቁ ግዙፍ የዐማራው ፈተና የሚገኘው በደብረ ታቦር ነው። ደብረታቦር መከላከያው፣ የአማራ አድማ ብተናና ፖሊስ ብቻ አይደለም የሚገኘው። በደቡብ ጎንደር ወያኔ እስከአሁን አለች። አልሞተችም። አልጠፋችም። ከሁሉም የዐማራ ክልል የወያኔ ሴል እስከ አሁን ድረስ ሳይወገድ እንዳለ የአመራር ስፍራውን ሳይለቅ የተቀመጠው ደቡብ ጎንደር ነው። በሰሜን ጎንደር ወኪል፣ በጎጃምም ወኪል ነው ወያኔ ያላት። የፖለቲካው ቅማንት እና የፖለቲካው አገው ሸንጎ ሰዎች በወሳኝ ሥፍራ በሥልጣን ላይ ያሉ ቢሆንም በደቡቡ ጎንደር ግን ይበዛሉ። አጥብቆ ወያኔን ናፋቂ ዐማራ መሳይ በዐማራ ላይ የተሾመ ጉግማንጉግ ነቀርሳ የሆነ ፀረ ዐማራ ኃይል የሚገኘው በዚሁ አከባቢ ነው ይባላል። ወያኔ በመቀሌም ሳይቀር ሞታ በደቡብ ጎንደር ግን እንዳለች ነው ያለችው ይላሉ። እናም የዐማራ ፋኖ በደቡብ ጎንደር ከአፍቃሬ ወያኔ ብአዴን ኃይል፣ ከሚሊሻውና ከአድማ ብተናው ጋር የኦሮሙማውን መከላከያ ደርቦ ለመግጠም የሚዘጋጀው ከወያኔ ርዝራዥ ወያኔ ዐማሮችም ጋር ጭምር ነው።  ይሄ ግድ ነው በቃ።

ህ፦ ጎጃም

"…የጎጃም ዐማራም እንዲሁ በዛ ያለ የጦር ግንባር ነው የሚጠብቀው። ፖለቲካ ወለዱ አገው ሸንጎና የኦሮሙማው መከላከያ ኃይል እንዳለ ሆኖ ልክ እንደ ደቡብ ጎንደር አፍቃሬ ወያኔው ብአዴን ከነ ርዝራዡ ያለበትም ስፍራ ነው። መቀሌ ድረስ ትግሬ ተርቧል ብሎ ጤፍ ጭኖ 90 ዓመቱ ትግራይ ድረስ እያነከሰ የሚሄድ ጎጃሜ ስታይ ትደነግጣለህ። ይኸው የተላከው ዱቄት ስንቅ ሆኖት ትግሬ ወደ ራያ ሲገባ ሽማግሌው ጎጃሜ ምን ሊሉ ይችላሉ ብለህ አትሰብ። የዐማራ ሚሊሻና የአድማ ብተና ተብዬውን ከመከላከያው ጋር በጎጃም ከዐማራው ፋኖ ጋር ይገጥማል። የጉምዝ ኃይሎች ከኦነግ ጋር ሆነው እንደ አዲስ ካልተነሡበት በቀር በዚያ በኩል ስጋት ቢኖረኝም ስጋቴ ግን የቀነሰ ስጋት ነው።

"…ቅሬታ ካላመጣ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ወያኔ በሩቅ ሆና ወሎን አልፋ እንደምንም ከጎጃም ፋኖ ጋር የመገናኘት እድል ቢኖራት የሚመኙና የሚናፍቁ ትግሬዎችን እያየሁ መሆኔ እያስገረመኝ ነው። አርበኛ ዘመነ ካሴ ከሚናገረውና ከሚሰጠው መግለጫ ተነሥቼ ለወያኔ መራር ጥላቻ እንዳለው ብገምት ብረዳም አብዛኛዎቹ የወያኔ ሰዎች ግን በጎጃም ፋኖ አመራሮች በተለይ ለጠበቃ አስረስ ማሬና ለማርሸት ያላቸውን ክብር ሳይ ይሄ ክብር ከምን እንደሚመነጭ ሊገባኝ ባለመቻሉ ቅዥብርብር ሲያደርገኝ ይኖራል። የሆነ ተንኮል ይኖርበት ይሆንን ብዬም እጠይቃለሁ? የሆነው ሆኖ እንደ ስትራቴጂም ሆነ፣ እንደ ታክቲክም ይዘውት እንደሁ ባላውቅም የወያኔ ሰዎች ግን እንደምንም ብለው ከጎጃም ፋኖዎች ጋር ኅብረት ለመፍጠር ሲላለጡ እያየሁ ነው። ምን አልባትም ልክ እንደ ደቡብ ጎንደሩ በጎጃም ፋኖ ውስጥም አፍቃሬ ወያኔ …👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ከምስጋናው ቀጥሎ የሚከተለው ርዕሰ አንቀጹ ነው አይደል…? አዎ… ትክክል ነው።

"…ነገር ግን የዛሬው ርዕሰ አንቀጼን ማሳጠር፣ መግታት አቃተኝ። ውስጤ እየፈላ የሚንተከተከውን ሁሉ ጻፍኩኝ። ስጋቴን፣ ፍርሃቴን፣ ደግሞም ተስፋዬን እንደ ኢዩ ጩፋ፣ እንደ ዳንሳም ባይሆን ነገር ግን ቀኝ ትከሻዬን የሸከከኝን ሁሉ በመጻፌ ጦማሩ ረዘመ፣ የሊማሊሞን ተራራ መሰለብኝ። እናም ወዳጆቼ ይሄን ዝልግልግ ተልባ መሳይ ርዕሰ አንቀጽ ልጥፍላችሁ ይቅር፣ ወይስ ከፋፍዬ ላቅርበው?

• ምን ትላላችሁ…? ምንስ ትመክሩኛላችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የነዳጅ ጉድጓዱ ከተገኘ፣ የባንኩ ፓስወርድ ተገኝቶ ለሕዝብ ሰደቃ ከሰጠ ወዲህ በኦሮሚያ ብር እንደ ቅጠል ነው አሉ። ርግፍ፣ ብትን ነው የሚልብህ አሉ። እንዲያውም ለአንድ ሴተኛ አዳሪ ለአንድ ቀን አዳር 2 ሚልዮን ብር በጨረታ የሚከፍሉ ወጣት የቄሮ ባለሀብቶች መፈጠራቸውን ስንሰማም እጅጉን ነው የተደመምነው።

"…አሁን በዚህም ይቀና ይሆናል እኮ…! ኢመቻቹ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ኢትዮጵያ ነው ኦሮሚያ…!

"…በገዛ ቀበቶአቸው የፊጥኝ አስሮ እስከ አሁን ድረስ ማን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደላቸው ያልታወቁትንና በተወለዱበት ከተማ በመቂ በቆሻሻ ገንዳ ላይ ተጥለው የተገኙትን የኦነጉን ባለ ሥልጣን የአቶ በቴ ኡርጌሳን የግፍ አሟሟት በመቃወም በኦሮሚያ ቄሮዎች በቀበቶ ራሳቸውን የፊጥኝ በማሰር ተቃዉሞአቸውን በዚህ መልኩ ሲገልጹ ውለዋል።

"…ከምር የአቶ በቴ የጭካኔ አገዳደል እስከአሁን ይዘገንነኛል። አቶ ሽመልስ እና አቢይ አሕመድ ግን ለምን እንደዚህ ጨካኝ፣ አረመኔ ሆኑ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሊነጋ ሲል ጠዋት እዚህ ቦታ የተቀመጥኩ እስከ አሁን ድረስ እንዳለሁ አለሁ። ትናንት ማታ ሶፋዬ ላይ እንዳመሸሁ እዚያው ተኝቼ አዚሁ ነጋብኝ። አሁን በጀርመን ሰዓት አቆጣጠር 19:00 ሰዓት ሆኗል። በአፌ ምሳም አልቀመስኩ ራትም አልበላሁም። ውኃም አልጠጣሁም። ልጄ አንሥታኝ የላከችልኝን ፎቶ ነው የለጠፍኩት።

"…ጠዋት ርዕሰ አንቀጼን ጽፌም ሳልለጥፍላችሁ ነው እንዲህ ሆኜ የዋልኩት። ነገ ጠዋት ከምሥጋና በኋላ እለጥፍላችኋለሁ።

"…እንዲህም ሆኜ ግን ድርቅ ክችች ብዬም ቢሆን አቀርቅሬ በአባቶቼ ጸሎት ልመና፣ አማላጅነትም "የጎንደር አንድነት 99.99999% ስኬታማ ሆኗል። በጎንደር ልዩነት ጠፍቶ ወደ አንድነት ለመምጣት ሁሉ ነገር አልቆ፣ ሁሉም ተገናኝቶ ከስምምነት ተደርሷል። የቀረውም ነጥብ ታህል ጉዳይ በሰላም ይጠናቀቃል። ጥርተውኝ፣ አምነውኝ፣ እኔን ዳኘን ብለው፣ አሸማልግለን ብለው ለዚህ ታሪካዊ ክብር ላበቁኝ የጎንደር ጀግኖችና አባቶች ክብር ይሁን። የረዳን የጠበቀን፣ እያከናወነልን ያለው ልዑል እግዚአብሔርም ክብር ምስጋና ይግባው። አሜን።

• ዛሬ ቲክቶክም ይለፈኝ። የነገ ሰው ይበለን።

Читать полностью…
Подписаться на канал