"ርዕሰ አንቀጽ"
"…በሚልዮን የሚቆጠር ትግሬ ሞቶ መጨረሻው በድርድርና በዕርቅ ነው የተቋጨው። አሁንም ሠራዊታችንን እያስፈጀን ከምናልቅ ሕዝቡ በፋኖዎቹ ላይ እንዲነሣና እንዲያግዘን የተገኘውን ሁሉ፣ ገበሬ፣ ቄስና ሼክ ሳንል እንፍጅ፣ እንጨፍጭፍ። የምዕራቡ ዓለም እንደሆነ መግለጫ አውጥቶ ልክ እንደ ትግሬው ጊዜ "አሳስቦኛል፣ አጣሪ ኮሚሽን ይግባ" ወዘተ ከማለት የዘለለ ምንም አያመጣም። መለስ ዜናዊ በኦጋዴን ያን ሁሉ ሶማሌ ጨፍጭፎ ማን ጠየቀው? በማይካድራ ያ ሁሉ ዐማራ በህወሓት ተጨፍጭፎ አሁን ስለሱ የሚያወራ አለ? የለም። ስለዚህ እርምጃ እንውሰድ። ከዚያ ብንሸነፍም እንኳ አይቆጨነም ነው የሚሉት አሉ ኦሮሙማዎቹ በሰሞነኛው ምክክራቸው። በዚህም የተነሣ ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ቤት ለቤት እየዞሩ ያገኙትን ዐማራ በሙሉ በጭካኔ፣ በፍጹም አረመኔያዊነት መረሸናቸው ተሰምቷል።
"…ሰሞኑን የትግሬና የዐማራ አክቲቪስቶች በስሱ "ሰሜናዊያን" የሚል እንቅስቃሴ መጀመራቸው በኦሮሞ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች አልተወደደም። ምን ሲደረግ? እንዴት ሆኖ? ለምን ሲባል ዐማራና ትግሬ ይነጋገራል? ትግሬዎቹን ዐማራን እንድትበቀሉ፣ ኤርትራን እንድትወጉ መሣሪያ ብንሰጣችሁ መልሳችሁ የኦሮሙማ መንግሥታችንን ልትወጉ? ሞተናታላ። እናንተና ዐማራን ሳናጫርስ፣ ሳናዳማ፣ ሳናቋስል ከቀረን የለናትማ እያሉ ነው።
"…የዐማራ ፋኖ በወሎ ዕዝም አገዛዙ በትግሬና በዐማራ ዘንድ እሳት ለመለኮስ እየሄደበት ያለውን ርቀትና ሴራ ተረድቶ መግለጫ መስጠቱ በኦሮሙማው ቤት አስነቅሏል። ጠሽ ነው እያደረጋቸው። ባይታመኑም አፍቃሬ ወያኔዎቹ፣ ፀረ ዐማሮቹ እነ አሉላና እነ ስታሊን ሳይቀር በድፍረት ፋኖ ፋኖ፣ ዐማራና ትግሬ መጣላት፣ መዋጋት የለባቸውም ብለው አደባባይ ወጥተው መናገር መጀመራቸውም ዐማሮችን ምንም ባይመስላቸውም ኦሮሞዎቹን ጨርቃቸውን አስጥሎ እያሳበዳቸው ነው።
"…ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ እና ሸዋም ወደ አንድ ዕዝ እየመጡ መሆኑም አገዛዙዝን አሳብዶታል። መሸነፉም አይቀርም። በተለይ እነ GGጂጂግግ ን ከዐማራ ትግል አባርሮ ዳር ካስያዙ፣ ለዐማራ የሚሰበሰብ ሀብትና ድጋፍ ከአዝማሪና ከበላተኛ እጅ ከወጣ፣ በትክክል ከተሰበሰበ፣ ለታለመለትም ዓላማ ከዋለ ኦሮሙማ በቅርቡ ያበቃለታል።
"…እስከዚያው ኦሮሙማው የእውር ድንበሩን ቤት ያፈርሳል። ሀገር ያምሳል። በልበላውም ጭሬ ልድፋው ይላል። የታረደ ዶሮ ነውና መንፈራገጡ አይቀሬ ነው። እሱም ጨካኝ ነበር እና ጨካኝ ታዞለታል። በየትኛውም የዓለም ታሪክ የጊዜ ጉዳይ እንጂ የሚሸነፍ መንግሥት እንጂ የሚሸነፍ ሕዝብ ኖሮም አያውቅ። በፍጹም የለም። ሕዝብ ያሸንፋል።
"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን እና ብር ባለበት ስፍራ በሙሉ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚመጡትንና የሚሰፍሩትን ጥንብ አንሣዎች እሽ እያልን እያባረርን ገንዘቡ፣ ዶላሩ የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
የዛሬውን ስንቋጭ…
"…ሁል ጊዜ አንድ ከበድ ያለ የትንኮሳ አጀንዳ ስጀምር የሚደነግጥ ይበዛል። ሰድቦኝ፣ አሸማቆኝ የሚያስቆመኝ መስሎት ግርር ብሎ የሚመጣው ግሪሳም ቀላል አይደለም። እኔ ማር ቆራጩ ዘመዴ ግን ጭሱን እያጨስኩ ማሬን ቁርጥ። ከዚያ ሲቆዩ ይከስማሉ።
"…አሁንም ዐማራውን ማስታወስ እፈልጋለሁ። ታስታውሱ እንደሆነ በአስራት ሚዲያ ስም ከ200 ሺ ዶላር በላይ ተሰብስቦ የት ይደርሳል የተባለና ተስፋ የተጣለበትን ሚድያ ተቋቋመ። ብዙም ሳይቆይ የተሰበሰበውን ዶላር ለመብላት ጥቁት ጎጠኞች በፕሮፌሰሩ ስም የተሰየመን ትልቅ ተሰፋ የተጣለበትን ሚዲያ አፈረሰውት ዝም ተባሉ።
"…አስራትን ያፈረሰው በጎጥና በጥቅም የተደራጀው ዲያስፖራ እንጂ ብልፅግና እኮ አይደለም። እነ ግንቦቴው ዓምደ ማርያም ዕዝራ የመሳሰሉ የFB ጎጠኞች ናቸው የአስራት ሚዲያን የገደሉት።
"…በአብን ስም ከ150 ሺ ዶላር በላይ ተሰበሰበ ተባለ። በዚህም አብኖችን የተነሡበትን ዓለማ አስትተው በጎጥ እንዲከፋፋሉ የተደረገው ዶላሩ ከተሰበሰበ በኋላ ነው። በወቅቱ አብኖች ሁሉም በሚባል ደረጃ አንድ ዓይነት አቋም ነበራቸው። አብዝተውም ለዐማራ ሕዝብ ይታገሉ እንደነበር ሁላችንም የምናስታውሰው ነው። ዶላሩን የሰበሰብት ግለሰብ ጎጠኞች ግን ዶላሩን ከሰበሰቡ በኋላ ብሩን እንድንሰጣችሁ እገሌን ከአብን አስወጡ፣ እገሌን አትመኑት እያሉ አብንን በልጅነቱ ብን አድረገው አጠፉት።
"…አሁንም በግለሰቦች ስም የሚሰበሰብ ዶላር ለፋኖ መከፋፋያ እንጂ አንድነትን አይፈጥርም። ትግል ላይ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሚባል መርህ አለ። ዛሬ ያልጠየቅነው የፋኖ አለቃ ነገ ሥልጣን ላይ ሲወጣ እንደ ዐቢይ አህመድ አሊ ሰለ ገንዘብ ምንጩና ኦዲት ሲጠየቅ አይመለከተኝም ማለት ከጀመረ አደጋ አለው ባይ ነኝ።
• አሁን ይሄ ጥያቄ ምኑ ያበሳጫል? አትሽኮርሞም መልስ ስጥ…
"…በመሃል ደግሞ ይሄን ጭካኔ እዩ፣ ተመልከቱ…
"…የዐማራ ፋኖ መከላከያን በገፍ እየማረከ ነው። ኦነጎችን ግን አባከና የሚላቸው የለም። ስለዚህ ምስኪን የመከላከያ አባላትን ኦነግም እንዲማርክና ዜና እንዲሠራለት ፈለጉ እነ ብሬ ጁላ። እናም ምስኪኑ መኴ በወነግ ተማረከ ተባለ። ሲማረኩም ዜናው በኦነግ ሚድያዎች ሁሉ ተዘገበ። ዜናውን የሚገዛው ሰው ግን ጠፋ።
፠ ቀይ ቁምጣ ያደረገውን ምርኮኛ ተመልከቱ።
"…ቆይተው ምርኮቹን ሰብስበው ረሸኗቸው። ፈጇቸው። ጨፈጨፏቸው። አብዛኛው ተጨፍጫፊ የመከላከያ ወታደር ከዐማራ፣ ከወላይታና ከደቡብ የተውጣጡት ወታደሮች ናቸው። እነዚህ ሁሉ በጭካኔ ታረዱ። ተጨፈጨፉም። ኦነጎችም ከጨፈጨፉት የወታደር አስከሬን ፎቶ ስር ሰልፊ ፎቶ ተነሥተው ለዓለም በተኑት። አሁን አሁን ለመከላከያም የሚያዝን ዐማራ ስለሌለ ለደንታው ነው ብሎ ዐማራው ነገርየውን አለፈው። በሴራ የሚፈጀው የመከላከያ ሠራዊቱ እልቂት በኦሮሚያ ቀጥሏል።
፠ ባለ ቀይ ቁምጣው ወታደር ተረሽኖም ቁምጣው አለወለቀም። አቤት ጭካኔ። ከምር ይዘገንናል።
"…ከጥቂት ቆይታ በኋላ እነ ጂጂግግን ወደ መዠለጡ እመለሳለሁ።
በድፍረት እናገራለሁ…!
"…ዋይ ዋይ ብዬ ተንጫጭቼ፣ ተሰድቤ፣ ተወቅጬ ዐማራ በዐማራነቱ ይሰባሰብ፣ ይታጠቅ፣ ይመክት ከዚያም ያነክት ብዬ ከብዙ አድካሚ፣ አሰልቺ ውትወታ በኋላ ብዙ ማገዶ ጨርሶ ዐማራው ተሰባስቦ፣ ታጥቆ፣ መክቶ፣ አሁን ማነከት ጀምሯል።
"…ዐማራ በዐማራነቱ መሰባሰብ የለበትም። ከከፍታው መውረድ የለበትም ወዘተ በማለት እነርሱ ከዘረኛው ተገንጣይ ከኦነግ እና ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ጋር ግንባር ፈጥረው ዐማራውን ግን እንዳይደራጅ ሾተላይ ሆነው እንደ ፈረንጅ ላም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማና ኢትዮጵያ የሚል ስም እያሳዩ አጠቡት። ዐማራውን እንደ ነዳጅ ጉድጓድ ተጠቀሙበት።
"…እናም እነዚያ ግምቦቴዎች እነ ብርሃኑ ነጋ፣ እነ አንዳርጋቸው ጽጌም ቢሆኑ ዐማራውን ሲያልቡት ከርመው አቢይ ብብት ስር ነው የተሸጎጡት። እስክንድር ነጋም ቢሆን ኤርምያስ ለገሰ ዋቅጅራን በአሜሪካ የአዲስ አበቤ ወኪል አድርጎ መርጦ ሲያበቃ ዛሬ አዲስ አበቤ በሙሉ በኤርሚያስ ጠቋሚነት በኦሮሙማው እየታሰረ ይገኛል የሚሉ መተርጉማንም አሉ። ዐማራ በጊዜ እንዳይደራጅ እንቅፋት የነበረው እስክንድር ነጋ ነበር።
"…ፋኖ ተደራጅቶ ትግል ሲጀምር እስክንድር ዐማራ ነኝ ብሎ ትግል ጀመረ። ዐማራ ነኝም አላለም። መነሻዬ ዐማራ መድረሻዬ ኢትዮጵያ ብሎ ነበር የተነሣው። ግምቦቴዎች ከበቡት። ገንዘብ ያዡ ሆኑ። እነ አበበ በለው ፣እነ ሀብታሙ አያሌውም በዐማራ ስም ከቢዝነሱ ጠበል ለመቋደስ በዙሪያው ተሰባሰቡ።
"…አሁን የእኔ ጥያቄ እነዚህን የዐማራን ትግል በእስክንድር ስር ተጠልለው ሊግጡት ያሰፈሰፉትን ግንቦቴዎች እነ ጂጂግግን ድድ ድዳቸውን እያልኩ ባንጫጫቸው ምን ይለኛል? ላንጫጫቸው አይደል…? …
• ኦንዲማቹ ወፍ አርግፍ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።
የGGጂጂግግ ዎች ነገር…
• ክንፉ ወዳጄ…
"…ተናግሮ አናጋሪ አያሳጣኝ ባልኩት መሠረት እስክንድር ስር የተኮለኮሎ ግንቦቴና ግንባሮች ፈጣሪ ይስጣቸውና ያለ ምክንያት እንዳልንበጫበጭ እነሱ ቀድመው እንደ ጦስ ዶሮ ተንበጫብጨውብኝ እኔም በነፃነት እንድንበጫበጭ እያደረጉኝ ነው። አስመሰግናለሁ እነ ጂጂግግዬ 🙏
"…ክንፉ ወዳጄ ማለት የደርግ ወታደር ሆኖ ወደ ራሺያ ለትምህርት ሄዶ ደርግ ሲፈርስ እርሱ ወደ አሜሪካ የፈለሰ እንደኔ ስደተኛ ነው። አሁን ጴንጤነትን ቢቀበልም ከቮድካ መላቀቅ ያልቻለ ሱሰኛ እግዚአብሔር የለሽ ደርግ ነው። መተዳደሪያው መጀመሪያ ግንቦት 7 ቀጥሎ ባልደራስ፣ ከዚያ ግንባሩ፣ አሁን ደግሞ ሠራዊቱ ብሎ የባፍሎ ኒውዮርክን ሕዝብ ቀደም ሲል በኢትዮጵያዊነት አሁን ደግሞ በዐማራነት ኪስ ገንዘባቸውን የሚያጥብ ላውነደሪያም የሆነ ግንቦቴ ነው። ይሄ ክፉ ግንቦቴ ነው እንደልቡ የሚያልበውን የሕዝብ ብር ዶላር ጉሮሮው ላይ ስለቆምኩበት "የየኔታ ዕዝራ ሀዲስን ፎቶ ፊታቸውን ቀፍፎ አውጥቶ የእኔን ፎቶ ከቶ የሚሳለቀው። ደርግ+ግምቦቴ+ግምባሩ+ ጴንጤነት= እናንተው ሙሉበት። ባይበሰጭብኝ ነበር የሚገርመው።
• ወንደሰን ተክሉ ወ/ሃና
"…ለእኔ ለራሴ ደውሎ እስክንድር ነጋ በሥጋ ዘመዴ ነው። የአክስት ይሁን የአጎት ልጆች ነን ብሎ ነግሮኛል። ነዋሪነቱ ኬንያ ናይሮቢ የነበረ ሲሆን፣ እነ ዶር አምሳሉ ከቦስተን ጋሻ ሚድያ የሚባል ከፍተው ሰጥተው እየከፈሉት ሲሳደብ የሚውል ጀዝባ ጫታም የሆነ፣ አሁን ወደ ኡጋንዳ ያሻገሩት ቀማቴ የሆነ ሰው ነው።
"…በነገራችን ላይ እስክንድር ነጋ እርሱ ጻድቅ ጻድቅ እየተጫወተ ነገር ግን በዙሪያው ከሲሲሊ ማፍያ የከፉ ጨካኝና አረመኔ ቅንጣት ታህል ለሕዝብ ርህራሄ የሌላቸውን ክፉ ሰዎች በዙሪያው ያከማቸው ሰው ነው። በስህተት ነው ብዬ ለመቀበል እቸገራለሁ።
• ጧ በል…!
የትንሣኤ ማግስት ሰኞ
"…የትንሣኤ ማግስት ሰኞ ማዕዶት ይባላል፦ ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ መሻገሩ እስራኤል ባህረ ኤርትራን፣ ኢያሱና ካህናቱ፣ ኤልያስና ኤልሳዕ ባህረ ዮርዳኖስን እንደተሻገሩት ያለ መሻገር አይደለም። ይህኛው መሻገር በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን እንጂ፡፡
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ዘወትር እሑድ በመረጃ ተለቭዥን በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው ሳምንታዊው መደበኛ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብራችን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።
• ዩቲዩብ 👉 YouTube: https://www.youtube.com/watch?v=6ZR3g1i2GAY
• ትዊተር 👉 Twitter: https://twitter.com/MerejaMedia
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
"…ሻሎም ! ሰላም !
"ርዕሰ አንቀጽ”
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።
"…ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ የሞቱ፣ ወደፊትም የሞትን ጽዋ የሚቀምሱ ሁሉ እሳትም ያቃጥላቸው፣ አውሬም ይብላቸው፣ ባህርም ይስጠሙ እንዴትም ሁነው ይሙቱ ብቻ በዚህች ምድር ላይ አፈር ሆነው በመቃብር ወስጥ አሉ። ይኖራሉም። ነቢያት ቢሆኑ ሐዋርያት፣ ጻድቃንም ሰማዕታትም ቢሆኑ ነገሥታትና መኳንንት ሁላቸውም ሟቾች ናቸው። በእያንዳንዳቸውም የመቃብር ሥፍራ ብንሄድ በዚያ የአጽማቸውን ቅሪት እናገኛለን።
"…ይህንኑ ሲያረጋግጥ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ በበዓለ ኅምሳ ቀን በኢየሩሳሌም ለተሰበሰቡት እንዲህ አለ፤ " ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።" የሐዋ 2፣29
"…የጨካኞቹ ነገሥታትም አፅም ከቀደሙቱ የእነፈርኦን፣ የእነ ናቡከደነጾር እና የእነዲዮቅልጥያኖስ፣ ከኋለኛው ዘመንም የእነሒትለር እና ሞሶሎኒም ቢሆን የትም ይሁን የት ብቻ በተቀበሩበት ሥፍራ አጽማቸው ከዚሁ ምድር ላይ እናገኘዋለን። ምስጥም አፈርም ቢበላቸው እንኳ ቅሬታቸው በዚህች ምድር እስከ ዳግም ምጽአቱ ድረስ ተጠብቆ ይኖራል። ይሄ ሃቅም እውነትም ነው።
"…በየትኛውም የምድራችን ክፍል ላይ የሚገኙ የመቃብር ሥፍራዎችን ብንጎበኝ በሰዎች አጽም የተሞሉ ናቸው። ከሰው ወገን ሆነው እስከ አሁን ሞትን ያልቀመሱ አባቶቻችን እንደ ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ እና ቅዱስ ያሬድን የመሳሰሉ ቅዱሳንም ቢሆኑ እስከ ጊዜው ድረስ እንጂ የጊዜው ጊዜ ሲደርስ ሞት እንደሁ አይቀርላቸውም። ከዘመናት በኋላ ወደ ምድር መጥተው የሞትንም ጽዋ ይቀምሳሉ።
※ የእኛ ጌታ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤልም ስለ እኛ ሲል ሞቷል። ሞቶ ግን በዚያው አልቀረም። የሞትም ኃይል አላሸነፈውም። ሞትን በሞቱ ድል አድርጎም ተነሣ እንጂ።" ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?" 1ኛ ቆሮ 15፣55 ተብሎ እንደተጻፈ። ክርስቶስ ወደተቀበረበት ሥፍራ ወደ ቀራንዮም ብንሄድ በዚያ የለም። ምክንያቱም ሞት ድል በመነሣት ተውጦአልና። መቃብሩም ባዶ ነው። "ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ " 1ኛ ቆሮ 15፣54 "…እንደተናገረ ተነሥቶአል ! ማቴ 28፣6
"…ይህንን እውነት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍት ተባብረው እንዲህ በማለት ያረጋግጡልናል ።
👉" መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ" 1ኛ ቆሮ15 ፣ 3-4
👉" ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።" ሉቃ 24፣5
👉" እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።" ማቴ 28፣6
👉" አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።"1ኛ ቆሮ15፣20
"…እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን" ሮሜ 6፥ 4-5
• ውድ ጓደኞቼ በሙሉ… ደግሜ እላለሁ በያላችሁበት እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በቸርነቱ፣ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።
• የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።” ኤር 17፥12…
• ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” መዝ 96፥6…
• ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።” 1ኛ ቆሮ 14፥40
• ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው።” ማቴ 17፥4
• መልካም የትንሣኤ ሌሊት… እንኳን አደራሰን…!
"…የሐረርጌ ቆቱ ወገኔም ራብና ችጋር ከቀዬ ከመንደሩ ፈንቅሎ አስወጥቶታል። ማን ድምጽ ይሁነው?
"…እነ ጃዋር መሐመድ በስሙ ነግደው ቢልዮነር የሆነበት፣ አቢይ አዳነች ሽመልስ ቢልዮነርም ሚንስትርም፣ ብሬዘዳንትና ከንቲባ የሆኑበት፣ ብዙዎች በስሙ ምለው ተገዝተው ኢንቨስተር የሆኑበት፣ ከኢትዮጵያውያን ጋር ሁሉ አጋጭተው ብቻውን ሜዳ ላይ ተገልሎ እንዲቀር ያደረጉት የሐረርጌ ሰው ጠኔ እና ራብ አሯሩጦት ከቤቱም አሰድዶት ይኸው ሜዳ ላይ እንዲበተን አደረጉት።
"…እነ ዳንኤል ዻባ፣ የሐረርጌው ቄሮ የድሬደዋው ጉማ ሳቀታም፣ እነ OMN, KMN ሳይቀር ዘጉት። ስለ ሀረርጌ ራብና ችጋር የሚናገር ጠፋ።
• መጅሊሱም ዝም…
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…የሞላላቸው፣ የደላቸው የነበሩ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዐማሮች ስደት ወጥተው በአንዱ አፍሪካ ሀገር ይኖራሉ። አንድ ወዳጄ ጋዜጠኛ ዘመዴ እንደው በማርያም የሆነ 1ሺ ዶላር ቢኖር የሆነ ሥራ ይጀምሩ ነበር። እናም እባክህ ከነ ልጆቻቸው ችግር ላይ ናቸው። የሆነ መላ ፈልግ ይለኛል። እኔ ለበዓል ካስተረፍኩት 200 ዩሮ አዋጣለሁ። 800 ዶላር ከ8 ሰው ካገኘሁ አንድ ሺ ዶላር አዋጥተን ባሉበት ሀገር እንጀራም መጋገር ጀምረው ከጊዜውም ቢሆን ከችግራቸው ይላቀቃሉ ብዬ ተስፋ ሰጠሁት። እናም ወደ አፍሪካዊት ሀገር አንድ አንድ መቶ ዶላር የምትልኩልኝ 8 ሰዎች፣ ወይም 200 ብር የምትልኩ 4 ሰዎች እፈልጋለሁ። ፍጠኑ።
"…ቄሮዎቹ አናጢ ባሏን ይገድሉባታል። ዜናውን በመረጃ ቴሌ ቭዥን አሳየሁት። ብዙ ሰው አለቀሰ። አንድ ወዳጄ በዴንቨር ኮሎራዶ የሚኖር ምን ላድርግ ዘመዴ እዘዘኝ አለ። ካለችበት ገጠር ወደ ከተማ መጥታ ልጆቿን ይዛ ቤት እንድትከራይ አደርኳት። ከዚያም ምጣድ፣ ሰፌድ፣ ቡሀቃ፣ ኩንታል ጤፍ፣ የማስጀመሪያ 500 ዶላር መደብን፣ ከኮረና በፊት ነው። ዛሬ ልጆቿም ሞተር ገዝተው በየሆቴሉ እንጀራ አከፋፋይ ናቸው። ኃይልሻ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወንድም ዓለም።
"…የትግራይ ልጅ ናት። አላውቃትም። መረጃ ቲቪ ላይ በቀጥታ የስልክ ጥሪ ብዙ ሰው ያስደመመ አስተያየት ሰጠች። ከመርሀ ግብሩ በኋላ ደወልኩላት። አይዞኝ አልኳት። ባሏ ጁንታ ነው ብለው አስረውባታል። እሷ እንደነገረችኝ ፖለቲካ ውስጥ የሌለ ሰው ነው። ልክ አሁን ዐማራው ሁሉ ፋኖ ተብሎ እንደሚታጎረው ማለት ነው። እናም የሚያማምሩ ልጆቿን ፎቶ ልካልኝ የማበላቸው እንኳን የለኝም አለችኝ። ባሏ ሲፈታ የባንክ ሂሳቡም ይፈታል። እናም ዘመዴ ቅበረኝ አለችኝ። ይሄን ሁሉ ችግሯን ደብቃ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ጦርነት ይብቃ፣ ይቁም ብላ ተረጋግታ በሰጠችው አስተያየት ተደምሜ የሚሆነው ሆነላት። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ማርያምን በውጭ ያላችሁ ወደ ድሮ ሰፈራችሁ ደውላችሁ 50 ዶላር እንኳ በመላክ ተመረቁ። ለወገን ደስታ ፍጠሩ። በማርያም ሞክሩት።
"…የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ በፋኖ ምክር እደመድማለሁ።
"…በመጀመሪያ በየ በረሀው እየተዋደቃችሁ ያላችሁ የዐማራ ፋኖዎች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው በዓል አደረሳችሁ እያልኩ ምክሬን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
• አንደኛ፦ የፋሲካን በዓል ተሰብስበን በአንድ ቦታ እናከብራለን ብላችሁ ባትዘናጉ ደስ ይለኛል። ምክንያቱም አራጁና አረመኔው አቢይ አሕመድ እናንተን ሊያጠቃ የሚችለው በዚህ አጋጣሚ ነው። እናም ተሰብስቦ በዓል ከማክበር ተቆጠቡ።
• ሁለተኛው፦
"…ቤተሰብ ናፈቀን የሚሉ ፋኖዎች ወደ ቤተሰብ ዘንድ ስልክ አይደውሉ። አለመደወል ብቻ ሳይሆን እናቴ ናፈቀችኝ፣ አባቴ በዓይኔ ውል አለ ብለው ወደ ቤተሰብ ዘንድ ሹልክም ፍጥጥም ብለው አይሂዱ። አስቻለው ደሴን የመሰለ ሰው የተበላው እናቴ ናፈቀችኝ ብሎ እናቱ ደጅ ጥሩነህ ተመስገን በዐማራ ልዩ ኃይል ነው ያስደፋው። እናም ተጠንቀቁ።
• የትንሣኤን በዓል ከኢትዮጵያ ትንሣኤ ጋር እኩል በጋራ እናንተም ከበረሃ፣ እኛም ከስደት ተመልሰን ለማክበር ያብቃን። መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን።
• የምፈልጋችሁ ስምንቶቹ ወዳጆቼ ግን በውስጥ መስመር አናግሩኝ።
• ቆይቼ እመለሳለሁ። እናንተም አስተያየት ለመስጠት ተዘጋጁ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
መልካም…
"…እንደተለመደው የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቶ ተትረፍርፏል። እግዚአብሔር ይመስገን። እግዚአብሔር ይመስገን ብለው እንደ ማመስገን በምስጋና መሃል ሌላ ወሬና ስድብ ያለቦታው አምጥተው ቤቱን ሲያቆሽሹ የነበሩ GGጂጂገግ ዎችንም እየቀሰፍኩ ከቤቴ አባርሬ አጽድቼአቸዋለሁ።
"…ዛሬ ደስ የሚያሰኝ ተግባር ላይ ነበር ያረፈድኩት። የትምህርት ቤት መምህራኖቼን፣ አቅመ ደካማ ወዳጆቼን በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን ስል ነው የዋልኩት። በእውነት ሁል ጊዜ ደስተኛ ነኝ ዛሬ ደግሞ እጅግ በጣም ነው ደስስ ያለኝ።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ አጠር ያለ እና የኑሮ ጫናውን በተመለከተ፣ እንዲሁም የፋሲካን ለማክበር አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው ለሚከማቹ ፋኖዎች እና የፋኖ አለቆች የሚደርስ መልእክት ነው። እንደነገርኳችሁ አጠር ያለች ናት።
"…ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።” ማቴ 23፥4
• ዝግጁ…
ይደመጥ…
"…አሪፍ ትንተና እና አሪፍ ተንታኝ ነው። ታተርፋበታላችሁና በፅሞና አድምጡት።
"…ስለ ዘመድኩን ግሩም መረጃ ነው ያለው። በሀፍታሙ ላይ እንደሚቀና… ዘመድኩን ከጸበል የወጣ ያመለጠ ሰይጣን እንደሆነ ሁሉ የሚደንቅ መረጃ ነው ያለው። ከምር ስሙት። እኔ ራሴ አስከዛሬ የማላውቀውን መረጃ ነው ያገኘሁበት።
"…ሀፍታሙን፣ ቴዎድሮስ ትርፌን፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ራሱ ተንታኙ እንደሚቃወም ይነግረንና ዘመድኩን ግን ሲቃወማቸው ይበሰጨኛል ይላል። 😂 ብአዴንንም እኮ እቃወመዋለሁ ሳሚዬ።
"…ተንታኙ ጆሮው አካባቢ ትኩር ብዬ ሳየው (ህወሓት ወለዱ ቅማንቴ ይመስላል) ሌላው ያነሳው ዋነኛ ነጥብ "የኢትዮጵያ ሕዝብ አርቆ አለማሰቡ፣ አለማገናዘቡን፣ በፈረንሳይኛ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለተማረ ደንቆሮ ነው የሚለው። አቢይ አሕመድ ሾርት ሚሞሪያም እንደሚለው ማለት ነው።
"…የተንታኙ ትንተና ሲጠቃለል ሀፍታሙ ዐማራ ነው ዘመድኩን ወሮሞና የሃይማኖት አክራሪ ነው። ሥዕለ አድኅኖ እና መስቀል አድርጎ ሕዝብ የሚዘርፍ አጭበርባሪ ነው ብሎ አሪፍ መረጃ ነው የሰጠው። እኔ በበኩሌ በተንታኙ እንዴት እንደተደመምኩበት አትጠይቁኝ። ወይ ዘመዴ አጭቤዋ ዛሬ ገና የሚገርም ተንታኝ እጅ ወደቀች። የት አባሽ እንደምትሄጂ እናያለን። በቃ ተያዝሽ እኮ ዘመዴ። የሀፍታሙ አያሌው አምላክ አጋለጠሽ። ኤትአባሽ ዘመዴ…?
"…ለምን እንደሆነ ባላውቅም ተንታኙ ግን ባይደነግጥ፣ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ ባይል፣ ቃላት ባይደጋግም፣ ሰገራው ደርቆበት ሽንት ቤት ገብቶ እንደሚሰቃይ ሰው አማርኛ ለማውራት ዐማራ ሆኖ ቃላት ለማውጣት ባያምጥ ጥሩ ነው። በተረፈ በቲክቶክ የተሰማራን የእነ GGጀጂግግ ን ሠራዊትም ድባቅ እንደምመታቸው መልእክት አስተላልፉልኝ።
• ሌባ ሁላ አለ ዘመዴ በነጠላ ዜማው። ቺድ የእንጭቅ ልጅ ያለው ማን ነበር…?
"…ኦነጎችም እየተንጫጩብኝ ነው። እኔ እኮ ሲያመኝ ጤና የለኝም። ደግሞ እነሱን ምናቸውን ነክቼ ነው ጓ እያሉብኝ ያሉት?
"…የዚህኛው ኦነግ ፔጅ ""የፔጁ ባለቤት" ወያኔ ነው የሚመስለኝ። ምክንያቱም ኦሮሞ አ ን ሲጽፍ ኣ አይልም። አማራ ለማለት ኣማራ የሚለው ትግሬ ብቻ ነው። 😂
"…ምን ተሻለኝ እነ GGጂጂግግ በአንድ በኩል ያብዱብኛል በዚያ በኩል ደግሞ እነ ሂዊ ኦነጌ ጓ ይሉብኛል። እኔ ብቻዬን አምላኬን ይዤ እንደ ቡሩሱሊ ዋ ያ ግሽ ዋይ ቋ እያልኩ እየተገለባበጥኩ መከትከት ነው። 😁
"…ልዩ ፍቅር ማለት ሀብታሙ ሁል ጊዜ እየተነሣ ሱፐር ስቲከር፣ ሱፐር ቻት ረዳን የምትለዋ ዶነር ናት። ባሕታዊ ገብረ መስቀል ደግሞ ዘመድኩን በ40 ብር ሸጠኝ የሚል ገተት ነው። ኦነግና ግምቦቴ ገጥመውኛል ገጥመውኛል።
• ፐፐፐ እኔ ዘመዴ የምሥራቁ ሰው መራታው ዘመዴ ግን ሳይታወቀኝ ባለ ከባድ ሚዛን ሆኜ የለም እንዴ?😂 እናንተ ግን ከእኔ ተነሱ ማን የሚያሸንፍ ይመስላችኋል እስቲ ገምቱ…?
የትንሣኤ ማግስት ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፦
"…በትንሣኤ ማግሥት ማግሰኞ በዚህ ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ የጌታን የተወጋ ጎኑን፣ የተቸነከሩ እጆቹን ካላየሁ አላምንም ብሎ ነበርና የጌታችንን የተወጋ ጎኑን፣ የተቸነከሩ እጆቹን ማየት ብቻ ሳይሆን ዳስሶ ጭምር "ጌታዬና አምላኬ" በማለት ጌትነቱ ከአምላክነቱ ጋር አስተባብሮ የመሰከረበት ዕለት በመሆኑ ለቅዱስ ቶማስ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ዕለቱ ቶማስ ተብሎ ይከበራል። ዮሐ 20፥ 27-29
"…ታሪኩ የተፈጸመው በትንሣኤ ሳምንት ባለው በእለተ እሑድ በዳግማይ ትንሣኤ ዕለት ቢሆንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አበው ታሪክ ከታሪክ እንዳይደራረብ ብቻ ሳይሆን ዳግማይ ትንሣኤ የጌታ ዳግም መነሣት ብቻ ሲታወጅ እንዲውል ብለው በትንሣኤ ማግስት ከሰኞ በኋላ በሚከተለው ቀን በዕለተ ማክሰኞ በዛሬው ዕለት ተከብሮ እንዲውል ሥርዓት ሠርተዋል። ቅዱስ ቶማስ በእመቤታችን ትንሣኤ ዕለትም ከሐዋርያቱ ጋር ያልነበረ፤ ከሀገረ ስብከቱ ህንድ ቆይቶ ሲመለስ በደመና ላይ እመቤታችን ስታርግ ያገኘ ሐዋርያም ነው። የሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በረከቱ ይደርብን። አሜን።
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።
ጎጃም ተጠንቀቅ…
• ጸሐፊው ወንደሰን ተክሉ ነው።
"…መጀመሪያ ሀብታሙ አያሌው ሻለቃ ዝናቡን አቅርቦ እነ ዘመነን፣ እነ አስረስን ከሸከሻቸው። ቆይቶ እነ ሻለቃ ዝናቡም፣ እነ ዘመነም አንድ ሆኑ፣ በጎጃም የዐማራ ፋኖን መሠረቱ። እስክንድርም ወደ ሸዋ ተመለሰ።
"…እናንላችሁ ሰሙኑን የእስክንድር ገንዘብ ያዝ ወሮ ሕይወት "አንዴ ማርሸትን፣ ሌላ ጊዜ ዝናቡን፣ ማንችሎትን በፀባቸው ጊዜ መስከረም ላይ በድብቅ የቀዳቻቸውን የድምፅ ቅጂ በሰፊው መልቀቁን ተያያዙት እነ ጂጂግግዎች።
"…ይሄ የካፒቴን ማስረሻ አድናቂ ሆኖ አሁን ከች ያለው ከኬኒያ ወደ ኡጋንዳ እንዲሰደድና በዚያ እንዲቀመጥ የተደረገው ከአበበ በለው ፊት ያለው የእስኬው የሥጋ ዘመድ ወንደሰን ተክሉ ነው።
"…እነ ዘመነ ካሤን እየሰደቡ፣ እያዋረዱ፣ ካፒቴን ማስረሻን ነጥለው ማመስገን ለምን ይመስላችኋል? …ዐማራ ባይጠይቅ እኔ እጠይቃለሁ።
"…የእስክንድር ነጋ ጠበቃ ነኝ፣ የሀብታሙ አያሌው ተሟጋች ነኝ፣ የግንባሩም፣ የሠራዊቱም ተከራካሪ ነኝ ባዩ ኦሮሞው ሀብታሙ በሻህም በአንድ ቪድዮው ላይ ከነመከታው ጋር የቆመ መስሎ እነ ጋሽ አሰግድን፣ እነ ኢንጅነር ደሳለኝን ሬሳችሁን ልቀሙ፣ ጨፍጭፈናቸዋል ብሎ በድፍረት የተናገረውም ያለ ነገር አይደለም።
"…ጎጄ መለኛው የታቀደለትን የመከፋፈል ሴራ በንግግር፣ በጥበብ ያልፈዋል፣ ይሻገረዋል ብዬ አምናለሁ።
"…እኔየምለው ግን ያልገባኝ ነገር እኔ ለምጠይቀው ጥያቄ እነ ግግጂጂዎችን ምን ያናድዳቸዋል? እህዕ…
• ጎጄ መለኛው ጠንቀቅ ነው… ሃኣ…!
እስኬው መልስ ስጠኝ…!
• ግንባሩ ለምንና እንዴት ፈረሰ…?
• በፋኖ ሁሉ ስም የተሰበሰበው ዶላር ከምን ደረሰ…?
• ኦዲተር ይድትር 😂 ሲባል ለምን ተከለከለ?
• ግንባሩ መፍረሱ ሳይታወቅ አበበ በለውና ሀብታሙ አያሌው ሕዝባዊ ሠራዊት ብለው 2መቶ ሺ ዶላር አካባቢ ሰብስበው ብሩን የት አደረጉት?
• ለግንባሩ የተሰበሰበው ብር በኢትዮ 360 ብር ላይ ተጨምሮ ነው ብለው ሻለቃ የተናገሩት እንዴት የግንባሩ ብር በሀብታሙ አያሌው ድርጅት የባንክ አካውንት ላይ ተጨምሮ ተሰበሰበ?
• አንተ ለዚህ ሁሉ ውዝግብ ካለህበት መልስ መስጠትን ለምን ፈራህ? መግለጫ ለመስጠት የምታገኘውን ኔትወርክ ምላሽ ለመስጠት ሲሆን እንዴት አጣህ…?
• የፎቶ ቦለጢቃንማ አቢይ አህመድም እኮ አሳምሮ ይጫወተዋል? እናም የፎቶ ቦለጢቃ ቀርቶ ለጥያቄዎቼ መልስ ይሰጠኝ።
"…ዴየስስ አይልም እና የዋሻ ስር የፎቶ ቁማር በአስቸኳይ ይቅር። ገና ወደ ዋናው አጀንዳዬ አልገባሁም። በዐማራ ስም አበበ በለው ሰሞኑን ዐማራውን ለመጋጥ መዘጋጀቱንም ሰምቻለሁ። የእነ አበበ በለው ድርጅትም ገንዘብ የመሰብሰብ ፈቃድ የለውም። በአሜሪካ ሕግ መሠረት የሚያስቀጣ ነው። አለቀ።
• ዐማሮች ደፍረው መናገር ካልጀመሩ እኔ የሐረርጌው ቆቱ መራታው ዘመዴ ደፍሬ እናገርላቸዋለሁ።
• ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ሳላደማ ወይ ንቅንቅ።
ይሄኛውም ይደብራል…
"…ወንደሰን ተክሉ ማለት በቀዳሚው ልጥፌ ላይ ያጋራኋችሁ ኬንያ ተሰድዶ ጫት ካልቃመ አይኑ የማይገለጥ ኮተታም የእስክንድር ነጋ የሥጋ ዘመዱ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ የሆነ ቀማቴ ሰው ነው። አሁን የእስክንድር የሠራዊቱ የአሜሪካ ገንዘብ አሰባሳቢ ወኪል ሆኖ የተሰየመው የቦስተኑ ዶር አምሳሉ ተፈራ ነው ከኬኒያ ወደ አሜሪካ ለማሻገር ሲል ወደ ኡጋንዳ የወሰዱት።
"…ለእኔ የክንፉና የወንዴ ስለ እኔ መቸክቸክ በጣም ነው የተመቸኝ። ሁለቱም የዘወትር ጸሎቴ ውጤቶች ናቸው። እኔ አንድ ጉዳይ ላይ ክፍት አፌን ለመክፈት አስቀድሞ አናጋሪ ነገር እፈልጋለሁ። ያለ አናጋሪ ዝም ብዬ ማንም ላይ ፊጥ አልልም። ሁል ጊዜ ተናግሮ አናጋሪ የማያሳጣኝ አምላኬ ይክበር ይመስገን።🙏
"…ጌጥዬ ያለው ደግሞ ጋዜጠኛ ነው። የማከብረው፣ የምወደው ከልቡ ጋዜጠኛ ነው። ከባልደራስ ጊዜ ጀምሮ ከእስክንድር ነጋ ስር ያልጠፋ ጋዜጠኛ ነው። በቀድሞ በጎጃም አሁንም በሸዋ ከእስክንድር ስር ያልጠፋ ጋዜጠኛ ነው። እስከ ሞት ድረስ ለእስክንድር የታመነ ጋዜጠኛ ቢኖር ጌጥዬ ብቻ ነው። በዚህ አቋሙ አከብረዋለሁ።
"…ጌጥዬ እስክንድርን ከቅዱሳን ከጻድቃን እንደ አንዱ ደምሮ፣ አነጻጽሮ መጻፉን አልደግፍም። አልቀበልምም። ጌጥዬ ምንአልባት ዜና መዋዕሉ ለእስክንድርን እየጻፈ ሌሆን ይችላል። አንድም ሠራዊት የሌለው ሰው የፋኖን የፖለቲካ ክፍተት ልሙላ ብሎ ወደ ጫካ የገባን እስኬውን ከአሁኑ ከቀደሙቱ ቅዱሳን አበው ጋር አነፃፅሮ መጻፉን አልደግፍም። ቅድስና በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚሰጥ ማዕረግ ነው።
"…የጌጥዬስ እሺ የሚያስቀኝ የእስኬው የአጎት ልጅ ይሄንኑ ሼር አድርጎ የዘመዱን የእስኬውን ጽድቅና ቅድስና ዕወቁልኝ ማለቱ ነው። ይሄም ልክ አይደለም ይላል የእናንተው… ወፍ አርግፍ ዘመዴ ከራየን ወንዝ ማዶ…😂
• እነ ጂጂግግ እየተንጫጫችሁ…
"ርዕሰ አንቀጽ”
"…በ15 ቢልዮን ዶላር ወጪ ግዙፍ ቤተ መንግሥት ከመካከለኛ ሀይቅ ጋር በየካ ተራራ ላይ እያስገነባ የሚገኘው ኦሮሙማ፣ በካርዱ መርጦ ሾመኝ ለሚለው ለመራጩ ለደሀው ሕዝብ ዓመት በዓል ጠብቆ አንድ እንጀራ በቀይ ወጥ እና በአልጫ አቅርቦ ከመመገብ ባለፈ በማዕድ ማጋራቱ ቤተ መንግሥት መምጣት ላልቻሉ ደጋፊዎቹ እንደ ኮረፌ፣ ጠጅና ጠላ የመሰለ መጠጥ በውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ሰጪ ተቋሙ በኩል በመጠቀም በእያንዳንዱ ቤት በሰፊው ማቅረብ መጀመሩ እየተነገረ ነው።
"…ውኃ አለች ወይ…? … ውኃ መጣች ወይ…? ውኃ… ውኃ… ውኃ የሚል ድምጽ የበዛው የውኃ ጉዳይ ምን ሆኖ ነው?
"…እናንተ ሰፈር ውኃ በሳምንት ስንት ቀን ነው የምትመጣው? …የምትመጣውስ በቀን ነው በሌሊት በጨለማ… ያለ ውኃ ጽዳታችሁ እንዴት ነው? …የሽቶ ብዛት ያለውኃ ጽዳት ሊሸፈን ይችላልን?
"…ለማትመጣዋ ውኃ ወርኃዊ ክፍያዋ ስንት ደረሰ? አንድ ጀሪካን ውኃ ዋጋው ስንት ገባ…? በአህያ የሚመጣው የጉድጓድ ውኃ ዋጋው ጨመረ ወይስ ቀነሰ? የታሸገ ውኃስ 1ሊትሩ ዋጋው ስንት ገባ?
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"…በር ላይ የቆመውን ባሰብኩ ጊዜ…😭
"…ይሄን ሥዕል ባየሁ ቁጥር ልጅነቴ ነው ትዝ የሚለኝ። በዚህ ዕድሜ ላይ ሆነህ ከቤትህ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ሳይኖር ሲቀር፣ ከጎረቤት የሚሸትህን የዶሮ ወጥ፣ የጠላና የድፎ ዳቦ ሽታ እያሸተትክ፣ በጎረቤቶችህ በራፍ በደጃፋቸውም ላይ በመመላለስ ከአሁን አሁን ቢጠሩኝ፣ ናግባ ቢሉኝ ብለህ በመቀላወጥ መንከራተት እንዴት እንደሚያምና እንዴት ያለ ህመም እንደሚሰማ እንደ እኔ በልጅነቱ ችግር አግኝቶ ያሳጣው ሰው ያውቀዋል። ልብስማ የማይታሰብ ነው።
"…እናም ወገኖቼ ክርስቲያኖች ሁላችሁ በዓልን ስናከብር ብቻችንን አይሁን። ለምስኪኖች ማዕድ ማጋራቱንም ቸል አንበል። ስደተኞችና ተፈናቃዮችን፣ ምስኪን ጎረቤቶቻችንንም ሁሉ በማሰብ ይሁን። ሀገር ተርቦ ያለልክ ቁንጣን እስኪያስቸግረን፣ እስኪያሰቃየን ድረስ እየተፋን ምግብ እና መጠጥ በማብዛት አይሁን። ጭፈራው አይብዛ። ስካር ዳንሱም አይብዛ። ሚልዮኖች በራብ በሚጠበሱበት ሃገር ጥቂቶቻችን አናብዛው። እናስብ። በመጠን ኑሩ። ሁሉ በልክ ይሁን።
"…እኔ የልጅነት ጊዜዬ አግኝቼ ያጣሁበትን ወቅት ተበቅዬዋለሁ። ለምስኪኖች ሥራ በመፍጠር፣ ያለኝን በማካፈል የልጅነት ችጋሬን በደግነት ተበቅዬዋለሁ። አሁንም ወደፊትም ዕድሜ እስከሰጠኝ በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለሌሎች ደስታን፣ ሀሴትን በመፍጠር ድህነትን እበቀለዋለሁ። ለልጆቻችሁ ልብስ ስትገዙ ለጎረቤታችሁም ልጅ ወርወር አድርጉለት። ሀገሩን ጠልቶ፣ ሀብታም የተባለ ተበቃይ ትውልድ ሆኖ የልጆቻችሁን ዘመን እንዳያበላሸው አስቡበት።
"…በምሳሌ አስረዳለሁ። በር ላይ የቆመው ህፃን ቢጠፋ ቢጠፋ ወታደር ይሆናል። ከዚያ ኩዴታ ፈጽሞ አቢይ አህመድን ሊሆን ይችላል። ከዚያ ተማሪ እያረደ፣ ትምህርት ቤትም እየዘጋ፣ ሀብታም አጋች፣ ዘራፊና ቀማኛ ትውልድ ፈጥሮ ይበቀልሃል።
• አስቡበት…!
"…መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ" 1ኛ ቆሮ15 ፣ 3-4… "…እንደተናገረ ተነሥቶአል ! ማቴ 28፣6 "…ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ " 1ኛ ቆሮ 15፣54
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ…!
በመጨረሻም…!
"…ተሃድሶው አቶ ሰረቀ ብርሃን የጰጰሰባት፣ ደፋሪው አቶ አሮን የጰጰሰባት ትግራይ፣ የቅዱስ ያሬድን ዜማ፣ የደብረ ዓባይን ቅዳሴ አሽቀንጥራ ጥላ "ጌታቸውን ተቀብላለች" ይግርመናሎ አለ ወዲ ሀጎስ።
"…የቅዱሱ ሊቅ የቅዱስ ያሬድ ሥርዓተ ማኅሌት በትግራይ ይሄን መስሏል። መጀመርታ በወያኔ ጥጋብ እሷ ባመጣችው በላ ትግሬ አስራቡት። አደኸዩት። ከዚያ እንጀራ ከፈለግክ ብልፅግናን እና የብልጽግናን ነቢያት ተቀበል አሉት። መቼም ራብ ክፉ ነው ትግሬም ይኸው ሰተት ብሎ "ለጌታቸው ልጆች እጁን ሰጠ። እጅ ሰጠ አልኩህ ትግሬ። ትግሬም እንደ ዳንኤል ክብረት ማዕተቡን አስበጠሱት። ኪራላይሶን…🙏🙏🙏
"…አደይን ራሱ ሳይ ዝላዩ ላይ ቡዓ እንዳይገጥማቸው ስቅቅ ነው ያልኩት።
መልካም…
"…ርዕሰ አንቀጹ ተነቧል። መነበቡንም ያወቅኩት ቤተሰብ ይዘው ወደ አንዲት አፍሪካዊት ሀገር የተሰደዱ አግኝተው ያጡ አንድ ስደተኛ ቤተሰቦችን በተመለከተ በዚያው በርዕሰ አንቀጹ ላይ ጽፌ ጥሪ ማድረጌን ተከትሎ የጎረፈልኝን ምላሽ በመመልከቴ ነው። በደንብ መነበብ ብቻ ሳይሆን የእኔ ቤተሰቦች ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ስለሆነም ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ።
"…እኒህ አግኝተው ያጡ ከነልጆቻቸው የተሰደዱ ስደተኞች በዚያው ባሉበት የስደተኛ ካምፕ አካባቢ መጠነኛ ሥራ ለማስጀመር ያስችላቸው ዘንድ እንዲየው 1ሺ ዶላር ቢገኝ ብሎ ጉዳዩን ካመጣ አንድ ጋዜጠኛ ወዳጄ ጋር የተመካከርነውን ጽፌው ነበር። በዚያውም እኔ ዘመዴ ራሴ 200 ዩሮ በመስጠት የተሰጠኝን በማካፈል እጀምራለሁ ብዬም ቃል ገብቼ ነበር። እናም 8 ባለ አንድ መቶ፣ ወይም 4 ባለ 200 ዶላር ለጋሾችን ባገኝም ብዬ ጽፌ ነበር።
"…ብዙም ሳይቆይ ለጋሱ ሕዝብ ጎረፈ። እኔ ዘመዴ 200$+ ወሮ ዕንቁ 200$+ ኒቆዲሞስ 200$+ ቲጂ 200$+ እሴተ 100$+ የሰፈሬ የአራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ልጅ ብርሃነ መስቀል ከእንግሊዝ 100 ፓውንድ በጠቅላላ 700$ ሲደመር 200 ዩሮ+ 100 ፓውንድ በአጠቃላይ 1ሺ ገንዘብ ሞላ። ድጋፍ የምንሰጠው ቤተሰብም አፈር ልሰን እንነሣለን፣ ማቴሪያል ከተሟላልን ሌላውን እግዚአብሔር ያውቃል ብለዋል።
"…ገንዘቡ በአድራሻው ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር ይሄዳል። እኔ ጋር የሚላክ፣ የሚነካካም በእኔም ዘንድ የሚያልፍ ገንዘብ የለም። ለሰጣችሁ በሙሉ እግዚአብሔር ይስጣችሁ። በወጣ ይተካላችሁ። ዛሬ ደስ ደስ እያለኝ ውዬ ማምሸቴ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን።
• እኔ ችግርን አጣጥሜ ስለማውቃት፣ በችግር ወቅት በጭንቅ ሰዓት ያላሰባችሁት ሲሳይ ሲመጣም እንዴት ደስ እንደሚያሰኝ ስለማውቅ ይህን አደረግሁ። እናንተም ለሌሎች እንዲሁ አድርጉ…!
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…እስኪ ተይቅርታ ጋር ትብብር ጠይቄ ነው። ካምፓስም ባስገበው ኢኮኔሚ ድጋፍ መስጠት አንችልም በጀት የለም ብለውኝ ነው። ተማሪ እገሌ እባለሁ። በእንትን ካምፓስ የእንትን ተማሪ ነኝ። ነዋሪነቴ ጎጃም ዲማ ጊዮርጊስ ነው። እናም በጣም ኢኮኖሚ እጥረት ስላለብኝ ዘመዴ ትብብር ጠይቄ ነው። ተይቅርታ ጋር 1000 ብር ላስቸግርህ። አገር ቤት ጦርነት እና ቤተሰቦቸ ትንሽ በኢኮኖሚ ደከማስለሆኑ ነው ። ብድር ተማሪወች አበድረውኝ ለመክፈል እና በግቢ ጉባየ ለተንሳይ መዋጮ ኖሮብን ነው።
"…ዘመዴ አሁን ምንም ብር የለኝም ግቢ ጉባየ ስንበት ትምህርት ቤት መዋጮ እና ብድር ተማሪወች አበድረውኝ ነበር። እናም ልብስም መቀየሪያም የለኝ። ሙቀት ከመሆኑ የተነሣ አንድ ልብስ ስውነታችንን በጣም ያቃጥለናል። ካላስቸገርኩህ አሁን ሰኔ እንመረቃለን። ጓደኛቸ ሱፍ አሰፍተው ጨርሰዋል። እኔ በብር እጦት ምክንያት አላሰፈውም...
• ምን ያህል ብር ነው የምትፈልገው?
Ok
Zemed ለመመረቂያ የሚፈጀው ሱፍ ያሰፉ 7,000 ብር ነው። ሸሚዝ 1000 ብር ነው። ጫማ የሚፈጅ 2,000 ብር ነው። እና አሁን ላይ መቀየሪያ ልብስ ስለለኝ አሁን መቀየሪያ ልብስ ለመግዛት ሱሪ 1,000 ብር ይፈጃል። ሸሚዝ 500 ብር እና ሹራብ 300 ብር ይፈጃል። የተንሳይ የግቢ ጉባየ መዋጮ 300 ብር እና የሚከፈል ክፍያ 500 ብር አለብኝ። ጠቅላላ ወጭ የሚፈጀው ዘመዴ12,600 ብር ነው።
"…አላውቀውም። ምንአባቴ ይቅረብኛል? ለኪሱ እንዲተርፈው አድርጌ እኔው ካለኝ ላይ ጨምሬ ላኩለት… አሁን በምን ዓይነት ደስታ ላይ እንዳለ የፈጠረው እግዚአብሔር ይወቅ። ይሄ የዛሬ ነው።
"…ደግሞ ሌላ ቀን። የሚጠራውን ስልኬን አንስቼ ሃሎ አልኩ። ከዚያኛው ወገን ጸሎተ ኪዳን ይሰማኛል። እናም አንዲት እናት በእንባ የታጀበ ታሪክ አጫወተችኝ። ደኅና ኑሮ የሚኖሩ ሆነው ታሪኩን ግን አሁን በዚህ ሥፍራ መግለጽ የማልፈልገው ታሪክ አጫወቱኝ። እናም ቤተሰቡ ሊበተን ነው። እኔ ደግሞ ያለወትሮዬ ራሴን ቤተሰቡ ውስጥ ከትቼ ተጨነቅኩ። ሺ ችግሮችን ብሰማም ልቤ ከደነደነ ቆየ። በዚህኛው ግን እንቅልፍ አጣሁ።
"…ከመሥሪያ ቤት ባሏን ወስደው ያስሩታል። ዳኞቹና ዐቃቢያነ ሕጎቹ መኖሪያ ቤትሽን በአራጣ አስይዘሽ ተበድረሽ ጉቦ ክፈይን ይሏታል። ራሳቸው ዳኞቹ አራጣ አበዳሪ አላቸው። ተበዳሪው ብሩን መክፈል ካልቻለ አባዳሪው ለፖሊሱ ይከሳል። ፖሊሱ ለዐቃቤ ሕጉ ያስተላልፋል። ዐቃቤ ሕጎ ለዳኞቹ ይመራል። ዳኞቹ ተበዳሪው ላይ ይፈርዳሉ። መጀመሪያ በአራጣ ባበደሩት ብር ሌላው የዳኞቹ አባል ቤቱን ሄዶ ይገዛዋል። ዐማራ፣ ኦርቶዶክስና ጉራጌ በዚህ መልክ ነው በዘዴ እየገፈፉ እያሳበዱ ያሉት። አይ ኦሮሙማ ጭካኔው አይጣል ነው።
"…እናም ሚስት ከፍላ ከፍላ እጅ አጠራት። ቤቱን ሊሸጡ ከጫፍ ደረሱ። የቀራት ትንሽ መቶ ሺህ ብሮች ነበሩ። አሁን ከዚህ ብር ላይ የዚህን ወር የሚያበድረኝ ሰው ፈልግልኝ። እኔ ቼክ ልጻፍ። አንተንና እሸቱን ነው በአእምሮዬ የሚያመላልስብኝ። እሸቱ ራቀኝ። አንተ በቴሌግራም ስለምከታተልህ ደፍሬ ጻፍኩ። ዘመዴ ማበዴ ነው። ባለቤቴም ከሥራው አባረውታል። ዱብ ዕዳ ነው የወረደብን ነው የምትለኝ መከራው የገጠማት ሴት። ጨነቀኝ አይገልጸውም።
"…እኔም ጨክኜ የሆኑ ወዳጆቼ ጋር ግግም ብዬ ሰው። ታሪኩን አስረዳኋቸው። 1ሺ ዶላር አገኘሁ። የሆነች እህቴም ጋር ደወልኩ እንዲሁ የሆነ ብር አገኘሁ። ሌላም ሰው ጋር ደወልኩ እንዲሁ የሆነ ነገር አገኘሁ። አንድ ወዳጄ ጋር ብደውል፣ ብደውል ስልኩን አላነሣ አለኝ። ሳምንት ያህል አላነሣልኝም። ከራሴ ጨመርኩና ለሴትየዋ ላኩላት። ሰዎቹም በባንኳ እንዲልኩላት አደረግኩ። ሙሉ እዳዋን ከፈለች። ባልና ሚስት እያለቀሱ ደወሉልኝ። ቤተሰብ ከመበተን፣ ቤታቸውም ከመሸጥ ዳነ። ተረፉ። አሁን ከደስታ ብዛት መናገር አይችሉም። ዕዳው በሙሉ ተከፈለ። እኔም ተገላገልኩ። እንቅልፌን መተኛት ጀመርኩ። የገረመኝ ነገር ግን 200 ወይ 100 ዶላር ላስቸግረው ደጋግሜ የደወልኩለት ወዳጄ ብሩ በተከፈለ ማግስት ዘመዴ ደውለህልኝ ነበር አለኝ። ሳላየው፣ ሳይመቸኝ ቀርቶ ስልክህን አለመለስኩም አለኝ። እኔም በል ተወው ለዛሬ እግዚአብሔር አልፈቀደልህም ብዬ አለፍኩት።
"…በዚህ ሰሞንም ሳደርገው የከረምኩት ይሄንኑ ነው። ትምህርት ቤት ከፍለው እኔን በነፃ ያስተማሩኝን መምህራኖቼንና በጡረታ ላይ እንዳሉ የሰማኋቸውን በሙሉ እየደወልኩ እንኳን አደረሳችሁ ብዬአቸዋለሁ። ቲቸር ታዬ ወልደ ገብርኤል ብቻ ነው የሚቀረኝ። ቲቸር መኮነንን ኃይለየሱስንም አድራሻውን የሚሰጠኝ ባገኝ ውለታ ከፋይ ነኝ። የቄስ ትምህርት ቤት መምህሬን የኔታ ኃይለየሱስን በወር በወር ምንም እንዳይጎድልባቸው አድርጌ በስተእርጅና የሰው እጅ እንዳያዩ ካፈረግሁ አምስት ወይ አራት ዓመት አለፈኝ። በዚህም እና በዚህ መሰል ምክንያት እኔ ዘመዴ ደስተኛም ጤነኛም ነኝ።
"…ይሄን ከባድ ዘመን እንዲህ በመረዳዳት ካላለፍነው እጅግ ከባድ ነው። በተለይ ውጭ ያላችሁ 100 ዩሮ የስንት ደሀ ቤት ቀዳዳ ይሸፍናል። በተለይ ሴቶች በውጭ ያላችሁ ጎረቤቶቻችሁ፣ አብሮ አደጋችሁ፣ ሴት ሆነው የሞዴስና የቅባት የሚቸገሩ ስላሉ እንዲየው በየወሩ ቢቀር በዓመት በዓሉ ጎብኟቸው። ጎብኟቸው በማርያም። አዎ በእውነት አሁን ደስስ የማይል ጊዜ ነው። ምግብ ጥያቄ ባልሆነበት ሀገር ተቀምጦ በሜካፕ ያበደ ፎቶ እየለቀቁ የምስኪኖችን ልብ ለስደት ከማሸፈት ዘመኑን በመረዳዳት አሳልፉት። ለጭፈራ፣ ለሱስ አትላኩ። ችግር ለመፍታት የሚያስችል ድጋፍ አድርጉ።
ለምሳሌ እኔ የበኩር ልጄ አሁን እየተማረ ዓርብ ማታ እና ቅዳሜ ከሰዓት በሳምንት ለ8 ሰዓት ያህል የተማሪ ሥራ ጀምሯል። እናም ከዚያችው ከተማሪ ደሞዙ ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ ልጅ እንዲረዳ ነግሬ አስይዤው አሁን አንድ ልጅ ኮሌጅ ያስተምራል። ሴቷ ልጄም ሥራ ስትጀምር እንዲሁ ነው የእሱን ፈለግ የማስከትላት። የባለቤትን አይነገርም። የዜግነት ግዴታ መወጣት ማለት እንዲህ ነው።
"…አስታውሳለሁ ሀገር ቤት እያለሁ ብዙ ጊዜ ቸግሮኝ ያውቃል። ሆኖም ግን አንድም ቀን ከአንድም ሰው ብድር ሳልጠይቅ፣ ችግሬንም ለማንም ሳልናገር ብቻ የሆነ ሰው የሆነ ቀን ከአቅሜ በላይ የሆነ ብር እያሸከመኝ እግዚአብሔርን የበለጠ እያመለኩት እንድኖር አድርጎኛል። በተለይ አንድ ወዳጄን አልረሳውም። እንዴት ሰርፕራይዝ ያደርገኝ እንደነበር እኔ ነኝ የማውቀው። ሰው መዝሙር ቤት አለው፣ ቤት አለው እያለኝ የእንቁላል መግዣ የማጣበት ጊዜያቶች ነበሩ። እናም አንዴ ትዝ ይለኛል ይኸው ወዳጄ እፈልግህሃለሁ ብሎ ይደውልልኛል። እኔ ደግሞ የሌለ ደብሮኛል። አልወጣም አልኩት። ሰፈርህ ነኝ ውጣ አለኝ። ወጣሁ። አንድ በሬ የሚያክል በግ፣ ሁለት ዶሮ፣ ብዙ እንቁላል፣ ቅቤ የቀረው የለም። እንኳን አደረሰህ አለኝ። በደስታ የምገባበት ነው የጠፋኝ። ምን አስጨነቀህ? ስለው እንጃ ውስጤ ብቻ ለዘመዴ ይሄን፣ ይሄን አድርግለት ብሎ አስጨነቀኝ፣ ምክንያቱን እኔም አላውቀው አለኝ።
"…ዛሬ ያ ስሜት ተሰማኝ። እናም ለዚያ ወዳጄ ደወልኩለት። ሰላምታ ተለዋውጠን የባንክ ቁጥርህ እኮ ጠፋብኝ አልኩት። ጮኸ፣ አይ አንተ ፈጣሪ፣ ዘመዴ በጨለመብኝ ሰዓት ነው የደወልክልኝ አለኝ። ብቻ ማርያም ትድረስልህ አለኝ። አበደ። እሰይ ብድሬን መለስኳት ማለት ነው። ብድር በምድር። ሳልሞት ሳይሞት ለችግሬ ጊዜ የደረሰልኝን ደረስኩለት። እኔ የፈነጠዝኩትን ፈንጠዝያ እርሱም ፈንጥዞ አየሁት። ከዚህ በላይ እርካታ ምን አለ? 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
• ቀዳም ሥዑር
"…በተፈጥሮዋ ቀዳሚት ሰንበት የጾም ቀን አይደለችም። በጾም ጊዜ በጾም ወራትም የፍስክ ምግብ ባይበላባትም ባዶ ሆድ አይዋልባትም። በዓመት አንድ ቀን ግን በዐቢይ ጾም የመጨረሻ ሳምንት የጾም ቀን ሆና ትውላለች። በዚህ ምክንያት ቀዳም ሥዑር ወይም የተሻረችዋ ቀዳሚት ትባላለች።
• ለምለም ቅዳሜ
"…የጥፋት ውኃ መጉደሉን ለማየት የተላከችው ርግብ የውኃውን መጉዳል ለማብሰር ይዛ የመጣችውን ለምለም ሳር ቄጤማ ለማስታወስ፣ በዘመነ ሐዲስ የኃጢአት ውኃ በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ መጉደሉን ለማብሠር ለምለም ቅዳሜ ይባላል። "…ከዚያም በኋላ ደግሞ እስከ ሰባት ቀን ቆየ፤ ርግብንም እንደ ገና ከመርከብ ሰደደ። ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች፤ በአፍዋም እነሆ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃ እንደ ቀለለ አወቀ። ዘፍ 8፥ 10-11
• ቅዱስ ቅዳሜ
"…እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና። 2፥ 2-3 በጥንተ ተፈጥሮ ከሥራው ሁሉ ያረፈበት እለተ ቀዳሚት ሰንበት በኋለኛው ዘመን ሰው ሆኖ እኛን ለማዳን የመጣው እግዚአብሔር ወልድ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከመስቀል ሞት በኋላ በመቃብር ያረፈበት እለት ስለሆነ ቅዱሱ ቅዳሜ ይባላል።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
• ቆዩኝማ አንዴ ልጠይቅ…
• በዐማራ ስም ያውም በፋኖ ስም ያለውክልና ብር መሰብሰብ ልክ አይደለም ማለት በዚያ ላይ የሚሰበሰበው ገንዘብ የት ነው የሚገባው? ያለ ውክልና የሚሰበሰብ የዐማራ ገንዘብ ምድር ላይ ለፋኖ የሚደርስ ብር የለም ማለቴ ምኑ ነው የሚያናድደው?
• ጨካኝ አረመኔ ሁላ ሠርተህ ብላ። ለአገልግሎትህ በዶነር ቦክስ፣ በፔይፓል፣ በባንክ እርዱኝ ማለት እያለ፣ ቲክቶክ ሠርቶ መብላት እያለ እንዴት በዐማራ ስም ያለ ዐማራ ፋኖ እውቅና ዳያስጶራው ዐማራ ብሩን ይገፈገፋል ብሎ መጠየቅ እንዲህ ያንጨረጭራል?
• ኦዲተር የማያውቀው በዐማራ ሕዝብ ስም የሚሰበሰብ ዶላርና ዩሮ በአስቸኳይ መቆም አለበት ማለት ምኑ ያበሳጫል። ኧረ GGጂጂግግ ዎች ተረጋጉ። 😂😂
• ያለ ፋኖ እውቅና ገንዘብ መሰብሰብ ትክክል አይደለም። አለቀ። ዋሸሁ እንዴ?
የግል አስተያየቴ ነው።
"…ሚልዮን ዶላሮችን በጭር ቀን ሰብስቦ በሳምንቱ ፈረሰ የተባለው የእስክንድር ነጋው የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር በማግስቱ በአርቲስት አበበ በለው እና በመምህር ሀብታሙ አያሌው አማካኝነት በእስክንድር ነጋ ቡራኬ የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት መቋቋሙ በይፋ ታወጀ። የሕዝባዊ ግንባሩ መሪ የነበሩት ሻለቃ ዳዊትም ሕዝባዊ ግንባሩ ፈርሶ ሕዝባዊ ሠራዊቱ ሲቋቋም በአበበ በለው አማካኝነት በሕዝባዊ ሠራዊቱ ምስረታ ላይ እንዳይገኙ መከልከላቸውን በይፋ ለጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በሚድያ ተናገሩ።
"…በእለቱ አበበ በለውና ሀብታሙ አያሌው 200 ሺ ዶላር በዐማራ ፋኖ ስም መሰብሰባቸው ተነገረ። ለእያንዳንዱም የፋኖ ዕዝ እኩል እኩል ማካፈላቸውም ተነገረ። አሁን ሂሳብ እንሥራ። በሸዋ ሁለት ዕዝ ነው ያለው። የመከታውና የአሰግድ። ለሁለቱም 7500 ዶላር ለእያንዳንዳቸው መስጠታቸው ተነገረ። አሰግድ ቆይቶ ደርሶኛል ቢልም እነ መከታው እስከአሁን ብሩ እንዳልደረሳቸው ነው የሚናገሩት። ምሬ ወዳጆ፣ እነ ነፍሱን ይማረውና ውባንተም አልደረሳቸውም። ቢደርሳቸውስ እንደምንም 100 ሺ ዶላር ቢወጣ ቀሪው ዶላር የት ገባ?
"…ለምሳሌ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባ 05 ሳንቲም እርዳታ የለውም። እንዲያውም ሰሞኑን ነው እኔን ራሱ ደውለው ያናገሩኝ። እንዴት ነው በዐማራ ስም በመከራ በችግሩ ዶላር ሰብሳቢዎች፣ ቴስላ እያሽከረከሩ፣ የሚልዮን ዶላር የተከፈለ ቤት ውስጥ እየኖሩ መሬት ላይ ፋኖ በገንዘብ ሸምተው እየገዙ ትግሉ ፈቀቅ እንዳይል እየጎተቱ የሚኖሩት። ለእነሱ ከርስ መሙላት ሲባል ዐማራው ለፋኖ የማይደርስ ገንዘብ መበዝበዝ አለበት ወይ…?
"…በምድር ላይ ያለው ፋኖ ዕውቅና ያልሰጠው ማኅበርም ሆነ ግለሰብ ዝም ብሎ በዐማራ ስም ገንዘብ መሰብሰብ አለበት ወይ…? እነ GGጂጂግግ ዎችም በጨዋ ደንብ መልሱልኝ።
• ቆይቼ እመለሳለሁ…
በነገራችን ታች…
"…በትናንትናው እለት በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓም ከእስር ተፈትተው ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተሰምቷል።
እየገለጽን፣ በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት አፋጣኝ ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን።
"…በእስር ላይ የቀሩት ሌሎች ምስኪኖች እንደሆኑና እንደ እነ ዶር ቀሲስ ሙልጌታ ያሉትን መነካካት ግን እንዲህ በቀላሉ በዋዛ የሚታለፍ እንዳልሆነ፣ አገዛዙም እነሱን አስሮ ከሚያተርፈው ይልቅ የሚያጣው ነገር እንደሚበዛ ገብቶት በቶሎ እርምጃ መውሰዱ የሚጠበቅ ነበር።
"…የፈለገ ቢሆን፣ ማኅበሩም ላይ የፈለገው ቂም ቢኖረው የአቢይአማካሪው በቀሲስ ዶር ሙሉጌታ ላይ ይጨክናል ተብሎም አይጠበቅም። አምባሳደር ዓለምፀሐይም ብትሆን ሙሌ ታስሮ አርፋ ትተኛለች ተብሎ አይጠበቅም። የሆነው ሆኖ ይሄ ሙከራ ነው። የአንበሳውን ጥርስ አንደ መነቅነቅ ያለ ነገር ነው። ለማንኛውም ማኅበሩ ይሄ የእነ አቢይ ሙከራ በቀጣይ ላሰቡት መብረቃዊ ውድመት ምልክት ስለሆነ ወገብ አጥብቆ ታጥቆ መጠበቁ ይበጃል።
• እብድ ውሻ ከለከፈህ…