zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …ይዞ መምጣቱ ሌላ ትኩሳት መፍጠሩም እየታየ ነው። ሀብታሙ አያሌው በኢየሩስ ተክለጻድቅ በኩል በትናንትናው ዕለት ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን አነጋግራ ስለ ሕዝባዊ ሠራዊቱ እንዲናገር ወትውታ ያሰጠችው ቃል በጎጃም በእነ ዘመነ ካሴ በኩል ቁጣን ቀስቅሷል። ጋዜጠኛ ወግደረስ አቅም ያለው ጋዜጠኛ ሲሆን መረጃ ቴሌቭዥን የዐማራ ክልል ዳይሬክተር አድርጎ የቀጠረው በወር ከፍተኛ ደሞዝ እየተከፈለው በእሳት ውስጥ እያለፈ የሚያገለግል ጀግና ጋዜጠኛ ነበር። ይህን ጋዜጠኛ ነው እንግዲህ ሀብታሙ አያሌው ስንት ብር ጨምሮ ከፍሎ እንደወሰደው ሳይታወቅ በትናንትናው ዕለት ወደ ሚድያ መጥቶ ጎጃምን የሚከፋፍል መረጃ ሲያሰራጭ የታየው። ለዚህም ሓላፊነቱን የሚወስዱት እንደ ተቋም ኢትዮ 360 ሲሆን፣ በግለሰብ ደረጃ ከእነ ዘመነ ካሴ ጋር የግል ፀብ ውስጥ የገባው ሀብታሙ አያሌው እና ወይዘሮ ኢየሩሳሌም ተክለ ጻድቅ ናቸው። ዋጋ ቲከፍላሎ አለ ኦሮሞው አዝማሪ። የጎጃም ዕዝ ተብሎ የተቋቋመው ሠራዊትም ጫካ ውስጥ ሆኖ መግለጫ ሲሰጥ ታይቷል። ቪድዮውም ደርሶኝ አይቼዋለሁ።

"…ሌላው መልካሙ ዜና እኔ አውቶሚክ ቦንብ የሆነውን አጀንዳዬን ካፈነዳሁ በኋላ እነ ዶር አምሳሉ በፋኖ ስም ገንዘብ መሰብሰቡን አቁመዋል። በተለይ አሜሪካማ ቀጥ ነው ያለው። ካናዳም ወፍ የለም። ነገር ግን ሰሞኑን የጀርመኑ ማዕረግ በካናዳ 100 ሺ ዶላር በሠራዊቱ ስም ሰብስበናል ሲል ተደምጧል። በእውነት ተሰብስቦ ከሆነ ለየትኛው ሠራዊት ነው የተሰበሰበው? እንጠይቃለን። በየ እስቴቱ የተቋቋሙ የዶላር ማለቢያ ቻፕተሮች አንዳንዶቹ በይፋ ነው ነው ከእነ ሀብታሙ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ያቆሙት። በፈረንሳይ ሀብታሙ አያሌውን እና ሽመልስ አበራን ጠርተው ገንዘብ ሊሰበስቡ የነበሩት የዐማራ ማኅበራት በፍጥነት ነው የሽሜንና የሀብታሙን ስም አውጥተው ውሳኔ የወሰኑት። ጀርመን ሙኒክ ሁለት ቦታ ተከፍለው እየተወያዩ መሆናቸውን ሰምቻለሁ። በሙኒኩ የእነ ሀብታሙ አያሌው ስብሰባ ላይ ከኢትዮጵያ ጭምር መጥተው ሀብታሙን የሚያገኙት የብአዴን ሰዎች እንዳሉ ነው የሰማሁት። የሸከከኝ ነገር የጀርመኑ አጀንዳ ጎንደር ላይ ትኩረት አድርጎ እንዴት ጎንደሮችን ማበጣበጥ እንደሚቻል ለመምከር ነው የሚሉ መተርጉማን አሉ። ሜጀር ጀነራል ውብአንተን "በእስክንድር ዕዝ ስር አልገባም" ስላለ ብቻ እንዴት እነ ሀብታሙ አያሌው እሱ እኮ ብአዴን ነው ብለው አዋክበው፣ ስሙን አጥፍተው፣ አዋርደው፣ ለሞት እንደደረሰም አይተናል። ውብ አንተ ከተሰዋ በኋላ የአዞ እንባ አፍሳሾቹም እነሱው ሆነው ነው የገኙት። እናም ሀብታሙ አያሌው ከዐማራ ፋኖ የውስጥ ጉዳይ እጁን ካላነሣ ዐማራ ፍዳው ይበረታበታል።

"…በሀብታሙና በእስክንድር ደጋፊዎች እኔ ዘመዴ የምከሰሰውም ዐማራ አይደለም። እሱ የሀረር ቆቱ ነው። ስለዚህ ከቆቱው ዘመዴ ይልቅ ዐማሮቹ እነ ሀብታሙ አያሌው የፈለጉትን ያድርጉን የሚል መሃይም ደናቁርቶች ንግግር እሰማለሁ። ሲጀመር እኔ ዐማራ አይደለሁም። ኦሮሞም ጉራጌም፣ ትግሬም ነኝ አላልኩም። እኔ የሐረርጌ ቆቱ ነኝ አልኩ በቃ። እኔ አለኝ ያልኩትን ከተናገርኩ በኋላ በግድ ወስዶ ነኝ ያላልኩት ብሔር ላይ መለጠፉ ነውር ነው። እኔ ዐማራም አልሁን ለምን ኡዡንቡራዊ አልሆንም ስህተት ነው ያልኩትን መተቸት ማን አባቱ ነው የሚከለክለኝ? ዘመዴ ቆቱ ስለሆነ አያገባውም እነ ሀብታሙ ዐማራ ስለሆኑ ያገባቸዋል ማለት ዘመዴ አያገባህም ብአዴን ግን ዐማራ ስለሆነ ያገባዋል ከማለት በምን ይለያል? ፋኖ ብአዴንን ዐማራ ሆኖ የሚጠርገው ለዐማራ በጠላትነት፣ በባንዳነት፣ በጨቋኝነት ከዘመዴ ይሻለናል ተብሎ ታልፏል እንዴ? እናም የሀብታሙ ዐማራነት ለዐማራ ጥፋት የሚያመጣ ከሆነ ያው ብአዴን ነው። ጧ በል፣ ፈንዳ።

"…ነገሮች እየጠሩ ነው። ጫጫታው እየቀነሰ ነው። የለንደን ፋኖ የመወያያ ግሩፕ ኮተት ልጥፎችን አድሚኖቹ እያጸዱ፣ ባን እያደረጉ ስለሆነ እጅግ ደስ አሰኝተውኛል። የአውሮጳም የመወያያ ግሩፕ የሽመልስ እና የአቶ ወንደሰን ትውከት ማስመለሻ ከመሆን ጸድተው ስላየሁ እጅግ ደስ ብሎኛል። እነ ሀብታሙም የገንዘብ ምንጩ ቀጥ ሲል ማበጣበጣቸውም በዚያው ቀጥ ይላል። የፋኖዎቹ አንድነት በመሬት ላይ እጅግ ደስ ይላል። በቅርቡም ብዙ የምሥራቾችን እንሰማለን። ጎጃሞችም በጥበብ ነገሮችን ይፈቱታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እነ ሀብታሙም ወደ ቀልባቸው ይመለሳሉ፣ ታላቁ እስክንድር ነጋም ግንባር፣ ሠራዊት የሚለውን በይፋ አፍርሶ ወደ አንዱ ዕዝ ስር ተጠቃልሎ በይፋ መግለጫ እንደሚሰጥም እጠብቃለሁ። ያን ጊዜ እነ ግግጂጂትግ ድባቅ ይመታሉ። መንጋውም ጮጋ ይላል ሌባ ሁላ። 

ጎበዝ…

"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!

~ ከ1:00 ሰዓት በኋላ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍተዋለሁ። እስከዚያው ርዕሰ አንቀጹ በጥሞና ይነበብ። ያነበባችሁ ሓሳባችሁን ጽፋችሁ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ስድብ ያስቀስፋል። አመሰግናለሁ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ። 

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ለዘመናት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አይነኬ፣ አይደፈሬ መስለው የከረሙትን፤ እንደ ታቦት፣ እንደ ቤተ መቅደስ የሚፈሩት፣ የሚከበሩትን እኔ ዘመዴ በድፍረት ነክቼአቸዋለሁ። ክንብንባቸውንም ገልጬ ለዓለሙ ሁሉ ገመናቸውን አሳይቻቸዋለሁ። ብዙዎች እንደ ዖዛን የምቀሰፍ፣ ደርቄም የምቀር መስሏቸው መፍራታቸውን ዐውቃለሁ። የማይነኩ ነካ አሁን ገና ዘመዴ ተሳሳተ ብለው የሰጉልኝም ነበሩ። ውለው ሲያድሩ ግን አሸናፊነቴ ሲታወጅ የቀደመ ፍርሃታቸውን ሳይሸሽጉኝ ጽፈውልኛል፣ ገልጸውልኛልም። የሆነው ሁሉ የሆነው ሁሉን ማድረግ በሚችለው በልዑል እግዚአብሔር አጋዥነት ነው። ዘወትር ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ የምላት ወላዲተ አምላክም በምልጃዋ ስላልተለየች ነው። ክብሩን ሁሉ እግዚአብሔር ይውሰድ።

"…እኔ ይሄ ግሩም ከባድ ቅዱስ የሆነው የሳይበሩ ዓለም ትግል የትርፍ ጊዜ ሥራዬ አይደለም። 24/7 365 ቱንም ቀናት ሌት ተቀን፣ ክረምት ከበጋ፣ ዓመት እስከ ዓመት ያለማቋረጥ፣ ያለመሰልቸት እንደ ሰጎኗ ከእንቁላሉ ላይ ዓይኔን ሳላነሣ በትኩረት የምሠራው ሥራ ነው። እንዲያው ሲደብረኝ፣ መሄጃ ሳጣ፣ ዝም ብዬ ቲክቶክ ገብቼ የምቀደድ፣ ቴሌግራም ላይ የምበጠረቅ፣ ያለ መረጃ በትርፍ ጊዜዬ የምዘባርቅም ሰው አይደለሁም። አስሬ ለክቼ አንዴ የምቆርጥ፣ በአቆራረጤም ፍፁም የሆነ የቆረጣ ስልትን የምከተል፣ ልዩ ጥበብንም የምጠቀም ሰው ነኝ። ይሄን ከድሮ ጀምሮ ስከተለው የኖርኩት የትግል መርህ እና መንገድ ነው። ወደፊትም በዚሁ አግባብ ይቀጥላል።

"…ሸከከኝ ስል ቀድሜ ስለማውቀው ነገር ነው እንጂ ስለሚታየኝ ራእይ አይደለም። ቀድሜ የማውቀው ነገር፣ ደግሞም ሁሉም ቦታ፣ በሁሉም ስፍራ ግሩም ግሩም የሆኑ ረቂቃን ወፎች ስላሉኝም ጭምር ነው። ሌላ ምንም የተለየ ተአምር የለውም። ለአንድ ነገር ትኩረት ሰጥተህ፣ ጊዜ ሰጥተህ፣ መዳረሻ ግብ አስቀምጠህ፣ አስሬ ለክተህ አንደዜ የመቁረጥ ልማድን ካዳበርክ በኋላ የምትደርስበት ራሱን የቻለ ተፈጥሮአዊ ማእረግ አለ። እኔ አሁን እዚያ ማእረግ ላይ ደርሻለሁ ብል ማጋነን አይሆንብኝም። በጥባጭ የት እንዳለ ከልምድ ዐውቄአለሁ። በጥባጩ ወይም በጥባጮቹ እንዴት እንደሚዠለጡም ከልምድ ዐውቄአለሁ። ከዚያ እንዴት አደብ እንደሚገዙም እንዲሁ ከልምድ ዐውቄአለሁ። ስለዚህ አሸናፊ ነኝ።

"…አሁን በተነሣው የግንባሩ፣ የሠራዊቱና የግንቦቴዎች ጉዳይ ብዙ አስቤበት፣ ከራሴው ጋር ብዙ መክሬበት፣ ስብሰባ፣ ጉባኤ ተቀምጬበት፣ በጸሎት የሚያግዙኝ በጸሎት እንዲያግዙኝ አስደርጌ የገባሁበት ነው። ሦስቱም ልምድ ያላቸው፣ ገንዘብ ያላቸው፣ በገንዘባቸው ተሳዳቢ፣ አሸማቃቂ፣ አሳቃቂ፣ አስፈራሪ፣ አስዶካኪ ግሪሳ ሠራዊት ያላቸው በጥፋት፣ በተንኮል ጥርሳቸውን የነቀሉ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር፣ የሰውም ርህራሄ የሌላቸው፣ ሳዲስቶች፣ ማታለልን እንደ ሙያ የሚቆጥሩ፣ ከስማቸው ፊት ያለውን ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ አቶ፣ ወሮ፣ ጋዜጠኛ፣ ኢንጂነር ወዘተ የሚለውን ስም እንደ የቡዳ መድኃኒት፣ የመብረቅ መከላከያ አድርገው የሚጠቀሙ፣ ሁለት ጠጉር ያበቀሉ፣ መላጣ፣ በምርኩዝ ሁላ የሚሄዱ ስለሆነ እነሱን መንካት እንደሚያስቀስፍ ነገር ስለሚቆጠር ማንም የማይደፍራቸውም ነበሩ እስከ ዛሬ። እኔ ዘመዴ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ ደፈርኳቸው። አፈራረስኳቸውም።

"…አሁን ጫጫታው ቀንሷል። ዋነኛው የገንዘብ ምንጫቸውም ደርቋል። የጥፋት የግኑኝነት መስመራቸውም ተቋርጧል። ድንጋጤ ኀዘን ወርሷቸዋል። ማንንም ማታለል፣ መቀፈል እንዳይችሉ ተደርገው ተደቁሰዋል። ቁጥራቸው እንደ ቀይ ቀበሮ ቀንሷል። እንደ ምኒልክ ድኩላ በስንት ጊዜ አንዴ ብቅ ብለው የሚታዩም ሆነዋል። የቀሩትም እንዲሁ ይደመሰሳሉ። ብቻ ከእኔ የሚጠበቀው እስክንድር ነጋን እየጠበቅኩ በእሱ ዙሪያ የከበቡትን ጆፌ አሞሮች፣ የጥንብ አንሣ ፖለቲከኞች ደጋግሜ መውቀጥ፣ መቀጥቀጥ ነው። ደጋግሜ መውገርም ነው። አሣር ፍዳቸውንም ማሳየት ነው። በመረጃና በማስረጃ ድራሽ አባታቸውን ማጥፋት ነው። አለቀ።

"…እኔ ሁላችሁም እንድታውቁልኝ የምፈልገው የምሠራው ሥራ በምድር ላይ ያሉት ታጋዮች፣ የፋኖ መሪዎች የነገሩኝን፣ ያዘዙኝን ብቻ ነው። ሀብታሙ አያሌውን ከትግላችን ውስጥ እጁን አስወጡልን ያሉት የፋኖ አለቆቹ ናቸው። በጠበጠን፣ አወከን፣ ለያየን፣ ሰደበን፣ አዋረደን፣ ከፋፈለን፣ ሊበትነን ነው፣ እንደ አለቃችን አክት ያደርጋል፣ አልታዘዝ ስንለው በሚዲያ ባለው ተደማጭነት ስማችንን ያጠፋዋል። ፈላጭ ቆራጭ ልሁን ባይ ነው። የአንዳችንን ትግል ወስዶ ሌላው እየሰጠ ይከፋፍለናል። አንተ የምልህን ካልሰማህ ብአዴን ነህ ብዬ አሳየህሃለሁ ይለናል። ከአበበ በለው ጋር ሆነው ማኒፌስቶ አዘጋጅተው በዚህ ተዳደሩ፣ እስክንድርን መሪ አርጋችሁ ምሩጡ ይለናል። እረፍ ስንለው መዓቱን ያወርድብናል። እባካችሁ ይሄን ሰው አንድ ነገር አድርጋችሁ ከትግላችን አስወጡልን። ይሄ ነበር የፋኖ አመራሮች ዋነኛ ጩኸት። የፈለገ ሰው ደውሎ ያጣራ።

"…እናም እኔም ይሄን የአርበኞች ጩኸት፣ ጥሪ ሰምቼ ነው የመጣሁት። ዋነኛው ችግሬም ሀብታሙም ሆነ አበበ በለው የተጠለሉት በእስክንድር ነጋ ስር መሆኑ ነው። እነሱ ሲነኩ እስክንድርም የግድ መነካቱ አይቀርም። እስክንድር ሲነካ ደግሞ የሀብታሙ አያሌው፣ የአበበ በለው፣ እንደ ተቋም የአዲስ ድምጽ እና የኢትዮ 360 ደጋፊዎች ግንባር ፈጥረው መንጫጫታቸው አይቀርም። የሚጠበቅም ነው። እነሱ ሲንጫጩ ደግሞ መንጋው፣ ጎጋው፣ ግራና ቀኝ የማያገናዝበው፣ ነገሩ እስኪጠራ ከዳር ቆሜ ልታዘብ የማይለው፣ አእምሮ ስልቡ፣ ስሜታዊው ግሪሳም ወጀቡን ተቀላቅሎ እንደሚመጣም የታወቀ ነው። የሚጠበቅም ነው። እሱን በአግባቡ ማኔጅ ማድረግ ነው ከእኔ የሚጠበቀው።

"…ይሄም ብቻ አይደለም እኔ እዚህ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት የመሰለ ትግል ውስጥ ስገባ ቀን የሚጠብቁልኝ፣ ጊዜ የሚጠብቁልኝ፣ መቼና እንዴት ባገኘነው የሚሉ ፖለቲካ ወለዶቹ፣ የወያኔ ጥፍጥፍ ቅማንቴና አገው ሸንጎው ስታዲየም ሙሉውን መንጋው ሁላ ግር ብሎ የሚመጣበት ነው። አታዩም ትግሬዋ ወያኔ ሳትቀር ዘመዴን አገኘሁት ብላ ለእስክንድር ደጋፊ ሆና እኔን ተቃዋሚ መስላ ዐማሮች ይሄን ልጅ ከትግላችሁ አርቁት፣ አስወጡት እስከማለት ስትደርስ። ትግሬ ብቻ አይደለም ይሄን አጋጣሚ ካገኘንማ እኛም አለን በማለት ኦነግ፣ የዐማራው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ኦፌኮና ብልፅግና በሙሉ ግር ብሎ ስታዲየሙን ሞልቶ ይጮህብኛል። በዚህ ላይ አንዳንድ የወሎ የወሀቢይ እስላም ዐማሮች፣ ሙሉ የኦሮሞ ወሀቢይ እስላሞች፣ የጎጃም ቅባት ሃይማኖቶች፣ የዓለም ብርሃኖች፣ የደቡብ እና የወለጋ ጴንጤዎች፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለማፍረስ የባከኑት የተሃድሶ ቡድን አባላት፣ የመምህር ግርማ ካዳሚዎች በሙሉ የዘመቻው አካል ነው የሚሆኑት። በዚህ ግርግር ነው እንግዲህ ዘመዴን መጣያው አሁን ነው ብለው እነ ጂጂግግትግ ሁሉ አንድ ላይ ቆመው እንውረድበት ብለው የሚመጡት።

"…የእኔ ተግባር እንደ ማር ቆራጭ ሆኖ መዘጋጀት ነው። በጭስ ለሚሸሹት ጭሱን እየለቀቅኩባቸው፣ ሌላውን ጓንትና መሸፈኛ አጥልቄ በጥንቃቄ ማሩን ብቻ ቆርጬ ወደ ቦታዬ መመለስ ነው። ለእዚህ ዓይነቱ ትግል ልምድ ስላለኝ ምርጥ የቀዶ ጥገና ሃኪምም ነኝ። መርፌ፣ መቀስ፣ ፋሻ፣ ምላጭ በቀደድኩት ሆድ ውስጥ የማልረሳ፣ ጉበት ላክም ብዬ ጣፊያ ቆርጬ የማልወጣ፣ ለምጥ የመጣችውን የሬሳ ማድረቂያ፣ ለግርዛት የመጣውን የምጥ መርፌ የማልወጋ፣ ታርጌቴን፣ ኢላማዬን ሳልስት ቱ ዘፖይንት እንዲል ሱሬ የነገሩን ብልት ህብለ ሰረሰሩን…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትንሣኤ ሳምንት ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ትባላለች፦

"…ሴቶች የሚታወሱበት፣ የሚዘከሩበት ዕለት ነው። ዓለም ማርች 8 ብሎ ሴትን ሁሉ መታሰቢያ ቀን ሰጥቶ እንደሚያከብር ያለ ሳይሆን በዕለተ ትንሣኤ ሌሊቱን ወደ ጌታ መቃብር ሲመላለሱ ያደሩ ሴቶች የድካማቸውና ጌታን የመሻታቸው ዋጋ መታሰቢያቸው ይሁን ብላ ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀኑን የሰየመችው።

"…ጌታ ከከሚከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ ያህል ሕዝብ መሃከል የመረጠው 12 ሐዋርያት፣ 72 አርድዕት፣ 36 ቅዱሳት አንስት መርጦ ነበር። ከተመረጡት 120 ቤተሰብ መካከል 36 ቱ ሴቶች ናቸው። ስማቸውና የመታሰቢያ ወርሐዊ በዓላቸውም በቤተ ክርስቲያን ይከበራል። በተለይ የትንሣኤ ሌሊት ትንሣኤውን ሽተው ወደ መቃብሩ ሲመላለሱ ቅዱሳን መላእክትን ያዩበት የተደነቁበትና በመቃብሩ ያለውን መዓዛ ትንሣኤ አሽትተው የተመሰጡበት ዕለት ስለሆነ እንዲሁም ድካማቸው ከንቱ እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነው።

"…አንድም ጌታችን አስቀድሞ ለእነርሱ ለሴቶቹ ታይቶ ትንሣኤውን ያረጋገጠበት ስለሆነ እነርሱ ከአምላክነቱ ግርማ የተነሳ ረቡኒ ብለው ያደነቁበት ዕለት መታሰቢያ ስለሆነ። አንድም በጠቅላላው ከሕማማቱ እስከ ትንሣኤው ብዙ የእንባ መሥዋዕት ያቀረቡ እናቶች የሚታሰቡበት ስለሆነ አንስት አንከራ ተብሎም ይጠራል የዛሬው ቅዳሜ።

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የገዳይና ሟች ውይይት፦

• ገዳዬ ጋሽ ወርቅነህ ተስፋዬ፦ በ +14707670531 ስልክ ቁጥሩ ደውሎ ነው ቀጠሮ የሚይዝልኝ። አንተ ቆሻሻ ሰላም ብትገዛ ይሻላል እሰከነቤተሰቡ ነው የማጠፋሀ። ብታርፋ ይሻላል። አንተ የሀረር  ጅብ።

~ ሟች እኔ ዘመድኩን በቀለ፦ መልካም ጋሽ ወርቅነህ ተስፋዬ። መቼ ነው እኔንም ቤተሰቤንም የምታጠፋው። ተዘጋጅተን እንጠብቅህ ወይስ ድንገት እንደ ክርስቶስ ነው የምትመጣው? እስቲ ይሄንኑ ለሕዝቡ ሁሉ ከነ ስልክህና ስምህ ይፋ አደርገዋለሁ።

• ገዳዬ ጋሽ ወርቅነህ ተስፋዬ፦ በጣም ጥሩ አንተ ከብት።

~ ሟች እኔ ዘመድኩን በቀለ፦ "…ናልኝ እንጂ ወርቄ። ና ጋሽ ወርቅነህ። ወይስ አንተ ከደመህ እኔ ቤተሰቦቼን ይዤ ልምጣና ታጠፋን ይሆን? ላቅልል ብዬ ነው። 😁

• ገዳዬ ጋሽ ወርቅነህ ተስፋዬ፦ በቅርብ ቀን አንተ ደብተራ።

• ሟች እኔ ዘመድኩን በቀለ፦"…እጠብቃለሁ። በማለት ተለያየን እላችኋለሁ። ቆይቼ እመለሳለሁ። አቶ ወርቅዬ ግን ማናቸው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆…ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…አሁን እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ምን ቀራቸው? ምንም ምንም አልቀራቸውም። የእስክንድር የአክስት ልጅ ከኬኒያ ወደ ኡጋንዳ የሄደውና በጫት ጭማቂ የሚንቀሳቀሰው የትልቅ ትንሽ የጋሻ ሚዲያ ባለቤትም አሁን ሰሞኑን ሸከከኝ ያልኳችሁን የጎጃምን ካርድ መዝዞ ከመንዘባዘቡ በቀር ምንም ሊያመጡ አልቻሉም። በግንባሩ ገንዘብ ያዥ በሕይወት በላቸው አማካኝነት እነ ማርሸት፣ ዝናቡ ላይ የተቀነባበረው የእነ GGጂጂግግ አጀንዳ ሰሚ አጥቶ ነው የከሸፈው። አሁንም በተመስገን ጥሩነህ ዘመድ በካፒቴን ማስረሻ በኩል አዲስ አጀንዳ ብለው ይዘው የመጡት በሙሉ ፉርሽ ይሆናል። መና ይቀራል። ሰሞኑን እስክንድር ነጋም የምሥራች ያሰማናል ብለን እንጠብቃለን። የሸዋ ጉዳይ በድል ሲጠናቀቅ የእስክንድር ግንባርና ሠራዊት ነገርም አብሮ ነው መቋጫ የሚያገኘው። እስክንድርም ከሸዋዎች ቃል እንደማይወጣ ተስፋ አለኝ። የሚከስሩት እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ብቻ ናቸው።

"…ሀብታሙ አያሌውም ልክ ይገባል። መስመርም ይይዛል። እጁን ከፋኖዎች ውስጥ ሳይወድ በግዱ ይሰበስባል። አበበ በለውም እንደዚያው። ሌሎቹም እንደዚያው። መተቸት፣ አቅጣጫ መጠቆም የአባት ነው። ከዚያ በዘለለ ግን የአንዱን ድል ለሌላው ሰጥቶ መዘገብ ከዚህ በኋላ አይሞከርም። ደውሎ የፋኖ አመራሮችን ማስፈራራት፣ ከእስክንድር ስር ካልሆናችሁ ስማችሁን ነው የምናጠፋው እያሉ ማስፈራራት፣ እንደ ባለጌ አግድም አደግ በቆሻሻና በወረዱ የስድብ ቃላት የፋኖ አመራሮችን መስደብ፣ በገንዘብ ማስኮብለል ወዘተ አይሠራም። ይሄም በቅርቡ መቋጫ ያገኛል።

"…ምድረ ኮተት፣ አውርቶ አደር፣ ተሳዳቢ መንጋ ሁላ ሥርዓቱን ሳይወድ በግዱ ይይዛል። በእስክንድር ነጋ ጀርባ ታዝለው ወደ ዐማራ ፋኖ ትግል ዘው ብለው ለመግባት አዳዲስ ከረባትና ሱፍ አዘጋጅተው የነበሩ ድልብ፣ አቀንጭራ የዚያ ዘመን ሰዎችም አደብ ይገዛሉ። ይሄኛው ትውልድ እሳት የላሰ ትውልድ ነው። ደፋር ጠያቂም ነው። በኢህአፓ፣ በደርግ፣ በወያኔ፣ በግንቦት ሰባት እና አሁን በኢዜማ ተከስተው የዐማራን ትግል ቀርጥፈው ሲበሉ የነበሩ ሾተላዮችን የማይታገስ ትውልድ ተፈጥሯል። አሁን በዐማራ ትግል ፊት ለፊትም ሆነ ከጀርባ ነገር መጎንጎን አይቻልም። አይሞከረምም። የነቃ ጠያቂ የዐማራ ትውልድ ነው የተፈጠረው።

"…ዓሥራት ቲቪን ላቋቁም ብለህ ከዐማራው ላይ ዶላር ገፈህ ያስፈረስክ፣ ኢሣት የተባለ ዐማራን እሳት ሆኖ ላስፈጀ ገዳይ ድርጅት በኢትዮጵያዊነት ስታስግጠው የከረምክ። ለዐብን ተብሎ የተዋጣ ገንዘብ ለራስህ ቀርጥፈህ በልተህ ስታበቃ አሁንም ጎንደርን ለሁለት ለመክፈል የዓይናርህን በውኃ ሳታብስ ዓይንህን በጨው ታጥበህ የተደነሰርክ፣ በግንባሩ ስም፣ በትሪፕል ኤ፣ በዋፋ፣ በወፏ ስም ወዘተ ዐማራን ኪሱን ስታራቁት የኖርክ ፕሮፌሽናል ሌባ ሁላ አሁን ታርፋታለህ። ዶክተር ሁን ኢንጂነር፣ ፕሮፌሰር ሁን ወዛደር፣ ቄስ ሁን ሼክ፣ ኡስታዝ ሁን ሰባኪ መምህር ለደንታህ ነው። የማይነካ፣ የማይተች ታቦት የመሰለ ስም ያለው የለም። ሁልሽም ትዠለጫለሽ። አለቀ። ጋዜጠኛ ነኝ ብለህ ሚድያ ይዘህ ብትለፋደድ፣ እሱ ከባድ ነው እንዴት እንናገረዋለን የሚል ትውልድ አሁን የለም። የኅልውና ትግል ነው ወዳጄ። ሚዲያ ላይ ወጥተህ ብትለፈልፍ በሚዲያ መልስ እሰጥሃለሁ። በቲክቶክ ብትመጣ በቲክቶክ እቀነድብህሃለሁ። አለቀ።

"…ፈረንሳዮች ግን ክበሩልኝ ነገሩ ገብቷችሁ ሀብታሙ አያሌውን እና ሽመልስ አበራ ጆሮን ለገንዘብ ማሰባሰቡ ጠርታችሁ ስታበቁ በሁለቱ ላይ ጥያቄ ሲነሣ ተሰባስባችሁ ሁለቱም እንዳይገኙ መወሰናችሁ ያስመሰግናችኋል። ጀርመን በተለይ ብአዴኖች ሁላ ከኢትዮጵያ መጥተው እንደሚሳተፉ ሰምቻለሁ። በተለይ በጎንደር መሃል ቅርቃር በመክተት አሁንም ጎንደርን ለመበጣጠስ፣ ወሎንም፣ ጎጃምንም፣ ሸዋንም ለመበታተን ፕሮጀክት ተቀርጾ እየተደከመ መሆኑን ተጨባጭ መረጃዎች እየተሰሙ ነው። ነገር ግን ይሞከራል እንጂ አይሳካም። እናም በአውሮጳ ያላችሁ የዐማራ ማኅበራት ብትታገሱ ነው የሚሻለው። እኔን ያናገረኝ አንዱ የማኅበር መሪ ሀብታሙ አያሌው የሚጠላቸውን እነ አሰግድን እየደገፈ እነ መከታውን እንደሚጠላ ነው የታዘብኩት። የተምታታ ነገር። የዐማራ ማኅበር ነኝ ብሎ አንዱን ፋኖ ወድዶ ሌላውን ፋኖ መጥላት ማለት ይሄ ራሱ ብልግና ነው። አስቡበት።

"…የእኔ ዓላማ ግልጽ ነው። የዐማራ ፋኖን ትግል ለዐማራ ፋኖ ተዉለት። የዐማራ ፋኖን ትግል በገንዘብ ለመርዳት ከተፈለገም የዐማራ ፋኖዎች በሚሰጡት ውክልና እና ሓላፊነት ብቻ አክብሮ መመራት ነው። ይኸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ወደፊት ያሰብኩት አንድ ነገርም አለ። እሱን ነገርም በሸዋ ዐማሮች እጀምራለሁ። ይኸውም ምንድነው የሸዋ ዳያስጶራ በተለይ ተደማጭ የሶሻል ሚዲያ አንቀሳቃሾች የሆኑ የሁለቱም ደጋፊዎችን በጋራ አወያይቼ ልዩነታቸውን አጥብበው በአንድ እንዲሰለፉ ለማድረግ ፈልጌአለሁ። ሁለቱንም አካላት አውርቼ ፈቃደኞች ናቸው። በዝግ ቤት ተነጣጥሰው፣ ተገማግመው፣ ስህተታቸውን ተራርመው አንድ ላይ እንዲሰለፉ ለማድረግ መንገድ ጀምሬአለሁ። ምድር ላይ ያሉት አንድ እንደሆኑት ሁሉ በአየር ላይ ያሉትም አንድ መሆን አለባቸው። ከዚያ ወደ ጎጃም፣ ወሎ፣ ጎንደርም እንዘልቃለን። ሌባ ሌባው ግን እንደ አጋንንት ራሱ ጩሆ ይወጣል። ጤነኛው መንጋ ግን በሰላም በጋጣው ይኖራል።

"…ይሄን ሁሉ በራስ ተነሳሽነት ከፈጸምኩ በኋላ፤ የዐማሮችን ጉዳይ ለዐማሮች ትቼ እኔ ወደ ዐውደ ምህረቴ እመለሳለሁ። እስከዚያው ግን ፈንዳ ጧ በል እንጂ ንቅንቅ የለም። ስትሳደብ፣ ስታቅራራ ብትውል አልሰማህም። ነገርኩህ የማይተች አንድም ሰው የለም። ሁሉም ይተቻል። የዐማራ ትግል ንፁሕ ወርቅ ነው። መጀመሪያ ጭቃ የሆነ ወርቅ። እሳት ውስጥ ገብቶ ተቃጥሎ የወጣ ወርቅ ነው የዐማራ ፋኖ ትግል። እድፋም፣ ኮተታም፣ ነውረኛ ለዐማራ ትግል አስፈላጊ አይደለም። ሌባ፣ የደም ነጋዴ፣ ውሸታም እንዲሁ አስፈላጊ አይደለም። ምንም ብትለኝ አልሰማህም። እኔ የማዳምጠው ፈጣሪዬን እና በምድር ከስቃዩ ስፍራ ላይ ያሉትን አባቶቼን ብቻ ነው። ድሮም ቡሆን ቲክቶከራም ቲክቶከራም ነው። ምን አባቱ ያመጣል? ስድብ እንደሆነ ቀለቤ ነው። ልብሴ ነው። ስትሰድበኝ ውለህ ብታድር አይሞቀኝ አይበርደኝ። ጭራሽ ብሎ ብሎ ስታሊን እኔን ከዐማራ ፋኖ ትግል ይውጣ ይበለኝ? እሱስ እሺ እነ ጂጂግግ ግን ምን ነክቷቸው ነው ስታሊን ልክ ነው ዘመድኩን የምትባል ሰይጣን የሰይጣን ቁራጭ ከዐማራ ትግል ውጣልን የሚሉት። እኔ ኬሬዳሽ። ይኸው ነው።

ጎበዝ…

"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።

• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ። 

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ያመሰግን ዘንድ፣ ትንሣኤውንም ያውጅ ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ ሰው ሞልቷል። በምስጋና መሃል ኮተት ሓሳብ የሚደነቅሩ ባን ይደረጋሉ ብዬ ቃል በገባሁላችሁ መሠረት ወደ 33 የሚጠጉ በምስጋና መሃል የራሳቸውን ኮተት ይዘው መጥተው ሊዘበዝቡ የሞከሩ ሰዎች ተቀስፈዋል። አለቀ። ይህ የቤቴ ህግ ነው። በምስጋና ሰዓት ሌላ ወሬ መዘብዘብ ያስቀስፋል።

"…ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ተለመደው ሰናፍጭ ወደ በዛበት፣ ቃሪያ በሚጥሚጣ ወደ ሆነው ርዕሰ አንቀጻችን ነው። በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችንም ልክ እንደ ትናንቱ ብቻዬን አንድም ምድራዊ አጋዥ፣ ተደርቦ የሚሟገት፣ የሚከራከርልኝ ሳያስፈልገኝ ሓሳቤን በአደባባይ ለሽያጭ አቀርባለሁ። ሓሳቤን የወደደ ይገዛዋል፣ ይሸምተዋል። ሓሳቤን ያልወደደው ይነካዋል። ሱቄ በራፍ ላይ ቆሞ ስድስድ መጫወት ከባድ የመቀሰፍ አደጋም ያመጣበታል። ተናግሬአለሁ።

"…ሰሞኑን ባነሣሁት ሓሳብ፣ በተፈጠረ ፍትጊያ ይሄ ነው ተብሎ የማይገለጽ ዝብርቅርቅ ያለ ነገር ወደ መስተካከል መጥቷል። ጫጫታውም እየበረደ ነው። የሸከኩኝ ነገሮች ሁሉ ፍጥጥ ብለው እየወጡ ነው። በጎጃም የፈራሁት እና ስጽፈው የቀወጡ ሁሉ ዛሬ ሲንበጫበጩ ሳይ በሳቅ ነው የምፈርሰው። ግራቀኝ የማያይ፣ ነገር የማይመረምር፣ ቲክቶክ ስላገኘ ብቻ የሚበጠረቅ ሰው አግኝተው የሚጦዙ ሰዎች ለእኔ መዝናኛዬ ናቸው። ታስቁኛለሽ ነገር ማለት ነው።

"…ወዳጄ ብቻህንም ብትቆም ከመንጋው ጋር ልክ ባልሆነ ልዩነት አንድ ለመምሰል አትላላጥ። አሁን ይሄ ሁላ ጥቁር ዣንጥላ ውስጥ አንድ ቀይ ዣንጥላ መኖሩ በራሱ ውበት አይደል እንዴ? ልዩ እኮ ነው። የሌለ ውብ እኮ ነው። እኔ ዘመዴ ማለት ቀዩ ዣንጥላ ማለት ነኝ። አላምርም…? 🎷🎷🎷😂

"…ከነከስኩ ሳላደማ አልመለስ አይደል? እናም ፒፕሉን ላንጫጫ ልመጣ ነኝ። ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አሁን ለአስተያየት ክፍት ነው። ከፀያፍ ስድብ በቀር አስተያየት መስጠት መብት ነው። የተቃውሞም ቢሆን የተፈቀደ ነው። መሳደብ ግን እፉ ነው። ያስቀስፋል። አስተያየት ያልሰጠ ወላጅ ያመጣል ስላላልኩ ካልገባህ ዝም በል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እንደ መልስ ያለ ነው።

"…ዝርዝሩን👇 ከታች ጽፌዋለሁ። ከ30 ደቂቃ በኋላ የአስተያየት መስጫ ሳጥኑን እከፍትላችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሟች ከመሞቱ በፊት ከመልአከ ሞት ጋር ይተሻሽ ነበር አሉ። ከአስብቶ አራጅ፣ ከሰር ውስጥ እባብ፣ ከሸማቂ ጓደኛ ከቁማርተኛ ወዳጅ ዘመድም ይሰውራችሁ።

• የእነ ዶር አምባቸውን፣ ጄነራል ሰዓረ መኮንንም ነፍስ ይማር…!

• አሜን… 🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍

ጎበዝ…

"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።

• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ። 

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም… የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። በመቀጠል ወደ ርዕሰ አንቀጻችን እንሄዳለን።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን በወልቃይት ዙሪያ እነ ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉት፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩት እነ ግንቦቴ እና ግንባሮችን የሚለበልብ፣ ጆፌ አሞሮቹንን እና የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞችን የሚያቃጥል ርዕሰ አንቀጽ ነው።

"…ይህ በእኔ በድርጅቱ ዘመዴ፣ በወፍ አርግፍ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ የተጻፈን ርዕሰ አንቀጽ በያላችሁበት ሆናችሁ ለማንበብ፣ አንብባችሁም በጨዋ ደንብ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ዛሬ የእረፍት ቀኔም አይደል…? …እናም የስደት ሀገር ጓደኞቼ ወዳለሁበት ከተማ መጥተው በራየን ወንዝ ዳርዳር ወክም ምግብም ስንበላ አምሽተን ገና አሁን ወደ ቤቴ መመለሴ ነው። የመንደራችን ኮማቾች እንዴት እንዴት እንደቆዩም ገና አረፍ ብዬ እጎበኘዋለሁ።

• ሌላው ግን ሌባ ነው። የነገሰው ይበለን። አሜን ሃሌሉያ…🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አሁን ደግሞ የእናንተ ተራ ነው። በርዕሰ አንቀጹ ላይ እኔ ላነሣሁት ሓሳብ በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ መልክ ሓሳባችሁን የመግለጽ መብታችሁን ተጠቅማችሁ በጨዋ ደንብ መተንፈስ ትችላላችሁ። በጨዋ ደንብ። ተናግሬአለሁ።

"…እነ GGጂጂግግ እና TGቲጂትግም በጨዋ ደንብ ነው ሓሳብ የሚሰጠው እሺ። ዘመኑ 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። የኢህአፓና የደርግ፣ የወያኔና የግንቦቴ፣ የግንባርም የስድብ፣ የነውር መንፈስ፣ እንደ አብዮቱ ጊዜ ጉልቤ ጉልቤ ልጫወት ብሎ ሄጵ ብሎ ነገር ማለት አይቻልም።

• 1…2…3… ጀምሩ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ርዕሰ አንቀጽ"

"…ሰሞኑን እያነሣሁ ያለሁት እና የጀመርኩት አጀንዳ ለይቶ የሚያንዘረዝራቸው እና የሚያዝረከርካቸው አካላት እየበዙ ሲመጡ ሳይ ከሚጠበቀው በላይ እየደነቀኝ፣ እየገረመኝም ነው። የእኔ ጥያቄ አጭርና ግልፅ ነበር። "ከእንግዲህ ወዲህ መሬት ላይ ከሚገኙት ከዐማራ ወኪሎች ፈቃድና ይሁንታ ያላገኘ ማንኛውም ማኅበርም ሆነ ግለሰብ በዐማራ ሕዝብ ስም ገንዘብ መሰብሰብ መቆም፣ መከልከል አለበት ነው ያልኩት?" ይህን ጤነኛ ጥያቄ እውነት ነው ብሎ እንደመቀበል የዐማራን ትግል መተዳደሪያቸው ያደረጉ አካላት ግን በያሉበት "ጓ" እያሉ ነው። እኔ ግን አልፋታቸውም።

"…ዐማራው አሁን አዘናጊ አጀንዳዎች ላይ ቆቅ ሆኗል። አብሮ አይነጉድም። ስለ ቀይ ባህር ሲወራ፣ ስለ አሰብ፣ ስለ ወደብ፣ ስለ ኤርትራና ሶማሊያ ሲወራ ለደንታህ ነው ብሎ የማዘናጊያ አጀንዳውን ቀርጥፈህ ብላው ብሎ እርሱ አራት ኪሎን ታርጌት አድርጎ እየወቀጠው ነው። ከሁሉ ከሁሉ እንደ ህወሓት አሁን በዐማራው የከሰረ ቡድን የለም። ይሄ አሁን ከሱዳን ጋር ተያይዞ የሚወራው ወሬ ራሱ ዐማራን ማዘናጊያ ነው ባይ ነኝ። ልብ ብላችሁ አስተውላችሁ ከሆነ ህወሓት ዐማራን የምትወርበት ዋነኛ ስልቷ ዐማራን ልትወር ሳምንት እስኪቀራት ድረስ ልትወር ወዳሰበችበት የዐማራ ከተማ ሰርጎ ገብ በስደተኛ መልክ ቀድማ ታስገባለች። ከዚያ ከኤርትራ ጋር ልዋጋነው ብላ በየሚዲያዋ በስፋት ታስወራለች። ዐማራ የዚያን ግዜ እባብነቷን ይረሳና ይዘናጋል። ከዚያ ባላሰበበት ድንገት በሰርጎ ገቧ በተለያየ አቅጣጫ የጥይት እሩምታ ታስተኩስና ከዚያ ከተማ ውስጥ የተዘጋጁ የህወሓት ሰዎች ህወሓት መጣችብን ብለው ከተማዋን ጥለው እንዲሸሹ ታስደርጋለች። ያንጊዜ ዐማራውም የሚሰደደው ወገን ይመስላቸው እና ትግሬን ተከትሎ ከተማዋን ለቆ ይወጣል። ከዚያ ጥግ ይዞ የነበረው የህወሓት ወታደር እንደ ጀግና ተሰልፎ ወደ ከተማዎች ይገባል። እየሆነ ያለው ይሄው ነው።

"…ስለዚህ አሁንም ህወሓት ለሱዳን ለጀነራል እንትና ረዳች ወታደሮቿም ተሰልፈው ተዋጉ የሚለውም በጥርጣሪ ነው መታየት ያለበት። ከሆነም ጡሩ ነው የሚጠዛጠዙት በሱዳን የሰፈረው አራጁ የትግሬ ሳምሪ ቡድን እና ራሱ ሱዳኖች ናቸው። ነገር ግን ዐማራ ይሄ ሲወራ ማድረግ አለበት ብዬ የማምነው በትግራይ በኩል የበለጠ ኃይሉን ማጠናከር እና የወያኔን እንቅስቃሴ መቆጣጠር አለበት እላለሁ። ምክንያቱም ከሦስት ቀን በኋላ በወልቃይት ወይ በሆነ ቦታ ዐማራን አዘናግቼዋለሁ ብላ ልትወር ልትመጣ ትችላለች። ዐማራው ከሱዳንም ከመቀሌም የሚመጣውን ጠብቆ መቀንደሽ አለበት ባይ ነኝ።

"…ዐማራው ስስ ልቡን አሳምረው ነው የሚያወረቁት። በፕሮፓጋንዳ እሳት የላሱ ናቸው ትግሬዎቹ። ኦሮሞና ዐማሮች በዚህ በኩል ደካማ ናቸው። ከዐማራው ይልቅ አሁን አሁን ደግሞ በፕሮፓጋንዳው ኦሮሞዎቹ ተፍተፍ ማለት ጀምረዋል። ይሄን ለማወቅ OMN ን መከታተል በቂ ነው። OMN የተቃዋሚ ጣቢያ ነው። ነገር ግን አቢይን የሚቃወሙ መስለው ለአቢይ አጀንዳ ነው የሚሰጡት። አዲስ አበባ ፒያሳ ከመፍረሱ በፊት OMN ላይ ነው የተቦካው፣ የተጋገረው። ቴሌ፣ አየር መንገድ፣ ንግድ ባንክ፣ በፌደራልም ሆነ በአዲስ አበባ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኛው ዐማራ ይበዛዋል ብሎ ሲከካ፣ ሲቦካ የነበረው OMN ላይ ነው። ከዚያ ነው አዳነች እና አቢይ ወስደው የሚጋግሩት። ይናበባሉ።

"…ዐማራው ገና አልተግባባም። ወደ መግባባት እየሄደ ነው እንጂ ገና ነው። የዐማራውን የፕሮፓጋንዳ፣ የገንዘብ ምንጭ የተቆጣጠሩት በሙሉ ፀረ ዐማራ የዐማራ ስም ያላቸው ናቸው። ኦሮሞዎችም፣ ትግሬና ጉራጌዎች ሁሉ የዐማራን የገንዘብ ምንጭ በቁጥጥራቸው ስር ያደረጉ ናቸው። በሃይማኖት ምክንያት ፅንፈኛ ሆነው ፀረ ዐማራ አቋም እና አመለካከት ያላቸው የጴንጤና የወሃቢይ እስላሞችም እንደዚያው ግግም ብለው የገንዘብ ምንጩ ላይ ላይነሱ ተዘፍዝፈዋል። አብዛኛዎቹ ረኸጦች ናቸው። ቤታቸውን እንኳ በሥርዓት የማይመሩ። ፈቶች፣ ጋለሞቶች ሁሉ ሞልተውበታል። ብአዴን የራሱን ቡድን አደራጅቶ በሰርጎ ገብነት የዐማራው ትግል ውስጥ አፍስሶታል። እናም ብአዴንም በራሱ ሰርጎ ገቦች አማካኝነት ገንዘብ አጠባዋ ላይ መሰማራት ይከጅላል።

"…እነ ግንቦት ሰባት መተደዳሪያቸው የዐማራው ገንዘብ ነው። ዐማራው ለግንቦቴዎች ላሜቦራቸው ናቸው። በነፃ የሚታለብ ላሜ ቦራ። የዳያስጶራው ዐማራ ጥቂትም ይሁን ብዙ ገንዘብ የተጠየቀውን ገንዘብ ወርውሮ ዞር ማለት ነው የለመደው። የሰጠው ገንዘብ የት እንደደረሰ፣ ለማን እንደተሰጠ አይቆጣጠርም። የመቆጣጠርም ልምድ የለውም። ዐማራን ገንዘብ ለማለብ ሁለት ነገር ይዘህ መቅረብ አለብህ። ፍቅርን እየሰበክ ሰንደቅ ዓላማና ኢትዮጵያ የሚል ስም ይዘህ መምጣት አለብህ። ከዚያ አለቀ። ለስብሰባ የጠራኸውን ዐማራ አዳራሹን በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም አሸብርቀህ፣ የቴዲ አፍሮን ኢትዮጵያ የሚል ዘፈን ትከፍትለታለህ። በቃ አለቀ። ከዚያ እያለቀሰ ነፍሱን ሁላ ይሰጥሃል።

"…የሚገርመው ይሄ ዶላር፣ ፓውንድ፣ ዩሮ ለጋሹ ሕዝብ ለእርዳታ ማሰባሰቡ የጠራው አካል በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ገንዘብ የመሰብሰብ መብት አለው ወይ? ሥልጣንም አለው ወይ? ገንዘብ ሰብሳቢዎቹ የኋላ ታሪካቸው ምን ይመስላል? እነማን ናቸው? ብሎ አይጠይቅም። የሰጠው ገንዘብ ለታለመለት ዓላማም ውሏል ወይ? ኦዲትስ ይደረጋል ወይ? ቴስላ መኪና፣ የቤት ዕዳ ተከፍሎበታል ወይ? ፓርቲ ተጨፍሮበታል ወይ ብሎ አይጠይቅም። ሰጠ፣ ለገሰ፣ ጨፈረ በቃ ወደቤቱ ነው የሚሄደው። ከዚያ ገንዘብ ሰብሳቢዎቹ ብሩን ሲጨርሱ ድጋሚ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ እያሳዩ፣ ኢትዮጵያ የሚል ዘፈን እያሰሙ ለአጠባ ይጠሩታል። ከዚያ በድጋሚ ታጥቦ ይሄዳል።

"…ለአዝማሪና ለአርቲስት፣ ለግንቦቴ ቦቲያም የሰጠውን ብር በህልሙ እያሰበ በቃ ትግሉ ከጫፍ ደርሷል ብሎ ቢጠብቅ፣ ቢጠብቅ ወፍ የለም። ምክንያቱም ገንዘቡን ሆን ብለው ሌሎች አካላት ቀድመው እየወሰዱ፣ ልክ እንደ ውኃ ግድብ ከትረው ይይዙታል። ውኃ ዶላሩ ወደ መስኖው ገብቶ አትክልቶቹን ውኃ እያጠጣ እንዳያለመልማቸው፣ ለፍሬም እንዳያበቃቸው እነ ግንቦቴና ግንባሩ ግድብ ሆነው እንደ ደንቃራ ከፊቱ ይቆማሉ። ትግሉ ፋኖ ችግኙ በውኃ እጦት ይጠወልጋል። በቶሎ ፈጣሪ በተአምራቱ ዝናብ ከላይ ካለዘነበ እና ችግኝ ፋኖ ውኃ ካላገኘ ይጠወልጋል፣ ይደርቃል። ይሞታልም። ስለዚህ አሁን ግድቡን ማፍረስ የግድ ነው። አዎ በፋኖና በለጋሱ የዐማራ ዳያስጶራ መካከል ያለውን ግብዳ ግድብ ማፍረስ ያስፈልጋል። ምቀኛ ሁላ።

"…ጭራሽ አሁንማ እነ ግንቦቴና ግንባሩ መለፋደዳቸው ሳያንስ ትግሬዋ ሂዊ ቲጂዋ በስታሊን በኩል ዋይ ዋይ ማለት ጀምራለች። እኔ ላይ ከግንቦቴዎች ጋር ዘመቻ መክፈት ሁሉ ጀምረዋል። ስታሊንማ እንደ ዘንድሮ፣ እንደሰሞኑን አዝኖብኝ፣ ተናዶብኝ፣ ተበሳጭቶብኝ አያውቅም። ራያን ወያኔ እየወረረች አሉላና ስታሊን ስለ ዐማራና ትግሬ እርቅ በአማርኛ ይሰብካሉ። ትግሬዋ ቲጂ ስፖንሰር አድርጋ ያሳተመችውን የባንዳው ያየህ ሰው ሽመልስን መጽሐፍ ተጋፍቶ የሸመተው ዐማራው ነው። ፋኖና ኤርትራ የትግሬ ሴትን አስገድደው ደፈሩ የሚል ለትግሬ የሚራራ መጽሐፍ ዐማራው ተሻምቶ ይገዛል። ይሄ መረገም ካልሆነ ምን ልትለው ትችላለህ? አሁን ደግሞ ስታሊን እንዴት ዘመዴ እስክንድር ነጋን ይናገረዋል? ገንዘቡ የት ሄደ ብሎ ይጠይቀዋል? እስክንድር ነጋን እንደ መሪ የማይቀበል ዐማራ ዐማራ አይደለም ብሎ ጭራሽ ለዐማራው መሪ ልምረጥልህ ብሎ ተከስቷል። ነገርየው …👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትንሣኤ ማግስት ረቡዕ አልአዛር ይባላል፦

"…ሞቶ የነበረው የማርታና የማርያም ወንድማቸው አልዓዛር ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መግነዝ ፍቱለት፣ መቃብር ክፈቱለት ሳይል ሰማይና ምድርን፣ ብርሃንና ጨለማን በፈጠረበት በቃሉ ብቻ ተናግሮ፣ አልአዛር፣ አልአዛር ተነሥ በማለት ከሞት ያስነሣበት ዕለት የሚታሰብበት ዕለት ነው። ዮሐ 11፥40

"…ጌታችን አልአዛርን ከሞት ያስነሣው መጋቢት 17 ቀን ነው። በዚሁ ቀን መታሰቢያ እንዳያደርጉለት የግርግር ወራት ሆነ። መጋቢት 22ም ሆሳዕና ሆነ። መጋቢት 23ም ርግመተ በለስ አንጽሖ ቤተ መቅደስ ሆነ። በዓሉ ከበዓል ይዋል ብለው አበው የውኃ በዓል ከውኃ ብለው ቃና ዘገሊላን ከጥምቀት ጥግ ጥር 12 እንዳዋሉ ሁሉ ትንሣኤው ከትንሣኤ ጋራ እንዲሄድ በጌታ ትንሣኤ ማግሥት በሚመጣው ረቡዕ በዛሬው ዕለት እንዲከበር አደረጉ። የጌታን ትንሣኤ አክብረን ዛሬ የአልአዛርን ስናስብ እኛም ትንሣኤ እንዳለን እናስባለን እና የዛሬውን ቀን አልአዛር ብለን እናከብረዋለን።

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍…ሰርሰሬ አሳር አብልቼ ደም ሳይነካኝ የምወጣ ነኝ እኔ ዘመዴ። አሁንም ያደረግኩት እንደዚያ ነው።

"…አሁን አሸናፊነቴ ታውጇል። የቀሩት ጥቂት በቀቀኖች ናቸው። 100 እና ሁለት መቶ ሰው ቲክቶክ ላይ ሰብስበው ዋይ ዋይ የሚሉ ምስኪኖች ናቸው የቀሩት። ለምሳሌ ከእነዚህ ከቀሩት ውስጥ የተለየ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር የማልነካቸው አሉ። በጣም ሲበዛ ወዳጆቼ የሆኑ አፍቃሬ እስክንድር የሆኑ ናቸው የቀሩት። ለምሳሌ እስራኤል የነበረው እና አሁን ካናዳ ያለው ወንድሜን ዮሴፍ ይጥናን እንዲች ብዬ አንዳች ነገር አልናገረውም። አሱ ለዐማራ ትግል ያበረከተውን አስተዋጽኦና ተጋድሎ የማውቀው እኔ ነኝ። ሰሞነኛ ታጋይ አይደለም። እኔ ሕዝብ ይሰማኛል፣ መቀደድ፣ መበጥረቅ እችላለሁ ብዬ አፌን ልከፍትበትም አልሻም። ብዙዎቻችሁ እየሰደበህ ነው ብላችሁ ቆርጣችሁ የላካችሁልኝን አይቼዋለሁ። ነገር ግን እኔ የሚገባኝ ነገር ይገባኛል። ዮሴፍ ይጥና እስክንድር ነጋን ከልቡ የሚወድ፣ የሚያከብር ሰው ነው። እና እኔን ደውሎ ቢያናግረኝ ምላሽ የሚያገኘውን በስሜት ወጥቶ ሆድ ለባሰው ማጭድ አውሰው እንዲሰድበኝ አደረጉት እንጂ ሌላ ጉዳይ የለውም። እስክንድር ወጥቶ መግለጫ ሲሰጥ ሁሉ ነገር ያቆማል።

"…ሀብታሙ በሻህ ከስሯል። አይ አም ፕራውድ ጋላ ነኝ ብሎ በገዛ እጁ ተበጥርቆ አሁን የፈለገ ነገር ቢል ማን ሊሰማው? ማን ሊያዳምጠው? ሱሬ ይሄን ዓይነቱን ሰው " He's already dead" ሲል ሰምቻለሁ። የሞተ፣ ያበቃ፣ ያለቀለት ሰው ነው እንደማለት መሰለኝ። ሌላኛው ሀብታሙ የሚባል የሀረርጌ ኦሮሞም አለ፣ ከሳሚ ቅማንቱ ጋር ሆኖ ዋይ ዋይ የሚል። ሀብትሽ ፈሪ ኦሮሞ ነው፣ እንደ ቅማንቴው ሳሚ መገለጥ አይፈልግም። ሌላኛው የካዛንችሱ ማእረግ ነው። ምስኪን የጀርመን ስደተኛ ወንድሜ ነው። ምንም ቢል የማልቀየመው ምስኪን ተብታባ ወንድሜ ነው። ምስጢረኛዬ፣ የመረጃ ምንጬ፣ እናም አፍቃሬ እስክንድር ስለሆነ እሱም የፈለገውን ቢል አልቀየመውም። የአዲስ አበባ የሸገር ልጅ አይደል? እስክንድር መግለጫ ሲሰጥ፣ ሥርዓት ሲይዝ አብረው ሥርዓት የሚይዙ ስለሆነ በእነዚህ የአዲስ አበባ የአራድዬ ልጆች የሚቀየም ልብ የለኝም። ይንበጫረቁ።

"…እርግጠኛ ሆኜ መናገር ባልችልም ትናንት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ሰጠ በተባለው የሕዝባዊ ሠራዊት በጎጃም መግለጫ ላይ የእስክንድር ነጋ እጅ ያለበት አይመስለኝም። አይመስለኝም ነው ያልኩት። ምክንያቱም እስክንድር ነጋ ሌላ ግሩም ውሳኔ ላይ መድረሱን እና ማዕበሉን ሁሉ ፀጥ የሚያሰኝ ውሳኔ ለመወሰኑን መወሰኑን በቅርብ ስለማውቅ፣ ስለሰማሁም ነው። እስክንድር በሸዋ የደረሰበት ውሳኔ ያስደነገጣቸው ብአዴኖች ናቸው የምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ዘመድ፣ ከስድስት ወር በፊት አየር ኃይል ለፓይለቶች ስልጠና ይሰጥ የነበረውን ካፒቴን ማስረሻ ሰጤን፣ ብአዴን ሚሽን ሰጥቶ የሌለ እና ጎጃምን ለሁለት ይከፍልልናል ብለው ያሰቡትን መግለጫ እንዲሰጥ ያስደረጉት። ከትግሉ ወጥቻለሁ ብሎ፣ በቅርቡ ታምሞ የተኛን፣ እድሜ ማራዘሚያ የሚወስድ ሕመምተኛን ሰው ከአልጋ አስነሥተው መግለጫ ያሰጡት ሆን ብለው ነው የሚሉም አሉ። ልብና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ሁሉን ይመረምራል እንጂ በነገሩ እስክንድር ያለበት አይመስለኝም። ቢኖርበትም ግን ታሪኩ ይበላሻል እንጂ ምንም አይፈጠርም። በዚህ ምክንያት ለሚፈሰው ደም ግን ኃላፊነቱን የሚወስደው እስክንድር ይሆናል። ይመርራል ግን ዋጠው።

"…የእነ ዘመነ ካሴ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ቢሆን በፊት እነ ሻለቃ ዝናቡ ይሄዱበት በነበረው ፍጥነት እስካልሄዱና የባህታዊ፣ የቅዱስ ቅዱስ፣ የሚድያ ላይ ፕሮፓጋንዳ ላይ ብቻ ተወስነው ከቀሩ አይደለም በብአዴን ድጋፍ በማስረሻ ሰጤ ስም የሚመጣው ሕዝባዊ ሠራዊት አይደለም የራሱ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ለለውጥ ይነሣባቸዋል። በተለይ ደግሞ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ላይ ከሕዝብ የሚጎርፉ ቅሬታዎች በአመራሩ በጊዜ ካልታረመ በቅርቡ ከሩቅ በሚመጣ ኃይል ሳይሆን ከውስጥ በሚነሣ ኃይል ችግር ይገጥመዋል። ግብርን፣ ያለ አግባብ እስርን፣ በቂም በቀል፣ በድሮ ፀብ፣ የሓሳብ ልዩነትን ባለማስተናገድ፣ ጥቂት አምባገነናዊ ባሕሪን በተላበሱ ግለሰብ አመራሮች ስህተት ችግር ይገጥማቸዋል። ሆደ ሰፊ፣ ዲሲፒሊናቸው የተመሰከረላቸው፣ መጡልን እንጂ መጡብን የመይባሉ መሆን አለበቸው። በጎጃም በዐማራ ፋኖ ስም ጠላት ያሰማራቸው ወንበዴዎች እንዳሉ ሁሉ በራሱ በጎጃም ፋኖ አማካኝነት የሚፈጸሙ ስህተቶች፣ አንባገነንነቶች አደጋ እንዳይፈጥሩበት እሰጋለሁ። ይሄ በጎጃም ብቻ ሳይሆን በጎንደርም፣ በወሎና በሸዋም ካለ በፍጥነት ታርሞ ወደፊት መገስገስ ያለበት አለበት ባይ ነኝ። አሁን የእነ ዘመነ ፋኖ ቆፍጣና፣ ወታደር ካልመሰለ፣ እንደ ወታደርም ቆራጥ መሆን ካልጀመረ፣ በውይይት ማመን ትቶ ጥያቄ የሚጠይቁትን ወደ ማሰር ከገባ ስንዝር፣ ጋት አይራመድም። አኩራፊ ይነሣበታል። ችግር ይፈጠራል። በፍጥነት እርማት ይወሰድ።

"…ትግሉ ቀጥሏል። የእነ መሳይ መኮንን አንከር ሚዲያና የእነ ሀብታሙ አያሌው ምኒልክ ሚዲያ በመረጃ ቴሌቭዥን ላይ የሚጠቀሙ ጋዜጠኞችን በሙሉ "ከእኛ ጋር ሥሩ" እያሉ መወትወት ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ስደቱን፣ ትግሉን ከእስክንድር ጋር የጀመረ፣ ውጣውረዱን፣ ስቃዩን አብሮ ከእስክንድር ጋር የተጋፈጠ፣ ከእስክንድር ጋር እስከ ቀራንዮ ብሎ የወሰነ ስለሆነ በእሱ ላይ ምንም የከፋ ጥያቄ የለኝም። እንዲህ ዓይነት ቆራጥ፣ ቀን አይቶ የማይከዳ፣ ደግሞም ለጥያቄዎች ሁሉ በትሁት አንደበት፣ በእርጋታ የሚመልስ፣ ምንም ይሁን ምንም በጽናት እስከ መጨረሻው ሓሳቡን የማይቀይር፣ የማይወላውል ቀጥ ያለ የማይልመጠመጥ ሰው ለእኔ ጀግናዬ ነው። የፈለገ የስህተት መንገድ ላይ ቢሆን ወጥ አቋም ያለው ሰው ለእኔ ጀግና ነው። አከብረዋለሁ። በኡጋንዳም ያሉት ከመረጃ እንዲወጡ ያለተደከመ ድካም የለም።

"…ትናንት ሀብታሙ አያሌው የግንባሩ ገንዘብ የበሉ ካሉ ይጠየቁ። አብረን እንጠይቃለን ሲል ተደምጧል። ዌል እንግዲክ እንዲል አትሌት ኃይሌ ዌል እንግዲክ እኛም ወደ መጠየቁ እንገባለን። በኢትዮጵያ ትንሣኤ ማኅበር ለግንባሩ የተሰበሰበ ከዌልስ ፋርጎ፣ እና ከሌሎችም የግንባሩ ባንኮች ወደ ኢትዮ 360ዎች የባንክ አካውንት በተጨባጭ እስከ 200 ሺ ዶላር መግባቱ ተረጋግጧል። አልገባም ካሉ ወጥተው ይናገሩ። ሻለቃ ዳዊትም ያስረዳ። ይሄን ብር አውጥተው አይደለም ጋዜጠኛ ፋኖስ እየገዙበት አይደለምን? እሱን ስለገንዘቡ የአሜሪካ መንግሥት ይጨነቅበት። አቶ ኃይሌ የተባለ ሰው ከሂውስተን የላኩት 100 ሺ ዶላር የት ገባ? እነ አቶ ኃይሌ ከሂውስተን የላኩት መቶ ሺ ብር ወደ ቻይና ካምፓኒ የተላከው ለምን እንደሆነም የእስክንድር ገንዘብ ያዥ ወ/ሮ ሕይወት አድማሴ ትጨነቅበት። ሻለቃ ዳዊት የግንባሩ ገንዘብ የተሰበሰበው በኢትዮ 360 የባንክ አካውንት ላይ ነው ብለው አስቀድመው የተናገሩትንም እሱንም አይአርኤስ ይጨነቅበት። በባንክ ኦፍ አሜሪካ የታገደው አንድ ሚልዮን 28 ሺ ዶላርም ይለቀቅ አይለቀቅ የሚታወቅ ነገር የለም። ከተለቀቀም የት እንደደረሰ የማስረዳት ሓላፊነቱ የሚወድቀው በአቶ ሙልጌታ እና ወ/ሮ ሕይወት አድማሴ ጫንቃ ላይ ነው። በዚህ በግንባሩ ገንዘብ የተገዙ ፋኖዎች መገዳደል ከጀመሩ አደገኛ ነገር ነው። ማስረሻ ሰጤን ትናንት የጋሻ ሚዲያ ባለቤቱ የእስክንደር የአክስት ነው የአጎት ልጅ አቶ ወንደሰን ተክሉ ሕዝባዊ ሠራዊት ብሎ…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬ አርፍጄ አምሽቼ፣ አርፍጄ ተኝቼ፣ አርፍጄ በመነሳቴ የምስጋና ሰዓታችንን አርፍደን ለመጀመር ተገድደናል። ሆኖም ግን እንደተለመደው የጌታንም ትንሣኤ ያውጅ ዘንድ የምንጠብቀው 1ሺ ሰው ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወዴት ነው? አዎ ወደ ርዕሰ አንቀጻችን።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን የሚመለከተው ሰሞኑን እንወጣው ከማይመስለው ከከባዱ ሱናሚ ወደ የቧንቧ ውኃ ጠብታ ነጠብጣቦች መሸጋገራችንን የምንመለከትበት፣ አይነኬ አድርገው፣ በሌለ ከፍታም ላይ ራሳቸውን አስቀምጠው የቆለሉትን፣ እንደ ጭድ ክምር፣ እንደ እምቧይ ካብ የናድነበትንና እነዚያ ቀናትም አልፈው ዛሬ ውርውር የሚሉ ድንቢጦችን የምናይበት ሰዓት ላይ መድረሳችንን የምናይበት ነው።

"…በሀብታሙ አያሌው አዲሱ የሕዛባዊ ሠራዊቱ ካርታ ላይ እስክንድር ነጋ አለበት ወይ? የሚል ጥያቄም የምናይበት፣ ምን አልባትም እነ ሀብታሙ እስክንድር ከእጃቸው ሊወጣ ሲል ትናንት አረቄያም ብሎ የሰደበውን ማስረሻ ሰጤ የእድሜ ማራዘሚያ እየወሰደ ሕመሙን ከሚያስታምምበት አልጋ ላይ አምጥቶ ያስለፈለፈው ያለምክንያት አይደለም የሚሉ መተርጉማንም ትርጓሜም እናያለን።

"…በጎጃምም ይሁን በሸዋ፣ በጎንደርም ይሁን በወሎ የሕዝባዊ ሠራዊት በሚባል ቡድን ምክንያት ፋኖዎች ቢመታቱ፣ ደምም ቢፋሰሱ የዚህ ተጠያቂው በዋነኝነት ሀብታሙ አያሌው ሲሆን የእሱ የግል አሽከር አገልጋዩ ወሮ ኢየሩሳሌም ተ/ጻድቅም ተጠያቂ ናት።

"…ጋዜጠኛ ወግደረስ የመረጃ ቲቪ የዐማራ ክልል ዳይሬክተር የነበረ ሲሆን ለጋዜጠኛው መረጃ ቴቪ ከነ አጃቢዎቹ በወር ደሞዝ ይከፍለው ነበር። እሱን ነው ሀብታሙ አስኮብልሎ የወሰደው። መረጃም ውሉን አቋርጧል።

• ይሄንና ይሄን የመሰለ ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እድሜ ለወፎቼ የገዳዬን 😂 …ሙሉ አድራሻ፣ ለነ ሙሉ ስሙ። ዕድሜው፣ ወቅታዊ ስልኩ ጭምር አግኝቼዋለሁ። እሱ ከቀረ እኔ ራሴ እሄድለታለሁ። ለአስተርጓሚነት ሱሬን አስቸግረዋለሁ።

"…ወደ ዋናው ቁምነገር እንምጣ።

"…እርግጥ ነው ለዘመናት የማይነካ ስፍራን ነክቻለሁ። እንደ ታቦት፣ እንደ መቅደስ የሚታዩ ግለሰቦችና ቡድኖችን አደባባይ አስጥቼአቸዋለሁ። ማፍያው ቡድን ሃይማኖት የለውም። አብዛኛው በሀገሩ ላይ ቂም የያዘ እልኸኛና በቀለኛ ስደተኛ ነው። ሀገሩን በአፉ የሚጠራ ግን በልቡ የሚረግማት ጨካኝ ነው ሲባል ጭካኔው እንዲህ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም።

"…ይሄ ቡድን ከጃንሆይ ጊዜ ጀምሮ ሲቃወም የመጣ ቡድን ነው። ኔትወርክ አለው። ሲፈልገው ቅንጅት ይሆናል። የልደቱ አያሌው ቲፈዞም ይሆናል። የበየነ ጴጥሮስ፣ የመራራ ጉዲናም ደጋፊ ይሆናል። በቀለ ገርባን፣ ጃዋር መሀመድን አዝሎ ለመሮጥ ሁኔታዎች ብቻ ነው የሚጠብቀው። አቢይ አሕመድ እግር ስር ለመደፋት ሰከንድ አያስብም። ወያኔን ብቻ እየረገመ ለወያኔ አባት ለሻአቢያ ሲገረድ ቅሽሽም አይለው።

"…ኑሮው በቅፈላ ላይ የተመሰረተ ነው። ሳይሠሩ፣ ምንም ዓይነት የሥራ ታሪክ የሌላቸው ግን አሁን የሪልስቴት ባለቤት የሆኑ አሉ። ቀሪ እድሜአቸውን በኢትዮጵያ ድሆች፣ በተፈናቃይና በጦርነት፣ አሁን ደግሞ በዐማራ ስም ዘርፈው ያስቀመጡትን ለመብላት እንኳ ሆዳቸው በቃኝ አያውቅም። ፔርሙዳ ሆድ ሁላ።

"…አሁን ደግሞ አምና ኖሞር ላይ ሰልፍ የወጡትን ዐማሮች ፖሊስ ጠርተው ያሳሰሩ ገተቶች ዓይናቸውን በጨው ታጥበው በዐማራ ፋኖ ስም በእስክንድር ነጋ ስር ተኮልኩለው ብቅ አሉ። እኔ እነዚህን የሰው ቡልጉ ጭራቆች ነው የመታኋቸው። 95% ደብድቤአቸዋለሁ። ከዚያ በመቀጠል በፋኖ ስም ሀብታም የሆኑትን፣ ኤክስቫተር ገዝተው፣ ቪላ ሰርተው ያሉትን ወደ መቀንደሹ እሄዳለሁ።

•✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አሁን ደግሞ በርዕሰ አንቀጹ ላይ የተሰማችሁን ስትፈልጉ ተችታችሁ የመተንፈስ ተራው የእናንተ ነው። ግን በጨዋ ደንብ።

• 1…2…3…ጀምሩ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“ርዕሰ አንቀጽ”

"…ሲጀመር እኔ ዘመዴ ከሀብታሙ አያሌውም ሆነ ከአበበ በለው ጋር፣ ከእስክንድር ነጋም ሆነ ከማስረሻ ሰጤ ጋር ከሌሎችም ጋር ቢሆን የግል ጠብ የለኝም። አይኖረኝምም። በሚስትም፣ በርስትም የሚያጣላን ነገር የለም። የሓሳብ ልዩነት መቼም ይፈጠራል፣ የሓሳብ ልዩነቱ አንዳንዴ በውስጥ ይፈታል፣ በውስጥ ለመፍታት ያልተቻለው ደግሞ እንዲህ አደባባይ ይወጣና ሕዝብ አዳም ፊት ለአድማጭ ተመልካቹ ይቀርብ እና የቀረበው ሓሳብ ደጋፊና ተቃዋሚ አፍርቶ ከሁለት ጎራ ይቆሙና እነዚያ ኃይላት በዚያ በቀረበ ሓሳብ ላይ ተጠዛጥዘው ባሻቸው መልክ ወቅጠው፣ ፈትገው፣ ፈጭተው፣ ዱቄት አድርገው፣ አቡኩተው ይጋግሩታል። አለቀ። የቀረበው ሓሳብም እንዲሆን የተፈለገው ዳቦ ወይ እንጀራ ሆኖ ለአቅመ መብል እንዲደርስ ነው።

"…የእኔ ሰሞነኛ አጀንዳዎች ምንድናቸው? ያልን እንደሆነ በጣም ግልፅና ግልጽ ናቸው። እስቲ አንዳንዶቹን ከብዙ በጥቂቱ ተራ በተራ እንመልከታቸው።

፩ኛ፦ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና በሸዋ የሚገኙ የተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶች የየራሳቸው አንዳንድ የፋኖ አደረጃጀት ይኑራቸው። ሌላ አምስተኛ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ የሚባል አደረጃጀት መኖር የለበትም። አራቱ ጠቅላይ ግዛቶች መጀመሪያ ሁለት ሦስት የነበረውን አደረጃጀቶቻቸውን ወደ አንድ ካመጡ በኋላ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሲደርስ ደግሞ አራቱም ጠቅላይ ግዛቶች በጊዜአቸው ወደ አንድ የፋኖ ማእቀፍ ውስጥ ይገባሉ። ወደ ግዙፉ የዐማራ ፋኖ። ስለዚህ አምስተኛው ግንባር፣ ድድ፣ ጥርስና አገጭ የሚባለው አደረጃጀት ጣልቃ የገባ ነውና ወደ አንዱ ይጠቃለል ነው ያልኩት።

• ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ግን ከመሬት ተነሥተው ፎገሉ። ይሄ የእኔ ሓሳብ ምኑ ተጠልቶ እንዲህ ጓ እንዲሉ እንዳደረጋቸው ግን ጌ"ጌታቸው" ይወቅ።

፪ኛ፦ ለዐማራ ፋኖ ተብሎ የሚሰበሰበው ገንዘብ ላይ የእስከዛሬው ሚልዮን ዶላር በኪሳራ ይታይ እና ከዚህ በኋላ ያለው አካሄድ ግን ተጠያቂነትን በሚያመጣ መልኩ ይሁን። ደግሞም ከእንግዲህ በኋላ ራሳቸው የፋኖ አመራሮች በሚወክሉት ሰውም ሆነ ቡድን በኩል ገንዘቡ ይሰብሰብ እንጂ ማንም እየተነሣ በዐማራ ስም ገንዘብ እየለመነ የእከኩ ማራገፊያ አያድርግ፣ ሥርዓት ይበጅለት። 70 የዐማራ ማኅበራት ፈርሰው አንድ ብቁ የዐማራ ማኅበር ይመሥረት ነው ያልኩት።

• ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ግን ይሄም ጉዳይ ሲነሣ እንደ እብድ ነው ያደረጋቸው። እንዲያውም አንደኛው በላተኛ፣ ኑሮውን በዐማራ ችግር ላይ የመሠረተ፣ ሲያዩት፣ ሲሰሙት የዐማራ ተቆርቋሪ የሚመስል ሰው በድፍረት ምን ቢል ጥሩ ነው። "እሺ እንዲህ ከሆነ እኛ ምን ሠርተን ልንበላ ነው?" ሠርተህ ብላ ኦንድሜ። ድንጋይ አፈር አባህ ያስበላህ የአባቴ አምላክ። አንተ በዐማራ ስም የዐማራን መከራ እያራዘምክ ከዚያ በምታገኘው ገንዘብ ፏ ሽር ብትን ብለህ ያለ ስጋት አማሪካ ትኖራለህ። የዐማራ ችግር ከተፈታ ጦምህን እንደምታድር ነው የሚሰማህ። ኧረ ወዲያ ያንተስ ነገር። ስትንበጫበጭ ውለህ ታድራለህ እንጂ የዐማራ ትግል ከግለሰብ አናት ወርዶ ተቋማዊ ይሆናል። የእናንተን ምላስ ፈርተው ከጓሮ የተደበቁ ምርጥ የዐማራ ልጆችም እናንተ ገለል ስትሉላቸው ወደፊት መጥተው ሥራቸውን ይጀምራሉ። እኔ ደግሞ በብዕሬ እናንት ሾተላዮቹን እጠርጋችኋለሁ።

፫ኛ፦ ለግንባሩ ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ከምን ደረሰ? ግንባሩ ተቋቋመ ተብሎ በታወጀ ማግስት ገንዘቡ ተሰብስቦ ሲያበቃ የግንባሩ መፍረስ ሳይነገረን እንዴት በአበበ በለው እና በሀብታሙ አያሌው አማካኝነት ሠራዊቱ የሚል አደረጃጀት መጣ? አበበ በለው የግንባሩን ሰው ሻለቃ ዳዊትን ለምን አባረረ? የአበበ በለው ሥልጣን እምን ድረስ ነው? የግንባሩም ሆነ የሠራዊቱም መሪ እንዴት እስክንድር ነጋ ሆኖ ተመረጠ? ማነውስ የመረጠው? የግንባሩም ሆነ የሠራዊቱ ሠራዊታቸው የት ነው ያለው? አንድ ሰው ብቻውን እንዴት ሰራዊትም፣ ግንባርም ሊሆን ይችላል? ወዘተረፈ የሚል ጤናማ ጥያቄ ነበር ያነሣሁት።

• ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ግን የሌለ ጓ አሉ። ስለ ገንዘቡም ሆነ ስለ ግንባሩ አንተ ምን አገባህ? አበበ በለውን፣ ሀብታሙ አያሌውን፣ እስክንድር ነጋን አትናገርብን። እነሱ ዐማሮች ናቸው። የፈለጉትን ያድርጉ። አንተ የሐረርጌ ቆቱ ነህ አያገባህም ወዘተ የሚል ለፍዳዳ ዘጊ ቃል ይዘው ወደ አደባባይ ወጡ። ማን እንደሆንኩ የት አባህ ታውቀኛለህ? ምደረ እንቦጭ ሁላ። እኔማ አንተ ዐማራነትን ተፀይፈህ ስትንበጫበጭ በነበረ ጊዜ ዐማራ በዐማራነቱ ይደራጅ ብዬ ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ ስጮህ ነበር። የሆነው ሆኖ ስለ ግንባሩ መምከን፣ ስለ ሠራዊቱ መፈጠር የሚተነፍስ፣ የሚያስረዳም፣ የሚያብራራም ጠፋ። "ጭራሽ ትግሬው እስታሊን ነፍሴ ለዐማራ ለፋኖ ጠበቃ ሆኖ ከች አለ። እስክንድር የአሜሪካ የሞቀ ቤቱን ጥሎ ነው በረሀ የገባው። እስክንድርን መሪ አድርጎ የማይቀበል ዐማራ፣ ዐማራ አይደለም" ብሎ እርፍ አለ ወለይ። እኔ ግን በጥያቄዬ ቀጠልኩ። የእነ GGጂጂግግ እና የእነ TGቲጂትግ መንበጫበጭ ለአፍታም ያህል ከጉዞዬ አላቆመኝም።

፬ኛ፦ ሌላው ያነሣሁት ጥያቄ ምኒልክ ቴቪን ለመመሥረት መረጃ ቲቪን ለማፍረስ የእስክንድር ጠበቃ ነን፣ እስክንድር አማላጃችን ነው። የዐማራ መዳኛ መንገዱ፣ ሕይወቱም በእስክንድር ነጋ እጅ ነው የሚሉት የግንባሩ ሰዎች እና እነ ሀብታሙ አያሌው፣ እየሩስ ተክለ ጻድቀ እና አበበ በለው የሄዱበት ያረፈደ የድሮ ስግጥ ያለ መሰሪ አካሄድን ነው የተቃወምኩት። ሚዲያ መቋቋሙ አስፈላጊ ሆኖ ሳለ ገና ለገና የዩቲዩብ ሱፐርቻት ገቢ ስለሌለን የራሳችንን ጣቢያ ከፍተን ገቢ እንፍጥር ብለው ላወጡት ፕሮጀክት ሲባል በነፃ በነፃነትም ያቀርቡበት የነበረውን ፕላትፎርም ተመራርቆ፣ መለያየት ሲቻል አዋርዶ፣ አፍርሶ፣ አኮስሶ መሄድ ነውር ነው ያልኩት።

• በዚህም ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ጓ ነው ያሉት። ኤልያስ ክፍሌን፣ ግርማ ካሣን እና እኔ ዘመዴን የሌለ ሞለጩን። አዋረዱን። ሰደቡን። በተለይ ሽመልስ የተባለ ጎጋ እንደ ቁራ ሲያንቋርር የሚውል ሞኝባገኝ እና አቶ ወንደሰን ተክሉ የእስክንድር ነጋ የእህት ነው የወንድም ልጅ ነው የተባለ እና በጫት ጭማቂ የሚንቀሳቀስ ደባል ሱሳም የትልቅ ትንሽ ቅሌታም ሰው ከፊት አድርገው፣ እነ ወዳጄና ከምር እናቴ ወሮ ሸዊት፣ በኒውዮርክ አስተናጋጄ፣ ተቀባዬ ወሮ ማርታ፣ እነ ዶክተር አምሳሉ፣ እነ አቶ ክንፉ በሚወረውሩለት ዶላር እንደ አበደ ውሻ ሲጮህብን ከረመ። ሰውን በማሸማቀቅ ከእውነት ለማውጣት፣ ለማራቅ ይሄዱበት የነበረው የድሮ መንገድ ለዘንድሮ አላዋጣም። በተለይ አቶ ሽመልስ የመረጃ ቲቪ ባለቤቶችን በፎቶ አውጥቶ የሠራው ነውር እጅግ ቀፋፊ ነበር። የለንደን ፋኖ የመወያያ ግሩፕም የእነ ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ግሩፖች መጠራቀሚያ ቢሆንም እንዲህ ዓይነት ነውሮች በፔጃቸው ሲለጠፉ አለመታገሳቸውን ሳላደንቅ አላልፍም። ከስር ከስር እግር በእግር እየተከታተሉ ነው ሲደልቱ የማየው። ይሄም አንድ ለውጥ ነው። በተለይ 40 ዓመት አሜሪካ ኖሮ ዘንድሮም ላልሰለጠነ ሰገጤ መቶ ኪሎ ፋራ ይሄ መንገድ ቅስም ሰባሪ ነው የሆነው።…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትንሣኤ ማግስት ዓርብ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች።

"…ዓርብ ማለት የሥራ መክተቻ፣ ምዕራብ፣ መግቢያ ማለት ነው። ይህች ዕለትም እንደ ዕለተ ሐሙስ ሦስት ስያሜዎች አሏት፡፡ ይኸውም፡- አንደኛው ከሆሳዕና ቅዳሜ በፊት ያለችው ዓርብ የጌታችን ጾም የሚፈጸምባት፤ የጾመ ድጓው ቁመትም የሚያበቃባት፣ በመሆኗ በቤተ ክርስተያን "ተጽዒኖ" ስትባል፤ በሕዝቡም ዘንድ በሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤው ከባዱን ሥራ ስለሚያቆምባት "የወፍጮ መድፊያ፣ የቀንበር መስቀያ" ትባላለች፡፡ ሁለተኛውም በመጀመሪያ የሰው አባትና እናት አዳምና ሔዋን ስለተፈጠሩባት፣ ኋላም በሐዲስ ኪዳን ጌታችን ለቤዛ ዓለም መከራ ተቀብሎ ስለተሰቀለባትና የማዳን ሥራውን ስለፈጸመባት "ዕለተ ስቅለት አማናዊቷ ዓርብ" ትባላለች። ሦስተኛው ደግሞ የዛሬዋ ዓርብ በሰሙነ ትንሣኤው ያለችው "ቤተ ክርስቲያን" ትባላለች።

"…ጌታችን ከልደቱ እስከ ሞቱ ያደረገው የማዳን ጉዞ በሙሉ የተፈጸመው ዓርብ ነው። “ወይቤ ተፈጸመ ኵሉ” እንዲል። ዓርብ የቤተ ክርስቲያን ሁለመናዊ ምስጢር የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች። ማለትም ዓርብ ለቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆኑ ዋና ዋና ምስጢራት ተሟልተዋል። ለምሣሌ የመስቀል አዳኝነቱ ከእርግማንነቱ ተለይቶ ታውቋል፤ የሕንጻዋ መሠረት ቀራኒዮ ተተክሎላታል፤ ሥጋ መለኮት የምትፈትተው በቀራኒዮ ተቆርሶላታል፤ ልጆቿን ከማኅጸነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምትወልድበት ማየ ገቦ ፈስሶላታል። ስብከት፣ ትምህርት፣ ተአምራት፣ ትንሣኤ ተደርጎላታል። ይህንን ሁሉ ምሥጢር ያገኘችው በዕለተ ዓርብ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ተባለች።

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለልጥፉ መልስ…

"…ዛሬ ብዙ ሰዎች ይሄንን ልጥፍ ሲልኩልኝ ውለዋል። ይመስለኛል ከዛሬ ጋር በዚህ ገጽ ላይ ስሜ ወጥቶ ሰዎች ሲልኩልኝ ይሄ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። እኔ የመሰለኝን ግለሰብም ሆነ ቡድን በገባኝ መጠን እንደምተቸው ይሄም ሰው ሆነ ቡድን በእኔ ላይ የፈለገውን ነገር የፈለገውንም ሓሳብ በፈለገው መልኩ ቢጽፍ አልቃወምም። የፈለገውን መጻፍ፣ መተቸት ይችላል። ሙሉ መብቱም የተጠበቀ ነው። ከእኔ የሚጠበቀው ለአቅመ መልስ መስጠት ብቁ ከሆነ መልስ መስጠት ብቻ ነው። እናም በገጼም ላይ ለጣፊው ስለበዛ ለዚህም አጭር መልስ እሰጣለሁ ማለት ነው።

"…መምህርት መስከረም አበራ ፈልጋ ያገኘችኝ ራሷ ናት። እኔ እስከሚገባኝ፣ እስከምረዳው ድረስ "ዘመዴ" ብለው ፈልገውኝ የሚመጡ ጴንጤዎች የዐማራ ትግል እንቅፋት ይሆናሉ ብዬ አላምንም። ለምሳሌ መዓዛ መሀመድ፣ ጌታቸው በየነ፣ እና መስከረም አበራ "በጌታ" ስለሆኑ ለአቢይ አሕመድ ያደሉ ይሆን የሚል ስጋት ቢኖርብኝም ከአቶ ጌታቸው በቀር ሌሎቹ ለዐማራ ዋጋ ሲከፍሉ ነው ያየሁት። ኦርቶዶክስም እስላምም ሆነው ለዐማራ ትግል እንቅፋት የሚሆን የለም ማለቴ እንዳልሆነ ግን ይታወቅልኝ። ለዐማራነት ብዙ ዋጋ የሚከፍሉ ጴንጤዎችንም ዐውቃለሁ።

"…አንድ ቀን በስደት ባለሁበት ሀገር ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ተቀምጬ ሳወጋ ለእኔ የደወለችልኝም፣ የጻፈችልኝም ራሷ መስኪ ናት። ረጅም ሰዓት አውርታኝ ዓይን ገላጭ ምልከታም የሰጠኋት እኔው ዘመዴ ነኝ። ከዶክተር ወንደሰን ጋር እየሠራሽ ከሆነ አለቀልሽ ያልኳትም ራሴው ነኝ። ሁለት ቀን ደውሎልኛል እንጂ በአካል አላገኘሁትም ያለችኝም ራሷ መስኪ ናት። ያልኩት አልቀረም እነ ትንግርቱ በቦሌ ወጥተው እነ መስኪ ከርቸሌ ገቡ። የሆነውም እኔ ያልኩት ነው።

"…አሁን ከቴዲ ርዕዮት ጋር የሚሠራው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ እና ጋዜጠኛ ዳዊት እኮ የዋስ መብታቸው ተጠብቆላቸው ከእስር ቤት ወጥተው ነበር። ፖሊስ ድንገት የዶር ወንደሰንን ኮምፒዩተር ሲመረምር የጋዘኛ ዳዊትና የዶር ወንደሰንን የስልክ ልውውጥ ዶ/ሩ ቀድቶ ካስቀመጠው ኮምፒዩተር ላይ አግኝተው ተሯሩጠው የዋስትና መብቱን ቴዲን ፈትተው እሱን እስከ አሁን በእስር ላይ የሚያማቅቁት። ይሄን ይት አባቱ ያውቃል መንጋው?

"…መስኪንም የተቃወምኳት ከላይ ባስቀመጥኩት ንግግራ ነበር። እንዴት ፋኖን ከቄሮ ጋር እኩል በኢ መደበኛነት ትፈርጃለሽ? ነበር ያልኳት? መስከረም የዩኒቨርሲቲ መምህርት ናት። እኔ ደግሞ ሀ ገደሉ የማይገባኝ ተማሪዋ ነኝ። ተማሪ ደግሞ መምህሩን መጠየቅ የቆየ ልማድ ነው። እና እኔ የምታወቀው ተማሪ መምርቷን ለጠየቅኩት ማንነቱ የማይታወቅ ምንአልባትም ጎጤ ብአዴን ወይም ራሷ ወያኔን ሊሆን የሚችል ማንነቱ የማይታወቅ አካል አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆኖ ዋይ ዋይ ቢል እንዴት እሰማዋለሁ። ያውም መዓዛ መሀመድን ተቸህ የሚለኝ፣ መዓዛ እኮ ብተቻት አልተቀየመችኝ። እህቴ ናት። የገባት ናት። ደውላ ነው የምታስረዳኝ። ቴዎድሮስ ትርፌንና እነ ትሪፕል AAA ን ተቸህብን የሚል ሰው ግን ጤናማነቱ ያጠራጥራል። የፕሮፌሰሩን ስም አሟልቶ አጥርቶ እንኳን የማያውቅ ተደብቆ የሚተኩስ ልፈራ ይቅርና ሚሳኤል የተሸከመ አገዛዝ መቼ ፈራሁ አባቴ።

"…የእኔ ተግባር እየሠራሁት ያለው ሥራ ወደዳችሁም ጠላችሁም ፍሬ እያፈራ ነው። ከሰሞኑ ብዙ የምሥራቾችን ትሰማላችሁ። እናም እኔ ሥራ ላይ ነኝ። ማንም አየር ላይ ቢለፈልፍ መስሚያዬ ጥጥ ነው። የእኔ ግኑኝነት ምድር ላይ ካሉት አናብስት ከሁሉም ጋር ነው። ጎበዝ ጥያቄና ጥላቻ እየለየን እንጂ። እነ GGጂጂግግ እና TGቲጂትግ ግን እጃችሁን ከፋኖ አመራር ጣልቃ ገብነት አውጡ ነው። ይሄ ጥያቄዬ የሚያስወቅሰኝ ከሆነ ግደለኝ። አልሰማህም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልስ ነው።

"…ዝርዝሩን👇 ከታች ጽፌዋለሁ። ከ30 ደቂቃ በኋላ የአስተያየት መስጫ ሳጥኑን እከፍትላችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጼ እንደተነበበ እያየሁ ነው። ይህ የእኔ የዘመዴ ሓሳብ ነው። እኔ ተንፍሼ፣ ተገላግዬ፣ ጤናማ እንቅልፍ ሲወስደኝ፣ እናንተ ሳትተነፍሱ ቀርታችሁ እየተብሰከሰካችሁ በሽተኛ ሆናችሁ እንዳትቀሩ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ።

"…በርዕሰ አንቀጹ ብትበሳጩ እንኳ እነ GGጂጂግግ እና TGቲጂትግ እንደ ዘመነ ኢህአፓ ኢድዩ፣ ደርግ መኢሶን ገዜ በጉልቤ፣ በደንፉ፣ እንደ ኦነግና ወያኔ በስድብ በነውር ቃል አትምጡ። ስሜታችሁን ተቆጣጥራችሁ በጨዋ ደንብ ሞግቱኝ። የተመልካች አይን አታቆሽሹ።

"…ቀንተህ ነው፣ ፈንድተህ ነው፣ ምንጥስዮ፣ ቅብጥርስዮ ብትል ፍንድት አባክ ያድርግህና አልሰማህም። ሥነ ሥርዓት ይዘህ ሞግተኝ። አይችልም፣ መሃይም ነው ምናምን ብላ ብላ በትለኝም እልህሃለሁ መሃይም ቤት ምንአበህ ትሠራለህ? እደግመዋለሁ ሥነ ሥርዓት ይዘህ ተቃውሞ እንኳ ቢኖርህ ለ400 ሺ ሰው በነፃ ሓሳብህን ሽጥ። ያለበለዚያ ብሎክባን በሚባል በቴሌግራም ሰይፌ ወገብ ዛላህን ቆምጬ ነው የምገላግልህ። በዙህ አባባሌ ብትበሳጭም እንኳ ትእግስትን ተለማመድ።

"…1…2…3…ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ወልቃይትን በተመለከተ መከላከያ ሠራዊቱ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል የሚለውን የወያኔና የኦነግ አክቲቪስቶችን ሰበር ዜና ከሰሙ በኋላ ቀደም ሲል ለተነሣባቸው የዶላር ብክነት፣ የትግል መጥለፍ፣ የሸውከኝነት ጥያቄ መሸፈኛ ይሆናቸው ዘንድ አጀንዳ ለማስቀየስ ከትናንት ጀምሮ የግንቦት ሰባት እና የግንባሩ፣ የሠራዊቱም ሰዎች አዲስ ነጠላ ዜማ መልቀቅ ጀምረዋል። "ዘመድኩን አዲስ አጀንዳ አምጥቶ እኛ በእሱ ስንጨቃጨቅ ብልጽግና ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ ሰጠ። መከላከያም አካባቢውን ተቆጣጠረ።" በማለት ለወልቃይት በመከላከያ ስር መውደቅ እኔን ተጠያቂ በማድረግ ራሱን በራሱ ሲያረካ የሚውል ጎጋ መንጋ ደጋፊአቸውን በቲክቶክ መድረክ ሰብስበው፣ ነጠላ ዘቅዝቀው፣ ደረታቸውን እየደቁ፣ ፊታቸውን እየነጩ ዋይ ዋይ ሲሉም ይታያሉ። ዥልጥ ሁላ…

"…እነዚህ ጆፌ አሞሮች፣ የጥንብ አንሣ ፖለቲከኞች አዙሮ የሚያይ አንገት፣ የሚመረምር አዕምሮ አልታደሉም። ከዶላር ስብሰባ፣ በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክና በቲክቶክ ቀደዳ ላይ ሽንጣቸውን ይዘው የሀገሪቱ ቦለጢቃ እንደገባው ሰው አክት እያደረጉ ከመንበጫበጭ በቀር ትናንት እየሆነ ስለነበረው፣ ዛሬም እየሆነም ስላለው፣ ነገም ምን ሊከሰት እንደሚችል የመመርመር ፀጋና እውቀት የተቸራቸውም አይደሉም። ቲክቶከር ሲበዛ ጎመን ጠነዛ አለ አጎቴ ሌኒን። ከምር እውነቱን እኮ ነው። ተሰብስቦ መቀደድ፣ መንደቅደቅ ብቻ።

"…ለማንኛውም እውቀት አልባ ኔፓ የግንባሩና የግንቦቱ ቲክቶከሮች ልታውቁ የሚገባው ድሮም ቢሆን በወልቃይት የነበረ ፋኖ አልነበረም። ከወልቃይት የወጣም የገባም መከላከያ የለም። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ራሱ የአቢይ አሕመድ ብልፅግና አባል፣ ፀረ ፋኖ፣ የፋኖን ትግል ተቃዋሚ፣ ፋኖ እንዴት መከላከያ ላይ ይተኮሳል ባይ የሆነ ሰው እኮ ነው። ደመቀ የዐማራ ፋኖ አሳዳጅ፣ በብልፅግና በጀት የተከዜ ዘብ የሚል ሚልሻ አሰልጥኖ መከላከያን አጋዥ አድርጎ የሚንቀሳቀስ፣ ትግሬዎቹ የእኛ ዘመድ ነው ብለው የሚኮሩበት፣ የጎንደር ፋኖዎችን ወልቃይት እንዳይደርሱ ያደረገ፣ ከአብን ሰዎች ጋር በወልቃይት መሬት ንግድ፣ ከብአዴን ጋር የሰሊጥ ንግድ ላይ የከረመ ሰው ነው። እና በወልቃይት ያለው፣ የነበረው ብልጽግና ከሆነ፣ መከላከያመም ከሆነ በምን ሎጂክ ነው መከላከያ ወልቃይትን ተቆጣጠረ ተብሎ ዜና የሚሠራው? እኔ አልገብቶኝም?

"…ይሄ ቀን እንደሚመጣ መናገሬን፣ መጮሄን ወደ ኋላ ልጥፎቼን ዞር፣ ዞር ብሎ ማየት መመልከት እኮ ነው። ኮሎኔሉ በራያ ጉዳይ፣ በመተከል እና በደራ ጉዳይ አይመለከተኝም። ብልፅግናን አስቀይመን ወልቃይትን ማጣት የለብንም በማለት ለኦሮሙማው ሲገረድ ኧረ ተዉ ስንል "ጀግናችንን አትንካብን" ብለህ እዬዬ ያልክብኝን ረሳኸው እንዴ? ለዐማራ አቢዮት ጉልህ ድርሻና አስተዋጽኦ እንዳለው በድፍረት እንደመሰከርኩለት ሁሉ ደግሞ አሳምነው ጽጌን ሲቃወም እና ሲሰድበው፣ በዐማራ ርስቶች ላይ ቸልተኝነት፣ አለመተባበርን ሲያሳይ፣ ጎንደሬዎችን ራሱ ከወልቃይት አርቆ ከኤርትራውያንና ከአብን፣ ከብአዴን ሰዎችም ጋር ሽር ብትን ሲል፣ ከግንቦቴዎች ጋር ሲሞዳሞድ ጥቂቶች ኧረ ይሄ ነገር ስንል ጮጋ ያልሽ ሁላ ዛሬ የምን ድንገት መጥቶ ዋይ ዋይ ማለት ነው። በዚህ ሁላ የዐማራ ፋኖ ትግል፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ እና በራሱ በጎንደር ፋኖ የሞት ሽረት ትግል ሲያደርግ ኮሎኔሉ ምን ዓይነት አስተዋጽኦ ለትግሉ አደረገ? ነፍሱን ከአግአዚ ጦር ያዳነው የጎንደር ህዝብ በብልፅግና ጦር ሲቀጠቀጥ ኮሎኔሉ ምን ተነፈሰ? አሁንስ ቢሆን ከራያ በኋላ አደጋው ለወልቃይት ነው ሲባል ምን አለ? ንገረኛ…!

"…ነገርኩህ። እስከአሁን ወልቃይትን ሲያስተዳድር የነበረው ብልፅግና ነው። ወልቃይት ይጠበቅ የነበረው በመከላከያ ሠራዊት ነው። መከላከያ ነው ወልቃይትን  በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ሲመራ የነበረው። የዐማራ ፋኖ ስለ ወልቃይት እንዲያወራ፣ እንዲቆጭ እንጂ ኮሎኔሉ የትኛውን የፋኖ አመራር ወደ ራሱ አቅርቦ አብሮ ሲሠራ ታይቶ ነው? ለማንኛውም የማይነጋ መስሏት በቋት ውስጥ… ይባል የለ? አዎ እንዴዢያ ነው። መንጋቱ አይቀር። ቀኑ እንደሁ መድረሱ አይቀር። የእነ ኮሎኔል ደመቀም፣ የብአዴንም፣ የአብንም፣ የሰሊጥ ነጋዴው ሁላ አሰለጠኑ የተባሉትን የተከዜ ዘብ ወታደር ይዘው የሚፈጥሩትን አብሮ ማየት ነው።

"…ደግሞስ ስለ ዐማራ ፋኖ ተጋድሎ ዝም ጭጭ ብለው የከረሙት ግገ ሁላ አሁን ወልቃይት ተያዘ፣ ተከበበ ሲባል እንደ ግሪሳ ወፍ ግርርር ብለው መጥተው፣ ከጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ፣ ከጆፌ አሞሮቹ ጋር ሆነው የምን እንጀፍ፣ እንጀፍ ማለት ነው? ይልቅ ለዐማራ የምመክረው ግንባሩ፣ ሠራዊቱ የሚለውን ገተት ተወውና የዐማራ ፋኖ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና በሸዋ ላይ ወጥረህ ሥራ። ገንዘቡ ለፋኖ እንዳይሄድ ግድብ የሆኑትን እነ የትግሬ ሚስት ያውም ጁንታ አቅፈው የሚተኙትን የዶላር ቀበኞች አስወግድ። እንደ ሀብታሙ አያሌው፣ እንደ አበበ በለው ያሉትን የዐማራ ፋኖ ማኒፌስቶ አዘጋጆችን አደብ አስይዝ። አደብ አስገዛ። ገንዘብ ከእነ GGጂጂግግ እጅ ፈልቅቀህ አውጣ። አውጣና ለፋኖዎቹ ለራሳቸው አድርስ።

"…ዶላር፣ ፓውንድን እንደ ወንዝ ውኃ እንቁጠረው። ፋኖን ደግሞ እንደ ችግኝ። እና የገንዘብ እርዳታው ለፋኖ አስፈላጊው ነው እንበል። ነገር ግን ውኃ ዶላሩ፣ ችግኝ ፋኖው ጋር ሳይደርስ GGጂጂግግ የሚባል ግድብ መሃል ላይ ተሰንቅሮ ገጭ አለ። እናም ውኃ ዶላሩ ለፋኖ ችግኙ ሳይደር ቀረ። የፋኖ ችግኙ እጣ ፈንታ ምንድነው የሚሆነው? መድረቅ፣ መጠውለግ፣ መኮስመን፣ መክሰም። ይሄ የወያኔ ሴራ ነው። ምክንያቱም ገንዘብ ፋኖ ጋር እንዳይደርስ በማድረግ ፋኖን ማዳከም። የራስን ኪስ ማደለብ። አንድ ዶክተር፣ ኢንጅነር የማይበላውን እየበሉ ፋኖን ማበጣበጥ። ዶላሩ ለፋኖ እኮ የግድ አይደለም። ዝናብ አለ። ከሰማይ የሚወርድ፣ የእግዚአብሔር ዝናብ። ፋኖም እስከአሁን ገትሮ የያዘው በፈጣሪ ዝናብ ነው። በተአምራቱ። እኔ እንዲህ ነው የማምነው። እኔ የችግሩን ህብለ ሰረሰር በድፍረት ነክቼዋለሁ። የእነ GGጂጂግግም ሆነ የእነ TGቲጂትግ መንጫጫት ጉዳዬ አይደለም። ኬረዳሽ ነኝ። አይመለከተኝም። አያገባኝም። ጫጫታው ግን አስቂኝ ነው። አብደዋል፣ ጨርቃቸውን ጥለዋል አይገልጻቸውም።

"…የወልቃይትን ጉዳይ ስዘጋው ሌላ አዲስ ስጋቴን በድፍረት በማፈንዳት እወዳለሁ። ይኸውም ምንድነው ያላችሁኝ እንደሁ የእነ እስክንድር ሠራዊቱ የሚባለው አካል ለተነሡ ለጥያቄዎች በጊዜ መልስ ይስጥ። ያለ በለዚያ ተወደደም ተጠላም ጎጃምም፣ ጎንደርም፣ ሸዋም፣ ወሎም በማያባራ የእርስ በእርስ የደም መቀባባት ውስጥ ይገባሉ። እኔ የምነግራችሁ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ ነው። ይሄ ነገር ከፈነዳ በቅድሚያ ሓላፊነቱን የሚወስደው አቶ ሀብታሙ አያሌው ነው። ቀጥሎ አበበ በለው። ተናግሬአላሁ። እነዚህ ሰዎች በአስቸኳይ ከዐማራ ፋኖ ትግል እጃቸውን ያንሡ። አንዴ ወያኔ የሆነ ወያኔ ሆኖ ነው የሚቀረው። አንዴ ኢህአዴግ ሆኖ የነበረ ሰው በምንም ተአምር ብአዴንነቱ፣ ኢህአዴግነቱ ፈጽሞ በቶሎ አይለቀውም። እናም የበግ ለምድ የለበሱ አስመሳዮች በጊዜ ከፋኖ የውስጥ ፍትፈታ ዘወር ይበሉ። አልያ ምን አለ በሉኝ ሀገር ደም እንባ ነው የሚያነባው። የሌሎቹ ይቆየን ጎጃም ላይ ግን መለኮት ጣልቃ ካልገባ በቀር፣ ጎጃም ብልህ ስለሆነ ተነጋግሮ በጊዜ ችግሩን ካልፈታ የሚፈጠረውን በቅርብ ጠብቁ። ተናግሬአለሁ…! ተናግሬም ያልተፈጸመ ስጋቴን ቆጥራችሁ ንገሩኝ። ለቲክቶክ መወያያ ይሄ ይበቃችኋል።…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትንሣኤ ማግስት ሐሙስ አዳም ይባላል።

"…ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንህሃለሁ" ተብሎ ቃል በተገባለት መሠረት አባታችን አዳም ከአምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን የሲኦል ኑሮ በኋላ የተገባለት የተስፋው ቃል የተፈጸመበት እለት መታሰቢያ ቀን ነው። ጌታችን ተሰቅሎ በሲኦል የነበሩትን ሁሉ ነፃ ያወጣው በእለተ አርብ ነው። ታዲያ በትንሣኤ ማግሥት በትንሣኤ ሳምንት በእለተ አርብ ማክበር ሲቻል ምነው በእለተ ሐሙስ መከበሩ ቢሉ እለተ አርብ ለበለጠው ለአምላካቸውና ለአዳኛቸው ለክርስቶስ ስቅለት ስለሆነ በዚሁ ዕለት ይከበራል። እንኪያስ ይሁን ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ አለመዋሉ ሐሙስ መዋሉ ለምንድ ነው ቢሉ፥ ከእሑድ እስከ ሐሙስ ሲቆጠር አምስት ቀን ይሆናል። አምስት ከእኩል ሲፈጸም አድንሃለሁ ብሎት ነበር እና ያ እንደተፈጸመ ለማጠየቅ ነው።

"…ዘንድሮ ደግሞ በዚህች ዕለት የሁላችን አባት ለአዳም የተሰጠው የተስፋ ቃል ስለመፈጸሙ ፣ አዳም ከነልጆቹ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻ ስለ መውጣቱ በሚታሰብበት፣ በሚዘከርበት፣ በሚሰበክበት እለት ለአዳም ነፃ መውጣት ለመዳኑም ምክንያት የሆነችው ፀሐይ ክርስቶስን ያሰገኘችዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የልደት ቀኗ አብሮ ገጥሞ እየተከበረ ይገኛል።

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይሄን ቆርጠህ ያላክልኝ ልጅ ግን ምን አጭሰህ፣ ምንስ አስበህ ነው? ምን እንድል ፈልገህ ነው? ተንኮለኛ…

"…ወለይ የተናገረው እኔን አይመስለኝም። እደግመዋለሁ በፍጹም እኔን አይመስለኝም። ደግሞም ለእስክንድር መቆርቆር መብቱ ነው። ዐማራ ከትግሬ ልምድ ይውሰድ፣ ልምድ ይቅሰም ያለውንም ዐማሮች መልስ ይስጡበት። የሊጥ ስርቆቱን፣ የዱቄት ሌብነቱን፣ የ80 ዓመት መነኩሴ መድፈሩን፣ የጭና ተክለሃይማኖት፣ የማይካድራውን ጭፍጨፋ የትኛውን ልምድ ይውሰዱ? ምናምን ያልከኝንም ራሱን ጠይቀው እንጂ ወደ እኔ አትግፋው። ራስህን ችለህ ጠይቅ ተሟገት።

"…ቲክቶክ ላይ አበባ አምጡ የምለው እኔ መሆኔን በምን ዐውቀህ ነው አንተን ነው ያልከኝ። ስሜን ሳይጠራ ስሜን እንደጠራ አድርገህ ነገር ማቀሳሰርህን አልወደድኩትም። እኔ ቲክቶክ የምጠቀመው በሳምንት አንደዜ ማክሰኞ ብቻ ነው። ያኔ ግን ኮፍያ እንደጉድ ነው።

"…የእስታሊንን ንግግር እያየሁ ከታች የሚሽከረከረውን ጽሑፍ እያነበብኩ ነበር። ስታሊን የጻፈው ተሽከርካሪ ጽሑፍ ልመና ነው። "ልመናው በትግርኛ አይደለም በአማርኛ እንጂ" በካሽአፕ እና በዜል፣ በሱፐር ስቲከርም፣ በሱፐር ቻትም እርዱኝ ነው የሚለው። በጽዮን ማርያም በአቡነ አረጋዊ ማለት ነው እኮ የቀረው። 😂 ያልከኝንም ተመልሼ ሳየው ክፋትህን፣ ተንኮለኛ መሆንህ ነው ያየሁበት።

"…እኔ ስለ ወያኔ የማውቀውን አንዳች ነገር ግን ልንገርህ። ወያኔ የደርግ ጄነራሎችን ተዋግታ ማሸነፍ ሲያቅታት በሙሉ ከእኔ ጋር ነው የሚሠሩት እያለች ቀረጣጥፋ ነው በደርግ ያስበላቻቸው። ትግሬዎቹን ወያኔን ወጥረው ገትረው የያዙአትን ራሷ ወያኔ እኮ ናቸው ብላ አስወርታ ሞኙ ደርግ ቀርጥፎ በልቷቸው ከዚያ ከደደቢት ወጥተው አዲስ አበባ በዓመቱ ነው የገቡት። የወያኔን ሙገሳ በዚህ መልክ ነው የማየው።

• ሂዊ ከዐማራ ላይ እጇን ታንሣ…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ከባድ እንደሆነ ያወቅኩት ትግሬ ለእስክንድር አዝና አደባባይ ለምስክርነት ስትመጣ ነው።

"…እኔ ዘመዴ በአቶ ነጋ ልጆች ላይ ጥያቄ አንሥቼ መጠየቅ መብቴ ነው። በአቦይ ስብሃት ነጋ፣ በወሮ ቅዱሳን ነጋ፣ በዶፍቶር ብርሃኑ ነጋ እና በጋዜጠኛ ፋኖ እስክንድር ነጋ ላይ ጥያቄ ማንሣት መብቴ ነው። ያየህ ሰው ሽመልስ በጻፈው መጽሐፍ ገፅ 172 ላይ አቦይ ስብሃት ነጋ እና እስክንድር ነጋ በእስር ቤት እንዴት በሰላም ያወሩ፣ ይከራከሩ እንደነበር ያነበበ ሰው አሁን የህወሓት ልሳን አቶ እስታሊን እንዴት እስክንድር ነጋ በዘመዴ ይተቻል ብሎ ጨርቁን ጥሎ ባያብድ ነበር የሚገርመው።

"…አቶ አስክንድር ነጋን የከበቡት በሙሉ አብዛኞቹ ሚስቶቻቸው ትግሬ ናቸው። የእስክንድር ገንዘብ አሰባሳቢው የቦስተኑ ጎንደሬ ዶር አምሳሉ ተፈራ ሚስቱ ትግሬ ናት። የሚስቱ እህት የቲዲኤፍ ገንዘብ አሰባሳቢ ናት። የግንባሩም፣ የሠራዊቱም ገንዘብ ሰብሳቢ ዶር አምሳሉ የዐማራም፣ የትግሬም ገንዘብ እንዴት ይሰበስባል? እስክንድር ነጋስ ሚስቱ ሰርካለም ብሔሯ ምን ይሆን? እርሷም ትግሬ ሆና ብቻ በሳቅ ፍርስ እንዳልል። የአበበ በለው፣ የሀብታሙ አያሌውም መመርመር አለባቸው። በደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ኢትዮጵያውያንን 48 ሚልዮን ብር ያጠበ ወንበዴ ሁላ አሁን በትግሬ ተከብቦ የዐማራን ገንዘብ መቦጥቦጥ አይችልም። ዐማራ በዐማራ ብቻ። አለቀ። በዚህ ቅር የሚልህ ካለህ በአናትህ ተተከል። እደግመዋለሁ በአናትህ ተተከል።

"…እኔ የመርህ ጥያቄ ነው ያነሣሁት። የኢትዮ 360 አባላት ወርሀዊ ወጪ በራሱ 31ሺ ዶላር ነው። ይሄን ወጪ ለመሸፈን ደግሞ ዐማራው ላቡን ጠብ አድርጎ ማዋጣት አለበት። ከፌስቡክ ተለቃቅሞ ለሚተነተን ትንተና 31 ሺ ዶላር ፌር አይደለም። ምድረ ሌባ ሁላ ሠርተህ ብላ። ዘራፊ ሁላ ተንቀዳቅሰህ ብላ። አበበ በለውንም ሆነ ሀብታሙ አያሌውን ከብአዴንነትና ከፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ነጥዬ ያወጣኋቸው እኔ ዘመዴ ነኝ። ዐማራ ዐማራ ብዬ ጮሄ ዐማራው ዐማራ ሆኖ በዐማራነቱ እንዲነሣ፣ እንዲቆም ያደረግኩት እኔ ነኝ ስል ቅሽሽ አይለኝም። ፌክ ኢትዮጵያኒስት በሙሉ ኖ ሞር እያለ ለአቢይ አሕመድ ሲገረድ፣ የዐማራን ስደት፣ ጭፈጨፋ አላይም አልሰማም ብሎ በኦሮሞና በትግሬ እንደከብት እየተነዳ በአሜሪካና በአውሮጳ ጎዳናዎች እንደ ቁራ ሲያንቋርር፣ በሰልፋቸው ላይ የዐማራን ጉዳይ ያነሡ ዐማሮችን ሲሳደብ፣ ሲደበድብ፣ ፖሊስ አስመጥቶ ሲያሳስር እኔ ዐማራ ዐማራ ብዬ ስጮህ ነበር። አሁንም የትግሬን ሰበካ እየሰማህ ወልቃይትንም እንደራያ እንዳታጣው ተጠንቀቅ። የሚሰማው ሁሉ ደስ አይልም እና ወደ ልብህ ተመልከት። እናም አሁን የግንቦቴ፣ የትግሬ እና የኦሮሞ ካባ አጥልቀው ዐማራ፣ ዐማራ፣ ፋኖ ለማለት ግርር ብለው ከመጡት ግሪሳዎች በበለጠ የዐማራ ጉዳይ የሚያገባው፣ የሚመለከተው እኔ ዘመዴን ነው። ቅር የሚልህ ካለህ ፈንዳ … ጧ በል…  ምንአባህ ታመጣለህ…?

ጎበዝ…

"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።

• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ትንሣኤ ክርስቶስን ያውጅ ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ ሰው ሞልቷል። 1ሺ ሰው ሳያመሰግን ወደ ሌላ መረጃዎች እንደማንሄድ በሁሉ ዘንድ የታወቀ የተረዳ ነው። 26 ሺ ሰው አንብቦ 1ሺ ሰው ነው በጣቱ ጽፎ ትንሣኤውን ያወጀው። አሁን የአመስጋኙ ቁጥር ስለሞላ ወደ ቀጣዩ አጀንዳችን እናልፋለን። ቀጣዩ አጀንዳችንም "ርዕሰ አንቀጽ" ነው።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ደግሞ "እስክንድርን ለምን ይነካዋል? 😂 ዐማሮች ዘመድኩንን ከትግላችሁ አስወጡት እያሉ ከነ GGጂጂግግ ጋር ስለገጠሙት፣ በአንድ ፖፖ ካልተጸዳዳን፣ አንድ ሙታንቲ የውስጥ ግልገል ሱሪ ካልበሰን እያሉ በትግርኛ እምቧይፅጺጭፃፅፀቑ እያሉ ስላሉት የTGቲጂቲግ ሰዎች በስሱ እጽፍላችኋለሁ።

"…መቼም እኔ ዋነኛውን ስስ ብልታቸውን አግኝቼዋለሁ። የዓባይ ግድብ ወደ ግብፅ እንዳይሄድ የመገደብ ያህል ነው በጉሮሮአቸው ላይ የቆምኩት። ዐማራ ብሬን ለዐማራ ማለቱ እነ GGጂጂግግ እና TGቲጂትግን አሳብዷቸዋል። እስክንድር ነጋን እናድነዋለን፣ እንከላከልለታለን ብለው ዋይዋይ እያሉ ነው።

"…በነገራችን ላይ ዛሬ እንደሰማሁት ከሆነ አርበኛ አሰግድ መኮንን አንድ ሻለቃ ሙሉ ሰርገው የገቡ የዓለም ብርሃን አማኞችን መሳሪያ አስወርዶ ዘብጥያ አውርዷቸዋል። ጎጃም የነበረው የዓለም ብርሃን ሴል ሸዋም ወሎም መታየት ጀምሯል። ተመነጠሩ ነው የተባለው።

"…ለማንኛውም መልካም የማላዘን ሳምንት ለእነ GGጂጂግግ እና TGቲጂትግ። እህሳ ጎዶኞቼ አጭሯን ቅመሟን ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ፣ አንብባችሁም ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በቲክቶክ መንደራችን ልመጣ ነኝ…!

"…የፋሲካ ማግስትም አይደል? ጠላ ባይኖርም በአንቦ ውኃ የተበጠበጠ ጠጅ መሳይ ብርዝ አይጠፋም እና ወጉ ደርሶኝ ዛሬ እንግዳ ከቤቴ መጥቶ እስከ አሁን ድረስ የሀገር ቤት ባህል ወጉን በጠበቀ መልኩ ስናወጋ ውለን ተመራርቀን ተለያየን።

"…ርዕሰ አንቀጽ ከጻፍኩ በኋላ አስተያየት ሲሰጥ እኔው ራሴ በዘበኝነት ሰይፌን ይዤ በቲጂ መንደሬ በራፍ እቆምና እንደ GGጂጂግግ የመሳሰሉ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ በጥባጭ የጥንብአንሳ ፖለቲካ አራማጅ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶችን መቆማመጥ፣ መቅሰፍ ስላለብኝ እኔ ከሌለሁ የማንም ሰካራም ግምቦቴ ገብቶ ቤቱን አጠንብቶ እንዳይበጠብጠን በማሰብ በሩን ዘግቼ እንግዶቼን ሳስተናግድ ውያለሁ። አሁን በሩ ክፍት ነው። ምክንያቱም አለኋ…!

"…ስሙኝማ ለማንኛውም በቲክቶክ መንደራችን አዳሜና ሔዋኔን ነጭ ነጯን ልግት ልመጣ ነኝ። በሉ ሂዱ ዝለቁልኝማ።

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…
Подписаться на канал