"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ሰሞኑን በጀመርኩት የአየር ላይ ውጊያ እየደረሰ ያለውን ጥፋት እና ውድመት በመመልከት እነዚህ የምታዩአቸው ሰማያዊ ሥልጣን፣ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ በእጃቸው የተሰጣቸው መንፈሳውያን አባቶቼና ወንድሞቼ በጨዋ ደንብ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበውልኝ እኔም ከእናንተ ከአባቶቼማ ቃል አልወጣም በማለት ጊዜአዊ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ፈርሜአለሁ።
"…እኔ ዘመዴን ገዝተው የተኩስ አቁም እንድፈርም ያስገደዱኝ አባቶቼ ክቡር ቆሞስ አባ ጽጌ ሥላሴ የባልቲሞር ቅድስት ሥላሴ አስተዳዳሪ፣ ቀሲስ ነዋይ ካሳሁን፣ ቀሲስ ሱራፌል ወንድሙ፣ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው ናቸው።
"…ዐወቅኩሽ ናኩሽ አይሠራም። ወዳጆቼ፣ ጓደኞቼ፣ ወንድሞቼ ቢሆኑም በተሰጣቸው ሰማያዊ ሥልጣን ይበልጡኛል። ሳሚ፣ ሱሬ እያልኩ በአደባባይ ብጠራቸውም ነገር ግን አባቶቼ ናቸው እናም ወደ ግዝት ሳይገቡ ከሰፊ ውይይት በኋላ ያዘዙኝን ጊዜአዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አክብሬ ተቀብያለሁ። በስምምነታችን መሠረትም የተኩስ አቁም ትእዛዙን አከብራለሁ። ከቃላችሁማ አልወጣም።
"…በጊዜአዊው የአባቶች የተኩስ አቁም ምክንያት የአየር ላይ ውጊያውን እዚህ ላይ ገታ እናደርግና ወደ ቀደመው የምድር ላይ ውጊያ፣ መረጃም ወደ መለዋወጡ በሙሉ ኃይላችን እንገባለን። ዛሬ ለግል ጉዳይ ከምኖርበት ከተማ ወጣ ብዬአለሁ። እስክመለስ ድረስ በተመቸኝ ሰዓት ሁላ ወጣ ገባ እያልኩ መጎብኘቴ አይቀርም።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው የዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"…በሞተ ሰው ስም አይነገድም። በሌለ ድርጅት ስም አይቀፈልም። ነውር ነው። ወንጀልም ኃጢአትም ነው። ከሌለ በቃ የለም ነው። የምን እኝኝ ማለት ነው?
"…በጎጃም የጎጃም ፋኖ ብቻ ነው ያለው። ሀብታሙ አያሌው ለምንድነው የሌለ፣ መስራቾቹ የለም፣ ፈርሷል ያሉትን ሕዝባዊ ሠራዊት የሚባል አደረጃጀት አምጥቶ ጎጃም ውስጥ መትከል የፈለገው? ለምንድነው አበበ በለውና ሀብታሙ አያሌው ጎጃም ላይ ሴራ ማሴር፣ መከፋፈል የፈለጉት? ለምንድነው የብልጽግናን ሠራዊት ውጦ ያስቀረውን የጎጃም ፋኖ ሕዝባዊ ሠራዊት በሚል መተካት፣ ማበጣበጥ የተፈለገው? ኢህአዴጋዊነት ይውደም።
"…አቶ ኃይለ ገብርኤል እና ሻለቃ ዳዊት የግንባሩን መፍረስ፣ የሕዛባዊ ሠራዊቱን ያለመሳካት በይፋ አውጀዋል። እስክንድር ነጋ ደግሞ እነ ዶክተር አምሳሉ ብር ያሰባስቡለት ዘንድ መግለጫ ሰጥቷል። ቦስተኖች ደግሞ የሰበሰቡትን ብር ለአንድ ግለሰብ ድርጅት አንሰጥም ብለው ብሩን ይዘዋል። ይሄን ማጥራት የሚችለው እስኬው ብቻ ነው።
"…የእነ ሀብታሙ ሕዝባዊ ሠራዊት ዓላማው ምንድነው? ተዉ፣ ተዉ ብለናል ብሎ ማስፈራራትን ምን አመጣው?
"…መልስ እስኪገኝ ጥያቄዎቼ ይቀጥላሉ። በጭባጮች ዝም በሉ። ነገርየው ገብቷችሁ ነገር ግን እንዳልገባው አክት የምታደርጉም እረፉ። እረፉ ብያለው እረፉ።
• በጦማሬ ሌባሌባውን መዠለጤንና እና መውገሬን እቀጥላላሁ። ሌባ ሁላ ሰምተሃል። በዐማራ ስም አትሸቅሏትም፣ አትሸቅሏትም። አለቀ።
መልካም…
"…ርዕሰ አንቀጹን እንዳነበባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ተራው የእናንተ ነው።
"…በተጻፈው ላይ ብቻ ነው አስተያየት የምንሰጠው። የምትሰጡት አስተያየት የሌላችሁ አስተያየት ያልሰጠ ወላጅ ያመጣል ብዬ ስላላዘዝኩ ዝም ብትሉ ይመረጣል።
"…የተነሣው ሓሳብ ብጥብጥ ይፈጥርልኛ፣ ስንጥቅ ያሰፋልኛል ብለህ በማይመለከትህ ነገር አስተያየት ለመስጠት የምትመጣ ገንገበት ሰገጤ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ምጥንቃቅ ግበሩ። ተጠንቀቁ ለማለት ነው።
"…በአጀንዳው መነሣት ደንፉ የያዛችሁ ግንቦቴና ግንባሮችም በተነሣው ጉዳይ ላይ የተቃውሞም ቢሆን ሓሳባችሁን እንደሰለጠነ ሰው በጨዋነት ሞግቱ እንጂ እንደለመዳችሁት በመቶ ሺ ሰዎች ፊት ነውር ቃላት መጠቀም አይቻልም። ባለጌነት፣ ሓሳብ አልባ ግትርነት ያስቀስፋል።
"…ቀንተህ ነው፣ ወዝተህ ነው፣ ፈርተህ ነው፣ ምንአለ በውስጥ ብትጨርሱ፣ እገሌን ለምን ትናገርብኛለህ ወዘተ ርዕሰ አንቀጹን የማይመለከት ስለሆነ ትጸዳታለህ።
"…ከቤት ውጭ ስለሆንኩ ነገ ረቡዕ እንጂ ለዛሬ ቲክቶክ አይኖረንም። ስለዚህ ባለሁበት ቦታ ሆኜ አስተያየቶቻችሁን ለመኮምኮም እሞክራለሁ። መወያየት ድፈሩ።
•1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍
"ርዕሰ አንቀጽ”
"…17 ዓመት ሙሉ ስለ ፊውዳላዊው ሥርዓት ጨቋኝነት፣ ባዶ ካዝና ስለመረከቡ፣ እኚኚኚ ማለት ሀገር አላሰደገም። ለወሬ ፍሬ የለውም። 27 ዓመት ሙሉ ስለ ደርግ አምባገነናዊነት፣ ጨፍጫፊነት፣ አረመኔነት፣ ባዶ ካዝና መረከብ እያወሩ እኚኚኚ ማለትም እኚኚ ብላዎቹን ባለ መርከብ ሻጭ፣ ህንፃ እንደ ችግኝ ተካይ፣ ዲታ፣ ሀብታም፣ ኢንቨስተር ከማድረግ በቀር ለሕዝብ ጠብ ያለ ነገር አላመጣለትም። ያለፈው ስድስት ዓመት ደግሞ ይብሳል።
"…የአቢይ አሕመድ የኦሮሙማ መንግሥት የፊውዳል የዘውዳዊውን ሥርዓት በኦሮሚኛ ንግግሩ ወራሪ፣ ጨቋኝ፣ ባርያ አሳዳሪ፣ ቅኝ ገዢ ይለውና በአማርኛ ንግግሩ ደግሞ ጥበበኞች፣ ትጉሆች፣ ለኢትዮጵያ አንድነት የለፉ ይላቸዋል። ሃውልት አሠርቶ በቤተ መንግሥታቸው ያስጎበኛቸዋል። የአቢይ አሕመድ መንግሥት እንደ ደርግ፣ እንደ ኢህአዴግ የግልም የሀገርም ጠላት እንዳይኖረው አድርጎ ሁሉን ልቀፍ ብሎም ማጠፊያ ያጠረው የጨነቀው ነው የሆነው።
"…አቢይ አልሆንለት ብሎ ፣ ተቃውሞ በርትቶበት ጣጣውን ፈርቶ ነው እንጂ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያምን እኮ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ሀራሬ ልኮ ለማምጣት የፎገላ ግልብ ሰው እኮ ነው። ለደርግ ኢምፔሪያሊዝም፣ ሶማሊያ፣ ኦነግ፣ ሸኣቢያና ወያኔ፣ ኢዲዩ፣ መኢሶን፣ ኢህአፓ ወዘተ ጠላቶቹ ነበሩ። ሀገር እንዳላሳድግ እነዚህ የጎን ውጋት ሆኑብኝ ብሎ ከፓርቲዎች ጋር እየተጣላ የጦስ ዶሮ ነበረው። ወያኔም እንደዚያው አልሸባብ፣ ኦነግ፣ ሻአቢያ፣ ግንቦት ሰባት ወዘተ እያለች የጦስ ዶሮ ነበራት። ቀሽም አቅሟን የምታላክክበት። አቢይ አህመድስ? አንዳች ምክንያት የለውም። ኦነግን ከነመሳሪያው፣ ግንቦት ሰባትን ከነ ኮተቱ አስገብቶ ሚንስትር ያደረገ ነው። የእሱ ፀብ አሁን ከሕዝብ ጋር ነው። ሕዝብ ደግሞ አይሸነፍም።
"…ወደ አሁኑ ትግል ስንመጣ ሰድስት ዓመት ሙሉ አቢይ ጨፍጫፊ ነው፣ አቢይ ውሸታም ነው፣ አቢይ መሀይም ነው፣ አቢይ አራጅ ነው፣ አቢይ ሌባ ነው፣ አቢይ አሳሪ ነው፣ አቢይ አረመኔ ነው ስንል ከርመናል። እሱም አልካደም፣ አላስተባበለም። እየጨፈጨፈ፣ እያረደ፣ እያፈናቀለህ እያሳየህ ነው። እና ታዲያ ዛሬም ስለዚያው አረመኔ ሰው መልሶ መላልሶ መበጥረቅ፣ ማላዘን ነው ወይንስ ይሄ አረመኔ የሚወገድበትን ስልት መቀየስ? የቱ ነው የሚሻለው?
"…ፕሮፌሰር እገሌ፣ ዶክተር እገሊት፣ አቶ እገሌ፣ ወሮ እገሌ፣ ኮማንደር፣ ሻምበል እገሌ የአቢይ መንግሥትን ክፉኛ ተቹ፣ የአቢይ አገዛዝን አረመኔያዊነት በሚገርም ሁኔታ አጋለጡ፣ እርቃኑን አስቀሩት፣ ራቁቱን አቆሙት፣ ክንብንቡን አስጣሉት፣ ለምዱን ገፈፉት ብላ ብላ ማለት ለትግሉ ምን ይጠቅማል። እሱንማ እኔም እንደ አቅሚቲ፣ ሞጣና ብሪጅስቶንም፣ ዮኒ ማኛም ወዘተረፈ ስንበጠረቀው እንውላለን እኮ። በተለይ እኔ አረመኔነቱን በፎቶ፣ በቪድዮ ሁሉ ነው ይፋ የማደርገው። ስለ ብልጽግና መንግሥት አይረቤነት፣ ስለ ህወሓት መሠሪነት፣ ሌብነት፣ እባብነት 30 ዓመት ሙሉ መዘብዘቡ ምንም አያመጣም።
"…ይሄን የዘመናት መትግ፣ በትውልድ ላይ የተለጠፈ መርገም ለማስወገድ መንገድ፣ ጉዞ ተጀምሯል። ከወሬ የዘለለ ውጤት ተኮር ለውጥ ለማምጣት ትግል ተጀምሯል። በኢትዮጵያ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት አገዛዙን ሊገዳደረው የሚችለው ነገድ ዐማራው ብቻ ነው። ከትግሬዋ ህወሓት፣ ከኦሮሙማው ብልጽግና የሚቃጣ መከራን የመቀልበስ አቅም ያለው ዐማራው ብቻ ነው። ሌሎች ብሔሮች በአጋዥነት ዐማራውን በጸሎት፣ በገንዘብ፣ እናም በአካል በመቀላቀል ሊያግዙት ቢችሉ ነው እንጂ እንደ ዐማራ ለመገዳደር ቦታው እና ሁኔታዎች አይመቿቸውም። ስለዚህ ይሄ እርግማን የሆነ አገዛዝ በኢትዮጵያ ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ እንዲወርድ ከተፈለገ ዐማራውን ማገዝ የግድ ነው።
"…ዐማራውን ማገዝ ሲባል ደግሞ ይሄ መታወቅ አለበት። ዐማራውን ለማገዝ የሚመጡት ሁሉ ማወቅ ያለባቸው፣ መከተል ያለባቸውም መርህ ሊኖር ይገባል። አዎ ሁሌ መከበር፣ መከተል፣ መመሪያ መቀበል ያለባቸው ምድር ላይ ደማቸውን እያፈሰሱ፣ አጥንታቸውን እየከሰከሱ፣ አንዲት የማትተካ ውድ ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ እየገበሩ ያሉትን የፋኖ አመራሮች ብቻ ነው። በዐማራ ፋኖ ላይ አዛዥ፣ ናዛዥ፣ ዲክታተር ልሁን የሚል ማንኛውም ሰው ልክ እንዳልሆነ ሊነገረው ይገባል።
"…ዋናው ትግል እዚህ ላይ ነው። ቆዳቸውን ለመቀየር፣ አቋማቸውን እንደ አክሮባቲስቶች ለመተጣጠፍ ቅሽሽ የማይላቸው፣ የማይቸገሩ፣ ነውር ጌጣቸው የሆነ፣ ቃላባይነትን እንደ ልብስ እንደ ሸማ የሚለብሱ ሰዎችን መጋፈጥ ይገባል። አሁን የምድሩ ስለተያዘ የአየሩን አጋንንት መዋጋት ይገባል። ውጊያው ቀላል ባይሆንም ግን ታሸንፋለህ። ሌባን፣ ዘራፊን፣ በአቋራጭ መጥቶ ትግል ለመጥለፍ የሚንደፋደፈውን በሙሉ አጥብቆ መዋጋት ይገባል።
"…በምድሩ ላይ ውጊያ ፋኖ የሚያሸንፈው ሊገጥመው የመጣውን ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀ፣ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ነው። ግዙፉ ሠራዊት ከነታጠቀው የጦር መሣሪያ እኮ ሲታይ እጅጉን ያስፈራል። ጀቱ፣ ሂሊኮፕተሩ፣ ድሮኑ ቦንብ ተሸክሞ በሰማይ፣ ታንኩ፣ ሮኬቱ፣ ሚሳኤሉ፣ ቢኤም፣ ዲሽቃው፣ መትረየስ፣ ሞርታሩ በምድር፣ ስናይፐር፣ ክላሹም ተሰላፊ ነው። እናም የምድሩ ፋኖ ይሄን አይቶ አይሮጥም፣ አይሸሽም፣ በድንጋይም በዱላም፣ በክላሽና በቆመህ ጠብቀኝ ይዋደቃል። ይማርካል፣ ጥሎ ይወድቃል፣ በመጨረሻም ያሸንፋል። ለጠላት አይሮጥም። ጠላትን የምታሸንፈው ከቤቱ ስትሄድለት፣ ከሜዳው ስትገጥመው ጭምር ነው።
"…የአየሩም እንደዚያው ነው። የምድሩ ገበሬ መስሎ፣ ቄስ፣ ሼክ፣ አዛውንት፣ ወጣት፣ ታጋይ፣ ምርኮኛ መስሎ ሰላይ ሆኖ ፈተና እንደሚሆነው የአየሩም፣ የሳይበሩ፣ የሚዲያውም እንደዚያ ነው። በተለይ የአየሩ አደገኛ ነው። ገንዘብ በቀላሉ ይሠራል፣ ምድር ላይ ባሉት ፋኖዎች በሙሉ ይነግዳል። ጎፈንድሚ እንደጉድ ነው። እያረፈ፣ ውስኪውን እየጠጣ፣ በርገሩን እየጎመደ፣ ዳሌና ጭን ሽንጥም እያማረጠ፣ ከፌስቡክ፣ ከዩቲዩብ፣ ከቴሌግራም እና ከቲክቶክ የተለጠፈ እየገረበ፣ ለአንድ ወይም ለሁለት ሰዓት ሜካፕ ተቀብቶ ኮሜዲም ትራጄዲም ቲያትር ሠርቶ ስለሚወርድ ከባድ ነው። የአየሩ የሳይበሩ ሠራዊት ከባድ ነው። ከባድ የሚሆነው የሚገጥመው ስለሌለ ነው። የስድብ ሠራዊት ስለሚያሰማራ፣ አሸማቃቂ ሠራዊት ስለሚበትን ብዙዎች ይፈሩታል።
"…የአየሩ ሠራዊት ድሮን አይፈራም። ታንክና ሚሳኤልም አይፈራም። የአየሩ ሠራዊት ቁጭ ብሎ በአንዲት ወይፋይ በአንዲት ስልክ መበጥረቅ ስለሆነ አይደማም፣ አይሞትም። የአየሩ ሠራዊት የሚፈራው አንድና አንዲት ነገር ብቻ ነው። የእንጀራ ገመዱ፣ የፈረንጅ ላሙን ዳያስጶራ፣ የሚታለበውን ዶላር የሚያስቆምበት ኃይል ሲመጣ ያን ጊዜ ድባቅ ይመታል። ያን ጊዜ ሀሞቱም፣ ቅስሙም፣ ጅስሙም ይፈስሳል። የአየሩ ሠራዊት እንደ ድሮው የቴሌ ስልክ ያለ ሳንቲም አይሠራም። ያለ ሳንቲም አይንቀሳቀስም። እሱን መላልሰህ ከደበደብክበት ከአየር ወርዶ ኡበሩን ሠርቶ ይበላል።
"…መክረህ፣ መክረህ፣ ዘክረህ አልሰማ ያለውን ዋጋውን መስጠት በብእር ነው። ብዙ ሰው ሾርት ሚሞርያም ነው ተብሎ ስለተፈረጀ እንደዚያ ይመስለዋል። አይደለም። ሰዎች መጀመሪያ በሚነሱ ክርክሮች ነገሩ ላይገባቸው፣ ላይረዱት ይችላሉ። ከዚህ የተነሣም እንደ መንጋ እንደ ግሪሳ ወፍ ግርርር ብለው መጥተው ሊሰፍሩብህ ይችላሉ። ያኔ ደንግጠህ ከሸሸህ፣ ከተደበቅክ፣ ከተሸሸግህ አለቀልህ። የአየሩን የሳይበሩን ሠራዊት የምታሸንፈው በጽናት ነው። እንደ ፋኖ በመጋፈጥ ነው። ትመክታለህ፣…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ" 1ኛ ቆሮ 15፥ 3-4
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…እንግሊዝኛ ቢሆን ሱሬን እጠይቀው ነበር። አረብኛውንስ አላውቅም። ከምር አላውቅም። 😂 ውኃ ግን በአረብኛ ምንድነው?።ያው ውኃ ነው?
Читать полностью…በነገራችን ታች…
"…እኔ የምላችሁ… የኢትዮ 360 ው አቶ ሀብታሙ አያሌው ለግንባሩ ተብሎ የተሰበሰበን ብር የበላ፣ የወሰደም ካለ አቅርቡና በይፋ ይጠየቅ ሲል ነበር። እናም እኔም አሁን በግንባር ቀርቤ ልጠይቅ ነኝ። ከዚያ በፊት ግን 76,571,78 ዶላር በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ስንት ነው የሚመጣው? እስቲ ምቱት። 😂
"…ይሄን ያህል ሚልዮን ብር ከአንዱ የአሜሪካ አውጥተው ሃም ካደረጉ ቀሪውንስ ብር ምን አድርገውበት ይሆን?
"…ይህቺ በፎቶ የምታዩአት ቀድሞ የባልደራስ፣ አሁን ደግሞ የግንባሩ ገንዘብ ያዥ የሆነችው ወሮ ሕይወት እና አቶ ሙልጌታ ሳያውቁት መቸም የሚሆን ነገር የለም። ዶላሩ የተሰጠው ለኢትዮ 360 ሚዲያ ነው።
• ሻለቃ ዳዊት ይሄንን ጉድ ያውቃሉ ወይ…?
• አቶ አበበ በለውስ ታወቀዋለህ ወይ…?
• ብሩክ ይባስ፣ ልዩ እና ይድኔ፣ ሽመልስስ ታውቁታላችሁ ወይ? ንገሩነ?
"…በእስክንድር ነጋ ስር ተሰብስቦ በፋኖ ስም የተሰበሰበን የደም ገንዘብ መብላት ነውርም፣ ወንጀልም፣ ኃጢአትም አይሆንም ወይ?
"…ፋኖ የሚቀይረው ልብስ አጥቶ በቅማል፣ የሚበላው አጥቶ በራብ እየተሰቃየ፣ ለደሙ አልኮል ፋሻ እየተቸገረ እየታየ፣ ለፋኖ ተብሎ የተሰበሰበ ገንዘብ ዝም ብሎ መብላት ይቻላል ወይ…? ግፍ አይሆንም ወይ…?
"…ከሕዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ ቲክቶክ ላይ ሲሰድቡኝ ለሚውሉ አክእንትፊስቶች በመርጨት፣ በመክፈልም እኔ ዘመዴ የጀመርኩትን ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል ነገር ያስቆማል ወይ…?
• ይሄ ከአንደኛው ባንክ የተገኘ መረጃ ነው። ሌላ ሌላውም ይቀጥላል። እደግመዋለሁ 76,571,78 ሳንቲም በኢትዮጵያ ሲመታ ስንት ሚልዮን ብር ነው?
"…ሪሲቱን ማየትስ ትፈልጋላችሁ…? ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ይሄን የጀመርኩትን ሳላደማማ ሌላ ጉዳይ አልጀምርም።
• ፋኖን መከፋፈል ያስቀስፋል።
መልካም… ለርዕሰ አንቀጹ ንባብ ሙሉ የአንድ ሰዓት ጊዜ ተሰጥቷል። ሁላችሁም አንብባችሁ እንደፈጸማችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁ ይከፈታል። ያነበባችሁ ሰዎች በተጻፈው ላይ የሚጨመር ጨምራችሁ፣ የሚቀነስ ካለም ቀንሳችሁ ሓሳባችሁን በጨዋ ደንብ መስጠት ትችላላችሁ።
"…ነገር ግን ምንም ሳታነቡ፣ አንብባችሁም ስላልገባችሁ፣ ገብቷችሁም ለመበጥበጥ የምትመጡ፣ ከርዕሰ አንቀጹ ሓሳብ ውጪ ፀያፍ ስድብ ለመሳደብ የምትመጡ በፔጄ ላይ ልትቆዩ የምትችሉት "ለጥቂት ሰከንዶች ብቻ" መሆኑን እንደታውቁ ከወዲሁ ለማሳሰብ እወዳለሁ። እቀስፍሃለሁ እያልኩ ነው።
• 1…2…3… ጀምሩ…
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…አቢይ ይሄን የሚያደርገው ለምንድነው ቢሉ በጭፍጨፋው ዐማራው የበለጠ እንዲያመርር፣ ለሽማግሌ እንኳ እሺ እንዳይል፣ በደምፍላት፣ በብስጭት እንዲገፋ ለማድረግ ነው። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መረጃ የሚያገኘው ከኢቢሲ፣ ከኢቴቪ፣ ከፋና፣ ከአሚኮ፣ ከዋልታና ከመንግሥታዊ መገናኛ ብዙኅናች ስለሆነ የተቃዋሚዎችን ድምጽ የመስማት ዕድሉ የጠበበ ነው። ሕዝቡም በኢቲቪ የሚሰማው የአቢይን ፋኖን "ወንድሞቼ መገዳደል ይብቃን" የሚለውን ፉገራ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰሜን ሸዋ፣ በጎንደር፣ በጎጃምና በወሎ አቢይ እያስጨፈጨፈ መሆኑን አያይም። ቢያይም የወገኖቹ መጨፍጨፍ፣ የገበሬዎች መረሸን ያንገበገበው ፋኖ በእልህ ሲዝት ስለሆነ ፋኖ በሕዝቡ ዘንድ ጥጋበኛ፣ ለሥልጣን ሲል መንግሥትን ለመገልበጥ የሚሄድ፣ የሰላም ጥሪን የማይቀበል፣ የሚገፋ ነው የሚል ሥዕል በአእምሮው እንዲሥል ያደርጋል። ከዚህ የተነሣ ሕዝቡ በፋኖ ተናዶ ከአቢይ ጎን እንዲቆም ለማድረግ የተሠራ ቁማር ነው።
"…የአቢይን "ወንድሞቼ መገዳደል ይቅር" ንግግር የሚገዙ የዋሕ ኢትዮጵያውያንን ከጎኑ በማሰለፍ ወደ ልክ እንደ ትግራዩ ግዜ ሕዝቡ ተባብሮ ወደ ዐማራ በማዝመት ዐማራን ከነጭራሹ ከበሻሻም በላይ ምድረ በዳ ለማድረግ እንደ ትግሬ አንድ ሚልዮን ሳይሆን ከአስር እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን ዐማራ በአስተማማኝ መልኩ ከጨፈጨፈ፣ ከረሸነ በኋላ እንደለመደው በእርቅ ሰበብ እንደ አረጋ ከበደ ዓይነቱን ደብረ ጽዮን፣ ጌታቸው ረዳን የመሰለ ሮቦት ይዞ ሳይጠየቅ፣ ሌሎች እንጂ ጃዊሳ፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ያሏችሁ እኔማ ወንድሞቼ፣ መገዳደል፣ መጨፋጨፍ ይቅር ብዬ እኮ ስማጸን ነበር እያለ ሊያጃጅል ይቆምራል። ለዚህ ነው ወለጋ ላይ መንግሥቱ የኦሮሞ ነው፣ የሰበሩንን ሰብረናል፣ ከባርነት ነፃ ወጥተናል ብሎ በድፍረት ተናግሮ፣ ራሱም የኢትዮጵያ ሳይሆን የኦሮሞ መሪ መሆኑን ሰብኮ ሲያበቃ ትናንት ባሕርዳር ሄዶ "ወንድሞቼ፣ መገዳደል ይብቃ፣ ኑ አረጋ ከበደ ስር ገብታችሁ ክልሉን አልሙ ብሎ ቀልዶ፣ እሱ ይሄን እያለ ግን ትግሬው የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃ በላይና ብርሃኑ ጁላ ከይልማ መርዳሳ ጋር በመሆን ሰሜን ሸዋን የደም ጎርፍ አድርገው አጥለቀለቁት።
"…አቢይ ከራሱ ሸኔ ጋር ሊደራደር ሲልም እንዲሁ ነው የሚያደርገው። አቢይ ወደ ጫካ አልገቡ ብለው ሥራ ላይ ተፍተፍ የሚሉ የኦሮሞ ወጣቶችን ወደ ጫካ እንዲገቡ ከማግባባት ባለፈ ብዙ ዘዴዎችን ይጠቀማል። ለምሳሌ በከተማ በሞተር ሳይክል እና በባጃጅ አገልግሎት በመስጠት ኑሮአቸውን የሚገፉ የኦሮሞ ወጣቶችን የኦሮሞ ፖሊስ ንብረታቸውን ሰብስቦ ያስረዋል፣ ወጣቶቹ ይበሳጫሉ። ገሚሱ ይሰደዳል፣ ገሚሱ ወደ ሸኔ ይገባል። የአቢይ ዓላማው ተሳካ ማለት ነው። አቢይ ከራሱ ሸኔ ጋር መጀመሪያ ስለድርድር ያስወራል፣ ቀጥሎ በድሮንና በአራጅ መከላከያው በኩል ንፁሐን ኦሮሞዎችን ይጨፈጭፋል፣ ድርድር ተብዬውም በዚያው ይቀራል። እዚያው ጫካ ሆነው ዐማራውን እያረዱና ሀብቱን እያራቆቱ እንዲቀመጡ ያደርጋል። አፄ ኃይለሥላሴ ኢሳይያስ አፈወርቂን በረሃ ልከው ሚሽኑን ጨርሶ ወደ ሰላማዊ ኑሮው መመለስ እንደሚፈልግ ሲልክባቸው ንጉሡ እዚያው ሁን ብለው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል ሀገር አፍራሽ ገንጣይ እንዳደረጉት ሁሉ አቢይም እንደዚያው ነው እያደረገ ያለው።
"…አቢይ ይሄን የሚያረገዉ ደግሞ ለሁለት ነገር ነው።
1ኛ፦ እንደ ገዳ ልዩ የኢንደስትሪ ዞን የተባሉ ትልልቅ የኦሮሞ ፕሮጀክቶች ተገንብተው እስከሚያልቁ ድረስ የኢትዮጵያ መከላከያንና የራሱን ሸኔዎች ጭምር በመጠቀም ሌላውን ነገድ ያደቅቃል። በወያኔ ድንቁርና መጀመሪያ ትግሬን አደቀቃት፣ አወደማት፣ ሽባም አድርጓት ሲያበቃ በመጨረሻ አሁን ባሪያ ገረድ አደረጋት። አቢይ የትግሬን ስስ ልብ ዐውቆአል። ትግሬ ኢትዮጵያን በሞኖፖል ይዞ እየገዛ ሀብት ካላፈራ በራሱ አቅም ምንም ማምጣት እንደማይችል ስለሚያውቅ ራያ፣ ጠለምትና ወልቃይት የሚባል ሳር ትግሬ አንገት ላይ አስሮ በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ እያለ ወደ ገደል ይከተዋል። ከትግሬ ቀጥሎ ዐማራ ይኸው እየተዋደቀ ነው። ዐማራን በሻሻ ካደረገ በኋላ ወደ ሱማሌ ክልል ይገባል። ለምሳሌ ከወለጋው ዐዋጅ ማግስት በኢትዮ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ የዐማራና የደቡብ ተወላጆች ተመርጠው መታሰር ጀምረዋል። አቢይ የዐማራውን በድል ቢወጣ በቀጥታ ወደ ሌሎቹ ክልሎች ዘምቶ ነው የሚያጸዳቸው።
"…ሰዉ ሁሉ ጉዳቱ በትግራይ ያለው ትግሬ፣ በዐማራ ክልል ብቻ ያለው ዐማራ፣ በኦሮሚያ ውስጥ ያለው ዐማራ ብቻ እየመሰለው ይቸገራል። አይደለም ከጦርነቱ ውጪ በሰላማዊ ቀጠና ውስጥ የሚኖሩ የዐማራና ሌላው ኢትዮጵያዊም ፍዳውን እየበላ ነው። ልጆች፣ ሚስት፣ ሠራተኞችና ባለሀብቱን ራሱን ጭምር በማገት ሙሉ ፋብሪካ እስከማሸጥና በኦሮሞ ስም በማዞር፣ ገዢውም እነሱ እራሳቸውና ኮሚሽን የሚከፈላቸው በውጪ ባለሀብት ስም የሚጡ ነጮችና አረቦችን ጭምር በመጠቀም ገንዘብ በመሰብሰብ በኢኮኖሚ ይዳብራሉ። ኦሮሙማው በኢትዮጵያ ስም በብድር ከሚያገኘው በተጨማሪ እንደ ኤምሬት ዓይነቷ በቀጥታ ገንዘብ በመስጠት ኦሮሞ ለሚያደርገው የዘር ጭፍጨፋ ድጋፋቸውን ይሰጣሉ። ለኦሮሞ እታገላለሁ የሚሉ አንዳንድ ምስጢሩን ከሚያውቁ ሸኔዎች በቀር ብዙዎቹ ሸኔዎች ይሄን ፌቨር ስለማያውቁ እንደፈለገም ይነዳቸዋል። ለሽንት ቤት፣ ለማእድ ቤት፣ ለቀለም መግዣ ወዘተ ከዜጎች ላይ በሰበብ አስባቡ የሚሰበሰበው ገንዘብ የኦሮሞ ሜጋ ፕሮጀክቶች እውን እስኪሆኑ ድረስ ይቀጥላል። አሁን እየታየ እንዳለው ሌላው ኢትዮጵያዊ ሕጋዊ ደሀ እየሆነ ነው። እየታሰረ ነው። እየታገተ ቤተሰቡ እየተበተነ ነው። ወደ ውጭ እየተሰደደ ነው። ሌላው ዜጋ ሕጋዊ ደሀ እየሆነ የተመረጡ ኦሮሞዎች ግን ቅንጡ ቢሊየነር፣ ለፌስቡክ ላይክና ኮመንት ሼር 1ሺ ብር የሚከፍል፣ አንዲት ሴተኛ አዳሪ ለአንድ ቀን አዳር ሁለት ሦስት ሚልዮን ብር በጨረታ የሚከፍል ሆኗል።
2ኛ፦ አቢይ ሁሉንም ክልል በሻሻ ካደረገ በኋላ የራሱን ሸኔ በተለያየ ሁኔታ ከሸኔ ውስጥ ያወጣና ቀሪውን ሸኔ ነገሩ ገብቶት እመለሳለው ቢል አሸባሪ ሸኔ ነበር ብሎ ያስረዋል። ይደመስሰዋልም። ስለዚህ ትግሬ እስኪንኮታኮት፣ ዐማራ እስኪደቅቅ፣ ሌሎች ክልሎች እስኪገብሩ፣ ጉራጌ እስወርሞት ከመሃሉ ተነቅሎ እስኪጠፋ ድረስ እዚያው ጫካው ያቆየውና አንዴ አሸባሪ ተብሏል የኦሮሞ ክርስቲያኑንና ዋቄፈታውን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ይደመስሳቸዋል። ያኔ አረቦቹ ኢትዮጵያ በግልጽ ይከሰታሉ። ለዚህ ነው የኦሮሚያ መጅሊስ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በመላው ዐረብ ሀገራት በመሪ ደረጃ በታላቅ ክብር እየተንቀሳቀሱ ያሉት። ኦሮሞ አረብኛ እንዲማር ታዞ እየተማረ ነው። በቀጣይ ኢትዮጵያን የሚገዙት ዐረቦች ባሪያ ስለሚያስፈልጋቸው እንዳይቸገሩ ከወዲሁ አረቢኛ ለኦሮሞ እስላሞች በይፋ እየተሰጠ ነው። ታስታውሱ እንደሆነ አቢይ ፓርላማ ላይ መጪውን 40 እና 50 ዓመታት የሚወስኑ ነገሮች በዚህ 5 ዓመት ውስጥ ይከሰታሉ ብሎ ነበር። ይህን በተናገረ ማግስት ወዲያው ጅማ ውስጥ የፍልስጤምን ባንዲራ ለኢሬቻ በዓል ይዞ ወጣ፣ በሳምንቱ ፍልስጤም እስራኤልን ወጋች። እሱም ከዚያ ዐማራውንና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን መጨፍጨፉን ቀጠለ። ጭራሽ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ፍልስጤም ሀገር ትሁን የሚለው አጀንዳ ላይ እጁን አውጥቶ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በምዕራባውያኑ ጥርስ ውስጥ ከተታት። ዐረቦቹ አቢይን ቢልዮን ዶላር አውጥተው የሚረዱት ያለምክንያት አይደለም። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም…
"…እንደተለመደው ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ የአመስጋኝ ቁጥር ሞልቷል። በምስጋናው መካከል ሊሳደቡ፣ ሊያነውሩን የመጡ ወደ 17 የሚደርሱ ፀያፍ ተሳዳቢዎችም በሚገባ ተቀስፈዋል። በምስጋና መሃል ሌላ ወሬ የሚያወራ ይቀሰፋል። ይወገዳል። ቤቴን ከቆሻሾች በማጽዳቴ እንዴት ያለ ሰላም እንዳገኘሁ ተመልከቱ።
"…በመቀጠል የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ወለጋና ባህርዳር ነው የሚወስደን። ለትግራይ እናቶች የአፍ መሸፈኛ እንጂ ጥይት አልልክም ብሎ አንድ ሚልዮን ትግሬ ቀርጥፎ የበላው ዘንዶ አሁን ደግሞ ለዐማራ ድልድይ ሠርቻለሁ በማለት እንዴት በድሮን እንደሚጨፈጭፍ እናያለን።
"…እዚሁ የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ላይ የዐማራ ፋኖ ወደ አንድነት ሲመጣ እነ ሀብታሙ አያሌው እንዴት አድርገው ሊከፋፍሉት እንደተነሡም ረገጥ አድርገን እንመለከታለን። ከአንድ ሰዓት በኋላም ርዕሰ አንቀጹን አንብባችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ የውይይት ሰንዱቁ ክፍት ይሆናል። ከዚያም በጨዋ ደንብ የሚቀርቡ የተቃውሞ ሃሳቦችን እያከበርን፣ ከርዕሱ ውጪ የሚዘላብዱትን ሰካራምና መሃይም ኮመንቶችን እያጸዳን፣ በጨዋ ደንብ እንወያያለን። በነገራችን ላይ እንዴት እንዴት ያሉ አስተያየት ሰጪዎች በቤቴ ተፈጥረዋል መሰላችሁ።
~ እህሳ ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?
ጉድ ፈላ…
"…ጽንፈኛው ኃይል፣ ዘራፊው፣ አሸባሪው፣ ጃዊሳው የምትለዋ ቃል ተዋጠች። ተዋጠች እና "ስለ ዐማራ ተቆርቁራችሁ ጫካ የገባችሁ" በሚል ቃል ተተካች።
• ወጥር ፋኖዬ…!💪🏿💪✊
እደግመዋለሁ…በደንብ ይደመጥ…!
"…በጎጃም፣ በሸዋ፣ በጎንደር፣ በወሎ ፋኖዎች እርስ በእርስ ከተታኮሱ፣ ከተገዳደሉ፣ ደም ከፈሰሰ ተጠያቂዎቹ በዋነኝነት ሀብታሙ አያሌው ሲሆን፣ እስክንድር ነጋ፣ አበበ በለው እና ኢየሩሳሌም ተክለ ጻድቅ ናቸው። ኢትዮ 360 ሚዲያም እንደ ተቋም የዚህ ቆሻሻ ታሪክ ባለቤት ይሆናል ማለት ነው።
"…የሙያ ሥነ ምግባር ጠብቀው፣ ከዲክታተሩ ሀብታሙ አያሌው ስር ያሉትን ጋዜጠኛ ብሩክ ይባስን፣ ይድኔን እና ልዩን አይመለከትም። በተቋም ደረጃ በሀብታሙና በጄሪ ምክንያት በሚመጣው ዳፋ ካልተጠየቁ በቀር በግል የሉበትም። ዋነኛው ተጠያቂ ሀብታሙ አያሌው ነው።
"…አሁንም ወደ ገደለው ነገር አልገባሁም። እነ አበበ በለው በጎጃም፣ በወሎ፣ በሸዋና በጎንደር ያዘጋጁትን የደም ማፋሰስ ፕላን ኦሮሙማውም ሆነ ወያኔ አላዘጋጁትም። ሕዝብ ለፋኖ ብሎ በሰጠው ገንዘብ ፋኖ ገዝቶ ፋኖን ለመከፋል፣ ለማገዳደል መጣር ወንጀል ነው።
"…እኔ መንጋ ጎጋ ግንቦቴና ግንባሩ፣ ጥርሱ፣ ብብቱ የሚባል ኮተት አልፈራም። የሀብታሙ በሻህና የማእረግ መንተባተብን ከቁብ አልቆጥርም። እኔ ምድር ላይ እነ ሀብታሙ እየፈጠሩ ያሉትን አደገኛ ጥፋት እንድታስቆሙ እየወተወትኩ ነው። ሀብታሙ አያሌውን ሰከን እንዲል፣ አቅሙን ዐውቆ እንዲቀመጥ ምከሩት እያልኩ ነው። ሀብታሙም፣ አበበ በለውም አሁን በትንሹ መተንፈስ ጀምረዋል። ወደ ጫወታው ሲገቡ እኔም ወደዚያው እገባለሁ። እስከዚያው ግን እረፉ በሏቸው።
"…ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ይሄን ሳላደማ ሌላ አጀንዳ አላመጣም። አዛኜን ሌላ አጀንዳ አላመጣም። አበደን…!
የትንሣኤ ሳምንት እሑድ ዳግም ትንሣኤ ይባላል።
"…በቀዳሚው ትንሣኤ በሳምንቱ በሚውለው በዛሬዋ ዕለተ እሑድ የሚውለው ቀን "ዳግም ትንሣኤ" ወይም በተለምዶ ዳግማይ ትንሣኤ ተብሎ ተዘክሮ ይውላል። በዚህ ቀን በትንሣኤው ዕለት ማታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ ቤት ሳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ በመካከላቸውም ተገኝቶ "ሰላም ለዅላችሁ ይኹን" በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው በወቅቱ ሐዋርያው ቶማስ በስፍራው አልተገኘም ነበር፡፡ከሔደበት ሲመጣ ግን የጌታን ትንሣኤ እና ለእነሱም መገለጡን በነገሩት ጊዜ "እናንተ አየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ሰምቼአለሁ" ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? በፍጹም አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም" አለ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን አይቶ እንዲያምን ሲል ነው ጌታ በትንሣኤ ሳምንት በ8 ተኛው ቀን ሐዋርያቱ በዝግ ቤት ሳሉ ዳግም ተገልጾ ቅዱስ ቶማስንም "ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ" ብሎ አሳይቶ፣ እርሱም አይቶና ዳስሶ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎም የመሰከረበት እለት በመሆኑ ዳግም ትንሣኤ ተብሎ ይዘከራል። ዮሐ 20፥ 24-30
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።
• እኔ የምለው…
"…በአንደበቴ የምናገረው፣ በጣቶቼ የምጽፋቸው ሓሳቦች ቆይቶም ቢሆን እየገባችሁ ነው አይደል…?
"…ካልገባህ ደጋግሜ ስግትህ ይገባሃል። አንተ ብቻ ተሳድበህ ከመቀሰፍህ በፊት በትእግስት ከዳር ቁመህ በጥሞና ተከታተል።
"…ተሳድበህ ቀስፌ ካባረርኩህ በኋላ ቆይተህ ሲገባህ በጓሮ በር መጥተህ ብትለፋደድብኝ አልሰማህም። ይሄን ዕወቅ።
• የምለው ገብቷችኋል…ኣ…? 😁
“…ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።” ማር 16፥9
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
• ይሄንንም እቃወማለሁ…!
"…ገንዘብ ከሰጠ በኋላ ገንዘቡ የት እንደ ደረሰ የማይጠይቀው፣ መከታተልም ላይ ዳተኛ የሆነው የአሜሪካው ላሜ ቦራው የዶላር ምንጭ የሆነው የምስኪኑ ዐማራ ሰንዱቅ ሲዘጋ የአውሮጳውን ላሜ ቦራ ለመጋጋጥ መላላጥ ነውር ነው። ወንጀልም፣ ኃጢአትም ነው።
"…ዶላር ለማግኘት፣ ለመቀፈል፣ ለመቀፍቀፍም አሜሪካ በብዙ ነገር ከአውሮጳ እጅግ የተሻለ ነው። በአውሮጳ ዩሮ እንደ አሜሪካ ፈግተህም የምታፍሰው አይደለም። የአውሮጳ ስደተኛ ገንዘብ የሚያገኘው በእሳት ቀለበት ውስጥ አልፎ በብዙ ፈተናና መሰናክል ነው። አውሮጳ "የእለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ" ተብሎ የሚጸልይበት እና ልክ እንደ አሜሪካና እንደ ካናዳ ገንዘብ በብዙ አማራጭ የሚገኝበት አይደለም። እናም በምድር ላይ ያለው የትኛውም የዐማራ ሕዝብ ያለወከለው ማኅበርም ይሁን ዕድር በዐማራ ስም ገንዘብ መሰብሰቡን ሊያቆም ይገባል። ይሄን ለመጠየቅ የግድ ዐማራ መሆን አይጠበቅብኝም። ለምን ኳላላምፑር አልመጣም። ኢህእ…
"…እኔ ዐማራው ይደራጅ፣ ዐማራው ይሰባሰብ፣ ዐማራው ይታጠቅ፣ ዐማራ መዳኛው ከሰማይ ፈጣሪው፣ በምድር ደግሞ ነፍጡ ብቻ ነው እል በነበረ ጊዜ "አማራ ብሔርተኛ ልሆን አልችልም" ይል ፋኖን እየሰደቡ፣ እየዘረጠጡ፣ አይበለውና አሁን አቢይ አሕመድ ቢሞት ምን ይውጠናል ሲል የከረመ መንጋ ሁላ ዛሬ ኮቱን አውልቆ፣ አዲስ የፋኖና የዐማራ ካቦርታ ደርቦ በአዲስ ኮት መጥቶ ዛሬም ዐማራን ለመበጥበጥ ጻድቅ፣ ጻድቅ ለመጫወት መሞከር አበደን ኢንደንደአሙ። አይቻልምም።
"…በአውሮጳ የሚሰበሰበው ገንዘብ በጎጃምና በጎንደር፣ በሸዋም በወሎም አዲስ ለተቋቋመው የእስክንድር ነጋው ሕዝባዊ ሠራዊት ተብዬ ከፋፋይ ቡድን ማጠናከሪያ ላለመሆኑስ ምን ማረጋገጫ አለ?
• ወጥር ዘመዴ… ጓዴ…ውዴ…😂😂😂
👆ከላይኛው የቀጠለ✍✍✍ …ታነክታለህ። ኢላማህን የምትመታው ደጋግመህ ስትደበድበው ነው። ደጋግመህ መረጃ ስትለቅበት ነው። ደጋግመህ ስፍራህን ሳትለቅ ስትሞግተው ነው። ፅናት ነው አሸናፊ የሚያደርግህ።
"…በተለይ እኔ አሁን የነካሁት ስፍራ በጣም አደገኛ ስፍራ ነው። ሴንሴቲቭ ይለዋል ሱሬ እንዲህ አይነቱን ስፍራ። አዎ እሱን ነው የነካሁት። ጫጫታው ከባድ ነበር። ግን ወዲያው ቀነሰ። እንደ ማር ቆራጭ ጓንት እና ማስክ አድርጌ ስለሆነ የገባሁበት የተናዳፊዎቹ እሾህ አላገኘኝም። አያገኘኝም። ለባልቴት ወንዶችና ለጭፍን ደጋፊዎች ቦታና ስፍራ የለኝም። የዐማራን ትግል በንፅህና የማያግዝ አስመሳይ ሌባ ሁሉ በሱፐር ሶኔክ ሚሳኤል ብእሬ ድባቅ ይመታል። ይወገራል። ይወቃል። ምንም ዓይነት ምሕረት የለኝም። አይኖረኝምም።
"…እስክንድርም ቢሆን ሌላ ዓለማ ከሌለው በቀር፣ ትጉሉን መደገፍ፣ ማገዝ እንጂ መምራት አይችልም። የትግሉ መሪ የሚሆነው ታጋዩ የመረጠው አካል ብቻ ነው። የአበበ በለው እና የሀብታሙ አያሌው ፕሮፓጋንዳ፣ ልፍለፋ፣ ዛቻ እና ጉራ ምንም አያመጣም። የዐማራ ፋኖን ትግል በገንዘብ እጦት አድርቆ፣ በገንዘብ እጦት አጠውልጎ ሲያበቁ የዐማራ ፋኖን ለመከፋፈል ከሕዝብ በተሰበሰበ ገንዘብ መፏለል ኢንደንደአሙ። እስክንድር በጎጃም ፋኖ፣ በጎንደር ፋኖ፣ በወሎ ፋኖ፣ በሸዋ ፋኖም የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ መፈቀድ የለበትም። አይፈቀድምም። ሸዋ ምድር ላይ መኖር ያለበት የፋኖ አደረጃጀት አንድ የሸዋ ፋኖ አደረጃጀት ብቻ ነው። ጎጃምም፣ ጎንደርም፣ ወሎም እንደዚያው። በሸዋ ምድር ላይ ሆኖ ጎጃም ላይ በጎጃም ፋኖ አደረጃጀት ላይ ሌላ አደረጃጀት መፍጠር ነውር ነው። ሕገ ወጥነትም ነው። እስክንድር እኔ በጎጃሙ ሕዝባዊ ሠራዊት ጉዳይ የለሁበትም ካለ በአደባባይ ወጥቶ ማስተባበል ግዴታው ነው። እስክንድር ሸዋ ተቀምጦ ጎጃም ውስጥ ከማስረሻ ሰጤ ጋር መፏለል፣ መበጥበጥ የለበትም። ይሄን ይዘው እነ ሀብታሙ አያሌው እና አበበ በለው ነገሩን ለማጦዝ መንጠራወዝ የለባቸውም። አይቻልም አይፈቀድም።
"…ከአሜሪካ ኑሮውን ትቶ፣ ከሞቀ ቤቱ ወጥቶ፣ ልጁንና ሚስቱን ትቶ ወዘተ ብሎ እስክንድርን እንደ ልዩ ፍጡር ቆጥሮ በማጀገን ሌላውን ማኮስመን አይቻልም። ሌላው ሚስትና ልጅ የለውም እንዴ? ሌላው የሞቀ ቤት ትዳር የለውም እንዴ? እነ ግንቦቴዎች ለእስክንድር የጽድቅ አክሊል ደፍተው የሚናውዙት ለምን እንደሆነ ይገባናል። እረፉ ሊባሉ ይገባል። እስክንድርም ቢሆን ጫካ ስላለ መልስ መስጠት አይችልም የሚባለው ነገርም ልክ አይደለም። እስክንድር ኔትወርክ የሚያገኘው ብር ሰብሳቢ ኮሚቴ ሲሾም፣ መግለጫ ሲያወጣ ብቻ ነው እንዴ? ይሄም ትክክል አይደለም። እስክንድር በጥባጭ፣ ሌላ ተልእኮ ከሌለው በቀር በግልጽ አደባባይ ወጥቶ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል። አልያ ሸዋ ተቀምጦ ጎጃም ውስጥ መበጥበጥ ሌላ ተልእኮ ያለ ነው የሚያስመስለው።
"…አሉ ደግሞ ግንቦቴዎች ዘመነን፣ አሰግድን እየሰደቡ እስክንድርን የሚያጀግኑ፣ ውባንተን እያወረዱ እስክንድርን የሚያጀግኑ። እስክንድር ጎጠኛና ዘረኛ ስላልሆነ፣ የአዲስ አበባ ልጅ ስለሆነ ጎጠኞቹ፣ ዐማሮቹ አይወዱትም ሁላ የሚል ትንተና የሚሰጡ አሉ። ይሄም ትክክል አይደለም። እስክንድር ጎጠኛ ስለሆነ መሰለኝ ትግሬን፣ ኦሮሞን ሳይመርጥ የዐማራን ትግል መርጦ ሊታገል የገባው። ለዚህም መሰለኝ አንዴ የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር፣ ሌላ ጊዜ የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት እያለ ገንዘብ በዐማራ ስም የሚሰበስበው። ለዚህ ነው መሰለኝ በዐማራ ክልል ዐማራን ላደራጅ እያለ የሚንከራተተው። እስክንድር ዘረኛ ሆኗል። የዘር ጫወታውን ተቀላቅሏል። ስለዚህ ከመረቁ ስጡኝ ከሥጋው ጦመኛ ነኝ አይሠራም። የዐማራ ፋኖ ታጋይ ነው ታጋይ ነው አለቀ።
"…ሁሌ እንደምለው ደፋር መሆን፣ ይሉኝታን ማስወገድ ይገባል። ስህተት መሆኑን እያወቃችሁ ሰዎች ምን ይሉኛል በማለት በይሉኝታ መሎጎም ትክክል አይደለም። ዛሬ ስትተቹት የሚያኮርፍ የፋኖ መሪ ነገ በለስ ቀንቶት ሥልጣን ቢይዝ ከአቢይ የበለጠ አረመኔ የማይሆንበት ምክንያት የለም። የዐማራን ትግል እሾሆች በድፍረት በመጋፈጥ መንቀል ያስፈልጋል። የዐማራን ትግል እንቅፋቶች ወገብ ታጥቆ ከመንገድ ላይ ገለል እንዲሉ ማድረግ ያስፈልጋል። በቅዱሱ የዐማራ ትግል አይነኬ የሚባል ነገር የለም። በኦነግና በወያኔ መንገድ ዐማራው ታግሎ አያሸንፍም። ዐማራው ፍጹም ጨካኝ፣ ከእነሱ የባሰ አረመኔ ነው መሆን ያለበት። ያኔ ፍየሎቹ ሮጠው ወደ ፍየሎቹ ጋጣ ይገባሉ።
"…በሰሞኑ ግርግር ትዝብት ልቋጭ። ሰሞኑን እኔ ባነሣሁት አጀንዳ ሁለት ጎራ ተፈጥሮ መንጠራወዝ ነበር። የጎጃሙን ሴራ እኔና መሬት ላይ ያለነው ብናውቅም መንጋው ስለማያውቅ ነገሩን እኔ ስጀምረው ጎጃማዌውም፣ ጎንደሬውም፣ ወሎዬውም፣ ሸዋዬውም ጓ ብሎብኝ ነበር። ጎጃም ተጠንቀቅ ስል ሟርት ነበር የሚመስላቸው። ማስረሻ ሰጤ ለእኛም መግለጫ ልኮ ሴራው ስለገባን አፈንንበት። ቆይቶ በጋሻ ሚዲያና በሀብታሙ አያሌው በኩል ይፋ ሲያደርግ መንጋው ተገለበጠ። የእኔን ፎቶ ዘቅዝቆ ይሰድበኝ የነበረው ሁሉ ዘመዴ ጀግና ብሎ እሪሪ ማለት ጀመረ። እኔ እንደሁ አይሞቀኝ አይበርደኝ። አሁን ጌታዬ ቲክቶክም ሆነ ፌስቡክ ማንን እየወቀጠ፣ እየረገጠ እንደሆን መመልከት ነው። አለቀ።
"…ባለ ሾርት ሚሞሪያም የቲክቶክ ሰፈር ዐማሮችን ይዘው እሪሪ ሲሉብኝ የከረሙት እነ ማእረግ ዘካሳንቺስ፣ እነ ሳሚ ቅማንቴው ሁላ ሩጠው ትግሬው ፓስተር ኤድመንድ ቤት ሄደው እስክንድርን አድንልን ብለው ምልጃ ጠየቁ። ይኸው የግንባሩን ልጆች እንደ እናት ሰብስቦ አይዟችሁ፣ ይሄ ዘመድኩን የተባለ እብድ ነው አይደል ያስለቀሳችሁ፣ ግድየለም፣ አብረን እንውቀጠው፣ ውቀጡት፣ እንዴት አባቱ ቢደፍራችሁ ነው ዘመድኩን፣ የሀረርጌው ቆቱ እንዲህ የዠለጣችሁ? ሃኣ…? እኮ ምን ሲደረግ? በሉ ኑ ተሰብሰቡ። መላ እንፈልግለት ብሎ ሰብስቦ ትግሬው ፓስተር እያላገጠባቸው ነው። እደግመዋለሁ። አልፋታችሁም።
ጎበዝ…
"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
መልካም…
"…እንደተለመደው ዛሬም ከ1ሺ በላይ ወዳጆቼ የክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ክብር ዐውጀዋል። ዛሬም የክርስቶስን ትንሣኤውን በሚያውጁ አማኞች መሃል ጣልቃ ገብተው ለመረበሽ የሞከሩ አሳዳጊ የበደላቸው ወደ 11 የሚያህሉ ነውረኛ ተሳዳቢዎች ተቀስፈዋል። ቤቱን ተመልከቱት። እንዴት እንደሚያምር። እኔ ቤት ቀልድ የለም። በምስጋና ሰዓት ምስጋና ብቻ። በጭቅጭቅ፣ በክርክርም ጊዜ የለ ጸያፍ ቃል መወያየት ይቻላል። አይደለም እንዴ? ፒፕሉን እኮ በግድ አደብ አስገዛሁት። አሁን ይሄን መልእክት አይቶ ሄጵ ብሎ ለመሳደብ በደንፉ የሚመጣም አይጠፋም። ሲመጣ ቀስፌ እገላግለዋለሁ። ስሜትን መቆጣጠር መልመድ አለብን። አለቀ።
"…ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። ዛሬም እኔ ዘመዴ ትግተጋ፣ ነቆራ ላይ ነኝ። አይሰለችህም እንዴ? ምን አስበህ ነው? በቃ ተፋታቸው? ብላ ብላ ምናምን አይሠራም። በድፍረት የማይነካውን ነክተን እንወያያለን። እንሟገታለን። እኔ አንዴ ነክሻለሁ፣ ነክሻለሁ ነው። ከነከስኩ ደግሞ ሳላደማ የምፋታው ነገር የለም። ለልፈጽም አልጀምርም።
"…ስጀምር እንደ ዝናብ በማበስበስ አይደለም። እንደ ነፋስም በመታገል፣ በመገፈታተር፣ በኃይል አይደለም። እኔ እንደ ፀሐይ ነው የምታገለው። ፀሐይ ቀስ ብላ ነው የምትወጣው። ለስለስ ብላ ቀስ በቀስ ነው ሙቀቷን የምትለቀው። መጀመሪያ ካፖርቱን፣ ቀጥሎ ኮቱን፣ ሸሚዙን፣ ኮፍያውን አስወልቀዋለሁ። ጫማና ሱሪም አስወልቃለሁ። የውስጥ ሱሪና ግልገል ሱሪ፣ የጡት ማስያዣ ሳያወልኩ እጅ ካልሰጡ አልፋታም። እንደ ዝናብ በመደብደብ፣ እንደ ነፋስ በኃይል በመገፍተር ሳይሆን እንደ ፀሐይ ነው ለብ፣ ለስለስ ብዬ ነው ገብቼ ጨርቅህን የማስጥልህ።
"…እህሳ… የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ? የደበረህ ካለህ ጥፋ፣ አፍ መክፈት ያስቀስፋል።
በመጨረሻም…
"…በመጨረሻም አንዱ የጨሰ የሀብትሽ ደጋፊ ይድረስልኝ ለዚያ ለኤልያስ ክፍሌ ብችላ ለፀበልተኛው ዘመድኩን ነቀለ ብሎ የላከልኝን ቪድዮ ለ400 ሺ እድምተኞቼ በሙሉ እንዳለ፣ እንደወረደ ለጥፌላቸዋለሁ። እኔ የሰው አደራ አልበላም። የሰው መልእክት አላስቀርም።
"…እኔ የኤልያስ ክፍሌ ቡችላ ዘመድኩን ነቀለ (ፀበልተኛው) 😂 ይሄን ቪድዮ ስለጥፍ በሙሉ ፈቃደኝነት ነው። አሁን ወደ ጨዋታው እየተገባ ስለሆነ እጅግ በጣም ደስስ ይላል።
"…ኤልያስ ክፍሌ ሆይ አቶ ሀብታሙ አያሌው ጉድ ሊያደርግህ፣ ወጥ በወጥ ሊያድርግህ ዝግጅቱን አጠናቅቋልና ምላሽ ለመስጠት ተዘጋጅ። ሀብትሽ እንደሁ ቀላል ሰው አይምሰልህ። አንተ እነ መለስ ዜናዊን፣ ስብሐት ነጋን፣ እነ አላሙዲን በአሜሪካ ከስሰውህ በአሜሪካ ሕግ ተከራክረህ እንዳሸነፍካቸው እንደዚያ አይምሰልህ። ተናግሬአለሁ።
"…ሀብትሽ እንዳለው እስክንድር ነጋም ወደ ጫወታው የግድ መግባት አለበት። ዶሴዎች መመርመር አለባቸው። እነ ሻለቃ ዳዊትም፣ እነ ዶክተር አምሳሉም፣ እነ ልጅ ተድላም ተዘጋጁ። የዲሲ ግብረ ሀይል፣ ከዶላሩ ጋር ንኪኪ ያላችሁ በሙሉ ራሳችሁን ለማንጻት ተዘጋጁ።
"…የዐማራ ትግል ንፁሕ ነው። የዐማራ ትግል መለኮታዊ ጣልቃገብነት ያለው ነው። የዐማራ ትግል ፀዐዳ ነጭ ሀጫ በረዶ የመሰለ ነው። የዐማራ ትግል መቅደስ ነው። የዐማራ ትግል ትንሣኤው ስለደረሰ ኮተቱ በሙሉ ከዐማራ ትንሣኤ በፊት ይራገፋል።
"…ኔቨር አለ ሱሬ አበደን በዐማራ ስም ከእንግዲህ ወዲህ መነገድ የማይታሰብ ነው። የዐማራ ሕዝብ የዋሕ ነው ሲባል ሞኝ፣ ዥል፣ ምንም የማያውቅ፣ ደንታቢስ ነው ማለት አይደለም። በጭራሽ አይደለም። እያንዳንድሽ ትመረመሪያታለሽ።
• ዘመድኩን ነቀለ ነኝ 😂 (ፀበልተኛው)
መጥቻለሁ…!
"…የግንባሩ ገንዘብ የተሰባሰበው የዐማራ ትንሣኤ ዘ-ኢትዮጵያ በሚል ድርጅት አካውንት። ድርጅቱ በአሜሪካ ውስጥ የተወቀ ሦስት የባንክ አካውንት ወይም ከዚያም በላይ ሊኖረው ይችላል። እነዚህን የባንክ አካውቶች ከአራት ሰው በስተቀር ሌላ የሚያወቀው የለም።
"…በባንኩ ገንዘብ የሚያዘው ግን እስክንድር ነጋ እስክንድር ነጋ ብቻ ነው። እስክንድር አውጡ ሲላቸው ያወጣሉ። ስጡ ላላቸው ይሰጣሉ። ይሄንን ሻለቃ አያውቁም። ኦዲተር አያውቀውም። ዶላሩን የሚታጠበው ሕዝብም አያውቅም። በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር በዚህ መልኩ ነው የሚታጠበው። እነ አበበ በለው ስለ ዶላር ሲነሣ እንዲህ ከቁጥጥር ውጪ አውጥቶ የሚያንዘረዝረው ለዚህ ነው።
"…ይሄ ብር የዋጣው በወርሀ ጥቅምት ሲሆን ለግንባሩ ተብሎ የተሰበሰበው ብር ግን መሰከረም ወር ላይ ነው። እንግዲህ እንጠይቃለን። ቀጣይ ይዤ የመመጣው መረጃና ማስረጃ ደግሞ ይብሳል። ተናግሬአለሁ። ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ሳላደማ አልመለሳትም። ልብ በሉ 76,571,78 $ በኢትዮጵያ ወደ 9 ሚልዮን ብር አከባቢ ነው። እና ይሄ ሁሉ ሚልየን ብር በምን ሂሳብ ነው ወደ አንድ የግል ድርጅት ሂሳብ የሚገባው? በስህተት ወደ ቻይና ሄደ የተባለውንም ጨምሩበት። ጠይቁ በተባለው መሠረት ጥያቄአችን ይቀጥላል።
"…ወዳጄ የዐማራ አምላክ አይተኛም። አያንቀላፋም። ሁሉም ነገር ይጋለጣል? ገና በአሜሪካ ሕግ መሠረት እንነጋገራለን።
• ተረጋጋ ይለኛል እንዴ ደግሞ… ገና መች ጀመርኩና ነው የምረጋጋው። በደንብ ተንፍሱ…በዚያውም መልስ እፈልጋለሁ። አፍጥኑት።
• ወዳጆቹ እረፍ በሉት…!
"…አቢይ አህመድ ባህርዳር ሊሄድ ሲያስብ የተመስገን ጥሩነህን በጋብቻ ዘመድ ቤተሰቡ የሆነውን እና ከትግሉ ሜዳ በሕመም ምክንያት የራቀውን ካፒቴን ማስረሻ ሰጤን ከተኛበት አልጋ አንሥተው አምጥተው የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በጎጃም ተመሠረተ ብለው ዐወጁ። ዐዋጁንም እንዲያጮኸው ትናንት ማስረሻ ከሀገሩ ልጅ በባለሀብቱ በአቶ ወርቁ አይተነው ስሙ ተጠራ ብሎ እንዳልፎጋላበት፣ እንዳልሰደበው አሁን ደግሞ ያን የከመረበትን አቧራ አራግፎለት የጎጃም ፋኖን ለሁለት ለመክፈል ተጋጋጠ።
"…መለኛው ጎጃሜም ነገርየውን ሳያጮኸው፣ ሳያጦዘው ሙያ በልብ ብሎ ሥራውን ጀመረ። እርግጠኛ ነኝ የበላይ ዘለቀ ልጆች ነገርየውን በጥበብ ይሻገሩታል ብዬም አምናለሁ።
"…ማስረሻ መግለጫ ለሁሉም ሚድያዎች ልኳል። ሚዲያዎቹ በሙሉ አልተቀበሉትም ውድቅ ነው ያደረጉበት። ኢትዮ 360 ግን አይደለም መግለጫውን ብአዴን ለስብሰባ ጠርቶ የሰበሰባቸውን ሚሊሻዎች ፊት ጨለማ የዋጠው ቪድዮ ሁላ ሠርተው ላኩለት። እሱም የተላከለትን ቪድዮ ይዞ ፎገላ።
"…ልብ በሉ ሀብታሙ አያሌው እና አበበ በለው የዐማራን ችግር ጠምቀው፣ መከራውን በማርዘም፣ በጎፈንድሚ፣ ዶላር እየሰበሰቡ በዐማራ ደም ልጆቻቸውን ማሳደግ፣ ሕይወታቸውን በዚህ መግፋት ይፈልጋሉ። ለዚህ ነው ዜናውን ያጮሁት። ምድር ላይ የሌለን ኮተት ለሆዳቸው ሲሉ ነው ያጮሁት። ጎጃምም፣ ጎንደርም፣ ሸዋም፣ ወሎም በጥበብ ይወጡታል። 💪💪🏿💪
"…ተመልከቱ ግም ቦቲ 7 ቶች በሙሉ የማስረሻ ሰጤን ፎቶ ፕሮፋይል ፒክቸራቸው አድርገው ረጅም ሰዓት ድረስ ቲክቶክ ላይ የሚጣዱትም አንገታቸውን እየደፉ ነው።
"…እደግመዋለሁ በጎጃም ምድር በስህተት እንኳ ፋኖዎች ቢመታቱ ሓላፊነቱን የሚወስዱት ይሄ ነገር ያጮሁት እነ ሀብታሙ አያሌው እና አበበ በለው ናቸው።
• የደም ገንዘብ ባይበላስ ቢቀር…
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ፒያሳ፣ ለገሀር የጸዳው ለዓረቦቹ ነው። የሚሠራው መዝናኛ፣ የሚገነባው ግንባታ ሁሉ ለነገዎቹ ባለ ሀገሮቹ የኦሮሞ ሕዝቦች ነው። ዐማራና ሌላው ብሔር በዶዘርም፣ በድሮንም እየጸዳ ነው። አሁን የኦሮሞ ባለሀብቶች ጫካ ባሉ ልጆቻቸው አማካኝነት የኢትዮጵያውያኖችን ፋብሪካ በእገታ ምክንያት እየገዙ ነው። ስለዚህ በዚህ ትግል የዐማራ ፋኖ ከተሸነፈ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ለቁርስ ነው የሚሆኑት።
"…ለዚህ ነው የዐማራን ትግል መደገፍ ሀገር ማትረፍ ነው የምለው። ለዚህ ነው እስክንድር ነጋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አበበ በለው፣ ኢየሩሳሌም ተክለ ጻድቅ ከዐማራ ፋኖ የውስጥ ሥራ እጃችሁን አውጡ የምለው። ለዚህ ነው የዐማራን አንድነት ከሚሸራርፍ ተግባር እነ ሀብታሙ በቶሎ ይታቀቡ ዘንድ የምወተውተው። በጎጃም፣ በጎንደር፣ በሸዋና በወሎ ሀብታሙ አያሌው ከሕዝብ በተሰበሰበ ዶላር ፋኖ እየገዛ፣ እየከፋፈለ ያለውን ክፉ ሥራ ያቁም የምለው። "እኔ ዐማራ ብሔርተኛ አይደለሁም፣ ዘቅጬ ወርጄ ብሔርተኛ አልሆንም በማለት በድፍረት የተናገረው ሀብታሙ እየሠራ ያለውን ተግባር በድፍረት ዐማሮች ካላስቆሙት እመኑኝ ዐማራ ኪሳራ ይደርስበታል።
"…ሀብታሙ አያሌው ትናንት በምን እንደሆነ በማይታወቅ ሁኔታ ከጎጃም ዐማራው ባለሀብት ከአቶ ወርቁ አይተነው ጋር በተጣላ ጊዜ አቶ ወርቁ አይተነውንም፣ ማስረሻ ሰጤንም ጥንብ እርኩሳቸውን እንዳላወጣ ዛሬ እነ ዘመነ የሚመሩት አንድ የዐማራ ፋኖ በጎጃም መመሥረቱን ተከትሎ በጎጃም ክፍፍልን ለመፍጠር በሙሉ ኃይሉ ከአበበ በለው ጋር ተናብቦ በመሥራት ትናንት ሰካራም ጠጪ ሲሉት የነበረውን የማስረሻ ሰጤን የጎጃም ዐማራ ተገዳዳሪ አድርገው ስለው ሲያቀርቡት ታይቷል። አረቄያም ተብሎ ትናንት በሀብታሙ አያሌው የተሰደበው ማስረሻም ዛሬ ጀግና ተደርጎ ሲንቆለጳጳስ ታይቷል። የግንቦት ሰባት አክቲቪስቶችና አባላት በሙሉም የማስረሻ ሰጤን ፎቶ ፕሮፋይል ፒክቸራቸው አድርገው ተከስተዋል። ተናግሬአለሁ፣ ዛሬም እደግመዋለሁ ሀብታሙ አያሌው ለዐማራ የደገሰው የጥፋት ድግስ ወለል ብሎ ታይቷል። እናም በስህተር ጎጃም ውስጥ፣ ጎንደር እና ሸዋ ወሎ ፋኖዎች እርስ በእርስ ከተታኮሱና ከተገዳደሉ ደማቸው በሀብታሙ አያሌው፣ በእስክንደር ነጋ፣ በአበበ በለው እና በኢትዮ 360 ዎች እጅ ነው። የዐማራ ፋኖ ትግሉን ከክልሉ እንዳያወጣ ነገር እየሠራ እያባላ ያለው ሀብታሙ አያሌውን ጨከን ብላችሁ ካላስቆማችሁ እመኑኝ በፀፀት የማይድን ደም መፋሰስ ይሆናል። አቢይ የተመስገን ጥሩነህን ዘመድ አረጋ ከበደን ለዐማራ ሹሞ አለጋጠበት። አቢይ እንደገና ህመምተኛውን የተመስገን ጥሩነህን ዘመድ ማስረሻ ሰጤን ከአልጋ ላይ አንሥቶ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚል ስም አሰጥቶ በሀብታሙ አያሌው በኩል ፕሮሞሽን ሥራ እንዲሠራለት ሆነ። የምኒልክ ቴሌቭዥንም በብልጽግና ባለሀብቶች እንዲደገፍ የሚል ትእዛዝ ለአንዳንድ ባለሀብቶች መድረሱ መረጃዎች እየወጡ ነው። ለምሳሌ የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መግለጫ ለሚዲያዎች ሁሉ ተልኳል። ለመረጃ ቲቪ ተልኳል፣ ለሕብር ራዲዮም ተልኳል። ለእኔም ተልኳል። ነገር ግን ከሀብታሙ አያሌው እና ከእስክንድር ዘመድ ከጋሻ ሚዲያ በቀር ያቀረበ የለም። ህብርም ሌላውም ጋር ደውላችሁ ማጣራት ትችላላችሁ። ደጋገምከው አትበሉኝ እና በሀብታሙ አያሌው፣ በአበበ በለው ስህተት ፋኖዎች እርስ በእርስ ቢመታቱ ተጠያቂነቱን ከእነርሱ ላይ አላወርድም። መዝግቡልኝ።
"…በመጨረሻም የዛሬውን ርዕሰ አንቀጼን የምቋጨው በጎንደር ነው። የእነ ሀብታሙ እጅ ጎንደርም ገብቶ ሁለት ፋኖዎችን ሲያታኩስ ውሏል። ዛሬ ይብረድ አይብረድ የማውቀው ነገር የለም። ሰኔ 30 በድጋሚ ለትግሬ ልትሞሸር እየተዘጋጀች ላለችው ጎንደር እነ ሀብታሙ በግል በገዙት ፋኖ እየረበሿት፣ ዘንዶው አቢይ አሕመድ ደግሞ በጎን ያዘጋጀላትን የጥሎሽ መዓት በተመለከተም ቆይቼ የምለው ይኖረኛል። እስከዚያው…
ጎበዝ…
"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…የዐቢይ የወለጋ ጉዞ የተጠና፣ በደንብ የተዘጋጁበት፣ መልእክቱም ለኦሮሞ ወሳኝ ነበር። በወለጋ አቢይ አሕመድ የተገኘው ዘንጦ፣ ተረጋግቶ፣ ሽር ብትን ብሎ ነው። በወለጋ ወደ እስታዲየሙ የተጠሩት ከአራቱም የወለጋ ዞኖች የተውጣጡ የብልጽግና አባላት፣ ጥቂት የኦሮሞ ወሀቢይ እስላሞችና ሙሉ በሙሉ ግን የጴንጤ አማኝ ኦሮሞዎች ናቸው የተገኙት። ዝግጅቱም መንፈሳዊ የወንጌል ኮንፍረንስ ሁላ ነበር የሚመስለው። ስብከትም ነበረው። በጌታ ያመናችሁ አዳዲስ አማኞች ወጥታችሁ ጌታን ተቀበሉ ማለት ብቻ ነበር የቀረው።
"…አቢይ አሕመድ በወለጋ ጉዞው በዚያው በወለጋ ክፍለ ሀገር አለ የሚባለው ኦነግ ሸኔ በክልሉ አለመኖሩን ቢኖርም የብልጽግና የዐማራ ማጽጃ ማሽን እንጂ የኦሮሞ ብልጽግና ጠላት ያለመሆኑን በገሀድ አሳይቷል። በወለጋ ያ ሁሉ የአቢይ ብልፅግና አገዛዝ ደጋፊ ነጭ በነጭ ቀሚስ ኮት ሱሪውን ለብሶ ስታዲዮም ሙሉ ዘጭ ብሎ ሞልቶ፣ ከስብሰባው በኋላም እየሱስ ጌታ ነው እያለ እየዘመረ ወደየመጣበት ዞን ሲመለስ አንዲትም ኮሽ ያለች ነገር የለችም። በወለጋ ያለው ኦነግ ሽሜ ከአቢይ አሕመዱ ብልጽግና የተሰጠውን ዐማራን ከክልሉ የማጽዳት የቤት ሥራ በሚገባ እንደተወጣ ማሳያው የአቢይ አሕመድ የወለጋ የስታዲዮም ትርኢት አንዱ ማሳያ ነው። የኦሮሞ አክቲቪስቶች ነን የሚሉ የአቢይ ሽመልስ ጨዋታና ቁማር ያልገባቸው ጥቂት የማይባሉ ጎጋዎችን የዚያን ዕለት አገላብጬ በርብሬ ሳያቸው ብልጦቹ ነገሩን የሚያውቁ የገባቸው በሙሉ አልተነፈሱም። ግማሽ ትግሬ የሆኑ ፀረ ዐማራ የኦነግ አክቲቪስቶች ግን ነገሩ ስላልገባቸው ሲያብዱ ነው የዋሉት። የወለጋ ኦሮሞ ማንም ሳያስገድደው፣ የቀሪ መዝገብ ሳይያዝበት፣ ይሄ ሁሉ ሕዝብ እንዴት አቢይን ደግፎ ሊወጣ ቻለ ብለው ነው ሲያብዱ የዋሉት።
"…አቢይ በወለጋ ለኦሮሞ የድል መልእክት ማስተላለፍ የፈለገው ገና ከጅምሩ አውሮጵላን ውስጥ እያለ ነው። ይኸውም ከተሾመ እስከ አሁን ያልተቀየረውን ሽመልስ አብዲሳን ሙሽራ አስመስሎ፣ አስውቦ ከፊት ወንበር አስቀምጦ፣ እሱም ሙሽራ መስሎ ከፊት ወንበር ተቀምጦ፣ በፕሮቶኮሉ መሠረት በአጠገቡ አፈ ጉባኤውን ታገሰ ጫፎን ማስቀመጥ ሲገባው ጎጃሜውን ተመስገን ጥሩነህን እና አባ አረቄ ጎንደሬውን አገኘሁ ተሻገርን ከመኝታቸው ቀስቅሶ፣ ፊታቸውን እንኳ በቅጡ ሳይታጠቡ፣ ዓይናራቸውን ሳይጠርጉ፣ ለሀጫቸው በከንፈር በአፋቸው የቡሃቃ እቃ መስሎ፣ ንፍጣቸውን በአፍንጫቸው ላይ ደርቆ እየታየ፣ አፋቸውን ሳይጉመጠመጡ፣ ቡቱቱ፣ ጨርቃም አስመስሎ እንደ አሽከር ገረድ ይዟቸው ሄዶ እነሱን ጎልቶ አስቀምጦ ነው ለወለጋዎች መልእክት ያስተላለፈው።
"…ዘንዶው አቢይ አህመድ በወለጋ ተሳስቶ በአማርኛ አላወራም። በወለጋ ያወራው ሙሉውን በኦሮሚኛ ብቻ ነው። ለመቶ ዓመታት ያህል በባርነት ውስጥ አስገብተውን የነበሩትን ሰባብረን አሁን ኦሮሞ ነፃ ወጥቷል። አንዳንድ ያልገባቸው፣ ነገሩ ያልተገለጸላቸው ጫካ የገቡ ኦሮሞ የኦሮሞ ልጆች እረፉ እና ነፃነታችሁን አጣጥሙ በሏቸው በማለት መልእክቱን አስተላልፏል። ይሄን ሲል ኦሮሚኛ የማይሰሙት እና ኦሮሞን በባርነት መቶ ዓመት ገዛው የተባለው ዐማራ ከሚባል ነገድ የወጡቱ ተመስገንና አገኘሁን አስቀምጦ ነው። ይሄ ከምር ሰዎቹ አገኘሁ ተሻገር እና ተመስገን ጥሩነህ ከተከበረ ማኅበረሰብ የወጡ እና የተገኙ ቢሆንም በግል ግን የተዋረዱ፣ የተነወሩ ሆነው ነው የተገኙት። በወለጋ ዲስኩር አቢይ በግልጽ ቃል በቃል "አሁን ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የኦሮሞ መንግሥት ነው" በማለት ዐውጇል።
"…በወለጋ አቢይ ያን ዐዋጅ ዐውጆ ከወጣ በኋላ ኦነግ ሸኔ በንዴት በሚመስል ነገር ግን በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት በቀጥታ ወደ ወለጋ ዐማሮች መንደር በመግባት ጭፍጨፋ ለመፈጸም የሞከረ ሲሆን ከአቢይ ድንፋታ ቀጥሎ ይሄ እንደሚሆን ይጠብቁ የነበሩት ዐማሮችም የመጣውን የአቢይ ሸኔ መንጋ መክተው በቂ ተተኳሽ ከነ ከባድ መሣሪያ መረከቡ ተሰምቷል። የወለጋ ዐማራ አሁን ከምንግዜውም በላይ ነቅቶ እየጠበቀ መሆኑም ተሰምቷል።
"…ዘንዶው ከወለጋው ጉዞ በኋላ በሳምንቱ በቀጥታ የሄደው ወደ ዐማራ ክልል ጎንደር ጎርጎራና ጎጃም ባህርዳር ነበር። የዐማራ ክልሉ ጉዞ እንደ ወለጋው ጉዞ የደመቀ ሊሆን አልቻለም። ያለ የሌለ ክፍለጦሮን፣ ብረት ለበስ ታንክና የአየር መቋወሚያ፣ በሰማይ ድሮንና የጦር ሄሊኮፕተሮችን አሰልፎ፣ በባዶ ድልድይ ላይ ቪድዮ እና ፎቶ ተነሥቶ፣ የብልጽግና አባላትን በሙሉ ኀዘን ላይ ያለውን ዐማራ ለማብሸቅ ነጭ በነጭ አልብሶ፣ እሱ ግን ጥቁር የኀዘን ልብስ ለብሶ፣ የተመስገን ጥሩነህን ዘመድ፣ ታላቅ ወንድሙ የታወቀ ጠንቋይ የሆነውን አረጋ ከበደን እኔ መርጬላችኋለሁ እና ተቀበሉ፣ በማለት አላግጦ፣ አሹፎ፣ ቀልዶ፣ ሳይቆይ፣ ውሎም ሳያድር ቀረጻ ከፈጸመ በኋላ በቀጥታ አዲስ አበባ ገብቶ ቆሻሻ ያላቸውን ዜጎች ያጸዳው ሰውዬ ሽንት ቤት ያስፈልጋችኋል እና ለሽንት ቤት ማሠሪያ ገንዘብ አውጡ ልመና ላይ ሲጣድ ታይቷል። የሚሠራው ድራማ መቼም ቀላል አይደለም። የሆነው ሆኖ ግን አቢይ ወለጋ ሲሄድ ወለጋ ኦነግ ሸኔ የሚባል ተቃዋሚ እንደሌለው አስመስክሯል። ወደ ዐማራ ክልል ሲሄድ ግን ባህርዳር ላይ የጀመረውን ቅዘን አዲስ አበባ ሮጦ መጥቶ ሽንትቤት ጎልቶት ታይቷል። የዐማራ ፋኖ በአንድ ዓመት ውስጥ ኃይሉን አሳይቷል።
"…አቢይ ባህርዳር ላይ "ለዐማራ ዲሞክራሲ፣ ለዐማራ መብት፣ ለዐማራ ነጻነት፣ ለዐማራ ጥቅም ስትሉ ወደ ጫካ የገባችሁ ወንድሞች እባካችሁ መገዳደል ይብቃን፣ መተላላቅ ይብቃን" ዓይነት አስመሳይ እባባዊ መርዝ ንግግር እያደረገ በዚያው ሰዓት አካባቢ በሰሜን ሸዋ በትምህርት ቤት ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽሞ የዐማሮችን ደም አፍስሷል። የደም ግብሩ ለዘንዶው ነው። ለድልድዩ ማስመረቂያ የዐማራ ደም ያስፈልግ ነበር እና ወዲያው በዚያው በዐማራ ክልል የዐማሮችን ደም አፍስሶ ገብሮላቸዋል። አቢይ ባሕርዳር ላይ የሰላም ዐዋጅ እያወጀ፣ በግብረ ሰዶማውያን ባንዲራ ያጌጠ የባህርዳር ድልድይ እየመረቀ በሸዋ ይፋት ቀጠና በቀወት ወረዳ የለን ቀበሌ ጉሎ ትምህርት ቤት ላይ በሁለት ዙር በተፈጸመ የድሮን የቦንብ ጥቃት የትምህርት ቤቱን 4 መምህራንና ከ27 በላይ ንፁሃን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በድሮኖቹ ቦንብ የተጨፈጨፉት ዐማሮቹ ከሞቱት ሌላ እግራቸውን እና እጃቸውን ያጡት ወገኖች ህክምና ተቋም መድረስ ባለመቻላቸው ብዙ ደም ፈሷቸው ቤተሰብ እያያቸው ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል። አቢይ ሰይጣን ነው። እነኚህን ሁለት ነገሮች እንዴት አንድ ላይ ይፈጽማል? የሚል ሰውም የትየለሌ ነው። ይሄ ለአቢይ የተለመደ ቀላሉ ሥራ ነው። "ለትግራይ እናቶች አፍ መሸፈኛ ማስስ እንጂ ጥይት አልልክም እያለ እርሱ ግን የድሮን ቦንብ ነበር ሲያዘንብባቸው የከረመው። ያውም በትግሬው አብርሃም በላይ ትእዛዝ። አሁን ግን አቢይ በዋናነት የሚፈልገው ዐማራን ከትግራይ በባሰ መልኩ ማጥፋት፣ ማውደም ነው። ያን ነው የሚፈልገው። ስለዚህ ፋኖ እሺ ብሎም ወደ ሰላም እንዲመለስ እኮ አይፈልግም። ከተመለሰማ ሰላም ካለማ አቢይ ሀገር መምራት አይችልም። ስለዚህ አቢይ በአፉ ጻድቅ ጻድቅ እየተጫወተ፣ ወንድሞቼ እህቶቼ እያለ እየደሰኮረ በጎን እዚያው ጎጃም ውስጥ ወጣቶችን ረሽኖ አስከሬናቸው እንዳይነሣ አድርጎ ፀሐይ ሲያስመታ ይውሏል። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።"1ኛ ቆሮ15፣20
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ዘወትር እሑድ በመረጃ ተለቭዥን በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው ሳምንታዊው መደበኛ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብራችን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።
• ትዊተር 👉 Twitter: https://twitter.com/MerejaMedia
• በራምብል 👉 Rumble: https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://www.youtube.com/watch?v=5Sg_s6sj7M0
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
"…ሻሎም ! ሰላም !
"…ልብ በሉ…አስተውሉም።
"…የጋሻ ሚድያ ባለቤቱ አቶ ወንደሰን ተክሉ ነው። አቶ ወንደሰን ተክሉ ደግሞ በፎቶ ላይ የምታዩት ከአበበ በለው ፊት ያለው በጫት ጭማቂ የሚንቀሳቀስ ሶዬ ነው። አሁን ሰውዬው ከኬኒያ ወደ ኡጋንዳ እንዲዘዋወር ተደርጓል። አቶ ወንደሰን የእስክንድር ነጋ የእህት ወይም የወንድም ልጅ ነው። የሚደጎመውም በህዝባዊ ሠራዊቱ መሪ በቦስተኑ ዶር አምሳሉ ቡድን ነው።
"…ደግሜ እላለሁ።ጎጃም ውስጥ መኖር ያለበት አንድ የዐማራ የፋኖ አደረጃጀት ብቻ ነው። እስክንድር ነጋም ለዐማራ ለመታገል ከሆነ የወጣው ገብቶ መታገል ያለበት በአንድ የዐማራ የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ እንጂ ፋኖን ለሁለት ወደሚከፍል አጀንዳ ውስጥ መግባት የለበትም። ሀብታሙ አያሌው፣ አበበ በለውም የሚፎክሩት ይሄንኑ አንድ የፋኖ አደረጃጀት ለሁለት የመክፈል አቅም እንዳላቸው ሆነው ነው።
"…ደጋግሜ ተናግሬአለሁ አሁንም እናገራለሁ በየትኛውም የዐማራ ክልል ውስጥ ፋኖና ፋኖ ከተተኳከሰ ተጠያቂዎቹ እስክንድር ነጋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አበበ በለው እና ኢየሩስ ናቸው። ግንቦት ሰባቶች እንዳሉ ሆነው ማለት ነው።
• ፋኖን አትከፋፍሉት። እረፉ። ደግሞ ናና እንዲህ ለምን ትላለህ ብለህ ስደበኝ አሉህ። ሌባ ሁላ…😂
መልካም…
"…ዘወትር የምንጠብቀው አንድ ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። ከምስጋናው በመቀጠል በቀጥታ የምንሄደው እንደ ልማዳችን ወደ ርዕሰ አንቀጽ ነበረ። እሷ ዛሬ አትኖርም። በዚሁ ወደ መወያየቱ እንገባለን።
"…የእስክንድር ጉዳይ ዛሬም ማጨቃጨቁን እንደቀጠለ ነው። ወያኔው ፓስተር ኤድሞንድ እነ ሀብታሙ በሻህን ሰብስቦ ሲያላቅሳቸው ውሏል። ዩሪ ታደሰ አስተያየት ሊሰጥ ቢፈቀድለትም ማእረግና ግንቦቴው ሀብታሙ በስድብ አጥረግርገው ሊያሸማቅቁት ሞክረዋል። ፓስተሩ ይናገር ብሎ ሲከራከርለትም ታይቷል።
"…የእስክንድርም ሆነ የግንቦቴዎቹ መዳኛቸው ዐማራውና የዐማራው ትግል ብቻ ነው። እስክንድርና ግንቦቴዎቹ መመራት ያለባቸው በዐማራው ፋኖ ሥነልቦና መመሪያና ሕግ ነው። በዐማራ መሬት ላይ ለዐማራ ነፃነት ይታገል ዘንድ የሚፈቀድለት የዐማራ ፋኖ ብቻ ነው። አይ አልፍልግም እኔ የምታገልበት መርህ አለኝ የሚል ካለ ወደ ሙከጡሪ፣ አዲዳዕሮ፣ ዳውሮ፣ ጅባትና ሜጫ ጫካ ገብቶ መታገል ይችላል። በዐማራ ቤት፣ በዐማራ ትከሻ ላይ ሌላ ደባል ትግል በዐማራ ሀብት እና ኪሣራ መታገል አይቻልም። እርምህን ታወጣለህ።
"…አይደለም ፓስተር ኤድመንድ ወያኔው ጋር አብይ አህመድ ስር ብትለጠፍ፣ ከቤት ቤት፣ ከጣሪያ ጣሪያ ስትዘል ውለህ ታድራለህ እንጂ ወፍ የለም። ይልቅ በቶሎ ንስሐ ግቡ።
"…እደግመዋለሁ። በዐማራ ምድር አንዲት ደም በወንድማማቾች መሐል ቢፈስ ከአበበ በለው እና ከሀብታሙ አያሌው ራስ አይወረድም። በዚህኛው የሠራዊት ምስረታ ላይ ቀደም ብዬ እስክንድር ነጋ እንደሌለበት የተናገርኩትን ትናንት ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ከአበበ በለው ጋር በነበረው ቆይቷ አረጋግጦልናል። ይሄ ማለት እስክንድር ወጥቶ መግለጫ እስካልሰጠ ድረስ ብቻ ነው እንደ ንጹሕ የሚቆጠረው። አለቀ።
"…ለማነሣው ሓሳብ ምላሽ መስጠት እንጂ መሳደብ ትርፉ ኪሳራ ነው።
ልጠይቅ ነኝ…!
…የካንሳስ እና ሚዙሪ አካባቢ ነዋሪዎች በሻለቃ ዳዊት እና በጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ታጋዩ ኋላ ፋኖ በሆነው በታጋይ እስክንድር ነጋ ለሚመራው የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር በከተማቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ኢቨንት አዘጋጅተው ከ60 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ አሰባስበው በተሰጣቸው መንገድ ብሩን ገቢ ያደርጋሉ።
"…ቆይተው የካንሳስና የሚዙሪ ነዋሪዎች ይህን የተሰበሰበ ገንዘብ በምን አገልግሎት ላይ እንደዋለ ንገሩን በማለት ዶክተር አምሳሉን ይጠይቃሉ። ዶክተር አምሳሉ ምን ቢል ጥሩ ነው "ዝም ብላችሁ እመኑን፣ አትጠይቁን። ይላል። ይባላል እንዴ?
"…ሕዝቡም ይህን መልስ ሲሰማ ጥያቄውን ይዞ በከተማቸው ዐማሮችን ሰብሳቢ አቶ ጌታነህ ዓለምን ይጠይቁታል። እሱም ጉዳዩ አሳስቦት የግንባሩን ሰዎች ብሩ የት ገባ ይላቸዋል። አጥጋቢ መልስ ሲያጣ የከተማውን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ ጠይቆ ከማኅበሩ ይለቃል። የለቀቀበትም ምክንያት ምንድነው ብዬ ስጠይቅ ያገኘሁትን መልስ እንካችሁ።
• አቶ ጌታነህ፦ "…በዶነር ቦክስ የተሰበሰበው ገንዘብ የት ገባ?
• ገንዘብ ያዧ ወሮ ሕይወት አድማሴ ፦ "ይቅርታ በስህተት ወደ አንድ የቻይና ካምፓኒ ገብቶብን ነው።"
"…የእኔ ጥያቄ ለፋኖ ተብሎ አሜሪካን ሀገር የተሰበሰበ ገንዘብ በምን አግባብ ነው ወደ ቻይና ካምፓኒ ባንክ የሚገባው? ይሄ ሐሰት ከሆነ ወጥተው ይሞግቱኝ። ኦዲት አስደርጉ ሲባልስ ታንቀን እንገኛለን ብሎ ጓ ማለት ምን ማለት ነው? ሀብታሙ አያሌው እየመጣሁ ነው ጠብቀኝ። አበበ በለውም እንደዚያው።
•ማርያምን አልፋታችሁም አዛኜን አልኳችሁ…! ቆይ ቻይና ምን አገባት በግንባሩ ገንዘብ…?
"…መልካም…
"…የቪድዮዎቹ ማብራሪያ ወደ በኋላ ጊዜ ሲገኝ ይኬድበታል። ኮማንደር ሀብታሙ ግን ዛቻና ቂጣቸው ገንፍሎ ወጥቷል። በሠራዊታቸው የዐማራ ፋኖን ሊውጡ መዘጋጀታቸውን አልደበቁም። የዌልስ ፋርጎው ባንክ ዶላር እና የባንክ ኦፍ አሜሪካው ዶላር በደንብ እያንዘረዘራቸው ነው።
"…ትናንት ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ከመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ጋር ይገናኛል ብሎ ያጥረገረገው ሰውዬ ዛሬ ያንኑ ሰካራም ያለውን ሰው የሕዝባዊ ሠራዊቱ መሪ ነህ ብሎ ሲክበው ይታያል። በጎጃም ምድር ደም ከፈሰሰ ተጠያቂው ራሱ ሀብታሙ አያሌው ነው። እስክንድር ነጋም በቶሎ ማብራሪያና መግለጫ ካልሰጠ ከመጠየቅ አያመልጥም።
"…ውይይታችን ይቀጥላል። የበቅሎ ልጆች ተረጋጉ። 😂 …ሓሳብ በጨዋ ደንብ ይንሸራሸር። ተንፒሱ።