የዋንጫ ዝግጅቱ ቀጥሏል…
"…የዐማራ ፋኖ በራስ አቅም እንደምታዩት ዝግጅቱን አጧጡፎ ቀጥሏል። የጥሎ ማለፍ ውድድሩም በራሱ ሜዳና በደጋፊው ፊት ስለሆነ ነጥብ ይጥላል ተብሎ አይጠበቅም።
"…ጋቸነ ሲርናው የኦሮሙማው ቡድንም በራሱ ሜዳ በሀገሪቱ ሀብት ለጥሎ ማለፍ ለዋንጫ ለሚደረገው ውድድር ዝግጅቱን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከደጋፊው ፊት ርቆ በዐማራ ሜዳ ላይ የመከላከያን ማልያ ለብሶ ስለሚገጥም የዐማራው ፋኖ ሜዳ ሳይከብደው እንደማይቀር ነው እየተነገረ ያለው።
"…የትግሬ ቡድን ከዋንጫ ጨዋታው በጥሎ ማለፍ ቀደም ብሎ የተሰናበተ ሲሆን በጥሎ ማለፍ ለዋንጫ ጨዋታ ለሚጋጠሙት የዐማራ ፋኖና የኦሮሙማው ጋቸነ ሲርና ብድን እኩል ባልሆነ ኃይል እያቃጠረ እየደገፈ እንደሚገኝ ነው የሚነገረው።
"…የዐማራ ፋኖ የሺ ዘመናት የጫወታ ልምድ ስላለው ይሄን ከ500 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የገጠመውን የጥሎ ማለፍ የዋንጫ ጨዋታ በድል ለመወጣት ሌት ተቀን በመዘጋጀት ላይ መሆኑም ታይቷል። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉት ደጋፊዎቹም ከምንግዜውም በተሻለ መልኩ የድጋፍ አሰጣጣቸው ላይ እርምት እየወሰዱ በግሩም ሁናቴ ድጋፋቸውን እየሰጡት መሆኑም ተመልክቷል።
"…ከዚህ ቀደም ፎርጅድ የፋኖ ደጋፊዎች በደጋፊ ማኅበር ስም ተመዝግበው የገንዘብ ብክነት በመፈጸማቸው የዐማራ ፋኖ ቡድን የትጥቅ አቅርቦቱ ሳስቶበት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን አሠራሩን በመገምገም አመራሮች በመቀየር እና የድጋፍ አሰጣጡንም እያዘመኑት በመሆኑ የተሻለ ከበፊቱ የተሻለ እንደሆነም ታዛቢዎች ይናገራሉ።
"…መጪው ክረምት ለተጋጣሚዎቹ ወሳኝ ወቅት ነው።
“…ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ፦ ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ?” 1ኛ ቆሮ 15፥12
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…እዚህ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር የሚገኘው የዐማራ ፋኖ የሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ይወጉት ዘንድ አቢይ አህመድ የላካቸውን እና ከሞት የተረፉትን የፌደራል ፖሊስ አባላት የተሃድሶ ሥልጠና እየሰጣቸው ነው።
• ትገባለህ መውጣት ኢንጂሩ። ቤርሙዳ ነው ስልህ…
"…ወንድ ከወንድ እንዲህ ገጥሞ ሲሸናነፍ እኮ በጣም ደስ ይላል። የእንጭቅ ልጅ ወንድ መግጠም ትቶ በድሮን ገበያተኛ እና ትምህርት ቤት ይደበድባል።
• ብልቅጥና መውደቁ፣ መደምሰሱ እንደሁ አይቀር… ማርያምን እውነቴን ነው።
"…ለሀበሻ እንኳ ችግር የለውም። ተዛዝለንም፣ ተቃቅፈንም መሄድ ልማዳችን ነው። ነገር ግን ይሄን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የማሲንጋን ፎቶ የሀገሩ የአማሪካ ሰዎች፣ ጓደኞቹ፣ ቤተሰቦቹ በሙሉ ይሄን ፎቶ የእኛ ጉድ ፕሮቶኮል የለሽ ካገኘው ሁሉ ጋር ተንጠልጣይ፣ ተሻሽ ሰው ሁናቴ ቢያዩ ሊሰማቸው የሚችለውን ስሜት አስባችሁታልን…?
Читать полностью…👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ … ከቀና አስተሳሰብ ጎን ለጎን በጥላቻ አንዱ አንዱን ዘርጥጦ ለመጣል፣ አንዱ አንዱ ላይ ሽብልቅ ለመክተት የሚደረግ የቴክቶክም ሆነ የዙም ውይይት ለማንም አይጠቅምም። በዚህ በኩል ገና ከአሁኑ እገሌ ወደፊት ከመጣ የእነ እገሌ ቡድን ሥልጣን ከያዘ ለእኛ ለእነ እገሌዎች አደገኛ ነው፣ ስለዚህ እነ እገሌን እና እገሌን ከወዲሁ ማግለል ይገባናል የሚል ንትርክ መፍጠር በፍጹም ዐማራ ነኝ ብሎ ለዐማራ ከሚታገል ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የሚጠበቅ አይደለም። በአስቸኳይ ሊታረም ይገባዋል።
"…የፋኖ ትግል በነፍጥ ታጅቦ ከተጀመረ ገና አንድ ዓመቱ ነው። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ የተፈጠረውን የፋኖ ትግል የአካሄድ ትግል ስህተት ያለበትን አካሄድ በግምገማ ገምግሞ ማስተካከያ ሰጥቶ፣ ብዙሃኑ ወደ ትግሉ የመጡቱ ዐማራ ቢሆኑም የተለያየ ርዕዮተ ዓለም ከሚከተሉ የፖለቲካ ግሩፖች የመጡ ጭምር መሆናቸው ታውቆ ወደ አንድ ወጥ አስተሳሰብ ለማምጣት ከወዲሁ መጣር ይገባል። ሽፍታ የነበሩና በዚያው የህልውና ትግሉን የተቀላቀሉ አሉ። እነዚህን ከጫካቸው፣ ከሰፈራቸውና ከመንደራቸው የወጣ አስተሳሰብ እንዲኖራቸውና ሀገራዊ አስተሳሰብ እንዲላበሱ ማድረግም ይገባል። ከአብን የመጡ የፋኖ መሪዎች አሉ። ከብአዴን የመጡ የዐማራ ፋኖ መሪዎች አሉ። ከመኢአድ የመጡም አሉ። ከአርበኞች ግንቦት 7 የመጡ የፋኖ አመራሮች እና ታጋዮች አሉ። ለኢዜማ ተወዳድረው ከምርጫው በኋላ የመጡ ፋኖን የተቀላቀሉ አሉ። በኢትዮጵያዊነት የሚታገሉ፣ መነሻዬ ዐማራ መድረሻዬም ዐማራ የሚሉ አሉ። መነሻዬ ዐማራ፣ መድረሻዬ ኢትዮጵያ የሚሉ አሉ። የግንባሩ ነኝ፣ የእዙ ነኝ፣ የፋፍዴን ነኝ የሚሉም አሉ። እነዚህን ሁሉ ወደ አንድ አስተሳሰብ ለማምጣት ድርድሩ፣ ፍትጊያው፣ ውይይቱ መፍጠን አለበት። ትግሉ ሳይቋረጥ ምክክሩ፣ ውይይቱ በስፋት መቀጠል አለበት።
"…ደቡብ ወሎ ደርሶ የመጣ አንድ ሰው እንዲህ አለ። የፋኖ ታጋዮቹ ቀለባቸውን በለስ እና ቀጋ ለቅመው ሲበሉ ያያል። ጥቂቶችም ቆሎ እየበሉ ነበር። እናም ጠየቃቸው። ሜዳው ሙሉ የገበሬ ከብት ነው። ለምን ገበሬው እንዲረዳችሁ አታደርጉም? ለምን ይሄ ሁሉ ከብት እያለ እናንተ ትራባላችሁ? በማለት ሓሳብ ያቀርብላቸዋል። መለሱለታ። እኛ ወደ ትግል ሜዳ የወጣነው የዚህን ምስኪን ሕዝብ መከራ ለማስቀረት ነው። እናስ መከራውን ለማስወገድ ወጥተን ስናበቃ ከብቱን እየበላን መከራውን ልንጨምርበት አይገባም። ይህን ካደረግንማ ከትግሬ እና ከኦሮሞ ነፃ አውጪዎች በምን ተሻልን? አይሆንም፣ አናደርገውም እንዳሉት ሲናገር ሰምቻለሁ። የዐማራ ትግል በዚህ መልክ ጥራት ባለው ከፍ ባለ ሞራል እና ስብእና መመራቱ የሚጠበቅ ነው።
"…ከዚህ በተጨማሪ ግን ዘግይተው አገዛዙ መውደቁ አይቀርም ብለው የዐማራ ፋኖን የተቀላቀሉ አንዳንድ የቀድሞ የአድማ ብተና አባላት፣ የሚሊሻ አባላት፣ የግምቦት 7 እና የኢዜማ፣ የአብንም አባላት ደርሰው መጥተው በፋኖ አመራር ላይ ከመሰየማቸው በአንድ አንድ አካባቢዎች በሕዝቡ ላይ እያፈጸሙ ያሉት ሰቆቃና ግፍ ህወሓትን የሚያስናፍቅ እንደሆነ ከሚደርሱኝ መረጃዎች እያየሁ ነው። የሸኔን መንገድ ተከትሎ ዐማራውን እያገቱ ሚልዮን ብር ክፈሉ ማለት እጅግ አስነዋሪ፣ አንገት ሰባሪ ድርጊትም ነው። ብአዴን በነበሩ ጊዜ ይታገሉአቸው የነበሩትን በአንድ ጊዜ የፋኖ አመራር በማድረግ መልሰው እነዚያኑ ብአዴን ሳሉ የሚያሳዱአቸው የፋኖ አለቆች አድርጎ መሾሙም ትክክል አይመጣም። የፋኖ አመራር ሆነው እነርሱ ቤተሰቦቻቸውን ክፉ እንዳያገኛቸው ወደ አዲስ አበባ ልከው ሲያበቁ ከሀገሩ መውጫ፣ መሸሻ የሌለውን ምስኪን የዐማራ ሕዝብ እንደ ሸኔ እያገቱ በረሀ ተቀምጠው ጮማ እየቆረጡ ዝንጥ ብሎ የማፍያ ኑሮ መኖር እጅግ አስነዋሪ ድርጊት ነው። ቆይቶም መዘዙ ከባድ ነው።
"…እንዴት ሰው ከደሀ ገበሬ ላይ ብር ተቀብሎ አዲስ አበባ ለላካቸው ቤተሰቦቹ ከደሀ ገበሬው ላይ በእገታ የተቀበለውን ብር ለቤት ኪራይ፣ ለትምህርት ቤትና ለቀለብ እየላከ ለዐማራ ነው የምታገለው ይላል? አገዛዙ ዝረፉ ብሎ አሰልጥኖ የላካቸውን በፋኖ ስም የሚነግዱትን በተለያየ ጊዜ እውነተኛ ፋኖዎቹ እያጋለጡ በአደባባይ እየገረፉ ሲያዋርዷቸው ባየንበት ዓይናችን ፋኖ ነን ብለው በሚዲያ የሚቀርቡ፣ ሕዝቡም በፋኖነት አምኖ የተቀበላቸው የሚታወቁ የፋኖ አካላት ግን በእንደዚህ ዓይነት ነውር ውስጥ መግባታቸው እጅግ ፀያፍ ነገር ነው። ይሄ ነገር ከአሁኑ በእንጭጩ ካልተቀጨ በቀር ወደፊት የሚያመጣው አደጋ ከባድ ነው ብቻ ሳይሆን የከፋም ጭምር ነው። መቼም ተጨባጭና ዘግናኝ መረጃ ሳልይዝ እንደማላወራ ይታወቃል።
"…ያም ሆነ ይህ የዐማራ ፋኖ ትግል ሃላል ነው። የዐማራ ትግል መቅደሱ ክፍት ነው። መንበሩን እያየህ በክብር፣ በፍርሃት የምትመለከተው ነው። ቆሻሻ ሰገራም በረገጥክበት ጫማህ ዘው ብለህ የምትቀላቀልበት አይደለም የዐማራ ትግል። ነጭ ሽንኩርት በልተህ አፍህን፣ ምላስህንም ሳትታጠብ ከነ ክርፋታም፣ ግማታም፣ ጥንባታም አፍህ ዘው ብለህ ገብተህ የምታግማማውም አይደለም የዐማራ ትግል። እጅህንም፣ መላ አካላትህንም ታጥበህ፣ ነጭ በነጭ ሸማህን ለብሰህ የምትገባበት ትግል ነው የዐማራው ትግል። ታጠብ አልኩህ።
"…ከዚህ በፊት እንዳልኩት የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ትግል ጨለማ ነው። ጥቁር ነው። ጨለማና ጥቁር ደግሞ ነገሮችን ይሰውራል፣ ይሸሽጋል፣ ይደብቃል። ለዚህ ነው የትግሬ ነጻ አውጪዎች ሚልዮን ትግሬ አስፈጅተው ምንም እንዳልተነካባቸው አሁንም እየሳቁ የሚሽለጠለጡት። የኦሮሞውም እንደዚያው ነው። የዐማራ ትግል ግን ነጭ ወረቀት ነው። ፀአዳ ፏ ያለ ሃጫ በረዶ የመሰለ ትግል ነው። መንገደኛ ሁሉ ሲያየው ፐ ብሎ የሚያደንቀው። በዚህ ነጭ ፀአዳ ሃጫ በረዶ በመሰለ ትግል ላይ የፈለገ ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ ኢንጂነር፣ ቄስም ሆነ ሼክ፣ ጋዜጠኛም ሆነ ኢንቬስተር፣ ወላ ያፈለገው ይሁን ትግሉን ቢቀላቀል መደበቅም፣ መሸሸግ አይችልም። እንደ ትግሬና ኦሮሞ በሀሰት ትርክት፣ በቀይ እና በጥቁር ከለር ውስጥ ለመደበቅ አይመችም። ነጭ ወረቀት ነው የዐማራ ትግል። ጥቁር ነጥብ ይዘህ ብትመጣበት ጎልጉሎ ያወጣሃል። ስህተትህ ነጥብ ቢያክልም አገልቶ ያወጣሃል። የዐማራ ትግል ቆሻሾችን አይደብቅም። መደበቅም የለበትም።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
መልካም…
"…ዘወትር ያመሰግን ዘንድ፣ የትንሣኤውንም ዐዋጅ ያውጅ ዘንድ የሚፈለገው የአመስጋኝ ቆጥር ሞልቷል። ከምስጋናውና ከክርስቶስ ትንሣኤ ዐዋጅ በመቀጠል በቀጥታ የምናመራው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ደግሞ አንድ ጊዜ ትጥቅ ፈታ፣ ሌላ ጊዜ ሊፈታ ነው፣ አሁን ደግሞ ሊፈታ ነው፣ ወደፊት ይፈታል 😂 እየተባለ በፈረንጅ አፍ፣ በትግርኛና በአማርኛ ጭምር ዜና ስለሚሠራለት እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም ስለሚባለው ስለ ወያኔ ሠራዊት ጉዳይ በስሱ እናወራለን።
"…የፋኖስ ጉዳይ ትግሉ እንዴት እየሄደ ነው? የሚለውንም በስሱ እንመለከትና ከዚያ ደግሞ የእናንተ ሓሳብ ይከተልና ስንወያይ እንውላለን።
"…አይታችሁ፣ ተመልክታችሁ እንደሆነ በፔጄ ላይ ኮተታም አስተያየቶች ቀርተው አንጀት የሚያርሱ፣ ዕውቀት የሚጨምሩ፣ ብሉኝ፣ ብሉኝ፣ ጠጡኝም የሚያሰኙ ግሩም ግሩም የሆኑ በምርጥ ባለሙያ የሚዘጋጁ ሓሳቦች በገበታው ላይ በነፃ እየቀረቡ ነው። ጣታቸውን ቁርጥማት አይንካው። ብዕራቸው ይለምልም።
"…ይህ በሆነ ጊዜ ባለጌ፣ ተሳዳቢውን ጣቴን ሳይደክመኝ እያጸዳሁት ነው። ረባሽ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል እንዲሉ ሰካራሞች ረባሽ፣ አለሌ፣ የሓሳብ ድርቅ ያጠቃውን በማስወገድ ስድብ ፈርተው፣ ሓሳባቸውን መሸጥ፣ ዕውቀታቸውን ማካፈል የሚፈልጉትን ወደፊት እናመጣቸዋለን።
• ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?
"ኦሮጵያዊው ጳጳስ እንዲህ ነው የሚሉት"
"…ሀገራችን ኦሮሚያ ነው፣ እምነታችን ተዋሕዶ ነው። ፓትሪያሪካችን አንድ ነው። ተሥሎ አለ ነገ ከመጣችሁ ትጎበኙታላችሁ።
1• ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ
2• ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ
3• ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት
4• ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
5• ይዘሉታል፣ አይጠሩአቸውም
6• ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ናቸው። 7 ተኛው ደግሞ ለኦሮሞ ይገባል። አዎ ይገባል። ሥልጣን ላይ ያለው ኦሮሞ አይደል? አዎ 7ተኛ ፓትርያርክ ለኦሮሞ ይገባል። የኦሮሞ ፓትርያርክ አያስፈልገንም ወይ? ባርነትን መቃወም፣ መዋጋት እዚህ ላይ ነው እንጂ መንደር ለመንደር እየዘሮ ከበደ እርዳኝ፣ አለሚቱ እርጂኝ፣ ትግል ላይ ነንና ቲሸርቲ እርዱን እያሉ ሰው ማታለል እይደለም፣ የሚታለልም የለም።
"…ትግሉ ያለው 7ተኛ ፓትርያርክነት ላይ ነው። መታገል ከፈለግክ ከእኔ ጋር 4ኪሎ ናና ኦሮሞ ፓትርያርክ ይኑረው እያልክ ጩህ። ትግል ማለት ይህ ነው። ይህ ነው እንጂ ትግል ማለት፣ ያ ቁልቢ ገብርኤል ያለውንና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚገኝውን ብርና ወርቃችንን ትተን እዚህ ተገንጥለን ብንቀር ወደ ድህነት ልንገባ ነው አይደል እንዴ? ለማን ልንተወው ነው? እሱም እኮ የእኛ ነው። እሱን እየተካፈልን እኖራለን እንጂ እዚህ ተገንጥለን ወደ መንደር ገብተን ከድሆች ላይ ገንዘብ ለመዝረፍ አይሆንም።
"……እንደከዚህ ቀደሙ ከዚህ ከአጥቢያ ወደ 4 ኪሎና 5 ኪሎ የሚሄድ ብር የለም። ከ4 ኪሎና 5 ኪሎ ወደ ታች የሚመጣ እንጂ እንደ ድሮው ወደ ላይ ማጓዝ አይቻልም። 👏👏👏👏 እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ለኦሮሞነት መቆም፣ ለዚህ ሕዝብ መቆም። ደግሞም በወሬ አይደለም። በፕሮፓጋንዳም አይደለም። በሥራ ነው እንጂ። ይላሉ 7ተኛው የኦሮጵያ ዕጩ ፓትርያርክ።
• እስቲ አስተያየት ስጡበት።
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ህወሓት እና ብልፅግና ተስማምተው ህወሓት ወደ ማዕከላዊው መንግሥት ቀርባ ቁልፍ ቁልፍ የወሳኝነት የሥልጣን ሥፍራዎችን የምታገኝ ከሆነ አሁን በፓትርያርክነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እየመሩ ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በዕድሜ ምክንያት እንደራሴ ተሹሞላቸው አረፍተ ዘመን እስኪገታቸው ድረስ ወደመረጡትና ወደ ወደዱት ገዳም ገብተው ቀሪ ዘመናቸውን በዚያ ሊያሳልፉ እንደሚችሉ እንደተስማሙ ጭምር ያልተጣራ ያልተፈተገ ገብስ ወሬ እየተሰማ ነው።
"…ከዚያ በፊት በኢትዮጵያ የተሾሙት ቅዱሳን ፓትርያርኮች ከዐማራና ከትግሬ ስለነበር አሁን ግን ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀጥሎ የኦሮሙማው መንግሥት 7ተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ነገዱ ከኦሮሞ ለሆነ ወገን የግድ እንዲሰጥ መግባባት ላይ መደረሱም ነው የሚነገረው። ይሄን ጉዳይ ሊቃወሙ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩና ለምን ሊሉ ይችላሉ ብለው ያሰቧቸውን የማኅበራት መሪዎች እና ግለሰቦች ጭምር በሙሉ ከወዲሁ ወደ ማጎሪያ ጣቢያና ወደ ዘብጥያ እንዲወርዱ የተወሰነ ሲሆን ከዘብጥያ መውረዱ በተጨማሪ ተቃውሞ የሚያስነሣ ካለ ለማስደንገጥ ያህል እንደ ቀልድ የሚገደሉም ይኖራሉ እየተባለም ነው።
"…በተለይ ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በቀር በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ መንግሥታዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ተቋማት በሙሉ ለምሳሌ የፕሮቴስታንትና የእስልምናው መጀልስን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በኦሮሞ ነገድ ተወላጆች ተይዞ ከእነዚህ ውስጥ በማይታወቅ ኃይል ያም ኃይል እግዚአብሔር ነው ብለን በምናምን በእኛ በእርሱ ፈቃድ ሳይሳካ ቀርቷል። ጨፍጭፈውም አልተሳካም። እናም ይሄን በቁጥጥራችን ስር ሳናስገባ የቀረነውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኦሮሞ ነገድ አባል ለመምራት የተፈለገው ዓይነት ዋጋ መከፈል እንዳለበትና በዘመነ ብልፅግና ይሄን ታሪክ ሳናሳካ ከሥልጣን መውረድም፣ መወገድም የለብንም መባሉ ነው የተሰማው። ይሄንንም ለማሳካት የኦሮሙማው አገዛዝ እስከአሁን በታማኝነት ሲያገለግለው በኖረው በዳንኤል ክብረት ላይ ሸክሙን መጣሉ ነው የሚሰማው። በዳንኤል የውስጥ አዋቂነትና መሪነት 7ተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ነገዱ ከኦሮሞ ወገን የሆነ ለመሾም ከጫፍ መድረሳቸው እና የምረጡኝ ዘመቻ መጀመሩም ነው እየተነገረ ያለው።
"…አምሳሉ ፍሬንዳችን አባ ተክሌ ኋላ አቡነ ሩፋኤል አባታችን በአገዛዙ ለኦሮሙማው ፓትርያርክነት የታጩ ሲሆን አፍቃሬ ኦሮሞነታቸው እንጂ አቡነ ሩፋኤል በአባታቸው ጎንደሬ፣ በእናታቸው ትግሬ መሆናቸው አልሸሹም ዞር አሉ አሁንም ዐማራና ትግሬ ነው ፓትርያርክ የሚሆነው እኮ የሚሉ ጓ እያሉ ያሉ ኦሮሞዎች ከወዲሁ መከሰታቸው እየተነገረም ነው። "ንፁሕ" ኦሮሞ ናቸው ተብለው ለፓትርያርክነት በስም ዝርዝር የተዘረዘሩ ናቸው ተብለው የተጠቀሱት በሙሉ ወይ በእናታቸው አልያም በአባታቸው በኩል ወይም ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ዐማራ ሆነው በመገኘታቸው ኦሮሙማው በጣም ግራ እንደተጋባ ነው የሚነገረው። ጉዲ ሰዲ…
"…7ተኛው ዕጩ ፓትርያርክ እንዲሆኑ ፓትርያርክ መራጩ ዳንኤል ዓይኑን የጣለው ዕጩ ፓትርያርኩ ምንም እንኳ ነገዳቸው ከትግሬና ከዐማራ ቢሆንም በኦሮሚያ መወለዳቸው፣ የኦሮሚኛ ቋንቋንም ቢሆን በስሱ ለመናገር መሞከራቸው፣ በዚያ ላይ በጫካ ላለውም፣ በቤተ መንግሥት ላለውም የኦነግ አገዛዝ ታማኝ አገልጋይ መሆናቸው፣ በቤተ ክርስቲያኒቱም ትምህርት የገፉ ባለመሆናቸው ለመታዘዝ አረጋ ከበደን በመሆናቸው፣ የቀደመው የጵጵስና ሹመታቸውም በጋምቤላ ይኖሩ ለነበሩ ለትግራይ ባለሀብቶች አስተማማኝ ሃይማኖታዊ ከለላ እንዲሰጡ ታስቦ የነበረ መሆኑ፣ በዚያ ላይ እንደነ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በቄሮ፣ እንደነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሁሉም ነገድ የተጠሉ፣ እንደነ ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ በዝሙት ምክንያት የተጻፈ የተገለጠ መረጃ የለሌባቸው፣ ሳይነገራቸው፣ ሳይለመኑ ለአገዛዙ በፈቃዳቸው ገሌ መሆናቸው፣ ከሁሉም በላይ በዋናነት ትምሮ ላይ 0 መሆናቸው ተመራጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ነው የሚባለው።
"…ለዚህም ሲባል ከወዲሁ እነ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በራሳቸው ስህተትና ፍላጎት አሜሪካዊ ዜግነታቸውን መቀየር ባለመፈለጋቸው ምክንያት ወደ ሀገር እንዳይገቡ ከተከለከሉት አንሥቶ ዳንኤል ክብረት የሲኖዶሱ ጸሐፊ የነበረውና ወደ ደቡብ አፍሪካ በዋና ሥራ አስኪያጅነት ተመድቦ የነበረው መሪጌታ ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለ ያሬድን ወደ ዘብጥያ በማውረድ አፋር ሰመራ በረሃ ወርዶ እንዲታሰር በማድረግ፣ ዳንኤል እግረ መንገዱንም የማኅበረ ቅዱሳንን የልብ ትርታ ለማዳመጥ የማኅበሩን የሥራ አመራሮች አሳስሮ የነበረ ሲሆን የማኅበሩን ሙቀት ከለካ በኋላ ግን ሌሎቹን በዘብጥያ እንዲቆዩ በማድረግ እነሱ እንዲፈቱ አድርጓል ነው የሚባለው።
"…የሆነው ሆኖ አገዛዙ ዳንኤል ክብረትን ከተጠቀመበት በኋላ ጋርቤጅ ውስጥ እንደሚወረውረው ቢያውቅም ቂም ያለበት በሚመስል መልኩ ባሳደገችው፣ ለክብርም ባበቃችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በዚህ መልኩ መነሣቱ ግን በቤተ ክርስቲያን ልጆች ዘንድ አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል። እናም እንደተለመደው የቤተ ክርስቲያኒቱ ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የቅዱስ ሲኖዶሱ መሪ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ኖሮ የታሰበው ሁሉ ካልተሻረ በቀር ከፊታችን የምንሻገረው ነገር ግን የሚያንገራግጭ ፈተና እንደ አማኝ የሚጠብቀን መሆኑም ይሰማል። ከእስር፣ ከድብደባም አልፎ እስከ ሰማእትነት የሚያደርስ ፈተና እንደተዘጋጀልን ነው የሚሰማው።
"…የአሁኑ ፈተና እምብዛም ወደ ምእመናን ዘንድ የማይወርድ እንደሆነ ቢገመትም ቤተ ክህነቱ አካባቢ ግን ጽዳት እንደሚኖርም እየተሰማ ነው። በተለምዶ ጳጳሳቱ በቡድን በቡድን ተቧድነው ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባም ገብተው በቡድን ተቧድነው የመከሩትን ሳይሆን የጉባኤው መሪ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እሱ ባወቀ ፊታቸውን ፀፍቶ፣ አንደበታቸውን ከፍቶ ኋላ ላይ ምን ሆነን፣ ምንስ ነክቶን ነው በማለት እስኪገረሙ ድረስ ሓሳባቸውን እያስቀየረ እርሱ እግዚአብሔር የወደደውንና የፈቀደውን ይሠራባቸው እንደነበር ይታወቃል። አሁንም ካልተወን በቀር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ካልተለየን በቀር የእነ ዳንኤል ክብረት ቡድን ምንም ያህል ሴራ ቢያሴር ሊሳካለት አይችልም ነው የሚሉት አስተያየት ሰጨዎቹ።
"…መቼም የዘንድሮው ክረምት የሞት ሽረት ክረምት ነው። ፋኖም ሥልጠናውን አጠናቆ የዋንጫ ጨዋታውን እየጠበቀ ነው። በተለይ በአንዳንድ ቦታዎች ያሉ የፋኖ አመራሮች ጥልቅ ተሃድሶና ግምገማ አካሂደው እንደ ንስር ታድሰው ከተነሡ ትንሣኤ ኢትዮጵያ መቅረቡ ነው። ከቀናት በኋላ እኔ ራሴ ዘመዴ ከአየር ላይ ውጊያው ወደ ተዝረከረከ የፋኖ አማራሮች ውጊያ ሙሉ መንፈሳዊ ትጥቅ ታጥቄ መክተቴ አይቀርም። ያበጠውን አፈንድቶ ልክ እንደ አየር ላይ ውጊያው መሬት ላይም የተበላሸ፣ የተግማማ፣ የከረፋውን፣ ሕዝብን እያስመረረ ያለውን፣ በጊዜ ካልታከሙት ሕይወት የሚያጠፋውን የፋኖ አመራሮችን እና አካሄዶችን ስህተት ወደ መዋጋቱ እገባለሁ። ዐማራ ፋኖ ያሸንፋል። ነገር ግን እታገልለታለሁ የሚለውን ሕዝብ ከወያኔና ከደርግ በከፋ መልኩ የመከራ ዶፍ አውርዶ ከወዲሁ ሥልጣን ላይ ሳይወጣ የሚያሰቃይ ስመ ፋኖ ጭምብላም በመረጃና በማስረጃ በሙሉ ኃይሌ እጋፈጠዋለሁ። እኔ ብቻዬን የማይነካ ነክቼ ለመዝመት ዝግጁ ነኝ። አንድም የሚያግዘኝ ሰው አልፈልግም። ይሄን መልእክቴን የሚያነቡ የማከብራቸው ፋኖዎች በሕዝብ ላይ የሚሠሩትን
“…ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤” ሮሜ 6፥5
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…ወዳጄ አሁንም ዛሬም የፎቶ ቦለጢቃ የኢትዮጵያን ችግር ይፈታል ብለህ ትገግማለህ እንዴ?
"…የአቢይ የፎቶ ቦለጢቃ የትግራይ እናቶችን መሬት የተንጠባጠበ እህል ከመልቀም አያድንም። (ወልቃይትና ራያ ቢሰጠን እኮ እንዲህ አንሆንም ነበር በለኝ አሉህ)
"…የሚገርመው ሊስትሮዋን የጠረገችበትን ሳንቲም እንደ ደቡብ መምህራን ደሞዝ ሳይከፍላት ገፍትሯት ነው የሄደው።
"…አዛውንቷን ሴት እግሩን አስሞ ነው የሄደው።
"…ፋኖዬ ወጥር፣ ሶዬም ምንም ዓይነት መረጋጋት በፊቱ አይታይም። ደም አስክሮት እያንቀዠቀዠው ነው። ይኸው ፋኖ የታል? እኔ በነፃነት አዲስ አበባ ላይ እየተንቀሳቀስኩ ነው የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነው እየተላላጠ የሚለፋው፣ የሚደክመውመ።
"…ሳክሱም ወዙም አልቋል። ሚኒስትሩን ሁሉ ሥራ አስፈትቶ መንደር ለመንደር ማንከራተት ቀሽምነት ነው። አሁን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከአቢይ ስርስር እያለ በሊስትሮ፣ በወፍጮ ቤት አብሮት መዞሩ ከውጭ ጉዳይ ሥራ ጋር ምን ያገናኘዋል? ደግሞም እንደ ሰው ከአቢይ አጠገብ ጉብ ሲል ዞር ብሎ አይቶት ንቆት ጥሎት ሄደ። አይ ጋሽ ታዬ አጽቀሥላሴ። ሲያልቅ አያምር አሉ።
• አራጁ ሆይ ግን አትድከም። እህል ውኃህ አልቋል።
• ማኔ ቴቄል ፋሬስ…!
መልካም…
"…የለም፣ ተበታትኗል፣ ጠፍቷል። በየቦታው የተንጠባጠበውን ፋኖ ከየቦታው መለቃቀም ነው የቀረን የተባለለትን አጅሬ ፋኖን "ልዕለ ኃያሏ አማሪካ" የለም ፋኖ ሆይ አቢይ አህመድ እንዳለው አንተ እንደ ህወሓት፣ እንደ ኦነግ ክብር፣ ቦታ፣ የሚሰጥህ አይደለም እና አቢይ አሕመድ እንዳለው እዚያው ከአረጋ ከበደ ጋር በቄስና በሼክ ተደራደር። ተደራደርና ከአረጋ ጀበደ ሥር ሆነህ ብልፅግናን አገልግል የሚል ቃና ያለው መግለጫ በአምባሳደሯ በኩል አዲስ አበባ ላይ ዐውጃለች።
"…ይህን በማስመልከት በእኔና በእኔን መሰል ጓደኞቼ በኩል የተሰማንን ስሜት በዛሬው ርዕሰ አንቀጽ በኩል ይፋ አድርገን ለንባብ አብቅተናል። እናንተስ ምን ትላላችሁ። በጎደለው ሞልታችሁ እስከ መኝታ ሰዓታችን ድረስ ሓሳባችሁን መስጠት ትችላላችሁ። እኔም ቁጭ ብዬ ምሽቱን በእናንተ ምልከታ ስደመም አመሻለሁ። ከርዕሰ አንቀጹ ሓሳብ ውጪ ሌላ ቅብጥርጥር አይፈቀድም። በፍጹም አይፈቀድም።
"…በነገራችን ላይ የእኔ የዘመዴ ቤት ደረጃው ከፍ ብሏል። ወደ ሰማይ ወደ ጨረቃ ተመንጥቋል። የእኔ የዘመዴ ቤት የምታዩት፣ የምትዳስሱት ነው። በነጭ ሰሌዳ ላይ ዕውቀታቸውን፣ እውነታቸውን የሚያካፍሉን ትጉሕ ኢትዮጵያውያን እሰደባለሁ፣ እወቀጣለሁ ሳይሉ በቅንነት ሓሳባቸውን እንደ ጅረት የሚያፈሱበት፣ ለሀገር የሚጠቅም ሓሳብ የሚፈልቅበት፣ ኮሜንቶችም እንደ ርዕሰ አንቀጽ የሚኮመኮሙበት ቤት ነው። ሓሳብ የሌላችሁ በትሕትና ሓሳብ ሸምቱ፣ ግዙ። አትርፉ። በሉ እንግዲህ ዳይ…
• እንድ…ሁለት… ሦስት…ጀምሩ…!
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …እንዳይነካ ምን እናድርግ በማለትም የመከሩ ይመስለኛል። ለዚህም እንደ መፍትሄ ያቀረቡት "በሸኔ ዙሪያ የፌኩን ድርድር ለሦስተኛ ዙር አንቀሳቅሰው ሸኔም እደራደራለሁ እንዲል ማስደረግ። ሕወሓትም ራያን በመውረሩ ተጸጽቷል፣ ትጥቅም ሊያውርድ ነው፣ ከብልፅግናም ጋር ድርድር፣ ወይይት ላይ ነው ተብሎ ዜና ይሠራል። በመሐል የአቢይ ወለጋ ሄዶ፣ መምጣት፣ ባህርዳር ደርሶ መመለስ ሁላ ይወራል። ያኔ ይሄ ሾርት ሚሞሪያም ተብሎ የተሰደበ ሕዝብ ሁሉም እሺ ሲሉ ፋኖ ብቻ እምቢ አለ በማለት ያንንም በፕሮፓጋንዳ ማሽኖቻቸው በኩል በማስዋራር የመላ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ወደ ፋኖ እምቢተኝነት ላይ ብቻ በማተኮር፣ ቀሪው ዜጋም ይናደዳል፣ ሌላውንም ሁሉ ይረሳዋል። ሸኔም ራሱ ጻዲቅ መስሎ እንዲታይ ይደረጋል።
"…በዚህም አለ በዚያ አቢይ ድርድሩ በእሱ የበላይነት እንዲጠናቀቅ ነው እየፈጋ፣ እየተላላጠ ያለው። ለዚህም እደግመዋለሁ መጀመሪያ ኦሮሞውን ነቀምቴ ወለጋ ድረስ ሔዶ ኦሮሞ ከአቢይ ጎን እንዳለ ለማሳየት፣ በዚያውም ፋኖ የሚደነግጥ ከሆነ እንዲደነግጥ ለማድረግ ጣረ። ኦሮሞውንም ሰብስቦ "በግልጽ ቋንቋ ዐማራ ማለት ሲቀረው፣ ትግሬም ማለት ሲቀረው "የማይረቡት ለምን 100 ዓመት እንደገዙን፣ እንደገደሉን ታውቃላችሁ? እያለ በኦሮሚኛ ቋንቋ እና በኮዳቸው ተጠቃቅሰው ኦሮሞውን ደነፉ አስይዞ በዐማራው ላይ አስነሥቶት መጣ። ይሄም አላረካው ሲል ሁሉም ኦሮሞ በአንድነት ተነሥቶ ከጎኑ ይቆም ዘንድ ይነሳ በዚያውም ፋኖ አሜሪካንን ፈርቶ ወደ ድርድሩ እንኳ ቢመጣ እኛ ኦሮሞዎች አስፈሪ ሆነን እንድንታየውና በፎርፌ ቁማሩን እንድንበላው ኦሮሞ ሁሉ ሰልፍ ውጣ ስንለው ዳር እስከ ዳር ሴራውን አውቆ እንዲወጣልን ብለው "ለኦሮሞ ብቻ ከአፍሪካ አንደኛ የሆነውን የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን" አስመረቀ። ለዐማራው ደግሞ ድልድይ አስመረቀ። ይሄ ለኦሮሞ ምን እንደሆነ ስለሚገባዉ ከጎኔ ይሆናል ይነሣል ፋኖም አሜሪካንን እና ይሄን የኦሮሞ ኃይል ፈርቶ ለድርድር ይመጣል። ያኔ በኢትዮጵያ መንግሥትነታችን ስም ለተሃድሶ በሚል ፋኖ የሚባል በሙሉ አንድ ሳይቀር አስላጭተን እናስገባዋለን በማለት ነው እነ አቢይ የጠነዛ ቁማራቸውን በሕልማቸው የሚያልሙት።
"…አቢይ ድርድር የምትለውን ቃል ከአፉ ያወጣው በዚህ ሰዓት አቡነ አብርሃምን አስከትዬ ባህርዳር ብሔድ ፋኖ ቢያገኘኝ እንኳ ላይገድለኝ ይችላል በማለት እንደምንም ብሎ ባለው ኃይል ተፋልጦ ጎርጎራንና ድልድዩን በሩጫ አስመርቆ፣ በእስስት ባህሪው ተቀይሮ የወለጋውን የዘር ጭፍጨፋ ዐዋጁን ረስቶ አዘናግቶ፣ ፋኖን ወንድሞቼ በሚል ጨዋ ንግግር ዐማራ አረጋ ከበደን የመሰለ መንግሥት አግኝቷል ስለዚህ የሆነው ነገር ሁሉ ሆኖ አልፋል፣ እባካችሁ መገዳደል ይብቃን፣ በጫካ ያላችሁ ወንድሞች ኑና እንነጋገር፣ ከአረጋ ከበደ ስር ሆናችሁ ያወደምንባችሁን ክልል እንሥራላችሁ በማለት የቁጩ የፉገራ መልእክቱን ለፈረንጇ ለአሜሪካ ለትላንቱ ለመሲንጋ ንግግር እንዲመች አድርጎ አስቀምጦ ተመልሷል። አሜሪካም ከአቢይጋ ሴራውን ተባብራ እንዳልሠራች መስላ ፋኖን ባትደራደሩ ትጎዳላችሁ ብላ ፋኖ ፈርቶኝ ይመለሳል፣ በቃ አሜሪካ ከምጨርሰን ዘራችንን አቢይ ይጨርሰው በማለት መሳሪያዬን አውርጄ እንደ ትግሬ እገረዳለሁ የሚል መስሏት ነው ማስፈራሪያዋን ይዛ የመጣችው።
"…አሁን አቢይ ቢሳካለት እና ፋኖ በቃ ፈርቻለሁና ልደራደር ብሎ ቢመጣም እኮ የሚያረገው ያው ሥልጣንህን ልቀቅ እንዳይሉት ድርድሩን ከእኔ ጋር ሳይሆን ከአረጋ ከበደ ጋር እዚያው በማራ ክልል አድርጉ ብሎ ነው ዐውጆ የመጣው። ጨፍጫፊዋ የትግሬ ነፃ አውጪ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር፣ ጨፍጫፊው ኦነግ ኘም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ተወያይ፣ ተደራደር ተብሎ ተጨፍጫፊውና አሸናፊው ዐማራ ግን አቢይ በመረጠለት የአእምሮ ዘገምተኛ ከአረጋ ከበደ ጋር እንዲወያይ ይሰበካል። አጅሬ አሜሪካም ይሄንኑ የአቢይ ሴራ ይዛ ባትደራደሩ ትጎዳላችሁ ብላ መጣች። ስለዚህ በተሸናፊነት መንፈስ ድርድሩ ቢጀመር አንዱ ዋናዉ አቢይ የሚያረገው ነገር በቀን በሌሊት፣ በእግረኛ በአየር ኃይል ገጥሞት ያልቻለውን ፋኖ በተሃድሶ ሰበብ ፀጉሩን ላጭቶ መቀመቅ መክተት ነው። ቀጥሎ ዐማራ የተባለን እስከ ከ15 እስከ 25 ሚሊየን የሚያህለውን በመጨፍጨፍ ማጥፋት ነው። ከዚያም በጋቸነ ሲርና አማካኝነት በመላ ኢትዮጵያ ዐማሮች መኖሪያ ቤተታቸውን፣ የእርሻ መሬታቸውን፣ ፋብሪካቸውን በሙሉ በመውረስ በዶ እጃቸውን ማስቀረት ነው። የዐማራ ፋኖ መሸነፍ የዐማራን ዘር ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ ማስደረግ ነው። ይሄ የዐማራውን ንብረት ሲቆጥር እና መቼ ነው የእኔ የማደርገው እያለ በምኞት ፈረስ እየጋለበ ለሃጩን ሲያዝረበርብ እድሜውን ለጨረሰው የኦሮሞ ጽንፈኛ አሸወይና ነው የሚሆንለት። ዐማራን ለመግደል ታጥቆ ጫካ ለከረመውም፣ ላልታጠቀውም በነፃ ያድለዋል፣ ከዚያ ዐማራ ሕጋዊ ደሀ ሆኖ ከሞት የተረፈው እንደ ኩርድ ሕዝብ ሀገር አልባ ሆኖ ይቀራል ማለት ነው።
"…አሁን ሰው መረዳት ያለበት አሜሪካ ማናት? የሚለውን ነው። የአሁኑ የአሜሪካ አምባሳደር የኦሮሞ ዘር አለበት ተብሎ የተወራውን ወሬ ችላ ሳይሉ መመርመርም ያስፈልጋል። አምባሳደሩ ባለፈው ጊዜ ዓለምአቀፍ ሕጋዊ ስም ያላትን አዲስ አበባን ኦሮሞዎቹን ለማስደሰት ሲሉ ፊንፊኔ ብለው የጠሩት ያለ ምክንያት እንዳልሆነ መረዳትም ያስፈልጋል። አሜሪካ ሶሪያን፣ አፍጋኒስታንን፣ ሊቢያን ወዘተ እንዳስወደመች ሁሉ አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ ላይ ከገንጣይ አናሳ ዘረኛው ወያኔና ኦነግ ጎን ቆማ አብርሃም ሊንከናዊውን የዐማራ ፋኖን እየተቃወመች እያደረገች ካለችው በተለየ መንገድ ነው ያጠፋቻቸው? በፍጹም። ለምን ይሄ ይመጣል ብላ ዐማራው በወለጋ እና በተለያዩ ቦታዎች እንደዚያ በሜንጫ፣ በካራ፣ በፋስ፣ በመጥረቢያ፣ በጩቤ፣ በክላሽ እና በመትረየስ ሲጨፈጭፉት እና ሲዘምቱበት ሲያፈናቅሉትም እያየች ለሌላው የጮኸችውን 0.01% ለም አልጮኸችም? ሲርበው በየስደተኛ ካንፐ ድረስ ሄጄ እንደትግሬ ልደግፈው ለምን አላለችም? ዛሬስ ለምን ከአላማጣ የተፈናቀለውን ዐማራ ልክ ለትግራይ ተፈናቃዮች እንደምትለፈልፈው የተፈናቀሉም ይመለሱ እንደምትለው ሁሉ መጪው የክረምት ወራት ነው፣ የሚበሉትን ቢያንስ ከወዲሁ ይረሱ፣ ይሄ ክረምት ሳይወጣ ወደ ቀዬአቸው ይመለሱ ለምን አትልም? አትልማ። ምክንያቱም ከነገሩ ጀርባ አለችበትና አትልም።👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …አሁንም ምዕራባውያኑ ለዐማራ ፋኖ አዝነው አይደለም ድርድር ድርድር የሚሉት። የእንግዴ ልጃቸው አጅሬ ብልፅግና ወደ ሞት አፋፍ መድረሱን ሲያዩ፣ ሲረዱ ነው ድርድር የሚል ካርታ ይዘው የመጡት። ከሰሞኑ ሰፋ ያለ የድርድር ወሬ እንሰማ ዘንድም ግድ ነው። ዋናው ነጥብ ግን ይህን ወሬ የሚያራግቡት እነማን እንደሆኑ ነቅሰን ማውጣት ይጠበቅብናል። ግንቦቴዎችም በድርድር ሒሳብ
የፖለቲካ ውስጥ ሰርገው ለመግባት እያሰፈሰፋ መሆናቸውም ማወቅ ተገቢ ነው። ሌባ ሁላ…
"…በአሜሪካ ጉዳይ ሁለት ነገር ማድረግ አለብን የሚሉ ወገኖችም እያየሁ ነው። አምባሳደር ኤርሲን ማሲንጋ በአብርሃም ሊንከን ዘመን የነበረውን ጦርነት ያስታወሱትና በመጨረሻም መሪው አብርሃም ሊንከን የያዘው ሓሳብ ትክክለኛ ስለነበር አሜሪካ ወደ አንድነት መጣች ሲሉ ተደምጠዋል። ማሲንጋ ያልገባቸው በመሪ ደረጃ አብይ እና አብርሃም ሊንከን ተቃራኒ ጎራ ያሉ መሪዎች መሆናቸው ነው። የእነሱ አብርሃም ሊንከን የነፃነት እና የመሬት ባለቤትነት የነዋሪዎች ነው ሲል የእነ ዊልከስ ቡዝ በድን ደግሞ ባርነት እና መሬት የባላባት እንጂ የሕዝብ እና የነዋሪዎች አይደለም ነበር እያሉ ሲሟገቱ የነበረው። በተገላቢጦሽ እእኛው ጉድ አብይ አሕመድ አብርሃም ሊንከን መሆን ሲገባው በተቃራኒው ሀገሩን በዘረኝነት እና በባሪያ አሳዳሪነት ልምራው ሲል ነው የተገኘው። ለዚህ ነው ፋኖ ለእነ አቢይ አብርሃም ሊንከን የሆነባቸው። የፋኖ ስሙ ራሱ ነፃነት እና አንድነት ሲሆን የፋኖ አካሄድ የአብርሃም ሊንከንን መንገድ ተከትሎ ዜጎችን የሀገር ባለቤት የሚያደርግ የአሜሪካ ዓይነት ለውጥም ሊያመጣ ሆነ። ይህ ከሆነ ደግሞ ነገ በምሥራቅ አፍሪካ ተገዳዳሪ ኃይል ይሆናል። ስለዚህ ፋኖ ወይ መሸነፍ አለበት ካልሆነ ደግሞ በአሜሪካ ስር መሆን አለበት። ብልጽግና ደግሞ አሁን ባለው አሰላለፍ ለአሜሪካ ጥቅም ስጋት አይደለም። ኤርትራ እና ዐማራ ወደ ምሥራቅ አውሮጳ ሩሲያ ሊሄዱ ይችላሉ የሚል ግምት ቢወስዱም አይፈርድባቸዉም። መቼ ፖለቲካ ብልጫ እንጂ ጽድቅና ምናኔ አይደለም።
"…ስለዚህ ይላሉ ዐማሮቹ እንደ እስራኤል ግዛታችን በሰሜን በደቡብ፣ በምሥራቅና በምዕራብ ከዚህ ከዚህ ሀገር ጋር የሚዋሰን ዐማራ የሚባል ሀገር ልንፈጥር ነውና አግዥን የማታግዢን ከሆነና ይሄን አረመኔ ሥራት፣ ዘር አጥፊ ጨፍጫፊ ሥርዓት እየተንከባከብኩ እቀጥላለሁ የምትዪ ከሆነ በግልፅ ከሩሲያ እና ከሌሎች ፀረ አሜሪካ ኃይሎች ጋር ከአረቦችም ጋር ቢሆን መወገን እንችላለን። የትግሬና የኤርትራ መንገድ ለአሜሪካ ፖሊሲ የማያስፈልግ፣ የኦነግም መንገድ ለአሜሪካ የማይመች፣ ዘረኝነትን፣ መከፋፈልን፣ መለያየትን የሚመርጥ፣ የአብርሃም ሊንከን መንገድ ያልሆነ መንገድ እየተከተሉ በብሔራዊ አንድነት የምታምነው አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ሲሆን ግን አናሳዎቹን ወያኔና ኦነግን ማቀፏን በመቃወም ዐማራ አሜሪካን ራሷን ሊያስተምራት ይገባል። ትግራይ እና ኤርትራ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሕዝብ መኖሪያ ነበሩ፣ ናቸውም። ለጥቅማቸው ሲሉ ግን አረብኛ ቋንቋና አረባዊነት የተቀበሉት ወደው አይደለም። ስለዚህ ይላሉ ዐማሮቹ ለአሜሪካ በግልጽ ፖሊሲ ነድፈን መጀመሪያ ደጋፊሽ ነን ደግፊን እንላታለን። አይ ከእናንተ ይልቅ ገንጣይ አስገንጣይ፣ ወንበዴ ዘረኛ ከፋፋዮቹን ወያኔና ኦነግን ነው የምሰማው ብላ አልሰማም ካለች በግልፅ ከወዳጅ አጋር ሀገር ፍለጋ ዓይናችንን ወደ ማማተሩ ወደ መሄድ እንገደዳለን ነው የሚሉት።
"…አሁን ለዐማሮቹ የውጭ ዲፕሎማሲውን የሚያሰናስሉበት፣ የሚያቀላጥፉበት ወቅት ነው። ፋኖ ከጫካ ዓልፎ በነጩ ቤተ መንግሥትም የግድ አጀንዳ ሆኗል። የድሮን ጭፍጨፋ፣ የሚሳኤል ድብደባም እንደማያጣፋቸውም ታውቋል። እናም ውሳጣዊ ጉዳይን ለጥቃት ላለማጋለጥ ሲባልም በረጋ መንፈስ በመመካከር እንደ ንሥር ታድሶ መምጣት የግድ ይላል። ይህ ካልሆነ አሜሪካ በአይን ቁራኛና በጥርጣሬ እያየችን መሆኑን አውቀን ወይ በጉያዋ እንግባ አልያም በራሷ ጥቅም እንምጣባት። ከቶ የፋኖ ትግል የአሜሪካ ዓይነት ጦርነት ሆኖ ውጤቱ ነፃነት እና አንድነት ይሁን። በዚህ መንገድ ተሂዶ የዐማራ ፋኖ ካሸነፈ የአብርሃም ሊንከኗ አሜሪካ ዳግም ትፈጠራለች። ለዚህ ነው ለአማሪካ ለዋናዋ በጥባጭ ለራሳ ነግሮ ከጎናችን ሁኚ ብሎ መጠየቅ፣ አይ እምቢኝ አሻፈረኝ የወያኔና የኦነግ መንገድ ነው የሚስማማኝ ካለች መልካም ብሎ በተቃራኒው መንገድ መቆም። ያኔ ወዳ ሳይሆን በግዷ ትመጣለች። ዐማራን አሜሪካ የናቀችው እና እንደ ቆሞ ቀር ያየችው ዐማራ በዲፕሎማሲው ጎራ ዝም፣ ጭጭ፣ ጮጋ ስላለ ነው። የዐማራ ቦለጢቀኞች እስከ አሁን ድረስ ዐማራ ነኝ የሚል ድፍረት በማጣታቸውና በእነ ግንቦቴዎች የዛር መንፈስ የታሰሩ በመሆናቸው ነው። የተማሩ ዐማሮች ቅርፊቱን ሰብረው ከወጡና በዐማራ ሥነ ልቦና፣ በዐማራነት ልክ እንደ ትግሬው እና ኦሮሞው ደፈር ብለው ማውራት ከጀመሩ ነገሩ ሁሉ እዚያው ላይ ያልቃል። የዐማራ ስም ይዞ ውስጡ ትግሬና ኦሮሞ፣ ግንቦቴም ሆኖ ለዐማራ መከራከር ግን አይቻልም። ጥርት ያለ ዐማራዊ የዘር ሀረግ አሁን ላለው የዘር ፖለቲካ የግድ ነው።
"…አሜሪካ በዚህ ሰዓት በግልጽ በአደባባይ ለፋኖ መግለጫ ያቀረበችው ለምንድነው? መግለጫው የማስፈራራት ይዘት ለምን ያዘ? በግልጽ አንደራደርም ብለው የወጡትንና አሁን ድረስ በግልጽ ዐማራን እየጨፈጨፉ ያለውን እነ ኦነግ ሸኔን ጨዋ አድርጋ ሥላ ስታበቃ አሁንም የመደራደር ፍላጎት ያላቸው በማስመሰል በአደባባይ መናገሩ ለምን ተፈለገ? ወዳጄ አሁን አቢይ በትግራይ፣ በዐማራና በኦሮሚያ ሀገር የማስተዳደር ህልሙ እንደተጨናገፈበት ዐውቋል። ኦሮሞ እንኳ አይጨበጥም ወለጋ ምስክር ነው። ትግሬም ነፋስ ነው አይጨበጥም አቢይ ጨፍጭፎት፣ ሚልዮን ትግሬን አርዶ አሁንም ሲገረዱለት ስለሚታይ አይጨበጡም። ወልቃይትና ራያን በአቢይ በኩል እናገኛለን ብለው ተስፋ ስለሚያደርጉ አይጨበጡም። የሆነው ሆኖ ግን አቢይ አሕመድ ትግሬን ከጎኑ ለማሰለፍ ሲል ገንዘብ እየሰጠ ሰክረው ደጅ እንዲያድሩ ቢያደርጋቸው እንጂ ደፍሮ ወርቂ ሕዝቢ ብሎ እንደ ቀድሞው ሊገዛቸው አይችልም። ፔሬድ አልፏል ዕድሉ።
"…በዐማራ ግን ሙሉ በሙሉ ተቀባይነቱን አጥቷል። ዐማራ አቢይን ለስቅላት ፍርድ ነው የሚፈልገው። አቢይ አሁን ባህርዳር እንኳ ተመልሶ መሄድ የማይችልበት ደረጃ መድረሱ ታይቷል። ስለዚህ እነ አቢይ አሜሪካ ፋኖን እድታስፈራራለት ፈልጓል። አሜሪካ ኦነግ ሸኔ ለእርሷ ፖሊሲ የሚመች ስለሆነ ኢትዮጵያን የሚያዳክም ዐማራን የሚያጠፋ የማይጠየቅ ማሽኗ ስለሆነ ለሸኔ ከለላ ሰጥታ ኢትዮጵያንም ዐማራንም ሊያተርፍ የሚችለውን ፋኖን በግልፅ በመግለጫ በስውር ወንጀል በመደበቅ፣ አቢይን፣ ወያኔንና ኦነግን በመደገፍ ስትወግረው ትታያለች። አሜሪካ ሀሳቧ የማስፈራራት ስሜት እንዲኖረው የፈለገችው ለሳይኮ ነው። እነርሱ ለምሳሌ አሜሪካ ሰሜን ኮሪያን ልመታ ነው። ኒዩኩለር የጦር መሣሪያ ልትጠቀም ነው ብላ ታስወራለች። ሰሜን ኮሪያም እንደዚያ ትቀደዳለች። ነገር ግን በሳምንቱ ያ ሁሉ ቀደዳና ዓለምን ያሸበረ ወሬ ወፍ የለም። ዝም ብለው በወሬ የሚፈታፈቱበት ነው ማለት ነው። አሁንም የአሜሪካ ፋኖንን የተናገርኩት፣ የተቆጣሁት እኔ አሜሪካ ስለሆንኩ ፋኖም የእኔን ቁጣ ሰምቶ፣ ተንበጭብጮ እታረቃለሁ የሚል ከሆነ እንሞክረው፣ የሚለውንም እንስማ ነው። ጨዋታው የሳይኮ ነው።
"…አሜሪካ የዐማራ ገዳዮችን፣ የዐማራ ጨፍጫፊዎቹን እነ…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም…
"…ዘወትር ጠዋት ጠዋት ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው የአመስጋኝ ቁጥር ሞልቶ ፈስሷል። የትናንት ማታው መመሪያዬ በመከበሩ ምክንያት በምስጋና መሃል ጣልቃ በመግባታቸው የተቀሰፉት ብዛታቸው እስከአሁን ከ5 አልበለጠም። እንዲያውም ባን ያደረግኩት የሁለት ስድአደግ ተሳዳቢዎችን ፀያፍ ስድብ ብቻ ነው። የቀሪዎቹን ያለማወቅ ነው ብዬ ኮመንታቸውን ከትንሣኤው ዐወጅ መሃል የማንሳት ሥራ ነው የፈጸምኩት።
"…ከምስጋናው በኋላ በቀጥታ የምናመራው ወደ ተወዳጁ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችንም በትናንቱ የአማሪካ ለፋኖ "ብትደራደሩ ይሻላችኋል" የሚለውን በቁጣ፣ የትእዛዝ የሚመስል መግለጫን በተመለከተ ነው ርዕሰ አንቀጻችን የሚዳስሰው።
"…ፎቶዎቹን ስታዩ፣ ስትመለከቱ ሀገሪቱ የትግሬና የኦሮሞ ብቻ አይመስልም። 😂 ጉድ እኮ ነው። ፈጣጣነት። ታስቁኛለሽ። አይ ፋኖ እንዲያው ምን አባቴ ላድርግህ የእኔ ጌታ። 🙏💪💪🏿✊
"…እናስ ወዳጅ ጓደኞቼ ሆይ ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?
• እስከ ነገ ጠዋት…
"…በአየር ላይ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ነገሩ አሳስቦናል ያሉና እንደራሴ የማምናቸው፣ በስም የተጠቀሱና በፎቶግራፍ የተገለጹት ራሳቸውም ከእኔ በላይ ታጋይ የሆኑ፣ ሆዳም፣ አድርባይ ያልሆኑ ታጋይ አባቶቼ አክብረውኝ መጥተው ለሆነች ጉዳይ "ጊዜያዊ" የተኩስ አቁም ስምምነት እንዳደርግ በጠየቁኝ መሰረት እነሱ ባሉኝ መሠረት ሳልጨርስ የማላቆመውን ትግል የአባቶቼን ቃል አክብሬ በእኔ በኩል ለጊዜው ከቃላቸው ላልወጣ የፈጸምኩትን ተግባር መለጠፌ ይታወሳል።
"…ከልጥፉ በኋላ ከደጅ ውዬ ኮመንት ወደ ማንበብ ስገባ ያየሁት ነገር እጅግ ነው ደስ ያለኝ። የእኔዎቹ አንባቢ ጓደኞቼ በእጅጉ ሲደሰቱ ሳይ በሌላ በኩል ጦማሩን የማያነብቡ፣ ቢያነቡም የመልእክቱ ትርጉም የማይገባቸው፣ ቢገባቸውም በእኔ ጥላቻ የናወዙና የሚያደርጉ የሚሠሩትን የሚያሳጣቸው፣ በግል ጠብ ሳይሆን የተነሣው የሓሳብ ሙግት እንደሆነ የተጠየቀው ጥያቄ መሆኑን የማያውቁ ገተቶች የአባቶቼን ምክር ተቀብዬ "ለጊዜው" ልብ አድርጉ "ለጊዜው" በቀነ ገደብ የታጠረ፣ ይፋ ያልሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች የተካተቱበትን የተኩስ አቁም ስምምነት መፈጸሜን ተከትለው የበለጠ ባለጌ ስድ አደግ ሲሆኑ አየኋቸው።
"…በጀመርኩት ጦርነት የተገኘውን ድል የምናውቅ እናውቀዋለን። አላቆመውም እንጂ ከእንግዲህ ባልቀጥልበት እንኳ ረጅሙን ፈትፋች እጅ መቁረጤ ይታወቃል። እንዴት እንደምሠራ፣ ለምን እና መቼ ምን መሥራት እንዳለብኝ የማውቅ እኔ ሆኜ ሳለ "የእንቅቡ እያለ የምጣዶቹ የመንጫጫት" ነገር የሚጠበቅ ግን ደግሞ አስቂኝ፣ አስገራሚም ነበር። ለማንኛውም እኔ የጀመርኩት ነገር የብልፅግናን ቋንጃ የቆረጠ፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎና በጎንደር መሬት ላይ ያሉትን የፋኖዎችን መንደር በደስታ ያስፈነጠዘ፣ አይነኬ፣ አይሞከሬ የሚመስሉ ትናንሽ ጣኦታት በሙሉ የተነፈሱበት፣ ከእንግዲህ ወዲያ በዐማራ ትግል በፋኖ የውስጥ ጉዳይ ማንም እንደፈለገ ተነሥቶ መፈትፈት እንደማይችል በማኅተም አስረግጬ ለዓለሙ ሁሉ ያወጅኩበት የድል ጦርነት ነበር ያደረግኩት። ብዙ ሺ ቁስለኛ የተረፈረፈበት ጦርነት።
"…ቢያንስ ቢያንስ እንኳ የስንቱን ጭንብል እንደገፈፍኩ የማውቀው እኔ ዘመዴ ነኝ። የኦነግ ፔጆች፣ የትግሬ አክቲቪስቶች፣ የብልጽግና ካድሬ በሙሉ "ዘመድኩንን አሁን ነው ያገኘነው ብለው በጀማ ለመሳደብ አሰፍስፈው የመጡበት፣ የትግሬው ፓስተር እነ ኤድመንድ እንኳ የዘመድኩን በቀለ ትግል ለዐማራው ትግል ይጠቅማል? ወይስ አይጠቅምም? ብለው እነ ሀብታሙ በሻህ፣ እነ ቅማንቴው ሳሚ፣ ምስኪን ተብታባው ወዳጄ ማዕረግ ዘካዛንቺስ፣ እንደኔው የሀረርጌ መረታ ቆቱ የግንባሩ የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት አዝማች፣ የእነ ማዕረግ አለቃ የሆነው የኦቦ ሀብታሙ በቀለ ጉደታን ጭንብል የገፈፍኩበት ነው። እነ እስታሊን ሳይቀሩ ዋይዋይ ያሉበት፣ እነ ደሩ ዘሐረሩ እንኳ የወዳጄ የእስክንድር ነጋ ደጋፊ ሆነው የተገለጡበትን ከባድ የጨበጣ ውጊያ ነበር ሳደርግ የከረምኩት። 💪🏿✊💪
"…ሚሽኑ በሚገባ ግቡን መትቷል። በዐማራው ትግል ውስጥ እጀ ረጃጅም አይነኬ ጣኦታት በሙሉ ደቅቀዋል። ቢያንስ ቢያንስ ከ100%ቱ ለፋኖ ሾተላይ ከሆነው ከባድ ደንቃራ የሆነ ችግር ውስጥ በመብረቅ ብልጭታ ታህል የችግሩን 0.5 % በመጥቀስ የመሬት መንቀጥቀጥ ፈጥሯል። ዝምብሎ ማንም አይነካኝም፣ ማንም አያየኝም ብሎ መፏለል እንደማይቻል በገሃድ ታይቷል። እናም ከእንግዲህ "ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ ነው ወዳጄ። አለቀ። ውጊያውም ይቀጥላል።
"…ሌላው በሺ የሚቆጠር የግንባሩን፣ የግንቦቴውን፣ የብልፄ፣ የሂዊና የኦነግን ድብልቅልቅ ሠራዊት እሬቻውን አብልቼዋለሁ። ሙልጭ አድርጌ ነው ድራሽ አባታቸውን ከፔጄ ያጸዳሁት። እኔ ያላየኋቸውን ባለጌ ስድአደጎችንም እናንተ "block” ዘመዴ ብላችሁ የጠቆማችሁኝን በሙሉ ጠራርጌ አጽድቻለሁ። አጀንዳ ለማስቀየስ የሚመጣውን፣ በሰላም የሚሟገቱ፣ አስተያየት የሚለዋወጡ የቤቴን ደንበኞች የሚሰድቡ በሙሉ ተጠርገው ወጥተዋል። ቤቱ የጨምላቆች ቤት አይደለም። የነውረኞች ቤት አይደለም።
"…በእናትህ ብሎክ አድርገኝ ብሎ የሚቀልድ ሳገኝም ሰከንድ አላቆየውም። ሰከንድ አልኳችሁ። ሌላው ደግሞ ጡዘቱን የሚፈልግ ተንኳሽ አለ፣ የተቆረቆረ መስሎ፣ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆኖ ነገሩን ለማጋጋል የሚመጣም አለ። እኔ ዥልጥ አይደለሁም። የማኅበራዊ ሚዲያ ኤክስፐርት ነኝ። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከብቶችን እንዴት እንደማግድ በደንብ ነው የማውቀው። ሰዎችን እንዴት አክብሬ እንደምይዝም በሚገባ ነው የማውቅበት። አቃጣሪ፣ አስመሳዩን፣ ሸውከኛ መንደሬውን፣ ጨጓራውም ካሊሲውም የጨሰውን በደንብ ነው የማውቀው። ፎታቹን፣ አዛኝ ቅቤ አንጓቹንም አሳምሬ ነው የማውቀው። የተበላሹ፣ የተመረዙ እንቁላሎችን ከቅርጫቴ ወዲያው ሌላውን ሳይመርዙብኝ በአየር ላይ የማሰናብታቸው።
"…ሌላው ቢቀር ጠዋት ጠዋት በእግዚአብሔር ሰላምታው ወቅት በትንሣኤው ዐዋጅ መሐል አንድም ሰው ሌላ ነገር ቢቀባጥር ወገብ ዛላውን ነው የማጸዳው። በጨዋ ደንብ የሚሞግቱኝን፣ አክብሬ እሞግታቸዋለሁ። ሙግቱ በእናትህ እንዲህ ትሁን ሲተካ አፍታም አላቆየው። እቀነጥሰዋለሁ። አንድ ሰው ፈልጎኝ ከመጣ በኋላ የቤቴን ሕግ በሰጨውም፣ አልበሰጨው፣ ተዋጠለትም አልተዋጠለት የግድ ማከበር አለበት። አይ ካለ ወደማይቀረው ወገብ ዛላ እሸኘዋለሁ። የሚቀርበት እሱ እንጂ እኔ አይደለሁ ምን እንዳይቀርብኝ?
"…ከእኔ ፔጅ ከተባረረ በኋላ እኔን መልሶ ለማንበብ ወይ የሚስቱን ስልክ፣ ወይ የባሏን፣ ወይ አዲስ ሲም ካርድ ከፍርዬ ዘንድ ሄዶ ያወጣል። እንጂ ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ቢል አበደን የእኔ ፔጅ ተመልሶ አይገባም። ሌሎች እኔን ደግፈው ሌላ ሰው የምትሰዳደቡም እንዲሁ ዕጣ ፈንታችሁ መቀሰፍ ነው።
"…አንድ ለእናቱ፣ ሺ ለጠላቱ ሆኜ ለጠላት ሁሉ የእግር እሳት ሆኜ መለብለቤን እቀጥላለሁ። ይሄን የምለው እኔ ዘመዴ ነኝ። የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ ባለ ማዕተቡ ዘመዴ ነኝ።
• ሰምተሃል…!
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…የኦሮሙማው ብልጽግና አገዛዝ ማለት ስለ ሕግ፣ ስለ ሥርዓት፣ ስለ ዓለምአቀፍ ድንጋጌዎችን ማክበር ወዘተረፈ ደንታው አይደለም። ብልጽግና ማለት የፍንዳታ ጎሮምሶች ስብስብ ነው።
"…የሰው ልጆችን፣ ዜጎችን፣ እንስሳትና እጸዋትን ብቻ ሳይሆን ተቋማትን ገዳይ ነው። አቢይ አሕመድ ኮቴመናና እግረ ደረቅ ነው። ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ ያለገደለው ነገር የለም። ትምህርትን ከነተማሪዎቹ ነው የገደለው። ዩኒቨርሲቲዎች ተዘግተዋል፣ ትራንስፖርት ሞቷል። ከቦታ ቦታ መዘዋወር ቀርቷል።
"…ብልጽግና መልአከ ሞትም ነው። የሃይማኖት ተቋማትን መሪዎች ከነ አማኞቹ የገደለ፣ የሚገድል መልአከ ሞት ነው። እስከ አሁን በቅጥቀጣ ብዛት አልሞት ያሉት ተቋማት ቢኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ነበሩ። የተዋሕዶ ይቆየንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን በምታዩት መልኩ እየገደለው ነው።
"…ይህ ሁሉ ሟች በሮጲላ ሄደ በኮንኮላታ መመታቱ፣ መማረኩ እንደሁ አይቀር። ወታደር የሚያሸንፈው የመንግሥት ሳይሆን የሕዝብ ድጋፍ ሲኖረው ነው። ስንቅ ካልሰጠው፣ መንገድ ካልመራው፣ ሱታመም ካላከመው፣ መንደሩን፣ ሰፈሩን፣ ጋራ ሸንተረሩን፣ አቀበት ቁልቁለቱን ካላሳየው፣ ካልመራው፣ አንጥፎ፣ ጎዝጉዞ ካልተቀበለው፣ ከልጆቹ፣ ከአባቶቹና ከወንድሞቹ ሊዋጋ የመጣን እንደጠላት የሚያየውን አካል ድልን አይመኝለትም። ተሸናፊ ነው። እኔ መሸነፉ ሳይሆን በመሃይሞች እየተመራ ከዜጎች በተጨማሪ ተቋማትን መግደሉ ነው። የዱርዬ፣ የቦርኮ ሥራ ነው እየተሠራ ያለው። ደንታ ቢሶች፣ ጨካኞች እጅ ነው ኢትዮጵያ የወደቀችው፣ አፈ ጮሌ፣ አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤዎች ላይ ነው ኢትዮጵያ የወደቀችው። በደም፣ በላብ የተሠራን ሀገር በመሃይም ሜካፓም ደናቁርት እንዲህ ትርከስ?
• ምድረ ይዞ ሟች…!
በፋኖ ስምማ በጭራሽ አይሆንም…
"…አገዛዙ አሰልጥኖ ይላካቸው፣ ወይ ብአዴን ግንቦት 7 እና ወያኔም ያሰማሯቸው ብቻ በፋኖ ስም የተከበረውን፣ የፋኖ ትግል የሚያዋርዱ፣ የተቀደሰውን የፋኖን ትግል የሚያራክሱ ሰርጎ ገብ ፌካፌካም የቁጩ ዘራፊ ፋኖ አሰዳቢ ሌቦችን እንዲህ መንጥሮ በማውጣት እርምጃ መውሰድ ለትግሉ እጅግ ጠቃሚ ነው።
"…እነዚህን ብቻ ሳይሆን ቤተ ሰቦቻቸውን አዲስ አበባ ልከው፣ ቤትም ተከራይተውላቸው በዐማራ ፋኖ ስም ዐማራ እያገቱ በሚልዮን ብር የሚቀበሉ፣ የሚደበድቡ፣ ዐማራውን አማርረው ፋኖ መጣልኝ ሳይሆን ፋኖ መጣብኝ ብሎ ፋኖን እንደ ስጋት ምንጭ እንዲያይ እያደረጉ ያሉ፣ ወያኔ ማሪኝ፣ ብአዴን ይቅር በለኝ የሚያሰኙ አለሌ የማፍያ ጠባይ ያላቸውንም ፋኖ አሰዳቢዎች በድፍረት መጋፈጥ ያስፈልጋል።
"…የዐማራ ትግል የህልውና ትግል ነው። በዐማራ ትግል ውስጥ ተደብቆ አረመኔያዊ ተግባር መፈጸም የከፋ ወንጀልም ነው። የፋኖ ግምገማ መጀመር አለበት። የዐማራ ገበሬ መደመጥ አለበት። በነጩ ሸማ ላይ ያረፉ ነጠብጣብ ቆሻሾች የዐማራን ትግል ማቆሸሽ የለባቸውም።
"…በሸኔና በወያኔ የተማረረውን ሕዝብ በዐማራ ፋኖ ስም ማማረር ይቅር የማያስብል ወንጀል ተደርጎ መፈረጅ አለበት።
• በለው…!
"…በትግራይ ምድር እንኳን በአምስት መቶኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድን የመሰለ ጻድቅ ይቅርና በ1977 ም በራብ በጠኔው አስከፊ ዘመን እንደዚህ አጽሙ የገጠጠ ትግሬ ዐማራና ኦሮሞም አልነበረም።
"…ደብረ ጽዮን እንኳ ሥጋ ቅብ መባሉ ቀርቶለት ኡሙንዱኖኢሹ ዱንቡሽቡሽ ቦንቦሊኖ በመሰለበት በዚህ ዘመን ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ነው ብለው ዛሬ በአክሱም አደባባይ አንድ ገመምተኛ ቁስለኛ ታጋይ የላብራቶሪ አፅምም የመሰ ነገር አምጥቶ በአንድ ነጥብ ምናምን ሚልዮን ብር ወጪ ቅዱስ ያሬድ ነው ብሎ እዩልኝ ማለት ፈጽሞ ነውር ነው።
"…ይኸውልህ በኢትዮጵያ በጀት መንቀሳቀስና በራስ አቅም መንቀሳቀስ ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው። ሁልጊዜ ከኢትዮጵያ ሲለዩ እጅም ዕውቀትም ያጥራል። ኮቴ መናና፣ አቅለቢስ፣ ውቃቢ የራቀህ ነው የምትሆነው። ይሄ በኤርትራም የታየ ነገር ነው።
"…ለማንኛውም ገንዘብም፣ ዕውቀትም ከሌለህ በአደባባይ እንዲህ ከመዋረድ፣ ለአህዛብም ሁሉ መሳቂያ መሳለቂያ ከመሆን ቢቀርስ? ያው ልትመርቁት ወጥታችሁ ከሕዝቡ በተነሣ ተቃውሞ ሃውልቱን አፍርሱና ሌላ ታጋይ ያልመሰለ ጻድቅ ካህን ሥሩ ተባላችሁ አይደል? እንዲያው ሃውልት አይውጣለት ተብሎ የተረገመ ፓርቲ… አባ ሠረቀ ግን ፈጣሪ ይይልህ። በአንተ ቤት… ብቻ ይቅር… ምን ክፉ አናገረኝ።
• የጥዑመ ልሳን፣ የካህነ ስብሐት የሊቁ ማኅሌታይ የቅዱስ ያሬድ በረከቱ ይደርብን። አሜን።
"ርዕሰ አንቀጽ”
"…በፕሪቶሪያው ውል ስምምነት መሠረት ህወሓት የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች ባሉበት ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አስረከበች፣ ህወሓት ወደ 50 ሺ የሚጠጉ ወታደሮቿን ትጥቅ አስፈትታ ወደ ኅብረተሰቡ ቀላቀለች ብላ ብላ የሚል እንኩቶ ዜና በአማርኛ ለቅቀው አየር ምድሩን ሲያጨናንቁ ይከርሙና ድንገት ከትግሬ ዳያስጶራ ለምን? የሚል ጥያቄ በትግርኛ ቋንቋ ሲዥጎደጎድባቸው ደግሞ ያንኑ ዜና የሠሩት እነ ጌታቸው ረዳ፣ እነ ጻድቃንና ደብረጽዮን ገጭ ብለው ይመጡና በትግርኛ ቋንቋቸው "የምንፈታው ትጥቅ፣ የምናስረክበው መሣርያ፣ የምንበትነው ሠራዊት የለም" ብለው እርፍ ይላሉ። ወዲያው ደግሞ የሆነ ቀን ለገሰ ቱሉ ይወጣና ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት እየጣሰ ነው ሲል ጌታቸው ረዳ ደግሞ ብቅ ብሎ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በቀና ልብ አብረን እየሠራን ነው። መሳሪያም አስረክበናል፣ መሬታችንን ልንረከብ ነው ብሎ መግለጫ ይሰጣል።
"…በመሃል ቱጂው የአረጋ ከበደ የብላኔ የብአዴን አገዛዝ ደግሞ ይመጣና "ህወሓትን ጠብ አጫሪ፣ ፀረ ሰላም፣ ወራሪ" አድርጎ ይከስሳታል፣ ህወሓት ራያን የወረረችው እኛ ከፋኖ ጋር እየተዋጋን ስለሆነ ነው ብሎ መግለጫም ይሰጣል። ለዚህ መግለጫ ህወሓትም መልሶ ሌላ ድራማ ይሠራል። ብልፅግናም እንደዚሁ፣ እንግዲህ ይህ አስቀድሞ መሳሪያ አስረከበ የተባለው ዜና ነው አሁን ደግሞ ከትናንት ጀምሮ እንደ አዲስ ህወሓት መሳሪያ ሊያስረክብ ነው፣ ሠራዊቱን ሊበትን ነው የሚል ወሬ በዜና መልክ ቀሽሮ እየቀረበ ያለው። በእኔ ግምገማ የተፈታ ትጥቅ፣ ያስረከቡት መሣሪያ፣ የበተኑት ሠራዊትም የለም። አለቀ።
"…ከልምድ እንደታየው ህውሓት ዐማራን ለመውረር ሲያስብ መጀመሪያ ዐማራን የሚያጃጃል፣ የሚያዘገይ፣ የሚያደነዝዝ ዜና ይዞ ይወጣል። የትኩረት አቅጣጫን የሚሰርቅ፣ አስቀያሽ፣ ላቦሮ የሆነ ዜና ሠርቶ ያሠራጫል። ከዚያ ሕዝቤ በዚያ ዜና ላይ ሲነታረክ እርሱ በጓሮ በኩል ወረራውን ይፈጽማል። እንበልና እሺ መሣሪያ አስረከበ እንበል መሣሪያውን የሚያስረክበው ለማነው? ብልፅግናም ጠላቱ ነው። ለብልፅግና አብዶ ነው የሚያስረክበው? ደግሞስ የትስ ነው የሚያስረክበው? በጎረቤት ሀገር በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ላይ የትግሬን ጦር ለአማጽያኑ ልኮ የሚያዋጋ ድንበር ተሻጋሪ አሸባሪ ድርጅት፣ ያለ ጦርነት፣ የለውጊያ ህይወቱን መምራት የማይችል ድርጅት ለማን ብሎ ነው መሳሪያ የሚያስረክበው?
"…ይልቅ ህወሓትና ኦሮሙማውን የሚያስማማቸው ነገር ሁለቱም በቅርቡ ሀገር የሚያስደርጋቸውን ህልም እያለሙ መሆኑ ላይ ብቻ ነው። በተለይ ትግራይ ሀገር የሚያሰኛትን መስፈርት በሙሉ ለማሟላት እየደከመች ነው። በተለይ ወልቃይትንና ራያን በጨበጣም፣ በጓዳ ውልና በሴራም፣ በሥራም በእጇ ካስገባች በኋላ ለመገንጠል እንደምትፈልግ ምሑራኖቿ በአደባባይ ወጥተው በቴሌቭዥን በይፋ እየተናገሩ ነው። ለዚህም ሲባል ኦሮሞም የሚፈልገው ካለ እናግዘው፣ እሱም እኛ የምንፈልገውን ያግዘን በማለት በዐማራ ርስትና በኢትዮጵያ ህልውና ላይ እየተደራደሩ ነው። አሁን እኮ እነ እስታሊን የፋኖ ቁጥር እለት ከእለት እየጨመረ ነው፣ የመከላከያ ሠራዊቱም በዐማራ ክልል እያለቀ ነው የሚል ዜና የሚሠሩት እኮ ዐማራን ለማጀገን ፈልገው የሚመስለው ዐማራ አይጠፋም። እንደዚያ የሚያስብ ዐማራ ካለ ተሳስቷል። እነ እስታሊን በፈረንሳይኛ እያሉ ያሉት "እናንተ የወልቃይትንና የራያን ጉዳይ በቶሎ አመቻቹልን። እኛም የቅዱስ ፓትርያርክነቱን ጉዳይ በቶሎ እንጨርስላችኋለን" ነው። ፈረንሳይኛው ይሄው ነው።
"…አቢይ አሕመድም ተጨንቋል። አዎ ተጨንቋል። መንታ መንገድ ላይ ነው ቆሞ ያለው። ህወሓትን እንዳያምናት አምኖም ወልቃይትን እንዳያስረክበት ከዚያ በኋላ አይደለም አገዛዙ ራሱ ኦሮሙማው ያልቅለታል። ወልቃይትን ሙሉ በሙሉ እንዳያስረክባት ደግሞ የወልቃይትን ፖታሽ የሚፈልጉት ምዕራባውያን ወልቃይትን ለትግሬ ካላስረከበ ምንም ዓይነት ብድር፣ ፈረንካ፣ ዱዲ፣ ጢና አምስት ሳንቲም አንሰጥህም ብለው በዶላር ድርቅ መትተውታል። ወያኔ በጓሮ በር በነጮቹ እጁን እያስጠመዘዘችው ነው። ካልሆነ ዐማራ ተመልሶ መጥቶ ሥልጣን ላይ ከሚወጣና የሁለታችንም ጨፍልቀን የመግዛት ህልማችን ከሚያከትም ያለንን ኃይላችንን አንድ አድርገን፣ ዐማራን በሻሻ የማድረጉን ጉዳይ አብረን እንጨርስ እና በቶሎ እንስማማ። ወደ ሥራም እንግባ ነው እያሉ ያሉት። ኃይል ካነሰን ሸኔን እና ኦነግን በአየር አምጥተህ መቀሌ ታራግፋለህ ከዚያ አለቀ ነው የሚሉት። ጌታቸው ጉዲና አስቀድሞ አቢይ አህመድን ካልበላው ነው ይሄም የሚሆነው። ይሄን ቃሌን መዝግቡልኝ።
"…ዐማራስ አሁን ምን እያደረገ ነው? አዎ ዐማራ በምድር ያለው ፋኖ ድምፁን አጥፍቶ እየሠራ ነው። በሥራው ውስጥ ሴራና ሸውክ የለም ማለት አይደለም። ድብን አድርጎ አለ። ግን እሱንም ቢሆን በኃይለኛው እየታገለ ለመፍታት እየሞከረ ነው። የምድሩ ፋኖ ከባድ የውስጥ ሽኩቻዎችን እየተጋፈጠ፣ ሌት ተቀን ያለመሰልቸት እየተመካከረ፣ እየተወያየም፣ በቶሎ የሚፈታውን ወዲያው እየፈታ፣ በጊዜ የማይፈታውን ደግሞ ያለመሰልቸት እያዋለ እያሰደረ እየተመካከረበት ነው።
"…ፌክ ፋኖዎች ሕዝቡን እያማረሩት፣ ትግሉን ለመጥለፍ የብአዴንና የውጭ ኃይሎች ኢንቨስት ያደረጉባቸው ኃይሎች እየተሟሟቱበት እንደሆነም እያየን ነው። የዐማራ ፋኖን አሁን አሁን የተማረው ኃይል ማለትም ፕሮፌሰሮች፣ ዶክተሮች፣ ኢንጂነሮች፣ የፖለቲካ ጠበብቶች ሁሉ በረሀ ድረስ እየወረዱ በገፍ እየተቀላቀሏቸው ነው። ወታደራዊ ሥልጠናውም ደረጃው ከፍ ብሏል። የዐማራ አድማ ብተና፣ የዐማራ ሚሊሻ፣ የብአዴን ካድሬ፣ ባለ ሥልጣን የነበሩ ግለሰቦች ሁሉ ፋኖን እየተቀላቀሉት ነው። በዚህ ሁሉ ታዲያ ጥርጣሬ፣ ሙግት፣ ክርክሩ እየቀጠለ በመመካከርና በንግግር የሚጠሩ ጉዳዮቸረ እያጠሩ እየመጡ የተሻለ ቁመና ላይ ይደርሳሉ ተብሎም ይጠበቃል። አዎ ፋኖ ግምገማ የግድ ያስፈልገዋል። በቀጣይ መደረግ ስላለበት፣ ስላሳለፈውም ትግል ግምገማ ያስፈልገዋል። ግምገማ ግድ ነው። ደካማ ጎኑን አርሞ፣ ጠንካራ ጎኑን አጎልብቶ ወደፊት ለመስፈንጠር፣ ክፍተቱን ለመሙላት፣ ስህተቱን ለማረም ግምገማ ግድ ነው።
"…በዚያው ልክ ደግሞ በአንጻሩ መቼ እንደሆነ አይታወቅም እንጂ በእርግጠኝነት የዐማራ ፋኖ ማሸነፉ አይቀርም በሚል ከወዲሁ ዐማሮቹ ለሥልጣን ፉክክሩ መንደፋደፍ የጀመሩም አሉ። ይሄም ቢሆን ለክፉ የሚሰጥ አይደለም። ጤናማም ተፈጥሮአዊም ነው። ደግሞም የሚጠበቅም ነው። ውጊያ ብቻ ሳይሆን ከውጊያው በኋላ ሀገረ መንግሥቱን የሚመሩ አካላት የግድ ያስፈልጋሉ። በዚህ ጉዳይም ከወዲሁ መመካከሩ ክፉ አይደለም። እንዲየውም ዘግይተዋል። በዚህ ወቅት እንዲህ ማሰባቸው እንዲያውም ልበ ሙሉነታቸውን፣ አገዛዙን ለመገርሰስ እርግጠኛ መሆናቸውን፣ ወኔያቸውን እና በራስ መተማመናቸውን የሚያሳይ ነው።
"…በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ዐማራ ነን የሚሉ ኃይሎች በሙሉ ያለ ሴራ፣ ያለ መጠላለፍ፣ የለ ሸውክ በጀርባ ከሚያደርጉት እንደ ተማረ እንደሰለጠነ ሰው ዓለምአቀፍ የዐማራ ጉባኤ ጠርተው ምክክር፣ ጭቅጭቅ፣ ክርክር ቢያደርጉ፣ በጤናማ መልኩ ሸጋ ነው። ከአቢይ መውደቅ በኋላ ስለምትኖረው ኢትዮጵያ ጉዳይ ሀገሪቷ ምን መምሰል አለባት ብሎ ከወዲሁ መወያየት ቢጀምሩ ክፋቱ አይታየኝም። ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ እንዳይሆን ከወዲሁ እንዲህ ማድረግ ይሄም ጤናማ ነው። ነገር ግን … ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
“…ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” ዮሐ 11፥25
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
ግፍ ከወዲሁ ያቆማሉ ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ።
"…አገዛዙም የይድረስ ይደረስ ለብለብ ኮማንዶና አየር ወለድ ማስመረቁን ቀጥሏል። የዐማራ ሚሊሻም ፋኖን እየተቀላቀለ ሲሆን፣ መዋጋት የሰለቸው፣ የመረረውም የጁላ ሠራዊት ለኦነግ ሸኔና ለዐማራ ፋኖ እጁን በሀላል እየሰጠም ይገኛል። አሜሪካም ለፉገራም ይሁን ለፉከራ የሚመስል ጓ ያለ መግለጫም አውጥታ ከአገዛዙ ጋር የባልና ሚስት ዓይነት ጭቅጭቅ ሲፈጠር ታይቷል።
"…እኔ ግን እላለሁ… የሁሉ ነገር ማስተካከያው መፍትሄው በዐማራ ፋኖ እጅ ውስጥ ነው ያለው። የቤተ ክርስቲያንም ሆነ የቤተ መስጊድ ችግር የሚፈታው በዐማራ ፋኖ እጅ ነው። ቀጣዮቹ ቀናት፣ ሳምንታትና ወራት ወራት በተለይ ደግሞ መጪው ክረምት ፋኖ የውስጥ አካሄዱን ገምግሞ፣ ፈትሾ፣ በድፍረት ወደፊት ከመጣ ብዙው ውስብስብ የሀገሪቱ ችግርና ሰቆቃ መፍትሄ ያገኛል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን አሁን ለፓትርያርክነት ለሚሻኮቱት ሙዳየ ምጽዋቱን ከመሙላት ይልቅ ለዐማራ ፋኖ ቀለብና ስንቅ ቢመጸውቱት፣ ቢራዱት ሳያጸድቅ አይቀርም የሚሉ መተርጉማንም አሉ።
"…እንደ ሁል ጊዜው ዛሬም እንዲህ ብዬ እጮሃለሁ…
• ኧረ ጎበዝ…
"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ ሁሉ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው መጥተው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን ከዶላር ቅርምቱ ላይ እሽሽሽ ብለን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ የዐማራ ፋኖ በተቆጣጠራቸው ግዛቶች ውስጥ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ ይቀጥል።
• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"…መልካም…
"…ዘወትር እግዚአብሔርን ያመሰግን የክርስቶስን ትንሣኤ ያውጅ ዘንድ፣ የሚጠበቀው 1ሺ ሰው ሞልቷል። ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።
"…በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ያፋኖ ተጋድሎ ሳይረሳ ስለ 7 ተኛው ዕጩ የኦሮጵያ ፓትርያርክ ቀኝ ትከሻይን ሸክኮኝ ጻፍ ጻፍ ስላለኝ ልጽፍነኝና እናንተስ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?
• እደግመዋለሁ ዝግጁ ናችሁ ወይ…? እንዲህ ብዬ ስጠይቅ ቤቴ አዎ ዝግጁ ነነ በሚል ቃል ሲሞላ፣ ሲጥለቀለቅ ሠራዊት ያሰለፈ ጀነራል የሆንክ ያህል ነው የሚሰማኝ። 😂😂😂
• ዝግጁ ናችሁ…?
ኮመንቱና ኮማቾቹ…!
"…ኧረ ቆይ እኔ የምለው እነ ገሜ ገመቹ ግን ምን ሆነው ነው ለመቀሌው የብልጽግና እና የወዩ ዜና እንዲ አዋራ የሚያቸሱት? ለመቀሌ ዜና እነ ትርሃስ፣ እነ ተክላይ፣ እነ ተጋደልቲ ሸዊት የት ሄደው ነው የኦሮሞ ኮማቾች ብቻቸውን ዋይ ዋይ የሚሉት? ሂዊ እንደሁ 1 ሚልዮን ትግሬ የጨፈጨፈባትን የኦሮሞ ብልጽግናን የቀን ጉዳይ እንጂ እንደሁ በዋዛ አትረሳለት። ኧረ ቀስ እነ መገርሳ…
"…አይ ኦሮሞ አለ አራጅ አቢይ አሕመድ። ደግሞ እኮ አማርኛ አጣጣላቸው ሲያምር። ቁቤን ውኃ በላት አላለም ጉማ ሳቀታ…😂😂😂
ብልጽግናም "ጓ" አለ።
"…አዲስ አበባን ፊንፊኔ ብሎ ጠርቶ ጮቤ ያስረገጣቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋ ትናንት በአሜሪካ ግቢ በሰጠው "ፋኖ ብትደራደር ይሻልሃል" መግለጫ የኢትዮጵያው አገዛዝ ዛሬ ጓ ማለቱ በእንደዜ ልጥፍ 5 ጊዜ ኤዲት ባደረገው መግለጫው ላይ እየታየ ነው። ሆሆይ አማልዱኝ ብሎ ሽማግሌ ልኮ ደርሶ ጓ ማለት ግን ኢደብራል። ህወሓትን ከመቀሌ ደቡብ አፍሪካ፣ ሬድዋን ሁሴንን ከአዲስ አበባ ጆሮአቸውን አንጠልጥላ አንቃ ወስዳ ሁለቱንም ልጆቿን አስማምታ ያስታረቀች እኮ አማሪካ ናት። ወያኔን ሚልዮን ልጆቼን አቢይ ገደለብኝ ብለሽ እንዳታለቅሺ ብላ ፀጥ ያሰኘቻትም እኮ አሜሪካ ናት። ዕህእ…
"…እና ዛሬ ትናንት የአማሪካው አምባሳደር የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያው አገዛዝ ምን ቢል ጥሩ ነው። "…የለም የለም የትናንቱ የአምባሳደሩ ንግግር "በተረጋገጠ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ፣ በ100% የሕዝብ ምርጫ ወደ ሥልጣን የመጣን መንግሥት እንጥላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ፣ ንጹሐንን ከሚያግቱና ከሚያሸብሩ አካላት ጋር መንግሥትን እኩል ወንበር ላይ ያስቀመጠ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለበት ያልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ፣ ከሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ወዳጅነት ላይ ከተመሰረተው ግንኙነት የተቃረነ እና የተፈጸመውም ዲፕለማሲያዊ ስህተት ስለሆነ ከኤምባሲው ጋር በመሥራት የተፈጠረውን ስህተት እንዲታረም አደርጋለሁ ብሏል።
• ይሄም የዐማራ ፋኖን አይመለከተውም። ለፉገራም ይሁን ለፉተታ ፋኖን አይመለከተውም። ደግሞም ፋኖ ነፍሴ በቤተሰብ ጠብ መሃልም አይገባም። ሃላስ…
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ "…ኦቦሌሶ አይህ አሜሪካ ስለ ዐማራ መኖር አለመኖር ሳይሆን የሚያስጨንቃት ኢትዮጵያ ውስጥ ህወሓት እና ኦነግ ብልጽግና ኢትዮጵያን የማዳከም ፖሊሴዬን ያግዙኛል፣ ልምድ ስላላቸው እንደእነ ሶሪያ ሴራዬን ይረዱኛል፣ ስለዚህ ማንም ከህወሓት እና ከአቢይ በተቃራኒ የሚቆምን ተባብረን እናጠፋዋለን ነወ ሀሳቧ። አንዳንድ እንደ አልበርት አንስታይን ልፈላሰፍ የሚሉም ከረባታም ዐማሮች አሜሪካ በምሥራቅ አፍሪካ ጥቅሟን ለማስከበር ነው እንዲህ የምታደርገው፣ ፋኖም የፈለገው ቢሆን እንደራደር ሲባል እምቢ ማለት የለበትም እያለ ከጀርባው ተቆጥሮ የማያልቅ መጸሐፍ ደርድሮ ሲበጠረቅ ይታያል። ፋኖ ድርድር አልናቀም። አልጠላም። ድርድርም ሥርዓት አለው ነው እያለ ያለው። ለምሳሌ እዚሁ ኢትዮጵያ ያሉትን ጨፍጫፊዎቹን ኦነግ ሸኔን እና ህወሓትን በዓለም መድረክ ሲያደራድሩ በአንጻሩ የእነ አቢይ አሕመድን ይሄን ስድ ያልተጠመቀ፣ ያልተገረዘ ሸለፈታም አተላ አፋቸውን አደብ ያስገዛውን ፋኖን ከቀንድ አውጣው አረጋ ከበደ፣ ከአእምሮ ዘገምተኛ ጋር ተደራደር ማለት ኢደቢራል።
"…ፋኖዬ መጪው ክረምት ነው። ሰምተሃል…!
"…ጎበዝ የድርድሩ ሓሳብ እንዳለ ሆኖ… እግረ መንገዳችንን"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን ከዶላር ቅርምቱ ላይ እሽ ብለን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ወያኔ፣ ኦነግና ብልጽግናን አቅፋ ተጨፍጫፊውን ለማስፈራራት መነሣቷ ዥልጥነቷን ያሳያል። ዐማራን ያለማወቅም ነው። ብታውቀውም ስለምትፈራው ዐማራው ወደፊት እንዲመጣ አትፈልግም። የሚገርመው ዐማራው እንደ ወያኔና እንደ ኦነግም የራሴን ሀገር እመሠርታለሁ ቢልም አትደግፈውም። ራሴንም ኢትዮጵያንም ከገንጣይ አስገንጣይ ወንበዴ እከላከላለሁ ቢልም አትደግፈውም። አሜሪካ ዐማራ እንዲሆንላት የምትፈልገው ልክ እንደ ኩርዶች ሀገር አልባ ሆኖ የትግሬና የኦሮሞ ባርያ ሆኖ እንዲኖር ነው። ይሄን ደግሞ የዐማራ ባህሪው፣ አፈጣጠሩ አይፈቅድለትም። ስለዚህ የምታደርግ፣ የምትሠራውን ነው ፋኖ ያስጠፋባት። ኮምፓሷን ነው የሠረቀው። ያበላሸው። እኔ እንደ ዘመዴ እንደ አንድ የዐማራ ወዳጅ ለአሜሪካ የምመክረው፣ በእርግጠኛ ነኝ አማሪካኖቹም የቴሌግራም ገጼን እና ነጭነጯን መስማታቸው ስለማይቀር ብዬ ነው። አሜሪካ ሆይ ዐማራን ለመረዳት ሰባት ሱባኤ ያስፈልግሻል። ዐማራ ረቂቅ ሕዝብ ነው። ዐማራ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት የሚመራው ሕዝብ ነው። ዐማራ አምላኩ እግዚአብሔር የሆነለት ሕዝብ ነው። ዐማራነት መንፈስ ነው። የኢትዮጵያዊነት ጠባቂ ዘብ ነው። እናም ከአናሳዎቹ ጋር ገጥመሽ ታላቋን ኢትዮጵያና ታላቁን ዐማራ ማጥፋት አይቻልሽም እና በቶሎ እጅሽን ከዐማራ ላይ አንሺ ልላት እፈልጋለሁ። ለዐማሪካ ብሔራዊ ጥቅም አቻ ምርጫሽ ወያኔና ኦነግ ሳይሆኑ የሚሻልሽ ዐማራው ነበር። እሱ ካልተመቸሽ ንኪው። ዐማራ ለመገረድ የማይመች ሕዝብ ነው። አከተመ።
"…እስከአሁን በሚደረገው የዐማራ ሕዝብ የድሮን ጭፍጨፋ አሜሪካ በቴክኖሎጂ ሳታግዝ ቀርታለች ተብሎ አይጠረጠርም። ፋኖን በድሮን ለመጨፍጨፍ ግን ተደከመ እንጂ አልተቻለም። ድሮኑ ሕዝብ በመጨፍጨፉ እንዲያውም ለዳተኛው፣ ለተኛው ዐማራ ሁሉ መቀስቀሻ ነው የሆነው። ከዚህ በኋላም ከባድ የድሮን ጭፍጨፋ ይካሄዳል። ነገር ግን በጭፍጨፋው እጥፍ አዳዲስ ቂመኛ፣ ተርብ፣ ተናዳፊ የዐማራ ፋኖ ይወለዳል። አሁን የዐማራ ምድር ሙሉ በሙሉ የፋኖነት መሰልጠኛ ካምፕ ሆኗል። የእነ አሜሪካና አቢይ ሓሳብ ዐማራን በድሮን ስንጨፈጭፈው መርሮት፣ ፈርቶም ለድርድር እጅ ይሰጥና ከዚያ ድርድሩ ልክ እንደወያኔ ለአቢይ ተገርደው በአቢይ የበላይነትም ተጠናቅቆ አቢይ የሁላችንንም ዓላማ ያሳካልናል። አየር መንገዱን እንገዛለን፣ ባንኩን፣ ቴሌውንና መብራቱን፣ ወርቅና አልማዝ፣ ነዳጁን እንዳሻን እናደርገለዋለን ብለው ነው የሚያስቡት። የሚመኙት።
"…ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ዐማራው ድርድር የመይቀበል አምባገነን ነው ተብሎ ልክ እንደ ህወሓት መላው ኢትዮጵያንም እናስነሣበታለን ብለውም ያስባሉ። የበሻሻው አራዳ አቢይም አሕመድም ይኸው ወለጋ ሔጄ ሕዝቡ እንዴት እንደተቀበለኝ አይታችኋል። ባህርዳር ድረስም ሔጃለሁ። ፋኖም፣ ሸኔም አቅም የላቸውም። ስለዚህ እናንተ ፋኖን ካስፈራራችሁልኝና በድሮን ስጨፈጭፈውም ዝም ካላችሁኝ ፋኖ ፈርቶ ለድርድር ይመጣል። የዐማራ ብልፅግናን ተረክበው በአረጋ ከበደ ስርም ሆነው ሊገረዱልኝ ይችላሉ። ይሄንንም እዚያው ባህርዳር ሔጄ ዐውጄ ነው የመጣሁት ብሎ መግለጫውን አማሪካ እንድታወጣለት አድርጎም ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ዐማራው ድርድሩን በይፋ መግፋት ሳይሆን እርሱ አሸናፊ ነውና አሸናፊው እስራኤል እንደሚያደርገው ማድረግ ይኖርበታል። ተሸናፊ ወያኔ ነው። ወያኔ ደግሞ አሁን የአቢይ ገረድ ናት። ወያኔን ከበላይነት ወደ በታቸኝነት የቀየራት ምንድነው ያልን እንደሆነ በአደባባይ ስለተሸነፈች ነው። አሁን ከአቢይ ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ የላትም። ስለዚህ የዐማራ ፋኖ ከባድ ከባድ በቅድመ ሁኔታዎች የታሞላ የአሸናፊነት ዘውዱን ጭኖ መቅረብ አለበት። ያውም እሱ በመረጠው ቦታና መንግሥታት ባሉበት ሀገር ነዋ። ለአኔሪካም እረፊ ማን ጠራሽ? ማን አሸማግሊን አለሽ? ሀገራችንን ኢትዮጵያ ከዓለም ላይ ድራሽ አባታቸው ከሚጠፉ 10 ሀገሮች መካከል አንዷ ናት ብለሽ አቅደሽ እኛንም ሊስቱ ውስጥ ከተሽ ከብልፅግና ወንጌሎች ጋር ተስማምተሽ እንደነ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ አፍጋኒስታን ወዘተ ይጠፋሉ ብለሽ አጥፊ፣ አውዳሚ አቢይ አሕመድ የተባለ ቦንብ ጠምደሽ የተቀመጥሽ መሆንሽን የማናውቅ ይመስልሻል ወይ? ብሎ በድፍረት መንገርም ያስፈልጋል። እንዲህ ተብሎም ካልተነገራት አሁንም ከዚህ በላይ ሌላ ነገር ይዛ ትመጣለች።
"…ለዚህ ነው አቢይ ሀገር ከተማውን እያፈረሰ የሚያሳያት። ሀገር ማፍረሱን ይዤላችኋለሁ እናም ዐማራው ከመጣ ግን የማይሞከር ነው፣ አየር መንገዱም አይሸጥም፣ ቴሌና መብራት ኃይሉም አይሸጥም፣ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ብቻ የሚል ሕግና ዐዋጅ ነው የሚወጣው። ስለዚህ ፋኖን በጋራ እናጥፋው፣ እርዱኝ ነው የሚለው አቢይ አሕመድ። አሜሪካ የፋኖን ሓሳብ የምትቀበለው የዐማራው ፋኖ ጠንክሮ በዝረራ ያሸነፈ እንደሁ ብቻ ነው። አሜሪካ ኮከቡ የሌለበት ባንዲራን ተሸክሞ የሚፋለመውን የዐማራ ፋኖ አምና ተቀብላ ከጎኑ ለመቆም ፋኖ አቢይን ድባቅ መምታት አለበት። በጦርነት ብቻ ሳይሆን በቢሮክራሲው፣ በዲፕሎማሲው ሁላ ድባቅ መምታት አለበት። አሜሪካ በአቢይ ተስፋ ሳትቆርጥ ከፋኖ ጎን ልትቆም አትችልም። አሜሪካ በእነ መሳይ መኮንን በኩል ፋኖዎችን ኢንተርቪው እያደረጉላት "የፋኖ ቀጣይ ዓላማ ምንድነው? የሚለውን እዚያ ጋር ስለሚናዘዙላት እሱን እያስተነተነች ፋኖም እየለበለባት ወደፊት መቀጠል ነው።
"…በተለይ የእነ ናሁሰናይ የአዲስ አበባው የፋኖ ኦፕሬሽን፣ የፋኖዎች ልዩነታቸውን አጥብበው ወደ አንድነት መምጣት እና የዐማራን ትግል ጠላፊ ሾተላዮችን በድፍረት እየጸዱ መምጣት አቢይንም ሆነ ምዕራባውያኑን እጅግ በጣም አስደንግጧል። ከአሁኑ በበለጠ አንድ ሆኖ ሲመጣ ደግሞ ፋኖ አቢይን ከአመድ እንደሚቀላቅለው ሁላቸውም ዐውቀዋል። ስለዚህ አቢይ አሕመድ እንጀራ እናቱን አማሪካን ቶሎ ድረሺልኝ፣ አልያ ዓላላማችንን ከዳር ሳናደርሰው ገደል መግባቴ ነው። አለ። አማሪካም በማሲንጋ መግለጫ በኩል ከች አለች። ከች አለችና እውነት በዐማራው ትግል ውስጥ ያስገባናቸው ሰርጎ ገቦች፣ አስመሳይ ሌቦች በሀገር ውስጥም፣ በውጭ ሀገርም ያሉት ሰዎቻችንም በአንድም በሌላ ምክንያት ተለቅመው እየወጡ ነው። በዚህ ላይ ፋኖ አንድ እየሆነ ነው። አሁን ዋናው ዓላማችንን ዐማራን ማጥፋቱን ሳንለቅ በምን ዓይነት ስልት እንግባባቸው? ምን ዓይነት ኦፕሬሽን እንሥራ? ተባብለው የተመካከሩ ይመስላል። በቃ ማድረግ ያለብን ፋኖን በአሜሪካ አስፈራርቶ ወደ ድርድር እንዲመጣ ማድረግ ነው። አሜሪካ የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካዋ ሊበላሽባት እንደሆነና በዚያ እንደተጨነቀች በማስመሰል ኢትዮጵያ ውስጥ የግድ ሰላም ይውረድ ብለን ፋኖን አስፈራርተን ወደ ድርድር ማምጣት አለብን ያሉ ይመስለኛል። ጭዌው ከዚህ አያልፍም።
"…:አቢይም ለእነ አማሪካ ሁል ጊዜ እኮ ፋኖን ተደራደር ስንልው ሰዉ ሁሉ ስለሸኔ እና ህወሓት ዐማራን ስለ ማፈናቀላቸው፣ ማረዳቸው፣ መጨፍጨፋቸው ያነሣብናል። እንደ ሕወሓት ሚልዮን ትግሬ አስጨፍጭፈው በቃ የሞተ አንዴ ሞቷል ብሎ ዐማራ ለድርድር አይቀመጥም ስለዚህ ዐማራን ለድርድር ስንጠራው ስለ ወያኔ እና ስለ ሸኔ እንዳያነሳ፣ አቢይንም…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…መሳይ መኮንን በየጊዜው ለቃለ መጠይቅ ከሚያቀርባቸው ጎምቱ ኢትዮ አሜሪካዊው ከዲያቆን ዮሴፍ የተለመደ የዘወትር ቃለ መጠይቅ ውስጥ የማይጠፋ ቃል በመውሰድ ርዕሰ አንቀጻችንን እንጀምራለን።
• CIA አቢይን ተቆጥቷል።
• ሴናተሮቹ አቢይን ተቀይመውታል።
• የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሰውየውን ጠልተውታል። በማለት ዲያቆን ዮሴፍ ዐውቆም ሆነ ሳያውቅ በአሜሪካ ንዴት እና ቁጣ፣ ደስታ እና ኅዘን ላይ የተንጠለጠለ ትግል የተጀመረ ይመስል ዘወትር እንዲህ እያለ ከመሳይ መኮንን ጋር መመላለሰቻው አስቂኝ ነው። ነገር ግን በዚህ የአሜሪካ ንዴት፣ ቁጣ፣ ደስታና ኀዘን የዘናጋ እና የሚደነዝዝ አንድም የዐማራ ፋኖ ትግል አልተጀመረም። በዚህም የሚዘናጋ ዐማራም የለም።
"…ትናንት ሱሬ ሥራ ላይ ስለነበረ በኢትዮጵያ የአማሪካ አምባሳደር የሆኑትን የአምቡ ማሲንጋን ዐዋጅ ይተረጉምልኝ ዘንድ ለሌላ አንድ ወዳጄ ልኬለት ነበር። ዝርዝር ማብራሪያ ስጠብቅ ተርጓሚው በአጭር ቃል እንዲህ አለኝ። ok አዳመጥኩት ሰውየው አልቻልኩም አድኑኝ ብሎ አሜሪካ ቂጥ ውስጥ ተወሽቀ end Oof a story ! 😱 ብሎ ነው የመለሰልኝ። ለሱሬ መልሼ ስልክለት ሱሬም ያለኝ ምንድነው "እንግዲህ የዚህን ሰው ንግግር ሥረ መሠረት ማየት ይኖርብናል? መቼ፣ ለምን በዚህ ሰዓት ተናገረው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። እኔ እንደገባኝ እንደተመለከትኩት ያው ብልፅግና በአሜሪካ በኩል አድኑኝ እያለች ነው የሚመስለኝ ብሎ ትርጉሙን በአንድምታ ተርጉሞልኛል።
"…አሜሪካ ትናንት በድሮው የአሜሪካ ጊቢ ውስጥ ሆና የቁጣ መግለጫ ስታወጣ ብልፅግና ደግሞ በአደም ፋራህ መሪነት መቀሌ ከእነ ደብረጽዮን ጋር እየተደራደረ ነበር። አቢይ አሕመድ ደግሞ ከተማ ለከተማ ሊስትሮ ሲያስጠርግ፣ አሮጊቶችን አቅፎ ሲያናግር፣ የተበላ የተባነነበትን የፎቶ ቦለጢቃ ድራማ ሲሠራ ነው የዋለው። ሁሉም ግን ብላሽ ነው። ከአንባሳደሩ መልእክት ቀደም ብሎ የአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪቃ የቀንዱ ልዩ መልእክተኛ መዶሻውን ይዞ አዲስ አበባ ነበር የከረመው። ከኦሮሞ የቦለጢቃ ፓርቲ መሪዎች ከመራራ ጉዲና እና ከዳውድ ኢብሳም ጋር ሲሞዳሞዱ፣ ሲሳሳቁም ነበር። ከብልፅግና ሰዎችም ጋር እንዲሁ ሲወያዩ ነበር የከረሙት። መቀሌም ሽር ብትን ሲሉ ነው የከረሙት። ወዳጄ እንደ ጦስ ዶሮ ስትሽከረከረው ትውላለህ እንጂ የፋኖን መለኮታዊ፣ ምስጢራዊ አስኳል አታገኘውም።
"…አሁን ማንም ይሁን ማን ተወደደም ተጠላም የናቁት፣ የትም አይደርስም ብለው የዘበቱበት፣ በጥቂት ቀናት ሱሪውን እናስፈታዋለን ብለው ፎክረው፣ ደንፍተው የዘመቱበት፣ በ7 ቀን፣ ሌላ ጊዜ በአንድ ወር፣ ከዚያም 3 ወር ድራሽ አባቱን እናጠፋዋለን በለው ለአለቆቻቸው ጭምር ቃል የገቡለት አጅሬ ፋኖ ሳይታሰብ በጥቂት ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ በቀጠናው ላይ የሚያስፈራ ትልቅ ኃይል ሆኗል። ብልፅግና ዐዋጅ ዐውጆ ፋኖን በ7 ቀን አጠፋለሁ ብሎ ያለ የሌለውን ኃይል ጠቅልሎ ዐማራ ክልል ከገባም ድፍን አንድ ዓመት ሞላው። ፋኖም ይሄን እስከ አፍንጫው ድረስ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታጠቀን፣ በሰማይ በድሮንና በጦር አውሮፕላኖች የታገዘን ግዙፍ ኃይል ማንቁርቱን ጉሮምባውን እያነቀ መሳሪያውን እየነጠቀ ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያ ዘጭ አድርጎ በዚሁ አንድ ዓመት ወስጥ በሚገባ ታጥቋል። አሁን በቀጠናው ላይ የፋኖ ኃይል እየገነነ መምጣቱ እና ከኤርትራ ብሎም ከሱዳን ፈጣኖ ደራሸ ጋር ያለውም አካሄድ አሜሪካን እንቅልፍ ነስቷታል።
"…በዚህ ጉዳይ ላይ ከአንድ ወዳጄ ጋር ስንወያይ ያለኝን ነገር እዚህ ጋር ብጽፈው ወደድኩ። "ይኸውልህ ዘመዴ… አንድ ጉድ ሊሆን የሚችል በተለይ የአሜሪካ ባህል የሆነ ሴናርዮ ወይም ትንቢት ልንገር። እዚህ ላይ ፋኖ መሸወድ የለበትም። አሜሪካ ፋኖን ተደራደር ብላ ካለች በኋላ ፋኖም ከፈለገ በድርድሩ ላይ ሩሲያም ትገኝልኝ ሊልም ይችላል። ለድርድሩ አብይንና ኦሮሙማን እጅና እግራቸውን ጎማምዶ ስም ብቻ የሚያስቀር የድርድር ሀሳብ ይዞ ይቀርብና እንደሚጠበቀው ሰውየው አይ ይሄንንማ አልቀበልም ሲል አሜሪካ በግልፅ በአብይ ላይ እርምጃ ልትወስድበትም ትችላላች። ለድርድሩ መሳካት እንቅፋት እየፈጠረ ነው በሚል ጓ ልትልበት ትችላለች። ለአሜሪካ ቋሚ ወዳጅ፣ ቋሚ ጠላት የሚባል ነገር የላትም። አማሪካ ሁሉንም ነገር ከጥቅሟ አንፃር ነው የምትመለከተው። ለአሜሪካ ሁሉም ነገር እንደ ማስቲካና ሸንኮራ ያለ ነው። ታኝክሃለች፣ ከዚያ ጣእምህ ሲያልቅ ትተፋህና አዲስ ማስቲካ ገዝታ ማኘክ ትጀምራለች። 😱 ያ… አሜሪካ በዚህ የታወቀች ነች ብዬ ነው።
"…ለምሳሌ የዐማራ ፋኖ ለተጨፈጨፈው የዐማራ ሕዝብ አሻድሌና ሀሰን፣ ሺመልስ አብዲሳና አቢይ አሕመድ ይሰቀሉልኝ ማለት ሁላ ይችላል። ለወደመው ሀብት ካሣ ለፈረሱ ቤቶች ሁላ በእጥፍ መጠየቅ ይችላል። በሀገሪቱ ወሳኝ ምርጥ የሥልጣን አካባቢ ወይም ቦታ እንደ መከላከያና ደኅንነቱን፣ ከጠቅላይነት እስከ የውጭ ጉዳዩን ድረስ ዐማራ የመጠየቅ፣ የመያዝም መብቱን መጠቀም ይችላል። ይሄ ብቻ አይደለም የተሰደዱት እነ ዘመዴ ሁላ ታላቅ ሕዝባዊ አቀባበል ተደርጎላቸው በክብር ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ማለት ሁላ ይችላል። 😀 ሕገ መንግሥቱ ድራሹ አባቱ ይጥፋ፣ ኮከቡ ከባንዲራው ላይ ይፋቅ፣ ከሥራ የተባረሩ፣ የተቀነሱ ዐማሮች ካሣ ተሰጥቶአቸው ወደ ሥራ ገበታቸው ይመለሱ፣ ቤታቸው የፈረሰ፣ ንብረታቸው የወደመ ይተካላቸው። ብሔራዊ የኀዘን ቀን ይታወጅ፣ ማለት ሁሉ ይቻላል። ፋኖ ድርድር አልቀበልም ሳይሆን የድርድሩን ይዘት፣ ቦታ፣ በድርድሩ ላይ እንዲገኙለት የሚፈልጋቸውን ሰዎች፣ ቅድመ ሁኔታዎችን ዘጭ አድርጎ በማቅረብ መሞገት እንጂ ድርድር በደፈናው አልቀበልም ማለት ክፉ ውሳኔ ነው የሚሆነው። አቢይ ይሰቀልም የድርድሩ አካል መሆን ነው ያለበት። እንደወያኔና እንደ ኦነግ ያለ ጆሮ ተይዞ ድርድር ሳይሆን በአሸናፊነት ሥነ ልቦና ልክ እንደ እስራኤል ነው… ኣሃ… የምለው ይገባችኋል።
"…አንድ ግብዳ ትልቅ ቋጥኝ የሆነ እውነት መረዳት ያለብን ፋኖን አይደለም መሳሪያውን ሱሪውን እናስወልቀዋለን ተብሎ በአደባባይ እንዳልተፎከረ ዛሬ በዚህ ልክ ራሷ አሜሪካ መጥታ "ድርድርማ አልፈልግም አይባልም" ብላ ፋኖ ለድርድር መጋበዙን አምና መናገሯ በራሱ ትልቅ ድል ነው። እዚህ ላይ ማወቅ እና መርሳት የሌለብን አቢይ አሕመድ የተባለ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ክፉ ሰው መልምሎ፣ አሰልጥኖ፣ ፈትቶ የለቀቀብን ዋነኛዋ የኢትዮጵያ ጠላት ዕቅድ አውጥቶ፣ ፈንድ ለግሶ፣ ሽፋን ሰጥቶ ይህን ሁሉ ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋ እንዲያደርግ መርቆ የላከው ሀገር አሜሪካ መባሉን መረሳትም የለበትም።
"…የምዕራቡ ዓለም አካሄድ የተበላበት ቁማር ነው። ብልፅግናን እንዲወገድ ህወሓትን በል ሂድ ግፋ እያሉ ለአዲስ አበባ ትንሸ ኪሎ ሜትር ቀረው ሲሉ እንደነበር ሁላችንም እናስታወሳለን። ታዲያ እንርሱ እንደጠበቁት ሳይሆን ሲቀር እና ህወሓት መሸነፏ ሲታወቅ እውንም ሲሆን አሜሪካ መር ምዕራባውያኑ ምንድነው ያደረጉት? አዎ ህወሓት ፈጽሞ እንዳትጠፋ በድርድር ሒሳብ ነው ከሞት ያዳኗት። በተመሳሳይ ሁኔታ…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ " 1ኛ ቆሮ 15፣54
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…ዛሬ የቤቴን በር ከፍቼ ጠፍቼ ነው የዋልኩት። በቤቴ ምን ይፈጠር ምን እስከአሁን የማየት እድል አላገኘሁም። ረባሽ፣ በጥባጭ ይግባ አይግባም አላወቅኩም። ገና አሁን ወደ መኖሪያ ከተማዬ ከራየን ወንዝ ማዶ ዋሻዬ መግባቴ ነውና እስቲ እጎበኘዋለሁ። ባለጌ፣ ስድአደግ፣ ፀያፍ ካገኘሁም ሳፀዳው አመሻለሁ።
"…ዛሬም ከመንገድ መልስ ስለሚሆንብኝ፣ ለዛሬም ቲክቶክ መግባት አልችልም። በሌሊት ተነሥቼ ጉዞ ጀምሬ አሁን በምሽት ስለሆነ ወደ ቤቴ የምደርሰው በቀጥታ ወደ አልጋዬ እንጂ ወደ ቲክቶኬ ሄጄ ስንቶኮቶክ አላመሽም።
"…በተረፈ የጊዜያዊ የዓየር ላይ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስከ አሁን እንደተከበረ ነው። እስከ አሁን ከአባቶቼ ቃል የሚያወጣኝ ድርጊት አየሩም ላይ በምድርም ላይ እስከ አሁን አልገጠመኝም። በምድር ላይ ሁሉ ነገር አሸወይና ነው። የአየር ላዩን አሁን ገና ገብቼ በአስተያየት መስጫ ሰንዱቄ ከፍቼ ለመመልከት እሞክራለሁ።
"…የነገ ሰው ይበለነ… በጠዋት የጌታን ትንሣኤ እናውጅና ወደ ቀደመው ርዕሰ አንቀጻችን እንገባለን። አሜሪካ በዚህ ሰዓት ፋኖን የሚያስፈራራ መግለጫ ለምን ማውጣት አስፈለጋት የሚለውን በገባን ልክ ነጭ ነጯን እናወራለን። ፋኖስ ምን ያስተካክል በድፍረት ሰሞኑን ማውራት እንጀምራለን።