zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሚኪ ቤት ስገባ…

"…ስኳድ ምስጌ ሂዱ ባለን ማስታወቂያ መሰረት ወደ ሚኪ ቤት ኮተት እያልኩ መሄድ። እዚያ ሚኪ ቤት ስገባ ማንን ቲክቶክ ላይ ተጥዶ ባገኝ ጥሩ ነው? ከምር አታምኑኝም በቀጥታ ያገኘሁት ከራሳ ሰሜን ሸዋ ከቀለጠው የጦርነት ሜዳ መሃል 😂😂 ተረጋግቶ ተቀምጦ ቲክቶክ የሚጠቀመውን የእስክንድር ደንገጡር፣ ሻለቃ መከታው ማሞ የሚመራው የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ የፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊ የሆነውን ኢንጂነር ፋኖ አዶናይ አበበን።

"…አይገርምላችሁም? በቀለጠ ጦርነት መሃል ለእስክንድር የፖለቲካ ሓላፊ ኢንተርኔት ተፈቅዶለት ቁጭ ብሎ ከሚኪ ጦሽ ጋር ስለ ፀረ ዐማራው፣ ፀረ ጎጃሙ ስኳድ በእስክንድር ነጋ በኩል ሊከፍቱ ስለሚላላጡበት ጣና ሚዲያ እየመከረ ነው። ኢትዮ 360 እንዳከሰራቸው በዚህ ነው ያወቅኩት። ሀብታሙም፣ አበበ በለውም በሚፈለገው መጠን ወደፊት አላራመዱትም። እነ ስኳድ ምስጌን፣ እነ እስኬውንም አላኮሩም። ስለዚህ በእነ ፔይንኪለር እና በእነ እሸቱ ገጠሬው ፊት አውራሪነት እነ አዶናይ በስመ ጎንደር ሸዋን ለማሾቅ ቆዳ ቀይረው ብቅ። አሁን ምስክርነቱን ሰምተን እንመለሳለን።

• አዶናይ ማለት ከእስኬው ጋር የገጠር ቤርጎ ቁጭ ብላ ቲክቶክ የምትጠቀመዋ ናት። ያው ፍልሚያ ላይ አይደል ያለነው። መግጠም ነው እንግዲህ። መግጠም ነው።

• እየኮመታችሁ…!!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቪድዮ ፩

"…ሸዋ ሳሲት በሚባል ቦታ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚያስተዳድረው የሻለቃ መከታው ማሞ ልጆች ካምፕ አድርገው የተቀመጡበት ስፍራ ላይ ድንገት የኦሮሙማው ጦር ይገባባቸዋል። እስክንድር የገዛው የመከታው ጦርም ወደ ኋላ ያፈገፍጋል። የመከታው ጦርም ከጦሩ ጋር መሸሽ ያልቻሉ 15 ቁስለኞችን ጥለዋቸው ነበር የሸሹት አሉ። የኦሮሙማው ጦር በደረሰ ጊዜም እነዚህን ሸሽተው ማምለጥ ያልቻሉ የመከታው ልጆችን ይይዙና ያለ ርህራሄ ይረሽኗቸዋል። መረሸን ብቻ ሳይሆን ቀርጸው በቲክቶካቸው ይለቁታል። (እኔም ከዚያው ነው ያገኘሁት) ምርኮኛና ቁስለኛ መረሸን በዓለምአቀፍ ሕግ የጦር ወንጀል ይመስለኛል። ብቻ ይሄን ቪድዮ ያዙልኝ።

ቪድዮ ፪

"…ሰሜን ወሎ ነው። የዐማራ ፋኖ በወሎ ከብርሃኑ ጁላ ሠራዊት ጋር ውጊያ ይገጥማል። ገጥሞም ይሸነፋል። የኦሮሙማው የጁላ ሠራዊትም እንደ ልማዱ ይማረካል። መማረኩ ብቻ ሳይሆን ፍሪዳም፣ ሰንጋም ታርዶለት፣ ጠጅ ተጥሎ፣ ጠላ ተጠምቆለት፣ ሻወር እየወሰደ፣ ያማረ ጽዱ ልብስም ተቀይሮለት፣ በመከላከያ እያለ የማያገኘውን ምግብ እየበላ በሸነና እያለ ፈታ ብሎ በእንክብካቤ ይኖራል።

"…እኔምለው ግን ፋኖ ገንዘብ፣ ስንቅ ተርፎት ነው? እጸድቅ እንደሁ ብሎ ነው? እንዲራሩለት ነው? ፋኖ ተተኳሽ አለው? ሠራዊቱ ጠግቦ በልቶ አድሮ ነው? የኦሮሙማው ጦር ፋኖን ቢማርክ በዚህ መልክ ነው የሚይዘው? ታሞ ሆስፒታል የተኛን ፋኖ አውጥቶ በመኪና ጭንቅላቱ ላይ ሄዶ የሚጨፈልቅ፣ ፋኖ አከማችሁ እያለ ሃኪሞችን ለሚረሽን የገዳይ አገዛዝ ወታደር እንዲህ ልነጠፍልህ ማለት፣ አብልቶ፣ አጠጥቶ፣ የተለመነ ዶላር፣ የገበሬ ቀረጥ የኪስ ገንዘብ ሰጥቶ መስደድ ፌር ነው ወይ? ከምር ብዙ ጥያቄ ነበረኝ ጠፋኝ። ምን ልጠይቅ ነበር በናታችሁ? ቆይ ሳስታውስ እጠይቃችኋለሁ።

•አትማርክም እንጂ ሱማሌ ብትማርክ እንዲህ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።” ኤር 17፥12… “…ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” መዝ 96፥6። “…ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን።” መዝ 65፥5

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…

"…ከአንድ የመሸጋገሪያ ሙዚቃ በኋላ አንድ አድርስልኝ የተባልኩትን ማስታወቂያ ለቅቄላችሁ ለዛሬ እንሰነባበታለን።

• መርዞ ና…!😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…!


"…ፈጣሪም እያየህ ለምን ዝም አልክ እንዳይለኝ ይሄን ጎምቱ የዐማራ ትግል መሪ ዶፍቶሩን ነኝ ባይ እስቲ አሁን ደግሞ አማርኛ ላስተምረው…

• ዶፍቶርዬ…

• ስራ አይባልም ሥራ እንጂ
• ህዝብ አይባልም ሕዝብ እንጂ
• ሶሎሞን አይባልም ሰሎሞን እንጂ
• አጣናው ወይስ አጠናው? ?? ይህን አላውቅም።
• ብሄርተኛ አይባልም ብሔርተኛ እንጂ
• አማራ አከራካሪ ነው ዐማራ፣ ኣምሓራ የሚሉም አሉና። እሱን አላርምህም። ሌላውን ግን ከአንድ ዶፍቶርነቱ 12 ዓመት ከፈጀበት ስኳድ አይጠበቅም። የሕዝብህን ቋንቋ ጠንቅቀህ ሳታውቅ እንዴት ነው የእነ ጌታ አስራደ አለቃ የሆነከው። በእውነት ልክ አይመስለኝም። ግን ደግሞ አያገባኝም። አማርኛህን ብቻ ካስተካከልክ ለእኔ በቂዬ ነው። ✍✍

~ በዚያውም 65 ሺ ዶላራቸውን መልስ።

ጉድ በል ጎንደር
አማርኛ መምህር መጣልህ ከሐረር …ማለት አሁን ነው። እንዲህ እንዲህ እያልኩ አስተነፍሳችኋለሁ። ዐማራን እንደማትወክሉም አሳያችኋለሁ።

• ከፈንድ ስብሰባው መልስ እንጠብቅህሃለን። እውነት ጎንደር ስኳድ አይደለም። ስኳዶቹማ በስም ይታወቃሉ። ይዠለጣሉም። 😁

• ደግሞ አንተን ሳርምህ የጎንደር ሕዝብ አማርኛ አይችልም አለኝ ብለህ በጎንደር ፋኖ ስም መግለጫ አውጥተህ በአበበ በለውና በሀብታሙ አያሌው ሰበር ዜና ብለህ አሰድበኝ አሉህ…? 😂 …አድማጭ ተመልካቾችም እያያችሁ ዝም አትበሉ። የዐማራ ፋኖ መሪውን ዶፍቶር አማርኛውን አርማችሁ ዐማራ አድርጉት። 😂

"…ተቀበል ይቀጥላል…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…!

"…በወላይታ ስምንተኛው ሺ ገባ ወይስ ቀረ…?

"…እየገጠማችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…!

"…የኦሮሞ ብልፅግና ሲፈልግ ከሻአቢያ፣ ሲያሻው ከሱዳን፣ በል ሲለው ከሶማሊያ፣ ደስ ሲለው ደግሞ ከግብፅ ጋር ማንንም ሳያማክር በሃላል ይሠራል። ይሄን እንደ መብትም ያየዋል። ደግሞም መብቱ ነው።

"…መልካም… ታዲያ ያው የኦሮሞ ብልፅግና ከሻአቢያ ጋር ሲታረቅም፣ ሲጣላም ለዐማራ አላማከረም። ከኦነግም ጋር ታንዛኒያ ድረስ ሂዶ ሲደራደር ለዐማራ አላማከረም። ከግብፅ ጋር ሲጣላም፣ ሲታረቅም ዐማራን አላማከረም። ከወያኔ ጋር ሲጣላ አጋዥ ፈልጎ ለዐማራ ከነገረ ዐማራን ካማከረና ትግሬና ዐማራን ደም አቃብቶ ሲያበቃ ከወያኔ ጋር ሲታረቅ እንኳን ሊያማክረው ጭራሽ ዐማራን ድራሽ አባትክ ይጥፋ ነበር ያለው። ሃቅ።

"…አሁን የምር ይሁን የፌክ ወያኔ ለሁለት ተከፍላለች። ሻአቢያና የኦሮሞ ብልፅግናም የተጣሉ መስለው እየታዩ ነው። የአቢይ ብልፅግና ከጌታቸው ረዳ ጋር የመሥራት ፍላጎት አለው የሚሉም አሉ። መብታቸውም ነው።

"…የሆነው ሆኖ የእኔ ጥያቄ አሁን የዐማራ ፋኖ ከሻአቢያም ጋር ይሁን፣ ከትግሬ ጋር፣ ከሱዳኑ ሃሚቲ ጋርም ይሁን ከሌላ ኃይል ጋር ተነጋግረው ቢሠሩ፣ ቢታገሉ ኃጢአቱም፣ ወንጀሉም እምኑ ላይ ነው? ለዐማራ ሲሆን ክልክል፣ ለብልግና ሲሆን የተፈቀደ የሚሆነው ለምንድነው? ስላልገባኝ ነው። ጀስት ጥያቄም ነው። የገባችሁ እስቲ መልሱልኝ…!

• ብሊስ… ብሊስ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የደራሲ አዜብ ውርቁን ጦማር በ10 ደቂቃ ውስጥ 3 ሺ ሰው አንብቦታል። አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው። ቶሎ ቶሎ ሓሳባችሁን ስጡበትና ወደ ዕለቱ የተቀበል የመሰንቆ ግጥም መርሀ ግብራችን እናልፋለን።

• እየኮረደራችሁ…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አሁን ደግሞ ሳምንታዊው የግጥም፣ የቅኔ ማዕበል የሚፈስበት የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችን እስኪደርስ የደራሲ አዜብ ወርቁን ምርጥ ዕይታ የሚያሳይ ግሩም የሆነ ጦማር እጋብዛችኋለሁ።

• የፈራረሰው 😂 የኮሪደር ልማት ፎቶ አዜብ ወርቁን አይመለከትም። የቶፕ ቪው፣ የመብራት ቀረጻው የኮሪደር ልማት የእነ ቶሎቶሎቤት ግድግዳው የሌማት ትሩፋት የሆነው የእነ ደርምሴ ድርምስምስ ፎቶው የራሴ ምልከታ ነው። ሆኖም ግን አዜብ ጦማር ላይ ጥድፊያውን ለማሳየት ስለፈለግኩ ነው ፎቶውን መለጠፌ። እንጂ አዜብን አይመለከታትም።

"…የአዜብን ጦማር ካነበባችሁ በኋላ እናንተም የምታውቁትን የልማት ተነሺነት ገጠመኝ እንድታወጉንም ትመከራላችሁ። እንዲህና እንዲያ እያልን ቅዳሜ ከሰዓታችንን ውብ አድርገን የቴሌግራም መንደራችንን በሳቅ፣ በእንባና በለቅሶ፣ በደስታና በሀዘን ሰው ሰው የሚሸቱ መርሃ ግብሮችን አያሳየን ፈታ ስንልበት እናመሻለን።

• ለምጠይቃችሁ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ስትረባረቡ ሳይ እኔም የመጻፍ አፒታይቴ ይከፈታል። ዝም ስትሉ ግን ሰው የሌለ ስለሚመስለኝ እኔም ጮጋ በል በል ያሰኘኛል።

• አላችሁ አይደል?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጣና ቴቪን እንርዳ… 😁

"…አዝማሪው ግን ነገ ቅዳሜ ከሰዓት አይሻልም ነበር…?

• ዳሩ እኔ ምን አገባኝ…?

• ተቀበል… ግጥም ስጡት ለአዝማሪው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

⛔️ ማስጠንቀቂያ⛔️

• ይህን የጎንደር ዐማራን የማይወክል የስድ አደጎች የብልግና ንግግር የዐማራም የኢትዮጵያም ሕፃናት እንዳያዩት ይመከራል።  በእኔ በኩልግን ከስኳድ ጋር ጦርነት ላይ ስለሆንኩ ለውጊያው የምመርጠው መሣሪያ የለም።

"…እምቢኝ እምቢዮ በባለ ማዕተቡ ጎንደሬ ስም አላስነግድም…! ሌባ ሁላ።

"…ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ጎንደሬዎች የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሽከሮቹ በባለ ማዕተቡ ጎንደሬ ስም ለመነገድ የተነሡት ስኳድ ዛሬ ደግሞ በዶፍተር ደረጄ ቤት የልመና አኩፋዳ ከረጢታቸውን ይዘው ዋይ ዋይ ቢሉም አባ ከና የሚል ጠፍቷል። ወፍ የለም ስልህ።

"…ይሄን እብድ ከእኔ የባሰ መራታ የሆነ ሚኪን ይዘው ለልመና ቢሰለፉም ጎንደሬ አራዳ ነው። ጎንደሬ ነቄ ነው። ገንዘቤን ለማንና የት እንደምሰጥ እኔ ነኝ የማውቀው ብሎ ግግም፣ ውግም ብሏል።

"…የእነ የኔታ ዕዝራ፣ የሊቀ ሊቃውንት ሀገሩ ጎንደር በእንደዚህ ዓይነት ጋጠወጥ፣ ምግባረ ቢስ አይወከልም። የሀገሬ የሀረርጌ ልጆች እንኳ በዚህ መጠን ጮክ ብለው አይናገሩም። በፍጹም ይሄ የጎንደር ዐማራ ስብዕና አይደለም።

"…እነ ዶክተር ምስጋናው አንዷለም፣ እነ እሸቱ ገጠሬው፣ እነ በረደድ፣ እነ ዶክተር አምሳሉ ጨንቋቸዋል። እስክንድር ነጋ ብር አልቆበታል። በሀብታሙ አያሌው ምላስ፣ ትእቢት ምክንያት ትልቅ ኪሳራ ደርሶበታል። እናም አሁን በእነ ማማር አለባቸው በኩል አስቀድመው ሊግጡት ያሰቡትን ዐማራ እኔ ስለታደግኩት አሁን ቢጨንቃቸው ይሄ ጎንደሬ ነው ብለው በዚህ ቀውስ በኩል ሊግጡት መጥተዋል። በውኑ ይሄ ሰው የጎንደር ዐማራ ስብዕና አለውን? መልሱን ለእናንተ። 

• ሌባ ሁላ… ወፍ የለም ስልህ። ሊበላ…? ሃኧ…? 😂 ነክሼሃለሁ ሳላደማህ መች እፋታህና…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬም እንደ ትናንቱ እስከ አሁን ድረስ ዓመታዊውን ዝርዝር የሥራ ዕቅዴን በሚያሳየው ርእሰ አንቀጽ ስር መጥቶ 😁 ከመሳቅ፣ ዝ👍 ግጨው፣ ፈጣሪ ይርዳህ🙏እንጸልይልሃለን፣ እንካ 🏆 አሪፍ 👌 ነው ከማለት ውጪ ብው 😡 ብሎ የተናደደ ሰው አላየሁም። ይሄ ነገር እንዴት ነው? 😂? ተደጋገመብኝሳ…? እንዴት የሚበሳጭብኝ ይጠፋል? አንድ እንኳ? ኧረ ባባታቹ፣ ባናታቹ ፌር አይደለም።

"…ለማንኛውም በዓመታዊ የሥር ዕቅዴ ላይ መቼም የሚቀነስ የለም የተረሳ ካለ ግን ጨምሩና አስተያየት ሰጥታችሁ በጋራ እናጽድቀውና ወደ ሥራችን እንገባለን።

"…1…2…3…✍✍✍ ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍

"…የእኔ ሥራ ትንሽ መኮርኮር ነው። ማኖ ማስነካት፣ ፋውል ማሠራት ነው። ጠቅ አድርጎ ማስተንፈስ ነው። ከዚያ እንዲለፈልፍ ማደርግ። ውቃቢውንም፣ ቀልቡንም መግፈፍ ነው። ፕሮፌሰር ይሁን ዶክተር፣ ታጋይ ይሁን አታጋይ፣ ዶፍቶር ይሁን ኢንጂነር፣ አክ እንትፊስት ይሁን ጆርናሊስት ለደንታው ነው። በዐማራ ትግል ላይ ሾተላይ ሆኖ መገለጥ የሚሞክር ካለ አልፋታውም። እንዘጭ፣ ጓ ግርግጭ ነው የማደርገው። መደበቂያ፣ መሸሸጊያ እንዲያጣ ነው የማደርገው። በበቃኝ ነው ከሴራው የማስወጣው። አልፋታውም። አልለቀውም። እኔ የነካሁት፣ የለከፍኩት ደግሞ በቁሙ ነው የሚደርቀው። እግዚአብሔር ሲጣላህ አርጩሜ አድርጎ እኔን ይልክብሃል። ከዚያ ማኔ ቴቄል ፋሬስ ነው። ለምን የፈለግከውን ቅዱስ ቅዱስ አትጫወትም። አልፋታህም። ጠብቀኝ።

"…ጎንደሬ ነኝ ብለህ የጎንደር ሕዝብ፣ ወሎዬ ነኝ ብለህ የወሎ ሕዝብ፣ ጎጃሜ ነኝ ብለህ የጎጃም ሕዝብ፣ ሸዋዬ ነኝ ብለህ የሸዋ ሕዝብ ጉያ ስር ለመደበቅ ብትሞክር፣ ብታዳክርም አልለቅህም። ከሕዝብ ነጥዬ፣ ጎትቼ አውጥቼ፣ በጥንቃቄ የቀዶ ጥገና አድርጌ ለብቻህ በአደባባይ ላይ እርቃንህን አስጥቼ ነው የምቀጣህ። አረፋ ነው የማስደፍቅህ ስልህ። የሴራ ፖለቲካህን ሁሉ እንደ ተበላ ዕቁብ ቁጠረው። እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ እኔ ዘመዴ መራታው የሐረርጌ ቆቱ፣ እኔ ዘመዴ የምሥራቁ ሰው የተዋሕዶ ልጅ፣ ባለ ማዕተቡ እኔ ዘመዴ የአንተ የሰገጤውን የክፍለ ሀገር ልጅ የሴራ ቦለጢቃ እንደ አምቦ ውኃ ብትንትኑን ነው የማወጣልህ። ጠብቀኝ።

"…ዛሬም እደግመዋለሁ። የዐማራ ትግል ቅዱስ ትግል ነው። የዐማራ ትግል የህልውና ትግል ነው። የዐማራ ትግል እንደ ቤተ መቅደስ ያለ ቅዱስ የትግል ስፍራ ነው። ከነ ግማታም፣ ክርፋታም፣ ፈንገሳም እግርህ እየጠነባህ የምትገባበት ትግል አይደለም። የዐማራ ትግል የዓለምን የፖለቲካ ሥርዓት ሊቀይር የሚችል ታላቅ ትግል ነው። ይሄን ቅዱስ የዐማራ ትግል እስክስታ እየወረድክ፣ በኪንታሮት ቁስል፣ በጃል የእንቧይ ካብ ቁልል የምትመራው፣ የምትጠልፈው፣ አፍህን የምትከፍትበት አይደለም። የዐማራ ትግል ማለት የማንም መንገደኛ የሚቀጥፈው የደሀ ገበሬ ማሳ እሸት አይደለም። እግርህን ታጥበህ፣ እጅህን ፈትገህ፣ ሰውነትህን ታሽተህ፣ ጽድት፣ ንጥር፣ ንጥት ብለህ የምትገባበት ቅዱስ ጉባኤ እንጂ ተዝረክርከህ የምትገባበት አይደለም። የዐማራን ትግል ምላስህን አርዝመህ ብትመጣ ምላስህን በሰይፉ ምላሴ ቆምጬ እገላግልህሃለሁ። ቲፎዞ ይዘህ ተግተልተልትለህ ብትመጣ ከነ ቲፎዞህ አደባይሃለሁ፣ ቀዝቃዛ በረዶ ነው የምቸልስብህ። አንተ እንደፈለግክ ሁነህ የዐማራ ፋኖ ትግል ጠላት ሁነህ ና እኔ ዘመዴ ደግሞ እንደ አመጣጥህ አድርጌ አስተናግጄ እመልስህሃለሁ። ቃሌ ነው።

"…ሌላው በዘንድሮው በዘመነ ዮሐንስ የመረጃ ቲቪን አባላት ለማብዛት እጥራለሁ። እኔም በነፃ ማገልገሌን አቁሜ በደሞዝ ለመሥራት፣ እየተከፈለኝ ለማገልገል እሞክራለሁ። ሌሎች ሠራተኞችም ተቀጥረው የሚያገለግሉበት፣ የመረጃ ቲቪ ተደራሽነትም የሚሰፋበትን መንገድ አጠንክሬ ማፈላለጉን እቀጥልበታለሁ። በእኔ በዘመዴም ሆነ በመረጃ ቴቪ መርሀ ግብሬ ላይ የሚመጣውን ማንኛውንም አካል እንደ አመጣጡ አስተናግደዋለሁ። በፈልገው መንገድ የፈለገው ሰው፣ ሚልዮን ሺ ቢልዮን ባታልዮን ጦር ይዞ ይምጣ አስተናግደዋለሁ። እኔ የዝሆን ቆዳ ስለሆነ ያለኝ ስድብ፣ ፉገራ፣ ፉተታ ከጉዞዬ አያቆመኝም። ውሾች ይጮሃሉ ግመሉ ዘመዴ ግን ጎምለል፣ ጎምለል እያለ ወደፊት ጉዞውን ይቀጥላል። መረጃ ቴቬን አጠልሽተው፣ አዋርደው፣ ስሙን አጥፍተው ሲያበቁ በመረጃ ቴሌቭዥን መቃብር ላይ ሊጸድቁ ፈልገው የነበሩትን በሙሉ እበቀላቸዋለሁ። ሥራቸውን ነቅዬ ነው በተመልካች ድርቅ የማስመታቸው። የበሉበትን ወጪት የሰበሩትን ሁሉ ልክ አገባቸዋለሁ። ዳይ ወደ ኡበር ሥራህ ንካው። ቀፋላ ሁላ።

"…ከዚህ በተጨማሪ ዘንደሮ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ነውና በሰው ተኮር ሥራዎችም ላይ እናተኩራለን። ልክ እንደ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ሁሉ በሌሎችም ሥፍራ ላይ ያሉ ተፈናቃዮችን በስሱ እንጎበኛለን። የጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮችን ፕሮጀክትም እንደ ሠርቶ ማሳያ እናደርገዋለን። የጀመርነውንም እስከመጨረሻው ድረስ እንሄድበታለን። ወላጅ አልባ ተፈናቃይ ሕፃናትን የቴሌግራም ተከታታይ ጓደኞቼን በግል ስፖንሰር እያደረጉ እንዲያስተምሩ፣ እንዲንከባከቡ፣ እንዲያሳድጉም በማድረግ የጽድቅ ሥራን እንሠራለን። በወር ለአንድ ሕፃን 50$ እጅግ በቂ ነው። በዚያ መሠረት ለሁላችሁ የሚታይ ሰው ተኮር ሥራም በዘመነ ማቴዎስ እንሠራለን። ተዘጋጁ።

"…የቲክቶክ መንደር ቀፋላዎችን፣ ዘራፊዎችን፣ ሌባ ወንበዴ፣ ማጅራት መቺዎችንም ልክ እናገባቸዋለን። ሕዝብን መግፈፍ ዘንድሮ ያበቃለታል። ሌባ ሁላ ልክ ይገባታል። እኛ እየሠራን ሌቦችን ከጨዋታ ውጪ እናደርጋቸዋለን። አልፋታቸውም። ማርያምን አልፋታቸውም። በድሆች ኮሚሽን ይዞ መሸቀል ብሎ ነገር የለም። አዳሜና ሔዋኔ ሠርተህ ትበላታለህ። ነግሬሃለሁ። ዘንድሮ አላርፍ ካለ አጎቱ የደብረ ብርሃን ባህር ገላጭ አደገኛ ጠንቋይ ከነበረው እና በደም ተዋርሶ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ ከሚል የትግሬና የኦሮሞ ዲቃላ ከሆነ ከከሸፈ አክ እንቲፍስትም ጋር የሌለ ጦርነት ነው የምገባው። አንት አጎትህ ታደሰ የነበረ የጠንቋይ ልጅ እረፍ። አላርፍ ካልህ አሳይሃለሁ። በአጠቃላይ ማኅበራዊ ሚዲያውንም እናጸዳዋለን።

"…እኔ ዘመዴ ከእናንተ ከጓደኞቼ የምፈልገው አንገብጋቢ ነገርም አለ። እሱም ምንድነው ያላችሁ እንደሁ ጸሎት። አዎ ጸሎት ብቻ ነው የሚያስፈልገኝ። አንዲት አቡነ ዘበሰማያት እና ጸሎተ ማርያም። በቃ ሌላ ምንም ነገር አልፈልግም። እኔን ብላችሁ፣ ለእኔ አግዛችሁ ከአንድ ሰው ጋር አፍላፊ አትካፈቱ። እኔ እኔን ብላችሁ ስደቡልኝ፣ ተሟገቱልኝ፣ ተከራከሩልኝ ብዬ የቀጠርኩት፣ የለመንኩት፣ የተማጸንኩት አንድም ሰው የለም። እኔ ለእኔው እኔ ራሴው እበቃለሁ። እናንተ ብቻ ጸልዩልኝ። በቃ ይኸው ነው። ለኮተታም መልስ ስትሰጡ፣ ብዕራችሁን ስትዘሩ አትዋሉ። በእውነት፣ በማስረጃና በመረጃ እኔው እንደልማዴ አደባያቸዋለሁ። አሁን ስለወያኔና ስለ ብልጽግና ክፋት ለመስበክ ጉልበቴን፣ ጊዜዬን የማጠፋበት ሰዓት አይደለም። ለብልጽግናም፣ ለወያኔም ምሳቸው ተገኝቷል። እሱን ነው ማጠናከር ነው። ፋኖን ማጠናከር።

"…ስጠቀልለው ዘንድሮ ዘመነ ማቴዎስንም ልክ እንደ ዘመነ ዮሐንስ እሳት ለብሼ፣ እሳት ጎርሼ ነው የምመጣው። እንደ ዜጋ ስለ ሀገሬ፣ እንደ አማኝ ስለ ሃይማኖቴ እየመሰከርኩ፣ እየተናገርኩ፣ እየተሟገትኩ እግዚአብሔር ቢፈቅድ፣ በሕይወት ብንኖር እንዲህና እንዲያ እያደረግግሁ፣ ይህንና ያን በመሳሰሉት ተግባራት ላይም እየተሳተፍኩ ዓመቱን ለማሳለፍ ነው ዕቅዴ። የብዙ የፖለቲካም፣ የሃይማኖትም ጋለሞቶችን ቅስምም፣ ጅስምም፣ ቅልጥምም ለመሰባበር ነው ተዘጋጅቼ ያለሁት። ዘንድሮ የምር ነው እብድ እብድ የምጫወተው። ቀሽሞች ምንም ሊያመጡ አይችሉም። በፔጄ ላይ ስማቸውን ጠቅሼ ታዋቂ አላደርጋቸውም ብዬ ንቄአቸው፣ ተጠይፌአቸው ከምተዋቸው ትንንሽ አነስተኛና ጥቃቅኖች በቀር ዘንድሮ ዘንዶ ዘንዶውን ጭንቅላቱም አናቱም ላይ ነው ቆሜ ትንፋሽ የማሳጣው። 👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እህሳ ጎበዝ… እኔ ዘመዴ ዘመዳችሁ በቀጠሮአችን መሠረት ለዛሬ መስከረም 3/2017 ዓም አቀርብላችኋላሁ ያልኳችሁን ዓመታዊ የሥራ ዝርዝር ዕቅዴን በርእሰ አንቀጽ መልክ ልለጥፍላችሁ ነኝ። እናንተስ ርእሰ አንቀጼን አንብባችሁ ዓመታዊ ዝርዝር የሥራ ዕቅዴን ለማጽደቅ ዝግጁ ናችሁ?

• እስቲ ዝግጁ ነነ በሉኝማ በማርያም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነገ መስከረም 3/2017 ዓም ዓመታዊ የሥራና የትግል ዕቅዴ ይፋ የሚሆንበት ዕለት ነው። የአማሪካ ፕሬዘዳንቶች የሚጓጓዙበት U.S Air Force ሮጴላ ግን እንዴት አባቱ ነው የሚመች በናታቹ፣ ባባታቹ? ኢ…? ግሩም ነው።

• አስነጥስህሃለሁ…!😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ስኳድ ምስጌ "ለፀረ ጎጃም ፀረ ዐማራው ጣና ቴቪ ፈንድ ወደ ሚሰበስበው ) ጋሽ ሀሺሽ የጁንታ ባል ሚኪ ቤት እንሂድ እያለ ነው። እንሂድና ጉድ ላሳያችሁ እንዴ…?

"…የሚገርመኝ ጥያቄ ግን አለ። ለምንድነው የትግሬ ሚስት ያገቡ አካላት ፀረ ዐማራ ፋኖ የሚሆኑት? ያልተመለሰልኝ ጥያቄ ነው።

• እስክንድር ነጋ ~ ሚስት ትግሬ
• ዶር አምሳሉ ገንዘብ ያዥ~ ሚስት ትግሬ
• ሚኪ ሚዲያ~ የልጆቹ እናት ትግሬ
• አበበ በለው~ ወላጅ እናት ከየት ናቸው ነው ያላችሁኝ።
• ሃብታሙ አያሌው~ ባለቤቱ ከየት ትሆን?

"…ብቻ ገራሚ ነገር ነው። ለማንኛውም እንሂድ ወይ…? እንሂድና ሰዎች ላስተዋውቃችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ስላልገባኝ ካልደበራችሁ የሆነ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ነበር። የምሽት የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብራችን እስኪጀምር የሆነ ቪዲዮ አሳይቼአችሁ ሓሳብ እንድትሰጡበት ፈልጌ ነበር። ትንሽ መረር የሚል ቪድዮ ነው። ሕፃናት፣ ነፍሰጡሮች፣ የደም ግፊትና የልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች እንዲያዩት አይመከርም።

"…ልጠይቅ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• አቤ ሙንኦኖኖ…?

"…የጣና ቲቪ ሼር አለው እንዴ? ተው አቤ። ተው። ተው እረፍ። እኔ በጣም ነው የምወድህ። የማከብርህም። ተው እረፍ።

"…ወያኔንም፣ ኦነግንም አትስደብብን ብለን ጳጳስ፣ ቄስ ሁላ ልከንበት መክረነዋል አላለም። ከኦነግና ከወያኔ ጋር እየተታኮሰ፣ እየተገዳደለ ሲያበቃ እኔ ዘመዴን ወያኔን አትስደብብን አላለም ጋሽ አበበ በርሄ። 😂😂

"…እነ አበበ በለው ከእነ ሀብታሙ አያሌው ጋር ተጠቃቅሰው መረጃ ቲቪን በሆያ ሆዬ አዋክበው ሊያፈርሱ ዳከሩ። እኔ ዘመዴ ደግሞ ራሳቸውን እነዚህን የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ከሀዲዎችን ሰባበርኳቸው። ታሪኩ ይኸው ነው።

"…በተረፈ ፋኖዎች ወጥተው ዘመድኩን ተሳስቷል፣ ሀብታሙ አያሌውን፣ እስክንድር ነጋን፣ አበበ በለውን፣ ምስጋናው አንዷለምን ከነካህብን እንቀየምሃለን፣ እናስቀይምሃለን ብለዋል የምትለውንም ቀደዳ አልሰማህም። እኔ ማንንም እንደምተቸው፣ እንደምሸነቁጠው እኔንም ማንም ሊተቸኝ፣ ሊሸነቁጠኝ መብት አለው። መብቱም ነው።

"…ታዲያ ስትተቸኝ የመልስ ምት እንዳለ እንዳትዘነጋ። ስታስነጥሰኝ እኔም መልሼ እንደማስነጥስህ ማወቅ አለብህ። እገሌ ወእገሌ ብሎ ነገር የለም። ትችትህ ትክክል እስካልሆነ ድረስ እኔም ልክ አስገባሃለሁ።

"…ብሩክ ይባስ በቀደም ዕለት በአንድ ፋኖ ሲያስደብኝ ነበር። አበበ ጢሞም ዋይ ዋይ ሲልብኝ ነበር። ሁለቱንም ንቄ የተውኳቸው እፉዬ ገላ ሆነው ስለታዩኝ ነው።

"…በቀደም አርበኛ ሰሎሞን አጣናው ደውሎልኝ ነበር። ከምር ትልቅ ሰው ነው። ዘመዴ እንዲህ ብሏል ብለው ነግረውት እሱን ለማጣራት ነበር የደወለልኝ። ክርስቲያን፣ ባለ ማዕተብ ስለሆነ ወሬ ሲነግሩት አልተቆጣም። ወደ እኔ ደወለ። ተነጋገርን። እኔ እንዲህ እንዳላልኩ ነግሬው ብዙ አውርተን ተለያየን  መፍትሄው ይሄ ብቻ ነው።

• አይዞኝ አቤ። ገጥመናል ገጥመናል ነው። ቻለው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…!

"…አቢይ አህመድ እንደ ትግሬና እንደ ዐማራዎቹ ባይገድላቸውም ኦሮሞዎቹንም ጢባጢቤ ተጫውቶባቸዋል የሚሉ አንዳንድ መተርጉማን አሉ። አቢይ እንዴት ተራ በተራ ቁማር እንደበላቸው እንመልከት።

"…ጀዋር መሀመድ። አቢይ ማይም ነው ብሎ እምቡር እምቡር አበዛ። በገመድ አስሮ ጥጃው ጃዌን ለቀቀው። ጃዌ ሃገር አልበቃው ብሎ ሲቦርቅ ገመዱን አሳጠረበትና በደረቅ ሱፋጭ ፀጉርን ላጭቶ ዘብጥያ ወረወረው። ጃዊ ተንፍሶ ወጣ። ምርጫ ቀረበለት እንደ ሃጫሉ ከአፈር ትቀላቀላለህ ወይስ ትፈረጥጣለህ። ጃዌም አለ። ኧረ ልፈርጥጥበት ብሎ ነካው። ወደ ሀራሬ ሳይሆን ወደ ናይሮቢ።

"…ፓስተር በቀለ ገርባ ጃዋር ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናል ብሎ ለጃዋር ተገረደ። በአማርኛ ለሚጠይቃችሁ ዕቃ አትሽጡም አለ። ፈነዳ። በመጨረሻም በሱፋጭ ተላጭቶ ዘብጥያ ገባ። ኦሮሞን ኦሮሞ አይገድለውም ብሎም ምርጫ ሰጠው። ፍርጣ፣ ወይም ደፍት? ነካው በቄ። ነካው ወደ አማሪካ።

"…ኦነጉን ሌንጮ ለታን ደግሞ አርቆ ሳዑዲ አረቢያ ለከው። እዚያ ዱቅ ብሎ አለሙን እየቀጨ ሀገር ሰላም ሆነለት። ሲቆይ አብይ አህመድ ድንገት አንደኛውን ሌሊት ሲያይ ባደረው ህልም ላይ ውቃቢው የኦሮሞ ወዳጆቹን ሙልጭ አድርጎ ማጥፋት እንዳለበት ይጠቁመዋል። ከዚያ ወደ ሥራ ገባ። ለአሜሪካ ፍሬንዶቹ ልልከው ነኝና አዋርዱልኝ ብሎ አሜሪካ አምባሳደር አድርጎ ላከው። አሜሪካም ቅሌቱን አንብባ ጥፋ ከዚህ አለችው። ሌንጮ ጨረቃ ላይ ዱቅ። ሬድዋን እንዳይበጠብጠው ከኢሱ ጋር ተጠቃቅሶ አስመራ ዓመት ሙሉ የቁም እስር እንዳሰረው ማለት ነው።

~ ቀጀላ መርዳሳ~ ጨረቃ ላይ
~ ዳውዳ ኢብሳ~ አልጋ ላይ (ዳይፐር)
~ በቴ ኡርጌሳ~ ወደሰማይ ቤት ሸኘው
~ ከማል ገልቹ~ አርሰህ ብላ ብሎ ወደ ገጠር…
~ ዲማ ነገዎ… ከሀገር እንዳይወጣ አድርጎ ጨረቃ ላይ

• የዘነጋሁት ካለ ጨምሩበት

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…!

"…በኮሪደር ልማቱና በወንዝ ዳር ልማት ስም በአጭር ቀን ትፈርሳላችሁ ተባልን የሚሉ ብዙ የአዲስ አበባ ነዋሪ ድምጾችን እየሰማሁ ነው። ጎንደርም፣ ዲላና አዋሳ፣ ደብረ ዘይትም እንዲሁ ዋይ ዋይ የሚሉ አሉ።

• አዲስ አበባ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ሙሉ በሙሉ፣ ትምህርት ቤቱ ሁላ ይነካል እየተባለ ነው። በካሳንቺስ መነሃሪያ የሚተርፍ የለም።

• ፈረንሳይ ለጋሲዮን በጫካ ቤተመንግሥቱ ፕሮጀክት ምክንያት እስከ መስከረም 20 ድራሽ አባታችሁ ይጥፋ መባላቸው እየተነገረ ነው።

• ከሽሮሜዳ እስከ መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን ድረስ በተመሳሳይ ቀን፣ በተመሳሳይ ሁኔታ የተወሰኑቱ በኮሪደር ልማት የተወሰኑቱ ደግሞ ወንዝ ዳር በርቀት ላይ ቢኖሩም በወንዝ ዳር ልማት በሚል እንደሚያፈርሱ ተነግሯቸዋል ተብሏል።

"…ብቻ ከመስከረም 20 እስከ መስከረም 30 ድረስ ብዙ ክፍለ ከተሞች ድራሻቸው ጠፍቶ መሬቱ አበባ ይተከልበታል ተብሏል።

• የሚነሡት ሰዎች የት ነው የሚያርፉት…? የቀበሌ ቤት ውስጥ ያሉ፣ ደባሎችስ ምን ይውጣቸው ይሆን…?

• ያለ ወረቀት በቃል ብቻ መጥቶ ተነሥ ብሎ መንገር ማለትስ ምን ማለት ነው?

• የማይፈርሰው የትኛው ሰፈርና ከተማ ነው?

• ኦሬክሶቹ ግን ምን አስበው ነው…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…!

"…ይሄም የእኛው የማንሸሽገው ዕዳችንም ጉዳችንም ነው። እስቲ የሆነ ሓሳብ ስጡበት…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል ጀምሯል…

• ግጥም ስጡትማ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!
       ✍️✍️✍️…በአዜብ ወርቁ

"…የልማት ተነሺ ተብሎ ሰዎች ድንገት ቤታቸው ሲፈርስ ስለገጠማቸው ጉዳት ብዙ የሚያሳዝኑ ታሪኮች ሲነገሩ ሰምቻለሁ። ነገሩ ቢያሳዝነኝም፣ የስሚ ስሚ አይቼ ሳልመረምር አስተያየት ብሰጥ ሚዛናዊ አልሆን ይሆናል፣ እሳሳት ይሆናል በሚል ከማዘን በስተቀር ምንም አላልኩም ነበር፣ አሁን ግን ለልማት ድንገት መፍረስ የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት።

"…የማወራው ስለአንድ ሰው ታሪክ ነው፣ ተቆጥሮ ህዝብ ስለሚባለው፣ ሀገር በማቅናት ውስጥ ማህበረሰብ በመስራት ውስጥ አስተዋጽኦ ስላለው አንድ ሰው ነው።

የሕይወት ታሪኩ እንዲህ ነው ...

"…ገና ጎረምሳ እያለ ከተወለደበት ገጠር ወጥቶ 250 ኪሎሜትር በእግሩ ተጉዞ አዲስ አበባ ገባ። አዲስ አበባ በግለሰቦች ንግድ ቤት ተቀጥሮ ከጽዳት አንስቶ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርቶ ከራሱ አልፎ ወላጆቹን ቤተሰቡን ረድቶ፣ ትዳር መስርቶ፣ ልጆች አፍርቶ፣ የግል ንግድ ከፍቶ ሲኖር ቆይቶ የዛሬ 60 ዓመት አካባቢ ከፈረንሳይ ኤምባሲ ወረድ ብሎ ከሃይዌዩ ድልድይ ስር የግንብ ግድግዳ ላይ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” የሚለው ጽሑፍ በደማቁ በቀይ ቀለም ከተጻፈበት ፊትለፊት ወደ ቤላ በሚወስደው ቀኝ መታጠፊያ መንገድ ላይ መሬት ገዝቶ ቆንጆ ቤት ሠርቶ ኑሮውን መሰረተ።

"…12 ልጆችን አሳድጎ፣ አስተምሮ ለወግ ለመዓረግ አበቃ፣ የልጅ ልጅ አየ። አሁን የ 94 ዓመት አዛውንት ነው። ጠንካራ፣ ደግ፣ ሠራተኛ፣ ተጫዋች፣ ቀልድ ዐዋቂ፣ ሰው ሁሉ የሚወደው፣ ሰውን ሁሉ የሚወድ፣ ሃይማኖቱን አክባሪ እምነቱን አጥባቂ ነው። የግቢ አትክልት ይወዳል። ግቢው በወይን፣ በአቩካዶ፣ በኮክ፣ በአፕል፣ በቡና ዛፍ የተሞላ የሚያምር ግቢ ነው። የአትክልት ፍቅሩ ለራሱ ቤት ብቻም አይደለም፤ ሰፈር ውስጥ እየዞረ በሰው ቤት በዘመድ ቤትም ችግኝ  ከቤቱ እየወሰደ ይተክላል።

"…ይህ ጠንካራ ሰው በቅርቡ በህመም አልጋ ላይ ዋለ። “በቂ ኖሬያለሁ ሆስፒታል እንዳትወስዱኝ በኖርኩበት ባረጀሁበት ቤት አስከሬኔ ይውጣ” አለ። ልጆቹ ቃሉን አከበሩለት ቤቱ ውስጥ እንዳለ ሀኪም እያየው በልጆቹ፣ በልጅ ልጆቹ በቤተዘመድ በጎረቤት ተከቦ እንዲያስታመሙት አደረጉ። ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማ በሰፈሩ አንድ ዜና ተሰማ። ከወረዳ የመጡ ሰዎች እየዞሩ ለልማት እየመዘገቡ ነው የሚል።

"…የአዲስ ዓመት በዓል ማግስት መስከረም 2 መጥተው በ20 ቀን ውስጥ ቤታችሁ ለልማት ሊፈርስ ስለሆነ ለመስከረም 3 ጠዋት ለስበሰባ ኑ የሚል መልእክት በቃል ብቻ ተነገረ። እንዲህ ያለ ዱብ እዳ ሲሰማ ለሕግ ጉዳይ መዋሉ ቢቀር እንኳን ህልም ይሆን እንዴ ብሎ ድጋሚ ዓይቶ ለማረጋገጥ የሚያስችል ብጣቂ ወረቀት አልተሰጠም። ልክ እንደ ክፉ መርዶ ነጋሪ በር አንኳኩተው በቃል ትእዛዝ ሰጥተው ሄዱ።

"…መስከረም 3 በስብሰባው ላይ ስልክም ሆነ ማንኛውም ድምጽ እና ምስል መቅጃ ይዞ መግባት ባልተፈቀደበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢዎቹ ቤታችሁ ለልማት ይፈርሳል የሚለው መርዶ ተነገራቸው።

• ለምን?

~ ለጫካ ፕሮጀክት ልማት።

• መቼ?

~ እስከ መስከረም 20።

"…ተሰብሳቢው ደነገጠ። “ልጆቻችንን ትምህርት ቤት አስመዝገበናል፣ ዩኒፎርም አሰፍተናል፣ የደከመ ታማሚ  ቤታችን ስላለ ጊዜው አይበቃንም፣ የዕለት ጉርሴ ከቤት ኪራይ የማገኘው ብቻ ነው፣ ምን ልሁን? የሚሉ አዛውንቶች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ጮኸው አልቅሰው ተናገሩ። ሁለት ሳምንት አላችሁ ተባሉ።

• ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል??

"…በየቤቱ ያለ እቅድ፥ ያለ ኑሮ... ለቅሶ፣ ጽኑ ታማሚ፣ ሰርግ፣ አራስ፣ የደረሰች ነፍሰጡር....ቤቱ ይቁጠረው። ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል? ምንድነው ጥድፍድፉ? ልማት ታስቦ እንደሆነም እኮ በረጅም ጊዜ እቅድ ላይ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሊቀመጥ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ሰው ነው።

"…ነዋሪው እንዴት ይነሳ? ወዴት ይሂድ የሚለው እንጂ ትግበራ ከተጀመረ በኋላ በመጨረሻው ሰዓት ለነዋሪው በቀናት ውስጥ ትነሳለህ ብሎ በቃል መንገር እንዴት? ሰው ያነሰ ቅድሚያ ነው የሚሰጠው? ልማቱ ለሰው ነው አይደል??

"…ይህ ቤተሰብ የመራ፣ ሀገር ያቀና፣ ስንቱን ያስተማረ፣ የዳረ፣ አስታሞ በክብር የቀበረ፣ የተጣላን አስታራቂ የሐገር ሽማግሌ፣ አልጋ የያዘ መንቀሳቀስ፣ መንቃት የማይችል፣ ፈጣሪው ጋ እስኪሄድ ቀኑን የሚጠብቅ አረጋዊ እስከ መስከረም 20 ይነሳ ቤቱ ይፈርሳል ተባለ።

"…እንዴት ይሄድ? የት ይሂድ? በኖረበት ሰፈር ባቋቋምው እድር፣ በሚወደው አብሮ በኖረው የሰፈር ሰው ላይሸኝ? የሀገር ትርጉም ሲነገር “አባት የሞተ እንደሁ በሀገር ይለቀሳል” አልተባለም ነበር እንዴ? እና ለአባት የሚለቅሰበት፣ ለቅሶ የሚቀመጡበት ሀገር የለም??

"…ልማት ማንም አይጠላም፣ ማማር፣ መታደስ ማንም አይጠላም። የሰው ልጅን ግራ ሲያጋባ ለድንገተኛ ስጋት ሲዳርግ፣ ሰው ሁሉ የኔስ ተራ መቼ ይሆን እያለ በጭንቀት እንዲኖር ሲገደድ፣ ክብርን ሲነካ፣ ሰውነትን ሲያፈርስ ግን አዎን ልማት ይጠላል!!

"…ይሄን ጽሑፍ የምታዩ የልማት ደጋፊ ነን ባዮች ኮመንት ላይ መጥታችሁ፣ "እና ሀገር አይልማ? ሀገር ሲለማ አይናችሁ የሚቀላ፣ የልማት አደናቃፊዎች" ትሉ ይሆናል። እውነቱ ግን የልማት አደናቃፊ እናንተ ናችሁ።

"…እንደግፈዋለን የምትሉት ልማት በሰዎች እንዲጠላ፣ ሰው እንዲያለቅስበት፣ የምትታትሩ ዛሬን እና ሆዳችሁን ብቻ የምታዩ፣ ከሆዳችሁ ውጪ ሌላ ነገር የመደገፍ አቅም የሌላችሁ ሰባራ ሸንበቆዎች የልማት ጠላቶቹ ናችሁ።

"…ድንገት እንደ ሱናሜ አደጋ ቤታችሁ የፈረሰባችሁ ወገኖቼ፡ እስቲ ተናገሩት እንዴት ሆናችሁ? እንዴት አለፋችሁት?

"…እስቲ እውነተኛ ታሪካችሁን፣ ስሜታችሁን፣ ትኩስ ትዝታችሁን አጋሩን ታሪክ ይጻፍ። ለሚመለከተው አካልም ሰውን ሳያፈርስ፣ ቤት አላልኩም ሰውን ሳያፈርስ ሰዉም ተቀብሎት ሊሠራ እንደሚችል ትክክለኛ ጥቆማ እና ድጋፍ ይሁነው። በማለት አዜብ ጦማሯን ትቋጫለች።

• አዜብ ወርቁ ተዝብቷን በዚህ መልኩ ገለጸች። ተነፈሰችም። እናንተስ ምን ትላላችሁ…? ከ10 ደቂቃ በኋላ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ሰቆ 3፣ 22-23 “…ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።” መዝ 113፥3።”

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነፃ የማስታወቂያ ሰዓት ነው…!

"…መረጃ ቲቪን ከጨዋታ ለማውጣት ተብሎ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሸር፣ በተንኮል፣ በሴራ የተከፈተው እና ለፋኖ በተሰበሰበው ብር ሀብታሙ አያሌውንና ስታፉን ሲቀልብ፣ የቤት ኪራይ ሲከፍል የከረመው የምኒልክ ቲቪ፣ ሀብታሙ አያሌውንና ሽሜ አበራ ጆሮን ይዞ በዐማራ ስም አውሮጳን ከእነ ጌራ ግንቦቴ ጋር ሊግጥ የነበረው በአውሮጳ ከስዊድን ግንቦት 7 በቀር የጠሩት ሁሉ እንዲሰርዙ ከተደረገ በኋላ ወደ ካናዳም ሄዶ የተባረረው፣ ቬጋስና አትላንታም ክፍ ቺድ ከዚ የተባለው ቡድን አሁን ደግሞ በጎንደር ስም ዐማራን ሊግጥ አይኑን በጨው ታጥቦ መጥቷል።

"…በነገው ዕለትም ይሄ ወራዳ ጎንደር አሰዳቢ ቡድን ይሄ ጎንደሬ ነኝ በሚል በፍፁም የጎንደር ሰው ስብዕናና ማንነት በሌለው ሰው የቲክቶክ ቤት ለእስክንድር ነጋ አዲሱ ቴሌቭዥን ጣቢያ እርዳታ ለመሰብሰብ ቀጠሮ ይዟል። እንዳትቀሩ። 😂😂😁

• እንደ እኔ ደግ ከወዴት ይገኛል? ምስጋና ባይኖረኝም ይኸው በነፃ ማስታወቂያ እየሠራሁ እኮ ነው።

• እያሟሟቅሁ እንጂ ጦርነቱን ግን ገና አለመጀመሬ ይታወቅልኝ።

• እባክዎ ጣና ቴቪን መርዶም ቢሆን ያርዱ። ሓሳብ ጣል ጣል አድርጉላቸው። ፈረንካ ቢጠፋ ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ አስተያየት በመስጠት ተባበሩአቸው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የአይጥ ምስክር…

"…ጠንቋይም፣ የጠንቋይ ልጅም፣ ቃልቻም የቃልቻ ልጅም፣ አስማተኛ፣ የአስማተኛ ልጅም፣ መጫኛ የሚያቆም፣ ባህር የሚከፍል አጋንንትም፣ ዲያብሎስም፣ ሳጥናኤልና ሰይጣንም አልፈራም።

"…ከወሎና ከአፍራሳ የሆነችው ሀብታሙ አያሌውን እስክንድር ነጋ እንደ ኮንዶም ተጠቅሞባት፣ በወር ከ65 ሺ ዶላር በላይ መቀለብ አቅቶት መረጃ ቲቪን አፍርሶ በምኒልክ ቴቪ በኩል አበበ በለውን እስክስታ፣ ሀብታሙ አያሌውን እሩምታ እያስመታሁ እሸቅላለሁ፣ ይሄን ላሜ ቦራ ዳያስጶራ አጥበዋለሁ ብሎ ቢደክምም እኔ ዘመዴ ታክል ገብቼ ወፍ የለም አስባልኩት። ወፍ የለም። ሊበላ…!

"…አሁን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ገንዘብ ሲጠርበት ጎንደሬ የሚመስሉ ፀረ ጎንደሬ የጎንደር ጠላቶችን ይዤ፣ ጎጃምና ጎንደርን የሚያጣላ አጀንዳ ጣና ቴሌቭዥን ብዬ፣ ጎንደሮችም ያን አይተው ብሸውዳቸው፣ ባታልላቸው ብሎ በአዲስ መልክ ቢመጣም እኔ ዘመዴ ገጀራ ሆኜ ጣና ቴሌቭዥን የእስክንድር ነጋ መሆኑን በነጭ ነጯን ላይ ዐዋጅ አወጅኩ። የጎንደር ሕዝብ ብልህ ነው። የፖለቲካ ነቢይ ነው። እናም ባነነባቸው። መረጃ ቲቪን ቢረግሙ፣ እኔን ቢያሳቅሉ ወፍ የለም።

"…ሀብታሙ አያሌው መተፋቱን አላወቀ፣ አልገባው፣ አሁን ሲብስበት የምስጋናው አንዷለም ፖስትር እየተልከሰከሰ ላይክ ይለይካል። እነ ጋሻው መርሻ ሀብታሙን ሊበቀሉት የደገሱለትን ድግስ አላወቀ ዝም ብሎ በጭፍን የእውር ድንብሩን ይንበጫበጫል።

• አጨልላችኋለሁ። ለፋኖ የተሰበሰበ ገንዘብ የበላችሁትን በሙሉ መፈጠራችሁን እስክትጠሉ ነው የምተገትጋችሁ።

"…ውጊያውን ጀመርኩ ማለት ነው። 😂 …ጠብቀኝ ፀረ ፋኖ ምድረ የጠንቋይ ልጅ አጋንንታም ኋላ። በባለ ማዕተቡ ጎንደሬ ስምማ አትነግዷትም።

• አበደን አትነግዷትም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍

"…ሌላው ዘንድሮም አጀንዳ በማክሸፍ ላይ ብቻም አንጠመድም። አጀንዳም በመስጠት ጭምር እንሳተፋለን እንጂ። በአገዛዙ አክ እንቲፍስቶች የሚለቀቅ አጀንዳ ይዘህ ዋይዋይ እሪ እሽኮለሌ የምትል ለደንታህ ነው። እኔና ጓደኞቼ በሙሉ ግን የተለቀቀ ቪድዮ፣ የተሰራጨ ፎቶ፣ የተሠራ ዜና አይተን፣ ሰምተንና አንብበን ለምን፣ እንዴት፣ መቼ ብለን ሳንጠይቅ ዋይ ዋይ አንልም። እኛ ነቄ ጠያቂዎች ነን። አስሬ ለክተን አንዴ ነው የምንቆርጠው። እኔና ጓደኞቼ ቪድዮ ብቻ ዓይተን፣ ኢንተርቪው ብቻ ሰምተን ነጠላ ዘቅዝቀን የምናለቅስ አይደለንም። ለእሱ ሚልዮን ማይሞች አሉላቸው። ሳያላምጡ የሚውጡ፣ ሳይጠይቁ የሚቀውጡ ሚልዮኖች አሉላቸው። እኛ ግን የተረጋጋን ነን። ቆም ብለን ግራና ቀኝ ዓይተን ነው የምንራመድ፣ አስሬ እንለካለን አንደዜ እንቆርጣለን።

"…ይኸው ነው የዘንድሮ የዘመነ ማቴዎሱ የ2017 ዓም የእኔ የዘመዴ ዘመዳችሁ ዓመታዊ ዕቅዴ፣ የሥራ ፕላኔ። ከተሰጠኝ 365 ቀን ውስጥ የዛሬን ሳገባድደው የሚቀሩኝን 362 ቀናት በብዙ አትርፌበት ለማለፍ እጥራለሁ። እንዲያው በዓመት ውስጥ በትንሹ ለ365 ሕፃናት ቀጥተኛ ስፖንሰር ባገኝ ከእኔ በላይ ማን ይጠቀማል? ማን ያተርፋል? ማንስ ይጸድቃል? አዎ ይሄን ነው የማደርገው። ይሄን ነው የምሠራው። በእኔ እጅ 05 ሳንቲም፣ ድንቡሎ፣ ጢና ዱዲ ሳያልፍ በቀጥታ ችግረኛ ሕፃናቱንና ስፖንሰሮቹን በማገናኘት የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ። ያለኝን ተሰሚነትና፣ ተደማጭነት በሚታይ፣ በሚዳሰስ፣ በሚጨበጥ መልኩ ለሀገር ለወገን በሚጠቅም ተግባር ላይ አሳልፈዋለሁ። ደሀ ተበደለ፣ ፍርድ ተጓደለ ማለቴን ሳላቋርጥ ከስር ከስሩ እንዲህ ዓይነት የጽድቅ ሥራም በመሥራት የተሰጠኝን ዘመን በደስታ አሳልፋለሁ።

"…አንተ ቆቱ፣ አንተ ጋላ፣ አንተ እብድ፣ አንተ መራታ፣ አንተ ሌባ፣ አንተ ወያኔ፣ አንተ ነፍጠኛ፣ አንተ ኦነግ፣ አንተ ብልጽግና፣ አንተ ዘማዊ፣ አንተ ተሳዳቢ፣ አንተ ለፍላፊ፣ አንተ ቀፋፊ፣ ዘመድኩን ነቀለ ወዘተ የሚሉ ከተሸናፊ ተጋጣሚዎቼ ዘንድ የሚከፈለኝ ደሞዜ ነው። አደራ አደራ ደሞዜን እንዳታቋርጡብኝ። ተናግሬአለሁ። ስኳድ ሰምተሃል። ቲክቶከር ሰምተሃል። ግንባሩ፣ ሠራዊቱ፣ ግንቦቴ እና ፌክ ኢትዮጵያኒስቱ፣ ብልፄ፣ ወዩ ሂዊ፣ ኦነግም ሰምታችኋል። አደራ ደሞዜን እንዳታስቀሩብኝ። አደራ። እኔ በእናንተ ካልተሰደብኩ ከባህር እንደወጣ ዓሣ ነው የምሆነው። የእኔ አየር ኦክስጅኖች እናንተ ናችሁ። በወንድ ልጅ አምላክ እንዳትጨክኑብኝ። ስደቡኝ። አሰድቡኝ። እንደ ንስር ታድሼ እንድወጣ እርዱኝ። አግዙኝ።

"…እናንተ የእኔዎቹ ግን ደሞቼ፣ ጓደኞቼ ዘመዴ "አክሊለ ገብርኤል" የጀመረውን አስፈጽመው። ፍጻሜውንም አሳምርለት። ጀምሮ ከመተው ሰውረው። ኃይልህን፣ ዕውቀትህን፣ ጥበብህንም፣ ዕድሜም፣ ብርታትም፣ ጤናውንም ስጠው ብላችሁ ለጸሎት በቆማችሁ ግዜ ሁሉ በጸሎታችሁ ለሰከንድ ታህል አስቡኝ። የኢትዮጵያን ትንሣኤ በጋራ ለማየት እንዲያበቃንም አጥብቃችሁ ስለእኔም ስለ ኃጥእ ባሪያው ወንድማችሁ በብዙ ጸልዩልኝ። በመጨረሻም ዓመታዊውን የሥራ ዕቅዴን የቴሌግራም ቤተሰቦቼ በሙሉ ድምጽም ባይሆን በጥቂት ተቃውሞ፣ በጥቂትም ድምጸ ተአቅቦ ታጸድቁልኝ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ። በብዙ አመሰግናለሁ።

•••

ሻሎም…!   ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
መስከረም 3/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ነው። ዘመነ ማቴዎስ ወንጌላዊ። ምንም እንኳ በወንጌል ተራ ቁጥር በቀዳሚነት ተቀምጦ ብናገኘውም ቀድሞ በመጻፍ ግን ወንጌለ ማርቆስ ይቀድማል ይላሉ ሊቃወንቱ። ማቴዎስ ምልክቱ የሰው ገጽ ነው። ክንፍ ያለው የሰው መልክ። በቅድስት ሥላሴ ሥዕል ላይ የሥላሴን መንበር ተሸክመው የምናያቸው አርባዕቱ እንስሳ (እሳታውያን ኪሩቤል) ማለትም የሰው፣ የላም፣ የአንበሳ እና የንስር ሥዕሎች በ4ቱም ወንጌላውያን ላይ ተመድበው ተሰይመውም እንመለከታቸዋለን። ገፀ ሰብዕ የተወከለው ለወንጌላዊው ማቴዎስ ነው። ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር “…የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።” ማቴ 1፥1 ይህ ነው ብሎ ስለሚጀምር፣ አንድም ወንጌላዊው በ28 የወንጌል ምእራፉ 28 ጊዜ አካባቢ አይሁድን ለማሳመን ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት እየጠቀሰ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት እና ፍጹም ሰው መሆን ለማጠየቅ በወንጌሉ "የሰው ልጅ" እያለ በመስበኩ፣ በአጠቃላይ ሰው ተኮር በመሆኑ በገጸ ሰብእ ተወክሏል። ለእኔም ይህ 2017 ዓም ሰው ተኮር ሥራ፣ የሰው ልጅ የሚከብርበት፣ ድልን፣ ነፃነትን የሚቀዳጅበት ዓመት እንዲሆን እየተመኘሁ በሰው ተኮር ሥራዬ ላይ ትኩረት ሰጥቼ አሳልፋለሁ ማለት ነው።

"…እኔ ዘመዴ ዘንድሮም በአምና ካቻምናው የትግል መስመሬ የምቀጥል ሲሆን ከአምና ካቻምናው ትንሽ ለየት የምልው እንደ አምና ካቻምናው በብዙ ልቅሶ፣ በብዙ ዋይታ፣ በብዙ እሮሮ ላይ አላተኩርም። ደረት የሚያስደቁ፣ ዋይ ዋይ አስብለው ፊት በሚያስነጩ፣ አልህ በሚያሲዙ፣ ምላጭ በሚያስውጡ፣ እዬዬ ዜናዎችም ላይ አላተኩርም። አልቃሻ፣ ተነጫናጭ፣ እሪ ቁቁም ኡኡኡም ባይ ዜና ባገኝ እንኳ እንደ ድሮው ሰፍ ብዬ አልዘግብም ሳይሆን ብዘግብም አላጮኸውም። ዘንድሮ ለመዘገብ አሰፍስፌ የምጠብቀው የድል ዜና ብቻ ነው። ከዜሮ ተነሥቶ እዚህ የደረሰውን አንድ ዓመት የሞላውን የዐማራ ፋኖን የድል ዜና ብቻ። እሱን መስመር ነው አነፍንፌ እያሸተትኩ የምዘግበው። ልቅሶና ዋይታ፣ እዬዬ ሙሾ አውራጅ አልቃሾችን፣ “…ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው።” ማቴ 8፥22 እንዲል መጽሐፍ እዚያው ቁጭ ብለው ባሉበት፣ ግብር ተጨመረብን፣ ነዳጅ ጨመረብን፣ ከሥራ ተፈናቀልን፣ ሁለት አውቶቡስ ሙሉ ታግተን በሰው ሚልዮን ብር ለቄሮ ከፍለን ወጣን እያሉ እዬዬ እንዲሉ በመተው እኔ ግን ከጀግኖቹ መንደር እውላለሁ። አመሻለሁ አድራለሁም። አከተመ።

"…እኔ ዘመዴ አክሊለ ገብርኤል የዘመኑን የአሁን የቅርብ ጊዜውን የዐማራ ፋኖን ትግል አምጠው ከወለዱት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ ነኝ ብዬ ስናገር ቅሽሽ ሳይለኝ ነው። ለዚህ ደግም ምስክር መቁጠር ሳያሻኝ፣ ሳያስፈልገኝም፣ በድፍረትም፣ በኩራትም ነው ደረቴን ነፍቼ የምናገር። የዐማራ ፋኖ ትግል መሪ ግን አይደለሁም። ዐማራ ታጥቆ ለነፃነቱ እንዲታገል ከወተወቱ ሰዎች መሃል ግን አንዱና ምንአልባትም ዋነኛው ነኝ። ስለሆነም ከዐማራ ፋኖ ትግል ላይ ልክ ሰጎን ከእንቁላሏ ላይ ዓይኗን ዘወር እንደማታደርገው ሁሉ እኔ ዘመዴም ዓይኔን ለአፍታም ቢሆን ከዐማራ ፋኖ ትግል ላይ አላነሣም። የፈለገ ይበድ፣ የፈለገ ይጩህ፣ የፈለገ ይፍረጥ፣ ይነሣ፣ ይቆመጥ፣ ይዝረክረክ ለደንታው ነው። እኔ መስሚያዬ ጥጥ ነው። ጆሮዬን ደፍኜ ነው የዐማራ ፋኖን ትግል በንቃት የምከታተል። የፈለገ ጎንደሬ ነኝ፣ ጎጃሜ ነኝ፣ ወሎዬ ነኝ፣ ሸዋዬ ነኝ የሚል ይነሣ፣ ይቃወመኝ፣ ይቀደድብኝ፣ እንደፈለገም ይበጥረቅ፣ ሲሰድበኝ፣ ሲያወርደኝ ውሎ ይደር እኔ ዘመዴ ግን አልሰማውም። የዐማራ ፋኖን ትግል ለማበላሸት፣ ለማቆሸሽ፣ ለማጠልሸት፣ ለመጥለፍ፣ ለማዘግየት፣ ለማወክ፣ ለመበጥበጥ፣ አይደለም የሚሞክር የሚያስብ እንኳ ካለ አጥብቄ እታገለዋለሁ። በጭቃ ዥራፍ ብዕሬ እዠልጠዋለሁ። በስልና ሹል የብዕር ጥርሴ እነክሰዋለሁ፣ አደማዋለሁ። እሳት በሚተፉት ብዕሮቼም ጥፍሩንም፣ ጥርሱንም አወላልቅለታለሁ። አመድ ዱቄት ነው የማደርገው። ምንአባቱ እንደሚያመጣ እናያለን።

"…ዘንድሮ በ2017 ዓመተ ምሕረትም ልክ እንደ አምናው በንቃት የሀገሬን ጉዳይ እከታተላለሁ። ያለፈው ዓመት ዘመነ ዮሐንስ ነበር። ወንጌላዊው ዮሐንስ የተወከለው ክንፍ ባለው ንስር ነው። በንስር መወከሉም ምስጢረ ሥላሴን፣ ምስጢረ ሥጋዌን አምልቶ፣ አርቅቆ በመጻፉ ነው። ንስር ከደመና በላይ ርቆ በምድር ላይ ያለን ቁራጭ ሥጋ ማየት እንደሚችል ቅዱስ ዮሐንስም ለሰው ልጅ፣ ሥጋ ለባሽ ለሆነው የማይታይ የማይገለጠው የመለኮት ምስጢር ተገልጦለት ወንጌለ ዮሐንስን ስለጻፈ ነው በንስር የተመሰለው። “…በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” ዮሐ 1፥1 እያለ ስለጻፈ፣ የቃል ኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔር መሆን ያየ፣ የተመለከተ፣ ያ ቃል “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” ዮሐ 1፥14 በማለት ምስጢረ ተዋሕዶን የአምላክን ሰው መሆን፣ የሰውን አምላክ መሆን አርቅቆ ስለጻፈ ነው በንስር የተመሰለው።

"…ባለፈው ዓመት በዘመነ ዮሐንስ እኔም ዘመኑን ዋጅቼ ነበር ያሳለፍኩት። የተደበቁ በዐማራ ትግል ላይ የተሴሩ ድብቅ ሴራዎችን እንደ ንስር ከሩቅ ከራየን ወንዝ ማዶ ሆኜ በማየት ነበር በአደባባይ ሳዝረከርከው፣ ልክ ሳገባው ያሳለፍኩት። ባለፈው ዓመት የስንቱን ሰው መሳይ በሸንጎ ጭንብል ነው የገፈፍኩት። የስንቱን አስመሳይ ቀጣፊ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ነው ለምዱን የገፈፍኩት። የሥንቱን አፈጻድቅ ርጉምነት፣ የስንቱን የቤት ቀጋ የውጭአልጋ እሾህ፣ ሚስማር ሆኜ ስነቅል የከረምኩት። አይነኬ፣ አይደፈሬ ሆነው በዐማራ ትግል ውስጥ እንደ ጳጳስ እንደ ሼህ ይፈሩ፣ ይከበሩ የነበሩ ስንቶችን ጎልያዶች ነው የዳዊት ጠጠር ሆኜ አጋድሜ በዝረራ የጣልኩት። አልባሌ ተራ ለአቅመ ምእመንነት እንኳ እንደማይደርሱ አድርጌ ያሳየሁት። ታላቁን ታናሹ፣ ጋዜጠኛውን መጋኛ እንደመታው አጣምሜ ያስቀረሁት። ስንቱን የዐማራን ችግር፣ ብሶት፣ ሰቆቃ መተዳደሪያቸው አድርገው የያዙትን ልክ አግብቼ በዩቲዩብ፣ በሳተላይት ቴሌቭዥን ጭምር ስለማርያም ብለው መለመን እስኪቃጣቸው ያደረስኩት፣ ስንቶቹን ነው በዐማራ ስም ብር ሊዘርፉት ያሰፈሰፉትን ሁሉ ገጀራ ሆኜ አጨብጭበው እንዲቀሩ ያደረግኩት። ቁጠሯቸዋ።  ዘንድሮም እንደዚያው ይብስብኛል። ዘንድሮም ከአምና ካአቻምናው በበለጠ መልኩ እረፍት እነሳቸዋለሁ። እፋለማቸዋለሁም። ወጥር ዘመዴ።

"…ውጊያው በምላስና በብዕር ስለሆነ ምንም ወጪ የለውም። ለዚህ ውጊያ ምንም ዓይነት በጀትም፣ የሰው ኃይልም፣ ስንቅም አያስፈልገውም። ጎፈንድሚ፣ የሲያትል፣ የቶሮንቶ ቻፕተር ምንትስዮ፣ ቅብጥርስዮም አይፈልግም። እኔ ዘመዴ 18 ዓመት ያለፈኝ ጎልማሳ ስለሆንኩኝ አጋዥ፣ ቲፎዞም አያስፈልገኝም። ተጨማሪ መረጃ የሚለግሱኝ ወፎችን ካልፈለግሁ በቀር እኔ ብቻዬን ለሺ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ፋኖ አስመሳይ ሌባ ሁላ እበቃለሁ። እኔ ብቻዬን አልኳችሁ። ብቻዬን እበቃቸዋለሁ። እንደከፍት እነዳቸዋለሁ። ሺ የቲክቶክ ሠራዊት፣ ሺ ምላሳም ተሳዳቢ ዩቲዩበር፣ ፌስቡከር ቀጥረው ሲበጠረቁ ውለው ቢያድሩ እኔ ዘመዴ ኬሬዳሽ። አይሞቀኝ አይበርደኝ። ደማቸውን እያፈለሁ፣ ንዴታቸው በንፍጥ፣ በለሃጭ፣ በላብ፣ በትውከትና በተቅማጥ መልኩ እንዲወጣላቸው አደርጋቸዋለሁ። ዘንድሮ ሥራዬ ያ ነው የሚሆነው። አበቃ።…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው? ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቃና፥ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው። እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ። ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች። አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ አልሰማቸውም። እንደ ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፥ እንደ አደባባይም ጭቃ እረግጣቸዋለሁ። መዝ 18፥ 31-42

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እግዚአብሔር ይመስገን…!

"…የዛሬው የጎንደር የቀበሮ ሜዳው የአዲስ ዘዓመት፣ የአዲስ ተስፋው ለተፈናቃዮች የተደረገው የምሳ ግብዣ መርሀ ግብር በብዙ በረከት ተትረፍርፎ በሰላም እና በደስታ ተፈጽሟል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ አይዳረስ ይሆን ተብሎ የነበረውንም ጭንቀት እግዚአብሔር በበረከት አትረፍርፎ ድንቅ አድርጓል። እንዲያውም አንድ ሰንጋ ተርፏቸው ለመስቀል ይሁናችሁ ብዬአቸዋለሁ። የዛሬውን ሙሉ ዝግጅት እሑድ በመረጃ ተለቭዥን በነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።

"…1 ዩኒፎርም 700 የኢትዮጵያ ብር ነው። 100 ዶላር የ17 ተማሪ ይችልላችኋል። የቀረን ትንሽ ነው። ተረባረቡ።

"…ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን። ለሰጪዎችም እግዚአብሔር ይስጥልን።

Читать полностью…
Подписаться на канал