zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በ😂😂😂 ክፍል ፫

"…ሜይ 25 ኢፓድ፣ ሜይ 30 ደግሞ መከላከያ እና አሚኮ ይሄንኑ መከረኛ የአርማጨሆ ሓላፊ ሶዬ ሸሚዙን ቀይረው በእነዚያው ልጆች ዜናውን ሠሩት።

"…አልጨረስኩም። የጨረስኳችሁ መስሏችሁ ነው ጠብቁኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

😂😂😂

"…ከ55 ደቂቃ በፊት አሚኮ የለቀቀው ዜና ነው። ገና ሽማግሌዎቹ ሳይላኩ ፋኖዎቹ የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው በሰላም ተመልሰው ራሳቸው መልሰው ሌሎቹ ፋኖዎች ጥሪ አቀረቡ ይላል።

""…ተመልሼ እመጣለሁ። እስከዚያው የሓላፊውን ማለትም ሱፍ በሸሚዝ ያደረገውን ሶዬ እና ከጫካ ተመላሽ ፋኖ የተባሉትን ሶዬዎች ያዙልኝማ።

• ከ5 ደቂቃ በኋላ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተሸንፌያለሁ፥ ሓሳቤንም ሰርዤአለሁ…

"…በ106 የተቃውሞ ድምጽ፣ በ195 አብላጫ ድምጽ በኬንያ ፓርላማ የጸደቀውን የግብር ማሻሻያ ዕቅዳቸው በኬንያ ሕዝብ ጠንካራ ተቃውሞ ምክንያት ለደም መፋሰስ ያበቃ ተቃውሞ ከተደረገ በኋላ በፓርላማ ጸድቆ አልፎ ለፊርማ ፕሬዘዳንቱ ጋር የመጣውን ዐዋጅ አልፈርምም በማለት ውድቅ ማድረጋቸው ተዘግቧል።

"…የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዲህ አሉ። እኔ ሕዝብን ልመራ ነው በሕዝቤ የተመረጥኩት፣ የመረጠኝ ሕዝብ ከተቃወመኝ ሕዝቤን ማዳመጥ አለብኝ። ስለዚህ "ተሸንፌያለሁ። ሓሳቤንም ሰርዢያለሁ።" ይሄ ማለት ስትማር፣ ስትሠለጥን፣ ደግሞም ሰው ስትሆን የምትወስነው ውሳኔ ነው።

"…እንደ ወያኔ ከጫካ፣ ከዱር ወጥተህ ሥልጣን ስትይዝ፣ እንደ ደርግ ከወታደር ቤት ብረት ስትገፋ ከርመህ መጥተህ ንጉሥ አንቀህ፣ ምሁራንንና ተማሪ ጨፍጨፈህ፣ ሀገር በደናቁርት አስወርረህ ስታበቃ፣ እንደ መሀይሙ ሀ ገደሉ አረመኔው አቢይ አሕመድ ርቦህ ወታደር ቤት ገብተህ ራብህን አስታግሰህ ከሞት ተርፈህ በ4ተኛ ክፍል ሰርተፊኬት በጥንቆላ ትንቢት የዶክትሬት ዲግሪ ተቀብለህ አጭብርባሪ የደም ነጋዴ ሳትሆን ስትቀር የምትተገብረው ተግባር ነው። ኬንያውያን ዕድለኞች ናቸው።

"…በኬንያ ዐመጽ ሲነሣ የብልፅግና ሚዲያዎች አልዘገቡም። ዝም፣ ጭጭ ጮጋ ነበር ያሉት። ባህርዳር ሄደው ከፋኖ አስታርቁን ብለው ሼክና ቄስ እግር ላይ ሲደፉ የዋሉትን ብልግናዎች ሲዘግቡ ዋሉ እንጂ። የኬንያ መንግሥት ወታደር ሲያሰማራ ለዘገባው ኢቢሲን፣ ኦቢኤንን፣ ፋናን የቀደመ የለም። አሁን ደግሞ ሩቶ "በሕዝቤ ተሸንፌአለሁ" ሲል መልሰው ዝም ጭጭ በቀቀኖቹ የአገዛዙ ሚዲያዎች። እንዲያውም አቢይ አሕመድ ደውሎ ምን ማድረግህ ነው? ሳይለው ይቀራልን?

• በዓለም ላይ የሚሸነፍ መንግሥት እንጂ የሚሸነፍ ሕዝብ የለም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …አዛብተናል ብለው በገምገማቸው እናም አሁንም
ይህንን በፋኖ ላይ እንደግመዋለን ብለው ስለሚያስቡ ነው።

፫ኛ፦ ሦስተኛው ሌላው የፋኖ ኃይልን እርስ በርስ በአቋም ይከፋፍልናል የሚለው እንደ ዋና ትርፍ ወስደው ነው በብልጽግና በኩል የድርድሩን ሓሳብ ይዘው የተከሰቱት። ይሄንን የድርድር ጥሪ ስናደርግ ድርድሩ የሚቀበል እና የማይቀበል በሚል በዚህ በኩል የእርስ በርስ ሽኩቻና መከፋፈል በፋኖ በኩል ሊፈጥር ይችላል በሚል ይሄንንም እንዳንድ ጠቀሜታ ወስደውት ሊሆን ይችላል የሚም አለ።

፬ኛ፦ አራተኛው አጀንዳና የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመንጠቅ አስበው ሊሆን ይችላል። አሁን ፋኖ የያዛቸውን የሕዝብ አጀንዳዎች ወደ ብልፅግናዎች በመውሰድ እኛ እንመልሳቸዋለን በሚል ጠያቂዎችም  ሲመጡ እነዚህንም አጀንዳ በመንጠቅና አጀንዳ አልባ ናቸው ለማለት ወደ ሕዝብ መልሶ ፕሮፖጋንዳ ለመሥራት ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት አለ።

፭ኛ፦ አምስተኛው መጥተዋል በሕዝቡ ግፊት እኛ ድርድር ብንቀበልም ሌላው አካል ድርድርን ስለማይቀበል እና ለሕዝብም ስለማያስብ ሓላፊነትም ስለማይሰማው ይህንን ኃይል ለመደምሰስ በምናደርገው ዘመቻ ላይ ለሚፈጠሩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሰብዓዊ ቀውሶች ላይ ተጠያቂ አንሆንም። እኛ ሓላፊነታችን ይኸው በእናንተ ግፊት ተወጥተናል ለማለት እና ይሄንን በሰፊው ለማራገብ ታስቦ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየቶች መጥተዋል በማለት ነው ጋዜጠኛ በለጠ ሓሳቡን የሚቋጨው።

"…በመሰረተ ሓሳብ ደረጃ ድርድር አይጠላም። አይገፋም። ድርድር ያለ ነው። ድርድር ግን አቻ በሆኑ በሁለት መሸናነፍ በማይችሉ አካላት መካከል የሚደረግ እንጂ እያሸነፍከው ካለኸው ሓይል ጋር ድርድር ብሎ ነገር የለም። የሁለተኛውም፣ የአንደኛውም የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀው በድርድር አይደለም። የኢራቅ፣ የሊቢያም ጦርነት ያለቀው በድርድር አይደለም። የእስራኤል እና የፍልስጤም ጉዳይም በድርድር አይደለም የሚያልቀው። የሩሲያና የኬቭንም ማየት ይቻላል። ወያኔ ከምጠፋ፣ ከምደመሰስ ነፍሴን አትርፉልኝ። ለኦሮሙማ ባሪያ፣ ለኦሮሙማ ጠላቶች ደግሞ የጭን ቁስል ሆኜ አገለግላለሁ፣ ኦሮሙማ ሲልከኝ ወዴት፣ ሲጠራኝ አቤት፣ ሲሰድበኝ እንደ ምርቃት ቆጥሬ እኖራለሁ፣ አማልዱኝ፣ ቅበሩኝ ብላ ፕሪቶሪያ ድረስ ሩጣ፣ ናይሮቢ ደጅ ጠንታ፣ ዐማራ ከሚገዛ ኦሮሙማው ይግዛኝ ብላ የተገረደችበትን የግርድና ውል ድርድር ነው ብለህ እዚህ ጋር መጥተህ አትጥቀስ። እና ውሉን ባትፈርም ኖሮ ወያኔ ዛሬ ትኖር ነበር? መልስልኝ።

"…የእናንተን ሓሳብ ደግሞ ጨምሩበት። የመጀመሪያው አማሪካ በእስክንድር ነጋ በኩል የሞከረችው የድርድር ሓሳብ ከስሯል። ተቋጥሏል። አሁን ደግሞ በማን በኩል ይሆን የሚሞክሩት? ያለሁሉም የፋኖ አደረጃጀት ፈቃድ እና ስምምነት ለብቻው ወጥቶ እኔ ከብልፅግና ጋር እደራደራለሁ የሚለውን የፋኖ አደረጃጀት የትኛው ይሆን? እደግመዋለሁ የእስክንድር ነጋው የእነ ሀብታሙ በሻህ የኦሮሙማው ቡድን ቀልጧል። በእነ ገዱ አንዳርጋቸው በኩል የሚመጣውን እንጠብቅ ወይስ በእነ…………………? በኩል። ተወያዩበት። እንወያይበት።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ለዐማራ ሕዝብ የመጨረሻ የተባለ ፈታኝ የሆነ መሰናክል ከፊቱ ተደቅኗል። መሰናክሉ ከዚህ ቀደም ከገጠሙት መሰናክሎች የተለየ ሆኖ ግን አይደለም። ያለፈው ከባድ መሰናክል ሲታለፍ እንደ ምጥ ስለሚረሳ እንጂ ከበፊቱ የተለየ አይደለም። ሆኖም ግን ምጥ ሁል ጊዜ አዲስ ነው። አስጨናቂ ነው። ማርያም ማርያም ብሎ ቀበቶ አላልቶ ከመጸለይ በተጨማሪ ደም እየፈሰሰም ቢሆን ምጡን በኦፕራሲዮንም ቢሆን ልጁ በማውጣት ይገላገሉታል። ምጡን እርሺው ልጁን አንቪው የሚባለውም ከዚያ በኋላ ነው። ይህን አሁን ለዐማራ እንደ ምጥ፣ እንደ መሰናክል የሚቆጠር ጊዜ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በተለመደው እና በሚታወቅበት የአባቶቹ ጥበብ፣ ፅናት፣ ብልሃት፣ ጀግንነት፣ እምነት ጭምር ተጠቅሞ በጥልቅ መረዳት እና በመግባባት በመናበብም ዐማራው ተራራው ካለፈው እስከአሁን ድረስ ሊደርስበት ወዳቀደው ግብ እና ወደሚፈልገው የስኬት ማማ በክብር ይደርሳል። ይወጣልም። ለዚህ ግን እንደ አብርሃም ቆራጥ፣ ታማኝ፣ አማኝ፣ ምስጢር ጠባቂ፣ ወሳኝም መሆን አለበት።

"…ተወደደም ተጠላም አሁን ዐማራ ከብልግና ጋር ምድር ላይ የሚካሄደውን ጦርነትም በለው ውጊያ ሙሉ በሙሉ አሸንፏል። የኃይል ሚዛኑን አዛብቶታል። ያውም በዝረራ ነው ኦሮሙማን ያሸነፈው። ለዚህ ደግሞ በጥቂት ቆራጥ ጀግኖች ልጆቹ ተጋድሎና በዐማራ መልክአ ምድሩ ራሱ ተዋጊ ሆኖ፣ ለጠላት የማይመች፣ በዚያም ላይ ለዘመናት በዐማራ ላይ የተሠራው ግፍ ፅዋው ሞልቶ በመፍሰሱ በጥቂት የሰው ኃይል እና በጥቂት መስዋዕትነት ግዙፉን የኦሮሙማ ጥምር ጦር አድቅቆ ለመፈረካከስ አብቅቶታል። ተመልከት ከባዶ እጅ ከዲሞፍተር፣ ከቆመህ ጠብቀኝ ወደ ጥቁር ክላሽ፣ ስናይፐር፣ ሞርታር እና ዲሽቃ መታጠቅም የተሸጋገረው፣ ከጥቂት ቡድን ወደ ሻለቃ፣ ዕዝ፣ ብርጌድና ክፍለጦር ያደገው ዝም ብሎ አይደለም። ዐማራ ስለሆነ ነው በአንድ ዓመት ይሄን ሁሉ የከወነው። ለዚህ ደግሞ የምርኮኛው ብራኑ ጁላ፣ የዘማዊው ወዲ ትግራይ የአበባው ታደሰ፣ የከሀዲው ዳንኤል ክብረት፣ የአረመኔው አስብቶ አራጁ አቢይ አሕመድ አገዛዝ የሚመራው ጦር በሰፊው ይመሰገናል። አሁን ጦርነቱ አልቋል። አሁን የሚቀረው የመጨረሻው ቁማር፣ የመጨረሻው የካርታ ጨዋታ የጠቅላይ የተጣለው ቁማር ብቻ ነው። መጠንቀቅ እዚህ ላይ ነው።

"…እዚህ ጋር ስመ ጥሩን የኦሮሞ ቁማርተኛ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳን በድፍረት እጠቅሳለሁ። ኦሮሙማው እሳት የላሱ ቁማርተኞች እንዳሉት፣ ፖለቲካ ቁማር እንደሆነ ከዚህ በፊት በአደባባይ የተናገረው ሽመልስ አብዲሳ ነው። ፖለቲካ የቁማር ጨዋታ ነው። ጨዋታውን ተጫወት ዋናው ግን እንዴትም አድርገህ ቁማሩን ማሸነፍ እንደሚጠበቅብህ ማወቁ ላይ ነው። እኛም ያደረግነው እንደዚያ ነው ነበር ያለው ኦቦ ሽመልስ። ልብአድርጉ "ኦሮማራ" የተባለውን ፍልስፍና የዐማራ ሕዝብ በጉጉት ያየው፣ የተመለከተው፣ ሰላም፣ ተስፋ፣ ዕድገት፣ ፍቅርንም የጠበቀበት መፈክርም ፍልስፍናም ነበር ለዐማራው። የኦሮማራው ፍልስፍና ግን ለኦሮሙማው ቡድን የቁማር መጫወቻ ካርዱ ነበር። ዐማራን የተስፋ ዳቦ እያስገመጠ፣ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ የሚለውን የዐማራን ተረት መልሶ ለራሱ እየተረተ ሠራለት። ዓባይን ተሻግሮ ቁማሩን በላነው ብሎ ተስፋውን አጨንግፎ ፎከረበት። ዐማራ እንደ ሞኝ፣ እንደ ጅል፣ እንደከርፋፋ፣ እንደማያስብ፣ እንደዘገምተኛም ተቆጠረበት። ኦሮሙማው ግን የዐማራን መሪዎች ቀርጥፎ በልቶ ሸለለበት። ጌረርሳ ጌረረበት። ጄነራል አሳምነውን እና ዶክተር አምባቸው ገድሎ አርዶ ብልታቸውን ቆርጦ ግንባሩ ላይ ለጥፎ መፎከር ብቻ እስኪቀረው አቅራራበት። ከዚያ መለስ ሁሉን አድርጓል ኦሮሙማ።

"…ኦሮሙማው ዐማራ የሚወዳቸውን፣ የሚያፈቅራቸውን፣ ሕይወቱን እስከመስጠት ድረስ የሚታመንባቸውን ቅዱስ ነገሮችን በሙሉ በማሳያት እና በጆሮው በማሰማት ደጋግሞ ዐማራውን ደጋግሞ አርዶታል። አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ዓላማ ኦሮሙማው አያምንበትም። ነገር ግን ለዐማራ እያሳየ እያስጨፈረው እያዘመረውም ደጋግሞ አርዶታል። አሁንማ በየትኛውም የብአዴን የአዳራሽ ስብሰባ ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ተሰቅሎ አታዩም። በሰሞኑ የዐማራ የሰላም ኮንፍረንስ ላይ ጄኔራሎቹ ትከሻ ላይ ካለው ባጅ በስተቀር በአዳራሹ ውስጥ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም እንዲያዝ፣ እንዲሰቀልም አልተደረገም። ምክንያቱም ኦሮሙማው የዐማራውን የብአዴን አመራር በደቡብ ወሎ የወሀቢይ እስላሞች ስለተካ ዐማራ ምድር ላይ ሰንደቅ ዓላማ ማሳየት በራስ ላይ ነገር መጠምዘዝ መሆኑን ስለተረዳ አጥፍተውታል። አሁን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በዐማራ ፋኖ እጅ ላይ ብቻ ቀርታለች። እሷን ነው ነፍስ ዘርታ ሞታ ተነሥታ፣ ወድቃም ተነሥታ ትውለበለባለች ብለን የምንጠብቀው። ትግሬ ከምድሩ፣ ኦሮሞ ከምድሩ ያጠፋትን ሰንደቅ ዓላማ ዐማራው ሞቶ ዳግም ፋሽስቶችን አስወግዶ ይሰቅላታል፣ ያውለበልባታል ብለን ተስፋ የምናደርገው።

"…ሌላው ኦሮሙማ ዐማራን የሸወደው፣ ቁማሩንም የበላው የኢትዮጵያን ስም ደጋግሞ በመጥራት ነው። የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ የሚያደርገውን የሚያሳጣው ዐማራን ጉድ የሠሩት በዚህ ቅዱስ ስም ነው። ምን ኦሮሙማው ብቻ ግንቦት ሰባት በለው፣ ባልደራስ በለው፣ ግንባሩ በለው፣ ሠራዊቱ በለው ሁላቸውም ዐማራውን ያደነዘዙት በዚህ ቅዱስ ስም ነው። የእነ ዳንኤል ክብረት አማካሪነትም እዚህ ላይ ነው የተፈለገው። ኦሮሙማውን የጠቀመውም እዚህ ላይ ነው። ዐማራ ሊሸነፍለት፣ ሊወድቅበት፣ ሊንበረከክበት፣ ሊታለል ሊሞኝበት የሚችላቸውን እሴቶች የዐማራን ሥነ ልቦና ጠንቅቆ የሚያውቀው ዳንኤል ክብረት በደንብ ነው ኦሮሞዎቹን የጋታቸው። ዐማራ ምን ቢያይ፣ ምን ቢሰማ እንደሚሞኝ፣ እንደሚታለል ለኦሮሙማው ምክር ከሰጡት ግንባር ቀደሙ ሰው ዳንኤል ክብረት ነው። በምክር ዳንኤል እንዴት አፍ እንደሚያስከፍት ከእኔ በላይ ምስክሩ የለም። ኦሮሞ የሚባባል ሀገር ግንባታ ላይ ያሉትን ሰዎች እያወቃቸው ይህን ሀገረ መንግሥት ግንባታ ዐማራው እንዳያደናቅፍባቸው ዐማራውን በሚወደው፣ በሚታመንለት አሴት ጠርንፎ መያዝ ነበረባቸው። እናም ስንኖር ኢትዮጵያዊ፣ ስንሞት ኢትዮጵያዊ ብለው እየደሰኮሩበት አርደው፣ አርደው ከመሬት ከመሩት። ከመሩትና ለምን ትገድሉኛላችሁ ብሎ ሲጠይቅ ደግሞ "ገዳይ ተሸናፊ፣ ሟች አሸነፊ ነው" ብለው ቀለዱበት። ዝም በል ብትሞትም ለአስከሬንህ ጥላ እንዲሆን ችግኝ እተክልልሃለሁ ብለውም ቀለዱበት። ዐማራው ይሄን ሁሉ ነው ችሎ አልፎ ከዚህ የደረሰው። በቃ ደጋግሞ ቁማር ተበልቷል። አሁን ግን ሁሌ መበላት የለም ብሎ ገግሞ ከሰልፍ ወደ ሰይፍ ተሸጋግሮ ነው ብአዴንን አስወግዶ ወደ ድል የሚወስደውን መንገድ የጀመረው። ይሄኛውን የፋኖ ቁማር ነው ኦሮሙማ ያልቻለው።

"…እደግመዋለሁ ዐማራ ይሄንኛውን ከፊቱ የተደቀነውን መሰናክል በጥበብ፣ በእምነት፣ በቁርጠኝነት፣ በጀግንነት እና በጀብድ ካለፈው አበቃ አሸናፊነቱን በይፋ ያውጃል። አልያ ግን ኦሮሙማው ዐማራ የሚባልን የሰው ዘር ከኩርዶችም በላይ እንዳይነሣ አድርጎ ከምድረ ገፅ ድራሹን ያጠፋዋል። ኦሮሙማ እንደ ትግሬ ነፃ አውጪ ብልጥ አይደለም። እንደ ወያኔ በሲስተም ዘርህን አያጠፋውም። ደንታው አይደለም። በዐማራ ዘር መጥፋት ጮቤ የሚረግጡ የዓለም መንግሥታት ምንም እንደማይሉት፣ እንደማይቆጡት የሚመስለው ኦሮሙማ በግልጽ ነው ጨፍጭፎ የሚከምርህ። ገገማ ነው ስልህ ኦሮሙማ። ኦሮሙማ ሃይማኖት ስለሌለው ለተናገረው፣ ለገባው ቃል አይታመንም። ሼምም አያውቅም። በሼም በኩል ከወያኔ ጋር👇 ከታች ይቀጥላል✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የተጻፈውም ጽሕፈት፦ ማኔ ቴቄል ፋሬስ ይላል። የነገሩም ፍቺ ይህ ነው፤ ማኔ ማለት፥ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቈጠረው ፈጸመውም ማለት ነው። ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው። ፋሬስ ማለት፥ መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው። ዳን 5፥ 25-28

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በርቶ የምታዩት የሞባይል ስልኩ ቫይብሬት ላይ ስለሆነ ነው። 😂😂😂 …የትግሬው ልጅ ጋሽ እናጠፋቸዋለን፣ እንደመስሳቸዋለን እንኳ አደብ ገዛ እኮ። ዐማራን እሰብራለሁ ብሎ ራሱ ቅስሙም፣ ጅስሙም ተሰብሮ አረፈው።

• እንዲያው ምን ይሻለኛል በናታቹ፣ ባባታቹ። ይሄን ዓይኔን ምን ባደርገው ይሻለኛል? በፋኖ ሞት? ኤ…?

• ቆይቼ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አረመኔው አስብቶ አራጁ ልቡሰ ሥጋ ጋኔሉ ብልፅግና ለምን እንዲህ ተጣድፎ በሼክ በመነከሴ በአቦ በሥላሴ ከፋኖ ጋር እርቅ፣ ድርድር እንደሚል ቪድዮ ላሳያችሁ…?

• ዘግናኝ ስለሆነ ቆራርጬ ብለጥፈውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ ያለ ብቻ የሚመለከተው ቪድዮ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወደው አይስቁ አለ አጎቴ ሌኒን… 😂😂😂 ኮሞዲኖው አሚኮ መቼ ነው ደግሞ እንዲህ ብሎ የለጠፈው?

"…ስማኝ ልንገርህማ… ከብአዴን፣ ከኦሮሙማው ብልጽግና ጋር ለእርቅ ብሎ የሚቀመጥ ፋኖ ካለ እመነኝ ሲኦል ነው የሚገባው። የዘላለም ቤቱም ትሉ ከማያንቀላፋበት፣ እሳቱም ከማይጠፋበት ዘወትር ጥርስ ማፏጨት ባለበት በገሀነመ እሳት ነው የሚወረወረው። መኖሪያው እዚያ ነው።

"…ባለቀይ ቦኔቱ የጁላ ሠራዊት ያላንበረከከውን የዐማራ ፋኖ ባለ ነጭ ቦኔት አጥላቂ ቄሶችና ሼኮችማ ተሸውዶ ጉድ ይሠራል ብዬ አላምንም።

"…የሆነው ሆኖ ብሎ ብሎ ያቃተውንና የተሸነፈውን የኦሮሞ ብልጽግና ኃይል አሸናፊው ፋኖ በእርቅ፣ በድርድር ሰበብ ወጥመዱ ውስጥ ገብቶ ነጥብ ከጣለለት አለቀለት። አጣጥሞ ይበላዋል። የዐማራም ትግል 200 ዓመት ወደ ኋላ ይመለሳል። አምነህ ግባበት።

"…አሁን ዐማራ የሚያስፈልገው ጄኖሳይደሩን አገዛዝ መገርሰስ፣ መደምሰስ፣ እረፍት ማሳጣት፣ እጁን ጠምዝዞ በአፍጢሙም በአናቱም መትከል፣ ማስጨነቅ፣ መቀጥቀጥ ብቻ ነው። ዐማራ አስተማማኝና ለሕዝቡም ዘላለማዊ ዋስትና የሚሰጥ መንግሥት በሀገሪቱ መመሥረቱን እስኪያረጋግጥ ድረስ እርቅ፣ ድርድር እያለ እንዳይዘናጋ ይጠንቀቅ።

"…ዐማራ እንደ ትግሬ እንዳይሸወድ። ዳንኤል ክብረት ፊት ቆሞ መሳቂያ፣ መሳለቂያ ከመሆኑ በፊት የዐማራ ፋኖ ይጠንቀቅ።

"…ዛሬ እኮ የተሰበሰበው በድኑ ብአዴን ነው። መሸነፉን ያወጀው ብአዴን ነው። ከተሸናፊ ጋር ድርድር፣ እርቅ የሚባል ነገር የለም። ለውጥ ነው የሚያስፈልገው። ያቆሰልከውን ነብር ካልገደልከው መልሶ ይበላሃል አለ ዶር ዳኛቸው እንደዚያ ነው። የተቀጠቀጠውን እባብ አፈር ልሶ እንዳይነሣ አርቀህ ስቀለው።

• እደግመዋለሁ… ከአረመኔው ብልፅግና ጋር የሚታረቁ ካሉ በቀጥታ ሲኦል ይገባሉ። ገሀነመ እሳት መኖሪያቸው ነው። አለቀ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ኬኒያ ነው…!

"…ሰሞኑን የሳሙኤል ሩቶ መንግሥት በኬንያ ጥቂት ታክስና ቀረጥ እጨምራለሁ ብሎ ያወራል። ፓርላማውንና የመንግሥቱን የዘወትር እንቅስቃሴ እንደ ሰጎን እንቁላል ዓይኑን ቸክሎ የሚከታተለው የኬንያ ሕዝብ እንዳትሞክረው እረፍ ብለው የቃል ማስጠንቀቂያም ሰጡ። በዳቦና በመሳሰሉት ላይ ትንሽ ሳንቲም ይጨምራል ነው መንግሥቱ የሚለው። አይሆንም፣ ኑሮ ይወደድብናል። የምግብ ዋጋ ይጨምርብናል። የቤት ኪራይ፣ የትራንስፖርት ዋጋ ሰማይ ይነካብናል ነው ያለው ሕዝቡ።

"…ዛሬ የኬኒያ ፓርላማ ሕጉን ለማጽደቅ ተሰበሰበ። ሕዝቡም የምታጸድቁትን ሕግ አብረን እናያለን ብሎ ከፓርላማው ደጃፍ ተሰበሰበ። ፓርላማው የኬንያ ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያ በተለይ እንደ አዲስ አበባ ሕዝብ መስሎት በምን ታመጣላችሁ እብሪት ሕጉን አፀደቀው።

"…ከዚያ በኋላ የሆነውንማ አትጠይቁኝ። መድኃኔዓለም ፍረድ፣ አንቺ የጭንቅ አማላጂቱ የለሽማ፣ የአላህ፣ ያረቢ ዝምታህ እሰከመቼ ነው? ኧረ ራራልን፣ ታረቀን ፈጣሪ ብለው እንባቸውን ወደ ሰማይ እየረጩ፣ በልባቸው እየተሳደቡ፣ እየተራገሙ ወደ የቤታቸው አልሄዱም።

"…ፓርላማውን ጥሰው ገቡ። የፓርላማ አባላቱም ግርር ብለው ወደ መደበቂያ ዋሻ ወደ ምድር ቤቱ ገቡ። በዚያም በላያቸው ላይ ዘግተው የቁም እስረኛ ሆኑ። የራበው ሕዝብ መሪዎቹን በኬንያ እየበላ ነው።

"…አዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ላይ ነች። ትግራይ አስገድዶ ደፋሪዎችን የትግሬ ጊዚያዊ መንግሥት ያስቁምልን የሚል ሰልፍ ላይ ነች። ኦሮሚያ ምን ላይ እንዳለች አይታወቅም። አፋርና ሱማሌ በድንበር ይገባኛል ጦርነት ላይ ናቸው። ብአዴን ቄስና ሼክ ሰብስቦ የፋኖ ያለህ እንታረቅ እያለ ነው። ሽሬ ላይ ጀነራል ምግበ እና ጀነራል ብርሃኑ በቀለ ለሰኔ ሠላሳው ወረራ ፅቡቅቲ ውይይት አካሂደዋል። የኬንያው በረከት ይደረብን።

• እየኮመታችሁ…!✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ነው። ቃለ መጠይቁ በአማርኛ ነው። ማን ጫነባቸው? እንጃ አባታቸው? ወደው አይስቁ አሉ። ጠላቴ የሚሉትን ዐማራ በአማርኛ ያሙታል። እንዲያውም ሰሞኑን ትግሬዎቹ እነ ስታሊን፣ እነ ቶማስ ጃጀው፣ እነ የኦሮሞ አክቲቪስቶች የእስክንድር ነጋ እና የሻለቃ መከታው ደጋፊ ሆነው ተከስተው ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ነው። ሐሙስ ዕለት እነ አበባው ታደሰ ፋኖ እርስ በእርስ እየተዋጋ ነው የሚለውን ሟርት ዛሬ መከታውና አሰግድ በጦርነት ተጋጠሙ ብለው ጮቤ እስከመርገጥ ደርሰዋል። እስክንድር እንዲያሸንፍ ሱባኤ ሁላ ይዘዋል። በሳቅ ሊገድሉኝ ነው።

"…እነ የኦነግ አክቲቪስቶች ትኩረት አጥተው በስቃይ ላይ ናቸው። ፋኖ መከላከያን ማረከ ሲባል በማግስቱ እንደምንም የመንደር ጎረምሳ ሰብስበው መከላከያን ማረክን ብለው ይለጥፋሉ። በአማርኛ። የዐማራ አድማ ብተና እና የዐማራ ሚልሻ ወደ ፋኖ ተቀላቀለ ሲባል መንጋ የኦሮሞ ልዩ ኃይል እና አረቄ የጨረሰው የኦሮሞ ሚልሻ አሰልፈው ኦነግን ተቀላቀሉ ይላሉ። ስለ ፋኖ በተወራ ቁጥር ኦነግ ሸኔ በዚህ ወጥቶ በዚህ ገብቶ ይላሉ። አቢይ ወለጋ ላይ ተጸዳድቶ ሲወጣ ተደብቀው አገኘሁ ተሻገር ባህርዳር ሲሄድ ፋኖ የት አለ ብለው እሪሪ ይላሉ። ማፈሪያ ሁላ።

"…አዎ ዐማራ አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ መሆን የለበትም። እገሌ ታሰረ፣ እገሌ ተፈታ ብሎ ዋይ ዋይ ማለት የለበትም። በሆነ ቦታ የተጣሉ ፋኖዎችን አጀንዳ አድርጎ አጋግሎ ማቅረብም ልክ አይደለም። በዐማራ ጉዳይ የጥል ሰበዝ መዝዛችሁ አጀንዳ ለማድረግ የምትጥሩ የዐማራ ልጆች ብትጠነቀቁ መልካም ነው። የከፋ ደረጃ የደረሰ እና አደጋ የሚፈጥር፣ ሕዝብ ጣልቃ ገብቶ እንዲፈታው የሚደረግ ጉዳይና ችግር ካልገጠመህ በቀር ችግሩን ሁሉ አደባባይ አታውጣው። በውስጥ ጨርሰው። የራስ እግርና እግር በሚጋጭበት ምድር ላይ ሁለት ፋኖዎች ክፉ ደግ ተነጋገሩ ብሎ ነገር ማጋጋል ደግ አይደለም። ይሄ ሊታረም ይገባል። የሆነው ሆኖ ፋኖ ልዩነቱን በንግግር፣ በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በጥፊ በካልቾ፣ በድንጋይ በክትክታም ቢሆን ፈትቶ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የለም። ከዚህ ካለፈም በጥይት ተፈታትሾ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የለም። አሁን የዐማራ ትግል የኦነግ፣ የግንቦት ሰባት፣ የብልፅግና፣ የወያኔ አክቲቪስቶች እና የብአዴን ካድሬዎች የበሬው እንትን ይወድቅልኛል ብለው ለሀጫቸውን እያዝረከረኩ በመጎምጀት ከሚጠባበቁት በቀር ወፍ የለም። አይቆምም።

"…ገዱ አንዳርጋቸው፣ ይልቃል ጌትነት ስለ ዐማራ ጉዳይ ከማሲንጋ ጋር ተነጋገሩ። ተወያዩ እሱ አጀንዳህ ሊሆን አይገባም። ገዱ አንዳርጋቸውም፣ ይልቃል ጌትነትም ለደንታቸው ነው። የፋኖ እንቅፋት ሆኖ የከረመ ሁላ አሁን ፋኖ ሊያሸንፍ ሲል ግርር ብሎ መጥቶ ከፊት ልሰለፍ ቢል ማን ይሰማዋል? ብልፅግና ፕላን ቢ፣ ፕላን ሲ ብሎ ላስቀመጠው አጀንዳ መፍትሄው ያለው መሬት ላይ፣ ምድር ላይ ባሉት ጀግኖች እጅ እንጂ በቦሌ አየር መንገድ ሰተት ብለው ወጥተው ሲያበቁ አሁን የዐማራ ጠበቃ ነን በሚሉ ግለሰቦች አይደለም። አጀንዳ አታድርጉት። ጉልበት ሲኖርህ ወዳጅህ ይበዛል። ከዋርካ ስር መጠለል የማይፈልግ አለ እንዴ? ጨፈቃ ሆነህ ማን ይቀርብሃል? እንቦጭ፣ እንባጮም ሆነህ ማን ይጠጋሃል? ግዘፍ፣ ዝግባ፣ ዋርካ ሁን ያኔ አይደለም አማሪካ አውሮጳና አፍሪካም ከስርህ ይደፋሉ።

"…የወያኔም አጀንዳ ግንቦት 30 አለፈ። ሰኔ 30ም ደረሰ። ዐማራም ግን ሥራ ላይ ነው። አጀንዳ መቀበል ድሮ ቀርቷል። ቢያንስ ቢያንስ ዐማራው ቢፈዝ እንኳ እኔ የሐረርጌው መራታ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ አልፈዝም። የአየሩን አጀንዳ ሰጪ ሁላ ራሴ አጀንዳ እሆነዋለሁ። እነ ጂጂን፣ ግንቦቴና ግንባሩን ብቅ እያልኩ እንደ ጠበል አስለፈልፋቸዋለሁ። መሬት ላይ ሁከት ለመፍጠር የተዘጋጁትን አየር ላይ አጋንንቶች ራሴ አጀንዳ ሆኜ ስለ እኔ ብቻ እንዲያወሩ አድርጌ አዘገያቸዋለሁ። ዘመድኩን ጋላ ነው፣ ዘመድኩን ቆቱ ነው። ዘመድኩን ሌባ ነው። ዘመድኩን አጭበርባሪ ነው። ዘመድኩን ከዐማራ ትግል ይውጣልን ወዘተ ብለው ቀንና ማታ ሌሊቱን ሁሉ እንዲለፈልፉ፣ ስሜን እያነሱ ከመሬቱ ትግል እጃቸውን እንዲያነሱ አደርጋቸዋለሁ። ዐማራ እስኪያሸንፍ የአየሩን የዐማራ አጋንንት እኔ ጠርንፌ ሽባ አድርጌ እይዘዋለሁ። ጠንካራ አጀንዳ ከፈጠሩ በየሳምንቱ ማክሰኞ ማክሰኞ፣ ጠንካራ አጀንዳ ካልፈጠሩ ደግሞ በ15 ቀን አንድ ቀን ብቅ እያልኩ በቲክቶክ መንደር ቀውጬው አረጋግቼአቸው እመለሳለሁ። እናም ዐማራ በዚህ በኩል እንዳያስብ። በእኔ በወዳጁ ይኩራ።

"…እኔ ለዐማራ ጥብቅና የምቆመው ወድጄና ፈቅጄ ነው። ግንቦቴዎችን፣ ግንባሩና ሠራዊቱ ነን ባዮችን፣ ሂዊና ኦኔ፣ ብልፄም እኔን ቢሰድቡኝ ነው። ቢወርዱብኝ ነው። ሌላ ምንም አቅም የላቸውም። ሌባ ሁላ። ዐማራ አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ መሆን በጭራሽ የለበትም።

"…ብልጽግና በቀይ ቦኔት ያልቻለውን የዐማራ ፋኖ ነጭ ሻሽ በጠመጠሙ ቄሶች፣ ነጭ ቆብ ባጠለቁ ሼሆች፣ ነጭ ጺም ሪዝ ነጭ ሽበት በወረራችው ሽማግሌዎች አይፈታም። አይንበረከክም። ተወደደም፣ ተጠላም ብልፅግና ለፋኖ እጁን ይሰጣል። እመኑኝ ፋኖ ያሸንፋል። ዐማራ ወደ ሥልጣን ይመጣል።

• ይህን አልክ ብሎ የሚከፋ ካለ በአናትህ ተተከል በሉልኝ። አደራ አደራ እንዳትረሱት ንገሩልኝ።

• ድል ለዐማራ ፋኖ፣
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው አንድ ሺ ሰው ከአንድ ሺም አልፏል። ስለእውነት በቴሌግራም መንደር የእኔ ትክክለኛ ወዳጆች ከአንድ ሺ ወይም ከሁለት ሺ አይበልጡም። የእኔ ትክክለኛ ወዳጆች የጋራ አምላካችንን ስሙን ጠርተው እግዚአብሔር ይመስገን ብለው መልስ የሚሰጡኝ ብቻ ናቸው። ቁጥራቸው ራሱ የተመጠነ ነው። እኔ እነዚህን ወዳጆቼን ይዤ ተአምር ሁሉ መሥራት እችላለሁ።

"…አንድ ሺ አመስጋኝ እስኪሞላ ድረስ ቁጭ ብዬ ስማቸውን እያነበብኩ አብሬ አመሰግናለሁ። ከምስጋና ሌላ ሌላ አጀንዳ የሚጽፈውን እያጸዳሁ አብሬ እቆያለሁ። አሁን አሁንማ አመስጋኞቹን ከምር በስም ሁላ እያወቅኳቸው እየመጣሁ ነው። የመጀመሪያዎቹን አስራ ሁለቱን አመስጋኞች ❤️❤️❤️ በልብ ቅርጽ ፍቅሬን የምገልጽላቸውማ እስኪነጋ ድረስ ነው የሚናፍቁኝ። ሁሉንም የቤተሰብ ያህል እየቆጠርኳቸው ነው። 100 ሺ ሰው ምስጋናውን አይቶት አመስጋኙ ግን 1ሺ ሲሆን ድንቅ ነው የሚለኝ። አዲስ አበባ ችግር እንዳለ ቢገባኝም ሌላው ግን አይገባኝም። አንዳንዴ የማውቃቸው የለመድኳቸው ስሞች ሳያመሰግኑ ሲቀሩ ሳይ ምንሆነው ይሆን እስከማለት ሁላ እደርሳለሁ። ማርያምን እውነቴን ነው።

"…ከምስጋናው ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ምንድነው? አዎ ወደ ርዕሰ አንቀጻችን። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ደግሞ አጀንዳን ይመለከታል። አጀንዳ። ቀኝ ትከሻዬን ሲሸክከኝ የምጽፈውን ታውቃላችሁ አይደል? እሱኛውን አጻጻፍ ተጠቅሜ ነው ዛሬ የምጽፍላችሁ። እህሳ እናንተስ ርዕሰ አንቀጼን ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመጨመር ዝግጁ ናችሁ?

• አንድ 100 ያህል ሰው እስቲ ዝግጁ ነነ ይበል። ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ያልገባኝ ነገር…

"…የዘንዶው አማካሪ ዳንኤል ክብረት ፋኖ እንደ ዐሞሌ ጨው ሟምቶ ጠፍቷል አላለም ነበር ወይ?

"…ትግሬው አበባው ታደሰ፣ በላይ ስዩምም ፋኖ ጠፍቷል። ደምስሰነዋል። የቀሩት ጎጃም ላይ አንድ 10፣ ሸዋም አንድ 10፣ ወሎ አንድ 20 ፍሬ ነው። ብልፅግና ተመልሶ እግር ተክሏል፣ እንዲያውም እነ ፋኖ እርስ በእርሳቸው እየተጣሉ እንዳይገዳደሉ እኛ መሃል ገብተን እየጠበቅን ነው።

"…አረጋ ከበደም የክልሉን 97% ከፋኖ ነፃ አውጥተን መደበኛ አስተዳደሩን መልሰናል አላለም ወይ። ፋኖ እጅ ሰጥቷል፣ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሷል አላሉም ወይ…?

"…ታዲያ ዛሬ ጋሽ ሽጉጤን ጠጥቼ እንደ አጼ ቴዎድሮስ እዚህችው ፍግም ብዬ እሞታለሁ ባዩ ጋሽ ኡዞ አገኘሁ ተሻገር እና ቀንድ አውጣው ከየት አምጥተው ነው ይሄን ሁሉ አለመቻል የሚያወሩት? የዐማራ ተማሪዎች ተምረውስ የት ሊደርሱ? ታፍነው፣ ተደብድበው፣ አዲስ አበባ መግባት አትችሉም ተብለው፣ በጅምላ ረፍርፈው የጣሏቸውን የት ረስተው ነው ዛሬ ስለተማሪዎች መጨነቅ የጀመሩት? አይ ኡዞ… ታስቁኛለሽ እኮ።

"…በድሮን ጨፍጭፈህ፣ ሠራዊት አዝምተህ አውድመህ፣ አርደህ፣ ገድለህ ያላሸነፍከውን፣ ያላስቆምከውን የዐማራ ትግል "የትኛው የሃይማኖት አባት መጥቶ ነው የሚያስቆምልህ? በጥፊ የተጠናገሩት አባት? ወይስ የታረዱት የሃይማኖት አባቶች ናቸው ፋኖ ጋር ሄደው የሚያስታርቁህ? የምን እርቅስ ነው? የምን ድርድር? ከተደመሰሰ ፋኖ ጋር የምን ድርድር ነው?

"…በቃ አትዘብዝቡ። አልቻላችሁም እናም እጅ ስጡ፣ በፈቃደኝነትም ለፍርድ ቅረቡ። ህወሓትን አስገብተን፣ ወያኔን አስመጥተን ዐማራን ዳግም እናንበረክከዋለንም ብላችሁም አታስቡ። አበደን ተሸንፋችኋል። ስልጣኑን ለዐማራ ፋኖ ልቀቁ። ከዚያ ውጪ ሰላም ኢንጂሩ።

• ማኔ ቴቄል ፋሬስ …

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጹ ተነቧል። ቀጥሎ ደግሞ በቀረን ሰዓት የእናንተን ሓሳብ አስኮምኩሙን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ሰላም የመንፈስ ፍሬ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ ላይ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።” ገላ 5፥22 በማለት ነው ሰላምን የሚገልጻት። ሰላም የመንፈሳውያን፣ የደስተኞች፣ ፍቅር የበዛላቸው፣ ትእግስተኞች፣ በቸርነት በበጎነት፣ እምነት ያላቸው ሰዎች በየውሃትና ራስን በመግዛት ልምምድ ውስጥ ያሉ ሰዎች ገንዘብ የሚያደርጓት ናት። እነዚህ አይደለም ምድራዊ ሰማያዊ መንግሥቱን ወራሾች ናቸው።

"…ዓለም ዛሬ ሰላም የሚለውን ቃል የሚያውቀው በጽሑፍ ብቻ ነው። በአመጸኞች አንደበት ሰላም ስትጠራ ራሷ ሰላም ይገርማታል። ይደንቃታልም። ሰላም የሚገኘው በመንፈስ ፍሬ ውስጥ ለተካተቱ ብቻ ነው። ሰላም በዜና ስለተነገረ፣ ወርክሾፕ፣ ስብሰባ፣ ሲምፖዚየም ስለበዛ አትመጣም። አትገኝምም። ሰላምን በሥጋ ሥራ ልምምድ ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞችም ሆኖ ሃይማኖተኞች ሲፈነዱ ይውሉአታል እንጂ፣ ሲፈርጡ ይከርሟታል እንጂ አያገኟትም። ሰላም ልክ እንደ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አትሸወድም። አትፎገርምም። ሰላም መሃሙድ ስለዘመራት፣ ይልማ ሃይሉ ስለዘመራት፣ በቅዳሴና በአዛን ስለወተወቷት አትመጣም። በሥጋ ሥራ ውስጥ ያለ ሰላምን አያገኛትም። ይሄንንን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይገልጠዋል።

"…የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው። እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ገላ 5፥ 19-21

"…እና ይሄ ዲምላይታም ሜካፓም ወሴ ዝሙታም መንግሥት ነው ሰላምን የሚያመጣው? ርኩሰቱ ምድሪቱን የሞላው፣ መዳራቱ ጌጥ እስኪሆን የሚታየው፣ ካገኘው ወንድ ጋር የሚተሻሽው ወሴ፣ የጣኦት አምልኮን የብሔራዊ በዓል ለማድረግ በጀት የመደበ፣ ሟርተኛ፣ የለ ጥል ሀገር መምራት የማይችል፣ ክርክሩ አዝግ፣ 40 ቢልየን ችግኝ በሁለት ሺ ገበሬ በሦስት ቀን እተክላለሁ የሚል ቡትርፍ ቀዳዳ፣ ቅንዓቱ ለከት የሌለው፣ ቁጣው በማረድ የሚገለጽ፣ አድመኛ፣ መለያየትን በሕገ መንግሥት አንቀጽ ሰጥቶት የሚፎገላ፣ ምንፍቅና ሃይማኖቱ የሆነ፣ ምቀኛ፣ መግደል እንጀራው የሆነ፣ የሰካራም ስብስብ እየዘፈነ፣ እያቅራራ፣ እየሸለለ ሰላም ሰላም ቢል ማን ይሰማዋል? ማንም።

"…አዲስ አበባም ካድሬ ሰብስበህ፣ የፓርቲህን አባላት ሰብስበህ፣ መክረህ፣ ዘክረህ፣ በሕዝብ የተጠሉ፣ ከሕዝብ ተደብቀው ሸሽተው አዲስ አበባ የተሸጎጡ ጉደኞችን እየቀለብክ ሰብስበህ ሰላም ሰላም ብትል አልተገናኝቶም። ሕዝብ ሁሌ ሾርት ሚሞሪያም አይሆንም። ሕዝብን አንዴ፣ ሁለት ሦስቴ ግፋ ቢል እስከ አስር ጊዜ ልታታልለው ትችላለህ። እሱንም በመሃል እንደ ወያኔ አስቀያሽ አጀንዳ እያመጣህ ማለት ነው። ቅንጅቶችን ዘብጥያ ወርውረህ በማግሥቱ ዓባይን ልገድብ ነው ብለህ ሕዝቡን ከዓባይና ከቅንጅት ዓባይ ይበልጣል ብሎ እንዲረሳቸው እያደረግክ ከሆነ ነው እንጂ እንደ አቢይ አሕመድ ሺ ሰው ጨፍጭፈህ ስታበቃ አረንጓዴ አሻራ፣ ቀይ ባሕር፣ ሕንድ ውቅያኖስ ብትል ማንም አይሰማህም። ገተት።

"…ሐሙስ ዕለት አዲስ አበባ በትግሬው አበባው ታደሰ የሰበሰብከውን ካድሬ ሰኞ ዕለት ባህርዳር ድረስ አረቄያሙን አገኘሁ ተሻገርን ይዘህ ሄደህ ስለ ሰላም ስትለፋደድ ብትውል ወፍ የለም። ሰካራም እንኳን ሰላም ቤት አይሠራም። ቤት ቢሠራ እንኳን በጊዜ አይገባም። መለስ ዜናዊን ሲያመልክ ያረጀን ሰውዬ፣ ለኃይለማርያም ደሳለኝ አሽከር፣ ለአቢይ አህመድ ገረድ የሆነ ሰውዬ ስለ ሰላም አውርቶ የዐማራ ሕዝብ አንጀት ሲላወስ እግዚአብሔር ያሳያችሁ። በድኑ ብአዴን መገረድ እንጂ ስለሰላም የትአባቱ ያውቅና ነው ሰላም ሰላም የሚለው? ሰላምን የሚያውቃት አርነት የወጣ፣ ነፃ የሆነ ሕዝብ ብቻ ነው። ሰላም በወሬ አይገኝም።

"…ባህርዳር ዙሪያ ጦርነት፣ ጎጃምና ደቡብ ጎንደር የቀለጠ ውጊያ ላይ ሆኖ አበባው ታደሰ አንገቱን ደፍቶ የሚያደርገው አጥቶ፣ አረጋ ከበደ ማድያቱ ጆሮ ግንዱን አልፎ፣ ቡቶክስ በሜካፕ ተቀብቶም ከ30 ደቂቃ በኋላ አጽመ ርኩሳን መስሎ እንደ ሬሳ፣ እንደ አስከሬን በድን ሆኖ የሚመራው ክልል የምን ሰላም ነው የሚሰብከው? ሰላም በወሬ አይመጣም። አክቲቪስቶች ስለ አክተቨሰቱ፣ ጋዜጠኞች ዶክመንተሪ ስለሠሩ ሰላም የለም። ሰላም ሰላማውያን ሰዎችን ነው የምትፈልገው። ሰላምን የሚያመጧት ሰላማውያን ብቻ ናቸው።

"…ለምሳሌ ትግሬን ተመልከት። ፕሪቶሪያ ሰላምን፣ ናይሮቤ ሰላምን አላመጣለትም። ውጊያ ያቆመው ጥይትና ተዋጊ ስለጨረሰ ነው። ቀለብ ስለጨረሰ ነው። ስንቅና ትጥቅ ሳይኖረው እንዴት ይዋጋል? አሁን ትንሽ ስንቅ፣ ጥቂት ቀለብም፣ ኦሮሙማም አግዝህሃለሁ ስላለው ጦርነት እየጎሰመ ነው። ግን አያዋጣውም። ኦሮሙማን አምኖ ወደ ጦርነት መግባት ትግሬን ከምድረ ገጽ ቢያጠፋው ነው እንጂ ምንም አይጠቅመውም። ትግሬ ሰላሙን ያጣው በገዛ ልጁ በወያኔ አማካኝነት ነው። ወያኔ እስካለች አይደለም ትግሬ ኢትዮጵያም፣ አይደለም ኢትዮጵያ ምሥራቅ አፍሪካ ሰላም አያገኝም። ወያኔ አእምሮው ከዲሽቃና ከባዙቃ ጥይት የተሠራ ነው። ስለዚህ ወያኔ እያለ ሰላም የለም።

"…ብአዴን የወያኔ ልጅ ነው። ኦህዴድ የወያኔ ልጅ ነው። ኦነግም እንደዚያው፣ ወላጅ አባትን ፀረ ሰላም እያልነው ልጆች ሰላማውያን ሊሆኑ አይችሉም። ልጆች ሁሉን የተማሩት ከወላጃቸው ከወያኔ ነው። ወያኔ ከሃዲ ነው። ብአዴንና ኦህዴድ ሲክዱህ አትደነቅ። ለምን ትደነቃለህ? ልጅ አባቱን ነው የሚመስለው። መርከብና አውሮጵላን ኮንዶሚንየም በቁሙ የሠረቀ ወያኔን ረግመህ ኦህዴድን በሌብነት፣ ብአዴንን በሰሊጥ ስርቆት ለምን ታማዋለህ? የሌባ ልጅ ሌባ ነው።

"…ወያኔ ያለ ጦርነት በሕይወት መኖር አትችልም። የወያኔ ልጆችም እንደዚያው። አሁን ለብልጽግና ሀገር በሙሉ ሰላም አድርገህ ብትሰጠው ብልፅግና በሰላም ሀገር፣ ሰላማዊ ሕዝብን መምራት፣ ማስተዳደር አይችልም። ብልፅግናም የወያኔ ልጅ ነውና ያለ ቀውስ መኖር አይችልም። በሌባ ታጅቦ፣ በዘራፊ ታጅቦ፣ በገዳይ፣ በአጋች ታጅቦ ነው ብልጽግና መኖር የሚችለው። ፀብ ያለሽ በዳቦን ሰላም ብትሰብከው፣ ብትነግረውም ሰላምን አያውቃትም። የሚሞትለት የደሀ ልጅ እስካለ ድረስ ደንታውም አይደለም። መፍትሄው ሰላምን የመንፈስ ፍሬ ልጆች ዐማሮቹ በፍቅር ማምጣት አለባቸው። በፀሐይ ሙቀት አይነት ፍቅር ሰላምን ለሕዝቡ ማምጣት አለባቸው።

"…አንድ ሰው ነው አሉ። ኮፍያ ባርኔጣ በራሱ ላይ ደፍቶ፣ ካፖርት፣ ኮት፣ ሸሚስ አጥልቆ በመንገድ ሲሄድ ፀሐይና ነፋስ፣ ዝናብ ሆነው ተወራረዱ አሉ። የዚህን ሰው ልብስ እኔ አስወልቅ፣ እኔ አስወልቅ ብለው ነው የሚወራረዱት። ውርርዱ መደቡ ስንት ብር እንደነበር አልተገለፀም። ብቻ ተወራረዱ። እናም እነ ጨረቃ፣ እነከዋክብት፣ እነ ደመና ታዛቢ ሆነው ውድድሩን መመልከት ይጀምራሉ። የመጀመሪያው ሞካሪ አጅሬ ነፋስ ሆነ።

"…ነፋስ ሆይ እየተወረወረ መጥቶ እንደ ብርሃኑ ጁላ ጦር ሰውየው ላይ ይላተማል። ሰውዬው ምን እየተካሄደ እንደሆነ ዐላወቀም "የዛሬው ነፋስ ደግሞ ምንድነው?" እያለ ካፖርቱን ቆልፎ፣ በአንድ እጁ ባርኔጣውን አጥብቆ ይዞ፣ ወደፊት አላስኬድ ያለውን ነፋስ በግንድ ተከልሎ ልብሱን እንቅ አድርጎ ይዞ የነፋሱን ትግል አመለጠው ታግሎ።👇 ከታች ይቀጥላል። ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በ😂😂😂 ፪

"…በፈረንጆቹ May 27 በእኛ ግንቦት 19 ልክ የዛሬ ወር እኮ የብሬ ላላጁላ መከላከያ፣ የዳንኤል ክብረት ኢፓድ፣ አሚኮም እኮ ይሄንኑ ዜና ብለው ሠርተውት ነበር።

"…ሌላው ለደንታው ነው። ሾርት ሚሞርያምም ሊሆን ይችላል። እኔ ግን ዘመዴ የሐረርጌ ሰው እኮ ነኝ። የምሥራቅ ሰው ባለማዕተብ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር የተዋሕዶ ልጅ። ሥራዬ እኮ ነው ሴራ መክሸፍ። ሙያዬ ነው የሰለጠንኩበት።

"…ምንአለበት የሓላፊውን ሶዬ ሸሚዙን እንኳ ቢቀይሩለት? ሃኣ…? 😂😂 እሱስ ምኑ ዥልጥ ነው በአባጃሌው አንዴ ኮቱን አጥልቆ፣ አንዴ አውልቆ ብሮባጋንዳ የሚሠራበት? ምንሁኖ ነው?

"…አልጨረስኩም ጠብቁኝ ከ5 ደቂቃ በኋላ ደግሞ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አላችሁ አይደል…?

"…እኔ አፍራሹ አሸበርቲው ዘመዴ ዘመዳችሁ ሰገጤ ፋራው የብልጽግናው አገዛዝ ጨፍኑ ላሞኛችሁ ብሎ ዛሬውኑ የጀመራትን ቀሽም ፕሮፓጋንዳ እያሳየሁ ላፈርስ ነኝ።

~ ላፍርሰው አይደል…? 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ወደ ኋላ ላይ ቁጥሩ ካልጨመረ በቀር እስከ አሁን 6 ሰዎች ብቻ ርዕሰ አንቀጹን በማንበብ መበሳጨታቸውን 😡 በኢሞጂ ከማየቴም በቀር ወደ 18 ሺ ያህል ሰው በፀጥታ ማንበባቸውን እያየን ነው። ከርዕሰ አንቀጹ ንባብ ቀጥሎ የምንሄደው በቀጥታ የእናንተን ሓሳብ ወደ መስማት፣ ወደ መኮምኮሙ ነው።

"…ከትናንት ጀምሮ ኦሮሙማው ብልፅግና ፋኖ ላይ ያለ የሌለ ኃይሉን በዘመቻ መልክ ያሰማራል፣ ከሶማሊያ ጋር ጦርነት ይጀምራል፣ ከሱዳንም፣ ከደቡብ ሱዳንም ጋር ውጊያ ይጀምራል፣ አጀንዳ በማስቀየስ አደናግሮ ሽምግልና እያለ በጎን ወረራ ለመፈጸም ይሞክራል። ፋኖ ይሄን ታሳቢ በማድረግ፣ የኦሮሙማውን ጦር ባለመማረክ በመደምሰስ ብልግናውን ማከናነብ ያስፈልጋል።

• 1…2…3…ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ✍✍✍ …ተመሳሳይ ናቸው። ሼመኛው፣ ይልኙንታ የሚያጠቃው ዐማራ ይሄን የኦሮሙማን ጥርብ ሰገጤነት ዐውቆ ነው በጥንቃቄ ወደ መጨረሻው የድል ዙፋን መራመድ ያለበት። እደግመዋለሁ በጥንቃቄ፣ አስሬ ለክቶ አንዴ በመቁረጥ፣ ሥልጣን፣ ገንዘብና ሀብትን ታሳቢ ባለደረገ፣ ስግብግብ ባለመሆን ለራስ ሳይሆን ለነገው የዐማራ መጪ ትውልድ በማሰብ ነው የዐማራ ፋኖ መንቀሳቀስ ያለበት።

"…ብልፅግና በ1 ሳምንት ሱሪውን አስፈታዋለሁ ብሎ ወደ ዐማራ ክልል ገብቶ ይኸው 1 ዓመት ሙሉ በሰማይ በምድር ዐማራን ደብድቦ ደብድቦ ብሎ ብሎ ያቃተውን፣ ማሸነፍም ያልቻለውን ፋኖ። አጥፍቼዋለሁ፣ ደምስሼዋለሁ፣ በአንዳንድ ኪስ ቦታዎች የቀሩትን የመለቃቀም ሥራ ነው እንጂ የሚቀረኝ ጨርሻቸዋለሁ፣ አሁን ብአዴን እግር እየተከለ ነው። ማዳበሪያ እያከፋፈልኩ ነው። አንጻራዊ ሰላም በመገኘቱ ትምህርት ጀምሬአለሁ፣ ቱሪስት እየፈሰሰ ነው። ኢንቨስትመንቱ እየተቀላጠፈ ነው። በዚህ አንድ ሳምንት፣ እንኳ በአዲስ አበባው ስብሰባ ፋኖ ተበታትኗል። ጎጃም ላይ አንድ 10፣ ሸዋም እንደዚያው፣ ወሎ ላይ ምሬ አንድ 20 ታጣቂ ይዞ ነው ያሉት እንጂ ፋኖ የለም። ተደምስሷል። ወደ አራት ኪሎ እንዳታስብ በሉት፣ እንዲየውም ፋኖ እርስ በእርሱ እየተጣላ እኛ እሱን በማስታረቅ እየደከምን ነው እያለ እንዳልፎገላ በአራተኛው ቀን ባህርዳር ላይ ተሰብስቦ ፋኖን አስታርቁን ብሎ ቄስና ሼክ ለምን መረጠ ብሎ ነው ዐማራው መመርመር ያለበት። አለቀ።

"…አዲስ አበባም የተሰበሰቡት ብልጽግናዎች ናቸው። ካድሬዎች ናቸው። የአቋም መግለጫ አወጡ የተባሉትም ብልፅግናዎች ናቸው። የዐማራ ባለሀብቶች የተባሉትም በፊት ከወያኔ ጋር አሁን ከብልፅግና ጋር ወደፊት ከፋኖም፣ ከኦነግም ጋር የሚሠሩ ናቸው። የትኛውም የፋኖ አደረጃጀት፣ የፋኖ ደጋፊ ባልተገኘበት ስትሰበሰብ ውለህ፣ አስር አይደለም ሚልዮን የአቋም መግለጫ ብታወጣ ማን ሊሰማህ ነው? አዲስ አበባ ላይ ስብሰባ ሲመራ የነበረው አበባው ታደሰ ባህርዳር ላይ ስለሄደ ምን ይጨምራል? ምንስ ይቀንሳል? ለውጡ ምኑ ላይ ነው? የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ብአዴኖችን ሰብስበህ መግለጫ ስታወጣ ብተውል መላላጫ ከመሆን የዘለለ ምንድነው የምታመጣው? ዐማራው እንደሆን አዚሙ ተገፍፎለታል። ዐማራው እንደሆን ትብታቡ ወድቆለታል። አሁን ብርሌ ከነቃ ይሆናል ዕቃ? በፍጹም።

• በአንድ ቀን ፋኖ ሳይጠይቅ ብልፄ እሺ እናንተ ካላችሁ እደራደራለሁ ለምን አለ?

"…ይሄን ነው መተንተን። ይሄንን ነው ማየት መመልከት ያለብን። በነገራችን ላይ በብልፅግናም፣ በመሬት ላይ ባለው ብአዴንም በኩል ወሎዬዎቹ እየተራወጡ ነው። በፋኖ በኩል አላልኩም። ይመዝገብልኝ። ገዱ አንዳርጋቸው መሬት ላይ ኔትወርክ ሳይኖረው እዚህ ድረስ በድፍረት አይገለፅም። ፀገዴና ጠገዴ ብሎ የጎንደርን መሬት ለትግሬ የሰጠ ሰው፣ ለዐቢይ አሕመድ እስከ እርግናው ዘመን ድረስ ታማኝ አሽከር ባርያ ተደርጎ ያገለገለ ሰው። አርቲስት ከአየር መንገድ በሚመለስበት ሀገር በፓርላማ አገዛዙን በዚያ መልክ ተቃውሞ በክብር ወደ አውሮጳ፣ ከዚያም ወደ አማሪካ የሄደ ሰው፣ አሁን ደግሞ በፊት ሲያስረው፣ ሲገርፈው፣ አሸባሪ ሲለው ከነበረው በአቋሙ ከምቀናበት ከኢንጅነር ይልቃል ጋር ገጥሞ የሚታየው መሬት ላይ ኮኔክሽን ሳይኖረው ቀርቶ ነው ማለት ይቸግረኛል። አንዳንድ ሰዎች ገዱንም፣ መዓዛንም፣ ይልቃልንም፣ ትንግርቱንም በተመለከተ ለፋኖ እስከጠቀሙ ድረስ ለምን እንገፋቸዋለን የሚል አባባል ሲናገሩ ይሰማል። ይሄ ፋኖን አለማወቅ ነው። እኔ ፋኖን አደራድሬ፣ አነጋግሬ አይቻለሁ። በፋኖ ውስጥ ያለውን የተማረ የሰው ኃይል ካለማወቅ የመጣ ነው። ፕሮፌሰር፣ ዶክተሩ፣ ኢንጂነሩ የት እንዳለም ያለማወቅ ነው። እናም አሁንም ባረጀ፣ ዐማራን በፈጀ፣ ባስፈጀ፣ ለፍርድ በሚቀርብ ብአዴን ካልተወከልኩ ማለት ደደብነት ነው። ስታሸንፍ ወደ አንተ የሚመጣ ይበዛል እንጂ ስታሸንፍ አንተ በየቢሮው የምትሄድበት ምንም አይነት ምክንያት የለም። ደግሞም የፋኖ ውክልና ሳይኖር በፋኖ ስም መንቀሳቀስ ልክ አይደለም። በግል ግን መብታቸው ነው።

"…ደግመን እንጠይቅ ለምንድነው አሁን በዚህ ሰዓት ብልፅግና ከፋኖ ጋር እየተሽኮረመመ መደራደር የፈለገው? ለምንድነው ? ይሄን በቅጡ መተንተን አሸናፊ ያደርጋል። የባህርዳሩ ስብሰባ ላይ ከመጀመሪያው ከአዲስ አበባው ስብሰባ ጀምሮ ያልተገኘውና ስብሰባው ካለቀ በኋላ የሄደውና በማራኪው ትግሬው አበባው ታደሰ ፊት ቀርቦ ሲንተባተብ የዋለው ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ የጎንደሩን ሻለቃ መሳፍንትን እና የጎጃሙን አርበኛ ዘመነ ካሴን በስም እየጠራ ሲዘልፍ ነው የዋለው። የሆነው ሆኖ ግን እናንተ ካመናችሁባቸው እና ካስገደዳችሁን እነርሱም ፈቃደኛ ከሆኑ እኛ በፈለጉበት ቦታ ለመደራደር ፈቃደኞች ነን በማለት ለምንድነው የተናዘዘው? ፋኖ ፀቡ ከአገዛዙ፣ ከፖለቲካው ክንፍ ጋር ሆኖ ሳለ ጄኔራሎቹ ከፋኖ ጋር እንደራደራለን የሚሉት በምን ሥልጣናቸው ነው? ምንስ አገባቸው? ምን ይመለከተዋል? ሌባ ሁላ። ተመልከቱ ኦሮሙማው አራጅ ብራኑ ጁላ በባህርዳር እኛ ከፋኖ ጋር እንደራደራለን ሲል ኦሮሙማው ጃዋር መሀመድ ከናይሮቢ ዐማራ የዐማራ ፋኖ የጄነራሉን የድርድር ጥሪ እንዳትገፉ፣ ከጄነራሎቹ ጋር ተደራደሩ በማለት ፌስቡኩ ላይ ለምን ጻፈ? ለጠፈ? በቃ የለመደች ጦጣ ሁል ጊዜ ፈጣጣ መሆኗ ግን አይደብርላትም እንዴ? እዚያው ሸኔህን ምከር አባው ሊሉት የግባል ፋኖዎቹ።

"…በባህርዳር ብልፄ 15 አባላት ያሉት አመቻች ኮሚቴ መርጧል። ይሄ አመቻች ኮሚቴ የተባለው ፋኖዎቹ ጋር ይሄድና ፋኖዎቹ ለመደራደር ፈቃደኛ እንደሆኑ ሲያረጋግጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመደራደሪያ ስፍራዎችን የሚያዘጋጅ ነው የተባለው። እንግዲህ ይሄንን በተመለከተ የድርድር ጉዳዩ ላይ መሰረታዊ ነው ወይስ ደግሞ ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳና ፍጆታ የቀረበ ነው? የሚለውን ወንድም በለጠ ካሳ ያነሣቸውን ሓሳቦችን እንይና እናንተም የራሳችሁን ጨምራችሁበት ለዛሬው እናብቃ። ሲጀመር ብልጽግና ይህንን የድርድር ጥሪ ሲያደርግ ምናስቦ? ምንስ እንዲያተርፍ ፈልጎ ነው በሚለውን ጉዳይ ላይ ተራ በተራ የተሰጡትን መላ ምቶች እንመልከት።

፩ኛ፦ የመጀመሪያው ሰላም ወዳድ ሆኖ በዓለማቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ ለመታየት እና እስከ አሁን በፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ እና ሰቆቃ ተጠያቂ እንዳይሆን ለሰላም ያለውን ዝግጁነት ለማሳየትና በዚህ ፕሮፖጋንዳ ለመሥራት አስቦ ነው። ልክ 1ሚልዮን ትግሬ ጨፍጭፎ ሲያበቃ ደብረ ጽዮንና ጌታቸው ረዳ እናንተም ከምትሞቱ፣ ከምገድላችሁ በዘር ማጥፋት አልጠይቃችሁም ተስማሙኝ እንዳላቸው አሁንም ዐማራን እንደዚያ ሊለው ፈልጎ ነው። ከገዳይ ጋር የሚደራደር ዐማራ የተረገመ ይሁን ብለዋል እነ አባ።

፪ኛ፦ ሁለተኛው ድርድር በሚል ጩኸት መሬት ላይ ያለውን የመጨረሻ ኃይል አውጥቶ አሟጦ በመጠቀም የፋኖን ኃይል በማዛባት ጊዜ ለመግዛት እና ራሱንም ለማደራጀት አስቦ ነው ይህንን እያደረገ ያለው የሚሉ አሉ። እስከ ሰኔ 30 የሚል የትግሬ ዘመቻ አለ ከዚያ በኋላ ክረምት ስለሆነ እስከዚያ የድርድር ጉዳይን እያነሳ እራሱ እንደገና የማደራጀት ሥራ ለመሥራት ሊሆን ይችላል የሚሉም አሉ። ከዚህ ላይ በማሳያነት ከሸኔ ጋር የተደረገውን ድርድር በተመለከተ መጥቀስ ይቻላል። የሸኔ መሪዎችን ከቄለም ወለጋ ጫካ ለመውሰድ ወደ አካባቢ በሂሊኮፕተር በገባበት ጊዜ ሸኔ የሚገኝበትን የአካባቢውን ጫካዎች በማጥናት በታንዛኒያ ድርድር እየተደረገ በወለጋ ከፍተኛ ውጊያ በማድረግ የሸኔን ኃይል…👇ከታች ይቀጥላል ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…በሚገርም ሁኔታ የዛሬው እግዚአብሔርን የማመስገን ፍጥነታችሁ አስደንቆኛል። የእናንተ መፍጠን እና ለምስጋና መረባረብ ርዕሰ አንቀጹን ለማዘጋጀት እኔ ላይ ከባድ ጫና ፈጥሮብኛል። በዘመነ ፋሲካው 1ሺ አመስጋኝ የሚሞላው ከቀኑ 10 እና 9 ሰዓት አካባቢ ነበር። እኔ ርዕሰ አንቀጽ ለማዘጋጀት ይሄ መዘግየታችሁም ይመቸኝ ነበር። ሆኖም ግን ዛሬ እኔ እንደ ሰሞኑ ትዘገዩ ይሆናል፣ አመስጋኙም ሕዝብ እንደ ወትሮው እንደ ዘመነ ትንሣኤው ይንቀረፈፋል ብዬም ጠብቄ በመዘናጋት አልፈጠንኩም ነበር። እናም ነገም አመስጋኙ እንዲሁ የሚፈጥን ከሆነ መዘግየት በእኔ በኩል እንዳይከሰት፣ ርዕሰ አንቀጼን ሌሊት አዘጋጅቼ ጠዋት ከምስጋና በኋላ በቶሎ መለጠፍ ይኖርብኛል ማለት ነው።

"…ለዛሬ ያዘጋጀሁትን ርዕሰ አንቀጽ ጽፌ ስጨርሰው ለዐማራው እንደ ኮሶ የሚመር እንደ እንቆቆ፣ እንደመተሬ የሚያንገሸግሽ ነገር ግን የሚፈውስ፣ የሚያሽር ሲሆን፣ ለዐማራ ጠላቶች በረኪና በሉት፣ ዲዲቲ፣ የአይጥ መርዝ፣ ገመድ ገዝተህ ታነቅ።

"…በነገራችን ላይ ነጮቹም፣ ብልፅግናዎቹም ወደ እኔ አትደውሉ። አታነጋግሩኝም። "ወይ ናና ተደራደር፣ ወይ ደግሞ ተፋታንም አትበሉኝ" እኔ ዐማራ ስላልሆንኩ ዐማራን ወክዬ ከእናንተም ጋር ሆነ ከሌሎች ጋር አልደራደረም፣ አላወራም። ነገር ግን በዐማራ በኩል የሚመጣውን ትንሣኤ ስለማይ የትንሣኤውን እንቅፋቶች አልፋታም። ይሄን መብቴን የሚነፍገኝ የለም።

"…ትንሽ ጠብቁኝ የኦሮሙማን የድርድር ቁማር እርቃኑን የሙያስቀር፣ ዐማራውን እንደ ቆቅ ንቁ፣ እንደ ዝሆን ግዙፍ፣ እንደ ንስር ጥልቅ ዓይን የሚሰጠውን ርዕሰ አንቀጽ እያዘጋጀሁ ነው። በምስጋና ስለፈጠናችሁ ነው እኔ በርዕሰ አንቀጽ የዘገየሁት። የባህርዳሩን ስብሰባም ጉድ፣ የመነኮሳቱን ነውር ሁላ ተራበተራ እንመለከታለን።

•በትእግስት ጠብቁኝ እሺ ፍሬንዶቼ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የአብይ እና የአሜሪካ ውድድር

"…የአቢይ አህመድ ፈጠራ የሆነው የኦነግ ሽሜ የቁጩ መሆን፣ የዐማራ ፋኖ ማየል፣ መከላከያውን መደምሰስ፣ እሜቴ አሜሪካን በጓሮ በር ከገዱ አንዳርጋቸው እስከ መራራ ገዱና እነ ይልቃልን ጭምር ማናገር መጀመሯን ያየው ብልጡ ብልፄ ጉዱ ጀንበር እንዳዘቀዘቀችበትም ዐውቋል።

"…አምባሳደር ማሲንጋ የፋኖ ሓላፊዎችን ጭምር በስልክ አገኘሁ ብሎ መናገሩ አሜሪካ አብይን ላሽ በል ልትል ወደ ጫፉ እየሄደች መሆኑንም የአቢይ የእናቱ ከራማ የአባቱም ውቃቢ ነግሮታል። እናም አጅሬ አብይ አሜሪካ ሳትቀድመው ሊቀድማት ፈለገ።

"…ያ የድሮው የዋሕ ዐማራ ያለ መስሎት ዐማራን በጅዶ ምላሱ ሊያታልለው፣ በቄስ በሼክ ሊያባብለው ዐማራን ከሸለፈታም ስድብነት ወደ እህቶቼና ወንድሞቼ ቀይሮ ቶሎ ታርቆም በአንድ ድንጋይ ሁለት ቁማር መብላትም ፈለገ።

"…ይኸው ያለ በደላቸው ሽንታም ዐማራ ብለው እየሰደቡ ያሰሯቸውን የዐማራ እስረኞችንም በቁጥ ቁጥ እየፈታ አንጀት ለመብላት በብዙ ዳከረ።

"…አጀንዳ ጠረረ። ወደብ ወደብ ቢል ወፍ የለም።  የሶማሊያው መሪ አሜሪካ ደርሶ ከተመለሰ በኋላ ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን በሶማሊያ የጦር ሰፈር እንዲኖራት አንፈቅድምም ብሎ ወሽመጡን ቆረጠው።

"…የከሰሩት የብልፅግና አክ እንቲፍስቶች እነ ስዩም ተሾመ፣ እነ ናቲ አንደግምም ወይ፣ እነ ጃጀው፣ እነ ዳንኤል ክብረት ሳይቀር ፋኖን መሳደብ አቁሙ የመባላቸውን ሩጫ ስታዩ ሰውየው የቆሻሻ ቅርጫት ወስጥ ሊጣል መሆኑ አይታይችሁምን? ይሄን ሚልዮኖችን አርዶ የበላ ቡልጉ ለፍርድ ማቅረብ እንጂ የምን ድርድር ነው?

"…አይ ዐማራ ሰማችሁት? ቅበሯቸው ሲል። ለጠላቱ እንኳ የሚራራ ፍጥረት እኮ ነው ዐማራ።

• ማርያምን ሙቼ እኮ ነው የምወዳችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እጅ ስጥ አላልኩህም አፍር ብላና…!

"…የዐቢይ አሕመድ፣ የብርሃኑ ጁላ ሠራዊት ተደምስሷል። እጅ ስጡ ተብሎ እጅ የሰጡት ተርፈዋል። ሌላው እንዳለ እምሽቅ ተደርጎ ተደምስሷል።

"…አሜሪካም ይሄን በደንብ አሳምራ ዐውቃለች። አበባው ታደሰም አንገቱን የደፋው ለዚያ ነው። የአቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪው ገዱ አንዳርጋቸውና ሰሞኑን ዐማራ ዐማራ መጫወት የጀመረው አቶ ይልቃል ጌትነትን በታማኝነት አኔሪካ ይዛ የሽግግር መንግሥት ብላ የመጣችው ዐማራው የኦሮሙማውን ጨፍጫፊ፣ አራጅ ጦር ድራሽ አባቱን ሥላጠፋው ነው።

"…አቢይ አህመድ፣ ዳንኤል ክብረት፣ እነ ብርሃኑ ጁላ፣ አበባው ታደሰ ጭምር የደቡብ እና የኦሮሞን ልጆች በዐማራ ምድር የአሞራ ቀለብ ነው ያደረጓቸው። የሬሳውን መዓት ቆራርጬ ካልላኩላችሁ ይዘገንናል።

"…አንዳንዶች በዐማራ ክልል ያለውን ድምጽ አልባ የወታደር እልቂት በደንብ አልገባቸውም። ብልፅግና መሸነፉን እንዳያምን በዐማራ ተሸነፍኩ ማለትን እንደ ውርደት ነው የቆጠረው። ስለዚህ ያለው አማራጭ ቄስና መነኩሴ ልኮ በእርቅ ሰበብ ፋኖን አስገብቶ እንደ ወያኔ አፈር ከደቼ ማብላት፣ ፍርፋሪ እንኳ ሳይሰጥ መሳቂያ መሳለቂያ ማድረግ ነው።

"…የገባው አይወጣም። ወታደሩ ወገን ነበር። የወገን አስከሬን መለጠፍ ስለዘገነነኝ ነው እንጂ እልቂቱ እልቂት አይደለም። ለዚህ ሁሉ እልቂት ተጠያቂው ብልፅግና ለፍርድ ሳይቀርብ ዕርቅ ብሎ ነገር የለም።

• ቆይቼ ሰቅጣጩን እየቆረጥኩ ሌላም እለጥፍላችኋለሁ።

• የፈለገ ማንም ተስፋ ቢቆርጥ እኔ ዘመዴ በዐማራ ፋኖ ተስፋ አልቆርጥም። ዐማራ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።

• መጪው ደግሞ ክረምት ነው። ብልፅግና እንኩትኩቱ እንደሚወጣ በደንብ ዐውቆታል። እናም ጥድፊያው ለዚያ ነው። ማርያምን፣ አዛኜን ዐማራ ያሸንፋል…💪🏿✊💪

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እና ምን ይጠበስ? መነኩሴውስ ምን አገባው? ድርሳነ ሚካኤል የሚያነብ መሰለው እንዴ? ይሄኛው ትግል የተለየ ነው። መነኩሴው ወደ ገዳምህ።

"…የዐማራ ፋኖ ትግል 4 ኪሎ ለመግባት እንጂ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት እኮ አይደለም።

• ቄስም ሼክም፣ ጳጳስም ፓስተርም አያገባውም። አለቀ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የኬንያን ፓርላማ ሰብረው የገቡት የራባቸው የኬንያ ተቃዋሚዎች በዚያም ለፓርላማ አባላት የተዘጋጀ ጣፋጭ ምሳ አግኝተው አንደበሉም ተዘግቧል።

• የራበው ሕዝብ የጠገበ መንግሥት ይበላል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የእኔን ሓሳብ የሆነው ርዕሰ አንቀጼን 5 የ😡 የመበሳጨት፣ የመብገን፣ የመናደድ፣ የመጨስ፣ የመቃጠል፣ የማረር ፊት ካሳዩ ደንበኞቼ በቀር ከ10 ሺ ሰው በላይ ማንበቡን ቴሌግራም ሪፖርቱን በገጼ ላይ ገጭ አድርጓል። 😡 ይሄን ፊት ከዚህ በኋላም በብዛት አይ እመለከትም ይሆናል።

"…ለማንኛውም አሁን ተራው የእናንተ ተራ ነው። እናንተ ደግሞ ከእኔ የቀረ፣ የጎደለ ካለ ጨምራችሁ፣ ከእኔ የበዛ፣ የተረፈ ካለ ቀንሳችሁ የእናንተን ሓሳብ የምታስኮመኩሙን ሰዓት ነው። ቤቱ ለባለጌ አይመችም። ተቃውሞም ካለ በጨዋ ደንብ ይስተናገዳል። ስድብ ያስቀስፋል።

• 1…2…3…ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…አሁን አሁን ዐማራው ተራራው የማንንም ልቅምቅም የሰው ልክ አያውቅም ቱሪናፋ ሁላ አጀንዳ እየቃረመ ከመቀበል ራሱ አጀንዳ ፈጥሮ፣ ጋግሮ ወደ መስጠት፣ ወደ መለገስ፣ ወደ ማከፋፈል ተሸጋግሯል። ይሄ ደግሞ በእጅጉ ጠቅሞታል። እስከ ዛሬ ድረስ የትግሬ ነፃ አውጪም ሆነ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን ባዮች የአለቃቸውን የሲአይኤን የአጀንዳ አፈበራረክ፣ አዘገጃጀትና አተራረክ በጅምላና በችርቻሮ አዘጋጅተው ስለማከፋፈል የሚያስረዳውን ማንዋል እያነበቡ ዐማራውን በራሱ ጉዳይ መፍትሄ እንዳያመጣ እነሱ ፈብርከው በሚሰጡት አጀንዳ ተወጥሮ በላይ በላዩም አጀንዳ እየከመሩበት በአካልም፣ በመንፈስም ሲበታትኑት ኖረዋል።

"…የዐማራ አንቂዎች አይደለም በተቋም፣ በፓርቲ ደረጃ ተፈብርኮ የተበተነ አጀንዳ ይቅርና በዮኒ ማኛ፣ በመስፍን ደበሌ፣ በሞጣ ቀራንዮ፣ በናትናኤል አንደግምም ወይ፣ በስዩም ተሾመ፣ በቶማስ ጃጀው፣ በጌትነት አልማው፣ በስታሊን እና በአሉላ ሰለሞን ወዘተረፈ ተራ የፖለቲካ ፓርቲ ገሌ ጋለሞቶች ተዘጋጅቶ ለሚበተን አጀንዳ ጎጋዎቹ የሚያቀረሹትን ቅርሻት ተቀብሎ ነጠላ ዘቅዝቆ፣ እንደ መንደር ኃይለኛ ሴት ወገቡን በእጁ ጥርቅም አድርጎ ይዞ እንጥሉ እስኪያብጥ፣ ልቡ እስኪፈነዳ ድረስ ቆሞና ተቀምጦ ምላሽ ለመስጠት ይጋጋጥ ነበር። ያነዜ ዐማራ አጀንዳ ለመፍጠር፣ ለማቀበልም አልታደለም ነበር።

"…አሁንስ? አሁንማ አባቴ ዐማራው ሲሳይ አጌና የሚባል ገሌ ጋዜጠኛ እስከነ መኖሩም አያውቅ። ናቲ አንደግምም ወይ ቢጨንቃት የጌታ ልጅነቷን መስክራ የጴንጤ መዝሙር ወደመጋበዝ መውረዷን እንኳ አልሰማም። ሞጣን ለመደበሪያ፣ ጊዜ ለማሳለፊያ፣ እነ ቶማስ ጃጀውን ሙድ ለመያዣነት ይጠቀምበት ካልሆነ በቀር አባከና የሚላቸው ዐማራ የለም። አሁን የነፃ አውጪዎቹ አክቲቪስቶች በሙሉ በኦሮሚኛና በትግርኛ የሚሰማቸው ቢያጡ ልመናም፣ ቅፈላም፣ እዬዬም፣ ጮቤም መርገጥ ሲያምራቸው ልፈፋቸው በአማርኛ ሆኗል። ትኩረት ለመሳብ፣ አጀንዳ ለመስጠት የሚጋጋጡት በአማርኛ ብቻ ሆኗል።

"…በፊት በፊት የዐማራ ጠላቶች ዐማራን ምን ዓይነት አጀንዳ ወርውረንለት እናስለፍልፈው፣ እናዘናጋው፣ እናተራምሰው ብለው ነበር የሚፍጨረጨሩት። አሁን ግን ወፍ የለም። በፊት በፊት ጃዋር መሀመድ እንዲህ አለ፣ ሽመልስ አብዲሳ እንዲህ ብሎ አቀረሸ፣ አዳነች አቤቤ በዚህ ወጣች፣ አቢይ አህመድ በዚህ ገባች፣ ዳንኤል ክብረት እንዲያ ጻፈ፣ የሆነ አረብ ሀገር ያለ ገገማ እንዲህ አለ ለሚለው ሁሉ ዐማራው የራሴ የሚለውን ምላሽ ይዞ በፌስቡክ፣ በቲክቶክ፣ በዩቲዩብ እና በቴሌግራም ተሰይሞ ይንጠራወዝ፣ ሲንተከተክም ውሎ ያድር ነበር። አሁን ግን የፈለገ አጀንዳ ቢወረወር አባከና የሚለው ዐማራ የለም። ወላሃንቲ አለ ትግሬ።

"…ዳንኤል ክብረትም ኃይሉን አሟጥጦ ጨረሰ። አቢይ አሕመድም እጅ እጅ አለ ቸከ መነቸከ። በቴሌቭዥን፣ በራዲዮ፣ በጋዜጣ አጀንዳ ተፈብርኮ ቢወጣ በጣቱ የሚነካው ሳይሆን ዞር ብሎ የሚያየው ዐማራ ሁላ ነው የጠፋው። በፊት በፊት ሥራ ፈት የነበረው ዐማራ አሁን ሥራ ላይ ስላለ ለመንደሬዎች ወሬ ቦታ፣ ጊዜ መስጠት አቁሟል። ምንም ዓይነት ሥራ የሌለው፣ በምድር ላይ እየተካሄደ ያለውን ጉዳይ የማያውቅ፣ መረጃም የሌለው አዲስ መጪ ዐማራ ነው አሁን በዚህ ጊዜ ለቲክቶክ ወሬ፣ ለፌስቡክ አጀንዳ ጆሮ ሰጥቶ የሚንከላወሰው። ይነስም ይብዛ፣ በእውቀትም ይሁን በስሜት አሁን ሁሉም ዐማራ እንደየአቅሙ አጀንዳ ሰጪ ሆኗል።

"…በፊት በፊት ትግሬ የትግሬ ዘፋኞች ብቻ ነበሩ ስለትግሬ፣ ስለተጋሩ፣ ስለትግራይ የሚዘፍኑት። ዐማራው ወይ በእነሱ ዘፈን ይጨፍራል አሊያም በቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ያብድ ነበር። በፊት በፊት የኦሮሞ ዘፋኞች ስለኦሮሙማ፣ ስለኦነግ፣ ስለ አባገዳና ስለ ገዳ ሥርዓት ዘፈን አውጥተው ራሱ ዐማራውን የሚሰድብ፣ የሚያንቋሽሽ ዘፈን አውጥተው ለገበያ ሲያቀርቡ ትርጉሙ ሳይገባው ከኦሮሞ በላይ አዋራ ያጨስ የነበረው ዐማራው ነበር። ቢያንስ ስለ ጎንደር፣ ስለ ጎጃም፣ ስለ ሸዋ ስለ ወሎ፣ ስለ ቴዎድሮስ፣ ስለ በላይ ዘለቀ፣ ስለ ሚኒልክ ደፍሮ ይዘፍን ነበር እንጂ የዐማራ አርቲስቶች እንዲህች ብለው ስለ ዐማራነት እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ አይዘፍኑም ነበር። ምክንያቱም እነ ግንቦት 7 ዐማራ በዐማራነቱ እንዳይኮራ ዐማራ ዐማራ ነኝ ካለ ከከፍታው ይወርዳል። እንደ ትግሬና ኦሮሞ መውረድ የለበትም። ዐማራ የሚያምርበት ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲል ነው ብለው በሱዳን አስማት ጠፍረው ይዘውት ስለነበር ነው።

"…አሁንስ? አሁንማ ምኑ ይጠየቃል? ቀረርቶው፣ ፉከራው፣ ሽለላው ሳይቀር ምድሪቱን አጥለቅልቆታል። ከቀደምቶቹ ጩጬ ሚጢጢዬ የትግሬ እና የኦሮሞ የዘር ዘፋኞች ግዙፉ ዐማራ ከኋላቸው ተነሥቶ ቀድሞ ከፊት ጉብ ብሎ አርፎታል። ዳኜ ዋለ፣ ፋሲል ደሞዝ፣ ተመቸ ንጉሥ፣ መሃሪ ደገፋው፣ ተዋቸው አዳነ፣ ሞላ ሰጥአድርጌ ወዘተ እናንተም ጨምሩበት። ዘረገፉታ። በፊት ለኢትዮጵያ ያዥጎደጉዱላት የነበረውን ጥበብ አሁን እነርሱም እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ለራሳቸው፣ ለወገናቸው ለዐማራው ያፈሱት ጀመር። ልክ እንደ ዓባይ እንደ ወንዛቸው ያንቆረቁሩት ጀመር። ዋሸሁ እንዴ?

"…በፊት በፊት ዐማራ ነኝ ለማለት ዐማራው ይሳቀቅ፣ ያፍር፣ ይሽኮረመም ነበር። አሁን ደረቱን ነፍቶ ነው ዐማራ ነኝ የሚለው። ትግሬ ጁንታ ሲባል ቀውጢ ፈጥሮ ለምን ጁንታ እባላለሁ ብሎ እሪሪ ሲል ነበር። ዐማራው ጃውሳ ሲባል አዎ ጃውሳ ነኝ ምንአባህ ታመጣ ብሎ ድራሽ አባቱን አጠፋው። አዎ የአሁኑ ዐማራ ይለያል። የአሁኑ ዐማራ በጀግኖቹ ልጆቹ ምክንያት ቀና ብሎ፣ ኮራ ቀብረር ብሎ አንተ ማነህ? ሲባል ዐማራ ነኝ ብሎ በሙሉ ልቡ በድፍረት ይናገራል። ዐማራነት አብቧል። ዐማራነት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ኩራት ወደ መሆን፣ ተስፋ ወደ መሆን ተሸጋግሯል። ራሳቸውን ደብቀው የነበሩ ሁላ አሁን ዐማራ ነኝ ሲሉ ቅሽሽ አይላቸውም። ጋዜጠኛ እና አርበኛ ፋኖ እስክንድር ነጋ፣ ሀብታሙ አያሌው እና እነ አበበ በለው እንኳ ዕድሜ ለዐማራ ፋኖ በአደባባይ ዐማራ ነን ወደ ማለት ተሸጋግረዋል። ይሄ ታላቅ ድል ነው ለዐማራ።

"…ዐማራነት የታማኝነት፣ የፅናት፣ የአይበገሬነት፣ የአሸናፊነት፣ የድል አድራጊነት፣ የአማኝነት፣ የሁሉን ቻይነት፣ የታጋሽነት፣ የጥንካሬ፣ የውበት፣ የድፍረት መገለጫ ሆኗል። ከዜሮ ተነሥቶ ሂሮ መሆን ከፈለክ ከዐማራ ተማር። ከባዶ እጅ ከመውዜር ከምንሽር ተነሥቶ ዲሽቃ ሞርታር እስከመታጠቅ፣ ከትንሽዬ ስብስብ ክፍለጦር እስከመመስረት መድረስ እንዲህ በቀላል የሚታይ አይደለም። ሌባ ነው። ዘራፊ ዘራፊ ቀማኛ ነው። ደመሰስነው፣ አጠፋነው የተባለው ዐማራ ይኸው በቀን አስሬ፣ አንዴ አዲስ አበባ፣ ሌላ ጊዜ ባህርዳር፣ ደግሞ ደሴ፣ ከዚያ ጎንደር ያሰባስባቸዋል። ምክንያቱም ዐማራ ነዋ።

"…እኔ የኦሮሞዎቹን ፔጅ እከታተላለሁ። የትግሬዎቹንም እንደዚያው። የዐማራው ትግል ትግሬዎቹን ማልቀሻ እንኳ ምክንያት ነው ያሳጣቸው። በትግራይ ፋኖ የለም፣ ሻአቢያ የለም። ቢኖርም ጫፍ ላይ ነው። ነገር ግን በትግራይ ሴቶች ይደፈራሉ፣ ይታገታሉ፣ ይሰወራሉ፣ ይገደላሉ። አሁን በትግራይ የህወሓት ፖለቲካ ብልሽትሽቱ ወጥቶባታል። ራበኝ፣ ጠማኝ፣ አትድፈሩን፣ አትግደሉን በሚሉ ሰልፈኞች ተሞልቷል። ለዐማራ እንኳን አጀንዳ ሊሰጡ በራሳቸው እጃቸው ላይ የፈነዳው አጀንዳ ናላቸውን አዙሮታል። የኦሮሞዎቹም እንደዚያው ነው። በፊት በፊት ኦሮሞዎቹ የሚያወሩት በኦሮሚኛ፣ የሚጽፉት በላቲን ነበር። አሁንስ። ኧረ የምን ላቲን። እህሳ የሚቀሽሩት በአማርኛ…👇ከታች ይቀጥላል✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ጥፋት መጥቶአል፤ ሰላምም ይሻሉ እርሱም አይገኝም። ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል። …ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።ሕዝ 7፥ 25-27

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የጉድ ሀገር…

"…ኦቦ ቀጄላ መርዳሳ የኦሮሞ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ሊቀ መንበር (ኦነግ) የኦሮሞ ቅኝ ገዢ ናት ብለው ከቅኝ ገዢዋ ኢትዮጵያ ነፃ ለመውጣት የሚታገለው ነፃ አውጪ ድርጅት ፕሬዘዳንት ነው። የኦነግ ማለት ነው።

"…ፀረ ኢትዮጵያ አቢይ ታዲያ ይሄን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፕሬዘዳን ካለበት በባትሪና በእግር ፈረስ አፈላልጎ አግኝቶ አምጥቶ የኢትዮጵያ ባሕል እና ስፖርት ፕሬዘዳንት አድርጎ ይሾመዋል። ባንዲራው የኦርቶዶክስ ነው አላምንበትም ብሎ በድፍረት የሚናገር ሰው አምጥቶ ይሾመዋል።

"…ይሄ ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ነፃ ለማውጣት የሚታገል ሰው ነው እንግዲህ አሁን ብሪክስ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ እየተሰበሰበ የሚገኘው። 😂😂😂

• አይ ኦሮሞ አለ አቢይ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍"…ተረኛው ዝናብ ሆነ። እያስገመገመ መጣ። ሰውየው ላይ ዶፉን አወረደ። ለቀቀው። ሰውየውም ኮፍያውን እንደ ጥላ ተጠቅሞ፣ ልብሱን በላዩ ላይ አጣብቆ፣ እግሩን እንዳይወድቅ ተጠንቅቆ፣ አለፈው ልብሱን ሳያወልቅ። ማባራቱ አይቀርምና ዝናብዬ ሆዬም አባራ። ሰውየውም ልብሱን ሳያወልቅ መንገድ ጀመረ።

"…ተረኛ ልብስ አስወላቂ ፀሐይ ሆነች። እንደ ነፋስም በጉልበት፣ እንደ ዝናብም በማበስበስ፣ በዱላ ልብሱ እንደማይወልቅ ዐውቃ ተረድታለች። እናም በራሷ ጥበብ በዘዴ ልብሱን ማስወለቅ ጀመረች። መጀመሪያ በስሱ ፀሐይ ሙቀቷን ለቀቀች። ሰውየው ራሱን፣ ጭንቅላቱን ሲያልበው ኮፍያውን አወለቀ። ቀጥላም ሙቀ ን ከብርሃን ጋር በተን አድርጋ መርጨት ጀመረች። ሰውየው እየሞቀው መጣ። መጀመሪያ ካፖርቱን፣ ከዚያ ኮቱን፣ ከዚያ ሸሚዙን እያለ ቀስ በቀስ ማውለቅ ጀመረ። ፀሐይም ውድድሩን አሸነፈች። ሳትላተም፣ ሳታበሰብስ በስስ ሙቀት ብቻ በፍቅር ልብሱን አስወለቀች።

"…ዐማራ የወያኔንም የኦሮሞ ብልጽግናንም ልብስ አስወላለቅ አይቷል። ተምሯልም። ከሁሉም ትምህርት ወስዷል። አዎ እንደ ፀሐይ ነው መሆን ያለበት። ሙቀት እየረጨ በገዛ እጁ ጨርቁን ጥሎ እንዲወጣ ነው ማድረግ ያለበት። መከላከያ ከዐማራ ክልል ሟምቶ ይወጣል። ማድረግ ቢችል ዐማራን ከፋፍሎ መውጣት ነው። ወልቃይትን አበጣብጦ፣ ፀለምት ላይ ከትግሬ ጋር ጦርነት ከፍቶ፣ ራያን ከወሎ አባልቶ፣ አገው ሸንጎና ቅማንት አናክሶ፣ ግዙፉን ክልል አራት አምስት ቦታ ቆራርጦ እወጣለሁ ቢል ነው። ይሄም ለብልጽግና አያዋጣውም። ዐማራ እና ብርሌ አንድ ናቸው። ብርሌ ከነቃ ይሆናል ዕቃ? አይሆንም። ዐማራም እንደዚያ ነው አሁን።

"…የእኔን ተዉት እስቲ እናንተ መስክሩ፣ ተናገሩም።  አጅሬ የኦሮሞ ብልፅግና በበበድኑ በብአዴን በኩል ለዐማራ ሰላም ማምጣት ይችላልን? እንደኔ እንደኔ ከዐማራ ፋኖ በቀር አይደለም ለዐማራ ለኢትዮጵያ ራሷ ሰላም የሚያመጣ ሌላ አንድም አካል የለም። አበደን የለም።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጼ ስለ ሰላም ነው የሚያወራው።

"…ሰላም እንዲህ ቀልድ መች ሆነችና? ትግሬው አበባው ታደሰ ዐማራን አንገት ሳያስደፋ ከምኔው እሱ አንገቱን ደፋ? አይ የዐማራ አምላክ። እጹብ ድንቅ እኮ ነው።

"…በቅርቡ ደግሞ ዐማራን አንገቱን ሊያስደፉት የተነሡት አሥራት ሴንቸሪ ሞል እና በላይነህ ክንዴ አንገታቸውን ይደፋሉ። የታቦት ሽያጭ እና የመተት ገንዘብ እና ሀብትም ድራሹ ይጠፋል። ሰከላ ያለው በሰንሰለት ታስሮ የሚማቅቀውም የአበባው ወንድም ከአጋንንት እስራት ይፈታል።

• ወደ ርዕሰ አንቀጹ እንሂድ።

Читать полностью…
Подписаться на канал