zemedkunbekelez | Неотсортированное

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Подписаться на канал

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…5

"…ወንድ ከወንድ ጋር ሲገጥም፣ ገጥሞም ሲጥል፣ ወይም ሲወድቅ እኮ ተፈጥሮአዊ ነው። ወንድ ከወንድ ሲገጥም ገጥሞም ሲማርክ ወይ ሲማርክ ደንብ ነው፣ የቆየ ደንብ። የሚያስጠላ የሚደብረው መንግሥት ነኝ ብሎ፣ ባንክና ታንክ በእጁ ይዞ ሲያበቃ እንደ ወንድ ወንዶችን መግጠም ሲያቅተው፣ ገጥሞም ሲሸነፍ ሕፃን ሴት፣ አረጋዊ፣ ነፍሰ ጡር ሳይል የሚረሽነው ከንቱ ነው። ምርኮኛ የሚመራው ጦር ዕጣ ፈንታው መማረክ፣ እጅ መስጠት ብቻ ነው።

• በዐማራ ክልል የኦሮሙማን መከላከያ መፍራት ከቆመ ዓመት አለፈው…

• ቆይቼ ሲነዱት አሳያችኋለሁ። 💪💪🏿

• ተቀበል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…3

"…ሲገድልህ፣ ሲጨፈጭፍህ ውሎ ጥይት ሲያልቅበት እጅ መስጠቱ ሳያንስ "ወተት ነው የምጠጣው። ወተት ስጡኝ ለሚል ምን ትመክራላችሁ… ወተት፣ ጮማ ስጡኝ ብሎ ያማርጣል እንዴ ምርኮኛ…?

• ሓሳብ ስጡበት…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል… 1
ከ~ GG

ጭንቅላቴ ጠቦ ሆዴ ከሚሰፋ፣
ለኔ ደስታ ብየ ሕዝብ ከሚከፋ፡
የገዛ ወገኔን  በእጄ ከማጠፋ፤
ይቅርብኝ መኖሩ ለሕዝቤ ስል ልጥፋ።
ታሪክ አላጠፋም  ደግሞ  እንደ ሚኒሻ፣
ወገኔን አልነክስም እንደአበደ ውሻ፣
አላጎነብስም አልሆንም ቅጥረኛ፣
አይደለሁም ፖሊስ የጥዋት መጋኛ፣
ለማተቤ ምሞት ፋኖ ነኝ ሀቀኛ:
ድል ለዐማራ ፋኖ!!

ተቀበል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

…ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።” 2ኛ ቆሮ 9፥15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በጎንደር ዝምታው ተሰብሯል።

" …የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር የሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊው ፋኖ አርበኛ መልካም ጣሴ ይናገራል። ከላይ የምታዩት መልከ መልካሙ ሸበላው የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ ምክትል የጦር ኣዛዥ ፋኖ ተሾመ አበባው ነው።

"…የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ እነ ጋሽ መሳፍንትን የመሳሰሉ 7 የበላይ ጠባቂ አባት አርበኞች ስር ያለ እና አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የዕዙ መሪ ሲሆን ነገር ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጋዜጠኛ እስክንድር ስር በመግባታቸው ምክንያት እንደ ጎንደር የብዙ ጎንደሬዎችን ቅስም ሰብረው ነበር። ነገር ግን ይኸው ዕዝ ሰሞኑን የሚያበሥረን የመሥራች እንዳለ ሆኖ በተለይ ሰሞኑን በወልቃይት ጉዳይ የሰጠው መግለጫ "ከዩጋንዳ እስከ አማሪካ፣ ከሙሉዓለም ገ/መድኅን እስከ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ድረስ ያሉትን ወፋፍራም ትግል ጠላፊ ስኳዶች በብርቱ እያንጫጫቸው ይገኛል። ጎንደር አዚሟ እየተገፈፈላት፣ አንድነቷም እየቀረበ ነው። መስቀልም አንጠልጥለው፣ ዳዊት እየደገሙ፣ ዱአም እያደረጉ ሶላት እየሰገዱ በነፃነት ነፃ የሚያወጡላት ልጆቿ ወደፊት እየመጡ ነው።

"…ሚኒሊክ ሚዲያ ባለቤቶች ለእነ ሀብታሙ አያሌው፣ ለእነ አበበ በለው፣ ለእነ ዶፍቶር አምሳሉ የቀረበ ጥያቄ ሲሆን እነ ዶፍተር ምስጋው አንዷለምም ጥያቄውን ሰምተው ምላሽ ቢሰጡበት መልካም ነው።

• አድምጡት። አድምጡትና ምኒልክ ቴሌቭዥኖች የሕዝብን አስተያየት ያነብባሉና አስተያየታችሁን እዚሁ ልጥፍ ስር አስቀምጡላቸው። ለስኳድም ጭምር ነው ታዲያ።

• ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ከላይኛው የቀጠለ "…በሸዋ የእስክንድርና የመከታው ጦር እየተበተ ነው። ብዙዎች ወደ እነ ደሳለኝ እየተቀላቀሉ ነው። የመከታው የጦር አዛዥ ጫታሙ ሱሳሙ፣ መከታውን ያግዘው ዘንድ ከፌደራል ፖሊስ ወደ እነ መከታው የተቀላቀለው ኤርሚያስ ብቻ ነው አሁን ሕዝቡን እያስጨነቀ፣ የገበሬውን ፍየልና በግ እያነከተ፣ እየበላ ጫትና ሺሻውን እየማገ፣ የድህነት እድገቱን የሕዝብ ከብት አርዶ በመቀለብ፣ ሴቶቹን በመድፈር ዓለሙን እየቀጨ ያለው እንጂ ሌሎቹ በጊዜ ተሸብልለዋል። አቤ ጢሞም መውጫ ስላጣ እንጂ ከመሳይ መኮንን ጋር የባጥ የቆጡን የሚለፈልፈው ነዳጅ ጨርሷል። ሌሎች ብርጌዶችም መግለጫ ሁላ ማውጣት ጀምረዋል። እንዲያውም ከሰሞኑ ይሄ በሸዋ ይከሰታል ብለው የሚወራውን ልንገራችሁማ። ለምታውቁአቸውና በመከታው ማሞ ስር ለሚገኙ ፋኖዎችም ደውላችሁ ንገሩልኝ። አደራ።

"…ዘመዴ በጣም አስቸኳይ እና ጥብቅ መረጃ ነው ብለው ነው የመረጃ ምንጮቼ መረጃውን ያደረሱኝ። ከእስክንድር እንዳልለይ መጽሐፍ ቅዱስ አስይዞ አስምሎኛል ብሎ ሞቴን ከእስክንድር ጋር ያድርገው በማለት ሠራዊቱን ይዞ ገደል የገባው የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አዛዥ መከታው ማሞና በስሩ የሚመራው የሥራ አስፈፃሚ አባላት ከመንግሥት ጋር ተደራድረው ለመግባት መስማማታቸውን በዚያው በሚገኙ የውስጥ አርበኞች አማካይነት ሾልኮ የወጣው መረጃ ያረጋግጣል።

"…በአማራ ፋኖ የውስጥ አርበኞች አማካኝነት ሾልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚለው ለአቶ መከታው ማሞ ከጥቅምት 29/2017 ዓም እስከ ኅዳር 04/2017 ዓም ድረስ ባሉት ቀናቶች ውስጥ እሱ የሚመራቸውን የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የዐማራ ፋኖ አባላትን በይፋት ቀጠና ለስብሰባ በሚል ሽፋን ጥሪ ካስተላለፈ በኋላ በድሮን ለማስመታት መስማማቱ ነው ነው የተነገረው። ከመከታው እና ከሥራ አስፈፃሚ ቡድኑ ጋር የተስማሙት ጀነራል አበባው ታደሠ፣ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እና ዓለምሸት ደግፌ መሆናቸውም ታውቋል።

የስምምነቱ አካል የተደረጉት ነጥቦች :_

1. መከታው ማሞና ቡድኑ ያለ መከሰስ መብት፤
2. በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እና
3. በፈለጉት ሀገር ሄደው እንዲኖሩ የቪዛ ጭና ጉዞ ሰነድ ሁኔታን ማመቻቸትን ያጠቃልላል ሲሉ መረጃውን ያወጡት የዐማራ ፋኖ የውስጥ አርበኞች ገልጸዋል። ይህ መረጃ የደረሳችሁ የዐማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ ሴራውን እንዲከሽፍ እንድታደርጉ እናሳስባለንም ነው የሚለው መልእክታቸው። ለማንኛውም መጠንቀቁ አይከፋም።

"…በመጨረሻም ሰሞኑን በአሩሲና በጉራጌ ክልል የሰቆቃ ድምጽ እየተሰማ ነው። ግልገል ነፍጠኛ ብለው ለእርድ ያዘጋጁትንና ቀን የሚጠብቁለትን ጉራጌና ከጉራጌም ክርስቲያን ኦርቶዶክሱ ጉራጌንና በዚያ የሚገኙ የዐማራ ተወላጆች በከባድ ሰቆቃ ውስጥ መሆናቸውም እየተሰማ ነው። የዚህ አካባቢ ደግሞ ትንሽ ለየት የሚለው ጉራጌንና ዐማራን ከአካባቢው ለማጽዳት ኦሮሙማ ብቻዬን ለምን እጠቆራለሁ በማለት በፓስተሮቹ በኩል በተደረገ ቅስቀሳ አማካኝነት " የኩሽ ኅብረት" የሚል ጥምር ፈጥረው ሴማውያን ብለው የፈረጇቸውን በሙሉ የማጽዳት ሥራ እየሠሩ መሆናቸው ነው የተሰማው። ኦሮሙማው ትጥቅ አውርድ ሲልህ እንዳለቀልህ፣ ለእርድ እያዘጋጀህ መሆኑን ልታውቅ ይገባል። በጉራጌም የሆነው ይሄው ነው። መጀመርያ ቀደም ብለው ሙሉ በሙሉ የዐማራውን ገበሬ ትጥቅ አስወረዱ። ካስወረዱ በኋላም አሁን ላይ እነሱ በሚፈልጉት መልክ አዋራጅ የሆነ አሰቃቂ አገዳደል መግደል ጀመሩ። ከሁሉም ጀርባ ግን ኦህዴድ አለ ነው የሚለው ከስፍራው የወጣ መረጃ። የንስር ጋዜጠኛው "ለመከላከልስ ጥረት አላደረጋቹህም? ብለው ለጠየቁት  ጥያቄ የአካባቢው ኗሪዎች የሚከተለውን ምላሽ መስጠታቸውንም ዘግባዋል።

"…ጠቡ የተነሳው ከትናንት ወዲያ ሁዳድ 5 ቀበሌ አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከንባታ ሚኒሻ ታግቶ ነበር። ከዚያ እዚያ አከባቢ የነበሩ የዐማራ አንዳንድ ሽማግሌዎች ከንባታዎቹን ለመኑ። ከንባታዎቹ እንቢ አሉ። ትናንት ደሞ ያ የታገተውን ልጅ ብር አልከፍል ሲሉ በምላጭ ፊቱን ተለተሉት እና ማታ 1:30 አከባቢ ደግሞ ዳርጌ ላይ አንድ የከንባታ ተወላጅ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው ተገደለ። ይህን መነሻ በማድረግ ነው አሁን ዐማራን ቤት ለቤት መግደል እና ቤት ማቃጠል የጀመሩት። ሁሉም በደንብ ታጥቀዋል። በኦህዴድ ሰልጥነዋል። ዐማራዎች ለመከላከል ማንም አልሞከሩም። እንደሚታወቀው የዐማራ ትጥቁን የኦህዴድ እና የዞኑ አመራሮች አስቀድመው አሰቃይተው በግድ ተቀብለውታል። እንኳን ገበሬው የዐማራ ሚኒሻው ትጥቅ የለውም።

"…እነሱ ግን ሁሉንም ወጣቶች አደረጅተው በየ አዳራሻቸው እና ሰብስበውው "ፌስታል ይዛቹ ነው የመጣቹት ፌስቴል ይዛቹ ትሔዳላቹ" 1ከምባታ ቢሞት በጅምላ ዐማራ እንገድላለን" እያለ በስብሰባቸው ላይ ሊቀመንበሩ ይነግራቸው ነበር። ተብሏል። መከላከያና ፌድራል ፖሊስ አካባቢው ላይ እያሉ ቤት ሲቃጠል ንብረት ሲወድም ሕዝቡ ሲጨፈጨፍ አስቁሙሉን ብለን ብንማጸናቸውም ትዕዛዝ አልተሰጠንም በማለት ፊት ነሱን። ለመከላከልም አልፈለጉም ይላሉ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት የወረዳው ነዋሪዎች። ለወረዳው ነዋሪዎች በጥቃቱ ምን ያህል ሰው ተጎዳ? አሁንስ ምንድነው ዋስትናቹህ ብሎ የቢዛሞ ሚዲያ ለጠዬቃቸው ጥያቄ ጥቃቱ አሁንም አልፎ አልፎ የቀጠለ በመሆኑ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ማወቅ አልቻልንም ያሉት የቀበሌዋ ነዋሪዎች። ቤት ሲቃጠል አብረው የተቃጠሉትን ዐማራዎች እስከ አሁን አጽማቸዉን እንኳ ለመሰብሰብ እንደተቸገሩ ተናግረዋል። አክለውም እስከ አሁንም ብንጮህ ሊደርስልን የቻለ የሕግ አካል የለም ያሉት ዐማራዎች አሁን ላይ በአንድ ቀን እንኳን ቢያልቁ ምንም ዓይነት የሕግም የኃይልም ዋስትና እንደሌላቸው እና በገዳዮቻቸው ተከበው እንዳሉ ነው ለቢዛሞ ሚዲያ የገለጹት።

"…የሩዋንዳው እልቂት የተፈጸመው የፕሬዘዳንት አውሮጵላን ተመትቶ በመውደቁ ነበር። አሁንም ኦሮሙማው ሁሉንም ብሔር አንድ ሰው ቢሞትብን እናንተን ነው የምንጨርሰው እንዲሉ እያስደረገ ከከምባታዎች የፈለገውን ገድሎ አርዶ በመጣል ይሄን ያደረገው ዐማራው ነው በማለት የዘር ጭፍጨፋውን ለማድረግ ይችላል የሚሉም አሉ። አሁን ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ዐማራና ኦርቶዶክስን መግደል፣ የዐማራ እስላምን መግደል በሕግ የማያስጠይቅ፣ በሥርዓቱ የሚያሸልም ስለሆነ ያልታጠቁ ዐማሮችና ኦርቶዶክሶች ላይ ትንሽ ጠንከር ከበድ ያለ ነገር ሊመጣ ይችል ይሆናል። የሆነው ሆኖ ግን ዐማራው በክልሉ ቢያረፍድም እንኳንም ቀደም ብሎ ታትጥቆ ውጊያ ጀመረ። ተወደደም ተጠላም፣ የፈጀውን ሰውና የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ ዐማራው ከማሸነፍ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም። ድርድር፣ ግርግር፣ ወላ ሃንቲ ነገር አያተርፈውም። ዐማራ መዳኛው ማሸነፉ ብቻ ነው። ከከሃዲው አቢይ ጋር ድርድር ማድረግ ማለት እንደ ትግሬ የአቢይ ገረድ፣ ባርያ፣ ጫማ ላሽ፣ ሰቀቀናም መሆን ብቻ ነው። ዐማራ ሦስት አማራጮች ናቸው ያሉት።

1ኛ፦ ማሸነፍ
2ኛ፦ ማሸነፍ
3ኛ፦ ማሸነፍ…  አለቀ። ከማሸነፍ በቀት ለዐማራ ሌላ ምርጫ የለውም። ያለበለዚያ ዐማራ እንደ ኩርድ ነው የሚጠፋው።

• በታሪክ የሚሸነፍ መንግሥት እንጂ የሚሸነፍ ሕዝብ የለም። አኬር መገልበጡ እንደሁ ግን አይቀርም።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም….!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 29/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …ዐማራው ከነቃ፣ ከታጠቀ መዳረሻውን ስለሚያውቁ ነገርየውን ለማኮላሸት አስቀድመው ዋይ ዋይ ይሉብኝ ነበር። ኦሮሞዎቹም ኦሮማራ በሚል ማደንዘዣ ያስተኙት ዐማራ በጊዜ ነቅቶ ጉዳችን ይፈላል ብለው ይወርዱብኝ ነበር። የደቡብ ፓስተሮች፣ ጴንጤዎች፣ የስልጤና የኦሮሞ፣ የወሎ የኦሮሞ ዲቃላ የወሃቢይ እስላሞች ስንትና ስንት ቪድዮ ሠሩብኝ? ወረዱብኝ? የጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹ እነ ቶማስ ጃጀው፣ እነ ዓምደማርያም ዕዝራ፣ ከጎጃም ወዶ ገቡ ገሌው ረዳት ፍሮፌሶር ጌትነት አልማው፣ ጉራጌው የደብረ ብርሃኑ ፍሮፌሰር፣ የአሩሲ ዐማራውና በግድ የወረመው ስዩም ተሾመ፣ የከንባታ ነው የሃድያው የመሃል ሜዳ ፓስተር ደሳለኝ፣ የሰው ነጋዴው ኮሮና ዳዊት፣ እስቲ ያልወረደብኝን ንገሩኝ? ከኦርቶዶክስ የወሎው ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ጀምሮ ጓ ያላለብኝ አልነበረም። እኔ ግን ያየሁትን ስላየሁ ዋይዋይ ዐማራ ሆይ ግድየለህም ቢያንስ ተሰባሰብ፣ በጉዳዩ ላይ ምከር፣ ቀስብለህ ታጠቅ፣ ከዚያ መክት፣ በመጨረሻም አንክት ብዬ ወተወትኩኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ዐማራውም ሰማኝ። ሰማኝ እግዚአብሔር ይስማው። ተዘጋጀ፣ ቀኑን ጠብቆ ዛሬ ይኸው አዳሜና ሔዋኔን ወጥ በወጥ እያደረገ ይገኛል።

"…እየተካሄደ ያለው ጦርነት ነው። በጦርነት ደግሞ መውደቅ መነሣት፣ መሞት መመቁሰል፣ መማረክ፣ መማረክ፣ መክዳት መኮብለል፣ ባንዳነትም፣ ጀግንነትም የሚኖር ነው። ይሄ ተፈጥሮአዊ ነው። የሆነው ሆኖ ግን አሁን በተጀመረው የዐማራ ትግል የዐማራ ሕዝብ ለአፍታም ያህል ይሸነፋል ብዬ አስቤም አልሜም ዐላውቅ። እስከአሁን ጦርነቱ የተራዘመው፣ የተነዘዛውም ቆርጦ በሙሉ ልቡ ወደ ትግሉ የገባው ዐማራ በፐርሰንት ሲሰላ ገና 0. 11223 መሆኑ ነው። 1% ከመቶ እንኳ የሚሆነው ዐማራው ቆርጦ አልተነሣም። በዚህ ነው እንግዲህ ይሄው ቆርጦ የተነሣው ዐማራ ዓለምአቀፍ ንዝረት የፈጠረው። በዐማራ ተሸነፍኩ ማለት ውርደቱ ስለሆነ ዋጥ አድርጎት ነው እንጂ አገዛዙ በፋኖ ሽባ ሆኗል። ፋኖ አገዛዙን ሽባ አድርጎታል። ገንዘብ አሳጥቶታል። አድቅቆታል። ብቻውንም እያስወራው ነው። ዐማራው በሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን በዳያስጶራም ያለው ገና አልተነሣም። አዚሙ አልተገፈፈም። በግንቦት ሰባት፣ በፌክ ኢትዮጵያኒስቱ የተተበተበው ትብታብ አልረገፈለትም። ነቅቷል ግን ገና አልባነነም። አልተነሣም። ታጥቦ ኮተቱን አላስወገደም። ይሰማል ግን ዓይኑ አልተገለጠም። የሆነ ቀን መንቃቱ አይቀርም። እንግሊዝን በሚያህል ትልቅ ሀገር፣ በዚያ ያለው ዐማራ ሙሉ ለሙሉ ሳይነሣ እኮ ነው ሁለት ሦስት የለንደን ፋኖዎች ሚጢጢዬዋን ኤምሬትስን ድንብርብሯን ያወጧት። ክብር ለለንደን ፋኖዎች። በሁለት ሦስት ሰው ብቻ።

"…በሀገር ቤት እስክንድር ነጋም ሳንካ በመሆን ትግሉን አልጎተተም ማለት አይቻልም። ድብን አድርጎ ጎትቶታል። በዚህ ማመን አለብን። ከአሜሪካ መልስ ወደ ጫካ ገባሁ ያለውና ብአዴን አስሮ በመፍታት ያጀገነው፣ ውጋኝ፣ ደምስሰኝ ብሎ መርቆ ሸኝቶ የላከው፣ ወደ ጫካም የሸኘው እስክንድር ነጋ የቀደመ የጋዜጣ ላይ፣ በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ የተገነባውንና በመታሰር በመፈታት "ታላቁ" የሚል ቅጽል ስም ያገኘው፣ ዕድሜ ልኩን ለኢትዮጵያዊነት ሲታገል የነበረው ሰው ድንገት ፋኖ ትጥቅ ትግል መጀመሩ የማይቀር መሆኑን ሲያውቅ ዘሎ ገብቶበት ትግሉን በጥብጦታል። እስክንድር ነጋ ብቻውን መንግሥት ያልቻለውን የዐማራ ፋኖን የመከፋሉን ሥራ እሱ አድርጎት አሳይቷል። ጎንደርን ሦስት ቦታ ከፋፍሎ አሁን ደግሞ ሀብቴንና ፋፍዴንን ወደራሱ አድርጓል። የውባንተ ልጆች እነ ባዬ፣ እነ ሳሚ ብቻ ናቸው ወጊድ እኛ የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ነን ብለው ኢግኖር የገጩት። በወሎም ሁለት ቦታ ነው የከፈላቸው። በምሬ ወዳጆ የሚመራው የዐማራ ፋኖ ወጊድ ሲለው በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ የሚመራው ፋኖ ለእስክንድር ነጋ ገብሯል። በሸዋም አሰግድንና መከታውን አጣልቶ ሸዋን ለሁለት ከፍሎ እሬቻቸውን አባልቷል። በጎጃም ብቻ ነው ያልተሳካላት። ጎጃም መሬው የእስክንድር ነጋን የጎጃም ሴል፣ ኔትወርኩን በሙሉ ቆራርጦ አንድ ወጥ አደረጃጀት በመፍጠር ድባቅ መትቶታል። እስክንድር ሾተላይ በመሆን የዐማራን ትግል አዘግይቶታል። በመጨረሻም ባዶውን በመቅረት አውላላ ሜዳ ላይ ተዘርፍጧል።

"…እስክንድር ነጋ የምድሩን ታጋይ ብቻ ሳይሆን የአየር ላይ ታጋዮችን ሳይቀር ነው እንደ አሜባ የበታተነው። ገንዘብ የሚገዛውን በገንዘብ፣ ሆዱን ያለ በሆዱ ጠልፎ ጥሏል። ከሁሉም ከሁሉም ዳያስጶራው በአንድ ልብ ትግሉን እንዳያግዝ አስቀድሞ የጉፈንድሚ ኮሮጆውን ይዞ በመዞር ብሩን ሰብስቦ በማቅለጥ ዳያስጶራው ፔኒ፣ ዲዱ፣ ጢና ሳንቲም እንዳይረዳ ደንቃራ ሆኗል። እስክንድር ለሰናይ ቲቪ ለመነ፣ ለባልደራስ ለመነ፣ ለግንባሩ ለመነ፣ ለምኖ ግን ብሩን እምጷ ቀሊጦ ነው ያደረገው። ሚስቱ ሠርካለም ምን ዓይነት ኑሮ እንደምትኖር የሚያውቅ የለም። እሷም የባልደራስ ገንዘብ አሰባሳቢ ነበረች። ወጥሬ ይዤአታለሁ የአደባባይ ሰው ስለሆነች ቀርባ እንድታስረዳን መወትወቴን እቀጥላለሁ። አበበ በለው አትንካት ስላለኝ አልምራትም። መጠየቅ ምን ችግር አለው? ደግሞም ጋዜጠኛ አይደለች እንዴ? እንደ ጉድ ትጠየቃለች። አዎ የዳያስጶራውን እርዳታ ያስቀረው የእስክንድር ነጋና የቲሙ ስግብግብነት ነው። 20 ሚልዮን ዶላር መሰብሰብ ሲችሉ በሁለትና ሦስት ሚልዮን ዶላር ለሃጫቸውን አዝረበረቡ። የደሀ ነገር። ግንባሩን አፍርሰው በሠራዊቱ ስም ለመለመን ሰንዳ ብለው ሲመጡ የጉረሮ አጥንት ሆንኩባቸው። ሕዝቡም ዳግም ከመጋጥ ታደግኩት። እነሱም ከስረው ቀሩ።

"…እነ ሻለቃ ዳዊትም ድርጊቱን ተቃውመው ወጡ። አክቲቪስት ጋዜጠኛው ሁሉ ተበጣጠሰ። የዳበረ የመከፋፈል ልምድ ያለው የጎንደሩ ስኳድ የፖለቲካው ቆማንት የትግሬ ዲቃላው ሁሉ ደንግጦ ግር ብሎ መጣ። በእስክንድር ጀርባ ታዝሎ ትግሉን ለመጥለፍ ይዳክር የነበረው መንጋም በገሀድ ተገለጠ። የጎንደር የዐማራ ጴንጤዎች፣ ጥቂት ፀረ ዐማራ አቋም ያላቸው የጎንደር የአይሁድ እምነት ተከታዮች፣ የጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች፣ የጎንደር ፀረ ዐማራ የብአዴን የወሃቢይ እስላሞች ተሯሩጠው ግርር ብለው መጡ። ፓስተራቸውን ምስጋናው አንዷለምን ይዘው መንግሥታቸው ብልጽግናን ከመፍረስ ለማዳን ተገለጡ። የጎንደር ፋኖ መስቀል አድርጎ፣ ዳዊት እየደገመ ለምን ይዋጋል ? ብሎ የጠንቋይ ልጁ ዶፍተር በግልፅ ጓ አለ። ለእነ ውባንተ የተዋጣውን 60 ሺ ዶላር ቀርጥፈው በሉ። ወልቃይትን እንደ ነዳጅ ጉድጓድ የሚቆጠሩት ወልቃይቴ ነኝ ብለው በጎንደር ዐማራ ስም የሚነግዱት ነጋዴዎች በሙሉ ጫጫጫ ብለው ወጡ። እኔም አምላኬን ይዤ ብቻዬን ገጠምኳቸው። ገጥሜም አፈር ከደቼ አበላኋቸው።

"…ባይገርምላችሁ የጎንደሩ ጉዳዩ በመጨረሻ የሃይማኖት ሆኖ ተገለጠ። ይሄን ለማረጋገጥ ከፈለጋችሁ ከቲክቶክ መንደር ሰባብሬ ያባረርኳቸው እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ትናንት ወደ ትዊተር ስፔስ ሄደው ያደረጉትን ማየቱ ብቻ በቂ ነው። ስፔሱን የከፈተችው ፈትለ ጴንጤ ናት አሉኝ የእነ አያሌው ቡድን ነው የሚነግረኝ። ማዕዶት ይሁዲ ናት አሉኝ። ናቫ አክራሪ ጴንጤ ናት ያሉኝ ሲሆን አይ ፈትሊ ድብልቅ ናት። ጴንጤ ብቻ አይደለችም ግራ የገባት ጴንጤም፣ ኦርቶዶክስም አይሁድም ናት። ዘመነ ካሤንና አንተን አምርራ ከመጥላቷ በቀር ብዙም ክፋት የለባትም። ትንሽ ጥራዝ ነጠቅነትም ያጠቃታል ነበር ያሉኝ። አልማዝ ኤርትራዊና ወልቃይቴ ናት። በዊድ የተበላሸች ጤነኛ… 👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የሳምንቱ የመጨረሻው ርእሰ አንቀጻችንን ሳዘጋጅ ነው የቆየሁት። ርእሰ አንቀጹ ሦስትና አራት ጉዳዮችን የዳሰሰ ነው። አረመኔው የአቢይ አሕመድ አገዛዝ የንጹሐንን ጭፍጨፋ በሰፊው ተያይዞታል። እሱንም እንዳስሰዋለን።

"…በዐማራ ፋኖ በወሎ ግንባር መጀመሪያ ተማርከው በወሎ የዐማራ ፋኖዎች ተሃድሶ ተሰጥቷቸው የተለቀቁ የምርኮኛው የብርሃኑ ጁላ ወታደሮች በድጋሚ አገዛዙ ልኳቸው አሁንም መማረካቸው ነው የደረሰኝ መረጃ የሚያሳየው። እሁድ በመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ ላይ በሰፊው በቪድዮ ጭምር እመለስበታለሁ። ጠብቁኝ።

"…ተመልከቱ ንፁሐንን ሲጨፈጭፍ የወለ አረመኔ የአረብ ተላላኪ የምርኮኛ ልጅ በዐማራ ፋኖ ሲማረክ "ወተት የለም፣ ወተት ስጡኝ" ነው የሚለው። ስሙት ገበሬውን "ወተት የለም" ብሎ ሲጮህ። ተማርኮም ወተት ስጡኝ። 😂 ወደው አይስቁም እኮ። "ወተት ስጡኝ አላለም" ይሄ ገዳይ ምርኮኛ ሰብስቦ በራብ ለሚሰቃዩት ለፋኖዎች የማያቀርቡትን ሰንጋ ጥሎ ፍሪዳ አርዶ አብልቶ፣ ወተትና እርጎ የማጠጣቱንስ ነገር እናንተ እንዴት ነው የምታዩት? የምትመለከቱትም? እስቲ በዚህ በምርኮኛ ጉዳይም ተወያዩበት።

• ርእሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቲሽ ኃይሌ በጠበጠው

"…ከቲክቶክ ዠልጬ ያባረርኳቸው ስኳዶች በሙሉ እንዳለ ነቅለው ወደ ቲዊተር ስፔስ ተሰደዋል። ለዶፍቶር ፓስተር ምስጋናው የገጽታ ግንባታ ተብሎ ራሷን የጎንደር ልዕልት ብላ በምትጠራው በፈትለ ቤት ነበር የተዘጋጀው። ፈትሊ ኃይለኛ የእስኬው ደጋፊ ናት። አቤት እኔንና ዘመነ ካሤን እንዴት አምርራ እንደምትጠላን አትጠይቁኝ። ዘመነ ካሤ የጎጃም መሪ መሆን የለበትም ብላም ቪድዮ ሠርታለች። እንደነገርኳችሁ ፕሮግራሙ ለፓስተር ምስጌ የገጽታ ግንባታ ነበር የተዘጋጀው። ውኃ በላው እንጂ። መጀመረያ ለእኔ ወፎች የተነገረው የተለያዩ ሰዎች መጥተው ምስጋናውን አድንቀው ጎንደር እንዴት እየተጠቃ እንዲያወሩ ነበር። በዚህ መሠረት አንዷ የጣና ቲቪ ሰው መጥታ የጎንደር ሕዝብ እንደ ሕዝብ እየተሰደበ፣ አዳዲስ ስም እየተሰጠው፣ ስኳድ ፋፍዴን እየተባባለ ብላ ረጅም ሰዓት አወራች። ፋፍዴን የሚባል የለምም አለች።

"…እዚህ ላይ ነው ኃይሌ የገባው። ኃይሌ በግሉ እኔ ዘመዴ ላይ ቅሬታ ቢኖረውም ለዐማራ ግን ከልቡ ነው የሚሠራው። የዲሲው ሠልፍ ላይ ራሱ በውጭ ሚዲያ ላይ ሁላ ቃለመጠይቅ ተደርጎለት ደስ ብሎኛል። ምን ፋፍዴን አላውቅም ትያለሽ? ፋፍዴን ማለት ከጎንሽ ያለው ምስጋናው ነው እሱን ጠይቂው። አታስመስሉ። በዚያላይ ጎንደርን የተናገረውን ሰው በግለሰብ ስም ጠርታችሁ መናገር ስትችሉ አንድ ሕዝብ ሌላውን እንደሰደበ አድርጋችሁ አታቅርቡ። ፋፍዴህን ጣና ምናምን ግን ምስጋናው ነው ሲላት ቀወጡት። ቤቱንም ዘጉት።

"…ኃይሌ የጎንደር ዕዝ ተወካይ የሲሳይ ጓደኛ ነው። ምስጋናው ደግሞ ሲሳይን አምርሮ ነው የሚጠላው። ቲሽ ሲያናድድ ደኅና እየቀዳኋቸው አቋረጡት። ስሜታችሁን ተቆጣጥራችሁ ተመልሳችሁ ክፈቱና ሳልተኛ በፊት ልቅዳችሁ።

• በሉ በሉ የእንጀራ ገመዶቼ ተመልሰው መጡ ማዕዶት እየወቀጠችኝ ነው በሉ ልቅዳቸው። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቆይ ግን ዶፍቶር ሌባ ይባላል…?

"…የሄ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ የሆነ ሳሚ የሚሉት ልጅ እንዴት ያለ ደፋር ነው በናታቹ። እንዴት በስንት ልፋት በ12 ዓመቱ ዶፍተር የሆነን ቅማንቴ ስኳድ ሌባ ብሎ ይጠራል? በእውነት ይሄ ነገር ጥሩ አይደለም። ልክም አይደለም። ግን ምን አገባኝ።

"…ምስጋናው የእነ ውባንተን 60 ሺ ዶላር ስለሰረቀ፣ ስለዘረፈ ሌባ መባል አለበት ግን? ምንሼ ነው? የደላው ስንት እንደ እስክንድር ነጋ፣ እንደነ ሀብታሙ አፍራሳ፣ እነደነ አቤ እስክስ ሚልዮን ዶላር ሃም አድርጎ ይሰርቃል ምስጌን 60 ሺ ዶላር ዘረፈ ብሎ ማማት፣ መሳደብ ነውር ነው። መሰለኝ።

"…ስኳድ ለእኔ እንጀራዬ ነው ስል በምክንያት ነው። እነ ወርቁ አይተነው፣ እነ ዘመነ ካሤም በቶሎ ክፍያኔ ጨምሩ፣ ጨምሩ ብያለሁ። ተናግሬአለሁ። ሳሚ ቅማንቴ አንተም ንገርልኝ። 🙏 ብሊስ…

"…የስኳድ ዶፍተርን ሌባ ማለት ግን አግባብ ነው? እስቲ እናንተም ፍረዱ። ምስጌ መመረቂያው ብርቧቅስ የመሰንቆ የአዝማሪ ወግ ነው አሉኝ።

"…ሳልረሳው No12 ናይጄሪያዊ የመሰለን ሸበላ የስኳድ ዶፍተር በአደባባይ ሌባ ብሎ መናገር አግባብ ነው ግን…? ሃቱ…😁

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እኔን እኮ ነው…😂

"…ሳሚ ቅማንቴው ዶር ምስጋናው አንዷለም ሌባ ነው ሲል ተው አይባልም ስለው ነበር። 😂 …ቪድዮው አለኝ። ተው ሳሚ ምንም እንኳ አንተ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ስኳድ ብትሆንም ተው በ2 ዓመቱ ዶፍተር የሆነን የጠንቋይ ልጅ ፓስተር ሌባ ብለህ መጥራት ልክ አይደለም ብዬው ነበር። ከፈለጋችሁ ቪድዮውን እለጥፍላችኋለሁ። ከፈለጋችሁና ለጥፍልን ካላችሁ ነው ታዲያ።

"…ይኸው ዛሬ ደግሞ ከሌላኛው ጠሽ ጋር ሆኖ ሲቦጭቀኝ ውሏል። ተው እንጂ ሳሚ ተው እንጂ። እንጀራዬማ ናችሁ። እንደ ስኳድ እንጀራዬ፣ እንደ አገው ሸንጎ እንጀራዬ፣ እንደ ግንባሩ፣ ጥርሱ፣ አንገቱና ደረቱ የስክንድር ጠዋት ተመርቶ ከሰዓት መርካቶ የሆነ ድርጅቶች እንጀራ የሚሆነኝ ከየት ይምጣልህ? ተው በእንጀራዬማ አትምጣ።

"…አሁን እንኳ እናንት የሰው ጅሎች ባትኖሩልኝ፣ ይሄን ቪድዮ አደባባይ ወጥታችሁ እየለፈለፋችሁ ባልቀርጻችሁ በምን የቤቴን ደንበኞች አዝናና ነበር? በምን የቤቴን ደንበኞች ፍላጎት እና የወሬ ሱስ አምሮት አረካ ነበር? ኑሩልኝ ሚኪጠሽዬ፣ ሰሚ ዲቃላው የእኔ እንጀራ ኑሩልኝ። 😂 ጎበዝ የእንጀራ ገመዶቼን መርቁልኝ።

"…ወርቁ አይተነው፣ ዘመነ ካሴም ደሞዜን ጨምሩ። ይኸው ተናግሬአለሁ ደሞዜን ጨምሩ። ሳሚ ቅማንቴ አንተም ታገልልኝ። በሚኪ ቤት፣ ወይ በእሴት ቤት፣ ወይ ደግሞ በዶር ደረጀ ቤት፣ ወይም በእሸቱ ገጠሬው ቤት ለእኔ ለዘመዴ ይሰበሰብልኝ ዘንድ አመለክታለሁ። ሳሚዬ ይሄን አጀንዳ በደንብ አውሩበት። የእነ ወርቁ ክፍያ ብዙም አርኪ አይደለም። ዘመነማ ስቁንቁን ነው። ባለፈው ለሻይ ብሎ የሰጠኝ 36754364 ዶላር ለምን ላድርጋት? እንደ ልፋቴ ምንም እየተከፈለኝ አይደለም። እስቲ እናንተን ተጠግቼ የወልቃይትን ሰሊጥ ልሞክር። እሱ ሳይሻል አይቀርም።

• በርቱ የእንጀራ ገመዶቼ…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዛሬው እጅግ ደስ ይላል። ከወትሮው በተለየ መልኩ ወደ 32 ሰው ያህል 😡 ብው ብሎ ሲቆጣ፣ ሲናደድ፣ ሲበሳጭ ታይቷል። 13 ሺ ሰው አንብቦ 32 ፍሬ ሰዎች 😡 ብው ብለው ተናደው ማየት ለእኔ ኪሳራ ቢሆንም የተናዳጁ ቁጥር ወደ 100 እና ሁለት መቶ ከፍ እንዲል መጣሬ አይቀርም። ገና ብዙ እንደሚቀረኝ ነው የተረዳሁት።

"…አንበሳ ዘመዴ፣ ብራቮ፣ የእኛ ዝሆን፣ ነብር፣ ሚዳቋ፣ ድኩላ እያሉ በደንና የዱር እንስሳት ስም ከመሞገስ ምንም ትርፍ አላገኝም። የእኔ ትርፍ እንዲህ ብው ብለው የሚያነቡኝ ሰዎች ናቸው። ያመራምሩኛል። ያንቀሳቅሱኛል፣ እንዳነብ፣ እንድጠይቅ ያደርጉኛል። እንደ አሽከር፣ እንደ ባሪያ ጎሽ ዘመዴ ብቻ መባሉ እኔን ይደብረኛል። የተቃራኒ ቡድንን ጨጓራ መላጥን የመሰለ ነገር ምን አለ?

"…እህሳ…? እናንተ ደግሞ እስቲ ተናገሩ። ጻፉ፣ ተንፍሱ። ዛሬ ቀሲስ ሳሙኤል ቀጠሮ ስላለው ኢትዮ ቤተሰብ ሚድያ አይኖረንም። ሳምንት ጠብቁን። እስከዚያው ድረስ እስኪ እናንተ ደግሞ በርእሰ አንቀጹ ላይ ሓሳባችሁን…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆 ② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ረጅም ዓመት አሜሪካ ቆይተው አቢይ አሕመድ ራሱ ተሳፍሮበት በደው አውሮጵላን ጭኗቸው ሲመለስ ቦሌ አውሮጵላን ማረፊያ አውሮጵላኑ ለረጅም ሰዓት የቆመውና ሕዝቡ ሁላ ደንግጦ የነበረው ሌላ ችግር ተፈጥሮ አልነበረም። ብዙ ሰው በወቅቱ ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ ስለመጡ ለእሳቸው ዊልቸር ምናምን እስኪዘጋጅ ጊዜ ወስዶ ነው ተብሎ ተወርቶም ነበር። ነገር ግን አውሮጵላኑ ያን ያህል ሰዓት የቆመው የዛሬው የአህያ ሥጋ ሰባኪ ብፁዕ አቡነ በርናባስ አባ ወልዴ ትንፋሻቸው አጥራ፣ የልብ ምታቸው ቆሞ፣ ሁሉም ደንግጦ ነበር። ጉድ ፈላብን ብለው የደነገጡትን ቤት ይቁጠረው። ዳንኤል ክብረት በሰባኪነቱ ወራት አባ ወልዴ ደርቢው ስለነበሩ ጎትቶ አምጥቶ አስወገዳቸው ተብሎ ይወራል ተብሎም ተፈርቶ ነበር ይላሉ እዚያው ሮጲላው ውስጥ የነበሩት የዓይን እማኞች። ሰው ከዚያ ከሞት መንገድ በተደጋጋሚ ድኖ፣ ከሞት አምልጦ እንዴት ዘወትር ስለ አህያ ሥጋ ይሰብካል?

"…የብልፅግና ጳጳሳት፣ የብልፅግና መምህራን ሌላ ዓለም ላይ ናቸው። የብልፅግናው አለቃ ወዳጃቸው አቢይ አሕመድ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለመራባችን፣ ላለማደጋችን ተጠያቂ ናት ብሎ በፓርላማ ይከስሳል አቡነ ባርናባስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የአህያ ሥጋ የፈቀደች ይመስል የአህያ ሥጋ አልተከለከለም ብለው ሲያላዝኑ ይውላሉ። የአቡነ ባርናባስ ዘር ጎንደሬው የጎንደር ዐማራው በብልፅግና ወንጌል መንግሥት እየተጨፈጨፈ ነው። እየጸዳ ነው። በሰሜን ጎንደር ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የአርሶአደሩ ከብቶች በራብ ምክንያት አልቀዋል። የጎንደር ሰው በአብዛኛው ተሰዷል። ዘወትር በአቢይ ወታደሮች የሚጨፈጨፈውን ጎንደሬ ቤት ይቁጠረው። አቡነ ባርናባስ ግን ስለዚህ ጭፍጨፋ ትንፍሽ አይሏትም። እሳቸው ተራማጅ በመምሰል በአገዛዙ ዘንድ ክብርና ሞገስን ማግኘት ነው የሚሹት። አቡነ ባርናባስ ይሄ ብቻ ሳይሆን ለኦሮሙማው በደንብ መገረዳቸውን ለማረጋገጥ የኢሬቻ በአል የታንክስ ጊቪንግ የአሜሪካውያኑ በአል የመሰለ በአል ነው በማለት እወደድ ብለው በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምህረት ለዋቃ ጉራቻን እና ለእነ አቴቴ ጊምቢ በድፍረት እውቅና የሰጡ የአጋንንት ምስክር ናቸው። ባይበላስ ቢቀር።

"…የእኔ ምክር አባ ባርናባስዬ ሆዬ። የእኔ የቀድሞ ወዳጅ እባክዎ ከፈለጉ የአህያ ልኳንዳ ይክፈቱ። አህያ አርደውም ይብሉ። የሚያባላዎም ካገኙ አብረው ይብሉ። አያገባንም። እርስዎ ግን  የጵጵስና አስኬማዎን እንዳጠለቁ መልክዎን አሳምረው በየጊዜው ወደ ሚዲያ እየመጡ ቤተ ክርስቲያን የተሳሳተች ይመስል እንደ አያናፉብን፣ አይጩሁብን። መቀደስ፣ መስበኩ ቢቀር አሁን በየጊዜው መጥቶ የዜጎች ወቅታዊ አንገብጋቢ ጭንቀት የውሻ ሥጋ አምሮት ይመስል አይዘላብዱብን። ከምር ይደብራል። መቼም የዘንድሮ ጵጵስና መሳቂያ መሳለቂያ ሆኗል። በቀደም አንዱን ፔኒሲዮን ገብቶ የወጣ ጉደኛ ራሳቸው ጴንጤዎቹ አፍረው በቤታቸው ሴት ይዞ ስላደረ ነውረኛ የላኩልኝን እያየሁ መሳቀቄ ሳያንስ እርስዎ ደግሞ በየጊዜው አማረልኝ ብለው እየተጨመሩ አህያ፣ አህያ እያሉ አይረብሹን። አዛጉን እኮ። ቋቅ ነው ያሉት። በቃ ይጥፉ፣ ይደበቁ። ወይም በግልጽ ማሊያዎትን ቀይረው ይሰለፉ።

"…የእኔ ወቀሳ ይሄ ጉዳይ እጅግ ያሳሰቦት፣ ያስጨነቅዎት፣ ለምን የአህያ ሥጋ አንበላም ብሎ የጨቀጨቆት ሕዝብ ካለ እንዲህ በየዩቲዩቡ እየዞሩ እርሶ የነቁ፣ የገባዎት፣ ሌሎች ያልነቁ፣ ያልገባቸው፣ እርስዎ የበራልዎት፣ ሌሎች የጨለመባቸው፣ ያልበራላቸው አስመስለው መቅረቦት ላይ ነው። እርስዎ የጠነቀቁ ሊቅ፣ ሌላው ግን ደንቆሮ መሃይም አስመስለው መቅረቦትን ነው። የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ከሕዝብ እና ከአህዛብ ወገን የመጡ እንደሆነ ይታወቃል። ሕዝብ የተባሉት እስራኤላውያን ወደ ክርስትናው ሲመጡ በሀዲስ ኪዳን ሁሉ የተፈቀደ መሆኑን ቢያውቁም ሐዋርያት ግን አለመብላታቸውን፣ የኦሪቱን የምግብ ሥርዓት ይዘው በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ማመናቸውን አክብረው፣ አጽድቀውላቸው ነው ያስቀጠሉት። ከአህዛብ ወገን የመጡቱ ደግሞ የአይሁድ ዓይነት የምግብ ሥርዓት ስለሌላቸው እንደ አመጣጣቸው አስተናግደዋቸዋል። "የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።" ሮሜ 7፥3 በማለት አስቀምጠውታል። አይደለም ምግብ ቀንን ማክበር ላይ ለሚነሡ ጥያቄና ክርክሮች "…ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል፤ የሚበላም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለጌታ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም እግዚአብሔርንም ያመሰግናል። ሮሜ 7፥6 በማለት ገልጾታል። ደግሞም የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ሮሜ 7፥17 "በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ንጹሕ ነው፥ በመጠራጠር የተበላ እንደ ሆነ ግን ለዚያ ሰው ክፉ ነው። ሮሜ 7፥20። "…ሥጋን አለመብላት ወይንንም አለመጠጣት ወንድምህም የሚሰናከልበትን አለማድረግ መልካም ነው። ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ለራስህ ይሁንልህ። ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቈጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብፁዕ ነው። ሮሜ 21-22

"…እደግመዋለሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትመጣዋ መጀመሪያ ሕገ ልቦና፣ ከዚያ ሕገ ኦሪትን ተቀብላ የኖረች በሀዲስ ኪዳንም አዲሱን ኪዳን ቀድማ የተቀበለች እንደሆነ ይታወቃል። ኢትዮጵያ በሦስቱ ሕግጋት ያለፈች ናት። መደቧም ከአሕዛብ ወገን አይደለም ከኦሪት አምልኮ ወደ ሀዲስ ኪዳን የአምልኮ ሥርዓት የተሸጋገረች ናት። ለዚህ ነው ከጽድቅና ከኩነኔ ጋር ጋር የማይመደቡ ነገር ግን የኦሪቱን ሥርዓት ይዛ የቀጠለችው። ግዝረት የኦሪት ሕግ ነው። እኛ በሀዲስ ኪዳን ይዘነው ቀጥልናል። ከንጽሕና ጋር እንጂ ከኩነኔና ጽድቅ ጋር ግን የሚያገናኘው ነገር የለም። በዘመነ ብሉይ ሴቶች በወር አበባቸው ጊዜ ከማኅበረሰቡ ተገልለው ይቀመጡ ነበር። እኛ ደግሞ በሀዲስ ኪዳን መገለሉን አስቀርተን ሴቶች በወር አበባቸው ጊዜ ቤተመቅደስ እንዳይገቡ መከልከል ጨምረን አስቀጠልን። ይሄም ከኃጢአተኝነት ጋር ግንኙነት የለውም። ስሙን ራሱ የወር አበባ ነው ብላ ስም ያወጣችለት ቤተ ክርስቲያን። ወንዶችም ሕልመ ሌሊት ቢገጥማቸው፣ ወንዶችም ሴቶችም ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ፣ ኃይለኛ ሳል እንኳ ቢገጥማቸው ወደ ቤተ መቅደስ እንዲገቡ አትፈቅድም። ይሄ ሁሉ ከኃጢአት ጋር የተያያዘ አይደለም። አንዳንዱ ከንጽሕና ጋር ከጠረን ጋር የተያያዘ ሲሆን ሌላው ደግሞ የቅዳሴም ይሁን የማኅሌት አገልግሎት ሥርዓቱን ከማወክ ከድምፅ ብክለት ከመረበሽ ጋር ስለሚያያዝ ነው። ነጭ ሽንኩርት በልተህ እየሸተትክ ባትከለከልስ ቤተ መቅደስ ቀድሞውኑ ምእመናን መሃል እንዴት ትቆማለህ? አፍህን ሳትጉመጠመጥ፣ እየሸተትክ ሚስትና ልጆችህን እንድትስም የምትሳቀቀው ሰውዬ እንዴት ብለህ ነው ምንአባትክስ ሆነህ ነው ጉባኤ መሃል ህዝብ አፍና አፍንጫ ስር የምትቆመው? ይሄ ከጽድቅና ከኩነኔ ጋር የሚመደብ አይደለም። የተበጨቀ፣ የገማ፣ የከረፋ፣ ታጥቦ የማያውቅ ቦቲ ጫማ ውስጥ የከረመ እግርና ካልሲ አድርገህ እንዴት ሌላው በግምባሩ ተደፍቶ የሚሰግድበትን ምንጣፍ ላይ እየተረማመድክ ምንጣፉን ታግማማለህ? ቤተ ክርስቲያን በቀላሉ በውኃ አስወግደህ ጠረንህን አሳምረህ የምትገባበት እንጂ እየተግማማህ፣ ብብትህና እግርህ እየሸተተ የምትቆምበት አይደለም። ሁሉ ንፁሕ ነው ሲባል ግማታችንን አያካትትም። ደግሞም ከጽድቅና ከኩነኔ ጋር የሚያያዝ አይደለም።…👇 ② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዛሬው ርእሰ አንቀጻችን ሌላ ነበር። የተዘጋጀው ሌላ ነበር። ነገር ግን እኚህ መፍቀሬ አህያ፣ መፍቀሬ አሳማ፣ መፍቀሬ ውሻ የሆኑ ሰው በተደጋጋሚ ወደ ሚዲያ እየወጡ የውሻና የአህያ ቄራ እንዲከፈት የሚያበረታቱ አፍቃሬ ብልጽግና የሆኑ ሰው እጠይቅ፣ እሞግት ዘንድ ቀኝ ትከሻዬን ስለሸከከኝ የጭቃ ዥራፌን ይዤ ለመምጣት ተገድጃለሁ። አልበዛም እንዴ? ሆሆይ?

"…ሁሌ አህያ፣ ሁሌ ውሻ፣ ሁልጊዜ የአሳማ፣ የአይጥ፣ የጉርጥ፣ የቅማል፣ የትኋንና የቁንጫ፣ የሙጀሌ ሁላ ብሉ ማለት ምን የሚሉት መለከፍ ነው? እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ ይበላል ብሎ መዘብዘብ ምን የሚሉት ነው?

"…የማያልቀው ቃለ ወንጌል ካለቀቦት መደበቅ፣ መሸሸግ፣ በአርምሞ፣ በጸሎት መቆየት እንጂ ዘወትር ወደ ዩቲዩብ እየመጡ ቃሉን ሳይቀይሩት የአህያ ቄራን ማስተዋወቅ የጤና አይመስልም። ኦርቶድክስን ለማዋረድ የተሰለፉ ጳጳሳት ነፍ እንደሆኑ እናውቃለን። ቤተ ክርስቲያኒቱ በእነዚህ የአህያ ቄራ ፕሮሞተሮች አትዋረድም። ልካቸውን እንዲያውቁ ግን ሊነገራቸው ይገባል። ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል ይል ነበር አጎቴ ሌኒን።

"…ጎንደሬ ዘመዶቻቸው በአቢይ አሕመድ የብልጽግና ሠራዊት የዘር ጭፍጨፋ ይፈጸምባቸዋል እሳቸው ያንን እንደማውገዝ በየጊዜው አማረብኝ፣ ጴንጤዎች የገባው፣ ተራማጅ፣ የጌታ ሰው አለኝ ብለው ክብራቸውን ጥለው በቤተ ክርስቲያኒቱ ማዕረግ እና ስም ተጠቅመው እየመጡ ያቀረሻሉ፣ ያስታውካሉ። የእሳቸውን ትውከት መጥረጉ ራሱ አድካሚ ሥራ ነው የሆነብን። የገሚሱን ኮንዶም በየፔኒሲዮኑ እንለቅማለን የእኚህን የአህያ ሥጋ አፍቃሪ፣ የአሳማ ሥጋ ወዳጅ ትውከት ደግሞ በየዩቱዩቡ ስንጠርግ እንውላለን።

"…ጎንደር ግን ምን ጉድ ነው የፈላባት? የእነ የኔታ ዕዝራ ሀገር እንዲህ አህነት ሃሃሃ፣ ዉዉዉ ወዳጅ አፍርታ ትረፈው?

• ሃ ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ተመስገን ነው ዛሬስ ብዙ ሰው 😡 ብው ለብሎ አልተናደደብኝም። ከዚህ መልእክት በኋላ የሚመጡ እንደተጠበቀ ሆኖ 5 ሰው ግን ያንሳል። መሰለኝ።

"…እስቲ ደግሞ ቀጥሎ የእናንተን ልስማ። የእኔን በርእሰ አንቀጼ ላይ ተንፍሻለሁ። እናንተን ደግሞ እስቲ ልስማ…

• ✍✍✍ … ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…4

"…ዐማራ ማምረሩን አየህልኝ። ይሄ ዛሬ በአጎት ሀገር ጀርመን በፍራንክፈርት ከተማ የሚኖሩ ዐማራውያን በኢትዮጵያ ምድር ላይ ጨካኝ፣ አራጁ፣ ነፍሰ ገዳዩ አረመኔው የኦሮሙማው አገዛዝ ያለ ርህራሄ በጅምላ ሕፃን፣ አረጋዊ፣ ነፍሰጡር ህመምተኛ ሳይል፣ በዓረቦች ቦንብ በድሮንና በጀት ለሚጨፈጭፋቸው ወገኖቹ ድምፁን ለማሰማት ግልብጥ ብሎ የወጣው ሕዝብ ነው።

"…እስከዛሬ ድረስ በፌክ ኢትዮጵያኒስቶች አዚም ተተብትቦ ዐማራ ነኝ እንዳይል፣ ዐማራ ሆኖ እንዳይንቀሳቀስ ተውሎበት የነበረው ዐማራ አሁን አዚሙ እየተራገፈለት ይመስላል። ለኦሮሞ ሞት፣ ለትግሬ በኤርትራ ወረራ፣ በአጠቃላይ ዘር ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይመርጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ችግር ሲደርስ ግልብጥ ብሎ ድምጹን ሲያሰማ የነበረው ዐማራ ለእሱ ጊዜ ሲሆን ሌሎች ቢደበቁም እሱ እንኳን ለራሱ ለሌሎችም ሲተርፍ ነበር እና ይኸው ብቻውን ዐማራ ነኝ ብሎ ግልብጥ ብሎ መውጣት ጀምሯል። ይሄ ስኬት ጅማሮ ነው።

"…ያልነቃው ገተት ዐማራ ሲነቃ፣ ልክ እንደ ትግሬ፣ እንደ ኦሮሞ፣ ልክ እንደ ኦሮሞና እና እንደ ደቡብ ጴንጤ፣ ልክ እንደ ኦሮሞ ወሃቢያ በቃል ኪዳን፣ በዓላማ ጨከን፣ ቆረጥ፣ ኮምጨጭ ብሎ ሲነሣ አስቡት።

"…ዐማራ በዚህ መልክ ከተነሣ በቀጣይ ሾተላይ ዶላር ዩሮ የማያሳድድ፣ ከርሳም ለትውልዱ ለነገዱ የሚያስብ፣ 7 ወደላይ፣ 7 ወደ ጎን ተቆጥሮ ዐማራ የሆነ ድርጅት ያስፈልጋል። ልክ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ለነገዱ ታማኝ የሆነ ድርጅትም ያስፈልገዋል።

• ብራቮ ዐማራ…!

• ተቀበል። ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ስዊድን፣ እንግሊዝ፣ ኖርዌይ፣ ሆላንድ፣ ወዘተ ያለህ ዐማራም አትሽኮርመም። እንደ ጀርመን ዐማራ ግልብጥ ብለህ ውጣ።

• እየኮመታችሁ…!


በዝህን ስዓት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…2

"…የቅዳሜ ከሰዓት ተቀበል መርሀ ግብራችን እንደቀጠለ ነው። አድማጭ ተመልካቾቻችንም ከያሉበት ሆነው ተዋዱጁን የተቀበል የግጥም መርሀ ግብራችንን እየተከታተሉ መሆናቸውን በሚያደርሱን የፎቶና የቪድዮ መረጃ እያሳወቁን ነው።

• ተቀበል… እየገጠማችሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የቅዳሜ ከሰዓት በኋላው የተቀበል መርሀ ግብራችን አሁን በይፋ ጀምሯል። እንደተለመደው ለአዝማሪው ለባለመሰንቆው ግጥም በመስጠት መርሀ ግብራችንን እንጀምራለን።

"…ከእናንተ የተመረጠ ግጥም በመለጠፍ መርሀ ግብራችንን እንጀምራለን።

• ተቀበል…

• ግጥም ስጡት…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የመርሀ ግብር ማስታወቂያ

• እንደ ተለብዥን ብሮግራም በጽሑፍ ብቻ ተወዳጅ እየሆነ የመጣው የእኔ የዘመዴ የቴሌግራም ቤጅ…😁 በነገው ዕለት ስለሚኖረው መርሀ ግብር ከወዲሁ ለአድማጭ፣ አንባቢ ተመልካቾቹ ያስታውቃል።

"…በቅድሚያ በእግዚአብሔር ሰላምታ ቀናችንን በምስጋና እንጀምራለን። 1ሺ ሰው ፈጥኖ "እግዚአብሔር ይመስገን" በማለት ተረባርቦ፣ ተሻምቶ ካመሰገነ በኋላ በቀጥታ ወደ አጫጭር መረጃዎች ወደማድረስ እንገባለን።

• በአንድ በእኔ በሀረርጌው መራታ በዘመዴ ጣቶች ተሰንዶ እንደ ግዙፍ ተቋም፣ ብዙ ሺ ሠራተኛ እንዳለው ጣቢያ በግሩም ሁኔታ ተዘጋጅቶ ወደ እናንተ የሚቀርበው ሳምንታዊው የቅዳሜ ከሰዓት የተወዳጁና የተናፋቂው "የተቀበል" የግጥም፣ የቅኔ መርሀ ግብራችንም ተሰናድቶ ወደ እናንተ ይቀርባል። ከወዲሁ እናንተም ግጥም፣ ቅኔያችሁን ጽፋችሁ ታዘጋጁ ዘንድ ትበረታታላችሁ። አልችልም አይባልም።

• በነገው መርሀ ግብራችን ሙግቶች፣ ክርክሮች፣ ውይይቶችም ይኖራሉ። ብቁ ሆነው የተገኙ ካሉና ለአቅመ ነቆራ የደረሱ ካሉም እንደተለመደው ያው 😡 የሚያደርግ የሚያስነቅል "ነቆራም" ይኖረናል። ጥያቄዎችንም በስፋት እንጠይቃልን።

• የነገ ሰው ይበለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የእኔ ርእሰ አንቀጽ ተነብቧል። ቀጥሎ ደግሞ የእናንተ ተራ ነው። የጥቂት ሰዎችን አስተያየት እናነብና በቀጣይ ጊዜ ካለን ከጎንደር ዕዝ ፋኖዎች ከእነ ሀብቴ ግሩፕ የደረሰኝ ለሕዝብ ሁሉ አድርስልን የሚል መልእክት አስደምጣችኋለሁ።

"…አሁንም ጊዜ ካለን ዶር አምሳሉን፣ ወ/ሮ ሕይወትን፣ አቶ ሙልጌታንና አቶ ኤርሚያስን፣ እንዲሁም ኤርሚያስ ለገሰን፣ ወዳጄ መስፍን አማንና የእስክንድር ነጋ ባለቤት ወሮ ሰርካለም ፋሲል በኮሚቴነት የመሩትና ከሕዝብ የተሰበሰበ በመቶቪዎቸ የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደደረሰ መጠየቄን እቀጥላለሁ።

"…አበበ በለው ለምን የእስክንድር ሚስት ስም በገንዘብ ጉዳይ ስሟ ይነሣል ብሎ ለወቀሰኝ ወቀሳም ለምን እንደምጠይቅ የቪድዮ መረጃ ጭምር ይዤ እሞግታለሁ።

"…አንድ 50 ያህል ሰው በርእሰ አንቀጹ ላይ አስተያየቱን ከሰጠ በኋላ ምሽታችንን በጦፈ ክርክር፣ ሙግት እና ውይይት ደመቅ አድርገን እናሳልፋለን።

• ✍✍✍ ጀምረ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …አይደለችም ነበር ያሉኝ። አያሌው ግን ነፍስህ አይማርም። ብቻ የጎንደር ጉዳይ ሳይወድ በግዱ እየጠራ ነው። በቅርቡም ተአምር ትሰማላችሁ። ዛሬ ማታም ከጎንደር ፋኖ የደረሰኝን አንድ ግሩም ቪድዮ እለቅላችኋለሁ። ከእስክንድር ነጋም ጋር በይፋ ይለያያሉ። የፓስተር ምስጋናው ፋፍዴንም ይከስማል። እነ ሀብቴና ባዬም ይታረቃሉ። ጎንደርም እንደ ጎጃም አንድ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ጎንደርን እነ እስክስ አበበ በለው አያዙትም። እጃቸውን ሳይታጠቡ ገብተው አይፈተፍቱበትም። አስሬ ለክቶ አንዴ የሚቆርጥ የጎንደር ዐማራ ተፈጥሯል። ወልቃይት አትገባም የተባለው የጎንደር ዐማራ ፋኖ መግለጫ ማውጣትም። ወልቃይት ገብቶ ማስተንፈስም ጀምሯል። አለቀ። እነ ምስጋናው ቢቃወሙትም እነ ሀብቴ በወልቃይት ጉዳይ መግለጫ ማውጣት ጀምረዋል።

"…እንደ ሁላችንም በእስክንድር ነጋ የአየር ላይ የስም ግንባታ የተሸወዱም ዐማሮች አሉ። እኔን ራሱ አንድ ወቅት ትዊተር ስፔስ ላይ ጋብዘውኝ የነበሩ ቅኖችን ዐውቃለሁ። ያኔ ቀርቦ ያወራኝ በጣም የማከብረው የሲያትሉ ወንድሜ መታገስ ነበር። እስከ አሁን ምንም ያልተቀየረ፣ የትም ቦታ በክፉ የማያነሣኝ፣ ባዘዘኝ ቁጥር ስታዘዘው የኖርኩት መታገስ ነበር የጋበዘኝ። እነ ሲሳይ ሙሉ ዋኘውም ቢሆን የሚጠሉኝ በጥቂት ነገር ነው። ሀብታሙ በቀለ ኦነግ እናቱን የገደለበት የሀረርጌ ዐማራ ነው። እነ አኪላ ናቸው ሰው ብሎ ተጠግቷቸው ከእነርሱ ጋር መሥራትም ጀምሮ ተንኮላቸው ኋላ ላይ ሲገለጥለት ስለተለያቸው "የአያቱን ስም ጉደታ" ብለው ኦሮሞ ነው ብለው ስሙን ያጠፉት እንጂ ክፋት የሌለው ሰው ነው የሚሉም አሉ። አይ እሱማ ኦነግ ነው የሚሉም አሉ። ሰውየው በሙያውም የተከበረ፣ እንደ ሌላው ቀፋይ ከትግሉ ሳንቲም ሊለቅም ያልመጣ፣ ቦይንግ ካምፓኒ የሚሠራ ዘጭ ያለ ገቢ ያለው ነው የሚሉት የሚያውቁት። ከፈለጋችሁ ስልኩን ለጥፌላችሁ ደውላችሁ ልታረጋግጡ ትችላላችሁ።

"…ሀብታሙ እኔን መስደብ፣ መጥላት የጀመረውም በእስክንድር ስለመጣሁበት እንጂ ምንም ምክንያት የለውም እኔን ለመጥላት። ኃይሌም ተራማጅ ጎንደሬ ነው። የጎንደር ዐማራ። እኔን አምርሮ ቢጠላኝም እነ ምስጋናውን በሚጠላበት የጥላቻ መጠን ግን እኔን አይጠላኝም። ሚዛናዊም ነው። ለጎንደር ብቻ ሳይሆን ለመላው ዐማራም ነው የሚሠራው። ለዚህ ደግሞ ከምርልጅ ተድላ ራሱ ምስክር ነው። እነ ምስጋናውን አምሮሮ ነው የሚጠላቸው። እነሱ በግምባሩ ምስረታ ወቅት ለእስክንድር ደም ሰጥተው ሲሟገቱ እነ ምስጋናው የሉም ነበር። ከሃዲው እስክንድር የለፉለትን እነ ሲሳይን፣ ሀብታሙን ትቶ በዶር አምሳሉ አስናቀ በኩል ፓስተር ምስጋናውን በላያቸው ላይ አምጥቶ በመሾም ነው ያሳበዳቸው። እነ ሲሳይ እና መታገስ እስከ አሁን ተስፋ አልቆረጡም። ከፓስተር ምስጋናው ጋር ቢጣሉም ድርጅቱንም ይደግፋሉ። የሐረርጌው መራታ ብላዘሬ ሀብታሙ በቀለ እንዲያውም ሰሞኑን እስክንድር ነጋን በግልጽ መተቸት ጀምሯል። ብራቮ የሀገሬ ልጅ። በርታ።

"…እስክንድር እንደ ቆንጆ ሴት ፉንጋ አስከትሎ በመሄድ ቆንጆ መምሰል፣ ደደብ ማይም ይዞ እየዞረ ሊቅ መስሎ መታየት ስለሚፈልግ እንጂ እነ ዲሲ ግብረ ኃይልን፣ እነ ሕይወት፣ ኤርሚያስን ይዞ የተንገታገተው በዚያ መንገድ ሄዶ ከሚሾቅ እነዚህ ፊደል የቆጠሩትን ቢቀርብ ኖሮ ባይተርፍም በጊዜ ሳይነጋ ፖለቲካዊ ሞት አይሞትም ነበር ብዬ እላለሁ። ሀብታሙ አያሌው ቀፋይ ነው። በብታሙ በቀለ ሲያትል ነው የሚኖረው ለቦይንግ ነው የሚሠራው። ቢሠጥ ቢለግስ አንጂ የተለገሰ አይነካም ብዬም አምናለሁ። ሲሳይ ኢፒዲሞሎጅስት ነው እሱም ሲያትል ነው የሚኖረው። አሁን ቴዲ ሀዋሳ ቤት ገብቶ ከነ በቀለ ወያ ከማይሞቹ ጋር ወርዶ ሲታይ የኡበር ሹፌር ነው የሚመስለው። ምንም ቢጠሉኝ አክብሮቴ ግን እንዳለ ነው። መታገስ ሆይ መልእክቱን አድርስልኝ። በጊዜ ቢነቁ ይፈወሳሉ። አለበለዚያ እነሱም አብረው ይከስማሉ።

"…እንዲህና እንዲያ እያለ የዐማራው ትግል ተንጦ፣ ተንጦ እንደ ቅቤ አናት ላይ መውጣቱ እንደሁ አይቀርም። የአየር ላይ ወሬኞችም መስመር መያዛቸው አይቀርም። የምድር ላይ ከፋፋዮችም መሸነፋቸው አይቀርም። የሰለቸውም ወደ አገዛዙ በእርቅ ስም መግባቱ አይቀርም። የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችም ለምዳቸው ቀስበቀስ መገፈፉ አይቀርም። ቀስበቀስ በዐማራ ጫንቃ ላይ የተጣበቁ አልቅቶችም መራገፋቸው አይቀርም። ይንጠባጠቧታል ስልህ። ዛሬ እኮ የኦሮሞ አክቲቪስቶችና የትግሬ አክቲቪስቶችን ገፅ ብትመለከቱ ታሪክ ተቀይሯል። ትግሬ እንደውም ፋኖን መደገፍ ጀምሯል። ኦሮሞም አፍሮ ነው እንጂ "ፋኖ ጋቸነ ቢያ" ብሎ ቢዘፍን አይጠላም። አዎ ጉልበት ያስከብርህሃል። ፋኖም ዐማራን ማስከበር ጀምሯል። ይሄ ለእኔ ትልቅ ለውጥ ነው። በተለይ አሁን አገዛዙ አንዲት ነፍሰጡር ከመግደል፣ የአንድ ደሀ ገበሬ በሬና ቤት ለመግደል የአንድ ሚልዮን ዶላር ቦንብ ሲጠቀምና ሲከስር እንደማየት የሚደንቅ ነገር የለም።

“…እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።” ዕብ 9፥22። ነፃነት በነፃ፣ በብላሽ አይገኝም። ነፃነት የሚገኘው በላብ፣ በጨቀየ ደም፣ በአሰቃቂ መስዋእትነት ጭምር ነው የሚገኘው። መጀመሪያ ይሄ ይታወቅ። ደም መፍሰሱ ደም ስለሚያፈላም ለዐማራ ትግል ቆስቋሽ ቤንዚን ነው። አገዛዙ ንፁሐንን በጨፈጨፈ ቁጥር ቂም የሚቋጥረው ለትግሉም ነዳጅ የሚሆው ይበዛል። ዐማራም የዚያኑ ያህል ጀት ሆኖ ስለሚነሣ እጅጉን ይጠቅመዋል። አያስለቅስም። ዓለም የዚህን አረመኔ ገበናም እያየ ለፍርድ ስለሚያመቸው፣ በውጭ የተኛውንም የዐማራ ዳያስጶራ ስለሚያነቃው፣ እንደ በቀደሙ እንደ ዲሲው፣ እንደ ፍራንክፈርቱ፣ እንደ ትናንቱ እንደ ሲያትሉ ዐማራውን አንድ ላይ ስለሚያቆመው ለዐማራ ትግል ጥሩ ነው። ዛሬ በዐማራ ክልል ኦሮሙማው በድሮን የሚያፈርሳቸው ትምህርት ቤቶች ነገ ሌላ ቦታ አይፈርሱም ሟቾችም አይገድሉም ማለት አይደለም። በቀለኛ ትውልድ ነው እየተፈጠረ ያለው። በተለይ ተሸንፎ የሚሮጠው የኦሮሞ ጽንፈኛ ጴንጤና የወሃቢያ እስላም ወታደር እና የደቡብ ጴንጤ ወታደር ወንድ የተባለ ዐማራ መጨፍጨፉ የሌለ በቀል፣ የሌለ እልቂትም ፈጣሪ ነገር ነውና እነ ብራኑ ጁላ፣ እነ ብራኑ በቀለ በጊዜ ቢየስቡበት መልካም ነው። 👇 ③ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…የህወሓት ጀነራል የነበረው ሓየሎም ዓርአያ የተባለው የተናገራት መልእክት ናት ተብላ የምትነገር ዝነኛ አባባል አለች። "ወደ ሕዝብ መተኮስ የጀመርክ ዕለት ውድቀትህ ይጀምራል። እኔም "አባባሏን እገዛታለሁ" ግሩም አባባል ናት። አንድ በሕዝብ የተመረጥኩ መንግሥት ነኝ የሚል አካል ወደሚያስተዳድረው ሕዝብ አፈሙዝ አዙሮ መተኮስ፣ በድሮንና በጀት ቦንብ ሕዝብ መፍጀት ሲጀምር የጊዜ ጉዳይ እንጂ መውደቁን እንዳረጋገጠ ነው የሚያሳያው። ይሄ ተፈትኖ የተረጋገጠ እውነት ነው። ንፅት፣ ጽድት ያለ እውነት። ያውም ጥሬ ሃቅ። በዚህ መንገድ የተጓዙ አምባገነን መሪዎች የቆዩትን ጊዜ ያህል ሁሉ በተለያየ ዘዴ በሥልጣን ላይ ይቆዩ እንጂ የሆነ ቀን ከመኝታችን ስንነሣ ታሪካቸው ተቀይሮ እንደ ጋዳፊ ቱቦ ውስጥ፣ እንደ ሳዳም ሁሴን የአይጥ ጉድጓድ ውስጥ ተጥለው እናገኛቸዋለን። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው። ቀኑ ሲደርስ ኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ፣ የቶፕ ቪው ቀረጻ፣ የፋና ዶክመንተሪ፣ የዳንኤል ተረታ ተረት፣ ኮሪደር ልማት፣ መናፈሻና ሪዞልት አያድንህም።

"…ከትግራይ መልስ የኦሮሙማው አገዛዝ በቀጥታ ያመራው በጎጃም በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ ከዐማራ ሕዝብና ከዐማራ ሠራዊቱ ፋኖ ጋር ነው ጦርነት የገጠመው። የዐማራ ክልሉ ጦርነት ለአገዛዙ ልክ እንደ ትግራዩ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያን ሕዝብ በውጭም፣ በሀገር ውስጥም አስተባብሮ አንድ ላይ ማዝመት አልቻለም። ኤርትራንና የሱማሌ ወታደሮችንም መጋበዝ አልተቻለም። የዐማራ ክልሉ ጦርነት በፍጹም ለኦሮሙማው ፕሮፓጋንዳ የሚመች አልሆነም። ልፕሮፕገንድ ቢል እንኳ የሚሰማ የለም። አይኖርምም። እንዲያውም በተቃራኒው የዐማራ ፋኖን ይንቅ፣ ያጣጥል የነበረው ሌላው ሕዝብ ሁላ አሁን አሁን የኦሮሙማው ዱላና በትር በአንድም በሌላም መልኩ ጀርባው ላይ ማረፍ ሲበረታበት፣ ኦሮሙማው እየዠለጠው ደም እንባ ሲያስለቅሰው "የፋኖን መምጫ ቀን እንደ ምጽአተ ክርስቶስ መናፈቅ ጀምሯል።" አዎ የዐማራ ክልሉን ጦርነት ሕዝብን አስተባብሮ፣ ሰንጋ አርዶ እና በሶ አስቋጥሮ፣ ወኔ ቀስቃሽ ክሊፕ እያሠራ በስሜት ወደ ዐማራ ክልል ጦርነት በገፍ የሚልከው ሰው የለም። ዳያስጶራውም እንኳ እንደ ትግሬ ጦርነቱ ጊዜ "ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን ነን" እያለ ደረቱ ላይ እጁን ለጥፎ በእንባ ፍቅሩን እየገለጸ፣ ገንዘቡን እያዋጣ፣ በነጮቹ ጎዳና ላይ ከኤርትራውያን ጋር ፍቅር በፍቅር ሆኖ የድጋፍ ሰልፍ ለብልፅግና የሚያደርግ አንድም ሰው የለም። አንድም አልኳችሁ።

"…አቢይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት በአማርኛ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ የሚያደነቁረን፣ ኦሮሞ በተሰበሰበበት ስፍራ ሁሉ ደግሞ ራሱ አቢይ አሕመድ በተገኘበት ሁሉ ንግግር ሲያደርግ "ኦሮሞ ከ150 ዓመት የነፍጠኛ ቅኝ ግዛት ነጻ መውጣቱን" ሳይሳቀቅ፣ ሳይፈራ፣ ሳያፍር ነው የሚሰብከው። በአዲስ አበባ ኦሮሞ ጠል ሕዝብ አለ ብሎ ሳይሳቀቅ ንግግሩ አቶሚክ ቦንብ መሆንን የማያውቅ ማይም ነው እኮ አሁን ያለው መንግሥት ተብዬ። በአማርኛ የኢትዮጵያ፣ በኦሮምኛ ግን የኦሮሞ መንግሥት መሆኑን በድፍረት የሚናገር ዘረኛ እኮ ነው። መንግሥታችን ተነካ ብለው ከሰንዳፋ፣ ከቡራዩ፣ ከሱሉልታ እየጎረፉ የነበሩ ኦሮሞዎችን በጥበብ አስቆምኩ ብሎ በገደምዳሜ እኔ ብነካ በአንድ ጀንበር መቶ ሺዎች እረዱ ብሎ ጥሪ የሚያስተላልፍ፣ በአደባባይ ያውም በፓርላማ የሚናገር አገዛዝ እኮ ነው ሀገር እየመራ ያለው። ማንም አያቆመንም፣ የ150 ዓመት የደም ውጤታችን ነው። አራት ኪሎ ሲያምርህ ይቀራል። ወዘተ እያሉ ክሊፕ የሚለቁለት ደጋፊዎች ፈትቶ የለቀቀ አገዛዝ እኮ ነው።

"…ወደ ዐማራ ክልል ዘማች ያጣው ዳግማዊ ደርጉ የኦሮሙማው አገዛዝ እንደ አባቱ እንደ ደርግ አፈሳ ጀምሯል። ከሚደርሱኝ የትየለሌ መረጃዎች መካከል አሁን አሁን የሚበዙቱ ልጄ ታፈሰ፣ አፈሱት ልጄን የሚል ነው። ዕድሜው 15 ነው፣ የ8 ተኛ ክፍል ተማሪ ነው። ትንሽ ልጅ ነው ብንልም ሰሚ አጥተናል ነው የሚሉት ወላጆች። እንዲያውም አፋሾቹ አዲስ ቢዝነስ መጀመራቸው ነው የሚነገረው። ድሮ ድሮ በሊቢያና በየመን፣ በኦሮሚያም ሸኔ ነበር እያገተ ይሄን ያህል ብር ክፈሉ ይል የነበረው። አሁን ደግሞ ሚሊሻና ፖሊስ የተመደበበትን ኮታ ለማሟላት ሲል በጅምላ ያፍስና በታፈሱት ልጆች ላይ የማስለቀቂያ ብር ይመድባል። እንደ ቤተሰቡ የገቢ መጠን ከፍተኛው እስከ መቶ ሺ፣ ዝቅተኛው 25 ሺ መመደቡ ነው የሚነገረው። መክፈል የቻለ ይለቀቃል። መክፈል ያልቻለ ወደ ጦላይ ይላካል። በዚህ መንገድ ደርግም ሞክሮ አላሸነፈም።

"…የአሁኑን ለየት የሚያደርገው የአቢይ አሕመድን አገዛዝ መንግሥቴ ነው የሚሉ ባለ ድርሻ አካላት መብዛታቸው ነው። ከእነዚህ ባለ ድርሻ አካላት መካከል በዋነኝነት የኦሮሞ የወሀቢይ እስላም፣ የኦሮሞ ጽንፈኛ ጴንጤ እና ዋቄፈናዎች ዋነኛ መሪና መንግሥታችን ነው ብለው እሱ ከወደቀ ያልቅልናል በማለት የሚዋደቁቱ መሆናቸው ነው። አገዛዙ ቢሮክራሲውንም የሞላው በእነዚህ አካላት ነው። እነርሱ ሳይዘምቱ ነገር ግን ደግሞ እንደ ገረድ የሰበሰቧቸውን የደቡብና የዐማራ ታዛዦቻቸውን ይዘው መንግሥታቸው እንዳይወድቅ ይጋጋጣሉ። የጴንጤ ፓስተሮች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጴንጤ ምእመናኖቻቸው አገዛዙን መጠበቅ፣ ከአገዛዙ ተፋላሚ ፋኖዎች ጋር የብልፅግና ወታደር በመሆን መጋደል፣ መዝመት፣ መሞት እንዳለባቸው፣ ለዚህም "ጌታቸው በራእይ፣ እግዜራቸው በሕልም፣ መንፈሱ ደግሞ ተገናኝቶ እንደነገራቸው በመግለጽ የደቡብ ጴንጤንም በመስበክ ወደ ዐማራ ክልል ይሄን ምስኪን የደቡብ ጴንጤ እና ሙስሊም ወደ ሞት እየነዱት ይገኛሉ። ነፍስ ይማር።

"…እኔ በበኩሌ የቀን ጉዳይ እንጂ የዐማራ ክልሉ ጦርነት አሁን አሁን አያሰጋኝም። እንኳን አሁንና ድሮ ድሮ ከዓመት በፊት ባዶ እጁን በብላሽ በግሬደር ይቀበር የነበረ የዐማራ ሕዝብ እኮ ነው አሁን በባዶ ሜዳ በብላሽማ አልወድቅም። አልሞትምም በማለት ከአረመኔው አገዛዝ ጋር የገጠመው። እኔ በበኩሌ እመኝ፣ እንዲሆን እፈልግ የነበረው ነገር ነው የሆነልኝ። ስለቴ ነው የሰመረው። በሰለጠነ መልኩ በሰላማዊ ሰልፍ፣ በአቤቱታ፣ ፍረዱልን፣ አትግደሉን፣ የመዘዋወር፣ የመማር፣ የመሥራት መብታችን ይከበርልን ብለው የጠየቁ ዐማሮች የማንም ሥርዓተ ቢስ መሳቂያ፣ ማሾፊያ ከመሆን አልፈው በአንድ ቀን 3ሺ አራት ሺ ዐማሮች ጨፍጭፈው "ለአስከሬናቸው ጥላ ይሆን ዘንድ ችግኝ እንተክልላቸዋለን" ብለው ሲያሾፉ የበገንኩትን ያህል አሁን ቢያንስ ጥሎ መውደቅ መጀመሩን በማየቴ ፈጣሪዬን አመስግኛለሁ። እንደ ትግሬ ነፃ አውጪ በትእቢት፣ በጉራ፣ በፉከራ፣ በማቅራራት፣ ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ እያለ በመፎግላት ሳይሆን፣ ይሄን የአረነኔውን የኦሮሙማውን ዕብደት ሊያስቆም የሚችለው ከዐማራው በቀር ሌላ ኃይል በዚያች ምድር እንደሌለ ቀኝ ትከሻዬን ይሸክከኝ ስለነበር ለዚያ ነበር እንቅልፍ አጥቼ፣ 24/7 ዐማራ፣ ተነሥ፣ ተሰባሰብ፣ ታጠቅ፣ ተዘጋጅተህ ተቀመጥ እያልኩ እንደ ዕብድ አቅሉን እንደሳተ ሰው ዋይዋይ እል የነበረው። አሁን ተሳክቷል። የተጀመረም ነገር መጠናቀቁ አይቀርም።

"…በወቅቱ የዐማራ ጴንጤዎች፣ የዐማራ የወሃቢ እስላሞች፣ የጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች፣ በጎጃም ከሃዲዎቹ የፖለቲካው አገው ሸንጎዎች፣ በወሎም፣ በሸዋም ነፈዝ ጎጋ የበድኑ ብአዴን ገረዶች እንደ ጉድ ነበር የሚጮሁብኝ። የሚሰድቡኝ። በጎጃሜ ነን ባዮቹ በንቅሴው ሞጣ ቀራንዮ እና በስፐርም በፖስታ ላክልኝ ወሮ ትእግስት ብሪጅ ስቶን በኩል እንደ ጉድ ይወርዱብኝ ነበር። ትግሬዎቹ …👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ኢየሱስም መልሶ፡— ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል፡ አላቸው። ዮሐ ፥ 11፥ 9-10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በመጨረሻም…!

"…ወዲህ ወዲያ እያልኩ ስዋከብ አንድ ታላቅ በአል አምልጦኝ ስናደድ ነው የዋልኩት። በአሉ ትናንት ነበር። ለወትሮው ፌስቡኩ፣ ቲክቶኩም ይቀውጠው ስለነበር ትዝ ይለኝ ነበር። ዘንድሮ ግን እንዲሁ ላይሞላ ነገር ስንጦሎጦል ረሳሁት። ከመቅረት መዘግየትም ይሻላል እንዲሉ አበው እና እመው እኔም ብዘገይም አሁን ሳስታውሰው ብቅ ብያለሁ።

"…በቀደም ዕለት "የታላቁ" እስክንድር ነጋ የዲሲ ሚኒሻዎች ሞቅ ደመቅ አድርገው ቁጥሩ ያልተጠቀሰውን የእስኬውን ልደት ሊያከብሩ እየተዘጋጁ ሳለ እኔ ቀዥቃዣም አይደለሁ? ያ አበበ አስክስ በነገር ጎንተል አድርጎኝ የእስክንድር ሚስት ከባሏ ጋር የሰበሰበችውን ዶላር የት እንዳደረሰችው ቀርባ ታስረዳ ስላልኩ ሲጮህብኝ ለምን ትጮህብኛለህ እያልኩ ከአቤ ጋር አንድ ሁለት ስንባባል ለካንስ የዲሲ ሚኒሻዎች ኬክ አዘጋጅተው ተዘጋጅተው ሳለ በእኔ ነቆራ ምክንያት ደንግጠው ሴቶቹ እየረገሙኝ ትተውት ነበር።

"…ኋላ ላይ ይሄማ ጥሩ አይደለም ብዬ፣ የኬክ መግዣ ለምኜላቸው፣ የሆነች ትንሽዬ ኬክ ይዘው ወደ ቀድሞው ኢትዮ 360 የአሁኑ የምኒሊክና የጣና ቲቪ ስቱዲዮ ሄደው የእስኬውን ልድት አክብረዋል። ሀብትሽና ብሩኬም 60 ሺ ዶላራቸውን እያስታወሱ ለ7 ደቂቃ ያህል እስኬውን ዘክረውት አምሽተዋል። በእውነት ገንዘብ ያዥዋ ሕይወት፣ ሽመልስ ጠሽ፣ ዱኒዬ፣ ኤርሚ ዲሲ ግብረ ኃይል ክር ይገባችኋል። የእስኬው ሚስት ሰርኬም "ፋኖ እስክንድር ነጋ" ብላ በቀየረችው የፌስቡክ ገጿ የባለቤቷን ፎቶ ለጥፋ እንኳን ተወለድክ ብላዋለች። ጎበዝ።

"…እነ ዘመነ፣ሀብቴ፣ ምሬ፣ ደሳለኝ፣ ባዬ፣ ሳሚ ቅር አይበላችሁ። የሆነ ቀን ይከበርላችኋል። እኔስ እሺ ስዋከብ ነው የታላቁን ልደት የረሳሁት። እናንተ ግን ምን ሆነን ነው የረሳነው ልትሉ ነው?

• የእነ ብሩኬ ድምጽ ግን ምነው ድክም ብሎ ሰለለብኝሳ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ሙን ኡኖው ኖ…?

"…በመጨረሻም… ርካሽ እና የማይረባቸውን አይረቤ የጴንጤዎችን ድጋፍ፣ መወድስ፣ አጉል መወደድ እና ሙገሳ ለማግኘት ሲሉ አስር ጊዜ ወደ ዩቲዩበሮች ዘንድ በመሄድ "አዲስ ኢየሱስ እና፣ አዲስ ጌታ ለማስተዋወቅ የሚዳክሩት እንዲሁም የአህያ ሥጋ፣ የውሻ ሥጋ ይበላል። አይጥና ጉርጥ፣ ቅጫምና ቅማል፣ ትኋንም ይበላል፣ በማለት ለአህያ ቄራ ሙግት የገጠሙትና እኛ ርኩስ ነው ያልን ይመስል አስሬ ባገኙት መድረክ ሁሉ "እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ቅዱስ ነው" እያሉ ለወላዷ ማኅጸነ ለምለም ለእምዬ ተዋሕዶ ምጥ ካላስተማርኩ ሞቼ እገኛለሁ በማለት ዋይ ዋይ የሚሉትየትናንቱን የአባ ወልደ ተንሣኤ አያልነህ ወይም የአሁኑን የብፁዕ አቡነ ባርናባስን የአህያ ሥጋ ብሉ ቃለመጠይቅ የነበረበት የእግረኛው ሚዲያ ላይ የነበረው ልጥፍ ለጊዜው ተነሥቷል። ወይም ፕራይቬት ሆኗል። በብዙ ጴንጤዎች የአድናቆት የድጋፍ ኮመንት ተሞልቶ የነበረው የጳጳሱ ቪድዮ ለጊዜው አሁን እንዳይገለጥ ተሸፍኗል። ለብፁዕ አቡኑ "ውሻ፣ አህያ ይበላ" ባዩም ምን እንደሚሰማቸው ባይታወቅም እነ መኔ ግን "ኦርቶዶክስ ድሮም እውነት ሲነገር አትወድም፣ ወልዴ ጌታ ይባርክህ፣ ሃሌ ሉያ እያሉ ሳይጸልዩላቸው አይቀርም። ክፈት አንተ ዩቲዩብ፣ ሻላላበላላ አሜን ነው?

"…ይልቅ ሳሚ ቅማንቴው ዶፍተር ምስጋናውን ሌባ ያለበትን ቆይቼ እለጥፍላችኋለሁ። ጠብቁኝ። የአህያ ሥጋን እርሱት። 😂😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጥያቄ ነው…

"…የአህያ ሥጋውን ሰባኪ ስኳድ ሰበካ ለጊዜው ኢግኖር እንግጨውና ወደ አየር ላይ ስኳዱ ነቆራዬ ብመለስ ምን ይመስላችኋል? …ስሜን ያነሱበት ቪድዮ ስለደረሰኝ ለተነሣው ስሜ ወጋ ወጋ ጠቅ ጠቅ ባደርጋቸውስ ምን ትመክሩኛላችሁ…?

• ጥያቄ አስተያየታቸውን አስቀድሜ በዙያው መልስ ልስጥ ወይስ ምንትላላችሁ…? እስኳድን፣ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን ፀረ ጎንደር ዐማራውን ትንሽ ባንጫጫውስ…? 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ይሄም ቢሆን እንኳ ቤተ ክርስቲያኒቱ ስንዱ ቤተ ክርስቲያን ናት። አከራካሪ ጉዳዮች እንኳ ቢኖሩ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ይወሰንና ይፋ ይሆናል እንጂ እንደ አቡነ ባርናባስ ሁል ጊዜ ወደ ዩቲዩብ እየሮጡ የአህያ ቄራ ባለቤቶችን ለማስደሰት ሲባል አጀንዳ መፍጠር ትክክል አይደለም። ከባዱን አጀንዳ ሰው የተባለ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እየፈረሰ፣ ዘር እየተጨፈጨፈ ያለበትን የእልቂት አጀንዳ፣ ሰው ከቀዬው ተፈናቅሎ መከራ የሚያይበትን ጉዳይ ለማስቀየስ ወቅት ጠብቆ፣ በየጊዜው እንሽላሊት፣ ጉርጥ፣ አህያ ይበላል አይበላም ብሎ አጀንዳ ማስቀየሪያ የሚሆን አጀንዳ ይዞ መምጣት ትክክል አይደለም። ለምሳሌ በእስልምና አህያ የተፈቀደ ነው። ጅብም ሌላም የተፈቀደ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ብሉ ተብሎ ቢፈቀድም አይበሉትም። ለምን የተባለ እንደሆን ባህል የሚባል ተጽእኖ ፈጣሪ አለና ነው። የተፈቀደለትን ላለመብላት እንኳ ባህሉ ተጽዕኖ ይፈጣራል።

"…አሁን አባ ባርናባስን እንዲህ አያድርጉ፣ ሥርዓት ይዘው በቤተ ክርስቲያኒቱ የቀኖና መስመር ሆነው ሕጉን ጠብቀው ያገልግሉ። ይሄንኑ ጥያቄ ዩቲዩበር ዘንድ ሄደው ውክቢያ የሆነ አጀንዳ ከሚፈጥሩ በራሷ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሚዲያ ላይ ሓላፊነት ወስደው ይሟገቱ፣ በዚያ ያቅርቡ። እንደ ቲክቶከር መፈንዳት አግባብ አይደለም። በስፋት ማብራሪያ መስጠት በማይቻልበት መድረክ ላይ ቁንጽል ሓሳብ ይዘው እየመጡ አያዝጉን። መሳቂያ፣ መሳለቂያም አያድርጉን። የእርስዎ በኢየሱስ ላይ ያልዎትን መረዳት ከወ/ሮ ብርቄ፣ ከእትዬ የብርጓል፣ ከጋሽ ደምሴ "ቅዱስ ገብርኤል አምላኬ" ብለው ከሚጸልዩት የዋሕ፣ ምስኪን እናቶችና አባቶች ጋር አነፃፅረው እኔ ሊቅ ነኝ አይበሉ። በቃ እርስዎ ገብቶዎታል። ስለ ታቦት፣ ስለ ቅዱሳን፣ ስለ ኢየሱስም እርስዎ ገብትዎታል። እንደገባዎትም በቃ ዐወቅንሎት። ሌሎቹ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምንም አያውቁም። አልተማሩምም። እናም እባክዎ አያዝጉን። አያደንዝዙን። እናት ቤተ ክርስቲያን ከተጣለ፣ ከተወረደ በኋላ ሳጥናኤልን ዲያብሎስን የርኩሰት ምንጭ ብላ መመደብ በቀር ከፍጥረታት እርኩስ ያለችው ፍጥረትም የለም። አይዘብዝቡን። እባክዎ።

"…ይልቅ በቦንብ እየተጨፈጨፉ ስላሉት ዘመድዎችዎ ምንም አልሰሙምን? የአብነት ተማሪዎችን ጭፍጨፋ አላዩምን? አብያተ ክርስቲያኑ በኤምሬትስና እና በጥንተ ጠላታችን በቱርክ ቦንብ እየነደደች መሆኑን አልሰሙምን? አሁን አስጨናቂው ጉዳይ የአህያ ሥጋ መብላት ነው ወይስ በአርአያ ሥላሴ አምሳል የተፈጠረውን ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ማሰብ? እባክዎ ይለመኑን። እስቲ ሕዝቡን ያጽናኑት። እንኳን የአህያ ሥጋ ዳቦ በሻይ መብላት ያቃተውን ወገንዎን ይጸልዩለት። የአህያ ሥጋን በሰላሙ ጊዜ ለመስበክ ያደርስዎታል። አቤቱ አምላኬ ሆይ መጨረሻዬን አሳምርልኝ የሚባለው የእናት የአባቶቻችን ጸሎት ከምር ትክክለኛ ጸሎት ነው።

"…ምን አለ በሉኝ ጥቂት ቆይተው "የጾታ እኩልነት ብለው፣ ወደ አፍ የሚገባ አያረክስም ከአፍ የሚወጣ ብለው ጾምን ይቅር ባይሉ ምንአለ በሉኝ። አቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ እድገት ዋናዋ ተጠያቂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶና ጥንታዊው እስልምና ናቸው። እስያ ሄጄ ስመጣ ታምሜ ነው የምመጣው። ራበን አትበሉ ቅጠል ብሉ ወዘተ ያለውን ሰበካ እነ አባ ወልደ ትንሳኤ አስቀጥለው በቅርቡ ባይዘበዝቡን ምን አለ በሉኝ። የጾታ እኩልነት ብለው ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት ቢጋባ ምንአለበት ባይሉ ምንአለ በሉኝ። ጠብቁ። እንደ ኳታር ሃይማኖቴ የማይፈቅደውን አርማ አልቀበልም ብሎ ቆራጥ ለመሆን ባንታደልም የጥፋት መንገድ ጠራጊዎች በሃይማኖት ካባ ተጠቅልለው በውስጥ መሰግሰጋቸውን መደበቅ አይቻልም።

• እርስዎ የፈለጉትን ይብሉ። እኛን ግን ይተዉን አባ። ኧረ አምላኬ ከተናግሮ አናጋሪ ጠብቀኝ። ምን ጉድ ነው የገጠመን። በጎንደር፣ በሸዋ፣ በወሎና በጎጃም ንፁሐን እየተጨፈጨፉ የሚያሳይ ቪድዮና ፎቶ ደርሶኝ እያየሁ ማኅበራዊ ሚዲያው በእኚ ዘወትር የአህያ ሥጋ የአሳማ ሥጋ መብት ተቆርቋሪ ሊቀጳጳስ አጀንዳ መጥለቅለቁን ሳይ አዘንኩኝ። እንዲያው ሌሎቹስ እሺ እኚህ ጎንደሬ ምን ልሁን ነው የሚሉት?

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 28/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…የዛሬ ዕለታዊ የዘወትር ተግባሬን ከመጀመሬ በፊት እንደ ልማዴ የመልእክት መቀበያ ሰንዱቆቼን በመክፈት ከተለያዩ ሰዎች ዘነደድ ተኝቼ ሳለሁ የተላኩልኝን መልእክቶች ለማንበብ፣ ቪድዮዎችንም ለማየት፣ የድምጽ መልእክቶችንም ለመስማት የመልእክት መቀበያ ሰንዱቆቹን ስከፍት አንድ ተደጋጋሚ የሆነ የተቆራረጠ ተመሳሳይ ቪድዮ ተልኮልኝ አገኘሁ። ለኪዎቹ ብዙዎች ናቸው። ቪድዮውን የሚልኩልኝ ደግሞ በዚሁ በማኅበራዊ ሚዲያ መንደር ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ የማውቃቸው ጽንፈኛ ጴንጤዎች፣ የወሃቢይ እስላሞችና ጥቂት ጎጋ የሆኑ የማላውቃቸው ኦርቶዶክሳዊ መሳይ አፍ ብቻ አጭቤ የበለጸጉ የነጠላ ክርስቲያን ወንድም እህቶቼ ዘንድ ነበር። የሚገርመው ከአንድም ፖለቲካው ከገባው ከማውቃቸውና ከማደንቃቸው ወዳጆቼ ዘንድ ይሄ ቪድዮ አልደረሰኝም።

"…ለደግነቱ ቪድዮውን እኔ ማታ ዓይቼው ነበር የተኛሁት። እግረኛው ሚዲያ ላይ ጋዜጠኛ መሪጌታ ተክለሃይማኖት እና የቀድሞው አባ ወልደ ተንሣኤ ያደረጉት የአህያ ሥጋ ውይይትን ነበር ጎጋዎቹ ጴንጤዎች እና የወሃቢይ እስላሞች፣ የእኛዎቹም አፈጣዲቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነን ባዮች ይልኩልኝ የነበረው። ወሃቢዮችም የሚልኩልኝ በእስልምና ፈረስ እና አህያ፣ ጅብም ጭምር መብላት የተፈቀደ ስለሆነ ይኸው በእናንተም የተፈቀደ ነው ለማለት እንደሆነ ይገባኛል። ጴንጤዎቹ ከዚህ በፊት በዶግማ በቀኖናቸው የሚከለክላቸው ሕግ ያለ ይመስል እነርሱም ይኸው በኦርቶዶክስም ይፈቀዳል ብለው አይጥና ጉርጥ፣ አህያና ጅብ ለመብላት ምስክር መጥራታቸው ነበር። የእኛዎቹ አፈጣድቆችም ወይ ለመስለም፣ ወይ ለመጰንጠጥ መሃል ላይ የቆሙ ሆነው ነጠላና ስማቸው ብቻ ተዋሕዶ መስሎ በኑሮ ግን እንደ አህዛብ የሆኑቱ ናቸው ሲያጨናንቁኝ የነበረው።

"…አባ ወልደ ተንሣኤ በጥንት ጊዜ ከመጰጰሳቸው እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ ከመባላቸው በፊት ማለት ነው አንደበተ ርቱዕ ሰባኪ ነበሩ። ነበሩ ነው ያልኩት። የማይደክሙ፣ የማይሰለቹ ወንጌላዊም ነበሩ። የአባ ወልዴ የድሮ ስብከቶች በኦርቶዶክሳውያን አማኞች ዘንድ ተወዳጆችም ነበሩ። "ከመልካም ሽቶ መልካም ስም ይበልጣል፣ የፈቃድ እብድት፣ የቅዱሳን አማላጅነት በዐፀደ ሥጋ፣ በዓፀደ ነፍስ፣ ቅዱሳን መላእክት፣ ድንጋዩን ማን ያንከባልልናል ወዘተ በሚሉ ርእሶች የተዘጋጁ ስብከቶቻቸውም ዝነኛና አይረሴም ናቸው። ምእመናንን የሚያንፁ፣ መናፍቃንን የሚመልሱ፣ ለንስሐ የሚያበቁ ግሩም ግሩም የሆኑ ትምሕርቶች ነበሯቸው። አብዛኛውን ስብከቶቻቸውን በካሴትም፣ በቪኤችኤስም፣ በሲዲና በቪሲዲ የኢትዮጵያ ወኪል ሆኜ ያሰራጨሁላቸሁም እኔው ራሴ ዘመድኩን በቀለ ነበርኩ። እናም በዚህ ይታወሳሉ። በተለይ ስለ ዕጣን የሰበኩትን አልረሳውም።

"…አባ ወልዴ ኋላ ብፁዕ አቡነ ባርናባስ እያረጁ ሲመጡ መላ ስብከታቸው የፓስተር ቶሎሳ ጉዲና፣ የዳዊት ሞላልኝን እየመሰለ መጣ። ከቤተ ክርስቲያን መምህራን ይልቅ የመሃይም ደናቁርቱ የእነ በጋሻው ደሳለኝ፣ የእነ ትዝታው ሳሙኤል አድናቂ እየሆኑ መጡ። እንደ ጀማሪ ጴንጤ አዲስ እንደሰሙት ነገር ኢየሱስ፣ ኢየሱስ በማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስን የማታውቀው ይመስል እንደ አዲስ ኢየሱስ ክርስቶስን ካልሰበኩ ብለው ወበሩ። ያዙኝ ልቀቁኝም አበዙ። ኧረ ግድየሎትም ይተዉ ቢባሉ እምቢኝ አሉ። እንደ ጀማሪ ጴንጤ ጌታ፣ ጌታ ማለት አበዙ። ስሙን በነጠላ መጥራት አቁማ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ከስሙ በፊት "ጌታችንና አምላካችን፣ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ" ብላ ወልደ አብ ወልደ ማርያምን አክብራ የምትጠራውን፣ የምታመልከውን ጌታ ልክ እንደ ኢዩ ጩፋና እስራኤል ዳንሳ የቆሎ ጓደኛቸው አድርገው በየ ዐውደ ምሕረቱ መለፈፍ ጀመሩ። የቀደመ ልፋታቸውና ድካማቸው እየታሰበ ገሚሱም በግልፅ እየሞገታቸው በመጨረሻ ጳጳስ ሆነው ከመደድረኩ ጠፍተው ቤተ ክርስቲያንና ምዕመናን ከብፁዕነታቸው የቅልውጥና ትምህርቶች አረፉ። ተገላገሉ። ሰው ቢጠፋ ቢጠፋ ከእዩ ጩፋ ይቀላውጣል እንዴ?

"…አቡነ ባርናባስ መቼ ነው እንዲህ የሆኑት ብዬ የጋራ ወዳጆቻችንንም ጠይቄ ነበር። እነዚያ ሰዎች እንደነገሩኝ ከሆነ የጀመራቸው በዚህ ጊዜ ነው ብለን እርግጠኛ ሆነን ሰዓቱንና ቀኑን መናገር ባንችልም ነገር ግን የሆነ ጊዜ እዚሁ አሜሪካን ሀገር ታመው የጭንቅላት ይሁን የሆድ ዕቃ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ታመው ድነው ከተነሡ በኋላ የገጠማቸው ነገር ነው ብለው ነው የነገሩኝ። በቀዶ ጥገናው ወቅት ፈረንጆቹ ምን አብረው እንደጨመሩባቸው ፈጣሪ ይወቅ። ከዚያ በኋላ ነው ጵጵስናን ሲሸሹ፣ አልፈልግም ሲሉ የነበሩቱ መነኮስ ተሯሩጠው በውጪው ሲኖዶስ በኩል እንዲጰጵሱ የተደረገው። ከጵጵስናው በኋላም ብሶባቸው ስለሀገር፣ ስለሕዝብ፣ ስለወገን፣ ስለ አብያተ ክርስቲያናት መውደም፣ መቃጠል፣ ስለ መነኮሳት፣ ካህናት መታረድ፣ ስለ ምእመናን መፍለስ ግድ ሳይሰጣቸው ዘወትር ወራትና ወቅት እየጠበቁ አትርሱኝ ባይ ሆነው ዘወትር ጋዜጠኛ መሪጌታ ተክለሃይማኖት ጋር እየቀረቡ "አህያ፣ ጅብ፣ ተኩላ፣ ቀበሮ፣ ጅብ፣ ትል፣ አባጨጓሬ፣ ጉርጥ፣ አይጥ፣ አሳማ፣ ቅማል፣ ትኋንና ቁንጫ፣ ቅጫም ሁላ ይበላል። የተፈቀደ ነው የከለከለም የለም የሚሉት። ምን ጉድ ነው የገጠመን። ኦፕራሲዮኑን የሠራቸው ሰው ቻይናዊ ይሆን እንዴ? እንዴት ሰው ሁል ጊዜ ወደ መድረክና ወደ ሚዲያ በመጣ ቁጥር የአህያ ሥጋ ስብከት፣ የዓሳማ ሥጋ ይናፍቀዋል?

"…አባ ወልዴ ከፈለጉ ይብሉ። የአህያ ሥጋ አይደለም ለምን የአርጃኖ አይበሉም። ምንድነው ሁሌ መዘብዘብ? ምንድነው ስንት የሚነገር፣ ስንት የሚሰበክ ስብከት እያለ ሁሌ የአህያ ሥጋ፣ የውሻ ሥጋ ይበላል አይበላም ብሎ ማላዘን? ዘመዶቻቸውን እዚያ ጎንደር አቢይ አሕመድ በድሮንና በጥይት ይበላቸዋል እሳቸው ሁሌ እየመጡ የአህያ ሥጋ፣ የአህያ ሥጋ ምንድነው ጉዱ? ከአህያ ጋር ፀብም ዝምድናም ይኑራችሁ አይኑራችሁ አላውቅም ግን አሁን ዝም ብዬ ሳይዎት ከአህያ ሥጋ፣ ከአሳማ ሥጋ ጋር የተለየ መለከፍ ሳይገጥሞት አይቀርም ባይ ነኝ። የሳደገውን በሬ አርዶ መብላትን ሳይቀር የሚንሰፈሰፍ፣ የተላመደውን በጉን ማረድ ሰው እንደ መግደል፣ የገዛ ልጅን እንደማረድ ቆጥሮ በሬዬን አላርድም ብሎ ለራሱ እንዲበላ የተፈቀደ ከብት አርዶ ለመብላት አንጀቱ ለሚንሰፈሰፍ የሀገሬን ገበሬ ደርሶ የአህያ ሥጋ ይበላል አይበላም ስበካ ያውም በጳጳስ አፍ ተደጋግሞ መወትወት ምን ታስቦ ነው? እኔ አልገባኝም። እንዴት ሰው ሁሌ የአህያ ሥጋ ይበላል እያለ ይሰብካል? ያውም ጳጳስ። ጉድ እኮ ነው።

"…በትናንትናው ቪድዮ ላይ ኮመንቶቹን ሳነብ ነበር። አባ ወልዴን ሲያደንቁ ያየኋቸው በሙሉ ጴንጤዎች መሆናቸው ሌላውን ቢያስደነግጥም እኔ ግን ከቁብም አልቆጥረው። የታወቀ ነዋ። "የእኔ አባት ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ይሸፍኖት፣ የጌታ ሰው፣ እኚህ የበራላቸው ናቸው፣ እንደርስዎ አይነት ሰባኪ ቢነሣ የት በደረስን ወዘተ የሚል ሱናሚ የሆነ የመነፈቀ ኮመንት ሲጎርፍላቸው ነው ያየሁት። እስከአሁን ከቆጠርኩት ወደ 770 ኮመንቶች መካከል የጴንጤዎቹ ደስታ የተለየ ነበር። ይሄ የሚጠበቅ ነው።…👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ዓይኖችህም ከሚያዩት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ።”ዘዳ 28፥34 “…በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አይሰማችሁም።” 1ኛ ሳሙ 8፥18

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ሰውየው ከውጭ የሚመጣ ዕቃ ላይ ከፍተኛ ታክስ ሊጥል በመዘጋጀቱ የኑሮ ውድነቱ ላይ ጫና ያደርጋል የሚል ግምት አለኝ። እንደ አብነት ሀገር ቤት የመኪና ዋጋ ሦስት እጥፍ የደረሰው በምን ምክንያት እንደሆነ አብዛኛው ሰው ይገነዘባል ብዬ አምናለሁ። እንደ አንድ ስደተኛ ሴትዮዋ ለስደተኞች ያላት ክብርና መብታቸውን ለማስጠበቅ ያላትን ተነሳሽነት እደግፋለሁ። ሌላው የመንታ ሴቶች አባት በመሆኔ እና በርካታ ኢትዮጵያዊያን ብዙ ሴት ልጆች ስላሏቸው በዚች የወንዶች ዓለም ላይ በልዕለ ኃያሏ ሀገር አሜሪካ ለመጀሪያ ጊዜ ጥቁር ሴት ፕሬዚደንት ብትመረጥ ለጥቁር ሴት ልጆቻችን ጥሩ ምልክት በመሆን ለተሻለ ሥራ መነቃቃት ትፈጥራለች ብዬ ስለማምን እደግፋታለሁ። (ሴቶችዬ አሽቃበጥኩ ወይ? ደግ አደረኩ😁)

"…በጣም በርካታ ኢትዮጵያዊ ጀርባውን ሊሰጣት የሚችልበት የሚመስለኝ የተመሳሳይ ጾታን ምናምንን በተመለከተ እኔም እንደ አንድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጅ ድርጊቱን አምርሬ እጠላዋለሁ። ነገር ግን በእዚህ ጉዳይ ሰውየው ሥልጣን ላይ በነበረበት አራት ዓመታት ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ሥራ ሲሠራ  ስላላየሁ በቀጣይ ከወሬ በዘለለ ሊሠራ ይችላል ብዬ አላምንም። ነገር ግን ይኼ ጉዳይ ከእኛ ባህል አኳያ በቀላሉ የማንመለከተው በመሆኑ ጉዳዩ ከሁለቱም ወገን ከፌደራል ይልቅ በስቴት ደረጃ ከስኩል ቦርድ ጀምሮ የሚመረጡ አመራሮችን የእኛን አቋም የሚደግፉ ሰዎችን እየፈለግን እንደ ኮሚኒቲ ተደራጅተን በመንቀሳቀስ ማሳመን ስንችል የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንችላለን ብዬ አምናለሁ። መዘንጋት የሌለብን ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ ዘ-ጋርዲያን እንደዘገበው 69% የአሜሪካዊያን ድጋፍ እንዳለው ስመለከት እኛም ደንግጠናል እንዳለው ሰውዬ በጣም መደንገጤን መዋሸት አልፈልግም።

"…በአጠቃላይ የእኔ እይታ መግቢያዬ ላይ ለመጠቆም እንደሞከርኩት ሁለቱም ምርጫዎቼ ባይሆኑም ከጥቁር ጠሉ ሰውዬ ይልቅ እሷን እመርጣለሁ። እንደመውጫ ከሰሞኑ ከአንዳንድ ሀበሾች ከታዘብኳቸው ነገሮች መካከል ድንበር አቋርጦ በሜኪሲኮ በኩል የገባ ሀበሻ ሰውየውን ሲደግፍ አያለሁ😁 ይኼ ያስቃል። አንተ ቀድመህ ገባህ ሌላው ወንድምህስ? በየት ይግባ ? ሌላው ባይደን ያወጣውን 5ለ1 ፖሊሲ ለመጠቀም ወንድሙን ኬኒያና ኡጋንዳ ልኮ እየጠበቀ ያለ ሀበሻ ሰውየውን ወጥሮ ሲደግፍም እመለከታለሁ እና አልተገናኝቶም 😁 እጄን በእጄ አይሆንም ወይ ? በተዛባ መረጃ እራሳችንን የሚጎዳ ነገር ከመፈጸም እንጠንቀቅ !! ማዳም ፕሬዚዳንት Kamala Harris መልካም ዕድል። በማለት ሓሳቡን ቋጭቷል። የሆነው ሆኖ በመጨረሻ የተስፍሽ ምርጫ ተሸንፏል። እሱም በጨዋ ደንብ ለሪፐብሊካን መራጮች እንኳን ደስ አላችሁ በመላት የመልካም ምኞቱን ገልጿል።

"…ስንጠቀልለው የሚበጀን የቱ ነው? ፈረንጆቹ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር፣ ኦርቶዶክስን እንደ ሃይማኖት፣ ዐማራን እንደ ነገድ አይወዱም ብሎ ከዳር መቀመጡን አልደግፍም። ትግሬዎች እኮ እንዲያውም ለዲሞክራት ተመራጮች ገንዘብ ሁላ አዋጥተው ይሰጣሉ መባልን ሰምቻለሁ። አሁን ምንም ይባል ምንም ፕሬዘዳንት ትራምፕ 47ኛ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል። እንደ ፌቨን ዮሐንስ ጦማርም ከሆነ የትራምፕ ምርጫ ብዙ ነገር ይቀያይራል። የዓለም ፓለቲካ አሰላለፍም ይቀየራል። ለእኩሉ በረከት ለእኩሉ ስጋት ይሆናል። በተለይ ተላላኪ የአፍሪካ መሪዎች እኩሎቹ ቁርጠት ይለቅባቸዋል። አንዳንዶች ደግሞ እንዳሻቸው እንዲሆኑ የትራምፕ ሥርዓት ስለማይፈቅድላቸው ከወዲሁ ጭንቅ ይገባቸዋል። የሆነው ሆኖ የእነ ዩክሬን ጦርነትም መቋጫ ያገኛል ተብሎ ይገመታል። እነ ጋዛም እፎይታ ሳያገኙም አይቀሩም። ካሁን ቀደም የተለኮሱ ጦርነቶች ተዘግተው አዳዲስ ክስተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ።

"…ለማንኛውም አጎት ትራምፕ ይመቻቸው። እሳቸው የኢኮኖሚ ሊቅ ናቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን በደንብ ያኖሩ፣ ትልቅ ቦታ ያደረሱ፣ በትምህርታቸውም ይህ ቀራቸው የማይባሉ፤ የማይጠሩበት ሁለት PHD ምሩቅ ሲሆኑ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ብዙ አበርክቶት የነበራቸው ናቸው። ትራምፕ ቤተሰቦቻቸውን በቅንጦት ያኖሩ ሲሆኑ ሥርዓት ላይ ደግሞ ምንም የማያወላዱ ናቸው። አይደለም ልጆቻቸውን የልጅ ልጆቻቸውን ስለ አልኮል፣ ሱስ፣ አልባሌ ነገር በደንብ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ እና በደንብ የሚከታተሉ መሆናቸው ይነገርላቸዋል። የትራምፕ ልጆች ተፅኖ ፈጣሪ እና ባለፀጎች ናቸው። አንዱ ልጃቸው ደግሞ እሳቸውን ይተካል፤ የወደፊቷ አሜሪካ መሪ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል። ይህ እንግዲህ የአባት ሥራ፣ ክትትል መሆኑ ግልፅ ነው። ጥሩ ቤተሰብ ውስጥ የአገር መሪ ይፈጠራል ማለትም ይህ ነው።

"…ለአብዛኛው ዓለም ሰው ኋይትሃውስ ገብቶ ለመውጣት እንደ ትልቅ የሚታይ ቢሆንም ለትራምፕ ቤተሰብ ግን እንደ ቆሸሸ ቤት ነው የታየው። ለምን ቢባል የትራምፕ ቤት እጅግ ዘመናዊና ቅንጡ ከመሆኑ የተነሳ ነው። ትራምፕ ካሁን ቀደም ምርጫ አሸንፈው ወደ ኋይትሃውስ ሊገቡ ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ፍቃደኛ አልነበሩም። ትራምፕ ግን ተሸንፈው ውጡ ሲባሉ አልወጣም ብለው ነበር። ትራምፕ ነውጠኛ ቢባሉም ለአገራቸው የተሻለ የሚያስቡ መሆናቸው ግልፅ ነው። ከእነ ሩሲያ እና ቻይና ጋር እንኳን የተካረረ ነገር የላቸውም። ያ ማለት የዲፕሎማሲ በራቸው ክፍት አድርገዋል ማለት ነው። ለማንኛውም አጎት ትራምፕ እንኳን ደስ ያለዎ! እርስዎ የጥረት ሰው ነዎት ስልና ስደግፍዎ በምክንያት ነው። ዲሞክራቶች ፀረ ተፈጥሮ ናቸው። ከእግዚአብሔር ሥራ ተፃራሪ ስለሆኑ ትራምፕ ደግሞ ለፈጣሪና ለፍጡርን ድንበር ያላቸው ወዝ ያላቸው ስለሆኑ ነው። ለአማኬላዎች ርህራሄ የላቸውም። እሳቸው ሮያል ፋሚሊ ቤተሰብ ያላቸው በሥርዓት የኖሩ፤ ሥርዓት እንዲኖር የሚሠሩ በመሆናቸው ግልፅ ነው ትላለች ሔቨን ዮሐንስ።

• እናንተስ ምን ትላላችሁ…?

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 27/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…
Подписаться на канал