በሴርያ ክለቦች እኩል ከሆኑ አሸናፊው በምን ይለያል ?
ብርቱ ፉክክር እየተካሄደበት በሚገኘው የጣልያን ሴርያ ውድድር ኢንተር ሚላን እና ናፖሊ በእኩል 71 ነጥብ ይገኛሉ።
ሁለቱ ክለቦች ሊጉን በእኩል ነጥብ የሚያጠናቅቁ ከሆነ የዋንጫ አሸናፊው በሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የሚለይ ይሆናል።
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀ ተጨማሪ ሰዓት እንደማይኖር እና በቀጥታ ወደ መለያ ምት እንደሚያመሩ ተነግሯል።
ሴርያው ከዚህ ቀደም ክለቦች እኩል በሚሆኑበት ሰዓት የእርስበርስ ግንኙነትን ይጠቀም የነበረ ቢሆንም ከሁለት አመት በፊት አዲስ ደንብ ማውጣቱ ይታወሳል።
ክለቦች ለመውረድ በሚደረገው ፉክክር እኩል ሆነው ቢገኙ በተመሳሳይ አንድ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የሚያደርጉ ይሆናል።
ክለቦች በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ እኩል ነጥብ ከያዙ የመጨረሻ ደረጃ ለመለየት የእርስበርስ ግንኙነት እንደሚታይ ተጠቁሟል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የቪኒሰስ ዘጋቢ ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው !
ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ ፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየርን የተመለከ ዘጋቢ ፊልም እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል።
አሁን ላይ በአሜሪካው ግዙፍ የሚዲያ ተቋም ኔትፍሊክስ የተዘጋጀው ዘጋቢ ፊልሙ ከሳምንታት በኋላ ለእይታ ሊቀርብ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
ዘጋቢ ፊልሙ ግንቦት 7/2017 ዓ.ም ለህዝብ እይታ እንደሚቀርብ ተነግሯል።
ዘጋቢ ፊልሙ የ 24ዓመቱ ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየርን የህይወት ውጣ ውረድ እና የእግርኳስ ህይወት እንደሚዳስስ ተገልጿል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#wanawsportswear_x_Coop
ጠንካር ሕብረት ጠንካራ የስራ ባህልን እና ቦታን እንደሚያዳብር የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በደንብ ተረድቷል!
20ኛ የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ በባንኩ ሠራተኞች መሀከል የተካሄደው የወዳጅነት ግጥሚያ የአንድነት እና ወንድማማችነት መንፈስ ለሰራተኞች የሚያጎናጸፍ ነው!
ለድርጅትዎት እድገት እና አንድነት የሚጨነቁ ከሆነ ዋናው የስፖርት ትጥቅ ብራንድን ምርጫዎት ያድርጉ!
⭐️ ዋናው ወደፊት🔜🔜🔜
ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውጪ ሆነ !
ትሪክ አይሽሬው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከእሁዱ የ 2025 ለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ መሆኑን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል።
አትሌቲ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን ውድድር መሳተፍ እንደማይችል አዘጋጆቹ እንዳሳወቃቸው ገልጸዋል።
ቀነኒሳ በቀለ በሰጠው አስተያየትም “ በእሁዱ የለንደን ማራቶን ወደ ውድድር ለመመለስ ጓጉቼ ነበር ባለመሳካቱ በጣም ተበሳጭቻለሁ “ ብሏል።
ከውድድሩ ውጪ የሆነው በጉዳት መሆኑን ያረጋገጠው ቀነኒሳ በውድድሩ ለሚካፈሉ አትሌቶች መልካም ምኞቱን ገልጿል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ኪሊያን ምባፔ ወደ ልምምድ ተመለሰ !
የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በዛሬው የቡድኑ መደበኛ ልምምድ ላይ መሳተፉ ተገልጿል።
ፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድ በአርሰናል በተሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት እንደነበር ይታወሳል።
በተጨማሪም የመስመር ተጨዋቹ ፌርሊንድ ሜንዲ በዛሬው የቡድኑ መደበኛ የቡድን ልምምድ ላይ መሳተፉ ተነግሯል።
ሪያል ማድሪድ ነገ ምሽት 4:30 ከሄታፌ ጋር የሊግ መርሐ ግብሩን ያደርጋል።
ሁለቱም ተጨዋቾች በቅዳሜው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ ወደ ሜዳ እንደሚመለሱ ተገልጿል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨዋች ለማስፈረም ንግግር ጀመሩ !
ማንችስተር ዩናይትድ የዎልቭሱን የፊት መስመር ተጨዋች ማቲውስ ኩንሀ ለማስፈረም ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።
ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ከዎልቭስ ጋር ፍሬያማ ንግግር ማድረጋቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ዎልቭስ ማንችስተር ዩናይትድ የተጫዋቹን ኮንትራት ማፍረሻ 62.5 ሚልዮን ፓውንድ እንዲከፍሉ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።
የተጨዋቹ የዝውውር ሒሳብ ለረጅም ጊዜ ተከፋፍሎ ክፍያው እንደሚፈፀም ተነግሯል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ተጫዋቹን ለአስር ቁጥር ቦታ ተጨዋች እንደፈለጉት ተዘግቧል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ኦዶች ዛሬም ከፍ ብለዋል!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
ተጠናቀቀ | ቶተንሀም 1 - 2 ኖቲንግሃም ፎረስት
⚽ ሪቻርልሰን ⚽ አንደርሰን
⚽ ክሪስ ውድ
- የኖቲንግሀም ፎረስቱ አጥቂ ክሪስ ዉድ በውድድር አመቱ አስራ ዘጠነኛ የፕርሚየር ሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።
- ቶተንሀም በውድድር ዘመኑ አስራ ስምንተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
- አንቶኒ ኢላንጋ 2025 ከገባ ወዲህ ከየትኛው ተጨዋች በበለጠ በሊጉ ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
- በተጨማሪም በውድድር ዘመኑ በአስራ አምስት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ይህም በእግርኳስ ህይወቱ ከፍተኛው ነው።
- ኖቲንግሃም ፎረስት ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ በማድረስ ሶስተኛ ደረጃውን በድጋሜ መረከብ ችሏል።
- በቀጣይ ቶተንሀም ከሊቨርፑል እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ብሬንትፎርድ ይጫወታሉ።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
እረፍት
ቶተንሀም 0 - 2 ኖቲንግሃም ፎረስት
⚽ አንደርሰን
⚽ ክሪስ ውድ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባሕርዳር ከተማ ወሳኝ ድል አሳክቷል !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር ባሕርዳር ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የባሕርዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቸርነት ጉግሳ 2x እና አቤል ማሙሽ 2x ከመረብ ሲያሳርፉ አሸናፊ ሐፍቱ ለመቐለ 70 እንደርታ አስቆጥሯል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
2️⃣ ባሕርዳር ከተማ :- 40 ነጥብ
1️⃣4️⃣ መቐለ 70 እንደርታ :- 28 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ሐሙስ - መቐለ 70 እንደርታ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
አርብ - ባሕርዳር ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ እረፍት ተሰጥቶታል !
ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ አል ነስር ነገ ከዳማካ ጋር በሚያደርገው የሊግ መርሐግብር እንደማይሳተፍ ተገልጿል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነገው መርሐግብር በአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ እረፍት እንደተሰጠው ተነግሯል።
በሀምሳ ሰባት ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አል ነስር ነገ ምሽት 1:05 የሊግ ጨዋታውን ከዳማክ ጋር ያደርጋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ማድሪድ ዣቢ አሎንሶን ከፈለገ አናስቆመውም “
የባየር ሌቨርኩሰኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፈርናንዶ ካሮ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ከክለቡ ጋር የተለየ ስምምነት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
ሀላፊው ሲናገሩም “ ከዚህ በፊት ዣቢ አሎንሶ የተጫወተበት ክለብ ፈልጎት ከመጣ ላናስቆመው ስምምነት አለን “ ብለዋል።
ይህንንም ተከትሎ ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶን ፈልጎ ከመጣ አናስቆመውም ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል።
“ ዣቢ አሎንሶ የወደፊት ቆይታውን በሚቀጥሉት ሶስት ወይም አራት ሳምንታት ውስጥ መወሰን አለበት እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ መጠበቅ አንችልም።“ ሲሉ ሀላፊው ገልጸዋል።
አክለውም “ ከሪያል ማድሪድ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለን ሁለቱም ክለቦች እርስበርስ ይከባበራሉ “ ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" የነገው ጨዋታ ፍፃሜ ነው " ጋርዲዮላ
የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የክለቡ ደጋፊዎች ለነገው የአስቶን ቪላ ወሳኝ ጨዋታ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።
“ የአስቶን ቪላ ጨዋታ የፍፃሜ ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እነሱ ለሻምፒየንስ ሊግ ቦታ ቀዳሚ ተፎካካሪያችን ናቸው ልናሸንፋቸው ይገባል ብለዋል።
ደጋፊ ጠንካራ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ያቀረቡት ጋርዲዮላ “ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ትልቅ ድጋፍ ያስፈልገናል " ሲሉ ድባቡ ሊቆም አይገባም ሲሉ ተናግረዋል።
“ ኡናይ ኤምሬ የሉዊስ ኤንሪኬው ፒኤስጂ ላይ ያደረገውን አይቻለሁ የሚደንቅ እግርኳስ እየተጫወተ ነው በጣም ምርጥ ቡድን ሰርቷል።“ ፔፖ ጋርዲዮላ
በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ማንችስተር በ 5️⃣8️⃣ ነጥብ አራተኛ እንዲሁም አስቶን ቪላ በ 5️⃣7️⃣ ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።
ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።
ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።
ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።
⏩ የማንችስተር ሲቲ እና ኤቨርተን
1ኛ. @Amour_love21
2ኛ. @Yohananss
3ኛ. Getachew
⏩ የባርሴሎና እና ሴልታቪጎ
1ኛ. @firew456
2ኛ. @Yon1_bab
3ኛ. @Godmanjesus
⏩ የቼልሲ እና ፉልሀም
1ኛ. Roba $
2ኛ. ጉዱ ካሳ
3ኛ. @Amour_love21
⏩ የአርሰናል እና ኢፕስዊች
1ኛ. @kukuwzJesus
2ኛ. @Ibsii4
3ኛ. ጉዱ ካሳ
⏩ የማንችስተር ዩናይትድ እና ዎልቭስ
1ኛ. @A2121Z
2ኛ. @Lizibon
3ኛ. @Samiijesus
⏩ የሊቨርፑል እና ሌስተር ሲቲ
1ኛ. @Ablex2020
2ኛ. @Solagrati_a
3ኛ. @Miku1121
⏩ የሪያል ማድሪድ እና አትሌቲክ ቢልባኦ
1ኛ. @MaryD41
2ኛ. @bbbbbiye
3ኛ. @Matomiyasu1
🔴 አሸናፊዎች @Kidusyoftahe ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ ሽልማታቸውን መውሰድ ይችላል።
@tikvahethsport
ሀዋሳ ከተማ ድል አድርጓል !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግብ ዓሊ ሱሌይማን 2x ከመረብ ሲያሳርፍ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሱሌማን ሀሚድ አስቆጥሯል።
7️⃣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 35 ነጥብ
1️⃣5️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 27 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ቅዳሜ - ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና
አርብ - ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መቻል
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ቡካዩ ሳካ ለነገው ጨዋታ ይደርሳል ?
የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ ያጋጠመው ጉዳት የከፋ አለመሆኑን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።
" በልምምድ ወቅት የሚያሳየውን መጠበቅ እና መመልከት አለብን ነገርግን ከባድ ነገር ያለ አይመስልም " ሲሉ አርቴታ ስለ ጉዳት ሁኔታው አስረድተዋል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አክለውም ቡካዩ ሳካ በነገው የክሪስታል ፓላስ ጨዋታ የሚጫወትበት ትልቅ እድል አለው ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ
በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።
እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።
አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።
ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848
#ShemelesBekele18
ኢትዮጵያ መድን መሪነቱን አጠናክሯል !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ አበራ 2x ከመረብ አሳርፏል።
ኢትዮጵያ መድን ሊጉን በአስራ አንድ ነጥብ ልዩነት እየመራ ይገኛል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 51 ነጥብ
1️⃣3️⃣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ :- 29 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
አርብ - ባሕርዳር ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ቅዳሜ - ኢትዮጵያ መድን ከ አርባምንጭ ከተማ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
በጣልያን ቀጣይ ጨዋታዎች ተራዘሙ !
የፊታችን ቅዳሜ ሊካሄዱ የነበሩ የጣልያን ሴርያ ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ መራዘማቸው ይፋ ተደርጓል።
ጨዋታዎቹ የተራዘሙት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ስርዓት ቀብር የሚፈፀምበት ቀን በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።
ትላንት ሊደረጉ የነበሩ የጣልያን ሊግ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ለሌላ ጊዜ መራዘማቸው የሚታወስ ነው።
ይህንንም ተከትሎ የሊጉ መሪ ኢንተር ሚላን ከሮማ ቅዳሜ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ቶተንሀም የአካዳሚ ቡድን ይመስላል “ ካራገር
የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ጄሚ ካራገር አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴ ኮግሉ የቡድኑን ችግር ከመፍታት ይልቅ ደጋግመው እያወሩ ነው በማለት ተናግሯል።
“ አንሄ ፖስቴኮግሉ በሚሰጠው ቃለመጠይቁ ሁሉ ስለ ተመሳሳይ ችግር መናገሩን ቀጥሏል ፤ ነገርግን ችግሮቹን ማስተካከል ያለበት እሱ ራሱ ነው “ ሲል ጄሚ ካራገር ተናግሯል።
“ የቶተንሀም የተከላካይ ክፍል የዋህ ነው “ የሚለው ካራገር ቡድኑ ሲታይ የአካዳሚ ቡድን እየተመለከትክ ነው የሚመስለው በማለት ገልጿል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ በላሊጋ መጫወት እፈልጋለሁ “ ሮሜሮ
አርጀንቲናዊው የቶተንሀም ተከላካይ ክርስቲያን ሮሜሮ በውድድር አመቱ መጨረሻ ቶተንሀምን ሊለቅ እንደሚችል አረጋግጧል።
“ በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ውስጥ ነን አመቱን በጥሩ ሁኔታ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ ከዛ በኋላ የሚሆነውን እናያለን “ ሲል ሮሜሮ ተናግሯል።
“ ትኩረቴ የበለጠ ለማደግ የሚረዳኝን ቦታ መፈለግ ነው “ የሚለው ክርስቲያን ሮሜሮ በስፔን ሊግ መጫወት እና ለሁሉም ትልቅ ዋንጫዎች መፎካከር እፈልጋለሁ ብሏል።
ክርስቲያን ሮሜሮ ከዚህ በፊት ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር ሲነሳ እንደነበር የሚታወስ ነው።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
Can PlayStation
PlayStation 5 Fat Dubai Used
-2 Orginal jestic
-5 game installed include Fc25
-4K Video output Resolution
-best Conditions
-Full accessories
-6 months garranty without Power Supply
ዋጋ=80,000
CAN TV
Television ከኛ ጋር በፈለጉት አይነት በቅናሽ እኛ ዘንድ ያገኛሉ
ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል
ብዛት አቅርበናል
ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ
🤝Tanks for choice
አድራሻ፡፦
ቁጥር 1 መገናኛ መተባበር ህንፃ
ቁጥር 2 መገናኛ 22 Taxi መያጃ ጡር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር F14
ቁጥር 3 ቦሌ ብራስ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ ምድር ላይ
ስልክ፦ 0910529770 ወይም 0977349492
0914646972 ይደውሉ
ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
/channel/CanPlaystation
👍Update Your Life
Can PlayStation እና Tv Market
አል ኢቲሀድ መሪነቱን አጠናክረ !
በሳውዲ አረቢያ ሊግ ሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐግብር አል ኢቲሀድ ከአል ኢቲፋቅ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የአል ኢቲሀድን የማሸነፊያ ግቦች ካሪም ቤንዜማ ፣ ዳኒሎ እና ሆሴም ኦር ከመረብ ሲያሳርፉ ቪቲንሆ እና ዳኒሎ በራሱ መረብ ላይ ለአል ኢቲፋቅ አስቆጥረዋል።
ካሪም ቤንዜማ በውድድር ዘመኑ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስምንት ማድረስ ችሏል።
በሌላ ጨዋታ አል ሂላል ከአል ሻባብ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።
አል ኢቲሀድ በቀጣይ ሶስት ጨዋታዎች የሚያሸንፍ ከሆነ በይፋ የሊጉን አሸናፊነት ያረጋግጣል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ አል ኢቲሀድ :- 68 ነጥብ
2️⃣ አል ሂላል :- 62 ነጥብ
6️⃣ አል ሻባብ :- 51 ነጥብ
7️⃣ አል ኢቲፋቅ :- 40 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ረቡዕ - አል ራኢድ ከ አል ሂላል
ረቡዕ - አል ነስር ከ አል ኢቲሀድ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
በርንሌይ እና ሊድስ ወደ ፕርሚየር ሊግ አደጉ !
በሻምፒዮን ሺፕ መርሐግብር በርንሌይ ከሼፍልድ ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
በርንሌይ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ዘጠና አራት በማድረስ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
የሼፍልድ ዩናይትድን መሸነፍ ተከትሎ ሊጉን የሚመራው ሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አድገዋል።
ሊድስ ዩናይትድ ከሁለት የውድድር አመታት የሻምፒዮን ሺፕ ቆይታ በኋላ በድጋሜ ወደ ፕርሚየር ሊግ ተመልሰዋል።
በርንሌይ በበኩሉ ከአንድ የውድድር አመት በኋላ ወደ ሊጉ ማደጉን አረጋግጧል።
ሼፍልድ ዩናይትድ በቀጣይ ሶስተኛ ክለብ ሆኖ ሊጉን ለመቀላቀል የጥሎ ማለፍ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
#BostonMarathon
ለ 129ኛ ጊዜ የተካሄደው ተጠባቂው የቦስተን ማራቶን ውድድር ከደቂቃዎች በፊት ሲጠናቀቅ በሁለቱም ፆታዎች ኬንያዊያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል።
የወንዶቹን ውድድር ኬንያዊው አትሌት ጆን ኮሪር 2:04:45 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት አጠናቋል።
የተመዘገበው ሰዓት በውድድሩ የ 129 ዓመታት ታሪክ ሶስተኛው ምርጥ ሰዓት በመሆን መመዝገቡ ተገልጿል።
በሴቶች ማራቶን ውድድር ኬንያዊቷ ሻሮን ሎኬዲ 2:17:22 በሆነ ሰዓት ሪከርድ በማሻሻል ማሸነፍ ችላለች።
አትሌት ሻሮን ሎኬዲ የውድድሩን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች።
በሴቶች ማራቶን ውድድር የተካፈለችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Wanawsportswear
ትልቅ ጨዋታ ትልቅ መድረክ!!
የ 2018 14ኛው ሀበሻ ሚዲያ ካፕ አዝናኙ ሲዝናና የዋናው ስፖርት የጨዋታ ኮከቦች!
ውድድሩ በውቡ የጊዩን ሆቴል ሜዳ ላይ እንደቀጠለ ነው!
© ሀበሻ ሚዲያ ካፕ |⭐️ ውድድር ካለ ዋናው አለ
ድሬዳዋ ከተማ ድል አድርጓል !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር ድሬዳዋ ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግብ አስራት ቱንጆ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ፋሲል ከነማ ሁለተኛ ተከታታይ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣1️⃣ ፋሲል ከነማ :- 33 ነጥብ
1️⃣2️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 29 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ሐሙስ - ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ
ሐሙስ - ፋሲል ከነማ ከ ሀድያ ሆሳዕና
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኤል ክላሲኮ ጨዋታን ማን ይመራዋል ?
የፊታችን ቅዳሜ በባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ የኮፓ ዴላሬ ፍፃሜ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።
ተጠባቂውን የኤል ክላሲኮ ጨዋታ የ 39ዓመቱ ዳኛ ሪካርዶ ቡርጎስ በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ሆኖል።
ዳኛው ከዚህ በፊት በሶስት አጋጣሚዎች የኤል ክላሲኮ ጨዋታን የመሩ ሲሆን ሁለቱን ባርሴሎና ሲያሸንፍ አንዱን ሪያል ማድሪድ ረቷል።
ዋና ዳኛው ከዚህ በፊት 2017 በሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና መካከል በተደረገው የስፔን ሱፐር ካፕ ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶን በቀይ ካርድ አሰናብተው ነበር።
የኮፓ ዴላሬ ፍፃሜ ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 5:00 የሚካሄድ ይሆናል።
ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?
@tikvahethsport @kidusyoftahe
በጣልያን የሚደረጉ ጨዋታዎች ተሰረዙ !
በዛሬው ዕለት ሊካሄዱ የነበሩ የጣልያን ፕሮፌሽናል እግርኳስ ጨዋታዎች በሙሉ መሰረዛቸው በይፋ ተገልጿል።
ጨዋታዎቹ የተሰረዙት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን አሳውቋል።
ይህንንም ተከትሎ አራት የጣሊያን ሴርያ እና አስር የሴሪ ቢ ጨዋታዎች መሰረዛቸው ተገልጿል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe