መቻል ድል አድርጓል !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከአዳማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የመቻልንን የማሸነፊያ ግብ ሽመልስ በቀለ ከመረብ አሳርፏል።
ሽመልስ በቀለ በውድድር ዘመኑ አስረኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።
መቻል ተከታታይ ሶስተኛ ጨዋታቸውን አሸንፈዋል።
3️⃣ መቻል :- 38 ነጥብ
1️⃣6️⃣ አዳማ ከተማ :- 21 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ረቡዕ - አዳማ ከተማ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
አርብ - ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መቻል
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ግብ ያለማግባት ችግር የመላ የቡድኑ ነው “ አሞሪም
የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የቡድኑ ግብ ማስቆጠር ችግር የተጨዋቾች ሳይሆን የሙሉ ቡድኑ መሆኑን ገልጸዋል።
“ ቡድኑ የበለጠ ግቦችን ማስቆጠር አለበት “ ያሉት ሩበን አሞሪም “ ችግሩ የራስሙስ ሆይሉንድ ብቻ ሳይሆን የመላው ቡድኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ዴንማርካዊው የፊት መስመር አጥቂ ራስሙስ ሆይሉንድ ግብ ካስቆጠር በርካታ ጨዋታዎች መቆጠራቸውን ተከትሎ ትችቶች ሲቀርቡበት ነበር።
ራስሙስ ሆይሉንድ ባለፉት ሀያ ስምንት ጨዋታዎች ኳስና መረብን ማገናኘት የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
Can PlayStation
PlayStation 5 Fat Dubai Used
-2 Orginal jestic
-5 game installed include Fc25
-4K Video output Resolution
-best Conditions
-Full accessories
-6 months garranty without Power Supply
ዋጋ=80,000
CAN TV
Television ከኛ ጋር በፈለጉት አይነት በቅናሽ እኛ ዘንድ ያገኛሉ
ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል
ብዛት አቅርበናል
ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ
🤝Tanks for choice
አድራሻ፡፦
ቁጥር 1 መገናኛ መተባበር ህንፃ
ቁጥር 2 መገናኛ 22 Taxi መያጃ ጡር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር F14
ቁጥር 3 ቦሌ ብራስ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ ምድር ላይ
ስልክ፦ 0910529770 ወይም 0977349492
0914646972 ይደውሉ
ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
/channel/CanPlaystation
👍Update Your Life
Can PlayStation እና Tv Market
ኤሲ ሚላን ሽንፈት አስተናግደዋል !
በጣልያን ሴርያ የሰላሳ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤስ ሚላን ከአታላንታ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።
የአታላንታን የማሸነፊያ ግብ ኤደርሰን አስቆጥሯል።
ኤሲ ሚላን በውድድር ዘመኑ አስረኛ ጨዋታቸውን ተሸንፈዋል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
3️⃣ አታላንታ :- 64
9️⃣ ኤሲ ሚላን :- 51 ነጥብ
ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?
አርብ ⏩ አታላንታ ከ ሊቼ
እሁድ ⏩ ቬኔዝያ ከ ኤሲ ሚላን
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ
የሪያል ማድሪድ እና አትሌቲክ ቢልባኦን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።
የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?
√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።
√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 4:00 ሰዓት ብቻ ነው።
🔴 ይነበብ
አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።
መልካም ዕድል !
@tikvahethsport
" ዋንጫ ለማሸነፍ ተቃርበናል " አርኖልድ
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው አሌክሳንደር አርኖልድ ቡድናቸው የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት መቅረቡን ገልጿል።
ለዛሬው ድል የደጋፊው ሚና ጉልህ መሆኑን የገለፀው አርኖልድ “ አሁን ዋንጫውን ለማሸነፍ ተቃርበናል “ ሲል ከጨዋታው በኋላ ተናግሯል።
ስለወደፊት ቆይታው የተጠየቀው አርኖልድ “ ሁልጊዜም እንደምናገረው ስለወደፊት ቆይታዬ ማውራት አልፈልግም “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
“ የምንጫወተው ለደጋፊው ነው ፤ በአሁኑ ሰዓት በሊቨርፑል ከነበሩኝ ምርጥ ጊዜያት አንዱን በማሳለፍ ላይ ነኝ “ አርኖልድ
አርኖል አክሎም “ ዛሬ ያስቆጠርኩት የማሸነፊያ ግብ በአለም ሁሉ ላሉ የሊቨርፑል ደጋፊዎች መታሰቢያ ይሁንልኝ " ብሏል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሯል !
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን የሊግ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግብ አሌክሳንደር አርኖልድ አስቆጥሯል።
የአሰልጣኝ አርኔ ስሎቱ ቡድን ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ ከተከታያቸው አርሰናል ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አስራ ሶስት አስፍተዋል።
ሊቨርፑል በቀጣይ ሶስት ነጥብ የሚያሳካ ከሆነ የሊጉን ዋንጫ ማሸነፉ የሚረጋገጥ ይሆናል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ ሊቨርፑል :- 79 ነጥብ
1️⃣9️⃣ ሌስተር ሲቲ :- 18 ነጥብ
ቀጣይ መርሐ ግብር ?
እሁድ - ሊቨርፑል ከ ቶተንሀም
ቅዳሜ - ዎልቭስ ከ ሌስተር ሲቲ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
76 '
ሌስተር ሲቲ 0 - 1 ሊቨርፑል
⚽ አርኖልድ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
65 '
ሌስተር ሲቲ 0 - 0 ሊቨርፑል
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ደጋፊው ይወቀው ችግሩ ይቀጥላል “ ሩበን አሞሪም
የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድ የገጠመው ችግር አሁንም እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
“ ከደጋፊው ጋር ግልጽ መሆን አለብን “ ያሉት አሰልጣኙ ቡድናችን ብዙ ነገር ይጎለዋል ነገሮችን ለማሻሻል ብዙ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።
አክለውም “ ሁኔታው እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ይቀጥላል ከዛ በኋላ አንድ ነገር ማድረግ ይጠበቅብናል “ በማለት ተናግረዋል።
“ ግብ ካላስቆጠርክ ጨዋታ መብለጥ ጥቅም የለውም ጠቃሚው ውጤቱ ነው ጨዋታውን ተቆጣጥረን ነበር ምርጥ ተጨዋቾቻቸውንም አስቁመናል ነገርግን የቆመ ኳስ ነገሩን ቀየረው ያበሳጫል።“ሩበን አሞሪም
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
37 '
ሌስተር ሲቲ 0 - 0 ሊቨርፑል
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ባለን የዋንጫ እድል ማመን አለብን “ ትሮሳርድ
የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ትሮሳርድ አርሰናል የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ አሸናፊነት እድል እንዳለው ገልጿል።
ከጨዋታው በኋላ ስለ ዋንጫ ፉክክሩ የተጠየቀው ሊሳንድሮ ትሮሳርድ “ ባለን አድል ማመን አለብን “ ሲል ተደምጧል።
አክሎም “ የሊቨርፑል ውጤት ላይ ትኩረት ማድረግ የለብንም “ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ሳካ ህመም ውስጥ ነው “ አርቴታ
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከባድ ጉዳት እንዳላጋጠመው ከጨዋታው በኋላ ገልጸዋል።
“ ቡካዩ ሳካ ህመም እየተሰማው ነው ነገርግን ከባድ የሚመስል ነገር የለም “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አክለውም ቡድናቸው በዛሬው ጨዋታ ያሳየው እንቅስቃሴ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴
- ዎልቭስ ከአርባ አምስት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድ በአመቱ ውስጥ ሁለቱንም የሊግ ጨዋታዎች አሸንፈዋል።
- አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን ማሸነፉን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ቶተንሀም እና ኤቨርተን በፕርሚየር መቆየታቸውን አረጋግጠዋል።
- አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ ሊቨርፑል በዚህ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊነቱን ማረጋገጥ አይችልም።
- ጋብሬል ማርቲኔሊ ለአርሰናል ግብ ባስቆጠረባቸው ተከታታይ አርባ አራት ጨዋታዎች አርሰናል ተሸንፎ አያውቅም።
- ማንችስተር ዩናይትድ በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እየተመራ ካደረጋቸው ሰላሳ አራት ጨዋታዎች አስራ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
- ዎልቭስ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አምስት ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል።
- ኮል ፓልመር ባለፉት አስራ ስድስት ጨዋታዎች ምንም ግብ ማስቆጠር አልቻለም ግብ ካስቆጠረ 1292 ደቂቃዎች አልፈዋል።
- አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ ወዲህ ቡድኑ 5️⃣3️⃣ ግቦች ተቆጥረውበታል።
ማንችስተር ዩናይትድ በአንድ የውድድር አመት አስራ አምስት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሲሸነፍ በታሪክ የመጀመሪያው ነው።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#Wanawsportswear✅️
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆናችሁ የዋናው ስፖርት ቤተሰቦች እንኳን ለፋሲካ በዓል አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የመተሳሳብ እንዲሆን እንመኛለን።
መልካም በዓል!
ማህበራዊ ገጾቻችን
Instagram|Facebook |TikTok |X|wanawsportswear?si=TSJ9HZINs4MzMPj2">Youtube
🌍በኢትዩጵያ የተመረተ 🌍
🎆መልካም በአል🎆 | ⭐️ዋናው ወደፊት🔣🔣🔣Читать полностью…
“ አርሰናል የገጠምነው ምርጡ ቡድን ነው “
የኢፕስዊች ታውኑ ዋና አሰልጣኝ ኬራን ማኬና አርሰናል እግርኳስን በትልቅ ደረጃ እተጫወተ ያለ ክለብ ነው በማለት ተናግሯል ።
" በዚህ አመት ከገጠምናቸው የፕርሚየር ሊግ ክለቦች አርሰናል ምርጡ ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ኬራን ማኬና ተናግረዋል።
“ አርሰናል አስደናቂ አቅም አላቸው ለእኛ ጨዋታው አስቸጋሪ ሆኖብን ነበር በተለይ ተጨዋች በቀይ ከወጣብን በኋላ “ ኬራን ማኬና
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
አሸናፊዎች እነሆ!
እንደተለመደው ደንበኞቻችን ማሸነፋቸውን ቀጥለዋል።
ተራው የእርስዎ ነው !
አሁኑኑ Betika.et ላይ ይወራረዱ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
ሪያል ማድሪድ ወሳኝ ድል አሳክቷል !
በስፔን ላሊጋ ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ሪያል ማድሪድ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግብ ፌዴሪኮ ቫልቬርዲ በመጨረሻ ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
2️⃣ ሪያል ማድሪድ :- 69 ነጥብ
4️⃣ አትሌቲክ ቢልባኦ :- 57 ነጥብ ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ረቡዕ - ሄታፌ ከ ሪያል ማድሪድ
ረቡዕ - አትሌቲክ ቢልባኦ ከ ላስ ፓልማስ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ዴ ብሮይን በፕርሚየር ሊግ መቆየት ይፈልጋል !
ቤልጂየማዊው አማካይ ኬቨን ዴብሮይን በቀጣይ ሌላ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለብ ለመቀላቀል ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
ቀጣይ ክረምት ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚለያየው ኬቨን ዴ ብሮይን የትኛውንም ክለብ ልቀላቀል እችላለሁ በማለት ገልጿል።
ኬቨን ዴብሮይን አክሎም አሁንም በትልቅ ደረጃ መፎካከር የሚያስችል አቅም አለኝ ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን ሽንፈት ገጠመው !
በጣልያን ሴርያ የሰላሳ ሶስተኛ ሳምንት መርሐግብር ኢንተር ሚላን ከቦሎኛ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።
የቦሎኛን የማሸነፊያ ግብ ኦርሶሊኒ ማስቆጠር ችሏል።
ኢንተር ሚላን በውድድር ዘመኑ አራተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
ቦሎኛ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ በማድረስ ደረጃውን አሻሽሏል።
ኢንተር ሚላን የአስራ ሶስት ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዟቸው በቦሎኛ ተገቷል።
በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?
1️⃣ ኢንተር ሚላን :- 71 ነጥብ
4️⃣ ቦሎኛ :- 60 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ቅዳሜ - ኢንተር ሚላን ከ ሮማ
ሰኞ - ዩዴኒዜ ከ ቦሎኛ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ሌስተር ሲቲ ከፕርሚየር ሊጉ ወረዱ !
ሌስተር ሲቲ በሊቨርፑል መሸነፉን ተከትሎ ከእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ወደ ሻምፒዮን ሺፑ መውረዳቸው ተረጋግጧል።
በአስራ ስምንት ነጥብ አስራ ዘጠነኛ ደረጃን የያዙት ሌስተር ሲቲዎች ከሊጉ የወረደ ሁለተኛው ክለብ ሆነዋል።
በአሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ የሚመራው ሌስተር ሲቲ በመጣበት አመት ወደ ሊጉ ተመልሶ ወርዷል።
ሳውዝሀምፕተን ቀደም ብለው ከሊጉ መውረዳቸውን ማረጋገጣቸው ይታወቃል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
84 '
ሌስተር ሲቲ 0 - 1 ሊቨርፑል
⚽ አርኖልድ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ ከሴሑል ሽረ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
ስሑል ሽረ በውድድር ዘመኑ ካደረጋቸው ሀያ አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ሶስቱን ነው።
አርባምንጭ ከተማ ያለፉትን ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም በአንዱ ሲሸነፍ በሶስቱ አቻ ተለያይቷል።
8️⃣ አርባምንጭ ከተማ :- 35 ነጥብ
1️⃣7️⃣ ስሑል ሽረ :- 18 ነጥብ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
54 '
ሌስተር ሲቲ 0 - 0 ሊቨርፑል
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
እረፍት
ሌስተር ሲቲ 0 - 0 ሊቨርፑል
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
23 '
ሌስተር ሲቲ 0 - 0 ሊቨርፑል
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
Whether you trade stocks, forex, cryptocurrencies, or commodities, the techniques in "The Candlestick Trading Bible" will provide you with the knowledge and confidence needed to succeed.
Start your trading journey today with this powerful guide and take control of your financial future.
"Trading in the zone" serves as a guide for traders to develop the mental skills nessary for consistent success in the markets.
የትኛውም ትሬደር እጅ ላይ ሊኖሩ የሚገባቸው ሁለት መጽሐፍት!!! ለሀገራችን ትሬደሮች ጥራቱን በጠበቀ ህትመት ለገበያ በቁ!!! በሁሉም የመጽሐፍ መደብሮች ላይ ያገኟቸዋል።
@Guramaylebooks 0912319263
አርሰናል እና ቼልሲ ሲያሸንፉ ዩናይትድ ተሸንፏል !
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን 4ለ0 ሲያሸንፍ ማንችስተር ዩናይትድ በዎልቭስ 1ለ0 ተሸንፏል።
ቼልሲ በበኩሉ ከፉልሀም ያደረገውን መርሐግብር 2ለ1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።
የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ትሮሳርድ 2x ፣ ንዋኔሪ እና ጋብሬል ማርቲኔሊ ማስቆጠር ችለዋል።
ዎልቭስን አሸናፊ ያደረገ ግብ ሳራቢያ በቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።
የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ፔድሮ ኔቶ እና ታሪቅ ጆርጅ ሲያስቆጥሩ ለፉልሀም ኢዎቢ ከመረብ አሳርፏል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
2️⃣ አርሰናል :- 66 ነጥብ
5️⃣ ቼልሲ :- 57 ነጥብ
1️⃣4️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ :- 38 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ረቡዕ - አርሰናል ከ ክሪስታል ፓላስ
ቅዳሜ - ቼልሲ ከ ኤቨርተን
እሁድ - በርንማውዝ ከ ማንችስተር ዩናይትድ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
90 '
ኢፕስዊች ታውን 0 - 4 አርሰናል
⚽⚽ ትሮሳርድ
⚽ ማርቲኔሊ
⚽ ኔቶ
ፉልሀም 1 - 2 ቼልሲ
⚽ ኢዎቢ ⚽ ጆርጅ
⚽ ኔቶ
ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 1 ዎልቭስ
⚽ ሳራብያ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe