ኢንተር ሚላን ተጨዋቹ ጉዳት አጋጠመው !
የጣልያን ሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን ወሳኝ የፊት መስመር ተጨዋቹ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።
ኢንተር ሚላን ተጨዋቹ በተደረገለት የህክምና ምርመራ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው መረጋገጡን ይፋ አድርጓል።
ማርከስ ቱራም ኢንተር ሚላን እሁድ ከቦሎኛ ጋር የሚያደርገው የሊግ መርሐግብር እንደሚያመልጠው ተገልጿል።
ኢንተር ሚላን ከአምስት ቀናት በኋላ ከኤሲ ሚላን ጋር የኮፓ ኢጣልያ ግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም ከአስራ ሁለት ቀናት በኋላ ከባርሴሎና ጋር የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች አሉባቸው።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሲቲ የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !
ማንችስተር ሲቲ ነገ ከኤቨርተን ጋር በሚያደርገው የሊግ መርሐግብር የግብ ጠባቂው ኤደርሰንን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።
“ኤደርሰን ለነገው ጨዋታ አይደርስም ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ አላውቅም “ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፊል ፎደን ትላንት ወደ ልምምድ መመለሱን የገለፁት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አካንጂ በተመሳሳይ በጨዋታው ሊሳተፍ ይችላል ብለዋል።
ጆን ስቶንስ እና ናታን አኬ ለጨዋታው እንደማይደርሱ አሰልጣኙ ጠቁመዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
Can PlayStation እና Tv Market
እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤ ለፋሲካ በአል በሰላም አደረሳቹ እያልን በአል ምክንያት በማረግ Television እና ጂፓሶቻችን ላይ ልዩ ቅናሽ አድገናል
Television በፈለጉት Size እና አይነት እኛ ጋር ያገኛሉ
CAN PLAYSTATION
PlayStation ከኛ ጋር በፈለጉት አይነት በቅናሽ እኛ ዘንድ ያገኛሉ
🤝Tanks for choice
አድራሻ፡፦
ቁጥር 1 መገናኛ መተባበር ህንፃ
ቁጥር 2 መገናኛ 22 Taxi መያጃ ጡር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር F14
ቁጥር 3 ቦሌ ብራስ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ ምድር ላይ
ስልክ፦ 0910529770 ወይም 0977349492
0914646972 ይደውሉ
ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
/channel/CanPlaystation
👍Update Your Life
የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ታውቋል !
በሳምንቱ አጋማሽ የተደረጉ የ ሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመለስ ጨዋታዎችን ተከትሎ ከቀረቡ እጩዎች ውስጥ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ተለይቷል።
በዚህም መሰረት የቦርስያ ዶርትመንዱ የፊት መስመር ተጨዋች ሴርሁ ጉራሲ የሻምፒየንስ ሊግ ሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።
ሴርሁ ጉራሲ ዶርትመንድ ባርሴሎናን ባሸነፈበት ጨዋታ ሀትሪክ በመስራት የጨዋታው ኮከብ እንደነበር ይታወሳል።
የመድፈኞቹ አማካይ ዴክላን ራይስ ሁለተኛ ፣ ላውታሮ ማርቲኔዝ ሶስተኛ እንዲሁም ኦስማን ዴምቤሌ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ያለኝ ተሰጥኦ የፈጣሪ ስጦታ ነው “ ሊዮኔል ሜሲ
አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ያለው የእግርኳስ ተሰጥኦ የፈጣሪ ስጦታ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።
ያለህ ተሰጥኦ አብሮህ የተወለደ ነው ወይስ በጥረት የተገነባ ? ተብሎ የተጠየቀው ሊዮኔል ሜሲ “ እኔ የተወለድኩት በዚህ መንገድ ነው “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
“ በእርግጥ ራሴን ለማሻሻል እና በደንብ ለመጎልበት ጠንክሬ እሰራ ነበር “ የሚለው ሊዮኔል ሜሲ “ ነገርግን ከልጅነቴ ጀምሮ የተቀየረ ነገር የለም እንደዚሁ ስጫወት ነበር “ ብሏል።
ሜሲ አክሎም " ተሰጥኦዬ የበለጠ ለመጠቀም የሞከርኩት ከእግዚአብሔር የተሰጠኝ ስጦታ ነው “ ሲል ተሰጥኦ ያለጥረት ብቻው በቂ አይደለም ሲል አስረድቷል።
“ ፈጣሪ ሁሉንም ነገር ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ ፤ ሁሉንም ነገር አሸንፌያለሁ ተጨማሪ መጠየቅ አልችልም።“ ሊዮኔል ሜሲ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ቲክቫህ ስፖርት ለክርስትና ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልካም የስቅለት በዓል ይመኛል።
መልካም በዓል!!
@Tikvahethsport
✝️ እንኳን ለበአሉ በሰላም አደረሳችሁ!
ሰሞኑን ከምንወዳቸው ጋር እየተገናኘን እናሳልፍ! ለቀን፣ለሳምንት እና ለወር የሚያገለግሉ ያልተገደበ የዳታ ጥቅሎችን በ50% ቅናሽ አዘጋጅተንላችኋል! መልካም በአል!
#SafaricomEthiopia
#Easter
#Furtheraheadtogether
" ለማመን የሚከብድ ድንቅ ጨዋታ ነበር " ማጓየር
የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ሀሪ ማጓየር የምሽቱ ጨዋታ አስደናቂ እንደነበር ገልጿል።
" ጨዋታው አስደናቂ ጨዋታ ነበር " ያለው ማጓየር ጨዋታውን ተቆጣጥረናል ሶስተኛ ግብ የሚሆን የግብ እድሎችም ነበሩን ብሏል።
ኦሎምፒክ ሊዮን ጥሩ እግርኳስ መጫወቱን የገለፀው ማጓየር ነገርግን እነሱን አስቁመን በጥሩ መንፈስ ጨዋታውን ቀልብሰነዋል ብሏል።
ኮቢ ማይኖ በበኩሉ “ የማይታመን ውጤት ቅልበሳ ነው “ ያለ ሲሆን አክሎም ኳሷ እንደደረሰችኝ በቻልኩት አቅም ለመረጋጋት ሞክሪያለሁ " ሲል ተናግሯል።
ጨዋታውን " የህይወቴ በእብደት የተሞላው ጨዋታ ነው " ሲል የገለፀው ሌኒ ዮሮ ምን እንደተፈጠረ እስካሁን መረዳት አልቻልኩም ብሏል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ኦልድትራፎርድ ላይ አብቅቷል አይባልም “ አሞሪም
የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከድሉ በኋላ “ እዚህ አብቅቷል የሚባል ነገር የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።
“ በስታዲየማችን የመጨረሻ ፊሽካ ካልተነፋ ነገሮች በጭራሽ አብቅተዋል አይባሉም “ሲሉ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።
“ ሀሪ ማጓየርን አጥቂ ያደረግንበት ምክንያት በጭንቅላት ገጭቶ ማስቆጠር የሚችል ብቸኛው ተጨዋቻችን እሱ ስለሆነ ነው “ ሩበን አሞሪም
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ
ማንችስተር ዩናይትድ 5 - 4 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
⚽ ፈርናንዴዝ ⚽ ቼርኪ
⚽ ማይኖ ⚽ ላካዜት
⚽ ማጓየር
ድምር ውጤት :- 7-6
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
119 '
ማንችስተር ዩናይትድ 4 - 4 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
⚽ ፈርናንዴዝ ⚽ ቼርኪ
⚽ ላካዜት
ድምር ውጤት :- 6-6
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
108 '
ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 4 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
⚽ ቼርኪ
⚽ ላካዜት
ድምር ውጤት :- 4-6
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
100'
ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 2 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
ድምር ውጤት :- 4-4
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 2 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
ድምር ውጤት :- 4-4
- ሁለቱ ክለቦች በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አቻ መለያየታቸውን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰላሳ ደቂቃ አምርተዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !
በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ቼልሲ ከፖላንዱ ክለብ ዋርሳዋ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የዋርሳዋን የማሸነፊያ ግብ ፔክሀርት እና ካፑዋዲ ሲያስቆጥሩ ለቼልሲ ኩኩሬላ ከመረብ አሳርፏል።
ሰማያዊዎቹ ጨዋታውን በድምር ውጤት 4ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፈው ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።
ቼልሲ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በኮንፈረንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ተሸንፏል።
ቼልሲ በግማሽ ፍፃሜው የሬፒድ ዌን እና ጁርጋርደንን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።
ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች እነማን ናቸው ?
⏩ ሪያል ቤቲስ ከ ፊዮሬንቲና
⏩ ቼልሲ ከ ሬፒድ ዌን / ጁርጋርደን
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ካላፊዮሪ በፒኤስጂ ጨዋታ ወደ ሜዳ ይመለሳል !
ጣልያናዊው የመድፈኞቹ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ በፒኤስጂ ጨዋታ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።
“ ሁሉም ነገር በትክክለኛው መንገድ ከተጓዘ በፒኤስጂ ጨዋቻ ይመለሳል ብዬ አስባለሁ “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አክለውም ካላፊዮሪ ሜዳ ላይ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ መጀመሩን አረጋግጠው ትንሽ ቀድሞ ሊመለስም ይችላል ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
"100% ጉርሻ! እንኳን ደህና መጡ!
የመጀመሪያ ብቁ የሆነ ውርርድዎን ሲያደርጉ የተወራረዱበትን ገንዘብ መጠን እስከ 100% እንደ ጉርሻ ያገኛሉ።
አሁኑኑ Betika.et ላይ ቤተሰብ ይሁኑ!!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!"
ነገሌ አርሲ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አደገ !
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ " ለ " እየተወዳደረ የሚገኘው ነገሌ አርሲ እግርኳስ ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ያደገበትን ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።
ነገሌ አርሲ ዛሬ ከስልጤ ወራቤ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ደሴ ከተማ አቻ መለያየቱን ተከትሎ ነገሌ አርሲ የነጥብ ልዩነቱን ወደ አራት አስፍቷል።
ይህንንም ተከትሎ ነገሌ አርሲ አንድ ጨዋታ እየቀረው የ 2018 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለብ መሆኑን አረጋግጧል።
ነገሌ አርሲ እና ሸገር ከተማ በዘንድሮው የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን የተቀላቀሉ ክለቦች ሆነዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ባሉን ተጨዋቾች ደስተኛ ነኝ “ አርኔ ስሎት
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው እሁድ ከሌስተር ሲቲ ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አርኔ ስሎት ምን አሉ ?
- " የቨርጅል ቫን ዳይክ አዲስ ኮንትራት ምርጥ ተጨዋቾቻችን ማቆየት እንደምንፈልግ ያሳየ ነው።
- አሌክሳንደር አርኖልድ ከጉዳት ተመልሷል በእሁዱ የሌስተር ሲቲ ጨዋታ ተጠባባቂ ሆኖ የሚጀምር ይሆናል።
- ባሉን ተጨዋቾች ደስተኞች ነን የመሐመድ ሳላህ እና ቨርጅል ቫን ዳይክን ኮንትራት ማራዘም በራሱ ትልቅ የዝውውር መስኮት ነው።
- ከውል ጋር ያለው ችግር የገንዘብ አልነበረም ተጨዋቾቹ ውል ካልተሰጣቸው እቃ መግዣ ገንዘብ አይኖራቸውም ማለት አልነበረም ፣ አጠቃላይ ስለወደፊት ቆይታቸው ነበር።
- ባለፈው ክረምት ቡድኑን አልቀየርነውም ነገርግን ደረጃው አልወረደም ነበር።" ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ወደኋላ አሽቆልቁለናል “ ሬስ ጄምስ
የቼልሲው አምበል ሬስ ጄምስ ቡድናቸው በምሽቱ ጨዋታ ደካማ እንቅስቃሴ ማድረጉን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።
“ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለናል ነገርግን ቡድኑ የተጫወተው የወረደ እግርኳስ ነበር “ ሲል ሬስ ጄምስ ስለ ጨዋታው ተናግሯል።
ሬስ ጄምስ አክሎም “ ቡድኑ በጨዋታው ምንም መሻሻል አላሳየም ወደኋላ አንድ እርምጃ አሽቆልቁሏል “ ሲል ገልጿል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#Wanawsportswear✅️
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
መልካም በዓል!
ማህበራዊ ገጾቻችን
Instagram|Facebook |TikTok |X|wanawsportswear?si=TSJ9HZINs4MzMPj2">Youtube
🌍በኢትዩጵያ የተመረተ 🌍
🎆መልካም በአል🎆 | ⭐️ዋናው ወደፊት🔣🔣🔣Читать полностью…
" የተሻለ ውጤት ይገባን ነበር " ፓውሎ ፎንሴካ
የኦሎምፒክ ሊዮኑ ዋና አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ በማንችስተር ዩናይትድ የገጠማቸውን ሽንፈት “ እጅግ አሳዛኝ “ ሲሉ ገልፀውታል።
“ የተሻለ ውጤት ይገባን ነበር “ ያሉት አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ “ በጣም አሳዛኝ ነው ነገርግን በተጨዋቾቹ ጥሩ ስራ ኮርቻለሁ " ብለዋል።
አክለውም “ በጨዋታው ምን እንደተፈጠረ ለመረዳት በጣም ከባድ ነው ፤ እውነት ለመናገር ጨዋታውን ያሸነፍን መስሎኝ ነበር።“ ሲሉ ተደምጠዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትድ በሊጉ ወጣት ተጨዋቾች ይጠቀማል !
ማንችስተር ዩናይትድ በቀሪው የፕርሚየር ሊግ መርሐግብር ወጣት ተጨዋቾችን እንደሚጠቀም አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።
አሰልጣኙ በሰጡት አስተያየትም ቡድናቸው በቀጣይ ሙሉ ትኩረቱን ዩሮፓ ሊግ ላይ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
“ ፕርሚየር ሊግ ላይ የአካዳሚ ተጨዋቾችን እንጠቀማለን “ ያሉት ሩበን አሞሪም " አሁን ግዴታ ሙሉ ትኩረታችንን ዩሮፓ ሊግ ላይ ማድረግ አለብን " ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትድ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለ !
ማንችስተር ዩናይትድ ከኦሎምፒክ ሊዮን ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ 5ለ4 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የቀያይ ሴጣኖቹን የማሸነፊያ ግቦች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ ዳሎት ፣ ኡጋርት ፣ ማጓየር እና ኮቢ ማይኖ አስቆጥረዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታውን በድምር ውጤት 7ለ6 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በግማሽ ፍፃሜው አትሌቲክ ቢልባኦ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
120 '
ማንችስተር ዩናይትድ 5 - 4 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
⚽ ፈርናንዴዝ ⚽ ቼርኪ
⚽ ማይኖ ⚽ ላካዜት
⚽ ማጓየር
ድምር ውጤት :- 7-6
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
113 '
ማንችስተር ዩናይትድ 3 - 4 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
⚽ ፈርናንዴዝ ⚽ ቼርኪ
⚽ ላካዜት
ድምር ውጤት :- 5-6
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
102'
ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 3 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
⚽ ቼርኪ
ድምር ውጤት :- 4-5
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ፍራንክፈርት 0-1 ቶተንሀም
⚽ ሶላንኬ
⏩ ቶተንሀም ጨዋታውን በድምር ውጤት 2ለ1 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
90+4 '
ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 2 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
ድምር ውጤት :- 4-4
ፍራንክፈርት 0-1 ቶተንሀም
⚽ ሶላንኬ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
84 '
ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 2 ሊዮን
⚽ ኡጋርቴ ⚽ ቶሊሶ
⚽ ዳሎት ⚽ ታግሊያፊኮ
ድምር ውጤት :- 4-4
ቼልሲ 1-2 ዋርሳዋ
⚽ ኩኩሬላ ⚽ ፔክሀርት
ድምር ውጤት :- 4-2
ፍራንክፈርት 0-1 ቶተንሀም
⚽ ሶላንኬ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe