tikvahethiopia | Неотсортированное

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1527057

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Подписаться на канал

TIKVAH-ETHIOPIA

#ምላሽ

“ ተሳታፊዎችን በተመለከተ '90% የብልጽግና አባላት ናቸው' ብሎ ፓርቲው ያቀረበው በምን ማስረጃ ተመስርቶ እንደሆነ የማስረዳት ሸክም አለበት ” - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (አሕአፓ)፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ስላደረገው አጀንዳ ማሳባሰብና መረከብን በተመለከተ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ትችት አቅርቧል። 

አሕአፓ፣ “ኮሚሽኑ በአማራም ሆነ በሌሎች ክልሎች የሚያደርገው እንቅስቃሴ ውጤት ያመጣል ብለን አናምንም” ሲል ነው የገለጸው።

ፓርቲው፣ ይህን ያለው ከምን ተነስቶ እንደሆነ ስንጠይቀውም፣ “ ከተሳታፊዎች ልዬታ ጀምሮ ገለልተኛ የሆነ ሂደት የለውም፤ ማንን ነው የሚያሳትፈው? ብለን ስንመለከት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የብልፅግና ፓርቲ ተወካዮች/ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ሰዎች ናቸው ” ነበር ያለው።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በበኩሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

ለፓርቲው ትችት ምላሽ የጠየቅናቸው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደ ማርያም፣ “ተሳታፊዎችን በተመለከተ '90% የብልጽግና አባላት ናቸው' ብሎ ፓርቲው ያቀረበው በምን ማስረጃ ተመስርቶ እንደሆነ የማስረዳት ሸክም አለበት” ብለዋል።

አክለውም፣ “ያለምንም ማስረጃ እንደዚህ ዓይነቱን አስተያየት ማቅረብ ኃላፊነት ይሰማዋል ከሚባል ፓርቲ የሚጠበቅ አይደለም” ነው ያሉት።

" የወረዳ የተሳታፊዎች ልየታ የተካሄደው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት፣ በሃይማኖት ተቋማት፣ በኢትዮጵያ መምህራን፣ በኢትዮጵያ ዕድሮች፣ በኢትዮጵያ ሲቪል ማህረሰብ ተወካዮች የጋራ አስተባባሪነትና አስፈጻሚነት ነው" ብለዋል።

"ከእነዚህ ሆነ ከሌሎች አካላት በማስረጃ ተረጋግጦ የቀረበ ቅሬታ የለም። ኢሕአፓ አባል የሆነበት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤትም በዚህ ረገድ ያቀረበው ቅሬታ የለም" ሲሉም ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ ኮሚሽኑ ታጣቂዎችን ካለማሳተፍ አንፃር ከፓርቲው የተሰነዘረበትን ብርቱ ትችት በተመለከተስ ምን መለሱ?

“እንደሚታወቀው የምክክር ሂደት ሰላማዊ ሂደት ነው። ኮሚሽኑ በዚህ ሂደት እንዲሳተፉ ሁሉንም ነፍጥ አንግበው ጫካ የገቡትን ኃይላት በይፋ ጋብዟል። በአካል መገኘት የማይችሉ ከሆነ አሉን የሚሏቸውን አጀንዳዎች በሚያመቻቸው አግባብ እንዲልኩ ጠይቋል።

ከዚህም አልፎ ተርፎ የእርስ በርስ ፍጅቱ እንዲቆም ሁሉም ወገኖች ወደ ቀልባቸው ተመልሰው እንዲደራደሩ በየትኛውም አገር ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፍላጎቱ መሆኑን አሳውቋል።

ከዚህ ውጪ ሊደረግ የሚችል ነገር ካለ ሀገር የጋራ እንደመሆኗ መጠን ኢሕአፓም መፍትሄ የሚለውን ሃሳብ ይጠቁመን። በሀገር ጉዳይ አንዱ ተቺ ሌላው ተተቺ የሚሆንበት አግባብ የለም” ብለዋል።

ፓርቲው፣ “ከዚህ ቀደም ታጣቂዎችን ለማሳተፍ ምን አይነት ዋስትና ትሰጧቸዋላችሁ?” ብሎ ኮሚሽኑን ሲጠይቅ፣ ገና ስምምነት ላይ እንዳልተደረሰ እንደተገለጸለት፣ ይህ ሳይፈታ ምክክር ማድረጉ ለውጡ ምኑ ላይ እንደሆነ ላቀረበው ጥያቄ ምን ምላሽ እንዳላቸውም ኮሚሽነሩን ጠይቀናል።

እሳቸውም በምላሻቸው፣ “ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆናቸውን ሲያሳውቁ የሚፈልጉትን፣ ተቀባይነት ያለው ሕጋዊ ከለላና ዋስትና የሚመቻች ይሆናል” ነው ያሉት።

የታጣቂዎች አጀንዳ ሳይካተት ሙሉ አጀንዳ ተቀብያለሁ ማለት ይቻላል ወይ? ለሚለው ጥያቄም ኮሚሽነሩ፣ “አሁንም አልረፈደም በራችን ክፍት ነው መላክ ይችላሉ። ኑና አጀንዳ ውሰዱ የሚሉም ከሆነ አሉበት ድረስ ለመሄድ ፈቃደኞች ነን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ኮሚሽኑ ሰሞኑን አንድ የፋኖ አደረጃጀት አጀንዳ እንዳስገባ መናገራቸውን ተከትሎ፣ እውነትም ከፋኖ አደረጃጀት መካል ለኮሚሽኑ አጀንዳ ያስገባ አለ? ለሚለው ጥያቄ ኮሚሽነር መላኩ በምላሻቸው፣ “ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን በሰጡት ቃለመጠይቅ ታጣቂው ቡድን ስሙ እንዲገለጽ አለመፍቀዱን ገልጸዋል። ስሙ እንዲገለጽ ካልፈቀደ ደግሞ መብቱን ማክበር ግዴታችን ነው” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ዋልያዎቹን ሲያድኑ የተያዙ ተጠርጣሪዎች እስከ 12 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ይጠብቃቸዋል " - የአማራ ክልል ደን እና ዱር እንሳት ልማት ጥበቃ ባለስልጣን

ከ8 መቶ በላይ የነበረው የዋልያ አይቤክስ ዝርያ በ2016 ዓ/ም በተደረጉ የሁለት ዙር ቆጠራዎች 306 ብቻ መቅረታቸዉ መረጋገጡን የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፖርክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዚህም በሀገራችን ብርቅዬ እንሰሳ የሆነው ዋልያ የህልውና አደጋ ላይ መውደቁን የፖርኩ ኃላፊ አቶ ማሩ ቢያድግልኝ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ደንና ዱር እንሳት ጥበቃ ባለስልጣን ይህንኑ ስጋት ይጋራል። በቅርቡ በተደረገው ጥናት ቁጥሩ ከ300 በታች እንደሚሆንም ነው የገለጸው።

በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የዱር እንሳት ልማትና ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አበባው አባይነህ ምን አሉ ?

" በአካባቢው ያሉ አንዳንድ የታጠቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ዋልያውን አድነው ለምግብነት እያዋሉት ነው።

ከትላንትና በስቲያ ሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም ዋልያ ሲያድኑ ከነበሩት ግለሰቦች መካከል ሁለቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 353 ላይ ' ብርቅየ የዱር እንስሳትን የገደለ ' እስከ 12 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣ የተደነገገ ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎችም ይህው የእስር ቅጣት ይገጥማቸዋል።

ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ድርጊት በፓርኩ ውስጥ የፈፀመ አንድ ግለሰብ በ12 ዓመት እስር ተቀጥቷል።

ለዋልያዎቹ ቁጥር መቀነስ ከፀጥታው መደፍረስ ጋር በተያያዘ በህግ መላላት ምክንያት ህገ ወጥ አደን መስፋፋቱ  ዋነኛ ምክንያት ነው " ብለዋል።

የጃን አሞራ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ምን አለ ?

የጃን አሞራ አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም በወረዳው " ቧሂት " ተብሎ በሚጠራው የፓርኩ ክፍል ውስጥ በቡድን ተደራጅተው ዋልያ በጥይት በመግደል አርደው በአህያ እየጫኑ እያለ እንደተረሰባቸው ያስረዳሉ።

በዚህም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ከአዳኞቹ ጋር ባደረገው የተኩስ ልውውጥ ሁለቱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ ሶስቱ ማምለጣቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የድርጊቱ ፈፃሚዎች ከግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ በወንጀል የሚፈለጉ መሆናቸውንና ሲፈልጉ ወደ ፓርኩ በመግባት ወንጀል የሚፈፅሙ ሲያሻቸው ደግሞ " ፋኖ ነን " በማለት ታጣቂ ቡድኑ ወዳለበት በመግባት የሚያምታቱ ናቸው ብለዋል።

የተያዙት ተጠርጣሪዎችም አብረዋቸው የነበሩትን ጨምሮ በተመሳሳይ የአደን ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችን መጠቆማቸውን ገልጸዋል። ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድም እንቅስቃሴ ተጀምሯል ነው ያሉት።

በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘው ዋልያ ቁጥር የመቀነሱ ምክንያት የሰሜኑ የሀገሪቱ ጦርነት እና አለመረጋጋት ፣ በአካባቢው የተከሰተ ድርቅ፣ የደን ምንጣሮና አደን መሆናቸውን አደረግነው ባሉት ጥናት ማግኘታቸውን የጃን አሞራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማ ገልፀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyBahridar

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በቀጣይ 10 ቀናት እስከ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ ነው " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

➡️ " ወደ 242 ልጆች ነገ አርብ ከማይናማር ወደ ታይላንድ እንደሚገቡ ነግሮናል " - ኮሚቴው


የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በማይናማር በአስከፊ ሁኔታ የሚገኙ ወደ 700 የሚጠጉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገለጸ።

የሚኒስቴሩ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ እስካሁን ወደ 130 ዜጎች ከማይናማር መመለሳቸውን አስታውሰው፣ ቀሪዎቹን ኢትዮጵያውያንም ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

ቃል አቀባዩ በዚህም፣ " በቀጣይ 10 ቀናትም እስከ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

ኮሚቴው ሰሞኑን ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ " ያለውን የቁጥር መፋለሱን ኒው ዴልሂ ያለውንና የቶኪዮ ኢምባሲ ስለአለመገጣጠሙ  አንስተን " ነበር ብሏል።

" ‘ ምንም ችግር አያመጣም ዲኬቢኤ ያለው ስክሪንአውት ተደርጎ ወደ ታይላንድ መንግስት ስላልተላለፈ ነው። መጓጓዝ ይጀመር እንጂ የሚያስቸግር የለም ’ " እንዳለው ገልጿል።

የመመለስ ሂደቱን በተመለከተም፣ " ወደ 242 ልጆች ነገ አርብ ከማይናማር ወደ ታይላንድ እንደሚገቡ ነግሮናል። የነገን ቀን እየጠበቅን ነው " ሲል ኮሚቴው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ኮሚቴው፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ሀገራቸው በመመለስ የበኩሉን እንዲያደርግላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሲጠይቁ እንደነበር አመልክቷል።

" 'ይሄ አየር መንገድ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ነው። ከእነዚህ ልጆች መካከል ይህን አየር መንገድ የሚመራ ልጅ ሊፈጠር ይችላል' " የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ነግሮናል።

አየር መንገዱ፣ " 'የተቃጠለባቸውን ቲኬት፣ የሚቀጡትን ቅጣት በማኔጅመንት ወስነን እናነሳለን። ሚስተናገዱበትንም ሁኔታ እናመቻቻለን፣ ጨራሽ ትኬት የሌላቸውን ከኢንጂኦ ጋ ሆነን የተወሰነ ፐርሰንት አድርገን እናስተናግዳቸዋለን፤ ያ ካልሆነም ከመንግስት ጋር ተነጋግረን መፍትሄ እንፈጥራለን። ማንም እዛ አይቀርም ' " እንዳላቸውም ኮሚቴው  ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም ጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሲከናወን።

#ኤፍኤምሲ #ሰላምካቶሊክቲቪ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#KeneniAdugna

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ የችሎት ሂደትን እንዳይታደሙ በፍርድ ቤት ታገዱ።

ዛሬ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በፍቅረኛው ወጣት ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ህልፈት ተጠርጥሮ በምርመራ ሂደት ላይ የሚገኘው የአርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጉዳይ በታየበት ችሎት ነው ፍርድ ቤቱ መገናኛ ብዙሃን ችሎቱን እንዳይታደሙ ያገደው፡፡

በዛሬው ችሎት ፖሊስ የመገናኛ ብዙሃን በተለያዩ ጊዜያት “ የችሎቱን ውሎ በተደጋጋሚ አዛብተው ዘግበውታል ” በሚል የምርመራ ሂደቱ ላይ እክል በመፍጠራቸው በችሎቱ እንዳይታደሙ ጠይቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በችሎቱ የተጠየቁት የተከሳሽ ጠበቃ በፊናቸው ፖሊስ ያቀረበውን አቤቱታ እንደሚደግፉ ገልጸዋል፡፡

ችሎቱም ግራ ቀኙን ካደመጠ በኋላ " መገናኛ ብዙሃን ካሁን በፊት አንድ ጊዜ ተከሳሽ ለፋሲካ በዓል ወጥቶ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ጠይቋል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሟች የግል ማህደር (ዳይሪ) በተከሳሽ ጠበቃ እጅ ነው የሚገኘው የሚሉ የተዛቡና ሀሰተኛ ዘገባዎች ማቅረባቸው በችሎቱና በምርመራ ሂደቱ ላይ እክል እንደሚፈጥር በመታመኑ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች (ጋዜጠኞች) ችሎቱን እንዳይታደሙ " በሚል ብይን ሰጥቷል።

በዛሬው ችሎት የታደሙትን ጋዜጠኞችን በዳኛ ትዕዛዝ እንዲወጡ ተደርገዋል።

መጋቢት 01 ቀን ሌሊት ለመጋቢት 02 ቀን 2017 ዓ.ም. አጥቢያ የመኖሪያ ቤቷ ከሚገኝበት ህንጻ ወድቃ ህይወቷ ማለፉ በተሰማው በወጣት ቀነኒ አዱኛ ህልፈት በፖሊስ የተጠረጠረው ፍቅረኛዋ ድምጻሚ አንዱዓለም ጎሳ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ይገኛል።

የመረጃው ባለቤት ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “ ሪኤግዛም ተፈትነው ቢያልፉም ” ቴምፖ ማግኘት እንዳልቻሉ፣ በመጨረሻም በድጋሚ ትፈተናላችሁ እንደተባሉ፣ አሰራሩም ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ በድጋሚ መፍትሄ ጠየቁ።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በድጋሚ ባሰሙት ቅሬታ ፥ “ ኤግዚት ኤግዛም አምና ብንወድቅም ዘንድሮ ለስድስት ወራት ተዘጋጅተን ነው ለፈተና የቀረብነው። ተፈትነን ውጤታችንን አይተናል፤ የመውጫ ፎርምም ጨርሰናል። ዶክሜንት ስጡን ስንላቸው ግን ‘ታግዷል’ አሉን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ስንጠይቅም ‘ትምህርት ሚኒስቴር በሰኔ ትፈተናላችሁ ብሏችኋል’ አሉን። አምና ተማሪዎች ወደቁ ሲባል ለምን ? ብሎ ያልጠየቀ አካል ዘንድሮ ለምንድን ነው ተማሪዎች ያለፉት ብሎ እንዴት ሞራላችንን ያቆሽሻል ? " ብለዋል።

ተማሪዎቹ ችግር ካለ ሀሳባቸውን በነፃነት የሚገልጹበት መድረክ እንዲዘጋጅ ቢጠይቁም እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

" ሰሞኑን ተማሪ ከተማ ቤት ከተከራየበት በልዩ ኃይል እየተፈለገ እየታፈሰ እየታሰረ ነው። ከ7 እስከ 8 ተማሪዎች ሆነን ነው ቤት የተከራየነው " ብለዋል።

አብረዋቸው የተፈተኑት ዶክሜንት እንደተሰጣቸው የነሱ የታገደበት ምክንያቱን እንዳላወቁ ግን ሰኔ ወር ላይ ድጋሚ መፈተን እንዳለባቸው እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

" ማለፊያ ውጤት አምጥተን እያለ ሰኔ ላይ ድጋሚ የምንፈተንበት አሳማኝ ምክንያት ምንድን ነው ? ብሎ ጥያቄ ማቅረብ ቀርቶ ከግቢው አካባቢ፣ ከከተማውም አይዲ ይዘን ከተገኘን የ2012 እና 2013 ባች ተማሪዎች ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ነው የሚወሰዱት " ብለዋል።

" የመብታችንን ጥያቄ ልጠይቅ ባልንበት ወቅት ከ20 በላይ ተማሪዎች ታስረው የደረሱበት ያልታወቀበት፣ ከከተማም እየታፈሱ ተማሪዎች እየታሰሩ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ተማሪዎች ወዳልተፈለገ ፓለቲካ እየገቡ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎቹን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ዩኒቨርሲቲውና ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም።

ስለጉዳዩ የጠየቅነው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት የቀረበውን ቅሬታ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደተጋገረ ገልጾ፣ " ከትምህርት ሚኒስቴር ‘ታንጄብል የሆነ ነገር ስለያዝን ፈተናው ይደገማል’ በሚል ነው ይዘውት ያሉት " ብሏል።

አክሎ፣ " እኛም ታንጄብሉ ነገር ምን አይነት ነው? በሚለው እየተነጋገርን ነው ያለነው እንጂ እንዲደገም ተነግሯቸዋል " ነው ያለው።

ታዲያ የሚፈተኑ ከሆነ ዩኒቨርሲቲው የዶርም አገልገሎት እንኳ ሊሰጣቸው አይገባም ነበር ወይ ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽም፣ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው ጋር እንደሚወያይ፣ የታሰሩ ተማሪዎች ስለመኖራቸው ግን እንዳልሰማ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#YonatanBTFurniture

መጪው የትንሣኤ በአል በእርስዎ ቤት ውስጥ ልዩ ትርጉም ያለው የማይረሳ ይሆናል።
በአሉን ምክንያት በማድረግ በሁሉም የቤት እቃዎቻችን ላይ 💰ከ10% - 25%💰 እውነተኛ ቅናሸ ማድረጋችንን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን።
ይምጡ የወደዱትን የቤት እቃ የግልዎ ያድርጉ‼️
🎯ከ1984 ጀምሮ
🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላለቀሉ
Telegram 👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook 👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Instagram 👉 Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok 👉 yonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">TikTok/yonatanbtfurniture

📍አድራሻችን
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)

☎️ ይደውሉልን ፦ +251957868686 / +251995272727 / +251993828282

#YonatanBTFurniture

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ይጠቀሙበት የነበረው ዝነኛው ዳሽ ፋይፍ (5) ወይም ቡፋሎ አውሮፕላን ከ37 ዓመታት በኋላ ተጠግኖ የበረራ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደረገ።

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ፤ አውሮፕኑን ከተጣለበት ጥሻ አንስቶ ማደሱን ገልጿል።

ይህን አውሮፕላን ለመጠገን ከ1 ዓመት በላይ ጊዜ መውሰዱን የገለጸው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ለትራንስፖርት ፣ ለፓራሹት ዝላይ እና የካርጎ አገልግሎት መሥጠት ይችላል ብሏል።

የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱን ኃይለማርያምን ከሀገር ይዘው የወጡት በወቅቱ ኮፐይለት የነበሩት ካፒቴን ያሬድ ተፈራ በአንድ ወቅት ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ በሰጡት ቃለ ምልልስ ስለዚህ ዳሽ ፋይፍ (5) ስለተሰኘው አውሮፕላን ተናግረው ነበር።

ዳሽ ፋይፍ (5) ወይም ቦፋሎ አንድ ስያሜ ሲሆን ዲሃቪላንድ ካናዳ ከሚሰራቸው አውሮፕላኖች አንዱ እንደሆነ ጠቁመው ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዳሽ 6 እና ዳሽ 5 የተባሉ አውሮፕላኖች ነበሩት።

ሁሉም ዳሽ 6 አውሮፕላኖች የሀገር ውስጥ በረራ የሚካሄድባቸው የነበረ ሲሆን ዳሽ 5 የካርጎ፣ የመንገደኛ ፣ የቻርተር ኦፕሬሽን ይሰራበት ነበር። ዳሽ 5 ቁጥሩ 5 ስለሚል አነስተኛ ቢመስልም ከዳሽ 6 ይበልጣል በግዝፈት። ይህ አውሮፕላን በመንገደኛ ደረጃ 42 መንገደኛ የሚይዝ ነው።

አሰራሩም ዲዛይኑም የተለየ ሲሆን በጣም ትልቅ ሁለት ሞተር ነው ያለው። በጣም ለማረፍ አስቸጋሪ የሆኑ ሜዳዎች ላይ ያልተጠረጉ ሜዳዎች ላይ ማረፍ ይችላል። እንደ ወታደራዊ ኦፕሬሽንም የሚያገለግል ነው።

በአጭር የሆነ ራንዌይ ፣ ኮሮኮንች ላይ ፣ ሳር ባለው ሜዳ ላይ ማረፍና መነሳት ይችል የነበረ በጣም ጉልበት ያለው ስለነበር ሲሮጥ ሲንደረደር ቡፋሎ የተባለውን እንስሳ ይመስል እንደነበር አስረድተው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

Photo Credit - FDRE Defense Force

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#USA #CHINA

ቻይና እስከ 245% ሊደርስ የሚችል ታሪፍ እንደተጣለባት አሜሪካ አስታውቃለች።

ኋይት ሃውስ ባወጣው መግለጫ ቻይና አፀፋዊ እርምጃ በመውሰዷ እስከ 245% የሚደርስ ታሪፍ እንደተጣለባት ገልጿል።

በመግለጫው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት ከገቡ በኋላ የአሜሪካን ኢኮኖሚ ዳግም ለማሳደግ አሜሪካን ቀዳሚ ያደረገ የንግድ ፖሊሲ እየተከተሉ እንደሆነ የተመላከተ ሲሆን ከ75 በላይ ሃገራት ከአሜሪካ ጋር አዲስ የንግድ ስምምነት እንዲኖር ተወያይተዋል ብለዋል።

በውይይቶቹ የተነሳ በሃገራቱ ላይ የተጣለው ታሪፍ እንዳይተገበር የተወሰነ ስለመሆኑ ኋይት ሃውስ ገልፆ ቻይና ግን አፀፋዊ እርምጃ በመውሰዷ እንዲተገበርባት ሆኗል ብሏል።

ኋይት ሃውስ ጨምሮም ከወራት በፊት ቻይና እንደ ጋሊየም እና ጀርማኒየም ያሉ ወሳኝ የቴክኖሎጂ ቁሶች ወደ አሜሪካ እንዳይላኩ ከልክላለች ያለ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ ለመኪና ሰሪዎች፣ ለኤሮስፔስ እና ለወታደራዊ ግልጋልት የሚውሉ 6 የከበሩ ማዕድናትን ወደ ውጪ እንዳይላኩ ከልክላለች ብሏል።

ኋይት ሃውስ ቻይና በትክክል ምን ያህል መጠን ያለው ታሪፍ እንደተጣለባት ባይገልፅም አስከ 245% ሊደርስ እንደሚችል ገልጿል።

መረጃው የአናዶሉ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

📞 የድምጽ ጥቅል እንግዛ! በጉርሻ ደቂቃዎች እንንበሽበሽ! ከሳፋሪኮም ወደ የቴሌ የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎችን በመግዛት ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም 100% ጉርሻን እናጣጥም! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ማይናማር

“ ምርር ሲለን ለመውጣት ሞክረን አፈሙዝ ተደቅኖብን ተመልሰናል። ስጋታችን እየጨመረ ነው ” - ኢትዮጵያውያን በዲኬቢኤ ካምፕ

🔴 “ በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዲኬቢኤ አርሚ ተነጋግሮ ኒው ዴህሊ ላለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የልጆቹ ስም እንዲተላለፍ ማድረግ አለበት ” - ኮሚቴው

በማይናማር ዲኬቢኤ ካምፕ ያሉ 255 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከመንግስት  ምላሽ ባለመገኘቱ በራሳቸው ውሳኔ ወደ ታይላንድ ለመሻገር የወሰኑት ብሶት የወለደው ሙከራ ባለመሳካቱ፣ ባሉበት ካምፕ በከፋ ሁኔታ እንደሚገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ምን አሉ ?

ከእገታ ከወጡ በኋላ ከ45 ቀናት በላይ እንዳስቆጠሩ፣ ካሉበት ካምፕ በኃይል ለመውጣት ወደ ሀገር ለመመለስ የመንግስት ምላሽ በመዘግየቱ ወደ ቀድሞው አስከፊ ቦታ ትወሰዳላችሁ እየተባሉ እንደሆነ ገልጸዋል።

ግፉ ስለበዛባቸው ከትላንት በስቲያ ሻንጣቸውን ሰብስበው ከካምፑ ለመውጣትና ወደ ታይላንድ ለመሻገር ቢሞክሩም ጥበቃዎቹ እንደመለሷቸው፣ አሁንም መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያውያኑ፣ “ምርር ሲለን ለመውጣት ሞክረን አፈሙዝ ተደቅኖብን ተመልሰናል። ስጋታችን በጣም እየጨመረ ነው” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

255ቱ የሚሆኑት ዜጎች “ከካምፕ ወጥተን እንደሆን እንሁን” ብለው በምሬት በማይናማሩ ካምፕ ወደ ታይላንድ ለመሻገር እንደሞከሩ፤ በዚህም “ተመለሱ” ተብለው አፈሙዝ ጭምር እንደተደቀነባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

“ ከፍቷቸው ነው ሻንጣቸውን ሰብስበው ብንሞትም እንሙት ብለው ተሰባስበው የወጡት። መሳሪያ ሲደቅኑባቸቅ ነበር” ሲልም አስረድቷል።

“ አሁንም ቢሆን በቶኪዮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው ጉዳዩ የሚመለከተው። ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአስቸኳይ ከዲኬቤ አርሚ ጋር ተጋግሮ ኒው ዴህሊ ላለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የልጆቹ ስም ዝርዝር እንዲተላለፍ ማድረግ አለበት ” ሲልም መፍትሄውን ጠቁሟል።

ኢትዮጵያውያኑን ለማምጣት የኢትዮጵዬ አየር መንገድ ቃል እንደገባለት፣ የ495 ልጆች የመመለስ ጉዳይ ተስፋ ባለው ሂደት ላይ እንደሆነ፣ የቀሪዎቹ 255 ልጆች ስም ዝርዝርም ወደሚመለከተው አካል እንዲላክ አሳስቧል።

የታይላድ ባለስልጣናት ካልፈቀዱ ልጆቹ ወደ ታይላንድ ለመሻገር ብሊ ጥበቃዎቹ እንደማይፈቅዱላቸው የገለጸው ኮሚቴው፣ “ኒው ዴህሊ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቶኪዮ ያለፍ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አይናበቡም ” ብሏል።

“ የ725 ዜጎች ዝርዝር ተላልፎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይዞት እያለ፤ ኒውዴይሊ ያለው የ495 ዜጎች ስም ዝርዝር  ብቻ ሲሆን፣ 255 ዜጎቼ የት ገባ? ብለው መነጋገር ነበረባቸው። አሁንም በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ መፍትሄ ያሰጥልን ” ሲል አሳስቧል።

“ ኤምባሲዎች በቁጥጥሩ ሥር ነው ያሉትና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን ሊጠይቅልን ይገባል። ፓስፓርታቸውን የተቀሙ፣ የጉዞ ሰነድ የሌላቸው ልጆቻችን አሉ ” ብሎ፣ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲያስተካክል ጠይቀል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvaethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ዋሪት ፈርኒቸር !

ክቡራን ደንበኞቻችን! መጪው በዓል የሰላም፤የፍቅር እና የስኬት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ከልብ እየተመኘን፡ ምቾታቸውን እና ጥራታቸውን  የጠበቁ ምርቶቻችንን በሁሉም  የማሳያ ቅርንጫፎቻችን ከልዩ ቅናሽ ጋር አዘጋጅተን እንጠብቅዎታልን!

ወደ ማሳያ ክፍሎቻችንን በመምጣት ይጎብኙን !
* 22 - ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* አዳማ - ሶረቲ ሞል * ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት * ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
*ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706 / 07

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አሽከርካሪ እንደ ቢሮ ሠራተኛ ጠዋት ወጥቶ አመሻሽ ከ11፡00 ሰዓት በኋላ እንዳይቀሳቀስ እየተገደበ ነው " - የጣና አሸከርካሪዎች ማኅበር

በሀገሪቱ የተለያዩ ሥፍራዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ዕገታዎችና ግድያዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሽከርካሪዎችና የታጋቾች ቤተሰቦች ጥያቄ አቅርበዋል።

ባለፈው ወር መጋቢት 8/ 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ልዩ ስሙ " አሊዶሮ " በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል ሲጓዝ በነበረ " ፈለገ ግዮን " የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ እገታ መፈፀማቸውና አብዛቹ ተጓዦች ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል።

ታፍነው ከተወሰዱበት ዕገታ፣ አንድ ሚሊዮን ብር ከፍለው ስለተመለሱ አክስታቸው  የተናገሩ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የደጀን ከተማ ነዋሪ፣ " ዕገታ ዜጎችን እያማረረ ነው " ብለዋል።

ታጣቂዎቹ አክስታቸው እንዲለቀቁ 1.5 ሚሊየን ብር ጠይቀው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ዕገታው መፈጸሙን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከደጀን ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት አጽፈው ገንዘብ በማሰባሰብ 1 ሚሊየን ብር አዘጋጅተው ለታጣቂዎች በባንክ አስገብተው አክስታቸው ከታገቱ ሁለት ሳምንት በኋላ እንደተለቀቁላቸው ገልጸዋል።

ሁለት ወንድሞቹ የታገቱበት የክልሉ ነዋሪ ደግሞ እስካሁን እንዳልተለቀቁ ተናግሯል።

ታጣቂዎች ለወንድማማቾቹ ከ2.5 ሚሊየን ብር በላይ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

እስካሁን 450,000 ብር ተሰብስቦ ለታጣቂዎቹ እንዲደርስ ቢደረግም፣ ቀሪውን ክፍያ ካልከፈሉ እንደማይለቀቁ ተነግሯቸው እንደገና እየሰበሰቡና ሁኔታውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አስረድቷል።

ሆኖም የኑሮ ሁኔታው አስቸጋሪ መሆንና የታጋቾች መብዛት ገንዘብ ለመሰብሰብ መሰላቸት እንደፈጠረ አክሏል።

" አሁን ማንም ሰው ምን ማድረግ ይችላል ? የዕገታ ሁኔታ አስቸጋሪ ሆኗል " ብሏል፡፡


የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ ምን አሉ (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

" የሚያሠጉ ቦታዎች በምንላቸው በተለይ በኦሮሚያ ክልል የወለንጭቲ መስመር እኛም ክትትል ስናደርግ በፀጥታ አካላት በፓትሮል ሲጠበቅ አይተናል፡፡ ነገር ግን በሆነ ቅጽበት ችግሩ እየተፈጠረ ነው።

ለአብነት በቅርቡ ወለንጪቲ ማደያ ላይ አንድ አሽከርካሪ በታጣቂዎቸ ተገድሏል።

በተመሳሳይ በቅርቡ ከሱሉልታ ወደ ፍቼ በሚወስደው መስመር ሁለት አሽከርካሪዎች ታግተውብናል።

ሆኖም ከ2015 ዓ.ም በፊት ይፈጸም ከነበረው ዕገታና ግድያ አንፃር አሁን ድርጊቱ በመጠን እየቀነሰ መጥቷል።

ለአብነት ያህል መሳቀቅ ይበዛባቸው በነበሩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ድርጊቶች ቀንሰዋል ፤ ማህበሩም ይሄን ያምናል " ብለዋል።

ጋዜጣው ድርጊቱ መቀነሱን ገምግማችኋል ወይ? ባለፉት 2 ዓመታት እየቀነሰ መጥቷል ስትሉስ በምን ዓይነት ንፅፅር ላይ ተመሥርታችሁ ነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር።

አቶ ሰለሞን " ከ2015 ዓ.ም. በፊት በቀን 20 እና 30 የሚደርሱ አሽከርካሪዎች ይታገቱ ነበር፣ አሁን ግን ድርጊቱ እየቆየ እንደሚፈጸም እያየን ነው " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

" በአጠቃላይ ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ የተረጋገጠ ከ120 በላይ የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ተገድለዋል፡፡ ከሁሉም አካባቢዎች የተረጋገጠ መረጃ ስለማይመጣልን እንጂ፣ ቁጥሩ ከዚህ ከፍ የሚልበት ዕድል አለ " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ማኅበሩ ፤ " የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኦሮሚያ ክልልና የፀጥታ አካላትን ስንጠይቅ ምላሽ ይሰጡናል። ነገር ግን ችግሩ ያለው የከተማ አስተዳደሮች ላይ ነው፡፡ ከቀናት በፊትም ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በድጋሚ ደብዳቤ አስገብተናል " ሲል ገልጿል።

" በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ ግን አስቸጋሪ ስለሆነ በክልሉ ድንገተኛ ክስተቶች ይፈጠራሉ፡፡ ይኼ ነው ብለን ሐሳብ የማንሰጥበት ችግር ነው ያለው " ብሏል፡፡

የጣና አሸከርካሪዎች ማኅበር ዋና ጸሐፊ አቶ ሰጡ ብርሃን ምን አሉ  (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

" የእገታ ድርጊቱ እየቀነሰ ሳይሆን እየጨመረ ነው። ድርጊቱ ቀነሰ የሚባል ሳይሆን እየጨመረ ነው፡፡ በተለይ ዕገታ እየተለመደና ጭካኔዎች እየበዙ ናቸው።

ከዚህ በፊት ለ24 ሰዓት በነፃነት እንጓዝ ነበር፣ አሁን ግን እንቅስቃሴያችን የተገደበ ሆኗል፡፡ አሽከርካሪ እንደ ቢሮ ሠራተኛ ጠዋት ወጥቶ አመሻሽ ከ11፡00 ሰዓት በኋላ እንዳይቀሳቀስ እየተገደበ ነው፡፡

የትራንስፖርት ዘርፉ ግን በዚህ ሁኔታ መሥራት አይችልም፡፡ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የራሱ የሆነ ተዕፅኖም ይኖረዋልም

የችግሩን ጥልቀትና አሳሳቢነት በተመለከተ ለፌዴራል፣ ለአማራ፣ ለኦሮሚያና ለአፋር ክልሎች ደብዳቤ አስገብተናል፤ ተነጋግረናል። ዘላቂ መፍትሔ ግን አለመገኘቱን አልተገኘም " ብለዋል።


የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ምን አሉ (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ ዋና ዋና መንገዶችን ተከትሎ በትራንስፖርት ተጠቃሚ ዜጎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የዕገታ እና የግድያ ድርጊቶች ቁጥጥርን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ጄይላን አብዲ ፦

" ዕገታ የተለመደ ወቅታዊ ድርጊት (ፋሽን) እየሆነ መጥቷል፡፡ ለኅብረተሰቡ እንግዳ ነበር፣ አሁን ግን ሚዲያው እያስፋፋው ይገኛል፣ ስለዚህ በልኩ ነው መገለጽ ያለበት።

' ዕገታ እዚህ ቦታ ላይ ተፈጸመ፣ ተፈጠረ ማለት አይጠቅምም ' በአጋቾች ላይ ምን ዓይነት ዕርምጃ ተወሰደ የሚለው ነው ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት፡፡

ዕርምጃ ሲኖር ለሕዝብ እናሳውቃለን " ብለዋል።


ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት የሆኑትን ፦
➡️ ከበሮ፣
➡️ ጸናጽል፣
➡️ መቋሚያና እንዲሁም ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች መመዝገባቸውን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዜማ ንዋያተ ቅዱሳቱ እና ቅዱሳት መጻሕፍቱ ተመዝግበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆናቸው ከባለሥጣኑ በወጣው ደብዳቤ መረጋገጡን ገልጻለች።

መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የበዓል ገበያዉ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ መሸመት ከአቅማችን በለይ ሆኗል " - የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች

➡️ " በዓሉን ታሳቢ በማድረግ  በቂ ምርት ለማቅረብ ተሞክሯል " - የከተማዉ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ


መጪዉን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በሁሉም ምርቶችና ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ጭማሪ ማስተዋላቸዉን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ " በቀናት ልዩነት ዉስጥ በእያንዳንዱ የሸቀጥና ሌሎች ለበዓሉ አስፈላጊ የሚባሉ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል " ብለዋል።

ለአብነትም ፦
- እንቁላል ከ13 እና 15 ወደ 20 ብር
- ሽንኩርት በኪሎ ከ45 ወደ 70 እና 80
- ቅቤ በኪሎ ከ800 ወደ 1000 ብር
- ቲማቲም በኪሎ ከ40 ወደ 65
- ዶሮ አንዱ ከ500-650 ወደ
850-1000
- ስኳር በኪሎ ከ110 ብር ወደ 650 ብር
- በርበሬ በኪሎ ከ600 ወደ  800 ብር
- ዘይት የሚረጋ የሚባለው
             ° 20 ሊትር ከ4500 ወደ 6200
             ° 5 ሊትር ከ1200 ወደ 1600
             ° 3 ሊትር ከ800 ወደ 1050
- ዘይት ባለ ሃይላንድ
             ° 5 ሊትር ከ1400 ወደ 1750
እየተሸጡ መሆኑንና የጤፍ እና የምስር ዋጋ በአንፃሩ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ ማሳየቱን ገልፀዋል።

አስፈላጊዉ ቁጥጥር ካልተደረገ እስከ በዓሉ መዳረሻ ቀናት የዋጋ ጭማሪዉ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል የሚናገሩት ሸማቾቹ በበዓሉ ዋዜማ ቀናት ዋጋ ለመጨመር ምርት የሚሰዉሩና እያሉ " የለም " የሚባሉ ሸቀጦችና ምርቶች ስለመኖራቸዉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " ለበዓሉ አስፈላጊ የሚባሉ ልዩ ልዩ የጥራጥሬ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የሸቀጥና ቅመማ ቅመሞች እጥረት እንዳይኖር በማህበራት ዩኒየኖች አማካኝነት በቂ ምርት ለማቅረብ ተሞክሯል " ያለ ሲሆን " የዋጋ ጭማሪዎች እንዳይኖር አስፈላጊውን የቁጥጥር ስራ እያከናወንኩ ነዉ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸዉ አንዳንድ ጅምላ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማህበራት የተወሰኑ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ምርት የማሸሽና በየመደበቅ ስራ እየሰሩ መሆኑንና ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ብቻ መሸጥ የሚገባቸዉ ማህበራትም ለቸርቻሪ ነጋዴዎች እያሰራጩ መሆኑን ገልፀው ቁጥጥር እና ክትትሉ ካልተጠናረ የበዓል ገበያዉ ከዚህም በላይ ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ጭማሪ ሊታይበት ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ የአማራ ክልል ተወላጅ ሆነው ያለአግባብ ለታሰሩ ሰዎች ድምፅ ያልሆነ ኮሚሽን ታጣቂዎችን ወደ ጠረንጴዛ አምጥቶ ያወያያል የሚል እምነት የለንም " - ኢሕአፓ

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 4 ቀን 2017 ዓ/ም በአማራ ክልል ከተለያዬ ባለድርሻ አካላትና የማህበረሰብ ተወካዮች ለዋናው ጉባዔ የሚሆኑ አጀንዳዎችን መረከቡ ይታወቃል።

ኮሚሽኑ በክልሉ ያደረገውን ይህንኑ ሂደት ተከትሎ፣ በተለይ የታጠቁ ኃይሎችን ካለማሳተፍ አንፃር ከኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ብርቱ ትችት ተሰንዝሯል።

ፓርቲው፣ የኮሚሽኑን በባሕር ዳር ከተማ የአጀንዳ ማሰባሰብ ልየታ ሂደት በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ታጣቂዎችንና ጥያቄ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ያላሳተፈ ነው ” ሲል ተችቶታል።

የፓርቲው ዋና ፀሐፊ ወ/ሪት ምስጢረስላሴ ታምራት ምን አሉ ?

“ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ታጣቂዎችን አሳትፌያለሁ ብሏል፣ እነማን እንደሆኑ ግን ግልፅ አልተደረገም። ተሳትፈዋል ተባለ እንጂ አመኔታ የለውም። 

የአማራ ክልል ተወላጅ ሆነው ያለአግባብ ለታሰሩ ሰዎች ድምፅ ያልሆነ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ታጣቂዎችን ወደ ጠረንጴዛ አምጥቶ ያወያያል የሚል እምነት የለንም።

በኮሚሽኑ ገለልተኛነት አመኔታ የለንም።

ከዚህ በፊት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ያሉ ታጣቂዎችን ለማሳተፍ ምን አይነት ዋስትና ትሰጧቸዋላችሁ ? ብለን ስንጠይቅ ኮሚሽኑ በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ገና ለስምምነት ላይ አለመድረሱን ነው የነገረን፣ ይሄን ሳይፈቱ ምክክር ማድረግ ምኑ ላይ ለውጥ እንዳለው ግልጽ አንደለም።

ከታጣቂዎቹ ‘ተሳትፈናል’ የተባለ ነገር የለም። ኮሚሽኑ ‘አሳትፈናል’ ካለ ተወካዮች እነማን ናቸው? ሊዘረዝር ይገባል፣ ካልሆነ አሁንም ፓርቲያችን ጥያቄ አለው።

አሁንም ድረስ የክልሉ የህዝብ እንደራሲዎች፣ ወንጀልን የሚያጋልጡ ጋዜጠኞች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም ህዝብ ይወክለናል ያላቸው የምክር ቤት አባላት በእስር ላይ ናቸው።

መንግስት ‘ህገወጥ ናቸው’ ብሎ የፈረጃቸውን ታጣቂዎች ሊያሳትፍ ይቅርና ለታሰሩ ንጹሐን ዜጎች ሰፊ ድምፅ መሆን ያልቻለ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ታጣቂዎችን ወደ አንድ ጠረንጴዛ አምጥቶ ያወያያል የሚል እምነት የለንም።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች ክፍሎች በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውጤት ያመጣል ብለን አናምንም ” ብለዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ውጤት አያመጣም ያሉት ከምን አንፃር እንደሆነ የጠየቅናቸው  ፀሐፊዋ፣ “ ከተሳታፊዎች ልየታ ጀምሮ ገለልተኛ የሆነ ሂደት የለውም፤ ማንን ነው የሚያሳትፈው? ብለን ስንመለከት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የብልፅግና ፓርቲ ተወካዮች/ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ሰዎች ናቸው ”  ሲሉ መልሰዋል።

“ አሁንም ቢሆን የሚወያየው ከራሱ ፓርቲ ጋር ከሆነ በዝግ መወያየት ይችላል። ነገር ግን ‘ሀገርን አመካክራለሁ’ ካለ መሳተፍ ያለበት የፓለቲካ ልዩነት፣ ከታሰሩ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ከህዝብ ተወካዮችና ልዩነት ካላቸው ሰዎች ጋር ” መሆን እንዳለበት አስተዋል።

አክለውም፣ “ ኮሚሽኑ ግን ይሄን አድርጓል? ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ ነገር ነው። ይሄ ሁሉ ባለሆነበት ሁኔታ በአማራ ክልል ብቻም ሳይሆን በየትኛውም ክልል ኮሚሽኑ የሚያደርገው ምክክር ውጤታማ ይሆናል ብለን እንደፓርቲም ሆነ እንደግለሰብ  አናምንም ” ነው ያሉት።

(ኮሚሽኑ ከፓርቲው ለተነሳበት ትችት ምላሽ የሰጠ ሲሆን በቀጣይ ይቀርባል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba : በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረውን የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ አገልግሎት ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ ውሳኔ ሃሳብ ላይ ካቢኔው ውሳኔ አሳለፈ።

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

ከነዚህም አንዱ ተቋርጦ የነበረዉ የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን የሚመለከት ነበር።

በዚህም አገልግሎቱን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ ማሳለፉ ተነግሯል።

ሌላኛው ፦
- የብርሃን አይሰውራን፣
- የመነን
- የገላን ቦርዲንግ ትምህርት ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃ እና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩ እና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማዉ ትምህርት ቢሮ እንዲሆን የቀረበዉን ደንብ መርምሮ አጽድቋል።

ካቢኔው ሀገራዊ ፋይዳ አላቸው ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም ጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲከናወን።

#ኤፍኤምሲ #EOTCTV

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

መቅረዝ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!


የላቀ ክብር ለፕሮፌሰሮች

ላለፉት ሁለት ድንቅ የስራ ዓመታት በተሰጣቸው ሙያዊ ጸጋ በታማኝነት ፣ በብቃት እና በጥራት ህዝባችንን እያገለገሉ የሚገኙትን ፕሮፌሰሮቻችንን ስለማይተካው መልካም አገልግሎታቸው ከልብ እያመሰገንን ፤ በሚመጣው ሚያዚያ 23 እስከ 25 ድረስ እናንተን ለማገልገል ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡

- ፕሮፌሰር ጌታሁን መንግስቱ - የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስትና የነርቭና ራስ ህመም ህክምና ስፔሻሊስት
- ፕሮፌሰር ድላየሁ በቀለ -የማኅጸን እና ጽንስ ስፔሻሊስት እና የሽል ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት
- ፕሮፌሰር ማህተመ በቀለ -የጠቅላላና፣ የትልቁ አንጀትና ፊንጢጣ ቀዶ ህክምናና የንቅለ ተከላ ሰብ ስፔሻሊስት

እነዚህ አንቱ የተባሉ ፕሮፌሰሮቻችን እናንተን ለማገልገል ሙሉ ቀን ይጠብቋችኋል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉ።
የሚገባዎትን ጥራት ያለው ህክምና ያግኙ!!

መቅረዝ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!
Instagram | Facebook |meqrezhealthservices">Tiktok |Linkedin |Website

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ራሳችንን ለአዲሱ የታሪፍ ስርዓት በሚገባ ለማዘጋጀት፣ የ90 ቀናት የእፎይታ ጊዜው እንደሚራዘም ተስፋ እናደርጋለን” - ማሕሙድ ዓሊ ዩሱፍ

የአፍሪካ ሕብረት በአሜሪካ በተጣለው አዲስ ቀረጥ ላይ ስጋቱን ገለፀ።

የአፍሪካ ህብረት፣ የፕረዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአፍሪካ ሀገራት ላይ የጣለው አዲስ ቀረጥ እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ ዓሊ ዩሱፍ፣ ፕረዝደንት ትራምፕ ያኖሩት አዲስ ታሪፍ/ቀረጥ፣ በአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

“ አሜሪካ በአፍሪካ ምርቶች ላይ የጣለችው አዲስ ቀረጥ፣ የአባል ሀገራቱን ኢኮኖሚ ያዳክማል ” በማለትም አክለዋል፡፡

ፕረዝደንት ትራምፕ ያሳለፉት አዲስ የቀረጥ ውሳኔ፣ ከቻይና በስተቀር፣ በሌሎች ሀገራት ዘንድ ከሶስት ወራት በፊት እንዳይተገበር፣ ወይም ለ90 ቀናት ሳይተገበር እንዲቆይ አዘዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበሩ ማሕሙድ ዓሊ ዩሱፍም ፤ የአፍሪካ ሀገራት ውሳኔውን ለመተግበር በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ፣ ለ90 ቀናት እንዳይተገበር የተላለፈው ውሳኔ፣ ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቀዋል፡፡

“ ራሳችንን ለአዲሱ የታሪፍ ስርዓት በሚገባ ለማዘጋጀት፣ የ90 ቀናት የእፎይታ ጊዜው እንደሚራዘም ተስፋ እናደርጋለን ” ሲሉም ገልፀዋል ሊቀመንበሩ፡፡

የፕረዝደንት ትራምፕ አዲስ የቀረጥ ፖሊሲ፣ በተለይም እ.ኤ.አ ከ 2000 ዓ.ም ጀምሮ የአገዋ ዕድል ተጠቃሚዎች የሆኑ 32 የአፍሪካ ሀገራትን ይበልጥ ሊጎዳ እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡    

የአፍሪካ ሀገራት፣ እንዲህ ዓይነት ችግሮችን ለመቋቋም እንዲችሉ፣ የታሪፍ ከለላዎችን የማስወገደውን የአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ስምምነትን (AfCFTA) ትግበራ እንዲያፋጥኑም ሊቀመንበሩ በአፅንኦት ጠይቀዋል፡፡

የአህጉራዊው የነፃ ንግድ ስምምነት መተግበር፣ ከሌላው ክፍለአለም የሚመጡ መሰል ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ያስችላል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት፣ አህጉራዊውን የነፃ ንግድ ስምምነትና ሌሎችም አሰራሮችን በመጠቀም፣ እንዲህ ዓይነት ተግዳሮቶችን ወደ እድል እንዲቀይሩም ጠይቀዋል፡፡

የአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ስምምነት፣ (AfCFTA) የአፍሪካ ህብረት እስከ 2063 ዓ.ም ድረስ ሊያሳካቸው ካነገባቸው አጀንዳዎች አንዱ ሲሆን፣ በተሳታፊ ሀገራት ብዛት፣ ከአለም ትልቁ የነፃ ንግድ ቀጣና እንደሆነ ይገለፃል፡፡

የነፃ ንግድ ቀጣናው፣ የአህጉሪቱን 1.4 ቢሊዮን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግና የአፍሪካ ሀገራትን በንግድ ግንኙነት የሚያስተሳስር እንደሆነም ይነገራል፡፡

የነፃ ንግድ ስምምነቱ፣ 90 ከመቶ በሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ምርቶች ላይ የሚጣሉ ቀረጦችን ሙሉ በሙሉ የማንሳት እቅድ ይዟል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

“ ገንዘብ የማይቀጣ በእስር ይለወጥለታል። በእስር የማይቀጣ ደግሞ አጭር የሆነ የሰውነት ማሟሟቂያ ቅጣቶችንም ይቀጣል ” - ባለስልጣኑ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 ዓ/ም የዘጠኝ ወራት ሪፓርት ግምገማን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም፣ “ ከአምናው ዘጠኝ ወር ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው የዘጠኝ ወሩ አፈጻጸማችን 64% የደንብ ጥሰት የቀነሰበት ነው ” ብሏል።

ይህን ያሉት የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ በመንገደኞች ላይ የሚጣለውን ቅጣት ተመጣጣኝ አለመሆን በተመለከተ ስለሚነሳው ቅሬታ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን መለሱ ?

“ ህጎች፣ ደንቦች የሚወጡበት የህዝቡን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው። ሌላ ተልዕኮ የለውም። እንደ ራሳችን ሰውነት፣ ልብስ የምንከባከብበት ቱሩፋታችን ነው ማለት ይቻላል የኮሪደር ልማቱ።

በሳይክል መንገድ የሚሄድ ሰው በሳይክል መንገድ እንዲሄድ ፤ እግረኛውም በእግረኛው መንገድ እንዲሄድ የተደረገበት፣ በሳሮች፣ ፋውንቴሽኖች አካባቢ ቆሻሻ እንዳይጣል የተደረገበት በርካታ ስልጠናዎች ተሰጥዋል።

ቀጥሎ ህግ የማስከበር ሥራ ስራ ነው። ቅጣቱ የዚህን ያህል የጎላምና በጣም የከፋም አይደለም። የቅጣት ደረጃዎች አሉ።

ገንዘብ የሚቀጣ ይቀጣል። ገንዘብ የማይቀጣ በእስር ይለወጥለታል። በእስር የማይቀጣ ደግሞ አጭር የሆነ የሰውነት ማሟሟቂያ ቅጣቶችንም ይቀጣል።

አህያ በኮሪደር ላይ መንዳት (በተለይ በቪአይፒ መንገዶች ከቦሌ እስከ ቤተ መንግስት ሌሎችም አካባቢዎች ላይ) ተቀባይነት የሌለው ነው። 

ማህበረሰቡም ሚዲያዎችም እንዲያውቁት የምንፈልገው በከተማችን ውስጥ ምንም አይነት የእንስሳት ዝውውር የማይፈጠርባት ከተማን ከመፍጠር አንፃር አጠንክረን የምንሰራበት ይሆናል። 

የቀጣናቸውም ቅጣቶች እንደሚባለው ሳይሆን በሁለት፣ ሦስት (በቦሌ፣ በጊዮርጊስ የፈጸምናቸው) አካባቢዎች አሉ። እሱም ደግሞ የተጋነነ ቅጣት አይደለም ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት ነው። ግን ወደ ፊት አጠናክረን የምንሄድበህ ይሆናል ” ብለዋል።

ከወንዝ ዳር ልማት ጋር በተያያዘ ትላልቅ ተቋማትና ፋብሪካዎች ይቀጣሉ፣ ሁልጊዜ ግንዛቤ እየተፈጠረላቸው ነው ይባላል፤ ግን በመቶ ሺዎች፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይቀጣሉ ምክንያቱ ምንድን ነው ? የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸዋል።

ሻለቃ ዘሪሁን ምን መለሱ?

“ የደንብ ቁጥር 181 የወንዝ ዳርቻ ደንብን በተመለከተ ተቋማችን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ ከአረንጓዴና ውበት ቢሮና ከመንገዶችና ውሃ ባለስልጣን ጋር በመሆን አብረን ነው እየሰራን ያለነው። 

በወንዝ ዳርቻ ላይ በርካታ ግንዛቤዎች ተሰጥተዋል። አንደኛ ጥናቶች ተጠንተዋል። ትላልቅ የሚባሉ ሰባት ወንዞች አሉ። በተለይ ፍሳሾችን ወደ ወንዝ የሚገቡበት ሁኔታ አለ። ያ ተጠንቷል። በተጠናው መሠረት ተጋላጭ ናቸው የተባሉ የመንግስት የግል ተቋማትና የግለሰብም ጭምር ግንዛቤ ተሰጥቷል።

ግንዛቤ የመስጠት ችግር የለም። ሰው ያንን ተቀብሎ የመተግበር ችግር ነው። የምናስተካክለው ህግን በማስከበር ነው ማለት ነው። ስለዚህ ህግን በማስከበር በርካታ ርቀቶች ሂደናል። 

በፋብሪካዎች፣ በትላልቅ የመንግስትም ሆነ የግል ሆስፒታሎች የሚወጡ ፍሳሾች አደገኝነታቸው በናሙና ይወሰዳል፣ በላብራቶሪ ተረጋግጦ እንደአደገኝነቱ መጠን በደንቡ ላይ የተቀመጠ የህግ መቀጮ ስላለ በዚያ መሠረት ይቀጣል።

በዚህ ያገኘነው ውጤት፥ ወደ 2,850 በላይ ወደ ወንዙ የሚገቡ ከተለያዩ ተቋማት የሚፈሱ ፍሳሾች ቆመዋል። የራሳቸውን ስፍቲ ታንከር የመስራት ለውጥ አለ ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቤተክርስትያኒቱ ንዋያተ ቅዱሳት ባልተገባ ቦታዎች ላይ በመታየታቸው ነው ማስመዝግቡ አስፈላጊ የሆነው " - ቤተክርስቲያኗ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ከበሮ ፣ ጸናጽል ፣ መቋሚያ እንዲሁም ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት ይገኙበታል በአዕምሯዊ ንብረትነት አስመዝግባለች።

ቤተክርስቲያኗ " ቅርሶቹን በአዕምሯዊ ንብረትነት ማስመዝገብ አስፈላጊ የሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቤተክርስትያኒቱ ንዋያተ ቅዱሳት ባልተገባ ቦታዎች ላይ በመታየታቸው ነው " ብላለች።

መላከ ሰላም ቀሲስ ዳዊት ያሬድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የቅርሳቅርስ ጥበቃ፣ ቤተ መጻሕፍትና ወመዘክር እንዲሁም ሙዚየም መምሪያ ዋና ኃላፊ ናቸው።

ኃላፊው ቤተ ክርስትያኗ ቀደምት የእምነት ተቋም በመሆኗ " በርካታ የአምልኮ መፈፀሚያ ንዋየ ቅዱሳት ባለቤት ናት " ብለዋል።

ቤተ ክርስትያኗ የእነዚህን ቅርሶች የባለቤትነት ማረጋገጫ ለማውጣት ንዋያቱ ከየት መጡ፣ ማንነታቸው ምንድን ነው የሚለውን ስታስጠና ቆይታለች ብለዋል።

የባለቤትነት መብት ሕጋዊ ማረጋገጫ የመያዙ ዋነኛ አስፈላጊነትን በተመለከተም ፥ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ - ባለመረዳትም ሊሆን ይችል ይሆናል፤ የቤተክርስትያኒቱ ንዋየ ቅዱሳት ባልተገባ ቦታዎች ላይ የመታየት ሁኔታዎች እየተፈጠሩ በመምጣታቸው ነው። " ብለዋል።

የአእምሯዊ ንብረት መብት ከተረጋገጠላቸው ከቤተክርስቲያኒቱ የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት መካከል ፦
- ከበሮ፣
- ጸናጽል፣
- መቋሚያ
- መስቀሎች ጨምሮ 10 ልዩ ልዩ ማለትም የድጓ፣ የዝማሬ፣ የመዋሲት፣ የቅዳሴ መጻሕፍት የሚገኙበት ሲሆን ቤተክርስትያኒቱ " በአግባቡ ተመዝግበው የማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱ እጄ ላይ ደርሷል " ብላለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በቀጣይ ለሌሎች መጻሕፍት ፣ ለኪነ ሕንፃዎች ፣ ለአልባሳት እና ለቅዱሳት ሥእላት ጭምር የአዕምሯዊ ባለቤትነት መብት ለማውጣት ጥረት ላይ መሆኗን ይፋ አድርጋለች።

አዕምሯዊ ንብረት ምንድን ነው ? ያንብቡ https://telegra.ph/DW-04-16

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ መመሪያው፣ የቤት ሰራተኞች መሰረታዊ መብቶቻቸው ተጠብቀውላቸው እንዲሰሩና፣ ጉልበታቸው ሲደክምም እንደ ጡረታ ያሉ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላል ” - የቤት ሰራተኞች ማህበር ህብረት

የቤት ሰራተኞችን የጡረታና የሌሎችም ማህበራዊ ዋስትና አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ የስራ ቅጥር ውልና መመሪያ በቅርቡ እንደሚወጣ፣ አንድነት የኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ማህበር ህብረት አስታወቀ፡፡

የህብረቱ ፕረዝደንት ሒሩት አበራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ መመሪያው በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ገልፀው፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ግብአት የታከለበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መመሪያው ፀድቆ በስራ ላይ ሲውል፣ የቤት ሰራተኞችን መሰረታዊ መብቶች የሚያስጠብቅ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚያስተካክልና የስራ ከባቢያቸውንም ምቹ እንዲሆን የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ከሁሉም በላይ ግን፣ መመሪያውና የስራ ቅጥር ውሉ፣ የቤት ሰራተኞች ጉልበታቸው ሲደክም እንደ ጡረታ ያሉ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡

ፕረዝዳንቷ ሒሩት አበራ በዚህ ጉዳይ ላይ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ የስራ ቅጥር ውሉንና መመሪያውን እያዘጋጀው ያለው የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ነው፡፡ መመሪያው በቅርቡ ይወጣል፡፡ በጣም በቅርብ፡፡

መመሪያው ለሰራተኛውም ለአሰሪውም የሚጠቅምና ግንኙነታቸውንም የሚያሻሽል ነው የሚሆነው፡፡

የስራ ቅጥር ውሉና መመሪያ በአሁኑ ወቅት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ኹኔታ ከግምት ያስገባ ነው፡፡

መመሪያው የቤት ሰራተኞችም አሰሪዎችም መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ ያደርጋል፡፡ 

አሁን ባለው ሁኔታ፣ የቤት ሰራተኞች የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ተጠቃሚዎች አይደሉም፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረት ግን የቤት ሰራተኞች እንደማንኛውም ሰራተኛ መብቶቻቸው ይከበራሉ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ መሟላት ያሉባቸው ቅድመ ሁኔታዎች አሉ፡፡

እነዚህ ዜጎች እንደማንኛውም ሰራተኛ መታየት አለባቸው ካልን፣ እነሱም ሊያሟሉዋቸው የሚገቡ መስፈርቶች ይኖራሉ፡፡ ሰራተኞቹ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያገኙ መሆን አለባቸው፡፡

የቤት ሰራተኞች ለገበያው ብቁ እንዲሆኑም ስልጠናዎች ይሰጣሉ፣ ያሉባቸውን የሙያ ክፍተቶች ለመሙላት ይሰራል፡፡ አሰሪውም ለሚከፍለው ደመወዝ ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል፡፡ በሀገር ደረጃ፣ ህገወጥ ስደትን ለመቀነስ የሚያስችል ይሆናል ብለን ነው የምናምነው፡፡

ነገሮችን ሰፋ አድርጎ የሚያይ መመሪያ ነው እየወጣ ያለው፡፡

መመሪያው ከወጣ በኋላ፣ በአፈፃፀም ወቅት ተግዳት እንዳይገጥመው፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እያከናወንን እንገኛለን፡፡

በአሁን ወቅት የቤት ሰራተኞች በስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚዋዋሉት ውል ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት የሌለው፣ ሐላፊነትን የማይሰጥና መብትና ግዴታን የማይለይ ነው፡፡
መብትና ግዴታውን የማያውቅ ሰው ደግሞ የሚጣልበት ቅጣት አይኖርም፡፡ ይህ መመሪያ ግን በቤት ሰራተኞች አስተዳደር በኩል ያሉትን ችግሮች ይፈታል፡፡

ለአሰሪና ሰራተኛ መብትንና ግዴታን ለይቶ የሚሰጥ ነው፡፡ ለሁለቱም ጠቃሚ የሆነ፣ የቤት ሰራተኝት ዘርፍ፣ ሞያተኞችም መርጠው የሚገቡበት የስራ መደብ እንዲሆን የሚያደርግ መመሪያ ነው፡፡

በቤት ሰራተኝነት ዘርፍ፣ ለአስር አመታት ያህል የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያደረጉና ጥናትም ያደረጉ አንድ ባለሙያ በበኩላቸው፣ ዘርፉ ህጋዊ መሰረት ቢኖረውና በህጋዊ ማዕቀፍ ቢደገፍ፣ ለሀገር ኢኮኖሚ ጠቃሚ የሆነ ኢንዱስትሪ መሆን ይችላል ” ብለዋል፡፡

ከአራት አመታት በፊት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት፣ በሀገሪቱ ወደ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰራተኞች እንዳሉ የገለፁት ባለሙያው አቶ መሲ ቸኮል ማሬ፣ እነዚህ ዜጎች የተለያዩ ችግሮች እንደሚደርሱባቸውም በጥናት አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ 


ባለሙያው አቶ መሲ ቸኮል ማሬ ምን አሉ ?

በጥናታችን መሰረት፣ ከ8 አመት ህፃናት ጀምሮ በቤት ሰራተኝነት የሚያገለግሉ ሴቶች አሉ፡፡ በተለይም ህጻናቱ፣ ከገጠር ወደ ከተማ እየወሰዱ በቤት ሰራተኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠናል፡፡

ከገጠር ወደ ከተማ ወደሚገኝ አሰሪ ሲላኩ፣ ትምህርት ይማራሉ በሚሉ ምክንያት ነው፡፡ በጥናታችን እንዳየነው ግን ብዙዎቹ አልተማሩም፣ ወይም ያቋረጡ ናቸው፡፡

አሰሪዎች ደሞዛቸውን እየቆረጡ ለቤተሰቦቻቸው እንደሚልኩ፣ ፆታዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው፣ በዚህም ላልተፈለገ እርግዝና ተዳርገው እንደሚወልዱ አይተናል፡፡

ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ፣ እንዲሁም የጤና ችግር ይደርስባቸዋል፡፡ ወደ እምነት ስፍራዎች እንዲሔዱና እንዲያመልኩ አይፈቀድላቸውም፣ በቂ ምግብና፣ እረፍትና እንቅልፍ አያገኙም፣ ምቹ የመኝታ ቦታም አይሰጣቸውም፡፡

በአሰሪዎቻቸው የአስገድዶ መድፈር ችግር ይደርስባቸዋል፣ በዚህም ወልደው ጎዳና የሚወጡበት ሁኔታ አለ፡፡

ጡረታና የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ባለመኖሩ አብዛኞቹ መጨረሻቸው ጎዳና ይሆናል፡፡

' እቃ ሰርቃችኋል፣ ሰብራችኋል፣ ጥፋት ፈፅማችኋል ' ተብለው በአሰሪዎቻቸው ያለደመወዝ ይባረራሉ፡፡

በቤት ሰራተኝነት ሲቀጠሩም ያለ የስራ ውል ስለሆነ፣ ደመወዛቸውን ሲከለከሉ፣ ጥቃትም ሲደርስባቸው ከፍትሐብሔርና ከወንጀል ህጉ ውጪ ሌላ ህግ ስለሌለ፣ ፍትሕ አያገኙም፡፡

ወደ ሴቶች ጉዳይ መስሪያ ቤቶች ሲሔዱም፣ ' የእናንተ ጉዳይ እኛን አይመለከተንም ' ይባላሉ፡፡

መገለል፣ አድልዎ፣ ስድብ፣ ድብደባ፣ ማንቋሸሽ ይደርስባቸዋል፡፡ 

የቤት ሰራተኛ ነኝ ብለው ደፍረው እንዳይናገሩ አድርጓቸዋል ችግሩ፡፡

አሰሪዎች ደግሞ ከሙያ አንፃር፣ ከመታመን አኳያ፣ የቤት ሰራተኞች ክፍተት እንዳለባቸው ያነሳሉ፡፡ ይህ ዘርፍ በህግ ቢደገፍ አሰሪዎችም ሰራተኛውም ግዴታቸውንና መብታቸውን ያስከብራሉ፡፡

ዘርፉ በህግ ከተደገፈ ዜጎች ሀገር ለቀው የህገወጥ ስደት ሰለባ አይሆኑም፡፡ ዘርፉ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚታይበትና ብዙ የሰው ሀይል የሚይዝ በመሆኑ፣ ዜጎች እንደ አንድ የስራ ምድብ ሊያዩት ይችላሉ፡፡

ቤተሰቦቻቸውንና ሀገራቸውን የሚደግፉበትም ይሆናል፡፡ ዘርፉንም ለማሳደግ ያስችላል፣ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አስተዋፅኦ እንዲኖረውም ያደርጋል ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ባንኮች የሚሰጡት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መስማት ለተሳናቸው ተደራሽ አይደለም ” - ኦርጋናይዜሽኑ

➡️ “ እኛ ኦፕሬሽኑን አንመራም። ኦፕሬሽኑን በግሉ ባንኩ ነው የሚመራው ” - የኢትዮጵያ ባንኮች ማኀበር

በኢትዮጵያ ያሉ የግልና የመንግስት ባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ መስማት ለተሳናቸው ተደራሽ እንዳልሆነ ቅሬታ ቢያቀርቡም መፍትሄ አለመሰጠቱን “ ዴፍ ኮሚዩኒቲ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ” ገለጸ።

የኦርጋይዜሽኑ ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛና መምህር ናትናኤል ሽፈራው፣ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጡ የተለያዩ ባንኮች በደብዳቤ ጭምር ቢጠይቁም፣ መፍትሄ እንዳልተገኘ ገልጸው፣ ባንኮች በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ማስታወቂያዎችን እንዲያስተረጉሙ ጠይቀዋል።

ሥራ አስኪያጁ ምን አሉ ?

“ ባንኮች የሚሰጡት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መስማት ለተሳናቸው ተደራሽ አይደለም። በኢትዮጵያ ከ5 ሚሊዮን በላይ መስማት የተሳናቸው ዜጎች አሉ።

ነገር ግን የባንክ ህጎች፣ ዐዋጆች መመሪያዎች፣ መስማት የተሳናቸውን ያማከሉ ባለመሆናቸው በአገልግሎት አሰጣጡ ከፍተኛ ችግሮች እየተፈጠሩ ነው። መስማት የተሳናቸው ሰዎች ከባንክ ቤት ገንዘብ ወጪና ገቢ ለማድረግ በየጊዜው የመግባባት ችግር ያጋጥማቸዋል።

አካውንት ለመክፈት፣ ውል ለመዋዋል ለምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ ገንዘብ ከፍለው ስለሚስተናገዱ ላላስፈላጊ ወጪም ይዳረጋሉ። ገንዘብ ወጪና ገቢ ለማድረግ ወረፋ እንዲጠብቁ ቢደረግም ተራቸው ደርሶ ስማቸው ሲጠራ መስማት ስለማይችሉ በተደጋጋሚ ተራቸው ያልፋቸዋል ” ብለዋል።

‘ቅድሚያ ስጡን’ ብለው ቢጠይቁም ‘የእጅ ጉዳት፣ የእግር ጉዳት የለባችሁም አዛውንት፣ ነፍሰጡርም አይደላችሁም፤ እንደማንኛውም ተገልጋይ ወረፋ ጠብቁ’ በሚል ቅድሚያ እንደማይሰጣቸው ከራሳቸውና ከሌሎች  ገጠመኝ በመነሳት አስረድተዋል።

በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች በምልክት ቋንቋ ባለመተርጎማቸው መስማት የተሳናቸው እንደ ሌሎች ደንበኞች ማወቅ ያለባቸውን መረጃ እያጡ፣ እየተገለሉ መሆኑን ገልጸዋል።

ማስታወቂያዎች በምልክት ቋንቋ እንዲተረጎሙ ባንክ ቤቶችን ደብዳቤ ቢጠየቁም ለጉዳዩ ዝቅተኛ ግምት በመስጠት በማጉላላት የቢሮ ክራሲ አሰራራቸው ጥያቄው እንዳይሳካ መንስኤ ሆኗል ” ሲሉም ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅነው የኢትዮጵያ ባንኮች ማኀበር፣ በጉዳዩ ላይ የተጠቀሱት ባንኮች እንዲጠየቁ ገልጾ፣ “እኛ ኦፕሬሽኑን አንመራም። ኦፕሬሽኑን በግሉ ባንኩ ነው የሚመራው” ብሏል።

በቅሬታ አቅራቢዎቹ ጥቆማ መሠረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቃቸው ቅሬታ ከቀረበባቸው ባንኮች የአንዱ ባንክ የቀድሞ አመራር፣ ሥራ እንደለቀቁ ገልጸው፣ “ያኔ ሰዎቹ አቅርበው ይሆናል እኛ ጋ። ግን ጥያቄውን በወቅቱ ማቅረብ የነበረባቸው ማርኬቲንግ ዲፓርትመንት እንደሆነ ነግረናቸዋል ” ሲሉ አስታውሰዋል።

ቅሬታ የቀረበባቸው ባንኮችን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ተጨማሪ ሙከራ ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ የምናስተናግዳቸው ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነገ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያካሂድ ይፋ አድርጓል።

በነገው ዕለት 70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለጨረታ እንደሚቀርብ አመልክቷል።

ፍላጎት ያላቸው ባንኮች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀርቧል።

ከዚህ ቀደም የብሔራዊ ባንክ በየ2 ሳምንቱ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያወጣ መግለጹ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አሜሪካ በኤርትራ ጨምሮ በሌሎችም ሀገራት ያሉ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው።

አሜሪካ ወደ 30 የሚጠጉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ዲፕሎማቲክ ጽሕፈት ቤቶቿን ልትዘጋ መሆኑን ሮይተርስ የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰነድን ጠቅሶ ዘገበ።

የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር አብዛኞቹ በአፍሪካ እና በአውሮፓ የሚገኙ ቢያንስ 27 የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎችን የሚዘጋ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ጎረቤት ሀገር
#ኤርትራ አንዷ ናት።

በውሳኔው መሠረት ይዘጋሉ የተባሉት አስሩ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ፦
- በኤርትራ፣
- በግሪናዳ፣
- በሌሶቶ፣
- በማዕካላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣
- በሉክዘንበርግ፣
- በሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣
- በጋምቢያ፣
- በደቡብ ሱዳን፣
- በማልታ እና በማልዲቭስ የሚገኙ መሆናቸውን ሮይተርስ የተመለከተው ሰነድ ያመለክታል።


ከሚዘጉት ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች ባሻገር ኤምባሲ እና በርካታ ቆንስላዎችን በመያዝ ግዙፍ የዲፕሎማቲክ ሥራ በሚከናወንባቸው እንዳ ጃፓን እና ካናዳ ያሉትን ተልዕኮዎች በማዋሃድ መጠናቸውን የመቀነስም ሐሳብ አለ።

ሰነዱ ከፍተኛ ወጪ በማስወጣት ውድ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ የተመደበባቸው ናቸው ያላቸውን በሞቃዲሾ ሶማሊያ እና በኢራቅ ያሉ የዲፕሎማቲክ አባላትን መጠን የመቀነስ ሐሳብም መቅረቡን አመልክቷል።

ዶናልድ ትራምፕ ወደ ፕሬዝዳንትነት ከተመለሱ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት በተለያዩ መስኮች ከአገሪቱ ፍላጎት ጋር አይጣጣሙም ያላቸውን ተቋማት በመዝጋት እና እርዳታዎችን በማቋረጥ ላይ ይገኛል።

የትራምፕ የቅርብ ሰው በመሆኑት ማርኮ ሩቢዮ የሚመራው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በጀት እስከ ግማሽ የሚደርሰውን እንደሚቀነስ ሮይተርስ የተመለከተውን የመሥሪያ ቤቱን ሰነድ ጠቅሶ አመልክቷል።

በዚህም ሳቢያ በበርካታ አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎችን የመዝጋት ሐሳብ ሀሳብ ነው ያለው።

የአሜሪካ መንግሥት ለውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ከሚያወጣው ገንዘብ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለመቀነስ አቅዶ የበጀት ጥያቄውን ለአገሪቱ ምክር ቤት ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው።

መረጃው የሮይተርስ እና ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

" 4 ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች ከዚህ በኋላ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አገልግሎት ይሰጣሉ " - የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

ከዚህ በኋላ 4 ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች በአንድ አቅጣጫ ብቻ አገልግሎት እንደሚሰጡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

በመሆኑም ፦
- ከጥይት ቤት  እስከ ፓርላማ ትራፊክ መብራት፣
- ከቤተመንግስት ፖርክንግ እስከ ጥይት ቤት
- ከፓርላማ ትራፊክ መብራት እስከ ሳይንስ ሙዝየም ድረስ ያሉ መንገዶች ቀድሞ ከነበረው ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ወደ አንድ አቅጣጫ መንገድ ተቀይረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳን መስመሮቹ እንደ ቀድሞው ባለ ሁለት አቅጣጫ ሆነው አገልግሎት መስጠታቸውን መቼ ይጀምራሉ ? ሲል ጠይቋል።

በምላሻቸው በአንድ አቅጣጫ እንጂ ወደበፊቱ ተመልሶ በሁለት አቅጣጫ አገልግሎት እንደማይሰጡ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አስቀድመው " ለሁለት ቀን ወደ አንድ አቅጣጫ (One way) ተደርገው አገልግሎት ይሰጣሉ " በሚል ለቲክቫህ  ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

ሆኖም  " ለሁለት ቀን ያልኩት በአንድ አቅጣጫ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች እና የጎደሉትን የማሟላት ስራ ለመስራት ነው " ሲሉ መንገዶቹ በቀጣይነትም ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ ሆነው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።

አክለውም " የትራፊክ ስራ ዳይናሚክ ነው፣ እንደ የአስፈላጊነቱ  በየጊዜው የማሻሻል ስራዎች ሊኖሩ ይችላሉ " በማለት ጠቁመዋል።

ከዚህ በኃላ ግን መንገዶቹ ባለ አንድ አቅጣጫ ብቻ እንደሆኑ አስገንዝበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

Via @Tikvahethmagazine

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወስኗን።

በትግራይ መምህራን ማህበር ጠበቆች የቀረበውና በጦርነቱ ጊዜ ያልተከፈለ የ17 ወራት የመምህራን ደመወዝ ሲመለከት የቆየው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ውሳኔውን ሰጥቷል።

ተከሳሾቹ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ፣ የፋይናንስ  ቢሮ ፣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም የገንዘብ/ የፋይናንስ ሚንስቴር ሲሆኑ ጉዳያቸው በሌሉበት ሲታይ ቆይቷል።

ፍርድ ቤቱ የቀረበለት ክስ መርምሮ የመምህራኑ የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወስኖ ፋይሉ ወደ መዝገብ ቤት መልሶታል። 

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደሚቀበሉትና እንዳረካቸው የተናገሩት አስተያየት ሰጪ መምህራን ውሳኔው ቶሎ በመተግበር በከፋ ሁኔታ የሚመገኙ መምህራን መታደግ ይገባል ብለዋል።

ተከሳሾቹ ውሳኔው በማስመልከት እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

መምህራን ያካተተ የ17 ወራት ያልተከፈለ የመንግስት ሰራተኞች ውዙፍ ደመወዝ የመከፈል ጥያቄ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት የጀመረ ነው።

በቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዳይታይ የሚከልክል መምሪያ እስከማውጣት ደርሶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

ፎቶ፦ Tigrai TV

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በስህተት ወደ አካውንቴ የገባልኝን 3.5 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ መልሻለሁ " - አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስህተት ወደ አካዉንቱ የገባን 3.5 ሚሊዮን ብር ተመላሽ ያደረገ ግለሰብ ምስጋና እየተቸረው ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ በስም ተጠቃሹን ግለሰብ አግኝቶ ያነጋገራቸው ሲሆን የባንክ ባለሙያ አስተያየት እና ምክርም ጠይቋል።

በስህተት የገባላቸዉን 3.5 ሚሊዮን ብር የመለሱት አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል ምን አሉ ?

" ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር ሂደት በተፈጠረ ስህተት ከሌላ ግለሰብ ወደ አካዉንቴ የገባን 3.5 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ ተመላሽ አድርጊያለሁ።

እኔም የስራ ሰዉ ነኝ እንደዚህ አይነት ክስተት ልያጋጥመኝ ይችላል፤ ስለዚህ ገንዘቡ የኔ ስላልሆነና ለባለቤቱ መመለስ ስላለብኝ ሳላቅማማ መልሻለሁ " ሲሉ ጉዳዩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

አቶ በህጉ አክለዉም " ብዙ ሰዎች ሞኝ እንደሆንኩ፣ መመለስ እንዳልነበረብኝና ብመልስም ከላዩ ቀንሼ መሆን እንደነበረበት አስተያየት ሲሰጡ ሰምቻለሁ፤ ዳሩ ግን ቅድም እንዳልኩት የኔ ያልሆነ ነገር የኔ አይደለም፤ በተለይም እኔም በቢዝነስ አለም ዉስጥ እንዳለ ሰዉ ነግ በኔ እንደሆነ በመረዳት ማድረግ ያለብኝ ነዉ ያደረኩት "ብለዋል።

የአዋሽ ባንክ ባለሙያ ስለሁኔታዉ ምን አሉ ?

የአዋሽ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ኦፕሬሽንናል ማናጀር አቶ ፉፋ አሰፋ ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር አቶ ቦንሳ ታደለ የተባሉ የባንካችን ደንበኛ ከአንዱ ባንክ አካዉንት ወደ ሌላ ባንክ አካዉንት በአካል ተገኝተዉ በማንዋል ፅፈዉ ሂሳብ ሲያስተላልፉ አንድ ቀጥር ተሳስተዉ ፅፈዉ በመስጠታቸዉ 3.5 ሚሊዮን ብር ወደ አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል አካዉንንት ተላልፏል " ሲሉ ገልፀዋል።

ባንኩ ለአቶ በህጉ በመደወል ሁኔታውን ማስረዳቱንና አቶ በህጉም ተባባሪ በመሆን ለባለቤቱ ገንዘቡን ተመላሽ ማድረጋቸውን አስታውቋል።

ለሁሉም የባንክ ተጠቃሚዎች የባንክ ባለሙያዉ ምን አሉ ?

" ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር ሂደት ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ የመፈጠር ዕድሉ ሰፊ ነዉ። ሁሉም ሰዉ በብር ዝዉዉርና አጠቃላይ በባንክ አጠቃቀም ወቅት ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አቢሲንያ ባንክ
#የሁሉም_ምርጫ

ገደቡም ክፍያውም ተነስቷል!

ውድ ደንበኛችን! የባንካችንን አዲሱን የሞባይል መተግበሪያ ተጠቅመዉ ከሂሳብዎ ወደ ሌላ የባንካችን ሂሳብ ገንዘብ ያለ ገደብ እንዲሁም ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይችላሉ። #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…
Подписаться на канал