ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሚዘጋጀው የኢትዮጵያ ታምርት ሩጫ እና ኤክስፖ ተጋብዘዋል
📱 ሩጫው መቼ ነው ?
የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ መነሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ መስቀል አደባባይ የሚጠናቀቅ ሲሆን #ሚያዚያ_19 /2017 ዓ.ም ይከናወናል።
በዚህ ሩጫ ውድድር ፦
1ኛ ለሚወጡ 300,000 ሺህ ብር
2ኛ ለሚወጡ 200,000 ሺህ ብር
3ኛ ለሚወጡ 100,000 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።
በሁለቱም ፆታ እስከ 10ኛ የሚወጡ አሸናፊዎችም #በሽልማት ይንበሸበሻሉ!
🎽 ቲሸርቱን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኙታል
📞 ለበለጠ መረጃ 0975070707
⚙️ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ መቼ ነው ?
የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከሚያዝያ 25 እስከ 29/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።
ማንኛዉም ልዩ፤ ጥራትና ተወዳዳሪ ምርት ያላቸው አምራቾችና ኢንዱስትሪዎች በ #ኢትዮጵያ_ታምርት ኤክስፖ 2017 ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
📞 ለበለጠ መረጃ በ 0906555552 ወይም 0988080808 ይደውሉ
#ኢትዮጵያታምርት #ኢንዱስትሪሚኒስቴር
#MoE
" ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)
በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።
ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።
" ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)
ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለአፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።
በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል።
" የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#TPLF : " ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ሆኖው መሾማቸው እደግፋለሁ " ሲል በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት አሳውቋል።
የፕሬዜዳንቱን ሹመት ከኢትዮጵያ መንግስት የተስማመበት የሚቀበለውና የሚደግፈው መሆኑ ገልጿል።
ፓርቲው ፥ ስልጣኑ ባከተመው በአቶ ጌታቸው ረዳ ሲመራ የነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር የጠፋው ጊዜን ለማካካስ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልፆ " የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚፃረሩ የተናጠል አዋጆች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች ከማውጣት እንዲቆጠብ " ብሏል።
ድርጅቱ " ብሄራዊ የክህደት ቡድን " ሲል የገለፀው አቶ ጌታቸው ረዳ በበላይነት ሲመሩት የነበሩት ጊዚያዊ አስተዳደር ከስልጣኑ እንዲወገድ " የህዝቡ አስተዋፅኦ " ከፍተኛ ነበር በማለት ገልጿል።
የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አዲሱ ፕሬዚዳንት ሊገጥማቸው ስለሚችል ተግዳሮት ተናግረው ነበር።
በዚህም ፥ " ፓርቲው ፕሬዝዳንቱን እንደሾመው ያስባል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ራሳቸው እንደሾሙት ይናገራሉ እንደ አለመታደል ያጋጥመዋል ብዬ የማስበው አንዱ ተግዳሮት አሁንም ሥልጣኑን ጠቅልሎ ለመያዝ ከሚፈልገው የህወሓት አንጃ የሚመጣው ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የሥልጣን ጥማት ነው " ብለው ነበር።
ፕሬዜዳንቱ ይህንን የመጋፈጥ አቅምና ክህሎቱ ይኖራቸዋል ወይ ? የሚለው ጉዳይ ወደፊት የሚታይ እንደሆነ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
@tikvahethiopia
#ምርጥ_ዕቃ
የፋሲካን በዓል ምክኒያት በማድረግ በሁሉም የቤት ዕቃዎቻችን ላይ ልዩ ቅናሽ አድርገናል። በቴሌግራምዎ ስለ ዕቃዎቻችን ተጨማሪ መረጃ ለማየት ይሄንን👇
👉 t.me/MerttEka 👈
👉 t.me/MerttEka 👈
ይጫኑ። ካሉበት ሆነው ይዘዙን፣ እንልክልዎታለን።
አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ ሱቅ 376
#Update
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምን ምላሽ ሰጠ ?
" ለሀገራዊ ፕሮጀክት ሲባል በቦታዉ የነበሩ ነዋሪዎችና የፌደራል ፖሊስ ካምፕን ወደ ሌላ ቦታ በማዛወር የፀዳ ቦታን የመስጂድ ይዞታ እንደነበረ አስመስሎ ማቅረብ የተሳሳተ መረጃ ነው " - ክፍለ ከተማው
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፤ በቅድሚያ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኃላም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት " ጨለማን ተገን በማድረግ ፈርሷል " ስላሉት የተባረክ መስጂድ አጥር ጉዳይ አሁን ለሊት መግለጫ አውጥቷል።
ክፍለ ከተማው ፤ " በዛሬው እለት እሁድ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ሜክሲኮ አካባቢ የመንግስት አካላት የመስጂድ አጥርን አፈረሱ የሚል መረጃ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘዋወር መዋሉ ይታወቃል " ብሏል።
ማንኛውም የመንግስትና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ህገወጥ ድርጊቶች ሲፈፀሙ በህግ አግባብና ህጋዊ ውሳኔን መነሻ በማድረግ ሲከላከል መቆየቱን ወደፊትም የሚተገብረው ትልቁ ኃላፊነቱ መሆኑን አንስቷል።
" በዛሬው እለት በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የዋለው መረጃ ቤተ እምነትን ሽፋን በማድረግ መንግስት ዉሳኔ ያልሰጠበት መሬትን ያለአግባብ ከህግ ዉጪ ለመያዝ የተደረገ ተግባራዊ እንቅስቃሴን ለመከላከልና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተወሰደ እርምጃ ነው " ብሎታል።
" ጉዳዩን በተሳሳተ መንገድ መተርጎም በምንም ዓይነት ተቀባይነት ያለው ድርጊት አይሆንም ፤ ህዝባችንም እጅግ አስተዋይ ህዝብ በመሆኑ ጉዳዩን በሚዛኑ የሚረዳ እንደሚሆን እናምናለን " ብሏል።
" ተባረክ መስጂድ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከመስጂዱ አባቶችና ምዕመናኑ ጋር በቅርበት አብሮ ከሚሰራቸው፣ ወደፊትም አብሮነቱን ከሚያጠናክራቸው የእምነት ተቋማት መካከል አንዱ ነው " ያለው ክ/ከተማው ፥ " ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የመስጂዱ አስተዳደር ከህጋዊ ይዞታዉ ዉጪ ያለ መሬት ላይ የማስፋፊያ ጥያቄ ለአስተዳደሩ አቅርቧል በሚል ሰበብ ለሀገራዊ ፕሮጀክት ሲባል በቦታዉ የነበሩ ነዋሪዎችና የፌደራል ፖሊስ ካምፕን ወደ ሌላ ቦታ በማዛወር የፀዳ ቦታን የመስጂድ ይዞታ እንደነበረ አስመስሎ ማቅረብ የተሳሳተ መረጃ ነው " ሲል አሳውቋል።
" ቦታው ከዚህ በፊት የፌደራል ፖሊስ ካምፕና የነዋሪዎች የነበረ ሲሆን ቦታውን በማፅዳት ሀገራዊ ፋይዳ ላለዉ ፕሮጀክት በሀገራዊ ፕሮጀክት ኮንትራክተሩ አማካኝነት ሙሉ ባዶ ቦታዉ በኤጋ ቆርቆሮ እንዲታጠር ተደርጎ የቆየ ነው " ብሏል።
" ነገር ግን ይህ እውነት ሆኖ ሳለ አሁን ግን ቦታውን ያለምንም ህጋዊ ፍቃድ የመስጂዱ እንደሆነ በማስመሰል በመንግስት የታጠረዉን ቦታ ያለምንም ህጋዊ ፍቃድ የመስጂዱን ታፔላ እና በር በመስራት የመስጂዱ አካል በማስመስል ህገ ወጥ ተግባር ከመፈጸሙም በተጨማሪ በመስጂዱ ይዞታ ስር ያልነበረ ቦታ ' መንግስት አፈረሰዉ ' በሚል እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎች ፍፁም ህጋዊ መሰረት የሌላቸዉ መሆኑን የእምነቱ አባቶችና ተከታዮች በሚገባ ልትረዱት ይገባል " ሲል አስገንዝቧል።
" ያለአግባብ በተዛባ መረጃ ላይ ተመስርታችሁ ያልተገባ እንቅስቃሴ የምታደርጉ አካላትም ከድርጊታችሁ መታቀብና ቀረብ ብሎ መረጃና ማስረጃ አጣርቶ መረዳትን እንድታስቀድሙ " ሲል በመግለጫው አሳስቧል።
ክፍለ ከተማው ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልግ ለማንኛውም አካል መረጃ ለመስጠት በሩ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።
@tikvahethiopia
#መቄዶንያ
በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ቀደምት ተገልጋይ የነበረው የጌዲዮን ሙላቱ ስርዓት ቀብር መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘው አያት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
በስርዓት ቀብሩ ላይ የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠን ጨምሮ የማዕከሉ አረጋውያን አንዲሁም ወዳጆቹ ተገኝተዋል።
ጌዲዮን በትልልቅ ሆስፒታሎች የልብ ሕክምና ሲደረግለት የነበረ ሲሆን፤ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በድንገተኛ ሕክምና ክፍል ተኝቶ ልዩ ክትትል እየተደረገለት በትናትናው ዕለት ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በሕክምና ላይ እያለ በ37 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
መረጃው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ.ም በዓለ ሆሣዕና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከብሯል።
ቅድስት ቤተክርስቲያን ፥ " የሆሣዕና በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሣዕና በአርያም በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው " ብላለች።
#EOTCTV
@tikvahethiopia
" በቀን የተሰራን የመስጂድ አጥር ጨለማን ተገን አድርጎ ማፍረስ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የተባረክ (ጀርመን) መስጂድ አጥር በፀጥታ አካላት በጨለማ እንዲፈርስ መደረጉን አሳወቀ።
የመስጂድ ኻዲሞችም ታስረዋል ብሏል።
ምክር ቤቱ፤ መስጂዱ ህጋዊ ካርታ ያለው እና ከ1967 ጀምሮ ሲሰገድበት የቆየ እንደሆነ ገልጿል።
" አካባቢውን በአዲስ መልክ ለማልማት መንግስት የጀመረውን እንቅስቃሴ በመደገፍ እና መስጅዱን በአዲስ መልክ ለመስራት ፕሮጀክት ተዘጋጅቶ ለሚመለከተው የመንግስት ተቋም ገቢ ተደርጎ ክትትል እየተደረገ ነበር " ብሏል።
" አካባቢውን እያለማ የሚገኘው ኢግልስ ሂል የፌደራል የሜጋ ፕሮጀክት ተወካዮች፣ የወረዳ እና ክ/ከተማ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት የመስጅዱን ዙሪያ በማጠር እና በሰላማዊ መንገድ ለአካባቢው ጀመዓ በማስረከብ መስጅዱ እየተሰገደበት ይገኛል " ሲልም አስረድቷል።
የከፍተኛ ም/ቤቱ ከከተማ መስተዳድሩ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አስተዳደር ጋር በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጉን ገልጾ አጥሩ ባለበት ሁኔታ በውይይት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ከስምምነት ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል።
ከዚህም በተጨማሪ ረመዳን 28 የአካባቢው ጀመዓ ባዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ በአካል በመገኘት የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ እየሰሩ መሆኑን እንዳሳወቁም ገልጿል።
" ይህ በእንዲህ እያለ በሰላማዊ መንገድ በቀን የተገነባውን የመስጅድ አጥር ጨለማን ተገን አድርጎ ማፍረስ እና በመስጅዱ ውስጥ የሚገኙ የመስጅድ ኻዲሞችን ማሰር በምንም መመዘኛ ህግ ማስከበር ሊሆን አይችልም " ሲል ምክር ቤቱ አሳውቋል።
ድርጊቱን አጥብቆ እንደሚያወግዝ ፤ በመጨረሻ የፌደራል የሜጋ ፕሮጀክት ተወካዮች እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ባሉበት የተገነባው የመስጅድ አጥር ወደ ነበረበት እንዲመለስ እና ያለምንም ጥፋት ከመስጅድ የታሰሩት ሰዎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ አሳስቧል።
መረጃው ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተላከ ነው።
@tikvahethiopia
https://ethiocoders.et/
ነጻ የትምህርት እድል !
አይገርምም ?
ለአምስት ሚልዮን ኢትዮጵያዉያን ነፃ የትምህርት ዕድል!!!
እጅዎ ላይ ባለ ስልክና ታብሌት ጊዜና ቦታ ሳይገድቦት ተመዝግበዉ በመማር ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሠርተፊኬት ያግኙ።
ነፃ የኦንላይን ሥልጠናዎቹ ፦
- በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ
- በዳታ ሳይንስ
- በዌብ ፕሮግራሚንግ እና
- በአንድሮይድ ማበልፀግ ናቸው
እርሶም በመረጡት የትምህርት ዘርፍ በአጭር ጊዜ ተምረዉ ህይወትዎንና ሙያዎን ያዘምኑ።
ከመገረም ወጥተን እናስገርም!!!
ኢትዮ ኮደርስን ለመቀላቀል
ከታች ባለዉ ሊንክ ተጭነዉ ይመዝገቡ
https://ethiocoders.et/
#USA #CHINA
የአሜሪካ እና የቻይና የታሪፍ ጦርነት !
ወደ አሜሪካ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከጣሏቸው የአፀፋ ታሪፎች ነፃ መሆናቸውን የአሜሪካ የጉምሩክ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
➡️ ስማርት ስልኮች፣
➡️ ኮምፒዩተሮች
➡️ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ክፍሎች ትራምፕ ከጣሉት ታሪፍ ነፃ መደረጋቸውም ተዘግቧል።
ውሳኔው የመጣው የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር በቻይና ላይ የ145% አጠቃላይ ታሪፍ መጣሉን ካስታወቀ በኋላ ሲሆን የታሪፉ መጣል እንደ አፕል ላሉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክ ምርት አምራቾች ስጋትን ፈጥሮም ነበር።
አፕል 90% የሚሆነውን የአይፎን ስልክ የሚያመርተው እና የሚገጣጥመው በቻይና ሲሆን ካውንተር ፖይንት የተሰኘው የጥናት ተቋም አፕል በአሜሪካ ያለው ክምችት ለ6 ሳምንታት ብቻ የሚሆን እንደሆነና እሱ ካለቀ የምርቱ ዋጋ መጨመር እንደሚጀምር ገልጾ ነበር።
አፕል ከአይፎን በተጨማሪ 80% የሚሆነውን አይፓድ እና ከ50% በላይ የሚሆነውን የማክ ኮምፒዩተር ምርቶቹን በቻይና እንደሚያመርት ተገልጿል።
አፕል ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነውን የአይፎን ምርት የሚሸጠው በአሜሪካ እንደሆነ ሲነገር በቻይና ላይ ታሪፍ መጣሉን ተከትሎ አብዛኛውን ምርቱን በህንድ ማምረት ለመጀመር ማሰቡም ተነግሮ ነበር።
አፕል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፀፋ ታሪፍ በሃገራት ላይ መጣል ከጀመሩ በኋላ የገበያ ዋጋው በ640 ቢሊየን ዶላር መቀነሱ የተዘገበ ሲሆን ከ600 ቶን በላይ ክብደት ያላቸው 1.5 ሚሊየን የአይፎን ስልኮችንም ከህንድ ወደ አሜሪካ በአውሮፕላን አጓጉዞ ማስገባቱ መዘገቡ ይታወሳል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንትና አንዳንድ ምርቶች በሚታወቁ ምክንያቶች እሳቸው ከጣሉት ታሪፍ ነፃ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረው ነበር።
ትራምፕ በጣሉት ታሪፍ የተነሳ የአይፎን ስልክ ዋጋ በሶስት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ስጋቶች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶቹ ከአፀፋዊ ታሪፉ ነፃ መሆን ትልቅ ዕድል እንደሚሆን ተዘግቧል።
በውሳኔው መሰረትም #ሳምሰንግን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራቾች ወደ አሜሪካ ምርታቸውን ሲልኩ ይጠብቃቸው ከነበረው የ10% መሰረታዊ ታሪፍም ነፃ መሆናቸው ተነግሯል።
ከታሪፉ ነፃ የሆኑ 20 የምርት ዘርፎች የተቀመጡ ሲሆን ለሴሚ ኮንዳክተር መሳሪያነት የሚያገለግሉ ማሽኖችም ከታሪፉ ነፃ መሆናቸው ታውቋል።
ኋይት ሃውስ፣ የአሜሪካ የአለም አቀፍ ንግዶች ኮሚሽን እና የአሜሪካ የንግድ ቢሮ በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።
#ዓለምአቀፍ #የታሪፍጦርነት #ቻይና #አሜሪካ
@tikvahethiopia
" እየተስተጋባ የሚገኘው የጤና ባለሙያዎች ድምፅ የሁላችንም ድምፅ ነዉ " - የጤና ባለሙያዎች ማህበራት
⚫️ " ባለፉት ዓመታትም እንደዚሁ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታ እየተስተጋባ መልሶ የሚቀዘቅዝበት ሁኔታ አለ !! "
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየታየ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን እና የጤና ባለሙያዎች ማህበራትን አነጋግሯል።
የጤና ባለሙያዎቹ እንዲፈቱላቸው በሚፈልጓቸው ጉዳዮች ላይ ድምጻቸውን እያስተጋቡ ይገኛሉ።
➡️ " ሕይወት ስናድን ኖረናል አሁን ግን እኛን መታደግ ይገባል ! "
➡️ " ለጤና ባለሙያዎች የሚከፈለው ደመወዝ ስራና ድካማችንን የሚመጥን አይደለም ! "
➡️ " እኛ ከጎረቤት ሀገራትንና ሙያዉ ከሚፈልገዉን የደመወዝ መጠን አንፃር ሳይሆን የሚያስፈልገንን አድርጉልን ነዉ ያልነዉ ! "
➡️ " ሕይወት የሚታደጉ የጤና ባለሙያዎች ለራሳቸዉ የጤና ኢንሹራንስ የላቸዉም ! "
➡️ " የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በአግባቡ ይከፈሉ ! "
➡️ " የተራበ ሐኪም የሚሰጠዉ የጤና አገልግሎት መቼም ዉጤታማ አይሆንም ! "
➡️ " የጠየቅነዉ በአግባቡ ሕይወት እንድንታደግ እኛን ታደጉን ብለን ነዉ ! "
➡️ " የጤና ባለሙያ እየራበው፣ እየጠማው፣ ለቤት ኪራይ የሚከፍለው ሳይኖረው እና ጤናዉ እየታወከ እንዴት የሌላዉን ጤና ይጠብቃል ? "
➡️ " በርካታ ሐኪሞች ሌላዉን ለማዳን ሲሉ ጤናቸዉን አጥተዋል ብዙዎችም ቤተሰቦቻቸውን በትነዉ ሞተዋል ዳሩ ግን ለነሱም ሆነ ለቤተሰቦቻቸው ኢንሹራንስ የለም ! "
የሚሉት የጤና ባለሙያዎች እያሰሙት ካለው ድምጽ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ነርሶች ፣ አዋላጆችና ላብራቶሪ ባለሞያዎች የጤና ማህበራት ጉዳዩን በማህበራዊ ሚዲያዎች መመልከታቸዉን ገልፀዉ " ጥያቄዉን የምንጋራዉ ነዉ " ብለዋል።
ባለሞያዎቹ " ለጤና ዘርፉ ተገቢው ትኩረት ባለመሰጠቱ የሚፈለገዉ ዉጤት እየተመዘገበ አይደለም፤ ለአብነትም ከነርስ የጤና ሙያ መስክ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ባለሙያዎች ቢኖሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካቶች መስኩን እየለቀቁ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም ፤ " በሀገራችን ሁሉንም የጤና ባለሙያ ዘርፎች ያካተተ አንድ የጋራ ማህበር አለመኖሩ ለችግሮች ፈጣንና የማያዳግሙ ዉሳኔዎች እንዳይሰጡ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል " ብለዋል።
በዝርዝር ያነሱት ሃሳብ ምንድነው ?
" ከዚህ ቀደም ወደ ዉጪ ሀገራት ይደረግ የበረዉ የባለሙያዎች ስደት አሁን አሁን ሙያ በመቀየር ሀገር ዉስጥ ሆኗል።
በቅርቡ በፀደቀዉ የጤና ፖሊሲ ላይ የጤና ባለሙያዎች የጤና መድህን ድርሻ መንግስት እንዲሸፍን ቢወሰንም በቂ ካለመሆኑም በላይ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ክፍተት አለ።
የጤና ባለሙያዎች በሚሰሩባቸዉ የጤና ተቋም ሳይቀር ከፍለው እንዲታከሙ ነዉ የሚደረገዉ ፤ ይህ ሙያዉንም ባለሙያዉንም እየጎዳው ነዉ።
በርካታ የጤና ባለሙያዎች በስራ ላይ እያሉ በሚደረሰባቸው የጤና፣ የስነ አዕምሮና አካላዊ ጉዳቶች የሕክምናና የማካካሻ ድጋፎችን አያገኙም።
ጤናን ከተቀዳሚ የሀገሪቱ ፖሊሲዎች አንዱና ዋነኛዉ ነዉ በምትል ሀገር በጤና ባለሙያዎች ላይ የሚስተዋለዉን የደሞዝ፣ የጤና ኢንሹራንስና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ጉዳይ በመንግስት በኩል ተገቢው ትኩረት አላገኘም።
ባለፉት ዓመታትም እንደዚሁ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታ እየተስተጋባ መልሶ የሚቀዘቅዝበት ሁኔታ አለ።
በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መንግሥት የጤና ባለሙያዎች ሕይወት የሚታደጉ እንደመሆናቸዉ መጠን ተመጣጣኝ የደመወዝ ክፍያ፣ ሙሉ የጤና ኢንሹራንስና ነፃ የጤና መድህን አገልግሎት ሊያሰጣቸዉና ጥቅማ ጥቅሞቻቸዉን ማስከበር ሲገባዉ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በበዓላት የሚሰሩባቸዉን የትርፍ ሰዓት ክፍያቸዉን ጭምር በሚከለክሉና በግዳጅ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚደረጉባቸዉ አከባቢዎች ላይ የመፍትሔ እርምጃ አለመዉሰዱ ችግሩን አባብሶታል " ብለዋል።
እንደ መፍትሔ በጠቆሟቸው ሃሳቦች ምን አሉ ?
🔴ለጤና ባለሙያዎች ስራቸዉን የሚመጥን የደመወዝ ማስተካከያ ቢደረግ እና የጤና ኢንሹራንስ ለጤና ባለሙያዎችና ለቀጥተኛ ተጎጂ ቤተሰቦቻቸው ቢሰጥ።
🔴በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢፀድቅም አፈፃፀም ላይ ሰፊ ክፍተቶች ስላሉ የጤና መድህን አገልግሎትን ያለ ገደብ እንዲያገኙ ቢደረግ።
🔴በትርፍ ሰዓት ክፍያ ጉዳይ ፈጣን እንዲሁም የማያዳግም ዉሳኔ ቢሰጥ።
🔴በጤና ባለሙያዎች ማህበር በኩል በልዩነት አንድ የጋራ ማህበር አልያም " የጤና ባለሙያዎች ካዉንስል ቢቋቋም " በዘርፉ በየጊዜዉ የሚነሱ ችግሮችን በዘላቂነት እንዲፈቱ ያደርጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዛሬ ቅደሜ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ 2017 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም መገምገማ መጀመሩን ገልጸዋል።
በግምገማው " የሚቀጥሉትን ሶስት ወራት ሥራዎቻችንን እቅድ ለማጠናከር የሚረዱ ውይይቶችን እናካሂዳለን " ብለዋል።
በዚሁ የግምገማ መድረክ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሾሙት የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተሳታፊ ሆነዋል።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
አዲስ አበባ በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች አንድ አቅጣጫ ብቻ ሆነው ለዛሬና ለነገ እንዲያገለግሉ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።
የትኞቹ መንገዶች ናቸው ?
🛣 ከጥይት ቤት እስከ ፓርላማ ትራፊክ መብራት
🛣 ከቤተመንግስት ፖርኪንግ እስከ ጥይት ቤት
🛣 ከፓርላማ ትራፊክ መብራት እስከ ሳይንስ ሙዝየም ያሉ መንገዶች ናቸው።
በእነዚህ መንገዶች ቀድሞ የነበረው ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ (Two way) የነበሩት ለሁለት ቀን ወደ አንድ አቅጣጫ መንገድ (One way) ተደርገው አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሏል።
" አሽከርካሪዎች በተተከሉ የመንገድ ትራፊክ ምልክቶች መሰረት እንድትጓዙ " ሲል ባለ ሥልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
ይህ የሆነው በምን ምክንያት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳን ጠይቋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ፥ " ይህ የተደረገው ማንዋሊይ እየተሰራ ነው፣ መንገዶቹ ላይ አቅጣጫ ጠቋሚ፣ የቀለም ስራ እና ሌሎችም የሚሰሩ ስላሉ ነው በ one way የተደረገው " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
አያይዘውም " ዛሬ እና ነገ ስራው ተሰርቶ ያልቃል፣ ነገ ሁሉም ነገር ይጠናቀቃል፣ ከሰኞ ጀምሮ ሙሉ አገልግሎት መስጠቱን ይቀጥላል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
Via @Tikvahethmagazine
#ኢትዮጵያ_ታምርት_ኤክስፖ2017
#ትፈለጋላችሁ
✅ ጥራት እና ተወዳዳሪ ምርት ካሎት ይፈለጋሉ !
✅ ለየት ያለ እና ጥራት ያለዉ ምርት ያላችሁ ትፈለጋላችሁ!
ማንኛዉም ልዩ፤ ጥራትና ተወዳዳሪ ምርት ያላቸው አምራቾችና ኢንዱስትሪዎች በ #ኢትዮጵያ_ታምርት ኤክስፖ 2017 ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከሚያዝያ 25 እስከ 29/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።
በዚህ ኤክስፖ መሳተፍ የምትፈልጉ በሙሉ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ።
📞 ለበለጠ መረጃ በ 0906555552 ወይም 0988080808 ይደውሉ
#ኢትዮጵያታምርት #ኢንዱስትሪሚኒስቴር
" በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑ ተደንግጓል " - ፖሊስ
ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆነ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያስረጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ፖሊስ ግለሰቡ ሚሊዮን ድሪባ የሚባል እንደሆነና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስል በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸውን ያነሱበት ጉዳይ እንደሆነ ገልጿል።
ከሚነሳው ቅሬታ ባሻገር የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል ብሏል።
ግለሰቡ በጎዳናዎች ላይ የተለያዩ አፀያፊ በተለይም የሴቶችን ክብር የሚነካ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች በመፈፀም የቀረፃቸውን ምስሎች በመልቀቅ በፈፀመው ህገ ወጥ ተግባርና በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።
በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ አንዳንድ ምስሎች ተገቢነታቸውን የሳቱና ያፈነገጡ እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ ገልፆ ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በሚለቁ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
#DireDawa
" የትኛውም አሽከርካሪ ላይ የሚደርስን የትኛውም አይነት ህገወጥ ተግባር አንታገስም ! " - ድሬዳዋ ፖሊስ
በድሬዳዋ " ፎርስ " እየተባለ የሚጠራው ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር ሹፌር ላይ አፀያፊ ህገወጥ ተግባር የፈጸመ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የድሬዳዋ ፖሊስ አሳውቋል።
አሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት አልታገስም ሲልም ገልጿል።
በድሬዳዋ ፖሊስ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ ም/ኮማንደር ይሔነው ሽፈራው ፥ " አፀያፊ ድርጊቱ የተፈጸመው ህብረተሰቡን በሰላማዊ ሁኔታ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያጓጉዝ ፣ የሚያደርስ እና የሚመልስ የፎርስ አሽከርካሪ ላይ ነው " ብለዋል።
ድርጊቱ የተፈጸመው ' ሳቢያን አንበጣ ' አካባቢ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
" ግለሰቡ ከፎርስ አሽከርካሪው ጋር አለመግባባት ሲፈጠር የተሽከርካሪውን ቁልፍ ጭምር ነቅሎ ይዞ ሲሄድ የሚታይበት ምስል በቀጥታ ወደእኔ ነው የተላከልኝ ከዛ ወዲያ በአቅራቢያው ላለው ለጎሮ ፖሊስ ጣቢያ መረጃውን ሰጠናቸው እነሱም ወዲያው ድርጊቱን የፈፀመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውለውታል " ብለዋል።
ህብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ተግባራት ሲመለከት መረጃ እየሰጠ መሆኑ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።
ም/ኮማንደር " የትኛውም አሽከርካሪ ላይ የሚፈጸምን የትኛውም አይነት ህገወጥ ተግባር አንታገስም፤ እንዲህ ያለው ድርጊት የሚፈጽሙትን በትዕግስት አናይም " ብለዋል።
" በከተማችን ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች በእኩብ አይን ነው የምናያቸው ፤ ከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ምንም አይነት ጥቃት ሳይደርስባቸው አገልግሎት እንዲሰጡ እንፈልጋለን " ሲሉ አክለዋል።
የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር አበበ ጥላሁን ፥ " መጋቢት 5 ከምሽቱ 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ላይ ነው ' በቀጠናችሁ የተፈጸመ ወንጀል ነው ' በሚል በቪድዮ መረጃው የደረሰን " ብለዋል።
" የተላከውን ቪድዮው ስንመለከት MM ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የታክሲ መሳፈሪያ ቦታ ላይ በታክሲ ተራ አስከበሪ አማካኝነት የተፈጸመ የወንጀል ተግባር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ድርጊት ፈጻሚው ተራ በአስከባሪነት እዛ ይሰራ የነበረ ኤርሚያስ ማሞ የተባለ ግለሰብ እንደሆነና ሚያዚያ 6 በስራ ቦታው ላይ እያለ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን አመልክተዋል።
" ማንኛውም ግለሰብ ድሬዳዋ ላይ ወንጀል ፈጽሞ ማምለጥ አይችልም " ብለዋል።
የድሬዳዋ ፖሊስ በቅርቡ በአንድ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌር ላይ " አጸያፊ " ሲል የጠራውን ተግባር የፈጸመ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል።
#DirePolice
#TikvahEthiopiaFamilyDD
@tikvahethiopia
ሰሙነ ሕማማት !
ከሆሳዕና በዓል (እሁድ) ስድስት ሰዓት እስከ አርብ (ስቅለት) ማታ ድረስ ያሉት ቀናት ሰሙነ ሕማማት ናቸው።
ሳምንቱ " ዘመነ ፍዳ " የሚታሰብበት ጊዜ ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰሙነ ሕማማት ወቅት " የፈጣሪን ህመም " ታሳቢ ያደረግ ልዩ ህግና ስርዓት አለ።
ቤተክርስቲያን ወትሮ የምታከናውናቸው ስርዓቶች በሕማማት ቀናት አይከናወኑም።
ህዝበ ክርስቲያኑ በሰሙነ ሕማማት የፈጣሪውን መከራ በማሰብ በተለየ ስርዓት ነው ቀናቱን የሚያሳልፈው።
በሰሞነ ሕማማት የትኞቹ የቤተ ክርስቲያን ስርዓቶች አይተገበሩም ?
በሰሙነ ሕማማት በቤተ ክርስቲያን " ግብረ ህማማት " የሚባል መጽሀፍ ይነበባል ፤ ለሳምንቱ የተዘጋጀ ልዩ ጸሎት ይደረጋል።
የሌሎች ስርዓቶች ክዋኔ ይገታል።
በሰሙነ ሕማማት ፦
- ቅዳሴ አይቀደስም (ከጸሎተ ሀሙስ ውጭ)
- ማህሌት አይቆምም
- ጸሎተ ፍትሀት አይደረግም
- መስቀል አይሳለምም
- ክርስትና አይነሳም
- ኑዛዜ አይሰጥም አይቀበልም
እነዚህ ስርዓቶች በሆሳዕና ዕለት አስቀድመው የሚከናዎኑ ናቸው።
ምዕመናን ሰሙነ ሕማማትን በምን ስርዓት ይከውናሉ ?
በቤተ-ክርስቲያኗ " የመከራ ዘመን " የሚባለውን 5500 ዓመትን በመወከል አምስት ቀናት ተኩል የሆነው ሰሙነ ሕማማት በምመናን ዘንድ በተለያዩ ድርጊቶች ይታሰባል።
የሚተገበሩት ድርጊቶች ሀዘንን ለመግለጽ እንዲሁም ከአስተምሮ ጋር መልዕክ ያላቸው ናቸው።
ምእመናን በሰሙነ ሕማማት ፦
- ከመጨባበጥና መሳሳም በመራው
- በባዶ እግር በመቆም
- በስግደት
- በጸሎት
- ራስን ዝቅ ማድረግ ያስባሉ።
አባቶች በሕማማት ሳምንት ምዕመኑ ፦
° ወደ ራሱ ጠልቆ በመግባት መጸለይ እንዳለበት
° ሰው ስለ ኃጢያቱ ማሰብ እንዳለበት
° ስለ ሀገሩ ማዘን እንዳለበት
° ለሰላም መጸለይ እንዳለበት
° የሰው ልጅ ሰላም እንዲያገኝ ሰላም ያጣው ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ መጸለይ እንዳለበት
° ፈጣሪ የተቀበለውን መከራ በማሰብ ለሀገር ሰላም እንዲሰጥ ህይወታችንን ያስተካክል ዘንድ መለመን እንዳለበት
- ከኃጢያታችን ይቅር እንዲለን መጸለይ እንዳለበት ያስገነዝባሉ።
(መላከ ገነት ክብሩ ገ/ጻድቅ - ከዚህ ቀደም ለአል አይን ከሰጡት ቃል)
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
" ለመንገድ ስራ የተከማቸ አፈር በህፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት አጥፍቷል " - የወላይታ ከተማ ፖሊስ
በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ለመንገድ ስራ ተብሎ የተከማቸ አፈር በአካባቢው ሲጫወቱ የነበሩ ሕፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋዉ የተከሰተው በትናትናዉ ዕለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ መሆኑን የገለፁት አዛዡ በስፍራው የነበሩት ከ7 እስከ 9 ዓመት የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሶስት ሕፃናት እንደነበሩ ተናግረው ሕይወቱ ካለፈዉ ታዳጊ በስተቀር በሌሎቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋን።
ሕፃናቱ እየተጫወቱ የነበረበት ቦታ ለአደጋ ተጋላጭ መሆን እየጣለ ካለዉ ከባድ ዝናብ ጋር ተዳምሮ ለአደጋዉ መከሰት መንስኤ ሆኗል ሲሉ አስረድተዋል።
ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋው ፥ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንደሚሰራና በሶዶ ከተማ አስተዳደር የዉስጥ ለዉስጥ የአስፋልት መንገድ ስራ እያከናወነ የሚገኘዉ የቻይና ተቋራጭም አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ ቦታዎችን ጥበቃ እንዲያስቀምጥ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አስታዉቀዋል።
ከአደጋው ጋር ተያይዞ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ከአስር በላይ ሕፃናት ሕይወት እንዳለፈ ተደርጎ የሚሰራጨዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ ያሉት ፖሊስ አዛዡ እንደዚህ ዓይነት መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Yaya Wallet !
ለወዳጆችዎ ቀላል አማራጭን፤ ለኪስዎ ገቢን ይፍጠሩ!
ጓዶችዎን የዘመነ የክፍያ አማራጭ ተጠቃሚ እያደረጉ በእያንዳንዷ የገንዘብ ዝውውር ቦነስ ያግኙ!
✅ የያያን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://yayawallet.com/install
✅ ስልክ ቁጥርዎን ወይም የፋይዳ መታወቂያዎን በመጠቀም በቀላሉ ይመዝገቡ!
✅ የሪፈራል ኮድዎን ለጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያጋሩ
ያያ ዋሌት፤ ባጋሩት ቁጥር ዕድሉ የሚጨምር!
ለተጨማሪ መረጃ፡ https://shorturl.at/TKqnz ይጎብኙ ወይም በ 957 ላይ ሃሎ ይበሉ!
" ጨለማን ተገን በማድረግ የተፈፀመውን የማፍረስ ድርጊት በፅኑ እናወግዛለን " - ጠቅላይ ም/ቤቱ
በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የተባረክ መስጅድ አጥር በለሊት እንዲፈርስ የተደረገበትን ድርጊት በፅኑ እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳቋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፥ " ከ1967 ዓ.ል ጅምሮ ለ50 ዓመታት መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ባለው ተባረክ መስጂድ ላይ ከህጋዊ አሰራር ውጪ የተፈፀመውን የማፍረስ ድርጊት በፅኑ እናወግዛለን " ብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር በህጋዊ መንገድ የመስጅዱ ቅጥር እንዲታጠር ቢያደርግም ትላንት ሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ ከመንግስት የስራ ሰዓት ውጪ እንዲፈርስ መደረጉ ጠቅላይ ምክር ቤቱን እንዳሳዘን ገልጿል።
ይህን ተግባር የፈፀሙ አካላት በህግ አግባብ እንዲጠየቁና መስጅዱ የደረሰበት ኪሳራ ተሸፍኖ ድጋሚ እንዲታጠር ለማድረግ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አመልክቷል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፥ " መስጅዶች የሙስሊሞች ቤተ አምልኮ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ዐይን ብሌናቸው የሚጠብቋቸው መሰባሰቢያቸውና የልብ መርጊያቸው ጭምር በመሆናቸው ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይፈፀሙም በዚሁ አጋጣሚ እናሳስባለን " ብሏል።
በሌላ በኩል የተባረክ መስጅድ ኢማም ሸይኽ ሙሳ አደም ለሃሩን ሚዲያ በሰጡት ቃል ፥
" ተባረክ (ጀርመን) መስጂድ ህጋዊ ካርታ ያለው ከ1967 ጀምሮ ሲሰገድበት የቆየ ነው " ብለዋል።
" ሙስሊሙ ማህበረሰብ ባላወቀበት ሁኔታ በህጋዊ መልኩ የተሰራን የመስጂድ አጥር እና ታፔላ በውድቅት ሌሊት መጥቶ ማፍረስ ህገወጥ ተግባር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ለሰላማችን ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ባለ አካል በዚህ መልኩ በውድቅት ለሊት የመስጂዱን አጥር እና ታፔላ ማፍረስ በእጅጉ አሳዝኖናል " ሲሉ አክለዋል።
" አሁንም የሚመለከተው የመንግስት አካል ህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተፈፀመውን ትልቅ በደል በመልከት የመስጂዱን አጥር እና ታፔላ ወደነበረበት እንዲመለስ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
#ተባረክመስጂድ #አዲስአበባ
@tikvahethiopia
" ሆሣዕና '' (የዐብይ ጾም 8ኛ ሳምንት)
ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣዔ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።
ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው።
ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች እና ሕፃናት '' ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም '' በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት ነው፡፡
ይህ ዕለት በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘንባባ ተይዞ፣ እየተዘመረ እጅግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ይታሰባል።
በዐብይ ጾም ከሰርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሣዔ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡
በዚህ ጊዜ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ካህናት መስቀል በእጃቸው አይዙም፣ አያሳልሙም ፣ ይፍቱኝ ተብሎ ወደካህን አይቀረብም፤ ይህ ሳምንት የጌታን የመጨረሻው ስቃይ የሚታሰብበት ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
#Repost
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የሆሳዕና በዓል በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በልደታ ማርያም ካቴድራል ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌል፣ የሃይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተው ነበር።
#ሰላም_ካቶሊክ_ቲቪ
@tikvahethiopia
#WegagenBank
🔔 ታላቅ የምስራች
የዓለም አቀፍ ክፍያ በወጋገን ቪዛ ቀለለ💰💷💳
🔶 ይፍጠኑ 🔶 ይክፈሉ 🔶 ይደሰቱ
የወጋገን ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ቪዛ አገልግሎት ካሉበት ሆነው ሳይጉላሉ በቀላሉ ክፍያዎችን መፈፀም እና የኦን ላይን /በይነ መረብ ግብይት እንዳሻዎ መፈፀም ያስችልዎታል!
📌 በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ በቀላሉ!
የበረራ ትኬት መቁረጥ ፣ የሆቴል አገልግሎት ፣ የትምህርት ቤት እና ሌሎች ክፍያዎችን መፈፀም እንዲሁም በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኙ ታላላቅ የኦንላይን ግብይት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ (E-Commerce) ግብይት ማካሄድ ይችላሉ!
#WegagenBank #Visa #card
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ!
Telegram | Facebook
https://linktr.ee/WegagenBank
ከመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል የተላለፈ የሀዘን መልዕክት ፦
" በመቄዶንያ ማህበረሰብ፣ በጎብኚዎቻችንና በረጂዎቻችን ዘንድ ተወዳጅ የነበረውና የመቄዶንያ ቀደምት ተገልጋይ የነበረው ጌዲዮን ሙላቱ በዛሬው ዕለት በማረፉ እጅግ ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶናል።
ጌዲ በ1980 ዓ.ም አዲስ አበባ ጎላ ሚካኤል አከባቢ ተወልዶ ያደገ ሲሆን በ1999 ዓ.ም የ19 ዓመት ወጣት ሆኖ ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ በስትሮክ ምክንያት ከአንገቱ በታች ፓራላይዝድ ሆኖ ሰውነቱን ማዘዝና በአንደበቱ መናገር አይችልም ነበር።
እናትና አባቱ ከሱ ጉዳት በፊት ስለሞቱ አክስቱ እየተንከባከበችው ጎላ ሚካኤል በሚገኘው ጠባብ ቤት ውስጥ ለብዙ ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ እየተሰቃየ የኖረ ሲሆን በ2005 ዓ.ም ወደ መቄዶንያ ማዕከል ሲገባ መናገር የማይችለው ጌዲ ደስታውን የገለፀው በብዙ እንባ ነበር፡፡
ጌዲ በመቄዶንያ ግቢ ውስጥ ልዩ መኝታ ክፍል ተሰጥቶት በየዕለቱ ልዩ ልዩ እንክብካቤና ህክምና እየተሰጠው በደስታ ይኖር ነበር፡፡
በተለያዩ ትልልቅ ሆስፒታሎች የልብ ህክምና ሲደረገለት የነበረ ሲሆን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በድንገተኛ ህክምና ክፍል ተኝቶ ልዩ ክትትል እየተደረገለት በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ረፋድ 5:00 ሰዓት በህክምና ላይ እያለ በ37 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል፡፡
ህይወቱን ለማትረፍ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስፔሻሊስት ሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገው የነበረ ሲሆን ላደረጉት ርብርብ እጅግ አድርገን ለማመስገን እንወዳለን።
ለመቄዶንያ መስራቾች ብንያምና እሌኒ፣ ለአረጋውያኑና አዕምሮ ህሙማኑ፣ ለመቄዶንያ ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም ለጎብኚዎቻችንና ለለጋሾቻችን በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን!
የጌዲዮን ሙላቱ የቀብር ስነ-ስርዓት ነገ ረፋድ መቄዶንያ ፊትለፊት አያት መድኃኒዓለም ቤ/ክ ይካሄዳል! "
#Mekedonia
@tikvahethiopia
" ጤና ሚኒስቴር ' አጽድቄዋለሁ ' የሚለው አዋጅ የጤና ባለሞያዎችን ችግር የሚፈታ ነው ይላል ነገር ግን ችግሮቻችን እነኚህ ብቻ አይደሉም " - ሃኪም
➡️ " አዋጁ የጤና ባለሞያዎችን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ ነው " - ጤና ሚኒስቴር
የጤና ባለሞያዎች " ለዘመናት እየጠየቅናቸው ያሉ በጤናው ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮቻችን ይፈቱ" ሲሉ ድምጻቸውን በተለያየ መንገድ በዘመቻ እያሰሙ ናቸው።
በርካታ ባለሙያዎችም ጥያቄያቸውን እና ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎቹ በተለያዩ መንገዶች እያካሄዱ የሚገኙትን ዘመቻ ለመከታተል ባደረገው ጥረት በርካታ ባለሙያዎች በተናጠል እንዲሁም አንዳንድ የሞያ ማህበራት ዘመቻውን እያስተጋቡ መሆኑን ለማስተዋል ችሏል።
10 ነጥቦችን ይዞ የተነሳው ዘመቻ ፦
- የኢኮኖሚ፣
- የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣
- የሃኪሞች የሥራ ቦታ ደህንነት ፣
- የቤት እና የትራንስፖርት አቅርቦት፣
- አግባብነት ያለው ወቅታዊ የሥራ ክፍያ
- ለአለም አቀፍ የሥራ ገበያ የሚወዳደሩበት የብቃት መመዘኛ የፈተና ማዕከላት በሃገር ውስጥ እንዲቋቋሙ ይጠይቃል።
ንቅናቄው የኢትዮጵያ የህክምና ማህበር ድጋፍ ያለው ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ለማህበሩ ፕሬዝዳንት ፣ ስራ አስፈጻሚዎች እና የህዝብ ግንኙነት ክፍል ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የማህበሩ አባል ከሆኑ እና ስሜ አይጠቀስ ብለው ከጠየቁ የጤና ባለሞያ ንቅናቄው የማህበሩ ሙሉ ድጋፍ ያለው ስለመሆኑ አረጋግጠዋል።
" ማህበሩ ከዚህ በፊት ሲያነሳ የነበራቸው በርካታ ጥያቄዎች ነበሩ ባለመመለሳቸው ምክንያት ድጋሚ ጥያቄውን በማንሳት ለጤና ሚኒስቴርም ደብዳቤ እንሚያስገቡ እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮም እየተዘጋጀ ያለ ደብዳቤ መኖሩን መረጃው አለኝ " ብለዋል።
የጤና ባለሞያና የማህበሩ አባል በዝርዝር ባነሱት ሃሳብ ምን አሉ ?
" የንቅናቄው የመጀመሪያ አላማ የጤና ባለሞያዎችን መብት ማረጋገጥ ነው።
መብት ስንል ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መብት ሊሆን ይችላል በዋናነት ኢኮኖሚያ ያለብን ጫና መስተካከል አለበት።
የአንድ ሃኪም የሚከፈለው ደሞዝ እና የሚኖርበት ሁኔታ ሲታይ በጣም አሳፋሪ ነው።
እየተራበ የሚያገለግልበት ሰዓት ታሳቢ ተደርጎ ፣ምን ያህል ድካም እንዳለበት እና ምን ያህል ሰዓት እንደሚሰራ ታሳቢ ተደርጎ ሊከፈል ከሚገባው ጋር አይመጣጠንም።
የትኛውም ሆስፒታል የሚሰራ ሃኪም ሳይከፍል መታከም አይችልም እንደማንኛውም ህብረተሰብ ካርድ አውጥቶ እና ከፍሎ ነው የሚታከመው ይህ መሆን የለበትም በሚያገለግልበት ሆስፒታል ነጻ የህክምና አገልግሎት ሊመቻችለት ይገባል።
ጤና ሚኒስቴር ' አጽድቄዋለሁ ' የሚለው አዋጅ የጤና ባለሞያዎችን ችግር የሚፈታ ነው ይላል ነገር ችግሮቻችን እነኚህ ብቻ አይደሉም በአንድ በኩል ብቻ ችግሩን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት አመርቂ አይደለም ከዚህ ቀደምም የተነሱ ጥያቄዎች አሉ አንዱን ክንፍ ብቻ ፈትተህ ሙሉ በሙሉ ችግሮቹ ተፈተዋል ብለህ የምትናገረው አይደለም።
የእኛ ጥያቄ ችግሮቹ በሙሉ ይታዩ ነው ከችግሮቹ መካከል አንድ ነጠላ ነገር ብቻ አውጥተህ ይኸው ችግራቹን ፈትተናል ችግር የለም ተብሎ ለማድበስበስ የሚኬደው ጥረት ተገቢ አይደለም " ብለዋል።
የጤና ሚኒስቴር ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ገባኤ ላይ የጸደቀው " የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 " የጤና ባለሞያዎችን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ ነው ብሏል።
ለመሳያነት በጠቀሳቸው ጉዳዮች ምን ምን ናቸው ?
1/ የጤና ዘርፍ ሰራተኛ መብት በሚደነግገዉ አንቀጽ ስር የጤና ዘርፍ ሰራተኛ በስራው ባህሪይ ምክንያት ተጋላጭ ለሚሆንባቸው በሽታዎች ቅድሚያ የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳለዉ እና የጤናው ዘርፍ የመንግስት ሰራተኛ የጤና መድህን አባልነት ሙሉ መዋጮ በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን እንደሚደነግግ።
2/ ከሕክምና አገልግሎት ጋር የተያየዙ ክሶች ስለሚቀርቡበትና ስለሚሰሙበት ሁኔታን በተመለከተ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተጠረጠረ ማንኛውም የጤና ባለሙያ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት በቁጥጥር ስር የሚውለው ባለሙያዉ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ምክያታዊና አሳማኝ ጥርጣሬ እንዲኖር የሚያስችል ማስረጃ ሲኖር ብቻ መሆኑን ይደነግጋል።
አዋጁ በፍጥነት ታትሞ እንዲወጣ ከማድረግ ጎን ለጎን ከነዚህ እና ሌሎች ጋር ተያይዞ ለአፈጻፀም በአዋጁ ዉስጥ የተመላከቱ ደንቦችና መመሪያዎች በሚመለከተዉ አካል እየተዘጋጁ ይገኛሉ ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ፋይዳ
የፋይዳ ልዩ ቁጥር በማጋራት የሚፈጠር ምንም አይነት ስርቆት አይኖርም፡፡
የፋይዳ ልዩ ቁጥር (ባለ 12 አሀዝ) ልዩ ቁጥር በህይወት ዘመን አብሮ የሚቆይ የማይቀየር ቁጥር ሲሆን የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (16 አሀዝ) ቁጥር የሚባለው ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የሚቀየር ቁጥር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር አንድ ግለሰብ ትክክለኛት ለማረጋገጥ አገልግሎት የሚያገለግል ነው፡፡
ነገር ግን ይህ ቁጥር በባዮሜትሪክ መረጃ የተደገፈ ልዮነትን የሚገልፅ በመሆኑ የአንድን ሰው ፋይዳ ቁጥር በማጋራት የሚመጣ ምንም አይነት የማንነት ስርቆት ወይም ሌላ አገልግሎት ተመሳስሎ የሚገለገልበት አግባብ የለም።
#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ፋይዳለሁሉም
#የኢትዮጵያልጆች👏
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የሁዋዌ " ቴክፎርጉድ ግሎባል " ውድድርን #አንደኛ በመሆን አሸነፉ።
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል።
ውድድሩ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የቆየ ሲሆን በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎችን ካካተተው ዝግጅት ጋር የተካሄደ ነው።
በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ፦
➡️ ከአዲስ አበባ፣
➡️ ከሐረማያ፣
➡️ ከጅማ፣
➡️ ከወልቂጤ
➡️ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (AASTU) ዩኒቨርስቲዎች ነው ያሰባሰበው።
ቡድኑ በውድድሩ ከሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ አርጀንቲና አየርላንድ፣ ማላዊ፣ ቬትናም፣ አረብ ኤምሬትስና ሌሎችን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ 12 ልዩ ቡድኖች ጋር ተወዳድሯል።
የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋም በዝግጅቱ በእንግድነት ተገኝታለች።
ተማሪዎቹ በምን ፕሮጀክት አሸነፉ ?
ተማሪዎቹ የእንስሳትን ህመሞች አስቀድሞ ለመለየት በተዘጋጀውና በአርተፊሻል አስተውሎት (AI) በጎለበተው ኤርሊ ቬት (EarlyVet) በተሰኘው ፕሮጀክታቸው ነው የተወዳደሩት። በዚህም ትኩረት ለመሳብ ችለዋል።
ይህ የፈጠራ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በተለይም ግብ 2 " ዜሮ ርሃብ " እና ግብ 15 " ህይወት በምድር " ከሚለው ጋር የተጣጣመ መሆኑና በግብርና እና በእንስሳት ጤና ላይ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን በውድድሩ ተብራርቷል።
የሁዋዌ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ሊሚንግ ዬ ምን አሉ ?
ዳይሬክቱ ፥ በቡድኑ ስኬት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው " ድሉ የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ልዩ ችሎታ እና ፈጠራ የታየበት ነው " ብለዋል።
መጪው ትውልድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የቴክኖሎጂ ገጽታ ውስጥ እንዲበለጽግ በሚያስፈልገውን ድጋፍ እና እድሎች ማመቻቸቱን ለማስቀጠል ሁዋዌ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ቡድኑ ለዓለም አቀፋዊ ውድድር እድል ያገኘው በግንቦት 2016 ዓ.ም በኤሳውራ ሞሮኮ በተካሄደው የክፍለ አህጉራዊ የቴክፎርጉድ (Tech4Good) ውድድር ወቅት ከ17 የአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ 28 ቡድኖች ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣቱ ነው።
መረጃው ከሁዋዌ ኢትዮጵያ የተላከ ነው።
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ሲያካሂድ የነበረእን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ አጠናቋል። አጀንዳዎችንም ተረክቧል።
@tikvahethiopia
ዋሪት ፈርኒቸር !
ክቡራን ደንበኞቻችን ! መጪው በዓል የሰላም፤ የፍቅር እና የስኬት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ከልብ እየተመኘን፡ ምቾታቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶቻችንን በሁሉም የማሳያ ቅርንጫፎቻችን ከልዩ ቅናሽ ጋር አዘጋጅተን እንጠብቅዎታልን!
ወደ ማሳያ ክፍሎቻችንን በመምጣት ይጎብኙን !
* 22 - ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* አዳማ - ሶረቲ ሞል
* ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
* ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
* ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706 / 07