tikvahethiopia | Неотсортированное

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1527057

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Подписаться на канал

TIKVAH-ETHIOPIA

#JigjigaUniversity

“ ፈተና አልፈን ቴምፖ እየጠበቅን ባለንበት ድጋሚ በሰኔ ትፈተናላችሁ ተባልን በሰላሚዊ ሰልፍ ስንጠይቅ። የተመታ ተማሪ አለ ”  - የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን

🔴 “ የኛም የመጀመሪያ ጥያቄያችን ነው። እየተከራከርን ነው ”  - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት

➡️ “ ጉዳዩ ‘ፈተና በሁለተኛ ጊዜ የተቀመጡት ተማሪዎች ውጤታቸው ‘ችቲግ’ ምልክት አለው’ በመባሉ ትምህርት ሚኒስቴር ሆልድ ስላደረገ ነው" - የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
ተመራቂ ተማሪዎች ፈተና አልፈው፣ ቴምፖ እየተጠባበቁ ባሉበት ወቅት ቴምፖ ተከልክለው ‘በድጋሚ ትፈተናላችሁ’ በመባላቸው ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ምሩቃኑ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ሪኤግዛም ተፈትነን አልፈናል። ሁለት ወራት ከቆዬን በኋላ ባላወቅነው ነገር ‘ቴምፗችሁ ታግዷል፤ ተሰርዟልና ድጋሚ ሪኤግዛም ትወስዳላችሁ’ ተባልን። 

ሁለት ወራት ሙሉ ምላሽ አላገኘንም ነበር። ‘የተመረቃችሁ ተማሪዎች ከግቢ ውጡ’ እያሉ ጫና ሲፈጥሩብን ተሰብስበን ስንጠይቅ ‘ሪኤግዛም ነው የምትወስዱት’ አሉን። ‘ፈተና ተኮራርጃችኋል፣ ከፍተኛ ውጤት መጥቷል ' ነው ነገሩ።

ቢሮ ለመጠየቅ ስንሄድም በፓሊስ አስከብቦ ድብደባ የተፈጸመበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። የተመታ ተማሪ አለ። የሄድነው ለመጠየቅ ነው፣ ያልተገባ ነገር አልጠየቅንም።

ከኛ ግቢ የተፈተኑ ኮሌጆች ነበሩ ጥር ላይ ከኛ እኩል። እነርሱም ወስደዋል። ከሃረሚያ ዩኒቨርሲቲ መጥተውም ቴምፖ ወስደዋል እዚህ የተፈተኑት። ለግማሹ ተሰጥቶ ለግማሹ ነው የተከለከለው።

ተማሪው ተቸግሯል። ቤት ተከራይቶ፣ የቀን ሥራ እየሰራ የሚኖር አለ። ለቤተሰብ አልፈናል ብለን አውርተናል። ፈተና አልፈን ቴምፖ እየጠበቅን ባለበት ድጋሚ ሰኔ ትፈተናላችሁ ተባልን በሰላማዊ ሰልፍ ስንጠይቅ ” ብለዋል።  

“ እኛ ጋር የተፈተኑ የጤና እና የኒውትሬሽን ተማሪዎች እንግዲህ ቴምፖ ወስደዋል። የተፈተነው ግን አንድ ላይ ነው። የተፈተነው አንድ ላይ ነው ‘ተኮራርጃችኋል’ የሚባል ነገር ካለ ለግማሹ ተሰጥቶ ለግማሹ ለምን ይከላከላል ? ” ብለው ቢጠይቁም አጥጋቢ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው በመግለጽ፣ አሁንም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

ስለጉዳዩ ምንነት የጠየቅነው ማኀበሩ በሰጠን ቃል፣ “ ' ኩረጃ 'በሚል ነው። የጅግጅጋ ብቻ ሳይሆን የሦስት ዩኒቨርሺቲዎች ነው የተያዘው። የጎንደር፣ ወለጋ፣ ጅግጅጋ። የጅግጅጋው በአጠቃላይ ነው ታጥፎ የነበረው ” ብሏል።

“ የጤና ተማሪዎችን ቴምፖ አስለቅቀናል። የሌሎቹም ሂደት ላይ ነው ያለው ” ማኀበሩ፣ “ የቅሬታ ሰሚን ምርመራ እየጠበቅን ነው። ምክንያቱም እኛም የምናነሳው ጥያቄ ስላለ ” ሲልም አክሏል።

ማኀበሩ፣ “ የኮረጁ ዩኒቨርሲቲዎች ተብለው ነው የተያዙት ” ያለ ሲሆን፣ መጀመሪያ ላይ ተማሪዎቹ ተኮራርጀው ከሆነ ለምን ቅድሚያ አልተነገራቸውም? ውጤት ካዩ በኋላ ለምን ይህ ሆነ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ “ የኛም የመጀመሪያ ጥያቄያችን ነው። እየተከራከርን ነው ” ብሏል።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቃቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት በሽር አብዱላሂ (ዶ/ር) በሰጡን ቃል፣ “እኔ አሁን አዲስ አበባ ነው ያለሁት። እየተከታተልሁ ነው። ጉዳዩ ፈተና በሁለተኛ ጊዜ የተቀመጡት ተማሪዎች ውጤታቸው ‘ችቲግ’ ምልክት አለው’ በመባሉ ትምህርት ሚኒስቴር ሆልድ ስላደረገ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር ጋር ገብተን ተነጋግረናል ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ውጤታቸው ችግር ካለበት ይታይና የተወሰነ ልጆች ችግር ካለባቸው ተለይቶ ይለቀቅላቸው የሚል ነው የኛ ሀሳብ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። 

ተማሪዎቹ መውጫ ፈተና እንዳለፉና ውጤታቸውን እንዳዩ፣ ቴምፖ ለመቀበል እየተጠባበቁ ባሉበት ወቅትም ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተኑ እንደተባሉ ነው ቅሬታ ያነሱትና ይህ አግባብ ነው ? የሚል ጥያቄ ለፕሬዜዳንቱን አቅርበናል።

“ እኛም ይሄን ሪፖርት ይዘን ትምህርት ሚኒስተር በማቅረብ ስብሰባ በመግባት ተነጋግረናል። ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ግን ይሄን ነገር አይተን በኋላ ውሳኔ እንሰጣለን በማለት ነው የተለያየነው ” ሲሉ መልሰዋል ፕሬዜዳንቱ።

አክለውም፣ “ ግን መጨረሻ እንደገና ‘በሰኔ ይፈተኑ’ የሚል ነው ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣው። እኛም ተቃውሞ አለን። ችግር ያለባቸው ጥቂት ተማሪዎች ሊኖሩ ይችላሉ ግን ውጤታቸው መለቀቅ አለበት የሚል ሀሳብ ነው የኛም አቋም ” ነው ያሉት።

“ ጉዳዩን ከትምርት ሚኒስተር እየተነጋገርን ነው ትምህርት ሚኒስተር ኦረዲ የወሰኑት ጉዳይ አለ። እንደ ዩኒቨርስቲው ማኔጅመትም የተማሪዎቹ ውጤት በደንብ ተጣርቶ ይለቀቅላቸው የሚል ነው የኛ ሀሳብ ” ብለዋል።

ለቅሬታው ያለውን ምላሽ ለማካተት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ያደረግነው ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን፣ ምላሽ ከሰጠ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ " ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት፣ የፕሪቶርያን ስምምነት እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ምክር በማከል ሰፊ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል " ብለዋል።

" የአቶ ጌታቸው ረዳ የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ የሚቀሩ ቁልፍ ሥራዎችን የሚያከናውን አካል፣ ግዝያዊ መንግሥቱ መቀጠለ አለበት የሚል ድምዳሜ ከተያዘ በኋላ፣ ይሄንን ሽግግር ማን መርቶ ከግብ ሊያደርስ ይችላል ? የሚሉ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ዛሬ በይፋ እና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩን እና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም መካሄዱን አሳውቀዋል።

" ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሰው ናችው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችን እና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸው " ብለዋቸዋል።

" አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምነት በብዙ አካላት የታመነ ነው። የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላም እና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ " ብለዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የታለ ዲግሪያችን ብለን ስንጠይቅ ' አናውቅም፣ አልታተመም ፣ ይታተማል ' እያሉ እያመላለሱን ነው " - ቅሬታ አቅራቢዎች

➡️ " ዲግሪያቸውን ማጣት አልነበረባቸውም ስጡኝ ብለው መጠየቅም አልነበረባቸውም የእኛ ስህተት ነው "- ዩኒቨርሲቲው

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ከተመሰረተበት 1999 ዓ/ም ጀምሮ ላለፉት አመታት ላስመረቃቸውን ተማሪዎች ኦርጂናል ዲግሪ ባለመስጠቱ ተመራቂዎች የውጭ እና የሃገር ውስጥ የስራ እድሎች እያመለጡን ነው የሚል ቅሬታ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ማሰማታቸውን ይታወሳል።

የየኒቨርሲቲው ተመራቂዎች ሲመረቁ የወሰዱት ጊዜያዊ (Temporary) ዲግሪ መሆኑን በመግለጽ አስፈላጊውን የኮስት ሼሪንግ ክፍያቸውን በመፈጸም ኦርጅናል ዲግሪያቸውን ከዩኒቨርሲቲው ቢጠይቁም በየጊዜው " ይሰጣችኋል " ከማለት ውጪ ምንም ምላሽ አላገኘንም ብለው ነበር።

ዩኒቨርሲቲው " ኦርጂናል ዲግሪውን መስጠት ያልተቻለው ከባድ የሚባል የበጀት እጥረት በመኖሩ ነው ከስር ከስር በመስራት ለተማሪዎቹ ዲግሪያቸውን እንሰጣለን " የሚል ምላሽ በወቅቱ ለቀረበው ቅሬታ ሰጥቷል።

ነገር ግን ተመራቂዎች በድጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ምን አሉ ?

" ' ተጀምሯል ይታተማል ' ይሉናል የተወሰነ ቀን አይነግሩንም ሃላፊነት ውስዶ የሚያሰራ ሰው የለም።

የስራ እና የትምህርት እድል ለመጣለት ተመራቂ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ ክፍያ በማስከፈል አስቸኳይ በመስራት የሚሰጥበት እድል አለ እዚህ ግን ለአጣዳፊ ነገሮች እንኳ ምንም አይነት አሰራር አልዘረጉም።

የታለ ዲግሪያችን ብለን ስንጠይቅ ' አናውቅም፣ ፣አልታተመም ፣ ይታተማል ' እያሉ እያመላለሱን ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ጉዳዩን በመያዝ ዩኒቨርሲቲው አመራር ምላሽ የጠየቅን ሲሆን የየኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተረፈ ጌታቸው ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል።

ለቅሬታው ምን ምላሽ ሰጡ ?

" አሁን ያለው የበላይ አመራር ተቀይሮ ከሄደ በኋላ የተመራቂዎችን የወረቀት ስራ የመለየት ፣የማስተካከል እና የማጣራት ስራዎችን ሰርተን አሁን እስከ 2009 ድረስ ያሉ ተመራቂዎች ላይ ደርሰናል።

ኮሚቴ አዋቅረን አሁን ቁጭ ብለው እየሰሩ ነው ይህንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እስከ 2016 ያሉ ተመራቂዎችን ውጤት ለብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤት አምጥተን የምንሰጥ ይሆናል።

ከዚህ ቀደም የወሰዱ ተመራቂዎች በጣም አጣዳፊ የሆኑ ጥያቄዎች ሲያቀርቡ የነበሩ ልጆች አንድ ላይ ተሰርቶላቸው የተሰጣቸው ይመስለኛል ይህ ደግሞ ተገቢ አይደለም።

ተቋም ከሆነ መሰራት ያለበት የሁሉም ነው ይህንንም አዘጋጅተን የሁሉም ተጽፎ እስከ 2009 ያሉ ተመራቂዎች ጋር ደርሰናል አጠቃለን ለህትመት እንልካለን።

በዚህ ወር ውስጥ ለብርሃን ሰላም ጋር ውል እናስራለን እስከ ሰኔ ወር ድረስ የሙሉ ተመራቂዎች (እስከ 2016 ያሉትን) እንሰጣለን።

ህትመቱም የሚከናወነው እንደ ተመረቁበት አመት በቅደም ተከተላቸው ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኦርጂናል ዲግሪው በጊዜው ስላልተሰጣቸው የውጭ የስራ እና የትምህርት እድል እያመለጣቸው መሆኑን የሚያነሱ ተመራቂዎች አሉ ለእነሱስ ምን ታስቧል ? ሲል ጠይቋል።

" ለእኔም የደወሉልኝ ልጆች አሉ መረጃ የሚያቀርቡ ከሆነና የብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤትም የሚተባበረን ከሆነ መረጃውን አሲዘን በይፋዊ ደብዳቤ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው መጠየቅ እንችላለን።

ሁሉም ተማሪ የእኔ ይቅደምልኝ ሊል ይችላል ይህ ደግሞ በየአመቱ ከፋፍለን ለማተሚያ ቤት ስለምንሰጣቸው ለአሰራር ያስቸግራል።

ውል የምንገባው የማጣራት ስራችንን ከጨረስን እና የሚታተመውን ብዛት ካወቅን በኋላ ነው እስካሁን ውል አልገባንም ውል ከመግባታችን በፊት ማስረጃ ያላቸው ሰዎች በዚህ ወር አስቀድመው ይምጡ።

ኦርጂናል ዲግሪ ተብለው የተጠየቁበትን ደብዳቤ ማስረጃ ማምጣት የሚችሉ እና የስራ እድሉ እንደደረሳቸው የሚያሳይ ኦፊሻል ኢሜል ማሳየት የሚችሉ ከሆነ መረጃውን አያይዘን ቅድሚያ እንልካለን " ሲሉ መልሰዋን።

ዩኒቨርስቲው ከተመሰረተ 18 ዓመት ሆኖታል በተለያየ ጊዜ ላስመረቃቸው ተማሪዎች በጊዜው ኦሪጂናል ዲግሪ መስጠት ለምን ተሳነው ? ስንል ጥያቄ አንስተናል።

እሳቸው ወደ አመራር ከመጡ አጭር ጊዜ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ጉዳዩ አግባብ አይደለም ብለዋል።

" ይሄ በጣም ነውር ነው ይሄን ያህል አመት ሳይታተም ሰው የሚፈልገው ኦሪጂናል ዲግሪ ሳይሰጠው መቆየት እንደ ተቋም አግባብ አይደለም።

ከዛ በኋላ የተመሰረቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንኳን እየሰጡ ባሉበት እና ማተሚያ ቤቶችም ባሉበት የሚፈለገውን ኦሪጂናል ዲግሪ ለመስጠት መቆየት አልነበረበትም።

እኛም እየሰራን ያለነው በሬጅስትራር አካባቢ ያሉ ሊፈቱ የሚገቡ ስራዎችን እየሄድንበት ነው ዲግሪያቸውን ማጣት አልነበረባቸውም ስጡኝ ብለው መጠየቅም አልነበረባቸውም የእኛ ስህተት ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በገዛ ቤታቸዉ በር ላይ በመኪናቸዉ ዉስጥ ነው የተገደሉት " - የአቶ ዳኛ ግርማ ባልደረቦች

➡️ " አስከሬናቸው እስካሁን ከሆስፒታል አልወጣም ! "


በደቡብ አፍሪካ ፒተር ማሪትስበርግ ከተማ ነዋሪና በሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተወካይ አመራሮች ዉስጥ አንዱ የሆኑት አቶ ዳኛ ግርማ በትላንትናዉ ዕለት መኖሪያ ቤታቸው በር ላይ በገዛ መኪናቸዉ ዉስጥ እስካሁን ማንነታቸዉ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸዉን የስራ ባልደረቦቻቸዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" አቶ ዳኛ በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ መካሪ አባትና አስታራቂ ሽማግሌ ነበሩ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሃሳባቸዉን ያጋራቱት አንድ የስራ ባልደባቸዉ ፤ በስራ ላይ ዉለዉ ወደ ቤታቸው እየገቡ በነበረበት ወቅት የግቢያቸዉ በር ላይ ከመኪናቸው ሳይወርዱ ጥቃቱ እንደተፈፀመባቸው ገልፀዋል።

" ለኢትዮጵያውያን አንድነት እንዲሁም በሰዉ ሀገር በመተጋገዝ ሰርቶ ስለመለወጥ ዘዉትር ሲሰሩ የኖሩ የኢትዮጵያዊያን አባት ነበሩ " ያሉን በቅርበት የሚያዉቋቸዉ አንዲት የደቡብ አፍሪካ ነዋሪ " ግፈኞች እኝን ጀግና አባት ነጠቁን " ሲሉ ተናግረዋል።

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ (ማህበረሰብ) ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ሀቢብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት አቶ ዳኛ ግርማ ፊጣን ከ18 ዓመታት በፊት ከፈረንጆቹ 2007 ጀምሮ ለኢትዮጵያውያን አንድነትና አብሮነት ሲታገሉ እንደሚያቋቸዉና በተገደሉበት ዕለትም ይህንኑ የማስታረቅ በጎ ተግባር አከናዉነዉ ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ እንደነበር ገልጸዋል።

ከኢትዮጵያ ኤንባሲ እና ከሀገሪቱ ፖሊስ ጋር በመሆን ገዳያቸዉን ለመከታተልና ለማስያዝ በጋራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ማክሰኞ እሳቸዉ በሚኖሩበት ፒተር ማሪትስበርግ ከተማ የአስከሬን አሸኛኘት ስርዓት እንደሚደረግላቸው እና በማግስቱ በጆሃንስበርግ ትልቅ የሽኝት ፕሮግራም ለማድረግ እንደታሰበም አቶ ዮሐንስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከአውቶብስ እያስወረዱ ነው በጥይት የመቷቸው እስካሁን 3 ሰዎች ሙተዋል ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችም ቆስለዋል " - የጎንቻ ሲሶ ወረዳ አስተዳዳር

በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ከመርጦ ለማርያም ወደ ግንደወይን በህዝብ ትራንስፖርት ይጓዙ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ 3 ሰዎች ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን የጎንቻ ሲሶ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ የኔዋ ደመቀ በሰጡት ቃል ድርጊቱን የፈጸሙት " ፅንፈኛ " ሲሉ የጠሩት ኃይል ነው።

" ዛሬ ማለትም መጋቢት 29/2017 ዓ/ም ከመርጦ ለማርያም ወደ ግንደወይን በደብረ ያቆብ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሾተል ማጠቢያ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ታጣቂዎች አውቶብሱ ላይ በከፈቱት ተኩስ እናትና ልጅን ጨምሮ 3 የጎንቻ ሲሶ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ተገድለዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አቶ የኔዋ አክለዉም በአካባቢው ምንም አይነት ጦርነት አለመኖሩን አመልክተዋል።

" በአካባቢው ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይል ሰሞኑን ህዝብ እንዳይንቀሳቀስ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ እንደነበር ሰምቻለሁ " ብለዋል።

ድርጊቱ የተፈፀመው እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ በመሆኑ የቆሰሉትን ሰዎች ቁጥር ማወቅ አልተቻለም የሞተም ይኖራል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የ3ቱ ሟቾቹ አስከሬን ይኖሩበት ወደ ነበረው እነቸኮል ቀበሌ መላኩን ገልፀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyBDR

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

“ አስከሬኑን ይዘው ትላንት ምሽት 11 ሰዓት አዲስ አበባ ገብተዋል። ዛሬ ቀጨኔ ተቀበሩ ” - የረዳቱ የቅርብ ሰው

➡️ " የኔ ቤተሰቦች ሦስት ናቸው። ከሦስቱ አንዷ ሞታለች።
ትላንት ተቀበረች " - ቤተሰብ

ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ ነበር የተባሉ የአንድ ተሽከርካሪ ተሳፋሪዎች ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ/ም ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ “ጎሃ ፅዮን” እና “ ቱሉ ሚልኪ ” የተሰኘ ቦታ ሲደርሱ የግድያና እገታ ጥቃት እንደደረሰባቸው መገለጹ ይታወቃል። 

በታጣቂዎች ታገተ የተባለው መኪና ባለቤት የመኪናው ረዳት መገደላቸውን፣ ሁለት የሟች ቤተሰቦችም ተገደሉ የተባሉት ረዳት ዛሬ መቀበራቸውን፣ ሌላኛው የሟች ቅርብ ቤተሰብ ደግሞ ሌሎች ሁለት ተሳፋሪዎች መገደላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የተሽከርካሪው ባለቤት ምን አሉ ?

የተሽከርካሪው ባለቤት ትላንት በሰጡን ቃል፣ 62 ሰዎችን አሳፍሮ የተነሳው የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መታገቱ በስልክ እንደተነገራቸው፣ ረዳቱ መሞቱን እንደሰሙ፣ ሹፌሩ እስካሁን ያለበትን እንደማያውቁ ተናግረዋል።

እኝሁ አካል፣ ስለጉዳዩ እንዲያጣሩ ሰዎችን ወደ ቦታው መላካቸውን፣ የተላኩት ሰዎች ስልካቸው ባለመስራቱ ምንም መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ተጨማሪ መረጃ ስንጠይቃቸው ልቅሶ ላይ እንደሆኑ ገልጸው፣ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የሟች ቅርብ ሰዎችስ ምን አሉ ?

የሟቹ የቅርብ ቤተሰብ ዛሬ በሰጡን ቃል ደግሞ፣ " አስከሬኑን ይዘው ትላንት ምሽት 11 ሰዓት አዲስ አበባ ገብተዋል። ዛሬ ቀጨኔ ተቀበሩ " ብለዋል።

" አንዱ ሟች ረዳት ነው። ሹፍርና ይሰራ ነበር፤ ግን በእግሩ ላይ ህመም አድሮበት በኋላ ረዳት ሆኖ ነው እየሰራ የቆየው " ብለው፣ " ምስጋና ለአንዳንድ ደጋግ ኢትዮጵያውያን አስክሬኑን ገንዘው አዘጋጅተው ለጠበቁን ሰዎች ይሁን። እንደዚህም አይነት ሰዎች አያሳጣን " ነው ያሉት።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሟች ልጅ ጓደኛ በበኩላቸው፣ " አባታቸው ነበር የሚያስተዳድሯቸው። ሟቹ ጓደኛዬን ጨምሮ ሦስት ልጆች አሏቸው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በቀጨኔ ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥርዓት ዛሬ እንደፈጸመ ገልጸው፣ ልጆቹ ሲያስተዳድራቸው የነበረ አባታቸውን በቅጽበት ስላጡ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሌሎች የሟቾች ቤተሰቦች ምን አሉ ?

አንድ የሟች ቤተሰብ፣ "ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ ባሱ ተኩስ ተነሳበት ጎሃ ፅዮን አካባቢ ነው)፤  የኔ ቤተሰቦች ሦስት ናቸው። ከሦስቱ አንዷ ሞታለች። ሁለቱ እህትማማቾች ነበሩ አንደኛዋ ቤተሰብ ነች። ሁለቱ ተረፉ አንዷ ግን ሞታለች ተቀበረች " ሲሉ ነግረውናል።

መንግስት፣ ሚዲያዎች ጉዳዩን ትኩረት እንዳልሰጡት ገልጸው፣ "ብቻ ወደት እየሄድን እንደሆነ በጣም ያሳስባል። ፈጣሪ አገራችንን ሰላም ያድርግ እንጂ የመንግስቱ ነገርስ ጭር የሚልም የለም " ሲሉ አዝነዋል።

ሌላኛው የቤተሰብ አባል ደግሞ፣ ሁለት ተሳፋሪዎች መገደላቸውን፣ ቤተሰብ ሀዘን ላይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከተሳፋሪዎቹ መካከል ከፊሎቹ ታግተው እንደተወሰዱ፣ ለጊዜው ቁጥሩን በውል ማወቅ ባይቻልም በርካቶች እንደተገደሉ የተመላከተ ሲሆን፣ ታግተው ተወሰዱ የተባሉት ዬት እንዳሉ ማወቅ አልተቻለም።

ትላንት ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቃቸው በፌደራል ፓሊስ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ፣ ሌላ ሥራ ላይ እንደሆኑ ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ በድጋሚ ስለእገታው ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ መኩራ ስናደርግም ስልካቸውን አላነሱም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

አቶ ጌታቸው ረዳ ምስጋና ቀርቦላቸው ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንትነት ተሰናበቱ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

በተለይ አቶ ጌታቸው የተገኘው ሰላም እንዲጸና ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና አመራር የፌደራል መንግስት እውቅና እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ ሥራዎች በጋራ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለነበራቸው ቆይታም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር በመሆን ለሁለት ዓመት መርተዋል። አሁን ላይ አዲስ የክልሉ ፕሬዝዳንት እንዲሰየም ሂደት ላይ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በጠቅላላው 349,943,588.66 የአሜሪካ ዶላር ለደንበኞቼ አቅርቢያለሁ " - አቢሲንያ ባንክ

አቢሲንያ ባንክ በያዝነው የበጀት ዓመት የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ ወደ 350 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማቅረቡን አሳውቋል።

በበጀት ዓመቱ ባንኩ ለደንበኞቹ በጠቅላላው 349,943,588.66 የአሜሪካ ዶላር ማቅረቡን ገልጿል።

አቢሲንያ ባንክ በዚህ ጊዜ ውስጥ ለደንበኞች ካቀረበው የምንዛሪ ድልድል ውስጥ በሶስተኛዉ የሩብ ዓመት ከ1 ሺ በላይ ደንበኞች ወደ ሀገር ውስጥ አስፈላጊ የገበያ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ ለማስቻል 189,082,861.80 ዶላር እንዲያገኙ ማድረጉን አመልክቷል።

አቢሲንያ ባንክ በቀጣይ የውጭ ምንዛሪ ሀብቱን በአግባቡ በማስተዳደር፣ ከአገራዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር በማጣጣም ግልጽና ፍታዊ የውጭ ምንዛሪ ድልድል ተግባራዊ በማድረግ፣ የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል።


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" 24 ሰዎችን ሲያጭበረብሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋም አካባቢ በመሆን " አስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት መሰጠት ቆሟል እኛ እናሰራላችሁ " በማለት ተገልጋዮችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ 2 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መ/ቤቱ አሳወቀ።

ግለሰቦቹ ተቋሙ ለ5 ቀን 20 ሺህ ብር የሚያስከፍለውን 28 ሺህ ብር በመቀበል ፣ የተሳሳተ መረጃ በመስጠትና ያልተገባ ክፍያ በመጠየቅ 24 የተቋሙን አገልግሎት ፈልገው የመጡ ደንበኞችን እንዳጭበረበሩ ተመላክቷል።

በቁጥጥር ስር ሊወሉ የቻሉት ከፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በደረሰ ጥቆማ መሰረት እንደሆነም ተቋሙ ገልጿል።

ተገልጋዮች የከፈሉትን ክፍያ ማስመለስ እንደተቻለም አመልክቷል።

የኢሚግሬሽንን አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣ ደንበኛ በተቋሙ መረጃ ዴስክ በመቅረብ መረጃዎችን ማግኘት ይገባዋል ያለው ተቋሙ ዜጎች እንዳይጨበረበሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NationalDialogue

“ ህገ መንግስቱ ላይ የአማራ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ኩርፊያ አለው። የታሰሩ የምክር ቤት አባላት ይፈቱልን ” - የማህበረሰብ ተወካይ ተሳታፊዎች 

🔴 “ ትልቁና ዋነኛው ችግር በአሁኑ ወቅት ወጥቶ መግባት ነው። ወጥተን እንዴት ወደ ቤታችን እንመለስ ? ” - ተሳታፊ

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል እያካሄደው ባለው አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር መድረክ ማህበረሰቡን የወከሉ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ጦርነት ሊቆም፣ ህገ መንግስቱ ሊሻሻል፣ የታሰሩ የምክር ቤት አባላት ሊፈቱ እንደሚገባ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

የማህበረሰብ ተወካዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

አንድ የማህበረሰብ ተወካይ ፦ “ እኔ የመጣሁት ከሰሜን ሸዋ ዞን ገምዛ ወረዳ ነው፤ ያለንበት ቦታ በየቀኑ ሰው የሚሞትበት ምሥራቅ አማራ ነው። የጸጥታው ሁኔታ ከባድ ነው።

ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጋር ነው ግጭት የሚፈጠረው ይህንን ግጭት የወለደው የወሰንና የማንነት ጥያቄ ነው። እየተማከርንበት ያለውም እርሱ ነው። ችግሩን ለመፍታት፣ መንግስት የህዝቦችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆን አለበት።

ዜጎች አርሰው የማይበሉበት ሁኔታ ላይ ደርሰዋል። ብዙዎቹ እየተፈናቀሉ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን መሬቱ ሳይታረስ ባዶ አድሯል። በሚቀጥለው ወቅት የሚጠበቀውን ምግብ ከዛ መሬት ላይ ማግኘት አይቻልም።

የክልሉና የፌደራል መግስት ትኩረት እዲሰጡ አየተነጋገርን ነው። ብዙ ህፃናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል። ይህም ዜጋን ለማስቀጠል አስቸኳይ ምላሽ ስለሚፈልግ እየተመካከርን ነው።

ግን ትልቁና ዋነኛው ችግር በአሁኑ ወቅት ወጥቶ መግባት ነው። ወጥተን እንዴት ወደ ቤታችን እንመለስ? ይሄ ከፍተኛ ምክክር የሚያስፈልገው ነው እንደ ማህበረሰብም እንደ መንግስትም ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ” ብለዋል።

ሌለኛው
የማህበረሰብ ተወካይ ምን አሉ ?

“ የታሰሩ የምክር ቤት አባላት ይፈቱልን። ህገ መንግስቱ አድሏዊነት እና ወቀሳ ያልበዛበት ህገ መንግስት ሊሆን ይገባል። ከኮንስትራክሽን ፣ ከመገድ ሥራ ፣ ከኢኮኖሚ አንፃር / በጀት አመዳደብ ፍትሃዊ ይደረግልን።

የሀገራችን እድገት መጥፎ ትርክቶችን እያነሳን መወቃቀስና መገዳደል የለብንም። ችግሮች እልባት እንዲሰጣቸው ማድረግ ነው እንጂ መገዳደል ተገቢ አይደለም።

የህዝብን ድምፅ መስማት ያስፈልጋል። ህዝብ ተሰሚነት ከሌለው ዋጋ የለውም መንግስትም ቢሆን ቀጣይ የህዝቡን ድምፅ ማዳመጥ አለበት። ችግር አለ። ችግር የለም የሚባልበት ቦታ ካለ አጠያያቂ ነው። ” ብለዋል።

የሃይማኖት አባት ምን አሉ ?

“  ተወካዮች በምክክሩ መፍትሄ ይገኛል ብለው የማህበረሰቡን ችግር እየመዘዙ እየተናገሩ ነው። ምክክሩ መመቻቸቱ ጥሩ ነው።

ይህንን ከዚህ ህዝብ የወጣውን ሀሳብ ይዞ የሚተገብር ሰው ከጠፋ ችግር ነው።

አሁን እውነት እየተነገረ ነው። አንዳንዶቻችን አንተዋወቅም ሀሳባችን ግን ጭብጡ አንድ ነው።

አማራ ሰውን የሚወድ፣ ጠንቃቃ፣ ቶሎ የማይቆጣ ህዝብ ነው። ውስጡ ካዘነና ከተቆጣ ደግሞ አማራን ለማሸነፍ የሚቻለው ባኮረፈበት እውነት ከተመጣበት ብቻ ነው። በተቀየመበት ነገር ከተመጣ ይሸነፋል፣ እሺ ይላል ግን በሽንገላ የለም።

ህገ መንግስቱ ላይ የአማራ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ኩርፊያ አለው። አንቀጽ ነቅሶ ይሄ በድሎኛል ይላል። በሌሎች ክልሎች በሚኖርበትም እንደ ሰው አልተቆጠረም። የፌደራል ህገ መንግስት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈለገበት ቦታ የመኖር፣ የመስራት መብት አለው ይላል። 

አሜሪካ ያሉት ኢትዮጵያውያን እኮ ፓለቲካ አመራር ውስጥ ገብተው በአሜሪካ ምርጫ ውስጥ እየሰሩ ነው። እዚህ ግን እዚሁ ተቀምጠን ይገፉናል። በኦሮሚያ ክልልስ ቢሆን ኦሮምኛ ተማሩ ማለት ነው የሚጠቅመው ወይስ ‘ኦሮምኛ ቋንቋ ስለማትችል ድራሽ ይጥፋ’ ማለት ? ” ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ 
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Amhara

“  በተለያዩ ክልሎች ያሉ አማራዎች እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ፣ ስራ አጡ እየበዛ፣ አማራ ‘አረጓዴ ቢጫ ቀይ ባንድራ፣ ቲሸርት ለብሰሀልና ወደ አዲስ አበባ አትገባም፣ ከአዲስ አበባ መውጣት አለብህ’ እየተባለ እየወጣ በተለያዩ አካባቢዎች ያለው እሮሮ የጸጥታ ችግሩን ወልዶታል። መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል ” - ተሳታፊ

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል በሚያካሂደው አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር እየተሳፉ ያሉ የማህበረሰብ ተወካዮች ለኮሚሽኑ የሚያቀርቧቸው አጀንዳዎች ተፈፃሚነት አግኝተው የህዝቡ ችግር ይፈታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ተፈናቃይ ተሳታፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ሊሞ ወረዳ ባርቁቤ ቀበሌ የተፈናቀሉ አንድ የእድሜ ባለጸጋ ፥  “ ትራክተር፣ ከገጠርና ከከተማ የነበረኝ ቤት ተቃጥሎ ሕይወታችንን በመከራ ይዘን ተፈናቀልን።

የተባባሰ ጦርነት መጥቶብን እየተሰቃየን አንዲት ወረዳ ነው ያለነው። መጠለያ ካምፕ የለንም። ቤት ተከራይተን፣ የቀን ስራ እየሰራን ተሰቃይተን ነው ያለነው፤ ብዙ ቤተሰብ ያለው ቤት አይከራይም ‘መጸዳጃ ቤት ይሞላብናል’ እየተባልን እየተሰቃየን ነው። 

ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ ነው የተፈናቀልነው። በወቅቱ የተጎዱ ብዙ ሰዎች አሉ። በእኛ አካባቢ ወደ 18 ሰዎች ሕወታቸው አልፏል። የ6 ቀበሌዎች ንብረት ምንም የለም። መሬቱ ዝም ብሎ ተቀምጧል፤ ባዶ ጫካ ነው። 

ስለዚህ ለምክክሩ መጠራታችን ጥሩ ነው። ግን በህዝብ አቅም (ግፊት) መንግስት አስተካክሎ ይመራናል የሚል እምነት የለንም። ከሆነልን ወደ ቄያችን እንመለሳለን። የቀሩ እነዚያም በችግር፣ በእስራት፣ በጦርነት ነው ያሉት። እኛም እንዳንሄድ ችግር ነው እዚህም እንዳንቆይ ችግር ነው።

በኛ ሀሳብ የሚሳካ ከሆነ ህገ መግስቱ ተሻሽሎ ‘አማራ ነው? ኦሮሞ ነው? ትግሬ ነው? ወላይታ ነው? ሀድያ ነው? አፋር ነው? ማነው?’ የሚባለው ቀርቶ በአንድነት ኢትዮጵያ ብትመራ ደስ ይለናል ” ብለዋል።

ሌላኛው ተፈናቃይ ምን አሉ ?

“ ሰሜን ሸዋ ዞን መራኛ 01 ቀበሌ ተፈናቃይ ነኝ። መንግስት እኛጋ እየደረሰ፣ እየጮኸና ህዝቡ እያለቀ እያዬ ነው ከዓይኑ የተሰወረ ነገር የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ በየትኛውም ክልል፣ በአራቱም ማዕዘን እንደሻማ እየቀለጠ ነው። 

የግድ እኔ ጋ እስከሚደርስ አንተ ጋ እስከሚደርስ መጠበቅ አያስፈልግም። አሁን እኛን የገጠመን ሰው ሲሞት ስንት ሰው ሞተ ? የሚለው ነው።

መንግስት ይሄን በደንብ ያውቃል፣ ያያል እየሄደም መረጃ ይሰበስባል፤ አጥፍተው ሲመጡ ‘ጎሽ’ ነው የሚባሉት። አጥፊው ነው እየተሸለመ የመጣው። መፍትሄ ይሆናል ብለን ተወክለን መጥተን የሞቱትን ለማሳት ሳይሆን እንዳይሞት እየሰራን ነው። በምድር ሰው ሞቶ እደገና አይበቅልም ” ብለዋል።

ተሳታፊ ወጣት ምን አለ ?

“ ሀገር ስትመክር ወደ ዘላቂ ሰላም እንደምትወጣ አምነን ነው የመጣነው። የሀገሪቱ የበላይ ጠባቂ መንግስት እስከሆነ ድረስ ዜጎቹን የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት። ሁሉንም በእኩል እጅ አይቶ የሚስተናገድ ከሆነ ያ ወደ ሰላሙ መገድ ያመጣናል። 

ተከፋፍለን በሀሰት ትርክት እርስ በራሳችን እየተበላላን ወደ ማንወጣው አዘቅት ገብተናል። አባቶቻችን ያቆዩልንን ሀገር ተማርን የምነለው አካላት ሌላ ውስጥ እያስገባናት ነው። መማር አገር ለማፍረስ ከሆነ ባንማር ይሻለን ነበረ ግን ተማርን እስከተባልን ድረስ ሀገርን ማዳን አለብን።

መግስት የሚወስደው የቤት ስራ አለው።

በአማራ ክልል ወጣቱ የስራ እድል እየተፈጠረለት አይደለም። በሌላ ቦታ ላይ እድል እየተፈጠረላቸው ነው። አብዛኛው አማራ ክልል የጸጥታ ችግር ያለበት ነው። ግን ይሄ የጸጥታ ችግር የህዝብ ብሶት የወለደው ነው።

በተለያዩ ክልሎች ያሉ አማራዎች እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ፣ ስራ አጡ እየበዛ፣ አማራ ‘አረጓዴ ቢጫ ቀይ ባንድራ፣ ቲሸርት ለብሰሀልና ወደ አዲስ አበባ አትገባም፣ ከአዲስ አበባ መውጣት አለብህ’ እየተባለ እየወጣ በተለያዩ አካባቢዎች ያለው እሮሮ የጸጥታ ችግሩን ወልዶታል። መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል ” ብሏል።

(የማህበረሰብ ተወካዮች በምክክሩ ዙሪያ ያነሱት ሀሳብ በቀጣይ ይቀርባል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ የሟች ቤተሰቦች አስክሬን ለማምጣት ሄደዋል ” - የአንዱ ሟች ቤተሰብ

ትላንት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ “ጎሃ ፅዮን” እና “ቱሉ ሚልኪ” መካከል ታጣቂዎች አንድ ሙሉ ተሽከርካሪ ተሳፋሪዎችን መገታቸው ከዛም ውስጥ የተገደሉ መኖራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አንድ የሟች የቅርብ ቤተሰብ  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ አንድ የልጆች አባት እንደተገደሉ፣ ነገ የቀብር ሥርዓታቸው ይፈጸማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸው፣ “ የሟች ቤተሰብ አስከሬን ለማምጣት ሄደዋል ” ብለዋል።

ሌላኛው የሌላ ሟች ጓደኛ በበኩላቸው፣ ሹፌሩን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ተሳፋሪዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ፣ የሟቾቹን አስክሬን ወደ ትውልድ ቦታቸው ለማምጣት የሟች ቤተሰቦች ዛሬ ወደ እገታ ቦታው እንደሄዱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሟቾች ወላጆች የሟቾቹን አስክሬን ገና ሊቀበሉ በመሆኑ፣ ሀዘናቸውም ስለበረታ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት የሚያስችል መረጋጋት ላይ አለመሆናቸው ተመልክቷል።

የሹፌሮችን ውሎ የሚከታተለው ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር በበኩሉ፣ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉት ተሳፋሪዎች መካከል በርካቶች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ከስፍራው መረጃ እንደደረሰው  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከተገዱሉት ተሳፋሪዎች ባሻገር ታፍነው የተወሰዱ እንዳሉም ያመለከተ ሲሆን፣ እገታው የተጸመው ትላንት (ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን 2027 ዓ/ም) መሆኑን ተናግሯል።

ስለእገታው ከመንግስት እስካሁን በግልጽ የተባለ ነገር ባይኖርም፣ በእገታው ቦታ የፌደራል ፓሊስ ደርሶ እንደነበር በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቅናቸው በኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ፣ ስራ ላይ እንደሆኑ በመግለጻቸው ለጊዜው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም። ምላሽ ከሰጡን የምናቀርብ ይሆናል።

የትላንቱ እገታ በተፈጸመበት አካባቢ ከ19 ቀናት በፊት ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ በርካታ ተሳፋሪዎች ይዞ ሲጓዝ የነበረ " ፈለገ ግዮን " ባስ ታጣቂዎች አስቁመውት ሙሉ ተሳፋሪዎች መታገታቸውን የአይን እማኝ ሹፌሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀው ነበር።

ከእገታው በኃላ የታጋች ቤተሰቦች በሚሊዮን ብር እየተጠየቁ ነው።

/channel/tikvahethiopia/95170?single

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ለትምህርትና ለህክምና ቅድሚያ ሰጥቻለሁ " - ባንኩ

አዋሽ ባንክ ባንክ ባለፉት 3 ወራት ከ498 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለደንበኞቹ ማቅረቡን አስታውቋል።

ባንኩ ይህንን የውጭ ምንዛሬ ያቀረበው ለ2200 ለሚሆኑ የባንኩ ደንበኞች መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዚሁ ጊዜ ለተለያዩ የሀገር ውስጥ ባንኮች ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ዕገዛ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ይህም ባንኮች የዶላር እጥረት ሲገጥማቸው በኢንተር ባንክ ያደረገላቸውን የዶላር ሽያጭ መጠን የሚያሳይ ነው።

በሦስት ወር ጊዜ ውስጥም ባንኩ ፦
- ለዘይት ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ ፣
- ለነዳጅ 79 ሚሊዮን ዶላር፣
- ለስኳር 20 ሚሊዮን ዶላር፣
- ለሩዝ 11 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መስጠቱን አስታውቋል።

" ባንኩ ለትምህርት እና ለህክምና ቅድሚያ ሰጥቻለሁ " ማለቱን ተከትሎ ለምን ያህል ዜጎች አገልግሎቱን እንደሰጡ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የባንኩ የብራንዲንግ እና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሰለሞን ጀቤሳ " በከፍተኛ መጠን " ሲሉ ትክክለኛ መጠኑን ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

" ለትምህርት ለህክምና የሚጠየቁት አነስ አነስ ያሉ ወጪዎች ናቸው። በቁጥር በጣም ብዙ ሰዎች ይሆናሉ ...[ዋናው] ለእነዚህ ጥያቄዎች ትኩረት መስጠታችን ነው " ያሉት ዳይሬክተሩ ከትምህርት እና ከጤና ጋር ጥያቄ ለቀረበባቸው አብዛኞቹ ፍላጎቶች ግን ምላሽ መስጠታቸውን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በመመሪያው መሰረት ምርታቸውን በንጥረ ነገር ያበለጸጉ አምራቾች እንደ ገና መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል " - የምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን

ከፋብሪካዎች የሚወጡ የምግብ ዘይትና የዱቄት ምርቶች በንጥረ ነገር እንዲበለፅጉ የሚያስገድደው ረቂቅ መመሪያ በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ይገባል መባሉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብ ምዝገባና ፈቃድ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ አስፋው በንጥረ ነገር የበለፀጉ የምግብ ዘይቶችና የዱቄት ምርቶችን ለመመዝገብ የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

መመሪያው ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በመመሪያው መሰረት የበለጸጉ ምግቦችን የማያመርቱ የምግብ ዱቄት እና የዘይት አምራች ድርጅቶች ምርትን የማሰራጨት የገበያ ፈቃድ አይሰጣቸውም ብለዋል።

ሃላፊው በዝርዝር ባነሱት ሃሳብ ምን አሉ ?

" አዲስ ነገር አይደለም ከዚህም በፊት ይታወቃል የምግብ ዱቄት እና የዘይት ምርቶች በንጥረ ነገር እንዲበለጽጉ የሚል ግዴታ በአዋጅ የተጣለው በ2014 ዓም ነበር።

ይህንን ለማስፈጸም በምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን የተለያዩ መመሪያዎች ይዘጋጃሉ ይህ መመሪያም የስንዴ እና የዘይት አምራች ድርጅቶች ምርታቸውን በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከማስመዝገባቸው አስቀድሞ ምን ምን ነገሮች ማሟላት አለባቸው የሚለውን የያዘ መመሪያ ነው።

መመሪያውን ከአምራቾች ጋር የማወያየት ሥራ እየሰራን ነው።

ምርቶቹ ከዚህም በፊት የተመዘገቡ ነበሩ ነገር ግን በአስፈላጊው ንጥረ ነገር ሳይበለጽጉ ነበር እንዲመዘገቡ የተደረጉት አሁን ደግሞ በመመሪያው መሰረት አምራቾች ምርታቸውን በንጥረ ነገር ካበለጸጉ በኋላ እንደ ገና መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ ቀደም ምግብን በሚመለከት የሚያስመዘግቡበት መመሪያ ነበር የአሁኑ መመሪያ ሊካተት ስለሚገባው ንጥረ ነገር (ቫይታሚን) ራሱን ችሎ ወጥቶ ነው።

መመሪያው እንደመጀመሪያ ለዱቄት፣ ለዘይት እና ጨው ተብሎ ቢወጣም ከዚህ በኋላ ማንኛውም አምራች ' ምርቴን በንጥረ ነገር አበለጽጋለሁ ' ብሎ ቢመጣ የሚስተናገድበት መመሪያ ነው የተዘጋጀው።

በመመሪያው መሰረት ማንኛውም በንጥረ ነገር የበለጸገ ምርት ደረጃ ሳይለጠፍበት ወደ ገበያ የማይወጣ ሲሆን በምርቶቻቸው ላይ በማንኛውም ጊዜ ለውጥ ካደረጉ ለባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።

መመሪያው በአመራር ደረጃ ከሳምንት በፊት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል የሚስተካከሉ ነገሮች ሃሳብ ተሰጥተውበታል ከሦስት ሳምንት በኋላ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ExitExam

ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎችን መረጃ አሰጣጥ አስመልክቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደብዳቤ ልኳል።

ሚኒስቴሩ ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገራዊ የቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኖ የአፈጻጸም መመሪያ ወጥቶ ተግባር ላይ መዋሉን አስታውሷል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ሰርተፍኬት (Temporary Degree) ወይም ትራንስክሪፕት ላይ አልፏል (PASS) ወይም ወድቋል (FAIL) በሚል እንዲቀመጥ ብሏል።

ከላይ በተያያዘው ሰርተፍኬት ፎርማት መሠረት እንዲፈጸምም ሚኒስቴሩ አዟል።

Credit : Federal Education and Training Authority

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ሲረከቡ የፈረሙት " የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር የተልዕኮ አፈጻጸም የቃል ኪዳን ሰነድ " ምን ይላል ?

1. የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሂደት፣ በጅምር ያለው እንዲጠናቀቅ እና በቀሪ አካባቢዎችም #በፍጥነት እንዲተገበር ማድረግ፤

2. በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት ትጥቅ የመፍታት እና የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ተግባር በአፋጣኝ እንዲጠናቀቅ ማድረግ፤

3. በክልሉ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ማድረግ፤ ለሕዝብ ደኅንነት፣ ለሰላም እና ለጸጥታ ጠንቅ የሆኑ ጉልህ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ማድረግ፤ ለዚህም ተገቢውን የቁጥጥር እና የሕግ ማስከበር ሥራ መሥራት፤

4. መደበኛ የልማት ሥራዎች፣ መንግሥታዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶች፣ እንዲሁም የመልሶ ግንባታ ሥራዎች እንዲሣለጡ ማድረግ፤

5. ከሕገ መንግሥታዊ እና ከሕጋዊ ሥርዓት፣
#ከሀገር_ሉዓላዊነት እና ከፕሪቶርያ ስምምነት ያፈነገጡ ግንኙነቶች እና እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ማድረግ፤

6. ክልሉ ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፤ በክልሉ የሲቪክ እና የፖለቲካ መብቶች ተግባራዊ የሆኑበት፣ የፖለቲካ ብዝኃነትን የሚያስተናግድ ደሞክራሲያዊ ዐውድ እንዲፈጠር መሥራት፤

7. የክልሉ ሕዝብ፣ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የፖለቲካ ተዋንያን
#በሀገራዊ_የምክክር_ሂደት እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤

8. የክልሉ መንግሥታዊ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን እንቅስቃሴዎች የሀገሪቱን ሕዝቦች ትሥሥር እና መልካም ግንኙነት የሚያጠናከሩ፣ ሕግ እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን የሚያስከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ፤

ጄነራል ታደሰ ወረደ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት በመሆን ሥራቸውን ሲጀምሩ ከላይ የተዘረዘሩትን ኃላፊነቶችን በትጋት እና በታማኝነት ለመወጣት ቃል ገብተው
#ፈርመዋል

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን ተረከቡ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አቢሲንያ_ባንክ
በረቀቀ ቴክኖሎጅ የተዘጋጀውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ
- በ5 የቋንቋ አማራጭ
- ከአቢሲንያ ወደ አቢሲንያ አካውንት ያለምንም ክፍያ እና ያለገደብ ገንዘብ ለማስተላለፍ
- ኪውአር ስካን አገልግሎት
ለማግኘት ዛሬውኑ ወደ አቅራቢያዎ ቅርንጫፍ በመሄድ አገልግሎቱን ያግኙ #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray : በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ከባባድ ፆታዊ ጥቃቶችና ሞት የሚፈፅሙ ተከሳሽና ወንጀለኞች ጉዳዮች በሚከታተሉና ህጋዊ ውሳኔ በሚሰጡ ዳኞች ላይ በተለያየ መንገድ የሚገለፅ ጫና እየደረሰ ነው ሲል የትግራይ የዳኞች ማህበር አማረረ።

ማህበሩ ከባባድ ወንጀሎች ለሚከታተሉና ህጋዊ ውሳኔ ለሚሰጡ ዳኞች አስፈላጊውን የደህንነትና የፀጥታ ከለላ እንዲሰጥ አበክሮ ጠይቀዋል።

ማህበሩ በላከው መግለጫ ፤ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ከባባድ ፆታዊ ጥቃቶችና የሞት ጉዳዮች የሚከታተሉ ውሳኔ የሚሰጡ ዳኞች ስራቸውን ነፃና ገለልተኛ ሆነው ለመከወን እጅግ ተቸግረዋል ብሏል።

" ዳኞቹ ስራቸውን ተረጋግተው በሰከነ የህግ አካሄድ እንዳይመለከቱ በተለያዩ መንገዶች ጫና እየደረሰባቸው ነው ስለሆነም ላለባቸው የደህንነታቸው አደጋ በቂ ከለላ በማጣታቸው ምክንያት ስራውን ከማቆማቸው በፊት የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በመመካከር ችግሩ በአፋጣኝ መፍታት አለበት " ሲል አሳስቧል።

" ከጦርነቱ በኋላ የትግራይ ዳኞቸ በከፍተኛ ፓለቲካዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ቅርቃር ውስጥ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ ጥያቄያቸው ይመለስላቸው " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

በፌደራል እና በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ዳኞች የሚያገኙት የደመወዝ ጭማሪና ጥቅማ ጥቅም የክልሉ ዳኞች እንደተነፈጉ ገልጾ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሌሎች ክልሎች እየተተገበረ ያለውን የጥቅማ ጥቅም አሰራር ለመመለስ " በጥናት ላይ ነኝ " በማለት ከአንድ ዓመት በላይ ማስቆጠሩ ልክ አይደለም ሲል ወቅሷል።

የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት  የአገሪቱ ህግና የትግራይ ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የዳኞች የጥቅማጥቅም ፣ የደመወዝ ፣ የደህንነትና መሰል ጥያቄዎች እንዲመልስ ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሜታ በኢትዮጵያ ግጭቶች ላይ በነበረው ሚና ዙሪያ በኬንያ ሊከሰስ ነው።

አብርሃም ማዕረግ እና ፍስሃ ተክሌ የተባሉ የቀድሞ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አጥኚዎች ከካቲባ ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር ሜታ ከ
2020-2022 በትግራይ በነበረው ጦርነት ወቅት መጥፎ መረጃዎችን እንዲሰራጩ አድርጓል በማለት ከሰውታል።

የአብርሃም ማዕረግ አባት የሆኑት ማዕረግ አማረ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩ ሲሆን በ2021 ፌስቡክ ላይ የጥላቻ ፅሁፎች ከተሰራጩ በኋላ እንደተገደሉና ፍስሃ ተክሌም የሰብዓዊ መብት ስራ በመስራቱ ጥላቻ እንደደረሰበት ተናግሯል።

የካቲባ ኢንስቲቲዩት ጉዳዩን ወደ ህግ የወሰደውም ሜታ በሚያስተዳድረው የፌስቡክ ፕላትፎርም ላይ የነበረው ጥላቻ የኬንያን ህገ መንግስት የሚፃረር በሚል ነው።

ከሳሾች የፌስቡክ አልጎሪዝም ለሰብዓዊ መብቶች መጣስ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የጥላቻ እና አደገኛ መረጃዎችን አጉልተው ያሳያሉ ብለዋል።

በፌስቡክ ተሰራጭቷል በተባሉ የጥላቻ እና የአመጽ ድርጊቶች ሜታ ተጎጂዎች 2.4 ቢሊዮን ዶላር " የማቋቋሚያ ፈንድ " እንዲከፍል ተጠይቋል።

ጉዳዩ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ግሎባል ዊትነስን ጨምሮ በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ድጋፍ አግኝቷል።

ሜታ በበኩሉ ጉዳዩ የኬንያን ፍርድ ቤት እንደማያገባው እና የአገልግሎት ደንባቸው የሚኖርን ክስ በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች እንዲታይ ብቻ እንደሚገድብ አስታውቋል።

(ኬንያን ዎልስትሪት)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ኬላውን ያሳለፈኝ ጠባቂ አስረውታል - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ' UMD ' ከተባለ ሚድያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም ከመቐለ ለስራ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ ወደ አውሮፕላን ማረፍያ በመኪናቸው እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ስለተቃጣባቸው የመግደል ሙከራ ይፋ አድርገዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ምን እንደገጠማቸውም አብራርተዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

" በዚህ ሁለት ዓመት ያልጠብቅኩት የገጠመኝ ልንገርህ ፤ እኔን የመያዝ ፍላጎት እንዳላቸው የማውቀው ነገር አልነበረም።

ወደ አዲስ አበባ ለስራ እየተጓዝኩ ኬላ ዘግተው ፕሬዜዳንት እንዲያግቱ ብቻ እንዳይመስልህ በማንኛውም መለኪያ የትግራይ ህዝብ የማይመጥን ነውር ለመፈፀም ነው ሙከራ ያደረጉት።

የትግራይ ህዝብ መንግስትነት AUTHORITY በጣም ያከብራል። አምባገነንነት ( አናርኪ)  እንዲፈጠር ፍላጎት የሌለው ህዝብ ነው። መንገድ ላይ ማገታቸው አልበቃ ብሎ ፤
#አወጣኸኝ የሚባል የአንድ ኮር አዛዥ ፓትሮል ይዞ እስከ አውሮፕላን ማረፍያ በር ድረስ መጥቷል። ወደ ውስጥ ያልዘለቀው በቦታው የፌደራል ፓሊስ የጥበቃ አባላት ስለነበሩ ነው።

የአየር መንገዱ ሴኩዩሪቲ እኔ ጋ ደውሎ ' ጌታቸው ገባ ወይ ? ብቻውን ነው ወይስ ሌሎች ሰዎችን ይዟል ? ' ብለው ጠይቀውኛል ' ብሎ ነግሮኛል።

እኔ አልመሰለኝም ነበር ፤ ለካ የነሱ ተላላኪዎች በሚድያ ' አመልጠዋል ' ብለው ሲናገሩ የነበሩት አውነታቸው ነበር። ለካ እኔ በማላውቀው መንገድ አምልጫለሁ። ያሰቡት ነገር ነበር።

ከመቐለ ከወጣሁ በኋላ ያወቁትና በጣም ያሳቀቀኝና ያሳሰበኝ ጉዳይ እኔ በማምለጤ ተደዋውለው በስልክ በቁጭት ያወሩ ሁለት ሰዎችን አውቃለሁ። በጣም እማከበራቸው ትልልቅ ወታደራዊ አመራሮች ናቸው።

' እንዴት ሊያመልጥ ቻለ ? ' እያሉ ነው በቁጭት የሚያወሩት። ' እንዴት ያመልጠናል/? ' ብለው ነው ያወሩት። እኔን መግደል (PHYSICAL ELIMINATION) እንደሚያስቡ በግልፅ ቋንቋ እየነገርኩህ ነው።

ወደ አየር መንገድ በሚወስድ አስፋልት መንገድ እኔ ሳላውቀው ኬላ ሰርተው መኪናዬ አቆሙት። የኬላው ጠባቂ እኔ መሆኔን እናረጋግጥ እንደውል አለ። የመኪናዬ መስኮት አውርጄ ማን ጋር ነው የምትደውለው ? አልኩት። ይህንን ስለው ተሳቆ አሳለፈኝ። በአለቆቹ እንጂ በኬላ ጠባቂው አልፈርድም። ምክንያቱ አለቆቹ አድርግ ያሉት ነው ያደረገው።

ነገሩ በቀላሉ ስላለፈ እንጂ ግጭት ቢፈጠር በኔ ጠባቂዎችና በኬላው በነበሩ መካከል ነው የሚሆነው። ችግሩ የአወጣኸኝም የኬላው ጠባቂም አይደለም። የአዛዦቹ ነው።

ኋላ ሳጣራ ኬላውን ያሳለፈኝ ጠባቂ አስረውታል።

የትግራይ ህዝብ ስርዓትና ህግ ያውቃሉ ብሎ የሚያስባቸው ሰዎች ስለ ሰው ማስወገድ ስለ ፕሬዜዳንት መግደል ያስባሉ ብዬ አስቤ አላውቅም። ኋላ ሳስበው ግን ለካ የነበረ ባህል ነው። በሌላ ቦታ እንደ ኦሮሚያ ምናምን ስትፈፀመው የነበረ ከሆነ በዚህም ትፈፅመዋለህ። ያው የቆየ ልማድና ባህል ነዋ። 

እኔን የቤት እስረኛ የማድረግ ፍላጎት እንደነበራቸው አወቃለሁ ምክንያቱ እኔ ከነሱ በላይ መረጃ አለኝ ነበረኝና። ከዚህ አልፈው እኔን እስከመግደል ይሄዳሉ ብዬ አላሰብኩም። እኔ ይህንን ሳሰበው ይዘገንነኛል ያስስበኛል። እዚህ ድረስ ነው እንዴ ? የደረስነው ብዬ ይከነክነኛል። "

#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አመራሩም፣ ሰራተኛውም ይቀያየራል ብየ አስባለሁ ሁሉም የሚስማማውን ቦታ ያገኛል " - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን በፖርላማ ከጸደቀ እና አዲስ አመራር ቦታውን ከተረከበ 19 ወራትን አሳልፏል።

በእነዚህ ጊዜያት አዲስ ጅማሮ በአንጋፋው መካነ አዕምሮ ( Reimagining Our Future) በሚል የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ጨምሮ በርካታ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎቾን አውጥቷል።

ከእነዚህ ማሻሻያዎች አንዱ የፕሮግራም ማሻሻያዎችና አዲስ ተቋሟዊ ቅርጽ መገንባት እንደሆነ የዩኒቨርስቲው ተ/ፕረዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ለተሰበሰቡ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ገልጸዋል።

በዚህም ዩኒቨርስቲው በመጀመሪያ ድግሪ ከ80 በላይ የነበሩትን ፕሮግራሞች ወደ 60 የማምጣት፣ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ ከ400 በላይ የነበሩ ፕሮግራሞች ደግሞ ወደ 352 ዝቅ የማድረግ ሥራዎች መስራቱን አስረድተዋል።

አዲስ ተቋማዊ ቅርጽ ለምን አስፈለገ ?

" የሥራ ክፍሎች መበራከት የተጋነነ የዩኒቨርስቲ ወጪ እንዲኖር " እድል መፍጠሩን በመግለጽ ተመሳሳይ የሚመስሉ ሥራዎች በተለያዩ ቦታዎች ተደጋግመው መስራታቸው ለለውጡ መነሻ መሆኑን ጠቅሰዋል።

" ወጪ መቆጠብ የማይችል ራስገዝ ሆኖ መቀጠል አይችልም " ያሉት ፕረዚዳንቱ ዓላማው ወጪ መቀነስ ጭምር መሆኑን አስረድተዋል።

" የአካዳሚክ ፕሮግራሞቻችንን ገምግመናል፤ የፕሮግራሞችን ምስስል የምናይበት Software Develop ተደርጎ Similarity Index አይተን በጣም የተቀራረቡትን የማዋኻድ፤ የማዋዋጥ የማጣመር ሥራ ሰራን ፕሮግራሞቹ ሰብሰብ አሉ " ሲሉ የመዋቅር ለውጥ ሂደቱን ያስረዳሉ።

ታዲያ ይሄን ተከትሎ የሠራተኛ ቅነሳ ይኖራል ?

ይሄንን ጥያቄ ያነሳንላቸው ፕረዚዳንቱ "የኮሌጅ ቁጥር ስለጨመረ ብዙ ሰራተኛ ይቀጥራል፣ ቁጥሩ ስለቀነሰ ትንሽ ሰራተኛ ይቀጥራል ማለት አይደለም" በማለት የመዋቅር ለውጥና የሰው ኃይል ፍላጎት መካከል ልዩነት መኖሩን ያስረዳሉ።

"አሁን ያለውን 8 እና 9 ሺህ የሚጠጋ ሰራተኛ በአንድ ኮሌጅ ማስተዳደር ይቻላል" የሚል ሀሳብ በማንሳትም፥ ዩኒቨርሲቲው ብዙ ሥራዎችን የሚሰራ በመሆኑ አስፈላጊ ብቃት ያላቸው ብዙ ሰራተኞች ይፈልጋል። "በስተት እና ባጋጣሚ ዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚሰሩ ነገር ግን ዩኒቨርሲቲውን የማይመጥኑ አሉ፣ ይህንንም የመቀነስ ሊኖር ይችላል" ሲሉ ጠቁመዋል።

"አቅም ያላቸው መምህራኖችን ለመሳብ እና ውስጥ ያሉትን ለማቆየት ጥሩ ክፍያ መክፈል ያስፈልጋል፣ ዛሬ የሚከፈላቸውን የምናውቀው ነው " ሲሉ የክፍያ ሥርዓቱም በቀጣይ እንደሚሻሻል ጠቁመዋል።

ቀሪ ሥራ ምንድን ነው ?

ዶ/ር ሳሙኤል በምላሻቸው፤ "አዲስ መዋቅር አሲዘናል፣ በዚህ መዋቅር ውስጥ የሚገባን የሰው ሃይል በምን መልኩ እንመድብ ብለን ጥናት አካሂደን ጨርሰናል፣ የሥራ አመራር ቦርዱ ሲያፀድቀው ወደ ትግበራ እንገባለን" ብለዋል።

"ከ2/3 በላይ ሄደናል። አሁን የፊኒሺንግ ሥራ ላይ ነው ያለነው። ሰራተኛውን ፈጻሚውን አመራሩን እንደገና መልሶ ማሰማራት ይፈልጋል፤ እሱ ላይ እየሰራን ነው ያለነው" ሲሉ ሂደቱ ያለበትን አስረድተዋል።

አክለውም፤ "በዚህ መዋቅር ውስጥ የሚገባው የሰው ኃይል በምን መልኩ እንመድብ የሚለውን ጥናቱ ተጠናቋል። የሥራ አመራር ቦርድ ሲያጸድቀው ወደ ትግበራ ይገባል" ሲሉ በቀሪው ወራት የሰራተኞች ዳግም ምደባ ለኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።

"አመራሩም፣ ሰራተኛውም ይቀያየራል ብየ አስባለሁ ሁሉም የሚስማማውን ቦታ ያገኛል" የሚል ሃሳብ ያነሱት ፕረዚዳንቱ "ጠንካራ ሰራተኛ የሚፈለገው ቦታ ላይ እንዲመደብ ማድረግ የመጨረሻ ሥራ ይሆናል። አቅም ያላቸው አመራሮች ደግሞ ወደ ፊት መጥተው ተቋሙን እንዲመሩ ይደረጋል ይሄን ማሳካት ነው የመጨረሻው [ዙር] ማለት ነው።" ሲሉ ገልጸዋል።

ዩኒቨርስቲው ከሚያገኘው ገቢ ምን ያህል ወጪውን እየሸፈነ ነው?

ዩኒቨርስቲዎች ራስገዝ ናቸው ማለት መንግስት በጀት አይመድብም ማለት እንዳልሆነ በመጥቀስ "የዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝነትና በኃብት ራስን መቻል የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ራስ ገዝነት ያላቸው አስዳደራዊ ነጻነትን ማስፋት ነው" ሲሉ ፕረዚዳንቱ ያስረዳሉ።

በዘንድሮው ዓመት ብቻ ወደ 4 ቢሊዮን ብር መንግስት መድቦለታል ወደ 1 ቢሊዮን ራሱ እንዲያመነጭ ይፈለጋል። ይሄ ማለት ወደ 20 በመቶ ማለት ነው። ይሄንን ለመገልበጥ በራስ አቅም 80 በመቶ ለመሸፈን ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችልም ተናግረዋል።

በቀጣይ ዓመት 1.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት እንደሚሰራ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።

😉የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በክፍል አንድ ለጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ https://youtu.be/mfR_fLZXYuE?si=pIJXssnk8pBxtDiI ላይ ይመልከቱ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ለ ' ምርመራ ' በሚል ተወስደዉብን የቆዩ የግል ስልኮቻችንና ኮምፕዩተሮቻችን ተመልሰዉልን ክሳችንም እንዲቋረጥ ተደርጓል " - ታስረዉ የተለቀቁ የገዜ ጎፋ ነዋሪዎች

➡️ " ክሳቸዉ እንዲቋረጥ የተደረገዉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የዞኑ ተወላጅ አመራሮችና ምሁራን ባካሄዱት የልማት ዉይይት እና የይቅርታ መድረክ ምክረ ሃሳብ ነዉ " - የዞኑ ፍትሕ መምሪያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ባሳለፍነው ዓመት ተከስቶ በነበረዉ የመሬት ናዳ ምክያት ጉዳት የደረሰባቸዉና የተፈናቀሉ ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገዉ ሂደት ዙሪያ ያሉ ችግሮችን አስመልክቶ ለሀገር ዉስጥና የዉጪ ሚዲያዎች " ትክክለኛዉን መረጃ በመስጠታችን ለእስር ተዳርገናል ፤ የግል ስልኮቻችንና ኮፒዩተሮቻችን ያለ አግባብ ተወስደዉብናል " ሲሉ በቁጥር 8 የሚሆኑ የገዜ ጎፋ ወጣቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን ገልፀዉ ነበር።

የዞኑ መንግስትና የገዜ ጎፋ ወረዳ ፖሊስ በበኩላቸው " ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩና ሕዝብን በመንግስት ላይ ሲያነሳሱ ነበር " በማለት ክስ እንደመሰረተባቸዉና የሞባይል ስልኮቻቸዉንና ኮምፕተሮቻቸዉም ለምርመራ መያዛቸዉን ገልፆልን ነበር።

እነዚህ ወጣቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በወቅቱ ለምርመራ በሚል ተወስደዉባቸዉ የነበሩ የግል ስልኮቻቸዉና ኮምፕዩተሮቻቸዉ እንደተመለሰላቸዉ ተናግረዉ ተከፍቶባቸው የነበረዉ ክስ እንዲቋረጡ መደረጉን አስታውቀዋል።

" በመንግስት በኩል የነበሩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ቃል እንደተገባና በሕብረተሰቡ ፊት ይቅርታ ተጠይቀናል " ሲሉ ታስረዉ ከተፈቱት መካከል ሃሳባቸዉን ያጋሩን ወጣቶች ለሕዝብ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት በጋራ ለመስራት ከመግባባት መደረሱንም ገልፀዋል።

የጎፋ ዞን ፍትሕ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምመላሽ ቢላቴ በበኩላቸው ፤ " በቅርቡ በዞኑ በተካሄደዉ ከዞኑ አልፎ በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ቦታዎች ተሹመዉ ሀገራቸዉንና ሕዝባቸዉን የሚያገለግሉ ከፍተኛ አመራሮችንና ምሁራንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የአከባቢው ተወላጅ በተገኙበት የዉይይት መድረክ ተካሂዷል " ብለዋል።

በዚህም ማጠቃለያ በተቀመጠዉ ምክረ ሃሳብ መሰረት ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩ 8 ግለሰቦች ክሳቸዉ እንዲቋረጥ መደረጉንና ለምርመራ ተይዘዉ የነበሩ ሞባይልና ኮምፕዩተሮቻቸዉ እንዲመለስ መደረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

" ጥፋት ስለሌለባቸዉ ክሳቸዉ አልተቋረጠም " የሚሉት ኃላፊዉ የሕዝብን ጥቅም በማስቀደም በይቅርታ ወደ ጋራ ልማት ለመመለስ ታስቦ ወደዚህ ዉሳኔ መደረሱን አስታዉቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MPESAEthiopia

🔥ይጋብዙ ፣ ይሸለሙ 🔥

📣አሁንም እንደቀጠለ ነው 📣

የቴሌግራም ቻናላችንን ያጋሩ፣ 💥👉🏽👉🏽ትክክለኛውን ቦት ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ🎁

ከእናንተ የሚጠበቀው የሳፋሪኮም መስመራችሁን በመጠቀም የተጠቀሱትን ቅደም ተከተሎች መተግበር ነው🫰🏽

ያስተውሉ 👉🏽 በእርስዎ ጋባዥነት የሚቀላቀለው ሰው ቁጥር ሲጨምር የሚያገኙት የአየር ሰዓት መጠንም እየጨመረ ይሄዳል 😱 እንዲሁም ተጋባዦቻችሁ ገፁን ከተቀላቀሉ በኃላ “back” የሚለውን ተጭነው “check subscription” እንዲያደርጉ ያሳስቡ 🔥

የቴሌግራም ቻናላችን 👉🏽 /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 /channel/official_safaricomet_bot

መልካም እድል 🎁💥🤩

#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#FurtherAheadTogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሐይቻ ጅብቾ ቦራሚ !

የጌዴኦ ብሔር ታሪክ ውስጥ በቀዳሚነት ከምጠቀሱ ታሪካዊ አባቶች አንዱ የወንጌል አርበኛ ሐይቻ ጅብቾ ቦራሚ በ112 ዓመታቸው ማረፋቸውንና ስርዓተ ቀብራቸውም መፈጸሙን የጌዴኦ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የባህል ጉዳዮች መረጃ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ከተማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አቶ ዳንኤል " ሐይቻ ጅብቾ ቦራሚ ለብሔጉ ነጻነት እና እኩልነት የታገሉ ጀግና ነበሩ " ብለዋል።

" በህይወት ዘመናቸውም ለብሔርና ብሔረሰቦች አንድነት ሰላምና መቻቻል አበክሮ የተጉ ፣ አንድነትን ያሰፈኑ፣ ሰለምን ያረጋገጡ የህዝብ አባት ነበሩ " ሲሉ ገልጸዋል።

በ1905 የተወለዱት ሐይቻ ጅብቾ ቦራሚ የወጣትነት ጊዜያቸውን በነጻነት ትግልና በተለይም የጭሰኛና ባላባት ስርዓትን በመቃወም ያሳለፉ መሆኑን አካባቢውንም በአውራጃነት ማስተዳደራቸውን ገልጸዋል።

" ሀይቻ ጅብቾ ታሪክ ከማይዘነጋዉና ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እየተላለፈ ከሚነገርላቸዉ አኩሪ ስራቸዉ ዉስጥ በወቅቱ ብሔሩ በተሳሳተ መንገድ ይጠራ የነበረበትን ' ዴራሳ ' የሚል የወል ስያሜ በመቃወም በ1938
#ጌዴኦ ተብሎ እንዲጠራ አስደርገዋል " ሲሉም አክለዋል።

ሐይቻ ጅብቾ ለህዝብ ፣ ለመንግሥት ብቻ ሳይሆን ለወንጌል አገልግሎት ትልቅ መስዋእትነትን የከፈሉ አባት እንደነበሩ ተገልጿል።

‎ውልደታቸው በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ የሆኑት ሐይቻና የወንጌል አርበኛ አቶ ጅብቾ ቦራሚ በተወለዱ በ112 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን ‎የቀብር ስነስርዓታቸው መኖሪያቸውን አድርገው በነበሩበት በአባያ ወረዳ ቡናታ ቀበሌ በቡናታ ቃለህይወት መቃብር ተፈጽሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ጊዜያዊ አስተዳደሩ በብዙ ውጣ ውረድ  ተቋቁሞ ፕሬዜዳንት ሆኜ መምራት ስጀምር በቀናት ውስጥ ' ባንዳ ' የሚል ስያሜ ተለጠፈብኝ " -  አቶ ጌታቸው ረዳ

ትላንት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " UMD " ለተባለ ሚድያ ዘለግ ያለ ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል።

በርካታ ጉዳዮች ባነሱበት ቃለ-መጠይቃቸው " አሁንም ትግራይ መላ ቅጡ በማይታወቅ ሁኔታ ላይ ናት ፤ በርካታ የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ ጭንቅና መከራ ውስጥ ይገኛል " ብለዋል።

" በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሲመሰረት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ጦርነቱ በመምራት ከፍተኛ ሚና የነበረን 5 ስራ አስፈፃሚዎች ወደ ፕሬዜዳንት የኋላፊነት ቦታ እንዳንመጣ ፍላጎት ነበረቸው " በማለት ወደ ኋላ ተመልሰው አስታውሰዋል።

ይህን ሃሳብ እሳቸው ቢቀበሉትም የተቀሩት አራቱ ስራ አስፈፃሚዎች የጠቅላይ ሚንስትሩን ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸው ተናግረዋል።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማቋቋም በአላስፈላጊ ክርክር አራት ወራት ፈጅተናል፤ በብዙ ውጣ ውረድ መጋቢት 21/2015 ዓ.ም ተቋቁሞ ፕሬዜዳንት ሆኜ መምራት ስጀምር በቀናት ውስጥ ' ባንዳ ' የሚል ስያሜ ተለጠፈብኝ " ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ ጌታቸው " በዚያው ዓመት ወርሃ ግንቦት የባሰውኑ ' ከሃዲ ' ተባልኩኝ " በማለት ተናግረዋል።

" አራቱ የህወሓት ስራ አስፈፃሚዎች በየሦስት ወሩ ለማድረግ የሚፈቅደውን የድርጅቱ ውስጠ ደንብ በመጣስ በየሦስት ቀኑ ፍሬ በሌለው ስብሰባ በመጥመድ ከመንግስታዊ ስራ ውጭ እንድሆን አበክረው ሰርተዋል ፤ በዚሁ ተማርሬ ኃላፊነቴ በራሴ ፍቃድ መልቀቅ ባለመቻሌ ተናደው እኔን ጨምሮ 16 የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ' ከሃዲዎች ከጂዎች ' ብለው በመፈረጅ አላሰራ አሉን " ብለዋል።

" የተቀረው የህወሓት የስራ አስፈፃሚ በፕሪቶሪያው የተኩስ ማቆም ስምምነት እንደ ሽንፈት የሚቆጥር ፣ በተፈናቃዮች እጣ ፈንታ የሚቆምር ፣ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጡት ተልእኮዎች እንዳይፈፅም ከላይ እስከ ታች በእቅድ የሰራ አደናቃፊ " ብለውታል አቶ ጌታቸው።

አቶ ጌታቸው " ለውጥ የማይቀበሉ ፤ የተቸከሉ " ሲሉ የገለፁዋቸው የህወሓት 4ቱ ስራ አስፈፃሚዎች እሳቸው ወደ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት በመጡበት ማግስት የሚሰራ በሌለበት 55 የድርጅቱ ሰዎች በምክትል የስራ ኃላፊ ደረጃ እንዲሾሙ ፕሮፓዛል እንዳቀረቡላቸው ፤ ይህንን ያህል ቁጥር ያለው ስራ ሳይሰራ ደመወዝ የሚከፈለው አመራር ለመመደብ ቢቸገሩም ከክርክር በኋላ 35
#በግድ መመደባቸው ገልጸዋል።

ድርጅታዊ ውስጥ ደንብ በመጣስ የ65 እና የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የማእከላይ ኮሚቴ አመራር እንዲሆኑ መመረጣቸው በርካታ ቁጥር ያለው አመራር ከሃላፊነት ምድብ ውጭ ሆኖም ቁጭ ብሎ በፊት የነበረው ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲያገኝ የሚያደርግ እጅግ ዘግናኝ አሰራር ክልሉን ጠልፎ መጣሉ አቶ ጌታቸው ገልፀዋል።

" ጡረታ የማይፈቀድበት ክልል ቢኖር ትግራይ ነው "  ያሉት አቶ ጌታቸው  ፤ ከጦርነቱ በፊት በ2012 ዓ.ም 800 ሚሊዮን ብር የነበረው የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቋቁሞ ስራው በ2015 ዓ.ም ሲጀምር ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ማሻቀቡ በክልሉ ያለው ቅጥ ያጣ በልሹ አሰራር የሚያሳይ ነው ብለዋል።

" በትግራይ ያለው አሁናዊ ፓለቲካዊ ቀውስና ችግር ህወሓት ብቻውን ስልጣን እንዲቆጣጠር ያለው ያልተገራ ፍላጎት የፈጠረው ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " ይህንን ሁሉንም ነገር በብቸኝነት የመያዝ ያልተገራ የህወሓት ፍላጎት የማይሸከም በተግባር የተደገፈ ለውጥ በትግራይ መፈጠሩ ማሳያዎችን በመጥቀስ አስረድተዋል።

ከትናንት ወዲህ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከዱባይ ' bird story agency ' ለተባለ ሚድያ በሰጡት ቃለመጠይቅ " በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እመለሳሎህ ማለታቸው " ተከትሎ ትናንት ወደ አዲሰ አበባ መመለሳቸው በአንዳንድ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ቢፃፍም ፤ ፕሬዜዳንቱ ለUMD ሚድያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ስለዚሁ ጉዳይ ያሉት የለም።

NB. አቶ ጌታቸው ረዳ አራቱ ስራ አስፈጻሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሃሳብ ውድቅ እንዳደረጉ በገለጹበት አውድ ስም ባይጠቅሱም በይፋ የሚታወቁት ስራ አስፈጻሚዎች ፦
1. ደብረፅዮን (ዶ/ር)
2. ወ/ሮ ፈትለወርቅ
3. አቶ ኣለም ገብረዋህድ
4. አቶ ጌታቸው ኣሰፋ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" አሁን ላይ ግጭቱ ቆሟል ሕዝብ የማወያየትና የሞቱትን የመቅበር ስራ ሲሰራ ነዉ የዋለው " - የደራሼ ወረዳ ነዋሪዎች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ በጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ከመጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸዉን የአከባቢውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናግራቸው ይታወሳል።

በወረዳዉ የሀይ'በረና እና ኦኖታ አከባቢ ነዋሪዎች ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ግጭቱ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አከባቢው በመግባቱ መቆሙን ተናግረዋል።

በግጭቱ ምክንያት ሕይወታቸዉን ያጡትን የመቅበርና ሕዝቡን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መዋሉንም ገልጸዋል።

" የሞተዉ ሰዉ ቁጥር በጣም ብዙ ነዉ አስከሬናቸው እየተፈለገ ያሉም አሉ " ያለን አንድ የአከባቢው ነዋሪ " የተቃጠለዉ ቤት ብዛት ከቁጥር በላይ ነዉ " ሲሉ ሁኔታዉን አብራርተዋል።

" የኛ ሁለት አጎቶች እስካሁን የገቡበት አልታወቀም፣ ልክ ግጭቱ እንደቆመ ቤተሰብ እያፈላለግን ነዉ " ያለን ሌላኛዉ አስተያየት ሰጪ " አሁን እየመሸ ስለሆነ የምናገኝ አይመስለንም፣ ሞተዉ ይሁን በህይወት ያሉ ፈጣሪ ነዉ የሚያዉቀዉ " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዋሪዎችን ሃሳብ ተከትሎ በድጋሚ ወደ ጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ብርሃኑ ኩናሎ ደዉሎ የነበረ ሲሆን ሕዝብ እያወያዩ ብቻ እንደሆነ በመግለፅ ከዚህ ያለፈ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሰው ይምጣ ሲመጣ ግን የተመዘገበ ሰው መሆን አለበት። በአንድ ቦታ ወንጀል ሰርቶ  የመጣ ሰው አዲስ አበባን መደበቂያ ማድረግ የለበትም " - ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ

የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለኅብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ለማስገንዘብ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።

በዚህ መድረክ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ለተሳታፊዎች በተለይ ከሲቪል ምዝገባ እና ከቆሻሻ አስተዳደር ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መድረኩን ተከታትሎ ነበር።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ምን አሉ ?

" ከዚህ ቀደም አንድ ሰው አንድ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ባለመቻላችን በሁለት በሦስት ማንነት መታወቂያ ማውጣት፤ የታክስ ማጭበርበር እንዲሁም በተጭበረበረ ማንነት የንብረት ቅሚያ ይከናወን ነበር " ብለዋል።

አሁን ላይ " አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ስም መታወቂያ ያወጣ ሰው ዳግም በዛ ስም መታወቂያ የማያወጣበትን ሥርዓት ፈጥረናል " ሲሉ በሲቪል ምዝገባ ረገድ የተሰራውን ሥራ አስረድተዋል።

አብዛኛው ሰው የፋይዳ መታወቂያ የሚመዘገበው በአስገዳጅ መልኩ ነው የሚሉት ኢንጂነር ወንድሙ " ይሄ መሆን አልነበረበትም " ሲሉ የማኅበረሰቡ ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

" ለምንድነው ፋይዳ የማትመዘገበው ? ሲባል ' ምን ያደርግልኛል ' የሚል ሰው በጣም ብዙ ነው ፤ ነገ ከፋይናንስ፣ ከታክስ፣ ከቤት ኪራይ፣ ከመንጃ ፈቃድ፣ ከንብረት ባለይዞታነት ጋር ይያያዛል " ሲሉ ጠቁመዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ የስበት ማዕከል መሆኗን በመጥቀስ ህጋዊ ያልሆኑ ፍልሰቶች መኖራቸው በከተማው መሰረተ ልማት ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አንስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታን አጭር ማብራሪያ ጠይቋቸዋል።

ምን መለሱ ?

" አዲስ አበባ ውስጥ ያለውን ሰው ማወቅ አለብን ፤ በአግባቡ የተመዘገበ መሆን አለበት። መንግስት አገልግሎት የሚያቀርበው ለ5 ሚሊዮን ነው ለ8 ሚሊዮን የሚለው መታወቅ አለበት።

ሰው ይምጣ ሲመጣ ግን የተመዘገበ ሰው መሆን አለበት። በአንድ ቦታ ወንጀል ሰርቶ  የመጣ ሰው አዲስ አበባን መደበቂያ ማድረግ የለበትም ከተማ አስተዳደሩ ያወቀው ነዋሪ መሆን አለበት። ያንን ማድረግ የሚያስችል ሥራ እየሰራን ነው ያለነው " ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ከዚሁ ከሲቪል ምዝገባ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጉዳይ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ ያለው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጉዳይ ነው።

ለሚቀጥለው ዓመት የትምህርት ዘመን ምዝገባ የፋይዳ መታወቂያ በመስፈርትነት በማስቀመጥ ለዚህም በአንድ ወር ውስጥ 450 ሺ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ ስራ ቢጀመርም መመዝገብ የተቻለው 130 ሺ የሚሆኑትን መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

" ወላጆች የተሟላ መረጃ አይልኩልንም " ያሉት ኢንጂነር ወንድሙ አንዳንዶቹ ለራሳቸውም የፋይዳ መታወቂያ የሌላቸው መሆኑን በመጥቀስ የግንዛቤ እጥረት ለሥራው ፈተና መሆኑን አንስተዋል።

በተመሳሳይ ከሞት እና ጋብቻ ሰርተፊኬት ጋር ተያይዞ የማስመዝገብ ባህሉ ደካማ መሆኑን በማንሳት በተለይ ከሞት ምዝገባ ጋር ተያይዞ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት እዛው ሰርተፊኬት የሚያገኙበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው ብለዋል።

አዲስ አበባ ከተማ ወደ 5 ሚሊዮን ነዋሪዎች አሏት ተብሎ እንደሚታሰብ በዚሁ መድረክ የተገለጸ ሲሆን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ድረገጽ ላይ ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ የተመዘገቡ 2.7 ሚሊዮን እንዲሁም የዲጂታል መታወቂያ የወሰዱት 2.1 ሚሊዮን የሚሆኑት ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#UoG

🚨 " አሁንም በርካታ የታመሙ ተማሪዎች ወደ ህክምና ተቋሙ እየሄዱ ነው "- ተማሪዎች

➡️ " በሽታው የተከሰተው ከምግብ ወይም ከውሃ ጋር የተያያዘ መሆኑን ገና እየተጣራ ነው " - አብርሃም ዘገየ የተማሪዎች ዲን


በጎንደር ዩንቨርስቲ የፋሲል ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፋክሊቲ ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መታመማቸውን ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከባለፈው እሮብ ጀምሮ በግቢው " በውሃና በምግብ ብክለት ነው " ብለው በጠረጠሩት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች መታመማቸውን ህክምና ላይ ያሉ ተማሪዎች አመልክተዋል።

ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁን በግቢው ተማሪ መሆናቸውን እና አሁን በህክምና ላይ መሆናቸውን የገለፁልን ተማሪዎች ግቢው ውስጥ ባለው የህክምና ተቋም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች እየታከሙ መሆኑን ገልፀዋል።

ለተሻለ ህክምናም ወደ ጎንደር ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የተላኩ እንዳሉም ተማሪዎች ተናግረዋል።

በግቢው የአምስተኛ ዓመት ተማሪ እንደሆነ የነገረን ተማሪ ባለፈው እሮብ ምሳ ላይ የተመገቡት ፓስታ እርሱን ጨምሮ በርካቶችን ለህመም እንደዳረጋቸው ይጠረጥራል።

የትኩሳት፣ የተቅማጥ እና እጅና እግር የመቆረጣጠም ምልክት እንዳለው የሚናገሩት ታማሚዎች ወደ ህክምና ተቋም የሄዱ ተማሪዎች በሙሉ " ታይፎድ " ነው እንደተባሉ ተማሪው ተናግሯል።

ሌላው የሶስተኛ አመት የኤሌክትሪካል እንጂነሪንግ ተማሪ መሆኑን የነገረንና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን ተማሪ ደግሞ ምግቡ፤ የሚጠጣው ውኃም ተበርዟል ይላል። ህክምና ተደርጎለት መድሃኒት እየወሰደ እንደሆነ የሚናገረው ይህ ተማሪ የውሃ እጥረት በግቢው ስር የሰደደ ችግር ነው ብሏል።

ከየት እንደሚመጣ የማይታውቅ ውኃ በቦቴ ተጭኖ ይመጣል በጥራቱ ሁሌ እንጠራጠር ነበር። በተለይ ሰሞኑን ከተማሪዎች መታመም ጋር በተያያዘ አብዛኛው ተማሪ የታሸገ ውሃ ገዝቶ እየጠጣ ይገኛል ብሏል።

ተማሪዎቹ ለተማሪዎች ህብረት ተወካይ ችግሩን ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

የኢንጅነሪግ ተማሪዎች ብቻ በሚማሩበት በጎንደር ዩንቨርስቲ የፋሲል ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፋክልቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳት የሆነውን ተማሪ ተመስገን ችግሩ መከሰቱንና እርሱን ጨምሮ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታመማቸውን ገልጾ፥ ችግሩ ከውሃው ነው በመባሉ ትላንት በታንከሩ ያለው ውሃ ተቀይሮ በኬሚካል በታከመ ውሃ መቀየሩን ተናግሯል።

በጎንደር ዩንቨርስቲ የፋሲል ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፋክልቲ የተማሪዎች ዲን አብርሃም ዘገየ በግቢው ከመቶ በላይ ተማሪዎች ወደ ክሊኒክ ታመው መሄዳቸውን ጠቅሰው ከመጡት ውስጥ 84 ተማሪዎች ብቻ " ባክቴሪያ " ተገኝቶባቸው መድሃኒት ተሰጥቶቸው እያገገሙ ነው ብለዋል።

ከዚህ ህመም ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጎንደር ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የሄዱት ከ5 እንደማይበልጡና ከእነዚህ ውስጥ ተጏዳኝ የጨጏራና ሌሎች ችግሮች ያለባቸው ናቸው ተብለው ታክመው የተመለሱ ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።

ቀለል ያለ ስሜት ላላቸው ተማሪዎችም ኦ አር ኤስ እየተሰጣቸው ነው፤ ከዩንቨርስቲው አመራር ጋር በመሆን የመድሃኒት ችግር እንዳያጋጥምም ወደ ክሊንኩ አስገብተናል ያሉት አብርሃም የውሃና የምግብ ችግር ነው የሚለውን ምክንያት
#እየተጣራ ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

“ እናቶች የሚያለቅሱበት፣ የወላጆች ልጅ አልባ መሆን ሊቆም ይገባል” - ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም

➡️ “
ወንድም ወንድሙን ለምን ይገድላል? ለምን ያሳድዳል? ብለን የምንጠይቅበት መድረክ ነው” - ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስታዲዬም ዛሬ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።

በዚህም የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች፣ የሃማይኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተሳታፊዎች፣ የባህል ማዕከል፣ የክልሉ ማርሽ ባንድ የተገኙ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩም የኃማይኖት አባቶች ባደረጉት ጸሎት ተጀምሯል።

በዚህም ከአምስት ባድርሻ አካላት የተወከሉ ከ6000 በላይ ወኪሎች ይሳተፋሉ፣ በተለያዩ ወረዳዎች ማኀበረሰቡን የወከሉ 4500 ወኪሎች በመጀመሪያዎቹ አራት ቀናት በአገራዊ አጀንዳ ውይይት ያደርጋሉ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ምን አሉ?

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም፣ “ኢትዮጵያ በመደማማት ያተረፈችው ነገር የለም። የጦርነት አዙሪት፣ እርስ በእርስ ለማስቆም ያስችላል በሚል ምክክሩ ተጀምሯል” ብለዋል።

“እርስ በእርስ መጨራረስን በቃ ልንል ይገባል። እናቶች የሚያለቅሱበት፣ የወላጆች ልጅ አልባ መሆን ሊቆም ይገባል” ያሉት ኮሚሽነሩ፣ “ለምንድን ነው የምንገዳደለው?” ሲሉ ጠይቀዋል።

ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ አማርኛን ያስተማረ የአማራ ህዝብ መሆኑን ጠቅሰው፣ “የቤሰብ ፀብ ቢፈጠር ዝም ብለን ማዬት አለብን?” ሲሉ ጠይቀዋል።

ዐድዋን የመጀመሪያ፣ ዓባይ ግድብን ሁለተኛ ድል ጠቅሰው ሀገራዊ ምክክሩን “3ኛው ዓድዋ” ሲሉ የጠሩት ዮናስ (ዶ/ር)፣ ምክክሩ፣ ህዝብን ከህዝብ ለማግባባት፣ በተከፉ ቁጥር ትጥቅ አንግበው ጫካ የሚወጡ አካላት በመወያዬት እንዲያምኑ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። 

 ምክትል ዋና ኮሚሽነር ወ/ሮ ሂሩት ገ/ስላሴ፣ “ያለፉት ዘመናት አልፈው ተርፈው በትጥቅ ትግል ተይዘዋል” ብለው፣ የትጥቅ ትግል ጊዜያዊ እንደሆን እንጂ ዘላቂ መፍትሄና ሰላም እንደማያመጣ አስገንዝበዋል።

ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር)፣ “ወንድም ወንድሙን ለምን ይገድላል? ለምን ያሳድዳል? ብለን የምንጠይቅበት መድረክ ነው። ለዝመት፣ እንደፍራለን አሁን ደግሞ ለማዳመጥ የምንደፍርበት ወቅት ነው ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።

ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር)፣ አለመግባባቶች እንደሚስተዋሉ ገልጸው፣ ለዚህም አማራ ክልልም አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ በሚሊዮን የሚቅጠሩ ህፃናት ከትምህርት ቤት በር መድረስ እንዳልቻሉ፣ በርካታ ወጣቶች ወደ ጫካ ለመግባት ለመግባት መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ለዚህም ምክክር እንደሚያስልግ፣ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ ሲያደርጉ እንደቆዩ ገልጸው፣ ለታጣቂዎች አሁንም በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Подписаться на канал