ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#በያያ_ደርሶኛል
ከያያ ዋሌት ወደ ሁሉም ባንኮች፣ ከሁሉም ባንኮች ወደ ያያ ዋሌት ማንኛውንም ክፍያ ይክፈሉ ይቀበሉ!
መተግበሪያውን በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://yayawallet.com/install ስልክ ቁጥርዎን አለያም የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ቁጥርዎን በመጠቀም በቀላሉ ይመዝገቡ!
ክፍያ በያያ!
ለተጨማሪ መረጃ 957 ላይ ይደውሉ
#YaYaWallet #YaYa #EasyRegistration #InstantTransaction #SecureTransaction #DigitalWallet #ክፍያ_በያያ
#Update
" ኮሌራ መሆኑን በናሙና ተረጋግጧል " - የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አፈፃፀም ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከመጋቢት 19 / 2017 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ በሶስት የፀበል ቦታዎች በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ አራት ሰዎች መሞታቸውንና ከ600 በላይ ሰዎች መያዛቸውን ገልፀዋል።
ሟቾቹ ሁለቱ ከጃዊ ሁለቱ ከአንዳሳ ፀበል መጥተው በባህር ዳር ከተማ ህክምና እየተደረገላቸው እያለ መሞታቸውን ተናግረዋል። ይህ የሆነው በአንድ ሳምንት ውስጥ መሆኑ የበሽታውን ስርጭት አስፈሪ ያደርገዋል ብለዋል።
በሽታው የተከሰተባቸው ቦታዎች ፦
- በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኘው " በርሜን ጊዮርጊስ "
- በሰሜን ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ "አንዳሳ" ፀበል
- በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ "ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራው ፍል ውሃ ፀበል እንደሆነ ሲስተር ሰፊ ተናግረዋል።
የበሽታው ስርጭት በዚህ ሳምንት ውስጥ እንዲስፋፋ ያደረገውን ምክንያት ሲገልፁ " ህብረተሰቡ በስፋት ወደ ፀበል ስፍራዎች በመጓዙ ነው " ብለዋል።
በእነዚህ የፀበል ስፍራዎች ደግሞ በቂ የሆነ የንፁህ ውሃ አቅርቦትና በቂ የሆነ መፀዳጃ ስፍራ አለመኖሩ የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ አድርሶታል ሲሉ ነው የገለጹት።
በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ " ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራ ፍል ውሃ ፀበል ባለፈው ሰኞ መጋቢት 22/2017 ዓ.ም በተከሰተ በሽታ ሁለት ሰዎች መሞታቸውንና 50 ሰዎች ታመው ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ስለሺ ወለሊ ለቲክቫህ መናገራቸው ይታወሳል።
በወቅቱም የበሽታውን ምንነት ለማወቅ ለክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ናሙና መላኩን አቶ ስለሽ ተናግረው ነበር።
ሲስተር ሰፊ ደርብ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከጃዊ ሆስፒታል የተላከው ናሙና #ኮሌራ መሆኑን #መረጋገጡን ተናግረዋል።
ባለፍት አራት ወራት ውስጥ ማለትም ታህሳስ 24፤ 2017 ዓ.ም በቋራ ወረዳ በርሚል ጊዮርጊስ ከተከስተው የኮሌራ ወረርሽኝ ጀምሮ እስከ ትላንት መጋቢት 25፤ 2017 ዓ.ም ድረስ በወረርሽኙ 11 ሰዎች ሲሞቱ ከ1ሺ 1መቶ 42 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸውን ሲስተር ሰፊ አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ዛሬ በፊስ ቡክ ገፁ ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሌራ በሽታ እንዲጠብቅ የሚያሳብብ ፁሁፍ አሰራጭቷል።
በቢሮው የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት የመጀ/ደረጃ ጤና ክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድሜነህ ልየው እንዳሉት በክልሉ ከሚገኙ 20 ዞኖች ውስጥ 45 ወረዳዎች የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን ጠቁመዋል።
የ2ኛው ኮሌራ ወረርሽኝ ከተከሰተ ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 5ሺ 4መቶ 36 ህሙማን በበሽታው እንደተያዙ እና ከእነዚህ ውስጥ 75 ሰዎችን ለሞት መዳረጉን አክለዋል፡፡
በሽታው በስፋት በተከሰተባቸው የጸበል ቦታዎች የጤና ባለሙያዎች በጊዜያዊነት በመመደብ የህሙማን ልየታ፣ የህክምና አገልግሎት፣ እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል።
ጊዜያዊ የኮሌራ ህክምና ማዕከል ቦታዎችን በቋራ ሆስፒታልና በበርሚል ቅዱስ ጊዮርጊስ ፀበል ቦታ በማዘጋጀት ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirDar
@tikvahethiopia
#SouthEthiopia
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ " በደንና እርሻ " ምክንያት እንደተነሳ ነዋሪዎች በገለፁት ግጭት በርካታ ቤቶች መቃጠላቸዉንና የሰዎችም ሕይወት መጥፋቱን የአከባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ባሳለፍነዉ ሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ/ም በደራሼ ወረዳ ሀይ'ቤና ኦኖታ ቀበሌያት አከባቢ ወየሳ ተብሎ በሚጠራ ጥብቅ ደን ዉስጥ ባለ እርሻ ተነሳ የተባለዉ ግጭት አለመብረዱ ተነግሯል።
" በአከባቢዉ ከአንድ ዓመት በፊት ተመሳሳይ ግጭት ተከስቶ የበርካቶች ሕይወት እንዲያልፍና መጠነ ሰፊ የንብረት ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል" ያለን አንድ የአከባቢዉ ነዋሪ " ያ ቁስል ሳይደርቅ ዳግም ግጭት ተቀስቅሶ ዉድመት እያስከተለ ነዉ " ብለዋል።
" ከ2011 ዓ/ም ወዲህ በአከባቢው ተደጋጋሚ መሰል ግጭቶች ይከሰታሉ " ያለን ሌላኛው የአከባቢ ነዋሪ " ግጭቶቹ በጥቂት ግለሰቦች ጀምረዉ በቀላሉ የማይበርዱት የፖለቲካ ፍላጎትና የአከባቢው አመራሮች ተሳትፎ ስላለበት ነዉ " ሲሉ ተናግረዋል።
" የፀቡ መነሻ የተባለዉ 'ወየሳ' ደን ከቀበሌያቱ ራቅ ያለ ቢሆንም ከሰኞ መጋቢት 22 /2017 ዓ/ም ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ወደ መንደር በመምጣት ቤቶችን የማቃጠል፣ የተኩስ እሩምታና ሰዎችን የመግደል አረመናዊ ተግባራትን የሚፈፅሙትን አካላት እነማንም ይሁኑ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና በሕግ እንዲጠየቁ ማድረግ ያስልጋል " ያሉን አንድ መምህር እሳቸዉን ጨምሮ ብዙ ሰላማዊ ሰዎች ሸሽተዉ ጫካ ዉስጥ መጠለላቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ነዋሪዎች አሁን ላይም ተኩስ ፣ የቤቶች ማቃጠልና የእህል ዝሪፊያ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
አልፎ አልፎም ከአዲስ አበባ አርባ ምንጭ ኮንሶ ጂንካ ድረስ የሚዘልቀዉ ዋናዉ መንገድ ለሰዓታት እየተዘጋ እንደንደሚከፈት አስታዉቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የዜጎችን ደህንነት እና ሰላም በተመለከተ እንዲሁም ችግሩን ለመፍታት ምን እየተሰራ እንደሆነ የአከባቢዉንና የክልሉን አመራሮች ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።
የጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ኩናሎ " ኑና እሳቱ ዉስጥ ሆናቹ ዘግቡ እኔ እሳቱ ዉስጥ ነኝ ማዉረት አልችልም " በማለት መልሰዋል።
የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ግንኙነት ኪንታቦ ደግሞ " እኔ ግንኙነት አይደለሁም " እያሉ ስልክ በመዝጋት ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገነህ ብዙነህ በአካባቢዉ ግጭት ከተነሳ በኋላ ወደ ስፍራው ማቅናታቸዉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቢሯቸዉ መረጃ አግኝቶ ወደ ሞባይል ስልካቸዉ ላይ በተደጋጋሚ ቢደውልም ሊያገኛቸው አልቻለም።
(በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን የምናቀርብ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
" በትግራይ ያለው የፓለቲካ ሁኔታ ለድህንነቴ ያሰጋኛል ! " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዱባይ ይገኛሉ።
በዱባይ ሆነውም ' bird story agency ' ለተባለ ሚድያ ቃለ-መጠይቅ ሰጥተዋል።
ለህክምና በዱባይ እንደሚገኙና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ የገለፁት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው አስከ አሁን በኋላፊነታቸው እንደሚገኙ በመግለፅ መንግስታዊ ስራዎች እየተከታተሉና እየፈረሙ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
" በቀጣይ ትግራይን ማንም ይምራት ብዙ አያሳስብም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ማንኛውም የትግራይ መሪ ከፌደራል መንግስት በመቀራረብና በመመካከር የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በማክበር ግዝታዊ አንድነትና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ መስራት አለበት " ብለዋል።
የፌደራል መንግስት ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተገዢ በመሆን ከፌደራል መንግስት ውጪ ያሉ ታጠቂዎች ከትግራይ እንዲወጡ መስራት አለበት ሲሉ አስገንዘበዋል።
በትግራይ ላለው የፓለቲካ ቀውስ መፈጠር የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ተጠያቂ ያደረጉም ሲሆን " ይህንን ሀቅ በመቀበል ለዚህ ውድቀት የዳረገንን አስተሳስብ መቀየር የትግራይ ችግር ይፈታል " ብለዋል።
" ያለው በእድሜ የገፋ አመራር በ20 እና በ30 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ለሚገኙ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ቦታውን መልቀቅ አለበት " ሲሉ አክለዋል።
" ትግራይ ደጋግመው ወደ ስህተት በዘፈቁዋት አመራሮች መመራት የለባትም " በማለትም አሳስበዋል።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ያለው የፓለቲካ ቀውስና አካሄድ ለድህንታቸው እንደሚያሰጋቸው በዚሁ ቃለ ምልልድ ወቅት ገልጻዋል። ይህም ክልሉን መልሰው የመምራት ዕድላቸው መሟጠጡ አመላካች ነው ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" እሳቱ እስከ አሁን ባለመቆሙ እየተባባሰ ነው " - አባ ገብረ ማርያም ሲሳይ
ከቢሾፍቱ ከተማ በስተሰሜን በኩል በ13 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ኤረር ቅድስት ልደታ ወበአታ ወብርሃነ ሰላም መድኃኔዓለም አድነት ገዳም ትላንት ቀን 7:00 ላይ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ እስካሁን አልጠፋም ተብሏል።
የገዳሙ ምክትል አስተዳደሪ አባ ገብረ ማርያም ሲሳይ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋው ትላንት ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 ሰዓት ጀምሮ ነው የተከሰተው " ብለዋል።
የቃጠሎው መነሻ እስከ አሁን እንዳልታወቀ ፤ እሳቱ እስከ አሁን ባለመቆሙ እየተባባሰ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
አደጋው በደቡብና ምሥራቅ አዋሳኝ ቦታ ላይ ባለው የቅዱስ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የጨፌ ሣር ነዶ ወደ ዐጸዱ እየተጠጋ እንደሚገኝ እና የእሳቱ ጭስ የኤረር ተራራን እንደሸፈነው አስረድተዋል።
የዐቢይን ጾም አስመልክተው በአታቸውን ዘግተው በሱባኤ ላይ የሚገኙ አባቶች በጭሱ ምክንያት መታፈናቸውን እንዲሁም በተራራው ውስጥ የሚኖሩ የዱር እንስሳት አደጋ ላይ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
እሳቱ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ለቢሾፍቱ ወረዳ ቤተ ክህነትና ለከተማው አስተዳደር ማሳወቃቸውን የገለጹ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ከሦስትና ዐራት ዓመታት በፊት ተመሳሳይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በገዳሙ መከሠቱንም አስታውሰዋል፡፡
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ነው።
@tikvahethiopia
“ በታጣቂዎች በኩል በዚህን ቀን እንመጣለን የሚል ምላሽ የለም። ግን ልዑካናቸውን እንደሚልኩ ተስፋ እናደርጋለን ” - ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከነገ ጀምሮ በአማራ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እንደሚካሄድ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በዚህም፣ በክልሉ 4,480 ተሳታፊዎች በባሕር ዳር ከተማ ለሦስት ቀናት እንደሚመክሩ፣ ሂደቱ በተለያዩ ሁነቶች እስከ ሚያዚያ 6/2017 ዓ/ም እንደሚቆይ ገልጿል።
በቦታው የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች በምክክሩ ለመሳተፍ ይሁንታ አቅርበዋል ? ሲል ለኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ጥያቄ አቅርቧል።
ኮሚሽነር ዮናስ (ዶ/ር) ምን መለሱ?
“ በታጣቂዎች በኩል በዚህን ቀን እንመጣለን የሚል ምላሽ የለም። ግን ልዑካናቸውን እንደሚልኩ ተስፋ እናደርጋለን ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
አክለው፣ “ ልዑካን ቡድን እንዲልኩ ጥሪ አቅርበናል። አሁንም ጥሪ እናቀርባለን። ካቀረቡ ድምፃቸውን ሰምተን ጥያቄዎቻቸውን አድምጠን ለሚመለከተው እናቀርባለን ” ብለዋል።
“ ትጥቅ እንዲፈቱ አንጠይቃቸውም። ከጠየቅንም ስህተት ነው። እኛ አማካሪዎች፤ አባቶች ነን። ትጥቅ የማስፈታት ሥራው የመንግስት ነው ” ሲሉም ተናግረዋል።
በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ እናትን ጨምሮ የተወሰኑ ፓርቲዎች “መጀመሪያ ጦርነቱ መቆም አለበት” በሚል እሳቤ በክልሉ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት እንደማይሳተፉ ለኮሚሽኑ አሳውቀው ነበር፤ ከዚያ ወዲህ ተነጋገራችሁ? አሁን ይሳተፋሉ? ሲል ኮሚሽነሩን ጠይቋል።
ኮሚሽነር ዮናስ (ዶ/ር)፣ “የተለዬ ለውጥ አላገኘንም። ነገር ግን ያለን አቋም በጣም አዎንታዊ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ወገኖቻችን እንዴት እንደሚያግዙን እኔ ምስክር ነኝ። በተለይ በአዲስ አበባው ላይ ስናካሂድ በጣም ደጋፊዎቻችን የነበሩ ሰዎች ናቸው” ሲሉ መልሰዋል።
“ ሀሳባቸው ረድቶናል። ዛሬም ያ ሀሳባቸው አይቋረጥም የሚል እምነት አለን እንደ ኢትዮጵያውያን። ይሄኮ የቤተሰብ ፀብ ነው። ስለዚህ እነርሱም ተመልሰው አሁን እንደቀድሞው እንተባበራለን የሚል እምነት አለን ” ነው ያሉት።
ኮሚሽር መላኩ ወ/ማርያም ምን አሉ ?
በክልሉ የጸጥታ ችግር ከመኖሩ አንጻር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ምን እንደነበር ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም ደግሞ፣ “ የተለያዩ ማህበረሰቦች ያለመሸማቀቅና ፍርሃት፤ ፋኖዎች ምናልባት ከማያነሱት በላይ ” ጥያቄዎች እንዳነሱ ገልጸዋል።
“ ህዝቡ የሚያውቅ፣ የሚረዳ፣ ዲሲፕሊንድ ህዝብ ነው። አገሩን የሚወድ ህዝብ ነው። ልዩነት የሚያደርግ አይደለም። ለሌላውም የሚያሳስበው ነው” ብለው፣ “ የተወካዮች ልየታ የተካሄደው ልክ በሌላ አካባቢ እንደተካሄደው ነው ልዩነት የለውም ” ሲሉም ተደምጠዋል።
በክልሉ 263 ወረዳዎች የተሳታፊ ልዬታ እንዳካሄዱ፣ አራት ወረዳዎች እንዳላካሄዱ ገልጸው፣ የአራቱን ወረዳዎች ስም ዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
ከ10 ዩኒቨርሲቲዎች 26 መምህራን፣ 2, 232 ተባባሪ አካላትን (385ቱ ሴቶች ናቸው) እንዳሰለጠኑ የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ “በተሳታፊ ልየታ ረገድ ደግሞ 13,900 ወንዶች፣ 5,698 ሴቶች፣ በድምሩ 19,598 ሰዎች በዚህ ሂደት እንዲያልፉ ተደርጓል” ብለዋል።
አክለውም፣ “መላውን አማራኔ ያካለለ ነው ማለት ነው። የቀሩት አራት ወረዳዎች ናቸው በታወቀ ምክንያት” ነው ያሉት።
ኮሚሽነሩ፣ "የሴቶች ተሳትፎ 30.3%፣ አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ 5.7፣ የተገለሉ ሰዎች ተሳትፎ 4%፣ የውስጥ ተፈናቃዮች 6.9% ነው" ሲሉም አስረድተዋል።
"የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ሸኔ፣ ፋኖ ምንድን ነው የሚፈልጉት? አዲስ የፓለቲካ ስርዓት እንገንባ፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እናምጣ፣ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነበት አገር እናድርግ ቁጭ ብለን ተነጋግረን። እዚህ ውጪ ምንድን ነው የሚፈለገው?" ሲሉ ጠይቀዋል።
"መንግስትም ሌሎችም በጠመንጃ የሚያሳኩት ነገር የለም። ሊያሳኩም አይችሉም" ሲሉም ተደምጠዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" 10ኛ ክፍል ላይ ሀገር አቀፍ ፈተና ሳይወስዱ ወደ 11 የተዘዋወሩ ተማሪዎች ልዩ የማካካሻ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፣ ካልሆነ ግን መውደቅ ይቀጥላል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር በየጊዜው በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ተከትሎ አካሄድኩት ባለው እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ጥናት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መገኘታቸውን ገልጿል።
የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ከተካሄደ በኋላ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ከሚችሉት በላይ ተማሪዎችን ያስተምራሉ ያለ ሲሆን ከዚህ በፊት 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረውን ፈተና በመቅረቱ ሳይፈተኑ 11ኛ ክፍል መግባታቸው ለችግሩ ዋና ተጠቃሽ ምክንያት መሆኑን አመላክቷል።
በትምህርት ቤቶች በሚሰጠው የሞዴል ፈተና እና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው የሀገር አቀፍ ፈተና ሰፊ ልዩነት እንዳለውም ገልጿል።
" በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መካከል የማለፍ ንፅፅር ሲታይ ልዩነት አለ " ያለው ሚኒስቴሩ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማምጣት ወደ ከፍተኛ ተቋም ይገባሉ፣ ይሁን እንጂ በቂ አይደለም፣ ብዙ ነገሮች መሻሻል እንዳለባቸው ጥናቱ አሳይቶናል " ብሏል።
ጥናቱ ምን አይነት የትምህርት ዘርፍ ችግር ነው ይሄን ያክል ውድቀት ያመጣብን ፣ ከተማሪዎች መውደቅ እና ማለፍ ጋር ተያይዞ የትምህርቱ ባህሪ ምንድን ነው የሚለውን እና በአጠቃላይ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የያዘ ነው።
በሁሉም የትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ ችግሮችን ያሳየው ይሄ ጥናት በመጨረሻም የመፍትሄ ሃሳቦችንም አቅርቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር ምን የመፍትሄ ሃሳብ አቀረበ ?
" ከዚህ በፊት 10ኛ ክፍል ላይ ይሰጥ የነበረውን ሀገራዊ ፈተና ሳይወስዱ 11ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ልዩ የማካካሻ ፕሮግራም ያስፈልጋቸዋል። ይሄ ካልሆነ ግን መውደቅ ይቀጥላል ፣ ምክንያቱ የሚፈለገውን ያህል እውቀት እና ክህሎት ይዘው አይወጡም።
በገጠር በተለይም በአርብቶ አደሮች አካባቢዎች ላይ ያለው የትምህርት ዘርፍ ልማት አነስተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እጅግ ወደ ኋላ እየቀረ ስለሆነ ማካካሻ መሰራት አለበት።
ሌላው ደግሞ ከትምህርት አመራር፣ መምህራን እና ከአቅም ግንባታ ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች ውጤት በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት ተደረጎ የትምህርት አመራሩ አቅም እስካልሰጠ ችግሮቹ ይቀጥላሉ።
ለመምህራን የደመወዝ ጭማሪ ብቻ ሳይሆን መምህሮችን የሚያቅፍ የ insensitive package እስካልመጣ ድረስ ችግሮቹ ይባባሳሉ።
በተጨማሪም በሀብት ክፍፍል ላይ ክፍተት በመኖሩ በትምህርት ዘርፉ ልማት ላይ ተግዳሮት መኖሩን ያሳያል፣ ይሄም መፈታት አለበት " ሲል መፍትሄ ያለውን ሃሳብ አቅርቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር ጥናቱን ባቀረበበት ወቅት የህዝብ ተወካዮች የተለያዩ አስተያየቶች፣ ጥያቄዎች እና ሃሳቦችን አቅርበዋል።
በጥናቱ ላይ የመፍትሄ ሃሳቦች መቅረባቸው ጥሩ ሁነው ሳለ እንደዚሁ ተወርተው መሬት ላይ ሳይወርዱ ከቀሩ ትርጉም አልባ ናቸው፣ በመሆኑም ሁሉም በአፅንኦት ሊመለከተው እንደሚገባ በተወካዮች ተጠቁሟል።
ከ1 እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አነስተኛ ነው፣ ይሄም አሁን ላለንበት ውጤት ማጣት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ፤ በጥናቱስ ላይ ለምን ይሄ ሳይካተት ቀረ፣ ምክንያቱም የትምህርት መሰረቱ ከታች ጀምሮ ስለሆነ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስቷል።
የተለያዩ ተማሪዎች በህገወጥ መንገድ ወደተለያዩ ሀገሮች እየተሰደዱ ነው፣ ተማሪዎች ይሄ ሲፈጠር ተረጋግተው መማር እየቻሉ አይደለም፣ ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ጅቡቲ ላይ ለሶስት ቀናት ሥራ ባለመኖሩ ነዳጅ ወደ ኢትዮጵያ አልገባም " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን
በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎች ከሰሞኑን እጅግ ረጃጅም የናፍጣ ሰልፍ አለ።
በርካቶችም ናፍጣ ለመቅዳት ረጅም ሰዓታት እየተሰለፉ የስራ ሰዓታቸው እየባከነ ይገኛል።
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ፤ " ባለፉት ቀናት በአንዳንድ አካባቢዎች የነዳጅ እጥረት በተወሰነ መልኩ ተከስቷል " ሲል ለኤፍ ኤም ሲ ተናግሯል።
የነዳጅ እጥረቱ በጅቡቲ የኢድ አልፈጥር በዓልን ተከትሎ ለሶስት ቀናት ሥራ ባለመኖሩ ነዳጅ ወደ ኢትዮጵያ ካለመግባቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ነው ሲል አሳውቋል።
የተከሰተውን የናፍጥ እጥረት ለመፍታት ከመጠባበቂያ ዴፖ ለማደያዎች የማከፋፈል ሥራ ተሰርቷል ብሏል።
የነዳጅ ሰልፉ ከዋጋ ጭማሪ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነም መ/ቤቱ ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል ጠቁሟል።
ፎቶ፦ ኤፍ ኤም ሲ
@tikvahethiopia
" ወደ ቀድሞው ካምፓኒ ሊመልሱን ነው። መንግስት በፍጥነት የማያስወጣን ከሆነ ላለመመለሳችን ምንም ዋስትና የለንም " - ከ730 በላይ ዜጎች በማይናማር
በማይናማር በታገቱበት ወቅት ሲሰሩት የነበረውን አስከፊ ስራ እንዲያቆሙ ተደርገው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከወር በላይ የመንግስትን ምላሽ ሲጠባበቁ የነበሩ ከ730 በላይ ኢትዮጵያውያን ቀድሞ ወደነበሩበት የእገታ ቦታ ሊወሰዱ በመሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።
ኢትዮጵያውያኑ ዛሬስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ?
“ወደ ሀገራችን ለመውጣት ዛሬ ነገ እያልን ወደ ካምፓኒ ተመለሱ ተባልን።
ከመጥፎው ስራ አውጥተውን የነበሩት ሚሊታሪዎቹ 'መንግስታችሁ የማይፈልጋችሁ ከሆነ ወደ ቀድሞው ካምፓኒ ተመለሱ፣ እናንተን ቁጭ አድርገን የምንመግበው የለንም' ብለውናል።
የኢትዮጵያ መንግስት እኛን የመመለስ አቅም የለውም ወይ? መልሱ አዎ ከሆነ ተመልሰን እዛ ከምንገባ እዚሁ እራሳችንን እናጠፋለን የመጨረሻ አማራጫችን እሱ ነው። ዛሬ ተስፋ ቆርጠናል፤ ጭንቀታችን በርትቷል ስለዚህ መልስ እንፈልጋለን።
ተገደን የማጭበርበር ስራ የነበርንና በሚሊተሪ ድጋፍ ነጻ የወጣን 735 ኢትዮጵያውያን በማይናማር ሁለት ሚሊተሪ ካምፖች ሆነን የሀገራችን ምላሽና የማጓጓዝ ስራ በመጠበቅ ሁለተኛ ወራችን እያገባደድን ነው።
ይህም ከካምፓኒ ለመውጣት ስንጠየቅ ከነበረው 5000 ዶላር ነጻ ያደረገንና የኢትዮጵያ መንግስትም ስካም ፓርኮቹ ድረስ ገብቶ ዜጎቹን ለማውጣት ተፈጥሮበት የነበረውን ፈተና ያቀለለ ምቹ አጋጣሚ ነበር።
በቆየንባቸው የሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የወላጆች ኮሚቴ ሂደቱ እየተሰራበት እንደሆነ በሚደርሱን መረጃዎች እየተጽናናን ቆይተናል።
በቆይታችን ሚሊተሪው የተያዘውን ምግብ ቢያቀርብም ከሃይማኖታችንና ከሀገራችን የአመጋገብ ባህል ጋር ፈጽሞ የማይሄድ በመሆኑ በውድ ዋጋ በሽያጭ የሚያቀርቧቸውን ምግቦች እየገዛን እንጠቀም ነበር።
አሁን ግን ሁላችንም እጃችን ላይ የነበረንን ገንዘብ ጨርሰን ምግብና መድኃኒት ምንገዛበት የሌለን በመሆኑ ለረሃብና ለጤና ችግር ተጋልጠናል።
ከቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ማገገም ያልቻሉ፤ በተፈጥሮ አደጋው ተጎድተው ደም አሁንም የሚፈሳቸው፤ በአንጀትና አንገት ህመሞች ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ ማይችሉ ህሙማን ባሉበት ህክምና በማይገኝበት ጠረፍ ላይ መሆናችን ከዚህ እንድንወጣ ለሚዲያዎችና ለመንግሥት ተቋማት እያሳወቅን የቆየን መሆኑም ይታወቃል።
ይህ ሁሉ ችግር ያልፋል ብለን በኢትዮጵያ መንግስት እና ኢምባሲዎቹ እየተሰሩ ያሉ እኛን የመመለስ ስራ በተስፋ እየጠበቅን ባለንበት ወቅት ሁላችንንም ያስደነገጠ እና ተስፋችን የቀማን ችግር ተከስቷል።
ከአረመኔያዊ አያያዝ አውጥቶ ካምፕ ውስጥ ያስገባን ሚሊተሪ የሀገራችን ምላሽ እየተጠባበቀ ቢቆይም በኢትዮጵያ መንግስትና በኤምባሲዎች የሚሰራው እኛን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እጅጉን ስለተጓተተ፣ ከ29 ሀገራት ዜጎች እኛ ብቻ በመቅረታችን ሚሊተሪው በኢትዮጵያ መንግሥት ተስፋ ቆርጦ ወደ ካምፓኒዎች እንደሰንመለስ እያዋከበን ነው።
ይህም በብዙዎቻችን ላይ ትልቅ ሽብርና መደናገጥ የፈጠረ አደገኛ ክስተት ሆኖ ለጭንቀት ዳርጎናል።
በመሆኑም፣ ሚዲያዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ኤምባሲዎች ለዚህ አደገኛ ሂደት ፈጣን ምላሽ በመስጠት ወደ ሀገራችን መመለስ ካልቻሉ መመለስ የማንችለው የ735 ወጣቶች ህይወት አደጋ ውስጥ እየገባ እንደሆነ ለማሳወቅ እንፈልጋለን” ሲሉ ተማጽነዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
TIME IS RUNNING OUT!
Applications for the Jasiri talent Investor will close in TWO DAYS on Friday, April 5th. Don’t hesitate, apply today!
To apply: https://bit.ly/40Ai4oR
For more information @jasiri4africa
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ ምንድነው ?
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?
" በዚህ አመት ከቻልንና ለሚቀጥለው ዓመት ተግባራዊ ማድረግ ከቻልን ጥሩ ነው ካልቻልን ግን በእርግጠኝነት በ2019 ዓ/ም የምንጀምረው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ የሚባል ፕሮግራም ነው።
ድሮ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች [እንደ እኔ እድሜ የጠገባችሁ ካላችሁ ታውቁታላችሁ] የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 3ኛ ዓመት ሲጨርሱ 4ኛ ዓመት ከመግባታቸው በፊት ለ1 ዓመት በነፃ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ለማገልገልም ለራሳቸውም ተግባራዊ ትምህርት እንዲያገኙ በየክልሉ ሄደው በየሙያቸው ይሰሩ ነበር ለ1 ዓመት።
Basic ወጪያቸው ብቻ ከፍሎ ከዚያ ሲመለሱ 4ኛ ዓመት ይሆናሉ ብዙ ጥቅም ነበረው አንደኛ ተመልሰው ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 4ኛ ዓመት የበለጠ በስለው ነው የሚገቡት ስለማህበረሰባቸው አውቀው ነው የሚገቡት ፤ ብዙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ከዛ በኃላ እነኚህ ሰርቪስ የወጡ ልጆች ሲያስተምሩ አስተማሪነትን ወደውት እዛው በአስተማሪነት የቀሩ ብዙ ሰዎች አሉ።
ይሄን ፕሮግራም እንጀምራለን " ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ዓመት ወይም በ2019 ዓ/ም ተግባራዊ ለማድረግ ባቀደው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪድ ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ከመመቀራቸው በፊት በየክልሉ ሄደው ማህበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ ይደረጋሉ።
4 ዓመት ተምረው የሚጨርሱ 3ኛ ዓመት ፤ በ5 ዓመት ተምረው የሚጨርሱ 4ኛ ዓመት ላይ ወጪያቸው ተከፍለ አገልግሎት ይሰጣሉ። ይህ አዲስ የሚጀምረው ፕሮግራም በተለይ የመምህራንን እጥረት ለመቅረፍም አንዱ መንገድ ተደርጎ ተወስዷል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
ቪድዮ፦ ኢቢሲ
@tikvahethiopia
#MoE
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።
ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ ጥናት አቅርበዋል።
ውይይትም ሲደረግ ነበር።
በዚህም ወቅት በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።
ላለፉት ዓመታት (እሳቸው በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ) ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።
ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
'' የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ '' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ " በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።
ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።
ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።
በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።
ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ " የመምህራን ባንክ " ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።
ባንኩ " በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን " ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
@tikvahethiopia
“ 1000 ብር የሚከፈለው ሠራተኛ አለ። የደመወዝ ጭማሪም አልተፈጸመልንም ” - የይርጋጨፌ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች
➡️ “ ሆስፒታሎች ሊስታቸው በሲቪል ሰርቪስ የሠራተኞች ዝርዝር ዳታ ቤዝ ውስጥ የለም። እንዲገባ የተደረገው ጭማሬው ከተደረገ በኋላ ነው” - ሆስፒታሉ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ 230 ጤና ባለሙያና ሠራተኞች አዲሱ የደመወዝ ጭማሪና የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመፈጸሙ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞቹ ምን አሉ ?
“ የካቲት 12/ 2017 ዓ/ም ‘ይከፈላችኋል ብር ተገኝቷል’ የሚል ተስፋ ሰጥተውን ነበር። ነገር ግን እስካሁን ምንም የለም። ለተቋማዊ ገጽታ እንጂ ለሠራተኞች የተጨነቁ አይመስሉም። 1000 ብር ደመወዝ የሚከፈለው ሠራተኛ አለ። የደመወዝ ጭማሪው አልተከፈለንም ” ብለዋል።
“ 1000 ብር የሚከፈለው መንግስት ሠራተኛ አለ። ቢያንስ ለእነርሱ እንኳ መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል ” ሲሉ አሳስበው፣ ለጤና ባለሙያዎች ጭምር የአምስት ወራት የደመወዝ ጭማሪ እንዳልተከፈላቸው ገልጸዋል።
“ ለዞኑ የደመወዝ ጭማሪ በታህሳስ ተከፍሏል። ጭማሪው አገር አቀፍ ሆኖ ሳለ ለዞኑ ታህሳስ ላይ ክፍያ ሲፈጸም፤ እኛ ለምን አልተከፈለንም? ብለን ስንጠይቅ ‘የእናንተ ፋይል ተረስቶ ሊሆን ይችላል’ ተባልን ” ነው ያሉት።
በዚህም ኑሮ ውድነቱ በየቀኑ እየጨመረ፣ የሚከፈላቸው ደመወዝ ዝቅተኛ በመሆኑ ቤተሰብ ለማስተዳደር፣ ልጆች ለማስተማር እንደተቸገሩ ገልጸዋል።
ሆስፒታሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን ምላሽ ሰጠ ?
በቅሬታው መሠረት፣ የደመወዝ ጭማሬና የዱቲ ክፍያ ለምን እንዳልተፈጸመ ምላሽ የጠየቅው ይርጋጨፌ ሆስፒታል፣ ደመወዝ በሁሉም አለመጨመሩን፣ የዱቲ ክፍያ ግን መፈጸሙን የሚመለከት ምላሽ ነው የሰጠው።
አንድ የሆስፒታሉ አመራር በሰጡን ቃልም፣ “ ደመወዝ ጭማሪ የሆስፒታላችን ብቻ ሳይሆን ክልላዊ ጉዳይ ነው። የዱቲ ክፍያ እንደኛ ሆስፒታል የዱቲ ውዝፍ የተከፈለበት ሆስፒታል ስሌለ የተሳሳተ መረጃ ነው ” ብለዋል።
ስለደመወዝ ጭማሬው ከክልል የተባላችሁ ነገር የለም ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ ሆስፒታሎች በቦርድ ነው የሚተዳደሩት። ሊስታቸው መደበኛ በሆነ በሲቪል ሰርቪስ የሠራተኞች ዝርዝር ዳታ ቤዝ ውስጥ የለም። እንዲገባ የተደረገው ጭማሬው ከተደረገ በኋላ ነው” ሲሉ መልሰዋል።
እኚሁ አካል፣ “ አሰራር ነው እንደዛ የሚያደርጋቸው፤ የብዙ ሺሕ ሠራተኞችን ይሄን ዳታ ፊልተር ማድረግ ጊዜ ይወስዳል። ከዚህ ጋር በተገናኘ እንጂ በሌላ ጉዳይ አይደለም። ፋይናላይዝ እየተደረገ ያለ ስለሆነ እንደ ሀገር ተቋማትም በዚህ እስቴፕ ውስጥ እያለፉ ናቸው ” ነው ያሉት።
የሆስፒታሉ ባለሙያዎች የደመወዝ ጥያቄ በማንሳታቸው “ እስራትና ድብደባ ” እንደተፈጸመባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከወራት በፊት መግለጻቸው አይዘነጋም።
ስለደመወዝ ቅሬታው በወቅቱ የጠየቅነው የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ፣ “ እነርሱ ጋ ብቻ አይደለም ያልተከፈለው፤ ከ2,000 በላይ ሠራተኞች እንደ ዞን ያልተከፈላቸው አሉ ” የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።
“ ከክልል ፋይናንስ ገንዘብ እንዲለቀቅ በሂደት ላይ እንደሆነ፣ እንደተለቀቀ ክፍያ እንደሚከፈል ተግባቦት ላይ ተደርሷል ” ነበር ያለው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
የዛሬውን የመርሲሳይድ ደርቢን ማን ያሸንፋል? ኮመንት ላይ እንገምት! በዕለታዊ 1.1 ጊባ + 1.1 ጊባ ጉርሻ የዳታ ጥቅል ከዳር እስከ ዳር በሚገኘው በሳፋሪኮም ኔትወርክ ላይ በDSTV በቀጥታ እንከታተል!
በM-PESA ላይ ስንገዛ
እለታዊ 1.1 ጊባ + 1.1 ጊባ ጉርሻ በ30 ብር ብቻ!
🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#Myanmar #Thiland
➡️ በማይናማር የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር 2,900 ተጠጋ።
ከቀናት በፊት በማይናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 2,900 ሲጠጋ ፤ በታይላንድ 72 ሰዎች ደብዛቸው እንደጠፋ መሆኑን ዢንዋ ኒውስ ዘግቧል።
የማያንማር አስተዳደር ምክር ቤት ይፋ ባደረገው መረጃ በማያንማር የሟቾች ቁጥር 2,886 ደርሷል፣ 4,639 ሰዎች ተጎድተዋል እና 373 ደብዛቸው ጠፍቷል።
በአጎራባች ታይላንድ፣ በዋና ከተማዋ ባንኮክ 72 ሰዎች አሁንም ደብዛቸው እንደጠፋ ነው።
ባንኮክ በመሬት መንቀጥቀጡ የመንግስት ኦዲት ቢሮ ህንጻ ወደ ፍርስራሽነት የተቀየረ ሲሆን በዚሀ ቦታ አስከሬን ፍለጋ ቀጥሏል።
በማይናማር እና ታይላድ ከቀናት በፊት በሬክተር ስኬል 7.7 እና 6.4 የሆነ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
" በመቶ ሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ንብረት ይዘን ለሁለት ቀናት ተሰልፈናል ፤ ስጋት ሊገለን ነዉ " - ቡናና ሸቀጦች ጭነዉ የተሰለፉ አሽከሪካሪዎች
➡️ " ሰልፉ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም አማራጭ ስለሌለን እየተጠባበቅን ነዉ !! "
በሀገራችን አብዛኞቹ አከባቢዎች ባለዉ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ምክንያት በየማደያዉ ረጃጅም ሰልፎችን መመልከት የየዕለት ተግባር ሆኗል።
በተለይም አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ ናፍጣ ለመቅዳት በየማደያዉ ለቀናት ተሰልፈዉ የሚጠባበቁ አሽከርካሪዎች ምን አይነት ጊዜ እንደሚያሳልፉና ሌላዉ ሰዉ አይረዳልንም ያሉትን ስሜት በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አጋርተዋል።
ሁለት የተሳቢ አሽከርካሪዎች " እኛ የጫነዉ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣና ለሀገራችንም የዉጪ ምንዛሪን የሚያስገኝ የታጠበ ቡና ነዉ " ብለዋል።
" እኛ ጭንቀታችን ለሁለት ቀናት ተሰልፈን በተስፋ ከምንጠባበቀው ነዳጅ በላይ ተመርምሮና ተወግቶ ከቅምሻ ማዕከል በማሸጊያ ሽቦ ከታሰረ በኋላ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለመጓዝ የተዘጋጀን ቡና ጭነን መሰለፉችን ነዉ " ሲሉ ገልጸዋል።
" አንድ የታሸገ ሽቦ ቢትቆረጥ ከቀናት ሰልፍ በኋላ ወደ ተገላገልነዉ የቡና ጥራት ማስመርመሪያ ወረፋ ዳግም መመለስን ጨምሮ የመሰረቅ ስጋት እንዲሁም በቆየን ቁጥር በቡናዉ ጥራት ላይ ሊያጋጥም የሚችል የጥራት ጉድለት አደጋ ለከፍተኛ ስጋት ዳርጎናል " ብለዋል።
የእንስሳት ተዋፆ ወተት፣ አይብና ቅቤ ጭኖ መሰለፉን የነገረን ሌላኛው አሽከርካሪ " በወቅቱ ወደ አሰላ ካልደረስኩ ድርጅቴ ኪሳራዉ ከፍተኛ ነዉ " ሲል ገልጿል።
አንድ አሽከርካሪ ደግሞ ከቡታጅራ ወደ ሀዋሳ ተሳፋሪዎችን ይዞ ከመጣ በኋላ ለመመለስ በነዳጅ እጦት ምክንያት ለሶስት ቀናት መጉላላታቸዉን አስረድቷል።
ከአዲስ አበባ ሸቀጣ ሸቀጥ ጭኖ ወደ ዉሮ እየተጓዘ ላለፉት ሁለት ቀናት ነዳጅ በማጣቱ በሀዋሳ ከተማ በሁለት የተለያዩ ማደያዎች ተሰልፎ ማደሩን የነገረን ሌላኛው አሽከርካሪ በተስፋ የሚጠባበቁት ነዳጅ ደርሷቸዉ ቢቀዱ እንኳን በተያዘላቸው ቀን ለመድረስ ለአደጋ የተጋለጠ ጉዞ ለማድረግ እንደሚገደዱ ተናግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተዘዋውሮ አሽከርካሪዎችን ባነጋገረበት ወቅት በሀዋሳ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ ከሚያነሱ ማህበራት መካከል የአንዱ ማህበር እንደሆነ የተነገረ የቆሻሻ መኪና ነዳጅ ጨርሶ ሰዓታትን አልፎ ከአንድ ቀን በላይ ይፈጃል በተባለዉ ሰልፍ መሃል የነበረ ሲሆን በአከባቢው መጥፎ ጠረን ተፈጥሮ በተነሳበት ተቃዉሞ በሰዉ ሃይል ተገፍቶ ነዳጅ ተቀድቶለት ተሸኝቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
“ የአሜሪካ ታሪፍ መጨመር፣ በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል ” - አቶ ክቡር ገና
➡️ “ እርምጃው፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳትም ስለሚያስከትል፣ ሌሎች የገበያ መዳረሻዎችን ማፈላለግ ይገባል ! ”
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ሰሞኑን ባደረጉት አዲስ የቀረጥ ጭማሪ እርምጃ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ40 በላይ የአፍሪካ ሀገራትን አካቷል፡፡
እርምጃው ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ በምታስገባቸው ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ እንዲጣልባቸው አድርጓል፡፡
ይህ አዲሱ የፕረዝደንት ትራምፕ እርምጃ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና ወደ አሜሪካ ገበያ በሚገቡ የኢትዮጵያ ምርቶች ላይ ምን ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ባለሙያ፣ “ ተፅዕኖ መፍጠሩ አይቀሬ ነው ” ብለዋል፡፡
የቀረጥ ወይም ታሪፍ ጭማሪው፣ ወደ አሜሪካ ገበያ የሚላኩ ሸቀጦች ዋጋቸውን ያንረዋል፣ ይህ ደግሞ በሸማቹ ማኅበረሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው ሲሉ ተናረዋል፣ የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ክቡር ገና፡፡
በኢኮኖሚ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት አንጋፋው ባለሙያ አቶ ክቡር ገና በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከምትልካቸው ምርቶች ቡና እና ጨርቃጨርቅ ትልቁን ድርሻ እንደሚይዙ ገልፀው፣ አሁን እነዚህ ምርቶች አሜሪካ በሚደርሱበት ጊዜ ዋጋቸው ይጨምራል ብለዋል፡፡
የሸቀጦቹ ዋጋ ሲጨምር፣ ገዢዎቹ ይቀንሳሉ፣ ያ ደግሞ ሀገር ውስጥ ያሉ አምራቾች ምርታቸው ሊቀንስ እና በአቅምም ሊያንገዳግዳቸው ይችላል ሲሉም አክለዋል፡፡
አቶ ክቡር ገና በዝርዝር ምን አሉ ?
“ እርምጃው የኤክስፖርት ኢኮኖሚውን ይጎዳዋል፡፡ ቀደም ሲል አባል የነበርንበት የአጎዋ ዕድል (የአፍሪካ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ ገበያ የሚገቡበት አሰራር) ተጠቃሚዎች ነበርን፡፡ ያ ዕድል ተቋርጦዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምርቶች ቀረጥ ተክፍሎባቸው ነበር ወደ አሜሪካ ገበያ ሲገቡ የነበሩት፡፡ አሁን የተጨመረው የ 10 በመቶ ታሪፍ ቀደም ብሎ በነበረው ላይ ነው፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ላኪዎችን ያዳክማል፡፡ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
በአብዛኛው አንዲህ ዓይነት ለውጥ በሚመጣበት ጊዜ፣ የውጭ ምንዛሪ ግብይት (የገንዘብ መዘርዘሪያ መጠን) ላይ የሆነ ተፅዕኖ ያስከትላል፡፡ እርምጃው ብርን ሊያጠነክረው ይችላል፣ አለያም የበለጠ ሊያዳክመው ይችላል፣ እሱን ቀጥለን የምናየው ይሆናል፣ ግን ተፅዕኖው አይቀሬ ነው፡፡ ”
የትኞቹ ሸቀጦች የበለጠ ይጎዳሉ ?
“ በትክክል ምንድነው የሚፈጠረው የሚለው በትግበራው ወቅት ነው የሚታየው፡፡ ለምሳሌ እዛ ያሉት ኢምፖርተሮች (ከእኛ ላኪዎች ሸቀጦችን የሚረከቡ የአሜሪካ ነጋዴዎች)፣ አሁን በዚህ የታሪፍ መጨመር ምክንያት የሸቀጥ ዋጋ ጨምሮባቸዋል፡፡
አሁን እነሱ ምን ይወስናሉ፣ ጭማሪውን ራሳቸው ሸፍነው ትርፋቸውን ቀንሰው እቃውን ለሸማች ያቀርባሉ ወይስ ጭማሪውን በቀጥታ ለተጠቃሚው ያስተላልፋሉ የሚለው ገና የሚታይ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ እርምጃው የትኞቹን ሸቀጦች የበለጠ ይጎዳል የሚለውም እንደዚሁ ቀጥሎ የሚታይ ነው፡፡
ለምሳሌ በአሜሪካ ገበያ ብዙም ተወዳዳሪ የሌለው የኢትዮጵያ ሸቀጥ ብዙም ተፅዕኖ ላይደርስበት ይችላል፣ ምክንያቱም ሸማቹ አማራጭ ስለሌለው ዋጋውም ቢጨምርበት እቃውን ይገዛዋል፡፡
የሆነ ሆኖ ግን ታሪፉ የምርት ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል፣ ያ ደግሞ በሸማቾች ዘንድ የመግዛት ፍላጎት ይቀንሳል፣ ከዛም የምርት መጠን ይዳከማል፣ ገዢ ከሌለ የኢትዮጵያ አምራቾች ሊያመርቱ አይችሉም፡፡ ”
መፍትሔው ምንድነው የሚሆነው ?
“ መፍትሔው ያንን የሚተካ ሌላ ገበያ መፈለግ ነው፡፡ ከአሜሪካ ወጥቶ የሌሎችን ሀገራት ገበያ ማፈላለግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ተፅዕኖው ከመበርታቱ በፊት ሌሎች የንግድ መዳረሻዎችን ማፈላለግ ይገባል፡፡
ታሪፉ የተጣለው በሁሉም ሀገራት ላይ ስለሆነ፣ የትኛው ሀገር የበለጠ ይቋቋመዋል የሚለው ገና በትግበራ ወቅት የሚታይ ይሆናል፡፡ የታሪፍ ለውጥ መምጣት የፖሊሲ ለውጥ ለማድረግም ይረዳል፡፡
ወደ ሌሎች ዘርፎች እንድነገባ ሊያስገድድ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የቱሪዝም ዘርፉን ማጠናከርና ማስፋፋት ይገባ ይሆናል፡፡ በተጣለው ታሪፍ ምክንያት የሚታጣውን ገቢ ለማካካስ ማለት ነው፡፡
በቅድሚያ ግን የእርምጃውን ተፅዕኖ በደንብ ማጥናትና የመውጫ መንገዶችን ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ተፅዕኖው ምን ሊሆን እንደሚችል ማየት ይኖርብናል፡፡ ”
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 122.5 ሚሊዮን ዶላር ለደንበኞቹ ድልድል ማድረጉን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 711 ደንበኞቹ ያቀረቡትን የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ በመገምገም ለ698 (98%) ለሚሆኑ ደንበኞቹ በድምሩ የ122.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድልድል ማድረጉን ገልጿል።
"የቀሩት ጥቂት ደምበኞችም ጥያቄ ተጨማሪ የመረጃ ማጥራት ስራ ተሰርቶ በቅርቡ የሚታይላቸው ይሆናል።" ሲል አስታውቋል።
ባንኩ " በቀጣይም ለደንበኞቼ የውጪ ምንዛሪ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ " ሲል ገልጿል።
@tikvahethiopia
🎉✨ ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017 ተከፈተ!!
የመግቢያ ትኬትዎን በቴሌብር ሲቆርጡ:-
🚘 NETA AYA 2024 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና
🏍 Dodai የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል
📱 ስማርት ስልኮች
የሚያሸልም የዕጣ ቁጥር ይደርስዎታል።
❇️ ልጆጲያ (Kidzopia): ለሕጻናት ልዩ መዝናኛ እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች
❇️ የጾም ፌስት: የጾም ብፌ በ150 ብር ብቻ
💁♂️ በተጨማሪም በቴሌብር ያሻዎትን ሲገበያዩ እስከ ብር 2500 ላለው 10% ተመላሽ ያገኛሉ!
ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ወይም *127# ይጠቀሙ!
📍 በኤግዚቢሽን ማዕከል
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
“ ተደብቆ የተገኘ አሽከርካሪ እስከ 500 ሺሕ ብርና ሦስት አመት እስራት እንዲቀጣ የተቀመጠ ዐዋጅ አለ። ይሄ አግባብ አይደለም ” - ማኀበሩ
አሽከርካሪዎችን በተመለከተ የሚወጡ ህጎች አሳታፊነት የጎደላቸውና አሽከርካሪዎች ሥራ እንዲያቆሙ የሚያደርጉ በመሆናቸው ሊጤኑ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር አሳሰበ።
ግብዓት የሚያጓጓዙ ሹፌሮች በጸጥታ ችግር መንገድ ላይ በሚጉላሉበት፣ የሚጓጓዙበት ሪዘርቭ ነዳጅ እንዳይጭኑ በሚከለከሉበት ሁኔታ በአራትና አምስት ቀናት ከጂቡቲ ወደ መሀል ሀገር ካልደረሱ እስከ 500 ሺሕ ብር የተጣለባቸውን ቅጣት ማኀበሩ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተቃውሟል።
ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ?
የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ፥ “ ህግ ሲወጣ አሳትፉን ብለን ለነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን በተደጋጋሚ ደብዳቤ አስገብተን ሊያነጋግሩን ፈቃደኞች አይደሉም።
ህግ ሲወጣ ማህበሩ መሳተፍ አለበት። የሚጎዱና ተደራራቢ ህጎችን በማውጣት አሽከርካሪዎች ከስራ እንዲፈናቀሉ እንጅ ህግ እንዲከበር አያደርግም። ያሽከርካሪን ችግር ሳያዳምጡ ህግ ማውጣቱን ማህበሩ አይቀበለውም።
ወንጀለኛ ከሆኑ አሽከርካሪዎች አይያዙ የሚል አመለካከት የለውም ማህበሩ። ግን አሰራሩ ሙሉ ለሙሉ ለሹፌሮች ብቻ እየተደረገ ባሽከርካሪዎች የመስራት ፍላጎት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያስከተለ ነው።
ሹፌሮች ረጅም መንገድ በሚጓዙበት ወቅት ለሚጓጓዙበት የሚሆን ሪዘርቭ ነዳጅ በታንከራቸው ይጭናሉ፤ ግን ከተሳቢ ታንከር ወደ ፊተኛው መኪና ሽፍት ሲያረጉ‘ነዳጅ እየቀሸብክ ነው; ተብሎ የሚያዙበት አጋጣሚ እየተፈጠረ ነው። ይሄ ትክክል አይደለም።
ከጅቡቲ ሞያሌ የሚሄድ አሽከርካሪ ሪዘርብ ነዳጅ ካልያዘ መንደር ላይ ሊያጣ ይችላል። ባሁኑ ወቅታዊ ሁኔታ ነዳጅ በየቦታው አይገኝም። ስለዚህ ሹፌርን ሆን ተብሎ ለመበደል ምክንያት እየተፈለገ ነው ” ብለዋል።
ሌላኛው የማኀበሩ አመራር ምን አሉ ?
“ አንድ አሽከርካሪ ነዳጅ ከጅቡቲ አድስ አበባ ከጫነ በአራት ቀን መድረስ አለበት ተብሏል። ካልደረሰ 480 ሺሕ ብር፣ ተደብቆ የተገኘ እስከ 500 ሺሕ ብር የሚያስቀጣ መሆኑን ወስነዋል። ከ300 ሺሕ እሰከ 500 ሺሕ ነው ቅጣቱ። ግን ሪዘርቭ ነዳጅ እንዳይያዝም ከልክለዋል።
አንድ አሽከርካሪ በዋና ታከሩ የያዘው ነዳጅ አያደርሰውም እየተጓዘ ነዳጅ ካቋረጠው ወረፋ ይዞ እንደማንኛውም ደረቅ ጭነት የጫነ ተሽከርካሪ ተሰልፎ ነው የሚቀዳው፤ ከወረፋ መካከል አውጥተው ‘ተደብቆ የተገኘ ሹፌር ይዘናል’ ተብሎ ለሚዲያ ፍጆታ ይቀርባል።
የነዳጅ ጫኚ መኪና የሚቀዳበት የተለየ ማደያ የለም። ይሄ በሌለበት በዛ ቀን አልደረስከም ተብሎ መያዝ፣ ካገኙት ማደያ እንኳ ሪዘርቭ ይዘው ሲሄዱ ሪዘርቩን ሲያገላብጥ ‘እየቀሸበ ነው’ ተብሎ መጠየቁ አሽከርካሪውን ስራ ወደ ማቆም እያደረሰ ነው።
በጣም አስቸጋሪ ደረጃ እየደረስን ነው። ባሽከርካሪ ጉዳይ የሚወጣ ህግ ካለ ቀድመን በመሳተፍ የህጉ የግብአት አካል መሆን አለብን።
ነዳጂና ኢነርጂ ባለስልጣንን ጠይቀን፤ ‘አናስገባም’ አሉን በፅሑፍ አምጡ ተባልን በእጅ ፅሑፍ ሀሳባችንን ገለጽን፤ ነገር ግን ‘ሌላ አካል ስላነጋገርን አናነጋግርም’ የሚል መልስ ሰጡን፤ ሕጋዊ ደብዳቤም ፅፈን አስገባን አሁንም የተሰጠን የፅሑፍም ሆነ የቃል መልስ የለም።
ለንግድና ቀጠናዊ ትስስርም ደብዳቤ አስገባን። ፕሮግራም ተይዞልን ህጉ በነጋሪት ጋዜጣ ከመታወጁ በፊት ንግግር እናድርግ ብለን ሄደን ጠየቅን፤ ግን የሚያነጋግረን አጣን። ሕጉ በነጋሪት ጋዜጣ ታወጀ ወደ ተግባር ገባ።
ሹፌር እንደማንኛውም ሙያ እኩል ነው እንዲባልና የሙያውን ዋጋ እንዲሰጠው ነው የምንሰራው። በተደራጀን ቁጥር ወደ መገፋት እየመጣን ነው። ማህበሩ ባይኖር በአንድ ቀን ስራ ሊቆም ይችላል። ሀሳባችነን ስናቀርብ ተደማጭነት ካጣን ምን እናደርጋለን።
ኮማድ ፖስት ባለበት ከጅቡቲ ነዳጅ የሚጭኑ ሹፌሮች በአራት ቀናት አዲስ አበባ ሊደርሱ አይችሉም። ሰዓቱን እንኳ ለመሸፈን ሪዘርቭ ነዳጅ እንዳይዙ ከተከለከለ በምን ሊደርሱ ይችላሉ? ሁለቱ የሚጋጭ ነው።
‘ሪዘርቭ ነዳጅ አትያዝ’ ከተባለ አሽከርካሪው ሞያሌ ድረስ በምን ሊቀሳቀስ ይችላል? ካለበት ቦታ እንኳ ነዳጅ ቀድቶ ሪዘርቭ ይዞ እንዳይደርስ እንዳይቀዳ ማዕቀብ ተጣለ። ካልደረስክም ትቀጣለህ ተባለ ህጉ አልተገናዘበም።
አንድ ቻግኒ ተመድቦ የነበረ አሽከርካሪ ከጅቡቲ ቻግኒ 6 ቀን አልፏል ተብሎ ተቀጥቷል። በነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ፊርማ እነዚህ ሰዎች እንዲቀጡ፤ ተሽከርካሪው ካለው ካምፓኒ 480 ሺሕ ብር እንዲቆረጥ ተደረገ።
በወጣው ነጋሪት ጋዜጣው መሠረት፥ ተደብቆ የተገኘ ሹፌር ይቀጣል ይባላል። ተሽከርካሪኮ ከመንገድ ውጪ አይሄድም ማደያ፣ ኬላ ላይ ሰልፍ ይዟል፤ ወይም በጸጥታው ምክንያት ከዚህ ሰዓት በኋላ አይኬድም በመባሉ ከተማላይ ቁሟል ማለት ነው።
ግን ተደብቆ የተገኘ አሽከርካሪ ከ300 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ብርና የሦስት አመት የእስራት ቅጣት ነጋሪት ጋዜጣ የተቀመጠ ዐዋጅ አለ። ይሄ አግባብ አይደለም ” ነው ያሉት።
(ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንለት ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምላሽ እንደሰጠ ይቀርባል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ምርጥ_ዕቃ
ከላይ በምስሉ የሚታዩትን እና በርካታ የቤት ዕቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸጥን ነው።
በቴሌግራምዎ ስለ ዕቃዎቻችን ተጨማሪ መረጃ ለማየት ይሄንን 👉 t.me/MerttEka 👈 ይጫኑ። ካሉበት ሆነው ይዘዙን፣ እንልክልዎታለን።
አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ ሱቅ 376
" የውጭ ምንዛሪ ጨረታው፣ የአቅርቦት እጥረቱን በዘላቂነት አይፈታውም፡፡ መፍትሔው ኢኮኖሚው ላይ መስራት ነው " - የቢዝነስ፣ ኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ይርጋ ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ እንደሚያወጣ ሰኞ ዕለት፣ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ባለፈው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የውጭ ምንዛሬ ግብይት በነፃ ገበያ እንዲመራ ከተወሰነ በኋላ፣ ብሔራዊ ባንክ ማክሰኞ ዕለት መጋቢት 23 ቀን 2017 ሶስተኛውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ማውጣቱን እና በዚህም 50 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ማቅረቡን አመልክቷል፡፡
ዓላማውም፣ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት የመፍጠር ግብን ለማሳካት እንደሆነ ጠቁሟል፡፡
በዚህ ጉዳይ ዙርያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሙያዊ አስተያየት የሰጡ አንድ ባለሙያ በበኩላቸው፣ ይህ አካሔድ የተለያዩ ጠቀሜታዎች ቢኖሩትም፣ የውጭ ምንዛሪ ግብይቱን ግን በዘላቂነት አያረጋጋውም ብለዋል፡፡
በውጭ ምንዛሪ ፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ መሆኑን የገለፁት ባለሙያው፣ መፍትሔው ያለው ውስን የውጭ ምንዛሪን በጨረታ ማቅረብ ላይ ሳይሆን፣ አጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ መስራት ነው ይላሉ፡፡
የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ማውጣት፣ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያ የሚቆጣጠርበትና በነፃ ገበያ ጣልቃ የሚገባበት አንዱ መንገድ ነው በማለት የገለፁት፣ የቢዝነስ፣ ኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ይርጋ ተስፋዬ፣ ይህ እርምጃ የውጭ ምንዛሪ ግብይቱን ለአጭር ጊዜ ለማረጋጋት መልካም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
(ሙሉ አስተያየታቸውን ከላይ ያንብቡ)
@tikvahethiopia
#Update
የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !
ባለቤቱን / የትዳር አጋሩን ድል ባለ ሰርግ ደግሶ አግብቷት ሲያበቃ ከቀናት በኋላ የገደላት ወንጀለኛ ግለሰብ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ።
የግድያ ወንጀሉ በወርሃ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም በውቕሮ ከተማ ነው የተፈፀመው።
ማቿ ሙሽሪት ሊድያ ኣለም እሁድ ተድራ ሓሙስ በባለቤቷና ሙሽራው በጭካኔ ተገድላለች።
ገዳዩ ወንጀለኛ ገድያውን ፍፅሞ ወድያውኑ ለፓሊስ እጅ መስጠቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።
ጉዳዩ ሲከታተል የቆየው የምስራቃዊ ዞን ማእከላይ ፍርድ ቤት ዛሬ መጋቢት 25/2017 ዓ.ም ከ6 ወር በኋላ ባዋለው ችሎት የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፈዋል።
ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ፤ ገዳይ ወንጀለኛው ከሟችዋ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት በመነሳት ጎሮሮዋ አንቆ በመግደል ፤ ከሞቷ በፊት ሁለት አይኖችዋ ጎልጉሎ በማውጣት እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ መገድሉ አረጋግጫለሁ ብሏል።
ግለሰቡ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 539 (1) ሀ መሰረት በእድሜ ልክ ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
⭐ የ0711 ቁጥሮዎን አሁኑኑ ለድርጅትዎ ይግዙ! 🎉
የ500 ብር የአየር ሰአት በመግዛት ነጻ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም ስልክ፣ 1000 ወደ ቴሌ መስመር ደቂቃ እና 6 ጊባ ዳታ አግኝተው እና የሚታወቁበትን ቁጥሮዎን በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኔትወርክ ላይ አስጠብቀው ይቀጥሉ! በተጨማሪም የተለያዩ የዳታ እና የድምጽ ጥቅል ስጦታዎችን ያግኙ!
#Own0711 #MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
“ የብድር ጣሪያው አለመነሳት በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ” - የፋይናንስ ባለሙያ
የብሔራዊ ባንክ፣ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ፣ ባለፈው ሳምንት ሁለተኛ ስብሰባውን በማካሔድ የተለያዩ ምክረ ሀሳቦችን ሰጥቷል፡፡
በኮሚቴው ውሳኔዎ ተፅዕኖ ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አንድ የፋይናንስ ባለሙያ፣ “ ውሳኔው በስራ ፈጠራና በገቢ ማመንጨት በኩል ዋጋ ያስከፍለናል ” ብለዋል፡፡
በቡና ባንክ ዋና የስትራቴጂ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሙሉነህ አያሌው በሰጡን የግል አስተያየት፣ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ መምጣቱን እንደገለፀ አውስተው፣ ነገር ግን፣ “ መልሶ ያንሰራራል ” የሚል ስጋት ስላለው፣ ቀድሞ የነበሩትን ገደቦች አላነሳም ይላሉ፡፡
ከኮሚቴው ውሳኔዎች አንዱ፣ ቀደም ሲል በባንኮች የብድር ዕድገት ላይ የተቀመጠው የ18 በመቶ ገደብ በነበረበት እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ ውሳኔ የባንኮችን የማበደር ዕድል ይቀንሳል ይላሉ፡፡
ይህን በምሳሌ ሲያስረዱም ፥ “ አንድ ባንክ ባለፈው ሰኔ ወር 2016 ላይ የብድር መጠኑ 100 ቢሊዮን ከደረሰ፣ የሚቀጥለው ሰኔ ላይ 2017 ላይ 118 ቢሊዮን ነው ማድረስ የሚችለው ማለት ነው፡፡ ለዛውም፣ የሰበሰበው ብድር ተቀንሶ፣ ያልሰበሰበው ብድር ተደምሮ ነው እዛ መድረስ አለበት የሚባለው፡፡ በዚህ ስሌት ባንኩ ባለፈው አመት የሰጠው ብድር ብቻ ሳይሆን ከተመሰረተ ጀምሮ የሰጠው ብድርም ሊሆን ይችላል፡፡ እስካልተሰበሰበ ድረስ በብድርነት ይያዛል፡፡ ባንኩ ያልሰበሰበው ነባር ብድርና የሰጠው አዲስ ብድር ተደምሮ ነው የሚሰላው፡፡ በብድር ወለዱ ብቻም ጣሪያው ላይ ሊደርስ ይችላል፡፡ አንድ ባንክ፣ ባለፈው አመት 100 ቢሊዮን ብድር ከነበረውና የዚህ ወለዱ 18 ከመቶ ከሆነ፣ በዚህ አመት ምንም ብድር ሳይሰጥ የአምናው ብድር ብቻውን 118 ቢሊዮን ይሆናል፡፡ ሳያበድርም ሳይሰበስብም ጣሪያውን ሊደርስበት ይችላል ” ብለዋል።
አቶ ሙሉነህ አያሌው የዚህ ተፅዕኖው ምን እንደሆነ እንዲህ ሲሉ አስረድተዋል።
“ ይህ ውሳኔ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ያቀዘቅዘዋል፡፡ በስራ እድል ፈጠራ እና በገቢ ማመንጨት በኩል ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ የብድር አቅርቦት መኖር፣ ሰዎች ተበድረው ስራ እንዲሰሩና የስራ እድል እንዲፈጥሩ ያበረታታል፡፡ የብድር አቅርቦት ከሌለ ኢንቨስትመንት ይዳከማል፣ የስራ ዕድል አይኖርም፣ ሰዎች ገቢ አያመነጩም ማለት ነው፡፡ ያ ባለመሆኑ ይህንን ዋጋ ነው እየከፈልን ነው ያለነው፡፡ ”
የብድር አቅርቦቱ ውስን ስለሆነ፣ ባንኮች የብድር አሰጣጥ ላይ ጠበቅ ያሉ መስፈርቶችን ይጠቀማሉ ብለዋል፣ ባለሙያው፡፡
እሳቸው እንደሚሉት፣ አንድ እቃ ከገበያ ሲጠፋ፣ አለያም አቅርቦቱ ሲቀንስ ዋጋው እንደሚወደደው፣ የባንኮች ብድርም በተመሳሳይ አቅርቦቱ ሲቀንስ ዋጋው (ወለዱ) ይወደዳል፡፡ አቶ ሙሉነህ ይህን እንዲህ በማለት አብራርተዋል፡፡
“ ገበያው ውስጥ የሚኖረው ብድር ትንሽ ነው፣ የተበዳሪ ብዛት ደግሞ ብዙ ነው፡፡ ስለዚህ ባንኮች ያለቻቸውን ትንሽ የብድር ገንዘብ ለጨረታ ያቀርቡዋታል ማለት ነው፡፡ ያለቻቸውን ውስን ብድር ለመስጠት ጠበቅ ያለ መመዘኛ ያስቀምጣሉ፡፡
አንደኛው መመዘኛ የብድር ዋጋ (ወለዱን) ማስወደድ ነው፡፡ ሌላኛው መስፈርት ደግሞ “አስተማማኝ ተበዳሪ ” የሚል ይሆናል፡፡ ብድራቸውን በእርግጠኝነት ይመልሳሉ ለሚባሉ፣ ለተመረጡ ተበዳሪዎች ብቻ ያቀርባሉ፡፡ ይህ ማለት የስጋት መጠኑ ወደ ዜሮ ለተጠጋ ተበዳሪ ነው፡፡ ትንሽ ስጋት ላለበት ተበዳሪ አይሰጡም፡፡ ስጋቱን የምትቀንሰው ለብድር መያዣ በሚቀርበው ዋስትና (ለምሳሌ ቤት ወይም መኪና) ነው፡፡
የቤትና የመኪና ዋስትና ይዘው ከሚመጡ ተበዳሪዎች መካከል፣ የቤት ዋስትና የሚያቀርበው ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡ መሬት ላይ ያለ ነገር ወድቆ አይወድቅም ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ መኪና ዋጋው እየቀነሰ ስለሚሔድና አደጋዎችም ስለሚኖሩ ከቤት በላይ ተመራጭ ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ ከዚህ ውጪ ደግሞ፣ የንግድ ፍላጎታቸውን ያያሉ፡፡
ለምሳሌ ዳያስፖራ ለሆኑና በኤክስፖርት ንግድ ላይ ለተሰማሩ ተበዳሪዎች በውጭ ምንዛሪ ስለሚከፍሉ ቅድሚያ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ብድሬን በብር እከፍላለኹ የሚለው ተመራጭ አይሆንም፡፡ ባንኮቹ ያላቸው የብድር ገንዘብ ውስን ስለሆነ፣ ከንግድ አንፃር የትኛው ያዋጣናል ይላሉ፣ ጠበቅ ያለ የብድር መመዘኛም ያወጣሉ፡፡ ”
በዚህ ኹኔታ ተጎጂ የሚሆኑት ዘርፎች የትኞቹ ናቸው ?
“ የአምራቹ ዘርፍ የትርፍ ህዳጉ ጠባብ ነው፡፡ እንደ ግብርና እና ማኑፋክቸሪንግ የመሰሉ ዘርፎች በዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ብዙ ኢንቨስትመንት ስለማይስቡ ይጎዳሉ፡፡ ይህን ውስን የብድር አቅርቦትን የመሳብ ዕድል አይኖራቸውም፡፡ ሰፊ የትርፍ ህዳግ ያላቸው ቢዝነሶች ግን አሁንም አዋጭ ስለሆኑ ብድር ሊያገኙ ይችላሉ፡፡”
መፍትሔውስ ምንድነው ?
“ የብድር ጣሪያው ገንዘብ እንዳይፈጠር አድርጓል፡፡ ብድር ተሰጥቶ ወለድ ካልተሰበሰበ ገንዘብ አይፈጠርም፣ ባንኮች ተቀማጭ አያገኙም፡፡ የብድር ጣሪያውን ማንሳት ብቻም መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡፡ የብድር ጣሪያው ቢነሳም ባንኮች በቂ ብድር ያቀርባሉ ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት አለባቸው፡፡ ለእጥረቱ ትልቁ መነሻ የሆነው የቁጠባ አቅም መዳከሙ ነው፡፡ ጥቅል የሀገር ውስጥ ቁጠባ በተከታታይ አመታት እየቀነሰ ነው የመጣው፣ ገንዘብ እየተቆጠበ አይደለም ማለት ነው፡፡ ሌሎች በርካታ ምክንያቶችንም መጥቀስ ቢቻልም፣ የቁጠባ መዳከም የባንኮችን የጥሬ ገንዘብ ክምችት አቅም አዳክሞታል፡፡ ይህ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ወደ ባንኮች የሚመጣው ተቀማጭ ገንዘብ የቁጠባ ውጤት ነው፡፡ ይህ ካልተስተካከለ ችግር ነው፡፡”
ብሔራዊ ባንክ የባንክ ለባንክ የገንዘብ ግብይት በመፍቀድና፣ ንግድ ባንኮች ከብሔራዊ ባንክ የአጭር ጊዜ ብድር እንዲወስዱ በመፍቀድ፣ ያለባቸውን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት እየሰራ ቢሆን፣ ይህ ግን ዘላቂ መፍትሔ አይሆንም ብለዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
ግዛት
አዲሱን ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ድራማ #ግዛት ን የመጀመሪያ ክፍሎች ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ!
⬇️
https://bit.ly/3FHxdhk
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #AbolTV
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " መደበኛ ያልሆነን የጎዳና ላይ ንግድ ስርዓት ለማስያዝ ይረዳል " ያለውን ደንብ አውጥቷል።
የደንቡን መውጣት ተከትሎ ንግዱ የሚካሄድበት ሰዓት በ5 ፈረቃ ተከፋፍሎ ይፋ ሆኗል።
በዚሁ መሰረት ፦
➡️ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 1:00 ሰዓት የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የአልባሳት እና መጫሚያዎች ንግድ እንዲካሄድ፤
➡️ ከንጋቱ 1:00 ሰአት እስከ ረፋዱ 3:00 ሰዓት እንደ ብስኩት ፣ ሻይ ፣ ቡና ፣ የታሸገ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች ያሉ እና ለቁርስ የሚሆኑ ቀላል ያሉ ምግቦች ንግድ እንዲካሄድ ፤ የጫማ ፅዳት ወይም ሊስትሮ አገልግሎት በዚሁ ሰዓት እንዲካሄድ፤
➡️ ከረፋዱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 የመፅሃፍት ፣ መፅሄቶች እና ጋዜጦች ንግድ እንዲካሄድ፤
➡️ ከቀኑ 6:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ቀላል ምግቦች በመባል የሚታወቁት እንደ ኬክ ፤ ብስኩት ፤ ሻይ ፤ ቡና ፤ የታሸገ ውሃና ለስላሳ መጠጦች ንግድ እንዲካሄድ፤
➡️ ከአመሻሽ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ተኩል የተጠበሱ ምግቦች ፣ ጁስ ፣ ብስኩት ፣ ኬክ ፣ ሻይ ፣ ቡና ፣ የታሸገ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች እንዲሁም አልባሳት እና መጫሚያዎች ፣ ቀላል የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ፣ የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲኮስች ንግድ እንዲካሄድ የከተማ አስተዳደሩ መርሃ ግብር አውጥቷል።
ንግዱ የሚካሄድባቸው ቦታዎች #ወደፊት እንደሚለዩና ይፋ እንደሚደረጉ የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።
መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ " ኮንትሮባድን ያበረታታል፤ ለትራፊክ መጨናነቅ እና አደጋም መንስኤ ይሆናል እንዲሁም በህጋዊ ንግዱ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል " በሚል በከተማው አስታዳደር ቁጥጥር እንዲደረግበት ሲሞከር እንደነበር ይታወሳል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ነው።
@tikvahethiopia
“ ሹፌር ትጥቅ የማይለብስ ፤ ከቀበቶ ውጪ የማይታጠቅ፣ የሚያረካ ክፍያ ሳይከፈለው በየዋህነት ለህዝቡ የሚያገለግል ነው ፤ ሊገደል ፣ ሊሰቃይ አገባውም !! ” - የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር
በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት አካባቢ ሰሞኑን የከባድ መኪና ሹፌሮች በታጣቂዎች ድብደባና እገታ እንደተፈጸመባቸው፣ በቦቴዎች የጫኑት ነዳጅም በመንገድ ሲፈስ የሚያሳይ ቪዲዮ በማኀበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ተስተውሏል።
ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበርም፣ በወቅቱ ነዳጁ እንፈሰሰ ገልጾ፤ “ አንድ ሹፌር በጥይት ተመትቷል፤ ሁለት ሾፌሮች ታግተው ተወስደዋል ” ብሏል።
አሽከርከርካሪዎቹ ከጂቡቲ ነዳጅ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ ስለጉዳዩ የጠየቅነው የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ምላሽ ያለውን ማብራሪያ ሰጥቷል።
ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?
“ በማንኛውም መልኩ በየትኛውም ወገን ቢሆን ለህዝብ የሚጠቅምን ሀብት ማባከን ተገቢ ነው ብሎ አያምንም ማኀበሩ።
ነዳጁ ስለፈሰሰ ማነው ተጠቃሚው ? በከፍተኛ ሁኔታ የሚቸገረው የዛ አካባቢ ህብረተሰብ ነው። የዛ አካባቢ ህብረተሰብ ሲቸገር ደግሞ የነዳጅ ካምፓኒው፤ የመኪና ባለቤት፤ ሸቀጣሸቀጥ ነጋዴዎች ይቸገራሉ።
ይሄ ድርጊት ዘርፈ ብዙ ችግር ያለበት ነው። ማኀበራችን እንደዚህ አይነት ጥፋቶችን ሙሉ ለሙሉ ያወግዛል።
ነዳጅ፤ ማዳበሪያ ጭኖ ስላጓጓዘ ነው ? አሽከርካሪ ምን ስላደረገ ነው የሚመታው ? በዚህ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ አካላት አሽከርካሪዎቻችንን አትግደሉብን።
አሽከርካሪዎች የሚያሳድጓቸው ልጆች፤ ሚጠሯቸው ወላጆች አሏቸው ይሄንን ሁሉ ነው የምታሳጡት። ስለዚህ እበካችሁ አትግደሉን።
በሰሞኑ በጋይንቱ ክስተትም የተመቱና የቆሰሉ ልጆች አሉ የሚል መረጃ ደርሶናል።
ሾፌር ለሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው። ለኢትዮጵያ ወደብ ሆኖ የሚያገለግል የውጩን ወደ ሀገር የሚያመጣ፣ የውስጡን ወደ ህብረተሰቡ የሚያስደርስ አሽከርካሪ ሊገገደል ቀርቶ እንክብካቤ ሊደረግለት ነው የሚገባው።
ትጥቅ የማይለብስ፤ ከቀበቶ ውጪ የማይታጠቅ፣ በየዋህነት ለህዝቡ የሚያገለግል፤ የሚያረካ ክፍያ ሳይከፈለው እንደ አገሪቱ ሁኔታ በጣም በችግር ላይ ያለ አሽከርካሪ በማንኛውም አካል ሊገደል አይገባውም ” ብሏል።
የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን፣ ስለአሽከርካሪዎቹ ሆነ “በጥይት ተመትቶ ባከነ” ስለተባለው ነዳጅ ማብራሪያ ከተሰጠ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" አሁንም በርካታ ሰዎች ፍል ውሃው ከሚገኝበት ስፍራ ወደ ሆስፒታሉ ታመው እየገቡ ነው " - የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
በጃዊ ወረዳ " ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራ ፍል ውሃ በተከሰተ በሽታ የሰው ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
በአማራ ክልል፤ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 22/2017 " ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራ ፍል ውሃ ፀበል ተከስቷል በተባለ በሽታ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስታውቋል።
የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስለሺ ወለሊ በሽታው ኮሌራ መሆኑና አለመሆኑን ለማጣራት ለአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ናሙና መላኩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
በተመሳሳይ 50 ሰዎች በበሽታው ተይዘው ሆስፒታል መግባታቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ ወደ ሆስፒታል የመጡት ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
አሁንም በርካታ ሰዎች ፍል ውሃው ከሚገኝበት ስፍራ ወደ ሆስፒታሉ ታመው እየገቡ መሆኑን አንስተዋል።
ሁለቱ የሞቱት ሰዎችም ከፍል ውሃው ታመው ወደ ሆስፒታል እየመጡ እያለ ሆስፒታሉ በር ላይ ህክምና ሳያገኙ መሞታቸውን አክለዋል።
በሽታው ኮሌራ መሆኑን ለማረጋገጥ ናሙና ወደ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።
እንደ አቶ ስለሺ ገለፃ ከታመሙት ውስጥ አንዳንዶቹ ከባህዳር አንዳሳ ፀበል እና ከወንቅሸት ገዳም ፀበል ቆይተው የመጡ እንደነበር መረጃ የተገኘ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተመሳሳይ ፤ በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ እና በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በኮሌራ ወረርሽኝ በርካታ ሰዎች እየተያዙ መሆኑን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጹን አሚኮ ዘግቧል።
ኢንስቲትዩቱ ፤ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ የሚደርሰው የበሽተኛ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በተለይ በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በቀን ውስጥ በርካታ ሰዎች በበሽታው እየተጠቁ መሆኑን ገልጿል።
ኮሌራ ምንድነው ?
ኮሌራ አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት በማስከተል ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው።
የኮሌራ የተበከለ ውኃ እና ምግብን በመጠቀም የሚከሰት ሲሆን ሰዎች በብዛት በሚሠባሠቡባቸው ቦታዎች በተለይም ንጹህ የመጠጥ ውኃ እና ንጹህ የመጸዳጃ ቦታ በሌለበት አካባቢ በቀላሉ ይተላለፋል።
በሽታውን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል ?
° የግል እና የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ፣
° ንጹህ ውኃን መጠቀም፣
° ምግብን አብስሎ መመገብ
° ምግብ ከማብሰል በፊት፣ ሕጻናትን ካጸዳዱ በኋላ እና ከህመምተኛ ጋር ንክኪ ከተደረገ በኋላ እጅን በሳሙና መታጠብ አስፈላጊ ነው።
ውኃን በኬሚካል አክሞ እና አፍልቶ መጠቀም የሚገባ ሲሆን የበሽታው ምልክቶች ከታዩ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያስፈልጋል።
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar
#AMC
ፎቶ፦ ጃዊ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopia
#Tigray
" ሦስት ሳምንት ሳይሞላው የሦስት ወር ደመወዝ በሃሰት ማህተም በመጠቀም ከድርጅቱ የብር ካዝና አለአግባብ መመዝበሩ አረጋግጫለሁ " - ጋዜጠኛ ሓለፎም ንርአ
➡️ " ጉዳዩ በህግ የተያዘ ነው " - አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 አከባቢ በ136ኛው የንጉስ ነገስት ሃፀይ ዮሃንስ መታሰብያ ዝግጅት ተገኝተው መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በዚያው ወደ አሉላ አባነጋ የአውሮፕላን ማረፍያ በመሄድ ወደ አዲስ አበባ ከተጓዙ 22 ቀናት ተቆጥረዋል።
አዲስ አበባ ሆነው የፕሬዜዳንትነት መጠሪያቸው ቢጠቀሙም ላለፉት 22 ቀናት መቐለ በሚገኘው ቢሯቸው ገብተው የከወኑት አንዳች የህዝብ አገልግሎት የለም።
ፕሬዜዳንቱ " ለስራ " በሚል ምክንያት ከመቐለ ትግራይ ከወጡ በኋላ በክልሉ ያሉት ሚድያዎች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ?
የዚህ መረጃ ዋና የምልከታና የትኩረት ነጥብ ይኸው ጉዳይ ነው።
ባለፉት ሦስት ሳምንታት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ከነበሩት ሦስት ሚድያዎች ፦
- የትግራይ ቴሌቪዥንና ሬድዮ
- የድምፂ ወያነ ቴሌቪዥንናሬድዮ
- 104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ለውጦች ተከስተዋል።
ከለውጦቹ አንዱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ለሚድያዎች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሁም መጋቢት 22 በግላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያሰራጩት፣ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም በእሳቸው ስም የሚመራ ህወሓት ያወጣውን መግለጫ በሦስቱ ሚድያዎች አልተሰናገደም።
በድምፂ ወያነ ፣ ትግራይ ቴሌቪዥንና ሬድዮ በግልፅ የተደረገ የአመራር ለውጥ ባይኖርም የትግራይ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ ተሻለ በቀለ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ከመቐለ መወጣታቸውን ተከትለው ወጥተው ዛሬ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም ወደ ቢሯቸው መመለሳቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ለማረጋገጥ ችሏል።
ለሦስት ሳምንታት ያህል ከመቐለ የመውጣታቸው ምክንያት በትግራይ ከተፈጠረው ቀውስ ተያይዥነት ይኑረው አይኑረው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ አልቻለም።
በቀድሞ ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሚድያ ፍቃድ አግኝቶ በመቐለ ከተማ አስተዳደር ስር እንደሚተዳደር የሚነገርለት 104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ደግሞ " እኔ ነኝ ስራ አስኪያጅ " የሚል ክርክር ከተነሳበት መቆየቱ ይታወቃል።
የፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ከመቐለ ከተማ መውጣት ተከትሎ " በመቐለ ከተማ አስተዳደር ተሹሚያለሁ " በሚል የይገባኛል ጥያቄ በሚድያዎች ጭምር በግልፅ ሲያቀርቡ የቆዩት ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ የቆዩትን የኤፍ ኤም ጣብያው ስራ አስኪያጅ ሓለፎም ንርአ በመግፋት ጣቢያውን ተቆጣጥረውታል።
" አካሄዱ ህገ-ወጥ ነው " በማለት የታቀወሙትና " አሁንም እኔ ነኝ ህጋዊ ስራ አስኪያጅ " በማለት የሚሞጉቱት ጋዜጠኛ ሓለፎም ንርአ የኤፍ ኤም ጣብያው የባንክ ሂሳብ እንዲዘጋ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ መስራት ቤት የድርጅቱን ማህተም በመጠቀም ፅፈዋል።
መጋቢት 16/2017 ዓ.ም በፃፉት " የ ይታገድልኝ " ጥያቄ እሳቸው የሬድዮ ጣብያው ህጋዊ ስራ አስኪያጅ መሆናቸው በመጥቀስ የሚድያው ፈራሚዎች እንዳይቀየሩ በማሳሰብ ከእውቅናቸው ውጪ ማንኛውም የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ይታገድልኝ ብለዋል።
ስራ አስኪያጁ የእገዳ ደብዳቤ ከመፃፉ በኋላ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባጋሩት ሰፊ ሃተታ ፤ ሬድዮ ጣብያውን " በህገ-ወጥ መንገድ ተቆጣጥሮታል " ሲሉ የከሰሱት ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ " ሦስት ሳምንት ሳይሞላው የሦስት ወር ደመወዝ በሃሰት ማህተም በመጠቀም ከድርጅቱ የብር ካዝና አለአግባብ መመዝበሩ አረጋግጫለሁ " ብለዋል። የብር መጠኑ ግን በይፋ አላስቀመጡም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ስለ ቀረበባቸው ክስ ማብራርያ እንዲሰጡ ወደ አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ በተደጋጋሚ ደውሎ ነበር።
" ጉዳዩ በህግ የተያዘ ነው " ከሚል አጭር ምላሽ ውጪ ዘርዘር ያለ በቂ ማብራርያ ሊሰጡ አልፈገሉም።
በአጠቃላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ከመቐለ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ በክልሉ በሚገኙ ሚዲያዎች ግልጽ የሆኑ ለውጦች ታይተዋል።
በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ትግራይ ክልልን ለመምራት የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ቆይታው መጋቢት 5/2017 አብቅቷል። ቆይታው ለአንድ አመት እንዲራዘም የሚፈቅድ አዋጅም ፀድቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia