tikvahethiopia | Неотсортированное

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1527057

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Подписаться на канал

TIKVAH-ETHIOPIA

#ምርጥ_ዕቃ

ከላይ በምስሉ የሚታዩትን እና በርካታ የቤት ዕቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸጥን ነው።

በቴሌግራምዎ ስለ ዕቃዎቻችን ተጨማሪ መረጃ ለማየት ይሄንን 👉 t.me/MerttEka 👈 ይጫኑ። ካሉበት ሆነው ይዘዙን፣ እንልክልዎታለን።

አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ ሱቅ 376

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

" የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው ማግኘት ይቻለል " - የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን

ከመጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ እንዲሰጥ መፈቀዱን የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ በመንጃ ፈቃዱ ላይ ወደ ተገለጸው እና ፋይሉ ወዳለበት ክፍለ ከተማ (የመታወቂያ አድራሻ) የሚገኝ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ቢሮ መሄድ ግድ ይል ነበር።

ከነገ በኃላ ግን በየትኛውም አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ መንጃ ፈቃድ ማሳደስ ይቻላል ተብሏል።

ተገልጋዮች በሚቀርባቸው ቅርንጫፍ ፋይላቸው ያለበት ቅርንጫፍ ሳይጠየቅ የጤና ምርመራ ሰርተፍኬትን በመያዝ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት እንዲያገኙ መወሰኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ተመላላሽ የሕክምና ቀጠሮ ቢኖረንም ሆስፒታሉ ዝግ ስለሆነ አገልግልት ማግኘት አልቻልንም " - ተገልጋዮች

➡️ " ከ6 እስከ 9 ወራት ታግሰን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ከአቅማችን በላይ ሆኖ ስራ አቁመናል" - የጤና ባለሙያዎች

🔴 " የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " - የዞን አስተዳዳሪ

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ከ6 እስከ 8 ወራት የሰሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመክፈሉ ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ በመግለፅ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸዉን አሰምተዉ ነበር።

በወቅቱ የዞኑ አስተዳዳሪ ቅሬታዉ ተገቢ መሆኑን በመግለፅ " ከክልል ብድር ጠይቀናል በጥቂት ቀናት ስለሚፈፀም የ5 ወራት ክፍያ በአንድ ላይ በመፈፀምና ቀሪዉን በየወሩ እንዲከፈላቸዉ ይደረጋል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዉ ነበር።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን ዳግም ያደረሱት የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያዎች " ከቅሬታዉ ምላሽ በኋላ ተጨማሪ አንድ ወር ታግሰን ለሙያ ቃል ኪዳናችንና ሕብረተሰቡን ማገልገል ስላለብን በችግሮች ዉስጥ አልፈን እየሰራን ብንቆይም አሁን ላይ ከአቅማችን በላይ በመሆኑ ስራ አቁመናል " ሲሉ ገልፀዋል።

" ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ካለመፈፀሙም ባሻገር አመራሮች ነገሮች እንዲመቻቹላችሁ ' የብልፅግና ፓርቲ ሕንፃ ግንባታ መዋጮ የአንድ ወር ደመወዝ አዋጡ ' ብለዉን ሁሉም ባልተስማማበት ከመደበኛ ደመወዝ እየቆረጡ ነዉ ፤ በዚህም ለዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀዉሶች ተዳርገናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ዶክተር ሆነህ ' ቸገረኝ አበድረኝ ' ማለት ያሳቅቃል ይህ በሞራልም እየጎዳን ነዉ " ሲሉ ስሜታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያጋሩ ዶክተሮች ተናግረዋል።

እንዲሁ ሌላ የጤና ባለሙያ " ለህክምና የመጣች አንዲት ታካሚ ዱቤ ልትጠይቀኝ መስሎኝ ተደብቅያለሁ " ሲል እያሳለፉ ስላለው ህይወት ተናግረዋል።

ተገልጋዮች ምን አሉ ?

" በሀንጣጤ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ስለነበረን ግን ወደ ሆስፒታሉ  ቅዳሜ ጠዋት ስንሄድ ግቢዉ ዝግ ነበር፤ ጥበቃዉ የጤና ባለሙያዎች አለመግባታቸውን ነገረን " ሲሉ አንድ የሆስፒታሉ ተገልጋይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እኚሁ ተገልጋይ አማራጭ አጥተዉ በስልክ ከሕክምና ባለሙያዎች ባገኙት ምክር ከግል የጤና ተቋማት መድሐኒት ለመግዛት መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ሳምንቱን በስራ ላይ አሳልፈዉ ለልጃቸዉ ሕክምና ቅዳሜ ወደ ሆስፒታሉ ቢመጡም ሐኪሞች ባለመኖራቸው ለሰዓታት ጠብቀዉ መዉጣታቸውን የገለፁት ሌላኛዉ የሀንጣጤ ከተማ ነዋሪ ከእሳቸዉም ዉጪ ሌሎችም አገልግሎት ለማግኘት መጥተዉ ሲያማርሩ ማየታቸዉንና ችግሩ ከጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጋር የተያያዘ መሆኑን መስማታቸውን ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ ለአከባቢዉ ሕብረተሰብ ከሚሰጠዉ አገልግሎት አንፃር የሚመለከታቸዉ አካላት ፈጣን መፍትሔ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

የዞን አስተዳዳሪ ምን አሉ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መንግስቱ ማቴዎስን ለምን በተገባላቸዉ ቃል መሰረት ክፍያው አልተፈፀመላቸዉ ሲል ጠይቋል ? አቶ መንግስቱ በምላሻቸው " አሁን ጥረት እያደረግን ነዉ፤ ከላይ በጀት ሲገኝ ነዉ ችግሩ የሚፈታዉ " ያሉ ሲሆን " ልጆቹም ስራ ለመስራትም ፈቃደኛ አይደሉም፣ መስራት የሚፈልግ ይቀጥላል ያልተመቸዉ ሊለቅ ይችላል " ብለዋል።

" ኖሪማሊ ጉዳዩ እኔን የሚመለከተኝ አይደለም፤ ወረዳዉ ነዉ ባለቤቱ " የሚሉት የዞኑ አስተዳዳሪ " ሠራተኞቹ እየሄዱበት ያለው አካሄድ ተገቢ አይደለም፤ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የሆስፒታሉ ሰራተኞች የትርፍ ሰዓት ስራ ብቻ ማቆማቸዉንና በተደጋጋሚ ቃል እየተገባ ስለማይፈፀምላቸዉ ስራ ማቆማቸዉን ገልፀዉልናል ይህን ማድረጋቸው ያስጠይቃቸዋል ወይ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳላቸዉ ጥያቄ  " መደበኛ ስራ ነዉ እያቆሙ ያሉት፣ ከደሞዝ መቁረጥ እስከ ማሰናበት እርምጃ ይወሰድባቸዋል " ብለዋል።

" በአንፃሩ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆም መብታቸዉ ነዉ ሲሉም " ተደምጠዋል።

ሰራተኞች ስራ ከማቆማቸዉ በፊት በጽሑፍ ለወረዳ ፣ ለዞኑና ለክልሉም ጤና ቢሮ ጭምር ቅሬታቸዉን ማቅረባቸውን ገልፀዉልናል ፤ በሆስፒታሉ የጤና ክትትል የበራቸዉና ለሕክምናም መጥተዉ በዕረፍት ቀናት አገልግሎት ባለማግኘታቸዉ የተቸገሩ ተገልጋዮችም ቅሬታቸዉን አሰምተዉናል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳላቸዉ ጥያቄ አቶ መንግስቱ " በአካል ካልመጣችሁ ከዚህ የበለጠ መረጃ ልሰጣችሁ አልችልም ! " በማለት አቋርጠዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ በድጋሚ አልተሳካም፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ስንችል የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ

የታመሙብን፣ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የማይችሉ ልጆች በመካከላችን አሉ ” - በማይናማር የኢትዮጵያውያን አስተባባሪ

በታጋቾች ተገደው ሲሰሩት ከነበረው ፋታ የማይሰጥ አስከፊ ስራ ወጥተው በማይናማር በተለያዩ ካምፕች በሚሊታሪ ቁጥጥር ስር ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግስት በአፋጣኝ እንዲደርስላቸው ዛሬም በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተማጽነዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ዛሬስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ?

አንድ ወጣት ፦

“ ለመንግስት የምናቀርበው ጥያቄ አለ። ትኬት መሸፈን የማይችል፤ እንደ ዜጋ የማይቆጥረን፤  ‘አልፈልጋችሁም’ የሚለንም ከሆነ፣ በኤንጂኦ በኩል እንኳ ወደ ሌላ ሀገር እንድንሻገር ግልጽ የሆነ ምላሽ እንፈልጋለን። 

ወይ ፕሌን ልኮ ያስወጣን ካልሆነ ‘አልፈልጋችሁም፤ ዜጎቼ አይደላችሁም’ ብሎ ይካደን አማራጫችንን እንውሰድ፤ ይህን እንዲያደርግልን እንፈልጋለን ” ብሏል።

ሌላኛው ወጣት በሰጠን ቃል ፦

“ ባለንበት ቦታ ሁኔታዎች እየከበዱ ነው። ሲያሰሩን የነበረውን ሥራ ለቀን ከወጣን ከወር በላይ ሆነን። በጭንቀትና ድብርት ውስጥ ነን። 

መንግስት እንደ ዜጋ የማይቆጥረን እና ‘ወደ ሀገር እንዲገቡ አልፈልግም’ የሚለን ከሆነ በግልጽ ይንገረን። በመንግስት በኩል ስለኛ እንዲህ ተብሏል እየተባለ አይደለም ” ነው ያለው።

ሌላኛው ወጣት በበኩሉ ፦

“ ሥራውን አቁመን ሌላ ካምፕ ከገባን 4ዐ ቀናት አልፎናል። እስካሁን ግን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳችንን በተመለከተ ምንም ነገር የለም። 

አብረውን ከነበሩ የ29 ሀገራት መካከል አብዛኛዎቹ ለዜጎቻቸው ያላቸውን ክብር በመግለጽ ወስወዋቸል። የቀረነው አብዛኞቻችን ኢትዮጵያውያን ነን።

መንግስት ‘አልፈልግም፤ ዜጎቼ አይደሉም’ ብሎ የሚክደን ከሆነ በኤንጂኦም ቢሆን ወደ ሌላ ሀገር ከዚህ መውጣት እንፈልጋለን። በግልጽ መንግስት ይጠየቅልን” ብሏል።

ሌሎች ሁለት ወጣቶች ደግሞ ፦

“ የኛን ባህልና ሃይማኖት የማይቀበለውን ምግብ ስንሰጥ ለመጣል እንገደዳለን። ለምሳሌ አሳማ ከሩዝ፤ የዶሮ ጣት ሳር ከሚመስል አትክልት ጋር ስንሰጥ ጥለን በጦም አንጀታችን እንውላለን።

ውሃ በጃር ነው የሚመጣው፤ የቀደመ ይቀዳል፤ ያልቀደመ በጥም አፉ ይደርቃል። የምግብና የውሃ እጥረት አለ። BDF ሚሊታሪ ካምፕ ውስጥ ነን። ብዛታችን 260 ኢትዮጵያውያን ነው።

እኛ ደግሞ ያለነው DKBA የሚባለው ካምፕ ውስጥ ነን። ብዛታችን 255 ኢትዮጵያዊ ነን። የምንመገበው በቀን አንድ ጊዜ ነው፤ በቂ የመጠጥ ውሃም አናገኝም። 

የምናድረው ካርቶን አንጥፈን ወለል ላይ ነው። በዚህ ሁኔታ ከአንድ ወር በላይ ቆየን፤ ምንም አዲስ ነገር አልሰማንም። መጀመሪያ ከ21 ሀገራት ዜጎች በላይ ነበርን አሁን ሁሉም ሀገሮች እያስወጡ የ5 ሀገር ዜጎች ብቻ ቀርተናል። እነሱም በቅርቡ እንወጣለን ነው የሚሉት። 

እኛ ግን ምንም መልስ አላገኘንም። በቆየን ቁጥር ምን እንደሚያጋጥመን አናውቅም " ሲሉ ያሉበትን ሁኔታና ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በሌሎች ካምፓች የሚገኙ ከ480 በላይ ዜጎችም ተመሳሳይ ችግር እየገጠማቸው መሆኑ ተመልክቷል።

በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያውያን አንድ አስተባባሪ ምን አለ ?

“ ያለው አጠቃላይ ሁኔታ በጣም አስጨናቂ እየሆነ መጣና ብዙዎቹ እየተጨነቁብን ተቸግረናል። የወላጅ ኮሚቴ በጣረው ልክ ችግራችን ሊቀረፍ አልቻለም። 

ጃፓን ኤምባሲ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ያለብንን ከ600 በላይ ልጆች ስም ዝርዝር ልኮ አፕሩቭ ተደርጎ ከተመለሰ በኋላ እንደገና ወደ ሚሊታሪ ደግሞ፥ ወደ ታይላይድና ኢትዮጵያ እንድንጓዝ መፃፍ ነበረበት። ያንን አላደረገም።

መንግስት ሂደቱን እያስኬደ ቢሆንም መጓተትና መዘግዬት አለ። በዚያ ምክንያት አራት የተመሙብን፤ ራሳቸውን ችለው የማይንቀሳቀሱ ልጆች በመካከላችን አሉ።

ሰርጀሪ የተሰሩ አሉ። እዚህ ደግሞ ሰርጀሪ መሰራት በጣም ከባድ ነው። ሀኪሞቹ ታማኝ አይደሉም። ሰርጀሪ የተሰሩ ልጆች ብዙ ችግር ደርሶባቸዋል። 

ሁሉም ሰው ኪሱ ባዶ ነው። የሚቀርበው ምግብም ለመመገብ የማይሆን (ከእኛ የአመጋገብ ባህል ጋር አብሮ የማይሄድ) በመሆኑ ለመመገብ ተቸግረናል። ምግብ መግዛት፣ የታመሙትን ማሳከም አልተቻለም ” ብሏል።

ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በማይናማር ስላሉ ዜጎች ጉዳይ ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ አልተገኘም። ተቋሙ አሁንም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ እናስተናግዳለን።

(ጉዳዩንም እስከ መጨረሻው እንከታተለዋለን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#HoPR : ዛሬ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚያሻሽለው አዋጅ ፀድቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።

አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 የሚያሻሽል ሲሆን፤ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብለጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡

አዋጁ የክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ስልጣን፤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።

አዋጁ የፌደራል መንግስት በክልሎች የሚያቋቁመውን ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ዘመን ለሁለት ጊዜ የማራዘም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።

የአፈ ጉባኤው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተቀባይነት ካላገኘ፤ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቋቋመበት ክልል " በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ምርጫ እንዲደረግ " ያስገድዳል።

ይህ አዋጅ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ስርአት ለመደንገግ በ1995 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ያሻሻለ ነው።

#HoPR #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🎁🎬 በቴሌቲቪ ምርጥ ሀገርኛ ፊልሞችን ይመልከቱ፤ እስከ 100 ሺህ ብር ይሸለሙ!!

ፊልሞቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ በመግዛት በየሳምንቱ እስከ 100ሺህ ብር፣ ስማርት ስልክ እንዲሁም ሌሎች ሽልማቶችን ያግኙ!

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ላይ ወይም በመተግበሪያ teletv.et/download ያገኙታል፡፡

ለበለጠ መረጃ ወደ 9801 ይደውሉ!


#teletv
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት  ፤  " በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ የተደረገው የሂጃብ መልበስ ክልከላ እስከ አሁን አልተነሳም " ሲል አሳውቋል።

ይህን ያሳወቀው ትላንት በመቐለ በተካሄደው የዒድ ሶላት ወቅት ነው።

ምክር ቤቱ ዋና ፀሓፊ ሀጂ መሀመድ ካሕሳይ " የሂጃብ መልበስ ክልከላ እስከ አሁን አልተነሳም " ያሉ ሲሆን " አሁንም ጥያቄያችን እንዲመለስ ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

የሃይማኖት መቻቻልና መከባበር የአንድ አገርና ህዝብ መልካም ጌጥና መለያ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

ክልከላው " የሃይማኖት እኩልነትና የመማር መብት የሚፃረር ነው " ያሉ ሲሆን   ምክር ቤቱ ጉዳዩ በህግ እየተከታተለው እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በመተባበር ታሪካዊውና ሃይማኖታዊውን የአልነጃሺ መስጂድ በማልማት የቱሪስቶች መዳረሻ ለማድረግ ያለመ " አልነጃሺ 00 " በማለት የተሰየመ ፕሮጀክት ግንባታ ለማካሄድ ጥናት ማጠናቀቃቸው ተነግሯል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ግዕዝ

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ ጥናት መስክ በዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን መቀበል ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን ስርዓተ ትምህርት እንዳዘጋጀ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማድረግና ስርዓተ ትምህርት በመቅረፅ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱን፥ ትምህርቱን ለመጀመር በተዘጋጀ የምክክር አውደ ጥናት ላይ ተገልጿል።

የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በሰርተፊኬት እና በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ከሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል፦
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ይጠቀሳሉ።

Via
@tikvahuniversity

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አርባምንጭዙሪያ

🔴 " ፀረ-ሠላም ሃይሎች በአንድ ሚሊሻ ቤት ላይ እሳት ለኩሰዉ የሁለት ጨቅላ ሕፃናት ሕይወት አልፏል "- የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ

➡️ " የገዢው ፓርቲ አመራሮች ኢዜማን ለመወንጀል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም " - የወረዳው ኢዜማ ተመራጭ


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዘይሴ ወዘቃ ቀበሌ የወረዳዉ አስተዳደር " ፀረ ሰላም የኢዜማ ከባላትና አመራሮች ናቸዉ " ባላቸዉ አካላት በአንድ የአከባቢዉ ሚሊሻ ቤት ላይ ሌሊት በተጣለ የእሳት አደጋ የሁለት ጨቅላ ሕፃናትን ሕይወት መቀጠፉን ገለጿል።

በአካልና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ወረዳው ገልጿል።

የወረዳዉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ሶፎንያስ ጥጦስ  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ጥቃቱ የተፈፀመዉ መጋቢት 19 ከሌሊቱ 5:30 ጀምሮ ነው የጥፋት ቡድኑ አስቀድሞ ተዘጋጅቶ በአካባቢዉ በአንድ የወረዳ አመራር ቤት ላይ አደጋ ለማድረስ ሞክሮ ነበር " ብለዋል።

" በቀበሌዉ የተለያዩ ቦታዎች የተኮስ እሩምታ በመክፈት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በቀበሌዉ የአንድን ሚሊሻ ቤት በማቃጠል ላይ እያሉ ሚሊሻዉና አቅም ያላቸዉ የቤተሰቡ አባላት ሸሽተዉ በማምለጣቸዉ መሸሽ ያልቻሉ ሁለት የ7 እና 4 ዓመት ሕፃናትን ከነሕይወታቸው አቃጥለዋል " ሲሉ ከሰዋል።

" ቡድኑ ከዚህ ቀደምም መሰል ጥቃቶችን ይፈጽም ነበር " ያሉት አቶ ሶፎንያስ " የጥፋት ቡድኑ አባላት ጫካ የመሸጉ የኢዜማ አባላትና አመራሮች ናቸዉ በአከባቢዉ የገዢዉን ፓርቲ አባላት እና አመራሮች ደግሞ ኢላማቸዉ ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ኮሜ ኮታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " ከጥቃቱ አድራሾች አንዱ ተይዟል በአሁኑ ወቅትም መደበኛ ፖሊስ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አድማ ብተና እና የፌዴራል ፖሊስ በጋራ በመሆን በአከባቢዉን ተሰማርተዋል ጥፍተኛዉን ለሕግ የማቅረብና ሕዝቡንም የማረጋጋት ስራ እየሰሩ" ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ወረዳዉ ኢዜማ ፓርቲ ተመራጭና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ አማንያስ ክአን ደዉሎ ነበር።

እሳቸውም  " ይህ ፍፁም ከእውነታዉ የራቀ የዉሸት ውንጀላ ነዉ " ብለዋል።

" የዘይሴን ማህበረሰብ እርስ በርስ በማባላት በጋራ ቆሞ የጠየቀዉን የመዋቅር ጥያቄ ለማስቀረት የተሸረበ ሴራ ነዉ " ሲሉም ገልጸዋል።

አቶ አማንያስ ፤ የገዢዉ ፓርቲ አመራሮች ሕዝቡ ኢዜማ ፓርቲን እንዲጠላ ደጋግመው የመወንጀል ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል ብለዋል።

" ይህም የዚሁ አካል ነዉና ገለልተኛ አጣሪ ቡድን በአከባቢዉ ያለዉን ግፍና ጭቆና ማጣራት ቢችል ጥሩ ነበር "  ሲሉ ገልፀዋል።

" የገዢው ፓርቲ አመራሮች ኢዜማን ለመወንጀል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም " ሲሉንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ የተፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት አዉግዟል።

አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች እና የመንግስት አመራሮች ድርጊቱን ከፓርቲው ጋር ያያዙበትን መንገድ እንዲሁም የስም ማጥፋት ዘመቻ በቸልታ እንማይመለከት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እንደሚከታተል በመግለፅ ፓርቲዉ በእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባር እንደማይሳተፍና ድርጊቱን የፈፀሙ አካላት በአፋጣኝ ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ዒድ_አልፈጥር

1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን ጥዋት ላይ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ተከናውኗል።

በየከተሞቹ ባሉ የዒድ ሶላት መስገጃ ስፍራዎች ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሰባሰብ የዒድ ሶላት ስነስርዓት አከናውኗል።

ከዒድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን የ1446ኛውን ዒድ አልፈጥር በዓል እያከበረ ነው።

በየከተሞቹ የነበረውን የዒድ ሶላት ስነስርዓት በፎቶ ይመልከቱ
@tikvahethmagazine

ዒድ ሙባረክ !

ፎቶ፦ አዲስ አበባ / ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ዒድ ሙባረክ !

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።

ይህ እጅግ የተባረከ ቀን በሰላም እጦት ለሚሰቃዩት ሁሉ እውነተኛና ዘላቂ ሰላም እንዲሁም ፍቅርን ያምጣልን።

በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ አንድነት የሚጠነክርበት ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

ዒድ ሙባረክ !

(Tikvah Ethiopia Family)


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

ነገ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ እሁድ ከሚከበረው ከ1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ጋር ተያይዞ የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

ዝግ የሚሆኑት መንጋዶች የትኞቹ ናቸው ?

➡️ ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ቅዱስ ዑራኤል  አደባባይ በተመሳሳይ ከቦሌ አካባቢ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ፣

➡️ ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣

➡️ ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፣

➡️ ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ -ሳንጆሴፍ መብራት አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ፣

➡️ ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ  ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ቡልጋሪያ መብራት ላይ፣

➡️ ከቅድስት ልደታ ፀበል በAU ቅዱስ ሚካኤል መታጠፊያ ወደ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ AU ሚካኤል መታጠፊያ፣

➡️ ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት  ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ፣

➡️ ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ  መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት  ፈረሰኛ መብራት ላይ፣

➡️ ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ፣

➡️ ከመርካቶ አካባቢ በአቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ አቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ላይ

➡️ ከፒያሳ በባንኮዲሮማ መብራት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ባንኮዲሮማ መብራት ላይ፣

➡️ ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ሴቶች አደባባይ ላይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ ነው ተብሏል።

#AddisAbabPolice

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ የሸዋል ወር ጨረቃ ፍለጋ እየተካሄደ ይገኛል።

ጨረቃ ዛሬ ከታየች የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ እሁድ ይውላል። ጨረቃ ዛሬ ካልታየች በዓሉ ሰኞ ይውላል።

Stay Updated !

#Haramain

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ቦቴዎች ላይ ያለው የነዳጅ ቅሸባ እስካሁን አልተቀረፈም፤ ምክንያቱም ራሱን ችሎ ሲስተም ስለሚፈልግ ” - የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን

➡️ “ በሳምንት አንድ ቦቴ እዛ አካባቢ ቃጠሎ አለ ! ”


በነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች በኩል የሚፈጸመው የነዳጅ ቅሸባ አሁንም አለመቀረፉን፣ በተለይ በአፋር ክልል ሰመራና ዴቸቶ የቦቴ ቃጠሎ እንደለ የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

“ሰመራና ዴቼቶ ከፍተኛ ሙቀት አለ” ያለው ባለስልጣኑ “በሳምንት አንድ ቦቴ እዛ አካባቢ ቃጠሎ አለ። የሴፍቲ ጉድለቶች ስላለባቸው ነው መኪናዎቹ” ብሏል።

ይህን ያሉን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ምክንያቱን ሲያስረዱም፣ “ሞቃት አካባቢ ነው፤ መቀሸብ ስለሚፈልጉ፣ የካሊቪሬሽን ችግር ስላለ፣ ቁመው በጀሪካን ለመቅዳት በሚያደርጉት ጥረት እየተፈጠረ ያለ ችግር ነው” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን ለመከታተል የሚያስችል ሲስተም መዘርጋታችሁን ከአመት ገልጻችሁ ነበር፤ አሁንም ቅሸባ አለ? ለውጥ የለውም? ሲል ለወ/ሮ ሳህረላ ጥያቄ አቅርቧል።

ዳይሬክተሯ ምን መለሱ?

“ቅሸባውን በሁለት መልኩ ማየት ያስፈልጋል፤ አንደኛው ቦቴዎች ላይ የሚደረግ ነው። ቦቴዎች ላይ ያለው የነዳጅ ቅሸባ እስካሁን አልተቀረፈም፤ ምክንያቱም ራሱን ችሎ ሲስተም ስለሚፈልግ። 

ለምሳሌ፥ 47 ሺሕ የሚይዝ ከሆነ 46 ሺህ ወይ 45,000 ሊትር ይይዛል ተብሎ ሪፓርት ይደረጋል። ስለዚህ ያቺ 2,000 በመንገድ ላይ እየቀሸቧት የምትወጣዋ ነች። 

የማደያ ማህበራት፣ ‘ከፍተኛ የሆነ ቅሸባው ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል’ በሚል ከፍተኛ ጩኸት እያነሱ ነው። ትክክለኛ ኮንሰርን ነው። አንዱ እዚያ ላይ የሚደረግ የቅሸባ ችግር ነው ያጋጠመን። 

ሁለተኛው የነዳጅ ቅሸባ፥ ዲስፔንሴር ላይ ሲመጣ ነው።

የመቆጣጠሩ፣ የሰርቲፊኬሽን ፕሮሰሱ ላይ የለንበትም። የንግድና ቀጠና የሚሰራው ቢሆንም ግን በኛ ክትትል ጊዜ የምናያቸውም አሉ። ከኢንዱስትሪው ጋርም ስንነጋገር በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነሷቸው ችግሮች አሉ" ብለዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ብለን አንዱ ያደረግነው ስማርት ፊዩል ስቴሽን የምንለው 360 ድግሪ ችግሮቹን በሙሉ ከመሰረቱ መፍታት መፍታት የሚያስችል፣ ቦቴው ምን ያክል ሊትር ነዳጅ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው? ምን ያክል ሊትርስ መያዝ ይችላል? የሚለውን ለማወቅ፤

ቦቴው በእንቅስቃሴው ጊዜ ከተከፈተ፣ እንደተከፈተ ለኛ የሚያሳየን ሲስተም እንዲኖረን ለማድረግ፣ ሲስተም በሁለት ቦቴዎች ተሞክሮ ውጤታማ ሆኗል።

በማደያም ሞክረነው ውጤታማ ሆኗል። አሁን ይህንን ስራ ነው አክሽን ፕላን አውጥተንለት ቀድመን ዋና ዋና ከተሞች ላይ ለመተግበር ዝግጅት ላይ ነው ያለነው" ብለዋል።

ወ/ሮ ሳህረላ አክለው፦ 

"ነገር ግን የቅሸባው በተለይ አፋር ቀደም ብሎ ቤንዚልን ከዬት ይጠቀሙ ነበር? የሚለውን እንደ ባለስልጣን የተወሰኑ አሰስ ለማድረግ ሞክረናል።

እነዚህ ተሽከርካሪዎች ሲመጡ ቤንዚን በጀሪካን ይቀዱላቸዋል። ስለዚህ ያንን ነው የሚጠቀሙት ማለት ነው። እርሱን መነሻ አድርገው በተለያየ መልኩ ያንን ሲያደርጉ ነበር። አሁንም ጩኸቱ አልቀነሰም።

የቅሸባ መጠኑ እየጨመረ በመምጣቱ እንደ ንግድና ቀጠና ትስስር ያኔ እንደምንም ተሞክሮ የነበረው ኢንድስትሪው ነው ‘እየተጭበረበርኩኝ ነው’ የሚለውና ከኢንድስትሪው የተወጣጣ ሰው በባታው ካሊቪሬሽን ሲሰራ እንዲያይ፣ ሪፓርት እንዲንዝ፣ ወርክ ፍሎውን ማሻሻል የሚያስፈልጋቸው የአጭርና ረጅም ጊዜ ተብሎ ነው ሲሰራ የነበረው። 

ነገር ግን እርሱ የተወሰነ ከሄደ በኋላ ብዙም ውጤት አላመጣም። 

ምክንያቱም እየተሰራበት ያለው የቆዬ ሲስተም አለ፤ ያንን በማስተካከል ፍሎው ሜትርና ዲፒስቲክ ባሉ ዓለም በደረሰባቸው ነገሮች አይደለም የካሊቭሬሽን ሲስተሙ የሚሰራው፤ አንዱ ችግርም እርሱ ነው።

ግን በዘላቂነት ለመፍታት ያው ካሌቭሬሽኑ ችግር ቢኖርበትም በቦቴዎች ለመግጠም የሞከርናቸው ላይ በመንገድ እየሄደ ለመክፈት ቢሞክር ከጅቡቲ ከወጣ በኋላ በየመንገዱ መክፈት አይችልም።

አንዱ ጥሩ ነገር እርሱ ነው። ሌላው ቦቴው ምን ያክል ሊትር ነው ጭኖ እየተጎዘ ያለው? የሚለውንም ቦቴው ላይ የሚገጠም ሲስተም አውቶማቲካሊ ለሴንትራል ኦፊስ ሪፓርት ያደርጋል ማለት ነው።

ጅቡቲ አንዴ ተጭኖ ሲወጣ ኢትዮጵያ ሲደርስ ወዲያውኑ ለማዬት ጅፒኤሶቹ እንዲገጠሙ ተደርጓል። ጂፔኤሱ ፕሮፎችን አንድላይ እንዲነበቡ አድርገን። አሁን ያለው ሲስተም አንዱ ኢንተግሬት አድርገን ወደ ዳሽንቦርድ ማምጣት የምንችልበት ሲስተም ነው።

ስለዚህ እንዴት እስኬል ይደረግ? ፍይናንሱ እንዴት ከፈቨር ይደረግ? የሚለውን ነው፣ አንደር ዲስኬሽን ያለው እንጂ ማደያ ላይ ያለው በጣም ስማርት ፊዩልስቴሽን ፕሮጀክታችን ወጤታማ በጣም ሆኗል።

የተባበሩት፣ ሲኤምሲና መቻሬ ኖክ ላይ ነው የተገጠመው የቦቴዎቹ ደግሞ የሲኤምሲ የተባበሩት ያሉ ቦቴዎች ላይ ነው የገጠምናቸው” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#በያያ_ደርሶኛል

ከያያ ዋሌት ወደ ሁሉም ባንኮች፣ ከሁሉም ባንኮች ወደ ያያ ዋሌት ማንኛውንም ክፍያ ይክፈሉ ይቀበሉ!

መተግበሪያውን በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://yayawallet.com/install ስልክ ቁጥርዎን አለያም የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ቁጥርዎን በመጠቀም በቀላሉ ይመዝገቡ!

ክፍያ በያያ!
ለተጨማሪ መረጃ 957 ላይ ይደውሉ

#YaYaWallet #YaYa #EasyRegistration #InstantTransaction #SecureTransaction #DigitalWallet #ክፍያ_በያያ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አስደሳች ዜና ለወጋገን ዓለም አቀፍ ቪዛ የክፍያ ስርዓት ተጠቃሚዎች!

ወጋገን ባንክ ለወጋገን ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚ ደንበኞቹ ካሉበት ሆነው በቀላሉ የተለያዩ ክፍያዎችን መፈፀም እና የኦን ላይን/ የበይነ መረብ ግብይት ማከናወን የሚያስችላቸውን አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

በአዲሱ አገልግሎት ደንበኞች በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኙ ታላላቅ የኦንላይን ግብይት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ( E-Commerce) ግብይት ማካሄድ ይችላሉ፡፡

በተጨማሪም ደንበኞች የወጋገን ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርዳቸውን በመጠቀም በማንኛውም ጊዜ ካሉበት ቦታ ሆነው የበረራ ትኬት መቁረጥ ፣ የሆቴል አገልግሎት ፣ የትምህርት ቤት እና ሌሎች ክፍያዎችን መፈፀም ይችላሉ፡፡

በአቅራቢያዎ በሚገኙ ቅርንጫፎቻችን በመመዝገብ የወጋገን ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚ ይሁኑ ዓለም አቀፍ ክፍያዎን ያቀላጥፉ!

#WegagenBank #Visa #Mastercard #wegagenBank #bank #ባንክ #ወጋገን #ዜና
 
Telegram | Facebook

/channel/WegagenBanksc

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

" ትግራይ ከተደገሰላት የባሰ አዘቅትና አዙሪት የምናድንበት ጊዜ አሁንና አሁን ብቻ ነው " አለ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን።

አቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ቡድን ባወጣው መግለጫ  "ልዩነቶቻችን በይደር በማቆየት ቂምና ቁርሾ ቀርፈን እኔነትንና ጠቅላይነት አስተሳሰብ ከውስጣችን በማስወገድ ትግራይ እናድናት " ብሏል።

ትግራይ ከገባችበት ቀውስና አጣብቂኝ " ያድናታል ብዬ አምኜበታለሁ  " ያለውን የመፍትሄ ሃሳብ ለውይይት ማቅረቡ ያስታወቀው ቡድኑ ከቀረበው የተሻለ ክልሉን ማዳን የሚችል የመፍትሄ ሃሳብ ካለ ለማዳመጥ ዝግጁ መሆኑ ገልጿል።

ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩትን ህወሓት በግልፅና ጠንካራ ቃላት የተቸም ሲሆን ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለአንድ ዓመት መራዘሙ በመቀበል የሚከተሉት ሦስት የመፍትሄ ሃሳቦች አቅርበዋል :-

- ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሁሉም አመለካከቶች በማቀፍ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማእከል በማድረግ መዋቅሩ ተጠናክሮ በአስቸኳይ መቋቋም አለበት።

- ዕድሜውን የተራዘመው ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋም የሚያስችል ሁሉም አመለካከቶችና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈራራሚዎች ያካተተ ፓለቲካዊ ውይይት ይቅደም።

- የትግራይ ሰራዊት ታጣቂዎች ወደ ማረፍያ ካምፓቸው ተመልሰው የሰላምና የፀጥታ ስራ ሙሉ በሙሉ በህዝባዊ ፓሊስ ይተካ ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር እስከ ቀበሌ ድረስ ህዝብ ነፃ ሆኖ በመረጣቸው አስተዳዳሪዎች እንዲመራ ፣ ተግባሩ በአንድ ወር ውስጥ እንዲከናወን።

... ብሏል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት የህወሓት ቡድን ከደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ቡድን ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

TIME IS RUNNING OUT!
Applications for the Jasiri talent Investor will close in 5 DAYS. Don’t hesitate, apply today!

To Apply: https://bit.ly/40Ai4oR

For more information @jasiri4africa

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba : የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ለህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቢሶች ወደ ስራ መግባታቸውን አሳውቋል።

አውቶብሶቹ በሁሉም የከተማችን አቅጣጫዎች ለነዋሪዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል።

ከተማ አስተዳደሩ በመንግስትና የግል አጋርነት መርሃግብር የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኦፕሬተር በመሆን ዛሬ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ መሆኑ ተመላክቷል።

#MayorOfficeofAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አቢሲንያ_ባንክ

ሀገር ቤት ሩቅ ቢመስልም በካሽ ጎ ሃዋላ ለወዳጅ ዘመድ ቅርብ ይሁኑ!
#CashGo #visa #mastercard  #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NBE : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መደበኛና ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያወጣ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ እንደሚጀምር አስታወቀ።

ጨረታዎቹ ለሚቀጥሉት በርካታ ወራት የሚካሄዱ ሲሆን፣ ዓላማውም የማዕከላዊ ባንኩን የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ግብን ለማሳካት ነው ብሏል።

የማዕከላዊ ባንኩ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በታሪኩ ከፍተኛው እንደሆነ ገልጾ በተለይ ከቅርብ ወራት ወዲህ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ብቸኛው የወርቅ ገዥ ለሆነው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቀረበው የወርቅ መጠን ከፍተኛ መሆን የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት ከተገመተው በላይ እንዲጨምር እንዳደረገው ጠቁሟል።

ከዚህ ከተጠበቀው በላይ ከሆነው የውጭ ምንዛሪ ግኝት አንጻር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቀጣይወራት በመደበኛነት በየሁለት ሳምንቱ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታዎችን ለማካሄድ መወሰኑን አሳውቋል።

ይህ አካሄድ በማዕካላዊ ባንክ እየተከማቸ ካለው የውጭ ምንዛሪ የተወሰነውን መጠን ለግሉ ዘርፍ ለማቅረብና የማዕከላዊ ባንኩን የገንዘብ ፖሊሲ ዓላማ ለማሳካት የሚረዳ እንደሆነ አመልክቷል።

ፍላጎቱ ያላቸው ባንኮች በተሰጠው የጊዜ ሰሌዳና በተቀመጠው አኳኌን የጨረታ ስነዶቻቸውን እንዲያስገቡ ባንኩ ጥሪ አድርጓል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

📞 የድምጽ ጥቅሎችን እየገዛን በጉርሻ ደቂቃዎች እንንበሽበሽ! ከሳፋሪኮም ወደ የቴሌ የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎችን በመግዛት ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም 100% ጉርሻን እናጣጥም! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ ምንድነው ያሉት ?

ከትግራይ ክልል " ለስራ " በሚል ምክንያት ከወጡ 20 ቀናት ያስቆጠሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን ለህክምና አንዴ ወደ ዱባይ ሌላ ጊዜ ወደ ባንኮክ ተጉዘዋል እየተባለ ሲነገርባቸው ነበር።

ትላንት እሁድ በሰዓታት ልዩነት ሁለት መልእክቶችን አጋርተዋል።

አንዱ ለህዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የሚል ሲሆን ፤ ሌላኛው ለተቀናቃኞቻቸው " ድሉ የህዝብ ነው " የሚል ጠንካራ ትችት አዘል መልእክት ነው።

" ላለፉት 20 ቀናት በትግራይ እየታየ ያለው ፓለቲካዊ ቀውስ ' ስልጣን ወይ ሞት ' የሚል ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት የደሎተው ሴራ መጨረሻው ምዕራፍ ማሳያ ነው " ብለዋል።

ይህ ደሞ አንዳንድ የተሻለ ስምና ዝና ያላቸውን ግለሰቦችም ለስህተት የዳረገ ፍፃሜ ነው በማለት ተግባሩ አጣጥለውታል።

ፕሬዜዳንቱ " ኋላቀር ቡድን " ሲሉ የገለፁት አካል የጊዚያዊ መንግስቱ መዋቅር በመጣስ ማህተም ከተቆጣጠረ በኋላ በመጀመሪያ እርምጃው በትላለቅ ከተሞች ለደጋፊዎቹ በስፋት መሬት አከፋፍሏል ፤ ገቢ የሚያስገኙለትን የሽያጭ ስራዎች ፈፅሟል ብለዋል።

" መሬት ከመሸጥና ከማከፋፈል አልፎ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው መመለስና ግዛታዊ አንድነት ማረጋገጥ ከመፈክር በዘለለ ጣጣው አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ኋላቀር ቡድን " ሲሉ የገለፁት አካል ሁለተኛ ትኩረቱ ወደ
#ፌደራል እየተመላለሰ የፕሬዜዳንት ስልጣን እንዲሰጠው መለመን ሆኗል ሲሉ አብራርተዋል።  

" ቡድኑና አሽከሮቹ በህልምና በቀልባቸው የማይለቁዋቸው ሁለት አጀንዳዎች መሬትና ስልጣን ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቡድኑ የሚያስተባብራቸው አካላት የተፈናቃዩ ተስፋና የወጣቱን ህልም በመቀማት ወደ ሁለተኛ ዙር ትርምስ ሊከቱን ታችና ላይ በማለት ስለሚገኙ ህዝቡ ሃይ ሊላቸው ይገባል " ሲሉ አክለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያጋሩትን ጠንከር ያለ ፅሁፍ " ድል የህዝባችን ነው " ሲሉ ቋጭተውታል።

#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ብርሃን ባንክ !

የ500 ብር ተሸላሚ ይሁኑ
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የሳምንቱን የ EPL (English Premier League) ተጠባቂ ጨዋታዎች የብርሃን ባንክ ቴሌግራም ገጽ ተቀላቅለው ይገምቱ : የ500 ብር ተሸላሚ ይሁኑ!
1. Nottingham Forest vs. Manchester United April 01(ማክሰኞ)
2. Chelsea Vs. Tottenham April 03 (ሐሙስ)
3. Manchester United Vs. Manchester City April 06(እሁድ)

የብርሃን ባንክ ቴልግራም ገጽ፡ /channel/berhanbanksc

ማሳሰቢያ፡- ውድድሩ ጨዋታው ከመጀመሩ አንድ ሰዐት በፊት ይጀመራል
✔️ለማሸነፍ በመጀመሪያ ቻናሉን መቀላቀልዎን ያረጋግጡ!
✔️ የተስተካከሉ መልሶች ለሽልማት ብቁ አያደርጉም!

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#premierleague #football #competition #berhanbank #stressfreebanking

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ረመዷን በሰላም እና በአንድነት ጾመን በአላህ ፈቃድ ለደስታችን የዒድ አል ፊጥር ቀን መድረስ ችለናል ይህ የሆነው በአላህ እዝነትና ፈቃድ ነውና አሏህን እናመሰግነዋለን።

በኢድ ቀን ማንም ሳይከፋ እንዲውል ልናደርግ ይገባል።

በየትኛውም አይነት አጋጣሚ የተቀያየመ ሰው ካለ ይቅር መባባል እና ችግሮችን በመነጋገርና በመወያየት ልንፈታ ይገባል። " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል።

1446ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ነገ እሁድ የሚከበረውን 1446ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ ገልጿል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EidAlFitr

የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ እሁድ ይውላል።

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ በመታየቷ 1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ እሁድ ተከብሮ ይውላል።

ዒድ ሙባረክ !

#Haramain

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ramadan : በሳዑዲ አረቢያ የሸዋል ጨረቃ ፍለጋ እየተካሄደ ነው።

የጨረቃ መታየት አለመታየትን ተንተርሶ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ አልያም ሰኞ ይሆናል።

Stay Updated !!

#Haramain #Tumair #SaudiArabia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MPESASafaricom

M-PESA ከማትጠብቁት የ5% ተጨማሪ ገንዘብ እና ከ1ጊ.ባ ነፃ ኢንተርኔት ጋር ከኬንያ ድረስ መጥቷል! ገንዘባችንን በM-PESA እንቀበል በሽልማት እንንበሽበሽ!

#MPESASafaricom #MPESAEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

13 ኪ.ግ የሚመዝን እጢ (ካንሰር) በተሳካ ሁኔታ በቀዶ ህክምና ተወግዷል።

በመቅረዝ ሆስፒታል፣ በዶ/ር ካሳው ደምሌ (አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም እና ሄፓቶቢሊሪ ቀዶ ጥገና ሐኪም) የተመራ ዘርፈ ብዙ የቀዶ ጥገና ሕክምና ባለሙያዎች ቡድን፣ ከ61 ዓመት ሴት ታካሚ 13.0 ኪሎ ግራም እጢ {retroperitoneal liposarcoma} በተሳካ ሁኔታ ተወግዷል።

ከቀዶ ጥገናው መልስ ታካሚዋ በቅርብ ክትትል ተደርጎላት ፤ በጥሩ ጤንነት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።

የታካሚ መረጃ እና ምስል ለመጠቀም ፍቃድ ተገኝቷል።

መቅረዝ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ

ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በ 0921636465 / 0952272727 ይደውሉ።

Читать полностью…
Подписаться на канал