ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
“የተነሳበትን አካባቢ ጉዳት አድርሷል። ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም” - ባለስልጣኑ
በአፋር ክልል ሃላይዳጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርክ ከተነሳ ቀናት ያስቆጠረው ቃጠሎ በቁጥጥር ሥር ባለመዋሉ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ናቃቸው ብርሌው በሰጡን ማብራሪያ፣ የእሳት ቃጠሎ በተነሳበት አካባቢ ጉዳት እንዳደረሰ፣ የጉዳት መጠኑን የሚታወቀው ቃጠሎው ሲቆም መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ናቃቸው በዝርዝር ምን አሉ ?
“ በእርግጥ ብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ነው የእሳት ቃጠሎው የተነሳው። ምክንያቱ በሂደት የሚጣራ ቢሆንም በሰው ሰራሽ ምክንያት እንደተከሰተ ነው የሚገመተው።
በባሕሪው ብሔራዊ ፓርኩ ሳራማ ምድር (Grass land) ነው። ለመቆጣጣር አስቸጋሪ እንደነበር ነው ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው።
በአካባቢው አውራ ጎዳና መንገድ የሚሰሩ፣ የአፋር ብሔራዊ ክልል ከአሚባራ ወረዳ ጋር በመተባበር የፍየር ብሬኪንግ (የመጥረግ፣ የመቁረጥ ስራ) በግሬደር እየተሰራ ነው።
ፋየር ብሬኪንግ ተርቷል እሳቱ ወደ ሌላኛው ክፍል እንዳይዛመት የመጥረግ ሥራ እየተሰራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
አሁንስ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ውሏል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ “ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ፣ ወደልላኛው የፓርኩ ክፍል እንዳይስፋፋ ነው የቆረጣ ሥራ የሚሰራው ሳሩ ልክ የመንገድ ያክል በግሬደር እየተቆረጠ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።
“ የተነሳበትን አካባቢ ጉዳት አድርሷል። ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
እስካሁን በቃጠሎው በምን ያክል ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ታውቋል ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ “ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ሲውል ወይም መጥፋቱ ሲረጋገጥ የጉዳቱ አይነቱና መጠኑ የሚታወቀው ያኔ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።
“ እስቲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የሰው ኃይል የሎጂስቲክስ ድጋፍ በማድረግ፣ ባለሙያዎችን በመመደብ በአዋሳኝ የሚገኘው የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ተሽከርካሪዎችን ጭምር በመውሰድ እሳቱን ለሚያጠፉ ኃይሎች ድጋፍ እየተደረገ ነው ” ብለዋል።
ሰሞኑን በተለያዬ ፓርኮች እየተከሰቱ ያሉ የእሳት ቃጠሎን ምንነት ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽም፣ “ በእርግጥ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች የሚከሰቱት ከወቅቱ ጋር ተያይዞ ነው። ከፍተኛ ሙቀት፣ ደረቅ የአየር ሁኔታ ስላለ ” ነው ያሉት።
“ እነዚህ ጥብቅ ቦታዎች በባህሪያቸው ደንም ይሁን ሳር ስላላቸው ትንሹም ቃጠሎ በቀላሉ የመስፋፋት እድል አለው። ብዙዎቹ የሚስተዋሉትም በተፈጥሮ አይደለም በሰው ሰራሽ ነው የሚሰቱት ” ብለዋል።
ማህበረሰቡ እሳት ቃጠሎ ሲያጋጥም በማጥፋት እንደሚተባበር፣ ከማህበረሰቡ ውስጥ እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጽሚ አንዳንድ እንደማይጠፉ ገልጸው፣ " በጋራ ለመከላከል ሲከሰት ለማጥፋት የሚደረገውን ሁሉ ጥረት በህገ ወጦች ላይ በማተኮር ሁሉም ኃላፊነቱን ቢወስድ ” ሲሉ አሳስበዋል።
“ በአንዳንድ አካባቢዎች ሲኬድ ከግጥሽ ጋር የተያያዙ ናቸው። አዲስ ሳር እንዲያወጣላቸው የሚደረጉ ድርጊቶች አሉ። እናም የብዙኀንን ተሳትፎ ስለሚጠይቅ ሁሉም በኃላፊነት ቢከላከል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
(ጉዳዩን ተከታትለን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
" ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር መቆም አይቻልም " - የትራንስፖርት ቢሮ
ወደ አዲስ አበባ ከተለያዩ የአፍሪካ ብሎም ዓለም አገራት እንግዶች እየገቡ ናቸው።
ይህን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ማታ 12:00 ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ፦
- በኤሌክትሮኒክ ታክሲ ስርዓት (ኤታስ) አገልግሎት የሚሰጡ የሜትር ታክሲ፣
- የላዳ፣
- የታክሲ እና መሰል ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር መቆም እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
#ጥቆማ
ብሩህ እናት !
ሴቶችን እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያሸልም “ ብሩህ እናት ” የተሰኘ የፈጠራ ውድድር መዘጋጀቱ ተገለጸ።
የሴቶችን ድካም የሚያቀሉ ቴክኖሎጂ ተኮር የፈጠራ ሀሳቦችን በማቅረብ ለሚያሸንፉ ሴቶች ቋሚ ችግር ፈቺ ተቋም የሚሆኑበትና ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ብር የሚያሸልም ውድድር ለሴቶች ብቻ ማዘጋጀቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል።
የፈጠራ ውድድሩ የተዘጋጀው ከኢንተርፕርነሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከእናት ባንክ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ ጋር በጋራ በመሆን መሆኑን መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በዚህም “ ማሰልጠን፣ መሸለም፣ ማብቃት ” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢ ላሉ ሴቶች እድሉ እንጀተመቻቸ፣ ከተመዘገቡት 5ዐ የተሻለ ሀሳብ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ስልጠና እንደሚሰጥ አመልክቷል።
“ ፕሮግራሙ ላይ የላቀ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሴቶች ተወዳዳሪዎች መከካልም 10 ለሚሆኑት አሸናፊ የቢዝነስ ሀሳብ ፈጣሪዎች እውቅናና የገንዘብ ሽልማት እንዲያገኙ ይደረጋል ” ሲል መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል።
ለውድድሩ አሸናፊዎች ሽልማቱ ምንድን ነው ?
ከተመዝጋቢዎቹ የተሻለ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሀሳብ ያቀረቡ 1ዐ ተወዳዳሪዎች እንደየደረጃቸው ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ሽልማት መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በገለጻው መሠረት፣ ለ1ኛ አሸናፊ 500 ሺሕ፣ ለ2ኛ አሸናፊ 400 ሺሕ፣ ለ3ኛ አሸናፊ 300 ሺሕ፣ ለ4ኛ አሸናፊ 200 ሺሕ፣ ለ5ኛ አሸናፊ 150 ሺሕ እንዲሁም ከ6 እስከ 10ኛ ላሉ አሸናፊዎች 100 ሺሕ ብር ይሸለማሉ።
በመግጫው የተገኘው እናት ባንክ በበኩሉ፣ ለአሸነፉበት ሴቶች ቴክኖሎጂ ተግባራዊነት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ብድር እንደሚያመቻች ገልጿል።
ምዝገባው መቼ ተጀምሮ ? መቼ ይጠናቀቃል ?
ምዝገባው ከዛሬ (ሰኞ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጅምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ደረስ እንደሚከናወን ተነግሯል።
ለተወዳዳሪዎች የቡት ካምፕ ስልጠና ከመጋቢት 8 እስከ መጋቢት 19/2017 ዓ/ም እንደሚሰጥ እና የውድድሩ ማጠቃለያና ሽልማት መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሚሆን የተመላከተ ሲሆን፣ ለተጨማሪ መረጃ 0948874085፣ 0913154944 መደወል ይቻላል ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
“ በ6 ወራት ለ66 ሺህ 741 የማህበረሰብ ክፍሎች የሥነ አዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ” - አማኑኤል ሆስፒታል
አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 ዓ/ም፣ “ በ6 ወራት ለ66,741 የማህበረሰብ ክፍሎች የሥነ አዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በዚህም 64,256 የተመላላሽ፣ 257 ህፃናት የአዕምሮ፣ 410 ሰዎች የሱስ ህክምና መሰጠቱን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዩ የኔአለም ገልጸዋል።
እንዲሁም ለ240 የተሃዲሶ፣ ለ921 የአስተኝቶ፣ ለ1,564 ሰዎች ደግሞ የድንገተኛ የህክምና አገልግሎት መሰጠቱን አቶ አብይ አስረድተዋል።
በተመላላሽ፣ በአስተኝቶና በድንገተኛ የህክምና አገልግሎት ከተሰጣቸው ታካሚዎች መካከል 36,300 የጤና መድን ተጠቃሚዎች መሆናቸው ተመልክቷል።
በተመላላሽና በተኝቶ ህክምና በስድስት ወራት የወንጀልና የፍትሃ ብሔር ተመርማሪ ለሆኑ 413 የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት መስጠቱም ተገልጿል።
“ በሆስፒታሉ አማካኝ አስተኝቶ የቆይታ ጊዜ በ2016 ዓ/ም ከነበረው 36 ቀናት በ2017 ዓ/ም 6 ወራት ወደ 33 ቀናት ማድረስ፣ የአልጋ የመያዝ ምጣኔም በመጀመሪያ 6 ወራት መጨረሻ ላይ 85.2% መፈጸም ተችሏል ” ተብሏል።
ሆስፒታሉ ከ1930 ዓ/ም ጀምሮ በተኝቶ፣ በተመላላሽ፣ በድንገተኛ፣ የጭንቅላት ምርመራ፣ በኤሌክትሪክ ንዝረት፣ በህፃት የአዕምሮ፣ ከህግ ጋር የተያያዙ የአዕምሮ ህክምናና ምርመራ እንዲሁም የነርቭ ህክምናዎችን እየሰጠ የሚገኝ አንጋፋ ሆስፒታል ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
⛺️🗺 ሃይኪንግ ላይ ሆናችሁ ዳታ መጠቀም ፈልጋችሁ ታውቃላችሁ? እነሆ አዲስ ቅመም!
💨⚡️ የትም ይዛችሁት መሄድ የሚያስችላችሁ 3000 mah የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😋
ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
#መቄዶንያ
ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው !
ትላንት የካቲት 1/2017 ዓ/ም በጀመረው የመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እስኩን 120,000,000 ብር ተሰብስቧል።
መቄዶንያ በሚያስገነባው ሆስፒታል ጭምር ያለው ህንፃ ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት አጋጥሞታል። ህንፃው ለማጠናቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። ለማጠናቀቅ ወደ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል።
በቀጥታ ይከታተሉ 👇
https://www.youtube.com/live/q0bMjwt9PvM?feature=shared
የምትችሉትን ሁሉ ድጋፍ አድርጉ።
@tikvahethiopia
የIMF ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ምን አሉ ?
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (IMF) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በኢትዮጵያ የስራ ቆይታ አድርገዋል።
በዚህም ወቅት ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ጨምሮ ከፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።
የነበራቸውን ቆይታ በተመለከተ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር በጋራ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
ምን አሉ ?
ዳይሬክተሯ ፤ " የኢትዮጵያ ሪፎርም ከባድ እና ጊዜ የሚወስድ ነው ፤ እባካችሁ ታገሱ " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያውያን ለትዕግስት እንዲያሳዩ እና ከመንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጥረቶች ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
ጆርጂዬቫ ፥ " የሪፎርሙን ግቦች ለማሳካት የአንድነት አስፈላጊ ነው " ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
" ኢትዮጵያ የተቀበለችው ሪፎርም ከባድ እና ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም እጅግ ትልቅ ውጤት ያስገኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
" ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪዬን አቀርባለሁ " ያሉት ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ " ህብረተሰቡ ከሪፎርሙ ጀርባ በመሰባሰብ በአንድነት ድጋፍ ማድረግ አለበት " ብለዋል።
ጆርጂዬቫ ፥ ኢኮኖሚውን የበለጠ አጥጋቢና ብቁ ለማድረግ ብዙ የሚሠራ ሥራ አለ " ብለው " እባካችሁ መንግሥት ሥራውን እንዲያጠናቅቅ ድጋፍ አድርጉ " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
የዋጋ ንረትን ለመፍታት የሚሰራው ስራ ውስብስብ መሆኑን ያልሸሸጉት ዳይሬክተራ " የዋጋ ንረትን ወደ ታች ለማውረድ ጠንካራ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲዎች፣ የኢኮኖሚውን የማምረት አቅም ማስፋት፣ የወጪ ንግድና የውጭ ምንዛሪ ገቢን ማሳደግ እና የግሉ ሴክተርን ማብቃት ይጠይቃል " ብለዋል።
ሌላው ያነሱት ጉዳይ በG20 የጋራ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን የዕዳ መልሶ ማደራጀት ድርድር በተመለከተ ነው።
ጆርጂዬቫ ፤ " የዕዳ መልሶ ማዋቀር ሂደት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛል ፤ ከኢትዮጵያ አበዳሪዎች ጋር ባለኝ ግንኙነት ይህ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
የIMF ፕሮግራም አካል ሆነውን የታክስ እርምጃዎችን በተመለከተም ፤ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለብሄራዊ በጀቱ ድጋፍ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የታክስ አቅሞችን መለየታቸውን ጠቁመዋል።
ጆርጂዬቫ ፥ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት ከIMF የመጀመሪያ ትንበያዎች መብለጡን ማብራራታቸውን ዘሪፖርተር አስነብቧል።
የማኔጂንግ ዳይሬክተራ ንግግር ተከትሎ " መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የሚገናኝ አይደለም " የሚሉ አስተያየቶች ሲሰጡም ተመልክተናል።
@tikvahethiopia
#መቄዶንያ
" ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው !! "
መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በሚያስገነባው ሆስፒታል ጭምር ያለው ህንፃ ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው እግዛ እንዲደረግ ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።
ዛሬ “ በሰይፉ ኢቢኤስ የዩቱብ ቻነል ” ድጋፍ ማድረጊያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው።
ደጋጎች ሁሉ ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።
የድጋፍ ማድረጊያ አማራጮች ከላይ ተያይዘዋል።
መቄዶንያ “ ህንፃው ለማጠናቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። ለማጠናቀቅ ወደ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” ማለቱ አይዘነጋም።
በቀጥታ ይከታተሉ 👇
https://www.youtube.com/live/q0bMjwt9PvM?feature=shared
@tikvahethiopia
" ፋይናንስ ቢሮ ይግባኝ በመጠየቁ አፈጻጸሙ ከትላንትና በስቲያ ጀምሮ ታግዶ ነው ያለው " - እናት ፓርቲ
እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የጣሪያ ግድግዳ / ንብረት ግብር መመርያ እንዲቆም የመሠረተው ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ መመሪያው "ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም " ሲል ፍርድ ቤት ጥር 9 ቀን ብይን መስጠቱን ፓርቲው ማስታወቁ ይታወሳል።
ይህንንም የፍርድ ቤት ውሳኔ በጋዜጣዊ መግለጫው አሳውቆ የነበረው ፓርቲው የፋይናንስ ቢሮ ይግባኝ በመጠየቁ ምክንያት የውሳኔው አፈጻጸም ከትላንትና በስቲያ ጀምሮ መታገዱን የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰይፈሥላሴ አያሌው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የፓርቲው ፕሬዝዳንት በዝርዝር ለቲክቫህ በሰጡት ሃሳብ ምን አሉ ?
" ጥር 9 ቀን 6:30 ላይ ውሳኔውን ከፍተኛ ፍ/ቤት አሳልፎ 7:30 ላይ የፋይናንስ ቢሮ አቃቢ ህግ በቃለ መሃላ ' ለከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ይግባኝ እስከምል ድረስ አፈጻጸሙ ይታገድልን ለ15 ቀንም ፓርቲው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጥ ' አሉ።
የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ መጠበቅ ስለነበረብን እኛም ለ15 ቀናት ጠበቅን 15 ቀኑ የሞላው አርብ ነበር ሰኞ መግለጫ ሰጠን።
በ15 ቀን ውስጥ ይግባኝ ባይጠይቁም ከትላንት በስቲያ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አፈጻጸሙ ታግዶ እንዲቆይ በሚል ይግባኝ መጠየቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ቢሮአችን ላይ ተለጥፎ አግኝተናል።
እየተነጋገርን ያለነው ስለ ህግ ጉዳይ ነው ክፍያው ይቀጥል አይቀጥል አይደለም እኛ እያልን ያለነው ከተማ መስተዳደሩ የጣለው ግብር ከህግ አግባብ ውጪ እንደሆነ ነው መሆኑን ደግሞ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አረጋግጦልናል።
እያንዳንዱ ከህዝብ የሚሰበሰብ ሳንቲም የህግ መሰረት ሊኖረው ያስፈልጋል ይህ የጣራና ግድግዳ ግብር እየተሰበሰበ ያለው ከህግ አግባብ ውጪ ነው የሚከፈለው ገንዘብ መቆም አለበት ብለን ነው ክስ የመሰረትነው።
ፍርድ ቤቱም ክፈሉ አትክፈሉ አይደለም እያለ ያለው ነገር ግን ለክፍያ መመሪያ የነበረው በሚያዝያ 2015 የወጣው እና እንዲፈጸም የሚያስገድደው መመሪያ መሻሩን ነው የገለጸው።
በዚህም መሰረት የህግ ውሳኔ አፈጻጸም አካሄድ ቢኖረውም የከተማ መስተዳደሩ ይህንን ግብር ወደ ፊት እንዲሽረው ይጠበቃል።
የፋይናንስ ቢሮ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢጠይቅም የከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሳኔ ያጸድቀዋል ብለን ነው የምናምነው ቢሽረው እንኳ ሰበር ሰሚ ችሎት በመኖሩ ጉዳዩን እስከመጨረሻው እንገፋበታለን።
የኢትዮጵያ ህዝብ 10 ሺ፣20 ሺ እና ሚሊየን ለጣራ እና ግድግዳ በሚል ከፍሎ አያውቅም እንዲህ መክፈል የተጀመረው ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ ነው መቼም ይጀመር መመሪያው ህገ ወጥ ነው " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#USA : ከቀናት በፊት በአሜሪካ አላስካ ግዛት 9 መንገደኞችን እና 1 አብራሪን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን ደብዛው ጠፍቶ ከቆየ በኃላ በአየር እና ምድር በተደረገ አሰሳ ስብርባሪው ተገኝቷል።
በአደጋው በሕይወት የተረፈ ሰው የለም።
የ3 ሰዎች አስክሬን በነፍስ አድን ሰራተኞች ተገኝቷል።
ይህ አደጋ በአሜሪካ ከ1 ሳምንት ባነሰ ጊዜ የደረሰ 3ኛው የአቬዬይሽን አደጋ መሆኑን የቪኦኤ ዘገባ ያሳያል።
በአሜሪካ፣ ፔንሲልቫኒያ ግዛት፣ አንድ አነስተኛ የሕክምና ማጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ ጄት በርካታ ሕንጻዎች በሚገኙበት ሰፈር ውስጥ ተከስክሶ በህይወት የተገኘ እንደሌለ ይታወቃል።
ከዚህ አደጋ በፊት ደግሞ በዋሽንግቶን ዲሲ 60 መንገደኞች እና 4 የበረራ ሰራተኞችን የያዘ የመንገደኞች አውሮፕላን 3 ሰዎች ከያዘ የጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ አንድም ሰው በህይወት አለመገኘቱ መገለጹ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
#GlobalBank
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል።
አገልግሎት መስጠት የጀመረው የዲጂታል ባንኪንግ ማዕከል የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ገንዘብ ገቢ ማድረግና ወጪ ማድረግ፣ ቀሪ ሂሳብና የሂሳብ መግለጫ ማሳየት፣ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን መመንዘር፣ የተለያዩ ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላል።
በተጨማሪም ያለ ኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ማግኘት፣ ቼክ መመንዘርና ገቢ ማድረግን ጨምሮ ደንበኞች የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት መጠቀም በሚፈልጉበት ወቅት በማዕከሉ በመገኘት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ታብሌቶች መጠቀም ያስችላቸዋል።
ማዕከሉ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ክፍል ያለው መሆኑንና ተቀዳሚ (corporate) ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የቪዲዮ ባንኪንግ አገልግሎት ማገኝት የሚያስችላቸው አገልግሎትም እንደሚሰጥ ጠቅሷል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ይህ ማዕከል ሥራ መጀመሩ ባንኩ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር የባለአክሲዮኖችን ጥቅም ከፍ ከማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።
ባንኩ በዘንድሮው አመትም ከታክስ በፊት ብር 757.6 ሚሊዮን ማትረፉን የገለጸ ሲሆን የቅርንጫፍ ብዛቱንም ወደ 238( ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ) ከፍ ማድረግ ችሏል። በአሁን ሰዓትም ባንኩ ከ 1.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት አሳውቋል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደ/ር ተስፋዬ ቦሩ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የባንክ ካፒታል ዕድገት ዝቅተኛ ጣሪያ በቀረው ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳካ ገልጸዋል።
ባንኩ የተቀማጭ ሂሳቡን ከ 20.6 ቢሊዮን ብር በላይ ያደረሰ መሆኑንና የባንኩ ጠቅላላ ሃብት ደግሞ ከ 26.6 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱንም አስታውቋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሜክሲኮ አካባቢ ለዋና መ/ቤት ግንባታ በተረከበው 5,550 ካ.ሜ ቦታ ላይ የወደፊት የዋና መ/ቤት ህንፃ ለመገንባት በሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ እየሰራ ይገኛል።
#GlobalBankEthiopia
" ፈጣሪ ምን ይሳነዋል ? የማይገመተው በሱ ፍቃድ ሆኗል። በወጣትነቴ ያጣሁትን የልጅ ጥማት በእርጅና ጊዜ መልሶልኛል ፈጣሪ ይመስገን ! ልጄን የማሳድግበት ጤና ይስጠኝ እድሜ ይጨምርልኝ " - በ76 ዓመታቸው ወንድ ልጅ የወለዱት ወ/ሮ መድህን ሓጎስ
የመቐለ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መድህን ሓጎስ በ76 ዓመታቸው ወንድ ልጅ የመታቀፋቸው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል።
የድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን በእናቲቱ መኖሪያ የተዘጋጀውን የክርስትና ድግስ ላይ ተገኝቶ ያጠናቀረውን ፕሮግራም ከትላንት ጀምሮ በሰፊው ህዝብ ጋር ሲዳረስ ነበር።
እናቲቱ በ76 ዓመታቸው መውለዳቸው በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ያለመ የ ' X ' ዘመቻም አለ።
የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች " እናቲቱ በተለመደው ተፈጥሯዊ መንገድ ነው የውለዱት " ፤ " የለም በህክምና ቴክኖሎጂ በመታገዝ ነው ልጃቸውን የታቀፉት " የሚሉ ክርክሮች በማንሳት ሲፅፉ ታይተዋል።
እናቲቱ በድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን እና ሰግለለት ለተባለ ዩቱብ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የተከራካሪዎቹን ጥያቄ ያልመለሰ ድፍን ያለ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
የመቐለው አባላችን ፤ እናቲቱ በትግርኛ ቋንቋ ለሚድያዎች የሰጡት ቃለ-መጠይቅ እና የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ያገኘውን መረጃ ከታማኝ የመረጃ ምንጭ ጋር ለማቀናጀት ጥረት አድርጓል።
ወ/ሮ መድህን ሓጎስ ከዚህ በፊት ልጅ እንዳልወለዱ ፤ የአሁኑ የመጀመሪያ ልጃቸው መሆኑን በልጃቸው ክርስትና ቀን በአንደበታቸው አረጋግጠዋል።
ወ/ሮ መድህን በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ፅንሳቸውን እስከ 8 ወር ድረስ ደብቀውት እንደነበር ከመግለፅ ባለፈ በተለመደው መንገድ ነው የወለዱት ወይስ በህክምና የታገዘ የስነ ተዋልዶ ዘዴ (IVF or In Vitro Fertilization) ጥበብ ያሉት ነገር የለም።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከታማኝ ምንጭ ባገኘው መረጃ እናቲቱ የወለዱት በኢንቪትሮ ፈርትላይዜሽን (IVF) ማለትም የወንዱ ዘር እና የሴቷን እንቁላል አውጥቶ ከማህፀን ውጪ በላብራቶሪ ውስጥ እንዲዋሃዱ የሚደረግበት በህክምና የታገዘ የስነ ተዋልዶ ዘዴ መሆኑን ተረድቷል።
ወ/ሮ መድሂን ህክምናውን ለማግኘት ወደ ታይላንድ ተጉዘዋል።
በዚያው ፅንሱ የ3 ወር ዕድሜ እስኪ ሞላው ድረስ ቆይተዋል።
ከሦስተኛው እስከ ወሊድ ባሉት ጊዜያት የፅንስ ክትትል በመቐለ በሚገኝ አንድ የግል ህክምና ተከታትለው በቀዶ ህክምና ለመውለድ መቻላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
በኢትዮጵያ የወሊድ ህክምና በህግ የተፈቀደው IVF / In Vitro Fertilization የህክምና ጥበብ በመቐለ ጨምሮ በአዲስ አበባ እንደሚሰጥ እየታወቀ እናቲቱ ለምን ውጭ ድረስ ለመጓዝ እንደፈለጉ የታወቀ ነገር የለም።
በ76 ዓመታቸው ነው ልጅ ለማቀፍ የቻሉት ወ/ሮ መድህን ሓጎስ እሳቸውም ልጃቸውም በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።
" ፈጣሪ ምን ይሳነዋል ? የማይገመተው በሱ ፍቃድ ሆኗል። በወጣትነቴ ያጣሁትን የልጅ ጥማት ፤ በእርጅና ጊዜ መልሶልኛል ፈጣሪ ይመስገን። ልጄን የማሳድግበት ጤና ይስጠኝ እድሜ ይጨምርልኝ " ብለዋል።
ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ. በመስረከም 7/2019 የህንድዋ አንድህራ ፕራደሽ ግዛት ተወላጅ የሆኑት ወ/ሮ ማንጋያማ ያራማቲ በ73 ዓመታቸው በIVF ልጅ በማግኘት በእድሜ ትልቋ ተብለው ነበር።
ባለፈው ዓመት ሳፊና ናሙኩዋያ የተባሉ ኡጋንዳዊ ሴት በIVF ህክምና የመንትያ ልጆች እናት መሆን እንደቻሉ በስፋት ተዘግቦ ነበር።
እንደ አንድ የጤና መረጃ አሜሪካ ውስጥ ከሚወለዱት ህጻናት 2% የሚሆኑት በIVF, or In Vitro Fertilization የህክምና መንገድ ሲሆን ከ8 ሚሊዮን በላይ ህፃናት በዚህ መንገድ ተወልደዋል።
NB. ኢንቪትሮ ፈርትላይዜሽን (IVF) ማለት የወንዱ ዘር እና የሴቷን እንቁላል አውጥቶ ከማህፀን ውጪ በላብራቶሪ ውስጥ እንዲዋሃዱ የሚደረግበት በህክምና የታገዘ የስነ ተዋልዶ ዘዴ ነው። በላብራቶሪ ውስጥ የተፈጠረው ፅንስ በሚፈለገው ደረጃ እድገቱን ከቀጠለ በኋላ ወደ ሴቷዋ ማህፀን በማስገባት የተፈጥሮ እርግዝና ሂደቱን እንዲቀጥል የሚደረግ ይሆናል፡፡
በዚህ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ የጤና ባለሙያ ማብራሪያ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
🎁 በቅናሽ ላይ ቅናሽ የተደረገባቸው ልዩ ጥቅሎች በቴሌብር ሱፐርአፕ!!
✨ ከመደበኛ ጥቅሎች እስከ 25% ልዩ ቅናሽ የሚያገኙባቸውን የድምጽ እና የኢንተርኔት ጥቅሎች በዕለታዊ፣ ሳምንታዊ እና ወርኃዊ አማራጮች ያገኟቸዋል፡፡
🔗 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ብቻ!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
“በሌሎች ተብሎ የተገለጸው ቃጠሎ በምርመራው ያልተደረሰባቸው ማለት ነው” - ፌደራል ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ በ2017 ዓ/ም በ6 ወራት በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች የተከሰቱ 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎችን መንስኤ “በፎረንሲክ ምርመራ” ማጣራቱን የሚገልጽ ውጤት ይፋ አድርጓል።
50 ቃጠሎዎች በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ፣ 11 በመካኒካል ችግር ፣ 10 ሆን ተብሎ ፣ 17 በቸልተኝነት፣ 15 በሌሎች ምክያቶች የደረሱ መሆናቸውን ገልጿል።
አጠቃላይ ባለፉት 6 ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 96 እና በክልሎች ደግሞ 7 በአጠቃላይ እንደ ሀገር 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ደርሰው የአደጋ መንስኤዎችን ማጣራቱን ጨምሮ ገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር የተከሰተ አደጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።
በግማሽ ዓመቱ በ582 መኖሪያ ቤት፣ በ12 ተሽከርካሪዎች፣ በ1965 ንግድ ቤቶች፣ በ6 ፋብሪካዎችና የተለያዩ ድርጅቶች በቃጠሎ ምክንያት ጉዳት ስለመድረሱ አመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ 15 ቃጠሎ በሌሎች ምክንያቶች እንደተከሰቱ ገልጿችኋል፤ ሌሎች ሲባል ምንድን ናቸው? የሚልና ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለፌደራል ፓሊስ አቅርቧል።
በፌደራል ፓሊስ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ፣ “በሌሎች ተብሎ የተገለጸው ቃጠሎ ስቲል በምርመራው ያልተደረሰባቸው ማለት ነው” ሲሉ መልሰዋል።
“ለምሳሌ እሳት አደጋ ይደርስና ከዛ ቦታ ላይ ለማስረጃ የሚሆኑ ኢቪደንሶችን፣ ማስረጃዎችን ማጥፋት፣ ቁሳቁሶችን ጠራርጎ ማውጣት እሳቱ ከጠፋ በኋላ። አሁን ይሄ አይነት ቃጠሎ በምን እንደተፈጠረ አይታወቅም” ብለዋል።
“ሆን ተብሎ በሰው” የደረሱ 10 ቃጠሎች በፈጸሙ እርምጃ ተወስዷባቸዋል? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ የሰጡን ምላሽ፣ ደግሞ፣ “ተጠያቄ ይሆናሉ ተጣርቶ። ይሄ ፕሮሰስ ላይ ነው። ኢቪደንሱ ተገኝቷል። በዚህ ኢቪደንስ መሰረት ይጠየቃሉ” የሚል ነው።
“ለምሳሌ አንድ ሰው ‘ራሱን አቃጥሎ ነው የሞተው’ ብሎ ሰው ቢገድል ኢቪደንሱ ሲገኝ፣ ግድያው በሰው መሆኑ ሲረጋገጥ ለግድያውም ተጠያቂ ነው የሚሆነው” ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን ያክል ሰዎች ናቸው? “ሆን” ብለው በማቃጠል የተጠረጠሩት? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ኃላፊው፣ “አሁን ስለእሳቱ ብቻ ነው መግለጽ የፈለግነው። ወደፊት ይገለጻል” ከማለት ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
በቸልተኝነት የደረሰ ቃጠሎ ማለትስ ምን ማለት ነው? ለሚለው ጥያቄም፣ “ለምሳሌ ሻማ አቀጣጥሎ ሳያጠፋ ቢተኛ፣ ተሽከርካሪ ላይ ጌጁ ሙቀት መጨመሩን እያሳዬ አሽከርካሪው እርምጃ ካልወሰደ በቸልተኝነት ይቃጠላል እንደዛ ማለት ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“በቸልተኝነት ማለት ባልተገባ ሁኔታ ወይም በነግሊጀንስ ማለት ነው” ነው ያሉት አቶ ጀይሉ።
ደረሱ በተባሉት 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ምን ያክል ንብረት እንደወመስ ታውቋል? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ፣ “እሱ ሌላ ነው። አሁን ዋናው ነገር በምን ተቃጠለ የሚለው ነው የተጣራው” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#USA
አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን አፍና ገደለች።
አሜሪካዊው የ52 ዓመቱ ድሜትሪስ ፍሬዘር በአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
ግለሰቡ በአላባማ በርሚንግሀም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፓውሊን ብራውን የተባለች የ2 ልጆች እናትን በመኖሪያ ቤቷ ገብቶ አስገድዶ ከደፈረ በኋላ #እንደገደላት ተገልጿል።
በሌላ ጊዜ የ14 ታዳጊ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙ መረጋገጡን ተከትሎ በተደራራቢ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበት ነበር።
ይህንንም ተከትሎ ተከሳሽ ድሚትሪስ ፍሬዘር በሞት ፍርድ እንዲቀጣ የተላለፈበት ሲሆን የፍርድ ሂደቱ የተካሄደው የሞት ፍርድ የማይተላለፍበት ሚቺጋን ግዛት ውስጥ በመሆኑ ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮለት ነበር።
በአላባማ ወንጀል መፈጸሙ በፍርድ ቤት መረጋገጡን ተከትሎ ወደ አላባማ እስር ቤት ተላልፎ ሊሰጥ ችሏል።
አላባማ ግዛት የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ፍርደኞችን አየር አጥሯቸው እንዲሞቱ የሚያደርግ ህግ ስላላት ይህም ወንጀለኛ በናይትሮጅን ጋዝ ታፍኖ ህይወቱ እንዲያልፍ መደረጉን ሮይተርስን ዋቢ በማድረግ አል አይን ኒውስ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
#Tigray
በእንዳስላሴ ሽረ ከተማ በህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ የእጅ ቦምብ 10 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉደት ደረሰባቸው።
የሰው ህይወት አለማለፉን ለመረዳት ተችሏል።
የቦምብ ጥቃቱ አድራሾች እና ግብረ አበሮቻቸው ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እና ምርመራ እያደረግኩ ነው ብሏል ፖሊስ።
ጥቃቱ መቼና ? የት ? እንዴት አጋጠመ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፤ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞችን አግኝቶ አነጋግሯል።
ጥቃቱ የካቲት 3/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ቀበሌ 05 በሚገኝ የአንድ ግለሰብ የመዝናኛ ስፍራ ነው የደረሰው።
የመዝናኛ ቤቱ ባለቤት ሰሞኑን ከማያወቀው ሰው በሞባይል እየተደወለ የማስፈራርያ መልእክት ይደርሰው እንደነበር ፤ የመልእክቱ አንኳር ነጥብ " እስከ 400 ሺህ ብር እንዲከፍል " ይህንን ካላደረገ ግን አደጋ እንደሚደርስበት የሚገልጽ ማስጠንቀቅያ ነው።
ግለደቡ የማስፈራርያ ዛቻውን በሰዓቱ ለፓሊስ ያደርስ እንደነበረ ነው የተነገረ ሲሆን ጥቃቱ ከመድረሱ ከአንድ ቀን በፊት ሳይቀር ዛቻውን ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር።
የመዝናኛ ቤቱ ባለቤት ስጋቱ አይሎበት ፓሊስ ጣብያ ድረስ በመሄድ የጉዳዩን አሳሲበነት አስረድቶ ፓሊስ በተባለው አከባቢ ከየካቲት 2/2017 ዓ.ም በመከታተል እያለ ቦምቡ መጣሉ ከከተማው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ ያመልክታል።
የተጣለው ቦምብ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን አንድ ሴት የምትገኝባቸው ሦስት ሰዎች ላይ ከባድ ፡ ሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የከተማው ፓሊስ ተጠርጣሪዎች ከግብረ አበሮቻቸው ጋር ለመያዝ ክትትል እና ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉ ገልፆ ህዝቡ መረጃ በመስጠት ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።
ከቀናት በፊትም በከተማዋ በአስፋልት ዳር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች አንድ ሰው ተገድሎ መገኘቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን አጋርቶናል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
ለሀጅ ጉዞዎ አስቀድመው በመቆጠብ ህልምዎን ዕውን ያድርጉ!
ወጋገን ባንክ በወጋገን አማና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱ ለሀጅ ጉዞ የሚውል ሀጅ ሙዳረባ የተሰኘ ትርፍን የሚያጋራ የቁጠባ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቹ በአክብሮት ይገልፃል፡፡
ስለሆነም እርስዎም ወጋገን ባንክ የሸሪዓን ህግጋት መሰረት አድርጎ በሚሰጠው ሀጅ ሙዳረባ የቁጠባ ሂሳብ አስቀድመው በመቆጠብ የሀጅ ጉዞ ህልምዎን ከወዲሁ ዕውን እንዲያደርጉ ስንጋብዝዎ በደስታ ነው!
#WegagenBank #Bank
Follow us and get more information...
https://linktr.ee/WegagenBank
" የግለሰቧ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የልደት ምስል ቀረጻ ከተቋሙ አመራሮች እውቅና ውጭ የተደረገ ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው የልደት ምስል ቀረጻ ከተቋሙ ማናጅመንት እውቅና ውጭ የተደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ " አንዲት ግለሰብ በአውሮፕላኑ መወጣጫ ደረጃ ላይ የተለያዩ ዲኮሮችን በማድረግ የተነሳችው ፎቶ ሲዘዋወር ታይቷል ፤ ግለሰቧ የተነሳችው ለጥገና በቆመ አውሮፕላን ላይ ነው " ብሏል።
" ድርጊቱ ከተቋሙ አመራሮች እውቅና ውጭ የተደረገ ነው " ሲልም ገልጿል።
" ይህ ክስተት ስላስከተለው ማንኛውም አይነት ችግር ወይም አሉታዊ ግንዛቤ ከልብ እናዝናለን " ያለው ተቋሙ " በአሁኑ ወቅት ጉዳዩን እየመረመርን ነው የተቋሙም አሰራር ሳይከተሉ ይህንን ዝግጅት ባዘጋጁት ላይ የእርምት እርምጃ ይወሰዳል " ሲል አሳውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቪዲዮው ላይ ከምትታየው ግለሰብ ምንም አይነት ክፍያ እንዳልተቀበለ እና ከግለሰቧ ጋር ምንም አይነት የውል ስምምነት እንደሌለው ህዝቡ ይወቅልኝ ብሏል።
አየር መንገዱ ውስጥ ይህ ሁሉ ሲፈፀም እና ሲከናወን የአየር መንገዱ አካላት የት ነበሩ ? ያመቻቸውስ ማነው ? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው።
@tikvahethiopia
“ ገዢው ብልጽግና እንደ ፓርቲም አንቆጥረውም ” - አዲሱ የመኢአድ ተሿሚ ፕሬዜዳንት
መላው ኢትዮጵያ አንድነት ደርጅት (መኢአድ) በቅርቡ ፓርቲውን ለስድስት ዓመታት በመሩት አቶ ማሙሸት አማረ ምትክ አቶ አብርሃም ጌጡን ፕሬዜዳንት አድርጎ ሾሟል።
አንዲሱ የፓርቲው ፕሬዜዳንትም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገዢውን ፓርቲ በብርቱ ተችተዋል።
" ጠባብ " የሚል ትችት የሚሰነዘርበት የኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳርን ለመቋቋም ምን ያህል ተዘጋጅተዋል ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው ተሿሚው ብርቱ ትችት ያነገበ ምላሽ ሰጥተዋል።
አዲሱ የመኢዓድ ተሿሚ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም ጌጡ ምን አሉ ?
“ እንደ ተመራጭ መሪ በድንገት አይደለም የመጣሁት፡፡ ለ26 አካካቢ ዓመታት ፖልቲካሊ አክቲቭ ሆኘ ረጅም ትግል እያደረኩ ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር የመኢአድ አባላትም ከፍተኛውን ድምጽ ሰጥተውኛል፡፡
በኢትዮጵያ ፖለቲካ መጻዒው እጣ ፋንታችን ስናየው እውነት ለመናገር የአሁኑን ገዢ ፓርቲ ፓርቲ ነው ብለን ለመናገርም ይከብዳል፡፡ ገዢ ፓርቲ የሚባለው ሁሉንም እኩል የሚገዛ ነውና፡፡ መልቲ ፓርቲ ሲስተም የተገነባባቸው ዓለማት የሚመሩት በዴሞክራሲ ህግ ነው፡፡
የዴሞክራሲ ስርዓት የሚያድግ የነበረው ደግሞ በዚያች አገር በሚኖረው የፖለቲካ ኃይል ነው፡፡ የኛ አገር የፖለቲካ ሂደትና ባህሪ ምን ነበር ? አሁንስ ምን እየሆንን ነው? ብለን ስናስብ ገዢ ፓርቲ አለ ማለት አይቻልም፡፡
ገዢ ፓርቲ የፖለቲካ ስፔሱ ነጻ ሆኖ የፓለቲካ አክተሮች ሜዳው ላይ ወርደው፣ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ ሰጥተው መራጩም ተመራጩም ተሳትፎ ወደ ስልጣን የሚመጣበት መሆን አለበት፡፡
የመረጠውንም ያልመረጠውንም እኩል ማስተዳደር፣ ኃላፊነቱን፣ ግዴታውን ሲወጣ ገዢ ፓርቲ ይባላል፡፡ ከዚህ አንፃር ገዢውን ብልጽግና እንደ ፓርቲም አንቆጥረውም፡፡ ፓርቲ በውስጡ ብዙ ነገሮችን መያዝ አለበት።
የፓለቲካ ፓርቲ ማለት የራሱ ፕሮግራም፣ ርዕዮተዓለም፣ አደረጃጀት ያለው ነው፡፡ አሁን ስልጣን ላይ ያለው የፖለቲካ ኃይል ፋንዳሜንታል የሆኑ ነገሮች በውስጡ የሉትም፡
ዝም ብሎ የተደራጀ፣ የሕዝብ፣ ብሶትና ትግል በአጋጣሚ አስፈንጥሮ ወስዶ ቤተ መንግስት ያስቀመጠው የፖለቲካ ኃይል ነው፡፡ ህዝቡ ከነበረበት የለውጥ ፍላጎት ተነስቶ መርጦታል፡፡
ከተመረጠ በኋላ ግን አገሪቱ ወዴት እየሄደች ነው? ምንድን ነው የሆነችው? ሰርቫይዝ ማድረግ የምትችልብት መሰረታዊ አገራዊ ምሰሶዎች አሉ ወይ? ተብሎ ሲታሰብ በጣም አደጋ ነው፡፡
ድሮ ኢትዮጵያ መስቀልኛ ጥያቄ ገብታለች እንል ነበር። መስቀልኛ ጥያቄ የሚባለው በመስቀልኛ ቦታ ተቁሞ ግራ ቀኝ ሲታይ ነውና አሁን ግን መቆምም አይቻለም፡፡ መቆሚያ፣ መንቀሳቀሻ መሬት የለም።
የጸጥታና ሰላምን የሚያስከብር ኃይል በሌለበት ቀጣይ የአገሪቱ የፖለቲካ እጣፋንታ ምን ይሆናል? ለሚለው ጥያቄ ፈጣሪ እጁን ዘርግቶ ኢትዮጵያን ካልጠበቃት አሁን ባለው ተጨባጪ ሁኔታ ከባድ አደጋ ላይ ናት።
ይህን ብለን ግን በዝምታ ቁጭ እንልም፡፡ መኢዓድ ፓርቲ ኢትዮጵያዊነትን በማስቀደም በቀጣይ አሸናፊ ሆኖ ሊወጣ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም የአንድንት ኃይሎች የሚባሉትን አሰብስብን የፖለቲካ ትግል ያደርጋል።
መንግስት የህዝብን ድምጽና ሰቆቃ አዳምጦ የፖለቲካ መፍትሄ ሊሰጥ ተቋቋመ ተቋም መሆን አለበትና አብሶሉት ሞናርኪዎች ሲያደርጉት እንደነበረው እንዲያደርግ አንፈቅድለትም፡፡ ለዚህም ብርቱ ትግል እናደርጋለን፡፡
ሰው ሚያሳድዱ፣ የሚያግቱ፣ በመሳሪያ የሚጨፈጭፉ አካላት ስልጣንን መከታ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ግን በየትኛውም መስኮት ሂደው መደበቅ አይችሉም፡፡ ይህን እንነግራቸዋለን። የፖለቲካ ጥበቡ ለህዝብ መፍትሄ መፈለግ ነውና እሱን እናሳያለን ” ብለዋል።
በቀጣዩ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ያላቸውን ዝግጅትና ፓለቲካዊ አስቻይ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ፣ “ የመጀመሪያ ስራችን በምርጫና ሥራ ወደ ስልጣን መምጣት ነው ” ሲሉ መልሰዋል።
“ ይህን ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን። ህዝቡ በቲፎዞ ካርድ መብቱን ሰጥቶ እንደአሁኑ ቤቱ እንዲፈርስ፣ ህልውናውን እንዲያጣ አናደርግም። ኢትዮጵያ በከፍተኛ ችግር እንዳለች የሚጠባ ህጻን የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን አስተካክለን ጥሩ ተመራጮች ሆነን ለመቅረብ ዝግጅት እያደረግን ነው ” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
መክፈል አልተመቸኝም የማይሉበት!
ብርሃን ስኩል_ፔይ ባሉበት ቦታ ሆነው ለልጆችዎ ትምህርት ቤት ክፍያ ሳያስቡ; በብርሃን ሞባይል ባንኪንግ ወይም ኢንተርኔት ባንኪንግ ተጠቅመው ክፍያ የሚፈፅሙበት ምቹ አገልግሎት ነው።
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን፡፡
#schpay #berhanschoolpay #schoolfee #payment #berhanbank #bank #stressfreebanking #bankinethiopia
🔊 #የሠራተኞችድምጽ
" ቋሚ ሠራተኞች ሆነን ሳለ በደሞዝ ማሻሻያው አልተካተትንም " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ሠራተኞች
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙን ተከትሎ የሚከሰቱ የኑሮ ዉድነትና ተያያዥ ጉዳዮችን ታሳቢ በማድረግ የመንግስት ሠራተኞች ደሞዝ ማሻሻያ ተደርጎ ከጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
በሲዳማ ክልል፤ ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን፤ ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ የመንግስት ሠራተኞች ግን " ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በቋሚነት ተቀጥረን እየሰራን ያለን ቢሆንም በአዲሱ የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ አልተካተትንም " ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስገብተዋል።
ቅሬታቸዉን ካደረሱን መካከል ፦
- በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን፣
- ማዘጋጃ ቤቶች፣
- በትምህርት ዘርፍ ፣
- በሴቶችና ሕፃናት እንዲሁም በሕብረት ስራ ጽ/ቤቶች የሚሰሩ ሠራተኞች ናቸው።
" በወቅቱ በአግባቡ ማስታወቂያ ወጥቶ ተመዝግበንና ተወዳድረን ማለፋችን ተረጋግጦ የቋሚነት ደብዳቤ ተሰጥቶን ላለፉት አምስትና ስድስት ዓመታት ደሞዝ ሲከፈለን በቆየንባቸው መደቦች ላይ እየሰራን ባለንበት በአዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ አለመካተታችን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርጎናል " ብለዋል።
" ለወረዳዉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ጽ/ቤት እና ለክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ቅሬታችንን በአካልና በፅሁፍ ብናቀርብም ተገቢዉ ምላሽ አልተሰጠንም ጉዳዩን ለኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም ለማቅረብ መረጃ እያደራጀን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ፤ የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አቢኖ ፥ " በወረዳዉ በ2012 ዓ/ም የነበረው አግባብነት በሌለው ቅጥር በአንድ መደብ ሶስትና አራት ሰዎችን በተደራራቢነት የመቅጠር ሁኔታዎች አሁን ለተፈጠረው ችግር ዋነኛ ምክንያት ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።
ከዞኑና የክልሉ ፐብልክ ሰርቪስ ጋር በመናበብ መፍትሔ እያፈላለጉ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
በወቅቱ ይህን ተግባር የፈፀሙ አመራሮች እና የሰዉ ሃብት ልማት ኃላፊዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የሚናገሩት ኃላፊዉ በወረዳዉ በዚህ መልክ ተጠቀጥረዉ በአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ያልካተቱና በቀጣይ መፍትሔ የሚፈለግላቸዉ 470 በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ዉስጥ የተለዩ ሰራተኞች ስለመኖራቸዉ አክለዋል።
የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ፐብልክ ሰርቪስና የሰዉ ሃይል ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ በዛብህ ባርሶ በበኩላቸው በ2011 እና 2012 በአከባቢው ሕገወጥ ቅጥሮች መፈፀማቸውን ገልጸዋል።
በወረዳዉ አጣሪ ቡድን ተቋቁሞ በአዲሱ ደሞዝ ያልተካተቱንና በወረዳው ቅጥር ያልተፈፀመባቸዉ ክፍት መደቦችን የመለየት ስራ መከናወኑን አንስተዉ በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ብቻ 407 ክፍት መደቦች መኖራቸዉን ለማወቅ መቻሉን ገልፀዋል።
የክልሉ የበላይ አመራሮች በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መሰረት እነዚህን ሠራተኞች በነዚህ ክፍት መደቦች የመደልደልና ሌሎችም ሕጋዊ አመራጮች በመፈለግ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እልባት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስከመጨረሻ ተከታትሎ መረጃውን ይልካል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
ልታስመርቀዉ ከቤተሰቦቿ ተደብቃ የመጣች እጮኛዉን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የገደለዉ ግለሰብ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ጉርባ በሚባል ቀበሌ የገዛ እጮኛዉን ጭካኔ በተሞላበት መልኩ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት አንገቷን በመቁረጥ ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገዉ ወጣት በፅኑ እስራት መቀጣቱን የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ጋፋሮ ቶማስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ ነሐሴ 16/2016 ዓ/ም በአርባምንጭ ከተማ ጉርባ ቀበሌ ነው።
ተከሳሽ ዮናስ ጫፊቄ የተባለው ግለሰብ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ዓመት ተማሪ የሆነችዉን ሟች ሊዲያ ዮሐንስ እሱን ለማስመረቅ ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በመጣችበት ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት አሰቃቂ ድርጊቱን መፈፀሙን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።
ወጣቷ " እጮኛዬ ይመረቅልኛል " በሚል ደስታ ከቤተሰቦቿ ተደብቃ ተከሳሽ ተከራይቶ ወደ ሚማርበት ቤት መጥታ በዋዜማዉ ለምረቃዉ የሚሆኑ የዲኮር፣ የዳቦና ለስላሳ መጠጦችና በቡና ዝግጅት ቤቱን አሰማምራ በምሽቱም ግቢ ዉስጥ ያሉ ተከራዮችን ጠርተዉ ከሸኙ በኋላ ሟች ሀገር ሰላም ብላ በተኛችበት ከሌሊቱ 7 ሰዓት ገደማ እራሷን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ በቢላዋ አንገቷን አርዶ መግደሉን የምርመራ መዝገቡን ዋቢ አድርገው ፖሊስ አዛዡ ገልፀዋል።
ፖሊስ አዛዡ አክለው እንደገለጹት ፥ በወቅቱ በተደረገዉ ማጣራትም ሆነ በክስ መዝገቡ ላይ እንደሰፈረዉ ወንጀለኛው " ወደ ዩኒቨርሲቲ በሄድሽበት ሌላ የወንድ ጓደኛ ይዘሻል " በሚል ነው በር ዘግቶ አሰቃቂ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው።
ፖሊስ በዚህ ዘግናኝ ወንጀል ዙሪያ ተገቢዉን ማጣራትና ምርመራ አድርጎ ለዐቃቤ ሕግ ማቅረቡን አስታውቀዋል።
ዐቃቤ ሕግም ክስ በመመስረት ለፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙን የሰዉ፣ የሰነድና የህክምና ማስረጃዎችን በማቅረብ አስረድቷል።
በቀረቡ ማስረጃዎች እና ምስክሮች ግራ ቀኙን ሲያጣራ የቆየዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት በቀን 29/5/2017 ዓም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ዮናስ ጨፊቄ በተከሰሰበት በአሰቃቂ ሁኔታ ነብስ የማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑንም ኢንስፔክተር ጋፋሮ ቶማስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
" የመክፈያ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብራችሁን ያልከፈላችሁ እንድትከፍሉ እናሳስባለን " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ " በተለመዶ የጣራና ግድግዳ ግብር እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩን ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ እንድትከፍሉ እናሳስባለን " ብሏል።
በዚሁ መግለጫው ግብሩ የከተማ ቦታና ቤት ግብር በከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 መሰረት የሚሰበሰብ ግብር መሆኑ መገንዘብ እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን 429 ሺህ 829 ግብርከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል ብሏል።
የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ግብር ከፋይ ነዋሪዎች ያለቅጣት መክፈያው ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከየካቲት 30 በፊት እንዲከፍሉ እና ያልከፈሉ ነዋሪዎች ግን ቅጣቱን ከነወለዱ ለመክፈል እንደሚገደዱ " ገልጸዋል።
አቶ ሰውነት " እናት ፓርቲ ካስተላለፈው መልእክት ጋር በተያያዘ እኛን የሚመለከተን ነገር የለም " ያሉ ሲሆን ለቢሮው የደረሰው ምንም አይነት የፍርድ ቤት እግድም ሆነ መመሪያ አለመኖሩን በመግለጽ " ሰው ጋር መዘናጋት ይታያል ይህ ደግሞ ለቅጣት ሊዳርጋቸው ይችላል በቀረው ጊዜ ክፍያችሁን ፈጽሙ " ሲሉ አሳስበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
ስለ M-PESA ኢትዮጵያ አዳዲስ ዜናዎች እና አገልግሎቶችን ለማወቅ ማህበራዊ ሚዲያ ገፃችንን እንቀላቀል! 💚📲
Telegram- /channel/+-cP9IxZdfKBkNTQ0
Facebook: https://www.facebook.com/share/14qsy45H7u/?mibextid=wwXIfr
Titkok- mpesa.ethiopia?_t=ZM-8tcz302wLwL&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@mpesa.ethiopia?_t=ZM-8tcz302wLwL&_r=1
LinkedIn- https://www.linkedin.com/company/m-pesaethiopia/about/
Instagram: https://www.instagram.com/mpesa.ethiopia/
Youtube- M-PESAEthiopia" rel="nofollow">http://www.youtube.com/@M-PESAEthiopia
Twitter- https://x.com/m_ethiopia58462?s=21
#MPESAEthiopia
" ለቅሬታችን ተገቢዉን ምላሽ ባለማግኘታችን ለርዕሰ መስተዳድሩ አቅርበናል " - የአረካ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መምህራን
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን አረካ ከተማ በሚገኘዉ የአረካ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የሚሰሩ አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ክፍያ " አልተከፈለንም " ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።
በቁጥር ከአንድ መቶ በላይ የሆኑ የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በአድራሻ የፃፉትንና የተፈራረሙበትን የቅሬታ ደብዳቤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስገብተዋል።
ሰራተኞቹ በሰጡት ቃልም " መንግስት ለኑሮ ዉድነት ማካካሻ በማለት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥቅምት 1/2017ዓ/ም ጀምሮ ክፍያ የፈፀመ ቢሆንም እስካሁን የማሻሻያዉ ልዩነት አልተከገለንም " ሲሉ ገልፀዋል።
" ስራ ሳናቆም ተደጋጋሚ ቅሬታ ስናቀርብ ቆይተናል " የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ " ከዚህ ቀደም ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ አብዘኞቻችን የተሰጠንን የደረጃ ዕድገት ክፊያ ተግባራዊ አልተደረገም በዚያ ላይ ይህ ሲጨመርበት ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እየዳረገን ነዉ " ብለዋል።
ኮሌጁ ስለ ጉዳዩ ምን ይላል ?
የአረካ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ ጻድቁ ሳሙኤል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ የደሞዝ ማሻሻያው አለመከፈሉ ትክክል መሆኑን አረጋግጠዋል።
" የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ በክልሉ ያሉ የሁሉም ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎችን መረጃ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በመሰብሰብና በማደረጃት ክፍያዉን እንደሚፈፅም ምላሽ ስለሰጠ እየተጠባበቅን እንገኛለን " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደቡብ ኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮን ምላሽም ጠይቋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቢዮት ደምሴ በቢሯቸዉና በክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ እጅ ያለዉ የሰራተኞች ቁጥር መረጃ ከ5 መቶ በላይ ሰዉ የቁጥር ልዩነት በማሳየቱ የማጣራቱ ስራ እስኪጠናቀቅ ክፍያው አለመፈፀሙን ተናግረዋል።
" አሁን ላይ ሁሉም ኮሌጆች መረጃዎችን አጠናቀዉ ወደ ፐብሊክ ሰርቪስ የመላኩ ስራ ስለተጠናቀቀ በአጭር ቀናት ዉስጥ ችግሩ ይፈታል " ሲቡ ያላቸዉን ሙሉ እምነት ገልፀዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክንክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ስር 35 ኮሌጆች መኖራቸዉን ከነዚህም ዉስጥ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ በሚገኘዉ አረካ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከ150 በላይ አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ስለመኖራቸዉ ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
🔈 #የሹፌሮችድምጽ
“ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ባለማድረጋቸው ለአጃቢ እስከ 2,000 ብር ለመክፈል ተገደናል። በቀናት ብቻ ከ12 በላይ ሹፌሮች ታግተዋል ” - ማኀበሩ
የጸጥታ መደፍረስ በሹፌሮችና ተሳፋሪዎች ግድያና እገታ ማስከተሉን፣ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ባለማድረጋቸው አሽከርካሪዎች ለአጃቢ 2,000 ለመክፈል መገደዳቸውን ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
“ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ባለማድረጋቸው ለአጃቢ እስከ 2,000 ብር ለመክፈል ተገደናል። በቀናት ብቻ ከ12 በላይ ሹፌሮች ታግተዋል ” ሲልም በሁነቱ ተማሯል።
በአማራ ክልል ከገንዳውሃ ወደ ጎንደር ባለው መንገድ ረቡዕ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ/ም አንድ ሰው ተገድሎ፣ ሁለቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጿል።
“ በአስር ቀናት ደቡብ ጎንደር 3 ሹፌሮች፣ በደባርቅ ዙሪያ 2 ረዳቶችና 6 ሹፌሮች፣ ገንዳውሃ 2 ሹፌሮች፣ አብርሃጀራ አንድ ሹፌር በታጠቁ አካላት ታግተዋል። በአብርሃጅራ ሹፌር ተተኩሶበት አምልጧል፤ ሁለት ቦቴዎችን ወቅንና ገደብዬ መካከል አግተዋቸዋል ” ነው ያለው።
ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል በዝርዝር ምን አለ ?
“ ከአሸሬ እስከ ሶረቃ የሚያስፈራ ቦታ አለ። በፈቃድ ለታጠቁ የአካባቢው ሰዎች 2,000 ብር እየከፈልን ነው የምናልፈው። በቅርቡ አንድ አጃቢ አጋች መትቷል ሹፌር ሊያግት ሲል ወርዶ ተኮሰበት።
ጨንቆን ነው እንጂ ይሄ ሂደት ደግሞ መጥፎ ነው። ህግ ባለመከበሩ ምክንያት ለሹፌሮች እለታዊ መፍትሄ ሆኗል። ግን የአጃቢነት ስራ እየሰሩ ያሉ ሰዎች እንዴት ነው የአካባቢ ሰላም እንዲመለስ የሚፈልጉት?
ስለዚህ እገታ ያለባቸው ቦታዎች ይታወቃሉ። በአርማጭሆ በኩል ከከተማው አፍንጫ ስር ከ10 ጊዜ በላይ እገታ ተፈጽሞበት ቦታው ላይ የጸጥታ አካል አይቀመጥም።
የጸጥታ ዘርፉ ትኩረት ቢሰጥ ችግሩን መቆጣጠር ይችላል። ምክንያቱም በአንድ አጃቢ ከፍለን የምናልፈው አካባቢ ነው። መዝረፊያ በሮች የሚታወቁ ናቸው” ብሏል።
ለአጃቢ ከመክፈል በተጨማሪ ሹፌሮች ከጸጥታ ስጋት አንጻር በ100ዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ዙሪያ ጥምጥም እንዲጓዙ እየተገደዱ መሆኑም ተገልጿል።
ማኀበሩ በመንገዱ ዙሪያ ምን አለ ?
“ በደባርቅ በኩል ባለው መንገድ ከደብረ ታቦር ጋይንት መንገዱ ችግር ትልቅ አለበት። መንገዱ አማራ ክልል ከጅቡቲ የሚገናኝበት ነው። ማደበሪያ የሚገባው በጋይንት ነው። በሚሌ፣ ጭፍራ፣ ሃራ፣ ወልዲያ አድርጎ በደብረ ታቦር አድርጎ ይመጣል።
ግን ማዳበሪያ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች በዚህ አመት በጸጥታው ችግር ምክንያት ተጨማሪ መንገድ እየተጓዙ በአዲስ አበባ በኩል ለመምጣት ተገደዋል። ከደጀን በእጀባ ነው የሚመጡት ወደ ጎጃምና ጎንደር ጭምር።
በጸጥታው ችግር ተሽከርካሪዎች ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ ተጨማሪ መንገድ ለመሄድ ተገደዋል። ይህ ለአርሶ አደሩም ጉዳት አለው። 1,950 ብር ነው አንድ ኩንታል ማዳበሪያ ከጅቡቲ የሚመጣው። ትራንስፓርት ኮስቱ 1,900 ብር ሲሆን፣ የማዳበሪያው ዋጋ ይንራል።
በጋይንት ቦቴዎች ይሄዳሉ። ጭነው ይመጡና በጸጥታው ችግር መመለሻ ሲያጡ በደባርቅ፣ ዛሪማ፣ በሽሬ፣ ከሽሬ መቀሌ፣ ከመቀሌ አብዓላ አድርገው በአፍዴራ ይወጣሉ። ይሄ ማለት ከ600 በላይ ተጨማሪ ኪሎ ሜትር ይጓዛሉ።
በጎንደር መተማ መንገድ በመተማ በኩል ነው ኢምፖርት ኤክስፖርት የሚገባው። የመተማ ጎንደርን መንገድ የጸጥታ ችግሩን በመፍራት አሽከርካሪዎች በአብርሃጅራ ዙረው እየገቡ ነው።
180 ኪሎ ሜትር ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች 140 ኪሎ ሜትር በመጨመር 320 ኪሎ ሜትር ይጓዛሉ ” ብሏል።
(ስለጉዳዩ ለጸጥታ አካላት ጥያቄ የምናቀርብ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ከሞተር ሣይክል ሲቀነስ በነበረ ቤንዚን ምክንያት የተነሳ እሳት አንድ ቤት መሉ በሙሉ ሲያወድም በሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል " - የታርጫ ከተማ ፖሊስ
በዳዉሮ ዞን የተርጫ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ሙሉጌታ መንግስቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳስታወቁት በትናንትናው ዕለት ምሽት 2 ሰዓት ገደማ በከተማ አስተዳደሩ " ቦዲ ቀበሌ " አንድ ግለሰብ ከማደያ በሞተር ሣይክል የቀዳዉን ቤንዚን ወደ ፕላስትክ ሀይላንዶች እየቀነሰ በነበረበት ወቅት ለብርሃን ተብሎ ከተለኮሰዉ ሻማ ከቤንዚኑ ጋር በመሳሳቡ ምክንያት በተፈጠረ የእሳት አደጋ ከቁጥጥር ዉጪ በመሆኑ ጉዳት ማድረሱን አስታዉቀዋል።
ሰዓቱ አመሻሽና ወቅቱም ነፋሻማ ስለነበር እሳቱን በቀላሉ ለመቆጣጠር አዳጋች አድርጎት እንደነበር ተናግረዋል።
ፖሊስ አዛዡ እሳቱን ለማጥፋት የአካባቢዉ ሕብረተሰብ በነቂስ ባይረባረብ ግለሰቡም ሆነ ባለቤቱ ሕይወታቸዉ ያልፍ እንደነበር ተናግረዋል።
በአደጋዉ አቶ አስናቀ አበራ በተባሉ ግለሰብና ባለቤታቸዉ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የአደጋዉ መንስኤ የነበረዉን ሞተር ሳይክል ጨምሮ ቤታቸውም ሙሉ በሙሉ መዉደሙን ፖሊስ አስታዉቋል።
በአሁኑ ወቅተም ጉዳት የደረሰባቸውን ሁለቱ ግለሰቦች በታርጫ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየየተደረገላቸው ነው።
የቤንዚን እጥረት መኖሩን ተከትሎ በየአካባቢው በየቤቱ የሚደረጉ የቤንዚን ማከማቸት ለእሳት አደጋዎች ምክንያት በመሆን በሰዉ ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም ም/ኢንስፔክተር ሙልጌታ መንግስቱ አሳስበዋል።
@tikvahethiopia
#ነዳጅ
የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።
የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
➡ አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር
➡ አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር
➡ አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር
➡ የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር
➡ አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር
➡ አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር
#ነዳጅ #ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ተወሰነ።
ከዚህ ቀደም የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑ ተገልጾ ነበር።
በዚህ መሰረት ቁጥራቸው 88,717 የሆኑ ግብር ከፋዮች የህትመት ጥያቄ ማቅረብ መቻላቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ገልጸዋል፡፡
ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ጥያቄያቸውን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸው ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም በውይይቱ ተወስኗል፡፡
እስከ አሁን ድርስ የህትምት ጥያቄ ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የህትምት ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተባለ ሲሆን የሲስተም መጨናነቅ እንዳይፈጠር የሲስተም ማሻሻያዎችን ማከናውን፣ የህትመት እና ስርጭት ተግባራት በሚፈለገው ደረጃ ለማከናወን ተጨማሪ የህትመት ማሽኖችን ወደ ስራ ማስገባት እና አትሞ በፍጥነት ማሰራጨት እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።
@tikvahethiopia
➡️ " ቆጣሪው መንገድ ላይ ያለ በመሆኑ ማንም ሰው እየቀጠለ ይጠቀማል ሌሎች በተጠቀሙት እኛ ልንጠየቅ አይገባም " -ነዋሪዎች
🔴 " ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን መረጃ ከእናንተ እንፈልጋለን " -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
በቦሌ አራብሳ ሳይት 3 ብሎክ 534 እና 535 ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር የገቡበትን ውዝግብ በሚመለከት የአገልግሎቱ የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ በአካባቢው በመገኘት እውነታውን መመልከት እንደሚቻል ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
በዚህም መሰረት ያለውን እውነታ ለመመልከት እና ቅሬታውን ለመፍታት ከቀናት በፊት የአገልግሎቱ የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር ፣ የሪጅኑ የህግ ክፍል፣ የጸጥታ አካላት እና ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ምልከታ ተደርጓል።
በምልከታው ወቅትም የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብም በቦታው በመገኘት ከአገልግሎቱ ሃላፊዎች እና ነዋሪዎች እውነታውን ለመመልከት ጥረት አድርጓል።
አገልግሎቱ በአራብሳ የጋራ መኖሪያ መንደር ሳይት ሶስት ሃይልን ከቆጣሪ ላይ በህገወጥ መንገድ ቀጥለው ሲጠቀሙ እንደተደረሰባቸው በመግለጽ የቆጣሪውን እዳ እንዲከፍሉ በማሳወቅ ሃይል ያቋረጠባቸው ብሎኮች 534፣ 535፣ 550 እና 551 ናቸው።
የቲክቫህ አባል ቦታው ተገኝቶ እንደተመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት " በህገ-ወጥ መንገድ ቆጣሪን እንዳይቆጥር በማድረግ ሃይል ሲጠቀሙ እንደነበር ደርሼበታለሁ " በማለት ሃይል ካቋረጠባቸው አራት ብሎኮች ውስጥ ሁለቱ ማለትም ብሎክ 550 እና 551 ሃይል ተቀጥሎላቸው አገልግሎት እያገኙ ነበር።
የእነዚህ ቆጣሪዎች እዳ ባልተከፈለበት እና ከሌሎች ብሎኮች ጋር በጋራ ሃይል በተቋረጠበት ሁኔታ ለእነርሱ በማን እና በምን ሁኔታ ተቀጠለ ? የሚል ጥያቄ ለሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
ዳይሬክተሩም ፤ የቆጣሪዎቹ እዳ ባልተከፈለበት ሁኔታ የእነሱ ሃይል መጠቀም ከእርሳቸው እውቅና ውጪ መሆኑን ገልጸዋል።
ከተቋረጠ በኃላ በራሳቸው ሃይሉን ቀጥለው ይጠቀሙ ወይስ የአገልግሎቱ ሰው ቀጠለላቸው የሚለውን ጉዳይ ማጣራት በማድረግ " አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።
በመቀጠለም ምልከታ የተደረገው ብሎክ 534 እና 535 ላይ ሲሆን እነዚህ ብሎኮች " ሃይል በህገ ወጥ መንገድ ቀጥለው ሲጠቀሙ በኢንስፔክሽን ወቅት ተገኝተዋል " በሚል ሃይል ከተቋረጠባቸው ወር እንዳለፋቸው ተናግረዋል።
አገልግሎት በበኩሉ " ሃይሉን ያቋረጥኩት ከጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች ለአንድ ዓመት ከአራት ወር በላይ ቀጥዬ ተጠቅሚያለው ያሉ እና የሚጠቀምም ስለመኖሩ በደረሰኝ ጥቆማ መሰረት ነው " ብሏል።
ነዋሪዎች ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ቀጥለው አለመጠቀማቸውን ተከራክረዋል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሞያዎች ግን የቆጣሪውን ሃይል ባቋረጡበት ወቅት እነዚህ ብሎኮች መጨለማቸውን እንደማስረጃ በመጥቀስ ሃይል በህገወጥ መንገድ እየተጠቀሙ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል።
" ሃይል የተቋረጠብን ለብሎካችን የገባው ስሪ ፌዝ ቆጣሪ በመቆረጡ እንጂ ከተጠቀሰው ቆጣሪ ላይ ሃይል አልቀጠልንም " ሲሉ የተከራከሩት ነዋሪዎች " ቆጣሪው መንገድ ላይ ያለ በመሆኑ ማንም ሰው እየቀጠለ ይጠቀማል ሌሎች በተጠቀሙት እኛ ልንጠየቅ አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።
" ከጋራ መኖሪያ ብሎኩም የተጠቀመ ቢኖር ለይቶ እነሱን ተጠያቂ ማድረግ የአገልግሎቱ ሃላፊነት ነው ሁሉም ባላጠፋው ለወር ያህል ነዋሪው ለምን ይቀጣል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
አገልግሎቱም በምላሹ " ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን መረጃ ከእናንተ እንፈልጋለን " ቢልም ነዋሪዎች ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ በመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሪጅኑ ዳይሬክተር በቦታው በተገኙበት ወቅት ለነዋሪዎች መፍትሔ ለመስጠት ሃይሉን እንዲቀጠልላቸው ያደረጉ ሲሆን ለህገ ወጥ ድርጊት ምክንያት የተባለውን ቆጣሪም ከቦታው እንዲነሳ አድርገዋል።
ዳይሬክተሩ አቶ ብርሃኑ ሲጠቀሙ የነበሩትን አካላት ማንነት ከነዋሪዎቹ ወይም ኮሚቴዎቹ ማግኘት እንደሚፈልጉ እና በጊዜ ሂደት ማንነታቸውን የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የኤሌክትሪክ ሃይሉ በድጋሚ እንዲቀጠል በተደረገበት ወቅት በብሎኩ ካሉ ሁለት ቆጣሪዎች ለመታዘብ እንደተቻለው 1,500 ብር የተሞላው በ19/02/17 ዓ/ም የነበረ ቢሆንም ሃይል እስከተቋረጠበት 15/04/17 ዓም ድረስ ባለው ሁለት ወር ውስጥ ከካርዱ ጥቃም ላይ የዋለው ከ 10 ብር በታች ሆኖ ተገኝቷል።
" ቆጣሪው ሲገናኝ ያሳየው የብር መጠን 1,492. 5 አና 1,455.32 ብር ነው ይህ ማለት በ2 ወር ጊዜ ውስጥ የተጠቀሙት ከ10 ብር በታች ነው ይህ ሁሉ ህብረተሰብ በ10 ብር 2 ወር ሊጠቀም አይችልም ያማለት ቀጥታ ሲጠቀሙ እንደነበር ተጨባጭ ማስረጃ ነው " ሲሉ አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።
በብሎኮች በመዟዟር በተደረገው ምልከታ በቀጥታ ያለቆጣሪ ከመስመር ላይ በመቀጠል ሃይል የሚጠቀሙ ሰዎች ስለመኖራቸው ለመታዘዘብ ተችሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia