ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
" ከግምገማ በኋላ በደረስንበት ውጤት ነዋሪዎቹ መቶ በመቶ ጥፋተኞች ናቸው " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ለኮንስትራክሽን ሥራ በገቡ እና እንዲነሱ ባልተደረጉ ቆጣሪዎች ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ከእነዚህ ቆጣሪዎች በህገወጥ መንገድ ሃይል እንዲጠቀሙ ምክንያት ሆኗል መባሉ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተመዘገቡት ቆጣሪዎች አማካኝነት በጋራ መኖሪያ መንደሩ በሚኖሩ ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ አገልግሎት ላይ የዋለ ከ400 ሺህ ብር በላይ እዳ ተመዝግቧል " ይከፈለኝ " ሲል በተደጋጋሚ ኮርፖሬሽኑን በደብዳቤ መጠየቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቆ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን ምላሽ ጠይቋል።
ኮርፖሬሽኑ ጥፋቱ ያለው ነዋሪዎች ጋር ነው ብሏል።
" በህገ ወጥ መልኩ ቀጥለው ለምን ጸጥ ብለው ይጠቀማሉ ? " ሲልም ጠይቋል። ' እንዳይቆጥር አድርገው ቀጥለው ሃይል ተጠቅመዋል ለገንዘቡም ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉት እነርሱ ናቸው " ሲል መልሷል።
ጉዳዩን በተመለከተ ግምገማ መደረጉ የገለጸው ኮርፖሬሽኑ " በደረስንበት ውጤት ነዋሪዎቹ መቶ በመቶ ጥፋተኞች ናቸው በቅርቡ የነዋሪ ኮሚቴን፣ ኮንትራክተሮችን ጠርተን የጠራ ነገር እንይዛለን " ሲል አሳውቋል።
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ በላይ ሞቱማ (ኢንጂነር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን ምላሽ ሰጡ ?
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/TikvahEthiopia-02-07
@tikvahethiopia
#Gambella
ከነገ ጀምሮ በጋምቤላ ክልል የመንግስት የሥራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል።
የሥራ ሰዓት ለውጥ የሚደረገው በሙቀት መጨመር ሳቢያ ነው።
በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለሥራ ምቹ ባለመሆኑ ከነገ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጀምረው የሥራ ሰዓት ለውጥ ለ3 ወራት ይቆያል።
በዚህ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 6 ፡30 የነበረው ከ1፡00 እስከ 5፡30 ይሆናል።
እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 9፡00 እስከ 11፡30 የነበረው ከ10፡00 እስከ 12፡30 እንዲሆን የክልሉ አስተዳደር ወስኗል።
የሥራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር ተጠቁሟል።
@tikvahethiopia
#ኦርቶዶክስተዋሕዶ #ጾመነነዌ
አባታዊ መልዕክት !
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከመግለጫቸው የተወሰደ ፦
" ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል።
ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣ የድርቅ መከሠት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን።
ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት 3 ቀን 2017 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን። "
(የቅዱስነታቸው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
ትግራይ ?
🔴 " በትግራይ በማንኛውም መመዘኛ ጦርነት የሚጋብዝ አንዳች ሁኔታ የለም " - በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት
🚨" በአሁኑ ወቅት በትግራይ በማንኛውም ደቂቃ በሆነ ሰው በሚፈጠር ስህተት ለግጭት የሚዳርግ ሁኔታ ሰፍቷል " - አቶ ጌታቸው ረዳ
ከቀናት በፊት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ተንተርሶ ለትግራይ ህዝብ በተለይም ለትግራይ ሊህቃን ጠንካራ መልዕክት እና ምክር ማስተላለፋቸው ይታወሳል።
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ፥ " ህዝቡ ያለፈው አልበቃ ብሎት የትናንት ቁስሉ ሳይሽር አሁንም በሽብር እና በጦርነት ወሬ ስሜት ወስጥ ይገኛል " ብለዋል።
በፓለቲካ ፣ በንግድ ፣ ፀጥታ ፣ አካዳሚ እና ሚድያ እና በሌሎች የስራ ዘርፎች ለተሰማሩ የትግራይ ልሂቃን ወገኖች ባስተላለፉት መልዕክት " የትግራይ ህዝብ እስከ ዛሬ የተሰቃየው የከፈለው ዋጋ ይብቃው ፤ ልዩነትን በመነጋገር እና በውይይት የመፍታት ባህልንና ልምድ ታጠቁ " ብለዋል።
ልሂቃኑ ከፌደራል መንግስት እና ሌሎች ሃይሎች ያላቸው ልዩነት በአገሪቱ ህገ-መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመግባባት ለመፍታት ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
ለዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ሄር ምላሽ ያሉትን ሰጥተዋል።
ምላሹን የሰጡት 50ኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ነው።
በደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ሄር ምን አሉ ?
➡️ " ጠቅላይ ሚንስትሩ የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ህልውና የነበረው ተሳትፎ አስመልክተው የተጠቀሙበት አገላለፅ ልክ ነው። የትግራይ ህዝብ ሚና ባሉት ደረጃ ነው መገለፅ ያለበት ብለን እናምናለን። የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ ነፃነት ፣ ልማት እና ዴሞክራሲ የከፈለው ዋጋ እጅግ ውድ ነው። እሳቸው በፅሁፋዊ መልእክታቸው የተጠቀሙበት አገላለፅ የምንጋራው እና ክብር የምንሰጠው ነው " ብለዋል።
➡️ " የመልእክታቸው አንኳር ነጥብ ህዝቡ ጦርነት ስለማያስፈልገው የትግራይ መሪዎች እና ልሂቃን ልብ ግዙ ተመካከሩ የሚል ነው። የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ህዝብ ጦርነት አይወድም ፤ አይገባውም። በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብም ጦርነት አያስፈልገውም። ይሁን እንጂ የትግራይ ህዝብ ባለፉት 100 ዓመታት ከማእከላዊ መንግስቱ ያደረጋቸው ጦርነቶች ከመሬት ተነስቶ ያደረጋቸው ተንኳሽ እንደሆነ በሚያደምጥ መልኩ በደብዳቤው የቀረበ አገላለፅ ልክ ነው ብለን አንወስድም " ሲሉ ተናግረዋል።
➡️ " የትግራይ ህዝብ ላለፉት 100 ዓመታት እና ከዛ በላይ የተዋጋው የሚወሩትን ፣ መብቱን የሚነፍጉትን እና ድምፁን የሚያፍኑትን ለመከላከል ሲባል መሆኑ ልብ ማለት ይገባል። ስለሆነም የትግራይ ህዝብ ጦረኛ እና ተንኳሽ በሚመስል መልኩ የቀረበ አገላለፅ ልክ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ትናንት ፣ ዛሬ ይሁን ነገ አይገዛም አይምበረከክም። ልግዛህ ላምበረክክህ ለሚለው ወራሪ መልሱ እምቢ ነው። ከዚህ ውጭ ጦርነት ጀማሪ ሆኖ አያውቅም ፤ ማንንም ሄዶ አይወርም ልግዛህ አይልም ፤ ስለሆነም ጦርነት ጀማሪ በሚመስል የቀረበው አገላለፅ ልክ አይደለም " ብለዋል።
➡️ " እኛ እንወረራለን እንጂ አንወርም ፤ ጦርነት ይከፈትብናል እንጂ በማንኛውም ህዝብ ላይ ጦርነት አንከፍትም " ሲሉ ገልጸዋል።
➡️ " ማንኛውም የትግራይ ፓለቲካዊ ፓርቲ ፣ ስቪክ ማህበር እና ህዝቡ ከማንኛውም ህዝብ በላይ በጦርነት የወደመ የተጠቃ ፣ ጦርነት እጅግ አፍራሽ መሆኑ ስለሚያውቅ አሁንም የጦርነት ፍላጎት የለውም " ብለዋል።
➡️ " በትግራይ በኩል ለጦርነት የሚጋብዝ አንድም ምክንያት የለም ። እርግጥ ነው በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ልዩነት እና መሳሳብ አለ። ይህንንም በሰለጠነ የፓለቲካ አግባብ ይፈታ እንደሆነ እንጂ ወደ ጦርነት የሚመራ ምክንያት ሊሆን አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።
➡️ " ያለንን የፓለቲካ ልዩነት በውይይት እና በሰለጠነ የፓለቲካ አግባብ እንፈታዋለን እንጂ ወደ ጦርነት የሚያስገባን አይሆንም " ብለዋል።
➡️ " ከፌደራል መንግስት ጋር የሚያገናኘን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ነው። ስምምነቱ ማእከል በማድረግ የጎደለን ነገር በውይይት ለሞምላት ነው 'እንወያይ ' የሚል ጥሪ እያቀረብን ያለነው። እንወያይ የፕሪቶሪያ ስምምነት ተፈፃሚ ይሁን ፣ ወራሪዎች በሃይል ከያዙት ግዛታችን ይውጡ ፣ የግዛት አንደነታችን ይከበር ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ ፣ የሁለትዮሽ ፓለቲካዊ ውይይት ይጀመር ወደ መደበኛው ህገ-መንግስታዊ ስርዓት የምንመለስበት ሁኔታ ይፍጠን ብሎ መጠየቅ የጦርነት መንስኤ ሊሆን አይችልም " ብለዋል።
➡️ " የ2013 ዓ.ም ጦርነት ከመጀመሩ ጥቂት ሳምታት ቀደም ብሎ በጠቅላይ ሚንስትሩ የአሁኑ አይነት ተመሳሳይ የፅሁፍ መግለጫ ተሰጥቶ ነበር። ያኔም ' ወደ ትግራይ ማሰክ እንጂ የጥይት ቁምቡላ አንልክም ' ተብሎ ነበር። ቅኔ ነው የነበረው። አሁንም በውጭ ሲታይ ለስላሳ እና ጣፋጭ ውስጡ ሲታይ ግን ' ተጠንቀቁ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ሁኔታ ነው ያለው ' የሚል እንድምታ ያለው ደብዳቤ ነው የተሰራጨው " ብለዋል።
➡️ " ደብዳቤው ሆን ተብሎ ህዝብ ለማሸበር የተደረገ ነው። ይህ በትግራይ ህዝብ ላይ እየቀጠለ ያለውን በደል አካል አድርገን ነው የምንቆጥረው። የትግራይ ህዝብ ማስፈራራት አይገባም። አሁንም ' መጣሁብህ ገደልኩህ ' ማለት ለትግራይ ህዝብ ተገቢ አይደለም። የትግራይ ህዝብ አሁን የሚያስፈልገው የበደል ካሳ ፣ ሰላም ፣ ልማት እና ውይይት ነው በመሪዎች መካከል የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰለጠነ ውይይት መፍታት ያስፈልጋል " ብለዋል።
➡️ " በአሁኑ ወቅት ህወሓትም ሆነ የትግራይ ህዝብ የጦርነት ፍላጎት የላቸውም። በመላው ትግራይ ጦርነት የሚጋብዝ እንዳች ምልክት የለም። መብታችን ፣ ማንነታችን ይከበርልን ፣ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ሁሉም ነገር ይፈፀም የሚል ግን ጥያቄያችን አስኪመለስ ድረስ የምናቆመው አይደለም ይህ ዓይነት ጥያቄ በፍፁም የጦርነት መንስኤ ሊሆን አይችልም " ብለዋል።
➡️ " በትግራይ ለጦርነት የሚጋብዝን አንዳች ነገር የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት 50ኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 በጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማክበር እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት በማስመልከት የክልሉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
አቶ ጌታቸው በዚሁ ወቅት በህወሓት አመራሮች መካከላል ባለው ክፍፍል የግጭት ስጋት ስለመኖሩ ጠቋሚ ቃል ሰጥተዋል።
" በአሁኑ ወቅት በትግራይ በማንኛውም ደቂቃ በሆነ ሰው በሚፈጠር ስህተት ለግጭት የሚዳርግ ሁኔታ ሰፍቷል " በማለት ነው ስጋታቸው የገለጹት።
ትግራይ ክልል ከአስከፊው ጦርነት ገና በቅጡ ያላገገመ ሲሆን አሁን ደግሞ ህዝብን በከፍተኛ ስጋት ላይ በጣለ የአመራሮች ክፍፍል እየታመሰ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ካቢኔ ምን ውሳኔዎች አሳለፈ ?
የአዲስ አበ ባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 4ተኛ አመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
የመጀመሪያው በከተማዉ አስተዳደር በጀት ተመድቦላቸዉ የተገነቡ እና በመጠናቀቅ ያሉትን አዳዲስ ሆስፒታሎችን የሚመለከት ነው።
በዚህም ሆስፒታሎቹ ዘመኑን በዋጀ ህክምና መሳሪያ ለማሟላት እና አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ አገልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካከበቱ #የግል_ሴክተር ጋር በአጋርነት ለመስራት ዉሳኔ አሳልፏል።
ሁለተኛ አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን በውል #ለ3ተኛ_ወገን ለማስራት የወጣውን ረቂቅ ደንብ መርምሮ በማየት ካቢኔዉ አፅድቋል።
በሶስተኛ ደረጀ የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላላቸው እና ተኪ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኢንዲስትሪዎች ባቀረቡት #የማስፋፊያ_ቦታ ጥያቄዎች ላይ በመወያየት እና የአተገባበር አቅጣጫ በማስቀመጥ ካቢኔው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
አራተኛ የኮሪደር ልማት ውጤት ከሆኑት ሥራዎች አንዱ የብዙሀን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ችግሮች የሚያቃልል እና የትራፊክ ፍስቱን የሚያሻሽለው የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብን በመመርመር ማፅደቁን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@tikvahethiopia
" ፍትህ የለም እንጂ ፍትህ ካለ እኔ ነጻ ሰው ነኝ። ፍርድ ቤት በነጻ ለቆ ለደረሰብኝ በደል ሁሉ ካሳ ሊያሰጠኝ በቻለ ነበር " - አቶ ዮሐንስ ቧያለው
እነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ መንግስትና የሽብር ወንጀል ችሎት በረበባቸው ክስ የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደረሰው የሰነድ ማስረጃ ለማወቅ ችሏል።
አቶ ዮሐንስ ቧያለው በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል፣ " የቀረበብኝን ውንጀላና አሉባልታ አልቀበልም። ወንጀልም አልፈጸምኩም " ማለታቸውን ሰነዱ ያወሳል።
አክለው፣ " ፍትህ የለም እንጂ ፍትህ ካለ እኔ ነጻ ሰው ነኝ። ፍርድ ቤት በነጻ ለቆ ለደረሰብኝ በደል ሁሉ ካሳ ሊያሰጠኝ በቻለ ነበር። ግን እንዴት ሆኖ/ ራሱ ነጻ ያልሆነ ማንን ሊያደርግ ይችላል " ነው ያሉት።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ18/07/2016 ዓ/ም በስማቸው በሚጠራው መዝገብ ላይ ያቀረበውን ክስ " ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም " ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
የተቃውሟቸውን ምክንያት የገለጹበት ሰነድ፣ " ሁሉም የክስ ጭብጦች በፈጠራ ተሞሉ ናቸው " ይላል።
የክስ ጭብጡ፣ " ‘የሽብር ቡድን አመራር በመሆን፣ አባል በመሆን፣ ራሱን በመሰየም፣ በማደረጃት፣ የሰራተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና ጽንፈኛ ፋኖን በመምራት የሽብር ወንጀል ፈፅሟል’ ይላል " ሲሉ አስረድተዋል በሰነዳቸው።
ዮሐንስ በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል፣ " የተጠቀሰው ሀሳብ በአንድ በኩል መረጃ አልባና ከእውነት የራቀ ሲሆን፣ በሌላ መልኩ ደግሞ የአንድን የህዝብ ባህላዊ ተቋም ለመክሰስ የሞከረ ሆኖ አግኝቼዋለሁ " ሲሉ ወንጅለዋል።
" መረጃ አልባነቱን " ጭምር በገለጹበት ሰነድ አቶ ዮሐንስ ምን አሉ ?
“ በኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰየመ አሸባሪ ቡድን ማን እንደሆነ፣ በዚህ ቡድን ላይ የእኔ ኃላፊነትና የፈጸምኩት ወንጀል ምን እንደሆነ ከመግለጽ ይልቅ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ራሱ በጭንቅላቱ የፈጠረው ‘አሸባሪና ጽንፈኛ ቡድን አመራርና አባል ነው’ የሚል የፈጠራ ድርሰት መቅረቡ ነው።
በአንጻሩ አንድን የህዝብ ባህላዊ ተቋም ፍትህ ሚኒስቴር (ጠቅላይ አቃቢ ህግ) በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን በመተላለፍና በደመኝነት መንፈስ ‘አሸባሪ’ ብሎ መሰየሙ ነው።
ፋኖ የአማራ ህዝብ ተቋም ሆኖ እያለ የፋኖ አመራርና አባል የሆኑ ሰዎች አሸባሪ ናቸው ብሎ መክሰስ ህዝቡን እንደ ህዝብ ከመክሰሱም በላይ ለአማራ ህዝብ ተቋሙ ያሳየውን ንቀት የሚያረጋግጥ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
የአማራ ጠላት የሆነው ዘረኛው ስርዓትም ይሁን በመሳሪያነት እያገለገለ ያለው ጠቅላይ አቅቢ ህግ ሊያውቁት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ሁሉም አማራ ፋኖ መሆኑን ነው። የእኔ ‘ፋኖ’ መሆንም በቀጥታ ከአማራነቴ ጋር የተያያዘ ነው።
ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው መላው የአማራ ህዝብ እስካሁን ድረስ ምናአልባትም በጉዲፈቻና በሞጋሳ ከተሸጡት ጥቂት የአብይ አህመድ ቡድን የሆኑ የካቢኔ አባላት ውጪ ሁሉም አማራ ፋኖ እንደሆነ ሁሉ እኔም በፋኖነቴ አላፍርም። እኮራለሁ እንጂ !
ቄሮነትና አባገዳነት ወንጀል እንዳልሆነው ሁሉ ፋኖነትን መንካት በአንድ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከመሆኑም በላይ ምንጊዜም ቢሆን በማንነቴ ላይ የሚመጣን ጥቃት እንደ ባንዳዎችና በጉዲፈቻ እንደተሸጡ የስራዓቱ (የብልጽግና ቡድን) አባላት ዝም ብዩ ልቀበለው እንደማልችል በድጋሚ ላረጋግጥ እወዳለሁ።
ፋኖነት ወንጀል ሳይሆይን በክብር የሚሰውለት አማራዊነት ነው " ብለዋል።
አቶ ዮሐንስ ቧያለው ሙሉ የእምነት ክህደት ቃል ገለጻ የያዘው ሰነድ ከላይ የተያያዘ ሲሆን የአቶ ክርስቲያን ታደለ የእምነት ክህደት ቃል ደግሞ በቀጣይ ይቀርባል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
📣 የ Jasiri Talent Investor Fully-Funded Program ተመልሷል
ባለሽበት የስራ መስክ በቂ የሆነ ችሎታ ካለሽ፣ አዲስ እና በፍጥነት የማደግ አቅም ያለው ተቋም የመመስረት ፍላጎት ካለሽ፣ እንዲሁም ችግር የመፍታትና ተጽዕኖ የመፍጠር ብቃት ካለሽ ይህ ዕድል ላንቺ ነው።
ሙሉ ወጪሽ ተሸፍኖ በሩዋንዳ የ 3 ወር ስልጠና፤ የቢዝነስ መነሻ፤ ቢዝነሱ እስኪቋቋም ለተወሰኑ ወራት የሚያቆይ የኪስ ገንዘብ የሚታገኚበት፤ ስልጠናሽን ጨርሰሽ ወደ ኢትዮጵያ ስትመለሺ ለተወሰነ ግዜ የምትጠቀሚበት የጋራ ቢሮ (co-working space) ተመቻችቷል።
8ኛው ዙር ለመቀላቀል፣ ዛሬውኑ ተመዝገቢ!
👉 https://bit.ly/40Ai4oR
ለበልጠ መረጃ @jasiri4Africa
🤔ሊቨርፑል ወድ ፍፃሜ ማለፍ ይችላል?🏆
🔥ዛሬ ማታ ሊቨርፑል ቶተንሃምን ከ 1-0 ሽንፈቱ በኋላ በአንፊልድ ስታዲዮም ይገናኛሉ!
ቶተንሃም ውጤቱን ማስጠበቅ ይችላል?
🎊 ከጥር 5 እስከ መጋቢት 22 ባሉት ቀናት አሁን ካሉበት ከጎጆ ፓኬጅ ወደ ቤተሰብ ከፍ ሲሉ… እኛ ሜዳ ፓኬጅን እንመርቅሎታለን!
👉ይሄንን ፍልሚያ በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
“ በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ብዙ ድልድዮች ዘላቂነት ያላቸው አይደሉም የብረት ናቸው። ወደ ኮንክሪት እንዲቀየሩ ጥያቄ እያቀረብን ነው ” - የሰሜን ወሎ ዞን መንገድ መምሪያ
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የሚገኘውና ከባድ ጭነት ያየዘ ተሳቢ ሲጓዝበት ትላንት የተሰበረው ብረት ድልድይ በኮንክሪት መሰራት እንደሚገባው፣ ይህንንም ለፌደራል አካላት ማሳሰቡን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የድልድዩ መሰበር ያስከተለውን የትራንስፓርት እንቅስቃሴ መስተጓጎል ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄም፣ ለጊዜው ተለዋጭ መንገድ እየተዘጋጀ መሆኑን የዞኑ መንገድ መምሪያ ገልጿል።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፀሐይነው ሲሳይ ምን አሉ?
“ትላንት ከሰዓት በኋላ የተሰበረው መንገዱ ከወልዲያ ቆቦ አላማጣ ቆቦ የሚያዘልቅ፣ ከትግራይ ክልል የሚያገናኝ፣ ከፍተኛ ትራፊክ የሚተላለፍበት መንገድ ነው።
ከፍተኛ ጭነት የጫነ ተሳቢ መኪና ሲጓዝበት የብረት ድልድዩ ከነመኪናው ታጥፏል። የፌደራል መንገድ ስለሆነ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት አድርሰናል።
በሰዓቱም ችግር እንዳይፈጠር ተራ የሚያስጠብቁ አካላት እንዲያውቁት ተደርጎ ሥራ እየተሰራ ቆይቷል። ትላንትና ህብረተሰቡ እንዳይጉላላ በቅብብሎሽ ሰው እንዲተላለፍ ጥረት አድርገናል።
መንገዱ አስቸኳይና ተለዋጭ መንገድ ስለሌለው ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ማሽን መድቦ በሰዓቱ ደርሷል። ሥራም ጀምሯል። ተለዋጭ መንገድ ከፈታ እየተደረገ ነው። ከፈታው አልተጠናቀቀም።
አሁን እየተሰራ ነው። የትራፊክ መጨናነቁን በከፈታው ትንሽ ማስተንፈስ ተችሏል። ሥራው እንደቀጠለ ነው። ግን ዘላቂ ነው ማለት አይቻልም። ለጊዜው ካጋጠመው ችግር አኳያ ነው ተለዋጭ መንገድ እየተሰራ ያለው” ብለዋል።
አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከመጠን በላይ ጭኖ ነው ወይስ የድልድዩ የጥራት ችግር ነው? ስንል ላቀረብነው ተጨማሪ ጥያቄም ምላሽ ያሉትን ነግረውናል።
ምን መለሱ?
“በሚመለከታቸው ባለሙያዎች እናሳያለን። ግን ጭነቱም ክብደት እንዳለው ያሳያል። ተሽከርካሪው የድንጋይ ከሰል ነው ተጭኖ ወደ ድልድዩ የገባው የጭንት ክብደት ሊኖር እንደሚችል ያሳያል።
የሌላም ከሆነ ይታያል። በዋናነት ግን ድልድዩም ቢሆን የብረት ድልድይ ነው። ለስምንት ዓመታት አገልገልግሏል።
ይህ ብቻ ሳይሆን አካባቢው፣ በዚሁ በቀጠናችን በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ብዙ ድልድዮች ዘላቂነት ያላቸው አይደሉም የብረት ናቸው። ወደ ኮንክሪት እንዲቀየሩ ጥያቄ እያቀረብን ነው። ሌሎችም የሚያሰጉን ይኖራሉ” ነው ያሉት።
ይሄው ድልድይ በሰሜኑ ጦርነት የመሰበር አደጋ ደርሶበት ነበር እንዴ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ “ይሄኛው ሳይሆን አላውሃ ድልድይ ነበር ጉዳት የደረሰበት። እሱም የብረት ነው። ይሄም እዛው ቀጥሎ ያለ ነው” ብለዋል።
አሁን የመሰበር አደጋ የደረሰበት ድልድይ ለመጠገን ምን ያክል ወጪ እንደሚጠይቅ ስንጠይቃቸው ደግሞ፣ “እኛ ሥራ እንዲሰራ ነው ጥያቄ እያቀረብን ያለነው። ርዝመቱ ከ48 እስከ 50 ሜትር ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
“ቀላል ወጪ ይጠይቃል ተብሎ አይታሰብም። ምንም ቢሆን ከመሰራት ውጪ አማራጭ የለውም። ፌደራል ተለዋጭ መንገድ የለውም። መንገዱ ክልልን ከክልል፣ ወረዳዎችን ከዞን የሚያገናኝ ነው” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የምትጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ ተሳፋሩ " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (#ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።
በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የሚጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራቸው እንዲሳፈሩ አየር መንገዱ አሳስቧል።
ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት እንደሚቀጥል ገልጿል።
" ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን " ብሏል።
@tikvahethiopia
#MoE
በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በክረምት መርሐግብር ሲከታታሉ ለቆዩ መምህራን የመውጫ ምዘና ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።
የምዘና ፈተናው መምህራኑ በሚኖሩባቸው አቅራቢያ ባሉ አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደተጠናቀቀ ማለትም ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።
ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ ማሳሰቡ ይታወቃል።
Via @tikvahuniversity
" የአዲስ አበባ ጅማ እና የአዲስ አበባ ደብረ ማርቆስ የፈጣን መንገድ ፕሮጀክቶች ለገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ቦርድ ቀርበዋል " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር " ከአዲስ አበባ በተለያዩ መስመሮች የሚወጡ 4 አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችልጥናት እየተደረገ ይገኛል " ብሏል።
ጥናቱ እየተደረገ የሚገኘው ፦
➡️ ከአዲስ አበባ ደሴ ፣
➡️ ከአዲስ አበባ ጅማ ፣
➡️ ከአዲስ አበባ ደብረማርቆስ
➡️ ከአዲስ አበባ ነቀምት በሚዘልቁት መንገዶች ላይ እንደሆነ ጠቁሟል።
" የፍጥነት መንገዶቹ የሚገነቡበት የጥራት ደረጃ ፣ የሚኖራቸው አጠቃላይ የጎን ስፋት ከፍ ያለ እና የሚገነቡበት መልክአ ምድር አብዛኛውን ተራራማ ቦታዎችን የሚሸፍን በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ ወጪ እና የቆረጣ ስራዎችን የሚጠይቁ ናቸው " ሲል ገልጿል።
በጥናቱ መሰረት ፕሮጀክቶቹ የሚኖራቸው ርዝመት በአማካይ 300 ኪሜ እንደሆነና ግንባታቸው በተለያዩ ምዕራፎች እና በተወሰነ ኪሎሜትር ተከፋፍሎ እንደሚጀመር አመልክቷል።
በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቶቹ የአዋጭነት፥ እንዲሁም መሰረታዊ የዲዛይንና የዝግጅት ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጾ ለዝግጅት ሥራው የሚያስፈልጉ የጥናት ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብሏል።
አራቱን የፍጥነት መንገዶች ለመገንባት የሚያስፈልገው ወጪ የሚሸፈነው በመንግስትና የግል አጋርነት ትብብር ነው ብሏል።
ከፍጥነት መንገዶቹ መካከል የአዲስ ጅማ እና አዲስ ደብረ ማርቆስ ፕሮጀክቶች ለገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ቦርድ የቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በቅርቡ ይቀርባሉ ሲል አሳውቋል።
ፕሮጀክቶቹም በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ትብብር ቦርድ ከጸደቁ በኋላ ወደ ቀጣይ ስራ ይገባሉ ተብሏል።
@tikvahethiopia
ከወልደያ ቆቦ የሚያስኬደው የሃሚድ ውሃ ወንዝ የብረት ድልድይ ወደ መቐለ የደንጋይ ከሰል ጭኖ በሚሄድ መኪና ተሰብራል።
ጉዳትም ድርሷል።
የአማራ ክልል የመንገድ ቢሮ ጉዳቱን በተመለከተ ለፌዴራል የመንገዶች አስተዳደር በደብዳቤ ሪፖርት አድርጓል።
ከወልድያ - ቆቦ - አላማጣ ባለው ዋናው የአስፓልት መንገድ ከቆቦ ከተማ 14 ኪ.ሜ ርቀት ወደ ወልድያ በኩል በሚወስደው በሮቢትና ጎብየ ከተማ መካከል የሚገኝው " የሃሚድ ውሃ ወንዝ " ላይ 50 ሜትር ርዝመት ያለው ተገጣጣሚ የብረት ድልድይ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከዛሬ 8 ዓመት በፊት ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አስታውሷል።
አሁን ላይ የብረት ድልድዩ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚበዛበት ከመሆኑ የተነሳና በከባድ ጭነት ምክንያት በደረሰበት ጉዳት የተሰበረ መሆኑን ጠቁሟል።
በዚህም ወልድያ ወደ ቆቦ እና አላማጣ የሚወስደው የአስፓልት መንገድ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ማቆሙን ቢሮው ገልጿል።
በአካባቢው ብቸኛ ስለሆነና ተለዋጭ መስመር መግቢያና መውጫ መንገድ ባለመኖሩ የትራንስፓርት አገልግሎት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ሙሉ በሙሉ መቋረጡን አመልክቷል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በአካባቢው የተፈጠረውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ጉዳት የደረሰበትን የሃሚድ ውሃ ወንዝ የብረት ድልድይ በአፋጣኝ የጥገና ስራ እንዲያደርግለትና ክፍት እንዲሆን ጠይቋል።
@tikvahethiopia
" ከአደጋው በህይወት የተረፈ የለም " - የሶባ ቦሩ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሶባ ቦሩ ወረዳ በወርቅ ቁፋሮ ስራ ላይ የነበሩ 8 ሰዎች ላይ አፈር ተደርምሶባቸዉ የሁሉም ሕይወት ማለፉን የወረዳዉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ አሸናፊ ድንቆ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋው በትላንትናው ዕለት ከቀኑ 9 ሰዓት አከባቢ ' ቃንጣቻ ' ተብሎ በሚጠራዉ ቀበሌ በባህላዊ መንገድ የወርቅ ማዕድን በማዉጣት ስራ ላይ በነበሩ 8 ሰዎች ላይ መድረሱን ኃላፊዉ ገልጸዋል።
በአከባቢዉ የሚስተዋለዉ ባህላዊ የወርቅ አወጣጥ ስርዓትና በቸልተኝነት የሚደረጉ ሽሚያዎች ለናዳዉ ምክንያት ሊሆን ይችላል ያሉት ኃላፊዉ ሟቾቹ ሁሉም ወንዶች መሆናቸው አስታዉቀዋል።
የአስከሬን ፍለጋዉ ሂደት ፈታኝ እንደነበር ገልጸው አደጋዉ ከደረሰበት ሰዓት አንስቶ እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ በሰዉ ሃይልና በማሽን በመታገዝ የፍለጋ ስራዉ መከናወኑንና በዛሬው ዕለት የሁሉም የቀብር ሥነ ስርዓት መፈፀሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
አቶ አሸናፊ የጉጂ ዞን ሰባ ቦሮ ወረዳ በወርቅ ፣ ታንታሌም ፣ አምርላንድን በመሳሰሉ የማዕድን ሃብቶች የበለፀገ አካባቢ መሆኑንና ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ በርካታ ሰዎች በማዕድን ማዉጣት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚሰሩ ገልፀዉ ከዚህ ቀደም አከባቢዉ ላይ መሰል አደጋዎች ተከስተዉ እንደማያውቁም ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
#Ethiotelecom
የካቲት 07 ይጠናቀቃል፤ ፈጥነው የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ባለቤት ይሁኑ!!
💁♂️ የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይከናወናል፤ የመሸጫው ጊዜ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት የኢትዮ ቴሌኮም የቀጥታ ድርሻ ባለቤት ይሁኑ!!
🗓 እስከ የካቲት 07/2017 ዓ.ም ብቻ!
📖 የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን https://teleshares.ethiotelecom.et/ ያንብቡ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 128 ይደውሉ !
#telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#USA
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።
ትራምፕ " በአሜሪካ እና የቅርብ አጋሯ እስራኤል ላይ ቅቡለነት እና መሠረት የሌለው ተግባር እየፈጸመ ነው " ሲሉ የከሰሱትን የዓለም አቀፉ የጦር የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ላይ ማዕቀብ የጣሉበት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ላይ ፈርመዋል።
ትራምፕ ICC ላይ የጣሉት ዕቀባ እና ቪዛን የሚያጠቃልል ነው።
የቪዛ ዕቀባው የአሜሪካ ወይም የአጋሯቿ ዜጎች ላይ ምርመራ የሚያደረጉትንና የሚረዱ ግለሰቦች እና ቤተሰቦቻችን ዒላማ ያደረገ ነው።
ታራምፕ ይህንን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የፈረሙት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ዋሽንግተንን እየጎበኙ ባሉበት ወቅት ነው።
ባለፈው ጥቅምት ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ኔታኒያሁ በጋዛ ፈጽመውታል ባለው የጦር ወንጀል ምክንያት የእስር ትዕዛዝ አውጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
አሜሪካ የዚህ ዓለም አቀፍ ተቋም አባል አይደለችም። በተደጋጋሚም በአሜሪካ ዜጎች ላይ በፍርድ ቤቱ የሚተላለፍ ውሳኔዎችን ውድቅ ማድረጓን ቢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
24 - ሰዓት የሚሰሩ ሁለት ቅርንጫፎች እንዳሉን ያውቃሉ?
ሕብረት ባንክ በስካይ ላይት ሆቴል ውስጥ ስካይ ላይት ንዑስ ቅርንጫፍ እንዲሁም በሒልተን ሆቴል ውስጥ ሒልተን ቅርንጫፍ ላይ የ24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ /channel/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
#ኢትዮጵያ
ሀገራዊ የጾም ፀሎት ጥሪ ከመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን !
መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 15 ድረስ የሚዘልቅ ሀገራዊ የጾም ፀሎት አውጃለች።
ቤተክርስቲያኗ በልመና / ምልጃ ጸሎት ወቅት ፦
➡️ " በሀገሪቱ በተለያዩ ሥፍራዎች ያሉ የፖለቲካ ኃይሎች በኃላፊነት መንፈስ በጋራ ለሀገር እና ለህዝብ በአንድነት መስራት የሚችሉበትን ጥበብ፤ እውቀትና ማስተዋል እግዚአብሔር እንዲሰጣቸው እንለምን። "
➡️ " በሀገራችን በሚገኙት የኦሮሚያ፤ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ያለው አፍተኛ የጸጥታ ችግር ጌታ እንዲያቆመው እንጸልይ። "
➡️ " በምድሪቱ ላይ ፍትህ እንዲሰፍን እንዲሁም በተለያዩ የሥልጣን ደረጃዎች ያሉ የመንግስት አካላት ሕዝቡን በከፍተኛ ኃላፊነት፤ አክብሮትና ቅንነት ማገልገል የሚችሉበትን ጥበብ፣ ማስተዋልና የልብ ስፋት እግዚአብሔር እንዲሰጣቸው እንለምን። "
➡️ " የሀገራችን ኢኮኖሚ ስርዐት ድሃው ማህበረሰብ ሰርቶና በልቶ እንዲያድር ፍትሐዊ እንዲሆን እንጸልይ፡፡ "
... ብላለች።
(የቤተክርስቲያኒቱ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Kenya
በUSAID እርዳታ ስራ የተቀጠሩ ብዙሃኑ በጤናው ዘርፍ ላይ ያሉ ከ40 ሺህ በላይ ኬንያውን ስራ አጥ ሊሆኑ ነው።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ አስተዳደር ከUSAID ጋር በተገናኘ እርዳታ እንዲቆም ውሳኔ ማሳላፋቸውን ተከትሎ በተለይ በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በአሜሪካ እርዳታ የተቀጠሩ ሰራተኞች ስራ አጥ ይሆናሉ።
ከነዚህ ሀገራት መካከል ጎረቤታችን ኬንያ አንዷ ናት።
በሀገሪቱ በአሜሪካ መንግሥት እርዳታ ስራቸውን የሚሰሩ ከ40,000 በላይ ሰራተኞች ስራ አጥ ይሆናሉ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ በጤናው ዘርፍ ላይ ያሉ መሆናቸውን ከሲቲዝን ቴሌቪዥን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
በኢትዮጵያ ከUSAID እና CDC ጋር በተገናኘ ድጋፍ በጤና ዘርፍ ስራ እየሰሩ ያሉ ከ5,000 በላይ ሰራተኞች ውላቸው እንዲቋረጥ ጤና ሚኒስቴር ትዕዛዝ መሰጠቱን ነግረናችሁ ነበር። ይህ በጤና ሚኒስቴር ብቻ የታዘዘው ነው። ሌሎች በUSAID እርዳታ የሚሰሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ልብ በሉ።
@tikvahethiopia
“ በአጠቃላይ አቃቢ ህግ በእኔ ላይ መስርቶ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸውን ወንጀል አልፈጸምኩም” - አቶ ክርስቲያን ታደለ
እነአቶ ክርስቲያን ታደለ ዛሬ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ጉዳዩን ከሚከታተሉ ሰዎችና ቃላቸውን ካቀረበበት ሰነድ መረዳት ትችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው አቶ ክርስቲያን የእምነት ክህደት ቃል የሰጡበት ሰነድ፣ “በአጠቃላይ አቃቢ ህግ በእኔ ላይ መስርቶ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸውን ወንጀል አልፈጸምኩም። ጥፋተኛም አይደለሁም” ይላል።
አቶ ክርስቲያን በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ምን አሉ?
“ለ550 ቀናትም በግፍና ጭካኔ እገታ ውስጥ የምገኘው ለአንዲት ደቂቃ እንኳን በጥፋተኝነት የሚያስቀጣ አንዳችም የወንጀል ድርጊት የሚያቋቁም የህግ መተላለፍ ስለፈጸምኩ አይደለም። የአማራ ሕዝብ የሚያነሳቸውን የህልውና ጥያቄዎች በይፋ በማቅረቤ፣ በሕዝቤ የሚደርሰውን ግፍ፣ በደል በማስረጃ በመሞገቴ፣ የገዢውን ፓርቲ አፈናና የመንግስት አሰራሮችንና አመራሮችን ብልሹነትና ዘረፋ በመታገሌ ነው ” ብለዋል።
“ ተደጋጋሚ የአመራር ብልሹነት ባሳዩ አካላትም የወንጀልና የፍትሃብሔር ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ክስ እንዲመሰረት ፍትህ ሚኒስቴር አዝዥለው ” የሚሉና ሌሎች ድርጊቶችን በአደባባይ እንደታገሉ ገልጸዋል።
“ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በአሰራራቸው የፋይናንስ ገልጸኝነትና ህጋዊነት እንዲከተሉና እንዲረጋገጡ እንዲሁም ኦዲት ለመደረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቄከለሁ ” ነው ያሉት።
እነዚህን ጥያቄዎች እንዳልጠይቅ አንዳንድ አመራሮች ለማግባባት እንደሞከሩ ገልጸው፣ “ አንዳንዶቹም ሊገድሉኝ፣ ሊያስሩኝና አንዳች ነገር ሊያደርሱብኝ እንደሚችሉ ጭምር ነግረውኛል፤ መልዕክትም አድርሰውኛል ” ብለዋል።
“ አንዳች ወንጀል አልፈጸምኩም ” ያሉት ክርስቲያን፣ “ ይህን በተመለከተ ከክሱ ይዘት ብቻ ሳይሆን በራሴ መንገድ ይህን ክስ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብብኝ ካደረገው አካል ዘንድም አረጋግጫለሁ ” ሲሉ አስረድተዋል።
“ እኔ አማራ የሆንኩት አማራ ሆኘ ስለተወለድኩ ነው። የከማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ የሆንኩትም ፈቅጄ፣ መርጨና ወድጄ ነው። በየትኛውም ቦታና ሁኔታ ለአማራነቴ ጥብቅና መቆምም ተፈጥሯዊ ግዴታዬ ነው ” ብለዋል።
“ አማራዊ እሴቶታችን ለኛ ቅዱስ ነው ” ብለው፣ “ ይሁንና አቃቢ ህግ ባቀረበው የፓለቲካ ውንጀላ ሰነድ ላይ፣ ‘አማራ ርስቱን ተቀምቷል፤ አገሪቱ በአማራ እሴት መመራት አለባት’ የሚል የርዕዮተዓለማዊ አቋም መያዛችን ክስ ሆኖ ቀርቧል” ብለዋል።
“ ይህ የአቃቢ ህግ ክስ ግን መንግስት ከአማራና ከአማራነት የጸዳች ኢትዮጵያ ነው ወይ የሚፈልገው ? የሚል ሙግት ያስነሳል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከአማራና ከአማራነት በስተቀር እንዲሆኑ የሚደነግግ ህግስ አለ ወይ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል “ በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ‘ቋሪትና ደጋ ዳሞት ላሉ የሽብር ቡድን አስተባባዎች በስልክ ሐምሌ 25/2015 ዓ/ም በመደወል መከላከያን ማጥቃት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በማሳወቅ እንዲመቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል’ ” ማለቱን ጠቅሰል።
“ አቃቢ ህግ ለዚህ ክስ አስረጅ የሆነ አንዳችም ማስረጃ አላቀረበም ” ብለዋል።
(ሙሉ የእምነት ቃላቸውን የሰጡበት ሰነድ ከላይ ተያይዟል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
“ ለአእምሮ ህሙማን ብቻ በየወሩ እስከ 5 ሚሊዮን ብር መድኃኒት እንገዛለን። የህክምና ባለሙዎች እጥረት አለብን ” - የመቄዶኒያ ህክምና ክፍል
የመቄዶንያ አረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል ህክምና ክፍል የመድኃኒት መወደድና የስፔሻሊት ሀኪሞች እጥረት እንደፈተነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የማዕከሉ የህክምና ክፍል አስተባባሪ አቶ ዮናስ ሙሉጌታ በሰጡን ቃል፤ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ እውቀት ያለው በእውቀቱ፣ ጳጳሳቱ በጸሎታቸው እርዳታ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የማዕከሉ ህክምና ክፍል በዝርዝር ምን አለ?
“በመቄዶንያ ካሉት 8,000 ሰዎች ወደ 2000 የሚሆኑት የአእምሮ ህሙማን ናቸው። የአእምሮ ህሙማኑ መድኃኒቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ አገር ውስጥ አይገኙም።
ቢኖሩም ውስን ፋብሪካዎች ናቸው የሚያመርቷቸው ጥሬ እቃ ከውጪ አገር እያስመጡ። የተወሰኑ መድኃኒቶችም በቀጥታ ከውጪ አገር ነው የሚመጡት።
ከገበያ የሚጠፉ መድኃኒቶችም አሉ ከምንዛሪ እጥረት ጋር በተያያዘ። መድኃኒቶቹ መጥፋታቸው ህሙማኑ ህመሙ እንዲያርሽባቸው ይዳርጋቸዋል። ወደ ጤንነታቸው ለመመለስም ጊዜ ይወዳል።
አዲስ አበባ፣ ሰንዳፋ፣ ፃድቃኔ፣ ሶማሌ ክልል ጎዴ፣ አማራ ክልል ደሴ፣ ሀረር፣ ድሴዳዋ በብዛት የአእምሮ ህሙማን የሚገኙባቸው ቦታዎች ናቸው።
በመቄዶንያ ደግሞ የአእምሮ ህሙማንና አረጋዊያን ብቻ ሳይሆኑ ያሉት የደም ግፊት፣ ስኳር፣ አስም፣ ካንሰር፣ የኩላሊት (ዲያሌሲስ የሚያደርጉ) ህሙማንም አሉ።
የአእምሮ ህሙማን መድኃኒቶች በጣም ውድ ናቸው። የምንገዛው ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ነው። ለአእምሮ ህሙማን ብቻ በየወሩ እስከ 5 ሚሊዮን ብር እንገዛለን። የህክምና ባለሙያዎች እጥረት አለብን” ብሏል።
“ካለው ቁጥር አንጻር የባለሙያዎች ቁጥር በቂ አይደለም። ሳይካትሪ እንኳ ወደ 18 ነው የሚሆኑት። ግን ስፔሻሊስቶች ያስፈልጉናል። ባለሙያዎች በበጎ ፈቃደኝነት እንዲያገለግሉ እንፈልጋለን” ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
“በወር ለአንድ እንኳ ሰዓት የህክምና አገልግሎት ቢሰጡ ለህሙማኑ ቀላል አይደለም” ያሉት የህክምና ክፍሉ፣ “የአእምሮ ስፔሻሊቲ፣ የዓይን፣ የጥርስ፣ የፊዚዮትራፒ፣ የሳይኮሎጁ ባለሙያዎች እጥረት አለብን” ብለዋል።
በሙያቸው ወደ ውጪ አገር ሂደው በትላልቅ የህክምና ተቋማት፣ ፋብሪካዎች የሚሰሩ ወገኖች መድኃኒት ቢልኩላቸው መቄዶንያ በህጋዊ መንገድ ፕሮሰስ አድርጎ መቀበል እንደሚችል፣ ድጋፉ ቢገኝ ህሙማን ሳያቋርጡ ህክምናቸውን መከታተል እንደሚችሉ ተመልክቷል።
#ማስታወሻ : የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በSiefu Show Tube ላይ ድጋፍ ለማድረግ ይዘጋጁ።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈትን ተከትሎ ምን ውሳኔ አሳለፈ ?
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ከዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራር አካላት ጋር የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ውይይት ማካሄዱን ገልጿል።
ውይይቱ በተለይ ቤተሰቦቹ ሊደገፉ በሚችሉባቸውና ሃኪሙ በህይዎት ዘመኑ ያከናወናቸው ልዩ ሙያዊ አስተዋጽኦችን መዘከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ዶ/ር አንዱአለም ምንም እንኳን የተሰጠውን ጸጋ ሳይሰስት በመጠቀም ለበርካቶች የዘርፉ ባለሙያዎችና በሙያው ላገለገላቸው በርካታ ህሙማን የቅን አገልጋይነት ተምሳሌት የነበረ እንቁ ባለሙያ ቢሆንም ገና በ37 ዓመቱ የተቀጠፈ በመሆኑ ለህጻናት ልጆቹና ቤተሰቡ ትቶ ያለፈው ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሌለው መሆኑ ተገልጿል።
የቀረቡለትን በርካታ ዓለምአቀፍ የስራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገኑን ለማገልገል ቆርጦ የነበረ ባለሙያ ከመሆኑም በላይ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ክፍል የነበረውን ልዩ አበርክቶና የቀዶ ጥገና ክፍሉን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሻሻል እየጣረ የነበረ እና እውን ለማድረግ ጫፍ ላይ ደርሶ ያለፈ መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የነበረውን ሞያዊ አቅም ተጠቅሞ ራሱን ለተገልጋዮች በቅንነት ሰጥቶ ያለፈ ታላቅ ባለሙያ እንደነበረ የስራ ባልደረቦቹ ፣ተማሪዎቹ እና አገልግሎቱን ያገኙ ደምበኞቹ የሚመሰክሩለት ድንቅ ሃኪም የነበረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል።
በመሆኑም ፦
➡ የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤
➡ ባለቤቱ ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤
➡ ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሰራው እሱ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈቱ ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረ በመሆኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስሙ ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤
➡ የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምለት፤
➡ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስሙ BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም፤
➡ ለ40ኛ ቀኑ መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶ/ር አንዱአለም የህይዎት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል።
ውሳኔው ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
#BDU
@tikvahethiopia
#Update
የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !
ሓበን የማነ የተባለች ወጣትን በጭካኔ በመግደል ክስ የተመሰረተበት ዳዊት ዘርኡ የተባለ ወንጀለኛ ዛሬ ጥር 28/2017 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።
ፍርዱን ያሳለፈው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ነው።
አሰቃቂ ግድያው በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነበር የተፈፀመው።
ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል በቢላዋ ተገድላ መገኘቷንና ጥቅምት 20 /2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቀብር ስነ-ሰርዓት መከናወኑ በወቅቱ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።
ፓሊስ አሰቃቂ የግድያ ተግባሩ አስመልክቶ በወቅቱ በሰጠው መረጃ ፤ የነፍስሄር ወጣት ሓበን የማነ አስከሬን ከ2 ቀን በኋላ ነው በተገደለችበት የሆቴል ክፍል የተገኘው።
ገዳይ ወንጀለኛው አሰቃቂ ተግባሩ በመቐለ ከተማ ከፈፀመ በኋላ በአማራ ክልል በኩል በድብቅ ለውጣት ሲያሴር ደሴ ከተማ በአማራ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ለትግራይ ክልል ፓሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል።
በወቅቱም ለደሴ ህዝብና ለአማራ ክልል ፖሊስ ምስጋና ቀርቦ ነበር።
ፓሊስ ጉዳዩ አጣርቶ አቃቤ ህግ ክሰ መስርቶ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ዛሬ እሮብ ጥር 28/2017 ዓ.ም የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ባዋለው ችሎት ወንጀለኛው በዕድሜ ልክ ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
🎁 ስድስት ወር ሙሉ ዳታ እንደልብ! ለረጅም ጊዜ የሚቆዩትን ሜጋ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 1,000 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ሶሻል ሚዲያዉን ፏ ፏ እናድርግ! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም አስተማማኝ ኔትወርክ ጋር ወደፊት!⚡️
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ፍትህ ! ፍትህ ! ፍትህ !
" ሀኪም ህይወት እያተረፈ ፣ህይወቱን መነጠቅ የለበትም! " - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ከስራ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ በመገደሉ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ፍትህን በመጠየቅ ላይ ናቸው።
" ፍትህን እንሻለን ! " በሚል የፍትህ ጥያቄ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የዶ/ር አንዷለም ዳኜ ሐዘን በማስመልከት ፍትህ ጥያቄ በተማሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የቀረበበት የሀዘን ምሽት በጥበበ ግዮን ግቢ መካሄዱ ተገልጿል።
➡️ ለሃኪሞቻችን ጥበቃ ይደረግልን፤
➡️ አዳኙ ፣ አካሚው ሃኪም ለምን ተገደለ ፤
➡️ አትግደሉን፣
➡️ መድሃኒቱ ሃኪም ጥይት አይገባውም ወዘተ የሚሉ መፈክሮችና የፍትህ ጥያቄ አዘል ምልዕክቶች በስራ ባልደረቦቹ፣ በተማሪዎቹ እና በወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ቀርበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው " አንድን ትልቅ ሃኪም ቀብሮ ገብቶ ዝም ማለት እንደ ዩኒቨርሲቲ ከብዶናል " ብሏል።
" የተገደለብን፣ የተነጠቅነው፣ በርካታ የሆስፒታላችን ደንበኞች ፣ ህሙማን እንዲያድናቸው በወረፋ ቀጠሮ ይዘው የሚጠብቁትን የህዝብ ተስፋ፤ የአገር አንጡራ ሃብት ፣ ኢትዮጵያ ሃገራችን ሰፊ ሃብት ያፈሰሰችበትን ወጣት ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪም ነው፡፡ ፍትህ መጠየቃችንን እንቀጥላለን ! " ሲል አክሏል።
ሁሉም የፍትህ ጥያቄ ዘመቻውን እዲቀላቀል ጥሪ ቀርቧል።
ይኸው ከቀናት በኃላ እንኳን ዶክተር አንዷለም ዳኜን ስለገደሉ አካላት ምንም በይፋ የተነገረ ነገር የለም።
#JusticeforDrAndualemDagnie
#Healing_Hands_Should_Never_Be_Silenced_by_Guns.
#Protect_Physicians_Protect_Humanity.
#Protect_Physicians_Protect_the_Right_to_Heal.
#No_Physician_Should_be_killed_While_Saving_Others.
#Stop_the_Violence_Against_Those_Who_Heal.
#Physicians_Deserve_Safety_Not_Bullets.
#Stop_Killing_the_Healers_of_Humanity.
#Protect_the_Hands_That_Heal, #Not_the_Hands_that_Kill.
#No_Conflict_Justifies_the_Killing_of_a_Physician.
#Defend_the_defenders_of_health.
#Doctors_need_protection_not_persecution.
#Justice_for_Dr_Andualem_Dagnie
@tikvahethiopia
" ከፕሬዜዳንቱ እና ካቢኔው በላይ የሆነ የማይታዘዝ ሃይል ተፈጥሯል "- አቶ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ
በትግራይ ከጊዚያዊ አስተዳደር " ከፕሬዜዳንቱ እና ከካቢኔው በላይ የሆነ የማይታዘዝ ሃይል ተፈጥሯል " ሲሉ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ ተናገሩ።
" ጊዚያዊ አስተዳደሩ በግልፅ ባያውጅም መቐለ ጨምሮ በመላ ትግራይ በስሙ መጠራት ያለበት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አለ " በማለት አክለዋል።
ከህዳር 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የመቐለ ከንቲባ ሆነው በጊዚያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ የተሾሙት እና ህዳር 23/2017 ዓ.ም አንድ ጊዜ ብቻ ቢሯቸው ከገቡ በኋላ ያልተመለሱት ከንቲባው " ላዛ ትግርኛ " ለተባለ ሚድያ ሰፊ ቃለመጠየቅ ሰጥተዋል።
" ወታደራዊ ሃይል በመጠቀም ከመንግስት በላይ ሆኖ ከንቲባ ስራውን እንዳይሰራ ፤ ህዝብ ከከንቲባ ማግኘት ያለበት አገልግሎት እንዳያገኝ መከልከል የህግ ተጠያቂነት ከማስከተል በተጨማሪ በታሪክ ያስወቅሳል " ብለዋል።
ከ8 ወራት በፊት ሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን ፤ ከ4 ወራት በፊት ማእከላዊ ዞን እንዲያስተዳድሩ በጊዚያዊ መንግስት ፕሬዜዳንት ፊርማ የተመደቡ ሃላፊዎች ተግባራቸው እንዳይፈፅሙ ስሙ ባልጠቀሱት ወታደራዊ አዛዥ የሚታዘዙ ጠበንጃ ባነገቡ ታጣቂዎች እንደተስተጓጎሉ ጠቅሰዋል።
እሳቸውም " ከፓሊሰ አቅም በላይ ያልሆነውን ጉዳይ የመቐለ አስተዳደር ዙሪያ በታጣቂዎች በማጠር ወደ ቢሮ እንዳይገቡ ከሁለት ወር በላይ መከልከላቸው እጅግ አሳዛኝ እና የመንግሰት ትእዛዝ የጣሰ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ብለዋል።
ፕሬዜዳንቱና ካቢኔው ሦስት ጊዜ ወደ ስራ ገበታቸው ገብተው ስራቸው እንዲሰሩ ቢያዝም አስተዳደሩን እንዲጠብቁ በታዘዙ ታጣቂዎች መከልከላቸው እጅግ እንዳሳዘናቸው እና እንዳበሳጫቸው ተናግረዋል።
" መንግስት መንግስት መምሰል አለበት ትእዛዝ እና ውሳኔ በማክበር እና በማስከበር ከመንግስት በላይ መሆን የሚፈልገውን አካል ማቆምን ማስታገስ ይገባዋል " ብለዋል።
" ከፕሬዜዳንት እና ከካቢኔ በላይ በመሆን ታጣቂዎች በአስተዳደሩ ዙሪያ ያስቀመጠ አካል የወጣቶች ቁጣ እና መልእክት ተቀብሎ ያሰማራቸው ታጣቂዎች በአስቸኳይ ማንሳት አለበት " ያሉት ከንቲባው " ጉዳዩ ፓሊስን ይመለከታል ከፓሊስ አቅም በላይ ከሆነ የአድማ ብተና ሃይል ይሰማራል ፤ ከዚህ ውጭ ከአቅሜ በላይ ሆኗል የሚል ጥያቄ ባልቀረበበት ታጣቂ ሰራዊት ማስቀመጥ ከህግ በላይ መሆንን ያመለክታል " ሲሉ ስሙ ያልጠቀሱት ታጣቂዎች አሰማርተዋል ያሉትን አካል ተችተዋል።
መቐለ ካሉዋት 7 ክፍለ ከተሞች እና 33 ቀበሌዎች ዙሪያዋ የተወጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ከንቲባ ስራውን እንዲጀምር ፤ ህዝቡ መንግስታዊ አገልግሎት እንዲያገኝ ፤ የጊዚያዊ አስዳደሩ ትእዛዝ እንዲከበር ድምፃቸው አስምተዋል ያሉት ከንቲባ ብርሃነ " አሁንም መልስ ካላገኙ ከበፊት በላቀ ቁጥር ወጥተው ድምፃቸው ማሰማታቸው ይቀጥላሉ " ሲሉ ዝተዋል።
መቼ ወደ ተመደቡበት ስራ እንደሚገቡት ለቀረበላቸው ጥያቄ የተቆረጠ ቀን እንደማያወቁ ተናግረዋል።
" ትግራይ ከገባችበት ፓለቲካዊ ቀውስ የምትወጣበት እንዱ እና ዋነኛ መንገድ መንግስት ሲኖራት የመንግስት ትእዛዝ እና ውሳኔ ሲከበሩ ነው ስለሆነም ከህግ እና መንግስት በላይ በመሆን ታጣቂ ያሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ " ሲሉ አሳስበዋል።
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እና በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተመደቡላት ከንቲባዎች ከስራ ውጭ ሆኖዉባት ከንቲባ ያጣቸው የትግራይ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ከተማ የሆነችው መቐለ የከንቲባዋ ፅህፈት 'ታሽገዋል ' የሚል ወረቀት ተለጥፎለት በግራና ቀኝ በቆሙ ፓሊሶች እንዲሁም ዙሪያዋ በታጣቂዎች ለ24 ሰዓት መጠበቅ ከጀመረች 64 ቀናት ተቆጥረዋል ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን አድርሶናል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
The Ministry of Irrigation and Lowlands is set to host the inaugural “International Conference on Irrigation and Climate-Resilient Production 2025”, taking place from Feb 12-14, 2025 at Adwa Victory Memorial Museum. This conference will set the stage for transformative policies that advance our nation’s food sovereignty, climate-smart practices, and water-efficient technologies.
---
በጉጉት የሚጠበቀው “ዓለም አቀፍ የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ-2025” በኢፌዴሪ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ከየካቲት 5-7 2017 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይቀርባል። ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ እና ወሳኝ ኮንፈረንስ የሀገራችንን የምግብ ሉዓላዊነት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ አሰራሮችን እና ውሃን ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን የሚያራምዱ የለውጥ ፖሊሲዎችን ለማስረጽ ከፈተኛ ሚና ይጫወታል።
Cultivating Resilience: Global Perspectives on Irrigation Development and Climate Adaptation
For more details, contact info@mills.gov.et
#FDRE #ICICRP2025 #MILLs #Irrigation #ClimateResilience #FoodSovereignity
----------------
Follow our socials:
Website: https://mills.gov.et
FB/X/Tel: @MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9
ከ5 ሺህ በላይ ሰራተኞች ውላቸው እንዲቋረጥ መመሪያ ተሰጠ።
ጤና ሚኒስቴር በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ (USAID) ድጋፍ የተቀጠሩ ከ5 ሺህ በላይ ስራተኞችን ውል እንዲቋረጥ መመሪያ ሰጠ።
ጤና ሚኒስቴር ከአሜሪካ መንግሥት በሲዲሲ (CDC) ወይም ዩኤስኤይድ (USAID) አማካኝነት በተገኘ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጃንዋሪ 24 ,2025 ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ እንደደረሰው ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ተፈርሞ ለሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች የተሰራጨው ደብዳቤ " በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ የተቀጠሩ እና ተቋማችሁ ከCDC ወይም USAID ጋር በሚያደርገው ውል መሰረት የተቀጠሩ ሰራተኞችን በተመለከተ ስራ ላይ እንዲውል አሳስባለሁ " ይላል።
ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የደብዳቤውን #ትክክለኛነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡን ተጨማሪ ማብራሪያ በመላው ሃገሪቱ በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ አማካኝነት በኮንትራት እያገለገሉ ያሉ ሰራተኞች ቁጥር 5 ሺህ እንደሚሻገር ገልጸዋል።
ሚንስትሩ " ሰው እንዲዘጋጅ ነው እንጂ የአሜሪካ መንግሥትም ሃሳቡን ሊቀይር ይችላል የተቀየረ ነገር ካለ የሚቀጥል ይሆናል አሁን ባለው ሁኔታ ግን ድጋፉን ካቋረጠ ሌላ መፍትሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል " ብለዋል።
" ለዚህ ደግሞ ሰራተኞቻችን እንዲዘጋጁ ከመንግስት ጋርም ንግግር እየተደረገ ነው ያለው የመንግስት ሰራተኞች ስራውን እንዲያስቀጥሉ የCDC እና USAID ሰራተኞች ስራውን እንዲያቆሙ ተወስኗል " ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በዝርዝር ምን አሉ ?
" እኛን በዋናነት የሚመለከተን በጀቱ በቀጥታ በእኛ በኩል ስለሚመጣ የሲዲሲ ሰራተኞችን ነው ዩኤስኤይድ ግን ቅጥር የሚያከናውነው በራሱ በኩል ነው ውሉንም የሚያቋርጡት ራሳቸው ናቸው።
የአሜሪካ መንግሥት ሃሳቡን ቀይሮ ሌላ መረጃ የሚያስተላልፍ ከሆነ እኛም ሌላ መረጃ የምናስተላልፍ ይሆናል አሁን ባለው የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ግን ኮንትራታቸውን ማቋረጥ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ደብዳቤ አስተላልፈናል።
ከ5 ሺ በላይ ይሆናል ትክክለኛ ቁጥራቸውን ለማወቅ መረጃ የመሰብሰብ ስራ እየሰራን ነው ሁሉም በኮንትራት ናቸው ኮንትራታቸው በየአመቱ ይታደሳል ስራቸውም ከኤች አይ ቪ ጋር የተገናኙ ስለሆነ አብዛኞቹ የቆዩ ሰራተኞች ናቸው።
በጣም አስፈላጊ በመሆናቸው ነበር በዚህ ያህል በጀት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረው 15 እና 20 ዓመት የሞላቸውም አሉ ስራው ላይ ችግር ሊያመጣ ይችላል።
በአንድ ጊዜ ይሄን ያህል ሰው ከሴክተሩ ከተቀነሰ ችግር ሊፈጠር ይችላል ዋናው ነገር ግን ስራው እንዳይስተጓጎል ሃላፊነቱን ላለው የመንግስት ሰራተኛ እያስተላለፉ መሄድ ያስፈልጋል።
ቀላል ስራ አይደለም የሚጠብቀን የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን።
የመጨረሻ ውሳኔዎችን አልሰማንም ከአሜሪካ መንግሥት በየጊዜው የተለያዩ ውሳኔዎች እየተላለፈ ስለሆነ ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ ነው የሚባለው ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ተመሳሳይ ነገር ነው እያደረጉ ያሉት ከሁሉም ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅትም በቦርድ ደረጃ ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።
ሰራተኞችም እንዲያውቁ እኛም ጫናውን ለማሳወቅ እና መፍትሄው አብሮ ለመፈለግ እንዲቻል ለመንግሥትም አሳውቀናል ስራ እንዳይጎዳ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል።
በዚሁ ከቀጠለ ሌላም ከባባድ ውሳኔዎች ሊወሰን ይችላል የመድኃኒት ግዢ እና ሌሎችም ድጋፎች ሊቋረጡ ይችላሉ አይታወቅም እንዳይቋረጥ እና እንዲቀጥል እኛም እንደሃገር የምንችለውን ጫና እናደርጋለን።
በውስጥ አቅም በውስን የሰው ሃብት ባለን በጀት ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ በሽታዎች ተመልሰው ከፍ እንዳይሉ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረግን እንገኛለን በሚቀጥሉት ጊዜያት የሚመጡ ውጤቶችን እና ቀጣይ ውሳኔዎችን እናሳውቃለን " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#መቄዶንያ
“ ህንፃው ለማጠናቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። ለማጠናቀቅ ወደ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” - መቄዶንያ
መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በሚያስገነባው ሆስፒታል ጭምር ያለው ህንፃ ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው እርዳታ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።
ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ “ በሰይፉ ኢቢኤስ የዩቱብ ቻነል ” ድጋፍ ማድረጊያ መርሀ ግብር ስለሚጀመር ደጋጎች ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ በአንጽንኦት ተጠይቋል።
ይህ የተባለው ዛሬ በመቄዶኒያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
የመቄዶንያ መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ደግሞ፣ “ ይህን ህንፃ ጀምረነዋል። ለማጠቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” ብለዋል።
ህንፃው ምን የማጠቃለያ ስራዎች ቀርተውት ነው ድጋፍ ያስፈለገው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ ሴራሚክ የባኞ ቤት እቃዎች፣ 7 ሊፍቶች፣ የኤሌክትሪክ ፊኒሽንግ እቃዎች ገና ናቸው ” ሲሉ መልሰዋል።
በመቄዶንያ ምን ያክል የአእምሮ ህሙማን አሉ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ወደ 2,500 የአእምሮ ሆሙማን፤ ከ2,000 በላይ ዳይፐር ተጠቃሚዎች፣ ከዚያ ውጪ ያሉት አረጋዊያን ናቸው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ፣ “ በ44 ቅርንጫፍ ከ8,000 በላይ ሰዎች አሉ። በየጊዜው ሰው እየጨመረ ነው የሚሄደው። ህክምና የሚፈልጉ ሰዎች ጭምር ናቸው ያሉት ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከ8,000 በላይ ወገኖችን ከጎዳና በማንሳት በ44 ቅርንጫፎች በቀን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ሰብዓዊ ድጋፍ የሚረዳ ማዕከል ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
የአፖሎ አካውንት በመክፈት ወይም የአፖሎን መተግበርያ ለሌሎች በማጋራት አንዲሁም ገንዘብ ተቀማጭ በማድረግ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ።
የመርሃ ግብሩን ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች ያግኙ፡፡
/channel/BoAEth/1525
አፖሎን በማውረድ ተሳታፊ ይሁኑ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች: https://apps.apple.com/eg/app/apollo-digital/id1601224628
ለህዋዌ ስልኮች ፡https://appgallery.huawei.com/app/C108966741
#መጣሁልሽ #አምሮኛል_መጣሁልሽ #ApolloWinBig #DepositAndWin #JoinApolloGetRewarded