tikvahethiopia | Неотсортированное

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1531512

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Подписаться на канал

TIKVAH-ETHIOPIA

🚨#Alert

" የወጣው መግለጫ ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው ! " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

" ህጋዊ ያልሆነ ቡድን ደግፎ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማፍረስ ፤ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን እና ሰራዊቱን ለመበተን መንቀሳቀስ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ " የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር አስታወቀ።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ ጥር 15/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ስም የወጣው መግለጫ አላማውን የሳተ እና ሰራዊቱ ከተሰጠው ተልእኮ ውጭ ነው ብሏል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ " በሰራዊት ከፍተኛ አዣዦች ስም የወጣው መግለጫ እንደማያውቀው በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ያልተለመደ ተግባር ነው " ብሎታል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ " ያልተለመደ ተግባር " ሲል የገለፀውን ውሳኔ አስመልክቶ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን እና ሁኔታውን መርምሮ ዝርዝር ማብራርያ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

" በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ስም የወጣው መግለጫ ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው " ብሏል ጊዚያዊ አስተዳደሩ።

" ሃላፊነት የጎደለውን ውሳኔው ወደ ታች ለማውረድ ጥድፍያ የተሞላበት እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑ ደርሼቤታለሁ " ያለው የጊዚያዊ አስተዳደሩ " የሚያስከትለው አደጋው እጅግ ከፍተኛ  መሆኑ በመረዳት ተግባሩ በአስቸኳይ መቆም አለበት " ሲል አስጠንቅቋል።

" መላው የፀጥታ አካላት ህገ-ወጥ ውሳኔው የህዝቡን ችግር የሚያባብስ የጦርነት አዋጅ እና ስርዓት አልበኝነት የሚያስከትል መሆኑ በመገንዘብ በፅናት እንድትቃወሙት ትእዛዙን ተግባራዊ እንዳታደርጉ አስታውቃለሁ " ሲልም አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የትግራይ ጉዳይ ወዴት ?

በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች እንደሆኑ የገለጹ መኮንኖች ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ' የተዳከመ ' ያሉት በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተነስቶ በሌላ እንዲዋቀር መወሰናቸውን ገልጸዋል።

" የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ውሳኔ አሳልፈናል " ብለዋል።

" በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊነቱን በአግባቡ አልተወጣም የሌሎች መጠቀሚያ ሆኗል " የሚል  ክስም አቅርበዋል።

" በጊዜያዊ አስተዳደሩ ቁልፍ ሥልጣን የነበራቸው አመራር እና አባላት ከተሰጣቸው ተልዕኮ ውጪ የሕዝብን ጥቅም ወደ ጎን በመተው ክህደት በመፈጸም የውጭ ኃይል መሣሪያ ሆነዋል" ብሏል።

በሕዝብ ጥቅም ላይ ስለደረሰው ጉዳትም ሆነ " የውጭ ኃይል " ያሉት አካል ማንነትን በተመለከተ በግልጽ የተናገሩት ነገር የለም።

የወታደራዊ አመራሮቹ በሰጡት መግለጫ በስፋት ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ድክመት ሲናገሩ የነበረ ሲሆን " የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም እየሞከረ ነው " የሚል ክስም አቅርበዋል።

ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ለተካሄደው (በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን) የህወሓት 14ኛ ጉባኤ እውቅና በመስጠት በጉባኤው ውሳኔ መሠረት የጊዜያዊ አስተዳደር የአመራሮች ለውጥ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንን ጉባኤ የምርጫ ቦርድ እንዲሁም ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እውቅና እንደነፈጉት ይታወሳል።

ወታደራዊ አመራሮቹ " ህወሓት የትግራይን ጊዜያዊ አስተዳደር ለማሻሻል ያሳለፈው ውሳኔ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን " ያሉ ሲሆን " ሠራዊቱን ወክለው በጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት የሆኑትን ግለሰቦች በመገምገም እምነት የሚጣልባቸው ያልሆኑትን በሌሎች እንዲተኩ ወስነናል " ብለዋል።

" ጊዜያዊ አስተዳደሩን በሠራዊቱ ላይ የሚካሄደውን የስም ማጥፋት ዘመቻን መከላከል አልቻለም " በሚል ' በክህደት ' ወንጅለውታል።

በአሁኑ ወቅት በትግራይ ውስጥ ያለው ችግር " ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚሻ ነው " ያሉት አመራሮቹ " ማንኛውም ነገር ከትግራይ ሠራዊት አቅም በላይ አይደለም ይህንን ሰበብ በማድረግ የሚደረግ ጣልቃ ገብነትን አንቀበልም " ብለዋል።

አመራሮቹ በደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን በግዚያዊ አስተዳደር ያለው 50+1 ድርሻ እንዲረከብ እንደሚፈልጉ ተናግረዋን።

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ኃይሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር እንደሆኑ የገለጹት መኮንኖቹ በግልጽ ለደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ቡድን ያደላ አቋም ይዘዋል ፤ ይህ ደግሞ አሁን ላይ በክልሉ ያለውን ሁኔታ አስፍሪ አድርጎታል የሚሉ አስተያየቶች ሲሰጡ መመልከት ችለናል።

ህወሓት በአቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሁለት ተከፍሎ ላለፉት ወራት እጅግ በጣም በከረረ የመግለጫ እና የሚዲያ ምልልስ ላይ ሲሆን የታጣቂ ኃይሎች እስካሁን በክልሉ ጉዳይ በይፋ አቋማቸውን ሲገልጹ አልታዩም ፤ የዛሬው ለደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ያደላ የድጋፍ መግለጫ ጉዳዩ ወዴት ያመራ ይሆን ? የሚል ስጋት ደቅኗል።

ትግራይ በርካቶች ያለቁበትን እጅግ አስከፊ የሆነ ጦርነት አስተናግዳ ከህመሟ  ገና ያላገገማች ሲሆን አሁን በክልሉ ያለው መካረር መፍትሄ አለማግኘቱ ብዙዎችን እያሳዘነ ይገኛል።

#BBCTigrigna
#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በአደጋው የ25 ሰዎች ሲሞቱ፣ 14 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " - ፖሊስ

በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ወሎ ዞን ፤ ዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ የ25 ስዎች ሕይወት አልፏል።

ዛሬ ጥር 15 2017ዓ.ም ከጥዋቱ 12 :00 ከኩርባ ከተማ ተነስቶ ወደ ደሴ ከተማ ሲጓዝ ነው አደጋው የደረሰው።

የዳውንት ወረዳ ፖሊስ ፅሕፈት ቤት ታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-32917 የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከኩርባ ከተማ በግምት 9 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ልዩ ቦታው 04 ቀበሌ ሰጎራ ከተባለ አካባቢ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት ገልጿል።

በአደጋውም የ25 ሰዎች ሲሞቱ፣ 14 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል።

በ15 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መደረሱ ተገልጿል።

ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በደላንታ እና ደሴ ሆስፒታሎች ተወስደዋል።

መረጃው የሰሜን ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ዋና እምባ ጠባቂ ተሹሞለታል።

በተሿሚዎቹ ላይ ከፖለቲካ ገለልተኛ ስለመሆናቸው ጥያቄ ቢቀርብም ሹመታቸው ፀድቋል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ዋና እምባ ጠባቂ ሆነው በህ/ተ/ም/ቤት ተሹመዋል፡፡

የኔነህ ስመኝ (ዶ/ር) ምክትል ዋና እምባ ጠባቂ፣ አቶ አባይነህ አዴቶ ደግሞ የዘርፉ እምባ ጠባቂ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ዶ/ር የኔነህ ስመኝ በአማራ ክልል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ሆነው እንዳገለገሉ ተነግሯል፡፡

አቶ አባይነህ አዴቶ ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ  ክልል የፍህና ህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል።

እጩዎቹ " ከሁሉም ክልል በህዝብ ይፋዊ ጥቆማ ከተሰጠ በኋላ ከም/ቤቱ በተመረጡ የእጩ አቅራቢ ኮሚቴ በተለያዩ መመዘኛዎች መሰረት በተሰጣቸው ነጥብ የተመረጡ ናቸው " ተብሏል፡፡

ከመመዘኛዎቹ መካከል ከፖለቲካ ፓርቲ ነፃ የሆኑ የሚለው አንዱ ቢሆንም ሁሉም እምባ ጠባቂ ሆነው የቀረቡ እጩዎች የመንግስት ከፍተኛ ተሿሚዎች የነበሩ እንደመሆናቸው ገለልተኝነታቸው አጠራጣሪ ነው የሚል ጥያቄ ከምክር ቤት ተነስቶ ነበር፡፡

በተጨማሪም በሰብአዊ መብቶች ላይ የሰሩ የህግ ሰዎች ጠፍተው ነው ወይ ? የሚል ጥያቄም ቀርቧል፡፡

ለዚህ ጥያቄ አፈ ጉባኤው ዝርዝሩን የእጩ አቅራቢ ኮሚቴው ፈትሿል ከማለት ውጭ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም፡፡

በምክር ቤቱ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስተር የሆኑት ተስፋዬ ቤልጅጌ (ዶ/ር) ፤ " የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆነው የነበረ ቢሆንም ከፓርቲው እንዲወጡ ይደረጋል እንጂ እንዳይሾሙ የሚከለክል ህግ የለም " ሲሉ በአጭሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ያም ሆኖ ሹመታቸው በምክር ቤት የፀደቀላቸው የኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም ተሿሚዎች በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ በመፈፀም ሀላፊነታቸውን ተረክበዋል፡፡

የዲሞክራሲ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች ከፖለቲካ ገለልተኛ እንዲሆኑ ኢትዮጵያ እውቅና የሰጠችውና የብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት አሰራርን በተመለከተ እ.አ.አ በ1993 የወጣው የፓሪስ መርሆች ያስገድዳል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋምን ጨምሮ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ ሀላፊዎች ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ነዳጅ

⛽️“ ነዳጅን በኮፓን የማድረግ እሳቤው በነዳጅ እጦት ተማረን ግዴታ የኤሌክትራክ ተሽከርካሪ እንድንጠቀም ለማድረግ ነው ” - አሽከርካሪዎች

➡️ “ ማደያ የነበረው ነዳጅ ሲጎድል የወሰዱትን በሁለት፣ በሦስት እጥፍ ጨምረው የመሸጥ ሁኔታዎች እንዳሉ በጥናት አረጋግጠናል” - ቢሮው

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከጥር 30 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ነዳጅ የሚቀዳው ኩፓን እንደሆነ የሚገልጽ ሰርኩላር ከቀናት በፊት አውርዷል።

እንደ ቢሮው ገለጻ ከሆነ መመሪያውን ለማውረድ የተገደደው በተለይ ባለሁለትና ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ነዳጅ በተደጋጋሚ በመቅዳት በውድ ዋጋ እየሸጡ ሌሎቹን ለነዳጅ እጥረት እያጋለጡ በመሆኑ ነው።

መመሪያውን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎች ደግሞ፣ “ ነዳጅ በኩፖን እንዲሆን የተደረገው በአሽከርካሪዎች ሳቢያ ነው መባሉ የተጨፈለቀ እሳቤና እንደማንፈለግ ማሳያ ነው ” ሲሉ ትችታቸውን አቅርበዋል።

ጉዳዩን በጥናት ደርሰውበት ከሆነም ድርጊቱን የፈጸሙት ላይ እርምጃ መውሰድ እንጅ ሁሉን በአንድ ላይ ጨፍልቆ መውቀስ ተገቢ እንዳልሆነ ገልጸው፣ “ ነዳጅን በኮፖን የማድረግ እሳቤው በነዳጅ ተማረን ግዴታ የኤሌክትራክ ተሽከርካሪ እንድንጠቀም ለማድረግ ነው ” ብለዋል።

“ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪውንም መጠቀም አይገደንም ” ያሉት አሽከርካሪዎቹ፣ “ ግን በየትኛው የተሟላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው የምንጠቀመው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ነዳጅ በኮፖን እንዲቀዳ የተላለፈውን መመሪያ ተከትሎ ላቀረቡት ቅሬታና ስጋት ምላሽ እንዲሰጡ የቢሮውን ምክትል ኃላፊና የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ታዲሁንን ጠይቋል።

ምን መለሱ?

“ ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ጋር የሚገናኝ ነገር የለም፡፡ 

የአገሪቱ የቀጣይ አቅጣጫ በእርግጥ እየተከተልን ካለነው ዓለማዊ አጠቃላይ ሁኔታ አኳያ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን መጠቀም ጠቀሜታው የጎላ ነው ወደዛም ነው የምንሄደው በሂደት፡፡ 

ግን ዛሬ በአስገዳጅ ሁኔታ ይህን ፈጽሙ የሚል የተቀመጠ አቅጣጫ የለም፡፡ የኛም ፍላጎት ይሄ አይደለም፡፡ ችግሩን መፍታት ስላለብን ነው፡፡ 

ደብዳቤውም ሲጻፍ አጠቃላይ በክልሉ ያሉ ባለሁለትም ሆነ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ይህንን ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ኢንቴንሽን የለውም፡፡ ይሄን አይነት እይታ የለንም፡፡

ግን ችግሩን የሚፈጥሩ አካላት በስፋት አሉ። ችግሩ በገሃድ የሚታይ ነው፡፡ የህዝቡም ቅሬታ ነው፡፡ ስለዚህ ካለው ነገር አኳያ ችግሩን ለመቅረፍ ከተቀመጡ አሰራሮች ውስጥ አንዱን ተግባራዊ ወደ ማድረግ ነው የገባነው፡፡ 

ይሄ ሲባል ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ደረጃ ወንጀል እየሰራ ነው የሚል እይታ የለንም፡፡ ግን ችግር የሚፈጥሩ አካላትን ለይቶ እርምጃ ለመውሰድ ያገለግለናል ” ብለዋል።

አጠቃላይ መመሪያውን መተግበር ያስፈለገበትን ምክንያት በተመለከተ ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽስ ምን አሉ ?

“ ምርት በስፋት ይገባ ነበር ከዚህ በፊት። የሚመጣው ምርት ግን በተቃራኒው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚወጣበት፣ የሚባክንበት ሁኔታ አለ። ምርትን ከካምፓኒዎች ተቀብለው የሚያሰራጩ የማደያ ባለቤቶችም አሉ። 

ሁሉም ማለት አይቻልም የተወሰኑት ግን ለሚፈለገው አገልገግሎት እንዳይውል ጨለማን ተገን በማድረግ የድለላ ሥራ ለሚሰሩ አካላት በመስጠት የመጣን የነዳጅ ምርት ግማሽ ወይም ሙሉውን ዋጋ ጨምረው በአይሱዚ ጭነው የማውጣት ሁኔታዎች አሉ። 

ከዚያ ባሸገር ግን እንደ ክልል በጣም የተቸገርነው የባጃጅና ሞተር ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ከቀዱ በኋላ ውስጥ ለውስጥ ባሉ ቤቶች ውስጥ ወስደው ወደ ልላ እቃ በመገልበጥ በቀን ብዙ ዙር በመመላስ ነዳጅ ይቀዳሉ። 

ያ ሲሆን ማደያ የነበረው ነዳጅ ሲጎድል የወሰዱትን በሁለት፣ በሦስት እጥፍ ጨምረው የመሸጥ ሁኔታዎች እንዳሉ በጥናት አረጋግጠናል። አብዛኛዎቹ ላይ እርምጃ ወስደናል።

ስለዚህ ይሄን ችግር ለመፍታት ሲባል ከዚህ በፊት በሪፎርም የተቀመጠ አሰራር ስለነበረ ይሄን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ተብሎ ነው በአዲስ መልክ ሰርኩላር የተጻፈው።

ስለዚህ በአካባቢው ያሉ የንግድ ተቋማት ኮፖን ያዘጋጃሉ። ኮፓን ሲያዘጋጁ የአሽከርካሪው ስም፣ ፎቶ፣ የተሽከርካሪው ታርጋና ውስጥ ክፍል ያለ የሞተር ሚስጢር ቁጥር በማካተት ነው የሚዘጋጀው።

ያ ሲሆን ለአሽከርካሪው ትክክለኛ ምድባ ይደረለታል። በዚህ መልክ ስምሪት ይሰጥና በተፈቀደለት ቦታ ተኪዶ ነዳጅ ይቀዳል። ለአገልግሎት ሲያውል ተመልሶ ይቀዳል። ” ብለዋል።

ይህ በጥናት ጭምር የተረጋገጠ ከሆነ ነዳጅን አውጥቶ በመሸጥ አኳያ በተጨባጭ ምን ያህል አሽከርካሪዎችና ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል? ስንል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

ቢሮው ምን ምላሽ ሰጠ ?

“ ዋናው መሠረቱ፣ ምንጩ ማደያው ስለሆነ እሱ ላይም ቁጥጥር ተደርጓል። በተደጋጋሚ ከተለያዩ አካባቢዎች እርምጃ የተወሰደባቸው ወደ ሰባት ማደያዎች አሉ።

ወላይታ ዞን ወደ 4 ቦታዎች፣ ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ ላይ፣ ጌዲዮ ዞን ላይ ይርጋጨፌ ከተማ፣ ሌሎቹም ጋ የነበሩትን አሽጎ በህግ ሂደት የተከሰሱበት ሁኔታ አለ። 

የነዳጅ ምርቶችን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙት ቁጥር ስፍር የለውም።

የተሽከርካሪዎቹ  ቅርብ ጊዜ ነው በጥናት የተረጋገጠው። ከዚያ አኳያ ይህን ሰርኩላር መበተን ነበረብን። ግን በተጨባጭ ችግሩን እያወሳሰቡ ያሉት እነርሱ ናቸው። ” ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🔴 “ በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል ” - ማኀበሩ

🔵 “ 20% የደመወዝ ጭማሪ አድርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል ” - ሠራተኞቹ

“ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰናል ” - ፌደሬሽኑ

በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ መሠራተኞች ማኀበር ሥር የሚተዳደሩት የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና የሲምካርድ አፕሩቫል ሠራተኞች በማኀበሩ ላይ ቅሬታ ማቅረባቸውን ከሰዓታት በፊት መረጃ አድርሰናችሁ ነበር። 

ቅሬታ የቀረበበት ማኀበሩ በወቅቱ ማብራሪያ ሳይሰጥ የቆዬ ሲሆን፣ በኋላ ለቀረበበት ቅሬታ በሰጠን ምላሽ፣ “ስምምነት ላይ ደርሰናል” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማኀበሩ የሰው ኃብት አቶ በፍቃዱ አበራ፣ “ስብሰባ ላይ ነበርኩ። ውይይት ላይ የነበረ ጉዳይ ነው። ውይይቱም በሰላም ተጠናቋል” ብለዋል።

ሠራተኞቹ ብዙ ቅሬታ አላቸውና በምን ተስማማችሁ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “አጠቃላይ እንደቀረፍን ነው ልነግርህ የምችለው። በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል” ነው ያሉት።

ስምምነት ላይ ደርሳችኋል ስንል የጠየቅናቸው ሠራተኞቹ በበኩላቸው አሁንስ ምን አሉ ?

“ ተነጋግረናል ሥር ጀምረን ከዛ ለማስተካከል፡፡ 20% የደመወዝ ጭማሪ አደርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል፡፡

'የትራንስፖርት ጉዳይም ይስተካከላል፣ አሁን ባለው የሥራ ማቆም ምክንያት ማንም ሰው እንዳይባረር፣ ሌሎችንም ጥያቄዎች ደግሞ በኅብረት ስምምነት ገብተን እንፈታልን’ ብለው ሁሉም ሠራተኞች እንዲመለሱ ነው የስማማነው፡፡

ችግሩ ተፈትቷል፡፡ የሚዲያ ትኩረት አጣንና በመጨረሻ በማይሆን ነገርም መስማማት ግዴታ ሆነብን፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በላይ ሥራ ካቆምንም የሥራ ዋስትና አይኖርም ብለን እጅ ሰጥተናል፡፡ 

አንገብጋቢው ጉዳይ የደመወዝ ጉዳይ ስለነበረ እሱ ላይ 20% ጭማሪ በቀጣይ ወር ኢፌክቲቭ እንደሚሆን፣ ከዚያ ውጪ ሌሎች የሚሻሻሉ ነገሮችን በውይይት ተቀራርበን መስራት አለብን በሚለው ተነጋግረናል ” ብለዋል።


የ20% ደመወዝ ጭማሪ እዳደረገላቸው ነው የገጹት ሠራተኞቹ፣ ይሄ እውነት ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ የማኀበሩ የሰው ኃብት፣ “ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ከመስጠት እቆጠባለሁ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ ተደርጓል የተባለው የደመወዝ ጭማሪ ትክክል ነው? ሲል በውይይቱ ሲሳተፍ ለነበረው ለትራንስፓርትና መገናኛ ሠራተኛ ማኀበራት ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ጥያቄ አቅርቧል።

የፌደሬሽኑ ፕሬዜዳንት አቶ አባትሁን ታከለ ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ ደመወዝ ጭማሪ በኀብረት ስምምነቱ የሚቀመጥ ነው። ኀብረት ሰምምነት አልነበረም። ወደፊት በኅብረት ስምምነት እንደምናስቀምጥ፣ ዘላቂ መፍትሄ እንደምናመጣ ተግባብተናል ከአሰሪው ጋ።

ነገር ግን ለጊዜው አሁን ያለውን ሁኔታ አገናዝበን አሰሪው ከታች ከ5% ተነስቶ ወደላይ ከፍ ብሎ፣ ሠራተኞም ከላይ ወደታች መጥተው፣ በኛም መሠረት ከየተካቲት 1/2017 ዓ/ም 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምነት ላይ ደርሰናል።

አሁን ሠራተኞቹ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ከነገ ጀምሮ ሥራ ይገባሉ ”
ብለዋል።

ሠራተኞቹ ቅር የተሰኙባቸው ከደመወዝ ውጪ ያሉ ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በምን ተስማማችሁ! ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ፕሬዜዳንቱ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ሌሎች የተነሱ ወደ ዘጠኝ ጥያቄዎች ነበሩ፣ ለጊዜው በኅብረት ስምምነት ወደፊት የሚፈተለ አሉ። የትራንስፓርት ጉዳይም በኀብረት ስምምነት የሚፈታ ነው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በ6 ወራት የተመዘገበ ፍቺ ሲጨርም ጋብቻ ቀንሷል።

የአዲስ አበባ ሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ የተቋማቸውን የበጀት አመቱን የስድስት ወራት አፈጻጸም ትላንት ሪፖርት አድርገዋል።

በዚህም ወቅት እንደገለጹት ከተከሰተው 21,674 ጋብቻ ለመመዝገብ ታቅዶ 15,574 (72.65%) ምዝገባ ማደረግ እንደተቻለ ተጠቁሟል። ቁጥሩ ከ2016 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 7% የምዝገባ ቅናሽ አሳይቷል።

ከተከሰተው ፍቺ 4,873 ለመመዝገብ ታቅዶ 3,769 ፍቺ የተመዘገበ ሲሆን ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 33.99% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።

በተጨማሪ ፦

➡️ ከተከሰተው ሞት 15,716 ለመመዝገብ ታቅዶ 11,376 (72.38%) ምዝገባ በማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 29.83% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።

➡️ ከተወለዱ ህፃናት ውስጥ 37,750 ለመመዝገብ ታቅዶ 41,183 መመዝገብ መቻሉ ተጠቁሟል። ይህም በከተማው ምዝገባ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።  ከ2016ዓ.ም አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር 103% ብልጫ አሳይቷል።

በሌላ በኩል ፥ ባለፉት 6 ወራት 25,581 የክልል መሸኛዎች ትክክለኛነት እንዲጣራ ለክልሎች መላኩን የገለጸው ተቋሙ አገልግሎት ለማግኘት ሪፖርት ያደረጉ 9,504 አመልካቾችን መሸኛ መርምሮ የነዋሪነት ምዘገባ አድርገው አገልግሎት እንዲያገኙ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

ተጨማሪ
@addisvaitalpress

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia
🎁 ስድስት ወር ሙሉ ዳታ እንደልብ! ለረጅም ጊዜ የሚቆዩትን ሜጋ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 1,000 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ኳስ እንከታተል! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም አስተማማኝ ኔትወርክ ጋር ወደፊት!⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከውጭ የሚመጣ ተሟጋች አያስፈልገንም !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሂጃብ ጉዳይ ምን አሉ ?

" ከውጭ የሚመጣ ተሟጋች አያስፈልገንም። ጉዳዩ በራሳችን ነው የምንጨርሰው። ያለን አንድነት እና መፈቃቀር ሊነካ አይገባም።

የአክሱም ህዝብም በዚህች ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዳለው ነው የማውቀው። አንዳንድ በክፋት የተሰማራ ካልሆነ፥ እያያችሁት እንዳለ ይህ ጉዳይ ያላሳዘነው፣ መፍትሔ መበጀት አለበት ያላለ የለም።

ችግሩ እንደሚፈታ ነው ማምነው፣ ያለን ግንኙነትም የሚያሳየው ይህ ነው። በመዘግየቱ ግን ለሙስሊሙ ማሕበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ልጆቹ ወደትምህርት ቤት መላክ የሚፈልግ የትግራይ ህዝብ ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ አለብን ብዬ ነው የማምነው። "


Quote - #DW

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

" የሀጅ  ጉዞ ምዝገባ ጥር 15 ይጀምራል የሀጅ ጉዞ ዋጋ አሁን ባለው  625,000 (ስድስት መቶ ሃያ አምስት ሺ) ብር ነው " - ጠቅላይ ምክር ቤቱ

የ1446ኛው የሀጅ እና ዑምራ ጉዞ ምዝገባ ከጥር 15 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ብቻ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገልጿል።

ምዝገባው ጥር 15/2017 በሁሉም የክልል እና የከተማ አስተዳደር የምዝገባ ጣቢያዎች ይጀመራል።

የሳውዲ ሀጅ ሚኒስቴር ባስቀመጠው አሰራር መሰረት ያለው የምዝገባ ጊዜ አጭር በመሆኑ ሁጃጆች (ተጓዦች) በወቅቱ ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀርቧል።

የዘንድሮ የሀጅ እና ዑምራ የጉዞ ዋጋ 625 ሺህ ብር መሆኑ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ " የጉዞው ዋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የታየው የዶላር ጭማሪና በአየር መንገዶች ላይ ያለው የትኬት ዋጋ መናር ዋጋው ከፍ እንዲል አድርጎታል " ብሏል። 

" የሀጅ ዋሃ ከዶላር አንፃር የ4,921 ዶላር ቅናሽ እንዲደረግበት ቢደረግም በብር ግን ጭማሪ አሳይቷል " ሲል ገልጿል።

ጠቅላይ ምክር-ቤቱ የአገልግሎት ዋጋን በመቀነስ በዕቅድ የተያዙ ፕሮጀክቶችን በማጠፍና በሳውዲ የሚቀርበውን አገልግሎት ተመጣጣኝ እንዲሆን በማድረግ 108 ሺህ ብር ቅናሽ እንዲኖረው ማድረጉን አሳውቋል።

የዶላር ዋጋ ከፍ በማለቱ ግን ብሩ መጨመሩ ተገልጿል።

ባለፈው ዓመት ለአንድ ሀጅ ዋጋ አጠቃላይ ብር 329,000 እንደነበር ይወሳል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

💥 የኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX) ክፍያዎን በቀላሉ በቴሌብር ይፈጽሙ!!

ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX) ጋር በተያያዘ የሥልጠና፣ የአባልነት፣ እንዲሁም የቡና፣ ጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ምዘና ክፍያን ጨምሮ ሌሎች ክፍያዎችን በፈጣኑ ቴሌብር መክፈል ተችሏል፡፡

💡 ከ ECX ሲስተም በሚያገኙት ልዩ የክፍያ ማጣቀሻ ቁጥር በቀላሉ በቴሌብር መክፈል ይችላሉ!

👉 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ወይም *127# ይጠቀሙ!

ቴሌብር ሱፐርአፕ ➡️ ክፍያ ➡️ ግብር እና የመንግሥት አገልግሎት ➡️ የመንግሥት አገልግሎት ክፍያዎች ➡️ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ዛሬ ጠዋት 1 ሠዓት ከ30 ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ' ጠባሴ ' አካባቢ ሲደርስ መንገድ ስቶ በመውጣቱ የሦስት እግረኞችን ሕይዎት ቀጠፈ፡፡

ከሟቾቹ አንዷ ልጆቿን ወደ ትምህርት ቤት ስትሸኝ የነበረች እናት ናት።

ከሟቾች በተጨማሪም በአደጋው የ1 ዓመት ከ7 ወር ሕጻንን ጨምሮ በ9 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር እንደሆነ ጠቁሟል። አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ ነው ተብሏል።

መረጃው የኤፍኤምሲ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች ! " - ሰልፈኞች

በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል።

ሰልፉ የተዘጋጀው በትግራይ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት አማካኝነት ነው።

ምክር ቤቱ ዛሬ " ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ተገኝተው ነበር።

ሰልፈኞቹ ፦

- ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይመለሱ !
- ህገ-መንግስት ይከበር !
- ፍትህ ለእህቶቻችን ነፃነት ለሁሉ !
- ሂጃብ መልበስ ሃይማኖታዊ መብትና ግዴታ ነው !
- ሂጃቤ መልኬ ነው !
- የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይከበር !
- ሰላም እና ፍትህ ለትግራይ !
- መብታችን ይጠበቅልን !
- ከተበዳዮች ጎን እንቁም !
- ፍትህን እንጠይቃለን !
- ከሂጃባችን ጋር ታግለናል፤ ሂጃባችን ለብሰን እንማራለን !
- ሂጃባችን ምርጫችን እና መብታችን ነው !

... የሚሉና እና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።

በመቐለ ሮማናት አደባባይ ለተሰባሰቡት ሰልፈኞች መልእክት ያስተላለፉት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዜዳንት ሸኽ አደም ዓብደልቃድር  ፥ " ትግራይ የሃይማኖቶች የመቻቻል የነፃነት ተምሳሌት ነች፤ ይሁን እንጂ ይህንኑ ስልጡንነት ወደ ኋላ በሚመልስ መልኩ ልጆቻችን ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ ከዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እንዲቀሩ ተደርገዋል "  ብለዋል።

ችግሩ ሳይባባስ እንዲፈታ ለሁለት ወራት በላይ የተለያየ ጥረቱ መደረጉ ያወሱት ፕሬዜዳንቱ  " ትምህርት ቤቶቹ የክልሉ እና የአገሪቱን ህግ በማክበር የሂጃብ ክልከላውን በአጭር ጊዜ ማንሳት አለባቸው ፤ ጥያቄያችን በአጭር ጊዜ ካልተመለሰ ግን ጥያቄያችን እስከ መጨረሻው ድረስ በሰላማዊ መንገድ እንቀጥላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

" የክልሉ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ክርስትያን ወንድሞቻችን ችግሩ ክጅምሩ እንዲፈታ ብዙ ጥረት  አድርጋችሃል " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ችግሩ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስም የጀመራችሁት ትግል ተጠናክሮ ይቀጥል " በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም የሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ጉዳዩ ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት እንዳያመራ የሚያስገነዝብ ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ከትምህርት ገበታቸው የተስተጓጎሉ ሴት ተማሪዎች መካካሻ ትምህርት እንዲያገኙ ያለሙ የሚያወሱ 12  ጥሪዎች እና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ መልእክቶች ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር በማቅረብ እና  በማስተላለፍ ከረፋዱ 4:30 ሰልፉ ተጠናቋል።

ሰላማዊ ሰልፉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የከተማዋ የፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥበቃ ያደረጉ ሲሆን በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፥ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ ክልከላ አድርገዋል የተባሉት በአክሱም ከተማ የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የጋራ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥተዋል።

ት/ቤቶቹ ምን አሉ ?

" 1. የሴት ሙስሊም ተማሪዎች የሂጃብ አጠቃቀም አስመልክቶ በትግራይ ያለው ህግ እና አተገባበሩ ምን ይመስላል ?

ትምህር ቤቶቻችን የትግራይ ትምህርት ቢሮ በ1995 ዓ.ም ያወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ነው እየተጠቀሙ ያሉት ። አዲስ ፖሊሲ ወይም መመሪያ እና ደንብ በትምህርት ሚንስቴር ከወጣ ደግሞ ከትምህርት ቢሮ ጋር ተነጋግሮ ይህንን መመሪያ እና ደንብ ተጠቀሙ ብሎ ይልክልናል ። እኛም ተግባራዊ እናደርጋለን። ይህን ባለልሆነበት ' እህያውን ፈርቶ ዳውላውን ' የሆነ ጥያቄ እና ጫና ግን ግራ የሚያጋባ ነው።

በ1995 ዓ.ም የወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ደግሞ ተማሪዎች መምህራን ወላጆች ተወያይተው ያፀዱቁት ላለፉት 22 ዓመታት እየተጠቀሙት ያለ መመሪያ ደንብ ነው።

በ1995 ዓ.ም የወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ደንብ ደግሞ እንዲታይ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ከወላጅ ተማሪዎች ጥያቄ ተነስቶ ነበር ። የተነሳው ጥያቄ መሰረት በማድረግ በመመሪያ እና ደንቡ ውይይት ተካሂዶ ታህሳስ 6/2017 ዓ.ም በአንድ ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ፀድቀዋል።

በውይይት እና ድምፅ አሰጣጡ የሙስሊም እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ተሳትፈውበት በሙሉ መግባባት መተማመን የተደረሰበት ነው። ታድያ ከአሁን በፊት ታይቶ የማይታወቅ የሂጃብ ክልከላ ጥያቄ ከየት ? እንዴት መጣ ? ትምህርት ቤቶታቻችን ግራ ገብቶዋቸዋል።

2. የትምህርት ቤት ዩኒፎርም አለባበስ ደንብ እና ስነ-ሰርዓት ምን ይመስላል ?

በ1995 ዓ.ም በፀደቀው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መምሪያ እና ደንብ መሰረት ትምህርት ቤቶቻችን የሚከተለውን የአለባበስ ስርዓት እንዲተገብሩ ያስገድዳል።

የቤተክርስትያን ካህናት እና ዲያቆናት ተማሪዎች ሻሽ መጠምጠምያ ፣ ነጠላ ማድረግ አይፈቀድም። ወንድ ተማሪዎች ባንከር ፣ ፍሪዝ የፀጉር አቆራረጥ አይፈቀድም።

ሴት ተማሪዎችም ነጠላ ፣ መሃረብ ፣ ሻሽ መጠምጠምያ ፣ ጥቁር የሃዘን ሻርፕ ፣ ሂል ጫማ ፣ ሱሪ ፣ የማንኛውም ሃይማኖት አለባበስ የሚያንፀባርቅ ልብስ እንዲለብሱ አይፈቀድም። ይህ የሆነበት ደግሞ በመካከላቸው የሃብት የሃይማኖት ልዩነት ፈጥሮ የመማር የማስተማር ሂደቱ እንዳይታወክ ለማድረግ ያለመ ነው።

ይህ ህግ ደግሞ ክርስትያን ፣ ሙስሊም መምህር የተማሪ ወላጅ ተወያይተው ያፀደቁት እና የሚተዳሩበት ነው። አሁን ታድያ ምን አዲስ ነገር ተፈጥሮ ነው በትምህርት ቤቶቻችን ላይ የሚዘመተው ? 

 3. ስለ ዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች መሬት ላይ ያለው መረጃ ምንድነው ?

በአክሱም አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉ።  በአራቱ ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ ለ12ኛ ክፍል አገር  አቀፍ ፈተና የሚቀርቡት  ተማሪዎች 1044 ናቸው።

ከነዚህ 1044 ተማሪዎች 17 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ 17 ሴት ተማሪዎች ለ22 ዓመታት በቆየው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ እና ደንብ በመቀበል 7 ሴት ተማሪዎች ፈተናው ለመውሰድ ፎርም ሞልተዋል።

10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ከአክሱም ከተማ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በተዘረጋ የውጭ ተፅእኖ ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸው ፎርም አልሞሉም። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ' 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እንዲስተጓጎሉ ተደረገ ' እየተባለ ነው የሚወራው። 142 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻችን የሌሉ የፈጠራ ድርሰቶች ናቸው።

የተቀሩት 10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ቢሆኑ ፎርም መልተው ለመፈተን ፍላጎት አላቸው ፤ ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፣ ከመቐለ ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በየቀኑ እየተደወለ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ የቆየውን አብሮነት እና መቻቻል የሚጎዳ ለህዝብ እና አገር የማይጠቅም መወገዝ ያለበት ተግባር ነው። "

... ሲሉ ትምህርት ቤቶቹ በጥምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በላኩት የፅሁፍ ምላሽ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle
#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በአቢሲንያ የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች የATM ካርድ በቆማችሁበት በሰከንዶች ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሂጃብ #ሰልፍ

በሂጃብ ጉዳይ ነገ መቐለ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሂጃብ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሄድ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ፥ የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ መደረጋቸውና ከትምህርት ገበታ መራቃቸው መግለጹ ይታወሳል።

በአክሱም የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሂጃብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ባለፉት ሁለት ወራት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለሦሥት ጊዜ ደብዳቤ የፃፈው እንዲሁም የፍርድ ቤት ትእዛዝ አልቀበልም በማለታቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ መገደዱን ገልጿል።

በዚህም ነገ ጥዋት 1 ሰዓት በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ አሳውቋል።

ሁሉም ፍትህ ፈላጊ የሰልፉ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርቧል።

ሰልፉ ከቀናት በፊት ዓርብ ጥር 9 ሊደረግ የነበረ ቢሆንም የጥምቀት በዓል ዋዜማ በመሆኑ ምክንያት ነው ለነገ የተዘዋወረው።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ ተከታታይ መረጃዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል ፤ ነገ ማክሰኞ ጥር 13/2017 በመቐለ ከተማ የሚካሄደውን ስልፍም ተከታትሎ ያቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሁለት ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ አንድ ሰው ከባድ አንድ ሰው ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል " - ፖሊስ

ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሠዐት በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ  ዙብአንባ ቀበሌ  ልዩ ቦታው ሞፈር ውሀ ጅረት አካባቢ ከአበባ ወደ መሀልሜዳ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ መንገድ ስቶ በመገልበጡ 2 ሠወች ወዲያው ሲሞቱ አንድ ሠው ከባድና አንድ ሠው ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የአማራ ፖሊስ አሳውቋል።

ተጎጅዎች በደብረብረሀን ሪፈራል ሆስፒታል እየታከሙ ናቸው።

ዛሬ በዚሁ  በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ፤ ዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገና ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ የ25 ስዎች ሕይወት ማለፉ ይታወቃል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray " በየመዋቅሩ ያሉ ም/ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ በመሆኑ መሾምና መሻር አይችሉም " ብሎ የነበረው የትግራይ  ክልልጊዚያዊ  አስተዳደር ምክር ቤቶቹ ህጋዊ መሰረት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ደንብ አፅድቀዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የወረዳ ምክር ቤቶች የሚያጠናክር እና ህጋዊ መሰረት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ያለውን ደንብ ከሰሞኑን አፅድቋል።

" የፀደቀው ደንብ የወረዳ ም/ቤቶች ተጠናክረው የህዝቡ ተሳትፎ እና ውክልና በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል የተፈጠረው አለመግባባት የሚቀርፍ ሁሉን በሚያግባባ መልኩ ስራቸው እንዲፈፅሙ የሚያስችላቸው ነው "  ብሏል።

ደንቡ ተፈፃሚነት እንዲኖረው ሁሉም የበኩሉ እንዲወጣ ያሳሰበው  የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ አስከታች ድረስ ያለው መንግስታዊ እና አስተዳዳራዊ መዋቅር ተጠናክሮ ህዝቡ የሚገባውን አገልግሎት ማግኘት አለበት ብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ቦይንግ 777F እቃ ጫኝ አውሮፕላን መረከቡን ገልጿል።

ይህ አውሮፕላን የካርጎ ጭነት አገልግሎት አድማስን ለማሳደግ የራሱ አስተዋፅዖ ከማበርከቱ በተጨማሪ እያደገ የመጣውን የካርጎ አገልግሎት ለማስተናገድ የራሱ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የላቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

አሁን የገባው አዲስ የካርጎ አውሮፕላን አየር መንገዱ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ረገድ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን የሚያግዙና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ተቋማት የሚለገሱ ቁሳቁሶችን ወደ ሀገር ውስጥ ይዞ መምጣቱ ተገልጿል።

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#TPLF

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማዕከላዊ ዉጥጥር ኮሚሽን ፥ የኢትየጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ትእዛዝ እና ውሳኔን አልቀበለውም / ተቀባይነት የለውም ብሏል።

" ቦርዱ ያሳተላለፈው ውሳኔ እና ትእዛዝ ህጋዊ መሰረት የሌለው ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የሚጣረስ ነው " ሲል የገለጸው ኮሚሽኑ " ቦርዱ ትዕዛዝ እና ውሳኔ ከመስጠት እንዲቆጠብ " ሲልም ገልጿል።

የቁጥጥር ኮሚሽኑ " የኢትየጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ጥር 10/2013 ዓ.ም ህወሓትን ከህጋዊ የፓለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር ሰርዞ ነበር ፤ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ግን ነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ህጋዊነቱ ተመልሶለታል " ብለዋል።

" ህወሓት ከነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደ አዲስ የፓለቲካ ፓርቲ መመዝገቡ ተቀባይነት እንደሌለው ፓርቲው ወድያውኑ ገልፀዋል " ሲልም ጠቁሞ " ይሁን እንጂ ቦርዱ ፓርቲው ያቀረበውን 'የአልቀበልም" ምላሽ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ 'ልክ አይደለም ' " ሲል አብራርተዋል።


" የህወሓት ህጋዊነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሙሉ በሙሉ እንዲመለስ (Reinstate) እንዲደረግ እንጠይቃለን " ያለው ኮሚሽኑ ፤ " ከዚህ ውጭ ያለው ውሳኔ እና ትእዛዝ ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

ከቀናት በፊትም የነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን ባወጣው መግለጫ " ለሁለትዮሽ ውይይት ዝግጁ ነኝ የምርጫ ቦርድን የተናጠል ውሳኔ ዛሬም ይሁን ነገ አልቀበልም " ማለቱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በሕጉ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።

ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል።

ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራሮችን ለሁለት የከፈለ ጉባኤ መደረጉ አይዘነጋም። በወቅቱም ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትን እና ስርዓቱን ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና እንደማይሰጥ ማስገንዘቡ ይታወሳል።


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🌟 Jasiri is calling aspiring entrepreneurs to join Cohort 8 of the Talent Investor Program!
At Jasiri we believe that businesses can and should be a force the common good. Since 2021, we’ve supported 227 entrepreneurs who have created 93 ventures, with 81 still active across 42 industries in Rwanda, Kenya, and Ethiopia.
These ventures tackle challenges in healthcare, education, agriculture, technology, and more—creating 2,035 jobs and positively impacting 12,627 individuals with their solutions.
Be part of this incredible story of impact. Apply now at 👉 jasiri.org/application.

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የስራ ማቆም አድማ የመቱት ሰራተኞች ምን አሉ ?

🚨“ በቂ ደመወዝ አይደለም የምናገኘው። ከማክሮ ኢኮሮሚው ጋርም የሚመጣጠን ስላልሆነ ተመግበን ማደር አልቻልንም” - የሥራ ማቆም አድማ የመቱ ከ350 በላይ ሠራተኞች

➡️ “ በዚሁ ዙሪያ ስብሰባ ላይ ነኝ ” - ድርጅቱ

በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ የሰራተኞች ማኀበር ሥር እንደሚተዳደሩ የገለጹ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና የሲምካርድ አፕሩቫል ከ350 በላይ ሠራተኞች ዘርፈ ብዙ ቅሬታዎች ስላልተፈቱላቸው ከትላንት ከሰኞ ጅምሮ ሥራ ማቆም አድማ ለመምታት መገደዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሚከፈላቸው ደመወዝ በቂ እንዳልሆነ፣ ድርጅቱ 80 ሰራተኞችን ያለ አግባብ እንዳሰናበተ፣ የትራንስፓርት አገልግሎት ባለመኖሩ በድርጅቱ ለማደር የሚገደዱ ሰራተኞች እንዳሉ አስረድተዋል።

ሰራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ?

“ አይሰን ኤክስፕሪያንስ የሚባለው ድርጅት የሳፋሪኮምን የኮል ሴንተሩንና የሲምካርድ አፕሩቫሉን ፕሮሰስ ወስዶ የሚሰራ ድርጅት ነው።

በዚህ ድርጅት ላይ ያለን ቅሬታ፣ በቂ ደመወዝ አይደለም የምናገኘው። ከማክሮ ኢኮሮሚው ጋርም የሚመጣጠን ስላልሆነ ተመግበን ማደር አልቻልንም።

ማታ አራት ሰዓት ከሥራ ለሚወጡ ሰዎች ትራንስፓርት የለም። ግማሽ መንገድ ወስዶ ከዚያ ‘በራሳችሁ ሂዱ’ ነው የሚለው። ይህ አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ጭራሽም ትራንስፓርት የሌላቸው ሠራተኞች ከመስሪያ ቤቱ አድረው የሚወጡ አሉ። 

አመታዊ እረፍት ሠራተኞች በፈለጉት ጊዜ አይሰጣቸውም። ከሁለት ዓመት በላይ የተጠራቀመ የአመት እረፍት ያላቸው ልጆች አሉ። ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ሠራተኞች ቅነሳ አለ። በርካታ ችግሮች ናቸው ያሉት።

በእነዚህ ጉዳዮች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በተገኙበት ስብብሰባ አድርገን ነበር። የመጣው ለውጥ ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። 

የመጨረሻውን ስብሰባ ያደረግነው ያለፈው አርብ ነበር። እንደማንስማማና ኃላፊነታችንን እንዳነሳን ተናግረናል። ከሰኞ ጀምሮም ሠራተኛው መብቴን በሕግ አስከብራለሁ ብሎ የሥራ ማቆም አድማ እያደረገ ይገኛል።

አሁን የሰፋሪኮም የጥሪ ማዕከል አይሰራም። ሲም ሽያጭ ላይ አፕሩቭ ከሚሰሩ ልጆችም ጭምር ነው አድማ ያደረግነው ስለዚህ ሁለቱም ሰርቪሶች አይሰሩም።

ይህን ከማድረጋችን በፊት ከሁለት ዓመታት በፊትም ተወያይተን ስላልተስማማን አድማ አድርገን ነበር፡፡ አሁንም በ10 ቀናት ጥያቄያችንን መልሱልን ብለን ከወር በፊት ደንዳቤ አስገብተን ነበር፡፡ ምላሽ አልተሰጠንም፡፡

ደብዳቤውን ካስገባን በኋላ አንድ ወር በፈጀ መደራደር በአራት ጊዜ ቀጠሮ ለመደራደር ሞክረን ነበር፡፡

ኢሰማኮ፣ የሰራተኛ አሰሪዎች ፌደሬሽንና ሌሎች ተቋማት በመካከል ገብተው ለማደራደር ሞክረው ካቅም በላይ ስለሆነ ሥራ የማቆም አድማ ለማድረግ ተገደናል፡፡ ዛሬ ሦስተኛ ቀናችን ነው፡፡

አይሰን ኤክስፕሪያንስን ስንጠይቅ አሁን 'ግቡልንና እናስተካክላለን' የሚል ሀሳብ እያመጡ ነው። ግን የሚጨምሩት ደመወዝም የሚያስማማን አይደለም፡፡ እስከ 15 ፐርሰንት እንጨምራለን' ነው እያሉ ያሉት፡፡

ሥራ ለማቆም የተገደደው መሰረታዊ ፍላጎታችን ማሟላት ስላልቻለ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ በየጊዜው እየጨመረ ነው ያለውና ድርጅቱ መፍትሄ ይስጠን፡፡

የምንሰራበት ሰዓት ከቀኑ 2 እስከ 11 ሰዓት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሽፍት ሌሊትም ሥራ  እንገባለን፡፡ በሌሊት ሽፍት የትራንስፖርት አገልግሎት አናገኝም። ህይወታችንን ለአደጋ የሚጥል ሥራ ነው እየሰራን ያለነው
ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ የሚመለከታቸው አካላትና ድርጅቱ ለቅሬታው የተሻለ ምላሽ ቢሰጡ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረ ሲሆን፣ ጉዳዩ በቀጥታ አይሰን ኤክስፕሪያንስን እንጂ እሱን እንደማይመለከት ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪም፣ ለቀረበበት ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ከአይሰን ኤክስፕሪያንስ አቶ በፍቃዱ አበራን ጠይቋል።

አቶ በፍቃዱ፣ በጉዳቹ ዙሪያ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ ተጠይቀው በሰጡት ቀጠሮ ወቅት ሲደወልም ስልክ ለማንሳት ለጊዜው ፍቃደኛ አልሆኑም።

በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለጉዳዩ አስተያዬት እንዲሰጡ ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኀበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዚደንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ለጊዜው የማይመች ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልጸው ቀጠሮ ሰጥተዋል።

የሚመለከታቸው አካላት በቅሬታው ላይ አሁንም አጥጋቢ ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። (የቅሬታ አቅራቢዎቹ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔈 #የነዋሪዎችድምፅ

🔴 እዛው አካባቢ በዘመናዊ መኖሪያ ቤት የማስፈር ሀሳብ ታጥፎብናል ” - ቅሬታ አቅራቢ ነዋሪዎች

🔵 “ በመመሪያው መሠረት እንደማንኛውም የቀበሌ ተነሽ እንዲስተናገዱ ነው አቅጣጫ የተሰጠው ” - የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀድሞ መሬት ልማት አስተዳደር አካል

ከዓመታት በፊት ኤግል ሔልስ የተሰኘው ድርጅት ለገሀር አካባቢ በያዘው የግንባታ ፕሮጀክት ላይ የቦታው ነዋሪዎች መንግስት የገባላቸው ቃል ታጥፎ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ መገደዳቸው እጅጉን ቅር እንዳሰኛቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ስሞታቸውን ልከዋል።

“ ከስድስት ዓመታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቃል የተገባውን እዛው አካባቢ በዘመናዊ ቤት የማስፈር ሀሳብ በማጠፍ ቦሌ አራብሳ በቆርቆሮ በተሰሩ ቤቶች ” እንዲሄዱ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ቅር ያሰኛቸውን ቆርቆሮ ቤት የሚያሳይ ቪዲዮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ነዋሪዎቹ፣ ለጉዳዩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደርን፣ የወረዳ 10 መሬት ልማት ጽሕፈት ቤትን ተጠያቂ አድርገዋል።

ለቅሬታው ማብራሪያ የጠየቅናቸው አዲሱ የክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደርና ወረዳ 10 መሬት ልማት አስተዳደር አካላት የቅሬታውን ዝርዝር በጽሞና ከሰሙ በኋላ ለጊዜው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ ከ15 ቀናት በፊት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር የነበሩትን (አሁን ከስፍራ የለቀቁ) አካል ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቋል።

በቦታው ቤት ‘ይሰራላችኋል’ ተብለው የነበረ ቢሆንም ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ ስለመገደዳቸው ነዋሪዎቹ ያቀረቡትን ቅሬታ የገለጽንላቸው እኚሁ አካል በሰጡት ምላሽ፣ “ 27 ናቸው እዛ አካባቢ ያሉት ነዋሪዎቹ። የዛኔ ተብሎ ነበር። አሁን ደግሞ ሰዎቹ እንዲነሱ ሆኗል ” ብለዋል።

“ ሙሉ ለሙሉ ይዞታቸውን ‘አስረክቡን’ እያሉ ነው። ስለዚህ መንግስት ምን አደረገ፦ ቤቶቹን ድሮ በምድር ባቡር ነበር ያከራየው ለሰዎቹ፣ ወደ መንግስትም አልተመለሰም ዝም ብሎ ለነዋሪዎቹ በምድር ባቡር ሰጣቸው ” ነው ያሉት።

“ ምድር ባቡር አሁን ጥሎ ሲወጣ መንግስት ወደ መንግስት አዞረና በመመሪያው መሠረት እንደማንኛውም የቀበሌ ተነሽ እንዲስተናገዱ ነው አቅጣጫ የተሰጠው ” ሲሉ አክለዋል።

በመርሀ ግብር ማስጀመሪያው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጭምር ነዋሪዎቹ ሳይፈናቀሉ በአካባቢው መኖሪያ ቤት እንደሚገነባ ገልጸው ነበር፤ አሁን ያ ቃል ታጥፎ ነው ? ስንል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

የቀድሞው የክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ፣ “ 27 ብቻ አይደለም የነበሩት የዛኔ። እነዚህ 27ቱ የቀሩበት ምክንያት የምድር ባቡር ቤቶች ስለነበሩ ነው ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ ሌሎቹ የቀበሌ ቤቶችኮ ሙሉ ለሙሉ ተነሱ” ያሉት እኚህ አካል “ ይሄንን መንግስት ያደረገው እነዚህ ሰዎች ነዋሪ ናቸው። ነዋሪ መበተን የለበትም ቀበሌ ቤትም ባይሆን የመንግስት ቤት ስለሆነ በመንግስት ቤት መመሪያ መሠረት አገልግሎት ይሰጣቸው ነው ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ወቅት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ምን ብለው ነበር ?

" የኛ ፍልስፍና ሀብታሞች ገንዘብና እውቀት ይዘው መጥተው እነርሱም ሞር ሀብታም የሚሆኑበት፣ በአካባቢው ያለውን ነዋሪ ሞር ስደተኛና ድሃ የሚደረግበት ሁኔታ መቆም አለበት የሚል ጽኑ አቋም አለን።

በዚሁ ምክንያት እዚህ አካባቢ ላይ የሚኖሩ ከ1,600 የሚበልጡ ቤተሰቦች፣ አባወራዎች አንደኛ ለዘመናት የኖሩበት፣ ከአዲስ አበባ ምናልባት ከአካባቢ አገራትም ከተማ በእነርሱ ይገነባል።

ሁለተኛ ለእነርሱ የመኖሪያ ቤት መስሪያ 1.8 ቢሊዮን ብር ኤግል ሔልስ ለመንግስት ስለሰጠ እዚሁ ቦታ ላይ ቤት ይገነባላቸውና አሁን ካላቸው የኑሮ ደረጃ የተሻለ የቤት ባለቤት ያደርጋቸዋል።

ሰፈሩ እዛም ውስጥ ያሉ እስከዛሬ ሲገፉ የነበሩ ሰዎችን ስናስታውስ ያንን ችግር የሚቀርፍ ይሆናል። ይህንን የመንግስት የተጀመረ አሰራር ወደ ፊት ወደ አርሶ አደሮች፣ ወደ ግለሰቦች ለማስፋፋት እንፈልጋለን።

አንድ ሰው ቦታ ኖሮት ሌላ ሰው በዚያ ቦታ ማልማት ሲፈልግ ሰውየውን ሳያፈናቅል፣ ከአጠቃላይ ፖሮጀክቱ 5ም፣ 10ም ፐርሰንት ሰጥቶ ሰውየውም አድጎ አዲስ የመጣውም ባለሃብት አብሮ የሚያድግበት ነገር ስለሚፈጥር እዚህ ቦታ ላይ ለኤግል ሔልስ አልሰጠንም። 

ቦታውን መንግስት 27 ፐርሰንት ሼር ውስዷል። ይሄ የሆነበት ምክንያት ጆይንት ቤንቸር ለመፍጠር ነው።

የነበረውን እያጠፋን፣ በአካባቢው ያለውን ሰው እየገፋን ሳይሆን ሰው ባለበት፣ ታሪካችንም ባለበት ግን የተሻለና ያማረ ነገር መፍጠር በውስጡ የያዘ በመሆኑ ይህንን ለሚያደርገው ኩባንያውንም፣ ቸር ማኑንም በሙሉ ልብ ስለማምን ዝርዝር ዲዛይን ዝርዝር ውይይት አድርገናል። 

ካሁን በኋላ ከዚህ ያነሰ፣ ሰው የሚያፈናቅል፣ ለአካባቢው ሰው ቤት የማይሰራ ባለሃበት ከሆነ ሂዳችሁ ከኤግል ልምድ ውሰዱ ይባላል ” ብለው ነበር። 


ይሁን እንጂ ይህ ቃል ታጥፎ ነዋሪዎቹ ወደ ቦሌ አራብሳ እንዲሄዱ መገደዳቸውን ገልጸዋል። 

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ቢያንስ 20 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው አልፏል " - IOM

ከጅቡቲ የተነሳች ስደተኞችን የጫነች መርከብ የመን አቅራቢያ በደረሰባት የመስጠም አደጋ ቢያንስ 20 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው ማለፉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አሳወቀ።

ከአደጋው 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የመናውያን የጀልባዋ ቀዛፊ እና ረዳቱ መትረፋቸውም ተገልጿል።

35 ስደተኞችን አሳፍራ ከጅቡቲ የተነሳችው ጀልባ ዱባብ አቅራቢያ ባጋጠማት ብርቱ ነፋስ ለአደጋው መጋለጧን ተመላክቷል።

በየመናዊ ካፒቴን እና ረዳቱ አማካኝነት ከጅቡቲ የባሕር ጠረፍ ጀልባዋ ስደተኞች አሳፍራ ቅዳሜ ዕለት በምሽት ነበር ጉዞ የጀመረችው።

አደጋው በርካታ ስደተኞች የሚጋፈጡትን አሳዛኝ አደጋ እንደሚያሳይ የገለጸው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሕገወጥ ስደት መንስኤ ለሆኑ ችግሮች መፍትኄ እንዲፈልጉ ጥሪውን አቅርቧል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ፍለጋ በጅቡቲ በኩል ወደ የተለያዩ የአረብ ሃገራት እንደሚሰደዱ በተደጋጋሚ ይነገራል።

ባለፈው ጥቅምት ወርም በተመሳሳይ አደጋ ከጅቡቲ የተነሱ 45 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተሳፈሩበት ጀልባ በደረሰበት አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። 

የየመን ባሕር አካባቢ ለስደተኞች አደገኛ ከሆኑ የባሕር መስመሮች አንዱ መሆኑን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አመልክቷል።

ኢትዮጵያውን ስደተኞች ላይ ስለደረሰው አደጋ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰማ ነገር የለም።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ዌብሳይቱ ላይ የሚያሳየን ንግድ ፈቃዱ እንደታደሰ ነው ግን ፕሪንት አያደርግም። ... ክፍያውንም እንደ ከፈልን ያሳያል ግን ክፍያ አልከፍልንም ፤ ይሄ ደግሞ የሲስተም ችግር ነው " - ቅሬታ አቅራቢ

የንግድ ፈቃድ ያለ ቅጣት ማደሻ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ/ም ይጠናቀቃል።

የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሃምሌ 1 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ያለ ቅጣት እንዲካሄድ ፕሮግራም ወጥቶ ሲካሄድ ነበር።

በኃላም ተጨማሪ ቀን ተጨምሮ እስከ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ተራዝሟል።

ይህ የተጨመረው ቀን ማለትም ያለ ቅጣት ማደሻ ሊጠናቀቅ 3 ቀን ብቻ ቀርቶታል።

ተገልጋዮች በኦንላይን ፈቃድ ለማሳደስ በስራ ቀናት እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

የንግድ ፈቃድ በኦንላይን የሚታደሰው በ
www.etrade.gov.et ላይ ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ ፈጽመው ምስክር ወረቀት በመጠባበቅ ላይ ያሉ ' የምስክር ወረቀት ያትሙ ' (Print Certificate) የሚለውን ቁልፍ በመጫን የምስክር ወረቀታቸውን ማግኘት ይችላሉ።

ከዚሁ ከንግድ ፈቃድ እድሳት ጋር በተያያዘ ግን አንዳንድ ተገልጋዮች እክል ገጠመን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት ልከዋል።

ከነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች አንደኛው  ፦

"  ክሊራንስ በታህሳስ 30 ላይ ነበር የጨረስኩት ፤ ከጨረስኩበት ሰዓት ጀምሮ ንግድ ፈቃዱን ለማደስ ክፍያ በምከፍልበት ሰዓት አንደኛ ክፍያው እንደ ተከፈለ ነው የሚያሳየኝ ፤ ሁለተኛ የመክፈያ ቁጥር ተብሎ የተሰጠኝ ቁጥርን ቴሌብር ላይ ስሞክረ ' ይሄ ክፍያ ተከፍላል ' ነው የሚለው።

በሲስተሙ ምክንያት ምንም ነገር መስራት እና ፈቃዱን ማደስ አልቻልኩም። ዌብሳይቱ ላይ የሚያሳየን ንግድ ፈቃዱን ፕሪንት አያደርግም ግን እንደ ታደሰ ያሳያል። ክፍያውንም እንደ ከፈልን ነው የሚያሳየው። ግን ክፍያ አልከፍልንም ይሄ ደግሞ የሲስተም ችግር ስለሆነ ነገ ከነገ ወዲያ ያስጠይቀናል።

ሲስተም እስከሆነ ድረስ ቅጣቱን እና ወለዱን ይዞ ነው። አሁን ባለው እንኳን ቅጣት 2,500 ነው ከዛ የጊዜ ገደብ ተሰጥቶ ካለፈ ወደ 10 ሺህ ከፍ ይላል።

እኛ ባላጠፋነው ፤ በጊዜው ክሊራንስ ጨርሰን ብንገኝም በሲስተም ምክንያት ማደስ አልቻልንም። ለዚህ መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" ኦንላይን ባሉበት ማራዘም ይችላሉ የሲስተም ችግርም የለም እስከ አሁን ያላደሱ ነጋዴዎች ቅጣት ውስጥ መግባት ይገባቸው ነበር ነገር ግን እስከ ጥር 15 ያለቅጣት እንዲያራዝሙ ተፈቅዶላቸዋል።

ችግርም ካለ የተጠቃሚዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ነው የሚሆነው አሁንም ሲስተሙ እየሰራ ነው ከሦስት ቀን በኃላ ግን ሊያበቃ ይችላል።

አዋጁ የሚለውን ትተን ለንግዱ ማኅበረሰብ በማሰብ ያለቅጣት ከታህሳስ 30 በኋላ ለ15 ቀን እንዲያድሱ ፈቅደናል ሲስተሙ 24 ሰዓት ይሰራል ኤረር (Error) የሚላቸው የአጠቃቀም ችግር ነው በጣም የለማ ሲስተም ነው ያለን።

ለውጤታማነቱም በዚህ አመት በ6 ወር ውስጥ ሁለት ሚሊየን ሃምሳ ሺህ (2,050,000) ሰዎች ንግድ ፈቃድ የማውጣት እና የማደስ አገልግሎት አግኝተዋል።

የሚቀር ነገር አይጠፋም አልፎ አልፎ የሲስተም መቆራረጥ ሊኖር ይችላል ነገር ግን በአብዛኛው አፈጻጸማችን ውጤታማ ነው።

ይህ ሁሉ ሰው ካሳደሰ የሚቀረው ጥቂት ነው በርካታ ሰው ተገልግሏል በነጋዴዎች ችግር ካልሆነ በቀር ከሃምሌ ጀምሮ ማሳደስ ይችሉ ነበር ለምን እስካሁን አረፈዱ በመጨረሻ ሰዓት እንደዚህ አይነት ቅሬታ ማቅረብ ምክንያታዊ ሊሆን አይችልም " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

" አባታችንን አፋልጉን ! "

አባታችን ገብረማርያም መለሰ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በኃላ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም።

እድሜያቸው 85 ዓመት ሲሆን መጥፋታቸውን ለፖሊስ አመልክተናል።

በሰዓቱ ለብሰውት የነበረው ጥቁር ጃኬት ነበር። ከዘራም በእጃቸው ይዘዋል።

መጨረሻ ጊዜ የነበሩበት ቦታ ወሰን 02 አካባቢ ነው።

ቤተሰብ ተጨንቋል አባታችንን አፋልጉን፤ መረጃ ለመስጠት 0911452386 ላይ ደውሉልን። " - ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል " - የአምቦ ከተማ አስተዳደር

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር በአንቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበሩና የሃይማኖት ስም በማጥፋት ወንጀል የተጠረጠሩ 3 ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ተማሪዎቹ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበረው የጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በታቦት እና በሃይማኖቱ ላይ ሲሳለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ
#ቲክቶክ በተባለው የማህበራዊ ሚዲያ ከለቀቁ በኋላ እጅግ በርካታ ሰዎች ጋር ደርሶ ቁጣን ፈጥሯል።

የአምቦ ከተማ አስተዳደር በድርጊቱ የተሳተፉ እና በማህበራዊ ገጾች ላይ የለጠፉ 3 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ (እንደታሰሩ) ገልጾ የአምቦ ዩኒቨርሲቲም የዲሲፕሊን ቅጣት ለማስተላለፍ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስተውቋል።

Via
@tikvahethmagazine

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የትግራይን ህዝብ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል" - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ " ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች መልእክት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለዋል።

ሰልፉን የጠራው የትግራይ ርስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያዘጋጀው መልእክት የተቀበሉት ፕሬዜዳንቱ አቶ ጌታቸው ፥" ከጦርነት ወጥተን በተነፃፃሪ ሰላም በምንገኝበት ጊዜ ሴት ሙስሊም እህቶቻችን በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ሲከለከሉ ማየት በጣም የሚያሳዝን ነው " ብለዋል።

" ችግሩ ገና ከጅምሩ ከትምህርት ቤቶቹ አመራሮች ፣ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ በመነጋገር ለመፍታት ጥረት ሲደረግ ቆይተዋል። እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ያልነበረት ጉዳይ ነው። አሁንም የትግራይ ህዝብ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል " ብለዋል።

" ጉዳዩ ቶሎ መታረም እንዳለበት የሚያግባባን ቢሆንም ፤ ከስሜት በፀዳ አስተዋይነትና ዘላቂነት ባለው መንገድ መሆን እንደሚገባ ሁላችንም መገንዘብ ያስፈልጋል " በማለት አክለዋል።

ችግሩ በፍጥነት እንዲፈታ አስተዳደራቸው ዝግጁ እንደሆነና እንደሚሳራም አመልክተዋል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የተነሳ ጥያቄ አጀንዳ መሆን አልነበረበትም ብሎ እንደሚያምን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተባባሪዎቹ እና ተሳታፊዎቹ ላሳዩት ጭዋ የሆነ ባህሪ ምስጋና አቅርበዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ ፍፁም ሰላም በሆነ መንገድ መጠናቀቁን ሰልፉን በቦታው ሆኖ ሲከታተል የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች  "  - ሰልፈኞች

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ጥር 13/2017 ዓ.ም "ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል በመቐለ ከተማ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል።

ሰልፈኞቹ ፦

- ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት መአድ ይመለሱ !

- ህገ-መንግስት ይከበር !

- የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይከበር !

- ሰላም እና ፍትህ ለትግራይ !

የሚሉና እና ሌሎች መፈክሮች በማስማት ላይ ናቸው።

በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዝርዝሩ ያቀርባል። 

Photo Credit - Tigrai TV

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሁለት ፆታዎች ብቻ ነው ያሉት እነሱም #ወንድ እና #ሴት ናቸው " - ፕሬዝዳንት ትራምፕ

47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሮ እንደገቡ ከሚሰሯቸው ዋነኛ ስራዎች አንዱ በሀገሪቱ ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እውቅና መስጠት ነው።

ይህም በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣን የመልቀቂያ ጊዜ ለትራንስጀንደር / ፆታቸውን ለሚቀይሩ ሰዎች የሚሰጠውን ከለላና ጥበቃ የሚሽር ነው።

ለወንድ እና ለሴት ብቻ እውቅና መስጠት ትራፕም ከሚያስተላልፏቸው ትዕዛዛት አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ታውቋል።

ትራምፕ ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ ፥ " ከዛሬ ጀምሮ / ከእንግዲህ ወዲህ / የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ እውቅና የሚሰጠው ለሁለት ፆታ ብቻ ነው እነሱም ወንድ እና ሴት " ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

የአሜሪካ መንግሥት ከአሁን በኃላ እውቅና የሚሰጠው ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እንዳሆነ የገለጹት ትራፕም ፤ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ብዝሀነት፣ እኩልነትና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ለማስወገድ የአፈጻሚ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፤ ፆታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ የሚያደርግ ትዕዛዝም ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትራምፕ " ሰዎች ተፈጥሯዊ ፃታቸውን መቀየር የለባቸውም " ብለው የሚያምኑ ሲሆን ከዚህ ቀደም ፆታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ መነገሩ ይታወሳል።

15 ሺህ ፆታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።

ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉ መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቪድዮው የፎክስ ኒውስ መሆኑን ይገልጻል።

#USA #PresidentDonaldTrump

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አዲስአበባ #መታወቂያ

“ ወደ 33 ሺሕ የሚሆን መረጃ ለሰላምና ጸጥታ ልከናል በየክልሉ ተጠርቶ እንዲመጣ በአንድ ወር ውስጥ ” - CRSSA

ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ለሚመጡ ተቋርጦ የቆየው የአዲስ አበባ መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት መቼ እንደሚጀመር ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን በተደጋጋሚ መጠየቁ ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ መቼ ይጀመራል? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው ኤጀንሲው፣ “ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” የሚል መስጠቱ አይዘነጋም።

አገልግሎቱ ባለመጀመሩ በድጋሚ መቼ እንደሚጀመር ስንጠይቀውም፣ “ ነሐሴ አጋማሽ 2016 ዓ/ም የትምህርት ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኃላ እንሰጣለን ” ነበር ያለው።

ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላም አገልግሎቱን የመስጠት ተግባሩ ሲጓተት ቆይቷል።  

አሁንስ አገልግሎቱ ተጀመረ ?

አሁንስ ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ለሚመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት የመስጠት ስራው ተጀመረ ? ተብሎ የተጠየቀው ኤጀንሲው አገልግሎቱ እንደተጀመረ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የኤጀንሲው ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ አለማየሁ ምን አሉ ?

“ አገልግሎቱ ከተጀመረ ወር ሆኖታል። በሁለት መልኩ ነው ሥራውን እየሰራን ያለነው።

አንደኛው ቀርበው ሪፓርት እንዲያደርጉ፣ የፋይዳ ቅድመ ሁኔታ አደረግን። ከተጠሩት ውስጥ ቀድመው ሪፓርት ያደረጉት በጣም ጥቂት ናቸው።

ከዚያ ባሻገር ደግሞ ለሚዲያ በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ክልል የመጡ መሸኛዎችን መልሰን ለክልል እንልካለን ማንነታቸውን ለማረጋገጥ ብለን ነበር። 

በዚህም በዛም መልኩ እንግዲህ እኛ ጋ ሪፓርት ያደረጉ ሰዎች ቁጥር ካመለከቱት ቁጥር ጋር ሲያያዝ በጣም አንሷል መጥተው ሪፓርት ያደረጉ ማለት ነው።

እናጣራለን ስንልም ሀሰተኛ ሰነድ ላይ ያለው ሁኔታ ትንሽ ፍርሃት ፈጥሯል መሰለኝ። ወደ 33 ሺሕ የሚሆን መረጃ ለሰላምና ጸጥታ ልከናል በየክልሉ ተጠርቶ እንዲመጣ በአንድ ወር ውስጥ።

ያ ማለት ሀሰተኛ መሸኛ ይዞ መጥቶ እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ያደረገውን፣ ሀሰተኛ መሸኛ ያስገባውንም ሰው ወደ ወንጀል ተጠያቂነት እናመጣለን የማይቀር ነው።

ዞሮ ዞሮ አገልግሎቱ ክፍት ነው ”
ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ኤጀንሲው ከ42 ሺሕ በላይ ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ወረፋ እየጠበቁ ያሉ አገልግሎት ፈላጊዎችን መረጃ አጣርቶ አገልግሎት እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር።

(በቀጣይ ተጨማሪ መረጃ እናቀርባለን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Подписаться на канал