ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#SafaricomEthiopia
🍋 እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! ድሮም ጥምቀት የሚያምረው በጋራ ሲያከብሩት እኮ ነው! የዕለታዊ ዳታ ጥቅሎችን ስንገዛ ለ24 የሚቆይ የ100% ጉርሻ: የድምፅ ጥቅል ስንገዛ 100% ጉርሻ እናግኝ። የበዓሉን ልዩ ድባብ ለሌሎች እናካፍል!
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#USA ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለመሀላ ፈጸሙ።
ፕሬዚዳንቱ ወደ ቢሮ እንደገቡ 200 ገደማ ትዕዛዞች ላይ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ተናግረዋል።
ፕሬዜዳንቱ ፊርማቸውን ከሚያኖሩባቸው ትዕዛዞች መካከል ፦
- በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከአሜሪካ ማባረር ፤
- ጾታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ ማድረግ ፤
- ብዝሀነት፣ እኩልነትና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ከጦር ሠራዊቱ ማስወገድ ዋነኞቹ ናቸው።
ትዕዛዞቻቸው በፍ/ቤት ሙግት ሊቀርብባቸው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethiopia
“ የትራንስፓርትም ዋጋ ጨምሮባቸዋል። መድኃኒትም ከውጭ ነው የሚመጣውና በሁሉም ዋጋ ጨምሮባቸው በጣም በከፍተኛ ሲቃይ ናቸው ህሙማኑ ” - ማህበሩ
“ 400 ሺሕ ሰዎች ዲያሌሲስ ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛዎቹ ዲያሊስ ማድረግ ስለማይችሉ ትተው ነው ያሉት ” በማለት የኩላሊት ህክምና እጥበት በጎ አድራጎት ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የማኀበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን አሰፋ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ?
“ ብዙ ወጣቶች ናቸው ዲያሌሲስ እያደረጉ ያሉት። ኩላሊት ደግሞ ከዘመድ ካልሆነ ከእኛ ሀገር ከሌላ ቦታ ማገኘት አይቻልም።
ትልቁ ችግር የኩላሊት ማግኘት ነው። ህሙማኑ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ፍላጎት ቢኖራቸውም የሚሰጣቸው ሰው የለም። ቢኖርም እንኳ ቢኖር አንዳንዱ ማች አያደርግም።
አብዛኞቹ ዲያሌሲስ ማድረግ ላይ ነው ትኩረታቸውን የሚያደርጉት ንቅለ ተከላውን እስከሚያደርጉ ድረስ።
የትራንስፓርትም ዋጋ ጨምሮባቸዋል። መድኃኒትም ከውጭ ነው የሚመጣው በሁሉም ዋጋ ጨምሮባቸው በጣም ከፍተኛ ሲቃይ ላይ ናቸው ህሙማኑ።
ድጋፍ የሚያደርገው ሰውም በጣም እየቀነሰ ስለመጣ ህሙማኑ በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው። ዲያሌሲስ ሁለት ጊዜ፣ አንዴ የሚያደርጉ አሉ። አንዳንዶች የሚበሉትን፣ የሚጠጡትን እየቀነሱ ይገኛሉ” ብለዋል።
በኢትዮጵያ ስንት የኩላሊት ህሙማን አሉ ? ከእነዚህ መካከል ስንቶቹ ህክምና የመከታተል እድል አግኝተዋል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ ፦
“ 400 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ዲያሌሲስ ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛዎቹ ዲያሌሲስ ማድረግ ስለማይችሉ ትተው ነው።
ግማሹ ጸበል ይሄዳል። ስለማንሰማ እንጂ ህይወታቸው የሚያልፈው ይበዛሉ። ዲያሌሲስ በማድረግ የሚታገለውን ነው የምናውቀው። ያም ቢሆን ሲቸግረው አንድም ሁለትም ጊዜ ዲያሌሲስ የሚያደርግ አለ በወር ውስጥ።
ይተዛዘናሉ። ሦስት ጊዜ ዲያሌሲስ የሚያደርገው ሰውዬ ‘ሁለት ይበቃኛል’ ብሎ አንዱን ለሌላ ይሰጣል። በእንደዚህ እየታገሉ ነው ያሉት።
የምንችለውን እያደረግን ለተወሰኑ ሰዎች ነው ለመድረስ የቻልነው ለብዙ ሰዎች መድረስ አልቻልንም። ምንክንያቱም ድጋፉ በደንብ ተጠናክሮ እየቀጠለ አይደለም።
ህብረተሰቡም ደግሞ ስለ ጉዳዩ ያገባኛል ብሎ ትኩረት ሰጥቶ ሲረዳ አንመለከትም። የሚያጭበረብረው ሰውም በዝቷል ” ሲሉ አስረድተዋል።
ማህበሩ ፤ “ ሰው ለመርዳት ችግር የለበትም ይረዳል። ትልቁ ችግር ማስታወስ ላይ ነው ያለው። እናንተም ለህብረተሰቡ በማስታወስ እርዱን ” ሲል አሳስቧል።
“ ትልቅ መፍትሄ ይሆናል ብለን የምናስበው ከሞተ ሰው ኩላሊት እንዲወሰድ የህግ ማዕቀፍ ሲወጣ ነው ” ያለው ማኀበሩ፣ “ ሲጸድቅ ሰዎች ሰላም ያገኛሉ። እስከዚያ ድረስ ዲያሌሲስ እያደረጉ መቆየት ግድ ይላቸዋል ” ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ዋሪት ፈርኒቸር እስከ ጥር 23 ቀን 2017 ድረስ የሚቆይ እስከ 30% ታላቅ ቅናሽ አድርጓል።
እንዳያመልጥዎ ! አሁኑኑ ይጎብኙን!
*ወሎ ሰፈር- ከጋራ ሙለታ ህንጻ ጎን
* 22 - ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* አዳማ - ሶረቲ ሞል
* ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
* ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706 / 07
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ !
" እየሄዳችሁበት ያለው መንገድ ሁሉንም የሚያጠፋ ፤ የተገኘችውንም ሰላም የሚያደፈርስ በመሆኑ ህዝባችሁ የሚሰጣችሁ ምክር እና ተግሳፅ ተቀብላችሁ በስክነት እና በማስተዋል የህዝባችሁን ጥያቄ እንድትመልሱ አደራ እንላለን " - ቅዱስነታቸው
ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ምክር እና ተግሳፅ አስተላለፉ።
ቅዱስነታቸው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ጥር 6/2017 ዓ/ም በፃፉት ደብዳቤ ነው።
ቅዱስነታቸው በዚሁ ደብዳቤ ፤ ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለማነጋገር እንዳልተሳካላቸው ገልፀው ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መሄዳቸው አሳስቧቸው ለመሪዎቹ ሃሳባቸው በፅሁፍ ለመገለፅ መገደዳቸው አስፍረዋል።
አመራሮቹ በትግራይ ያለው ጊዜ የማይሰጥ ተደራራቢ ችግር ከመፍታት ይልቅ ከመደማመጥ እና መከባበር በወጣ አኳኋን እርስ በርስ በመዘላለፍ መጠመዳቸው እንዳሳዘናቸው ጠቅሰዋል።
መሪዎቹ ጥበብን እና የሰለጠነ አሰራርን እንዲታጠቁ መክረዋል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ " ካህናት አበው ፣ የቤተክርስትያን ሊቃውንት ፣ ምእመናን ፣ የአገር ሽማግሌዎች የዕድሜ ባለፀጎች በሃዘን እያነቡ አካሄዳችሁን እንድታስተካክሉ ሲለምኗችሁ እና ሲመክሯችሁ ሰክናችሁ ማሰብ እና ማዳመጥ የተሰናችሁ ምክንያት ምን ይሆን ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
" ' የእኔ አካሄድ ብቻ ነው ልክ ' በሚል እልህ እና አስተሳሰብ የፈረሰ እንጂ የተገነባ ህዝብ እና አገር የለም " ሲሉ በአፅንኦት ያስገነዘቡት ቅዱስነታቸው ፤ " የናንተ መለያየት አልበቃ ብሎ በአንድነት እና በመከባበር የኖረውን ህዝብ ለማራራቅ እየሄዳችሁበት ያለው ርቀት ህዝብን ለማገልገል መቆማችሁን ጥያቄ ውስጥ የሚከት የጥፋት እና የመጠፋፋት መንገድ በመሆኑ ቆም ብላችሁ አስቡ " ሲሉ አሳስበዋል።
ይህ ሳይሆነ ከቀረ መሪዎቹ እየተከተሉት ያለው የጥፋት መንገድ የተገኘውን ሰላም የሚያደፈርስ አገርን እና ህዝብን ለከባድ ቀውስ የሚያጋልጥ እንደሆነ አስረግጠው ገልጸዋል።
የተፈጠረው የሃሳብ አለመጣጣም ለመፍታት ከአመራሮቹ አቅም በላይ እንዳልሆነ ያስታወሱት ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ መሪዎቹ ችግሮቻቸው በጥበብ እና በሰለጠነ አሰራር በመፍታት ጅምር ሰላሙን በማፅናት ህዝባቸውንና አገራቸውን በልማት ለመካስ ከልብ እንዲተጉ የአባትነት ምክራቸውን ደግመው ደጋግመው አስተላልፈዋል።
ጥር 6/2017 ዓ.ም ተፅፎ ዛሬ ጥር 11/2017 ዓ.ም በበዓለ ጥምቀቱ ይፋ የሆነው የቅዱስነታቸው የምክር እና የተግሳፅ ደብዳቤ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ አባል በስልክ ደውሎ አረጋግጧል።
እስካሁን ለደብዳቤው የተሰጠ ምላሽ የለም።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ትላንትና በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ " ጎቱ ኦኖማ " በተባለው አከባቢ በተራሮች ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ዛሬ መጥፋቱ ታውቋል።
የፎቶው ባለቤት የወረዳው ኮሚኒኬሽን ነው።
@tikvahethiopia
#ጥምቀት
የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ ፤ በሀገሪቱ በሚገኙ የጥምቀተ ባህር ስፍራዎች ቀሳውስት እና ሊቃውንት ለምዕመናን ትምሕርት ሰጥተው፣ ጸሎት ተደርጎና ጥምቀተ ባሕሩ ተባርኮ ሥርዓተ ጥምቀቱ ተካሂዷል።
አሁን ላይ ዛሬ የሚገቡ ታቦታትን የማስገባት ስነስርዓት ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ፎቶዎቹ ከተለያዩ የማህበራዊ ገጾች የተሰበሰቡ ናቸው።
@tikvahethiopia
#ጥምቀት
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ! በዓሉ በደስትና በረከት የተሞላ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።
መልካም የጥምቀት በዓል !
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
" በተራሮቹ ላይ የተከሰተው እሳት ከመስፋፋቱና ከፍተኛ ችግር ከማስከተሉ በፊት ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ እና አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን " - ወረዳው
በኦሮሚያ ክልል፣ በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ " ጎቱ ኦኖማ " በተባለው አከባቢ ከሰዓት 10 ሰዓት አከባቢ በተራሮች ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
የእሳቱ መከሰት መንስዔው በድርቅ ምክንያት የተከሰተ ነው ያለው ቢሮው የተከሰተውን ቃጠሎ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለማጥፋት እየተሞከረ ነው ሲል አስታውቋል።
ሆኖሞ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያው በ 'እሳተ ገሞራ' የተከሰተ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል ገልጿል።
በተራሮቹ ላይ የተከሰተው እሳት ከመስፋፋቱ እና ከፍተኛ ችግር ከማስከተሉ በፊት ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ቢሮው ባወጣው መረጃ ጠይቋል።
Via @tikvahethmagazine
#ከተራ2017
የ2017 ዓ/ም የጥምቀት ከተራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በቤተክርስቲያኗ ሥርዓት እና ትውፊት ተከብሮ ውሏል።
ዛሬ ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት ገብተዋል።
በነገው ዕለት በመላው ሀገሪቱ የጥምቀት በዓል ይከበራል።
@tikvahethiopia
ወጋገን ባንክ !
በወጋገን ካርድ በፖስ ማሽኖቻችን ክፍያ ሲፈፅሙ ተመላሽ እንዳለው ሰምተዋል ?
በወጋገን ክፍያ ካርድዎ ለአጠቃቀም ምቹ፣ ፈጣን እና አስተማማኝ በሆኑት የወጋገን ፖስ ማሽኖች ተጠቅመው በሆቴሎች እና ሬስቶራንቶች ፣ሱፐር ማርኬቶች፣ ሆስፒታሎች ፣ የገበያ ማዕከላት እንዲሁም በተለያዩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላገኙት አገልግሎት እና ለገዙት ዕቃ ክፍያ ሲፈፅሙ የገንዘብ ተመላሽ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ልብ ይበሉ !
እስከ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በወጋገን የክፍያ ካርድዎ በፖስ ማሽኖቻችን ክፍያዎን ሲፈፅሙ ግብይትዎ ቀልጣፋ፣ ምቹ እና አስተማማኝነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የተመላሽ ገንዘብ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ዛሬውኑ ፈጥነው የወጋገን ካርድዎን ይውሰዱ
ለበለጠ መረጃ ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል በ866 ነፃ የስልክ መስመር ይደውሉ! በተጨማሪም ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይቀላቀላሉ https://linktr.ee/WegagenBank
#ጎንደር
በታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ጎንደር ሁሉም ታቦታት ፒያሳ በመገናኘት ወደ ማደሪያ ቦታቸው እየተጓዙ ይገኛሉ።
የጥምቀት ከተራ በዓል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።
ጎንደር የጥምቀት በዓል እጅግ በጣም በደማቅ ሁኔታ ከሚከበርባቸው የሀገራችን አካባቢዎች አንዱ ሲሆን ለዘንድሮው በዓል በርካታ እንግዶች በዓሉ ላይ ለመታደም ጎንደር ተገኝተዋል።
ፎቶ፦ ማህበረ ቅዱሳን እና ፋኖስ ፒክቸርስ
@tikvahethiopia
#Update : ቲክቶክ በመጪው እሁድ በአሜሪካ አገልግሎቱን እንደሚያቆም አስታውቋል።
ቲክቶክ የተጣለበት እገዳ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር ከመጪው እሁድ ጀምሮ መተግበሪያውን በአሜሪካ ለማቆም እንደሚገደድ ገልጿል።
ኩባንያው በሰጠው መግለጫ ዋይት ሃውስ እና የፍትህ ዲፓርትመንት " ቲክቶክ በቀጣይነት እንዲቀጥል ለማህበራዊ ሚዲያው መሰረታዊ የሚባሉ ግልጽነት እና ማረጋገጫ መስጠት ተስኗቸዋል " ብሏል።
መንግሥት የተጣለበትን እገዳ በመጣሱ እንደማይቀጣ ጣልቃ ገብቶ ማረጋገጫ ካልሰጠው በስተቀር ቲክቶክ " ነገ እሁድ መተግበሪያውን ለማጨለም እገደዳለሁ " ሲል ይፋ አድርጓል።
170 ሚሊዮን ተጠቃሚ ያለው ቲክቶክ እስከ ነገ ድረስ ካልተሸጠ በስተቀር በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዳይውል የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትላንት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።
እገዳው አስቀድሞ በስልካቸው ላይ ቲክቶክን የጫኑ ተጠቃሚዎችን አይጎዳም የሚል እሳቤ ነበር ፤ ነገር ግን እገዳው ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ የመተግበሪያው ማሻሻያዎች አያገኙም በዚህም የማህበራዊ ሚዲያው በጊዜ ሂደት ከጥቅም ውጭ ይሆናል ተብሎ ነበር።
ሆኖም ቲክቶክ ባወጣው መግለጫ ለነባር ተጠቃሚዎችም ሆነ መተግበሪያውን አውርደው መጫን ለሚፈልጉ አዳዲስ ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ አገልግሎቱን እንደሚያቆም ጠቁሟል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia
መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ እንኳን ለ2017 ዓ/ም የጥምቀት #ከተራ በዓል አደረሳችሁ !
መልካም በዓል !
@tikvahethiopia
#ንጉስ
ጥምቀት ሲነሳ ሎሚ ውርወራ ፣ ሳቅ እና ጨዋታው አይረሳ!
እንኳን አደረሳችሁ! ደስ ደስ የሚል በዓል ይሁንላችሁ😊 ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ /channel/Negus_Malt
#ደስደስበንጉስ #Epiphany
#nonalcoholic #ንጉስ #DesDesWithNegus #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት#ንጉስማልት
እንኳን ለብርሃን ባንክ 15ኛ አመት አደረስዎ!
ያለፉትን አስራ አምስት አመታት አብራችሁን ለነበራችሁ ደንበኞቻችን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!
15 ዓመታት በታማኝነትና በትጋት!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#15thanniversary #berhanbank #bank #Stressfreebanking #bankinethiopia #finance
ከዚህ በታች የተቀመጡትን ትክክለኛ የባንኩን ገፆች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
👇👇👇
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
በትራፊክ አደጋ 7 ሰዎች ህይወት ወድያውኑ ተቀጠፈ።
ከሟቾች በተጨማሪ ስድስት ተጓዦች በከባድ ተጎድተዋል።
አደጋው ዛሬ ጥዋት ትግራይ ከመቐለ 50 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ወቕሮ ክልተ አውላዕሎ ዓደቀሳንድድ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነው የደረሰው።
አደጋው የደረሰው ሚኒባስ መኪና ከቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ጋር ተጋጭተው እንደሆነ የክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።
አሰቃቂ ግጭቱ የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ አውቶቡሱ ከመቐለ ወደ ሓውዜን ሲጓዝ ሚኒባሱ ደግሞ ከሓውዜን ወደ መቐለ ሲጓዝ በጠመዝማዛ ቦታ ላይ ነው የተከሰተው።
በዚህም ሹፌሩ ጨምሮ 7 ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች በከባድ ሁኔታ ተጎድተዋል።
የአደጋው መነሻ እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
መረጃው የድምጺ ወያነ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" ቅድሚያ የምንሰጠው ለአሜሪካ ነው። እሱ ደግሞ ነገ ይጀምራል " - ትራምፕ
ትራምፕ በመጀመሪያ የሥልጣን ቀናቸው በርካታ ትዕዛዞችን ለማስተላለፍ ቃል ገቡ።
የዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ዛሬ የሚከናወን ሲሆን ቃለ መሐላ በፈፀሙ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ " በታሪካዊ ፍጥነት እና ጥንካሬ " እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል።
ይህ የተናገሩት በዋሺንግተን ዲሲ በሺዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎች ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።
ትራምፕ ያላቸውን ፕሬዝደንታዊ ኃይል ሁሉ ተጠቅመው ስደተኞችን በገፍ ለማባረር፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የሚያተኩሩ መመሪያዎችን ለመቀነስ እና የስብጥር (ዳይቨርሲቲ) ፕሮግራሞችን ለማስቆም ቃል ገብተዋል።
" ቅድሚያ የምንሰጠው ለአሜሪካ ነው። እሱ ደግሞ ነገ ይጀምራል " ሲሉ ተናግረዋል።
አክለው " ነገ ቴሌቪዥን ስትመለከቱ እንደምትዝናኑ እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።
ትራምፕ ከበዓለ ሲመታቸው በኋላ 200 ገደማ ትዕዛዞች ላይ ፊርማቸውን እንደሚያሰፍሩ ይጠበቃል።
አንዳንዶቹ ትዕዛዞች እንደ ሕግ የሚቆጠሩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ፕሬዝደንታዊ መመሪያዎች ናቸው።
ትራምፕ " እኔ ሥልጣን በያዝኩ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የባይደን አስተዳደር ያስተላለፋቸው ትዕዛዞች ይሰረዛሉ " ብለዋል።
የሰው ሰራሽ ክህሎትን (AI) ዕድገት የሚያፋጥን እንዲሁም ኢላን መስክ የሚመራው ዶጅ የተባለ መሥሪያ ቤት እንዲቋቋም የሚወጣ ትዕዛዝ እንደሚፈርሙ አሳውቀዋል።
በተጨማሪ፦
➡️ እኤአ በ1963 ስለተገደሉት ጆን ኤፍ ኬኔዲ መረጃዎችን እንደሚለቁ፤
➡️ ወታደራዊ ኃይሉን 'አይረን ዶም' እንዲሠራ እንደሚያዙ፤
➡️ ብዝሀነት፣ እኩልነት እና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ከጦር ሠራዊቱ እንደሚያስወግዱ፤
➡️ ፆታ የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት እንዳይሳተፉ እንደሚያደርጉ፤
➡️ የትምህርትን ሥልጣን ለአሜሪካ ግዛቶች አሳልፈው እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።
ትራምፕ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጋዊ ወረቀት የሌላቸውን ስደተኞች ከአሜሪካ እንደሚያባርሩ ገልጸዋል።
" እናንተን በጣም ደስተኛ የሚያደርጉ ብዙ ትዕዛዞች ማየታችሁ አይቀርም " ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።
#BBC
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት 12ኛውን ዙር አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ያበስራል::
ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የጥራት ማወዳደሪያ መስፈርቶችን መሠረት አድርጎ ባዘጋጀው የልህቀት ሞዴል(EQA Excellence Model) አማካኝነት፣
• አምራቾችን
• አገልግሎት ሰጭዎችን
• የመንግሥት ተቋማትን
• ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን
• የጤና ተቋማት
• አገር በቀል ምንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና
• የኮንስትራክሽን ድርጅቶችን
በየዓመቱ እያወዳደር እውቅናና ሽልማትን ይሰጣል::
በመሆኑም ከጥር 05 -የካቲት 15 ቀን 2017ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 011- 554 14 45/ 09 02 55 22 66 ይደውሉ
ኑ! ድርጅቶቻችሁን እና ተቋሞቻችሁን በዓለም አቀፍ የልህቀት መሥፈርቶች ያወዳድሩ!
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት
#Update
" ያለ አሜሪካ ፍቃድ/ይሁንታ ቲክቶክ የለም " - ትራምፕ
👉 " 50% የቲክቶክን ድርሻ አሜሪካ መያዝ አለባት ! "
ትራምፕ ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል ሊያደርጉ ነው።
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ገጻቸው ላይ ዛሬ ባወጡት ፅሁፍ ፤ ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራቱን እንዲቀጥል እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።
ለዚህም በስልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያ ቀን (ነገ ማለት ነው) ቲክቶክ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል የሚያስችል እርምጃ ይወስዳሉ / ልዩ የሆነ ትዕዛዝ ይሰጣሉ።
ትራምፕ በዚሁ ፅሁፋቸው አሜሪካ የማህበራዊ ድረ-ገፁን ግማሽ (50%) በባለቤትነት መያዝ እንዳለበት ጠቁመዋል።
ነገ ወደ ቢሮ ገብቼ ስራ ከጀምርኩ በኃላ " ቲክቶክ እንዲጨልም አልፈልግም " ሲሉ ገልጸዋል።
ትራምፕ እንደ ጋራ ሽርክና አሜሪካ በቲክቶክ ውስጥ የ50% የባለቤትነት ድርሻ እንድትወስድ ሀሳብ አቅርበዋል።
ይህ ማለት ከወላጅ ኩባንያው ባይትዳንስ ወይም ከአዳዲስ ባለቤቶች ጋር " በአሜሪካ እና በመረጠችው ግዢ መካከል ትብብር ሊፈጥር ይችላል።
ትራምፕ " ይህንን በማድረግ ቲክቶክን እንታደገዋለን ፣ በጥሩ እጆች ውስጥ እናቆየዋለን " ብለዋል።
" ያለ አሜሪካ ፍቃድ ቲክቶክ የለም " ያሉት ትራምፕ " ከኛ ይሁንታ ጋር በመቶ ቢሊዮን ዶላር ምናልባትም ትሪሊዮን የሚቆጠር ዋጋ አለው " ሲሉ ጽፈዋል።
ቲክቶክ ከዚህ ቀደም " ከምሸጠው ሙሉ በሙሉ ዘግቼ አሜሪካን ብለቅ ይሻለኛል " ማለቱ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱን ቤተሰቦች ዋቢ በማድረግ ኢዜአ ዘግቧል።
አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል፡፡
@tikvahethiopia
#ጥምቀት
የ2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ ስነ-ስርአቶች እየተከበረ ይገኛል።
ዛሬ ጥዋት የእምነቱ ተከታዮች በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ በዓለ ጥምቀቱን በማህሌት ፣ በቅዳሴ፣ በመንፈሳዊ መዝሙሮች እና በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብረዋል።
በተለይም በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በተገኙበት ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተከብሯል።
ፎቶ፦ Pax Catholic TV
@tikvahethiopia
አሜሪካ ቲክቶክን ዘጋች።
' ቲክቶክ ' የተባለው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ እስከ ዛሬ እሁድ ድረስ እንዲሸጥ ካልሆነ ግን እንዲታገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል።
በዚህም ቲክቶክ በመላ አሜሪካ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ እንዳይሰራ ተደርጓል።
መተግበሪያው ገና እግዱ ተግባራዊ የሚሆንበት ሰዓት ሳይደርስ ቀደም ብሎ (ከሰዓታት በፊት) ነው የዘጋው።
በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ስክሪን ላይ ፥ " ቲክቶክን ለማገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል በዚህም አሁን ቲክቶክን መጠቀም አይችሉም " የሚል ፅሁፍ ነው የሚታየው።
ቲክቶክ ትራምፕ ስልጣናቸውን ተረክበው ወደ ቢሮ ሲገቡ መፍትሄ ለማበጀት አብረዋቸው እንደሚሰሩ እንደጠቆሟቸው በማመልከትም እስከዚያው ድረስ ተገልጋዮቹ እንዲጠባበቁት ጠይቋል።
ትራምፕ ቲክቶክ መተግበሪያ ካልተሸጠ እንዲታገድ የሚለው ህግ እንዲዘገይ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ከመታገድ ሊያድነቱ አልቻሉም።
ፕሬዜዳንታዊ ስልጣናቸውን ሲረከቡ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ? የሚለው በቀጣይ ይታያል።
ቲክቶክ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ነበሩት።
@tikvahethiopia
#Peace🏳
የጋዛ ተኩስ አቁም ነገ ተግባራዊ ይሆናል።
የተኩስ አቁሙ ነገ ተግባራዊ እንደሚሆን የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ነገ በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ላይ የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጧል።
የጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ቅዳሜ የተኩስ አቁሙን አፅድቋል።
ተኩስ አቁሙ ስራ ላይ ሲውል 1,904 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤቶች እንደሚለቀቁ የእስራኤል መንግሥት አሳውቋል።
ሀማስ ደግሞ ከ98 እስራኤላውያን ታጋቾች መካከል 33ቱን ለ6 ሳምንታት በሚዘልቀው የተኩስ አቁም ወቅት ይለቃል።
ግብፅ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ለመላክ እየተዘጋጀች ነው።
በሌላ በኩል ግን ሀማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ከተገለጸ በኃላ 122 ፍልስጤማውያን በእስራኤል መገደላቸውን የጋዛ የሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ኤጀንሲ ገልጿል።
እስካሁን በ15 ወራት ጦርነት የተገደሉት ፍልስጤማውያን ቁጥር 46,899 ደርሷል። 110,725 ሰዎች ታጎድተዋል።
መረጃው ከዶቼ ቨለ የተገኘ ነው።
@tikvahethiopia
#Update
🚨“ በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ
ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰጠው መግለጫ በመነሳት፣ “ አንዳንድ ሚዲያዎች መንግስት በማይናማር የታገቱ ዜጎችን አስለቀቀ ” በማለት መዘገባቸው ስህተት መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የታጋቾቹ ቤተሰቦች በዝርዝር ምን አሉ ?
“ አጋቾች ያገቷቸውን ልጆቻችንን ‘መንግስት አስለቀቀ’ መባሉ ትክክል አይደለም።
አጋቾቹ ሲቀጧቸው የተጎዱ፣ በህመም ሳቢያ መስራት የማይችሉ ልጆችን ከካምፕ አውጥተው ታይላንድ ድንበር ሲጥሏቸው ሰብአዊ መብት ላይ የሚሰሩ ኤን.ጂ.ኦ አንስተው ታይላንድ በመውሰድ አሳክመው ህንድ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን ነው ኢትዮጵያ እንዲገቡ ያደረጓቸው።
አንዳንድ ሚዲያዎች የዘገቡትና መንግስትም ድፍን ባለ መልኩ የሰጠውን መግለጫ መነሻ በማድረግ ማይናማር ያሉ ልጆች የተለቀቁ የመሰላቸው አድማጮች ‘ እንኳን ደስ አላችሁ ’ የሚለን በዝቷል። እውነታው ይሄ አይደለም።
ይህን ጉዳይ ህዝብ ይረዳው። ማይናማር ከታገቱት ልጆች መካከል እንዲለቀቁ በተደረገ ጥረት ማንም አልተለቀቀም።
ታይላንድ ያሉት ናቸው እንጂ ማይናማር ያሉት አይደሉም የወጡት። ዋሽተው ነው። ዜናውን አካብደውታል። እኛን ምንም ተስፋ አልሰጡንም። ‘አትምጡ’ ነው ያሉን ” ሲሉ አስረድተዋል።
የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?
“በዚህ መልኩ (ታጋቾች ተለቀዋል በሚል) የዘገቡት ሚዲያዎች ሁለት፣ ሦስት ጊዜ ድምፅ እንዲሆኑን ጠይቀናቸው ሳለ ‘ እንከሰሳለን ’ ብለው ነው የፈሩት። አሁን ግን ያልተወራውን ማስተላለፍ ከኢቲክስ ውጪ ነው። በጣም ቅር ብሎናል። እውነታውን አሳውቁልን።
በታይላንድና በማይናማር ድንበር ያሉት ልጆች እንጂ ወጡ የተባሉት ከማይናማር ግዛት ካሉት ጋር እንደማይገናኝ በህንድ የሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ነግሮናል።
የኤምባሲው ሰዎች ‘እኛ የሚመለከተን ታይላንድ አካባቢ ያለውን ብቻ እንጂ የማይናማሩ የሚመለከተው ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነውና ማይናማር ያሉትን አንድም ነገር አልሰራንም’ ብለው ቃል በቃል ነው የነገሩን።
ከኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በመግቢያ ንግግራቸው ያስተላለፉት ትክክለኛውን ‘ታይላንድ አካባቢ ያሉትን’ ብለው ነው።
ነገር ግን አንዳንድ ሚዲያዎች በስቃይ ላይ ያሉ ልጆችን መንግስት እያስወጣ እንዳለ አድርገው ነው መግለጫውን የዘገቡት። ይህ ቅር አሰኝቶናል።
ሌሎች አገራት እኮ ዜጎቻቸውን ያስወጡት ከትራደሽናል ሊደሮች፣ ከኤምባሲዎች ጋር ሆነው በመስራት ነው። የኛዎቹ ግን ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም።
አንዱን ኢትዮጵያዊ የመራቢያ አካሉን የዘር ፍሬ ነቅለውታል። በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ።
አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ በችግር ላይ ያሉ ልጆችንን ካሉበት ስቃይ እንዲታደጋቸው በአጽንኦት እንጠይቃለን ” ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር፣ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው በርካታ ሽልማቶች
ውስጥ አንዱ ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ፣ በመቀሌ ለዕድለኛ ወጥቷል፡፡
ዕድለኛው አሸናፊ አቶ የማነ ነጋሽ ፣ ሽልማታቸውን ጥር 10 ቀን 2017ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ በተከናወነ
ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ተረክበዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ዕድለኞች ሚሪንዳ እና ፔፕሲ ጠጥተው
ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
#ከተራ2017 : በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እና ትውፊት መሰረት የከተራ በዓል እየተከበረ ይገኛል።
በገጠርም በከተማም ያሉ ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት በማምራት ላይ ይገኛሉ።
በተለያዩ የባህል አልባሳት ያሸበረቁ ምዕመናን፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና መዘምራን ታቦታቱን አጅበው ወደየማደሪያቸው በመሸኘት ላይ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፎቶዎቹን ከተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ማሰባሰቡን ይገልጻል
@tikvahethiopia
" ...ሙሉ ተሳፋሪውን ነው የወሰዷቸው። መጀመሪያ የተመታው ግን አንድ ሹፌር ነው - " ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር
አዋሽ ፓርክ አካባቢ ሰሞኑን አንድ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ሙሉ ተሳፋሪዎች ከነአሽከርካሪው መታገታቸውን ጣና የከባድ ተሽከርከሪ አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ማኀበሩ በሰጠን ቃል " አዋሽ አካባቢ ፓርክ አለ። እዚያ አካባቢ ታጣቂዎች ተሽከርካሪውን በጥይት መትተውት ሰው ቆስሏል " ብሏል።
" ተሽከርካሪው ተቃጥሏል። ኤክስፓርት ይሁን ሌላ የጫነ ተሽከርካሪ አልታወቀም። ተሳፋሪ ሰዎችንም ይዞ ነበር " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።
ተሳፋሪዎቹና ሹፌሩ ከምን ደረሱ ? ለሚለው ጥያቄ ማኀበሩ በምላሹ፣ " ሹፌሩም ታግቷል። ተሳፋሪውንም እንደዚሁ ሙሉ ተሳፋሪ ወስደዋል " ነው ያለው።
ተሳፋሪ ከያዘ ተሽከርካሪው የህዝብ ማመላለሻ ነበር እንዴ ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ ማኀበሩ፣ " በተለምዶ ' አባዱላ ' የሚባለድ ሚኒባስ ነው፣ አዎ የሕዝብ ተሽከርካሪ ነበር " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ምን ያክል ሰዎች እንደታገቱ ሲጠየቅም፣ " ቁጥሩ አልታወቀም። ሙሉ ተሳፋሪውን ነው የወሰዷቸው። መጀመሪያ የተመታው ግን አንድ ሹፌር ነው " ሲል መልሷል።
ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት እንነማን እንደሆነ ሲያስረዳ፣ በዛ አካባቢ ላይ ከሸኔ ታጣቂዎች ውጪ ከማኀበረሱ የወጣ እንዲህ አይነት ድርጊት ከዚህ ቀደም አጋጥሞ እንደማያውቅ ነው የገለጸው።
ለአመታት ይኸው የሚባል ዘላቂ መፍትሄ ያልተገኘለት የታጠቁ አካላት ሹፌሮች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ልጅን ያለ አባት፣ ወላጅን ያለ ልጅ እያስቀረ በመቀጠሉ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ አሁንም ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠይቋል።
ደረሰ ለተባለው ጥቃትና እገታ የባለስልጣናትን ምላሽ ለማካተት የተደረገው ሙከራ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ለጊዜው አልተሳካም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ኢትዮ ኢንተርናሽናል ስተዲ ሴንተር ከፍተኛ ትምህርታቸውን በአለም አቀፍ ተቋማት መከታተል ለሚፈልጉ የግንዛቤ መርሃግብር አዘጋጅቷል።
የፊታችን ማክሰኞ ጥር 13 ከጥዋቱ 1 ሰዓት እስከ 6:30 ድረስ በአዲስ አበባ EISC አዘጋጅነት 65 ከሚሆኑ የNCUK አጋር ዩኒቨርስቲዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የሆኑት ተቋማት ተወካዮች እዚሁ አዲስ አበባ ተገኝተው የተማሪዎችን ጥያቄዎች ያስተናግዳሉ።
በመርሃግብሩ ለይ ተሳታፊ ለመሆን በዚህ ሊንክ ይመዝገቡ : https://eisc.uk/universities-fair-2025/
#ማሳሰቢያ 1 : የፕሮግራሙ ተሳታፊ ለመሆን ምንም አይነት ክፍያ ተማሪዎች አይጠየቁም።
#ማሳሰቢያ 2 : ለትምህርት እድል ተብሎ የሚከፈል ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የለም። ፕሮግራሙ ከማንኛውም አይነት ክፍያ ጋር የሚገናኝ አይደለም።
“ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ነው እየመነጨ ያለው። ደብረ ብርሃን የተሰማ ነገር የለም” - አታላይ አየለ (ፕ/ር)
ትላንት ከሌሊቱ 10፡46 በደብረ ብርሃን አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የጀርመን የጂኦ ሳይንስ ጥናትና ምርምር ማዕከል ድረጽ መረጃ አውጥቷል ፤ ይኸው መረጃም ሲዘገብ ተስተውለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵዮጵያ በበኩሉ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከዘርፉ ተመራማሪ ማብራሪያ ጠይቋል።
ደብረ ብርሃን አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል መባሉን እውነት ነው ? ብለን የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ሮ)፣ " ኧረ ውሸት ነው " ሲሉ መልሰዋል።
" ደብረ ብርሃን አካባቢ የለም። እዛው አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ነው እየመነጨ ያለው። ደብረ ብርሃን የተሰማ ነገር የለም " ነው ያሉት።
" የዘርፉ ተቋማት በሚያወጡት መረጃ፣ ' ከደብረ ብርሃን ይህን ያህል ኪሎ ሜትር፣ ወይ ከመተሃራ ይህንን ያህል ኪሎ ሜትር ' ይላሉ ስም እየጠሩ። ከዛ በመለስ ግን እንደዚህ የሚባል ነገር የለም። ደብረ ብርሃን አሁን ከየት የመጣ መንቀጥቀጥ ነው? " ሲሉ ነው ምላሽ የሰጡት።
ከዚህ ቀደም ከደብረ ሲና በ52 ኪሎ ሜትር ተከሰተ ለተባ የመሬት መንቀጥቀጥ በተለመለተ፣ ከሚከሰትበት የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የቦታ ለውጥ አደረገ ማለት እንዳልሆነ ተመራማሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።
" በአንዳንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም " ነበር ያሉት።
አዋሽ ፈንታሌ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ንዝረቱ እየተሰማ እንደሆነ ይታወቃል።
ሌላው በተያያዘ፣ የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንስ በምን ደረጃ ላይ ነው ያለው ? በሚል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ለቀረበላቸው ተጨማሪ ምላሽ ሰጥተዋል።
አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን ምላሽ ሰጡ ?
" ምንም የተለዬ ነገር የለም እንደቀጠለ ነው። ከቀን ቀን ትንሽ ለውጥ ያለው ይመስላል። ግን ነገ ይቆማል የሚባል ነገር አይደለም።
ስቲል ይታያል እንቅስቃሴ። የሚረግብ አይመስልም በአጭሩ።
ዌብ ሳይት ተለጠፈ የሚለው ሳይሆን ለሊት 10 ገደማ ተፈጠረ የተባለው አካባቢ አንድ ነው ሪፓርት የተደረገው ግን ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስካሁን ስንት ተፈጠረ ብትለኝ ከ100ዎች በላይ ሊሆኑ ይችላሉ።
ያ ማለት የሚረግብ አይነት አይደለም " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia