ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#TPLF
" የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ
በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ አተኩሮ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም ቡድኑ ፦
- እስከ አሁን ያልተረጋገጠው የትግራይ ግዛታዊ አንድነት፤
- ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው አለመመለስ፤
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያወጣውን መግለጫ፤
- የፕሪቶሪያ የሰላም ውል አፈፃፀም በሚሉ አጀንዳዎች ላይ መወያየቱን ገልጾ " ቀጣይ የመፍትሄ እና የትግል አቅጣጫ አስቀምጫለሁ " ብሏል።
የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት እውቅና የሰጠው የትግራይ ግዛታዊ አንድነት አለመረጋገጡ ጠቅሶ " ተፈናቃይ እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው ሃዘን እና ቁጣ ተስምተኞናል ይህንን አስመልክቶ ' ይበቃል ' በሚል የተካሄደው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እደግፋለሁ " ብሏል።
ቡድኑ በመግለጫው " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በአግባቡ እንዳይፈፀም የኢትዮጵያ መንግስት እንቅፋት እየሆነ ነው ፡ በትግራይ ውስጥ የበቀለ #ከሃዲ_ሃይልም በተጨማሪ ስምምነቱ እያደናቀፈ ነው " የሚል ክስ አሰምቷል።
እንዴት እንደሆነ ባያብራራም " ችግሩ ከስር መሰረቱ ለመለወጥ ቆርጬ ተነስቻለሁ " ብሏል።
በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ DDR ተቀባይነት ያለው እንደሆነ የገለፀም ሲሆን " ይሁን እንጂ DDR እንደምክንያት በመጠቀም የትግራይ ሰራዊት ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ ተቀባይነተ የለውም " ሲል ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ህወሓት ህጋዊ ጉባኤ እንዲያካሂድ በማስመልከት በቅርቡ ያወጣው ቀን ገደብ ያካተተ መግለጫ አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ ፥ " ቦርዱ ' ጉባኤ አካሂዱ ' የሚል ጨምሮ በተንኮል የተተበተቡ የተለያዩ ትእዛዞች ከመስጠት ተቆጥቦ የተፈጠሩ ልዩነቶች በፓለቲካዊ ውይይት ለመፍታት የተጀመረው ጥረት በማስቀጠሉ ላይ ያተኩር " ብሏል።
" ህወሓት ሁሌም ለሁለትዮሽ ውይይት ዝግጁ ነው ፤ የትግራይ ህዝብ ትግል እና መስዋእትነት የሚያራክስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔ ግን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።
ህወሓት ጊዚያዊ አስተዳደሩ በማቋቋም የአንበሳ ድርሻ እንደነበረው እና እንዳለው የጠቀሰው መግለጫው " አሁንም እንዲጠናከር ይሰራል ይሁን እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማጠናከር እና ለመቆጣጠር በሚል ይቋቋማል የሚባለው ካውንስል አካል መሆን አልፈግም " ሲል ግልፅ አድርጓል።
በሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በመግለጫው ማጠቃለያ ፤ " የኢትዮጵያ መንግስት ከጣልቃ ገብነት ተቆጥቦ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በቅን ልቦና በመፈፀም ለዘላቂ ሰላም እንዲሰራ " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
የህወሓት ቡድን ለሁለት ተከፍሎ የለየለት አለመግባባት ውስጥ ከገባ ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ከወራት በፊት ለሁለት የተከፈሉት አመራሮች እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች አዲስ አበባ ሄደው ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት አድርገው ነበር።
ወደ መቐለ ከተመለሱ በኃላ ግን እስከ ዛሬ መግባባት ሳይፈጥሩ በመግላጫ ምልልስ ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደግሞ ህወሓት በልዩ ሁኔታ የተመዘገበው ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን በመግለጽ ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።
ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጾ ነበር።
ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራሮችን ለሁለት የከፈለ ጉባኤ መደረጉ አይዘነጋም። በወቅቱም ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትን እና ስርዓቱን ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና እንደማይሰጥ ማስገንዘቡ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
⚠️ የፀጥታ ኃይል ዩኒፎርም በአግባቡ የለበሰና መሳሪያ በአግባቡ የታጠቀ ሰው እጁ ወደኃላ የፊጥኝ የታሰረ ወጣትን አንገላቶ ሲተኩስበት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ቪድዮ በማህበራዊ ሚዲያው ተሰራጭቷል።
ለጊዜው ቪድዮ የት ፣ መቼ እንደሆነ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ለማየት የሚከብድ ጭካኔ መፈጸሙን ያመላክታል።
ቪድዮው ላይ 5 የፀጥታ ኃይል ልብስ በአግባቡና በስርዓት የለበሱ ሰዎች ይታያሉ።
ከነዛም አንዱ መሳሪያውን እንደታጠቀ አንድን የፊጢኝ ወደ ኃላ የታሰረ ወጣት አንገላቶት ሲያበቃ ከጀርባው ጭንቅላቱ ላይ ሲተኩስበት ይታያል።
በቪድዮው ላይ እንደማታየውም ይህ ድርጊት ሰዎች በተሰበሰቡበት ፊታቸው ላይ የተፈጸመ ነው።
ስለ ቪድዮውም ሆነ ስለ ድርጊቱ በይፋ ወጥቶ የተናገረና ያብራራ አካል እስካሁን ብቅ አላለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድርጊቱን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ለማነጋገር ይጥራል።
ባለፉት ጊዜያት መሰል የጭካኔ ተግባራት በሀገራችን አንድም በፀጥታ አካላት፣ በታጣቂ ኃይሎች እንዲሁም ደግሞ ሲቪል በለበሱ አካላት ሲፈጸም ታይቷል።
ሰው በቁሙ ሲቃጠል፣ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል፣ ገደል አፋፍ ላይ ተረሽኖ ወደ ገደል ሲከተት፣ በድንጋይ ተወግሮ ሲገደል ... ብዙ ብዙ ለማየት የሚከብዱ ድርጊቶች ተፈጽመው በቪድዮ ማስረጃ ጭምር ታይተዋል።
" በቪድዮ ያልተቀረፀ ስንት ጭካኔና ግፍ ይኖር ይሆን ? " የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሱ በርካታ ተግባራት ባለፉት ዓመታት ተመዝግበው ተቀምጠዋል ፤ የአሁኑ ቪድዮ ጉዳይ ምንድነው ? የተገደለው ወጣትስ ማነው ? የት ነው ? መቼ ነው ? የሚለውን የተደረሰበትን እና ያገኘነውን መረጃ እንለዋወጣለን።
@tikvahethiopia
#MoE
በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ከትላንት ጀምሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ምዝገባው እስከ ጥር 14/2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ታውቋል።
ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ምዝገባ ማድረግ አይቻልም።
ምዝገባው በ https://exam.ethernet.edu.et ላይ የሚካሄድ ሲሆን ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ በቀጣይ ይፋ ይደረጋል።
የመፈተኛ User Name እንዲሁም Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ማንኛውም አይነት ጥያቄ ዘውትር በሥራ ሰዓት በኢሜል ngat@ethernet.edu.et በስልክ ቁጥር 0911824528 / 0913678404 / 0913949676 / 0910076453 / 0923106826 / 0913866717 / 0911335683 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ተብሏል።
Via @tikvahuniversity
የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ ? የመንጣቱስ ምክንያት ምንድን ነው ?
በአስደናቂነቱ ፣ በታሪካዊነቱና በኪነ ህንጻ ጥበቡ ብዙ የተባለለት እና እና በአራት አስርት ዓመታት በፊት በዩኔስኮ የዓለማችን ቅርስ አንዱ ሆኖ የተመዘገበው የፋሲል ግንብ ተሰነጣጥቆ እና አርጅቶ መቆየቱ በርካቶች ሲያነሱት የነበረ ጉዳይ ነው።
በእርጅናም የህልውና ስጋት እንደገጠመውም ሲነገር ነበር።
የጥገና እድሳት እየተከናወለት ያለው ታሪካዊው የፋሲል ግንብ በቅርቡ ይፋ ተደርጓል።
ታሪካዊው ሽሯሟ ቀለም ያለው የፋሲል ግንብ ቀለሙ ነጥቶ መታየቱ ለበርካታ መላምት ክፍት እንዲሆን አድርጎታል።
የታሪካዊው ግንብ ቀለም ለዘመናት ከሚታወቅበት ተለውጦ ለምን ነጣ ? የሚል ጥያቄ እንዲነሳም ምክንያት ሆኗል።
አንዳንዶች " ቅርሱ በአግባቡ አልታደሰም፤ የታወቅበትን ታሪካዊነቱንና ቀለሙንም እንዲያጣ ተደርጓል " ብለዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ በጥገና እድሳቱ በአማካሪነት እንዲሁም በጥናት የተሳተፉት አንጋፋው አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ምን አሉ ?
" የፋሲል ግንብ ህንጻ ሲገነባ በአነስተኛ ድንጋዮች እና በኖራ ሲሆን፣ ለረጅም ዓመታት ዝናብ፣ በፀሐይ እና በተፈጥሯዊ ሂደቶች ውስጥ ሲያልፍ በርካቶች የሚያውቁትን ይሄንን ' ሽሯማ ' መልክ አምጥቷል።
አሁን እድሳቱ የተደረገበት ኖራ አዲስ በመሆኑ ቀለሙ ነጣ ብሏል።
የእድሳት ሥራው የተከናወነው የፋሲል ግንብ በመጀመሪያ በተገነባበት ማቴሪያል (ቁስ) በዋናነት በኖራ እና በድንጋይ ነው።
የቅርስ አጠባበቅ ሕግን በተከተለ መልክ ነው የተሠራው።
የኖራው አዲስ መሆን ብቻ ይሄንን ነጣ ያለ ቀለም አምጥቷል። የኖራ እና የድንጋይ መልኩ ከተወሰነ ዓመታት በኋላ ወደ ድሮው መልኩ ይመለሳል።
ልዩነቱ አዲስ የመሆን እና የማርጀት ጉዳይ ነው።
የፋሲል ግንብ መጀመሪያ ሲሠራ ኖራው ለብዙ ወራት ወይም ለዓመታት ተቀብሮ የነበረ ነው አሁንም ሲታደስ መነሻውን ተከትሎ ኖራው ለበርካታ ጊዜያት እንዲቀበር ተደርጎ ጥገናው ተካሂዷል።
ቅርሶች በተፈጥሮ፣ በፀሐይ፣ በዝናብ፣ በአቧራ ምክንያት በዓመታት ቀለማቸው እየተቀየረ የሚሄድ ነው ፤ ይሄኛውም ከዓመታት በኋላ የሚታወቀውን ቀለም ይይዛል።
በዓለም አቀፉ የቅርስ ጥገና ሕግ መሠረት ዋነኛው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በተሠራበት ቁስ (ማቴሪያል) ታድሷል ወይ ? የሚለው ነው በተሠራበት ድንጋይ እና ኖራ መልሶ መጠገኑ ዋናው ነገር ነው።
ይህንንም በትክክል መሥራቱን አረጋግጠናል።
በአንዳንድ ሁኔታዎች የድሮ ቀለሙን ለማምጣት ለመልክ ሲባል ኬሚካል ይቀላቀላ እነዚህ ግን ኬሚካል ነክ ነገሮች ስለሆኑ ያልታሰበ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ቀለሙ እንደ ድሮው ቢመስል እንወድ ነበር፤ ሆኖም ለቀለም ተብለው የሚጨመሩ ነገሮች ያልታሰበ አደጋን በቅርስ ላይ ያመጣሉ።
በዓለም የቅርስ አጠባበቅ ደረጃ ዋነኛው ነገር ቅድሚያ የሚሰጠው የመነሻ ሃሳቡ ነው። ኖራው ትክክለኛ እና አስተማማኝ በመሆኑ የጥንቱ እንደያዘ የጥገና እድሳቱ እየተከናወነ ነው።
መነሻውን ሳይለቅ ጥርሳችንን ነክሰን የሠራንበት ነው።
የቀደመ መልኩ በጊዜ ብዛት ይመጣል የነበረው ገጽታ በጊዜ ሂደት ይመለሳል።
በሽሯሟ መልኩ የሚታወቀው የፋሲል ግንብ መቼ ተመልሶ ይመጣ ይሆን ? የሚለው ዝናብ ሲመታው እና የአየር ሁኔታዎች ሲፈራረቁበት እየተቀየረ ይሄዳል።
ህንጻው ወደ ቀደመ ቀለሙ ለመመለስም ከሦስት እስከ አራት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል።
አንዳንድ ቦታ ላይ በጣም የጠቋቆሩ የግንቡ አናት ላይ አካላት ነበሩ። ድንጋዮቹ ወደ ነበሩበት ለመመለስ እስከ አምስት ዓመት ድረስ የሚደርስ ወይም የግንቡ አናት ላይ ያሉትን ጠቆር ያሉትን የቀደመ ገጽታ ለማምጣት ከዚያ ረዘም ያለ ጊዜ ይወስዳል " ብለዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።
@tikvahethiopia
✨🎁 ጥምቀት የሞባይል ጥቅል!!
እስከ 20% በሚደርስ ቅናሽ ያቀረብናቸውን ልዩ የበዓል ጥቅሎች በ*999#፣ በማይ ኢትዮቴል እና አርዲ ቻትቦት ይግዙ!
👉 ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ሲገዙ 20% ቅናሽ ከተጨማሪ 20% ስጦታ ጋር ያገኛሉ!
🗓 ከነገ ጥር 10 – 13/2017 ዓ.ም
መልካም የጥምቀት በዓል!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
#Update
🧕" የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ በመጣስ አሁንም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች / ልጆቻችን ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይገቡ ከልክሏል " - የተማሪዎች ቤተሰቦች
👉 " የተጣሰ የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የለም ፤ የትምህርት ህግ እና ደንብ ያከበሩ ተማሪዎች ወደ ክፍል ገብተው መማር ጀምረዋል ፤ ቀሪዎቹ እንዲመለሱ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ነን " - የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር
የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ጥር 6/2017 ዓ.ም በፃፈው የእግድ ትእዛዝ ሴት ሙስሊም ተማሪዎቹ ሂጃባቸው ለብሰው እንዲማሩ ፤ በክልከላ የተሳተፉ አካላት ለጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸው እንዲሰጡ ቢያዝም ተግባራዊ አልሆነም ብለዋል የተማሪዎች ቤተሰቦች።
የተማሪ ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ (መቐለ) በሰጡት አስተያየት ፤ " የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከተማሪዎች የሂጃብ መልበስ ክልከላ ጋር በተያያዘ በአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት በኩል በ5 አካላት ላይ የእግድ ደብዳቤ ቢያፅፍም ተግባራዊ አልሆነም ተጥሷል " ብለዋል።
የእግድ ትእዛዙን ከጣሱት አንዱ የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሆኑን የጠቀሱት የተማሪ ቤተሰቦች ፤ " ትምህርት ቤቱ የእግድ ትእዛዙን በመጣስ ጥር 7 እና 8/2017 ዓ.ም ተማሪዎቹ ክፍል ገብተው እንዳይማሩ በማድረግ ተደራራቢ ጥፋቶች እየፈፀመ ነው " ሲሉ ከሰዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ " ከህግ በላይ መሆን ልክ አይደለም የፍርድ ቤት ትእዛዝ እና የሃይማኖት መብት ይከበር " ሲሉ ምሬታቸው ገልፀዋል።
በተማሪዎች ቤተሰቦች በኩል ለቀረበው አስተያየት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ምላሽ የሰጡት የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ፥ " ትምህርት ቤታችን ' የፍርድ ቤት እግድ እና ትእዛዝ በመጣስ ተማሪዎቹ እንዳይማሩ ከልክሏል ' የሚባለው ስህተት ነው " ብለዋል።
" ለተማሪ ሴት ልጆቻችን በቅርብ እና በሩቅ ሆኖው ' እንቆረቆራለን ' ከሚሉት በላይ እናስብላቸዋለን " ያሉት ርእሰ መምህሩ " አሁንም ጉዳዩ ከሚገባው በላይ ማጋነን እና ማቀጣጠል እንዲሁም ለፓለቲካዊ ፍጆታ ማዋል ለአገር እና ህዝብ አይጠቅምም " ሲሉ አብራርተዋል።
" የትምህርት ቤታችን አስተዳደር የፍርድ ቤት ትእዛዝ እና እግድ ሳይጠብቅ የተፈጠረው አለመግባባት እንዲፈታ ሌት ተቀን በመስራት ላይ እንገኛለን " ሲሉ ገልጸው " የፍርድ ቤቱ ቃል አክብረን የትምህርት ቤቱ መምሪያ እና ደንብ በመጠበቅ ጥቂት የማይባሉ ሴት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መልሰናል የተቀሩት ለመመለስ ደግሞ በማያቋርጥ ጥረት ላይ እንገኛለን " ብለዋል።
" ከ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ የቀሩት እንዲካተቱ ከሚመለከታቸው አካላት ተከታታይ ስራዎች እየሰራን " ሲሉ አክለዋል።
ከሂጃብ መልበስ ጋር ተያይዞ ከ2017 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እንዲቀሩ የሆኑት 159 የአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ጉዳይ ክልላዊ እና አገራዊ አጀንዳ ከመሆን በዘለለ በህግ እንዲታይ ወደ ፍርድ አምርቷል።
ከሂጃብ አጠቃቀም ክልከላ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው በተባሉት በአክሱም ከተማ የሚገኙ 5 አካላት ለጥር 16/2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸው እንዲሰጡ ፤ ጎን ለጎን ደግሞ ሴት ሙስሊም ተማሪዎቹ ሂጃባቸው ለብሰው ትምህርታቸው እንዲቀጥሉ የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ጥር 6/2017 ዓ.ም አዟል።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ጥር 8/2017 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በፃፈው ደብዳቤ ፤ የሂጃብ መልበስ ክልከላው እንዲያነሳ አሳውቋል።
በተያያዘ መረጃ ከሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ጋር ተያይዞ ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይገቡ መከልከሉ ለመቃወም የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለዓርብ ጥር 9/2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ እንዲካሄድ የጠራው እና የተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ የጥምቀት በዓል ዋዜማ በመሆኑ ምክንያት ወደ ጥር 13/2017 ዓ.ም ማዘዋወሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከምክር ቤቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
በዓሉን አስመልክቶ የተደርገው ልዩ ቅናሽ ሳያመልጥዎ እነዚህን ውብ እቃዎች የግልዎ ያድርጉ።
የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላለቀሉ፦
Telegram 👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook 👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Instagram 👉 Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok 👉 yonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">TikTok/yonatanbtfurniture
📍አድራሻችን
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)
ስልክ ፦ +251957868686/ +251995272727/ +251993828282
ቪድዮ ፦ #ሀማስ እና #እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው መነገሩን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ደስታቸውን ለመግለፅ በጋዛ አደባባይ ወጥተዋል።
" አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! " ይህ በስምምነቱ መረጃ የተደሰቱ ፍልስጤማውያን ድምፅ ነው።
በርካቶች የሰላም ወሬ በመንፈሱ በደስታ አልቅሰዋል ፤ አንብተዋል ፤ ፈጣሪ ቀጣዩን ጊዜ ደግሞ የሰላም ያደርግላቸው ዘንድ ተማፅነዋል።
ፍልስጤማውያን ስምምነቱን ተከትሎ እስራኤል የያዘቻቸውን ያሰረቻቸውን ወገኖቻቸውን ትፈታለች ብለው ተስፋ አድርገዋል።
በአስከፊው ጦርነት እጅግ በርካታ ፍልጤማውያን ህጻናት፣ ሴቶች፣ እናቶች ፣ አዛውንቶች አልቀዋል። ላለፉት 15 ወራት የሰቀቀን ህይወት ሲገፉም ነበር።
ስምምነቱ ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላምን ያመጣ ይሆን ? በቀጣይ የሚታይ ይሆናል።
#ሰላም 😭 #Peace 🕊 #سلام
@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ።
ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወርቁ ደስታ ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ " በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ዴዔታ በርኦ ሀሰን፥ ደግሞ " ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም " ብለዋል።
" አሁን ላይ ከ400 በላይ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እያስመጡና እየገጣጠሙ ናቸው " ያሉ ሲሆን ሁሉም የኃይል መሙያ አላቸው " ሲሉ ገልጸዋል።
የመረጃው ባለቤት ኤፍኤምሲ ነው።
@tikvahethiopia
#Update
" ያለፈው ይብቃ አሁን የተጣለባችሁን ሃላፊነት በአስቸኳይ ፈፅሙ " - ተፈናቃዮች
" ይበቃል ! ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል መቐለ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ አበቃ።
ሰልፉ 3 ተከታታይ ቀናት የተካሄደ ሲሆን የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀቀው።
በዚህም ተፈናቃዮች " የፌደራል መንግስት ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ታማኝ እና ተገዢ በመሆን ስምምነቱን በሙሉነት እንዲያስፈፅም " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የፕሪቶሪያ የሰላም ውል እንዲፈረም ያሳየው ቁርጠኝነት ተግባራዊ እንዲሆንም ሚናውን ማጉላት አለበት ብለዋል።
ሰልፈኞቹ የትግራይ ክልል የቀድሞ ይዞት በህገመንግስቱ መሰረት ወደነበረበት እስከሚመለስ ሰላማዊ ተቃውሞ ማሰማታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በተለይ ደግሞ ለሁለት የተሰነጠቁት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ለስልጣን እና ወንበራቸው ሲሯሯጡ የተፈናቃዮች ስቃይ መዘንጋታቸው በምሬት የነቀፉት ሰልፈኞቹ " ያለፈው ይብቃ አሁን የተጣለባችሁ ሃላፊነት በአስቸኳይ ፈፅሙ " በማለት ጥሪ አቅርበዋል ።
" ይበቃል ! ወደ ቄያችን መልሱን ! " ሰላማዊ የተቃውሞ ስልፍ ተሳታፊዎች ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፣ ለህወሓት እንዲሁም በክልሉ ለሚገኙ የተለያዩ የተባበሩት መንግስት የእርዳታ ድርጅቶች የአቋም መግለጫቸው አድርሰዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMeKelle
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
ዛሬውኑ የKimem Itel Pro ስልክ ከሳፋሪኮም ወስደው፣ ክፍያውን ቀስ እያሉ ይክፈሉ። እስከ 3000 ብር ቅድሚያ ክፍያ በመክፈል ቀሪዉን አመቺ በሆኑ የክፍያ አማራጮች እየከፈሉ በ10,747ብር ይግዙት። ለበለጠ መረጃ ወደ 700 ወይም *777*6# ይደዉሉ። እንዳያመልጥዎ!
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #1Wedefit #Furtheraheadtogether
#ሂጃብሂጃብ #አክሱም
" ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ #እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ ታዟል " - ፍርድ ቤት
በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎችን ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ክልከላ አድርገዋል በተባሉት አካላት ላይ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ህጋዊ ክስ መስርቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ከምክር ቤቱ ጠበቃ አረጋግጧል።
በተመሰረተው ክስ መሰረት ተከሳሾች ለጥር 16/2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸው እንዲሰጡ የመጥሪያ ትእዛዝ ተፅፎላቸዋል።
የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ለተከሳሾች የፃፈው የመጥሪያ ትእዛዝ ሙሉ ይዘት ምን ይላል ?
ከሳሽ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሲሆን ተከሳሾች ደግሞ :-
➡ የአክሱም ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት
➡ የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
➡ አብራሃ ወ አፅብሃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
➡ ወርዒ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
➡ ክንደያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ናቸው።
በዚሁ ደብዳቤ ላይ ተከሳሾች በወሰኑት አስተዳደራዊ ውሳኔ መሰረት የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን በቀረበቅ ማመልከቻ መረዳት እንደተቻለ ተገልጿል።
ፍርድ ቤቱ ፤ የተሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔ እግድ ካለተጣለበት በሴት ተማሪዎቹ ላይ የማይመለስ የመብት ጥሰት ሊያጋጥም ስለሚችል ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ አዟል።
ተከሳሾችም በቀረበው የእግድ ማመልከቻ መሰረት ቀርበው ቃል እንዲሰጡ በፍርድ ቤቱ ለቀን 16/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ተቀጥረዋል።
NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠበቃ ማረጋገጥ ችሏል።
159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከሂጃብ ክልከላ በተያያዘ ትናንት የተጠናቀቀውን 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የሚያስችላቸውን ፎርም ሳይሞሉ መቀረታቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መግለጹ ይታወሳል።
ጉዳዩን እስከመጨረሻውን የምንከታተለው ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
🔈 #የተማሪዎችድምጽ
" በዩኒቨርሲቲው አመራር ለደህንነታችን ስጋት ወደ ሆነ አካባቢ ትሄዳላችሁ ተብለናል "- ተማሪዎች
በቁጥር 1,300 አካባቢ ይሆናሉ የተባሉ የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ከዋናው ግቢ 5 ኪ/ሜ ያህል ርቆ ወደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ትዘዋወራላችሁ መባላቸው ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ የሚዘዋወሩበት ግቢ " በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ የሚደረግበት አካባቢ ነው " ያሉ ሲሆን " በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች እየለቀቁ ባለበት ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለደህንነታችን ስጋት ወደ ሆነ አካባቢ ትሄዳላችሁ ብሎናል " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ ከደብረማርቆስ ከተማ በ5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ2015 ዓ/ም ህዳር ወር ጀምሮ ለ7ወር አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በክልሉ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከየካቲት 7/2016 ዓም ጀምሮ ተማሪዎቹን ወደ ዋናው ግቢ በማዘዋወር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አደርጎ ነበር።
እስከ አሁን በዋናው ግቢ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት የጤና ተማሪዎች " ከሚመጣው ቅዳሜ 10/05/17 ዓም ጀምሮ ወደ ቀድሞ ግቢ እንደምንዘዋወር ተነግሮናል " ብለዋል።
ተማሪዎቹ ትዘዋወራላቹ የሚል ውሳኔ ከሰሙበት ቀን ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር በተደጋጋሚ ሲጠይቁ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።
በ 02/05/2017 ዓም የጤና ኮሌጅ ዲን አና ሌሎች የጤና ትምህርት ክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት ባደረጉት ስብሰባም " ለሚደርስባቹ የህይወት አደጋ ዩኒቨርሲቲው ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም እርስ በእርሳቹ ተጠባበቁ አናንተ ስትሄዱ የቦታዉ ሰላም ይረጋገጣል " መባላቸውን ተናግረዋል።
በትላንትናው ዕለት የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ጨምሮ የሚመለከታቸው የክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት በድጋሚ ባደረጉት ስብሰባ ተማሪዎች ውሳኔያቸውን እስከ አርብ እንዲያሳውቁ እና ከቅዳሜ ጀምሮ እንደሚዘዋወሩ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የዩኒቨርሲቲው አመራር ዝርዝር ማብራሪያ ጠጥተዋል።
ምን አሉ ?
" እንዲሄዱ የሚደረግው የቦታ ጥበት በመኖሩ ነው ተማሪዎቹ መጀመሪያ ግቢያቸው ይህ አልነበረም ተደርበው ነው ያሉት።
የትምህርት ማቴሪያሎቻቸው በሙሉ እዛ ነው የሚገኙት ዩኒቨርሲቲውም የሚቀበላቸው አዳዲስ ተማሪዎች አሉ ይሄ ሁሉ ተጨማምሮ የመማሪያ ክፍል እጥረት ስላለ እና ጸጥታውም በአንጻራዊነት መሻሻል ስለሚያሳይ ነው እንዲሄዱ የተወሰነው።
ተማሪዎቹ ' እንሂድ ' ብለው ሰኔ ወር ላይ ጠይቀው ነበር እንዲዘገዩ ያደረግነው እኛ ነን በወቅቱ ጸጥታው ይህንን ለማድረግ የማያስችል በመሆኑ አሁን እንሂድ ስንል ነው ቅሬታ የተፈጠረው " ብለዋል።
በአካባቢው በሚታየው የጸጥታ ችግር አካባቢያቸውን የሚለቁ ሰዎች እንዳሉ ተሰምቷል ምን አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታዎች ኖረው ነው ተማሪዎቹ የሚዘዋወሩት ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ አመራሩን ጠይቋል።
እሳቸውም ፦
" አካባቢውን እየለቀቀ ያለ ሰው አለ የሚለው ውሸት ነው የሚለቅ ሰው ሊኖር ይችላል ክረምት እና ከክረምት በፊት በፍርሃት የሚወጡ ነዋሪዎች ነበሩ አሁን ግን ነዋሪውን በአካል አወያይተናል ነዋሪውም መምጣታቸውን ይፈልጋል።
ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ነው ልል አልችልም ካለው ተለዋዋጭ ሁኔታ አንፃር አሁን ያለንበትም ተቋም ቤቱም ሆነ ከተማው ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም ግን የተለየ ስጋት የለም የሚል ድምዳሜ ነው ያለው " ብለዋል።
በዋናው ግቢ ቆይተው ቢማሩ ለደህንነታቸው የበለጠ አስተማማኝ አይሆንም ወይ ? ስንል ጥያቄ አንሰተናል።
" እዚህም ቢሆኑ እዛም ቢሄዱ ችግር የሚመጣ ከሆነ ሊደርስባቸው ይችላል ' ያኛው ግቢ የበለጠ ለአደጋ ተጋላጭ ያደርገናል ' ብለው ቢያስቡ እንኳ በአሁኑ ሰዓት በዋናው ግቢ ትምህርቱን ለማስቀጠል የማያስችሉ ሁኔታዎች አሉ ትምህርቱ እየተጎዳ ስለሆነ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#AsiyaKelifa🇪🇹
ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ኽሊፋ የ2025 ሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመረጠች።
የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓመታዊ የስልጠና መርሃ ግብር፣ ከሁዋዌ ታዋቂ የማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
ይህ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የ2025 የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደሮችን መርጦ አሳውቋል።
ከተመረጡት 12 አምባሳደሮች መካከል በኢትዮጵያ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነችው አሲያ ኽሊፋ ትገኛለች።
ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓላማውን ያደረገው በዓለም ዙሪያ ያሉ ወጣት ተማሪዎችን በአጭር ጊዜ ስልጠና የዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን አረዳዳቸውን ማሳደግ ነው።
ለዚህም አጫጭር ስልጠናዎችን፣ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እና የተመራቂዎች ማህበር እንቅስቃሴዎች (አልሙናይ) ተሳትፎ እንዲጎለብት ይሰራል።
የባህል ልውውጦች አስፈላጊነት እና የስራ ፈጣሪነት መንፈስ ማዳበር ላይም ትኩረት ያደረገ ሲሆን ከተሳታፊዎች መካከልም ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑትን ሴቶች በማድረግ የተለያዩ ልዩነቶችን ለማስተናገድና ለማካተት ቁርጠኛ ሆኖ ይሰራል።
የአሲያ የአለምአቀፍ አምባሳደር ሆና ለመመረጧ በሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር 2024 ፕሮግራም ስኬታማ ተሳትፎ ማድረጓ አስተዋጻኦ ያደረግ ሲሆን ይሄውም እ.ኤ.አ. በ2025 በቻይና ውስጥ በሚካሄደው የአይሲቲ ታለንት ዲጂታል ጉብኝት በአካል እንድትሳተፍና የተግባር ልምድ እንድታገኝ፣ እንዲሁም በሌሎች ትልልቅ አለም አቀፍ ዝግጅቶች ላይ ተገኝታ የቴክኖሎጂ ተግባራዊ እውቀት እንድትካፈል እድል ይሰጣታል።
የአለምአቀፍ አምባሳደር ፕሮግራም የተቀረጸው የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር እ.ኤ.አ. ከ2008 ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያሉትን የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች ግንኙነት ለማጠናከር ነው።
የፕሮግራሙን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ለማስፋትና የተሳታፊዎች መማማርና ትስስር እድሎችን ለመፍጠር ያተኮረ ነው። ፕሮግራሙ ወጣት መሪዎች የፕሮግራሙን ዋና እሴቶች የሆኑትን ዲጂታላይዜሽን፣ ፈጠራ፣ ስራ ፈጠራ እና ዘላቂነትን እንዲላበሱ ይሰራል።
የአለምአቀፍ አምባሳደሮችን የመምረጥ ሂደት በፕሮግራሙ ድህረ ገጽ በኩል ማመልከቻ በማስገባት የሚጀመር ሲሆን፣ እጩዎች ግንዛቤያቸውን እና አመለካከታቸውን ለመገምገም የታለሙ ስድስት ቃለ መጠይቆች ላይ በመሳተፍ ምላሽ ይሰጣሉ። ከዚያም የዳኞች ቡድን ሁሉንም ማመልከቻዎችና ምላሾች ይገመግማል፣ አመልካቾች ስለ ዓለም አቀፍ አምባሳደር መርሃ ግብር ያላቸው ግንዛቤ፣ የመግባባት ችሎታ፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተሳትፎ እና ለድርጊት ያላቸው ቁርጠኝነት ላይ በመመርኮዝ የእጩዎች መረጣን ያከናውናል።
መረጃው ትምህርት ሚኒስቴር ነው።
#አሲያኽሊፋ 👏 #AsiyaKelifa
@tikvahethiopia
#Update #Axum
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።
" ያልተመዘገበ አይፈተንም " ማለቱ ይታወሳል።
ከሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ ጋር ተያይዞ በአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ውዝግብ ባለመግባባት ተቋጭቷል።
159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።
ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተለው የቆየው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጥር 6 ቀን 2017 ከሰዓት በኋላ ወደ አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ደውሎ አግኝቷቸዋል።
ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
" - በትምህርት ቤታችን ከተለመደው የአለባበስ ስርዓት የተለየ የተሰጠ የአለባበስ ትእዛዝ የለም።
- ሴት ሙስሊም ተማሪዎቻችን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከትምህርት ቤቱ አመራር በአካል በመምጣት እንዲወያዩ ማስታወቅያ በመለጠፍና ስልክ በመደወል ጥረት ተደርጓል ለመምጣት ፍቃደኛ ኣይደሉም።
- የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ጉዳዩ እንዲረግብ ከትምህርት ቤታችን ፣ ከከተማዋ ከንቲባ ከአገር ሽማግሌ እና ከክልል ትምህርት ቢሮ ሰላማዊ ልመና ቢቅርብላቸውም ጉዳዩ ለማርገብ ፍቃደኛ አልሆኑም።
- በአጠቃላይ የፈተና ፎርም ያለ መሙላትና ያለ መፈተን ፍላጎቱ ከተማሪዎቻች ፍላጎት ውጪ የውጭ ተፅእኖ እና ግፊት አለበት።
- ልጆቻችን በቀላሉ በመግባባት ሊፈታ በሚችል ጉዳይ ከፈተና ውጪ መሆናቸው እንደ ርእሰ መምህርና ወላጅ እጅግ እሞኛል አበሳጭቶኛል " ... ብለዋል።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ታህሳስ 22 ቀን 2017 ከህገ-መግስት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ክልከላ ውጪ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " ሂጃብ " እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ባወጣው ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፥ " ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎችን ለህዝባችን እናሳውቃለን " ማለቱ ይታወሳል።
ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት ጥያቄዎቹ በሚመለከተው አካል ጀሮ ዳባ ልበስ መባላቸውን በማረጋገጡ በታህሳስ 30 ቀን 2017 ባወጣው አጭር መግለጫ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ክስ መመስረቱ ግልጽ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አመራሮች ስለ ጉዳዩ አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ ማብራርያ እንዲሰጡ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
ከ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጭ የሆኑት 159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ወዴት ያመራ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።
@tikvahethiopia
#TikTok📱
' ቲክቶክ ' አሜሪካ ውስጥ ከእሁድ ጀምሮ እስከ ወዲያኛው እንዲዘጋ ወይም እንዲሸጥ የሚለውን ውሳኔ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደገፈ።
ዛሬ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ' ቲክቶክ ' በአሜሪካ እንዲዘጋ ካልሆነም እዲሸጥ ለሚጠይቀው የፌደራል ህግ ድጋፍ ሰጥቷል።
' ቲክቶክ ' ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ ሆናል።
ከዚህ ቀደም መተግበሪያው " የአሜሪካውያንን የግል መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ይሰጣል በዚህ የብሔራዊ ጸጥታ አደጋ ደቅኗል " በሚል እንዲታገድ ካልሆነም ለአሜሪካ ሰዎች እንዲሸጥ የሚል ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።
ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም የተላለፈውን ውሳኔ ደግፏል።
ይህን ውሳኔ ተከትሎ ' ቲክቶክ ' ከእሁድ ጀምሮ ይታገዳል።
የእግዱ ተግባራዊነት ' ቲክቶክ 'ን ከአፕስቶር እና ፕሌይስቶር ላይ እንዲወገድ ያደርጋል።
አዲስ ተጠቃሚዎች ' ቲክቶክ ' ማውረድ አይችሉም ፤ ነባር ተጠቃሚዎች አፕዴት ማድረግ አይችሉም።
ተመራጩ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ' ቲክቶክ ' ን ለመታደግ እና የመታገዱ ውሳኔ እንዲዘገይ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን የመጨረሻ ያለውን ውሳኔ አሳልፏል።
እንሆ ስልጣኑ ያበቃው የባይደን አስተዳደር " ህጉን ማስተግበር የቀጣዩ አስተዳደር ኃላፊነት ነው " ብሏል።
የ' ቲክቶክ ' ን እገዳ ለማዘግየት የሞከሩት ትራምፕ ሰኞ ስልጣናቸውን ይረከባሉ። ህጉን ማስተግበርም በሳቸው ላይ ተጥሏል።
ትራምፕ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኃላ በሰጡት ቃል " ውሳኔውን እኔው ወስናለሁ ፤ ውሳኔው እኔ ጋር ነው ምን እንደማደርግ ታያላችሁ " ብለዋል።
170 ሚሊዮን ተጠቃሚ አሜሪካ ውስጥ ያለው ' ቲክቶክ ' እስከወዲያኛው ይታገድ ይሆን ? ወይስ ከዚህ በኃላ ትራምፕ ማድረግ የሚችሉት ነገር ይኖር ይሆን ? በቀጣይ ይታያል።
መረጃው ከኤፒ፣ ፎርብስ፣ ሲኤንኤን የተሰባሰበ ነው።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba #እንድታውቁት
የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።
ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት መንገዶች ይዘጋሉ።
አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
➡️ ከ6 ኪሎ አደባባይ - ምኒልክ ሆስፒታል
➡️ ከምኒልክ ሆስፒታል - መከላከያ 3ኛ ሻለቃ አደባባይ
➡️ ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ - 6 ኪሎ አደባባይ እንዲሁም አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ
➡️ ከዋልያ ቢራ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
➡️ ከአቃቂ ዋናው መንገድ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
➡️ ከ08 - አቃቂ ድልድይ ድረስ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናሉ።
በተጨማሪ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በ11ዱም ክ/ከተሞች ጥምቀተ ባህር ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በ500 ሜትር ክልል ውስጥ ታቦታት ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም በሚሄዱባቸው መንገዶች ለአጭር ጊዜም ይሁን ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
@tikvahethiopia
🔈 #የጤናባለሞያዎችድምጽ
🔴 " እስከሚከፈለን ድረስ ወደ ሥራ ላለመመለስ ተስማምተናል ለሁሉም ባለሞያ እስከሚከፈል ድረስ አንሰራም " - የጤና ባለሞያዎች
🔵 " ዝም ያለ አካል የለም ዘግቶ መሄዳቸው ትክክል አይደለም " - የጤና ቢሮ ሃላፊ
በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በዘጠኝ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የትርፍ ሰዓት ስራ(ዲዩቲ) ክፍያ ስላልተከፈላቸው 05/05/17 ዓ/ም ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል።
ባለሞያዎቹ ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በተለያዩ ጊዜያት ያልተከፈላቸው የ1 አመት ከ 5 ወር በላይ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ መኖሩን ተናግረዋል።
እስከ ክልሉ የበላይ አካላት ድረስ ሄደን ጠይቀናል በተደጋጋሚ የሚሰጠን ምላሽ ግን " ታገሱ " የሚል ነው በዚህ ምክንያት ተነጋግረን ስራ ለማቆም ተገደናል ነው ያሉት።
" አብዛኛው ባለሞያ ከወረዳው ሸሽቶ ወደተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ ተደብቆ ነው ያለው አመራሮችም በአንቡላንስ ቤት ለቤት በመሄድ የህክምና ባለሞያዎችን እያፈለጉ እያስፈራሩ ነው " ብለዋል።
ባለሞያዎቹ " በተለያዩ ጊዜያት ከወረዳ እና ከዞን አመራሮች ጋር በርካታ ውይይቶችን አድርገናል ነገር ግን ' ግብር እስከሚሰበሰብ ጠብቁ፣ ገንዘብ የለም ታገሱ ' ከማለት የዘለለ እስካሁን ምንም ምልሻ ባለመግኘታችን እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ተገደናል ነው " ያሉት።
" እስከሚከፈል ድረስ ወደ ሥራ ላለመመለስ ተስማምተናል ለሁሉም ባለሞያ እስከሚከፈል ድረስ አንሰራም የተጠራቀመ ክፍያው እስከ 100 ሺ የደረሰለት ባለሞያም አለ " ብለዋል።
" በዚህ ደመወዝ ፣በዚህ ኑሮ ውድነት መኖር አልቻልንም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ነው የደረስነው ልጆች ያላቸው ልጆቻቸውን ማሳደግ አልቻሉም መስራትም መኖርም አልቻልንም ይሄንን እርምጃ ስንወስድም ወደ ፖለቲካ ተቀይሮ ' ትታሰራላቹ ' ወደ ሚል ማስፈራሪያ ተሸጋግረዋል " ሲሉ አክለዋል።
ባለሞያዎቹ በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ጤና ጣቢያዎች አድማው ቢቀጥልም ለወሊድ ለሚመጡ እናቶች ብቻ አንዳንድ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ነገር ግን በሁሉም ጤና ጣቢያዎች መደበኛ ስራዎች ማቆማቸውን ተናግረዋል።
የአዳባ ወረዳ የጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሽመልስ ፈይሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የባለሞያዎቹ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ አለመከፈሉን አረጋግጠዋል።
ሃላፊው በዝርዝር ምን አሉ ?
" በየደረጃ ያሉ ቢሮዎችን እየጠየቁ መምጣት ይችሉ ነበር እኔ የቢሮ ሃላፊ ነኝ ወደ እኔ የመጣ የለም ስራቸውን ነው ዝም ብለው ያቆሙት።
የኑሮ ውድነት በሃገሪቱ እና በአለም ያለ ሁኔታ ነው የትርፍ ሰዓት ስራ ባይሰሩም በመደበኛ ስራቸው መገኘት ነበረባቸው የሙያ ስነምግባሩ ይህንን አይፈቅድም።
የገቢ ማነስ ይኖራል፣ የጸጥታ ችግርም ሊኖር ይችላል በእነዚህ ምክንያቶች ነው እንጂ ዝም ያለ አካል የለም ዘግቶ መሄዳቸው ትክክል አይደለም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለሞያዎቹ የጠየቁት ከአመት በላይ ሳይከፈላቸው ስለቀረ ክፍያ ነው ችግሩ በምን ያህል ጊዜ ይፈታል ብለን እንጠብቅ ሲል ጠይቀናቸዋል ? በምላሻቸው ፦
" ከእዚህ በፊት ጥያቄውን ለበላይ አካል አቅርበው ጉዳዩ ወደ ወረዳ እንዲመለስ ተደርጎ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈታል ተብሎ ነበር ለዚህ እንቅስቃሴ እያደረግን ባለበት ሰዓት ነው ይሄ የተፈጠረው ገቢ ላይ የተመሰረት አከፋፈል ነው የሚኖረው ከስር ከስር እየተከፈለ በጊዜ ሂደት ችግራቸው ይፈታል " ብለዋል።
የቦርድ አባላት በየጤና ጣቢያው በመሄድ ሰራተኛው መጥቶ የራሱን ቅሬታ እንዲያቀርብ ጠይቀው እስካሁን መጥቶ ያቀረበ አካል የለም እኛም መፍትሄ ለመስጠት ተቸግረናል ብለዋል።
ሃላፊው ባለው ሰራተኛ ስራው እንዲቀጥል ለማድረግ እየጣርን ነው ያሉ ሲሆን " የሰራተኛው ችግር ምን እንደሆነ በቢሮ ደረጃ አናውቅም መጥቶ ያቀረበልን አካልም የለም " ነው ያሉት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወረዳው የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ከክፍያ ጋር ተያይዞ የሚያነሱትን ጥያቄ ለመቅረፍ ወረዳው ምን ያህል ብር ይፈልጋል ሲል ጠይቋል።
ሃላፊው " የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን በየጊዜው ስለሚጨምር ይሄን ያህል ነው ማለት ያስቸግራል ነገር ግን በ 2016 ዓም ብቻ ያልተከፈላቸውን ክፍያ ለመፈጸም እስከ 5 ሚሊየን ብር ያስፈልጋል " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ሕብር ሙዳይ የቁጠባ ሒሳብ
ሙዳይ ተቀማጭ ሒሳብ በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የሚከፍቱት የቁጠባ ሒሳብ ሲሆን፤ አገልግሎቱ የቁጠባ ባህልን ለማዳበር አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቆጣቢዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ ደንበኞችን ለማበረታታት በነፃ የገንዘብ ቁጠባ ሣጥኖች የሚሰጥበት የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ /channel/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
" ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው " - የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር
የታገቱት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ፦
" በህገወጥ ዓለምአቀፍ ደላሎች ተታለው ወደ ማይናማር ፣ ታይላንድ፣ ቻይና ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ወደሚገኙ ህገወጥ ካምፓች ተወስደው የሚገኙ ዜጎችን ለማስመለስ በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶች ቀጥለዋል።
ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው።
እስካሁን በምናደርገው እንቅስቃሴ የ19 ሀገራት ዜጎች ተመሳሳይ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለውና ታግተው ወደ ማይናማር በመግባት ለከፋ ችግር የተዳረጉ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በማይናማር 380 የሚል ቁጥር ተጠቅሷል ይሄ የቁጥር የተወሰደው እዚህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተለያዩ ዜጎች ልጆቻቸው ታግተው እዚህ መጥተው ካመለከቱት ነው።
በዚህ መሰረት ክትትል ለማድረግ እንዲረዳን ቶኪዮ ለሚገኘው ኤምባሲያችን የተላለፈው ቁጥር ይህ ነው። ትክክለኛው የታጋቾች ቁጥር አይታወቅም።
ቶኪዮ የሚገኘው ኤምባሲያችን ከማይናማር ኤምባሲ ጋር ዜጎቻችንን ለማዳን በትብብር እየሰራ ነው። የ380 ዜጎች ስም ዝርዝር እና ፓስፖርት ኮፒ ቶኪዮ ለሚገኘው የማይናማር ኤምባሲ እንዲደርስ ተደርጓል።
የማይናማር መንግሥት ታጋቾችን ለመልቀቅ ጠረት በማድረግ ላይ ሲሆን ከአጋቾች አምልጠው ለመንግሥት እጅ የሚሰጡ ዜጎች ምህረት በማድረግ በነጻ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ትብብር በማድረግ ላይ ይገኛል።
ፈታኝ የሆነው ዋናው ጉዳይ የታገቱት ዜጎች የሚገኙት በማይናማር እና ታይላንድ መካከል በሚገኙ ከማይናማር መንግሥት ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ስፍራዎች መሆኑ ነው። ይህ ስራውን አክብዶታል።
ሌላው ፤ በዚህ ኢሰብዓዊ ወንጀል ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገራት ሰው አዘዋዋሪዎች ተቀራርበው እየሰሩ መሆኑ ነው።
እስካሁን መንግሥት ከዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ጋር ጭምር ባደረገው ጥረት በ6 ወር ውስጥ 34 ዜጎች ከአጋቾች ነጻ ወጥተው ወደ ታይላንድ እና ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል።
ከአጋቾች አምልጠው ህጋዊ ሰነድ ስለሌላቸው በእስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 7 ዜጎቻችንም በምህረት እንዲለቀቁ ማድረግ ተችሏል።
ዜጎችን የመታደጉ ስራ ብዙ ጥረትን የሚጠይቅ በመሆኑ ቶኪዮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሚስዮን በተጨማሪ በኒዉዴልሂ የሚገኘው ኤምባሲም ተልዕኮ ተሰጥቶት መንቀሳቀስ ጀምሯል " ብለዋል።
NB. አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ወጣቶች ደህንነቱ ወዳልተጠበቀ ስፍራ እየሄዱ ያሉት ከስራ ቅጥር ጋር ተያያዥ በሆኑ የማተለያ ስልቶች በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል። የችግሩን ምንነት እና አስከፊነት ህብረተሰቡ እንዲያውቅ የማድረጉን ስራ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
@tikvahethiopia
" የሀገር ሀብትና የኢኮኖሚ አዉታር የሆነዉ የቡና ምርት በቀልጣፋ አገልግሎት እጦት ለጥራት ችግር እየተዳረገብን ነዉ " - የቡና አቅራቢዎች
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሀዋሳ ምርት ጥራት ምርመራና ሰርትፊኬሽን ማዕከል በሀገራች ከፍተኛ ቡና አምራች ከሚባሉ ሲዳማ፣ ጌዴኦ፣ ሻኪሶ ፣ ቡሌሆራ እና አማሮ አከባቢዎች የሚገኙ ምርቶች የጥራት ልኬት እና ሰርትፊኬሽን አግኝተዉ ቡናን ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚቀርቡበት ማዕከል ነው።
በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሀዋሳ ከተማ ተቋሙ ከሚገኝበት የቀድሞዉ የደቡብ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ግቢ ዙሪያ በአራቱም አቅጣጫ ቡና የጫኑ በርካታ ተሸከርካሪዎችን ማየት የተለመደ ሆኗል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምክንያቱን ለማጣራት ክትትል አድርጓል።
የቡና አቅራቢዎች እና አሽከርካሪዎችን ያነጋገርን ሲሆን ፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተቋሙ ባለዉ የወረፋ ብዛትና ተያያዥ ችግሮች ላላስፈላጊ ወጪ መዳረጋቸዉንና አልፎም ለሀገር ትልቅ የገቢ ምንጭ በሆነዉ የቡና ምርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑን ተናግረዋል።
" ቡና በባህሪው እንደ ሙሽራ እንክብካቤ ይፈልጋል " ያሉን አንድ የቡና ላኪ " በቦታዉ ባለዉ ወረፋ መብዛትና ተገቢነት በለሌዉ የተሽከርካሪ አቋቋም ለከፍተኛ ኪሳራ እየተዳረግን ነዉ " ብለዋል።
" በማዕከሉ ዙሪያ ተሰልፈን አምስትና ስድስት ቀናትና አለፍ ሲልም ከዛም በላይ አስር ቀን የመቆየት ሁኔታዎች አሉ " ያሉን ሌላኛዉ አስተያየት ሰጪ የቡና አቅራቢ " ቡና ሳይወጋ በሻራ ዉስጥ ታፍኖ ለረጅም ቀናት ስለሚቆይ ወደ ማዕከላዊ ገበያ በሚናቀርብበት ወቅት የጥራት ደረጃ መዉረድና በከፍተኛ ሁኔታ የኪሎግራም መቀነስ እያጋጠመን ነዉ " ብለዋል።
" ቀልጣፋ አገልግሎት ባለማግኘታችን በእኛና በተሽከርካሪ ባለቤቶች እንዲሁም በቡና አቅራቢዎች እና ጉዳይ አስፈፃሚዎች መካከል አለመተማመኖች እየተፈጠሩ ነዉ " ያሉን አሽከርካሪዎች " ለፓርኪንግ፣ ምግብ ፣ አልጋ መሰል አላስፈላጊ ወጪዎችን እያወጣን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
" ቡና በሀገር ደረጃ ባለዉ ከፍተኛ የገቢ ምንጭነት ልክ ትኩረት አልተሰጠውም " የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ " ፈጣን መፍትሔ ካልተበጀለት ጉዳቱ ከኛ አልፎ አምራች አርሶአደሮች፣ ሰፊ የስራ ዕድል በተፈጠረላቸው ወጣቶችና በሀገር የዉጪ ምንዛሪ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ማሳደሩ አይቀርም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሀዋሳ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፊኬሽን ማዕከል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ስሜን አነጋግሯል።
እሳቸውም ፤ የዘንድሮ የቡና ምርት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ቀደም ሲል ከነበረዉ የቦታ ጥበትና ተያያዥ ችግሮች ጋር ተዳምሮ ለአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ አለመሆን ዋነኛ ምክንያት መሆናቸዉን ተናግረዋል።
የችግሩን አሳሳብነትና የቡናን ሀገራዊ ጥቅሙን በመግለፅ ለሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ደብዳቤ መፃፋቸዉንና ምላሽም እየተጠባበቁ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ መልኩ የቡና ምርቶች ወደ ማዕከሉ በሚደርሱበት ወቅት አስፈላጊዉ የእርጥበት መጠን ላይ ሳይደርሱ የሚመጡበት አጋጣሚዎች ስላሉ ተገቢዉ የእርጥበት መጠናቸዉ ላይ እስኪደርሱ ድረስ መወጋትም ሆነ የቅምሻ ልኬት ስለማይደረግላቸዉና ለኮንትሮባንድ እንዳይጋለጡ ሲባል ወደ ኋላ ስለማይመለሱ በማዕከሉ እንዲቆዩ ስለሚደረግ የተሽከርካሪዎች ክምችት እንደሚፋጠርም አስታውቀዋል።
ማዕከሉ ለሲዳማ፣ ለደቡብ ኢትዮጵያና ኦሮሚያ ክልል ቡና አምራች አከባቢዎች አገልግሎት የሚሰጥና የሀገራችንን ዋነኛ የኢኮኖሚ አዉታር የሆነዉን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ የሚያቀርብ እንደመሆኑ መጠን በተለይም የሲዳማ ክልል መንግስትና ተጠሪ ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተዉ መፍትሔ ቢሰጡ ጥሩ ነው ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬን አነጋግሯል።
" ቡና ለሲዳማ ክልል ልዩ ትርጉም ያለዉ የገቢ ምንጭና የክልሉም መለያም ጭምር ነዉ " ያሉ ሲሆን በ2017 ዓ/ም ብቻ ከክልሉ ከ37 ሺ ቶን በላይ ቡና መሰብሰቡን ገልፀዉ በዘንድሮዉ ሀገር አቀፍ የቡና ቅምሻ ወድድር (ካፕ ኦፍ ኤክሰሌንስ) ከ1ኛ እስከ 39ኛ ድረስ የወጡት የክልሉ አምራች አርሶ አደሮች መሆናቸውን አስታዉቀዋል።
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሀዋሳ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፊኬሽን ማዕከል ያለበትን ጫና የክልሉ መንግስት መረዳቱንና በአጭር ጊዜ ዉስጥ አፋጣኝ መፍትሔ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
📱 ወጋገን ኢ-ብር ለምቹ እና ቀልጣፋ ክፍያ !
በወጋገን ኢ-ብር ሞባይል ዋሌት አገልግሎት በመጠቀም የሞባይል አየር ሰዓት መሙላት፣ የበረራ ትኬት መቁረጥ፣ የውሃ አገልግሎት ክፍያ ፣የትምህርት ቤት ክፍያ፣ ትራንስፖርትን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያ በምቾት እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መፈፀም ይችላሉ፡፡
🔶 ወጋገን ኢ-ብር ፈጣን፣ ቀላል እና አስተማማኝ የክፍያ አማራጭ!
የ ኢ-ብር የሞባይል ዋሌት መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር በማውረድ ወይም ወደ *602# በመደወል እና ወጋገን ባንክን በመምረጥ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
🔶 የኢ-ብር መተግበሪያ ለማውረድ👇
ፕሌይ ስቶር 🔶 አፕ ስቶር
ለበለጠ መረጃ ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል በ866 ነፃ የስልክ መስመር ይደውሉ! በተጨማሪም ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይቀላቀሉ https://linktr.ee/WegagenBank
#ወጋገን #ኢብር #ፈጣን #አስተማማኝ #ክፍያ
#Peace🏳
ሃማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነገረ።
ሀማስ የስምምነት ፕሮፖዛሉን መቀበሉን በይፋ ሲያሳውቅ የእስራኤልም ይፋ ታደርጋለች ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል።
ሁለቱ አካላት ወደ ስምምነት እንዲመጡ አሜሪካ፣ ኳታር እና ግብፅ ለበርካታ ሳምንታት ሲሰሩ ነበር ተብሏል።
እንደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የተኩስ አቁም ስምምነቱ በመጀመሪያው ዙር ለ6 ሳምንታት ይቆያል።
ሃማስ 33 ታጋቾችን ለመልቀቅ እስራኤል ደግሞ 1,000 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን ለመልቀቅ መስማማቷ በስፋት እየተነገረ ነው።
' አል አረቢያ ' አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የእስራኤል ባለስልጣንን ዋቢ ለማድረግ ሀማስ ለተኩስ አቁም እና ታጋቾችን ለመልቀቅ መስማማቱን ፅፏል።
' አልጀዚራ ' ደግሞ እስራኤል ከስምምነቱ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ያልተፈቱና ያላለቁ ጉዳዮች እንዳሉ በመጠቆም የመጨረሻው ማጠቃለያና መፍትሄ በቀጣይ ሰዓታት ውስጥ እንደሚገኝ ዘግቧል።
ስምምነቱን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ያፀድቁታል ተብሎ ይጠበቃል። የእስራኤል መንግስት ነገ ድምጽ ይሰጣል።
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ " ስምምነት ላይ ተደርሷል ሀማስም ታጋቾችን ለመልቀቅ ተስማምቷል ፤ ታጋቾች በአጭር ጊዜ ነጻ ይሆናሉ " ብለዋል።
የሁለቱ ወገኖች ስምምነት ለ15 ወራት የዘለቀውን እጅግ በጣም አስከፊ ጦርነት ያስቆማል ተብሎ ትልቅ ተስፋ ተጥሏል።
የስምምነቱን መረጃን የሰሙ ፍልስጤማውያን ጋዛ ውስጥ እያነቡ አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን እየገለጹ ነው።
ይህ ስምምነት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት እስራኤል ጋዛ ቡሬጂ የስደተኞ ካምፕ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በርካታ ፍልስጤማውያንን ገድላለች።
ባለፉት 15 ወራት በነበረው እጅግ አስከፊ ጦርነት ከ46 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 1,200 እስራኤላውያን ተገድለዋል 250 ታግተው ተወስደዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከአልጀዚራ፣ አል አረቢያ፣ ፍራንስ 24 ነው ያሰባሰበው።
@tikvahethiopia
ስጋትን የፈጠረው HMV ቫይረስ !
በቅርቡ በሰሜን ቻይና የኤችኤምፒቪ ቫይረስ መስፋፋት ስጋት ፈጥሯል።
Human Metapneumovirus ወይም HMPV የሚባለው ቫይረስ የመጣው ዓለም በኮኖናቫይረስ ከተወረረች ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው።
በቻይና ሰባት ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሞተዋል።
የቻይና ባለሥልጣናት እንዳሉት ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች ያሉ እና በኤችኤምፒቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
ሆኖም ግን ሆስፒታሎች በህሙማን ተጨናንቀዋል የሚለውን አስተባብለዋል።
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሕንድም ተገኝተዋል።
ኤችኤምፒቪ አዲስ ቫይረስ ነው ?
የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ተቋም (ሲዲሲ) እንደሚለው፣ በአሜሪካ ቫይረሱ የተገኘው በአውሮፓውያኑ 2001 ቢሆንም ከዚያ በፊትም ሳይኖር እንደማይቀር ይገመታል።
ምልክቶቹ ከጉንፋን ወይም ብርድ ጋር ይመሳሰላሉ።
➡️ ሳል፣
➡️ የሰውነት ሙቀት መጨመር፣
➡️ የአፍንጫ መታፈን፣
➡️ ትንፋሽ ማጠርን ያካትታሉ።
ከዚህ ከፍ ያሉ ምልክቶችም ሊታዩ ይችላሉ።
ሲዲሲ ቫይረሱ በሁሉም ዕድሜ ክልል እንደ ብሮንካይተስ እና ኒሞኒያ ያሉ የላይኛው እንዲሁም የታችኛው መተንፈሻ አካላት ህመምን ያስከትላል።
በአብዛኛው ቫይረሱ የሚታየው በልጆች፣ በአዛውንቶች እና እቅተኛ በሽታ የመከላከል አቅም ባላቸው ሰዎች ላይ ነው።
ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ ገብቶ ምልክት እስከሚያሳይ ድረስ ከ3 እስከ 6 ቀናት ይወስዳል።
የህመሙ ጥንካሬ ያህል የሚያሳየው ምልክትም ይለያያል።
ከሌሎች የመተንፈሻ አካላት ህመሞች ጋር ተመሳሳይ ነው።
በቅዝቃዜ ወቅት የበለጠ ቫይረሱ የመስፋፋት ዕድል እንዳለው ሲዲሲ ገልጿል።
ቫይረሱ እንዴት ይተላለፋል ?
ቫይረሱ ካለበት ሰው ወደ ጤናማ ሰው የሚተላለፈው በሳል እና በማስነጠስ አማካይነት ነው።
እንደ መጨበጥ ባሉ በሌሎች የሰውነት ንክኪዎች እንዲሁም ቫይረሱ ያለበትን እቃ ከነኩ በኋላ አፍ፣ አፍንጫ እና ዓይንን በመንካትም ይተላለፋል።
ሰዎች በብዛት ቤት በሚያሳልፉበት ቀዝቃዛ ወቅት ይሰራጫል።
ለምን በቻይና ተከሰተ ?
በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቻይና ሆስፒታሎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል ያጠለቁ ሰዎች ምሥሎች እየታዩ ነው።
ሆስፒታሎች በኤችኤምፒቪ ቫይረስ በተያዙ ሰዎች ተጨናንቀዋል እየተባለም ነው።
የቻይና የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ተቋም ኃላፊ ካን ቢዎ እንዳሉት በአገሪቱ በቀዝቃዛ ወቅቶች በቫይረሱ ሰዎች ይያዛሉ።
እንዲሁም ከ14 ዓመት በታች ያሉ እና በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል።
ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል የሚለውን ግን አስተባብለዋል።
በአውሮፓውያኑ 2024 በመተንፈሻ አካል ህመም የተያዙ ሰዎች ካለፉት ዓመታት አንጻር ቁጥራቸው መቀነሱን ኃላፊው ተናግረዋል።
ሴንተር ፎር ኢፒደሚክ ሪስፖንስ የተባለው ማዕከል የመሠረቱት ፕሮፌሰር ቱሊዮ ደ ኦሊቬራ እንደሚሉት፣ ኤችኤምፒቪ በቻይና በቅዝቃዜ ወቅት ህመም ከሚያስከትሉ አራት ቫይረሶች አንዱ ነው።
ሳይኒክቲል ቫይረስ፣ ብርድ አና ኢንፍሉዌንዛም በቅዝቃዜ ወቅት ህመም ያስከትላሉ።
በቻይና ያለውን ቅዝቃዜ እና የአራቱን ቫይረሶች ሥርጭት ከግምት በማስገባት የሆስፒታሎች መጨናነቅ የሚጠበቅ ነው ብለዋል ባለሙያው።
ቻይና መነሻው ምን እንደሆነ ያልታወቀ ኒሞኒያን የሚያጠና ቡድን ማቋቋሟን አስታውቃለች።
በመተንፈሻ አካል ህመም የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በዚህ ወቅት እንደሚጨምርም ተገልጿል።
ኮሮናቫይረስ ከአምስት ዓመት በፊት ሲነሳ አሁን ያለው ዝግጁነት አልነበረም።
ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት
@tikvahethiopia
EFMA
ድርጅታችን የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራች ኢንዱስትሪ ማህበር ከተመሰረተ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በሴክተሩ ሳሱ አምራቾች ድምፅ በመሆን በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ዓመት መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. አባለቱ በተገኙበት አራተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን አካሄዷል፡፡
ማህበሩ ዋና ዋና የሚባሉ ፐፈርኒቸር አምራቾችን አባል በማድረግ የሚሰራ ሲሆን በየቀኑም አዳዲስ አባላት ማህበሩን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ፤ ለእርስዎም በፈርኒቸር እና ተዛማች ስራዎችና ምርቶች ላይ ተሰማርተዉ የሚሰሩ ከሆነ የማህበሩ አባል በመሆን በርካታ ጥቅሞችን ያግኙ፤ የማህበሩን አላና እና ስራዎች ለማየት የማህበሩን ዌብሳይት ይጎብኙ።
https://efma.topbestsimilar.com/
#TikTok
' ቲክቶክ ' የተሰኘው መተግበሪያ አልባኒያ ውስጥ ለአንድ አመት እንደሚታገድ መገለጹ ይታወሳል።
" እገዳው በኦንላይ የንግድ ስራ የሚሰሩ / ማርኬቲንግ ላይ ያሉ እንዲሁም የንግግርና ሃሳብ ነጻነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያመጣል " በሚል የመብት ተሟጋች ነን በሚሉ አካላት እገዳው ቢተችም የሀገሪቱ መንግሥት እገዳውን ተግባራዊ ያደርጋል ተብሏል።
ቲክቶክ በቀጣይ ሳምንታት ይወርዳል ተብሏል።
ሀገሪቱ ' ቲክቶክ 'ን ለማገድ ውሳኔ ያሳለፈችው ከሳምንታት በፊት በኦንላይን በተነሳ ፀብ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተወግቶ መገደሉን ተከትሎ ነው።
በቅርቡ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ በአልባንያ መዲና ቲራና ከመምህራን፣ ወላጆችና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ፥ " ቲክቶክ የሰፈር ወሮበላ ነው። ለአንድ ዓመት ቲክቶክ እናግዳለን። ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ዕድገት የሚከታተሉበት አሠራር እንዘረጋለን " ሲሉ ተናግረው ነበር።
" በቻይና ቲክቶክ የሚያገለግለው ለልጆች ትምህርት፣ ለተፈጥሮ ጥበቃና ባህልን ለመጠበቅ ነው። ከቻይና ውጭ ያለው ቲክቶክ ግን ርካሽና አሳሳች ነው። ይሄን ለምን እንፈልጋለን ታዲያ ? " ሲሉም ገልጸው ነበር።
' ቲክቶክ ' የተሰኘው መተግበሪያ ፤ አልጎሪዝሙ ልቅና ሱስ የሚያሲዝ ተድርጎ የተሰራ ፤ ቁጥጥር የሌለው ፤ ለማህበረሰብ ግንኙነት ለልጆች ፣ ወጣቶች ጠንቅ ፤ በቻይና ያለውና በሌላው የተቀረው ዓለም ላይ ያለው ይዘት ልዩነት ያለው በሚል ይተቻል።
አሜሪካ ደግሞ ከቻይና የመረጃ ምንተፋ ጋር በማገናኘት እስከመጨረሻው ድረስ ከሀገሪቱ ለማገድ ጫፍ ደርሳ እግዱን ተግባራዊ የምታደርግበትን ቀን እየጠበቀች ነው።
ባይትዳንስ የተባለው የቲክቶክ ፈጣሪ ድርጅት በተለያየ ጊዜ የሚቀርብበትን ክሶች ሁሉ ውድቅ ሲያደርግ እንደነበር አይዘነጋም።
#TikTok
@tikvahethiopia
" 16.3 ቢሊዮን ብር ሰብስበናል ! " - ICS
" ባለፋት ስድስት ወራት 10 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደን ከ16.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስበናል። ከ721 ሺህ 623 በላይ ፓስፖርቶችን የማተም ስራም ተሰርቷል። ከታተመው 98 በመቶው ለተገልጋዮች ተሰጥቷል " - ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት (የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር) #EPA
@tikvahethiopia
1.ICT Consulting(ICT Infrastructure and Support)
2.Structured Network Cabling (Design/Installation/Documenting & Testing)
3.ICT Infrastructure (Enterprise Grade CCTV, Wireless, Time Attendance)
4.ICT Support (Endpoint Protection)
5.Email Security(SPF/DMARC/DKIM)
6.Business Website Design (Maintenance & Updates | Security & Backups)
7.Visual Branding and Advertising Design (Logo Design | Product Catalog)
Miniapp => http://t.me/SeventechSolutionsBot/app
Phone => +251-717-73-23-73
Chat => /channel/seventechsolutions
#Update
በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ከፍተኛ ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን እሳቱ አሁንም ሎስ አንጀለስን ማንደዱን ቀጥሏል።
እሳቱ እስካሁን ካደረሰው ውድመት በላይ ሊያደርስ ይችላል ተብሏል።
በአካባቢው ያለው የንፋስ ሁኔታ እሳቱን እያባባሰው ነው ተብሏል።
ከተነሱት ሰደድ እሳቶች አንዱን ብቻ ነው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለው።
ባለስልጣናት #ቀጣዮቹ ንፋሶች አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የንፋስ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ በማለት መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
እስከ ትላንት ባለው 24 ሰዎች ሲሞቱ 16 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።
የግል ትንበያ ተቋም የሆነው " አኩዌዘር " እስከ ትላንት ባለው በእሳት ቃጠሎ የተነሳ የደረሰው ኪሳራ ግምት ከ250 እስከ 275 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል።
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የመንበረ ጸባዕት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ገብቷል፡፡
የፎቶ ባለቤቶች ፦ ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል እና የኢኦተቤ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopia