ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
" በአዲስ አበባ ከተማ ' ቃሊቲ አካባቢ ' ባለ ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች ይገኛሉ " - ኢሰመኮ
በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው መያዝ እና ወደ ማቆያ ማእከላት ማስገባት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ስለሚያስከትል ሊቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።
ኮሚሽኑ " ከጎዳና ላይ ለሚነሱና ወደማቆያ ለሚገቡ ሰዎች ሰብአዊ መብቶችን ያማከለ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል "ም ብሏል።
ኢሰመኮ ዛሬ በላከልን መግለጫ ፥ በሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በጎዳና ላይ ያሉ ሕፃናት በጅምላ ተይዘው የሚቆዩበትን ሁኔታ በተመለከተ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ሲዳ አዋሽ ወረዳ በሚገኘው ማቆያ ማእከል ተይዘው የነበሩ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ያደረጉ ሰዎችን (በተለምዶ አጠራር ‘‘ ጎዳና ተዳዳሪዎች ’’ ተብለው የሚታወቁ) ሁኔታ አስመልክቶ ክትትል በማድረግ የተለዩ ክፍተቶችንና ምክረ ሐሳቦችን የያዘ መግለጫ ማውጣቱ አስታውሷል።
በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. ባደረጋቸው ክትትሎች ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ “ ቃሊቲ አካባቢ ” ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ባለ ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማእከል/ቦታ የማስገባት ድርጊት አሁንም መቀጠሉን አመልክቷል።
ወደ ማቆያው ከገቡት ሰዎች መካከል በማእከሉ ከመቆየት እና የእርሻ ሥራ ከመሥራት እንዲመርጡ በማድረግ፤ የእርሻ ሥራ ለመሥራት የመረጡ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ እርሻ ጣቢያዎች ተወስደው እንዲሠሩ እንደሚደረግ ለመገንዘብ መቻሉን ጠቁሟል።
ይህም " የነጻነት መብታቸውን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶቻቸውን የሚጥስ ነው " ብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ፣ የሚደረጉ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ጉባኤዎች እንዲሁም ከሌሎች ተመሳሳይ ኹነቶች ጋር በተያያዘ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን በኃይል በማንሳት በአንድ ስፍራ እንዲቆዩ የማድረግ አሠራር እንዲቆም ፤ ወደመጡባቸው አካባቢዎች የመመለስ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ሰብአዊ መብቶቻቸውን ባከበረ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ እና ችግሩ ሁሉ አቀፍ የፖሊሲ ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ የኢሰመኮ ክትትሎች መጠቆሙን አስታውሷል።
ኢሰመኮ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውትወታ እያደረገ መሆኑን ጠቁሟል።
ጎን ለጎን የነጻነት መብትን ከማክበር እና ከማስከበር አኳያ እንዲሁም በጊዜያዊ ማቆያ ማእከሉ ከንጽሕና እና ከጤና አጠባበቅ ጋር በተያያዘ በሰዎች ሕይወትና ጤና ላይ አደጋ የሚጥሉ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ውይይቶችን በማድረግ ጉዳዩን በመከታተል ላይ እንደሆነ በላከል መግለጫ ገልጿል።
#EHRC #Ethiopia
@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በይፋ የአክሲዮን ግብይት ተጀመረ።
የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዛሬ ዓርብ የአክሲዮን ሽያጭና ግዢ ግብይቱን በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
የአክሲዮን ገበያ ሥራውን በይፋ ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ " በጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ግብይት በዛሬው ዕለት ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውለናል " ብለዋል።
የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያው ዋና ዳይሬክተር ጥላሁን ካሳሁን በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ 50 ያህል ኩባንያዎች በዚህ ገበያ ላይ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለግብይት እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።
በተለምዶ ክፍት ገበያ በመባል የሚታወቀው የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ የተማከለ የፋይናንሺያል ገበያን የሚያመለክት ሲሆን የተዘረዘሩ ኩባንያዎችን የዋስትና ሰነዶች፣ኮሞዲቲዎች ጨምሮ በአክሲዮን ሻጮች እና ገዥዎች መካከል የሚገዙበት እና የሚሸጡበት ማዕከል መሆኑ ይታወቃል።
የመረጃው ባለቤት ካፒታል ጋዜጣ ነው።
@tikvahethiopia
" የቁስ አካላቱ ሞያሌ ላይ አልወደቁም " - ነዋሪዎች
በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ ነገር ሞያሌ ላይ አለመዉደቁን ነዋሪዎች ገለጹ።
ትላንት ምሽት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍሎች ሰማይ ላይ ከተለመዱት ተወርዋሪ ኮከቦች በተለየ መልኩ በመጠን የገዘፈና በዘገምተኛ አኳሃን ሲጓዝ እንደነበር የተገለጸው ብርሃናማ የተቀጣጠሉ ቁስ አካላት " ሞያሌ አከባቢ ወድቋል " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ምንጫቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።
ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሞያሌ ኢትዮጵያ እና ጋምቦ አካባቢዎች ባደረገው ማጣራት ብርሃናማዉ አካል በተመሳሳይ መልኩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ወደ ሶማሊያና ምስራቃዊ ኬንያ አቅጣጫ ማለፉንና በአከባቢው አለመዉደቁን ለማወቅ ችሏል።
በሞያሌ ጋምቦ የሚገኘው የመረጃ ምንጫችን ስለጉዳዩ በሰጠው ቃል " በሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር አከባቢ መደጋገሙን ስንሰማ ስለነበር በዚህም ክስተት ሰዉ ሁሉ ደንግጦ ነበር፤ ነገሩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ሲያልፍ አይቻለሁ " ብሏል።
አክሎ " ሪችት ይመስላል-ሞያሌ ወደቀ የሚል ነገር ሰምቼ እስከ ማርሳቤትና ናይሮቢ ድረስ ደዋዉዬ አጣራሁ ያሉኝ ነገሩ ናይሮቢ አልደረሰም፤ ነገር ግን የማርሳቤት ሰዎች ሰማይ ላይ አይተነዉ ኡጂሩ በተባለች የኬንያ ድንበር አድርጎ ወደ ሶማሊያ መሄዱን ነግረዉኛል " ሲል ገልጿል።
አንዳንድ ጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የስነ ከዋክብትና ስፔስ ሳይንስ አጥኝዎች ይኸው ተቀጣጣይ ነገር " የጠፈር ፍስራሾሽ " ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።
በኢትዮጵያም ይሁን በኬንያ ተቋማት በኩል ቁርጥ ያለ ነገር ባይነገርም በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በኩል ጉዳይን በዝርዝር ለማሳወቅና ለማብራራት ስራዎች እየተሰሩ ነው።
ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ማገባደጃ በኬኒያ ሙኩኩ በተባለ ገጠራማ መንደር 500 ኪ.ግ የሚመዝን ቀለበታማ የጋለ ብረት መውደቁ የተነገረ ሲሆን የሀገሪቱ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል ማስታወቁ አይዘነጋም።
#TikvahEthiopiaFamily #Moyalle #Gambo
@tikvahethiopia
ሕብር ብልሕ የሴቶች ዋዲያህ የቁጠባ ሒሳብ
በሕብር ሐቅ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መካከል አንዱ የሆነውን የሕብር ብልሕ የሴቶች ዋዲያህ የቁጠባ ሒሳብ በመክፈት ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
ጁመዓ ሙባረክ!
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ /channel/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
#interestfreebanking #womenssaving #Hibirhaq
#telebirr
🌟 10% የገንዘብ ስጦታ ከተጨማሪ የዕድል ሽልማቶች ጋር!!
የገናን በዓል አስመልክቶ ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎን ዓለም አቀፍ ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ 10% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡
💁♂️ በተጨማሪም 6ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ሲቀበሉ አጓጊ ለሆነው ልዩ የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!
1️⃣5️⃣ የቤት ዕቃዎች - እያንዳንዳቸው 100,000 ብር
2️⃣0️⃣ የበግ ስጦታዎች - እያንዳንዳቸው 15,000 ብር
5️⃣0️⃣ የበዓል አስቤዛ - እያንዳንዳቸው 10,000 ብር
3️⃣0️⃣0️⃣ የኪስ ገንዘብ - እያንዳንዳቸው 5,000 ብር
🌍🎁 እንዲሁም በርካታ የሞባይል ዳታ ጥቅሎች
የሚቀበሉት የገንዘብ መጠን ሲጨምር የጨዋታ ዕድልዎም ይጨምራል!
🗓 እስከ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
#USA 🔥 በአሜሪካ ፤ በሎስ አንጀለስ ታሪክ አውዳሚ ነው በተባለ የሰደድ እሳት እስካሁን በውል ያልታወቁ ሰዎች ሲሞቱ ፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል።
እሳቱ በሎስ አንጀለስ ከተማ በብዙ ስፍራ እየተዛመተ ነው ተብሏል።
የሰደድ እሳቱ የሆሊውድ ምልክት በሚገኝበት የሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ እየተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።
በሎስ አንጀለስ እና በአጎራባች ግዛቶች ቢያንስ 5 ሰደድ እሳቶች የተያያዙ ሲሆን ሶስቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አልተቻለም።
1. ፓሊሳድስ
ፓሊሳድስ የተሰኘ መጠሪያ የተሰጠው ሰደድ እሳት በሎስ አንጀለስ የተቀሰቀሰው ማክሰኞ እለት ሲሆን በግዛቲቷ ትልቁ ነው። የፓስፊክ ፓሊሳድስ አካባቢን ጨምሮ ከ17 ሺህ 200 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰፊ ግዛት አውድሟል።
2. ኢቶን
ኢቶን የተሰኘው ደግሞ በሰሜናዊ የሎስ አንጀለስ እን አልታዴና ባሉ ከተሞች እየተዛመተ የሚገኝ ሲሆን 10 ሺህ 600 ሄክታርን መሬት በመሸፈን በግዛቲቷ ሁለተኛው ትልቁ እሳት ሆኗል።
3. ኸረስት
ኸረትስ የተሰኘው ሰደድ እሳት ማክሰኞ እለት ተከስቶ ከሳን ፈርናንዶ በስተሰሜን በኩል እየተዛመተ ይገኛል። ይህም እሳት 855 ሄክታርን ይሸፍናል።
4. ሊዲያ
ይህ ደግሞ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በሎስ አንጀለስ በስተሰሜን ተራራማዋ አክቶን አካባቢ ተቀስቅሶ ወደ 350 ሄክታርን መሬት በመሸፈን ተዛምቷል።
5. ሰንሴት
ይህ ሰደድ እሳት ረቡዕ ምሽት ላይ በሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች የተከሰተው ሰደድ እሳት ሲሆን ከሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ 20 ሄክታር እያደገ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ወደ 43 ሄክታር ተዛምቷል።
ውድሌይ እና ኦሊቫስ የተሰኙት ሰደድ እሳቶች በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአካባቢው የእሳት አደጋ ባስልጣናት ገልጸዋል።
የመረጃው ምንጮች ፦ ቢቢሲ እና ሲኤንኤን ናቸው።
ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia
#Update
ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባዔ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት ተቃውሞ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በተጨማሪ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅንም አጽድቋል፡፡ አዋጁ በሶስት ተቃውሞ ፣በአራት ድምፅ ተአቅቦ ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።
@tikvahethiopia
#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር።
በርካታ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መንቀጥቀጡ እና ንዝረቱ ከእንቅልፋቸው እንደቀሰቀሳቸውና ጠንክሮ እንደተሰማቸው መልዕክት ልከዋል።
በተለይ አዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጠንከር ብሎ ንዝረቱ ተሰምቷል።
ከንዝረቱ ጋር በተያያዘ መልዕክት የላከ የቤተሰባችን አባል ፥ " 7:09 ለቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቶናል ከዚህ በፊት ተሰምቶን አያውቅም ፤ ኳስ እያየን ቆይተን በጥቂቱም ቢሆን ለ 5-10 ሰከንድ የቆየ ንዝረት ተሰምቶናል ፤ Odd የሆነ ስሜት አለው ግራ መጋባት ፈጥሮብን ነበር " ብሏል።
ውድ ቤተሰቦቻችን የጥንቃቄ እርምጃዎችን አንብቡ ፦ /channel/tikvahethiopia/93267?single
@tikvahethiopia
" ጥያቄያችን ግልፅ ነው ፤ አሁንም ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች !! " - የትግራይ የእሰልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፥ በአክሱም ከተማ ከሙስሊም ተማሪዎች የሂጃብ መልበስ ክልከላ ጋር ተያይዞ ወቅታዊ ማብራርያ ዛሬ ምሽት ሰጥቷል።
ምክር ቤቱ በማብራርያው ፥ የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ የተደረገው ክልከላ ሃይማኖታዊ እና ዓለማዊ የሰው ልጆችን መብት የሚጋፋ ከመሆኑ አኳያ ችግሩን ለመፍታት በብዙ አማራጮች ተሞኩረዋል ብሏል።
ከሙከራዎቹ አንዱ በክልሉ ትምህርቲ ቢሮ የተደረገው እንደሆነ ጠቁሟል።
ህግ የጣሰው ክልከላ እንዲነሳ " ትምህርት ቢሮ ያልተሳካ ሽምግልና እና መተግበር የማይችል ደብዳቤ ከመፃፍ የዘለለ ያመጣው ተጨባጭ ለውጥ የለም " ሲል ገልጿል።
የትምህርት ቤቱ አንዳንድ አመራሮች ከራሳቸው የሃይማኖት ፍላጎት ፤ የትምህርት መብት አተያይ በመነሳት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳይገቡ ተደርገዋል ብሏል ም/ቤቱ።
" የተማሪዎች የትምህርት ገበታ ክልከላ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸውንና በሂጃብ ክልከላ ምክንያት ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያዘልቃቸው ዕድል እንዲዘጋ መደረጉ ነው " ሲል ገልጿል።
ምክር ቤቱ " ከቀናት በፊት በአቋም መግለጫችን እንደጠቀስነው ክልከው በአፈጣኝ ካልተፈታ በህግ ክስ እንጠይቃለን ባልነው መሰረት ጉዳዩ ወደ ህግ ወስደነዋል " ብሏል።
በዚህም በቀጣይ " እወስደዋለሁ " ያለውን እርምጃ መተግበር መጀመሩ አስታውቋል።
" ጉዳዩ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሴቶች መብትና የሰው ልጆች የመማር መብት ጥሰት አኳያ መታየት አለበት " ያለው ምክር ቤቱ " ጉዳዩ ሁሉም ትግራዋይ እንዲያወግዘው " ሲል ጥሪ አቅርቧል።
ምክር ቤቱ በመግለጫው ማጠቃለያ " ጥያቄያችን ግልፅ ነው ፤ አሁንም ሂጃብዋ ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Update
በትግራይ ክልል ፤ አክሱም ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ መከልከል ጋር ተያይዞ የተከሰተው ውዝግብ አሁንም መቋጫ አላገኘም።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጉዳዩ በማስመልከት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ በሰጠው መግለጫ " የመብት ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃ እንወሰዳለን " ብሎ ነበር።
በመግለጫው " የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ አስመልክቶ ያወጣው ህግ እንዲከበር እንጠይቃለን " ማለቱም ይታወሳል ።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዛሬ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አክሱም ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጠው ፤ ከምክር ቤቱ መግለጫ በኋላ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወደ አክሱም በማምራት ከትምህርት ቤቱ አመራሮች ፣ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎች ተወያይተዋል።
የመረጃ ምንጫችን " ውይይቱ መሬት ላይ ጠብ የሚል ለውጥ አላመጣም " ብሏል።
" የቢሮ ሃላፊው የትምህርት ሚንስቴር ህግ ፣ መመሪያ እና ደንብ መሰረት ያደረገ ትእዛዝ መስጠት ሲገባቸው ፤ ጉዳዩን ለማሸማገል ያደረጉት ጥረት ተጎጂ ተማሪዎቹ መታደግ አልቻለም " ሲል አክሏል።
ስለሆነም ችግሩ በቀጣዩ ቀናት መፈታት ካልተቻለ 160 የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች እጣ ፈንታ አደጋ ላይ ይወድቃል ሲል የመረጃ ምንጩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተናግሯል።
የመቐለ ቲክቫህ አባል ለትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ቅርበት ካላቸው ወገኖች ባገኘው መረጃ ደግሞ ከውዝግቡ ጋር በተያያዘ ይሁን ለሌላ ስራ ጉዳይ ነገ የፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ የሃይማኖት አመራሮች መቐለ ትግራይ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Update
በነገው ዕለት ፓርላማው በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህግና ፍትህና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ፥ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሏል።
ከንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ፦
" #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል። "
የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ለመደንገግ ከተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ፦
" የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ፣ ሊሸጥ ከሚገባው ሰው ቦታና የግብይት ስርዓት ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ወይም አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስርና ከብር 50 ሺህ እስከ ብር 100 ሺህ የሚደርስ ቅጣት ይፈጸምበታል።
መንግሥት ከሚያወጣው የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ውጪ በተደጋጋሚ የመገበያየት ወንጀል እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል እስከ 3 ዓመት እስርና እስከ 300 ሺህ ብር ቅጣት ያስጥላል። "
🔴 ስለ ንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ቀደም ያጋራናችሁን ዝርዝር መረጃና ሰነድ በዚህ ይገኛል ፦ /channel/tikvahethiopia/88315
🔵 ስለ ነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓት ስለሚደነግገው ረቂቅ አዋጅ ያጋራናችሁ ዝርዝር መረጃ ደግሞ በዚህ ይገኛል ፦ /channel/tikvahethiopia/92370?single
@tikvahethiopia
#Earthquake
በአፋር ክልል አዋሽና አካባቢው እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም ድረስ ቀጥሏል።
ትላንት ቀን እንዲሁም ለሊቱን ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በመዘገበው ብቻ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ 4.7 ፣ 5.3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ከሁሉም ከፍ ያለው ለሊት የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.3 ሲሆን የመሬት መንቀጥቀጡ አዋሽ እና አካባቢው በርካታ ሰዎችን ከእንቅልፋቸው ቀስቅስቋል።
ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞችም ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተው በነበረው ቃል ፤ ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራዎች መካከል ሲሆን የሚታየው ርዕደ መሬት የዛ ውጤት ነው።
የዛ እንቅስቃሴ የፈጠረው መንቀጥቀጥ ሞገድ በመሬት ውስጥ ተጉዞ ነው አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማው።
@tikvahethiopia
#Abyssiniabank
አይዞን ለበዓል እኛ አለን።
ከአፖሎ እንዴት አነስተኛ ብድር መውሰድ እንደሚቻል ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ፡ /channel/apollodigitalproduct/220
ለአንድሮይድስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
የነዳጅ ዋጋ ምን ያህል ብር ጨመረ ?
ቤንዚን በሊትር 91 ብር ከ14 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 10 ብር ከ33 ሳንቲም ጨምሮ 101 ብር ከ47 ሳንቲም ገብቷል።
ናፍጣ ደግሞ በሊትር 90 ብር ከ28 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን 8 ብር ከ7 ሳንቲም ጨምሮ 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል።
በሌሎች የነዳጅ ምርቶች ላይም በትንሹ ከ8 ብር በላይ ተጨምሯል።
ከሁሉም በላይ በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ የተጨመረው ከፍ ያለ ሲሆን በሊትር 31 ብር ከ8 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎ 77 ብር ከ76 ከነበረበት ወደ 109 ብር ከ56 ሳንቲም ገብቷል።
@tikvahethiopia
#China #Tibet
ለሊቱን እና ጥዋት ላይ በዓለም በተለያዩ ሀገራት የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል።
ከነዚህ ውስጥ እጅግ የከፋው እና የ53 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመሬት መንቀጥቀጥ በቻይና ፤ ቲቤት ግዛት ደርሷል።
የቻይና የመሬት መንቀጥቀጥ ኔትዎርክ ሴንተር በሬክተር ስኬል 6.8 የተመዘገበ ነው ብሏል።
የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ግን የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 7.1 የተመዘገበ ነው ሲል አመልክቷል።
በሬክተር ስኬል 6.8 ሆነ ከዛም በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እጅግ ጠንካራና አደገኛ ከፍተኛ የሆነ ውድመት ሊያደርስ የሚችል ነው።
በቲቤት 6 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ 7.1 ነው።
በመሬት መንቀጥቀጡ ህንጻዎች ፣ መኖሪያ ቤቶች ተደርምሰዋል።
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የቻይና ሚዲያዎችን ዋቢ በማድረግ በትንሹ 53 ሰዎች እንደሞቱ ነገር ግን ከፍርስራሽ ስር ያሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ በዚህም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የነፍስ አድን ስራ ላይ ተሰማርተዋል።
አደጋው ተራራማ በሆኑ የገጠራማ ክፍሎች የደረሰ ሲሆን ዋና ወደሚባሉ ከተሞች እንኳን አልተጠጋም።
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በሰሜን ህንድ እና በኔፓል ዋና ከተማ ካታህማዱ ሌሎችም ቦታዎች በእጅጉ ተሰምቷል።
ባለስልጣናት ዜጎቻቸው እንዲረጋጉ እና ቀጣይ ለሚመጣው ሾክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።
ስፍራው በተደጋጋሚ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያስተናግድ ነው።
የመሬት መንቀጥቀጥ ቅፅበታዊ ፣ ለመገመት እና ለመተንበይ የሚያስቸግር የት ቦታ እንደሆነ እንጂ መቼ እንደሚፈጠር የማይታወቅ በመሆኑ ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ ንቁ ሆኖ መጠበቅ ይገባል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ያሰባሰበ ሲሆን ቪድዮዎቹና ፎቶዎቹን ከቲቤት እና ኔፓል የማህበራዊ ትስስር ገጾች ነው የወሰደው።
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ? የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ያንብቡ : /channel/tikvahethiopia/93267?single
@tikvahethiopia
" ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን " - ቅዱስነታቸው
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።
ቅዱስነታቸው ፤ በሀገራችን በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
" ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ አባታዊ ጥሪ በድጋሚ እናስተላልፋለን " ብለዋል።
ቅዱስነታቸው ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት በሕዝቡ ላይ ተጨማሪ ችግርና ጭንቀት እያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል።
" በትሕትና መንፈስ እርስ በርስ መገናዘብ ተፈጥሮ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል ታደርጉ ዘንድ አደራችን የጠበቀ ነው " ብለዋል።
በተጨማሪም ቅዱስነታቸው በትግራይ ክልል ስለሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ጉዳይ በአባታዊ የሰላም ጥሪ መልዕክታቸው አንስተዋል።
" መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን " ብለዋል።
በሌላ በኩል ቅዱስነታቸው በመሬት መንቀጥቀጥ እየተጨነቁ ላሉ እና ስለተጎዱ ልጆቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
" የመሬት መንቀጥቀጥ ባለበት አካባቢ እየተጨነቃችሁ ያላችሁ ልጆቻችን ረድኤተ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን በጸሎት የምታስባችሁ መሆኑን እየገለጽን መላው ኢትዮጵያውያን ለጉዳቱ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ለሚኖሩት ወገኖቻቸው አቅማቸው በፈቀደው መጠን ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን " ብለዋል።
(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
" የሟሟቱ ሁኔታ በሚመለከታቸው አካላት እየተጣራ ይገኛል " - አክሱም ዩኒቨርሲቲ
በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሽረ ካምፓስ ተማሪ ህይወቱ እንዳለፈ ዩኒቨርስቲው አስታወቀ።
" ተማሪያችን ካሕሱ ሃይሉ በእፅዋት ሳይንስ የትምህርት ክፍል የአንደኛ ዲግሪ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ነበር ብሏል " ዩኒቨርስቲው።
ዩኒቨርሲቲው የተማሪው ሕይወት ያለፈው ከካምፓስ ውጪ ሌሊት ባጋጠመ ድንገተኛ ግጭት እንደሆነ ጠቁሟል።
ግጭቱ በምን ምክንያት እንደነበረ ፣ ከምን ጋር እንደሆነ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።
የተማሪ ካሕሱ ሃይሉ ሃደራ የሟሟት ሁኔታ በሚመለከታቸው አካላት እየተጣራ ይገኛል ያለው ተቋሙ ውጤቱ በሚመለከታቸው አካላት ይፋ እንደሚደረግ ገልጿል።
@tikvahethiopia
" ከ260 በላይ ቤተሰቦች ጦም ለማደርና ለለልመና ለመውጣት ይገደዳሉ " - ነዋሪዎች
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ፤ በዋድላ ወረዳ በ11 ቀበሌዎች በተለያዩ ቀናት የሰብል ክምር ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ መድረሱ ተሰምቷል።
" ምክንያቱ አልታወቀም " በተባለው የእሳት ቃጠሎ የ154 አርሶ አደሮች እህል ሰብል ክምር መቃጠሉን የዋድላ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።
በ03 ቤተሆር ቀበሌ ቀጭኔ ጎጥ ጥር 1/2017 ዓ/ም በደረሰው ቃጠሎ ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደሮች የቃጠሎው መነሻ በውል አለመታወቁን ገልፀው ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል፡፡
በዚህ ቀበሌ ብቻ የ52 አርሶ አደሮች የመህር ሰብል ክምር የተቃጠለ ሲሆን የአንዳንዶቹ ከዚህ ከተቃጠለው ሰብል ውጭ ሌላ ምንም ሰብል/አዝመራ እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡
በዚህ ቀበሌ ብቻ የ52 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር ሙሉ በሙሉ ሲቃጠል በቤተሰብ ደረጃም ከ260 በላይ የቤተሰብ አባላት ጦም ለማደርና ለለልመና ለመውጣት እንደሚገደዱ የአካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል።
የዋድላ ወረዳ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን መሪ አቶ ምትኩ ሞላ ምን አሉ ?
" በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል።
እስካሁን ባለው መረጃ 770 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል " ብለዋል።
የዋድላ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙሉየ ረታ ምን አሉ ?
" እንደ ወረዳ በ11 ቀበለሌዎች በ152 ክምር ላይ ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን 154 አርሶ አደሮች የጉዳቱ አካል ሁናዋል።
የደረሰው ውድመት በኩንታል 4 ሺ 560 ሲሆን ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል።
አሁንም ቢሆን አርሶ አደራችን የመውቂያ ማሽን ይምጣልን ጥያቄ እያቀረቡ ስለሆነ ማሽኑን መንግስት ቢያቀርብልን አርሶ አደራችን ተጠቃሚ እናደርጋለን።
አሁን ላይ በወረዳችን የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ስለሆነና ወረዳው ይህን የተጎዳ የህብረሰብ ክፍል መረዳት ስለማይችል መረጃውን ለረጅ ድርጅቶች በማጋራትና የምትችሉትን ሁሉ በማገዝ የሰብዓዊነታችሁን ሚና እንድተወጡ " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከዋድላ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia
#Kenya
ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ብርሃን ያላቸው የቁስ አካላት ስብስብ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍልም ታይተዋል።
እነዚህ ቁስ አካላት በኬንያ ቱርካና፣ ማርሳቢት፣ ሞያሌ አካባቢ መታየታቸውን የኬንያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል።
ምንም እንኳን ቁስ አካላቱ " የጠፈር ፍርስራሾች ናቸው በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል (ኬንያ - ኢትዮጵያ ድንበር) ወድቀዋል ፤ ሲወድቁም ከፍተኛ ድምጽ ተሰምቷል ፤ ከሚቃጠል ነገር ጭስም ታይቷል ሽታም ነበረው " እያሉ ብዙ ተከታይ ያላቸው የኬንያ ፀሀፊዎች X ላይ ቢፅፉም የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ በይፋ የሰጠው ማረጋገጫ የለም።
እስካሁን የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ፥ ቁስ አካላቱ ኬንያ ውስጥ ስለመውደቃቸው ማረጋገጫ አልሰጠም ስለ ጉዳዩ መግለጫም አላወዋጣም።
ከሰሞኑን በኬንያ ማኩኒ ካውንቲ ሙኩኩ በተባለች ትንሽዬ መንደር ከሰማይ ወርዷል የተባለ 2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለውና 500 ኪሎግራም ክብደት ያለው ቁስ በርካቶችን አስደንግጦ ነበር።
የኬንያ የስፔስ ኤጀንሲ ሰዎች ቁሱ ወደወደቀበት ስፍ በማቅናት ምንነቱን ለማጥናት የሞከሩ ሲሆን ወደ ህዋ የመጠቀ ሮኬት ቁርጥራጭ ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል።
ቀለበት ቅርጹ ከሮኬት ከተነጠለ በኋላ የሚፈረካከስ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የየትኛው ሀገር ወይም ኩባንያ ንብረት እንደሆነ የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው። እስካሁን መደምደሚያ ላይ አልተደረሰም።
ተቋሙ " እንደዚህ አይነት ቁሶች (በኬንያ የወደቀው ቀለበት) ወደ ምድር ምህዋር ሲመለሱ ራሳቸውን እንዲያቃጥሉ አልያም ወደ ውቅያኖሶች እንዲገቡ ተደርገው የሚሰሩ ናቸው " ሲል ነው ያብራራው።
እንደ ኒውዮርክ ታይምስ መረጃ ከሆነ ባለፉት ስድስት አስርት አመታት በሀገራት መካከል የሚደረግ የህዋ ላይ ፉክክር መጠናከር ከሰማይ ላይ የሚወድቁ ቁሶች እንዲበራከቱ አድርጓል።
ባለፈው አመት ባወጣ የአውሮፓ የጠፈር ኤጀንሲ መረጃ በዝቅተኛ የምድር ምህዋር ውስጥ ከ14 ሺህ ቶን በላይ ቁሶች እንዳሉ ተገምቷል ፤ ከዚህ ውስጥም ከሲሶ በላዩ ለህዋ ምርምር የማያስፈልጉ ቁሳቁሶች ናቸው።
እንደ መረጀው ፥ በየአመቱ ከ110 በላይ የሳተላይት ማምጠቅ ሙከራዎች ይደረጋሉ ፤ በጥቂቱ 10 ሳተላይቶች እና ሌሎች የምርምር ቁሳቁሶች ወደ ትንንሽ ስብርባሪዎች ይቀየራሉ። ይህም ከህዋ ላይ ወደ መሬት የሚወድቁ ነገሮች እንዲበራከቱ አድርጓል።
መረጃው ከኬንያ የማህበራዊ ትስስር መድረኮች፣ ከኒውዮርክ ታይምስ፣ ከቢቢሲ፣ ከአል አይን ፣ ከኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ነው የተገኘው።
@tikvahethiopia
" የማጣራት ሥራውን እስክናጠናቅቅ ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ በትህትና እንጠይቃለን " - የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ
የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ መታየታቸው ሪፖርት እንደደረሰው ዛሬ ጥዋት አሳውቋል።
" በደረሰን ተንቀሳቃሽ ምስል ለመመልከት እንደቻልነው የእነዚህ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዮር አለቶች ይመስላሉ " ብሏል።
" ስብስቡ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል " ሲል አክሏል።
" የክስተቱን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችለን ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራን የምንገኝ ሲሆን ፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል " ብሏል።
" የማጣራት ሥራ እንኪጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ በትህትና እንጠይቃለን " ሲል ጥሪውን አቅርቧል።
#ESSS
@tikvahethiopia
" ሰማይ ላይ ያየነዉ እንግዳ ነገር ፍርሀት ዉስጥ ጥሎናል " - ነዋሪዎች
ዛሬ ምሽት በበአርባ ምንጭ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ቡርጂ ፣ ሱሮ ባርጉዳ (ምዕራብ ጉጂ ዞን) እና ሌሎችም በርካታ ስፍራዎች በሰማይ ላይ የታየዉ ተምዘግዛጊ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ነገር ፍርሃት አንደጫረባቸዉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ " ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ብርሃናማ ነገር በሰማይ ቅርብ ርቀት ወደ ደቡብ አቅጣጫ መጓዙን አስተዉለናል " ብለዋል።
" አልፎ አልፎ እንደሚስተዋሉ ተወርዋሪ ኮከቦች ቶሎ ታይቶ የሚጠፋና በፍጥነት የሚጓዝ አለመሆኑ ነዉ ፍርሃት የጫረብን " ያሉን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች አሁንም " በርከት ያለ ህዝብ ሰማይ ሰማዩን እያዬ እየተጠባበቀ ይገኛል " ብለዋል።
ይኸው ተቀጣጣይ ብርሃናማ ነገር በኢትዮጵያ አልፎ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ አካባቢዎች እንዲሁም በኬንያ ሞያሌ በኩብ ታይቷል።
ለመሆኑ ነገሩ ምንድነው ? በሚል የዘርፉን ጉዳይ ወደሚከታተሉ አካላት ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም። ስልክም አያነሱም።
የባለሙያዎችን እና የዘርፉን ጉዳይ የሚከታተሉ ተቋማት ስልክ ተነስቶ መረጃው እንደደረሰን እናቀረባለን።
ሲሆን ሲሆን ለእኛ ሀገር እንዲህ ያለ ክስተት ሲያጋጥም እንዲሁም ዜጎች ግርታ ውስጥ ሲገቡ ወደ ሚዲያ ወዲያው ወጥቶ ማብራሪያ መስጠት ነገሩን ግልጽ ማድረግ ይገባ ነበር።
ቴክኖሎጂው ፤ የማህበራዊ ሚዲያው በእጃችሁ ላይ ነው ምናለ ቅልጥፍ ብላችሁ ሙያዊ ማብራሪያ ለምታገለግሉት ህዝብ ብትሰጡ ?
@tikvahethiopia
🚨 #Alert
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 23 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲሆን የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 5.0 መመዝገቡን አሳውቋል።
የአሜሪካ ጃኦሎጂካል ሰርቬይ ደግሞ በሬክተር ስኬል 4.9 መለካቱን አመላክቷል።
ንዝረቱ አዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች ተሰምቷል።
@tikvahethiopia
#Lottery : የገና ስጦታ ሎተሪ ዕጣ ዛሬ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዕድል አዳራሽ መውጣቱን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አሳውቋል።
በዚህም ፦
1ኛ የዕጣ ቁጥር ➡️ 1331140 (አስር ሚሊዮን ብር)
2ኛ የዕጣ ቁጥር ➡️ 1003012 (አምስት ሚሊዮን ብር)
3ኛ የዕጣ ቁጥር ➡️ 0273783 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር)
4ኛ ዕጣ ➡️ 1975332 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)
የወጡት የዕጣ ቁጥሮች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
" ህጻኑ እና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ " - ዶክተር ደሳለኝ ተስፋዬ
በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ ወረዳ ዙቤይራ ሙሀመድሳኒ የተባለች እናት 6 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ልጅ ተገላግላለች፡፡
ህጻኑ በናዳ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና መወለዱን በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ደሳለኝ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ደሳለኝ በአሁኑ ሰዓት ህጻኑ እና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) ገልጸዋል።
ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቤቴልሄም አመኑ የተባለች እናት 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወንድ ልጅ በተደረገላት የቀዶ ህክምና በሰላም መገላገሏ ይታወሳል።
እንደ ሮችስተር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል ከ37 እና 41 ሳምንታት እርግዝና መካከል የሚወለዱ ህጻናት አማካይ ክብደታቸው 3.2 እስከ 3.4 ኪሎግራም ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው የልጆች እድገት ስታንዳርድም የሚወለዱ ህጻናት አማካይ ክብደት ከ3.2 እስከ 3.4 ኪሎግራም ነው።
@tikvahethiopia
“ ከሀገር ውስጥ ቱሪስቶች 17 ሚሊዮን 704 ሺሕ 800 ብር፣ ከውጪ ሀገር ቱሪስቶች 3 ሚሊዮን 287 ሺሕ 324 ብር ገቢ ተገኝቷል” - ሰሜን ወሎ ዞን
የልደት በዓል በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን በሰላም መከበሩን የሰሜን ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያና የላሊላ ከተማ አስተደደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ አቶ ጥላሁን አባተ በሰጡን ቃል፣ “ በዓሉ ያለምንም ችግር ነው የተከበረው ” ብለዋል።
በዓሉ ላይ ምን ያክል ቱሪስቶች ታድመው ነበር ? ምን ያህል ገቢስ ተገኘ ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ጥላሁን አባተ ፦
“ የሀገርም የውጪም ቱሪስቶች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።
የሀገር ውስጥ ቱሪስት ብዛት፦ ወንድ 564 ሺሕ 260፣ ሴት 320 ሺሕ 950፣ በድምሩ 885 ሺሕ 210 ነበሩ።
የውጪ ሀገር ቱሪስት ወንድ 312፣ ሴት 181 በድምሩ 493 ቱሪስቶች በበዓሉ ታድመዋል።
ከሀገር ውስጥ ቱሪስቶች 17 ሚሊዮን 704 ሺሕ 800 ብር፣ ከውጪ ሀገር ቱሪስቶች 3 ሚሊዮን 287 ሺሕ 324 ብር ገቢ ተገኝቷል።
በአጠቃላይ ወደ በዓለ ልደቱ ለመታደም የገባ ተሽከርካሪ ቁጥርም 531 ነበር ” ብለዋል።
አማራ ክልል የጸጥታ ችግር እንዳለበት የሚታወቅ ክልል ነው ፤ ከእቅዳችሁ እና ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የቱሪስቶች ብዛት ቀንሷል ? ስንል ላቀረብንላቸው ተጨማሪ ጥያቄ ፦
“ የሀገር ውስጥ ቱሪስት ፍሰቱን ስንመለከት አብዛኛው ሰው ለእምነት ጉዞ ስለሚያደርግ ከእቅዳችን አንጻር ሲታይ ቁጥሩ የተሳካ ነበር።
የውጪ አገር ቱሪስት ግን እንደሚታወቀው የስትራቴጂክ እቅዳችን በጣም ብዙ ነበር። ነገር ግን የውጪ ቱሪስቶች አንድን አካባቢ ለመጎብኘት ብዙ ቅድመ ሁኔታዎች ያስፈልጋሉ።
የሰላም መረጋጋትና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ይወስናሉ። ከዚህ አንጻር ሲታይ ቁጥሩ የውጪ ሀገር ቱሪስት መጠነኛ ነበር። ግን ከኮቪድ ጀምሮ ካለፉት 5፣ 6 ዓመታት ሲታይ የዘንድሮው የተሻለ ነው ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ስለበዓሉ ውሎና ፍፃሜ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የላሊበላ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንድምነው ወዳጅ በበኩላቸው፣ “ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ የተከናወነ በዓል ነው ያከበርነው ” ሲሉ ገልጸውታል።
“ በዓሉ አጠቃላይ እንደ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ኢትዮጵያዊ ትውፊቱን ባማከለ መልኩ ተከናውኗል። ወጣቶቹም ጥቅል ማህበረሰቡም በምንፈልገው መልኩ የተቃኘና የተጠቃለለ በዓል ነበር ” ነው ያሉት።
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን እድሳት ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ስንልም ጠይቀናል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-08
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ለልምድ ልውውጥ " በሚል ከተላኩበት ኖርዌይ ያልተመለሱት የፓርቲ አባላት ምን አሉ ?
🔴 " በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራም ተደርጎብኛል መመለስ የማልችልበት ውስብስብ ጉዳይ ነው የገጠመኝ " -ወ/ሮ አበበች ደቻሳ
🔵 " መመለስ የማልችልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ በማወቄ ላለመመለስ ወስኛለሁ " -ወ/ሮ ቅድስት ግርማ
የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ወ/ሮ አበበች ደቻሳ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ በመስከረም አጋማሽ ለልምድ ልውውጥ ወደ ኖርዌይ በሄዱበት እዛው መቅረታቸውንና ወደ ሀገር አለመመለሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ሁለቱ የፓርቲ አባላት ወደ ኖርዌይ ያቀኑት መስከረም 18/2017 ዓ/ም የነበረ መሆኑን እና በፖለቲካ ችግሮች ምክንያት እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ መገደዳቸውን ከሚገኙበት ሃገር ሆነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።
ከሃገር እስከወጡበት ጊዜ ድረስ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የድባጤ ወረዳ የውሃ ፣ማዕድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ሃላፊ እና በቦዴፓ የሴቶች ዘርፍ ሃላፊ የነበሩት ወ/ሮ አበበች ደቻሳ ፥ " ብዙ መስዋዕትነት ከፍያለሁ በተደጋጋሚ እኔም ባለቤቴም ለእስር ተዳርገናል አባቴም በግፈኞች ተገድሏል አለመመለሴ እርግጥ ነው ላለመመለስም ወስነናል " ብለዋል።
የመቅረት ውሳኔው የታሰበበት ሳይሆን ድንገተኛ ውሳኔ መሆኑን ጠቁመው " ስወጣ ሄጄ እቀራለሁ ብዬ አስቤበት አልነበረም ከነ ችግሩ በሃገሬ እታገላለሁ ብዬ እንጂ፣ ነገር ግን ከተመለስኩ ካሳለፍኩት በላይ የሆነ ችግር እየጠበቀኝ መሆኑን ስላረጋገጥኩ ነው የቀረሁት " ሲሉ ገልጸዋል።
" የሃገሪቱ ፖለቲካ ችግር ውስብስብ ከመሆኑም በላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው " ያሉት ወ/ሮ አበበች " በክልሉ ያለው አመራር በኢንቨስትመንት መሬት እና በማዕድን ቦታዎች ዝርፍያ ተሰማርቷል " ሲሉ ከሰዋል።
በወረዳው የማዕድን ጽ/ቤት ሃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት የታዘቡትን ሲያስታውሱ " ትልቁ ችግር ሙስና ነው ይህንን ተቃውመህ በህይወት መኖር አትችልም ይህን አዕምዬ ሊቀበል አልቻለም ብዙ ታግያለሁ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ይደርሱኝ ነበር በመጨረሻም ለእስር ተዳርጌ ነበር በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራም ተደርጎብኛል መመለስ የማልችልበት ውስብስብ ጉዳይ ነው የገጠመኝ " ብለዋል።
ከሃገር ከመውጣታቸው በፊትም ከባለቤታቸው እና ከልጆቻቸው ጋር ለእስር ተዳርገው እንደነበር ገልጸው ባለቤታቸው ብቻ በተለያዩ ጊዜያት ለ3 ወራት ያህል ለእስር ተዳርገው እንደነበር አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዉ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ በበኩላቸው ላለመመለሳቸው ምክንያት ፓርቲያዊና ሃገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እንደምክንያት ጠቅሰዋል።
" እንዳልመለስ ያደረጉኝ ድንገተኛ ምክንያቶች ቢኖሩም እዚህ ከመጣሁ በኃላ መመለስ የማልችልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ በማወቄ ላለመመለስ ወስኛለሁ " ብለዋል።
" ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል ብዬ የማምን ሰው ነኝ " ያሉት ወ/ሮ ቅድስት ፥ " ነገር ግን እያደረግናቸው ያሉ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግሎች ቆመንለታል ያልነውን ማህበረሰብ ከመገደል ፣ መፈናቀል እና ሞት አላዳነውም " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
" ምንም እንዳላየ ሆኖ መቀጠል ከአዕምሮ በላይ ነው ሃገር ውስጥ ሆኖ ይህን ማድረግ አይቻልም ለህዝቤ ድምጽ መሆን ያስፈልጋል ብዬ ስለማምን ነው ይሄን ውሳኔ የወሰንኩት " ሲሉ ከሀገር ወጥተው የቀሩበት ምክንያት አስረድተዋል።
ከዚህ ቀደም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የኢዜማ አባል ፤ አባሏ በስራ ገበታቸው ላይ አለመኖራቸው በማስረዳት " ለምን እንዳልተመለሱ የምናውቀው ነገር የለም " ማለቱ ይታወሳል።
ወ/ሮ ቅድስት በበኩላቸው " ከመቅረቴ ቀደም ብዬ ያለውን ነገር እና ላለመመለስ መወሰኔም ለፓርቲው ስራ አስፈጻሚዎች አሳውቄያለሁ ኢዜማ ውስጥ ያለው መቧደን እና መገፋፋቱ ፓርቲው እደርስበታለሁ የሚልበት ቦታ ላይ የማያደርስ በመሆኑ ፣ ይህም ለእኔ ፈታኝ መሆኑን እና የእኔ መገፋት ከመንግስት ብቻ ሳይሆን ከፓርቲውም ጭምር መሆኑን አሳውቅያለሁ " ብለዋል።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኩል ለልምድ ልውውጥ ወደ ኖርዌይ ያቀኑት የምክር ቤቱ የሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚዎች ውስጥ የሚገኙ የኢዜማ ፣ ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፣ ኦነግ እና የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ወብን) ፓርቲ አባላት የነበሩ ሲሆን #የኦነግ እና #የወብን አባላት የልምድ ልውውጡን አጠናቀው በወቅቱ ወደሃገር ተመልሰዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
🚨#ኮሬ
ታጣቂዎች አደረሱት በሚባል ጥቃት ከዘጠኝ ዓመታት በላይ የንጹሐን ግድያ ልጓም ባልተገኘለት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን አሁንም “ ንጹሐን ተገድለዋል ” ተብሏል።
ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የዞኑ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ባለፉት 48 ሰዓታት ብቻ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ” ብለዋል።
በዞኑ ኬረዳና ጀሎ በተሰኙት ቀበሌዎች አንታዮ ዦላና አድማሱ አሰፋ የተባሉ ሰዎች ታጣቂዎቹ ሰነዘሩት በተባለ ጥቃት መገደላቸውን ከቤተሰቦቻቸው መረጋገጡን ነው የገለጹት።
አቶ አንታዮ ዦላ የተገደሉት ከትላንት በስቲያ ታኀሳስ 28 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል ኬረዳ ቀበሌ መሆኑን አስረድተው፣ “ ገዳዮቹ ከጋላና ወረዳ ሻሞሌ ሽዳ ታጥቀው ወደ ኮሬ ዞን ዘልቀው ገብተው ነው ” ብለዋል።
“ በዚሁ ቀበሌ ጥቃት ከመፈጸም ተጨማሪ የቤት እንስሳትን ዘርፈዋል ” ብለው፣ “ አድማሱ አሰፋ ደግሞ ታኀሳስ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6:30 ገደማ ጄሎ ቀበሌ ተገድሏል ” ሲሉ ገልጸዋል።
“ ገዳዮቹ የጋላና ወረዳ የቡልቶ ጃልደሳ ታጣቂዎች ወደ ኮሬ ዞን ዘልቀው በመግባት ጥቃት ፈጽመው ነው ” ብለዋል።
“ ባለፉት ቀናት ጥቃት ለመሰንዘር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንደነበር ከህዝብ አስተያየት መረጃ መመልከት ተችሎ ነበር። መረጃዎቹ ከጃሎ፣ ኬረዳ፣ ዞቀሣ፣ ጋሙሌ፣ ሻሮ፣ ጎልቤ፣ ቆቦ፣ ዶርባዴ ቀበለያት ተሰባስበዋል” ነው ያሉት።
የንጹሀን ጥቃቱ እንዲቆም ለመንግስት አሳስበው እንደሆን በቅርቡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የዞኑ ሕዝብ ተወካይ አምዛዬ አወቀ (ዶ/ር)፣ በፓርላማ ቢያሳውቁም ድርጊቱ እንዳልቆመ ገልጸው ነበር።
“ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዱ ግድያ ይገለጻል፤ የአንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ” ብለው፣ “መንግስት ትኩረት ቢሰጥ ኖሮ ያ አካባቢው የሚያስቸግር አይደለም ጠባብ ቦታ ነው ገላና ሸለቆና ነጭ ሳር ፓርክ እነዚህ ሽፍቶች የሚንቀሳቀሱበት ነው ” ብለው ነበር።
ከዚህ ቀደም ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው በክልሉ ምክር ቤት የቀድሞ አማሮ ምርጫ ክልል ተወካይ አቶ ዜናነህ አዱላ በበኩላቸው፣ “ አካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በጸጥታ ችግር የወደቀ ነው ” ማለታቸው ይታወሳል።
“ በአካባቢው ላይ ከመንግስት ተቃርኖ የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ መኖሩ ሁኔታውን አባብሶታል” ብለው፣ “ ‘መንግስት ቸልተኛ ሆኗል’ የሚል ግምገማ አለን ” ሲሉ ተናግረው ነበር።
ከወራት በፊት ቃሉን የሰጠን ዞን ኮሚኒኬሽን “ ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ” ማለቱ አይዘነጋም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ቪድዮ፦ ይህ እጅግ ረጅም የነዳጅ ሰልፍ በልደት በዓል ዋዜማ አዲስ አበባ ላይ የነበረ ነው። ከሰሞኑን የነዳጅ ማደያዎች እንዲህ ነበሩ።
አንዳንዶቹ " ቤንዚን የለም !! ፤ ናፍጣ የለም !! " እያሉ ሲለጥፉ ነበር።
ዜጎች ነዳጅ ለማግኘት ረጅም ሰልፍ ተሰፍለው እየዋሉ ስራቸው ሲበደል ፤ ሲጉላሉ ከርመዋል። ዛሬ ግን የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል።
ሁሌም የወር መጨረሻ በመጣ ቁጥር ከወትሮ የተለየ ሰልፍ ፤ መጉላላት ይኖራል " የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር ነው " በሚል። የነዳጅ ቦቴዎች መንገድ ላይ ሆን ብለው ይዘገያሉ።
ከሰሞኑን " የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር ነው " በሚል አፋር ላይ በየጥሻው ውስጥ ገብተው ተደብቀው የነበሩ በርካታ ቦቴዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ ተደርገው ወደ መዳረሻቸው እንዲሄዱ ስለመደረጋቸው መነገሩ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
#ነዳጅ
ቤንዚን በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል።
ዛሬ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መወሰኑን አሳውቋል።
በዚሁ መሰረት ፦
➡ አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር
➡ አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር
➡ አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር
➡ የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር
➡ አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር
➡ አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ተወስኗል።
#ነዳጅ #ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የልደት በዓል በጥንታዊቷ ከተማ #ላሊበላ እየተከበረ ይገኛል።
Credit - Lalibela Communication
@tikvahethiopia