#ኢትዮጵያ
መደበኛ ባልሆነ ማቆያ ቦታ፣ ያሉበት ሳይገለጽ እንዲቆዩ የተደረጉ እና አስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎች እና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በተመለከተ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እና ፍትሕ ሊሰጣቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳስቧል።
ኮሚሽኑ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ሪፖርት ልኮልናል።
ከሪፖርቱ ውስጥ የተገኘ ማሳያ ፦
(የአስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎች)
🔴 አቶ መንበረ ቸኮል ምስጋናው፣ የግንባታ ባለሙያ፣ የ7 እና የ4 ዓመት ዕድሜ ያላቸው 2 ሕፃናት ልጆች አባት ሲሆኑ፣ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ “ሰፈራ” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጸጥታ አካላት ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ የተወሰዱ ሲሆን፣ ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ የማይታወቅ በመሆኑ ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ጭንቀትና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ተጋልጠው ይገኛሉ።
🔴 አቶ ዘላለም ግሩም ፍላቴ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባልና አሽከርካሪ ሲሆኑ፣ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ልዩ ስሙ “ዲቦራ ትምህርት ቤት” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጸጥታ አካላት ሰሌዳ ቁጥሩ ባልታወቀ ተሽከርካሪ ከተወሰዱ ጀምሮ፣ ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ የማይታወቅ በመሆኑ ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ጭንቀትና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ውስጥ ይገኛሉ።
(በተለያየ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ወይም ያሉበት ሳይታወቅ በተራዘመ እስር ሁኔታ ቆይተው የተለቀቁ)
➡ አቶ አማረ ግዳፍ፣ ባለ3 እግር ተሽከርካሪ በተለምዶ “ባጃጅ” በማሽከርከር ሥራ ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ “ወሰን መስቀለኛ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 6 የሲቪል ልብስ እና 1 የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ በለበሱ ሰዎች እና ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ ተወስደው፣ ላለፉት 6 ወራት ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ ቆይተው በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ አቶ ዓለማየሁ ከፈለ ተሰማ የተባሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነሐሴ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 1 በተለምዶ “ፍላሚንጎ” በሚባለው አካባቢ ሲቪል ልብስ ለብሰው መታወቂያ በያዙ 6 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተወስደው፣ በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ አቶ መቼምጌታ አንዱዓለም፣ ባለትዳርና የ2 ሕፃናት ልጆች አባት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት አካባቢ “ብስራተ ገብርኤል” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የታክሲ አገልግሎት ከሚሰጡበት አካባቢ ከነተሽከርካሪያቸው የሲቪል ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት ተወስደው፣ በተለምዶ “ራሺያ ካምፕ” ተብሎ በሚጠራው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኖሪያ ለ7 ወራት ከቆዩ በኋላ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ተለቀዋል።
➡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና የልጆች አባት የሆኑ ተጎጂ፣ ነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ገደማ ከግል የሥራ ቦታቸው ሲቪል እና የደንብ ልብስ ለብሰው ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አባላት ተይዘው፣ ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ ጦር ኃይሎች አካባቢ በተለምዶ “ራሺያ ካምፕ” ተብሎ በሚጠራው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኖሪያ እንደቆዩ አስረድተዋል። ከዚያ ቀን ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ እና የፌዴራል ፖሊስ ጣቢያዎች ቢያፈላልጓቸውም በምን ምክንያት እንደተያዙ ለማወቅ ሳይቻል፣ ለ2 ወራት ከቆዩ በኋላ ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላው ተጎጂ ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት አካባቢ ሲቪል እና የደንብ ልብስ ለብሰው ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አካላት በተለምዶ “ፓትሮል” በሚባል ተሽከርካሪ በግዳጅ ተወስደው ባልታወቀ ቦታ ከቆዩ በኋላ፣ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ ሌላ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ተጎጂ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እና ባለትዳር ሲሆኑ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ በተለምዶ “ስታዲየም” በሚባለው አካባቢ ከሚሠሩበት ቦታ ሲቪል በለበሱና ሽጉጥ በታጠቁ፣ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ በለበሱና ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አካላት ሰሌዳ ቁጥር በሌላቸው ዳለቻ ቀለም እንደሆኑ በተገለጸና በተለምዶ “ሎንግቤዝ” እና “ፓትሮል” ተብለው በሚጠሩ መኪናዎች ተጭነው ተወስደው፣ ከ6 ወራት እስር በኋላ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ በተመሳሳይ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተጎጂ ከግል የሥራ ቦታቸው የተወሰኑት ሲቪል እና ሌሎች የደንብ ልብስ በለበሱና በታጠቁ የጸጥታ አካላት መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተያዙ በኋላ፣ ዐይናቸውን በጨርቅ ተሸፍነው ተወስደው ያሉበት ሳይታወቅ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቆዩ በኋላ፣ በድጋሚ ዐይናቸውን በጨርቅ ተሸፍነው አዲስ አበባ ከተማ፣ “ኃይሌ ጋርመንት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንዲወርዱ መደረጋቸውን አስረድተዋል።
(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#AAiT
Announcement of Professional Training Programs
1. Python Programming + Data Analytics and Visualization
2. Python Programming + Artificial Intelligence
By: Addis Ababa University,
Addis Ababa Institute of Technology (AAiT), School of Electrical & Computer Engineering
Registration Deadline: October 25, 2024
Training Starts on: October 28, 2024
Online Registration Link: https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Telephone: 0940182870 / 0913574525
Email: sece.training@aait.edu.et
For more information: https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Telegram : /channel/TrainingAAiT
ትላንትና መርካቶ ሸማ ተራ እሳት አደጋ ሲከሰት እጅግ በሚያሳፍር ሁኔታ አንዳንድ ህሊና የሌላቸው ሰዎች ዝርፊያ ላይ ተሰማርተው ነበር።
በዛ ጭንቅ ሰዓት፣ ሁሉም እሳቱን ለማጥፋ ሲረባረብ እነሱ ግን የራሳቸው ሃቅ ያልሆነን የሰው ንብረት ሲዘርፉ ነበር።
ከአሳዛኙ የእሳት አደጋ በተጨማሪ ይህ የዝርፊያ ተግባር የአካባቢው ነሪዎችን አሳዝኗል።
ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ ፥ አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ ይገኛል።
በሌላ በኩል ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አሳውቋል።
የአደጋውን መንስኤ የለማጣራት ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አመልክቷል።
Photo Credit - Yeraguel Baria
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ' መርካቶ ሸማ ተራ ' ከትላንት ምሽቱ ከባድ የእሳት አደጋ በኃላ ዛሬ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።
ከቆርቆሮ እና ከኮነቴነር ቤቶች አቅራቢያ ወዳለው ' ነባር የገበያ ማዕከል (ህንጻ) ' የተዛመተው እሳት የህንጻውን አንደኛውን ክፍል ክፉኛ አውድሞታል።
እስካሁን ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ሪፖርት አልተደረገም።
በትላንት ምሽቱ የእሳት አደጋ ምንም እንኳን ይፋዊ የጉዳት መጠን ባይገለጽም የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው።
በርካቶች ብዙ የደከሙበት ንብረታቸው በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፥ " በአደጋው የደረሰውን የጉዳት መጠኑን የተመለከተ ዝርዝር ጥናት ተደርጎ ከባለሃብቶች እና ከህብረተሰቡም ጋር በመሆን በፍጥነት መልሶ የማቋቋም ስራ ይሰራል ፤ ቦታውንም ወደ ቀደመው የንግድ ተግባር እንዲመለስ የማድረግ ስራ እንሰራለን " ብሏል።
@tikvahethiopia
🔈 #የሰራተኞችድምጽ
" የምንሰራው ስራና የሚከፈለን ወርሃዊ ደመወዝ አይመጣጠንም ፤ ድካማችንን የሚመጥን ክፍያ አናገኝም " - ሰራተኞች
በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራው ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ድርጅት አንዱ በሆነ መስፍን ኢንዳትሪያል ኢንጅነሪነንግ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የመብት ጥያቄ እንዳላቸው ገለጹ።
ሰራተኞች ዛሬ ስራ በማቆም ወደ ትእምት ( ትግራይ መልሶ ግንባታ) ዋና ቢሮ በመጓዝ " የመብት ጥያቂያችን ይመለስ " ብለዋል።
ብዛታቸው ከ150 በላይ የሆኑ ሰራተኞቹ ፦
➡️ የሚሰሩት ስራና የሚከፈላቸው ወርሃዊ ደመወዝ እንደማይመጣጠን፤
➡️ በድርጅቱ በቀን አስከ 20 ሰዓታት የሚሰሩ ሰራተኞች ቢኖሩም የሚያከፈላቸው ከፍያ እጅግ አነስተኛ መሆኑ፤
➡️ ደርጅቱ አትራፊ ቢሆንም ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ፤
➡️ ከጥቅማጥቅም ፣ ያልተከፈለ ውዙፍ ደመወዝና የሰራተኛ ቅጥር ጋር የተያየዘ ጥያቄ እንዳላቸው ገልጸዋል።
" ለረጅም ጊዜ የመብት ጥያቄያችንን የሚመጥን አስቸኳይ መልስና መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።
ለሰራተኞቹ ዘግይተው መልስ የሰጡት የትእምት የሰው ሃይል አስተዳደር ተኽለወኒ ገ/መድህን ፥ " ቀጣዩ አርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ከትእምት ኢንደውመንት አመራሮች በጋራ በመሆን ጥያቄያችሁ እናደምጣለን " በማለት ሸኝተዋቸዋል።
መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪነንግ በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራ ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ካምፓኒዎች አንዱ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
የአቢሲንያ ስኩል ማኔጅመንት ሲስተም ኢ-ላይብረሪ የትምህርት እና አጋዥ መጻሕፍት ዳውንሎድ በማድረግ መጠቀም ያስችላል፡፡
የአቢሲንያ ባንክ ፌስቡክ ፔጅን ሊንኩን በመጠቀም ይቀላቀሉ፡ https://www.facebook.com/BoAeth
#BoAschoolmanagement #school #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
ምርጫ ቦርድም የክፍያ ጭማሪ አደረገ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ አድርጓል።
እስካሁን ድረስ ፦
➡️ ለሀገር አቀፍና ለክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ሰርተፊኬት ለማግኘት 100 ብር፤
➡️ ለሙሉ ዕውቅና ለሀገር አቀፍና ክልላዊ ፓርቲ 200 ብር፤
➡️ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን በጉባኤ አሻሽለው ሲያቀርቡ 30 ብር ይከፍሉ ነበር።
አሁን በተደረገው ጭማሪ ፦
🟢 ጊዜያዊ ዕውቅና ክፍያ 👉 15,000 ብር (አስራ አምስት ሺህ ብር)
🟡 የሙሉ ዕውቅና ክፍያ 👉 30,000 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር)
🔴 የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ 👉 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር) ገብቷል።
@tikvahethiopia
🔈#መርካቶ
" እኔ የመርካቶ ልጅ ነኝ፤ እዛውም ነው የምሰራው።
ዛሬ በአይኔ ያየሁት የእሳት አደጋ እጅግ አስከፊ ነው።
በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል። የአላህ ጥበቃ ሆኖ እኔ በአካባቢዬ ላይ የሰው ህይወት አልተጎዳም።
ነገር ግን በእሳት አደጋው እጅግ በጣም አዝነን እያለ ተጨማሪ ሃዘን የፈጠረብን ብዙ አለ።
አንዱ የተለያዩ አካላት ለዝርፊያ ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው።
አንዳንድ ሰው በዚህ የከፋ ጊዜ አብሮ ተጋግዞ እሳቱን ማጥፋት ሲገባው የራሱ ያልሆነን ንብረት ለመዝረፍ ሲሯሯጥ ማየት እጅግ ያሳዝናል።
ሌላው በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተከታይ ለማፍራት ሲባል ያልተባለውን በማለት፣ ያልተደረገውን ተደርጓል በማለት ' ላይክ ፣ ሼር ፣ ፎሎው ' አድርጉን እያሉ በዚህ የችግር ወቅት ያልተገባ ነገር የሚያደርጉ ሰዎችን መመልከቴ አሳስዝኖኛል።
አንዳንዶቻችን ህሊናችንን በዚህ ልክ ማጣታችን እጅግ አሳፋሪ ነው። ነገ እኛን ምን እንደሚገጥም እኮ አናውቅም።
ይህ ከባድ አደጋ እውነተኛ መንስኤው እና የጉዳቱ መጠን በፍጥነት እንዲጣራልን እንፈልጋለን።
ብዙ ለፍቶ አዳሪ ዜጋ እጅግ የደከመበት ፣ የለፋበት ንብረቱ በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል። " - ሃሚ (መርካቶ)
@tikvahethiopia
#Update
ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ በመርካቶ ሸማ ተራ የተነሳውን እሳት እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም።
ርብርቡ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ተሰምቷል።
የአዲስ አበባ እሣትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው ምን አሉ ?
- የእሳት አደጋው የተከሰተው 1 ሰዓት ገደማ ነው።
- እሳት መነሳቱን በሰማን ጊዜ አብዛኛዎቹ የእሳት ማጥፊያ መኪናዎች ርብርብ እንዲያደርጉ አሰማርተናል።
- መኪናዎች በወቅቱ ነበር የደረሱት፤ ከደረሱ በኃላ የእሳቱ ባህሪና ሁኔታ ሲታይ ለሌሎች አጋዥ አካላት ፦
° አየር መንገድ
° ፌዴራል ፖሊስ
° ሌሎች ከተማ ውስጥ ያሉ ውሃ አቅራቢ ተቋማት በሙሉ እንዲረባረቡ ተደርጎ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት እያደረግን ነው።
- ቦታው በጣም አስቸጋሪ ነው።
- በሁሉም አቅጣጫ በኩል መኪና ገብቶ እሳቱን ለማጥፋት በጣም ፈትኖናል። በተለይ በዙሪያ የሚቀመጡ እቃዎች ቶሎ ተገብቶ የእሳቱን መሰረት እንዳይመታ አድርጓል።
- አካባቢው በቆርቆሮ የተያያዘ ነው። መንገዱ በጣም ጠባብ ነው። ገብተን ለማጥፋት ተቸግረናል።
- በአጋጣሚ ባለሱቆች፣ ነጋዴዎች ዘግተው ወጥተው ነበር። የቆሙ መኪኖችንም ለማስነሳት ችግር ሆኖብን ነበር።
- አሁን ላይ ከቅድሙ እየተሻሻለ ነው። የመቀነስ እና የመጥፋት አዝማሚያ አለው። በተለይ ከዚህ እንዳይሰፋ ወደታች ከወረደ በጣም ሰፊ ቦታ ነው ያለው ቆርቆሮ በቆርቆሮ እሱ ጋር እንዳይደርስ ከበን ለመያዝ ሞክረናል።
- አጋዦች ከመጡ በኃላ እሳቱ ባህሪው እንዳይሰፋ ተሞክሯል። አሁንም ህብረተሰቡ አግዞን ለማጥፋት እየሞከርን ነው። እናጠፋዋለን ብለን እናምናለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ከኤ ኤም ኤን ነው የወሰደው።
@tikvahethiopia
#Update
መርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ እስካሁን አልቆመም።
እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም።
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነው " ብለዋል።
አሁን ላይ " በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia
#Update በመርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው እሳት እስካሁን ሊጠፋ አልቻለም።
እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ከእሳቱ መፋፋምና ከቦታው አለመመቸት የተነሳ ሁኔታውን እንዳከበደው በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል።
እሳቱ ያልደረሰባቸው ሱቆች እቃቸውን ከስፍራው እያሸሹ ናቸው።
እስካሁን የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቀም በርከት ያሉ ሱቆች ግን እየተቃጠሉ ናቸው።
ተጨማሪ መረጀዎችን እንልክላችኋለን።
@tikvahethiopia
#ደመወዝ : የደመወዝ ጭማሪ ተፈቅዶና በጀቱም ጸድቆ ክፍያው ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዛሬ አሳውቋል።
ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደው በጀት፣ የአፈጻጸም መመሪያውንና የክፍያ ትዕዛዙን ለ12ቱ ክልሎች፣ ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና ለፌደራል ተቋማት ዛሬ መተላለፉም ተገልጿል።
(ከጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ይፋዊ የደመወዝ ስኬል ከላይ ተያይዟል)
#CivilServiceCommission
#MekuriaHaile
@tikvahethiopia
#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ፤ " በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጸል " ብሏል።
ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia
የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።
የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
የመቁረጫ ነጥቡ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
ሴጅ ማሰልጠኛ !
የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principles and Practices of Accounting) የ5 ወር የቅዳሜ እና እሑድ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝጸ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ 👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#Infinix_TV
አለም አቀፉ የቲቪ እና የሞባይል ስልኮች ሲስተም አምራች ከሆነው ጎግል አንድሮይድ ጋር ይፋዊ ስምምነት ያለው የኢንፊኒክስ X5 ስማርት ቲቪ ከሌሎች ስማርት ቲቪዎች በተለየ መልኩ ተጨማሪ አፕሊኬሽኖች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተለየ መልኩ ማግኘት እና ማስጠቀም ያስችላል፡፡
@Infinix_Et | infinixet?_t=8qe2yVJoUeU&_r=1">@Infinixet
#InfinixTVX5 #Infinix #ElevateYourSpace #Poweredbyandriod11 #tvx5
“ አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ፣ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው? ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር።
የመምህራን የስልጠና ክፍያ እጅግ አነስተኛ መሆን ከኑሮ ውደነት ጋር ተያይዞ ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጡት የነበረውን የሙያ ስልጠና አለመስጠታቸው የትምህርት ጥራት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ እያደረገ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠየቀ።
ከማኀበሩ የተሰነዘሩ ቅሬታዎች ምንድን ናቸው ?
“ ከትምህርት ሥርዓት አንጻር በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ጥራት ችግር ብቻ ልንለው አንችልም። የትምህርት ቀውስ ነው። ቀውስ ውስጥ ገብተናል። ወደ መምህራን ችግሩን የመግፋት ነገር ይታያል። ይሄ ትክክል አይደለም።
ሲጀመር የመምህርት ስልጠና ዋጋ አልተሰጠውም። ለምላሌ ፦ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እጩ መምህራን ከተወሰኑ ኮሌጆች ውጪ 450 ብር ተሰጥቷቸው ውጪ ሆነው እንዲማሩ የሚደረጉት።
አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው ? ችግሩ እዚያ ጋ ነው የሚጀምረው።
እጩ መምህራን ወደ ኮሌጅ ውስጥ ሲገቡ 450 ብር ይከፈላቸዋል። ፍላጎታቸውን ስለማይሟላ ትምህርት ላይ ትኩረት ሳያደርጉ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ይንቀሳቀሳሉ። ይሄ የመምህርነትን ሙያ ጥራቱን ቀንሶታል። ስለዚህ ጉዳዩ ሊታረብበት ይገባል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ጥናት አጥንቷል። በዚያ መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል።
በሌላ በኩል ፥ ወደ መምህርነት ሙያ ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንሲ ተብለው እነዚህ የመቐለ ፣ ባሕር ዳር፣ የአዲስ አበባ፣ ጅማና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንን የሚያሰለጥኑ ነበሩ ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች።
ነገር ግን ላለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ምንም አይነት ተማሪ ወደ መምህርነት ሙያ እንዲገባ እያሰለጠኑ አይደለም።
ይሄ ደግሞ በቀጣይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችንን በድጎማ መምህር ልናስይዝ አይደለም ወይ ! ይሄ ወዴት እየሄደ ነው ?
በተያያዘ፣ የመፅሐፍት ስርጭት ችግሮች አሉ። ችግር መኖር ብቻ ሳንሆን አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በአንድ ላይ ኮምባይን የሆኑ ትምህርት ቤቶች አሉ።
ለምላሌ ፦ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባይሎጂ አንድ ላይ ናቸው። በአንድ መምህር ነው የሚሰጡት። ይህም መምህራን ኬሚስትሪውን ፓርት ያስተምሩና ፊዚክስና ባይሎጂው የተመረቁበት ስለማይሆን ለማስተማር እየተቸገሩ ነው።
በሌሎች የትምህርት አይነቶችም ተመሳሳይ ችግር አለ። መምህር ያልተዘጋጀባቸው ሥርዓተ ትምህርቶች አሉ። የትምህርት ጥራቱን እየጎዳው ያለው አንዱ ችግር ይሄ ነው። አጠቃላይ ትምህርቱ ሴክተሩ በቂ ትኩረት አላገኘም። በቂ ፋይናንስ እየተመደበለት አይደለምና ሊመደብለት ይገባል።
መምህራንም የተለያዬ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሲፈጠሩ መብታቸውን ለማስከበር ወደ ሕግ ተቋማት ስለሚሄዱ የትምህርት ጊዜ ይዘጋል። ይሄ ደግሞ የትምህርት ጥራት ላይ ችግር አምጥቷል። ”
እነዚህ ቅሬታዎች የትምህርት ሚኒስቴር በተገኘበት መድረክ እንደቀረቡ ማኀበርሩ ገልጾልናል።
የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ያሳሰበው ማኀበሩ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በተነሱት ቅሬታዎች ዙሪያ መፍትሄ ለማምጣት አሳይመንት ይዞ እንደሄደ አመላክቷል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ኦርቶዶክስተዋሕዶ
" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው
የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን ጀምሯል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባኤውን መጀመረ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከመልዕክታቸው ፦
" የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡
ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡
በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክክል መምራት ይጠበቅበታል፡፡
ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡
እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡
ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅርና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡
ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡
ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡
በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት ? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡
ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡
በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ "
(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
በርካታ ቦታዎች በሊዝ ጨረታ እንዲሸጡ ቀረቡ።
አዲስ አበባ ውስጥ 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ለሊዝ ጨረታ መቅረቡ ተሰምቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት ለሊዝ ጨረታ እንደቀረበ አሳውቋል።
የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉ ነው የተሰማው።
ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታ የቀረቡ መሬቶች መኖራቸው ተነግሯል።
ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ 4ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ ነው።
143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት / ቦታ ለሊዝ ጨረታ ሲቀርብ በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ቢሮው መግለፁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃ ፦
🔴 ለአንድ የጨረታ ሰነድ የሚከፈለው የማይመለስ ብር 2,300 ብር ነው ተብሏል።
🔴 የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 08/2017ዓ.ም እስከ ጥቀምት 21/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በ (2merkato.com link :- https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) ላይ ነው መግዛት የሚቻለው።
🔴 ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ እንዳለባቸው ተገልጿል።
🔴 አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል ተብሏል።
የጨረታ ቁጥር እና የቦታዎቹን ኮድ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች በዚህ ማግኘት ይቻላል : https://www.aalb.gov.et/blogs/detail/72
@tikvahethiopia
#Infinix_TV
አዲሱ ኢንፊኒክስ TV X5 ከጥግ እስከ ጥግ ያለምንም የስክሪን ገደብ እየተመለከቱ እስኪመስሎት ድረስ ፍሬም አልባ ወይም Bezel Less ተደርጎ ተመርቷል ይህም በቴሌቭዥኖት የሚያዩት ምስልን ከዕውነታ መለየት እሰኪያቅት ድረስ ልዩ ያደርገዋል፡፡
@Infinix_Et | infinixet?_t=8qe2yVJoUeU&_r=1">@Infinixet
#InfinixTVX5 #Infinix #ElevateYourSpace #Perfectview #tvx5
#BRICS+
16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሩሲያ ይጀመራል።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ለመሳተፍ ካዛን ከተማ ገብተዋል።
ከኢትዮጵያ መሪ በተጨማሪ ፥
- የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን
- የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ
- የደቡብ አፍሪካው ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሩስያ፣ ካዛን ገብተዋል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እንዲሁም የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ፣ ሌሎችም መሪዎች እና የሀገራት ተወካዮች ወደ ሩስያ እያቀኑ ይገኛሉ።
Video Credit - RT
@tikvahethiopia
#ሶማሌክልል
" መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ ሰዎች በሌሉበት ምክክሩ የተሳካ ይሆናል የሚል ግምት የለንም "- ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሶማሌ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር አጀንዳ የመሰብሰብ የምክክር ምዕራፍ እያደረገ ነው።
ከባለድርሻ አካላት መካከል የፓለቲካ ፓርቲዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ በውይይት መድረኩ የተገኘው ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።
ስለውይይቱን ሂደት፣ የኮሚሽኑን አካታችነት፣ የታጠቁ ኃይሎች፣ የባሕር በርን በተመለከተ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ኢሴ ባናሃጂ አቡቦከር ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ?
" የኢትዮጵያዊያን ግጭትን የምናስወግድበት የራሳችን ባህሎች አሉን። ባህሎቻችንን ባለመከተል በአገራችን ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ስለሆነ እነዚህን ችግሮች ይቀርፋል ተብሎ ነው መድረኩ የተዘጋጀው።
በመድረኩ የሶማሌ ህዝብን ወክለን መጠየቅ ያለብንን ነገር እየተወያዬን ነው።
(ለምሳሌ ህዝቡ ከዚህ በፊት በነበሩት መንግስታት የደረሰበት በደል፤ ቅሬታ፣ ቁስል አለው)፤ በቅድሚያ ህዝቡ ያለበት ቁስል ይታከም። ብዙ አጀንዳዎች አሉ።
ከአካታችነት አንጻር እኛ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ አገራዊ ውይይቱ የበለጠ ውጤታማ ይሆናል ብለን የምንጠብቀው በመድረኩ ያልተካተቱ ሰዎች ቢካተቱበት ነው።
መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ ሰዎች በሌሉበት ምክክሩ ሰክሰስፉል ይሆናል የሚል ግምት የለንም።
እነርሱ እንዲካተቱ ነው እንደ ፓለቲካ ፓርቲ ደጋግመን እየጠየቅን ያለነው። መድረኩ ለማንም የሚጠቅም እንጂ ማንም የሚከስርበት አይደለም።
መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ አካላትም ወደ መድረኩ መጥተው ሀሳባቸውን አቅርበው በሚያግባባን ሀሳብ እንድንግባባ፣ በማያግባባ ሀሳብ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ተሰብስቦ ሪፈረንደም እንዲያደርግ ነው አስተያየት የምንሰጠው " ብለዋል።
በመድረኩ የተዳሰሱ ጉዳዮችን በተመለከተም፣ " የፓለቲካ ፓርቲዎች እንደ ጥያቄ ያቀረቡት አጀንዳ፣ ለምላሌ የኛ ፓርቲ፣ አሁንም አገራችን እየተመራችበት ያለውን ፌደራሊዝም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ሌላው የኢትዮጵያ ባንዲራን በተመለከተ ነው። ስለኢትዮጵያ ባንዲራ የኛ ፓርቲ ያለው አመለካከት ባንዲራው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ አይወክልም የሚል ነው " ብለዋል።
" ስለዚህ አሁን ያለው ባንዲራ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ አንድ ላይ በመሆን ሁሉንም የሚወክል ምልክት ተደርጎበት ባንዲራ ላይ ለውጥ እንዲደረግ የሚል አስተያየት ነው ያቀረብነው " ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር ወደብ በተመለከተ ተጠይቀው ባደረጉት ገለጻ፣ " እንደ ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ኢትዮጵያ የባሕር ወደብ እንድታገኝ በጣም እንፈልጋለን " ብለዋል።
" ግን እንደ ፓርቲነት ይሄን ባሕር የምንፈልገው ከዚህ በፊት የባሕር በር የሌላቸው ብዙ የአፍሪካ አገሮች ባሕር ያገኙበትን መንገድ ተከትለን ኢንተርናሽናል ሕግ በሚፈቅደው ሁኔታ እንዲሆን ነው " ሲሉ አክለዋል።
ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር ባደረገችው የባሕር በር ሥምምነት ክልሉ ያደረበት ስጋት አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው በምላሻቸው፣ " አዎ። ኢትዮጵያ መንግስት ከሱማሌላንድ ጋር ያደረገው ሥምምነት እኛ ላይ አንዳንድ ስጋት ፈጥሮብናል " ነው ያሉት።
" ባሕር ያልነበራቸው አገሮች ከጎረቤት አገሮች ጋር ኢንተርናሽናል ሕግን መሠረት ባደረገ መንገድ ተፈራርመው ባሕር እየተጠቀሙ ነው። የነርሱን ልምድ በተከተለ መንገድ የባሕር በር ብናገኝ ፍላጎታችን ነው " ብለዋል።
የኦጋዴን ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ከሀገራዊ ምክክሩ እንዳገለለ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀ ሲሆን፣ ፓርቲው በዝርዝር ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት ፓርቲው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለጊዜው አልተሳካም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
" እዚህ ላይ ባይገታ እሳቱ ሰፊ አካባቢዎች ላይ ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ሃብትም ይወድም ነበር " - አቶ ፍቅሬ ግዛው
በመርካቶ ሸማ ተራ የደረሰው ውድመት አሳዛኝ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው አሁናዊ ሁኔታውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኮሚሽነር ፍቅሬ ፤ " አሁን ላይ እሳቱን በቁጥጥራችን ስር አድርገናል ፤ የማጥፋትና የመልቀም ስራ ነው የሚቀረን " ብለዋል።
" እጅግ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ እዚህ ላይ ባይገታ በጣም ብዙ ቦታ ፣ ሰፊ አካባቢዎች ላይ እሳቱ ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ከዚህ የበለጠ ሃብትም ይወድም ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።
" የአካባቢው አስቸጋሪትነት እሳቱን ለመቆጣጠር ረጅም ሰዓታት ወስዷል " ያሉት ኮሚሽነሩ " ከዚህ በኃላ ብዙ ጉዳት ያደርሳል ብለን አናስብም፤ ተቆጣጥረነዋል ማለት ይቻላል " ብለዋል።
" እሳቱ ዳግም እንዳይቀጥል ቦታውን አዳሩን በሙሉ ተቆጣጥሮ ቅሪት ነገሮች ካሉ እነሱን እያጠፋን እንቀጥላለን ፤ ህብረተሰቡ እሳት ሊያቀጣጥሉ የሚችሉ ነገሮችን ያስወግድ " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራው ካሉ ነዋሪዎች በደረሰው መልዕክት በእሳቱ በርካታ ንብረት መውደሙን ፣ ከቆርቆሮ ቤቶቹ ወጥቶ አጠገብ ያለ ህንጻ ተያይዞ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን፣ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ባይጠፋም ከቅድሙ አንጻር ሲታይ እሳቱ የከፋ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia
#Update
“ አደጋውን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ” - አቶ ንጋቱ ማሞ
መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ መከሰቱን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ከኮሚሽኑ ቃላቸውን የሰጡትን አቶ ንጋቱ ማሞ፣“ አደጋውን ለመቆጣጠር እርብርብ እየተደረገ ነው ” ብለዋል።
“ ከመሸ ነው ጥሪ የመጣው። ጥሪው እንደመጣ በአቅራቢያው ካሉ የአዲስ ከተማ፣ አራዳ ክፍለ ከተሞች ልከን ነበር ” ብለዋል።
“ ነገር ግን በእነርሱ የሚሸፈን ስላልሆነ ከሁሉም ቅርንጫፍ ጣቢያ የአደጋ መቆጣጠር ማሽነሪዎች፣ አደጋ ጊዜ ሠራተኞች፣ አምቡባንሶች፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች፣ አመራሮች ጭምር ቦታው ላይ ሆነው አመራር እየሰጡ ነው እሳቱን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ” ሲሉ አክለዋል።
“ የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች እሳቱ ወደተነሳበህ ቦታ ላይ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ቦታው ትንሽ አስቸጋሪ አድርጎታል ” ያሉት አቶ ንጋቱ፣ “ ዞሮ ዞሮ ርብርብ እየተደገ ነው ” ብለዋል።
“ በዚህ ሂደት የጸጥታ ኃይሎች የአካባቢው ማህበረሰብ አሉ። አደጋውን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
ያሉትን ሂደቶች እንደሚያደርሱን የገለጹ ሲሆን፣ መረጃው እንደደረሰን የምናጋራ ይሆናል።
ቪድዮ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ እስካሁን አልጠፋም ፤ ሰው ንብረት እያሸሸ ነው " - በስፍራው የሚገኙ ሰዎች
በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
እሳቱ ከተነሳ በርከታ ደቂቃዎች ቢቆጠሩም እስካሁን መቆጣጠር እንዳልተቻለ በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ገልጸዋል።
" እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ በስፍራው እሳት አደጋዎች ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ምንም ሊጠፋ አልቻለም። በስፍራው ላሉ የአደጋ ሰራተኞች ተጨማሪ ቦቴና እገዛ ያስፈልጋል ፤ በውሃ ብቻም የሚሆን አይደለም " ብለዋል።
" በአካባቢው ያሉ እሳቱ ያልደረሰባቸው ሰዎች ንብረታቸውን እያሸሹ ይገኛሉ " ሲሉም አክለዋል።
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
መልካም ሰኞ! መልካም ሳምንት!🙌
💫ከዳር እስከ ዳር በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢንተርኔት! እንገናኝ!✨ የተመቸንን ሼር እናድርግ!👍ከወደድነው ጋር እንደልብ እንገናኝ!
አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!
የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።
የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !
🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2
° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 እና ከዚያ በታች፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 137 እና ከዚያ በታች፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤
🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦
° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 142 እና ከዚያ በላይ፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 እና እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በላይ፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤
🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦
° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 179 እና ከዚያ በላይ፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 167 እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 170 እና እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤
⬇️
የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !
🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2
° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በታች፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤
🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦
° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 140 ከዚያ በላይ፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 136 እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤
🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦
° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 172 ከዚያ በላይ፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 164 እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 165 እና እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 160 እና ከዚያ በላይ፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤
#TikvahEthiopia🇪🇹
@tikvahethiopia
#AddisAbaba #Education
“ በሂሳብና እንግሊዘኛ መፅሐፍት ላይ እጥረት በመታየቱ ተጨማሪ ህትመት እየተካሄደ ነው ” - አ/አ ትምህርት ቢሮ
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት መፅሐፍ ማሳተም ላይ እንደ አገር በተለያዩ ትምህርት ቢሮዎች ክፍተቶች እንዳሉ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት በ2017 የትምህርት ዘመን መፅሐፍትን አሳትሞ ለተማሪዎች ማዳረስ ተቻለ ? ሲል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥያቄ አቅርቧል።
የቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሰጡት ቃል፣ “ በተወሰኑ ትምህርቶች ላይ፤ ሂሳብና እንግሊዘኛ መፅሐፍት እጥረት በመታየቱ ምክንያት ተጨማሪ ህትመት እየተካሄደ ነው። ሪዘርቭም እያደረግን እንገኛለን ” ሲሉ ተናግረዋል።
የመፅሐፍት እጥረቱ በምን ደረጃ ነው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረባቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “ ይህንን ሬሽዎ በተለይ ከግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ላይ ያለ ችግር ነው ” ብለዋል።
“ እነርሱም መፅሐፉን ወስዶ ለማሰራጨት ፍላጎት ማጣት፣ ይሄ ደግሞ የራሳቸው መፅሐጽት አትመው ለመሸጥ ከሚመነጭ ነገር ስለሆነ እሱ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እየወሰድን ትምህርት ቤቶች ወስደው ለተማሪዎቻቸው ተደራሽ እንዲያደርጉ አድርገናል ” ነው ያሉት።
“ ከሁለተኛ ደረጃና ቅድመ አንደኛ ደረጃ በስተቀር ለሁሉም አንድ ለአንድ ተዳርሷል ” ሲሉም ተናግረዋል።
“ ለሁለተኛ ደረጃም ትምህርት ሚኒስቴር አሳትሞ ሰሞኑን ባስገባው መሠረት ለሁሉም ተማሪዎች ማዳረስ ተችሏል" ያሉት ኃላፊው፣ " ባለፉት ሁለት ዓመታት በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተማሪዎቻችን ጋር ተደራሽ ለማድረግ ተሞክሯል” ብለዋል።
በሌላ በኩል፣ ከተማሪዎች ምገባ ጋር በተያያዘ መጋቢ እናቶች ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ የሚከፈላቸው ገንዘብ አነስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ።
ይህንኑ በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ የጠየቅናቸው ዘላለም (ዶ/ር)፣ “ በተማሪ 22 ብር የነበረው በዚህ ዓመት ወደ 32 ብር አሳድጎላቸዋል። ስለዚህ ያ ጥያቄ ተመልሷል ማለት ነው ” ብለዋል።
“ በቀን 800 ሺሕ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ ይመገባሉ ” ሲሉ ተናግረዋል።
በተያያዘም በትምህርት ቤት አካባቢዎች ያሉ ሱስን የሚያበረታቱ ቤቶች እንዳሉ፣ ይህም ተማሪዎችን ከዓላማቸው የሚያደናቅፍ ከመሆኑ አንጻር በቂ ትኩረት ተሰጥቷል? ሲልም ቲክቫህ ጥያቄ አቅርቧል።
ዘላለም (ዶ/ር) በምላሻቸው፣ “ትክክል ነው። የተማሪዎችን ሀሳብ፣ ልቦና የሚሰርቁ ጉዳዮች በትምህርት ቤት አካባቢዎች እንዳይኖሩ ባለፉት ዓመታት ጠንካራ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።
“ ከ3000 በላይ የሚደርሱ የተለያዩ መማር ማስተማር ሂደቱን ሊያውኩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ እርጃ ተወስዷል ” ብለው፣ “ አሁንም እንደዛ አይነት ፍላጎቶች በትምህርት ቤቶች ብቅ ብቅ እንዳይሉ መልሶ ጠንካራ እርምጃና ክትትል ያስፈልጋል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Infinix_TV
ኢንፊኒክስ X5 ስማርት ቴሌቪዥን ከፍተኛ የምስል ጥራት ላይ ብቻ ሳይሆን ከምስሉ ጋር የሚስማማ የድምፅ ቴክኖሎጂን ቴሌቭዥኖቹ ላይ አካቷል፡፡ 20 ዋት ስፒከሮች በዶልቢ የድምፅ ቴክኖሊጂ ታጅበው እይታዎትን ሙሉ ያደርጉታል፡፡
@Infinix_Et | infinixet?_t=8qe2yVJoUeU&_r=1">@Infinixet
#InfinixTVX5 #Infinix #ElevateYourSpace #Perfectsound #tvx5