#ረቂቅአዋጅ
የከተማ መሬትን በድርድር በሊዝ ማስተላለፍ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው።
የከተማ መሬትን ከጨረታ እና ከምደባ በተጨማሪ #በድርድር በሊዝ ማስተላለፍ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ሊቀርብ መሆኑን ' ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ' አስነብቧል።
አዲሱ የአዋጅ ረቂቅ፤ ከተሞች በምደባ ለማቅረብ ካዘጋጁት መሬት መጠን ውስጥ፤ ቢያንስ 20 በመቶውን ለቤት ግንባታ አገልግሎት መዋል እንዳለባቸው ግዴታ ይጥላል።
" የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ " እንደወጣ የተገለጸው ይህ አዋጅ፤ ነገ በሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እንዲቀርብ አጀንዳ ተይዞለታል።
ረቂቅ አዋጁ " መሬትን በድርድር በሊዝ ለማስተላለፍ " ምን ይላል ?
➡️ ረቂቅ አዋጁ መሬትን በድርድር በሊዝ ለማስተላለፍ የሚፈቅደው ድንጋጌ ይገኝበታል።
➡️ 13 ዓመት ያስቆጠረው ነባሩ አዋጁ፤ የከተማ ቦታ በሊዝ እንዲያዝ የሚፈቀደው በጨረታ ወይም በምደባ ስልት ብቻ ነበር።
➡️ በአዲሱ አዋጅ የተካተተው ' የድርድር ' ስልት፤ በጨረታ እና በምደባ አግባብ ለተጠቃሚ ሊተላለፉ በማይችሉ የከተማ መሬቶች ላይ፤ አንድ አልሚ " ለተለዩ ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው አገልግሎቶች " መሬት በሊዝ ይዞ ማልማት የሚፈቀድበት ነው።
➡️ ይህ ተግባራዊ የሚደረገው " አግባብ ያለው አካል " ከአልሚዎች ጋር በሚያስቀምጠው " የልማት እቅድ መሰረት " እና " ከአልሚው ጋር በመደራደር " ነው።
➡️ የከተማ መሬት በድርድር ሊተላለፍ የሚችለው " ሀገራዊ እና ክልላዊ የከተማ ልማት ስፓሻል ፕላንን " መሰረት በማድረግ ነው ይላል ረቂቅ አዋጁ።
➡️ በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ ለሚቀርቡ የልማት ጥያቄዎች፤ መሬት በድርድር አግባብ ሊተላለፍ እንደሚችል በአዲሱ አዋጅ ተደንጓል።
➡️ በፌደራል መንግስት ለሚተዳደሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለከፍተኛ የትምህርት እና የጤና ተቋማት እንዲሁም ለምርምር ዘርፍ ፕሮጀክቶች የከተማ መሬት በድርድር ሊተላለፍ እንደሚችል ተዘርዝሯል።
➡️ የአገልግሎት ዘርፉን የሚደግፉ ባለኮከብ ሆቴሎች እና ለቱሪስት ልማት ለሚውሉ ሪዞርቶችም የሚቀርቡ የመሬት ጥያቄዎች በድርድር አሰራር ሊስተናገዱ ይችላሉ።
➡️ በግሉ ዘርፍ አሊያም በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በሽርክና ሊለሙ የሚችሉ የከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶችም፤ በዚሁ የመሬት አሰጣጥ አግባብ እንደሚስተናገዱ በአዋጁ ላይ ሰፍሯል።
➡️ ለሪል ስቴት ወይም ለቤት ልማት የሚቀርቡ የመሬት ጥያቄዎች፣ የግዙፍ የገበያ ማዕከላት (ሞል) ፕሮጀክቶች፣ ትላልቅ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች እና ማከፈፋያዎች፣ ለዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ህንጻ ግንባታዎች የሚውሉ ቦታዎች፤ በተመሳሳይ መልኩ በድርድር ማግኘት እንደሚቻልም ተመላክቷል።
➡️ በድርድር አግባብ የሚስተናገዱ ፕሮጀክቶች " የሚመጣዉ ልማት ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት፤ ለልማት በተመረጠው ቦታ ነባር ተጠቃሚ የሆኑ ባለይዞታዎች መስተንግዶና ተጠቃሚነት፣ በዙሪያ ባሉ ማህበረሰቦች ተጠቃሚነትና ጉዳት ቅነሳ እንዲሁም የመሰረተ ልማት አቅርቦት ድርሻ " ከግምት ውስጥ እንደሚገባ የአዋጅ ረቂቁ አትቷል።
➡️ የከተማ ቦታ በድርድር አግባብ እንዲተላለፍ የሚደረገው፤ በክልሎች፣ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ አስተዳደሮች " ካቢኔ ሲወሰን ብቻ " ነው።
➡️ መሬት በድርድር የማስተላለፊያ ዋጋ፤ ከአካባቢው አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ በታች መሆን እንደሌለበትም በአዲሱ አዋጅ ተደንግጓል።
በምደባ ስለሚሰጥ የከተማ መሬትስ ምን ይላል ?
🔴 አዲሱ ድንጋጌ ' ከተሞች በምደባ ለማቅረብ ካዘጋጁት የመሬት መጠን " ውስጥ " ቢያንስ 20 በመቶ የሚሆነውን " ለቤት ግንባታ አገልግሎት መዋል እንዳለባቸው ግዴታ ይጥላል።
🔴 በአንድ ከተማ በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር፣ በጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም ወይም በተናጠል የከተማ መሬትን በምደባ ተጠቃሚ የሆነ ግለሰብ፤ በዚያው ከተማ " ለሁለተኛ ጊዜ በምደባ ተጠቃሚ እንዳይሆን " የሚያግድ አዲስ ድንጋጌም ተካቷል።
🔴 በአዲሱ አዋጅ፤ መሬት በጨረታ የሚያሸነፉ ግለሰቦች ለሚያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች ላይ ማሻሻያ ተደርጎበታል። እስካሁን በስራ ላይ ባለው የሊዝ አዋጅ፤ አንድ ተጫራች የመሬት ጨረታ አሸናፊ የሚሆነው፤ ባቀረበው የጨረታ ዋጋ እና የቅድመ ክፍያ መጠን ላይ ተመስርቶ በሚደረግ ስሌት ከፍተኛውን ነጥብ ሲያገኝ ነው። በአዋጅ ረቂቁ ላይ ይህ ተቀይሮ የሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች የሚለዩት፤ ከጨረታ ዋጋ እና የቅድሚያ ክፍያ በተጨማሪ የሊዝ ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ ተሰልቶ በሚገኘው የድምር ውጤት ነው። የጨረታ ዋጋ 65 በመቶ፣ የቅድሚያ ክፍያ 20 በመቶ እና የሊዝ ክፍያ ማጠናቀቂያ 15 በመቶ ነጥብ ይኖራቸዋል።
ተጨማሪ መረጃ ፦
🔵 አዲሱ አዋጅ የሊዝ መነሻ ዋጋ የሚከለስበትን ጊዜ ከ2 ዓመት ወደ 3 ዓመት ከፍ አድርጎታል።
NB. " የሊዝ መነሻ ዋጋ " ማለት ዋና ዋና የመሰረተ-ልማት አውታሮች የመዘርጊያ ወጪን፣ ነባር ግንባታዎችና ንብረቶችን ለማንሳት የሚያስፈልገውን ወጪና ለልማት ተነሺዎች የሚከፈል ካሳአን እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን መስፈርቶች ታሳቢ ያደረገ የመሬት ዝቅተኛ ዋጋ ነው።
🔵 ረቂቁ የመሸጋገሪያ ድንጋጌም ያያዘ ሲሆን አዋጁ ከመውጣቱ በፊት አግባብ ላለው አካል ለቀረቡ የከተማ መሬት ጥያቄዎች የሚሆን አንቀጽ አስቀምጧል። እነዚህ ጥያቄዎች አዋጁ ከጸናበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ወራት ድረስ፤ በነባሩ አዋጅ እና አዋጁን መሰረት አድርገው በወጡ ደንብ እና መመሪያዎች ውሳኔ የሚያገኙ እንደሚሆን ገልጿል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ ' ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ' ድረገጽ ነው።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
#EthiopianInstitutionoftheOmbudsman
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ስለ 1997 ተመዝጋቢዎች ምን አለ ?
" ለ20 ዓመታት ያህል ' ቤት ይደርሰናል ' ብለው እየጠበቁ ቢሆንም መንግሥት ምላሽ አልሰጠንም ያሉ ቢያንስ 67 ሰዎችን አቤቱታ ተቀለን እየመረመርን ነው።
' በ1997 ተመዝግበን ቤት ሳይደርሰን ለሌሎች ተሰጥቷል ' ፤ በሚል ተደራጅተው ጠይቀዋል፣ እኛም ጥያቄ አቅርበናል፡፡ ነገር ግን የከተማ አስተዳደሩ እስካሁን መልስ አልሰጠንም።
መልስ የማይሰጠን ከሆነ ለረዥም ጊዜ ጠብቀው ምላሽ ያልተሰጣቸውን ሰዎች አቤቱታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ የመጨረሻ ዕልባት እንዲያገኝ እናደርጋለን። "
ይህ ቃል ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በድሬደዋ እና ሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን መካከል አሁን በተከሰተ የሰደድ እሳት ምክንያት ለግዜው የባቡር እንቅስቃሴ መቆሙን ኢንጂነር ታከለ ኡማ አሳውቀዋል።
" እሳቱን ለመቆጣጠር እና አገልግሎቱን ለማስጀመር የድሬደዋ የእሳት አደጋ እና የሽንሌ ዞን ሀላፊዎች ከጣቢያው ሰራተኞች ጋር በመሆን ባደረጉት ርብርብ እሳቱን ማጥፋት ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ
" የከንቲባዋ ቃል አሳዝኖናል " - የ97 ተመዝጋቢዎች
" የ1997 ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች 20 አመት ሙሉ የጠበቅነዉን ተስፋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ' 97 ሰጥተን ጨርሰናል ' ማለታቸዉ በጣም አሳዝኖናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ቁጠባችንን በአግባቡ እየቆጠብን የነበርን በሺዎች የምንቆጠር ዜጎች አለን " ብለዋል።
" እኛም ዜጎች ነን በኪራይ ቤት እድሜችን አለቀ " ሲሉ አክለዋል።
ነዋሪዎቹ ፥ " ለሕዝብ ዕንባ ጠበቂ ተቋም ደብዳቤ አስገብተናል አዲስ አበባ ቤቶች ኤጀንሲ ግን መልስ አልሰጣቸውም " ሲሉ አስታውሰዋል።
" ከዚህ ባለፈ የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮም መፍትሄ እንዲፈልግልን ብለን ነበር ጋር ግን ምላሽ ተነፍጎናል " ብለዋል።
" ወዴት እንደምንሄድ ጨንቆናል ፍትህ ተጓሎብናል ፤ አሁን ካለው የኑሮ ጫና አንጻር የቤት ኪራይ ትልቁ ፈተና ነው እባካችሁ መፍትሄ ፈልጉልን " ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#EHRC
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች እና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጎ ነበር።
ይህ ሪፖርት ከሰኔ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ/ም ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው።
በዚሁ የዓመታዊ ሪፖርት ፥ በግጭት ውስጥ ባሉ እና በትጥቅ ግጭት ውስጥ በቆዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች በተለያየ ጊዜ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ሴቶችና ሕፃናትን ፦
🔴 ለሞት ፣ ለአካል ጉዳት እንዲሁም ለወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃቶች መጋለጣቸው፤
🔴 በግጭት ዐውድ ውስጥ በቆዩት፦
° አፋር፣
° ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
° ትግራይ ክልሎች በቂ መልሶ የማቋቋም ሥራ ባለመከናወኑ በሕክምና ተቋማት የውሃና ኤሌክትሪክ ፣ የሕክምና ቁሳቁስ ፣ የአምቡላንስ ፣ የመድኃኒት ፣ የክትባትና የምግብ አቅርቦት ውስንነት ምክንያት እናቶችና ጨቅላ ሕፃናት በቅድመ ወሊድ ፣ በወሊድ ፣ ድኅረ ወሊድ ፣ በድንገተኛ ወሊድ ወቅት ሊያገኙት የሚገባቸውን መሠረታዊ አገልግሎቶች እያገኙ ባለመሆኑ የእናቶችና ሕፃናት ሞት እየጨመረ መምጣቱ፣
🔴 በሀገሪቱ በቀጠሉ ግጭቶች እና በተፈጠረው የደኅንነት ሥጋት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው በአሳሳቢነት ተጠቅሰዋል፡፡
(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Tigray
" እስከ በጀት መገደብ የሚደርስ ቅጣት ሊጣል ይችላል " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ተፈርሞ ባሰራጨው መመሪያ ፤ " የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች ማደናቀፍ እና በዘፈቀደ ህጋዊ ያልሆነ ሹመት መስጠትና መንሳት የበጀት ቅጣትና የህግ ተጠያቂነት ያስከትላል " ሲል አሳስቧል።
መመሪያ ደ/18/8/84 እንደሚለው " በህወሓት አመራሮች የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት ምክንያት በማድረግ መንግስታዊ ስልጣን እና ሃላፊነት የሌለው ' ቡድን ' በማለት የተጠቀሰው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የሚሰጠው ሹመት የመሻርና ሹመት የመስጠት ተግባር ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
በመሆኑም ፦
1. ቡድኑ የሚያካሄዳቸውን ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እንዲቆም ፤ ይህንን የጊዚያዊ መንግስቱ መመሪያ በመቀበል ፍርድ ቤት ጨምሮ የዞን እና የወረዳ የመንግስት መዋቅሮች ህጋዊ አሰራር እንዲከተሉና ህግ በሚጥስ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ፤
2. በክልሉ በየመዋቅሩ ያሉ ምክር ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ መሆኑን በመቀበል ሹመት ከመስጠትና ከመሻር እንዲቆጠቡ፤
... ሲል ማስጠንቀቅያ ሰጥቷል።
ከዚህ ባለፈ የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች የሚፃረር የከተማና የገጠር ወረዳ የአስተዳደር መዋቅር በጀት እስከመገደብ የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልበት በአፅንኦት አሳስቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyMeklle
@tikvahethiopia
#ጥቆማ
አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ፣ ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያዎች በNehabi No Code Website Builder በመጠቀም ችሎታቸውን የሚያሳዩበትን የነሃቢ ዌብሳይት ዲዛይነሮች ውድድር በይፋ ማስጀመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
" አሸናፊዎች እስከ 100,000 ብር የገንዘብ ሽልማት ድረስና ተጨማሪ ሽልማቶችን ያገኛሉ " ብሏል።
" ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ችሎታቸውን በመጠቀም አዳዲስ ነገሮችን እንዲያመጡ፣ AI Powered ዌብሳይቶችን እንዲያበለፅጉ እንዲሁም የራሳቸውን ተጨማሪ Plugins በማዘጋጀት እንዲሰሩ ይበረታታሉ " ሲል ገልጿል።
ምዝገባው እስከ ጥቅምት 29፣ 2017 ዓ.ም ድረስ ክፍት ነው ተብሏል።
ውድድሩ ላይ ለመመዝገብ ይህን ሊንክ ይጫኑ: https://nehabi.ashewa.com/contest/
@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
የብርሃን ጉዞጎ ተጠቃሚዎች ብቻ የሚያገኙትን ልዩ ቅናሾች እና ጥቅሞች ያግኙ፣ ይህም ጉዞዎን የበለጠ ተመጣጣኝ እና አስደሳች ያደርገዋል።
👉ደንበኞች በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው ከ10 በላይ አለም አቀፍ የአየር መንገዶች የበረራ ትኬቶችን ዋጋ ማወዳደር ያስችላል።
👉ደንበኞች በሚመርጡት አየር መንገድ የበረራ ትኬቶች ላይ ቅናሽ ዋጋዎች እንዲያገኙ ያስችላል።
👉ደንበኞች በሚመርጡት ሰዓት እና ዋጋ አስተማማኝ የበረራ ቡኪንግ ለመያዝ ያስችላል።
👉በሁሉም የባንካችን ቅርንጫፎች፣ በሞባይል ወይንም በኢንተርኔት ባንኪንግ ክፍያዎችን መፈጸም ያስችላል፡፡
👉ያለ ተጨማሪ ክፍያ ሳምንቱን ሙሉ ለ 24 ሰዓታት የባለሙያ ምክር እና እርዳታ እንዲያገኙ ያስችላል። ስለ ብርሃን ጉዞጎ (GuzoGo) አገልግሎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ0116506355 /0116507425 ወይም በነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥር 8292 ላይ ይደውሉ፤
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
Facebook
Telegram
Instagram
Twitter
LinkedIn
YouTube
#Update
" ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው " -የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ
ከክፍያ ጋር በተያያዘ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ዘግተው ስለወጡና ስራ ስላቆሙ ጤና ባለሞያዎች በተመለከተ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራ ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል።
" እኔ እንደ ተቋሙ ስራ አስኪያጅ ይከፈላቸው ብዬ እየጠየኩ ነው በዕለቱም ይህንን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ለመነጋገር ስሄድ ነው ዘግተው የወጡት " ሲሉ ተናግረዋል።
" ስመጣ ሁሉም ክፍል ዝግ ሆኖ ነው የጠበቀኝ ታካሚው ውጪ ሲጉላላ ነው የደረስኩት " ብለዋል።
ወረዳውም የተጠየቀውን ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ ነው ያሉት አቶ ተሰማ " ነገር ግን ' የገንዘብ እጥረት አለብኝ 'ታገሱ ' ብሏል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ጤና ጣቢያ ለአንድ ደቂቃም መዘጋት የለበትም " የሚሉት ሃላፊው " እነሱ ግን ዘግተው ወጡ እንደዚህ ሲሆን ማስታወቂያ አወጣን ' ወደ ስራቹ ተመለሱ ' የሚል አልመጡም በመሃል ወሊድ ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ የመጡት እናቶች ሪፈር በሚደረጉ ወቅት ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸዋል " ብለዋል።
" ላብራቶሪ ፣ ማዋለጃ ፣ መድሃኒት ክፍል ሁሉንም ዘግተው ነው የሄዱት ቁልፍ አስረክበው ቢሄዱ አንድ ነገር ነው ትልቅ ወንጀል ነው ሰርተው የሄዱት " ሲሉ ተናግረዋል።
ስራ አስኪያጁ አምናም በተመሳሳይ ከዲዩቲ ክፍያ ጋር በተያያዘ ሆስፒታሉ ተዘግቶ እንደነበር ገልጸዋል።
" ያኔ ምንም እርምጃ አልተወሰደም በዚሁ ከቀጠለ ጤና ተቋማት እየተዘጉ ህዝብ ያልቃል እርምጃ ካልተወሰደ ነገም ቢሆን እየዘጉ ይወጣሉ በዚህ መሃል ሰው ይሞታል የሞተ ሰውን ደግሞ መመለስ አይቻልም " ብለዋል።
በተቋሙ ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው የዘጓቸውን ክፍሎች ግን በህጋዊ መንገድ ሰብረን ገብተናል ሲሉ ገልጸዋል።
ለጊዜው ከሌሎች አካባቢዎች ባለሞያዎችን አምጥተው ሥራ ለመጀመር እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከ80 በላይ ባለሞያዎች በአንድ ጊዜ ነው ስራ ያቆሙት ምን ያህል ባለሞያዎችን አግኝታቹሃል ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ " ባሉት ዋና ዋና ጊዜ የማይሰጡ የወሊድ እና የድንገተኛ ህክምና ቦታዎች ላይ 7 ባለሞያዎች አምጥተናል ኦፕሬሽን ላይ ግን ሰው ማግኘት አልተቻለም " ብለዋል።
እነዚህ ባለሞያዎች ክፈተቱን ለመሸፈን የመጡ እንጂ ቋሚ ተቀጣሪዎች አይደሉም ሲሉ አስረድተዋል።
ስራ ያቆሙት ባለሞያዎች ተመልሰው ቢሙጡ ትቀበላላቹ ወይ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ " እስካሁን የመጣ ባለሞያ የለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
" ' በሌሎች ተገፋፍተን አስፈራርተውን ነው ' የወጣነው የሚሉ ባለሞያዎች አሉ የሚመለሱ ከሆነ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል ነገር ግን አስቀድመን ከማህበረሰቡ ጋር ውይይቶችን አድርገን ነው የሚሆነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ሃላፊው ፥ " ስራ በማቆማቸው ቀዳሚ ተጎጂ ማህበረሰቡ መሆኑን ጠቁመው ከሰኞ በኋላ ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋግረን ይመለሱ አይመለሱ የሚለውን የምንወስን ይሆናል " ሲሉ አክለዋል።
ወደ አመራርነት ከመጡ 2 ወራቸው እንደሆነ የገለጹት አቶ ተሰማ " በሆስፒታሉ ውስጥ የአከፋፈል ስርዓት ችግር አለ ከታካሚው አንጻር ትርፍ ባለሞያ ነው ያለው አንዳንድ የማሻሻያ ስራዎች እየሰራን ነው ተቋሙ ላይ መድኃኒት መኖር አለበት መድሃኒት በህገወጥ መንገድ የሚወጣበት ተቋም ነው። ይህ እንዳይሆን አንዳንድ ስራዎችን መስራት ጀምረናል ይህ ያስቆጣቸው ሰዎች አሉ " ብለዋል።
ቲክቫክ ኢትዮጵያ ሰራተኞቹ የጠየቁት የተጠራቀመ እና የሰሩበትን ክፍያ ነው በምን ያህል ጊዜ ችግራቸውን ትፈታላቹ ? የሚል ጥይቄ አንስቷል።
ስራ አስኪያጁ ፤ " እኔ ያሰራኋቸውን የሁለት ወር የዲዩቲ ክፍያ ለመክፈል 1.4 ሚልዮን ብር ያስፈልጋል ይህንንም ለመክፈል ቀኑን መወሰን አይቻልም ወረዳው ' ያለውን ነገር ተነጋግረን እንፈታለን ' ብለዋል ይከፈላቸዋል " ሲሉ መልሰዋል።
" ያልተከፈላቸውን ክፍያ ሁሉ ለመክፈል ወረዳው ዝግጁ ነው " ያሉ ሲሆን ነገር ግን የበጀት እጥረት በመኖሩ ቀኑን መወሰን እንደማይቻል ገልጸዋል።
በ2016 የጥር ወር ላይ የ4 ወር የዲዩቲ ክፍያ ባለመከፈሉ በተመሳሳይ ሰራተኞች ስራ አቁመው እንደነበር መዘገባችን የሚታወስ ነው።
በወቅቱ ሆስፒታሉ ከወረዳው ከሚገኙ የጤና ጣቢያዎች 17 ያህል ባለሞያዎችን ቀጥሮ ስራ አስጀምሮ ነበር።
ከዚያ በኋላም የአንድ ወር እንዲከፈላቸው ተደርጎ ወደ ስራ ተመልሰው የነበረ ሲሆን በጊዜያዊነት ተቀጥረው የነበሩት 17 ባለሞያዎች አብረው እንዲቀጥሉ ተደርገዋል።
አቶ ተሰማ እኚህ 17 ባለሞያዎች አሁን የስራ ማቆም አድማ ካደረጉት ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ባለሞያዎች ወደመጡበት እንዲመለሱ በወረዳው አስተዳደር መወሰኑን ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሆስፒታሉን ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ እና የአንጋጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ማርቆስ ማሞን በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ድሬዳዋ
በአማራ ክልል ባለው የፀጥታ ችግር ሳቢያ የመተማ መስመር በመዘጋቱ፣ በድሬዳዋ በኩል የሚደረገው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለጸ።
ይህንን የገለጸው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነው።
ቢሮው ፤ " የመተማ መስመር በመዘጋቱ ድሬዳዋ እንደ መተላለፊያነት ስለምታገለግል ከፍተኛ የዜጎች ፍልሰት በከተማዋ ታይቷል " ብሏል።
ከተማዋ በምሥራቅ አቅጣጫ ድንበር መተላለፊያ በመሆኗ ሥራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚሻገሩ ሰዎች ፍልሰታቸው እየጨመረ መሆኑን ገልጿል።
ፍልሰተኞቹ ድንበር ለመሻገርም ሆነ በአጋጣሚ ያሰቡት ሳይሳካላቸው ሲቀር ተመልሰው ድሬዳዋ ውስጥ የሚቀሩ መኖራቸው ተመላክቷል።
በፍትሕ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በበኩሉ ፥ ከተማዋ የመተላለፊያ በር በመሆኗ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ይፈልሳሉ ብሏል።
በቀን ከ80 አስከ 100 ያህል ከ14 እስከ 35 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በሕገወጥ መንገድ ለመውጣት ጥረት እንደሚያደርጉ ጠቁሟል።
➡ የሰላም ዕጦት
➡ ሥራ አጥነት
➡ በደላሎች መታለል ለዚህ ገፊ ምክንያት መሆናቸውንም ጽ/ቤቱ ጠቁሟል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ በድሬዳዋ በኩል የሚደረገው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው፣ አዘዋዋሪዎች በቴሌግራም፣ በፌስቡክና በሌሎች ማኅበራዊ የትስስር ገጾች ማስታወቂያዎች ነው ተብሏል።
ችግሩን ለመፍታት ዘመኑን የሚመስሉ የወንጀል ምርመራ ሒደቶችን በመከተል በፍርድ ቤት ከማስረጃ ምዘና በተያያዘ ችግሮች እንዳይፈጠሩ፣ የወንጀል አፈጻጸም ዘዴ ግምት ውስጥ ያስገቡ የሕግ ማሻሻዎች ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የተቋማት ግንባታን በሚገባ ማጠናከርና ያላቸውን ግንኙነት ማሻሻል ይገባል ያለው ጽ/ቤቱ ወንጀሉ በአንድ ቦታ ብቻ የሚያበቃ ባለመሆኑ በክልሎች፣ በወረዳዎችና በቀበሌዎች የሚገኙ የፀጥታ አካላት ሊተባበሩ እንደሚገባ አሳስቧል።
ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ሲሰደዱ አዘዋዋሪዎች የሰውነት ክፍሎቻቸውን እያወጡ መሸጥና ሌሎችም ወንጀሎችን ስለሚፈጽሙባቸው ለመከላከል፣ የአገሮች ቅንጅት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑም ተጠቁሟል።
ዜጎች ከሚነሱባቸው አካባቢዎች ያሉ የሕግ አካላት እስከ መዳረሻ አገሮች ድረስ ከፀጥታ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሠራሮችን ማሻሻልና ማዘመን ይገባል ተብሏል።
ድንበር ላይ የተያዙ ዜጎች ወደ መጡበት ለመመለስ የትራንስፖርትና የጊዜያዊ ማቆያ ችግሮች አሉ የተባለ ሲሆን ካለው ብዛት አኳያ ግን በቂ አለመሆኑን ተገልጿል።
በተለይ የባህር ላይ ወጀብ በማይኖርበት ወቅት ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እንደሚጨምር ተመላክቷል።
ከድሬዳዋ ጂቡቲ ርቀቱ 300 ኪሎ ሜትር በመሆኑ ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ድሬዳዋ አመቺ ከተማ በመሆኗ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ከተማዋ እንደሚፈልሱ ተነግሯል።
መረጃው ከሪፖርተር ጋዜጣ የተገኘ ነው።
@tikvahethiopia
#AsellaPortFashion
ጫማዎች፣ የሴቶች እና የወንዶች መዋብያ እቃዎች ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መርጠው ያለተጨማሪ ክፍያ እንልክሎታለን ጥራት ካለው አገልግሎት ጋር እንሰጣለን።
ስልክ ፦ 0963635178
የመረጡትን እቃ ይህን በመጫን ይላኩልን 👉
📥 @businesslidu
📥 @businesslidu2
📥 @asellaport1
እቃዎችን ለመምረጥ እንዲሁም ዋጋቸውን ለማወቅ ከታች ያለውን link ትጭነው join በማድረግ ይመልከቱ👇
/channel/+HSaoqnlQCrc1NjI8
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን 545 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላልፈ ጨረታ አውጥቶ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ ይገኛል።
ቤቶቹን " በተለያዩ ሳይቶች ያስገነባኋቸው ናቸው " ብሏል።
የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 1000 ብር ነው በ6 የመሻጫ ጣቢያዎች እየሸጠ ያለው።
የመኖሪያ ቤቶቹ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ግራር (235 ቤቶች) እና አየር ጤና (110 ቤቶች) እንዲሁም በጉለሌ ክ/ከተማ እንጦጦ (200 ቤቶች) እንደሚገኙ ተሰምቷል።
የአንድ ካሬ ሜትር የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 80,000 (ሰማንያ ሺህ ብር) እንደሆነም ከጨረታ ሰነዱ መመልከት ተችሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 30 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ተገዝተው መግባታቸው ተሰምቷል።
ተሽከርካሪዎቹ በ192 ሚሊዮን 286 ሺህ 516 ብር ከ76 ሳንቲም ነው የገቡት።
በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ የመንግስት ግዥ አገልግሎት 30 ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በመንግስት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት በዋጋ ማቅረቢያ የግዥ ዘዴ ለመፈፀም ጨረታ አውጥቶ ነበር።
በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት ዋጋ ማቅረቢያ ተወዳድረው አሸናፊ የሆኑ ሁለት አቅራቢዎች ፦
➡️ ባለ 7 መቀመጫ የሆኑ Volkswagen ID 6 Electric Vehicles ብዛት 20 units
➡️ ባለ 5 መቀመጫ የሆኑ Kia e5 Electric Vehicles ብዛት 10 units
ለማቅረብ ከአገልግሎቱ ጋር በገቡት አጠቃላይ የውል መጠን ከነቫቱ ብር 195,286,516.76 መሰረት አቅርበዋል ተብሏል።
@tikvahethiopia
" የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት መዘዙ ለአጎራባች ሃገራትም ተርፏል " - ካተሪን ፓቲሎ
የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በሱዳን ላይ ካስተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ በአጎራባች ሃገራት ላይ ብርቱ ኤኮኖሚያዊ ጉዳት ማድረሱን የዓለም የገንዘብ ድርጅት አስታወቀ።
በድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ካተሪን ፓቲሎ " የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት መዘዙ ለአጎራባች ሃገራትም ተርፏል " ብለዋል።
" ቀድሞውኑ በራሳቸው የውስጥ ጉዳዮቻቸው ተይዘው የነበሩ የሱዳን ተጎራባቾች በስደተኞች መጥለቅለቅን ጨምሮ ሌሎች የደህንነት እና የንግድ ተግዳሮቶች አስከትሎባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
የዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የትንበያ ሪፖርት እንደሚያመለክተው በጦርነቱ በተለይ በማዕከላዊ አፍሪቃ ፣ ቻድ ፣ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ላይ ከፍተኛ ኤኮኖሚያዊ ጉዳት ሊደርስ ይችላል።
በተለይ ከገቢዋ አብዛኛውን ከነዳጅ ዘይት ሽያጭ የምታገኘው ደቡብ ሱዳን ባለፈው የካቲት ወር ሱዳን ውስጥ ከዋነኞቹ የነዳጅ ዘይት ማስተላለፊያዎች ቱቦዎች በአንዱ ላይ ጉዳት ከደረሰባት በኋላ ነገሮች አሳሳቢ መሆናቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ እና በዩክሬን እየተካሄዱ ያሉ ሌሎች " ውጫዊ ግጭቶች " እንደ የምግብ ዋጋ ፣ ማዳበሪያ እና የኃይል ወጪዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን የዓለም የገንዘብ ድርጅት ገልጿል። #ዶቼቨለሬድዮ
@tikvahethiopia
BK C O M P U T E R S
ማንኛውንም አይነት አዳዲስ ላፕቶፖች ፣ ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች፣ ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛት እና ከታላቅ ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መጥተናል።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራትና በብዛት ከ1 አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ።
ለተጨማሪ መረጃ እና የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ።
Tg. /channel/BKComputers
Inbox @bkcomputer27
አድራሻ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከመሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን።
ስልክ ፦ 0911448148. 0955413433 we make IT easy!
#ዶክተርነቢያትተስፋዬ 👏 #ኢትዮጵያ
ከስፓይና ቢፊዳ የጤና እከል ጋር የተወለዱት ግለሰብ በማሌንዢያ የስፓይና ቢፊዳ ዓለም አቀፍ ኮንግረንስ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኑ።
ከ30 ዓመታት በፊት ከህመሙ ጋር የተወለዱት ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬ ፣ በማሊዥያ የስፓይና ቢፊዳ ዓለም አቀፍ ኮንግረስ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የሕይወት ዘመን ተሸላሚ የሆኑት፣ ያሳለፉትን የሕይወት ውጣ ውረድ ሌሎች ልጆች እንዳያልፉ በሕይወት ልምዳቸውና በሙያቸው ኢትዮጵያውያንን ለማገልገል በሚያደርጉት ጥረት ነው።
ለኢትዮጵያውያን የሚሰጡትን አግልግሎት አድማስ ለማስፋት “ አለያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት ” የተሰኘ በስማቸው ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት በመመስረት አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩም ተናግረዋል።
ድርጅታቸው ከሀገር ውስጥና ውጭ ካሉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በስፓይና ቢፊዳ እና ተያያዥ የጤና ችግር ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሟላ ድጋፍ ለማድረግ ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ቃል ገብተዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት በዓመት ከስፓይና ቢፊዳና ተያያዥ የጤና እክሎች ጋር አብረው የሚወለዱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም በርካታ ሕፃናት ከዚህ ችግር ጋር አብረው ከሚወለድባቸው ሀገሮች ግንባር ቀደም መሆኗን አስረድተዋል።
በመሆኑም ከጤና ሚንስቴር ፣ ከሆስፒታሎችና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር በዚህ ችግር የተጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች የክትትልና የማገገም አገልግሎት እንዲያገኙ በትጋት እየሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
የተሸላሚው የሕይወት ጉዞ ምን ይመስላል ?
ከ30 ዓመታት በፊት ከዚህ የጤና ችግር ጋር ተወልደዋል። ከዚህ ችግር ጋር አብረው በመወለዳቸው በሕይወታቸው ውስጥ ብዙ ውጣውረዶች አሳልፈዋል።
የተለያዩ ቀዶ ጥገና ሕክምናዎችንም አድርገዋል።
በልጅነት ጊዜያቸው በዚሁ በሽታ ሳቢያ ትምህርታቸውን ቤት ተቀምጠው እስከመከታተል ተገደዋል። በተለያዩ የጤና ችግሮች ውስጥም አልፈዋል።
እነዚህን ሁሉ ችግሮች በትጋትና በጥንካሬ ከቤተሰቦቼ ጋር በመሆን አልፈው የህክምና ትምህርት መማር ችለዋል።
ለአምስት አመታት የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው ከጨረኩበት ማግስት ጀምረው እንደሳቸው ሁሉ ከዚህ የጤና ችግር ጋር ለሚወለዱ ሕፃናት የተለያዩ ድጋፎችና የህክምና አገልግሎቶች እንዲያገኙ በማድረግ በሺዎች ለሚቆጠሩ ቤተሰቦች ተስፋ ለመሆን በቅተዋል።
ልጆች ከዚህ ከባድ የጤና ችግር ጋር አብረው እንዳይወለዱና መከላከል እንዲቻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ፎሊክ አሲድ በምግብ እንዲበለፅግ የማስተማርና የማስተዋውቅ ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ።
ለሁለት አመታት Reachanother foundation በሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ውስጥ የአገልግሎት ዳይሬክተር በመሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 8 ሆስፒታሎች ሕፃናት ጥራት ያለው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ባለሙያዎች ማስልጠን እና ግብቶችን የሟሟላት ሥራ በመስራት ላይም ይገኛሉ።
ስለ ስፓይና ቢፊዳ ይወቁ ፦ /channel/tikvahethiopia/74429?single
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት ማብራሪያ ሰጥቷል።
ቢሮው እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከአውድ ውጪ በተተረጎመ መንገድ እንደሆነ ጠቁሟል።
" የ1997 የጋራ መኖርያ ቤት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው የተሳሳተ መረጃ ትክክል ባልሆነ መልኩ ከአውድ ውጪ ተተርጉሞ የቀረበ ነው " ብሏል።
ቢሮው በሰጠው ማብራሪያ ምን አለ ?
" ከተማ አስተዳደሩ የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ለማስተላለፍ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2011 መሰረት ክፍል 3 አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 እና 2 መሰረት ብቁ እና ንቁ ማለትም ' የቤት ፈላጊዎች በገቡት ግዴታ መሰረት የቁጠባ መጠን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትክክል ተቀማጭ ማድረጋቸውን ከእጣ በፊት ያረጋግጣል ' ይላል።
ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢዎች በወቅቱ በመረጃ ቋት ውስጥ ንቁ እና ብቁ የነበሩ ተመዝጋቢዎችን ከተማ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አስተናግዶ ያጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በወቅቱ ብቁ ያልነበሩትን የ1997 ተመዝጋቢዎች እና ሌሎች የ2005 እጣ ያልደረሳቸው የቤት ፈላጊዎች እየተተገበሩ ባሉ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች እያስተናገደ ይገኛል፡፡
ስለሆነም በወቅቱ ብቁ እና ንቁ ያልነበሩ የ1997 ተመዝጋቢዎች ከየትኛውም የቤት ልማት መርሃ ግብር ውጪ እንደተደረጉ ተደርጎ የተሰራጨው የሀሰት መረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ እና ይህንን ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን ከተማ አስተዳደሩ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።
ከተማ አስተዳደሩ ተመዝግበው የሚጠባበቁትን ሆነ ሌሎች የከተማችዋን የቤት ፈላጊዎች ቤት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ አዳዲስ የቤት ልማት አማራጮችን በመቀየስ እየተገበረ ይገኛል " ብሏል።
#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministrationBureau
@tikvahethiopia
#የ97ተመዝጋቢዎች
" ምላሽ ካልተሰጠበት በ15 ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተ/ም/ቤት እናቀርባለን " - የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም
የጋራ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ቤት ለማግኝት ተመዝግበው ገንዘብ በባንክ ሲቆጥቡ የነበሩና እስካሁን ቤቱን ያላገኙ የ1997 ዓ.ም. ተመዝጋቢዎች አቤቱታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ካልሰጠበት፣ በ15 ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርበው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡
ተቋሙ ፤ ለ20 ዓመታት ያህል " ቤት ይደርሰናል " ብለው እየጠበቁ ቢሆንም መንግሥት ምላሽ አልሰጠንም ያሉ ቢያንስ 67 ሰዎችን አቤቱታ ተቀብሎ እየመረመረ መሆኑን ጠቁሟል።
አቤቱታውን ተከትሎም የከተማ አስተዳደሩን ማብራሪያ ጠይቋል።
ምላሽ ካልመጣ ተቋሙ የሚወስደው ዕርምጃ እንደሚኖ ገልጿል።
" በ1997 ዓ.ም. ተመዝግበን ቤት ሳይደርሰን ለሌሎች ተሰጥቷል ፤ በሚል ተደራጅተው ጠይቀዋል፣ እኛም ጥያቄ አቅርበናል፡፡ ነገር ግን የከተማ አስተዳደሩ እስካሁን መልስ አልሰጠንም " ብሏል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቅርቡ በነበረ የውይይት መድረክ ፤ ከዚህ በፊት በ2015 ዓ/ም በተላለፉት ቤቶች የ1997 ዓ/ም ቆጣቢዎች ሁሉም ዕጣ እንዲወጣላቸው መደረጉንና ለተመዘገቡት ሁሉ ቤት ተሰጥቶ መጠናቀቁን ገልጸው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ የሕዝብ ዋና ዕንባ ጠባቂ ተቋም በዚህ ሁኔታ ከከተማ አስተዳደሩ የደረሰው ምላሽ እንደሌለ አመልክቷል።
ለረዥም ጊዜ ጠብቀው ምላሽ ያልተሰጣቸውን ሰዎች አቤቱታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ የመጨረሻ ዕልባት እንዲያገኝ ይደረጋልም ብሏል።
በ1997 ዓ.ም. የቤት ምዝገባ በርካቶች ተመዝግበው ለ20 ዓመታት ሲቆጥቡ መቆየታቸውን የገለጸው ተቋሙ ፤ " መንግሥት የተሠሩትን ቤቶችን ለአርሶ አደር ልጆች ፣ ለፖለቲካ ሹመኞች እና ለተለያዩ ግለሰቦች እየሰጠ ነው " በማለት ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር ብሏል።
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባና በሸገር ከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ካሳና ተለዋጭ ቦታ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብ እንደነበር መረጃ የደረሰው ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ አሁን በመሀል አዲስ አበባ ከሚከናወነው የኮሪደር ልማት ጋር በተገናኘ የደረሰው የሕዝብ አቤቱታ እንደሌለ አመልክቷል።
በአሁኑ ወቅት ወደ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በብዛት እየቀረቡ ያሉ አቤቱታዎች ፦
° የሥራ ስንብት፣
° የመሬት አገልግሎት፣
° የጡረታ መብት
° የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን የተመለከቱ መሆናቸውን አመልክቷል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
@tikvahethiopia
#EHRC
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
በዚህም ሪፖርቱ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ ድጋፍ በአግባቡ ሊቀርብ እንዲሁም ደግሞ የሰብአዊ መብቶች መርሖችን ፣ የተፈናቃዮችን ክብር ፣ ደኅንነት እና ፍላጎት ያከበረ ዘላቂ መፍትሔ ሊመቻች እንደሚገባ አሳስቧል።
የኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ምን አሉ ?
" ኢትዮጵያ ውስጥ መፈናቀል በአብዛኛው እየተከሰተ ያለው በግጭቶች ምክንያት በመሆኑ ግጭቶችን በአፋጣኝ ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ መፍታትና እንዳይባባሱ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ፤ መፈናቀልን ለመከላከል እና በዘላቂነት መፍትሔ ለመስጠት ወሳኝ በመሆናቸው ትኩረት ሰጥቶ መተግበር ያስፈልጋል።
በተፈጥሮ አደጋም የሚከሰት መፈናቀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ በመምጣቱ ለቅድመ አደጋ መከላከል እና ለአደጋ ጊዜ ምላሽ አሰጣጥ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
የሰብአዊ መብቶች መርሖችን መሠረት ያደረገ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እንዲሁም የሽግግር ፍትሕ እና የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን መብቶችና ተሳትፎ በሚያረጋገጥ ሁኔታ እንዲተገበሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። "
(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Update
🔵 “ መምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን ” - የወላይታ ዞን መምህራን
🔴 “ ከ10,500 በላይ መምህራን ደመወዝ አልተፈጸመላቸውም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር
በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን ያልተከፈላቸውን ደመወዝ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታ ለማስገባት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ “ በፓሊስ መታሰራቸው ” ተሰምቶ ነበር።
የደመወዝ ቅሬታቸው ባለመፈታቱ የመብት ጥያቄ ለማንሳት ባደረጉት ፒቲሽን የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ነበር ፓሊስ “ አመጽ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል። የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል ” በሚል ያሰራቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም የታሰሩት መምህራን ተፈቱ ? የደመወዝ ቅሬታችሁስ መፍትሄ አገኘ ? ሲል ዛሬ ቅሬታ ያላቸው መምህራንን ጠይቋል።
ምን መለሱ ?
“ ምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። ሦስቱም መምህራን ተፈትተዋል። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን።
‘ መንግስትን ከሕዝብ አጣልታችኋል ’ የሚለው ክስ በፍርድ ቤት ሲቀርብ ምንም መረጃ የላቸውም። ከዚያ ጋር ተያይዞ ነው ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቃቸው።
የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።
አሁንም ደመወዝ እንዲከፈለን እንፈልጋለን።
መምህራን ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ሥራ ስለሚሰሩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በትክክል እንዲተገብሩ ደመወዝ መከፈል አለበት።
የሐምሌ ደመወዝ እስካሁን አልተከፈለም። ለመምህራንና ለጤና ባለሙያ 40 በመቶ፣ ለፓሊስ 20 በመቶ እንጂ ከዚህ ውጪ ደመወዝ አልተከፈለም።
አሁን እንደገና አጠቃላይ የትምህርት ባለሙያም ወደታች ወርዶ ‘የሐምሌን ደመወዝ እንከፍላለን’ በማለት አመራርም በአጠቃላይ ተረባርቦ መምህራን ወደ ስራ አስገብተዋል።
ፍርድ ቤትም ገና የራሱን ቀጠሮ እየሰጠ ነው የሐምሌ ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት ” ብለዋል።
ደመወዛቸው በወቅቱ አለመፈጸሙ ትልቅ ጥፋት ሆኖ እያለ ይህንኑ ቅሬታ መምህራን ታስረው መቆዬታቸው ግፍ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም በዚሁ ቅሬታ ላይ ምን እየሰሩ እንደሆነ የክልሉና የዞኑን መምህራን ማኀበር ጠይቋል።
የክልሉ መምህራን ማኀበር የመምህራንን መታሰር በተመለከተ እስካሁን ሪፓርት እንዳልተደረገለት/ቅሬታ ያደረሰው አካል እንደሌለ ገልጾ፣ በይበልጥ የዞኑ መምህራን ማኀበር እንዲጠየቅ አሳስቧል።
ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የወላይታ ዞን መምህራን ማኀበር ሊቀ መንበር መምህርት ባዩሽ ዘውዴ፣ “ በቅርቡ ታስረዋል ስለተባሉት መምህራን ለኛ ኦፊሻሊ የቀረበልን ምንም መረጃ የለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
“ ያመለከተልን አካል የለም። ከውጪ ወሬ ነው እየሰማን ያለነው። ወደ አክሽን እንዳንገባ የመጣልን መረጃ የለም ” ያሉት ሊቀመንበሯ፣ “ እንነጋገርበት ወደኛ መምጣት ይችላሉ ” ብለዋል።
የደመወዝ ክፍያን ቅሬታ በተመለከተም በሰጡን ምላሽም፣ ከ10 ሺህ 500 በላይ መምህራን ደመመወዝ እንዳልተፈጸመላቸው ገልጸው፣ ማኀበሩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዳሳወቀ አስረድተዋል።
የክፍያ አለመፈጸምን በተለመከተ ምላሽ እንዲሰጡ ከዚህ ቀደም የጠየቅናቸው የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጎደና፣ “ አራት ወረዳዎች ላይ መሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው። የሐምሌ ወር ክፍያ ላልተፈጸመላቸውም ወረዳዎች ገቢ ሰብስበው እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው ” ብለው ነበር።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" አባታችንን አፈልጉን " - ቤተሰቦች
ከላይ በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው አቶ አቡበከር ያሲን ኡመር ይባላሉ።
ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ ኮ/ቀ ክፍለ ከተማ ዓለም ባንክ አካባቢ ሲሆን፤ በቀን ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም።
የለበሱት ልብስ እና ጫማ እንዲሁም ደግሞ በወቅቱ የያዙት ሳምሶናይት ከተፍኪ ከተማ ትንሽ አለፍ ብሎ ባለ አካባቢ የተገኘ ቢሆንም ፤ የአካባቢው ፖሊስ እና የአደጋ ግዜ ሰራተኞች በውሀ ውስጥ እና በአካባቢው ፍለጋ አድርገው አቶ አቡበከርን ሊገኙ አልቻሉም።
አቶ አቡበከር እድሜያቸው ከ55 እስከ 60 የሚጠጋ ሲሆን፤ ረጅም ጠቆር ያሉ አባት ናቸው።
በወቅቱ ለብሰውት የነበረው ልብስ ወድቆ በመገኘቱ በአሁኑ ወቅት የአለባበሳቸውን ሁኔታ መለየት አልተቻልም።
በዚህም ምክንያት አባታቸው ከጠፉበት ሰዓት ጀምሮ ቤተሰባቸው በጣም ከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ ይገኛሉ።
እኚህን አባት ያያችሁ አሊያም ያሉበትን የምታውቁ ጥቆማ በመስጠት ተባበሩን ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ተማጽነዋል።
ፈላጊ ቤተሰብ ስልክ ፦ 0938704092
@tikvahethiopia
#WELL_Computer
ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች ታላቅ ቅናሽ !ጥሩ ላፕቶፕ ለመግዛት አሰበዋል? እንግዲያውስ 𝐖𝐄𝐋𝐋 ኮምፒውተር አለልዎት!
እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የ2023/24 ሞዴል ላፕቶፖች እና ኮምፒዩተሮችን ለጨረታም ሆነ ለግልዎ፣ የተለያዩ አዳዲስ ጌሚንግ እንዲሁም ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖችን ከአስተማማኝ ዋስትና ጋር እናቀርባለን።
አድራሻ፦ መገናኛ ከዘፍመሽ ዝቅ ብሎ 3ኤም ሲቲ ሞል / 3M City Mall 1ኛ ፎቅ ቁ. FL04 Well Computer
የሚፈልጉትን ላፕቶፕ ይምረጡ፦ /channel/welllaptop የአንድ ዓመት ሙሉ ዋስትና
Call Us: @cr7_well
ስልክ ፦0943847549 / 0910238672
#Safaricom
💫ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ወደ እናንተ እይቀረብን ነው!🙌👏 ከአስተማማኙ ኔትወርካችን ጋር አሁንም በአብሮነት ወደፊት!
አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!
የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
#SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#Update
" የጤና ባለሞያ ወንጀለኛ አይደለም " - የሆስፒታሉ ሰራተኞች
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከምባታ ጠምባሮ ዞን አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
የጤና ባለሞያዎቹ እስካሁን ወደ ሥራ ገበታቸው ያልተመለሱ ሲሆን ጥያቄያቸው ምላሽ ሳያገኝ የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸውልናል።
ስራ አቁመው በቆዩባቸው ቀናት ከወሊድ ጋር በተገናኘ ወደ ሆስፒታሉ መጥተው የነበሩ እናቶች ጉዳት እንዳጋጠማቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካነጋገራቸው ባለሞያዎች እና ከሆስፒታሉ አመራር ተረድቷል።
ጉዳያቹ ከምን ደረሰ ? ስንል በድጋሚ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የጤና ባለሞያዎች " የስራ ማቆም አድማውን አስተባብራቹሃል " በሚል 14 በሚሆኑ ባለሞያዎች ላይ የእስር ማዘዣ ወጥቶ እየተፈለጉ መሆኑን እና ይህንንም ፍራቻ ከአካባቢው ርቀው መደበቃቸውን ተናግረዋል።
" እኛ ስራ ካቆምን በኋላ የምንጠብቀው የሚመለከታቸው አመራሮች ችግራቹ ምንድነው ? እንዴት ዘጋቹ ? ምንድነው ችግሩ ? ብለው መጠየቅ እና መሰብሰብ ሲገባቸው ጭራሽ ወደ ማሳደድ ገብተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሸሽተን ነው ያለነው በፖሊስ ማዘዣ ወጥቶ በተገኙበት ይያዙ ተብሏል እየተፈለግን ነው። ለጊዜው ከአካባቢው ሸሽተናል " ሲሉ አክለዋል።
" ተቋሙ በቂ መድኃኒት እና የህክምና ግብአቶች የሉትም ለበርካታ ጊዜያት የመድኃኒት ግዢ አልተፈጸመም ሆስፒታሉን የምናገለግለው ባለው ነገር ነው " ያሉ ሲሆን ነገር ግን ስብሰባ ላይ ያለውን ችግር የሚናገሩ ሰዎች '" አድመኛ እና ሌላ አላማ ያላቸው ተብለው እየተፈረጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ባለሙያዎቹ " ይህንን ችግር ችለን እየሰራንም የሰራንበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ደሞዛችን ለምንም የሚበቃ አይደለም ነው " ያሉት።
" ስራ በማቆማችን የኛን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ በማህበረሰቡ ዘንድ እንድንጠላ ሥራ እየሰሩ ነው " ያሉ ሲሆን " እየተሰቃየ ቀን እና ማታ የሚሰራ ሰው የ2016 ዕዳውን ሳይከፍል ፣ የቤት ኪራይ ክፈል ወይም ልቀቅ እየተባለ በስቃይ ነው ያለው ባለሞያው ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥቶ ነው ስራውን የሚሰራው እረፍት ወጥቶ ሄዶ እናቱን እና አባቱን እንዳይጠይቅ የህክምና ስራ እረፍት የለውም " ብለዋል።
" ችግርህ ምንድነው ተብሎ አይጠየቅም ? ሲሪንጅ (Syringes) የለም ብለን ማውራት የለብንም እንዴ ? ማቴሪያል ለዚህ ተቋም ያስፈልጋል ህዝቡ መንገላታት የለበትም ብለን መጠየቅ የለብንም ? ይህንን ባወራን በፖሊስ መጥሪያ መውጣት የለበትም አግባብ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።
" ጤና ባለሞያ ወንጀለኛ አይደለም ይሄንን ሌላ ቦታ አላወራንም ስብሰባ ላይ ነው ያወራነው " ሲሉ አክለዋል።
ባለሙያዎቹ ፥ " እኛ ስራውን ከማቆማችን በፊት ሁሉም ባለሞያ ቀደም ብሎ ተኝቶ ታካሚዎችን ወደ ሌላ ቦታ ሪፈር አድርገን ነው የወጣነው " ያሉ ሲሆን እነሱ ግን ታካሚዎችን ትተን እንደወጣን በማስመሰል በማህበረሰቡ ዘንድ የማጥላላት ሥራዎችን እየሰሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ፥ " ለመንግስት የስራ ሰዓት ብለን ለምንሰራው ሥራ የሚከፈለን ደሞዝ ለእኛ በቂ አይደለም ኢኮኖሚውን መቋቋም አልቻልንም። " ብለዋል።
" የቆየ ችግር ነው ከ2015 ጀምሮ እየተቆራረጠ ነው የሚመጣው እያቃተን ነው ። የሚገባልን ደሞዝ እዳችንን ራሱ መክፈል አልቻለም። አሁንም ችግራችንን ከመፍታት ይልቅ ' ለሌላ ሆስፒታል ሰራተኞች ማስተማሪያ የሚሆን እርምጃ ይወሰድባቸው ' ተብሎ እየተፈለግን ነው ሲሉ ነግረውናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሆስፒታሉን አመራር አግኝቶ ስለ ችግሩ ጠይቋል። የአመራሩ ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#BK_COMPUTERS
ማንኛውንም አይነት አዳዲስ ላፕቶፖች ፣ ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች፣ ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛት እና ከታላቅ ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መጥተናል።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራትና በብዛት ከ1 አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ።
ለተጨማሪ መረጃ እና የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ።
Tg. /channel/BKComputers
Inbox @bkcomputer27
አድራሻ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከመሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን።
ስልክ ፦ 0911448148. 0955413433 we make IT easy!
#DStvEthiopia
🔥ከባድ ትንቅንቅ የማያጣው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ይመለሳሉ!
🏆 ምርጥ አቋም ላይ ያሉት ሊቨርፑል እና አርሰናል እሁድ ከምሽቱ 1፡30 በኢመሬጽ ይገናኛሉ!
ማን ይሆን 3 ነጥብ ማሸነፍ የሚችለው!
👉 ይህንን ድንቅ ፍልሚያ ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇 www.dstv.com/en-et
የዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇https://bit.ly/3RFtEvh
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
🔈#የመምህራንድምጽ
" መግለጫ እና ወሬ ሳይሆን የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን ፤ እኛ መኖር ከብዶናል !! " - ቃላቸውን የሰጡ መምህራን
ከሰሞኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን አድርጎ ነበር።
የማህበሩ ስብሰባ ላይ ፦
➡ መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣
➡ ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣
➡ በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣
➡ ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት፣
➡ ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩ፣
➡ በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣
➡ የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት፣ የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች ...ወዘተ በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተው ነበር።
በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ የትምህርት ሚንስቴር አመራሮች ተገኝተው ምላሽ እንደሰጡ በማህበሩ ተገልጿል።
ስብሰባው የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀው።
ይህንን የማህበሩን ስብሰባ መደረግ የሰሙና ማህበሩም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠውን ቃል ያነበቡ በርካታ መምህራን መልዕክታቸውን ልከዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ መምህራን ፥ " እኛ መግለጫና የማይጨበጥ ወሬና መስማት ሰልችቶናል የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።
" እኛ መኖር ከብዶናል !! ስብሰባ ከዛ መግለጫ ምን ይሰራልናል ? ምን ያህል ዋጋ እየከፈልን እንዳለን እኛ ነን የምናውቀው ልጅ ማሳደግ ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር እጅጉን ፈተና ከሆነብን ሰንብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ይህ ማህበር በየጊዜው መግለጫ ነው የሚሰጠን ምንድነው ጠብ የሚል ስራ የተሰራው ? ይሄን ይመልሱልን " ሲሉ ጠይቀዋል።
" መግለጫና ወሬ ምንድነው የሚሰራልን ? ችግራችንን ደጋግሞ መናገር መፍትሄ ከሌለው ጥቁሙ ምን ላይ ነው ? የማይታወቅ ችግር ያለ ይመስል ሁሌ አንድ አይነት ነገር መናገር ያሰለቻል ደክሞናል " ብለዋል።
" መብታቸውን የእንጀራ ጥያቄያቸውን የላባቸውን ደመወዝ ስለጠየቁ ብቻ መምህራን መታሰራቸውን ሰምተናል ይህ ሲሆን እንኳን መፍትሄ እየተሰጠ አይደለም " ሲሉ አማረዋል።
ቃላቸውን የሰጡ መምህራን ፥" በሚዲያው መግለጫ ሳይሆን ተግባራዊ መሬት ላይ የሚወርድ መፍትሄ ብቻ ነው የምንፈልገው " ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
" ሰራተኛው ኑሮው ቢከድበውና የሚጮኽበት እዲሁም ችግሩን ሰምቶ መፍትሄ የሚሰጠው ቢያጣ ነው ወደሚዲያ የሚቀርበው ስለዚህ እባካችሁ ድምጻችንን ይሰማና መፍትሄ ስጡን " ሲሉ አክለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Sudan
ዛሬም ድረስ አሸናፊ ያልተገኘለትና ዳፋው ለጎረቤቶች ሀገራት ጭምር የተረፈው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት የብዙ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
በርካቶችም ጦርነትን ሽሽት ሀገር ጥለው ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል።
የሱዳን ከተሞች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።
ሀገሪቱ ያሏት መሰረተ ልማቶች እንዳልነበሩ ሆነዋል።
ኢኮኖሚው ደቋል፤ ሞቷል።
የሚበላ የሚላስ የሚቀመስ ያጣው ሱዳናዊ እጅግ ብዙ ነው።
ተፋላሚዎቹ ቁጭ ብለው እንዲነጋገሩ ብዙ ቢሞከረም እምቢኝ እንዳሉ ናቸው። ጦርነቱንም አፋፍመው ቀጥለዋል።
ከዓመት ባለፈው የእርስ በርስ ጦርነት አንድም አሸናፊ አልተገኘም። ይልቁንም ሱዳን እንዳልነበረች ሆናለች። ዳግም ለማንሰራራት በርካታ አመታት ይወስድባታል።
ከላይ የተያያዘው ቪድዮ በአንድ ከተማ ያለውን አስከፊ ገጽታ የሚያሳይ ነው።
@tikvahethiopia
" የአንድ አመት ከሁለት ወራት በላይ እልቂት ቀላል እልቂት አይደለም !! "
በአማራ ክልል ከአንድ አመት በላይ የሆነውን ጦርነት ዛሬም መቋጫ አላገኘም።
በየጊዜው በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በሚካሄዱ ውጊያዎች የበርካታ ሰዎች ህይወት እያለፈ ነው።
ንጸሃን የጦርነቱ ሰለባ መሆናቸው ቀጥሏል።
የሰብዓዊ መብት ተቋማት በሚያወጧቸው ሪፖርቶች በድሮን ጭምር በሚፈጸም ጥቃት ንጹሃን ሰለባ እየሆኑ ነው።
ሴቶችና ህጻናት ፣ በእድሜም የገፉ ዜጎች ከፍተኛ ጉዳትና ዋጋ እየከፈሉ ናቸው።
በክልሉ እና ከክልሉ ውጭ በተለያዩ ከተሞች ' የፋኖ ' ደጋፊ ናችሁ በሚል ለእስር ለእንግልት የተዳረጉ ዜጎች በርካቶች ናቸው።
ጤና ተቋማት ስራ መስራት አልቻሉም።
የጤና ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው። የመድሃኒት ችግር በስፋት አለ። በተለይ ግጭት ሲኖር ከከተማ በወጡ አካባቢዎች ፤ ከተማ ውስጥ ሳይቀር መድሃኒት እና የጤና አገልግሎት ማግኘት ፈተና ሆኗል።
ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን ለመከታተል አልቻሉም። ላለፉት ተከታታይ አመታት የአማራ ተማሪዎች እጅግ በስቃይ ውስጥ እያለፉ ናቸው።
ዘንድሮ ለ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪ ይመዘገባል ተብሎ የነበረ ቢሆንም እስካለፈው መስከረም 8 የተመዘገበው 2 ሚሊዮን 295 ሺህ 150 ተማሪ ብቻ ነው።
በክልሉ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም የግቢ ጥሪ ተራዝሞባቸው ያለ ትምህርት ቤታቸው ቀጭ ብለው ይገኛሉ።
በሰሜኑ ጦርነት ክፉኛ የተዳከመው የክልሉ ኢኮኖሚ አሁን ላይ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ሆኗል።
ገንዘብ ያላቸው ስራ መስራት አልቻልም በሚል ወደ አዲስ አበባ እየገቡ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ብዙ ተነግሯል።
ከቱሪስቶች ብዙ ገቢ ያስገባ የነበረው የአማራ ክልል አሁን ላይ ለጉብኝት ብሎ ወደ ክልሉ የሚጓዝ ተጓዥ አጥቷል።
የክልሉ አሁናዊ ፀጥታ ሁኔታ ሰዎች በማገት ገንዘብ ለሚቀበሉ አካላት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ በርካቶች ታግተው ከፍለው ወጥተዋል። አንዳንዶች ከፍለው ሁሉ ተገድለዋል። ህጻናት ሳይቀሩ እየታገቱ ገንዘብ ይጠየቃል።
በክልሉ በተለይ በገጠራማ አካባቢዎች ተጠያቂነት እና ስርዓት የሚባለው ነገር ከጠፋ ሰነባብቷል።
በአጠቃላይ ክልሉ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው።
ለመሆኑን በአማራ ክልል ያለውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድና በድርድር እንዲፈታ ያመቻቻል ተብሎ የተሰየመው የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል እስካሁን ምን አደረገ ? ይህ የብዙዎች ጥያቄ ነው።
ሰሞኑን የሰላም ካውንስሉን አግኘትን ምን እየሰራችሁ ነው ? ህዝቡ ከዚህ መከራ የሚወጣበት ተስፋስ አለው ወይ ? ችግሩ በሰላም ይፈታ ይሆን ? ስንል ጠይቀናል።
ካውንስሉ ምን አለ ?
➡️ችግሮቹ በአንድ ጀንበር የሚያልቁ ስላልሆኑ ጊዜ እየወሰደ ነው የመጣው። የፋኖ ታጣቂዎችም አንድ አመራር ፈጥረው የክልሉን ህዝብ ጥያቄ ማስመለስ የሚችሉት በድርድር ነው። ' ለአማራ ህዝብ ጥያቄ ነው የቆምነው ' ካሉ ጥያቄው ሊመለስ የሚችለው በጦርነት አይደለም። በድርድሩ በፋኖም በኩል ፍላጎት ያላቸው እንዳሉ ሁሉ ፍላጎት የሌላቸው ወገኖችም አሉ። ከመንግስት ጋር ለመደራደር ፍላጎት የሌላቸው ወገኖች ‘ በጦርነት እንገፋለን ’ የሚሉ ናቸው። ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ደግሞ ‘ አንድ ሆነን ለመምጣት ሁኔታዎችን እያመቻቸን ነው ’ የሚሉ፣ የመንግስትን ቁርጠኝነትም የሚጠይቁ ናቸው።
➡️ ለድርድሩ መንግስት ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ? የሚሉ ወገኖች አሉ። መንግስት ቁርጠኛ ነው ብለን ለማለት ፈቃደኝነቱ በክልል ደረጃ የታዬ ቢሆንም፣ በፌደራል ደረጃም እንድምታ በመግለጽ ረገድ የሚገለጽ ነው። ነገር ግን በመግለጫ ደረጃ በፌደራል መንግስት አለመሰጠቱን ግምት ውስጥ አስገብተን ችግሮቹ በሂደት ይፈታሉ። ሁለቱንም ወገኖች ለውይይቱ ዝግጁ ሆናችሁ በፈለጋችሁት ቦታ፣ በመረጣችሁት አደራዳሪ፣ በራሳችሁ ማኒፌስቶ ጥያቄያችሁን አቅርባችሁ ችግሩ ይፈታ ብለን አሳስበናል።
➡️ ችግሩ በድርድር እንዲፈታ ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ ከኢንተርናሽናል ኮሚዩኒቲ ጋር (ከአሜሪካ፣ ከኢጋድ ከካናዳ መንግስት) ግንኙነት አድርገናል። ‘ሁለቱም ኃይሎች ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር የበኩላችን እገዛ እናደርጋለን’ ብለዋል።
ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ አማራ ክልል ያለው የተኩስ ልውውጥ ጠንከር ብሎ ታይቷል። ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ድርድር በመምጣት ፋንታ ወደ ጠንካራ ጦርነት ያስገባቸው ያልተስማሙበት ጉዳይ ምንድን ነው ? በሚል ለካውንስሉ ጥያቄ ቀርቧል።
ካውንስሉ ምን ምላሽ ሰጠ ?
" ድርድር በየትኛውም መንገድ ሊከናወን ይችላል። እየተዋጉ መደራደር፣ ተኩስ እያቆሙ መደራደር፣ የበላይነትን ይዞ መደራደር የድርድሩ አንድ ፕሪንሲፕል ነው።
ምናልባት እየተዋጉም ቢደራደሩ ፣ ተኩስ አቁመውም ቢደራደሩ ይሄ ድርድርን በውስጥ ያዘለ ድርድር ማድረግ የሚያስችላቸው ሁኔታ ሊኖረው ይችላል።
አሁን ላይም እየተዋጉም ቢሆን ' እንደራደር ' ሊሉ ይችላሉ። ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም። ሁሌም ይዋጋሉ። 14 ወራት ሆናቸው። ይሄ ውጊያ ምንም አዲስ ነገር አይደለም። ከዚህ በፊት የነበረ ነው።
እኛ አሁን ይሄ እንዳይቀጥል ነው እየነገርን ያለነው። ሁለቱም ወገኖች በየጊዜው ውጊያ ያውጃሉ በሚዲያቸው እንሰማለን። ፋኖዎቹም ያውጃሉ፤ በመንግስትም አዲስ ነገር አይደለም። "
ድርድር ለማድረግ 2ቱም አካላት በሙሉ ሥምምነት ያልቀረቡባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች ምንድን ናቸው ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ካውንስሉ ተከታዩን መልሷል።
“ በህዝብ ዘንድ ያለውን የከፋ ስቃይ እንዲያዩ ነው የምንመክረው። ሁለቱም ወገኖች ደግሞ ማዬት ያልቻሉት ነገር ህዝብ አሁን ያለበትን ስቃይ ነው።
እኛ ደግሞ ህዝቡ በየቀኑ እየሞተ ፣ እየደቀቀ ፣ ህልውናውን ጭምር ፈተና ውስጥ የከተተበት ጊዜ መሆኑን እናያለን።
ህዝቡን አብረነው ስለምንኖር በስሚ ስሚ አይደለም የምንሰማው በዓይናችን የምናየው መጥፎ ተግባር ከአጠገባችን ነው ያለው።
ስለዚህ ህዝቡ ችግር ላይ መውደቁን ሁለቱም ማዬት አለባቸው። " ብሏል።
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መንግስት እና በታጠቁ ኃይሎች ለአብነት ከ " ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት / ሸኔ " ጋር ድርድር ተሞክሮ ያለ ውጤት ተቋጭቷል ፤ በአማራ ክልል ድርድር ቢደረግ ተመሳሳይ የሆነ እጣ ፈንታ እንዳያጋጥመው ምን ይሰራል በሚል ለቀረበው ጥያቄም ካውንስሉ ምላሹን ሰጥቷል።
ካውንስሉ ፦
“ አንዳንዶቹ ችግሮቹን በውይይት ለመፍታት ቶሎ ብለው ወደ ድርድር ይመጣሉ። መንግስት የኃይል የበላይነትን ባገኘ ጊዜ የዓለም ኃያላን የመጡበትና ትብብር የተደረገበት፣ ፈጥነው የመጡበት ሁኔታ ነበር።
ምክንያቱም መንግስት የኃይል የበላይነት ስላገኘ ነው።
‘ ህዝብ የሚፈልገው ጦርነት ነው ’ ብሎ ካመነ ‘ ድርድርም አልፈልግም ’ ይልና ሲዋጋ ይቆያል። ይሄ የስልጣኔ አካሄድ አይደለም።
ካለፈው ድርድር መማር፣ ከዚህ በላይ ህዝቡ ሳያልቅ ወደ ውይይት መምጣት ያስፈልጋል። የአንድ ዓመት ከሁለት ወራት በላይ እልቂት ቀላል እልቂት አይደለም። የደረሰብን ፈተናም ቀላል አይደለም።
አለመታደል ነው እኮ። መማር አለብን። ሕዝብ እየተመታ፣ ህዝብ እየወደመ፣ ህዝብ ልጁን እያጣ፣ ትምህርት ቤት እየተዘጋ…‘ህዝብ ይደግፈኛል’ ማለት ካለመረዳት የሚመነጭ እንጂ መፍትሄው በእጃቸው ነው። ሁለቱም ኃይሎች ለድርድር ይቅረቡ "
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
ጉዞው ሰላም ነው ፤ እዚህ የሃገር ዉስጥ የበረራ ጉዞ ላይ 5% ተመላሽ ሲጨመርበት ደግሞ ፤ በጣም ሰላም ነው ፤ የሃገር ዉስጥ በረራ ትኬታችንን በM-PESA ከፍለን 5% ተመላሽ አሁኑኑ እናግኝ !
የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#FurtherAheadTogether