tikvahethiopia | Неотсортированное

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519094

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Подписаться на канал

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

አዲስ አበባ በአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ የሀገራት መሪዎችን እየተቀበለች ትገኛለች።

እስካሁን ድረስ የየትኞች ሀገራት መሪዎች ገቡ ?

🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት
🇨🇮 የኮትዲቯር ም/ፕሬዜዳንት ቲሞኮ ሚዬሊ ኮኔ
🇰🇲 የኮሞሮስ ፕሬዜዳንት አዛሊ ኡሱማኒ
🇳🇬 የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ቦላ አሕመድ ቲኒቡ
🇸🇱 የሴራሊዮን ም/ፕሬዜዳንት  መሀመድ ዡሌ ዣሎህ
🇸🇿 የስዋቲኒ ጠ/ሚ ሩሴል ዲላሚኒ
🇹🇩 የቻድ ጠ/ሚ ሉክሴ ማስራ
🇨🇻 የኬፕቨርዴ ፕሬዜዳንት ጆሲ ማሪያ ፔሬራ ኔቬስ
🇹🇬 የቶጎ ጠ/ሚ ቪክቶር ቶሜጋህ ዶግቤ
🇷🇼 የሩዋንዳ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ
🇸🇴 የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
🇲🇷 የሞሪታኒያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኦውልድ ጋዙዋኒ
🇿🇦 የደቡብ አፍሪካ ሲሪል ራማፎሳ
🇦🇴 የአንጎላ ፕሬዜዳንት ዣኦ ኤማኑኤል ሌሪንሾ
🇹🇳 የቱኒዝያ ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ያቻኒ
🇩🇯 የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢሳሜኤል ኦማር ጌሌህ
🇧🇮 የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኤቨሪስቴ ዳይሺሚዬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የአፍሪካ የልማት ባንክ ፕሬዜዳንት ዶክተር አኪንውሚ አዴሲና እና የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለሕብረቱ ስብሰባ አዲስ አበባ ናቸው።

ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እየተጠበቁ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- /channel/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የመቐለው የመሬት የሊዝ ጨረታ ውጤት አሁንም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።

አንዱ ተጫራች ለአንድ ካሬ መሬት በብር 131,531  አሸናፊ ሲሆን ፤ ሌላው ተጫራች አራት ቦታዎች ማሸነፉ ፤ ሌላው የንግድ ተቋም በ14 ቦታዎች ለመጫረት መሳተፉ በይፋ የተለጠፈውና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመሰራጨት የሚገኘው የጨረታ ወጤት ያሳያል።

የመቐለ ከተማ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የስራ ሂደት የመሬት ሊዝ ጨረታ ቁጥር 69 የካቲት 7/2016 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ተከትሎ ተቃውሞዎች በመደመጥና በመነበብ ላይ ናቸው።

አንድ የመቐለ ከተማ ነዋሪ የከተማ እድገት አስተዳደር  / Urban managment/  ሙሁርና የዩኒቨርስቲ መምህር በማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፁ ባጋራው ፅሁፍ " በአፍሪካ ደረጃ የመሬት ዋጋ ሪከርድ የተሰበረ ይመስለኛል። በመቐለዋ የትግራይ ከተማ ለአንድ ካሬ መሬት በ131 ሺህ ብር ተሸጦዋል። ይህ ማለት የቤት መስሪያ ዋጋ ሳይጨምር ለ240 ካሬ ነፃ መሬት በብር 31 ሚሊዮን 440 ሺህ ተሸጠዋል " ይልና  በማስቀጠል  " ይህ ማለት የመካከለኛ የታችኛው ከፍል የከተማ ነዋሪ መሬት አግኝቶ ቤት የመስራት ህልምባ ፍላጎቱ የሚያቀጭጭ እጅግ የተጋነነ ዋጋ በመሆኑ የክልሉ አስተዳደር ለከት ሊያበጅለት ይገባል " ሲል ያክላል። 

ሌላው አስተያየት ሰጪ በበኩሉ "ይህ ኢ-ፍትሃዊ አካሄድ ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የሃፍት ክፍፍል የሚፈጥር ነው። ከተማዋ የተወሰኑት ሃብታሞች መፈንጫ እንድትሆን በማድረግ ሌላ የማህበራዊ ቀውስ እንዲፈጠር ያመቻቻል። ይህ ደግሞ ስርዓተ መንግስት ያበላሻል። " በማለት በመሬት ሊዝ ጨረታ በመታየት ያለው እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የማቅረብ ጉዳይ እንዲታሰብለት ሲል ምክርና አስተያየት ይሰጣል።

" የመሬት ሊዝ ጨረታ ውጤቱ በቤት ኪራይ ላለነው የመንግስት ሰራ ተቀጣሪዎች እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው ። እኛ የልጆቻችን የመግብ : የልብስ : የትራንስፓርትና የወርሃዊ የትምህርት ክፍያ መሸፈን አቅቶን እየተሰቃየን ለአንድ ካሬ መሬት በብር 131 ሺህ መግዛት ማለት የአኗኗር ልዩነታችን መራራቅ ማሳያ ነው " ትላለች ሌላኛዋ ሰምረት የተባለች የመቐለ ከተማ እንስት በማህበራዊ የትስስር ገፅዋ ባሰፈረችው ፅሁፍ።

የካቲት 7/2016 ዓ.ም ይፋ የሆነው የመቐለ ከተማ የመሬት የሊዝ ጨረታ ቁጥር 69 ለመኖሪያና ለንግድ ስራ አገልግሎት ተብለው ለጨረታ ለቀረቡት ቦታዎች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡ 231 ግለሰቦችና ድርጅቶች የተለየ ሲሆን : አሸናፊዎች ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 35 ከመቶ ቅድሚያ ቀሪው 65 ከመቶ ደግሞ ከ30 እስከ 50 ዓመታት አጠቃልለው እንዲከፍሉ ማስታወቅያው ይጠይቃል።

ማስታወቅያው በማያያዝ አሸናፊዎች የቅድምያ ክፍያ በመክፈል የመሬት ተጠቃሚነት የምስክር ወረቀትና ሳይት ፕላን  እንዲረከቡና ውል እንዲያስሩ ከየካቲት 11 _ 22/2016 ዓ.ም ባሉት 10 ቀናት እንዲገኙ ሲያሳስብ : ባልተገኙት የስረዛ እርምጃ እንደሚወስድ በአስተዳደሩ ፅህፈት ቤት በራፍ በለጠፈውና በተለያዩ የክልሉ ሚድያዎች ባሰራጨው ደብዳቤ ማስጠንቀቁ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል። 
                                       
@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አቢሲንያ_ባንክ

ፈጣን እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ እንሆ ብለናል።

ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ማስታወሻ

ለአዲስ አበባ ከተማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፦

1ኛ. የሞተር ባለንብረቶች እንዲሁም በሞተር እየተንቀሳቀሳችሁ ስራችሁን ለምትሰሩ አባላቶች ከነገ አርብ የካቲት 8 /2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰአት ድረስ ሞተር ማሽከርከር ፍፁም ተከልክሏል። የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ክልከላውን በሚተላለፉ ላይ " ጥብቅ እርምጃ እወስዳለሁ " ብሏል።

                                 __

2ኛ. ለአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ #መሪዎች ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት መሪዎች እስኪያልፉ ድረስ መንገዶች ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ሊዘጉ ይችላሉ።

ፖሊስ አማራጭ / ተለዋጭ መንገዶችን ተጠቀሙ ብሏል።

➡ ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ   ፍላሚንጎ  - ኦምሎፒያ  -  ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ - ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ - ኤርፖርት

➡ ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - በብሔራዊ ቤተ - መንግስት - በፍልውሃ - በብሔራዊ ቴአትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ

➡ ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር - ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት መንገዶች እንግዶች የሚያልፉባቸው ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ፦

☑ ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን

☑ ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ - አፍሪካ ህብረት ዋናው በር - ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ግራና ቀ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።
  
                                __

3ኛ. 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል። የ2024 መሪ ቃል ፤ " ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት " የሚል ነው።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Grade12NationalExam

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞ ምዝገባ በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል።

የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ምን አሉ ?

- የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት የመመዝገቢያ መስፈርቱን ማሟላት አለባቸው። በተቀመጠው የጊዜ ገድብ ውስጥም መምዝገብ አለባቸው።

- ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / አማካኝነት ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም
ይሆናል።

- በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው ብለዋል ፦

1ኛ. ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ አለባቸው። ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ።

2ኛ. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል አለባቸው።

3ኛ. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ አለባቸው።

4ኛ. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት ይሆናል።

5ኛ. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወርዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች ይሆናል።

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሀዋሳ

" ... በነዳጅ እጥረት ስራችንን መስራት አልቻልንም። ተሰልፈን ነው የምንውለው " - አሽከርካሪዎች

" ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ ነው ችግር የተፈጠረው " - የከተማው ገበያ ልማት

በሀዋሳ ከተማ የነበረዉ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረትና ሰልፍ ተስተካከለ ተብሎ ጥቂት ጊዜያት ሳይቆይ ድንገት ችግሩ ማገርሸቱን ተከትሎ መጨረሻ የሌላቸው የሚመስሉ ሰልፎች በየማደያዉ እየታዩ ነዉ።

በከተማው ኑሯቸዉን ከህዝብ ትራንስፖርት ጋር ያደረጉ አሽከርካሪዎች ፤ " አሁን አሁን በረዣዥም ሰልፍችና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራችን በአግባቡ መስራት አልቻልንም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎች እንደሚሉት ሁሉም ማደያዎች በአግባቡ አለመስራትና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ መኪኖች ለነዳጅ ሰልፍ ተገፍተዉ ከመግባት ባለፈ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሳልቫቲዮ ገጥመዉ መምጣታቸው ቀኑን ሙሉ ተሰልፈዉ እንኳን መቅዳት እንዳይችሉ ምክኒያት እንደሆነባቸው ይገልጻሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ የሀዋሳ ከተማ ገበያ ልማት ቢሮ የስነልኬት ባለሙያው አቶ ሀብታሙ መኮንን ፤ ችግሩ መኖሩን አምነው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ የተፈጠረው ክፍተት ለችግሩ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።

ችግሩ ወደፊት ይቀረፋል የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ ገልጸዋል።

ለህዝብ አገልግሎት የማይሰጡ ታክሲዎች ሰልፍ ዉስጥ እየገቡ ስለመሆኑ መረጃዉ እንዳላቸውና እነዚህን ተሽከርካሪዎች ለመቆጣጠር ከከተማዉ መንገድ ትራንስፖርት ጋር በመነጋገር እንቅስቃሴ መጀመሩን  ጠቁመዋል።

ሀዋሳ ከተማ እጅግ በርካታ የነዳጅ ማደያዎች ያሉባት ሲሆን ነዳጅ የሚቀዳው ግን በተለያየ የአሰራር ዘዴ ነው። ለአብነት ዛሬ አንዱ ማደያ ከቀዳ ፣ ነገ እዛ ላይቀዳ ይችላል። ተገልጋዮች ከተማው ያወጣውን መርሀ ግብር በቴሌግራም በማየት ነው ነዳጅ መቅዳት የሚችሉት።

ከዚህ ባለፈ እሁድ እሁድ እለት ነዳጅ  ማግኘት የማይታሰብ ነው።

በሌላ በኩል ፤ በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ በሃይላንድ እየተደረገ በየሱቁ የሚቸበቸብ ሲሆን ይህም ከመቶ ብር በላይ (110 ብር) ነው የሚሸጠው።

መረጃው አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Embrace the power of collaboration and ignite the flames of innovation! Become part of Jasiri's talent investor community, where visionary co-founders await to align with your ambition, together forging ventures from inception to triumph. Let's unite under #Jasiri4Africa to pioneer change, inspire entrepreneurship, and foster a culture of collaboration that shapes the future of Africa's business landscape.

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

10 ዓመት ?

የ13 ዓመት ልጃቸውን አስገድደው በመድፈር የኤች.አይ.ቪ ተጠቂ ያደረጉ አባት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን (በቀድሞው አማሮ ልዩ ወረዳ) ኬሌ 01 ቀበሌ በተለምዶ " ማክሰኞ ሰፈር " ተብሎ በሚጠራዎ አካባቢ አንድ አባት በመጋቢት ወር 2015 ዓ/ም ልጃቸውን አስገድደው በመድፈር የኤች.ቪ.ኤድስ ተጠቂ እንዳደረጉና በእስራት እንደተቀጡ የዞኑ ፎትህ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ወንጀሉን የፈጸሙት አቶ ስንታየሁ ከተማ መኮንን የተባሉ የ42 ዓመት አባት የአብራካቸው ክፋይ የ13 ዓመት 8ኛ ክፍል ተማሪ ልጃቸው ላይ ነበር።

በለበሰችው ሻርፕ አፏን አስሮ ኃይል ተጠቅሞ ደፍሯታል።

ልጅቷ በተደረገባት ድርጊት ማሕጸኗን ሕመም ሲሰማትና መቋቋም ባለመቻሏ የዐቃቢ ሕግ 2ኛ ምስክር ለሆነች ጎረቤቷ እያለቀሰችና እያነከሰች ሂዳ የተፈጸመባትን በዝርዝር ተናግራ ጎረቤቷም ወደ ሕክምና ተቋም አብረዋት ሂደው አስመርምረዋታል።

በምርመራውም በሕፃኗ ላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የመደፈር ወንጀል መፈጸሙንና የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በደሟ መገኘቱን በሕክምናው ተረጋግጧል።

የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጉዳዩን ሰምተውት የወንጀል ምርመራ አድርገዋል።

የኮሬ ዞን ከፍተኛ አቃቢ ሕግ ክስ በመመስረት ጉዳዩን በወቅቱ ለነበረው የአማሮ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሹም ወንጀል ስለመፈጸማቸው በችሎት ተጠይቀው ‘አልፈጸምኩም’ ብለው ክደው ተከራክረዋል።

በክርክሩ ልጅቷ የ13 ዓመት ታዳጊ በመሆኗ ከ5-20 ዓመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑና በልጅቷ ላይ ዛቻና እንግልት በመፈጸማቸው አባት ዋስትናቸው ተነፍጎ በፓሊስ እጅ ሆነው እንዲከራከሩ ተደርገዋል።

ፍርድ ቤት የልጅቷን፣ የዐቃቢ ሕግ ቃል ሰምቶ ምክሮችም እንደ ዐቃቢ ሕግ ክስ በዝርዝር ወንጀል ስለመፈጸሙ አስረድተው፣ የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮችም አባት ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ ለማስተባበል ቢሞክሩም በግልጽ ያስረዱት ነገር እንደሌለ ተመላክቷል።

በዚህም ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኝ የምስክር አመሰካከር፣ የቀረቡ የሕክምና ሰነዶች ከተገቢ ሕጎች ጋር አይቶ ግለሰቡም ጥፋተኛ ብሎ በሙሉ ድምፅ ፍርድ ሰጥቷል።

ዐቃቢ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ሲጠየቅ በሕጉ በራሱ ከብዶ የተዘረዘረ ስለሆነ የለኝም ያለ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቃ ፤ ቀደም ሲል ደንበኛቸው በወንጀል ተፈርዶበት የማያውቅ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ፣ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መድኃኒት ተጠቃሚ ስለሆነ ለፍርድ ቤቱ 3 ማቅለያዎችን አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኝ ተመልክቶ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ እንደወስነበት የዞኑ ፍትህ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ ያቀረበው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

@tikvahethiopia
 

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

@samcomptech

⭐  አሁንም  አዳዲስ  ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ብዛትም ጥራትም በአንድ ቦታ እኩል የተገናኙበት  ሁሉንም አይነት ላፕቶፕ የያዘ የላፕቶፕ መደብር  አለን።

🟥ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች, ለጌመሮች, ለቪዲዮ ኤዲተሮች ,ለግራፌክስ ዲዛይነሮች  አዳዲስ  ላፕቶፕች እና ስልኮች  በቅናሽ  ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ይዘን ቀርበናል።
🔵 @samcomptech

👏የሚገርም ፍጥነት ያላቸው ፣ ቀላል እና ከ 10 ሰዓት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖች አሉን ፦

ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል  የሜፈልጉትን ይምረጡ  ።

/channel/samcomptech             

@sww2844

☎️ 0928442662/ 0940141114

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

ከ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የሚኒስትሮች ስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪዎች ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀ ፦

➡ ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ - ኦምሎፒያ - ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ - ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ - ኤርፖርት

➡ ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሔራዊ ቤተ - መንግስት -በፍልውሃ - በብሔራዊ ቴአትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ

➡ ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር - ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት መንገዶቹ እንግዶች ሲያልፉ አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለእንግዶቹ ቅድሚያ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑና ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት ተላልፏል።

ከዚህ ባለፈ ፦

☑ ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን

☑ ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ-አፍሪካ ህብረት ዋናው በር-ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ሐሙስ የካቲት 7 ቀን / 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

በአዱስ አበባ አጎና የተነሳው እሳት መጀመሪያ ላይ ከነበረበት የወደ መጥፋት ደረጃ ቢቀንስም እሳቱ ሙሉ በሙሉ አልጠፋም።

በስፍራው የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እና ተሽከርካሪዎች የሚገኙ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስም አጋዥ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስፍራው በመላክ እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

የእሳት አደጋ በተነሳበት ህንፃ ላይ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚገኙበት ነው።

የአደጋው መንስኤ እና ሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ይኖር እንደሆነ እስካሁን በውል አልታወቀም።

መረጃውን የላኩት በስፍራው የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ናቸው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በተለያየ ሶሻል ሚዲያ አስቸኳይ ፓስፖርት እናወጣለን ከሚሉ ህገወጦች ራሳችሁን ጠብቁ ፤ ... በኦንላይ ምንም አይነት አስቸኳይ. ፓስፖርት አይሰጥም " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት ምን ያስፈልጋል / ለምን ምን ጉዳዮች ይሰጣል አለ ?

- የህክምና ማስረጃ
- የትምህርት ዕድል ማስረጃ
- ለመንግስት ስራ ጉዳይ ለስብሰባ፣ ለወርክሾኘ
- ጊዜው ያላለፈ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ለባል/ለሚስት/ለልጅ
- ለአስመጭና ላኪ /ከፍተኛ ግብር ከፋይ/
- ፓስፖርት ላይ ጊዜው ያላለፈ የተመታ ቪዛ ካለ /ለማሳደስ/

ከእነዚህ ሰነዶች በአንዱ ዋናው ቢሮ በአካል በመገኘት ብቻ የተሟላ ማስረጃ በመያዝ በአስቸኳይ መስተናገድ ይቻላል ሲል አሳውቋል።

ክፍያ የሚከፈለው በቢሮ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል።

ዜጎች በተለያየ ሶሻል ሚዲያ " አስቸኳይ ፓስፖርት እናወጣለን " ከሚሉ ህገወጦች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በኦን ላይን ምንም አይነት አስቸኳይ ፓስፖርት የማይሰጥ መሆኑንም ገልጾ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ በተጨማሪ ማሽነሪ/ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ለማከናወን አልተቻለም ” - የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ "018 አለኋት" ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ከ20 በላይ ወጣቶች የቆፈሩት አለት በመናዱ ያሉበትን አልታወቀም ስለተባሉት ወጣቶች ሁኔታ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዞኑን ኮሚዩኒኬሽን ዛሬ (ጥር 6 ቀን 2016 ዓ/ም) ጠይቋል።

የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኢያሱ ዮሐንስ በሰጡት ቃል፣ “በተጨማሪ ማሽነሪ/ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ለማከናወን አልተቻለም። ቁፋሮው ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው” ብለዋል።

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተሁኖ በትብብር ቁፋሮ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ እካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) “ከ50 ሜትር በላይ ቁፋሮ ተከናውኗል” ሲሉ ተናግረዋል።

ቁጥሩ በማኀበራዊ ሚዲያዎች ከፍና ዝቅ እያለ ነው፣ በትክክል ስንት ወጣቶች ናቸው የጠፉት? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ “ቁጥራቸው ከ20 ያላነሰ እንደሆነ ነው ያሉን መረጃዎች የሚያመላክቱት። አካባቢው ላይ ወጣቶቹ ስለሚታወቁ እንደዛ የሚል ነው የተሰጠን መረጃ” ብለዋል።

እስካሁን ምን የተገኘ ፍንጭ አለ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ኢያሱ፣ “የተገኘ ነገር የለም። በመግቢያነት የሚጠቀሙበትን የዋሻውን ክፍል መሠረት አድርገው ነው የአካባቢው አስተዳደሮች ቁፋሮ ለማድረግ እየሞከሩ ያሉት” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለውም፣ “ተስፋ ተደርጎም እየተሰራ ያለው ከሁለትና ከሦስት ዓመታት በፊት ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞ ከ11 ቀናት ቆይታ በኋላ አራት ወጣቶች በሕይወት ተገኝተዋል። አሁንም እንደዚህ አይነት ዕድል ቢገኝ ተብሎ ነው እየተሰራ ያለው። ጥረቱ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል” ነው ያሉት።

ከሦስት ዓመታት በፊት በነቀረው ክስተት ጠፍተው የነበሩ ወጣቶች በሕይወት ሊገኙ የቻሉት በምን ሁኔታ እንነበር ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽም፣ “ተመሳሳይ ነው፣ ሲቆፍሩ ዋሻው ተንዶ ነው እነዛም አደጋው አጋጥሟቸው የነበረው” ብለው፣ “ሁኔታው ከተሰማ በኋላ የአካባቢው ማኀበረሰብ እንዳሁኑ የቁፋሮ ስራ በማከናወን ነው ሕይወታቸውን ለማትረፍ የሞከረው” ሲሉ አውስተዋል።

አክለውም፣ “ሕይወታቸውንም ያጡ ወጣቶች ነበሩ። ነገር ግን በጊዜው ወደ አራት የሚደርሱ ወጣቶች ሕይወት ማግኘት ተችሎ ነበር” ሲሉ በአሁኑ ክስተት የጠፉ ወጣቶች ይገኛሉ የሚል ተስፋ ሰጪ ያሉትን የቀድሞ ክስተት አስታውሰዋል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ሲሆን፣ ሁኔታውን በመከታተል የምናሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#UPDATE

በትግራይ ፤ በመቐለ ከተማ በዓይደር ሆስፒታል የሚገኘው MRI ማሽን ለ3 ዓመታት ተበላሽቶ እንደነበረ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት መረጃዎቹ ማመላከቱ ይታወሳል። 

የመመርመሪያ ማሽኑ በመበላሸቱ ምክንያት አንድ ሰው ከትግራይ ውጭ ሄዶ ለመታከም እስከ 50 ሺህ ብር ወጪ ይጠይቀው እንደነበረ የሆስፒታሉ ሃኪሞች ገልፀዋል።

አሁን ላይ ለኣመታር ተበላሽቶ የነበረው MRI የህክምና መመርመሪያ ማሽን ተጠግኖ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል ተብሏል።

በተያያዘ ሆስፒታሉ ለዓዲግራት ሆስፒታል አንድ የልብ ህክምና ማሽን ፣ 8 የህሙማን አልጋዎች ፣ የኦክስጅን መሳርያ ጨምሮ ሌሎች የህክምና እቃዎች በእርዳታ ሰጥቷል።

የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከትግራይ ባሻገር ለዓፋርና ለአማራ አዋሳኝ አከባቢዎች ጭምር የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ በኢትዮጵያ ካሉ ግዙፍ ሆስፒታሎች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል ሲል የዘገበው  የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                
@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አዳዲስ የ ZTE ስልኮች ከአስደሳች ስጦታ ጋር!

የዜድ.ቲ.ኢ ብሌድ ቪ50 ዲዛይን ስማርት ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ሲገዙ የአንድ ዓመት 2 ጊ.ባ ወርሃዊ የዩትዩብ ጥቅልን ጨምሮ፣ ለተከታታይ ሶስት ወራት 5 ጊ.ባ ወርሃዊ ዳታ ከ 200 ደቂቃ የድምጽ ጥቅል ስጦታ እናበረክትልዎታለን፡፡

በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በመሄድ ወይም በቴሌገበያ ድረ ገጽ https://telegebeya.ethiotelecom.et/ ይግዙ!

#BeyondConnectivity
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

አዲስ አበባ በአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ የሀገራት መሪዎችን እየተቀበለች ትገኛለች።

እስካሁን ድረስ ፦

🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት
🇨🇮 የኮትዲቯር ም/ፕሬዜዳንት ቲሞኮ ሚዬሊ ኮኔ
🇰🇲 የኮሞሮስ ፕሬዜዳንት አዛሊ ኡሱማኒ
🇳🇬 የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ቦላ አሕመድ ቲኒቡ
🇸🇱 የሴራሊዮን ም/ፕሬዜዳንት  መሀመድ ዡሌ ዣሎህ
🇸🇿 የስዋቲኒ ጠ/ሚ ሩሴል ዲላሚኒ
🇹🇩 የቻድ ጠ/ሚ ሉክሴ ማስራ
🇨🇻 የኬፕቨርዴ ፕሬዜዳንት ጆሲ ማሪያ ፔሬራ ኔቬስ
🇹🇬 የቶጎ ጠ/ሚ ቪክቶር ቶሜጋህ ዶግቤ
🇷🇼 የሩዋንዳ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ
🇸🇴 የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
🇲🇷 የሞሪታኒያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኦውልድ ጋዙዋኒ
ገብተዋል።

የአፍሪካ የልማት ባንክ ፕሬዜዳንት ዶክተር አኪንውሚ አዴሲና ለሕብረቱ ስብሰባ አዲስ አበባ ደርሰዋል።

ሌሎች በርካታ የአፍሪካ መሪዎች እየተጠበቁ ይገኛሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አዲስ አበባ ውስጥ መሪዎች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች ተለይተው እንግዶችን እየተቀበሉና እያስተናገዱ የሚገኘ ሲሆን በየዙሪያው ምንም ስጋት እንዳይኖር ጥብቅ ጥበቃ እየተደረገላቸው ይገኛል።

በሌላ መረጃ አዲስ አበባ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሊውዝ  አኒሲዬ ሉላ ዳሲልቫን ተቀብላ እያስተናገደች ትገኛለች። ፕሬዜዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለሥራ ጉብኝት መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

@samcomptech

⭐  አሁንም  አዳዲስ  ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ብዛትም ጥራትም በአንድ ቦታ እኩል የተገናኙበት  ሁሉንም አይነት ላፕቶፕ የያዘ የላፕቶፕ መደብር  አለን።

🟥ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች, ለጌመሮች, ለቪዲዮ ኤዲተሮች ,ለግራፌክስ ዲዛይነሮች  አዳዲስ  ላፕቶፕች እና ስልኮች  በቅናሽ  ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ይዘን ቀርበናል።
🔵 @samcomptech

👏የሚገርም ፍጥነት ያላቸው ፣ ቀላል እና ከ 10 ሰዓት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖች አሉን ፦

ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል  የሜፈልጉትን ይምረጡ  ።

/channel/samcomptech             

@sww2844

☎️ 0928442662/ 0940141114

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ጥቆማ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ #በግል_ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ ማድረጉንም አሳውቋል።

" በግል ከፍለው የአውሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚማሩ ስልጠናውን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ " ያለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ብሏል።

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ፦ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም ፦
* በሂሳብ፣
* በእንግሊዘኛ
* በፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ

2ኛ. ዕድሜ ፦ 18 እና ከዚያ በላይ

3ኛ. እንግሊዘኛ ፦ ደረጃ 4

4ኛ. ቁመት፦ 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ

5ኛ. የጤና ሁኔታ፦ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት

የስልጠናው ርዝማኔ 1 አመት ከ 3 ወር ነው ተብሏል።

" የተደረገው ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ፤ " የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻ ፦ etauinfo@ethiopianairlines.com / eaainfo@ethiopianairlines.com ያነጋግሩን " ብሏል።

ስልክ በመደወል መረጃ ለመቀበል የምትፈልጉም +251-115174600/8598 ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን ድረገፅ መመልከት ይቻላል ፦ ethiopianaviationuniversity.azurewebsites.net/admission/applyonline

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ ስፍራ ምን ተፈጠረ ?

በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል የራያ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች በትጥቅ የተደገፈ ግጭት እንደነበረ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል።

የካቲት 6 / 2016 ዓ.ም የተቀሰቀሰው መጠነኛ ነው የተባለው ግጭት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ጥረት ሊቆም እንደቻለ ነው የተነገረው።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት ቃል ፤ " በትግራዩ የራያ ጨርጨር አከባቢ ታጣቂ ምልሻና  በአጎራባች የአማራ ክልል ራያ ቆቦ ምልሻ መካከል ለአጭር ጊዜ የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተከስቷል " ብለዋል።

የካቲት 6/2016 ዓ.ም  በሁለቱ ክልል አጎራባች የተካሄደው ለአጭር ጊዜ የቆየ ግጭት ትክክለኛ መነሻው በግልፅ የማይታወቅ ቢሆንም በሁለቱም ወገን የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።

በትግራይ በኩል ያሉ ፀሃፊዎች " የራያ ቆቦ ታጣቂዎች የትግራይ የራያ ጨርጨር ታጣቂ ምልሻዎች ትጥቅ ፍቱ " በማለታቸው የተነሳ ነው ብለዋል።

በአማራ በኩል ደግሞ የትግራይ ኃይሎች " መሬታችንን እናስመልሳለን " በማለት በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ከፍተው ነው ብለዋል።

የተፈጠረውና ለአጭር ጊዜ የቆየውን ግጭት በአከባቢው የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዳረጋጋው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በትግራይና በአማራ ክልል አዋሳኝ ስፍራ አጭር ጊዜ የቆየውን ግጭት የሰሙ የተለያዩ ነዋሪዎች ተግባሩ ከማውገዝ አልፈው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሳንካ እንዳይሆን ስጋታቸው እየገፁ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት በኩል ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

ምላሽ ለማግኘት ቢሮ ድረስ የሄድን ሲሆን ስልክም ብንደውል አይነሳም።

በአሁን ሰዓት በአማራ ክልል ስር እየተዳደረ የሚገኘውን የአላማጣ ከተማን እየመሩ ያሉት ከንቲባ ግን በአማራ ክልል በኩል ያለውን ማብራሪያ ገልጸውልናል።

ተቀሰቀሰ የተባለው የጸጥታ ችግር እውነት ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የአለማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ በሰጡት ቃል፣ " በእርግጥ  #እንቅስቃሴ ነበር ። ያው እንቅሰቃሴው ከሽፏል ። ወረራ ለማድረግ ሙከራ አድርገው ነበር " ብለዋል።

ከወደ ትግራይ ክልል በኩል ታጣቂዎች በባላ በኩል እንደመጡ የገለጹት ከንቲባው ፣ " ወደ ሁለት ቀበሌዎች ሰርገው ገብተው ነበር ተመትተው ተመልሰዋል " ብለዋል።

አሁን ላይ የሰላም መደፍረሱ እንደቆመ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ከንቲባው የሰጡትን ተጨማሪ ማብራሪያ ነገ የምናቀርብ ይሆናል።

ይህ መረጃ የተዘጋጀው በመቐለው እና በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ቅንጅት ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba #ጋብቻ #ፍቺ #ልደት #ሞት

በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት አፈፃፀም ከባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ቁጥር የላቀ የኩነት እና የዲጂታል ምዘገባ መመዝገቡን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ኤጀንሲው ፤ ከ393 ሺህ በላይ የዲጂታል ምዝገባ እና ከ210 ሺህ በላይ የኩነት ምዘገባ መደረጉን ነው የገለጸው።

ከተመዘገበው ጠቅላላ ኩነት ፦

➡ 181 ሺ 983 ልደት፣
➡ 16,933 ጋብቻ፣
➡ 2,813 ፍቺ
➡ 8,761 ሞት ሲሆን ከዚህም ውስጥ በአንድ ዓመት ገደብ ውስጥ የተመዘገበው ፦
* አዲስ ጋብቻ 5,171
* በፍርድ ቤት በተከናወነ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ የተመዘገበ ፍቺ 1,296
* ሞት 2,312 መሆኑ ታውቋል።

ከ2015 ዓመት በንፅፅር ሲታይ ፦ አዲስ ልደት በ65%፣ ፍቺ በ106.7% እንዲሁም ሞት በ25.29% ጭማሪ ብልጫ ያሳየ ሲሆን ጋብቻ በ5% የቀነሰ መሆኑ ተገምግሟል።

በነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ ለ393,303 ነዋሪዎች በአዲስ፣ በምትክ፣ በእርማት እና በእድሳት የመታወቂያ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን 311 ሺ 446 (93%) የዲጂታል  መታወቂያ መሆኑ በአፈፃፀሙ የተሻለ አድርጓታል።

በተጨማሪም በዚሁ ዘርፍ 76,299 የያላገባ  ማስረጃ እንዲሁም 15,369 የመሸኛ (Clearance ) አገልግሎት በከተማዋ ተሰጥቷል።

ከተመዘገበው ኩነት ትንተና በዕድሜ ሲታይ ፦

☑ ልደት
6% ከ1 ዓመት በታች፣
28% ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት፣
26% ከ6 ዓመት እስከ 17 ዓመት እንዲሁም
40% ከ17 ዓመት በላይ መሆናቸው ትንተናው ያመላክታል፡፡

☑ ጋብቻ
72.8% የሚሆነው ተገቢ ከ18 - 40 ዓመት
27.2% የሚሆነው ከ41 በላይ መሆኑ ትንተናው አሳይቷል።

☑ ሞት
0.01% ከተወለደ ከ28 ቀን እስከ 1 ዓመት የተከሰተ ሞት፣
0.6% ከተወለደ ከ2 ዓመት እስከ 17 ዓመት የሞተ፣
22.9% ከተወለደ  ከ18 ዓመት እስከ 40 ዓመት የሞተ፣
28.5% ከተወለደ ከ41 ዓመት እስከ 60 ዓመት የሞተ፣
35% ከተወለደ 61 ዓመት እስከ 80 ዓመት የሞተ፣
12% ከተወለደ 81 ዓመት እስከ 100 ዓመት የሞተ፣
0.9% ከተወለደ ከ100 ዓመት በላይ የሞተ መሆናቸው ያመላክታል፡፡ 

በስድስት ወራት አፈፃፀም በከተማው የዲጂታል ምዝገባ እና ልደት ምዝገባ የተሻለ አፈፃፀም የታየባቸው መሆኑ ተነግሯል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ምንም እንኳን የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም ፤ አገልግሎቱን በጥራት ከመስጠት አንፃር የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ከአፈፃፀሙ እኩል ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የቀሪ ወራት አቅጣጫ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#CBE

CashGo (ካሽ ጎ) - ከውጭ ሀገራት ገንዘብ መላኪያ የሞባይል መተግበሪያ
===========================
በሞባይል ስልክዎ አማካኝነት ቪዛና ማስተር ካርድዎን በመጠቀም

• ከውጭ ሀገር በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ወይም ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ መላክ ይችላሉ፣ አሊያም
• ተቀባዩ ከ1900 በላይ በሚሆኑት የባንካችን ቅርንጫፎች መቀበል ይችላሉ!
**************
የCashGo ሞባይል መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ይጠቀሙ።

• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US

• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ከጠቀማችሁ

ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ተሽከርካሪዎች የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በጨረታ ለመሸጥ ያቀረባቸው ናቸው።

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተለያዩ ፦
- ያገለገሉ ቀላል ተሽከርካሪዎች
- ያገለገሉ ከባድ ተሽክርካሪዎች ፤
- ቁርጥራጭ የመኪና አካላት (ስክራፕ) እና የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (ስክራፕ) ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ እስከ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከጠዋቱ 03:00 እስክ 10:00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ከበብ በመገኘት የተሽከርካሪ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረት (ስክራፕ) ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች እስከ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ/ም ባሉት ቀናቶች የሚሸጡትን ተሽከርካሪዎች ለማየት ኮፈን ተከፍቶ ስለሚቆይ ዘውትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 3:09 እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ቢሾፍቱ በሚገኘው አውቶሞቲቭ ካምፕ ጀርባ በመሄድ ሞያተኛ ይዞ መመልከት ይችላሉ።

ጨረታው የካቲት 18/2016 ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት የሚዘጋ ሲሆን  በዚያው ቀን 4:30 ይከፈታል። የሁሉም ተሽከርካሪዎች ጨረታ የሚከፈተው በመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ክበብ ነው።

አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው ከከፈሉ በኃላ ተሽከርካሪዎቹን በ30 የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ግዴታ አለባቸው።

ለስም ማዞሪያ ወጪ እና ብረታ ብረቶችን ከቦታው ለማንሳት የሚያስፈልግ ወጪ  ሙሉ በሙሉ በገዢዎቹ ነው የሚሸፈነው።

ቁርጥራጭ ብረቶችን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ብረታ ብርት የማቅለጥ ፍቃድ የተሰጠው ብቻ ነው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምናልባት ለስራም ሆነ ለግል ጉዳያችሁ ከጠቀመ በሚል ነው ይህን መረጃ ያጋራው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ቃጠሎ በደረሰበት ህንፃ ላይ ምንም አይነት የቤተክርስቲያን አገልግሎት አይሰጥም ፤ ይሄንን አረጋግጠናል ! " - አቶ ንጋቱ ማሞ

ትላንት ምሽት በአ/አ በቀድሞ አጎና ሲኒማ ህንፃ ላይ የተነሳው እሳት ለመቆጣጠር እጅግ ፈታኝ እንደነበር የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ አሳውቋል።

እሳቱን መቆጣጠር ከባድ ያደረገው በፍጥነት በመስፋፋቱ ነው ተብሏል።

በእሳት አደጋው የህንፃው አንደኛ እና ሁለተኛ ወለሎች ከነሙሉ ንብረታቸው ወድመዋል።

ህንፃው ላይ የነበረው የውጭ የትርጉም ፊልም የሚያቀርበው " ያ " የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሙሉ በሙሉ ንብረቱ የታቀጠለ ሲሆን ቤተክርስቲያን ላይ ጉዳት ደረሰ ተብሎ የተወራው ግን የተሳሳተ መረጃ ነው።

የእስት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያው አቶ ንጋቱ ማሞ ምን አሉ ?

- አደጋው በቀድሞ የአጎና ሲኒማ ህንፃ ላይ ነው የደረሰው።

- በአደጋው ምክንያት አንደኛ እና ሁለተኛ ፎቆ ላይ ያሉ ንብረቶችን ጨምሮ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

- ከባድ ጉዳት ከገጠማቸው መካከል ያ የቴሌቪዥን ስቱዲዮ የፕሮዳክሽን ስራ የሚሰሩበት ተጠቃሽ ነው።

- እሳቱ እኛ ከመድረሳችን አስቀድሞ የተስፋፋ ስለነበር በቀላሉ ለመቆጣጠር ችግር ነበር።

- ለስቱዲዮ ሳውንድፕሩፍ ተብሎ አገልግሎት ላይ የዋለ ስፖንጅ እና የመሳሰለው ቁሳቁስ ለእሳቱ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል። ለጊዜው ያላወቅነው በርካታ የፕላስቲክ ወንበሮች አንደኛ ፎቅ ላይ ነበሩ እነሱም ተደማምረው እሳቱ ሰፍቷል።

- በእኛ በኩል እሳቱ ተስፋፍቶ ሌሎች ቦታዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ ተችሏል። ይህ ሂደት 5 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ፈጅቷል።

- አደጋው ለመቆጣጠር ከተሰማሩት ሰራተኞች አንዱ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል።

ከዚሁ ከእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ውድመት ከደረሰባቸው ውስጥ በአንደኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ " ቤተክርስቲያን ይገኝበታል " በሚል የሚሰራጨውን መረጃ በተመለከተ ፤ " የተሳሳተ መረጃ ነው " ብለዋል።

" እስካሁን ማረጋገጥ የተቻለው ያ የቴሌቪዥን ስቱዲያውን ነው " ያሉት ባለሞያው " ሌሎች ህንፃው ላይ የነበሩ የንግድ እና አገልግሎት ሰጪዎችን እያጣራን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ንጋቱ ፤ " ከቤተክርስቲያን ጋር ተያይዞ በዚህ ቃጠሎ በደረሰበት ህንፃ ላይ ምንም አይነት የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚሰጥበት አይደለም። ይሄን አረጋግጠናል። ከእምነት ተቋም ጋር ተያይዞ ምንም አይነት አደጋ አላጋጠመም ይሄን አረጋግጠናል። " ሲሉ አሳውቀዋል።

አጠቃላይ በአደጋው ስለደረሰው ጉዳት እና መንስኤ እስካሁን አልታወቀም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የውሃ ሽታ

እጁ ላይ ባለው የማስታወሻ ፅሁፍ ብቻ ፀሎትን በደንብ አወቃት። የበለጠ ሊያውቃትም ፈለገ ሊያገኛት ግን አይችልም። በህይወት ያለን ገዳይ ፍለጋ ውስጥ በህይወት ከሌለችው ፀሎት ጋር በፍቅር….
እንዴት? ለምን? የፀሎት የውሃ ሽታ መሆን ሮቤልን አወዛገበው።

ዛሬ ምሽት በ3:00 ሰዓት

እርስዎ ባልተጠበቀ መንገድ የሞተ ሰው ማስታወሻ ቢያገኙ ምን ያደርጋሉ?

በ አቦል ቲቪ 465

ፓኬጅ: ሜዳ

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች  ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #YewehaSheta #የውሃሽታ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#መርዓዊ

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን ነው የተከላከለው ፤ ... የመከላከያ ኃይል የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረግም " - መንግሥት

መንግሥት በመርዓዊ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ጉዳይ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ መንግሥት በመርዓዊ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን የ45 (ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ይላል) ሰላማዊ ሰዎች ግድያ አስተባብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ቢያንስ 45 ሲቪሎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መገደላቸውን ፤  " የፋኖ አባላት ናቸው " በሚል ተጠርጥረው የተያዙ እና ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሰዎች በተመሳሳይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን ማሳወቁ ይታወሳል።

የንፁሃን ግድያን እንዲሁም የኢሰመኮን ሪፖርት በተመለከተ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ድርጊቱን አስተባብለዋል።

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፤ በመርዓዊ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር አረጋግጠዋል።

" ታጣቂዎቹ በተለያዩ አቅጣጫዎች መከላከያ ሠራዊቱ የሰፈረበትን ካምፕ በአራት አቅጣጫ በማፈን መሣሪያ እና ሎጂስቲኩን ለመዝረፍ በመንቀሳቀሳቸው ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ ነው እርምጃ ወስዷል " ሲሉ ተናግረዋል።  

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ እርምጃ ሲወስድ እነዚህ ኃይሎች ተመልሰው ወደ ግለሰቦች ቤት ነው የገቡት " ያሉት ዶ/ር ለገሰ " ወደ ግለሰቦች ቤት በሚገቡበት ጊዜ በሕጉ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አሰሳ ሲያደርግ መልሰው ተኩስ ከፈቱበት " ብለዋል።

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን ነው የተከላከለው " ያሉት ዶ/ር ለገሰ ፤ " የመከላከያ ኃይል የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረግም " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች መግለጫ ያወጡ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በመንግሥት የፀጥታ ኃይላት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰዎች መካከል ከቤት እየተወሰዱ የተገደሉ መኖራቸውን መግለፃቸው ይታወቃል።

ይህንን በተመለከተ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ፤ " እንደዚያ አይነት እርምጃ ስለመወሰዱ ተረጋግጦ የመጣ መረጃ የለም " ብለዋል።

አክለውም " ሲቪል ይቅርና ታጣቂ እንኳን ለማጥቃት ሄዶ እጅ እስከሰጠ ድረስ የሚገደልበት ሥርዓት የለም። ሊሆንም አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" እንዲህ ሆኖ ከሆነም ራሱ መከላከያ ተቋሙ እርምጃ ይወስዳል" ሲሉ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የመርዓዊን ግድያ በተመለከተ በኢትዮጵያ የካናዳ ኤምባሲ " እጅግ ያሳስበኛል " ብሏል።

ተፈጽሟል የተባለውን ግድያ " የሚረብሽ ነው " ያለው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ በበኩሉ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ መንግሥት በበኩላቸው ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ይህ ጉዳይ የሚመለከተው በአማራ ክልል የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ እንደሆነ አሳውቀዋል።

" በጉዳዩ ላይ ምርመራ የሚያደርግ ሌላ አካል አይኖርም " ሲሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ለገሰ ጥሪውን ያቀረቡት የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ መንግሥት " ስለ ኢትዮጵያ ሁሌ እንዳሳሰባቸው ነው። ነገር ግን ይኸ ነው የሚባል የሚደረግ ነገር የለም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። 

" የራሳችን ተቋሞች አሉ። ተቋሞቻችን ለሕዝብ ተጠያቂ ናቸው የትኛውም አካል ጥፋት ካጠፋ፤ የትኛውም አካል ጉዳት ካደረሰ ሕጉ እና አሠራሩ በሚፈቅደው መሠረት እርምጃ ይወሰዳል " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀምሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ ካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደተጀመረ ገልጿል።

በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል።

ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት ከተማ እየተሰጠ ሲሆን የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የተመደቡ ታዛቢዎች በየተመደቡበት ተቋማት በመገኘት ስራ መጀመራቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

የሁለተኛ ዙር ፈተናው ፦
- በ47 የመንግስት ተቋማት
- በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች ይፈተናሉ።

ፈተናው የካቲት 11/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አመላክቷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ አጎና አካባቢ (የጎተራ ኮንዶሚኒየም መግቢያ) በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ ምሽቱን የእሳት አደጋ መነሳቱን የአካባቢው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

የእሳት ደጋው ከተነሳ ከአንድ ሰዓት በላይ እንዳለፈውና የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እሳቱ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

እስካሁን በህንፃውን አንደኛው ጎን ውስጥ የነበሩ ንብረቶች እየወደሙ ይገኛሉ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ቆይ አንዴ.....

አዲሱን እለታዊ ኮምቦ ጥቅላችንን ሞክራቹታል?

ለመግዛት *777*3# እንደውል::

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

👉Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
👉Telegram: /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
👉LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia
👉Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
👉 Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
YouTube: safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm" rel="nofollow">https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm

Читать полностью…
Подписаться на канал