tikvahethiopia | Неотсортированное

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519094

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Подписаться на канал

TIKVAH-ETHIOPIA

8118 ይደውሉ!

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከክፍያ ነፃ የጥሪ ማዕከል ባንኩን የሚመለከቱ ማንኛውንም ጥያቄዎች በተለያዩ አማራጮች ለመመለስ ዝግጁ ሆነው ይጠብቅዎታል፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ጋር በተያያዘ ለኮንስትራክሽን እና ለጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

የተከለከሉ መንገዶች ፦

➡ ቦሌ ድልድይ አካባቢ
➡ ከቦሌ ድልድይ እሰከ ሩዋንዳ ድልድይ
➡ ከቦሌ ድልድይ በወሎ ሰፈር  ደንበል አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ
➡ ከመስቀል አደባባይ እስከ አራት ኪሎ
➡ ከኡራኤል አደባባይ እስከ አትላስ ሆቴል
➡ ከኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እስከ ልማት ባንከ
➡ ከአራት ኪሎ እስከ አምባሳደር መናፈሻ
➡ ከብሄራዊ ቴአትር እስከ ሜክሲኮ አደባባይ
➡ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እና
➡ ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እስከ ቡልጋሪያ ማዞሪያ  ባሉት መንገዶች ላይ ተለዋጭ መረጃ እስከሚተላለፍ ድረስ የኮንስትራክሽን ከባድ እና የጭነት ተሽከርካሪንዎችን ማሽከርከርም ሆነ ማቆም የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።

ይህን ትዕዛዝ ተላልፈው በተገኙት ላይ እርምጃ እንደሚወሰው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪዎች እና በኦፕሬተር የሚንቀሳቀሱ ማሽኖች ፦
* ጎማዎቻቸውን ሳያፀዱ መንገዶቹን እያበላሹ መሆኑን
* ለረጅም ጊዜ በመንገዶቹ ላይ በመቆም
* የሚጭኑትን አሽዋ ፣የቦካ  ሲሚንቶ እንዲሁም የግንባታ ግብአቶችን በአግባቡ ሳያስሩ እና ሳይሸፍኑ  እያፈሰሱ በመጓዝ በሚፈፅሙት የደንብ መተላለፍ ጥሰት የመንገዶቹ ውበት እየተበላሸ እና የአገልግሎት ዕድሜያቸው እያጠረ መምጣቱን ገልጿል።

በመሆኑም የትራፊክ ህግና ደንብን በማስከበር የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ባሻገር ጤናማ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እንዲሁም  በከተማዋ በቀጣይ ቀናት  ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የፀጥታ አካላት ለሚያከናውኑት የፀጥታ ስራ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ከላይ የተዘረዘሩት መንገዶች ለእነዚህ ተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Ethiopian women with visionary ideas, it's your time to shine!

Jasiri is on the lookout for female entrepreneurs with groundbreaking business concepts. If you have the vision to lead and the determination to succeed, we're ready to help you make that leap.

Apply now at jasiri.org/application and join a community where your ideas have the power to create change.

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ለወላይታ ሶዶ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ስራ ጨረታ ወጣ።

የወላይታ ሶዶ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት በአቅራቢያ ባለው በአረካ ከተማ ይሰራል ፤ ለዚህም ፕሮጀክት ሥራ ለሚወዳደሩ ጨረታ ወጥቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፤ በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል፤ አረካ ከተማ አቅራቢያ ለሚያስገነባው የወላይታ ሶዶ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ፦
* የምህንድስና ዲዛይን፣
* የግንባታ ቁጥጥር፣
* የኮንትራት አስተዳደር
* የግንባታ ማማከር አገልግሎት የሚሰጡ ደረጃ 1 የመንገድ  እና አጠቃላይ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እንደሚፈልግ አሳውቋን።

አየር መንገዱ ያወጣቸው ዝርዝር መስፈርቶች ምንድናቸው ?

መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ አማካሪዎች የአውሮፕላን ማረፊያ ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ተጋብዟል።

☑ ተጫራቾች በአገር ውስጥ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ተመዝግበው የማማከር አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው፤

☑ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው

☑ በዘርፉ ለመስራት ለ2016 ዓ.ም ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣   

☑ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤

☑ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ሆን አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T436 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ በዚህ የኢሜይል አድራሻ ፦ WoldeM@ethiopianairlines.com በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር (150,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለበር።

ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት እንደማይኖረው ተገልጿል። 

ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ሲሆን አየር መንገዱ  ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው ተብሏል። 

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው ተብሏል።

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የሠራተኞች መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል ተብሏል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ :- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ   ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላ  ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በስልክ ቁጥር 011-517-8025 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

@samcomptech

⭐  አሁንም  አዳዲስ  ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ብዛትም ጥራትም በአንድ ቦታ እኩል የተገናኙበት  ሁሉንም አይነት ላፕቶፕ የያዘ የላፕቶፕ መደብር  አለን።

🟥ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች, ለጌመሮች, ለቪዲዮ ኤዲተሮች ,ለግራፌክስ ዲዛይነሮች  አዳዲስ  ላፕቶፕች እና ስልኮች  በቅናሽ  ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ይዘን ቀርበናል።
🔵 @samcomptech

👏የሚገርም ፍጥነት ያላቸው ፣ ቀላል እና ከ 10 ሰዓት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖች አሉን ፦

ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል  የሜፈልጉትን ይምረጡ  ።

/channel/samcomptech             

@sww2844

☎️ 0928442662/ 0940141114

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ' ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል ' እንዲሁም የ ' ፋኖ አባላት ናቸው ' በሚል ሲቪሎች ተገድለዋል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ በአማራ ክልል አሳሳቢነቱ ስለቀጠለው የትጥቅ ግጭት እና በሲቪል ሰዎች ላይ ስለተፈፀመው ከሕግ ውጭ ግድያ  ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ፤ የመንግሥት ኃይሎች በሰሜን ጎጃም ዞን፤ መርዓዊ ከተማ ከህግ ውጭ ግድያ መፈፀማቸውን አሳውቋል። እስካሁን ማንነታቸውን ለይቶ በተረጋገጠው 45 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። ቁጥሩ ግን ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ጠቁሟል።

ኢሰመኮ ምን አለ ?

- በመርዓዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ኃይሎች (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚጠሩት) መካከል ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ውጊያ ተካሂደ ነበር።

- እስከ አሁን ድረስ በተደረገ ክትትል ኮሚሽኑ ማንነታቸውን ማረጋገጥ የቻላቸውን ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎችን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች " ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል '' በሚል ምክንያት ከሕግ ውጭ ገድለዋል።

- " የፋኖ አባላት ናቸው " በሚል ተጠርጥረው የተያዙ እና ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሰዎች በተመሳሳይ ሁኔታ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

- እስከአሁን ድረስ ማንነታቸውን በመለየት ለማረጋገጥ የተቻለው 45 ሲቪል ሰዎችን ብቻ ሲሆን፤ ነገር ግን የጉዳቱ መጠን ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል ምክንያታዊ ግምት ለመውሰድ ተችሏል።

- ምስክሮች በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ ለኢሰመኮ ሲገልጹ፣ ለቀን ሥራ በጠዋት ከቤታቸው ወጥተው ድንገት ተኩስ ሲከፈት በአንድ ቦታ ተጠልለው የነበሩ 18 ሲቪል ሰዎች የተገደሉ መሆኑን ገልጸዋል።

- ምስክሮች ቀበሌ 02 አካባቢ በተለምዶ ሚሊኒየም ተብሎ በሚጠራ ሰፈር አንድ የጠፋ አባልን ሲያፈላልጉ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች " በፍለጋው አልተባበሩም " ያሏቸውን 8 ሲቪል ሰዎችን መግደላቸውን እንዲሁም 12 ባጃጆች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መቃጠላቸውን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ፦

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሽበል በረንታ ወረዳ የዕድውኃ ከተማ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው ከወጡ በኋላ ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ፣ እንዲሁም መንገድ ላይ የተገኙ ቢያንስ 15 ሰዎች (ሴቶችን ጨምሮ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ ተገድለዋል።

በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቋሪት ወረዳ፣ ወይበይኝ ቀበሌ፣ አብሥራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ለወታደራዊ ቅኝት በአካባቢው የተሰማሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሳ 6 ሲቪል ሰዎችን ከየቤታቸው አውጥተው ከሕግ ውጭ እንደገደሏቸው ምስክሮች ለኢሰመኮ አስረድተዋል፡፡

(ከኢሰመኮ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ምን አሉ ?

ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ከ2 ሳምንት በፊት በወላይታ ሶዶ ሆቴላቸው ባስመረቁበት ዕለት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ነበራቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በዋነኝነት ያነሳው ከፀጥታ ጋር በተገናኘ በስራቸው ላይ እየተፈጠረ ስላለው ተግዳሮት ነው።

ሻለቃ ኃይሌ የጎንደር ኃይሌ ሪዞርትን በተመለከተ ፤ " 56 ሩሞች አሉኝ፣ አራትም አምስትም ሰዎች እያደሩበት ነው " ብለዋል።

ይህም በክልሉ የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር እንደሆነ ጠቁመዋል።

ገቢው በምን ያህል ቀንሷል ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ " አለ እንዴ ለመሆኑ ቢዝነሱ " ብለው፣ " 56፣ 57 ሩም ተይዞ አምስት ሰዎች ስላሳደርክ ምንድን ነው ገቢው ? በግማሽ ፐርሰንት ነው ? በምን ፐርሰንት ነው? አላውቅም " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ፦

- እኔ አሁን እንደዚህ ሳወራ ‘እሱ ደግሞ ስለ ሆቴል ያወራል እንዴ? ሰው እንደዚህ እየሞተ’ ሊባል ይችላል። አዎ ልክ ነው። ሰው እየሞተ ነው። ግን እኔ ኃላፊነት አለብኝ እዛ ውስጥ ላሉ #ሠራተኞች።

- የሆቴል ቢዝነስ የሚበረታታ አይደለም። የገበያው መጥፋት አንዱ Problem ሆኖ፣ Major Problem ደግሞ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች መወደድ ነው። ከውጭ ማምጣት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። ብናመጣም በጣም ጥቃቅን ነገሮችን ነው።

- አሁን እኮ ባይገርምህ የምንበላበት ሰራሚክ ሰሀን ነው እያጣን ያለነው። ይሄ ለምን ሆነ ? አትልም የጋራ ችግር ነው። 

- ቁጥር አንድ የጸጥታውን ችግር ማስቆም። የጸጥታው ችግር ካልቆመ እንኳን ቱሪስት እኛም ወደዚህ ለመምጣት (ወደ ወላይታ ሶዶ) አልቻልንም።

- በ24 ሰዓት አርባምንጭ ደርሸ ስራየን እሰራ ነበር። የዛሬ 6 ዓመት አሁን ግን ያ ተረትተረት ሁኖ ቀርቷል። ወደዛ ዓመት ካልተመለስን ምንም ዋጋ የለውም።

- ይኼ ነገር እስካልሆነ ድረስ እንዳውም አሁን Instead of that ሆቴሎች እየተዘጉ እያየን እኛ አሁን እያዋጣችሁ ነው የምትከፍቱ ? ያልከኝ እንደሆነ ተስፋ አለን።

- የዛሬ 8 ዓመት በአንድ ቀን ሌሊት 2 ሆቴሎች ሲቃጠሉ ባለቤት ሊኖረው ይገባል።

- እኔ እየተወጣሁ፣ ‘ይሄንን ቀጥረህ አሰርተህ፣ ይሄንን እንዲህ አድርግ’ ሳይሆን፣ ዋናው ኢምፓርታንቱ ታክስ እየከፈልኩ ነው።  ታክስ ስከፍል ደግሞ መጠበቅ፣ ችግር ደግሞ ሲገጥመኝ መንግሥት እንደ መንግሥት ‘ኦ ይሄ እኮ ግለሰቤ ታክስ ሳስከፍለው ኑሬአያለሁ፣ አሁን ደግሞ እኔ ሰላሙንና ፀጥታውን ደግሞ በአግባቡ ባለመወጣቴ ለዚህ መክፈል አለብኝ’ ብሎ ማሰብ አለበት።

- እኔ አላቃጠልኩትም መንግሥት እንደ መንግሥት መወጣት ነበረበት። እኛ ለብዙ ዓመታት እንግዲህ በኢንቨስትመንት ተሰማርተን ትልቅ ስራ እየሰራን ነው።

- እኔ ብቻ አይደለሁም ብዙ ሰዎች እንባቸውን አፍሰው ወደ ላይ እረጭተው ተቀምጠዋል። ይሄ ደግሞ ትክክል አይደለም። አትሊስት እንደ መንግሥት ኃላፊነት የሆነ ነገር መደረግ አለበት እንጅ።

- ዛሬ ለመውቀስ አይደለም። አይደለም ይሄ እንዳው ዝም ተብሎ እንኳ የሆነ ተራ ጨርቅ እንኳ ተቃጥሎ ያስቆጫል። 

- እኔ አሁን ሻሸመኔ ላይ ስመጣ ሁል ጊዜ እዛ ግቢ በር ያ ሁሉ እቃ ተቃጥሎ ተከምሯል። በእውነት እንደ ልማት ያው እኔ ብቻ አይደለሁም የሀገር ሀብት ነው የሀገር ልፋት ነው።

ያንብቡ ፦https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-02-12

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አቢሲንያ_ባንክ

በቨርችዋል ባንካችን 24/7 ገንዘብ ማስገባት ይችላሉ።


አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ትግራይ

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው እለት በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ቃለመጠይቅ ለክልሉ ሚድያዎች ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ተሳትፎውበት ከፌደራል መንግስት ጋር በአዲስ አበባ ስለተካሄደው ውይይትና ውጤት አስመልክቶ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

አቶ ጌታቸው ፤ " ለፌደራል መንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፓርት አቅርበናል። በአከባቢያችን ያለው ፓለቲካዊ ሁኔታ እጅግ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ እንደ አገር የውስጥ ሰላማችን መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባ ከፌደራል መንግስት ጋር መግባባት  ተደርሷል " ብለዋል።

ከፌደራል መንግስት በተካሄደው ውይይት በሃይል ስለተያዙ የትግራይ ግዛቶች መነሳቱ ያብራሩት ፕረዚደንቱ " በተለይ በምዕራባዊ ዞን  በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰፋሪዎች በሰፈሩበት፤ የፌደራል ተቋማት ዴሞግራፊ ለመቀየር በሚንቀሳቀሱበትና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባልተመለሱበት ፤ መፍረስ የሚገባቸው ሳይፈርሱ ፤ ህዝባችን ነፃ ባልወጣበት ሁኔታ ሪፈረንደም ማድረግ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ወር መጋቢት የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትና የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በተገኙት የፕሪቶሪያ ስምምነት አተገባበር ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል ያሉት አቶ  ጌታቸው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለውይይቱ ስኬት የበኩሉ አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ህወሓት መልሶ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ የመመዝገብ ጉዳይ የሚመለከት ጥያቄም ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም፤ ከህወሓት የፓለቲካ ፓርቲነት ምዝገባ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ የፌደራል መንግስት እንደማይደግፈው በመግለፅ ያለው የህግ ክፍተት በአስቸኳይ ታርሞ ምዝገባው እንዲፈፀም ጉዳዩ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተመርቷል ብለዋል።

መረጃውን የትግራይ ሚድያዎችን ዋቢ አድርጎ ያዘጋጀድ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                 
@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በሞባይል ስልክዎ Wegagen Mobile መተግበሪያ ከፕለይስቶር ወይም ከአፕስቶር በማውረድ ምቾትዎ ተጠብቆ ሂሳብዎን ያንቀሳቅሱ ፡፡
ወጋገን ሞባይል ደህንነቱ የተጠበቀ መተግበሪያ ሲሆን ደንበኞች የሚከተሉትን አገልግሎቶች እንዲያገኙ ያስችላል፡፡
👉 በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሆነው ገንዘብ መላክና መቀበል ፣
👉 የሞባይል ስልክ በመጠቀም የሒሳባቸውን እንቅስቃሴ መከታተል፣
👉 ግብይት መፈፀም እና ገንዘብ ማስተላለፍ ፣
👉 በአምስት የቋንቋ አማራጮች አገልግሎት ማግኘት፣
👉 ለተለያዩ ከባንኩ ጋር ለሚሰሩ የተራድኦ ድርጅቶች የገንዘብ ልገሳ ማድረግ ፣
👉 የበረራ ቲኬት መቁረጥ ፣
👉 የትምህርት ቤት፣ የውኃ እና የተለያዩ አገልግሎቶች ፍጆታ ክፍያ መፈፀም ፣
👉 ገንዘብ ቴሌብርን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ማስተላለፍ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት ያስችላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ
#WegagenBank #WegagenMobile #MobileBanking
Follow us and get more information...
https://linktr.ee/WegagenBank

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ውጤት አልተገኘም "

ደቡብ ወሎ ዞን ፣ ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በርካታ ሰዎች ለማውጣት የሚደረገው ጥረት 4 ቀኑን እንደያዘ ተነግሯል።

የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የከበረ ማዕድን አውጪዎች ማኅበር በሰጡት ቃል  ፤ በቁጥር ከ8 እስከ 30 የሚገመቱትን ሰዎች ለማውጣት የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን ውጤት አልተገኘም።

የወገል ጤና ከተማ አስተዳደር ፍለጋውን በማሽን ለማገዝ የአካባቢው መልከዓ ምድር ምቹ ባለመሆኑ ጥረቱን አዳጋች እንዳደረገው አሳስውቋል።

በሕጋዊ መንገድ ተሰማርተው በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ናዳ የተጫናቸው ከ4 ቀናት በፊት ነበር።

ሌሎች የአካባቢው ወጣቶችም አብረው ሳይኖሩ እንዳልቀረ ተነግሯል።

አሁን ወጣቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም።

የወረዳው አስተዳዳር ባለፉት ቀናት ከ500 በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም፣ ወደ ዋሻው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከ10 ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥሩቱ አዝጋሚ ነው ሲል ገልጿል።

ወርቅ ዋሻ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ፤ በናዳው ተይዘው ከሚገኙት 8ቱ የማኅበሩ አባላት ናቸው ያለ ሲሆን እስካሁን በተደረገው ጥረት 150 ሜትር ርዝማኔ ወዳለው ዋሻ ዘልቆ ለመግባት መቆፈር የተቻለው 33 ሜትር ገደማ ብቻ ነው።

" የአካባቢው ሕዝብ ሌት ተቀን ርብርብ እያደረገ ነው " ያለው ማህበሩ በመንግሥት በኩል የተቀበሩትን ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅም ሆነ ከዋሻው ለማውጣት የተደረገ ድጋፍ የለም ብሏል።

የወገል ጤና አስተዳደር ግን የከተማ እና የወረዳው አመራሮች በሥፍራው እንደሚገኙ አስታውቆ ፤ " በቂ ድጋፍ ማድረግ ያልተቻለው አማራጭ ስለሌለ ነው " ሲል ገልጿል።

" ጥረቱን በማሽን ለማገዝ አልተቻለም፤ ማዕድን አውጪዎቹም ባህላዊ ማዕድን አምራች ተብለው የተሰማሩት ቦታው ከባህላዊ ቁፋሮ ውጪ የሚቻል ባለመሆኑ ነው። ቦታው ለእግር መንገድ እንኳን ምቹ አይደለም " ብሏል አስተዳደሩ።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ብርሃን ዘኢትዮጵያ "

የዓድዋ ድል ሲነሳ ስማቸው በግንባር ቀደምነት ከሚነሳው አንዱ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ናቸው።

" ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉም ይጠራሉ።

ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ የተወለዱት እቴጌ ጣይቱ በጊዜያቸው በሀገር አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ፣ ለዓድዋ ጦርነት ድል መሳካት ሚናቸው ከፍተኛ ነበር ፣ የውጫሌ ውል ችግር እንዳለበት በመረዳት እንዲሰረዝ ከፍተኛ ሙግት አድርገዋል፣ የዓድዋ ጦርነት እንደማይቀር ሲያቅዉም የአዲስ አበባ ሴቶችን በማስተባበር ሎጅስቲክስ አዘጋጅተዋል፤ ወደ ጦርነት ስፍራም የተመደበላቸውን ጦር  እየመሩ ተመዋል።

ከዚህ ባለፈም ለዛሬዋ የኢትዮጵያ መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ ምስረታ መሰረት የጣሉ ናቸው።

በርካታ ሴቶችም እቴጌ ጣይቱን በነበራቸው ብርታት፣ ብልህነት፣ ጥንካሬ፣ ሀገር ወዳድነት እንደ ዓርአያ ይመለከቷቸዋል።

እቴጌ ጣይቱ ልክ በዛሬው ቀን የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ/ም ነው  ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

ለክብራቸው እና ለሀገር ባለውለታነታቸው በደብረ ታቦር እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ (የዓድዋ ድል መታሰቢያ ማዕከል) ሃውልት ቆሞላቸዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Training on Artificial Intelligence using Python Programming and Google Colab

Few days left to register and few available spaces left to fill.

Register Now or join our telegram channel for more information @TrainingAAiT

By: School of Electrical & Computer Engineering at Addis Ababa University

Registration Deadline:
12 February, 2024

Training Starts on:
19 February, 2024

Registration:
Online Registration Link:
https://forms.gle/bdR6GUWVEUNwGHCq7

In Person Registration: 
Addis Ababa Institute of Technology (5 Kilo),
School of Electrical and Computer Engineering,
Main Building 1st Floor, Office Number: 124

Telephone: +251-940-182870 / +251-913-574525

Email: sece.training@aait.edu.et / menore.tekeba@aait.edu.et

Telegram Channel: /channel/TrainingAAiT

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በወንድሜ አንተነህ ጌታሁን ጉዳይ ፍርድቤት ለሁለተኛ ጊዜ የዋስ መብት ቢፈቅድም ፖሊስ ሊፈታልን አልቻለም " - ዳግም ጌታሁን

" ተጨማሪ ምርመራ በማስፈለጉ ፖሊስ ህጋዊ መንገድ ተጠቅሞ ተጠርጣሪዉን ሊያቆየዉ ችሏል " - ፖሊስ

አንተነህ ጌታሁን የተባለ ወጣት በሀዋሳ ከተማ " በሶሻል ሚዲያ የምትጽፈዉ ጽሁፍ ወጣቱን ለሽብር ያነሳሳል !! " በሚል በቀን 26/05/2016 ከጓደኞቹ ጋር በሚዝናናበት ወቅት በፖሊስ ተይዞ ታስሯል።

ይህ ወጣት አንተነህ ጌታሁን ሁለተኛ ጊዜ ፍ/ቤት ቀርቦ የዋስ መብቱ ቢከበርም ፖሊስ ሊፈታዉ ፈቃደኛ አልሆነም ሲል ወንድሙ ዳግም ጌታሁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" እሁድ ምሽት ከጓደኞቹ ጋር በመዝናናት ላይ እንዳለ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ለጥያቄ ትፈለጋለህ " በሚል ወሰዱት የሚለዉ ዳግም " የቀረበበት ክስ ተጨባጭ መረጃ የለዉም በሚል ፍ/ቤቱ የዋስ መብቱን ለ2ኛ ጊዜ መፍቀዱን ተከትሎ የታዘዘዉን 50 ሺህ ብር ብናስይዝም ወንድሜ ሊፈታ አልቻለም " ብሏል።

ወንድሙ የታሰረበት ዳግም ጌታሁን ፤ " እየመጡ ነው !! " በሚል የፋኖ ኃይሎችን የሚደግፍ ፅሁፍ በፌስቡክ ፅፈሃል በሚል እንደሆነ ተናግሯል።

በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የመምሪያዉ ፖሊስ አዛዣ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ እንደገለጹት ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ በህጋዊ መንገድ ተጨማሪ ጊዜ ተጠይቆበት ተጠርጣሪዉ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዉ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

አቶ አንተነህ ለሶስተኛ ጊዜ ነገ ሰኞ ፍርድቤት ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጉዳዩን ተከታትለን የምንዘግብ ይሆናል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#CBE

እጥፍ ወለድ....
********
ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ፤
አዲሱን የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱ!

• ከመደበኛው ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል ፣
• ለውጭ ሀገር ጉዞዎ ቅድሚያ የውጪ ምንዛሬ አገልግሎት እና
• የሞባይል ካርድ ስጦታም ያገኛሉ ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
***********

የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- /channel/combankethofficial

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

የሞተር እንቅስቃሴ ላይ ክልከላ ተጣለ።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሞተር ብስክሌተኞች በሙሉ ከአርብ የካቲት 08/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋት 2:00 ሰአት ድረስ በከተማዋ ውስጥ ሞተር ብስክሌት በፍጹም ማሽከርከር እንደማይችሉ የትራንስፖርት ቢሮ ክልከላ ጥሏል።

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አይመለከትም ተብሏል።

" የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ " ያለው ቢሮው " ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

@samcomptech

⭐  አሁንም  አዳዲስ  ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ብዛትም ጥራትም በአንድ ቦታ እኩል የተገናኙበት  ሁሉንም አይነት ላፕቶፕ የያዘ የላፕቶፕ መደብር  አለን።

🟥ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች, ለጌመሮች, ለቪዲዮ ኤዲተሮች ,ለግራፌክስ ዲዛይነሮች  አዳዲስ  ላፕቶፕች እና ስልኮች  በቅናሽ  ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ይዘን ቀርበናል።
🔵 @samcomptech

👏የሚገርም ፍጥነት ያላቸው ፣ ቀላል እና ከ 10 ሰዓት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖች አሉን ፦

ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል  የሜፈልጉትን ይምረጡ  ።

/channel/samcomptech             

@sww2844

☎️ 0928442662/ 0940141114

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6 እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ድረስ ይሰጣል።

የ2016 ዓ/ም የአመቱ አጋማሽ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከነገ ረቡዕ የካቲት 6 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ተልኮልናል ብለው ያጋሩትን የተሻሻለ የፈተና መርሃ ግብር የተመለከተ ሲሆን በዚህ መርሀ ግብር ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እስካ የካቲት 11 /2016 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

በፈተናው የመጀመሪያ ቀን በሺዎች የሚቆጠሩ የጤና ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ተላከልን ብለው አጋርተውት በተመለከትነው ዳታ ከ6 ሺህ በላይ የነርሲንግ፣ ከ1 ሺህ 900 በላይ የፋርማሲ፣ ከ1 ሺህ 700 በላይ የዶክተር ኦፍ ሜዲስን ተማሪዎች በመጀመሪያው ቀን ፈተናቸውን ከሚወስዱት ውስጥና ከፍተኛውን ቁጥር ከሚይዙት የጤና ትምህርት ዘርፍ ውስጥ ይገኙበታል።

ከዚህ ባለፈ በዘንድሮው የመውጫ ፈተና ከፍተኛ ተፈታኝ ከሚጠበቅባቸው የትምህርት ክፍሎች መካከል አካውንቲንግ ከ8 ሺህ በላይ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ ከ3 ሺህ በላይ ፣ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

በአመቱ አጋማሽ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በአጠቃላይ በሺዎች የማቆጠሩ የመጀመሪያ ዙር እንዲሁም ባለፈው ፈተና ውጤት ሳያመጡ የቀሩ የድጋሜ ተፈታኞች የሚወስዱ ይሆናል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በአጠቃላይ ፈተናው 47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች ይፈተናሉ።

በሌላ ለኩል ከጥቂት ቀናት በፊት ፤ " በኦንላይን ለሚሰጥ የአንድ ቀን ፈተና በመቶዎች ኪሎ ሜትር ተጉዘን እንድንፈተን ተነገረን " በሚል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን ያሰሙ ተመራቂዎች አሁን ላይ ፈተናውን ባሉበት ከተማ በተቋማቸው እንዲወስዱ ማስተካከያ መደረጉንና ስም ዝርዝራቸውም መውጣቱን ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚል ከባለፈው አመት ጀምሮ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ (በአመቱ መጨረሻና አጋማሽ) ላይ ይሰጣል።

(ከላይ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር እንደተላከላቸው የገለፁትን የ2016 የአመቱ አጋማሽ ተሻሻለ የፈተና መርሀ ግብርን አይዘናል)

ከተፈታኞች እና ከፈታኞች ምን ይጠበቃል ? አምና በነበረው ፈተና ከትምህርት ሚኒስቴር የተላለፈው ትዕዛዝ በዚህ መመልከት ይቻላል ፦ /channel/TikvahUniversity/10053

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመላው ተፈታኝ እጩ ምሩቃን ቤተሰቦቹ በሙሉ መልካም ፈተናን ይመኛል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EMA

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ አባል ፤ ከኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትዕግስት መኮንንን ጋር ቆይታ  አድርጎ ነበር።

በዚህም ወቅት መሰረታዊ የሚባሉ ጥያቄዎችን አንስቷል።

1ኛ. በጤና ተቋማት እየታዩ ያሉና ትኩረት የሚሹ ችግሮች ምንድን ናቸው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" አሁን በስፋት በዋነኝነት እንደተግዳሮት ሆኖ የሚታየው የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት መኖር ነው።

የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት በሚፈለገው ልክ ተቋማት  የሚጠበቅባቸውን ሥራ ለመስራት ትልቅ ተግዳሮት እየሆነ ነው። "

2ኛ. ማህበሩ #የጤና_ባለሙያዎችን ጉዳዮች ተደራሽ ማድረግ አንዱ ዓላማው እንደመሆኑ መጠን በደመወዝ እጥረት የጤና ባለሙያዎች ወደ ውስጥም ሆነ ውጪ አገራት እየፈለሱ (የትግራይ ክልል) መሆኑን በተመለከተ ማኅበሩ እንደማኀበር ምን እየሰራ ነው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" እርግጥ ነው ይሄ ነገር ማኀበሩ እውቅና የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ከሥራ ማጣት ጋርም ተያይዞ፣ ከተለያዩ ችግሮች አንፃር የባለሙያዎች ፍልሰት እንዳለ እሙን ነው። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ እንደዚህ ነው የሚል ጥናታዊ ፅሑፍ አልሰራንም።

ግን ችግሩ እንዳለ፣ በጥልቀት አትኩሮት መሰጠት እንዳለበትም ለተለያዩ አካላት ግብዓት ስንሰጥ ቆይተናል።

ይሄ አገሪቱም ካለችበት የኢኮኖሚ ጉዳይ፣ ለጤና ሴክተሩ ከሚሰጠው ትኩረት አንፃር እጥረት አለ፣ መድረስ ያለብን ደረጃ ላይ አልደረሰንም። ይህ ባለበት ሁኔታ የመፍለሱ፣ ሥራ የማጣቱ ጉዳይ እየታዬ ስለሆነ እንደ አገር ያለው ችግር ነው ለዚህ የዳረገው። "

3ኛ. የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱ ሕሙማን መጉላላት፣ የቀጠሮ መንዛዛት ስለሚገጥማቸው በወቅቱ መታከም ሲገባቸው ከሕመማቸው ጋር ለመቆየት እንደሚገደዱ ሕሙማን በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ማኀበሩ ምን እየሰራ ነው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" የታካሚዎች መጉላላት፣ በወቅቱ የሚፈለገውን የሕክምና አገልግሎት አለማግኘት አጠቃላይ የሥርዓት ችግር ቢሆንም፣ ችግሩን ምን አመጣው ? በሚለው ጉዳይ ብዙ ነገሮች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ለምሳሌ፦ የሕክምና መሣሪያዎች ግብዓት እጥረት መኖር፣ ለጤና ሴክተር የሚሰጠው የበጀት እጥረት፣ ከዶላር ጋር ተያይዞ ያለው ችግር በቀጥታ ለዚህ ችግር አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ቁጥሩን ለመግለጽ ለጊዜው ባላስታውሰውም ማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል።

እንደ አጠቃላይ በታካሚዎች፣ በሐኪሞች፣ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ውይይት የማኀበሩ 60ኛ ዓመታዊ ጉባኤ በዚህ ወር ሲደረግ ይነሳል። ይበልጥ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። "

#TikvahEthiopiaAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ነዳጅ ሲቀዱ የስልክ ቁጥርዎን መንገር ሳይጠበቅብዎ ቴሌብር ሱፐርአፕን http://onelink.to/fpgu4m በመጠቀም ብቻ ክፍያ ይፈጽሙ!

በቴሌብር ሱፐርአፕ አስቀድመው፣ ለአንድ ጊዜ ብቻ ታርጋዎን እና አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ተሸከርካሪዎን ነዳጅ ሲያስሞሉ የብር መጠኑን ብቻ በማስገባት ኪው.አር ኮድዎን በነዳጅ ቀጂዎ ስካን በማስደረግ ክፍያዎን በቀላሉ መፈጸም ይችላሉ።

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AU

የሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

በ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ም/ቤት ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ናቸው።

ከትላንትና ምሽት ጀምሮ የሶማሊያ ፣ ቡሩንዲ ፣ ኬኘቨርዲ ፣ ኮሞሮስ እና የካሚሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የህብረቱ የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከነገ ጀምሮ ለ2 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Training on Artificial Intelligence using Python Programming and Google Colab

Few days left to register and few available spaces left to fill.

Register Now or join our telegram channel for more information @TrainingAAiT

By: School of Electrical & Computer Engineering at Addis Ababa University

Registration Deadline:
12 February, 2024

Training Starts on:
19 February, 2024

Registration:
Online Registration Link:
https://forms.gle/bdR6GUWVEUNwGHCq7

In Person Registration: 
Addis Ababa Institute of Technology (5 Kilo),
School of Electrical and Computer Engineering,
Main Building 1st Floor, Office Number: 124

Telephone: +251-940-182870 / +251-913-574525

Email: sece.training@aait.edu.et / menore.tekeba@aait.edu.et

Telegram Channel: /channel/TrainingAAiT

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሜትርታክሲ #ሀይገርባስ

ገቢዎች ሚኒስቴር ስለ ሀይገር ባስ እና ሜትር ታክሲዎች ምን አለ ?

የገቢዎች ሚኒስቴር ፤ የሀይገር ባስ እና የሜትር ታክሲዎች የታክስ አከፋፈል ስርዓት ውሳኔ ሳያገኝ በእንጥልጥል ቆይቷል ብሏል።

ነገር ግን ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ በንግድና በታክስ ህጉ መሠረት ተፈጻሚ መደረግ እንዳለበት ተገልጾ ከገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ እንደተሰጠበት ገልጿል።

በዚህም ፦

1ኛ. የታክሲ ማህበራት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 17 መሰረት የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚጠበቅባቸው የደረጃ " ሀ " ታክስ ከፋዮች በመሆናቸው የሂሳብ መዝገብ ይዘው የሚጠበቅባቸውን ግብር አስታውቀው እንዲከፍሉ፤

2ኛ. ዓመታዊ ግብራቸውን በሂሳብ መዝገብ ካላቀረቡ በገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 እና በመመሪያ ቁጥር 138/2010 በትራንስፖርት ቁርጥ ግብር ስርአት መሰረት አመታዊ የገቢ መረጃ እየተወሰደ እንደ ድርጅት በተሸከርካሪዎቹ  ዓይነትና ምርት ዘመን ግብር በሚከፈልበት ገቢ ላይ 👉 30 በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር በግምት እንዲሰላና መዝገብ ባለመያዝ በህጉ መሰረት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጠየቁ፤

3ኛ. የአክሲዮን ማህበራት በንግድ ህጉ መሠረት ለአባላት የሚከፈለው የትርፍ ድርሻ (Dividend) ግብር  የሚከፈልበት ስለሆነ የሂሳብ መዝገብ ካልያዙ አመታዊ የተጣራ ትርፍ ላይ ወይም በቁርጥ ግብር የገቢ መጠን ተመስርቶ የንግድ ትርፍ ግብር ከተከፈለ ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ላይ የተከፈለው ግብር ተቀንሶ ቀሪው መጠን ላይ ህጉን ተከትለው ካፒታላቸውን እስካላሳደጉ ድረስ የትርፍ ድርሻ ግብር 👉 10 በመቶ እንዲከፍሉ እንዲደረግ እንደተወሰነ ለግብር ከፋይ የሀይገር ባስና ሜትር ታክሲ ባለንብረቶች አሳውቋል።

@tikvahethiopia‌‌

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ስለ ግብረሰዶማዊነት እና ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ቋሚ ሲኖዶስ ምን አሉ ?

ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ነው ስላላቸው ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ?

- ግብረ ሰዶማዊነት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተገለጸው ለአንድ ሀገርና ሕዝብ ከነጎረቤቶቹ መጥፋት ምክንያት የሆነ ተግባር ነው። የሰዶምና ገሞራ በመቅሰፍተ እሳት መቃጠል ከእነርሱ መቀጣትም  አልፎ ላለውና ለመጪው ትውልድ አስተማሪ የሆነ ምልክት እንዲሆን ነው።

- ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ግብረ ሰዶማዊነትን የምትቃወመው ተፈጥሮዋዊ ስላልሆነ ብቻ ሳይሆን በብሉይ  ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ትምህርት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ፣ ተቀባይነት የሌለው፣ ኃጢአት በመሆኑ ነው፡፡

- ቅድስት ቤተክርስቲያን ጾታዊ ግንኙነት ወይም የተቀደሰ ጋብቻ በተቃራኒ ጾታዎች ብቻ የሚፈጾም እንዲሆን ታስተምራለች።

- ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ ማንነት የሚንድ፣ መሠረተ እምነትንና ቀኖናን የሚሽር፣ ማኅበራዊ ዕሴት የሚያጠፋ፣ ከሥነ ምግባር መገለጫዎች በአሉታዊ ገጽ የቆመ፣ ሕሊናን የሚያውክ ለትውልድ ጥፋት፣ ለሀገር መውደም ምክንያት የሆነ አጸያፊ ተግባር ነው፡፡

- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ወደ ንሥሓና ድኅነት እንዲመጡ፣ ከሥጋና ከመንፈስ ስብራት እንዲፈወሱ ዘወትር ጥሪ ታደርጋለች እንጅ ማንም ሰው የኃጢአቱ ወይም የርኩሰቱ ተባባሪ እንዲሆን አትፈቅድም።

- በሀገራችን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ ነው።

- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ተግባር (የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ) በግልጥ በሕገ መንግሥታቸውና በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ድንጋጌዎቻቸው እንደ ጥሩ ነገር እንደ ፍትሐዊነትና አካታችነት በመቁጠር በይፋ የደነገጉ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት መኖራቸው ግልጽ ነው። እነዚሁ ሀገራት ያላቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም መከታ በማድረግ በእምነታቸው፣ በባሕላቸው በማኀበራዊ መገለጫቸው ይህን አጸያፊ ድርጊት ፈጽመው በማይቀበሉ የአፍሪካና የምሥራቁ ዓለም ሀገራት ላይ ቢቻል በማግባባት፣ ካልሆነም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር እንዲቀበሉ የጥፋት ልማዳቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎችን እንቃወማለን።

- ይህ ግብረ ርኩሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው፣ የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች ፣ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በሀገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ በጥብቅ እናሳስባለን።

- ከመገናኛ ብዙኃንና ከሌሎችም የመረጃ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለው ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ሃደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ። የሀገራችን መንግሥት ብሎም የአፍሪካ መንግሥታት የአህጉራችንን ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴቶች አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ቋሚ ጥብቅ ጥሪ እናቀርባለን።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

M-PESAን በማውረድ እና በመገበያየት ፤ አዳዲስ መኪኖች፣ ባጃጆችን፣ እንዲሁም ሌሎችም ብዙ ሽልማቶችን የማሸነፍ ዕድል እናግኝ።

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

🔗 የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ትክክለኛ ቴሌግራም ገፅችንን በዚህ ሊንክ ያገኛሉ: /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የቀረበው ሪፖርት ከእውነት የራቀ ነው " - የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ

በትግራይ ክልል " ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረዋል " በሚል ፓርላማ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት " ከእውነት የራቀ ነው " ሲል የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወቀሰ፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥር 28 ቀን 2016 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረው ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው ብለው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ፤ በክልሉ ከጦርነቱ በኋላ ስራ የጀመሩ ኢንዱስትሪዎችን በተመለከተ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበላቸው ሪፖርት በተጨባጭ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የተራራቀ ነው ሲል ሪፖርቱን ውድቅ አድርጓል፡፡

የቢሮው ም/ኃላፊ አቶ መሐሪ ገብረሚካኤል፤ " በአሁኑ ወቅት በክልሉ ስራ የጀመሩት ለትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ የሚያቀርቡ 2 መቶ አነስተኛ ፣ 5 መካከለኛ እንዲሁም 12 ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ናቸው " ብለዋል።

" ነገር ግን ' 2 መቶ 17 ኢንዱስትሪዎች ሁለገብ ድጋፍ ተደርጎላቸው ስራ ጀምረዋል ' ተብሎ የተገለጸው ከእውነታው ጋር የተራራቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከፍተኛ የብድር እና የወለድ መጠንን ጨምሮ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግር አሁንም ግዙፍ  ኢንዱስትሪዎች ስራ እንዳይጀምሩ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ በቀጠለበት አግባብ ሁለገብ ድጋፍ ተደርጓል ለማለት አያስደፍርም ሲሉ ተችተዋል።

በክልሉ በነበረው ግጭት የተነሳ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ከነበረበት ከፍተኛ ጉዳት በዘላቂነት እንዲያገግም መሬት የወረዱና ተጨባጭ ድጋፎች እንዲደረጉም ነው የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐሪ ጥሪ ያቀረቡት፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሀዱ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

@samcomptech

⭐  አሁንም  አዳዲስ  ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ብዛትም ጥራትም በአንድ ቦታ እኩል የተገናኙበት  ሁሉንም አይነት ላፕቶፕ የያዘ የላፕቶፕ መደብር  አለን።

🟥ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች, ለጌመሮች, ለቪዲዮ ኤዲተሮች ,ለግራፌክስ ዲዛይነሮች  አዳዲስ  ላፕቶፕች እና ስልኮች  በቅናሽ  ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ይዘን ቀርበናል።
🔵 @samcomptech

👏የሚገርም ፍጥነት ያላቸው ፣ ቀላል እና ከ 10 ሰዓት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖች አሉን ፦

ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል  የሜፈልጉትን ይምረጡ  ።

/channel/samcomptech             

@sww2844

☎️ 0928442662/ 0940141114

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ተመረቆ ተከፈተ።

ዛሬ በአዲስ አበባ መሀል ፒያሳ ላይ የተሰራው ግዙፉ የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተመርቆ ተከፍቷል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ፣ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ፣ የጦር መኮንኖች፣ ሚኒስትሮች ፣ የክልል ፕሬዜዳንቶች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ... ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እግዶችም ተገኝተው ነበር።

በስነስርዓቱ ላይ መልዕክት አስተላልፈው የነበረው ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፤ " የዓድዋ ድል ከሀገርና አኅጉር ተሻግሮ በዓለም የተስተጋባ አኩሪ ድላችን ቢሆንም ይህን በአንድ ቦታ በአግባቡ የሚገልጽ የዓድዋ ድል መታሰቢያ አለመገንባቱ የሚያስቆጭ ነው " ብለዋል።

" ዛሬ ላይ የዓድዋን ድል ታሪክ በሚመጥን አግባብ መታሰቢያ ተገንብቷል " ያሉት ፕሬዜዳንቷ ፤ ለዚህም ሐሳብ ከማመንጨት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደረጉትን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደርን አመስግነዋል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በበኩላቸው፤ " የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሌሎች የጥቁር ሕዝቦች ሀገራት ሊሠሩት ቢችሉም፤ የምኒልክ ልጅ፣ የባልቻ ልጅ፣ የገበየሁ ልጅ፣ የአሉላ አባ ነጋ ልጅ መሆን ግን አይችሉም " ብለዋል፡፡

" የድል መታሰቢያውን ሰርተንና ጥረን ያሳካነው ነው " ያሉ ሲሆን " ከ128 ዓመታት በኋላ ተገንብቶ ለትውልድ ማለፍ በሚችልበት መልኩ ኢትዮጵያን መስሎ ተሠርቷል " ሲሉ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የዓድዋ ድል መታሰቢያን ማርከስ ማለት የአባቶቻችንን አጥንት እና ደም ማርከስ ነው " ሲሉም ተደምጠዋል።

Photot Credit - PMOfficeEthiopia & S.H

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም አሪቦና ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ።

ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በተለምዶ " ሳዉዝ " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በደረሰ የተሽከርካሪዎች ግጭት በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

የሳይክል ፣ የሞተርና መኪና ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ ሳይክል ሲያሽከረክር የነበረ የ17 አመት እድሜ ያለዉ ታዳጊ ህይወቱ ሲያልፍ ፤ ሞተር ያሽከረክር የነበረዉ ወጣት ላይ ከፍተኛ አደጋ ደርሷል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያዊ የሰጡት የአካባቢው የትራፊክ አባል ሳጅን አገኘሁ አቡ ፤ ጉዳቱ በፍጥነት ችግር የተከሰተ መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ በህይወት ቢተርፍም ጉዳት ያስተናገደዉን ሞተረኛ ለህክምና ወደ ሪፈራል ሆስፒታል መላኩን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፥  ከአዲስ አበባ ወደ መተሀራ በሚወስደው ዋና መንገድ  በምስራቅ ሸዋ ቦሰት ወረዳ ልዩ ስሙ " አሪቦና "በተባለ ሥፍራ በደረሰ የመኪና አደጋ አንድ ሰው ሞቷል።

አደጋው የደረሰው " ኒሳን ፖትሮል " መኪና ከአይሱዚ መኪና ጋር ተጋጭተው ሲሆን አንድ ሰው ሲሞት ሌሎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢፕድ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ኢፕድ (አሪቦና)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ  " ዛሬ ይመረቃል።

አጫጭር መረጃዎች ስለ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ "  ፦

- በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከምድር በታች ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ  5 ወለል እና 8 በሮች አሉት።

- 8ቱ በሮች ፦
* የምሥራቅ ጀግኖች በር፣
* የምዕራብ ጀግኖች በር፣
* የሰሜን ጀግኖች በር፣
* የደቡብ ጀግኖች በር፣
* የፈረሰኞች በር፣
* የአርበኞች በር፣
* የፓንአፍሪካኒዝም በር ተብለው ተሰይመዋል።

- በመታሰቢያው ነጋሪትን ጨምሮ የኢትዮጵያውያን የተለያዩ (ባህላዊዎችን ጨምሮ) የጦር መሳሪያዎች ተቀምጠዋል።

- በዓድዋ ድል መታሰቢያው የአፄ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ፣ የ12ቱን የጦር መሪዎች ሀውልት፤ በጦርነቱ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ፈረሶች መታሰቢያ የአርት ሥራዎችም ሰፍረዋል።

- አንድ መቶ ሃያ ሺህ ጀግኖችን የሚዘክር  ማስታወሻ፣ የዓድዋ ድል ለፓንአፍሪካኒዝም ንቅናቄ ማሳያነቱንም ይዟል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፋውንቴንም ተሰርቶለታል።

- በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 500 ሰዎችን መያዝ የሚችል የፓንአፍሪካኒዝም አዳራሽ አለው።

- በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 300 ሰዎችን መያዝ የሚችል ዘመናዊ ሁለገብ አዳራሽ አለው።

- አራት ሺህ ሰዎችን መያዝ የሚችል የቤት ውስጥ የስፖርት ሜዳ እና አዳራሽ አለው።

- የህፃናት መጫወቻ፣ የንግድ ሱቆች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቢሮዎችና የአርት ጋላሪ አለው።

- ከአንድ ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ አለው።

- እያንዳንዳቸው 280 ሰዎችን መያዝ የሚችሉ 2 ሲኒማ ቤቶች አሉት።

- በቅርቡ ወደ ሀገር የገባችው " ፀሀይ አውሮፕላን " በዓድዋ ድል መታሰቢያ እንድትቀመጥ ተደርጓል።

- አጠቃላይ ስራው 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

ℹ️ 00 ኪ.ሜ መነሻ ቦታ ፦ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መሐከል ላይ የሚገኘው የኮምፓስ ምልክት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ነው።

Info ፦ EPA
Photo Credit ፦ Addis Ababa City Communication & Abel Gashaw /

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Подписаться на канал