" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህ/ተ/ም/ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ፤ " እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " ሲሉ ተናግረዋል።
" በትግራይ የተወሰነ አካባቢ ፣ በአማራ የተወሰነ አካባቢ ፣ በኦሮሚያ ፣ ምስራቁ ክፍልም እንዲሁ ድርቅ አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ይህ ምንም ጥያቄ የለውም ፤ ይህን ግን ማየት ያለብን እንደ ፖለቲካ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።
" ድርቅን መንግሥት አላመጣውም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " environmental crisis አለ ችግኝ እንትከል ሲባል ችግኝ ምን ያደርጋል ብለን ፤ ድርቅ እና ረሃብ አለ ስንዴ እናምርት ስንል ስንዴ ምን ያደርጋል ብለን ድርቅ መጣ ብለን ብንጮህ ትርጉም የለውም ትርጉሙ ተባብሮ ሰው እንዳይሞትብን ማድረግ ነው " ብለዋል።
በቦረና በተደረገ ርብርብ ምንም እንኳን ከብቶች ቢሞቱም ሰው አልሞተም ፤ በሶማሌ ክልልም እንዲሁ በርብርብ ሰው እንዳይሞት ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።
" አሁንም ትግራይ ፣ አማራ ፣ ኦሮሚያ ተርቦ እዚህ በልተን ማደር አንችልም ተባብረን ሰው እንዳይሞትብን ማድረግ አለብን ፤ ግን ድርቅን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ የምንጠቀም ከሆነ ጥፋት ነው " ብለዋል።
" ባለፉት 4 ወራት ወደ ትግራይ 500 ሺህ ኩንታል እህል በዋነኝነት በመንግሥት እና በተወሰኑ ደጋፊዎች ተልኳል ይህ ሶስት አራት ወር ሰው በምግብ እጥረት እንዳይሞት ያደርጋል። የትግራይ መንግስትም ያለውን resource / እህል ውስንም ቢሆን የከፋ ችግር ያለበት ቦታ ማድረስ አለበት፤ ያለው እህል በትክክል ካልተሰራጨ ችግር ሊያመጣ ይችላል " ብለዋል።
" ያለው resource በቂ ካልሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አቅም እያለውና የኢትዮጵያ ህዝብ በልቶ እያደረ አንድም ቦታ በረሃብ የሚሞት ሰው አይተን ዝም አንልም፤ ባለን አቅም ህዝባችንን አግዘን ይህችን ጊዜ እንዲሻገር እናደርጋለን " ሲሉ ተደምጠዋል።
" መንግሥት ለድርቅ ትኩረት አልሰጣም " የሚባለውን አስተያየትም አጣጥለውታል ሰው እንዳይሞት በዋነኝነት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያወጣ ነው ብለዋል።
" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት ሚሞት ሰው የለም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " ያለው ችግር ረሃብ እና አብሮ የሚመጣ በሽታ አለ በትግራይ ብቻ ሳይሆን ደቡብ ምዕራብ አካባቢ ብትወስዱ አዲስ የወባ ባህሪ አለ ያ የወባ ባህሪ በጥቂት ቀናት ሰው ይገድላል ከዚህ ቀደም የሚሰጡ መድሃኒቶችም ፈውስ አላመጡለትም ወባ ሲጨመር ፣ ተቅማጥ ሲጨመር በምግብ እጥረት እላዩ ላይ በሽታ ሲጨመር ሰው መቋቋም አቅቶት ሊሞት ይችላል " ብለዋል።
" ይሄ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ የሚሆን ነው " ሲሉ አክለዋል።
" ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምንም ጊዜ በላይ በታሪክ ተምርቶ የማያውቅ ምርት አለ " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ይህ ሁሉ እያለ ምርት አምራች አርሶ አደሮች " ወንድምህ ተርቦ እየሞተ ነው " ሲባሉ ዝም ይላሉ ብላችሁ አትጠብቁ ፤ መንግሥት እንኳን ባያደርግ ህዝቡ ተረባርቦ ሰው እንዳይሞት ጥረት ያደርጋል ብለዋል።
፣ መንግስት የሚራብበት ዜጋ ካለ ፕሮጀክት አጥፎ ህዝቡ በረሃብ እንዳይሞት ከህዝቡ ጋር የሚችለውን ሁሉ ይሰራል " ሲሉ ተናግረዋል።
በቅርቡ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ይፋ ባደረገው ሪፖርት በትግራይ እና በአማራ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ምክንያት 372 ሰዎች መሞታቸውን ፤
23 ህፃናት በአልሚ ምግብ እጥረት ምክንያት ተገቢዉን ዕድገት ባለማግኘታቸዉ ሞተው መወለዳቸውን ማረጋገጡ ማሳወቁ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
#Update
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተናገሩት መካከል ፦
" ... ዋናው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሥራ አጥነት ነው።
አብዛኛው ሰው cause ኖሮት አይደለም። ሥራ ፍለጋ ይሄዳል ያግታል ብር ይጠይቃል።
ዓላማ መር ትግል ሳይሆን እገታ መር ትግል ነው ያለው።
ይሄን ደግሞ በርከት አድርጎ ሥራ በመፍጠር ወጣቱ ወደ ሥራ እንዲሄድ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ ተግባሩ ነው ጥረት እየተደረገ ነው ማጠናከር ይኖርብናል። "
@tikvahethiopia
#አሁን
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
በስበስባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን በምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች እየቀረበላቸው ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
@tikvahethiopia
#Rodtechnologies
በፈጣን አና አስተማማኝ ሁኔታ የመኪናዎን እንቅስቃሴ ከየትኛውም ቦታ በስልክዎ ወይም በኮምፒተርዎ የሚከታተሉበት የGPS ቴክኖሎጂ እነሆ ፤ ለድርጅቶች የተለየ ፓኬጅ አዘጋጅተናል።
የGPS መተግበርያውን የሚለየው:
- ትክክለኛውን የመኪና እንቅስቃሴ እና አድራሻ በፈጣን ኔትወርክ ማሳየት ይችላል
- የመኪናዎን የቀን የጉዞ ታሪክ ወደኋላ በመመለስ ያሳያል - መኪናዎ ሲነካ የማስጠንቀቂያ መልእክት ይደርሶታል
- የድምፅ መቅረጫ ያለው
- ለአጠቃቀም እጅጉን ቀላል
- መኪናዎ ከተፈለገው የእንቅስቃሴ ክልል ውጪ ሲሆን መልእክት ይደርሶታል።
አድራሻ ፦ ዑራኤል አሜን ህንፃ
ያሉበት ድረስ መተን በነፃ እንገጥማለን
ይደውሉ፡ 0956569696
#ExitExam2016
ከጥቂት ቀናት በኃላ የሚሰጠውን ሀገር አቀፉን የመውጫ ፈተና " ካለንበት ዩኒቨርሲቲ / ተቋም በርካታ ኪሎ ሜትሮችን ርቀን ተጉዘን እንድንፈተን #መመደባችን ተነግሮናል " ያሉ ተመራቂ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።
ቅሬታቸውን ካሰሙት መካከል የተወሰኑት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጥቁር አንበሳ ' ስኩን ኦፍ ሜዲስን ' ተመራቂ ተማሪዎች ናቸው።
ተማሪዎቹ የካቲት 6 /2016 ዓ/ም መሰጠት የሚጀምረውን ፈተና ለመፈተን ከአዲስ አበባ ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሚርቀው ወሎ ዩኒቨርሲቲ እንደተመደቡ እንደተነገራቸውና ጉዳዩ ፍፁም ያልጠበቁት ዱብእዳ እንደሆነ አስረድተዋል።
" የምርቃት ቀናችን 10 ቀናት እየቀሩት የመውጫ ፈተና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ420 ኪ/ሜ ርቀን በወሎ ዩኒቨርስቲ እንደምንፈተን ተነግሮናል፤ ይህ ፍፁም ያጠበቅነውና ያልተለመደ ነው " ብለዋል።
ከተቋማችን እጅግ ርቀን ፈተናውን እንድንወስድ ተመድበናል ያሉት ተማሪዎች ፤ " ላለፉት 8 ዓመታት እዚህ ቀን ላይ ለመድረስ ከነቤተሰቦችን ከፍተኛ መስእዋትነት ከፍለናል፤ ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፈናል " ያሉ ሲሆን ቤተሰቦችም የልጆቸውን ድካም ፍሬ ለማየት እየተጠባበቁ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ተመራቂዎቹ ፦
- አሁን ባለው ሁኔታ ረጅም ጉዞ ማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ እየታወቀ፤
- ለምርቃት የቀረው አጭር ቀን ሆኖ ሳለና በርካታ ካምፓሶች በአዲስ አበባ እያሉ፤
- የብሄራዊ የመውጫ ፈተናው በኦንላይ እንደሚሰጥ እየታወቀ፤
- የደህንነታችን እና በዚህ የምርቃት ወቅት የቤተሰብ ኢኮኖሚ ጉዳይ ፍፁም ታሳቢ ሳይደረግ ለምን እንደዚህ ያለው ውሳኔ እንደተላለፈ በፍፁም ሊገባን አልቻለም፤ ማብራሪያም ሊሰጠን የወደደ አካል የለም ሲሉ ተናግረዋል።
በመሆኑም " ይህ ወደ ሌላ ቦታ ሄዳችሁ በኦንላይ የሚሰጠውን ፈተና ትወስዳላችሁ " የሚለው ነገር ተገቢ ባለመሆኑ እርምት እንዲደረግ ጠይቀዋል።
ከ ' ስኩል ኦፍ ሜዲስን ' ተመራቂዎች በተጨማሪ የተወሰኑ የምህንድስና ተማሪዎችም ተመሳሳይ ቅሬታቸውን አድርሰዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመራቂ ተማሪችዎች ጋር በውስጥ የደረሰ የመፈተኛ username ፣ password እንዲሁም የመፈተኛ ጣቢያ (ዩኒቨርሲቲ) የያዘ ፋይል ደርሶት ተመልክቷል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማት ተመራቂዎች መሰል ቅሬታዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሰዋል።
አንዳንድ ተመራቂዎች አሁን ካሉበት ዩኒቨርሲቲ ርቀው እንደሚፈተኑ በተወካዮቻቸው በኩል እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
በተመሳሳይ እነዚህ ተመራቂዎች ፤ በዚህ ወቅት ወደሌላ ቦታ እንዲጓዙ ተደርገው የኦንላይን ፈተና የሚወስዱበት ምክንያት ምንም ግልፅ እንዳልሆነላቸውና ይህ ነገር ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ማሰብና ማስተካከል እንደሚገባ አስገንዘበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችን ለማነጋገርና መረጃ ለመስጠት ጥረት ያደርጋል።
በአመቱ አጋማሽ ላይ የሚሰጠው የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ተራዝሞ ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል።
በዚህ ሳምንት የሞዴል ፈተና ይሰጣል።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።
ሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።
@tikvahethiopia
የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዙር ተረክ በM-PESA የባጃጅ አሸናፊዎቻችን ሽልማታቸውን ተረክበዋል!
አዲስ አበባ፣ አምቦ፣ ጅማ፣ ሰንዳፋ እና አዳማ እንኳን ደስ አላችሁ!
ቀጣይ በM-PESA የተዘጋጀው ምርጥ ሽልማት ማን የሚውስደው ይመስላቹዋል?
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
#WSU
➡ “ አንድ ዓመት መዘግየት በጣም ከባድ ነው። ግዴታ መማር እንዳለብን አስጠንቅቀውናል ” - የወላይታ ሶዶ ዩኒበርሲቲ ተማሪዎች
➡ “ የተማሩበት ታይም ምን ያህል ነው? ተብሎ መወሰን አለበት” - የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች በዚህ ዓመት መመረቅ ሲገባቸው “ አላወቅነውም ” ባሉት ምክንያት ለምረቃ አንድ ‘ዓመት ትጨምራላችሁ’ ተብለው እየተገደዱ መሆኑን አማረው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ለምን የእናንተ ብቻ ዘገዬ ወይም አንድ ዓመት ጭማሪ ተደረገ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።
* ስኬጁሉ ላይ ነው ችግራቸው። በኮሮና ምክንያት 2013 ዓ/ም ሁሉም ግቢዎች ተማሪዎቻቸውን የጠሩት ሰኔ ወር ላይ ነበር። እኛም ከሁሉም ግቢ እኩል ነበር የገባነው (ሰኔ 26)። ወዲያውኑ (45 ቀናት አቆይቶ) አስወጣን (ከግቢ) ምንም ባላወቅንበት መንገድ። አንድ ሲሚስተር ጨርሰን መወሰጣት ሲገባን ሚድን ፈትኖ አስወጣን።
* በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሚዲ የወሰድነውን ሁለት ሲሚስተር አድርጎ በአጠቃላይ አስተማረ። ሙሉ 3 ሲሚስተር ነበር ማስተማር የነበረበት ግን አንዱን ዓመት በሁለት ሲሚስተር ብቻ አደረገ። ስህተቱን የሰሩት እዚሁ ላይ ነው።
* ሬጅስተራር ላይ የሰፈረው “4ኛ ዓመት ናችሁ” ነው የሚለው። እኛ የምንማረው ግን ገና ሦስተኛ ዓመት ሁለተኛ ሲሚስተርን እየጀመርን ነው። ሌሎች ግቢዎች ግን አሁን 4ኛ ዓመት ሁለተኛ ሲሚስተርን እያስተማሩ ነው። የእኛ ሙሉ 3 ሲሚስተሮች ወደ ኋላ ቀርቷል ማለት ነው።
* ‘ወደ ኋላ ቀረን’ ብለን ስናመለክት ‘#አስተካክላለሁ’ ብሎ ‘3 ሲሚስተር አስተምራለሁ’ ካለ በኋላ ሁለት ሲሚስተር አስተማረና ካፌ ዘጋ። እንደዛ እየተደረገ አንድ ዓመት ባከነ። የእኛን የአንድ ዓመት በጀት ለምን እንደፈለጉት አናውቅም። ከሌሎች ግቢዎች በሚለይ ሁኔታ በሚያስጠላ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው።
የሚል ማብራሪያ በአንድ ተወካያቸው በኩል ሰጥተዋል።
“ ሌሎች ግቢዎች የእኛን ባቾች በዚህ ዓመት ያስመርቃሉ። የእኛ ግን በዚህ ዓመት አይደለም” ያሉት ተማሪዎቹ፣ “ በዚህ ሳምንት ክላስ አልገባንም። ነገር ግን ግዴታ በቀጣይ ሰኞ መግባት እንዳለብን ተነግሮናል። ግዴታ መማር እንዳለብን አስጠንቅቀውናል። ” ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም፣ “ አንድ ዓመት መዘግየት በጣም ከባድ ነው። ሙሉ 3 ሲሚስተር አስተምሮ ሰኔ ላይ ይፈትነን (እንመረቅ) አንልም። ቢያንስ ስለ Exit exam የሚሆኑ ኮርሶችን ወደዚህ አሸጋሽገውልን Exist ተፈትነን ቀጣዩን አንድ ሲሚስተር እንድንወስድ ያድርጉን። አንድ ዓመት ከመዘግየት ግማሽ ዓመት መዘግየት ይሻላል ብለዋል ” ሲሉ አሳስበዋል።
ቅሬታውን በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳለው ለመጠየቅ ወደ ዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮሽ የተደረገው ሙከራ ባይሳካም፣ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ኀብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ፍሬው ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ስኬጁል ላይ የተቀየረ ነገር የለም። ያልተጣራ መረጃ እንጂ በእኛ ፔጅ ላይ የተለጠፈ አይደለም ” ሲሉ አስተባብለዋል።
ተማሪ ፍሬው፣ “ የሚመረቁት መቼ ነው? ለሚለው የተማሩበት ታይም ምን ያህል ነው? የሚለው መወሰን አለበት” ያሉ ሲሆን፣ የዘንድሮ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ነው የምትመረቁት ተብለዋል ወይስ አልተባሉም? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄም ቀጥኛ መልስ በመስጠት ፋንታ፤ “በእስኬጁል መሠረት ነው እኮ ይሄ ውሳኔ” ብለዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#Rodtechnologies
በፈጣን አና አስተማማኝ ሁኔታ የመኪናዎን እንቅስቃሴ ከየትኛውም ቦታ በስልክዎ ወይም በኮምፒተርዎ የሚከታተሉበት የGPS ቴክኖሎጂ እነሆ ፤ ለድርጅቶች የተለየ ፓኬጅ አዘጋጅተናል።
የGPS መተግበርያውን የሚለየው:
- ትክክለኛውን የመኪና እንቅስቃሴ እና አድራሻ በፈጣን ኔትወርክ ማሳየት ይችላል
- የመኪናዎን የቀን የጉዞ ታሪክ ወደኋላ በመመለስ ያሳያል - መኪናዎ ሲነካ የማስጠንቀቂያ መልእክት ይደርሶታል
- የድምፅ መቅረጫ ያለው
- ለአጠቃቀም እጅጉን ቀላል
- መኪናዎ ከተፈለገው የእንቅስቃሴ ክልል ውጪ ሲሆን መልእክት ይደርሶታል።
አድራሻ ፦ ዑራኤል አሜን ህንፃ
ያሉበት ድረስ መተን በነፃ እንገጥማለን
ይደውሉ፡ 0956569696
#Hawassa
" ተማሪው ላይ ጾታዊ ትንኮሳ ፈጽሟል " በሚል #የተጠረጠረው ርእሰ መምህር በቁጥጥር ስር እንዳሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።
በሀዋሳ ከተማ ታቦር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወስጥ አንዲት ተማሪ ርእሰ መምህሯን " ጾታዊ ትንኮሳ ፈጽሞብኛል " በሚል ክስ መመስረቷን ተከትሎ ፖሊስ ተጠርጣሪዉን ግለሰብ ከስራ ገበታዉ ድረስ በመሄድ በቀን 20/05/2016 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ማዋሉን ለማወቅ ተችሏል።
የሀዋሳ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊዋ ወይዘሮ ፍሬህይወት ወልደጻዲቅ ጉዳዩን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጽያ የሀዋሳው አባል ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ፤ " የተጠቂዋ ቤተሰቦች ጉዳዩን ይዘዉ ቅድሚያ ለማመልከት የመጡት ወደእኛ ቢሮ ነበር " ያሉ ሲሆን ጉዳዩን ወደ ህግ እንዲወስዱት በማድረግ ማንኛዉንም የህግ ከለላና አስፈላጊ ድጋፎችን ሊሰጡ እንደሚችሉ ቃል ገብተው አንዳበረታቷቸው ገልጸዋል።
ከዚህ በኋላ ክሱ ተመስርቶ ተጠርጣሪዉ በህግ ጥላ እንደዋለና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ " አሁን ላይ የሀዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ መረጃዎችን አጠናክሮ የክስ ሂደቱን ከኛ ጋር ለመደገፍ እንቅስቃሴ ላይ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዉ በትምህርት ቤት ውስጥ ሲያዝ የነበረዉን ሁኔታ እና ድርጊቱን በተመለከተ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር የሚያውቀዉ ነገር እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የትምህርት ቤቱ ምክትል ርእሰ መምህር አቶ ሀንዳሞ ፈይሳ ፤ በወቅቱ ተጠርጣሪው ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብለዉ መሄዳቸውን ፤ አሁን ላይ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ሳምንት እንዳለፋቸው ገልጸዋል።
ክስ አቅራቢዋ ተማሪ ከትምህርት ገበታዋ ደጋግማ በመቅረቷ ምክንያት " ወላጅ አምጭ አታምጭ " በሚል ከሚመለከታቸዉ መምህራኖቿ እና ከተጠርጣሪው ርእሰ መምህር ጋር ስትጨቃጨቅ እንደነበር የሚያስታዉሱት አቶ ሀንዳሞ ፤ ይህ ጉዳይ ለእርሳቸውም ሆነ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ #አስደንጋጭ እና ግራ ያጋባ መሆኑን አስረድተዋል።
ፖሊስ አስፈላጊዉን ማጣራት አድርጎ እዉነቱ ላይ እስኪደርስ እየጠበቁ መሆኑንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሐዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።
@tikvahethiopia
#CBE
በአዲስ መልክ!
****
የነበሩትን አሻሽሎ፣
በርካታ አዳዲስ ነገሮችን አካቶ፣
ለአጠቃቀም ቀሎ፣
ፍጥነት እና ምቾት ጨምሮ፣
በአዲስ መልክ በቀረበው የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ይጠቀሙ!
****
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎን ያዘምኑ/ ይጫኑ!
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
***
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- /channel/combankethofficial
#ጥቆማ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ አቅርቧል።
ኮርፖሬሽኑ ፤ " ያለብኝን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቼ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንድችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው #የተጠናቀቁ ፦
➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን
➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሬ በሽያጭ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ " ሲል አሳውቋል።
ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከ27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/06/2016 ዓ.ም ድረስ ቅዳሜን እስከ 11፡00 ሰአት እና እሁድ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ማታ 1፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላል ተብሏል።
የሰነድ መሸጫ ቦታ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ማግኘቱን ያሳውቃል።
@tikvahethiopia
#Amhara #Merawi
በአማራ ክልል ፤ በየጊዜው በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መከላከያ እና በ " ፋኖ " ታጣቂ ኃይሎች መካከል ግጭቶች ይደረጋሉ።
በእነዚህ ግጭቶችም በሁለቱም በኩል ከሚሞተው የግጭቱ ተካፋይ ባለፈ ንፁሃን ሰዎች ሰለባ እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተገልጿል።
ምንም እንኳን #መንግሥት ፤ " ከእውነታው ያፈነገጠ እና ሚዛናዊነት የጎደለው " ብሎ ቢያጣጥለውም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮኒሽን (#ኢሰመኮ) ይፋ አድርጎት በነበረው ሪፖርት በክልሉ ፦
- የአንድ ዓመት ከሰባት ወር #ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች በድሮን መገደላቸው / የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው።
- በከባድ መሣሪያ ድብደባ ምክንያት #ሲቪል_ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱ።
- በመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት #ከሕግ_ውጪ የሆኑ ግድያዎች እንደሚፈፀሙ።
- ከዚህ ቀደም ግጭቶች በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦
➡" ፋኖን ትደግፋላችሁ "
➡" ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ "
➡" መሣሪያ አምጡ "
➡ " የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ በርካታ #ግድያዎች መፈጸማቸውን በይፋ ማሳወቁ አይዘነጋም።
ከሰሞኑን ዳግሞ በሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ/ም የነበረውን ውጊያ ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።
አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ገለጻ ፤ በሰሞኑ ተኩስ እሳቸው የሚያውቋቸው ብቻ 15 ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።
ከዚህም ባለፈ ግን ፤ " የሟቾቹን ቁጥር በዚህ ወቅት ለመግለጽ መሞከር የጥቃቱን አድማስ ያሳንዋል እንጂ አይገለጸውም" ብለዋል።
እኚሁ ነዋሪ በግፍ የተገደሉ ንጹሐን ሰዎችን ቁጥር በሂደት እንጂ አሁን ሁሉንም ማወቅ እንደማይቻል ገልጸው ፤ " የዚህ ህዝብ ጭፋጨፋ ግን መቼ ነው የሚያበቃው? " ሲሉ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች፣ የሆስፒታል ሰዎችና የአይን እማኞች በከተማው ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።
አብዛኞቹ ነዋሪዎች ግድያው የተፈጸመው በቤታቸው እና በመንገድ ላይ በተገኙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
አንድ የህክምና ባለሙያ 13ት ሰዎች ከአስፓልት ዳር መገደላቸውን እንደሚያውቁ ተናግረው በአጠቃላይ በከተማዋ በዚያ ዕለት 85 ሰዎች መገደላቸውን አመልክተዋል።
አንድ የአይን እማኝ በርካታ ቀብሮች ላይ መገኘታቸውን ጠቅሰው የሟቾችን ቁጥር " ከ100 በላይ ነው " ብለዋል። ጥቃቱ በተፈጸመ ማግስት ጠዋት ላይ 48 አስከሬን መቆጠራቸውን ተናግረው ፤ " ከማርዘነብ ሆቴል እስከ በረድ ወንዝ ድረስ ግራ እና ቀኝ አስከሬን ብቻ ነበር " ብለዋል።
የሟቾችን ቁጥር 115 ገደማ የሚያደርሱ አንድ የዐይን እማኝ ደግሞ መከላከያ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ስታዲየም እና ጤና ጣቢያ በተባሉ ሰፈሮች " ከ6 ዓመት ህጻን እስከ 75 ዓመት አዛውንት " ድረስ ግድያ ተፈጽሟል ብለዋል።
የሆስፒታል ሠራተኛ የሆኑት የዐይን እማኝ በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ6 ወር ነፍሰ ጡርን ጨምሮ 25 ሰዎች ቆስለው መጥተው " የተረፈ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።
" 24ቱ ሆስፒታል የመጡት ሞተው ነው። አንዲት የ6 ወር ነፍሰ ጡር ሴት ከነ ነፍሷ መጥታ ሆስፒታል እንደደረሰች አርፋለች። አጠቃላይ 25 ነበር የመጡት " ብለዋል።
ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፤ #በመርዓዊ_አስተዳደር ህንጻ ውስጥ በነበሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ሰኞ ጠዋት ድንገተኛ ጥቃት ፈፀመው እንደነበርና ለዚህ ምላሽ " የበቀል እርምጃ " በመወሰዱ ነው ለበርካታ ሰዎች ግድያ ምክንያት የሆነው ብለዋል።
ስለ ግድያው ምን ምላሽ እንዳለቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፣ " ስብሰባ ላይ ነኝ መልሸ ልደውል " ብለዋል።
መንገሻ (ዶ/ር) ይህን ያሉት እንዲያብራሩ የተፈለገውን ጥያቄ በዝርዝር ከሰሙ በኋላ ሲሆን፣ በድጋሚም ስልክ ሲደወል ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።
እንዲሁም፣ " እባክዎ ስልክዎን ያንሱና በኮሚዩኒኬሽን በኩል ያለውን የመርዓዊ ጉዳይ ማብራሪያ በመስጠት ኃላፊነትዎን ይወጡ " የሚል የፅሑፍ መልዕክት (SMS) ቢላክላቸውም ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።
በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
* የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ምክትል፣
* የክልሉና የሰሜን ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት፣
* የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ስለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለቸው ለማወቅ እና ሃሳባቸውን ለማካተት ስልክ ቢደውልም ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፤ " መረጃው ደርሶናል (የመርዓዊ ጉዳይ) ። እያረጋገጥን ነው " ብለዋል።
አክለው ፣ "የጸጥታ ጉዳይ ስለሆነ ትንሽ መንቀሳቀስና መረጃ መሰብሰብ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሊዘገይ ይችላል። ግን እያጣራን ነው" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
@tikvahethiopia
#ትግራይ
የመኪና አደጋ የአባትና ልጅ ህይወት ቀጠፈ።
ሦስት ተጓዦች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
ዛሬ ጠዋት ጥር 25/2016 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ መቐለ 5 ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ባለቤትነቱ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ የሆነ ትዮታ ዳብል ጋቢና መኪና ተምቤን ልዩ ቦታ " መነወ " በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ በውስጡ የነበሩ ሁሉም ተጓዦች ላይ የሞትና የጉዳት አደጋ አድርሷል።
በመኪናው የነበሩ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ማርኬቲንግ መምሪያ ሃላፊ ከነልጃቸው ህይወታቸው ሲያልፍ ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 3 ተጓዦች ደግም በመቐለ ዓይደር ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
የራስ አሉላ አባነጋ የትውልድ ቦታ የሆነው " መነወ " ጠመዝማዛ ቦታና ተደጋጋሚ የመኪና አደጋ የሚከሰትበት በመሆኑ መንገዱ ትኩረት እንደሚያሻው አደጋው አስመልክተው የሚሰጡ የህዝብ አስተያየቶች ያመለክታሉ።
የመኪና አደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ፓሊስ ትራፊክ ገልጿል።
መረጃውን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የላከው።
@tikvahethiopia
#እቴጌጣይቱ
" ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉ ለሚጠሩት ስመ ጥር የሀገር ባለውለታ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በትውልድ ቦታቸውና ለቁምነገር በበቁበት በደብረታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሀውልት ቆመላቸው።
ሀውልቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብቶ በዛሬው እለት መመረቁ ተነግሯል።
እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ነበር የተወለዱት።
ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ጋር ሚያዝያ 25 ቀን 1875 ዓ.ም በአንኮበር መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ከተጋቡ በኃላ ንጉሱ ዐፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በተቀዳጁ ማግስት ጥቅምት 27/1882 ዓ.ም ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ጣይቱ ተብለው ተሰይመዋል።
እቴጌ ጣይቱ ብጡል ፦
* በሀገር አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
* የጥቁር ህዝቦች ድል ለተሰኘውና ለዓድዋ ጦርነት ድል መሳካት ሚናቸው ከፍተኛ ነበር።
* ለአዲስ አበባ ከተማ መመስረት መሰረት ጥለዋል።
* የውጫሌ ውል ይሰረዝ ዘንድ ሞግተዋል።
* የዓድዋ ጦርነት አይቀሬ መሆኑ ሲታወቅ " ሴት ነኝ ጦርነት አልፈልግም፤ በሀገሬ ክብር ግን አልደራደርም " በማለት የአዲስ አበባን ሴቶች ሰብስበው ሎጀስቲክስ አዘጋጅተዋል። በአንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ማዕረግ (ራስ) ሆነው 5,000 ጦር በመምራት ወደ ማይቀረው ፍልሚያ ተመዋል። ... ሌሎች ብዙ ያልተዘረዘሩ ሀገራዊ ተግባርን ፈፅመዋል።
እቴጌ ጣይቱ የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ/ም ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
ፎቶ፦ የደብረ ታቦር ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopia
#Update
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሀገራዊ ሰላምና ፀጥታ ጋር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ " መንግሥት በቀጣይነት ሕግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል " ብለዋል።
" ሕግ ማስከበር አጠናክረን እንቀጥላለን " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " እጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀመጡ የሚለውን ጉዳይ አንስማማም አንቀበልም አናደርግም። መንግሥት ነን አቅም በፈቀደ መጠን ሕግ ለማስከበር እንሰራለን " ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ሕግ ለማስከበር ስንሰራ በየአንዳንዷ ሰከንድ ለሠላም ዝግጁ የሆነ ኃይል ካለ በራችን ክፍት ነው " ያሉ ሲሆን " ለውይይት ለሠላም፣ ለንግግር ክፍት ነን። ሕግ የማስከበሩን ሥራ ከንግግር እና ከውይይት ውጭ እንዲሆን አንፈልግም " ብለዋል።
@tikvahethiopia
#BeledHawo
በደቡባዊ ሶማሊያ ፤ ጌዶ ክልል ፣ በሌደሀዎ በተባለ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ኢትዮጵያውያን እና አንድ ሶማሊያዊ መገደላቸውን ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።
በዚህ ምክንያት በርካቶች ስጋት ውስጥ መሆናቸው ተነግሯል።
ታጣቂዎቹ ሌሊት ኢትዮጵያውያን ወደ ሚኖሩበት ቤት በመግባት በፈጸሙት ጥቃት 3 ሴቶች እና 3 ወንዶችን ሲገድሉ 1 ሶማሊያዊም መገደላቸው ተነግሯል።
ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በሶማሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ተወካይ በሰጡት ቃል ፤ ቅዳሜ ሌሊት 6 እሁድ 1 በተለያየ ስራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል ብለዋል።
" ከተገደሉት መካከል ሁለቱ ሕጻናት ሲሆኑ ፣ እናት እና አባቷ ተገድለውባት ብቻዋን የቀረች ሕጻንም አለች " ሲሉ አክለዋል።
" የተገደሉት ሰዎች ወደ አገራቸው ተመልሰው በሥነ ሥርዓት ቀብራቸው እንዲፈጸም እንፈልጋለን። መንግሥት ይህን ማድረግ ይችላል። ለተገደሉትም ፍትሕ እንዲሰፍንም እንፈልጋለን " ሲሉ አክለዋል።
ጥቃቱ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ እንደሆኑና በርካቶች ወደ አገር ቤት መመለስ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።
የበለደሀዎ አስተዳዳሪ አብዲራሺድ አብዲ ፤ ግድያው ሌሊት 9 ሰዓት መፈጸሙን እንደታወቀ አመልክተዋል።
ግድያ መፈፀሙ የታወቀው የአካባቢው የፀጥታ ባልደረቦች የተኩስ ድምጽ ከሰሙ በኋላ ሲሆን 7 ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን አስረድተዋል።
" ማቾቹ በአጠቃላይ ለሥራ የመጡ ስደተኞች ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።
በአካባቢው ሆስፒታል የሚሠራ አንድ ዶክተር በሰጠው ቃል በጥቃቱ የተገደሉ የ6 ኢትዮጵያውያን አስከሬን ወደ ሆስፒታሉ መምጣቱን አረጋግጧል።
በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች 6 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውንም ገልጿል።
ምንም እንኳን እስካሁን ከግድያው ጀርባ ማን እንዳለ ያልታወቀና ኃላፊነት የወሰደም አካል የሌለ ቢሆንም የአካባቢው አስተዳዳሪ " ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት ገዳዮቹ #የአልሸባብ አሸባሪዎች ናቸው " ብለዋል።
" እስካሁን አልተያዙም። ለምን ስደተኞን ዒላማ አደረጉ ለሚለው ጥያቄ፣ ይህ ግድያ በመላው አገሪቱ ከሚፈጸመው ግድያ የሚለይ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።
መረጃው የቢቢሲ ሶማልኛ አገልግሎት ነው።
@tikvahethiopia
“ ወደ 10 የሚደርሱ ደጋፊዎችና አባላቶች ታስረዋል” - አቶ ጀሚል ሳኒ
የጎጎት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጀሚል ሳኒ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “በአመራር ደረጃ ሦስት ከፍተኛ አመራሮች እስር ላይ ናቸው። ደጋፊዎች የተለያየ ቦታ ይታሰራሉ። ቁጥራቸው አንዱ ሲታሰር ሌላው የመፈታት ሁኔታዎች አሉ” ብለዋል።
“ወደ 10 የሚደርሱ ደጋፊዎችና አባላቶች ታስረዋል” ያሉት ኃላፊው፣ “ኪዚያ በተጨማሪም አካባቢው ላይ የፓርቲያችን አባላቶች ባይሆኑም ወጣቶችን የማሳደድ፣ የማሰር (በተለይ የክልል ጥያቄ ጋር አክቲቭ ሆነው ሲሳተፉ የነበሩትንም የአካባቢው ወጣቶች አሳሳዶ የመያዝ) ሂደቶች አሉ” ሲሉ ተናግረዋል።
የታሰሩ ሰዎችን ለማስፈታት ፓርቲው ምን ያህል ጥረት አድርጓል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም አቶ ጀሚል፣ “አብዛኛው እስሩ ፖለቲካል የሆነ እስር ነው ብለን ነው የምናስበው። ብዙ ጊዜ የፖለቲካ እስር ባለቤት አይኖረውም” ብለዋል።
አቶ ጀሚል አክለውም፣ “አሁንም አቃቢ ህጎች ‘ክስ እጃችን ላይ ምንም የለም’ ሲሉ ሁለት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ‘ይሄ ነው’ ነው ብለው በጥፋትም መልክ ወይም በክስም ቢሆን ያቀረቡት ነገር የለም” ሲሉ አስረድተዋል።
አቶ ጀሚል ሳኒ ስለ ጉዳዩ በዝርዝር ምን አሉ ?
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-02-06
@tikvahethiopia
#WellComputer
𝐖𝐄𝐋𝐋 ኮምፒውተር እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የ2022/23 ሞዴል ላፕቶፖች እና ኮምፒዩተሮችን ለጨረታም ሆነ ለግልዎ፣ የተለያዩ አዳዲስ ጌሚንግ እንዲሁም ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖችን ከአስተማማኝ ዋስትና ጋር እናቀርባለን። ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች ቅናሽ እናደርጋለን!
📍አድራሻ፦ መገናኛ ከዘፍመሽ ዝቅ ብሎ 3ኤም ሲቲ ሞል / 3M City Mall 1ኛ ፎቅ ቁ. FL04 Well Computer
የሚፈልጉትን ላፕቶፕ ይምረጡ፦ /channel/welllaptop የአንድ ዓመት ሙሉ ዋስትና እንሰጣለን!
Call Us: @cr7_well 0943847549 / 0910238672
የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ መቼ ነው ?
37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
44ኛው የአባል ሀገራቱ የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከመሪዎች ጉባዔ ቀደም ብሎ የካቲት 6 እና 7 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ሕብረት የ2024 መሪ ቃል " ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት " የሚል ነው።
የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ (አዲስ አባባ) እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
#Update
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ጥር 23 /2016 ዓ.ም የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
በዚህ መግለጫው ፤ ከፕሪቶርያ ስምምነት አፈፃፅም ጋር በተያያዙ በኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ላይ የተጠቀሰውና ከትግራይ ሉአላዊ ግዛት መረጋገጥ ጋር በተያያዘ " ጉዳዩን በሪፈረንደም ለመፍታት መረዳዳት ተደርሶ ነበር " በሚል የቀረበው መግለጫ ፍፁም የተሳሳተ ነው ብሏል።
" ጊዚያዊ አሰተዳደሩም ሆነ ፌደራል መንግስቱ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ሕገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ ጉዳዩን ለመፍታት ከደረሱበት ስምምነትም ሆነ ካላቸው ስልጣን ውጪ የሆነ ተግባር መሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳነው ስለሆነ ተቀባይነት የሌለዉ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን። " ሲል አክሏል።
ሌላው ፤ ከተፈናቃዮች መመለስ ጋር ተያይዞ " ትክክለኛ ተፈናቃዮች ተመልሰዋል " በሚል የቀረበው የመግለጫው ክፍል እጅግ አደገኛና በጉልበት የሃገሪቱ ካርታ ለመቀየር የፌዴራል መከላከያ ሆነ የጎረቤት ሃገራትን አቅም ተጠቅሞ የተደረገን አውዳሚ እንቅስቃሴ ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት የሚያግዝ ነው ብሏል።
ከምንም ነገር በላይ ግን " ትክክለኛ ተፈናቃይ " ፤ " ትክክለኛ ያልሆነ ተፈናቃይ " በሚል መፈታት የነበረበትን ችግር የበለጠ የሚያባብስ አደገኛ ትንታኔ ስለሆነ አንቀበለዉም ሲል አሳውቋል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው ፤ " አሁንም ከሚልዮን በላይ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች በአስከፊ ሁኔታ የሚኖሩበት፤ ያፈናቀላቸዉ ፀረ ህዝብ እና ሕገ ወጥ አስተዳደሪዎች ፌደራል መንግስቱ ከመንበራቸው ሊያስወግዳቸው ሲገባ አሁንም ሕግ አስከባሪዎች ነን ብለው በሚመፃደቁበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንደዚህ ዓይነት መግለጫ መውጣቱ የፌደራል መንግስቱ የመፍትሄው አካል መሆን ሲገባው የችግሩ አካል ለመሆን የወሰነ የሚያስመሰለው ስለሆነ በፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
" የፌደራል መንግስቱ ከፕሪቶርያ ስምምነት ወዲህ የወሰናቸው በተለይም ከበጀትና መሰል ጉዳዮች ጋር የተያያዙ አበረታችም ሆኑ መታረም ያለባቸው ጉዳዮች በሚመለከት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፓርት የሚቀርብ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የምንለው ነገር አይኖርም " ሲል አሳውቋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ፤ ሰላም በሁሉም የትግራይ እና የኢትዮጵያ አከባቢዎች በተሟላ መልኩ የሚረጋገጥበት ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ ከፌደራል መንግስት በመቀራረብ እንደሚሰራ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
Unleash your entrepreneurial spirit with the Jasiri Talent Investor Programme! We're seeking visionary entrepreneurs ready to create high-impact businesses that will shape the future. Our fully-funded 13-month program is uniquely designed to support your growth journey, providing the resources to foster Market-Creating Innovation and find the perfect product-market fit. With a focus on competency and a comprehensive support system, we're here to help you overcome any barriers to success. Apply for Cohort 6 now at jasiri.org/application and start building your venture with us. #JasiriTalentInvestor #Entrepreneurship #Innovation #BusinessGrowth #ApplyToday
Читать полностью…#Update
ትምህርት ሚኒስቴር በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ለሀሙስ የተጠራው ስብሰባ ወደ አርብ የካቲት 1/2016 ዓ.ም ጠዋት 3:30 ሰዓት መሸጋገሩን አሳውቋል።
ማንኛውም አስተያየት መስጠት ከሚፈልግ ሰው በሰዓቱ መገኘት ይችላል ተብሏል።
መመሪያዎቹ ፦
1ኛ. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣
2ኛ. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣
3ኛ. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ ናቸው።
@tikvahethiopia
#WellComputer
𝐖𝐄𝐋𝐋 ኮምፒውተር እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የ2022/23 ሞዴል ላፕቶፖች እና ኮምፒዩተሮችን ለጨረታም ሆነ ለግልዎ፣ የተለያዩ አዳዲስ ጌሚንግ እንዲሁም ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖችን ከአስተማማኝ ዋስትና ጋር እናቀርባለን። ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች ቅናሽ እናደርጋለን!
📍አድራሻ፦ መገናኛ ከዘፍመሽ ዝቅ ብሎ 3ኤም ሲቲ ሞል / 3M City Mall 1ኛ ፎቅ ቁ. FL04 Well Computer
የሚፈልጉትን ላፕቶፕ ይምረጡ፦ /channel/welllaptop የአንድ ዓመት ሙሉ ዋስትና እንሰጣለን!
Call Us: @cr7_well 0943847549 / 0910238672
#Amhara
ዛሬ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የውይይት መድረኮች ሲካሄዱ መዋላቸውን ከመንግሥታዊ የዜና አውታሮች የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።
ውይይቶቹ የተመሩት ከፌዴራል እና ከሌሎች የሀገሪቱ ክልል በመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ነበር።
በዋነኝነት ትኩረት ያደረገው በክልሉ ያለውን ችግር ለማዳመጥና የመፍትሄ ሃሳቡን ከህዝቡ ለመረዳት ነው ተብሏል።
ባለስልጣናት በነዚህ መድረኮች ላይ ክልሉ በሰላም እጦት በሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እየከፈለ ስላለው ዋጋና እየደረሰ ስላለው ጫና ሲናገሩ ተደምጠዋል።
መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ጥረት እያደረገ መሆኑንና ይህንንም ህዝቡ ሊደግፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ጥያቄዎችን በሃይል አማራጭ ለመፍታት መሞከር ውጤት እንደሌለውና ክልሉን ወደ ባሰ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚከት ጠቁመው ፤ ሰላማዊ መንገድ መከተል ዓይነተኛ መፍትሄ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ለጥያቄዎች ከትጥቅ ትግል ይልቅ በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋብ።
በተለይ በባህር ዳር ነበረ የውይይት መድረክ የክልሉ ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ፦
➡ የወሰንና የማንነት፣
➡ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት
➡ ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በሰላም የመኖር መብት ሌሎች ጥያቄዎች ታውቀው ያደሩ መሆናቸውና በቀጣይ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ መንግስት እየሰራ ነው ብለዋል።
ዛሬ ውይይት እንደተደረገባቸው ከተሰሙት አንዷ በሆነችው ደሴ የተገኙ ተሳታፊዎች ፤ የእርስ በእርስ ግጭቱ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ፦
☑ የኑሮ ውድነት
☑ የሥራ አጥነት
☑ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ሌሎችም ተዳምረው ህብረተሰቡን ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉ ተነስቷል።
የአማራ ህዝብ #አንኳር ጥያቄዎች በተገቢው ጊዜ እና ፍጥነት መመለስ ባለመቻሉ ዛሬ ለተደረሰው የሰላም እጦት ምክንያት መሆናቸውን ተሳታፊዎች አንስተዋል።
በመንግሥትና በታጣቂ ኃይሎች መካከል ሀቅ ላይ የተመሰረተ በእውነትም ሀገርን ከትርምስ ሊያወጣ የሚችል ውይይት ማድረግ እና ክልሉም አሁን ካለበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣት እንደሚገባ ተነስቷል።
ዛሬ በተመሳሳይ ጊዜ ውይይት ተደርጎባቸዋል ከተባሉ ከተሞች መካከል ባህር ዳር፣ ደሴ፣ ወልድያ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ እንጅባራ፣ ሰቆጣ ከተሞች ይጠቀሳሉ።
በአማራ ክልል ከተሞች በነበሩት መድረኮች ላይ ፦ የሶማሌ ፣ የኦሮሚያ ፣ የሲዳማ ፣ የሐረሪ፣ የቤኒሽንጉል ጉሙዝ ክልሎች ፕሬዜዳንቶች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከንቲባ ተገኝተው ነበር።
የሀገር መከላከያ ፣ የገንዝብ ፣ የሥራ እና ክህሎት ፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል አመራሮችም ተገኝተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ ቀደም በክልሉ ከተሞች መሰል የውይይት መድረኮች ሲዘጋጁ የነበረ ቢሆንም በአንድ ጊዜ በዚህ ልክ ከፍተኛ እና የክልል አመራሮች ወደ ክልሉ ከተሞች ውይይት ሲቀመጡ ይህ የመጀመሪያ ነው።
የአማራ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ቦታዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄዱ ግጭቶች ከግጭቱ ተሳታፊዎች ባለፈ ንፁሃን ሰለባ እያደረጉ፣ ወጥቶ ለመግባት ፣ ለንግድ ፣ ለቱሪዝምም ትልቅ እንቅፋት እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተነግሯል።
@tikvahethiopia
📣 ሰምተዋል?
በማንኪያ ሲሉ በጭልፋ ፤ በጭልፋ ሲሉ በአካፋ!
👉 ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ድረስ ከሚጠቀሙት ፓኬጅ ከፍ ካሉ በእኛ ወጪ ወደ ቀጣዩ ትልቅ ፓኬጅ ለአንድ ወር ከፍ ይላሉ!
⏰ ይህ አገልግሎት ክፍያ ከፈፀሙ ከ48 ሰዓት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።
*ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን
የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/2WDuBLk
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #StepUp
ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል የተባለ ፊልም ሊመረቅ ነዉ።
የሲዳማን ህዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታት እና የውይይት ባህልን በሰፊዉ ይዳስሳል የተባለው " አፊኒ " የተሰኘ ፊልም የካቲት 2 እና 3 በሀዋሳ ከተማ እንደሚመረቅ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።
ፊልሙን በፋይናንስ የደገፈው የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መሆኑንም ለመረዳት ተችሏል።
የፊልሙ ደራሲና ተዋናይ የሆኑት አቶ እለፋቸዉ ብርሀኑ (ልኡል) ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ " ፊልሙ የሲዳማ ባህላዊ የግጭት አፈታትና የንግግር ባህል የሆነዉን አፊኒ በዓለም ላይ የማስተዋወቅ አቅም ያለዉ ነው " ብለዋል።
ለዚህም ሲባል የፊልሙን ደረጃ ዓለማቀፍ ለማድረግ ታስቦ መሰራቱን ገልጸዋል።
" ፊልሙ በፋይናንስ በሰዉ ኃይልና በቴክኒክ የተሟላ ሆኖ መሰራቱ አስደስቶኛል የሚሉት " አቶ እለፋቸው " ለዚህም ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጥቶበታል " ብለዋል።
" ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ እና ተዋናይ አማኑኤል የመሳሰሉ አርቲስቶች የሲዳማን ውብና አስተማሪ የግጭት አፈታት ባህል የሚገልጽ የድርሰት ሀሳብ ውበትና ጉልበት ሰጥተውታል " ሲሉም አክለዋል።
በሌላ በኩል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የምርቃቱን ጉዳይ እና በማህበራዊ ሚዲያ ተመድቧል እየተባለ ስለሚነገረው በሚሊዮኖች ገንዘብ መጠን ጠይቋል።
አቶ እለፋቸው ብርሃኑ ፤ " ከፊልሙ ተዋንያን ባለሙያዎችና ፊልሙን በፋይናንስ ከደገፈዉ የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የተወጣጡ የምረቃ ኮሜቲ አባላት በቅርቡ ተቋማዊ ገለጻ ያደርጋሉ " ያሉ ሲሆን ለጊዜዉ ፊልሙ የካቲት 2 እና 3 ከመመረቁ ዉጭ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
መረጃዉ የሀዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።
@tikvahethiopia
M-PESA
ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር ‘ተረክ በ M-PESA’ መርሀ ግብር አሸናፊዎች መሸለማቸውን ድርጅቱ አስታወቀ።
በሁለተኛውና ሦስተኛው ዙር የ’ተርክ በ M-PESA’ ሽልማት መርሀ ግብር ከመኪናው በተጨማሪ እድለኛ ደንበኞች አራት ባጃጆች፣ 360 ስልኮችና በሺህዎች የሚቆጠሩ የአየር ሰዓት (በእያንዳንዱ ሁለቱም ዙሮች) ተሸልመዋል ተብሏል።
ሦስት መኪናዎች፣ 12 ባጃጆች፣ 1,080 ስልኮች እና በሺህዎች የሚቆጠሩ ሽልማቶች ለእድለኞች በቀጣይ (እስከ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም) እንደሚሰጡ ድርጅቱ ተመላክቷል።
ደንበኞች በአንድ ቀን የሚደርሳቸው ከፍተኛ የእጣ ብዛት 10 ሲሆን፣ "ይህም በየእለቱ፣ በሁለት ሳምንት አንዴ እና በወር አንዴ የሚወጡ ሽልማቶችን በሚያስገኘው እጣ አወጣጥ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችላችዋል" ብሏል ድርጅቱ።
ደንበኞች፣ ወኪሎች እና ነጋዴዎች በM-PESA ለሚያደርጉት ለእያንዳንዱ የ20 ብር ግብይት አንድ እጣ በአጭር የስልክ መልእክት እንደሚላክላቸው፣ M-PESAን መጠቀም በመጀመራቸው አምስት እጣ እንደሚያገኙ ተነግራል።
M-PESA ሳፋሪኮም አሸናፊዎችን በ+251-700 700 700 ብቻ በመደወል እንዴት ሽልማታቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ድርጅቱ አብስሯል።
እንደ ገለጻው ከሆነ፣ ደንበኞች የአየር ሰዓት ሽልማት ሲደርሳቸው ደግሞ ከተረክ በM-PESA አጭር የጽሁፍ መልእክት ይደርሳቸውና ወዲያው የአየር ሰዓታቸው የሚሞላ ይሆናል።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
➡ “ የፍርድ ቤት ማገጃ ጥሰው ዕቃችንን አውጥተው ሜዳ ኮብልስቶን ላይ ጣሉን ” - የቄራ ነዋሪዎች
➡ “ ከሳሾች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡና ይህን ቤት ለሌላ ሰው እንዳይሰጥ” - የፍርድ ቤት ደብዳቤ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ቄራ ዶሮ ተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኙ “ የድሃ ድሃ ” የተባሉ የቀበሌ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ሰዎች ፍርድ ቤት እንዳይወጡ የሚያዝ ደብዳቤ ቢጽፍላቸውም የእግዱን ውሳኔ በመጣስ የፓሊስ አባላት ከቤት አስወጥተው ሜዳ ላይ እንደጣሏቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹን ወክለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ከባለጉዳዮቹ መካከል አንዱ ፣ ቄራ ዶሮ ተራ 11 አባውራዎች እያንዳንዳቸው የቀበሌ ቤት ተከራይተው ይኖሩ እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ ቤቱ 'የቀበሌ ነው' ተብለው ውጡ እንደተባሉ፣ ይህን ተከትሎም፣ ፍርድ ቤት ክስ መስርተው ማገጃ እንዳስመጡ፣ በዚሁ ጉዳይ ፍርድ ቤት ለሁለት ጊዜያት ያህል ቀጠሮ እንደሰጣቸው አስረድተዋል።
አክለውም፣ “ ፍርድ ቤት ሁከት ይወገድልን ብለን ክስ መስርተን ማገጃ አስመጣን። ከዚያ ‘እናንተ በተከራያችሁት ክፈሉ’ ተብለን መክፈል ጀመርን። በዚያ ሁኔታ እያለን ሳንሰማ፣ ምንም ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ መጡና ‘በሦስት ቀናት ውስጥ ውጡ’ አሉን ” ሲሉ ገልጸዋል።
እኛም ፍርድ ቤት ሂደን ማገጃ አመጣን ያሉት ቅሬታ አቅራቢው፣ “ የፍርድ ቤት ማገጃውን ጥሰው ዕቃችንን አውጥተው ሜዳ ኮብልስቶን ላይ ጣሉን። የእገዳ ወረቀት አምጥተን እራሱ ‘ማንም ኣይከለክለንም፣ እንቀበልም’ ብለው ከቤት አስወጥተው ሜዳ ላይ በትነውን፣ አሽገውት ሄዱ። ውጪ ላይ ነን ” ሲሉ አማረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የፍርድ ቤት ደብዳቤ፣ “ ለን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 06 ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በከሳሽ እነ ኤሊያስ ዘርጋና በተከሳሽ የን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 06 ቤቶች አስተዳደር ባለው ክርክር ከሳሾች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡና ይህን ቤት ለሌላ ሰው እንዳይሰጥ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ ቁጥር 154 መሠረት ይህ የእግድ ትዕዛዝ እስከ 27/05/2016 ዓ/ም ድረስ ተሰጠ ” ሲል ያረጋግጣል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቤት ያስለቀቋቸው የአዲስ አበባና የፓሊስ አባላት መሆናቸውን በገለጹት መሠረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው አንድ የዶሮ ተራ ቀጠና ፓሊስ፣ ሰዎቹ የቀበሌ ቤት ነው ተብለው እንዲወጡ እንደተደረገ ገልጸው ተጨማሪ ማብራሪያ ከወረዳው ጠይቁ ብለዋል።
ይሁን እንጂ ከወረዳው እስከ ፓሊስ ኮሚሽን የተደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።
ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#AddisMayaPlayschool
We are registering!
1 to 4 years
Tel: 0906929258 / 0906839358
Email: info@addis-maya.com website:https://www.addis-maya.com/
Address : Bisrate Gebriel , Around Ireland Embassy (Residence)