ቀለል ያለ ግምት በመስጠት ይሸለሙ!
ግምትዎን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል /channel/GlobalBankEth ይስጡ!
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #GBE #ArsLiv #Arsenal #Liverpool #PremierLeague
የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከምን ደረሰ ?
" ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ መንገድ ይጠርጋል " የተባለው የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌለንድ ጋር ከተፈረመ ትላንት 1 ወር አልፎታል።
የመግባቢያ ስምምነቱ እኤአ ጥር 1 ነበር የተፈረመው።
ይህ ስምምነት በተፈረመበት ወቅት በመንግሥት ባለስልጣናት በኩል በተሰጡ ገለፃዎች ፦
* በ1 ወር ውስጥ የስምምነቱ ዝርዝር ይፋ እንደሚደረግ፤
* ስምምነቱ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሂደቱ ያልቃል / ወደ ተግባር / ስራ እንደሚገባ ተነግሮ ነበር።
እስካሁን ቀጣይ የስምምነቱን ምዕራፎች በተመለከተ / ሂደቱ ምን ላይ እንደደረሰ በይፋ የተሰጠ ማብራሪያ የለም።
ከጥቂት ቀናት በፊት በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ፤ ጉዳዩን ለማጠናቀቅ ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር ላይ እንደነበር መግለፃቸው ይታወሳል።
የስምምነት ፊርማውን ትከትሎም ግንኙነቶች እንደነበሩ፤ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትርም ጉዳዩን ለማሳለጥና መሰረት ለማስያዝ ኢትዮጵያ ቆይተው መመላሳቸውን ተናግረው ነበር።
የሶማሌላንድ ተወካዩ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ፤ ይዋል ይደር እንጂ ሁለቱ ኮሚቴዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እንደሚደረግ ፤ ይህ በጣም በቅርቡ እንደሚከናወን አመልክተው ነበር።
ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የዛሬ 1 ወር ኢትዮጵያን የባህር በር እንድታገኝ የሚያስችል ፤ ሶማሌላንድ ደግሞ ሉዓላዊ ሀገር እንደሆነች እውቅና ልታገኝ የምትችልበትን ዕድል ይፈጥራል የተባለ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል።
ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ የሰነበተ ሲሆን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል መቃቃርን ፈጥሯል ይህ መቃቃር እስካሁን ያልተፈታ ሲሆን በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በኩል የስምምነቱ ቀጣይ ሂደት በ1 ወር ውስጥ ያልቃል ፣ ዝርዝሩ ይፋ ይደረጋል ቢባልም እስካሁን ስለጉዳዩ የተባለ ነገር የለም።
@tikvahethiopia
ድንገተኛ ወጪ አጋጥምዎት፣ ገንዘብ አስፈልግዎታል?
ቴሌብር አለ!
ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብዎ ወዲያውኑ በቀላሉ ገንዘብ በቴሌብር ይጠይቁ እና ይቀበሉ።
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#Update
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተራዘመ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አንደኛ ልዩ ስብሰባው በአማራ ክልል የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት አራዝሞታል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሁለት ተቃውሞ በሶሰት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ለአራት ወራት የተራዘመው።
@tikvahethiopia
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስተያየት እንዲሰጥ መድረክ መመቻቸቱን አሳውቋል።
የትምህርት ሚኒስቴር : -
1ኛ. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣
2ኛ. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣
3ኛ. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ ምምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።
መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ መሰረት መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ ማዘጋጀቱን ጠቁሟል።
በዚህም መሰረት ጥር 30/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት መስጠት እንደሚቻል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
አፖሎ ካለ "ኢንተርኔት ተቋርጦ ገንዘብ መላክም መቀበልም አልቻልኩ" ማለት የለም።
*685# በመደወል አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#StateofEmergency
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል።
በዚህም ስብሰባው በዋነኝነት በአማራ ክልል እንደ አስፈላጊነቱም በመላው ሀገሪቱ እንዲፈፀም ለ6 ወራት ታውጆ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።
የምክር ቤት አባላት ዛሬ ከመሸ ለነገው ልዩ ስብሰባ " አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማረዘም " የሚለውን ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎች እንደተላከላቸው ተነግሯል።
የተወካዮች ምክር ቤት በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ እንዲሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያጸደቀው ነሐሴ 8/2015 ነበር።
ለ6 ወራት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀነ ገደብ በዛሬው ዕለት በመጠናቀቁ ነገ ም/ቤቱ በ " ልዩ ስብሰባ " አዋጁን ያራዝመዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህን መረጃ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የምክር ቤት አባላትን ዋቢ በማድረግ ነው ያሰራጨው።
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ ዛሬ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ለሶስተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር።
ሰልፈኞቹ በጋራ ከሚኖሩበት ሰፈር በሰልፍ በመውጣትና በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ፦
- የተገባልን ቃል ይተግበር !!
- አጉል ተስፋ ይብቃን!!
- ከአግባብ ውጪ ከወርሃዊ ራሽናችን መቁረጥ ይቁም !
- በሰውነታችን ውስጥ ያለው ብረት አውጡልን ! የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል።
የጦርነት አካል ጉዳተኞች ዛሬ በመቐለ ከተማ ያካሄዱት ሰላማዊ ስልፍ በማስመልከት መልስ እንዲሰጡ የመቐለ 104.4 ኤፍኤም ሬድዮ ጣብያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ናስር መምሑር ፤ " የጦርነት አካል ጉዳተኞቹ ያቀረቡት ጥያቄ በዝርዝር ለመስማትና ችግሮቻቸው በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ያለው ስራ በማስመልከት ለመወያየት ኮሚሽኑ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በመሆን ነገ ወደ መኖሪያ ካምፓቸው እንሄዳለን " ብለዋል።
" የአካል ጉዳተኞቹን ጥያቄዎች በስፋትና በጥልቀት በማድመጥ መፍትሄ እናስቀምጣለን " ሲሉ አክልዋል።
መረጃውን የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የላከው።
ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia
#FederalGovernment
የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚፈልግ የፌዴራል መንግሥት ገለጸ።
የፌዴራል መንግሥት ፤ ሕወሓት ትላንትና ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲከበር መጠየቁን #በአንክሮ እንደተመለከተው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ዋነኛው መፍትሔ የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን የኢፌድሪ መንግሥት በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል።
ይሄንንም በተመለከተ የፌዴራሉ መንግሥት ከመነሻው እስካሁን ያለው አቋም ወጥ እና የማይናወጥ መሆኑን በመግለጫው አረጋግጧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
" ህወሓት " ትላንትና ያወጣው መግለጫ በዚህ ተያይዟል ፦ /channel/tikvahethiopia/84794?single
@tikvahethiopia
#DStv
ቀላል እና ፈጣን መላ ለዲኤስቲቪ ደንበኞች በሙሉ!
ወደ ዲኤስቲቪ የጥሪ ማዕከል ሳይደውሉ በማንኛውም ሰዓት በሞባይልዎ *9299# በመደወል እና My DStv App ስምዎንና የስማርት ካርድ ቁጥርዎን አስገብተው የዲኤስቲቪ ክፍያ መጠንዎንና ቀኑን በቀላሉ ለማወቅ ፓኬጅ ለመቀየር ብሎም በቴሌብር ፣ በሲቢኢ ብር እና በአዋሽ ብር መክፈል ይችላሉ።
የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/2WDuBLk
የፕሌይ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/3qJ95Us
የአፕ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/45hIwEU
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#DrDessalegnChane
በ2013 ዓ/ም በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) መታሰራቸውን ቤተሰባቸውን ዋቢ በማድረግ አል አይን አማርኛው አገልግሎት ዘግቧል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ቤተሰብ አባል ፤ " ትናንት ጥር 22 ቀን 2016 ዓ .ም ምሽት 3:30 ላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት የጸጥታ ሀይሎች መጥተው ደሳለኝ ጫኔን ለጥያቄ እንፈልግሀለን ብለው ወስደውታል " ብለዋል።
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታስረው እንደሚገኙ ተናግረውም ፤ " የፌደራል ፖሊሶቹ ለጥያቄ እንፈልግሀለን " ከማለት ውጪ ምንም ያሉት ነገር የለም ሲሉም ተናግረዋል።
ዛሬ ጠዋት ጀምሮም ተጨማሪ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ መኖሪያ ቤቱ መጥተው ፍተሻ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ ጉዳዩን በተመለከተ ተጠይቀው ፤ " አሁን ላይ ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም " ሲሉ መናገራቸውን አል አይን አማርኛው ክፍል በዘገባው ገልጿል።
@tikvahethiopia
" ለ ' ህወሓት' የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ
በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ለ "ህወሓት" እውቅና ስለ መሰጠቱ የሚሰያጨው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተለይም በፌስቡክ ለ " ህወሓት " እውቅና ስለመሰጠቱ #ሀሰተኛ_መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን በተደረገ ቅኝት ማየት መቻሉን የገለፀ ሲሆን ለ " ህወሓት " የተሰጠ እውቅና #እንደሌለ ቢሮው ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው እለት ፦
- ለወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
- ለኩሽ ህዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ
- ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ለተባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን አሳውቋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ለ "ህወሓት" እውቅና ተሰጠ ተብሎ የሚሰራጨው #ሀሰተኛ_መረጃ ፥ መረጃውን የእውነት ለማስመሰል እየተደረገ ያለ ሙከራ መሆኑን የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያስረዳ ሲሆን " ለህወሓት የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " ብሏል።
ማንኛውም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን የተመለከተ መረጃ በቦርዱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እስካልወጣ ድረስ መረጃዎቹ ሀሰተኛ መሆናቸውንና ቦርዱን የማይወክሉ መሆኑን እንዲታወቅልኝ ሲል ቦርዱ አሳስቧል።
@tikvahethiopia
Jasiri Talent Investor Programme is now welcoming bold and brave aspiring women Ethiopian entrepreneurs ready to lead and innovate. It's more than a program—it's your opportunity to rise as a future leader. Apply for Cohort 6 today at jasiri.org/application and join a network committed to empowering women in business. #FutureFemaleLeaders #JASIRITalentInvestor #WomenEntrepreneurs #Ethiopia #Innovation #Leadership
Читать полностью…#TPLF #ህወሓት
ክልላዊ ፣ አገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ባካተቱ 6 ነጥቦች ላለፉት ከ41 ቀናት በላይ ስብሰባ መቀመጡን የገለፀው ህወሓት ዛሬ ባለ 6 ገፅ መግለጫ አውጥቷል።
ጥር 22/2016 ዓ.ም ባወጣው መገለጫ እንዳስታወቀው ረጅም ጊዚያት ወስዶ ያካሄደው የድርጅቱ የፓሊትና የማእከላይ ኮሚቴ የግምገማ ፣ የሂስና የግለሂስ መድረክ ወደ ቀጣዩ ጉባኤ የሚያሸጋግሩ ወሳኔዎች የተወሰኑበት ነው ብሏል።
ህወሓት በመግለጫው ፦
- ለትግራይ ህዝብ
- ለድርጅቱ አመራርና አባላት
- ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች
- ለኤርትራ ህዝብ
- ለዓለም ማህበረሰብና ለትግሉ ደጋፊዎች እንዲሁም ሌሎችም አካላት መልእክት አስተላልፈዋል።
ህወሓት በተለይ ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች ባስተላለፈው መልእክት ፤ " ህወሓት ለትግራይ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች የሰላም ስትራቴጂክ አማራጭ ከመሆን በዘለለ በማንም ህዝብ ላይ ጥላቻ አንደሌለው አረጋግጣለሁ " ብሏል።
" ከኤርትራ ህዝብ የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረግ የትግል አጋርነት ነበረን አጋርነቱና የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ መደጋገፉ ይቀጥላል " ያለው ህወሓት " የኤርትራ ህዝብ የኤርትራ ሰራዊት በሃይል ከያዛቸው የትግራይ ግዛቶች ለቆ እንዲወጣ ጫና እንዲያሳድር የሚያስታውስ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ህወሓት " ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብና ከትግላችን ደጋፊዎች " በሚል ባስተላለፈው መልእክት " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ፣ ስምምነቱ መሰረት ያደረገ ውይይት እንዲካሄድ ፣ የትግራይ የግዛት አንድነት እንዲረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ፣ የትግራይ መልሶ ግንባታ እንዲፋጠን ፣ ሰብአዊ ወንጀል የፈፀሙ በዓለም አቀፍ ህግ እንዲዳኙ እንዲደረግ የበኩላችሁ እንድትወጡ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል " ማለቱ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
ገንዘብ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ #አለመከልከሉን ገለጸ።
ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢል እንዳይገቡ #መከልከሉን ማሳወቁ አይዘነጋም።
የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህግ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ ምን አሉ ?
- በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በመከልከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዲገቡ የሚፈቅድ ምንም አይነት መመሪያም ሆነ ውሳኔ የለም።
- ገንዘብ ሚኒስቴር እያከናወነ ያለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ለማበረታታት እና በነዳጅ የሚሰሩ በብዛት እንዳይገቡ ተስፋ ለማስቆረጥ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ የተደነገገበት ሁኔታ አለ።
- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማገድ በዓለም የንግድ ድርጅት ህግ መሰረት የማይቻል በመሆኑ የሀገሪቱን የቀረጥ ስርዓት በመጠቀም ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚጠቀሙትን ማበረታታት ጎጂ የሆኑትን እንዳይስፋፉ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ነው።
- በትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ለፓርላማ ስለቀረበው ጉዳይ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።
- ገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት እንዲገቡ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ተደርጓል። አዋጁ፦
* ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው ለሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች 5% ኤክሳይዝ ታክስ
* ተበታትነው ገብተው ሀገር ውስጥ ለሚገጣጠሙ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚያስችል ነው።
* በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች እንደሚጠቀሙት የነዳጅ መጠን 10% እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተደርጓል።
- የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ነጋዴዎች ተግባራዊ ማድረግ የሚጀምሩት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት 38 የተለያዩ ምርቶች ከባንክ ፍቃድ /letter of credit/ እንዳይከፈትላቸው የሚከለክለው እገዳ ከተነሳ በኃላ ነው።
- በአሁን ወቅት ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ያሉት ተሽከርካሪዎች ክልከላው ከመደረጉ በፊት ተከፍቶ በነበረ LC እንጂ በልዩ ሁኔታ ተፈቅዶላቸው የሚያስገቡ ነጋዴዎች የሉም።
- የLC እገዳው ካልተነሳ በስተቀር ለንግድ ወይም ለመንግሥት መስሪያ ቤት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች በገንዘብ ሚኒስቴር እውቅና ብቻ አይገቡም። ክልከላው የማይመለከታቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGO) ቢሆኑም በነዳጅ የሚሰራ ተሽከርካሪ በሚያስገቡበት ጊዜ በኤክሳይዝ ታክስ ተስተናግደው ነው።
ይህ የገንዘብ ሚኒስቴር አስተያየት በተመለከተ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ኃላፊ እገዳው በመመሪያ / በውሳኔ የተገለፀ አይደለም ብለዋል።
ግን ሁሉም የሚመለከታቸው መ/ቤቶች ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በ100 ቀናት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በተደረገ ግምገማ በተሰጠው አቅጣጫ በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎች እንዳይገቡ መከልከሉን ገልጸዋል።
አንድ የጉምሩክ ኮሚሽን ኃላፊ ደግሞ በአሁን ወቅት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው በብሄራዊ ባንክ የወጣው ውሳኔ ላይ በመሆኑ ውሳኔው በተዘዋዋሪ በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ የተከለከለው አሁን አዲስ በተሰጠ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ ብቻ አይደለም ብለዋል።
ብሄራዊ ባንክ ጥቅምት 4/2015 ይፋ እንዳደረገው ወደ ሀገር እንዳይገቡ ክልከላ የተደረገባቸው 38 ምርቶች ውስጥ ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል። ከሞተር ነክ ምርቶች የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የተካተቱ ሲሆን እገዳው በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን እንደማያካት ይታወቃል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/reporter-01-31
ይህ መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።
@tikvahethiopia
" ... ለአንድ ሓጅ አጠቃላይ ብር 329,000 እንዲሆን ተወስኗል " - ከኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት
የዘንድሮው የሐጅ እና ዑምራ ምዝገባ ነገ ቅዳሜ ጥር 25 በይፋ የሚጀመር መሆኑ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።
የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ በባለፈው ዓመት 2015 ከነበሩት 18 የምዝገባ ጣቢያዎች ላይ 9 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመጨመር ወደ 27 ከፍ እንዲሉ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል።
የምዝገባ ጣቢያዎች ፦
- ስቴዲያም በሚገኘው የኦሮሚያ መጅሊስ ዋና ቢሮ፣
- ጦር ሃይሎች በሚገኘው የአዲስ አበባ መጅሊስ ዋና ቢሮ፣
- በሻሸመኔ፣ በጂማ፣ በሀረር፣ በጂግጂጋ፣ በድሬዳዋ፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በሀረሪ፣ በሐዋሳ፣ በቴፒ፣ በአሶሳ፣ በሰመራ፣ በባሌ በሮቤ፤ በወራቤ፤ በጎዴ፣ በሞያሌ የሚገኙ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
የሐጅ ዋጋ ተመንም ይፋ የተደረገ ሲሆን ወቅታዊ የዓለም ዓቀፍና አገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለአንድ ሓጅ አጠቃላይ ብር 329,000.00 (ሦሥት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ይህ የዋጋ ተመን ባለበት መልኩ የሚፀናዉ የዶላር ዋጋ አሁን ባለበት የሚቀጥል አሊያም በመደበኛ የአጨማማር ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ብቻ ነው ተብሏል።
ማንኛዉም የሐጅ ተጓዥ ለምዝገባ በአካል ወደ ምዝገባ ጣቢያዎች ለምዝገባ ሲቀርብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል ፡-
1.የመኖሪያ አካባቢያቸዉን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ
2. የታደሰ የጉዞ ሰነድ ፖስፖርት (የመጠቀሚያ ጊዜው ለመጠናቀቅ ከ11 ወራት በላይ የቀረው መሆን አለበት)
3. አንድ ጉርድ ፍቶ ግራፍ
4. የኮቪድና የቢጫ ወባ ክትባት ካርድ
በዕድሜ መግፋትና በተለያዩ አካላዊ ጉዳቶች ምክንያት እራሳቸዉን ችለው የሐጅ ስርዓቱን መፈፀም የማይችሉ ሁጃጆች አስፈላጊውን መስፈርት ከማሟላታቸው ባሻገር ሊያግዛቸው የሚችል አብሯቸው የሚጓዝ ደጋፊ ሰው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።
ሁጃጆች አስፈላጊ መስፈርቶች ማሟላታቸዉ በምዝገባ ጣቢያ ኃላፊ ሲረጋገጥና የባንክ ክፊያ እንዲከፍሉ ማረጋገጫ ሲሰጣቸው ብቻ የሐጅ መስተንግዶውን ክፍያ ዲፖዚት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
“ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ ነው ” - የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ
የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ፤ ጤና ባለሞያዎች ወደሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
“ የጤና ተቋማት የሥራ ማስኬጃ በጀት ይመደብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ግን ይሄ የለም ” ሲልም አመልክቷል።
የቢሮ የፈውስና ተሃድሶ ዋና የሥራ ሂደት ስምኦን ገ/ፃዲቅ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ ነው ” ብለዋል።
አሁን ‘ሁሉም ነገር ወደነበረበት ተመልሷል’ በሚባልበት ሁኔታ መቋቋም እንኳ ስላልቻሉ የፈለሱ የጤና ባለሙያዎችን በቁጥር ለመግለጽ ለጊዜው ባይቻልም አዲስ አበባን ጨምሮ የተሻለ ክፍያ ወዳለባቸው ሌሎች የውጪ አገራት ጭምር እየፈለሱ መሆኑ ነው የተገለጸው።
ስምኦን (ዶ/ር)፣ ለሠራተኞች ፍልሰት ምክንያቱ ፦
* የ17 ወራት ደመወዝ፣
* የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው፣ መሆኑን ገልጸው፣ “ደመወዝ አልተከፈላቸውም ማለት የዕለት ተዕለት ወጪ መሸፈኛ የቤትን ኪራይን ጨምሮ ሲቆይባቸው ነው የቆየው ” ብለዋል።
“ሌላውን ትተን የቤት ኪራይ እንኳ መክፈል አልቻሉም። አሁን የተበጣጠሰ የደመወዝ ክፍያ ቢኖርም በተጨማሪ ደግሞ የትርፍ ሰዓት ክፍያ የላቸውም” ያሉት የሥራ ሂደት ተተኪው፣ “የጤና ተቋማት የሥራ ማስኬጃ በጀት ይመደብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ግን ይሄ የለም ” ሲሉ የሁነቱን አሳሳቢነት አስረድተዋል።
“ ጤና ቢሮ፣ የክልል መንግሥትም ከፌደራል መንግሥት በሚያገኘው የደመወዝና የትርፍ ሰዓት ክፍያ ብቻ ሳይሆን የጤና ተቋማት የመድኃኒት መግዣና የሌላ ሥራ ማስኬጃ በጀት ይመድብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ይሄ የለም” ብለዋል።
ዶ/ር ስምኦን አክለውም፣ “መበጀት የነበረበት ያለፈው የ17 ወራት ደመወዝና ጥቅማጥቅም፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳለ ሆኖ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ደመወዝ መከፈል ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ ያለውም የተበጀተ በጀት የለም” ነው ያሉት።
በመሆኑም ከፌደራል መንግሥት ጀምሮ ያለው ሁሉም የሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሁሉ እየፈለሱ ያሉት የጤና ባለሙያዎች በቦታቸው እንዲቆዩ ለማድረግ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚጠባ ተጠይቋል።
መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።
@tikvahethiopia
25 ዓመታት በሕብረት
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
ቴሌግራም- /channel/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#AddisMayaPlayschool
We are registering!
1 to 4 years
Tel: 0906929258 / 0906839358
Email: info@addis-maya.com website:https://www.addis-maya.com/
Address : Bisrate Gebriel , Around Ireland Embassy (Residence)
“ ኑሮ ከብዷት ነው ! ”
ኑሮ ከብዷቸው ራሳቸውን ለማጥፋት ትልቁ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ጫፍ የወጡ አንዲት እናት በሕይወት ተረፉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጫው ካሬ ቀበሌ ወይሶ ሰፈር ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም፣ ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት ወ/ሮ ሂሩት በቀለ “ራሳቸውን ለማጥፋት” ረጅሙ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ጫፍ ላይ ወጥተው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከወረዳው ባለስልጣን ማረጋገጥ ችሏል።
ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት በክልሉ ወላይታ ሶዶ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን አስራት ፣ “ ማክሰኞ ዕለት (ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም) የመብራት ፖል ጫፍ ላይ ወጥታ፣ አውቶማቲክ ስለሆነ በራሱ ጊዜ ዘጋና ጠቆማ ሰጠን (ሰው ወደ ላይ እየወጣ እንደሆነ)፣ ከዚያ ከወረዳ ቲም ተዋቅሮ ፓሊስ፣ የወረዳው አመራርና የቀበሌ አመራር አንድ ላይ በመሆን ወደ ስፍራው ደርሰው ሴትዮዋ ጋ ሲደርሱ ጫፍ ላይ ወጥታ ነበር ” ብለዋል።
“ አንድ ላይ በመሆን እንድትወርድ ሰዎች ለምነው ነበረ፣ ‘አልወርድም’ ብላ በጣም አስቸግራ ነበር” ያሉት አቶ ተመስገን፣ “ሌሎቹ ሰዎች ተደብቀው ፓሊስ፣ የሴትዮዋ እናትና አባት አንድ ላይ ሆነው በመለመን ወረደች ” ሲሉ አስረድተዋል።
ወ/ሮ ሂሩት እንዲህ ያደረጉት ለምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ተመስገን፣ “ ኑሮ ከብዷት ነው። የሁለት ልጆች እናት ናት። ኑሮ ከብዷት ከባለቤቷ ሁሉ ተጣልታ ከቤተሰቦቿ ጋ ነች። እናትና አባቷ ጋ ሆና ነው ይሄ ክስተት የተፈጠረው ” ብለዋል።
ሴትዮዋ ሕመምተኛ ስለሆኑ ከወረዱ በኋላም ሶዶ ኦተና ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው ለጊዜው በወላይታ ሶዶ የሚገኘው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#Haile
" ሙሉን አፍርሰን እየገነባን ነው። ከመንግሥት ምንም ማካካሻ አልተደረገልኝም " - ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ
ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ከዚህ በፊት በሻሸመኔ በጸጥታ ችግር ስለወደመው ሆቴል ሁኔታ እና በጎንደር ከተማ በሚገኘው ሪዞርት በኩል በጸጥታ ችግር የገጠማቸውን የገቢ መቀዛቀዝን በተመለከተ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሆቴል ምረቃ መርሀ ግብር በተገኙበት ወቅት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ችግር የወደመባቸውን ሆቴል በተመለከተ ባደረጉት ገለጻ፣ እስካሁን መንግሥት መንግሥት ካሳ እንዳልከፈለና አሁንም ይከፍላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ነው የተናገሩት።
" ሙሉን አፍርሰን እየገነባን ነው። ከመንግሥት ምንም ማካካሻ አልተደረገልኝም " ያሉት ሻለቃ ኃይሌ፣ የሻሸመኔው ሆቴልም በቀጣይ ከሚመረቁት ሆቴሎችና ሪዞሮቶች መካከል አንዱ መሆኑን አስረድተዋል።
ከሻሸመኔው ሆቴል ውድመት ባሻገር በመከላከያና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በየወቅቱ የጸጥታ ችግር በሚስተዋልበት አማራ ክልል ጎንደር ከተማ ሪዞርታቸው ሲያገኝ የነበረው የገቢ ምንጭ መቀዛቀዙን ገልጸዋል።
ሻለቃ ኃይሌ፣ ከጎንደር ከተማ ሪዞርት በዓመት ከሚገኘው ግማሽ ያህሉ ገቢ በጥምቀት ወቅት ይሰራ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር የገቢ መቀዛቀዝ እንዳጋጠመ ሲገልጹ ተደምጠዋል።
መረጀውን የላከው በመርሀ ግብሩ የተገኘው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።
@tikvahethiopia
#FederalGovernment
የፌዴራል መንግሥት ፤ " የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚፈልግ " በገለፀበት የዛሬ መግለጫው ፤ በትግራይ ክልል ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ መኖሪያቸው ለመመለስ እንዲቻል የሚመለከታቸውን አካላት አቀናጅቶ ሥራ መጀመሩን አመልክቷል።
በአንዳንድ አካባቢዎች ትክክለኛ ተፈናቃዮችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ መደረጉንም ገልጿል።
የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጉዳዩ በዋናንት ከሚመለከታቸው ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል።
" በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት በሕወሓት በኩል ታጥቀው ሲዋጉ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ አለባቸው " ያለው የፌዴራል መንግሥት " ለዚህ የሚረዳ የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ፌዴራል መንግሥትም የሚጠበቅበትን የሰው ኃይልና በጀትም መድቧል " ብሏል።
የፌዴራል መንግሥት ፤ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን በተመለከተ ተገቢውን ርምጃ በእራሱ በኩል መውሰዱን ፤ ተጠያቂ መሆን ያለባቸውንም ተጠያቂ ማድረጉን ገልጿል።
ሌሎች ሥራዎችን ለማከናወን እንዲቻል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዐዋጅ ረቂቅ ዝግጅት መጠናቀቁን አሳውቋል።
ይህ ሂደት እንዲሳካም እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ የትግራይ ክልልም ተገቢው ሚና እንዲጫወት ይጠበቃል ብሏል።
የፌዴራል መንግሥት ፤ ለትግራይ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት ሲባል ማድረግ ያለበትን ተግባራት ሁሉ ከሚገባው ባሻገር ተጉዞ ማከናወኑን አሳውቋል።
ለክልሉ ሕዝብ መደረግ ያለባቸው ድጋፎችንም በራሱ ዐቅምም ሆነ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለማከናወን የፌዴራሉ መንግሥት ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሸዋ ሱፐርማርኬት አካባቢ በመገንባት ላይ ያለ ህንጻ የአፈር ክምር ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
ህይወቱ ያለፈዉና ጉዳት የደረሰበት ሰዉ በዚሁ የህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ናቸዉ።
አደጋው የተከሰተበት የህንጻ ግንባታ ስራ አሁንም ለአደጋ ስጋት በመሆኑ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የሚመለከታቸዉ አካላት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል።
በዚሁ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ከ3 ቀናት በፊት በህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የነበሩ 2 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፎ ነበር።
@tikvahethiopia
ሀይሌ ሆቴል ወላይታ ተመረቀ።
በአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ 1.1 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ ባለ 4 ኮከብ ሆቴል ተመረቀ።
ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ በዚሁ መርሀ ግብር ባደረጉት ገለጻ፣ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ፦
- በጅማ፣
- በደብረ ብርሃን
- በሻሸመኔ ከተሞች ሦስት ሆቴሎችን ለማጠናቀቅ ማቀዳቸውን ጠቁመዋል።
ሻለቃ ሀይሌ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ዞን አዲስ የተመረቀው ሆቴል 1.1 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት፣ ፕሮጀክቱ እንደዘገየ፣ ለዚህም የግንባታ ዕቃዎች መወደድ፣ ከውጪ የሚመጡ ዕቃዎች የምንዛሪ ዕጥረት ፈታኝነት ምክንያቱ እንደነበር አውስተዋል።
ሆቴሉ “107 ሩሞች አሉት” ያሉት ሻለቃ ሀይሌ፣ ላለፉት 4 ዓመታት መሬቱን ከመቀበል ጀምሮ የዞኑና የክልሉ ባለሥልጣናት ላደረጉላቸው ቀና ትብብር አመስግነው፣ “ሆቴሉ የህብረተሰቡ ሀብት ነው” ብለዋል።
ለአካል ጉዳተኞች አካታችነት በምን ደረጃ ነው? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሻለቃ ሀይሌ፣ “ዋናው ሊሰራ የታሰበው እሱ ነው። ዋናው ኮከብ ለማግኘት ያለ አካል ጉዳተኞች እኮ አይሆንም” ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት የሻለቃ ሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ በበኩላቸው፣ የሻለቃ ሀይሌ ሆቴልና ሪዞርት ግንባታዎችን ከኢትዮጵያ ባሻገር ወደ አህጉሪቱ ይዞ የመውጣት (ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ይዞ የመንቀሳቀስ) ዕቅድና ዓላማ መያዙን አመላክተዋል።
የሻለቃ ሀይሌ ሆቴልና ሪዞርት ወላይታ ሶዶ ጀነራል ማናጀር አቶ ጌትነት ታሪኩ በበኩላቸው፣ ሆቴሉ በውስጡ ምን ምን ይዟል ? ለሚሉት ጉዳዮች በሰጡት ማብራሪያ ፦
➡ 107 የዕንግዳ መቀበያ ክፍሎች፣
➡ በየፊናቸው እንደዬ አቅማቸው ከ15 - 600 ሰዎች የመያዝ አቅም ያላቸው 7 ቅንጡ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣
➡ የወላይታ ባህላዊንና የውጪውን ጨምሮ ሦስት የምግብ አዳራሽ ወይም ሬስቶራንቶች፣
➡ የለስላሳና የአልኮሎ መሸጫ ሁለት ባሮች
➡ የጤናና የውበት ሳሎኖች
➡ ጂምናዜም፣
➡ ማሳጅ፣
➡ ስቲም ባዝ ሩሞች መካተታቸውን ገልጸዋል።
አዲሱ ሆቴል የፈጠረውንና ለመፍጠር ያቀደውን የሥራ ዕድል በተመለከተም፣ በአሁኑ ወቅት 160 ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ፣ ሆቴሉ ሙሉ ለሙሉ ሥራውን ሲጀምር እስከ 300 ሰዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን አስረድተዋል።
መርሀ ግብሩ ሻለቃ ሀይሌ፣ ባለቤታቸው፣ የክልልሉ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላና የተለያዩ የመንግሥት አካላት ተገኝተዋል።
ዘገባውን ያደረሰን በመርሀ ግብሩ የተገኘው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#ባይቶና
በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው "ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የተባለ የፓለቲካ ድርጅት ሙሉ እውቅና ማግኘቱ አስታውቋል።
በእነ ዶ/ር ፀጋዛኣብ ካሕሱ ከሚመራው " ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የፓለቲካ ደርጅት ተነጥሎ የወጣው ባይቶና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሙሉ እውቅና ማግኘቱን ገልጿል።
በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው " ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የፓለቲካ ፓርቲ ጥር 22/2016 ዓ.ም ባሰራጨው መረጃ እንዳመለከተው ፤ ከጥቅምት 17 - 18 / 2016 ዓ.ም መስራች ጉባኤ ማካሄዱ አስታውሶ " ከብዙ ውጣ ውረድ ሁሉም መስፈርቶች በሟሟላት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሙሉ እውቅና አግኝቻለሁ " ብሏል።
ድርጅቱ ለሁሉም አመራሮቹ ፣ ለአባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ለመላው የትግራይ ህዝብና የትግል አጋሮቼ ላላቸው የአንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ማስተላለፉ የዘገበው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#CBE
በቲክቶክ ያግኙን!
*********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ትክክለኛ የቲክቶክ ገጽ (combankethiopia" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@combankethiopia) በመከተል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ!
********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
የመውጫ ፈተና ተራዘመ።
የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ መራዘሙን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ማረጋገጥ ችሏል።
የመውጫ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።
ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ይፋ ባደረገው መርሐግብር ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።
ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል።
የተፈታኞች ዝርዝር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚላክም ተገልጿል።
Via @tikvahuniversity
@tikvahethiopia
#Update
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የዑለማ ጉባዔ የ2ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ጉባኤው በመግለጫው ፦
- በየሳምንቱ የሚደረገው የጁምዓ ኹጥባ አርካኑን በጠበቀ መልኩ በአረብኛ ቋንቋ መሆኑ የተመረጠ ቢሆንም እንደ አስፈላጊነቱ ማህበረሰቡ እንዲረዳው በተለያዩ ቋንቋዎች ቢደርግ ችግር እንደሌለው ጉባኤው መስማማቱ ተገልጿል። በተጨማሪም የቁርአንናና የሐዲስ ጥቅሶች ባሉበት በአረብኛ ቋንቋ ተነበው መተርጎም አለባቸው ብሏል።
- በሸሪአ የተፈቀደው የጋብቻ አይነት በተቃራኒ ጾታዎች ማሃከል የሚደረግ ጋብቻ ብቻ ሲሆን የተፈጥሮ ህግንና ሸሪአን በተፃረረ መልኩ የሚደረገውን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግንኙነት በሸሪዓ በጥብቅ የተከለከለና የአላህን ቁጣ የሚያስከትል ተግባር በመሆኑ ጉባኤው #በጥብቅ_እንደሚያወግዝ አሳውቋል።
- የኢትዮጵያ ዑላማዎች ለሰላም ዘብ እንደሚቆሙ ፤ ህዝበ ሙስሊሙም ለአገር ሠላም ዘብ እንዲቆም ፤ በአገራችን የሚታዩት አለመግባባትና ግጭቶች በሰላማዊ መልኩ በውይይት እንዲፈቱ ለመንግስትና ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ሁሉ ጥሪውን አስተላልፏል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?
ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ፦
- በነዳጅ የሚሰራ #አዲስ ሆነ #አሮጌ የግል አውቶሞቢል መኪና ወደ ሀገር ማስገባት አይቻልም። ሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ኤሌክትሪክ ብቻ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።
- የነዳጅ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ከአምና ጀምሮ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ታግዷል። ግን እስከ ቅርብ ጊዜ በተለያየ መልኩ የሚገቡ ነበሩ። ለምሳሌ ፦ ከውጭ #ተመላሽ ዳይስፖራ ተብሎ እነሱ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም ነበር፤ እነሱ የነዳጅ ሲያስገቡ አይከለከሉም ነበር። ይህ ግን አሁን ላይ አይሰራም። የግል አውቶሞቢል በማንኛውም ምክንያት በዳይስፖራ ሰበብም ይሁን በምንም ሁኔታ እንዲገባ አይፈቀድም።
- የመኪና አስመጪዎች የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ብቻ ነው ማስገባት የሚችሉት።
- በጣም ያረጁ መኪናዎች ከአገልግሎት እንዲወጡ አዋጅ ወጥቷል። ህግም ወጥቶ መኪናዎች መስጠት የሚችሉት አገልግሎት በእድሜያቸው ልክ እንዲሆንና እድሜያቸው ከአገልግሎት ዘመናቸው ውጭ የሆነ ከገበያ ውና ከአገልግሎት እንዲወጡ የሚሄዱበት ሁኔታ እየተሰራ ነው።
- በተለይ አዲስ አበባ ትንንሽ ሰዎችን ከሚጭኑ ታክሲዎች ይልቅ በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎችን የሚጭኑ ብዝሃ ትራንስፖርት እየተበረታቱ ነው። በሂደት አዲስ አበባ ውስጥ እንደሌሎች ያደጉ ከተሞች 10 እና 12 ሰዎች የሚጭኑ ሚኒባስ ታክሲዎች ከአገልግሎት እየወጡ እንዲሄዱ ይደረጋል። ይህ መጨናነቁንም ፣ ብክለቱን ከከተማ ያስወጣል።
- የብዝሃ ትራንስፖርትን በማሳደግ የተሽከርካሪ ቁጥር ለመቀነስም ታስቧል። የብዝሃ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እንዲሆንም እየተደረገ ነው። አዲስ አበባ በቅርብ የሚገዛቸው ባሶች የኤሌክትሪህ ይሆናሉ።
- ከዚህ በኋላ የመኪና ሰሌዳ ዝም ብሎ አይሰራጭም። አስመጪዎች ሰሌዳ እየወሰዱ / በብዛት እየገዙ ድንበር አካባቢ ሄደው አዲስ / አሮጌ መኪና ላይ በመግጠም እንደነባር ህጋዊ መኪና እያሽከረከሩ የሚገቡበት ሁኔታ አለ። የተራጋ አሰጣቱን ለመቆጣጠር ይሰራል።
- በአዲስ አበባ የፓርኪንግ ቦታ በቅርብ ኖሮ መንገድ ላይ መኪና እንዳይቆም ለማድረግ እየተሰራ ነው። በከተማው በ2 ኪሎ ሜትር አቅራቢያ ፓርኪንግ ካለ ባልተፈቀደ ቦታ ማቆም እንዳይቻል አስገዳጅ ስራ እየተሰራ ነው።
- የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት እንዳይቸጉሩና ባሰቡት ሰዓት ያሰቡበት እንዲደርሱ፣ ሰልፍ ተሰልፈው መንገድ ላይ እንዳይቆሙ ለማድረግና የህዝብ ትራንስፖርት በፍጥነት እንዲመላለስ የግል መኪና ተጠቃሚዎች እንቅስቃሴ እንዲገደቡ ይደረጋል። ይህ የሚሆንበት ሰዓቶችም ተለይተው ተመርጠዋል። በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል።
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia