#EOTC
ቅዱስ ፓትርያርኩ " የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲካ ገለልተኛ በመሆን ሁሉን በፍቅርና በእኩልነት ማቀራረብ ይገባቸዋል " ሲሉ በ11ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸው ተናገሩ።
ፓለቲከኞቾም ባልዋሉበት እና ባልተፈቀደላቸው ቦታ በቤተክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ቅዱስነታቸው " የዘመናችን ትውልድ ከተግባር ይልቅ አስመሳይ ሆኖ መታየትን ከቅድስና ይልቅ ነውረ ኃጢአትን፤ ከትሕትና ይልቅ ትዕቢትን የተለማመደ ለሃይማኖትም ሆነ ለማኅበረ ሰብ ጤና ያልተመቸ ትውልድ እንደሆነ በግልጽ ይታያል ሲሉ ተግሳጽ አሰምተዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 11ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን አስመልክቶ ምን አሉ ?
- ያለንበት ዘመን ለእግዚአብሔር ክብርን የነሣ፤ ከፍቅርና ከአንድነት የራቀ ራስ ወዳድነትና በቃኝ አለማለትን የወረረው፤ በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ የተዋጠ ትውልድ የታየበት ዘመን ነው።
- የዘመናችን ትውልድ ከተግባር ይልቅ አስመሳይ ሆኖ መታየትን ከቅድስና ይልቅ ነውረ ኃጢአትን፤ ከትሕትና ይልቅ ትዕቢትን የተለማመደ ለሃይማኖትም ሆነ ለማኅበረሰብ ጤና ያልተመቸ ትውልድ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው፤ ይህን አደገኛ አዝማሚያ በማስተዋል ካልታረመ ሂዶ ሂዶ የእግዚአብሔርን ቁጣ ማስከተሉ አይቀርምና እንደ እግዚአብሔር ጥሪ ወደ እሱ ብንመለስ ይሻላል።
- እኛ የሃይማኖት አባቶችም አልጫ የሆነውን የዘመናችንን ትውልድ በትጋት አስተምረን በቈራጥነት ገሥጸንና መክረን ወደ እግዚአብሔር ካልመለስነው ከቁጣው አንድንም። ቅዱስ መጽሐፍ እንዳስተማረን አስተምረነው የማይመለስ ከሆነ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል! እኛ ባለማስተማራችን የሚጎዳ ትውልድ ካለ ግን እኛ የደሙ ተጠያቂዎች መሆናችንን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጾአልና ነው፤ የእኛ ኃላፊነት እስከዚህ ድረስ ከባድ መሆኑን ባንዘነጋውም እንደ ዓለሙ በልዩ ልዩ ደካማ አስተሳሰቦችና ተግባራት እየተሰናከልን መሆናችን የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ውሎ አድሮአል።
- እኛ የሃይማኖት አባቶች ዓለም ሲሳሳት ከመገሠጽ ይልቅ አብሮ ማጨብጨብ ተለማምደናል፤ ባናጨበጭብም ዝምታን መርጠናል ነገር ግን ኃላፊነቱን የተረከብነው ጥፋት ሲፈጸም ዝም ብሎ ለማየት አልነበረም፤ ከዓለሙ ጋር አብሮ ለማጨብጨብ ወይም አድማቂ ለመሆንም አልነበረም፤ ከቅዱስ ወንጌሉ መሠረተ ሐሳብ ፍንክች ሳንል ፦
* የእውነት፥
* የፍትሕ የሰላም፥
* የፍቅር፥
* የዕርቅ የይቅርታ የአንድነት፥
* የስምምነት ጠበቃ መሆናችንን ማሳየት ነበረብን፣ ሰውን ሁሉ በእኩልነት በመቀበልና የሁሉም እኩል አባቶች መሆናችንን በተግባር ማስመስከር ይገባን ነበር፤ የተዛባውን በማረም ትውልዱን ለማዳን ያደረግነው ጥረት የሚያረካ እንዳልሆነ ታዛቢው ሁሉ አይቶብናል፡፡
- ለፈተና የተጋለጡ ልጆቻችን ሁሉ የዜግነት የሃይማኖትና የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር ሰላም ፍቅር፥ ፍትሕ አንድነት በሀገር እንዲነግሥ ሁሉም ድንበሩን ጠብቆ ሕዝቡን የሚያገለግልበት ዓመት እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በርትተን መሥራት አለብን። ይህንን ብናደርግ በእውነትም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰናል ማለት ነው፤ እኛ ከተመለስን እሱም ወደ እኛ መመለሱ አይጠረጠርም፤ ስለዚህ አሁንም ወደእሱ እንመለስ፡፡
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
ደም እንለግስ !
" በወሊድ ወቅት ደም ለሚያስፈልጋቸው እናቶች ደም እንለግስ " ሲል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጥሪ አቅርቧል።
የሕክምና ኮሌጁ ለቲክቫህ ቤተሰቦች በላከው አጭር መልዕክት የፊታችን የካቲት 28 እና 29 ቀን 2016 ዓ/ም በኮሌጁ 5ኛ በር አካባቢ የደም ልገሳ እንደሚደረግ ጠቁሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ አሁን ላይ በወሊድ ወቅት ለእናቶች የሚሆን ደም በጣም እየተፈለገ እንደሆነ ተረድቷል።
ሁሉም የሚችል የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ፤ በሁለቱ ቀናት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በመገኘት ደም እንዲለግስ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ቦታውን ለማታውቁ Google Map ተጠቀሙ።
#AddisAbaba
@tikvahethiopia
ማንችስተር ሲቲ ወይስ ማንችስተር ዩናይትድ (#ይገምቱ!) https://vm.tiktok.com/ZMMNQqowU/
ለ10 የቲክቶክ ተከታዮቻችንን የሚያሽልም
1. ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቲክቶክ ቻናል ይከተሉ (#FOLLOW)።
2. ግምትዎን ብሃሳብ መስጫው (#COMMENT) ላይ ያስቀምጡ::
3. ቪዲዮውን ላይክ (#LIKE) እንዲሁም ሼር (#SHARE) ያድርጉ። https://vm.tiktok.com/ZMMNQqowU/
4. ውጤት ማስተካከል እና ከላይ የተጠቀሱትን ህግጋቶች የማያከብሩ ከውድድሩ #ውጭ ይሆናሉ።
5. ክ 10 በላይ ትክክለኛ መላሾች የሚለዩት #በዕጣ ይሆናል።
መልካም ዕድል!
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE #MCMU #EPL #MUTD #MCITY
#ኢትዮጵያ
ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አምጥቷል።
በግላስኮ ዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በወንዶች 3 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የነሃስ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።
ጌትነት ዋለ 4ኛ ወጥቷል።
ኢትዮጵያ በዚህ ርቀት በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ሳታሸንፍ ስትቀር ከ3 ተከታታይ ውድድሮች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ሰለሞን ባረጋ ከሁለት ዓመታት በፊት በዚሁ ውድድር ሲያሸንፍ ዮሚፍ ቀጀልጃ በ2016 እና 2018 የዚህ ውድድር አሸናፊ ነበር።
Via @tikvahethsport
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹
ኢትዮጵያ በግላስኮ በ2024 የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እየተሳተፈች ትገኛለች።
ከደቂቃዎች በላይ የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው ውድድሮች የትኞቹ ናቸው ?
🇪🇹 ምሽት 5:15 ➡️ 3000ሜ ሴቶች ፍፃሜ (ሂሩት መሸሻ ፣ ለምለም ሀይሉ እና ጉዳፍ ፀጋይ)
🇪🇹 ምሽት 5:40 ➡️ 3000ሜ ወንዶች ፍፃሜ (ጌትነት ዋለ እና ሰለሞን ባረጋ)
ውድድሩን በምን መመልከት ይቻላል ?
በDSTV " ቻናል 239 " ወይም ልዩ ቻናል 2 ላይ መከታተል ይቻላል።
ቲክቫህ ስፖርት👇
/channel/+VvwzStMNcNHmhK0x
" ደማቁ የዓድዋ የድል መታሰብያ በዓልን በእርስ በርስ ግጭት ማቆሸሽ አይገባም " - ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መልእክት አስተለልፈዋል።
ከ3 ዓመት ተኩል በኃላ በትግራይ ታሪካዊትዋ የዓድዋ ከተማ በመገኘት በዓሉን ለማክበር በመቻላቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።
ፕረዚደንትዋ #እንባ_እየተናነቃቸው ያለፈውን አስከፊ ጦርነት በማስታወስ ፣ ተፈናቃዮች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ በማንሳት ተናገረዋል።
" አሁን ከገባንበት እንድንወጣ ፈጣሪ ይርዳን ፤ በሃይማኖትና በዘር መከፋፈል ይብቃን " ብለዋል።
የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ በፕረዚደንትዋ ስሜታዊ ንግግር እጅግ ስሜቱ መነካቱ ከፊቱ ማንበብ እንደቻለ በስፍራው የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነግሮናል።
" የችግሮቻችን ምንጭ እውቀን ከስሩ ለማድረቅ መስራት አለብን " ያሉት ፕሬዜዳንቷ ፤ " ከእርስ በርስ ጦርነት ጊዚያዊ አሸናፊ እንጂ ዘላቂ አሸናፊ የለም ፤ ስለሆነም ከዚሁ በመቆጠብ በአንድነት ቆመን አገራችን ከውጭ ወራሪ መታደግ ይገባናል " ብለዋል።
" ኢትዮጵያውያን የዓድዋ የድል ዘላቂ እንዲሆን ከተፈለገ ወንድም ወንድሙ ላይ ጦር ከማንሳት መቆጠብ አለብን " ሲሉ አሳስበዋል።
" የሃሳብ ልዩነታችን ከጠብመንጃ በመለስ በጠረጴዛ ውይይት የመፍታት ልማድ ሳይሆን ባህል መፍጠር አለብን። ያለፈው ይብቃ ከስህቶቻችን እንማር " ብለዋል።
በሌሎች ክልሎች የሚታየው ገጭትም በሰላም እንዲፈታ መስራትና መተባበር አለበን ሲሉ ተናግረዋል።
ደማቁን የዓድዋ የድል መታሰብያ በዓል በአርስ በርስ ግጭት ማቆሸሽ አይገባም ማለታቸውንም በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጾልናል።
#TikvahFamilyAdawa
@tikvahethiopia
ቪድዮ ፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ዓድዋ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል።
#ኢትዮጵያ #ዓድዋ128
@tikvahethiopia
#Update
በታሪካዊቷ ዓድዋ እየተካሄደ ባለው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ባንዴራ የመስቀል ስነ-ሰርዓት ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ፣ የትግራይ ክልል ፣ የአፍሪካ ህብረት ባንዴራ በፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዲሁም የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ተወካይ በሆኑት ሜጀር ጀነራል ስቴፈን ራድያ ተሰቅሏል።
የባንዲራ መስቀል ስነስርዓቱ በኢትዮጵያ 🇪🇹 ህዝብ ብሄራዊ መዝሙር ታጅቦ መከናወኑን በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
@tikvahethiopia
#ዓድዋ #ፒያሳ
የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ እንደ ከዚህ ቀደሙ በ " ምኒሊክ አደባባይ " በዓሉን ማክበር የሚፈልግ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁሉ ተሰብስቦ እንዲያከብር አልተደረገም የሚል ቅሬታ ያደረባቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
አንድ በጥዋት በዓሉን አከብራለሁ ብሎ ወደ ፒያሳ " ምኒሊክ አደባባይ " ያቀና የአዲስ አበባ ነዋሪ ፥ ምኒሊክ አደባባይ በከፍተኛ የፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ ስር እንደነበር ፣ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ብቻ ማለፍ እንደሚቻል፣ ጥብቅ የሆነ ፍተሻም እንደነበር ገልጿል።
በዓሉን ለማክበር ወደ ዓድዋ መታሰቢያም ፍቃድ ከተሰጠው ውጭ መግባት እንደማይቻል በዚህም በዓሉም ለማክበር እንዳልቻለ ጠቁሟል።
ይህ የህዝብ በዓል በመሆኑ ህዝብ በመረጠው መንገድ ወይም ተካፋይ በሆነበት መንገድ ሊከበር ይገባ ነበር ሲል ያደረበትን ቅሬታ አጋርቷል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፤ " ዛሬ ከባለፈው ዓመት በበለጠ የዓድዋ በዓልን ለማክብር የመጣ ሰው ከቴዎድሮስ አደባባይ ጀምሮ መግባት ባለመቻሉ ሲመለስ ነበር። ፈረስ እና የተለያዩ የዓድዋ አልባሳትን የለበሱ ሰዎችም ሲመለሱ ነበር " ብሏል።
" በዓሉን ለማክበር ወደ ዓድዋ መታሰቢያ እየገቡ የነበሩትም በቀበሌ ይመስለኛል ባጅ የተሰጣቸው ብቻ ናቸው " ያለው ይኸው አስተያየት ሰጪ ፤ በዓሉ ሁሉም ለማክበር ባለመቻሉ እንዳደበዘዘው ጠቁሟል።
ይኸው አስተያየት ሰጪ ፤ " ካለፈው ሁለት ዓመት ጀምሮ ዓድዋን ከፒያሳ ምኒሊክ አደባባይ ለማላቀቅ ስራዎች የተሰሩ ይመስለኛል " ሲል ገልጾ " የኔ ጥያቄ የተገነባው ዓድዋ መታሰቢያ ከዚህ በኃላ ባለስልጣናት እና የሚፈልጉት ሰው ብቻ በብቸኝነት ለማክብረ ነው ? ወይስ በዓሉን ማክበር የሚፈልግ ህዝብ ተሰብስቦ እንዲከበርበት ነው ? " ብሏል።
መንግሥት የ128ኛው ዓድዋ ድል በዓል ከከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ ክብሩን በጠበቀ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑን እየገለፀ ይገኛል።
@tikvahethiopia
#ዓድዋ128 #ዓድዋ
ፕሬዝዳንት ሥህለወርቅ ዘውዴ በታሪካዊቷ ከተማ ዓድዋ ለሚከበረው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ላይ ለመገኘት ትግራይ ክልል ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቷ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ከመቐለ በሄልኮፕተር ወደ ዓድዋ በመጓዝ ላይ መሆናቸው በስፋት እየተነገረ ነው።
የዓድዋ በዓል የፌደራል መንግስት ባካተተ መልኩ መከበር የቆመው ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ነበር።
ከ4 ዓመት በኃላ ወደ ነበረው የበዓል አከባበር ለመመለስ እየተሞከረ መሆኑን በዛው በዓድዋ የሚገኘው የመቐለው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል መረጃውን አጋርቷል።
የፎቶ ባለቤት ፦ ድምፂ ወያነ (መቐለ)
@tikvahethiopia
የአምስተኛ ዙር የባጃጅ ተረክ አድራጊ ወሳኞች ታውቀዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ!
ሽልማቱ እንደቀጠለ ነዉ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ
/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC /channel/SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare
24/7 መጠየቅ ይቻላል!
#MPESASafaricom
#SafaricomET #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
ፎቶ ፦ የ128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ዋዜም በታሪካዊቷ #ዓድዋ ከተማ ከጥዋት እስከ ምሽት በተለያዩ የአደባባይ ላይ እና በሌሎች ስነስርዓቶች በድምቀት ሲከበር ውሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፎቶ ባለቤቶች ድምፂ ወያነ ፣ ኤላ ፎቶግራፊ ዓድዋ፣ መንደራት ዓድዋ ግሩፕ መሆናቸውን በዚሁ አጋጣሚ ይገልጻል።
@tikvahethiopia
#Amahra
በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም " ማንነታቸው አልታወቀም " የተባሉ #ታጣቂዎች አንድ መነኩሴ ሲገድሉ የገዳማት ንብረት ተዘርፏል።
በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በሚገኙ ሁለት ገዳማት " ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች " ባደረሱት ጥቃት አንድ መነኩሴ ሲገደሉ የገዳማቱ ንብረቶች እንደተመዘበሩ ተገለጸ።
ሀገረ ስብከቱ ስለጉዳዩ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ ምን አለ ?
- በሀገሪቱ ላይ የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር እንደ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም በሀ/ስብከቱ በሚገኙት በተለያዩ ወረዳዎች ሥር በሚተዳደሩ አድባራትና ገዳማት በተካሄደው ጦርነትና እየተፈጠረ ባለው ግጭት ብዙ ጉዳት ደርሷል።
- በማቻክል ወረ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በዋሻ አምባ አቡነ ተ/ሃይማት አንድነት ገዳም ታህሳስ 27 / 2016 ዓ.ም ሌሊት ማንነታቸው ያልታወቁ 8 ግለሰቦች ከገዳሙ ውስጥ በመግባት፡-
1ኛ. የገዳሙን አመሰራረትና የገዳሙን ሙሉ ታሪክ የያዘ የፊልም ዶክሜንት
2ኛ. የገዳሙ መጠበቂያ የሆኑ 2 ዘመናዊ ክላሾች ከእነ ሙሉ ተተኳሹ፤
3ኛ. በጥሬ ገንዘብ ከ100,000 /ከአንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ፤
4ኛ. ወርቅ በግራም 20 ግራም የሚመዝን
5ኛ. ለመነኮሳቱ በየጊ የሚሰፋላቸውን ሙሉ ጣቃ ልብስ
6ኛ. ዘመናዊ ተች የእጅ ስልኮች ብዛት 5
7ኛ. አምስት ጠገራ ብርና የአንገት ጌጣ ጌጦች
8ኛ. የጥበቃ ክፍሉን መጽሐፍና ብር 2000.00 በአጠቃላይ የተዘረዘሩትን የገዳሙን ንብረቶች ከመዘረፋቸውም በላይ ገዳማውያኑን በማንገላታትና የገዳሙን አበምኔት እማሆይ ወለተ ማርያም ገላውን አፍነው /አግተው/ በመውሰድ ከፍተኛ እንግልት አድርሰውባቸዋል።
- በአዋባል ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በመካነ ቅዱሳን ጣቢያ ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም የተፈጠረ ችግር ጥር 27 ለ28 አጥባህ ከሌሊቱ በ6፡00 ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ በቁጥር 5 የሆኑ ወንበዴዎች ገዳሙ ውስጥ ገብተዋል።
2 ክላሽ ጠበንጃ ፣ 1 ገጀራ ፣ 1 ሽጉጥ ፣ 1 አለንጋ የያዙ ታጣቂዎች የገዳሙን አበምኔት ቤት እንዲያሳዩአቸው ዘበኞችን በማፈን ይዘው መ/ሃይማኖት ቆ/አባ ሊባኖስን ፀበልተኛ እንደታመመ አስመስለው " ክፈቱ " ሲሏቸው " እኔ አልከፍትም " ወደ አባ ገ/ሕይወት ሂዱ ሲሉ ይነግሯቸዋል።
አባ ገ/ሕይወትም ጋር ሄደው በመሳሪያ አስገድደው ወደ ገዳሙ አባት መጋቢ ሃይማኖት ቆሞስ አባ ሊባኖስ አስታጥቄ በድጋሚ ሄደው " ክፈቱ " ሲሏቸው " ያለ ሰዓት አይከፈትም " የሚል ምላሽ ሲመልሱ የቤቱን በር በ5 ጥይት ደብድበዋል።
በድጋሚ የካቲት 20 ለ21 አጥቢያ ከምሽቱ በግምት 3፡00 ሰዓት ሲሆን ከገዳሙ ገብተው የእቃ ቤቱን በማንኳኳት የእናቶችንና የአባቶች7 ገዳም ቤቶችን በር ሲመቱ ቆይተው፦
👉 አባ ገ/ሥላሴ ታመነ የተባሉትን በገጀራ መተው #ፍገለዋቸዋል።
👉 ዲ/ን ዮሐንስ እና አብርሃም አያና ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰውባቸዋል።
👉 15 የሞባይል ስልክ ከፀበልተኛው ወስደዋል።
በቁጥር ያልታወቀ ገንዘብና ንብረት ወስደዋል።
በዚህም በ2ቱም ገዳማት ላይ ከፍተኛ የግድያ ፣ የድብደባና የንብረት ዝርፊያ እየተፈጸመ ስለሆነ ለወደፊቱም በቤተ ክርስቲያኗ፣ በገዳማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየገጠመን ስለሆነ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ሲል አሳስቧል።
@tikvahethiopia
የወልዲያ ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ካሳሁን በጥይት ተመተው መገደላቸው ተነግሯል።
ኃላፊው ትናንት ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የቅርብ ጓደኞቻቸውን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
ቃላቸውን የሰጡ ከጓደኞቻቸው አንዱ ፤ " ትናንት ጠዋት 2 ሰዓት አካባቢ ሆርማት በተባለ የከተማው አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በጥይት ተመትተው ተገድለዋል። አጥቂዎቹ ሸሽተው አምልጠዋል " ብለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በባለሦስት እግር ተሸከርካሪ (ባጃጅ) ሆነው ጥቃቱን መፈፀማቸው ነው የተነገረው።
ጓደኞቻቸው ፤ ከዚህ ቀደምም መኖሪያ ቤታቸው ላይ ከዚህ በፊት ቦምብ ተወርውሮ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በወልዲያ ገቢዎች ጽ/ቤት ይሰሩ እንደነበርና በነበራቸው የስራ ትጋት በክልል ደረጃ ተሸላሚ እንደነበሩም ግልጸዋል።
አቶ ዓለማየሁ የከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት ኃላፊ ሆነው ሲሰሩም ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ በርካታ ሥራዎችን ሲሰሩ እንደነበር ፤ ግድያውም ከዚህ ሥራቸው ጋር ሳይያያዝ አይቀርም የሚል ግምት እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡
ሬድዮ ጣቢያው ጉዳዩን በተመለከተ ለከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት ሲደውል " መረጃ በስልክ አልሰጥም " የሚል ምላሽ እንደተሰጠው በዘገባው ጠቅሷል።
@tikvahethiopia
#ሀዋሳ🕯
በቅርቡ ከአርባ ምንጭ ወደ ሐዋሳ ሲመለሱ በዎላይታ ዞን ውስጥ በመኪና አደጋ ህይወታቸዉ ላለፈ የሐዋሳ ከተማ ወጣቶች የሻማ ማብራትና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በከተማ ደረጃ ከንቲባዉ በተገኙበት ተካሄደ።
በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይዎታቸዉ ያለፉ የጤና ቡድን አባላትን ለመዘከር ያለመ የሻማ ማብራትና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተጎጅ ቤተሰቦች ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሲዳማ ባህል ሽማግሌዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
በሻማ ማብራት ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ከታየ ምርጫዬ ፤ " እንደሀዋሳ ብቻ ሳይሆን እንደሀገር አልቅሰናል " ብለዋል።
ከዚህ አይነት አስከፊ የትራፊክ አደጋ ለመዉጣት ጥንቃቄ ብቻ ሳይሆን ጸሎትም ያስፈልገናል ሲሉ ገልጸዋል።
የተጎጅ ቤተሰቦችን ለመደገፍ ለተሰናዳዉ ፕሮግራም በከንቲባዉ ቢሮ 3 መቶ ሺህ ብር እንዲሁም በግላቸዉ 10 ሽህ ብር በማበርከት ድጋፉን አስጀምረዋል።
ፕሮግራሙን ለመካፈል ተደግፎ የመጣዉና ከአደጋዉ የተረፈዉ ወጣት ፋሲል በበኩሉ ሀዘኑን መቋቋም ከባድ መሆኑን በመግለጽ በእንባ ታጆቦ ወደቦታዉ ተመልሷል።
በእለቱ ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ በጎፈንድሚና ለዚህዉ ተብሎ በተከፈተዉ የባንክ አካዉንት መሰብሰብ ተችሏል።
የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙን ያዘጋጀዉ ኮሚቴ " በድንገት ያጣናቸዉ ጓደኞቻችን ልጆችና ቤተሰቦች ለመርዳት ሁሉም ወጣት ድጋፍ እንዲያደርግ " ሲል ጠይቋል።
ለዚህ ሲባል የተከፈተዉ የባንክ አካዉንት ቁጥር 1000610475667 መሆኑን ገልጿል።
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች አሳሳቢ እየሆኑና እየሰፉ እንደሄዱ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ሴቶች ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችን በተመለከተ በዘርፉ ከተሰማሩ የተለያዪ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ተቋማት በመጋበዝ የካቲት 20 በአዲስ አበባ የውይይት መድክ አዘጋጅቶ ነበር።
በዚህም ላይ ከተገኙት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ሴቶች ማኀበር በተለይ በጦርነት ወቅት የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ፣ የሕጉን አተገባበር በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥቷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ታድሞ የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ፦
° በተለይ ከጦርነት፣ ከግጭት ጋር ተያይዞ ፆታዊ ጥቃቶች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ፣
በምን ያህል ሰዎች ፆታዊ ጥቃቶች እንደተፈጸሙ ለኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ሴቶች ማኀበር ጥያቄዎችን አቅርቧል።
የማኀበሩ የሕግ ድጋፍ መስጫ አስተባባሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳዬ ምን አሉ ?
➡ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የአቅም ግንባታ፣ ሌጋል ሪሰርች ፣ ሌጋል ኤይድ ይሰጣል። በሌጋል ኤይድ ሴክተራችን የተለያዩ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች (Sexual harassment, Sexual violence, አካላዊ ድብደባዎች) ሪፖርት ይደረጋሉ።
➡ በLegal aim unit ሪፖርት መሠረት በ2023 አዲስ አበባን ጨምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ በቢሯችን ሪፖርት የተደረጉ ከ4,000 በላይ የፆታዊ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በዚህ ደግሞ ችግሩ ምን ያህል አሳሳቢ እየሆነና እየሰፋ እንደሄደ ማየት እንችላለን።
➡ ሁሉም አካላት በትብብር መስራት ያለውን Finding ማሳወቅ፣ እንዲሁም ደግሞ መፍትሄ መፈለግ፣ ያለውን ጋፕ መድፈን ላይ በትብብር መሰራት አለበት።
➡ ኢትዮጵያ የተለያዩ ፆታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ያጸደቀቻቸው ሕጎች ቢኖሩም አፈጻጸሙ ላይ መሠረታዊ የሆኑ ችግሮች አሉ። ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ትኩረት ሊሰጡበት ይገባል።
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ሴቶች ማኀበር የተለያዩ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በመከታተል ሪፖርት የሚያደርግ፣ ከፆታዊ ጥቃት ነፃ የሆነች አገር ለመፍጠር የሚታትር፣ በሁለት ከተማ አስተዳደሮችና በ6 የክልል ከተሞች 55 በሚሆኑ ወረዳዎች የድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡ ሴክሽኖች ያሉት፣ ከተቋቋመ ከ28 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ተቋም ነው።
መረጃውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
🎉 ዛሬ ከምሽቱ 12፡30 የማንቸስተር ቀለም ይለያል! ቀይ ወይም ሰማያዊ!! 🔴🔵
🔥ከባድ ትንቅንቅ የማያጣው የማንቸስተር ደርቢ - ማንቸስተር ሲቲ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ🔥
🤔ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከደረሰበት ሽንፈት ለመመለስ ይጓጓል። ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳትና መሪነቱን ለመቆናጠጥ ይፋለማል፡፡
ይህ ታሪካዊ ፉክክር እንዳያመልጥዎ…
👉ሲቲ ከማንቼ የሚያደርጉትን ፍልሚያ ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#ትግራይ
" ' ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን 2 ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? ' ነው ያለችኝ ! " - ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ በነበረው የዓድዋ ድል በዓል ላይ እምባ እየተናነቃቸው 😭 ንግግር አድርገው ነበር።
እሳቸው በእንባ ንግግር ሲያደርጉ የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ ከፍተኛ የሀዘን ስሜቱ ከፊቱ ይነበብ እንደነበር በስፍራው የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምን አሉ ?
" ዛሬ ወደ ትግራይ ስመለስ በህሊናዬ የሚመጡብኝ ብዙ ትዝታዎች አሉብኝ።
ይቅርታ አድርጉልኝና አጋጣሚውን ተጠቅሜ ማንሳት እፈልጋለሁ።
በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው ከነበሩ ወገኖች መካከል አንዷ ፈንጠር ብላ የተቀመጠች አንዲት ሴት ለማነጋገር ሞክሬ ነበር።
በተፈናቃዮች ካምፕ ጉብኝት ልብን የሚሰብር ነው። ከቤት ንብረታቸው ወጥተው ፣ ክብራቸውን አጥተው ቁጭ ብለው ጉብኝት .. እኛ ደግሞ እንመጣለን ልናያቸው።
ታዲያ ያችን ሴት ጠጋ ብዬ ሳነጋግራት፤ በጥሩ አልመለሰችልኝም። ጥቂት ያመጣሁትን እቃ እንድታከፋፍልልኝ ነበር ልጠይቃት የነበረው ' ያንቺን እቃ አልፈልግም ' አለችኝ።
በሆስፒታል እና በመጠለያ ጣቢያቸው ሄጄ ያየዋቸዋን ሴቶች በእጅጉ አስባቸዋለሁ። እቺን ሴትዮ ለምንድነው የምትመልሽልኝ ስላት ' ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን ሁለት ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? ' ነው ያለችኝ መልስ የለኝም ፤ አይመልስም ብቻ ነው ያልኳት።
ጦርነቱ ተዛምቶ በአፋር ክልል ሰመራ ሆስፒታል ህክምና ላይ የነበሩ የተማረኩ የህወሓት ታጋይ ሴቶችን አግኝቻቸዋለሁ ሳናግራቸው ያሉኝ ከልቤ አይጠፋም ፤ ቦታቸው እዛ አልነበራም ትምህርት ቤት ነው።
ያሉኝ ' እኛ መመለስ የምንፈልገው ወደ ትምህርት ቤት ነው ' ይሄንን ወግቼ ያንን አሸንፌ የሚል ዓላማ አልነበራቸውም። በክፍላቸው ግርግዳ ላይ የፃፉት የለጠፉት የአፋር ህዝብ እንዴት ደግ እንደሆነ ነው። ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያዊ እንዴት እንደሚረዳዳ ነው።
ሌሎችም አሉ ብዙ እርጉዝ ሆነው ሶስት ልጅ ወልደው ሲንከራተቱ የነበሩ ... ለማንኛውም ብዙ መንከራተት ነበር።
ዛሬ እዚህ ቆሜ የትግራይ እናቶች ያሳለፉትን #ሰቆቃ በእውነቱ እረዳለሁ ለማለት ነው ይሄን ሁሉ የምናገረው። እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥዎ !!
ዞሮ ዞሮ የማንኛውም ግጭት መጨረሻው ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ የሰላም ስምምነት መፈረሙ አይቀርምና ይህ ሳይሆን ተጨራርሰን ተጨካክነን ፣ ዘርና ሃይማኖት መለያያ አድርገን ሃይማኖቶችን ከፋፍለን ሳይሆን በቅድሚያ መከላከል እንዳለብን መገንዘብ አለብን።
የዓድዋ ባለቤቶች እንዳልሆንን ገፅታችንን አጉድፈን አበላሽተናል። "
#TikvahFamilyAdawa
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ አማካኝነት በግላስኮ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።
ጉዳፍ ውድድሯን 2ኛ ሆና አጠናቃለች።
Via @tikvahethsport
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
#ትግራይ
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 😢 ፦
" ጠላት ሊወረን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፣ በሃይማኖት ፣ በፆታ ሳይለያይ የመሪውን ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክን ጥሪ በመቀበል ተሰባስቦ በመዝመት በነዚህ ተራሮች እና ኮረብታዎች ታሪክ እንዳልሰራ ሁሉ ለራሱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ፤ ለአፍሪካ አህጉራችን እንዲሁም ለመላው የተጨቆነ ህዝብ ተስፋ የሰጠ ሳለ በዚህች መሬት፦
- ወንድም በወንድሙ ላይ ቃታ የሳበበት የተጋደለበት
- ንፁሃን የተገደሉበት
- ብዙዎች የተሰደዱበት
- በርካቶች በገዛ ሀገራቸው የተንከራተቱበት፣ የተፈናቀሉበት
- ንብረት የወደመበት
- #ሴቶች_የተደፈሩበት ሁኔታ ታሪክ ጅብዱ በተሰራበት ምድር እንዲያይ ያደረግነው። እነዚህ ተራራዎች ለዚህም እማኝ እንዲሆኑ ያደረግነው።
እነዚህ ተራሮች መናገር ቢችሉ እንዲነግሩን የምንፈልገው ግን የህዝባችንን ጀግንነት፣ ታሪክ ሰሪነት፣ አንድነት ነው፤ ምስክሮቻችን ናቸው።
በትግራይ ጦርነቱ እንደጀመረ ሰሞን መጥቼ ነበር። ከጦርነቱ ሁለት ወር በፊት እዚህ ነበርኩ። የጦርነት ደህና ገፅታ የለውም እጅግ አስከፊውን ግን አላየሁም ብዬ ነው የማስበው። "
#TikvahFamilyAdawa
@tikvahethiopia
#ዓድዋ128
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በታሪካዊቷ ዓድዋ እየተካሄደ ባለው ስነስርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል።
" ድሉ በድምቀት እንድናከብር ያበቁን አባት አያቶቻችን ስንዘክር የአሁኑ ትውልድ አገርና ህዝብ የሚያሳድግ አንድነት ልማት ስር እንዲሰድ የሚያስችል እንቅስቃሴ በማድረግ መሆን ይገባዋል " ብለዋል።
ድሉ የመላው ኢትዮጵያውን ድል መሆኑን ያስታወሱት ጄነራል ታደሰ ፤ " የአሁኑ ትውልድ የአባት አያቶቹ ክብር በማስቀጠል ለአገርና ህዝብ አንድነት መስራት ይጠበቅበታል " ብለዋል።
ምክትል ፕሬዜዳንቱ ፤ " የ128ኛው የዓድዋ ድል መታሰብያ ስናከብር ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት ለማስቆም የተደረገው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተከትሎ ፦
➡ የትግራይ ወሰን አለመከበሩ
➡ ከቄያቸው የተፈናቀሉ እንዲመለሱ አለመደረጉ መዘንጋት አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።
" የፌደራል መንግስት የገባውን ውል እንዲፈፅም አሁንም ጥሪያችን እናቀርባለን " ሲሉ ጀነራል ታደሰ ወረደ መናገራቸውም በዓድዋ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል መረጃውን አድርሶናል።
#AdwaTikvahFamily
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ፒያሳ በሚገኘው የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " እየተከበረ በሚገኘው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ትርኢት አቅርቧል።
Photo Credit - Leuel Masrsha (WMCC)
@tikvahethiopia
#ዓድዋ
128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳይ ፣ የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለልስጣናት ተገኝተዋል።
በበዓሉ ላይ የአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችም በዓሉን ለማታደም በስፍራው ተገኝተዋል። መኮንኖቹ በበዓሉ ስፍራ ሲደርሱ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በዓድዋ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በበዓሉ ላይ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የታደመበት መሆኑን አመልክቷል።
ፎቶ፦ በቲክቫህ ቤተሰብ አባል እና ትግራይ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopia
#ዓድዋ
" ኢትዮጵያ ምን ጊዜም አሸናፊ ናት " - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ በተመረቀው " የዓድዋ ድል መታሰቢያ " እየተከበረ ይገኛል።
በዚሁ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መሪዎች፣ የተለያዩ ባለልስጣናት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ለመረዳት ተችሏል።
በዓሉ በሀገር መከላከያ ወታደራዊ ትርኢት እና በሌሎችም ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፥ የዓድዋ ድል ደማቅ ታሪክ የተጻፈበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
" ቀደም ሲል #ለትውስታ ብቻ ይከበር ነበር " ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ " ዘንድሮ ግን ድሉን የሚመጥን መታሰቢያ በዚህ ትውልድ ተገንብቷል " ብለዋል።
" የጦር መሪዎችን ጨምሮ ብሔር ብሔረሰቦች በመታሰቢያው መካተታቸውን የሚደነቅ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" የመከላከያ ሠራዊት የዓድዋ ጀግኖችን ሥራ ውርሱ አድርጎ ለሀገሩ በኩራት ዘብ ይቆማል " ብለዋል።
ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ " ሀገራችን ጠንካራ የመከላከያ ኃይል እንዳላት ለኢትዮጵያውያን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ " ነው ያሉ ሲሆን " የኢትዮጵያ መከላከያ ከሀገራችን አልፎ ለሌሎች ሀገራትም ኩራትና መከታ ነው ይህንንም የወደቀላቸው ይመሰክራሉ " ሲሉ ገልጸዋል፡፡
" ኢትዮጵያ ምን ጊዜም አሸናፊ ናት፤ ዛሬም የዓድዋ ጀግኖች ልጆች መሆናችንን እያስመሰከርን እንቀጥላለን " ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
#ዓድዋ
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል ቀን አደረሳችሁ !
" ዓድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእነርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ ዓድዋ
አፍሪካ እምዬ #ኢትዮጵያ❤
ተናገሪ
የድል ታሪክሽን አውሪ !! " - ጂጂ
መልካም የድል በዓል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ !!
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
አዲሱን የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ፣ ነባር የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች በቀላሉ አክቲቬት ማድረግ የሚችሉበት ቀላል መመሪያ - እነሆ!
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765
ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
ፎቶ፦ የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ዋዜማ በታሪካዊቷ ከተማ ዓድዋ በድምቀት ሲከበር ውሏል።
የበዓሉ ዋዜማ ከጥዋት አንስቶ እስከ ምሽት ድረስ በተለያዩ የአደባባይ እና ሌሎች ስነስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል።
የዓድዋ በዓል በተለይ ባለፉት ዓመታት በትግራይ ጦርነት ወቅት እጅግ ተቀዛቅዞ እንደነበር ፤ ሰዎችም በከፍተኛ ሀዘን ምክንያት በዓሉን በድምቀት ሲያከብሩት አልነበረም። ቱሪስቶችም በጦርነት ምክንያት ወደ ስፍራው መጓዝ አይደፍሩም ነበር።
ዘንድሮ ከተማው ሰላም መሆኑን ተከትሎ የበዓሉ ዋዜማ እጅግ በደመቀ በተለይም በአደባባይ ስርዓቶች ሲከበር ውሏል። በነገው ዕለትም የተለያዩ ዝግጅቶች ይኖራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ወደ ዓድዋ የተጓዘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል መረጃዎችን የሚያጋራን ይሆናል።
@tikvahethiopia
#ተመስገን_ደሳለኝ
ጋዜጠኛ ተመስገን “ትክክለኛ ፍትሕ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን ይነሱልኝ” ያሏቸው ዳኛ “ #አልነሳም” አሉ።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ/ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሚ ችሎት ቀርበው በነበረበት ወቅት፣ “የግራ ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ አሕመድ መሐመድ ትክክለኛ ፍትህ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን በዚህ ጉዳይ ከችሎት እንዲነሱልኝ ምክንቻቶቼን አቀርባለሁ” ብለው ያዘጋጁትን ምክንያታዊ ፅሑፍ በዝርዝር አቅርበው ነበር።
ችሎቱም የጋዜጠኛውን አቤቱታ ካደመጠ በኋላ፣ የዳኛውን ከችሎት መነሳትና አለመነሳትን ጉዳይ ለመወሰን፣ ጋዜጠኛ ተመስገን በዋናው ክሳቸው ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቀውን መለስ ለመቀበል ለጥር 28 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ አይዘነጋም።
ይሁን እንጂ ለጥር 28 ቀን 2016 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው ቀጠሮ፣ “አቤቱታ የቀረበባቸው ዳኛ ስልጠና ላይ ስለሆኑ ውሳኔ አልሰጠንም” በሚል ለየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶበት ተራዝሞ ቆይቷል።
በየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ/ምቱ ችሎት ደግሞ፣ ጋዜጠኛው ከችሎቱ እንዲነሱ አቤቱታ ያቀረቡባቸው ዳኛ “አልነሳም” ብለዋል።
ጋዜጠኛው ያቀረቡት የዳኛውን “ከችሎት ይነሱልኝ” አቤቱታ ችሎቱ ወድቅ ያደረገው፣ “እንዲነሱ የተጠየቁት ዳኛ መልካም ስብዕና ያላቸው መሆኑን” በመጥቀስ ነው።
ጋዜጠኛ ተመስገን፣ የተሳሳተ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ዋቢ አድርገው በመጥቀስ “ዳኛው ይነሱልኝ” ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ሳቢያ የ1,000 (አንድ ሺሕ ብር) ቅጣት ተፈርዶባቸው ክፍያውን ፈጽመዋል።
ጋዜጠኛው ተመስገን፣ ፍርድ ቤቱ ‹ዳኛው ስህተት ሰርተዋል ወይስ አልልሩም?› ወይም ‹ከሳሽ ያለአግባብ ጠቅመዋል ወይስ አልጠቀሙም?› በማለት የቀረበውን ቅሬታ መመርመሩን ወደ ጎን በመተውና የቀድሞ ስብእናቸውን መነሻ በማድረግ ቅሬታዬን ውድቅ ማደረጉ እጅጉን አስደንግጦኛል” ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም፣ “የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እኔን ስጋት ላይ የጣለ ነው” ያሉ ሲሆን፣ ጋዜጠኛው ላይ የቀረበውን የይግባኝ መልስ ለመስማትም ለመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ቀጠሮ ተስጥቷል።
መረጃውን አዘጋጅዮ የላከው የአ/አ ተክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#Amahra
በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 11 የቅኔ ተማሪዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 11 የቅኔ ተማሪዎች እንዲሁም 1 በግብርና የሚተዳደር የአካባቢው ነዋሪ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለው እንደሞቱ ተነግሯል።
የሟች ቤተሰቦች በሰጡቅ ቃል የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ገደማ እንደሆነ ተማሪዎቹ በጎጇቸው ሳሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ፦
- " ፋኖን ታስጠልላላችሁ " ፣
- " ለፋኖ አባላት ጥይት የማያስመታ መድኃኒት ትሰጣላችሁ "
- " እናንተም የፋኖ አባላት ናችሁ " በማለት 11 ተማሪዎች እንዲሁም የጩኸት ድምፅ ሰምቶ ወደ ጉባኤ ቤቱ ሲሄድ የነበረን የአካባቢው ነዋሪ መግደላቸውን ገልጸዋል።
አሁን የተገለጸው የሟቾች ቁጥር በዛሬው ዕለት በትክክል የተገኘ እንደሆነ እና በሰዓቱም በጉባኤ ቤቱ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ወደተለያየ አቅጣጫ ስለተበታተኑ የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር ሊልቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።
ከጥቂት ጊዜያት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ከ12 ያላነሱ የአቋቋም ተማሪዎች በአዴት ፍልሰታ ደብር ተገድለው እንደነበር ተገልጿል።
የዞኑ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስለ ጉዳዩ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። #ተሚማ
@tikvahethiopia
#Adwa128
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ስነስርዓቶች እንደሚከበር አሳውቋል።
በዓሉ በአ/አ ፒያሳ በሚገኘው የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም " እንደሚከበር ገልጿል።
የዓድዋ ጀግኖችን የሚዘክር የ34 ደቂቃ ዶክመንታሪ ፊልም፣ ቢል ቦርድ፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ሎጎ፣ መሪ ቃል እና ሠራዊቱ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ሆኖ የሚወያይበት ፅሁፍ ተዘጋጅቷል ተብሏል።
በዕለቱ የካቲት 23 ቀን ወታደራዊ የሰልፍ ትርኢት እና ድሉን የሚያስታውሱ ልዩ ልዩ ትርኢቶች ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይቀርባል ተብሏል።
@tikvahethiopia