ኢንስታግራም እንዲሁም ትሬድስ ወደ ቀደመው አገልግሎት ተመልሰዋል።
ልክ እንደ ፌስቡክ ሁሉ በሜታ ኩባንያ ስር ያሉት እነዚህም አገልግሎቶች ዛሬ ከአመሻሽ አንስቶ ለሰዓታት ተቋርጠው ነበር።
@tikvahethiopia
ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ትሬድ በመላው ዓለም ተቋርጠዋል።
በሜታ ስር ያሉት እኚህ አገልግሎቶች በምን ምክንያት እንደተቋረጡ የታወቀ ነገር የለም።
ኩባንያውም እስካሁን ማብራሪያ አልሰጠም።
@tikvahethiopia
ለስኬት ከሚሮጥ ጠንካራ ሰራተኛ ጀርባ ሁሌም ካባ አለ፡፡
🚐በታክሲ ሰልፍ ድካም፣ እንግልት፣ በመጋፋት ገንዘባችን መሰረቅ ፣ደክሞን ስራ ቦታ መገኝት .......... ሀሳብዎን ጣል ያድርጉ፣ ካባ የትራንስፖርት አገልግሎት በመዲናችን 📍አዲስ አበባ ለሰራተኞች እና ለድርጅት አዲስ አገልግሎት ይዞ መጥቷል።
በተመጣጣኝ ወርሀዊ ክፍያን በመክፈል ወደ ስራዎ በጊዜ ገብተው በጊዜ ወደ ቤትዎ ይመለሱ።
አሁኑኑ ይመዝገቡበ 0903534997 ይደውሉልን
ለመመዝገብ ይሄን ይጫኑ 👉 https://bit.ly/48uCuRW
በበርካታ ከተሞች ኃይል ተቋረጠ።
ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ በአካባቢዎቹ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።
ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ በንፋስ መውጫ አካባቢ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ አንደኛው ፌዝ በመበጠሱ ከንፋስ መውጫ - ጋሸና- አላማጣ - መሆኒ - መቐለ የሚሄደው መስመር ኃይል ተቋርጣል፡፡
መስመሩ በምን እንደተበጠሰ ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም የደረሰውን ጉዳት በአፋጣኝ በመጠገን አገልግሎቱን ለመመለስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ተብሏል
በሌላ በኩል ፤ ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ በመበጠሱ ከሸዋ ሮቢትና ከሚሴ ከተሞች በስተቀር አብዛኛዎቹ የሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡ ተነግሯል።
ከኮምቦልቻ በባቲ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የአፋር ክልል መዲና #ሰመራና የተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም በወልዲያ አላማጣ መስመር ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የትግራይ ክልል መዲና #መቐለን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከተሞች ኃይል እንደተቋረጠባቸው ተገልጿል።
በምን ምክንያት እንደሆነ ባያብራራም መስመሩ ከትናንት በስቲያ ከሰዓት በኋላ መበጠሱን የገለጸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ መስመሩን በመጠገን አገልግሎቱን ለማስቀጠል ጥረቶች ተጀምረዋል ብሏል።
@tikvahethiopia
#PurposeBlack
ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ምን አለ ?
- የቢጂአይ ኢትዮጵያ የዋናው መሥሪያ ቤት ሽያጭ ውልን በውልና ማስረጃ በኩል ለመፈጸም ዝግጁ ነን።
- ቢጂአይ ኢትዮጵያ የመንግስትን ግዴታ ቀድሞ ባለመወጣቱ በውል እና ማስረጃ መፈራረም አልተቻለም። ከታክስ ጋር በተያያዘ ክሊራንስ አልጨረሱም።
- ቢጂአይ ብዙ ማሟላት ያለበትን ዶክመንት አላሟላም። በዚህ ምክንያት በውል እና ማስረጃ ለመፈራረም አልፈለጉም።
- ለቢጂአይ 1 ቢሊዮን 150 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈፅመናል። ቀሪውን ገንዘብ በውልና ማስረጃ ስንፈራረም ለመክፈል ዝግጁ ነን።
- ክፍያው በ3 ዙር የሚፈፀም ሲሆን 2ኛው ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በውልና ማስረጃ ስንፈራረም ነው። ይህ ቀድሞ በፈጸመው ውል ላይ ተቀምጧል።
- ከታክስ ነፃ የሆኑበት ወረቀት ከቀረበ በውልና ማስረጃ እንፈራረማለን። እኛ ተገቢውን ዶክመት ካሟሉ በሁለተኛ ዙር የሚጠበቅብንን 2.5 ቢልየን ብር ለመክፈል ዝግጁ ነን።
- ቅዳሜ የካቲት 23 /2016 ዓ.ም በውልና ማስረጃ እንዋዋል የሚል ደብዳቤ ልከንላቸው ነበር። እነሱ ሕጋዊ መስፈርቶችን ማሟላት ባለመቻላቸው ውሉን አቋርጠናል የሚል መግለጫ ትናንት አውጥተዋል።
- እኛ ብሩን ለመክፈል ዝግጁ ነን በውልና ማስረጃ የማይፈራረሙ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንወስዳለን።
- ኃላፊነቱን እየተወጣ ያልሆነው በውልና ማስረጃ እንዲፈፀም ኃላፊነቱን ያልተወጣው ቢጂአይ ኢትዮጵያ እንጂ እኛ አይደለንም።
- አሁንም ግዢውን ለመፈፀም ዝግጁ ነን።
- ሌላ አማራጭ መሬቶችን ገዝተናል። መሰረት እየጣልን ነው። በገባነው ቃል ቤቶቹን በሚቀጥሉት 5 አመታት ሰርተን እናስረክባለን።
- ከመንግስት በሊዝ ስምምነት እንዲሁም 30/70 በሚል ስምምነት በግዢ ሂደት ላይ ያሉ መሬቶችም አሉ።
- ቤት ለመሸጥ ቃል ለገባንላቸው ደንበኞች ቤቱን እናስረክባለን።
በትላንትናው ዕለት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በላከልን ኢሜል አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ መቋረጡን ማሳወቁ ይታወሳል።
የሽያጩ ውል የተቋረጠው ፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎትና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ እንደሆነ መግለፁ አይዘነጋም።
#TikvahFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
የካራማራ ድል !
የካቲት 26/1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበት እና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።
በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ " ካራማራ " ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሷል።
በጦርነቱ መጀመሪያ ሶቪየት ህብረት ሶማሊያን ስትደግፍ ነበር በኃላ ላይ ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነት የነበራት አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራ ነበር።
በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመን እና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።
ከ16,000 በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን #ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።
በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡
በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ46ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል፡፡
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
እንደ አፖሎ የት ይገኛል! ፈጥኖ በመቆጠብ 9% ወለድ ቶሎ ማፈስ ነው።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
ፎቶ፦ በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው ጥንታዊ እና ግዙፉ መስጅድ " መስጅድ ጃሚዕ " በድጋሚ በሐጂ አሕመድ አብዲ (አጋዋይን) ተገንብቶ ዛሬ ሰኞ በይፋ ተመርቆ ለረመዷን ክፍት ሆኗል። በፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድን ጨምሮ ታላላቅ ዓሊምች የአካባቢው ሙስሊሞች ታድመው እንደነበር " ሀሩን ሚዲያ " ዘግቧል።
@tikvahethiopia
#ትግራይ
"...መግለጫው የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ ያመላከተ ነው " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም
የትግራይ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላም ቢሆን መሬቱን ለቆ እንዳልወጣ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደርን ጨምሮ ሀገራትና ተቋም በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።
በቅርቡ እንግሊዝ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ አውጥቶት በነበረ አንድ መግለጫ የኤርትራ ጦር በትግራይ ግዛት ውስጥ እንደሌለ፣ ባድመም ጨምሮ ሌሎችም አከባቢዎች ህወሓት በህገወጥ መንገድ ለሁለት አስርት ዓመታት ይዟቸው የቆዩ የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛቶች ናቸው ብሏል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኤርትራ ጦር በምስራቃዊና ሰሜን ምዕራብ የትግራይ አካባቢዎች ጨምሮ በተለያየ አካባቢ እንዳለ በተደጋጋሚ በመግለፅ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ያሉ የውጭ ኃይሎችን የማስወጣትና ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ኃላፊነት የፌዴራል መንግሥት መሆኑን ገልጿል።
የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ረዳዒ ኃለፎም በኤርትራ መግለጫ ዙሪያ ምን አሉ ?
- የኤርትራው ኤምባሲ መግለጫ የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ አመላካች ነው።
- ከአልጀርስ ስምምነት አፈፃፀምናና ሌሎች የድሮ በ90ዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎች ጉዳዮች ካሉ በህጋዊ መንገድ በዓለም አቀፍ ስርዓት እንዲፈፀም ማድረግ እንጂ ጉልበት አለኝ ብሎ በጉልበት የያዛቸውን አካባቢዎች " የኔ ናቸው " የሚል መግለጫ መስጠቱ ተቀባይነት የለውም።
- ከአልጀርስ ስምምነት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በኃይል የተወረረው መሬት ከተመለሰ በኃላ በህጋዊ መንገድ ሊፈፀም የሚችል ነው።
- መግለጫው አንድ ውለታ የዋለው በኃይል የያዧቸው አካባቢዎች እንዳሉ ገልጸ " በኃይል የያዝኩት የኔ ነው " የሚል መስፋፋት ነው። " የለሁም " አላለም መኖሩን አምኗል ይሄ የያዘው ቦታ ነው በጉልበት ስለያዝኩት " የኔ ነው " እያለ ያለው ይሄ በፍፁም ተቀባይነት የለውም።
- የፌዴራል መንግሥት ማስወጣት አለበት እነዚህን ኃይሎች ሁሌም እያልን ነው። ማለት ያለበትን ማለትም አለበት። ኃላፊነቱን መወጣት አለበት።
- በትግራይ ከኤርትራ ጦር በተጨማሪ የአማራ ክልል ታጣቂዎችም አሉ። ይህ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚፃረር በትግራይ ያለውን አሳሳቢ የተፈናቃዮች ችግር እንዳይፈታ ያደረገ ነው።
- እንዚህ ኃይሎች እያሉ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ማድረግና ማቋቋም አይቻልም። ከሞት አምልጠው የመጡ ገዳዮች ወዳሉበት እንዴት ነው የሚመለሱት ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ መሆኑን ይገልጻል።
@tikvahethiopia
የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ሽያጭ ተቋረጠ።
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ለቲክቫህ ገልጿል።
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዲኖር እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ እውን እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን " በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ምክንያት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደቱን ለማቋረጥ ተገደናል። " ሲል አሳውቋል።
" ስለዚህም በተዋዋይ ወገኖቹ ቀድም ሲል በተፈረመው የቀብድ ውል ውስጥ በተገለጹት ድንጋጌዎች መሠረት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ በይፋ ተቋርጧል " ብሏል።
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ከዋና መስርያ ቤቱ ሽያጭ ድርድር ጋር በተገናኘ በዚህ ወቅት ምንም አይነት ተጨማሪ አስተያየት እንደማይሰጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው የኢሜል መልዕክት አሳውቋል።
ቀደም ብሎ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሜክሲኮ የሚገኘውንና የቢጂአይ ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ዋና መሥሪያ ቤት አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረውን ሥፍራ ለመግዛት መስማማታቸውን ከሁለቱም ወገን መገለጹ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
#JASIRI: ታለንት ኢንቨስተር
- ለፈጣን ዕድገት አቅም ካላችሁ እና አዲስ ቢዝነስ ለመፍጠር ከቆረጣችሁ፤
- በማንኛናውም ዘርፍ ውስጥ ክፍተቶችን መለየት እና እድሎችን ማወቅ ከቻሉ፤
- ትኩረት ባደረጋቹበት ቦታ ሁሉ የስኬት፣ የችግር አፈታት እና ዋጋ የመፍጠር ልምድ ካላቹ፤
- በሙያዊ መስካችሁ ከፍተኛ መረጃ እና እውቀት ያላቹ ከሆነ፤
- በቡድናቹ ውስጥ ካሉ ተመሳሳይ ትልቅ ፍላጎት ካላቸው መስራቾች ጋር ለመገናኘት እና ከመሰረቱ ቬንቸር ለመገንባት እና በቡድን ለመስራት ዝግጁ ከሆናችሁ፤
- ስራዎን በሙሉ ጊዜ ለመገንባት ቃል ገብታቹ እና በሁሉም ታለንት ኢንቬስተር ደረጃዎች ለ14ወራት እንዲሁም በሩዋንዳ ባለው ፕሮግራም ለ3 ወር ተገኝታቹ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ ከሆናቹ፤
አሁኑኑ በ jasiri.org/application ላይ ይመዝገቡ
ሴት ስራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ በጣም እናበረታታለን!
#ፓስፖርት
አዳማ ላይም ፖስፖርት ለመውሰድ አስቸጋሪ መሆኑን ተገልጋዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት ቅሬታ አመላክተዋል።
" ሰው ከመብዛቱ የተነሳ ሰው በየቀኑ ፓስፖርቱን ሳይወስድ ሳምንት ተመለሱ ይባላል። " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " ፓስፖርት ለመስጠት የሚጠሩት በአልፋቤት ብሆንም Order የጠበቃ አይደለም። " ብለዋል።
" አንዱ የጠረውን በድጋሚ ሌላም አንስቶ የመጥራት ክስተት እንዳለ " አመላክተዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ተገልጋይ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ይህንን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርቷል።
N ከአዳማ ፦
" አዲስ ፓስፖርትን ለመውሰድ ያለው እንግልት አለ።
አዲስ ፓስፖርት ካመለከትኩ አሁን ላይ 11 ወራት ሆኖኛል፡፡
በየካቲት ወር 7ኛው (February 15) ቀን በቴሌግራም አካውንት ላይ አዲስ ፓስፖርት የመጣላቸው ስም ዝርዝር ውስጥ ስሜን ስላገኘሁት ልቀበል አውራ ጎዳና በሚገኘው አዳማ ቢሯቸው ሄድኩኝ፡፡
ሆኖም ግን እዛ ስድርስ የመ/ቤቱ ጥበቃዎች በዱላ ጥያቄ ለመጠየቅ ግራ ገብቶት ያለውን ሰው መምታቱትን ተያይዘውታል፡፡
ከዛም ብቸኛ የመረጃ ምንጭ የሆኑት እነርሱ (ጥበቃዎቹ) ስለሆኑ ዱላው ሳያገኘኝ ጥያቄዬን ለመጠየቅ ተጋፍቼ ሳበቃ የአንተ ዛሬ አይደለም የሚቀጥለው ሳምንተ ከሰኞ በኃላ ና አሉኝ የሄድኩት ማክሰኞ እለት ነበር (February 19)፡፡
ወደ መስሪያ ቤቱ የሚያስገባው በር ሁለት ሰው እንኩዋን የማያስገባ ነው እናም መረጃ ለማግኘት ወደ ውስጥ መግባት የማይታሰብ ነው፡፡
ቀጥሎም አርብ እለት (February 23) ሄድኩ እንደምንም ተጋፍቼ ስጠይቅ አንድ ጊዜ ረቡህ አንዴ ሃሙስ አለኝ ጥበቃው፡፡
በቀጣይ ስለተጠራጠርኩ ቀደም ብዬ ማክሰኞ (February 26) ሄድኩ ከዛም በዛ ቀን የነበረው ጥበቃ አርብ እለት ነው አለኝ፡፡አርብ ስሄድ(March 01) ስሄድ ሰልፍ ያዝ ተባልኩ፡፡
ሰልፍ ከያዝኩ በኃላ ተሰላፊዎቹን ስጠይቅ የአንተ እኮ ሀሙስ ነበር አሉኝ(February 29)፡፡
መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ላይ ያለ ማስታወቂያ አሳኙኝ ማስታወቂያውን አነበብኩት የተለጠፈው February 23 ነው፡፡ እናም ጥበቃዎች ቢያንስ ተገልጋይ ማስታወቂያ እንዲያይ ቢያደርጉ የሰውን እንግልት ይቀንሳሉ፡፡
እኔ ቤተሰብ አዳማ ስለሆነ መመላለስ እችላለሁ ነገር ግን ከሩቅ ቦታ ለሚመጡ ምን ያህል ከባድ ነው በዚ ላይ የጥበቃዎቹ ዱላ ተጨምሮበት ?
አመሰግናለሁ፡፡ "
@tikvahethiopia
#ቅሬታ
የፓስፖርት ጉዳይ ...
ከፓስፖርት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ወገኖች አሰፈላጊው ማስተካከያ እንዲደረግ አሳሰቡ።
" የተሰራ ፓስፖርት ለመስጠት ህዝቡ እጅግ በጣም ዘግናኝ በሆነ መልኩ እየተንገላታ ይገኛል። " ያሉት ለቲክቫህ መልዕክታቸውን ያደረሱ ወገኖች ፤ በቀን የሚሰጠው ፓስፖርት ውስን ነው ብለዋል።
" በቀኑ ስለማይሰጥም ባስቀመጡት ቀን ተገልጋዩ እየተመላለሰ መከራ እየበላ ነው። " ሲሉ ሁኔታውን ገልጸውታል።
በተለይ ጎተራ አካባቢ ሌሊት ወረፋ ለመያዝ ብር የሚጠይቁ እንዳሉ ፤ አንዳንዱ ከፍሎ ወረፋ እንደሚይዝ የሌለው ደግሞ ሌሊት ሂዶ ከገባ በኋላ ሰልፋን ይበትኑና ቀኑን ሙሉ በህዝብ ሲጫወቱ ውለው 10 ሰዓት ላይ በዱላ ደብድበው እንደሚያስወጡ በምሬት ገልጸዋል።
" በቀጣዩ ሳምንትም እንደዛው። " ሲሉ አክለዋል።
" የብዙ ሰው ቪዛ እየተቃጠለበት ለብዙ ወጪ እየተዳረገ " መሆኑን የሚገልፁት እነዚህ ወገኖች " በየወረዳው ቢበትኑ እንዲሁ። በፊደል ተራ በተለቀቀበት ቀን ቢሰጡ/they mix it/ ጥሩ ነው። የህዝብ እንግልት ግድ የሚሰጠው ካለ መፍትሄ ይፈልግ !! " ሲሉ አሳስበዋል።
@tikvahethiopia
ወጋገን ባንክ !
በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ወጋገን ሞባይል መተግበሪያን ከፕለይስቶር ወይም ከአፕስቶር በማውረድ ምቾትዎ ተጠብቆ ሂሳብዎን ያንቀሳቅሱ፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት የወጋገን ባንክ ሂሳብ በመክፈት የወጋገን የሞባይል ባንክ አገልግሎት *866# ይመዝገቡ፡፡
ከዚያም ቀጣዩን ሂደት ይከተሉ፤
(ሀ) መተግበሪያውን ከአፕስቶር ወይም ጎግል ፕሌይስቶር በማውረድ ስልክዎ ላይ ይጫኑ፤
(ለ) ወደ *866# በመደወል ተራ ቁጥር 8ኛ ላይ የሚገኘውን “Activate Your Mobile Application” የሚለውን ይምረጡ፤
(ሐ) በአጭር ፅሁፍ መልዕክት አገልግሎቱን ማስጀመሪያ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (Activation Code) ሲደርስዎት መተግበሪያው ላይ ይህንኑ ሚስጥራዊ ቁጥር ያስገቡ፤
(መ) የሚስጥር ቁጥር በመቀየር አገልግሎቱን መጠቀም መጀመር ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ፡፡
Download now:
Android:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.act.wegagen&hl
IOS:https://apps.apple.com/in/app/wegagen-mobile/id6472656143
የፌስቡክ አገልግሎት ተመለሰ።
ለሰዓታት ተቋረጠው ከነበሩት በሜታ ስር ከሚገኙት አገልግሎቶች አንዱ ፌስቡክ ዳግም መስራት ጀምሯል።
እዚህ ኢትዮጵያ ኢንስታግራም እና ትሬድ አሁንም እየሰሩ እንዳልሆነ ለመረዳት ተችሏል።
የሜታ አገልግሎቶች በምን ምክንያት እንደተቋረጡ እስካሁን በኩባንያው በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም።
@tikvahethiopua
" መስመሩ መበጠሱን ነው እንጂ ያረጋገጥነው በምን ምክንያት እንደተበጠሰ ማወቅ አልቻልንም " - አቶ ሞገስ መኮንን
ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እንዲሁም ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በመበጠሱ በሰመና መቐለን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እነዚህ ሁለት መስመሮች የተበጠሱበትን ምክንያት የጠየቅናቸው ሲሆን ፤ " መስመሩ መበጠሱን ነው እንጂ ያረጋገጥነው በምን በምን ምክንያት እንደተበጠሰ ማወቅ አልቻልንም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁለቱ መስመሮች መቼ ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ? ሲል ጥይቄ አቅርቧል።
አቶ ሞገስ መኮንን ፦
- በቀላል የሚገናኙ መስመሮች ይኖራሉ ፤ በቀላል ሊገናኙ የማይችሉ እና የተበጠሰበትን ቦታ ብቻ ሳይሆን መስመር መቀየር የሚያስፈልጉም ሊኖሩ ስለሚችሉ እነዚህን እርግጠኛ ባልሆንንበት በዚህ ቀን ሊባል አይችልም ብለዋል።
- ከትናንት በስቲያ ከሰዓት በኋላ ከደብረ ብርሃን- ሸዋሮቢት ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ የተበጠሰውን መስመር አገልግሎቱን ለማስቀጠል ግብዓቶችን የማሰባሰብ ስራ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
- ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋውን መስመር በተመለከተ የተበጠሰው ዛሬ ረፋድ ላይ መሆኑን በመግለፅ ከባህር ዳር ያለው ርቀት ከ100 ኪሎ ሜትሮች በላይ በመሆኑ ለጥገና ጊዜ የሚፈልግ መሆኑንና አገልግሎት ለማስጀመር ይሄ ነው የሚባል ቀን ማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመዋል።
#TikvahFamily
@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም የጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ኦፕን ጌትዌይ ኤፒአይ ፕሮጀክት የመግባቢያ ስምምነት በመፈረም ወደ ትግበራ ገባ!
ዓለም አቀፍ የሞባይል ኦፕሬተሮች ድምጽ የሆነው ግሎባል ሲስተምስ ፎር ሞባይል ኮሚዩኒኬሽንስ አሶሲዬሽን የሶፍትዌር አበልጻጊዎች ያበለፀጉትን መተግበሪያዎች ፈጣንና ቀላል በሆነ መንገድ አለም ላይ ካሉ ከማንኛውም ኦፕሬተሮች ኔትወርክ ጋር የሚያስተሳስሩበት የኦፕን ጌትዌይ ፕሮጀክት የቀረጸ ሲሆን እ.ኤ.አ የካቲት 24 እና 25 ቀን 2024 በተደረገውና ዋና ስራ አስፈጻሚያችን በተሳተፉበት የቦርድ እና የስትራቴጂ ኮሚቴ ስብሰባ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ ሪፖርት ተመልክቷል፡፡
በሪፖርቱም ዓለም ላይ ከሚገኙት 744 ኦፕሬተሮች የኦፕን ጌትዌይ አላማን የሚደግፉና ተግባራዊ ለማድረግ የተስማሙ 42 ኦፕሬተሮች የመግባቢያ ስምምነት መፈረማቸው የተገለጸ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን የመግባቢያ ስምምነት ከፈረሙ ጥቂት ፈር ቀዳጅ ኦፕሬተሮች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በአሁኑ ጊዜ የኦፕን ጌትዌይ ኤፒአዮችን (Open Gateway APIs) ለተመረጡ አገልግሎቶች (Use cases) በማዘጋጀት ላይ ሲሆን ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ትግበራውን ጀምሯል።
ዋና ስራ አስፈጻሚያችን ፍሬህይወት ታምሩ የኦፕን ጌትዌይ የመግባቢያ ስምምነቱ አበልጻጊዎች ያበለጸጉትን አዳዲስ ሶሉሽኖች የኦፕን ጌትዌይ ኤፒአዮችን ተጠቅመው ከኩባንያችን ሞባይል ኔትወርክ ጋር ማስተሳሰር የሚችሉበትን እድል የሚፈጥር እንደሆነ ገልጸዋል።
ኩባንያችን በቅርቡ ከሶፍትዌር አበልጻጊዎችና (developers) ሌሎች በዲጂታል ስነ-ምህዳሩ ከተሰማሩ ተዋንያን ጋር በጋራ በመስራት ተጠቃሚ መሆን እንዲቻል ስለ ኦፕን ጌትዌይ አሰራር የጋራ ውይይትና ዝርዝር ገለጻ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
#PurposeBlack
የፐርፐርዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አፈፃሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በአሁን ሰዓት #አሜሪካ ሀገር እንደሚገኙ ተነግሯል።
" አሜሪካ የሚገኙት ለስራ ነው " ያለው ድርጅቱ የፊታችን ሀሙስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱና መግለጫም እንደሚሰጡ አመልክቷል።
ዛሬ መግለጫ ሰጥተው የነበረው የድርጅቱ የቦርድ አባል እና የህግ አማካሪ ዶ/ር ኤርሚያስ ብርሃኑ ናቸው።
ፐርፐዝ ብላክ ከቤቶቹ ግንባታ እና ከአክሲዮን ባለቤቶች ጋር በተያያዘ ምን አለ ?
- ለቤቶች ግንባታ ሌላም መሬት መግዛቱን ገልጿል።
- አሁን በገባው ቃል መሰረት ቤቶቹን በሚቀጥሉት 5 አመታት ሰርቶ እንደሚያስረክብ አመልክቷል።
- " #ወሰን " አካባቢ ለቤቶች ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል ብሏል።
- የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያን አክሲዮኖች የገዙ ዜጎች ብራቸው #እንደማይመለስ ገልጿል። ነገር ግን ባለ አክሲዮኖች አክሲዮናቸውን መሸጥ ይችላሉ ብሏል።
- በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ ለ1 ሺ ባለ አክሲዮኖች የአክሲዮን ሽያጭ ካደረገ በኋላ የአክሲዮን ሽያጭ ማቆሙን ገልጿል።
- በተለዩ ቦታዎች መሬት እና ንብረትን ከግለሰቦች በመግዛት ፣ መሬት እና ንብረቱን አፍርሶ በመስራት እና ከባለሃብት ጋር አብሮ በማልማት በ3 አማራጮች ግንባታ ለመጀመር የሚጠቀማቸው አማራጮች መሆናቸውን አሳውቋል።
#TikvahFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
#ጥቆማ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ አስፈፃሚዎችን አወዳድሮ መቅጠር እንደሚፈልግ ገልጿል።
ቦርዱ ፦
👉 በአፋር ክልል (በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣በ ዞን 3 ቡሬሞዳይቱ እና ገዋኔ፤ በዞን 2 ዳሎል እንዲሁም በዞን 4 ጉሊና) የምርጫ ክልሎች
👉 በቤንሻንጉል ጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል፤ በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች
👉 በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ
👉 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ነው።
ይህንን ተከትሉ መስፈርት የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር እንደሚፈልግ ገልጿል።
➡️ ከ18 አመት በላይ የሆናቸው
➡️ ከዚህ በፊት በምርጫ አስፈጻሚነት ያገለገሉ
➡️ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆኑ
➡️ 12ተኛ ክፍል እና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጀት ያላቸው
➡️ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ መስራት የሚችሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ክፍት በሚሆነው የቦርዱን የማመልከቻ ሊንክ ፦ https://pw.nebe-elections.org/recruitment በመጠቀም ማመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል።
ቦርዱ ፤ የሴቶችን እና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እንደሚያበረታታ ገልጿል።
@tikvahethiopia
📣ሜሪ ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች
የተለያዩ አዳዲስ እና ዘመናዊ ላፕቶፖች፣ ጌሚንግ ላፕቶፖች እና ዱባይ ዮዝድ ላፕቶፖች እንዲሁም አክሰሰሪዎች በጥራት እና በቅናሸ እናቀርባለን!
የአንድ ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
በትዕዛዝ የምትፈልጉትን ዓይነት ላፕቶፕ እና አክሰሰሪዎች በአጭር ግዜ ውስጥ እናስመጣለን። 🌟 በብዛት ለምትገዙ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን!
አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ መገናኛ፣ ሲቲ ሞል ከደራርቱ ከፍ ብሎ 1ኛ ፎቅ የሱቅ ቁጥር G1-2-01
☎️ 0920726666 / 0940711692
ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ /channel/merry_05
#MerryComputers
ኤርፖርት ...
በፎቶው 👆 ላይ የምትመለከቷቸው አቶ ነቢዩ ሲራክ ይባላሉ ፤ በአንደኛው ፎቶ ላይ አብሯቸው የሚታየው ልጃቸው ነው።
ትላንት ምሽት ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄደውን ልጃቸውን ለመሸኘት ቦሌ ኤርፖርት በነበሩበት ወቅት አንድ የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ልጃቸው ላይ ፍፁም ከስነምግባር ያፈነገጠ ተግባር መፈፀሙን ገልጸዋል።
ልጃቸው ምንም እንኳን በሱዑዲ አረቢያ ተወልዶ ቢያድግም አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገርና ሀገሩን ኢትዮጵያን ወዶ ወደዚህ የተመለሰ ፣ እዚህም በስራ ላይ የተሰማራ ነው።
የትላንት ጉዞውም የስራ ነበር።
ልጃቸው አስፈላጊውን ዶክመንት ሁሉ አሟልቶ የሚጠበቅበትን አድርጎ ኢሚግሬሽን ቢሮ ሲደርስ አንድ ሰራተኛ " የት ነው የምትሄደው ? " ይለዋል። ልጅም ቦታውን ይናገራል። " ስራህ ምንድነው ? " ሲል ሌላ ጥያቄ ያስከትላል " ስራዬን ሴልስ ማን ነው " ሲል ይመልስለታል።
ከዚህ በኃላ የኢሚግሬሽን ሰራተኛው ፓስፖርቱን ንጥቆ ወርውሮ ፣ ከዚህ ሂድ በማለት ያንገላታዋል ፤ ልጅም " ፓስፖርቴን መልስልኝ " ሲለው " ፓስፖርትህን አልሰጥም ሂድ ውጣ " በማለት እስከ ድብደባ ሊደርስ እንደነበር አባት በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነው ተናግረዋል።
በኃላም አባት ለኢሚግሬሽንና ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ በተደረገው ማጣራት ከአንድ ሰዓት መጉላላት በኃላ ኢሚግሬሽን አልፎ ጉዞውን ማድረግ ችሏል።
" ህጋዊ ወረቀት ፓስፖርት ቪዛ ይዞ የሄደውን ሰው በዚህ ደረጃ ለምን ማንገላታት ያስፈልጋል ? ለምን ፓስፖርት መወርወር አስፈለገ ? ግልምጫ ማንጓጠጡስ ለምን አስፈለገ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
በአንዳንድ የኢሚግሬሽን እና ደህንነት ሰራተኞች የሚፈፀም ህገወጥ አሰራር ፣ እጅግ በጣም የብዙ ሰዎችን ልብ እየሰበረ መሆኑን ፤ ለጥቅም ተብሎ በሚሰራ ስራ እጅግ ከፍተኛ ግፍ እና በደል እየተፈፀመ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ነብዩ ፤ እንዲህ ያለው አሳዛኝ እና ህገወጥ ተግባር በሁሉም ሰራተኞች ይፈፀማል ባይባልም በአንዳንድ ሰራተኞች የሚፈፀም ህገወጥ ተግባር የተቋሙን የቅን አገልጋዮችን ስም እንደሚያጎፍ እና ማረም እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተውበታል።
አቶ ነብዩ ሲራክ ፤ ለረጅም አመታት የህገ ወጥ ስደትን በመቃወምና በመከላከል ፣ በህገወጥ መንገድ ወጥተው ሌላ ሀገር እየተቸገሩ ስላሉ ዜጎች ጉዳይ ላይ ስራ እንዲሰራ ብዙ እየደከሙ ያሉ ሰው ናቸው።
ይህ የአንድ ሰው ገጠመኝና በማህበራዊ ሚዲያ የወጣ ይሁን እንጂ በተለይ በተለይ በቦሌ ኤርፖርት በአንዳንድ ፦
- ስነምግባር በጎደላቸው
- የገዛ ዜጋቸውን በማያከብሩ
- ስራቸውን አክበረው በማይሰሩ፣
- ገንዘብ እና ጥቅም በሚያሳድዱ የኢሚግሬሽና ደህንነት ሰራተኞች ስንት ዜጎችን ተበድለው ፣ አንብተው ፣ የሚጮኹበት አጥተው ፣ መፍትሄ ተነፍገው ፣ መፍትሄ ፍለጋ የሚሄዱበትም ይሁን የሚደውሉበት አጥተው ይሁን ?
ተቋማት ፤ ሰራተኞቻቸው #ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው በአግባቡ እንዲያወቁት በማድረግ ህዝብን #ጎንበስ ብለው ማስተናገድ እንዲለምዱ ፣ ሙስና እና ጥቅምን እንዲፀየፉ የማድረግ #ግዴታ አለባቸው።
@tikvahethiopia
#BGI #PurposeBlack
" ነገ ጥዋት መግለጫ እንሰጣለን "- ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያን አ/ማ
በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ሲካሄድ የቆየው አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ ተቋርጧል።
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በባከልን ኢሜል የሽያጩ ውል የተቋረጠው ፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎትና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ነው።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ምን አስተያየት አለው የሚለውንና የሚሰጠው ምላሽ ይኖር እንደሆነ ለድርጅቱ ኃላፊዎች ስልክ ደውለንላቸው የነበረ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም ነገ ጥዋት 2 ሰዓት ይፋዊ መግለጫ / ምላሽ እንደሚሰጡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ድርጅቱ የሚሰጠውን መግለጫ ተከታትለን መረጃ እንልካለን።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየካቲት ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።
@tikvahethiopia
ከባንክ ሂሳብዎ ወደ M-PESA 1,000 ብር እና ከዚያ በላይ በማስተላለፍ ከ0.5% እስከ 50 ብር ድረስ ስጦታ ያግኙ።
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ
/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC /channel/SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare
24/7 መጠየቅ ይቻላል!
#SafaricomET
#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
#AddisAbaba
4 ኪሎ አካባቢ የሚገኙ ሁለት የእግረኛ መሸጋገሪያ የብረት ድልድዮች የማንሳት ስራ እየተከናወነ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንደሰርድን የሚያሟሉ አዳዲስ አራት የመንገድ ኮሪደሮች ግንባታ እንዲከናወን ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ 4 ኪሎ አካባቢ የሚገኙትን ሁለት የእግኛ መሸጋገሪያ የብረት ድልድዮች የማንሳት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አሳውቋል።
" 4 ኪሎ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የሚገኘው የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድይ ጉዳት ደርሶበታል " በሚል የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የተላለፈው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑ ተገልጿል።
የብረት ድልድዮችን የማንሳት ስራ በሁለት ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።
@tikvahethiopia
#ፓስፖርት
ፓስፖርት ፈልገው/ በሥራ ምክንያት ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጎራ ካሉ ረዥም ሰልፍ እና መጨናነቅ ማየት የተለመደ ነው።
የሰልፍ አሰላፊዎች ዱላም ሊያጋጥም ይችላል።
ወጣት፣ሴት፣ወንድ፣ልጅ ያዘሉ እናቶች እንዲሁም " ፓስፖርት ፈልገው ነው ? " እያሉ እግር በእግር የሚከተሉ ሕገወጥ ደላሎችም በአካባቢው ውር ውር ይላሉ።
አገልግሎቱ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ አሠራር ዘርግቻለሁ ቢልም አሁንም በርካታ ተገልጋዮችን አገልግሎቱ ደጃፍ ላይ መመልከት አልቀረም።
ተገልጋዮች ዐሻራ ለመስጠት እና ፎቶ ለመነሳት በመ/ቤቱ መገኘት ግዴታቸው በመሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው በወረፋው ምክንያት ላልተፈለገ እንግልት ይዳረጋሉ።
እንግልቱ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ከእንቅልፍ ተነስቶ ረዥም ሰልፍ ከመሰለፍ ይጀምራል።
በሌቦች መዘረፍም የሚያጋጥም ክስተት መሆኑን ተገልጋዮች በምሬት ይናገራሉ።
ለአላስፈላጊ እንግልት እና ወጪ ተዳርገናል የሚሉ ተገልጋዮች ሃሳባቸውን አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት በበይነ መረብ አማካኝነት ከተመዘገቡ ወራት እንዳለፋቸው ይገልጻሉ።
ተገልጋዮቹ አገልግሎቱ አካባቢ ወረፋ ለመያዝ ስንሞክር " እኔ ቅድሚያ ወረፋ ልያዝላችሁ ክፈሉኝ " በሚሉ ደላሎች እንዋከባለን ይላሉ።
እነሱ እንደሚሉት የመሥሪያ ቤቱን ሰልፍ አሰላፊዎች ወከባና ዱላ አልፎ ውስጥ መግባት መቻል መታደል ነው።
ተገልጋዮቹ በሌሊት ለመነሳት ሲሉ በአካባቢው ለአልጋ ኪራይ ከፍለው እንደሚያድሩና ለአላስፈላጊ ወጪም እንደሚዳረጉም ይገልጻሉ።
ሰልፉ ረዝሞ ወረፋ ሳይደርሳቸው ከቀረም ቅጣት እንደማይቀርላቸው ይናገራሉ።
በርካታ አገልግሎት ፈላጊ ሕዝብ በተገቢው መንገድ ከማስተናገድ ይልቅ በዱላ በመደብደብ ሥርዓት ለማስያዝ ሲሞከር ይታያል። ወደ መግቢያ በሩ ተጠግቶ መረጃ ማግኘት የማይታሰብ ነው።
የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱ ተስተካክሏል ይባል እንጂ አሁንም ችግሮቹ እንደነበሩ ናቸው ይላሉ ተገልጋዮች።
የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱ ሳይዘምን እንደዘመነ አድርጎ ማስተዋወቅም ፍጹም ተገቢነት እንደሌለውና ሕዝብ በለውጥ እንዳያምን እንደሚያደርግም ያስገነዝባሉ።
ሰሞኑን የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱን ለመመልከት በመ/ቤቱ የተገኙት የኢፕድ ጋዜጠኞች መረጃ ለመሰብሰብ ያደረጉት ሙከራ በፖሊሶች ክልከላ ተደርጎበታል።
የተቋሙ ኮሙኒኬሽን ዳሬክተር ወ/ሮ ማስተዋል ገዳ ምን ምላሽ ሰጡ ?
- ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ በሚመጡበት ወቅት በክብር መስተናገድ እንዳለባቸው እናውቃለን። ተገልጋዮችን በአግባቡ ባለማስተናገድ የዲሲፕሊን ችግር ያለባቸው ሠራተኞች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው።
- ተገልጋዮች ቅሬታ ሲኖራቸው ቅሬታ ለተቋሙ ማቅረብ አለባቸው።
- አዲስ ፓስፖርት ፈልገው በድረ ገጽ ሲያመለክቱ ፎቶግራፍ የሚነሱበትን እና ዐሻራ የሚሰጡበትን ቀንና ሰዓት የሚያሳውቅ በመሆኑ ተገልጋዮች በሰዓቱ ብቻ ቢመጡ ሰልፉ ሊቀንስ ይችላል። የተቀጠሩ ተገልጋዮች ሳይስተናገዱ አይቀሩም።
- በአካባቢው መጨናነቅ የሚፈጠረው ቀጠሮ ባላቸው ተገልጋዮች ብቻ ሳይሆን " ፓስፖርት ዘግይቶብናል " ብለው ለመጠየቅ በሚመጡ ተገልጋዮች ነው። አንድ ጉዳይ ለመጨረስ ከአንድ በላይ ሰው ስለሚመጣ ነው።
- የሌሊት ሰልፉ ከአገልግሎቱ እውቅና ውጪ ነው። ለሰልፉ ሰዓት የመገደቡን ጉዳይ በቀጣይ በጋራ የሚታይ ነገር ነው።
- ተገልጋዮች ለአስቸኳይ ፓስፖርት በሕገ ወጥ ደላሎች በኩል ለማስጨረስ ከመሞከር ይልቅ እራሳቸው በጥቂት ቀናት መጨረስ ይችላሉ።
ያንብቡ https://telegra.ph/EPA-03-04
ይህ መረጃ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው።
ፎቶ፦ Tikvah Family
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ ሆና አጠናቀቀች።
በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 5 በመሆን አጠናቃለች።
ከማርች 1-3/2024 በእንግሊዝ ግላስጎ ሲካሄድ የ19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሲካሄድ ነበር። በሻምፒዮናው ከ130 በላይ አገሮች የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶቸ ተሳትፈዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር በሴትና በወንድ በአጠቃላይ በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች ተሳትፋለች።
በዚህም #በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ #የወርቅ፣ በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋይ የብር እንዲሁም #በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል።
ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎች በሜዳልያ ሰንጠረዡ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 5ኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሳለች።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopia
📣ሜሪ ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች
የተለያዩ አዳዲስ እና ዘመናዊ ላፕቶፖች፣ ጌሚንግ ላፕቶፖች እና ዱባይ ዮዝድ ላፕቶፖች እንዲሁም አክሰሰሪዎች በጥራት እና በቅናሸ እናቀርባለን!
የአንድ ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
በትዕዛዝ የምትፈልጉትን ዓይነት ላፕቶፕ እና አክሰሰሪዎች በአጭር ግዜ ውስጥ እናስመጣለን። 🌟 በብዛት ለምትገዙ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን!
አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ መገናኛ፣ ሲቲ ሞል ከደራርቱ ከፍ ብሎ 1ኛ ፎቅ የሱቅ ቁጥር G1-2-01
☎️ 0920726666 / 0940711692
ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ /channel/merry_05
#MerryComputers
#ኢትዮጵያ
" የአንድ ሀገር ልጆች እየተገዳደሉ ናቸው !! "
ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዓድዋ በዓል ላይ የተናገሩት ፦
" ከአንዱ ሳናገገም ሌሎች ችግሮችም በሀገራችን አሉ።
በመካከላችን ድልድይ ሳይሆን ግንብ የመገንባት አካሄድም አለ።
ዛሬ በሌሎች ክልሎች ንፁሃን እየሞቱ ናቸው።
በአማራ ክልል እንደዚሁ ከውጭ የመጣን ጠላት ሳይሆን የአንድ ሀገር ልጆች እየተገዳደሉ ናቸው። ህዝቡም በከፍተኛ አደጋ ላይ እየተጣለ ነው።
በሌሎችም እንደዚሁ ኦሮሚያም የሚሞተው ንፁህ ሰው መሞት የሌለበት ነው።
ይሄ ሁላችንም አያገባኝም ሳይሆን ፤ እኔ ላይ አይደርስም ሳይሆን ፤ የት ይደርሳሉም ሳይሆን ሁላችንም ነቅተን ይሄን ያለንን ጀግኖች አባቶቻችን እናቶቻችን የሰጡንን ነፃነት ፣ አንገታችንን ከፍ እንድናደርግ የረዳንን ባንድነት የመስራትን እንደገና ማደስ ያስፈልጋል፤ ይህ ከታሪካችን ጋር መታረቅ ማለት ነው።
ይሄን አደራ ማለት እፈልጋለሁ። "
@tikvahethiopia