ተረክ በM-PESA ሊጠናቀቅ የመጨረሻው ቀን ዛሬ ነዉ፤ መኪናዋን ዛሬም የእናንተ መሆን ትችላለች!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
" ገዳሙ የ2016 ዓ/ም የማህበር ቀለብ መሸመት እስከማይችል ድረስ ኢኮኖሚያዊው ተጎድቷል " - ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም
በመላው ዓለም የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ ለዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ ቀረበ።
ጥሪውን ያቀረበው ገዳሙ ነው።
ይህ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳም ከቅብር አመታት ወዲህ የመነኮሳትን ህይወት መስእዋትነት እስከማስከፈል የደረሰ ለዘርፈ ብዙ ጥቃት መጋለጡን ገልጿል።
ገዳሙ ከዚህ ቀደም በገንዘብ ከተፈፀመበት ዝርፊያ ባለፈ በቅርቡ ለገዳሙ አይን የሆኑ 4 መነኮሳት አባቶች አሰቃቂ በሆነ መንገድ መገደላቸውን ይህም የመነኮሳትን ልብ የሰበረ እንደሆነ አመላክቷል።
በ2012 የተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ በሀገሪቱ በየትኛው ተቋም ላይ ያደረሰው አሉታዊ ተፅእኖ በገዳሙም ላይ እንዲሁ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን አሁን ላለበት እጅግ ዘርፈ ብዙ ችግር መጋለጥ የጀመረው ግን ህገወጥ ታጣቂዎች አካባቢው ላይ መንቀሳቀስ ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ ነው ብሏል።
ገዳሙ ፤ ህገወጥ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ወደ ገዳሙ በመግባት የጥበቃ ትጥቅ በመንጠቅ ገዳሙን በመዝረፍ አራቁተውታል ሲል ገልጿል።
ይህ ሁኔታ የ2016 ዓ/ም የማህበር ቀለብ መሸመት እስከማይችል ድረስ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን እንደጎዳው አስረድቷል።
በተለያዩ መስኮች እና አገልግሎቶች መንፈሳዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጸው ገዳሙ አሁን እየደረሰበት ያለው ጥቃት ሁለንተናዊ ችግር ላይ ስለጣለው የህዝበ ክርስቲያኑን ትብብር ግድ የሚልበት ደረጃ ላይ መደረሱን በይፋ አሳውቋል።
በመሆኑን በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች አቅማቸው በፈቀደ በገንዘብም ፣ በቁሳቁስ፣ በሞያ፣ በሃሳብ የእርዳታ እጃቸውን ለገዳሙ እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርቧል።
የገዳሙ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000011282222 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ወይም 31905877 (አቢሲንያ ባንክ) መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ውጭ ገዳሙ የመደበውም ሰው ይሁን ማህበር ስለሌለ ከተጠቀሰው አካውንት ውጭ #እንዳታስገቡ ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከገዳሙ አስተዳደር ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia
#Update
ዛሬ በአዲስ አበባ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ስትራቴጂካዊ ግምገማ ተጀምሯል።
እነማን ተገኙ ?
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት
- የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዛዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ
- የቀድሞው የኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ይገኙበታል።
የፌደራል መንግስትን ከወከሉት መካከል ፦
* የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣
* የፍትህ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣
* የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ ይገኙበታል።
ህወሓትን ከወከሉት መካከል ፦
° ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ሊቀመንበር)
° አቶ ጌታቸው ረዳ (ም/ሊቀመንበር እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት)
° ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ (የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት)
° ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ (በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ) ይገኙበታል።
@tikvahethiopia
#MertEka
እነዚህ የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የሁሉንም ዕቃዎች ዋጋ ይሄንን👉 t.me/MerttEka 👈 ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
አድራሻችን፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ሱቅ 376
በነገው ዕለት የዐቢይ ጾም እንዲሁም የረመዷን ወር ጾም ይጀምራል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልካም የዐቢይ ጾም እንዲሁም መልካም የረመዷን ጾም እንዲሆን ከልብ ይመኛል።
በነገው ዕለት የሚጀምሩት አጽዋማት የፈጣሪን በረከት ፣ ዕርቅ ፣ ምህረት ፤ ለመላው ሀገራችን ፍጹም ሰላም እና መረጋጋትን የሚያመጡ እንዲሆኑ እንመኛለን።
#ኢትዮጵያ #Ethiopia #ክርስትና #እስልምና
@tikvahethiopia
#ረመዷን
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፦
" ታላቁ የረመዳን ወር የእዝነት፣ የመተሳሰብ፣ የምህረት ወር በመኾኑ ደካሞችን፣ ችግረኞችን፣ ተፈናቃዮችን እንዲሁም ወላጅ አልባ ሕጻናትን በመርዳትና ማዕዳችንን በማካፈል በመተሳሰብና አላህን በመለመን ልናሳልፈው ይገባል።
የረመዳን ወር የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነጃ የምንወጣበት፣ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው የዒባዳ ወር ይሁንልን።
መንፈሳዊ ልዕልና የሚኖረው #ሰላም ሲኖር በመኾኑ፣ ለሀገራችን ሰላም እና ለሕዝባችን ደኅንነት ዱዐ ልናደርግ ይገባል።
ለመላው ሙስሊም ማኀበረሰብ እንኳን ለ1445 ዓ.ሂ /2016 የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ። "
@tikvahethiopia
#ቢጂአይ #ፐርፐዝብላክ
" ገንዘቡንም አልመልስም ሲል በደብዳቤ አሳውቋል " ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ
" የመመለስ አለመመለሱ ጉዳይ በቀብድ ውሉ መሰረት የሚታይ ነው " - ቢጂአይ ኢትዮጵያ
ስምንት ወራትን የፈጀውና ያለስኬት የተጠናቀቀው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደት አሁን ላይ ወደ ክስ ሂደት አምርቷል።
ገዢ ሆኖ የቀረበው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ ጊዜያዊ የእግድ ትዕዛዝ እንዲተላለፍለት ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቧል።
የእግድ ጥያቄው ምን ይላል?
- ተጠሪ (ቢጂአይ ኢትዮጵያ) ውሉን እንዳያቋርጥና እንዳይጥስ ታግዶ እንዲቆይ
- በብሔራዊ ባንክ ስር በሚተዳደሩ ማንኛውም ባንክ በተጠርጣሪ ስም ያለ እስከ 1ቢሊዮን 519 ሚሊዮን ብር ሳይንቀሳቀስ ታግዶ እንዲቆይ፤
- ለሽያጭ የቀረበው በአጠቃላይ ስፋቱ 29 ሺህ 896.51 ካ.ሜ የሆነው ይዞታ እንዲታገድ ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
ከዚህ በተጨማሪ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ " በውላችን አንቀጽ 6 መሰረት በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ቀርቦ ውሉን መፈረም ሲጠበቅበት ውሉን አቋርጫለው ክፍያውንም አልመልስም ሲል የህዝብና የደሃ ማኅበረሰብን ገንዘብ ከህግና ከሥርዓት ውጪ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ውሉን አቋርጧል፤ ገንዘቡንም አልመልስም ሲል በደብዳቤ አሳውቋል " ሲል ገልጿል
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሐሙስ የካቲት 28 ዕለት በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ የህግ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ነጋ ምህረቴ " ገንዘቡን የመመለስ ያመመለስ ጉዳይ በቀብድ ውሉ መሰረት የሚታይ ነው " ሲሉ ገልጸው ነበር።
ተጨማሪ መረጃ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የቢጂአይ የኮርፓሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በኃይሉ አየለ " ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ አስተያየት አይሰጥም " የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
የፍርድ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ ምን ይላል?
በብሔራዊ ባንክ ስር በሚተዳደሩ ማንኛውም ባንክ በተጠርጣሪ ስም ያለ እስከ 1ቢሊዮን 519 ሚሊዮን ብር ሳይንቀሳቀስ ታግዶ እንዲቆይ እና የክርክሩ ምክንያት የሆነው ይዞታ እንዲታገድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ተጠሪ ውሉን እንዳይቋረጥ እና እንዳይጥስ የቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገው ሲሆን ለዚህም "የውሉ ህጋዊነት ክርክር የሚያስነሳ ስለሆነ አመልካች (ፐርፐዝ ብላክ) ተጠሪ ውሉን እንዳይጥስ የጠየቀውን እግድ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም" ሲል በትዕዛዙ ላይ ጠቅሷል።
ይህ የእግድ ውል የሚቆየው ለ20 ቀናት (እስከ መጋቢት 17) ወይም ከግራ ቀኙ አንዱ አቤቱታ ሲያቀርቡ መሆኑን የካቲት 28 ስምት ቀን ባሳለፈው ትዕዛዝ ጠቅሷል።
መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
@tikvahethiopia
# Mert Eka
🎯 እነዚህ የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የሁሉንም ዕቃዎች ዋጋ ይሄንን👉 t.me/MerttEka 👈 ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
🎯አድራሻችን፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ሱቅ 376
#Ethiopia የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተደረገባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ የተደረገ ማስተካከያ !
Via Ministry of Finance
@tikvahethiopia
#ዐቢይ_ጾም
ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ2016 ዓ/ም የዐቢይ ጾመን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦
" ጾም ማለት እህልንና የእንስሳት ውጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም፤ የእንስሳት ውጤት የሆኑትን ላለመመገብ ከምንወስነው በላይ እኩያት ፍትወታትንና ኃጣውእን ላለማስተናገድ በቁርጥ መወሰን ይጠበቅብናል፡፡
ስንጾም መገዳደልን፣ መጣላትን፣ መለያየትን፣ መገፋፋትን በሆነ ነገር መጐምጀትን እርም ብለን በመተው ዲያብሎስን የምናሸንፍበት የአሸናፊነት ኅሊና መላበስ አሰብን፣ ከክፉ ጎሊና እና ተግባር የተለየን ያህል በአንጻሩ ደግሞ በጎ ነገርን ለመስራት በእጅጉ መበርታት ይጠበቅብናል፡፡
ዲያብሎስ ተስፋ ቆርጦ የሚሸሸው ይቅር ይቅር ስንባባል፤ ለሰላምና ለአንድነት፣ ለፍቅርና ለስምምነት ስንቆም ነው፣ ከዚህም ጋር በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ጸያፍ የሆነው ግብረ ኃጢአት በዚህች ምድር እንዳይፈጸም ማኅበረ ሰባችን በተጠንቀቅ ሲቆም ነው፤ እንደዚሁም ደም መፋሰስ፣ አለመተማመንና በሴት ልጆቻችን የሚደርሰው አካላዊ፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ ጥቃት ሲቆም ነው፡፡
ጸማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡
ይህ ዓይነት መልካም ሥነ ምግባር በእያንዳንዱ የማኅበረ ሰብ አእምሮ ቦታ አግኝቶ ሲተገበር ትክክለኛውን ጾም ጾምን ማለት እንችላለን፣ ዲያብሎስም በእርግጠኝነት በዚህ ይሸነፋል፣ የሰው ጣዕመ ሕይወትም በዚህ ይለመልማል፣ ምድሪቱም በእግዚአብሔር በረከት ትሞላለች፡፡ ይህ ቅዱስ ተግባር በወርኃ ጾሙ በደንብ እንድንተገብረው ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ለኦርቶዶክሳዊው ማኅበረ ሰብ መንፈሳዊና አባታዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#AmazonFashion
አማዞን ፋሽን ከታች ባለው ቲክቶክ ኣካውንታችንን ፎሎው በማረግ የ 20ሺ ብር ሽልማት ላይ ይሳተፉ::
ሙሉ ልብስ ኮት ሸሚዝ አና ጨርቅ ሱሪ በታላቅ ቅናሽ
☎️0919339250/ 0911072936
አድራሻ፦ ፒያሳ Down Town ህንፃ ምድር ላይ እና 2ኛ ፎቅ
👉amazonfashionethiopia?_t=8j8DJ50UqhR&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@amazonfashionethiopia?_t=8j8DJ50UqhR&_r=1
#ትግራይ
በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት የ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ውድመት እንደደረሰበት የገለጸልን የዓዲግራት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሃገረ ስብከት ተራድኦ ድርጅት ለ364 ሺህ 311 የጦርነት ተፈናቃዮች የድርቅና ረሃብ ተጠቂዎች እርዳት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገለፀ።
ከፓለቲካ ነፃ መሆኑ የሚጠቅሰው የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የተራድኦ ድርጅት በትግራይ ጦርነት ጊዜ ለሰብአዊ አገልግሎት ስራ ሲጠቅምባቸው የነበሩ 14 መኪኖች መዘረፉ አስታውሶ ዘራፊዎቹ ለሰብአዊ አገልግሎት መኪኖቹ እንዲመልሱ " በፈጣሪ ስም እማፀናለሁ " ብሏል።
የምግባረ ሰናይ ድርጅቲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወልደ ሃይለስላሴ ወደ ዓዲግራት ለተጓዘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት ቃለመጠይቅ እንደገለፁት ፤ ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ባለፈው 2023 የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ433 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለ364 ሺህ 311 ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ አቅርበዋል።
ከተረጂዎቹ 50 በመቶ በላይ ሴቶች መሆናቸው ያብራሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እገዛው በመላ ትግራይና ዓፋር ዞን 2 እንደተከናወነ አብራርተዋል።
ያንብቡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-09
#TikvahFamilyAdigrat
@tikvahethiopia
OMEGA COMPUTER TRADING
ሁሉንም አይነት ላፕቶፖች ያገኛሉ !!!
ከ4ተኛ አስከ 13ተኛ Generation ከ core i3 አስከ core i9 ከ 2GB አስከ 16GB Dedicated Graphics card ያላቸው
👉 አዳዲስ ጌሚንግ ላፕቶፖች
👉 ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች
ከመልካም መስተንግዶ ከተሟሉ ሶፍትዌሮች በ ጥራት እና በ ብዛት ላፕቶፖችን አና ዴስክቶፖችን ከ እኛ ጋር ያገኛሉ
👉 እንገዛለን እንሸጣለን ይዘው ይምጡ ይዘው ይሒዱ
👉ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር
የተለያዩ ዓይነት ላፕቶፓችን ለማየትና ለመምረጥ ሊንኩን ይጠቀሙ - Telegram- 👉 /channel/Omegacom21
አድራሻ፦ መገናኛ ማራቶን ህንፃ ግራውንድ
Inbox me - @Yime29
ስልክ - 0974060288
#ለጥንቃቄ
" ተጠርጣሪው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል " - ፖሊስ
" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ቪዛ እናስጨርሳለን ! " በሚል #ቲክቶክ በተሰኘው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።
" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚጓዙ ሰዎች ቪዛ እናስጨርሳለን ! " እያለ በቲክቶክ ሲያጭበረብር የነበረው ይኸው ግለሰብ ከ25 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን በማጭበርበር ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል።
በቲክቶክ ሀሰተኛ የግለሰቡ ማስታወቂያ የተጭበረበሩት አብዛኞች ወደ #ካናዳ ለመጓዝ ፍላጎት አሳይተው ከተጠርጣሪው ጋር የተገናኙ ናቸው።
" ያለምንም ቅድመ ክፍያ የቪዛ ፕሮሰስ እጨርሳለሁ " ቢልም ተበዳዮችን የተለያየ ቦታ እየቀያየረ እያገኛቸው ቪዛ እንዳለቀላቸው እየነገረ እና ሌሎች ምክንያቶችን እየሰጠ ከእያንዳንዳቸው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ተቀብሏል።
ተጠርጣሪው የማታለል ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ የታወቀው " ቪዛ አልቆልሃል " ተብሎ 600 ሺህ ብር የከፈለ አንድ ግለሰብ ወደ ካናዳ ሀገር ለመሄድ አየር መንገድ በተገኘበት ወቅት #ቪዛው_ሃሰተኛ መሆኑ ከተነገረው በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ነው፡፡
አሁን ላይ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በህግ አግባብ ቤቱ ሲበረበር ሀሰተኛ ሰነዶች እና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።
#AddisAbabaPoliceCommission
@tikvahethiopia
ልዩ ትኩረት የሚሻው የጎርፍ አደጋ !
በሶማሌ ክልል ከተከሰተ ከወራት በላይ ያቆጠረው የጎርፍ አደጋ አሁንም የክረምት ወቅት ከመድረሱ በፊት ልዩ ትኩረት አንደሚሻ ተፈናቃዮችና ኃላፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አንድ ተፈናቃይ በሰጡት ቃል ፦
" አሁን ከከፈልነው የስቃይ ዋጋ በላይ ሕይወታችንን እንዳናጣ አሁንም ቢሆን ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል።
የክረምት ወቅት እየመጣ የጎርፉ መጠን መጨመረ የሚታወቅ ነው፡፡ ሁሉም ከፍተኛ ስጋት አለው፡፡ ሁሉም የገፈቱ ቀማሽ መንግስት ወደ ሌላ ቦታ ሰፈራ ሊሰጠን ይገባል የሚል ፍላጎት ነው ያለው " ብለዋል፡፡
ለሌላኛው ተፈናቃይ ፦
" 30 ከብቶች በጎርፉ ተወስደዋል፡፡ ቤቴ ሰጥሞ ወድሟል፡፡ አሁንም ችግሩ እንዳይደገም ምንም ዋስትና የለም፡፡ እንዲህ አይነት ችግር ነው ያለው " ሲሉ አማረዋል፡፡
ከክልል አደጋ መካላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ያነጋጋርናቸው አንድ ሠራተኛ ፦
" ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት እየተሞከረ ነው። ሆኖም ለዘላቂ መፍትሄ የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው።
ለተፈናቃዮች ለአሁንም በቋሚነትም የሚቋቋሙበት ድጋፍ ያስፈልጋል። በተለይም እናቶች፤ አረጋዊያንን፤ ሕጻናት የክረምቱ ወቅት ሲመጣ በድጋሚ ለችግሩ ሰለባ ይሆናሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አለን " ብለዋል።
ያንብቡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-08-2
ወጋገን ባንክ ኢ- ስኩል
ከመዋዕለ ህፃናት እስከ 2ኛ ደረጃ ላሉ የትምህርት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያን በዲጂታል የባንካችን አገልግሎቶች ካሉበት ቦታ ሆነው ይፈፅሙ፡፡
በወጋገን ባንክ ኢ-ስኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች:-
•የተሟላ የትምህርት ክፍያ አስተዳደር ዝርጋታ
•የተለያዩ የትምህርት ቤት ክፍያዎች ዝርዝር መግለጫ
• የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያግዝ የአስተዳደር ስርዓት መዘርጋት
•ደህንነት እና ምስጢራዊነት የጠበቀ የተማሪ መረጃ አያያዝ
• ሪፖርት ማዘጋጀት፣ ለተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ማድረግ
ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ::
#WegagenBank #WegagenEschool #MobileBanking
Follow us and get more information...
https://linktr.ee/WegagenBank
#Tigray
" የኤርትራ ሰራዊት በራሱ ግዛት ነው ያለው የሚለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ ራስን ከማሞኘት ያለፈ ትርጉም የለውም " - አኒና የኢሮብ ማህበረሰብ መብት ጠባቂ ማህበር
አኒና የተባለው የኢሮብ ሲቪክ ማህበረሰብ ማህበር መጋቢት 1/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ኢትዮጵያ በሚገኙ 3 ዞኖች የሚገኙ በርካታ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ነዋሪዎች እያንገላታና ግፍ እየፈፀመ ይገኛል ብሏል።
ስቪክ ተቋሙ የኤርትራ መንግስት የካቲት 28/2024 ያወጣው መግለጫን በተመለከተ " የኤርትራ መንግስት የትግራይ ኢትዮጵያ መሬቶች መያዙ በዚህ በሰለጠነ የመረጃ ዘመን ፈፅሞ መካድ አይቻልም " ብሎታል።
የኤርትራ መንግስት የሰጠው መግለጫ ከእውነት የራቀና በፍፁም መወገዝ ያለበትን ነውም ብሏል።
የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ፦
- የዛላኣንበሳ ከተማ
- በጉሎመኸዳ ወረዳ ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ፣ ሸዊት ለምለምና ሰበያ
- በኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ ፣ ወርዓትለ ዓገረ ሎኽማና ዓሊቴና የተባሉ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ይገኛል ሲል ገልጿል።
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በታሕታይ ኣድያቦ የኩናማ ማህበረሰብና ሌሎች የሚኖሩባቸው ገማህሎ ፣ አደመይቲ ፣ የባድመ ከተማና አከባቢው ፣ ዓዲ ፀፀር ፣ ለምለም ሸዊት ፣ ሸምበሊና ፣ መንጠብጠብ ፣ ዓዲ ኣሰር ፣ ሰየምቲ አድያቦ በኤርትራ ስራዊት ስር እንደሚገኙ ፀሃይ የሞቀው ሃቅ ነው ሲልም አክሏል።
የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ማእከላዊ ዞን የእገላና ራማ አከባቢዎች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቆጣጥሮ የአከባቢው ህዝብ የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኝ በማድረግ ለበርካታ ችግሮች እንዳጋለጠው ያመለከተው አኒና የኢሮብ ስቪክ ማህበረሰብ መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ህዝቡ ከእንግልትና መከራ እንዲታደገው ጥሪ አቅርቧል።
አኒና የኢሮብ ሲቪክ ማሕበረሰብ ያወጣውን መግለጫ የተከታተሉ የመቐለ ነዋሪዎች ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት አስተያየት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች የፌደራል መንግስትና ህወሓት ፣ የአሜሪካ ፣ የአውሮፓ ፣ ኢጋድና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተዛቢዎች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ዛሬ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውል አተገባበርና አፈፃፀም አስመልክቶ በሚካሄደው ግምገማ በኤርትራ ሰራዊት ስር ስላሉ የትግራይ ኢትዮጵያ ግዛቶች ጉዳይ የውይይቱ አካል ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
PHOTO ፦ የመጀመሪያው ምሽት ተራዊህ ሶላት በሳዑዲ አረቢያ - #RAMADAN #ረመዷን ☪️
Photo Credit : Haramain
@tikvahethiopia
Empowering Africa, One Venture at a Time. Jasiri Talent Investor strives to remove barriers that hinder the success of new businesses. The program guides the Fellows from ideation to venture creation, by providing funding, coaching, strategic advisory, and guidance in the complex innovation space.
Application for Cohort 6 is ongoing, submit your application via http://jasiri.org/application
#Jasiri4Africa
#ረመዷን
ሙፍቲ ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦
" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።
ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤ ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "
መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመኛል።
@tikvahethiopia
ረመዷን ነገ ይጀምራል።
በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የታላቁና ቅዱሱ የረመዳን ወር ጾም ነገ ሰኞ ይጀምራል።
@tikvahethiopia
#Ethiopia
በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ትላንት በተጠናቀቀው የካቲት ወር በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል። ጉዳትም ደርሷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወሩ ስለነበሩት ሁኔታዎች ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት እጅግ በርካታ ቀናትን የወሰደ ሙከራ ቢያደርግም ምንም ምላሽ የሚሰጠ አካል አላገኘም።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ግን ስለነበሩት ሁኔታዎች እንደማያውቅ እና ክትትል ላይ እንደነበር በመግለፅ ያለውን ትንሽም ቢሆን አስተያየት ሰጥቶናል።
የተዘጋጀውን ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-10
@tikvahethiopia
የርገን ክሎፕ እና ፔፕ ጋርዲዮላ በፕሪሚየር ሊጉ የሚያደርጉት የመጨረሻ ፍልሚያ እንደሚሆን ይጠበቃል… ይህ ታሪካዊ ጨዋታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት በቀጥታ አያምልጥዎ።
🔥 በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ ክምሽቱ 12፡45 የዋንጫ ግስጋሴያቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸውን ወሳኝ ፍልሚያ በሱፐርስፖርት ቻናሎች ይከታተሉ🔥
ይህ ታሪካዊ ፉክክር እንዳያመልጥዎ…
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#ዐቢይ_ጾም
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የ2016 ዓ.ም የዓብይ ጾም መግቢያን በማስመልከት አስተላልፈዋል።
ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦
" ጌታችን ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ወንጌሉን ይሰብክ ዘንድ የአባቱን ተልእኮ ሊፈጽም ነፍሳትን ለማዳን የጠፉትን ለመፈለግ ተልእኮ ሲሆን ዲያብሎስ ያቀረበለት ጥያቄ ፈታኝነቱ አምላክን ከማገልገልና እርሱን ከማምለክ ይልቅ ለእኔ ተገዛ አገልጋይ ሁን የሚል አንድምታ ያለው ነው፡፡
የጌታችን ኢየሱስ መልስ ግን ከሰይጣን ጋር መስማማትን ሳይሆን እግዚአብሔር አምላክን ማምለክ ለእርሱ ብቻ መስገድና ለእርሱ አገልጋይ መሆን እንደሚገባ አስረግጦ ይናገራል፡፡
ዛሬም የብዙዎቻችን ፈተና እግዚአብሔር አምላክ በሰጠን ስልጣን ባስቀመጠን የኃላፊነት ቦታ ላይ በፍቅር እናገለግላለን ? ሲሾም ያልሰራ ጡረታ ሲወጣ ይጸጸታል እንላለን ወይንስ ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል በሚል ዓይነት ስልጣናችንን አላገባብ እየተጠቀምን ነው ? ሌሎች በአገልግሎታችን ይደሰታሉ ? አምላክን ያመሰግናሉ ? ወይስ በእኛ የአገልግሎት አሰጣጥ ይማረራሉ ? ይህ የጾም ወቅት ራሳችንን የምናይበት እና የምንፈተንበት ጊዜ ነው፡፡
ኃላፊነት ከሰሩበት ካገለገሉበት በረከቱ ለሁላችንም ነው፤ ፈተናችን የሚሆነው መስራት በሚገባን ጊዜና ቦታ ለሕዝባችን ማገልገል ሲገባን ስልጣናችንን ለማሳየትና ሌላ ተጨማሪ ከፍያ ተጨማሪ ክብር ከፈለግን፣ በማገልገላችን ልንከበር ሲገባ ቦታው ላይ በመቀመጣችን ብቻ ክብር ካልተሰጠን የሚል ስሜት ከተሰማን፣ ፈተናውን ወደቅን ማለት ነው፡፡
ፈተና የምንወስደው ለማለፍ እንጂ ለመውደቅ አይደለም፤ በዚህ የጾም ወራት ፈተናችንን ለማለፍ ልንዘጋጅ ይገባል፡፡ እንዲሁ የሚደረግ ጾም የለምና ለጥያቄአችን መልስ እንድናገኝና እግዚአብሔርን በማዳመጥ ፈቃዱን ለማድረግ እንጹም፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ፈተናችንን አልፈን ፣ ንስሐ በመግባት ከእርሱና ከሰዎች ሁሉ ጋር ታርቀን ካለን ላይ ለወገኖቻችን አካፍለን እርሱ ወደፈለገው የፍቅርና የሰላም ኑሮ መኖር እንድንችል ጾምና ጸሎታችንን ይቀበልልን፡፡
ለትንሳኤው ብርሃን በሰላም ያድርሰን፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Ethiopia
በረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው ላይ 8 የሰብዓዊ መብት የሲቪክ ድርጅቶች አስተያየት አቅርበዋል።
አስተያየት ያቀረቡት ፦
➡ የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል (CARD)
➡ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች (LHR)፣
➡ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA)፣
➡ ሴታዊት
➡ የኢትዮጵያ ሠራተኞች መብት ተሟጋች (ELRW)፣
➡ ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ (AHRE)
➡ ሁሉን አቀፍ ራዕይ ለዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያ (IVIDE)
➡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC) ናቸው።
ካቀረቡት አስተያየት መካከል ፦
" የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ፖሊሲው እስካሁን ለህዝብ ይፋ ባይደረግም፣ ባጭር ጊዜ ውስጥ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚፀድቅ መረጃዎች በመውጣት ላይ ይገኛሉ።
ነገር ግን ረቂቅ ፖሊሲውን በሚመለከት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ለጋሾች ጋር ከተደረጉ አጫጭር ውይይቶች በስተቀር በቂ ውይይት አልተደረገም።
ሰነዱ ይፋ ስላልሆነ ደርዝ ያለው አስተያየት ለመስጠትም ዕድል አልተገኘም።
ረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሰነዱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት ለህዝብ ይፋ ተደርጎ በባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጥበት በአፅንኦት እንጠይቃለን።
በዚህ ረገድ በሽግግር ፍትህ አማራጮች ላይ ሰፊ ውይይቶች መካሄዳቸውን በበጎ የምንወስደው ቢሆንም፣ በፖሊሲ ዝግጅቱ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደምንገኝ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው ላይ በቂ እና ፍሬያማ ውይይት እንዲደረግ አስቀድሞ ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዱ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን እንጠይቃለን።
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተጨማሪ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ፦
- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣
- የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን፣
- የእምባ ጠባቂ ተቋም፣
- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
- የመገናኛ ብዙሃን፣
- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣
- ምሁራን እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሰነዱን በዝርዝር ተመልከተው ከመፅደቁ በፊት አስተያየታቸውን እንዲያቀርቡ ዕድል እና በቂ ጊዜ ሊሰጥ ይገባል።
ይህን ማድረግም ለፖሊሲ ሰንዱ ጠቃሚ ግብዓት ከማስገኘት በተጨማሪ ፣ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው በህዝብ ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እና ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ያግዛል ብለን እናምናለን። "
(ሙሉ አስተያየታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
የተረክ በM-PESA ዕጣ ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ብቻ ቀርተዋል!
አስጨብጭቦን የሚወስዳት ማን ይሆን? እኛም ለማወቅ ጓጉተናል!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር " ታይተዋል " ስለተባሉ #ዩፎዎች ምንነት ባወጣው ሪፖርት ምን አለ ?
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር /ፔንታጎን/ ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ በራሪ አካላትን (#ዩፎ) መታየታቸውን በተመለከተ የማጠቃለያ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።
በሪፖርቱ ፦
➡ በአውሮፓውያኑ የ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር የታዩት እና ዩፎዎች ናቸው ተብለው የተደመደሙት በራሪ ነገሮች የአሜሪካ መንግሥት የሠራቸው የተራቀቁ #የስለላ_አውሮፕላኖች እና የህዋ ቴክኖሎጂ ሙከራ ውጤቶች ናቸው።
➡ የአሜሪካ መንግሥት ከሌላ ዓለም የመጡ እንግዳ ፍጡራን ማጋጠማቸውን በሚመለከት “ ምንም ዓይነት ” ማስረጃ የለውም።
➡ ዩፎ ተብለው መታየታቸው ከተገለጹት መካከል አብዛኞቹ ክስተቶች ከምድር ላይ የተነሱ የተለመዱ ነገሮች ናቸው።
➡ የተደረገው ምርመራ ውጤት በሕዝቡ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ዩፎዎችን በተመለከተ ያለውን እምነት በቀላሉ የሚለውጠው አይደለም።
➡ የዩፎዎችን መኖር በተመለከተ በሕዝቡ ውስጥ ጠንካራ እምነት አለ እና ለዚህም ፊልሞች፣ መጻሕፍት፣ ሙዚቃዎች እና ሌሎችም የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው። ያለውን አመለካከት በቀላሉ መለወጥ አዳጋች ነው።
➡ አስካሁን የተደረጉት ሁሉም ምርመራዎች እና ዝርዝር መረጃዎች በአብዛኛው እንግዳ ፍጡራን ወደ ምድር ስለመምጣታቸው የሚያመለክቱ ምንም ማስረጃዎች የሉም።
➡ ታዩ የተባሉት ነገሮች የተለመዱ ነገሮች እና በተሳሳተ መንገድ ከመረዳት የመነጩ ናቸው።
➡ ዩፎዎችን በተመለከተ የተደረገው ምርመራው ከ1945 (እአአ) ጀምሮ ያሉ መዛግብትን እና ምሥጢራዊ ሰነዶችን ጨምሮ በመንግሥት የተደረጉ ይፋዊ ምርመራዎችን ያከተተ ነው።
➡ በርካቶች ዩፎዎች ናቸው ያሏቸው ነገሮች ክብ በራሪ ነገሮችን ሲሆኑ፣ እነዚህ ግን በዚያ ዓይነት ቅርጽ ተሠርተው ሙከራ ሲደረግባቸው የነበሩ አውሮፕላኖች ናቸው። በካናዳ የተሠራውን ተመሳሳይ ቦምብ ጣይ አውሮፕላንም አንዱ ማሳያ ነው።
ለረጅም ዓመታት የአሜሪካ መንግሥት እነዚህን ምንነታቸው ያልታወቀ በራሪ አካላትን በተመለከተ በርካታ የምርምር ፕሮግራሞችን አካሂዷል፤ ነገር ግን አብዛኞቹ በእንግዳ ፍጡራን ዙሪያ የተደረጉ ምርምሮች #በምሥጢር ተይዘው ቆይተዋል።
አሁንም ድረስ በርካቶች እንግዳ ፍጡራን እንዳሉ የሚያምኑ ሲሆን፣ በአንድ ወር ውስጥ ከ50 አስከ 100 የሚደርሱ ዩፎዎችን መታየታቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶች ይቀርባሉ።
መንግሥት እነዚህን ክስተቶች ይደብቃል የሚለው ግምትም አሁንም መቀጠሉን የፔንታጎን ሪፖርት አመልክቷል።
ባለፈው ዓመት የቀድሞው የአሜሪካ የስለላ መኮንን ዴቪድ ግሩሽ በአሜሪካ ምክር ቤት ኮሚቴ ፊት ቀርቦ የአሜሪካ መንግሥት የእንግዳ ፍጡራን አካላትን እና በራሪ ነገሮችን ይዞ እንደሚገኝ እንደሚያምን መስክሯል።
ግለሰቡ ይህ እምነቱ እና ለም/ቤቱ የሰጠው ቃል በሰነዶች ላይ ያሉ መረጃዎችን፣ የድምጽ ቅጂዎችን እና ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ያደረገውን ውይይቶችን መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ተናግሮ ነበር።
Via BBC
@tikvahethiopia
ሊቨርፑል ወይስ ማንችስተር ሲቲ (#ይገምቱ!) /channel/+BiR6VdrAieQ3NzRk
ለ3 የቴሌግራም ተከታዮቻችንን ለእያንዳንዳቸው የ400 ብር ካርድ የሚያሸልም!
💥💥 የውድድሩ ሕግጋቶች 💥💥፣
1. ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል /channel/+BiR6VdrAieQ3NzRk ይቀላቀሉ,
2. ግምትዎን በሃሳብ መስጫው (#COMMENT) ላይ ያስቀምጡ,
3. ውጤት ማስተካከል እና ከላይ የተጠቀሱትን ህግጋቶች የማያከብሩ ከውድድሩ #ውጭ ይሆናሉ,
4. ከ 3 በላይ ትክክለኛ መላሾች የሚለዩት #በዕጣ ይሆናል።
መልካም ዕድል!
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE #LIVMANCITY #EPL #liverpoo.l #ManCITY
#ETHIOPIA
ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ/ም በፊት የባንክ ፈቃድ የተሰጠባቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደ።
ተሽከርካሪዎቹ እና እቃዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የተፈቀደው በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል የሚቀርቡ ሠነዶች አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎባቸው ነው ተብሏል።
ይህም የሚሆነው ለመጨረሻ ጊዜ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሸን ከፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
የውጪ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተደረገባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉን በመጥቀስ በሚኒስትር ድኤታው እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) የተፃፈ ደብዳቤን ለጉምሩክ ኮሚሽን ተልኳል።
ተሽከርካሪን ጨምሮ 28 ምርቶች ከጥቅምት 4/2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንደይፈቀድላቸው መወሰኑ ይታወሳል።
የውጭ ምንዛሬ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች ጋር ተያይዞ በአፈጻጸም ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ማስተካከያ ተደርጓል ተብሏል፡፡
በጥቅምት ወር በወጣው እና የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው 38 ዝርዝሮች ውስጥ የተካተቱ ምርቶች የሆኑ ግን ደግሞ ምርቶቹ እና ተሽከርካሪዎቹ በሕግ በተደነገገ ፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ ከሆነ በተደረገው ማስተካከያ ክልከላው አይመለከታቸውም ተብሏል ።
ተሽከርካሪዎች ጎረቤት አገር ወደብ ወይም ጉምሩክ ጣቢያ በደረሱበት ጊዜ በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ (ማሻሻያ) ቁጥር 1287/2015 አንቀጽ 2(24) ለአዲስ ተሽከርካሪ የተሰጠውን ትርጉም የሚያሟሉ ሆነው ነገር ግን ይህን ውሳኔ ሲጠብቁ የተሽከርካሪው እድሜ ያገለገለ ምድብ ውስጥ የገባባቸው ከሆነ በክልከላው ምክንያት በጎረቤት አገር ወደብ ወይም በጉምሩክ ጣቢያ የቆዩበት ጊዜ ሳይታሰብ እድሜው ጎረቤት አገር ወደብ ወይም የጉምሩካ ጣቢያ እስከደረሰበት ያለውን ጊዜ ድረስ ብቻ በማስላት እንዲስተናገዱ ማስተካከያ መደረጉ ተነግሯል።
የቀረጥ ነፃ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች የውጭ ምንዛሪ ክልከላው እንደማይመለከታቸው ማስተካከያውን የሚያስረዳው ደብዳቤ ላይ ተጠቅሷል።
የገንዘብ ሚኒስቴር የውጪ ምንዛሬ ክልካላው በተመለከተ በጥቅምት ወር 2015 ዓ/ም የተጻፈው ደብዳቤ እና በተለያየ ጊዜ የተሰጡ ማብራሪያዎች መሻራቸውንና በማስተካከያው መሰረት ተፈፃሚ እንዲሆን መወሰኑን ከደብዳቤው ላይ ተመልክተናል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
#ሀዋሳ
በሀዋሳ ከተማ የህዝብ ትንራንስፖርት አገልግሎት (ታክሲ) የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ፤ " የነዳጅ ጉዳይ ስቃያችንን አበላን ፤ የመፍትሄ ያለህ !! " ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ፤ "ሰርተን ከምንገባበት ለነዳጅ ሰልፍ ቆመን የምንውለበት እየበለጠ ነው " ብለዋል።
የነዳጅ ችግሩ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።
የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሆኑም በመግለፅ "
ካልሰራን ልጆቻን ምን ይብሉ ? ፤ እኛስ ምን በልተን እንደር ? ይህ ጉዳይ መፍትሄ ይፈልጋል " ብለዋል።
ከሳምንታት በፊት በዚሁ በሀዋሳ ከተማ ያሉ አሽከርካሪዎች ፤ " በረዣዥም ሰልፍችና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራችን በአግባቡ መስራት አልቻልንም " በሚል ምሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተው ነበር።
አሽከርካሪዎች ፤ ሁሉም ማደያዎች በአግባቡ አለመስራትና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ መኪኖች ለነዳጅ ሰልፍ ተገፍተዉ ከመግባት ባለፈ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሳልቫቲዮ ገጥመዉ መምጣታቸው ቀኑን ሙሉ ተሰልፈዉ እንኳን መቅዳት እንዳይችሉ ምክኒያት እንደሆነባቸው ገልጸው ነበር።
በወቅቱ እየተነሳ ላለው ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የሰጡት የሀዋሳ ከተማ ገበያ ልማት ቢሮ የስነልኬት ባለሙያው አቶ ሀብታሙ መኮንን ፤ ችግሩ መኖሩን አምነው ፤ ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ የተፈጠረው ክፍተት ለችግሩ ምክንያት እንደሆነ ገልጸው ነበር።
ችግሩም " #ወደፊት_ይቀረፋል " የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ ማመልከታቸው ይታወሳል።
@tikvahethiopia