#Update
በጂቡቲ ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈ ተሸከርካሪዎች በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ተጓጉዘው ወደ አገር ከገቡ በኋላ ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እንዲቆዩ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
ሚኒስቴሩ ፦
➡️ ለባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት
➡️ ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ የተሽከርካሪዎቹ አስመጪዎች በሚያቀርቡት መረጃ መሠረት፣ በየወቅቱ በጂቡቲ ወደብ የተከማቹ ተሽከርካሪዎችን መጠንና የቆይታ ጊዜ ከጂቡቲ ወደብ ባለሥልጣንና ከጉሙሩክ ኮሚሽን እንዲሰበሰብ አዟል፡፡
የባህር ትራንስፖርት የሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የወደብ ፎርማሊቲ አሟልቶ ተገቢ ክፍያ በመፈጸምና በድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ማከማቻ ሥፍራ በማዘጋጀት ተለዋጭ ውሳኔ እስኪሰጥ በራሱ ኃላፊነት እና በራሱ ወጪ ተሽከርካሪዎቹን እንዲያቆይ ተወስኗል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በሚሰጠው የደብዳቤ ዋስትና፣ ተሽከርካሪዎቹ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልባቸው እንዲጓጓዙ የትራንዚት ፈቃድ እንዲሰጥ የገንዘብ ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ በጂቡቲ ወደብ ተከማችተው የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እንዲጓጓዙ መወሰኑን አስታውቆ፣ በውሳኔው መሠረትም አስመጪዎች ንብረቶቻቸውን ወደ ደረቅ ወደብ እንዲያስገቡ አሳስቧል፡፡
ነዳጅ ለማስመጣት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ጫና ለመቀነስ በሚል በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ ውሳኔ መተላለፉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር በስፋት እንዲገቡ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መደረጉን መግለጹ አይዘነጋም፡፡
ሪፖርተር ጋዜጣ ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ምንጭ አገኘሁት ባለው መረጃ፣ አሁን ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ የተባሉት የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ከዕግዱ በፊት የተገዙ ናቸው።
በውጭ ምንዛሪና በፍራንኮ ቫሉታ ምክንያት በጂቡቲ ወደብ እንዲቆዩ የተደረጉ መሆናቸውን፣ ውሳኔው የተላለፈው ለተሽከርካሪዎቹ የሚከፈለው የወደብ ኪራይ እየጨመረ በመምጣቱ መሆኑ ተመላክቷል።
ተሸከርካሪዎቹ ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ፣ ሰነድ ያላቸው የተሽከርካሪ አስመጭዎች ድርጅቱ ያወጣውን የታክስና የመጓጓዣ ወጪ በመክፈል መረከብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የተሽከርካሪ አስመጪ " የአንድ ዓመት የወደብ ኪራይና የመጓጓዣ ወጪዎችን በመክፈል ተሽከርካሪዎቹን ቢረከቡ ገበያ ውስጥ ዋጋቸው ስለሚንር ሥጋት ገብቶናል " ብለዋል፡፡
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
" ከእንግዲህ በሽፍትነት / rebel በመሆን መንግሥትን መጣል አይደለም ፤ መነቅነቅ አይቻልም " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ከእንግዲህ በኃላ በሽፍትነት / rebels በሚመስል ነገር መንግስትን መጣል አይደለም መነቅነቅ እንኳን አይቻልም " አሉ።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ይህን ያሉት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ እና ታማኝ ግብር ከፋይ ባለሀብቶችን ሰብሰበው በመከሩበት ወቅት ነው።
ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮቹ ለጠ/ ሚኒስትሩ በዛ ያሉ ጥያቄዎችን ያቀረቡላቸው ሲሆን በየአካባቢው ከሚታየው ሁኔታ አንፃር #የሰላም ጉዳይ ከጥያቄዎቹ አንዱ ነበር።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው " ብለዋል።
ሰላምን በተመለከተ ያነሷቸው ሃሳቦች ሁሉ ጥሩ እንደሆነ ገልጸው " ሽማግሌ ነን እድሜያችን ልምዳችን ያላችሁ #ሸምግሉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
" እኔ የማረጋግጥላችሁ ግን በሽፍትነት / rebels በሚመስል ነገር ከእንግዲህ በኃላ የኢትዮጵያን መንግስት መጣል ሳይሆን መነቅነቅ አይቻልም። በጣም የተለያየን ነን ብቃታችን አይደለም የሚለያየው ያለን conviction ይለያያል እሱ ብር ነው የሚሰበስበው እኛ ስራ ነው የምንሰራውን እናውቃለን እያደረግን ያለነውን በቀላሉ የሚሆን አይመስለኝም " ሲሉ ተደምጠዋል።
" እነሱ ሰዎች ልብ ገዝተው ከመጡ በጣም በጣም በደስታ ነው የምንቀበለው ፤ እናተም ሞክሩ በሁሉም በምትችሉት መንገድ ሞክሩ " ብለዋል።
@tikvahethiopia
#SamiTech
አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech
በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ
አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114
https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
" 271 ዜጎችን ከእገታ አስለቅቄያለሁ " - ኮማንድ ፖስት
ላለፉት 25 ቀናት በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ውስጥ በታጣቂዎች እገታ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው የቀን ሰራተኞች ከእገታ ተለቀው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የጎጃም ኮማንድ ፖስት አንድ ኮር ፤ ታግተው የነበሩ 271 ዜጎችን ማስለቀቁን አሳውቋል።
ኮማንድ ፖስቱ በአራት አውቶብስ ተጭነው ሲጓዙ የነበሩት 273 ዜጎች እንደሆኑ እና " በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ እና በኤሊያስ ከተማ መካከል ሲደርሱ ነው በጽንፈኛኞች ታግተዋል " ብሏል።
ታጣቂ ቡድኑ ከ3 ሰዓት በላይ ወደማይታወቅ ቦታ አስገድዶ ከወሰዳቸው በኋላ ሁለቱን #በመረሸን ለቀናት ደብቆ ሲያሰቃያቸው መቆየቱን ገልጿል።
በኃላም " ኮሩ ወደ አካባቢው በመሠማራት ከበባ በማድረግ ምቹ ሁኔታ ሲጠባበቅ መከበቡን የተረዳው ፅንፈኛ ለቋቸው ሊሸሽ ችላል " ሲል አመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋርዱላ ዞን ባገኘው መረጃ በእገታ ላይ የነበሩና ከዞኑ ተመልምለው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ህዳሴው ግድብ ሲያቀኑ የነበሩ 246 ሰራተኞች ትላንት ምሽት ተለቀው በሰላም አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዞኑ ለሰራተኞቹ ከእገታ መለቀቅ ላለፉት ቀናት የፌዴራል መንግሥት ፣ የአማራ ክልል በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ቀይ መስቀል ትብብር ማድረጋቸውን እና የባለሃብቶች ጥረት እንዳለበትም ጠቁሟል።
የኧሌ ዞንም ፤ " ለጉልበት ስራ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሲሄዱ በአማራ ክልል በታጣቂዎች የታገቱ ዜጎች ተለቀዋል " ብሏል።
ዞኑ ፤ መንግሥት እና ባለሃብቱ አድርገዋል ባለው ጥረት ነው ታጋቾች ነፃ የወጡት።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል አማካኝነትም ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ነው ያመለከተው።
ከዞኑ ተመልምለው የሄዱት 38 የቀን ሰራተኞች ናቸው።
ከላይ ያሉት የሰራተኞች ቁጥር ድምር 284 ሲሆን ቀጣሪው ድርጅቱ ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ግን ይህን ቁጥር አይቀበለውም ታግተው የነበሩትም 272 ናቸው ነው የሚለው። ለዚህም በቂ የሰነድ ማስረጃ እንዳለው ይገልጻል።
ላለፉት ቀናት ወደ ስፍራው ከፍተኛ የድርጅቱን ኃላፊ በመላክ ሰራተኞቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ሳይሆኑ እንዲለቀቁ ጥረት ሲያደርግ የቆየው ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ታጣቂዎቹ በድምሩ 6 ሚሊዮን ብር ወስደው ልጆቹን እንደለቀቋቸው ገልጿል።
መጀመሪያ 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ በሶስት ሰው ስም ከተከፈለ በኃላ ሰራተኞቹ ተለቀው በ4 መኪና ጉዞ ጀምረው ለዋናው አስፓልት ትንሽ ሲቀራቸው አማኑኤል አቅራቢያ ሌላ የቡድኑ ክንፍ ይዟቸው 6 ሚሊዮን ብር ሲጠይቅ እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል።
በኃላ ግን ለእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር በመክፈል በድምሩ አጠቃላይ በ6 ሚሊዮን ብር እንዲለቀቁ መደረጉን ተናግሯል።
እንደድርጅቱ መረጀ ከተለቀቁት 271 ሰዎች አንዱ ሾልኮ የጠፋ ሲሆን በኃላም በስልክ ከቤተሰቦቹ ጋር መነጋገሩ ተገልጿል።
@tikvahethiopia
#Update
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ በፍቃዳቸው እንዲመልሱ ያስመቀጠው የመጨረሻ ቀን ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 14 ያበቃል።
ባንኩ ሰጥቶ የነበረው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው።
ገንዘቡን በአቅራቢያ ባለው ቅርንጫፍ ወይም በዲጂታል መንገድ ቀድሞ ገንዘቡ ወጪ ወደተደረገበት የባንኩ ሂሳብ ማስገባት ይቻል ነው የተባለው።
ዛሬ በሚጠናቀቀው የመጨረሻ ቀን የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ ደረጃ በደረጃና ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉን ባንኩ አሳውቋል።
ገንዘቡን የወሰዱ እንዲሁም ያዘዋወሩትን ሰዎች ስምና ፎቶግራፋቸውን በሚዲያ ለህዝብ እንደሚያሰራጭም አስጠንቅቋል።
አርብ ለሊት ከባንኩ ሲወጣና ሲዘዋወር ያደረው ገንዘብ በትክክል ምን ያህል እንደሆነ በይፋ ባይገለጽም ባንኩ ግን የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱ ሁሉ ገንዘቡን እንዲመልሱ እያስጠነቀቀ ነው።
" አሶሼትድ ፕሬስ " ባንኩ የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት የተወሰደበት ገንዘብ 2.4 ቢሊዮን ብር (40 ሚሊዮን ዶላር) መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ግን ፤ " የኦዲት ምርመራው ባለመጠናቀቁ የተወሰደውን ገንዘብ መጠን አሁን ላይ አይታወቀም " ብለዋል።
አጠቃላይ ኦዲት ተደርጎ ስላላቀም እስካሁን ምን ያህል እንደተመለሰ የሚታወቅ ነገር የለም።
@tikvahethiopia
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች ጥሪ አደረገ።
በዚህም በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ Freshman ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስትከታትለው ቆይተው የማለፊያ ውጤት በማምጣት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደበ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ከመጋቢት 26 እስከ 28/2016 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታውም ፦
➤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ
➤ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ አባይ ግቢ ነው ተብሏል።
በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን አቋርጠው ለአንደኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላቸውና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞሉ ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ያወጣው ጥሪ በማካካሻ መርሐ ግብር (Remedial Program) በ2016 ዓ/ም አዲስ የተመደቤ ተማሪዎችን #አይመለከትም ተብሏል።
Via @tikvahuniversity
#Update
" ምዕመናን #ክርስቲያናዊ_አለባበስ ለብሳችሁ እንድትገኙ እና የአቅማችሁን ያህል እድትለግሱ ጥሪ እናቀርባለን " - ማህበረ ቅዱሳን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ነገ እሁድ ከቀኑ 7:00 ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል።
ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
የመግቢያ ትኬቶች በ100 ብር እየተሸጡ ሲሆን ትኬቶቹን ፦
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ማግኘት ይቻላል ተብሏል።
ነገ በመግቢያ በር ላይም ትኬት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።
ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች / ምዕመናን ነገ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲሄዱ ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዲለብሱ እና የአቅማቸውን ያህል እንዲለግሱ ጥሪ ቀርቧል።
@tikvahethiopia
" ከእገታ ለማስለቀቅ 300 ሺህ ብር ክፈሉ ተብለን ብንከፍልም ልጃችን አልተለቀቀም፣ ያለበትንም ሁኔታ አናውቅም ፤ የድርጊቱ አቀናባሪ ሀገር ለቆ ሊወጣ እንደሆነ ሰምተናል " - አባት
ከወራት በፊት ማለትም ነሀሴ 27 ቀን 2015 ዓ/ም በታጣቂዎች የታገተ ልጃቸዉን ለማስለቀቅ 300 ሺህ ብር በሰው በሰዉ የከፈሉት ቤተሰቦች ትእዛዙን ቢፈጹሙም ታጋቹ ግን ዛሬም ሊለቀቅ አልቻለም ብለዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪነታቸው በሀዋሳ የሆነው አቶ ፍቅሬ አበራ የተባሉ አባት ፤ በወቅቱ በመተሀራ ከተማ የሆቴል ማናጀር የነበረዉ ልጃቸዉ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ በሆቴሉ ይሰራ የነበረዉን ልጅ ስህተት መስራቱን ተከትሎ የገንዘብ ቅጣት መቅጣቱን ተከትሎ ልጃቸው መተሀራ ከሚገኘዉ የስራ ቦታዉ ውስጥ ካለ ማረፊያ እንዲታፈን መድረጉን አመልክተዋል።
ከዛም 300 ሺህ ብር ለማስለቀቂያ እንዲከፍል መደረጉን ገልጸዋል።
አባት ፤ " በግል የስራ ጸብ ምክኒያት ባልደረባውን ለኦነግ ሸኔ አሳልፎ የሰጠዉ ግለሰብ ብሩን ብንልክም ልጃችን እንዳይወጣ አድርጎ ' ሰራሁለት ' ሲል መደመጡን " የሚገልጹት አባት ለዚህ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ በእጄ ላይ አለ ብለዋል።
ነገር ግን አቤቱታቸውን ሰምቶ መረጃቸውንም መርምሮ ወንጀለኛዉን አካል የሚይዝላቸው የህግ አካል እንዳጡ ተናግረዋል።
" አሁን ላይ ልጄን ለታጣቂዎች አሳልፎ የሰጠው ግለሰብ ከሀገር ለመዉጣት ፕሮሰስ ላይ እንደሆነ ሰምተናል " ያሉት አባት " የሚመለከተዉ አካል እጄ ላይ ያለዉን መረጃ ተጠቅሞ ፍትህ ያወርድልኝ ዘንድ እጠይቃለሁ " ሲሉ ተማጽነዋል።
አሁን ላይ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋናው ቢሮ ለማሳወቅ እንደተዘጋጁ ገልጸው የልጃቸውን አሁናዊ ሁኔታ ካለማወቃችን በላይ " ለዚህ ሁሉ ሀዘን የዳረገን አካል አለመያዙም አሳምሞናል " ብለዋል።
መረጃው የተዘጋጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#EthioElectronics
ኢትዮ ኤሌክትሮኒክስ ጥራታቸውን የጠበቁ እቃዎች ከዋስትና ጋር እኛጋር ያገኛሉ አዲሱን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀላሉ /channel/ethioelectronicsnew
አድራሻችን፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ የሱቅ ቁጥር 321ሱቃችን 321ቁጥር መሆኑን እና የራሳችን ሎጎ መኖሩን ያረጋግጡ እናመሰግናለን። ጥራት መለያችን ነው✌️
ለበለጠረጃ፦ ☎️በ0911047373 @Ethio2101Fitsum 0931698889 @Ethio21fitum ይደውሉልን።
#ሞስኮ
ዛሬ አርብ ታጣቂዎች በሩስያ ፣ ሞስኮ ወደሚገኝ ህዝብ ወዳለበት ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በመግባት አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ በመተኮስ በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።
የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ።
አንዳንድ ሪፖርቶች እስካሁን ድረስ ባለው በትንሹ 40 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።
በአዳራሹ ውስጥ ሰዎች ተሰባስበው የነበረው ለአንድ የሙዚቃ ድግስ ነበር።
ታጣቂዎቹ ቦንብም ሲወረውሩ ነበር የተባለ ሲሆን አዳራሹ ያለበት ህንፃ በእሳት ሲያያዝ ታይቷል።
የሩሲያ ሀገር ውስጥ ስለላ አገልግሎት ከጥቃቱ በኋላ #ሞት እና #የአካል_ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል ፤ የሟቾች ቁጥርን ግን አልገለጸም።
የሩስያ ጤና ሚኒስቴር የተጎዱ ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አሳውቋል።
በስፍራው የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ፥ ታጣቂዎቹ አውቶማቲክ መሳሪያ እየተኮሱ መግባታቸውን ፤ የእጅ ቦምብ / ተቀጣጣይ ቦምብ ሲወረውሩም እንደነበር ገልጿል።
ጋዜጠኛው ፤ " በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ለ15 እና 20 ደቂቃዎች እራሳቸውን ከጥይት ለመከላከል ወለል ላይ ተኝንተው እንደነበር በኃላ ሁኔታው ጋብ ሲል እና የፀጥታ ኃይል ሲመጣ መውጣታቸውን አስረድቷል።
የሩስያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ድርጊቱን " የሽብር ተግባር " ብሎታል።
እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወይም ሩስያ ይህ አካል ነው ያለችው የለም።
ቪድዮ ፦ ከሩስያ የማህበራዊ ሚዲያዎች
@tikvahethiopia
" እኔ የማውቃቸው ብቻ 6 ሰዎች ተገድለዋል " - የዕድሜ ባለፀጋ
በአጣዬ ከተማ እና በሰንበቴ ዙሪያ የታጠቁ ኃይሎች ሰሞኑን ከፈተቱት በተባለ ተኩስ ንጹሐን መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አንድ የአካባቢው ነዋሪ የእድሜ ባለፀጋ ፤ “እኔ የማውቃቸው ብቻ 6 ሰዎች ተገድለዋል። ወደ ደብረ ብርሃን የተላከ ቁስለኛም አለ ” ብለዋል።
ይህ መረጃ የአንድ አካባቢ ብቻ እንደሆነ ነው ያስገነዘቡት።
“ ካራ ለጉማ አዲስ አበባ መርካቶን ነው የሚመስለው ከአጣዬ በመጡ ተፈናቃዮች። ከዛፍ ስር፣ ት/ቤት ነው የተጠለሉት ” ብለዋል።
" አጣዬ 01 ቀበሌ ዘረፋ ነበር ፤ ሰንበቴም በተመሳሳይ ፤ አጣዬ ከተማ በጣም ወድሟል” ሲሉ አስረድተዋል።
ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አንድ የሰንበቴ ነዋሪ በበኩላቸው ሰሞኑን የተኩስ ጥቃት እንደነበር ተናግረው “ የኦሮሞ ተወላጆችም በ ' ፋኖ ' ታጣቂዎች ተገድለዋል። በእኛ አካባቢ ከ5 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ” ሲሉ ተናገረዋል።
“ በተለይ ከሳምንታት ጀምሮ ግድያ፣ ቃጠሎ ነው የሚስተዋለው። በርካታ ንጹሐን ቆስለዋል” ሲሉ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ " ህዝቡ አለቀ፣ ወደ ማን አቤት እንበል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ ከቀናት በፊት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፣ " ሰውም አልቋል፣ ሚሊሻውም የሚችለውን ያህል ሞከረ አለቀ " ብለው ለጥቃቱ " ሸኔ" ን ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ ለጥቃቱ " ፋኖ " ን ተጠያቂ ሲያደርግ ተስተውሏል።
ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መካሻው፣ ስልክ ባያነሱም “ ስብሰባ ላይ ሆኘ ነው ” ያሉ ሲሆን፣ የሚመቻቸውን ወቅት ስንጠይቃቸው “ አሚኮ ላይ መግለጫ ስለሰጠን ከዛ ማግኘት ይችላሉ ” ከማለት ውጪ በድጋሚ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
በሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አጎራባች ስፍራዎች በሚገኙ የአማራና የኦሮሚያ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ነው የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በበኩላቸው፣ “ ስብሰባ ላይ ነኝ ” ብለዋል።
የኢፌደሪ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ፣ የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ጸጥታና ኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች በተመሳሳይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
በማንኛውም ሰዓት ማብራሪያ ከተገኘ ይቀርባል።
#TikvahFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
#ደሴ
“ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ” - ደሴ ሆስፒታል
በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፣ በሆስፒታሉ በኩል የሚቃጠለው ቆሻሻ ወደ ቤታቸው እየገባ እንደተቸገሩ ፣ መጀመሪያ ዝም ብሎ ሜዳ ላይ ሲቃጠል እንደነበር ፣ ዘመናዊ ማስወገጃ ከተሰራ በኋላ ግን ሙሉ ወደ ግቢዎች ውስጥ እንደሚገባ ፣ በተደጋጋሚ ለችግሩ መፍትሄ ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።
መንደሮቹ በተለይም ህፃናት ልጆች ያሉባቸው እንደሆኑ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፣ አሁን ባሉበት ሁኔታ ከመኖር ለቤታቸው የሚመጥን ካሳ ከተከፈላቸው ቦታውን ለቀው መሄድም እንደሚሻላቸው ገልጸዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት #ቪዲዮም በቃጠሎው ወቅት ቆሻሻው ወደ ቤት እንደሚገባ ያስገነዝባል።
ነዋሪዎቹ ላነሱት ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሆስፒታሉ ባለስልጣን ፤ “ አሁን ያ ሁሉ አልፎ በዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ፣ ሕጋዊ ማስወገጃ ተሰርቶለት፣ ድሮ ከነበረው ችግር የወጣበት ቀን ነው ” ብለው፣ “ ከነበረው ችግር ወጣ ነው እንጂ ችግሩ ብሶ ቀጥሏል አልልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ በእርግጥ #ከሕዝብ_መኖሪያ ሊወጣ ተቋሙ ግድ ነው። አሁን ግን ያለው የቆሻሻ አወጋገድ በአዎሮፓ ህብረት እና በፈረንሳይ መንግሥት ተደግፎ Almost ሰባት ወሩ ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ ዘመናዊ የሆነ፣ ስታንዳርዱን የጠበቀ ማቃጠያ ተሰርቶለታል ” ነው ያሉት።
እኚሁ ባለስልጣን አክለውም ፣ “ ግን ከሰው መሀል ነው። ያ በሕጋዊ መንገድ ሲቃጠል እንደድሮው እንኳ ብናኝ እንኳ አያርፍባቸውም። ጭሱ ግን ሊሸት ይችላል ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ዘመናዊ ማቀጠያ ቢሰራም ቆሻሻው እየገባ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ባቀረቡት መሠረት ማብራሪያ እንዲሰጡ ለባለስልጣኗ ጥያቄ አቅርቧል።
እሳቸውም ፤ “ ጭሱ ታካሚንም ይረብሻል፣ ከሕዝብ መሀል መሆናችን ነውና ዋናው ትልቁ ችግር። ጭሱማ እንዴት ይቀራል ? ተኔሬተር ነውኮ ግን የሚጨሰው ” ነው ያሉት።
“ እነዚህ አሁን የሚጨስባቸው ጠቅላላ በካዳስከርና በከተማ ማስተር ፕላን የሆስፒታሉ ቦታዎች ናቸው ” ብለው ፣ “ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ፣ እንጂ አሁን ላይ እጅግ የተሻለ ነገር ነው ያለው ” ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም፣ “ ለምን ብትል በጣም ብዙ ተሰቃይተው አልፈዋል፣ ከዚህ አሁን ካለው በላይ። ግን ከጎኑ ያለው ሰው አይሸተውም አልልህም። ግን ከፍታው ከአራት ሜትር በላይ ሆኖ፣ ከአምስት፣ ከስድስት ሜትር በላይ ከፍ ብሎ የሚጨስ የተሰራበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ” ብለዋል።
“ አሁን ላይ ራሱ ሞዲፋይ አለው ተነሬተሩ። የተሰራው ማቃጠያ #ሞዲፋይ አድርገው አሁንም እዛው ላይ የሰሩት ከፍታውን ካለው ጨምረው ሊሰሩት እያሰቡ ነው። በቅርብ ቀንም ይሰራል። ሁለተኛ ደግሞ ከውጪ ያልገባ ጭስ አልባ ማቃጠያ ማሽን አለን። በቅርብ ጊዜ (ከወር በኋላ) ይደርሳል። ብዙ ነገሮችን የሚቀንስልን ” ሲሉም ተናግረዋል።
ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎች ግን ፤ በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ በየዕለቱ ስቃያቸውን እያዩ እንደሆነ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ የትንንሽ ልጆቻቸው ጤና አደጋ ላይ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።
#TikvahFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ " በግል ምክንያት " በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ለቀዋል።
ኮሚሽኑ የአምባሳደር ተሾመን ከኃላፊነር መልቀቅ በተመለከተ ፤ " በግል ጉዳያቸዉ ምክንያት በኮሚሽነርነት ላለመቀጠል ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ ከመጋቢት 3/2016 ዓ/ም ጀምሮ ለቀዋል " ብሏል።
በኮሚሽነሩ ምትክ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የውጭ ፖሊስ አማካሪ አቶ ተመስገን ጥላሁን መተካታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ኮሚሽኑን እንዲመሩ የተሾሙት ባለፈው ዓመት ጥር 2015 ዓ.ም. ነበር። ያለፈውን 1 ዓመት የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማደራጀት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከለጋሽ አካላት ለማሰባሰብ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።
በኢህአዴግ ዘመን ጉምቱ ከሚባሉት ባለስልጣን አንዱ የነበሩት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ፤ ከ1997 እስከ 2002 ዓ.ም. ድረስ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፤ ከዚህ ባለፈ የወጣቶች፣ ባህል እና ስፖርት እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ፣ በኃላም በዲፕሎማትነት ሰርተዋል።
@tikvahethiopia
" ' ሳር ቤት አካባቢ በአውቶብስ ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ ' እየተባለ በቲክቶክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ ነው " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።
ፖሊስ ፤ የከተማው ሰላም መሆን እንቅልፍ የነሳቸው አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች የተለያዩ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ስጋት ላይ ለመጣል በቻሉት መጠን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።
እነዚህ አካላት ህዝቡ ደህንነት እንዳይሰማውና ከተማውም ሰላም አንደሌለው ለማሳየት ብዙ ሞክረው አልሳካ ሲላቸው የፈጠራ ሀሰተኛ ወሬ በማህበራዊ ሚዲያ ይዘው መጥተዋል ሲል ገልጿል።
ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ጥቃት ለመፈፅም በህቡዕ የተደራጀ ቡድን እንዳለ በማስመሰል ሳር ቤት አካባቢ አውቶቡስ ላይ #ቦንብ_ማፈንዳቱን የሚገልፅ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩ ይገኛሉ ብሏል።
" ይህ ከእውነታ የራቀ በአዲስ አበባ ሰላም የለም ለማስባል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ ነው " ያለው ፖሊው ሁሉም የከተማው ነዋሪ ይህን ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።
ፖሊስ ፤ የከተማዋን ሰላም የማይፈልጉ አካላት የሌት ተቀን ህልማቸውን " ቲክ ቶክ /#TikTok " በተባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየገለፁ ናቸው ብሎ " በአዲስ አበባ ያለው ሰላም አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀጥታ ስራውን እያከናወነ ይገኛል " ሲል ገልጿል።
ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያዳብር እንደሚገባ አሳስቧል።
ሀሰተኛ መረጃን በሚያሰራጩ አካላት ላይም በህግ አግባብ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል።
@tikvahethiopia
#ቤቲንግ
➡️ " ቤቲንግ ቤቶች ዳግም #እንዳይከፈቱ ሕብረተሰቡ አሳስቦናል " - የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
➡️ " ሁሉንም ቤቶች በጅምላ መፈረጅ ትክክል አይደለም። ህጉን ተከትለው የሚሰሩና ብዙ ሰራተኛ ያላቸው ቤቲንግ ቤቶች አሉ " - የቤቲንግ ቤት ባለቤቶች
በአዲስ አበባ ከተማ በቤቲንግ ቤቶች እንቅስቃሴ ዙሪያ ሲካሄድ በነበረ የዳሰሳ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ ተሰምቷል።
ውይይቱ የተደረገው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኃላፊዎች ወይም ተወካዮች በተገኙበት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተቋቋመው ግብረሃይል አማካይነት ባለፈው ጊዜ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ የተገኙ የቤቲንግ ቤቶች በጥናት ተመስርቶ እንዲታሸጉ መደረጋቸውን ገልጿል።
በዚህም፦
1ኛ. አብዛኛው ቤቲንግ ቤቶች በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ላይ በመሆናቸው፣
2ኛ. የብሔራዊ ሎቶሪ ባወጣውን ደንብ መሠረት ዕድሜያቸው ከ21ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ገብተው ሲጫወቱ በመገኘታቸው፣
3ኛ. በቤቶቹ ውስጥ አዋኪ ድርጊቶች ማለትም፦ ጫት መቃም፣ አልኮል መጠጦች መጠጣት...ወዘተ ሲፈፀምባቸው በመገኘታቸው፣
4ኛ. ያለንግድ ፈቃድ ሲሰሩ በመገኘታቸው፣
5ኛ. የቡድን ፀብ የተከሰተባቸው መገኘታቸው ለመዘጋታቸው ምክንያት መሆኑን አስረድቷል።
ቢሮው፤ " ሕብረተሰቡም በቤቲንግ ቤቶች ደስተኛ እንዳልሆነ ተረድተናል " ብሏል።
ቢሮው ፤ ከዘርፉ ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ አመዝኖ እንደሚታይ ፤ ቤቲንግ ቤቶች ዳግም እንዳይከፈቱ ሕብረተሰቡም አሳስቦናል ሲል አሳውቋል።
በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱ ምክንያቶች የታሸጉ የቤቲንግ ቤቶች ፦
1ኛ. ለቤቲንግ ቤት ያከራዩ የቤት ባለቤቶች የንግድ ዘርፉን ቀይረው ከመጡ፣
2ኛ. " አገልግሎቱን አንፈልግም ካሁን ቀደም ሳናውቅ ስለገባንበት ከዚህ በኋላ አንሠራም " ብለው ማረጋገጫ ለሚሠጡና ቤቶቹ ተከፍተው ለሌላ አገልግሎት እንዲውሉ ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል ሲል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።
በሌላ በኩል፤ በአዲስ አበባ ስፖርት ውርርድ /ቤቲንግ/ በመንግስት ከታሸገ 3 ወር ሆኖታል የሚሉ በዘርፉ ላይ ያሉ አካላት ፤ ትክክለኛ መረጃ እያገኙ እንዳልሆነና በየ ወረዳው የሚነገራቸው የተለያየ ሃሳብ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
" ዘርፍ ቀይሩ ወይንም ዕቃ አውጡ እየተባልን ነው ፤ ብሄራዊ ሎተሪ እንደሚከፍትልን እና ዝግጅት እንድናደርግ ብሎም እድሳት አድርጎ ፍቃዳችንን ከሰጠ በኋላ ነው እንዲ የተጉላላነው " ብለዋል።
" በስራችን ብዙ ሰራተኞችን የያዝን እና ከፍተኛ ግብር ለሀገራችን የምናስገባን ድርጅቶች ማንገላታት አግባብ አይደለም " የሚሉት የዘርፉ ባለቤቶች " ስራ በሌለበት ወቅት ብዙ ስራ አጦች በከተማችን ባሉበት ሁኔታ ተጨማሪ ስራ አጦች እንድንሆን እየተደረግን ነው " በማለት ቅሬታ አቅርበዋል።
" ቤቲንግ መስራት ሲገባቸው አለአግባብ ከህግ ውጪ የሚንቀሳቀሱ ካሉ በህግ መጠየቅ እንጂ ሁሉንም በአንድ መፈረጅ አይገባም " ብለዋል።
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ቤቲንግ ቤቶች እስከ ወዲያኛው እንዲዘጉ ጫና እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
የዘርፉ ባለቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " በአጠቃላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተደርጎ ከእምነት ተቋማት ፣ ከትምህርት ቤት መራቅ ያለበትን ርቀት ተከትሎ እድሜ ከ21 አመት በላይ ብቻ እንዲጠቀም ተደርጎ ቢቀጥል ለሀገርም ለህዝብም ጥቅም ይኖረዋል " ብለዋል።
@tikvahethiopia
" በቅርቡ 5 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ በአንድ ባንክ ተልኮ ይዘናል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሁለት ቦታ (ከመንግስት ጋር እና ጫካ መንግስትን ለመጣል ከሚታገሉ ጋር) የሚጫወቱ አንዳንድ ባለሃብቶች አሉ ሲሉ ተናገሩ።
ይህን የተናገሩት ከታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት ነው።
ባለሃብቶቹ በምክክር መድረኩ ስለ #ሰላም ጉዳይ ያነሱ ሲሆን ጠ/ሚስትሩም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " ሰላም ተብሏል እውነት ነው አስፈላጊ ነው " ብለዋል።
" ድሮ ሀብታሞች አዝማሪ ቀጥረው ያጫውቱ ፣ ይገጠምላቸው ነበር ድሃው እራት እየበላ በግጥም ይተባበራል ፤ አሁን ድገሞ ሀብታሞች #ዩትዩበር ይቀጥራሉ ድሃው በላይክ እና ሼር ይተባበራቸዋል እነዚህ ሰዎች እንደፈለጉ ሲያተረማምሱ ይውላሉ " ሲሉ ተናግረዋል።
" ዩትዩበሮቹን ባንቀልብ ወደ ስራ ወደ ኢንድስትሪ ይገቡ ነበር ፤ ለዚህ አስተዋጽኦአችን ምንድነው ብሎ ስራ ፈጣሪው ባለሃብቱ ግብር ከፋዩ ቢያስብ ጥሩ ነው " ብለዋል።
" እኛ እና እናተ ከተባበርን ሙስና ይቀንሳል፣ አገልግሎት ሊሻሻል ይችላል " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " ጫካ ላሉ ሰዎች ብር ባለመላክ ብትተባበሩም እንዲሁ ይቀንሳል " ሲሉ ተናግረዋል።
" አንዳንድ በተለያየ ቦታ ሚታገሉን ሰዎች እስከ 10 ቤት በአባቱ፣ በወንድሙ ያለው ሰው አለ፤ በረሃ ታጋይ አታጋይ የሚባል ሰው። በጣም ሃብታሞች ናቸው እዛ ተቀምጠው መነገድ የሚቻል ከሆነ ሰላም ጋር ምን አመጣቸው ሰላም ከመጣ ንግድ የለም ማለት ነው " ብለዋል።
" ቤት አላቸው፣ በተለያየ አካውንት ባንክ ውስጥ ገንዘብ አላቸው በቅርቡ እንኳን 5 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ መጥቶ ይዘናል በአንድ #ባንክ ፣ ከፍተኛ ብር ይንቀሳቀሳል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሃብታሞች ማወቅ ፣ መብለጥ ፣ መላቅ ስለሚመስላቸው እዚህም ይጫወታሉ እዚያም ይጫወታሉ፤ እዚህ እኛን ' የተከበራችሁ ' ይላሉ እዛ ሄደው ' እንደናተ ጀግና የለም ' ይላሉ በዚህ ሰዎቹ እየተታለሉ እንደ ስራ መስክ ይዘውት ሀገር ያምሳሉ ወጣቶች ያልቃሉ ... ችግር አለ " ብለዋል።
" እናተም ልክ የድሃ ቤት እንደምትገነቡት ሁሉ በዚህም በኩል ችግሮች እንዲፈቱ ከልባችሁ ብታግዙ ያለው ነገር ይቀንሳል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ምንም እንኳን ስም ባይጠቅሱም ከሀገር የወጡ ባለሃብቶች እንዳሉ ገልጸዋል።
" የሆኑ የሆኑ ሰዎች ጠፍተው ይሄዳሉ ከዚህ። ከቆየ በኃላ ስንሰማ ለምንድነው የጠፋው ሚስተር X ጥሩት ወደሀገሩ ይመለስ ሲባል ሚስተር X አይፈልግም ያደረጋቸው ትራዛክሽኖች ሁሉ ይታወቃሉ ብሎ ስለሚያስብ አይፈልግም " ብለዋል።
" እኛ እንደ መንግስት አንድም ባለሃብት ከሆነ ክልል ጋር ግጭት ስላለ ከሀገር ውጣ ያልነው የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።
@tikvahethiopia
#EthioElectronics
ኢትዮ ኤሌክትሮኒክስ ጥራታቸውን የጠበቁ እቃዎች ከዋስትና ጋር እኛጋር ያገኛሉ አዲሱን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀላሉ /channel/ethioelectronicsnew
አድራሻችን፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ የሱቅ ቁጥር 321ሱቃችን 321ቁጥር መሆኑን እና የራሳችን ሎጎ መኖሩን ያረጋግጡ እናመሰግናለን። ጥራት መለያችን ነው✌️
ለበለጠረጃ፦ ☎️በ0911047373 @Ethio2101Fitsum 0931698889 @Ethio21fitum ይደውሉልን።
#ሩስያ
" ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው " - ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከትላንትና የሽብር ጥቃት በኃላ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ነገ መጋቢት 15 በመላው ሩሲያ የሀዘን ቀን እንደሚሆን ተናግረዋል። " የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ዜጎቻችን ይዘከሩበታል " ብለዋል።
አሁን ላይ በጥቃቱ ላይ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጠር ስር መዋላቸውን ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ፤ ሌላ የጅምላ ግድያ እንዳይፈጸም የጸጥታ ኃሎች ሰፊ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።
" በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፈ እና ያገዛቸው የትኛውም አካል ለህግ ይቅርባል " ሲሉ ዝተዋል።
ፕሬዜዳንቱ በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ 4 ወንጀለኞች ወደ ዩክሬን ሊያመልጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።
" አሁን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያመላክተው በዩክሬን በኩል ሽብርተኞች ለማስመለጥ የሚያስችል መንገድ በድንበር በኩል ተዘጋጅቶ እንደነበረ ነው " ብለዋል።
" ሩሲያ በዚህ የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሁሉንም አካላት ለይታ ትቀጣለች " ያሉት ፑቲን፤ " ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው፤ ከዚህ ውጪ ምንም አማራጭ እና ተስፋ የላቸውም " ሲሉ ዝተዋል። #አልአይን
@tikvahethiopia
#Update
➡ " ታጋቾቹ ተለቀው በሰላም #አዲስ_አበባ ገብተዋል " - የጋርዱላ ዞን አስተዳደር
➡ " ለማስለቀቂያ መጀመሪያ ከከፈልነው 4 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በእያንዳንዱ መኪና (4 መኪናዎች) 500 ሺህ ብር ከፍለናል " - ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን
➡ " አንድም ገንዘብ አልተቀበልንም " - ፋኖ ማርሸት ፀሀይ
በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ታግተዋል የተባሉ የቀን ሰራተኞች ከእገታው ተለቀው በሰላም አዲስ አበባ መግባታቸው ተነግሯል።
የጋርዱላ ዞን አስተዳደር ፤ " በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሐይቅ የሚያርፍበት ስፍራን ለመመንጠር ከዞኑ 246 ተመልምለው ሲጓዙ የነበሩና በአማራ ክልል የታገቱ ሠላማዊ ዜግች ተለቀዋል " ብሏል።
ታጋቾቹ ትላትን ምሽት መለቀቃቸውን ያሳወቀው የዞኑ አስተዳደር ዛሬ በሠላም ተጉዘው አዲስ አበባ መድረሳቸውን አሳውቋል።
ወደ ህዳሴው ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ ሲሄዱ የታገቱት 272 ሰራተኞች እንደሆኑ ገልጾ የነበረው ቀጣሪ ድርጅቱ ኒኮቲካ ኮንስትራሽን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል ታጋቾች መለቀቃቸውን አረጋግጧል።
የተለቀቁት ግን 271 ሰራተኞች እንደሆኑና 1 ሰው ሾልኮ መጥፋቱን ነገር ግን ከቤተሰብ ጋር መደዋወሉን አመልክቷል።
ድርጅቱ በመጀመሪያ #ለማስለቀቂያ 4 ሚሊዮን ብር ከፍሎ እንደነበር ተለቀው ሲሄዱ አማኑኤል አካባቢ ድጋሚ በሌላ የቡድኑ ክንፍ ተይዘው ለማስለቀቂያ 6 ሚሊዮን ብር መጠየቁን በኃልም በእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር ተከፍሎ ሰራተኞቹ መለቃቃቸውን አሳውቋል።
' የአማራ ፋኖ ምስራቅ ጎጃም ቃል አቀባይ ' ፋኖ ማርሸት ፀሀይ " ' ሰራተኞች ' የተባሉት ወደ ብርሸለቆ ሲያመሩ የነበሩ ምልምል ወታደሮች ናቸው ፤ ይመሯቸው የነበሩትም ማዕረግ ያላቸው ወታደሮች ነበሩ ፤ ምርኮኞች እንጂ ታጋቾች አይደሉም፤ ቁጥራቸውም 246 ነው " ብለው ነበር።
ትላንትና በሰጡት ቃል ፤ የግለሰቦቹን መለቀቀ አረጋግጠው ፤ " የተለቀቁት 240 ናቸው። አንድም ብር አልተቀበልንም " ብለዋል።
"ልጆቹን እንዲረከበን የቀይ መስቀል ማህበረን ጠይቀን ቀርቷል ፤ ሊቀበለንም አልቻለም። እኛ ከልጆቹ ጋር ባደረግነው ስምምነት የትራንስፖርት ወጪያቸውን ብንሸፍን በቀጥታ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚሄዱ ስለተነጋገርን እነሱም ስላመኑበት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሸኝተናቸዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም ፤ " ፋኖ ገንዘብ አይቀበልም። ገንዘብ መቀበል ብንፈልግ ኖሮ እኮ ከሁሉም እንቀበል ነበር። ከአንዱ ተቀብለን ከአንዱ የማንቀበልበት ምክንያት የለም። በስነስርዓት ለመከላከያ ስልጠና የሚመጡ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች ገንዘብ ተጠይቀናል ወደ ሚል ስም ማጥፋት ገብተዋል ምክንያቱም አላማቸው ስለተስተጓጎለ " ብለዋል።
" ገንዘብ ከማንም አልጠየቅንም " የሚሉት ማርሸት " እንደውም ለተሽከርካሪ ነዳጅ ሞልተናል፣ የሹፌሮች አበል ሰጥተናል እውነቱ ይሄ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ግን ታግተው የነበሩ ሰራተኞች ለማስቅለቅ በቅድሚያ 4 ሚሊያን ብር በሶስት ሰዎች ስም የገባበት ማስረጃ በእጁ እንዳለና በቀመጠልም በእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር በድምሩ 6 ሚሊዮን ብር መክፈሉን አሳውቋል።
የጋርዱላ ዞን እንዳሳወቀው 246 ታጋቾች ተለቀው ዛሬ አዲስ አበባ ደርሰዋል። ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች፣ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ የአማራ ክልል የመንግስት አካላት በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች የሃይማኖት ተቋማት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር ትልቅ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ ከጋርዱላ ዞን ኮሚኒኬሽን እንዲሁም ከቪኦኤ ሬድዮ ማግኘቱን ይገልጻል።
@tikvahethiopia
#Update
በትግራይ በእስር ላይ የነበሩ ተጨማሪ 100 የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እንደተለቀቁ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ዛሬ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በኩል ፥ " በምርኮ የቆዩት 100 ተጨማሪ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በምህረት ተለቀዋል " ብሏል።
ትናንት የተለቀቁት 112 ጨምሮ በሁለት ቀን የተለቀቁት የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥር 212 ደርሷል።
አሁንም ትግራይ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ ተጨማሪ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዳሉ ይነገራል።
@tikvahethiopia
# M-PESA
መክፈል፣ መገበያየት መቼም እንዲህ ቀሎ አያውቅም!
በፍሬሽ ኮርነር ያሻችንን ገዝተን በM-PESA ክፍያ በመፈፀም ወደ ሌላው የቀኑ ጉዳያችን መሄድ ነዉ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
#Update
ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።
ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል።
4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈፀመውን ድርጊት " #የሽብር_ጥቃት_ነው " ሲል ጠርቶ አውግዟል።
ለጥቃቱ #IS ኃላፊነቱን መውሰዱን በበይነ መረብ የወጣ አንድ ያልተረጋገጠ መግለጫ አመልክቷል።
የአሜሪካ ባለሥልጣናት ፤ IS ሩሲያን ለማጥቃት እንደሚፈልግ የሚያሳይ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
አሜሪካ በሞስኮ ከተማ " ሕዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች " ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሩሲያን አስጠንቅቃ ነበር።
ከ2 ሳምንታት በፊት በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ በርካታ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ሕዝባዊ ስፍራዎች እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር።
በማስጠንቀቂያው ላይ " ጽንፈኞች በሞስኮ ሕዝብ በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎችን (የሙዚቃ ኮንሰርትን ጨምሮ) የጥቃት ዒላማ ለማድረግ ዕቅድ አላቸው " የሚል ሪፖርትን እየተከታተልኩ ነው ሲል ገልጾ ነበር።
ኤምባሲው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ወደደረሰበት ስፍራ ዜጎቹ ዝር እንዳይሉ ምክር ማስተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
በኢትዮጵያ እውቁ እና የተዋጣላቸው የቀዶ ጥገና ሃኪም ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ባለፈው ሳምንት እሁድ መጋቢት 8 ሊነጋጋ ሲል ስፖርት ለመስራት ከቤት ወጥተው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ ባሰራጨው መረጃው የሟች ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ አስከሬን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሳሪስ አቦ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ ቀጠና 3 በተለምዶ " ማሞ ድልድይ " ስር ወድቆ መገኘቱን ገልጿል።
በወቅቱ አስከሬኑ ተነስቶ የአሟሟታቸውን ምክንያት ለማወቅ ለአስክሬን ምርመራ ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል እዲሄድ ተደርጓልም ብሏል።
ፖሊስ ፤ ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን ምርመራ ውጤት ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን ይገልጻል ብሏል።
" ሟች ዶ/ር በይሉ ሐይሉ ከከፍታው ላይ ቁልቁል ወደ ገደሉ በመውረድ አካላቸው ድንጋይ ላይ ስላረፈ በጭንቅላታቸው፤ በእግራቸው በጀርባ አጥንታቸውና በውስጥ የሰውነታቸው አካላት ላይ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ ያብራራል " ሲል ገልጿል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራ መቀጠሉን ከከፍታው የወደቁበትን ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ የምርመራ ውጤቶች ሲጠቃለሉ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አመልክቷል።
ከቀናት በፊት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ቤተሰቦች ፤ ጥዋት ለሩጫ በወጡበት በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተው መገኘታቸውን ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።
አንድ የሟች ቅርብ ቤተሰብ፣ " ቤተሰብ ጠቅላላ ' ወጥቶ ሞተ ' ነው የምናውቀው። ሚዲያ ላይ ካለው ውጪ አዲስ የሰማነው ነገር የለም " ብለው ነበር።
ዶክተር በሀይሉ ቤታቸው ቦሌ ሚካኤል እንደነበር የገለጹት እኚሁ የቅርብ ቤተሰብ " ሞተ ያሉት ወደ ሳሪስ በሚወስደው ድልድይ ጠዋት ወክ ሲያደርግ ነው። ዞሮ ዞሮ አስከሬኑን ፓሊስ ነው ያነሳው " የሚል ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተው ነበር።
@tikvahethiopia
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ | ለኢንስታግራም ተከታዮቻችን
የጥያቄውን ትክክለኛ ምላሽ ለሚያገኙ 3 ኢንስታግራም ተከታዮቻችን የ300 ብር የካርድ ስጦታ እናበረክታለን፡፡
🫵🏽 የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን ኢንስታግራም https://bit.ly/3NiRHOn ገፅን መወዳጀት ይኖርብዎታል፡፡
🧵 ተሸላሚዎችን የምንለየው በዕጣ ይሆናል፡፡
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE #questionandanswer
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን።
የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።
የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ 02 ቀበሌ በተለምዶ " ሳንቂ በር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
በዕለቱ የ5 ዓመቷ ህፃን ላይ አስገድዶ የመድፈር ድርጊት ከፈፀመ በኃላ በመኖሪያ ቤቱ ነው የተያዘው።
ጉዳዩን የተከታተለው የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋቢት 9 በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ወጣት የ6 ወር እስራት ፈርዶበታል።
ይህን መረጃ በ @tikvahethMagazine ላይ የተመለከቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " ቀልድ ነው ? ምን አይነት ፍርድ ነው ? ወንጀሉን ፍፁም የማይመጥን አሳዛኝ ፍርድ ነው " ብለውታል።
@tikvahethiopia
" የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ለቅቄያለሁ " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በስሩ የነበሩ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን በምህረት መልቃቁ አስታወቀ።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ዛሬ አመሻሽ ባሰራጨው መግለጫ ፤ " በያዝነው ወር የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የደረሰበት ደረጃ ለመገምገም በአዲስ አበባ መቀመጡ ተከትሎ በተደረሰው ስምምነትና በተቀመጠው የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በትግራዩ ጦርነት ተማርከው እስከ አሁን በእስር የቆዩት 112 የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት በምህረት ተለቀዋል " ብሏል።
እነዚህ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔ መሰረት የተለቀቁት መልካም አርአያ የነበራቸው እንዲሁም የፌደራል መንግስት በእስር የቆዩ የትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት በምህረት ለመልቀቅ የጀመረው እርምጃ እውቅና ለመስጠት ያለመ ነው ብሏል።
በቅርቡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት ተሳታፊዎች የትግራይ ተወላጅ እስረኞች / የሰራዊት አባላት እንዲፈቱ ጠይቀው ነበር።
በዚህም ወቅት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ እሳቸው በሚያውቁት አንድም የታሰረ ሰው እንደሌለ ተናግረው ፤ ስራ እንዲያቆሙ የተደረጉትም ወደ ስራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረው ነበር።
መንግሥት እስረኞችን ፣ የስራ አስፈፃሚዎችን ሳይቀር መፍታቱን በመናገር " ጌታቸው ጋር የቀሩ እስረኞች ነበሩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያልፈታቸው " ብለው ነበር።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
@tikvahethiopia
#ደሴ
ከደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ህዝብ መኃል በሚገኘው በሆስፒታሉ የቆሻሻ ምክንያት እየተሰቃቁ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቆሻሻው በሚወገድበት ጊዜ እስከ ቤታቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ይህ ሁኔታ የህፃናት ልጆቻቸውን ጤና እንዲሁም የራሳቸውን ጤና አደጋ ላይ እንደጣለውና እስከ ዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሆስፒታሉ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ገልጸዋል።
ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ከህፃናት ልጆቻቸው ጤና የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ ላሉበት ቦታ የሚመጥናቸውን ካሳ ካገኙ ቦታውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia
በውጭ አገር ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመድዎ በአጋሮቻችን በኩል በቴሌብር አለም አቀፍ ሃዋላ የተላከልዎትን ገንዘብ በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የቴሌብር ወኪል ሲቀበሉ የ 10% ስጦታ እንሸልምዎታለን !
ለተጨማሪ መረጃ bit.ly/3ArwoEO
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#Update
" 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ ከፍለናል ሰነዱ በእጄ አለ፤ ከለቀቋቸው በኃላ ድጋሜ በመያዝ 6 ሚሊዮን ብር ጠይቀዋል " - ቀጣሪ ድርጅቱ
ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ በግል ድርጅት ተመልምለው ወደ ስፍራው በአማራ ክልል፣ በምስቅው ጎጃም ፣ ጎዛመን በኩል አቋርጠው ሲጓዙ የካቲት 18/2016 ዓ/ም " በፋኖ ታጣቂዎች " ታገቱ የተባሉ ሠራተኞች እስካሁን ከእገታ አልተለቀቁም ሲል ቀጣሪው ድርጅት ገለጸ።
የቀጣሪው ድርጅት ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙልጌታ አለነ ፤ ላለፉት 24 ቀናት ታግተው የሚገኙትን 272 #የቀን_ሰራተኞች ጉዳት ሳያገኛቸው ለማስለቀቅ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ/ም 4 ሚሊዮን ብር በተለያዩ 3 ሰዎች አማካኝነት ክፍያ ፈፅመናል ብለዋል።
አቶ ሙልጌታ ፤ " ገንዘቡን #ተቀበሉን ከዛም ለቀቋቸው ከለቀቋቸው በኃላ እንደገና ጎዛመን የሚባል ቦታ ላይ ለዋናው አስፓልት 5 ኪ/ሜ ሲቀር እንደገና ሌላ ኃይል መልሶ ያዛቸው። ... የውሸት የውሸት ፖለቲካ የእውነት አምላክ ይፍረድልን ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረድልን " ሲሉ ተናግረዋል።
" 4,000,000 ብር (4 ሚሊዮን) ነው #የከፈልናቸው " ያሉት አቶ ሙልጌታ ፤ " የከፈልኩበት ሰነድ በእጄ አለ ፤ በ3 ሰው ስም ነው የገባው። ' አስገባ ' ተባልኩኝ አስገባሁ ተለቀቁ እንደገና ከተለቀቁ በኃላ ሌላ ቡድን ያዛቸውና ለእያንዳንዱ መኪና አሁን 1,500,000 ብር ተጠይቋል ፤ ልጆቹን ለቀይ መስቀል ነው አሳልፈን የምንሰጠው ብለውን እየጠበቅን ነው " ብለዋል።
መጋቢት 1 ተለቀው እና ድጋሚ ተይዘው ከሆነ ከቀናት በፊት ቃለ ምልልስ በሰጡበት ወቅት ይህን ገንዘብ ለአጋቾቹ #መክፈላቸውንና ተለቀው መያዛቸውን ለምን እንዳልተናገሩ ተጠየቀው ፤ " አንደኛ የነበርኩት እዛው አካባቢ ነው ለደህንነቴ አስቸጋሪ ነበር። ሁለተኛ ደግሞ ልጆቹን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረኩ ነበር በዛ የተነሳ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
ስራ አስኪያጁ ፤ ሰራተኞቹ #ከእገታው_ተለቀው መሄድ ከጀመሩ በኃላ በድጋሚ በቡድኑ ሌላ ክንፍ የተያዙት እዛው በምስራቅ ጎጃም ፣ ማቻከል ወረዳ አማኑኤል አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል።
ሲጓዙበት የነበረ 4 ተሽከርካሪ ቁልፍም በታጣቂዎች መወሰዱን ገልጸዋል።
6 ሚሊዮን ብር ማስለቀቂያ መጠየቁን አመልክተዋል።
' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ' እንደሆኑ የገለጹት ፋኖ ማርሸት ፀሀይ ግን ምንም አይነት የገንዘብ ጥያቄ አላቀረብንም ፤ ገንዘብም አልተቀበልንም ፣ ድርጅቱ ስም ማጥፋት ነው የያዘው ብለዋል።
ፋኖ ማርሸት " ይሄ ኒኮቲካ የሚባለው የኮንስትራክሽን ድርጅት የፋኖን ስም በዓላማ እያጠፋ ያለ ተቋም ነው። ምርኮኞች የተያዙት በ4ኛው ክ/ጦር በሚያስተዳድረው ቀጠና ነው። ክፍለ ጦራችን #አማኑኤል / ማቸከል፣ ጎዛመን እስከ ደ/ማርቆስ እና ልጆቹ አሁን ያሉበትን በረሃ ያጠቃልላል። ስለዚህ በዚህ ቀጠና እስካሉ የኛ ሙርከኞች ናቸው " ብለዋል።
" #ገንዘብ_የጠየቀ_አካል_የለም። ተጭነውባቸው ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም የመጡባቸው የአውቶብሶቹ ባለቤቶች (4 አውቶብሶች) ' አውቶብሶቻችን ስጡን ' ሲሉ አንሰጥም የሚል መልስ ሲሰጣቸው ' ለፋኖ ገንዘብ እንስጥና ድጋፍ አድርገን አውቶብሶቻችን ይመለሱ ' አሉ እኛ የገንዘብ ችግር የለብንም ፤ ገንዘብ አንጠይቅም አውቶብሶቹ ግን ቀይ መስቀል መጥቶ ልጆቹን ሲረከብ ተጭነው የሚሄዱባቸው ናቸው ብለን አቆይተናል " ብለዋል።
ልጆቹ ከነበሩበትም #እንዳልተንቀሳቀሱ ፣ ኒኮቲካም ሊቀበል እንዳልመጣ ገልጸው ድርጅቱ " የፋኖን ስም እያጠፋነው " ሲሉ ከሰዋል።
" እነዚህ ልጆች ታጋቾች ሳይሆኑ #ምርኮኞች ናቸው። ምርኮኞቹን ደግሞ ለቀይ መስቀል የምናስተላልፍበት ምክንያት ፦
1. እኛ ተንቀሳቃሽ ኃይል ስለሆንን፣
2. ለነሱ የምንመግበውን ምግብ ለወታደራችን ማዋል ስላለብን ፣
3. ዓለም አቀፍ የጦርነት ህግን አክብረን የምንዋጋ የነፃነት ታዋጊዎች / ኃይሎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው " ብለዋል።
እስካሁን ቀይ መስቀል እንዳልመጣ በአካል ከመጡ እናስረክባለን ሲሉ ተናግረዋል።
የተያዙት ደግሞ ድርጅቱ እንዳለው " 272 " ሳይሆኑን 246 ብቻ ናቸው ብለዋል።
ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን አሁን ጉዳዩ ከእኛ ከአቅማችን በላይ ነው ሲል አሳውቋል።
አቶ ሙልጌታ አለነ ፤ " ለሚመለከተው ሁሉ ስራውን ለሚያሰራን ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም በፅሁፍ አሳውቀናል ምንም መፍትሄ የለም #የድሃ_ልጅ ነው እየተሰቃየ የሚገኘው " ሲሉ ተናግረዋል።
" የአማራ ህዝብ እውነቱን ብቻ አይቶ ይዳኘን ፣ እነዚህ ወንድም ህዝቦች ናቸው የመጡት ለስራ ነው " ብለዋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰራተኞቹን ጉዳይ እንደሚያውቅ ፣ ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ጋር በመሆን እየሰራበት እንደሆነ ገልጾ ለጊዜው ለታጋቾች ደህንነት ሲባል ከዚህ በላይ አስተያየት እንደማይሰጥ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከቪኦኤ ሬድዮ /ጋዜጠኛ ዮናታን ዘብዲዮስ ማግኘቱን ያሳውቃል።
@tikvahethiopia
#MerttEka
ከላይ👆የምትመለከቷቸው የቤት ዕቃዎች ለእርስዎ ኑሮዎን ለማቅለል የሚያስፈልጉ ስለሆኑ በሱቃችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጡ ነው።
የሌሎች በርካታ ዘመናዊ የቤት ዕቃዎቻችንን ዋጋ/መረጃ በቴሌግራም ለማየት ከፈለጉ ይሄን👉 t.me/MerttEka 👈 ተጭነው ይመልከቱ። ቤተሰብም ይሁኑ🙏
አድራሻችን፦ አዲስ አበባ፣ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ ሱቅ ቁጥር 376