#PremierLeagueallonDStv
🔥ሁሉቱም ቡድኖች ምርጥ አቋም ላይ ናቸው! ማን ዩሆን 3 ነጥቡን የሚያሸንፈው?
👉 ይህንን ድንቅ ፍልሚያ ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
የዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#Update #ሲዳማክልል
“ ከሀዋሳ ወደ ሻምና ለመሄድ የመኪና መንገድ የለም። መንገድ ለመክፈት ደግሞ አርሶ አደሩ መሬት መስጠት አለበት። የግድ በእነርሱ መሬት ላይ ነው መንገዱ የሚወጣው ” - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ
በሲዳማ ክልል ሰሜን ሲዳማ ዞን ሲዳማ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ሁሩፋ ቀበሌ ባለይዞታዎች፣ “ ፓሊሶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል ” ሲሉ ለቲክቫህ ላቀረቡት አቤቱታ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ምላሽ ሰጥቷል።
ለዛውም በፍርድ ሂደት ላይ ባለ ጉዳይ “ ጠመንጃ በመደቀን ድብደባ መፈጸም ” ተገቢ ነው ? ስንል የጠየቅናቸው የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳዬሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አሀመድ፣ “ ህዝቡ ተደብድቧል የሚል ቅሬታ አልመጣም። ተደብድቦ ከሆነ የምናጣራ ይሆናል ” ብለዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ቅር ያሰኛቸው መንገድ መከፈቱ ሳይይሆን ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሂደት እያለ ደርጊቱ መፈጸሙ፣ በፓሊስ ደብደባ ስለተፈጸመባቸው፣ በንብረት ላይ ውድመት ስለደረሰባቸው፣ ካሳ ስላልተከፈላቸው በመሆኑ ነውና ለዚህስ ምላሽዎ ምንድን ነው ? ስንል ላቀረብው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ ሀሚድ አሀመድ ፦
“ አዎ በእርግጥ ፍርድ ቤት ያለ ኬዝ ነው። ከላይ ያለ አካል አቅጣጫ ሲያስቀምጥ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማይጠበቅበት ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።
ከጠቅላይ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ከመጣ እንደዚህ አይነት ጉዳዮች አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች የሚጠቅባቸው አይነት ነገሮች ሳይመጡ ሲቀሩ ላይጠበቅ ይችላል።
የሚገመት አይነት ንብረት አይደለም። ፎቶውን ሳይ የተወሰነ አትክልት ነገር አለ ፤ ድንች ፣ ቀይ ሽንኩርት ነበረ። ካሰ የሚከፈል ከሆነ እንደ ካሳ ነው የሚነጋገሩት። ካልሆነ ደግሞ በሌላ ካሳ እንዲከፈላቸው ነበር ማድረግ የነበረባቸው።
‘ በጭራሽ መንገድ አይወጣም ’ ነው እነርሱ ሲሉ የነበሩት። ካሳ ተከፈለ አልተከፈለ የግድ ይላል ህዝቡ ያነሳው ጥያቄ መንገድ የለንም’ የሚል ነውና።
ከሀዋሳ ወደ ሻምና ለመሄድ የመኪና መንገድ የለም። መንገድ ለመክፈት ደግሞ አርሶ አደሩ መሬት መስጠት አለበት። የግድ በእነርሱ መሬት ላይ ነው መንገዱ የሚወጣው።
የፍርድ ቤት ኬዛቸውንም ይከታተሉ። ይሄ ደግሞ እንዳይከታተሉ የሚያደርጋቸው ነገር አይደለም። ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ ፍርድ ቤቱ ካሳ ሊያስከፍልላቸው ይችላል።
እኔ ጉዳዩን አጣርቻለሁ። ባለፈው ፕሬዝደንቱ እዛ ሂደው ነበር። አጋጣሚ የፓሊስ ግንባታ ፕሮጀክት ሊያስመርቁ በሄዱበት ‘ እዛ መንገድ እንዲወጣ ነበር ’ ያሉት።
መንገድ በፊት ተከልክሎ ነበር እዚያ ቦታ እንዳይወጣና ፕሬዚደንቱ ካዩ በኋላ መንገዱ እንዲወጣ ነበር ያዘዙት። ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት ነው መንገዱ እንዲወጣ የተደረገው።
የመንገድ ከፈታ የትም ያለ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀዋሳ መጥተው በነበረበት ወቅት ማግስት ‘ምንድን ነው ችግራችሁ?’ ብለው ሲጠይቁ፣ ‘ሀዋሳ መውጫና መግቢያ መንገድ አጥተናል። ምንም መንገድ አልተከፈተልንም’ የሚል ቅሬታ ሲያነሱ ‘በሲዳማ ክልል ከተሞች የውስጥ መንገድ ሁሉም ቦታ እንዲከፈት ነበር አቅጣጫ አስቀምጠው የወጡት።
በክስ ያሉ ቦታዎች ነበሩ። መንገድ ከፈታ ላይ አንዳንድ ማህበረሰብ እንዲወጣላቸው ይፈልጋሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ እንዲወጣ አይፈልጉም።
አንዳንድ ንብረት ይነካል። ይሄ ደግሞ የምንደራደረው ጉዳይ አይደለም። የምንጓዘው፣ መድኃኒት የሚደርሰው፣ ችግር የሚፈታው በመንገድ ነው። ግን ‘መንገድ አይከፈት’ በማለት ሁከት እንዲነሳ የሚፈልጉ አካላት አሉ።
ወደ 6፣ 7፣ 8 ሰዎች ሆነው ነው እዛ ሲጨቃጨቁ የነበረው። ነገር ግን አብዛኛው መንገድ እንዲከፈትላቸው የሚፈልጉ አሉ። በዚህም ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው እንዲከፈት የተደረገው። ”
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ሲዳማክልል
🛑 " በፍርድ ቤት ሂደት ባለ ጉዳይ ፖሊሶች ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል " - ስሞታ አቅራቢዎች
🔵 " ከ200 በላይ ሰዎች ‘ይሰራልን’ ብለው አምነው ሁለት ሰዎች ካመጹ ምን ይደረጋል ? " - ሰሜን ሲዳማ ዞን አስተዳደር
በሲዳማ ክልል፣ ሰሜን ሲዳማ ዞንዝ፣ ሲዳማ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ሁሩፋ ቀበሌ " በፍርድ ቤት ሂደት ባለ ጉዳይ በጸጥታ አካላት የድብደባና ንብረት ጭፍጨፋ " እንደተፈጸመባቸው ባለይዞታዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቅሬታቸው በዝርዝር ምንድን ነው ?
" በፍርድ ቤት በሂደት የነበረ የመንገድ ጉዳይ ነበር። የዛሬ ሁለት ወር አካባቢ ነበር ነገሩ የተቀሰቀሰው።
የተቀሰቀሰውም በግድ መንገድ ለማውጣት የቀበሌ አመራሮች ‘መንገድ ይወጣል’ ብለው ጀምረው ነበር የክሱ ሂደት የተጀመረው።
ቤተሰብ ተበትኖ፣ ንብረት ወድሞ እንዴት መኖር ይቻላል ? በሚል ክስ ተነስቶ ጠበቃ ቆሞ እየተካሰሰ ነው። ግን ትላንት የወረዳው ፓሊስ ሙሉ ፓትሮል መጥቶ በግድ ሙሉ ንብረት አውድመው ሂደዋል።
በፍርድ ቤት ሂደት ባለጉዳይ ፖሊሶች ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል።
ድብደባ ካደረሱ በኋላ ስድብ፣ ማሸማቀቅና የዛቻ ቃል ተናግረዋል። ‘ለአርሶአሮቹ የሚያስፈልገው ሂደት ተሟልቶ ነው መንገድ መውጣት የሚችለው’ ተብሎ ውሳኔ አግኝቶ ነበር።
እንዲህ የሚያደርጉት ምንም አይነት ወረቀት የላቸውም። ጉዳዩ ወረዳ ላይ በክስ ሂደት ያለ ነው። የሚያፈርሱት ቦታ እንሰት፣ መቃብር፣ ደን፣ ጎመን፣ ባሕር ዛፍ አለው።
ይዞታው የአቶ በቀለ በዶሬ እና አቶ አዲሴ አንጂሎ ሲሆን፣ ወደ 18 ሁለት የቤተሰብ አባላት የሚተዳደሩበት ነው " ብለዋል።
" መንገዱ ያስፈልጋል ከተባለ እንኳ የይገባኛል ጥያቄው ውሳኔውን ሳያገኝ፣ ካሳ ሳይታሰብ ማንም መጥቶ ነው እንዴ መንገድ የሚያወጣው ? " ሲሉ ጠይቀው፣ ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
በፍርድ ሂደት ላይ ባለጉዳይ ለምን እንዲህ አይነት ድርጊት ተመፈጸመ ? ስንል የጠየቅናቸው የሰሜን ሲዳማ አስተዳደር አቶ አዱሱ ቃሚሶ፣ " በፍርድ ቤት የታገደ እኛ ጋ የመጣ ነገር የለም። ውሳኔው እስኪጸድቅ ድረስ ይሄ ቦታ ታግዶ ይቆይ የሚል አልደረሰንም " ብለዋል።
" የንብረት ጭፍጨፋ የተደረገው ከፍርድ ቤት ሂደት በኋላ ይሁን በፊት በሚለው ዙሪያ ያጣራሁት ነገር የለም ለጊዜው " ያሉት አስተዳዳሪው፣ ድብደባውን በተመለከተ ማጣራት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በሁሉም አካባቢዎች መንገድ የመክፈት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ " በእግርጥ መንገዱ የሚነሳው ያለ ካሳ ነው። ንብረቱ ብዙም አይደለም ከግራም ከቀኝም 3፣ 3 ሜትር ብቻ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ከ200 በላይ ሰዎች ‘ይሰራልን’ ብለው አምነውበት ሁለት ሰዎች ካመጹ ምን ይደረጋል? የሌሎቹ ተከፍቶ የሌላው አይተው ልማት ነው " ብለዋል።
" ጉዳዩ የእነርሱ ብቻ አይደለም። እስከ ቀበሌ ድረስ መንገድ ከፈታ እንዲደረግ እቅድ ታቅዶ ነበር። ህብረተሰቡ በመንገድ ተጠቃሚ መሆን አለበት "ነው ያሉት።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ሴጅማሰልጠኛ
ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principles and Practices of Accounting) የ5 ወር የቅዳሜ እና እሑድ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#AddisAbaba
“በክፍት ቤቶች ባለቤቶቻቸው አድሰው የፈለጉትን አገልግሎት ሊያውሉት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ማስታወቂያው የወጣው” - ኮርፖሬሽኑ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ ወደ ቤታችሁ ግቡ " በሚል ባወጣው ማሳሰቢያ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ዝርዝር ምላሽ ምንድን ነው ?
የኮርፖሬሽኑ ማብራሪያ ፦
“ ማስታወቂያው የወጣበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ‘ተቸገርን፣ ክፍት በሆኑ ቤቶች ወንጀል እየተሰራ ነው፣ እየተዘረፍን ነው፣ ሴቶች እየተደፈሩብን ነው’ ብለው እኛ ጋ ስለመጡ ነው፡፡
ቤቶቹን ቼክ ስናደርጋቸው ደግሞ እጣ ወጥቶባቸዋል፤ ውል ተፈጽሞባቸዋል፣ ግን ሰው አልገባባቸውም፡፡
ስለዚህ ነዋሪው ተቸግሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተደጋጋሚ ወደኛ ቢሮ የሚመጡ የየሳይቱ የነዋሪዎች ማኀበራት አሉ፡፡
ስለዚህ እነዚህ አካባቢዎች ላይ ያሉ ቤቶች በአግባቡ ቤት የደረሳቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ መሠረተ ልማቶቹም የተሟሉ፣ ሰው ገብቶ መኖር የጀመረባቸው በመሆናቸው ክፍት መሆን የለባቸውም፡፡ የቤት ባለቤቶች ቤታችሁን አድሳችሁ ግቡ፡፡
ቢፈልጉ አድሶ ማከራየት መብት ነው፡፡ የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ፡፡ ግን ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ይኑርበት ነው የኛ ጥያቄ፡፡ አካራይ አታከራይ የኔ መልዕክት ሊሆን አይገባም፡፡ ግን ቤቱን ኦውን ያድረጉ፡፡
ሰው ‘የጸጥታ ስጋት ብሎ ይጠይቀናል’፣ የጸጥታ መዋቅሩም እኛን ይጠይቀናል፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ደግሞ ቤት ደርሶት ያልገባበት ሰውም ጭምር በመኖሩ እጣ ያልወጣላቸውም ሰዎች ጭምር ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡ ‘ይሄው ክፍት ቤት አለ ይላሉ፡፡’
ስለዚህ በክፍት ቤቶች ባለቤቶቻቸው አድሰው የፈለጉትን አገልግሎት ሊያውሉት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ማስታወቂያው የወጣው፡፡
የማኅበራዊ ሚዲያ በበዛበት ዘመን በተለያዬ መንገድ ኢንተርፕሬት ሊደረግ ይችላል፡፡
ዋናው የመንግስት ኢንቴንሽን ግን ይሄ ነው፡፡
ክፍት ቤቶች ያሉት አብዛኛው ሳይት ላይ ነው የቤቶቹ መጠን ይለያያል እንጅ (አንዳንድ ቦታ ላይ አምስት፣ አንድ ቦታ ላይ ደግሞ አስር ሊሆኑ ይችላሉ)፡፡
ከተነሳው ቅሬታ አንጻር መሠረተ ልማት ያልተሟላባቸው ደግሞ የተወሰኑ ሳይቶች አሉ (እየተሟላባቸው ያሉ ማለት ነው)፡፡
ለምሳሌ በተደጋጋሚ የሚነሳው አራብሳ ሳይት (ፓኬጅ ሦስት) ነው፡፡ ወደ መጨረሻ አካባቢ ከተገነቡት ቤቶች መካከል ነው። አራብሳ ሦስት አብዛኛው መሠረተ ልማት ተሟልቷል፡፡
ለምሳሌ መንገድ አክሰስ ነው፡፡ አክሰስ ተሰርቶለታል፡፡ ወደ ዘላቂ መንገድ ለማስገባት ለሁለት፣ ሦስት ዓመታት ኢኮስኮ የተባለው ኮንትራክተር ቦታውን ይዞት ነበር ከመንገዶች ተረክቦ ለመስራት፡፡
ነገር ግን ሳይሰራው ቆዬ፡፡ ይሄ ጥያቄ በተደጋጋሚ የማህበረሰቡ ጥያቄ ስለሆነ አቅርበን አሁን ተርሚኔት ተደርጎ መንገዶች ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
ክረምቱን በሙሉ አክሰስ ወደ መስራት ዝግጅት ላይ ነው የነበሩት አሁን በተሟላ መልኩ ቋሚ መንገድ ሊሰራ ነው፡፡
የመጠጥ ውሃ ወደየ ሳይቱ፣ ወደዬ ብሎኩ ገብቷል፡፡
ፍሳሽን በተመለከተ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ሜጋ ፕሮጀክት እየተሰራ ነው፡፡ በውጭ ካምፓኒ ነው የሚሰራው፡፡ የበጀት እጥረት ገጥሟቸው ጋፕ ነበረ አሁን ግን በተሟላ መልኩ እየተሰራ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ ያልቃል፡፡
የአራብሳን አጠቃላይ ችግር ይህ ፕሮጀክት ነው የሚፈታው፡፡ ይህ እስኪሆን ድረስ ግን የኮሪደር ልማት ተነሽዎች እየገቡ ስለሆነ ሴፍቲ እስታንክ እየተቆፈረ ለጊዜው ፍሳሹ እንዲመጣ፣ ዘላቂው ሲሰራ ደግሞ በቋሚነት እንዲሆን እየሰራን ነው፡፡
አምስትና ስድስት ላይ በተመሳሳይ እየሞከርን ነው፡፡ የተወሰኑ ችግሮች አሉ ሰፈራ የሚባለው አካባቢ የወሰን ማስከበር ችግር አለው፡፡
ለምሳሌ ፍሳሽ፣ የመጠጥ ውሃ በዚያ በኩል ያልፋል ግን የወሰን ማስከበር ችግር አለ፡፡ መፈታት አለበት በሚል ከተማውም ይዞት ለመስራት ጥረት እያደረገ ነው፡፡
የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸውን ቦታዎች እናውቃቸዋለን፡፡ ችግሩ እንዲፈታም ጥረት እያደረግን ነው፡፡ እኛ እያልን ያለነው ይህን አይደለም፡፡
መሠረተ ልማት ተሟቶላቸው በአብዛኛው ነባር ሳይት የሚባሉ፣ ሕዝቡ ገብቶ እየኖረበት ያለ አካባቢ ክፍት ቤቶች አሉ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ነው ያነሳነው፡፡
ማስታቂያውን በተዛባ መልኩ ለማስተላለፍ የሚፈልጉ አካላት አሉ፡፡ ‘ቤት ሊነጠቅ ነው፣ ሊወሰድባችሁ ነው’ የሚል መልዕክት ላስተላለፍ የሞከሩ አሉ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ነባርና አዳዲስ የቤት ፍላጎቶችን ለማሟላት የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን አጥንቶ ወደ ተግባር በመግባት ላይ ነው ያለው እንኳን የነበረውን ወደዚህ ደረጃ ለማድረስ። ”
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ሕብረት ባንክ !
እንኳን ደስ አለን ! ሕብረት ባንክ ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆኑ የልዩ ተሸላሚ እና የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማቶችን ተቀበለ
ሕብረት ባንክ በአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች እውቅና የመስጠት መርሃ-ግብር ላይ የ2016 ዓ.ም የፕላቲኒየም ደረጃ ግብር ከፋይ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ በተከታታይ አራት አመታት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ በመሆኑ ልዩ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ ባንኩ ያገኛቸውን ሽልማቶች የባንኩ ተ/ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እጅ ተቀብለዋል፡፡
ሕብረት ባንክ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ከሚያገኘው ገቢ ላይ በታማኝነት ግብር በመክፍል ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ሽልማቱም ለዚህ ተግባር እውቅና የሠጠ ነው፡፡
ሽልማቶቹ የሁላችንም ያላሰለሰ የጥረት ውጤት በመሆናቸው ለሕብረት ባንክ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ አለን!
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ መረጃዎች እንዲደርስዎ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡፡ linktr.ee/Hibret.Bank
#DDR #Tigray
የእንግሊዝ (UK) መንግስት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም (DDR) የሚያግዝ የ16 ነጥብ 9 ሚሊዮን ፓወንድ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታዉቋል፡፡
የድጋፍ ማእቀፉን ያሳወቁት በብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሎርድ ኮሊንስ የተመራው ልዑክ በመቐለ በመገኘት የብሄራዊ ተሀድሶ ቦርድ አባል ሌ/ጀ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ እና ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንዲሁም የዩኤንዲፒ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የቀድሞ ተዋጊዎች ዲሞቢላይዜሽን ማእከል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
#UKinEthiopia
@tikvahethiopia
" አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ አሽከርክሩ " - ፖሊስ
ከሰሞኑን በአዲስ አበባ የደረሱት የትራፊክ አደጋዎች የሰው ህይወት ቀጥፈዋል ፣ ከባድ እና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል፣ ንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።
በአንድ ክ/ከተማ፣ በአንድ ቀን፣ በተለያየ ቦታና ሰዓት በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ አጠቃላይ የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ9 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።
አደጋዎቹ የደረሱት ቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ/ም ነው።
የጉዞ መስመሩን ከጎሮ ወደ ኮዬ ፈቼ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-69867 ኢት #ሲኖ_ትራክ ተሽከርካሪ ከከተማ አውቶቡስ ጋር ተጋጭቶ ትኬት ሊቆርጡ ወደ አውቶቡሱ ተጠግተው የነበሩ 3 ሴቶች እንዲሁም በአካባቢው ላይ ጧፍ ስትሸጥ በነበረች ሴት ላይ የሞት አደጋ ያስከተለ ሲሆን የከባድ መኪናው አሽከርካሪም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበታል፡፡
ከተከሰተው ሞት በተጨማሪ በ7 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
በዛው እለት ቡልቡላ መስቀለኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢም አካባቢ በደረሰው አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።
የጉዞ አቅጣጫውን ከመድኃኒያለም ወደ ማርያም ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-8660 ኢት #ሲኖ_ትራክ ተሽከርካሪ ከማርያም ወደ ኮዬ ይሄድ ከነበረ ኮድ 3-46737 ኦሮ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭተው የደረሰ አደጋ ነው።
በአንድ ቀን በ7 ሰዎች ላይ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ መድረሱ በእጅጉ አስዛኝ እንደሆነ የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ በአብዛኛው ለሚከሰቱት የትራፊክ አደጋዎች ዋነኛ ምክንያት ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረግ የሚደርሱ መሆናቸውን አስገንዝቧል።
አሽከርካሪዎች ከምንጊዜውም በላይ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የአካባቢውን߹ የመንገዱን እና የእግረኛውን የመንገድ አጠቃቀም ሁኔታ በተገቢው በማስተዋል ማሽከርከር እንደሚጠበቅባቸው ፖሊስ አሳስቧል።
ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር በኋላ ከሚመጣው መፀፀት እንደማያድን በመገንዘብ በጥንቃቄና በእርጋታ ማሽከርከር እንደሚገባ ፖሊስ ገልጿል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
#Ethiotelecom
🎀 ተጨማሪ 10% ስጦታ ያግኙ!
ከውጭ አገራት ከ99 ብር ጀምሮ የሞባይል አየር ሰዓት ወይም ጥቅል በአጋሮቻችን በኩል ሲላክልዎ ለ30 ቀናት የሚያገለግል የ10% ተጨማሪ ስጦታ ያገኛሉ፡፡
🗓 እስከ ታኅሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም!
ደንብና ሁኔታዎችን https://bit.ly/487Y93d ይመልከቱ!
#telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#ሪልስቴት
ያልተገነባ ቤት / ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው።
ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል።
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?
ቤት ለመገንባት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ያላገኙ የሪል ስቴት አልሚዎች ደንበኞችን #እንዳይመዘግቡ እና #ቅድመ_ክፍያ እንዳይሰበስቡ ይከለክላል።
በአሁኑ ጊዜ ባለው አሠራር መሠረት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ብቻ ወደ ሪል ስቴት ገበያው ሲቀላቀሉ የነበሩት አልሚዎች፤ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ " የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ " የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብት ሪል ስቴት አልሚዎች ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 50 ቤቶችን ገንብተው የሚያስከረክቡ መሆን አለባቸው።
የአገር ውስጥ እና የውጭ አልሚዎች ግንባታውን ለማከናወን የሚያስፈልገውን " የፋይናንስ አቅርቦት ምንጭ " የማቅረብ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦባቸዋል። ይሁንና ረቂቁ፤ " የቅድሚያ ቤት ሽያጭ ተጠቃሚነት " መብትን ከቅድመ ሁኔታ ጋር ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሰጥቷል።
ይህ አሠራር የሪል ስቴት አልሚዎች የቤት ግንባታውን ሳያከናውኑ ወይም በሂደት ላይ እያለ ለግንባታው የሚውልን ፋይናንስ የሚያሰባስቡበት እና ገንዘቡብ ለግንባታው የሚያውሉበት መንገድ ነው።
የቤት ግንባታው ሳይከናወን በፊት ከገዢዎች ጋር ውል ማሰር እና ክፍያ መፈጸም ኢትዮጵያ ውስጥ በሪል ስቴት ልማት ላይ በተሰማሩ አልሚዎች በኩል የተለመደ አሰራር ነው።
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ በዚህ ዓይነት መልኩ ለግንባታ የሚውለውን ሀብት ማሰባሰብ የሚፈልጉ አልሚዎች " አግባብ ካለዉ አካል ፈቃድ ማቅረብ " ይጠበቅባቸዋል። ይህም ግዴታ ነው።
የቅድመ ሽያጭ ዘዴን መጠቀም የሚፈልጉት ሪል ስቴት አልሚዎች፤ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡት ገንዘብ የሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ እና የገንዘብ አወጣጥ ላይም አስገዳጅ አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተጥሎባቸዋል።
አልሚዎቹ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ " የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ " እንዳለባቸው ረቂቅ ሕጉ ላይ ሰፍሯል።
አዲሱ ሕግ፤ ገንዘቡ የሚቀመጥበት ዝግ የባንክ አካውንት የሚከፈተው " አግባብ ባለው አካል ፈቃድ መሠረት " እንደሆነም ያስረዳል።
በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ ከረቂቅ አዋጁ መፅደቅ በኋላ በሚወጣ ደንብ ይወሠናል።
ከዚህም ባሻገር በቅድሚያ የተሸጠው ቤት ተገንብቶ ለተጠቃሚዎች እስከሚተላለፍ ድረስ የቤት የመሥሪያ ቦታው የይዞታ ማስረጃ " በሚመለከተው አካል እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥ " እንደሚታገድ ረቂቁ ይገልጻል።
ቤት ቀድመው በሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ እነዚህ አስገዳጅ አሠራሮች የተቀመጡት " ደንበኞች የሚደርስባቸውን እንግልት እና ኪሳራ ለመቀነስ በማሰብ " እንደሆነ የአዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል።
ረቂቅ አዋጁ በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ሌሎችንም ግዴታዎች ጥሏል።
በረቂቁ መሠረት፤ የሪል ስቴት አልሚዎች ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ተከልክለዋል።
" ያለደንበኛው ፍላጎት እና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም " ይህንን ለማድረግ በቅድሚያ ደንበኛው መስማማት እንዳለበት ያመለክታል።
ሪል ስቴት አልሚዎች ቤት ገዢዎችን መመመዝገብ እና ቅድመ ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉበት ጊዜም ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦበታል።
አልሚዎች ምዝገባ ማድረግ እና ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉት " የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከተረከቡ " በኋላ ነው።
" በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም " የሚለውም ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ከተቀመጡት ግዴታዎች መካከል ነው።
ለሪል ስቴት ልማት አሠራር የሚዘረጋው አዲሱ አዋጅ፤ ከግዴታዎች ባሻገር አልሚዎች ከመንግሥት " መሬት በስፋት " ማግኘት የሚችሉበትን ሂደትም ያስቀመጠ ነው።
ከመንግሥት መሬት " በስፋት " የሚቀርብላቸው አልሚዎች ረቂቁ ላይ ከተጠቀሱ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ቢያንስ አንዱን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በብዛት ቤቶችን መገንባት እና ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ " 40 በመቶውን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የማኅበረሰብ ክፍል ተደራሽ " ማድረግ የሚለው አንዱ ነው።
ይህንን ቅድመ ሁኔታ የሚከተሉ አልሚዎች የሚገነቡበት ቤት ብዛት " እንደ ከተሞች ደረጃ በአንድ ጊዜ ከ500 እስከ 5 ሺህ " ሊሆን እንደሚችል በረቂቁ ላይ ተጠቅሷል።
መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ መሬት " በስፋት " የሚያቀርበው " በአዲስ አበባ ከ5 ሺ በላይ ቤት ለሚገነባ እና ለሚያስተላልፍ " አልሚ እንደሆነ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
በሌሎች ከተሞች መሬት " በስፋት " የሚቀርበው እደሚኖራቸው " ተጨባጭ የቤት ፍላጎት " ሲሆን፣ " ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባሉ ከተሞች " ደግሞ ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች እንደሚቀርብላቸው ረቂቁ ያስረዳል።
ከመንግሥት መሬት " በስፋት " ማግኘት የሚፈልጉ አልሚዎች የተቀመጠባቸው ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተገናኙ ናቸው።
በአገር ውስጥ " በጥራት እና በብዛት የማይገኙ " ግብአቶችን በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ (ፍራንኮ ቫሉታ) የሚያስገቡ እንዲሁም የሚያገኙትን ትርፍ እስከ አስር ዓመት ከአገር ሳያወጡ አገር ውስጥ መልሰው የሚጠቀሙ አልሚዎች የዚህ አሠራር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
" የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት እና ግመታ " የተሰኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ የቀረበለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተጨማሪ ዕይታ ወደ ከተማ፣ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቶታል።
መረጃው ከቢቢሲ አማርኛ የተወሰደ ነው።
@tikvahethiopia
#MoE
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ 'Remedial' ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ መገለጹ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ " አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል " ባሉት መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
@tikvahethiopia
እሁድ ጥቅምት 3 ከሰዓት 9፡15 ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በችካጎ ማራቶን ይሳተፋሉ!
መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን! 💚💛❤️
ይህንን ደማቅ ሩጫ በቀጥታ በSS Africa ቻናል 227 በቤተሰብ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ስቴም ፖወር !
ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች ለ3ተኛ ዙር የቀረበ ጥሪ !
ስቴም ፖወር (STEMpower) ከፊንላንድ ኤምባሲ (Embassy of Finland Ethiopia) እና ከአይቢኤም (IBM) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሥራ አጥ ወጣት ሴቶችን ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ለመስጠት ያለመ " ትጋት " የተሰኘ ፕሮግራም አስተዋውቀዋል።
ባለፉት 2 ዙሮች 1700 በላይ ለሚሆኑ ሴቶች በ Project Management, Web Development , Cyber Security, Digital Marketing , Data Analytics , Information Technology , Job Readiness , Work Readiness ስልጠና የሰጠ ከመሆኑ በተጨማሪ የስራ እድል በመፈጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል አመቻችቷል፡፡
#ነጻ በሚሰጠውና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት በሚያስገኘው በዚህ ስልጠና እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ሴቶች ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እያሳወቅን ምዝገባው የሚቆየው ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10 , 2017 ዓ/ም ሲሆን ቀድማችሁ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን፡፡
እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ከስር ባለውን ሊንክ ይመዝገቡ
👉Link: https://forms.office.com/r/bJedLrdqmd
#Amhara
" በአማራ ክልል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ አራዝመዋል። ትምህርት ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለበት " - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት
በአማራ ክልል በ " ፋኖ " ታጣቂዎችና በመንግስት መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ ጊዜ ማራዘማቸው ይህም ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጭንቀት መደቀኑ ተሰምቷል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ የተማሪዎቻቸውን የቅበላ ጊዜ ማራዘማቸውን እንደተረዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ነው።
የህብረቱ ፕሬዚዳንት ሓየሎም ስዩም፣ " አራት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ አራዝመዋል " ብሎ ተማሪዎች በጭንቀት ውስጥ በመሆናቸው ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትከረት እንዲሰጡ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
በጸጥታው ችግር የተማሪዎቻቸውን የቅበላ ጊዜ ያራዘሙት፣ " ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር እና ኢንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች " መሆናቸውንም ተናግሯል።
" ወሎና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች አሁን መንገድ ስለተከፈተ ይቀበላሉ " ያለው የህብረቱ ፕሬዚዳንት ደባርቅ ዩኒቨርቲንም ቅበላውን ሳያራዝም እንዳልቀረ፣ " ሀፋ፣ ሀፋ " የሆነ ሀሳብ ላይ እንደሆነ አስረድቷ።
ህብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " ትምህርት ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለበት " ሲል አሳስቧል።
በአንጻሩ ወልዲያ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ተቀብለው እያስተማሩ መሆኑ ሲነገር ተስተውሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የተማሪዎቹን ቅበላ አራዝሟል ወይስ አላራዘመም ? ተማሪዎቹን ተቀብሎ እያስተማረ ነው ወይስ አልተጀመረም ? ሲል ወልዲያ ዩኒቨርሲቲን ጠይቋል።
ዩኒቨርሲቲው በምላሹ፣ " አላራዘመም። ተማሪዎቹ እስኪገቡ ድረስ እንጠብቃለን። የመንገድ መዘጋጋቱ ስለሚታወቅ እንደ ሀገር በይፋ ባናራዝምም የቻሉ እየገቡ ነው ያልቻሉ ይገባሉ በፈለጉት ሰዓት " ብሏል።
" በውስጥ ኮሚዩኒኬት ስላደረግን ከተማሪው ከተለያዩ ቅርብ ቦታ (ለምሳሌ ደሴ) እየመጡ ስላሉ አላራዘምንም " ሲልም አክሏል።
ትምህርት ተጀምሯል ? ስንል ላቀረበነው ጥያቄ " ትምህርት አልተጀመረም " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንለት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ፣ " ተማሪዎችን ተቀብለን እያስተማርን ነው። የኛ ተማሪዎች ገብተዋል። ሲኔር ተማሪዎች በሙሉ ግቢ ነው ያሉት " ብሏል።
" የአዲስ ገቢዎችን በተመለከተ ግን ትምህርት ሚኒስቴር አልመደበም ገና። እንደመደበ እንጠራለን። እኛ ምንም የምናራዝምበት ምክንያት የለም " ነው ያለው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዎቹን ቅበላ ያራዘሙ ዩኒቨርሲቲዎችን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉት ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር)፣ ' ዩኒቨርሲቲዎቹ የራሳቸው ስኬጁል አለ። እኛም የሰጠነው ስኬጁል አለ። ዩኒቨርሲቲዎቹ ይጠየቁ " ከማለት ውጪ ማብራሪያ ለመስጠት ተቆጥቧል።
#TikvahEthioiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
" ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይታደሳሉ " - የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን
ከአዲስ መንጃ ፈቃድና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ እንደሚታደሱ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣን መ/ቤቱ ፤ " ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል " ብሏል።
በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት እንደሚታደሱ አስታውቋል፡፡
አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ተመላክቷል።
ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆን ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ገልጿል።
@tikvahethiopia
' አሻም ' ስያሜውን እንዲቀይር በፍርድ ቤት ለምን ተወሰነ ?
“ ተከሳሽ ' አሻም ' ሚለውን የንግድ ምልክት መጠቀም ማቆም አለበት በማለት ተወስኗል ” - ፍርድ ቤት
አሻም ቴሌቪዝን ሲጠቀምበት የነበረውን አሻም የሚለውን ስያሜ መጠቀም አንዲያቆምና እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ/ም እንዲያሳውቅ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን በኩል ማሳሰቢያ እንደተሰጠው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለሥልጣኑ ይፋ ካደረገው ደብዳቤ ተረድቷል።
ባለሥልጣኑ ተቋሙ የስም ቅያሬ እንዲያደርግ ያሳሰበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍ/ብሔር ምድብ ችሎትና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰኑት ውሳኔን መሠረት በማድረግ ነው፡፡
የስም ቅያሬ ማሳሰቢያው ምንን መሠረት ያደረገ ነው ?
የትዕዛዙ መሠረት አሻም ቴሌቪዥን በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ ላይ በሚተላለፈው “ አሻም ” የተሰኘ ፕሮግራም ባቀረበበት የክስ መሠረት ነው።
ቲክቫህ ኢትየጵያ የተመለከታቸው ሰነዶች የስም ቅያሬ ጉዳዩ በይግባኝ እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተኪዶበት ከሳሽ ያቀረቡትን ክስ አሸንፈው ፤ የካሳ ጉዳይ ተጣርቶ ወደፊት እንደሚወሰን ፤ ነገር ግን የቴሌቪዥን ጣቢያው ' አሻም ' የሚለውን ስም መጠቀም እንዲያቆም ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
በ2014 ዓ/ም የተጻፈው የፍርድ ቤት ሰነድ ከሳሽ ' አሻም ' የሚለውን ስያሜ በብስራት ኤፍኤም 101.1 እንደሚጠቀምበት፣ ለዚህም ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የምስክር ወረቀት እንዳገኘበት፣ በንግድ ምልክቱ የመጠቀምና ሌሎች እንዳይጠቀሙ የመከልከል መብት በአዋጅ እንደተሰጠው መግለጹን ይተነትናል፡፡
“ ተከሳሽ የከሳሽን ፈቃድ ሳያገኝ እንዲሁም ፈቃድ ሳይጠቅይቅ ' አሻም ' በሚለው በከሻስ የተመዘገበ የንግድ ምልክት በመጠቀም የቴሌቪዥን ጣቢያ ከፍቶ ስርጭት ጅምሯል ” ይላል ሰነዱ።
ከሳሽ ተከሳሹን፣ “ ተከሳሽ የንግድ ምልክት መጠቀሙ ሆን ብሎ ያለአግባብ ለመበልጸግ የተደረገ ተግባር ነው ይህም ተግባር ያልተገባ የንግድ ውድድር ከመሆኑም ባሻገር በከሳሽ ንግድ ስራ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ” ሲልም ከሶታል፡፡
በዚህም ' አሻም ' የሚለውን የከሳሽን የንግድ ምልክት በቴሌቪዝን ጣቢያ ስያሜነት መጠቀም እንዲያቆም ተከሽ የከሳሽን የንግድ ምልክት እየተጠቀመ በመቆየቱ ከሳሽ ላይ በደረሰው ጉዳት 1 ሚሊዮን ብር እንዲከፈል እንዲወሰን ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡
ተከሳሽ (አሻም ቴሌቪዥን) በበኩሉ፣ ከ2009 ጀምሮ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ በሚል ስያሜ በቴሌቪዥን ማሰራጨት ሥራ እየተጠቀመበት እንደሆነ፣ እውቅና እንዳገኘበት በመግለጽ፣ “ ከሳሽ እኔን ሊከሰኝ የሚያስችለው የህግና የማስረጃ ድጋፍ የለውም ” ሲል አጸፋ መስጠቱን ሰነዱ ያስረዳል፡፡
' አሻም ' የሚለውን ስያሜ ያወጣው “ በህጋዊ መንገድ ከንግድ ቢሮ ” ክፍያ በመፈጸም መሆኑን፣ ቢሮው የሚጠቀምበት ሌላ ሰው ያለመኖሩን አጣርቶ የንግድ ስያሜን እንዲጠቀምበት እንደፈቀደለት በመግለጽ ምላሽ መስጠቱና ሌሎች ጉዳዮች በሰነዱ ተብራርተዋል፡፡
ጉዳዩ በእንዲህ አይነት በርካታ ሂደቶች ከተደረጉ በኋላም ተከሳሽ አሻም የሚለውን ስያሜ እንዲያቆም፣ ንግድ ባንክ በፍርድ ባለእዳ ስም የተከፈተ ሂሳብ ቁጥር ካለ እስከ 292 ሺሕ 850 ብር እንዲያግድ ውሳኔ ትዕዛዝ መሰጠቱ ታውቋል፡፡
የፍርድ ቤት ውሳኔው የክርክር ሂደቱን በዝርዝር ካስረዳ በኋላ፣ “ ተከሳሽ አሻም የሚለውን የንግድ ምልክት መጠቀም ማቆም አለበት በማለት ወስኗል ” ይላል።
ይህንንም የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያስፈጽም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን ታዟል።
(ይህ በከፊል የቀረበ መረጃ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሶት የተመለከተው ሙሉ የፍርድ ቤት ሰነድ ከላይ ተያይዟል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
ከሰሞኑን በኢትዮጵያ የዘር ፍሬ ልገሳ ማከናወንን የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።
ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ሕግ " የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ " ይሰኛል።
አስራ ሁለት ክፍሎች ያሉት ረቂቅ አዋጁ ፦
- ስለ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣
- ስለ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣
- ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች፤
- ስለ ጤና ዘርፍ የሰው ኃብት ልማት እና አስተዳደር፤
- ስለ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ቁጥጥርን የሚመለከቱ 60 አንቀጾች አሉት።
ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች የሚያወሳው የአዋጁ አራተኛ ክፍል ከዘረዘራቸው የጤና አገልግሎቶች መካከል አንዱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ነው።
በዚህ ንዑስ ክፍል ሥር የተካተተው አንቀጽ " ፈቃድ የተሰጠው የጤና ተቋም በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ የሕክምና አገልገሎት ሊሰጥ ይችላል " ሲል ሕክምናው በሕግ መፈቀዱን ይደነግጋል።
" የዘርፍ ፍሬ ልገሳ... ከዚህ ቀደም በሕግ የተፈቀደ ተግባር ያልነበረ” መሆኑን የጠቆመው የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ፤ በዚህኛው ረቂቅ አዋጅ “ልገሳውን ማከናወን እንደሚቻል የሚደነግግ እና የሚከናወንበትን ሥርዓት የያዘ ዝርዝር ድንጋጌ " መካታቱን አብራርቷል።
ከአስራ አንድ ዓመታት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው " የምግብ፣ መድኃኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር " ደንብ፤ ፈቃድ ያገኙ ተቋማት የሰው ሰራሽ ሕክምና መስጠት እንደሚችሉ ደንግጓል። የአዋጁ ድንጋጌ " አግባብ ያለው አካል ፈቃድ በሚሰጠው የጤና ተቋም እና የጤና ባለሙያ ሰው ሰራሽ የተዋልዶ ሕክምና መስጠጥ ይቻላል " ይላል።
ደንቡ ዘር ፍሬ ልገሳ ላይ ክለከላን ባያስቀምጥም በግልጽ በሕግ ተፈቀደ መሆኑንም አይጠቅስም።
ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በበኩሉ የዘር ፍሬ ልገሳ ማድረግ እንደሚቻል እና ሂደቱ ምን መሆን እንዳለበት አስፍሯል።
በረቂቁ መሠረት የዘር ፍሬ መሰብሰብ የሚቻለው ለዚሁ ዓላማ በጤና ሚኒስቴር የተለየ ተቋም ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው በሚኒስቴሩ ለተለየው ተቋም የዘር ፍሬውን መለገስ እንደሚችል ረቂቅ ላይ ሰፍሯል።
ይህ የአዋጁ ድንጋጌ ቢኖርም ረቂቁ የዘር ፍሬ ከለጋሾች የሚወሰደው " ከፍተኛ ጉዳት የማያስከትልባቸው መሆኑ በሕክምና ሲረጋገጥ ብቻ " መሆኑን አስቀምጧል።
በረቂቅ አዋጁ ድንጋጌ ከተቀመጠው አግባብ ውጪ " የዘር ፍሬ መለገስ፣ መሰብሰብ ወይም መሸጥ " የተከለከለ መሆኑ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
የዘር ፍሬ ለመሰብሰብ ከተፈቀደለት ተቋም በተገኘ የዘር ፍሬ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ-ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ተገልጋዮች ሊሰጥ እንደሚችል ያትታል።
በዚህ የሕክምና አገልግሎት " ልጅ ያገኙ ባለትዳሮች የሚወለደው ልጅ ሕጋዊ ወላጆች ይሆናሉ " ይላል።
በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለው በአራት አስገዳጅ ሁኔታዎች ብቻ መሆኑን ያስቀምጣል።
በዚህ መሠረት ፦
➡️ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በሕጋዊ ጋብቻ የተጣመሩ እና ለዚህም ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
➡️ " ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ የማይችሉ መሆኑ በዘርፉ ባለሙያ ሲረጋገጥ " መሆኑ ሰፍሯል።
➡️ የሚሰጠው ሕክምና አወንታዊ ውጤት ሊኖረው እንደሚችል እና በተገልጋዩ ጤና ላይ ጉዳት የማያስከትል መሆኑ በሕክምና ባለሙያ መረጋገጥ አለበት።
➡️ የባለትዳሮቹን " አገልግሎቱን ለማግኘት በመረጃ ላይ የተመሠረተ የጽሁፍ ፈቃድ " የሚጠይቅ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ባለትዳሮቹ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ ቢችሉም፤ " መውለዳቸው በጤናቸው ላይ ከባድ እክል የሚያስከትል መሆኑ በባለሙያ ከተረጋገጠ " ሕክምናውን ማግኘት እንደሚችሉ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
" የዘር ፍሬ ወይም ከማህፀን ውጪ የተዘጋጀ የዘር ፍሬ ውህድ ወደ ሴቷ ማህጸን ከመግባቱ በፊት በባለሙያ ውሳኔ ወይም በባለ ትዳሮቹ ፍላጎት በማንኛውም ጊዜ ሊወገድ ይችላል " የሚል ድንጋጌን አካትቷል።
ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ እንዲወገድ የተወሰነው የዘር ፍሬ ወይም ዘርፍ ፍሬ ውሃ " ከተገልጋዮች ፍቃድ ከተገኘ ለምርምር ዓላማ ሊውል ይችላል " ይላል።
የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ " በዘር ፍሬ ልገሳ ሥርዓት የሚወለዱ ልጆች እና ወላጆችን በተመለከተ የፌደራል ቤተሰብ ሕግ ላይ ከተቀመጠው የተለየ በመሆኑ ይህንኑ ልዩነት ከቤተሰብ ሕጉ ጋር ባልተፋለሰ መልኩ እንዲቀመጥ ተደርጓል " ይላል።
ተፈጻሚነት የሌላቸውን ሕጎች የሚዘረዝረው የረቂቁ ክፍል በቤተሰብ ሕግ አዋጁ " ስለመወለድ የሚደነግጉት የአዋጁ ... ድንጋጌዎች በዘር ፍሬ ልገሳ በተገኙ ልጆች እና ወላጆቻቸው ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም " ሲል ይደነግጋል።
ተፈጻሚነት አይኖራቸውም የተባሉት ድንጋጌዎች አባትነትን እና እናትነትን ስለማወቅ፣ ልጅነትን ስለመቀበል፣ ስለ ልጅነት ማስረጃ እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ናቸው።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው።
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
ሁሉንም የሃገር ውስጥ በረራዎች ትኬት በM-PESA እንግዛ ፤ በ5% ተመላሽ ተደስተን እንጓዝ! መልካም ጉዞ 5% ቅናሿን ይዞ !
የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#FurtherAheadTogether
ከንጉስ ማልት ጋር ተጨማሪ ደስስስስስስስስስስታን ያጣጥሙ!
ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ /channel/Negus_Malt
#ከአልኮልነፃ #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት #ንጉስማልት
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በእጣና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ባልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ/ም ባለቤቶቹ እንዲገቡ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡
ውሳኔው የተላለፈው ቤቶቹ “ሕገ ወጥ ተግባራት እየተፈጸመባቸው” መሆኑን በመጥቀስ ነው።
የቤቱ ባለቤቶች እስከ ተባለው ቀን ድረስ ካልገቡ ቤቶቹ በእጣና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፉ ኮርፖሬሽኑ መግለጹ አይዘነጋም።
ይህን ውሳኔ ተከትሎም የቤት ባለቤቶች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለሚዲያችን አቅርበዋል።
በተለይም በአራብሳ ሳይት የሚገኙ የቤቶቻቸው መሠረተ ልማት ያልተጠናቀቀላቸው ሰዎች ውሳኔው ብዥታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
የቤት ባለቤቶቹ መሠረተ ልማታቸው ሳይሟሉ እንዴት መግባት እንችላለን? ግዴታ መግባት ነው ወይስ ማከራየት ይቻላል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣
₀መሠረተ ልማት ባልተሟላባቸው ቤቶች እንዴት መግባት ይቻላል?
₀የቤቱ ባለቤቶች ግዴታ መግባት ነው ያለባቸው ማከራየት ይችላሉ?
₀ክፍት በሆኑ ቤቶች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ምንድን ናቸው?
₀እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጸመው በተጨባጭ በየትኞቹ ሳይቶች ነው? ሲል ኮርፖሬሽኑን ጠይቋል፡፡
አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የኮርፖሬሽኑ አካል፣ ማስታወቂያው የወጣው መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው ላልገቡ የቤት ባለቤቶች እንጂ መሠረተ ልማታቸው ላልተሟላላቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
“ያልተሟላቸውን እማ እንዴት ተብሎ!? የማሟላት ግዴታ አለበት መንግስት መሠረተ ልማቱን” ነው ያሉት፡፡
የኮርፖሬሽኑ በዝርዝር ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Passport
የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ተገልጿል።
የኢሚግሬሽን ዜግነትና አገልግሎት የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ገልጿል።
ፖስፖርት ለማደስ 5 ዓመት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ከአንድ ወር በኃላ ወደ ሥራ በሚገባው አሰራር መሰረት ግን ከ25 ዓመት በላይ ለሆናቸው ዜጎች በየ10 ዓመቱ እንደሚታደስ አገልግሎቱ ገልጿል።
#ICS #AHADU
@tikvahethiopia
“ ወደ ህክምና የሚመጡ የካንሰር ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ” - ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
የካንሰር ህሙማን ቁጥር ግልጽ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን፣ የማህጸን በርና የጡት ካንሰር ህሙማን 50 በመቶውን እንደሚሸፍኑ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
ካንሰር ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ሆስፒታሉ ምን ማብራሪያ ሰጠ ?
“ ግልጽ በሆነ ሁኔታ የካንሰር ህሙማን ቁጥር ጨምሯል እንጂ አልቀነሰም። በተለያዩ ምክንያቶች በዓለም ላይ እንደሚጨምረው ይጨምራል።
ሁለተኛ ደግሞ የህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት በዬጊዜው እየጨመረ ነው። ስለዚህ የፔሸንት ፍሎው እየጨመረ ይሄዳል።
ወደ ህክምና የሚመጡት የካንሰር ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። አብዛኛዎቹ ህሙማን የማህጸን በርና የጡት ካንሰር ታካሚዎች ናቸው።
እንዲያው በግርድፉ እስከ 50 ፐርሰንት ልንለው እንችላለን። የነዚህ ሰዎች ህክምና በሦስት፣ በአራት ህክምና ነው የሚካሄደው። በቀዶ ህክምና፣ በመድኃኒት፣ በጨረር፣ ታርጌትድ ቴራፒ (ተራ ሳይሆን ለዬት ያለ መድኃኒት) አለ።
ስለዚህ ቁጥሩ እየጨመረ ነው። ህክምናው ደግሞ መልቲሞዳል ነው። ከዚያ በተጨማሪ ካንሰሩ ደግሞ በጊዜው አይመጣም። ከተስፋፋ፣ ካደገ፣ ከተሰራጨ በኋላ ይመጣል። ይሄ ደግሞ ከካንሰሩ ህመም በተጨማሪ ተጓዳኝ ህመሞች ይዞ ይመጣል።
ለምሳሌ የማህን በር ካንሰር ያለባት እናት አድቫንስ አድርጎ ስትመጣ ያ ካንሰር የሽንት ቧንቧዋን ይዟት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ኩላሊቷ ይጎዳል ማለት ነው " ብሏል።
በመሆኑም በማህጸን ደም ሲኖር፣ ጡት ላይ ያበጠች ነገር ስትኖር በፍጥነት ወደ ሀኪም ቤት መምጣት፣ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በህክምና ልየታ ማሰራት ያስፈልጋል ተብሏል።
የጭማሪ ቁጥሩን ለመግለጽ ዳታ ማየት ቢያሻም የካንሰር ህሙማን ቁጥር እንደጨመረ፣ ከዚህም ባሻገር የመድኃኒት እጥረት ፈተና እንደሆነበት ሆስፒታሉ ገልጿል።
ምን አለ ?
“ ሲኤምኤል የሚባል የካንሰር ህመም አለ። ይሄ ህመም እጅግ በጣም ውድ መድኃኒቶች ነው የሚፈልገው። ይሄንን መድኃኒት አንድ ሰው መግዛት አይችልም።
ሀኪሞቻችንና ተቋሙ ከሌሎች ሀገራት ሀኪሞችና ተቋሞች ጋር በመተጋገዝ መድኃኒቶች እንዲመጡ ነው የሚደረገው። ከዛ በነጻ እናሰራጫለን።
ስለዚህ ይሄን መድኃኒት ገዝተን ቢሆን ወይም በእርዳታ ባናገኘው ኖሮ ህሙማኑ አያገኙትም ማለት ነው።
ሚሎቲኒቭ የምትባል የደም ካምሰር የህክምና መድኃኒትም አለች። 120 ህመምተኞች አሉ አዚህ አገር ላይ። ለ120ዎቹ ሰዎች 22 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋቸዋል። ይሄ የመድኃኒት በጀታችን ከአንድ ሦስተኛ በላይ ነው።
22 ሚሊዮን ብር የሆነውም ጤና ሚኒስቴር 50 ፐርሰንቱን ከፍሎ ነው። እንደገና ሆስፒታሉ ሰብሲሳይድዝ ሲያደርገው ሙሉውን በነጻ ያገኛሉ። ይህን ግን በዘላቂነት ማድረግ አንችልም። ቻሌንጅ አለ። መልስ ለመስጠት ራሱ ግራ ያጋባል። ”
የካንሰር ህመምህ በጊዜ ያለበት ደረጃ ከታወቀ በህክምና ክትትል መፍትሄ የሚገኝለት ደረጃው ጨምሮ ከታወቀ ግን መጨረሻው በቀጥታ ለሞት የሚዳርግ አደገኛ ህመም ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ቴክኖ !
ታዋቂው የሆሊውዱ ትራንስፎርመር ፊልም ከቴክኖ ጋር አብሮ በመሆን ስፓርክ 30 ስልክን ይዘው ብቅ እንዳሉ ያውቃሉ?
ካላወቁ ፊልሙንም አዲሱን የስፓርክ 30 ስልኩንም በቅርበት ለማየት እሁድ ጥቅምት 3 ከ 7 ሰዓት ጀምሮ በሴንቸሪ ሲኒማ በነፃ ጋብዘነዎታል፡፡ ከልጆቾት እና ቤተሰቦት ጋር አዲሱን ስፓርክ 30 ስልክን እያዩ በተለያዩ ስጦታዎች እየተንበሸበሹ አዲሱን ትራንፎርመርስ ፊልም በኛ ግብዣ ይመልከቱ፡፡
@tecno_et @tecno_et
#ኢትዮጵያ
" በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን ይስተናገዳሉ " - አማኑኤል ሆስፒታል
በየዓመቱ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 10 የሚከበረው " የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን " ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ " በሁሉም የሥራ ቦታ ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤና ጊዜው አሁን ነው " በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።
በኢትዮጵያ ጫፍ እስከ ጫፍ ያሉ የአዕምሮ ህሙማን ወገኖችን በማከም የሚታወቀው አማኑኤል ስፔላይዝድ የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታልም ህሙማኑን በስፓርታዊ ውድድሮች በማሳተፍ ጨምር በዓሉን አክብሮ መዋሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
" የበዓሉ ዋነኛ ዓላማ በዓለም ዙሪያ በአዕምሮ ጤናና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤን ለማሳደግና በአዕምሮ ጤና ክብካቤ ላይ የድጋፍ የሞብላይዜሽን ሥራዎችን ለማጠናከር ነው " ብሏል።
“በአዕምሮ ህሙማን የሚደረጉ መገለሎች አሉ። ሰብዓዊ መብታቸው ሲከበር አይታይም” ያለው ሆስፒታሉ፣ ማንም ሰው በህመሙ ላለመጠቃት ዋስትና የለውምና ህሙማኑን በሥራ ቦታ ጭምር ከማግለል እንዲቆጠብ አሳስቧል።
ይህን ያሉት የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቢይ የኔዓለም፣ ሆስፒታሉ በቀን የሚታዩ የአዕምሮ ህሙማን ብዛት በተመለከተም ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
" በቁጥር ደረጃ በአማካኝ በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን ይስተናገዳሉ። ቁጥሩ እንደ ሁኔታዎች ይጨምራም፣ ይቀንሳልም። ለምሳሌ አሁን ላይ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎችን ብንወስድ አረመረጋጋቶች አሉ።
እነዚህ አለመረጋጋቶች ደግሞ ሰዎች ወደ ህክምና እንዳይደርሱ ያደርጓቸዋል። ስለዚህ በቅርብ አካባቢ ያሉት ናቸው ወደ ህክምና ሊመጡ የሚችሉት።
ስለዚህ በአማካኝ በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን በተመላላሽ፣ በድንገተኛ በአስተኝቶ ይታያሉ " ነው ያሉት።
መንግስትና አጋር ድርጅቶች ትኩረት ሊሰጡባቸው የሚገቡ በሆስፒታሉ ያሉ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው ? ተብሎ ከቲክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦
" ሆስፒታሉ የግንባት መሠረተ ልማት እጥረት አለበት። ጠባብ በሆነ ቦታ ነው ህክምና የሚሰጠው አስካሁን።
ያው በጤና ሚኒስቴርም በሆስፒታሉ አቅምም የተወሰኑ ጊዜያዊ እፎይታ ሊሰጡ የሚችሉ ውስጥ ላይ የሚሰሩ ማስፋፊያዎች አሉ። እነርሱም በቂ አይደሉም።
ስታንዳርዱን የጠበቀ ግንባታ ነው ሊኖር የሚገባው። ያም በጤና ሚኒስቴር ተይዞ ገና ሌላ ቦታ ላይ የግንባታ ሂደት እየተካሄደበት ያለበት ሁኔታ አለ።
ስለዚህ አንደኛው የመሠረተ ልማት ችግር ነው። ሌላው በስፔሻላይዜሽን ደረጃ በሥነ አዕምሮ ላይ ሰብስፔሻሊቲ ባለሙያዎችም እጥረት የሚታይበት ሁኔታ አለ።
ስለዚህ አጋር ድርጅቶችም መንግስትም ይህንን ትኩረት ሰጥተው በጋራ መረባረብ ቢቻል እንደ አገር የአዕምሮ ጤናን ተደራሽ ማድረግ ማጎልበትም ይቻላል " ሲሉ መልሰዋል።
በሆስፒታሉ ስንት የአዕምሮ ስፒሻሊስት ሀኪሞች አሉ ? ያስፈልጋል ተብሎ የሚታሰበው ምን ያክል ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ምላሻቸው፣ " ሰባት ስፔሻሊስቶች አሉ። ግን በሬሽዎ ሲሰራ ይሄ በቂ አይደለም። በጣም አናሳ ነው። ከዚያ በላይ ነው የሚጠበቀው " የሚል ነው።
" ለአዕምሮ ጤና ክብካቤ ወይም ደህንነት ዋናውና ወሳኙ ከባቢያችን ነው። መሪ ቃሉም በሁሉም የሥራ ቦታ ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤና ግዜው አሁን ነው። ስለዚህ የሥራ ቦታን ደህነት፣ የሰራተኛውን ጤናማ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል " ሲሉ አስገንዝበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#WorldMentalHealthDay
"ሥራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአዕምሮ ጤና ችግር ያጋጥማቸዋል" - ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
የ2024 #የዓለም_የአእምሮ_ጤና_ቀን በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል። የዘንድሮው ቀን "የአእምሮ ጤና በስራ ቦታ ላይ" በሚል መሪ ሀሳብ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።
ከአለም ህዝብ 60 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በስራ አለም ላይ እንደሆኑ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።
በስራ ላይ ካሉት ሰራተኞች ውስጥም ግማሽ የሚሆኑት የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥማቸው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዛሬው እለት የዓለም የአእምሮ ጤና ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።
የስራ አለም ላይ ያሉ ሰራተኞች በሚገጥማቸው የአእምሮ ጤና ችግርም በየአመቱ 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚጠፋ ዶ/ር ቴዎድሮስ ጠቅሰዋል።
ሰራተኞችን ለአእምሮ ጤና ችግር የሚዳርገው ምንድነው?
- ዝቅተኛ የስራ ክህሎት፣ ችሎታ እና አፈፃፀም
- ከመጠን በላይ የሆነ የሥራ ጫና፤ የሰራተኞች እጥረት፤ አድልዎ፣ መገለል፣ ጥቃትና ትንኮሳ
- ረጅም፣ ያልተገደቡ እና ተለዋዋጭ የስራ ሰዓቶች
- አሉታዊ ድርጊቶችን የሚደግፍ ድርጅታዊ ባህል
- ከሥራ ባልደረቦች በቂ ድጋፍ አለማግኘት
- በቂ ያልሆነ ክፍያ፣ የሚጋጩ የሥራ ፍላጎቶች
የአእምሮ ጤና እንደሚያስከትሉ የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ስራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥመው የገለፁ ሲሆን የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ የሚደረገው ኢንቨስትመንት አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
ችግሩን ለመከላከል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ምን መደረግ አለበት አሉ ?
° አሰሪዎች የአእምሮ ጤና ችግር የሚያስከትሉ ችግሮችን በመለየት ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር እንደሚገባቸው፤
° የድርጅት ኃላፊዎች ጭንቀት ያጋጠማቸውን ሰራተኞች እንዲለዩ፣ የስራ ቦታ ላይ የሚያጋጥም የአእምሮ ጤና ችግርን እንዲቀርፉ መስራት እንደሚገባቸው፤
° የስራ ከባቢን ለሰራተኞች ምቹ እንዲሆን ማድረግ፤ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉም ሰራተኞች በንቃት እንዲሰሩ የሚያስችል የስራ ከባቢ መፍጠር እንደሚገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።
ሰራተኞች የአእምሮ ጤና ችግር በሚገጥማቸው ጊዜም ሰዎችን ማውራት፣ ባለሙያ ማማከር ወይም እራሳቸውን ማረጋጋት እንደሚኖርባቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ ገልፀዋል።
Via @tikvahethmagazine
" መንግስትን በሃይል ለመፈንቀል የሚደረግ ሙከራ የሚወገዝና ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን ይፋ አደርገናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ መስከረም 29/2017 ዓ.ም ከቢቢሲ FOCUS ON AFRICA ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህም ወቅት ፤ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በውይይት የሚፈታበት መንገድ ዝግ እንዳልሆነ አመላክተዋል።
" ሆኖም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ላይ እየተደረጉ ያሉ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት / መንግስትን በኃል ለመፈቀል የሚደረግ ሙኩራ የሚወገዙና ተጠያቂነት የሚስከትሉ መሆናቸው ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረጋችን ልክ ነው " ብለዋል።
" ሂደቱን ተከትሎ የተጠያቂነት አስራር ተግባራዊ እንደሚሆን ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ ነው " ሲሉ አክለዋል።
የትግራይ ህዝብ ችግሮች በተባባሱበት ወቅት ለምን አንድነታችሁ መጠበቅ አቃታችሁ ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ጌታቸው " ይህ ትልቅ ወድቀት ነው ፤ እንደ ድርጅት እና ስራ አስፈፃሚ አባል የሆንኩበት ህወሓት ወድቀዋል ፤ ቢሆንም ጥቂት አመራሮች መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነት በመረዳት ለመፍታት ስንሞክር ቀላል የማይባል ፈተና እና እንቅፋት እየገጠመን ይገኛል " ብለዋል።
ከዚህ በመመለስ ግን ፈተናውን ለማለፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
@tikvahethiopia
ቴክኖ !
የፊልም አድናቂ ከሆኑ ቴክኖ እና አዲሱ የሆሊውድ ፊልም ትራንስፎርመርስ ዋን በጋራ ስለተጣመሩበት ስፓርክ 30 ስልክ ሰምተዋል?
ካልሰሙ አዲሱን ስፓርክ 30 ስልክ በቅርበት እንዲሁም በቅርብ የተለቀቀውን ትራንስፎርመርስ ፊልም ከልጆት እና ቤተሰቦት ጋር እንዲኮመኩሙ ከ 7 ሰዓት ጀምሮ እሁድ ጥቅምት 3 በሴንቸሪ ሲኒማ በነፃ ጋብዘኖታል፡፡ ይሙጡ በስጦታ እየተንበሸበሹ እሁዶን ፈታ ይበሉ!
@tecno_et @tecno_et
በመሬት ናዳ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉባ ቆርቻ እና ሻናን ዱንጎ ወረዳዎች ትላንት ማክሰኞ በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሣ በተከሠተው የመሬት መናድ፣ 10 ሰዎች መሞታቸውን ወረዳዎቹ አሳውቀዋል።
የጉባ ቆርቻ ወረዳ አስተዳዳር ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ/ም በጃርጃታ ቀበሌ ውስጥ በተከሰተው የመሬት መናድ ምክንያት 4 ሰዎች ሲሞቱ በሌላ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ደግሞ አንድ ሰው ሞቷል።
በሻናን ዱንጎ ወረዳ በሌሊስቱ ቀበሌ በዚሁ ቀን በተከሰተው ሌላ የመሬት መናድ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳዳር ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።
ነፍስ ይማር !
@tikvahethiopia
መቐለ ?
የመቐለ ከተማ ም/ቤት ዛሬ አካሂዶታል በተባለ ሰብሰባ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ህወሓት ውስጥ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር ረዳኢ በርሀ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖው እንዲያገለግሉ በ1 የተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ እንደመረጣቸው ተሰምቷል።
የከተማዋ ም/ቤት ከተማዋ በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ ይትባረክ ኣምሃ በክብር እንዳሰናበተ ተነግሯል።
አዲሱ ' የመቐለ ከንቲባ ሆነው ተመርጠዋል ' የተባሉት ዶ/ር ረዳኢ በርሀ በድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና በተነፈገው 14ኛ የህወሓት ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ አባላት ዝርዝር ስማቸው እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል።
በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13 የቢሮ ፣ የኮሚሽን ፣ የኤጀንሲ እንዲሁም የዞን አመራሮችና አስተዳዳሪዎች ከሃላፊነት በማንሳት ባካሄደው ጉባኤ በተሳተፉ 14 አመራሮች " ለመተካት ወሰኛለሁ " ማለቱ ይታወሳል።
የፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አመራር ደግሞ እንቅስቃሴው የመንግስት ግልበጣ ነው ብሎ መግለጫውን በማውገዝ መግለጫውን ባወጡ የህወሓት ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ላይ " ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ " ማለቱ ይታወሳል።
በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስለ አዲሱ የመቐለ ከተማ ተሿሚ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
ይህን መረጃ እስከተዘጋጀበት ቀን እና ሰዓት ድረስ ምዕራባዊ ዞን ጨምሮ 6 የትግራይ ዞኖች በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተሾሙ አመራሮች የሚመሩ ሲሆን መቐለ ከተማ ዛሬ በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑ አዲስ ከንቲባ ተሹሞላታል ተብሏል።
#TikvahEthiopiaMekelleFamily
@tikvahethiopia
" አደጋው እጅግ አሰቃቂ ነበር " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ ዛሬ ረፋድ 4 :00 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ከጎሮ ወደ ኮዬ እየተጓዘ የነበረ ኮድ 3-69867 ቱርቦ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ከከተማ አውቶቢስ ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋ የደረሰው።
በዚህም የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 7 ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሷል።
በአደጋው የሞቱት ሁሉም ሴቶች ናቸው። ዕድሜያቸውም ከ20 እስከ 52 የሚገመቱ ናቸው።
3ቱ ሴቶች የአውቶቢስ ትኬት በመቁረጥ ላይ እያሉ ነው አደጋው የደረሰባቸው።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቤጂንግ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " አደጋው እጅግ አሰቃቂ ነበር " ብለዋል።
የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia